ፀሃይ በ4ኛው ቀን አልተፈጠረችም



እግዚአብሔር ፀሃይን የፈጠራት በመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚያ በ4ኛው ቀን ያደረገው ነገር ፀሃይ የተፈጠረችበትን ዓላም ማለትም የምድር ቀን ላይ ገዥ መሆንን እንድትፈጽም ነው ያደረጋት።

First published on the 14th of September 2022 — Last updated on the 14th of September 2022

ፀሃይ የተፈጠረችው በመጀመሪያ ነው

 

 

ዘፍጥረት 1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።

እግዚአብሔር በመጀመሪያዎቹ ሰባት ቀናት ውስጥ ምድርን ለሰዎች መኖሪያነት ምቹ እንድትሆን ከማበጀቱ በፊት አስቀድሞ ሁሉን ፈጥሮ ጨርሷል።

በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ቁጥር ውስጥ ምንም ዓይነት የጊዜ ርዝማኔ አልተጠቀሰም።

ምድር እና ሕዋ ሲፈጠሩ ምን ያህል ጊዜ ፈጀ ለሚለው ጥያቄ ደስ ያላችሁን ይህን ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል ብላችሁ ያሰባችሁትን ጊዜ መገመት ትችላላችሁ። ከዋክብትን እና በፀሃይ ዙርያ ያሉትን ፕላኔቶች በሙሉ ለመፍጠር ብዙ ቢሊዮን ዓመታት ፈጅቶ ሊሆንም ይችላል። እግዚአብሔር ጥድፊያ ውስጥ አልነበረም። ደግሞም ጊዜ የሚባል ነገር በሌለበት በዘላለማዊነት ውስጥ ነው እርሱ የሚኖረው። ፍጥረትን ሲፈጥር ቢሊዮኖች ዓመታትን ወስዶ ከሆነ ከሩቅ ያሉ ከዋክብት ብርሃናቸው ወደ ምድር እስኪደርስ ድረስ በቂ ጊዜ አግኝተዋል ማለት ነው።

ነገር ግን በዘላለማዊነት ውስጥ የሚኖረው እግዚአብሔር ፍጥረትን ሲፈጥር ስለወሰደው ጊዜ ለመገመት መሞከር ድካም ብቻ ነው ትርፉ።

 

የበረዶ ዘመናት

 

 

እግዚአብሔር ሕዋ እና ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ እና ምድርድን ምንም ነገር ሳይጠቀም እንዲሁ ፈጠራቸው።

ጊዜ ስላልተጠቀሰልን እግዚአብሔር ምድርን ሲፈጥር ምን ያህል ጊዜ እንደወሰደበት አናውቅም። እግዚአብሔር ምድር ሕይወትን ያኖር ብቃት እንዲኖራት ፈለገ፤ ስለዚህ በጥልቅ ውሃ ሸፈናት። ሕይወት ብዙ ውሃ ይፈልጋል። ነገር ግን ምድር ከፀሃይ በጣም እሩቅ ስለነበረች በጣም ቀዝቃዛ ነበረች። ስለዚህ በምድር ላይ የነበረው ውሃ የላይኛው ገጽታው በረዶ ነበር፤ ምድርም የበረዶ ኳስ ትመስል ነበር። ይህም የመጀመሪያው የበረዶ ዘመን ነው።

ከዚያም እግዚአብሔር በበረዶ የተሸፈነችዋን ምድር ወደ ፀሃይ ጠጋ ሲያደርጋት በረዶው መቅለጥ ጀመረ። በረዶው ሲቀልጥ ትልልቅ የበረዶ ግግሮች እየተንሳፈፉ በምድር ዙርያ ተንቀሳቀሱ፤ የበረዶ ግግሮቹም እንቅስቃሴ ምድር ቅርጽ እንዲኖራት አደረገ። እግዚአብሔርም ምድር እርሱ የፈለገው ዓይነት ቅርጽ እስኪኖራት ድረስ ትልልቆቹን የበረዶ ግግሮች በምድር ላይ ወዲያና ወዲህ አንቀሳቀሳቸው።

ተጨማሪ የበረዶ ዘመን ቢያስፈልግ እግዚአብሔር የበረዶዎቹን እንቅስቃሴ ብዙ ጊዜ መደጋገም ይችላል።

ከዚያ የበረዶ ግግሮቹ በሙሉ ቀልጠው የምድር ገጽ ሙሉ በሙሉ በጥልቅ ውሃ ተሸፈነ።

 

ውሃ ሲተን ከምድር ዙርያ ጥቅጥቅ ያለ ጥቁር ደመና ተፈጠረ

 

 

ውሃ ሲተንን ደመና ይሰራል።

ስለዚህ ከምድር ገጽ በላይ ጥቅጥቅ ያሉ ደመናዎች ተፈጠሩና እነዚህ ደመናዎች የፀሃይን ብርሃን ጋረዱ። ከደመናዎቹ በላይ ፀሃይዋ ድምቅ ብላ እያበራች ነበር፤ ከደመናዎቹ በታች ግን ውሃው ሁሉ በጨለማ ውስጥ ነበረ።

 

 

ደመናዎቹ ጥቅጥቅ ብለው ሲሰበሰቡ ከበታቻቸው ምድር ላይ ጨለማ ፈጠሩ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ሙሴ በራዕይ እየተመለከተ ነበር።

ራዕዩ በምድር ገጽ ላይ ባተኮረ ሰዓት ሙሴ ምድርን ሸፍኖ ከነበረው ውሃ በቀር ምንም ማየት አልቻለም። ውሃ የራሱ የሆነ ቅርጽ ወይም መልክ የለውም። ውሃ ሁልጊዜ የተቀመጠበትን ዕቃ ወይም ቦታ ቅርጽ ነው የሚይዘው። ምድርን የሚሸፍን ውሃ ሸለቆ እና ተራራ መሆን አይችልም፤ ሙሴ ማየት እስከሚችልበት ድረስ ሁሉ ሙሉ በሙሉ በምድር ዙርያ ጠፍጣፋ ነው።

ዘፍጥረት 1፡2 ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤

(የውሃው ገጽ ጠፍጣፋና ባዶ ነበረ፤ ምንም ዓይነት ቅርጽ አልነበረውም። አንዳችም ነገር የሌለው ባዶ ስፍራ ነበረ።)

ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤

(ከቀለጡት የበረዶ ግግሮች የተነሳ የተፈጠረው ጥልቅ ውሃ እና በረዶ በጨለማ ተሸፍኖ ነበር፤ ይህም ልክ ከባሕር ላይ በሚተንን የውሃ ትነት የተነሳ የሚፈጠረው ጥቅጥቅ ያለ ደመና የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር እንዳይደርስ እንደሚጋርድ ነው።)

የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።

 

 

ራሷን መፍጠር የማትችለዋን ምድር ከፈጠራት በኋላ እግዚአብሔር በምድር ላይ ሕይወትን ለማኖር ወሰነ።

በመጀመሪያ ሲሰራ የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ጊዜ የሚባል ነገር ስላልተጀመረ እነዚህ ስራዎች ምን ያህል ጊዜ እንደፈጁ ማወቅ አንችልም። የእግዚአብሔር መንፈስ በውሃዎች ላይ በማንዣበብ ከደመናዎች ስር ከነበረው ውሃ ስር በነበረው የምድር ገጽታ ስር የሕይወትን ዘር በመዝራት ተጠምዶ ነበር። እግዚአብሔር ሲንቀሳቀስ ሕይወት ባልነበረበት ስፍራ ሕይወት እንዲኖር ያደርጋል።

ስለዚህ እግዚአብሔር ደመናዎችን እና ውሃውን አስወግዶ በተዘራው ዘር ውስጥ የነበረው ሕይወት እንዲገለጥ አደረገ።

በዚህ ምስል ውስጥ ቢጫው ቀለም እግዚአብሔር ይወክላል።

 

 

 

ከውሃው በታች ዘሮችን ከዘራ በኋላ እግዚአብሔር በጨለማ እና በውሃ የተሸፈነችዋን ምድር ተመለከተ። እግዚአብሔር ምድርን በሕያዋን ፍጥረታት ለመሙላት የተዘጋጀበት የራሱ የሆነ እቅድ ነበረው።

እስከዚህ ድረስ በሰራው ሥራ ውስጥ ጊዜ አልተጠቀሰም። ስለዚህ እግዚአብሔር የተጠቀመው ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ አናውቅም።

ስለዚህ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1ን በማንበብ የምድር ዕድሜ ምን ያህል እንደሆነ መገመት አንችልም።

እግዚአብሔር ስለ ጊዜ በግልጽ የተናገረው ምድርን ከፈጠራት በኋላ በምድር ላይ ሕያዋን ፍጥረታትን ለማኖር ከወሰነ በኋላ ነው።

 

ከእግዚአብሔር አፍ የወጣ ቃል ጥቁሩን ደመና በተነው

 

 

እግዚአብሔር ከደመናው በታች ከነበረው ውሃ ውስር ከነበረው አፈር ውስጥ የነበሩትን ዘሮች ሕያዋን ለማድረግ ወሰነ።

ዘፍጥረት 1፡3 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

የፀሃይ ብርሃን አስቀድሞ ተገኝቶ ነበር ግን ጥቅጥቅ ያለውን ደመና አልፎ ወደ ምድር ሊደርስ አልቻለም።

 

 

 

እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” ብሎ ሲናገር የተናገረው ቃል ሄዶ ጥቅጥቅ ያለውን ደመና መታውና ደመናው ውስጥ የነበሩት የውሃ ሞለኪዩሎች ሙሉ በሙሉ ወደ ነበሩበት መሰረታዊ የኦክስጅን እና ሃይድሮጅን ጋዝ አተም ተመለሱ። እነዚህ ብርሃን አስተላላፊ ጋዞች በምድር ዙርያ ምድርን ከከባድ የፀሃይ ጨረር የሚከላከል ከባቢ አየር ሆኑ።

በዚህም መንገድ የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር መድረስ ቻለ።

 

 

በሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው ከባድ ኢንፍራሬድ የተባለው ጨረር በምድር ዙርያ ባለው ከባቢ አየር ውስጥ ይበታተንና ጉዳት የሌለው የፀሃይ ብርሃን በከባቢ አየር ውስጥ አልፎ ወደ ምድር ይደርሳል። ስለዚህ በምድር ዙርያ ሁልጊዜ አንድ ዓይነት የሙቀት መጠን ይፈጠራል ዝናብም አይኖርም። ዝናብ የሚፈጠረው ሞቃት አየርና ቀዝቃዛ አየር ሲገናኙ ነው። ለምሳሌ በቀዝቃዛ ቀን ሞቃት የሆነው ትንፋሻችሁ ቀዝቃዛውን የመኪና የግምባር መስታወት ሲነካው ትንፋሻችሁ በመስታወቱ ላይ እንደ ደመና ይሆንና እይታችሁን ይጋርዳል።

በ2000 ዓ.ም ፀሃይ አጠገብ የፈነዳችዋ ሊኒያር የተባለች ተወርዋሪ ኮከብ ስትፈነዳ 3.3 ሚሊዮን ቶን ውሃ በመበታተኑ ምክንያት የሃይድሮጅን እና የኦክስጅን ጋዝ ደመና ፈጥራለች። ይህም ሕዋ ውስጥ ውሃ በቀላሉ ወደ ሃይድሮጅን እና ኦክስጅን ሊከፋፈል እንደሚችል ያሳያል።

 

ዘፍጥረት 1፡4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።

እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው። ወደ ፀሃይ የዞረው የምድር ግማሽ አካል የቀን ብርሃን ውስጥ ነበረ። ለፀሃይ ጀርባውን የሰጠው ግማሽ የምድር አካል ደግሞ ጨለማ ውስጥ ነበረ። ጨለማ ራሱን የቻለ ፍጥረት አይደለም፤ ጨለማ የብርሃን አለመገኘት ብቻ ነው።

አለማመን ሐጥያት ነው፤ መንስኤውም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል አለማወቅ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ያልተመሰረተ ነገር ስናምን አለማመን ወይም መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ እንገባለን።

 

የእግዚአብሔር አንድ ቀን የእኛ 1,000 ዓመት ነው

 

 

ዘፍጥረት 1፡5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።

ጊዜ ለመጀመሪያ የተጠቀሰው በዚህ ቃል ነው።

በዚያ ጊዜ ሰዎች በምድር ላይ አልነበሩም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጊዜውን በሰዎች ቀን አቆጣጠር መለካት አላስፈልገውም።

የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ሰለሆነ ጊዜውን “በእግዚአብሔር ቀናት” ነው ሲለካ የነበረው።

“የእግዚአብሔር ቀን” ርዝመቱ ምን ያህል ነው? በሰዎች አቆጣጠር 1,000 ዓመታት ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

የመጀመሪያው ቀን የመዳን ተምሳሌት ነው። ልባችን በሐጥያትና በአለማመን ደመና የተጋረደ ነው። ንሰሃ ስንገባ የእግዚአብሔር ቃል የተጋረደብንን ሐጥያት እና አለማመን ይመታውና ሐጥያታችን ሁለተኛ መታየት እስከማይችል ድረስ ይደመስሰዋል። ከሐጥያት ጨለማ ነጻ ወጥተን ለሐጥያታችን በሞተልን በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ደስ እንሰኛለን። ልብ ብሉ፤ እርሱ ሁሌም ነበረ፤ ነገር ግን አሁን ሐጥያታችን ይቅር ተብሎልን ሲወገድልን ለመጀመሪያ ጊዜ እርሱ እንዴት ድንቅ እንደሆነ ማየት ቻልን።

እግዚአብሔር ደመናውን ለመበታተንና ጨለማውን ለመግፈፍ 1,000 ዓመታት መፍጀት አላስፈለገውም። ያን የሚያህል ጊዜ መውሰድ ፈልጎ ነው ያደረገው። 1,000 ዓመታት እስኪጠናቀቁ ድረስ ጠበቀ። የዛን ጊዜ የመጀመሪያው ቀን ተጠናቀቀና ሁለተኛው ቀን ተጀመረ።

 

ጠፈር ማለት ከባቢ አየር ነው፤ እሱም በዚያ ጊዜ አዲስ ነበረ እንጂ አላረጀም

 

 

ዘፍጥረት 1፡6 እግዚአብሔርም፦ በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል አለ።

ለሕይወት የመጀመሪያው አስፈላጊ ነገር ብርሃን ነው።

ቀጥሎ ሕይወት ያላቸው ነገሮች የሚተነፍሱት አየር ያስፈልጋቸዋል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በታች ባለው ምድርን በሸፈነው ባሕር ውስጥ ባሉት ውሃዎች እና ከላይ ደግሞ ደመናዎች ውስጥ ባለው ወደ ሃይድሮጅን እና ኦክስጅን የበታተነው ውሃ መካከል ያለውን ክፍተት ሞላው።

[እነዚህን ከላይ ያሉትን ጋዞች እግዚአብሔር በኖህ ዘመን እንደገና ውሃ ለመፍጠር ተጠቅሞባቸዋል፤ ከዚያም ይህንን ሁሉ ውሃ ወደ ምድር አዘነበው። ስለዚህ ምድርን ከጎጂ የፀሃይ ብርሃን እንዲከላከል ተብሎ ከባቢ አየር ውስጥ የቀረው ጋዝ በዝናብ መልክ ወደ ምድር ወረደ። ምድርም ከዙርያዋ የነበረው የሚጋርድ ከባቢ አየር ሲወገድ እንደ አልትራቫዮሌት የመሳሰሉ የፀሃይ ጨረሮች በቀጥታ ወደ ምድር ደርሰው ሰዎችን መምታት ስለቻሉ ሰዎች ከጥፋት ውሃ በኋላ በለጋ ዕድሜያቸው መሞት ጀመሩ።]

በ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ነገር ታይቷል።

 

ዩሮፓ የተባለችዋ የጁፒተር ጨረቃ በበረዶ ተሸፍናለች።

 

ጋሊሌዮ የተባለችዋ የጠፈር መመራመሪያ መንኩራኩር ወደ ጁፒተር ሄዳ በ1995 ደረሰችና ዩሮፓ ከተባለችዋ ጨረቃ ላይ ካለው የበረዶ ንጣፍ ስር ጨዋማ ውሃ መኖሩን አረጋግጣለች፤ ስለዚህ ከጨረቃዋ በረዶዋማ ገጽታ ስር ውቅያኖስ አለ ማለት ነው። በ2016 ሃብል የተባለው ቴሌስኮፕ አልፎ አልፎ ከዩሮፓ ላይ እየተነነ የሚሄድ የሃይድሮጅን እና የኦክስጅን ትነት ፎቶግራፍ አንስቶ አሳይቷል፤ ትነቱም ከዩሮፓ ገጽ ላይ ከተነሳ በኋላ ሕዋ ውስጥ በመቶዎች በሚቆጠሩ ኪሎሜትሮች ርቀት ይሄዳል። ሃብል የሃይድሮጅን ጋዝ እና የኦክስጅን ጋዝ ትነቶችን መከታተል ስለሚችል ሳይንቲስቶች በፎቶግራፉ ላይ እንደ ትነት መስሎ የሚታየው ውሃ ነው ይላሉ። ይህ በሕዋ ውስጥ የተገኘው ማስረጃ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ከምድር በላይ በታላቅ ከፍታ ውሃ ፈጥሮ ወደ ኦክስጅን እና ሃይድሮችን በመበታተን ከምድር ዙርያ በከፍታ ላይ ምድርን ከጎጂ የፀሃይ ጨረር ለመከላከል ከሰራው ብርሃን የሚያስተላልፍ የጨረር መከላከያ ጋር ይመሳሰላል።

 

ምድር ላይ ያለው አየር ግን በምድር የሚኖሩ ሕያዋን ፍጥረታንን (ሰወችን እና እንስሳትን) በሕይወት ማቆየት እንዲችል ከየዓይነቱ በትክክለኛው መጠን መመጣጠን አለበት። ከላይኛዎቹ ውሃዎች እና ከታችኛው ባሕር መካከል ያለው ክፍተት ከባቢ አየር ይባላል፤ ይህም ከባቢ አየር በትክክለኛው የጋዞች ምጣኔ መሞላት አለበት፡- በምንተነፍስ ሰዓት የበላነውን ምግብ በሰውነታችን ውስጥ ለማቃጠል 21 በመቶ ኦክስጅን ያስፈልጋል። ይህ የምግብ መቃጠል ሰውነታችን እንዲሞቅ ያደርጋል፤ የሰውነታችንም ትክክለኛ ሙቀት 37 ዲግሪ ነው። ከባቢ አየሩ ደግሞ 78 በመቶ ናይትሮጅን ጋዝ ያስፈልገዋል፤ ይህም ከባቢ አየሩ የተረጋጋ እንዲሆንና ኦክስጅን በዝቶ ሁሉም ነገር በእሳት ተቃጥሎ እንዳይጠፋ ነው። በ1967 አፖሎ የተባለችዋ መንኩራኩር በውስጧ የታመቀ 100 ፐርሰንት ኦክስጅን ነበራት፤ የዛኔ በድንገት የተፈጠረ የእሳት ብልጭታ ያስከተለው ከባድ ነበልባል በውስጧ የበሩትን ሶስት የጠፈር ተመራማሪዎች ማንም ሳይደርስላቸው፣ የመንኩራኩሩን በር ሳይከፍትላቸው ከመቅስፈት ገድሏቸዋል።

 

ዘፍጥረት 1፡7 እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ።

ከጠፈር በላይ ያሉት ውሃዎች የውሃ መሰረታዊ ቅመሞች ናቸው፤ ማለትም ኦክስጅን እና ሃይድሮጅን።

ሰዎች መተንፈስ የሚችሏቸው ጋዞች ያሉበት ከባቢ አየር ጠፈር ተብሎ ተጠራ። በአየር ውስጥ ያሉት ጋዞች ምጣኔ በጣም ትክክለኛ መሆን አለበት። ኦክስጅን ከ16 ፐርሰንት በታች ከወረደ እሳት መንደድ አይችልም፤ ስለዚህ በሰውነታችን ውስጥ ምግብ አይቃጠልም፤ ከዚህም የተነሳ ሙቀትና ኃይል አናገኝም። ኦክስጅን መጠኑ ከ21 ፐርሰንት ካለፈ እሳት በተፈጠረበት ሁሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ይሆናል።

 

ዘፍጥረት 1፡8 እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን።

ሰማይ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ቀጠና መሆኑን ስለምንረዳ እኛ ሰዎች ሰማይን ለማየት ወደ ላይ ቀና እንላለን። ስለዚህ ከባቢ አየራችን እራሱ የሰማይ ተምሳሌት ነው።

ምድር በዙርያዋ ከባቢ አየር ስላላት ከፀሃይ ብርሃን ውስጥ ከሚመጡ ቀለማት መካከል የአየር ሞሎክዩሎች ሰማያዊውን ቀለም በያቅጣጫው ይበታትኑታል። ሰማያዊው ቀለም የሞገድ ርዝመቱ አጭር እና በኃይል የተሞላ ነው። ከሰማያዊው ብረሃን ከፊሉ ወደ ምድር ይበተናል። ወደ ላይ ቀና ስንል ሰማያዊው ብርሃን ወደ እኛ ሲወርድ እናያለን። ለዚህ ነው ሰማዩ ሰማያዊ ቀለም ያለው የሚመስለን።

ይህም የእግዚአብሔር ዙፋን ተምሳሌት ነው።

 

ሕዝቅኤል 1፡26 በራሳቸውም በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።

(ሰንፔር ሰማያዊ ድንጋይ ነው።)

እግዚአብሔር በምድር ዙርያ ያለው አየር ለሕያዋን ፍጥረታት ለመተንፈስ ምቹ እንዲሆን ለማዘጋጀት 1,000 ዓመታት ወስዶ ሰራ።

በክርስትና ሕይወታችን የመጀመሪያው እርምጃ ከሐጥያታችን ንሰሃ መግባት ነው፤ ይህም “ብርሃን እንድናይ” ያስችለናል። ቀጣዩ እርምጃችን በዙርያችን የቅድስና አየር ማበጀት ነው።

ዕብራውያን 12፡14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡3 ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥

ሳይንቲስቶች በምድር ላይ ሕይወት የተጀመረወ በምድር ዙርያ ያለው አየር እንደ አሞኒያ እና ሜቴን በመሳሰሉ መርዛማ ጋዞች ተሞልቶ በነበረ ጊዜ ነው ይላሉ። ነገር ግን ጥንታዊ ዓለቶችን ሲመረምሩ በውስጣቸው እነዚህን ጋዞች ለማስረጃነት ሊያገኙዋቸው አልቻሉም። ሕይወት በመርዛማ ጋዞች መካከል ተጀመረ የሚለው ክርክር አሳማኝ አይደለም።

ከባቢ አየር ዕድሜው ስንት ነው?

 

ዩታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰራው ስዊድናዊ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ፕሮፌሰር መልቪን ኩክ የምድር ከባቢ አየር ዕድሜው ከ10,000 ዓመታት በላይ ነው ብሎ ገምቷል።

ምድር አርጅታ ይሆናል፤ ከባቢ አየር ግን ዕድሜው ገና ነው።

 

ውሃዎቹ ወደ አንድ ሥፍራ ሲሰበሰቡ ደረቁ ምድር ተገለጠ

 

 

ለሶስተኛው ደረጃ ጊዜ ደረሰ፤ ማለትም 3ኛው ቀን።

ዘፍጥረት 1፡9 እግዚአብሔርም፦ ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ውሃዎቹ ወደ አንድ ስፍራ ተሰበሰቡና ከምድር ገጽ ላይ ገለል አሉ። ባሕር እረፍትና ሰላም የሌለውን ሕዝብ ይወክላል።

ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።

ክፉዎች እውነትን ለመቃወም ሲሰባሰቡ ከጻድቃን አጠገብ ገለል ይላሉ። የብሱ ጻድቃንን ይወክላል። ሐጥያተኞች ጻድቃንን በመቃወም ከብዙሃኑ ጋር ለመቀላቀል በራሳቸው ጎራ ይሰበሰባሉ፤ ይህም ሁልጊዜ ወደ ስሕተት የሚመራ ቁልቁል መንገድ ነው።

ቤተክርስቲያኖች ወደ አንድነት የሚመጡበት ምክንያት ሁሉም የሚጋሩዋቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን ስለሚከተሉ ነው፤ ለምሳሌ፡- ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ። ልክ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደሚደረገው ልማድ በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ላይ አንድ ሰው አለቃ እንዲሆን ይሾማሉ። ቤተክርስቲያኖችም ልክ እንደ ሰው ዓይነት ስም ይሰጣቸዋል፤ ለምሳሌ የሮማ ካቶሊኮች፣ ሜተዲስቶች፣ ባፕቲስቶች፣ እና የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት አለበት ብለው ይተቹታል። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ሚስጥር ሁሉ መግለጥ ችለዋል፤ ለምሳሌ 7ቱን ነጎድጓዶች እና አዲሱን የኢየሱስ ስም። የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ትተው እነርሱ እንደሚሉት “ስሕተት የሌለባቸውንና ፍጹም የሆኑትን” የዊልያም ብራንሐም ንግግር ጥቅሶች እየተከተሉ ናቸው፤ ደግሞም ዊልያም ብራንሐም “የእግዚአብሔር ድምጽ” ነው በማለት እርሱን መለኮት አድርገውታል። አዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም። ቤተክርስቲያኖ ሁሉ በሰው አመራር ስር ከመሆናቸው የተነሳ የሰው ትዕዛዛት የእግዚአብሔርን ቃል ቦታ ወስደዋል። አዲስ ኪዳን ውስጥ የትም ቦታ ፓስተር የቤተክርስቲያን መሪ ነው ተብሎ አልተጻፈም። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ትኩረታቸው በሙሉ በራሳቸው ላይ ብቻ ሲሆን ዓላማቸው ለራሳቸው ሃብት ማካበት ብቻ ሆኗል። ይህ የራስ ወዳዶች ዘመን ነው። የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን “ሃብታም ነኝ፤ ምንም አያስፈልገኝም” ብላለች። ብዙ ሰዎች ምንም መታረም የማያስፈልጋቸው ይመስላለቸዋል።

ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በአንድነት በተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶችና በጨለማ ሃሳብ ስለተሳሰሩ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል እንፈልጋለን የሚሉ ሰዎችን ይቃወማሉ። ስለዚህ በምድር ላይ በየስፍራው እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ማረጋገጥ የሚፈልጉ ሰዎች ብቅ ብቅ ይላሉ፤ እነዚህም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምድር ተመስለዋል። ዛሬ እነዚህ ግለሰቦች በ2020 ዓ.ም እግዚአብሔር በኮሮና በሽታ አማካኝነት ቤተክርስቲያኖችን በዘጋ ጊዜ በተፈለሰፈው በዘመናዊው የዙም (ZOOM) ቴክኖሎጂ አማካኝነት እየተገናኙ በሕብረት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ችለዋል። ቤተክርስቲያኖች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መዘጋታቸው ለዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ግልጽ የሆነ ዘለፋ ነው።

ውሃ እረፍት የሌለውን ብዙ ሕዝብና ድብልቅልቅ አመለካከቱን ይወክላል። ምድር ግን ጥቂቶችን ነው የሚወክለው።

በሶስተኛው ቀን እግዚአብሔር ደረቁን ምድር ወደ ላይ ገፍቶ አወጣው፤ ደረቁም ምድር ከባሕር በላይ ብቅ አለ። ይህንም ትልቅና ብቸኛ አህጉር ሳይንቲስቶች ፓንጌያ (ምድር በሙሉ) ብለው ይጠሩታል።

በኖህ ዘመን ግን እግዚአብሔር ይህንን አንድ ትልቅ አህጉር ወደ ትንንሽ አህጉሮች ከፋፈለው።

ዘፍጥረት 1፡10 እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራው የውኃ መከማቻውንም ባሕር አለው፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ደረቁ የብስ ስም ወጣለት፤ ምድር ተብሎ ተጠራ። ውሃዎቹ ምንም ስም አልተሰጣቸውም።

 

ውሃዎቹን ወደ አንድ ሥፍራ የማከማቸቱ ሂደት ባህር ተብሎ ተጠራ።

በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎችን ለመቀበል እምቢ በማለታቸው ኢክዩሜኒካል በሚባል እንቅስቃሴ ወደ አንድነት ይመጣሉ። ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ፍጹም መመሪያቸው መቀበል ካቆሙ ቆይተዋል። ሕዝባቸውን ደስ ለማሰኘት ብለው የቃላትን ትርጉም ይለውጣሉ። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 በላይ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። በዚህ ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የምታምነው የክርስቶስ ሙሽራ ከሌሎች ሁሉ የተገለለች ብቸኛ ሆናለች። “ቤተክርስቲያን” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ተጠርታ የወጣች” ወይም “የተለየች” ማለት ነው። አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያምን በቤተክርስቲያኖች ዘንድ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ይሄዳል።

በዘመን መጨረሻ እንክርዳዶች የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ባለመቀበላቸው በአንድነት እየተሰበሰቡ እንደ ነዶ ይታሰራሉ።

ማቴዎስ 13፡29 እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።

30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።

 

በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን እምነቶች ተሰብስበው የአውሬውን ምስል ይፈጥራሉ፤ ከዚያም እንደ እንክርዳድ በአንድነት ይታሰሩና ወደ ታላቁ መከራ ገብተው ለመቃጠል ይዘጋጃሉ።

ፕሮቴስታንቶች የካቶሊኮችን ማስ የተባለ ስርዓት አንፈጽምም ይላሉ። ነገር ግን ክሪስማስ የሚውን ቃል ራሱ ክራይስትስ ማስ ብሎ የፈጠረው ፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ በ350 ዓ.ም አካባቢ ሲሆን በ274 ዓ.ም አረማዊው የሮም ንጉስ ኦሬልያን ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ ልደት ነው ብሎ ከፈጠረው የጣኦት አምልኮ በመኮረጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን የልደት ቀን እንድናከብር አላዘዘንም። ስለዚህ ክሪስማስን የሚያከብሩ ፕሮቴስታንቶች በስውር በልባቸው ፖፑ የፈጠረውን ሕግ የሚከተሉ ካቶሊኮች ናቸው። ስለዚህ ቤተክርስቲያንን የሚወክሏት ፕሮቴስታንት ሴቶች ሜካፕ መጠቀማቸው አያስደንቅም።

ነገር ግን ቃሉን ብቻ የምትከተል ንጹኅ የስንዴ ዘር እያደገች ናት። ዘሩ መጠኑ ከታጨደበት ተክል ጋር ሲወዳደር በጣም ትንሽ ነው፤ የተገኘበት ተክል አስቀድሞ ሕይወት ነበረው፤ ነገር ግን ኋላ የተጻፈው ቃል በጥቅሶች አማካኝነት እየተገለጠ ሲሄድ አብሮ መቀጠል አቅቶት ደረቀ።

 

ዘፍጥረት 1፡11 እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

ደመናዎቹ ጠፍተው የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር በደረሰ ጊዜ እና ሕያዋን ፍጥረታት ሊተነፍሱት የሚችሉት አየር በተዘጋጀ ጊዜ እንዲሁም ደረቁ ምድር ከባህር ከተለየ በኋላ እግዚአብሔር በምድር አፈር ውስጥ የተከላቸው ዘሮች የሚበቅሉበት ሰዓት ደረሰ። ተክሎች ከምድር አፈር ውስጥ መብቀል ጀመሩ፤ ይህም የመጀመሪያው የሕይወት ተዓምር ነበረ።

ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

እያንዳንዱ ተክል እራሱን የሚያባዛበት ዘሮች የያዘ ፍሬ ያፈራል።

የፍራፍሬ ዛፍ ዘር በፍሬው ውስጥ ነው የሚገኘው።

ፍሬያማ ለመሆን ዘሩ (የእግዚአብሔር ቃል) በፍሬው ውስጥ (በሕጻኑ ኢየሱስ) መገኘት አለበት።

ኢየሱስ እግዚብሔር ወደ መሆን አልተለወጠም። እርሱ ሁሌም እግዚአብሔር ነበረ።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው፡- ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥

የዘላለም ሕይወት ዘር የሚገኘው ክርስቶስ ውስጥ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

ዘፍጥረት 1፡13 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን።

በሶስተኛው ቀን የተደረገው እጽዋትን የመፍጠር ስራ የመንፈሳዊ ሕይወት ማለትም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተምሳሌት ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ የአንድን ግለሰብ ሕይወት ይቆጣጠርና የተቆጣጠረውን ሰው እግዚአብሔር ለሕይወቱ ወዳሰበለት ፍጹም ፈቃድ ይመራዋል። ከዚህ በፊት ሕይወታችንን በራሳችን እንመራ ነበር፤ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አማኞች ግን የሕይወታቸውን ቁልፍ ለእግዚአብሔር አሳልፈው ይሰጡትና ሕይወታቸውን እርሱ ይመራዋል።

እግዚአብሔር ቀጣዩን ስራውን ከመስራቱ በፊት ተጨማሪ 1,000 ዓመታት እንዲያልፉ ፈቀደ።

 

4ኛ ቀን፡ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት አገልግሎታቸውን መስጠት እንዲጀምሩ ተደረገ

 

 

ዘፍጥረት 1፡14 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤

እስካሁን ድረስ ነገር ሁሉ የሚከናወነው ምድር ላይ ነበር። ነገር ግን ምድር ከእርሷ በላይ በሆነው ዓለም ውስጥ ትክክለኛ ስፍራዋን የምትይዝበት ሰዓት ደረሰ፤ ስለዚህ ከፀሃይ፣ ከጨረቃ፣ ከከዋክብት አንጻር ቦታዋን ያዘች።

በክርስቲያን የሕይወት ልምምድ ውስጥ አንድ አማኝ ከጸደቀ፣ ከተቀደሰ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቀ በኋላ አራተኛው ደረጃ እግዚአብሔር በክርስቶስ አካል ማለትም በቤተክርስቲያን ውስጥ ያዘጋጀለትን ስፍራ ማግኘት ነው።

ቀን እና ሌሊት እንዲፈራረቁ ፀሃይ እና ምድር ደግሞ በራሷ ዛቢያ ላይ መሽከርከሯ ያስፈልገናል። ምድር በሰው አቆጣጠር በ24 ሰዓት ውስጥ አንድ ዙር መዞር አለባት። ምድር የምትዞርበትን ፍጥነት ከቀነሰች ቀኑ በጣም ይረዝምና ምድር ከልክ በላይ ትሞቃለች። ሰዎችም ደግሞ ለብዙ ሰዓታት ስራ ላይ ከመዋል የተነሳ በጣም ይደክማቸዋል። ምድር ፍጥነቷ ከጨመረ ደግሞ ቀኑ በጣም ስለሚያጥር ሰዎች ለአንድ ቀን መስራት የሚያስፈልጋቸውን ሥራ ማጠናቀቅ አይችሉም። በተጨማሪ ደግሞ ቀኑ በቂ ሙቀት ስለማያገኝ ተክሎች ከፀሃይ ማግኘት የሚገባቸውን በቂ የብርሃንና ሙቀት ሃይል አያገኙም።

ስለዚህ የቀኑ ርዝመት የሚወሰነው ምድር በራሷ ዛቢያ ላይ በምትዞርበት ፍጥነት ነው። የቀኑን ሙቀት በተጨማሪ የሚወስነው ምድር ከፀሃይ የምትገኝበት ርቀት ነው። በጣም ከቀረበች እንቃጠላለን፤ በጣም ከራቀች ደግሞ እንቀዘቅዛለን። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ሁሉ መስተካከል አለባቸው።

የዓመቱ ርዝማኔ የሚወሰነው ምድር በፀሃይ ዙርያ በምሕዋርዋ ላይ በምትሄድበት ፍጥነት ነው። ስለዚህ ምድር በሕዋ ውስጥ የምትሄድበት ፍጥነትም ትክክል መሆን አለበት። በጣም ከፈጠነች ዓመቱ ያጥርና ተክሎች ለማደግ በቂ ጊዜ አያገኙም። ምድር በፀሃይ ዙርያ የምትሄድበት ፍጥነት በጣም ከቀነሰ ደግሞ ዓመቱ በጣም ይረዝምና ክረምቱም በጣም ስለሚረዝም ክረምቱን ለማሳለፍ የሚበቃ የእህል ክምችት አይኖረንም።

 

በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ ሳዘርን ክሮስ የተባለ ኮከብ በመጠቀም ነው አቅጣጫ የምንለየው። ይህም ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ አቅጣጫ የሚያሳየን የቀራንዮ መስቀል መሆኑን የሚጠቁም ተምሳሌት ነው።

የሰሜን ኮከብ ሁልጊዜ ወደ ሰሜን ነው የሚያመለክተው። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፣ ዛሬ፣ እስከ ዘላለምን እንደማይለወጥ ያሳያል። እርሱ የማይለወጠው አዳኝ ነው።

 

ዕብራውያን 13፡8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

ምድር በፀሃይ ዙርያ በምሕዋርዋ ላይ መሄዷ ሰዎች በተለያዩ ወቅቶች የሰማዩን የተለያዩ ክፍሎች እንዲያዩ ያስችላቸዋል። ከዋክብትን ማታ ማታ ፀሃይ ከምትገኝበት አቅጣጫ በተቃራኒ ስንመለከት ብቻ ነው የምናያቸው።

በእያንዳንዱ ወቅት ለሶስት ወራት የሚታዩ የተለያዩ የከዋክብር ስብስቦች ወይም ኮንስተሌሽኖች አሉ። እነዚያ ከዋክብት ማታ ማታ በሚታዩበት ጊዜ ሁሉ ሰዎች ከዓመቱ በየትኛው ወቅት እንዳሉ ያውቁ ነበር። ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙት ካላንደር ወይም የዘመን መቁጠሪያ የከዋክብት ስብስብ ናቸው። ሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ላይ ጎልቶ የሚታየው የከዋክብት ስብስብ አንድሮሜዳ ተብሎ ስሙ በቀይ ቀለም የተጻፈው ነው።

 

 

ዘፍጥረት 1፡15 በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፤ እንዲሁም ሆነ።

እግዚአብሔር ምድርን ከፀሃይ እና ከጨረቃ በትክክለኛው ርቀት ላይ ነው ያስቀመጣት። ምድር ከፀሃ በ150 ሚሊዮን ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው መገኘት ያለባት። ምድር ከጨረቃ የምትርቀው 380,000 ኪሎሜትር ነው። ጨረቃ በባሕር ውሃ ላይ ስበት በማድረግ ማዕበል ትፈጥራለች። ይህም በባሕር ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር እንዲንቀሳቀስ ስለሚያደርግ መበስበስን ይከላከላል። ጨረቃ ትንሽ ቀረብ ብትል ማዕበሉ በጣም ከባድ ይሆናል። ጨረቃ ትንሽ ራቅ ብትል ደግሞ ማዕበሉ በጣም ያንስ ነበረ። ንጥረ ነገሩን ለማንቀሳቀስ የሚበቃ ማዕበል አይፈጠርም።

ዘፍጥረት 1፡16 እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።

በዚህ ቀን እግዚአብሔር ያለ ምንም ነገር “አልፈጠረም”።

መጽ ቅዱስ በዚህ ክፍል “ፈጠረ” የሚለውን ቃል አልተጠቀመም።

የተጻፈው ቃል “አደረገ” የሚለው ነው። “አደረገ” ሁለት ትርጉሞች አሉ። አንድን ነገር የተለያዩ ግብዓቶች በመጠቀም መስራት ማለት ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ አንድን ሰው ወይም ነገርን አንድ ነገር እንዲሰራ ማስገደድ ማለት ሊሆን ይችላል። ሰማይ እና ምድር አስቀድሞ ያለ ምንም ነገር ተሰርተዋል። ስለዚህ ሰማይ እና ምድር ያለ ምንም ግብአት አስቀድመው ተፈጥረው ስለነበረ አሁን እንደገና እነርሱን መፍጠር አላስፈለገም። አሁን ግን እግዚአብሔር ሰማይና ምድር የሆነ ነገር እንዲሰሩ ሊያደርጋቸው ፈለገ። ዋነኛ የብርሃን ምንጭ በመሆን ከምድር በላይ ያለውን ሰማይ መቆጣጠር አለባቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ “አደረገ” የሚለውን ቃል የሚጠቀም ሲሆን ትርጉሙም ሥራ እንዲሰሩ አደረጋቸው ማለት ነው፤ በቀን እና በሌሊት ላይ እንዲሰለጥኑ አደረጋቸው። ፀሃይ በቀን ላይ እንድትሰለጥን አደረገ፤ ጨረቃ ደግሞ በሌሊት ላይ እንድትሰለጥን አደረገ።

ይህን ትዕዛዝ የሰጣቸው ፀሃይ እና ጨረቃ ከተፈጠሩ በኋላ ነው፤ ስለዚህ እንደ አዲስ መፈጠር አላስፈለጋቸውም። “ፀሃይ እና ጨረቃ የሆነ ሥራ እንዲሰሩ አደረገ”። የተፈጠሩበትን ዓላማ እንዲፈጽሙ አደረጋቸው

እያንዳንዱ የታሰበለትን ሥራ እንዲያከናውን አደረገ

ብርሃናቸው ቀንን እና ሌሊትንመግዛት አለበት። ፀሃይ ቀንን ትገዛለች እንጂ ሌሊትን አትገዛም። ስለዚህ በሌሊት ጨለማ ምድርን ሲወርሳት ፀሃይ ብርሃንዋን ለምድር ለማድረስ ጨረቃ ታስፈልጋታለች። ሌሊት ከፀሃይ ተንጸባርቆ የሚበራውን ብርሃን የጨረቃ ብርሃን እንለዋለን። የጨረቃ ብርሃንም ጨረቃዋ ሙሉ በሆነች ጊዜ ሌሊት እያየን መንቀሳቀስ እንድንችል የሚበቃ ብርሃን ይሰጠናል።

ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ሕይወታችንን ሊገዛው ይገባል። ኢየሱስ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ ብርሃን ዓለምን ለቆ ሄደ። ጨረቃ (ማለትም ቤተክርስቲያን) በቦታው ተተካች፤ የቤተክርስቲያንም ስራ የእግዚአብሔርን ቃል ብርሃን ማንጸባረቅ ነው።

ቤተክርስቲያን የሰራችውና እስካሁንም የምትሰራው ስሕተት የራሳችንን ብርሃን የራሳችንን አመለካከት ማንጸባረቃችን ነው። ወይም ደግሞ የሌላ የታዋቂ ሰው አመለካከት እናንጸባርቃለን። ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያናችንን ልማዶች እናንጸባርቃለን። እነዚህ ሁሉ አመለካከቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ ካልሆኑ ጨለማ ናቸው።

ጨረቃ የራሷ ብርሃን የላትም። ጨረቃ በጨለማ ውስጥ ላላው ዓለም የፀሃይን ብርሃን ተቀብላ ማንጸባረቅ ብቻ ነው የምትችለው። የዕለት ተለት ሥራችን የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ማንጸባረቅ ነው። ሌላ ምንም ሥራ የለንም። በራሳችን ምንም ብርሃን የለንም፤ ስለዚህ ጠቃሚ የምንሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ብርሃን ስናንጸባርቅ ብቻ ነው።

አንድ የማስጠንቀቂያ ቃል እንናገር። ዓለም በፀሃይ (እግዚአብሔር) እና በጨረቃ (ቤተክርስቲያን) መካከል ስትገባ የምድር ጥላ ጨረቃን ይጋርዳታል፤ ይህም ሲሆን የጨረቃ ግርዶች ተፈጠረ እንላለን። ልክ እንደዚሁ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል ማንጸባረቅ ትተው ዓለማዊነትን፣ ዓለማዊ ፋሽንን እና ሃብትን ሲከተሉ ምስክርነታቸው ይጨልማል።

 

 

ዘፍጥረት 1፡17 እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤

እግዚአብሔር ወደ የመንግስተ ሰማያትን መንገድ ፍንትው አድርጎ የሚወስደውን ብርሃን ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል። ቤተክርስቲያንን ደግሞ የመሰረታት ክርስቲያኖች በንግግርም ሆነ በአኗኗር የመጽሐፍ ቅዱስን ብርሃን ለሌሎች ያንጸባርቁ ዘንድ ነው።

የሚያሳዝነው ነገር ጨረቃ በየወቅቱ ብርሃኗ የሚቀንስበትና የሚደበዝዝበት ጊዜ አለ። ፀሃይ ግን ድምቀቷ አይቀንስም። ችግሩ ያለው ከኢየሱስ አይደለም። ክርስቲያናዊ ምስክርነታችን ሲደበዝዝ ችግሩ ያለው ከቤተክርስቲያን ነው።

 

ዘፍጥረት 1፡18 በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

የእግዚአብሔር ቃል መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ይነግረናል (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው ቃል የፀሃይ ብርሃን ነው) ትክክል ያልሆነውንም ያሳየናል (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ሁሉ ለሰዎች መልካምና ቅን ቢመስለንም እንኳ መንፈሳዊ ጨለማ ነው)።

ለምሳሌ የሮማ ካቶሊክ ሐይማኖት ተከታይ የነበረችዋን ፖላንድን ኮምዩኒዝም ተቆጣጥሯት በነበረ ጊዜ ሕዝቡ በድህነት ተሰቃይተዋል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ የነበራቸው እምነት ጠንካራ ነበረ። ለብዙ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ በነበረችው ፖላንድ ውስጥ ኮምዩኒዝም እንዲወድቅ ፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በዚህም ጊዜ መልካም ነገር የመጣ ይመስል ነበር። ካቶሊኮችን ነጻ ለማውጣት ትልቅ እርምጃ የተወሰደ ይመስል ነበር። ነገር ግን ከዚያ በኋላ የሆነው ነገር ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስደንጋጭ ነበር፤ አብዛኞቹ የፖላንድ ሕዝቦች የአሜሪካን ባህል በመከተል ቁሳዊ ሃብት ለማካበት መሯሯጥ ጀመሩ። ለሃብት ሲስገበገቡ የብዙዎች እምነት ወደቀ። ስለዚህ አሁን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብዙዎች ሕዝቦቿ በፊት የነበራቸውን መንፈሳዊነት ጥለው ከእግዚአብሔር እየራቁ መሆናቸውን ስታይ ታዝናለች።

ለጊዜው ሐይማኖትንና ፖለቲካን መቀላቀል መልካም መፍትሄ ይዞ የሚመጣ እርምጃ ይመስል ነበር፤ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አላመጣም።

ፖለቲካ እና ሐይማኖ ሲቀላቀሉ የሚያፈሩት ፍሬ ሞት ብቻ ነው።

ባለፈው ክፍለ ዘመን ውስጥ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እና ካቶሊክ ግጭት ተመልከቱ።

እግዚአብሔር በምድር ላይ ሕይወትን በመፍጠር ሂደት ውስጥ በእያንዳንዱ እርምጃ መካከል 1,000 ዓመታት እንዲያልፉ አድርጓል።

 

ማታ እና ጥዋት። ሌሊቱ አልተጠቀሰም

 

 

ዘፍጥረት 1፡19 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን።

ሌሊት አልተጠቀሰም። ስለዚህ እግዚአብሔር ምን ሊነግረን ፈልጎ ነው።

 

የሌሊቱ ሰዓት የተላቁን መከራ ዘመን የሚገልጽ ተምሳሌት ነው።

በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን (በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን) ማብቂያ ላይ ኢየሱስ ሙሽራይቱን ለሰርግ ግብዣ ወደ ሰማይ ይወስዳታል። ኢየሱስ ብርሃን ነው፤ ስለዚህ ብርሃን ምድርን ትቶ በሄደ ጊዜ ምደር ወደ ጨለማ ውስጥ ትወድቃለች። ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው ንጋት ኢየሱስ ሲመለስ በምድር ላይ የሚሰርተውን የሺ ዓመት መንግስት ብርሃን ይወክላል። (ሒትለር እርሱ የመሰረተው ሰርድ ራይሽ የተባለው መንግስት ለ1,000 ዓመታት ይገዛል ብሎ ነበር፤ ነገር ግን ከ12 ዓመታት አላለፈም። ነገር ግን ለ1,000 ዓመታት እነግሳለሁ ሲል ማንን እየኮረጀ እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ።)

ሌሊቱ የሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ይወክላል፤ ይህም የሚሆነው ልክ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ነው፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ወደ ምድር ተመልሶ ይመጣል።

ዘካርያስ 14፡7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል

ሉተር በእምነት መዳን እና በእምነት መጽደቅ የተባለውን የእውነት ብርሃን መልሶ አመጣ። ዌስሊ መቀደስ እና በቅድስና የመኖርን እውነት መልሶ አመጣ። ጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅንና ተዓምራዊ ስጦታዎችን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። ከዚያም በመጨረሻ በወንጌል ሌሊት ጊዜ ልክ ከታላቁ መከራ ምሽት በፊት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መልሶ የሚያመጣ ነብይ ያስፈልገናል።

ዛሬ በክርስትና ውስጥ 160 ዋና ዋና ክፍፍሎች አሉ። ከነዚህ ክፍፍሎች ውስጥ የወጡ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያኖች የየራሳቸው እምነት አላቸው። በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዝኛ ብቻ ከ100 በላይ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። እያንዳንዱ ክርስቲያን በራሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትክክል ነኝ ብሎ ተመችቶች ሞቆት ተቀምጧል። ነገር ግን 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ልዩነታቸውን እንደያዙ ሁሉም ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ ከክርስቲያኖች መካከል አብዛኞቹ አሁን በእምነታቸው ውስጥ ያለባቸውን ስሕተት ስለማያውቁ ኋላ ባወቁ ጊዜ ያዝናሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ብሎ እንደተናገረ መረዳት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፤ በተለይ ደግሞ ትንቢታዊ ተምሳሌቶችን መረዳት ይጠቅማል። መጽሐፍ ቅዱስን የማናውቅ ከሆነን በቀላሉ እንታለላለን፤ በተለይም የዓለም ሁኔታ በጣም እየተቃወሰ ሲሄድ፤ እንዲሁም ቤተክርስቲያን እና ፖለቲከኞች በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃወም አመለካከት ሲያስተጋቡ ግራ እንጋባለን።

ስለዚህ በሌሊት በቤተክርስቲያን ታሪክ ማብቂያ ብርሃን ይኖራል፤ ይህም የሚሆነው ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያይቱ የሐዋርያትን አስተምሕሮ ወደታዘዘችው የቤተክርስቲያን ዘመን ትምሕርቶች ስትመለስ ነው።

 

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ሚስጥር የሚገለጠው በመጨረሻው ወይም በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።

አሁን ያለንበት ጊዜ የታላቁ መከራ ጨለማ ከመግበቱ በፊት የሚሆነው ሌሊት ነው።

ከዚያም እግዚአብሔር ሌሊቱን (ታላቁን መከራ) መጥቀስ ትቶ ወደ ጥዋት ንጋት ያልፋል (ይህም ኢየሱስ በምድር ላይ የሚነግስበት የ1,000 ዓመት መንግስት ነው)።

ይህም ማለት እውነተኛዋ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን፣ ሙሽራይቱ በ3½ የታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ አታልፍም ማለት ነው። የሙሽራይቱ አካላት በ3½ የመከራ ጊዜ አይገኙም ምክንያቱም መከራው በምድር ላይ በሚሆንበት ጊዜ እነርሱ ሌሊት በሌለበት፣ ጨለማ በሌለበት፣ ሐጥያት በሌለበት በሰማይ ይሆናሉ።

ስለዚህ የክርስቶስን ሙሽራ ታላቁ መከራ አያገኛትም።

እግዚአብሔር በፈጠራት ምድር ላይ ሕይወትን ለማኖር ሲወስን በ7 የእግዚአብሔር ቀናት ውስጥ ለመስራት ወሰነ፤ እነዚህም ቀናት በሰው አቆጣጠር 7,000 ዓመታት ናቸው። እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ሰዎች አልተፈጠሩም፤ ስለዚህ የሰዎችን የቀን አቆጣጠር መጠቀም አላስፈለገም።

ስለዚህ ምንም ሕይወት ያልነበረባትን ምድር እግዚአብሔር በ6,000 ዓመታት ውስጥ ገነት አደረጋት።

7ኛው ቀን ለእግዚአብሔር ልጅ ለአዳም እና ለሙሽራይቱ ምድርን ለ1,000 ዓመታት እንዲገዙ ተሰጣቸው።

ነገር ግን በዚያ ሰባኛ ቀን 1,000 ዓመታት ውስጥ አንድ ቀን ሴቲቱ እግዚአብሔር ባዘጋጀላት ኑሮ ተሰላቸች፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከተናገረው የተለየ “አስደሳች” አዲስ ትምሕርት ሰማች። ዓይኖቿን ከእግዚአብሔር ቃል ላይ አነሳች፤ የዛኔም ሐጥያት ወደ ዓለም ገባ፤ ሰይጣንም ዓለምን ተቆጣጠረ።

 

 

ሰይጣን በኤድን ገነት ውስጥ የእግዚአብሔርን እቅድ ካበላሸበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምድርን ለ1,000 ዓመታት ገዝቷል፤ የኤደንን ገነትም በሰዎች ጥላቻ ተሞልቶ ሞት ወደ ነገሰበት ምድረ በዳ ለውጦታል፤ ባለፈው ክፍለ ዘመን በተደረጉ ጦርነቶች ብቻ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ ሰዎች በቸልተኝነት የእግዚብሔርን ቃል ወደ ጎን ትተዋል፤ ምንም ጥቅም እንደሌለው ይቆጥሩታል። ምንመ ለውጥ ያመጣል? ሲሉ ይጠይቃሉ። በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ ስለሚሰማቸው ምንም የማያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል፤ ስለዚህ ምንም ዓይነት እርማት አይቀበሉም። ዓለምን እንደ መንፈሳዊ ሱናሚ ወይም ደራሽ ውሃ የሚያጥለቀልቃት ታላቅ መከራ ሲመጣ እነዚህ ሁሉ የሞኝነት አስተሳሰቦች ተጠርገው ይጠፋሉ። ዓለም የምትጠፋው ግን በእሳት ማዕበል ነው እንጂ እንደ ኖህ ዘመን በውሃ አይደለም።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡10 የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።

አሁን የሰው ቀን ነው። እንደፈለጋችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። በእግዚአብሔር ማመን ትችላላችሁ፤ እግዚአብሔርን ቸል ማለት ትችላላችሁ፤ ወይም እግዚአብሔርን መቃወም ትችላላችሁ። ነጻ ፈቃድ ተሰጥቷችኋል።

ታላቁ መከራ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ በዚያም ቀን ምድርን ለሺ ዓመት መንግስት ለማንጻት እግዚአብሔር በሐጥያተኛ ሰዎች ላይ እንደፈለገ ያደርጋል።

በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ክፋትን በሙሉ ያስወግዳን፤ ከዚያም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ከሙሽራይቱ ማለትም ከእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ጋር ሆኖ ለ1,000 ዓመት በመንገስ አዳም ማለትም የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ልጅና ሚስቱ ሊነግሱ ያልቻሉበትን ሰባተኛውን ቀን ይፈጽመዋል።

ራዕይ 20፡4 ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ

ብርሃን ሁልጊዜ ጨለማን ያሸንፋል። ብርሃን ጨለማን ማጥፋት ይችላል፤ ጨለማ ግን ትንሽዋን ብርሃን እንኳ ማጥፋት አይችልም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23