የቤተክርስቲያን ዘመናት - ሎዶቅያ ክፍል 1 - ሰባተኛው ዘመን - ከ1906 ጀምሮ

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ሎዶቅያ ግራ የሚያጋባ ዘመን ነው።

ይህ ዘመን አስደናቂ የሳይንስ ምጥቀት ከማሕበራዊ ቀውስ እና የስሕተት ትምሕርት ከክፋው የጨለማ አሰራር ጋር በአንድነት ጣራ የነኩበት ጊዜ ነው። ምቾት የሞላው የኑሮ ዘይቤ እና ብልጽግና በተስፋፋበት ዘመን ውስጥ ብዙዎች የጭንቀት መከላከያ ክኒን እየዋጡ ነው የሚኖሩት።

በዚህ አሁን ባለንበት የቤተክርስቲያን ዘመን መቃብር ላይ የሚጻፈው ጽሕፈት እንዲህ የሚል ሊሆን ይችላል፡-
“ባገኘሁት ነገር የነበረኝ እርካታ በሌላ ጥማት የተነሳ ተወስዶብኛል።”

ስግብግብነት፣ራስ ወዳድነት፣ እና እኔነት “ሰልፊ” የተባለውን የፎቶ አነሳስ ጨምሮ የዘመናችን መገለጫዎች ሆነዋል።

ስግብግብነት መንገዳችን እንዲጠፋብን አድርጓል። የተማርን ሰዎች መሆናችን ልበ ደንዳኖችና ንፉጎች ከመሆን አያድነንም። እውነታ አድርገን የምንከተለው እውነትን ሳይሆን የዚህን ዓለም የቁም ቅዠት ነው። ከዚህ ግኡዝ ዓለም ጋር የተጠላለፍንበት ገመድ እየጠነከረ የሚሄደው መንፈሳዊ እይታችንን በማደብዘዝ ነው።

ራሳችንን ጥሩ ክርስቲያኖች አድርገን እንቆጥራለን ግን በዘመኑ መጨረሻ ስለምትኖረው ቤተክርስቲያን ማለትም ስለ እኛ አንድ መልካም ነገር የሚናገር አንድ ምሳሌ ወይም አንድ ትንቢት እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ አናገኝም። “ጎስቋላ”፣ “ድሃ”፣ “ዕውር”፣ “የተራቆትህ” የሚሉትን ቃላት እንድ አድናቆት አድርገን ካልተቀበልን በቀር ስለ ዘመናችን አንዳችም የተባለ መልካም ነገር የለም። እነዚህ ቃላት ሁሉን ማየት ከሚችለው በማንም ከማይዘበትበት አምላክ የተሰነዘሩ ጠንካራ ግሳጼዎች ናቸው።

45 000 የተለያዩ ቤተክርስቲያናትና አስተምሕሮዎች ባሉበት በአሁኑ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እንዲያምኑ ከማድረግ ይልቅ እየተባለ ያለው “እኔ የማምነውን እመኑ” ሆኖ ቀርቷል። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እነርሱ እንደሚያምኑት ካላመንክ ተገደህ ማመን እንዳለብህ ይሰማቸዋል። ይህ አይነቱ ባሕርይ ነው የሰዎችን ነጻነት ፈጽሞ የሚያጠፋው። ሌሎችን ለማሳመን ስለ እምነትህ የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች ያስፈልጉሃል። በዚህ ዘመን ያጣነው ይህ ነው።

በአስመሳይነትና በቁሳቁስ ፍቅር በተጠመደ ዓለም ውስጥ ቤተክርስቲያን ነፍሳትን ለማዳን በታላቅ ትጋትና የስሜት ግለት የምትሮጥ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ እጅግ የቀዘቀዘች ሆናለች። ከዚህ የግለትና የቅዝቃዜ ውሕደት የተነሳ ቤተክርስቲያን ትኩስም በራድም ሳትሆን ለብ ያለች እና በቡድን የምታስብ ሆናለች። ይህም ልምምድ አንድ አማኝ ከሲዖል ለመዳን ወደ ጌታ ዘወር ባለ ጊዜ በግሉ ለመጽሐፍ ቅዱስ እና ለኢየሱስ የነበረውን የቀደመ ፍቅር ይሽረዋል። ስለዚህ የዳኑ ክርስቲያኖች ወዲያው አባል የሆኑባት ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችላቸው ቅርጽ ተቀርጸው ከሁሉ ጋር ተመሳስለው ይቀራሉ። ግለሰቦች ለራሳቸው ማሰብ እንዲያቆሙ ይማራሉ። ቤተክርስቲያን መመላለስ ግለሰቡ ወደ ቤተክርስቲያን ልማዶችና ባሕሎች ውስጥ እንዲቀላቀል ያደርገዋል፤ ስለዚህም አዲሱ አማኝ ልክ በተመሳሳይ ቁመት እንደተከረከሙ የጽድ ዛፎች ከሌሎች ሰዎች ሁሉ ጋር አንድ አይነት ይሆናል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
15 በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።
16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል የሚመጣው ከእግዚአብሔረ አፍ ነው።

ከአፉ መተፋት ማለት ቤተክርስቲያኒቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት እጅግ በጣም ርቃ ሄዳለች ማለት ነው።

ቤተክርስቲያኖች ሰዎችን ለማዳን በቂ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ክምችት አላቸው፤ ነገር ግን በሌላ ጎን ደግሞ እነዚህን የዳኑ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ለመምራትም በቂ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መኃይምነት እና ስሕተት አላቸው። ለመረዳት ከባድ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መረዳት አያስፈልገንም ማለትን ለምደዋል።

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያስፈልጉናል።

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

ክርስቲያኖች ቃሉን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈ ባለበት ሊወደድ የሚገባው የከበረ ሃብት እንደሆነ አድርገው ማየት ትተዋል። መጽሐፍ ቅዱስን በፍቅር ከማንበብ ይልቅ አሁን የተለመደው በደረቁ መተንተንና መወያየት ነው። ደስ ያለንን ጥቅስ መርጠን እኛ የምንፈልገውን እንዲናገርልን ከራሳችን ፍላጎት አንጻር እንተረጉመዋለን።

እንግዲህ ሎዶቅያዊቷ ቤተክርስቲያን ማለት ይህች ናት። ሎዶቅያ ውስጥ የነበረችዋን ቤተክርስቲያን ማለታችን አይደለም

“የሎዶቅያውያን” ቤተክርስቲያን
[የሎዶቅያ ቤተክርስቲየን የሚለው KJV በሚባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ተብሎ ነው የተጻፈው]

ሎዶቅያ ማለት “የሕዝቡ መብት” ማለት ነው።

ከታላቁ መከራ ማምለጥ ከፈለግን እውነትን ማወቅ አለብን። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከሲዖል መዳናችን ከታላቁ መከራ ለማምለጥ አያበቃንም። ከሲዖል በመዳን እና ከታላቁ መከራ በማምለጥ መካከል ልዩነት አለ።

ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

ይህ መዳን ከሲዖል መዳን አይደለም። ንሰሃ በገባችሁና ኢየሱስን አዳኝ አድርጋችሁ በተቀበላችሁ ቀን ከሲዖል ድናችኋል።

ይህኛው መዳን ግን ከፊታችን ሊመጣ ካለው ታላቅ መከራ ማምለጣችንን ስለማረጋገጥ ነው።

ማቴዎስ 24፡3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ደቀመዛሙርት ኢየሱስን ስለ መጨረሻው ዘመን ክስተቶች ሲጠይቁት እርሱ በሰጣቸው መልስ ውስጥ ትልቅ ትኩረት ያደረገው ቤተክርስቲያን ስለመሳቷ ነበር።

ካሉብን አደጋዎች ውስጥ ትልቁ በቀላሉ ልንታለልና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ርቀን ልንሄድ መቻላችን ነው። እውቀት በመጠቀበት በዚህ ዘመን እየኖርን በቀላሉ ልንስት መቻላችን ይገርማል። እውቀት ቢበዛልንም ግን እውነትን ከስሕተት መለየት የምንችልበት ጥበብ ይጎድለናል።

ዳንኤል 12፡4 ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።

በመኪና እና በአውሮፕላኖች ወዲያ ወዲህ እንሯሯጣለን፤ ይህም የመጨረሻው መቃረብ ምልክት ነው።

ከሲዖል ለመዳን ብዙ ነገር ማወቅ አላስፈለገንም። ያስፈለገን ኢየሱስ ብቸኛው አዳኛችን መሆኑን ማወቅ ከዚያም ንሰሃ መግባት ብቻ ነበር።

ከታላቁ መከራ ማምለጥ ግን ሌላ ጉዳይ ነው። ከታላቁ መከራ ለማምለጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮች ስለምን እንደሚናገሩ ማወቅ አለብን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የቤተክርስቲያን ልማዳዊ ትምሕርቶችና የተሳሳቱ እምነቶች እንዳንታለል ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢሮችን በትክክል መረዳት እንድንችል ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት መመርመር ይጠበቅብናል።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16 … እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

ከዳንን በኋላ እና በጸጋ እያደግን ስንሄድ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የክርስቶስን ልብ ይሰጠናል።

የክርስቶስ ልብ ሲኖረን መጽሐፍ ቅዱስን በምንማረ ጊዜ በደምብ መረዳት እንችላለን።

ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ምድር በተመለሰ ጊዜ በምድር ላይ ብዙም እምነት አገኛለሁ ብሎ ተስፋ አያደርግም።

እምነት የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ብቻ ነው የሚመጣው።

ሉቃስ 18፡8 … ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

ስለዚህ በመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያናት የሚያምኑት እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አይችሉም።

ቤተክርስቲያን ወንጌልን በማሰራጨት ልትተጋ ትችላለች፤ ነገር ግን ይህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲወዱ አያደርጋቸውም። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ለሚመላለሱ ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ በምስጢሮች የተቆለፈ መጽሐፍ ሆኖባቸዋል። ነገር ግን ዳንኤል እንደተናገረው መጽሐፍ ቅዱስ ምስጢሩ የማይፈታው የመጨረሻው ዘመን እስኪደርስ ብቻ ነው።

ዘካርያስ 14፡7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን እንግዳ የሆነ ብርሃንም ጨለማም ያልሆነ ዘመን ነው። ቤተክርስቲያን ሰዎችን ለማዳን ወንጌልን የመስበኳን ያህል (ብርሃን) የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢትን እና ከባድ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን የመረዳት አቅም የላትም (የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት አለመረዳት የሌሊት ጨለማ ነው)። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ጥቂት እውቀት አላቸው፤ ከዚያም የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ ቸል ይላሉ። በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቸል ተብሎ እንደሚታለፍ እና የትኛውን መለወጥ እንደሚቻል እናውቃለን ይላሉ። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ለራሳቸው እንዲስማማቸው የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትተው እንደሚያልፉ፣ የትኛው ላይ እንደሚጨምሩበትና ከየትኛው እንደሚቀንሱ የራሳቸውን ምርጫ አድርገዋል፤ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑበትም ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው። ከዚህም የተነሳ 45 000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችና አመለካከቶች ተፈጥረዋል።

ሌላው ግራ የሚያጋባ ነገር ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በየቤቱ መገኘቱ ነገር ግን ከመጻሕፍት መካከል ፈጽሞ ማንም የማያነበው መጽሐፍ መሆኑ ነው።

ታላላቅ ጦርነቶች የጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን አሳዛኝ ገጽታዎች ናቸው።

ጦርነት የሰው ልጅ ከተለማመዳቸው ጥንታዊ እና ከንቱ ሥራዎች ዋነኛው ነው። ሰው ብዙ ሰዎችን በገደለ ቁጥር ይበልጥ ብዙ ሰዎችን መግደል ይፈልጋል።

የመጀመሪያው በታሪክ የተመዘገበ ጦርነት የተካሄደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1469 አርማጌዶን በተባለ ቦታ ነው።

በዚህ ጦርነት የግብጹ ቱትሞሲስ 3ኛው ሶርያዎችንና አጋሮቻቸውን ድል ነስቷል።

የመጨረሻው በታሪክ የሚመዘገበው ጦርነት የአርማጌዶን ጦርነት ሲሆን እርሱም በሦስት ዓመት ተኩሉ ታላቅ መከራ ወቅት ነው የሚደረገው። የዚያን ጊዜ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐይማኖተኞች እና ከፖለቲከኞች ጥምረት ማለትም በመጨረሻው አውሬ ፖፕ እና ፖፑ በሚያደራጃቸው አሥር ወታደራዊ ጀነራሎች የሚመሰረተውን ታላቅ ሰራዊት ድምጥማጡን የሚያጠፋው። አሥሩ የጦር ሠራዊቶች በታላቁ መከራ ወቅት ሕዝቡ በኃይልና በግዳጅ የወቅቱ ሐሰተኛ ሐይማኖት ያዘዛቸውን ሁሉ እንዲከተሉ ያደርጓቸዋል። እምቢ የሚሉ አፈንጋጮች በሙሉ ይገደላሉ።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት በሚጠናቀቀው ታላቁ መከራ ውስጥ ይወድቃል፤ ጦርነቱም ሰው እግዚአብሔርን የሚዋጋበት ነው። ይህም ጦርነት የሚደረገው ከሦስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት የመጀመሪያው ጦርነት በተደረገበት፤ ሰይጣን ሰው ከሰው ጋር እንዲዋጋ ያነሳሳበት ቦታ ላይ ነው። ስለዚህ ጦርነት በጀመረበት ቦታ ላይ ያበቃል። ይህም የሚያሳየው ሰዎች በሦስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ልምድ ውስጥ ምንም ቁምነገር እንዳልተማሩ ነው። ይህን ስናስብ በምድር ላይ ያለን ጊዜ ወደ ማብቂያው መድረሱ አያስደንቀንም። እግዚአብሔር እንኳ የሰዎችን አለማስተዋል ለተወሰነ ጊዜ ካየ በኋላ ይበቃል ይላል። አልበርት አይንሽታይን ከዚህ ፍጥረታዊ ዓለም ውስን ገጽታዎች መካከል ወሰን የሌለው የሰዎች አለማስተዋል ብቻ ሳይሆን አይቀርም ብሎ ነበር።

አርማጌዶን ማለት “ወራሪ ተራራ” ነው።

ነብዩ ዳንኤል የማንም ሰው እጅ ያልፈነቀለው ድንጋይ አሕዛብን የሚወክለውን ምስል እግሩ እና አሥር ጣቶቹ ላይ ሲመታው አይቷል። ምስሉም ተሰባበረ።

ዳንኤል 2፡33 ጭኖቹም ብረት፥ እግሮቹም እኩሉ ብረት እኩሉም ሸክላ ነበረ።
34 እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ።

ድንጋዩም አድጎ ታላቅ ተራራ ሆነ። ስለዚህ ሦስተኛው የጌታ ምጻት ኃይላቸውን ለአውሬው አሳልፈው በሚሰጡት በአሥሩ የጦር ጀነራሎች ላይ ወረራ ለማካሄድ ነው።

ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

እንደ ነገሥታት ሥልጣን ይኖራቸዋል። አልተሾሙም፤ ዘውድም አልጫኑም ግን እንደ ነገሥታት ይገዛሉ። አምባገነን ገዢዎች ናቸው። ለሦስት ዓመት ከግማሽ በሚቆየው የታላቁ መከራ ወቅት እግዚአብሔር ለአጭር ጊዜ (ለአንድ ሰዓት) ኃይል ይሰጣቸዋል።

ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

ፖፑ የቤተክርስቲያን አምባገነን መሪ ነው። በስተመጨረሻ ሰይጣን ያስነሳው ሃያል ሰው ሐይማኖታዊ ኃይልን እና የገንዘብን ኃይል ከቫቲካን ይነጥቃል (ቫቲካን በምድር ላይ ካሉ የከተማ መንግስታት ሁሉ ትንሽዋ ናት - ማለትም ዳንኤል ውስጥ “አንድ ታናሽ ቀንድ” የተባለው)፤ ከነጠቀ በኋላ የመጨረሻው ፖፕ ሆኖ ይገለጣል። እርሱም የአውሬው ቤተክርስቲያናት ዋና ራስ ይሆናል። ምናልባትም ራሱን ዳግማዊ ጴጥሮስ ብሎ ሊጠራ ይችላል፤ ምክንያቱም ካቶሊኮች በሐሰት ጴጥሮስን የመጀመሪያው ፖፕ ብለውታል። (ነገር ግን የሮም ጳጳስ ራሱ ፖፕ ተብሎ መጠራት የጀመረው በ400 ዓ.ም. ነበር።)

ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።

ይህ በስተመጨረሻ ሥልጣን የሚወስድ ፖፕ በካርዲናሎች ጉባኤ ተመርጦ አይደለም ወደ ሥልጣን የሚወጣው።

አሥሩ አምባገነን የጦር ጀነራሎች የሚያቀርብላቸውን የሥልጣን ጥያቄ በቀላሉ ይቀበላሉ፤ በእጃቸው ያለውንም ወታደራዊ ኃይል እና ሥልጣን በእጁ ያስረክቡለታል፤ እርሱም ምድርን ሁሉ በአምባገነንነት ይገዛል። እነዚህ አሥር አምባገነን ጀነራሎች በምድር ላይ በልዩ ልዩ ሥፍራ ተመድበው የተሰጣቸውን ግዛት ስለሚቆጣጠሩ አመጽን ወይም ተቃውሞችን አፍኖ ለማስቀረት ሠራዊቶቻቸውን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ አያስፈልጋቸውም። ዘመናዊ የጦር ሠራዊትን ከአሜሪካ አንስቶ ራቅ ወዳለ ሃገር ለማንቀሳቀስ ቢያንስ ስድስት ወር ይፈጃል። ሁለት ወይም ሦስት የተለያየ ቦታ አመጽ ቢነሳ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ከዚያ በላይ አመጽ ለመከላከል አቅም የለውም። ስለዚህ አሥር ጀነራሎች በምድር ላይ በተለያየ ቦታ ቢሰፍሩ ዓለምን ሁሉ በአንድ ጊዜ መቆጣጠር የሚችል ዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል መዘርጋት ይችላሉ። ነገር ግን ዓለምን ሁሉ የሚገዛ አንድ መንግሥት ለመመስረት በመጨረሻው ፖፕ የሚመራ ማዕከላዊ ዕዝ ያስፈልጋል።

ዳንኤል 2፡34 እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ።
35 … ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ።

የዳኑትን ሰነፍ ቆነጃጅት ወይም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን በታላቁ መከራ ውስጥ የሚያጠፋቸው የመጨረሻው ፖፕ ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ፖፑ ከነጦርሠራዊቱ በአርማጌዶን ጦርነት ይጠፋል።

ከዚያም ኢየሱስ ዓለምን ሁሉ የሚገዛ እውነተኛ መንግሥት ይመሰርታል። የመንግሥቱም ዋና ከተማ በኢየሩሳሌም ይሆናል፤ የክርስቶስም ሙሽራ ዓለምን ትገዛለች።

ሉቃስ 19፡16 የፊተኛውም ደርሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው።

17 እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።

ተራራው መንግሥትን ይወክላል። ይህም መንግሥት ኢየሱስ ከሙሽራይቱ ጋር ዓለምን ለ1000 ዓመት በሰላም የሚገዛበት መንግሥት፤ ማለትም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጣችዋ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ናት።

ፐሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌምን የእሥራኤል ዋና ከተማ ብሎ እውቅና ሲሰጥ በእርሱ ላይ የተነሳበት አጋንንታዊ ጥላቻ ምክኒያቱ ምን እንደሆነ ለመገመት አይከብድም። ይህ እርምጃ ለሰይጣን በምድር ላይ ያለው ጊዜ እያለቀበት መሁኑን ያመለክተዋል። አሁን አይሁዳውያን ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውና ዋና ከተማቸውን መያዛቸው ለክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጊዜያቸው እያለቀ መሆኑን በግልጽ ስለሚያመለክታቸው አጋንንት የብዙ ሰዎችን ነፍስ የማጥፋት ጥድፊያ ውስጥ ገብተዋል። አጋንንት አዳም ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ ለ6000 ዓመታት ዓለምን ገዝተዋል። ጊዜያቸው እያከተመ መሆኑን ሲያውቁ ምን ያህል እንደሚበሳጩ መገመት አያቅታችሁም።
በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ እሥራኤል ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ጥላቻ ሞልቷል።

ሳይፕረስ (ቆጵሮስ) በቱርክ ተያዘች። ቲቤት በቻይና ተያዘች። ክሪምያ፣ ጆርጂያ በከፊል እና ዩክሬይን በከፊል በራሺያ ተያዙ። ሶርያ ውስጥ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሕዝቡ ላይ የክሎሪን ቦምብ ተጣለባቸው። ቻይና ተቃዋሚዎችን ታሰቃያለች። ቬኔዝዌላ ውስጥ ምግብ ለሕዝቡ በደምብ እንዳይዳረስ እገዳ ይደረጋል። በርማ ውስጥ አናሳ ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ይደረጋል። በ2000 ዓ.ም. አካባቢ ኮንጎ ውስጥ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ተገድለዋል። ፊሊፒንስ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ዕጽ በመጠቀምና በማዘዋወር የተጠረጠሩ ሰዎች ይገደላሉ። አይ.ኤስ.አይ.ኤስ በሶሪያ እና በኢራቅ ውስጥ ብዙ ሰዎችን በግፍ ይገድላል። ስለዚህ በዓለም ላይ ሰላምን እና ጸጥታን ለማስፈን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኤጀንሲ የቁጣውን መዓት እሥራኤል ላይ ያራግፋል። እሥራኤል የዓለም አቀፍ ጥላቻዎች ሁሉ ማራገፊያ ሆናለች።

በሎዶቅያ ዘመን ትክክለኛ እርምጃ ተደርጎ የሚቆጠረው መረጃዎችን አጣሞ መተርጎም እና አይሁዶችን መጥላት ነው።

የሜሴጅ አስተምሕሮ አራማጆች ትምሕርት መሰረቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይሆን የዊልያም ብራንሐምን ንግገሮች አሳስቶ መተርጎም ሆኗል (ለምሳሌ የ2016 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውስጥ ሒላሪ ታሸንፋለች)።

ወንድም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ሰጥተዋል ብሎ አያውቅም። ነገር ብን ብዙዎቹ የሜሴጅ አስተምሕሮ ተከታዮች ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል ይላሉ። በዚህም ሐሳብ ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እምነታቸውን ይመሰርታሉ፤ እንዲህ ማድረጋቸውም የሜሴጅ ቡድኖች እንዲከፋፈሉ ምክንያነት ሆኗል።

ኢየሱስ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ብሏል። እኛ ግን አልሰማነውም። ከእርሱ ይልቅ የሳቱትን ደግሞም በተከታዮቻቸው ላይ ገዥ መሆን የሚፈልጉትን የሜሴጅ አስተማሪዎችን መስማት መርጠናል። ሥልጣን ሱስ ያስይዛል፤ ገንዘብም ሱስ ያስይዛል።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን በገንዘብና በቁሳቁስ በጣም የተባረከች የበለጸገች በመንፈስ ግን በጣም የደኸየች ቤተክርስቲያን ናት፤ በጣም የሚያሳዝነውም ነገር በመንፈስ መደሕየቷን አለማወቋ ነው።

የዚህ ዓለም ሃብት የተዛባ ክፍፍል 90 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ 10 በመቶ በሚሆነው ሕዝብ እጅ ውስጥ እንዲቀር አድርጓል። እኩልነትና ፍትሕ ባለመኖሩ ጥቂቶች ብቻ በትድላ ይኖራሉ። እኩልነት አለመኖሩ መተማማን እንዲጠፋ ያደርጋል። ከዚህም የተነሳ ሰዎች ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ሲመጣ ለሁሉም ሥራ ስለሚሰጥ ሐብት በእኩልነት ያከፋፍላል ብለው ያምናሉ። ጀርመኖች ሒትለርን የመረጡር ለዚህ ነው።

ነገር ግን ይህ ጥሩ ሥርዓት አይደለም።

ሮም ዓለምን ስትቆጣጠር ብዙ ሰዎች ለሮም ሥርዓት ተገዢዎች ይሆናሉ፤ ምክንያቱም ሮም ለሰዎች ሁሉ መተዳደሪያ ሥራ ለመስጠት የዓምን የኢንዱስትሪ እና የምርት ዘርፍ ትቆጣጠራለች።

የመጨረሻው ፖፕ የዓለምን ሁሉ ኢኮኖሚ ይቆጣጠራል። ይህም እስከ ዛሬ ከሆነው የሚብስ ኢፍትሐዊ የሐብት ከፍፍልን ከማስከተል አልፎ የዓለማችንን ካፒታሊስት ስልጣኔ መጥፊያ ይሆናል።

ዳንኤል 8፡23 በመንግሥታቸውም መጨረሻ፥ ኃጢአታቸው በተሞላች ጊዜ፥ እንቈቅልሽን የሚያስተውል ፊተ ጨካኝ ንጉሥ ይነሣል።

ዳንኤል ሰይጣን በስተመጨረሻ ስለሚያስነሳው ኃያል ሰው ሲናገር እንዲህ ይላል።

ዳንኤል 8፡24 ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፤ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፤ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል።

የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ የአሥር አምባገነን ጀነራሎች ወታደራዊ ኃይል ይሰጠዋል፤ በዚህም ኃይል ተጠቅሞ ዓለምን ያንበረረክካል።

እርሱም ከአይሁዶች ጋር ቃልኪዳን በመግባት በኒው ዮርክ ዎል እስትሪት እስቶክ ኤክስቼንጅ ያከማቹትን ገንዘብ ይቆጣጠራል። ከአይሁዶች ጋር የገባውን ቃልኪዳን ባፈረሰ ጊዜ አይሁዶቹ በእስቶክ ኤክስቼንጅ ውስጥ ያላቸው ገንዘብ በሙሉ ከነኢንቨስትመንቶቻቸው ጋር ይወድማል።

ዳንኤል 8፡25 በመታለሉ ተንኰልን በእጁ ያከናውናል፤

ተንኮሉ የእጅ ሥራ ነው፤ ማለትም ማምረት።

የአሜሪካ ኢኮኖሚ ሲወድቅ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ሥራ አጦች ሆነው ይንከራተታሉ። ከዚያ በኋላ አሜሪካን ለማስተዳደር የሚበቃ ገንዘብ ማዋጣት የምትችለው ሮም ብቻ ትሆናለች። ከ 1.2 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ተከታዮችን እንደመሳቧ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ ቆንጅዬ ሴት ልትቆጠር ትችላለች። ቤተክርስቲያኒቱ ከባድ የጭካኔ ታሪክ አላት። እንድ ቆንጅዬና ጨካኝ ሴት ሆና አሜሪካን ትገዛለች። አሜሪካ ውስጥ ፕሬዚደንት ሩዚቬልትና ጀርመኒ ውስጥ ሒትለር ለሥራ አጥ ሰዎች ሥራ ለመስጠት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ነድፈው ነበር። ብዙ ፋብሪካዎችን በመክፈትና ሥራ ለብዙዎች በመስጠት ራሺያ በኑክሊየር ኃይል አሜሪካን እስከምታጠፋበት ጊዜ ድረስ የሮማው ፖፕ አሜሪካን ይገዛል።

ጀቫቲካኖች ጥሬ ገንዘብ፣ ወርቅ እና ብዙ ሃብት አላቸው። በዎል እስትሪት ያለው የእስቶክ ኤክስቼንጅ ገንዘብ የአይሁዳውያን ነው። ስለዚህ የመጨረሻው ፖፕ ገንዘባቸውን በቁጥጥሩ ስር ማድረግ ይችል ዘንድ ከአይሁዳውያን ጋር ቃልኪዳን ያደርጋል።

የዓለም ሁሉ የምርት ኢንዱስትሪዎች በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ስር ይሆናሉ።

63-0318 THE FIRST SEAL
ቫቲካንን በመቶ ቢሊዮን ቢሊዮን ዶላር ልትገዙ አትችሉም። ለምን መሰላችሁ፤ እስቲ አንዴ አስቡበት። መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል መሰላችሁ “የዓለም ሁሉ ሃብት በእርሷ ውስጥ ነው ያለው”።

በአቶሚክ ቦምብ ከመጋየቷ በፊት ባቢሎን (ሮም) ታላቅ ሃብት የሞላባት ከተማ እንደሆነች ነው የተገለጸችው፤ ይህም ሃብት ከወርቅ፣ ከእንቁዎች እና ከንግድ ወይም ኢንቨስትመንት እንዲሁም ከ 1.2 ቢሊዮን ተከታዮችዋ የሰበሰበችው ነው።

ራዕይ 18፡10 አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ … ባቢሎን፥ … በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና … ።

12 ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥
13 ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።

63-0318 THE FIRST SEAL
ቤተክርስቲያን ከተወሰደች በኋላ ሮም እና አይሁዶች እርስ በርሳቸው ቃልኪዳን ይገባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ከቅዱሳን ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ። አሁን እንግዲህ ልብ በሉ፤ ልክ እንደተጻፈው ቃልኪዳን ያደርጋሉ። ለምን? ይህች ሃገር አሜሪካ ጉዷ ፈላ፤ ሌሎች የገንዘባቸውን ዋጋ በተቀማጭ ወርቅ የሚተምኑ ሃገሮችም ሁሉ ጉዳቸው ፈላ። ለግብር በተከፈለ ገንዘብ የምንኖር ከሆነ እና የሰዎች ሁሉ እዳ ለአርባ ዓመታት ሳይከፈል ከቆየ ምን ልንሆን ነው? አንድ ነገር ብቻ ነው ሊደረግ የሚችለው። ይህም ገንዘብን ከገበያው ላይ መሰብሰብ እና ያልተከፈሉ ቦንዶችንና እዳዎችን ሁሉ መክፈል ነው፤ ይህን ደግሞ የማድረግ አቅም የለንም። ቦንድ በሙሉ በዎል እስትሪት እጅ ነው ያለው፤ ዎል እስትሪት ደግሞ በአይሁዶች ቁጥጥር ነው ያለው። ከዚያ የተረፈው በሙሉ በቫቲካን እጅ ነው።

ልክ እዚህ ኩባ ውስጥ እንዳለው ሰውዬ (ስሙ ማን ነበረ?) ካስትሮ እንዳደረገው ማለት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በማስተዋል የወሰደው እርምጃ ቢኖር የመገበያያ ሰነዶች ወይም ቦንዶችን ማጥፋቱ ነው። ልብ በሉ፤ እኛ ግን እንዲህ ማድረግ አንችልም። እነዚህ ሰዎች እንዲሁ አይለቁንም። የምድር ሃብታም ነጋዴዎች ቦንዱን በእጃቸው ይዘዋል፤ ስለዚህ ሊደረግ የሚችለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቦንዱን በሙሉ በሙሉ መክፈል ትችላለች። እሷ ብቻ ናት ይህን የሚያህል እዳ ለመክፈል የሚበቃ ገንዘብ ያላት። ደግሞ ለመክፈል አቅሙ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱም አላት።

ይህንን እዳ በምትከፍልበት ጊዜ ከአይሁዳውያን ጋር ቃልኪዳን ውስጥ ትገባለች፤ ከአይሁዳውያን ጋር ይህንን ቃልኪዳን በምታደርግበት ጊዜ… አሁን ልብ በሉ ምክንያቱም ይህን ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወስጄ ነው የምናገረው። ስለዚህ ይህን ቃልኪዳን በምታደርግበት ጊዜ ዳንኤል 2፡23 እና 25 ላይ እንደምናየው ፖፑ የኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጨምር ያደርጋል።

ይህንን ቃልኪዳን ከአይሁዳውያን ጋር ካደረገ በኋላ በሦስት ዓመት ተኩል መሃከል ላይ የአይሁድን ገንዘብ ጠቅልሎ በእጁ ካስገባ በኋላ ቃልኪዳኑን ያፈርሰዋል። ቃልኪዳኑን ባፈረሰ ጊዜ እስከ ቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ድረስ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይባላል፤ ምክንያቱም እርሱና ልጆቹ በክርስቶስ እና በቃሉ ላይ በጠላትነት ስለሚነሱ ነው።

ገንዘቡን በሙሉ ጠቅልሎ በእጁ ባስገባ ጊዜ ዳንኤል በመጽሐፉ እንደተናገረው ከአይሁዳውያን ጋር የገባውን ኪዳን ያፈርሰዋል፤ የሚያፈርሰውም ዳንኤል በተናገረው ሰባ ሱባኤ የመጨረሻው ሱባኤ እኩሌታ ላይ ነው። ከዚያ በኋላ ምን እንደሚያደርግ ታውቃላችሁ? የዓለምን ሁሉ ንግድ እና ገበያ በሙሉ በመቆጣጠር ከዓለም ሁሉ ጋር ስምምነት ያደርጋል፤ ምክንያቱም የዓለምን ሁሉ ሃብት በእጁ ያስገባል።

የዘመን ፍጻሜ ክስተቶች ከገንዘብ ማሰባሰብ ጋር በጥብቅ የተቆራኙ ናቸው።

ዳንኤል 11፡20 የዚያን ጊዜም በመንግሥቱ ክብር መካከል አስገባሪውን የሚያሳልፍ በስፍራው ይነሣል፤ ነገር ግን በቍጣው ሳይሆን በሰልፍም ሳይሆን በጥቂት ቀን ይሰበራል።

ይህ ትልቅ ሃብት የሚሰበሰብበት አዋጭ መንገድ ነው።

ሃብት በሙሉ በአንድ ቦታ ሲቆለል ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍልን የባሰ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ስለዚህ የተሰበሰበው ገንዘብ ዓለምን በአንድ የሚያስተሳስር ኢኮኖሚያዊ ኢንዱስትሪ ሲፈጥር የዘመኑ መጥፊያ መውደቂያው መንገድ የሚሆነው ገንዘብ ነው።

የመጀመሪያዋ የአሕዛብ የሐይማኖት እና የገንዘብ ሥርዓት ምንጭ የሆነችው ባቢሎን በወርቅ ራስ ተመስላለች። እንደ ሥላሴ ያሉ ወርቃማ ሃሳቦች በዲሴምበር 25 በሚከበረው በዓል ቀን የፀሐይ አምላክ የልደት ቀን ሲከበር ዛፎችን አድምቀዋል፤ በዙርያ የሚገኙ በጦርነት የተሸነፉ ሕዝቦች ሃብት ተዘርፏል።

እግዚአብሔር ግን ባቢሎን በሚዛን ተመዝና ቀልላ እንደተገኘች አጋልጧታል። ይህ የተዛባ ሚዛን መሆን ነው፤ በአንድ በኩል በጣም ብዙ በሌላ በኩል ደግሞ በጣም ትንሽ።

የሃብት ሚዛን ሲዛባ ለሰይጣን ትልቅ በር ይከፍትለታል።

ከዚያም ሰይጣን ያስነሳው ኃይለኛ ሰው ፖፑ ወደ ሥልጣን ይወጣል።

ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።

ከዚያ የሰዎችን አእምሮ በሐይማኖታዊ ሃሳብ የሚቆጣጠረው የአውሬው ምልክት ወደ ሥልጣኑ ይወጣል።

ራዕይ 13፡16 ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥
17 የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።

በዚያን ጊዜ የፖለቲካዊ-ሐይማኖታዊ-ቤተክርስቲያን ድርጅት አካል ካልሆናችሁ በታላቁ መከራ ወቅት ሥራ ሰርታችሁ ገንዘብ እያገኛችሁ መኖር አትችሉም።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

ምቹ በሆኑት የቤተክርስቲያን ወንበሮች ላይ ተደላድለን ተቀምጠን በመብራት ካሸበረቀው መድረክ ላይ በዲስኮ ሙዚቃ እና በተለያዩ መዝናኛዎች ታጅቦ እግዚአብሔር ተዓምራትን እየሰራ እንዲያዝናናን እንጠብቃለን። የምንኖረው ስነልቦናዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የሚቀርቡ ራስን ስለማሻሻል ከሚሰጡ ትምሕርቶች በምንም ያልተለዩ አነቃቂ ስብከቶችን በመስማት ሆኗል። ነገር ግን ልክ እንደ ስሜት አነቃቂ ስብከቶች ሁሉ የአዝናኝ ፕሮግራሞችም ዋጋ ወዲያው እየተጠፋ ይሄዳል። ሁል ጊዜ ራስን ስለማሻሻል ከመማር የተሻለ ቁምነገር የተሞላ ትምሕርት ያስፈልገናል። የመንፈሳዊ እድገት ሚስጥር ራስ ላይ ማተኮር አይደለም።

የዛሬዋ ዘመናዊ ቤተክርስቲያን እና በአዲስ ኪዳን የተመሰረተችዋ የመጀመሪያዋ በመከራ በስደት በድሕነት እና በብዙ ተግዳሮት ውስጥ ያለፈችዋ ቤተክርስቲያን በመካከላቸው ያለው ልዩነት በጣም እየሰፋ ሄዷል።

ኢየሱስ አዳኝ እንደሆነ ለዓለም የምትሰብከው ነገር ግን እራሷ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል ከቤተክርስቲያን ውስጥ አውጥታ የጣለችዋ “የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን”።

“የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ቤተክርስቲያን የተባለችው ለዚህ ነው። “የኢየሱስ ቤተክርስቲያን” አይደለችም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከውጭ ነው የቆመው።

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው፤ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ …

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ የሚያሳዝን ጥቅስ ነው። ኢየሱስ ስለ እርሱ ከምትሰብክ ቤተክርስቲያን ተገፍቶ በውጭ ቆሞ።

ልብ በሉ፤ ለመግባት የሚለምነው ግለሰብን ነው እንጂ ቤተክርስቲያንን በሙሉ አይደለም። ቤተክርስቲያኖች በቡድን ማሰብ በመጀመራቸው ከእግዚአብሔር ቃል ርቀው ሄደዋል።

ለምሳሌ፤ የጌታን ልደት እንድናከብር የሚነግረን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማግኘት ሞክሩ። “ክሪስማስ” “የገና ዛፍ” ወይም “ዲሴምበር 25” የሚሉ ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጋችሁ አግኙ።

ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥

ስለዚህ ሰብዓ ሰገል ስጦታ ይዘው ሲሄዱ የገቡት ወደ ቤት ውስጥ ነው፤ በዚያም ማርያም ብቻ ነበረች። ስጦታ ይዘው ሲመጡ በረት ውስጥ ወደ ነበረ ግርግም አልሄዱም። ይህንን ማመን በዓመት ውስጥ ከፍተኛ ንግድ ከሚጧጧፍበት ወቅት ጋር ያጣላችኋል።

ስለዚህ ትልቅ የገንዘብ ኃይል ሰዎችን ይገዛቸዋልና ሐሰተኛ የሆነ የበዓል አከባበር የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተክቷል።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከሚፈልጉት በላይ ስጦታዎችንና በጌጣጌጥ ያሸበረቁ የገና ዛፎችን ይፈልጋሉ። “በሃብት በልጽጌያለው” ማለት የሎዶቅያ መለያ ነው፤ በዚህ የተነሳ ነው ስጦታ አብዝተው የሚወዱት።

ጳውሎስ በዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚከበረውን “ዩልታይድ” የተባለ የፀሐይ አምላክ ክብረ በዓል ሲያስብና ክርስቲያኖች ታላላቅ ዓመታዊ በዓሎችን ሲያከብሩ በማየቱ እነርሱን በማስተማር በከንቱ ደክሞ እንዳይሆን ሰግቷል። ዲሴምበር 25 የዓለማዊ ባርነት አንዱ መገለጫ ነው፤ ያውም ለባቢሎናውያ እምነቶች ባርያ የመሆን ምልክት ነው።

ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?

10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።

ዲሴምበር 25 በየዓመቱ የክሪስማስ በዓል ቀን ነው። አሕዛብ የዩል ቀን ብለው ያከብሩት ነበር፤ እርሱም የፀሐይ አምላክ ዳግመኛ ተወልዶ በሰማይ ላይ ከፍ ብሎ የሚያበራበት ጊዜ ነው። “ዩል” ጥንታዊ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ሕጻን” ማለት ነው።

ገላትያ 4፡11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ በዓላትን የማክበር ልማድ አልነበራትም።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ግን የአሕዛብ የፀሐይ አምላክ የተወለደበት ቀን ላይ የኢየሱስን ስም ለጥፋበታለች። ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ደግሞ ደስ እያላቸው ይታለላሉ። የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ምርጫዋ የጳውሎስን ትምሕርት ጥላ መሄድ ነው፤ ምክንያቱም ጳውሎስ የሴቶች መብት ደጋፊ አልነበረም የሴት ሰባኪዎችም ደጋፊ አልነበረም።

1ኛ ጴጥሮስ 3፡1 እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ [ለ]ባሎቻችሁ … ተገዙላቸው
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡12 ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።

ሴቶች እንዲያስተምሩ በፍጹም አልተፈቀደም! ይህ እውነት ብቻውን ብዙ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖችን ያስቆጣቸዋል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን መመሪያቸው አድርገው መከተል አቁመዋል። ክሪስማስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ነው።

ሦስት የጥበብ ሰዎች በረት ውስጥ ነበሩ ብሎ በውሸት ማስተማር እና ከዚያም ከአሕዛብ ልማድ የተኮረጀ ደግሞም ከበረቱ ጋር ምንም ዝምድና የሌለው “የገና ዛፍ” መጨመር መጽሐፍ ቅዱስን ፊት ለፊት የሚቃወም ልማድ ነው።

ኤርምያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና።
3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

እግዚአብሔር በወርቅ እና በብር ባሸበረቁ ዛፎች እንደማይገረም ኤርምያስ በግልጽ ተናግሯል።

ቤተክርስቲያኖች ግን ዛሬ ክሪስማስን በዓመቱ ውስጥ ከሚከበሩ በዓላት ሁሉ በላይ ቅዱስ በዓል እንደሆነ ይቆጥራሉ።

ከዚያም ብሶ ዲሴምበር 25 እሥራኤል ውስጥ የክረምት አጋማሽ እና ከባድ ብርድ ያለበት ወቅት ነው። በዚያ ጊዜ በምሽት አንድም እረኛ ከበጎቹ ጋር ከቤት ውጭ አያመሽም። ከቤት ውጭ ቢያመሹ በሕይወት መትረፍ አይችሉም። ይህም ክሪስማስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ ነው።

ሉቃስ 2፡8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

ሉቃስ 2፡16 ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።

እነዚህ እረኞች ከበጎቻቸው ጋር በሌሊት ውጭ ሜዳ ላይ ነበሩ፤ ስለዚህ ወቅቱ የክረምት አጋማሽ አልነበረም።

ግን እኛ በሎዶቅያ ዘመን ውስጥ የምንኖር ግድ ይለናል? በጭራሽ። ማን ግድ የሚለው አለ? እንዲሁ ክሪስማስ ታላቅ በዓል ይመስለናል።

እግዚአብሔርን ማምለክ የራሳችንን መብት መከተል፤ የምንፈልገውን ማድረግ መስሎናል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን

አስተውሉ፡- ሎዶቅያ ማለት የሕዝብ መብት ነው።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን -- የሕዝቡ ቤተክርስቲያን። ሕዝቡ ለራሳቸው የተከሉዋት ቤተክርስቲያን ማለት ነው።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

ሴት ቤተክርስቲያንን ነው የምትወክለው።

ዘመናዊ ሴቶች በሰዎች ፊት ቆንጆ ሆነው ለመታየት በሰው ሰራሽ መዋቢያዎች ነው የሚጠቀሙት። ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖችም ለሰዎች ማራኪ ሆነው ለመታየት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ትምሕርቶች ያበጃሉ። ለሰዎች የሚያስተምሩት ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ነው።
አሁን እኛ ያለንበት ዘመን የራሱን የቤተክርስቲያን ሥርዓት አበጅቷል።

እግዚአብሔርን በራሳችን መንገድ እናገለግላለን። እግዚአብሔር በወጎቻችን እና በልማዶቻችን የሚገረም ይመስለናል ምክንያቱም እግዚአብሔርን በፈለግነው መንገድ የማምለክ መብት አለን።

ዲስኮ ሙዚቃ ስለምንወድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድራም አስገብተናል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለ ድራም አንዳችም አይናገርም። ግን ምን ቸገረን? ድራም እና ዲስኮ መደነስ እንወዳለን።

በዘመናዊ አስተሳሰብ መሰረት 45¸000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በየራሳቸው ልዩ መንገድ እግዚአብሔርን የማምለክ መብት አላቸው።

የምን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሙጭጭ ማለት ነው -- ልማዶቻችንን የመከተል እና የፈለግነውን የማድረግ መብታችን የተጠበቀ ነው።

እስፖርተኞች የጨዋታ ሕጎችን በትክክል የሚያስከብሩ ዳኞችን ይነቅፋሉ። እስፖረተኞች ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ሲሉ ሕግ መጣስ እንደሚችሉ ያምናሉ። በተመሳሳይ መንገድ ቤተክርስቲያኖችም ስሜታቸውን ወይም መብታቸውን የተጋፋ ሲመስላቸው መጽሐፍ ቅዱስን ይነቅፋሉ ወይም ቸል ይላሉ።

የመጨረሻው ዘመን መላ ቅጡ የጠፋው ባሕርይ ይህ ነው። ሰዎች ለአንድ ሰው መብት መከበር ሲሉ የፈለጉትን ጥፋት መፈጸም ይችላሉ።
የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ማለት ይህ ነው።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ሰዎች ግራ የተጋቡ፣ በሃሳብና በመረዳት እርስ በእርስ የሚጣረሱ፣ ቁጠኞች፣ ለመብታቸው ተሟጋቾች፣ ፈሪዎች፣ ጭንቀታሞች፣ የሚቆዝሙ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያላነበቡ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የሌላቸው ናቸው፤ ምክንያቱም የሚያምኑበትን ሃሳብ የሚደግፉላቸውን ጥቅሶች ብቻ ነው የሚያነቡት። የቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ አላስፈላጊ ዝርዝር፣ አፈታሪክ ወይም እርስ በርሱ የሚጋጭ እንደሆነ ተቆጥሮ ቸል ይባላል። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ልጆች የማያውቋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አያነቡዋቸውም። በዚህ ምስጋና ቢስ ዘመን ውስጥ ቃሉን አለማንበብ በእግዚአብሔር ፊት አሳዛኝ ባሕርይ ነው።

ገንዘብ፣ ትዕቢት፣ ራስ ወዳድነት፤ እነዚህ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የምታመልካቸው ሥላሴዎች ሲሆኑ ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ዕለታዊ የኑሮ ሃሳብ እያሳተ ይዞዋቸው ይሄዳል።

“ቤተክርስቲያናዊነት” ሥልጣን፣ ትርፍ እና ተራ ውድድርን ያማከለ ሐይማኖት ነው።

መሪዎች በሐይማኖታዊ መሰላል ላይ ከፍ ብለው ይወጣሉ፤ ከሚገኘው የገንዘብ ትርፍም ድርሻቸውን ያገኛሉ።

ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በከፊል ብቻ ያምናሉ። ከዚህም የተነሳ መኃይምነት፣ መሰረት የሌለው ምኞትና የተጣመመ ትምሕርት በአንድነት ሆነው የወንጌል እውነት ተደርገው ይወሰዳሉ። እኛም ቤተክርስቲያን የምትሰብከውን ሁሉ እናምናለን።

1963 እግዚአብሔር አሜሪካ ውስጥ ለዊልያም ብራንሐም ከሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር የገለጠበት ዓመት በመሆኑ ቁልፍ ዓመት ነው። ፌብሩዋሪ 28/1963 በፍላግስታፍ ከተማ ኖርዝ አዘሪዞና ውስጥ ፀሐይ በምትጥልቅበት ሰዓት ላይ ከ43 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የተነሳ ፎቶግራፍ አይተው የሜሴጅ ተከታዮች ፎቶው ላይ ያለው ምስል በራዕይ ምዕራፍ አሥር ውስጥ ያለው ታላቅ መልአክ ከደቡብ አሪዞና 200 ማይልስ ርቆ ወደሚገኘው ወደ ሳንሴት ፒክ ሲወርድ ነው ብለው ያምኑ ነበር። ፎቶውን ያዩ ሰዎች መልአኩ ዊልያም ብራንሐምን ሊያነጋግር ሲወርድ ነው ይላሉ። ነገር ግን ዊልያም ብራንሐም እዚያ ቦታ ላይ የተገኘው ደመናው ፎቶ ከተነሳ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው፤ ቦታውም ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ ወዲያ ነው። እርሱም ወደዚያ የሄደው ጃቨሊና የተባለ የአሳማ አይነት ለማደን ነው። የአደን ወቅት ማርች 1 ላይ ተከፈተ፤ ማለትም ደመናው ከታየ አንድ ቀን በኋላ። ማርች 4 ላይ ዊልያም በሂውስተን ቴክሳስ ከሳንሴት ፒክ 1000 ማይልስ የሚርቅ ቦታ ላይ ስብከት ሰበከ። በዚህም ምክንያት ወደ ሳንሴት ፒክ የመጣው ማርች 6 ላይ ነው። እርሱም ሁለት ወራት ያህል እስኪያልፉ ድረስ ስለ ደመናው ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም።

ቦታዎቹ እና ቀኖቹ ምን ያህል እንደተዛቡ አስተውሉ።

ከዚያ በኋላ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ዊልያም ብራንሐም ደመናው የሚያሳየው ሰባት መላእክት በማርች 8 ጠዋት ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ እንደሆነ አድርጎ ማሰቡ ነው።

መላእክቱ ከእርሱ ተለይተው ሲሄዱ አንዳችም የታየ ደመና አልነበረም።

ማንም ቀኖቹን እና ቦታዎቹን አልመረመረም።

ሜሴጅ አማኞች ለነብይ እርማት መስጠት አይቻል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ደመናው የታየበት ፌብርዋሪ 28 ቀን ለምን የአደን ወቅት ከመከፈቱ ሊቀድም እንደቻለ ማብራራት አይችሉም። ስለዚህ በጩኸት በመናገር ለማሳመን ይፈልጋሉ። ወንድም ብራንሐም ታላቅ ነብይ መሆኑ ባይካድም የተንቀሳቀሰባቸው ቀናት እና ቦታዎች ግን ይደበላለቁበት ነበር።

ይህም የሜሴጅ አማኞችን በማይጨበጥ ንፋስ ላይ ያስቀራቸዋል። ስለ መልአኩ የሚያስተምሩት ትምሕርት ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ በማይችሉት የተሳሳተ መረጃ ላይ ነው የተመሰረተው። ይህም በትምሕርታቸው ሙሉ በሙሉ የተታለለ ሰውን ብቻ ነው የሚያስገርመው።

አሁን እነዚህ ሁሉ ስሕተቶች እንደ እውነት ተደርገው አስተምሕሮ ውስጥ ተካትተዋል። ነገር ግን ሰዎቹ ስለነዚህ መረጃዎች ጥያቄ ሲገጥማቸው አስተምሕሮዋቸው ይለወጣል።

በስተመጨረሻም ዊልያም ብራንሐም ደመናው በሰማያት ያለው የሰው ልጅ ምልክት ነው አለ እንጂ የራዕይ 10 መልአክ ነው አላለም።

65-0718 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆኑ ፈቃዱን ለማድረግ መሞከር
በዚያ የቴሌስኮፕ ማዕከል ውስጥ ሆነው ከማዕከሉ ውጭ ያለውን ዓለም ሲመለከቱ እስካሁን ምን እንደተፈጠረ በመደነቅ ይጠይቃሉ። ታክሰን ውስጥ ያሉት ትልልቅ ቴሌስኮፖች ፎቶ አንስተውታል፤ እስካሁንም ምን? ይሆን እያሉ ይጠይቃሉ። እስካሁን ድረስ በጋዜጣ ላይ “ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን?” እያሉ ይጠይቃሉ። እዚያ ሰማዩ ላይ ሠላሳ ማይልስ ከፍታ ላይ ጉም የለም፣ አየር የለም፣ እርጥበትም የለም። ኦህ ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይገለጣሉ። እነዚህም ነገሮች ሲሆኑ በልዩ ልዩ ሥፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል።” “በዚያ ቀን” ሉቃስ ውስጥ እንደሚለው “የሰው ልጅ እንደገና ራሱን ይገልጣል፤ ወይም ይገለጣል።” ከዚያ ዓለም እንደ ሰዶም እና እንደ ገሞራ ትሆናለች። ኦህ!

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

ወሬው ግን ሲደጋገም በራሱ እየሰፋ ይሄዳል፤ ደግሞም በጣም ብዙ የሜሴጅ ትምሕርት ተከታዮች የራዕይ 10 መልአክ እራሱ ወርዷል ብለው ይከራከራሉ።

ነገር ግን መልአኩ የት እና መቼ እንደተገለጠ ሲጠየቁ ሁሉም የተለያየ መልስ ነው የሚሰጡት።

ስለዚህ ጠበቅ አድርጋችሁ ስትጠይቋቸው ስለ ቦታው እን ስለ ጊዜው ያለቸው መረጃ የተለያዩ የማይጨበጡ ቅርጾችን ይይዛሉ። ግን ሁላቸውም ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ሰጥተዋል ለማለት ስለሚፈልጉ መልአኩ ተገልጧል በሚለው ሃሳብ በአንድነት ይስማሙበታል።

ሆኖም ግን ዊልያም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ሰጥተዋል ብሎ በጭራሽ አልተናገረም።

እነርሱ ግን አጣፍጠው የሚያወሩት ወሬ በተወሰኑ እውነተኛ መረጃዎች ምክንያት እንዲከሽፍባቸው አይፈቅዱም።

የሚያሳዝነው ነገር አሁን ደግሞ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ብዙ ልዩ ልዩ ትርጓሜዎች አሉ። እያንዳንዱ የራሱ ትርጓሜ ትክክል እንደሆነ አድርጎ ይሟገታል። የሁሉንም ስትሰሙ ከመደናገር በቀር ምንም አታገኙም። ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። ነገር ግን እያንዳንዱ ተርጓሚ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሰባት የተለያዩ ነገሮችን በመጠቆም የነጎድጓዶቹ ቃል ናቸው ብሎ ይናገራል። በፍጹም ሊገጣጠሙ የማይችሉ ነገሮችን ለማገጣጠም እየሞከሩ ናቸው። የተጻፈው ቃል ላልተጻፈው ፍጻሜ ሊሆንለት አይችልም።

ለእግራችን ጽኑ መቆሚያ የሚሆነውን የእውነት ዓለት እስክናገኝ ድረስ አሸዋውን አጥልቀን መቆፈር አለብን። የሰዎች ንግግር ሲጠቀስልን የሰማነውን ሁሉ አምነን መቀበል አለማስተዋል ነው እንጂ እውነትን ለማገኘት ዋስትና አይሰጥም። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በቁጥር የበዙት ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ጥቅሶቹ ብዙ የተለያዩ አመለካከቶችን ፈጥረዋል።

አመለካከቶች መምጣት ያለባቸው ተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርተው መሆን አለበት። አስቀድመን አመለካከት ይዘን የሚመጡልንን መረጃዎች ከአመለካከታችን ጋር እንዲገጥምልን እያረግን መቀበልና መጣል የለብንም።

ከውሃው ፍሰት ጋር አብረው የሚሄዱት የሞቱ ዓሳዎች ብቻ ናቸው።

ክርስቲያኖች ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ ብለው ያምናሉ። የሰው ሕይወት ራሱ እርስበርሱ የሚጋጭ እውነታ ነው። እኛ ግን በራሳችን ሳይሆን ሁል ጊዜ የምናሳብበው በሌሎች ሰዎች ላይ ነው።

በዚህ ነውጥ በሞላበት ዘመናችን ውስጥ እንደ መልሕቅ አጽንቶ ሊይዘን የሚችለው የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ስሕተት የሌለበት የእውነት ቃል መሆኑን ማመን ነው።

በዚህ ጥናት ውስጥ በራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ የተጻፉትን ክስተቶች በጥልቀት ከማየታችን በፊት አሁን ስላለንበት ዘመን የተወሰኑ መንደርደሪያ ሃሳቦችን እናያለን።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን የጀመረው በ1906 መንፈስ ቅዱስ በአዙዛ እስትሪት ሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ በታላቅ ኃይል በፈሰሰበት ጊዜ ነው።

ያም ጊዜ ታላቅ የብልጽግና ጊዜ ነበረ። ሰዎች በልበ ሙሉነት ይንቀሳቀሱ ነበር። ሳይንቲስቶች የፊዚክስን ጥያቄዎች በሙሉ መልሰው የጨረሱ መስሏቸው ነበረ።

ልበሙሉነታቸው ግን ለብዙ ጊዜ አልዘለቀም፤ ምክንያቱም አልበርት አይንሽታይን በ1905 እና በ1916 መካከል አስደናቂውን ነገር ግን ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነውን ሬሌቲቪቲ ቲዎሪ ወይም የአንጻራዊነት ንድፈ ሃሳቡን ይዞ መጣ። ይህንንም ተከትሎ በጭራሽ እንዲህ ነው ብሎ ለመበየን አስቸጋሪ የሆኑት የኳንተም መካኒክስ እውነታዎች በ1920ዎቹ እና በ1930ዎቹ አካባቢ ተገለጡ። እነዚህም ለመረዳት ብዙ ጥረት ካላደረጋችሁ በቀር ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ ሳይንሶች ናቸው። ከዚያ ወዲያ ሳይንቲስቶች ፊዚክስን ሙሉ በሙሉ አውቀናል ማለታቸውን አቆሙ፤ በተለይም ዳርክ ኤነርጂ እና ዳርክ ማተር በድንገትና ባልተጠበቁበት ሰዓት ብቅ ካሉ በኋላ። ለምን ዳርክ ተባለ? ምክንያቱም ምንጩ ከየት እንደሆን አንዳችም ስለማናውቅ ነው።

ከዚያ በኋላ የአሜሪካ አፖሎ የጠፈር ተመራማሪ ከጨረቃ ድንጋይ እና ከምድር ድንጋይ በእድሜ የሚበልጥ የጨረቃ አቧራ ይዞ መጣ።

እየተማርን እውቀት እየጨመርን በሄድን ቁጥር ነገሮች ይበልጥ አደናጋሪ እየሆኑ ይሄዳሉ። ነገሩን ይበልጥ ግራ አጋቢ ያደረገው ደግሞ ደንጋዮቹ የተቀመጡበት አቧራ የተሰራበት ንጥረ ነገር ከድንጋዮቹ በጣም መለየቱ ነው፤ እንዲህም መሆኑ ከድሮ ጀምሮ ተቀባይነት የነበረውን አስተሳሰብ ማለትም አቧራው የመጣው ድንጋዮቹ ለአይር መለዋወጥ ተጋልጠው ሲፈራርሱ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ከንቱ አደረገው። ስለዚህ ድንጋዮቹ የመጡት ከሌላ ቦታ ነው ማለት ነው። ስለዚህ አሁን ስለ ጨረቃ ከድሮው የባሰ ግራ ተጋብተናል።

ሳይንቲስቶች ጨረቃ እንዴት እንደተሰራች አያውቁም።

ሳይንቲስቶች ዓለም እንዴት ወደ መኖር እንደመጣች ለማስረዳት ቢግ ባንግ የሚባል ቲዎሪ ፈጠሩ።

ከዚያም የዓለምን 95% የሚሆነውን ዳርክ ኤነርጂ እና ዳርክ ማተር አገኙ። የቢግ ባንግ ንድፈ ሃሳብ ዳርክ ኤነርጂ እና ዳርክ ማተር ሊኖሩ እንደሚችሉ ቀድሞ አላወቀም፤ ምንነታቸውንም ማብራራት አልቻለም። ስለዚህ ቢግ ባንግ ሊያስረዳ የሚችለው ከዓለማችን 5% ብቻ ነው። ይህም ቢግ ባንግን ጎደሎ ቲዎሪ አደረገው። የቢግ ባንፍ ቲዎሪን ያመጡት ኖቤል ተሸላሚው እስቲቨን ዋይንበርግ እና ፕሮፌሰር አላን ጋዝ አሁን ተዎሪውን ትተውታል።

እስቲቨን ዋይንበርግ የዓለምን ምስጢር ይበልጥ በተረዳን ቁጥር ትርጉሙ እየጠፋብን ይሄደዳል ብሏል። እንግዲህ ይህም ሌላ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ሕይወታችንን ቀለል የሚያደርገውና ምቾትን የሚጨምርልን ሳይንስ ከሞትን በኋላ ስለሚገጥመን ነገር ምንም ዋስትና ሊሰጠን አይችልም። ሳይንም የምንኖርበትን እውነተኛ ዓላማ እንኳ ሊያሳውቀን አይችልም ምክንያቱም ወዴት እየሄድን እንዳለን ሊነግረን አይችልም።

ቀጥሎ በጣም የሚያሳዝን ነገር ተከሰተ። ብዙ ክርስቲያኖች ዘፍጥረት ምዕራፍ 1ን ማመን አቆሙ ምክንያቱም ሳይንስ ካመጣላቸው ቢግ ባንግ ቲዎሪ ጋር አልተስማማላቸውም። አሁን ግን ሳይንቲስቶች ራሳቸው ቢግ ባንግን እየተዉት ነው። ስለዚህ ሳይንቲስቶቹን እንከተላለን ብለው ዘፍጥረት ምዕራፍ 1ን እንደ አፈ ታሪክ የቆጠሩት ክርስቲያኖች አሁን ምንም የሚይዙት የሚጨብጡት የላቸውም። የጨረቃ አቧራ ከጨረቃ ድንጋዮች በእድሜ የሚበልጥ እና በይዘቱም የተለየ እንደመሆኑ መጠን ሳይንቲስቶች ጨረቃ እንኳ እንዴት እንደተሰራች ማወቅ አልቻሉም። ስለዚህ መላው ዓለም እንዴት እንዴት እንደተፈጠረ እናውቃለን ቢሉ ቀልድ ነው። ቢግ ባንግ ራሱ ከእርሱ በኋላ የተገኙ ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን መተርጎም ያቃተው ተራ ንድፈ ሃሳብ ሆኖ ቀርቷል።

ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ ምክር ሰጥቶናል።

1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡20 ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤

የሳይንስ ንድፈ ሃሳብ ወይም ቲዎሪ መጽሐፍ ቅዱስን ከተቃረነ ሳይንስ አይደለም፤ የውሸት እውቀት፤ የውሸት ሳይንስ ነው።

የሎዶቅያ ዘመን በ1906 ሲጀምር በኢዱስተሪ አብዮት የተነሳ የኢንጂነሪንግ ጥበብ በታላቅ ፍጥነት እያደገ ነበር።

ከዚያም በ1912 የኢንጂነሪንግ ልበሙሉነት በኩርኩም ተመታ። ታይታኒክ የተባለችዋ የዓለማችን ትልቅ መርከብ በፍጥነት እየሄደች ሳለ ከተንሳፋፊ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ ከተሸከመቻቸው መንገደኞች ሁለተ ሦስተኛ የሚሆኑትን ይዛ ሰጠመች። የመርከቢቱ አርቆ ማሳያ መነጽር የተቆለፈበትን ሳጥን ቁልፍ የያዘው ሰራተኛ ልክ መርከቢቱ ከወደብ ከመንቀሳቀሷ በፊት በሌላ ሰው ተተክቶ ነበር ግን እንደ አጋጣሚ ሥራውን ሲለቅ ቁልፉንም በዚያው ይዞ ሄደ። አርቆ ማሳያ መነጽር ስላልነበራቸው ውቂያኖሱን ቀንና ሌሊት እንዲቃኙ የተመደቡ ሰራተኞች የበረዶውን ግግር አጠገቡ እስኪደርሱ ድረስ ሊያዩት አልቻሉም ነበር። በጣም ከተጠጉት በኋላ የመርከቢቱን አቅጣጫ ሊቀይሩ ሞከሩ። የሚገርም አጋጣሚ ነው፤ አንዲት ትንሽ ቁልፍ ባለመኖሯ ምክንያት ታላቂቱ መርከብ ሰጠመች።

አንድ ሰውዬ ታይታኒክ በጣም ትልቅ እና በጥሩ ሁኔታ ስለተሰራች እግዚአብሔር ራሱ እንኳ ሊያሰጥማት አይችልም ብሎ ነበር። ግን እንዲህ በድፍረት ሲናገር እግዚአብሔር እያደመጠው ነበር።

የመርከቢቱ መስመጥ የሰዎችን ሁሉ ልበሙሉነት አናወጠ። ያን የምታህል ታላቅ መርከብ ገና በመጀመሪያ ጉዞዋ ሰጠመች። ብዙ ባለጠጋ ሰዎች ሃብታምነታቸውን ለማሳየት በታይታኒክ ተሳፍረው ነበር። ድሃ ቢሆኑ ኖሮ ምናልባት በመርከቢቱ አይሳፈሩም ነበር። ስለዚህም ከመስመጥ ተርፈው በሕይወት ይኖሩ ነበር። ይህ ክስተት በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን መነሻ ላይ የማይረሳ ታሪክ ሰርቶ አልፏል። ሰው ከሰራቸው የብረት ማሽኖች ሁሉ ትልቁን ሰራ ነገር ግን ሥራ የተሳካ አልነበረም። የሰዎች ሁሉ ልብ በፍርሃት ራደ። ሰው የሕይወትን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ የሚያስችለው ብልሃት ቢኖረውም እንኳ በቂ ብልሃት እንደሌለው አወቀ።

አንድ የተገለጠልን መንፈሳዊ ሚስጥር አለ። እርሱም ኢየሱስ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ ለጴጥሮስ መስጠቱ ነው።

ማቴዎስ 16፡18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ጴጥሮስም እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ በዚህ መክፈቻ የመንግሥተ ሰማያትን በር ከፈተ፡-

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ይህንን መክፈቻ የምትጠቀም ቤተክርስቲያን ፈልጎ ማግኘት ከባድ ነው።

ስሙን ማን እንደሆነ በጭራሽም ሳያውቁ በሦስት ማዕረጎች ያጠምቃሉ። የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ ብትጠይቋቸው በመጀመሪያ ሚመልሱት ያጣሉ ከዚያ በኋላ ለማስረዳት ብዙ ትግል ውስጥ ይገባሉ። መከራ የሚበሉትም የሥላሴን ጽንሰ ሃሳብ ለማስረዳት ሲሞክሩ ነው።

ነገር ግን ያለ መክፈቻው ቤተክርስቲያናት የእግዚአብሔርን ስም ማወቅ አይችሉም፤ ምክንያቱም ሦስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደሚያይ ሰው እየተመለከቱ ሲሄዱ የታላቁን መከራ ተንሳፋፊ የበረዶ ግግር ሊያመልጡ አይችሉም፤ በአሁኑ ሰዓት ያሉን ታላላቅ ቤተክርስቲያኖችም ከዚህ የበረዶ ግግር ጋር ለመላተም በታላቅ ፍጥነት እየገሰገሱ ናቸው።
ለውሃ ጥምቀት የእግዚአብሔርን ሰብዓዊ ስም ማወቅ ትንሹ መክፈቻ ነው፤ ነገር ግን ያለዚህ መክፈቻ በቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ላይ ታላቅ ግጭት ይፈጠራል። የኃያሉ አምላካችን ስም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና

እግዚአብሔር ማንነት ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ውስጥ ነው የሚገኘው።

ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት እግዚአብሔር በሰው መልክ ሲገለጥ ነው።

በ1914 ብዙ ሃገሮችን በጦር መሳሪያቸው ኃይል የጨፈለቁ የአውሮፓ መንግሥታት በአንድ ጊዜ እብደት ሲመጣባቸው እርስ በራሳቸው ላይ ጦርነት ለማወጅ ወሰኑ። በአውሮፓ ኃያላን ሃገራት መካከል የጠፈጠረ ውስጣዊ ሽኩቻ በታላቅ ፉክክር ቅኝ ግዛቶችን እንዲይዙ ገፋፍቷቻ ነበር። የአውሮፓ ሃገራት በጭካኔ ቅኝ ግዛቶቻቸውን ሲበዘብዙ ስግብግብነት፣ ግብዝነት እና የተሰማሩበት የራስን ፍላጎት ብቻ የማስፈጸም ዘመቻ በሃብት እና በኃይል እንዲያድጉ አበቃቸው። ሰው የዘራውን ያጭዳል። ከዚያ በኋላ ኃያላን የአውሮፓ ሃገሮች እርስ በራሳቸውን ወጉ።

አንድ ነፍሰ ገዳይ ተነስቶ የኦውስትሪያ ልኡል ከነሚስቱ ገደለ፤ በዚያውም አንደኛ የዓለም ጦርነት ተጀመረ። ይህም ጦርነት ጥቅም ላይ ባዋለው የኬሚካል ፈንጂዎች እና በአሰቃቂነቱ ወደር ስላልነበረው “ጦርነቶችን ሁሉ የሚያስቆም ጦርነት” ተብሎ ነበር። ሃያ ሚሊዮን ሰዎች ሞቱ። ከዚያም በጦርነት የደቀቁትን ሃገሮች እስፓኒሽ ፍሉ የተባለ በሽታ በወረርሽኝ መጥቶባቸው 65 ሚሊዮን ሕዝብ ገደለባቸው።

ይህም ተደራራቢ ችግር ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት መንስኤዎችን ለማባባስ አስተዋጽኦ አደረገ፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነትም ከመጀመሪያው በአውዳሚነታቸው የሚበልጡ አቶሚክ ፈንጂዎች ተሰሩ።

ብልህ ሳይንቲስቶስ ትልልቅ እና ፈጣን የሆኑ የሞት መሳሪያዎችን እንዲሰሩልን አበረታተናል።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በተፈጸመበት ግፍ የጠነሳ ነፍሰ ገዳይነትና ጥላቻን በምድር ላይ በማንሰራፋቱ የፈላጭ ቆራጭነትና የጨለማ አጋንንት ኃይል በምድር ላይ ተለቅቋል።

54-0513 የአውሬው ምልክት
ይህ በሦስተኛው መልአክ አማካኝነት ለዓለም የመጣ መልእክት ነው። እናንተም ደግሞ የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ታውቃላችሁ፤ መልእክቱም ዛሬ በዚህ ዘመን እየተነገረ ነው ያለው። መጽሐፍ ቅዱስን የምታነቡ ከሆነ ይህ መልእክት ሦስተኛው መልአክ መልእክቱን ይዞ እየበረረ ነው።

መልእክቱን ተከትለው ሦስት ወዮዎች መጥተዋል። የመጀመሪያው ወዮ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ነው የመጣው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት። አሁን ደግሞ የት እንዳለን ታያላችሁ አይደል። እሺ። በመንገዱ መጨረሻ ላይ ቆመናል።

ራዕይ 8፡13 አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።

ይህ የሚከሰተው በታላቁ መከራ ውስጥ ነው። ይህ የመለከት ድምጽ ጥሪ ወይም የኢዮቤልዩ በዓል በታላቁ መከራ ወቅት አይሁዶች ወደ እሥራኤል እንዲመለሱ የሚደረግ ጥሪ ነው።

ነገር ግን ሙሽራዋ እነዚህ ክስተቶች ምን እንደሆኑ ትረዳ ዘንድ ሙሽራይቱ የእነዚህን ሦስት ወዮታዎች ቅምሻ ቀድማ ታገኛለች።
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በምድር ላይ የአምባገነንነት መንፈስ ተፈትቶ እንዲለቀቅ አደረገ። ይህም ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የመጀመሪያ ወዮ ነው።

ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ የሰላም ስምምነት የተደረገበት ደምብና ሁኔታ በጣም ከባድ ስለነበረ ድሕነት በጣም ተስፋፋ። ብዙሐኑ ጥቂት ብቻ ይዘው ጥቂቶች ብቻ ሃብታም የሚሆኑበት ሥርዓት በቀላሉ ጦርነትን የሚቀሰቀወስ ሁኔታ ነው።

ካቶሊካዊው ፈላጭ ቆራጭ ሙሶሊኒ ኢጣልያ ውስጥ ወደ ሥልጣን መጣ። በኮምዩኒስት ራሺያ ውስጥ ደግሞ ከአስር ሺ በላይ ሰዎችን የገደለው ሌኒን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የጨፈጨፈው እስታሊን ወደ ሥልጣን መጡ። ጀርመኒ ሒትለርን አበቀለች።

ሒትለርም በተፈጥሮው አምባገነን ሰው እንደመሆኑ ጀርመኒን ጨቁኖ ከመግዛቱም በላይ ጀርመናውያን በሥጋ እሥራኤል የሆኑትን አይሁዳውያን እንዲጠሉ ቀሰቀሳቸው።

ሁለተኛው ወዮ የተፈጸመው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው፤ በዚያንም ጊዜ ጀርመናዊው ፈላጭ ቆራጭ ሒትለት እነዚህን አጋንንታዊ ኃይላት በአይሁዳውያን ላይ በመልቀቅ ዛይክሎን ቢ የተባለ የመርዝ ጋዝ ተጠቅሞ ገደላቸው። ይህም የአይሁድ ዘርን ፈጽሞ የማጥፋት ዘመቻቸው ሲሆን እስከ 1945 ድረስ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን ገድለዋል። አላይድ ሃገሮች ጦርነቱን አሸንፈው ጀርመኒን ሲቆጣጠሩ ተጨማሪ 20 ሚሊዮን ሰዎችን ለመግደል የሚበቃ ዛይክሎን ቢ መርዝ ጋዝ በመጋዘን ውስጥ አግኝተዋል። ይህ ሰውን ገድሎ የማይጠግብ አጋንንታዊ እብደት ነው። ይህም ታሪክ ለሙሽራይቱ ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል ለማሳየት የሚሆን ትንሽዬ ናሙና ነው።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ አጋንንቱ በዚህ ታላቅ ቁጥር በሚሊዮኖች አይሁድን የማጥፋት ዘመቻቸውን አቋረጡ።

እነዚህ አጋንንት በምድር ላይ የተሰማሩት በአምባገነን መሪዎች አማካኝነት ነው። አሁን የት ተደብቀው ነው ያሉት? ታላቁ መከራ ሲመጣ ተመልሰው ይገለጣሉ፤ ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአይሁዶች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የአማተሮች ሥራ ነበር -- ወይም ወደፊት በሰው ዘር ላይ ለሚፈጸመው ይበልጥ የሚከፋ ጭፍጨፋ ማሟሟቂያ ነበር።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እነዚህ አጋንንት ዘዴያቸውን ቀይረው ወደ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ገብተዋል፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እሥራኤል ናት። ሥራቸውም ክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያምኑ ማድረግ እና ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ወደ ቀደመው ሐዋርያዊ አባቶች እምነት እንዳይመለሱ መከላከል ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርት ማመን ስንጀምር በመንፈስ መሞት እንጀምራለን።

ስለዚህ የአጋንንት ዓላማ እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈን ማስረዳት ወይም መግለጽ እስኪያቅተን ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳናውቅ ማድረግ ነው። ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ተዘጋጅተዋል። በእነዚህ ሁሉ ትርጉሞች አማካኝነት የተለዋወጡ ቃላት እና የአተረጓጎም ልዩነቶች የተነሳ ትክክለኛውን እውነት ማግኘት ከባድ ሆኗል።

በመቀጠልም እነዚህ መናፍስት በቤተክርስቲያናት መካከል ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻው ዘመን ነብይ መሆኑን ሽምጥጥ አድርገው የማስካድ ዘመቻ ጀመሩ።

ወንድም ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻው ዘመን ነብይ መሆኑን በተቀበሉ ወንድሞች መካከል ደግሞ እነዚሁ አጋንንት ሕዝቡ እርሱን “የእግዚአብሔር ድምጽ” ብለው በመጥራት አምላክ እንዲያረጉት ገፋፉዋቸው። ከዚያም ከወንድም ብራንሐም ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን ተክተው ቀሩ፤ “የሜሴጅ አማኞችም” (ይህ ስያሜ ራሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም) ከብራንሐም ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን በመተርጎም እውነት ይገኛል ብለው እስኪያምኑ ድረስ ተታለሉ። ይህ አይነቱ እርምጃ ለሰነፎች ይመቻቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በጣም አድካሚ ሥራ ነው።

በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በአስደንጋጭ ፍጥነት ቀነሰ።

ሙሴ በመጀመሪያው የሕዝብ መውጣት አይሁዶችን ከግብጽ አወጣ።

ኢየሱስ በሁለተኛው የሕዝብ መውጣት ቤተክርስቲያንን ከአይሁድ ሕዝብ መሃል አወጣ።

ሙሽራይቱ ደግሞ በሦስተኛው የሕዝብ መውጣት ከዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን መካከል መውጣት አለባት።

በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የምትከተል ቤተክርስቲያን የለችም።

የዛሬ ክርስቲያኖች የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉ የሐዋርያት መንፈሳዊ ልጆች እንደመሆናቸው ወደ ሐዋርያት አባቶች እምነት መመለስ አለባቸው።

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ … የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት ባንመለስ የኑክሊየር ቦምብ ፍንዳታ እና የሚያስከትለው ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚችል ጨረር እና ጨረሩም የሚፈጥረው የካንሰር በሽታዎች ወደ ሞሉበት ታላቁ መከራ ውስጥ እንወድቃለን።

ስለዚህ ልክ ሙሴ በተወለደበት ዘመን እና ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን ሕጻናት እንደተገደሉ ሁሉ ለጥንቶቹ ሐዋርያት መንፈሳዊ ልጆች የሆኑት የዛሬ (የዘመን መጨረሻ) ክርስቲያኖችም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራት ትምሕርት ባለማግኘታቸው በመንፈስ እየተገደሉ ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ማንንም ከተጠያቂነት አያድንም።

ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤

ብርቱ መልአክ -- ሰባተኛው መልአክ ለሰባተኛው የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

የዚህ ብርቱ መልአክ መልእክት የቤተክርስቲያኖችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አሰራርና ትምሕርት የሚያወግዝ መልእክት ነው።

የጋለሞታዎች እናት የሆነችው ባቢሎን የምትወክለው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ነው፤ እርሷም ራሷን እናት ቤተክርስቲያን ብላ ነው የምትጠራው ምክንያቱም ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የወጡት ከእርሷ ነው። የአጋንንት አሰራር በውስጧ ገብቶ ስለሰፈረባት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በስሕተቶች ተሞልታለች።

ሥጋዊ ፈላጭ ቆራጮች በሥጋ በሆነችዋ እሥራኤል ላይ አጋንንትን ለቀውባታል። ጦርነቱ ሲያበቃ አጋንንቱ ሰዎችን በሥጋ መግደላቸውን አቁመው ወደ ቤተክርስቲያን ገቡና የዚህ ዘመን መንፈሳዊ እሥራኤል የሆኑትን ቤተክርስቲያንን መጽሐፍ ቅዱስን አለማመናቸውን በመጠቀም በመንፈስ መግደል ጀምረዋል።

ስለዚህ ብዙ ቄሶችና የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕጻናትን ሲያማግጡ መጋለጣቸው አያስገርምም።

ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

ዋናዋ ጋለሞታ ራሷ የጋለሞታዎች እናትም ናት። መጽሐፍ ቅዱስ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የወጡትን የፕሮቴስታንት አብያተክርስቲያናት ጋለሞታዎች ብሎ ነው የሚገልጸው።

ስለዚህ በዓለም ላይ ያሉ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ በአንድነት የጋለሞታዎች ስብስበ ተብለው ነው የተገለጹት።

ይህም ሰው ሰራሽ የሆኑ አስተሳሰቦችን እና ጥልቀት የሌላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርቶችን እንዲሁም የሠው አስተሳሰቦችን የሚያቀርቡልንን ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች በጥርጣሬ እንድንመለከታቸው ሊያደርገን ይገባል።

ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ሌላ ድምፅ -- ይህ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እየገፋፋን ከዘመናዊቷ ቤተክርሰቲያን ተለይተን እንድንወጣ የሚያሰማን ድምጽ ነው።

ሌላ ድምፅ -- ይህ ማለት የዊልያም ብራንሐምን ጥቅሶች መደጋገም አይደለም።

የዊልያም ብራንሐምን ጥቅሶች ብንደጋግም ይህ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ነው።

ሌላ ድምፅ የሚለው ግን እያንዳንዳችን በልባችን ውስጥ በግል ከእግዚአብሔር የምንቀበለው መገለጥ ነው።

ማለትም በአማኙ እና በኢየሱስ መካከል የሚደረግ የግል ሕብረት ነው። ኢየሱስ ቃሉ ነው። ስለዚህ ሰው ለሆነ መሪ መገዛት አያስፈልግም። ይህ እያንዳንዱ ግለሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጥቅስ ሲያነብ በልቡ የሚወቅሰው የቃሉ ድምጽ ነው።

ቤተክርስቲያኖች በብዙ መንገድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀዋል፤ ይህም መጥፎ ነው ግን ሕዝቡ ይህን ማወቅ አይፈልጉም። ሰዎች ሁል ጊዜ የነሱ ቤተክርስቲያን ከሌሎች እንደምትሻል አድርገው ማሰብ ይወዳሉ። ለቤተክርስቲያናቸው የእምነት መግለጫ ታማኝ እንዲሆኑ በሚያደርግ ቡድናዊ አስተሳሰብ ውስጥ ተደላድለው መኖር ይፈልጋሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሃይምነትን ወይም ሐጥያትን የሚቀንስ ትምሕርትን መማር አይወዱም።

ስለዚህ ይህ ሦስተኛው የሕዝብ መውጣት ቤተክርስቲያናቸው መሳሳቷን ለመቀበል እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ቃል በሙሉ ልብ ለመቀበል ድፍረት ላላቸው ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ነው።

ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።

በሰዎች ዘንድ የተናቁት ጥቂት አማኞች ከሰባተኛው መልአክ ጥቅሶች ይማሩና እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሃሳባቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉች አማካኝነት ይመረምራሉ።

እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን መሆንን አጥብቀው የሚመኙ ነገር ግን የዛሬውን ዘመናዊ ተድላ እና ቁሳቁስ የማይወዱ፤ ሌሎችንም ለመምሰል እምቢ የሚሉ ግለሰቦች ናቸው።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እጅግ ብዙ የአባላት ቁጥር ባላቸው ቤተክርስቲያኖች ይደነቃሉ።

ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

መሃይምነትም ብዙ ሰዎችን ካስከተለ ይጨበጨብለታል። የሰነፎች ንግግር እንደ ባሕር ቢሞላ የሚፈጥረው ትልቅ ማዕበል ጠራርጎ ይዞን ይሄዳል።

ሰው ሁሉ የተከተለውን መንገድ ትተው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ፍለጋ የሚወጡ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው።

ነገር ግን የዚህ የሰባተኛ መልአክ አገልግሎት የራሱ የሆኑ ውስንነቶች አሉት። እርሱ የተላከው ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ሊመልሰን ነው። የራሱን ሃሳቦች ሊፈለስፍ አይደለም የተላከው።

ለተመረጡት ጥቂቶች የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ልክ የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበረችዋን ቤተክርስቲያን አማኞችን መምሰል አለባት። “ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ።”

በመጀመሪያው የቤተክርስቲያ ዘመን እና በመጨረሻው የቤተክርስቲያ ዘመን መካከል ምንም ልዩነት መኖር የለበትም።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

የመጨረሻው መልእክቱ የሚሆነው የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ወደመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን መመለሷ ነው የሚሆነው።

ማቴዎስ 19፡30 ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።

የመጀመሪያ እና የመጨረሻ አንድ አይነት ናቸው። በሁለታቸው መካከል ይህን ያህል የሚባል ልዩነት የለም።

እስቲ የአውሮፓ መንግሥታትን ተመልሰን እንመልከት።

የአውሮፓ ሃገሮች ከቅኝ ግዛቶቻቸው የዘረፉትን ሃብት ሁሉ ያለ በቂ ምክንያት በተቀሰቀሱ በሁለት የዓለም ጦርነቶች ላይ ተጠቅመው ሲጨርሱ ለኪሳራ ቅርብ ሆኑ። ከዚያ ቀጥሎ ቅኝ ግዛቶቻቸው አንድ በአንድ ከእጃቸው መውጣት ጀመሩ።

በቅኝ ተገዝተው የነበሩ ሃገሮች ነጻነታቸውን ከተጎናጸፉ በኋላም እንኳ እነዚሁ በጦርነቱ አማካኝነተ የተለቀቁ ደም አፍሳሽ አጋንንት ሥራቸውን ቀጥለዋል። ብዙዎቹ ቅኝ የተገዙ ሃገሮች ከአውሮፓውያን ገዥዎቻቸው ነጻ ለመላቀቅ ባደረጉት አሰቃቂ ትግል ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል።

ሁለቱ የዓለም ኃያል ሃገሮች አሚሪካ እና ራሺያ ሁለታቸውም አሸናፊ በማይሆኑበት ቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ገቡ። ሰውን ሁሉ ገድሎ ለመጨረስ የሚበቃ እና ተርፎም አስከሬኖችን በተጋደሙበት ለማስደነስ የሚበቃ የኑክሊየር ቦምብ አመረቱ።

“የሁለታችንንም መጥፋት ለማረጋገጥ” የሚችል መሳሪያ ተብሎ ተጠራ። ይህ በአጋንንት ጠንሳሽነት የተቀናበረ ፊዚክስ ነው።

በፊዚክስ እውቀት የመጠቁ አእምሮዎች የሰሩልን ሥራ ቢኖር ሁላችንን ወደ አርማጌዶን ኑክልየር ጦርነት አፋፍ ማምጣት ነው። የሰው ዘር ከአእምሮአችን በላይ በእውቀት አድጓል። ነገር ግን በዚህ የእውቀት ብዛት ልናመጣ የቻልነው መቆጣጠር የማንችለው የጥፋት ኃይል ነው።

የሚከተለው ስለ አሜሪካ የተመለከተ ትንቢት የተነገረው በ1964 ፖውል ሃርቬይ በተባለ ሬድዮ ላይ በሚታወቅ ሰው ነው።

እኔ ዲያብሎስ ብሆን

አሜሪካን በቁጥጥሬ ስር ለማድረግ የተቻለኝን ሁሉ አደርግ ነበር።

በመጀመሪያ ቤተክርስቲያኖችን አጣምማቸዋለው፤ የመጀመሪያው እርምጃዬም የሚሆነው የሾካኮች ዘመቻ ነው።

የእባብን ጥበብ በመጠቀም ለሔዋን ሹክ እንዳልኳት ለእናንተም “ደስ እንዳላችሁ አድርጉ” ብዬ ሹክ እላችኋለው።

ለወጣቶቹ መጽሐፍ ቅዱስ አፈታሪክ ነው ብዬ እነግራቸዋለው። ሕጻናትን ደግሞ ሰው እግዚአብሔርን ፈጠረ እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አልፈጠረም ብዬ አሳምናቸዋለው። ክፉውን መልካም መልካሙን ደግሞ ኋላ ቀር እና ክፉ ብዬ ለእያንዳንዱ ሰው አስተምረዋለው።

ከዚያ በተደራጀ ዘዴ ደራሲዎች ጸያፍ እና ልቅ ወሲባዊ ብልግና የሞላበትን የሥነ ጽሁፍ ሥራ ለሰዎች አዝናኝ እንዲመስል በአንጻሩ ደግሞ ሌላው አይነት መዝናኛ ሁሉ ደባሪ አሰልቺ እንዲመስል አደርጋለው።

ለፈለግሁት ሰው አደንዛዥ እጽ እሸጣለሁ። ለተከበሩ ሰዎች እና ወይዛዝርት አልኮል መጠጥ እሸጣለሁ። የቀሩትን ደግሞ በሚዋጡ መድሐኒቶች አደነዝዛቸዋለው።

እኔ ዲያብሎስ ብሆን ወዲያው ቤተሰብ ውስጥ ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲዋጉ አደርጋለው፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባላት እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ አደርጋለው፤ ሃገሮችም እርስ በርሳቸው ተጋጭተው በውስጣቸው ያሉት ሁሉ እንዲተላለቁ አደርጋቸዋለው።

ከዚያ የዜና አውታሮች ሁሉ ወሬውን እንዲያራግቡት አደርጋለው።

እኔ ዲያብሎስ ብሆን ትምሕርት ቤቶች የወጣቶችን አእምሮ በደምብ እንዲያሰለጥኑ ነገር ግን የስሜት ብስለትን ደግሞ ቸል እንዲሉ አደርጋለው። አስተማሪዎች ደግሞ ተማሪዎችን መረን እንዲለቋቸው አበረታታለው። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ አደንዛዥ እጽ አነፍናፊ ውሾች እና የብረታብረት መሳሪያ መመርመሪያ ማሽኖች በየትምሕርት ቤቱ በር ላይ ይገኛሉ።

በአሥር ዓመት ውስጥ በየእሥር ቤቱ ውስጥ ዳኞች እየመጡ ልቅ ወሲባዊ ስዕሎችን ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን እንዲያከፋፍሉ አደርጋለው። ቶሎ ብዬ እግዚአብሔርን ከፍርድ ቤቶች፣ ከትምሕርት ቤቶች እንዲሁም ከኮንግረስ ምክር ቤት ውስጥ እንዲያስወጡት አደርጋለው።

በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ በእምነት ቦታ ሥነ ልቦና ወይም ሳይኮሎጂ እንዲተካ ደግሞም ሳይንስ እንደ አምላክ እንዲመለክ አደርጋለው። ካሕናትና ፓስተሮች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን እንዲያማግጡ የቤተክርስቲያንንም ገንዘብ ያለ አግባብ እንዲጠቀሙ አደርጋለው።

ሃገሪቱ በሙሉ ቁማርን ትክክለኛ ሃብታም መሆኛ መንገድ ነው ብለው እንዲያስተዋውቁ ማድረግ ብፈልግ የሚያቅተኝ ይመስላችኋል?
ወጣቶች ትዳር የድሮ ፋሽን ነው ብለው እንዲያስቡ፤ በሐጥያት መኖር ደስ ያስኛል ያዝናናል እንዲሉ እና በቴሌቪዥን የምታዩት ሁሉ ጥሩ የኑሮ ዘይቤ ነው ብለው እንዲያምኑ አደርጋለው።

በዚህም መንገድ በአደባባይ ልብሳችሁን እንድታወልቁ እና መድሐኒት የሌላቸውን በሽታዎች ሸምታችሁ አልጋ ላይ እንድትወድቁ ላታልላችሁ እችላለው።

በሌላ አነጋገር እኔ ዲያብሎስ ብሆን አሁን ዲያብሎስ እያደረገ ያለውን ሁሉ አደርግ ነበር።”

1965 ለአሜሪካ በጣም መጥፎ ጊዜ ነበረ ምክንያቱም ያ ዓመት ፕሬዚደንት ጆንሰን የቬትናም ጦርነት እንዲባባስ ያደረገበት ዓመት ነበር።

የታሪክ ምሑራን አሜሪካ በ1965 እና በ1980 መካከል ራሷን ለማጥፋት የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች ይላሉ።

የወንድም ብራንሐም አገልግሎት የተጠናቀቀው በ1965 ነው። አሜሪካ የብራንሐምን መልእክት አልተቀበለችም። ስለዚህ በቀጣዮቹ 15 ዓመታት ውስጥ አሜሪካ በሔደችበት ሁሉ መሸነፏ አያስደንቅም።

የቬትና ጦርነትን እንዲጀመር ያደረገው ፕሬዚደንት ትሩማን ነው፤ ጦርነቱም የተጀመረው ፕሬዚደንት ትሩማን በኢንዶ ቻይና ጦርነት ውስጥ ፈረንሳይ ከሰሜን ቬትናም ጋር በምትዋጋበት ጦርነት ወታደራዊ ድጋፍ ሲያደርግ ነው (በዚያን ጊዜ ቬትናም ኢንዶ ቻይና ተብላ ትጠራ ነበር)። በ1954 ፈረንሳይ ለገባችበት ጦርነት 80 በመቶ የሚሆነውን ወጪ አሜሪካኖች ነበሩ የሚሸፍኑት። ይህም አሜሪካ ቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ እንድትገባ አደረጋት። በጦር ሜዳ ልምድ የነበረው ጀነራል አይዝንአወር ከ1952 እስከ 1960 የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበረ ሲሆን ወደ ጦርነቱ መግባት ስሕተት መሆኑን አውቋል፤ ነገር ግን በጣም የሚያሳዝነው የአሜሪካ ጦር አማካሪዎችን ደቡብ ኮሪያን እንዲረዱ በመላክ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ እንድትከርም አደረገ። ዓላማው ኮምዩኒዝም ወደ ደቡብ ቬትናም እንዳይስፋፋ ለመከላከል ነበር ግን የወሰደው እርምጃ ማለትም ቬትናም ውስጥ ነጻ ምርጫ እንዲካሄድ አለማድረጉ ትልቅ ስሕተት ነበር። ከእርሱ በኋላ የመጣው ፕሬዚደንት ኬኔዲ ካቶሊክ ስለነበረ ፖፕ ጆን 23ኛው ካቶሊክ የሆነችዋን የደቡብ ቬትናም ፕሬዚደንትን እንዲደግፍ አበረታታው። ኬኔዲ ግን ወታደራዊ ድጋፍ መጨመሩን ቢቀጥልም ጦርነቱን ለማሸነፍ በሚበቃ መጠን አልነበረም። ኬኔዲ በስውር ለመፈንቅለ መንግሥት ድጋፍ አደረገ፤ በዚህም መፈንቅለ መንግሥት በ1963 የደቡብ ቬትናም ፕሬዚደንት ተገደለ።

ኢዮብ 4፡8 እኔ እንዳየሁ፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥

መከራንም የሚዘሩ ይህንኑ ያጭዳሉ።

ኬኔዲ ራሱ በዚያው ዓመት በ1963 ከሦስት ሳምት በኋላ በጥይት ተመቶ ሞተ።

ፖፕ ጆን 23ኛውም በ1963 ሞተ።

ፕሬዚደንት ጆንሰን በ1965 ጦርነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደረገ፤ ነገርን ግን የእርሱ ሞኝነት ጦርነቱን አሜሪካ ውስጥ ተቀምጦ ሊመራ መሞከሩ ነበር። በጦርነቱ 58¸220 አሜሪካውያን አለቁ። የአሜሪካ ጋዜጦች እና የዜና አውታሮች በሙሉ የዎተርጌት ስለላ ቅሌት ላይ ደረሱበትና ፐሬዚደንት ኒክሰን ከሥልጣን እንዲወርድ አደረጉ። ከዚያም ኮንግሬስ አሜሪካ ጦርነቱን ትታ እንድትወጣ አዘዘ፤ ይህም አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሸነፈችበት ጦርነት ሆነ።

በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ይህ የማይረሳ የታሪክ አሻራ ነው።

ቀዝቃዛው ጦርነት ቬትናም ውስጥ አደገኛ እየሆነ ሄደ። ከጦርነቱም በሰው ብርታት መደገፍና መታመን እንደማንችል ትምሕርት አግኝተንበታል።

ኤርምያስ 17፡5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።

ልዕለ ኃያል ሃገር የሆነችዋ አሜሪካ በሃኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ በጦርነት ተሸነፈች።

መክብብ 9፡11 እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን … እንዳልሆነ አየሁ፤

ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር። አሜሪካኖች ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ስለነበራቸው ወንድም ብራንሐም ወደ እግዚአብሔር ቃል እንዲመለሱ ያደረገላቸውን ጥሪ ቸል ብለው ማለፍ የሚችሉ መስሏቸው ነበር።

እግዚአብሔር ግን በጠንካራው ወታደራዊ ኃይላቸው የነበራቸው ትምክሕት እንዲናወጥ አደረገ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ጀነራል አይዝንአወር ስሕተት እየሰራ መሆኑን እያወቀ ምንም የእርምት እርምጃ አልወሰደም፤ ደግሞም በፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ መግባት የሌለበት ፖፕ ጆን 23ኛውም ጀነራሉን ሲያበረታታው ነበር። ይህም ቀውስ የተጠናቀቀ ሃገር እንዲመሩ ባልተመረጡት የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ባደረጉት ግፊት ጽኑ ነበር።

ይህ ለዘመናችን ግልጽ ማስጠንቀቂያ ነው። በፖለቲካም ሆነ በሐይማኖት ብልሹ አመራር ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።

አሜሪካ የመጨረሻውን ዘመን ነብይ አልቀበል ማለቷ ደግሞም ወደ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ትምሕርት እንድትመለስ በዚህ የመጨረሻ ዘመን ነብይ የመጣላትን መልእክት አልሰማ ማለቷ የገባችባቸውን ጦርነቶች ማሸነፍ እንዳትችል እና ጦርነቶችንም የአሸባሪዎች ጨዋታ እንዲሆኑባት አደረገ።

ጋዜጦች እና የመገናኛ ብዙሃን አሁን ለሕዝቡ የሚያስተላልፉት ዜና እውነቱን ሳይሆን ሕዝቡ እንዲሰማ የሚፈልጉትን ብቻ ሆኗል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ከቤተክርስቲያን ወጎች ጋር በተለምዶ ትክክለኛ ተብለው ከሚቆጠሩ አስተሳሰቦች ጋር እየቀላቀሉ ያስተምራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጡትን ምስጢራት ብቻ ለማስተማር ፈቃደኛ ባለመሆን ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ቀጥ ብለው ወደ ፊት ሊመጣ ወዳለው ወደ ታላቁ መከራ እየገሰገሱ ናቸው።

የዘመናችን ሰው በቀላሉ ይታለላል ምክንያቱም ጋዜጦችና የመገናኛ ብዙሃን ነፍሰ ገዳዩን እንደ ቅዱስ ሰው አድርገው ያቀርቡለታል። አንዱ ምሳሌ ቼ ጉቬራ ነው። የቼ ጉቬራ ፎቶ ከወታደራዊ ኮፍያው ጋር በብዙ ቲሸርቶች ላይ ታትሟል። እርሱም የሰው ዘርን ከባርነት ነጻ ሊያወጣ የመጣ አብዮተኛ ተብሎ ይወደሳል። ለሕዝቡ ጥቅም የቆመ ቆራጥ አብዮተኛ ተብሎ ይመሰገናል። እውነቱ ግን ሰውየው ነፍሰ ገዳይ ሲሆን ያስነሳቸው አብዮቶችም ለማንም ነጻነት ሰጥተው አያውቁም፤ ይልቁንም የባሰ ባርነትን እና ፍርሃትን አመጡ እንጂ። የቼ ጉቬራ መፈክር እንዲህ የሚል ነበር፡- “አብዮተኛ ሰው በጥላቻ የተሞላ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ መሆን ያስፈልገዋል። የግድግዳውን ትምሕርት ማስፋፋት አለብን!” (ግድግዳው ሲል የቼ ተቃዋሚዎች ከመረሸናቸው በፊት በሰልፍ በአጠገቡ የሚቆሙበት ግድግዳ ማለቱ ነው።) “ጥላቻ” እና “ጭካኔ” ክርስቲያናዊ መታወቂያዎች አይደሉም።

ዘመናችን የመገናኛ ብዙሃን በሚያስተላልፉት የተዛባ መረጃ የሚያምን ዘመን ነው።

ሎዶቅያ ሐሰተኛ ዜና ሰው ሰራሽ እውነታ የተፈጠረበት ዘመን ሆኗል።

ሰዎች በጦርነት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድሉ የገዳይነት ችሎታቸው በወባ ትንኝ ብቻ ነው የተበለጠው። በዓለም ዙርያ ወባ አንደኛ ገዳይ ነው። ስለዚህ የተዋጣልን ገዳዮች ብንሆንም በትንሽዋ በደካማዋ የወባ ትንኝ ተበልጠናል። እንደ ባለ አእምሮ ብናስብ እርስ በርሳችን ከምንዋጋ በወባ ትንኝ ላይ ነበር ጦርነት ማወጅ ያለብን። ነገር ግን እንደ ባለ አእምሮ አጥርቶ ማሰብ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን መታወቂያ አይደለም።

እስቲ በመጨረሻው ዘመን ትልቅ እና በጣም መጥፎ ሚና የምትጫወተውን የሰሜን ንጉስ ራሺያ አንዴ እንመልከት።
በምድራችን ላይ ከአሕጉራት ሁሉ ጨለማው አሕጉር አሁን ቤተክርስቲያናችን ከያዘችው አቋም የሚቃረን ተጨባጭ እውነታንም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለመቀበል የተዘጋ አእምሮዋችን ነው። ለዚህ ነው ኢየሱስ ከቤተክርስቲያኖቻችን ሁሉ ውጭ የቆመው። በዚህ በጨለመ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በማይቀበል ዘመናችን ውስጥ እግዚአብሔር በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ ኃይለኛ የጥፋት መልእክተኛ እያዘጋጀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን አለመቀበል ማለት ለራሳችን አስተሳሰብ የሚመቹን ጥቅሶች ላይ ብቻ ትኩረት እናደርጋለን ማለት ነው።

በአዙዛ የጀመረው ጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ በ1917 ሰዎች በፈጠሩት የቤተክርስቲያን ቡድን መከፋፈል ጀመረ። እግዚአብሔርም ይህንን ጠላ። ስለዚህ በ1917 ራሺያ ውስጥ በሌኒን አማካኝነት የኮምዩኒስት አብዮት ተጀመረ። ከዚህም የተነሳቸው አዲሷ ኃያል ሃገር ራሺያ በኃይሏ እጅግ ታላቅ ትሆንና አሜሪካን ታጠፋለች።

ለጊዜው አሁን እግዚአብሔር ራሺያዎችን አግዷቸዋል።

አሜሪካ የጴንጤቆስጤ እና የመጨረሻውን ዘመን መልእክት ነጻነት ቀምሳለች። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ አሜሪካኖች ሁለቱንም እንቅስቃሴዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነታ አርቀው ልክ እንደ ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ወደ ሰዎች ፍልስፍናዎች ውስጥ አስገብተዋቸዋል።

ኤርምያስ 4፡6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

አንድ ትንቢት ድርብ ፍጻሜ ሊኖረው ይችላል።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ባቢሎን መምጫዋ ከእሥራኤል በስተሰሜን ነበር። በእኛ ዘመን ራሺያ አድፍጣ የተቀመጠችበት ቦታ ወደ ሰሜን ዋልታ ጠጋ ይላል።

ሆሴዕ 11፡1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

በዘጸአት ውስጥ እንደተጻፈው እግዚአብሔር እሥራኤልን እንደ ሕዝብ ከግብጽ ጠርቶ አወጣቸው።
ነገር ግን ይኸው ትንቢት ኢየሱስ የሁለት ዓመት ሕጻን ሳለ ከሸሸበት ከግብጽ የ12 ዓመት ልጅ ሆኖ ወደ እሥራኤል በተመለሰ ጊዜ ተጠቅሷል።

ማቴዎስ 2፡14-15 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

ኤርምያስ 46፡10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።

የኤፍራጥስ ወንዝ ስም የተጻፈበት E አጠገብ ያለው አጭር ቀይ መመስመር እስራኤል ያለችበት ቦታ ነው።

ከሰሜን በኩል ያለችዋ ራሺያ በስተመጨረሻ እንድትጠፋ ተወስኖባታል። እግዚአብሔር በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ እንደምትታረድ የመስዋእት እንስሳ ለይቷታል።

ሌላ ግራ የሚያጋባ ነገር ደግሞ፤ ምዕራባውያን ራሺያ በኢንዱስትሪ እና በኃይል ራሷን እንድትገነባ ድጋፍ ያደርጉላታል ግን ተመልሳ በእነርሱ ላይ በጠላትነት ትነሳባቸዋለች። ከዚያም ምዕራባውያን ከዚህች ኃያል ሃገር ራሳቸውን መከላከል ይጠበቅባቸዋል።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት እስታሊን ራሺያን (ሶቪየት ሕብረትን) በኢንዱስትሪ ለማሳደግ የሚሆን ገንዘብ ያሰባሰበው ገበሬዎችን፣ የከተማ ነጋዴዎችን፣ ቤተክርስቲያኖችን፣ እና ሙዜሞችን በመዝረፍ ነበር። በዚህ መንገድ በተሰረቀው ገንዘብ ፈንታ አሜሪካውያን፣ ጀርመናውያን እና ጥቂት ሌሎች ሃገሮች 1500 የኃይል ማመንጫዎችን እና የኢንዱስትሪ ፋብሪካዎችን ለእስታሊን አበርክተዋል።

ምዕራባውያን በስርቆት የተሰበሰበ ገንዘብን እንደ ክፍያ ሲቀበሉ ምንም አልጨነቃቸውም። የሶቪየት ምጣኔ ሃብት የቀድሞው የራሺያ ግዛት አይቶት ከሚያውቀው በላይ አደገ።

ወደ 50 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች ታሰሩ፤ ከዚያም ከባድ ቅዝቃዜ ባለበት ጉላግ ውስጥ በእስታሊን አማካኝነት በግዴታ የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ተፈረደባቸው። ኃይለኛ ሃገር መገንባት ዝርፊያ እና የባርያ ጉልበት ብዝበዛ ይጠይቃል። ሰዎቹ የታሰሩበት ካምፕ ቦታው በስፋት ከፈረንሳይ አይተናነስም።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች በተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች፣ ከቻይና ውስጥ ከነበሩበት ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩና (ይህ በጨዋ አነጋገር ተሰርቀዋል ማለት ነው) ራሺያ ውስጥ እንዲተከሉ ተደርገዋል። ራሺያ በጦርነቱ የመጨረሻ ዓመት ላይ የወረረቻቸው ሃገሮች ላይ የፈጸመችው ይህ ዝርፊያ ሶቪዬቶች ከዚያ በኋላ እስከ 1960ዎቹ ድረስ ላገኙት አስደናቂ የኢኮኖሚ እድገት ዋስትና ሆኗል። ከዚያ በኋላ ከክሩሼቭ ጀምሮ ከባድ ችግር ተከሰተ። ተከማችቶ የነበረው ሃብት እየተንጠባጠበ አለቀ። በዚህ ጊዜ ሳይቤሪያ ውስጥ የተገኘው የነዳጅ ዘይት እጅግ ረድቷቸዋል። ነገር ግን ከነዳጅ ዘይቱ ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተከፈቱት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ገብቶ የሚሰራ ሰው ከገጠሮች ሊገኝ አልቻለም።

ምርታማነት የምእራባውያንን ያህል ከማደጉ በፊት እያሽቆለቆለ መጣ። ብዙ ሰዎች፣ ብዙ ማሽኖች ተባብረው የሚያመርቱት ምርት መጠኑ እያነሰ ሄደ። ደግሞም ቀድሞ የነበረው የማምረቻ እቃ እና ማሽንም ለጥገና እና ለእድሳት እጅግ በጣም ብዙ ወጪ መጠየቅ ጀመረ።

እቃዎቹ ደግሞ በአዲስነታቸውም እንኳ በጣም ምርጥ እቃዎች አልነበሩም።

የ1970ዎቹ የነዳጅ ዘይት ቀውስ ያደጉትን ሃገሮች የለወጣቸው የኢንዱስትሪ አውታር ጊዜው እንዳለፈበት ያመለከተ ነበር። ለዚህም ምላሽ በመስጠት እነዚህ ሃገሮች በሳይንሳዊ እና በቴክኖሎጂያዊ ለውጥ ወደፊት የሚያንደረራቸው የአሰራር ለውጦችን አደረጉ። የረቀቀ የኢንፎርሜሽን ዘመን ብቅ አለ። ራሺያ ወደ ኋላ ተጎተተች፤ በዚህም የተነሳ እንደ ፑቲን ያለ ጨካኝ መሪ ሾመች። በዲሞክራሲ እና “በነጻ” ምርጫ ሽፋን ፈላጭ ቆራጭነት ተመልሶ መጣ።

በ2000 ዓ.ም. ፑቲን የሚባል አንድ ሰው ተመረጠ፤ ከዚያም የቴሌቪዥን ጣብያዎችን በመቆጣጠር እና ተቃዋሚዎቹን ወደ እስር ቤት በመጣል በስልጣን ቆየ። አንድ ተቃዋሚ ክሬሚሊን አጠገብ በጥይት ተመትቶ ሞቷል።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶሃን በ2002 ተመረጠ፤ ከዚያ ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ተቃዋሚዎቹን እስር ቤት በመጣል የሥልጣን ዘመኑን አራዝሟል።

ስለዚህ የፈላጭ ቆራጮች መነሳት አሁንም ትልቁ የፖለቲካ አጀንዳ ሆኗል። ፈላጭ ቆራጮችን በሥልጣን ላይ የሚያስቀምጥ የዲሞክራሲ ሥርዓት መጥቷልና እንልመደው። ከዚህ የተነሳ የመጨረሻው ፈላጭ ቆራጭ ማለትም አውሬው በሚነሳ ጊዜ የመንግሥታትን ሥልጣን ለመውሰድ አሁል ያለው የፖለቲካ አዝማሚያ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል።

ሌላው ግራ የሚያጋባ ነገር ደግሞ ሰዎች ኬሚካል ማዳበሪያ በመጠቀም ብዙ ምግብን ማምረት ችለናል ነገር ግን ኬሚካል ተጠቅመን እርስ በራሳችን እንገዳደላለን።

ፍሪትዝ ሄበር የተባለ ጀርመናዊ አይሁድ ለሕይወትም ለሞትም የሚሆን ኬሚካል በመቀመም የተካነ ቀማሚ ነው። ሄበር በ1909 አየር ውስጥ ያለውን ናይትሮጅን በመጠቀም አሞኒያ ሚመረትበትን ዘዴ በመፍጠሩ በ1918 የኬሚስትሪ ኖቤል ሽልማት ተሸልሟል። ዘዴው እስከ ዛሬ ድረስ የሄበር ፕሮሰስ ተብሎ ይጠራል። አሞኒያ ሰው ሰራሽ ማራበሪያዎችን ለመስራት ያገለግላል፤ ማዳበሪያውም የእህልን ምርት በብዙ እጥፍ ይጨምራል። ይህም “እንጀራን ከአየር ላይ መፍጠር” ተብሏል።

በጣም የሚያሳዝነው ግን ይህ ቀማሚ ኬሚስት ለጦር መሳሪያነት የሚያገለግሉ መርዝ ጋዞችን መፍጠር ጀመረ፤ ይህንንም ያደረገው ጀርመናዊ አርበኛ ተብሎ ዝናን ለማግኘት ከነበረው ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ነበር። ጀርመኒ ውስጥ በጣም ጠንካራ ጸረ አይሁድ እንቅስቃሴ ነበረ፤ እርሱ ደግሞ እንደ አይሁዳዊ ሳይሆን እንደ ጀርመናዊ ሊቆጠር እና ተቀባይነት ሊያገኝ ፈለገ። በ1915 የአርበኝነት ስሜቱ ሲገነፍልበት ለመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ያሚያገለግሉ መርዝ ጋዞችን ፈጠረ። መርዝ ጋዙን ጀርመኖች በጠላቶቻቸው ላይ ሲጠቀሙት የፈጠረው ሰቆቃ በቃላት ሊገለጽ አይችልም። ከዚያም በኋላ ደግሞ ይባስ ብሎ በ1920ዎቹ ውስጥ አይሁዳዊው ሄበር ለተባይ ማጥፊያ የሚሆን መርዝ ጋዝ በመፍጠር አስተዋጽኦ አደረገ። የዚህ ምርምር ውጤት ኋላ ጀርመኒ ውስጥ በኦሽዊትዝ፣ ማይዳኒክ እና በተለያዩ ሥፍራዎች አንድ ሚሊዮን የሚያህሉ አይሁዳውያንን ለመግደል አገልግሎት ላይ የዋለውን ዛይክሎን ቢ የተባለ መርዝ ጋዝ ለመፍጠር አስተዋጽኦ አድርጓል። እህል እንዲበዛ የሚረዳ ማዳበሪያ በመፍጠር ለብዙዎች ምግብ እንዲዳረስ እና ሰዎች በሕይወት እንዲኖሩ ያደረገ አይሁዳዊ ጠቢብ እራሱ ደግሞ በፈጠረው መርዝ ጋዝ ለብዙ አይሁዳውያን ሰቆቃ እና መጥፊያ በገዛ እጁ አመጣ።

በአሁኑ ሰዓት በዓለም ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ምግብ የሚበላው ይህ አይሁዳዊ በፈጠረው የናትሮጅን ማዳበሪያ አማካኝነት በእርሻ ላይ ምርት እንዲበዛ በማድረግ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ማዳበሪያን ባለፈው ክፍለ ዘመን ከተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ግኝት ብለውታል።

የፍሪትዝ ሄበር ስም ከአይንሽታይን እና ከኒውተን ስም ይበልጥ በየቤቱ ሊታወቅ የሚገባው ስም ነበር። ነገር ግን የሞት ነጋዴ እንደመሆኑ ስሙ ጨለማ ውስጥ ተሰውሮ ቀርቷል።

ይህም አራተኛው ማሕተም የሚፈታበትን የመጨረሻውን የቤተክርስቲያን ዘመን ያመለክታል።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

በዙፋኑ ዙርያ ካሉት እንስሳት አራተኛው በሰማይ የሚበር ንሥር ሲሆን ዓይኖቹ የተሰወረውን ሁሉ የማየት ኃይል አላቸው።

የንሥሩ ድምጽ የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ነው። ይህም ድምጽ ወንድም ብራንሐም ስብከቶቹን ቀድቶ ባስቀመጠበት ቅጂዎች ውስጥ ይገኛል፤ እነዚህም ከ1947 እስከ 1965 በቴፕ የተቀዱ ስብከቶች በአስደናቂ መንፈሳዊ እይታ የተሞሉ ናቸው።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ።

ግን አንድ ችግር ተፈጠረ። ዘመኑ ክብር በተሞላ የእውነት መነቃቃት ሊጠናቀቅ ሲገባው ዘመኑ ቀዩ፣ ነጩ፣ እና ጥቁሩ የክፋት ኃይላት የሆኑ ፈረሶች ተባብረው ሲነሱ ነው የሚጠናቀቀው -- ማለትም ሐይማኖታዊ አታላይነት፣ ፖለቲካ፣ እና አጋንንታዊ የሆነ የገንዘብ ኃይል ተባብረው እውነትን ለመደምሰስ ይነሳሉ። ጌታ ሲመጣ መንፈስ ቅዱስ ተመልሶ ወደ ላይ ይሄዳል። ሕይወት ምድርን ለቆ ሲሄድ ሞት በታላቁ መከራ አማካኝነት ወደ ምድር ኃይሉን በሙሉ አሰባስቦ ይገባል።

የተጻፉት ምስጢራት ሲገለጡ ለምድር ሕይወትን ይዞ ሊመጣ የሚገባው ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰዎች ያልተጻፉ ምስጢራትን ለመተርጎም በሚያደርጉት ጥረት በመጠመዳቸው በሕይወት ፈንታ ሞትን ይዞላቸው መጣ።

ልክ እንደ ሄበር ማለት ነው፤ የሄበር ፈጠራ የብዙዎችን ሕይወት አድኗል፤ ነገር ግን እረሱ በተለይ የሚታወሰው ሞትን በመፍጠር ነው። እንደ ጀርመናዊ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሞክር ነበር። ነገር ግን በስተመጨረሻ አይሁዳዊ ነህ ብለው ገፉት። በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት መሞከር እውነትን ማግኛ መንገድ አይሆንም።

የቤተክርስቲያን መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ሲሰብኩ ሕይወትን ይሰብካሉ። ከዚያ በኋላ ግን በብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥሮች ላይ ይስታሉ። በትክክል መፍታት ሲከብዳቸው የራሳቸውን ግምት ይናገራሉ። ስሕተት ደግሞ ሞትን ያመጣል። ይህን አይነቱን ስሕተት የሚሰሩት ደግሞ በተለይ ያልተጻፉትን የሰባቱን ነጎድጓዶች ድምጽ ለመተርጎም ሲሞክሩ ነው። እንዲህ አይነት ሙከራ የሚያደርጉት “ሜሴጅ” ከሚባለው ቡድን ውስጥ መቆጠር ፈልገው ነው። ይህ መጠሪያ ግን ልክ እንደ “ሉተራን” ወይም “ሜተዲስት” ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መጠሪያ አይደለም። ስለ ነጎድጓዶቹ ንግግር የፈለጉትን ቢሉ እንኳ ይስታሉ፤ ምክንያቱም ሊተረጉሙ የሚችሉት ምልክት አልተሰጠም። ምንም መሰረት የሌለው ግምታቸው የሞትን በር ይከፍታል።

ተከታዮቻቸው በታላቁ መከራ ውስጥ ይረግሙዋቸዋል፤ ምክንያቱም የዚያን ጊዜ የሚወዱዋቸው መሪዎቻቸው ወደ ሞት እንደመሩዋቸው ያውቃሉ። ወደ ታላቁ መከራ የሚሄዱ የዳኑ ክርስቲያኖች በሙሉ የአውሬውን ምልክት ለመቀበል እምቢ ካሉ ይገደላሉ፤ የአውሬውም ምልክት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የቤተክርስቲያን ትምሕርቶች አእምሮን መሙላት ነው። አእምሮውን በቤተክርስቲያን ሰው ሰራሽ ትምሕርቶች የተሞላ ሰው የቤተክርስቲያን ቃል ወገን ነው እንጂ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ከተናገረው ጋር ወገን ተደርጎ አይቆጠርም።

ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

በአትክልት ሥር ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችም አየር ውስጥ ያለውን ናይትሮጅን ተጠቅመው ማዳበሪያ መስራት ይችላሉ፤ ነገር ግን የሚፈጥሩት ማዳበሪያ ከዓለም ሕዝብ ግማሹን ብቻ ለማብላት ነው የሚበቃው። የቀረው ግማሽ በሰው ሰራሽ ማዳበሪያ በተመረተ እህል ነው የሚኖረው። ከ7 ሰዎች 3ቱ እድሜ ለሄበር እያሉ ነው የሚኖሩት።

ሄበር ለቢሊዮን ሰዎች በማዳበሪያ አማካኝነት ምግብ እንዲዳረስ አደረገ፤ ነገር ግን በጦርነት ውስጥ እና በጋዝ ቤት ውስጥ ከሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞቱ።

በውስጣችን ካለው ድቅድቅ ጨለማ የተነሳ እራሳችንን ፈርተን ጥግ ላይ ነው የምንኖረው።

በጨለማ ውስጥ ከመሆናችን የተነሳ የምናምነው እውነት መሆኑን እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አልቻልንም።

ሳይንስ ከደረሰባቸው ግኝቶች ሁሉ ትልቁ ሁሉም ነገር የተሰራው ከአተሞች መሆኑን ማወቁ ነው።

በጣም አደገኛው የሳይንስ ግኝት ደግሞ ሰዎች አተምን እንዴት መሰንጠቅ እንደሚቻል ማወቃቸው ነው።

አሁን ትዳሮችም ይሰነጠቃሉ ማለትም ይፈርሳሉ፤ ይህም ከባድ ማሕበራዊ ቀውስ ያስከትላል።

በሳይንስ ውስጥ የተሰራው ትልቅ ስሕተት ፍላጎታችንን እንዲሞላልን እንዲሁም ከክፉ እና ከአደጋ እንዲጠብቀን በሳይንስ መታመናችን ነው።

በነዚህ አቅጣጫዎች ሳይንስ አስደናቂ ሥራዎችን ሰርቷል፤ ነገር ግን ከባድ ዋጋዎችንም አስከፍሎናል። ብዙ የእለት ተለት ችግሮችን የሚፈታልን የፕላስቲክ ኢንዱስትሪ አሁን ሊወገድና ወደ አፈርነት ሊቀየር የማይችል የብክለት አደጋ አስከትሎብናል።

መድሐኒት ለረጅም ጊዜ በሕይት እንድንቆይ የማድረግ ተዓምርን ሰርቷል፤ ሕጻናትም እንዳይሞቱ አድርጓል። ይህን በማድረጉ ግን ሌላ ከባድ ችግር አስከትሎብናል፤ ማለትም ምድር ከምትችለው በላይ በሕዝብ ብዛት እንድትጨናነቅ አድርጓል።

የኤሌክትሪክ ኃይል መገኘቱ ሕይወታችንን ለውጦታል፤ ነገር ግን ይህንን ኃይል ማመንጨት የብክለት ችግርን ሊያስወግድልን አልቻለም። ብክለትን የማያስከትል የኃይል ምንጭ አሁን 10 በመቶ ያህል አለ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ 30 በመቶ ያህል የማደግ እድሉ እጅግ የመነመነ ነው። አንድ ቢሊዮን ሕዝብ እስከ አሁን ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ይኖራል። የሕዝብ ቁጥር በየ15 ዓመቱ በአንድ ቢሊዮን እየጨመረ በመሆኑ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል በፍጥነት ማምረት አለብን፤ ይህም ንጹህ ኃይል መፍጠር ከሚቻለው በላይ ነው።

የኑክሊየር በጣም ሊጠቅም ይችል ነበር ግን ቆሻሻ የማስወገድ ችግር ይፈጥራል፤ ከዚያም ሌላ የኑክሊየር ጥፋት ስጋትም አብሮት አለ፤ እንደ ሰሜን ኮሪያ ያሉ ትንሽ ሃገሮች በኑክሊየር ስጋት የተነሳ ነው አደገኛ ተብለው የሚፈሩት።

በፖለቲካ ውስጥ ያለው ሥልጣንም ተመሳሳይ ችግሮች አሉት። በፖለቲካ ውስጥ ያለው ኃይል ከሌብነት፣ ከሙስና እንዲሁም ከኢፍትሃዊነትና ከስግብግብነት ነጻ ሊሆን አይችልም።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ሥልጣን በገንዘብ ፍቅር ተበክሏል፤ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን ውስጥ የአመራር ወንበሮች በቤተሰብ አባላት ተይዘው የልጅ ልጆች የሚተኩበት የቤተሰብ ንግድ ሆኗል።

የሕክምናው ዓለም በአዳዲስ ቫይረሶች እና መድሐኒትን በሚቋቋሙ የበሽታ አምጪ ሕዋሳት ተጥለቅልቋል። አዲስ መፍትሔ ባገኘን ቁጥር አዳዲስ ችግሮች ይፈለፈላሉ። ከጀርሞች ጋር የምናደርገውን የሩጫ ውድድር ሳናሸንፍ ሌሎች ውድድሮች ውስጥ እንገባለን።

ኩፍኝን ካስወገድን በኋላ የአእምሮ ዝግመትን ለመከላከል ብለን ክትባት እናቆማለን፤ የዛኔ ደግሞ ኩፍኝ እንደገና ወረርሽኝ ሆኖ ይመጣል። የትኛው ይበልጥ ጎጂ ነው፤ ዘገምተኝነት ወይስ ኩፍኝ የሚያደርሰው ጉዳት? ከመገመት ውጭ ምንም ማድረግ አልቻልንም።

ዘመናዊ መድሐኒቶች በሽታን በመዋጋት ደረጃ ድንቅ ሥራ ሰርተዋል፤ ነገር ግን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በመድሐኒት ሱስ እየተጠመዱ ነው። መልካም እና ክፉ ሁል ጊዜም ሳይነጣጠሉ የሚሄዱ ይመስላሉ።

የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ንጹህ ውሃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ከሕዝብ መብዛት ጋር ተያይዞ የውሃ ብክለትም እየተባባሰ ነው።

መጓጓዣዎች በዚህ ዘመናዊ ዓለም እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን በሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት መንገዶች በመኪኖች ብዛት መጨናነቃቸውና አደጋዎች መብዛታቸውን ሳንወድ ተቀብለናል። ከዓለም ሕዝብ ግማሽ በላይ የሚሆነው በከተሞች ውስጥ ነው የሚኖረው። ሳይንስ ተጠቅመን የምንጥላቸው እቃዎች ፈጠረልን፤ ይህም ተራራ የሚያህሉ የቆሻሻ ክምችቶችን አስከተለ። እቃዎችን መልሶ የመጠቀም ሕግ የማስፈጸም ሞራሉ ያላቸው ሃገሮች በጣም ጥቂት ናቸው።

የወደፊቱን ዓለም በርቀት ስንመለከት ብዙም ተስፋ የሚሰጥ ነገር የለም። ሳይንስ መፍትሄዎችን ካመጣ በኋላ ከመፍትሄዎቹ ጋር ደግሞ መፍትሄ የሌላቸው ብዙ ችግሮችን ይዞ ይመጣል።

ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ያድኑናል ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን እንደማያድኑን አይተናል።

የዓለም ሙቀት መጨመር የሚነግረን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ ውስጥ ጣልቃ መግባታችንን እና ተፈጥሮን ማቃወሳችንን ነው።

ሳይንስ አእምሮዋችን ከሚችለው በላይ አስተምሮናል። የእድገት እርምጃዎችን እንራመዳለን ግን እድገታችን ከሚያስከትላቸው የብክለት ችግሮች ራሳችንን ማዳን አልቻልንም። ሳይንስ ያደረገው መልካም ነገር ሁሉ በሚያመጣቸው አሉታዊ ውጤቶች እየተጣፋ ነው።

ሳይንሳዊ እውቀት መልካምም ክፉም ነው። የተወሰነ የእውቀት ደረጃ ላይ ከደረስን በኋላ ይህ እውቀት የሚያስከትላቸውን ክፉ ውጤቶች የምንቆጣጠርበት ጥበብ ይጎድለናል።

“መልካምና ክፉውን ከምታሳውቀው ዛፍ እንዳትበሉ” የሚለው ማስጠንቀቂያ ሁልጊዜ ወደ ልቤ ይመጣል።

ነገር ግን ከዚህች ዛፍ ሳይንሳዊ ፍሬ ተስገብግበን እንበላለን።

ምድር ተበክላለች፤ ተመርዛለች፤ በሕዝብ ብዛት ተጨናንቃለች፤ ሙቀት በዝቶባታል።

ሳይንስ ለወደፊቱ ለልጅ ልጆቻችን የሚሰጠን ተስፋ የለውም።

ተፈጥሮን ምን አድርገን አበላሸናት? ተጥለን ልንቀር ይሆን?

እግዚአብሔር የለሹ ሳይንሳዊ ጥበብ የእግዚአብሔርን መኖር ያለማቋረጥ እየካደ ሲያስተምረን እግዚአብሔር ደግሞ መኖሩን እያሳየን ይሆን?

ሳይን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን መንፈሳዊ ሕብረት ሊያጠፋ ይፈልጋል፤ በዚህም የቁሳዊነት ተጠቂ ያደርገናል። ስዚህ በሁለት በኩል እንጎዳለን።

ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። እግዚአብሔረ ለሳይንቲስቶች ከብዙዎቻችን የበለጠ ጥበብ ሰጣቸው። ከዚያም ሳይንቲስቶች ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጥበብ ተጠቅመው እግዚአብሔር የለም ብለው ሊያረጋግጡልን ይፈልጋሉ። የተሰጣቸውን ጥበብ እና አእምሮ በከንቱ ያባክናሉ።

ትልቁ ጠላታችን ሐጥያት ነው። እኛ ሐጥያተኛ ሰዎች ግን ልዩ ልዩ ሳይንሳዊ ጥበብን በማዳበር ለራሳችን ሌላ ጠላት ፈጥረናል። ሳይንስ ጠቃሚም ጎጂም የሆነ ግራ አጋቢ ነገር ሆኗል።

ሳይንስ ሊያለማንም ሊያጠፋንም የሚችል ኃይል ነው።

የሳይንስን አጥፊ ጎን መቆጣጠር አለመቻላችን ዋነኛው ምክንያቱ ሐጥያተኝነታችን ነው።

በራሳችን ብርታት ሐጥያትን ማሸነፍ ስለማንችል ሳይንስ የሚያመጣቸው ጉዳቶች ሕይወታችንን ያበላሻሉ። በስተመጨረሻ ምነው ሳይንሳዊ ምርምር ውስጥ ባለገባን ብለን የምንጸጸትበት ጊዜ ይመጣል። ሶርያዎችን ስለ አውሮፕላኖች፣ ስለ ጦር መሳሪያዎች እና ስለ መርዝ ጋዞች ምን እንደሚሰማቸው ሂዱና ጠይቋቸው።

የሳይንስን አሉታዊ ውጤቶች ልናመልጥ አንችልም። ሳይንስ በሚሰራልን መልካም ነገር ሁሉ ውስጥ ክፋትንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድናስፋፋ መንገድ ይከፍትልናል።

በስተመጨረሻ አርማጌዶን ስልጣኔያችንን ሁሉ ጠራርጎ ያጠፋልናል።

ይህም እግዚአብሔር በፈጠርናቸው ሳይንሳዊ ግኝቶች እንዳልተደነቀ ያሳያል።

ስኳር አንደኛ የሕዝብ ጤና ጠላት ሆኗል። ይህም በቅኝ አገዛዝ ላይ የመጣ በቀል ነው። የአውሮፓ ሃገራት የተወኑትን ቅኝ ግዛቶች የያዙበት ዋነኛ ዓላማ ስኳር ፍለጋ ነው። በተለይም በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ መካከል ያሉትን የካሪቢያን ደሴቶች የያዙዋቸው ስኳር ለማምረት ነው። ስኳር ለማምረት የሚጠቀሙት እሳት እና ከፍተኛ ሙቀት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባሪያዎችን ያለ እድሜያቸው ገደላቸው።

ደግሞም ለዚሁ ለስኳር ምርት ተብሎ ነው ከ10 ሚሊዮን በላይ ባርያዎች ወደ ደቡብ አሜሪካ እና ወደ ካሪቢያን ደሴቶች የተወሰዱት።

(ሌሎች ሁለት ሚሊዮን ባሪያዎች በመርከብ አትላንቲክ ውቅያኖስን እያቋረጡ ሳለ መርከብ ውስጥ ሞተው ወደ ባሕር ተጥለዋል።) የሞቱት ባሪያዎች በሌሎች ስኳር አምራች ባሪያዎች ይተኩ ነበር፤ እነዚህም ብዙ ሳይቆዩ ቶሎ ይሞታሉ። ግማሽ ሚሊዮን ባሪያዎች በአሜሪካ ደቡባዊ ግዛቶች ውስጥ ያሉ የጥጥ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ ተመደቡ። ጥጥ ለቀማ ከባድ መከራ የሚያበላ ሥራ ቢሆንም የስኳር ፋብሪካ ውስጥ የመስራትን ያህል አደገኛ አይደለም። ባርያዎቹም አሜሪካ ውስጥ በጥጥ ለቀማ በተሰማሩበት ታላቁ ፕሬዚደንት አብራሃም ሊንከን በ1865 ነጻ እስኪያወጣቸው ድረስ ተባዝተው ቁጥራቸው 4 ሚሊዮን ደረሰ። ጆን ዌስሊ እንግሊዝ ውስጥ በ1750 አካባቢ ስለ መዳን እና ቅድስና በመስበክ ታላቅ መንፈሳዊ መነቃቃትን አመጣ። እንግዚሊዝ ውስጥ በዚህ መነቃቃ አማካኝነት ዊልያም ዊልበርፎርስ ዳግመኛ ተወለደና ለ20 ዓመታት ያለመታከት የእንግሊዝ ፓርላማ ባርነትን እንዲሽር ግፊት በማድረጉ በስተመጨረሻ በ1807 ባርነት ተሻረ።

እጃቸው በደም የተበከሉት የሸንኮራ አገዳ እርሻ ባለቤቶች አውሮፓ ሱሰኛ የሆነችበትን ስኳር እያመረቱ ይልኩላት ነበር። በ1965 ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ወደ ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን እምነት እንድትመለስ ያቀረበውን ጥሪ አሜሪካ አልቀበልም አለች። ከዚያ በኋላ አሜሪካ ውስጥ ስኳርን በብዛት ማምረት ተጀመረ። አሜሪካኖች ብዙ ግሉኮስ ወደ ፍሩክቶስ የሚለወጥበትን ዘዴ አገኙ። ደግሞም ከበቆሎ ከፍተኛ የስኳር መጠን ያለው የግሉኮስ እና የፍሩክቶስ ድብልቅ የሆነ ጣፋጭ ነገር ማዘጋጀት ቻሉ። የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት የእነዚህ ሁለት ነገሮች ውህደት ሞት የማስከተል ኃይል አለው። ሕዝቡ ግን ይህንን መርዛማ ውህደት ስኳር ይሉታል። ከ1970 እስከ 1990 ድረስ ከፍተኛ ፍሩክቶስ ያለበት ስኳር ፍጆታ አሜሪካ ውስጥ በሁለት እጥፍ አደገ። የትኛውም የምግብ አይነት ፍጆታ በዚህ መጠን አላደገም። አሜሪካኖች ከመጠን ያለፈ ውፍረት ተጠቂ ሆኑ ምክንያቱም ከፍተኛ ፍሩክቶስ ያለበት የምግብ ማጣፈጫ ውስጡ ሌፕቲን ስለሌለበት ሆዳችን ቢሞላም እንኳ ጥጋብ እንዲሰማን አያደርግም። ጣፋጭ አብዝቶ መብላት ከስኳር በሽታ ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው።

በዚሁ ጊዜ ነበር የሜሴጅ አማኞች ልዩ ልዩ የነጎድጓድ እምነታቸውን መፈልሰፍ የጀመሩት፤ ይህም እምነታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ባለገለጣቸው ሚስጥሮች ላይ ነበር። ስዚህ በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸው ትኩረት እየቀነሰ ሄደ፤ እነርሱን የሰውን ንግግር ጥቅስ እየወሰዱ የራሳቸውን ትርጓሜ በመስጠት አስተምሕሮዋቸውን መቅረጽ ጀመሩ። ይህም ቀስ በቀስ ነገር ግን ያለማቋረጥ እምነታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ እየራቀ እንዲሄድ አደረገ። አሁን ስለ ነጎድጓዶቹ ሚስጥር የሚያስተምሩ ሰዎች ትምሕርታቸው ትክክለኛ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈው ማሳየት አይችሉም። ይህም ከፖፑ ጋር በአንድ ጎራ እንዲመደቡ አድርጓቸዋል፤ ምክንያቱም ፖፑ አብዛኛውን እምነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፎ ትክክለኛነቱን ማሳየት አይችልም።

ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

መጽሐፍ ቅዱስን የናቀችዋ ሮም ከማይሳሳተው ፖፕዋ ጋር የጋለሞታዎች እናት ነች። የሜሴጅ ተከታዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ልዩ ልዩ እውነታዎች ላልተጻፉት ነጎድጓዶች ትርጓሜ ይሰጣሉ ብለው በማመን ተሳስተዋል። የተለያዩ የሜሴጅ ተከታዮች ያለተጻፈውን የነጎድጓዶች ቃል ለመተርጎም የሚጠቀሙዋቸው የተጻፉ እውነታዎች ይለያያሉ። ከዚህም የተነሳ ግራ የሚያጋቡ እጅግ ብዙ የተለያዩ የሰባት-ነጎድጓድ አስተምሕሮዎች ተፈልፍለዋል። ወንድም ብራንሐም “የእግዚአብሔር ድምጽ” ስለነበረ የእርሱ ቃላት እንከን የሌለባቸው “ስሕተት የማይገኝባቸው” ንግግሮች ናቸው ይላሉ። ይህም ልክ የፖፑ ንግግር በካቶሊኮች ዘንድ ስሕተት የሌለበት ተደርጎ እንደተቆጠረው ነው።

አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሚላክልን ቃል አልተገባልንም። የሜሴጅ አማኞች የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወርዷል ይላሉ ነገር ግን መልአኩ መቼ እና የት እንደወደረ በመካከላቸው ስምምነት የለም። ስለዚህ ለ50 ዓመታት ወርዶ እዚሁ ቆይቷል ይላሉ። ግን ምንድነው ያመጣው ውጤት? ማንም የሚያውቅ የለም።

ብዙዎች መልአኩ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የታየው ደመና ነው ይላሉ፤ ደመናውም በሰባት መላእክት ክንፎች የተፈጠረ ሲሆን በአሪዞና ውስጥ 42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ከታየ በኋላ ወደ ምድር ጭራሽም አልወረደም። ደግሞም ጌታ ራሱ በደመናው አማካኝነት በሚስጥር ወርዷል ይላሉ፤ ይህም ምስጢራዊ መገኘቱ ፓሩሲያ ይባላል ይላሉ። መላእክቱ ግን ከስምነት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ሰው ሳያያቸው ወንድም ብራንሐምን ለማግኘት ከፍላግስታፍ 200 ማይልስ በስተደቡብ ወዳለው ሳንሴት ፒክ ወርደው ነበር። ሳንሴት ፒክ የታክሶን ከተማን የሚያካትተው የሶኖራን በረሃ አካል ነው። ሰባቱ መላእክትም ከወንድም ብራንሐም ተለይተው ሲሄዱ ማንም ሳያያቸው ነው የሄዱት፤ ደግሞም ደመና አልፈጠሩም።

ስለዚህ ጌታ ወይም መልአኩ በረሃ ውስጥ ወረደ ምክንያቱም ሳንሴት ፒክ ሶኖራን በረሃ ውስጥ ነው ያለው። ግን ይህ እውነት ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በበረሃ ውስጥ አይመጣም።

ወንድም ብራንሐም ይኖርበት የነበረው ታክሶን እዚያው በረሃ ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ የእርሱም አገልግሎት የጌታ ምጻት አይደለም።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ፌብሩዋሪ 28 ቀን ታይቶ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የዋለው ደመና ወይስ ማርች 8 ቀን ሳይታዩ የመጡት መላእክት፡ የትኛው ነው የመልአኩ ወይም የጌታ መውረድ የነበረው? የሜሴጅ አማኞች የትኛው ክስተት የጌታ ወይም የመልአኩ መውረድ መሆኑን እርገጠኛ አይደሉም፤ ስለዚህ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን እራሳቸው በፈጠሩዋቸው አስተምሕሮዎቸ ላይ እንደሚከራከሩ ሁሉ የሜሴጅ አማኞችም በዚህ ይከራከራሉ።

ነገር ግን ማርች 24 ቀን 1963 ዓ.ም. የተሰበከው ሰባተኛው ማሕተም መልእክት ደግሞ ጌታን ወደ ምድር መልሶ የሚያመጣ ስብከት ነበር። ስለዚህ የትክክለኛው ጊዜ ጉዳይ አደናጋሪ ሆኗል።

63-1110 በወኅኒ ያሉ ነፍሳት
ሰባተኛው ማሕተም ወደ ምድር መልሶ ያመጣዋል
ግን ነገሩን የባሰ የሚያወሳስበው ደግሞ ሰባተኛው ማሕተም ገና ያልተፈታ መሆኑ ነው። ስለዚህ ጌታ እስከ ሐምሌ 1964 ድረስ እንኳ አልመጣም።

64-0719 የመለከት በዓል
ሰባተኛው መለከት ገና አልተነፋም፤ ታውቃላችሁ አይደል። ሰባተኛው መለከት ሲነፋ ምጻቱ ይሆናል።

እንደውም ጁላይ 1965 ከመሞቱ ከአምስት ወራት በፊት ወንድም ብራንሐም ራሱ የጌታን መምጣት እየተጠባበቀ ነበር።

65-0725 ተራራው ላይ ያለው መስህብ ምንድነው?
ወደ ተራሮቹ ሰላምታ እንልካለን፤ ፕሬስኮት አሪዞና ውስጥ ወንድም ሊዮ መርሲየ እና የእርሱ ቡድን ተራራው ላይ ወጥተው የጌታን መምጣት ይጠባበቃሉ።

የፕሬስኮት ከተማ የምትገኘው በፍላግስታፍ እና በሳንሴት ፒክ ከመተሞች መካከል ነው። ስለዚህ ወንድም ብራንሐምን ብትጠይቁት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም. በፍላግስታፍ ከተማ በከፍታ ላይ የታየው ደመናም ሆነ ማርች 8 ቀን 1963 ዓ.ም. ሳንሴት ፒክ አጠገው ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡት መላእክት ሁለታቸውም ክስተቶች የጌታ ምጻት አልነበሩም።

የወንደም ብራንሐም ተከታዮች የነጎድጋዶች መልእክታቸውን ለማዘጋጀት ብለው እርሱን የተናገራቸውን ጥቅሶች አመሰቃቀሉ።
ይህም የተለመደ ነገር ነው።

የነጎድጓድ ልጆች የተባሉትን ያዕቆብ እና ዮሐንስ ታስታውሳላችሁ? እነርሱ በተናገሩት አልስማማ ያሉት መንደርተኞች ላይ ከሰማይ እሳት ሊያውዱባቸው ፈለጉ።

ኢየሱስ ግን ምን አይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም አላቸው።

ልክ እንደ ዘመናዊዎቹ የነጎድጓድ አማኞች። ሃሳባቸውን የሚደግፍላቸው ጥቅስም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የላቸውም።

በምን አይነት መንፈስ ነው የተሞሉት? መጽሐፍ ቅዱስን በማታከብረዋ እናት ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነዋ።

መጽሐፍ ቅዱስን መከተል ባቆማችሁ ጊዜ የጋለሞታይቱ የሮም ልጆች ትሆናላችሁ።

ማርቆስ 3፡17 የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
ሉቃስ 9፡54 ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት።
55 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፦ ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም፤
56 የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።

የነጎድጓድ ትምሕርት የሚያስተምሩ የሜሴጅ አማኞች ትምሕርታቸውን አልቀበልም ብትሏቸው ስማችሁን ለማጥፋት እንዴት ቸኩለው እንደሚነሱ ታያላችሁ።

ነገሮች እስከ አሁንም አልተለወጡም። መንፈሱ እንደነበረ ነው።

65-0725 የተራራው መስህብ ምንድነው?
በታክሶን ለተሰበሰቡት ሰላምታንን እንልካለን፤ የጌታን ምጻት ለመጠባበቅ በዚያ ተሰብስበዋል። ደግሞም በሒውስተን ቴክሳስም ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት። እዚያ ቺካጎ ውስጥ ተሰብስበው የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም። በምሥራቅ በውቂያኖሱ ዳር ኒው ዮርክ ውስጥ እና ኮኔቲከት ውስጥ ለተሰበሰቡትና የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁትም። እዚህ ቢመጡ ለእነርሱ የሚሆን መቀመጫ ቦታም የለንም። ስለዚህ በስልክ በመጠቀም ቃሉን እንልክላቸዋለን። ዛሬ ማታ በክላርክስቪል ለተሰበሰቡት ለወንድም ጁንየር ጃክሰን እና ለቡድኑ እንዲሁም ለወንድም ራድል እና አብረውት የጌታን ምጻት ለሚጠባበቁት ቡድኖቹ ሰላምታ እንልካለን። እኛም ደግሞ ዛሬ ማታ እዚህ በቤተክርስቲያን በተሰበሰብንበት የጌታን ምጻት እንጠባበቃለን።

1965 ዓ.ም. በመጠናቀቅ ላይ ሳለ ወንድም ብራንሐም የጌታን መምጣት መጠባበቁን አላቆመም ነበር።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

በስውር መምጣት የሚባል ነገር የለም። ኢየሱስ በወንዶች እና በሴቶች ልብ ውስጥ ነው የሚኖረው።

ማቴዎስ 24፡3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

“መምጣት” የሚለው በግሪክ “ፓሩሲያ” የሚባለው ቃል ነው። ይህ ቃል በስውር መገኘቱን ሊያመለክትም ይችላል። ኢየሱስ ግን በስውር ስለመገኘት ወይም ስውር ስለሆኑ እልፍኞች እንዳናምን ተናግሮናል።

1ኛ ተሰሎንቄ 3፡13 ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥

“መምጣት” የሚለው የግሪክ “ፓሩሲያ” የሚለው ቃል ነው። ስለዚህ ለምንድነው በስውር መገኘት የማይሆነው? ምክንያቱም ኢየሱስ የሚመጣው ከትንሳኤ በኋላ ስለሆነ ሁላችንም ከቅዱሳን ሁሉ ጋር እናየዋለን።

1ኛ ተሰሎንቄ 2፡19 ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?

ጳውሎስ እርሱ ሲሰብክ ያመኑትን ሰዎች ኢየሱስ ሲመጣ ከኢየሱስ ጋር እንደሚያያቸው ያምን ነበር።

ይህ “ምጻት” የተገለጸው “ፓሩሲያ” የሚለውን ቃል በመጠቀም አይደለም። ስለዚህ “ፓሩሲያ” የሚለውን ቃል ከ“ምጻት” ጋር ለማገናኝት አትንጠራሩ።

ጳውሎስን እና ከሙታን የተነሱትን ቅዱሳን እስካሁን አላየናቸውም። ስለዚህ ኢየሱስ እስካሁን አልመጣም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡22 ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።
23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
ክርስቶስ ከሙታን በመነሳት የመጀመሪያው ሰው ስለነበረ በክርስቶስ ምጻት (ፓሩሲያ) ሙታን ከመቃብር ውስጥ ይነሳሉ።

ማቴዎስ 24፡37 የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት (ፓሩሲያ) እንዲሁ ይሆናልና።

39 የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት (ፓሩሲያ) ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

የጌታ ምጻት ቅዱሳንን ሲያድናቸው ዓለምን ግን ጠራርጎ ወደ ታላቁ መከራ ጥፋት ውስጥ ያስገባታል።

የሜሴጅ አማኞች የደመናው መታየት የሎዶቅያ ቤተክርቲያን ዘመን ማለቂ ነው ይላሉ።

ወንድም ብራንሐም ግን እንደዚያ አላለም።

65-1204 ንጥቀት
አሁን የምንኖረው በሎዶቅያ ዘመን ውስጥ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃን። ከዚህ በኋላ ሌላ ዘመን የለም። ሊኖር አይችልም። ስለዚህ በሎዶቅያ ዘመን እየኖርን ነው።

ይህ በመጨረሻ ስብከቱ የተናገረው ቃል ነበር፤ እርሱም አሁን በሎዶቅያ ዘመን እንደምንኖር ነው ያምን የነበረው።
ሎዶቅያ፤ ግራ የሚያጋባ ዘመን።

ሕክምና ብዙዎች ለረጅም እድሜ እንዲኖሩ አደረገ፤ ከዚህም የተነሳ አሁን በስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ1750 አካባቢ የነበረው ሕዝብ ቁጥር በስምንት እጥፍ ጨምሯል። ሰው ሁሉ አሁን ምዕራባውያን በሚኖሩበት የኑሮ ደረጃ መኖር ከፈለጉ ይህንን አይነቱን የሕዝብ ቁጥር እድገት ይዘን መቀጠል አንችልም።

በ1900 እና በ2000 ዓ.ም. መካከል ብቻ ከየትኛውም ክፍለ ዘመን የበለጠ ብዙ ሰው ተገድሏል። ይህ ክፍለ ዘመን ከዘመናት ሁሉ ይበልጥ በጭካኔ እና በደም ማፍሰስ የተሞላ ክፍለ ዘመን ነው፤ ሆኖም ግን የዓለም ሕዝብ ቁጥር አራት እጥፍ ጨመረ፤ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ተነስቶ በመቶ ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ ስድስት ቢሊዮን ደረሰ። በሁለት ታላላቅ የዓለም ጦርነቶች እና በኑክልየር ጥፋት ስጋት ውስጥ ሳለን ብዙ ሰዎች በዚሁ አስጨናቂ ጊዜ ውስጥ በመቶዎች ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሰላም እና በተድላ ኖረዋል።

ራሺያ ውስጥ ሌኒን እና እስታሊን፣ ቻይና ውስጥ ማኦ ዜዶንግ፣ እና ጀርመኒ ውስጥ ሒትለር ሁላቸውም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደሉ፤ ምክንያቱም በምቾታቸው መቆየት የሚችሉት በመግደል እንደሆነ ያምኑ ነበር።

በ1960ዎቹ አንዲት ባለትዳር ሴት በኑሮ ሸክም እንዳትቸገር የምትወልዳቸውን ልጆች ቁጥር መመጠን ትችል ዘንድ የሚረዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሐኒቶች ተፈጠሩ። ነገር ግን እነዚሁ መድሐኒቶች ወሲባዊ ልቅነት እንዲስፋፋ አደረጉ፤ በተለይም ያላገቡ ሰዎች እና የተፋቱ ሰዎች ራሳቸውን በመግዛት እንዳይኖሩ አደረጉ።

እንግሊዝና ፈረንሳይ ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የገቡት ፖላንድን ከጀርመኒ ወረራ እናድናለን ብለው ነበር። በዓለም ላይ ካሉት ነጻ ሪፓብሊኮች ሁሉ ጠንካራ የሆችዋ አሜሪካ የሒትለርን ወታደራዊ መንግሥት በጦርነት ያሸነፈችው በራሺያ ወታደራዊ መንግሥት ድጋፍ አማካኝነት ነው።

በቅኝ ግዛት ተይዘው የነበሩ ሃገሮች ነጻነቶቻቸውን ሲቀዳጁ የአውሮፓውያን የቅኝ አገዛዝ ፈረሰ። ከዚያም ዶላር በዓለም ላይ ታላቁ የገንዘብ አይነት በሆነ ጊዜ አሜሪካ የራሷን የገንዘብ ኃይል ገነባች፤ የአሜሪካ ንግድም በዓለም ላይ ሁሉ ተስፋፋ። አሜሪካ የዓለም ገበያ ላይ የነበራት የበላይነት አሁን እየቀረ ነው።

አውሮፓ ለዓለም ሕዝባዊ መንግሥትን አበርክታለች። አሁን የአውሮፓ ሕብረት መመስረቱ ዓለማው የሕዝባዊ መንግሥታትን ሕልውና ለማጥፋት ነው። 27 የአውሮፓ ሃገሮች ተባብረው የዓለምን ታላቅ ኢኮኖሚ ለመገንባት ቆርጠው ተነስተዋል። የአውሮፓ ሃገሮች በሙሉ አንድ የገንዘብ አይነት ማላትም ዩሮ መጠቀማቸው እና ዜጎቻቸው ያለ ቪዛ ከአንድ ሃገር ወደ ሌላ ሃገር መንቀሳቀስ መቻላቸው እንደ አአሜሪካ ያለ አንድ ትልቅ ሃገር ለመፍጠር ነው።

ብዙ ቤተክርስቲያኖች የአውሮፓ ሕብረት ባለ አሥር ቀንዱ አውሬ ነው ብለው ስተዋል። ነገር ግን የአባላት ሃገሮች ብዛት ወደ 27 ሲያድግ (እንግሊዝ ከሕብረቱ ስትወጣ 26) የሃገሮቹ ብዛት ከአሥር መብለጡ ይህንን ትርጓሜ ገደል አስገብቶታል። አንድ ራስ እና አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ የሮማ ግዛት ነው የነበረው። አሥሩ ቀንዶች የሮማ መንግሥትን ለማፍረስ የረዱ አሥር የባርቤሪያን ነገዶች ናቸው። እነዚሁ ነገዶች ከዚያ በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ኃይል እና ዝና ለመገንባት አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ዳንኤል 7፡7 ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።

ዳንኤል 7፡8 ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።

በአሥሩ ቀንዶች መካከል አንድ ትንሽ ቀንድ ብቅ ይላል፤ ከዚያም ሦስቱን ይነቅላቸዋል።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሥላሴ የምታምን ቤተክርስቲያን ናት። የሮማ መንግሥትነ ካፈራረሱት አሥር ነገዶች ውስጥ በሥላሴ የማያምኑት ሄሩሊ፣ ኦስትሮጎት፣ እና ቫንዳልስ የተባሉ ሦስት ነገዶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም በኢጣሊያ እና በሰሜን አፍሪካ ይኖሩ ነበር።

በ550 ዓ.ም. አካባቢ የኮንስታንቲኖፕል ንጉሥ ሮም ውስጥ ላለው ፖፕ ጥበቃ ለማድረግ ሲል እነዚህን ሦስት ነገዶች ፈጽሞ አጠፋቸው።

ስለዚህ ከዚያ ወዲያ ዓለም ወደ 900 ዓመታት የጨለማ ዘመን ስትገባ የሥላሴን እምነት የሚቃወም አልነበረም። ከዚያ በኋላ የቫቲካን ከተማ ተገነባች፤ ስፈቷም አንድ ኪሎ ሜትር ካሬ ነው። ፖፕ ሊዮ 4ኛው (847 - 855) በዙርያዋ ግምብ አጥር ያስገነባ ጊዜ ነው ከተማ የሆነችው። በከተማይቱ የሚኖረው ሕዝብ 800 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 600ው የቫቲካን ዜግነት አለው። ብዙዎቹ የቫቲካን ዜጎች በሌሎች ሃገሮች ውስጥ ነው የሚኖሩት። ቫቲካን በስፋትም በሕዝብ ብዛትም ከምድር ሃገሮች ሁሉ ትንሽዋ መንግሥት ናት። ነጻነቷ የታወጀው በሙሶሊኒ አማካኝነት በ1929 ነው። ያም ዓመት ዓለም በሙሉ የከሰረችበት ዓመት ነው፤ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት የጀመረው በዚያ ዓመት ነው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነጻነት እውቅናን የሰጠ ሁሉ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መውደቁን ሊያሳይ ስለፈለገ ነው።

ሕንድ ውስጥ ጋንዲ በእንግሊዞች ላይ አስደናቂ ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጉ እንግሊዞች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቅኝ ግዛታቸውን ለቀው ለመሄድ ተገድደዋል። ከዚያም ሙስሊም ፓኪስታን ከሒንዱ ሕንድ ስትገነጠል በሙስሊሞች እና በሒንዱዎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተገደሉ። አሥር ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በግድ ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ወይም ወደ ደቡብ ሄዱ፤ ይህም በታሪክ ውስጥ ከተከሰቱ የሕዝብ መፈናቀሎች ውስጥ ትልቁ ነው። ይህም ጋንዲ እድሜውን በሙሉ ላረደገው ሰላማዊ ትግል አሳዛኝ ፍጻሜ ነበር።

አይንሽታይን ጦርነትን የሚጠላ ሰላማዊ ሰው ነበረ። ነገር ግን እርሱ ባልጠበቀው መንገድ የፈጠረው E=mc2 የተባለ የኃይል ቀመር ለአቶሚክ ቦምብ መፈጠር መሰረት ጣለ።

በሳይንስ ቀውስ የሚባለው አንድ ትንሽ ክስተት ያልተጠበቀ ትልቅ አሉታዊ ውጤት ሲያመጣ ነው።

በ1979 የኢራን ሻህ በሃገሩ ከተቀሰቀሰው አብዮት ሸሽቶ ሄደ። ኢራናውያን አብዮተኞች አሜሪካውያንን ታጋቾችን ያዙ። ታጋቾቹን ነጻ ለማውጣት የመጡት ሄሊኮፕተሮች ሁለት የአሸዋ አውሎ ነፋስ ውስጥ በመግባታቸው ነጻ የማውጣት ተልእኮው ከሸፈ። ይህ ነጻ የማውጣት ዘመቻ ሳይሳካ ሲቀር ራሺያኖች የአሜሪካ ወታደራዊ ድክመት አድርገው ቆጠሩት፤ ምክንያቱም ከዚያ በፊት አሜሪካኖች በቬትናም ጦርነት ተሸንፈዋል። ስለዚህ ራሺያ አፍጋኒስታን ላይ ጥቃት ሰነዘረች። አሜሪካኖች ደግሞ አፍጋኖችን እና አጋሮቻቸውን በውትድርና አሰልጥነው የጦር መሳሪያ አስታጠቁዋቸው፤ እነርሱም በስተመጨረሻ ራሺያኖችን ወግተው አሸነፉ። ሶቪየት ሕብረት የሚበለው የራሺያ ግዛትም ከዚያ በኋላ ወዲያው ፈራረሰ።

አሜሪካኖችም ያሸነፉ መሰላቸው። ነገር ግን አፍጋኒስታን ውስጥ ቢን ላደንን ጨምሮ ጠንካራ ጦረኞችን አሰልጥነው ለቀቁ።
አፍጋኒስታን ውስጥ የተዋጋው ሳውዲ አረቢያዊው ቢን ላደን ሳውዲ አረቢያ ለአሜሪካ ከሳዳም ሁሴን ሳውዲ አረቢያን እንድታስጥላት ጥያቄ ባቀረበችበት ጊዜ ተቆጣ። አሜሪካ በ1991ዱ ጦርነት ኢራቅን አሸነፈች፤ ነገር ግን ይህ ጦርነት ቢን ላደንን ቀንደኛ የአሜሪካ ጠላት አደረገው። እርሱም ወደ አፍጋኒስታን ሄዶ ኒው ዮርክ ውስጥ ያሉትን መንትያ ሕንጻዎች በሴፕቴምበር 11, 2001 የሚያወድምበትን ሴራ ጠነሰሰ። ይህም ዓመት አሜሪካን ከታላቁ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዋ ጋር መልሶ በጦርነት ጎዳና ላይ እንድትራመድ ያደረጋት ታሪካዊ ክስተት ሆኗል።

ሁለት የአሸዋ አውሎ ነፋሶች አሜሪካ ኢራቅን እና አፍጋኒስታንን የምትወርርበትን መንገድ ጠርገዋል።

ልክ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እንዲከፈት ያደረጉትን ሁለት የፕሪንሲፕ ተኮሶች ይመስላሉ። ከዚያም ደግሞ ያልተሳካው የሰላም ስምምነት ደምብ ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አመራ።

ይህ አይነቱ ማስረጃ የሎዶቅያ ዘመን ማለቂያ በሁከታም እና ነውጠኛ መናፍስት የታጀበ መሆኑን ያመለክታል። ትንንሽ ክስተቶች ያልተጠበቁ ትልልቅ ውጤቶችን ሊያስከትሉ ይቸላሉ።

ነገር ግን በኢራቅ የተደረገው ጦርነት መንፈሳዊ ገጽታም አለው።

ነብዩ ኤርምያስ የባቢሎን ከተማ እንደምትጠፋ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ ተመልሳ እንደማትገነባ እና ሰውም እንደማይኖርባት ተንብዮ ነበር።

ኤርምያስ 50፡29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤

ኤርምያስ 50፡39 ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኵላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።

የኢራቁ ፈላጭ ቆራጭ ሳዳሙ ሑሴን ለራሱ እና በዳንኤል ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ለነበረው ለናቡከደነጾር መታሰቢያ እንዲሆን ባቢሎንን መልሶ ሊገነባ ወሰነ።

ከዚያም አሜሪካ ለነዳጅ አቅራቦቷ ጥበቃ ለማድረግ እና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያችን ፈትሻ ለማግኘት ኢራቅን በ2003 ወረረች። ጦርነቱ በጣም መራራ ነበረ፤ በስተመጨረሻውም ሳዳም ተገደለ። አሜሪካ ኢራቅን የወረረችበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር ግን የኤርምያስን ትንቢት ለመፈጸም ፈልጓል። ሳዳም ሑሴን ትንቢቱን ሊሽር ፈለገ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሳዳምን ለማጥፋት አሜሪካን ተጠቀመ።

በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እንዳንዳፈር እንማራለን።

በአንድ ነገር ሁል ጊዜ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ፤ እርሱም ይህ ነው፡- ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች አንዱ እንኳ መሬት ጠብ አይልም።

በተጨማሪ ኢራቅ በሁለቱ የአሜሪካ ወረራዎች ክፉኛ ከመውደሟ የተነሳ አሁን ሰዎች ፈጽማ የወደቀች መንግሥት እንደሆነች ያምናሉ።

ስለዚህ በፊት የእሥራኤል ቀንደኛ ጠላት የነበረችዋ ኢራቅ ለጊዜው ተሽመድምዳለች።

እግዚአብሔር ሕዝቡን እሥራኤልን እያታደገ ነው ማለት ነው።

ሶርያ በእርስ በርስ ጦርነት እና በከተሞቿ ውድመት በመጠመዷ የተነሳ ለጊዜው እሥራኤል ላይ አንዳችም ስጋት አትፈጥርም። በፊት ኃይል የነበሩት ሃገሮች ሶርያ እና ኢራቅ ለጊዜው እሥራኤልን የማጥቃት አቅም የላቸውም። እግዚአብሔር ጥርሳቸውን ሰብሮ ደካማ አድርጓቸዋል። ለምን? ምክንያቱም ኢየሱስ በታላቁ መከራ ወቅት ወደ አይሁዶች ይመለሳል። ስለዚህ አይሁዶች በሕይወት መቆየት አለባቸው። አደገኛ ጠላቶቻቸው በቁጥር ሲቀንሱላቸው በሕይወት የመቆየት እድላቸው ይጨምራል።

በአሜሪካ የምርጫ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ነውጥ ያስነሳው ምርጫ የ2016ቱ ምርጫ ነው። ከእጩዎች መካከል ሒላሪ ክሊንተን ከሁላቸውም ይበልጥ ተወዳጅ ነበረች፤ ደግሞም የባለሙያዎች ግምት ሁሉ ምርጫውን እርሷ እንደምታሸንፍ ነበር የተነበየው።

ዜናዎችን ልናምን አንችልም፤ ምክንያቱም ሰዎች እርስ በራሳቸው የሚነጋገሩት መስማት የሚፈልጉትን ነው።

ነገር ግን ሒላሪ ሰዎች እንደ “ባለጌ” በሚቆጥሩት በትራምፕ ተሸነፈች። እርሱም ማንኛውንም እጩ ገደል ሊያስገቡ የሚችሉ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ሁሉ በቀላሉ አልፎ አሸነፈ።

ስንት እና ስንት እንቅፋቶች እያሉበት ለምንድነው ያሸነፈው?

ምክንያቱም የአሜሪካ ኤምባሲን ወደ ኢየሩሳሌም በማዛወር ለኢየሩሳሌም እውቅና ለመስጠት ቃል ገባ።

አሁንም የምናየው ብዙ ችግሮችን ሁሉ አልፎ የሚፈጸመውን ትንቢት ነው።

ኢሳያስ 11፡12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።

የተደበላለቁ የእለት ተለት ክስተቶች ነውጥ መካከል የትንቢት ሞገድ በጸጥታ እየተንቀሳቀሰ ማንም ሊያስቆመው በማይችል ኃይል ይፈጸማል።

ነገር ግን እግዚአብሔር ማንን እየተጠቀመ እንሆነ እናስተውላለን?

የወደፊቱን ክስተቶች ለማየት ሰፋ ያለ ቅድመ እውቀት ያስፈልጋል።

በዓለም መሪያዎች የሚወሰዱ እርምጃዎች ብዙውን ጊዜ ማዘናጊያዎች ናቸው።

የሰው ድክመትም ሆነ የሰው ነጻ ምርጫዎች እያሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሁልጊዜ እነዚህን ሁሉ አልፎ ይፈጸማል።

ሙሴ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እግዚአብሔር ግን ለሥራው ተጠቀመበት።

እውነት በጣም ውስብስብ ከመሆኗ የተነሳ ከአስተዋይ ሰው በቀር ማንም ሊያውቃት አይችልም።

ፍንጮችን ማስተዋል እንድንችል መጽሐፍ ቅዱስን የበፊቱ የበለጠ ማወቅ ያስፈልገናል።

በትክክል ካልተረዳነው ወደ ኋላ ቀርተን ታላቁ መከራ ውስጥ እንገባለን።