ራዕይ 7 - ከታላቁ መከራ መውጣት
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ታላቁ መከራ ነነፎቹን ቆነጃጅት በፓስተሮቻቸው ከመገዛት ነጻ ያወጣቸዋል። ሁለት ነብያት 144,000ዎቹን አይሁዳውያን ነጻ ያወጧቸዋል።
- ራዕይ ምዕራፍ 6ን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት
- ራዕይ ምዕራፍ 7
- አራቱ የመሬት ማዕዘናት
- እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር ያለውን ጉዳይ በአራት የተለያዩ መንገዶች ያስተናግዳል
- እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመቤዠት በአራት መንፈሳዊ ደረጃዎች ይሰራል -- ሰይጣንም ይህንን ኮርጆ ተመሳሳይ ነገር ያደርጋል
- ሩቅ ቦታዎች
- የእግዚአብሔር ማሕተም ምንድነው?
ራዕይ ምዕራፍ 7 ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ በተጠቀሱት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች እና ራዕይ 8፡1 ውስጥ በተጠቀሰው 7ኛው ማሕተም መካከል ነው የሚገኘው።
ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው - ዝምታ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የጌታን ምጻት የሚመለከት ሲሆን እርሱም የዓለማችን ታላቁ ሚስጥር ነው። ማንም ሰው ይህንን ሚስጥር አውቃለሁ ብሎ አያታልላችሁ። ዝምታን ልንተረጉም አንችልም። እንዲህ ማለት ነው ብላችሁ ልትናገሩ ብትሞክሩ እንኳ እግዚአብሔር ዝም ባለበት ጉዳይ እየተናገራችሁ ናቸሁ። ስለዚህ ትሳሳታላችሁ።
ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።
እግዚአብሔር ዝም ባለ ጊዜ እኛም ዝም ማለትን መማር አለብን። እግዚአብሔር ወደዚህ ምድር ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ አንድ ታላቅ ነገር በሚስጥር ሊያደርግ አስቧል፤ ይህንንም ሚስጥር አስቀድሞ ሊደርስበት የሚችል ማንም የለም።
ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮችን ሊያደርግ አስቧል፤ ከዚህም አሰራሩ መንገዳችን ለእግዚአብሔር ሰማያዊ መንገድ ተገዥ እንዲሆን ያደርጋል።
64-0719M የመለከቶች በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተከፈተም። ሰባተኛው ማሕተም ምጻቱ ነው።
ስለዚህ ይህ ለምዕራፍ 7 የተዘጋጀ መግቢያ በሰማይ ያለ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል በአንድነት ተቀናጅቶ መንቀሳቀሱ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች ውስጥ እንደተገለጠው በምድር ላይ እንቆቅልሽ ለሆኑ ክስተቶች ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል ምክንያቱም ሰባተኛውን ማሕተም ሊፈጽመው የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
በፍጹም የማይገጣጠሙ የሚመስሉ መረጃዎችን ያለ ምንም እንከን የሚያገጣጥም መንፈሳዊ መርህ ማግኘት አለብን።
በዓለም መጨረሻ ሁከት ውስጥ በሚነሱ ያለተዛመዱ ክስተቶች መካከል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ማግኘት የምትችለው ሙሽራይቱ ብቻ ናት።
ምዕራፍ 6 ውስጥ በተጻፉት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች እና ምዕራፍ 8 ውስጥ በተጠቀሰው ሰባተኛ ማሕተም መካከል ምዕራፍ 7 በመግባቱ የፒራሚዱ አናት ላይ የሚደረገውን ዓይነት ጉልላት የሚመስል ቅርጽ እናያለን።
ይህም የክርስቶስን ምጻት የሚወክል ጥንታዊ ምልክት ነው።
የጌታ መምጣት እንቆቅልሽ ነው።
ጉልላቱ በፒራሚድ አናት ላይ ሲቀመጥ ፒራሚሙ በሙሉ ጉልላቱን ይመስላል። ከዚያ በኋላ የሙሽራይቱ አካላት አዲሱን አካላቸውን ይለብሳሉ።
1ኛ ዮሐንስ 3፡2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
ይህንን ክስተት የተለያዩ ወገኖች በተለያየ መንገድ ይለማመዱታል፡-
- ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ውስጥ አታልፍም።
- ኢየሱስ በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ 144,000ዎቹን አይሁዶች ኢየሩሳሌም ውስጥ ያገኛቸዋል።
- ቤተክርስቲያን ሲመላለሱ የነበሩ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን መከተል አስፈላጉ መሆኑን ያልተረዱ የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት ታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ።
ራዕይ ምዕራፍ 6ን በወፍ በረር ቅኝት እንመልከት
የመጀመሪያዎቹ አራት ማሕተሞች የሮማ ካቶሊክ እንዲት በዓለም ላይ ታላቅ ኃይል ሆና እንደምትነሳና ዓለምን በሐይማኖት እንደምትቆጣጠር ነው የሚገልጡት።
ፈረሱ ላይ የተቀመጠው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው። እርሱም ሰይጣን ከሰማይ ተጥሎ ወደዚህ ምድር በሚባረርበት ጊዜ በቀጥታ የሚቀመጥበትን ከፖለቲካ እና ከገንዘብ ኃይል ጋር የተጣመረ የቤተክርስቲያን ኃይል እያዘጋጀለት ነው። በዚህም መርዛማ ቅልቅል ውስጥ ሰይጣን ቀሪውን ቅመም ይጨምርበታል፤ ይህም የአስሩ ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ኃይል ነው።
በነጭ ፈረስ ላይ እንደመቀመጡ ሐይማኖታዊ ሽንገላን ይወክላል። ቀስት የሌለው ደጋን ማለት ሽንገላ ነው። በ860 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ የመጀጀመሪያው ዘውድ የጫነ የምዕራባዊቷ ቤተክርስቲያን መሪ ነበረ።
በ1315 ዓ.ም ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ መጫን ጀመረ።
በሁለተኛው ማሕተም እንደተገለጸው የሮማ ካቶሊክ ቤተክስቲያን ተቃዋሚዎቿን ጸጥ ለማሰኘት የሮማ መንግስትን ወታደራዊ ኃይል ድጋፍ ተቀበለች፤ ቀዩ ፈረስ ደም መፋሰስን ይወክላል።
ከዚያም ለባርቤሪያውያን ነገስታት ዘውድ በመጫንና ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግስተ ሰማያትን በር እንዲከፍትላቸው ማድረግ የሚችለው ፖፑ ብቻ ነው ብላ በማሳመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓ ውስጥ ፖለቲካዊ ስልጣን ተጎናጸፈች። ከዚያ ወዲያ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከተቃዋሚዎቿ በአስር ሺ የሚቆጠሩትን ገደለች።
ሶስተኛው ማሕተም ሲከፈት የሕይወት እንጀራ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲሸጡ ታይተዋል፤ ደግሞም የስርየት ወረቀትም ሲሸጡ ነበር። ቫቲካን ውስጥ ያሉት የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን እና ሲስታይን ቻፕል ሁለቱም የተገነቡት በስርየት ወረቀት ሽያጭ ከተገኘ ገንዘብ ነው።
ጥቁሩ ፈረስ የመንፈሳዊ ጨለማ ተምሳሌት ነው። ሰው ሰራሽ ዲኖሚኔሽናዊ ስርዓቶች የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ሾልከው ገብተው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስርዓቶችን እንዲኮርጁ አድርገዋቸዋል። የሰዎች አመለካከት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ተክቷል። ይህ ጨለማ እና ስሕተት እያደገ የመጣው ሰው ለሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች ዝቅ ብሎ ከመስገድ እና የሰው ልማዶችን የሚከተሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አባል ከመሆን የተነሳ ነው። በገንዘቧ ብዛት ምክንያት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኃይሏ እየተጠናከረ ሄደ። ሐይማኖት በራሱ ትልቅ ንግድ ሆነ። ባለጠጋዋ ቫቲካን ከተማ በምትመሰረትበት ሰዓት ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ያባረራቸው የገንዘብ ለዋጮች አጋንንታዊ መንፈስ ወደ ቤተክርስቲያን ገባ። ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ሃብት ማሳደድ ጀመሩ። የመንፈስ ቅዱስ ዘይት እና የመንፈሳዊ መገለጥ ወይን ግን ሉተርን ነክተውት መዳን በእምነት በጸጋ መሆኑን እንዲሰብክ፣ ዌስሊ ደግሞ ቅድስናን እንዲሰብክ አስችለውታል። ምሑራንም ተሰብስበው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም ትክክል አድርገው ተረጎሙ።
አራተኛው ፈረስ ሐመር ማለትም እሬሳ የሚመስል መልክ ያለው ነው። የዚህ ፈረስ መልክ የሶስቱ ቀለማት ማለትም ነጭ፣ ቀይ፣ እና ጥቁር ድብልቅ ነው። ይህ የሚንቀሳቀስ ሙት ፈረስ ነው ምክንያቱም ላዩ ላይ የተቀመጠበት ሞት ነው። ከሞት በኋላ በሁለተኛ ቀን የእሬሳ መልክ አረንጓዴ ወደ መሆን ይለወጣል። “ክሎሮስ” በግሪክ አመዳም ሲሆን በተጨማሪ አረንጓዴ ማለትም ነው።
ይህ አራተኛ ማሕተም የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመን ክፋቶች በሙሉ በአንድነት ሲገለጡ ያሳያል።
የሚበርረው ንስር ሚስጥራትን በመግለጥ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክስቲያን ዘመን እንዲመለስ ያደርጋል።
ከዚያ ወዲያ ሙሽራይቱ ወይም ልባሞቹ ቆነጃጅት ዳግም ምጻት ሲደርስ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ።
መንፈስ ቅዱስ ምድርን ትቶ ከመሄዱ የተነሳ ሕይወት ከምድር ስለሚሄድ ከአራተኛው ማሕተም የቀረው ክፍል ሞት በመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ አማካኝነት ወደ ምድር ሲገባ ነው የሚያሳየን፤ እርሱም ሰነፎቹን ቆነጃጅት ያጠፋቸዋል። እነዚህ ሰነፍ ቆነጃጅት ወደ ጥንቷ ቤተክስቲያን ያልተመለሱ ነገር ግን የዳኑ ክርስቲያኖች ናቸው፤ ስለዚህ እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ማረጋገጥ አልቻሉም። ከተጻፈው ቃል ይልቅ የሰውን ንግግር ጥቅሶች መርጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስን በቁም ነገር መቀበል አልተለማመዱም። በመጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ የፓስተራቸውን አመለካከት መስማት መርጠዋል።
በአራተኛው ማሕተም የቤተክርስቲያን ዘመናት ይጠናቀቃሉ። ልባሞቹ ቆነጃጅት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ፤ የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይሞታሉ። ቆነጃጅት ማለት ድንግል ወይም ንጹህ ሴቶች ሲሆኑ እነርሱም ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት የሚድኑ ክርስቲያኖች ናቸው።
አምስተኛው ማሕተም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ስለ እምነታቸው ለሞቱ አይሁዶች መዳንን እንደሰጣቸው ያሳያል። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ያመኑ አይሁዶችን አድኗቸዋል። መሲሁ በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር አይሁዶች መሲሁን እንዳያውቁት አሳወራቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የሚያምኑትንና ስለ እምነታቸው የተገደሉትን አይሁዶች ያድናቸዋል።
ለዚህ ነው አይሁዶች እጅግ መራራ ስደት የደረሰባቸው። አይሁዶች ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ፤ በዚያም 144,000ዎቹ ኢየሱስን በሚስጥር ያገኙታል። ከዚያ በኋላ ይገደላሉ። ነገር ግን በኩራት ይሆናሉ፤ ማለትም ጌታ ለአርማጌዶን ማለትም ለሶስተኛው ምጻት በሚመጣበት ጊዜ እነርሱ ቀድመው ከሞት በመነሳት ለሙሽራይቱ ጥበቃ ያደርጋሉ።
የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ፤ ምዕራፍ 7
በሁለተኛው ትንሳኤ ጊዜ በአምስተኛው ማሕተም (ራዕይ 6፡9-110) በተገለጸው መሰረት “ከመሰዊያው በታች ያሉ ነፍሳት” ነጭ ልብስ እና የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ነጭ ልብሳቸው ምንም ትርጉም አይኖረውም ነበር።
“አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።
ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።”
(አብረዋቸው የሚያገለግሉት 144,000 አይሁዶች ናቸው፤ እነርሱም በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ይገደላሉ።)
ከመሰዊያው በታች ካሉት ውስጥ ማናቸውም እንኳ የተገደሉት ስለ ኢየሱስ ምስክርነት እንዳልሆነ ልብ በሉ። የኢየሱስን ስም አጥብቆ እንደያዘው እንደ አንጢጳስ እንዳልሆኑ አስተውሉ። እነዚህ የዘላለም ሕይወት የተሰጣቸውና ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች አይደሉም። እነዚህ ሰዎች በትንሳኤ ጊዜ ይመጡና ለቃሉ ከነበራቸው አቋም የተነሳ ሕይወትን ይቀበላሉ። ደግሞም ለበቀል እንዴት እንደሚጮሁ አስተውሉ። እነዚህ ሰዎች የሙሽራይቱ አካል መሆን አይችሉም። ሙሽራይቱ ጉንጯን አዙራ እየሰጠች “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብላ ትጮሃለች። እነዚህ ሰዎች አይሁዶች ናቸው ምክንያቱም ከአምስተኛው ማሕተም ስር ነው የተገኙት፤ ምክንያቱም ከአሕዛብ ወገን የሆነችዋ ሙሽራይቱ በአራተኛው ማሕተም መፈታት ውስጥ ነው ተነጥቃ ወደ ሰማይ የሄደችው። ስለዚህ እነዚህ አይሁዶች ከመንፈስ የተወለዱ አይደሉም። እንደውም ኢየሱስ መሲሁ መሆኑንም አያምኑም። ነገር ግን ስለ አሕዛብ መዳን በእግዚአብሔር ስለታወሩ እግዚአብሔር ወደ እርሱ መምጣት ባይችሉም እንኳ ላወቁት ቃል ሁሉ ታማኝ ስለ መሆናቸው እንዲሁም በሒትለር እና በእስታሊን ዘመን ብዙዎቹ ስለ ቃሉ ብለው ስለተገደሉ የዘላለም ሕይወት ሰጥቷቸዋል።
ይህ አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት የሚመጡበት ሁለተኛው ትንሳኤ ነው። እነዚህ ሴቶች ቆነጃጅት ወይም ድንግል መሆናቸውን ልብ በሉ። በመንፈስ ቅዱስ አልተሞሉም ነበር፤ ስለዚህ የሙሽራይቱ አካል ውስጥ መካተት አልቻሉም፤ ዘይት የነበራቸው አምስቱ ግን የሙሽራይቱ አካል መሆን ችለዋል። ሆኖም እነዚህ ራሳቸውን የለዩ እግዚአብሔርንም የሚፈሩ ሰዎች ስለ ቃሉ ያወቁትን ያህል እንደ ቃሉ ለመኖር ይሞክሩ ስለነበር፤ ደግሞም የጌታን ሥራ ይደግፉ ስለነበረ በመጨረሻው ጊዜ ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች የሺ ዓመት መንግስቱን አያዩም፤ እነዚህን እውነቶች ስትማሩ እንደምትረዱት የሺ ዓመት መንግስቱ ከተረዳነው ወይም ካመንነው በላይ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ምዕራፍ 6 በስድስተኛው ማሕተም ነው የሚጠናቀቀው፤ እርሱም የሚናገረው የተፈጥሮ ኡደት በሚቋረጥበት በታላቁ መከራ ውስጥ ምን ዓይነት አሰቃቂ ነገሮች እንደሚፈጸሙ በማሳየት ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 7
ምዕራፍ 7 የሚነግረን የታላቁ መከራ ዓላማ ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ 144,000ዎቹን አይሁዶች ወደ ክርስቶስ እንዲመልሷቸው ለማድረግ መሆኑን ነው።
በተጨማሪ ታላቁ መከራ በቁጥር ብዙ ለሚሆኑትና እንቅልፋቸውን ለተኙት ለሰነፎቹ ቆነጃጅት አስደንጋጭ የመንቃት ጊዜ ይሆንላቸዋል። እነርሱ ኢየሱስን እና ቃሉን ረስተዋል፤ በዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖቻቸውም ታውረዋል። ቤተክርስቲያኖች በገዢዎቻቸው በፓስተሮች ቁጥጥር ስር ወድቀዋል፤ እነዚህም ቤተክርስቲያኖች ማንም አማኝ የፓሰተራቸውን አመለካከት እንዲቃወም አይፈቅዱም። በቤተክርስቲያን ውስጠ አባል ሆነው ለመቆየት ሰዎች በራሳቸው አእምሮ ማሰብን ማቆም አለባቸው፤ ጥያቄ መጠየቅም ማቆም አለባቸው። ማንም ሰው ለፓስተሩ ተሳስተሃል ብሎ የመንገር ድፍረት የለውም። በቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ሁሉም ፓስተሩ የተናገረውን መቀበል አለበባቸው።
ሰዎች በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ በሚሰማቸው ምቾት የተነሳ ቸልተኞች ይሆናሉ፤ ስለዚህ ምንም ችግር ይገጥመናል ብለው አያስቡም። ከዚህም የተነሳ ከቤተክርስቲያናቸው ውጭ የሆነና ሊረዳቸው የሚሞክረውን ማንኛውንም ሰው ይገፉታል። ስለዚህ የቤተክርስቲያናቸውን አስተምሕሮ ብቻ የሚያዳምጡ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ እውነት ማግኘት አይሉም።
ካቶሊኮቹ የሚመሩት በፖፑ ነው፤ እርሱም በመንፈሳዊ አስትምሕሮ ረገድ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው ባለ ስልጣን ነው።
ፕሮቴስታንቶች ቤተክርስቲያናቸውን ሲመሰርቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥርዓትን እንዲመስል አድርገው ነው የቀረጹት (ይህም የአውሬው ምስል ነው)፤ ካቶሊክን ሊመስሉ የቻሉት ፓስተሩ በቤተክርስቲያን ላይ አምባ ገነን ገዥ እንዲሆን አድርገው በመሾም ነው። ይህንን ስርዓት ብትቃወሙ ያባርሩዋችኋል።
ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
ታላቁ መከራ ሲጀምር ሰዎች የቤተክርስቲያናቸውን መሪዎች በመቃወማቸው ብቻ ይገደላሉ።
የዳናችሁ አማኞች ከሆናችሁ በታላቁ መከራ ውስጥ የሚፈጸመው አስፈሪ እውነታ የአውሬውን ምልክት ለመቀበል እምቢ ብትሉ ትሞታላችሁ፤ ምክንያቱም ምልክቱን መቀበል ከቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ጋር እንደ መስማማት ይቆጠራል።
ዛሬ ሰዎች ፓስተራቸውን መቃወም የሞት ያህል ያስፈራቸዋል።
በታላቁ መከራ ውስጥ ግን ፓስተሮቻቸውን ተቃውመው መሞት ያስፈልጋቸዋል። ይህም ብርታት ይጠይቃል። የዚያን ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሳለን ለምን ፈሪዎች ሆንን ብለው ይጸጽታቸዋል። ከቤተክርስቲያን ላለመባረር ብለው በማመቻመቻቸው ያዝናሉ፤ ተወዳጅ መሆንን ላለማጣት ብለው ስሕተትን እያዩ መቃወም ፈርተዋል።
ፓስተሮች ግን እርስ በራሳቸውም በአስተምሕሮ ይጣላሉ። ቤተክርስቲያን በብዙ ልዩ ልዩና የሚጋጩ አመለካከቶች የተሞላች ናት። ከዚህም የተነሳ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች አሉ። ሁሉም የተለያዩ ናቸው፤ ነገር ግን ሁሉም እኔ ትክክል ነኝ ይላሉ።
እነዚህ ሁሉ ልዩነቶች በቁም ነገር ማሰብ ለፈለገ ሰው በጣም ግራ የሚያጋቡ ናቸው። በታላቁ መከራ ሰቆቃ ውስጥ ሰዎች የቤተክርስቲያን አባል መሆናቸው ምንም ትርጉም አልሰጥ ይላቸዋል፤ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳያስተውሉ ያሳወራቸውን የቤተክርስቲያን መሪያቸውን መውደድም ያቆማሉ።
ማንም ሰው ቢሆን ያሳወረውንና ያታለለውን፣ በሰማይ ሊያገኝ የሚችለውን የክብር ስፍራ የሰረቀበትን ሰው ሊወድ አይችልም፤ ይህም ክብር የኢየሱስ ሙሽራ አካል መሆን ነው።
እነዚህ ሁሉ የማይቆጠሩ ሰዎች፤ የዳኑ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ባለማወቃቸው የተነሳ ሰነፎች ወይም ሞኞች የሆኑ ሰዎች በሰማይ ለዘላለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ዜጎች ይሆናሉ። ሙሽራይቱ ወደ ጌታ መጠጋት የምትችለውን ያህል ወደ ጌታ መጠጋት አይችሉም። መልሱን የማያውቁትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ በተጠየቁ ጊዜ መልሱን ማወቁ ምንም አይጠቅምም ብለው ይመልሳሉ፤ ወይም ይህን ሁሉ ዝርዝር አወቅን አላወቅን ምንም ልዩነት አያመጣም ወይም ይህ አይነቱ እውቀት በጣም አስፈላጊ አይደለም ይላሉ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አለማወቃቸውን ወይም ፍላጎት ማጣታቸውን የሚሸፋፍኑበት ዘዴ ይህ ነው።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት “የግድ ማወቅ አለብን?” ሲሉ ይጠይቃሉ፤ እነዚህ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ እንደ ክሪስማስ የመሳሰሉ የቤተክርስቲያን ልማዶችን ይመርጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ የክርስቶስን ልደት እንድናከብር አልጠየቀንም። ዲሴምበር 25 የተባለው ቀን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤ በአረማውያን በዓላት ውስጥ ግን ታዋቂ ቀን ነው።
ልባሞቹ ቆነጃጅት ግን “ማወቅ አለብን!” ይላሉ ምክንያቱም ስለ ኢየሱስ ማለትም ስለ ቃሉ ሁሉንም ነገር ማወቅ ይፈልጋሉ። ልባሞቹ ቆነጃጅት ከአረማዊነት ጉድጓድ ውስጥ ወጥተዋል፤ ስለዚህ ወደዚህ ጉድጓድ ውስጥ ተመልሰው መግባት አይፈልጉም።
የቤተክርስቲያን አመራር በሽማግሌዎች እጅ ቢደረግ ሽማግሌዎች ለአስተማሪዎች በር ይከፍቱላቸው ነበር፤ አስተማሪዎችም እውነትን ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለሕዝቡ ማስተማር በቻሉ ነበር። በዚህም መንገድ አማኞች ሁሉ የሙሽራይቱ አካል ለመሆን ዕድል ባገኙ ነበር። ነገር ግን በዘመናችን ፓስተሩ እና እርሱ የሚለውን ሁሉ አዎ አዎ እያሉ የሚቀበሉ ወዳጆቹ ብቻ ናቸው ማስተማር የሚፈቀድላቸው። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን በእንቅልፍ ውስጥ ደንዝዛ ትቀመጣለች፤ ከመጽሐፍ ቅዱስም ብዙውን ክፍል ሳታውቀው ትቀራለች።
አራቱ የመሬት ማዕዘናት
ራዕይ ምዕራፍ 7 የሚጀምረው ስለ አራቱ የመሬት ማዕዘናት አከራካሪ የሆነ ነገር በመናገረው ነው፤ ምክንያቱም መሬት ማዕዘን ያላት ሳትሆን እንደ ኳስ ክብ ቅርጽ ነው ያላት። ይህ ሃሳብ ኢሳይያስ 11፡12 ውስጥ ተደግሟል።
እግዚአብሔር ምን ሊነግረን እየሞከረ ነው?
ሁለቱም ጥቅሶች እግዚአብሔር ከእስራኤል ርቀው ያሉ አይሁዶችን የሚጠራበትን አሰራር ይገልጣሉ።
ራዕይ 7፡1 ከዚህም በኋላ በአራቱ በምድር ማዕዘን ቆመው አራት መላእክት አየሁ፥ እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።
ነፋስን መያዝ አይቻልም፤ ስለዚህ ይህ ቃል መንፈሳዊ ትርጉም ነው ያለው። እግዚአብሔር በዚህ ቃል የሆነ ነገር እያመላከተን ነው።
ነፋስ የጦርነት እና የግጭት ምሳሌ ነው። ስለዚህ ይህ ጥቅስ የጦርነት እና የግጭት ዘመንን ነው የሚያመላክተው። ጦርነት እና ግጭት በጣም ክፉ ነገሮች ናቸው ነገር ግን በእግዘአብሔር መላእክት ቁጥጥር ውስጥ ናቸው።
ጦርነት በሞላበት ታላቁ መከራ መካከል ኢየሩሳሌም ውስጥ ኢየሱስን ያገኙት ዘንድ እግዚአብሔር 144,000 አይሁዶችን ይጠራቸዋል።
ስለዚህ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት እግዚአብሔር ጦርነቶችን ተጠቅሞ አይሁዶችን ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው ይመልሳቸዋል።
ሮማዊው ጀነራል ታይተስ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምን በደመሰሰ ጊዜ 1,100,000 አይሁዶችን ገድሏል። በ135 ዓ.ም ሮማዊው ንጉስ ሃድሪያን 560,000 አይሁዶችን ገድሏል፤ ኢየሩሳሌምንም ደምስሷል፤ ከዚያም አይሁዶችን ከእስራኤል አውጥቶ ወደ ተለያዩ ሃገሮች በታተናቸው። ከዚያ ምድራቸውን ፓለስታይን ብሎ ጠራ።
ስለዚህ ወንጌል በተጀመረ ጊዜ አይሁዶች በብዙ ደም መፋሰስ ምክንያት ተበታተኑ። አረቦች እና ሌሎችም ሕዝቦች አይሁዶችን መጥላታቸው አይሁዶችን ለማያቋርጥ ስደት ዳርጓቸዋል።
እግዚአብሔር አይሁዶችን ወደ እስራኤል ሊመልሳቸው ሲጀምር የግጭት እና የጦርነት ነፋሳት እንደገና ይነፍሳሉ። አይሁዶች ደማቸውን በማፍሰስ ታላቅ ዋጋ ይከፍላሉ። ነገር ግን ጦርነቱ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላቸውም አራቱ ነፋሳት በእግዚአብሔረ ቁጥጥር ውስጥ ናቸው።
በምድር ላይ አራት ነፋሳት ብቻ አይደሉም ያሉት። እግዚአብሔር “አራት” ብሎ የሚናገረው የሆነ ነገር ለማመልከት ነው።
አራት ነፋሳት - እስራኤል ከአረቦች ጋር አራት ታላላቅ ጦርነቶች ገጥማ እንደነበር ልብ በሉ፤ እነዚህም የተደረጉት በ 1948፣ 1956፣ 1967 እና 1973 ነበር።
ነፋሳቱን መያዝ ማለት እነዚህ ጦርነቶች በሙሉ በመልአኩ ቁጥጥር ስር ነበሩ ማለት ነው። ጠላቶቿ በቁጥር ብዙ ቢበልጧትም በአራቱም ጦርነት እስራኤል አሸንፋለች። የ1948ቱ ጦርነት እስራኤል በቀላሉ ልትጠፋ የምትችልበት ጦርነት ነበር። የአረብ መሪዎች ያደረጉት ቀሽም ውሳኔ ለሽንፈት ዳርጓቸዋል።
አረቦች አይሁዶችን ከምድረ ገጽ መደምሰስ ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ አራት ጦርነቶች ያስከተሉት ውጤት አይሁዶች ለራሳቸው መኖሪያ የሚሆን ሃገር ማግኘታቸው ነው።
አራቱ የምድር ማዕዘናት የሚለው ቃል አይሁዶች ለሁለት ሺ ዓመታት ያህል በምድር ላይ ብዙ ቦታ መበታተናቸውን ይገልጻል። የልጅ ልጆቻቸው እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ሄደዋል።
ኢሳይያስ 11፡12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
የሐዋርያት ሥራ 26፡26 በእርሱ ፊት ደግሞ በግልጥ የምናገረው ንጉሥ ይህን ነገር ያውቃል፤ ከዚህ ነገር አንዳች እንዳይሰወርበት ተረድቼአለሁና፤ ይህ በስውር የተደረገ አይደለምና።
ስለዚህ ማዕዘን የተሰወረ ሚስጥርን ይወክላል።
ከዛሬይቱ ዓለም ክስተቶች በስተጀርባ እግዚአብሔር አይሁዶችን ወደ እስራኤል ለመመለስ በሚስጥር እየሰራ ነው።
ከ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት የተደረጉ የምርጫ ትንተናዎችና ግምቶች ሁሉ ዶናልድ ትራምፕን ያወግዙ ነበር። አስቀድሞ አንዳችም የፖለቲካ ልምድ ያልነበረው ሰው ከመሆኑ ባሻገር በስነ ምግባሩና በባሕርዩ ሁሉ የተነቀፈ ሰው ነበር። ሰውየው ባለጌ፣ ተሳዳቢ እና እንደፈለገ የሚናገር ምንም ስርዓት የሌለው ሰው ተደርጎ ይቆጠራል። በዓለም ዙርያ የፖለቲካ ጠበብቶች ግምት መሰረት ምርጫውን የማሸነፍ ምንም ተስፋ አልነበረውም። ነገር ግን አሸነፈ። ለምን? ምክንያቱም ኢየሩሳሌምን መልሶ የእስራኤል ዋና ከተማ ለማድረግ እግዚአብሔር በሚስጥር የላከው አገልጋይ ነው። ማንም ሰው ለደቂቃ እንኳ እግዚአብሔር ፕሬዚዳንት ትራምፕን እየተጠቀመ እንደሆነ አላሰበም። ሰይጣንን ጨምሮ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው አሞኝቷል።
በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተነሳ እስራኤል አንድ ማዕዘን አልፋለች። ጥንታዊ ትንቤት ተፈጸመ። ኢየሩሳሌም በምድር ላይ የእስራኤል ዋና ከተማ ሆነች፤ ይህም ሊሆን የቻለው ከ2,600 ዓመታት እግዚአብሔር በተናገረው ታላቅ ትንቢት ምክንያት ነው። እኛ ሰዎች ስለ ወደፊቱ በመተንበይ የተዋጣልን አይደለንም። የአሜሪካ የፖለቲካ ጠበብቶች ባደረጉት ትንበያ ሁሉ በዚያ ዓመት የተደረገውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማን እንደሚያሸንፍ በትክክል ሊተነብዩ አልቻሉም።
የዓለም መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጦች ሁሉ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ባህርይ ለፕሬዚዳንትነት የሚያበቃ አይደለም ይላሉ። በምድር ላይ በሚያዩት የትራምፕ ያልተጠበቀ ዓይነትና ስነምግባር የጎደለው ባህርይ ከመታወራቸው የተነሳ በሰማይ እግዚአብሔር በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ትንቢትን ለመፈጸም እንዴት እየተጠቀመበት እንደነበረ ማየት አልቻሉም። ምንም ሳይፈራ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ሰጠ። ወደፊት በዓለም ዙርያ ተበታትነው ያሉት 144,000 አይሁዶች በኢየሩሳሌም ተሰብስበው መሲሁን ያገኙትና ዳግመኛ ይወለዳሉ ወይም ከሰማይ ይወለዳሉ። ሰዎች በማያስተውሉት መንገድ እግዚአብሔር 144,000 አይሁዶችን ለመቤዠት ያዘጋጀው እቅድ ወደ ስኬት እየገሰገሰ ነው።
ፍጥረታዊ ማዕዘን ሁለት መንገዶች ወይም ሁለት ግድግዳዎች የሚጋጠሙበት ቦታ ነው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ቋንቋ ስናስበው ማዕዘን መንፈሳዊው እና ፍጥረታዊው የሚጋጠሙበት ቦታ ነው። የእኛ ዓይኖች ከጊዜ ግድግዳ አሻግረው ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ዓለም በስራ ላይ ሊመለከቱ አይችሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር የአሁኑን የአይሁድ ታሪክ ቅርጽ በማስያዝ ለአይሁዶች በታላቁ መከራ ውስጥ ካቀደላቸው እቅድ ጋር እንዲገጥም ለማድረግ እየሰራ ነው።
ማርቆስ 13፡27 በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።
በተጨማሪ ማዕዘን በጣም እሩቅ የሆኑ ቦታዎችንም ይወክላል።
ከእስራኤል ጋር ሥራውን በሚሰራ ጊዜ እግዚአብሔር 144,000 አይሁዶችን በመንፈስ ቅዱስ ስለ መሙላት ሲያስብ ዘላለማዊ ዕቅድ እየተመለከተ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ፍጥረታዊውንና ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ወደ አንድ እያመጣ ነው። እግዚአብሔር በምድር ላይ ተበታትነው የነበሩ አይሁዶችን ለመሰብሰብ ግጭቶችንና ጦርነቶችን ተጠቅሟል። አይሁዶቹ በእስራኤል ምድር ፍጥረታዊ በሆነ መንገድ መሰባሰባቸው ወደፊት በመንፈስ ቅዱስ ለሚሞሉት 144,000 አይሁዶች መንፈሳዊ መሰባሰብ መንገድ ይጠርጋል። ይህ መነቃቃት እግዚአብሔር ለመጨረሻው ጊዜ ከሰማይ እንዲወለዱ ላሰባቸው ልጆቹ ዝግጅት አስተዋጽኦ ያደርጋል። እግዚአብሔር አይሁዶችን አሳውሯቸዋል፤ ስለዚህ ለ2,000 ባለፉት ዓመታት ውስጥ የተቻላቸውን ያህል ለብሉይ ኪዳን ታማኝ ለሆኑትና ስለ እምነታቸው ለሞቱት አይሁዶች መዳንን ሰጥቷቸዋል። ይህ ሚስጥራዊ የሆነ የማዳን እቅድ በእሩቅ ሥፍራ ተበታትነው ያሉ አይሁዶች ከመሰዊያው በታች ሥፍራ እንዲያገኙ ዕድል ሰጥቷቸዋል።
54-0103M ጥያቄዎችና መልሶች
“መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ነፋሳት” የተባሉት ጦርነቶችና ግጭቶች ናቸው።”
በጦርነት እና በግጭት ጊዜ እስራኤሎች እንደገና ይሰባሰባሉ።
“አራቱ የምድር ማዕዘናት”
እግዚአብሔር ስለ ምድር የሚናገረውን ስንተረጉም በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ምድር ጊዜያዊ ናት። ለዘላለም ልትኖር አትችልም።
እግዚአብሔር ግን ጠለቅ ያሉ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ ከዘላለማዊ ሃሳብ አንጻር እያሰበ ነው። ይህም ሃሳቡ እንዲፈጸም ያሁኗ ምድራችን ከተሰራችባቸው አተሞች እጅግ በተሻሉ ነገሮች የተሰራች አዲስ ምድር ታስፈልጋለች። ሳይንቲስቶች ዓለማችን ለዘላለም ጸንታ ልትኖር እንደማትችል አምነዋል።
1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9 ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
የወደፊቷ ምድር ምን ልትመስል እንደምትችል እንኳ መገመት አንችልም።
እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን በኤድን ገነት ሳሉ ይህችን ምድር ረግሟታል። ስለዚህ እግዚአብሔር አዲስ ምድር ሊፈጥር አስቧል። አዲሲቷ ምድር አሁን ከምናውቀው የፊዚክስና የኬሚስትሪ ሕግ በተሻለ አሰራር ነው የምትሰራው።
እግዚአብሔር ለኢዮብ ምን እንዳለ ተመልከቱ።
ኢዮብ 38፡4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።
ኢዮብ 38፡6 ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥
በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?
ምድር በሕዋ ውስጥ ተንሳፍፋ ነው ያለችው። ታዲያ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ የምድር ማዕዘንና መሰረት እያለ ሲናገር ምን ማለቱ ነው? እነዚህ ማዕዘናትና መሰረቶች ምሳሌያዊ ናቸው ወይም እርግጥ የሚታዩ ናቸው?
ሳይንቲስቶች ዓለማችን ለዘላለም ጸንታ መኖር እንደማትችል ያምናሉ። ፀሃይ ወደፊት በውስጧ ያለውን ኑክሊየር ነዳጅ ተጠቅማበት ጨርሳ ትልቅ ቀይ ኮከብ ትሆንና ምድርን ትበላታለች።
እግዚአብሔር የሚናገረው ስለ ዘላለማዊ ምድር ነው። እኛ የምንኖርባት ምድር ጊዜያዊ ምድር ናት። ይህችም ምድር አንድ ቀን ትወገዳለች ምክንያቱም ዮሐንስ አዲስ ምድር አይቷል። ይህች ምድር ለእምነታችን የመፈተኛ ጊዜ ናት። የሳይንስ ቲዎሪዎች ስለ ኤቮልዩሽን ወይም ዘገምተኛ ለውጥ እንዲሁም ስለ ቢግ ባንግ ቢያወሩም እንኳ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ጠብቀው ለሚቆዩ ሰዎች ለዘላለም መኖሪያ እንድትሆን እግዚአብሔር አዲስ ምድርን ለማዘጋጀት አስቧል። መጽሐፍ ቅዱስን ለተቃወሙ እና ለነቀፉ ሳይንቲስቶች ሰይጣን ሞቅ ያለ አቀባበል አዘጋጅቶላቸዋል።
ራዕይ 21፡1 አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።
ብዙ ሳይንቲስቶች እንደሚያምኑት ኤቮልዩሽን የጀመረው ባሕር ውስጥ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ባሕርን ያፈነዳዋል፤ ከባህርም ውስጥ የሚወጣው ነበልባል ሕዋ ውስጥ ያሉትን ሳተላይቶች ያቃጥላቸዋል፤ የምድርንም ገጽ በሙሉ ያቃጥላል፤ የማዕድን ቁፋሮዎቻችንን እንዲሁም የሳይንሳዊ ስልጣኔያችንን ማስረጃዎች ሁሉ ያቃጥላቸዋል።
ኢሳይያስ 28፡16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ የሚያምን አያፍርም።
ይህ ፍጥረታዊ ድንጋይ አይደለም። ይህ ድንጋይ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው። በዘመን መጨረሻ የሚገኝ ሰው ሳይጠፋ እስከዚያ የሚደርሰው በስራ ሳይሆን በእምነት ነው።
“የሚያምን አይቸኩልም” ወይም አያፍርም የሚለው ቃል የዚያን ጊዜ የሁኑ ዓለም የተጥለቀለቀበት ውድድር፣ ሩጫ፣ ጋጋታና ሰዓት ቆጠራ በዚያ ጊዜ እንደማይኖር የሚያመለክት ነው።
በአዲሲቱ ምድር ውስጥ የገባ ሰው የተጻፈውን ቃል ያምናል። በመጽሐፍ ቅዱስ እና በኢየሱስ ማመን ወደ ዘላለማዊነት የሚያስገባ ጽኑ መሰረት ነው። ኢየሱስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ናቸው ወደ ዘላለማዊነት የሚያስገቡን።
ማቴዎስ 24፡35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
ሳይንቲስቶች ይህች ግኡዝ ዓለማችን ለዘላለም ጸንታ እንደማትኖር አውቀዋል። የአሁኗ ዓለም ከተሰራችባቸው አተሞች ይልቅ በተሻሉ ነገሮች የተሰራች ሌላ ዓለም ታስፈልገናለች። በሳይንሳዊ እውቀት እና በገንዘብ ላይ የተመሰረተች ሳትሆን በእምነት፣ በፍቅር፣ እና በየዋህነት ላይ የተመሰረት አዲስ ማሕበረሰብ ያስፈልገናል።
ዘላለማዊነት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።
ከዘላለም እስከ ዘላለም የማይቋረጥ ዓለም ሊኖረን የሚችለው በክርስቶስ ብቻ ነው። ዘላለማዊነት የሚገለጠው በክርስቶስ ነው።
ኤፌሶን 3፡21 ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
ኤፌሶን 2፡20 እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥
የአዲሲቷ ምድር መሰረት መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አዲስ ኪዳን የተጻፈው በሐዋርያት ነው፤ ብሉይ ኪዳን ደግሞ በነብያት። የአዲስ ኪዳንን መሰረት ከብሉይ ኪዳን መሰረት ጋር አጋጥሞ የያዘው የአዲሲቱ ምድር የማዕዘን ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ስለዚህ ምድር ለዘላለም መቆየት ትችል ዘንድ ሙሉ በሙሉ እንደገና በኢየሱስ መሰራት አለባት።
“አራት” ቁጥር የሚወክለው ምንድነው?
ኤርምያስ 49፡36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም።
አራቱ የሰማይ ማዕዘናት የሚያመለክቱን ወደ ልዕለ ተፈጥሮአዊው ዓለም ነው፤ በዚህ ዓለም ውስጥ በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ጦርነት ይደረጋል። ሰማይ አራት ሥፍራዎች ብቻ አይደለም ያሉት፤ ምክንያቱም ሰማይ እና የሰማይ ሰማያት አሉ፤ ይህም የእኛ አእምሮ ሊገነዘብ ከሚችለው በላይ የሆነ እውነታ ነው።
ዘዳግም 10፡14 እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።
“አራቱ የሰማይ ማዕዘናት” የሚለው ቃል “አራት እጥፍ ድርብ የሆነ ሰማያዊ እቅድን” ያመለክታል፤ ይህም እግዚአብሔር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያንን ለማዳን ያወጣው እቅድ ነው።
ሰማይን ብንመለከት እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ሆኖ በአራት እንስሳት ወይም ሕያዋን ፍጥረታት ተከብቦ እናያለን፤ እነዚህ ፍጥረታት በምድር ላይ ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ጥበቃ ያደርጋሉ።
ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
ሰማያዊ ወይም መንፈሳዊ እውነታ በሰዎች ቋንቋ በትክክል ሊገለጽ አይችልም፤ ምክንያቱም እኛ ሰዎች መንፈሳዊ ነገሮችን በትክክል የምንገልጽበት ትክክለኛ ቃላት የሉንም። ሰማይ እኛ መረዳት የማንችላቸው የራሱ የሆኑ መርሆች አሉት።
እነዚህ እንስሳት በዙፋኑ ዙርያ እና በዙፋኑ መካከል ነው የሚገኙት (ይህ ግን እግዚአብሔር ተቀምጦ የሚገኝበት ሥፍራ ነው)።
ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲሆን ፈቃዱን የሚገልጽበት ወይም የሚያከናውንበት አራት የተለያዩ መንገዶች አሉት። በ2,000 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ቤተክርስቲያንን የሚመራበትና ቅርጽ የሚያስይዝበት አራት መንገዶች አሉት። እነዚህ አራት ፍጥረታት ወይም መናፍስት በፊታቸውና በጀርባቸው ብዙ ዓይኖች አሏቸው። በምድራችን ላይ እንደዚህ ያለ ፍጥረት የለም - ዓይኖች የጥበብና የማስተዋል ምሳሌ ናቸው። እነዚህ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ፍጥረታት በጥበብ የተሞሉ ከመሆናቸው የተነሳ ስለ ወደፊቱ ከእኛ አስቀድመው ያውቃሉ፤ ከእኛ በስተኋላ የነበረውን የቤተክርስቲያን ታሪክም ያውቃሉ።
እነዚህ አራት ሕያዋን ፍጥረታት እግዚአብሔር ባለፉት 2,000 ዓመታት በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያንን የሰራበትን አራት ደረጃዎች ይወክላሉ።
ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
የእንስሳት ሁሉ ንጉስ እንደመሆኑ የአንበሳው መንፈስ ቤተክርስቲያንን በመጀመሪያው ዘመኗ መርቷታል፤ ኢየሱስ ንጉስ ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስም እንከን የሌለው የኢየሱስ ቃል ሆኖ በታየበት በዚያ ጥንታዊ ዘመን ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን መሰረቷት። በሬ በትጋት በብዙ ልፋት ይሰራል፤ በስተመጨረሻም ሥጋው በጣም ተፈላጊ ስለሆነ ይታረዳል። የበሬው መንፈስ በጨለማው ዘመን ውስጥ ክርስቲያኖች ከአስር ሚሊዮን በሚበልጥ ቁጥር እየተገደሉ በነበረበት ሰዓት በትጋት እየሰሩ እንዲታገሱ አስችሏቸዋል። በሰው የተመሰለው መንፈስ ደግሞ የተሃድሶ መሪዎች ዘመን ነው፤ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ጥበብ መዳን በእምነት ብቻ መሆኑን ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር እንዲገልጥ፤ ከዚያም እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ጆን ዌስሊ ቅድስናን እና የወንጌል ስርጭትን እንዲያስተምር አስችሏል፤ ይህም መነቃቃት ለታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት በር ከፈተ። የሰው አእምሮ በተባረከበት የሰው መንፈስ ዘመን ውስጥ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ከ1604 እስከ 1611 ባሉት ዓመታት ውስጥ በ47 ምሑራን ተተረጎመ፤ ከዚያ በኋላ ለ158 ዓመታት ያህል የትርጉሙ ትክክለኛነት ሲፈተሽ ቆይቷል፤ ይህም ፍተሻ የተደረገው በዋነኛነት የ1769ኙ እትም ከመዘጋጀቱ በፊት የቃላቱን ፊደሎች ለማስተካከል ነው። የትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የዚህን ያህል ብዙ ዓመታት ተወስዶበት ፊደሎቹ በጥንቃቄ የታረሙለት የለም። ስለዚህ ይህ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የወንጌል ስርጭት ዘመን እና የፔንቲኮስታል መንፈሳዊ መነቃቃት የጀርባ አጥንት ሊሆን ችሏል። ከዚያ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመረዳት ላይ ግን የሰው ጥበብ የማስተዋል ገደቡ ላይ ደረሰ።
ኢየሱስ አንዲትን ሐጥያተኛ ሴት ከከሳሾቿ ባዳነበት ጊዜ ለምንድነው ምድር ላይ በጣቱ ሁለት ጊዜ የጻፈው? በኤደን ገነት ውስጥ እግዚአብሔር የረገመው ምድርን መሆኑን አስታውሱ። ቤተክርስቲያኖች ይህንን ሚስጥር ለመረዳት መሞከር ይተዉና አይጠቅምም ይላሉ። ግን ትክክል አይደሉም። ኢየሱስ ያደረገው ነገር ሁሉ ይጠቅማል።
ኢየሱስ ብዙ ሺ ሰዎችን ያበላ ጊዜ ቁርስራሾች ሲሰበሰቡ 12 መሶብ እና 7 ቅርጫት የሆኑት ለምንድነው?
ማቴዎስ 16፡9 ገና አታስተውሉምን? ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ ሰዎች ያልበሏቸው ምን ያህል የምግብ ቁርስራሽ እንደሰበሰቡ እንዲያስተውሉ ፈልጓል። እናንተስ ታስተውላላችሁ? ለማወቅስ ፍላጎት አላችሁ? ወይስ ጥያቄውን ትሸሻላችሁ?
ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በጥቂት ምግብ ሺዎች ጠግበው የበሉበት ተዓምር ላይ ነው ትኩረታቸው። ኢየሱስ ግን ትኩረቱ ሰዎች አንበላም ብለው በጣሉት ቁርስራሽ ላይ ነው።
በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ 5,000 ሰዎች ጠግበው በሉ፤ ይህም ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል፤ ምክንያቱም እንጀራ እና ስጋ የአስተምሕሮ ምሳሌዎች ናቸው። ኢየሱስ ምግቡን ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀመዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ። ኢየሱስ በመንፈሱ የአዲስ ኪዳንን ሚስጥር ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ጽፈው አስቀመጡት። የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ከተጻፈው ቃል መማር አለባቸው።
የዚያን ጊዜ 5,000 ሰዎች ጠግበው በሉና አስራ ሁለት ቅርጫት የተረፈ ቁርስራሽ አንበላም አሉ። ይህ ሃብታም ሆኛለሁ፣ ባለጠጋ ሆኛለሁ፣ ምንም አያስፈልገኝም የምትለዋን የሎዶቅያ ቤተክስቲያንን ይወክላል። ይህች ቤተክርስቲያን በመጀመሪያው ዘመን የተጻፈውን ቃል እና ኢየሱስን ገፍታ አስወጥታለች። በመጨረሻው ዘመን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ አልቀበልም ብላ ትጥለዋለች። ነገር ግን የመጨረሻዋ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን የጣለችውን ቃል ሁለቱ ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ሰብስበው ያነሱና በዚሁ ቃል አስራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች ይመግቡበታል።
ስለዚህ ዛሬ ቤተክርስቲያኖች የክርስቶስ መንፈስ አለን ይላሉ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ሚስጥራትን ለምን መረዳት እንደማይችሉ አይገባቸውም። በተለይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን ከሆነ የመጣው ለምንድነው ብዙ ሚስጥራትን መረዳት ያልቻልነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ንስሩ በ1906 የሎሳንጀለስ አዙዛ ጎዳና ላይ በመጣው መነቃቃት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለስ አደረገ። በ1963 አሪዞና ውስጥ ሰባት መላእክት ወደ ዊልያም ብራንሐም መጥተው ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጻፈውን የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር እንዲገልጥ ትዕዛዝ ሰጡት። እነዚህ ሚስጥራት ቤተክርስቲያን ጳውሎስ እና ሌሎቹ ሐዋርያት ወዳስተማሩት ወደ ጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ እንድትችል ይረዷታል።
የወንድም ብራንሐምን አገልግሎት ከተረዳነው ሙሽራይቱ የሐዋርያትን ትምሕርት ዘር ከተዘራበት ከዘፍጥረት ጀምሮ ሁሉ እስከሚጠናቀቅበት እስከ ራዕይ መጽሐፍ ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት የጥንቷን ቤተክርስቲያን እምነት መከተል ትችላለች።
ስለዚህ እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ቤተክርስቲያንን በአራት መንገዶች መርቷል።
እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር ያለውን ጉዳይ በአራት የተለያዩ መንገዶች ያስተናግዳል
ለዚህ ነው መላእክቱ በአራት ማዕዘናት ላይ የቆሙት።
ሕዝቅኤል በግዞት ሃገር ስለነበሩ አይሁዶች ሲናገር በሕይወት ተመልሰው ለመኖር አራት ደረጃዎችን ማለፍ የሚያስፈልጋቸው የተበታተኑ አጥንቶች አንደሆኑ አድርጎ ገለጸ። በግዚት ሃገር ውስጥ ተበታትነው ሳሉ የሞተ ሰው አጥንት ይመስሉ ነበር። እነዚህን ሰዎች ወደ ሕይወት ለመመለስ እግዚአብሔር አራት ሥራዎችን ሰራ፤ ማለትም ጅማት ፈጠረላቸው፣ ሥጋ ፈጠረላቸው፤ ቁርበት ሰራላቸው፤ ከዚያም አራተኛውና ዋነኛውን ሥረ አደረገ፤ ይህም ከሞት ወደ ሕይወት ይመለሱ ዘንድ እስትንፋስን አገባባቸው።
አራተኛው ደራጃ በሁለቱ ነብያት በሙሴ እና በኤልያስ አገልግሎት ይከናወናል፤ ይህም አይሁዶቹ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት የዘላለም ሕይወትን መቀበላቸው ነው።
ሕዝቅኤል 37፡8 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።
9 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል አለኝ።
10 እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።
በመጨረሻው ደረጃ ላይ አራቱ ነፋሳት እንዴት እንደነፈሱ አስተውሉ። ትክክለኞቹ ግጭቶችና ጦርነቶች የሚካሄዱት በታላቁ መከራ ውስጥ ነው። ያም ጊዜ አይሁዶች ላይ ከባድ ጥቃት የሚሰነዘርበት ጊዜ ሲሆን ሁለቱ ነብያት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸውን በመጠቀም ነው እስራኤልን ከጥፋት የሚታደጓት።
በዚህ ግጭት ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያደርጋቸው አራት እንቅስቃሴዎች በልዕለ ተፈጥሮአዊው ዓለም ውስጥ በሰይጣን ሰራዊት በሚያደርጓቸው አራት የአጸፋ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ተቃውሞ ይገጥማቸዋል።
ሰይጣን በእስራኤል ላይ የሚሰነዝረው ጥቃት አራት አቅጣጫዎች አሉት።
1. ዓለም ሁሉ አይሁዶችን እንዲጠሉ ያደርጋል
2. አይሁዶችን የማሳደድ፣ የመግደል፣ እና የማጥፋት ጽኑ ፍላጎት በሰዎች ልብ ውስጥ ይቀሰቅሳል
3. የእስራኤልን ምድር ለአይሁዳውያን መኖሪያ እንዳትሰጥ ይከለክላል
4. መሲሃቸውን እንዳያገኙት ብሎ ብዙ አይሁዶች ወደ እስራኤል መመለስን እምቢ እንዲሉ ያደርጋል
በ1948፣ 1956፣ 1967፣ እና በ1973 የተደረጉ አራት የአረብና የእስራኤል ጦርነቶች አንድ ዓላማ አላቸው፤ ይህም “አይሁዶችን እናጥፋ፤ ጥርግርግ አድርገን ባሕር ውስጥ እንጣላቸው” የሚል ነው።
አይሁዶች የራሳቸው ሃገር እንዳይኖራቸው አራት የጦርነት ነፋሳት ነፍሰዋል። ነፋሳቱን የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጣቸው አራቱ መላእክት ዋነኛ ሥራቸው አይሁዶችን የጥንት ሮማ መንግስት በዓለም ዙርያ ከበታተናቸው ቦታ ሁሉ ሰብስበው በማምጣት የአይሁድ መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ ነው። ሮማውያን የአይሁዶችን ቤተመቅደስ በ70 ዓ.ም አፈረሱ፤ ሙስሊሞች ደግሞ በ692 ዓ.ም ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለውን የጥፋት እርኩሰታቸውን ሰሩ፤ በ705 ዓ.ም አል-አቅሳ የተባለውን መስጊድ ብዙዎች የአይሁድ ቤተመቅደስ ቆሞበት ነበር ብለው በሚያስቡበት የተቀደሰ ሥፍራ ሰሩ።
ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለመረዳት ብዙ ጥበብ ይጠይቃል። ሮም ቤተመቅደሱን አፍርሳ ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ላይ ቆመች። ከዚያ ሙስሊሞች መስጊዳቸውን በዚያው ቦታ ላይ ሰሩ። በዚያ ሥፍራ ሁለት ሐይማኖቶች ተወለዱ፤ እነርሱም የሮማ ካቶሊክ እና እስልምና ናቸው። ኢየሱስ ሁለቱንም አውግዟቸዋል። አይሁዶች ፈጽመው በሮማውያን ተሸነፉና ተበታተኑ ከዚያም በብዙ ሙስሊም ሃገሮች ተሸነፉ።
ነገር ግን ምንም ያህል የማይቻል ቢመስልም አይሁዶች ወደ እስራኤል መመለስ አለባቸው።
በአራት ጦርነቶች፣ በአራት ነፋሳት የዛሬዋ የእስራኤል መንግስት ተመሰረተች።
በ1967 አይሁዶች የስድስቱን ቀን ጦርነት አሸነፉ፤ ነገር ግን በጣም ብዙ ግዛቶችን ተቆጣጠሩ። የተስፋይቱ ምድር አካል ያልነበረውን የሲና ምድረበዳ ያዙ። ከዚያ በኋላ በ1973 በሲና ምድረበዳ ምክንያት ጦርነት ውስጥ ገቡና የያዙትን የሲና ምድረበዳ ለግብጽ መልሰው አስረከቡ።
እግዚአብሔር የሚፈልገው ለአብርሃም ሰጥቶ የነበረውን ብቻ እንዲይዙ ነው።
በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሔር ሙሽራይቱ በተጻፈው ቃል ውስጥ የሚገኘውን አስተምሕሮ ብቻ አንድታምን ይፈልጋል። ይህም የክሪስማስ ዛፍን እና የፋሲካ ጥንቸሎች እንቁላልን አያካትትም። ማጨስ፣ መጠጣት፣ መማል፣ ጸያፍ ቀልዶችን ማውራት፣ መደነስ፣ በሐጥያት መኖር፣ መፋታትና እንደገና መጋባት ለክርስቲያኖች አይፈቀዱም። እነዚህ ሁሉ ልማዶች እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች መኖሪያ አድርጎ ከሰጣቸው ግዛት ውጭ ናቸው። አንመለስም ብለን በነዚህ ልማዶች ብንጸና ታላቁ መከራ ይመጣና ከሐጥያት ልማዳችን ያላቅቀናል።
ኢየሱስ አይሁዶችን ለመመለስ ስለሚያግዙ ሁለት መላእክት ተናግሯል።
መልአክ መልእክተኛ ወይም ነብይ ነው። ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ ታላቁን የወንጌል መለከት ድምጽ ይዘው 144,000 አይሁዶች ኢየሩሳሌም ውስጥ ኢየሱስን አግኝተው እንደ መሲሃቸው ይቀበሉት ዘንድ ይሰበስቧቸዋል። ዳግመኛ ስትወለዱ በሰማይ መንፈሳዊ አካል ይዘጋጅላችኋል። እምነታችሁ ሲያድግ በዚያ መንፈሳዊ አካል ውስጥ ያሉ መንፈሳዊ ጡንቻዎች እየበረቱ ይሄዳሉ። ስትሞቱ መንፈሳችሁ ስጋዊ አካላችሁን ለቆ ይሄድና መንፈሳዊ አካላችሁ ውስጥ ይገባል።
144,000ዎቹ በሙሉ በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ይገደላሉ። በመንፈሳዊው የሰማይ ዓለም ውስጥ ከሚሰራው ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ስለተወለዱ ከእነርሱ ርቀው ሰማይ ውስት የተሰሩ መንፈሳዊ አካሎቻቸው በሙሉ ዳግመኛ የተወለዱትን እነዚህን ሰማእታት ለመቀበል ይሰበሰባሉ።
ማቴዎስ 224፡31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።
እነዚህ ከሰማይ የተወለዱ ዜጎች ናቸው። “ዳግመኛ የተወለዱ” ብለን የምንጠራው እንደነዚህ ሰማያዊ ከሆነው ከእግዚአብሔር መንፈስ የተወለዱትን ነው።
ሁለቱ ነብያት በዓለም ዙርያ ሁሉ አንዳዶቹ በጣም እሩቅ ቦታ የተበታተኑትን 144,000 አይሁዳውያን መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ መቶ አርባ አራት ሺ አይሁዳውያን ወደ ኢየሩሳሌም መምጣት፤ በዚያም ኢየሱስን አግኝተው እንደ መሲሃቸው መቀበል እና ዳግመኛ ተወልደው በመንፈስ ቅዱስ መሞላት አለባቸው። ከዚያ በኋላ ይሞታሉ ምክንያቱም በኩራት ናቸው። በሰማይ በተዘጋጀላቸው በማይሞተው ሰማያዊ አካላቸው ውስጥ ሆነው በትንሳኤ ከሞት ይነሳሉ። የእነርሱ ተልእኮ ጌታ ለአርማጌዶን ጦርነት በሚመለስበት ጊዜ ለሙሽራይቱ ጥበቃ ማድረግ ነው።
ራዕይ 14፡1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
4 ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።
ስለዚህ 144,000ዎቹ አይሁዳውያን ከሰማይ የተወለዱ ዜጎች ናቸው፤ ነገር ግን ለጊዜው ሁለቱ ነብያት ጠርተው ወደ እስራኤል እስኪመልሷቸው ድረስ በምድር ላይ ብዙ ቦታ ተበታትነው እየኖሩ ናቸው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመቤዠት በአራት መንፈሳዊ ደረጃዎች ይሰራል -- ሰይጣንም ይህንን ኮርጆ ተመሳሳይ ነገር ያደርጋል
ሰይጣን በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ አራት የአሕዛብ መንግስታትን በመጠቀም የተንኮል ስራውን ጀመረ።
ዳንኤል 7፡2 ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ በሌሊት በራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባሕር ላይ ይጋጩ ነበር።
3 አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች።
አራት አጋንንታዊ ኃይላት እንደ ጦረኛ መንግስታት ሆነው ተነሱ፤ እነርሱም ባቢሎን፣ ፋርስ እና ሜዶን፣ ግሪክ፣ እና ሮም ናቸው።
ባቢሎናውያን በጣም ጥበበኞች ነበሩ። እነርሱ የፈጠሩዋቸው አረማዊ ሐይማኖቶች ኋላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልከው ገብተዋል። የወርቅ ራስ የሚለው “ኮከብህ እንዲህ ይላል” የሚሉና የመሳሰሉ ትንበያዎችን የያዘ ወርቃ ሃሳብን እና በስላሴ ማመንን ያመለክታል። የኮከብ ትንበያዎች እስከ ዛሬ ድረስ በየጋዜጦችና መጽሔቶች ውስጥ ይገኛል።
ፋርስና ሜዶን ባቢሎንን ባሸነፉ ጊዜ የባቢሎን ካሕናት ሸሽተው ወደ ጴርጋሞን ገቡ።
ግሪክ ፋርስን ባሸነፈች ጊዜ አሌግዛንደር እራሱን አምላክ ነኝ ብሎ ሰየመ። አሌግዛንደር በሞተ ጊዜ መንግስቱ ለአራት ተከፈለ፤ አራቱን ግዛት የተቆጣጠሩ አራት ጀነራሎችም በተራቸው አማልክት ነን አሉ። ስለዚህ የባቢሎናውያን ሚስጥር ሊቀ ካሕንነት ወይም ፖንቲፍ የተባለው ስልጣን በጴርጋሞን (በግሪክኛ ጴርጋሞስ) ግዛት ውስጥ ለግሪኩ አምላክ-ንጉስ ተላለፈ፤ ጴርጋሞን የዚያ ግዛት ዋና ከተማ ነበረች። ግሪኮቹ ጴርጋሞስ ብለው ይጽፋሉ፤ የተለመደው አጻጻፍ ግን ጴርጋሞን ነው።
አራቱ ጀነራሎች ሞቱ፤ ከዚያ ወዲያ ግሪኮቹ ኃይላቸው ስለተዳከመ አንድ ግሪካዊ አምላክ ሊሆን ይችላል የሚለው ሃሳብ እየደበዘዘ ሄደ።
ነገር ግን ባቢሎናዊው ሊቀ ካሕናት በጴርጋሞን ውስጥ በነገሰ ጊዜ ካሕናት-ነገስታት በስልጣን የሚተካኩበትን ትክክለኛ የዘር ሃረግ መሰረተ፤ እነዚህ ካሕናት ነገስታት ከመጀመሪያዎቹ የባቢሎን ካሕናት የተወለዱ ናቸው። አረማውያን ባቢሎንን የባዕድ አምልኮ ትክክለኛ ማዕከል አድርገው ይቆጥሯት ነበር። ምስጢራዊ ሐይማኖት በመምራት ባቢሎናውያን የሚወዳደራቸው የለም። የጴርጋሞን ንጉስ ከትክክለኞቹ የባቢሎን ንጉስ-ካሕናት ወይም ከፖንቲፍ መወለዱ አምላክ ነኝ ብሎ እንዲያውጅ በቂ መብትና ተቀባይነት ሰጥቶታል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ133 ጴርጋሞን የሮማ መንግስት አካል ሆነች። ባቢሎናዊው ፖንቲፍ መንግስት ውስጥ ብዙም ሚና አልነበረውም፤ ከዚያ በኋላ በ63 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ ፖንቲፍ ሆነ። ዩልየስ ቄሳር የሮም አምባ ገነን መሪ ሆነ፤ ለባቢሎናውያን የፖንቲፍ ስልጣንም ትልቅ ክብርን አጎናጸፈ። ሮማውያን መሪዎች ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ እስከ 378 ዓ.ም ድረስ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ከዚያ በኋላ ግን ንጉስ ቴዎዶሲየስ ይህንን ማዕረግ ለመጠቀም እምቢ አለ፤ ያቀረበውም ምክንያት ክርስቲያን የአረማውያን ፖንቲፍ መሆን አይችልም የሚል ነበር። ቀጥሎም ቴዎዶሲየስ ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ በ382 ዓ.ም የሮም ኤጲስ ቆጶስ ለነበረው ለአጎቱ ለዳማሰስ አሳልፎ ሰጠ።
በ400 ዓ.ም የሮም ኢጲስ ቆጶስ እራሱን ፖንቲፍ ፖፕ ብሎ መጥራት ጀመረ።
የባቢሎናውያን ሚስጥራ ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክስቲያን ሾልከው በመግባት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የባቢሎን ሚስጥር አድርገዋታል። እስከ ዛሬ ድረስ ካቶሊኮች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የዓለም ቤተክርስቲያኖች ሁሉ እናት አድርገው ያዩዋታል። ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችን ደግሞ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልጆች አድርገው ይቆጥራሉ።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ራዕይ ምዕራፍ 6 የክርስቶስ ተቃዋሚው ሶስት የተለያዩ ፈረሶች ላይ ተቀምጦ ሲሄድ ያሳያል፤ እነዚህም ሶስት ፈረሶች ተጣምረው አራተኛውን ፈረስ ይሆናሉ።
- ነጭ የሐይማኖት ሽንገላ ተምሳሌት ነው ምክንያቱም ቀስት የሌለው ደጋን ፉገራ ነው። በ860 ዓ.ም ዘውድ በመጫን የመጀመሪያው የምዕራባዊ ቤተክርስቲያን መሪ ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ ነበረ።
- ቀይ ደግሞ ተቃዋሚዎችን ሁሉ የሚገድል ፖለቲካዊ ኃይል ተምሳሌት ነው። ባቢሎን አገዛዟ ሁልጊዜ በጉልበት ነው።
- ጥቁር ደግሞ በገንዘብ ኃይል ውስጥ የሚሰራ አጋንንታዊ ኃይል ምልክት ነው። ክርስትና ትልቅ ንግድ ሆነ። ገቢው እንዳይነካበት ከሚጠብቅ ፓስተር የበለጠ ጭካኔ ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው።
- የመጨረሻው ፈረስ ሐመር ወይም አረንጓዴ ነው (አረንጓዴ በግሪክ ክሎሮስ ነው)።
ቤተክርስቲያን ስትነጠቅ መንፈስ ቅዱስ ከምድር ለቆ ይሄዳል። ሕይወት ለቆ ሲሄድ ሞት ይገባል። እሬሳ መጀመሪያ ቀይ፣ ጥቁር፣ እና ነጭ ሲቀላቀሉ እንደሚሆነው ሐመር ወይም ነጭ አመዳም ይሆናል፤ ከዚያ በኋላ ወደ አረንጓዴ ይለወጣል። ይህ ፈረስ የሞተ ፈረስ ነው፤ ምክንያቱም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ሞት እየጋለበው ነው የሚገባው - እርሱም ሰይጣን ነው።
እነዚህ ቤተክስቲያን በታሪኳ ያለፈችባቸው አራት ደረጃዎች ለሮማ ቤተክርስቲያን እድገት አስፈላጊ ነበሩ፤ ከዚህም የተነሳ የሮማ ቤተክርስቲያን ዓለምን መግዛት ችላለች።
እያንዳንዱ ፈረስ መጋለብ የሚጀምረው ከአንድ ማሕተም መፈታት ጋር ተያይዞ ነው። ነገር ግን ከጀመረበት ማሕተም አልፎ ወደ ቀጣዩ ማሕተም ውስጥ መጋለቡን ይቀጥልና ታላቁ መከራ ውስጥ ሲደርስ ሶስቱ ፈረሶች ተጣምረው ስላሴዎች በመሆን በአራተኛው ማሕተም ውስጥ የመጨረሻው የሞት ፈረስ ይሆናሉ። አመዳም የነበረ እሬሳለ ሲበሰብስ አረንጓዴ ይሆናል። በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የዲያብሎስ ተከታዮች የሚራመዱ ሙታን ናቸው።
ሩቅ ቦታዎች
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አራቱ የምድር ማዕዘናት ሲናገር ምን ማለቱ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማዕዘናት ማለት እሩቅ ቦታዎች ማለት ነው። አጣም እሩቅ የሆኑ ቦታዎች።
ኤርምያስ 9፡26 ግብጽንና ይሁዳን ኤዶምያስንም የአሞንንም ልጆች ሞዓብንም በምድረ በዳም የተቀመጡትን
ዘዳግም 32፡26 እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ።
ራዕይ 7፡1 ከዚህም በኋላ በአራቱ በምድር ማዕዘን ቆመው አራት መላእክት አየሁ፥ እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።
ኢሳይያስ 11፡12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
“አራቱ የምድር ማዕዘናት” የሚለው ቃል ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል። ሁለቱም ጊዜ የተጠቀሰው ከአይሁዶች መሰብሰብ ጋር በተያያዘ ነው።
“ማዕዘናት” ማለት እግዚአብሔር ሰዎች የማያስተውሉትን ስውር ሥራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
ባራክ ኦባማ ከስልጣን ከመውረዱ ሁለት ሳምንታት በፊት የተባበሩት መንግስታት እስራኤልን እንዲያወግዙ በመፍቀዱ ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ተላልፏል።
የተባበሩት መንግስታት በ128 ለ 9 ድምጽ ሬዚዳንት ትራምፕን ተቃውመው ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንዳትሆን ድምጽ በመስጠታቸው ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ተላልፈዋል።
ሒትለር አይሁዶችን ለማጥፋት ሙከራ በማድረጉ እግዚአብሔር ለእስራኤል ካቀደው እቅድ ጋር ተላፏል። ሒትለር ለአይሁዶች ከነበረው ጥላቻ የተነሳ ከእነርሱ መካከል 6 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል። ነገር ግን ይህ አሳዛኝ እልቂት ዓለም ሁሉ ለአይሁዶች እንዲያዝን አደረገ፤ የተባበሩት መንግስታትም የድጋፍ ድምጽ በመስጠት አይሁዶች ፓለስታይን ውስጥ መኖሪያ ምድር እንዲያገኙ አደረገ።
የፓለስታይን አረቦች በ1948 እግዚአብሔር ለአይሁዶች ከነበረው እቅድ ጋር ተላለፉ። የአይሁድ መንግስት እና የፓለስታይን መንግስት እንዲኖር በመስማማት ፈንታ አረቦቹ ስግብግብ ሆኑና አይሁዶችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ጦርነት ከፈቱ። ለብዙ ተባብረው ቢዘምቱም እንኳ ተሸነፉ። በ1956 ተሸነፉ። በ1967 ተሸነፉ። በ1973 ተሸነፉ። አረቦች እስራኤልን ለማጥፋት ያገኙትን እድል ከመጠቀም ወደ ኋላ ብለው አያውቁም።
አራት ነፋሳት ነፈሱ፤ አራት የጦርነት ነፋሳት ነፈሱ፤ እስራኤል ግን ልትጠፋ አልቻለችም።
750,000 አረቦች በራሳቸው መሪዎች አማካኝነት እንዲወጡ ተብለው ከእስራኤል በመውጣታቸው ወይም የተወሰኑቱ በ1948ቱ ጦርነት ወቅት አይሁዳውያን ገፍተው ስላስወጧቸው የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ብለው አረቦች አረብ ውስጥ የሚኖሩ 800,000 አይሁዶችን አባረሩ።
በ1951 የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፍልስጤማውያን ስደተኞች ተብለው የተመዘገቡ 711,000 ስደተኞች ቁጥራቸው በጣም እንደተጋነነ ይናገራል፤ ከነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ የዌስት ባንክ እና የጋዛ ሰርጥ ነዋሪዎች ሲሆኑ ፍልስጤም ከመገልጠሏም በፊት በነዚህ ሃገሮች ውስጥ ነዋሪዎች ነበሩ። ስለዚህ ብዙዎቹ “ስደተኞች” ጦርነቱ ከመጀመሩም በፊት ስደተኞች የነበሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች በእንግሊዝ የባለ አደራ መንግስት ግፊት ነው ከሃገራቸው የወጡት። የተወሰኑ አይሁዳውያንም የ1948ቱ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በተመሳሳይ ግፊት ከፍልስጤም ግዛት ወጥተዋል።
ስለ ፍልስጤም የሚያጠናው የቤይሩት ጥናት በ1970 ተቋም ይፋ እንዳደረገው “ከተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን መካከል 68% የሚሆኑት አንድ የእስራኤል ወታደር እንኳ ሳያዩ ወይም አንድ የተኩስ ድምጽ ሳይሰሙ ነው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የሄዱት”።
በግዛቷ በጣም አነስተኛ የሆነችዋ እስራኤል 800,000 አይሁዶችን ሰብስባ ያዘች ምክንያቱም አራቱ መላእክት ምድረበዳ ውስጥ በርቀት ያሉ አይሁዳውያን የሚኖሩባቸውን የተረሱ ሥፍራዎች ተቆጣጥረዋል።
ስለዚህ የአረቦች ጥላቻ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንዲፈጸም አደረገ ምክንያቱም አረቦች እነዚህን አይሁዶች ፈልገው አገኙና ወደ እስራኤል ላኩዋቸው።
የእግዚአብሔር ስውር ፕላን የእስራኤል ጠላቶች ማየት በማይችሉበት መንፈሳዊ ማዕዘን ውስጥ እየተከናወነ ነው። የእስራኤል ጠላቶች አይሁዶችን እየቀጡ መስሏቸው ነበር። አይሁዶችም ራሳቸው እየተቀጡ መስሏቸው ነበር።
ከአውሮፓ በስፋት የሚበልጥ ግዛት የያዙት 22ቱም የአረብ መንግስታት (ካርታው ላይ ቀይ ቀለም የተደረገባቸው ሃገሮች) ከእስራኤል የተፈናቀሉ 750,000 አረቦችን (በቀይ ክብ መስመር ከተመለከተው ቦታ የተፈናቀሉትን) ተቀብለው ሃገራቸው ውስጥ ማኖር አቃታቸው
ራዕይ 7፡2 የሕያው አምላክ ማኅተም ያለውም ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፥ ምድርንና ባሕርንም ሊጐዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ፦
ዮሐንስ ፍጥሞ ደሴት ላይ ሆኖ ወደ ምስራቅ ጳውሎስ መልእክተኛ ሆኖ የተቀመጠባትን ኤፌሶን እንዲሁም ዊልያም ብራንሐም የተላከባትን ሎዶቅያ ማየት ይችላል። ጳውሎስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አስተማረ፤ እንዲሁም የአዲስ ኪዳን እውነትን መሰረተ። ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ወደ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እና ጳውሎስ ወዳስተማረው የአዲስ ኪዳን ትምሕርት መለሰ። ከፍጥሞ በስተ ምስራቅ የሚገኘው ሥፍራ ሊከተል የሚገባው አካሄድ ይህን ይመስላል።
ስለዚህ ዮሐንስ አንድ ብርቱ መልአክ በምስራቅ በኩል ሲነሳ ሲያይ ይህ መልአክ 144,000ዎቹን አይሁዶች ወደ መጀመሪያውና የመጨረሻው የቤተክስቲያን ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ ውስጥ ይገባል። ደግሞም መልአኩ ጳውሎስ የሰበከውን እንዲሁም ወንድም ብራንሐም መልሶ ያመጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለነዚሁ አይሁዳውያን ያመጣላቸዋል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
እግዚአብሔር ለ144,000 አይሁዶች ያቀደው እቅድ አለ። እነዚህ አይሁዶች በታላቁ መከራ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን መቀበል አለባቸው።
ጳውሎስ ወዳስተማረው የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ይመለሳሉ።
በዙፋኑ ዙርያ ያለው አንበሳ የጳውሎስን ዘመን ይወክላል። አንበሳ የአራዊት ሁሉ ንጉስ ነው። ስለዚህ ሁሉም የቤተክርስቲያን ዘመናት ጳውሎስ እና ሐዋርያት ላስተማሩት ትምሕርት እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጽፈው ላስቀመጡት እውነት መገዛት አለባቸው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ንጉስ የሚያደርገውም ይህ እውነት ነው።
የእግዚአብሔር ማሕተም ምንድነው?
የእግዚአብሔር ማሕተም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
ኤፌሶን 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
55-0312 የክርስቶስ ማሕተም
ክርስቶስን የሚገፉ እና ክርስቶስን የሚክዱ ከሆኑ ዲያብሎስ በክሕደታቸው ያትምባቸዋል። እግዚአብሔርን የሚወዱ እና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ከሆኑ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ፍጻሜያቸው ለዘላለም ይሆን ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ይታተማሉ።
ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ማሕተም ነው።
ራዕይ 7፡3 የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ አላቸው።
144,000ዎቹ መንፈስ ቅዱስን መቀበል አለባቸው።
ግምባሮቻቸው ውስጥ ያለው አእምሮዋቸው ነው፤ በአእምሮዋቸውም ያስባሉ። የሰው አእምሮ የሚሰራው በማሰብ ነው። እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሃሳብ ብቻ ያስባሉ። የሚያስቡት የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናረው ብቻ ነው።
እነዚህ አራት መላእክት ዓለምን ማጥፋት የሚችል የጦርነት ኃይል በእጃቸው ነው። ነገር ግን እስራኤል እንዳትጠፋ በዚያ ጦርነት ላይ ገደብ ይደረግበታል።
እግዚአብሔር አይሁዳውያንን ወደ እስራኤል መልሶ የሚያመጣበት ሚስጥራዊ እቅድ አዘጋቷል።
በ1914 ለተጀመረው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ስውሩ ምክንያት ፓለስታይንን ተቆጣጠረው የነበሩትን ኦቶማን ቱርኮች ለማባረር እና በእነርሱ ቦታ ፓለስታይንን እንግሊዞች እንዲቆጣጠሩ ተብሎ ነው። በ1917 እንግሊዝ ለአይሁዶች ፓለስታይን ውስጥ መኖሪያ ሃገር ልትሰጣቸው ቃል ገባች።
ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሳት ስውሩ ምክንያት 6 ሚሊዮን አይሁዶችን ለመጨፍጨፍ ነው፤ ይህም ለአጭር ጊዜ ዓለም ሁሉ ለአይሁዶች እንዲያዝንላቸው አድርጓል። ከዚያ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ለአይሁዶችም ለፍልስጤማውያንም መንግስት የሚመሰርቱበት ቦታ እንዲሰጣቸው ወሰነ።
ለ1948ቱ ጦርነት መቀስቀስ ስውሩ ምክንያት አረቦች የተባበሩት መንግስታት ፓለስታይን ውስጥ ሁለት መንግስታት እንዲኖሩ ያደረጉትን ውሳኔ እንዲቃሙ ለማድረግ ነው። እስራኤል ላይ ጥቃት በመሰንዘራቸው የፓለስታይን አረቦች የራሳቸውን ግዛት አጡ። ዮርዳኖስ ዌስት ባንክን እና ምስራቅ ኢየሩሳሌምን ያዘች። ግብጾች ጋዛን ተቆጣጠሩ። ሶሪያ የጎላ ተራሮችን ያዘች። ዮርዳኖስ እና ግብጽ እነዚህን ግዛቶች በጦርነት አሸንፈው ከመያዛቸው በቀር በነዚህ ግዛቶች ላይ ምንም ስልጣን የላቸውም።
የፍልስጤም አረቦች ምንም አላገኙም፤ የሚገርመው ነገር ደግሞ ግብጽና ዮርዳኖስ የነርሱን ግዛት ተቆጣጥረው እያዩ እንኳ ምንም ቅሬታ አላቀረቡም።
የ1967ቱ ጦርነት ስውር ዓላማው ግብጽ፣ ሶሪያ፣ እና ዮርዳኖስ የእስራኤልን መንግስት ምድረ ገጽ እናጠፋለን ብለው እንዲያውጁ ነው። ይህም አይሁዶች ዮርዳኖስን ከዌስት ባንክ፣ ግብጽን ከጋዛ፣ እና ሶሪያን ከጎላን ተራሮች ላይ እንዲያባርሩ ጥሩ ምክንያት ፈጥሮላቸዋል።
የአረቦች ጥላቻና ስግብግብነት የነበራቸውን ግዛት እንዲያጡ አድርጓቸዋል። በዚሁ ጊዜ የእስራኤል ግዛት ስፋቱ ሶስት እጥፍ አድጓል።
61-0730M ገብርኤል ለዳንኤል የሠጠው መመሪያ
ስለዚህ የአሕዛብ ዘመን ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ሲጠብቁ ነበር፤ ከዚያ በኋላ እርሱ ሲመጣ አይሁዶችን በሙሉ ያትምባቸዋል፤ 144,000ዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላሉ። የሚታተሙት 144,000ዎች እነዚህ ናቸው።
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። የሚያስደንቀው ነገር ይህ ጦርነት ያበቃው በ918 በዓመቱ በ11ኛ ወር 11 ሰዓት ላይ ጀርመኒ እጅ ስትሰጥ ነው። ጀርመኒ ገና ሙሉ በሙሉ አልተሸነፈችም ነበር፤ ነገር ግን በመላው ጀርመኒ ውስጥ መርከበኞች እና ሌሎችም ሰዎች ተቃውሞና ረብሻ አስነስተው ነበር፤ በተጨማሪ ብዙዎች ጀርመኒ ውስጥ በረሃብ እየተሰቃዩ ነበር። ስለዚህ ጦርነቱ ወዲያው ቆመ። እንግሊዝ ፓለስታይንን ከቱርኮች ነጥቃ ይዛ ነበር። በ1917 አየሁዶች ፓለስታይን ውስጥ የራሳቸው መኖሪያ እንዲኖራቸው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሴክሬታሪ ባልፎር ውሳኔ አደረገ።
ከዚህም የተነሳ እስራኤል በ1948 ራሷን የቻለች መንግስት ሆና እንድትመሰረት ምክንያት የሆኑዋት ስምምነቶችና ጦርነቶች ሁሉ ተጀመሩ።
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ዋነኛ መንፈሳዊ ምክንያት የቱርክ ሙስሊሞች ፓለስታይንን እንዲለቁ ለማድረግ ነው።
20 ሚሊዮን ሰዎች ያለቁበት ጦርነት ካበቃ በኋላ በጣም ከባድ የስፔይን ጉንፋን ወረርሽን ዓለምን ሁሉ አጥለቀለቀ፤ በዚህም ጉንፋን የተነሳ ከ65 ሚሊዮን እስከ 100 ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። ይህ ወረርሽን በብዙ ሃገሮች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ በዚያም ከባድና አስጨናቂ ዘመን ውስጥ የአምባ ገነንነት መንፈስ ከሲኦል ጉድጓድ ውስጥ ብቅ በማለት ራሺያ ውስጥ እንደ ሌሊን፣ ከዚያም እስታሊን፣ ኢጣልያ ውስጥ ደግሞ በሙሶሊኒ፣ እንዲሁም ጀርመኒ ውስጥ በሒትለር አማካኝነት ተገለጠ። ከነዚህ ሰዎች የሚያንሱ ሌሎችም አምባ ገነኖች ነበሩ፤ ለምሳሌ እስፔይን ውስጥ ፍራንኮ እና ዩጎዝላቪያ ውስጥ ደግሞ ቲቶ ናቸው።
እነዚህ ፍጥረታዊ አምባ ገነኖች በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ አጥፊና አውዳሚ የሆነ አጋንንታዊ አሰራርን አዘመቱ። የዚህም ክፋት ጫፍ የደረሰው ሒትለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት 6 ሚሊዮን አይሁዶችን በጨፈጨፈበት ሆሎኮስት ነው።
ጦርነቱ በ1945 ሲጠናቀቅ አጋንንቱ ይህንን ፍጥረታዊ ግድያ አቁመው ወደ ቤተክርስቲያን በመግባት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም እንዲሉ አደጓቸው፤ ቀጥለውም ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት እንዲመሰረት አደረጉ። ዋነኛው ዓላማቸው በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች አዲስ ኪዳን ውስጥ ወደተጻፈው እውነተኛ እምነት እንዳይመለሱ ለማድረግ ነው።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያልተጠበቀው ውጤት ብዙ ሃገሮች ለአይሁዶች አዝነው ፓለስታይን ውስጥ ሃገር እንዲሰጣቸው ድምጽ መስጠታቸው ነው። የፓለስታይን አረቦች ይህንን ተቃወሙ፤ ስለዚህ አምስት የአረብ መንግስታት ተባብረው አይሁዶችን ወጉ። በተዓምር አይሁዶች አሸነፉ።
ስለዚህ ፍልስጤሞች ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ተላለፉ። በአይሁዶች ላይ የነበራቸው ጥላቻና አይሁዶችን ለማጥፋት የተነሱበት ስግብግብነት መጨረሻው አይሁዶች ፓለስታይን ውስጥ ለማግኘት ከተስማሙበት የበለጠ ትልቅ ግዛት እንዲኖራቸው ማድረግ ሆነ።
ስለዚህ ሁለቱም የዓለም ጦርነቶች በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር ነበሩ። ማዕዘን ሁለት ጠርዞች ወይም ግድግዳዎች የሚጋጠሙበት ቦታ ነው - እነዚህም ፍጥረታዊውና መንፈሳዊው ናቸው። እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር እንድትመለስ ብሎ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ሲቆጣጠር ነበር።
61-0217 የአውሬው ምልክትና የእግዚአብሔር ማሕተም፤ ክፍል 2
የመጀመሪያውን የዓለም ጦርነት ማብቃት በተመለከተ እየጻፉ ነበር። የሰላም ስምምነት ስለማድረግ ሃሳብ ማን እንዳመጣ እስከ ዛሬ ድረስ ማንም አያውቅም። ካይዘር ዊልሄልም እኔ አይደለሁም ብሏል። የትኛውም ጀነራል እኔ ነኝ ብሎ ሃላፊነት አልወሰደም። ነገር ግን እንዴት እንግዳ ነገር እንደሆነ ልብ በሉ። ይህ የሆነው ኖቬምበር 11 ቀን ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ነበር። ከወሩ በአስራ አንደኛው ቀን፣ ከዓመቱ በአስራ አንደኛው ወር ከቀኑ በአስራ አንደኛው ሰዓት፤ እንዲሁም ለአስራ አንደኛው ሰዓት አስራ አንድ ደቂቃዎች ሲቀሩ። ይህ ሁሉ ምንድነው? ይህን ሁሉ ያደረገው ሚስጥር ምንድነው? ጦርነቱ እንዲቆም እግዚአብሔር ትዕዛዝ አውጥቷል። “አራቱን ነፋሳት ያዛቸው።” “ነፋሳት” ማለት “ጦርነት ወይም ግጭት” ነው። እስራኤልን ወደ ፓለስታይን እስክናስገባት ድረስ “አራቱን ነፋሳት ያዛቸው”፤ ጦርነቱን የዛኔውኑ በአስራ አንደኛው ሰዓት ቆመ ምክንያቱም…
ኢየሱስ ስለ አስራ አንደኛው ሰዓት የተናገረውን ታስታውሳላችሁን? በአስራ አንደኛው ሰዓት ስለ መጣው ሰውዬ ምን አለ? ሞኞች አትሁኑ፤ መንፈሳውያን ሁኑ። እስት ምን ብሎ ተናገረ? በአስራ አንደኛው ሰዓት የመጣው ሰራተኛ በመጀመሪያው ሰዓት ከመጣው ሰራተኛ እኩል ክፍያ ተቀበለ። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ ኋላ ተመልሶ ሄዶ አይሁዱን ያትመዋል፤ በመጀመሪያው ሰዓት የመጣው አማኝ እንደ ታተመ ሁሉ በአስራ አንደኛው ሰዓት የመጡትም ይታተማሉ። “አራቱን ነፋሳት ያዛቸው፤ የእግዚአብሔርን ባሪያዎች ግምባራቸው ላይ ማህተም አድርገን እስክንጨርስ ድረስ ዓለም እንዳትጠፋ ጠብቃት።”
የወይን እርሻ ውስጥ የሚሰሩትን ሰራተኞች ምሳሌ እንይ። የመጀመሪያዎቹ ሰራተኞች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩት ሐዋርያት ናቸው። የአስራ አንደኛው ሰዓት ሰራተኞች በታላቁ መከራ ዘመን የሚመጡ አይሁዶች ናቸው። እነርሱ ተመሳሳይ ዋጋ ተመሳሳይ መንፈስ ቅዱስ ይቀበላሉ።
54-0103M ጥያቄዎችና መልሶች፤ ክፍል 1
እንግዲህ ልብ በሉ፤ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ባሪያ አይደለችም። እኛ ልጆቹ ነን እንጂ ባሪያዎቹ አይደለንም። ቤተክርስቲያን ባሪያው ሆና አታውቅም፤ ልጆቹ ናት። አያችሁ? ባሪያዎቹ፤
ራዕይ 7፡4 የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
61-0217 የአውሬው ምልክትና የእግዚአብሔር ማሕተም፤ ክፍል 2
የእግዚአብሔር ማሕተም ምንድነው? የእግዚአብሔር ማሕተም ምንድነው? ኤፌሶን 4፡30 “ቤተክርስቲያን ወደ ክብር እስክትገባ የተዋጀችበትንና የታተመችበትን መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑ።” ደግሞም ሌላ ቃል ከኤፌሶን 1፡13 እንመልከት፤ ጳውሎስ በገላትያ 1፡8 እንዲህ ይላል፡- “ከሰማይ የመጣ መልአክም ቢሆን ሌላ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” አዎ። “ካመናችሁ በኋላ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ። ካመናችሁ በኋላ …”
እንግዲህ ባፕቲስት ወንድም እና ፕሬስቢተሪያን ወንድም፤ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። ያመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለናል ትላላችሁ። ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- “ካመናችሁ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ” በኋላ።
ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
144,000ዎቹን አይሁዶች በታላቁ መከራ ውስጥ እንመልከት።
አስራ ሁለት ነገዶች ተጠቅሰዋል፤ ግን ከነዚህ መካከል ዳን እና ኤፍሬም አልተጠቀሱም።
ራዕይ 7፡5 ከይሁዳ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ፥ ከሮቤል ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከጋድ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
6 ከአሴር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
7 ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
8 ከዛብሎን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከዮሴፍ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከብንያም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።
ይህ እንግዳ ነገር ነው። ዳን እና ኤፍሬም አልተጠቀሱም። ዮሴፍ እና ሌዊ ቦታቸውን ይዘዋል። ይህ ለምንድነው የሆነው?
ኢዮርብአም ለብቻው የእስራኤል መንግስት ሊመሰርት አስር ነገዶችን ሲወስድ የዳን እና የቤተል ከተሞች ውስጥ የወርቅ ጥጃ ጣኦቶችን አቆመ።
ቤተል የምትገኘው የኤፍሬም ግዛት ውስጥ ነው።
ይሁዳ አረንጓዴ የተቀባው ግዛት ሲሆን ይሁዳንና ቢንያምን ያጠቃልላል።
ራሔል ቢንያም ሲወለድ ሞተች። ይሁዳ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል። ቢንያም የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የሚቀበሉትን ነገር ግን በታላቁ መከራ ውስጥ የሚሞቱትን 144,000ዎቹን ይወክላል።
እስራኤል ነጩ እና ሁለቱ ቢጫ የተቀቡት ቦታዎች ናቸው፤ የወርቅ ጥጃ የተሰራበት ቦታ ይህ ነው።
የሰሜኑ የእስራኤል ግዛት ላይ የነገሰው ንጉስ ኢዮርብዓም ትልቅ ስሕተት ሰርቷል።
1ኛ ነገሥት 12፡28 ንጉሡም ተማከረ፥ ሁለትም የወርቅ ጥጆች አድርጎ፦ እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ትወጡ ዘንድ ይበዛባችኋል ከግብጽ ምድር ያወጡህን አማልክቶችህን እይ አላቸው።
29 አንዱን በቤቴል፥ ሁለተኛውንም በዳን አኖረ።
ስለዚህ የሰሜኑ መንግስት የወርቅ ጥጃዎችን ማምለክ ጀመረ።
መሳፍንት 4፡5 እርስዋም በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዛፍ ከሚባለው ከዘንባባው በታች ተቀምጣ ነበር፤
ቤተል ኤፍሬም ውስጥ ናት።
ዘዳግም 29፡18 ሄዶ የእነዚያን አሕዛብ አማልክት ያመልክ ዘንድ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ልቡን ዛሬ የሚያስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይኑርባችሁ፤ ሐሞትና እሬትም የሚያበቅል ሥር አይሁንባችሁ።
19 የዚህንም እርግማን ቃሎች የሰማ ሰው፦ ምንም እንኳ በልቤ ደንዳንነት ብሄድ፥ ለጥማቴም ስካር ብጨምር፥ ሰላም ይሆንልኛል ብሎ ሰውነቱን በልቡ የሚባርክ ቢኖር፥
20 የእግዚአብሔር ቍጣ ቅንዓቱም በዚያ ሰው ላይ ይጤሳል እንጂ እግዚአብሔር ይቅርታ አያደርግለትም፤ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈው እርግማን ሁሉ በላዩ ይኖራል፥ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።
የመጀመሪያው ሰማይ የሺ ዓመቱ የሰላም መንግስት ነው። ይህ ዘመን ኢየሱስ በምድር ላይ ስለሚነግስ የመጀመሪያው የሰማይ ኑሮ ቅምሻ ይሆናል።
“ከሰማይ በታች” ማለት ከሺ ዓመቱ መንግስት በፊት ነው። ታላቁ መከራ የሚመጣው ከሺ ዓመቱ መንግስት አስቀድሞ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በታላቁ መከራ ወቅት አስራ ሁለቱን ነገዶች ሲጠራቸው እነዚህ ሁለት ነገዶች የሉም።
ራዕይ 7፡9 ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤
እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ወደ ሰማይ ይገባሉ። እነዚህም ሰነፎቹ ቆነጃጅት ናቸው። እነዚህ ሰዎች ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ድነዋል፤ ነገር ግን በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያዩ ታውረዋል። በታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ከአለማመናቸው መንጻት ያስፈልጋቸዋል።
ኢየሱስ ወደ ምድር ወርዶ ሙሽራይቱን ለመውሰድ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ይነሳል። ከዚያ ወዲያ ምሕረት የለም። ስለዚህ ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ አሕዛብ አይድኑም።
አይሁዶች የብሉይ ኪነዳን መጽሐፍን ቢያምኑ እግዚአብሔር ሊያድናቸው ቃል ገብቷል። እግዚአብሔር ስላሳወራቸው መሲሃቸውን ሊቀበሉ አልቻሉም። ስለዚህ ለብሉይ ኪዳን ታማኝ ሆነው የጸኑ አይሁዶች የቻሉትን ያህል ከታዘዙ ለእምነታቸው ሲሞቱ ይድናሉ። እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ለየት ያለ ፍርድ ያደርጋል።
አሕዛብ ግን ምንም ማመሃኛ የላቸውም። እኛ እውነትን ላለማየት ራሳችንን የምናሳውረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ የቤተክርስቲያንን ልማዶች በመምረጥ ነው። የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን ከመስማት ይልቅ የቤተክርስቲያን መሪዎቻችንን እንሰማለን።
ራዕይ 7፡10 በታላቅም ድምፅ እየጮሁ፦ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ።
የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን ማስቀደም ትተዋል። አሁን በሕይወታቸው ቅድሚያውን ስፍራ የያዘው እግዚአብሔር ነው።
11 መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፉ፥ ለእግዚአብሔርም እየሰገዱ፦
12 አሜን፥ በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን አሉ።
13 ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ፦ እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ።
14 እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።
ሰባተኛው ማሕተም
እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው … (በሌላ አነጋገር ከታላቁ መከራ) …
… መጀመሪያ እስራኤልን በማየት እንጀምራለን፤ ከዚያም የነጻችዋን ቤተክርስቲያን እንጂ ሙሽራይቱን አይደለም፤ የነጻችዋ ቤተክርስቲያን በመከራ የነጻችዋ ናት
ራዕይ 7፡15 ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፥ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።
16 ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፥ ፀሐይም ትኵሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፤
17 በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።
ሰነፎቹ ቆነጃጅት ታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ። ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ከስንፍናቸው ይነጻሉ፤ ፓስተሮቻቸውን መከተላቸውም ስሕተት መሆኑን ይገነዘባሉ። ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ በጉ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ራስ መሆኑንና እርሱን ብቻ ሊከተሉ እንደሚገባ ይገነዘባሉ።
ነገር ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚሞቱ የ1,000 ዓመቱን የሰላም መንግስት ለማየት አለመታደላቸው ነው። ሁሉም ሰው በሚነሳበት አጠቃላይ ትንሳኤ ሲነሱ ለፍርድ ይቀርባሉ፤ ነገር ግን አይፈረድባቸውም፤ ምክንያቱም ከታላቁ መከራ በፊት ድነው ነበር። ከተጻፈው ከእግዚአብሔር ቃል በላይ የሰዎችን አመለካከት ከፍ በማድረጋቸው የተነሳ የሚከፍሉት ከባድ ዋጋ ይህ ነው። እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው። እነርሱ ከፍ ከፍ ያደረጓቸው ሰዎች ይጋለጣሉ፤ ይዋረዳሉ፤ ከእነርሱ ጋር አብረው ይገደላሉ። ስለዚህ እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት ሊማሩ የሚገባቸው ትምሕርት ከዳኑ ሰዎች በላይ ከፍ የተደረጉ ካሕናት አለመኖራቸውን ነው።
ከአማኞች በላይ ከፍ ያለ ሹመት የተሰጣቸው የአዲስ ኪዳን ካሕናት የሚባሉ የሉም። የዳኔ ክርስቲያኖች በሙሉ ካሕናት ናቸው።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
57-0908M ዕብራውያን ምዕራፍ 5 እና 6፤ ክፍል 1
በራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የሚበልጠው ማን እንደሆነ አሳዩኝ፤ የአጥቢያው ሽማግሌ ወይስ የአጥቢያው ፓስተር? እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ሉዓላዊ ሆና ራሷን ማስተዳደር አለባት።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎቿ ነው መተዳደር ያለባት።
አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ የትኛዋም ቤተክርስቲያን በፓስተር ተዳድራ አታውቅም። “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ስድስት ጊዜ ተወግዟል። ይህ የፓስተሮች አገልግሎት ቤተክርስቲያንን ለማስተዳደር የሚታመን አይደለም።
እረኛው ፓስተር ነው የሚል አንድም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ፓስተሮች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተሾሙት ነብያት እና ካሕናት መካከል በአገልግሎት አልተሰለፉም።
ስለዚህ ኤርምያስ የተናገረው ትንቢት ስለ አዲስ ኪዳን ፓስተሮች ነው።
ኤርምያስ 2፡8 ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥
ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና
ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥
ነፋሱ ጦርነትና ግጭት ነው -- ይህም መንስኤው ከመድረክ ላይ የሚመጣ የሰው ሰራሽ ሙቀት ብዛት ነው።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፡፡
2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
3 የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል።
4 የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነሱም አንድ አይጐድልም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
አዲስ ኪዳን እንደሚናገረው የሽማግሌዎች ኃላፊነት ቤተክርስቲያንን ማስተዳደርና መንጋውን መመገብ። ከዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስርዓት ርቀን ሄደናል።
ታላቁ መከራ ጉባኤዎች ሁሉ በፓስተሮቻቸው ላይ የነበራቸውን አመኔታ እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
የትኛውም ግለሰብ ቤተክርስቲያንን እንዲገዛ ስልጣን አልተሰጠውም።
ጳውሎስም ይህንኑ እውነት ነው የተናገረው።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ … እኔ አውቃለሁ።
የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች ስለሚሰብኩት ነገር ምንም ግድ የላቸውም፤ ስልጣን ላይ ከተቀመጡና ገንዘብ በእጃቸው ካደረጉ ይበቃቸዋል።
62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን
እነዚያ ሰዎች ሲወጡ አንዳንድ ጊዜ ለስድስት ወይም ለስምንት ብቻ ሆነው ይወጡ እንደነበር ታውቃላችሁ? እነርሱም አገሪቱን አናወጡ። እንደምታውቁት አቂላ እና ጵርስቅላ አጵሎስ በዚያ አካባቢ ታላቅ መነቃቃት አምጥቶ በነበረ ጊዜ በዚያች ቤተክርስቲያን ውስጥ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ። አንድ ቤተክርስቲያን ሙሉ ማለት ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ። ዛሬ እዚህ የተሰባሰባችሁ ሰዎች ከእነርሱ በቁጥር አምስት ወይም ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ ትበዛላችሁ።
እንደምታውቁት ኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋርያት ብቻ ነበሩት። እኛ ሁልጊዜ ትልቅ ነገር እናስባለን። እግዚአብሔር ግን በትልልቅ ቁጥሮች አይደለም የሚሰራው። እግዚአብሔር የሚሰራው በጥቂቶች ነው። አያችሁ? በዘመናት ውስጥ ሁሉ ሰዎችን ያገኘበትን ጊዜ ተመልከቱ። ሁልጊዜ ጥቂት ሰዎችን ነበር የሚፈልገው፤ እነርሱንም ያናግራቸዋል፤ ለአገልግሎት ይሾማቸዋል። እንዲህ ባለ መንገድ ለመስራት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኗል። እኛም እግዚአብሔር በመካከላችን እንዲሆንና እነዚህን ነገሮች ልናደርግ እንወዳለን።
ማቴዎስ 18፡20 እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።
እግዚአብሔር ትንንሽ ቡድኖችን ሊባርክ ነው ቃል የገባው።
ደግሞም ከቤተክርስቲያኖች ውጭ እንደሚቆም ቃል ገብቷል።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን እንደ ቡድን ጥሪ አያቀርብላትም። ኢየሱስ ጥሪ የሚያቀርበው ቤተክርስቲያን ውስጥ ላለ ግለሰብ ነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በየቤቱ ነበር የምትሰበሰበው።
ሮሜ 16፡3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
ሮሜ 16፡5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
ይህ ቃል ቤተክርስቲያን በየቤቱ ውስጥ ስለመሆኗ ጥሩ ምሳሌ ይሰጠናል።
ፊሊሞና 1፡2 ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤
በጣም የሚያሳዝነው ነገር ቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ አዲስ ኪዳን ከሚያስተምረው ትምሕርት ውጭ ሄደናል።