የቤተክርስቲያን ዘመን - ሎዶቅያ ክፍል 2 - የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት ዘመን እስከ 1965

ይህ የሎዶቅያ ጥናት ክፍል 2 ነው። የዚህን ጥናት ክፍል 1 ለማንበብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://churchages.net/am/study/amharic-laodicea-churchage-part1

ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ነው። ሎዶቅያ የሚለው ቃል ትርጉሙ “የሕዝብ መብት ወይም ፍትሕ” ማለት ነው። ይህም ትርጉም አሁን የምንኖርበትን ዘመን ቁልጭ አድርጎ ይገልጸዋል። ሰዎች ሁሉ ስለ መብታቸው ይሟገታሉ። ነገር ግን ስላለባቸው ሃላፊነት ብዙም አይገዳቸውም።

ዘመናችን የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው፤ ይህም ዘመን በ1906 ሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ አዙዛ እስትሪት በሚባለው አካባቢ መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ነው የጀመረው። በ1917 የፔንቲኮስታል እንቅስቃሴ መገነጣጠልና መከፋፈል ጀመረ። የሰዎች አመራር ቤተክርስቲያንን እስከሚያበላሽበት ጊዜ ድረስ እውነቱ አልተገለጠም ነበር።

የዘመናችን ትልቁ ሃላፊነት በተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውስጥ ያሉት ምሳሌያዊ አገላለጾችን ትርጉም ፈልጎ ማግኘት ነው።

ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤

በፍጻሜ ዘመን እግዚአብሔር ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተውሉ ይጠብቅባቸዋል።

በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እንደ መከር የሚታጨደው ዘር በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ከተዘራው ዘር ጋር አንድ አይነት መሆን አለበት። ይህ በተክሎች ሁሉ ላይ የሚሰራ የተፈጥሮ ሕግ ነው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ በመጀመሪያው ዘመን የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ታምን የነበረውን እውነት በሙሉ የምታምን ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር እስካሁን አላገኘም። እኛ ዛሬ የምንድንበት ዓላማ ይህ ነው፤ እንደመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንድናምን።

እግዚአብሔር ታላቅ የማዳን እቅዱን እንድናስተውልና በፍቅር እንቀበል ዘንድ የንስር ዓይን ሊሰጠን ይፈልጋል። የእግዚአብሔርን ሃሳብ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ተረድታዋለች፤ ከዚያ በኋላ በመጡት ዘመናት የተነሱት ቤተክርስቲያኖች ግን ጠፍቶባቸዋል። አሁን በእኛ ዘመን ሙሉው እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ አለበት።

ከ45000 በላይ የሚሆኑ በተለያየ ስም የሚጠሩ ቤተክርስቲያኖች እውነት ነው ብለው በየቡድናቸው የሚያስተላልፉት ሃሳብ አለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን እውነት በግላችን ተገልጦልን የምንረዳው እውነት አለ፤ ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ አለብን። ቤተክርስቲያኖቹ በየቡድናቸው ከሚያስተላልፉት ሃሳብ ፈቀቅ ማለት አለብህ፤ የአንዱ ቤተክርስቲያን ሃሳብ ከሌላው ጋር ይጋጫል፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ሲያምን የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ቸል ብሎ ያልፈዋል፣ አሳስቶ ይተረጉመዋል ወይም ደግሞ ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ጋር እንዲጣረስ አድርጎ ያስተምርበታል።

61-1119 ፍዱም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ

የጋኑ ክዳን እንደተከፈተ አስቡ፤ አጋንንትም ከውስጡ ወጥተው ሲሯሯጡ፤ በክርስትና ስም የዲያብሎስ ሰራዊት ሲንቀሳቀሱና በእግዚአብሔር ቃል ፈንታ የሰዎችን ስርዓት ሲያስተምሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ትተው የቲዎሎጂና የሴሚናሪዎችን አስተምሕሮ ይሰብካሉ።

የመጀመሪያው ዓለም ጦርነት በራሺያ እና በአውሮፓ ላይ የፈላጭ ቆራጭነትን መንፈስ ፈትቶ ለቀቀ።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደግሞ እንደ ሒትለር አይነቶቹ አምባገነኖች በኩል ጸረ እሥራኤል የሆነ አጋንንታዊ ኃይል እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ መጥቶ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ጨፈጨፈ።

በአካል መግደሉ ሲያበቃ እነዚህ አጋንንት ኢክዩሜኒካል የሚባለው የቤተክርስቲያኖች እንቅስቃሴ ውስጥ ገባ። እነዚህም ቤተክርስቲያኖች የመጨረሻውን ዘመን ልጆች ሐዋርያት ወዳስተማሩትና በአዲስ ኪዳን ጽፈው ወዳስቀመጡት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እምነት እንዳይመለሱ በማድረግ በመንፈስ ይገድላሉ። የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል አለማመን መንፈሳዊ ሞት ነው።

61-1119 ፍዱም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ

ወንድሜ ሆይ፡ የሲኦል ክዳን ተከፍቷል (እውነቴን ነው)፤ የአጋንንት ኃይልም ከየአቅጣጫው እየጎረፈ ነው። ይህ ኃይል ብዙ ሃገሮችን ተቆጣጥሯል። ፖለቲካውን ውስጥ ለውስጥ ተቆጣጥሮ ፍጹም አበላሽቶታል። ቤተክርስቲያኖችንም ከቡድናቸው በቀር ምንም እንዳያውቁ እስከማድረግ ድረስ ተቆጣጥሮዋቸዋል።

ከ1914 – 1918 በተደረገው በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አውሮፓ ውስጥ ሴቶች ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ ነበረ፤ በሥራ ላይ አደጋ እንዳይደርስባቸው ሲሉ ጸጉራቸውን ተቆረጡ። ለምን ረጅም ጸጉራቸውን በሻሽ አስረው ከመቆረጥ አላተረፉትም?

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ወንዶች ጸጉራቸውን ማስረዘም ጀመሩ፤ ፋብሪካ ውስጥ ሲሰሩም ራሳቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ጸጉራቸውን በሻሽ አሰሩ። ስለዚህ ዲያብሎስ ወንዶቹንም ሴቶቹንም የነበረባቸውን የሥራ ጫና ተጠቅሞ በማታለል የመጽሐፍ ቅዱስን ትዕዛዝ እንዲተላለፉ አደረጋቸው።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡14-15 ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥ ... ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?

የሴት ረጅም ጸጉር ወይም ጸጉርዋን አለመቆረጥዋ ለአባቷ ታዛዥ የመሆንዋ ምልክት ነው፤ ከዚያም በኋላ ስታገባ ደግሞ ለባሏ እንደምትገዛ ምልክት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡14-15 ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡5 ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።
6 ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።

ሴት ጸጉርዋን ብትቆረጥ ራሷን ታዋርዳለች የሚለው ቃል ትርጉሙ ባሏን ታዋርዳለች ማለት ነው።

ኤፌሶን 5፡23 … ባል የሚስት ራስ ነውና።

23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ …
24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት። ስለዚህ ጸጉርዋን የምትቆረጥ ሴት ባሏን እንደ ራስ አልተቀበለችውም፤ በዚህም የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ክርስቶስን ጌታ አድርጋ የማትቀበል ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል ብቻ የመኖር ፍላጎቷ ጠፍቷል። አካልን በሙሉ የሚቆጣጠረው ራስ ነው። የአሁኑ ዘመን ቤተክርስቲያን ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥጥር ውስጥ መመላለስ አትፈልግም።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተደረገባቸው ዓመታት መካከል ሐይማኖትን የመከተል ዝንባሌ በተለይም በተማሩ ሰዎች ዘንድ በጣም ወድቆ ነበር። ለምሳሌ የማንችስተር ኤጲስቆጶስ ከዚያም ደግሞ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዊልያም ቴምፕል የወንጌል ስብከትን አገልግሎት ትቶ በዚያ ፈንታ ተራማጅ ፖለቲካ ይሻላል ብሎ መርጧል።

በ1920ቹም በመጀሪያው የዓለም ጦርነት የሆነውን እልቂት ተከትሎ ታላቅ ሥነ ምግባራዊ ውድቀት መጣ። የስነልቦና ምሑሩ ወይም ሳይኮሎጂስቱ ፍሮይድ ወሲብን ትልቅ የመወያያ ርዕስ አድርጎ በመጻሕፍት አሳተመ። ይህም ርዕስ አደገኛነቱ ቤተክርስቲያናት የመጀመሪያው ሐጥያት ወሲብ መሆኑን ገልጠው ባለማስተማራቸው የተነሳ ነው። ከዚህም ሐጥያት የተነሳ ሔዋን ልጅ በመውለድ እንድተቀጣ ተወሰነባት። እግዚአብሔር ወሲብን የሚፈቅደው በጋብቻ ውስጥ ብቻ ነው። ስለዚህ ሰዎች ወሲባዊ ሐጥያት በጣም ከባድ ሐጥያት መሆኑን አላወቁም።

1ኛ ቆሮንቶስ 6፡18 ከዝሙት ሽሹ።

ይህ ዝሙት ሳይጋቡ የሚፈጸም ወሲብ ነው።

ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።

በሕግ አግብተህ ከሆነ እና ከዚያ በኋላ ከፈታህ እንደገና ማግባት አትችልም። እንደገና ካገባህ ዝሙት ማመንዘርህ ነው። ዛሬ ብዙ ቤተክርስቲያኖች የተፋቱ ሰዎችን የቀድሞ የትዳር ጓደኛቻ በሕይወት እያሉ እንደገና ይድሯቸዋል።

የመጨረሻው ቤተክርስቲያን ከድክመቶቿ አንዱ ወሲባዊ ልቅነት ነው፤ እርሱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው እጅግ የተስፋፋው። ከዚያም በ1960ዎቹ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል መፈጠርን ተከትሎ እንዲሁም በአደንዛዥ ዕጽ ቀስቃሽነት ከሚጫወቱት የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ጋር ከፍተኛ የሆነ ሥነ ምግባራዊ ውድቀት ተከሰተ። ብዙዎቹ ታዋቂ ሙዚቀኞች ራሳቸውን ባለመቆጣጠራቸውና ልቅ በመሆናቸው የተነሳ ዕድሜያቸው ገና 27 ዓመታ ሳለ ሞቱ።

ፈጣን ሙዚቃ፣ ነጻ ወሲብ እና የምስራቆች ባዕድ አምልኮ በ1963 ዝነኛ በሆኑት ቢትልስ በሚባሉ የእንግሊዝ የሙዚቃ ባንዶች አማካኝነት ተስፋፉ። በተጨማሪም 1963 ዓ.ም. ብዙ ሴቶች በአንድ ጊዜ ገላን አጋልጦ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ መልበስ የጀመሩበት ዓመት ነው። በ1963 ብዙ ሴቶች ወንዶችን በመኮረጅ ሱር መልበስ ጀመሩ። ሰይጣን ወጣቶችን ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት በማራቅ ሊያጠፋቸው የመልስ ምት ለማድረግ ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ ነው።

ለምን? ምክንያቱም ወንድም ብራንሐም የተሰወሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራትን ለመግለጥ ስድስቱን ማሕተሞች በመፍታቱ የተነሳ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለው መጽሐፍደ ቅዱስን ያለማወቅ እውርነት እጅግ ብዙ ወጣቶች ሰሦስተኛ ጊዜ ፈልሰዋል።

65-0123 የተቀደዱ ጉድጓዶች
እኛ አሜሪካኖች ራሳችንን ክርስቲያን ሕዝብ ብለን መጥራታችን ትልቅ ጥያቄ ይፈጥርብኛል፤ በየዓመቱ እኛ በተለይም ሴቶቻችን ልብሳችንን እያወለቅን ነው። ይበልጥ ደርበን ልንለብስ ሲገባን። ክርስቶስን ይበልጥ ስትለብሱ ያላችሁበት ሁኔታ ይበልጥ ጎልቶ ይታያችኋል። አንዳንዴ ጊዜ መንገድ ላይ ሰዎች ሚሆኑትን እያየሁ አእምሮዋቸው ጤናማ መሆኑን እጠራጠራለሁ። የሚያደርጉት ነገር ራሳቸውን የሰይጣን ወጥመድ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ነፍሳትን ወደ ሲኦል የሚያስገባ ድርጊት መሆኑን ያወቁ አይመስሉም።

1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡9 እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤

ዘዳግም 22፡5 ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።

በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የአለባበስ ጉዳይ ምንም አያሳስባቸውም። ስለ አለባበስ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችንም እንዳላ ያልፉዋቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰዎችን ወደ አርማጌዶን ጠራርጎ ስለሚወስድ የምስጢር አሰራር ያስጠነቅቃል።

ራዕይ 16፡13 ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤

ዘንዶው ሰይጣን ነው። አውሬው ማለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስትሆን እርሷም መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ወግና ሥርዓት የሚከተሉ የተደራጁ ቤተክርስቲያናት ሁሉ እናት ናት። ሐሰተኛው ነብይ የሐሰተኛዋ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነብይ ማለትም ፖፑ ነው።

እነዚህ ሦስቱ የክፋት ሠራዊት በአንድነት በቤተክርስቲያን ላይ አጋንንታዊ አሰራርን እንደ ጎርፍ እየለቀቁ ነው።

ራዕይ 16፡14 ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።

ዛሬ በዓለም ዙርያ 1,200,000 ካቶሊኮች አሉ። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከሁሉም ትልቅ ቤተክርስቲያን ናት።

እነዚህ ሦስት ሰይጣናዊ ኃይላት ዓለም አቀፍ የሆነ ተዓምር እየሰሩ ናቸው፤ ይህም ተዓምር ከካቶሊክ ውጭ የሆኑ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ኢክዩሜኒካል በተባለ እንቅስቃሴ አማካኝነት ወደ አንድነት መምጣታቸው ነው። በ2018 ዓ.ም የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ከ600000 እስከ 800000 የሚሆኑ ፕሮቴስታንቶች በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ይሳተፉበታል። ይህ የተደራጀ የፕሮቴስታንት ሐይማኖት በተደራጀው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሬ አምሳል ነው የተቀረጸው። የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ተዓምር የሚሆነው የአውሬው ፕሮቴስታንታዊ ኢክዩሜኒካል ምስል ከአውሬው ማለትም ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ወደ አንድነት መምጣቱ ነው።

እነዚህ ሦስት የሰይጣን ኃይላት የቤተክርስቲያንን ዓለም በአርማጌዶን ወደሚሆነው ጥፋት እየነዱ ሲወስዱ በዚህ መሃል ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ኢየሱስ ማስጠንቀቂያ ያስተላልፋል።

መዳን አለባችሁ አይለንም። በቅድስና መኖር አለባችሁ አይለንም። በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ አለባችሁ አይለንም። በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያኖች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ለእነዚህ ጉዳዮች ነው። እነዚህ ሁሉ ትልቅ ዋጋ አላቸው።

ነገር ግን ኢየሱስ የሚያስጠነቅቀን እንደ ጎርፍ እያጥለቀለቀ ከሚመጣው አጋንንታዊ አሰራር ነው። የሱናሚ ጎርፍ ወይም ትልቅ ደራሽ ውሃ ሲመጣ ሰዎች ሮጠው እንዲያመልጡ ነው ማስጠንቀቂያ የሚነገራቸው። ሰዎች ደራሽ ውሃን በራሳቸው ጉልበት ሊቋቋሙት መሞከር የለባቸውም። አጋንንታዊ አሰራር እንደ መንፈሳዊ ደራሽ ውሃ በቤተክርስቲያኖች ላይ እየጎረፈ ሲመጣ የሚያዋጣን ቀድመን ማምለጥ ነው።

ከዚያም አደጋ ከመምጣቱ በፊት እንደ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡- “እንዴት እንድትለብሱ ተጠንቀቁ”።

በእግዚአብሔር ዓይን ሥርዓት ያለው አለባበስ በጣም ወሳኝ ነው። ልብሳችን ገላችንን አጋልጦ ማሳየት የለበትም።

ራዕይ 16፡15 እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።

ለምንድነው በሥርዓት መልበስ ያለብን እና ገላችንን ማጋለጥ የሌለብን?

ኢየሱስ ራቁት ሆኖ ያገኘው ብቸኛው ሰው ሌጌዎን ነው፤ እርሱም ደግሞ ራቁት የነበረው በአጋንንት ተይዞ ስለነበረ ነው።

ስለዚህ ገላን አጋልጠው የሚያሳዩ ልብሶች እንድንለብስ የሚያደርገን የአጋንንት ተጽእኖ ነው። ገላችንን ባጋለጥንበት መጠን ምን ያህል በአጋንንት እንደተያዝን እናመለክታለን ማለት ነው።

ሉቃስ 8፡26 በገሊላም አንጻር ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር በታንኳ ደረሱ።

27 ወደ ምድርም በወጣ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፥ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ ልብስ ሳይለብስ በመቃብር እንጂ በቤት አይኖርም ነበር።

35 የሆነውን ነገር ሊያዩ ወጥተውም ወደ ኢየሱስ መጡ፥ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ ልቡም ተመልሶ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።

ወደ ልቡ እንደተመለሰ ወዲያው ማንም ሳይነግረው ሰውየው ራሱ ልብስ ለበሰ። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጤናማ ሰዎች ገላቸውን በሚገባ በልብስ ይሸፍኑ ነበር።

ያለንበት የመጨረሻ ዘመን አደጋው ገላን የሚያጋልጥ ልብስ አይደለም። አደጋው በእኛ ውስጥ ተቀምጠው ገላን የሚያጋልጥ ልብስ እንድንለብስ የሚገፋፉን አጋንንት ናቸው።

61-1119 ፍጹም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ
ማነው ብርቱ፤ ማነው ጠቢብ? ማነው ይህንን በሰባኪዎች ስም፣ በሜተዲስቶች፣ በባፕቲስቶች እንዲሁም በፔንቲኮስታሎች ስም ከሴቶቻችን ላይ ልብስ እያስወለቀ ያለውን ሌጌዎንን ሥርዓት ያስይዝልን ዘንድ ኃይል ያለው? እንደ ኤልዛቤል ፊታቸውን ተቀባብተው፣ ጸጉራቸውን አጋጊጠው፣ እንደ ወንድ ሱሪ ለብሰው መንጎራደዳቸው ሳያንስ ሰባኪዎቻችን ደግሞ ከመቀመጫ ተነስተው ያደንቋቸዋል፤ እነዚህስ አጋንንት አለባቸው … ሌጌዎን ነው እኮ ከሰውየው ላይ ልብሱን ቀዳዶ ያወለቀበት። ማነው ይህ የሚያጓራ ጋኔን?

እነዚያ ሁሉ በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ከጥልቁ ወጥተው የተለቀቁ አጋንንት ዛሬ በየቤተክርስቲያናቱ ውስጥ መሽገው ከሴቶች ላይ ልብስ እያስወለቁ ናቸው። የገላቸውን ግማሽ ያህል የተራቆቱ ሴቶች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፈልገህ እይ፤ ከዚያ አጋንንቱ የት እንደተደበቁ ታስተውላለህ።

እነዚህ አጋንንት በፍጥረታዊው ዓለም አምባገነን ሆኖ በተገለጠው በሒትለር እና በመሰሎቹ አማካኝነት የተለቀቁ የፈላጭ ቆራጭነት መናፍስት ናቸው። ፈላጭ ቆራጮች ሌላ ሰው ከስሕተታቸው ሊያርማቸው ሲሞክር አይቀበሉም። የቤተክርስቲያን ሴቶችን እንደተከበሩ እመቤቶች በሥርዓት እንዲለብሱ ንገራቸው፤ ከዚያ ወዲያ በቁጣ ይመልሱልሃል። የፈላጭ ቆራጭነት አጋንንት ሴቶችን አምባገነን ያደርጉዋቸዋል።

1ኛ ጴጥሮስ 3፡1 እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ [ለ]ባሎቻችሁ … ተገዙላቸው።

ነገር ግን ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ደስ እንዳላቸው ነው የሚለብሱት። ቢጠየቁ መብቴ ነው ብለው ይመልሳሉ። “በመብት” እና “በሃላፊነት” መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ማለት አለብን።

ራዕይ 16፡16 በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ አስከተቱአቸው።

ስለዚህ የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን እንደ ጎርፍ በመጣባት አጋንንታዊ አሰራር በመታለል ወደ ታላቁ መከራ ለመግባት በመጣደፍ ላይ ናት። መዳን ማለት ወደ ሲኦል አንሄድም ማለት ነው። መዳን ማለት ግን ከታላቁ መከራ ማምለጥን አያጠቃልልም። ከሲኦል መዳን በሥራ አይገኝም፤ በንሰሐ ብቻ ነው እንጂ። ከታላቁ መከራ ለመዳን ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ያስፈልገናል።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ቤተክርስቲያናት ስሕተትን ታቅፈው ሲቀመጡ እኛ ግን እስከመጨረሻው ጸንተን እውነትን መፈለግ አለብን።

ማቴዎስ 10፡22 … እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ወደ ሙታን ትንሳኤ እና የሙሽራይቱ አካል መለወጥ በሚያደርሰው መንገድ በትክክል የሚመራን።

ሮሜ 8፡23 እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።

ትንሳኤውን እንድናስተውልና የሚሞተው ሥጋችን ወደማይሞተው ይለወጥ ዘንድ የተፈተነውን ራሳችንን ልናቀርብ መትጋት አለብን።

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡15 … የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።

ፊልጵስዩስ 3፡11 … ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ …

ይህ ትንሳኤ በቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ የሚሆነው የሙሽራይቱ ትንሳኤ ነው። ጳውሎስ የዳነ በመንፈስ ቅዱስም የተሞላ ሰው ቢሆንም እንኳ ትንሳኤን እንደ ቀላል ነገር አልቆጠረም።

የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ዋነኛ ዓላማ ከታላቁ መከራ እናመልጥ ዘንድ ልናውቅ የሚያስፈልገንን ዋነኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት መግለጥ ነበር።

ቤተክርስቲያናት ሰዎችን ከሲኦል በማዳን ትልቅ ሥራ ሰርተዋል። ነገር ግን ካዳኑዋቸው በኋላ የዳኑትን ሰዎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ሰው ሰራሽ ወደሆኑ የቤተክርስቲያን ወጎች ነው የሚመሩዋቸው። ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ትተው ሰውን ማድመጥ ማለት ከኢየሱስ ጋር አይጋቡም ማለት ነው። የኢየሱስ ሙሽራ ለቃሉ ማለትም ለመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ መገዛት አለባት።

በ1963 ዊልያም ብራንሐም በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ያሉትን የስድስቱን ማሕተሞች ምስጢር ገለጠ። ያም ዓመት ለእውነት መገለጥ ቁልፍ የሆነ ዓመት ነበረ።

ማሕተሞቹ ሲፈቱ ከሮማ ካቶሊክ የሆነው የክርስቶስ ተቃዋሚ ቤተክርስቲያን አነሳስ ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጀምሮ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ላይ የካቶሊክ እምነት በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልኮ ገብቶ ዓለም አቀፍ ኃይል እስኪጎናጸፍ ድረስ ያለፈበትን ሒደት አሳይቷል። ከዚያም ሌላ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔር ለአይሁዶች የሚያደርገውን የጥበቃ እቅድ እና በታላቁ መከራ ወቅት ወደ አይሁድ ተመልሶ እንደሚመጣም ገልጠዋል።

ብርሃን ጨለማን ያስወግዳል። ፖፕ ጆን 23ኛው በ1963 ሲሞት ጆን ኬኔዲ ብቸኛው ካቶሊካዊ የአሜሪካ ፕሬዚደንት በ1963 ተገድሏል። የተገለጠው ቃል እኛ ልናስተውል ከምንችለው የበለጠ ኃይል አለው።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የፈላጭ ቆራጭነትን መናፍስት በምድር ላይ ፈትቶ ለቀቀ።

ከ1914-1918 በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የተደረገው የሕዝብ ጭፍጨፋ የፈረሰ ዓለም ውስጥ እንደምንኖር እነዲሰማን የሚያደርግ ታላቅ ትግል እና ምጥ ፈጥሯል። ከዚያም ርሕራሄ የሌለው የፈላጭ ቆራጭነት መንፈስ በፍርሃት በተዋጡትና ግራ በተጋቡት የአውሮፓ ሕዝቦች ላይ የአሸባሪነትን አለንጋ ይዞ በፍርሃት አንቀጥቅጦ እንዲገዛቸው መንገድ ተከፈተለት።

ይህን ተከትሎ እስፓኒሽ ፍሉ የተባለ ከባድ የጉንፋን በሽታ ወረርሽኝ በ1918-1919 በዓለም ሁሉ በመዛመት ተጨማሪ 65 ሚሊዮን ሰዎችን ገደለ። ይህም ሰዎች ሁሉ በድንጋጤ እንዲንገዳገዱ አደረገ።

የፔንቲኮስታል እንቅስቃሴ በ1917 በተለያዩ ሰው ሰራሽ ቡድኖች በመከፋፈሉ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበር። “ዲኖሚኔሽን” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

• የመጀመሪያው ፍልሰት የሆነው ሙሴ አይሁዶችን ከግብጽ ያወጣበት ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች አይሁዳውያን ሕጻናትን ገደሉ።
• ሁለተኛው ፍልሰት ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ከአይሁዶች መካከል ያወጣበት ነው። በዚያ ጊዜ ሔሮድስ አይሁዳውያን ሕጻናትን ገደለ።
• ሦስተኛው ፍልሰት ደግሞ ሙሽራዋን የሚሆኑትን ግለሰቦች ከቤተክርስቲያን ውስጥ ማውጣት ነው። እኛ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉት ሐዋርያት ይከተሉት ወደነበረው እምነት መመለስ ያለብን ልጆች ነን።

ስለዚህ ልጆች እንደገና መሞት አለባቸው። ፍልሰት ባለበት ጊዜ ሁሉ ይህ እየተደጋገመ ይሆናል።

ናፖሌዮን በ1815 ከተሸነፈ በኋላ አውሮፓ በለጸገች፤ ከዚያም እንጀራ ጠግበው ያደጉ ልጆችዋ በ1914 ጦርነት አማራቸው። በጦርነቱም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በማይረባ የውግያ ታክቲክ አማካኝነት አውቶማቲክ ጠብመንጃ እየተተኮሰ ባለበት ቀጥ ብለው ወደ ጥይቶቹ ውስጥ በመሮጥ ያለምንም ዓለማ ተጨፈጨፉ። የጦርነቱ አሰቃቂነት እየተባባሰ መሄዱ የእያንዳንዱ ሃገር መንግሥት በኢኮኖሚው ላይ እጁን እንዲዘረጋና በራሱ ዜጎች ላይ የፈላጭ ቆራጭነት ሥልጣንን እንዲጠቀም አስገደደው። መንግሥት በአምባገነንነት እያደገ ሄደ።

መንግሥት ጦርነቶችን ለማሸነፍ ሲል በየጊዜው እየጨመረ የሄደበት አስፈሪ ጭካኔ እና ግፈኝነት እያንዳንዱ ሃገር በአውዳሚነታቸውና በአጥፊነታቸው ኃይለኛ የሆኑ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መፍጠር እንዲሁም የጨቋኝነት ችሎታውን እንዲጨምር አስችሎታል። የፈላጭ ቆራጭነት መንፈስ በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው በምድር ላይ የተለቀቀው (1914-1918)። መንግሥት በሕዝቡ ላይ የፈላጭ ቆራጭነትን ሥልጣን በማናለብኝነት መለማመድ ጀመረ፤ ከዚህም የተነሳ ሃገርን በሙሉ ለሚቆጣጠር ፈላጭ ቆራጭ መሪ ወደ ሥልጣን መውጫ መንገድ ተከፈተ።

በ1906 የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ለማምጣት በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ ተጀመረ።

የሚያሳዝነው ነገር ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ሲፈልጉ በ1917 ጴንጤቆስጤ በቤተክርስቲያን ታፍኖ ቀረ። በዚህም መንገድ ሰዎች በተሾሙበት የሚገለጠው የፈላጭ ቆራጭ መንፈስ ወደ ጴንጤቆስጢያዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ገባ። ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሬ ምስል ነው፤ ማትም ፖፑ ሰው ሆኖ ሳለ በሮማ ካቶሊክ ውስጥ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ይገዛል።

እግዚአብሔርም ከቁጣው የተነሳ በ1917 በእግዚአብሔር የማታምነዋን ኮምዩኒስት ራሺያ የቅጣት በትር አድርጎ አስነሳ፤ ይህችንም ሃገር ለአሜሪካ የመጨረሻ ቅጣት ይጠቀምባታል። አግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ጣኦት አምላኪ የሆነችዋን ባቢሎን ልኮ አመጸኞቹን አይሁዳውያን በጦርነት እንድታሸንፍ በባርነት እንድትገዛ ማድረጉን አስታውሱ።

በ1917 ሌኒን ራሺያ ውስጥ እንዲገባ፣ የኮምዩኒስት አብዮት እንዲጀምር እና ራሺያን ከጦርነቱ እንዲያስወጣት በጀርመኒ ተልኮ ነበር።

ይህም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ምክንያቱም በቀጣዩ ጦርነት ኮምዩኒስት ራሺያ ተነስታ ጀርመኒን ድቅቅ አድርጋታለች።

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዊልሰን እና ከእርሱ ጋር የተባበሩት ሃገሮች የጀርመኒን ኢኮኖሚ የሚያዳክምና በቀጣይነት ለሌላ ጦርነት የሚጋብዝ አይነት የሰላም ስምምነት ጀርመኒ ላይ ጫኑባት። በዚህ አስጊ በሆነና ባልተረጋጋ ወቅት ጨካኝ የሆኑ እንዲሁም የወንበዴ ባሕርያ ያላቸው ሰዎች ተነሰተው ሥልጣን ላይ ተቀመጡ።

በዚህም መንገድ ራሺያ ውስጥ ሥልጣን በመያዝ ቀዳሚውና ስሙ የገነነው ሌኒን ነው። ሌኒን ሐይማኖትን የሚጠላ ሰው ነው፤ ግን የአንዳንድ በቅድስና የሚመላለሱ ክርስቲያኖች ተጽእኖ ያስፈራው ነበር። ሌኒን ፈጽሞ መቻቻል የማያውቅ እና ሰብዓዊ ርሕራሄ የሌለው ሰው በመሆኑ የመሰረተውን ኮምዩኒስት ድርጅት በጭካኔ ነበር የሚያስተዳድረው። የሥልጣን ጥም የተጠናወተው ሌኒን ኃይልን በመጠቀም በተደራጁ የነፍስ ግድያ ሰራዊቶቹ አማካኝነት የሽብር ዘመቻ በማድረግ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደለ። አንጋፋዊ የአብዮቱ መሪ በሚለው ስሙ እና ዝናው በመጠቀም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ላይ ሌኒን ታላቅ የጭካኔ እና የነፍስ ግድያ ሥርዓት አበጀ።

በ1924 ሌኒን ሞተና እስታሊን በቦታው ተተካ፤ ወዲያውም እስታሊን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በመግደል የራሺያ ታላቅ ፈላጭ ቆራጭ ሆነ።

በ1922 ሙሶሊኒ ኢጣሊያ ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ሆኖ ተነሳ፤ ወደ ሥልጣንም ሲወጣ አብሮት የነበረው ዝና 169 ውሽማዎች ያሉት የሴቶች አማጋጭ መሆኑ ነበር። አንድ የካቶሊክ ቄስ ሙሶሊኒን የሚቃወም ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ እንቅስቃሴ ሊጀምር ነበር ግን ፖፑ ከለከለው። በዚህም ምክንያት ሙሶሊኒ ምርጫውን ሊያሸንፍ ችሏል።

የሰው ዋነኛ ድክመቶች ሦስት ናቸው፡- ዝና፣ ሴት መውደድ፣ እና ገንዘብ።

ሌኒን ዝና ነበረው፤ ሙሶሊኒ ደግሞ ሴት ይወዳል። በ1929 በተፈጠረው ታላቅ የኢኮኖሚ ድቀት ዋነኛው መንስኤ ገንዘብ የነበረ ሲሆን በጊዜው የተከሰተው ኪሳራ ውስጥ ነው ሒትለር ጀርመኒ ውስጥ ወደ ሥልጣን የመጣው።

በ1929 ሙሶሊኒ የቫቲካን ከተማ ራሷን የቻለች ነጻ መንግሥት እንድትሆን አዋጅ አወጣ። ቫቲካን በዓለም ላይ ትንሽዋ መንግሥት ስትሆን የዳንኤል ትንቢት ውስጥ “ታናሽ ቀንድ” ተብላ የተገለጸችው ናት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ በሴት ማለትም በጋለሞታ ነው የምትመሰለው። ይህች ጋለሞታ ቤተክርስቲያን ዓለምን መቆጣጠሯ እና በመንግሥት ዘንድ እውቅና ማግኘቷ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ትምሕርት ፍጹም ተቃራኒ ነው። በፍጥረታዊው ዓለም ሃገሮች የከሰሩት ኪሳራ የሙሶሊኒ ድርጊቶች ያመጡትን መንፈሳዊ ኪሳራ አመላካች ነው።

ራዕይ 17፡1 ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤
3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
18 ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።

ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የምናገኛቸውን ፍንጮች ልብ ብለን ስናይ የሚናረነው በሰባት ተራሮች ላይ ስለተመሰረተችው የሮም ከተማ እንደሚናገር እናስተውላለን።

የሮማ ሪፓብሊክ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመተ ዓለም የተመሰረተ ጊዜ ሮማውያን (በሰማያው ቀለም እንደምናየው) መንደሮቻቸውን በገነቡባቸው በሰባቱ ኮረብታዎች ዙርያ አጥር ሰሩ። አጥሩ መንደሮቹን ወደ ከተማነት አሳደጋቸው፤ ከተማይቱም የሰባቱ ኮረብታዎች ከተማ ተባለች። ከወንዙ ማዶ ደግሞ ቫቲካን የሚባል ቦታ ነበረ። በ324 ዓ.ም. ኮንስታንቲን በቫቲካን ግዛት ላይ ቤተክርስቲያን ሰራ፤ ከዚያም ቀስ በቀስ በየክፍለ ዘመናቱ በቤተክርስቲያኒቱ ዙርያ ሌሎች ሕንጻዎች ተሰሩ።

ነገር ግን ኮረብታ ተራራ አይደለም። ስለዚህ እዚህ ውስጥ የተሰወረ ጠልቅ ያለ ሚስጥር አለ።

ደግሞም የሮም ከተማ የዓለም መንግሥታትን አትገዛም። ፈላጭ ቆራጩ ሙሶሊኒ በ1945 ከሞተ ወዲህ በኢጣልያ ውስጥ 48 ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሥልጣን ላይ አሳልፈዋል። በየአንድ ዓመት ተኩል አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የምትሾም ሃገር ዓለምን ሁሉ ለመምራት የሚበቃ መረጋጋት አይኖራትም።

በትንቢት ውስጥ “ተራራ” ምንድነው የሚወክለው?

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከብረት የተሰራ ታላቅ ምስል በሕልሙ አይቶ ነበር፤ ይሕም የሚወክለው አራት የአሕዛብ መንግሥታትን ነበር። እነርሱም ባቢሎን፣ ፋርስ፣ ግሪክ እና ሮም ናቸው።

ዳንኤልም አንድ ድንጋይ የምስሉን እግር ሲመታው በራዕይ ተመለከተ።

ምስሉ ተሰባብሮ ወድቆ ድንጋዩ ግን ታላቅ ተራራ እንዲሆን አደገ።

ዳንኤል 2፡35 ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ

ጌታ ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣ የምድር አሕዛብ በአርማጌዶን ጦርነት ተፈጭተው ይበናሉ።

ዳንኤል 2፡44 በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።

ተራራ የሚለው ቃል የሚወክለው መንግሥትን ነው።

ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ ኢየሱስ ምድርን ሲገዛ የሚሰፍነው የ1000 ዓመት ሰላም ብዙውን ጊዜ የሺህ ዓመት መንግሥት ተብሎ ይጠራል። ይህም እገዚአብሔር የሚመሰርተው መንግሥት ነው።

ማቴዎስ ምዕራፍ አሥራ ሦስት ውስጥ “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚል ርዕስ ያላቸው 13 ተከታታይ ምሳሌዎች አሉ። እነዚህ ምሳሌዎች የሚናገሩት እግዚአብሔር በመጨሻዎቹ 2000 ዓመታት በቤተክርስቲያን ሊሰራ ስላሰበው ሥራ ነው።

ስለዚህ ማቴዎስ ምዕራፍ 13 የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ዝርዝር ነው። እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን እግዚአብሔር እና ሰይጣን የሰዎችን ልብ ለማግኘት የተዋጉበት መንግሥት ወይም ተራራ ነው።

በ852 ዓ.ም. ፖፕ ሊዮ 4ኛው በቫቲካን ሕንጻዎች ዙርያ የመጀመሪያውን ግምብ አጥር ሰራ።

ቫቲካን ዙርያዋን በግምብ አጥር ስትከበብ የቫቲካን ከተማ ሆነች። በ1870 ፖፑ መኖሪያው በቫቲካን ከተማ ውስጥ ብቻ ሆነ።

አሁን በሮም ከተማ ዙርያ አጥር የለም። የእውነት ጠላት የሮም ከተማ አይደለችም - የቫቲካን ከተማ ናት እንጂ።

ራዕይ 17፡9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ በመገኘት ሰባቱን የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌዎች በሚወክሉት ሰባቱ ተራሮች ሁሉ ላይ ተቀምጣ የቆየችዋ የሮማ ካቶሊክ ብቸኛዋ የእግዚአብሔር ጠላት ናት።

ከዚያም በ1929 አምባገነኑ መሪ ሙሶሊኒ የቫቲካንን ከተማ በምድር ላይ ትንሽዋ ራስዋን የቻለች መንግሥት አድርጎ እውቅና ሰጣት።
ይህም ዳንኤል በትንቢቱ ውስጥ የተናገረለት ትንሽ ቀንድ ቫቲካ መሆኗን ያመለክታል።

ዳንኤል 7፡8 ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።

የሮማ መንግሥትን ለማፈራረስ አስተዋጽኦ ያደረጎ አሥር ባርቤሪያውያን ነገዶች የሮማ መንግሥትን ካፈራሰሱ በኋላ ፖፑ በአውሮፓ ውስጥ ታላቅ መሪ እንዲሆን ድጋፍ አድርገዋል። ከእነዚህ ባርቤሪያን ነገዶች ሦስቱ በሥላሴ የማያምኑ ነበሩ። የኮንስታንቲኖፕል ገዥ በኢጣሊያ እና በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ላሉ የሮማ ካቶሊክ ተከታዮች ሥጋት የነበሩትን በሥላሴ የማያምኑ ሦስት ባርቤሪያውያን ነገዶች ከ533 -554 ዓ.ም. በጨፈጨፋቸው ጊዜ በሥላሴ የሚያምነውን ፖፕ እንዳይሞት ሰዎች ከለላ አድርገውለታል። እነዚህም በሥላሴ የማያምኑ ነገዶች በሰሜን አፍሪካ የነበሩት ቫንዳልስ እና በኢጣሊያ የነበሩት ሄሩሊ እና ኦስትሮጎቶስ ናቸው። ስለዚህ አውሮፓ ለመቶዎች ዓመታት ወደ ጨለማው ዘመን ስትገባ የሥላሴ አስተምሕሮ አንዳችም ተቃውሞ አልገጠመውም። ከዚህም የተነሳ ለውጡ በተጀመረ ጊዜ ሰዎች የሥላሴን አስተምሕሮ ሳይመረምሩት እንዲሁ ተቀበሉት። ምክንያቱም ከለውጡ በፊት ለብዙ ዓመታት ሲማሩ የቆዩት ትምሕርት ነበር።

ከዚያም በዳንኤል መጽሐፍ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ያለው ትንቢት የአሊግዛንደር ዘግሬት ግዛት ለአራት ግዛቶች መከፋፈሉን በመናገር ግሪኮች ላይ ያተኩራል። አሊግዛንደር ብዙ ሃገሮችን አሸንፎ በመግዛት በብርታቱ ታላቅ የሆነ ቀንድ ተብሎ ተገልጧል።

ዳንኤል 8፡8 አውራውም ፍየል ራሱን እጅግ ታላቅ አደረገ፤ በበረታም ጊዜ ታላቁ ቀንዱ ተሰበረ፥ ወደ አራቱም የሰማይ ነፋሳት የሚመለከቱ አራት ቀንዶች ከበታቹ ወጡ።

ከ20 ዓመታት ጦርነት በኋላ የአሊግዛንደር ዘግሬት መንግሥት ለአራት መንግሥታት ተከፋፈለ። እነዚህም ግሪክ (በአረንጓዴ የተቀለመው ግዛት)፣ እስያ (ቢጫ)፣ ግብጽ (ወይንጠጅ)፣ እና ሁለት ክፍል ያለው የትሬሰ መንግሥት (ቀይ)።

“አራቱ የሰማይ ነፋሳት” የሚለው አገላለጽ እነዚህ ጦርነቶች መንፈሳዊ ገጽታ እንዳላቸውና ፍጥረታዊ ውጊያዊች ብቻ እንዳልነበሩ ያመለክታል። መንፈሳዊ ገጽታው ፖንቲፉ ወይም የክፉው ሊቀ ካሕናት ነው፤ እርሱም ከባቢሎን ከተማ ተነስቶ ወደ ጴርጋሞስ ከተማ የተዛወረው ማራኪው የባቢሎናውያን ምሥጢር ነው። ጴርጋሞን ከተከፋፈለው የግሪክ መንግሥት አንድ አካል እንደመሆኗ የሰይጣን ዙፋን ሆነች።

ራዕይ 2፡12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
13 የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤

ዳንኤል 8፡9 ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።

ከጥፋት ውሃ በኋላ ለማያምኑ ሰዎች አባት ሆኖ የተነሳው ናምሩድ የሚባል ሰው ነው። እርሱም ባቢሎን ውስጥ የባቤልን ግምብ ሰራ። ስለዚህ ባቢሎን ከጥንት ጀምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ነበረች።

ዳንኤል የባቢሎናውያንን ሚስጥር አመጣጥ ከግሪክ ጴርጋሞን (ሆዱና ወገቡ ከናስ የተሰሩት ታላቅ ምስል) ጀምሮ ተከታትሎ እስከ ሮማ ግዛት (ከብረት የተሰሩት እግሮች) ድረስ ያሳያል። የብረት እግሮቹም ቅርጻቸውን ይለውጡና ይሰባበራሉ፤ ማለትም የሮማ ግዛት ይበታተናል፤ ፖፑም የባቢሎናውያን ምስጢር ራስ ወይም ፖንቲፍ የሚለውን ማዕረግ ለራሱ ይወስዳል።

በዚህ ትንቢት ውስጥ ትንሹ ቀንድ (የባቢሎናውያን ሚስጥራት) ከአራቱ የግሪክ መንግሥታት መካከል ከአንዱ ውስጥ ነው የሚወጣው። የአሊግዛንደር ዘግሬት ጀነራል የነበረው ሊሲማከስ (ካርታው ላይ በቀይ ቀለም የተመለከተውን) ትሬስ የሚባለውን ግዛት ያስተዳድር ነበር። ጴርጋሞን የዚህ ግዛት አካል ነበረች። የባቢሎናውያን ፖንቲፍ ደግሞ ይኖር የነበረው ጴርጋሞን ውስጥ ነው።

የሊሲማከስ መንግሥት ከጊዜ በኋላ ተንኮታኩቶ ሲወድቅ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ281 እስከ 133 ባሉት ዓመታት ውስጥ በጣም ሃብታም የሆነችዋ የጴርጋሞን መንግሥት ተመሰረተች፤ ዋና ከተማዋም ጴርጋሞስ (ወይም ጴርጋመም) ነበር።

የፋርስ ንጉስ ቂሮስ ባቢሎንን ባሸነፈ ጊዜ የባቢሎናውያን የሥላሴ ሚስጥር ፖንቲፍ ሸሽቶ የሄደበት ከተማ ጴርጋሞስ ነበር። ንጉሥ እና ካሕን የነበረው አታለስ 3ኛው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ133 ዓመተ ዓለም ሲሞት የጴርጋሞንን ግዛት ለሮም ሰጠ። በዚህም መንገድ የባቢሎናውያን ምስጢራት ወደ ሮም ተሻገሩ፤ ደግሞም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዩልየስ ቄሳር ጉቦ በመክፈል ታዋቂ የባቢሎናውያን ምስጢራት ፖንቲፍ ለመሆን በቃ። ከዚያ ወዲያ የሮማ ነገሥታት ሁሉ ፖንቲፍ የሚባለውን የማዕረግ መጠሪያ ተጠቀሙበት።

በ378 ዓ.ም. ቴዎዶሲየስ የሮማ ገዥ በሆነ ጊዜ ፖንቲፍ የሚባለውን የማዕረግ ስም አልቀበልም አለ። ከ400 ዓ.ም. ጀምሮ ፖፑ ራሱን ፖንቲፍ ብሎ ይጠራ ነበር። በዚህ መንገድ የባቢሎናውያን የሥላሴ ሚስጥር ወደ ሮም ቤተክርስቲያን በመግባቱ ቤተክርስቲያኒቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን ማንም ሊያብራራው የማይችለውን የሥላሴ አስተምሕሮ በመቀበል የባቢሎን ሚስጥር ሆነች።

ሥላሴን ለማብራራት የተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ቀርበዋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ቃላት እና ሐረጎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም፡-
• ሥላሴ
• አንድ አምላክ በሦስት አካላት - ይህ የግሪክ ፍልስፍና ነው
• የመለኮት የመጀመሪያው አካል
• የመለኮት ሁለተኛው አካል
• የመለኮት ሦስተኛው አካል
• አብ እና ወልድ አንድ ባሕሪ ናቸው
• እግዚአብሔር ወልድ
• እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

ነገር ግን “እግዚአብሔር አብ” የሚል አዲስ ኪዳን ውስጥ አለ። “እግዚአብሔር አብ” ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ አልተጠቀሰም። በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ይህ ለምን እንደሆነ ማብራራት አይችሉም።

በጣም የሚገርመው ደግሞ “እግዚአብሔር ወልድ” እና “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጊዜም እንኳ አልተጠቀሱም።

ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ስሙ ይጠፋል። ሶስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም።

አንድ ክርስቲይንን “የእግዚአብሔር ስም ማን ነው?” ብላችሁ ጠይቁ። ከዚያም እንዴት እንደሚያመነታ እና ጥያቄውን ለማምለጥ ምን ያህል የአእምሮ ትግል እንደሚያደርግ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ቤተክርስቲያኖች የሚያምኑበት የሥላሴ አምላክ አንድ ስም የለውም።

በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ደጋግመው “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ፤ ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም። ሦስት ማዕረጎች አንድ ስም መሆን አይችሉም።

የሥላሴ ትምሕርት በ325 በኒቂያ ጉባኤ አማካኝነት በግድ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገባ በተደረገ ጊዜ ለመረዳት አስቸጋሪ ሃሳብ ነበረ፤ ደግሞም በንጉሥ ኮንስታንቲን አስገዳጅነት ነው ቤተክርስቲያን እንድትቀበለው የተደረገችው። ማንም በደምብ ስለማይረዳው እስከዛሬ ድረስ የሥላሴ ትምሕርት ግራ አጋቢ ትምሕርት ነው።

ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ ወይም መልእክተኛ ሲመጣ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ሰባተኛው መልአክ እንደመሆኑ ኢየሱስ በውጭው ሰው ነገር ግን በውስጡ የእግዚአብሔር ሙላት እንደነበረ ገልጧል።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ስለዚህ ከአይሁድ ሕዝብ በላይ መንፈስ ሆኖ ይኖር የነበረው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመኖር ሲል ሰው ሆነ። ከዚያም ኢየሱስ ሞተና በእኛ ውስጥ ይኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ወደ ምድር ላከው። እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ነው። መንፈስ የእግዚአብሔር ማንነቱ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ራሱ ቅዱስ መንፈስ ወይም መንፈስ ቅዱስ ነው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

መንፈስ ቅዱስ የዘላለም ሕይወትን ዘር በማርያም ማሕጸን ውስጥ አስቀመጠ። በሴት ማሕጸን ውስጥ ዘር የሚያስቀምጥ ሁሉ ለሚወለደው ሕጻን አባቱ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።

እግዚአብሔር ሰው ሆነ፤ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚለው የሰው ስም ተጠራ።

ኢየሱስ ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑን በመካድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአሕዛብን ባቢሎናዊ ሚስጥር ሥላሴን ተቀበለች። ይህ የአሕዛብ ሥላሴ ግሪኮች ጴርጋሞን ውስጥ በቆዩበት ጊዜ በግሪክ ፍልስፍና አማካኝነት ውበት አገኘ። እነርሱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጭራሽ የማይገኘውን አንድነት በሦስትነት፣ ሦስትነት በአንድነት የሚባል ሃሳብ አመጡ። ይህ ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም ኋላ ግን ቤተክርስቲያንን በብዙ አስቷል። የግሪክ ፍልስፍና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኘውን አብ እና ወልድ አንድ ማንነት አላቸው የሚለውን ሃሳብ ይዞልን መጣ። የባቢሎናውያንን ሥላሴ የቤተክርስቲያን ሥላሴ አድርጎ መቀየር በኢክዩሜኒካል እንቅስቃሴ ውስጥ ቤተክርስቲያኖችን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዋነኛው አስተምሕሮ ነው። ስለዚህ በተጨማሪ ሥላሴ ካቶሊክን እና ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን አንድ የሚያደርግ አስተምሕሮ ነው። ልጆች የሆኑት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ትልቁን ስሕተታቸውን የተማሩት ከእናታቸው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነው።

ዳነኤል 8፡9 ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥ ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም ወደ መልካሚቱም ምድር እጅግ ከፍ አለ።
የቫቲካን ከተማ መንግሥት በስተመጨረሻ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁሉ ራስ ሆና ተገለጠች፤ የአጋንንታዊ አሰራር ሁሉ መፈልፈያ ወደ ሆነው ወደ ምሥራቅም እጅግ ከፍ አለች።

ዘፍጥረት 4፡16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፤ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ።

ቃየን ወደ ምሥራቅ ሄደ፤ ውሸታም እና ነፍሰ ገዳይ መናፍስትም አብረውት ሄዱ።

ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጋለሞቶች እናት እንደመሆንዋ ልጆችን ወልዳለች፤ እነርሱም በለውጡ ጊዜ ከእናታቸው ተገንጥለው የወጡት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ናቸው። በመጀመሪያ ጊዜ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ንጹሕ ነበሩ። ግን ልክ እንደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከጊዜ በኋላ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎችን መፍጠር ጀመሩ።

ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችን እና ወጎችን በመቀበል ፐሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ጋለሞታዎች ሆኑ - ልክ እንደ እናታቸው።

የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን
ሉተር ከካቶሊክ እምነት ሲወጣ ሕዝቡ ለጥቂት ጊዜ በነጻነት ኖሩ። እርሱ ሲሞት ግን ሕዝቡ እርሱ ያምናል ብለው ባሰቡዋቸው ሃሳቦች ዙርያ ተደራጁና የራሳቸውን የእምነት መግለጫ እና የራሳቸውን ሃሳብ አጸኑ፤ ደግሞም እነርሱ ካሉት ተቃራኒ ነገር የሚለውን ሰው ሁሉ አወገዙ። ትንሽ ቅርጹን ከመለወጣቸው በቀር ቀት ብለው ወደ ካቶሊክ ነው የተመለሱት። ዛሬ ደግሞ ብዙ ሉተራኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ካቶሊክ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው።

ፖፑ ቤተክርስቲያንን እንደ ፈላጭ ቆራጭ ይመራታል።

ፕሮቴስታንቶች የፖፑን አርአያነት በመከተል ፓሰተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ይሾማሉ። በሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን መጀመሪያ ላይ ተፈተው የተለቀቁት የፈላጭ ቆራጭነት መናፍስት ዛሬ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ቦታ አግኝተው ተሰግስገዋል።

ደቡብ የሚለው ቃል የቤተክርስቲያንን ዓለም ሊወክል ይችላል፤ ልክ የደቡብዋ ንግሥት፣ የሳባ ንግሥት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሰችው።

ማቴዎስ 12፡42 ንግሥተ ዓዜብ [በእንግሊዝኛ የደቡብ ንግሥት] በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

ሴት የምትወክለው ቤተክርስቲያንን ነው። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ተብላ ተጠርታለች።

የካቶሊክ ትምሕርቶች ለምሳሌ ሥላሴ፣ በኢየሱስ ስም በማጥመቅ ፈንታ በሦስት ማዕረጎች ማጥመቅ፣ የገና በዓልን ማክበር፣ እንዲሁም የፋሲካ ጥንቸሎች እና የጥንቸል እንቁላሎች፣ ሕጻናትን በውሃ መርጨትና ይህንንም እንደ ጥምቀት መቁጠር የመሳሰሉ ትምሕርቶች እና ልማዶች ካቶሊክ ወዳልሆኑ ቤተክርስቲያኖችም ውስጥ ተዛምተዋል። (በነገራችን ላይ ጥንቸሎች ለአይሁዳውያን የማይበሉ እርኩስ እንስሳት ናቸው።)

ዳንኤል 8፡9 ላይ መልካሚቱ ምድር የተባለችው እሥራኤል ናት። ቫቲካን ታላቅ የወርቅ እና የከበሩ ድንጋዮች ሃብት አላት፤ ስለዚህ ቫቲካን ከአይሁዶች ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ ትነሳለች ምክንያቱም በአሜሪካ እስቶክ ኤክስቼንጅ ውስጥ ያለው ሃብት በሙሉ የአይሁዶች ነው።

ስለ “ትንሹ ቀንድ” የሚናገሩት ጥቅሶች ስለ ፖፑ ወደ ሥልጣን መውጣትና የትንሽዋ የቫቲካን ከተማ መንግሥት እና በዓለም ትልቅ እና ሃብታም የሆነችዋ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ ወደ መሆን ስለመምጣቱ የሚያመለክቱ ናቸው። ከዚያ ከቫቲካን ተነስቶ ፖለቲካዊ ሥልጣኑ ወደ ብዙ ሃገሮች ይደርሳል፤ ምክንያቱም በምድር ላይ በየሃገሩ የተበታተኑ ብዙ ካቶሊኮች አሉ።

ቫቲካን ከሁሉ የምታንስ የከተማ መንግሥት ናት ግን ከዚያች ከተማ ሆኖ ፖፑ በፖለቲካ መሪዎች እና በቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያደርጋል። የፖፕ ጆን ፖውል ዳግማዊ ቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከዓለም ዙርያ ሁሉ የተሰበሰቡ የመሪዎች ብዛት በዚህ ዘመን ካየነው የሰዎች ስብስብ ሁሉ የሚበልጥ ነበር። የሮማ ቤተክርስቲያን አመጣጧን በዘመናት ወደ ኋላ ቆጥራ ቀጥታ ከመጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ጋር የምትገናኝ ብቸኛ ቤተክርስቲያን ናት። ስለዚህ የሮማ ቤተክርስቲያን በብዙ አስቸጋሪ ዘመኖች ውስጥ ሳትጠፋ የመቆየት ዝና አላት። የሮማ ግዛትን ያፈራረሱት ባርቤሪያውያን ነገዶች ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታላቅ አድናቆት ያላቸው ለዚህ ነው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራሷን እናት ቤተክርስቲያን አድርጋ በመቁጠሩዋ እና ዓለምን በሙሉ ልትመራ በመፈለጓ በእነዚህ ሰባት “መንግሥታት” ወይም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የእውነት ጠላት ሆና ቆይታለች።

በ1825 ፖፕ ሊዮ 12ኛው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ እንደ ባለ ሥልጣን ሴት መቀመጧን የሚያሳይ ምስል ያለበት መዳሊያ አስቀርጾ ነበር።

ልክ ራዕይ 17 እንደሚገልጸው በእጅዋ ለዓለም ሁሉ የሚሆን የአስተምሕሮ ጽዋ ይዛለች።

ራዕይ 17፡4 ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤

ፑርጋቶሪ፣ ለሰሩት ሐጥያት ራስን መቅጣት፣ ለሐጥያት ሥርየት ገንዘብ መክፈል፣ ሕጻናትን ማጥመቅ፣ ታኦታት፣ የመቁጠሪያ ጨሌ፣ በመስቀል ማማተብ፣ ካሕናት እናዳያገቡ መከልከል - - እነዚህ ሁሉ ልማዶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።

የሮማ ካቶሊክ እምነት ዳንኤል ባየው የአሕዛብ ምስል እግር ውስጥ ባሉት የብረት ስብርባሪዎች ነው የተወከለችው። ሸክላው ሙሽራይቱን ይወክላል። የምስሉ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ፤ እነዚህም የአሥሩን ጣቶች ታላቅ መከራ ወደ ፍጻሜ ያመጣሉ።

አሥሩ ጣቶች ሥልጣናቸውን እና ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ-አውሬ የሚያስረክቡ ሰባት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ናቸው።

ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

እንደ ነገሥታት ስልጣን ይቀበላሉ። ይህም ማለት ይመራሉ ያስተዳድራሉ፤ ነገር ግን ዘውድ አይጭኑም። ስለዚህ ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።

ሌኒን ለአብዮቱ ከነበረው ቅናት የተነሳ በጣም ትልቅ ዝና ከማትረፉ የተነሳ በኮምዩኒስቶቹ ዘንድ እንደ አምላክ እስኪቆጠር ደርሷል። እሱ እና እስታሊን በጀመሩት ከአውሬ ያልተለየ ጭካኔ በሃገሪቱ ላይ የግፈኝነት እና የፈላጭ ቆራጭነት መንፈስ ከለቀቁባት በኋላ ራሺያን በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ውስት ኃያል ሃገር አድርገው ገምብተዋታል። ስለዚህ አሁን ምዕራባውያን በሃገራቸው ተጀምሮ የነበረውን ጴንጤቆስጤያዊ መነቃቃት ወደ ሰው ሰራሽ ቤተክርስቲያኖች በመለወጣቸው እግዚአብሔር በድብ የተመሰለችውን ሃያል ሃገር ራሺያ ወይም የሰሜኑ ንጉሥ አንድ ቀን ለቅጣት በምዕራባውያን ላይ ይልክባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአሜሪካ ቤተክርስቲያኖች በዊልያም ብራንሐም የመጣላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መገለጥ አልቀበል ብለዋል።

እርሱ የመጨረሻው ዘመን ነብይ መሆኑን የተረዱ ሰዎች እርሱ የተናገራቸውን ቃሎች በመጥቀስ እና እርሱ ለተናገራቸው ቃላት ትርጓሜ በመስጠት በመጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ እንኪጠቀሙዋቸው ድርስ ተሞኝተዋል። የሰባተኛውን መልአክ ድምጽ ያለ ልክ ከፍ አድርገውት የአምላክነት ክብር ሰጥተውት “የእግዚአብሔር ድምጽ አድርገውታል”።

ይህ ትልቅ ስሕተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከማንም የሰው ንግግር ሁሉ በላይ ነው።

1965 የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን
እውነተኛ ነብይ ሁልጊዜ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ቃል ይመራቸዋል፤ ሰዎች ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዲጣበቁ ያደርጋል እንጂ እራሱን ወይም የራሱን ንግግር እንዲፈሩ አያደርግም፤ ከዚያ ይልቅ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን እንዲፈሩ ያስተምራል።

እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ ይሁዳ ገንዘብ ፍለጋ መሰማራታቸውን ልብ በሉ።

የሜሴጅ ፓስተሮች በጣም ሃብታም ሆነዋል። ሜሴጅ ትልቅ የንግድ ሥራ ነው።

ይህም በዓለም አንደኛ ሃብታም ድርጅት የሆነችዋን የእናት ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በመኮረጅ ነው። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መሪዎችም በዝርፊያ ከተገኘው ሃብት ላይ ድርሻ ይፈልጋሉ።

ፓስተሩ የበጎች እረኛ ነው የሚል አንድም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም ግን ፓስተሮች የበጎች እረኛ ነን ይላሉ፤ በጎቹም መንጋዎቻችን ናቸው ይላሉ።

ስለዚህ በጎቻችንን የመሸለት መብት አለን ብለው ያምናሉ። ቤቶቻቸውን፣ መኪናዎቻቸውን፣ እያ የባንክ ሒሳባቸውን ስታዩ በእውነትም የተዋጣላቸው ሸላቾች ናቸው።

የሮማ ካቶሊኮች በሰዎች እየተመረጡ የሚሾሙ ተተካኪ ፖፕ አሉዋቸው፤ ይህም በዘመናት ውስጥ መንፈሳዊ ግዛታቸውን ለመገንባት ነው።

ፕሮቴስታንት ፓሰተሮችም ወንጌሉን የራሳቸው መንግሥት መገንቢያ አድርገውታል፤ እነርሱ ደግሞ ፓስተሩ ሲሞት የፓስተሩን ልጅ ነው በቦታው ፓስተር አድርገው የሚሾሙት። በዚህም መንገድ የቤተሰብ ንግድ ስለሚያደርጉት ገንዘቡ ከቤተሰብ አይወጣም።

ስለዚህ ቤተክርስቲያንን ማን ነው የሚለው ውሳኔ ላይ እግዚአብሔር ድርሻ እንዳይኖረው አድርገዋል።

ይህም አስደናቂ አይደለም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ መቆሙን አይተናል። ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚደረገው ነገር ድርሻ የለውም።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

ከዊልያም ብራንሐም በተወሰዱ የተለያዩ ጥቅሶች ላይ ትኩረት በማድረግ የዊልያም ብራንሐም ተከታዮች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ብዙ ልዩ ልዩ ትምሕርቶችን አዘጋጅተዋል። እነዚህ ልዩ ልዩ ትምሕርቶችም እንቅስቃሴውን እርስ በርሳቸው ለሚፎካከሩ ብዙ ቡድኖች ሰነጣጥቀዋቸዋል። ይህንም ስናስብ ዳንኤል ያየው የአሕዛብ ምስል እግሮቹ እንዴት አሥር ጣቶች ሆነው እንደተከፋፈሉ እናስታውሳለን።

በዚህ መንገድ የሜሴጅ አማኞች ልክ እንደ ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀው ሄደዋል። ትምሕርታቸው ትክክል ስለመሆኑ ሲጠየቁ የተወሰኑ የብራንሐም ጥቅሶችን ይጠቅሳሉ ግን ሃሳባቸውን የሚያፈርሱባቸውን ሌሎች ጥቅሶች ደግሞ እንዳላዩ ያልፉዋቸዋል። ትልቁ ስሕተታቸው እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አለመመርመራቸው ነው።

ወንድም ብራንሐም ግን የመጣው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ሊመልሰን ነበር።

65-0725M በመጨረሻ ው ጊዜ የተቀቡት
ስለዚህ ይህንን መላልሰን በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመዝነው ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን፤ እንጂ የሆነ ሰው በተናገረው ሃሳብ አማካኝነት አይደለም። ማንም ይሁን ማን እኔም ራሴ ወይም ሌላ ሰውም ቢሆን ግድ የለኝም “እንደ ቃሉ ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም”። አያችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ነው ያለው። “ሰው ሁሉ ውሸተኛ እግዚአብሔር ብቻ እውነተኛ ይሁን”። ማንም ይሁን ማን የእግዚአብሔርን ቃል ሊተካ አይችልም።

ኮምዩኒስቶች ተመሳሳይ ነገር ነው ያደረጉት። ሌኒንን የኮምዩኒስት አብዮት “ነብይ” አድርገው ተመለከቱት። ሌኒን ሲሞት ከተከታዮቹ ዋነኛው እስታሊን ነበር። በእስታሊን አመራር ውስጥ ግን ኮምዩኒስቶቹ ከሌኒን ትምሕርቶች እየራቁ ሄዱ። ከእስታሊን ጋር ብትከራከሩ በትይት ትገደላላችሁ ወይም ከሞት ለማምለት ወደ ሌላ ሃገር ትሰደዳላችሁ። ለእታሊን የታዘዙ ጨካኝ እና ለእርሱ አዎ አዎ የሚሉለት ሰዎች ብቻ ነበሩ በሕይወት መኖር የሚፈቀድላቸው። ነገር ግን ሌኒን ካስተማረው ትምሕርት እየራቁ በሄዱ ቁጥር ለማካካሻ እንዲሆን ሌኒንን ይበልጥ እያከበሩ፣ እንደ ጣኦት ለስሙ እየዘመሩ እና እርሱን እንደ አምላክ እየቆጠሩ መኖራቸውን ቀጠሉ። ብዙ የሜሴጅ ቡድኖች ይህ አይነቱ መንፈስ ተጋብቶባቸዋል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ርቀው ከሄዱ በኋላ ለሰዎች ንግግር ጥቅስ በሰጡት ትርጉም እየተመሩ ይኖራሉ፤ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ማለታቸውን ለማካካስ ወንድም ብራንሐምን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።

ሴቶችን የሚያማግተው ሙሶሊኒ የሮማን ካቶሊክ ቫቲካን ቤተክርስቲያንን ራሷን የቻለች የከተማ መንግሥት እንድትሆን ፈቃድ በመስጠት ለጋለሞቶች እናት ተደላድላ እንድትመሰረት እድል ሰጣት። ደግሞም ለቫቲካን ብዙ ገንዘብ ሰጠ። ሙሶሊኒ ድሮም ከጋለሞታዎች ጋር መተኛትና ለጋለሞታዎች መክፈል ልማዱ ነበር።

ይህም ቫቲካን በዓለም ላይ ታላቅ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በገንዘብ ኃይልም ታላቅ እንድትሆን አስቻላት። ከዚህ የተነሳ ቫቲካን በዓለም ፖለቲካ ውስጥም በጥልቀት ገብታ ተተበተበች። በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ሰይጣን የሚያስነሳው የክርስቶስ ተቃዋሚ የመጨረሻው ፖፕ ሆኖ የሚነሳው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነው። ስለዚህ ለክርስቶስ ተቃዋሚ መምጫው እየተዘጋጀለት ነው።

ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።

የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሆኖ የሚነሳው ፖፕ እንደተለመደው በካርዲናሎች ምክር ቤት ጉባኤ አማካኝነት ተመርጦ አይደለም ወደ ሥልጣን የሚወጣው። በዚያ ፈንታ የአሥር ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጮችን ድጋፍ ያገኛል። በሆነ መንገድ በንግግር አሳምኖም ሆነ አታልሎ ወደ ቤተክርስቲያን ዓለም ይገባና ሥልጣንን ነጥቆ ይወስዳል።

ከዚያም ደግሞ የአይሁዶች ጉዳይ አለ።

አይሁዶች በዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ብዙ ተሳክቶላቸዋል።

ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ተበታትነው ነበር። ነገር ግን ወደ እሥራኤልና ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱም በትንቢት ተነግሮላቸው ነበር። የዓለም እስቶክ ኤክስቼንጅ ገበያ በዋነኛነት የተቆጣጠሩት አይሁዶች ናቸው። ደግሞም በከባድ ጥላቻ የተጠሉ ሕዝቦች ናቸው፤ በተለይም ሙስሊሞች በጣም ይጠሉዋቸዋል።

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ነው ወደ እሥራኤል መልሶ ያስገባቸው? እግዚአብሔር የታላቁን መከራ አሰቃቂ ገጽታ በትንሹ ለማሳያ እንዲሆን ሒትለርን ተጠቅሟል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በናዚ ጀርመኒ አማካኝነት ሒትለር ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን በመጨፍጨፍ ያስነሳው መከራ የለማጅ አይነት መከራ ነው። ይህንን አሰቃቂ ጊዜ በመጠቀም እግዚአብሔር ሃገሮች ሁሉ ለእሥራኤል እንዲያዝኑላት አደረገ። ሃገሮች ሁሉ ሕሊናቸው ተወቀሰባቸውና ከፓለስታይን ምድር 15 በመቶ ያህሉን ለአይሁዶች ለመስጠት ተስማሙ። የቀረው ለፍልስጤማውያን አረቦች ተሰጠ። በ1967ቱ ጦርነት መጨረሻ አካባቢ የአይሁዶች ድርሻ ወደ 28 በመቶ አደገ።

የ1929 ዓመተ ምሕረቱ የዓለም ኢኮኖሚ ውድቀት ያመጣው የገንዘብ ኪሳራ ገንዘብ ቁልፍ ጉዳይ እንዲሆን አድርጓል። ኪሳራ በገባችዋ ጀርመኒ ውስጥ ሒትለር ተነሳ። ጀርመኒ በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ለመሸነፏ የምታመካኝበትን ስትፈልግ ነበር። ሒትለርም የጀርመንን ሕዝብ ቁጣ የሚያስተነፍስበት ምቹ ወገን አገኘ፤ ይህም የአይሁድ ሕዝብ ነበር። እንደ ትሮትስኪ የመሳሰሉ አንዳንድ አይሁዶች የብዙ ሰው ደም የፈሰሰበት የራሺያ ኮምዩኒስት አብዮት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ጀርመኖቹ ኮምዩኒዝም እንዳይመጣባቸው የነበራቸው ፍርሃት ጀርመኒ ውስጥ ለአይሁዶች የነበራቸውን ጥላቻ አባባሰባቸው። የእስቶክ ገበያ በአይሁዶች ቁጥጥር መሆኑ ተጨማሪ ጸረ አይሁድ ስሜቶችን አቀጣጠለ።

በ1939 የጀመረው የኢኮኖሚ ድቀት ዴሞክራሲያዊ መንግሥታትን አዳከመ ፤ ከዚህም የተነሳ የፈላጭ ቆራጭ መሪዎችን ጦርነት ናፋቂነት አደብ ማስገዛት አልቻሉም። እነዚህም መሪዎች በሕገወጥ መንገድና ኃይልን በመጠቀም ወደ ሥልጣን ወጡ።

በጨለማው ዘመን እና በመንፈሳዊ ተሃድሶ ላይ ተነስቶ የነበረው ተቃውሞ በ1648 እስኪያበቃ ድረስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በአጋንንታዊ ተጽእኖ እየተነዳች ከአሥር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተቃዋሚዎችዋን ገድላለች። ከዚያም ሰዎች ክርስቲያኖች እርስ በራሳቸው መገዳደል እንደሌለባቸው እየገባቸው ሲመጣ ግድያዎቹ ተቋረጠ። እነዚህ ሁሉ ክፉ የጥፋት አጋንንት ጆን ዌስሊ እና ሚሽነሪዎች ሰዎችን ንሰሃ መግባት እና በቅድስና መኖር እንዳለባቸው ሲያስተምሩ በሁኔታዎች አማካኝነት ተሰብስበው በሰይጣናዊ ጉድጓድ ውስጥ ታስረው ነበር። እንደ ፈላጭ ቆራጭ መሪ የሒትለር ሥራ እነዚህን አጋንንት በጽድቅ መኖርን ሲሰብኩ በነበሩ ቤተክርስቲያኖች አማካኝነት ታስረው ከቆዩበት ሲኦል ፈትቶ መልቀቅ ነበር። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረው ሰቆቃ እነዚህ አጋንንታዊ ኃይላት አምልጠው በነጻነት እንዲፈነጩ ነጻነትን ሰጣቸው። በሰላማዊ ጊዜ ቢሆን ክፋታቸውን መግለጥ ባልተመቻቸው ነበር። እነዚህ አጋንንቶች በፍጥረታዊ እሥራኤል አይሁዶች ላይ ተለቅቀው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ ብዙ ጥፋትን መፈጸም እንዲችሉ ፈትቶ የሚለቅቃቸው ፍጥረታዊ ፈላጭ ቆራጭ አስፈልጓቸዋል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሒትለር ከመላው አውሮፓ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን ሰብስቦ ገደለ። ከዚያም በ1945 እነ አሜሪካ እና ከአሜሪካ ጋር የተባበሩት ኃይላት ሒትለር ባደረገው የአይሁድ ጭፍጨፋ ሲደናገጡ ግድያው አቆመ።

እነዚህ ክፉ መናፍስት አሁን ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ወደ አንድነት ለማምጣት ሙከራ የሚያደርገው የኢክዩሜኒካል እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተው መሽገዋል። ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው ጀርመኒ ውስጥ የጦር ምርኮኞች ካምፕ ውስጥ የተለያዩ ቤተክርስቲያን አባላት በአንድ ላይ ታስረው በነበረበት ጊዜ ነው። በ1948 ይፋዊ እንቅስቃሴ ሆኖ ተጀመረ። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን በሰው ትመራለት ትተዳደራለች፤ ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን በፈላጭ ቆራጭነት ከሚመራው ከፖፑ የተቀዳ ሥርዓት ነው።

በ1933 እግዚአብሔር እና ሰይጣን ለፍጥጫ ሲዘጋጁ ነበር።

በ1933 ሒትለር የጀርመኒ ቻንስለር ወይም መሪ ሆነ።

በ1933 ሩዚቬልት የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆኖ ተመረጠ። እርሱም ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎችን እንደ መሸፋፈኛ ተጠቅሞ ለአራት ዙር በፕሬዚደንትነት ቆየ።

1920ዎቹ እና 1930ዎቹ አዲስ ለሚነሱ ፈላጭ ቆራጮች ጊዜያቸው ነበሩ። ሩዚቬልት በጃፓን ላይ የነዳጅ ዘይት ማእቀብ ጣለ፤ ይህም ጃፓኖቹ ወደ ፐርል ሃርበር ሄደው አሜሪካ ላይ ጥቃት እንዲሰነዝሩ አደረጋቸው። በዚህ ምክንያት አሜሪካ ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ገባች። ከዚያም ሩዚቬልት አቶሚክ ቦምብ እንዲዘጋጅ አዘዘ። በጦርነቱ ወቅት የአቶሚክ ቦምብ ሚስጥር ባልተፈተሹ ዲፕሎማሲያዊ ፖስታዎች ውስጥ ታሽጎ ከአሜሪካ ወደ ራሺያ ተላከ። ከዚህም የተነሳ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ አሜሪካም ራሺያም እርስ በራሳቸው ላይ የኑክሊያር ጦርነት ጥፋት ዛቻ መዛት ቻሉ። በአሁኑ ሰዓት የኑክሊየር አርማጌዶን ጦርነት ስጋት በዓለም ላይ እያንዣበበባት ነው።

54-0509 የአሜሪካ መወረር
ልንገራችሁ፤ ሚስተር ሩዚቬልት (ሰውየው ሞቷል፤ እረፍት እመኝለታለው፤ እንደሚያርፍ አምናለው) ሦስት ጊዜ ወይም አራቴ በፕሬዚደንትነት ሲቆይ ይህ የፈላጭ ቆራጭነት መጀመሪያ ነው።

60-12044M የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ
“ፕሬዚደንት ሩዚቬልት ከሁላቸውም የባሰ ወንበዴ ነው የሚሆነው።” አዎ እውነት ነው። ደግሞም ነበር።

60-1208 የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን
የሰንበት ትምሕርት ስጀምር ተመስጦ ውስጥ ገባሁ። የሰንበት ትምሕርታችንን እዚህ የድሮው ሜሰኒክ ሆም በቻርሊ ከርን ቤት ውስጥ ነበር የምንማረው፤ ጥቂት ነበርን። ከዚያም ይህ ፕሬዚደንት ሩዚቬልት ዓለምን ሁሉ ይዞ ወደ ዓለም ጦርነት ሲገባ አየሁ።

ሩዚቬልት ጦርነቱ ውስጥ አልገባም ብሎ በ1940 ምርጫ አሸነፈ ግን ወዲያው በ1941 አሜሪካን ወደጦርነቱ ውስጥ የሚያስገባበት ዘዴ ቀየሰ። ይህም እርምጃ አሜሪካ ውስጥ ያለው ትልቅ የጦር መሳሪያዎች አምራች ኢንዱስትሪ ለምዕራባዊ አንድነት ሃገራትና ለራሺያ ጦርነት እንዲያመርት አስቻለ። በጦርነቱ ወቅት እና ከጦርነቱ በኋላ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ትልቅ ንግድ ሆነ። ወታደራዊ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች የኮርያ እና የቬትናም ጦርነቶች እንዲደረጉ ገፋፉ ምክንያቱም የመሳሪያ ሽያጫቸውን ከፍ ያደርግላቸዋል። ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የጦር መሳሪያ ንግዶች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ 13 ጊዜ በአረብ እና በእሥራኤል መካከል ግጭቶች እና ጦርነቶች እንዲቀሰቀሱ ከማድረጋቸው አልፎ በሙስሊሞች እና በሙስሊሞች መካከልም ብዙ ጦርነቶች እንዲፈጠሩ አድርገዋል። ከ1945 እስከ 2001 ድረስ በዓለም ላይ 194 ታላላቅ ጦርነቶች ተካሂደዋል። በ1991 ምሥራቅ አውሮፓ ውስጥ ኮምዩኒዝም ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ግጭቶች አማካኝነት ሞተዋል። አሁንም በጎሳዎች እንዲሁም በብሔሮች መካከል ያሉ ጥላቻዎችን ለመቀስቀስ የሚበቃ የጦር መሳሪያ ሞልቷል።

በ1939 ሒትለር የጀርመኒ ቻንስለር ወይም መሪ ከሆነ በኋላ 60 ሚሊዮን ሰዎች ያለቁበትን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መቀስቀስ ይችል ዘንድ ኢጣሊያ ውስጥ ካለው ሙሶሊኒ ጋር ገጠመ። ከእነዚህ ውስጥ ስድስት ሚሊዮኖቹ ሰዎች የአይሁድን ዘር ለማጥፋት ባደረገው ሙከራ ነው የሞቱት። ረሃብ፣ ቸነፈር፣ እና የበሽታዎች ወረርሽኝም የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርገዋል።

ሩዚቬልት፣ ሒትለር፣ እና ሙሶሊኒ ሦስቱም ሚያዚያ 1945 ውስጥ ሞቱ።

ዘካርያስ 11፡7 እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፤ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ መንጋውንም ጠበቅሁ።

8 በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፤ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።

ለእርድ የሚሆኑት በጎች በሆሎኮውስት ጭፍጨፋ ያለቁት አይሁዳውያን ናቸው። የእነርሱም እልቂት ያበቃው ሒትለር ሲሞት ብቻ ነበር።

ነገር ግን እግዚአብሔርም እየሰራ ነበር።

በ1933 ወንድም ብራንሐም በኦሃዮ ወንዝ ውስት በኢየሱስ ስም እያጠመቀ ሳላ በላዩ ላይ ብርሃን በራ።

64-0427 ፈተና
ያም ደምጽ ወረደና እንዲህ አለ፡- “ለኢየሱስ የመጀመሪያ ምጽአት መንገድ እንዲተርግ መጥምቁ ዮሐንስ እንደተላከ ሁሉ ያንተም መልእክት ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።”

ይህ በጣም ትልቅ ተልእኮ ነበር።

ተልእኮው የወንድም ብራንሐምን ታላቅነት እንደ ሰውም ሆነ እንደ ነብይ የሚያጎላ አልነበረም። በጥንቃቄ ብታነቡት ትኩረቱ እርሱ በሰበከው መልእክት ላይ ነው። የብራንሐም መልእክት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉት ምሳሌያዊ አገላለጾች አማካኝነት ተሰውረው የነበሩትን ሚስጥሮች መግለጥ ነበር። እነዚህም መገለጦች ዓላማቸው ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ ለማድረግ ነበር።

የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ዋነኛ ዓላማው የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮችን መግለት ነበር።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ማሕተሞቹን ይወስድና ይፈታቸዋል ከዚያም ለሰባተኛው መልአክ ያሳያቸዋል፤ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች የሰባተኛው መልአክ ሚስጥሮች ናቸው።

እርሱ ታላቅ ነብይ ነበር ግን እግዚአብሔር ትኩረቱ ነብዩ ላይ አልነበረም -- እግዚአብሔር ትኩረት የሰተው ነብዩ ለሰበከው እውነት ነበር።

አንድ መሰረታዊ መርህ አለ፤ እርሱም መጨረሻ ላይ በመከር የሚታጨደው አዝመራ በመጀሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ መሆኑ ነው።

ይህ ከእግዚአብሔር ታላላቅ ምስጢራት አንዱ ነው፤ ምክንያቱም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እያደገች የመጣችው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር አካሉ ናት።

ዋናው መረሳት የሌለበት ቁም ነገር - ይህ ተልእኮ በምንም አይነት መንገድ ወንድም ብራንሐምን ከፍ ከፍ አላደረገውም። እንደ ሰው እንኳ የትልቅነት ክብር አልተሰጠውም። ቁም ነገር የነበረው እና ትልቅ ቦታ የተሰጠው እርሱ ሲያስተምር ለገለጣቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

አሁንም በደምብ አስተውሉ፤ ትኩረቱ ሰባተኛው መልአክ ላይ አይደለም፤ ማለትም ወንድም ብራንሐም ላይ አይደለም። ትኩረት የተደረገው ድምጹ ላይ ነው።

ወንድም ብራንሐም ከ1947 እስከ 1965 ባሉት ዓመታት ውስጥ መልእክቶቹን በድምጽ እየቀረጸ ያስቀምጥ ነበር። ከዚያም በኋላ አገልግሎቱ ተጠናቀቀ። እነዚህ ዓመታት ሰባተኛው መልአክ በታላቅ አገልግሎት በሥራ የሚገለጥበትን እና “ደምጹ የሚሰማበትን ዘመን” ይወክላሉ።

ከ1966 ጀምሮ እና ቀጣዮቹ ዓመታት “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ የሚሰማበት ዘመን” ናቸው፤ ስለዚህ በድምጽ ተቀድቶ ከተቀመጡትና በጽሑፍ ከታተሙት ስብከቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መማር አለብን።

አሁንም ትኩረት ለሰውየው አይደለም፤ በድምጽ ቀድቶ ላስቀመጣቸው መልእክቶች እንጂ።

ከ1947 እስከ 1965 “በሰባተኛው መልአክ ዘመን” ውስጥ እየሰበከ ሳለ ብዙዎቹ ተከታዮቹ ምን እያደረገ እንዳለ አያስተውሉም ነበር። ዛሬ በሕይወት ያሉት አብዛኛዎቹ የሙሽራይቱ አካላት በ1965 ገና አልዳኑም ነበር፤ በተጨማሪ ደግሞ ብዙዎቹም በዚያ ዓመት ገና አልተወለዱም ነበር።

ስለዚህ “በሰባተኛው መልአክ ቀን” ተማምነን ከቆምን የሚጠበቅብንን ሁሉ ከ1965 በፊት አጠናቅቀን መቀመጥ አለብን። ማናችንም ይህንን ፈተና አናልፍም።

ከ1965 ወዲህ ከ50 ዓመታት በላይ አልፈዋል፤ በእነዚህም ዓመታት ሰዎች ካሴቶቹን አዳምጠዋል፤ መጽሐፎቹንም አንብበዋል። ቀስ በቀስ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት ችለናል። ቀስ በቀስ ወደ በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩት ሐዋርያት ወደሚያምኑት እመነት በመመለስ ላይ እንገኛለን።

ያለፉት 50 እና ከዚያ በላይ ዓመታት “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ የሚሰማበት ዘመን” ነበሩ። እርሱ አሁን በምድር ላይ የለም ድምጹ ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ያስተምረን ዘንድ በምድር ላይ ቀርቷል።

“ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።”

ከቃሉ ውስጥ ይህኛው ክፍል ስለ ወንድም ብራንሐም የሚናገር አይደለም። ስለ እርሱ የሚናገር ከሆነ እርሱ ሚስጥራቱን ሙሉ በሙሉ እንዳልገለጠ የሚያመለክት ይሆናል። እርሱ ግን ምን እየተናገረ እንደነበር ጠንቅቆ ከማወቁም በላይ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር ከአስደናቂ የመለኮታዊ ኃይል ጋር ይገልጥ ነበር።

ስለዚህ “ይፈጸማል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሙሽራይቱ አካል ስለሆኑት ሰዎች ነው። እኛ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የእግዚአብሔርን ሚስጥር እርሱን መረዳት አለብን። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን ማወቅ አለብን። ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑን ማወቅ አለብን፤ እንጂ የሆነ ሰዎች የሾሙት አንድ ሰውዬ አይደለም የቤተክርስቲያን ራስ። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር አካል መሆኗን ማወቅ አለብን፤ ደግሞም ቤተክርስቲያን በመጨረሻዋ ልክ በጅማሬዋ እንደነበረችው መሆን እንዳለባትም ማወቅ አለብን።

የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤

11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ጳውሎስ የሚሰብከው መልእክት የእውነት ቃሉ ውስጥ ከተጻፈው ጋር ይስማማ እንደሆን እየመረመረች ነበር የምትቀበለው። ጳውሎስ ስለ ምን ይናገር እንደነበር ጠንቅቆ ያውቃል፤ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ ሳይቆይ ከምድር እንደሚሰናበትም ያውቃል።

ትልቁ አስፈላጊ ነገር የቤርያ ሰዎች ጳውሎስ እያስተማረ የበነረውን ትምሕርት ከመጽሐፍ ቅዱስ አመሳክረው ለራሳቸው መረዳት መቻላቸው ነው።

ልብ በሉ፤ ጳውሎስ ታላቅ ሐዋርያ ነው፤ ግን እርሱ እንኳ የተናገረውን ከመቀበላቸው በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረውታል።

ራእይ 2፡2 ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤

የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን
ሐሰተኞች ሆነው አገኛቸው። እንዴት አድርገው አወቁ? ምክንያቱም ከቃሉ እየተጠቀሱ አልነበሩም።

ዛሬ ማንኛውም ሐዋርያ ቢነሳ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ከተናገሩት የተለየ ነገር መናገር አይችልም። እያንዳንዱ ቃል በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ መመርመር አለበት።

ስለዚህ የዊልያም ብራንሐም መልእክት ትኩረቱ የመልእክተኛውን ታላቅነት ለማጉላት አይደለም። ይልቁንም ትኩረቱ እያንዳንዱ ሰው ወንድም ብራንሐም የሚናገረው እውነት መሆኑን ለራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምሮ ማረጋገጥ መቻሉ ነበር።

63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው
መልእክቱን በሙሉ እመኑ። እመኑ።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስት ካልተጻፈ ግን በፍጹም እንዳታምኑት።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ከሆነ በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ቃሉን ሊፈጽመው ቃል ገብቷል። ይህ እውነት አይደል? ከባድ እንደሆነ አውቃለው። አያችሁ ምንም ቀላል ነገር የለም።

እምነታችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፋችሁ መግለጥ ስትችሉ እና የመጽሐፍ ቅዱስን ቃሎች እርስ በርሳቸው ማያያዝ ስትችሉ የዛኔ መልእክቱን ተረድታችኋል ማለት ነው።

ሁለት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ዮሐንስ ሲናገር ሰምተው ምን እንዳደረጉ እንይ።

ዮሐንስ 1፡35 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥

36 ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።

የዮሐንስን ድምጽ የሰሙት ደቀመዛሙርት ዮሐንስ ወደ ራሱ እያመለከተ አለመሆኑን ተረድተዋል - እርሱ ያመለከታቸው ወደ ኢየሱስ ነው። የዮሐንስ ቃል ያመለከተው ወደ ኢየሱስ ነው። ደቀመዛሙርቱም ከዚያ ወዲያ የዮሐንስን ቃል ሲጠቅሱ መኖር አላስፈለጋቸውም፤ ምክንያቱም በራሳቸው ቃሉን መከተል ችለዋል።

ወንድም ብራንሐም ከተናገረው ቃል የተነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ምስጢራዊ ምልክቶችን እንዴት እንደምንተረጉም እንማራለን። ከዚያ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በራሳችን አንብበን ያለንበትን ዘመን መረዳት እንችላለን።

ትምሕርት ቤት ስትገቡ መጀመሪያ እንዴት እንደምታነቡ ትማራለችሁ፤ ከዚያ በኋላ በራሳችሁ ለመማር ታነባላችሁ።

ራዕይ ምዕራፍ 4 ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ የሰማይን ራዕይ ይገልጥልናል። በዚህ ራዕይ ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ክቡር ዘበኛ ቤተክርስቲያንን ማለትም አካሉን ሊጠብቁ በዙርያው በቆሙ አራት እንስሳት መካከል በዙፋኑ ተቀምጧል።

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

አንበሳው የሚወክለው አዲስ ኪዳንን የጻፉት የጥንት ሐዋርያት ያስተማሩትን እውነት ነው።

ጥጃው ደግሞ በጨለማው ዘመን በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት የተገደሉትን ስለ እውነት ብዙ የለፉትን ክርስቲያኖች ይወክላል።

ሰውየው ደግሞ እንደ ማርቲን ሉተር አይነት ተሃድሶ ያመጡትን ሰዎች ጥበብ ይወክላል፤ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት መሆኑን ገልጦ አስተምሯል፤ ጆን ዌስሊ ደግሞ ስለ ቅድስና ሰብኳል።

ጴንጤ ቆስጤ የመንፈስ ቅዱስን ልዕለ ተፈጥሮ ኃይል አሰራጭቷል፤ እርሱም በሚበርረው የንሥር ክንፎች ተወክሏል።

ወንድም ብራንሐም የተሰወሩትን ምስጢሮች ከነትርጉማቸው እንዲገልጥና በተጻፈው ቃል ውስጥ ጠለቅ ያለ እይታ እንድናገኝ ሊረዳን ተልኳል። ይህንንም የሚወክለው የንሥሩ አስደናቂ የማየት ችሎታ ነው።

ስለዚህ የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ከ1947 ጀምሮ በቴፕ በተቀረጹ መልእክቶቹ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች እንድናስተውል የሚረዳ የእውቀት አብዮት አስነስቷል።

ከሐዋርያት ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያንን ታሪክ እና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች ማስተዋል ቻሉ።
በፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ ሦስት ሳይንቲስቶች በ1947 የመጀመሪያውን የሬድዮ ማስተላለፊያ ፈለሰፉ።

ይህም ፈጠራ በኤልክትሮንክስ ላይ ታላቅ ለውት አመጣ። ኤልክትሮኒክስ ኢንተርኔትን በመጠቀም መረጃዎችን በፍጥነት በማሰራጨት የመረጃ አብዮትን አስከተለ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መረዳታችንን ለሰዎች ሁሉ ለማካፈል ኢንተርኔት ያስፈልገናል።

በ1947 በሰማይ ላይ ገዥነቷን ለማስመስከር በፈጠረችው አዲስ ፈጣን አውሮፕላን የድምጽ ወሰንን ሰብራ አለፈች። ይህንን የሚያመላክት ምልክታቸው ብሔራዊ አርማ አድርገው የሚጠቀሙት መላጣው ንሥር ነው። አሜሪካ የሰማይ ገዥ ሆነች። ወንድም ብራንሐም ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች መግለጥ ጀመረ።

በ1958 ወንድም ብራንሐም የእባቡ ዘር በሚል ርዕስ ባቀረበው ስብከት በኤደን ገነት የተሰራው የመጀመሪያው ሐጠያት ሚስጥር ምን እንደሆነ ገለጠ። ከዚያ ወዲህ የዘፍጥረት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕራፎች ጥንታዊ አፈታሪክ መምሰላቸው ቀርቶ ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁሉ ጋር በአንድነት ሆነው ልዩ ትርጉም እና መረዳትን ይሰጡናል።

በ1958 አንድ ሳይንቲስት በአንድ ሲልከን ቺፕ ላይ ትራንዚስተሮችን ወይም አስተላላፊዎችን አገናኘ። ይህም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ኢንተግሬትድ ሰርኪዩት በሚባለው ማስተላለፊያ አማካኝነት በጣም ትንሽ እና በጣም ኃይለኛ እንዲሆኑ አደረገ።

የወንድም ብራንሐምን ንግግር ተጠቅመው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር የሚገልጡ ክርስቲያኖች በቁጥር በጣም አናሳ ይሆናሉ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር ለማስተዋል በጣም በጥልቀት የማየት ብቃት ይኖራቸዋል።

የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደሆነ ከማስተዋል ጋር የመጣው የመገለጥ ብርሃን ድምቀቱ ለጨለማ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ፖፕ ፓየስ 12ኛው በ1958 ሞተ።

በ1960 የራሺያው መሪ ክሩሼቭ በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ጫማውን አውልቆ መድረኩን በጫማው ደለቀው። ይህም ከአንድ ሃገር መሪ የማይጠበቅ እንግዳ ድርጊት ነበረ። ነገር ግን የዓለምን ሁሉ ትኩረት ወደ ጫማውና ወደ እግሩ ስቧል። መድረክን በጫማ መምታት ደም ጭካኔን ያሳያል። ይህ ትልቅ መልእክት አለው ምክንያቱም በአሜሪካ ላይ የሚመጣውን የመጨረሻ ፍርድ ታስፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ራሺያን ልኳታል።

ጫማን ማውለቅ እና እግር በመንፈሳዊው ዓለም ምን ይወክላሉ?

ዳንኤል ያየው ምስል ውስጥ የሸክላ እና የብረት ድብልቅ የሆኑት እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ። ጫማ ሲወልቅ እግር ይገለጣል። ይህም የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መገለጥ ነው።

ደግሞም በ1960 ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ተከታታይ ስብከቶችን ሰበከ፤ በስብከቱም ባለፉት የ2000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ምን እንደተከሰተ አብራራ።

ከዚያም በ1963 ወንድም ብራንሐም በራዕይ ምእራፍ 6 ውስጥ ያሉትን ሰባት ማሕተሞች ሚስጥር ገልጦ አስተማረ።

ማሕተሞቹ እንደ ጫማ ማሰሪያ ነበሩ። ማሰሪያዎቹ ሲፈቱ ጫማው እንዲወልቅ እና እግር እንዲገለጥ አደረጉ። ስለዚህ የማሕተሞቹ መፈታት በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት መናፍስት እንዲገለጡ አደረገ። ማሕተሞቹ ሲፈቱ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንዴት በሰባቱ የቤተክርቲያን ዘመናት ውስት ይንቀሳቀስ እንደነበረና እንዴት አይሁዳውያንን ከምድር ገጽ ለማጥፋት ሙከራ እንዳደረገ ተጋለጠ።

ይህ የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሸፍኖ የነበረውን የምስጢራት መጋረጃ ከፈተው፤ ስለዚህ ተሰውረው የበነሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት አሁን መረዳት እንችላለን።

ማሰሪያዎች ተቋጥረው በነበረ ጊዜ የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት የታሰረውን ጫማ ብቻ ነበር ማየት የቻለው፤ ስለዚህም መፍታት ያልቻሉት ማሰሪያ ውስጥ ከስር የነበረውን የጫማውን ምላስ ብቻ ማየት ችለዋል። ስለዚህ የጴንጤቆስጤ መነቃቃት ልሳን (ምላስ) ላይ ብቻ ነበረ ትኩረቱ፤ ከዚህም የተነሳ የቤተክርስቲያንን ታሪክ ማየት አልቻሉም ነበር። ከዚህም የተነሳ የሮማ ካቶሊክን ሥላሴ፣ ሔዋን የዛፍ ፍሬ መብላቷን፣ ክሪስማስ፣ እና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያሉ በሦስት የማዕረግ መጠሪያዎች ማጥመቅን ይዘው ቀሩ። ነገር ግን ስሙ ማን እንደሆነ አላወቁም።

መጥምቁ ዮሐንስ የኢሱስን የመጀመሪያ መምጣት ለማስተዋወቅ የታላከ መልእክተኛ መሆኑን ስለ ራሱ አውቋል። ኢየሱስንም እንደ አንድ ሰው ከብዙ ሰዎች መካከል ለይቶ ማሳየት ችሏል።

ማርቆስ 1፡7-8 ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል… እያለ ይሰብክ ነበር።

ነገር ግን ዮሐንስ የኢየሱስን የጫማ ማሰሪያ መፍታት እንደማይችል አውቋል። የጫማውን ማሰሪያ ቢፈታ እግሩ ይገለጥ ነበር፤ እግሩ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል። ይህ መገለጥ ግን በሰባተኛው መልአክ ዘመን ነው የሚመጣው። ሰባተኛው መልአክ የተሰወረውን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እድገት በ2000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንዴት ቤተክርስቲያንን እና ዓለምን ወደሚቆጣጠርበት ኃይል እንደሚመጣ ይገልጣል።

እግር የማጠብ ሥነ ሥርዓት የሚወክለው ቤተክርስቲያን በሰባቱ ዘመናት ውስጥ እንዴት ለየዘመናቱ በተገለጠው የቃል ውሃ እየታጠበች እንደምትቆይ ያሳያል።

ዳንኤል እንዳየው ሸክላው ጭቃማ - እርጥብ ሸክላ ነው።

ዳንኤል 2፡43 ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥

ሙሽራይቱ ቀራንዮ ላይ ሮማዊው ወታደር የኢየሱስን ጎን በጦር ሲወጋው በፈሰሰው የመድሐኒት ውሃ ታጥባለች።

ዮሐንስ 19፡34 ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።

ዳንኤል ውስጥ የተገለጠው የአሕዛብ ነገሥታት ምስል ከአራት አይነት ብረቶች ነው የተሰራው፤ እነዚህም ብረቶች በውስጣቸው ሕይወት የላቸውም። እነርሱም አራት የአሕዛብ መንግሥታት ናቸው፡- የባቢሎን፣ የፋርስና የሜዶን፣ የግሪክ፣ እና የሮማውያን። በዚያው ጊዜ የመዳን ዘር በአይሁዶች ውስጥ ነበረ፤ እርሱም በናቡከደነጾር ሕልም ውስጥ የተገለጠው የአሕዛብ ምስል አካል አልነበረም።

ከዚያም በመስቀሉ ላይ መዳን ከአይሁድ ዘር አልፎ ከእነርሱ ወጥቶ በእግሮቹ ውስጥ ወዳሉት ሰባት ሸክላ እና ብረት ማለትም ወደ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ገባ። በእግሮቹ ውስጥ ሸክላው ብቻ ነው ሕይወትን መቀበል የሚችለው። ዘር በሸክላ አፈር ውስጥ መብቀል ይችላል። ሸክላ በረጠበ ጊዜ በሸክላ ሰሪው እጅ ውስጥ ሰሪው የፈለገውን ቅርጽ መያዝ ይችላል። ሸክላ አፈር ውሃ መምጠጥ ይችላል።

(በመንፈሳዊ አነጋገር ሙሽራይቱ የቃሉን ውሃ ጠጥታለች ማለት ነው።) ብረቶች ውሃ መጠጣት አይችሉም። በብረት የተመሰለችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በቃሉ ውስጥ የተሰጠንን እውነት አትቀበልም።

መሽራዋ ለዘመንዋ የተሰጣትን ቃል እንደ ውሃ ትጠጣዋለች።

ዳንኤል 2፡43 ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።

ብረቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ይወክላል፤ እርሷም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የመጀመሪያዋ በሰው ሥርዓት የተመሰረተች ቤተክርስቲያን ናት። እና ጥንታዊ የእውነት ጠላት እንደመሆኗ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስሕተትን በያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ አሰራጭታለች።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ሙሽራይቱ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መራራ ጦርነቶችን አድርገዋል። ሙሽራይቱ የተጻፈውን ቃል በማመን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ ሰዎችንና መሪዎችን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎችን በመከተል ሲዋጉ ቆይተዋል።

ኤፌሶን 5፡25 ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤

26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

ሙሽራይቱ ሸክላ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመታዘዝ ስትታጠብ ብቻ ነው እርጥብ የምትሆነው፤ እርሱም ንጹህ መንፈሳዊ ውሃ ነው።

ዮሐንስ 7፡38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።

39 ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።

ውሃ በተጨማሪ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራንን መንፈስ ቅዱስን ይወክላል። እግዚአብሔርን በመንፈስ እና በእውነት ነው ማገልገል ያለብን።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ሙሽራይቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት እውነትን በተሸከሙ ጠቅሶች አማካኝነት የሚመራት የመንፈስ ቅዱስ ሕይወት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔርን ለማገልገል ብቸኛው መንገድ ነው።

ዮሐንስ 14፡6 ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

እርጥብ የሸክላ አፈር የሚያጣብቅ እና ጭቃማ እንደመሆኑ ሌላ ትርጉምም አለው።

መዝሙር 40፡2 ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።

ይህ ደግሞ ሐጥያተኞች መሆናችንን፤ በጸጋው የዳንን ሐጥያተኞች መሆናችንን በተጨማሪም በመንፈስ እና በእግዚአብሔር ቃል እውነት መታጠብ በጣም እንደሚያስፈልገን ያስታውሰናል። የምንሰማው የተሳሳተ አስተምሕሮ ሁሉ በነፍሳችን ላይ ያለማመንን ጨለማ ይቀባናል። ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር ሲሆን ይህም የሚሆነው የምናምነውን በመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት ያልቻልን ጊዜ ነው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ዓላማ ወደ እውነት ሁሉ ለመመራት ነው።

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ቢኖርራ የወንድም ብራንሐምን መገለጦች ብትሰሙ ከዚያ በኋላ መሰረታዊ ጥያቄዎች - ለምሳሌ ኢየሱስ መሬት ላይ በጣቱ የጻፈው ለምንድነው - አይነት ጥያቄዎች ስትጠየቁ ሁል ጊዜ “እኔ እንጃ፤ አላውቅም” በማለት ፈንታ መጽሐፍ ቅዱስን በማስተዋል ማንበብ ትክክለኛውን መልስ መስጠት ትችላላችሁ።

“ከራሱ አይነግርምና።” ይህ በጣም አስፈላጊ እውነት ነው። ዛሬ ሰባኪዎችና ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ወደ ራሳቸው ትኩረት መሳብና ምን ያህል አስተዋዮች እንደሆኑ፣ ታላቅ እንደሆኑ፣ እንዴት መልካም እንደሆኑ፤ ምን ያልህ የጸጋ ስጦታ እንዳላቸው ወይም ምን አይነት መልካም ሥራ እንደሰሩ ማውራት ይወዳሉ። ነገር ግን ዛሬ በሕይወት ካሉ ሰዎች ውስጥ አንዳቸውም በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጠቀሱም፤ ስለዚህ ዛሬ ማናቸውም ታላቅ ሊሆኑ አይችሉም።

በመጨረሻው ዘመን በሕይወት ከሚኖሩ ሰዎች መካከል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ሰባተኛው መልአክ ብቻ ነው። ሌሎቻችን እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጠቀስ የምንበቃ አይደለንም፤ እግዚአብሔርም በመጽሐፉ ውስጥ እንድንጠቀስ አላደረገም። አንድ ሰው ራሱ ከፍ ባደረገ ጊዜ ወዲያው እግዚአብሔር ለምን እንደ ላከው ዓላማውን ይስታል። መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዘመን ንሰሐ ለመግባት እንድንቀና ያዘናል እንጂ ራሳችንን ከፍ ከፍ እንድናደርግ አይነግረንም።

ለመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

የረሳነው ነገር ቢኖር ታላቅ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ነው። በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በመቅረዞቹ መካከል የተመላለሰ እርሱ ብቻ ነው። ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አብሮ አልተመላለሰም። ወንድም ብራንሐም እና ጳውሎስ በእጁ የነበሩ ከዋክብት ብቻ ናቸው።

እናንተስ፣ እኔስ፣ ሌሎች ሰዎችስ ሁሉ ዛሬ የት ነን?

እጅግ በጣም ትንሽ እና ከነጥብም እንኳ ያነስን ከመሆናችን የተነሳ ዮሐንስ በራዕዩ ውስጥ አንዴም እንኳ አላስተዋለንም።

ዮሐንስ 16፡14 እርሱ ያከብረኛል፤

መንፈስ ቅዱስ ክብርን ሁሉ ለኢየሱስ ነው የሚሰጠው። የምናምነው ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተደገፈ እውነት መሆን አለበት።

ትኩረታችን ሙሉ በሙሉ ኢየሱስ ላይ መሆን አለበት። ሰውን ከፍ ከፍ ማድረግ ኒቆላዊነት ነው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ኒቆላዊነትን ይጠላል።

ራእይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።

የትኛውም ሰው በታላቅነት ከኢየሱስ ጋር ሊወዳደር አይችልም።

ዮሐንስ 13፡16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።

ኢሳያስ 42፡8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ… አልሰጥም።

ሰውን ከፍ ከፍ ማድረግ ፈጽሞ ስሕተት ነው።

በ1963 የስድስቱ ማሕተሞች ሚስጥር መገለጥ ይዞት የመጣው ብርሃን ድምቀቱ እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ድቅድቅ የነበሩ ጨለማዎች ድራሻቸው ጠፋ። በዓለም ላይ ታላቅ የሐይማኖት መሪ የነበረው ፖፕ ጆን 23ኛው በ1963 ሞተ፤ እንዲሁም በታሪክ ብቸኛው ሮማን ካቶሊክ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና በዓለምም ላይ ታላቁ የፖለቲካ መሪ የነበረው ጆን ኬኔዲ በ1963 በጥይት ተመትቶ ሞተ። በጨለማው ዓለም ውስጥ እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ መሪዎች ነበሩ።

ልክ አውሬውና ሐሰተኛው ነብይ አንድ ላይ በእሳት ባሕር ውስጥ እንደተጣሉ ይመስላል።

በቀጣዩ ዓመት በ1964 ራሺያ ውስጥ ክሩሼቭ ከስልጣኑ ተወገደ። ይህም ራሺያ ማለትም የሰሜኑ ንጉሥ በአርማጌዶን ጦርነት ላይ እንደሚሸነፍ ያመለክታል።

በራዕይ ምዕራፍ 8 እና 9 የተጠቀሱት ሰባቱ መለከቶች በታላቁ መከራ ወቅት አይሁዳውያን እንዲመለሱ ጥሪ የሚያሰማቸውን መለከት የሚነፋበትን የኢዮቤልዩ በዓልን ይወክላሉ። እነዚያ ሁለት ምዕራፎች የሚፈጸሙት በቤተክርስቲያን አይደለም።

ነገር ግን በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበረው ጊዜ አምስተኛው መለከት ምን እንደሚመስል በጥቂቱ ይጠቁመናል፤ በዚህም ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል ትንሽ ፍንጭ እናገኛለን።

የሲኦል ጥልቅ ተከፍቶ የፈላጭ ቆራጮችን መናፍስት በምድር ላይ ለቀቃቸው።

ነገር ግን አጋንንቱ ሁላቸውም አይደሉም የወጡት። የቀሩት ለታላቁ መከራ እንዲሆኑ ተወስነዋል። ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል የተወሰነ ፍንጭ እናገኝ ዘንድ ጥቂቶቹ ወጥተዋል።

እነዚህ እንደ ሒትለር ያሉ ፍጠረታዊ ፈላጭ ቆራጮች በዚያ ጊዜ ከሲኦል የመጡ ሰይጣናዊ ኃይላትን በምድር ላይ በመልቀቅ ፍጥረታዊ እሥራኤልን እየገደሉ እንዲያጠፉ ሰደዱዋቸው። ይህም የሆነ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው። ነገር ግን ዓላማቸው ይህ ብቻ አልነበረም። ሌላኛው ዓላማቸው በጦርነቱ ውስጥ ፍጠረታዊ እሥራኤልን ገድለው ሲያበቁ ከፍጥረታዊ እሥራኤል ተሸግረው ወደ መንፈሳዊ እሥኤል ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባት ነው።

አሁን ዓላማቸው በክርስቲያኖች ላይ መንፈሳዊ ግድያ መፈጸም ነው፤ ይህንንም ያሚያሳኩት ክርስቲያኖች የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እንዳያምኑ በማድረግ ነው። ይህ አይነቱ አጋንንታዊ አሰራር ልክ በ325 ዓ.ም. የተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ቤተክርስቲያን ሥላሴን እንድትቀበል እና የሮማ ጳጳስን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጋ እንድትቀበል እንዳስገደዳት ሁሉ በዚያው ተመሳሳይ መንገድ የዛሬዋን ቤተክርስቲያን ይቆጣጠራታል። በዚህ አጋንንታዊ ውጊያ ሥር ቤተክርስቲያኖች እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መመስረት ትተው አጋንንቱ ባደረጉባቸው ጫና መሰረት እምነታቸውን ሰው ሰራሽ በሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ አስተምህሮዎችና የፖፑን አርአያነት የተከተሉ ጨቋኝ የሰው አመራሮች ላይ ሊመሰርቱ ችለዋል።

ሰዓሊዎች የፈጠራ ጥበባቸውን ከየት እንዳገኙ ለማወቅ ከፈለጋችሁ በሕጻናት ኮሚክ መጻፎች ውስጥ ያሉትን ስዕሎች ልብ ብላችሁ እዩ፤ እነዚህ መጽሐፎች ውስጥ ጥልቁ በጥቂቱ ሲከፈት ምን እንደሚመስል ማየት ትችላላችሁ። ወደ ፊት በታላቁ መከራ ወቅት ጥልቁ ሙሉ በሙሉ ሲከፈት ከውስጡ ምን እንደሚወጣ አሁን ማሰብ አያቅታችሁም።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶቿ አማካኝነት በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያሉ መንፈሳዊ ልጆችን ወደ ሐዋርያዊ አባቶች አዲስ ኪዳናዊ እምነት ከመመለስ እየከለከለቻቸው ነው።

ዛሬ ስንት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሶች እና መሪዎች ሕጻናትን በማማገጥ እንደተጋለጡ ልብ በሉ። ይህ መንፈሳዊ ሐጥያታቸውን ያሳያል።

ራዕይ 9፡1 አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻው ንሰሐ መግባት እና ለሐጥያት ስርየት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ ነው፤ ከዚያም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ትቀበላላችሁ። ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር ለመክፈት ይህንን ቁልፍ ተጠሟል። በሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ኢየሱስ ለጴጥሮስ እንዲህ አለ፡-

ማቴዎስ 16፡19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ጴጥሮስ የዮሕንስን ጥምቀት ስላሰረው አሁን የዮሐንስ ጥምቀት አስፈላጊ አይደለም።

ከዚያም ጴጥሮስ ንሰሐን እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅን በተሰጠው መክፈቻ ተጠቅሞ የመንግሥተ ሰማያትን በር ክፍት አድጓል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻው ኢየሱስን ማክበርና ከፍ ማድረግ ደግሞም የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መታዘዝ በተለይም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በውሃ ስለመጠመቅ የጻፉትን ቃል መታዘዝ ነው።

ሰይጣን የሲኦል ቁልፍ አለው እርሱም ጥልቁ ጉድጓድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የእምነታችሁ መሰረት ማድረግ ስትተዉ ከዚያ መጨረሻ የሌለው የሰዎች ሃሳብ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ትገባላችሁ። እነዚህ የሰው ሃሳቦችም ያለማቋረጥ ይለዋወጣሉ።

ከዲያብሎስ ጋር ስትደንሱ በየሰከንዱ ሙዚቃውን ይቀያይረዋል።

ራዕይ 9፡2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

ፀሐይ ብርሃን ናት። ይህም ብርሃን የሚወክለው ቃሉን ነው።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እምነታቸው ትክክል መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ትተዋል።

አይሩ ወይም ደባቡ ጨልሟል። አየሩ ወይም ድባቡ ማለት በሚወያዩ ሁለት ሰዎች መካከል ያለው ስሜት ነው። ቤተክርስቲያን ከሚሄዱ ሰዎች ጋር ስትወያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጥቀሱና ሐሳባችሁ ከእምነታቸው ጋር ባይስማማ ከዚያ በኋላ ከእናንተ ጋር ለመወያየት ፍላጎታቸው ይጠፋል፤ የምትናገሩትንም ከልባቸው ማዳመጥ ያቆማሉ። ወይ ይናደዳሉ ወይ ደግሞ ፍላጎት ያጣሉ። ከዚያም ቀጥለው የውሸት ፈገግታ እያሳዩዋችሁ ከእናንተ ይሸሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት የማወቅ ፍላጎት የላቸውም። የሚፈልጉበት መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃቸው የማይጋለጥበትን የቤተክርስቲያን አመለካከት ብቻ ነው።

አጋንንታዊ አሰራር የሰዎችን አእምሮ በመበከልና አስተሳሰባቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ በማራቅ በትጋት እየተንቀሳቀሰ ነው። ዲያብሎስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊያርቃችሁ ነው ፍላጎቱ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እናንተን ከዲያብሎስ ሊያርቃችሁ እንደሚችል ያውቃል።

ራዕይ 9፡3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።

አንበጣዎች አጥፊ ተባዮች ናቸው። ሲመጡም በመንጋ ተሰብስበው አንድን ቦታ ውርር ያደርጉታል። ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቃረኑ አጋንንታዊ ሃሳቦች እንደ አንበጣ መንጋ ለወረራ ሲመጡ መቃመው በጣም ከባድ ነው። አጋንንት የሚሰማሩት በብልሃተኛ ሃሳቦቻቸውና በፍልስፍናቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነትን ለማትፋት ነው። ከዚያ በኋላ የብዙሃኑን አስተሳሰብ ለመቃወም ድፍረት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው።

በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የቡድን አስተሳሰብ ነው ሰዎችን የሚመራው እንጂ የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።

64- 0719 M የኢዮቤልዩ በዓል
አሁን የምንኖርበት ጊዜ የቤተክርስቲያን ባለስልጣናት እና አብረዋቸው የሚሰሩ መናፍስት በአንድነት ሁሉንም ወደዚህ ታላቅ እርድ እየሰበሰቡዋቸው ነው፤ ሊያጠፉዋቸው። አሁኑኑ ተጽፏል፤ በዚችው ሃገር ውስጥ፤ ከድርጅቱ ጋር ካልተባበራችሁ ቤተክርስቲያኖች ይዘጋሉ ተብሏል። ልክ እንደ አውሬው ምልክት ይህም አንድነት አሻጥር ነው።

ስለዚህ አውሬም ምን እንደሆነ አያችሁ አይደል? ኃይል ነው። ቤተክርስቲያናዊ ኃይል ነው፤ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- “ከእውነተኛው ነገር ጋር በጣም ከመመሳሰሉ የተነሳ ቢቻልስ የተመረጡትን እንኳ ሳይቀር ያስታል።” ነገር ግን ኢየሱስ ስለዚያ ቀን ለእኛ ደግሞ የገባልን ቃል አለ፤ እርሱም የገባልን ቃል እንደማንታለል ነው ምክንያቱም ቃሉ ማለትም ክርስቶስ እራሱ ከእኛ ጋር ይሆናል። እነርሱ መንፈሳዊ ፍጡራን አጋንንት ስለሆኑ በዓይናችሁ ልታዩዋቸው አትችሉም ነገር ግን የሚሰሩትን ሥራ ማየት ትችላላችሁ። ገብቷችኋል?

ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።

አረንጓዴ አትክልት የማይበሉ አንበጣዎች ፍጥረታዊ አንበጦች አይደሉም።

ዮሐንስ የአንበጦችን አውዳሚ ኃይል በመጠቀም ስለ አጋንንት መግለጹ ነው። አጋንንት መንፈስ ስለሆኑ ልንገልጻቸው አንችልም። ስለዚህ ዮሐንስ ከምናውቀው ነገር ጋር አስተያይቶ ነው የሚገልጥልን። እነዚህ አጋንንት የሚያደርሱትን መንፈሳዊ ጥፋት ሲያየው አስደንግጦታል። ያደረሱትም ጥፋት የመጽሐፍ ቅዱስ እምነትን ከሰዎች ውስጥ ጠራርጎ ማስወጣት ነው። የአጥፊነት ኃይላቸውን ሲያየው የአንበጦችን መንጋ አስታወሰው። ማንኛውንም ጥበቃ ከለላ ወይም ቅጥር የሌለውን ነገር ሁሉ ያጠፉታል። ከአጋንንት ጥቃት ጥበቃ የምናገኘው በእግዚአብሔር ማሕተም ማለትም በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት ብቻ ነው።

ኤፌሶን 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።

በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችን ማረጋገጫ የተጻፈው ቃል ውስጥ ያለውን እውነት መረዳት መቻላችን ነው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንረዳ ያስችለናል።

ኢየሱስ ዲያብሎስ በፈተነው ቁጥር ያሸነፈው “… ተብሎ ተጽፏል” በማለት ነው።

ዲያብሎስ እውነት የሚመስልን ሆኖም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ሃሳብ ሊያሳምነን ይፈልጋል።

በአንበጦች የተመሰሉት አጋንንት ግን ንጉሥ አላቸው። ንጉሥ ዘውድ ይጭናል። በምዕራቡ ዓለም ዘውድ የሚጭን ብቸኛ የሐይማኖት መሪ የካቶሊክ ፖፕ ነው። እርሱም ባለ ሦስት ድርብ ዘውድ ነው የሚጭነው።

በ1963 ፖፕ ፖውል 6ኛው ዘውድ ከጫነ በኋላ አውልቆ ሊያስቀምጠውና ሁለተኛ ላይጠቀምበት ወሰነ። ስለዚህ የካቶሊክ ፖፕ የነበሩ ሰዎች በ860 ዓ.ም ከነበረው ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ ጀምሮ እስከ 1963 ድረስ ለ1103 ዓመታት ዘውድ ጭነዋል። ይህም ዘውድ የጫኑ የምድር መሪዎች መካከል በዘመን ርዝማኔው ከሁሉ የበለጠ ነው።

ራዕይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።
ፖፑ እንደ ፈላጭ ቆራጭ ንጉስ አሁን ዘውድ አይጭንም፤ ነገር ግን አሁንም በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ፍጹም የበላይ የሆነ ሥልጣን አለው።

መልአክ መልእክተኛ ነው። ፖፑ ከጥልቁ የተላከ መልእክተኛ ነው - የጨለማው መልእክተኛ።

ብቸኛው ማምለጫችን የወንድም ብራንሐምን መገለጦች ወደ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እያየን መቀበል ነው። የተናገራቸውን ቃሎች ጠምዝዘን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ብንከተል እነዚያ አጋንንታዊ መናፍስት አስተውናል፤ ስለዚህ እኛም በፖፑ ጎራ ውስጥ ገብተናል ማለት ነው።

62-0318 የተነገረው ቃል የመጀመሪያው ዘር ነው - ክፍል 2

ስለዚህ ይህን ሁሉ የተናገርኩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ባይስማማ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ባይገጥም ስሕተት ነው።

አብዶን ማለት ውድመት እና ጥፋት ነው። ዛሬ የሰይጣን ትልቁ ዘመቻው የወንድም ብራንሐምን መልእክት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ መንገድ በመተርጎም ለማጥፋት ነው። ከዚያም መልክእክቱ ይጠፋል የሜሴጅ ተከታዮችም በታላቁ መከራ ውስጥ ወደሚጠብቃቸው ጥፋት ውስጥ ለመግባት ይፈጥናሉ።

አብዶን የጨለማው ግዛት መልአክ-ንጉሥ ነው፤ የሞት መልእክተኛ እና የሁመት ሁል ምንጭ ነው። የሜሴጅ መልእክቶች ልዩ ልዩነት እና ሰይጣን (አብዶን ተብሎም ይጠራል) በሜሴጅ አማኞች መካከል የፈጠረውን ሁከት ያመለክታል።

ቤተክርስቲያኖችም ደግሞ ወንድም ብራንሐም ያመጣውን መገለጥ ጸንተው ይቃወማሉ። ስለዚህ እነርሱም ከአንድ ሺህ በላይ በተለያዩ እምነቶች ተከፋፍለዋል።

ሰይጣንና አጋንንቱ በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ትልቅ ሁከት እየፈጠሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቀ በቤተክርስቲያን አባላት ዘንድ እየተባባሰ የመጣ ችግር ሆኗል።

64-0719 M የኢዮቤልዩ በዓል
አጋንንት መንፈስ ናቸው፤ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ፍጡራን ናቸው፤ በዓይን አይታዩም፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን ማየት ትችላላችሁ።

ያ እየገሰገሱ በመምጣት ሳይ ናቸው፤ የሚቃወማቸውንም ሁሉ ከፊታቸው ጠራርገው ለማጥፋት ተዘጋጅተዋል።

1965 ወንድም ብራንሐም አገልግሎቱን ያበቃበት ቀን ነበረ። እርሱ ከ1947 እስከ 1965 ድረስ የሰበከበት ዓመታት ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ብልጽግና የሆነበት ጊዜ ነበር። 1950ዎቹ የመትረፍረፍ ዓመታት ነበሩ። እግዚአብሔር አሜሪካን አሁንም ይባርካት፤ ግን ያ ጊዜ አሜሪካኖች የተገለጠውን የእግዚአብሔርን እውነት ለመቀበል ፈቃደኛ የነበሩበት ጊዜ አልነበረም።

አንዳንድ የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት ከ1965 እስከ 1980 አሜሪካ “ራሷን ለማጥፋት” የሞከረችበት ጊዜ ነበረ። ይህም አሜሪካ ወንድም ብራንሐም ያመጣላትን በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ እውነት አልቀበልም ስለማለቷ የከፈለችው ዋጋ ነው።

ይህ ሁሉ አሳዛኝ ክስተት የጀመረው በ1965 ፕሬዚደንት ጆንሰን ባለማስተዋል በቬትናም ጦርነት ውስጥ ብዙ ወጭ ለማውጣት ሲወስን ነው፤ ጦርነቱም ለአሜሪካ በብዙ መንገድ ኪሳራ አስከተለ። ፕሬዚደንት ኒክሰን አሜሪካን በጥበብ ከጦርነቱ ውስጥ አስወጣት። ከዚያ ወዲያ ግን የአሜሪካ ዜና አውታሮች በዎተርጌት በተፈጸመው ቅሌት የተነሳ ድምጥማጡን አጠፉት። ኮንግሬስ ውስጥ በዚያ ጊዜ የዴሞክራቶች ድምጽ ያመዝን ስለነበረ አሜሪካ ደቡብ ቬትናምን ጥላ ወጣች፤ ይህም ለአሜሪካ ታላቅ ውርደት እና ሽንፈት ሆነ። የአሜሪካ ጦር ሰራዊት ኃያል ነበር ቤትናም ውስጥም በጦርነት አልተሸነፈም ነበር ግን ልክ እንደ ዳንኤል ራዕይ ውስጥ እንደነበረው ምስል የሸክላ እግሮች ስለነበሩት በአሜሪካ የዜና አውታሮች እና በአሜሪካ ፖለቲከኞች ጥቃት የተነሳ ተሸነፈ። ቬትናም እና ካምቦዲያ (አሁን ካምፑቺያ) ውስጥ ለነበሩ ሰዎች አሜሪካ በ1975 ለቅቃ መሄዷ ትልቅ አደጋ ነበረ። አሜሪካ ለቅቃ ከሄደች በኋላ ሃገራቸው በ1980ዎቹ አካባቢ እስክትረጋጋ ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች አልቀዋል።

በዚያው ጊዜ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ካባድ የተማሪዎች ተቃውሞ እና አመጽ ተቀሰቀሰ። በአሜሪካ ከተሞች ውስጥም የዘር ግጭት ተፈጠረ፤ በእነዚህም ግጭቶች ብዙ የሰው ነፍስ እና የንብረት ጥፋት ሆነ።

አረቦች በ197ቱ ጦርነት በእሥራኤል በተሸነፉበት ጊዜ አካባቢ አረቦቹ የነዳጅ ዘይትን ዋጋ ከነበረበት በአራት እጥፍ ከፍ አደረጉት። ብዙ ሃገሮች ከዚህ የተነሳ ኪሳራ ገጠማቸው። አፍሪካ እና ኤዥያ ውስጥ ከአሥር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በምግብ እጦት ሞቱ። ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከመጡ ኢኮኖሚያዊ ጥፋቶች ሁሉ ከፍተኛው ነበር።

ፕሬዚደንት ካርተር በኢራን ንጉሥ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ የሰብዓዊ መብቶች ዘመቻ ተጠቀመ። ከዚህም የተነሳ ኢራንን ከንጉሡ የባሰ ፈላጭ ቆራጭ እና ጨካኝ እንዲሁም ጸረ አሜሪካ የሆነ አሸባሪ መንግሥት ተቆጣጠራት። ይህም ክፉ መንግሥት ኢራን ውስጥ በ1979 ብዙ ሺህ ተቃዋሚዎችን በመግደል ወደ ስልጣን መጣ። ኢራን ውስጥ አሜሪካውያንን አግተው ያዙ፤ ካርተርም የታገቱትን አሜሪካውያን ለማስለቀቀ ባደረገው ሙከራ የላካቸው ሄሊኮፕተሮች አውሎ ነፋስ ውስጥ ገብተው ተከሰከሱ። ከዚህም ጋር የአሜሪካ ክብርና ሞገስ አብሮ ተከሰከሰ።

በ1965 ፖፕ ፖውለ 6ኛው እና የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ አቴናጎራስ ቀዳማዊ በካቶሊክ እና በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች መካከል እንደ ጥል ግድግዳ ቆሞ የነበረውን የ1054 ዓ.ም. የእርስ በርስ ውግዘት ሰረዙ። ይህም ተለያይተው የነበሩ ቤተክርስቲያኖችን በኢክዩሜኒካል እንቅስቃሴ አማካኝነት ወደ አንድነት ለማምጣት የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነበረ። ከዚያ ወዲያ የኢክዩሜኒካል አንድነት እንቅስቃሴ በብዙ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ትልቅ መርህ ሆነ።

ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ ስንዴዎች እና እንክርዳዶች አብረው ያድጋሉ። ከዚያም መጀመሪያ እንክርዳዶች በኢክዩሜኒካል የአንድነት እንቅስቃሴ አማካኝነት መጀመሪያ ይሰበሰባሉ። በዚህም የአንድነት እንቅስቃሴ ውስጥ ፍቅር ወደ አንድነት ሲያመታ አስተምሕሮ ግን ያለያያል። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች ልዩነቶቻቸውን ደብዘዝ አድርገው በሰላም መተባበር እስከቻሉ ድረስ እያንዳንዳቸው የፈለጉትን የማመን ነጻነት አላቸው። ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው በ1948 ሲሆን ይህም በ1947 የማስተማር አገልግሎቱን የጀመረውን የመጨረሻው ዘመን ነብይ አገልግለቶቱን ሰይጣን ሊቃወመው የተነሳበት ጊዜ ነው።

ማቴዎስ 13፡30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።

ከ1965 በኋላ ባሉት ዓመታት የቤተክርስቲያን ዓለም በሁለት ታላላቅ ጽንፎች መካከል ዋዠቀች።

አንዱ ጽንፍ 800 ሚሊዮን ከሚሆኑ ፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ውስጥ 600 ሚሊዮኑን ወደ ይስሙላ አንድነት ለማምጣት የሚጥር ነው። የዚህም ጽንፍ ትኩረቱ የአስተምሕሮ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ወደ አንድነት መምጣትና መግባብት ነው።

ሌላኛው ጽንፍ ደግሞ ያለማቋረጥ ቤተክርስቲያን ውስጥ መገንጠል፣ መከፋፈል መሰነጣጠቅ ነው። የዚህም ውጤት በ2018 ዓ.ም ከ45,000 በላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እንዲኖሩ አድርጓል።

ከእነዚህ ሁለት ጽፎች አንዳቸውም ሕዝቡ ለጌታ ምጽአት እንዲዘጋጁ የማድረግ ተስፋ የላቸውም።

ወንድም ብራንሐም እንደ ሰው ጥልቅ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀትና መረዳት አግኝቷል፤ ደግሞም በእርግጥ አገልግሎቱ በ1965 እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ስለ ምን ይናገር እንደነበር ጠንቅቆ ያውቅ ነበር።

ግን ቁም ነገሩ ያ አይደለም። ወንድም ብራንሐም የመጣው ለጌታ ምጻት ራሱን ለማዘጋጀት አልነበረም። እርሱ የመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮችን ለመግለጥ እና በዚህም መገለጥ ተጠቅማ ሙሽራዋ ለጌታ ምጻት ራሷን እንድታዘጋጅ ነው።

ራዕይ 19፡7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።

ዋናው ቁም ነገር ሙሽራዋ ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮ መመለሷ እና የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ታምን ወደነበረው እምነት መመለሷ ነው። ይህ እስኪሆን ድረስ የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ግቡን አልመታም።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ስለዚህ የእኛ ችግር፡- እንዴት ነው ወደ እግዚአብሔር ጎተራ የምንሰበሰበው? የሚለው ጥያቄ ነው። እንዴት አድርገን መጽሐፍ ቅዱስን ብንማር ነው ለዳግም ምጻት የሚያዘጋጀንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ የምናገኘው?

ወንድም ብራንሐም ስለ መጨረሻው ዘመን ራዕይ አይቶ ነበር።

60-1113 ኩነኔ በውክልና
ከዚያ እነዚህ ሴቶች መመረጥ የማይገባው ሰው እንዲመረጥ ድጋፍ ሲያደርጉ አንዲት ታላቅ ሴት አሜሪካ ውስጥ በኃይል ስትነሳ አያለሁ።

እርሷም ያማሩ ልብሶችን የምትለብስና ውብ ሴት ነች፤ ነገር ግን ልቧ ጨካኝ ነው። እርሷም ይህንን ሃገር ወደ ጥፋትና ውድመት ትመራለች። (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ “ምናልባት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን” ብዬ ጽፌያለው።)

ሳይንስም እያደገ ይሄዳል፤ በተለይም የተሻሉ ማሽኖችን እና መኪኖችን በመፍጠር። የቤት መኪኖችዩእንቁላል ዓይት ቅርጽ እየያዙ ይለወጣሉ፤ በስተመጨረሻም መሪ የማያስፈልጋቸው መኪኖች ይመረታሉ። (አሁን መሪ የሌላቸው መኪኖች መመረት ጀምረዋል።) መኪኖቹን በሌላ አይነት ኃይል ይቆጣጠሩዋቸዋል።

ከዚያም አሜሪካ ተቃጥላ እሳቷ እየነደደ እንደሚቆይ ቦታ ሆና አየኋት። ይህም መጨረሻው አካባቢ ይሆናል። (ይህንንም በትዕምርተ ጥቅስ እንዲህ ብዬ አስቀምጬዋለው፡- “ይህ ሁሉ ይፈጸማል።” አሁን ልብ በሉ፤ ይህ ሁሉ ጌታ ያሳየኝ ነው ግን እኔ ደግሞ “ይህ ሁሉ ከ 1977 በፊት ይፈጸማል ብዬ እተነብያለው።”) በዚህ ትንቢት ጸንቼ እቆማለው ምክንያቱም እየተንደረደረ እየፈጠነ ሲመጣ አየዋለው፤ ይህች ሃገር ቦታዋን እስክታገኝ ድረስ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅባት አይቻለው።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 1.2 ቢሊዮን ያህል ተከታዮች አሏት። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ እንደመሆኗ ሴት ደግሞ ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። ስለዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ ቆንጅዬ ሴት ልትገለጽ ትችላለች፤ ምክንያቱም እጅግ ብዙ ሰዎችን ስባለች።

ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ሐይማኖትን እንደ ቆንጅዬ አድርገን ብንገልጽ ትክክል ነን።

ይህን ጥቅስ የሜሴጅ ሰባኪዎች ሲተረጉሙት በ2016 ሒላሪ ክሊንተን አሜሪካ ውስጥ የሚደረገውን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለ ነበር፤ ነገር ግን ትርጓሜያቸው ትክክል አለመሆኑን አለመፈጸሙን ሲያዩ በመካከላቸው ታላቅ ግራ መጋባት ተፈጠረ። ወንድም ብራንሐም ሒላሪ ክሊንተን ፕሬዚደንታዊ ምርጫውን ታሸንፋለች ብሎ አያውቅም። የሜሴጅ ሰባኪዎች ግን የብራንሐምን ንግግር እንደዚያ ብለው ተረጎሙት። ሒላሪ ክሊንተን ሱሪ መልበስ ታበዛ ነበር፤ ብራንሐም ደግሞ ይህንን ጥሩ አለባበስ አድርጎ አይቆጥርም።

ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ ሒላሪ ቆንጅዬ ናት ብሎ የሚያስብም ሰው የለም።

ይህም የሜሴጅ አማኞች የሰሩትን ከባድ ስሕተት ያሳያል። የወሰዱትን ጥቅስ እንደሚፈልጉት አድርገው ይለውጡትና ያልሆነ መልስ ያገኛሉ። ሁልጊዜ ጥቅስ ይወስዱና የሆነ አስደንጋጭ ክስተትን እንዲያመለክትላቸው አድርገው ይለውጡታል። ነገር ግን ትራምፕ በማሸነፉ መቶ በመቶ ስሕተት ሆነው ተገኙ።

ስለዚህ በጣም ትልቅ ትምሕርት መማር እንችላለን። ሒላሪ ታሸንፋለች ብለው የተነበዩ የሜሴጅ ሰባኪዎች እግዚአብሔር በነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ እና እንዳቀደ አንዳችም የሚያውቁት ነገር የለም። ስልጣን ስለሚወዱ ብቻ ሕዝቡን በግድ ይመሩዋቸዋል። ደግሞም በጣም ጥሩ ክፍያ ይከፈላቸዋል። ስለዚህ እውነቱን ቢሰብኩ ባይሰብኩ ግድ የላቸውም። ምንም አይጨነቁም።

እንዴት ይህን የሚያህል አሳፊሪ ስሕተት ሊሰሩ ቻሉ? ምክንያቱም እምነታቸውን በተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ሊመሰርቱ ሲገባቸው እነርሱ ግን እምነታቸውን ለሰው ንግግር ጥቅስ በሰጡት ትርጓሜ ላይ አደረጉ።

ለምንድነው ብዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች የሚሳሳቱት? ምክንያቱም አንዳችም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ድጋፍ የሌላቸው ጥቅሶች ላይ ነው ትምሕርታቸው የተመሰረተው።

61-1119 ፍጹም ብርታት በፍጹም ድካም ውስጥ
የማንቆርቆርያ ክዳን ሲከፈት እንፋሎት እንዴት እንደሚወጣ ታውቃላችሁ አይደል፤ በክርስትና ስም አጋንንት እንተንቀሳቀሱ የዲያብሎስም ኃይላት እንደልባቸው እየፈነጩ ነው። እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጎን ትተው የሰዎችን ትዕዛዝ እና የስነ መለኮት ሴሚናሪ አስተምሕሮ ያስተምራሉ።

ሴሚናሪ ሰዎች የራሳቸውን አስተሳሰብ ይዘው የሚሰበሰቡበት ጉባኤ ነው።

የተነበዩትን አስገራሚ ትንቢት የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ሳይኖረው በድፍረት መናገራቸው ሞኝነት እና አለማስተዋል ነው።

አመለካከታችንን የሚቃኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሌለን ጊዜ የሚነዳን ዲያብሎስ ነው።

61-1217 ክርስትና እና ጣኦት አምልኮ
መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ ብታውቁ እና የምትሰሩትንም ብታስተውሉ ይሻላችኋል፤ አለዚያ ክፉ መንፈስ በቀላሉ ይገባባችሁና ከዚያ እንደገባባችሁ ላታውቁ ትችላላችሁ። ከቃሉ የተቃረነ ነገር በሙሉ አትመኑ። ከቃሉ ጋር ጸንታችሁ ቁሙ።

ሒላሪ በ2016 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው ጸንተው ይከራከሩ የነበሩ አንዳንድ የሜሴጅ ሰባኪዎች ከዚያ በፊት በ1977 ደግሞ አሜሪካ በ1977 ትጠፋለች የሚለውን ጥቅስም አበክረው ሲያውጁ ነበረ። ይህም ጥቅሳቸው ስሕተት ነበረ። ስለዚህ ለአርባ ዓመታት ሁሉ ጥቅሶች ላይ የሙጥኝ ብለው ከቆዩ በኋላ እንኳ እስከዛሬም ድረስ እንደሳቱ ናቸው። ጉባኤዎቻቸውም በአስተማዎቻቸው የተጣመሙ የጥቅሶች ትርጓሜ ትምሕርት ከመደንዘዛቸው ብዛት የተነሳ አእምሮዋቸውን እቤት ትተው ወደ ቤተክርስቲያን እንደሚሄዱ ይመስል ስንት ዓመት ሙሉ የአስተማሪዎቻቸውን ስሕተት እያዩ አያስተውሉም።

1977ን በተመለከተ እግዚአብሔር ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር። አንድ ጥቅስ ከወንድም ብራንሐም አፍ የመጣ በሙኑ ብቻ አትመኑት። አንዳንድ ጥቅሶች ስሕተት ናቸው። በእርሱ ንግግር ውስጥ ያሉትን ሃሳቦች ወስዳችሁ ትክክለኛ መሆናቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መመርመር አለባችሁ። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው እውነትን ማግኘታችሁን የምታውቁት።

64-0823 ጥያቄዎችና መልሶች 1
ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ግን እኔ ስለ ሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ብለው የሚቀበሉ። ነጻ የሆነውን የሚቀበሉ በቃሉ ይኖራሉ።

የሰውን ንግግር ማመን የምትችሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መዝናችሁ እውነት ሆኖ ስታገኙት ብቻ ነው።

ስለዚህ የሜሴጅ ሰባኪዎች የሚሰሩት ሌላኛው ስሕተታቸው ደግሞ “ነብዩን ልታርሙት አትችሉም” የሚባለው አባባላቸው ነው። ይህ የ1977 ጥቅስ አንዳችም የሚደግፈው የመጽሐፍ ቃል የለም። ከዚህም አንድ ትልቅ ነገር እናስተውላለን። የሰው ጥቅስ ብታገኙና ጥቅሱ ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር ባይስማማ ጥቅሱን ጥላችሁ ሂዱ።

ወንድም ብራንሐም ምንም ያህል ብናደንቀውና ብንወደውም ሰው መሆኑን እና ሊሳሳት እንደሚችል መርሳት የለብንም። ስለዚህ የእርሱን ንግግሮች በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መመርመር አለብን፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ ነው ማመን ያለብን።

የሚያያቸው ራዕዮች እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውም መረዳት በጣም አስገራሚዎች ነበሩ። ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ካስተማሩኝ እጅግ የበለጠ አስተምሮኛል።

ነገር ግን መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ መሲሁ ላይሆን ይችላል ብሎ ትልቅ ስሕተት እንደሰራው ሁሉ ወንድም ብራንሐምም አልፎ አልፎ ስሕተቶችን ሰርቷል።

በ1963 ፌብሩዋሪ 28 ቀን በፍላግስታፍ ከተማ አካባቢ ስለታየው ታላቅ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የሰራው ስሕተት ብዙ አሉታዊ ውጤቶችን አስከትሏል።

በሰዓቱ ስለ ደመናው አንዳችም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፤ እርሱ ራሱ ጥቂት ወራት ካለፉ በኋላ ነው ስለ ደመናው የሰማው። ሳንሴት ፒክ አካባቢ ሰባት መላእክት ወደ እርሱ ማርች 8 ቀን መጥተው እንደነበር በማስታወስ ደመናው እነዚህ መላእክት ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ የተፈጠረ እንደሆነ አድርጎ ገመተ። ስለዚህ በ1963 ሰባቱ መላእክት ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ አሪዞና ውስጥ ሳንሴት ፒክ ውስጥ ከደመናው ስር ቆሞ እንደነበር ስለመሰለ እንደዚያው ብሎ አመነ። የሚያሳዝነው በተሳሳተ መረጃ ላይ ተመስርቶ ነው እንዲህ ያመነው።

ምክንያቱም ደመናው የታየው መላእክቱ እርሱን ለማግኘት ወደ ሳንሴት ፒክ ከመምጣታቸው ከ8 ቀናት በፊት ነው። ደመናው የታየበት ቦታ ደግሞ ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ራቅ ብሎ ያለው ፍላግስታፍ ከተማ ላይ ነው።

ደግሞም ደመናዎቹ ሁለት ነበሩ።
ይህ ፎቶ የተነሳው ከዊንስሎው ነው።

ትንሽዬ የጭስ ደመና አንድ ሮኬት ሲፈነዳ እየበነነ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ከትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ኋላ 20 ማይልስ ርቀት ላይ በስተምዕራብ በኩል ሆኖ ይሄድ ነበር። ትልቁም ደመና ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ወደ ዊንስሎው እየሄደ ሳለ በፍላግስታፍ ሰማይ ላይ ለ28 ደቂቃ ቆይቷል። ነገር ግን ትልቁ ደመናም ይሁን ትንሹ በሮኬት ጭስ የተፈጠረው ደመና ወደ ሳንሴት ፒክ አካባቢ አልሄዱም።

የዊልያም ብራንሐም ሴት ልጅ ቤኪ “Return to Sunset” በሚለው መጽሐፏ እንደጻፈችው ወንድም ብራንሐም ማርች 6 ቀን 1963 ጃቨሊና የሚባሉ አሳማዎችን ለማደን ወደ ሳንሴት ፒክ ሄዶ ነበር።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የአደን ወቅት ገና አልተጀመረም ነበር። የጃቨሊና አሳማ አደን ማርች 1 ይጀመርና ማርች 10 ቀን 1963 ነበር የሚጠናቀቀው። ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ፍብሩዋሪ 28 ቀንን በአደን ሊያሳልፍ አይችልም።

ደመናው በሰማይ ላይ የሰው ልጅ ምልክት ነበረ። ደመናውም ወንድም ብራንሐም እዚያ ሳይሄድ በፊት ነበር የተገለጠው፤ ደግሞም እርሱ ከነበረበት ቦታ 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ርቆ ነበር ደመናው የታየው። በጊዜው እርሱ ስለ ደመናው ምንም አያውቅም ነበር፤ አላየውምም።

ስለዚህ እግዚአብሔር የሰዎች ትኩረት ወደ ሰው ማለትም ወደ ወንድም ብራንሐም እንዲሆን አልፈለገም።

ይህ ደመና የሰዎችን ቀልብ ለመሳብ የሚያገለግል ምልክት ነበረ።

መላእክቱም ከስምንት ቀናት በኋላ ወደ ጄፈርሰንቪል ሄዶ በራዕይ ምዕራፍ 6 የተጻፈውን የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር እንዲገልጥ ሊነግሩት መጡ።

ስለዚህ እርሱ የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር በሚገልጥበት ጊዜ ስለሚሰብካቸው አስደናቂ ስብከቶች እግዚአብሔር የሰዎች ልቦና እንዲዘጋጅና ትኩረታቸው ወደ መልእክቱ እንዲሳብ ብሎ ምልክት እየሰጠ ነበር። እነዚህም ስብከቶች በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚከናወነውን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ስውር አሰራር የሚያጋልጡ ነበሩ።

እነዚያ መገለጦች ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች እንዲፈታና ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ትምሕርትና እምነት የምንመለስበትን መንገድ እንዲያሳየን አስችለውታል።

ወንድም ብራንሐም ሰው እንደመሆኑ ለኢየሱስ ምጻት ሊያዘጋጀን አይችልም። ነገር ግን እርሱ ያስተማረን መልእክቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አማካኝነት እውነትን እንዴት አጽንተን እንደምንይዝ ያሳዩናል።

ነገር ግን ከደመናው ፎቶግራፍ ተነስቶ በጣም ብዙ የተሳሳቱ ትምሕርቶች ተፈልፍለዋል።

ከዚህም ተነስተን የሰው ንግግር ሲጠቀስልን እያንዳንዱን ሃሳብ በዝርዝር ማጣራት እንዳለብን እንማራለን።

እነዚህ ስሕተቶች ወንድም ብራንሐም እግዚአብሔር እንዳልሆነ አጉልተው ያሳዩናል። ደግሞም የተወሰኑ ስሕተቶችንም ስለሰራ የእግዚአብሔር ድምጽ ተብሎ ሊጠራም አይችልም። ከወንድም ብራንሐም ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች ሙሉ በሙሉ ከስሕተት የጸዱ አይደሉም።

62-1007 የበሩ መክፈቻ
እዚህ አካባቢ አንዳንድ ሰዎች እርሱ ልኮናል ብለው እኔ ያልላክሁዋቸው ሰዎች በየቦታው እየሄዱ ሰዎች ሚስቶቻቸውን ትተው መንፈሳዊ አጋሮቻቸውን መፈለግ አለባቸው ብዬ እንዳስተማርኩ ይላሉ፤ ደግሞም እኔ ፈጽሜ እንደማልሳሳትም ያወራሉ። ይገርማል፤ ይህ በጣም አሳዛኝ ወሬ ነው።

ሰዎች ወንድም ብራንሐም በፍጹም አይሳሳትም ብለው ሲያወሩ እርሱ ግን ይህንን እጅግ የሚያሳዝን ወሬ ነው ብሎታል። እንዲህ ብሎ ማውራት ሚስትን ትቶ ሌላ ሴት ስለማግባት ከተባለው ሃሳብ ባልተናነሰ አሳዛኝ ነው።

ወንድም ብራንሐም ግን የተላከው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ትከተለው ወደነበረው የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ሊመልሰን ነው።
ከደመናው ፎቶግራፍ የተለዱ የተሳሳቱ እምነቶችን በጥቂቱ እንመልከት፡-

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፀሐይ በምትጠልቅበት ሰዓት አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ፎቶ የተነሳው ደመና “የጌታ ምጻት” በሳንሴት ፒክ ተብሎ ተሰይሞ ነበር፤ ነገር ግን ሳንሴት ፒክ ከፍላግስታፍ በስተደቡብ 200 ማይልስ ርቆ የሚገኝ ከተማ ነው።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 በሰባት መላእክት ክንፎች አማካኝነት የተፈጠረው ደመና ለሳንሴት ፒክ ከተማ ቅርብ አልነበረም። ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ በስተሰሜን ርቃ በምትገኘው የፍላግስታፍ ከተማ ላይ ነበር የታየው።

ሰባቱ መላእክት ማርች 8 ቀን 1963 ወደ ሳንሴት ፒክ ማንም ሰው ሳያያቸው ነው ወንድም ብራንሐምን ለማግኘት የመጡት። ከዚያም ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱም ማንም ሰው አላያቸውም፤ ደመናም አልፈጠሩም።

ደማናውን የሰሩት ሰባቱ መላእክት እና እነዚሁ ሰባት መላእክት ወንድም ብራንሐምን ሊያገኙ የመጡት በሁለት የተለያዩ ክስተቶች በሁለት የተለያዩ ጊዜዎች ነው። ደግሞ ክስተቶቹም የተፈጠሩባቸው ቦታዎችም በ200 ማይልስ ርቀትና በስምነት ቀናት ይለያያሉ። ሆኖም ብዙ የሜሴጅ አማኞች ሁለቱ አንድ ክስተቶች ናቸው ይላሉ።

የደመናውን ፎቶ ያትሙና “ክርስቶስ በሳንሴት ፒክ ከተማ” ታይቷል ይላሉ። ፈጽሞ ውሸት ነው።

መላእክቱ ሰው ሳያያቸው ወደ ወንድም ብራንሐም ወደ ሳንሴት ፒክ መምጣታቸው የጌታ ምጻት ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም በ1965 የወንድም ብራንሐም ሕይወት የመጨረሻ እድሜው ላይ ወንድም ብራንሐም ራሱ የጌታን መምጣት ሲጠባበቅ ነበር።

65-0725 የተራራው መስሕብ ምንድነው
ወደ ተራሮቹ ሰላምታ እንልካለን፤ ፕሬስኮት አሪዞና ውስጥ ወንድም ሊዮ መርሲየ እና የእርሱ ቡድን ተራራው ላይ ወጥተው የጌታን መምጣት ይጠባበቃሉ። በታክሶን ለተሰበሰቡት ሰላምታንን እንልካለን፤ የጌታን ምጻት ለመጠባበቅ በዚያ ተሰብስበዋል። ደግሞም በሒውስተን ቴክሳስም ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት። እዚያ ቺካጎ ውስጥ ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም።

በምሥራቅ በውቂያኖሱ ዳር ኒው ዮርክ ውስጥ እና ኮኔቲከት ውስጥ ለተሰበሰቡትና የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም። እዚህ ቢመጡ ለእነርሱ የሚሆን መቀመጫ ቦታም የለንም። ስለዚህ በስልክ በመጠቀም ቃሉን እንልክላቸዋለን። ዛሬ ማታ በክላርክስቪል ለተሰበሰቡት ለወንድም ጁንየር ጃክሰን እና ለቡድኑ እንዲሁም ለወንድም ራድል እና አብረውት የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ቡድኖቹ ሰላምታ እንልካለን። እኛም ደግሞ ዛሬ ማታ እዚህ በቤተክርስቲያን በተሰበሰብንበት የጌታን ምጻት እንጠባበቃለን።

ከዚያ ግን ሌሎች የሜሴጅ አማኞች ወንድም ብራንሐም ማርች 24 ቀን 1963 ሰባተኛውን ማሕተም ሲፈታ ጌታን ወደ ምድር መልሶ ያመጣዋል ይላሉ። እርሱ ግን ሰባተኛውን ማሕተም አልፈታውም። ሰባተኛው ማሕተም እስከዛሬ ድረስ ያልተፈታ ሚስጥር ሆኖ ቀርቷል።

63-1110 አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት

የሰባተኛው ማሕተም መፈታት ጌታን ወደ ምድር ያመጣዋል።

ነገር ግን ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም።

ልብ በሉ ጌታ ሰባተኛውን ማሕተም ከእኛ ሰውሮታል። አልገለጠልንም።

64-0719M የኢዮቤልዩ በዓል
ታውቃላችሁ አይደል፤ ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም።

ሌሎች ደግሞ የጌታን ምጻት ጉዳይ የባሰ ግራ አጋቢ ሲያደርጉት በሌላ መንገድ ሊያሳዩ ሞከሩ።

የጌታ “ምጻት” ማለት ጌታ ሶኖራ በረሃ ውስጥ በሚገኘው ሳንሴት ፒክ ከታክሶን ከተማ አጠገብ በሚስጥር “መገኘቱ” (ወይም ፓሩሲያ) ነው አሉ።

“ፓሩሲያ” የሚለው የግሪክ ቃል “መገኘት” ወይም “ምጻት” የሚል ትርጉም አለው። የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ፓሩሲያ ለሚለው ቃል የመረጡት የእንግሊዝኛ አቻ ቃል “ምጻት” የሚለውን ነው። እነርሱ የኖሩበት ጊዜ በዙፋኑ ዙርያ ካሉት እንስሳት የሦስተኛው እንስሳ ማለትም የሰው ዘመን ነበር -- ይህም የሰውን ጥበብ ያመለክታል። ለመተርጎም ዛሬ እና ካለን ጥበብ የሚበልጥ ጥበብ አግኝተዋል። እኛ ደግሞ እነርሱ ከነበራቸው የበለጠ የንሥር እይታ ተሰጥቶናል።

ስለዚህ የተረጎሙት ትርጉም ስሕተት አለው ብንል ሞኞች እንሆናለን። ስሕተት አለው ካልን ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የለንም ማለት ነው።

63-1124 ሦስት አይነት አማኞች

የክርስቶስ ተቃዋሚ ቃሉን አይክድም። በፍጹም አይክድም። ቃሉን አምነዋለው ብሎ ነው የሚናገረው ነገር ግን የተጻፈውን በሙሉ እዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንዳለው አምናለው አይልም።

ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቃል ብትቀይሩ ወደ ክርስቶስ ተቃዋሚ ጎራ ትገባላችሁ።

ሌሎች ደግሞ የጌታ ምጻት ጌታ ወደያንዳንዱ ሰው በግሉ ሲመጣ ነው ይላሉ። ያ ግን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።

ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ተደጋግሞ ተከስቷል፤ ነገር ግን አንድም ጊዜ የጌታ ምጻት ነው አልተባለም።

መልአኩ ሲናገር ኢየሱስ በትንሳኤ በተገለጠበትና ወደ ሰማይ ባረገበት በዚያው አካል ተመልሶ ይመጣል ብሏል።

የሐዋርያት ሥራ 1፡11 ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።

ጌታ ግን ሙታን ሳይነሱ እንዲሁም ሕያዋን ወደ አዲሱ አካል ሳይለወጡ በፊት አይመጣም።

ስለዚህ ወደ አዲሱ አካላችሁ ሳትቀየሩ በፊት የጌታ ምጻት የለም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 … በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤

እስካሁን እንደተመለከታችሁት ስለ ጌታ ምጻት በሚናገሩዋቸው ንግግሮች ውስጥ ምን ያህል ግራ እንደተጋቡ ማስተዋል ትችላላችሁ።

ከዚያ ደግሞ ደመናው ማለት የራዕይ ምዕራፍ አስር መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነው ሲሉ የባሰ ግራ ይጋባሉ።

ስለዚህ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ በጥቂቱ ለ28 ደቂቃዎች ተገልጦ የታየው ደመና ድንገት የራዕይ ምዕራፍ አስሩ መልአክ ወደ ምድር መውረድ ተደርጎ ተተረጎመ።

64-0119 ሻሎም
ነገር ግን ልብ በሉ፤ የሞት ጥላ ምድርን ሁሉ ቢሸፍን “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ ከሞት አስነሳዋለው” የሚለውን ቃል አስቡ። ስለዚህ ታላቁ መሪ ሲወርድና በትሩን ይዞ ሲመጣ ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም”። ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር ላይ አንድ እግሩን በባሕር ላይ አድርጎ በሚቆምበት ጊዜ በራሱም በላይ ቀስተ ደመና በሚታይበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ይምላል፡- “ከዚህ ወዲያ አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲመጣ ከሙታን መካከል ተለይታችሁ ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው መቃብራቸው ውስጥ ተኝተው ሲቀሩ እናንተ ትሄዳላችሁ።

ነገር ግን እስከ 1964 ድረስ ሁሉ ደመናው ከመጣበት አንድ ዓመት በኋላ ወንድም ብራንሐም መልአኩ እስኪወርድና ሙታንን በትንሳኤ እስኪያስነሳቸው እየተጠባበቀ ነበር።

ሌሎች ደግሞ መልአኩ መጥቷል ይላሉ (ግን የት ወይም መች እንደመጣ አያውቁም)፤ ደግሞም ከዚያ ጊዜ ወዲህ ባለፉት 55 ዓመታት ውስጥ መልአኩ ምን እንዳደረገም አያውቁም።

የመጀመሪያው የ1963ቱ በታክሶን የሕዋ ምርምር ማዕከል አማካኝነት ፎቶ የተነሳው ደመና እነዚህን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትርጓሜዎች ያመጣ ሲሆን የቤተክርስቲያን አባሎቻቸው ደግሞ ትክክለኛ አስተምሕሮ አድርገው ተቀብለዋቸዋል። ከዚያ ወዲያ ደግሞ ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ ከአራት ወራት በፊት ደመናው የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ብሎ ተረጎመው። ከምድር 20 ኪሎ ሜትር በላይ ባለው ከፍታ ውስጥ ደመናን ሊፈጥር የሚችል የውሃ ትነት የለም።

65-0718 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆኑ ፈቃዱን ለማድረግ መሞከር

በዚያ የቴሌስኮፕ ማዕከል ውስጥ ሆነው ከማዕከሉ ውጭ ያለውን ዓለም ሲመለከቱ እስካሁን ምን እንደተፈጠረ በመደነቅ ይጠይቃሉ። ታክሰን ውስጥ ያሉት ትልልቅ ቴሌስኮፖች ፎቶ አንስተውታል፤ እስካሁንም ምን? ይሆን እያሉ ይጠይቃሉ። እስካሁን ድረስ በጋዜጣ ላይ “ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን?” እያሉ ይጠይቃሉ። እዚያ ሰማዩ ላይ ሠላሳ ማይልስ ከፍታ ላይ ጉም የለም፣ አየር የለም፣ እርጥበትም የለም። ኦህ ይገርማል! “በላይ በሰማይ ምልክቶች ይገለጣሉ። እነዚህም ነገሮች ሲሆኑ በልዩ ልዩ ሥፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል።” “በዚያ ቀን” ሉቃስ ውስጥ እንደሚለው “የሰው ልጅ እንደገና ራሱን ይገልጣል፤ ወይም ይገለጣል።” ከዚያ ዓለም እንደ ሰዶም እና እንደ ገሞራ ትሆናለች። ኦህ!

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

እነዚህ ሁሉ የተለያዩ አመለካከቶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል እምቢ ያሉ ሰዎችን አእምሮና የማሰብ ችሎታ ለማደንዘዝ ነው አገልግሎታቸው።

በስተመጨረሻ ሌላው ግራ የሚያጋባ ነገር ደግሞ ሁለት ደመናዎች መኖራቸው ነው። አንዱ በመላእክት ክንፍ የተፈጠረ ልእለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሲሆን ሌላው ደግሞ በሚፈነዳ ሮኬት ጭስ አማካኝነት 42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የተፈጠረ የጭስ ደመና ነው። የሜሴጅ ደመና አማኞች ሁለት ደመናዎች እንደነበሩ መጥቀስ አይወዱም።

ታላቁን ደመና በተመለከተ ይህ ሁሉ አለማመን እና ስሕተት ሊኖር የቻለው ለምንድነው?

ከደመናው ጋር በተያያዘ አስተዋዮች መስለው ለመታየት ብለው አስደናቂ አስተምሕሮ ሊፈጥሩ ባደረጉት ሩጫ የሜሴጅ ተከታዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ርቀው ሄደዋል። የእግዚአብሔርን ቃል ብርሐን መሪያቸው አድርገው አይጠቀሙም፤ ከዚህም የተነሳ የተከተሉዋቸው የደመና ትምሕርቶች ወደ ጨለማ ውስጥ መግቢ መንገድ ሆነዋል።

በደመናው ከሚያምኑ ሰዎች ጋር በሃሳባቸው አልስማማም ብትሉዋቸው ወዲያው ባሕሪያቸው ሲለዋወጥ ታያላችሁ፤ በተለይም ደግሞ ስለ ደመናው የእነርሱን እምነት የሚቃረኑ እውነታዎች የምታውቁ ከሆነ። የሜሴጅ ሰባኪ በአሁኑ ሰዓት የሚከተሉትን “የደመናውን ትምሕርት” ቢጠራጠር ወዲያው ከሰባኪነቱ እንዲወርድ ይገደዳል።

ከላይ እንዳያችሁት የደመናው ትምሕርቶች ምንም መጨበጫ የላቸውም። ትምሕርታቸውን የሚያስረዳ አንዳችም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የላቸውም። ትምሕርታቸው በየጊዜው የሚለዋወጥ የሰው አስተሳሰብ ብቻ ነው። የደመናውን ቲዎሪ ለማረጋገጥ መሞከር ጉምን ለመዝገን እንደመሞከር ነው። ትምሕርቶቻቸውን በአንድ ጭብጥ ለማያያዝ የሚያገለግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አይገኝላቸውም።

ይህ ጥናት የሎዶቅያ ቤተክርስቲያንን ዘመን ከ1906 ጀምሮ እስከ 1965 ድረስ ያለውን የሚዳስስ ነው። ስለዚህ ወንድም ዊልያም ብራንሐም ያገለገለበትን ዘመን ይሸፍናል።

ከዚህም የተነሳ ይህ ጥናት “በሰባተኛው መልአክ ዘመን” የሚል ርዕስ ሊሰጠው ይችላል -- ምክንያቱም በዚያ ወቅት በሕይት ነበረ ደግሞም እየሰበከ ነበር።

ከዚያም ብዙዎቹን ስብከቶቹን በቴፕ ቀድቶ አስቀመጠና ሄደ። ከ1966 ጀምሮ እኛ ያለብን ሃላፊነት ስብከቶቹን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመውሰድ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችን ማንበብና መረዳት እንዴት እንደምንችል መማር ነው።

ከወንድም ብራንሐም ዛሬ የቀረልን ነገር ቢኖር በቴፕ ካሴቶች ላይ የተቀረጸው ድምጹ ነው።

ስለዚህ ከ1966 ጀምሮ ወዲህ ያለውን ዘመን በቀጣዩ የሎዶቅያ ዘመን ጥናት ክፍል “የሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” የሚል ርዕስ ልንሰጠው እንችላለን።