ሰባቱ መለከቶችና ሰባቱ ጽዋዎች፤ ክፍል 1



በታላቁ መከራ ውስጥ የሚነፉት 7 መለከቶች አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ያስገድዷቸዋል። 7ቱ ጽዋዎች መጽሐፍ ቅዱስን አልቀበልም ባለችው ዓለም ላይ ፍርድ ያመጣሉ።

First published on the 16th of April 2022 — Last updated on the 16th of April 2022

መገለጥ በሂደት የሚመጣ መረዳት ነው።

ማንኛውም እውነተኛ አስተምሕሮ ሌሎች አስተምሕሮዎችን ለመረዳት በር ይከፍታል።

የ7ቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት አስተምሕሮ በ7ኛው ዘመን ውስጥ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ አፍርቷል።

 

 

ልብ በሉ።

ወንድም ብራንሐም በሰባቱ ማሕተሞች ላይ የጻፈው ይህ መጽሐፍ “የ7ቱ ማሕተሞች መፈታት” አይደለም

አንድ ነገር ከመፈጸሙ በፊት “አስቀድሞ በመገለጡ” እና ኋላ ደግሞ “እውን ሆኖ በመፈጸሙ” መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።

ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በ7ኛው ዘመን ውስጥ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ አፍርተዋል።

የ7ኛው ማሕተም ሚስጥር መፈታት እስካሁን ገና አልተፈጸመም ግን ከሰባቱ ነጎድጓዶች ጋር የተያያዘ ነው፤ ሰባቱ ነጎድጓዶችም ድምጻቸውን የሚያሰሙት የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱ በኋላ ነው።

የሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጽ መሰማት የኋለኛውን ዝናብ ወይም የመከሩን ዝናብ ያመጣዋል ምክንያቱም እነዚህ ቅዱሳን ልክ እንደ መከር አዝመራ ከምድር ላይ ታጭደው ወደ ሰማይ ተነጥቀው ይሄዳሉ።

 

 

ስለ 7ቱ ማሕተሞች መፈታት በተሰጠው መገለጥ እና ማሕተሞቹ በውል በመፈታታቸው መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ ማሕተሞቹ የሚፈቱት ገና ወደ ፊት ሙሽራይቱ በሰማይ በምትሆንበት ጊዜ ነው።

መገለጡ ስለ ክስተቱ ብቻ ነው የሚነግራችሁ። ከዚያ በኋላ ምን አስከትሎ እንደሚመጣ እናንተው ትገነዘባላችሁ።

ነገር ግን መገለጡ በራሱ የነገሩ ፍጻሜ አይደለም።

የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ሰዎች የማሕተሞቹ መፈታት እንደሆነ አድርገው በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። ነገር ግን ትክክል አይደሉም ምክንያቱም ከማሕተሞቹ ግማሾቹ ያለፉ ታሪኮችን በተመለከተ ነው የሚናገሩት።

የቀሩት ግማሾቹ ማሕተሞች ግን ገና ወደፊት በታላቁ መከራ ውስጥ ሊፈጸም ስላለ ነገረ ነው የሚናገሩት፤ ይህንንም ሰዎች በደምብ አይረዱም።

ስለ ታላቁ መከራ የምናውቀው በጣም ጥቂት ነው፤ ስለዚህ መረዳት የምንችለው እግዚአብሔር አስቀድሞ ባሳየን የታላቁ መከራ ቅምሻዎች መሰረት ነው።

እነዚህ የታላቁ መከራ ቅምሻዎች የታዩት በተለይ በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ወቅት ነው።

ስለዚህ ስለ ወደፊቱ ታላቅ መከራ የሚናገሩት ማሕተሞች ገና አልተፈቱም፤ ቢፈቱ ኖሮ ዝርዝር ጉዳያቸውን ማወቅ በቻልን ነበር።

ወንድም ብራንሐም በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚፈጸሙት ሰባት መለከቶች እና ስለ ሰባቱ ጽዋዎች ሊያስተምር አንድ ዓመት ያህል ሲጠብቅ ቢቆይም እንኳ አላስተማረም።

ሶስቱ መንፈሳዊ ፈረሶች (ነጭ፣ ቀይ፣ ጥቁር) ያሉባቸውን ያለፉ ታሪኮች መረዳት እንችላለን፤ እነዚህም ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ በተጻፈው መሰረት የፈረስ ቀለማት የሐይማኖት ሽንገላ፣ የፖለቲካ፣ እና የገንዘብ አጋንንታዊ ኃይል የሚወክሉ ምልክቶች ናቸው። በዘመናችን እነዚህ ኃይላት ወደ አንድነት እየመጡ ናቸው፤ ስለዚህ በ “The Revelation of the Seven Seals” ወይም “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ”በሚለው መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ሲብራሩ የእውነትም ማሕተሞቹ የተፈቱ ይመስላሉ።

ነገር ግን ይህ መረዳት በሶስት ምክንያቶች የተሳሳተ ነው፡-

 

1. መጀመሪያ ማሕተሞቹ በሰማያት ከመፈታታቸው በፊት ሙሽራይቱ ተነጥቃ ወደ ሰማይ መሄድ አለባት።

ስለዚህ ማሕተሞቹ የሚፈቱት በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።

የወንድም ብራንሐም መገለጥ በታላቁ መከራ ውስጥ የሚሆኑት ክስተቶች ምን እንደሚመስሉ በጨረፍታ አሳይቶናል።

ታለቁ መከራ ውስጥ ምን ምን እንደሚከናወን ማወቅ ከፈለግን በሩቁ ጨረፍታውን ማየታችን አስፈላጊ ነው።

ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ዘመን ምድር ላይ አትገኝም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት መጀመሪያ በአይሁዶች ላይ ቀጥሎም በቤተክርስቲያናት ጥምረት ላይ የአጋንንት ሥራ ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀስ ፈቅዷል፤ ይህንንም ያደረገው እነዚህ ክፉ ኃይላት በታላቁ መከራ ውስጥ ምን እንደሚያደርጉ ለሙሽራይቱ ግንዛቤ ለመስጠት ነው።

 

2. ሁለተኛ ደግሞ ኢየሱስ ሙሽራይቱን በአየር ላይ ለመቀበል ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ይነሳል፤ ከዚያም ወደ ሰማይ ወስዷት የቤዛነትን መጽሐፍ ከፍቶ ሙሉ ዝርዝሩን ይገልጥላታል።

ሰባቱ ማሕተሞችም በውል ሲፈቱ ከዚያ ወዲያ ለአሕዛብ ምሕረት የለም።

ለዚህ ነው ታላቁ መከራ ጌታ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከወሰዳት በኋላ የሚጀምረው። በዚያ ጊዜ የሙሽራይቱ አካላት በአዲሱ በማይሞተው አካላቸው ውስጥ ስለሚኖሩ ከዚያ ወዲያ የሚቤዣቸው አያስፈልጋቸውም። ኢየሱስም ሰባቱ ነጎድጓዶች በሚገልጡት በአዲስ ስሙ ይጠራል።

1965 የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ፤ ምዕራፍ 8፤ ፊልደልፊያ

አዲሱን ስሜን እጽፍበታለሁ። አዲሱ ስሜ። ሁሉ አዲስ በሚሆንበት ጊዜ እርሱም አዲስ ስም ለራሱ ይወስዳል፤ ያ ስም ደግሞ የሙሽራይቱም ስም ይሆናል። ያ ስም ማን እንደሆነ ማንም ሊገምት አይድፈር። ማንም ሊክደው እንዳይችል በመንፈስ የሚሰጥ መገለጥ መሆን አለበት። ያለ ምንም ጥርጥር እርሱ ይህንን ስም ሊገልጥ እስከወሰነበት ቀን ድረስ ይጠብቃል። ለጊዜው መገመት ከምንችለው በላይ እጅግ አስደናቂ ይሆናል ብለን ማረፍ ይሻለናል።

የኢየሱስን አዲስ ስም በፍጹም ለመገመት መሞከር እንደሌለብን ወንድም ብራንሐም ነግሮናል።

ያ ስም ማን እንደሆነ ለማሰብ እንኳ አንችልም።

የሜሴጅ ፓስተሮች ግን አእምሮዋቸው ከተሞላበት ከጉራቸው ብዛት የተነሳ አስተዋዮች ተብለው ለመጠራብ ፈልገው ብዙ አዲስ ስሞችን ገምተዋል።

አዲስን ስም መገመት ስሕተት ነው። ወንድም ብራንሐም በጭራሽ እንዳንገምት ነግሮናል።

ይህ አሳዛኝ ጉዳይ ሐይማኖታዊ ሽንገላን የሚወክለው ነጩ ፈረስ ወደነዚህ ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልኮ መግባቱን ያመለክታል። አዲሱን ስም ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ አዲሱን የማይሞተውን አካላችሁን ስትለብሱ ብቻ ነው። ይህም የሚሆነው የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱ በኋላ ብቻ ነው።

አዲሱን ስም ማንም አያውቀውም፤ ይህን አትርሱ። ስለዚህ ማንም ቢሆን አዲሱን ስም አውቃለው ብሎ አይሸንግላችሁ።

ራዕይ 19፡12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው

በአሁኑ ሰዓት በአሮጌው አካላችን ውስጥ ነው ያለነው፤ ስለዚህ ብዙ የሐጥያት ይቅርታ ያስፈልገናል። ኢየሱስ በየዕለቱ በምሕረት ዙፋኑ ላይ እንዲገኝልን ያስፈልገናል። እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሱስ ስም እያለን መጸለያችን እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቃችን የኢየሱስን አዲስ ስም አለማወቃችንን ያሳያል። ምክንያቱም አዲሱ ስም ከተገለጠ በኋላ ኢየሱስ የተባለውን ስም መጠቀም እናቆማለን። ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ያህዌ ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ነገር ግን ኢየሱስ የተባለው አዲስ ስም የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ከተገለጠ በኋላ ያህዌ የተባለው የቀድሞ ስም አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።

የኢየሱስ “አዲስ ስም” ከተገለጠ በኋላ ሁለተኛ “አሮጌውን ስሙን” አትጠቀሙትም።

አካላችን የሚለወጠው ከሙታን ትንሳኤ በኋላ ብቻ ነው፤ ስለዚህ አዲሱ የኢየሱስ ስም የሚገለጠው በዚያ ጊዜ ነው።

 

3. ሶስተኛ ደግሞ ማሕተሞቹ በመገለጥ መልክ ተከፍተዋል፤ ይህም ምልክቶችን በመተርጎም አማካኝነት ሊፈጸሙ ስላሉ ነገሮች ፍንጭ ይሰጠናል።

ነገር ግን በሰባቱ ማሕተሞች መፈታት መገለጥ ውስጥ የተወሰኑ የጎደሉ ዝርዝር ነገሮች አሉ።

ሰባተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ አናውቅም። ኢየሱስ መች እንደሚመጣ ስለማናውቅ ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ሆኖብናል።

64-0719 የመለከቶች በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

ስድስተኛው ማሕተም ታላቁን መከራ በተመለከተ እንደሆነ እናውቃለን፤ ነገር ግን ከታላቁ መከራ ጋር ስለተያያዙ ክስተቶች ብዙም ዝርዝር አናውቀም።

በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚሆኑት ስለ 7ቱ መለከቶች እና ስለ 7ቱ ጽዋዎች ሙሉ መረዳት የለንም። ስለነዚህ ክስተቶች የምናውቀው በጣም ውስን ነው።

አራተኛውን ማሕተም በተመለከት መረዳታችን ግማሽ ብቻ ነው ምክንያቱም ሞት በተባለው ፈረስ ጋላቢ የተመሰለውን የመጨረሻውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ስሙን አናውቅም፤ ስለ እርሱ ዝርዝር ጉዳዮችንም አናውቅም።

ቁጥር 8 ላይ የተጠቀሰው አራተኛው ማሕተም ወደ ፊት ስለሚመጣው ታላቅ መከራ ነው የሚገልጸው።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

“የምድር አራተኛዋ እጅ” ማለት ሁለት ቢሊዮን ሕዝብ ነው። እስከ አሁን (2020 ዓ.ም) ድረስ ሰዎች በዚህ ያህል ከፍተኛ ቁጥር ተገድለው አያውቁም።

ስድስተኛው ማሕተም የሚፈታው በሁለቱ ነብያት ማለትም በሙሴ እና በኤልያስ ብቻ ነው፤ እነርሱም በታላቁ መከራ ውስጥ ይፈቱታል።

63-0323 ስድስተኛው ማሕተም

… ውሃን ወደ ደም ለመለወጥ እና በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ምድርን በመቅሰፍ ለመምታት ስልጣን ይኖራቸዋል።

ምንድነው? ከቃሉ በቀር እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ማድረግ የሚችል ምንድነው? ተፈጥሮን እንደፈለጉ ሊያሽከረክሯት ይችላሉ። ተመልከቱ። ስድስተኛው ማሕተም እንዲፈጸም የሚያደርጉት እነርሱ ራሳቸው ናቸው። ማሕተሙን ይገልጡትና ይፈቱታል። ይህም እግዚአብሔር የተፈጥሮ ኡደት እንዲቋረጥ የሚያደርግበት ኃይል ነው። ተመለከቱ፤ ስድስተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ኡደት መቋረጥ ነው።

አሁንስ አስተዋላችሁን? ይኸው ማሕተሙ። ማነው የሚያደርገው? ንጥቀት ከተፈጸመ በኋላ ነብያቱ ናቸው የሚያደርጉት። በእግዚአብሔር ኃይል፣ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ላይ ይፈርዳሉ። የምድር መንቀጥቀጥ ማስነሳት ይችላሉ፤ ጨረቃን ወደ ደም መለወጥ ይችላሉ፣ ፀሃይ ልትወድቅ ወይም በእነርሱ ትዕዛዝ ማንኛውንም ነገር ልትሆን ትችላለች። አሜን።

ይኸውላችሁ። ይኸውላችሁ። አያችሁ? ማሕተሞቹ በምድር ላይ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲፈቱ ሚስጥራቱ ሲገለጡ ተመለከታችሁ? አሁን ተመልከቱ እነዚህን ሁለት ነብያት፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሆነው በመቆም በፍጥረት ላይ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፤ ምድርንም ያናውጣሉ። እነዚህንም ነገሮች የሚያደርጋቸው ማን እንደሆነ ያስታውቃል። ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው፤ ምክንያቱም የእነርሱ አገልግሎት ነው በድጋሚ በምድር ላይ የሚገለጠው፤ የሁለቱም። ገባችሁ አሁን? ስድስተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ገባችሁ? እነዚያ ነብያት ናቸው። አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምንኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ። አያችሁ?

 

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውንም ሆነ ሰባተኛውን ማሕተም አልፈታም።

የመጀመሪያው ማሕተም እንኳ ሙሉ በሙሉ አልተፈታም። ትርጉሙ ምን እንደሆነ ያልታወቀ አንድ ነጎድጓድ አለ።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ሊሞት አንድ ወር ብቻ ሲቀረው እንኳ ወንድም ብራንሐም ይህ ብቸኛ ነጎድጓድ ሲፈጸም ለማየት ይጠባበቅ ነበር።

65-1127 መስማትን ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

በሕይወቱ የመጨረሻ በነበረችው ወር ወንድም ብራንሐም ብቸኛውን ነጎድጓድ፣ ታላቁን ድምጽ፣ የመላእክት አለቃውን ድምጽ፣ የእግዚአብሔርን መለከት፣ እና የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንን ትንሳኤ ይጠባበቅ ነበር።

በሌላ አነጋገር ማሕተሞቹን አልፈታቸውም፤ ይልቁንምወደ ፊት ማሕተሞቹ ሲፈቱ ምን እንደሚሆን በመገለጥ ወይም አጠር ባለ ማብራሪያ አማካኝነት አስረዳን እንጂ።

ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።

ዮሐንስ የመጀመሪያውን ማሕተም ሚስጥረዊ ምልክቶች እንደሆኑ አድርጎ ነው የጻፈው።

 

 

ሰባት መላእክት ወንድም ብራንሐምን አናገሩት፤ እርሱም ወደፊት በሰማይ የሚፈቱትን ሰባቱን ማሕተሞችና በእነርሱ ምክንያት ምን እንደሚሆን በራዕይ ተመለከተ።

ከዚህም የተነሳ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ሰባቱ ማሕተሞች በሰማይ ሲፈቱ ምን እንደሚፈጠር መረዳት አግኝተናል።

ከዚህ ቀጥለን በመጀመሪያው ማሕተም ውስጥ የተካተቱ ምልክቶች ምን ማለት እንደሆኑ እናያን።

ሚስጥራዊው ፈረስ ጋላቢ የካቶሊክ ፖፕ ስልጣንን ያስጀመረው በሐይማኖታዊ ሽንገላ (ቀስት የሌለው ደጋን) የሚሰራው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው። አንድ ፖፕ በሞተ ቁጥር አዲስ ፖፕ ይመረጣል። በምድር ላይ ከሁሉ ይበልጥ ለረጅም ጊዜ ሳይቋረጥ የቆየው የስልጣን መተካካት ይህ ነው። ከ1315 ዓ.ም ጀምሮ ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ መጫን ጀምረው ነበር።

 

 

ብቸኛው ነጎድጓድ ግን ምን እንደሆነ አልተብራራም። እስከ 1965 መጨረሻ ድረስ አልተፈጸመም።

ስለዚህ እስካሁን (2020 ዓ.ም) ገና አልተፈጸመም ።

ስለዚህኛው ነጎድጓድ ምንም ስለማናውቅ የመጀመሪያው ማሕተም በጥቂቱ ብቻ ነው የተገለጠው፤ ነገር ግን በሙሉ በዝርዝር አልተገለጠም

 

የመጀመሪያዎቹን ሶስት ከግማሽ ማሕተሞች በሚገባ መረዳት እንችላለን ምክንያቱም እነዚህ በብዛት በታሪክ ውስጥ ተፈጽመው ያለፉ ክስተቶችን በተመለከተ ነው የሚናገሩት።

(ብቸኛው ነጎድጓድ ነው በታሪክ ውስጥ ያልተፈጸመው።)

ነገር ግን አንድ ነገር ልብ ማለት አለባችሁ፤ ይህም በሐይማኖት ሽንገላ የሚሰራው ነጭ ፈረስ ጋላቢ ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ በማሞኘት በስውር በመካከላችን እየሰራ መሆኑን ነው። ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ? አዎ። በዚህ በመጨረሻው የሎዶቅያውያን ዘመን ውስጥ ስለሉ ቤተክርስቲያኖች እግዚአብሔር አንዳችም መልካም ነገር አልተናገረም።

ሐመር ፈረስ ላይ የተቀመጠው ሞት በታላቁ መከራ ውስጥ ብቻ ነው ፈረሱን የሚጋልበው።

ሞት ሰተት ብሎ የሚገባው ሕይወት ሲወጣ ብቻ ነው።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ሲነጥቃት ሞት የዚያን ጊዜ መግባት ይችላል።

ሮሜ 8፡10 … መንፈሳችሁ ግን … ሕያው ነው

ይህ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ማን እንደሆነ አናውቅም፤ ምን ሊያደርግ እንደሚመጣም በዝርዝር አናውቅም። ስለ ታላቁ መከራ የተሰጠን መገለጥ በጣም ጥቂት ነው።

ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ተከፍተው የማያውቁትን ስድስተኛውንና ሰባተኛውን ማሕተሞች ይከፍቱዋቸዋል።

ደግሞም አራተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ተከፍቷል ማለትም አይቻልም።

እስከ እኛ ዘመን ድረስ ያለው ብቻ ተገልጧል እንጂ መገለጡ ታላቁን መከራ አያካትትም።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መረዳት እንችላለን። በሰማይ ያለው አራተኛው እንስሳ የሚበርረው ንስር ነው፤ ስለዚህ ነብይን ይወክላል። ወንድም ብራንም ድምጹን መስማት እንችል ዘንድ ስብከቶቹን በድምጸ መቅጃ አማካኝነት ቀድቶ፣ በMP4 አስቀምጧል፤ በመጻሕፍት ጽፏል፤ በኢንተርኔትም ጭኗል።

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እንከን የለሽ ነው ከማይሉ ቤተክርስቲያኖቻችንና ከዲኖሚኔሽኖቻችን እንድንወጣ ነግሮናል።

የዚያን ጊዜ ብቻ ነው እርሱ የሰጠንን መገለጦች በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ላይ መከታተል የምንችለው።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

መጽሐፍ ቅዱስን አድምጡ፤ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ሰዎችን የሚጠራበት ድምጹ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው።

ወንድም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ አይደለም።

አዲስ ኪዳን ውስጥ “የእግዚአብሔር ድምጽ” ተብሎ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።

ወንድም ብራንሐም “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው

መልእክቱን በሙሉ እመኑ። ከልባችሁ እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ካልሆነ ግን በፍጹም አትመኑት

የወንድም ብራንሐም ስብከት እውነት የሚሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልዩ ልዩ ጥቅሶች አማካኝነት ልንከተለው ስንችል ብቻ ነው።

ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤

ታላቁ መልአክ የወረደው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሊገልጥና ቤተክርስቲያኖችን ሊያወግዝ ነው። የወንድም ብራንሐም አገልግሎትም ይህንኑ ነው የሚመስለው።

ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ደምጹ ከመልአኩ ጋር በምንም አይያያዝም።

ይህ መጽሐፍ ቅዱስን እንድንከተል የሚያደርገን በውስጣችን የሚሰማን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ነው።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

 

 

ስለ አራተኛው ማሕተም ስለሚናገረው ስለዚህ ሁለተኛ ጥቅስ ብዙም አናውቅም ምክንያቱም በዋነኝነት የሚናገረው ስለ ታላቁ መከራ ነው።

የፈረሱ ሐመር ቀለም የተፈጠረው ነጭ፣ ቀይ፣ እና ጥቁር ተደባልቀው ጥምረት በመፍጠራቸው ምክንያት መሆኑን እናውቃለን።

የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ማነው? አናውቅም።

የሚገደሉት የምድር አንድ አራተኛ ሕዝብ እነማን ናቸው?

እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ብዙም ዝርዝር አናውቅም ምክንያቱም ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ብቻ ናቸው ስድስተኛውን ማሕተም ፈተው በታላቁ መከራ ውስጥ የሚፈጸሙ ነገሮችን ዝርዝር የሚገልጡት።

የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ሁሉንም ነገር የሚገልጥ አይደለም።

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

ሚስጥራቱ። “ሚስጥሩ ይኸው።” ሚስጥር ማለት አስቀድሞ ተሰውሮ የነበረ ነገር ግን አሁን ደግሞ በመለኮት ኃይል የተገለጠ ቃል ነው፤ መገለጡም ሲመጣ በውስጡ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይኖረዋል

ሰባቱ ማሕተሞች በውል በሚከፈቱበት ጊዜ በማሕተሞቹ ውስጥ የተካተቱ ዝርዝር ጉዳዮችን በሙሉ ታውቃላችሁ።

ማሕተሞቹ የሚፈቱት ሙሽራይቱ ሰማይ ውስጥ በምትሆንበት ዜ ነው፤ በዚያም ጊዜ በምድ ላይ ታላቁ መከራ ይኖራል።

በዚያ ጊዜ በጉ የታላቁን መከራ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ ለሙሽራይቱ ይገልጥላታል።

 

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው አታላይ ሽንገላው ሙሉ በሙሉ አልተገለጠም።

እስከ ዛሬ ድረስ በስውር ሆኖ በመካከላችን እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ሶስቱ መንፈሳዊ ኃይላት ወይም ፈረሶች ደግሞ ማለትም ነጩ፣ ቀዩ፣ እና ጥቁሩ ፈረሶች ተደባልቀው ይጣመሩና በአንድነት ሐመር ፈረስ ይሆናሉ። ለዚህ ነው በጣም ብዙ የሜሴጅ ቡድኖች ያሉት።

በሜሴጅ መልእክት ስም ዛሬ በጣም ብዙ ስሕተት አየተሰራጨ ነው፤ ደግሞም በጣም ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች እየተሸነገሉ ነው፤ ከዚህም የተነሳ ጥንት ሐዋርያት ለቤተክርስቲያን ያስረከቡዋትን ሙሉ እውነት ማግኘት አይችሉም።

ሰው ሊያስተውለው በማይችል መንገድ ቀስ በቀስ ወንድም ብራንሐም “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ከመሆን አልፎ “የእግዚአብሔር ድምጽ” ወደ መሆን ከፍ ተደርጓል።

አዲስ ኪዳን ውስጥ ግን “የእግዚአብሔርን ድምጽ” እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም።

ወንድም ብራንሐም ፍጹም አይሳሳትም ብሎ መናገር ትልቅ ስሕተት ነው።

61-0118 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፣ ዛሬ እስከ ዘላለምም ያው ነው

እኛ በእውቀታችን ውስን ስለሆንን ስሕተት እንሰራለን። እግዚአብሔር ግን ሁሉን አዋቂ እና ውሱንነት የሌለበት ስለሆነ ስሕተት ሊሰራ አይችልም

62-1007 የበሩ መክፈቻ

… አንዳንድ ወንድሞች እኔ እንደላኳቸው እያወሩ ሰዎች ሚስታቸውን ትተው ትክክለኛዋን አጥንታቸውን ፍለጋ መውጣት አለባቸው እያሉ ይሰብካሉ፤ በተጨማሪ ደግሞ እኔ ልሳሳት እንደማልችል አድርገው ያወራሉ። … ከዚህም የባሱ አንዳንድ አስደንጋጭ ነገሮችን ይናገራሉ

 

የወንድም ብራንሐም መልእክት አንዳችም ስሕተት የለበትም ብሎ መናገር መዋሸት ነው፤ ምክንያቱም በትምሕርቶቹ ውስጥ ግልጽ ስሕተቶች አሉ።

ለምሳሌ አሜሪካ በ1977 ትጠፋለች ብሎ ተንብዮ ነበር፤ ነገር ግን አልተፈጸመም።

60-1113 ኩነኔ በውክልና

አሜሪካ ተቃጥላ፣ አመድ በአመድ ሆና አይቻለሁ። ይህም የሚሆነው ወደ መጨረሻ አካባቢ ነው። (ከዚያም “ይህ ይፈጸማል” ብዬ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ጽፌ አስቀመጥኩ። እንግዲህ ልብ በሉ ጌታ … ይህ ነገር ጌታ ያሳየኝ ነው፤ ነገር ግን እኔ ይህ ከ1977 በፊት ይፈጸማል ብዬ እተነብያለው።)

“የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ” በሚለው ትምሕርቱ ውስጥ ወንድም ብራንሐም ታላቁ መከራ ለሰባት ዓመታት ይቆያል ብሎ ነበረ።

61-0806 የዳንኤል ሰባኛ ሱባኤ

እግዚአብሔር ሰባኛውን ሱባኤ ወይም ሰባቱን ዓመታት ሲያስጀምራቸው በዚያ ሰዓት ቤተክርስቲያን አትኖርም።

 

የእባቡ ዘር በሚለው ትምሕርት ውስጥ ፈረንሳይ ውስጥ የተካሄደው የኒቅያ ጉባኤ ብሎ ተናግሯል። የኒቅያ ጉባኤ ግን የተካሄደው ፈረንሳይ ውስጥ አልነበረም።

ደግሞም ስለ ተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን ዘመንም ተናግሯል። እንደዚያ የሚባል የቤተክርስቲያን ዘመን ግን አልነበረም።

ከዚያ በኋላ ደግሞ የሎዶቅያ ጉባቼ በ325 ዓ.ም በኋላ ነው የተደረገው ብሏል። ይህም ትክክል አይደለም። የሎዶቅያ ጉባኤ የተደረገው ከ363 – 364 ዓ.ም ነበር።

የሜሴጅ ፓስተሮች እጅግ ከመታለላቸው የተነሳ ነብይን ከስሕተት ማረም ሐጥያት ነው ይላሉ።

58-0928 የእባቡ ዘር

… እነርሱም ለብዙ ዓመታት በዚህ ቀጠሉ (ሶስት መቶ ሃያ አምስት ዓመታት)፤ በስተመጨረሻም ወደ ኒቅያ ፍራንስ ሄደው ታላቁን የኒቅያ ጉባኤ አደረጉ።

… እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን እስከ ተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን ዘመን ድረስ እስኪደርሱ ለአንድ ሺ አምስት መቶ ዓመታት በጨለማ ዘመናት ውስጥ አልፈዋል፤

… እስከ ሎዶቅያ ጉባኤ ድረስ ደግሞ ሶስት መቶ ሃያ ዓምስት ዓመት ነው።

እስቲ እነዚህን ስሕተቶች አንድ በአንድ እናርም።

የተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን ዘመን የሚባል ዘመን የለም፤ የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን ለማለት ፈልጎ ነው።

በ325 ዓ.ም የተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ነው እንጂ የሎዶቅያ ጉባኤ አይደለም።

ኒቅያ ታናሹ እስያ ውስጥ ከኮንስታንቲኖፕል (ከዛሬዋ ኢስታንቡል) አጠገብ የምትገኝ ከተማ ናት።

 

 

ከሰው ንግግር የተወሰደ ጥቅስን ከመቀበላችን በፊት እውነት መሆኑን ማጣራት አለብን። እንደ ገደል ማሚቱ የሰማነውን ሁሉ ሳይገባን መድገም የለብንም።

57-0825 ዕብራውያን ምዕራፍ ሁለት፤ 1

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነብይ ቃል እውነት መሆኑ ከመረጋገጡ በፊት መጀመሪያ ይመረመራል ደግሞም ይፈተናል። ዛሬ ግዴለሽ እንደሆንነው እነርሱ ግዴለሽ አልነበሩም።

ወንድም ብራንሐም የተናገረውን ነገር እንደ እውነት ከመቀበላችን በፊት መጀመሪያ መመርመር እና ማጣራት አለብን።

ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም፤ ሁልጊዜ ትክክል ነው የሚሉ የሜሴጅ ተከታዮች የሰሙዋቸው ሰዎች የወንድም ብራንሐምን ስሕተቶች ለቅመው አውጥተው በማሳየት አሳሳችና ውሸታም ነው ብለው እንዲወሩ እድል ሰጥተዋቸዋል።

ከነዚህ ሁለት ጽንፎች መካከል በጥንቃቄ የምናልፍበት ጥበብ ያስፈልገናል።

ወንድም ብራንሐም የተናገረው አብዛኛው እውነት ነው። በመንፈስ ያገኘው መገለጥ ነው። ነገር ግን በተሳሳተባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ መሳሳቱን አምነን ስሕተቶቹን ማረም አለብን። ይህም ከአቃቂር አውጭዎች እጅ ላይ መሳሪያቸውን ያስጥላል።

በተጨማሪም ወንድም ብራንሐምን ወደማይሳሳት መለኮትነት ከፍ ማድረግና እርሱ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ማለት ከሚፈልጉ ሰዎች አደገኛና ጽንፈኛ አመለካከቶች እንጠበቅ ዘንድ “ማሕበራዊ ርቀት” ይፈጥርልናል። በ2020 ዓ.ም የመጣው ኮሮና ቫይረስ እግዚአብሔር “ማሕበራዊ ርቀትን” ለእኛ ያስተማረበት መንገድ ነው፤ ይህም ርቀት አስተሳሰባቸውንን መቆጣጠር ከሚፈልጉ ፓስተሮች አመለካከት መራቅ እንድንችል ነው።

“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጻፈው። ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ በትንቢት መንፈስ ፓስተሮች ስድስት ጊዜ ተወግዘዋል። አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ ፓስተር የቤተክርስቲያን መሪ ተደርጎ አያውቅም።

በፈረስ ላይ ስለተቀመጠው የክርስቶስ ተቃዋሚና ስለ ሐይማኖታዊ ሽንገላው፣ ሰዎችን በመጨቆን ራሱን ከፍ ማድረግ ስለ መፈለጉ፤ ገንዘብን እጅግ ስለመውደዱ ሙሉውን ዝርዝር ልናውቅ አንችልም፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ በፈረሱ ላይ ሆኖ እንደሚንቀሳቀስና ብዙዎችም በሽንገላው እንደተሳሰቱ ማወቅ እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የሜሴጅ ትምሕርቶች ሁሉ መነሻቸው ይህ ሽንገላ ነው።

አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን ከፍቶ ከሆነ ሌላ ሰው ከእርሱ በፊት ገልጧቸው መሆን አለበት።

ነገር ግን ማንም ሰው በፊት አልገለጣቸውም። የቤተክርስቲያን ሰዎች ማሕተሞቹን በተሳሳተ መንገድ ተረድተዋል።

 

 

በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ እንደተጻፈው እግዚአብሔር በሰማይ ማሕተሞቹን ከመፍታቱ በፊት ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን መግለጥ አለበት።

ይህ የሚሆነው ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ እንደተጻፈው ሙሽራይቱ ተነጥቃ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ ነው።

ራዕይ 4፡1 ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።

ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ ሙሽራይቱ በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ናት።

ራዕይ 5፡7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።

9 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

63-0324 ስለ ማሕተሞቹ የተነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ጥያቄ

በራዕይ [ምዕራፍ 5] ከቁጥር 5 እስከ 9 ድረስ በጉ መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ የሚዘምሩት እናማን ናቸው … እነዚህ የተመሰገኑት ቅዱሳን ናቸውን?

መልስ

“እነርሱም አዲስ መዝሙር ዘመሩ” እዚያጋ አቆምኩ። አያችሁ? ነገር ግን ይህን ተመልከቱ፡- “እንዲህ እያሉ ነው የዘመሩት፡- ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከወገን ሁሉ ዋጅተኸናል።”

አዎን፤ እነርሱ ናቸው። በጣም ይደንቃል። አያችሁ?

የሙሽራይቱ አካል እንደመሆናችሁ እናንተም በሰርጉ ግብዣ ላይ ኢየሱስ ሰባቱን ማሕተሞች ሲፈታ በሰማይ ከእርሱ ጋር በሰማይ ትሆናለችሁ።

ወንድም ብራንሐም ከሰባቱ ማሕተሞች መካከል ስድስቱን ብቻ ነው የገለጣቸው።

67-0719 የመለከቶች በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው። ይህም የዓለማችን ሁሉ ታላቅ ሚስጥር ነው።

ጌታ መጥቷል ብለህ በእርግጠኝነት የምታስብ ከሆንክ ሙሉ በሙሉ ተታለሃል ማለት ነው።

በሕይወቱ በመጨረሻዋ ወር ድረስ ወንድም ብራንሐም የጌታን ምጻት ሲጠባበቅ ነበር።

65-1204 ንጥቀት

በዚህ ዓለም ታሪክ መጠናቀቂያ ዘመን ውስጥ እየኖርን እንደሆንን አምናለሁ። እንደውም የጌታ መምጫ ጊዜ እኛ ከምናስበው በላይ በጣም ቅርብ ነው ብዬ አምናለሁ።

ከመሞቱ አንድ ወር በፊት እንኳ የጌታ ምጻት ገና ወደፊት እንደሚሆን ሲጠባበቅ ነበር።

65-1127 መስማትን ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

አቤት እናንተ ሰዎች እና ሴቶች ሁሉ የጌታ ምጻት ምን ያህል ቅርብ መሆኑን ማየት ብትችሉ

ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም ሊፈታ አልቻለም፤ ምክንያቱም ያ አገልግሎት ለሁለቱ አይሁዳውያን ነብያት ለሙሴ እና ለኤልያስ ተጠብቋል።

63-0323 ስድስተኛው ማሕተም

አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምንኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ። አያችሁ?

ስለዚህ ከአራተኛው ማሕተም ሚስጥር ውስጥ ግማሽ ያህሉ በዝርዝር አይታወቅም ምክንያቱም አራተኛው ማሕተም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሚነሳውን የመጨረሻውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ እና እርሱ የሚገድላቸውን አንድ አራተኛ የዓለም ሕዝብ የሚመለከት ነው።

ሁለቱ ነብያት በታላቁ መከራ ውስጥ የተፈጥሮ ኡደትን ለማቋረጥ የሚያስችላቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ተጎናጽፈው ሲመጡ ስድስተኛውን ማሕተም ይፈታሉ። በታላቁ መከራ ውስጥ ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት ይችላሉ ምክንያቱም ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ ማሕተሞቹን ሲፈታቸው በምድር ላይ ታላቁ መከራ ይሆናል።

 

 

ሁለት ማሕተሞች እና የሌላ አንድ ማሕተም ግማሽ እስካሁን አልተፈቱም።

(የአራተኛው ማሕተም ግማሽ፣ የስድስተኛው ማሕተም ግማሽ፣ እና የሰባተኛው ማሕተም ግማሽ አልተፈቱም።)

ስለዚህ ከማሕተሞቹ መካከል አንዳቸውም አልተፈቱም።

ማሕተሞቹ በውል የሚፈቱበት ጊዜ የታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው።

ስለዚህ የ7ቱን ማሕተሞች መገለጥ የ7ቱ ማሕተሞች መፈታት ነው ብላችሁ ግራ አትጋቡ።

“መገለጥ” የጉዳዩ “ዋነኛ ፍሬ ሃሳብ መታየት” ሊባል ይችላል። ነገር ግን ሳይገለጡ የሚቀሩ የተወሰኑ ጥልቅ የሆኑ ዝርዝሮች አሉ።

 

ኢሳይያስ ድንግል እንደምትወልድ መገለጥ ሰጥቷል፤ ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን አልተናገረም።

የኢሳይያስ መገለጥ የሚከተሉትን ዝርዝሮች አላካተተም፡-

ቤተልሔም ውስጥ የአንድ ግለሰብ የከብቶች ማደሪያ፣ ግብር የሚሰበሰብበት ወቅት፣ የተወለደውን ሕጻን ለማየት የሚመጡ እረኞች። ዮሴፍን እና ማርያምን ከቤተልሔም ወደ ናዝሬት ተሸክማ ስለምትመጣዋ አህያ ምንም አልተጠቀሰም።

በተጨማሪ በሆሳዕና ዕለት ኢየሱስን ተሸክማ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረሰችው አህያ ናት። ኢየሱስ በፈረስ ላይ ተቀመጦ አያውቅም ምክንያቱም ፈረስ ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ በተጻፈው መሰረት የክርስቶስ ተቃዋሞ መንፈስ ምልክት ነው።

 

ማሕተሞቹ በውል የሚፈቱት ሰማይ ውስጥ ነው።

64-0719 የመለከቶች በዓል

እነዚያ ማሕተሞች በሙሉ ሲፈቱ የአሕብ ታሪክ በዚያው ይዘጋል፤ ዘመን ያበቃል፤ ቤተክርስቲያን ተጠርታ ትሄዳለች።

“ዘመን ያበቃል።”

ዘመን የሚያበቃው ለሙሽራይቱ ነው፤ በዚያ ጊዜ የሙሽራይቱ አካላት ሁሉ ሰውነታቸው ተለውጠው ዘላለማዊ የሆነው አካላቸውን ይለብሳሉ።

የማይሞተው አካላችሁን ስትለብሱ ሐጥያት፣ በሽታ፣ እና ሞት አይነካችሁም።

ጊዜ እንደ መበስበስ፣ ማርጀት እና መሞት የመሳሰሉ ለውጦችን ያስከትላል።

የማይሞተው አካላችሁን ስትለብሱ በደም ስራችሁ ውስጥ የሚዘዋወረው ደም ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ አታረጁም፤ አትታመሙም፤ አትሞቱም። ከጊዜ እና ጊዜ ከሚያመጣቸው ለውጦችና ጣጣዎች ሁሉ ነጻ ትሆናላችሁ።

የምትለብሱት የማይሞት አካል ሽልማታችሁ ዘውዳችሁ ነው።

የማይሞተው አካላችሁ እምብርት አይኖረውም (እምብርት በአካላችን ላይ የቀረ የአውሬው ምልክት ነው) ደምም አይኖረውም።

የጣታችሁን ጫፍ ጭምቅ አድርጉትና ቀይ ሲሆን ታያላችሁ። ከሙታን የተነሱትን ቅዱሳን ስታገኟቸው ግን ጣታቸው ላይ የቀለም ለውጥ አታዩባቸውም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥

56-0340 መንገድ መጥረግ

የዚህ ዓለም ኑሮ ሲሰለቻችሁና ምርር ሲላችሁ፤ እንዲሁም በፊታችሁ ከቀረበው ምግብ ወይም ከሚስታችሁና ከልጆቻችሁ በላይ የበለጠ የጌታን መገለጥ ስትወዱና ስትናፍቁ የዚያን ጊዜ ለእናንተ ተዘጋጅቶ የሚጠብቃችሁ አክሊል አለ፤ ይህንንም የወርቅ አክሊል አምጥተው ራሳችሁ ላይ ይጭኑላችኋል፤ አካላችሁም ሕመም የሌለበት አካል ይሆናል … በእግዚአብሔር ክብር የተሞላ ዘውድ ይጫንላችኋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና አለመጥፋት ውስጥ ዘውድ ትጭናላችሁ። የተዘጋጀላችሁ፤ ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር በዚያ ቀን ሊሰጣችሁ ያሰበው ይህ ነው። ያንን ቀን ለማየት ነው የምንናፍቀው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የምናመልጥበት መንገድ አዘጋጅቶልናል።

 

ሰባተኛው ማሕተም የሚፈታው መልአኩ ወደ ምድር ከወረደ በኋላ ብቻ ነው።

61-0730 ገብርኤል ለዳንኤል የሰጠው መመሪያ

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የመጨረሻው ማሕተም ሲፈታ መልአኩ አንድ እግሩን ምድር ላይ አንድ እግሩን ደግሞ ባሕር ላይ አድርጎ ይቆማል፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ይዘረጋል፤ ከራሱ በላይ ቀስተ ደመና ይጋርደዋል፤ እርሱም ለዘላለም በሚኖረው ምሎ ዘመን ከዚያ ወዲያ እንዳበቃ ያውጃል።

የመጨረሻው ማለትም 7ኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። አልተከፈተም። እስካሁን ገና አልተገለጠም።

ስለዚህ መልአኩ ገና አልወረደም ምክንያቱም የሚወርደው ሙታንን ለማስነሳት ነው።

64-0119 ሻሎም

ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

63-1110 አሁን በወህኒ የሚኖሩ ነፍሳት

በሰባተኛው ማሕተም ተመልሶ ወደ ምድር ይመጣል።

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ራዕይ 10ኛው ምዕራፍ ማለቴ ነው፤ ቁጥር ደግሞ ከ1 እስከ 7 ድረስ። ዘመን ያበቃል። መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከእንግዲህ በኋላ አይዘገይም” ይህ ታላቅ ነገር በሚፈጸምበት ቀን ነው ይህ ሁሉ የሚሆነው። በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መጨረሻ ላይ ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የታላቁ መልአክ መውረድ ገና ወደፊት የሚፈጸም ነገር ነው።

ጊዜ የሚያልቀው ወደ ዘላለማዊነት ውስጥ ስትገቡ ነው።

ወደ ዘላለማዊነት መግባት የምትችሉት ውስጡ ደም የሌለውና እምብርትም የሌለው አዲሱ የከበረው አካላቸሁ ውስጥ ስትሆኑ ብቻ ነው።

 

በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከሰባቱ የቤተክስቲያን ዘመናት ውስጥ ሰባት ማሕተሞች ይወጣሉ።

ሰባተኛው ማሕተም የሚገለጠው በሰባቱ ነጎድጓዶች አማካኝነት ነው። ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሰባት ድምጻቸውን በሰባተኛው ማሕተም በሚፈታበት ወቅት ነው የሚያሰሙት

 

 

ኢየሱስ በመጀመሪያ ምጻቱ ወቅት በትንሳኤው እና ወደ ሰማይ ባረገበት ቀናት መካከል 40 ቀናት አልፈዋል።

የሐዋርያት ሥራ 1፡2 ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤

3 ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።

የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት በሚነሱበት ቀን እና ወደ ሰማይ ተነጥቀው በሚሄዱባቸው ቀን መካከል በተመሳሳይ የአርባ ቀናት ክፍተት ይኖራል።

 

 

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን በሚነሱበት ቀን እና ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል በምትነጠቅበት ቀን መካከል ባሉት 40 ቀናት ውስጥ ነው።

መከር ማለት የደረሱት የስንዴ ፍሬዎች ከአገዳቸው ላይ ሲታጨዱ ነው።

ስለዚህ ሞተው የነበሩት ቅዱሳን ከመቃብራቸው ላይ ታጭደው ይነሳሉ፤ ቀጥሎም ሙሉ የሆችዋ ሙሽራ ከምድር ላይ ታጭዳ ወደ ሰማይ ትወሰዳለች።

ይህ የመከር ዝናብ ወቅት ነው፤ በሌላው አጠራሩ ኋለኛው ዝናብ ይባላል።

ስብከቶቹን በድምጽ እየቀረጸ ያስቀመጠ ጊዜ የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ፊተኛውን ዝናብ ወይም የትምሕርትን ዝናብ አስጀምሯል።

 

 

ፊተኛው ዝናብ ወይም የትምሕርት ዝናብ እስከ ጌታ ምጻት ድረስ ይቀጥላል (የጌታ ምጻት ብዙውን ጊዜ ንጥቀት ይባላል)፤ ሙሽራይቱም በሰባቱ ነጎድጓዶች ዘመን ውስጥ መማሯን ትቀጥላለች።

ይህ ጊዜ በትምሕርት ዝናብ እና በመከር ዝናብ መካከል መደራረብ የሚሆንበት ጊዜ ነው።

ስለዚህ በምንለወጥበትና ወደ አዲሱ አካላችን ውስጥ በምንገባበት ሰዓት ፊተኛው የትምሕርት ዝናብ በሰባቱ ነጎድጓዶች ዘመን ይበልጥ ጨምሮ ዶፍ ሆኖ ነው የሚመጣ

ኢዮኤል 2፡23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።

ኋለኛው (የመከሩ) ዝናብ ከፊተኛው (ከትምሕርቱ) ዝናብ ጋር ለአንድ ወር ማለትም ለሰላሳ ቀናት ተደራርቦ ይመጣል።

የ30 ቀኑ የዝናቦች መደራረብ ከትንሳኤ እና ከንጥቀት መካከል ባሉት 40 ቀናት ውስጥ ነው የሚከናወነው።

 

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ይኸው አሁን ስድስተኛው ማሕተም ተከፍቶልናል፤ አሁን እናየዋለን፤ ሰባተኛው ማሕተም ግን ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ለሕዝብ ሊከፈት እንደማይችል እናውቃለን።

የሜሴጅ ፓስተሮች ሰባተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ እናውቃለን በማለት ሕዝቡን ያሞኛሉ።

ሰባተኛው ማሕተም የተሰወረው ከሕዝቡ ብቻ ነው ይላሉ፤ ሕዝቡ ማለታቸው የሜሴጅ ተከታይ ያልሁኑ ሰዎችን ነው፤ እነርሱን ሙሽራይቱ አይደሉም ይሏቸዋል።

ነገር ግን ተሳስተዋል፤ ምክንያቱም ቀጥሎ የምንመለከተው ጥቅስ ሰባተኛው ማሕተም ለእኛ ማለትም ለሙሽራይቱ ገና እንዳልተገለጠልን ያስረዳል።

63-1110 አሁን በወህኒ የሚኖሩ ነፍሳት

በጉ መጽሐፉን የወሰደው ልክ ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ ጊዜው ሲቀርብ ነው።

አስታውሱ ሰባተኛውን ማሕተም ከእኛ ሰውሮታል። አልገለጠልንም።

መልአኩ ቀን በቀን የማሕተሞቹን ሚስጥር እየገለጠ ቆሞ ነበር ነገር ግን ያኛውን ትቶ አለፈው። እንዲህ አለ፡- “በሰማይ ዝምታ ሆነ።” ማንም አላወቀም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።

የሰባተኛውን ማሕተም ሚስጥር አውቃለሁ የሚሉ ሁሉ በነጭ ፈረስ ላይ ለሚቀመጠው ለክርስቶስ ተቃዋሚ መልእክተኛ እየሆኑለት ነው።

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

የዚያ ማሕትም [የሰባተኛው] አንዱ ሚስጥር፤ ያልተገለጠበት ምክንያት፤ ሰባት ነጎድጓዶች ናቸው ድምጻቸውን ያሰሙት፤ ምንም እንከን አይወጣላቸውም፤ ምክንያቱም ማንም ስለ ነጎድጓዶቹ ቃል አያውቅም፤ ምክንያቱም ምንም አልተጻፈም።

አሁን ተመልከቱ፤ በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መከፈት ሰዓት የሆነውን አስተውላችሁ እንደሆን ሶስት ድርብ ሚስጥር ነው። ይህ እኔ ያለኝ … ይናገራል፤ ደግሞም ተናግሯል፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥረ ነው። በሰማይ ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጡታል።

እርሱም ልክ በክርስቶስ ምጻት ጊዜ ይሆናል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም ብሎ ተናግሯል።

7ቱ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ራሳቸው ናቸው የ7ኛውን ማሕተም ሚስጥር የሚገልጡት።

ሁለት ወገኖች ብቻ ማለትም ሙሽራይቱ እና ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ብቻ ናቸው ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ የሚገነዘቡ ወይም ምላሽ መስጠት የሚችሉት።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም። አሆን፤ እውነት ነው። እኔም ደግሞ በእነዚያ ሰባት ነጎድጓዶች አማካኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሙሽራይቱ እንዴት እንደምትዘጋጅ እና ለመነጠቅ የሚያስፈልጋትን እምነት እንዴት እንደምትቀበል ይገለጥላታል። ምክንያቱም አሁን ባለን እምነት መነጠቅ አንችልም። አንድ እርምጃ መጨመር ወደፊት መግፋት አለብን፤ ለመለኮታዊ ፈውስ እንኳ የሚበቃ እምነት የለንም።

ከመቅጽፈት ተለውጠን ከዚህ ምድር ላይ ተነጥቀን የምንሄበት በቂ እምነት ሊኖረን ይገባል።

አዲስ አካላ ከመልበሳችሁ በፊት መነጠቅና ጌታን በአየር ላይ መቀበል አትችሉም።

አዲስ የማይሞት አካል ማግኘት በዚህ ዘመን ውስጥ ከምታዩዋቸው ተዓምራት ሁሉ የሚበልጥ ተዓምር ነው የሚሆነው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን መልእክተ የመረዳታችሁ ማረጋገጫው አዲሱን አካላችሁን መቀበላችሁ ነው።

የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ተነጥቃችሁ ጌታን በአየር ላይ መቀበል የምትችሉት።

ከዚያ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ለሙሴ እና ለኤልያስ ታላቅ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይሰጧቸዋል።

63-0323 አራተኛው ማሕተም

ትናንትና ማታ ትልቅ ሰይፉን ይዞ ለመግደል ሲመጣ አግኝተነው ነበር። ነገር ግን እርሱ እራሱ በሰይፍ እንደሚገደል አይተናል፤ ይህም የቃሉ ሰይፍ ነው። የእግዚአብሔር ቃል፤ በሁለት ወገን የተሳለው ሰይፍ ይገድለዋል፤ ያጋድመዋል። ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን መስማት የሚችል ሕዝብ ሲመጣ እስኪያሰሙ ድረስ ጠብቁ። የእግዚአብሔር ቃል ስለታም ሰይፍ ነው፤ ይቆርጣል። እነርሱም ሰማያትን መዝጋት ይችላሉ፤ የፈለጉትን መዝጋር የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን

እርሱም ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ይገደላል፤ ይህም ቃል በሁለት ወገን ከተሳለ ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው። እነርሱ ከፈለጉ መቶ ቢሊዮን ዝንቦችን መጥራት ይችላሉ። አሜን። እነርሱ የሚናገሩት ነገር ሁሉ ይፈጸማል፤ ምክንያቱም ቃላቸው ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ታላቁ መከራ ሲጀምር ሰባቱ መለከቶች ብዙ አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ያስገድዷቸዋል።

በዚያው ጊዜ ደግሞ ዓለም የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ለመቀበል እምቢ በማለቷ ሰባቱ ጽዋዎች በምድር ላይ ፍርድን ያፈስሳሉ።

 

 

ሌላም ማጤን ያለብን ጉዳይ አለ።

ደግሞም ሌላ ብቸኛ ነጎድጓድ አለ፤ ይህም ነጎድጓድ ታላቁን ድምጽ ያስከትላል፤ ታላቁም ድምጽ ዋነኛውን ድምጽ፤ ዋነኛውም ድምጽ ደግሞ የእግዚአብሔርን መለከት አስከትሎ ይመጣል።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

 

የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ አንድ ብቸኛ ነጎድጓድ ድምጹን ያሰማል።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

 

 

ከ1947 – 1965 የሰባተኛው መልአክ ዘመን ነበር።

ከ1966 ዓ.ም ወዲህ ያሉት ዓመታት ሰባተኛው መልአክ ድምጹ የሚሰማበት ዘመን ናቸው፤ በዚህም ዘመን ውስጥ እኛ በድምጽ ተቀርጾ የተቀመጠውን መልእክቱን እንዲሁም የጻፋቸውን መልእክቶች እያዳመጥንና እያነበብን የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ለመረዳት እንጠቀምባቸዋለን።

ከትንሳኤ በኋላ ሰባቱ ነጎድጓዶች ያልተጻፉትን ሚስጥራት ይገልጣሉ (ሰባተኛው ማሕተም፣ ሰባት ነጎድጓዶች፣ አካላችንን እንዴት እንደምንለውጥ፣ እና አዲሱ የኢየሱስ ስም)።

ከንጥቀት በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወንጌል ተመልሶ ወደ አይሁዶች ይሄዳል። ሰባት መለከቶች አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ያስገድዷቸዋል።

65-1127 መስማትን ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ወንድም ብራንሐም ይህንን የተናገረው ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ነው።

በዚያ ጊዜ እንኳ የመልእክቱን “ድምጽ” ይጠባበቅ ነበር።

65-1204 ንጥቀት

ስለዚህ ድምጹ ማለትም መልእክቱ ሙሽራይቱን ይጠራታል።

… ጩኸት፤ የምን ጩኸት? ይህ ጩኸት ወይም ታላቅ ድምጽ ሙሽራይቱ ይዞ የሚመጣ ሕያው የሕይወት እንጀራ ወይም መልእክት ነው።

“ደምጹ” የተባለው እርሱ እውነትን ሲሰብክ አይደለም። “ድምጹ” ማለት የሙሽራይቱ አካላት በስተመጨረሻ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለራሳቸው መረዳት ሲችሉ ነው።

 

 

መልእክቱ ወይም “ድምጹ” አሁን እየተፈጸመ ያለ ሂደት ወደ መጠናቀቂያው መድረሱ ነው፤ ይህም የሚቀጥለው የሙሽራይቱ አካላት በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆንን እስኪለምዱ ድረስ ነው።

መልእክቱ ዓላማውን የሚፈጽመው የዚያን ጊዜ ብቻ ነው።

መልእክቱ ሁለት ክፍሎች አሉት።

መጀመሪያ ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ገልጦ አስተምሯል፤ ይህንንም ያደረገው እንዴት አድርገን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንደምናያይዝ ሊያሳየን ነው።

የመልእክቱ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ የሙሽራይቱ አካላት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጠቀም እውነትን ለራሳቸው ማረጋገጥ እንዲችሉ ማድረግ ነው።

64-0719 የመለከት በዓል

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ በተጻፈው መሰረት ሚስጥሩ ሁሉ ሲፈጸም የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር በሙሉ ለሙሽራይቱ ይገለጥላታል። ልክ አይደል ወይ? ራዕይ 10።

ሙሽራይቱ ሙሉ የሆነ የመጽፍ ቅዱስ መረዳት ሊኖራት ይገባል።

65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እርሱ ራሱ በዚያው ድምጹ ከፍ አድርጎ በመጮህ አላዛርን ከሞት ቀሰቀሰው። በታላቅ ድምጽ “አላዛር ሆይ ውጣ” ብሎ ጮኸ። አያችሁ? ስለዚህ ድምጹ እንቅልፍ የተኛችውን ሙሽራ፣ በሞት ውስጥ የተኛችዋን ሙሽራ ይቀሰቅሳታል

በድምጹ ሙታንን የሚቀሰቅሰው መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ክርስቶስ ነው።

64-0119 ሻሎም

ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የመላእክት አለቃ ሙታንን ሲያስነሳ እናያለን።

65-1204 ንጥቀት

ጩኸት፣ ከዚያም ድምጽ፣ ከዚያም መለከት።

ጩኸት፡- ሕዝቡን የሚያዘጋጅ መልእክተኛ።

ሁለተኛው ደግሞ የትንሳኤ ድምጽ ና፡ ይህም በዮሐንስ ወንጌል 11፡38-44 ውስጥ የተሰማው አላዛርን ጠርቶ ከመቃብር ያወጣው ያ ድምጽ እራሱ ነው።

ልብ በሉ። “ድምጹ” ማለት መልእክተኛው የመልእክቱን እውነት ሲሰማ አይደለም።

ድምጹ ስራው ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።

መጀመሪያ ሙሽራይቱ መጽሐፍ ቅዱስን በመረዳት ዝግጁ እንድርሆን ያደርጋታል፤ ቀጥሎ ደግሞ የሙታን ትንሳኤ ይፈጸማል።

“ድምጹ” ማለት ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን በመግለጥ እውነትን ሲሰብክ አይደለም።

“ድምጹ” ማለት የሙሽራይቱ አካላት በየግላቸው እውነትን ለራሳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ሲችሉ ነው።

ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ለእነርሱ የተከፈተ መጽሐፍ ይሆንላቸዋል፤ ከዚህም የተነሳ የሚያነብቡትን መረዳት ይችላሉ።

የመላእክት አለቃ ሲወርድ በእጁ የተከፈተ መጽሐፍ የሚይዘው ለዚህ ነው።

የሙሽራይቱ አካላት መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው መረዳት ለምደዋል። ይህንን የሚያሳየን ምሳሌያዊ ምልክት ዮሐንስ መጽሐፉን መብላት መቻሉ ነው።

 

 

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

መልአኩ የሚወርደው መጽሐፉን ለመክፈትና ማሕተሞቹን ለመግለጥ አይደለም።

መልአኩ የሚወርደው መጽሐፉ ስለተከፈተ ነው

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ሌሎቹ መላእክት መልእክተኞች ናቸው፤ ማለትም የምድር ሰዎች ናቸው። ይህኛው መልአክ ግን… እነዚ “በሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ላለው መልአክ፣” “በኤፌሶን ወዳለው መልአክ” ተብሎ የተጻፈላቸው ምድር ላይ የሚኖሩ መልእክተኞች ናቸው፤ ሰዎች ናቸው፤ መልእክተኞች ወይም ወደ ቤተክርስቲያን የተላኩ ነብያት ናቸው።

ይህኛው ግን ይህ ከምድር አልመጣም።

እርሱ የመጣው ከሰማይ ነው ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመዋል

ሚስጥሩም በተፈጸመ ጊዜ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ዘመን አይኖርም” በዚያን ጊዜም ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ። እንደው ለመነጠቅ ወደሚያበቃው እምነት ውስጥ እንዴት አድርገን እንደምንገባ የሚያሳውቀን ነገር ቢሆንስ? ነውን? እንሮጣለንን፤

ከግድግዳዎቹ በላይ እንዘላለንን?

አንድ ነገር ሊሆንና እነዚህ ያረጁ የተበላሹ ስጋዎቻችን ሊለወጡ ጊዜው ቀርቦ ይሆን?

ሰባቱ ነጎድጓዶች ለመነጠቅ እና አካላችንን ለመለወጥ ከሚያስፈልገን እምነት ጋር የተያያዙ ናቸው።

“ግድግዳው” በእኛ እና በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል መካከል ያለው ግድግዳ ነው።

ልዕለ ተፈጥሮአዊው የዘላለማዊነት አካል ነው፤ እኛ ግን የጊዜ እስረኞች ነን።

“የጊዜ ግድግዳ” ወይም “የዘመን ግድግዳ” የወደፊቱን ማየት እንዳንችል ይከለክለናል።

ባለመሞት ሞትን እንድናሸንፍ እና ከዚያም ዘላለማዊውን ማየት እና ወደ ዘላለማዊው መግባት ከሚከለክለን ከጊዜ ግድግዳ ላይ ዘለን በማለፍ ከፍጥረታዊው ወደ ዘላለማዊው እንሸጋገር ዘንድ የሰባቱ ነጎድጓዶች ድጋፍ ያስፈልገናል።

63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያቀርበውም

ኦ የዘላለም ሕይወት የሚቀበሉ ሰዎች ምንኛ አስደናቂ እንደሚሆኑ በቁጥር ቢያንሱም እንኳ! እንዲህ ይላል፡- “በሰራዊት መካከል ይሮጣሉ፤ ቅጥሩንም ይዘላሉ።”

አዎ፤ የሞት “ሰራዊት” ሊይዛቸው አይችልም፤ በመካከሉ ሮጣ ታልፋለች።

በፍጥረታዊው እና በልዕለ ተፈጥሮአዊው መካከል ያለውን “ግድግዳ” ዘላው ታልፈዋለች፤ ከዚያም ወደዚያ ታላቅ ዘላለማዊነት ወደ እግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ትገባለች። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ እናመሰግንሃለን። ጊዜው በጣም እየቀረበ መሆኑን እናውቃለን።

2ኛ ሳሙኤል 22፡29 አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።

በስተመጨረሻ ሊገድሉን ከሚፈልጉ የአጋንንት ሰራዊት መካከል በሩጫ ማለፍ እንችል ዘንድ ዓይናችን እንዲበራ ከመጽፍ ቅዱስ ብዙ የምንማረው ነገር አለ። ከዚያ በኋላ አዲሱን የማይሞተውን አካላችንን ማግኘት እንችላለን። ቀጥሎ በአዲሱ አካላችን አማካኝነት ከጊዜ ግድግዳ በላይ እንዘልና ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ተነጥቀን ወደ ዘላለማዊነት እንገባለን

2ኛ ሳሙኤል 22፡30 በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።

 

በቤተክርስቲያን ውስጥ ተመችቶን ቸልተኛ ሆነን መቀጠል እንደሌለብንና መለወጥ እንደሚያስፈልገን ማወቅ አለብን።

ወደፊት ድምጹን የሚያሰማ አንድ ብቸኛ ነጎድጓድ አለ፤ ይህም ነጎድጓድ ለሙሽራይቱ የመጀመሪያውን የማንቂያ ደወል ያሰማል።

63-0319 ሁለተኛው ማሕተም

እግዚአብሔር ሆይ አለማመናችንን እርዳ። ጌታ ሆይ አስወግድልን። የምንነጠቅበትን ጸጋ መቀበል እንፈልጋለን። ያ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ እና ቤተክርስቲያንም በምትነጠቅበት ጊዜ ልንቀበለው ዝግጁ መሆን እንፈልጋለን ጌታ ሆይ።

7ቱ ነጎድጓዶች አዲሱን አካላችንን የምናገኝበትን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይሰጡናል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰማይ ተነጥቀን የምንሄድበትን እምነት ይሰጡናል፤ ይህንንም ተከትሎ የእግዚአብሔር መለከት ይመጣል።

 

7ቱ ነጎድጓዶች በተጨማሪ ለሙሴ እና ለኤልያስ የተፈጥሮ ኡደትን የሚያቋርጡበት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይሰጡዋቸዋል።

ከዚያ በኋላ ከታላቁ መከራ ውስጥ ደግሞ7ቱ መለከቶች ይወጣሉ፤ መለከቶቹም ግትር የሆኑትን አይሁዶች ወደ እስራኤል ይመልሱዋቸዋል፤ ቀጥሎ ዓለምን ለመቅጣት 7ቱ ጽዋዎች ይመጣሉ።

የነጎድጓዶቹ ሚስጥር በ1963 ዓ.ም ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና በሰሩት በ7ቱ መላእክት እጅ ነው ያለው።

63-0317 እግዚአብሔር ራሱን ዝቅ አድርጎ ሲሰውርና በዚሁ ትሕትና ውስጥ ራሱን ሲገልጥ

እነዚህን ሰባት ነጎድጓዶች የያዙ ሰባቱ መላእክት በጊዜያቸው የያዙትን እንደሚሰጡ አምናለሁ።

ደመናው የተፈጠረው በ7ቱ መላእክት ነው፤ ነገር ግን የደመናው መታየት የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መውረድ አይደለም።

64-0119 ሻሎም

ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ሙታን አልተነሱም።

ስለዚህ ደመናው ከታየበት ቀን አንድ ዓመት አልፎ የተነገረው ይህ ንግግር ወንድም ብራንሐም ብርቱው መልአክ ገና ወደፊት ሊመጣ እንዳለ ይጠባበቅ እንደነበር ያመለክታል።

ደመናው የጌታ ምጻት አይደለም።

ጌታ ምድረ በዳ ውስጥ አይመጣም።

ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 የታየው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ሰሜን ነበር የተገለጠው፤ እየታየ የቆየውም ደግሞ ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ከምድር በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ለ28 ደቂቃ ነበር።

ሰባቱ መላእክት ደመናው ከታየ ከ8 ቀናት በኋላ ሳንሴት ፒክ አካባቢ ወርደው ወደ ወንድም ብራንሐም መጡ፤ ይህችም ቦታ ከፍላግስታፍ 200 ማይልስ ርቀት ላይ የምትገኝ ናት። በዚያ ቀን መላእክቱ ሲወርዱም ሆነ ወደ ሰማይ ሲወጡ ምንም ደመና አልተፈጠረም።

ሳንሴት ፒክ በታላቁ የሶኖራን በረሃ ውስጥ ነው የምትገኘው።

 

 

ክርስቶስ ደግሞ ወደ ምድረበዳ አይመጣም።

ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና መታየቱ ራሱን የቻለ ክስተት ተደርጎ አይቆጠርም (ምክንያቱም ደመናው በታየበት ሰዓት ፍላግስታፍ ውስጥ ከደመናው በታች ከነበሩ ሰዎች መካከል ምንነቱን ማስተዋል የሚችል ሰው አልነበረም፤ ወንድም ብራንሐም እንኳ ሶስት ወር እስኪያልፍ ድረስ ስለ ደመናው አልሰማም ነበር)፤ ነገር ግን ደመናው በሰማይ ላይ የተገለጠ የሰው ልጅ ምልክት ነበረ።

ይህም ምልክት የሰባቱ ማሕተሞች ሚስጥር ሊገለጥ ጊዜው ቅርብ መሆኑን የሚጠቁም ምልክት ነው፤ እነዚህ ሚስጥራት መገለጣቸውም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር መረዳት እንችል ዘንድ ይረዳናል።

መጽሐፍ ቅዱስ በአስደናቂ ሚስጥራት የተሞላ መጽሐፍ ነው፤ ነገር ግን እኛ ሚስጥራቱን ለመረዳት ያግዘን ዘንድ የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች ለመጠቀም ከመስነፋችን የተነሳ ሚስጥራቱን ቸል እንላለን።

ኤልሳዕ 42 ልጆች ሲሰድቡት የረገማቸው ለምንድነው?

ዮፍታሄ ልትቀበለው ከቤቱ ቀድማ የወጣችዋን ልጁን ለምንድነው የገደላት?

ማቴዎስ እና ማርቆስ መቃብሩ አካባቢ አንድ መልአክ ተገኘ ብለው ሲጽፉ ሉቃስ እና ዮሐንስ ለምንድነው ሁለት መላእክት ብለው የጻፉት?

ኢየሱስ ወደ ሰማይ መሄዱን ማቴዎስ ያልጻፈው ለምንድነው?

ማቴዎስ ውስጥ ስናነብ ማርያም የኢየሱስን እግር ያዘች ይላል፤ ዮሐንስ ውስጥ ግን ኢየሱስ አትንኪኝ ይላታል። ለምን?

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ እና የመሳሰሉ ብዙ ቀላል ሚስጥራት አሉ፤ ነገር ግን ብዙ ሰዎች እነዚህን ሚስጥራት መረዳት ስለማይችሉ ቸል ይሉዋቸዋል።

ብርቱው መልአክ ግን የተከፈተ መጽሐፍ ይዞ ነው የሚወርደው።

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ።

የተከፈተች “ታናሽ” መጽሐፍ።

በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ፍጹሙን እውነት የሚያምኑት።

ነገር ሁሉ ከዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ከምታገኙት ቅዱስ አምላክ ጋር የተያያዘ ነው።

ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የምትነቅፉ ከሆነ ኢየሱስን ትነቅፋላችሁ ማለት ነው። ኢየሱስን መንቀፍ ደግሞ ትልቅ ስንፍና ነው።

ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።

ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።

ሉቃስ 18፡8 ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ሙታንን ለማስነሳት ነው።

ሙታን ከመነሳታቸው በፊት ግን ሙሽራይቱ መጽሐፉን ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መቻል አለባት።

የወንድም ብራንሐም መልዕክት ዋነኛ ዓላማው ይህ ነው።

የሚያሳዝነው ነገር ለብዙዎቹ የሜሴጅ ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስ የተዘጋ መጽሐፍ ሆኖ ቀርቷል፤ ብዙውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መረዳት አልቻሉም።

እንደውም የሜሴጅ ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ብዙዎቹን ሚስጥራት እና እንቆቅልሾች መረዳት ስላለመቻላቸው እንኳ ግድ የላቸውም።

ምንም እውነተኛ ፍላጎት የላቸውም።

በመጨረሻው ዘመን ከባድ እንቅልፍ እንደተኙት እንደ አስሩ ቆነጃጅት ራሳቸውን ያታለሉበት ድንዛዜ እንዲለቃቸው አይፈልጉም።

በሜሴጅ ቡድኖች እና በቤተክርስቲያኖች መካከል የተሰራጨ መንፈሳዊ ቫይረስ መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ ይባላል።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

የመጀመሪያውን ማሕተም ይፈታውና ሰባተኛውን መልአክ ይገልጠዋል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሚስጥራት ወደ ፍጻሜ ማምጣት ብቻ ነው የሰባተኛው መልአክ አገልግሎት

65-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። ዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል። እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የምድር መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ይታያል። ”

ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች ሊገልጥ መዘጋጀቱን የሚጠቁም ምልክት ነው። ሰባተኛው ማሕተም ግን ከጌታ ዳግም ምጻት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ተገልጧል።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

“ከዚያች ወራት መከራ” የተባለው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በተደረገው ሆሎኮስት በተባለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ውስጥ የተገደሉትን ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች በተመለከተ ነው። በ1945 ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ እነዚያ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ስልታቸውን ቀይረው በ1948 የተመሰረተው የዓለም ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት ውስጥ ገቡ።

የአይሁዶች መጨፍጨፍ የታላቁን መከራ የሚገልጠው የስድስተኛው ማሕተም ጨረፍታ እይታ ነው።

ሆሎኮስት በተጨማሪ የስድስተኛው መለከትም ጨረፍታ እይታ ነው፤ ስድስተኛው መለከት በፍጥረታዊ እስራኤል ሕዝብ ላይ እንደ ሒትለር እና እስታሊን በመሳሰሉ አምባ ገነን መሪዎች አማካኝነት የአጋንንት አሰራር እንደሚለቀቅ አመልካች ነው።

64-0719M የመለከቶች በዓል

በሒትለር ዘመን ያ የስደት መለከት ድምጹ እንዴት ከፍ ብሎ እንደተሰማ አይታያችሁም? አይሁዶችም የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘመን በአንድ ሥፍራ መሰብሰብ ግድ ሆነባቸው።

በስድስተኛው ማሕተም ጊዜ ምን እንደሚፈጠር አስተውሉ። እነዚህ አጋንንት በአይሁዶች ላይ ተለቀቁ፤ በዚህም የአይሁዶች ስደት ተጀመረ። የሁለት መቶ ሺ ዓመታት ያህል ዕድሜ ያስቆጠሩ አጋንንት በእስታሊን፣ በሒትለር አማካኝነት ተለቅቀው አይሁዶችን አሳደዱ። “ይህ ግን የሮማ መንግስት አይደለም” ልትሉ ትችላላችሁ። መንፈሱ ግን አንድ ነው። እነዚህ መንግስታት በጥንቱ የሮማ መንግስት ዘመን በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸሙ ክፋቶችን ነው በድጋሚ የፈጸሙት። ስለዚህ ፍጥረታዊቷን እስራኤል ከመንፈሳዊቷ ቤተክርስቲያን ለይተን እንመልከት። በአይሁዶች ላይ ተለቀቁ።

ስለዚህ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመን የነበሩ ጨካኝ መሪዎች በጥንታዊቷ ሮም ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን ነፍሰ ገዳይ መናፍስት ፈተው ለቀቁዋቸው፤ እነዚህ መናፍስት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖችን ይገድሉ ነበር። ከሐዋርያት አብዛኞቹ ተገድለዋል።

ባርቤሪያውያን የሮማ መንግስትን ባፈራረሱ ጊዜ እነዚህ ጨካኝ መናፍስት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሾልከው ገቡ፤ ከዚያም በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖችን ገደሉ።

በካቶሊክ እና በፕሮቴስታንቶች መካከል የነበረው ሐይማኖታዊ ጦርነት በ1648 የቆመው ሁለቱም ወገኖች ሲበዛ ከመዳከማቸው የተነሳ ነበር። ጆን ዌስሊ ከፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ርቆ አገልግሎቱ ላይ ብቻ ትኩረት አደረገ፤ ስለዚህ ቅድስና እና የወንድማማች መዋደድ ላይ ያተኮረው አገልግሎቱ እስከ 1750 ድረስ ተጽእኖ እያደረገ ቀጠለ። ይህንንም ተከትሎ ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን መጣ። ከዚህ ተጽእኖ የተነሳ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቃዋሚዎቿን መግደል ለማቆም ተገደደች። ክርስቲያናዊ መርሆን እነዚህን ነፍሰ ገዳይ መናፍስት እንዳይሰሩ ተቆጣጠሩዋቸው።

በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ የተፈጸመው የሰዎች እልቂት ዴሞክራሲያዊ መንግስታት ጠላታቸውን ለመቋቋም ሲሉ አምባ ገነን እንዲሆኑና በጦርነት ወቅት በነበረው ኢኮኖሚያቸው ውስጥ የንግድ እና የምርት እንቅስቃሴዎችን ሁሉ እንዲቆጣጠሩ አስገደዳቸው። ጠላትን ለማስወገድ ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ በሃገራቸው ላይ ያላቸውን ቁጥጥር አጠናክረው የራሳቸውን ሕዝብ በጭቆና መግዛት ጀመሩ።

በነዚህ የጭካኔ እና የእልቂት ዘመናት ውስጥ ተዋጊዎች ሁሉ “ልባቸውም አእምሮዋቸውም” ጠፋ። ያለማቋረጥ የተፈጸመው ጭካኔ ሰብዓዊነት እንዲጠፋ ከማድረጉም በላይ ከጦርነቱ በኋላ ምሕረት የማያውቁ ፈላጭ ቆራጭ አምባ ገነን መሪዎች እንዲነሱ ምክንያት ሆነ። ይህ መንፈስ ራሺያ ውስጥ በሌኒን እና በእስታሊን፣ ኢጣልያ ውስጥ በሙሶሊኒ፤ እንዲሁም በስተመጨረሻ ጀርመኒ ውስጥ በሒትለር ገብቶ ይሰራ ነበር።

እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ አጋንንትን በአይሁዶች ላይ ለቀቁባቸው፤ በአይሁዶችም ላይ የተፈጸመው ግፍ የታላቁ መከራ ጨረፍታ እይታ ነው።

ራዕይ 9፡14 መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ፦ በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።

16 የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፥ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።

ኤፍራጥስ ወንዝ ኤደን ገነት ውስጥ ነበር፤ ስለዚህ ሐይማኖታዊ አንድምታ አለው።

ሐይማኖታዊ አጋንንት እንደመሆናቸው፤ አረማውያኑ እንዲሁም ሮማውያን በሥላሴ፣ በዲሴምበር 25፣ የጥንቶቹን በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖችን በመግደል ያምኑ ስለነበረ እነዚህ አጋንንት በ1948 የዓለም ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት ሲመሰረት በቀላሉ ወደ ምክር ቤቱ መግባት ችለዋል።

ስለዚህ 2ኛው የዓለም ጦርነት የስድስተኛውን ማሕተም (የታላቁ መከራ ምሳሌ) እና የስድስተኛውን መለከት (የዓለም ሕዝብ ለአይሁዶች ያላቸው ክርር ያለ ጥላቻ) ጨረፍታ እይታ ሰጥቶናል፤ ይህም ጥላቻ በ1945 ጦርነቱ ሲያበቃ አብሮት አብቅቷል።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።

“ፀሃይ” የብርሃን ምንጭ ስለሆነች የምትወክለው መጽሐፍ ቅዱስን ነው።

ቤተክርስቲያኖች እስከ ዛሬ ድረስ በእንግሊዝኛ ብቻ 100 የሚያህሉ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አዘጋጅተዋል። እነዚህ ዘመናዊ ትምሕርትን ተመርኩዘው የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜ እንደተከለሱና እንደተሻሻሉ ናቸው። የሜሴጅ አማኞችን ጨምሮ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በ1769 ዓ.ም በተዘጋጀው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ያምናሉ። ከዚህም የተነሳ በእነርሱ አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም አይደለም፤ ስለዚህም ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈንታ የሰዎችን ንግግር ጥቅስ ይከተላሉ። የፀሃይ ብርሃን (መጽሐፍ ቅዱስ) በሰዎች እጅ ተነካክቶ ብዙ ስለተለወጠ ፍጹም እውነት መሆኑ ቀርቷል፤ ብርሃኑም ደብዝዞ ጨልሟል።

ጨረቃ ደግሞ የፀሃይን ብርሃን ተቀብላ የምታንጸባርቀው ቤተክርስቲያን ናት። ዛሬ ቤተክርስቲያን እምነቷን በመጽሐፍ ቅዱስ መርምራ ማረጋገጥ ትታለች። የቤተክርስቲያን ሰዎች ፍጹም እውነት አድርገው የሚቀበሉት የሰዎችን ንግግር ጥቅስ እና የሰዎችን አመለካከት ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ብርሃን ማንጸባረቅ ትታለች።

“ከዋክብት”። የአብርሃም ዘሮች።

ፍጥረታዊዎቹ የአብርሃም ዘሮች አይሁዶች ናቸው፤ መንፈሳዊ ዘሮች ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው።

ዘፍጥረት 15፡5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።

ዳንኤል 12፡3 ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።

ከዋክብት ማለት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲከተሉ በማድረግ ወደ ጽድቅ የሚመልሷቸው ሰባኪዎች ናቸው።

ሮሜ 4፡5 ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

ከዋክብቱ ማለትም ሰባኪዎች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስተምሩ ከተጠሩበት ሰማያዎ ጥሪ ወድቀው በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ወዳላቸው ስሕተቶችና ወደ ታዋቂ ቤተክርስቲያኖች አጋደሉ።

ሰባኪዎች የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹሙ የእግዚአብሔረ ቃል መሆኑን ለሰዎች ማስተማር ትተዋል።

የሰው ንግግሮች መጽሐፍ ቅዱስን እየተኩ ናቸው።

“እከሌ ብሏል” የሚለው ነገር “ተብሎ ተጽፏል …” ከሚለው አነጋገር ይልቅ እየበዛ ሄዷል።

ይህ አሳዛኝ ስሕተት ነው።

“የሰማይ ኃይላትም ይናወጣሉ።”

ሰማይ ከባቢ አየር ተብሎ ሊጠራም ይችላል። ዲሴምበር 28 ቀን 1963 በመላእክቱ ክንፍ የተፈጠረው ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና በከባቢ አየር ፊዚክስ ላይ የተመሰረቱ ሳይንሳዊ ሕጎቻችን ሁሉ አናውጧቸዋል። ይህ የሆነው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ነው።

 

 

ይህ በእርግጥ ሳይንስ ሊያብራራው የማይችለው ሰማይ ላይ የተገለጠ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ምልክት ነው።

ሆኖም ግን እነዚያው 7 መላእክት እራሳቸው ከ8 ቀናት በኋላ ወደ ሳንሴት ፒክ ወርደው ወንድም ብራንሐምን በማናገራቸው የወንድም ብራንሐም አገልግሎት እውነተኛ መሆኑን የሚመሰክር ክስተት ሆኗል። ሳንሴት ፒክ ከፍላግሰታፍ በስተደቡብ 200 መቶ ማይልስ ርቀት ላይ ነው የምትገኘው። መላእክቱም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ የ7ቱን መለከቶች ሚስጥር ገለጡለት።

ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥

በዚያ ቀን የታዩት ደመናዎች ሁለት ነበሩ።

 

 

አንዱ ደመና በሰባቱ መላእክት አማካኝነት ሲሆን የተፈጠረው ሁለተኛው ግን ካሊፎርኒያ ውስጥ ከቫንደንበርግ አየር ኃይል ተወንጭፎ ሰማይ ላይ ከፈነዳው ሮኬት ጭስ እና ስብርባሪ ነው የተፈጠረው።

ይህ ፎቶግራፍ አሪዞና ውስጥ ከምትገኘው ከዊንስሎው ከተማ ነው የተነሳው፤ ይህች ከተማ ደመናዎቹ በሚያልፉበት መስመር ውስጥ ነበረች።

ሁለት የጭስ አምዶች መስሎ ከኋላ የሚታየው ሁለተኛው ደመና ለሁለት ምክንያቶች ያስፈልግ ነበር።

በመጀመሪያ ሳይንስ ለሁለተኛው ትልቅ ደመና ምንም ማብራሪያ እንደሌለው ያሳያል። አንድ ደመና ብቻ ቢታይ ኖሮ ሳይንስ ደመናውን የሮኬቱ ፍንዳታ የፈጠረው ጭስ ነው ብሎ ማለፍ ይችል ነበር።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ኢዮኤል በትንቢቱ የጭስ አምድ እንደሚታይ ተናግሮ ነበረ። ስለዚህ ከፍጥረታዊ ደመና የተለዩ ሁለት የጭስ አምዶች ሰማይ ላይ ከፍ ብለው መታየታቸው ግድ ነው።

ኢዮኤል 2፡30 በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ

 

 

ሳይንስ ለትልቁ ደመና ምንም ማብራሪያ መስጠት አልቻለም ምክንያቱም ሁለት ደመናዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ የሮኬት ፍንዳታ የፈጠረው ጭስ ነበረ። የተፈጥሮ ደመናዎች ከምድር ወደ ላይ ከ20 ኪሎሜትር በላይ ከፍ ብለው ሊፈጠሩ አይችሉም። ስለዚህ ከምድር 42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የተፈጠረ ደመና አንዳችም ተፈጥሮአዊ ማብራሪያ ሊኖረው አይችልም።

ሁለተኛው ደመና ብዙ ፎቶግራፎች ውስጥ ቢገኝም እንኳ ብዙ የሜሴጅ ሰዎች ግን መኖሩን ሊክዱ ይፈልጋሉ። ይህ ራስን ማታለል ነው። ማርች 1 ቀን ከምድር ከፍ ባለ ከፍታ ላይ የተለካ የነፋስ ፍጥነት መረጃዎችን ይጠቅሳሉ፤ ነገር ግን እነዚያ ነፋሶች ፍጥነታቸው በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ በተባለው ሰዓት ውስጥ ደመናዎቹን ከቫንደንበርግ ወደ ፍላገስታፍ ሊያደርሱ አይችሉም። ደመናው ግን ፎቶግራፍ የተነሳው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ፌብሩዋሪ 28 ቀን ቫንደንበርግ ውስጥ ምንም የነፋስ ፍጥነት ባልተለካበት ቀን ነው።

ሁለት ደመናዎች የሚታዩበትን ፎቶግራፍ ያያሉ፤ ከዚያ በኋላ ግን የነሱን ሃሳብ ስለማይደግፍላቸው ሁለተኛውን ደመና እንዳላዩ ያልፉታል።

አስተማሪ ማስረጃ አይቶ ቸል ማለት አይችልም። ፓስተር ከሆነ ግን ቸል ብሎ ማልፍ እንደሚችል ያስባል።

 

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች አብራርቶ ከጨረሰ በኋላ በሶስት ርዕሶች ላይ መስበክ ይፈልግ ነበር።

በ1963 ከሰባቱ ማሕተሞች በኋላ ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ መለከቶች እና ስለ ሰባቱ ጽዋዎች እንዲሁም ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች መስበክ ፈልጎ ነበር።

ስለዚህ እነዚህን ሶስት ርዕሶች እንደሚገባ አብራርቶ አላስተማረባቸውም።

63-0321 አራተኛው ማሕተም

ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ተመልሼ እመጣለሁ… በዚያን ጊዜ ገና ስለሚመጡት ስለ ሰባቱ መለከቶች በደምብ እናጠናለን። አያችሁ? እነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንድነት ይጠቀለላሉ፤ ከእነርሱም ጋር ሰባቱ ጽዋዎች ይፈስሳሉ።

እስከ 1963 ድረስ 7ቱ መለከቶች እና 7ቱ ጽዋዎች ገና አልተፈጸሙም ነበር።

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ራዕይ 10ኛው ምዕራፍ ማለቴ ነው፤ ቁጥር ደግሞ ከ1 እስከ 7 ድረስ። ዘመን ያበቃል። መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከእንግዲህ በኋላ አይዘገይም” ይህ ታላቅ ነገር በሚፈጸምበት ቀን ነው ይህ ሁሉ የሚሆነው። በዚህ በሰባተኛው ማሕተም መጨረሻ ላይ ነገር ሁሉ ይጠናቀቃል።

ይህን አስተውሉ የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ነው። የሰባቱ ማሕተሞች መጨረሻ ነው። የመለከቶቹ መጨረሻ ነው። የጽዋዎቹ መጨረሻ ነው፤ እንዲሁም የሺ ዓመት መንግስት መጨረሻም ነው፤ ይህ ሰባተኛው ማሕተም ነው።

ሰባተኛው ማሕተም በተፈጸመ ጊዜ ሁሉም ነገር ይጠናቀቃል።

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ፎቶግራፍ ከተነሳ ከሶስት ሳምንታት በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም የብርቱውን መልአክ መምጣት ወደ ፊት እንደሚፈጸም ነገር ይጠባበቀው ነበር።

1963 0324 ሰባተኛው ማሕተም

ተመልሼ መምጣትና ስለ መጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች ሰባት ሌሊት ማስተማር እፈልጋለሁ።

ስለ መለከቶቹ እና ስለ ጽዋዎቹ ለማስተማር ትልቅ ጉጉት ነበረው።

63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት

አሁን እንግዲህ ከሰባቱ መለከቶች እና ከሰባቱ ጽዋዎች ዘመን ጋር ተጋፍጠናል። የሁለት ሳምንት ኮንፈረንስ አዘጋጅተን ሁለቱንም አንድ ላይ ልንማር እንችላለን። ይህ ትምሕርት በድምጽ ተቀድቶ እንዲቀመጥ እፈልጋለሁ።

63-0728 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሚስጥር መገለጥ ነው

ተመልሰን ወደዚሁ ርዕስ እንመጣለን፣ ቆዩ አንዴ … ከዚያም ሰባቱ መለከቶች ወዲያው ይመጣሉ፤ ጌታ ከፈቀደ ሰባቱን መቅሰፍቶች እና ጽዋዎች እናያለን፤ ከዚያም ወደ ለሎች ርዕሶች እንቀጥላለን፤ እግዚአብሔር በመራን መንገድ አየሩም በረድ ሲልልን ትምሕርታችንን እንቀጥላለን።

63-0818 የአንድነት ጊዜ እና ምልክት

ራዕይ 10 የሚናገረው ስለ “ሰባተኛው መልአክ መልእክት” ነው። ስለዚህ አስተውሉ ይህ በቀጥታ ከሰባቱ መለከቶች ጋር የተያያዘ ነው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሰባት መለከቶችን የሚነፉ ሰባት መላእክት አሉ። ቀጥሎ የምንመለከተው ይህ ነው

ሰባቱ መለከቶች ከሰባተኛው መልአክ መልእክት በኋላ ተከትለው ነው የሚመጡት።

እነዚህ 7 መለከቶች ግን ለአሕዛብ አይደሉም፤ ሰባቱ መለከቶች በታላቁ መከራ ወቅት አይሁዶችን ወደ እስራአል እንዲመለሱ መጥሪያ ናቸው።

63-0818 የአንድነት ጊዜ እና ምልክት

ራዕይ 10 የሚናገረው ስለ “ሰባተኛው መልአክ መልእክት” ነው። ስለዚህ አስተውሉ ይህ በቀጥታ ከሰባቱ መለከቶች ጋር የተያያዘ ነው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሰባት መለከቶችን የሚነፉ ሰባት መላእክት አሉ። ቀጥሎ የምንመለከተው ይህ ነው።

ነገር ግን በቀጥታ እና በግልጽ እዚሁ ክፍል ውስጥ እንዲህ እንደሚል አስተውሉ፣ “መላእክቱ” እንጂ የሰባተኛው መልአክ መለከት ሳይሆን “የሰባተኛው መልአክ መልእክት” ነው የሚለው።

ስለዚህ መለከት የያዘው መልአክ ሳይሆን መልእክት የያዘው መልአክ ነው።

አያችሁ መልአኩ ያ ሰባተኛ መልአክ መለከቱን ብቻ ነፋ። ባለ መለከቱ መልአክ ይህኛው ነው፤ እርሱም መልእክት በሚያመጣው መልአክ ዘመን ውስጥ መለከቱን ይነፋል፤ መለከቱን የሚነፋው መልእክቱ ተነግሮ ሲጠናቀቅ ነው። ይህም መልእክት የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክት ነው።

ከዚያ በኋላ ደግሞ እንዲያከናውን የተሰጠው ሥራ … መለከቱን ሳይሆን መልእክቱን ማለት ነው፤ ቀጥሎም “የእግዚአብሔር ሚስጥር (ቃሉ ውስጥ የተጻፈው) በሙሉ ይፈጸማል።”

መልእክቱን የሚያመጣው ሰባተኛ መልአክ እና በታላቁ መከራ ውስጥ መለከት የሚነፋው ሰባተኛ መልአክ አንድ አይደሉም።

መልእክት የሚያመጣው መልአክ የተጻፈው ቃል ውስጥ ያሉትን ሚስጥራት ይገልጣል።

63-0818 የአንድነት ጊዜ እና ምልክት

ከዚያ በኋላ ደግሞ እንዲያከናውን የተሰጠው ሥራ … መለከቱን ሳይሆን መልእክቱን ማለት ነው፤ ቀጥሎም “የእግዚአብሔር ሚስጥር (ቃሉ ውስጥ የተጻፈው) በሙሉ ይፈጸማል።”

 

7ኛው መልእክተኛ መልአክ እና መለከት የሚነፋው 7ኛ መልአክ የተለያዩ መሆናቸውን ልብ በሉ።

ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች በስሕተት ወንድም ብራንሐም 7ኛው መለከት የሚነፋ መልአክ ነው ብለዋል።

መልእክቱ የራሱ የሆኑ ውስንነቶች አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን የእግዘአብሔር ሚስጥራት መግለጥ ብቻ ነው ሥራው

 

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ይህ ሁሉ በቤተክርስቲያን ዘመን እና በመላእክቱ ዘንድ ተነግሮ የነበረ መሆኑን አስተውሉ። አሁን ደግሞ ዛሬ ከምናጠናቸው ከሰባቱ ማሕተሞች ጋር መጥቶ በትክክል ይጋጠማል። አሁን የምንማራቸው ሰባቱ ማሕተሞች በዚህ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ሲመጡ ሰባቱ የተጻፉት ሞስጥራት መሆናቸውን እናስተውላለን። እንደምታውቁትም እነዚህ ሰባት ማሕተሞች የሰባቱ ቤተክርስቲያናት ሰባት መላእክት መገለጦች ናቸው፤ ነገር ግን በመጽሐፉ ጀርባ ላይ የተደረጉ ሌሎች ሰባት ማሕተሞችም አሉ፤ ስለዚህ ይህ ሚስጥር ከመጽሐፍ ቅዱስ በውጭው በኩል ነው

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ” የሆነ ነገር ሁሉ ትክክል አይደለም። ማለት የፈለገው አንዳንድ ሚስጥራት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሳይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሆነው ግን ሳይገለጡ ቀርቷል።

ሰባተኛው መልአክ ያልተጻፉ ሚስጥራትን አይገልጥም፤ እነዚህም ሰባተኛው ማሕተም፣ ሰባቱ ነጎድጓዶች፣ እና የኢየሱስ አዲስ ስም ናቸው።

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

እንዲህ ዓይነቱ መልእክት የተሰጠው ለሰባተኛው መልአክ ነው። መልእክቱ ምንድነው? እንዲህ ዓይነቱን መልእክት አስተውሉ፡- “መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ማጠናቀቅ።” ሰባተኛው መልአክ በነዚህ ድርጅቶችና ዲኖሚኔሽኖች ሁሉ ውስጥ ያልተቋጩ ሚስጥራትን በሙሉ ሰብስቦ መቋጨት ነው ሥራው። ሰባተኛው መልአክ ይሰበስባቸውና በአንድነት ወደ ፈጻሜ ያመጣቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስም እንዲሁ ብሎ ነው የተናገረው፡- “በተጻፈው መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ሚስጥራትን ሁሉ ይፈጽማል።”

… ቃሉ ይመጣል። “በውስጡ በኩል የተጻፈበት መጽሐፍ” በዚያ ጊዜ ይጠናቀቅና በሚስጥራቱ ሁሉ ተፈጽመው ይታወጃሉ።

… “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፈው ሚስጥር በሙሉ ይፈጸማል።” በዚያ ቀን ሚስጥሩ ሁሉ ይፈጸማል። የምናገረው አሁን ገባችሁ? እየተከታተላችሁኝ ነው? ከዚያ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጻፉት ሰባቱ ድምጾች የሚገለጡበት ጊዜ ይመጣል። መጽሐፉ ሲጠናቀቅ አንድ ነገር ብቻ ይቀራል፤ እርሱም በመጽሐፉ ጀርባ የተጻፉትና ዮሐንስ እንዳይጽፍ የተከለከለው ሰባቱ ሚስጥራዊ የነጎድጓድ ድምጾች ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱስ “ጀርባ” ማለት የተጻፉት ሚስጥራት ተፈጽመው በሚጠናቀቁበት ጊዜ መጨረሻ ላይ ናቸው ማለት ነው።

በተጨማሪም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም ማለት ነው። ብቻ ግን በሆነ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውረው ተቀምጠዋል።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ነጎድጓዶቹ ምን ብለው እንደተናገሩ ይነግረን ዘንድ አልተፈቀደለትም። ንግግራቸው ውስጥ ምን እንዳለ አልነገረንም።

እርሱ የተናገረው ለሙሽራይቱ እና ለሁለቱ የአይሁድ ነብያት የነጎድጓዶቹ አገልግሎት ምን እንደሆነ ብቻ ነው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች የት ሆነው ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ እንኳ አልተረጋገጠም። ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?

ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች እስከ ዛሬ ድረስ ትልቅ ሚስጥር ናቸው።

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ድምጹ የት እንደነበረ ተመልከቱ፤ መብረቁ ባለበት። በሰማይ አይደለም፤ በምድር ነው! ነጎድጓዶቹ ከሰማይ አልተናገሩም። የተናገሩት ከምድር ነው

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

በሰማይ ያሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ይህንን ሚስጥር ይገልጡታል። እርሱም ልክ በክርስቶስ ምጻት ጊዜ ይሆናል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ እርሱ መች እንደሚመጣ ማንም አያውቅም ብሎ ተናግሯል።

63-1110 አሁን በወህኒ የሚኖሩ ነፍሳት

ደግሞ ልብ በሉ፤ በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ሰባቱ መለከቶች በሙሉ ድምጻቸውን የሚያሰሙት በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ነው

መለከቶቹ በሙሉ ድምጻቸው የሚሰማው በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ነው፤ ያም የታላቁ መከራ ዘመን ነው።

ስለዚህ መለከቶቹ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሚኖሩትን አይሁዶች ነው የሚመለከቷቸው።

ሁለት መለከቶች (ሙሴ እና ኤልያስ) በጥንት ዘመን አይሁዶችን ለመጥራት አገልግለዋል።

7ቱ ነጎድጓዶች ለሙሴ እና ለኤልያስ በተፈጥሮ ላይ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ከሰጧቸው በኋላ እነዚህ ነብያት እስራኤል ውስጥ ተነስተው አይሁዶች ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ጥሪ ያደርጋሉ።

ዘኁልቁ 10፡2 ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።

3 ሁለቱም መለከቶች በተነፉ ጊዜ ማኅበሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይሰብሰቡ።

“በሩ” የኢየሱስ ምሳሌ ነው ምክንያቱም ወደ ሰማይ መግቢያው በር ኢየሱስ ነው።

ዮሐንስ 10፡9 በሩ እኔ ነኝ፤

ስለዚህ በሁለት መለከቶች የተመሰሉት ሁለቱ ነብያት አይሁዶችን ከመሲሃቸው ጋር ያስተዋውቋቸዋል።

ነገር ግን ወደ እስራኤል ለመመለስ እምቢ የሚሉ አይሁዶች እንዲመለሱ እግዚአብሔር ሰባት መለከቶች የተባሉ ሰባት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ክስተቶችን ያዘጋጅና እንዲመለሱ ያስገድዳቸዋል።

1963 0324 ሰባተኛው ማሕተም

እግዚአብሔር በልቤ ላይ ካስቀመጠው በዚህ ዓመት በበጋ ወቅት ወይም ሰኔ አካባቢ ወይም በክረምት ጌታ እስከዚያ ድረስ ከዘገየ ተመልሼ መምጣትና እንደገና ለሰባት ምሽቶች ስለ መጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች ማስተማረ እፈልጋለው

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ መለከቶች መስበክ ሁልጊዜ ይፈልግ ነበር።

63-1124 ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስ ምን ላድርገው

በዚያ ትምሕርት ቤት ስንገናኝ ስለ ሰባቱ መለከቶችም ለመስበክ እሞክራለሁ። ያ ቦታ እንደውም ሰፋ ያለ ስለሆነ ብዙ ሰዎችን ማስገባት እንችላለን።

ስለ ሰባቱ መለከቶች ለመስበክ ከአንድ ዓመት በላይ ዕድሉን ይጠብቅ ነበር።

63-1124 ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስ ምን ላድርገው

አንድ ላይ ተሰብስበን ስለ መጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች የምንማርበትን ዕድል እግዚአብሔር ይሰጠናል ብዬ አምናለሁ። ወደነዚህ ነገሮች እግዚአብሔር እንዲመራኝ እፈልጋለሁ፤ እናንተም ትማራላችሁ።

63-1229 መብራቱን ሊያበራልን የሚችል ሰው እዚህ አለ

… እግዚአብሔር ከፈቀደ እዚህ እንድንሰበሰብና ስለ ሰባቱ መለከቶች እንድንማር እፈልጋለሁ

64-0411 መንፈሳዊ የመርሳት በሽታ

ተመልሼ ስለመምጣትና በቅርቡ ድንኳን ተተክሎ ተሰብስበን እንደ ጌታ ፈቃድ ስለ መጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች እንድንማር አስባለሁ።

64-0614 ብቸኛው ኳስ

… ከዚያም ወደዚህ ወደ ጄፈርሰንቪል ተመልሼ መምጣትና ስለ ሰባቱ መለከቶች መስበክ እንዳለብኝ ምልክት ይሆነኛል፤ ሐምሌ ወይም ነሐሴ አካባቢ እመጣለሁ።

64-0705 ልዩ የጥበብ ሥራ

የጌታ ፈቃድ ከሆነ ስለ ሰባቱ መለከቶች መናገር እፈልጋለሁ። ይህም የስምንት ቀን አገልግሎት ነው የሚሆነው፤ ስለዚህ እዚህ ድንኳን ውስጥ ልንሆን አንችልም። ተለቅ ያለ አዳራሽ መያዝ ያስፈልገናል።

 

በስተመጨረሻም ወንድም ብራንሐም የመለከቶች በዓል የተሰኘ ጉባኤ አዘጋጀ፤ ይህም በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን የሚከበር የአይሁዶች አምስተኛ በዓል ነው። ይህ በዓል ለአይሁዶች የአዲስ ዓመት በዓል ነው።

ዘሌዋውያን 23፡24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።

64-0719 የመለከቶች በዓል

ዛሬ ጠዋት ላስተምር የምፈልገው ስለ ሰባቱ መለከቶች በዓል ነው። ይህ ወር የሰባቱ መለከቶች በዓል ወር ነው፤ ይህም ሰባተኛው ወር ነው፤ ስለዚህ ዘሌዋውያን ውስጥ በተጻፈው ሕግ መሰረት የመለከቶች በዓል የሚጀመርበት ቀን ሐምሌ 15 ነው።

[ሐምሌ በአሕዛብ ቀን አቆጣጠር 7ኛ ወር ነው። የአይሁድ 7ኛ ወር ወደ መስከረም ነው የሚጠጋው።]

… ለተወሰነ ጊዜ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ስለተጻፉት ስለ ሰባቱ መለከቶች ለማስተማር ሳስብ ቆይቻለሁ። አሁን ይህንን ትምሕርት ለጥቂት ሰዓታት እንከልሳለን። በዚህ ርዕስ አሁን የማላስተምርበት ዋነኛ ምክንያቴ በዚህ ጊዜ ስለዚህ ርዕስ እንዳስተምር መንፈስ ቅዱስ ስላልፈቀደልኝ ነው

… ይህ ትምሕርት አሁን ለቤተክርስቲያን ለምን እንደማይጠቅማት መንፈስ ቅዱስ አስረድቶኛል፤ ምክንያቱም ይህ ትምሕርት ከቤተክርስቲያን ጋር ፈጽሞ የተገናኘ አይደለም

… ሰባቱ መለከቶች ቤተክርስቲያንን እና ይህንን ዘመን የማይመለከቱበት ምክንያት የተጻፉት ስለ እስራኤል ብቻ ስለሆነ ነው። መለከቶቹ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ማድረጊያ ናቸው። እንድትገነዘቡ የምፈልገው አንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ፤ እርሱም ይህ ነው፡ ሰባቱ መለከቶች አሁን እኛ የምንኖርበትን ዘመን ለምን እንደማይመለከቱ እንድታውቁ ነው

[መለከቶቹ ቤተክርስቲያንን አይመለከቷትም፤ ዓላማቸው አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ መጥራት ነው።]

… እነዚህ መለከቶች ለእኛ ለምን ትርጉም እንደማይሰጡን አልገባችሁም? ሁላቸውም ድምጻቸውን የሚያሰሙት በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ነው።

በዚህ ርዕስ እንዳስተምር መንፈስ ቅዱስ ለምን እንደማይፈቅድልኝ አሁን ገብቷችኋል? እግዚአብሔር የሰማዩ አባት ምስክር ነው፤ በእጄ የያዝኩት ይህ መጽሐፍ ቅዱስም ምስክር ነው እውነቴን ነው። እስከ ትናንት ድረስ፤ እስከ ትናንት ወዲያ ድረስ አላወቅሁም ነበር፤ በመኝታ ክፍሌ ውስጥ ሳለሁ ወደ እኔ መጣና ገለጠልኝ።

መለከቶቹ ድምጻቸው የሚሰማው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።

64-0719M የመለከቶች በዓል

በሒትለር ዘመን ያ የስደት መለከት ድምጹ እንዴት ከፍ ብሎ እንደተሰማ አይታያችሁም? አይሁዶችም የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘመን በአንድ ሥፍራ መሰብሰብ ግድ ሆነባቸው።

ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ይበልጥ ለመረዳት ሙሽራይቱ ስለ ታላቁ መከራ ክስተቶች የተወሰኑ መገለጦችን ማግኘት አለባት። ሆኖም ሙሽራይቱ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ አትገባም።

ስለዚህ ታላቁ መከራ ምን እንደሚመስል እግዚአብሔር አንዳንድ መረዳቶችን አስቀድሞ የሚሰጠን እንዴት ነው?

እግዚአብሔር የታላቁን መከራ ቅድሚያ እይታ እንድናገኝ አድርጓል፤ ሆሎኮስት የተባለ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ተከስቷል፤ ይህም የታላቁ መከራ ግልገል ነው። በዚህም መንገድ መንፈሳዊ እስራኤል የሆኑን የሙሽራይቱ አካላት በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ የፈሰሰውን ግፍ ማየት ችለዋል።

ፍጥረታዊ አምባገነኖች የሆኑን ሒትለር እና እስታሊን ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ የሆኑ አጋንንትን በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ አሰማርተዋል።

ነገር ግን ጦርነቱ በ1945 ከተጠናቀቀ በኋላ እነዚህ አምባ ገነን መናፍስት ሐይማኖተኛ መስለው በ1948 ወደ ዓለም ቤተክርስቲያኖች ምክር ቤት ሰተት ብለው ገብተዋል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ቤተክርስቲያኖች ሾልከው በመግባት ሰዎች ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል የሂነውን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንዳያምኑ እና ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔረ ቃል አድርገው እንዳይቀበሉ ተጽኖ አድርገዋል።

ከዚያ ወዲያ እነዚህ መናፍስት ፓስተሮችን ያለ ልክ ከፍ ከፍ አድርገዋቸው ፓስተሮችን ትንንሽ አምባ ገነኖች እና የቤተክርስቲያን ራስ አንዲሆኑ አደርገዋቸዋል።

የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ብቻ ነው።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

አረማዊ ሮማውያን የተለያዩ ስላሴዎችን ያመልኩ ነበር። ስለዚህ እነዚህ መናፍስት እንዲህ ሲሉ በተጨማሪ ስም የሌለው ስላሴያዊ አምላክ ፈጠሩ፡- “በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ነገር ግን ያ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።

አሁን ደግሞ እነዚህ መናፍስት ዊልያም ብራንሐም የተናገራቸው ንግግሮች ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል ናቸው፤ ዊልያም ብራንሐም አይሳሳትም ይላሉ።

61-1119 ፍጹም ብርታት ከፍጹም ድካም ውስጥ

ከማንቆርቆሪያ ላይ ክዳን ሲከፈት አስቡ፤ አጋንንት እንደ ልባቸው ሲፈነጩ፤ የዲያብሎስ ኃይላት በክርስትና ስም ሲንቀሳቀሱ፤ የሰዎችን ትዕዛዝ ሲያስተምሩ፤ የስነ መለኮት ኮሌጆችን ደረቅ ትምሕርት ሲያጠጡዋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስን ትተው የሰው ትምሕርት ሲያስተምሩ።

ሃሌሉያ። ማነው የሚችል … ማነው አቅም ያለው፤ ማነው ጠቢብ? በሰባኪዎች፣ በሜተዲስቶች፣ እንዲሁ በፕነቲኮስታሎች ስም ሴቶቻችን ዕርቃናቸውን እንዲሄዱ እያደረገ ያለውን ይህንን ሌጌዎን ሰራዊት ሊያስቆመው የሚችል ማነው? እንደ ኤልዛቤል ፊታቸውን እየተቀቡ፤ ጸጉራቸውን እያስጌጡ፤ እንደ ወንድ ሱሪ እየለበሱ፤ ሰባኪዎቻችን ግን እውነቱን ሊነግሩዋቸው እንኳ ወኔ የላቸውም፤ … ልበሱን ከላዩ ላይ የቀደዱት ወታደሮች

 

“መጽሐፍ ቅዱስን ትቶ መሄድ” የሚያመራው “የሰውን ትዕዛዝ ወደ ማስተማር ነው”።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሲስቱና እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን ሲያቆሙ ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን እንደ እምነታቸው አድርገው ለመቀበል ይገደዳሉ።

“ወዲያ ወዲህ የሚመላለሱ አጋንንት”። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶች ሁሉ ምጫቸው ከአጋንንት ነው።

64-0726 ዘመናችሁን እና የዘመናችሁን መልእክት ለይቶ ማወቅ

እንግዲህ ሰባቱ መለከቶች እስራአልን ብቻ የሚመለከቱ መሆናቸውን ማየት እንችላለን።

… እኔም በትሕትና በእግዚአብሔረ ፊት ለጸሎት ተንበረከክሁ። እርሱም እነዚያ ሰባት መለከቶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት በስድስተኛው ማሕተም ስር መሆኑን ገለጠልኝ፤ እኔም ከዚያ ወዲያ በመለኮታዊ ኃይል ሰብኬዋለው። አያችሁ፤ ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር እጅ ነው። ከእስራኤል ጋር የተገናኘ ነገር ነው፤ እኛም ከስድስተኛው ማሕተም ስር አገኘነው፤ ይህን የተረዳችሁ ሁሉ የአይሁዳውያን ስደት ምን እንደሚመስል አስቡ።

… መለከቶቹ ሁሉ … ሁሉም በስድስተኛው ማሕተም ስር ነው የሚነፉት። ባላፈው እሁድ የመለከቶችን በዓል በተመለከተ እየተማርን ካቆምንበት ቀጥለን አይተናል፤ ሁሉንም የምትፈልጉ ከሆነ ትምሕርቱን ማግኘት ትችላላችሁ። ዓላማው ምንድነው? ዓላማው አይሁዶችን ከሁሉም የዓለም ክፍል አሯሩጦ ወደ ሃገራቸው መመለስ ነው። የሚፈጸመው በዚያ ነው

… ሰባቱ መለከቶች ድምጻቸው የተሰማው በስድስተኛው ማሕተም ውስጥ ነው።

ባለፈው ክፍለ ዘመን ውስጥ በተለይም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአይሁዶች ላይ የተቀሰቀሰው ጥላቻ የስድስተኛው ማሕተም ቅድሚያ እይታ ናቸው፤ በስድስተኛው ማሕተም ጊዜ ከአይሁድ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

አይሁዶችን እንዲህ በጭካኔ መግደል ብዙዎቹ አይሁዶች ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ እስራኤል እንዲሸሹ አድርጓቸዋል። እነዚህ ስደቶችም አይሁዶች ወደ እስራኤል እንዲመለሱ የሚያስገድዷቸው የሰባቱ መለከቶች ቅድሚያ እይታ ናቸው።

 

65-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

የአስር ቀን ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት ወደዚህ ተመልሼ ልመጣ ስሞክር ነበር፤ ላስተምርበትም ያሰብኩት ርዕስ የመጨረሻዎቹ ሰባት ጽዋዎች የሚል ነበር። ምክንያቱም በጽዋዎቹ መካከል መለከቶቹ አሉ። ከዚህ ቀደም ስነግራችሁ እንደነበረው … ስለ ሰባቱ መለከቶች ልሰብክ ባሰብኩ ጊዜ ስለ ጽዋዎቹ እና ስለ መቅሰፍቶቹም አንድ ላይ እሰብካለሁ ብያችሁ ነበር።

7ቱ መለከቶችም ሆኑ 7ቱ ጽዋዎች የሚፈጸሙት በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።

እነዚህ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች “በጽዋዎቹ መካከል” እየተፈራረቁ ይገለጣሉ፤ ጽዋዎቹ እየፈሰሱ ሳለ መለከቶቹም ይነፋሉ። ስለዚህ የጽዋዎቹ መፍሰስ ከመለከቶቹ መነፋት ጋር ተቀላቅሎ ነው የሚፈጸመው፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።

ሙሽራይቱ ግን የእነዚህን ሁሉ ፍጻሜ በቅድሚያ እይታ ብቻ ነው የምታየው።

በዚህ ርዕስ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን በዚሁ ጥናት ክፍል 2 ውስጥ እናቀርባለን።

65-0801 የዘህ ዘመን ክፉ አምላክ

ዛሬ ወደዚህ የመጣሁት ስለ መጨረሻዎቹ ጽዋዎች ላስተምራችሁ ነው፤ የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት የመጨረሻዎቹ ሰባት ጽዋዎች እና የመጨረሻዎቹ ሰባት መለከቶች እና የመጨረሻዎቹ ሰባት ነጎድጓዶች፤ ዛሬ ከምንኖርበት ዘመን ጋር አያይዘን እናያቸዋለን። የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት እና ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት አንጻር እንመለከታለን።

ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አራት ወራት በፊት ስለ 7ቱ ጽዋዎች፣ 7ቱ መለከቶች፣ እና ስለ 7ቱ ነጎድጓዶች የማስተማር ፍላጎት ነበረው።

ስለዚህ በግልጽ እንደምናውቀው ወንድም ብራንሐም በነዚህ ርዕሶች ላይ አላስተማረም።

 

ስለነዚህ ሶስት ሚስጥራዊ ርዕሶች ብዙ እውቀት የለንም።

 

64-0830 ጥያቄዎችና መልሶች - 4

ከሰባቱ ሚስጥራት ጋር በቁጥር የሚመሳሰሉት ሰባቱ ነጎድጓዶች ተገልጠዋልን? በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠው ነገር ግን ለእኛ እስከ አሁን ድረስ እንደ ነጎድጓድ አልተገለጡልንምን?

የለም፤ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ተገልጠዋል፤ የነጎድጓዶቹ ትርጉም በማሕተሞቹ ውስጥ ነው።

ነጎድጓዶቹ ማሕተሞቹ ውስጥ ተገልጠዋል አለ።

“የነጎድጓዶቹ ትርጉም”።

በሌላ አነጋገር በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የተሰጣቸው የሥራ ድርሻ ለማለት ነው።

የተሰጣቸው ሥራ፡- ለሙሽራይቱ ወደ ሰማይ የምትነጠቅበትን እምነት መስጠት። ለሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል መስጠት። የኢየሱስን አዲስ ስም መግለጥ። ጌታ የሚመጣበትን ሰዓት መግለጥ።

ያልተገለጠው ነገር በቀጥታ ምን ብለው እንደሚናገሩ ነው። የሚናገሯቸው ቃላት ምን እንደሆኑ አልተገለጠም። ይህ ማንም እንዳያውቀው ተሰውሮ የተቀመጠ ሚስጥር ነው።

አዲሱን ስም አናውቀውም።

ኢየሱስ መች እንደሚመጣ አናውቅም።

አሁን በምንኖርበት አካል ውስጥ ሆነን መነጠቅ አንችልም፤ ስለዚህ ለጊዜው ለመነጠቅ የሚያበቃ እምነት የለንም።

ነጎድጓዶቹ አዲሱን የማይሞት አካላችንን እንዴት እንደምንቀበል ያሳዩናል ምክንያቱም በማይሞተው አካላችን ውስጥ ስንሆን ብቻ ነው የመነጠቅ እምነት የምናገኘው።

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱ ነብያት የተፈጥሮ ኡደቶችን የሚያቋርጡበት ኃይል ገና አልተሰጣቸውም።

ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች የሚያከናውኗቸው ሥራዎች ምን እንደሆኑ ተገልጦልናል፤ ነገር ግን መች እንደሚሰሩ አልታወቀም።

መች እንደሚፈጸም እና እንዴት እንደሚፈጸም እስከ ዛሬ ድረስ ሚስጥር ነው።

65-0822 የሚያስብ ሰው ጭንቅላት

ሁላችንም በአንድ ሥፍራ ተሰብስበን ስለ ሰባቱ መቅሰፍቶች እና ስለ ሰባቱ ጽዋዎች እንዲሁም ስ ለሰባቱ መለከቶችና ስለ ሌሎች ርዕሶች የምንሰብክበትን ጊዜ እናፍቃለሁ። እነዚህ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከታትል የሚፈጸሙ ነገሮች ናቸው። ለዚህ ነው አንድ ሳምንት፣ አስር ቀን ወይም ከዚያም በላይ የሚፈጅብን፤ ስለዚህ በአንድ ጉባኤ ብቻ ልንጨርሰው አንችልም። አንድ ሳምንት ግን የሚበቃን ይመስለኛል።

“ስለ ሌሎችም ርዕሶች” የሚለው ሐረግ ከ7ቱ ጽዎች እና ከ7ቱ መለከቶች ጋር ተያይዞ ሌላም ነገር እንዳለ ያመለክታል። ይህ በግልጽ የሚያመለክተው ጉዳዩ ከ7ቱ ነጎድጓዶች ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው።

 

1965 የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ መግቢያ - የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ ምዕራፍ 1

ይህ ክፍል ውስጥ ራዕይ ምዕራፍ አንድ፣ ሁለት፣ እና ሶስት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ዋና ዋና አስተምሕሮዎችን (ለምሳሌ መለኮት፣ የውሃ ጥምቀት፣ ወዘተ.) የሚዳስስ ቢሆንም ዋነኛ ርዕሰ ጉዳዩ ግን የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ዝርዝር ጥናት ነው። የቀረውን የራዕይ መጽሐፍ በሙሉ ለማጥናትና በትክክል ለመረዳት ይህ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ማሕተሞቹ የሚመጡት ከዘመናቱ ውስጥ ነው፤ ከማሕተሞቹ ውስጥ ደግሞ መለከቶቹ ይወጣሉ፤ ከመለከቶቹ ውስጥ ጽዋዎቹ ይወጣሉ። ልክ የሮማዎች ሻማ ሲበራ እንደሚደምቀው የቤተክርስቲያን ዘመናት በታላቅ ድምቀት ይጀምራሉ፤ ያለዚያ መገለጥና ብርሃን ሊቀጥል አይችልም ነበር። ነገር ግን የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ድምቀት በመለኮታዊ መገለጥ ከተሰጠ በኋላ የራዕይ መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ በዓይናችን ፊት እስኪገለጥ ድረስ በብርሃን ላይ ብርሃን እየተጨመረ ይበራልናል። እኛም በመንፈስ ቅዱስ ነጽተንና ታንጸን ጌታችንና አዳኛችን ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በክብሩ ሲገለጥ ልንቀበለው እንዘጋጃለን።

1965 የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9

በሚልክያስ ምዕራፍ 4 እና ራዕይ 10፡7 ውስጥ የተጠቀሰው መልእክተኛ ሁለት ነገሮችን ያደርጋል። አንድ፡ በሚልክያስ 4 መሰረት የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል። ሁለት፡ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰውን የሰባቱን ነጎድጓዶች ሚስጥር ይገልጣል፤ እነዚህም ሚስጥራት የተሰወሩት በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ነው። እነዚህ በመለኮታዊ አሰራር የሚገለጡ “ሚስጥራዊ እውነቶች” ናቸው የልጆችን ልብ ወደ ጥንቶቹ አባቶች በእውነት የሚመልሱት። ልክ እንደዚሁ ይሆናል።

… እነዚያ ነጎድጓዶች ሚስጥራቸው ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም። እኛ ግን ማወቅ አለብን።

የሰባቱ ነጎድጓዶች መገለጥ ያለው በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ ነው።

ሰባቱን ነጎድጓዶች በተመለከተ በሰባቱ ማሕተሞች ውስጥ የተጠቀሱ ጥቅሶችን በሙሉ ተመልከቱ፤ የዚያን ጊዜም ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገራቸው መገለጦች ሁሉ ነጎድጓዶቹ ከሚሰሩዋቸው ሥራዎች ጋር ብቻ የተያያዙ መሆናቸውን ታያላችሁ። አገልግሎታቸውን ብቻ ነው የገለጠው።

የሚናገሯቸውን ቃላት ወይም ንግግሮች ገልጦ አያውቅም።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ሰባቱ ነጎድጓዶች ምን እንደሚሰሩ ነው የገለጠው እንጂ ምን ብለው እንደሚናገሩ አልገለጠም።

ደግሞም እስከ ዛሬ አንዳችም ነገር አልተናገሩም፤ የተባሉትን ሥራዎችም አልሰሩም።

65-0822 ክርስቶስ በራሱ ቃል ውስጥ ይገለጣል

ሰዎች ከኖሩባቸው ዘመናት መካከል ከሁሉ ይልቅ በሚያስፈራው ዘመን ውስጥ እያለፍን ነን። እኔም ሁላችን ጊዜ አግኝተን የምንሰበሰብበትን ሰዓት እየተጠባበቅሁ ነኝ… ሁላችንም ዕድል አግኝተን፣ እናንተም ከሥራ እረፍት አግኝታችሁ በአንድ ሥፍራ ብንሰባሰብ የሆነ ቦታ ተሰብስበን ስለ መቅሰፍቶቹ እነግራችሁ ነበር እንዲሁም በመጨረሻዎቹ ቀናት ስለሚፈጸሙ ነገሮች እነግራችኋለው፤ ሁለት ወይም ሶስት ሳምንት ያህል ጊዜ ብናገኝ፣ ጌታም እኔ እንዳስተምር ቢፈቅድና በሕይወት ቢያቆየኝ እነዚያ ነገሮች እንዴት እንደሚገለጡ እነዚያ ነጎድጓዶች እንዴት እንደሚመጡ እናይ ነበር። የዚያን ጊዜ ያ ሰው እና እነዚያም ሰዎች ምን ሲያልሙ እንደነበር ታውቃላችሁ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይፈጸማሉ፤ አያችሁ፤ የተገለጡት ነገሮች ምን እንደሆኑ ታስተውላላችሁ፤ እነዚያ ታላላቅ ነጎድጓዶች ከሰማይ ሲመጡ። ለነገሩ ሁላችሁም ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንደማውቅ ታውቃላችሁ። ነገር ግን ጊዜው እስኪደርስ እንጠብቅ፤ በተፈጸመም ጊዜ በራሱ ጊዜ ሲሆን ይበልጥ የተሻለ ይሆናል።

7ቱ መቅሰፍቶች ወይም ጽዋዎች የሚፈስሱበት ጊዜ እጅግ አስፈሪ ጊዜ ነው የሚሆነው።

“እነዚያ መቅሰፍቶችና ነገሮች”። “ነገሮች” የሚለው ቃል መለከቶችን ነው የሚተካው ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ሲያስተምር ጽዋዎችን ከመለከቶች ጋር አያይዞ ነው የሚናገረው፤ጽዋዎችና መለከቶች በታላቁ መከራ ውስጥ እየተፈራረቁ ነው የሚገለጡት።

“እጅግ አስፈሪ የሆኑት ጊዜዎች” ከ7ቱ ጽዋዎችና ከ7ቱ ነጎድጓዶች ጋር የተያያዙ ናቸው።

7ቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙበት ሰዓት ለሰው ልጆች በጣም መጥፎ ጊዜ ነው።

ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ብንሰማው ለእኛ እጅግ የሚከብድና የሚያንገዳግደን ወቅት ላይ ነው የሚመጡት።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ነገር ግን አስቡ፤ አሁን ይህንን እየጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ሌሎቹን ማለትም ሰባቱን ነጎድጓዶች ሊጽፍ ሲያስብ “አትጻፍ” አለው። ያየውን ሁሉ እንዲጽፍ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን ባሰሙ ጊዜ እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- “እነዚህን አትጻፋቸው።” ሚስጥራት ናቸው። ምን እንደሆኑ እስከ አሁን ድረስ አናውቅም፤ ነገር ግን ኋላ በጊዜያቸው ይገለጣሉ ብዬ አምናለው። ሲገለጡም ቤተክርስቲያን ከዚህ ዓለም የምትወጣበት ተነጥቃ የምትሄድበትን እምነት እና ጸጋ ይሰጧታል። እስከዚያው ድረስ በተገለጠልን እን በተረዳነው እንመላለሳለን፤ ባለፉት ዘመናት ውስጥ ሁሉን አይተናል። የእግዚአብሔርን ሚስጥራት አይተናል። በመጨረሻው ዘመን ሙሽራይቱ እንዴት ባለ ታላቅ ክብር እንደምትሰበሰብ ተመልክተናል። ይህም ሁሉ ሆኖ ግን እስካሁንም ድረስ ልናውቅ የማንችለው ነገር አለ። ሌላ ነገር አለ። ነገር ግን እነዚህ ሚስጥራት መገለጥ ሲጀምሩ … እግዚአብሔር እንዲህ አለ፡- “ቆይ፤ አሁን አትጻፋቸው። ጥቂት ጠብቅ። በዚያ ቀን እኔ እገልጠዋለው፤ ስለዚህ አሁን አትጻፈው፤ ምክንያቱም የሚያነቡት ይንገዳገዱበታል። ተወው፤ አትጻፈው። (አያችሁ?) ነገር ግን በዚያ ቀን ሊገለጥ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኔ እገልጠዋለው።”

በነጎድጓዶቹ ሰዓት ዓለም በታላቅ ነውጥ ትታመሳለች።

64-0209 የቀረው ጊዜ

ከነዚህ ማለዳዎች በአንዱ መላው ዓለም በጩኸት ይጥለቀለቃል፤ እንዳመለጣቸው በተረዱ ጊዜ ሁላቸውም ያለቅሳሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ። ታላቁ ንስር በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ኃይልን ተሞልቶ ክንፎቹን መዘርጋት ሲጀምር ጠፈርተኞቹ ሙሽራውን ለመቀበል ወደ ሰማይ ይመጥቃሉ፤ በእግዚአብሔር የበረራ ኃይል ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ትሄዳለች።

 

ሌላ ደግሞ አንድ ብቸኛ ታላቅ ነጎድጓድም አለ።

ስለዚህ ነጎድጓድ ያወቀውን አልገለጠውም።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ

ወደፊት የሆነ ዓይነት የማንቂያ ጥሪ ይደርሰናል።

ምናልባት የ2020ው ኮሮና ቫይረስ የማንቂያ ጥሪው ቅድሚያ እይታ ይሆናል።

ቤተክርስቲያናችሁ የተዘጋቸው እግዚአብሔር ደስ እንዳልተሰኘባት እንድታዩ ነው።

ማሕበራዊ ርቀት። ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጋችሁ አትመኑት።

ፍጹም የማይሳሳተው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

ጲላጦስ “እውነት ምንድነው?” ብሎ ከጠየቀና በኢየሱስ ላይ ከፈረደ በኋላ እጁን ታጠበ።

የሰው ንግግር ጥቅሶች እንዳንዶቹ ስሕተት እንዳለባቸው እየታወቀ ፍጹም ስሕተት የሌለባቸው እውነቶች አድርጎ መቁጠር የሜሴጅ ተከታዮች እውነትን እንደማያውቁ ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስንም ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል አድርገው ማየት ትተዋል። ስለዚህ አሁን ቫይረሱን ለመከላከል ሁልጊዜ እጃቸውን መታጠብ ግድ ሆኖባቸዋል።

እኛ ግን እየሰማን ነን?

65-0822 ክርስቶስ የሚገለጠው በራሱ ቃል ነው

ባለፈው ሳምንት በድምጽ የተቀረጹት መልእክቶች በቂ ቦታ ስናገኝ በቅርቡ የምንናገርበትን ታላቅና አሰቃቂ ነገር በተመለከተ ብዙ የሚገልጡላችሁ ነገር አለ። መልእክቱ በምድር ላይ ስለሚፈስሱት ጽዋዎች ስለ መጨረሻዎቹ መቅሰፍቶች ስለ ጽዋዎቹ መፍሰስ እና ስለ ሰባቱ ነጎድጓዶች፤ በምድርም ላይ ስለሚሆነው ቀፋፊ ክስተት ነው። ዛሬ ሰው ሁሉ የምድር ሕዝብ ሁሉ በነውጥ ውስጥ በፍርሃትና በመርበትበት ውስጥ ናቸው!

7ቱ ጽዋዎች የሚፈስሱት በታላቁ መከራ ውስጥ ሲሆን በጣም አሰቃቂ ሁኔታዎችን ያስከትላሉ።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ለመሄድ አይሁዳዊ ነብያቱን ደግሞ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ለመግባት ያዘጋጇቸዋል። ነጎድጓዶቹ ታላቅ ነውጥ በሞላበትና አስፈሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት።

65-0815 እርሱም አላወቀም

በምደር ላይ አስጸያፊ ነገሮች ይመጣሉ ብሏል። “የሴቶች ዓይነት ጸጉር ያላቸው አንበጦች” ረጅም ጸጉራቸውን የቆረጡ ሴቶችን ለማሰቃየት ብለው ነው ረጅም ጸጉር ያላቸው አንበጦች የሚመጡት። “እንደ አንበሳ ጥርስ አላቸው።” መቅሰፍቶቹን እና ማሕተሞቹን እንዲሁም ሰባቱን ነጎድጓዶች ገልጠን እስከምናያቸው ድረስ ብቻ ጠብቁ፤ ከዚያ በኋላ ምን እንደሚፈጠር ታያላችሁ። ወንድሜ ሆይ ወደ ጌሴም ለመሄድ ጊዜ ሳለ ወደ ጌሴም ብትሄድ ይሻልሃል። ከውጭ ላለው ነገር ምንም ትኩረት አትስጥ።

7ቱ ነጎድጓዶች አሰቃቂ ሁኔታዎችን ያስከትላሉ።

ረጃጅም ፀጉር ያላቸው አንበጦች የአምስተኛው መለከት አካል ናቸው።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት የቤተክርስቲያን ዘመን ሲያበቃና ታላቁ መከራ ሲጀምር ነው።

ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች መንገድ ያዘጋጃሉ፤ ይኸውም ሰባቱ መለከቶች ለአይሁድ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ እና ሰባቱ ጽዋዎች በዓለም ላይ ቅጣት እንዲያመጡ ነው።

64-0830

ምክንያቱም ስለ ሰባቱ መለከቶች አልሰበክሁም፤ እኔ የሰበክሁት ስለ መለከቶች በዓል ነው። ይህ ግልጽ ሆኖላችኋል።

 

በመለከቶች በዓል እና ራዕይ ምዕራፍ 8 እና 9 ውስጥ በተጠቀሱት መለከቶች መካከል ሰፉ ልዩነት አለ።

 

አይሁዶች የሚያከብሩት የመለከቶች በዓል ትኩረቱን የሚያደርገው በሁለት አይሁዳዊ ነብያት ላይ ነው፤ እነዚህም ሁለት ነብያት እስራኤል ውስጥ ቆመው መለከቶችን ይነፋሉ (ይህም የስብከታቸውና የልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸው ምሳሌ ነው)፤ መለከት የሚነፉት አይሁዶች ወደ እስራኤል እንዲሰበሰቡ ጥሪ ለማድረግ ነው።

ተልእኮዋቸው አይሁዶችን ሁሉ ወደ እስራኤል መጥራት ነው።

ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥

“ከነዚያ ወራት መከራ” የሚለው ቃል ኤይክማን አና ሒትለር በአይሁዶች ላይ ያመጡት የሆሎኮስት መከራ ሲሆን እርሱም የታላቁ መከራ ቅምሻ ነው።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ የነበሩ የሞት ካምፖች ውስጥ 6 ሚሊዮን አይሁዳውያን አልቀዋል።

“ፀሃይ ትጨልማለች”። መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል፤ እንደ ፍጹም ቃል የሚያየውም ሰው የለም። ኢየሱስም የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሆኑ ከቤተክርስቲያን ተገፍቶ ወጥቷል፤ ቤተክርስቲያኖችም ቃሉ ፍጹም ነው ማለትን ትተዋል። ፖፑ እና ዊልያም ብራንሐም ፍጹማን ተደርገው ተቆጥረዋል ምክንያቱም ንግግራቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ተክቷል። ስለዚህ በተወሰኑ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የካቶሊክ መንፈስ ገብቷል።

ማቴዎስ 24፡31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።

በዚህ ቃል የተገለጸው የታላቁ መከራ ዘመን ነው። እግዚአብሔር ሁለት “መላእክት” ወይም መልእክተኞችን ይልካል፤ እነርሱም ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው።

የወንጌሉ “መለከት”።

ሙሴ እና ኤልያስ የአይሁዶችን ልብ በኢየሱስ እና በአዲስ ኪዳን ወደ ማመን ይመልሷቸዋል።

አይሁዶች እስራኤል ውስጥ የሚሰበሰቡት እግዚአብሔር ከመካከላቸው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል “ከሰማይ ዳግም የተወለዱትን” 144,000 ሰዎች ለራሱ እንዲለይ ነው። እነዚህ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ ከሰማይ የተወለዱ ባሪያዎች ናቸው።

ዘሌዋውያን 23፡24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።

“መለከት” የሚለው በእንግሊዝኛ በብዙ ቁጥር ነው የተጻፈው።

ሁለቱ ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ እስራኤል ውስጥ አገልግሎት አላቸው።

እነዚህ ነብያት አይሁዶችን ወደ እስራኤልን ይጠሯቸዋል።

ሰባቱ መለከቶች ግን ከእስራኤል ውጭ የሚፈጸሙ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች ሆነው ዓለማቸው አይሁዶችን ገንዘብ እያተረፉ ከሚኖሩባቸ ሃገሮች ሁሉ ተነስተው ወደ እስራኤል እንዲመለሱ የሚያስገድዱ ናቸው።

በዚህ ጥናት 2ኛ ክፍል ውስጥ ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ መለከቶች ካስተማራቸው ትምሕርቶች ውስጥ ብዙ ጥቅሶችን ወስደን እንመለከታለን። እንዲሁም ስለ ሰባቱ ጽዋዎችም እናጠናለን።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23