ንስሳት አዳም ከተፈጠረ በኋላ ነው የተፈጠሩት?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዘፍጥረት 2፡18 ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ ዘፍጥረት 2፡19 እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትን … ሁሉ ከመሬት አደረገ
- የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በድንገት ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊሄድ ይችላል
- ይህ የዘመን ለውጥ ራዕይ ምዕራፍ 10ን ለመረዳት ያግዘናል
- ለወደፊቱ ለመዘጋጀት ካለፈው መማር አለብን
- ጥበብ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መቻል ነው
- እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ውስጥ የሚያርፍበትን ስፍራ እየፈለገ ነበር
- እውነተኛው ሐጥያት በነፍስ ውስጥ የሚገኝ አለማመን ነው
- የእግዚአብሔር ዲዛይን
- ዋነኛው ሐጥያት በጆሮ በኩል የሚገባ አለማመን ነው
- ለጥፋት የዳረጋት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው አስተሳሰቧ ነው
- ሴቲቱ በትዕቢት ተነፍታ ነው የተታለለችው
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በድንገት ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊሄድ ይችላል
ጥበብ እንዲህ ትላለች፡-
ምሳሌ 8፡26 ምድሪቱንና ሜዳውን ገና ሳይፈጥር የመጀመሪያውንም የዓለም አፈር።
27 ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥
እግዚአብሔር ምንም ነገር መስራት ከመጀመሩ በፊት ያለውን ጥበብ ሁሉ አሰባስቦ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር ስርዓትን አበጀ።
ይህም ስርዓት ሲከተሉት አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ይሰጣል።
ስለዚህ መጨረሻው የሚወሰነው እግዚአብሔር መጀመሪያ ባበጀው ስርዓት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ አልፎ አልፎ አንዳንድ ጠለቅ ያሉ እውነቶችን ለማሳየት በታሪክ ዘመን ውስጥ ወደ ኋላ እና ወደፊት ይመላለሳል።
ለምሳሌ ኢየሱስ መስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምጽ በጮኸ ጊዜ ራሱን ዝቅ አደረገና ሞተ። ከሶስት ቀናት በኋላ ከሞት ተነሳ።
ነገር ግን ማቴዎስ 27፡50-53 “በጮኸ ጊዜ” የሚለውን ቃል “መቃብሮች ተከፈቱ” ከሚለው ጋር ያያይዘዋል።
ነገር ግን መቃብሮች የተከፈቱት ኢየሱስ ሞቶ ከተቀበረ ከሶስት ቀናት በኋላ እርሱ ከሞት ሲነሳ ነው። ስለዚህ በነዚህ 4 ቁጥሮች ውስጥ ማቴዎስ የኢየሱስን ቀብር ሳይጠቅስ ያልፈዋል።
ከዚያም ከትንሳኤ በኋላ ደግሞ ማቴዎስ በቁጥር 59 እና 60 ወደ ኋላ በመመለስ ስለ ቀብሩ ይናገራል።
ማቴዎስ ለምንድነው “በጮኸ ጊዜ” ከሚለው ቃል ዘሎ ወደ ትንሳኤው የሄደው?
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው
እግዚአብሔር የጊዜውን ቅደም ተከተል ሲለውጥ አንድ በጣም ጠቃሚ ነገር ሊነግረን እየሞከረ ነው።
ይህ የዘመን ለውጥ ራዕይ ምዕራፍ 10ን ለመረዳት ያግዘናል
ብርቱው መልአክ (ወይም የመላእክት አለቃ) በራዕይ ምዕራፍ 10 እንደተጻፈው ወደ ምድር ሲወርድ
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
“በጮኸ ጊዜ” ማለት ማቴዎስ እንደ ጻፈው የመላእክት አለቃው ሙታንን አስነስቷል ማለት ነው።
ከዚያ ትንሳኤ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ለሙሽራይቱ አካላት ስጋቸውን እንዴት ወደማይበሰብስ አካል መለወጥ እንደሚችሉ ለማሳየት ድምጻቸውን ያሰማሉ።
ስለዚህ ይህ የመላእክት አለቃ ምን ሊሰራ ወደ ምድር እንደሚወርድ ያስረዳናል። ሙታንን ለማስነሳት ነው።
ይህንንም እውነት “በታላቅ ድምጽ ጮኸ” የሚለው በራዕይ 10፡3 የተጻፈው ቃል ያረጋግጥልናል።
ኢየሱስም በአላዛር ትንሳኤ ሰዓት ያደረገው ይህንኑ ነው።
ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።
64-0119 ሻሎም
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ የሚወርደው የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን ለማስነሳት ነው።
ይህን ፍንጭ የምናገኘው ማቴዎስ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት የተነሱበት ታላቅ ጩኸት ላይ ትኩረት ለማድረግ ብሎ ነገሮች የተከሰቱበትን ቅደም ተከተል በማቀያየሩ ነው።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ (ይህን ጩኸት በጮኸ ጊዜ ሙታን ተነሱ)። በጮኸም ጊዜ (ከትንሳኤው በኋላ) ሰባቱ ነጎድጓዶች በየድምጻቸው ተናገሩ።
ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች በየድምጻቸው የሚናገሩት ከትንሳኤ በኋላ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
ይህ የመጀመሪያው ትንሳኤ ነው። ከትንሳኤ በኋላ ደግሞ እንለወጣለን።
ስለዚህ የ7ቱ ነጎድጓዶች ድምጽ የሚሰማውና አካላችን የሚለወጠው በአንድ ጊዜ ነው።
ይህም በራዕይም ምዕራፍ 10 ውስጥ እንደተጻፈው 7ቱ ነጎድጓዶች በየድምቸው ከመናገራቸው በፊት የአዲስ ኪዳን ትንሳኤ እንዴት እንደሚፈጸም ፍንጭ ይሰጠናል። ይህም ፍንጭ 7ቱ ነጎድጓዶች መች ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ እና ዓላማቸውም ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል፤ ምክንያቱም የነጎድጓዶቹ ሥራ አካላችንን እንዴት እንደምንለውጥ ማሳየት ነው።
ማቴዎስ የብሉይ ኪዳንን ትንሳኤ በማሳየት ስለ አዲስ ኪዳን ትንሳኤ ግንዛቤ እንድናገኝ ይጠቁመናል።
ማቴዎስ በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት የሆነውን ዓይነት እንድንከተል እያመለከተን ነው። መጀመሪያ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት ተነሱ፤ ከዚያም ኢየሱስ ከ40 ቀናት በኋላ ወደ ሰማይ አረገ።
በብሉይ ኪዳን ነገሮች የተፈጸሙበትን ቅደም ተከተል ተጠቅመን ለአዲስ ኪዳን ትንሳኤም ተመሳሳይ ቅደም ተከተል ማግኘት እንችላለን። በመሃል የ40 ቀናት ክፍተት የነኖረው ለምንድነው? ከአዲስ ኪዳን ትንሳኤ በኋላ የሚሆን ነገር አለ። ያም ክፍተት 7ቱ ነጎድጓዶች በየድምጻቸው የሚናገሩበት ጊዜ ነው።
ነጎድጓዶቹ ከምድር ተነጥቀን ወደ ሰማይ የምንሄድበትን እምነት እንዴት እንደምናገኝ ያሳዩናል። ወደ ሰማይ መነጠቅ የምንችለው አዲስ አካል ከለበስን በኋላ ብቻ ነው። በዚህ ባረጀው አካላችን ውስጥ ሆነን ልንነጠቅ አንችልም፤ ስለዚህ በዚህ አሮጌ አካል ውስጥ ሳለን ለመነጠቅ የሚያስፈልገንን እምነት ለማግኘት መሞከር ምንም ጥቅም የለውም።
የሚያሳዝነው ነገር የሜሴጅ ሰባኪዎች ለመነጠቅ የሚሆን እምነት አለን ለማለት ብለው ስለ 7ቱ ነጎድጓዶች የተለያዩ አስተምሕሮዎችን ከ40 ዓመታት በላይ ሲሰብኩ ቆይተዋል። ነገር ግን ወደ ሰማይ በመነጠቅ ፈንታ አንዳዶቹ በምድር ተቀብረዋል።
ነጎድጓዶቹ አካላችንን እንዴት እንደምንለውጥ ሊያሳዩን ይገባል። በአዲሱ አካላችሁ ውስጥ ስትሆኑ ብቻ ነው መነጠቅ የምትችሉት። የዚያን ጊዜ ብቻ ነው የመነጠቅ እምነት ወደ ላይ ለመሄድ የሚረዳችሁ።
ይህ ሁሉ መረዳት የተገኘው ማቴዎስ የኢየሱስን ቀብር ሳይነግረን በፊት ስለ ትንሳኤው በመጥቀስ ነገሮች የሆኑበትን ቅደም ተከተል ለምን እንዳቀያየረ በጥንቃቄ በመመርመር ነው።
ይህም ቃርሚያ እንደመቃረም ነው። ቃርሚያ ማለት ከተጻፉ ጥቂት ፍንጮች ውስጥ ብዙ መረጃ ማግኘት ነው።
ማቴዎስ ለምንድነው በነዚያ 4 ቁጥሮች ውስጥ የኢየሱስን ቀብር ሳይጠቅስ ያለፈው?
ምክንያቱም ማቴዎስ በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የሚፈጸሙ ነገሮችን ቅደም ተከተል እያሳየን ነው፤ በዚያ ጊዜ ቀብር አይኖርም፤ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ አማኞች ከሙታን ይነሳሉ፤ ይህም የቀብር ተቃራኒ ነው።
ለወደፊቱ ለመዘጋጀት ካለፈው መማር አለብን
እስቲ አዳም ከእንስሳት በፊት የተፈጠ እንዲመስለን የሚያደርጉ ጥቅሶችን እንመልከት።
ከዚህ የጊዜ ቅደም ተከተል መዛባት ምን ልንማር እንችላለን?
ዘፍጥረት 2፡18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።
በዚህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ አዳምን ይጠቅስና ከዚያ በኋላ እንስሳት ከምድር እንደተሰሩ ይናገራል።
ዘፍጥረት 2፡19 እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላ እንስሳትነ ፈጠራቸው ማለት ነው?
አይደለም።
እግዚአብሔር ቅደም ተከተላቸው የተዛቡ የሚመስሉ ሁለት ክስተቶችን ሲናገር የሆነ ነገር ላይ ትኩረት እንድናደርግ እያመለከተን ነው።
እግዚአብሔር ትኩረት ያደረገበትን ሃሳብ ፈልገን ማገኘት አለብን፤ ይህም የክስተቶችን ጥልቅ ትርጉም ለመረዳት ያግዘናል።
[ይህም የጊዜ ልውውጥ ሐጢያት ወደ ዓለም ስለ መግባቱ የእባቡ እጅ ቢኖርበትም ግን እባቡን ተጠያቂ እንዳናደርግ ያመለክተናል።
ሔዋን ሐጥያት ሰርታ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሃሳብ ማመኗ የራሷ ጥፋት ነው። ፈታኙን ማመካኘት የለባትም።]
[እኛም ለምንሰራው ሐጥያት ተጠያቂ ነን። በሐጥያት ብንወድቅ የነበርንበትን ሁኔታ ማመካኘት አንችልም። በሐጥያት የምንወድቀው የእግዚአብሔርን ቃል ትተን በመሄድ የግል ትርፍ ለማሳደድ ስንሯሯጥ ነው። ይህም የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ለመሄድ ምን ዓይነት ማመካኛ ማቅረብ እንደማንችል ያሳያል። በሐጥያት ብንወቅድ ሌሎች ሰዎችን ሳይሆን ራሳችንን ነው ተጠያቂ ማድረግ ያለብን።]
ይህ ድምዳሜ ትክክል መሆኑን በማረጋገጫ እንመልከት።
ሐጥያት የመስራት ፍላጎት ከሰዎች ልብ ውስጥ ነው የሚመጣው እንጂ ከውጭ አይደለም። እነዚህን ፍላጎቶች ብንከተላቸው ያለንበት አካባቢ ሐጥያት የምንሰራበትን ዕድል ያመቻችልናል።
መነሻ ሃሳብ እንድናገኝ ወደ ኋላ መለስ ብለን እንይ።
ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።
27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
እግዚአብሔር መንፈስ ነው። ስለዚህ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር የአዳምን መንፈስ ያለ ምንም ነገር ፈጠረ።
አዳምም እንደ መንፈስ ሆኖ በውስጡ የሴትንም ባህርያት ይዞ በምድር ላይ ተንቀሳቀሰ።
ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
“ሙሉአት”። እንደገና ሙሉአት። ይህ ምን ማለት ነው?
መጀመሪያ የተፈጠረው ሰው አዳም ነው። ታድያ ከአዳም በፊት በምድር ላይ እንዴት ልንገኝ እንችላለን።
መዝሙር 139፡14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
15 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።
16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
እግዚአብሔር ምድርን ሲፈጥራት የእኛ አካላት የሚሰሩባቸውን ንጥረ ነገሮችም አስቀድሞ ፈጠረና በምድር ውስጥ አስቀመጣቸው። በምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘነው የምድር አፈር ውስጥ በነበርን ጊዜ ነው።
የአትክልት ስሮች ወደ አፈር ውስጥ ጠልቀው ይገቡና እነዚህን ንጥረ ነገሮች ስበው ወደ ላይ በማውጣት ምግብ ያደርጓቸዋል፤ ነፍሰጡር እናቶችም እነዚህን አትክልቶች ይበላሉ። ከዚህም የተነሳ በእናቶች ሆድ ውስጥ ያሉ ሕጻናት ከአትክልቱ በሚገኙ ንጥረ ነገሮች አካላቸው ይገነባል። ለዚህ ነው ነፍሰጡር ሴቶች በማሕጸናቸው ውስጥ ላለው ሕጻን የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በሚያስፈልግ ጊዜ ከተፈጥሮዋቸው ያልተለመዱ አምሮቶች የሚኖራቸው።
ከዚህም ጠቃሚ ትምሕርት እንማራለን።
አካላችን እንዲሁ በዘፈቀደ አይደለም የተገነባው። አካላችን የተሰራባቸውን የአፈር ቅንጣቶች እግዚአብሔር በመጀመሪያ በምድር ውስጥ በጥንቃቄ አዘጋጅቶ ነው ያስቀመጣቸው። አካላችንን በምድር ውስጥ ከሚገኙ የተወሰኑ ዓይነት ንጥረ ነገሮች በጥንቃቄ መገንባት እና እነዚህን ንጥረ ነገሮች በአትክልት በኩል አግኝተን በመብላት አካላችንን መጠበቅ አለብን።
ስለዚህ አሁን በአካል የምንኖረው ኑሮ ጥንት እግዚአብሔር አስቀድሞ በዕቅዱ በምድር ውስጥ ባስቀመጠው ጥበብ የተወሰነ ነው።
በፊት የምድር አካል የነበረው ሰውነታችን አሁን በምድር ገጽ ላይ እየተመላለሰ በሕይወት ይኖራል።
በመጀመሪያ የሰውነታችን ክፍሎች በምድር አፈር ውስጥ ነበሩ። እናቶቻችን የበሉት ምግብ እነዚህን የሰውነት ክፍሎቻችንን ከምድር ውስጥ ሰብስበው አካላችንን ሰሩት።
ይህ የአካላችን የመጀመሪያው ለውጥ ነው፤ ማለትም ተበታትነው የነበሩ የአካላችን ክፍሎች በእናትችን ማሕጸን ውስጥ ሳለን እናታችን በምትበላው ምግብ አማካኝነት ተሰበሰቡ።
በእናቶቻችን በኩል ከአፈር ወደ ስጋዊ አካል ተለወጥን። ከዚያ በኋላ አካላችንን እየገነባን በምንበላው ምግብ አማካኝነት ሰውነታችንን እየተንከባከብን በምድረ ላይ የተሰጠንን ስፍራ እንሞላለን። እኛ የምንበላውን ምግብ ነን።
አሁን ደግሞ ለሁለተኛው የአካላችን ለውጥ መዘጋጀት ያስፈልገናል፤ ይህም ለውጥ በደም ከተሞላ አካል ደም ወደሌለው የማይሞት አካል መለወጥ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
ስለዚህ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ደግሞ የምናድገው በመንፈስ ከምንበላው መንፈሳዊ ምግብ ነው (በምናምነው እና በምናውቀው)። ማንኛውም ቸል ብለን ያለፍነው ጥቅስ፣ በራሳችን ፍላጎት የለወጥነው ወይም ያልተረዳነው የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ነፍሳችን ልታገኝ የሚገባትን መንፈሳዊ ምግብ ያጎድልባታል፤ ከዚህም የተነሳ እምነታችን ደካማ ይሆናል።
ስለዚህ በመንፈሳዊ ሕይታችን የወደፊት ዕጣ ፈንታችን የሚወሰነው በፊት በነበረችዋ “መንፈሳዊ እናታችን” ነው፤ እርሷም መንፈሳዊ ምግብ የምታበላን እናት ቤተክርስቲያን ናት።
ሁለት አማራጮች አሉን። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተደራጀ ሐይማኖት እናት ናት። ይህም መንፈስ በስላሴ. ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣ የቤተክርስቲያን መሪ አይሳሳትም፤ እና የሰው ንግግር የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ይተካል በሚሉ ሃሳቦች እንድናምን ያደርገናል። የዚህ ሁሉ መጨረሻ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።
አለዚያ ደግሞ እናታችን በሐዋርያት የተመሰረተችዋ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ናት፤ በዚህች ቤተክርስቲያን ጥቂት ሰዎች ሕብረት እያደረጉ በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ይሰበሰባሉ፤ የሚመሩትም በሽማግሌዎች እንጂ በአንድ ግለሰብ አይደለም። እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔረ ቃል ውስጥ የተጻፈውን እውነት ለመረዳት ዕለት ዕለት መጽሐፍ ቅዱስን ይመረምራሉ። በስፍራ የተራራቁ ቤተሰቦች በዙም (Zoom) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሕብረት ማድረግ ይችላሉ። አንድ ቤተሰብ ትንሽ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም እግዚአብሔር በትንንሽ ሕብረቶች አማካኝነት ነው የሚሰራው።
ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
በሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስን ገፍተው ስላስወጡት ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል። ዛሬ ከቤተክርስቲያን ተገፍተው የወጡ ግለሰቦች ብቻ ናቸው ከቤተክርስቲያን ውጭ ኢየሱስን ማግኘት እና እውነትን ከእርሱ መማር የሚችሉት።
እነዚህ ሰዎች በኢንተርኔት አማካኝነት መገናኘትና እርስ በርሳቸው መማማር ይችላሉ። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዝርዝር ያልተጻፉት 7ቱ ነጎድጓዶች ከትንሳኤ በኋላ በየድምጻቸው በሚናገሩ ጊዜ እንድናስተውላቸው ይረዳናል። ነጎድጓዶቹ ድምጻቸውን የሚያሰሙት ከትንሳኤ በኋላ አካላችን ተለውጦ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል መነጠቅ እንድንችል ነው።
ማቴዎስ ምዕራፍ 7 ውስጥ የሚገኘው ሰባተኛው ምሳሌ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እርፍት በሌላቸው ሰዎች ባሕር ውስጥ የሚያልፈውን መረብ ይገልጻል። ይህም ኢንተርኔትን ወይም የመረጃ መረብን ይወክላል፤ በኢንተርኔት አማካኝነት ዌብሳይቶች በዓለም ዙርያ በተለያየ ስፍራ ለሚገኙ ግለሰቦች እውነትን ማድረስ ይችላሉ።
ዘፍጥረት 1፡28 ውስጥ “ሙሉአት” የሚለው ቃል ምድር ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የአካል ክፍሎቻችን ከምድር ውስጥ ወጥተው አካላችንን ከሰሩበት ጊዜ ጋር ያገናኘናል። በመንፈስ ደግሞ በሐዋርያት ዘመን ከእግዚአብሔር የመጀመሪያ ዕቅድ ጋር መገናኘት አለብን። የእኛ እምነት የእነርሱን እምነት ትንሳኤ ማምጣት አለበት። እኛ ልክ እንደ እነርሱ መሆን አለብን።
የወደፊታችን ሚስጥር የሚገኘው በኋለኛው ዘመናችን ውስጥ ነው።
ከዚያም ዘፍጥረት 1፡29 ደግሞ ወደፊት ወደ ዳግም ምጻት ይወስደናል። እነዚህ አሁን የምንንቀሳቀስባቸው ሕያው አካላት ወደማይሞቱ አካላት መለወጥ አለባቸው።
ይህን ለማድረግ መሰረታዊ ከሆነው መዳን እና ቅድስናን ከተማርንበት ከወንጌሉ ወተት አልፈን መሄድ አለብን። የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት ወደምንችልበት እና በዘመን መጨረሻ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሁሉ ስለሚገኘው ስሕተት ገልጦ ወደሚያሳየን ወደ ቃሉ ጠንካራ ምግብ ወደ አጥንቱ መሻገር አለብን።
ዘፍጥረት 1፡29 እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤
ሰው በተፈጠረ ጊዜ ወደፊት የሚለብሰውን አካል ለመጠበቅ የሚረዱ አትክልት ሁሉ መብል እንዲሆኑለት ተሰጥተውት ነበር። በዚህ ሰዓት አዳም ገና መንፈስ ስለነበረ ይህ ጥቅስ ስለ ወደፊቱ ነው የሚናገረው።
“ሙሉአት” የሚለው ቃል በጥንት ዘመን እግዚአብሔር ያበጀውና እኛም መፈጸም የሚጠበቅብን ስርዓት ጋር ያያይዘናል።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ሰው ራስ ሆኖ በሰው ሰራሽ አመለካከቱ ወደሚያስተዳድርባት ድርጅታዊ ወደ ሆነችው ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተደራጀ ሐይማኖት እንመለሳለን?
ወይም ወደ ጥንታዊቷ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እምነት እንመለሳለን?
“መብል ይሆናችሁ ዘንድ” ወደ ፊት መፈጸም ከሚገባን የእግዚአብሔር እቅድ ጋር ያገናኘናል።
እምነታችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ነውን?
አሁን የለበስነው አካል ከስጋ የተሰራ ስለሆነ ለሐጥያት ውድቀት የተጋለጠ ነው። ወደፊት የሚለወጠው አካላችን በውስጡ ደም ከሌለው ከማይሞት ስጋ የተሰራ ነው፤ በዚያ አካል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ቃል የተሰጠን ሰዎች እንሆናለን እንጂ ለሰዎች አመለካከት አንገዛም።
በሌላ አነጋገር በዚህ በአሁኑ ዘመን ብቻ የምንኖር ፍጡራን አይደለንም።
ሁላችንም ወይ ድሮ በኒቅያ ጉባኤ ላይ የሮማ ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችው ስላሴን በሚያስተምረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ ስርዓት ተጽእኖ ስር ነው ያለነው ወይም ደግሞ አዲስ ኪዳንን በጻፉት በሐዋርያት ትምሕርት ተጽእኖ ስር ነው ያለነው።
ጥበብ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መቻል ነው
ጥበባችን የተቀረጸው በመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታችን አማካኝነት ነው።
አስቀድሞ የተወሰነልንን አቋም እስክንይዝ ድረስ አስተሳሰባችን በመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታቸን አማካኝነት መቀረጽ አለበት።
አስቀድማ የነበረችው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ከሚመጣውና የሰውን ስልጣኔ አቃጥሎ ከሚያጠፋው የ3.5 ዓመት ታላቅ መከራ እንድናመልጥ እግዚአብሔር ላዘጋጀልን እቅድ እንድንበቃ የምታስችለን ብቸኛዋ መመሪያችን ናት።
ስለዚህ የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል እኛን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደነበሩት ወደ ሐዋርያት እምነት በመመለስ ወደፊት ለሚሆነው ለጌታ ምጻት እንድንዘጋጅ ይቀርጸናል። አሁን እኛ በጥንቱ (የሐዋርያት አዲስ ኪዳን ስርዓት) እና ወደፊት በሚሆነው የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ቅዱሳን ትንሳኤና አካላችንን እንዴት ወደማይሞተው አካል እንደምንለውጥ በሚያሳዩን በሰባቱ ነጎድጓዶች መካከል ቆመናል።
እስቲ እግዚአብሔር ወደፈጠረው ወደ መጀመሪያ ፍጥረት እንመለስ።
ዘፍጥረት 1፡30 ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፤ እንዲሁም ሆነ።
እግዚአብሔር ለእንስሳት ምግብ እንዲሆኑ በፈጠራቸው እንስሳት ወይም ተክሎች ላይ አንዳችም ችግር አልነበረም።
ሐጥያት ብንሰራ በትኛውም እንስሳ ወይም ተክል ማመካኘት አንችልም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁሉንም መልካም አድርጎ ነው የፈጠራቸው።
አንድ ትምሕርት እንማራለን። እግዚአብሔር ሁሉንም መልካም አድርጎ ፈጥሯል። ሐጥያት ብንሰራ ጥፋቱ የራሳችን ነው። ሐጥያት የመስራት ፍላጎት ከውጭ ሳይሆን ከውስጣችን ነው የሚመጣው። አንድን ሰው በልቡ ውስጥ ሐጥያት የመስራት ፍላጎት ከሌለው አንዲት ሐጥያተኛ ሴተኛ አዳሪ ሐጥያት ልታሰራው አትችልም።
ዘፍጥረት 1፡31 እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ ዛፉ፣ እጽዋቱ፣ ውሃ፣ አየር ወይም ምድር ሁሉም መልካም ናቸው። እግዚአብሔር ከፈጠረው ነገር ውስጥ አንድም ክፉ ነገር የለም።
ለእኛ የሚሆን ማስጠንቀቂያ እናገኛለን። የአውሬው ምልክት አንድ የሚታይ ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ አትፈልጉት። ንቅሳት፣ ማይክሮቺፕ፣ የማሕበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ ክሬዲት ካርድ፣ ወይም የቫይረስ መከላከያ ክትባት አይደለም።
ማቴዎስ 10፡28 ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።
ማንኛውም አካልን መግደል የሚችል ነገር ነፍስን መግደል አይችልም።
ነፍስ ልትጠፋ የምትችለው ባለማመን ብቻ ነው፤ ይህም መንስኤው መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ነው።
ዘፍጥረት 1፡31 እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።
ይህ የ6ኛው ቀን መጨረሻ ነበር። እያንዳንዱ ቀን 1,000 ዓመት ነው።
“ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ”። ሌሊቱ አልተጠቀሰም።
ዘካርያስ 14፡7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።
የማታው ሰዓት የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ያመለክታል። ይህ የብርሃን ሰዓት ነው ምክንያቱም የሙሽራይቱ አካላት መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው መረዳት ይችሉ ዘንድ የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ይገልጣል።
ጥዋት የሺ ዓመቱን መንግስት መጀመሪያ ያመለክታል፤ ይህም የእግዚአብሔር ሰባተኛ ቀን ነው።
የመጀመሪያው ሰባተኛ ቀን ሐጢያት ወደ ዓለም በመግባቱ ተበላሸ።
ሌሊቱን ባለመጥቀስ እግዚአብሔር ሙሽራይቱ በ3.5 የታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ እንደማታልፍ እያመለከተን ነው።
ማታ ማለትም በቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ከ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተውጣጣችው ሙሉ የሆነችዋ ሙሽራ ከትንሳኤ በኋላ ትገለጣለች። የሙሽራይቱ አካላት ወደ በሰማይ ወደሚደረገው የእራት ግብዣ ስለሚሄዱ በምድር ላይ የሚሆነውን የ3.5 ዓመታት ታላቅ መከራ አያዩም። ሙሉ የሆነችዋ ሙሽራ ለአርማጌዶን ጦርነትና ለሺው ዓመት መንግስት ንጋት ትመለሳለች።
ሌሊቱ ሳይጠቀስ ታልፏል። ሌሊት ብርሃን የሌለበት ሰዓት ነው። ሌሊቱ ታላቁን መከራ ይወክላል፤ ይህም ጨለማ የሚመጣው ቤተክርስቲያን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን አልቀበልም ብላ ገፍታ በማስወጣቷ ነው፤ ቃሉም አሁን በቤተክርስቲያን ተነቅፎ፣ ተገፍቶ፣ ተጥሎ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ይገኛል።
ዘፍጥረት 2፡1 ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።
ምዕራፍ 2 በ6ኛው ቀን መጨረሻ ላይ ነው የሚጀምረው። እግዚአብሔር ምድርን ማስዋብ ጨርሶ ለሰው መኖሪያነት ምቹ አድርጓታል። ባለ 1,000 ዓመት ስድስት ቀኖች አልፈዋል።
መንፈስ የሆነ ሰው እንስሳትን፣ ዛፎችን፣ ተክሎችን እና ምድርቱን በሙሉ ይገዛ ነበር።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ውስጥ የሚያርፍበትን ስፍራ እየፈለገ ነበር
ዘፍጥረት 2፡2 እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።
ይህ ጥቅስ ወደፊት ወደሚመጣው ዘመን ዘሎ ያልፋል።
የፍጥረት የተፈጠሩበት ዓላማ እግዚአብሔር እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ ነው።
የእግዚአብሔር ዋነኛ ዓለማ በፈጠራቸው ፍጥረታት ውስጥ የሚያርፍበተን ስፍራ ማግኘት ነው።
እግዚአብሔር ያረፈው አዳምን ማለትም የእግዚአብሔርን ልጅ እና ሚስቱን በ7ኛው የ1,000 ዓመታት ቀን ምድርን እንዲገዙ ሲተውላቸው ነው።
እግዚአብሔር ያረፈው አዳምን እና ሚስቱን በተለያዩ አካላት ውስጥ ካደረጋቸው በኋላ እና የኤድን ገነትን እንዲያስተዳድሩ ኃላፊነት ከሰጣቸው በኋላ ነው። ይህም ስራ ለእግዚአብሔር ብዙ ሰዓት አልፈጀበትም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃሉን ብቻ ተናገረና ፍጹም የሆነ የሰው አካል ተነስቶ በፊቱ ቆመ።
ከዚያም እግዚአብሔር ከአዳም አጥንት ወስዶ ለሴቲቱ አካል አበጀላት።
ከዚያ ወዲያ 7ኛው ቀን ለእግዚአብሔር እረፍት የሚያገኝበት ሰዓት ነበረ። ነገር ግን በዚያ የ1,000 ዓመታት ቀን ውስጥ የሆነ ሰዓት ሐጥያት ወደ ዓለም ገባ።
ሐጥያት አካላዊ የሆነ ድርጊት አይደለም።
በአካል የሚፈጸመው የሐጥያት ድርጊት የሐጥያት ውጤት ነው።
አካላዊ ሐጥያት የምንላቸው ሁሉ የዋነኛው ሐጥያት ማለትም የአለማመን መገለጫዎች ናቸው።
የተሳሳተ ባህርይ እና የተሳሳቱ ምኞቶች መንስኤያቸው ነፍስ ውስጥ የሚገኝ አለማመን ነው።
እውነተኛው ሐጥያት በነፍስ ውስጥ የሚገኝ አለማመን ነው
ዮሐንስ 16፡9 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤
አለማመን ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ቃል ውጭ የሆነ ሌላ ነገር ስታምኑ ነው።
የሰው ነፍስ የምትንቀሳቀሰው በእምነት (መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን በማመን) ወይም በአለማመን (መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ባለማመን) ነው።
ነፍስ ውስጥ የሚገኝ አለማመን አእምሮ ውስጥ ሐጥያት የመስራትን ፍላጎት ያመነጫል (አእምሮ ሌላ መጠሪያው መንፈስ ነው)።
ከዚያ በኋላ አካል የሐጥያት ድርጊትን ይፈጽማል፤ ይህም ድርጊት የአለማመን መገለጫ ነው።
አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ዘመንን አልፎ አዳም እና ሚስቱ የማይሞት ስጋዊ አካል ለብሰው በምድር ላይ ለ1,000 ዓመታት በደስታ ወደሚኖሩበትና እግዚአብሔር ወደሚያርፍበት ቀን ይሄዳል።
ዘፍጥረት 2፡3 እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።
ይህ አዳም እና ሴቲቱ በስጋዊ አካላቸው ውስጥ ሆነው እግዚአብሔር የፈጠራትን ምድር ሲገዙ እንዴት እንደሚኖሩ የወደፊቱን ሕይወታቸውን የሚገልጽ ቃል ነው።
ይህም የወደፊት እይታ የሚነግረን የፍጥረትን ዓላማ ነው። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የፈጠረውና ያበጀው ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ፈቃድ ይገዙለት ዘንድ ነው። ተፈጥሮ ለዘላለም መኖር እንድትችል ተደርጋ ነው የተዘጋጀችው። በውስጧ አንዳችም ችግር ወይም ስሕተት አልነበረባትም።
እግዚአብሔር ማረፍ የሚችለው ፍጥረት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ሲገዛለት ነው።
አንድ ሮኬት በጣም ኃይለኛ ተደርጎ ከተሰራ በታላቅ ጥንቃቄ መሰራት አለበት። ብዙ ሮኬቶች በጥቃቅን ስሕተቶች ምክንያት ተበላሽተዋል። ተፈጥሮ ለዘላለም ልትኖር የምትችለው ፍጹም ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የተስማማች እንደሆነና አንዳችም ስሕተት ያልተገኘባት እንደሆነ ነው። የእግዚአብሔርም ሃሳብ ይኸው ነበር። እግዚአብሔር የፈለገው ይህን ነበር።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሰው ነጻ ፈቃድ እንዲኖረውና በምድር ላይ ሕይወትን ተደስቶ እንዲኖር ፈለገ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሰው ስልጣንን ሰጠውና የፈለገውን እንዲያደርግ ፈቀደለት።
ይህም እግዚአብሔር ለሰው ያሰበው የመጨረሻ ሃሳቡ ነበረ። እግዚአብሔር ሰው ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ እየተገዛ እንዲኖር ፈለገ። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰው ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሲገዛ በግዴታ ሳይሆን በፍላጎቱ በምርጫው እንዲሆን ፈለገ። ሰው እግዚአብሔር በተናገረው በእያንዳንዱ ቃል ላይ ሙሉ እምነት ሊኖረውና አንዳችም አለመጠራጠር ነበረበት። በእግዚአብሔር ቃል ላይ አንዳችም መጨመር የለበትም፤ ከቃሉም አንዳች መቀነስ የለበትም።
ዘፍጥረት 2፡4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።
አሁን በዘመን ወደ ኋላ ተመልሰን ወደ መጀመሪያው እንሂድ።
ፍጥረት የተጀመረው እግዚአብሔር ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት እና ምድርን በመጀመሪያ ከምንም ነገር በፈጠረ ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ ጊዜ የሚባል ነገር እንኳ አልነበረም።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ባለ 1,000 ዓመታት ስድስት ቀኖችን ተጠቅመ ምድርን ለሰው ኑሮ ምቹ ትሆን ዘንድ ያበጃታል።
ምዕራፍ 2 የእግዚአብሔርን ሥራ በየቁጥሮቹ በዝርዝር በቅደም ተከተል ለማቅረብ የተጻፈ አይደለም።
እግዚአብሔር የተወሰኑ ነጥቦች ላይ ትኩረት ለማድረግ ፈልጎ በጊዜ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ይመላለሳል።
የእግዚአብሔር ዲዛይን
እግዚአብሔር ዘፍጥረት 2፡4 ውስጥ ወደ ኋላ በመመለስ ትኩረት ሊያደርግበት የፈለገው ነጥብ ምንድነው?
ዘፍጥረት 2፡4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።
“ቀን”? ይህ ምን ማት ነው?
ዘፍጥረት 1፡1 “በመጀመሪያ” ይላል። ቀን ወይም ቀኖች አልተጠቀሱም።
በዚህ ክፍል እንደምናየው እግዚአብሔር ጊዜ በማይቆጠርበት የፍጥረት ሥራው ከምንም ነገር የሆነ ነገር ማለትም ዓለምን ፈጠረ።
ከዚያ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 የተፈጠረችዋ ዓለም በስድስት ቀኖችን ውስጥ ለሰዎች መኖሪያነት ምቹ እንድትሆን ተደርጋ እንደተስተካከለች ይነግራናል።
ስለዚህ በመጀመሪያው ቀን ምን ተሰራ?
እያንዳንዱ መሃንዲስ አንድ ሕንጻ ከመስራቱ በፊት የሕንጻውን ፕላን ማዘጋጀት አለበት፤ ኋላም ሁሉም ነገር በፕላኑ መሰረት ተሰርቶ እንደሆን ያረጋግጣል።
ጥንት በመጀመሪያ እግዚአብሔር የዘላለማዊ ሃሳቡን ፕላን በአእምሮው ውስጥ አዘጋጀ። እግዚአብሔር ከጊዜ ቀጠና ውጭ ስለሆነና የወደፊቱን ልክ እንዳለፈው ጊዜ በቀላሉ ማየት ስለሚችል በፕላኑ ውስጥ እንደፈለገ ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መመላለስ ይችላል።
ዘፍጥረት 2፡4 ወደዚህ ቀን ወደ ኋላ በመመለስ እግዚአብሔር አንድም ነገር እንኳ በዘፈቀደ እንደማያደርግ ያሳየናል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ የማዳን እቅድ እንደ ፕላን አዘጋጀ፤ ከዚያ በኋላ የሰራው ነገር ሁሉ ከዚህ ዋነኛ ፕላን ጋር የሚጋጠም ነበረ።
በእግዚአብሔር የአሰራር ዘዴ ውስጥ አሁን የሚሰራው ሥራ ጥንት ካዘጋጀው ፕላን ጋር የሚገጥም ነው። በዚህም መንገድ የሚሰራው ሥራ ወደፊት ሰው እግዚአብሔር ለዘላለም ባዘጋጀው እቅድ መሰረት በታማኝነት ስለሚንቀሳቀስ እግዚአብሔር እንዲያርፍ የሚያስችለው ነው። ይህም በእቅዱ ውስጥ አንዳችም ስሕተት የለም ማለት ነው። ይህ የሚቻለው ግን የእግዚአብሔርን እቅድ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ብንከተል ነው።
ስለዚህ ሰው አስተሳሰቡን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ቃል ማስገዛት አለበት። ሰው በነጻነት በራሱ ፈቃድ ለእግዚአብሔር መገዛት አለበት።
የወደፊቱ ዘመን ጥንት በተጻፈው ፕላን መሰረት ነው የሚሆነው።
ዘፍጥረት 2፡5 የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤
በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እያንዳንዱ ተክል በሶስተኛው ቀን እያደገ ነበር።
እግዚአብሔር ግን በዚህ ቁጥር ውስጥ በጊዜ ወደ ኋላ ይመለሳል። ይህም በምድር ላይ አንዳችም ነገር ከመትከሉ በፊት የነበረ ጊዜ ነው።
እግዚአብሔር ትኩረት ያደረገው በታላቁ ዕቅዱ ላይ ነው።
እኛ ተክሎች ሁሉ እንዲሁ በዘፈቀደ ተበታትነው የበቀሉ ነው የሚመስለን።
እግዚአብሔር ግን በታላቅ እቅዱ እያንዳንዱን ተክል በትክክለኛ ቦታው እንዲበቅል ነው በአእምሮው ውስጥ ያቀደው። በዘፈቀደ የተደረገ ምንም ነገር የለም። እያንዳንዱ ጥቃቅን ነገር ሳይቀር አስቀድሞ ታቅዶበታል። ማንኛውም ነገር ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር በትክክል ካልገጠመ በቀር ዘላለማዊ ሊሆን አይችልም።
የኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ እስኪመጣ ድረስ አንድም ዝናብ አይዘንብም።
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ዝናብን ለመጥቀስ በጊዜ ወደፊት ቀድሞ ይሄዳል፤ ነገር ግን ዝናብ እስከ ኖህ ዘመን ድረስ ምን እንደሆነ እንኳ አይታወቅም ነበር። ዝናብም በመጣ ጊዜ በመርከብ ውስጥ ከነበሩ በቀር በምደር ላይ ያሉ ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ አስፈሪ ፍርድ ሆኖ ነው የመጣው።
ወደፊት ፍርድ እንደሚኖር የሚገልጸው ሃሳብ ይቀጥላል።
ምድርን የሚያርስ ሰው አልነበረም የሚለው ስለ ወደፊቱ የሚናገር ነው። በዚህ ሰዓት አዳም ገና መንፈስ ነበረ፤ ስለዚህ ስጋዊ አካል አልነበረውም። ስጋዊ አካል ከለበሰ በኋላ ተክሎችን መትከልና ምግብ ማዘጋጀት ይችላል። በመጀመሪያ ይህ ቀላል ስራ ነበረ ምክንያቱም አረም አልነበረም፣ ተባዮችም አልነበሩም። ነገር ግን በሐጥያት ምክንያት ምድር በተረገመች ጊዜ አረም በቀለ፣ ተባዮችም ተፈለፈሉና ምድር ላይ ሰብል ማምረት ብዙ ጉልበት የሚፈጅ አድካሚ ስራ ሆነ። ገበሬዎች የእውነት ላብ አንጠፍጥፈው ነው ለሕዝብ የሚበቃ እህል የሚያመርቱት። ዝናብ በጊዜው ላይዘንብ ይችላል፤ ሰብሎችም በድርቅ ምክንያት ሊሞቱ ይችላሉ።
ዘፍጥረት 2፡6 ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር።
ከዚያ ወዲያ እግዚአብሔር ሁሉ ነገር ቀላል ወደነበረበት ወደ 7ኛው ቀን መጀመሪያ ይመለሳል። ጉም ለስለስ ብሎ ምድርን ያጠጣታል። ከባድ ዝናብ ባለመኖሩ የምድር አፈር አይሸረሸርም። ኑሮ ለአዳም በእውነትም ቀላል ነበረ። የእግዚአብሔር እቅድ ፍጹም መልካም ነበረ። ሁሉም ነገር እግዚአብሔር መጀመሪያ ባዘጋጀው ፕላን መሰረት ይንቀሳቀስ ስለነበረ ሕይወት በጣም ቀላል ነበረ።
ዘፍጥረት 2፡7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
እግዚአብሔር ለአዳም የስጋ አካል ከምድር አፈር አዘጋጀለትና አስቀድሞ ፈጥሮት የነበረውን መንፈስ ወደዚህ አካል ውስጥ እፍ አለው።
ዘፍጥረት 2፡8 እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።
እግዚአብሔር ሰውን በኤድን ገነት ውስጥ ከማስቀመጡ በፊት አስቀድሞ ዛፎችን ተከለ።
እግዚአብሔር ኤድን ብሎ በሰየመው ግዛት በስተ ምስራቅ ልዩ የሆኑ ዛፎችን፣ ተክሎችንና ልዩ ልዩ እጽዋትን ተከለ። ይህም ሥፍራ የምድር ማዕከል ማለትም ሰው እንዲኖርበት የተዘጋጀ ልዩ ገነት ሆነ።
ዘፍጥረት 2፡9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
ይህ ጥቅስ በጊዜ ወደ ኋላ ይመለሳል። ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ ዛፎች በሶስተኛው ቀን ነበር የተተከሉት፤ ደግሞም ዛፎች በኤድን ገነት ውስጥ የተተከሉት ሰው ወደ ኤድን ገነት ከመግባቱ በፊት ነበረ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ምን እያሳየን ነው?
እግዚአብሔር ዛፎች የተተከሉት ሰው ስጋዊ አካል ከለበሰ በኋላ ነው ማለት አይደለም።
እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ዛፎች ከምድር ውስጥ እየበቀሉ መሆናቸው ለሰው መልካም እንደሆነ ነው። ከምድር አፈር ውስጥ የሚበቅል አንዳችም ሰውን ሊጎዳ የሚችል ነገር የለም። የዛፎቹ ፍሬ “ለመብል መልካም” ነበረ።
ምድር የአዳም አካል የመጀመሪያ ምንጭ ናት።
ስለዚህ ከምድር ውስጥ የሚበቅል ነገር ሁሉ ለአዳም መልካም ነው።
በሌላ አነጋግ ከምድር አፈር ውስጥ የሚበቅል ሆኖ አዳምን ሊጎዳ የሚችል ምንም ነገር አለነበረም።
የሰው አካል ክፍሎች በመጀመሪያ በምድር ውስጥ ተቀብረው ነበር የተዘጋጁት።
አንድም ክፉ ዛፍ አልነበረም።
ሰውን ሊጎዳ የሚችል የፍራፍሬ ዓይነትም አልነበረም።
ኢየሱስ ይህ ሃሳብ እውነት መሆኑን ወደ ሰው አፍ ገብቶ ሰውን ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም ብሎ በመናገር መስክሮለታል። (ነገር ግን ስለ መርዝ እየተናገረ አልነበረም)።
የምትበሉት ነገር ወደ ሆዳችሁ ገብቶ ሊጎዳችሁ አይችልም። ሊጎዳችሁ የሚችለው ከልባችሁ የሚወጣው ክፉ ምኞት ነው።
ማርቆስ 7፡18 እርሱም፦ እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?
19 ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።
20 እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።
21 ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥
22 መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤
23 ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።
ስለዚህ የኤድን ገነት ውስጥ የነበሩ ፍራፍሬዎች ሁሉ ለሰው መልካም ነበሩ።
አንድ ሰው በአፉ የዛፍ ፍሬ ስለበላ ሐጥያት ወደ ውስጡ ሊገባ አይችልም።
ዋነኛው ሐጥያት በጆሮ በኩል የሚገባ አለማመን ነው
ሐጥያት ወደ ሰው ውስጥ የገባው ሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የሐሰት ሃሳብ በጆሮው በኩል ሲያስገባ ነው።
እግዚአብሔር “ትሞታላችሁ” ብሎ ነበር፤ እባቡ በሰው እና በዝንጀሮ መካከል የሚገኝ እንስሳ ግን “ሞትን አትሞቱም” አለ። አንድ ቃል ብቻ ጨመረበትና ያንን ቃል ተከትሎ ሞት መጣ።
በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ስላሴ” የሚል ቃል ጨመረችበትና በጨለማው ዘመን ሞት ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖች ተገደሉ።
ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው መገዳደል ያቆሙት በ1648 ጀርመኒ ሙሉ በሙሉ እንድትወድም ካደረጋት በካቶሊኮች እና በፕሮቴስታንቶች መካከል ከተደረገው የ30 ዓመት ጦርነት በኋላ ነው። ይህም ጦርነት ጀርመኒ ላይ ያደረሰባት ጥፋት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ከመጣባት ጥፋት ይበልጣል።
ዘፍጥረት 2፡9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
በምድር ላይ የበቀለ ነገር ሁሉ መልካም ስለነበረ የትኛውም ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ ሰውን ሊጎዳ አይችልም።
ስለዚህ መልካም እና ክፉውን የሚያሳውቀው ዛፍ መንፈስ ነው፤ የሰይጣን መንፈስ ነው እንጂ ፍጥረታዊ ዛፍ አይደለም።
የሕይወት ዛፍም ፍጥረታዊ ዛፍ አይደለም። የዘላለም ሕይወት ሊሰጣችሁ የሚችል ዛፍ የለም። የዘላለም ሕይወት የምታገኙት ከኢየሱስ ብቻ ነው።
ስለዚህ የሕይወት ዛፍ የኢየሱስ መንፈስ ነው።
ሁለቱም ዛፎች የሰውን አእምሮ ለማግኘት ይጋደሉ ነበር። ሁለቱም ዛፎች በሰው ልብ ውስጥ ሃሳብ ለማስቀመጥ እየሞከሩ ነበር።
ክርስቶስ “የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ አለብን” ይላል። ይህም እምነት ነው።
ሰይጣን ደግሞ “የእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ያስፈልገናል?” ይላል። “ጥቂት ነገር ብንለውጥ ችግር የለውም”። ይህ አለማመን ነው።
የሰይጣን መንፈስ ከምድር ውስጥ አይደለም የወጣው፤ ለሰው ጎጂ የሆነውም በዚህ ምክንያት ነው።
ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ መብላት ሰውን ወይም አንዲትን ሴት ሊያረክስ አይችልም።
ሴቲቱን ያረከሳት ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነ ሃሳብ ተቀብላ ማመኗ ነው።
አዳም እና ሚስቱ በምድር ላይ የሚበቅሉ የዛፍ ፍሬዎችን ብቻ እየበሉ መኖር ነበረባቸው። ይህም ማለት ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚያገኙትን ብቻ ማመን ነበረባቸው። በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በጭራሽ አትለውጡት።
ዘፍጥረት 2፡15 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።
በዚህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ በቁጥር 8 ወደተጠቀሰው ዘመን ይመለሳል።
ዘፍጥረት 2፡8 እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።
በዚህ ክፍል ትኩረት የተደረገው እግዚአብሔር ሰውን በአንድ ስፍራ ማስቀመጡ ላይ ነው።
የአዳም ሥራ የኤድን ገነትን እግዚአብሔር ባወጣው እቅድ መሰረት መንከባከብ ነው።
አዳም እግዚአብሔር ባስቀመጠው ሥፍራ መቆየት ነበረበት። አዳም በአካል በኤደን ገነት ውስጥ መቆየት ነበረበት። በመንፈስ ደግሞ አዳም የእግዚአብሔር ቃል ባዘጋጀለት ድንበር ውስጥ መቆየት ነበረበት።
ዘፍጥረት 2፡16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
ትኩረት የተደረገው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መጣበቅ ላይ ነው። ይህም ትዕዛዝ እንጂ አስተያየት አይደለም።
እያንዳንዱ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ መልካም ነው። ሁሉም ፍራፍሬ መልካም ስለነበረ ሐጥያት ማለት የአንድ ዛፍ ፍሬ መብላት አይደለም።
ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚቃረነውን የሰይጣንን ሃሳብ ማዳመጥ - ሐጥያት ማለት ይህ ነው።
የሰይጣን ሃሳብ በሰው ነፍስ ውስጥ የጥርጣሬን ዘር ይዘራል፤ ጥርጣሬ ስር በሰደደበትም ቦታ እምነት ሊበቅል አይችልም።
ጥርጣሬ ፍሬ የሚያፈራው በአለማመን ተክል ላይ ነው። ከዚያ በኋላ በአንዳንድ ሥፍራ የተጻፉ የእግዚአብሔር ቃሎችን መጠራጠር እንጀምራለን።
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንድ ነገር ግልጽ ያደርግልናል።
የትኛውም የዛፍ ፍሬ ለሔዋን ውድቀት ተጠያቂ አይደለም። የዛፉ ፍሬ እግዚአብሔር በፈጠረው መልካም ምድር ላይ ያደገ ስለሆነ መልካም ነው።
ለጥፋት የዳረጋት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው አስተሳሰቧ ነው
ዘፍጥረት 2፡18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።
እግዚአብሔር ለአዳም ሚስት ሊያዘጋጅለት አሰበ፤ ነገር ግን እርሷን የሰራት እንደ አዳም እና እንደ እንስሳት ከምድር አፈር አይደለም።
ስለዚህ ሴቲቱ ከምድር አፈር አይደለም የተፈጠረችው።
ከአዳም የጎድን አጥንት የተሰራች ስለሆነች የአዳም አካል በመሆኗ ሙሉ በሙሉ በአዳም ላይ ጥገኛ ነች። እርሷም ሁልጊዜ ከአዳም ጋር መሆንና ሌላ ማንም የተናገረውን ሳይሆን አዳም የተናገረውን ብቻ ማመን ነበረባት።
ይህ ቤተክርስቲያንን ይወክላል። ዳግመኛ የተወለድነው ከኢየሱስ በመነጨው ደም፣ ውሃ፣ እና መንፈስ ነው። ስለዚህ ለቃሉ ማለትም ለኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ ሆነን መኖር አለብን እንጂ ሌላ ማንንም መስማት የለብንም።
ከምድር የተገኘ ነገር ሁሉ መልካም ነበር።
የሰይጣን መንፈስ የተሰራው ከምድር አፈር አይደለም፤ ስለዚህ በሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ስለዚህ ሴቲቱ በእግዚአብሔር ቃል ጸንታ ካልቆመች ሰይጣን ሊያሞኛት ይችላል።
ሐጥያትን ወደ ዓለም ያስገባው እባቡ ነው ብለን በእባቡ እናመካኛለን ግን እባቡ በሰይጣን እጅ እንደ መጠቀሚያ ብቻ ነው የነበረው። ጥፋቱ ሔዋን የወሰደችው አቋም ነው ምክንየቱም የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ብላ እባቡ የተናገረውን አመነች።
በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብም ሐጥያት አይደለም።
ነገር ግን ገንዘብ አእምሮዋችንን ሁሉ እስኪቀጣጠር ድረስ አመለካከታችንን ከለወጠው የዚያን ጊዜ የገንዘብ ፍቅር ሐጢያት ይሆንብናል። ገንዘብ ሰይጣን እኛን ለማታለል የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው። ግን በገንዘብ ማሳበብ አንችልም።
ችግሩ ያለው በልባችን ውስጥ ያለው ስግብግብነት ውስጥ ነው፤ ይህም ገንዘብን እንድንወድና ለግል ጥቅምና ትርፍ ብቻ እንድንሯሯጥ ያደርገናል።
ዘፍጥረት 2፡19 እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።
በዚህ ክፍል እግዚአብሔር እንስሳት ከምድር ወደተፈጠሩበት ወደ ስድስተኛው ቀን ይመለሳል።
ይህም እንስሳቱ ሲፈጠሩ ምንም ችግር እንዳልነበረባቸው በአጽንኦት ለመናገር ነው።
እነዚህ በራሳቸው ምንም ክፋት ማድረግ የማይችሉ ንጹህ ፍጥረታት ናቸው ነገር ግን ነፍስ አልነበራቸውም።
ሰው እምነቱ የሚገኘው ነፍሱ ውስጥ ነው።
እንስሳት ነፍስ ስለሌላቸው ከእግዚአብሔር ቃል በሚገኘው እምነት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ ሃሳብን በመቀበል በሚፈጠረው አለማመን መካከል ያለውን ልዩነት አያውቁም።
ሕዝቅኤል 18፡20 ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤
እንስሳት የሚንቀሳቀሱት በነጻ ፈቃድ ሳይሆን በደመ ነፍስ ነው። ስለዚህ እንስሳ በራሱ ፈቃድ ሆን ብሎ ሐጥያት መስራት አይችልም። እንስሳት ነፍስ ስለሌላቸው እንዲሁም ነጻ ፈቃድም ስለሌላቸው በሐጥያት ሊኮነኑ አይችሉም።
ነገር ግን በጌርጌሴኖን እንደሆነው ሰይጣን ወደ እንስሳት ውስጥ ሊገባ ይችላል። እነዚህ አጋንንት አሳማዎቹን አጣድፈው ወደ ገሊላ ባሕር ውስጥ ከተቱዋቸው። አሳማዎቹ ወደ ባሕር ገብተው ስለሞቱ ማንም የወቀሳቸው የለም። እንስሳት ነፍስ ስለሌላቸውም አሳማዎቹ በዚያ ሰዓት የገቡባቸውን አጋንንት ክፉ ተጽእኖ በራሳቸው መቋቋም አልቻሉም።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ እምነት ብቻ ነው ሰው የሰይጣንን ክፉ ተጽእኖ እንዲቋቋም የሚያስችለው።
በዚህ ክፍል እግዚአብሔር አጽንኦት ሰጥቶ የሚነግረን እባቡ የተፈጠረው ከምድር አፈር መሆኑን ነው።
ስለዚህ እባቡ በሰው እና በዝንጀሮ መካከል የሚገኝ ኦሪጅናል ፍጥረት ነው። ስለዚህ እባቡ ምንም ችግር አልነበረበትም። ነገር ግን እባቡም ነፍስ ስላልነበረው በእግዚአብሔር ቃል በማመን እና የእግዚአብሔርን ቃል በሚለውጠው አለማን መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አልቻለም።
ስለዚህ የሐጥያት መንስኤ እባቡ አይደለም። ሰይጣን ወደ እባቡ ገባ ምክንያቱም እንስሳ ከአጋንንት ራሱን መከላከል አይችልም። በሰው ነፍስ ውስጥ የሚገኘው እምነት ብቻ ነው ሰይጣንን የምንከላከልበት ኃይል። እባቡ ነፍስ ስላልነበረው ራሱን ከሰይጣን ሊከላከል አልቻለም።
ሴቲቱ በትዕቢት ተነፍታ ነው የተታለለችው
ዘፍጥረት 3፡5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።
እንደ አምላክ መሆንና ሕጻን ልጅ መውለድ እንደምትችል አሰበች። በፍጥረታት መካከል ይህን ማድረግ የሚችል አልነበረም። ትዕቢቷ ሃሳቧን ከእግዚአብሔር ቃል ርቆ እንዲሄድ አደረገው።
ሎዶቅያ ውስጥ ቤተክርስቲያን (በሴት የተመሰለችው) “ባለጠጋ ሆኛለው” ትላለች። ትኩረቷ የግል ጥቅሟ ላይ ነው።
የኤድን ገነት ውስጥ ሴቲቱ ልጅ በመውለድ “እኔ አምላክ ነኝ” ማለት የምትችል መሰላት። ትኩረቷ በራሷ ላይ ነበረ።
እባቡ ሰይጣን የተጠቀመበት መሳሪያ ብቻ ነው።
ሔዋን አዳም በነገራት ቃል ብትጸና ኖሩ ለጥፋት ባልተጋለጠች ነበር። እውቀትን ከሌላ አካል ባትቀበል ኖሮ፣ ከባሏ ጋር ጸንታ ብትቆም ኖሮ ለሞት ባልተጋለጠች ነበር።
እንስሳት ሐጥያት መስራት ስለማይችሉ ለሔዋን ውድቀት እባቡ ተጠያቂ አይደለም። እንስሳት ሁሉ የተፈጠሩት እግዚአብሔር በመጀመሪያ መልካም እና ንጹህ አድርጎ ከፈጠራት ምድር ነው።
የሴቲቱ ውድቀት መንስኤ ትዕቢቷ ነው።
ሼክስፒር እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር፡- “ትዕቢት ሆይ፣ አንቺ ሴት ነሽ”።
ሔዋን ትኩረቷ የራሷ ክብር ላይ ነበረ። ስለዚህ እያደናነቃት የሚያወራላትን ማንንም ቢሆን ትሰማለች።
ስለዚህ ሔዋን ለውድቀቷ እባቡን ተጠያቂ ማድረግ አትችልም።
“ሞትን ትሞታላችሁ” ብሎ እግዚአብሔር የነገራትን ቃል አስታውሳለች።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ የሆነውን “ሞትን አትሞቱም” የሚለውን ቃል ተቀበለች።
ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ የሆነ ሃሳብ እውነት እንደሆነ አድርጋ በሞኝነት በተቀበለች ጊዜ በዚያው ዕጣ ፈንታዋን ወሰነች።
እርሷ የሳተችበትን ቃል የተናገረው ማንም ይሁን ማን ለውጥ የለውም።
ለሔዋን ውድቀት ምክንያቱ ሐሰትን ለማመን መፍቀዷ ነው።
ሁላችንም እንደ እርሷ ነን።
በሐሰተኛ ትምሕርት ያሳሳታችሁን ሰው በጭራሽ እሱ አሳስቶኝ ነው ብላችሁ አታመካኙበት። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ለማመን ልባችሁን መክፈታችሁ የራሳችሁ ጥፋት ነው። የሚፈረድባችሁም በዚህ ነው።
ስለዚህ መደምደሚያችን እንዲህ የሚል ነው፡- ስሕተት ውስጥ ገብተን ከሆነ ማንንም ተጠያቂ አናድርግ፤ ተጠያቂዎቹ እራሳችን ነን።
መጽሐፍ ቅዱስ በዘመን ወደፊት እና ወደ ኋላ እየተመላለሰ ሲተርክ እግዚአብሔር ሊያስተላልፍልን የፈለገው መልእክት ይህ ነው።