ኔፊሊም ወይም ግዙፎቹ ሰዎች ማን ነበሩ?



ግዙፎቹ ሰዎች የተወለዱት ከባዕድ ፍጡራን ወይም ከመላእክት አይደለም። እነዚህ ሰዎች የቃየን ዘሮች ናቸው፤ ቃየን ደግሞ ከክፉው ማለትም ከእባቡ ነው የተወለደው።

First published on the 19th of October 2022 — Last updated on the 19th of October 2022

ዘፍጥረት 6፡1 እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው፤

2 የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።

3 እግዚአብሔርም፦ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና፤ ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ።

4 በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፤ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ።

5 እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ።

የዚህ ጥናት ርዕስ ከባድ ጥያቄ ነው። ለጥያቄውም ቀላል መልስ የለውም፤ ደግሞም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳቦች ከዚህ ክፍል ጋር ይገናኛሉ።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 6 ቁጥር 2 የእግዚአብሔር ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች እንዳገቡ ተጽፏል። ቁጥር 4 ላይ እንደተጻፈው ተጋብተው አብረው እየኖሩ ብቻ አልነበሩም። በተጋቡ ጊዜ ልክ ዛሬ በዓለም ላይ የምናየው የስነ ምግባር ውድቀት ነው የተፈጠረው። እንደ ታዋቂ እስፖርተኞች፣ የፊልም እስታሮች፣ እና ዝነኛ ሙዚቀኞች ሳይጋቡ ከተቃራኒ ጾታ ጓደኛቸው ጋር ዝም ብለው አብረው ይኖሩና ከጋብቻ ውጭ ልጆች ይወልዳሉ። ስለዚህ ዛሬ በዓለም ላይ የምናየው ክፋት ከጥፋት ውሃ በፊት የነበረው ነው።

እግዚአብሔርን ያስቆጣው ዋናው ነገር ከወሲብ ጋር በተያያዘ የበዛው የስነ ምግባር ጉድለት ነው። የነበረው የስነ ምግባር ውድቀት ሰዎች በሐጥያት እንዲኖሩና ከጋብቻ ውጭ ልጆችን እንዲወልዱ እስከማድረግ ደርሶ ነበር። ይህንንም ዓይነት አኗኗር ሕዝቡ ይደግፉ እና ያደንቁ ነበር፤ በተለይም በዚህ ዓይነቱ ሐጥያት የሚመላለሱት መሪዎችና ዝነኛ ሰዎች ሲሆኑ።

ዘላለማዊ ሕይወት በወሲብ ሊወለድ አይችልም። በወሲባዊ ግንኙነት በኩል የተወለደ ሕይወት በዚህ ዘመን ከ120 ዕድሜ የበለጠ መኖር አይችልም። ከ120 ዓመት በላይ የሚኖሩ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ይህም የዘላለም ሕይወት አይደለም። እግዚአብሔር የሰጠው ጥብቅ ትዕዛዝ ወሲብን የሚፈቅደው በተጋቡ ባልና ሚስት መካከል ብቻ ነው። ስለዚህ ወሲብ የዘላለም ሕይወትን ይሰርቅብናል፤ በሐጥያት መኖር ደግሞ ሰዎች በጋብቻ ውስጥ ሊኖራቸው የሚችለውን ስነ ምግባር ያጠፋል።

ስለዚህ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ከምድር ላይ ለማጥፋት ወሰነ። ስነ ምግባር የሌላቸው ሰዎች ሰማይ ውስጥ ቦታ አይኖቸውም፤ እግዚአብሔር በምድርም ላይ ቢሆን እንኳ አይፈልጋቸውም። ደግሞ ምድርን የፈጠራት እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛ አይደለንም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ውስጥ ሔዋን የተቀጣችበት ምክንያት ከመጀመሪያው ሐጥያት ጋር በተያያዘ ነው። አሁን ካሉት ቤተክርስቲያኖች መካከል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላለፉ ከማለት በስተቀር አዳምና ሔዋን የሰሩት ሐጥያት ምን እንደሆነ ማንም ሊነግራችሁ አይችልም። ነገር ግን የእውነት አዳምና ሔዋን የሰሩት ሐጥያት ምንድነው? ይህ ከቤተክርስቲያኖች አለማወቅ የተነሳ ተሰውሮ የቆየ ሚስጥር ነው።

የፍጥረታዊ ዛፍ ፍሬ ነው የበሉት? አይደለም፤ ምክንያቱም ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጻፈው በሶስተኛው ቀን እግዚአብሔር የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ መልካም ናቸው ብሏል። የትኛውም ዛፍ ክፉ ነው አልተባለም፤ መብላትም አልተከለከለም።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ

ስለዚህ ፍሬው እንደ ብርቱካን ዓይነት ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ ካልሆነ የሚወክለው ምንድነው?

ሁለታቸውም አንድ ዓይነት ፍሬ በመብላት ተመሳሳይ ሐጥያት ነው የሰሩት። እግዚአብሔር ግን በጣም የተለያየ ዓይነት ቅጣት ነው የቀጣቸው። ሔዋን በስቃይ እንድትወልድ አዳም ደግሞ ከምድር ላይ በብዙ ልፋትና በብዙ ድካም የሚኖርበትን ምግብ እንዲያገኝ።

ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሚስቱ እንዲበዙ እንዲባዙ ምድርንም እንዲሞሉ ነገራቸው። ይህም ወንዶች እና ሴቶች ልጆች እንዲወለዱ ብዙ ጽንስ መጸነስ ይጠይቃል።

ዘፍጥረት 5፡4 አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

ከዚያም እነዚህ ልጆች እርስ በራሳቸው ይጋባሉ። ይህም የሚያዋጣ መንገድ አይደለም ምክንያቱም የትኛውም ልጅ በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ተወልዶ የዘላለም ሕይወትን ሊቀበል አይችልም። በዚህም ምክንያት የወለዱዋቸው ልጆች በሙሉ ይሞታሉ። ይህም ብዙ ችግሮችን የሚያስከትል የአጭር ጊዜ መፍትሄ ነው፤ ችግሮቹም ዝሙት፣ መዳራት፣ የተማሪዎች እርግዝና፣ ኤችአይቪ ኤድስ፣ የአባለ ዘር በሽታዎች፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ የዝሙት ባርነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ወዘተ።

በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት መወለድ ለአደጋ መጋለጥ ነው ምክንያቱም መጨረሻው ሞት ነው።

(በሕይወታችን በጣም የሚያሳዝነው አንድ ነገር በልደት ቀናችን ከሚመጡ ሰዎች ይልቅ ለቀብራችን የሚመጡ ሰዎች በቁጥር መብዛታቸው ነው።)

ምዕራፍ 3 ውስጥ እግዚአብሔር ሔዋንን ጽንስሽን አበዛለው በማለት ይቀጣታል።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።

ሰዎች በምድር ላይ መባዛት አንዲችሉ ሔዋን ብዙ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን መውለድ አለባት፤ እነዚህም እርስ በርሳቸው እየተጋቡ ይዋለዳሉ። ስለዚህ ብዙ ጽንስ መጸነስ እንዴት ቅጣት ሊሆንባት ይችላል?

ሔዋን በዚህ ቅጣት የምትቀጣበት ዋነኛው ምክንያነት ማርገዟ ነው። የመጀመሪያው ሐጥያቷ ወሲባዊ ግንኙነትን መጀመሯ ነው። ወሲባዊ ግንኙነት በራሱ ልጆቿ እንዲሞቱ አደረገ። “በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ”።

ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥

ስለዚህ ከሴት የተወለደ ሰው በሙሉ ከ1,000 ዓመታት በላይ መኖር አይችልም። ከሁሉም የሚበልጥ ረጅም ዕድሜ የነበረው ማቱሳላ 969 ዓመታት ነው የኖረው።

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ንሰሃ ገብተው እርሱን የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉና በ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ዘመን ውስጥ ኖረው የሞቱ ቅዱሳንን ከሙታን ያስነሳቸዋል። እነርሱም አዲስ የከበረ አካል የሚቀበሉት ከምድር አፈር ነው እንጂ ከሴት ማሕጸን አይደለም። ታላቁ መከራ ከተጠናቀቀ በኋላ እነዚህ ቅዱሳን የሚያደርጉት የመጀመሪያው ነገር በሺ ዓመቱ መንግስት ውስጥ ከኢየሱስ ጋር አብረው መንገስ ነው። ለምን?

ለ1,000 ዓመታት በመኖር እግዚአብሔር በአዳም እና በሔዋን ላይ ተናግሮ ከነበረው እርግማን ነጻ መሆናቸውን ያሳያሉ። የመጀመሪያውን አንድ ሺ ዓመት በሙሉ በሕይወት በመኖር እነዚህ ቅዱሳን የዘላለም ሕይወትን እንደተቀበሉ አውቀው ወደ ዘላለማዊ ኑሮ ይሻገራሉ፤ በደም ስራቸውም ውስጥ የሚገኘው የዘላለም ሕይወት እንጂ ደም አይደለም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥

(ሒትለር እርሱ የመሰረተው ዘ ሰርድ ራይሽ የተባለው መንግስት ለ1,000 ዓመታት ይዘልቃል ብሎ መናገሩን ልብ በሉ። ኢየሱስን ሊኮርጅ መሞከሩ ነው። ነገር ግን የሒትለር መንግስት ከ12 ዓመታት አላለፈም። አስራ ሁለት ቁጥር የሒትለር ጠላቶች ማለትም የአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ቁጥር ነው። ሒትለር በ1945 ዓ.ም ሞተ። በ1947 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት እስራኤል ፓለስታይን ውስጥ የራሷ ሃገር እንዲኖራት በድምጽ ብልጫ አጸደቁ።)

የዘላለም ሕይወት እንዲገለጥና በስጋ እንዳትሞቱ በውስጡ ደም የሌለው በውጭው ደግሞ እምብርት የሌለው አካል ሊኖራችሁ ይገባል። በሰውነታችን ላይ የሚገኘው የአውሬው ምልክት እምብርት የምንለው ጠባሳ ነው። እምብርት ሊኖረን የቻለው በማሕጸን ውስጥ ከእናታችን ጋር በተገናኘንበት እትብት ምክንያት ነው፤ እናታችንም ከእናቷ ጋር እያለ እስከ ሔዋን ድረስ ይደርሳል፤ ሔዋን ደግሞ የሕያዋን ሁሉ እናት ናት። እትብቱ የእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ተምሳሌት ነው፤ ይህም በዘላለማዊነት ሳይሆን በጊዜ ቱቦ ውስጥ ተገድበን መወለዳችንን ያመለክታል።

ዘፍጥረት 3፡20 አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።

ሴቲቱ (የቤተክርስቲያን ምሳሌ) ስም የወጣላት ሐጥያት ከሰራች በኋላ ነበር። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ራሷን በሆነ ስም (ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ካቶሊክ፣ ፕንቲኮስታል፣ ሜሴጅ አማኝ፣ ወዘተ ብላ) የጠራች ጊዜ ያቺ ቤተክርስቲያን ወደ ሐጥያት ወይም አለማመን ወድቃለች ማለት ነው። አማኞች ራሳቸውን መጥራት ያለባቸው ክርስቲያን በሚለው ስም ብቻ ነው።

እባቡ ተረግሞ በደረቱ የሚሳብ እንስሳ ወደ መሆን ከመለወጡ በፊት ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንስሳ ነበር።

ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።

ስለዚህ በሰው እና በዝንጀሮ ዘር መካከል ሳይንቲስቶች ፈልገው ማግኘት ያልቻሉት አገናኝ ዘር እባቡ ነው። እባቡ መናገርና ማሰብ የሚችል ታላቅ እንስሳ ስለነበረ ከፓሮትም ከዝንጀሮም በላይ ነበረ። እባቡ እግዚአብሔር የሰጠውን የመናገርና የማሰብ ችሎታ ሔዋንን በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ልጅ እንድትወልድ በማድረግ ሐጥያት እንድትሰራ አሳመናት።

እባቡ በዝርያው ከዝንጀሮ የበለጠ ለሰው ቅርበት ነበረው። ልክ አንደ ሰው ይመስል ነበር። የሔዋንን ትኩረት ማግኘት የቻለውም በአካል ከአዳም ተለቅ ያለ እና ጠንከር ያለ ስለነበረ ነው። (በአካል ትልቅ የነበረው አሜሪካዊው ጀነራል ማካርተር ከጃፓኖቹ ንጉስ በቁመት ብዙ ይበልጥ ስለነበረ ጃፓኖቹ ከራሳቸው ንጉስ ይልቅ የአሜሪካዊው አድናቂ ሆኑ፤ ስለዚህ ማካርተር ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓንን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ጃፓኖቹ ይታዘዙት ነበር)።

ሴቶች የድንግልና ሕግ አላቸው። ወሲብ በሚፈጽሙ ጊዜ የድንግልና ሕጋቸው ስለሚቀደድ ደም ይፈስሳቸዋል። ሐጥያት የተጀመረው በዚህ መንገድ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለሐጥያት ስርየት ደም መፍሰስ አለበት አለ።

አዳም የሕያዋን ሁሉ አባት አልተባለም። ቃየን የአዳም ልጅ ተብሎ አልተጠቀሰም።

ከአዳም የተወለዱ ሰዎችን ሁሉ የሚጠቅሰው መጽሐፈ ዜና ቃየንን አይጠቅሰውም።

አዳም ዘፍጥረት 4፡1-2 ውስጥ እንደተጻፈው ሚስቱን አንድ ጊዜ አወቃት፤ እርሷም መንታ ልጆችን ወለደች።

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች

አንድ ወሲባዊ ግንኙነት አድርገው ሁለት ልጆች ተወለዱ።

ሔዋን ቃየንን ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። ይህም ትክክል ነው። ሕይወት ሊገኝ የሚችለው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰው ሕይወትን ሊፈጥር አይችልም። ሔዋን የቃየን አባት አዳም ነው ብላ ያልተናገረችው ለምንድነው? እናቶች ለወለዱት ልጅ አባት ባላቸው መሆኑን ኩራት እየተሰማቸው ነው የሚናገሩት።

1ኛ ዮሐንስ 3፡12 ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤

ቃየን የተወለደው ከክፉው ነው። ክፉው ማለት በእባቡ ውስጥ የነበረው ዲያብሎስ ነው።

ማቴዎስ 13፡38 እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው

39 የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤

ሔዋን እግዚአብሔርን በመጥቀሷ ምንም ሐጥያት ያልሰራች እንደመሰላት ታሳያለች። እግዚአብሔር ስለ መባዛት ነግሯት ነበር፤ እርሷም በምታወቀው መንገድ መባዛትን ጀምራለች።

ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።

ምግብ መብላት የወሲብ ምሳሌ ነው። ምግብ ከተበላ በኋላ ሆድ ውስጥ ነው የሚገባው። ሕጻን ልጅ በተፀነሰ ጊዜ የእናቱን “ሆድ” ያሳብጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ የቃየን ሰብዓዊ አባት ማን እንደሆነ አይናገርም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከሴቲቱ ዘር ጋር የሚዋጋ የእባቡ ዘር (ወይም ልጅ) እንዳለ ይናገራል።

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤

እባቡ በደረቱ የሚሳብ እንስሳ ወደመሆን ተለወጠ። ስለዚህ ቃየን የእባቡ ዘር (ወይም ልጅ) ነው። ቃየን ልክ ሰው የሚመስል ትልቅ አስገራሚ ቁመና ያለው የእባብ እና የሰው ድቅል ሆነ። የእግዚአብሔር ልጆች በሞተው በአቤል ፈንታ በተወለደው በሴት እና በሌሎቹ የአዳም ልጆች በኩል የተወለዱ ልጆች ናቸው። የሰው ሴቶች ልጆች ደግሞ የእባብና የሰው ድቅል ከሆነው ከቃየን የተወለዱ ሴቶች ልጆች ናቸው። ከነዚህ ድቅሎች ጋር ተጋብቶ መዋለድ እግዚአብሔር ሰዎች እንደ ወገናቸው መዋለድ አለባቸው ብሎ የተናገረውን ቃል መተላለፍ ነው። ከሁለቱ ወገኖች የተወለዱት ብዙዎቹ ግዙፍና ዝነኛ ሰዎች ሆኑ።

ዘፍጥረት 1፡11 እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

እግዚአብሔር ሁሉም ነገር እንደ ወገኑ እንዲዋለድ ነው የፈለገው። እንደ ቃየን ዓይነቱን ድቅል አልፈለገም።

አንዳንድ በዘረኝነት የሚያምኑ ሰዎች እነዚህን ጥቅሶች አጣምመው ይተረጉሙዋቸዋል። ስለተለያዩ የሰው ዘሮች ወይም ብሔሮች መናገራችን አይደለም። እየተናገረን ያለነው በእናቱ ከሰው በአባቱ ከእባብ የተወለደውን እንደ ቃየን ዓይነቱን ድቅል በተመለከተ ነው።

ዘፍጥረት 4፡17 ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፥ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፥ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሄኖሕ አላት።

የዝነኛ ሰዎች ጉራ ከተሞችን በራሳቸው ስም መሰየማቸው ነው። ሮሙለስ የሮም ከተማን ገነባ። ኮንስታንቲን ኮንስታንቲኖፕልን ቆረቆረ።

ዘፍጥረት 4፡21 የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።

እነዚህ ሰዎች በዘመናችን እንደምናውቃቸው የሮክ እና የፖፕ ዘፋኞች ናቸው፤ ለምሳሌ ራሱን የገደለው ከርት ኮቢያን እና የሕመም ማስታገሻ ከልክ በላይ ይጠቀሙ የነበሩት ማይክል ጃክሰን እና ፕሪንስ።

ዘፍጥረት 4፡22 ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች።

እነዚህ ልዩ ችሎታ ያላቸው ብረት ቀጥቃጮች ነበሩ፤ ማሽኖችን ይሰሩ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ዕድሜያቸው ከ1,000 ጥቂት ብቻ ነበር የሚጎድለው። የዕድሜያቸው ርዝመት ብዙ ዝናን ለማትረፍና በታሪክም ታዋቂ ለመሆን ዕድል ሰጥቷቸዋል። የኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ የመጣው አዳም ሐጥያት ከሰራ ከ1,700 ዓመታት በኋላ ነው። ይህም ለጥንታዊ ታሪክ በቂ ጊዜ ነው። እኛ አሁን ካለንበት ዘመን ወደ ኋላ አንድ ሺ ሰባት መቶ ዓመታት ያህል ብንመለስ የምንደርሰው የሮማ መንግስት ዘመን ላይ ነው። ይህን የሚያህል ዘመን ለጥንታዊ ሰዎች ታዋቂነትን ለማትረፍ በቂ ጊዜ ነው።

የአዳም ዘሮች የቃየንን ዘሮች ማግባታቸው ስሕተት ነበረ። እግዚአብሔር በድቅሎች ያልተበረዘ ንጹህ ዘር ነበር የፈለገው። የአዳም ዘሮች ከቃን ዘሮች ጋር በመቀላቀል ሐጥያት ሲሰሩ እግዚአብሔር ተቆጣ ምክንያቱም ከስነ ምግባር ውጭ በሆነ መንገድ ዝሙት እየፈጸሙ በመኖራቸው ንጹህ የሆነው ዘር ጠፋ።

ቃየን ወንድሙን ካናገረው በኋላ ገደለው፤ ቃየን ከክፋት ሊመለስ የማይችል ሰው ሆነ። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሲጠይቀው ፊት ለፉት ዋሸ፤ ለእግዚአብሔር ፊት ለፊት የዋሸው ብቸኛ ሰው ቃየን ነው።

ዘፍጥረት 4፡3 ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤

4 አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤

5 ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።

8 ቃየንም ወንድሙን አቤልን፦ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።

አቤል ጠቦት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መስዋእቱን ተቀበለ። ቃየን ያቀረበውን የአበባ፣ ፍራፍሬ እና አትክልት መስዋእት ግን እግዚአብሔር አልተቀበለም።

ቃየን አበባ፣ ፍራፍሬ፣ እና አትክልት ለሐጥያት መስዋእት ሆነው ሲቀርቡ እግዚአብሔርን ባለማስደሰታቸው ተናደደ።

ከዚያም የበግ ደም ማፍሰስና መስዋእት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ተቀባይነት ያለው ለምን እንደሆነ ወንድሙን አቤልን ጠየቀ። አቤልም በድንግልና የነበረችዋ ሔዋን ደሟ እንዴት እንደፈሰሰና ደሟን በማፍሰስ ሐጥያትን ያስተማራት እንስሳ መሆኑን ነገረው። የሔዋንን የድንቅልና ሕግ በመቅደድ ደም እንዲፈስሳትና ሐጥያተኛ እንድትሆን ያደረጋት በሰውና በዝንጀሮ መካከል አገናኝ የሆነው እንስሳ ነው። ከዚህም የተነሳ ሐጥያትን ለማስተስረይ ተቀባይነት ያለው የእነስሳ ደም ብቻ ነው።

ቃየንም በደረቱ እየተሳበ የሚሄው እባብ በፊት ከእንስሳት ሁሉ ታላቅ እና ውብ የነበረ ሔዋንንም የማረካት ፍጡር እንደነበረ ተረዳ። አሁን ግን ሲያየው እባቡ በደረቱ የሚሳብ የሚያስፈራ የሚያስጠላ እንስሳ ሆኗል። ይህም አስቀያሚ እንስሳ የቃየን አባት ነበረ።

ቃየን ይህን ሲሰማ የሚደርስበትን ድንጋጤና ንዴት አስቡ። ስለዚህ ቃየን ለቀሩት የአዳም ልጆች ይህንን ሚስጥር ሳይገልጥ በፊት አቤልን ዝም ማሰኘት ያስፈልጋል ብሎ አሰበ። ቃየን ከየት እንደመጣ ከማን እንደተወለደ እንዳይታወቅበት አቤልን ገደለ፤ የዛሬዋም ቤተክርስቲያን ይህንን ሚስጥር መግለጥ አቅቷታል።

ቤተክርስቲያኖች በሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ ቃየን የአዳም የመጀመሪያ ልጅ ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ቃየን መጽሐፈ ዜና ውስጥ የአዳም ልጅ ተብሎ አልተመዘገበም። ቃየን የተገኘው (የተወለደው) ከክፉው ነው። ክፉው የተባለውም አዳም ሊሆን አይችልም ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

ሉቃስ 3፡38 የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ

በአሁኑ ዘመን በዓለማችን ውስጥ ወሲባዊ ሐጥያቶች ልቅ ሆነዋል፤ ቤተክርስቲያን ግን ወሲብ የመጀመሪያው ሐጥያት መሆኑን አጥብቃ ትክዳለች።

የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እስፐርም ምን እንደሚመስል ተመልከቱ። ቅርጹ ልክ እንደ እባብ ይመስላል፤ ጭንቅላትና ረጅም ጭራ አለው።

 

 

 

ስለዚህ የወንድ እስፐርም የእባቡ ዘር ነው

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ …

15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤

በእስፐርም ሴል አማካኝነት ስለተለድን መሞታችን አይቀርም።

በእስፐርም ሴል አማካኝነት ስለተወለድን የእባብ ዘር ነን።

ከዚህ ማምለጫ ብቸኛው መንገድ ዳግመኛ መወለድ ነው።

እግዚአብሔር እባብ የተባለውን አውሬ ረገመውና በደረቱ እየተሳበ እንዲሄድ አደረገው፤ የእባቡም ዕጣ ፈንታ ይህ ሆኖ ቀረ። ለምን? ምክንያቱም የመጀመሪያው እባብ ሔዋን ላይ በደረቱ ተኝቶባት ነበር።

እግዚአብሔር ለእባቡ መንታ ምላስ ሰጠው፤ ይህም እውነትና ውሸትን ቀላቅሎ የመናገር ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው እባብ ለሔዋን እውነትን ከሐሰት ጋር ቀላቅሎ ነግሯታል።

እባቡ ሔዋንን እንዲህ አላት፡- “ዓይኖቻችሁ ይከፈታሉ፤ እንደ አማልክት ትሆናላችሁ”። አምላክ ለመሆን ሕይወትን መፍጠር መቻል አለባችሁ። ሔዋን ልጅ መውለድ ትችላለች። እባብ አሁን የዓይን ቆብ የለውም፤ ዓይኖቹን መክደንም አይችልም። እባቡ ከተቀጣበት ቅጣት አንዱ ዓይኖሩ ፍጥጥ ብለው እንዲቀሩ መደረጋቸው ነው፤ ይህም ከባድ ቅጣት ነው። እባብ ዓይኖቹን መጨፈን አይችልም፤ ይህም አስፈሪ እንዲሆን አድርጎታል።

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

ከብቶችና አውሬዎች አጥቢ እንስሳት ናቸው። እባቡ አጥቢ እንስሳ ከመሆን እንቁላል እየጣለ የሚራባ እንስሳ ወደመሆን ተለወጠ፤ ይህም ከአጥቢ እንስሳት በታች መሆን ነው። እባብ አፉ ውስጥ መርዝ አለው ምክንያቱም እባቡ ሔዋን የእግዚአብሔርን ቃል በተሳሳተ መንገድ እንድትተረጉም በማድረግ አስተሳሰቧን መርዞታል።

የመጨረሻው ጥያቄ ደግሞ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር አዳም እና ሔዋን በምን ዓይነት መንገድ እንዲዋለዱ ነበር ያሰበው?

ዘፍጥረት 2፡25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።

እግዚአብሔር በመጀመሪያ አዳም እና ሔዋንን በየዋሕነት ሸፍኗቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሳ ምንም ዓይነት የወሲብ ፍላጎት አልነበራቸውም። ልክ እንደ ሕጻናት ነበሩ።

የዘላለም ሕይወት ነበራቸው፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እስከቆዩ ድረስም አይሞቱም ነበር። በደም ስራቸውም ውስጥ ይመላለስ የነበረው ደም ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነበረ።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም

ዘፍጥረት 2፡23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

አዳም ስለ ሚስቱ ሲናገር ደም እንዳላት አልተናገረም።

ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ ስለለበሰው አካል ልክ እንደዚሁ ብሎ ነው የተናገረው። ደሙን ስለ ሐጥያታችን መስዋእት እንዲሆን አፍስሶታል።

ሉቃስ 24፡39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።

ሰውነታቸው ውስጥ ደም ከሌለ ወሲብ ሊፈጽሙ አይችሉም።

እግዚአብሔር ግን ነጻ ፈቃድ እንዲኖራቸው ፈልጓል።

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲሄዱበት ከፈለገው መንገድ በተለየ ሌላ መንገድ መሄድ ከፈለጉ መሄድ የሚችሉበትን አቅም እግዚአብሔር ራሱ ሊሰጣቸው ይገባል። ከዚህም የተነሳ ፍጥረታዊ ሕይወትን የሚወልዱበት አካል ተሰጣቸው፤ ነገር ግን ሰውነታቸው ውስጥ ደም በሌለበት ሰዓት ሊወልዱ አይችሉም።

ሰውነታቸው ውስጥ ደም እንዲኖር ለማድረግ ደም ስራቸው ውስጥ የነበረውን መንፈስ ቅዱስ መግፋት ይጠበቅባቸዋል።

የእግዚአብሔርን ቃል ለመተላለፍ ባሰቡ ጊዜ መተላለፋቸው አለማመን ነው። ከዚህም የተነሳ መንፈስ ቅዱስ ከውስጣቸው ወጥቶ ሄደ። እግዚአብሔርም በሕይወት እንዲኖሩ በሰውነታቸው ውስጥ የነበረውን ውስብስብ የደም ስር በደም እንዲሞላ አደረገ።

ዘፍጥረት 9፡4 ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፤

ዘሌዋውያን 17፡11 የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤

አካላችን ውስብስብ ነው፤ በውስጡ 60,000 ማይልስ ርዝመት ያለው ደም ስር አለ።

በሰውነታችሁ ውስጥ ያለው ዲኤንኤ በሙሉ በዚረጋ ከፀሃይ ጀምሮ በርቀት እስከምትገኘዋ ፕሉቶ የምትባል ፕላኔት ድረስ 17 ጊዜ ደርሶ ይመለሳል። ሰውነታችን እጅግ ውስብስብ የሆነ “ማሽን” ነው። ነገር ግን በደም አማካኝነት በሕይወት ስንኖር የተወሰኑ ዓመታት ብቻ እንቆይና እንሞታለን። ሰውነታችንን በሕይወት የሚያቆዩ ከአስር ሺ በላይ ዓይነት ልዩ ልዩ ፕሮቲኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለሚያረጁ ወዲያ በሌሎች ፕሮቲኖች መተካት አለባቸው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።

በደም ስራቸው ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ቃል እንዲታዘዙ ያደርጋቸዋል። በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ሰዎች ስለ ራሳቸው እየታበዩ አያወሩም። ለእግዚአብሔር ቃል ብቻ ታዛዥ ሆነው ይኖራሉ።

ያዕቆብ 1፡18 በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።

አዳም እና ሚስቱ የእግዚአብሔር ቃል የነገራቸውን እያደረጉ እስከኖሩ ድረስ ምንም ችግር አይገጥማቸውም ነበር።

ነገር ግን ነጻ ፈቃድ አዳዲስ ነገሮችን የማወቅ ፍላጎት ይፈጥራል። ሰዎች ሐጥያትን የማወቅ ጉጉት አላቸው፤ ሐጥያትም መጀመሪያ ሲያዩት ደግሞ ደስ የሚል አማራጭ ይመስላል። ሰዎች እጅግ ክፉ የሆነውን የሐጥያትን ውጤት ሲቀምሱ ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ አለመታዘዝ ምን ያህል አደገኛ መሆኑን የሚያስተውሉት።

ስለዚህ እኛ ሰዎች ነጻ ፈቃዳችን አደገኛ መሆኑን ማወቅ አለብን ምከንያቱም ነጻ ፈቃዳችን ትኩረቱ በራስና በትዕቢት ላይ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ሐጥያትና ወደ አለማመን እየነዳ ይወስደናል።

ኤርምያስ 10፡23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም።

ማህበረሰብና ዓለም ለመረዳት የሚከብዱ እጅግ ብዙ ፍንጮችን ያስተላልፋሉ። ስለዚህ በየዕለቱ ማድረግ የሚያስፈልጉንን ትክክለኛ ውሳኔዎች ማድረግ ያቅተናል። ደግሞም ሰይጣን በጣም ሃይለኛ እና ተንኮለኛ ጠላት መሆኑን እንኳ አናስተውልም። ሰይጣንን በራሳችን ብርታት ልንቃወመው ስለማንችል በእግዚአብሔር ቃል ኃይል መደገፍ ያስፈልገናል። ኢየሱስ ዲያብሎስን የተቃወመው፡- “… ተጽፏል” እያለ የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ ነው።

ኤርምያስ 17፡9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?

የሰው አእምሮ ልናውቀው ከምንችለው በላይ የተወሳሰበ ነው። ሃሳባችንን እንኳ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚበቃ ክሕሎት የለንም። ሃሳባችን ባለማወቃችን የተነሳ ብዙ ተጽእኖ ስለሚያድርበት የራሳችንን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አንችልም። ብዙውን ጊዜ የምንማረው ከሌሎች ነው፤ ከዚህም የተነሳ አእምሮዋችን ከሚችለው በላይ ልንማር ስለምንችለው ሳናውቀው በስሕተት ወጥመድ ውስጥ እንወድቃለን። የማወቅ ጉጉታችን በቀላሉ ሊያታልለንና እውነት የሚመስሉ ነገር ግን የመልካም እና የክፉ ቅልቅል የሆኑ ስሕተቶችን አምነን እንድንቀበል ሊያደርገን ይችላል።

ስለዚህ በራሳችን ነጻ ፈቃድ እሺ ብለን ነጻ ፈቃዳችንን እግዚአብሔር እንዲቆጣጠርልን ለእርሱ አሳልፈን መስጠት አለብን፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ እሺ ብለን መቀበል አለብን። ለራስ በመሞት ነው ለእግዚአብሔር ሕያው የምንሆነው።

የሐጥያት ውጤቶች የሚያስከትሉትን አስከፉ ውጤቶች እና ማቆሚያ የሌለው መከራ ስናይ ብቻ ነው ወደ እግዚአብሔር መጠጋትና ለነጻ ፈቃዳችን ሳይሆን ለእርሱ ፈቃድ መታዘዝ እንዳለብን የምንረዳው። ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እርሱ እንዲቆጣጠረው አሳልፈን መስጠት ከመቻላችን በፊት በራሳችን ሙከራ አድርገን መውደቅ አለብን።

አዳም እና ሚስቱ “ብዙ ተባዙ” የሚለውን ትዕዛዝ በራሳቸው ከመተርጎማቸው በፊት እግዚአብሔርን መጠበቅ ነበረባቸው።

ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥

እግዚአብሔር እንዲ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው።

ኢዮብ 38፡4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ?

7 የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥

ዕብራውያን 7፡9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤

ሁላችንም በስጋ አባቶቻችን ውስጥ አያቶቻችን ውስጥና ቅድመ አያቶቻችን ውስጥ ነበርን። ነገር ግን ይህን ማስታወስ አንችልም።

የአማኞች መንፈስ ከመጀመሪያው እግዚአብሔር ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ይህንንም ቢሆን ማስታወስ አንችልም።

በእግዚአብሔር ውስጥ በነበርን ጊዜ ወደፊት እግዚአብሔር ለሚተክላት ሙሽራዬ ብሎ ለሚጠራት ቤተክርስቲያን አካል ነበርን።

ሰው በእግዚአብሔር መልክ እንዲሆን እግዚአብሔር አዳም ብሎ የሰየመውን ትንሽዬ ወንድ መንፈስ ፈጠረ። በዚህም መንፈስ ውስጥ ወደፊት ሚስቱ የምትሆነው ሴት ባህርያት ነበሩት።

 

 

እንዲባዙ የተፈለገው መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ነበረ። ይህ ብቻውን ዘላለማዊ ሕይወት ከእነርሱ እንዲወለድ ያደርግ ነበር። ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

እግዚአብሔር ዘራቸው በውስጣቸው ያላቸውን የፍራፍሬ ዛፎች ፈጠረ።

ዘፍጥረት 1፡11 እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ኤልሳቤጥ ማርያምን እንዲህ አለቻት፡- “የማሕጸንሽ ፍሬ የተባረከ ነው”።

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ፍሬ የልጅ ምሳሌ ነው።

ስለዚህ እናትየው የፍራፍሬ ዛፍ ናት።

ሉቃስ 8፡11 የዘሪው ምሳሌ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይናገራል።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሚስቱ (ለፍራፍሬ ዛፍ) እንበዙ ፍሬያማ እንዲሆኑ (ልጅ እንዲወልዱ) ልጁም በውስጡ ዘር (የእግዚአብሔር ቃል) ያለው እንዲሆን ተናገራቸው።

የሚወለደው ሕጻን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት። ይህ ሊሆን የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ሴቲቱን ሙሉ በሙሉ ሲጋርዳትና በማሕጸኗ በድንግልና የሚወለደውን ኢየሱስ ሲፈጥር ነው። እርሱም ከተወለደ በኋላ ያድጋል፤ በምድርም ላይ ምንም ሐጥያት ስለሌለ መሞት አያስፈልገውም። ከዚያም ሲያድግ ቅዱሳኑን (አዳምን ሲፈጥር እንዳደረገው) ከምድር አፈር ይጠራቸዋል። ሁሉም ውስጣቸው በዘላለማዊ ሕይወት የተሞላ ስለሚሆን ለዘላለም ይኖራሉ። ሞትም ወደ ዓለም አይገባም ነበር።

ይህን እቅድ ሙሉ በሙሉ መፈጸም ለአዳምና ለሔዋን የሚቻል አልነበረም። ብቸኛ ተስፋቸው የነበረው እግዚአብሔር እራሱ የሁለታቸውን ወንድ እና ሴት መንፈስ ወስዶ በሰዎች አካል ውስጥ እስኪያኖር መጠበቅ ነበረ። ከዚህ በታች ያለው ምስል አዳም ለእግዚአብሔር ቃል እየታዘዘ እንዲኖር የሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ አዳም ውስጥ እንደነበረ ያሳያል። ከዚያ እንደ ዮሴፍና እንደ ማርያም ይሆናሉ።

 

 

ልክ እንደ ማርያም መንፈስ ቅዱስ ሔዋንን እስኪጋርዳትና በማሕጸኗ ውስጥ በድንግልና የሚወለደውን ወንድ ልጅ እስኪፈጥረው ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው። ይህንን እቅድ ወደ ፍጻሜ ማምጣት በሰዎች አቅም የሚቻል ነገር አልነበረም።

ገነት የሴት ምሳሌ ነው።

መኃልየ መኃልይ 4፡12 እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።

ሴት ጥበቃ የሚደረግላት ገነት ናት። የድንግልናዋ ሕግ እንደ መጋረጃ ሆኖ የሕይወት ምንጭ የሆነውን ማሕጸኗን ይጠብቀዋል። ማሕጸኗ በአካሏ መካከል ማለትም በገነት መካከል ነው የሚገኘው።

እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን እና በቤተመቅደሱ ውስጥ ከመጋረጃው ጀርባ መንፈስ ሆኖ ይኖር ነበር። ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ በጭራሽ መቀደድ የሌለበትን ልብስ ለብሶ ነበር።

እግዚአብሔር ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሊቀ ካሕናቱ አሮን መልበስ ያለበትን ልብስ በተመለከተ ተናግሮ ነበር።

ዘጸአት 28፡30 በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።

31 የኤፉዱንም ቀሚስ ሁሉ ሰማያዊ አድርገው።

32 ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።

ቀያፋ ኢየሱስን እየመረመረ በነበረ ሰዓት በጣም ተናደደና ይህንን ልብስ ቀደደ።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።

ልብሱን መቅደዱ የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ስለሆነ በዚያ ምክንያት ሕጉ አበቃ። እግዚአብሔርም ደግሞ ኢየሱስ ሲሞት የቤተመቅደሱን መጋረጃ በመቅደድ ምላሽ ሰጠ።

ቤተመቅደሱ ውስጥ የነበረው መጋረጃ እግዚአብሔር ይኖርበት የነበረውን ቅድስተ ቅዱሳንን ከውጭ ያሉ ሰዎች ማየት እንዳይችሉ ይሰውራል።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወት ነው፤ እርሱም መጋረጃውን በመቅደዱ ከዚያ ወዲያ ከመጋረጃው ጀርባ እንደማይኖር አሳወቀ። ከዚያ በኋላ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስተ ቅዱሳን መሆኑ የዘላለም ሕይወት ምንጭ መሆኑ ቀረ። ስለዚህ ከተቀደደ መጋረጃ ጀርባ ዘላለማዊ ሕይወት አይገኝም።

የሴት የድንግልናዋ መጋረጃ ሲቀደድ ከዚያ በኋላ የምትወልደው ሕጻን በውስጡ ዘላለማዊ ሕይወትን ሊይዝ አይችልም።

ማርያም በድንግልናዋ ከመጋረጃዋ ጀርባ ሕጻን ልጅ ጸነሰች። ይህም ዘላለማዊ ሕይወት የመጣው ከውስጧ እንጂ ከማሕጸንዋ ውጭ የመጣ አይደለም። ኢየሱስን የሕይወት ዛፍ የሚያደርገውም ይህ ነው። እርሱ ዘላለማዊ ሕይወት አለው።

እግዚአብሔርና ሰይጣን የሔዋንን ማሕጸን ለመጠቀም ሲሽቀዳደሙ ነበር።

እግዚአብሔር በድንግልና የሚወለደው ሕጻን እንዲወለድ የሔዋንን ማሕጸን መጠቀም ፈለገ፤ ከዚህም አንድ ጽንስ ለዘላለማ የማይሞት ሕይወት ይወለድ ነበር። ሰይጣን ደግሞ ሔዋን ብዙ ወሲባዊ ግንኙነቶችን በመፈጸም እንድትወልድ የምትወልዳቸውም ልጆች ከተቀደደ መጋረጃ ጀርባ ተጸንሰው ተወልደው ለተወሰኑ ዓመታት ብቻ ኖረው የሚሞቱ እንዲሆኑ ፈለገ።

 

ዛፍን የሕይወት ዛፍ ምሳሌ አድርጎ መጠቀም ለምን አስፈለገ?

በምድር ላይ ረጅም ዕድሜ የሚኖር ፍጥረት ዛፍ ነው። አሜሪካ ውስጥ ብሪስልኮን የተባለው ጥድ የ4,600 ዓመት ዕድሜ አስቆጥሯል። ይህ ዕድሜ እጅግ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ ለዘላለማዊ ሕይወት ምሳሌ መሆን ይችላል።

ወሲባዊ ግንኙነት የሚተረጎምበት ቃል እውቀት ነው ምክንያቱም ወሲብ ስጋዊ እውቀት ነው።

ዘፍጥረት 4፡25 አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፤ ወንድ ልጅንም ወለደች።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ይህንን መገለጥ አግኝታው ነበረ፤ ነገር ግን በጨለማው ዘመን ይህ መገለጥ ከቤተክርስቲያን ጠፋ።

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ለምትገኘዋ (በሴት ማለትም በክርስቶስ ሙሽራ ለተመሰለችዋ) ቤተክርስቲያን ሲናገር እንዲህ አለ፡-

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2-3 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ …

ጳውሎስ ንጽሕት የሆነች ድንግል ሴትን ከተሸነገለችው ሔዋን ጋር ያነጻጽራል። ሔዋን ከእባቡ ጋር ካደረገችው ነገር በኋላ ድንግልናዋን አጥታለች።

ስለዚህ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት መወለድ የእባቡ ዘር ያደርገናል። ሐጥያቶቻችንን መናዘዝ፣ ንሰሐ መግባት እና ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛችን አድርገን መቀበል ያስፈልገናል ምክንያቱም በተስፋ የተነገረው የሴቲቱ ዘር ኢየሱስ ነው። ከወሲባዊ ግንኙነት ውጭ የተወለደ ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው።

እግዚአብሔር በሴቲቱ ዘር አማካኝነት የእባቡን ዘር ሊያሸንፍ አሰበ። ዘሩም ኢየሱስ ነው።

ሴቲቱንም እግዚአብሔር እንዲህ አላት፡-

ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

ሴት ግን ዘር የላትም።

ስለዚህ ዘር (ወንድ ልጅ) ሊሰጣት ያስፈልጋታል።

ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና

ኢየሱስ ከድንግል ሴት ነው የተወለደው፤ ስለዚህ በወሲባዊ ግንኙነት በኩል አልተወለደም። ስለዚህ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ የተሰተ ስጦታ ነው።

ስለዚህ የሴቲቱ ዘር ሰብዓዊ አባት አልነበረውም።

የመጀመሪያው የእባቡ ዘር ቃየንም ሰብዓዊ አባት አልነበረውም።

ከሴት የተወለዱ ሰዎች ሁሉ መንፈሳዊ አባት የላቸውም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ አባታችን እንዲሆን ዳግመኛ መወለድ አለብን። የዛን ጊዜ ብቻ ነው ዘላለማዊ ሕይወት የሚኖረን።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23