ራዕይ 9 - የታላቁ መከራ ሰቆቃዎች
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ አይሁዶች በ7ቱ መለከቶች አማካኝነት ተጠርተው ወደ እስራኤል ይመለሳሉ። የጸረ አይሁድ አጋንንታዊ ዘመቻ መነሳት። የሮም አገዛዝ።
First published on the 8th of March 2022 — Last updated on the 8th of March 2022በ2020 የመጣው የኮሮና ቫይረስ (ወይም ዘውድ የጫነ ቫይረስ) የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውን?
የዓይን ሕክምና ባለሙያዎች በመሳሪያ ሲለካ 20፡20 የተባለውን የእይታ መጠን ፍጹም ነው ይላሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር በ2020 ዓ.ም እቅዱን በጥልቀት እና በግልጽ እንድናይ ያስችለናል።
በ2020 ዓ.ም የአንበጣ መንጋ ምስራቅ አፍሪካ እያወደመ ባለበት ሰዓት የኮሮና ቫይረስ መቅሰፍት በምስራቅ ከምትገኘው ቻይና ተነስቶ ምዕራቡን ዓለም ሁሉ አዳርሶታል።
እግዚአብሔር ወደ ፊት ስለሚመጣው የታላቁ መከራ ዘመን በጥቂቱ አሳይቶን እያስጠነቀቀን ይሆን?
5ኛው መለከት ሲነፋ የታዩት ዘውድ የጫኑ አውዳሚ አንበጣ የሚመስሉ አጋንንት ናቸው።
6ኛው መለከት ሲነፋ ደግሞ ፈረሰኞች የሚመስሉ ከምስራቅ የሚመጡ አጋንንት ይታያሉ።
እኛ ቅድሚያ የምናየው ኮሮና ቫይረስ ነው። ይህም ሁላችንን ሊያጠፋ የዛተ ከምስራቅ የመጣ ዘውድ የጫነ ቫይረስ ነው።
ይህም እንቅልፋቸውን ለተኙት ለልባሞቹ እንዲሁም ለሰነፎቹ ቆነጃጅት የማንቂያ ጥሪ ነው። ሴት ቤተክርስቲያንን ነው የምትወክለው።
አስሩም ሴቶች በሙሉ አንቀላፍተዋል። ይህም በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ያሉ ሁሉ አንቀላፍተዋል ማለት ነው።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
ራዕይ ምዕራፍ 8 እና 9 የሚናገሩት ስለ ሰባቱ መለከቶች ነው።
ሰባቱ መለከቶች በታላቁ መከራ ዘመን አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ የሚያስገድዱዋቸው ከተፈጥሮ ኃይል በላይ የሆኑ ክስተቶች ናቸው።
ሰባቱ መለከቶች ሙሽራይቱን አይመለከቷትም ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ትነጠቃለች።
እነዚህ ሰባት መለከቶች ከ7ቱ የአይሁድ ሐይማኖታዊ በዓላት መካከል 5ኛ በሆነው በመለከቶች በዓል ተመስለዋል።
መለከቶቹ እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች እንደገና መመለሱን ያመለክታሉ፤ ይህም የሚሆነው በጴንጤ ቆስጤ ቀን የተጀመሩት የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲጠናቀቁ ነው።
ዘሌዋውያን 23፡24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።
በአይሁድ የወር አቆጣጠር ውስጥ ሰባተኛው ወር ማለት በእኛ በአሕዛብ ዘንድ ጥቅምት ተብሎ የሚጠራው ነው።
አይሁዶች መለከቶችን የሚነፉበት ልዩ ቀን አላቸው፤ ይህም በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የተፈጥሮ ኡደትን የሚያቋርጡት ልዕለ ተፈጥሮአዊ የሆኑ መለከቶችን የሚያመለክት ነው።
ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸው ተጠቅመው 144,000ውን የተመረጡ ሰዎች ለመሰብሰብ ወንጌልን ይዘው ወደ እስራኤል ይሄዳሉ።
ለእነርሱ ዋነኛ ጠላታቸው የሚሆነው የመጨረሻው ከአሕዛብ መካከል የሚነሳው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ነው። እርሱም ካርዲናሎቹ ሳይሾሙት በራሱ ጉልበት የፖፕነት ስልጣንን ነጥቆ ይይዛል።
ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።
የመጨረሻው ፖፕ፣ ስሙ ምናልባት ፖፕ ጴጥሮስ ዳግማዊ ወይም 2ኛው ሊባል የሚችል ሲሆን በዓለም ዙርያ 1.4 ቢሊዮን ተከታዮች ያሉዋትን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስለ መንፈሳዊ ስልጣኗ ብሎ ይጠቀምባታል፤ እንዲሁም የዚህችን ሐይማኖታዊ ድርጅት ስፍር የሌለው ሃብት ለራሱ ዓላማ ያውላል።
ወታደራዊ ኃይል የሚያገኘው ከአስር ፈላጭ ቆራጮች ነው።
ዳንኤል 8፡24 ኃይሉም ይበረታል፥ ነገር ግን በራሱ ኃይል አይደለም፤ በድንቅም ያጠፋል፥ ያደርግማል፥ ይከናወንማል፤ ኃያላንንና የቅዱሳንን ሕዝብ ያጠፋል።
የመጨረሻው ፖፕ የራሱ የሆነ ወታደራዊ ኃይል የለውም። ስለዚህ የአስሩን ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ወታደራዊ ኃይል ይጠቀማል፤ ከዚያም እስራኤልን በጦርነት አሸንፎ 144,000ዎቹን ዳግመኛ የተወለዱ አይሁዳውያን እንዲሁም ሁለቱን ነብያቶቻቸውን ይገድላል።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
“እንደ ነገሥታት ስልጣን”። እነዚህ የንጉስ ስልጣን አላቸው ግን ዘውድ አልጫኑም። እነዚህ ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
እነዚህ አስር ፈላጭ ቆራጮች ሕዝቦቻቸውን በንጉሳዊ ስልጣን ጨቁነው ይገዛሉ። ነገር ግን ሰይጣን ገዥ አድርጎ ላስነሳው ሰው ማለትም ለመጨረሻው ፖፕ ታዛዥ ይሆናሉ።
ይህ ሰው የዓለምን ስልጣን የመቆጣጠር ፍላጎቱን ካሳካችለት በኋላ ቫቲካንን በኑክሊየር ቦምብ ደብድቦ ያጠፋታል። በዚህ መንገድ ሮም ከወደመች በኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚው እኔ እግዚአብሔር ነኝ ለማለት ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዳል።
ራዕይ 17፡16 ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።
ይህች ክፉ ሴት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋነኛ ማዕከል የሆነችዋ ቫቲካን ከተማ ናት።
ራዕይ 18፡9 ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤
10 ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው፦ አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
ተራ የዕሳት አደጋ በተነሳ ጊዜ ሰዎች ለማጥፋት ይሯሯጣሉ። ነገር ግን አደገኛ የኑክሊየር ጨረር በተነሳ ጊዜ ሁሉም ርቀው ይቆማሉ።
ሰይጣን በቫቲካን ከተማ ከተጠቀመባት በኋላ ዙፋኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዛወር ቫቲካንን በቦምብ ያጠፋታል። ሰይጣን እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሞክር ኮራጅ ነው። ዲያብሎስ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ከተማ መሆኗን ያውቃል።
2ኛ ነገስት 21፡4 እግዚአብሔርም፦ ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ ባለው በእግዚአብሔር ቤት መሠዊያዎችን ሠራ።
በታላቁ መከራ ውስጥ ከአይሁዶች ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ይገደላሉ።
ከዚያም የሚቀሩትን አንድ ሶስተኛ ቅሬታዎች ለማዳን ኢየሱስ ይገለጣል፤ እነርሱም በሚሌኒየሙ ወይም በ1,000 ዓመት መንግስቱ መጀመሪያ ላይ በሕይወት የሚኖሩ የአይሁድ ነገዶች ይሆናሉ።
በዚህ ጊዜ ነው አይሁዶች እግዚአብሔር ለአብርሃም ሊያወርሰው ቃል የገባለትን ሙሉውን ግዛት የሚወርሱት።
ይህም ግዛት ከሜዲተራንያን ባሕር ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ የሚደርስ ግዛት ነው።
ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።
9 ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ከአይሁዳውያን አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ከታላቁ መከራ ተርፈው ወደ ሺ ዓመት የሰላም መንግስት ይገባሉ።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
የመጨረሻው ፖፕ ኢየሩሳሌምን ይቆጣጠርና ለሚመሰርተው አንድ የዓለም ሐይማኖት እና አንድ የዓለም መንግስት ማዕከል አድርጎ ይጠቀማታል።
ታላቅ ውድመት በሚከናወንባቸው የታላቁ መከራ ዓመታት ውስጥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ጥበቃ ያደርጋል።
ራዕይ 11፡3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ወር 30 ቀናት ስለሆነ 1,260 ቀናት ማለት 42 ወራት ነው።
42 ወራት ማለት 3½ ዓመታት ሲሆን ይህም ታላቁ መከራ የሚፈጀው ጊዜ ነው።
ሁለቱ ምስክሮች ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው።
ኤልያስ ለ3½ ዓመታት በምድር ላይ ድርቅን አምጥቷል።
ያዕቆብ 5፡17 ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
ራዕይ 11፡6 እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።
ኤልያስ የ3½ ዓመታት ድርቅ በምድር ላይ ለማምጣት ተመልሶ ይመጣል።
ሙሴ ከ3,600 ዓመታት በፊት ግብጽ ውስጥ ውሃን ወደ ደም ለውጧል። በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ይህንን ተዓምር በድጋሚ ያደርገዋል።
ዘጸአት 7፡20 ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ።
እነዚህ ሁለት ነብያት አይሁዶችን ወደ ጉባኤ ለመሰብሰብ የሚያገለግሉትን ሁለቱን መለከቶች ይወክላሉ።
ዘኁልቁ 10፡2 ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።
እነዚህ ሁለት ነብያት በተፈጥሮ ላይ ያላቸውን ኃይል ተጠቅመው አይሁዶችን ወደ እስራኤል ይጠራሉ፤ ክርስቶስን እስኪያገኙና መንፈስ ቅዱስንም እስኪቀበሉ ድረስ ለ144,000ዎቹ ጥበቃ ያደርጉላቸዋል።
የብሉይ ኪዳኑ የመለከቶች በዓል አይሁዳውያን እስራኤል ውስጥ የመሰባሰባቸው ጥላ ነው።
ይህን ተከትሎ የሚከበረው የስርየት ቀን በዓላቸው ሲሆን ይህም አንቀበልህም ብለው የገፉት ክርስቶስ እርሱ ራሱ የተሰቀለላቸው መሲህ መሆኑን ሲያውቁ የሚያዝኑትን ሃዘን የሚያመለክት ጥላ ነው።
ዘሌዋውያን 23፡27 በዚህ በሰባተኛው ወር አሥረኛው ቀን የማስተስረያ ቀን ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት ቍርባንን አቅርቡ።
ዓይኖቻቸው የሚከፈቱበት ቁጥር 10፡7 ነው።
ራዕይ 10፡7 ዊልያም ብራንሐም ለተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ዓይናችንን የከፈተበትን አገልግሎት የሚገልጽ ቃል ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ቃል እራሱ እግዚአብሔር ነው።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚገልጥልን መልእክተኛ ወይም መልአክ ያስፈልገናል።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ቤተክርስቲያን ያረበችው አማራጭ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችንና ዲኖሚኔሽኖችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ ከ100 በላይ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። ይህም ደግሞ መንፈሳዊ እውነትን ለሚፈልግ ሰው የትኛው እውነት እንደሆነ ለመለየት አስቸጋሪ እንዲሆንበት ያደርጋል።
ራዕይ 9፡1 አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።
ሉቃስ 10፡18 [ኢየሱስም] እንዲህ አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።
ሰባቱ መለከቶች ድምጻቸው የሚሰማው በታላቁ መከራ ውስጥ ነው።
ስለዚህ እውነተኛዋ ሙሽራ መለከቶቹን አታያቸውም።
ነገር ግን ከታላቁ መከራ በፊት አስቀድመው በሚመጡት ቀናት ውስጥ ምን እንደሚከሰት እናውቅ ዘንድ እግዚአብሔር የታላቁን መከራ ቅድመ ዕይታ ይሰጠናል።
ማቴዎስ 24፡29 ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
“ከዚያች ወራትም መከራ” የሚለው ስለ ታላቁ መከራ የሚናገር አይደለም።
ይህ የታላቁ መከራ ቅምሻ ነው፤ የታሪክ ምሑራንም የአይሁዶች እልቂት ከ1039-1945 ብለው ይጠሩታል።
ማቴዎስ 24፡30 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥
ይህ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም አሪዞና ውስጥ ፍላግስታፍ አጠገብ ፎቶግራፍ የተነሱት መላእክት የፈጠሩት ደመና ነው።
እግዚአብሔር ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ከተጠቀሱት ከ7ቱ ማሕተሞች መካከል 6ቱን ሊገልጥ ጊዜው መቅረቡን የሚያሳይ ምልክት ነበረ።
7ተኛው ማሕተም ከኢየሱስ ዳግም ምጻት ጋር የተያያዘ ስለሆነ እስከ ዛሬ ድረስ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ይህም በዓለማችን ውስጥ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ ታላቁ ሚስጥር ነው።
ወንድም ብራንሐም አስደናቂ እውነታ ገለጠ።
ማቴዎስ 24፡29 ናዚ ጀርመኒ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት 6 ሚሊዮን አይሁዳውያንን የጨፈጨችበትን እልቂት በተመለከተ የሚናገር ጥቅስ ነው። ይህ በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ በፍጠረታዊ አምባገነኖች በተለይም በሒትለር አማካኝነት የመጣ ቅምሻ መከራ ነው። ይህም ቅምሻ መከራ የመጣው ሙሽራይቱ ወደፊት የሚመጣው ታላቅ መከራ ምን የሚመስል እንደሚሆን ግንዛቤ እንድታገኝ ይረዳት ዘንድ ነው።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
እኛም ይህን ተቀብለነዋል፤ በዓለም ውስጥም የለም፤ አለ ብዬ አላምንም ነገር ግን እነዚያ አይሁዶች በቅድመ ታላቅ መከራ ወቅት ውስጥ አልፈዋል። በዚህ በመጨረሻ ጦርነት ወቅት እነርሱ -- በዚያ ጊዜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠሉ ይሆናሉ። አይክመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አይሁዶችን ጀርመኒ ውስጥ ገደለ (ያው ችሎቱን በቅርቡ ተከታትላችኋል) ብዙ ሚሊዮን ንጹሃን አይሁዶች ተገድለዋል፤ የተገደሉትም አይሁድ ስለሆኑ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለም።
… ስለዚህ አይክመን ብዙ አይሁዶችን በገደለበት ቅደመ ታላቅ መከራ ውስጥ ያለፉ ሰማእታት። እነዚህ የመቶ አርባ አራት ሺዎቹ ሰማእታት ጥላ ናቸው፤ ይህንንም በስድስተኛው እና በሰባተኛው ማሕተም ውስጥ ነው የምናየው።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
አሁን ይህን ስሙ። ይህ ኢየሱስ በማቴዎስ 24፡29 እና 30 የተናገረው ነው።
ከነዚያ የመከራ ወራት በኋላ … (ይህ መከራ፤ ይህ ቀላል መከራ፤ እነርሱ ያለፉበት መከራ፤ አያችሁ?) ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ … የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤
ማቴዎስ 24 ውስጥ የተጻፈውን ቃል እንመልከት።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
… በጣም ፍጹም ነው። ኢየሱስ ማቴዎስ 24፡29 ውስጥ ምን ብሎ እንደተናገረ በድጋሚ ተመልከቱ። ከዚህ አይክመን ካደረገው ነገር በኋላ።
ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ … ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ … የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ፤ (አሁን ልብ በሉ።)
በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤
ከዚህ በታች የወሰድነው ቀጣዩ ጥቅስ ወንድም ብራንሐም በቱክሰን የጠፈር ምርምር ጣቢያ አማካኝነት ፌብሩሪ 28 ቀን 1963 ከምድር 42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ፎቶግራፍ ስለተነሳው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ነው የሚናገረው።
ደመናው በተፈጥሮ ደመናዎች ሊኖሩ ከሚችሉበት ከፍታ በጣም የራቀ ነበር። ከዚህም የተነሳ የከባቢ አየር ሳይንስ ሕጎችን በሙሉ ጥሷል። ከባቢ አየር ሰማይ ይባላል።
1965-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። ዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል። እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በልዩ ልዩ ሥፍራዎች የምድር መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማያት ላይ ይታያል። ”
ይህን የተናገረው ከመሞቱ አምስት ወራት በፊት ሲሆን ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ደመና “ሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ” ብሎታል። ደመናው በተፈጥሮ የተገኘ ደመና ነው እንዳይባል እጅግ በጣም ከፍ ብሏል። ከምድር ከ20 ኪሎሜትር ከፍታ በላይ ደመና ለመፍጠር የሚበቃ የውሃ ትነት የለም።
54-0513 የአውሬው ምልክት
ይህ ሶስተኛው መልአክ ለዓለም ሁሉ ያመጣው መልእክት ነው። የሶስተኛው መልአክ መልእክት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ይህ መልእክት አሁን በዚህ ዘመን እየታወጀ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ከሆናችሁ ይህ በሰማይ ላይ የሚበርረው የሶስተኛው መልአክ መልእክት ነው።
ይህን መልእክት ተከትሎ ሶስት ወዮዎች ይመጣሉ። የመጀመሪያው ወዮ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ አልፏል።
ሁለተኛው ወዮ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት መጥቷል።
አሁን ምን ውስጥ እየገባን እንዳለን ታያላችሁ። እሺ። አሁን በመንገዱ መጨረሻ ላይ ነው ያለነው።
በአምስተኛው መለከት መጨረሻ ላይ የታላቁ መከራ የመጀመሪያው ወዮ ያልፋል።
ራዕይ 9፡12 ፊተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ከዚህ በኋላ ገና ሁለት ወዮ ይመጣል።
የታላቁ መከራ የመጀመሪያ ወዮ ቅምሻችን ከ1914-1918 የተደረገው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ነው።
ስድስተኛው መለከት በታላቁ መከራ ውስጥ የሚመጣውን ሁለተኛውን ወዮ ነው የሚገልጸው።
የታላቁ መከራ የሁለተኛው ወዮ ቅምሻችን ከ1939-1945 የተደረገው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው።
ራዕይ 11፡14 ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል።
በ1918 እና በ1939 ማለትም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና በሁለተኛ የዓለም ጦርነት መካከል 21 ዓመታት ነበሩ።
ስለዚህ የሶስተኛው ወዮ ቅምሻ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ በፍጥነት በ21 ዓመታት ውስጥ መጣ።
1945 + 21 = 1966
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተጀመረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጦር ምርኮኞች እስር ቤት ውስጥ ነው። በእስር ቤት ውስጥ በነበሩበት ሰዓት ከተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች የመጡ አማኞች መተባበር ጀመሩ።
በ1948 የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በይፋ ሥራውን ጀመረ። ይህም ዓመት እስራኤል ነጻነቷን ያወጀችበት ዓመት ነበር።
በእልቂቱ ጊዜ ከጥንቱ የሮማ መንግስት የመጡ አሳዳጅ አጋንንት በአይሁዶች ላይ ተለቀቁባቸው። ይህም በ70 ዓ.ም አረማዊው የሮማ ጀነራል ታይተስ ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን ባፈረሰ እና 1,100,000 አይሁዶችን በገደለ ጊዜ የጥፋት አጋንንትን እንደለቀቃቸው ዓይነት ነው።
ከዚያም በ1948 ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲጠናቀቅ አይዳውያንን መግደል እንዲያቆሙ የተገደዱት እነዚህ ክፉ ነፍሰ ገዳይ መናፍስት የዊልያም ብራንሐምን አገልግሎት ለመቃወም እንዲያመቻቸው ወደ ዓለም የአብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ውስጥ ገቡ፤ ዊልያም ብራንሐም የሰባተኛውና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ነበረ። እርሱ ያመጣቸውን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተገኙ መገለጦችን የቤተክርስቲያን አባላት እንዳይሰሙ በማድረግ ቤተክርስቲያንን ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ ማቆየት ችለዋል።
ወንድም ብራንሐም ይዞት የመጣውን የመጨረሻ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥን አልቀበልም እንዲሉ በማድረግ እነዚህ ጨካኝ መናፍስት ቤተክርስቲያኖች ለስሕተት እና ለሰዎች አመራር ባሪያ ሆነው እንዲገዙ አድርገዋል። ከዚህም የተነሳ በዚህ ዘመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች እንደ መንፈሳዊ ልጆች ሆነው የጥንቷ ቤተክርስቲያን የመሰረቷት የአዲስ ኪዳን አባቶች ይከተሉት ወደነበረው ወደ ሐዋርያዊ እምነት እንዳይመለሱ አድርገዋቸዋል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
እርግማን ለረጅም ዘመን ይቆያል። ይህ እርግማን ከምድር ላይ ሳይጠፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆየው በ1945 ሒሮሺማ እና ናጋሳኪ በተባሉ የጃፓን ከተሞች ላይ የወደቀው የአቶሚክ ቦምብ ሬድዮ አክቲቭ ጨረር ነው። ይህም ወደፊት ሊመጣ ስላለው ስለ ታላቁ መከራ የሚናገር የመከራ ቅምሻ ነው።
ወንድም ብራንሐም ከ1947 – 1965 ያገለገለውን አገልግሎት ባለመቀበላቸው የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን መሪዎች የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት ወይም የቤተክርስቲያን አባላት ወደ ታላቁ መከራ እንዲገቡና እንዲገደሉ እያዘጋጁዋቸው ነው።
ይህም ሙሽራይቱ በሶስተኛው ፍልሰት ከቤተክርስቲያን በምትወጣበት ጊዜ የሚፈጸመው የሕጻናት እልቂት ነው።
አይሁዶች ከግብጽ የወጡበትን የመጀመሪያውን ፍልሰት ሙሴ መራ ጊዜ ፈርኦን ሕጻናት እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጠ።
ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት የወጣችበትን ሁለተኛውን ፍልሰት ኢየሱስ በመራ ጊዜ ሔሮድስ ሕጻናትን ገደለ።
ስለዚህ ስለ ታላቁ መከራ ግንዛቤ ለማግኘት ሙሽራይቱ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጻፉ ትንቢቶች መካከል የተወሰኑት ውስን በሆነ ደረጃ ሲፈጸሙ በቅድሚያ ታያለች።
ሶስቱ ወዮዎች።
የመጀመሪያው ወዮ በ1ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገደላቸው የተነሳ ከተቀሰቀሰው ቁጣ ውስጥ የወጡ አምባገነን መናፍስት በምድር ላይ መነሳታቸው ነው። ይህን ከ1918 – 1919 ተከትሎ ዓለም ሁሉ ላይ በመጣው እስፓኒሽ ፍሉ የተባለው የጉንፋን ወረርሽኝ አማካኝነት ከ60 እስከ 100 ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። ሌኒን፣ ሙሶሊኒ፣ እስታሊን፣ እና ሒትለር የተባሉ አምባገነኖች የዓለም መሪዎች ነበሩ።
2ኛው ወዮ ደግሞ እንደ ፍጥረታዊ አምባገነን ሒትለር በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ የለቀቃቸው ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ናቸው።
3ኛው ወዮ አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የዲኖሚኔሽኖችና የቤተክርስቲያኖች ወደ አንድ የዓለም ሐይማኖት ስርዓት ለመምጣት መሰባሰባቸው ነው። እነዚህ አሳዳጅ መናፍስት በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተሰግስገው ተደብቀው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እየተቃወሙ በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ይሾማሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ትክክል ያልሆኑ ሃሳቦቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሲያሳዩዋቸው እንዴት እንደሚቆጡና እንደሚናደዱ አስተውሉ። ስሕተትን ለመቀበል እምቢ የሚሉ ሰዎች በጭካኔ ይባረራሉ። ከዚያ በኋላ ሁሉም ስማቸውን ያጠፋሉ።
እንደዚሁ ደግሞ እጅግ ብዙ የሜሴጅ አማኞች የወንድም ብራንሐምን መልእክት ቸል ይላሉ፤ ያጣጥላሉ፤ ሲፈልጉ ያጣምማሉ፤ ከዚህም የተነሳ እምነቶቻቸው ትክክል መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማሳየት ያቅታቸዋል። ጥቅሶችን አገናኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ማብራራት ስለሚያቅታቸው ከሚመጣው ታላቅ መከራ መዳን አይችሉም።
65-0429 የሙሽራይቱ መመረጥ
ዛሬ የምናያት ዘመናዊ ቤተክርስቲያን ዓለማዊ ቤተክርስቲያን ናት። ዘመናዊቷ ዓለማዊ ቤተክርስቲያን እንዲሁም መንፈሳዊቷ ቤተክርስቲያን ሁለቱም ጸንሰው ወንድ ልጅ ይወልዳሉ።
ከሁለቱ አንዷ ዲኖሚኔሽናዊ ልጅ ትወልዳለች፤ ከነዚህ ቀናት በአንዱ ቀን በቅርቡ ትወልዳለች፤ ይህም የሚሆነው የዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ላይ በሚደረገው ስብሰባ ምክር ቤቱ በዲኖሚኔሽን በኩል የክርስቶስ ተቃዋሚውን ለዓለም ሲወልድ ነው። ይህ እውነት ነው። እኔ ይህ እስኪሆን ድረስ በሕይወት ላልኖር እችላለሁ። እናንተ አሁን ወጣቶች የሆናችሁ ግን ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ አንድ አገልጋይ አስቀድሞ መናገሩን አስታውሱ። መጨረሻው በዚህ መንገድ ነው የሚመጣው። ቤተክርስቲያን የዓለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤትን ባቋቋመች ጊዜ የአውሬው ምልክት ይመጣል። እረሷም ልጇን ማለትም የክርስቶስ ተቃዋሚውን ትወልዳለች።
ሌላኛይቱ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ግን በእግዚአብሔር ቃል ነው የምትጸንሰው፤ እርሷም አንድ አካል ማለትም ተሰርቶ የተጠናቀቀውን የክርስቶስን አካል ትወልዳለች፤ ይህም የተጠናቀቀው አካል ሙሽራይቱ ናት። የክርስቶስ አካል እስካሁን ተሰርታ አልተጠናቀቀችም። ስንት ናችሁ ይህን የምታውቁ ስንቶች ናችሁ? ወንድ እና ሴት አንድ ናቸው። ክርስቶስም ማለትም ቃሉ አንድ አካል ነው። ሁለቱ እንደገና አንድ አካል ይሆናሉ። በመጀመሪያው አዳም እንደነበረው ሰው እና ሚስቱ አንድ ናቸው።
ስለዚህ ራሷን ሙሉ በሙሉ ለክርስቶስ የሰጠችው እውነተኛይቱ ሙሽራ በራሷ ሃሳብ አትመራም።
የእርሱ ሃሳብ ፈቃዱ ነው፤ ፈቃዱ ደግሞ ቃሉ ነው።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ይገናኛሉ ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስን አያወቁም ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰሙት ትምሕርት በኪንግ ጄምስ ቨርዥን ከተጻፈው ቃል የራቀ ነው።
በታላቁ መከራ ውስጥ የሲኦል ጉድጓድ እራሱ ይከፈታል።
የዚህንም ቅምሻውን ማየት ጀምረናል።
ለምሳሌ በታላቁ መከራ ውስጥ ዓለም ሲኦልማ በሆነ እሳት የምትጠፋው እንዴት ነው?
2ኛ ጴጥሮስ 3፡6 በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤
በኖኅ ዘመን እግዚአብሔር ዓለምን በውሃ አጥፍቷል።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡7 አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።
አሁን ያለው ዓለም በኑክሊየር ቦምብ፣ በሚሳኤሎች እና በእሳተ ገሞራ ተቃጥሎ ሊጠፋ እየተጠበቀ ነው።
በ1945 አቶሚክ ቦምብ መፈጠሩን ተከትሎ በ1952 ከአቶሚክ ቦምብ 1,000 እጥፍ አደገኛ የሆነው የሃይድሮጅን ኑክሊየር ቦምብ ተፈጠረ።
አሁን ሊፈጸም የሚችለውን የኑክሊየር ቦምብ ፍንዳታ ጴጥሮስ በቃል ገልጾታል።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡12 የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
አልበርት አይንሽታይን E = mc2 የተባለውን ቀመር አዘጋጀ፤ ይህም ቀመር ኋላ አቶሚም ቦምብን ለመፍጠር አገለገለ።
የ1960ዎቹ ትውልድ ምንም የስነ ምግባር ሕገ የሌለው ትውልድ ነበረ። በዚያ ዘመን ወንድና ሴት ያለ ጋብቻ አብረው ይኖሩ ነበር። ጽንስ ማስወረድ፣ ፍቺ፣ እንደገና ማግባት የተለመዱ ሆኑ። የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣ የግብረ ሰዶማውያን መብት፣ ወጣቶች በወላጆቻቸው ላይ አመጸኛ እንዲሆኑ ያደረገ ሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃ ሁሉ የዚያ ዘመን ውጤቶች ናቸው።
ታላቅ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነው አይሁዳዊ ሳይኮአናሊስት ሲግመንድ ፍሮይድ የሥነ ምግባርንና የጨዋነት መርሆችን አጣጣለ።
ሙዚቃዎችም የሚያስደንሱ ሆነው ጀምረው ወደ አስጸያፊ ነገሮች እየተለወጡ ሄዱ።
1965-0711 ማፈር
ድሮ ድሮ የአፍሪካ ጫካዎች ውስጥ አውሮፓውያን ለአደን ሽርሽር ሲሄዱ የኤልቪስ ፕሬስሊ እና የፓት ቡን ዘፈኖችን እንዲሁም የሮክ ኤን ሮል ሙዚቃዎችን ለማዳመጥ ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ሬድዮዎች ተሸክመው ይሄዱ ነበር። አፍሪካውያኑም ፈረንጆቹ ሲደንሱ ጭንቅላታቸውን ሲንጡ ለማየት ይሰበሰቡ ነበር። አያችሁ፤ ነገር ግን እነርሱ እንደ ፓት ቡን እና እንደ ኤልቪስ ፕሬስሊ እና እንደ ሪኪ ኔልሰን አሜሪካውያን አይደሉም። ይሁዳዎችም አይደሉም፤ ነገር ግን … ያው መንፈስ ነው። ደግሞም መንፈሱ አሜሪካ ውስጥ ብቻ አይደለም፤ ሰዎችን ሁሉ ሰብስቦ ወደ አርማጌዶን ጥርነት ሊያዘምት መንፈሱ እራሱን በዓለም ዙርያ ሁሉ አሰራጭቷል። ምንም ይሁኑ ምን እንደዚያው ነው አኳኋናቸው… ከየትም ሃገር ይሁኑ ከአፍሪካ፣ ከሕንድ ያ ብልግናቸው በምድር ሁሉ ተዳርሷል፤ የተዳረሰውም አንድ ሰው ስለጀመረው ብቻ ነው።
ይህ የዳንስ ሙዚቃ ወጣት ልጆች ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ እንዲሆኑ፣ መጠጥ እንዲጠጡ፣ እንዲያጨሱ፣ የተለያዩ ዕጾችን እንዲጠቀሙ እና ከጋብቻ በፊት ወሲብ እንዲፈጽሙ ገፋፋቸው።
የዲስኮ ዳንኪራ ሙዚቃዎች በዓለም ዙርያ ሲሰራጩ ቸል ብለን እናያለን። ይህ ዓይነቱ ክፉ መንፈስ እየተስፋፋ መሄዱ ምንም አላሳሰበንም።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ድራም የተባለ ሙዚቃ መሳሪያ አንዴም አልተጠቀሰም። ነገር ግን በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ድራም እየተጫወቱ ነው የሚያመልኩት። ይህም እግዚአብሔር በጭራሽ ያልፈለገው ነገር ነው።
የምስራቅ ሐይማኖት መሪዎች በሃሳባቸውና በትምሕርታቸው “ካንሰር” ምዕራቡን ዓለም እየወረሩ ናቸው።
የሴቶች ልብሶች ከጎን እና ከኋላ በሚደረጉ ቅዶች ይበልጥ ገላቸውን የሚያጋልጡና ቆዳቸውን እስኪያሳዩ ድረስ ስስ እየሆኑ መጥተዋል። በዚህ ዘመን ሴቶች ባሎቻቸው ላይ አለቆች እየሆኑ መጥተዋል፤ ደግሞም ሱሪ መልበስ አብዝተዋል።
እየተባባሰ የመጣው የስነ ምግባር ውድቀት የማሕበረሰብ እና የቤተሰብን መሰረት እያናጋው ነው።
ካርል ማርክስ የተባለ አይሁዳዊ የፈጠረው የኮምዩኒዝም ቲዎሪ በራሺያ እና ቻይና ውስጥ እጅግ ክፉ ደም አፍሳሽ መንግስታትን ወለደ። ይህ ቲዎሪ ዓለም በሁለት የቀዝቃዛ ጦርነት ጎራዎች እንድትከፈል አደረጋት። እነዚህም ጎራዎች ካፒታሊዝም እና ኮምዩኒዝም ናቸው። የጦር መሳሪያ የማከማቸት ውድድሩ ተጧጧፈና ብዙ የኑክሊየር ሚሳኤሎች ተዘጋጅተው ተቀመጡ፤ እነዚህም የታላቁን መከራ እሳት በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
እኛ የማናስተውል የሰው ልጆች ራሳችንን ለማጥፋት የሚበቃ ሚሳኤል አከማችተናል።
ኢሳይያስ 14፡12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ!
ራዕይ 9፡2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።
ጉድጓዱ ማለት በተጻፈው ቃል ላይ ያልተመሰረተ ማንኛውም የስሕተት ትምሕርት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጭስ እይታን ይጋርዳል።
እንደ ክሪስማስ፣ ስላሴ፣ ወይም ያልተጻፉት ሰባት ነጎድጓዶች የተናገሩትን ቃላት ደግፋችሁ መሞገት ከጀመራችሁ ከዚያ ወዲያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ብዙ ቃላትን መጠቀም ግድ ይሆንባችኋል። ይህም ቀድሞ የነበረውን ግራ መጋባት እያባባሰው ይሄዳል።
በሲኦል ውስጥ የሚነድደው የእቶን እሳት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ብዙ የትምሕርት ጭሶችን ያመነጫል። ይህም ሰዎች ብርሃናችን የሆነውን የተጻፈውን ቃል ማየት እንዳይችሉ ዓይናቸውን ይጋርዳል።
ፀሃይ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ ናት። ቤተክርስቲያኖች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ባላቸው ግንዛቤ ብዙ ተሳስተዋል። ብዙ ጥቅሶች ቸል በተባሉ እና በተለወጡ ቁጥር የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን እየጨለመ ይሄዳል። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ድሆች በሆኑበት መጠን እምነት እና መጽሐፍ ቅዱስን ለመታዘዝም የሰዎች ፈቃደኝነት እየቀነሰ ይሄዳል።
ይህ ሁሉ በታላቁ መከራ ውስጥ ከዚህ እጅግ በከፋ መጠን የሚሆኑ ነገሮችን የሚያሳይ ቅምሻ ነው።
ራዕይ 9፡3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።
እንደ ጭስ ደመና ሰዎችን በጋረዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ውስጥ ተደብቀው የሚመላለሱ መንፈሳዊ አንበጦች አሉ። እነዚህ አንበጦች የጊንጥ መናደፊያ ያላቸው ስለሆኑ ፍጥረታዊ አንበጦች አይደሉም።
ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።
ፍጥረታዊ አንበጦች አረንጓዴ ተክሎችን ይበላሉ። እነዚህ ግን ፍጥረታዊ አንበጦች አይደሉም። እነዚህ አጋንንታዊ መናፍስት ናቸው።
የእግዚአብሔር ማሕተም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
ኤፌሶን 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችሁ ምልክቱ የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል አንብባችሁ መረዳት መቻላችሁ ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መረዳት የማይችል ሰው ሁሉ በውስጡ መንፈስ ቅዱስ የለም፤ ከዚህም የተነሳ በአጋንንት ሽንገላ ለመታለል የተጋለጠ ነው።
ኢየሱስ ስለ ዘመን መጨረሻ በጠየቁት ጊዜ ጠንከር ያለ መልስ ነው የሰጣቸው።
ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ዛሬ ግን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ራሳቸውን፣ ቤተክርስቲያናቸውንና ፓስተራቸውን በማድነቅ ተሞልተው እየተደሰቱ ይኖራሉ።
ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ብዙም አያሳስባቸውም።
የቤተክርስቲያን አባል ከመሆናቸው የተነሳ ምንም ችግር የማይገጥማቸው ይመስላቸዋል። እንዲህ ብለው የሚተማመኑትም በቋሚነት ቤተክርስቲያን ስለሚሄዱ እና ፓስተራቸው የተናገረውን ሁሉ ስለሚያምኑ ነው። ይህን ያህል ነው ራሳቸውን ያታለሉት።
ፊልጵስዩስ 2፡12 … በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች ከመኖራቸውና የተለያዩ ሆነው ሳሉ ሁሉም እኔ ትክክል ነኝ ከማለታቸው አንጻር በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ በጣም ብዙ ስሕተት መኖሩን አያስተውሉም።
ከጥልቁ ጉድጓድ የወጡ እነዚህ አጋንንት ተልዕኮ አላቸው።
ራዕይ 9፡5 አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።
አጋንንት ሰውን መግደል አይችሉም። ነገር ግን በአሰራራቸው የሰዎችን አእምሮ ማሰቃየት ይችላሉ። ይህም ስቃይ የሚመጣው ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ላይ መሆናቸውን ባስተዋሉ ጊዜ ነው።
ኮሮና ቫይረስ ዲሴምበር 2019 ቻይና ውስጥ በዱር አራዊት የምግብ ገበያ ውስጥ ተነሳ።
ራዕይ 13 ስለ ሁለት አውሬዎች ይናገራል። “ፌሮን” የሚለው የግሪክ ቃል የዱር፣ ለማዳ ያልሆነ፣ አውሬ የሆነ ማለት ነው። እንደዚህ ዓይነት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ባስቀመጠላቸው ገደብ ውስጥ መቆየት አይችሉም።
የአጋንንት አሰራር ሁሌም ቢሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውጭ ይዞን ይሄዳል።
ኮሮና ቫይረስ በ3½ ዓመት ታላቅ መከራ ውስጥ ለአምስት ወራት ሰዎችን የሚያሰቃዩት የአንበጣ መንጋዎች ቅምሻ ነው።
ራዕይ 9፡6 በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ አያገኙትምም፥ ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።
በዛሬው ዓለም ውስጥ ድባቴ ከፍተኛ ማሕበራዊ ችግር ሆኗል። በአጋንንት አሰራር ውስጥ መሳተፍ ድባቴ ያስከትላል፤ ድባቴ ውስጥ የገቡ ሰዎች ደግሞ በቀላሉ እንደ መፍትሄ የሚያስቡት ራስን መግደል ነው።
በየዓመቱ 800,000 ያህል የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን እየገደሉ ይሞታሉ፤ ይህም በየ40 ሰከንዱ አንድ ሰው ማለት ነው።
በእያንዳንዱ ራሱን በገደለው ሰው ልጅ ሌሎች ራሳቸውን ለመግደል ሙከራ አድርገው ስላልተሳካላቸው ብቻ በሕይወት የተረፉ 20 ሰዎች አሉ።
በ15 እስከ 29 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ላሉ ሰዎች ራስን መግደል ሁለተኛው ከፍተኛ የሞት መንስኤ ነው።
በ2020 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከቤት አትውጡ የሚል ትዕዛዝ መሰጠቱ ብዙ ሰዎች ለአእምሮ ሕመም እንዲጋለጡ አድርጓል። ሕዝቡ ወደፊት እንዴት ሰርተን ነው ገንዘብ የምናገኘው ብለው በመጨነቃቸው በተለይ ከሥራ የተባረሩ ሰዎች ለአእምሮ ሕመም ተጋልጠዋል።
ራዕይ 9፡7 የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤
ይህ እውነትን በግልጥ የሚናገር ቃል ነው።
ዘውድ የጫኑ አጋንንት። የኮሮና አጋንንት። (ኮሮና የሚለው ቃል ትርጉሙ ዘውድ ነው።)
ኮሮና ቫይረስ የነዚህ አጋንንት ቅድሚያ ማሳያ ነው።
ዮሐንስ እኛ በዓይናችን ማየት በምንችላቸው ፍጡሮች አማካኝን ክፉ መናፍስትን እየገለጸልን ነው። አንበጣዎችን ለአጋንንት ምሳሌ እንዲሆኑ የመረጣቸው በአውዳሚነታቸው ምክንያት ነው። በ2019 እና በ2020 እጅግ ታላቅ ጥፋት የሚያደርሱ የአንበጣ መንጋዎች ምስራቅ አፍሪካ ላይ ወረራ አድርገው ነበር። አንበጣዎቹ ለምግብ የሚሆኑ ሰብሎችን ሲያወድሙ ሕዝብ ይራባል። የአጋንንት አሰራር የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ የማመን አቅማችንን ያጠፋዋል፤ ከዚህም የተነሳ ለነፍሳችን የምናበላት ተስማሚ ምግብ እናጣለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ስናምን ነፍሳችን በረሃብ ትሰቃያለች።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶች ስሕተት እንዲበዛ ያደርጋሉ።
የአንበጣ መንጋዎቹ ምስራቅ አፍሪካን በወረሩ ሰዓት ነው ኮሮና ቫይረስ ወይም ዘውድ የጫነ ቫይረስ በምስራቅ ከቻይና ተነስቶ በዓለም ዙርያ የተሰራጨው።
ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ነው።
“ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት”። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ይላል። ይህ አነጋገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት የሚለው ቃል ከነዚህ አጋንንት ተጽእኖ የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሚያጣምሙ እና ስሕተትን የሚያስተምሩ ሰባኪዎችን ይገልጻል።
የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
መጽሐፍ ቅዱስን አለማመን እንደ ቫይረስ ከሰባኪዎች እና ከቤተክርስቲያን መሪዎች አፍ እየወጣ የሚሰራጭ በሽታ ነው። በተመሳሳይ መንገድ የኮሮና ቫይረስም ሰዎች ሲናገሩ ከአፋቸው በትንፋሽ እና በአክታ እንዲሁም በማስነጠስ ነው የሚተላለፈው።
አንበጦቹ ፈረስ ይመስላሉ። ራዕይ ምዕራፍ 6 የክርስቶስ ተቃዋሚው በነጭ፣ በቀይ፣ እና በብጫ ፈረስ ላይ እንደተቀመጠ ነው የሚገልጸው፤ እነዚህም የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ፈረሶች ኋላ ተቀላቅለው ሞትን የሚወክል አንድ ሐመር ፈረስ ይሆናሉ።
እግዚአብሔር የፈረሶች አድናቂ አይደለም።
መዝሙር 147፡10 የፈረስን ኃይል አይወድድም፥
በመጀሪያዎቹ አራት ማሕተሞች ውስጥ ያሉት ፈረሶች የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነውን ፖፑን ነው የሚሸከሙት፤ እርሱም ከ860 ዓ.ም እስከ 1963 ዓ.ም ለ1,000 ዓመታት ያህል ዘውድ ይጭን ነበር፤ 1963 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት የተገለጡበት ዓመት ነው።
የመጀመሪያው ማሕተም፡
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት። [“ቀስት” የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ ደጋን ነው የሚለው።]
ደጋን ይዟል፤ ቀስት ግን የለውም። ይህ ሽንገላ ነው።
ራዕይ 9፡7 አንበጣ ስለሚመስሉት አጋንንት ሲናገር እንዲህ ይላል፡- “በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩዋቸው”።
ይህ አስደናቂ ነው።
አጋንንት አንበጣዎች ዘውድ መጫናቸው ያስደንቃል። በዚህ መቅሰፍት ቅምሻ ውስጥ ዛሬ የምናየው ኮሮና ቫይረስ ነው። “ኮሮና” የሚለው የላቲን ቃል ትርጉሙ ዘውድ ወይም አክሊል ነው።
“ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ”። ፊታቸው እንደ ሰው ፊት የሆነው ለምንድነው? ይህ የሚያመለክተው ራሳቸውን የቤተክርስቲያን ራስ ብለው የሚጠሩ ሰዎችን ነው።
አጋንንቱ የሆነ ቦታ ሄደው ገዥ ለመሆን ቀስት ያስፈልጋቸዋል።
ኤርምያስ 9፡8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ፤
መጽሐፍ ቅዱስን የማይከተሉ ሰባኪዎች አፋቸው የገሃነም ደጅ ነው።
የሚተኩሱቸው ቀስቶች የሚያስተምሩዋቸው ሐሰቶች ናቸው።
እነዚህ ውሸቶች በሰዎች አእምሮ ውስጥ ተቀርቅረው ይቀመጡና ሰዎች እውነትን እንዳያስተውሉ ያደርጓቸዋል።
ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ አድማጮች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ይላሉ፤ ይቃወማሉ፤ ይቃረናሉ እንዲሁም የፈለጉትን ቃል ከውስጡ ይለውጣሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን በማንኛውም ዓይነት መንገድ መነካካት መልእክቱን መለወጥ ነው።
ኮሮና ቫይረስ መልኩን ስለሚለውጥ ቶሎ ቶሎ ይሰራጫል። በዋነኝነት የሚሰራጭበት መንገድ በሰዎች አፍ ውስጥ ባለው ምራቅ ነው። ይህም ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ብክለት ነው።
ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ሰው ሁሉ የስሕተት ትምሕርት ያደምጥና ስሕተቱን በአፉ ቃል ለቀጣዩ ሰው ያስተላልፈዋል።
ራዕይ 9፡8 የሴቶችን ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው፥ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፥
በታላቁ መከራ ውስጥ ጸጉራቸውን አሳጥረው የሚቆረጡ ሴቶችን ለማሰቃየት እነዚህ አጋንንት ጸጉራቸውን አስረዝመው ይገለጣሉ።
ሰይጣን በሚያገሳ አንበሳ ይመሰላል። አንድ ጊዜ በአንበሳ መንጋጋ ውስጥ ከገባችሁ ጥርሶቹ ይገድሏችኋል። ከዱር አንበሳ ተጠንቀቁ፤ ጭራሽም አትቅረቡት። ጉልበተኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አለብን የሚሉ ሰዎችን ቀጥቅጠው ካባረሩ በኋላ ጉባኤውን ለእነርሱ ሃሳብ እሺ ብሎ የሚገዛ አቅመ ቢስ ማሕበር ያደርጉታል። አፈንጋጮች ሁሉ ይባረራሉ።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡8 በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
ከአለማመን እና ከሐጥያት ጋር እቃቃ የሚጫወቱ ሁሉ በዲያብሎስ ስሕተት ውስጥ ይታሰራሉ።
በታላቁ መከራ ዘመን ሰይጣን በሙሉ ኃይሉ እንዲንቀሳቀስ ይፈታል። የዚያን ጊዜ እንቅስቃሴዎቹን የሚገድብበት መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ የለም።
ራዕይ 9፡9 የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፥ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።
ብረት የሮማ መንግስት ተምሳሌት ነው። ዳንኤል በተረጎመው ሕልም ውስጥ እግሮቹ ከብረት የተሰሩ ምስል አለ፤ ይህም በ395 ዓ.ም በምስራቅ እና በምዕራብ ለሁለት የተከፈለውን አረማዊውን የሮማ መንግስት ይወክላል። እግሮቹ አስር ጣቶች ያላቸው መሆናቸው በስተመጨረሻ ወታደራዊ ኃይላቸውን ለአውሬው (የመጨረሻው ፖፕ) በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሚያስረክቡትን አስር ፈላጭ ቆራጮች ለመወከል ነው።
የቤተክርስቲያን ስሕተት በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጦርነት ያውጃል። ይህም ጦርነት መጨረሻው አርማጌዶን ነው።
ራዕይ 9፡10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።
በዚህ ራዕይ ውስጥ “ጅራት” ተብሎ የተጠቀሰው ለሰዎች የሚነግሩት “ተረት” ወይም ታሪክ ነው።
የዳነ ክርስቲያን የቤተክርስቲያንን ስሕተት ሲያምን ታላቁ መከራ ውስጥ ገብቶ አሰቃቂ ሞት ይሞታል። ይህም በስተመጨረሻ ሐሰተኛ አስተምሕሮ ሰውን የሚነድፍበት ገዳይ መርዝ ነው።
ከዚህም ሌላው አስደንጋጭ ነገር አንድ ክርስቲያን ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ ያስተምሩት እና ያምናቸው የነበሩ የቤተክርስቲያን መሪዎች እንዳታለሉት ሲያውቅ ነው።
ደግሞም በዚያ ሰዓት ማንም ሊረዳው የሚችል የለም። በታላቁ መከራ ዘመን መንፈስ ቅዱስ በምድር ላይ ስለማይኖር የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ሊያገኙት አይችሉም።
ይህ ራዕይ 3½ ዓመታት በሚፈጀው ታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው።
ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምናየው ሁሉ የዚህ ራዕይ ፍጻሜ ቅምሻ ብቻ ነው።
ራዕይ 9፡11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።
ንጉስ ዘውድ ይጭናል።
ዘውድ የሚጭነው ዋነኛ የሐይማኖት መሪ ፖፑ ነው።
ዘውድ በመጫን የመጀመሪያው በ860 ዓ.ም የተሾመው ፖፕ ኒኮላው ቀዳማዊ ነው።
ይህ ዘውድ በ1315 ዓ.ም ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ሆኖ ለ1,100 ዓመታት ቆይቷል።
ፖፑ ከ8690 ጀምሮ ዘውድ ጭኖ ነበር፤ ከ1963 ጀምሮ ግን አዲሱ ፖፕ ፖል 6ኛው ወደ ስልጣን ሲመጣ ዘውዱን አወለቀ።
በ1963 ዊልያም ብራንሐም የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማሕተሞች ገለጠ፤ ከዚህም መገለጥ የተነሳ የተፈጠረው ደማቅ መንፈሳዊ ብርሃን ፖፑ እና ካቶሊካዊው የአሜረካ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል። ብርሃን ጨለማን ያጠፋል።
አዲሱ ፖፕ ጆን ፖል 6ኛው ባለ ሶስት ድርቡ ዘውድ ተጭኖለት ነበር ግን አውልቆ አስቀመጠው።
ራዕይ 9፡12 ፊተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ከዚህ በኋላ ገና ሁለት ወዮ ይመጣል።
“ወዮ” ማለት መርዶ ነው።
ሰዎችን ከሚረብሹዋቸው ነገሮች መካከል ዋነኞቹ ሞት እና የኢኮኖሚ ውድቀት ናቸው። የምትወዱዋቸው ሰዎች ወይም ገንዘባችሁ ሲጠፋባችሁ የሚሰማችሁ ሕመም በጣም ከባድ ነው። ይህ ዓይነቱ ገጠመኝ ከባድ ሐዘን፣ ድካም፣ እና ምሬት ያስከትላል።
በ1914 እና በ1918 ዓ.ም መካከል በአንደኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ የተለቀቀው የአምባ ገነንነት መንፈስ በዚያው ዘመን ከተነሳው እስፓኒሽ ፍሉ ከተባለ የጉንፋን ዝርያ ጋር ተጣምሮ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በዓለም ዙርያ ገድሏል።
የጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴ በ1917 ወደ ዲኖሜኔሽን በመለወጡ እግዚአብሔር ተቆጥቷል። ወደ ዲኖሚኔሽን ከመለወጣቸው የተነሳ ዊልያም ብራንሐም የተባለ ሰባተኛ መልእክተኛ የመጽሐፍ ቅዱስን መገለጦች ይዞ በመጣ ጊዜ ሊቀበሉት አልቻሉም።
በዚህም ምክንያት ቤተክርስቲያኖች ስሕተት ውስጥ ገብተዋል፤ በተለይም ዘፍጥረት፣ ዳንኤል፣ እና ራዕይ መጽሐፍ ላይ ተሳስተዋል።
በዚህ ላይ ይባስ ብሎ ደግሞ የኢጣልያው አምባ ገነን መሪ ሙሶሊኒ በ1929 ዓ.ም ለቫቲካን ከተማ ራሷን የቻለች መንግስት እንድትሆን እውቅና ሰጥቷታል። ይህች ታናሽ መንግስት በውስጧ የሚኖሩ የቫቲካን ፓስፖርት ያላቸው 150 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ በተለያዩ ሃገራት ሁለት ፓስፖርት ይዘው የሚኖሩ ዜጎቿ ደግሞ 650 ብቻ ናቸው። የቫቲካን ከተማ ስፋቷ አንድ ኪሎ ሜትር ካሬ ነው።
ከዚህ የተነሳ ቫቲካን በምድር ሁሉ ላይ ካሉ መንግስታት በስፋት ታናሽ ናት።
የቫቲካን ነጻነት የነብዩ ዳንኤል ትንቢት ውስጥ “ታናሽ ቀንድ” የተባለው እንዲገለጥ አድርጓል።
ለዚህ ነው እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ራዕዩን ዝጋ አትመው ብሎ ለዳንኤል ትዕዛዝ የሰጠው።
የዳንኤልን ትንቢቶች መረዳት የምንችለው ከ1929 በኋላ ብቻ ነው።
ዳንኤል 12፡4 ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።
ከዚያም ከ1947 እስከ 1965 ሲሰብክ የነበረው ዊልያም ብራንሐም በራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ 6 ውስጥ ከተጠቀሱት ሰባት ማሕተሞች መካከል ስድስቱን በመግለጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችንን ጨመረው። እነዚህም እውነቶች የቤተክርስቲያንን ዓለም ግራ ሲያጋቡ የነበሩ በተጻፈው ቃል ውስጥ የነበሩ ሚስጥራትን ገልጠን መረዳት አስችለውናል።
በአሁኑ ሰዓት ኮኖረና ቫይረስ ከቦታ ቦታ የሚደረጉ ጉዞዎችን ቀንሷቸዋል። ስለዚህ እቤታችን ቁጭ ብለን ዳንኤል ሊያስተምረን የፈለገው እውነት ላይ ትኩረት የምናደርግበት ጊዜ ነው። ሰዎች በቤታቸው መቀመጣቸው እውነትን ለራሳቸው መርምረው እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣቸዋል። ቤተክርስቲያኖች ወንድም ብራንሐም ያመጣላቸውን እውነት አንቀበልም ብለዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎች ወዲያ ወዲህ እንዳይሯሯጡ በማድረግ ኢንተርኔትን ወይም የመረጃ መረብን እንዲፈትሹና የእውነት እውቀታቸውን መጨመር እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
በ1929 ሙሶሊኒ ለቫቲካን ከተማ ነጻነት ከመስጠቱ በተጨማሪ እጅግ ታላቅ የገንዘብ ስጦታ ሰጥቷታል፤ እንዲሁም ከፍተኛ የግብር ቅናሽ አድርጎላታል። ይህም ገንዘብ በብዙ ሕገወጥ ንግዶች ላይ በመዋሉ የቫቲካንን ከተማ በምድር ላይ አንደኛ ሃብታም ድርጅት አድርጓታል።
እግዚአብሔር የሰጠው ምላሽ ምንድነው?
በ1929 ዓ.ም ዓለም ሁሉ ታላቅ የኢኮኖሚ ኪሳራ ውስጥ ወደቀች። ይህም ታላቁ የኢኮኖሚ ቀውስ ነው።
ይህም ቫቲካንን የክርስቲያናዊ እውነት ምንጭ አድርጎ መመልከት የሚያመጣውን ኪሳራ ያመለክታል።
ቫቲካን በዓለም ዙርያ ሁሉ ለተሰራጨው ዲኖሚኔሽናዊ ስሕተት ዋነኛ ምንጭ ናት።
ስለዚህ በ2020 ኮሮና ቫይረስ ልክ እንደ እስፓኒሽ ፍሉ ነው የተሰራጨው (ነገር ግን ደግነቱ የእስፓኒሽ ፍሉ ያህል ሰዎችን አልገደለም)። ደግሞም ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ የሚያሰጋ ያህል የምርት ገበያ ኪሳራ አስከትሏል።
ኢጣልያ ካርታ ላይ ቅርጽዋ እግር ይመስላል። ይህ ምን ያስታውሰናል።
ሱሪ እና ትልቅ ታኮ ጫማ ያደረገች ሴትን ያስታውሰናል። ይህም ምድርን ያጥለቀለቀ ፋሽን ነው።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። የጨቋኝዋ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።
ማቴዎስ 6፡27 ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
ትልቅ ታኮ ጫማ በማድረግ ሴቶች ቁመታቸውን መጨመር የሚችሉ ይመስላቸዋል።
ሴቶች ሱሪ በመልበስ ባሎቻቸው ላይ ጌታ የመሆን ፍላጎታቸውን ያንጸባርቃሉ።
ከኢጣልያ እግር ጣት በስተግራ ያለችዋን የሲሲሊ ደሴት ተመልከቱ።
ይህች ደሴት ዳንኤል በተረጎመው የናቡከደነጾር ራዕይ ውስጥ የአሕዛብ ምስሉን እግሩ ላይ የመታውን ድንጋይ ትመስላለች።
እግዚአብሔር ትኩረታችንን ወደ ኢጣልያ እንድናደርግ እያመለከትን ነው፤ ኢጣልያ በምድር አቀማመጥ ውስጥ እግሩን በድንጋይ ተመቶ የወደቀውና የጠፋው የዳንኤል ራዕይ ውስጥ ያለውን የአሕዛብ ምስል ትወክላለች።
ይህ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ነው።
ቫቲካን ከተማ። በጨቋኝዋ ሴት የተመሰለችው (ሱሪ ለባሽዋ) የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ በራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ በተጠቀሰው ባለ ሰባት ራሱ አውሬ ላይ ለመቀመጥ ራሷን ከፍ ታደርጋለች (ባለ ትልቅ ታቆ ጫማ አድርጋ)። ይህ ሁሉ ሊጠፋ ቀርቧል።
ፖፑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ሐይማኖትና ስሕተቶችን የሚያሰራጭ ሐሰተኛ ነብይ ነው።
54-0513 የአውሬው ምልክት
ሶስት ወዮዎች ተከትለውታል። የመጀመሪያው በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሆኗል። ሁለተኛው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሆኗል።
ራዕይ 9፡13 ስድስተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፥
በሁለተኛው ወዮ እንደ ሙሶሊኒ፣ እስታሊን፣ እና በተለይ ሒትለር የመሳሰሉ ፍጥረታዊ አምባ ገነኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፍጥረታዊ እስራኤልን ማለትም አይደሁዶችን ጨፍጭፈው የሚያጠፉ ፍጥረታዊ አጋንንትን ለቀቁ። ይህ የተፈጸመው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው (1939-1945)።
ራዕይ 9፡14 መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ፦ በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።
መለከት ጦርነትን ሊያመለክት ይችላል።
ኤፍራጥስ ወንዝ ከኤደን የሚፈስስ እንደመሆኑ መንፈሳዊ ትርጉም አለው። ኤደን ከመጀመሪያው ግብጽ ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን ምድር በአዳም ሐጥያት ምክንያት በተረገመች ጊዜ የምድር አቀማመጥ ብዙ ተለውጧል።
65-0829 የሰይጣን ኤደን
በስተመጨረሻ ሁሉን ሰርቶ ሲያበቃ ማዕከሉን ማለትም የምድርን ዋነኛ ማዕከላዊ ዕዝ በኤድን ምስራቅ በገነት አደረገ። እግዚአብሔር የዓለምን ዋና ከተማ ወይም መናገሻ ግብጽ ውስጥ በኤደን ገነት አደረገ፤ ከገነት በስተ ምስራቅ የዓለም ዋና ከተማ የሚገኝበት ቦታ ነበረ።
ዘፍጥረት 13፡10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ።
ኤፍራጥስ ወንዝ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የተስፋይቱ ምድር ድንበር ነበረ።
ራዕይ 9፡15 የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።
ይህ በታላቁ መከራ ውስጥ በቀጥታ ይፈጸማል። እነዚህ አጋንንት ከታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ አንድ ሶስተኛውን ለሚያህል ጊዜ ገዥዎች ይሆናሉ። ታላቁ መከራ 3½ ዓመታት ነው የሚፈጀው።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አይሁዶች ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ ታላቁ መከራ ምን ያህል አስከፊ እንደሚሆን በጨረፍታ ያሳየናል።
“የሰዎችንም ሲሶ” የሚለው የሰው ዘሮችን ቁጥር አንድ ሶስተኛ ማለት አይደለም።
እግዚአብሔር ሰዎችን ሶስት ዓይነት አድርጎ ያያል።
አይሁድ፣ አሕዛብ፣ እና በከፊል አሕዛብ በከፊል አይሁድ የሆኑ ሳምራውያን።
ስለዚህ አይሁዶች ከሰው ዘር መካከል በተመደቡበት ምድባቸው አንድ ሶስተኛውን የሰው ዓይነት ይወክላሉ።
የታላቁ መከራ ዘመን እያለቀ ሲሄድ እነዚህ አጋንንት ለአይሁዶች ባላቸው ጥላቻ እየከፉ ይሄዳሉ።
አራቱ መላእክት እነ ማን እንደሆኑ እርግጠኛ መሆን አንችልም፤ ነገር ግን እነርሱን ሊገልጡ የሚችሉ ያለፈውን የቤተክርስቲያን ዘመን ጉልህ ተጽእኖ ያመጡበትና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ጥፋቶችን ያስከተሉ አራት ሰዎች እናውቃል።
ልክ ሔዋን ግብረ ገብነትን እንደጣለች ሁሉ ሳይኮ አናሊስቱ ፍሮይድ ግብረ ገብነትን ጣለ፤ ሔዋን ግብረ ገብነትን መጣሏ ነው የሰው ዘርን ሁሉ ለጥፋት የዳረገው።
የአይንሽታይን ፊዚክስ ለኑክሊየር ቦምብ መንገድ ጠርጓል፤ ይህም ኑክሊየር ቦምብ ወደፊት ምድር ተቃጥላ የምትነጻበት እሳት ሆኖ ያገለግላል።
ካርል ማርክስ እና እርሱ የፈጠረው የኮምዩኒዝም ቲዎሪ ልክ የዳንኤል ራዕይ ውስጥ ያለው ምስል ላይ እንዳሉት ሁለት እግሮች ዓለምን ካፒታሊዝም እና ኮምዩኒዝም በሚባሉ ሁለት ጎራዎች ከፈለ። ይህም ቀዝቃዛ ጦርነት የዓለም ሕዝቦች ለመጨረሻው ጥፋታቸው የሚበቃ ኑክሊየር ቦምብ እንዲያመርቱ አደርጋቸው።
ቻርለስ ዳርዊን እግዚአብሔርን በሚክድበት የኤቮልዩሽን ቲዎሪ አማካኘነት በጣም ጥቂት ብቻ እውነተኛ አማኞች እስኪቀሩ ድረስ እግዚአብሔር የለም የሚለው ክሕደት እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የ1769ኙ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ናቸው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። ፍጹም እና አንዳች እንከን ወይም ስሕተት የማይገኝበት መጽሐፍ ነው።
የሜሴጅ አማኞችን ጨምሮ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ነው ብለው የሚያምኑ ክርስቲያኖች በግል አግኝቼ አላውቅም።
በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር አሁን የወንድም ብራንሐም ንግግሮች አንዳችም ስሕተት የለባቸውም ማለታቸው ነው።
62-1007 የበሩ መክፈቻ
… በጣም የሚያሳዝኑ ነገሮች ሰምታችኋል። ከነዚህም መካከል እርሱ ፍጹም ነው እያሉ ስለ እኔ ማውራታቸው ነው። ሌላም አስፈሪ ነገሮች ሲወሩ ትሰማላችሁ።
ወንድም ብራንሐም ፍጹም አይሳሳትም ብሎ መናገር በጣም ትልቅ ስሕተት ነው፤ አገልግሎቱንም ዋጋ ያሳጣዋል።
ራዕይ 9፡16 የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፥ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።
ይህ ቁጥር የሚነግረን ሁለት መቶ ሚሊዮን አጋንንት እንደሚንቀሳቀሱ ነው።
64-0719 የመለከቶች በዓል
ሒትለር እና አብረውት ያሉት ሰዎች አይሁዶችን ሲያሳድዱ እንዲሁም ያደረጉባቸውን ብዙ ግፎች ሲፈጽሙ፤ በዚያ ዘመን እስታሊን፣ ሒትለር እና ሌሎችም ፈላጭ ቆራጮች መነሳታቸውን ተመልከቱ። በቂ ሰዓት ቢኖረን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጡ ሰዎች ደግመን በዝርዝር እንናገር ነበር፤ እኛ ግን ከዚህ በፊት በደምብ አይተነዋል። በዚያው ዘመን ውስጥ ጀርመኒ እና ሌሎች ሃገሮች ውስጥ አይሁዶች በምድር ሁሉ ላይ ተበታትነው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን በነዚያ ሃያ ዓመታት ውስጥ አይሁዶች ላይ እጅግ መራራ ስደት ተነሳባቸው። እዚያው ሄጄ የአይሁድ ሕጻናትን አዋቂዎችን፣ ሴቶችን ሁሉ አቃጥለው ከገደሏቸው በኋላ አመዳቸውን ለእርሻ ማዳበሪያነት የተጠቀሙበትን ሁሉ አይቻለሁ። ግን ይህን ሁሉ ሊክዱ ይፈልጋሉ፤ እነርሱን በሙሉ ሰብስቦ ይህንን ግፍ የፈጸሙበት ቦታ ወስዶ ማሳየት ነው።
ያ ዘመን ለእስራኤል እጅግ መራራ ስደት ነበረ ምክንያቱም እንዲመለሱ እና ስርየት እንዲቀበሉ ጥሪ የቀረበላቸው ጊዜ ነው። እስራኤሎች እስከ ዛሬ በፍጥረታዊ በግ መስዋእትነት በሚደረግ የስርየት አገልግሎት ስር ነው ያሉት። እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ ነው ስርየት የሚያደርግልን፤ እነርሱ ግን አንቀበለውም አሉ፤ ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ ደሙ በእነርሱ ላይ ነው። ልብ በሉ፤ ለሕዝቡ የዝግጅት ጊዜ ነው! ስለዚህ ሰባተኛው መለከት እና ሰባተኛው ማሕተም አንድ ላይ መገኘታቸው እንዴት ፍጹም እንደሚያደርጋቸው አስተውሉ፤ እነዚህ የአይሁዶችን ስደት ነው የሚያመለክቱት።
ልብ በሉ ራዕይ ምዕራፍ 9 ቁጥር 13 በስድስተኛው መለከት ጊዜ ምን እንደሚፈጸም በደምብም አስተውላችሁ ተመልከቱ። ራዕይ 13፡9 በስድስተኛው መለከት ጊዜ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ታስረው የነበሩ ሁለት መቶ ሺ [በእርግጥ 200 ሚሊዮን] ፈረሰኞች ተፈተው ይለቀቃሉ። በዓለም ላይ አሁን ሁለት መቶ ሺ [በእርግጥ 200 ሚሊዮን] ፈረሰኞች የሉም፤ ነገር ግን ሁለት መቶ ሺ ፈረሰኞች ነበሩ [ተሳስቷል፤ 200 ሚሊዮን ናቸው]። ልብ በሉ። ኋላ ታነቡት ዘንድ በማስታወሻችሁ እንድትጽፉት እፈልጋለሁ።
ወንድም ብራንሐም ሲናገር 200 ሺ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ ግን እልፍ ጊዜ እልፍ፣ እልፍ ጊዜ እልፍ ነው የሚለው፤ ይህም 200 ሚሊዮን ማለት ነው።
እነዚህ ፍጥረታዊ ፈረሶች አይደሉም። እነዚህ ፈረሶች እሳት ይተፋሉ፤ የኢያሰጲድ ጥሩር ያደርጋሉ፤ ጭራ አላቸው። የጭራቸውም ጫፍ እባብ ይመስላል፤ ጫፉ ላይ የተናዳፊ እባብ ጭንቅላት አለው። አያችሁ? እነዚህ እስካሁን ድረስ ለብዙ ዓመታት ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ታስረው የቆዩ መንፈሳዊ ፈረሶች ወይም የሰይጣን ሰራዊት ናቸው፤ ስለዚህ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ያላቸው መናፍስት ናቸው። ይህ ምን ማለት ነው? የጥንቱ የሮማ መንግስት ማንሰራራት እና የአይሁዶች መሰደድ ነው። ለሁለት ሺ ዓመታት ያህል ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊሻገሩ አልቻሉም፤ እነዚህ ወደ ማዶው ሊሻገሩ የሚፈልጉ የሐይማኖት ቡድኖች ናቸው። እንደምታውቁት ኤፍራጥስ የኤደን ገነትን አቋርጦ የሚመጣ ወንዝ ነው። እነዚህ ሁለት መቶ ሺ [200 ሚሊዮን] አሳዳጅ አጋንንት በዚያ ወንዝ ውስጥ ታስረው ቆይተዋል።
በስድስተኛው ማሕተም ጊዜ ምን እንደሚፈጠር አስተውሉ። እነዚህ አጋንንት በአይሁዶች ላይ ተለቀቁ፤ በዚህም የአይሁዶች ስደት ተጀመረ። የሁለት መቶ ሺ ዓመታት ያህል ዕድሜ ያስቆጠሩ አጋንንት በእስታሊን፣ በሒትለር አማካኝነት ተለቅቀው አይሁዶችን አሳደዱ። “ይህ ግን የሮማ መንግስት አይደለም” ልትሉ ትችላላችሁ። መንፈሱ ግን አንድ ነው። እነዚህ መንግስታት በጥንቱ የሮማ መንግስት ዘመን በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸሙ ክፋቶችን ነው በድጋሚ የፈጸሙት። ስለዚህ ፍጥረታዊቷን እስራኤል ከመንፈሳዊቷ ቤተክርስቲያን ለይተን እንመልከት። በአይሁዶች ላይ ተለቀቁ።
64-0719M የመለከቶች በዓል
አስተውሉ፤ በዚህ ክፍል እንደምናየው ፍጥራታዊ ኃይል ያላቸው ገዥዎች (አምባገነን መሪዎች) እስራኤል በተባለች ፍጥረታዊ ሕዝብ ላይ ተለቀቁ። ከዚያስ ምን አደረጉ? ሄደው ጦርነት ከፈቱና ብዙዎችን አሳደዱ ደግሞም ገደሉ።
አሁን ግን በመንፈሳዊው ዓለም [በቤተክርስቲያን] ያለነው እኔ … እናንተ ነን…
ይህን እውነት ታስተውሉ ዘንድ እግዚአብሔር ዓይናችሁን ያበራላችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክንያቱም ይህ የሚናገረው ለቤተክርስቲያን ብቻ አይደለም። ይህ መልዕክት በድምጽ ተቀርጾ በዓለም ሁሉ ይሰራጫል። እኔም ደግሞ ዓላማዬ ማንንም ማስከፋት ሳይሆን እውነትን መናገር ነው።
ከጥንቱ አረማዊ የሮማ መንግስት ማንሰራራት ጋር ተያይዞ የተፈጠረው የቤተክርስቲያን ዓለም ከመጀመሪያው ይጠላቸው የነበሩትን አይሁዶች ያሳድዳቸዋል። አንበሳው ጥርሱን አግጥጦ እንደመጣ እየረጋገጠ ይሰብራቸዋል። ሮም ከድሮውም ጀምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ናት! በዚሁ በጠላትነት መንፈስ ነው ሮም በዓለም መንግስታት አማካኝነት ተፈታ የተለቀቀችው፤ ምክንያቱም የዓለም ሐይማኖታዊ ስርዓት ሮምን የሚደግፍ ነው። አሁን ይህ መንፈስ ተፈቶ ተለቋል።
ይህ መንፈስ በምድር ላይ ምን አደረገ? ጌታ እንደተናገረው “በተንኮሉ” እና በሽንገላው ተጠቅሞ ሥራውን እየሰራ ነው። ምን ሰርቷል? የዓለም ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ወደ አንድነት የሚመጡበትን ኢክዩሜኒካል ካውንስል የተባለ ምክር ቤት በማደራጀት በክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አማካኝነት ሁሉንም በአንድ ላይ ሊገድላቸው እየተዘጋጀ ነው። እንዴት አድርጎ? በምድራዊነት በተጠመደችው ቤተክርስቲያን መንፈስ በኩል።
ማንን ለማጥቃት ነው የተለቀቀው? ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችን ሳይሆን ሙሽራይቱን ነው!
ቤተክርስቲያኖች ሁሉ፣ የሰውን ንግግር መጥቀስ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ጨምሮ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የምታምነዋን ሙሽራይቱን ፈጽመው ይጠሉዋታል።
ነገር ግን አሁን የምላችሁን ስሙ፤ ሙሽራይቱ በዚህ ፈተና ውስጥ አታልፍም። መጽሐፍ ቅዱስ ሙሽራይቱ ለዚህ ፈተና እንደማትጋለጥ ተናግሯል። ቤተክርስቲያን ታልፍበታለች፤ ሙሽራይቱ ግን አታልፍበትም። አልገባችሁም ወይ? አገልጋዮች፣ ወንድሞች አይታያችሁም?
“ቤተክርስቲያን ወደ ፍጽምና መድረስ እንድትችል በስደት ውስጥ ማለፍ አለባት” ትላላችሁ። ሙሽራይቱን ወደ ፍጽምና የሚያመጣተ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው።
“በታላቁ በኤፍራጥስ ወንዝ የታሰሩትን”።
ሮማውያን ግፈኛ ገዳዮች ነበሩ። ነገር ግን መንፈሳቸው ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን መግባት አልቻለም።
በጨለማው ዘመን ውስጥ ሲሰለጥን የነበረው ገዳይ መንፈስም ከተሃድሶው በኋላ መንቀሳቀስ አልቻለም።
በተለይም በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ውስጥ እንደ ጆን ዌስሊ የመሳሰሉ ሰዎች ስለ ቅድስና እና የወንድማማች መዋደድ ሲሰብኩ ይህ ነፍሰ ገዳይ መንፈስ መስራት አልቻለም።
የአሁኗ ዘመን ቤተክርስቲያንም ብትሆን አይሁዶችን በብዛት ለመጨፍጨፍ የተነሳውን ይህን መንፈስ አትታገሰውም።
አረማዊዎቹ ሮማውያን ታይተስ በተባለው ጀነራል መሪነት በ70 ዓ.ም 1,100,000 አይሁዶችን ገድለዋል። ከዚያም በኋላ በ135 ዓ.ም በንጉስ ሐድሪያን ዘመን በተጠናቀቀው ባር ኮችባ በሚባለው ዓመጽ ዘመን ተጨማሪ 560,000 አይሁዶችን ገድለዋል። አረመኔው የሮማ መንግስት አይሁዶችን በጭቆና ገዝቶ ከዚያ በኋላ እጅግ በጣም ብዙዎቹን ገድሎ ከእስራኤል ምድር አባሯቸዋል።
እነዚህን ነፍሰ ገዳይ መናፍስት በምድር ላይ በድጋሚ ለማሰማራት ሰይጣን ፍጥረታዊ የሆኑ አምባ ገነን የፖለቲካ መሪዎችን ተጠቅሟል።
በአይሁዶች ላይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተፈጸመው ጭፍጨፋ በስድስተኛው መለከት አማካኝነት ታላቁ መከራ ውስጥ ለሚፈጸመው ጭፍጨፋ ቅምሻ ነው።
ራዕይ 9፡17 ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፥ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።
ፈረሶቹ የሚወክሉት በመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች ውስጥ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የሚቀመጥባቸውን ፈረሶች ነው።
ዲያብሎስ መጽሐፍ ቅዱስን የማይከተሉ ሰባኪዎችን አፍ እየተጠቀመ የሚያገሳ አንበሳ ነው፤ አፋቸውንም ተጠቅሞ ሰዎችን በእሳት እና በዲን ወደሚቃጠል የገሃነም እሳት ውስጥ የሚያስገቡ አስተምሕሮዎችን ያስተላልፋል (ዲን እሳት በውስጡ ባለው መርዛማ የሰልፈር ዳይ ኦክሳይድ ጭስ እያፈነ ያሰቃያል)። ጭሱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን ሁሉ ይወክላል፤ እነዚህ ትምሕርቶች ለምሳሌ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣ እና 7ቱ ማሕተሞች ተፈተዋል የሚሉ ትምሕርቶች ናቸው።
አሞጽ 3፡7 ላይ እንደተጻፈው ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት መገለጥ አለባቸው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ወንድም ብራንሐም 7ቱን ማሕተሞች አልፈታቸውም ምክንያቱም ከእርሱ በፊት አስቀድሞ አልተገለጡም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ማሕተሞቹ የሚያሳምን ትምሕርት ያቀረበ ሰው እርሱ ነው።
ደግሞም ማሕተሞቹ የሚፈቱት ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ እንደተጻፈው በሰማይ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ከሄደች በኋላ ብቻ ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ ሙሽራይቱን በሰማይ በዙፋኑ ዙርያ ነው የምናገኛት።
63-0324 ማሕተሞቹን በተመለከተ ጥያቄና መልስ
ጥያቄዎች
በራዕይ ምእራፍ 5 ቁጥር 9 በጉ መጽሐፉን ሲወስድ የሚዘምሩት እነማን ናቸው -- የተነጠቁት ቅዱሳን ናቸውን?
መልስ፡
አይደሉም …
… የሆነ ችግር አለ። የሆነ ችግር አለ …
… ነገር ግን አያችሁ እዚያ ላይ እንዳስቆመኝ? ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። የዚህን ቃል ሌላኛውን ክፍል አንብቤው አላውቅም ነበር። አያችሁ፤ እዚህ ደርሼ “ከዚያ…” ሙር ተመልከቱ። “እነርሱም አዲስ መዝሙር ይዘምራሉ” እዚህጋ አቆምኩ። አያችሁ? ግን ደግሞ ተመልከቱ “ከሕዝብ፣ ከወገንን ከቋንቋም ሁሉ ዋጅተህ” ብለው የዘመሩት መዝሙር።
በእርግጥ እነርሱ ናቸው።
… እግዚአብሔርም ያንን ስሕተት እንዳልሰራ ለመጠንቀቅ ስለፈለገ መልሶ ጠራኝና የቀረውን ጥቅስ በሙሉ እንዳነብ አደረገኝ።
… “እነርሱም አዲስ መዝሙር ዘመሩ …” ወደዚህ ስንመጣ ግን ምን እንደሚል ታያላችሁ? ቀጥለን ወረድ ስንል “የዋጀን” ይላል። ያለ ምንም ጥርጥር ስለ ሙሽራይቱ ነው፤ ማለትም የተነጠቁት ቅዱሳን።
ወንድም ብራንሐም ከባድ ስሕተት ውስጥ ገብቶ ነበር። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከስሕተት መልሶታል። ስለዚህ ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉት ሕዝብ ሽራይቱ መሆኗን አረጋግጦ ተናግሯል። ስለዚህ ምዕራፍ 6 ውስጥ በጉ ማሕተሞቹን በሚፈታበት ሰዓት ሙሽራይቱ በሰማይ ናት።
1964-0719 የመለከቶች በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስከ አሁን አልተከፈተም።
ይህን የተናገረው ስለ ሰባተኛው ማሕተም ከሰበከ ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ነው፤ ነገር ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም።
ሰባተኛው ማሕተም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፈም። ጸጥታ ብቻ ነው። ስለዚህ ሰባተኛው ማሕተም ከመፈጸሙ በፊት ሊገለጥ አይችልም።
ሰባተኛው ማሕተም የጌታን ምጻት የሚመለከት ሲሆን ይህም በዓለማችን ሚስጥራት ሁሉ ትልቁ ሚስጥር ነው።
ይህን ሚስጥር ተረድተነዋል የሚሉ ሁሉ የቁም ቅዠት ውስጥ ገብተዋል።
ስለዚህ እውነትን መመዘኛችን ይህ ነው። ሰባተኛው ማሕተም አልተፈታም።
የስድስተኛው ማሕተም መፈታትስ?
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምን61ኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ። አያችሁ?
6ኛው ማሕተም የሚፈታው በሁለቱ ነብያት ማለትም በሙሴ እና በኤልያስ ነው። ይህም እነርሱ በብልሃት ፈጥረው የሚያመጡት ሃሳብ አይደለም። እነዚህ ነብያት አገልግሎታቸውን የሚፈጽሙት የተፈጥሮን ኡደት ማቋረጥ በሚችል ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል በመጠቀም እስራኤልን ለማጥቃት የሚመጡትን የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ሰራዊት በማጥፋት ነው።
እውነትን መመዘኛ 2። 6ኛው ማሕተም የሚፈታው እስራኤል ውስጥ በሁለቱ ነብያት በታላቁ መከራ ዘመን ነው።
ስለዚህ ሰባቱ ማሕተሞች ገና አልተፈቱም። ይህ የሚሆነው ቤተክርስቲያን ከምድር ላይ ከተነጠቀችና ሙሽራይቱም ወደ ሰማይ ከገባች በኋላ ነው።
ሙሽራይቱ በሰማይ ሆና ሰባቱ ማሕተሞች ሲፈቱ በዝርዝር በምትመለከትበት ሰዓት ምድር በታላቁ መከራ ትታመሳለች። ለዚህ ነው ሁለቱ ነብያት ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት። ምክንያቱም ማሕተሞቹ በታላቁ መከራ ጊዜ ውስጥ ይፈታሉ።
ራዕይ 9፡18 ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።
እነዚህ አጋንንት ታላላቅ ሰባኪዎች ናቸው፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን አይከተሉም። አስተምሕሮዋቸው ሐሰተኛ ከመሆኑ የተነሳ ከአፋቸው የሚወጣው ሞት ነው።
“የሰዎች ሲሶ” ወይም አንድ ሶስተኛ አይሁዶች ናቸው።
ታላቁ መከራ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ሲቀርብ እነዚህ አጋንንት በአይሁድ ላይ ያላቸው ጥላቻ እየባሰ ይሄዳል።
ጭስ ማለት እውነትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑ ስሕተቶች የሰው ልማዶች ጋር በመቀላቀል የሚፈጠር ዓይንን የሚጋርድ መጋረጃ ነው።
ራዕይ 9፡19 የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፤ ጅራታቸው እባብን ይመስላልና፥ ራስም አላቸው በእርሱም ይጐዳሉ።
ሰባኪዎች በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱት በስብከታቸው ነው።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የተጠቀሰው “ጅራት” ሰባኪዎች ለጉባኤው የሚያወሩት ተረት ወይም ሽንገላ ነው።
ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ ፈቀቅ እንድትሉ ሊያደርጉዋችሁ ከተሳካላቸው በወጥመዳቸው ተጠምዳችኋል ማለት ነው።
መጎዳታችሁን በትክክል የምታውቁት ከእንቅልፋችሁ ስትባንኑ እና ሰባኪዎች ባስተማሩዋችሁ ስሕተት አማካኝነት ከእውነተኛይቱ ሙሽራ ለይተዋችሁ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ጋር ታላቁ መከራ ውስጥ እንዳስገቡዋችሁ ስታዩ ነው። ለዘላለምም በዚያ ትቆያላችሁ። ሁልጊዜ የተታለሉ ሰዎች ተብላችሁ ትታወቃላችሁ።
ራዕይ 9፡20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤
አጋንንት ትኩረታቸው ሰው ሰራሽ ነገሮች ላይ፣ “የእጆቻቸው ሥራዎች” ላይ ነው።
“ንሰሃ አልገቡም”። አጋንንት ሰዎችን በሐሰተኛ ትምሕርት እንዲያምኑ ሲያደርጉ ሰዎቹ ልባቸው ውስጥ የሚገባው ትዕቢት ከስሕተቶቻቸው መመለስ እንዳይችሉ እና ንሰሃ እንዳይገቡ ያደርጋቸዋል።
ራዕይ 9፡21 ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።
በሐይማኖታዊው ዓለም ውስጥ ብዙ አስቀያሚ ነገሮች ይከናወናሉ። ከነዚህ አስቀያሚ ድርጊቶች መካከል ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በመከተል የሰባኪዎችን ስሕተት የሚቃወሙ ሰዎችን ስም ማጥፋት ነው።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሴቶችን በመመኘት፣ ገንዘብን በመውደድ እና ዝናን በመፈለግ ሐጥያት ቢሰሩም በቤተክስቲያናቸው ውስጥ የአጋንንት አሰራር የመንገሱ ትልቁ ማስረጃ ከዚህ ሁሉ ስሕተታቸው መመለስና ንሰሃ መግባት አለመቻላቸው ነው። ስሕተት የትዕቢት ጓደኛ ነው።
ንሰሃ ባለመግባታቸው ሁልጊዜ ትክክለኞች ነን ይላሉ፤ ስለዚህ ሊሳሳቱ እንደማይችሉ አድርገው ያስባሉ። ይህ ግን የፖፑ ጉራ ነው።
በ5ኛው መለከት ውስጥ እንደተመለከትነው ፖፑ የአጋንንት ንጉስ ነው።
ፍጹም አልሳሳትም ብሎ ማሰው ሰውን ወደ ፖፑ ጎራ ይቀላቅለዋል።
ራዕይ 16፡12 ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።
ኤፍራጥስ ወንዝ በድጋሚ መጠቀሱ ይህንን ቃል ከስድስተኛው መለከት ጋር ያገናኘዋል።
6ኛው መለከት በተነፋ ጊዜ የሚገለጡት 200 ሚሊዮን አጋንንት በዚህ ክፍል ውስጥ የምስራቅ ነገስታት ተብለው ተጠርተዋል።
የዘመኑ ምልክት የሆነው ኮሮና ቫይረስ ራሱ በምስራቅ ከምትገኘው ከቻይና ተነስቶ ነው የመጣው።
ራዕይ 16፡13 ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤
ይህን ከምስራቅ በሚመጡ አጋንንት የሚደረገውን ወረራ ስናጠና በውስጡ ሰይጣናዊ ስላሴ እናያለን።
ዘንዶው ዲያብሎስ ነው። የሮማ መንግስት አርማ ዘንዶ ነው።
የሮማ ካቶሊክ አወሬ ራስ ፖፑ ነው።
ፖፑ በተጨማሪ ሐሰተኛው ነብይ ነው፤ ማለትም የሐሰተኛ ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ነብይ ነው።
ሁለት መናፍስት በአንድ ሰው ውስጥ ሊያድሩ ይችላሉ?
ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደሚከተለው አነጋገረ።
ማርቆስ 5፡8 አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና።
“ርኩስ መንፈስ” የሚለው ነጠላ ቁጥር ነው።
ማርቆስ 5፡9 ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፥
ተናጋሪው ክፉ መንፈስ ራሱን በብዙ ቁጥር መግለጡን ልብ በሉ።
ከአንድ በላይ የሆኑ መናፍስት በአንድ ሰው ውስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ።
ስለዚህ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ በሐይማኖታዊው አውሬ መንፈስ እንዲሁም በሐሰተኛው ነብይ መንፈስ ተሞልቶ ይነሳል።
ከዚያ ዲያብሎስ ወደ ይሁዳ ውስጥ እንደገባ ሁሉ ወደ መጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ ውስጥም ይገባል።
ሉቃስ 22፡3 ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤
ሶስቱም መናፍስት፣ ማለትም የአውሬው መንፈስ፣ ሐሰተኛው ነብ፣ እና ሰይጣን ወደ ክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ውስጥ በአንድነት ይገባሉ።
የክርስቶስ ተቃዋሚውም አንድ በሶስት የሆነ ስላሴያዊ ሰው ይሆናል። ቤተክርስቲያኖችም ያምኑበታል።
ነገር ግን እነዚሁ ቤተክርስቲያኖች ኢየሱስ እራሱ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ዛሬ ማመን አይችሉም።
ራዕይ 16፡14 ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።
የእነዚህ ሶስት መናፍስት ተልዕኮዋቸው ወደ አርማጌዶን ጦርነት ይወጡ ዘንድ ቤተክርስቲያናትን ሁሉ ወደ አንድነት አምጥቶ ማስተባበር ነው።
ቤተክርስቲያኖች ስም በሌለው ስላሴያዊ አምላክ ስር ወደ አንድነት ይመጣሉ።
ካቶሊኮችና ፕሮቴስታንቶች በዋነኝነት የሚጋሩት እምነት ስላሴ ነው።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን እኔ ታላቅ ነኝ ትላለች። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ከሁሉም ይልቅ ብዙ ተዓምራት ያደረግሁ እኔ ነኝ ትላለች።
ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ የማናምነው ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር እንጣላለን። ምንም ያህል ተዓምራት ብናይ እንኳ ቃሉን የማንቀበል ከሆንን ከንቱ ነው።
ፖፑ አሁንም በክፉው ለተያዘው አጋንንታዊ ሥርዓት ዋና ራስ ነው።
አጋንንቱ የሚሰሩት ተዓምር ቤተክርስቲያናትን ወደ አንድነት ማምጣት ነው።
ወደ አንድነት ለመጡት ቤተክርስቲያናት ራስ የሚሆናቸው ፖፑ ነው።
እንክርዳዶቹ በታላቁ መከራ እሳት ውስጥ ይቃጠሉ ዘንድ አስቀድመው ይሰበሰቡና አንድ ላይ ይታሰራሉ።
የስንዴ እና እንክርዳድ ምሳሌ እንዲህ ይላል።
ማቴዎስ 13፡30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።
ቤተክርስቲያናት መጀመሪያው ራሳቸውን ወደ አንድነት መሰብሰባቸው አስፈላጊ ነው። ከዚያ በኋላ በታላቁ መከራ ውስጥ ይቃጠላሉ።
ታላላቅ ሰዎች ሁሉ እንደ ነገስታት በአንዲት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ወይም በአንድ የዓለም መንግስት ስልጣን ስር ይሰባሰባሉ።
በክፉው የተያዙ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ መጨረሻቸው በአርማጌዶን ይሆናል።
በዚህ ጦርነት ውስጥ ቤተክርስቲያናት ያዳናቸውን ጌታ ኢየሱስን ይዋጉታል።
ስለ ኢየሱስ የምታስቡት ነገር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደምታስቡ ያሳያል። ምክንያቱም ኢየሱስ እራሱ ቃሉ ነው።
አብዛኞቹ ቤተክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ይነቅፋሉ።
የተወሰኑ ጥቅሶችን ቸል ይላሉ፤ ይቃወማሉ፤ ወይም እንደፈለጉ ቃላቱን ይቀይራሉ።
ብዙ ጥቅሶችን ምንም እንደማይጠቅሙ ወይም አላስፈላጊ ዝርዝሮች እንደሆኑ ይቆጥሯቸዋል።
ስለ ኢየሱስም የሚያስቡት እንደዚሁ ነው።
ስለዚህ አይሁዶች በስተመጨረሻ ኢየሱስ ላይ ሞት እንደፈረዱበት ሁሉ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችም መጨረሻቸው ኢየሱስን መዋጋት ነው። ይህንንም የሚያደርጉት መሪዎቻቸው አድርጉ ስለሉዋቸው ብቻ ነው።
ማርቆስ 15፡11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።
ሕዝቡ ከኢየሱስ ይልቅ ነፍሰ ገዳይን እንዲመርጡ በማድረጋቸው የአይሁድ መሪዎች ሕዝባቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ወረዱ።
የሐይማኖት መሪዎችን መከተል ይህን ያህል አደገኛ ነው።
ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንዳያምኑ በማድረግ የቤተክርስቲያን መሪዎች ዛሬም በኢየሱስ ላይ ይፈርዳሉ።
ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን የኢየሱስን ሃሳብ ነው።
አንድን ሰው ከሃሳቡ ልንነጥለው አንችልም።
ማቴዎስ 27፡20 የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።
ዋነኛው ችግር ያለው በሐይማኖት መሪዎች ዘንድ ነው።
ሕዝቡ የሐይማኖት መሪዎችን አዳምጦ ተታለለ። ሕዝቡ የሐይማኖት መሪዎችን እየተከተሉ በ70 ዓ.ም እንደ ከብት ታረዱ።
በ33 ዐ.ም ኢየሱስን ይገድልላቸው ዘንድ ሮማዊውን ጴንጤናዊ ጲላጦስን ለመኑት።
ከዚያ በኋላ ግን ሮማውያኑ በ70 ዓ.ም ተመልሰው መጥተው እነርሱንም ገደሉዋቸው።