አትብሉ የተባለው ዛፍ ምንድነው?



የኤድን ገነት ውስጥ ሐጥያት የመጣው በወሲብ ነው። መዳን የመጣው ደግሞ በድንግልና በተወለደ አዳኝ አማካኝነት ሲሆን እርሱም የተወለደው በሰው የመዋለድ ስርዓት አይደለም።

First published on the 2nd of August 2022 — Last updated on the 2nd of August 2022

 

ሔዋን የእግዚአብሔርን ልጅ በድንግልና እንድትወልድ ታስቦላት ነበር

 

አትብሉ የተባሉት ፍሬ ምን ነበረ?

ይህን ለመረዳት “የእግዚአብሔር እቅድ ለኤድን ምን ነበረ?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብን።

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ ምንም ነገር ሳይጠቀም መንፈስ የሆነውን ሰው አዳምን ፈጠረ።

“መፍጠር” ማለት ምንም ነገር ሳይጠቀሙ መስራት ነው።

መንፈስ ከሆነ ነገር አይደለም የሚሰራው።

ከዛፍ ጠረጴዛ “መስራት” ትችላላሁች፤ ነገር ግን ምንም ነገር ተጠቅማች መንፈስ ልትሰሩ አትችሉም። ስለዚህ ምንም ነገር ሳይጠቀም መንፈስን ሊፈጥር የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

አዳም በመንፈሱ ውስጥ የተወሰኑ የሴት ባህርያትም ነበሩት።

በስጋ ሲሆን ግን የወንድ እና የሴት ባህርያትን በአንድ አካል ውስጥ ማስቀመጥ መልካም አይደለም።

አዳም ግን መንፈስ-ሰው በነበረ ጊዜ ሚስቱ በውስጡ የምትገኝ መንፈሳዊ ባህርይ ነበረች፤ ይህም የክርስቶስ ሙሽራ የሆኑ አማኞች በአንድነት ሁልጊዜ በክርስቶስ ልብ ውስጥ እንደሚገኙ ማለት ነው። በዚህ መንገድ ሁልጊዜም ቢሆን የክርስቶስ መንፈስ አካል ናቸው።

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ስለዚህ አዳም በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ ማለት አዳምም መንፈስ ነበረ ማለት ነው።

ቀዩ መስመር የእግዚአብሔርን መንፈስ ይወክላል ብላችሁ አስቡ። ከመሃል ያለው ጥቁር ነጥብ ደግሞ የዘላለም ሕይወትን የሚቀበሉ ሰዎችን ባህርያት ሁሉ ይወክላል።

 

 

ትንሹ ቀይ ቅርጽ የአዳምን መንፈስ ይወክላል፤ በውስጡ ያለው ጥቁር ነጥብ ደግሞ ከእርሱ ስትወጣ ሚስቱ የምትሆነውን የሔዋንን ባህርይ ይወክላል።

ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤

ከመጀመሪያው ሰው ሁሉ በእግዚአብሔ ውስጥ ነበረ። መዳንን የሚቀበሉ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ነበሩ።

ሰው ልክ በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ።

እግዚአብሔር አስገራሚ የባህርይ ጥንካሬ አለው።

ይህም ማለት ሰው መከራ ተቀብሎ ብዙ ችግሮችን አሸንፎ ለእግዚአብሔር ታዛዥ መሆንን መማር አለበት ማለት ነው። መልካም ባህርይ እንደ ስጦታ ሊሰጥ አይችልም። መልካም ባህርይ በብዙ ልምምድ፣ በትግል፣ እውነትን በመውደድ ከሚደረግ መስዋእትነት ውስጥ ነው የሚመጣውና የሚያብበው።

ስለዚህ እግዚአብሔር የሰው መንፈስ በውስጡ የተቀመጠውን ብቃት በምድር ላይ የሚያዳብርበትን ሁኔታዎች እያመቻቸ ነበር።

ራዕይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።

እግዚአብሔር በዋነኛነት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፤ ነገር ግን ከዘላለም ጥንት ጀምሮ በውስጡ የተወሰኑ ሰብዓዊ ባህርያትም ነበሩት።

እግዚአብሔር የመረጣቸው ቅዱሳን ከመጀመሪያው በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ቃሉን በመናገር ሰዎች አድርጎ እስኪፈጥራቸው እየጠበቁ ነበር።

ዘፍጥረት 1፡27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

ስለዚህ አዳም በዋነኛነት ወንድ መንፈስ ነበረ፤ ነገር ግን በመንፈሱ ውስጥ የሴት ባህርያትም ነበሩት።

ዘፍጥረት 5፡2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው

አዳም እና ሚስቱ አንድ መንፈስ ነበሩ፤ ምክንያቱም አንድ ስም ነበራቸው።

ተፈጠሩ ማለት ያለ ምንም ጥሬ እቃ ተሰሩ ማለት ነው። ስለዚህ ሲፈጠሩ መንፈስ ነበሩ። መንፈስ ከሆነ ጥሬ እቃ ሊሰራ አይችልም። የሁለቱ ስም በአንድነት አዳም ነበረ። አንድ መንፈስ ነበሩ።

አካል አልተፈጠረም፤ ምክንያቱም ከምድር አፈር ነው የተሰራው።

 

 

መንፈሳዊ መባዛት የሚከናወነው በድንግልና በተወለደ ልጅ አማካኝነት ነው

 

 

አዳም እና ሚስቱ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ ስጋዊ አካል አልነበራቸውም። አዳም መንፈስ ብቻ ነው የነበረው።

ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።

በስጋ መባዛት የሚከናወነው በሴት አካል አማካኝነት ነው።

መንፈስ የሚባዛው በወንድ በኩል በመንፈሳዊ መንገድ ነው።

ሁለቱም መንፈስ ነበሩ። “መባዛት” ማለት በመንፈስ መዋለድ ነው።

ይህ ምን ማለት እንደሆነ አላወቁም።

ባያውቁም እግዚአብሔር እስኪፈጽመው ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው። ይህም ልክ አሁን እኛ የጌታን መምጣት እንደምንጠባበቀው ነው።

ጌታ እንዲመጣ ማድረግ አንችልም።

ዳንኤል በራዕይ እንዳየው የጌታ ምጻት እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ እንደሚመጣ ድንጋይ ነው። የጌታ ምጻት የሰው እገዛ አያስፈልገውም።

የተሰጠን ትዕዛዝ እስከመጨረሻ “ታማኝ ሁኑ” የሚል ነው።

ዘፍጥረት 1፡11 እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

 

“ተባዙ” ማለት ዘሩ የሚገኘው ፍሬው ውስጥ ነው ማለት ነው።

እነዚህ ተምሳሌቶች ትርጉማቸው ምንድነው?

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

 

በድንግልና የተወለደው ልጅ የማርያም ማሕፀን ፍሬ ነው።

እናት ፍሬ የምታፈራ ዛፍ ናት።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው፡- ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው

ፍሬያማ ለመሆን ማርያም በውስጡ ዘር ያለበት ፍሬ ሊኖራት ይገባል።

በውስጡ የእግዚአብሔር ቃል ሙላት ያለው ልጅ መውለድ አለባት።

አማኑኤል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር።

ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ለመንፈሳዊ መባዛት የሚያስፈልጉት ከላይ በቆላስይስ የተጠቀሱት ናቸው።

በድንግልና የተወለደው ኢየሱስ ያድጋል፤ የሚሞትለት ሐጥያትም አይኖርም ነበር።

ከዚያም ኢየሱስ ቃሉን ብቻ በመናገር ቅዱሳንን ሁሉ ከምድር አፈር ውስጥ ጠርቶ ይፈጥራቸው ነበር፤ በትንሳኤ ቀን ይህንኑ ነው የሚያደርገው።

ይህ ቢፈጸም ኖሮ ምድርን ለመሙላት ትክክለኛ በቂ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ብቻ ይፈጠሩ ነበር።

 

 

አዳም ስጋዊ አካል የለበሰው ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ ነው

 

 

እግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፤ ነገር ግን በውስጡ ሰብዓዊ ባህርያትም አሉት፤ እነዚህን ሰብዓዊ ባህርያት በሰው አካል ውስጥ ሊገልጣቸው ፈለገ።

እግዚአብሔር የተለየ ስጋ አዘጋጀ፤ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ነው፤ በእርሱም ልዕለ ተፈጥሮአዊ ባህርዩን ገለጠው።

እግዚአብሔር ግን የራሱን ሰብዓዊነት የሚገልጥባቸው የሰው አካላትም ለማዘጋጀት አስቦ ነበር።

እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ውስጥ ከሰብዓዊነቱ የተወሰነ መጠን ሊገልጥ ስለሚፈልግ ሁላችንም ሙሉ በሙሉ እንድንታዘዘው ይፈልጋል።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚአብሔር የሰው መንፈስ በወንድ አካል ውስጥ አስቀመጠው።

ዘፍጥረት 2፡7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

አዳም በስጋዊ አካል ውስጥ ከገባ በኋላ ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ።

ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሊያጋጥመው ስለሚችለው አደጋ ወዲያው አስጠነቀቀው፤ ይህም አደጋ የእውቀት ዛፍ ነው።

ዘፍጥረት 2፡9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

“መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ”። ስለዚህ በገነት መካከል የነበረው ዛፍ ይህ ብቻ አይደለም ማለት ነው።

ሁለቱ ዛፎች በጣም የተቆራኙ ናቸው። እጅግ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እግዚአብሔር ለአዳም ሁለቱን የመለየት ስጦታ ሰጠው።

ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ነው እግዚአብሔር ለሴቲቱ አካል አዘጋጅቶላት በራሷ አካል ውስጥ ያኖራት። ስለዚህ ለአዳም የነበረው የመለየት ስጦታ ለሴቲቱ አልነበራትም።

ዝም ብላ ባሏን መስማት ነበረባት፤ እርሷ ግን በራሷ ያወቀች መሰላት።

ይህም በእግዚአብሔር መንፈስ እና በሰይጣን መንፈስ መካከል ትግል እንዲጀመር አደረገ።

የክርስቶስ መንፈስ (የሕይወት ዛፍ) እና ሰዎች በሰውኛ እውቀት እያስደነቀ የሚያታልለው የሰይጣን መንፈስ መካከል ግጭት ተጀመረ። ይህ መንፈሳዊ ጦርነት የሚካሄደው በሰው አእምሮ ውስጥ ነው፤ ጦርነቱ የሚደረገው እግዚአብሔርና ሰይጣን የሰውን አስተሳሰብ ለመግዛት በሚያደርጉት ጥረት ነው፤ ምክንየቱም ሰው ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶታል።

የእኛ ባል ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ቃሉን ብቻ መጥቀስ ነው ያለብን።

ቤተክርስቲያን ግን በራሷ ያወቀች መስሏት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ እየሄደች የራሷን አስተምሕሮ ታበጃለች።

እግዚአብሔር አስተሳሰባችን ለቃሉ እንዲገዛ ይፈልጋል።

ሰይጣን የራሱ ባሪያ ሊያደርገን ስለሚፈልግ መልካም እና ክፉ ሃሳቦችን ቀላቅሎ ያቀርብልናል። ቤተክርስቲያን መዳን በኢየሱስ ደም ነው ብላ በማስተማሯ መልካም አድርጋለች፤ ነገር ግን በዚያ ላይ ጨምራ ደግሞ ስም የሌለውን ስላሴያዊ አምላክ ትሰብካለች፤ በዚህም የተነሳ የሰይጣን መሳሪያ ሆናለች። ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ልትሰጡ አትችሉም።

የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም እያሉ ያወራሉ፤ ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ምንም አያውቁም።

ስለዚህ እውነትን እና ስሕተትን ቀላቅሎ ማቅረብ ከሁሉ ይበልጥ አደገኛ ማሳሳቻ ነው።

ትክክል እና ስሕተት የሆኑ አስተምሕሮዎችን የሚያምኑ ቤተክርስቲያኖች የዳኑ ክርስቲያኖችን ይዘው ወደ ታላቁ መከራ ያስገቡዋቸዋል፤ እነርሱም በታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ። እነዚህ ሰንፍ ቆነጃጅት ናቸው። ንጹህ ሴቶች። ድነዋል ግን ሰነፎች ናቸው።

ወደ አዳም እንመለስ።

አዳም ስጋዊ አካል ውስጥ በገባ ጊዜ ለፈተና ተጋላጭ ሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ አንድ ዛፍ የሚመስሉ ሁለት ዛፎች በገነት መካከል መኖራቸውን ለአዳም በመንገር አስጠነቀቀው። ይህ የምን ተምሳሌት ነው? ሕይወት ሊሰጥ የሚችል ፍጥረታዊ ዛፍ የለም። ጠቢብ ሊያደርገ የሚችል ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ የለም። የትኛውም ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ በእውነት እና በስሕተት መካከል ያለውን ልዩነት እንድታውቁ ሊያደርጋችሁ አይችልም።

የሕይወት ዛፍም መልካም እና ክፉውን ከምታሳውቀው ዛፍ ጋር በኤድን ገነት መካከል ነበር።

ዘፍጥረት 3፡22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤

ብቸኛው የዘላለም ሕይወት ምንጭ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ የሕይወት ዛፍ እርሱ ነው።

አዳም ሐጥያት ሰራ። እግዚአብሔርም አዳም ለዘላለም ሐጥያተኛ ሆኖ እንዲቀር አልፈለገም።

ኤርምያስ 17፡7 በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።

8 በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ … ዛፍ ይሆናል።

ዛፍ በእግዚአብሔረ የሚያምን የጻድቅ ሰው መንፈስ ተምሳሌት ነው። ይህም መንፈስ የሕይወት ወንዝ ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈቀቅ አይልም።

ኢየሱስ የሕይወት ዛፍ ከሆነ ሰይጣን ደግሞ አታላይ የሆነው የመልካም እና ክፉ መንፈስ ነው።

ይሁዳ ሐዋርያ ነበረ (የቤተክርስቲያን መሪ፣ መልካም)፤ ነገር ግን ገንዘብ አፍቃሪም ነበር (ክፉ)። ክፉ እና መልካም ሲቀላቀሉ ውጤቱ አደገኛ ነው የሚሆነው።

የኮምዩኒዝም አስተምሕሮ ክፉ ነው ግን ክርስቲያኖችን ለማሳሳት ብዙም አቅም የለውም። እውነት እና ስሕተትን ቀላቅሎ የሚያስተምር የቤተክርስቲያን ፓስተር ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማሳት ይችላል።

የቤተክርስቲያን ትልቅ ውድቀት መነሻው በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሞላው የገንዘብ ፍቅር ነው።

ኢየሱስ የሆሳእና ዕለት ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አባረራቸው፤ ከዚያ በቀጣዩ ሰኞ የካሕናት አለቆች በሆሳእና ዕለት ተቀብለውት የነበሩት ሕዝብ ከሶስት ቀናት በኋላ ሐሙስ ዕለት ይገደልልን ብለው እንዲጠይቁ አሳመኑዋቸው።

ኢየሱስ ሐሙስ ዕለት ሞተ፤ ምክንያቱም እሑድ ዕለት ጠዋት እስከሚነሳ ድረስ ሶስት ቀን እና ሶስት ሌሊት መቃብር ውስጥ መቆየት ነበረበት።

ሐሙስ ሌሊት፣ አርብ ሌሊት፣ ቅዳሜ ሌሊት።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ልባቸው ከገንዘብ ጋር በጣም የተቆራኘ ነው። ገንበዛቸውን ለማስጠበቅ ብለው እውነትን ይገልዳሉ።

 

አሁንም ወደ አዳም እንመለስ።

እግዚአብሔር ከአዳም መንፈስ ውስጥ የሴቲቱን ባህርይ ነጥሎ አወጣና ለብቻ በሌላ አካል ውስጥ አኖራት።

ስጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ አይችሉም። በውስጡ ደም ያለው ማንኛውም ነገር ለዘላለም መኖር አይችልም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥

ስለዚህ አዳምና ሔዋን ደምስራቸው ውስጥ ደም አለነበራቸውም። በደምስራቸው ውስጥ ይዘዋወር የነበረውና በሕይወት ያኖራቸው የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው።

ዘፍጥረት 2፡23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

ደም በጭራሽ አልተጠቀሰም።

ደም በሌለበት ወሲብ ሊኖር አይችልም ምክንያቱም የወንድ ወሲባዊ አካል የሚነቃቃው በደም አማካኝነት ነው።

ስለዚህ ራቁታቸውን መሆናቸው ምንም አይታወቃቸውም ነበር።

ዘፍጥረት 2፡25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።

በሁለታቸው መካከል ምንም ወሲባዊ ፍላጎት አልነበረም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ አዳም እና ሚስቱ አንድ መንፈስ ነበሩ።

መንፈስ ወሲባዊ ግንኙነት ሊያደርግ አይችልም።

ምዕራፍ 1 ውስጥ ወንድም ሴትም የሆነውን አዳም የተባለውን መንፈስ እግዚአብሔር እንዲባዛና ምድርን እንዲሞላ ነገረው። ይህም መንፈሳዊ መባዛት ነው። እነርሱ ግን ይህ ምን ማለት እንደነበር አልገባቸውም።

ስለማያውቁ ከእነርሱ የሚጠበቀው እግዚአብሔ እቅዱን በራሱ መንገድ እስኪፈጽመው ድረስ መጠበቅ ነበር።

አንዳች ነገር ቢያደርጉ ስሕተት ነው የሚሆነው ምክንያቱም የእግዚአብሔረ ሃሳብ ከእኛ ሃሳብ ከፍ ያለ ነው። ደግሞም እግዚአብሔር ምን እንደሚያስብ ልናውቅ አንችልም።

ስለዚህ ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚአብሔር በተለያዩ ሁለት አካላት ውስጥ ሲያኖራቸው አስቀድሞ ለአዳም ስለ እውቀት ዛፍ ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኋላ ነበር።

የወሲብ ትርጉሙ “ስጋዊ እውቀት” ነው።

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥

በተጨማሪ ደግሞ እግዚአብሔረ ስጋ ለለበሰችዋ ሴት የድንግልና ማሕተም ሰጣት። ይህንንም ያደረገው ወሲብ የእግዚአብሔር ፈቃድ አለመሆኑን እንዲያውቁ ነው።

የዘላለም ሕይወት በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ወደ ልጆች ሊተላለፍ አይችልም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ አዳም አንዴ ስጋ ከለበሰ በኋላ እግዚአብሔር ስለ እውቀት ዛፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠው።

አዳም ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጻፈው መንፈስ በነበረ ጊዜ ወሲብ የመፈጸም ዕድል አልነበረውም፤ ስለዚህ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠውም።

ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጻፈው ፍጥረታዊ ዛፎች ሁሉ መልካም ነበሩ።

በሶስተኛው ቀን ዛፎች ሲፈጠሩ ክፉ ዛፍ ወይም እንዳይበሉ የተከለከሉት ዛፍ አልነበረም። ሁሉም ነገር መልካም ነበረ።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ

 

ስለዚህ የእውቀት ዛፍ ፍጥረታዊ ዛፍ አልነበረም። የእውቀት ዛፍ የሰይጣን መንፈስ ነው።

የሰይጣን እውቀት አደገኛ፣ ክፉ እና አታላይ ነው።

 

 

ነጻ ፈቃድ ከወሲባዊ አካላት ጋር ነው የተሰጣቸው ይህም መምረጥ እንዲችሉ ነው

 

 

ወሲባዊ አካል ለምን ተሰጣቸው?

እግዚአብሔር ካዘጋጀው የመጀመሪያ እቅዱ ውጭ ሌላ አማራጭ መኖር ነበረበት። እግዚአብሔር ለሃሳቡ እንዲታዘዙ ሊያስገድዳቸው አልፈለገም።

ስለዚህ እግዚአብሔር እራሱ በእቅዱ ውስጥ ካሰበው መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ከመባዛት ሌላ አማራጭ ስጋዊ የመባዣ ንገድ እንዲኖር አደረገ።

መልካም ባህርይ ተፈትኖ ካልታየ በቀር እውነተኛ መልካም ባህርይ ሊሆን አይችልም፤ ጠላት በሌለበት ጦርነት አንደማይኖር ሁሉ፤ ጦርነት በሌለበትም ድል የለም።

መልካም ባህርይ ሊገለጥ የሚችለው ከብርቱ ጠላት ጋር በሚደረግ አደገኛ ፍልሚያ ነው።

በግላችን መቆጣጠር የማንችላቸው ፈተናዎች ሲበዙብን ነው ትዕግስት ሊገለጥብን የሚችለው።

ባህርይ እንደ ስጦታ ሊሰጥ አይችልም። ባህርይ የሚቀረጸው በብዙ መከራ እና ሽንፈት ውስጥ በማለፍ ነው።

ጦርነት ከሌለ ድል የለም።

እምነት የሚያድገው በራሳችን ልንፈታቸው የማንችላቸው ፈተናዎችን ስንጋፈጥ ነው።

ስለዚህ እንድናድቅ የሚቃወመን ጠላት ያስፈልገናል።

በሰው ውስጥ ያለው እኔነት የማወቅ ጉጉትን ይፈጥራል።

ሁልጊዜ አዲስ ነገር ማወቅ እንፈልጋለን።

ነገር ግን በተፈጥሮ መሃይሞች እንደመሆናችን መጠን ለእምነታችንም ሆነ ለስነ ምግባራችን ትምሕርትና ምሪት ያስፈልገናል።

የሚያስፈልገን ምሪት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለሚገኝ ቃሉን ማመን መለማመድ አለብን።

 

ከሰው አእምሮ ውስጥ ዋነኛው አስፈላጊ ክፍል ፈቃድ ነው። ፈቃድ ከሌለን ሮቦት እንሆናለን።

እግዚአብሔር የፈለገውን እንድናደርግ ሊያስገድደን ይችላል። ነገር ግን በራሳችን ነጻ ፈቃድ ተነስተን የማድረግ ፍላጎት ሲኖረን ይሻላል።

ነገር ግን ከፈለግን ልንመርጥ የምንችለው ሌላ አማራጭ እንደ ፈተና ሆኖ ካልቀረበልን በቀር ነጻ ፈቃድ የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም።

በራሳችሁ ነጻ ፈቃድ ታማኝ እንድትሆኑ ብፈልግ መስረቅ እንድትችሉ የሆነ ቦታ የተወሰነ ገንዘብ አስቀምጬ መሄድ አለብኝ። ምንም የመስረቅ ዕድል ከሌላችሁ የእውነትም ታማኙ ሁኑ አትሁኑ ማወቅ አልችልም።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ ሒትለርና አብረውት የነበሩ ሰዎች ከምድር በታች የተሰራ መጠለያ ውስጥ ነበሩ። ሁሉንም ሲጋራ ማጨስ ከለከላቸው። ሒትለር ሁላቸውም ሲጋራ ማጨስ ያቆሙ መሰለው። በሰጣቸውም ትዕዛዝ ደስ አለው። ልክ እርሱ ሲሞት ያደረጉት የመጀሪያው ነገር ሲጋራ አውጥተው ማጨስ ነበር።

ስለዚህ ማጨስ ያቆሙት የምራቸውን አልነበረም።

እግዚአብሔር ደግሞ ሰዎች ለእርሱ የታዘዙ እየመሰላቸው እንዲታለሉ አይፈልግም፤ የሚፈልገው የእውነት እንዲታዘዙት ነው። እግዚአብሔር ደስ የሚለው ሰው ከልቡ ደስ ብለትና ፈልጎ እንዲታዘዘው ነው።

እግዚአብሔር አስመሳይነትን አይወድም። እግዚአብሔር በሰው ልብ ውስጥ የተሰወረውን ነገር ነው የሚመለከተው።

የእግዚአብሔርን እውነት መውደድን መለማመድ ያስፈልገናል፤ እግዚአብሔርም ስለሚራው ሥራ ምንም ማጉረምረም የለብንም። ይህም ለመማር የሚከብድ ትምሕርት ነው።

ማድረግ ከምትፈልጉት ነገር ይልቅ ማራኪና ይበልጥ አስደሳች የሚመስል ነገር ቀርቦላችሁ እርሱን እምቢ ማለት ስትችሉ ብቻ ነው የእውነት ምን ማድረግ እንደፈለጋችሁ የምታውቁት።

ስለዚህ እግዚአብሔር ለአዳምና ለሴቲቱ ወሲባዊ አካላትን በመስጠት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመተላለፍ በጣም ፈታኝ የሆነ አማራጭ አቀረበላቸው።

በምድር ላይ ከሚፈጸሙ የሐጥያት ዓይነቶች ሁሉ በብዛት የሚበልጠው ወሲባዊ ሐጥያት ሊሆን ይችላል።

ይህም ብዙ ሰዎች ሊከተሉ የሚፈልጉት የተሳሳተ መንገድ ነው።

ሰዎች እግዚአብሔርን መከተል ካልፈለጉ በዚህ መንገድ እራሳቸውን ከእግዚአብሔር እቅድ ገለል ያደርጋሉ።

 

እግዚአብሔር አዳም እና ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ልጆችን እንዲወልዱ ፈለገ ብለን እናስብ።

በዚህ መንገድ የተወለዱ ልጆች ዘላለማዊ ሕይወት አይኖራቸውም። ወላጆች ለልጆቻቸው የዘላለም ሕይወትን ሊሰጡ አይችሉም።

አዳም ከ900 ዓመታት በላይ ኖረ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ስለዚህ ስንት ልጆች ይወለዳሉ? በጣም ብዙ።

በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ቢወለዱ ልጆቹ አይሞቱም ነበር።

ዓለም በሕዝብ ብዛት እስክትጨናነቅ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባታል? ብዙም አይፈጅባትም።

ይህም ለዘላለም ጸንቶ ሊኖር የሚችል ስርዓት አይደለም። ይህ የዘላለማዊነት መንገድ አይደለም።

እግዚአብሔር የሚወለዱ ልጆችን ቁጥር ቢገድብ ሰዎች የፈለጉትን ያህል ልጅ የመውለድ ነጻነታቸውን ይከለክላቸው ነበር።

ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው የፈለገው ሰው ነጻ ፈቃድ እንዲኖረው ነው።

በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎች ብዙ ሰዎች ላይ ችግር አምጥተዋል። ከነዚህም መካከል ለምሳሌ ኤድስ የማይፈወስ በሽታ ነው።

አስገድዶ መድፈር፣ ዝሙት፣ መዳራት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ወሲባዊ ጥመት፣ ልጆችን ማማገጥ ከወሲብ እና ከነጻ ፈቃድ ጋር ተያይዘው የመጡ ሐጥያቶች ናቸው።

ስለዚህ ይህ በጎ ስርዓት እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

እግዚአብሔር ከመጀመሪያውም የተሻለ ሃሳብ ነበረው ማለት ነው።

አዳም እና ሴቲቱን በስጋዊ አካል ውስጥ ሲያኖራቸው ልክ እንደ ዮሴፍና እንደ ማርያም እንዲሆኑ ፈልጎ ነው። ዮሴፍ እና ማርያም እግዚአብሔርን ከመጠበቅ ውጭ ምንም ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር አልነበረም። የመጀመሪያውን እርምጃ የሚወስደው እግዚአብሔር ነው።

አዳም እና ሚስቱ የኤድን ገነት ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ከኖሩ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ይጸልላትና በማሕፀንዋ ውስጥ የሚፈጠረውን ወንድ ልጅ በድንግልና ትወልድ ነበር።

ማሕፀንዋ ለሚወለደው ልጅ ማደጊያ ሆኖ ብቻ ያገለግል ነበር።

ዕብራውያን 10፡5 … ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

መኃልየ መኃልይ 4፡12 እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።

የአትክልት ስፍራ የሴት ተምሳሌት ነው።

ለጥበቃ ተብሎ ከአትክልት ስፍራ ዙርያ አጥር ይታጠራል። ሴቶች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ሊመጣ የሚችለው በድንግልና ማሕተም ከተጠበቀ ማሕፀን ብቻ ነው።

ዘፍጥረት 2፡9 … በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

ገነት የሴት ተምሳሌት ነው።

“በገነት መካከል” የሚለው በሴቲቱ አካል ውስጥ መካከለኛውን ስፍራ ያመለክታል። እርሱም ማሕፀንዋ ያለበት ቦታ ነው።

በድንግልና በመውለድ ዘላለማዊ ሕይወት እንዲተላለፍ ማድረግ ትችል ነበር።

አለዚያ ደግሞ መልካምም ክፉም ባህርያት የተደባለቁበትንና ከዓመታት በኋላ የሚሞት ፍጥረታዊ ሕይወትን የማስተላለፍ አማራጭም ነበራት።

ሐጥያት ሲገባ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ ወሲብ መልካም ተደርጎ እንዲቆጠር ፈቀደ።

ይህም የእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ነው።

ስለዚህ ወሲብ መልካምና ክፉ ሆነ።

ዛሬ መልካም እና ክፉ ተብለው ሊገለጹ የሚችሉ ጥቂት ድርጊቶች አሉ። ከነዚህ መካከል አንዱ ወሲብ ነው።

 

 

ወሲብ የሚፈቀደው በሕግ በተጋቡ ወንድ እና ሴት መካከል ብቻ ነው

 

 

እግዚአብሔር በድንግልና ስለ መውለድ ያሰበውን እቅድ ሔዋን ካበላሸች በኋላ እግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃዱን ገለጠ፤ ይህም በወሲባዊ ግንኙነት በኩል መባዛት ነው። ይህ ሃሳብ ከመጀመሪያው አደገኛ ነበረ።

ስለዚህ ለእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ግለጽ የሆኑ ሕጎች አስፈለጉ።

ወሲብ ከጋብቻ በፊት እና ከጋብቻ ውጭ ክፉ ነው። ወሲብ በጋብቻ ውስጥ መልካም ነው።

እግዚአብሔር ግን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥብቅ ትዕዛዞችን ሰጥቷል።

የጋብቻ ቃልኪዳን መደረግ የሚችለው በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ ነው፤ ሕጋዊ ከሆነም እስከ ሞት ድረስ ይጸናል።

መፋታት እና በሕይወት ካለ የትዳር አጋር ጋር እንደገና መጋባት የሚባል ነገር የለም።

ፍቺ የጋብቻ ቃልኪዳንን ሊያፈርሰው አይችልም።

ማርቆስ 10፡11 እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤

ማርቆስ 10፡12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው።

እግዚአብሔር ለእያንዳንዲቱ ሴት የድንግልና ማሕተም ይሰጣታል። እስክታገባ ድረስ ድንግል ሆና እንድትቆይ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

ድንግል ካልሆነች ከማግባቷ በፊት ይህን ለባሏ ቀድማ መንገድ አለባት። ድንግል አለመሆኗን ቀድማ ካልተናገረች የጋብቻ ቃልኪዳንዋ ዋጋ የለውም።

ለምን?

ወንድ የሚስቱ ራስ ነው። ሚስት ለባሏ መገዛት አለባት።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና

ኤፌሶን 5፡22 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

ሴት ድንግልናዋን ለማስጠበቅ ትታገላለች፤ የሰርጓ ቀን ግን ድንግልናዋን በፈቃዷ ለባሏ ትሰጣለች።

ድንግልናዋን መስጠቷ ትሑት ያደርጋታል። ላለመስጠት ጨክና የታገለችለትን ነገር መስጠቷ ነው ትሑት የሚያደርጋት።

ከባሏ በፊት ከሌላ ሰው ጋር ተኝታ ከሆነ ያ ሌላ ሰው ትሑት አድርጓታል።

ስለዚህ ለባሏ በሙሉ ልቧ ላትገዛለትና ላታከብረው ትችላለች።

ባሏ ከሰርግ በፊት ይህን ማወቅ አለበት።

ድንግል ያልሆነች ሴትን ያገባ ሰው ሚስቱ እንደ ባል ላትቆጥረው ትችላለች።

ሊያገባት ከወሰነ እርሷ እንደ ባል ባታክረውም እንኳ የጋብቻ ቃልኪዳኑ የጸና ነው።

ስለዚህ ድንግል ያልሆነች ሴትን የሚያገባ ሰው በጥንቃቄ ማሰብና መጸለይ አለበት።

ዘዳግም 22፡23 ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥

24 ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ከአንዲት ሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ አብሯት የተኛ ሰው ድንግልናዋን ይወስደዋል፤ ይህም ያስነውራታል ወይም ትሁት ያደርጋታል። ከተጋቡ በኋላ ይህ ሰው ባሏ መሆን አለበት።

ኤድን ውስጥ እግዚአብሔርና ሰይጣን የሴቲቱን ማሕፀን ለመያዝ ሲወዳደሩ ነበር።

በመላእክት አለቃ ሚካኤል አማካኝነት እግዚአብሔር በሰማይ ሊሲፈርን ተዋጋውና ረግሞት ወደ ሰይጣንነት ቀየረው።

ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ።

ኤድን ውስጥ እግዚአብሔር ከእንስሳት ሁሉ የበላይ የነረውን እባብ ረገመው፤ እባቡ ከዝንጀሮዎችና ከጦጣዎች ሁሉ በላይ ነበረ፤ መናገርና መከራከር ማሳመን ይችል ነበር፤ እግዚአብሔር ወደ እባብነት (በደረቱ የሚሳብ እንስሳ) እንዲሆን ለወጠው፤ ምላሱም መንታ እንዲሆን አደረገው፤ መንታ ምላስ የውሸታሞች ስም ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ እባብ አፉ ውስጥ መርዝ አለው። እባቡ ለሔዋን የነገራት ውሸታም መርዛማ ውሸት ነበረ።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ሰይጣን እንስሳ እንዲናገር አደረገ ተብሎ አልተጻፈም። እባቡ ከእንስሳት ሁሉ የበላይ ስለነበረ መናገር ይችል ነበር።

ሔዋን ኢየሱስን በድንግልና እንድትወልድ ነበር የታሰበላት። የእግዚአብሔር ሙላትም በእርሱ ውስጥ ይሆን ነበር።

ኢሳይያስ 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

እርሱም ትልቅ ሰው ሆኖ ያድጋል ነገር ግን የሚሞትለት ሐጥያት አይገኝም።

ከዚያም ኢየሱስ ቅዱሳንን በቃሉ ከምድር አፈር ይፈጥራቸዋል፤ ይህም በትንሳኤ ቀን ሙታንን በቃሉ እንደሚጠራቸው ነው። የዚያኔ ምድርን ለመሙላት የሚበቃ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ብቻ ይፈጠሩ ነበር። ሲኦል ውስጥ ገብተው የሚቃጠሉ ትርፍ ሰዎች አይኖሩም ነበር።

ይህ ነበረ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ እቅድ።

 

 

ሰዎች በመልካም ስነ ምግባር እንዲታነጹ ችግርና መከራ ያስፈልጋቸዋል

 

 

ለነዚህ አዲስ ሆነው ለተፈጠሩ ሰዎች ባህርይና መልካም ስነ ምግባር ማዳበር ከባድ ይሆንባቸው ነበር። ትዕቢት እና ራስ ወዳድነት ለማስወገድ ከባድ ይሆንባቸዋል።

ከዘመናት አንጻር ስንመለከተው ሐጥያተኞች ሆነን ተወልደን እግዚአብሔር ሐጥያታችንን ይቅር ያለበትን ፍቅሩን ማየታችን የተሻለ ነው። በእጆቹ ላይ ያሉት ጠባሳዎች ስለ ሐጥያታችን የከፈለልንን ዋጋ ለዘላለም ያስታውሱናል።

አዳኝ የሚያስፈልገን መሆናችን እንዳንታበይ ያደርገናል። በሐጥያት ምክንያት የተበላሸን መሆናችንን እና ወደ ሲኦል እየተነዳን የነበርን መሆናችንን ማወቅ ለሐጥያት ያለንን ፍላጎት ይቀንሰዋል። የሐጥያትን አስከፊነት እንድናውቅና ሐጥያት የሌለባትን ዓለም እንድንናፍቅ ነው በሐጥያት የተወለድነውና ሐጥያት የሚያስከትለውን መከራ እና ሐዘን እንድናይ የተደረግነው።

ሰዎች ዓለምን የሚገዙበት አገዛዝ ምን ያህል አስከፊ መሆኑን ማየት እንድንችል ነው ሰው በሚገዛበት ዓለም ውስጥ የተወለድነው። ይህም ዓይናችንን ከሰው ላይ አንስተን ዓለምን ለመምራት ብቃት ወዳለው ብቸኛ ሰው ወደ ኢየሱስ እንድናይ ያደርገናል።

ከሐጥያት የምናመልጥበት ብቸኛው መንገድ ንሰሃ መግባትና ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን መቀበል ነው። ሐጥያታችንን ይቅር ከተባልን በኋላ ሌሎች ሐጥያተኞች ላይ ከመፍረድ መቆጠብ አለብን፤ በዚህም ለሰዎች መራራትንና መልካምነትን እንለማመዳለን።

ችግርና መከራ ከደረሱብን በኋላ እምነታችንና ተስፋችን በራሳችን ወይም በሌላ ሰው ላይ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ ላይ ይሆናል።

የሔወንን ቅጣት ተመልከቱ።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤

እግዚአብሔር፡- “ይህ ስላደረግሽ …” ብሎ አልተናገራትም።

እግዚአብሔር ስለ ቅጣቷ ምንም ምክንያት አልሰጣትም። ሐጥያት መስራቷን ማወቅ እስከሚሳናት ድረስ ነበር የተታለለችው።

ዛሬም የቤተክርስቲያን ሰዎች ሔዋን የሰራችው ስሕተት ምን እንደሆነ ሊነግሯችሁ አይችሉም። አንድ የዛፍ ፍሬ በላች ይላሉ።

ማቴዎስ 15፡11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥

የምንበላው ነገር ሊያረክሰን አይችልም፤ ምክንያቱም በአንጀታችን ውስጥ አልፎ ወደ መጸዳጃ ቤት ይወርዳል።

እግዚአብሔር የቀጣት ስላረገዘች ነው። ፀንሳ ነበር።

ስለዚህ ዛሬ ቤተክርስቲያንም ልክ እንደ ሔዋን የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደሆነ አታውቅም።

አዳምና ሔዋን ሁለቱም ሐጥያት ሰርተዋል፤ የተቀጡት ቅጣት ግን የተለያየ ነበረ።

እግዚአብሔር ሔዋንን ልጅ በመውለድ ቀጣት። ይህ አዳም ሊቀጣበት የማይችለው ቅጣት ነው።

ስለዚህ ሁለቱም የዛፍ ፍሬ ከሆነ የበሉት የሆነ ችግር አለ ማለት ነው።

እባቡ ከእንስሳት ሁሉ ተንኮለኛና በአእምሮም የላቀ ነበረ። ከጦጣዎች በላይ እና ለሰው የቀረበ ነበር።

ሔዋን ከእባቡ ጋር ዝሙት ሰራች።

አዳም እንደ ጋለሞታ በድንጋይ ሊወግራት ይገባ ነበር።

ነገር ግን በጣም ስለወደዳት አብሯት ሐጥያት መስራትንና ከእርሷ ጋር መሞትን መረጠ።

ሔዋን ሐጥያት ከሰራች በኋላ ብቻ ነው አዳም ለእርሷ ራስ እና ጌታ የሆነው።

 

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል

 

ልክ እንደዚሁ ኢየሱስም እኛን እጅግ በጣም ከመውደዱ የተነሳ ሊገድለን አልቻለም፤ ስለ እኛ ሐጥያት መሆንን እና ስለ ሐጥያታችን መሞትን መረጠ። በዚህም መንገድ እኛ ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወትን መቀበል ቻልን።

2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

ሐጥያተኞች ስለነበርን ክርስቶስ አሁን የእኛ ራስና ጌታ ሆኗል።

ፈቃዳችንም ወደ እረሱ እና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መሆን አለበት። ይህም ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱስ የ1769ኙ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን ትርጉም ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም መመሪያችን አድርገን መቀበል አለብን። እውነትን ለማወቅ ያለን ጉጉት በሙሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ሊወስደን ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማያስፈልጉ ጥቅሶች፣ ስሕተቶች፣ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች፣ የተሳሳት ትርጓሜዎች አሉ ብለን በጭራሽ ማሰብ የለብንም።

ምሳሌ 30፡5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩትን በሙሉ ስለ ኢየሱስ እየተናገራችሁ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሉዋት ብሎ የሰጠው ትዕዛዝ ለሔዋን ወሲባዊ ግንኙነት በማድረግ መሰላት። ይህ ትዕዛዝ ሊፈጸም የሚችልበት ሌላ መንገድ ያለ አልመሰላትም።

ስለዚህ እኛ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትልቅ እቅድ ሙሉ በሙሉ ማየት ስለማንችል ውስን በሆነው ጭንቅላታችን እንታለላለን። የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ መሃይምነታችንን አለማወቃችን ነው።

ምን እንደማናውቅ እንኳ አናውቅም። ደግሞም በጣም ብዙ የማናውቀው ነገር አለ።

ስለዚህ ማመን ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው።

የሴቲቱ ማሕፀን መልካም እና ክፉውን የሚያሳውቀው ዛፍ ነው።

በድንግልና እንድትወልድ እግዚአብሔር ከተጠቀመበት መልካም ነው። እባቡ ለወሲባዊ ግንኙነት ቢጠቀምበት ክፉ ነው።

ሔዋን ማሕፀንዋን ማለትም መልካምና ክፉውን የምታሳውቀውን ዛፍ ሐጥያተኛ ሕይወት እንዲወለድ ለማድረግ ሰይጣን ሊጠቀምበት እንደሚችል አላወቀችም።

ወይም ደግሞ እግዚአብሔር ማለትም የሕይወት ዛፍ ማሕፀንዋን ተጠቅሞ በድንግልና የሚወለደውን ልጅ ለማምጣት እንደሚችል አላወቀችም።

ሐጥያት ከገባ እና እግዚአብሔርም የይሁንታ ፈቃዱን ከፈቀደ በኋላም የሴቲቱ ማሕፀን መልካምና ክፉውን የሚያሳውቅ ዛፍ ሆኖ ቀጥሏል።

ወሲብ መልካም የሚሆነው በሕግ በተጋቡ ወንድ እና ሴት መካከል ብቻ ነው። ከዚው ውጭ የሆነ ማንኛውም ወሲባዊ ግንኙነት ክፉ ነው።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅማ መዳን ለሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዲመጣ አድርጋለች፤ ይህም መልካም ነው።

ነገር ግን ቤተክርስቲያን ይህንኑ መልካም መጽሐፍ ቅዱስ ጠምዝዛ በመጠቀም እና የሰዎችን ጥቅስ በመስበክ እንደ ስላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ ክሪስማስ፣ ሁዳዴ፣ በ1963ቱ ደመና የጌታ መምጣት፣ ዊልያም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ፣ እና ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው፤ ዊልያም ብራንሐም የሰው ልጅ ነው ብለው አንድን ሰውዬ ከፍ ማድረግን የመሳሰሉ ክፉ ነገሮችን ሰርታለች።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን መልካም ሃሳብም ክፉ ሃሳብም ታመነጫለች።

 

 

ወንድም ብራንሐም ፍጹም ሰው ስላልሆነ ስሕተቶችን ሰርቷል

 

 

54-0514 የእግዚአብሔር ማሕተም

በ96 ዓ.ም ታይተስ በመጣ ጊዜ ኢየሩሳሌም በሮም የጦር ሰራዊት ተከበበች።

ይህ ልክ አይደለም። ትክክለኛው ዓመት 70 ዓ.ም ነው።

61-0806 የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ

… የእግዚአብሔር ኃይል ከአይሁድ ጋር ለ1,954 ዓመታት ነበረ። እግዚአብሔር ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ያሳለፈው ዘመን በአይሁዶቹ አቆጣጠር እና በገላትያ 3፡16-17 መሰረት 1,954 ዓመት ነው። ብዙ ጥቅሶች አሉኝ ግን ለአሁን ይህ ይበቃል። ከዚያም ክርስቶስን አንቀበልም ካሉ በኋላ ለስሙ የሚሆን ሕዝብ ለመውሰድ ወደ አሕዛብ ዘወር አለ። ይህን የሚመሰክር ጥቅስ ትፈልጋላችሁ? የሐዋርያት ሥራ 15፡14።

ስለዚህ ዓመታቱን ስንቆጥር (አድምጡ) ልክ አስራ ሰባት ዓመታት ይቀሩናል፤ እኛም ደግሞ ልክ ይህንኑ የሚያህል ጊዜ ነው የተሰጠን፤ ምክንያቱም ከ33 ዓ.ም ወዲህ እግዚአብሔር እኛን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየመራን ነው ያለው፤ ስለዚህ ለእኛም የተሰጠን 1,954 ዓመት ነው

በቁጥር ስሌት ላይ የተሰራውን ከባድ ስሕተት ተመልከቱ።

ኢየሱስን አይሁዶች አንቀበልም ያሉት በ33 ዓ.ም ነው። (በዚያው ስብከት ውስጥ ኢየሱስ የሞተው በ30 ዓ.ም ነው ብሎ ይናገራል። ይህ ስሕተት ነው።)

33 + 1954 = 1,987 እንጂ 1,977 አይደለም።

በስሌቱ ውስጥ 10 ዓመታትን አሳስቷል፤ ነገር ግን ይህንን ስሕተት ማንም አላየም ምክንያቱም ማንም ስራዬ ብሎ በቁም ነገር አልተከታተለም።

እንደምናውቀው በ1977 ምንም ነገር አልተፈጠረም፤ ስለዚህ የተናገረው ትንቢት ስሕተት ነበረ።

60-1113 ውግዘት በውክልና

ከዚያም አሜሪካ በእሳት ተቃጥላ እንደፈራረሰች ቦታ ሆና አየኋት። ይህም ወደ መጨረሻ አካባቢ የሚፈጸም ነው። (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ እንዲህ አልኩ፡- “ይህ ይፈጸማል ብዬ እተነብያለው።” ስለዚህ አስታውሱ … እግዚአብሔር ያሳየኝ ይህ ነው ግን “ከ1977 በፊት ይፈጸማል ብዬ እተነብያለሁ።”)

ትንበያው ስሕተት ነበረ። አሜሪካ በ1977 አልጠፋችም።

ስለዚህ ዊልያም ብራንሐም ፍጹም አይደለም። እርሱም እንደ ሌሎች ይሳሳታል።

እግዚአብሔር ግን በጭራሽ አይሳሳትም።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም እግዚአብሔር አይደለም፤ የእግዚአብሔር ድምጽም አይደለም።

ወንድም ብራንሐም በራዕይ 10፡7 እንደተጻፈው የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ነው።

ራዕይ 10፡7 … ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ …

 

 

የ1963ቱ ደመና የሰው ልጅ በሰማይ ላይ የመታየቱ ምልክት ነው

 

 

በ1963 የቱክሰን ጠፈር ምርምር ጣቢያ በ42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ፎቶግራፍ ያነሳው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የሰው ልጅ በሰማይ መኖሩን የሚያሳይ ምልክት ብቻ ነው።

የሜሴጅ ፓስተሮች ይህ ደመና የጌታ ምጻት ወይም የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር መውረድ ነው ይላሉ። ምልክት መሆኑን መቀበል አይፈልጉም። ምልክት ሳይሆ ፍጻሜ ነው ይላሉ።

 

 

1965-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል ከዚያ በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል።”

 

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

ወንድም ብራንሐም ምድር ላይ በነበረ ጊዜ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ በፍጹም ወደ ምድር አልወረደም፤ ምክንያቱም መልአኩ ወደ ምድር ወርዶ ቢሆን ኖሮ ሙታንን ባስነሳ ነበር። ትንሳኤ ግን እስካሁን አልሆነም።

64-0119 ሻሎም

ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

የዚህ ዘመን ስሕተቶች በጣም የረቀቁ ከሆናቸው የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እያገናኙ የማያጠኑ ሰዎችን በቀላሉ ያሳስቷቸዋል።

ማቴዎስ 24፡24 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ማርች 8 ቀን 1963 ዓ.ም ታላቁ ሶኖራን በረሃ አጠገብ ወደሚገኘው ሳንሴት ፒክ ሰባት መላእክት መጥተው ወንድም ብራንሐምን አገኙት። ስለዚህ እነዚያ ሰባት መላእክት የጌታ ምጻት ሊሆኑ አይችሉም፤ ደግሞ ጌታም ወደ በረሃ አይመጣም። የሜሴጅ አማኞች ይህንን በማመናቸው እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት በቀላሉ ይታለላሉ።

 

 

 

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ ተባዙ ይላል ምዕራፍ 3 ውስጥ ግን እጅግ አበዛለሁ ይላል

 

 

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

 

እግዚአብሔር ለእባቡ ሐጥያቱን ነግሮታል። እግዚአብሔር እባቡን ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ከነበረበት ረገመውና በደረቱ የሚሳብ እንስሳ አደረገው።

እባቡ በሆዱ እንዲሳብ ነው የተረገመው።

ስለዚህ እባቡ የሰራው ሐጥያት ሔዋንን ወሲብ ለማስተማር በእርሷ ላይ በደረቱ መተኛቱ ነው።

ሴቲቱ በመጀመሪያ የደም ስሮቿ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ነበሩ። ስለዚህ በውስጧ ዘላለማዊ ሕይወት ነበራት።

ሔዋን የእባቡን ወሬ ማመን ስትጀምር መንፈስ ቅዱስ ከእርሷ ውስጥ ወጥቶ ሄደ። ከዚያም እግዚአብሔር በሕይወት ሊያቆያት ስለፈለገ ደም ስሮቿን በደም ሞላቸው።

ከዚያም እባቡ ድንግልናዋን ሲወስድ ደም ፈሰሳት።

ተረግሞ በደረቱ ወደሚሳብ እንስሳ ከመለወጡ በፊት እባቡ ሔዋንን አስረገዛት።

የሰው ዘር በሐጥያት የወደቀው በዚህ መንገድ ነው።

በአንዳንድ ቋንቋዎች ሴት ስታረግዝ በእርግዝና ወደቀች ይባላል።

ከዚያ በኋላ ሔዋን ድንግል ማሕፀን ስላልነበራት እግዚአብሔር ማሕፀንዋን ሊጠቀም አልቻለም።

የሰራችው ሐጥያት ሊስተካከል የሚችል አልነበረም። ድንግልና አንዴ ከጠፋ በኋላ ሊመለስ አይችልም።

ስለዚህ የመጀመሪያው ሐጥያት አንድ እንስሳ የሴቲቱን ደም ማፍሰሱ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር የሌላ እንስሳ ደም ለሐጥያት ማስተሰርያ አድርጎ ተቀበለ።

ሔዋን የሞት ፍርድ መጣባት ምክንያቱም የሐጥያት ደሞዝ ሞት ነው።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤

ሔዋን በሆዷ ፅንስ ይዛ ነበር። አርግዛ ነበር።

አዳም ባሏ ስለነበረ እግዚአብሔር ከአዳም ስለመፀነሷ ብሎ ሊቀጣት አይችልም።

ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ብሏል።

እግዚአብሔር ይህ ትዕዛዝ እንዲፈጸም የፈለገው ኢየሱስ በድንግልና ተወልዶ የሚፈልገውን ቁጥር ያህል ቅዱሳንን ከምድር አፈር በቃሉ ኃይል እንዲፈጥር ነበር። የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ያ ነበር። ኢየሱስ በትንሳኤ ቀን ይህንኑ ነው የሚያደርገው።

ሐጥያት ከሰሩ በኋላ ግን እግዚአብሔር በወሲባዊ ግንኙነት “እጅግ እንዲባዙ” ተናገረ።

ጻድቃንም ሐጥያተኞችም በወሲባዊ ግንኙነት እና በነጻ ፈቃድ ይወለዳሉ።

አሁን ግን እርግዝና እና ልጅ መውለድ የእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ መሆናቸውን ለማሳየት ከባድ ነው።

እግዚአብሔር ወሲባዊ ግንኙነትን የሚፈቅደው በአንድ ወንድ እና በሚስቱ መካከል ብቻ ነው። ሰይጣን ሰዎች ይህንን ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲጥሱ ይገፋፋቸዋል።

በዚህ ምክንያት ነው ፍቺ፣ እንደገና መጋባት፣ የተመሳሳይ ጾታ መብት፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ዓለምን እያጥለቀለቁ ያሉት።

ይህን ሐጥያት የሚሰሩ ሁሉ ራሳቸውን የታላቁ መከራ ማገዶ እያደረጉ ናቸው፤ ነገር ግን ወደ ታላቁ መከራ እየሄዱ መሆናቸውን እንኳ አያውቁም።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።

 

ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እንደ ንጽሕት ድንግል መሆን አለባት ብሎ ጽፏል።

እባቡ ከሔዋን ጋር ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ሔዋን ድንግልናዋን አስወስዳለች።

እባቡ ሔዋንን አታለላት ወይም ሸነገላት። ይህ ውርደት እስካሁን ድረስ ሴቶች በአንዳንድ እንስሳት ስም መጠራትን በመጥላታቸው ይንጸባረቃል፤ ለምሳሌ በብዙ ሃገሮች ሴቶች ላም ሲባሉ አይወዱም።

አዳም አልተታለለም። ስለዚህ ወንዶችን ወይፈን ብትሏቸው እንደ አድናቆት ይቀበሉታል። መርከበኞች ራሳቸውን የባሕር ውሾች ብለው ይጠራሉ።

እባቡ አዳምን አላታለለውም፤ ስለዚህ ወንዶች በሆነ እንስሳ ስም ሲጠሩ አይበሽቁም።

1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤

አዳም ሚስቱ ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ከእባቡ በመማሯ ሐጥያት መስራቷን አውቋል።

ነገር ግን በጣም ይወዳት ስለነበረ እያወቀ አብሯት ሐጥያት ሰራ፤ ይህንንም ያደረገው እግዚአብሔር የመዳን መንገድን ያዘጋጃል ብሎ በማመን ነው።

አዳም እያወቀ ሐጥያት የሰራው ከሚስቱ ላለመለየት ብሎ ነው። የወደቀው ለእርሷ ከነበረው ፍቅር የተነሳ ነው።

እስካሁን “በፍቅር ወደቀ” የሚል አገላለጽ እንጠቀማለን።

በሐጥያት ውስጥ ሆነን ኢየሱስ አየንና መጥቶ ሐጥያታችንን በመሸከም ስለ እኛ ሐጥያት ሆነ።

ኢየሱስ ከሙሽራይቱ ጋር መቆየት የሚችልበትና እርሷንም ከሐጥያት የሚያድንበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነበር። ለእኛ የነበረው ፍቅር ይህን ያህል ነው።

በኤድን ገነት ውስጥ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር ንሰሃ እንዲገቡ አላዘዛቸውም፤ ምክንያቱም ሔዋን የሰራችው ሐጥያት ሊሻር የሚችል አልነበረም።

እግዚአብሔር ልጁ የሚወለድበት ድንግል ማሕፀን ፈልጓል። ሔዋን ደግሞ ከእባቡ ጋር ከተገናኘች በኋላ ድንግል አልነበረችም፤ እግዚአብሔርም ይህን ሐጥያት ሊሰርዝላት አልቻለም።

ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር የማርያምን እምነት እስኪያገኝ ድረስ 4,000 ዓመታት ጠብቋል።

 

 

የእባቡ ዘር የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እስፐርም ነው

 

 

ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

 

 

የእባቡ ዘር የወንድ የዘር ፍሬ ነው። ቅርጹ እንደ እባብ ይመስላል።

ከዚያ ወዲህ ሰው ሁሉ በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ተወለደ። ስለዚህ ሐጥያተኞች ሆነን ነው የተወለድነው። ብቸኛው ያለ ሐጥያት የተወለደው ሰው በድንግልና የተወለደው ኢየሱስ ነው።

57-0915 ዕብራውያን ምዕራፍ ሰባት - 1

እግዚአብሔር ሴቲቱን ከአዳም ጎን ወስዶ ሰራት። ትክክል አይደል? ከዚያም ሴቲቱ ደግሞ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ወለደች።

62-0211 አንድነት

በፍጹም የዛፍ ፍሬ አልነበረም! ራቁቷን መሆንዋን እንዴት አወቀች? የተወለድነው በዚህ መንገድ ነው። ሴቲቱ የሰራችው ሐጥያት ወሲባዊ ግንኙነት ነው።

63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት

ሕጉ ዘመድ የሆነ የሚቤዥ ሰው ነው የሚፈልገው፤ ነገር ግን በምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ ከወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ ነው።

አሁን የገባችሁ ይመስለኛል። ይህ ነው ሐጥያት የተጀመረበት መንገድ። ስለዚህ አሁን ያለበት ሁኔታ ይታያችኋል?

የእባቡ ዘር የመጣው በዚህ መንገድ ነው። ገባችሁ?

በወሲብ ምክንያት ከመጣው ሞት ለመዳን የምንችለው ያለ ወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ የሚቤዠን የስጋ ዘመድ ስናገኝ ነው።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤

“ስትወልጂ ጭንቅሽን አበዛለሁ”? ይህ እንግዳ አነጋገር ነው። ብዙ ተባዙ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቷት ነበር።

እርሷ ግን ልክ ባልሆነ መንገድ አደረገችው።

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አንድ ጊዜ ብቻ ነበር መፀነስ ያለባት። በዚህም ፅንስ የሚወለደው ልጅ አድጎ ሰዎችን ሁሉ ከምድር አፈር በቃሉ ኃይል ይፈጥር ነበር።

አሁን ግን ከእባቡ ፀንሳ በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። እርጉዝ ነበረች።

ስለዚህ እግዚአብሔር በዚህ መንገድ መፀነሱን እንደሚያበዛባት ተናገረ። ሰዎች ሁሉ ክፉ ሰዎችም መልካም ሰዎችም በዚህ መንገድ ነው የተወለዱት።

ነገር ግን በወሲባዊ ግንኙነት መውለድ ስሕተት መሆኑን እንድታውቅ ስትወልድ ሁልጊዜ በሕመም ትወልዳለች።

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።

አንድ ፅንስ ብቻ ፀንሳ መንታ ልጆችን እንደወለደች ይመስላል።

ነገር ግን የኤድን ገነት ውስጥ ሆና የፀነሰችው ፅንስስ?

ሔዋን የቃየንን አመጣጥ ለመሸፋፈን ብላ ከእግዚአብሔር አገኘሁት አለች። ያም እውነት ነው። ሕይወት ሁሉ ምንጩ ከእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን ቃየንን ለምን ከአዳም ወልድኩ አላለችም?

ምክንያቱም አዳም ለመጀመሪያው ልጇ፣ ለመጀመሪያው ፅንሷ አባት ስላልነበረ ነው።

ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።

ምግብ ስትበሉ ወደ ሆዳችሁ ይገባል። ወሲብ እርግዝናን ያስከትላል፤ እርግዝናም ሆድን ያሳብጣል። ስለዚህ መብላት የወሲባዊ ግንኙነት ተምሳሌት ነው።

ቃየን የሰው እና የእባብ ዘር ክልስ ሆኖ የተወለደ ግዙፍ ፍጡጥ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።

መጽሐፈ ዜና ውስጥ ቃየን የአዳም የበኩር ልጅ ተብሎ አልተመዘገበም።

ቃየን የመጀመሪያው ሐሰተኛ እና ነፍሰ ገዳይ ነበረ። እነዚህ ሁለት ባሕርያት የሰይጣን መገለጫዎች ናቸው፤ ሰይጣንም ከሰው በታች ከእንስሳት በላይ በነበረው እባብ ውስጥ ሲገባ እነዚህን ሁለት ባህርያት ይዞ ነው የገባው።

ዮሐንስ 8፡44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

 

 

እምብርታችን በሰውነታችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው

 

 

የእውቀት ዛፍ የሰዎችን በወሲባዊ ግንኙነት መወለድ የሚያመለክት ተምሳሌት ነው ብለው መደምደም እንችላለን።

ይህም እውነት በአንድ ቀን ውስጥ እንድንሞት ያስፈርድብናል።

ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን እንደ አንድ ሺ ዓመት ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

ማቱሳላ 969 ዓመታት ኖረ። ከሴት የተወለደ አንድም ሰው ለ1000 ዓመታት አልኖረም።

እምብርታችን ከእናታችን ጋር ያገናኘን የነበረው እትብት ሲቆረጥ የቀረ ጠባሳ ነው። እናታችንን ደግሞ ከእናቷ ጋር ያገናኛታል። ይህም ከእናት ወደ እናት እያለፈ የሕያዋን ሁሉ እናት ከሆነችው ከሔዋን ጋር ያገናኘናል። በእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ሰዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ተወልደዋል።

አዳም የሕያዋን ሁሉ አባት አልተባለም።

ዘፍጥረት 3፡20 አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።

ምንም ያህል ጠቢባን ብንሆን እምብርታችን እንድንሞት የተፈረደብን ሰዎች መሆናችንን የሚመሰክር ጠባሳ ነው።

እምብርት የሚያመለክተን ነገር አንድ ሕጻን ልጅ ሲወለድ በውስጡ ዘላለማዊ ሕይወት እንደሌለው ነው።

ባለ እምብርቱ ብርቱካን በውስጡ ዘር የሌለው መሆኑን የሚያመለክት “እምብርት” አለው።

 

 

ሰውነታችን ላይ የእምብርት ጠባሳ ይዘን እንደመወለዳችን መጠን የሞት ፍርድ ተሸክመን ነው የተወለድነው።

ከዚያ መቃብራችን ደግሞ ምድር ላይ ጠባሳ ያሳርፍባታል።

ፍጥረታዊ ሕይወታችን ጠባሳ አለበት።

ጌታ በሚመጣ ጊዜ የከበረ አካል እንለብስ ዘንድ ዳግመኛ መወለድ ያስፈልገናል።

በዚያ በከበረ አካል ላይ እምብርት አይኖርም፤ በውስጡም ደም አይኖርም።

የሙሽራይቱ አካላት በአዲሱ አካላቸው ውስጥ ሆነው በሺ ዓመት መንግስት ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሳሉ።

ለምን 1,000 ዓመት?

እግዚአብሔር በምድር ላይ ሕይወትን ለመፍጠር 6 ቀናት ወይም 6,000 ዓመታት ተጠቅሟል።

7ኛው ቀን የእግዚአብሔር ልጅ (አዳም) እና ሙሽራይቱ በምድር ላይ ለ1,000 ዓመታት እየኖሩ የሚነግሱበት ዘመን ነበር።

ከዚያም ክርስቶስ ይወለድና ያድግ ነበር።

እርሱም ቅዱሳንን ሁሉ በቃሉ ኃይል ከምድር አፈር ይፈጥራቸው ነበር።

ነገር ግን በዚያ 7ኛ ቀን ወይም 1,000 ዓመታት ውስጥ ሰይጣን መጥቶ ይህንን እቅድ አበላሸ።

 

 

ሰይጣን ምድርን ለ6 ቀናት ወይም ለ6,000 ዓመታት ገዝቷል፤ የኤድን ገነትን የመሰለችዋን ውብ ምድር አበላሽቷታል።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ እና ሙሽራይቱ (እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን) የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነውን ፖፕ በአርማጌዶን ጦርነት ለመምታትና የሰይጣንን የ6,000 ዓመታት መንግስት አፍርሰው አዲሱን የ1,000 ዓመት መንግስት ለመመስረት አብረው ይመጣሉ።

ሙሽራይቱ እና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በአዲሱ አካላቸው ለ1,000 ዓመታት ከኖሩ በኋላ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ሐጥያት ምክንያት ካመጣባቸው እርግማን ነጻ መውጣታቸውን ይገነዘባሉ።

በመጀመሪያው አንድ ሺ ዓመት ውስጥ መኖር ከቻላችሁ ከዚያ ለዘላለም መኖር ትችላላችሁ ማለት ነው።

ብቸኛው ተስፋችን በድንግልና የተወለደ አዳኝ ነው።

ከመጀመሪያው ሐጥያት እርግማን ነጻ የሆነ ብቸኛ ሰው ኢየሱስ ነው።

በዚህም ምክንያት ኢየሱስ የሕይወት ዛፍ ነው።

በእርሱ ከስጋ ሳይሆን ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለን።

እርሱም ፈጽሞ የማይሞት አዲስ ስጋዊ አካል ይሰጠናል።

ይህ የማይታመም፣ የማይቆስል፣ እንዲሁም ፈጽሞ የማይሞት ዘላለማዊ አካል ሽልማታችን ዘውዳችን ሆኖ ይሰጠናል።

56-0304 መንገድ መጥረግ

የዚህ ዓለም ኑሮ ሲሰለቻችሁና ምርር ሲላችሁ፤ እንዲሁም በፊታችሁ ከቀረበው ምግብ ወይም ከሚስታችሁና ከልጆቻችሁ በላይ የበለጠ የጌታን መገለጥ ስትወዱና ስትናፍቁ የዚያን ጊዜ ለእናንተ ተዘጋጅቶ የሚጠብቃችሁ አክሊል አለ፤ ይህንንም የወርቅ አክሊል አምጥተው ራሳችሁ ላይ ይጭኑላችኋል፤ አካላችሁም ሕመም የሌለበት አካል ይሆናል … በእግዚአብሔር ክብር የተሞላ ዘውድ ይጫንላችኋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና አለመጥፋት ውስጥ ዘውድ ትጭናላችሁ

የተዘጋጀላችሁ፤ ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር በዚያ ቀን ሊሰጣችሁ ያሰበው ይህ ነው። ያንን ቀን ለማየት ነው የምንናፍቀው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የምናመልጥበት መንገድ አዘጋጅቶልናል።

ሮሜ 8፡22 ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።

23 እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።

ሁለቱ የዓለም ጦርነቶችና ኮሮና ቫይረስ የምጥ ጣሮች ናቸው፤ ይህም ምጥ ምድር ኢየሱስ የሚነግስበትን የ1,000 ዓመቱን የከበረ መንግስት ለመውለድ የምታምጠው ምጥ ነው።

አርማጌዶን የመጨረሻው አስጨናቂ ምጥ ነው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23