አምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ማለት ምን ማለት ነው?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የነብዩን ንግግር ጥቅሶች ወደ ሐዋርያት ትምሕርት ወስደው በማመሳከር እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ የሚችሉ አስተማሪዎች ያስፈልጉናል።
- ከጉባኤው በላይ ከፍ ያሉ አገልጋዮች ትክክለኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች አይደሉም
- የ5ቱ አገልግሎቶች ካሕናት ከፍ ከፍ መደረጋቸው ትክክል አይደለም
- መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሮችን ስድስት ጊዜ ማውገዙ አስፈሪ ነገር ነው
- መሰረቶቹ ሐዋርያት እና ነብያት ናቸው
- ሐሰተኛ አስተማሪዎች የሚነግሯችሁ መስማት የምትፈልጉትን ነው
- እውነተኛ አስተምሕሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የሚመሰረተው
ከጉባኤው በላይ ከፍ ያሉ አገልጋዮች ትክክለኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች አይደሉም
የቤተክርስቲያን አመራር አስተምሕሮ በብዙ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያኖ የገጠሙዋቸውን ድረጅታዊ ችግሮችና ፈተናዎች (ሚዛናዊነት በጎደለው) በስጋዊ ጥበብ ለመፍታት ባደረጉት ሙከራ የተነሳ በብዙ ለውጦች ውስጥ አልፏል። ስለዚህ ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ የቤተክርስቲያን አመራር ጽንሰ ሃሳብ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ብዙ እየራቀ እየራቀ ሊሄድ ችሏል።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሕዝቡ ወይም ከጉባኤው በላይ ከፍ ያለ የአሮን ክሕነት ነበረ። ከፍ ብሎ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ቆሞ የነበረው ይህ የአሮን ክሕነት አዲሱ ኪዳን ሲጀምር ተሽሯል።
ኢየሱስ ሲመጣ ሕዝቡ ወደውት ነበረ፤ መሪዎቻቸውና ከፍ ያሉት ካሕናት ግን ለእነርሱ አስጊ ተቀናቃኝ ሆኖ ታያቸው።
ሕጉ ራሱ የወደቀው የአይሁድ አለቆች ሕዝቡ በሆሳዕና እሁድ ዕለት ኢየሱስን ከፍ ከፍ ካደረጉት በኋላ በቀጣዩ ሐሙስ ዕለት ይሰቀል ብለው እንዲያምጹ በማድረጋቸው ነው።
ኢየሱስ እሑድ ጠዋት ከሞት ከመነሳቱ በፊት ልክ እንደ ዮናስ መቃብር ውስጥ ሲስት ሌሊት ማደር ነበረበት።
ሐሙስ ሌሊት። አርብ ሌሊት። ቅዳሜ ሌሊት።
“የስቅለት አርብ” የሚለው አነጋገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ማቴዎስ 12፡40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
ሉቃስ 22፡2 የካህናት አለቆችና ጻፎችም እንዴት እንዲያጠፉት ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።
ማርቆስ 15፡11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።
ካሕናት ብዙ ችግር ፈጥረዋል፤ የአይሁድ ሕዝብ ላይ ጥፋት ያመጡበት ካሕናት ናቸው።
ሰዎች በራሳቸው አእምሮ ማሰብ ትተው ከፍ ከፍ ያሉ መሪዎቻቸውን በጭፍን ይከተላሉ። ሁልጊዜም ቢሆን ከሕዝቡ በላይ ከፍ ያሉና ሕዝቡ የእነርሱን እምነት እንዲከተሉ የሚያስገድዱ መሪዎች አሉ።
ይህ ከሰዎች ባሕርይ ውስጥ ትልቁ ስንፍና ሲሆን ብዙ አስከፊ ውጤቶችን አስከትሏል።
የቤተክርስቲያን አመራር በጣም ወሳኝ ነው።
ኢሳይያስ 9፡16 ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።
53-0614A EARNESTLY CONTENDING FOR THE FAITH THAT WAS ONCE DELIVERED TO THE SAINTS
እውነቱን ለንገራችሁ፤ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር መንፈስ ነው የምትመራው። መንፈሱ ሲሄድ አብረው ይሄዳሉ። እግዚአብሔር ከጳጳሳት ጋር ብቻ ለመንቀሳቀስ አይደለም ቃል የገባው።
በቤተክርስቲያን፣ በሁሉም ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪዎች ሽማግሌዎች ናቸው።
57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት-1
በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአጥቢያዋ ሽማግሌ የሚበልጥ ማን እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ።
እውነቴን ነው ወገኖች፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነጻ መሆን አለባት፤ እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራሷን ታስተዳድር።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
ጳውሎስ የአጥቢያ ቤተክርስቲያኖችን አመራር በሽማግሌዎች እጅ ነው አደራ ያስቀመጠው። አንድ ሰው ብቻ አለቃ እንዲሆን አልሾመም።
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
መንጋውን መጠበቅ የእረኛው ሃላፊነት ነው። እረኛው ደግሞ አንድ ሰው አይደለም።
እረኛው የሽማግሌዎች ሕብረት ነው።
የሐዋርያት ሥራ 20፡29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ … እኔ አውቃለሁ።
ተኩላዎች ዝቅ ብለው አይታዘዙም። ተኩላዎች መንጋውን ይጨቁናሉ።
ቤተክርስቲያንን የሚጨቁን አንድ ብቸኛ መሪ ተኩላ ነው።
የ5ቱ አገልግሎቶች ካሕናት ከፍ ከፍ መደረጋቸው ትክክል አይደለም
በብሉይ ኪዳን ዘመን አይሁዶች በእነርሱ እና በእግዚአብሔር መካከል ከፍ ባለ ስፍራ ሆነው የሚያገለግሉዋቸው የአሮን ካሕናት ነበሩዋቸው።
በአዲስ ኪዳን ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከፍ ባለ ጊዜ ከክርስቲያን ግለሰቦች በላይ ከፍ ብሏል።
ሰይጣን በአዲስ ኪዳን ውስጥ በቤተክርስቲያን ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ ያሉ ካሕናት “በአምስቱ አገልግሎቶች” ስም ሊመሰርት ያለማቋረጥ ሲሞክር ቆይቷል። ይህንን ስርዓት በመመስረት ስለተሳካለት ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ላይ ሊኖረው የሚገባውን ተጽእኖ ማዳከም ችሏል። የአመራር መዋቅሩ መጽሐፍ ቅዱስን ያልተከተለ ከሆነ ሌሎችም እንቅፋት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ቸል ብሎ ማለፍና ሰው ሰራሽ ልማዶችንና አስተሳሰቦችን መቀበል ቀላል ይሆናል።
ቅዱሳን ሰዎችን ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ የኒቆላውያን ስራ ይባላል። ከሰው አመለካከት አንጻር የኒቆላውያን ስራ ለቤተክርስቲያን አስተዳደር አዋጪ መንገድ ይመስላል፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያንን ለማስተዳደር አንድን ሰው አለቃ አድርገው የሚሾሙበት አሰራር ነው። ችግሩ ግን እግዚአብሔር ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ መጥላቱ ነው። በኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን የነበረችዋ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሰዎችን በአለቅነት ከፍ ማድረግን በመቃወሟ እግዚአብሔር አድንቋታል።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
54-0512 ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት
… የኒቆላውያን ክሕነት እዚያው ኤፌሶን ውስጥ ነው የተጀመረው። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በሶስት መቶ ዓመት ዕድሜው ውስጥ ውድቀት የጀመረው እዚያው ኤፌሶን ውስጥ ነው። የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ኒቆላውያን የራሳቸውን የወንድማማች ክሕነት ስርዓት በመፍጠር አዲስ አስተምሕሮ አመጡ … የራሳቸውን ክሕነት መሰረቱ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እነርሱ የሚያደርጉት ነገር የኒቆላውያን “ሥራ” ተባለ። ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ አስተምሕሮ ሆነና ወደ ባቢሎን ሄዶ ሲመለስ እዚህ ደግሞ በመጨረሻው ዘመን ውስጥ በክርስትና ካባ ተጠቅልሎ መጣ፤ አሁን ጥቂት ቅሬታዎች ከውስጡ ወጥተው ይድናሉ።
60-1205 የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን
ጳውሎስ ተኩላ ያላቸው ሰዎች “ኒቆላውያን” ሆነዋል።
ልክ እንደ አሮን ክሕነት የሚመስል ክሕነት ሊፈጥሩ እየሞከሩ ነበር፤ እንዲህ ዓይነቱ ክሕነት ግን ለአዲስ ኪዳን አስተምሕሮ ባዕድ ነው። አሜን! ኒቆ የሚለው የግሪክ ቃል “ማሸነፍ፣ ማንበርከክ” ማለት ነው። “ማንን ነው የሚያንበረክኩት?” ምዕመናንን፣ መንፈስ ቅዱስን።
በአዲስ ኪዳን ሁላችንም ካሕናት ነን። ከአንድ ካሕን በላይ ከሊቀ ካሕኑ ከኢየሱስ በቀር ማንም የለም።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ … ናችሁ፤
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዴት እንድትገነባ ነው የፈለገው?
ኤፌሶን 2፡20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤
ብሉይ ኪዳን መልእክቱን ከአዲስ ኪዳን ጋር በጥብቅ በማስተሳሰር ሁልጊዜ የኢየሱስን የበላይነትና ታላቅነት ያጎላል።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡2 በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታንና የመድኃኒትን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።
ከአስተምሕሮ አንጻር የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ከጻፉ ነብያት እና አዲስ ኪዳንን ከጻፉ ሐዋርያት ጋር መስማማት አለብን።
ይሁዳ 1፡17 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚናገር ጥቅስ ይህ ብቻ ነው፤ ስለዚህ እንዴት እንደምንተረጉመው በጣም መጠንቀቅ አለብን።
በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በነዚህ የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አምስት ሰዎችን ሊመድቡ ይቸኩላሉ፤ ከዚያም ፓስተሩን የኮሚቴው ሊቀመንበር ያደርጉታል። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ግን እንዲህ ታደርግ ነበርን? እውነተኛዋ ምሳሌያችን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት።
ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
ስለዚህ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ተሰብስበው አንድ ቤተክርስቲያን መሆን ይችላሉ። ነገር ግን በመካከላቸው አምስቱንም አገልግሎቶች በሙሉ ላያገኙ ይችላሉ።
ስለ አምስቱ አገልግሎቶች የሚናገረውን ይህንን ጥቅስ አውዱን እንመርምር።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
12 ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
እነዚህ ክርስቲያኖችን ወደ ፍጹምነት የሚያደርሱ አምስት አገልግሎቶች ናቸው። ይህ ታላቅ ኃላፊነት ነው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
ፍጹምነት የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ከማመን እና ቃሉ ውስጥ ካለው ጸጋ በመጠቀም ነው።
ስለዚህ አምስቱ አገልግሎቶች የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ መግለጥ መቻል አለባቸው።
“ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ”
አምስቱ አገልግሎቶች መገንባት ወይም ማነጽ ያለባቸው የክርስትናን አካል በሙሉ ነው፤ አገልግሎታችሁ ላይ ቢገኙም ባይገኙም መላው የአካል ብልቶች መታነጽ አለባቸው። የትኛውም “ቤተክርስቲያን” ቢሄዱ እንኳ መታነጽ አለባቸው። እነዚህ አገልግሎቶች በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እና በዓለም ዙርያ ሁሉ የሚሰሩ ናቸው። ዛሬ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ሁሉም የተለያዩ ሆነው ግን ሁሉም እኛ ትክክል ነን ይላሉ። ስለዚህ አንድ ከባድ ችግር አለ ማለት ነው። የእምነት አንድነት የሚባል ነገር ጠፍቷል። ቤተክርስቲያኖች መሪዎቻቸውን ይከተላሉ፤ እርስ በራሳቸው ይቀዋወማሉ፤ እንደተሰነጣጠቀ መስታወት በብዙ ቡድን ተከፋፍለዋል።
ኤፌሶን 4፡13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
እምነት የምናገኘው ከተጻፈው ቃል ነው። አንድ መሆን የምንችለው የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ አለብን። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ ደግሞም እርሱ ቃሉ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት እያደግን ስንሄድ ወደ ፍጹምነት የምንሄድበት መንገዳችን እምነታችንን በተጻፈው ቃል ላይ በማድረግ ነው።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምረን ሰው ያስፈልገናል።
ኤፌሶን 4፡14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እያያዘ ጤናማ ትምሕርት የሚያስተምረን ሰው ያስፈልገናል።
አስተምሕሮ ስልጣን የሚኖረው ምንጩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን ብቻ ነው።
የአንድ ሰው ብልጥ አመለካከት ስልጣን የለውም። ተንኮለኛ ሰዎች ሕዝብን ለማሳሳት የተጻፈውን ቃል ይለውጡታል።
ቃሉ ማለትም ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።
ኤፌሶን 4፡15 ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
ዮሐንስ 17፡17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
አገልጋዮች እውነትን መውደድ አለባቸው። ለተጻፈው ቃል ፍቅር ሊኖራቸው ይገባል። ቃሉ ክርስቶስ ስለሆነና ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ስለሆነ።
ይህ በጣም አስፈላጊ ግንዛቤ ነው። ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን በመሰረቱ ጊዜ የትኛውንም ግለሰብ በቤተክርስቲያን ላይ አለቃ አድርገው አልሾሙም። አስራ ሁለት ደቀመዛሙርት ተባብረው ነበር ቤተክርስቲያንን የመሩዋት። አዲስ ኪዳንን የጻፉት ደግሞ ስምንት ሰዎች ናቸው። አመራር ሁልጊዜ በሕብረት የሚከናወን ኃላፊነት ነው። የትኛውም ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ አያውቅም። ክርስቶስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ መሆን የሚችለው። እኛም የምንሰማው እርሱን ብቻ ነው። እርሱ ቃሉ ነው። ስለዚህ እኛ ቃሉን ብቻ ነው መስማት ያለብን።
ኤፌሶን 4፡16 ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
አካል ሁሉ የሚለው ክርስቲያኖችን በሙሉ ያጠቃልላል እንጂ ከሌሎቹ ሁሉ እኔ እሻላላሁ የምትለዋን አንድ ቤተክርስቲያን ማለት አይደለም። እያንዳንዱ የአካል ብልት የራሱ የሆነ ብቃትና የስራ ድርሻ አለው። የአካል ብልቶች አንዳቸው ከሌላው ጋር መመሳሰል አያስፈልጋቸውም። ክርስቲያኖች ሌሎች ክርስቲያኖችን መኮረጅ ወይም ለመምሰል መሞከር የለባቸውም። የአካል ብልቶች የሚጠበቅባቸው ለአካሉን ራስ መገዛት ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ማለትም ቃሉ ነው።
ኤፌሶን 4፡17 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
አሕዛብ ከፍጥረታቸው ጣኦት አምላኪ ሕዝብ ናቸው። ይህ በተፈጥሮዋችን ውስጥ ያለ ድክመት ነው። ስለዚህ ለራሳችን ደስ በሚያሰኘን እና በሚመቸን መንገድ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር የለብንም። ሰብዓዊ የሆነው የሐይማኖት ዝንባሌያችን ከንቱ ነው።
ማርቆስ 7፡7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ … የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ …
ለራሳችን የሚመቸንን ዓይን የአምልኮ ዘይቤ መፍጠር የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው መታዘዝ ያለብን። እግዚአብሔርን በራሳችን አምሳል መፍጠር የለብንም። ፍላጎታችንን እና ጥላቻችንን በእግዚአብሔር ቃል ላይ መጫን የለብንም።
ኤፌሶን 4፡18 እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤
እግዚአብሔር የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ማለትም የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዕውር ናት ብሏል። ይህን ያለው እምነታችንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለማናረጋግጥ ነው።
ክርስቲያኖች የአንድ መሪ አመለካከት እየተከተሉ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን አይመረምሩም፤ ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በጣም ይጎድላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ክርስቲያኖችን የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይሞች አድርጓቸዋል። አይሁዶች አንዲትን ሴት በድንጋይ ሊወግሩ ፈልገው ሲቀርቡ ኢየሱስ ለምንድነው መሬት ላይ ሁለት ጊዜ በጣቱ የጻፈው? ክርስቲያኖች ይህንን ጥያቄ ሲጠየቁ አናውቅም ብለው ከዚያም ስለ አለማወቃቸው ምንም ግድ ሳይላቸው ይሄዳሉ። ኢየሱስ ብዙ ሺ ሰዎችን በተዓምራት እንጀራ ካበላ በኋላ አንድ ጊዜ 12 መሶብ ሌላ ጊዜ ደግሞ 7 መሶብ ቁርስራሽ ለምን እንደተረፈ ደቀመዛሙርቱ ገብቷቸው እንደሆነ ጠይቋቸዋል። ዛሬ ግን ክርስቲያኖች ስለ ጉዳዩ ለደቂቃም እንኳ አያስቡበትም። ቤተክርስቲያን ውስጥ አለማወቅ ደስታ ሆኗል። ምን አስጨነቀን? ባናውቅስ? ምንም አይጠቅመንም ይላሉ።
እውነት?
አንድ ጥቅስ ያልገባው ከሆነ እናንተንም አትጨነቁበት ምንም አይጠቅማችሁም የሚል ፓስተር አለማወቁ እንዳይታወቅበት እራሱን እየጠበቀ ነው እንጂ እናንተን በእድገታችሁ እየረዳችሁ አይደለም።
መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን መመለስ የማትችሉ ከሆነ ዕውር ናችሁ ማለት ነው ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ስትመለከቱ በውስጣቸው ምንም ብርሃን አይታያችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል አይተን “ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም” ስንል ወይ መጽሐፍ ቅዱ ብርሃን አይደለም (ይህ እውነት አይደለም) ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ብርሃን አይሰጥም ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን አለማጥናት ይሻላል እልን ነው፤ አለዚያ ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ብርሃን እንዳናይ ታውረናል ማለት ነው።
አምስቱ አገልገሎቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ መመራት ሊያስተምሩን ይገባል። ነገር ግን ዕውር መሆኗን በማታውቅ በመጨረሻ ዘመን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እነዚህ አምስት አገልግሎቶች የት ናቸው?
ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ቡድን ምንም አያስፈልገኝም ይላል። ከቡድናቸው ውጭ ከሆነ ሰው የሚመጣላቸውን እርማት አይቀበሉም። የሚያስፈልጋቸውን ምሪትና እውቀት በሙሉ የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ያቀርቡላቸዋል።
ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ስለተሞሉት ልባም ቆነጃጅት ምን እንደሚል ተመልከቱ።
ማቴዎስ 25፡4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
ዛሬም ልባሞቹ ቆነጃጅት በሙሉ ተኝተዋል።
እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ይህንን እውነት ይክዳል፤ አልተኛንም ይላሉ፤ እኛ ነቅተናል፤ የተኙት ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች ናቸው።
ማርቆስ 13፡35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና
36 ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ።
ዋናው ጉዳይ ይህ ነው። “አምስቱ አገልጋዮች” የተባሉት የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው በቤተክርስቲያን ላይ ስልጣን በመያዝ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ እንቅልፍ ተኝተው እንዲቀሩ ያደረጓቸው።
እንቅልፍ ስለተኙት ልባሞቹ ቆነጃጅት የተነገረው ምሳሌም በመንፈስ ቅዱስ የተመሉ፣ ልባም የሆኑ በመብራታቸው ውስጥ ዘይት የያዙ ክርስቲያኖች በሙሉ አንቀላፍተዋል ይላል።
ነገር ግን የየትኛዋም ቤተክርስቲያን አባላትና መሪዎች ስለ ራሳቸው ሲያስቡ ይህ እውነት መሆኑን አይቀበሉም።
ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ተሳስቷል ማለታቸው ነው። በዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች በዚህ ምሳሌ ውስጥ ያለውን ብርሃን መቀበል አይችሉም ምክንያቱም ምሳሌው እነርሱን ይወቅሳቸዋል። ብርሃኑን ማየት ካልቻሉ ታውረዋል ማለት ነው።
ይህም ለመታለላቸው ግልጽ ማስረጃ ነው።
የዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች ልባሞቹን በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉትን አማኞች በሙሉ እንቅልፍ ማስተኛት ችለዋል።
ምሳሌ 10፡5 በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል።
በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ክርስቲያኖችም ጭምር መረዳት ያልቻሉዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቸል ሲሉ ወይም ሲቃወሙ ምንም አይመስላቸውም። እንቅልፍ የተኙ ሰዎች ዓይናቸው ላይ ብርሃን ብታበሩባቸው አትረብሹኝ ብለው ያባርሯችኋል።
የቤተክርስቲያን አባላት መረዳት ያልቻሉዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ስታቀርቡላቸው የሚሰጡዋችሁ መልስ ይህን ይመስላል።
መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ ለአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ለስለስ ባለ አነጋገር ተናግረው አያውቁም።
ዋናው ጥፋት ያለው በቤተክርስቲያን አመራር ውስጥ ነው።
ክርስቲያኖች ሁሉ የሙሽራውን መምጣት ከሚጠብቁት አምስት ልባም ቆነጃጅት መካከል ነን ይላሉ። ነገር ግን ክርስቲያኖች በሙሉ አምስቱ ልባም ቆነጃጅት እንቅልፍ መተኛታቸውን አያስተውሉም። ይህንን ቃል አይቀበሉትም።
ደግሞም የተኙትን ልባሞቹንም ሰነፎቹንም ከእንቅልፍ የሚያነቃቸው ድምጽ ምን እንደሆነ አያውቁም።
እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አባላት መሪያቸው እንዳነቃቸውና ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ግን እንቅልፍ ውስጥ እንደሆኑ ይናገራሉ። ድምጹ ግን ሁሉንም ልባሞቹንም ሰነፎቹንም በአንድ ጊዜ እኩል ነው የሚያነቃቸው። ይህ ግን እስካሁን አልተፈጸመም ምክንያቱም አብዛኞቹ ቤተክርስቲያኖች እስከ ዛሬ በመረጡት መንገድ እየሄዱ ናቸው።
ድምጹ ግን የመጣው ከአስሩ ቆነጃጅት መካከል አይደለም። አስሩም በሙሉ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩ። ስለዚህ ድምጹ የሚመጣው ከቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውጭ ነው። ድምጹ በፊት ከነበረ ከአንድ ታላቅ ሰባኪ አይደለም የመጣው። ድምጹ በመጨረሻው ሰዓት እንቅልፍ በሚከብድበት እኩለ ሌሊት ላይ ነው የመጣው። ያ ድምጽ ምንድነው? ይህን ታውቃላችሁ ወይስ ታውራችኋል?
ያለፈው ክፍለ ዘመን ውስጥ ታዋቂ የነበረው ታላቅ ወንጌላዊ ቢሊ ግራም እንዲህ ብሎ ነበር፡- ጌታ ቤተክርስቲያንን ዛሬ ወደ ሰማይ ቢነጥቃት ነገ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉ አገልግሎቶች በሙሉ ምንም ሳይሆኑ እንደነበሩ ይቀጥላሉ። ይህ ለዛሬ ቤተክርስቲያኖች ጠንካራ ተግሳጽ ነው።
ክርስቲያኖች የዘመን መጨረሻ ላይ ደርሰናል ይላሉ፤ ነገር ግን የመጨረሻው ዘመን የሆነችዋ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን - ዕውር የሆነችዋ ቤተክርስቲያን አካል መሆናቸውን ይክዳሉ። የትኛዋም ቤተክርስቲያን ዕውር መሆኗን ማመን አትፈልግም። እውነተኛው ራስ ክርስቶስ ግን ከሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል። የትኛዋም የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ከዚህ ውጭ ነች ተብሎ አልተጻፈም።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጦ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚል ሁሉ ሐሰተኛ ራስ ነው።
በዚህ ዘመን ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ይላል።
ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ብሎ መናገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ሃሳብ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ፓስተሮችን ስድስት ጊዜ ማውገዙ አስፈሪ ነገር ነው
እስቲ ከፓስተሩ እንጀምር።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፓስተሩ ምን ይላል?
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
አዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ፓስተር የሚናገር ብቸኛው ጥቅስ ይህ ነው።
በአምስት አገልግሎቶች ውስጥ ፓስተር አራተኛ ደረጃ ላይ ነው የተጠቀሰው። ይህ የመሪነትና የገዥነት ስልጣን ሊሰጠው ይችላልን? በፍጹም አይችልም።
“ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው”። መጽሐፍ ቅዱ እንደዚያ አይልም።
“አስራት የፓስተሩ ድርሻ ነው”። መጽሐፍ ቅዱ እንደዚያ አይልም።
“ፓስተሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ይገልጣል”። መጽሐፍ ቅዱ እንደዚያ አይልም።
“ፓስተራችሁን ተከተሉ ምክንያቱም እርሱ እስከ መጨረሻው ያዛልቃችኋል”። መጽሐፍ ቅዱ እንደዚያ አይልም።
“ከፓስተራችሁ በላይ መኖር ወይም ከእርሱ በላይ ማወቅ አትችሉም”። መጽሐፍ ቅዱ እንደዚያ አይልም።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ፓስተሩን ከፍ ከፍ አድርጋ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ብላ መሾሟ ሙሉ በሙሉ ትልቅ ስሕተት ነው።
ስለ ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ምን እንደሚል እንመልከት።
ፓስተር ስምንት ጊዜ ተጠቅሶ ከዚያ ውስጥ ስድስት ጊዜ ተወግዟል።
ይህም እግዚአብሔር የሚገረምበት አገልግሎት አይደለም። ኢየሱስም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች አድናቂ አልነበረም። የቤተክርስቲያን መሪዎች በጣም ከባድ ችግር አለባቸው።
ኤርምያስ 3፡15 እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ ጥቅስ ብቻ ነው ስለ ፓስተሮች በጎ ነገር የሚናገረው።
ነገር ግን ይህ ቃል የሚናገረው ስለ 1,000 ዓመቱ የሰላም ዘመን ነው፤ በዚያ ጊዜ የሁሉም ሃገር ህዝቦች ለምድር ዋና ከተማ በምትሆነው በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ። የኢየሱስ ዙፋንም በዚያ ነው የሚቀመጠው።
በሺው ዓመት መንግስት ዘመን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን፣ እርሱ ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኑን ሰዎች ሁሉ ይገነዘባሉ።
ሕዝብም ሁሉ የጌታ ስም ማን እንደሆነ ያውቃሉ።
ስለዚህ ስለ ፓስተሮች የተነገረው ይህ በጎ ቃል ስለ ዛሬዎቹ ፓስተሮች አይደለም፤ በዚህም ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች በስላሴ ያምናሉ፤ ስለዘህ የእግዚአብሔርን ስም አያውቁም። እግዚአብሔር ሶስት አካላት ነው ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ የእግዚአብሔርን ስም ልታውቁ አትችሉም።
ኤርምያስ 3፡17 በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን የእግዚአብሔር ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርስዋ ይሰበሰባሉ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልከኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም።
በነብዩ ኤርምያስ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ፓስተሮች የተጻፉት ሌሎች ጥቅሶች በመልካም አይደለም የሚያነሱዋቸው።
ኤርምያስ 2፡8 ካህናቱም፡- እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።
“አላወቁኝም”። የአንድን ሰው ስም የማታውቁ ከሆነ ያንን ሰው በእውነት አታውቁትም።
ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች የስሉስ አምላካቸውን ስም አያውቁም። ለሶስት ሰዎች የሚሆን አንድ ስም ማግኘት አይችሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ አያውቁም።
ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
አንድ ሰው የቤተክርስቲያን አለቃ ሆኖ ተቀመጠ ማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈለግ ያቆማል ማለት ነው። የራሱን ሃሳብ ማስፈጸም ይጀምራል። እርሱን የሚቃወሙ ሰዎች በሙሉ ይባረራሉ።
እያንዳንዱ ፓስተር የግል አመለካከቱን ያራምዳል፤ ይህም ቤተክርስቲያን በ45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች እንድትከፋፈል ምክንያት ሆኗል።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
ፓስተሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ትተው ወደ ሰው ንግግር ጥቅስ ፈቀቅ ይላሉ። ከዚህም የተነሳ ተከታዮቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን ብዙም አያውቁም። በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተቀባይነት ማግኛ መንገድ ፓስተሩን ማሞጋገስ ነው። ጉባኤው የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይም ሆኖ ይቀራል፤ ስለዚህ እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አይችሉም። ሕዝቡ ከሃሳባቸው ጋር የሚጋጩ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን ይቃወማሉ።
ቤተክርስቲያን በሚሄዱ ሰዎች ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ትልቅ ችግር ነው።
ኤርምያስ 17፡16 እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልቸኰልሁም፥
ከዚህ ቃል አንጻር ፓስተር መሆን እግዚአብሔርን አለመከተል መሆኑን ልብ በሉ።
የጉባኤ አለቃ መሆን አንድ ሰው እግዚአብሔርን እንዲከተል አያነሳሳውም።
የአንድ ጉባኤ ተቆጣጣሪ ፓስተር መሆን ማለት ፓስተሩ የእግዚአብሔርን ቃል እየተከተለ አይደለም ማለት ነው። ፓስተሩ የጉባኤ አለቃ ነው የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
ፓስተሮች እግዚአብሔርን መከተል ከፈለጉ የጉባኤ ሃላፊ ከመሆን መውረድ አለባቸው።
ነገር ግን ገንዘቡ እና ስልጣኑ በጣም ፈታኝ ናቸው፤ ስለዚህ ፓስተሮች ከስልጣናቸው ለመውረድና እግዚአብሔርን ለመከተል ልባቸው አይነሳሳም።
ስለዚህ የቤተክርስቲያን ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እየመረጡ ይሰብካሉ።
ኤርምያስ 22፡22 ግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥
ነፋስ የሚያመለክተው ግጭት ወይም ጦርነትን ነው።
ፓስተሮች ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አለብን የሚሉ ሰዎችን በመዋጋት ስልጣናቸውን ያስጠብቃሉ፤ አመለካከታቸውንም በሕዝቡ ላይ በግድ ይጭናሉ። ዋናው ሃሳባቸው ከጉባኤው የሚያገኙት የገንዘብ ምንጭ እንዳይቋረጥባቸው ነው። የፓስተሩን አመለካከት አሜን ብለው የማይቀበሉ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ አይፈለጉም። ከፓስተሩ ጋር ካልተስማማችሁ ብዙ ጦርነት ይነሳል።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፡፡
ኢሳይያስ 9፡16 ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።
65-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ብቸኛው ስፍራ
ታክሰን ውስጥ አሁን በዚህ ማለዳ የሚያዳምጡ ሰዎች የሆነ ጊዜ …
ከዚህ በፊት ሰዎችን ሁሉ “ቤተክርስቲያን ሂዱ፤ የትኛውም ቤተክርስቲያን ቢሆን ሂዱ” እያልኩ እገፋፋቸው ነበር።
ሰዎችም ለመሄድ ሲያመነቱና ወደ ሌላ ቦታ ሲሄዱ አይቻለሁ። እኔም “ምን ነካቸው” እያልኩ አስብ ነበር።
ወደ አንዳንዶቹ ቤተክርስቲያኖች ሄድኩ፡- “መጀመሪያ የሄዳችሁ ቀን ወደናንተ ቀረብ ይሉና፡ የኛ ቤተክርስቲያን አባል ሁኑ ይሉዋችኋል። እሺ ካላላችኋቸው አይቀበሉዋችሁም።” አያችሁ? አያችሁ? በግድ የእነርሱ ቤተክርስቲያን አባል እንድትሆኑ ይሏችኋል። ግዴታ ያደርጉባችኋል፤ ባቢሎን ማለት ይህ ነው።
በክርስቶስ ግን ተመርጣችሁ ነው ወደ እርሱ የምትመጡት፤ በግዳጅ አይደለም፤ ላባችሁ ወደ እርሱ ይስባችኋል።
እግዚአብሔር በዚያ ዘመን ስሙን በባቢሎን አላኖረም። ልብ በሉ።
ዛሬም ስሙን በባቢሎን ማለትም በቤተክርስቲያኖች ዘንድ አያኖርም።
እነርሱማ ስሙን በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ያደርጋሉ፤ እርሱ ግን ስሙን በዚያ አላደረገም።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት የሚኖራችሁ ከፓስተሩ ጋር እስከተስማማችሁ ድረስ ብቻ ነው።
ከፓስተሩ ጋር ከተጋጫችሁ ከቤተክርስቲያን ለመልቀቅ ትገደዳላችሁ።
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
ይህ መልካም ምስክርነት አይደለም። እግዚአብሔር በፓስተሮች አይገረምም።
በዓለም ላይ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ፓስተር እኔ ትክክል ነኝ ብሎ ማሰቡ አያሳምንም። ሁሉም ፓስተሮች ትክክል ነኝ ስለሚሉ ሁሉም ከሁሉም ጋር ትምሕርታቸው ይጋጫል።
53-0614A አንድ ጊዜ ለቅዱሳን ለተሰጠችዋ እምነት መጋደል
እውነቱን ለንገራችሁ፤ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር መንፈስ ነው የምትመራው። መንፈሱ ሲሄድ አብረው ይሄዳሉ። እግዚአብሔር ከጳጳሳት ጋር ብቻ ለመንቀሳቀስ አይደለም ቃል የገባው።
በቤተክርስቲያን፣ በሁሉም ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪዎች ሽማግሌዎች ናቸው።
57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት-1
በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአጥቢያዋ ሽማግሌ የሚበልጥ ማን እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ።
እውነቴን ነው ወገኖች፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነጻ መሆን አለባት፤ እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራሷን ታስተዳድር።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
ሽማግሌዎች በሙሉ ሰባኪዎች አይደሉም። ነገር ግን ሁሉም ሽማግሌዎች ቤተክርስቲያንን በማስተዳደር ውስጥ ሚና አላቸው።
ቤተክርስቲያን የምትመራው በሰባኪዎች ብቻ አይደለም።
እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን ውስጥ ፓስተሮችን አንድ ጊዜ ብቻ ነው የጠቀሰው።
በዚህ ቃል ውስጥ አገልግሎቶች በቅደም ተከተላቸው ተጽፈዋል። መጀመሪያ ሐዋርያት፣ ሁለተኛም ነብያት፤ ሶስተኛም አስተማሪዎች። ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሌሎች አገልግሎቶች።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
አስተማሪዎች ሐዋርያት እና ነብያት የጻፉትን ቃል በመጠቀም እውነትን ያብራራሉ።
ሰዎች እውነትን ከእግዚአብሔር ቃል መማራቸው በጣም አስፈላጊ ነው።
ፓስተሮች ጭራሽም አለመጠቀሳቸውን አስተውሉ።
ፓስተር እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ የሾመው የአገልግሎት ዘርፍ አይደለም።
ሽማግሌዎች በአንድነት ሆነው ነው ሁሉንም የአገልግሎት ዓይነት የሚያከናውኑት።
በዚህ ሁሉ ውስጥ ዋናው ነገር ጤናማ አስተምሕሮን መመስረት ነው።
የሚሰጠው ትምሕርት ሙሉ በሙሉ ፍጹም እውነት ካልሆነ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከንቱ ናቸው።
መሰረቶቹ ሐዋርያት እና ነብያት ናቸው
ሐዋርያት መጀመሪያ የተጠሩት በኢየሱስ ነው።
ሉቃስ 6፡13 በነጋም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ጠራ፥ ከእነርሱም አሥራ ሁለት መረጠ ደግሞም ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 2፡42 በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።
ቤተክርስቲያን ማመን ያለባትን መሰረታዊ አስተምሕሮ ሐዋርያት ጽፈዋል።
የሐዋርያት ሥራ 15፡6 ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።
ሐዋርያቶች ብዙውን ጊዜ ከአጥቢያ ሽማግሌዎች ጋር እየተማከሩ ቤተክርስቲያን መከተል ያለባትን መሰረታዊ ትምሕርት አዘጋጅተዋል።
የሐዋርያት ሥራ 16፡4 በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው።
5 አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።
ሐዋርያት የጻፉትን፤ ዛሬ አዲስ ኪዳን ብለን የምንጠራውን መጽሐፍ በማመን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ተመሰረተች።
2ኛ ቆሮንቶስ 12፡12 በእርግጥ የሐዋርያነት ምልክት በመካከላችሁ በምልክትና በድንቅ ነገር በተአምራትም በሁሉ ትዕግሥት ተደረገ።
ሐዋርያት የተባሉት ሰዎች ጥሪያቸው እውነት መሆኑን ለማስመስከር ታላላቅ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ምልክቶችንና ድንቆችን አድርገዋል።
ራዕይ 2፡2 ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
ሌሎች ደግሞ ሐዋርያት ነን ሊሉ ሞከሩ። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ግን የምታምነው የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት በጻፉት አዲስ ኪዳን መጽሐፍ ብቻ ነው። የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የተናገሩትን የማትናገሩ ከሆነ ውሸታሞች ናችሁ። ስለዚህ ከአስተምሕሮ አንጻር ኋላ የመጡና ሐዋርያት ነን የሚሉ ሰዎች ምንም አዲስ ነገር አላመጡም። ብቸኛው ዋጋ ያለው አስተምሕሮ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የጻፉት ነው።
በወንጌል ስርጭት ዘመን ብዙ የወንጌል ሰባኪዎች ሐዋርያት ተብለዋል። ነገር ግን አስተምሕሮን በተመለከተ ምንም የሚሉት ነገር አልነበራቸውም። እነርሱ ማለት የሚችሉት የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ያሉትን ብቻ ነው። ወንጌል ሰባኪዎች መጽሐፍ ቅዱስን በተቃረኑበት ጉዳይ ሁሉ ተሳስተዋል።
ራዕይ 21፡14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
ሐዋርያት ሊለወጥ የማይችለው እውነት የተመሰረተው በሐዋርያት ላይ መሆኑን ታላቋ ቅድስት ከተማ ትመሰክራለች።
ኤፌሶን 2፡20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤
ሐዋርያት አዲስ ኪዳንን ጻፉ። ነብያት ደግሞ ብሉይ ኪዳንን ጻፉ። እውነት የተመሰረተው በነዚህ ላይ ነው። መሰረቱ የተመሰረተው በጥንት ዘመን ነው። ቤተክርስቲያን ደግሞ በመሰረቱ ላይ ለ2,000 ዓመታት ስትገነባ ቆይታለች።
ሐዋርያት እና ነብያት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማሻሻል የሚችሉ ዘመናዊ አገልጋዮች አይደሉም።
አንድ ሰው የትንቢት ስጦታ ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን ይህ ስጦታ የቤተክርስቲያን መሰረት አይደለም። የእምነታችን መሰረት የብሉይ ኪዳን ነብያት የጻፉት ቃል ነው።
ትልልቆቹ እና ጠንካራዎቹ ድንጋዮች መጀመሪያ መሰረት ይሆናሉ፤ ይህም የሚደረገው የሕንጻው ሙሉ ክብደት በእነርሱ ላይ ተደላድሎ እንዲቆም ነው። ከተመሰረተው መሰረት ውጭ የትም መሄድ አንችልም። መሰረት በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ መገንባት ብቻ ነው የምንችለው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡10 የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጳውሎስ የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት መሰረተ።
ሰዎች ግን ጳውሎስ ያስቀመጠውን መሰረት አስወግደው ቤተክርስቲያንን ወደ ጨለማ ዘመን ውስጥ አስገቡዋት። ከዚያ በኋላ የተሃድሶ መሪዎች ቤተክርስቲያንን ጳውሎስ ወደመሰረተው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት መለሷት።
ሚክያስ 5፡5 ይህም ለሰላም ይሆናል፤ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።
ስምንት አለቆች ማለት አዲስ ኪዳንን የጻፉ ስምንት ሰዎች ማለት ነው።
ሰባት እረኞች ማለት ቤተክርስቲያን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንድትመለስ ያበረታቷት የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኞች ናቸው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
አንድ ቤት በድንጋይ ሲገነባ ሶስት መሰረታዊ ስራዎች መሰራት አለባቸው።
1. መጀመሪያ ድንጋዩ ከተራራ ተቆፍሮ ይወጣል። ይህ የወንጌላዊው ስራ ነው። “የዳነው” ድንጋይ ቅርጹ አልተስተካከለም ነገር ግን ለቤት ስራ ዝግጁ ነው።
2. በሁለተኛ ደረጃ ድንጋዩ ተጠርቦና ተሞርዶ ቅርጽ መያዝ አለበት። ይህ የፓስተሩ ስራ ነው። ፓስተሩ አዲሱን አማኝ የኑሮ ችግሮችን እንዴት እንደሚወጣ እና በእግዚአብሔር እያመነ የተሻለ እንዲሁም በቅድስና የተሞላ ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚቻል ያስተምረዋል። ይህ የወንጌሉ ወተት ነው። አማኞች በመንፈስ ቅዱስ እስኪጠመቁ ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እንዲያምኑ እና እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ መበረታታት ያስፈልጋቸዋል።
3. በሶስተኛ ደረጃ ቅርጽ የያዘው ድንጋይ ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርቶችንና የወንጌሉን ጽኑ መብል በመብላት በእግዚአብሔር መንፈሳዊ ሕንጻ ውስጥ የራሱን ቦታ ማግኘት አለበት። አንድን ሰው በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ቦታ ማስያዝ የአስተማሪ አገልግሎት ነው።
ስለዚህ አምስቱን አገልግሎቶች እንመልከት።
የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምሕሮ እውነት ከማጽናት ጋር የተያያዙ ሶስት አገልግሎቶች ብቻ ናቸው ያሉት።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
እውነተኛ አስተምሕሮ የሚጸናበት ስርዓት ይህ ነው። ከዚህ ቅደም ተከተል ውጭ ብትንቀሳቀሱ ሁሉን ነገር ታበላሻላችሁ።
መጀመሪያ ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ጽፈው የጸጋውን ወንጌል አስተምሕሮ መሰረቱ። ማንም ቢሆን በምንም መንገድ አዲስ ኪዳንን ሊለውጥ አይችልም።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሌላ የእውነት መሰረት አለ። ነብያት ማለት የአዲስ ኪዳንን ቅርጽ እና ጥላ ያመለከቱ የብሉይ ኪዳን ነብያት ሲሆኑ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈው ትምሕርት እነርሱ ካሳዩት ጥላ ጋር በትክክል ይገጥማል።
በተጨማሪ የአዲስ ኪዳን ነብያት ወደፊት ሊሆኑ ስላላቸው ብዙ ነገሮች ትንቢት ተናግረዋል፤ ከነዚህም ውስጥ ሐዋርያ እና ነብይ የሆነው ዮሐንስ የጻፈው የራዕይ መጽሐፍ ይገኝበታል።
ነገር ግን በሰባተኛው ወይም በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚመጣ አንድ የነብይ አገልግሎት አለ፤ ይህም ከሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ የስድስቱን ትርጉም በማብራራት የተሰወሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን የሚገልጥ ሲሆን የዚህ አገልግሎት ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተዘግተው የተነበሩ ሚስጥራትን መግለጥ ነው። የጌታን ምጻት የሚመለከተው ሰባተኛው ማሕተም እንደምናውቀው ሚስጥር ሆኖ ይቆያል። ጌታ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ይህ አገልግሎት ግን በሁለተኛ ደረጃ ነው የተሰለፈው ምክንያቱም የዘመን መጨረሻ ላይ የተላከው ነብይ አዳዲስ አስተምሕሮዎችን ይዞ ሊመጣ አይችልም፤ የእርሱ ተልዕኮ ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ ነው።
ራዕይ 22፡9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።
ለዮሐንስ ብዙ ነገር የገለጠለት ይህ ታላቅ ነብይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ለመጠበቅ ምን ያህል እንደተጠነቀቀ ልብ በሉ። ዮሐንስ ነብይም ሐዋርያም ነው። ነገር ግን እርሱ የጻፈው አዲስ መገለጥ አስቀድሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ከነበረው እውነት በአንድም ነጥብ እንኳ የሚጋጭ አልነበረም።
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
መጥምቁ ዮሐንስ የአይሁድ አባቶችን ወደ ልጆቻቸው፣ ወደ ኢየሱስ እና ወደ ሐዋርያት መለሳቸው። ከዚያ በኋላ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት አድገው የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አባቶች ሆኑ። እኛ በዚህ በዘመን መጨረሻ ላይ ያለን አማኞች ደግሞ ወደ መጀመሪያዎቹ ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ ያለብን ትንንሽ ልጆች ነን።
“ነብያት” (በብዙ ቁጥር) ተብሎ የተጻፈው እንደ ሙሴ የመሳሰሉ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉ ነብያትን የሚያመለክት ቃል ነው።
ማርቆስ 1፡2 እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥
ማቴዎስ 22፡37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።
38 ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
39 ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።
40 በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።
ማቴዎስ 26፡56 ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።
በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ የትንቢት ስጦታ ያላቸው ነብያት አሉ፤ እነርሱም አገልግሎታቸው በዘመናቸው ያለችውን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ማበረታታት ነው።
ነገር ግን እነዚህ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ነብያት አስተምሕሮ ላይ ምንም የሚናገሩት ነገር የላቸውም። የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ብቻ ናቸው አስተምሕሮ ላይ መወሰን የሚችሉት።
የሐዋርያት ሥራ 11፡27 በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤
28 ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
የሐዋርያት ሥራ 13፡1 በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።
የሐዋርያት ሥራ 15፡32 ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።
ሐሰተኛ አስተማሪዎች የሚነግሯችሁ መስማት የምትፈልጉትን ነው
ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት አስተማሪዎች ናቸው።
አዲስ ኪዳንን እና ብሉይ ኪዳንን አንድ የሚያደርግ ልዩ አገልግሎት አላቸው። ልዩ ልዩ ጥቅሶችን በማገናኘት መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ እየመረመሩ ትምሕርቶቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መመስረት አለባቸው። አንድን ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራዕይ ያሉ ጥቅሶችን በሙሉ በማገናኘት ማጽናት ለየት ያለ ክሕሎት ነው።
በጣም ብዙ እና አድካሚ ስራ ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ዕድሜያችንን በሙሉ ማጥናት የሚጠይቅ ባለ ብዙ ገጽ መጽሐፍ ነው።
ሰዎች ይህንን ከባድ ስራ ከመስራት ይልቅ በቀላሉ የሰው ንግግር ጥቅሶችን እና ሰው ሰራሽ አመለካከቶችን ማንበብ ይመርጣሉ።
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡3 ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
4 እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ።
“ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ” ማለት ለሕዝቡ መስማት የሚፈልጉትን እየመረጡ ይነግሩዋቸዋል ማለት ነው።
ፓስተሮች የተወሰኑ ጥቅሶችን እየመረጡ የራሳቸው የሆነና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ትምሕርት ያዘጋጃሉ። እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈው እውነት መሆኑን ማሳየት አይችሉም፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ማስረጃ ተጠቅሞ መሳሳታቸውን የሚያሳያቸውን ማንኛውንም ሰው ያባርራሉ።
ሐሰተኛ አስተማሪዎች ለፓስተሮች የተሳሳተ ትምሕርት በመገዛት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛሉ፤ ለሕዝቡም ሕዝቡ መስማት የሚፈልጉትን እየመረጡ ያስተምራሉ።
ኤርምያስ 5፡31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ሰውን መታዘዝና ሰውን መከተል በጣም ቀላል ነው። ሰዎች በዚህ ዓይነት ቀላል እና የሰነፍ አካሄድ ውስጥ መመላለስ ይወዳሉ።
ዕብራውያን 5፡12 ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችሁ ዝቅተኛ ከሆነ ከትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ እግር ስር ተቀምጣችሁ አልተማራችሁም ማለት ነው።
ሰዎች የቤተክርስቲያን መሪውን ንግግር በመድገው ዝነኛ ይሆናሉ።
ለመጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጡት ትኩረት በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ክርስቲያኖች በጣም ቀላልና መሰረታዊ የሆኑ እምነቶቻቸውን እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ለማረጋገጥ ይቸገራሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይምነት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ትልቅ ችግር ነው።
ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
እውነተኛ አስተምሕሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው የሚመሰረተው
ትክክለኛ ትምሕርት የሚቀርበው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እርስ በርሳቸው ሲገጣጠሙ ነው። ሌላው ነገር ሁሉ የጠቢብ ንግግር ቢመስልም እንኳ ምንም የማይጠቅም ጊዜን የሚያባክን የሰዎች አመለካከት ነው።
ማቴዎስ 28፡19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤
ኢየሱስ ማስተማር “የሚለውን” ቃል “እያስተማራችኋቸው” በማለት ይጠቀማል።
ይህም ለትምሕርት ትልቅ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ያሳያል፤ ደግሞም አስተምሕሮ ምን ያህል በቀላሉ ሊበላሽ እንደሚችልም ያመለክታል።
በትምሕርት ውስጥ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መታሰብ አለበት። አገልጋዮች ከአስተሳሰባቸው ጋር የማይሄዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ቸል ብለው ሊያልፉ ይችላሉ።
ስለዚህ በዓለም ላይ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መኖራቸው አያስደንቅም።
እውነተኛ ትምሕርት አንቀላፍተው የነበሩ ሰዎችን ከእንቅልፍ ይቀሰቅሳቸዋል።
እውነትን ማስተማር ዓላማው አስተማሪውን በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ወይም ዝነኛ ማድረግ አይደለም።
ማስተማር ከጥምቀት በፊት ነው የተጠቀሰው ምክንያቱም ከማስተማር ይልቅ አስፈላጊ ነው። የተሳሳተ ትምሕርት ብታስተምሩዋቸው በተሳሳተ ጥምቀት ይጠመቃሉ፤ ከሙሽራይቱ አካልም ውጭ ይሆናሉ፤ ከዚህም የተነሳ ከመጀመሪያቸው የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅትን ይቀላቀላሉ።
አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ማዕረጎች ናቸው። ከነዚህ አንዱም እንኳ ስም አይደለም።
ስለዚህ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማነው?
እግዚአብሔር ሶስት አካል ወይም ስላሴ ከሆነ ስም የለውም ማለት ነው።
ምክንያቱም ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ማውጣት አይቻልም።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
ስለዚህ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ይህን መገለጥ ማግኘት ስለ መለኮት ማወቅ ይጠይቃል።
ስለዚህ ወደ ጌታ ለመጠጋት በምናደርገው በያንዳንዱ እርምጃ ውስጥ ጤናማ ትምሕርት ወሳኝ ነው።
63 0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያመጣውም
አስተማሪ ልዩ ሰው ነው። ቁጭ ብሎ የመንፈስ ቅዱስን ቅባት እየተቀበለ ቃሉን ይወስድና በመንፈስ ቅዱስ እያገናኘ ስለሚያስተምር ወንጌላዊም ይሁን ፓስተሩ ከአስተማሪ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም።
ከዚህ በታች የተጠቀሰው የአገልግሎቶች ዝርዝር ክርስቲያኖች በእምነት የሚጸኑበት መንገድ ነው።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
የመዳን ትምሕርት መጀመሪያ ሐዋርያት በጻፉት በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ነው የጸናው። ነብያት ማለት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው። የብሉይ ኪዳን ነብያት ኢየሱስ መሲህ መሆኑን ይመሰክራሉ። ከዚያ ወንጌላውያን ደግሞ አገልግሎታቸውን የሚጀምረው ሰዎች ሐጥያትነታቸው እንዲታወቃቸው በማድረግ ሲሆን ይህም ንሰሃ ወደ መግባትና ምሕረትን ወደ መፈለግ ያመራል።
ፓስተሮች አዲሶቹን አማኞች ተቀብለው የወንጌሉን ወተት ያጠጡዋቸዋል፤ ማለትም እምነታቸው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመስርቶ እንዲጸና መሰረታዊ የወንጌል እውነቶችን ያስተምሩዋቸዋል። ይህ ሲሆን አማኙ ወደ ቅድስና እና ወደ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መሄድ ይችላል።
ከዚያ በኋላ አስተማሪዎች አማኙ እግዚአብሔር ለዘመኑ ወዳሰበለት ዕቅድ እንዲገባ መንገድ ያሳዩታል።
ከእግዚአብሔር ቃል ብቻ የሚሰብኩ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥር የመግለጥ ጸጋ ተሰጥቷቸዋል። ይህ ብቻ ነው እያንዳንዱ አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ መረዳት እንዲችል የሚያግዘው።
እያንዳንዱ ሰው መፍታት ያለበት ትልቅ እንቆቅልሽ በእግዚአብሔር ትልቅ ዕቅድ ውስጥ የተዘጋጀለትን የግል ቦታውን ፈልጎ ማግኘት ነው። ሰዎች ግን ከዚህ እንቆቅልሽ ጋር ከመታገል ይልቅ በቤተክርስቲያን የሕብረት ልምምድ ውስጥ ተውጠው ለመቅረት ይቸኩላሉ።
ኢየሱስ ግን የቆመው ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ከጌታ ጋር ጠለቅ ያለ ልምምድ የላቸውም።
ከጌታ ጋር ጠለቅ ያለ ትውውቅና ልምምድን ትተው በፓስተሩ ስሕተት መስማማትና በሕዝብ መካከል ባለው የሕብረት ልምምድ ተሸፋፍነው መቅረትን ይመርጣሉ።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ
“ማንም”። እግዚአብሔርን ቤተክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ትቷታል። ጥሪ እያቀረበ ያለው ለግለሰቦች ብቻ ነው።
መሪያችንን እንከተል የሚባልበት ቤተክርስቲያን የመመላለስ ልምምድ ከንቱነቱ ወይም ችግሩ ሰነፎቹን ቆነጃጅት በስንፍና እንዲተኙና እንዲያንቀላፉ የሚያደርግ መሆኑ ነው። ከዚያም ተነሱ ንቁ የሚለው ጥሪ ሲመጣ ሁላቸውም ንጉሱን ለመቀበል እንዲወጡ ያደርጋቸዋል። ስለዚህ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው ከሚወዳት ቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄዳል።
እንቅልፍ አስተኝቶ የሚያስቀረን ሐሰተኛ ትምሕርት ነው።
በጨለማ እንተኛለን፤ እውነት ግን ብርሃን ነው።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
ፓስተሮች የማስተማር አገልግሎት አልተሰጣቸውም። የፓስተሮች አገልግሎት ሰዎች የግል እና የቤተሰብ ችግሮቻቸውን ወደ እነርሱ ይዘው ሲመጡ ማማከርና መፍትሄ መስጠት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ማጽናት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ይህም የአስተማሪ አገልግሎት ነው።
ቤተክርስቲያን በተሳሳተ አስተምሕሮ ውስት በምትዋልልበት ሰዓት ሌሎቹ አገልጋዮች የአስተማሪን አገልግሎት እንዲሸፍኑ ማድረግ አግባብ አይደለም፤ ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ ሕዝቡ የስሕተት ትምሕርት እየተቀበሉ ሲኖሩ ለጌታ ምጻት አይዘጋጁም።