ስለ 7ቱ ነጎድጓዶች የሚታወቀው ምንድነው? ብዙም አይደለም



ሰዎች ስላልተጻፈ ነገር እንዴት ብዙ ሊያውቁ ይችላሉ?

First published on the 12th of February 2022 — Last updated on the 12th of February 2022

 

ነጎድጓዶቹ ሲናገሩ ዮሐንስ የሰማው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም

 

መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ቃል እንጀምር።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

 

ስለዚህ እነዚህ ነጎድጓዶች የተናገሩት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገር አይደለም፤ ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ነገር ሁሉ ጋር መስማማት አለባቸው፤ ከ31,100 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ ጋር መስማማት አለባቸው።

የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሊቃረኑ አይችሉም።

እውነተኛው መጽሐፍ ቅዱስ በ1769 የተዘጋጀው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ራዕይ 5፡1 በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።

ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሲጠና ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይጠቀሳል ብሎ ማንም አይጠብቅም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት አሉ፤ ደግሞም ያልተጻፉ ነገር ግነ ከእኛ የተሰወሩ ሚስጥራትም አሉ። እነዚህ በመጽሐፉ በስተጀርባ የተጻፉ ተብለው ነው የተገለጹት። ከአገላለጹም እንደምንረዳው በጀርባ በኩል በመጽሐፉ ሽፋን ላይ እንደተጻፉ ይመስላል። በሌላ አነጋገር በመጽሐፉ ሽፋኖች መካከል ባሉት ገጾች ውስጥ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ አልተጻፉም ማለት ነው።

በጀርባ በኩል ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን በሙሉ አንብባችሁ ከተረዳችሁ በኋላ ነው እነዚህን ሚስጥራት ልትደርሱባቸው የምትችሉት ማለት ነው።

ስለዚህ መጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት መረዳት አለባችሁ፤ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ያልተጻፉትንና የተሰወሩትን ሚስጥራት መረዳት የምትችሉት። ከዚህም የተነሳ የተጻፈውን ቃል ተግተን ማጥናት እና ያልተገለጠውን ለመረዳት በጉጉት መጠባበቅ አለብን።

የተጻፉት ሚስጥራት ራዕይ ምዕረፍ 6 በተጠቀሱት በሰባቱ ማሕተሞች ታትመው ተዘግተዋል።

ያልተጻፉት ሚስጥራት ሁለተኛ ዙር “በሰባት ማሕተሞች” ታትመው ተሰውረዋል፤ ይህም ራዕይ ምዕራፍ 10፡3-4 ተጠቅሷል፤ ዮሐንስ ግን እነዚህን ሚስጥራት ሊጽፍ አልተፈቀደለትም። እነዚህ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ያሉ ያልተጻፉ ሰባት ማሕተሞች ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸው።

ያልተጻፉ ሚስጥራት ምንድናቸው?

ማቴዎስ 24፡36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም

 

ስዚህ የኢየሱስን መምጫ አውቃለሁ ብላችሁ ብታስቡ ተሳስታችኋል።

ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው

 

አሁንም ማንም አያውቅም። አዲሱን ስም የምታውቁ ከሆነ ተሳስታችኋል።

ኢየሱስ የሚመጣበት ጊዜ እና አዲሱ ስሙ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም፤ ስለዚህ እነዚህን ሚስጥራት ከተጻፉት ገጾች ውስጥ መፈለግ ከንቱ ድካም ነው። እነዚህን ሚስጥራት አናውቃቸውም። ሲገለጡ ብቻ እነርሱ መሆናቸውን ልናውቅ እንችላለን እንጂ።

ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።

 

ዝምታ ብቻ። የፈለጋችሁትን ያህል ብትመረምሩ ከዝምታ ውጭ ምንም አታገኙም። ዝምታን መተርጎም አይቻልም። ይህም ያልተጻፈ ሚስጥር ነው።

ስለዚህ ሰባቱ ያልተጻፉ ሚስጥራት በሰባቱ ባልተጻፉት ነጎድጓዶች ታሽገዋል።

ዘዳግም 29፡29 ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።

 

እግዚአብሔር የተጻፉትን ቃሎች ሚስጥር ለነብያቱ ይገልጥላቸዋል።

ሚስጥር የሆኑት ነገሮች ያልተጻፉት የእግዚአብሔር ሚስጥራት ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች እግዚአብሔርን ብቻ የሚመለከቱ ናቸው።

ለምሳሌ፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዛት የሚታወቀው የእግዚአብሔር ስም ያህዌ ነው። በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ሰው ሆነና ኢየሱስ የሚለውን አዲስ ስም ተቀበለ።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ የኢየሱስ ስም አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ የተባለው አዲስ ስም ከተገለጠ በኋላ ያህዌ የሚለው ስም ሁለተኛ አልተጠቀሰም።

የእግዚአብሔርን ስም በትክክል ስንጽፈው YHWH ነው። ይህ ስም እንዴት እንደሚነበብ ማንም አያውቅም። ስለዚህ ማንም ይህ ስም እንዴት እንደሚነበብ ስለማያውቅ ማንም ሊጠቀመው አይችልም።

በ1500ዎቹ ዓመታት እንግሊዞች “J” ፊደልን ፈጠሩ እርሱም “ይ” ተብሎ የሚነበበውን “Y”ን ተካ።

ስለዚህ ሊነበብ የማይችለው YHWH እንደገና ሊነበብ የማይችል JHVH ሆነ።

የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች YHWHን (ወይም JHVH) LORD ብለው ተረጎሙ።

ከዚያ በኋላ ሰዎች በራሳቸው JHVH የሚባሉት ፊደሎች ላይ አናባቢዎችን ጨመሩና Jehovah ማለትም ይሖዋ የሚል ስም ፈጠሩ (ይህ ሰው ሰራሽ ስም ነው)።

እግዚአብሔር አዲስ ስም ማለትም የኢየሱስን ሰብዓዊ ስም በተቀበለ ጊዜ ይህንን አዲስ ስም ለማርያም እና ለዮሴፍ የገለጠላቸው ሰው ወይም ነብይ አለመሆኑን ልብ በሉ።

የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ማለትም የተወለደበት ጊዜ ለማርያም እና ለዮሴፍ በሰው አማካኝነት አይደለም የተገለጠላቸው።

አዲሱንም ስም ያወጀው ገብርኤል የተባለ የሰማይ መልአክ ነው።

ነብዩ ኢሳያስ ድንግል መሲሁን እንደምትጸንስ ገለጠ። ነገር ግን ቁልፍ የሆኑ ዝርዝሮች ማለትም መች እንደሚጸነስ እና ሰብዓዊ ስሙ ማን እንደሚሆን በሰውም ሆነ በነብይ አልገለጠም።

ዊልያም ብራንሐም ከተናገራቸው ንግግሮች የተወሰኑ ጥቅሶችን እንመልከት፡-

መጽሐፉ ተጽፏል ነገር ግን አስተውሉ፤ በሰባት ማሕተሞች ታትሞ ተዘግቷል። ሰባቱ ማሕተሞችም (ራዕይ 10) በምድር ላይ ሰባተኛው መልአክ የመጨረሻ ድምጹን (ራዕይ 10፡7) እስኪያሰማ ድረስ አይፈቱም፤ አያችሁ? “የመጨረሻው መልአክ ድምጹን በሚያሰማበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይጠናቀቃል።” ያም አሁን እኛ የምንኖርበት ዘመን ነው።

በሎዶቅያ ዘመን እየኖርን እንዳለን ሁላችንም እናውቃለን። ከአሁኑ ዘመን ሌላ የሎዶቅያ ዘመን ሊኖር አይችልም። ይህ ዘመን ብቻ ነው። ስለዚህ በሎዶቅያ ዘመን ውስጥ እየኖርን ነን። ያ መጽሐፍ የታሸገባቸው እነዚህ ሰባት ማሕተሞችም ለሰዎች ሁሉ ሚስጥር ናቸው፤ በዚያ ቀን ግን ይገለጣሉ። ጌታ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው። ሚስጥሩ በሚገለጥበት ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ውጭ አይሆንም ምክንያቱም ከቃሉ ላይ መቀነስም ሆነ በቃሉ ላይ መጨመር አይቻልም። ሁልጊዜ ከቃሉ ውስጥ ብቻ ነው። የሚመጣው መገለጥ ግን እውነትን ለማሳየትና ከጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉ ጋር የሚገጥም የሚስማማ መሆኑን ለማሳየት ነው። እግዚአብሔርም ያ መገለጥ እውነት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣል።

“መነጠቅ” ዲሴምበር 4 ቀን 1965

 

ማሕተሞቹ የታተሙት በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ይመስለኝ ነበር፤ ስለዚህ መጽሐፉ ያልተጻፈበት ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን አንድ በግልጽ የምናውቀው ነገር እንደዚያ ሊያደርግ አለመቻሉን ነው። የሆነ መጽሐፉ ውስጥ የተጻፈ ነገር አይደለም … መጽሐፉ ውስጥ የተሰወረ ነገር ነው እንጂ።

“መንፈሳዊ ምግብ በጊዜው” ጁላይ 18 ቀን 1965

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ በሌለበት የሰው ምናብ በራሱ አስቦ የማያመጣው ጉድ የለም። የሰው አእምሮ ዓይንን የሚጋርዱ አመለካከቶችና ማለቂያ የሌላቸው ፍልስፍናዎች የሚወጡበት ጥልቅ ጉድጓድ ነው። ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር በማገናኘት ፈንታ የሰዎችን ትርጓሜና ጥቅስ ተሸክመን እንቀራለን።

ራዕይ 9፡1 አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

 

አዲስ ፖፕ ሲመረጥ ለሕዝቡ የሚደረገው ምልክት ነጭ ጭስ ነው። ነገር ግን ጭስ መልካም ተምሳሌት አይደለም። የሰው ልብ በጨለማ የተሞላ ነው።

ምንም ፖፕ ካልተመረጠ ደግሞ የሚሰጡት ምልክት ጥቁር ጭስ ነው።

 

ስለ ነጎድጓዶቹ የሚሰጡ ትምሕርቶችና ትርጓሜዎች ሁሉ መሰረታቸው ነጎድጓዶቹ ቃላቸውን አሰምተዋል በሚለው ሃሳብ ላይ ነው።

 

“ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል” የሚለው ንግግር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አይደለም

 

ወንድም ብራንሐም አንድም ጊዜ ነጎድጓዶቹ ቃላቸውን አሰምተዋል ብሎ አያውቅም።

ስለዚህ የነጎድጓዶቹ ትምሕርቶች ሁሉ የተመሰረቱት በዚህ በሌለ ጥቅስ ላይ ነው።

የዝግመተ ለውጥ ወይም ኤቮልዩሽን ንድፈ ሃሳብም የተመሰረተው በሌለ ማስረጃ ላይ ነው።

ሳይንሳዊው ቢግ ባንግ የተባለው ቲዎሪ የተመሰረተው በሌለ ዳርክ ማተር እና እና በሌለ ዳርክ ኤነርጂ ላይ ነው።

የሰው ጥበብ ሁልጊዜ ሰዎች በተንኮል እንዳላወቁ በሚያልፉት ወይም በሚሰውሩት የሆነ የጎደለ ነገር ላይ ነው መሰረቱ።

ስለዚህ የነጎድጓድ አስተምሕሮዎች በዋነኝነት የሰው አመለካከቶች ትርጓሜዎች ናቸው፤ ምክንያቱም ሁላቸውም ወንድም ብራንሐም ያላለውን ብሏል የሚሉ ናቸው።

ኢየሱስ ከመወለዱ በፊትም እንኳ ሐሰተኛ ክርስቶሶች ነበሩ። አያችሁ? እኔ ክርስቶስ ነኝ የሚሉ ሰዎች በፊትም ነበሩ። ይህም ሰይጣን በትንቢት የተነገረው ቃል ከመፈጸሙ በፊት የሚያምኑ ሰዎችን አእምሮ ግራ ለማጋባት የሚሰራው ተንኮል ነው። በቃ ይህ ብቻ ነው። ገማልያል በዘመኑ ለነበሩ አይሁዶች ይህንኑ አይደል የነገራቸው? እንዲህ አለ፡- “ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፡- እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነስቶ ነበርና፤ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ”።

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን ብንከተል ያንን ነገር በተመለከተ የተሳሳቱ አመለካከቶች ይሰራጫሉ።

ይህም አመለካከታችሁን ወይም አቋማችሁን ለመፈተን ነው፡ ምርጫችሁ በሰው ብልሃት የተፈጠሩ ትርጓሜዎች ናቸው ወይም የእግዚአብሔር ቃል?

ነገር ግን እነዚያ ነገሮች ሁሉ ሊመጣ ላለው ለእውነተኛ ነገር መንገድ ጠራጊዎች መሆናቸውንና እውነተኛውም ሲመጣ ሰዎች እንደሚደነግጡ ታውቃላችሁ

“ሁለተኛው ማሕተም” ማርች 19 ቀን 1963

 

አሁን ግን እርሱ ከመምጣቱ በፊት ጥቂት ግራ መጋባት ይፈጠራል፤ ምክንያቱም ሰይጣን እውነተኛውን ነገር ለማደናቀፍ የተቻለውን ሁሉ አስመሳይ ነገር በብዛት ያሰማራል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትናም፣ ዛሬም እስከ ለዘላለም ያው ነው” ጁላይ 4 ቀን 1963

ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ሐሰተኛ መሲሆች እስራኤል ውስጥ ነበሩ።

ስለዚህ የነጎድጓዶች ድምጽ ከመምጣቱ በፊት “የነጎድጓዶች ትርጓሜ” ቀድሞ ይመጣል።

ሉቃስ 18፡8 … ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

 

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ላይ የመሰረቱ ብዙ ሰዎችን አያገኝም።

ዛሬ ሰዎች ወንድም ብራንሐም ያስተማራቸውን ትምሕርት አያምኑም ወይም ከእርሱ ንግግሮች ውስጥ የፈለጉትን ጥቅስ መርጠው ይወስዱና እንደ ፍላጎታቸው ይተረጉማሉ። የምንድነው በሰዎች ብልሃት አይደለም።

እስቲ ለጥቂት መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ እንስጥ፡-

የሰዎችን ግምታዊ መልሶች ሁሉ ላለመስማት ከወሰንን ስለ ነጎድጓዶቹ ምንድነው ልናውቅ የምንችለው?

ከስሕተት ልንድን የምንችለው በአንድ ርዕስ ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ጥቅሶችን ሁሉ በማገናኘት ነው።

ኢሳይያስ 28፡13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።

ሐሰተኛ ትምሕርትን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምራችሁ እውነተኛነቱን ልታሳዩ አትችሉም። ስታጠኑ በስተመጨረሻ ትምሕርቱን የሚቃረን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ታገኛላችሁ።

ኢሳይያስ 8፡20 ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም።

 

የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ብትቃወሙ መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ትወድቃላችሁ። ሲጨለም ሰዎች ያንቀላፋሉ።

ለዚህ ነው ኢየሱስ በሰጠው ምሳሌ ውስጥ ልባሞቹ ቆነጃጅት እንኳ ሳይቀሩ እንቅልፍ የተኙት።

 

ጥያቄ 1 - የነጎድጓድ አስተምሕሮዋችሁን በተመለከተ ዳንኤል ያየውን ራዕይ ልታሳዩን ትችላላችሁ?

 

መጽሐፉ በሰባት ማሕተሞች ታትሞ አየው። ከዚያም በኋላ … ዳንኤልም ያየው ተመሳሳይ ነገር ነው፤ ከዚያ ነጎድጓዶቹ በተናገሩ ጊዜ ሊጽፍ ሲያስብ፡- “አትጻፍ” አለው። ይህ ግልጽ ባይሆንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው የሚገኘው፤ ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ቀናት ይገለጣል። እኛ በመጨረሻው ጊዜ ነውአሁን ወደ ቃዴስ ደርሰናል።

“እምነት” ዲሴምበር 13 ቀን 1953

 

ዳንኤል የሰባቱን ነጎድጓዶች እንደሰማና እንደተከለከለ ዮሐንስ ደግሞ ድምጾችን ሰማና ይህ መጽሐፍ ተዘጋ፤ የመጽሐፉም ጀርባ በሰባት ማሕተሞች ተዘጋ፤ ነገር ግን እነዚህ ማሕተሞች በሚፈቱበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል። በሌላ አነጋገር እግዚአብሔር ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ይገለጣል፤ የሚገለጠውም ሶስት አካላት ሆኖ ሳይሆን አንድ አካል ሆኖ ነው። የእግዚአብሔር ሚስጥር ይገለጣል፤ ከዚያም ይህ ሚስጥር ሙሉ በሙሉ ሲገለጥ ሰባቱ ሚስጥራት ለቤተክርስቲያን ግልጥ ሆነው ይፈታሉ፤ ምክንያቱም በዚያ ጊዜ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ትመላለሳለች እርሱም በመካከላችን ሕያው ሆኖ መገኘቱን በምልክቶች ያሳያል። እኛም በዚያ ጊዜ በመካከላችን ሕያው የሆነውን ክርስቶስን እናመልከዋለን።

“የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን” ዲሴምበር 5 ቀን 1960

ያልተጻፉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ከማሰማታቸው በፊት የተጻፉት ሚስጥራት ሙሉ በሙሉ መገለጥ አለባቸው።

የመጽሐፉ ጀርባ (ያልተጻፉት ሚስጥራት) በሰባት (ባልተጻፉ) ማሕተሞች ታትሞ ተዘግቷል፤ እነዚህም ሰባቱ ያልተጻፉ ነጎድጓዶች ናቸው።

ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል ሰምቷል ነገር ግን አልጻፈም።

ቀጥሎ ደግሞ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሱ ሰባት ያልተጻፉ ማሕተሞች አሉ። እነዚህም በሰባተኛው መልእክተኛ ወይም በሰባተኛው መልአክ አማካኝነት ነው የሚገለጡት።

ስለዚህ ሰባት ማሕተሞች ሁለት ጊዜ ይገኛሉ። የመጀመሪያዎቹ የሚገለጡት የተጻፉ ማሕተሞች ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ ያልተጻፉት ማሕተሞች (ነጎድጓዶቹ) ናቸው፤ ነጎድጓዶቹም ሙታን በትንሳኤ እስከሚነሱ ድረስ ሚስጥር ሆነው ይቆያሉ።

የዚያን ጊዜ የመጀመሪያው ዘመን ቅዱሳን እና እኛ በአንድነት አብረን እንሰማቸዋለን።

ሁልጊዜ ከመጀመሪያው ዘመን ቅዱሳን ጋር በእምነታችን መስማማት አለብን።

ዳንኤል ነጎድጓዶቹን አይቷል፤ ሰምቷልም። ስለ ነጎድጓዶቹ ምን ብሎ ገለጸ? ዳንኤል ነጎድጓዶቹን አልገለጸም።

ምን ብለው ተናገሩ አለ? ዳንኤል ምንም አላለም።

የነጎድጓዱ ቲዎሪያችሁ ዳንኤል ስለ ነጎድጓዶቹ ከተናገረው ጋር መስማማት አለበት።

“የመጽሐፉ ጀርባ” ማለት መጽሐፉ ውስጥ በቀጥታ አልተጻፈም ግን መጽሐፉ ውስጥ በሆነ መንገድ ተሰውሯል ማለት ነው።

ነገር ግን ስለ “መጽሐፉ ጀርባ” ሁለተኛ ተጨማሪ መረዳትም አግኝተናል።

“የመጽሐፉ ጀርባ” ማለት የሚፈጸመው መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉት ዋና ዋና ክስተቶች ሁሉ ከተፈጸሙ በኋላ ነው ማለት ነው።

ሰባቱን ነጎድጓዶች የዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ፈልጋችሁ ለማግኘት ሞክሩ።

ዳንኤል ነጎድጓዶቹ ምን እንደሆኑ ወይም ምን ብለው እንደተናገሩ አልነገረንም።

ስለዚህ እኛም ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ ወይም ምን ስለመሆናቸው መናገር አንችልም።

የ7ቱን ነጎድጓዶች ዓላማ ፤ ምን ሊያከናውኑ እንደሚመጡ ማወቅ ትችላላችሁ። የሚሰሩት ምን እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

ነገር ግን ሙታን በትንሳኤ እስከሚነሱ ድረስ ነጎድጓዶቹ ምን እንደሆኑ ወይም ምን ብለው እንደተናገሩ ማወቅ አትችሉም።

ንግግራቸው ምን እንደሆነ ማወቅ አትችሉም።

 

 

ጥያቄ 2 - የነጎድጓድ አስተምሕሮዋችሁን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ታምንበት ነበር?

 

እናንተ ስለ ነጎድጓዶቹ የሰጣችሁትን ትርጓሜ ጳውሎስ እና የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰብከዋልን?

ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ልናገኝ የምንችለው ዮሐንስ በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የጻፈውን ብቻ ነው።

የጥንቷ ቤተክርስቲያንም ስለ ነጎድጓዶቹ ያወቀችው ይህንን ብቻ ነው።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

 

ራዕይ 10፡7 እርሱም የእግዚአብሔር ነብይ ይሆናል፤ ሚልክያስ 4፡6 ውስጥ እንደተጻፈው የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል። የመጨረሻውን ዘመን ምርጦች መልሶ ያመጣቸውና እነርሱም እውነተኛ መሆኑ ልክ እንደ ጳውሎስ የተመሰከረለትን ነብይ ይሰሙታል። እውነትን በጳውሎስ ዘመን እንደነበረች አስተካክሎ ያስተምራል። በዚያም ቀን ከእርሱ ጋር የሚሆኑት የተመረጡ ሰዎች እነርሱ ናቸው ጌታን የሚገልጡት፣ አካሉ የሚሆኑት፣ ድምጹ የሚሆኑትና የእርሱን ሥራ የሚሰሩት። ሃሌሉያ! አያችሁ?

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9

እኛም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ወዳመነችበት እውነት መመለስ አለብን።

እነርሱ የሰባት ነጎድጓዶች አስተምሕሮ አልነበራቸውም። እነርሱ የሚያውቁት ነገር ቢኖር ነጎድጓዶቹ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆናቸውን ነው። ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ አልጻፈም።

እኛም ልክ እንደዚሁ ዓይነት እምነት ሊኖረን ይገባል።

እንግዲህ ልብ በሉ። አሁን ወደ ዘመን መጨረሻ ደርሰናል። ለክ ለዕመጀመሪያዋ ሔዋን ተስፋ እንደተሰጠ ሁሉ አሁን ለመንፈሳዊቷ ሔዋን ተስፋ ተሰጥቷታል… የመጀመሪያይቱ ሔዋን ቃሉ እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷት ነበር፤ ከበዓለ ሃምሳ ለሆነችዋ መንፈሳዊቷ ሔዋንም በኒቅያ ጉባኤ ከወደቀች በኋላ በመጨረሻው ዘመን ቃሉ እንደገና ተመልሶ እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷታል። ከዚያም … ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከፈለጋችሁ ራዕይ ምዕራፍ 10ን አንብቡ። እርሱም እንዲህ አለ፡- “የመጨረሻው መልአክ በሚገለጥበት ጊዜ ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ሲያሰማ የእግዚአብሔር ሚስጥር በሙሉ ይፈጸማል (አያችሁ?) ይህም ወደ ቃሉ የመመለስ ጊዜ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የመጨረሻው ዘመን መልእክተኛ አማኞችን ወደ መጀመሪያይቱ እምነት ወደ አባቶች እምነት ይመልሳቸዋል ይላል። ግን የሚቀበሉ ይመስላችኋል? አይቀበሉም። በመጨሻዎቹ ቀናት በሚልክያስ 4 ውስጥ እንደተናገረው ጌታ የመጀመሪያውን ቃል መልሶ ያመጣዋል፤ እርሷ ግን አልተቀበለችውም።

“ሶስተኛው ማሕተም” ማርች 20 1963

አዲስ የነጎድጓዶች አስተምሕሮ እየፈጠርን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ልንመለስ አንችልም።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን ወዳመነችው እምነት መመለስ አለብን።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የነበራትን ያንኑ የተጻፈ እውነት እንቀበላለንን?

የሜሴጅ ተከታዮች የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበረውን መሰረታዊ እውነት ይዘው መጽናት አይፈልጉም። ያልተጻፉት ነጎድጓዶች፣ ሰባት ማሕተሞች፣ የእግዚአብሔር አዲሱ ስም እና ጌታ መች ተመልሶ እንደሚመጣ በመሳሰሉ ሚስጥራት ላይ መፈላሰፍ ይመርጣሉ።

ከዚህም የተነሳ በተጻፈው እውነት ላይ የነበረን ትኩረት እየቀነሰ ነው።

የዚህ ዘመን ትክክለኛው መልእከት ቃሉ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት መግለጥ ነው።

ይህ ጥያቄ ነው። አሁን ላሳያችሁ የምፈልገው ራዕይ ምዕራፍ 10 ነው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እናየዋለን፤ ቀጥሎ ሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንመለከታለን። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል።” የምንጠይቀው ጥያቄ ይህ ነው፡- በዚህ ተከትለን ብንሄድ አሁን ይፈጸማልን? “እምነት አገኛለሁን?” ሚልክያስ 4 በዚህ ጊዜ ይፈጸማልን? “የልጆችን እምነት ወደ አባቶች እምነት፣ ወደ መጀመሪያው፣ ወደ ቃሉ ይመልሳልን”? አያችሁ?

“በዘመን መጨረሻ ላይ የተቀቡት” ጁላይ 25 ቀን 1965

እግዚአብሔር በብልሃት የተሞሉ አዳዲስ ቲዎሪዎቻችንን አይፈልጋቸውም። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ያመነችውን እንድናምን ነው የሚፈልገው።

እኔም በዚያ ተቀምጬ ሳለ አንድ ድምጽ እንዲህ አለኝ፡- “ያዕቆብ ወደ ሕዝቡ እንደተሰበሰበ ሁሉ አንተም ወደ ራስህ ሕዝብ ተሰብስበሃል።”

እኔም እንዲህ አልኩ፡- “እያንዳንዱ መሪ በዚህ መልኩ ሊፈረድበት ይገባል?”

ድምጹ፡- “አዎ።”

እኔም እንዲህ አልኩ፡- “ጳውሎስስ?”

እርሱም እንዲህ አለ፡- “እርሱም ከራሱ ሕዝብ ጋር ፍርድ ይቀበላል።”

“እንግዲህ” አልኩ “የእርሱ ወገኖች የሚገቡ ከሆነ የእኔም ይገባሉ ምክንያቱም እኔ የሰበክሁት እርሱ የሰበከውን ቃል ነው።” እንዲህ አልኩ፡- “እርሱ በኢየሱስ ስም እንዳጠመቀ እኔም በኢየሱስ ስም አጥምቄያለሁ። እኔም ሰብኬያለው …”

ብዙ ሚሊዮኖች እየጮሁ በአንድ ላይ “በዚህ ቃል እናርፋለን” አሉ።

“የመጀመሪያው ማሕተም”

በፍርድ ቀን የሚፈረድብን ከጳውሎስ እና ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጋር ምን ያህል ተስማምተን እንደሆን ታይቶ ነው። የሚፈረድብን የነጎድጓድ ቲዎሪዎቻችን ምን ያህል በብልሃት የተሞሉ መሆናቸው ታይቶ አይደለም።

“እንዲሁም ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ።”

ይህ ጠንከር ያለ ንግግር ነው …

በመጀመሪያ እውነተኛውን ቃል ለሕዝቡ ያመጡት ሐዋርያት ናቸው። ያ የመጀመሪያው ቃል … የኤፌሶን ሰዎች ጳውሎስ ሲያስተምራቸው የሰሙት ቃል እውነት መሆኑን ያውቃሉ። ጳውሎስ እጁን ከጫነባቸው በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር። ሐሰተኞቹን ሐዋርያት ዓይን ዓይናቸውን እያዩ እንዲህ አሉዋቸው፡- “እናንተ የምታስተምሩን ጳውሎስ ካስተማረን ጋር አንድ አይደለም። ስለዚህ ሐሰተኞች ናችሁ።” ይህንን ስናገር ልቤ እንደ እሳት ይቃጠልብኛል። ወደ ቃሉ እንመለስ! ሐዋርያውን፣ ነብዩን፣ አስተማሪውን የምትመረምሩ እናንተ አይደላችሁም፤ የሚመረምራቸው ቃሉ ነው።

ብዙ ሳይቆይ በቅርቡ ለዚህ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን የተላከ ነብይ ይመጣል፤ እርሱም ከእግዚአብሔር የተላከ እውነተኛ ነብይ ይሁን አይሁን ታውቃላችሁ። እውነት ነው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ከሆነ ታውቃላችሁ፤ እውነተኛ ከሆነ እግዚአብሔር ለጳውሎስ የሰጠውን ቃል በትክክል ይናገራል። ለጥቂት ደቂቃ እንኳ ከቃሉ ፈቀቅ አይልም።

በዚያ በመጨረሻ ዘመን ውስጥ ብዙ ሐሰተኛ ነብያት በሚነሱ ጊዜ እነርሱ የሚናገሩትን ባታምኑ እንደምትጠፉ ደጋግመው ሲነግሩዋችሁ በጥንቃቄ ስሟቸው፤ የመጨረሻው ዘመን ነብይ ሲገለጥ ግን የእውነት ትክክለኛው ነብይ ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጮሃል፡- “ወደ ቃሉ ተመለሱ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ።” የራሱን መገለጥ ይዞ አይደለም የሚመጣው፤ የራሱን ትርጓሜ ይዞ አይመጣም፤ ቃሉን ብቻ ይዞ ይመጣል እንጂ። አሜን፤ አሜን!

የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን፣ የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 3

ከመልእከቱ ከተጠቀሱ ጥቅሶች ውስጥ ጥምቀት መደረግ ያለበት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መሆኑን ተምረናል። አሁን ግን ይህ አስተምሕሮ እውነት መሆኑን ወደ ጥቅሶች ሳንመለከት ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማረጋገጥ እንችላለን።

ጥቅሶቹን የምንጠቀምባቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ነው።

ጥቅሶቹ መጽሐፍ ቅዱስን ሊተኩ አይገባም።

የነጎድጓድ አስተምሕሮዋችሁን አንድም የሰው ንግግር ጥቅስ ሳትጠቀሙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እውነት መሆኑን ማሳየት ትችላላችሁ?

የመከሩን ጊዜ እየተጠባበቅን ነን። በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚታጨደው ፍሬ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ነው።

 

 

በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነጎድጓድ አስተምሕሮ ካልተሰበከ እኛም ስለ ነጎድጓዶች መስበክ የለብንም። እኛ ከእነርሱ ይልቅ ብልሆች ወይም የተሻልን መሆን የለብንም። እኛ ወደ እነርሱ ነው መመለስ ያለብን፤ ስለዚህ ልክ እነርሱ ያመኑትን ማመን አለብን።

ከእነርሱ የተለየን መሆን የለብንም። እኛ ተጨማሪ ዝርዝሮች ሊገለጡልን ይችላሉ፤ በመሰረታዊ እምነታችን ግን ከእነርሱ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለብን።

 

 

ጥያቄ 3 - ራዕይ 6፡1 ላይ የተናገረው ብቸኛው ነጎድጓድ ምን ነበረ?

 

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

 

ስለዚህ በሰማይ ውስጥ የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ አንድ ነጎድጓድ ነበረ።

ይህ ነጎድጓድ ምን ነበረ? መች ነው ድምጹ የሚሰማው?

በራዕይ ምዕራፍ 10 ውሰጥ ከተጠቀሱት ከ7ቱ ነጎድጓዶች ጋር የተያያዘ ነው።

ምን ይሆናል መሰላችሁ፤ ዮሐንስ የሰማቸው ነገር ግን እንዲጽፍ ያልተፈቀደለት ሰባቱ ነጎድጓዶች፤ የነዚህ ነጎድጓዶች ድምጽ በሚመጣበት ጊዜ ነው ተሰውሮ የነበረው ሚስጥር የሚገለጠው

… አሁንስ ለምን? እስቲ እናረጋግጠው። ለምን? ይህ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባት ተከታታይ ነጎድጓዶች አሉ።

እነዚህም ነጎድጓዶች ማንም የማያውቀው ሚስጥር ይዘዋል።

ሌላ ደግሞ ራዕይ 6፡1 ውስጥ በሰማይ የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ የሚገለጥ አንድ ብቸኛ ነጎጓድ አለ። ይህ ነጎድጓድ ምንድነው?

ስለዚህ ብቸኛ ነጎድጓድ ምን እናውቃለን?

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

“ሰሜቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየችህ” ኖቬምበር 27 ቀን 1965

ይህን የተናገረው ኖቬምበር 1965 ዓ.ም ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ነበር።

ድምጹ ወይም መልእክቱ የሚመጣው ገና ወደ ፊት እንደሆነ ነው የተናገረው።

ታላቁ ድምጽ ዊልያም ብራንሐም እውነትን ሲሰብክ ማለት አይደለም። ድምጹ የሙሽራይቱ አካላት እውነትን ለራሳቸው መረዳት ሲችሉና ያመኑትንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማረጋገጥ ሲችሉ ነው።

ስድስቱን ማሕተሞች ገልጧቸው ብዙ ጊዜ ካለፈ በኋላ እንኳ ገና ወደፊት ስለሚገለጥ ብቸኛ አንድ ነጎድጓድ ይናገራል። ይህም ብቸኛ ነጎድጓድ ከሙታን ትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው።

ሰባተኛው ማሕተም ጭራሽም አልተፈታም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው።

 

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።
64-0719 የመለከቶች በዓል

በሕይወቱ የመጨረሻ ወር እንኳ ከሰማይ ስለሚመጣው ታላቅ ድምጽ ወደፊት እንደሚሆን ነበር የሚናገረው።

አንድ ቀን ከሰማይ ታላቅ የመለከት ድምጽ ይመጣል፤ “በክርስቶስም ሆነው ያንቀላፉት ቀድመው ይነሳሉ።”

“ንጥቀት” ዲሴምበር 4 ቀን 1965

ልክ ከመሞቱ በፊት ወደፊት ሊመጣ ስላለው ብቸኛ ነጎድጓድ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ተናግሯል።

ታሕሳስ እርሱ የሞተበት ወር ነው። በዚህም ወር ውስጥ ወደፊት ሊመጣ ስላለው አንድ ነጎድጓድ እየተናገረ ይጠባበቅ ነበር።

እግዚአብሔር ሆይ አለማመናችንን እርዳ። ጌታ ሆይ አስወግድልን። የምንነጠቅበትን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን። ያ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ እና ቤተክርስቲያንም በምትነጠቅበት ጊዜ ልንቀበለው ዝግጁ መሆን እንፈልጋለን ጌታ ሆይ።

“ሁለተኛው ማሕተም” ማርች 19 ቀን 1963

ይህ አንድ ነጎድጓድ ወደፊት ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ በምትነጠቅበት ጊዜ ነው የሚመጣው። ይህ ነጎድጓድ ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ የተረዳነው ነገር የለም። ነገር ግን መምጣቱ የማይቀር ነገር ስለሆነ ይህንን ታላቅና ሚስጥራዊ ክስተት መጠባበቅ አለብን።

አሁንስ ግልጽ ሆነላችሁ? የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ መጽሐፉ ውስጥ የነበሩ ማሕተሞች የታወጁት ሚስጥራት የሚከተሉት ናቸው፡- ጽድቅ፣ ቅድስና፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ ፕሮቴስታንቶች፤ ከዚያም ግጭቶቻቸውና ጦርነቶቻቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብዙ ያልተቋጩ ነገሮችን ሲያመጡ ሰባተኛው መልአክ ይመጣና ሁሉን ሰብስቦ በማብራራት ይቋጫቸዋል። አያችሁ? ከዚያ መጨረሻው ይሆናል፤ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ። ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል ሊጽፍ ነበረ። ነገር ግን “አትጻፍ፤ አትመህ ዝጋ” ተባለ። የመጀሪያው ማሕተም ሲፈታ መጽፉ ውስጥ ካሉት ማሕተሞች መካከል አንዱ ነው የተፈታው፤ ሲፈታም ከነጎድጓድ ጋር ተፈታ

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

ስለዚህ ወደፊት አንድ ቀን ያልተጠበቀ ነጎድጓድ ድምጹን ያሰማል። ያልተጠበቀውን መጠባበቅ አለብን።

መች? እኛ ባልተጠባበቅነው ጊዜ።

 

 

የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ የማሕተሞቹ መፈታት አይደለም

 

ብቸኛው ነጎድጓድ ከመጀመሪያው ማሕተም መፈታት ጋር የተያያዘ ነው።

በጥንቃቄ አስቡ።

ስለ ማሕተሞቹ የሚያብራራው መጽሐፍ የፊት ሽፋኑ፡- “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ይላል”።

 

 

አሁን ይህን ልብ በሉ። “እግዚብሔር አስቀድሞ ለነብያቱ ሳይገልጥ በፊት አንዳችም ነገር አያደርግም” አለ አሞጽጽ ከዚያም በኋላ እኛ ሥራውን እናያለን ስለዚህ አሁን እየገለጠ ያለውን ነገር ሊፈጽመው እያሰበ መሆን አለበት። እግዚአብሔር በፍርድ ሊገለጥ እያሰበ ነው ብዬ አምናለሁ። የሆነ ነገር ሊያደርግ እየተዘጋጀ ነው። ይህም የሚነግረን አንድ ነገር ቢኖር የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ መሆኑን ነው። በመጨረሻው ዘመን በሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ላይ ነው የምንገኘው። ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚገለጡት በመጨረሻው ዘመን ብቻ ነው።

“ሁለተኛው ማሕተም” ማርች 19 ቀን 1963

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

ስለ ማሕተሞቹ መፈታት የተሰጠውን መገለጥ ከማሕተሞቹ በውል መፈታት ጋር አታምታቱ፤ ማሕተሞቹ የሚፈቱት ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ነው፤ ማለትም ቤተክርስቲያን በራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ከተነጠቀች በኋላ ነው።

ሐዋርያው ዮሐንስ የጻፋቸውን ማሕተሞቹን ወንድም ብራንሐም ቢፈታቸው ኖሮ በዮሐንስ እና በወንድም ብራንሐም መካከል አንድ ሌላ ነብይ ተነስቶ ሰባቱ ማሕተሞች ምን ማለት እንደሆኑ ይገልጥ ነበር።

ነገር ግን ማንም ይህን አላደረገም። ሰባቱ ማሕተሞች ወንድም ብራንሐም በ1963 ሊገልጣቸው እስከ ጀመረበት ጊዜ ድረስ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነበሩ።

ራዕይ 4፡1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

 

በዚህ ክፍል ውስጥ የምናየው ነገር አለ እርሱም ከነዚህ ነገሮች በኋላ ድምጽ ሲያናግረው ሰማ … ምን ነበር የሰማው? መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ትቶ ወጣ። “ከነዚህ ነገሮች በኋላ” የሚለው በመጀመሪያው ቁጥር ላይ ነው (ምዕራፍ 4 ውስጥ)። ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ በሰማይ የተከፈተ በር … ራዕይ 4፡1 ይህ ማለት የቤተክርስቲያን ዘመን ካለፈ በኋላ ነው፤ ከዚያ ወዲያ በር ተከፈተ። በዚህ ውስጥ ሁሉ ካለፍን በኋላ በሩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድተናል። በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል ሲመላለስ የነበረው ድምጽ እራሱ ነው በሰማይ እንዲህ እያለ ሲናገር ዮሐንስ የሰማው፡- “ወደዚህ ውጣ።” ዮሐንስም ወደ ላይ ወጣ። ይህም ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ እንደምትሄድ የሚያሳይ ምሳሌ ነው

“ራዕይ ምዕራፍ አራት” ክፍል 3፤ ጃንዋሪ 8 ቀን 1961

 

ከነዚህ ነገሮች በኋላ … የቤተክርስቲያንን ዘመን ካየ በኋላ … የቤተክርስቲያን ዘመናት በሙሉ ሲያልፉ ካየ በኋላ

… የቤተክርስቲያን ዘመን ተጠናቀቀ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ሥራውን በቤተክርስቲያን ውስጥ ጨረሰ።

… “ከዚህ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለው፤ ከቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ”

የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ዮሐንስ ወዲያው ወደ ሰማይ ተነጥቆ መሄዱ የተነጠቀችውን ቤተክርስቲያን የሚያሳይ ተምሳሌት ነው። የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ይህ የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያው ንጥቀት ይመጣል። ልክ ዮሐንስ ወደ ሰማይ እንደተነጠቀ ቤተክርስቲያንም ተነጥቃ ወደ እግዚአብሔር ፊት ትገባለች።

“ራዕይ ምዕራፍ አራት” ክፍል 1፤ ዲሴምበር 31 ቀን 1960

 

የራዕይ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ምዕራፎች በቤተክርስቲያን ላይ የሚሆኑ ነገሮችን ይገልጻሉ። ከዚያም ከ3ኛው ምዕራፍ ጀምሮ እስከ 19ኛው ምዕራፍ ቤተክርስቲያንን አናገኛትም። ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ተነጥቃ ትሄዳለች ከዚያም በራዕይ ምዕራፍ 19 ወደ ምድር ትመለሳለች።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

 

 

ራዕይ ምዕራፍ 5 የሚፈጸመው ምዕራፍ 4 ውስጥ ከተጻፈው ንጥቀት በኋላ ነው

 

እስቲ ወደ ጥቅሱ እንመለስ፡- ዙፋን በሰማይ ቆሟል … (ቁጥር 2) … በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ። ልብ በሉ፤ “ዙፋን” እና ተቀማጭ። በዚህ ሰዓት በምድር በመቅረዞች መካከል እየተመላለሰ አልነበረም። ይህ የሆነው ከንጥቀት በኋላ ነው። እርሱ በዙፋኑ ላይ በክብር ተቀምጧል። ከዚያ ወረድ ብላችሁ እንድታስተውሉ የምፈልገው ነገር አለ፤ ይህንንም 5ኛው ምዕራፍ ውስጥ እናገኘዋለን፤ የተቀመጠበት ዙፋን የምሕረት ዙፋን አይደለም። ከዚያ ወዲያ የምሕረት ዙፋን የለም፤ ዙፋኑ የፍርድ ዙፋን ነው። የጸጋ ዙፋንም አይደለም። የፍርድ ዙፋን ነው ምክንያቱም ከዙፋኑ የሚወጡት እሳት፣ መብረቅ እና ነጎድጓዶች ናቸው፤ ከዚያ ወዲያ ምሕረት ያበቃል፤ የቤተክርስቲያንም ዘመን አብቅቷል። “እርኩሱ ይርከስ፤ ጻድቁም ይጽደቅ፤ ቅዱሱ ይቀደስ” ስለሚል ከዚያ ወዲያ የምሕረት ዙፋን የለም።

“ራዕይ ምዕራፍ አራት” ክፍል 1 ቅዳሜ ዲሴምበር 31 ቀን 1960

 

አሁን ደግሞ ወደ 5ኛው ምዕራፍ እንሸጋገራለን። ይህ የሚናገረው ስለ ሰባቱ ማሕተሞች አይደለም። ይህ የሚናገረው በቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ስላለው ክፍተት ነው። ቀጥሎ ስድስተኛውም ምዕራፍ አለ … የራዕይ መጽሐፍ በተለይ 4ኛው ምዕራፍ ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ከሄደች በኋላ የሚፈጸመውን ነገር ይገልጣል፤ ቤተክርስቲያን በራዕይ መጽሐፍ በ3ኛው ምዕራፍ ውስጥ ተነጥቃ ትሄዳለች፤ ከዚያም እስከ ራዕይ መጽሐፍ 19ኛው ምዕራፍ ድረስ አትመለስም።

“በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በ7ቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት” ማርች 17 ቀን 1963

 

ዮሐንስም ሲመለከት ዙፋኑ ላይ “አንድ” ብቻ ነው ያየው። በጉ መጽሐፉን በዙፋን ላይ “ከተቀመጠው” እጅ ሲወስድ የምናየው ከራዕይ 5፡6-8 በፊት አይደለም (እርሱም በጊዜ ቅደም ተከተል ራዕይ 4፡2-3ን ተከትሎ ነው የሚሆነው)

“የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ ምዕራፍ 1

የቤተክርስቲያን ዘመናት የተገለጹት ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ ከሆነ ቤተክርስቲያን ምዕራፍ 4 ውስጥ እንደተጻፈው በቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ላይ ትነጠቃለች። ስለዚህ ምዕራፍ 5 ውስጥ በጉ መጽሐፉን የሚወስደው ቤተክርስቲያን ተነጥቃ በሰማይ ከሆነች በኋላ ነው

ከዚያም ይህን ተከትሎ ምዕራፍ 6 ውስጥ ሰባቱ ማሕተሞች ይፈታሉ። ምዕራፍ 5 እና ምዕራፍ 6 ውስጥ የተገለጹት ክስተቶች የሚፈጸሙት ሰማይ ውስጥ ነው።

ራዕይ 5፡6 በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።

7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።

8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።

9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

 

በራዕይ ከቁጥር 5 እስከ 9 ድረስ በጉ መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ የሚዘምሩት እናማን ናቸው --- እነዚህ የተነጠቁ ቅዱሳን ናቸው? አይደሉም፤ ራዕይ 6 … 5 እና 9 እንደሚነግሩን አይደሉም። ካስተዋላችሁ እነዚህ ቅዱሳን አይደሉም። ጌታ የራሱ የሆኑትን ገና አልሰበሰበም። አያችሁ? እነዚህ ቅዱሳን አይደሉም። ካስተዋላችሁ እነዚህ ሽማግሌዎችና እንስሳቱ ናቸው፤ እነርሱም ይዘምራሉ።

አንድ ስሕተት አለ። አንድ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ። ያው በቃ ከዚህ ውጭ ምንም የለም። አንድ ነገር ተፈጽሟል። አያችሁ? የሆነ ቦታ የተፈጠረ ችግር አለ። እንዴት ናችሁ ሁላችሁም ሰላም ናችሁ? የታመመ ወይም በሽታ ያለበት ሰው የለም?

[ከጉባኤው መካከል አንድ ሰው ወንድም ብራንሐም ራዕይ 5፡9ን እንደገና እንዲያነብ ጠየቀው - ኤዲተር]

ካነበበም በኋላ … አራቱ እንስሳት እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወድቀው ሰገዱ፤ በእያንዳንዳቸውም እጅ በገና እና የወርቅ ጽዋዎች ነበሩ በጽዋዎቹም ውስጥ እንደ ሽቶ መዓዛ ያላቸው የቅዱሳን ጸሎቶች ነበሩ።

እነርሱም አዲስ መዝሙር ዘመሩ እንዲህ እያሉ፡- መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማሕተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና … (ይኸውና። እዚህ ላይ ተሳስቼ ነበር። አያችሁ?) … በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ …

አዎን በትክክል። ስለዚህ ምን ይመስላችኋል? የመንፈስ ቅዱስ መገኘት በዚህ ከሌለ እንግዲህ እዚህ ምን አለ? እርሱ … የሚገርማችሁ ያነበብኩት የዚያን ጥቅስ የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው። እርሱም ያው … ወይም በዚያ ክፍል የተጻፈ ነገር ሲሆን እኔም የግድግዳ ሰዓት እየተመለከትኩ ለመረዳት እየሞከርኩ ነበር። ነገር ግን እንዳያችሁት እርሱ እዚያ ላይ አስቆመኝ አይደል? ክብር ለጌታ ይሁን። የቀረውን ክፍል አላነበብኩም። እዚህ እንደደረስኩ፡ “እንግዲህ …” ተመልከቱ። “እነርሱም አዲስ መዝሙር ዘመሩ” እዚያጋ አቆምኩ። አያችሁ? ነገር ግን ይህን ተመልከቱ፡- “እንዲህ እያሉ ነው የዘመሩት፡- ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከወገን ሁሉ ዋጅተኸናል።” አዎን፤ እነርሱ ናቸው። በጣም ይደንቃል። አያችሁ?

… ዛሬ ደግሞ ሌላም ነገር ከእግዚአብሔር ተቀብያለሁ። እግዚአብሔርም ያንን ስሕተት እንዳልሰራ ለመጠንቀቅ ስለፈለገ መልሶ ጠራኝና የቀረውን ጥቅስ በሙሉ እንዳነብ አደረገኝ።

እኔም በዚያ ሥፍራ የሆነ ነገር ከላዬ ላይ ተንከባልሎ እንደወረደ ተሰማኝና እንዲህ የሚለኝን ድምጽ ሰማሁ፡- “ተመለስ፤ ተመለስ።” እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፡- “ተመለስ፤ ወዴት? የያዝኩትን አቁሜ ለበሽተኞች ወደ መጸለይ ልመለስ? ምንድነው -- ምን ይሆን? ምን አድርጌያለሁ?” እኔም ወደዚህ ጥያቄ ስመጣ አንድ ሰው እንዲህ አለኝ፡- “ጥቅሱን እንደገና ደግመህ አንብበው።” እኔም ደግሜ አነበብኩትና ከዚህ ጥያቄ በታች እዚያው ነበረ (አያችሁ?) ራዕይ 6። እኔም የመጀመሪያውን አነበብኩ፤ ሲነበብ ልክ እንደ መጀመሪያው ይመስላል (አያችሁ?) “እነርሱም አዲስ መዝሙር ዘመሩ …” ወደዚህ ስንመጣ ግን ምን እንደሚል ታያላችሁ? ቀጥለን ወረድ ስንል “የዋጀን” ይላል። ያለ ምንም ጥርጥር ስለ ሙሽራይቱ ነው፤ ማለትም የተነጠቁት ቅዱሳን። ስለዚህ … በእርግጥ … በጉ መጽሐፉን በእጁ ይዟል። ምልጃ የሚያደርግበትን የጸጋ ዙፋን ትቶ ሄዷል። አያችሁ?

“ስለ ማሕተሞቹ ጥያቄዎችና መልሶች” ማርች 24 ቀን 1963

ይህ ልዩ ክስተት ነው። እየሰበከ ሳለ ሲሳሳት እግዚአብሔር አረመው። ስለዚህ ይህ ነጥብ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ልብ በሉ - ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ በዙፋኑ ዙርያ ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከሕዝብ ሁሉ ተለይተው ስለመዋጀታቸው የምትዘምረው ሙሽራይቱ ናት።

ወንድም ብራንሐም መጀመሪያ ሙሽራይቱ አይደለችም ብሎ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር አረመውና ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ በዙፋኑ ዙርያ ያለችው ወደ ሰማይ የተነጠቀችዋ ሙሽራ መሆንዋን እና ይህም ትዕይንት ልክ ምዕራፍ 6 ውስጥ ሰባቱ ማሕተሞች ከመፈታታቸው በፊት መሆኑን ተገነዘበ።

የማሕተሞቹ መፈታት የሚከናወነው በቀጣዩ ምዕራፍ ውስጥ ነው፤ ይህም ሙሽራይቱ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው። ከዚያ በኋላ ማሕተሞቹ በውል የሚፈቱት ምዕራፍ 6 ውስጥ ነው።

እንግዲህ ማሕተሞቹ በእርግጥ የሚፈቱት መች ነው?

ከትንሳኤ በኋላ ከምድር ተነጥቃችሁ፤ ሰማይ ገብታችሁ፤ በዙፋኑ ዙርያ በምትቆሙበት ሰዓት ነው።

እነዚህ መለከቶች የተነፉት ለአይሁዶች ነው (ገብቷችኋል?) እንጂ ለአሕዛብ አይደለም። እነዚያ ማሕተሞች ሲፈቱ የአሕዛብ ዘመን ያበቃል፤ ጊዜም ያበቃል፤ ቤተክርስቲያን ትጠራለች።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ወንድም ብራንሐም ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ ሄዶ ወደፊት እነዚህ ማሕተሞች በሚፈቱበት ሰዓት ምን እንደሚፈጸም ሊያሳየን ተመልሶ መጣ።

ከዚህም የተነሳ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች (መፈታት) መገለጥ ልናገኝ ችለናል።

የማሕተሞቹን መፈታት በመገለጥ አስቀድመን አይተናል።

ይህንን ስለ ሰባቱ ማሕተሞች በተጻፈው መጽሐፍ ሽፋን ላይ ማየት ትችላላችሁ።

ሽፋኑ “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” ይላል።

አሞጽ 3፡7 እግዚአብሔር አስቀድሞ ለባሪያዎቹ ለነብያት ሳይገልጥ በፊት ምንም ነገር እንደማያደርግ ይናገራል።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም

 

እግዚአብሔር መጀመሪያ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ሳይገልጥ በፊት ምንም አያደርግም።

እግዚአብሔር ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት አስቀድሞ መገለጥ ሳይሰጠን ሰባቱን ማሕተሞች ሊፈታ አይችልም።

ማሕተሞቹ በመገለጥ መከፈት አለባቸው፤ መገለጡም ወደፊት ስለሚሆነው ክስተት ቅድሚያ ዕይታ እንድናገኝ ያስችለናል፤ ስለዚህ ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት ስለመፈታታቸው መገለጥ እናገኛለን።

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን የምር ፈቷቸው ቢሆን ኖሮ እርሱ ከመፍታቱ በፊት ማን ነበር የገለጣቸው?

 

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈጸመም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

 

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈጸመም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ነገር ግን ብዙ ቦታዎች ላይ ማሕተሞቹ ተፈተዋል እያለ ይናገራል።

ስለ ሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መገለጥ አግኝተናል። ከጊዜ መጋረጃ በስተጀርባ ሄዶ ወደፊት የሚሆነውን የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት አየ፤ ከዚያም ወደፊት ማሕተሞቹ በሚፈቱ ጊዜ ምን እንደሚፈጠር ሊነግረን ተመልሶ መጣ።

የሰባተኛው ማሕተም መፈታት መገለጥ ማሕተሙ የክርስቶስ ዳግም ምጻት ሚስጥር መሆኑ መታወቁ ነው። ሚስጥሩን ግን ማንም አያውቀውም።

እግዚአብሔር እነዚህ ሰባት ድምጾ በነጎድጓድ ድምጽ እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት አለው (አያችሁ?) ምክንያቱም … በጉ ማለትም ክርስቶስ መጽሐፉን በእጁ ወስዶ ሰባተኛውን ማሕተም ፈታው። ነገር ግን እንደምታዩት የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም። ነገር ግን እርሱ እንደተናገረው መምጫውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ደግሞ ስለዚህ ባለ ሰባት ነጎድጓድ ሚስጥርም ሊያውቁ አይችሉም። ስለዚህ እንደምታዩት የተያያዘ ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ስለዚህ ስለ ሰባተኛው ማሕተም አናውቅም።

መልአኩ በግራዬ በኩል ቆሞ ነበር፤ ከግራ ወደ ቀኝ ብንቆጥር የመጨረሻው ወይም ሰባተኛ መልአክ ይሆናል ምክንያቱም በግራዬ በኩል ነበር የቆመው፤ እኔ እርሱን ለማየት ወደ ምዕራብ ስለመለከት ነበር፤ እርሱ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ሲመጣ ለእኔ ከግራዬ በኩል ነው የሚሆነው፤ ስለዚያ የመጨረሻው መልአክ መልእክት ነው የሚሆነው፤ እርሱም ወሳኝ መልእክት ነው። ጭንቅላቱን እንዴት ዘወር እንዳደረገና በትልል ክንፎቹ ወደ እኔ እየበረረ እንደመጣ የነገርኳችሁ ትዝ ይላችኋል። ይህም ሰባተኛው ማሕተም ነው። በጣም ታላቅ ነገር ነው። እኛም … እኛም እስካሁን ምን እንደሆነ አናውቀም ምክንያቱም ገና አልተፈታም

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

በጉ መጽሐፉን የወሰደው ልክ ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ ጊዜው ሲቀርብ ነው። አስታውሱ ሰባተኛውን ማሕተም ከእኛ ሰውሮታል። አልገለጠልንም። መልአኩ ቀን በቀን የማሕተሞቹን ሚስጥር እየገለጠ ቆሞ ነበር ነገር ግን ያኛውን ትቶ አለፈው። እንዲህ አለ፡- “በሰማይ ዝምታ ሆነ።” ማንም አላወቀም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

“በወኅኒ ያሉ ነፍሳት” ኖቬምበር 10 ቀን 1963

 

ነገር ግን አስተውሉ ይህን ሁሉ ቀን ኖኅ መርከቡ ውስጥ ነበረ። ሙሽራይቱ ክርስቶስ ውስጥ ሆና ተሰውራለች፤ የመጨረሻው የሙሽራይቱ አካል ተዋጅቷል። ስድስተኛው ማሕተም ተገልጧል። ሰባተኛው ማሕተም ጌታን ወደ ምድር ያመጣዋል

“በወኅኒ ያሉ ነፍሳት” ኖቬምበር 10 ቀን 1963

 

ስለ ሰባተኛው ማሕተም የተሰበከው ማርች 25 ቀን 1963 ነው። አንዳንድ አማኞች ስለ ሰባተኛው ማሕተም በተሰበከ ጊዜ የጌታ ምጻት ሆኗል ይላሉ።

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም፤ ታዲያ ማሕተሙ ሳይፈታ ጌታ እንዴት ሊመጣ ይችላል?

አንዳንዶች ደመናው የጌታ ምጻት ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ደመናው የመጣው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ነው።

ስለዚህ የጌታ ምጻት በየትኛው ቀን ነው? ደመናው የታየበት ቀን ነው ወይስ ስለ ሰባተኛው ማሕተም የተሰበከበት ቀን?

የአደን ወቅት የተጀመረው ማርች 1 ቀን ነው። ወንድም ብራንሐም ሂውስተን ውስጥ የሰበከበት ቀን ማርች 4 ነው። ከዚያ በኋላ ነው እርሱ ወደ አደን የሄደው። 7ቱ መላእክት ወደ ሳንሴት ፒክ መጥተው እርሱን የጎበኙት ማርች 8 ቀን ነው። ስለዚህ ደመናው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ከሳንሴት ተራራ ወደ ሰሜን በ200 ማይልስ ርቀት ላይ ፍላግስታፍ ከተማ አጠገብ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ፎቶግራፍ በተነሳ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ሳንሴት ተራራ አካባቢ ላይ አልነበረም። ደመናው ፎቶግራፍ በተነሳ ጊዜ ከምድር 27 ማይልስ ከፍታ ላይ ነበር፤ ከዚያም ከፍታ ምንም ዝቅ አላለም። ስለዚህ ደመናው የኢየሱስ ወደ ምድር መመለስ ሊሆን አይችልም።

ደመናው ሳንሴት ፒክ ውስጥ በጭራሽ አልታየም።

 

 

ደመናው ፍላግስታፍ አካባቢ ነው የታየው፤ የታየበትም ቀን 7ቱ መላእክት ማርች 8 ቀን 1963 ወንድም ብራንሐምን ለመጎብኘት ወደ ሳንሴት ፒክ ከመምጣታቸው ከ8 ቀናት በፊት ነው። የዛን ዕለት 7ቱ መላእክት ምንም ደመና አልሰሩም። መላእክቱ የመጡበት ሳንሴት ፒክ ከተማ ከፍላግስታፍ በስተ ሰሜን 200 ማይልስ ትርቃለች።

የፓሩሲያ አማኞች ደግሞ የጌታ ምጻት በ1933 ወንድም ብራንሐም በኦሃዮ ወንዝ ውስጥ ሲጠመቅ የታየው የእሳት አምድ ነው ይላሉ።

እንዲህ ከሆነማ በ1950 ሂውስተን ውስጥ ከወንድም ብራንሐም ጭንቅላት ዙርያ ቀለበት ሲሰራ ፎቶግራፍ የተነሳው የእሳት አምድም የጌታ ምጻት ሊባል ነው።

 

 

ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ግራ የሚያጋቡ የተለያዩ ቀናት የጌታን ምጻት ከዚህ በፊት ከታዩ ክስተቶች ጋር ማያያዝ ከንቱ መሆኑን ያመለክታሉ።

እግዚአብሔር የክርስቶስን ምጻት ታላቅ ሚስጥር እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ አይገልጥም።

ማሕተሞቹ ሁሉ ተፈተዋል ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ ስድስተኛው ማሕተም ጋ ስትደርሱ የሚገጥማችሁን ችግር ተመልከቱ።

ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው፤ ምክንያቱም የእነርሱ አገልግሎት ነው በድጋሚ በምድር ላይ የሚገለጠው፤ የሁለቱም። ገባችሁ አሁን? ስድስተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ገባችሁ? እነዚያ ነብያት ናቸው።

አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምን61ኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ።

“ስድስተኛው ማሕተም” ማርች 23 ቀን 1963

ሀለቱ የአይሁድ ነብያት ስድስተኛውን ማሕተም በታላቁ መከራ ውስጥ ነው የሚፈቱት።

ስድስተኛው ማሕተም ሲፈታ በተፈጥሮ ኡደቶች ላይ ብዙ መዛባት ያስከትላል።

… ውሃዎችን ወደ ደም ለመለወጥ በውሃ ላይ ስልጣን አላቸው፤ ምድርንም እንደፈለጉ በመቅሰፍት ለመምታት በውሃ ላይ ስልጣን አላቸው።

ምንድነው? ከቃሉ በቀር እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ማድረግ የሚችል ምንድነው? ተፈጥሮን እንደፈለጉ ሊያሽከረክሯት ይችላሉ። ተመልከቱ። ስድስተኛው ማሕተም እንዲፈጸም የሚያደርጉት እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ማሕተሙን ይገልጡትና ይፈቱታል። ይህም እግዚአብሔር የተፈጥሮ ኡደት እንዲቋረጥ የሚያደርግበት ኃይል ነው። ተመለከቱ፤ ስድስተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ነው።

አሁንስ አስተዋላችሁን? ይኸው ማሕተሙ። ማነው የሚያደርገው? ንጥቀት ከተፈጸመ በኋላ ነብያቱ ናቸው የሚያደርጉት። በእግዚአብሔር ኃይል፣ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ላይ ይፈርዳሉ። የምድር መንቀጥቀጥ ማስነሳት ይችላሉ፤ ጨረቃን ወደ ደም መለወጥ ይችላሉ፣ ፀሃይ ልትወድቅ ወይም በእነርሱ ትዕዛዝ ማንኛውንም ነገር ልትሆን ትችላለች። አሜን።

“ስድስተኛው ማሕተም” ማርች 23 ቀን 1963

ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታው ከንጥቀት በኋላ ብቻ ነው። ከንጥቀት በፊት አይፈታም ምክንያቱም ስድስተኛው ማሕተም ታላቁን መከራ የሚገልጽ ነው።

ከታላቁ መከራ ጋር የተያያዘውን ስድስተኛውን ማሕተም የአይሁድ ነብያት ይፈቱትና እንዲፈጸም ያደርጉታል። እነርሱ የዚህም ሚስጥር ዝርዝሮች ሁሉ ያውቃሉ።

እኛ አሕዛቦች ስለ ስድስተኛው ማሕተም ያገኘነው መገለጥ በከፊል ብቻ ነው። እኛ የምናውቀው ስድስተኛው ማሕተም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ከሚኖሩ አይሁዶች ጋር የተያያዘ መሆኑን ብቻ ነው። ነገር ግን የታላቁን መከራራ ዝርዝር ጉዳዮች አናውቅም።

 

ሰባቱን ጽዋዎች እና ሰባቱን መለከቶች መረዳት አንችልም

አራተኛው ማሕተም ሲፈታ በሐመር ፈረስ ላይ ተቀምጦ የታየውና ሞት የሚባለው የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ማን እንደሆነ አናውቅም። ዛሬ በምድር ላይ ከሚኖሩ 8 ቢሊዮን ሕዝብ መካከል የክርስቶስ ተቃዋሚው የሚገድላቸው 8 ሚሊዮን ሰዎች እነማን እንደሆኑ አናውቅም። መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱ በአየር ላይ ጌታን እንድትቀበለው ከምድር በሚነጥቃት ጊዜ ሕይወት ከምድር ተለይቶ ይሄዳል። ሞት መግባት የሚችለው ሕይወት ሥፍራውን ሲለቅ ብቻ ነው።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

 

 

ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታበት ጊዜ ደርሷል፤ በጣም ቅርብ ነው፤ ሲፈታ ደግሞ ኦ ምን እንደሚሆን ልነግራችሁ አልችልም። መጨረሻው … ሙሽራይቱ ተነጥቃ ሄዳለች። ንግስቲቱ በቦታዋ ለመሆን ሄዳለች። ይህ ሁሉ እየሆነ ሳለ አሁን ከንጉሱ ጋር እየተጋባች ናት። የእስራኤል ቅሬታዎችም ማሕተም እየተደረገባቸው ናቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተዘጋጅተዋል፤ ከዚያ ፍጥረት ሁሉ ዝግጁ ይሆናል። የሚያስደንቅ ጊዜ ይሆናል።

“ስድስተኛው ማሕተም” ማርች 23 ቀን 1963

ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታው ሙሽራይቱ በሰማይ ጋብቻዋን እየፈጸመች ሳለ ነው።

በመልእክቱ ውስጥ ስድስተኛውን ማሕተም ገልጦ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ ነው የተናገረው። ይህም ወደፊት የሚሆን ነው።

ስድስተኛው ማሕተም ታላቁ መከራ ነው። ታላቁ መከራ አሁን በምንኖርበት ዘመን ሆነን ልናስበው የማንችለው ዓይነት ከባድ የመከራ ጊዜ ነው።

 

 

8ኛው ምዕራፍ የሰባተኛውን ማሕተም መቼት ይገልጣል፤ በዚያም ከሰባተኛው ማሕተም በቀር ሌላ ምንም አልተገለጠም። ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም የተገለጠ ነገር የለም። ደግሞም ከራዕይ ምዕራፍ 7 ጋር የሚያያይዘው ምንም ነገር የለም። የሰባተኛውን ማሕተም መገለጥ በተመለከተ ፍጹም የሆነ ጸጥታ ብቻ ነው ያለው። እኔ ደግሞ ጊዜ ባገኝ ስለ 7ኛ ማሕተም ከዘፍጥረት ጀምሬ የተጻፈውን በሙሉ ላሳያችሁ (ጥቂት ቦታዎች እሞክራለሁ።) ከመጀመሪያው ከዘፍጥረት ጀምሮ እነዚህ ማሕተሞች ይህ ሰባተኛው ማሕተም እስከ መጽሐፉ መጨረሻ ድረስ ይገኛል።

ዛሬ ጠዋት እነዚህን ነገሮች አንስተን ስንነጋገርባቸው ትዝ አይላችሁም? ዛሬ ማታ በድጋሚ ስናነሳቸው ልብ በሉ፤ ሰባተኛው ማሕተም ጋ ስንደርስ ከዚያ ማለፍ አንችልም።

ኢየሱስ እራሱ ስለ መጨረሻው ዘመን ሲናገር ስለ ስድስቱ ማሕተሞች ተናገረ፤ ሰባተኛውጋ ሲደርስ እርሱም ዝም አለ። ይኸው። አያችሁ? ይህ ትልቅ ነገር ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ስድስት ማሕተሞች በውስጣቸው ያለው ምሳሌ ስለተብራራልን ተገልጠዋል።

ሰባተኛው ማሕተም ውስጥ ግን አንዳችም ምሳሌ የለም። ስለዚህ የሰባተኛው ማሕተም መገለጥ የለንም።

ከዚህም የተነሳ ሰባተኛው ማሕተም አሁን ሊፈታ አይችልም።

ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።

 

 

የሰው ልጅ በሚገለጥበት በመጨረሻው ዘመን እየኖርን እንዳለን ታምናላችሁ? የመጨረሻው ዘመን ማለት በሉተር፣ በዌስሊ በባፕቲስቶች፣ በፔንቲኮስታሎች ሁሉ ሲሰበክ የነበረው ቃል በሙሉ የሚሰበሰብበት ጊዜ ነው። ሰባተኛው መልአክ የተሰጠው ተልእኮ የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር መግለጥ ነው። ሚስጥር ሁሉ በሰው ልጅ ነው የሚጠቃለለው፤ የዘመን ሙላቱ ወደ ቃሉ ሙላት ደርሷል፤ ይህም የአካሉን ሙላት ለመግለጥ ነው። ይህም ቃሉ ነው፤ በአፍ የተነገረው ቃል በቃሉ ተገልጦ ቃሉን ይገልጠዋል።

“ቃሉን ማረጋገጥ” ኦገስት 16 ቀን 1964

በዚህ ክፍል ወንድም ብራንሐም የእርሱ አገልግሎት ያልተጻፈውን ሰባተኛውን ማሕተም ሳይሆን የተጻፉትን ስድስቱን ማሕተሞች መግለጥ መሆኑን አረጋግጧል። ለዚህ ነው ባለ “ስድስት ማሕተም” ሚስጥር ብሎ የሚጠራው።

 

 

በሰማይ ታላላቅ ምልክቶች፤ መላእክት እንደ ከዋክብት በዝተው ሲመጡ! ሳይንቲስቶችም ቀና ብለው ሲመለከቱ፤ ነገር ግን ከመፈጸሙ ወራት አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር። ይኸው። መጽሔት ላይ ታትሞ ማየት ይቻላል። ነገር ግን ከመፈጸሙ ወራት አስቀድሞ ተነግሯል። ሰባት መላእክት ወረዱና እንዲህ አሉ፡- “ባለ ስድስት ማሕተሙ የእግዚአብሔር ሙሉ ሚስጥር ይገለጣል።” ያው ልክ እንደተናገረው አስቀድሞ ከመሆኑ በፊት እንደተነበየው ተፈጽሟል።

“ተጽእኖ” ኦገስት 3 ቀን 1963

ሰባቱ መላእክት መጀመሪያ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ፍላግስታፍ አጠገብ ምልክት እንዲሆን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሰሩ።

ከስምንት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ለወንድም ብራንሐም ሰባቱን ማሕተሞች ይገልጥ ዘንድ ትዕዛዝ ሊሰጡት ወደ ሳንሴት ፒክ መጡ።

ከዚያም እርሱ ከማርች 17 - 23 የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማሕተሞች ገለጠ

ማርች 24 ቀን 1963 በተሰጠው ትምሕርት ሰባተኛው ማሕተም ማለትም የጌታ ምጻት ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ነው የተገለጠው።

ሶስት ትልልቅ ነገሮች ሆነዋል። እነርሱም ምልክቱ፣ ተልዕኮው፣ እና የስድስቱ ማሕተሞች መገለጥ ናቸው።

ከዚያ ወዲያ የቀሩት ሚስጥራትም እየተከፈቱ ይገለጣሉ።

 

 

ደመናውን ፎቶግራፍ ያነሳው አንድ ሳይቲስት ነው፤ እርሱም ስለ ደመናው ማብራራት አልቻለም ምክንያቱም ደመና ለመስራት በቂ ውሃ በሌለበት ከፍታ ላይ ነበር ደመናው የተፈጠረው።

ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድን ግራ ያጋባው ነገር ሁለት ደመናዎች መኖራቸው ነው፤ አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ደግሞ ትንሽ ነው፤ በሁለቱ መካከልም የ20 ማይልስ ክፍተት ነበረ። ትንሹ ደመና ከ4 ሰዓታት በፊት ከቫንደንበርቅ አየር ኃይል ተወንጭፎ በ43 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የፈነዳ ትልቅ ሮኬት መሆኑን ያውቃል።

ትልቁ ደመና ግን እንቆቅልሽ ሆነበት።

 

 

ይህ ፎቶ ሁለቱ ደመናዎች ከዊንስሎው ሲታዩ ምን እንሚመስሉ ያሳያል። ሁለቱ ደመናዎች ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ከፍላግስታፍ በስተ ሰሜን ለ28 ደቂቃ ታይተዋል። በዚያ ሰዓት ወንድም ብራንሐም ከዚያ 200 ማይልስ ርቃ በምትገኘው ታክሰን ከተማ ውስጥ ነበር።

ወንድም ብራንሐም ይህ ደመና በላይ በሰማይ የተሰጠ ምልክት ነው ይላል።

የጌታ ምጻት ነው አላለም፤ ነገር ግን በሰማይ ላይ የተገለጠ የሰው ልጅ ምልክት ነው ብሏል።

የአንድ ክስተት ምልክት እራሱ ክስተቱ ነው ተብሎ መወሰድ የለበትም።

አሁን … እስቲ እኔ ሳነብ አብራችሁኝ አንብቡ። ይህንን ታላቅ ክስተት የሚገልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን አነጻጽሩና እዩ፤ እኛም በቤዛነት መጽሐፍ ውስጥ ከስድስተኛው ማሕተም ስር የተሰወረውን ሚስጥር እናያለን።

ደግሞ ልብ በሉ፤ እነዚህ የተሰወሩ ሚስጥራት ናቸው። ስድስተኛው ማሕተም ደግሞ ራሱን የቻለ አንድ ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ማለትም ስድስት ጥቅልሎች በአንድ ላይ ሆነው ነው፤ ሲፈታም የቤዛነትን መጽሐፍ በሙሉ ይገልጠዋል። ምድር በሙሉ የተዋጀችው እንዲህ ነው።

“ስድስተኛው ማሕተም” ማርች 23 ቀን 1963

የቤዛነት መጽሐፍ በሙሉ በነዚህ በስድስቱ በተጻፉት ማሕተሞች ነው የተገለጠው።

የዳንነው ቃሉ ውስጥ በተጻፈው ነው።

ወንድም ብራንሐም ለጌታ ምጻት ሊያዘጋጀን ነው የተጻፉትን ሚስጥራት የገለጠልን።

የተጻፉትን ስድስት ሚስጥራት መግለጥ በቂ ነውን?

የበዓለ ሃምሳ በዓል ወቅት የሚጠናቀቀው በሰባተኛው መለከት ነው፤ ከዚያ የሚቀጥለው የጌታ ምጻት ነውና … ሰበተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው፤ ደግሞም መለከቱ የሚነፋው ለአይሁዶች ነው። ስድስተኛው መለከት ለአይሁደች ይነፋል፤ በሚነፋበትም ጊዜ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ ለእነርሱ ያሳውቃቸዋል፤ ለግማሽ ሰዓትም የዝምታ ጊዜ ይሆናል። መለከቶቹ ሁሉ ድምጻቸው በሚሰማው ስድስተኛው ማሕተም በሚፈታበት ጊዜ መሆኑን አስተውሉ። ስድስተኛው ማሕተም የሚስጥራቱ ሁሉ ፍጻሜ ነው፤ ልክ ሰባተኛው ማሕተም ከመፈታቱ በፊት በስድስተኛው ማሕተም ሚስጥራቱ ይጠናቀቃሉ።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ስድስቱን ማሕተሞች መግለጥ የተጻፈውን የቃሉን ሚስጥር ለመግለጥ በቂ ነው።

ያልተጻፈውን ሰባተኛው ማሕተም ለእግዚአብሔር እንተወዋለን። እርሱ ብቻ ነው ሊፈጽመው የሚችለው።

 

ጥያቄ 4 - ነጎድጓዶቹ በወንድም ብራንሐም አገልግሎት ዘመን ቃላቸውን አሰምተዋልን?

(ዝጋው አ-ት-ጻ-ፈ-ው) … ሰባቱ ነጎድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፋም።

በጀርባው በኩል ነው። መጽሐፍ ሲጠናቀቅ … ተመልከቱ በፊት ለፊት በኩል አላለም፤ በጀርባው በኩል ነው ያለው። ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ የዛኔ ከመጽሐፉ ጋር የሚቀሩት እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጾች ብቻ ናቸው፤ እነርሱም ገና አልተገለጡም። መጽሐፉ ውስጥ እንኳ አልተጻፉም።

… እነዚህ ማሕተሞች በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ነው ያሉት። ሰባተኛው መልአክ ድምጹን በሚያሰማበት ጊዜ በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ ይፈጸማሉ

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

ወንድም ብራንሐም “መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን” ሚስጥራት የመግለጥ ተልዕኮ ነው የተሰጠው።

የእርሱ አገልግሎት በመጽሐፉ ጀርባ ላይ የተጻፉትን ሚስጥራት ለመግለጥ አይደለም። አንዳንድ ሚስጥራት መጽሐፉ ውስጥ ነው የተጻፉት። አንዳንድ ሚስጥራት ደግሞ መጽሐፉ ውስጥ አልተጻፉም። እነዚህ ሚስጥራት መጽሐፉ ውስጥ ተሰውረው ነው የሚገኙት፤ ነገር ግን እንተረጉማቸው ዘንድ አንዳችም እነርሱን የሚወክል ምሳሌ ወይም ምልክት አልተቀመጠልንም።

ከነዚህ ካልተጻፉ ሚስጥራት መካከል ቢያንስ አራት አሉ፡-

እነዚህ ሚስጥራት ከወንድም ብራንሐም አገልግሎት ውስጠ አልተካተቱም።

እነዚህን ነጥቦች በጥናታችን ውስጥ ኋላ አንድ በአንድ እንወያይባቸዋለን።

በተጨማሪም የወንድም ብራንሐም አገልግሎት በታላቁ መከራ ዘመን የሚኖሩ አይሁዶችን የተመለከተም አልነበረም፤ ለምሳሌ ሰባቱን ጽዋዎች እና ሰባቱን መለከቶች አይመለከትም።

አሁን ደግሞ የመለከቶች በዓል ይሆናል። ይህ በዓል እስራኤላውያን የሚሰበሰቡበት ነው፤ የመለከቶች በዓል ሲመጣ ሁላቸውም ይሰበሰባሉ።

ለተወሰነ ጊዜ ከዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ሰባቱ መለከቶች ለመናገር ስጠብቅ ነበር። ስለዚህ አሁን በጥቂት ደቂቃ ውስጥ አንከልሰዋለን፤ በዚያውም በርዕሱ አሁን የማልናገርበትን ምክንያት አብረን እናያለን፤ ዋናው ምክንያት በዚህ ጊዜ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ እንድናገር መንፈስ ቅዱስ ስላልፈቀደልኝ ነው። ለተማሩ ሰዎች ይህ የሕጻን ቀልድ ሊመስላቸው እንደሚችል አውቃለሁ፤ ለክርስቲያኖች ግን እንደዚያ አይደለም። እኛ ግን የምንከተለው የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ብቻ ነው።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

 

ስለ ሰባቱ መለከቶች እየሰበክሁ በነበርኩ ጊዜ ወደዚህ ክፍል ስደርስ እንዲህ ብዬ አሰብኩ፡- “እንግዲህ ሌላ ምንም ነገር ለማሰብ አልሞክርም። እርሱ ራሱ በጊዜው እስኪገልጥልኝ ድረስ እጠብቃለሁ።” ትናንትና ደግሞ ወደ ክፍል ገብቼ ራሴን እየጠየቅሁ ሳለ … ወይም ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ከትናንት ወዲያ ማለቴ ነው። በደምብ ለመረዳት ፈልጌ ወደ ጸሎት ክፍል ገብቼ ስጠባበቅ የዛኔ ነው መንፈስ ቅዱስ ይህንን ያበራልኝ፤ ከዚያም ይህ መገለጥ በዚህ ጊዜ ለቤተክርስቲያን ለምን እንደማይጠቅማት ገለጠልኝ፤ የማይጠቅማት ከቤተክርስቲያን ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር ስለሌለ ነው

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ወንድም ብራንሐም “የመለከቶች በዓል” በሚል ርዕስ ሊሰብክ ፈለገ፤ እግዚአብሔር ግን እነዚህ ሚስጥራት ለአሕዛብ ቤተክርስቲያን የተሰጡ አይደሉም አለው። እነዚህ ሚስጥራት በታላቁ መከራ ውስጥ የሚያልፉትን የአይሁድ ቅሬታዎች የሚመለከቱ ናቸው። ስለዚህ በሰባቱ መለከቶች ላይ የአንድ ሳምንት ትምሕርት መስጠት አልቻለም፤ ነገር ግን ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ከዚያም በኋላ ደግሞ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የአንድ ሳምንት ትምሕርቶችን ሰጥቶ ነበር፤ ምክንያቱም እነዚህ ሚስጥራት ከአሕዛብ ወገን የሆነችዋን ሙሽራይቱን የሚመለከቱ ናቸው።

ሚስጥራትን ሁሉ ተረድተናል የምትሉ ከሆነ እስቱ የዳንኤል ትንቢት ውስጥ የተጠቀሱትን 2,300 ቀናት አብራሩ። ይህ ከባድ እንቆቅልሽ ነው።

ወንድም ብራንሐም ሙሽራይቱ ታላቁን መከራ እንድታመልጥና ለቤተክርስቲያን ንጥቀት እንድትዘጋጅ የሚረዱዋትን ሚስጥራት ሁሉ ገልጦ አስተምሯል።

ስለዚህ ከታላቁ መከራ ጋር የተያያዙ ሚስጥራት ሙሽራይቱን አይመለከቷትም ምክንያቱም ሙሽራይቱ ከታላቁ መከራ ታመልጣለች።

… ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ባሰማ ጊዜ ድምጹን በማሰማቱ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ይጠናቀቃሉ። ከዚያም ከተገለጠ በኋላ ብርቱው መልአክ ከሰማይ ይወርዳል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው (ይህ መልአክ በምድር ላይ የሚኖር መልእክተኛ እንደሆነ አስተውሉ)። ክርስቶስ ወደ ምድር ይወርዳል (ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ታዩታላችሁ)፤ ከዚያም አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን ደግሞ በባሕር ላይ ያኖራል፤ ከራሱ በላይ ቀስተደመና አለ፤ እግሮቹ -- እግሮቹ እንደ እሳት ወዘተ. ፤ እርሱም እጆቹን አንስቶ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖው ምሎ ከዚያ ወዲያ ጊዜ እንደማይኖር ይናገራል።

ይህንንም መሃላ ካደረገ በኋላ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ

ከዚያም ይቀጥልና እንዲህ ይላል፤ ልክ እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ከማሰማታቸው በፊት ሚስጥራቱ በሙሉ ይገለጣሉ

“ሶስተኛው ማሕተም” ማርች 20 ቀን 1963

መልአኩ የሚወርደው ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ነው።

ልክ ሰባቱ ነጎድጓዶች ከመምጣታቸው በፊት ሚስጥራቱ ይገለጣሉ።

ደመናው የታየው ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ከፍ ብሎ ነው እንጂ ከሳንሴት ተራራ በላይ አይደለም።

ደመናው የታየው ማሕተሞቹ ከመገለጣቸው ሁለት ሳምንታት ቀድሞ ነው።

ስለዚህ ደመናው መልአኩ አይደለም።

 

 

ከዊንስሎው እንደታየው ሁለት ደመናዎች ነበሩ

 

ይህ ፎቶ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ የቀረበላችሁ ዶ/ር ጄምስ ማክዶናልድ ትልቁን ደመና ሚስጥራዊ ደመና ብሎ የገለጸበት ምክንያት ሁለት ደመናዎችን በማየቱ መሆኑን እንድታስታውሱ ነው። አንድ የሮኬት ፍንዳታ ሊያብራራልን የሚችለው ስለ አንዱ ደመና ብቻ ነው እንጂ ስለ ሁለቱም ሊገልጥልን አይችልም። ስለ ሁለቱም ደመናዎች ሊያብራራልን የሚችል አንዳችም ፍጥረታዊ ማብራሪያ የለም። ስለዚህ ከደመናዎቹ አንዱ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው።

 

 

ሁለተኛው የጭስ ደመና የተፈጠረው ያን ዕለት ከሰዓት በኋላ ቀደም ብሎ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተወነጨፈ ሮኬት ሲፈነዳ ነው። ከፍንዳታው የወጣው የጭስ ደመና በ7 መላእክት ከተሰራው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ከኋላ ከኋላ እየተከለ ነበር። ሁለቱ ደመናዎች ከፍላግስታፍ አልፈው ሲሄዱ የጭሱ ደመና ከልዕል ተፈጥሮአዊው ደመና ኋላ 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነበር። ዋነኛው ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ለ28 ደቂቃ ብቻ ነበር የታየው።

በሰባት መላእክት የተሰራው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ከምድር በላይ 27 ማይልስ ከፍታ ላይ ከነበረበት ዝቅ አላለም።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን ወንድም ብራንሐም ፍላግስታፍ ውስጥ አልነበረም ሳንሴት ፒክ ውስጥም አልነበረም፤ ስለዚህ ደመናውን አላየውም፤ ምክንያቱም የአደን ወቅት በቀጣዩ ቀን ማርች 1 ነው የተከፈተው። ደግሞም ማርች 4 ቀን ሂውስተን ውስጥ ፍጹሙ በሚል ርዕስ የሰበከው ስብከትም አለ። ከዚያ በኋላ ነው ማርች 6 ቀን ለአደን ወደ ሳንሴት ፒክ የሄደው።

ቅዱስ ጴጥሮስ ከምድር በጣም ራቅ ባለ ከፍታ ላይ ሰማይ ውስጥ በጭስ እንፋሎት ስለሚፈጠር ደመና ትንቢት ተናግሮ ነበር። ይህም ልክ የዝናብ ደመናዎች በውሃ ትነት እንደሚፈጠሩ ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤

ይህ የጭሱ ደመና ነው።

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

ይህ ደግሞ በመላእክቱ ክንፍ የተፈጠረው ትልቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ነው።

ከዚያም ሰባቱ ማሕተሞች ካለፉ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶችን እናገኛለን

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

 

አሁንስ ግልጽ ሆነላችሁ? የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ መጽሐፉ ውስጥ የነበሩ ማሕተሞች የታወጁት ሚስጥራት የሚከተሉት ናቸው፡- ጽድቅ፣ ቅድስና፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ ፕሮቴስታንቶች፤ ከዚያም ግጭቶቻቸውና ጦርነቶቻቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብዙ ያልተቋጩ ነገሮችን ሲያመጡ ሰባተኛው መልአክ ይመጣና ሁሉን ሰብስቦ በማብራራት ይቋጫቸዋል። አያችሁ? ከዚያ መጨረሻው ይሆናል፤ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የሰባተኛውን መልአክ መልእክት ስንመለከት ሚስጥራቱ በውስጡ ያሉት ሚስጥራት በሙሉ በዚያ ጊዜ ሊገለጡ ይገባ ነበር (ይህ ራዕይ 10፡1-7) በዚያው ጊዜ ሊገለጡ ይገባ ነበር።

ከዚያ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች እንግዳ የሆነ ድምጻቸውን ሲያሰሙ፤ ዮሐንስም ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ሊጽፍ ነበረ … የተናገሩትን … ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ሰምቷል ግን -- ግን አልጻፈውም ምክንያቱም እንዳይጽፍ ስለተከለከለ ነው። ስለዚህ ይህ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። በምሳሌ እንኳ አልተጻፈም። የምናውቀው ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ብቻ ነው

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

 

… ከዚያም በኋላ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ከፍተን የሰባተኛው መልአክ መልእክት እንደሚኖር ተመለከትን። የሰባተኛው መልአክ መልእክት በተሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥራት በሙሉ ይገለጣሉ። ከዚያ በኋላ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ

“በክፍተቱ መካከል መቆም” ጁን 23 ቀን 1963

 

 

ከዚያም እነዚህ ሰባት ማሕተሞች ካለፉ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎጓዶችን እናገኛለን፤ ዮሐንስ እንዲጽፍ ከታዘዘ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ግን እንዳይጽፍ ተከለከለ። ነጎድጓዶቹ ድምጻቸውን በሚያሰሙ ሰዓት ክርስቶስ ወይም በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ያለው መልአክ እግዶቹን በባሕር እና በምድር ላይ አድርጎ ሲቆም እናያለን፤ እርሱም ጊዜ ከዚያ ወዲያ መጠናቀቁን በመሃላው ያረጋግጣል።

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

 

 

የራዕይ 10 መልአክ ሚስጥሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው ወደ ምድር የሚወርደው

 

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ሚስጥር ለመግለጥ አይደለም።

አስተውሉ፤ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ታላቁ ደመና ፎቶግራፍ ተነሳ፤ ይህም ቀን የአደን ወቅት ከመከፈቱ በፊት ነበረ። ስለዚህ ደመናው ፎቶግራፍ በተነሳ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ለአደን አልወጣም ነበር። የአደን ወቅት የተከፈተው ማርች 1 ቀን ነው። ከዚያ በኋላ ማርች 8 ቀን ሰባት መላእክት ለወንድም ብራንሐም ተገለጡና ሰባቱን ሚስጥራት የመግለጥ ተልዕ ኮ ሰጡት። የአደን ወቅት ማርች 10 ቀን ተዘጋ። ከሳምንት በኋላ ከማርች 17 ቀን ጀምሮ ሳምንት ሙሉ በተዘጋጁ ተከታታይ ስብሰባዎች አማካኝነት ይህ ተልዕኮ ተፈጸመ። ከዚያ በኋላ ለ3 ዓመታት በተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውስጥ ያሉ ተጨማሪ ሚስጥራት ተገለጡ። እነዚህ መገለጦች ያቆሙት ዲሴምበር 1965 ወንድም ብራንሐም በአደጋ ሲሞት ነው። ስለዚህ ለንጥቀት እንድንዘጋጅ የሚያበቁን የተጻፉት ሚስጥራት በሙሉ ተገልጠዋል። ከዚህም የተነሳ 7ቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ሊያሰሙ የሚችሉት ከ1965 በኋላ ነው። በተጨማሪም የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር ሊወርድ የሚችለውም መልእክቱ በ1965 ከተጠናቀቀ በኋላ ብቻ ነው።

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ሚስጥራትን ለመግለጥ አይደለም።

መልአኩ ወደ ምድር የወረደው በእጁ የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ ማለትም ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ነው። ስለዚህ ደመናው መልአኩ አይደለም።

ደመናው በውስጡ የያዘው ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ለ28 ደቂቃ ሰማይ ላይ ተንሳፍፈው የነበሩ መላእክትን ነው፤ እንጂ አንድ መልአክ አይደለም።

ደመናው ሰባቱ ማሕተሞች ከመገለጣቸው በፊት ታይቶ ጠፋ።

ደመናው በተገለጠ ጊዜ ወንድም ብራንሐማ ከፍላግስታፍ 200 ማይልስ ርቃ በምትገኘው ታክሰን ከተማ ውስጥ ነበር።

ሌሎቹ መላእክት የምድር መልእክተኞች የሆኑ ሰዎች ናቸው። ይህኛው መልአክ ግን … ይህኛው ግን ከምድር አይደለም የመጣው።

ይህኛው የመጣው ከሰማይ ነው፤ ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተጠናቅቀዋል።

ሚስጥራቱ ሲጠናቀቁ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከእንግዲህ አይዘገይም” ከዚያም ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

መልአኩ የሚወርደው ሚስጥራቱ ስለተገለጡ ነው።

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።”

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”።

ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ።

ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

“ሻሎም” ጃንዋሪ 19 ቀን 1964

 

መልአኩ ማለትም ክርስቶስ በራዕይ ምዕራፍ 10 በተጠቀሰው ኃያል መልአክ መልክ ሲገለጥ ሙታንን ለማስነሳት ወደ ምድር ይመጣል። በዘመናት ውስጥ ሙታን ሁሉ በተቀበሩበት በምድር እና በባሕር ላይ ይቆማል። ይህም እርሱ በመጨሻው ጠላት በሞት ላይ የሚቀዳጀው የመጨረሻው ድል ነው። ይህ የአንበሳው ግሳት ነው፤ እርሱም የሕይወት ንጉስ ነው።

መልአኩ ሚስጥራትን ለመግለጥ አይመጣም። ሚስጥራቱን 7ኛው መልአክ ገልጧቸዋል።

ከትንሳኤ በፊት መልእክቱ መምጣት አለበት፤ መልእክቱም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንደምታምነው ተመሳሳይ እምነት እንዲኖረንና ለትንሳኤ እንድንዘጋጅ ይረዳናል። የመጀመሪያዎቹ አማኞች የሚያምኑትን ካመንን ብቻ ነው እነርሱን ልናያቸው የምንችለው። በመጨረሻ የሚታጨደው ፍሬ መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ነው።

 

 

ልብ በሉ፤ ራዕይ 5፡1። እስቲ አሁን ይህን ስሙ። በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው በቀኝ እጁ ውስጥ በውስጡ የተጻፈበት መጽሐፍ አየሁ … (ጽሕፈቱ ከውስጥ በኩል ነው ያለው) … እና በጀርባው በኩል በሰባት ማሕተሞች ታትሟል።

ጽሕፈቱ ከመጽሐፉ ውስጥ ነው ያሉት ነገር ግን በጀርባው ላይ ደግሞ ሰባት ማሕተሞች ታትመውበታል፤ እነዚህም ማሕተሞች መጽሐፉ ውስጥ የሉም። አሁን የሚናገረው ባለ ራዕዩ ዮሐንስ ነው። አስታውሱ፤ መጽሐፉ ውስጥ አይደለም የተጻፈው። “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፈው ሚስጥር በሙሉ ይፈጸማል።” በዚያ ቀን ሚስጥሩ ሁሉ ይፈጸማል። የምናገረው አሁን ገባችሁ? እየተከታተላችሁኝ ነው?

ከዚያ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጻፉት ሰባቱ ድምጾች የሚገለጡበት ጊዜ ይመጣል።

መጽሐፉ ሲጠናቀቅ አንድ ነገር ብቻ ይቀራል፤ እርሱም በመጽሐፉ ጀርባ የተጻፉትና ዮሐንስ እንዳይጽፍ የተከለከለው ሰባቱ ሚስጥራዊ የነጎድጓድ ድምጾች ናቸው

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?”

 

ሰባተኛው መልአክ የተጻፉትን ሚስጥራት በሙሉ ይገልጣቸዋል።

ደግሞም ያልተጻፉ ሰባት ማሕተሞች አሉ (እነርሱም 7ቱ ነጎድጓዶች ናቸው)

መጀመሪያ የ7ኛው መልአክ መልእክት - ይህም ክርስቶስ የተገለጠው ቃል ሆኖ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣቱ ሲሆን ዓላማው እኛን ወደ ቀደመችዋ ቤተክርስቲያን ትምሕርት ሊመልሰን ነው።

መጽሐፉ ሲጠናቀቅ፤ የተጻፉት ሚስጥራት ሲገለጡ ክርስቶስ እንደ ራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ሆኖ ይመጣና ሙታንን ያስነሳል።

ከዚያ በኋላ 7ቱ ነጎድጓዶች ቤተክርስቲያንን ሁሉ ክርስቶስ በሥጋዊ አካሉ ተገልጦ ለሚመጣበት ለዳግም ምጻቱ ለማዘጋጀት ድምጻቸውን ያሰማሉ።

ከዚያ በኋላ ሙሽራይቱ ክርስቶስን በአየር ላይ ልትቀበለው ትነጠቃለች።

መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት ከሚገለጡት ሚስጥራት አንዱ ይህ እንደሚሆን ተናግሯል። መንፈሳዊ ዝሙት የሚፈጽሙ ፕሮቴስታንቶች በሰው ሰራሽ አስተምሕሮዋቸውና በአመጻ በተሞሉ ጽዋቸው ብዙ ሰዎችን ወደ ስሕተት ይመራሉ፤ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከተሞላውና በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ከሚታየው የእግዚአብሔር ኃይል እየራቁ እንዲሄዱ ያደርጋሉ።

ይህ እውነት ከሆነ እግዚአብሔር ይደግፈዋል፤ ደግሞም እግዚአብሔር ደግፎ አሳይቷል፤ ወደፊትም ይደግፋል። ነገር ግን ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ ቃሉ ይጠናቀቃል

ስለዚህ አንድ የቀረ ነገር ብቻ አለ። እርሱም አሁን የማናውቀው የሰባቱ ነጎድጓዶች ንግግር ነው፤ ነጎድጓዶቹም ድምጻቸውን ያሰሙት በከንቱ አይደለም። እግዚአብሔር ያለ ዓላማ ለጨዋታ ብሎ የሚያደርገው ነገር የለም። እኛ ልንቀልድ እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን አይቀልድም። በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉም ነገር “አዎን እና አይደለም” ነው። እግዚአብሔር በጭራሽ አይቀልድም። እርሱ ሁልጊዜ ሲናገር እውነቱን ከልቡ ነው የሚናገረው።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

ቃሉ ሲጠናቀቅ ሚስጥራቱ ሁሉ ይገለጣሉ። ከዚያ በኋላ የሚቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ያውም ሰባቱ ነጎድጓዶች።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በመጨረሻው ቀን መልእክተኛ እንደሚመጣ ተነግሮናል፤ እርሱም ያልተቋጩ ትንንሽ ጉዳዮችን ሰብሰብ አድርጎ ይቋጫቸዋል። ከዚያም ይህ መልአክ ድምጹን በሚያሰማበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል፤ ይህም መልአክ የምድር መልእክተኛ ነው። ከዚያም አንድ መልአክ ከሰማይ ይመጣል፤ ሲመጣ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ በራሱ ላይ ቀስተ ደመና አድርጎ ከዚያ ወዲያ ጊዜ እንደማይኖር ይምላል፤ መልአኩ መሃላ ይፈጽማል። ይህም ነገር እየተፈጸመ ስናይ በጣም ትሁት ልንሆን ይገባናል።

“ተጽእኖ” ጃንዋሪ 12 ቀን 1963

ሚስጥሩ ሲጠናቀቅ ከሰማይ የሚወርድ አለ - እርሱም መልአኩ ነው።

የሆነ ሰው እንዲህ አለ፡- “ወንድም ብራንሐም፤ መቸም ሰባቱ ማሕተሞች የሚገለጡት በመጨረሻው ቀን ነው፤ እንዴት ነው ወደ እግዚአብሔር የምንቀርበው፤ ትልቅ ሚስጥር አይደለምን?” በፍጹም፤ ሊሆን አይችልም።

“ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቃል የሚያጎድል ወይም አንድም ቃል የሚጨምርበት ሰው ቢኖር ከሕይወት መጽሐፍ ውስጥ እድሉ ይጎድልበታል።” ይህ ምንድነው፤ እዚያ በፊት የጎደለውን ነገር የሚሞላ መገለጥ ነው። አስቀድሞ እዚህ ተጽፏል። እዚህ ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ አስቀድሞ የተጻፈውን ለመግለጥ ነው። አያችሁ? ምክንያቱም ከውስጡ አንድም ነገር ማጉደል አትችሉም፤ አንዳችም ልትጨምሩበት አትችሉም።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፉት ሰባቱ ማሕተሞች በ7ኛው መልአክ አማካኝነት ሲገለጡ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ሚስጥራትን ሁሉ ያብራራሉ።

ያልተጻፉትን ሚስጥራት አይገልጡም።

ደግሞም ስለ ታላቁ መከራ ሁሉንም ነገር አይገልጡም። ያ መገለጥ አይሁዶችን ነው የሚመለከተው።

ቤተክርስቲያንን የሚመለከቱ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በኋላ የጠፉባትን የተጻፉ ሚስጥራትን ይገልጣሉ።

የጨለማው ዘመን ካለፈ በኋላ የተሃድሶ መሪዎች እንደ መዳን፣ ቅድስና፣ የወንጌል ስርጭት፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና የመሳሰሉ ሚስጥራትን ተረድተው ነበር። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወሩ አንዳንድ ሚስጥራትን መፍታት አልቻሉም ነበር፤ ለምሳሌ ሐጥያት እንዴት እንደተጀመረ፣ ኢየሱስ ሁሉን ቻይ ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን፣ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ምሳሌዎችን፣ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ፣ ወዘተ። የጴንጤ ቆስጤ ተሃድሶ መሪዎች ያልተገለጡላቸው ሚስጥራት እነዚህ ናቸው።

ጊዜ ወደ መጠናቀቂያው ሲደርስ እናያለን። ከጥቂት ጊዜ በኋላ እግሩን በምድርና በባሕር ላይ አድርጎ የሚቆመው መልአክ እንደሚመጣና እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ከአሁን በኋላ ጊዜ እንደማይኖር እንደማይዘገይ ለዘላለም በሚኖረው ስም እንደሚምል እንጠባበቃለን። በዚያ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር እንደሚጠናቀቅ ተጽፏል። አባት ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ባለ ሶስት ድርብ ሚስጥር እንደተገለጠልን ገብቶናል። ደግሞም ከሰማይ የመጡትን እነዚያን ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች እየተጠባበቅን እንደሆንን ገብቶናል፤ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ይህ እውነት በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ታትሟል።

“ታላቅ ምልክት” ጁን 24 ቀን 1962

ሚስጥራቱ ሲጠናቀቁ ከዚያ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ

 

ስለዚህ አሁን ድምጹን ማሰማት ሲጀምር ሚስጥሩ ይፈጸማል። አሁንም ልብ በሉ። ከዚያ በኋላ በሰባት ማሕተም የተዘጉት የራዕይ ምዕራፍ 10 ድምጾች የሚገለጡበት ጊዜ ይመጣል። ገብቷችኋል? የመጽሐፉ ሚስጥራት ሁሉ ሲጠናቀቁ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሁሉም ሚስጥራት ይፈጸማሉ እንዳለው …

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

 

51-5 አላውቅም። ጊዜው ደርሷልን? ሚስጥሩ በሙሉ ተጠናቅቋል? የመለከቱ ድምጽ በስፍራ ሁሉ ተሰምቷል? በውኑ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ሊያሰሙ ሚስጥራቸውን ሊገልጡና ጌታ ለራሱ ለሰበሰባቸው ጥቂት ሰዎች እርሱ ሲመጣ በአየር ላይ ይቀበሉት ዘንድ የመነጠቅን እምነት ሊሰጡዋቸው እየተዘጋጁ ናቸውን፤ እነዚህ መላእከት ሲመጡ ወዲያው እንለወጣለን፤ ከመቅስፈት፣ በዓይን ጥቅሻ እንለወጥና በጌታ ሆነው ካንቀላፉት ጋር ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል አብረን እንነጠቃለን።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

ይህን የቤዛነት መጽሐፍ ብዙዎች ሙሉ በሙሉ እንደማያስተውሉት እናውቃለን፤ በስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ሰዎች ሲመረምሩት ነበሩ ነገር ግን በስተመጨረሻ ሰባተኛው መልአክ ሚስጥሩን መግለጥ ሲጀምር እነዚህ ሰዎች ሁሉ ነካክተው የተዉትን በአንድነት ሰብስቦ ይቋጫል። ሚስጥራቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል መልክ ይወርዳሉ ፤ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መገለጥ በሙሉ ይገለጣል።

[ምጻት 1. ሚስጥራቱ ከሰማይ የሚወርዱት በሰባተኛው መልአክ አማካኝነት እንዲገለጡ ነው]።

ከዚያ በኋላ መለኮት እና ሌሎች ነገሮችን የተመለከቱ ሚጥራት በሙሉ ይገለጣሉ። ሚስጥራት በሙሉ፡ የእባቡ ራስ፣ እና ሌላም የሚገለጥ ነገር ሁሉ ይገለጣል።

በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ድምጽ ሲሰማ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሲመረምሩቸው የነበሩ ያልተቋጩ ነጥቦች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ይቋጫሉ። ማሕተሞቹ ሲፈቱ እና ሚስጥራቱ ሲገለጡ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይወርዳል፤ መልእክተኛው ማለትም ክርስቶስ ይመጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ ያሳርፋርል፤ ከራሱም በላይ ቀስተደመና ይታያል።

[ምጻት 2. መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ማሕተሞቹ ከተፈቱና ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ነው]

በዚህ ምጻት ጊዜ ይህ ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ መሆኑን አስታውሱ።

[የትኛው ምጻት? ምጻት 1 - ሚስጥራቱ? ወይስ ምጻት 2 - መልአኩ?]

“በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት” ማርች 17 ቀን 1963

 

ነገር ግን ወንድም ብራንሐም ስለ ሁለት ምጻቶች ተናግሯል።

አንደኛው የሚስጥራቱ መምጣት ሲሆን ከዚያ በኋላ ደግሞ የመልአኩ መምጣት።

መልአኩ የሚመጣው ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ እና ሚስጥሩ ተገልጦ ሲጠናቀቅ ብቻ ነው።

ክርስቶስ ሙታንን ለማስነሳት እንደ ብርቱው መልአክ ሆኖ ከመምጣቱ በፊት መጀመሪያ ክርስቶስ በተገለጠው ቃል መሰረት መምጣት አለበት።

መልአኩ ማሕተሞቹን የመግለጥ ተልዕኮ ሊሰጥ አይመጣም።

ይህንን ተልዕኮ ለመስጠት ሰባት መላእክት ማርች 8 ቀን 1963 መጥተዋል - የመጣው አንድ መልአክ አይደለም።

መልአኩ ሲወርድ እንደ ደመና አይደለም የሚመጣው። ፌብሩዋሪ 29 ቀን 1963 የአደን ወቅት ማርች 1 ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ደመናው ሰማይ ላይ ከፍ ብሎ ለ28 ደቂቃ እየተንሳፈፈ ፎቶግራፍ ተነስቷል

ማርች 8 ቀን ወንድም ብራንሐም አደን ላይ ሳለ በጠዋት ሰባት መላእክት በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፉትን ሰባቱን ማሕተሞች እንዲገልጥ ትዕዛዝ ሊሰጡት ወደ እርሱ መጡ

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን መግለጥ የጀመረው ከማርች 17-25 ቀን 1963 ነው።

መገለጡም ለወንድም ብራንሐም በጣም ጠለቅ ያለ መረዳትን ስለሰጠው ብዙ ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ ሚስጥራትን መግለጥ ችሏል። ይህም የተጻፉት ሚስጥራት መገለጥ ዲሴምበር 1965 ጌታ ወደ ራሱ እስኪሰበስበው ድረስ ቀጥሎ ነበር።

ስለዚህ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ሊመጣ የሚችለው ሚስጥራቱ ከተጠናቀቁ ከ1965 በኋላ ነው።

አስተውሉ፤ መልአኩ የሚወርደው ማሕተሞቹ ከተፈቱ ወይም ከተገለጡ በኋላ ብቻ ነው።

በየትኛው ምጻት (በሚስጥራቱ መምጣት ወይም በመልአኩ መምጣት) ጊዜ ነው ሰባተኛው መልአክ ምድር ላይ የሚገኘው?

ወንድም ብራንሐም ይህን ሃሳብ በቀጣዩ አንቀጽ ውስጥ ያብራራልናል፡-

አሁንም ወደ 10ኛው ምዕራፍ ተመልሶ ከሚመጣው ጊዜ በኋላ ሚስጥራቱ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይናገራል፤ ማሕተሞቹም ይፈታሉ ከዚያም በኋላ ዘመን እንደማይኖር ይታወጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ሁሉ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል”።

በጣም ቅርብ ነን ደርሰናል። ይህ እውነት ነው።

“በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ልዩነት” ማርች 17 ቀን 1963

መልአኩ የሚመጣው ሚስጥራቱ ከተጠናቀቁ በኋላ ነው።

ይህ ስብከት የተሰበከው ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከሁለት ሳምንት ከግማሽ በኋላ ነው፤ በዚያ ጊዜ ወንድም ብራንሐም እንዲህ እያለ ነበር፡- “መልአኩ ሊገለጥ ጊዜ ቀርቧል”።

በግልጽ መረዳት እንደምንችለው ደመናውን እንደ መልአኩ አልቆጠረውም።

“ቀርቧል” ይላል። መልአኩ ወደፊት በቅርብ እንደሚመጣ እየተጠባበቀ ነበር።

ስለዚህ ደመናው መልአኩ አልነበረም።

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን እየገለጠ ሳለ መልአኩ አልመጣም።

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ብቻ ነው።

ሚስጥራቱ ወደ ምድር በሚወርዱበት ጊዜ ማለትም ክርስቶስ በተገለተው ቃል መልክ በሚመጣበት ጊዜ ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ መገኘት አለበት።

ሙሽራይቱ ተነጥቃ ወደ ሰማይ ለመሄድ የሚያስፈልጓትን ሚስጥራት ካብራራ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ማለትም ክርስቶስ በመልአኩ መልክ ወደ ምድር የሚወርደው።

ይህ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር የሚወርደው ለምንድነው?

የሙታንን ትንሳኤ ለማከናወን ነው።

ትንሳኤ ገና ወደፊት የሚፈጸም ክስተት ነው። ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ደመናው ሲገለጥ ትንሳኤ አልተፈጸመም።

ወደ ጨለማ ዋሻ ውስጥ እየገባን ነው፤ እርሱም የሞት ዋሻ ነው። ሁሉም ሰው ወደዚህ ዋሻ ውስጥ ይገባል። በያንዳንዱ የልብ ምታችን ወደዚህ ዋሻ አንድ እርምጃ ቀረብ እንላለን። እኔ ራሴ አንድ ቀን ወደዚህ ዋሻ እገባለው። የመጨረሻዋ የልብ ትርታዬጋ ስደርስ እንደ ፈሪ እየተንቀጠቀጥኩ መግባት አልፈልግም፤ ራሴን በጌታ ጽድቅ መሸፈን እፈልጋለው፤ ጽድቁን ለብሼ ነው ወደዚህ ዋሻ ውስጥ መግባት የምፈልገው፤ እርሱን በትንሳኤ ኃይሉ ላውቀው እፈልጋለው። እነርሱም … መልአኩ ታላቅ ድምጽ ያሰማል፤ መለከቱም ድምጹን ያሰማል፤ በዚያ ጊዜ ከሙታን መካከል ወጥቼ መነሳት እፈልጋለው

“መጠባበቅ” አፕሪል 05 ቀን 1950

ወንድም ብራንሐም ይህ መልአክ ወደ ምድር መጥቶ ሙታንን እንዲያስነሳ ሲጠባበቅ ነበር። ይህም ገና በአገልግሎቱ መጀመሪያ በ1950 ነበር።

 

262 ሁላችንም ድል ነስተናል። በብዙ ጦርነቶች ውስጥ ድል አድራጊዎች ሆነናል። ደግሞም በጣም በቅርቡ ታላቅ ድል እየመጣልን ነው። የድል ቀናችን የእግዚአብሔር ልጅ ሰማያትን ቀዶ በመላእክት አለቃ ድምጽ ሲመጣ በቅርቡ ይገለጣል፤ ጌታም ዳግም ይመጣል። መቃብሮች ይከፈታሉ፤ ሙታንም ከመቃብሮቻቸው ወጥተው ይሄዳሉ

“የድል ቀን” አፕሪል 21 ቀን 1963

በ1963 ደመናው እየሄደ ሳለ ፎቶግራፍ ከተነሳ ከሁለት ወራት በኋላ ወንድም ብራንሐም መልአኩ መጥቶ ሙታንን እንዲያስነሳ ሲጠባበቅ ነበር። (ክርስቶስ በመልአክ መልክ ሲገለጥ መጠሪያው የመላእክት አለቃ ነው።)

ሶስት ነገሮች ይሆናሉ። ድምጽ … ጩኸት፣ ድምጽ፣ መለከት መሰማት አለበት ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት። ስለዚህ ጩኸት … ኢየሱስ ወደ ምድር በሚወርድበት ጊዜ ሶስቱንም የሚያደርገው እርሱ ነው።

ጩኸት፤ ምንድነው ጩኸቱ? ጩኸቱ ወደ ምድር ሁሉ የሚሄደው መልእክት ነው፤ መጀመሪያ ሕያው የሆነው የሕይወት እንጀራ ሙሽራይቱን ይወልዳታል።

እርሱ ወደ ምድር መውረድ ሲጀምር የመጀመሪያው የሚመጣው ነገር ታላቅ ድምጽ ወይም ጩኸት ነው። ጩኸቱ ምንድነው? ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ የሚያደርግ ድምጽ ነው።

የመጀመሪያው ነገር የዚህ ድምጽ መሰማት ነው። የመጀመሪያው ነገር መለከት ወይም ድምጽ ነው … ጩኸት፤ ከዚያ ወዲያ ድምጽ፤ ከዚያም መለከት።

ጩኸት፡ መልእክተኛ ሕዝቡ እንዲዘጋጁ ያደርጋል።

ሁለተኛው የትንሳኤ ድምጽ ነው፡ ዮሐንስ 11፡38-44 ውስጥ የተሰማው አላዛርን ከሙት የቀሰቀሰው ያ ድምጽ እራሱ ነው።

ሙሽራይቱ እንድትዘጋጅ ማድረግ፤ ከዚያም የሙታን ትንሳኤ፤ አያችሁ፤ ከዚያ አብሮ በንጥቀት መሄድ። አሁን ሶስቱን የሚፈጸሙ ነገሮች ልብ በሉ። ቀጣዩ ምንድነው? መለከት። ድምጽ … ጩኸት፤ ድምጽ፤ መለከት።

ሶስተኛው ነገር መለከት ነው። ሁልጊዜ በመለከት በዓል መለከት ሲነፋ ሕዝቡ የዓል ድግስ ለመብላት ይሰበሰባሉ። ይህም በሰማይ የሚደገሰው የሙሽራይቱ እና የበጉ ሰርግ እራት ድግስ ነው። አያችሁ?

መጀመሪያ የሚመጣው መልእክቱ ነው። መልእክቱም ሙሽራይቱን ይሰበስባታል። ቀጣዩ ደግሞ ያንቀላፋችው ሙሽራ ከሙታን የምትነሳበት ነው፤ በሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ የሙሽራይቱ አካላት በሕይወት ካሉት ጋር አብረው ይነጠቃሉ። መለከቱ፣ በሰማይ የሚደረገው ድግስ። ወዳጆቼ ሆይ የሚፈጸመው ይህ ነው።

“ንጥቀት” ዲሴምበር 4 ቀን 1965

በሞተበት ወር በታሕሳስ 1965 ወንድም ብራንሐም ትንሳኤ ገና ወደፊት እንደሚሆን ይጠባበቅ ነበር። ይህ እምነቱ በአገልግሎት ዘመኑ ሁሉ ሳይለወጥ ቆይቷል።

ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ወንድም ብራንሐም የአንድ ነጎድጓድ ድምጽ ጩኸት ድምጽ እና የትንሳኤ ድምጽ ሲጠባበቅ ነበር።

 

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

ጩኸቱ ማለት ወንድም ብራንሐም ሚስጥራቱ ወደ ምድር በወረዱ ጊዘ ሲቀበላቸው አይደለም።

ጩኸቱ ማለት ሙሽራይቱ ሚስጥራቱን ለራሷ መረዳተ ስትችልና ዋና ዋና የሆኑትን ጥቅሰች በራሷ ማገጣጠም ስትች ነው።

 

ጥያቄ 5 - ሰባቱ ነጎድጓዶች እና ሰባቱ ማሕተሞች በመካከላቸው የሚያገናኛቸው ምንድነው?

የኢየሱስ ሰባቱ ነጎድጓዶች በመጨረሻው ዘመን ነበር የመጡት። ራዕይ 10፡3-4፡- እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

እነዚያ ነጎድጓዶች የተናገሩትና ማንም የማያውቀው ነገር ምንድነው። እኛ ግን ማወቅ ያስፈልገናል። የዚህንም ሚስጥር መገለጥ ማግኘት የሚችለው ነብይ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያስቀመጣቸውን ሚስጥራት በነብያት አማካኝነት እንጂ ሌላ የሚገልጥበት መንገድ የለውም። ቃሉ ሁልጊዜ በነብይ ነበር የሚመጣው ወደፊትም በነብይ ነው የሚመጣው።

“የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን” የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9 በ1965 ታተመ

የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚለውን መጽሐፍ ያሳተመው ወደ አገልግሎቱ መጨረሻ ነበረ። በዚያ ጊዜ እንኳ “የነጎድጓዶቹ ሚስጥር” ምን እንደሆነ አላወቀም። “ማንም አያውቅም”።

ነብይ እንደመሆኑ መጠን ስለ ነጎድጓዶቹ መገለጥ ማግኘት ነበረበት ነገር ግን ምንም አላወቀም ምክንያቱም የነጎድጓዶቹ መልእክት ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ነው የተጻፈው።

ይህ እንዴት ሌሆን ይችላል?

ከሰባቱ ሚስጥራት ጋር በቁጥር የሚመሳሰሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ተገልጠዋልን? በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠው ነገር ግን ለእኛ እስከ አሁን ድረስ እንደ ነጎድጓድ አልተገለጡልንምን?

የለም፤ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠዋል፤ የነጎድጓዶቹ ትርጉም በማሕተሞቹ ውስጥ ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች እንዲገልጡ … ድምጻቸውን ያሰሙት ሰባቱ ነጎድጓዶች ነገር ግን የተናገሩትን ቃል ማንም ያልሰማቸው … ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል አውቋል፤ ነገር ግን እንዳይጽፍ ተከልክሏል። ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- “ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን የሰባቱ ነጎድጓዶች ሰባት ሚስጥራት ይገለጣሉ።” ሰባተኛውም መልአክ የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ነው። አያችሁ?

ጥያቄዎችና መልሶች 4 ሲኦዲ ኦገስት 30 ቀን 1964

 

ስለ ነጎድጓዶቹ የተቀበለውን መገለጥ እንድናገኝ ስለ ሰበቱ ማሕተሞች በሰበከ ጊዜ ምን ብሎ እንደተናገረ ማየት አለብን።

ይህ ወሳኝ ፍንጭ ነው።

ወንድም ብራንሐም ነጎድጓዶቹ ስለ ምን እንደሚናገሩ ገልጧል።

ምን እንደሚያደርጉ፤ ወይም ዓላማቸው ምን እንደሆነ ማለት ነው፤ እንጂ ምን ብለው እንደተናገሩ አይደለም።

የነጎድጓዶቹን ዓላም በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ገልጧል፤ ነገር ግን ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ አልነገረንም፤ የነጎድጓዶቹን ቃል አልነገረንም።

 

የዚያ ማሕትም አንዱ ሚስጥር፤ ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ምንም እንከን አይወጣላቸውም፤ ምክንያቱም ማንም ስለ ነጎድጓዶቹ ቃል አያውቅም፤ ምክንያቱም ምንም አልተጻፈም። ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ላይ ደርሰናል ማለት ነው። በእርግጥ ደርሰናል።

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ ምንም የምናውቀው ነገር የለም። ስለ ሰባተኛው ማሕተም አንዳች የምናውቀው ነገር የለም። ሁለቱን የሚያገናኛቸው ይህ ነው። የማይታወቁት ሰባት ነጎድጓዶች ወደፊት ያልታወቀውን 7ኛውን ማሕተም ይገልጡታል፤ እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

 

ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም

የነጎድጓዶቹን መገለጥ (ዓላማቸው ምን እንደሆነ) ልናገኝ እንችላለን፤ እነደዚህም ሆኖ ግን ምን ብለው እንደተናገሩ ስለማናውቅ ነጎድጓዶቹ ለእኛ ሚስጥር ሆነው ቀርተዋል።

ይህ በሰባት ማሕተሞች የታተመ መጽሐፍ የሚገለጠው ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተጻፉት በሰባቱ ነጎድጓዶች ዘመን ነው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ነገር ዝጋው አትመው፤ አትጻፈው። የማናውቀው ነገር ይህ ነው። ይህ ገና ሊገለጥ ያለ ነገር ነው፤ እነዚያ ነጎድጓዶች የተናገሩት ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም

“በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት” ማርች 17 ቀን 1963

ከሰባቱ ማሕተሞች ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፈዋል፤ ስለዚህ ሊገለጡ ይችላሉ።

ነጎድጓዶቹ የተናገሩዋቸው ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም፤ ስለዚህ ሊገለጥ አይችልም።

በ7ቱ ነጎድጓዶች እና በ7ቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት ይህ ነው።

ደግሞ ሰባተኛውም ማሕተም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። ሙሉ በሙሉ ዝምታ ነው። ምንም ፍንጭ አልተሰጠንም።

ስለዚህ ባልተጻፈው ሰባተኛ ማሕተም እና ባልተጻፉት ሰባት ነጎድጓዶች መካከል የሚያገናኝ ነገር አለ።

በሰባት ማሕተሞች ታትሞ ተዘግቷል

ይህም ከሰባቱ ነጎድጓዶች የተለየ ነገር ነው።

“በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ክፍተት” ማርች 17 ቀን 1963

ያልተጻፉት ነጎድጓዶች ሰባቱ ማሕተሞች አይደሉም ግን የነጎድጓዶቹ ዓላማ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጧል።

ነገር ግን አሁንም ሚስጥሩ እንደተጠበቀ ነው፡- ይህም ነጎድጓዶቹ የተናገሩት ቃል ነው።

ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው (ዝምታ ብቻ) ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱ ሚስጥራት ሁሉ ታላቅ የሆነውን ሚስጥር በተመለከተ ነው፤ ይህም ሚስጥር የጌታ ምጻት ነው። ስለዚህ ሚስጥር አንዳችም የምናውቀው ነገር የለም። ስለዚህ ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ የማናውቅ ከሆነ ነጎድጓዶቹ ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዙ መሆን አለባቸው።

የነጎድጓዶቹ ዓላማ ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ ነው ምክንያቱም ነጎድጓዶቹ ከዚህ ከጊዜ ቀጠና እንወጣ ዘንድ አካላችን እንዴት እንደሚለወጥ ነው የሚያሳዩን።

ስለዚህ በውስፁ የተጻፈበት መጽሐፍ የዛኔ ይጠናቀቃል፤ እነዚህ ሚስጥራት ሁሉ የሚገለጡት ከተጠናቀቁ በኋላ ነው።

ስለዚህ በደምብ እርግጠኞች እንድትሆኑ እንደገና ላንብብላችሁ። ተመልከቱ።

ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ (የመጨረሻው መልአክ) ድምጹ በሚሰማበት ዘመን … የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል

የእግዚአብሔር ሚስጥር ምንድነው … ከሚስጥራቱ ውስጥ አንዱ ምንድነው? ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 3 እንዲህ ብሎ ጻፈ፡- “እግዚአብሔርን የመምሰል ሚስጥር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው … በሥጋ ተገለጠ።” በዓይናችን አየነው፤ በእጆቻችን ዳሰስነው፤ በክብር አረገ። እግዚአብሔር በመላእክት ታለ በምድርም ጸደቀ።

በእርግጥ ታላቅ ሚስጥር ነው፤ ነገር ግን ሚስጥሩ ተገልጧል፤ እርሱም አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት አምላክ አይደለም፤ አንድ አምላክ በሶስት የአገልግሎት ቢሮዎች ነው። በሙሴ ጊዜ በአባትነት ተገለጠ፤ በልጅነት በክርስቶስ ተገለጠ፤ በመንፈስ ቅዱስ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ዘመን ተገለጠ፤ አንዱ አምላክ በሶስት ዘመናት ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ተገለጠ እንጂ ሶስት አምላክ አይደለም።

ሚስጥሩ አሁን ተጠናቅቋል። መጽሐፍ ቅዱስ ሚጥሩ እንደሚጠናቀቅ ተናግሯል።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት የእግዚአብሔር መገለጦች ናቸው። ከአይሁዶች በላይ፣ ከአይሁዶች ጋር፣ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ።

1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ

እግዚአብሔር መጀመሪያ በክርስቶስ ስጋ ውስጥ ተገለጠ፤ ቀጥሎ ደግሞ የቤተክርስቲያን አካል በሁሉ ክርስቲያኖች ስጋ ተገለጠ።

እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን እንደ አብ የተገለጠ ጊዜ ከአይሁዳውያን በላይ ነበረ።

 

 

እግዚአብሔር እንደ ልጅ ወይም ወልድ ሆኖ ሲገለጥ ከአይሁዳውያን ጋር ነበረ። አማኑኤል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር። የመለኮት ሙላት በክርስቶስ ውስጥ ነበረ (ቆላስይስ 2፡9)።

 

 

ዮሐንስ 14፡17 እርሱም … የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።

 

 

ወንድም ብራንሐም የተጻፉትን ሚስጥራት ገለጠ፤ ይህም “በውስጡ የተጻፈበት መጽሐፍ” ነው።

እነዚህም ለዳግም ምጻት ለመዘጋጀት የሚጠቅሙን የተጻፉ ሚስጥራት ናቸው።

የመለኮትን ሚስጥር ገለጠ።

ስለዚህ ይህ መልአክ ተናግሮ ሲያበቃ በውስጡ የተጻፈበት መጽሐፍ የዛኔ ይጠናቀቃል። ስለዚህ አሁን ይህን አስተውሉ። የሰባተኛው መልአክ መልእክት ሲጠናቀቅ የመለኮት ሚስጥር፣ የእባቡ ራስ ሚስጥር፣ የሌሎች ነገሮች ሁሉ ሚስጥራት፣ ዘላለማዊ ልጅነት እያሉ የሚያወሩት ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል። ዘላለም መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የሌለው ከሆነ እንዴት እርሱ ዘላለማዊ ልጅ ሊሆን ይችላል። ልጅ ማለት የተወለደ ማለት ነው። ከተወለደ እንዴት ዘላለማዊ ልጅ ይሆናል?

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፈው የተሰወሩ ሚስጥራትን ለምሳሌ የመለኮት ሚስጥር፣ የእባቡ ዘር ሚስጥርን ገለጠ። እነዚህ ሁሉ የተሃድሶ መሪዎችን ግራ አጋብተው የነበሩ ሚስጥራት ናቸው።

አስተውሉ የተጻፈው መጽሐፍ … ይህ መልአክ እነዚህን ሁሉ ያልተቋጩ አገልግሎት ሉተር የታገለባቸውን፣ ዌስሊ የታገለባቸውን፣ እና ፔንቲኮስታሎች የታገሉባቸውን ሁሉ ሲያጠናቅቅ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አንድ ደግሞ የሚመጣ አለ፤ ማለትም ይህ መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ውስጥ እነዚህ ሚስጥራት ሁሉ … ኢየሱስ ብቻ ብለው የሚያስተምሩት አንድ አምላክ የሚሉት ትምሕርት፣ እንዲሁም አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ እያሉ የሚያስተምሩት በኒቅያ ጉባኤ የተጀመረው የሥላሴ ትምሕርት ሁሉም አንድ ዓይነት ነው። ሁለቱም ተሳስተዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እውነቱን ገልጦ ይነግረናል

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

 

አስተውሉ፤ ራዕይ 5፡1። ይህን ስሙ።

በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው በቀኝ እጁ ውስጥ በውስጡ የተጻፈበት መጽሐፍ አየሁ … (ጽሕፈቱ ከውስጥ በኩል ነው ያለው) … እና በጀርባው በኩል በሰባት ማሕተሞች ታትሟል

ጽሕፈቱ ከመጽሐፉ ውስጥ ነው ያሉት ነገር ግን በጀርባው ላይ ደግሞ ሰባት ማሕተሞች ታትመውበታል፤ እነዚህም ማሕተሞች መጽሐፉ ውስጥ የሉም። አሁን የሚናገረው ባለ ራዕዩ ዮሐንስ ነው። አስታውሱ፤ መጽሐፉ ውስጥ አይደለም የተጻፈው። “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፈው ሚስጥር በሙሉ ይፈጸማል።” በዚያ ቀን ሚስጥሩ ሁሉ ይፈጸማል። የምናገረው አሁን ገባችሁ? እየተከታተላችሁኝ ነው?

ከዚያ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጻፉት ሰባቱ ድምጾች የሚገለጡበት ጊዜ ይመጣል።

መጽሐፉ ሲጠናቀቅ አንድ ነገር ብቻ ይቀራል፤ እርሱም በመጽሐፉ ጀርባ የተጻፉትና ዮሐንስ እንዳይጽፍ የተከለከለው ሰባቱ ሚስጥራዊ የነጎድጓድ ድምጾች ናቸው።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

ነብዩ መጽሐፉ ውስጥ የነበረውን ጽሕፈት ገለጠው እንጂ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ያሉትን መጽሐፉ ውስጥ ያልተጻፉትን ሰባት ማሕተሞች አልገለጣቸውም።

በመጽሐፉ ጀርባ ወይም የጀርባ ሽፋን ላይ ያሉት ሰባት ማሕተሞች ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸው።

እዚሁ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የተጠቀሱት ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዮሐንስ ራዕይ ሲናገር የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው ብሎ የለምን? መገለጥ ነው ተብሎም ግን በውስጡ አንዳንድ የተሰወሩ ሚስጥራትን ይዟል። ሚስጥሩ ምን ይሆን? ሚስጥሩ ሰባቱ ነጎድጓዶች ውስጥ ነው ያለው። ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ነገር ዮሐንስ ሊጽፈው ነበር ግን ወዲያው ድምጽ ከሰማይ መጥቶ- “አትጻፈው፤ አትመው፤ ዝጋው። ከመጽሐፉ ጀርባ ላይ አኑረው” አለው። ስለዚህ ሊገለጥ ይገባዋል። ሚስጥሩ ያለው እዚህ ውስጥ ነው።

አሁን ግን እነዚህ ነገሮች በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተገልጠውልናል። የዛፍ ፍሬ አለመሆኑ ተገልጦልናል፤ የዛፍ ፍሬ ሳይሆን ወሲባዊ ጉዳይ ነው። መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች ነግሮናል … በዚህ መገለጥ ፊት መቆም የሚችል ማንም አላገኘሁም። በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የትኛውም ሰባኪ በዚህ ሲስማማ አላየሁም። ግን ብዙዎቹን ጠይቄያቸዋለሁ።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የተጻፈበት የዮሐንስ ራዕይ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻው መጽሐፍ ነው።

በዚህ የራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባቱ ነጎድጓዶች ይገኛሉ። እነዚህ ነጎድጓዶች የጌታን ምጻት ሚስጥር ይዘዋል።

ይህም እኛ የማናውቀው ሚስጥር ነው።

የቤተክርስቲያን ዘመናት እና ማሕተሞች የቀሩትም ነገሮች እንዲሁ ናቸው። ማንኛውም ሰው እነዚያን ሰባት ነጎድጓዶች ተረድቻለሁ ሲል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ከሆነ ስሕተት አለበት

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

ነጎድጓዶቹ የሆነ እኛ የማናውቀው ሚስጥር ይዘዋል። ነጎድጓዶቹ የያዙት ሚስጥር ተጽፎ ባይገኝም እንኳ ግን ከተጻፈው ቃል ጋር በሆነ መንገድ መስማማት አለባቸው።

ለምሳሌ ነጎድጓዶቹ 7ቱ የፍጹም ሰው መገለጫዎች ናቸው ብትሉ እንደዚህ ዓይነቱ የነጎድጓዶች መገለጥ የጴጥሮስ መልእክት ውስጥ ተጽፏል። ስለዚህ ትክክለኛ ትርጓሜ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን እነዚህ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች በስተመጨረሻ ንግግራቸውን በሚያሰሙበት ቀን ጴጥሮስ የጻፈውን አይቃረኑም።

 

ጥያቄ 6 - ወንድም ብራንሐም 7ቱ ነጎድጓዶች ምን እንደተናገሩ ገልጧልን?

 

“መች ነው የሚሆነው ወንድም ብራንሐም?” እኔ የት አውቅና። አላውቅም … ያ ማሕተም ሚስጥር የሆነበት አንዱ ምክንያት እስካሁን አለመፈታቱ ነው፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ከዚያም በኋላ ማንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ አልተጻፈም። ስለዚህ ወደ መጨረሻው ዘመን ቀርበናል፤ መጨረሻው ላይ ነን።

“ሰባቱ ማሕተሞች” ማርች 24 ቀን 1963

እባካችሁ ራሳችንን እንግዛ።

ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አናውቅም፤ እርሱም ከክርስቶስ ምጻት ጋር የተያያዘ ታላቅ ሚስጥር ነው፤ እኛም ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አንዳች አናውቅም

ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃላት እናውቃለን ብትሉ ከግምት ማለፍ አትችሉም ምክንያቱም ስለተናገሩት ቃላት አንድም የተጻፈ ማስረጃ የለም።

 

7ተኛው ማሕተም እና 7ቱ ነጎድጓዶች አልጻፉም። የሚያገኛቸው ነገር ሁለቱም ሳይጻፉ መቅረታቸው ነው።

ስለዚህ በሆነ መንገድ ይገናኛሉ። ከትንሳኤ በኋላ በጌታ ዳግመ ምጻት ጊዜ ቤተክርስቲያን ከምድር ወደ ሰማይ ከመነጠቋ በፊት ለንጥቀት እንድንዘጋጅ 7ቱ ነጎድጓዶች በሆነ መንገድ ቃላቸውን ያሰማሉ። ሰባተኛው ማሕተም ከዳግም ምጻት ጋር የተያያዘ ነው።

ይህ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው። ዮሐንስም እንዳይጽፈው ተከልክሏል፤ በምልክት እንኳ መዝግቦ እንዳያስቀምጠው ተከልክሏል። ለምን? በሰማይ ዝምታ የሆነው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሚስጥሩ ሊጋለጥ ይችላል። አሁን አስተዋላችሁ? እንዲህ ሁሉ ታላቅ ከሆነ መካተት ነበረበት ምክንያቱም ሊፈጸም ግድ ነው፤ ነገር ግን ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ …

ሰባት ነጎድጓዶች በተከታታይ ቃላቸውን ተናገሩ … አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት በተከታታይ። ከዚያ የተናገሩትን ሰማያትም ሊጽፉ አልቻሉም፤ የተናገሩትን ሰማያትም ሊያውቁ አልቻሉም፤ በጭራሽ ምክንያቱም ከእነርሱ በኋላ የሚቀጥል ነገር የለም። ከዚያ በኋላ የጸጥታ ጊዜ ነው የሆነው። ይህ ሚስጥር ለመላእክት እንኳ አልተገለጠም። ለምን?

ይህንን ሚስጥር ሰይጣን ቢያገኘው ታላቅ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል። እርሱ አንድ የማያውቀው ነገር አለ። ምንም ነገር በራሱ መተርጎም አይችልም፤ የትኛውንም ስጦታ ኮርጆ ማስመሰል አይችልም (እየተማራችሁ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለው)። ይህንን ሊያውቅ አይችለም። ይህ ሚስጥር ቃሉ ውስጥ እንኳ አልተጻፈም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። መላእክትም ሆኑ የትኛውም ፍጥረት አያውቁትም። ቢያውቁና አንድ ነገር ትንፍሽ ብለው ቢናገሩ ሚስጥሩን ሊያባክኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ ምንም ባለማወቃቸው የተነሳ ምንም መናገር አይችሉም።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ነጎድጓዶቹን በተመለከተ ዮሐንስ ሙሉ በሙሉ ዝምታን መርጧል። በሰማይ ሆነው ሰባተኛው ማሕተም ሲፈታ ያዩ ሁሉ ጸጥ ብለዋል።

እነርሱ በሰማይ እንዳደረጉ እኛም በምድር እናድርግ። ዝመ እንበል።

ሚስጥሩን ብታውቁና ለአንድ ሰው እንኳ ብትገልጡት ታላቅ ጥፋት ታደርሳላችሁ

በጦርነት ወቅት የሰራዊታችሁን ሚስጥር በአደባባይ ብታወጡ በክሕደት ወንጀል ተከስሳችሁ ትረሸናላችሁ።

ስለዚህ እውቀታችሁን ለራሳችሁ ያዙት።

አይሁዶች ይህን ጥያቄ በጠየቁት ሰዓት አስተውላችኋል? ማቴዎች ምዕራፍ 24 ውስጥ የተጻፈውን ትንቢት ከስድስቱ ማሕተሞች ጋር ባነጻጸርነው ጊዜ ሰባተኛው ማሕተም ለብቻው ተነጥሎ እንደቀረ አይታችኋል፤ ምክንያቱም (አያችሁ?) ክርስቶስ እራሱ እንዳለው የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ መላእክቱ እንኳ አያውቁም። የሚገርማችሁ ደግሞ የትም ቦታም አልተጻፈም። እነርሱም ዝም አሉ፤ በዚያን ጊዜ ምንም አልተፈጸመም። መላእክት አያውቁትም።

ጌታ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ይህንን ታላቅ መገለጥ የሚገልጡ ሰባት ነጎድጓዶች አሉ።

ስለዚህ ለእኛ … አምናለው፤ ካላወቅን እና እኛ -- ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ አይታወቅም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ይገለጣል፤ ሊገለጥ በሚገባው ሰዓት ይገለጣል። ስለዚህ እኛ እንድናደርግ የሚጠበቅብን ነገር በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ አክብሮትና ፍርሃት እርሱን ማገልገል እና ማድረግ እንዳለብን የምናውቅን ሁሉ ማድረግ እንዲሁም መልካም የክርስትና ሕይወት መኖር ነው።

ይኸው አሁን ስድስተኛው ማሕተም ተከፍቶልናል፤ አሁን እናየዋለን፤ ሰባተኛው ማሕተም ግን ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ለሕዝብ ሊከፈት እንደማይችል እናውቃለን

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

አንዳንዶች ሕዝብ ማለት ሙሽራይቱ ማለት ነው ይላሉ።

በጉ መጽሐፉን የወሰደው ልክ ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ ጊዜው ሲቀርብ ነው። አስታውሱ ሰባተኛውን ማሕተም ከእኛ ሰውሮታል። አልገለጠልንም። መልአኩ ቀን በቀን የማሕተሞቹን ሚስጥር እየገለጠ ቆሞ ነበር ነገር ግን ያኛውን ትቶ አለፈው። እንዲህ አለ፡- “በሰማይ ዝምታ ሆነ።” ማንም አላወቀም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

“በወኅኒ ያሉ ነፍሳት” ኖቬምበር 10 ቀን 1963

ይፋ የሚደረገው መረጃ ለሕዝብ መልእክት ማሰራጫ ዘዴዎችን በመጠቀም ለሕዝብ እንዲደርስ የሚደረግ መልእከት ነው።

ይህ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ሕዝቡ ማለት እኛ እና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ ማለት ነው።

“ማንም” የሚለው ሙሽራይቱን ያካትታል።

“መች ነው የሚሆነው ወንድም ብራንሐም?” እኔ የት አውቅና። አላውቅም … ያ ማሕተም ሚስጥር የሆነበት አንዱ ምክንያት እስካሁን አለመፈታቱ ነው፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ከዚያም በኋላ ማንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ አልተጻፈም። ስለዚህ ወደ መጨረሻው ዘመን ቀርበናል፤ መጨረሻው ላይ ነን።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ሕዝቡ ማለት ወንድም ብራንሐምንም ይጨምራል። “አላውቅም።”

ይህ በድምጽ የተቀዳ መልእክት የሆነ ቦታ ሄዶ የሆኑ ሰዎች እጅ ውስጥ ቢገባ ከውስጡ ምንም ዓይነት ፍልስፍና እንዳታወጡለት። ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ነገር እግዚአብሔርን ማገልገላችሁን መቀጠል ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ሚስጥር እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ እግዚአብሔር ለዮሐንስ እንኳ እንዲጽፈው አልፈቀደለትም። ሚስጥሩ የተነገረው በነጎድጓዶች ድምጽ ነው፤ እግዚአብሔር ግን … የሚያውቀው ነገር ስለነበረ … እንደሚገለጥ ተስፋ ሰጠን፤ ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ አልተገለጠልንም

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

ስለዚህ አስታውሱ፤ ሰባተኛው ማሕተም ያልተከፈተበት ምክንያት (አያችሁ?) ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ማንም ሊያውቀው ስለማይገባ ነው

ልብ በሉ። አሁንም ልብ በሉ፤ ለመጨረሻው ዘመን መልእክት ይህ ማሕተም ነው የሚገለጠው። ደግሞም ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጧቸዋል፤ ነገር ግን ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አይናገርም። የመጨረሻው ዘመን ማሕተም መከፈት ሲጀምር መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው የሚሆነው

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ልብ በሉ፤ ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም። ስድስት ማሕተሞች ብቻ ናቸው የተፈቱት።

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባተኛው ማሕተም ያገኘው መገለጥ ሰባተኛው ማሕተም ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ ሙሉ ሚስጥር መሆኑን ብቻ ነው። ሰባተኛው ማሕተም ምንን በተመለከተ (ዳግም ምጻትን) እንደሆነ እናውቃለን ነገር ግን ምን እንደሆነ በጭራሽ አናውቅም ምክንያቱም ዝምታን መተርጎም አንችልም።

እግዚአብሔር እነዚህ ሰባት ድምጾ በነጎድጓድ ድምጽ እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት አለው (አያችሁ?) ምክንያቱም … በጉ ማለትም ክርስቶስ መጽሐፉን በእጁ ወስዶ ሰባተኛውን ማሕተም ፈታው። ነገር ግን እንደምታዩት የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም። ነገር ግን እርሱ እንደተናገረው መምጫውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ደግሞ ስለዚህ ባለ ሰባት ነጎድጓድ ሚስጥርም ሊያውቁ አይችሉም። ስለዚህ እንደምታዩት የተያያዘ ነው

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ሰባተኛው ማሕተም ሲከፈት የተገለጠው ማንም ሊያውቀው የማይችል ሚስጥር መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ነው። ስለዚህ በአንድ በኩል ስንረዳው የተከፈተው ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ መሆኑን እንድናውቅ ነው። በሌላ አነጋገር ይህ ሚስጥር ምንን በተመለከተ መሆኑን እናውቃለን።

ነገር ግን በእርግጥ አልተፈታም ምክንያቱም ይህን የተሰወረ ሚስጥር በተመለከተ ምንም አናውቅም።

መች ነው የሚሆነው ወንድም ብራንሐም?” እኔ የት አውቅና። አላውቅም … ያ ማሕተም ሚስጥር የሆነበት አንዱ ምክንያት እስካሁን አለመፈታቱ ነው፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ከዚያም በኋላ ማንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ አልተጻፈም። ስለዚህ ወደ መጨረሻው ዘመን ቀርበናል፤ መጨረሻው ላይ ነን።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

ዛሬ ይህን ያህል ነው መረዳት የቻልነው፤ ምክንያቱም የቀረው በሙሉ ተገልጧል፤ ይህኛው ግን አልተገለጠም። እቤቴ ውስጥ ተቀምጬ ይህንን ሰማሁ -- ወይም አልሰማሁም ብል ይሻላል፤ ከመስማት ይልቅ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሲገለጥ አየሁት። ስለዚህ አሁን መሄድ የምንችለው ይህን ያህል ነው። እንግዲህ እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔርን እንደምታገለግሉ እና ትክክለኛውን ነገር እንደምታደርጉ፤ በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደምትወዱ አምናለሁ፤ ሌላውን ሁሉ እግዚአብሔር ያደርግላችኋል።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ወንድም ብራንሐም 7ቱ ነጎድጓዶች ሲናገሩ ሰምቶ አያውቅም። በራዕይ አይቷቸዋል፤ ነገር ግን የተናገሩትን አልሰማም።

ሰባቱ ነጎድጓዶች እስከሚናገሩ ድረስ ምን እንደተናገሩ ልናውቅ አንችልም።

የሰባተኛው ማሕተም መገለጥ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ይታይ ዘንድ መከፈቱ ነው። ይህ ሚስጥር ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዘ ነው።

እንግዲህ ከዚህ ማሕተም ስር ያለው ታላቅ ሚስጥር ምን እንደሆነ አላውቅም። እኔ አላውቅም። ላየውም አልቻልኩም። ምን እንደሆነ ተገልጦ አላነበብኩትም። ምን እንደሆነ ምን እንደሚል አላውቅም። ነገር ግን የማውቀው አንድ ነገር አለ፤ እርሱም የሚናገሩት ሰባቱ ነጎድጓዶች መሆናቸውን እና ተራ በተራ በአንድነት ሁሉም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ታላቅ ሚስጥር እንደሚገለጥ ነው።

ይህንንም ባየሁ ጊዜ ትርጓሜውን ለማወቅ ፈለግሁ፤ እርሱም እዚያው ነበረ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም። ይህ ነው እውነቱ ወዳጆች ሆይ። አያችሁ? እነዚህ ሚስጥራት ሊገለጡ ጊዜው አልደረሰም፤ ነገር ግን በጣም እየቀረበ ነው። አያችሁ? በጣም እየቀረበ ነው። ስለዚህ እናንተ ማስታወስ የሚጠበቅባችሁ ነገር በጌታ ስም እንደተናገርኳችሁ ነው፤ ሁልጊዜ ዝግጁ ሁኑ ምክንያቱም አንድ ነገር የሚሆንበትን ጊዜ አታውቁም

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

የሰባቱ ነጎድጓዶች ንግግር ትርጓሜ ሊገኝ አልቻለም ምክንያቱም ንግግራቸው የመጣው እንደማይታወቅ ልሳን ነው።

እግዚአብሔር ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ እንድናውቅ አልፈለገም። ጊዜው ደርሶ በሚናገሩ ጊዜ ብቻ ነው የምናውቀው።

በአሁኑ ሰዓት ምንም ያህል ብንመራመር ልናውቅ አንችልም። የማይታወቅ ቋንቋን እንዴት ልትተረጉሙ ትችላላችሁ?

“ይህ ሶስተኛው መልእክት ይሆናል፤ እናንት ለማንም አትናገሩ።”

ሳቢኖ ኬንዮን ውስጥ እንዲህ አለ፡- “ይህ ሶስተኛው መልእከት ነው።” ደግሞም አብረውት የሚሄዱ ሶስት ትልልቅ ነገሮች አሉ፤ ከነዚህም አንዱ ዛሬ ተገልጧል፣ ወይም ትናንት፤ ሌላኛው ዛሬ ተገለጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አለ፤ እርሱንም ልተረጉመው አልችልም ምክንያቱም በማይታወቅ ቋንቋ ነው የተነገረው። እኔም በዚያ ቆሜ ቀጥ ብዬ አየሁት፤ ይህም የሚመጣው ሶስተኛው መልእክት ነው። የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስም … ኦ አምላኬ። ሰማይ ሁሉ ጸጥ ያለበት ምክንያት ይህ ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ወንድም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች ሲናገሩ አይቷል ነገር ግን የንግግራቸው ትርጓሜ በማይታወቅ ልሳን ነው። ከነጎድጓዶቹ ጋር አብረው የሚሄዱ ሌሎች ሁለት ነገሮች አሉ ግን ምን እንደሆኑ አልነገረንም። ስለዚህ አሁን የፈለግነውን ያህል ብንመራመር ልናውቃቸው አንችልም።

መፈላሰፍ ለአለማወቃችን መድሐኒት ሊሆን አይችልም።

እግዚአብሔር ሥራውን እንዴት አድርጎ እንደሚሰራ ልናውቅ አንችልም፤ ሚስጥር ነው። ማንም ምንም አያውቅም። መላእክት እንኳ አልገባቸውም። እግዚአብሔርም አልገለጠውም። ሰባተኛው ሚስጥር ሥር ሰባተኛው ማሕተም በተፈታ ጊዜ የዝምታ ጊዜ የሆነበት ምክንያት ይህ ነው። ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ መች እንደሚመለስ ሰዎች ማወቅ ፈለጉ። እርሱም እንዲህ አላቸው፡- “መች እንደሆን የሰው ልጅ እንኳ አያውቅም።” አያችሁ፤ እግዚአብሔር ይህን ማንም እንዳያውቅ በሚስጥር ይዞታል። ሚስጥር ነው። ለዚህ ነው በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል የዝምታ ጊዜ የሆነው። ከዚያም ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ያሰማሉ ግን ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ነገር እንዲጽፍ አልተፈቀደለትም ምክንያቱም የነጎድጓዶቹ ንግግር ውስጥ የጌታ ምጻት ሚስጥር አለ። ጌታ እስከ ዛሬ ያልገለጠው ነገር የምጻቱን ጊዜ ነው፤ እንዴት እንደሚመጣ እና መች እንደሚመጣ አልገለጠም። አለመግለጡም ጥሩ ነገር ነው

“ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሚስጥር መገለጥ ነው” ጁላይ 28 ቀን 1963

 

ምን ሊከሰት እንዳለ የማውቀው ነገር የለም። አላውቅም። የማውቀው ነገር ቢኖር ይህ ሚስጥር የተያዘው በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ውስጥ መሆኑን ነው። ሁላችሁም ገብቷችኋል?

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ለጥያቄ 6 ፍንጭ እዚሁ እናገኛለን። የነጎድጓዶቹ ሥራ ምንድነው?

ጌታ መች የሚመጣበት ጊዜ ሚስጥር የተያዘው በነጎድጓዶቹ ነው።

ነገር ግን አስተውሉ፤ እንግዲህ ሰባተኛውን ማሕተም በከፈተው ጊዜ መልሶ እንደገና አጠፋው። አያችሁ? ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ማየጥ እንችላለን፤ ስለዚህ እነዚህ ሚስጥራት የሚገለጡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ስለዚህ እስከዚህ ደርሰናል፤ የቀረው ሁሉ ኢየሱስ ለሙሽራይቱ ተመልሶ ምድር ላይ በሚገለጥበት ጊዜ ይታወቃል ወይም በዚያ ጊዜ በሚከሰተው በማንኛውም ነገር አማካኝነት ይገለጣል።

ስለዚህ እስከዚያው ድረስ ሁላችንም እየጸለይን ጤናማ የክርስቲያን ሕይወት እየኖርን ምጻቱን እንጠባበቅ

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

ይህ ሰባተኛ ማሕተም ለሁሉ ነገር ማብቂያ መሆኑን ማወቅ አለብን። እውነት ነው። በሰባቱ ማሕተሞች በታተመው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉ ነገሮች (ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ በቤዛነት መጽሐፍ ውስጥ ታትመው የተቀመጡ ነገሮች) በውስጡ የተጻፉ ነገሮች አንድ በአንድ ይጠናቀቃሉ። መጨረሻቸው ነው፤ በትግል ውስጥ የምትኖረዋ ዓለም መጠናቀቂያዋ ነው። የፍጥረት ትግል ማብቂያ ነው። የሁሉ ነገር መጨረሻ ነው። በዚያ የመለከቶቹ ማብቂያ ይሆናል። በዚያ የጽዋዎቹ ማብቂያ ይሆናል። የምድር መጨረሻ ነው። የ… እንደውም የጊዜም ጭምር መጨረሻ ነው። ጊዜ ያበቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህ እንደሚሆን ተናግሯል።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ቁጥር ከ1 እስከ 7። ጊዜ ያበቃል። መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ጊዜ አይኖርም” ይህ የሚሆነው እነዚህ ትልልቅ ነገሮች በሚፈጸሙ ጊዜ ነው። በሰባተኛው ማሕተም መጨረሻ ላይ በዚህ ዘመን ውስጥ ያለ ሁሉም ነገር ያበቃል።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ እስካሁን አልመጣም። በግልጽ መረዳት እንደምንችለው መልአኩ ከሶስት ሳምንታት በፊት ቀደም ብሎ ፎቶግራፍ የተነሳው ደመና አይደለም።

ይህ ታላቅ ነገር በሚሆንበት ዘመን።” ወንድም ብራንሐም በግልጽ ይናገር እንደነበረው የመልአኩ መምጣት ገና ወደፊት እንደሚሆን ነበር የተጣባበቀው።

ይህን አስተውሉ፤ የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ነው። የሰባቱ ማሕተሞች መጨረሻ ነው። የመለከቶቹ መጨረሻ ነው። የጽዋዎቹ መጨረሻ ነው፤ እንዲሁም የሺ ዓመት መንግስት መጨረሻም ነው፤ ይህ ሰባተኛው ማሕተም ነው።

ልክ ሮኬት ወደ አየር ላይ እንደመተኮስ ነው፤ ያም ሮኬት እዚህ ይፈነዳል፤ ወደላይ ይሄዳል፤ ከዚያም እንደገና ይፈነዳል። አምስት ኮከቦችን ከውስጡ ያወጣል። ከነዚያ ኮከቦች አንዱ ይፈነዳና ከውስጡ አምስት ኮከቦችን ያወጣል፤ ከዚያም ከነዚያ ከዋክብት አንዱ ይፈነዳና አምስት ኮከቦችን ያወጣል (አያችሁ?) ከዚያም ኮከቡ ይጠፋል። ሰባተኛው ማሕተም እንዲህ ነው፤ በሰባተኛው ማሕተም የዓለም ዘመን ያበቃል። የዚህን ዓለም ዘመን ይቋጨዋል። የዚህንም፤ የዚያንም የሁሉንም ዘመን ይቋጫል። ዘመንን ይቋጫል … ሁሉም ነገር የሚጠናቀቀው በዚያ በሰባተኛው ማሕተም ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

የዚህ ዓለም ስርዓት በ1963 አላበቃም። የሚያበቃው በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።

ስለዚህ እንዴት አድርጎ ነው የሚሰራው? ይህንን አናውቀውም፤ አይደል? አናውቅም። እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚሆኑበትና የሺ ዓመት መንግስቱ የሚጀመርበት ጊዜ ነው።

የዚህ ማሕተም መፈታት እጅግ ታላቅ ክስተት ከመሆኑ የተነሳ በማሕተሙ መከፈት በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ መስፈኑን አስቡ። ይህ አስደናቂ አይደለምን? ምን ይሆን? በሰማይ ጸጥታ ሆነ። ለግማሽ ሰዓት ያህል ምንም ነገር አልተንቀሳቀሰም።

እየተዝናናችሁ ባላችሁበት ጊዜ ግማሽ ሰዓት ረጅም ጊዜ ሊሆንባችሁ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ግማሽ ሰዓት በሞት እና በሕይወት መካከል ሲሆን የአንድ ሺ ዓመት ያህል ሊረዝምባችሁ ይችላል። እጅግ ታላቅ ነገር ከመሆኑ የተነሳ ኢየሱስ አንድም ጊዜ አልጠቀሰውም፤ ሌሎቹም አልጠቀሱትም። ዮሐንስ ሊጽፈው አልቻለም ምክንያቱም አልተፈቀደለትም። ስለዚህ … ዮሐንስ አልጻፈውም፤ የዝምታ ጊዜ ሆነ።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

እኛም አርአያነታቸውን መከተል አለብን።

ያልተጻፉት ሚስጥራት ምንን የሚመለከቱ መሆናቸውን እናውቃለን ነገር ግን ምን እንደሚሉ በዝርዝር አናውቅም።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አናውቅም።

አዲሱን የጌታን ስም አናውቅም።

ጌታ መች እንደሚመጣም አናውቅም።

አሁን እዚህ ላይ ማቆም አለብኝ። አያችሁ? በዚህ ርዕስ ላይ ከዚህ በላይ መናገር እንደሌለብኝ እየተሰማኝ ነው። አያችሁ? ብቻ ግን አስታውሱ፤ ሰባተኛው ማሕተም ያልተፈታበት ምክንያት () ሰባተኛው ማሕተም ያልተገለጥበት ምከንያት ስለእርሱ ማንም ሊያውቅ ስላልተፈቀደ ነው

አስተውሉ። ለዘመን መጨረሻ የተዘጋጀው ይህ ማሕተም ነው። ደግሞም ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጧቸዋል፤ ነገር ግን ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አይናገርም። የመጨረሻው ዘመን ማሕተም መከፈት ሲጀምር መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው የሚሆነው። ያንን ከማወቃችን በፊት … ደግሞ አስታውሱ፤ ራዕይ 10፡1-7 በሰባተኛው መልአክ መልእክት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች በሙሉ ይታወቃሉ። እኛ አሁን የምንኖረው በመጨረሻው ዘመን ነው፤ እርሱም ሰባተኛው ማሕተም የሚከፈትበት ዘመን ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ስድስት የተጻፉ ማሕተሞች ተገልጠዋል፤ ነገር ግን ሰባተኛው ማሕተም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም፤ ስለዚህ ወንድም ብራንሐምም ይሁን ሌላ ማንም ሰው ሊገልጠው አይችልም። አንድ ሰው ያልተጻፈ ነገርን እንዴት አድርገ ሊገልጥ ይችላል?

እግዚአብሔር የክርስቶስን የመጀመሪያ ምጻት ሚስጥር እንዴት ነው የገለጠው? በመላእክት አማካኝነት የእግዚአብሔር አዲስ ሰብዓዊ ስም ተገለጠ።

ከዚያም መላእክት ማንም የማያውቃቸው እረኞችጋ ሄደው ኢየሱስ በግርግም ውስጥ የሚገኝበትን ቦታ ነገሩዋቸው።

ይህንን እውነት ለዮሴፍ እና ለማርያም የነገሩዋቸው ሰዎች አይደሉም።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ

 

ሉቃስ 1፡26 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥

30 መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።

31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።

 

አሁን ተመልከቱ፤ በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መከፈት ሰዓት የሆነውን አስተውላችሁ እንደሆን ሶስት ድርብ ሚስጥር ነው። ይህ እኔ ያለኝ … ይናገራል፤ ደግሞም ተናግሯል፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥረ ነው። በሰማይ ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጡታል። እርሱም ልክ በክርስቶስ ምጻት ጊዜ ይሆናል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም ብሎ ተናግሯል

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

የሰባተኛው ማሕተም መፈታት ሶስት እጥፍ ድርብ ሚስጥር ነው

ከነዚያ ሶስት እጥፍ ድርብ ሚስጥራት አንዱ ምን ብለው እንደተናገሩ አንዳችም የማናውቃቸው ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸው።

ከሶስት እጥፍ ድርብ ሚስጥራት መካከል ሁለቱ ምን እንደሆኑ ጭራሽም አናውቅም።

ስለዚህ የሰው ጥበብ በመጠቀም እንዚህን ሚስጥራት መርምራችሁ ለማግኘት አትሞክሩ።

ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት እንዴት ሕይወት መፍጠር እንደሚቻል መርምራ ደረሰችበት ግን በዚያው ከባድ መከራ አመጣች።

ሣራ አብርሃም እንዴት በአጋር በኩል ወንድ ልጅ ሊያገኝ እንደሚችል መርምራ ደረሰች፤ ነገር ግን ሌላ ጣጣ አመጣች። የዚህም ውጤቱ በመካከለኛው ምሥራቅ የነዳጅ ዘይት ቀውስ፣ የዋጋ ግሽበት፣ እና ሽብር የፈጠሩ የአረቦች እና የእስማኤል መወለድ ነው። በጥላቻ የተሞሉ ሽብርተኛ የጅሃድ ነፍሰ ገዳዮች የዚህ ሃሳብ ፍሬዎች ናቸው።

ስለዚህ ሰዎች መፈላሰፍ ብናቆም ይሻለናል።

ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጣጣ አያስፈልገንም።

ስለዚህ እባካችሁ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል መርምራችሁ ለማግኘት ሙከራችሁን አቁሙ።

በቃ ለእግዚአብሔር ተዉለት። እርሱ የእኛን እገዛ አይፈልግም።

ዮሐንስ የሰማቸው እና የተናገሩትን እንዳይጽፍ የተከተከለው እነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ሚስጥሩ የተሰወረው ከነዚያ ሰባት ተከታታይ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ስር ነው

ይህን የምንለው ለምንድነው? ለምን? ይህ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

ስለዚህ ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ አናውቅም፤ ነገር ግን ምን ሊያደርጉ እንደሚመጡ ማወቅ እንችላለን።

ለሙሽራይቱ ተነጥቃ ወደ ሰማይ የምትሄድበትን እምነት ይሰጧታል።

ነጎድጓዶቹ ድምጻቸውን ከዚህ በፊት አሰምተው ከሆነ ንጥቀት ለምን እስካሁን አልተፈጸመም?

እርሱም በእግዚአብሔር ትዕዛዝ በትሩን ዘረጋና እንዲህ አለ፡- “እንቁራሪቶች ይውጡና ምድርን ይሸፍኑ።” እንቁራሪቶቹም ብዙ ክምር እስኪሆኑና ምድር ከእነርሱ የተነሳ እስክትገማ ድረስ ወጡ፤ የእንቁራሪተቹም ክምር አስራ አምስት ሜትር ያህል ይሆናል። እንቁራሪቶቹም በፈርኦን ቁም ሳጥን ውስጥ ገቡ። ደግሞም … አንሶላቸውን ግልጥ ሲያደርጉ ከአንሶላው ስር፣ ከአልጋቸው ስር፣ አምስት መቶ እንቁራሪቶች ያገኛሉ። በሄዱበት ሁሉ እንቁራሪት በእንቁራሪት ነበረ። እንቁራሪቶቹ ከየት መጡ? እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። የተናገረው ሁሉ ያደርጋል!

በምድር ላይ አጸያፊ ነገሮች እንሚመጡ ተናግሯል። “የሴት ዓይነት ፀጉር ያላቸው አንበጦች፣” እነዚህ ባለ ረጅም ፀጉር አንበጦች የሚመጡት ፀጉራቸውን የቆረጡ ሴቶችን ለማሳጣት ነው። “ጥርሳቸው እንደ አንበሳ፣ በጭራቸው ላይ የጊንጥ ዓይነት መናደፊያ ያላቸው አንበጦች፤ እነርሱም ሰወችን ለወራት ያሰቃያሉ።” መቅሰፍቶቹን እና ማሕተሞቹን ማጥናት እስከምንጀምር ድረስ ጠብቁ፤ ከዚያም ምን እንደሚፈጠር ታያላችሁ። ስለዚህ ወንድሜ ወደ ጌሴም ምድር ለመሄድ ጊዜ ሳለ ወደ ጌሴም መሄድ ነው የሚያዋጣህ። በውጭ ላለው ነገር ትኩረት አትስጥ።

“አያውቀውም” ኦገስት 15 ቀን 1965

በ1965 ወንድም ብራንሐም ስለ ነጎድጓዶቹ ለመስበክ እየተዘጋጀ ነበረ።

በዚህ ስብከቱ ነጎድጓዶቹን በታላቁ መከራ ውስጥ ከሚፈስሱ መቅሰፍቶች ጋር ያያይዛቸዋል።

“ማሕተሞች” ብሎ ይናገራል፤ ነገር ግን ስለ ማሕተሞቹ አስቀድሞ ሰብኳል። ጽዋዎች ማለቱ ይሆን?

በታላቁ መከራ ውስጥ የሚፈስሱ ሰባት ጽዋዎች ማለቱ ይሆን?

ባለፈው ሳምንት በድምጽ የተቀረጹት መልእክቶች በቂ ቦታ ስናገኝ በቅርቡ የምንናገርበትን ታላቅና አሰቃቂ ነገር በተመለከተ ብዙ የሚገልጡላችሁ ነገር አለ። መልእክቱ በምድር ላይ ስለሚፈስሱት ጽዋዎች ስለ መጨረሻዎቹ መቅሰፍቶች ስለ ጽዋዎቹ መፍሰስ እና ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች፤ በምድርም ላይ ስለሚሆነው ቀፋፊ ክስተት ነው። ዛሬ ሰው ሁሉ የምድር ሕዝብ ሁሉ በነውጥ ውስጥ በፍርሃትና በመርበትበት ውስጥ ናቸው!

“ክርስቶስ በቃሉ ነው የሚገለጠው” ኦገስት 22 ቀን 1965

ምንም በማያሻማ ሁኔታ ነጎድጓዶቹን ከጽዋዎቹ እና በታላቁ መከራ ውስጥ ከሚፈስሱት መከራዎች ጋር ያያይዛቸዋል። ጊዜው 1965 ዓ.ም የነበረ ሲሆን በዚያ ዓመትም ጭምር ስለ ጽዋዎቹ እና ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች ይሰብክ ነበር። በዚያም ዓመት እንኳ ገና ወደ ፊት እንደሚፈጸሙ ነበር የሚያስተምረው።

ዛሬ ወደዚህ የመጣሁት ስለ መጨረሻዎቹ ጽዋዎች ላስተምራችሁ ነው፤ የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት የመጨረሻዎቹ ሰባት ጽዋዎች እና የመጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች እና የመጨረሻዎቹ ሰባት ነጎድጓዶች፤ ዛሬ ከምንኖርበት ዘመን ጋር አያይዘን እናያቸዋለን። የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት እና ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት አንጻር እንመለከታለን። እስከ ዛሬ በዝርዝር ልንመለከታቸው ጊዜ አላገኘንም። ስለዚህ ጊዜ ስናገኝ ወዲያው … ለዚህ የሚሆን ቦታ እዚሁ ወይም ሉዊቪል ኒው አልባኒ ውስጥ ቦታ ልናገኝ እንችላለን ወይም ድንኳን እንተክላለን፤ በዚያም እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ጊዜ ድረስ እንቆያለን።”

“የዚህ ክፉ ዘመን አምላክ” ኦገስት 1 ቀን 1965

እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች በትጋት እየሰበከ እና ከታላቁ መከራ ክስተቶች ጋር አያይዞ ሲያብራራ ነበር።

 

ጥያቄ 7 - ወንድም ብራንሐም የ7ቱን ነጎድጓዶች ዓላማ ገልጧልን?

 

ጥያቄ፡ ከሰባቱ ሚስጥራት ጋር በቁጥር የሚመሳሰሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ተገልጠዋልን? በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠው ነገር ግን ለእኛ እስከ አሁን ድረስ እንደ ነጎድጓድ አልተገለጡልንምን?

መልስ፡

የለም፤ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠዋል፤ የነጎድጓዶቹ ትርጉም በማሕተሞቹ ውስጥ ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች እንዲገልጡ … ድምጻቸውን ያሰሙት ሰባቱ ነጎድጓዶች ነገር ግን የተናገሩትን ቃል ማንም ያልሰማቸው … ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል አውቋል፤ ነገር ግን እንዳይጽፍ ተከልክሏል። ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- “ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን የሰባቱ ነጎድጓዶች ሰባት ሚስጥራት ይገለጣሉ።” ሰባተኛውም መልአክ የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ነው። አያችሁ?

ጥያቄዎች እና መልሶች 4 ኮድ ኦገስት 30 ቀን 1964

ሰባቱ ማሕተሞች የሚለውን መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ አንብቡ። በዚያ መጽሐፍ ውስጥ የትም ቦታ ወንድም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ቃል አልነገረንም።

ነገር ግን በሰባቱ ማሕተሞች መጽሐፍ ውስጥ ነጎድጓዶቹ ስለ ምን እንደሚናገሩ አካፍሎናል።

በሌላ አነጋገር ዓላማቸው ማለትም በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የተሰጣቸው ሥራ ምን እንደሆነ ነግሮናል።

ነገር ግን አስቡ፤ አሁን ይህንን እየጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ሌሎቹን ማለትም ሰባቱን ነጎድጓዶች ሊጽፍ ሲያስብ “አትጻፍ” አለው። ያየውን ሁሉ እንዲጽፍ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። ነገር ግን እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተናገሩ ጊዜ “እንዳትጽፍ” ተብሎ ተነገረው። ሚስጥሮች ናቸው። ምን እንደሆኑ እስከ አሁን ድረስ አናውቅም፤ ነገር ግን ኋላ በጊዜያቸው ይገለጣሉ ብዬ አምናለው። ሲገለጡም ቤተክርስቲያን ከዚህ ዓለም የምትወጣበት ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት እና ጸጋ ይሰጧታል። እስከዚያው ድረስ በተገለጠልን እን በተረዳነው እንመላለሳለን፤ ባለፉት ዘመናት ውስጥ ሁሉን አይተናል። የእግዚአብሔርን ሚስጥራት አይተናል። በመጨረሻው ዘመን ሙሽራይቱ እንዴት ባለ ታላቅ ክብር እንደምትሰበሰብ ተመልክተናል። ይህም ሁሉ ሆኖ ግን እስካሁንም ድረስ ልናውቅ የማንችለው ነገር አለ። ሌላ ነገር አለ። ነገር ግን እነዚህ ሚስጥራት መገለጥ ሲጀምሩ … እግዚአብሔር እንዲህ አለ፡- “ቆይ፤ አሁን አትጻፋቸው። ጥቂት ጠብቅ። በዚያ ቀን እኔ እገልጠዋለው፤ ስለዚህ አሁን አትጻፈው፤ ምክንያቱም የሚያነቡት ይንገዳገዱበታል። ተወው፤ አትጻፈው። (አያችሁ?) ነገር ግን በዚያ ቀን ሊገለጥ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኔ እገልጠዋለው።”

“የመጀመሪያው ማሕተም” ሰኞ ማርች 18 ቀን 1963 ዓ.ም የተሰበከ

በሚልክያስ ምዕራፍ 4 እና ራዕይ 10፡7 ውስጥ የተጠቀሰው መልእክተኛ ሁለት ነገሮችን ያደርጋል። አንድ፡ በሚልክያስ 4 መሰረት የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል። ሁለት፡ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰውን የሰባቱን ነጎድጓዶች ሚስጥር ይገልጣል፤ እነዚህም ሚስጥራት የተሰወሩት በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ነው። እነዚህ በመለኮታዊ አሰራር የሚገለጡ “ሚስጥራዊ እውነቶች” ናቸው የልጆችን ልብ ወደ ጥንቶቹ አባቶች በእውነት የሚመልሱት። ልክ እንደዚሁ ይሆናል።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9

 

የነጎድጓዶቹ ዓላማ እኛን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መመለስ ነው።

የበዓለ ሃምሳ ዕለት ከነበሩ አባቶች ጋር በእውነት አንድ መሆን የምንችለው በትንሳኤ ከተነሱ በኋላ ነው።

እነርሱ በአዲስ አካል ውስጥ ይሆናሉ፤ እኛም አካላችን ሊለወጥልን ያስፈልገናል። የነጎድጓዶቹ አገልግሎት አካላችንን እንዴት እንደምንለውጥ ማሳየት ነው ምክንያቱም ከትንሳኤ እና አካላችን ከመለወጡ በፊት ጌታ አይመጣም።

ስለዚህ ነጎድጓዶቹ አገልግሎታቸው ምን እንደሆነ ይገለጥልን ዘንድ ሰባቱን ማሕተሞች እንመልከት፤ ማለትም ምን እንደሚያደርጉ እና ዓላማቸው ምን እንደሆነ እንመልከት።

ይህ ማንም የማያውቀው ሚስጥር ነው። ዮሐንስም እንዳይጽፈው ተከልክሏል፤ በምልክት እንኳ መዝግቦ እንዳያስቀምጠው ተከልክሏል። ለምን? በሰማይ ዝምታ የሆነው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሚስጥሩ ሊጋለጥ ይችላል። አሁን አስተዋላችሁ? እንዲህ ሁሉ ታላቅ ከሆነ መካተት ነበረበት ምክንያቱም ሊፈጸም ግድ ነው፤ ነገር ግን ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ

አስተውሉ፤ ሰባቱ መላእክት መለከታቸውን ሊነፉ ሲመጡ አንድ ነጎድጓድ ነበረ። እስራኤል ሲሰበሰቡ የመለከት ድምጽ ነበረ። ጊዜ ሲያበቃ የመጨረሻው መለከት … አንድ ነጎድጓድ፣ ነገር ግን እዚህ ቃል ውስጥ የምናየው ደግሞ ሰባት ነጎድጓዶች በመደዳ እንደሚመጡ ነው፡ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት፤ ይህ ፍጹም ቁጥር ነው። ሰባት ነጎድጓዶች በመደዳ ይናገራሉ … አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት፣ አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት። በዚያን ጊዜ ሰማያት እንኳ ሊጽፉ አልቻሉም። ሰማያት ሊያውቁ አይችሉም፣ ምንም ነገር፤ ምክንያቱም አንዳችም ፍንጭ የሚሰጥ ነገር የለም። የዝምታና የእረፍት ጊዜ ነው። በጣም ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ከመላእክት እንኳ ሳይቀር ሚስጥር ሆኖ ተሰውሯል። አሁንስ?

ይህንን ሚስጥር ሰይጣን ቢያገኘው ታላቅ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል። እርሱ አንድ የማያውቀው ነገር አለ። ምንም ነገር በራሱ መተርጎም አይችልም፤ የትኛውንም ስጦታ ኮርጆ ማስመሰል አይችልም (እየተማራችሁ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለው)። ይህንን ሊያውቅ አይችለም። ይህ ሚስጥር ቃሉ ውስጥ እንኳ አልተጻፈም። ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። መላእክትም ሆኑ የትኛውም ፍጥረት አያውቁትም። ቢያውቁና አንድ ነገር ትንፍሽ ብለው ቢናገሩ ሚስጥሩን ሊያባክኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ ምንም ባለማወቃቸው የተነሳ ምንም መናገር አይችሉም።

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

የትኛውም የጦር ጀነራል የውግያ እቅዱን ወይም ስልቱን እስከ መጨረሻዋ ሰዓት አይገልጥም።

እርሱም በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ “ሕይወት” የሚል ተጽፎበታል፤ በሌላ ወገን ደግሞ [ሐመር ፈረስ ላይ የተቀመጠው] ሶስት የተለያዩ ኃይላት ተደባልቀው የሚኖሩበት ሰው አለ፤ እርሱም ሞት ይባላል፤ ምድራዊ የሆኑ ልኡካኖቹን አስከትሎ ይሄዳል፤ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የተወለዱ አገልጋዮቹን፣ ቅዱሳንን አስከትሎ ይመጣል።

እርሱ በላዩ ላይ ሞት ተጽፎበታል፤ ክርስቶስ ግን ሕይወት ተጽፎበታል። ከእርሱ ጋር ያሉትም በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠዋል፤ እነርሱም “ከዓለም ፍጥረት በፊት የተመረጡ” ይባላሉ (አሜን።) እነርሱም ለቃሉ ታማኝ ናቸው። አሜን። ይህ በጣም ደስ ይለኛል። የተጠሩ፣ ከዓለም መፈጠር በፊት የተመረጡ፤ ቀጥሎም በፍላጎታቸው ለቃሉ ታማኝ የሆኑ፤ እነዚህ ሁሉ በአዲስ ወይን እና በዘይት ተነቃቅተው እርሱ ሲመጣ ሊቀበሉት ይሄዳሉ። ነጎድጓዶቹ ድምጻቸውነ አሰምተው ሚስጥራትን እንዲሚገልጡላቸው ያውቃሉ። አያችሁ?

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

ነጎድጓዶቹ እስካሁን ድረስ ገና ወደፊት እንደሚመጡ ነው የሚጠበቁት፤ ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ለተመረጡት ሰዎች ጌታን ፊት ለፊት ለማየት የሚችሉበትን ብቃት ይሰጧቸዋል።

የሚናገሩት ወደፊት መሆኑን አስተውሉ። ምስጢራቸውን የሚናገሩት ወደፊት ነው።

ምን ሊከሰት እንዳለ የማውቀው ነገር የለም። አላውቅም። የማውቀው ነገር ቢኖር ይህ ሚስጥር የተያዘው በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች ውስጥ መሆኑን ነው። ሁላችሁም ገብቷችኋል?

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

 

አይሁዶች ይህን ጥያቄ በጠየቁት ሰዓት አስተውላችኋል? ማቴዎች ምዕራፍ 24 ውስጥ የተጻፈውን ትንቢት ከስድስቱ ማሕተሞች ጋር ባነጻጸርነው ጊዜ ሰባተኛው ትንቢት ለብቻው ተነጥሎ እንደቀረ አይታችኋል፤ ምክንያቱም (አያችሁ?) ክርስቶስ እራሱ እንዳለው የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ መላእክቱ እንኳ አያውቁም። የሚገርማችሁ ደግሞ የትም ቦታም አልተጻፈም። እነርሱም ዝም አሉ፤ በዚያን ጊዜ ምንም አልተፈጸመም። መላእክት አያውቁትም፤ ጌታ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ይህንን ታላቅ መገለጥ የሚገልጡ ሰባት ነጎድጓዶች አሉ

ስለዚህ ለእኛ … አምናለው፤ ካላወቅን እና እኛ -- ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ አይታወቅም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ይገለጣል፤ ሊገለጥ በሚገባው ሰዓት ይገለጣል። ስለዚህ እኛ እንድናደርግ የሚጠበቅብን ነገር በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ አክብሮትና ፍርሃት እርሱን ማገልገል እና ማድረግ እንዳለብን የምናውቅን ሁሉ ማድረግ እንዲሁም መልካም የክርስትና ሕይወት መኖር ነው።

“ሰባተኛው ማሕተም” እሁድ ማርች 24 ቀን 1963 የተሰበከ

አሁንም ስለ ነጎድጓዶቹ የተነገረው ገና ወደፊት እንደሚመጡ ነው።

“እኛም” መች እንደሚሆን አናውቅም።

ነጎድጓዶቹ ምንድነው የሚሰሩት? ጌታ መች እንደሚመጣ ይገልጣሉ። ሰይጣን የእግዚአብሔርን እቅድ እንዳያበላሽ ይህ የሚሆነው በመጨረሻው ሰዓት ነው።

አሁን ግን በጉ ለዮሐንስ በቤተክርስቲያን ምሳሌ ለቤተክርስቲያን ምን እንደሚጽፍላት የእግዚአብሔርን ቃል እያሳየው ነውቸ አሳየውና እንዲህ አለው፡- “ይህን እንዳትናገር እንዳትጽፍ። ዮሐንስ ሆይ ተመልከት ግን እንዳትጽፈው።” ከሰባተኛው ማሕተም ስር ያለው ምንድነው፤ እንዳትናገር እንዳትጽፍ፤ ይህን ሚስጥር በዮሐንስ በኩል ብገልጠው በዘመናት ውስጥ ሁሉ የእግዘአብሔር ዕቅድ ይከሽፍ ነበር፤ ስለዚህ ሚስጥር ነው። አያችሁ? እርሱ የሚፈልገው …

ስለመምጣቱ … እንዲህ አለ፡- “እኔ የምመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም፤ ግን እመጣለሁ።” አያችሁ? መች እንደሚመጣ ማወቅ እኔን አይመለከተኝም፤ ከእኔ የሚጠበቀው መዘጋጀት ነው። አያችሁ? ስለዚህ …

“የመጀመሪያው ማሕተም” ማርች 18 ቀን 1963

መች እንደሚመጣ ለማወቅ መሞከር እንኳ እኛን አይመለከተንም። ይህን ጉዳይ መነካካት ይቅርባችሁ።

ልክ እንደምትሞቱበት ቀን ነው። የምትሞቱበትን ቀን አለማወቃችሁ ለናንተ መልካም ነው።

ዛሬ ያሉን መነቃቃቶች በዚህ ምክንያት ነው … ዲኖሚኔሽናዊ መነቃቃቶችን አይተናል እንጂ እውነተኛ መነቃቃት አላየንም። በፍጹም በፍጹም። መነቃቃት አይተን እናውቃለን አትበሉ። መነቃቃት አይተን አናውቅም። ብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን አባላት አሏቸው፤ ነገር ግን መነቃቃት አይተው አያውቁም። በፍጹም።

ሙሽራይቱ መነቃቃት ውስጥ ገብታ አታውቅም። አያችሁ? መነቃቃት መጥቶ አያውቅም።ሙሽራይቱን የሚቀሰቅሳት የእግዚአብሔር ኃይል ታይቶ አይታወቅም። አያችሁ? መነቃቃት እስኪመጣ እየተጠባበቅን ነን። እውነተኛ መነቃቃት ሲመጣ ሰባቱን ነጎድጓዶች ያመጣቸውና ሙሽራይቱን ይቀሰቅሳታል። ጌታም ይልከዋል። እንደሚልከው ቃል ገብቷል።

አሁን ተመልከቱ። አሁን ሙት ነበረች

“ሶስተኛው ማሕተም” ማርች 20 1963

እግዚአብሔር ሆይ አለማመናችንን እርዳ። ጌታ ሆይ አስወግድልን። የምንነጠቅበትን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን። ያ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ እና ቤተክርስቲያንም በምትነጠቅበት ጊዜ ልንቀበለው ዝግጁ መሆን እንፈልጋለን ጌታ ሆይ።

“ሁለተኛው ማሕተም” ማርች 19 ቀን 1963

 

የራዕይ ሰባት ነጎድጓዶች … ሙሽራይቱ ለመለወጥ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምታገኝ ጌታ ይግለጥላት።

“የመጀመሪያው ማሕተም” ማርች 18 ቀን 1963

ኢየሱስ በስጋዊ አካሉ ውሃ ላይ ተራምዷል። ይህንንም ተዓምር እኛ ደግመን ልናደርገው አንችልም።

ከትንሳኤ በኋላ ኢየሱስ በከበረ አካሉ ውስጥ ሆኖ በአየር ላይ ሄደ። ወደፊት በንጥቀት ጊዜ እኛም ጌታ እንዳደረገው በአየር ላይ መሄድ አለብን።

እርሱ ሲመጣ ልንቀበለው ወደ አየር ላይ ከፍ ብለን መራመድ አለብን።

ነጎድጓዶቹ ይህንን ችሎታ ነው የሚሰጡን።

እያንዳንዳችሁ ልባችሁን በሙሉ አንጹ። እያንዳንዱን ሐጥያትና ሸክም ከመንገዳችሁ አስወግዱ። ምንም ነገር እንዲያስጨንቃችሁ አትፍቀዱ። በምንም አትፍሩ። የሚያስፈራ ነገር የለም። ኢየሱስ የሚመጣ ከሆነ እጅግ በጣም -- ዓለም ሁሉ ሲናፍቀውና ሲጠባበቀው የቆየው የኢየሱስን መምጣት ነው። አሁን የሚገለጥ አዲስ ነገር ካለ፤ ከሚመጣ አዲስ ነገር ጋር በተያያዘ -- የአዲስ ስጦታ መምጣት ከሆነ አስደናቂ ይሆናል። ቤክርስቲያን ትነጠቅ ዘንድ የሰባቱ ነጎድጓዶች መገለጥ ከሆነ አላውቅም። የማውቀውን አሁን ነግሬያችኋለው።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ማርች 30 ቀን 1962

ሰባቱ ነጎድጓዶች ጌታ ሲመጣ ለቤተክርስቲያን “እንዴት ተነጥቃ እንደምትሄድ” ይገልጡላታል።

እሁድ ዕለት ላገለግል ወደዚህ መጣሁ፤ እራሴንም ነቅንቄ ላላቅቅ ሞከርኩ። ሰኞ ዕለትም ግን እንደገና እዚሁ ነበረ። አሁን እዚሁ አለ። እኔም አላውቅም፤ ወገኖች ሆይ አላውቅም። ወንድሞቼ ስለሆናችሁ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነኝ። አላውቅም

ጊዜው ደርሷልን? ሚስጥሮ በሙሉ ተጠናቅቋል? የመለከቱ ድምጽ በስፍራ ሁሉ ተሰምቷል? በውኑ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ሊያሰሙ ሚስጥራቸውን ሊገልጡና ጌታ ለራሱ ለሰበሰባቸው ጥቂት ሰዎች እርሱ ሲመጣ በአየር ላይ ይቀበሉት ዘንድ የመነጠቅን እምነት ሊሰጡዋቸው እየተዘጋጁ ናቸውን፤ እነዚህ መላእከት ሲመጡ ወዲያው እንለወጣለን፤ ከመቅስፈት፣ በዓይን ጥቅሻ እንለወጥና በጌታ ሆነው ካንቀላፉት ጋር ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል አብረን እንነጠቃለን።

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ማርች 30 ቀን 1962

እንደገና ነጎድጓዶቹን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከአካላችን መለወጥ ጋር ያያይዛቸዋል። የክርስቲያን ጸሎቶች ሙታንን አስነስተዋል፤ የበሽታ ዓይነቶችን ሁሉ ፈውሰዋል።

ነገር ግን አካላችንን እንዴት ነው የምንለውጠው? እንዴት ነው ተነስተን በአየር ላይ የምንራመደው?

ይህን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ አንድ አዲስ ነገር መቀበል ይጠይቃል። የእኛ ብልሃት ሊያደርገው አይችልም።

ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም። አሆን፤ እውነት ነው። እኔም ደግሞ በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ እንዴት እንደምትዘጋጅ እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምትቀበል ይገለጥላታል። ምክንያቱም አሁን ባለን እምነት መነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ መጨመር ወደፊት መግፋት አለብን፤ ለመለኮታዊ ፈውስ እንኳ የሚበቃ እምነት የለንም። ከመቅጽፈት የምንለወጥበትና ከዚህ ምድር ተነጥቀን የምንሄድበት በቂ እምነት ሊኖረን ይገባል፤ ደግሞም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከጥቂት ዘመን በኋላ የተጻፈበትን ቦታ እናገኛለን።

“የመጀመሪያው ማሕተም” ማርች 18 ቀን 1963

ሰባቱ ነጎድጓዶች ለሙሽራይቱ ከዚህ ምድር ተነጥቃ የምትሄድበትን በቂ እምነት ይሰጧታል።

ይህ ተነጥቆ መሄድ አሁን ከለበስነው አካል ወደ ከበረው አዲስ አካል ከመለወጣችን ጋር የተያያዘ ነው።

ከዚያ በኋላ በአየር ላይ ተነጥቀን በመሄድ ኢየሱስን እንቀበለዋለን።

እነዚህ ሁለት ታላላቅ ነገሮች ሁለቱም ይፈጸማሉ።

እነዚህ አንድ ብልጥ ሰባኪ ሙሽራይቱን የሚያባብልበት ወሬ አይደሉም።

 

 

7ቱ ነጎድጓዶች የሚናገሩት ለአይሁዶችም ጭምር ነው

 

ትናንትና ማታ ትልቅ ሰይፉን ይዞ ለመግደል ሲመጣ አግኝተነው ነበር። ነገር ግን እርሱ እራሱ በሰይፍ እንደሚገደል አይተናል፤ ይህም የቃሉ ሰይፍ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፤ በሁለት ወገን የተሳለው ሰይፍ ይገድለዋል፤ ያጋድመዋል። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋር የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

“አራተኛው ማሕተም” ማርች 21 ቀን 1963

እውነታ፡

ይህ በፍጹም ያልተጠበቀ ኃይለኛ ነገር ነው።

ስለዚህ ራዕይ ምዕራፍ 11 ውስጥ በተጻፈው መሰረት ሰባቱ ነጎድጓዶች እስራኤል ውስጥ ወደ ሁለቱ ነብያት ይሄዳሉ።

ኤልያስ ሰማያትን ይዘጋል። 7ቱ ነጎድጓዶች በሁለቱ ነብያት አማካኝነት ለሚገለጠው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ቁልፍ ናቸው።

ስለዚህ ነጎጓዶቹ መጨረሻ ላይ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ለመንጠቅ ጊዜው ሲደርስ ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሁለቱ አይሁዳውያን ነብያት ይሄዳሉ።

ወንጌል ወደ አይሁዶች የሚመለሰው መች ነው? የአሕዛብ ዘመን ሲጠናቀቅ ነው። ወንጌሉ ወደ አይሁዶች ተመልሶ ሊሄድ ጊዜው ቀርቧል። እንደው ዛሬ በእኛ ዘመን ሊፈጸም ያለ ነገር ልነግራችሁ በቻልኩ ኖሮ። ሊፈጸም ያለው ይህ ታላቅ ነገር ከራዕይ ምዕራፍ 11 ሁለቱ ምስክሮች ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ ወንጌልን ወደ አይሁድ መልሰው ሲወስዱ ይጀምራል። እኛም ለዚህ ተዘጋጅተናል፤ ሁሉ ነገር ዝግጁ ነው። አይሁዶች መልእክቱን ለአሕዛብ እንዳመጡ ሁሉ አሕዛብም መልእክቱን መልሰው ለአይሁዶች ይዘው ይሄዳሉ፤ ከዚያም በኋላ ንጥቀት ይመጣል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 1

ሰባቱ ነጎድጓዶች አይሁዶችንም አሕዛብንም ይመለከታሉ። ነጎድጓዶቹ የሚናገሩት ለሙሽራይቱ ብቻ አይደለም።

የራዕይ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ምዕራፎች ቤተክርስቲያን ላይ የሚፈጸሙ ነገሮችን ሁሉ ይገልጻሉ። ከዚያም ከ3ኛው ምዕራፍ ጀምሮ እስከ 19ኛው ምዕራፍ ቤተክርስቲያንን ሁለተኛ አናያትም። በራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ ትሄዳለች፤ ከዚያም ራዕይ ውስጥ በ19ኛው ምዕራፍ ነው ሙሽራ ሆና ከሙሽራ ጋር አንድ ላይ ወደ ምድር የምትመለሰው። ከዚያም በኋላ ከ19ኛው ምዕራፍ እስከ 22ኛው ምዕራፍ መቋጫ ድረስ ስለ ሺ ዓመት መንግስት እና የሺውን ዓመት መንግስት ተከትለው ስለሚሆኑ ነገሮች ብቻ ነው የሚናገረው።

ከ4ኛው እስከ 19ኛው ምዕራፍ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ነው የሚሰራው።

“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964

 

ይህ ለመረዳት ከባድ ነው። ነገር ግን ምዕራፍ 10 ውስጥ የተገለጹት ክስተቶች እስራኤልም ላይ እንደሚፈጸሙ ያመለክተናል።

ራዕይ ምዕራፍ 10 የሚገኘው በ4ኛው እና በ19ኛው ምዕራፍ መካከል ነው። ስለዚህ አይሁዶችንም ይመለከታል።

ራዕይ ምዕራፍ 10ን ከትንቢተ ዳንኤል ጋር ማገጣጠም መቻል አለባችሁ።

 

በሰባት ማሕተሞች የታታመው መጽሐፍ የሚገለጠው የራዕይ 10 ሰባት ነጎድጓዶች በሚገለጡበት ጊዜ ነው። ልብ ብላችሁ እየተከታተላችሁ ከሆነ … እስቲ ለጥቂት ጊዜ ራዕይ ምዕራፍ 10ን እንመልከት፤ በዚህም ጠለቅ ብለን ከመግባታችን በፊት የተወሰነ ግንዛቤ ታገኛላችሁ። ይህ የሚሆነው በመጨረሻ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ አዳምጡ።

… ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ …

ብታስተውሉት ይህ ክርስቶስ ነው (አያችሁ?) ምክንያቱም እርሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የቃልኪዳኑ መልእክተኛ ተብሏል፤ አሁን ደግሞ ቀጥታ ወደ አይሁዶች ሊመጣ ነው ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ጊዜ አልቋል። አያችሁ? መልካም።

… ፊቱም … እንደ ፀሃይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ

ራዕይ ምዕራፍ 1 ውስጥ የተጠቀሰውን መልአክ ታስታውሱታላችሁ? ተመሳሳይ ነገር ነው የምታገኙት። መልአክ መልእክተኛ ነው፣ እርሱም የእስራኤል መልእክተኛ ነው። አያችሁ? አሁን ወይም ቤተክርስቲያን ለመነጠቅ ስትዘጋጅ ሊወስዳት ይመጣል

“በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ” ማርች 17 ቀን 1963

 

ይህንን መልአክ እንዴት በሁለት መንገድ እንደሚጠቅሰው ልብ በሉ።

ቤተክርስቲያን ለመነጠቅ እየተዘጋጀች ናት፤ ጌታም ቤተክርስቲያንን ሙሽራይቱን ሊወስዳት እየመጣ ነው።

እንደገና ደግሞ ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኋላ መልአኩ ወደ አይሁዶች ይመጣል።

ታላቁ መልአክ እና ሰባቱ ነጎድጓዶች ቤተክርስቲያንን እና አይሁዶችን የሚመለከቱ ድርብ ፍጻሜ አላቸው።

እዚህ ደረጃ ላይ ሲደረስ ነገሮች ይወሳሰባሉ። ከቀደሙት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ እና በሕይወት ያሉ የሙሽራይቱ አካላት አዲሱን አካላቸውን ለብሰው ሲለወጡ ጊዜ የሚባል ነገር ይወገዳል። አዲሱን አካላችሁን ስትለብሱ ለጊዜ ተገዥ አትሆኑም። የቀሩት ሌሎች ሰዎች ግን በጊዜ ተጽእኖ ውስጥ ይቀጥላሉ። ሙሽራይቱ ከጊዜ ቀጠና ውጭ የምትሆንበትን ሁኔታ አሁን መረዳት አንችልም። አሁን መረዳት የምንችለው የምንኖርበትን ዓለም ብቻ ነው፤ ይህም ዓለም በጊዜ የተገደበ መሆኑን እንገነዘባለን።

ነገር ግን በሆነ መንገድ ሰባቱ ነጎድጓዶች እና መልአኩ (ይህ መልአክ ክርስቶስ በመልአክ መልክ የሚገለጥበት ነው) ከአሕዛብ ለሆነችዋ ሙሽራ እንዲሁም ለአይሁድ ቅሬታዎች መልእክት አገልግሎት አላቸው። በሆነ ሚስጥራዊ መንገድ እነዚህን ሁለት ወገኖች ያቆራኙዋቸዋል።

ሁለቱም ወገኖች ከሰባቱ ነጎድጓዶች ታላቅ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይቀበላሉ። ሙሽራይቱ የማይሞት አካል ተቀብላ ወደ ሰማይ ትነጠቃለች። ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት የተፈጥሮን ኡደት ማቋረጥ ይችላሉ።

 

አዲሱን የኢየሱስን ስም ማንም አያውቀውም

 

እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በመጣ ጊዜ ኢየሱስ በተባለው የሰው ስም ተጠራ። እንደ ሰው በይፋ ሶስት ምጻቶች አሉት። የመጀመሪያው ምጻቱ ቤተክርስቲያንን ለማዳን በነር። ሁለተኛው ምጻቱ ቤተክርስቲያን አደጋ ሲያንዣብብባት በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ እራት ግብዣ ሊወስዳት ነው፤ ወደ ሰማይ በተነጠቀች ጊዜ በምድር ላይ ከሚሆነው ጥፋት ታመልጣለች፤ በዚያ ጊዜ አውሬም ለሶስት ዓመት ተኩል ምድርን ይገዛል። ሶስተኛው ምጻቱ ከቤተክርስቲያን ጋር በመሆን በአርማጌዶን ጦርነት አውሬውን ድል ለመንሳትና በምድር ላይ የ1,000 ዓመት መንግስትን ለመመስረት ነው፤ ይህም የመጀመሪያው ሰማይ ይባላል። ከአዳም ውድቀት በኋላ በምድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገለጠው የሰማይ ቅምሻ ነው።

ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ መልአክ ሆኖ ሊገለጥም ይችላል፤ እንደ መልአክ ሆኖ በተገለጠ ጊዜ ከሶስቱ ይፋዊ ምጻቶቹ እንደ አንዱ አይቆጠርም። ከሰዎች መካከል ታላቁ ሰው እንደነበረ ሁሉ ከመላእክትም ሁሉ ታላቁ መልአክ ነው። እንደ መልአክ ሚካኤል በሚባል ስም ይጠራል። የመላእክት አለቃነት ማዕረጉ ከመላእክት ሁሉ ታላቅ መልአክ ያደርገዋል። እግዚአብሔር እንደ መልአክ ሆኖ ሲገለጥ በተፈጥሮአዊም በልዕለ ተፈጥሮአዊም መንገድ ነው። ስለዚህ ለእኛ ለሰዎች ይህንን ሚስጥር ቀድመን መረዳት የማይቻል ነገር ነው። እግዚአብሔር በሰዎች መካከል ለማዳን ሲገለጥ እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ነው የሚሰራው ምክንያቱም ሰይጣን ማወቅ የለበትም።

ኢየሱስ በምድር ላይ ስሙ ቤዛ ነው ስሙ ኢየሱስ ነው። ምድር ላይ በነበረ ጊዜ እርሱ ለሕዝቡ ቤዛ ነበረ፤ ይህ እውነት ነው። ሞትን እና ሲኦልን ድል ከነሳና ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ግን አዲስ ስም ተቀብሏል። ለዚህ ነው የፈለጉትን ያህል ቢጮሁ እንኳ ምንም የማያገኙት፤ አዲሱ ስም በነጎድጓዶቹ ውስጥ ይገለጣል። አያችሁ?

“የመጀመሪያው ማሕተም” ማርች 18 ቀን 1963

የሜሴጅ ሰዎች ባደረጉት ምርምር በመካከላቸው ብዙ ስሞች አዲሱ የኢየሱስ ስም ተብለዋል።

ኢየሱስ አሁን አዲስ ስም ካለው ኢየሱስ የተባለውን አሮጌውን ስሙን መጠቀም ማቆም አለባችሁ።

አዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ኢየሱስ በተባለው አዲስ ስም በተጠራ ጊዜ ከዚያ በኋላ ሁለተኛ ያህዌ የተባለውን አሮጌውን ስሙን አልተጠቀመም።

ከኢየሱስ ስም በቀር የምንድንበት ከሰማይ በታች ሌላ ስም የለም። ስለዚህ አካላችን እስኪለወጥ ድረስ እና አዳኝ የማያስፈልገን ጊዜ ላይ እስክንደርስ ድረስ ኢየሱስ የሚለውን ስም በማወቅ እንኖራለን።

የሐዋርያት ሥራ 4፡12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።

የኢየሱስን አዲስ ስም የምታውቁት አዲሱን አካላችሁን ስትለብሱ ብቻ ነው።

ይህን ሚስጥር አስተውሉ። በፈረስ ላይ ተቀምጦ ይመጣል … እንደምታውቁት ቤተክርስቲያን እንድትለወጥ የሚያደርግ ነገር አለ። የሆነ ነገር አለ። አስተውሉ። ከእርሱ በቀር ማንም ሰው አያውቀውም። አሁንም አስተውሉ፤ ከእርሱ በቀር ማንም ሰው አያውቀውም

“የመጀመሪያው ማሕተም” ማርች 18 ቀን 1963

ነጎድጓዶቹ የጌታን አዲስ ስም ይገልጣሉ። ይህም ቤተክርስቲያን ከመለወጧ እና አዲስ አካል ከመልበሷ ጋር የተያያ ነው። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው አዳኝ የማያስፈልጋችሁ ምክንያቱም የቤዛነት ስራ ይጠናቀቃል።

ይህን አዲስ ስም ማንም አያውቀውም። ስለዚህ አዲሱ ስም ብላችሁ ባሰባችሁበት ሃሳብ ሁሉ ተሳስታችኋል።

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አዲስ ስም ማንም አያውቀውም ይላል። ካልተጻፉት ነጎድጓዶች ጋር ከተያያዙት ያልተጻፉ ሚስጥራት አንዱ ነው።

ራዕይ 19፡12 ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤

 

ስሙን አንድንም ሰው አያውቀውም። መርምረን እናገኛለን ብላችሁ ግራ መጋባት ላይ ግራ መጋባት አትጨምሩ። አዲሱን አካላችንን በለበስን ጊዜ እግዚአብሔር ይገልጠዋል። በዚህ በደም የተሞላ አካል ውስጥ ስንኖር በጸጋ የዳንን ሐጥያተኞች ነን፤ ስለዚህ አዳኝ ያስፈልገናል። የኢየሱስ ደም ያለስፈልገናል።

አዲሱ አካላችሁ ውስጥ ምንም ደም አይኖራችሁም።

ስለዚህ በዚያን ጊዜ መስቀል ላይ የተሰቀለ በደም የተነከረ አዳኝ አያስፈልጋችሁም።

የዚያን ጊዜ ብቻ ነው በአዲሱ ስማችሁ የምትጠሩት። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው የእርሱን አዲስ ስም የምታውቁት።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 … ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።

 

ራዕይ 19፡11

ሰማይ ተከፍቶ አየሁ … (አሜን) … እነሆም አምባላይ ፈረስ፣ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፣ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።

ዓይኖቹም … እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም … ብዙ ዘውዶች … (ኦ ወንድሞች ሆይ፤ በቅዱሳን አማካኝነት ዘውድ ጭኗል ማለት ነው። አያችሁ?) … ከእርሱም በቀር አንድስ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው። (ልብ በሉ፣ ያን ስም ልናውቀው አንችልም -- በጭራሽ አናውቀውም፤ አያችሁ?)

በደምም የተረጨ ልብስ … (እስቲ እንይ) … በደምም የተረጨ ልብስ ተጎናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል … (“ነው” ሳይሆን ተብሎአል ነው የሚለው)

“ሁለተኛው ማሕተም” ማርች 19 ቀን 1963

አዲሱን ስም አናውቀውም።

ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተባለ። ስሙ “የእግዚአብሔር ቃል” አይደለም

አንዳንድ የሜሴጅ ቡድኖች አዲሱ ስም “ቃል” ነው ይላሉ።

ቃል ማዕረግ ነው። ማዕረግን በስም ፈንታ አትተኩ። የስላሴ አስተማሪዎች ሶስት ማዕረጎችን ሲጠቀሙ እንዲሁ ዓይነት ስሕተት ነው የሰሩት።

… እርሱም ከእርሱ ሌላ ማንም የማያውቀው ስም ተጽፎበት ነበር …

እርሱም በደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል … (አሁን ልብ በሉ፣ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም፣ ስሙ እንደዚያ ተባለ እንጂ። አያችሁ?) … ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተባለ።

“የፍጥሞ ራዕይ” ዲሴምበር 4 ቀን 1960

 

248 የአምላኬን ስም እጽፍበታለሁ፤… እርሷም ወደ ምድር የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት … ወይም የእግዚአብሔር ከተማ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም … ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ፤ እኔም አዲሱን ስሜን እጽፍበታለሁ።

አዲሱ ስም ማን እንደሆነ ለመናገር ባልሞክር ይሻላል አይደል?

“የፍልድልፍያ ቤተክርስቲያን ዘመን” ዲሴምበር 10 1960

አዲሱን ስም ማንም የሚያውቀው ስለሌለ ይህ የጠቢብ ምክር ነው።

አዲሱን ስም ለመገመት መሞከር ቢቀርባችሁስ?

መገመት ስታቆሙ የዚያን ጊዜ ከወንድም ብራንሐም ትምሕርቶች ጋር ትስማማላችሁ።

“አዲሱን ስሜን እጽፍበታለሁ።”

አዲሱ ስሜ። ሁሉ አዲስ በሚሆንበት ጊዜ እርሱም አዲስ ስም ለራሱ ይወስዳል፤ ያ ስም ደግሞ የሙሽራይቱም ስም ይሆናል። ያ ስም ማን እንደሆነ ማንም ሊገምት አይድፈር። ማንም ሊክደው እንዳይችል በመንፈስ የሚሰጥ መገለጥ መሆን አለበት። ያለ ምንም ጥርጥር እርሱ ይህንን ስም ሊገልጥ እስከወሰነበት ቀን ድረስ ይጠብቃል። ለጊዜው መገመት ከምንችለው በላይ እጅግ አስደናቂ ይሆናል ብለን ማረፍ ይሻለናል።

“የፊልድልፍያ ቤተክርስቲያን ዘመን” የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 8

አዲሱ ስም ከእኛ የመገመት አቅም ውጭ ነው። በፍጹም ለመገመት ወይም ተመራምራችሁ ለማግኘት መሞከር የለባችሁም። ሙሉ በሙሉ ብንተወው ይሻላል። ውስን የሆነው ምናባችን ይህንን ድንቅ ስም አስቦ አስቦ ሊደርስበት አይችልም።

በነጎድጓዶቹ ውስጥ ያለው ድምጽ የት እንደነበር ተመልከቱ፤ በሰማይ ሳይሆን በምድር ነው። ነጎድጓዶቹ ከሰማይ አልተናገሩም፤ የተናገሩት ከምድር ነው

“ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?” ዲሴምበር 30 ቀን 1962

ከዚህ በታች በተጠቀሰው ጥቅስ ውስጥ ነጎድጓዶቹ ከምድር ይመጣሉ ይላል።

አሁን ተመልከቱ፤ በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መከፈት ሰዓት የሆነውን አስተውላችሁ እንደሆን ሶስት ድርብ ሚስጥር ነው። ይህ እኔ ያለኝ … ይናገራል፤ ደግሞም ተናግሯል፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥረ ነው። በሰማይ ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጡታል። እርሱም ልክ በክርስቶስ ምጻት ጊዜ ይሆናል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም ብሎ ተናግሯል …

“ሰባተኛው ማሕተም” ማርች 24 ቀን 1963

ነጎድጓዶቹ በሰማይ ናቸው ብሏል።

እኛም በተረዳንበት መጠን እነዚያን ከሰማይ የሚመጡትን ምስጢራዊ ነጎድጓዶች ሲገለጡ ለማየት የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ በማሕተም በታሸገው መጽሐፍ ውስጥ ለማግኘት እየፈለግን ነን

“ታላቅ ምልክት” ማርች 24 ቀን 1962

ነጎድጓዶቹ ከሰማይ ናቸው ወይስ ከምድር?

እንግዲህ ስለ ነጎድጓዶቹ የተረዳነው ምን ያህል ነው? ብዙም አይደለም።

 

ትልቅ ማስጠንቀቂያ። ነጎድጓዶቹን እራሳችን መፍጠር አለብን?

ሰይጣን ፎጋሪ ነው፤ ግርግርና ሁካታ ይወዳል፤ ነጎድጓድና መብረቅ ብልጭታ ያበዛል። እኔ ግን እነግራችኋለው ወንድሞች ሆይ ከሙታን የተነሳው የኢየሱስ ክርስቶስ ከፀሃይ ይልቅ የደመቀ ክብሩ በምድራዊ ነገር ተጠምደው እንቅልፍ የተኙ ሙታንን ሁሉ በእግዚአብሔር ያምኑ ዘንድ ቃሉን በሙሉ ልባቸው ይቀበሉ ዘንድ የሌሉ ነገሮችን እንዳሉ አድርገው ይጠሩ ዘንድ ይቀሰቅሳቸዋል።

“ሲያብሎስ ኃይል” ኦክቶበር 5 ቀን 1955

 

ድምጹ በመጨረሻ ተናገረ። እርሱም የመጨረሻው ነገር ነው።

ኃይለኛ ነፋስ፣ ነጎድጓድ፣ እና ሁሉንም ነገር አይተናል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ድምጽ የሚናገርበት ሰዓት አሁን ደርሷል። ሲናገርም እርሱ ራሱ መሆኑን ያረጋግጣል። ነጎድጓዱን የላከው እርሱ ነው። እነርሱ ግን ድምጹን በማዳመጥ ፈንታ ነጎድጓዱን ተከትለው ሄዱ። እርሱም ነፋሱን ላከ፤ እነርሱ ግን ድምጹን ማዳመጥ ትተው ነፋሱን ተከትለው ሄዱ።

“ምን ትሰማለህ ኤልያስ” አፕሪል 12 ቀን 1959

የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

 

መጽሐፍ ቅዱስን አድምጡ፤ ዛሬ በዚህ ዘመን የሚጠራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች የተለያዩ ሃሳቦችን መፍጠር የትም አያደርሰንም።

ስለ ነጎድጓዶቹ በተሰጡ የተለያዩ ትርጓሜዎች መካከል ብዙ ግጭት አለ። ስለዚህ ለመተርጎም መሞከሩ ምን የማይጠቅም ድካም ነው።

ከግል ትርጓሜያችሁ በመነሳት አዲሱ ስም ምን እንደሚሆን መገመት እውነተኛው በተገለጠ ጊዜ አልቀበልም ብላችሁ እንድትቃወሙት ያደርጋችኋል።

ትዕግስተኛ መሆንና የእግዚአብሔርን ጊዜ መጠበቅ አለብን። አንድ ነጎድጓድ በራሳችን መፍጠርም ሆነ የሰባት ነጎድጓዶችን ያልተጻፈ ንግግር ለመተርጎም መሞከር የእግዚአብሔርን ዕቅድ አንድ እርምጃ እንኳ ወደፊት አያራምድም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23