ራዕይ 17 - ፖፑ ዓለምን ይገዛል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ፖፑ ዓለምን መግዛቱ እኛ ክርስቲያኖች የቱጋ እንደሳትን ያሳየናል። ይኸውም ካቶሊኮች በስልጣን ከፍ እያሉ ሄደው ዓለምን ሲቆጣጠሩ ፕሮቴስታንቶችንም ጭምር እንደሚገዙዋቸው ነው።
First published on the 28th of October 2021 — Last updated on the 28th of October 2021የሰው ዘር ለምንድነው ወደ እግዚአብሔር የፍርድ ቁጣ ቀን እየተጣደፈ የሚሄደው?
ይህ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ትምሕርቶችን የማዳመጥ እና የመከተል ውጤት ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 17 ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አነሳስ እና መስፋፋት በዝርዝር ያስረዳል፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የተሳሳቱ ትምሕርቶች ሁሉ ምንጫቸው ይህ መንፈስ ነው።
ጠላት በወጥመዱ እንዳይይዘን የምንፈልግ ከሆነ ጠላት ማን እንደሆነ ማወቅ አለብን።
ይህ ምዕራፍ የሰው ዘር ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ፍርድ እየተጣደፈ የሚሄድበትን ምክንያት ዘርዝሮ እየነገረን በዚያም አንዳንድ ጠንከር ያሉ እውነቶችንም ይገልጥልናል። ሰይጣን ለሁለት ሺ ዓመታት እጅግ ብዙ ሰዎችን ለማሳሳት ሲጠቀምበት የቆየውን በደምብ የተደራጀ የስሕተት አሰራር ምን እንደሆነ ገልጾ ያሳየናል። ሰይጣን እኛን ለማሳሳት አንድ ነገር ብቻ ካደረገ በቂው ነው፤ እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር እንድናምን ማድረግ ነው።
እኛ ደግሞ ከእንቅልፋችን ካልነቃን እነዚህ ስሕተቶች ጠራርገው ታላቁ መከራ ውስጥ ያስገቡናል።
ራዕይ 17፡1 ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤
ሰባቱ ጽዋዎች በታላቁ መከራ ውስጥ ይፈስሳሉ፤ እነዚህ ጽዋዎች እግዚአብሔር በሐጥያት ላይ መቆጣቱን የሚገልጡ ሲሆኑ ይህም ሐጥያት አለማመን ነው፤ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ለማመን እምቢ ማለት። መጽሐፍ ቅዱስ ከተናገረው ቃል ውጭ ሌላ ነገር ማመን ሐጥያት ነው።
ለፍርድ ከተላኩ መላእክት አንዱ ምን ዓይነት ሐጥያት ቢበዛ ነው እንዲህ ዓይነት ታላላቅ ፍርዶች ሊመጡ የቻሉት የሚለውን ጥያቄ ለዮሐንስ ሊመልስለት መጣ። እንዴት ነው ሰው እንዲህ ሁሉ ዓይነት ጣጣ ውስጥ ሊገባ የቻለው?
እግዚአብሔርን እንዲህ ሁሉ ያስቆጣችው ዋነኛዋ ሐጥያተኛ ሴት ናት።
ሴት ስንል አንዲት ሴት ወይስ ሴት የተመሰለችበት ነገር?
ይህች ሴት በብዙ ውሆች ላይ ትቀመጣለች። አንዲት የምትታወቅ ግለሰብ ሴት ብዙ ውሆች ላይ መቀመጥ አትችልም፤ ስለዚህ ይህች ሴት ተምሳሌታዊ ሴት ናት።
ሴት ምንድነው የምትወክለው? ቤተክርስቲያንን።
ይህ ምዕራፍ እግዚአብሔር በሐጥያት ላይ የተቆጣውን ቁጣ ስለሚገልጽ በጣም ወሳኝ ምዕራፍ ነው። በማን ላይ ነው ፍርድ የተፈረደው?
ማወቅ አለብን። ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ወይም ሚስት ትባላለች።
ራዕይ 19፡7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤
3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
ዮሐንስ ግን አንዲት ሌላ ሴትም አይቷል፤ እርሷም በሰዎች የተበላሸች ክፉ ሴት ናት።
መልካም ሚስት ለባሏ ታማኝ ሆና ትኖራለች። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ የተናገረውን ቃል ብቻ ታምናለች። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው ማመን ያለብን።
ይህች ዮሐንስ ያያት ቤተክርስቲያን ሰዎች የተናገሩትን ታምናለች። ይህች ሴት ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ እና አመለካከት ጋር ተጣብቃ ቀርታለች።
የሰው ጭንቅላት ሰዎች አእምሮዋችን ውስጥ ከሚያስቀምጧቸው አመለካከቶች እና ሃሳቦች በመነሳት አስተምሕሮዎችን የሚጸንስ መንፈሳዊ ማሕጸን ነው።
እምነታችን የተመሰረተበት ሃሳብ በሙሉ ምንጩ መጽሐፍ ቅዱው ውስጥ ከተጻፈው ቃል ብቻ መሆን አለበት። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለተጻፈ ሃሳብ አእምሮዋችን ውስጥ ቢከቱ፤ ይህም ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎችን እንድንጸንስ ቢያደርገን ለክርስቶስ ታማኝ አልሆንንም ማለት ነው።
ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
ማንኛውም የምናምነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ከሆነ ጊዜ እያባከንን ነው።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ካመንን ከእግዚአብሔር ጋር መጣላታችን ነው።
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
ባሕር ማለት በሕይወት ጫና ምክንያት እረፍት አጥተው ወዲያ እና ወዲህ የሚንከራተቱ እንዲሁም ጊዜያዊ እና ተለዋዋጭ በሆኑ በየዘመኑ በሚመጡ የሰው አመለካከቶችና ፋሽኖች እየተገፉ የሚዋልሉ ብዙ ሕዝቦች ማለት ነው። ሰዎች በኃይለኛ እና ማራኪ አነጋገር ባላቸው ሰባኪዎች በቀላሉ ይማረካሉ።
ስለዚህ ይህ ምዕራፍ ዓለምን መቆጣጠር ስለሚፈልግ አንድ ታላቅ ኃይል ይገልጥልናል።
ናፖሌዎን አውሮፓን በሙሉ ሊቆጣጠር ሞክሮ አልተሳካለትም። ሒትለርም ሞክሮ አልተሳካለትም። ኮምዩኒዝም ዓለምን ሊመራ ሞክሮ አልሆነለትም። ለምን? ምክንያቱን ከእነዚህ ታላቅ እንቅስቃሴዎች አንዳቸውም እንኳ የሐይማኖትን ኃይል ስላልተጠቀሙ ነው። ሰው ሲፈጠርም ጀምሮ በውስጡ መንፈሳዊ እርካታን የሚፈለግ ባዶነት እና ረሃብ አለበት።
ባሕር ውስጥ በጥልቀት የሚንቀሳቀሱ ሞገዶች በስውር የሚሰሩ ሰይጣናዊ መናፍስት የሚያመጡትን ተጽእኖዎች ይወክላሉ፤ እነዚህም አጋንንታዊ አሰራሮች የሰዎችን አስተሳሰብ በቀላሉ በማንቀሳቀስ ለዓመጽ ማነሳሳት እና ከአንድ ቡድን ጋር ወግኖ ሌላ ቡድንን እንዲቃወሙ የማሰማራት ኃይል አላቸው። ይህ ዓይነቱ ዝንባሌ ከቡድናችን ውጭ የሚመጡ እርማቶችን እና አስተያየቶችን ለመቀበል እምቢ እንድንል ያደርጉናል። ነገር ግን መንጋውን ተከትላችሁ ስትሄዱ አረንጓዴው ሳር ተግጦ አልቆ ትደርሳላችሁ። ስለዚህ በራሳችሁ አእምሮ ማሰብ ልመዱ።
ገደራ በሚባል ቦታ ኢየሱስ እንደ ሌጌዎን ብዙ የሆኑ አጋንንትን ከአንድ ሰው ውስጥ ባስወጣ ጊዜ እነዚህ መናፍስት አሳማዎች ውስጥ ገቡና አሳማዎቹ ተጣድፈው ባሕር ውስጥ ሰመጡ። ይህም ክፉ መናፍስት እንዴት ተጣድፈው ወደ “ባሕር” ማለትም እረፍት የሌለው ብዙ ሕዝብ ውስጥ እንደሚገቡ እና በዚያም መኖሪያቸውን እንደሚያደርጉ ያሳያል።
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በግል ሕብረት የምታደርግ ናት፤ ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ታምናለች፤ ትከተላለች። የተቀሩት የቤተክርስቲያን ሰዎች “የቤተክርስቲያናዊነትን” ልማዶች፣ ስርዓቶች እንዲሁም በዚህ ውስጥ ያሉ ምቾቶችን እየተከተሉ ይኖራሉ።
ክርስቲያን እንደመሆናችን የሆነ ሐይማኖታዊ ስርዓትና እምነት እንፈልጋለን፤ በዚህም እንደሚመቸን እግዚአብሔርን ማምለክና ማገልገል የምንችል ይመስለናል። ነገር ግን የሰዎች አመራር እና የሰው ልማዶች ቤተክርስቲያኖች አሁን እየተነሳ ባለው አውሬ ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ነው የሚያደርጓቸው።
ለቤተክርስቲያን ፈተና የሆነባት አንዱ ጠላት እስልምና ነው፤ ምክንያቱም እስልምና በውስጡ ሐይማኖተኝነት ስላለ በሰዎች ልብ ውስጥ ለረጅም ዘመን መቆየት ይችላል። እስልምና ውስጥ አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ብዙ ሰዎችን ገድለው አብረው መሞት መንግስተ ሰማያት መግቢያ አቋራጭ መንገድ ነው ብለው ስለሚያምኑ አጥፍተው ለመጥፋት ፈቃደኛ ናቸው። የሐይማኖተኝነት አስተሳሰብ ይህን ያህል ኃይል አለው። የትኛውም ዓይነት ኃይል ፖለቲካን እና ሐይማኖትን ቀላቅሎ ካልተጠቀመ በቀር ዓለምን በደምብ መቆጣጠር አይችልም።
ስሕተት የሚመጣው ከቤተክርስቲያን ውስት መሆኑን ስንሰማ መደንገጥ የለብንም። ኢየሱስ በምድር ይኖር በነበረ ጊዜ ክፉው ሰው አጠገቡ ያለው ይሁዳ ነበረ። የኢየሱስ ተከታይ፣ የተመረጠ ደቀመዝሙር ነበረ እንጂ ከሩቅ የተላከ ሰው አልነበረም።
ይሁዳ የቤተክርስቲያን መሪ ነበረ፤ ያውም ሐዋርያ። ስለዚህ ስሕተት የሚገኘው በቤተክርስቲያን መሪዎች ውስጥ ነው።
ስለዚህ ይህች የወደቀች ሴት በስሕተት የተሞላች ቤተክርስቲያን ናት፤ እርሷም ተጽእኖዋ አድጎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነት አግኝታለች።
ራዕይ 17፡2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።
ነገስታት የሚወክሉት ፖለቲካዊ ኃይልን ነው። ስለዚህ ይህች ቤተክርስቲያን ትልቅ ፖለቲካዊ ተጽእኖ አላት። የዓለም መንግስታት ይህችን ቤተክርስቲያን ያማክራሉ።
ይህች ቤተክርስቲያን በሐይማኖት እና በፖለቲካው ዓለም ትልቅ ክብር አግኝታለች።
ዝሙት ማለት ይህች ሴት አላገባችም ማለት ነው። አግብታ ቢሆን ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እርሷ ሲናገር አመነዘረች የሚለውን ቃል ይጠቀም ነበር። ስለዚህ ይህች ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሚስት ነኝ ብትልም የክርስቶስ ሚስት አይደለችም።
ስጋዊ ሰዎች ለመደሰት ብለው ወይን ይጠጣሉ። በመንፈሳዊ ቋንቋ ወይም የሚወክለው መንፈሳዊ መገለጥ የሚያመጣውን መነቃቃት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገር ሲገለጥልን ወይም ሲገባን ደስተኞች ያደርገናል።
የዚህች ቤተክርስቲያን መገለጦች ግን የሚያስደስቱ ቢሆኑም የተሳሳቱ ናቸው ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዝሙት አይፈቀድም። ዝሙት ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ወሲብ ነው። ይህች ሴት የወደቀች ቤተክርስቲያን ስለሆነች ለክርስቶስ ሚስት አትሆነውም፤ ምክንያቱም እርሱ የሚያገባት ሴት ድንግል ናት። ይህች ቤተክርስቲያን ሰዎችን የሚያስደስታቸውን ነገር ታቀርባለች ግን የምታቀርብላቸው አስደሳች ነገር ልክ ከጋብቻ በፊት እንደሚደረግ ወሲብ የተሳሳተ ነገር ነው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡13 ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ።
14 ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ።
15 ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤
ደቀመዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እጅግ ከመነቃቃታቸው የተነሳ ሲራመዱ እንደ ሰከረ ሰው ይንገዳገዱ ነበር።
በእኛ በክርስቲያኖች መካከል ያለ ዋነኛ ድክመት ብልጣ ብልጥ ሰዎች የፈጠሩት ደስ የሚል ሃሳብ አእምሮዋችንን በቀላሉ መቆጣጠሩ ነው። ከዚያ ልክ እንደ ጠጡ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት መርምረን ስሕተታችንን ማረም ያቅተናል።
እነዚህን የሚገርሙ የሰው ሃሳቦች እና ማራኪ ስርዓቶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን የመመርመር ብቃት የለንም፤ ስለዚህ ዝም ብለን እናምናቸዋለን ምክንያቱም ደስ ይሉናል፤ ይስማሙናል።
ሐይማኖት ማለት ለራሳችን በሚመቸን መንገድ እግዚአብሔርን ልናመልከው እንደምንፈልግ ስንነግረው ነው። ክሪስማስን አስቡ (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል)፣ ዲሴምበር 25 (ኤርምያስ ምዕራፍ 10 ውስጥ እንደተጻፈው እኛ መከተል የሌለብን የአሕዛብ ልማድ)።
ኤርምያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና።
3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
ሰብዓ ሰገል የገቡት ወደ ቤት እንጂ ወደ በረት ውስጥ አይደለም፤ ኢየሱስ በዚያ ሰዓት የሁለት ዓመት ልጅ ነበረ። ደግሞም በዚህ ክፍል ውስጥ ማርያም ብቻ ናት የተጠቀሰችው እንጂ ዮሴፍ አልተጠቀሰም።
ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
እኛ ክርስቲያኖች ግን በክሪስማስ ፖስት ካርድ ምስሎች፣ ተወዳጅነትን በሚፈልጉ ሰባኪዎች፣ በየዓመቱ ከምናየው የኢየሱስ መወለድ ድራማ ወይም ፊልም ከመፍዘዛችን የተነሳ ሰብዓ ሰገል በረት ውስጥ እንዳልገቡ ለማመን እምቢ እንላለን። በክሪስማስ ወቅት ለልጆቻችን (ወይም ስጦታ መስጠት ይገባናል ብለን ለምናስበው ሰው ሁሉ) የምንሰጠው በሰብዓ ሰገል ምክንያት ነው። ከዚህም የተነሳ ክሪስማስ ከኃይለኛው የገንዘብ ፍቅር መንፈስ ቃር የተቆራኘ በዓል ሆኗል፤ እኛ የአሕዛብ ክርስቲያኖችም ይህንን የንግድ እና የሐይማኖት ልማድ ሰብረን መውጣት አቅቶናል። ስጦታ ለመግዛት ገንዘብ አጥተን ቢከብደንም እንኳ የግድ እንገዛለን። ከዚህ የተነሳ የክሪስማስ በዓል ለብዙዎች የጭንቀት ወቅት ነው።
በኖህ ዘመን ከመጣው የጥፋት ውሃ በኋላ የመጣው የባቢሎናውያን የክሕነት ስርዓት በብልጠት የተሞላ ነው። ሃሳባቸው እስከ ዛሬ ያስደንቀናል። ስንት ክርስቲያኖች ዛሬ ኮከባቸውን በዞዲያክ የኮከብ ትንበያ እንደሚከታተሉ አስቡ፤ ይህም ራሱ ከጥንት ባቢሎን የመጣ ልማድ ነው።
ሰካራሞች ከተጨባጭ እውነታ ይልቅ የሚያወሩት ስሜታቸውን ነው።
ክሪስማስ በጣም ከባድ ጉዳይ ባይሆንም እንኳ ቃሉን ትተን ሰዎችን እንድንከተል የሚያስገድደንን በሰዎች ግፊት ውስጥ የሚሰራውን ኃይለኛ መንፈስ ያሳያል። ክርስቲያኖች ግን ልክ እንደ ሰካራሞች በክሪስማስ ፍቅር ተጠምደው ቀርተዋል።
ነገር ግን ክርስቲያኖች ከእምነታቸው ጋር በተያያዘ ከክሪስማስም ይልክ ከበድ ባሉ ጉዳዮች ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል አያውቁም።
የውሃ ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁለት የተለያዩ መንገዶች ተገልጾአል። ከዚህም የተነሳ በደምብ ማሰብ ይጠበቅብናል።
ማቴዎስ 28፡19 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
ክርስቲያኖች ሰካራም መንፈሳዊያን ከሆኑና በትክክል ማሰብ ካልቻሉ እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ለማስታረቅ አጥርተው ማየት ያቅታቸዋል፤ ስለዚህ በችኮላ እና በቀላሉ አንዱን እንደ ስሕተት ቆጥረው ይተዉታል፤ ሁለተኛውን ትክክል ብለው ያምኑታል። ነገር ግን እውነቱን መቀበል ከፈለግን ሁለቱንም መታዘዝ አለብን። አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ስሕተት ነው ብለን አለመቀበል አደገኛ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች ካሉ ፍጹም የሆነ እውነት አይኖረንም ማለት ነው።
“ጴጥሮስ ተሳስቷል፤ ስለዚህ ኢየሱስ የተናገረውን ማመን ይሻለኛል” ብሎ መናገር አደገኛ ፍልስፍና ነው፤ ምክንያቱም ይህ ሐዋርያቱ ምን እያደረጉ እንደነበር አያውቁም እንደማለት ይሆናል።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲጸልይ እንዲህ አለ፡-
ዮሐንስ 17፡20 ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤
ስለ ኢየሱስ መማር የምንችለው ከደቀመዛሙርቱ ብቻ ነው።
ደቀመዛሙርቱ የተናገሩትን አንቀበልም ካልን የተሳሳትነው እኛ ነን እንጂ እነርሱ አይደሉም።
በዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን ትምሕርቶች መመለስ ይጠበቅብናል።
ስለዚህ መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ይህ ነው፡- “የእግዚአብሔር ስም ማነው?”
ክርስቲያኖች በዚህ በጣም ይቸገራሉ። ሰዎች ስለ ስላሴ አስተምረውናል (ስላሴ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም)፤ አንድ አምላክ በሶስት አካላት (ይህ አባባልም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም)። የሮማ ካቶሊኮች ይህንን ሃሳብ ፈጥረው ከ250 ዓ.ም እስከ 500 ዓ.ም ባለው ጊዜ በሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ አዳበሩት።
እኛ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ ይህን ሃሳብ ያለ ምንም ጥያቄ ተቀብለን ዋጥነው።
በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ስም ጠፋብን፤ ምክንያቱም ሶስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ ልክ እንደ ካቶሊኮች በስሙ ፈንታ “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የተባሉ ሶስት ማዕረጎችን ተክተናል።
ነገር ግን የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ ጴጥሮስ ነግሮናል። ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የሰራነው ትልቅ ስሕተት ከባቢሎናውያን የመጣ አረማዊ የስላሴ አስተሳሰብ ተቀብለን “ክርስቲያናዊ” ስላሴ መፍጠራችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀውን ስላሴ የተባለ ቃል ትታችሁ የመለኮት ሙላት (የእግዚአብሔር መንፈስ) ሰው በሆነው በኢየሱስ አካል ውስጥ መኖሩን እመኑ፤ የእግዚአብሔርም ሰብዓዊ ስሙ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ነው።
ቆላስይስ 2፡8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
እንደ አብ ሆኖ ሲገለጥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከአይሁዶች በላይ ነበረ።
እንደ ወልድ ሆኖ ሲገለጥ አማኑኤል፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነበረ።
ዮሐንስ 14፡17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
መንፈስ ቅዱስ ማለት እግዚአብሔር በወንዶች እና በሴቶች ልጆቹ ልብ ውስጥ በማደር በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሲኖር ነው።
ይህንን ቅባቱ እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እንለዋለን።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ከውስጣቸው ሆኖ ለመቆጣጠር በቤተክርስቲያን ውስጥ ይኖራል።
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለት እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ፣ ከሕዝቡ ጎን እና በሕዝቡ ውስጥ መሆኑን ያመለክታል። ይህም እግዚአብሔር ሰውን በተመለከተ ያለው እቅድ በሙሉ ነው።
እግዚአብሔር ኢየሱስ የተባለውን ሰብዓዊ ስም በተቀበለ ጊዜ የእግዚአብሔር መገለጦች እነዚህ ናቸው።
ክርስቶስ ማዕረግ ነው፣ ትርጓሜውም የተቀባው ማለት ነው።
የግሪኮች ፍልስፍና ሶስት በአንድ ወይም አንድ አምላክ በሶስት አካላት የሚለውን ሃሳብ ፈጠረ። ከእነዚህ አባባሎች አንዳቸውም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም።
የግሪኮች ፍልስፍና አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው አለ። “ባህሪ” የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አይደለም።
ዘላለማዊ ልጅነት የሚለውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ አይደለም።
የግሪክ ፍልስፍና አብ እና ወልድ በባህሪ አንድ ናቸው በአካል ግን አንድ አይደሉም ይላል። “አንድ ባህሪ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
የግሪክ ፍልስፍና በግሪክ ቋንቋ ስለ እግዚአብሔር ሊገልጹ ከፈለጉት ሃሳብ አንጻር የግሪክ ቃላት ትክክል ናቸው፤ ነገር ግን ግሪኮቹ የመረጡዋቸው ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም።
ካቶሊኮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ የስላሴ ሃሳብ አዳበሩ። እኛ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ ተቀብለነው ስላሴ እና ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሃሳቦች እውነት ናቸው ብለን እወነት መሆናቸውን ለማሳየት በከንቱ እየተጋደልንላቸው ነን። ስለዚህ ካቶሊኮች እና ፕሮቴስታንቶች አንድ ዓይነት አቋም ነው ያላቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር በደስታ እናምናለን።
ልክ እንደ ሰካራሞች ፕሮቴስታንቶች ስላሴ በተባለው የካቶሊኮች ትምሕርት ተጠምደው ቀርተዋል፤ ሃሳቡ እውነት ነው ብለው ሲከራከሩም በስሜታዊነት እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት አይደለም።
ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
በራሀው።
አሳዛኝ እውነት። የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲያስተምራችሁ ከፈለጋችሁ በሰው ዘንድ ተቀባይነት አይኖራችሁም። በረሃ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለ እውነት የምንከፍለው የመጀመሪያው ዋጋ በሰዎች መገፋት ነው። ነገር ግን በዚያ የብቸኝነት በረሃ ውስጥ ከገባ በኋላ ዮሐንስ በረከቶቹን ተቀብሏል፡ የሆነ ነገር አይቷል። ውስጣዊ ዓይኖቹ ወይም ማስተዋሉ በድንገት በራለት። ብዙ ሕዝብ በሚንጋጋበት ቦታ ሆነን እውነትን ማየት አንችልም፤ ምክንያቱም ይበልጥ የምንፈልገው ከብዙሃኑ ጋር መስማማት እና በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው። ሰዎችን ማስደሰት የሚፈልጉ ሁሉ ብዙም እውነትን አይማሩም። እውነት ከብዙሃኑ ሃሳብ ጋር ይጋጫል፤ ስለዚህ ከሕዝቡ ተለይተን ለብቻችን ለመቆም ካልቆረጥን በቀር እውነትን መማር አንችልም።
አውሬ ማለት ኃይል ነው። ነገር ግን ይህ ታላቅ ኃይል በላዩ ቤተክርስቲያን ተቀምጣበታለች፤ ተቆጣጥራውማለች። አውሬው ቀይ ነው። ይህም የሐጥያት ቀለም ነው፤ በተጨማሪ ደግሞ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የታላቅነት ቀለም ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሯት ካርዲናሎች ልብሳቸው ቀይ ቀሚስ ነው።
ኢሳይያስ 1፡18 ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን
62-1104M የስድብ ስሞች
ድርጅቶችን ይቃወማል እያሉ ይጮሁብኛል። ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች ራሳቸውን “የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖች እና የክርስቶስ ቤተክርስቲያኖች እና ሜተዲስት ቤተክርስቲያኖች እና ቤተክርስቲያኖች” እያሉ የሚጠሩ የስድብ ስሞች ናቸው። እነርሱ ቤርጎዎች ናቸው እንጂ ቤተክርስቲያኖች አይደሉም።
አንዲት ቤተክርስቲያን ብቻ አለች፤ እርሷም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት። ምንድናት ይህች ቤተክርስቲያን? በምድር ላይ የጌታን ሥራ የምትሰራው የኢየሱስ ክርስቶስ ሚስጥራዊ አካል ናት፤ የዚህች እውነተኛ ቤተክርስቲያን አካላት ከእነዚያ ጉባኤዎች የተወጣጡ እውነተኛ አማኞች ናቸው። ወደዚህ የክርስቶስ አካል ውስጥ ትወለዳላችሁ እንጂ ሄዳችሁ አትቀላቀሉም።
እርሷ ግን “የስድብ ስሞች ሞልተውባታል፤” ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ፕሬስቢተሪያን፣ ሉተራን፣ እነዚህ ሁሉ ራሳቸውን “የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን” ብለው ይጠራሉ። የስድብ ስሞች! “በስድብ ስሞች” እና “በተሳዳቢ ስሞች” መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። እነርሱ ራሳቸውን “የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያኖች” ብለው ይጠራሉ በዚህም ስም በዓለም ፊት ራሳቸውን ይገልጣሉ፤ የካርታ ጨዋታ ጌሞች ያዘጋጃሉ፣ የመጠጥ ድግስ፣ የእራት ግብዣ እና ብዙ ሌላም ዓይነት ዓለማዊ ልምምዶችን ይፈጽማሉ።
ራሳችንን ክርስቲያን ብለን ከመጥራት ውጭ ሌላ ምንም ብለን የመጥራት ስልጣን የለንም።
ከ45,000 በላይ የሚሆኑ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ ትክክለኛ ናቸው ለማለት ብለው ሰዎች በቁጥር እጅግ ብዙ የሚሆኑ ስሞችን ለራሳቸው አበጅተዋል። ይህ ታላቅ የዲኖሚኔሽናዊ ክርስትና ድርጅት የአውሬው አካል ያደርገናል፤ ይህም ዲኖሚኔሽናዊ ድርጅት የብዙ ቤተክርስቲያኖች “ስሞች የሞሉበት” ድርጅት ነው።
እውነተኛ ሙሽራ በባሏ ስም ብቻ ነው የምትጠራው፤ እንጂ በሌላ በማንም ስም አትጠራም። የኛ ባል ስሙ ክርስቶስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እኛ ክርስቲያኖች ነን።
የሐዋርያት ሥራ 11፡26 ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
የሐዋርያት ሥራ 26፡28 አግሪጳም ጳውሎስን፦ በጥቂት ክርስቲያን ልታደርገኝ ትወዳለህ አለው።
1ኛ ጴጥሮስ 4፡16 ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
እውነትን ከፈለግን ልክ እንደ ዮሐንስ የሰው አመለካከቶች እና ልማዶች ወደሌሉበት ብዙ ሰዎች ወደሌሉበት ወደ መንፈሳዊ በረሃ መሄድ አለብን።
“ከወንዙ ጋር አብራችሁ ፍሰሱ” የሚለው መፈክር ያለበት ችግር አቅጣጫው ሁልጊዜ ቁልቁል መሆኑ ነው። እውነት በሰው ዘንድ ተወዳጅ አያደርገንም።
ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
አውሬው ሙሉ በሙሉ ቀለሙ ሐምራዊ ነው። ይህም የሚያመለክተን ሰዎች ሳያስተውሉ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ በታላቅ ኃይል እና ስልጣን እንደምትነሳ ነው።
ዮሐንስ በራዕይ ምዕራፍ 13 ያየውን የመጀመሪያውን አውሬ ተመልከቱ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የካርዲናሎች ቀለም የሆነው ሐምራዊ ቀለም አልተጠቀሰም።
ይህ አውሬ አደገኛ እና አጥፊ የሆነ ወታደራዊ ኃይል የታጠቀው ነፍሰ ገዳዩ አረማዊ የሮም መንፈስ ነው። ይህ አውሬ ከስላሴያዊ አማልክቶቹ ጋር የግሪኮችን፣ የፋርሶችን እና የባቢሎንን ክፋት እና ሚስጥራት ጠጥቷል።
ራዕይ 13፡1 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
የዚህ አውሬ የመጨረሻ ወታደራዊ ኃይል የሚሆኑት እንደ ነገስታት የሚገዙ 10ሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ናቸው፤ እነርሱም የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ አውሬ ዓለምን መቆጣጠር እንዲችል ወታደራዊ ኃይላቸውን ይሰጡታል።
3 ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥
ሰባቱ ራሶች ሰባቱ የሮም ኮረብታዎች ናቸው። የሶስቱ አማልክት የጁፒተር፣ ጁኖ፣ እና ሚነርቫ ቤተመቅደስ ያለበት የካፒቶላይን ኮረብታ የሮማ መንግስት ማዕከል ነበረ፤ በ476 ዓ.ም ምእራባዊው የሮማ መንግስት በባርቤሪያውያን እጅ በፈራረሰ ጊዜ ለሞት የሚያበቃ ቁስለ የቆሰለው ይህ ማዕከል ነው። ሶስቱ አማልክቶቸቸውም ሶስት ስም ያላቸው ሁለት ወንዶች አማልክት እና አንዲት ሴት አምላክ ነበሩ። ከዚያም አረማዊው የሮማ መንፈስ ዋና ማዕከሏን ካኤልያን ኮረብታ ላይ ባለው በላተራን ቤተመንግስት ባደረገችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ከሞት ተነሳ። ሶስቱን አማልክቶቻቸውን ወደ ስላሴ ሶስትነት ለወጡና አንድ አምላክ በሶስት አካላት፡ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አሉ። ነገር ግን ይህ ስላሴያዊ አምላክ ስም የለውም። ለሶስት አካላት አንድ ስም ማውጣት አይቻልም።
በራዕይ ምዕራፍ 17 ዮሐንስ ይህንን አረማዊ ሮማዊ አውሬ ሲያይ ቀለሙ ሐምራዊ ነው፤ ይህም የሚያመለክተው አውሬው በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቁጥጥር ስር መሆኑን ነው። አንዲት ሴት ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዚህ መንፈስ ላይ ተቀምጣ እየጋለበችው ትቆጣጠረዋለች።
ስለዚህ የሮማ መንግስት በፈረሰ ጊዜ በዚያ ውድቀት ውስጥ ሳትጠፋ የቀረችው ብቸኛ ድርጅት የሮማካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። ይህም የሮማ መንግስት ወይም ቄሳር ያጣውን ኃይል እና ስልጣን በሙሉ ፖፑ በእጁ እንዲያስገባ አስችሎታል። ፖፑ የቤተክርስቲያን ስልጣን ይዞ ጀመረ፤ ከዚያ የገንዘብ ኃይልን እና የፖለቲካ ኃይልን ጨምሮ ያዘ። በስተመጨረሻ 10ሩ ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ኃይላቸውን ይሰጡታል።
ዮሐንስ ይህች ሴት ማለትም የካቶሊክ ቤትክርስቲያን በአንድ ክፉ አውሬ ማለትም አረማዊ ኃይል ላይ ተቀምጣ ተቆጣጥራው አየ። ስላሴ፣ የገና ዛፍ፣ የኩዳዴ ጾም፣ መነኮሳት፣ ሴት መነኮሳት፣ ካርዲናሎች፣ ገዳማት፣ የእናት እና ልጅ አምልኮ፣ የጸሎት መቁጠሪያዎች ሁሉም ከአረማውያን የመጡ ልማዶች ናቸው። ይህ ሐይማኖታዊ ፖለቲካዊ እና የገንዘብ ኃይል ለሁለት ሺ ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለሚለዋወጠው የዓለም ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ ሁኔታ ምላሽ ስትሰጥ ወይም ያገኘችውን አጋጣሚ ስትጠቀምበት በብዙ ሙራዎች ያደገና የዳበረ ኃይል ነው። ስልጣን ለመያዝ ያደረገችው ሩጫ አንድ ቀን ዓለምን ሁሉ በኃይሏ የምትቆጣጠርበት ዓለም አቀፋዊ የቤተክርስቲያን ድርጅት እንድትገነባ አስችሏታል። አውሬው ላይ ተቀምጣ የምትጋልበው እሷ ብቻ ናት። አውሬውን ሊቆጣጠረው የሚችል ሌላ ማንም የለም።
እኛ ፕሮቴስታንቶች በካቶሊኮች ስኬት እና ለብዙ ዘመናት ሳትጠፋ በቆየችው ዓለም አቀፋዊት ሐይማኖታዊ ድርጅታቸው እንገረማለን፤ ከመገረማችንም የተነሳ አሁን ለአውሬው ምስል ልናዘጋጅለት በርትተን እየሰራን ነን። ይህም ምስል የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን መፎካከር የሚችልና ትልቅ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለው ዓለም አቀፋዊ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ድርጅት ነው። ልክ እንደ ካቶሊኮች እኛም ፕሮቴስታንቶች በፍጹም መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንከተል ብለን መጨነቅ ትተናል። ስኬታማ ቤተክርስቲያን የመሆን ሃሳባችን የተመሰረተው በምናከማቸው የገንዘብ ብዛት እና ጉባኤ ውስጥ በሚገኙ የአባላት ቁጥር ሆኗል። መቸም ከአንድ ቢሊዮን ሕዝብ በላይ አባላት ያላትን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለመኮረጅ በምናደርገው ጥረት እኛም ሃብታም የሆኑ ብዙ የጉባኤ አባላት መሰብሰብ ግድ ሆኖብናል።
በጣም ጠንካራ መንፈሳዊ ኃይል ሌላ ሰውን ለመምሰል እንድንሞክር፣ እንድንከተልና እንድናመልክ የሚያደርግ መንፈስ ነው። የእስፖርት ዝነኛ ሰዎችን “አይዶል” የፊልም ዝነኞችንም “አይዶል” ማለትም በእንግሊዝኛ ጣኦት እንላቸዋለን። ከፍ እናደርጋቸዋለን እናደንቃቸዋለን። ቤተክርስቲያንም እንደዚሁ ዝና ያላቸውን በሰው የተከበሩ መሪዎችን ታቀርብልናለች። በብዙ ካቶሊኮች ዘንድ ማርያም እንደ አምላክ ትታያለች፤ ጸሎታቸውንም ወደ እርሷ ይጸልያሉ። ብዙዎች እኛን እንዲያድነን ኢየሱስ ላይ ግፊት ልታደርግበት ትችላለች ብለው ያምናሉ። ሕዝብ ሁሉ በዚህ ዓይነቱ ሰውን ከፍ በማድረግ መንፈስ ተጠምዷል። የቤተክርስቲያን መሪያችንን “በቀለ” ወይም “ማሞ” ብለን መጥራት እንኳ አንችልም። “ፓስተር በቀለ” ወይም “ፓስተር ማሞ” ብለን ነው የምንጠራቸው። በአዲስ ኪዳን ዘመን አገልጋዮችን እንዲህ ብለው አይጠሩም ነበር። “ፖፕ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው፤ ቢጠቀስም ደግሞ ከእምስት የአገልግሎት ዓይነቶች አራተኛ ሆኖ ነው የተጠቀሰው።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
ስለዚህ ፓስተርን የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ስራ ነው። ከአንድ ጥቅስ ተነስተን እንደዚያ ዓይነት ድምዳሜ ማድረግ አንችልም።
እረኛ ፓስተር ነው የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም።
ስለዚህ አንድ ሰውን መሪ አድርጎ በቤተክርስቲያን ላይ ከፍ ከፍ ማድረግ እኛ ክርስቲያኖች ማድረግ የሚገባን ነገር አይደለም።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
ልብ በሉ፤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሲመሰርት ስለ ፓስተሮች ምንም አልተናገረም።
ስለዚህ ቤተክርስቲያንን ፓስተሮች እንዲገዙ ማድረግ የዛሬዎቹን ቤተክርስቲያኖቻችንን የመሰረታቸው እግዚአብሔር ሳይሆን ሰዎች እንደሆኑ ያመለክታል። ፖፑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ ከሆነ፣ አንድ ፓስተር ደግሞ የአንድ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ራስ ከሆነ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ሆኖ መቆሙ አያስደንቅም (ራዕይ 3)። ማንም ሰው ሁለት ራስ ሊኖረው አይችልም።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ
ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ለግለሰቦች ጥሪ ያቀርባል። ለቤተክርስቲያን አይደለም ጥሪ የሚያቀርበው።
ራዕይ 17፡4 ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ አንደኛ ሃብታም ድርጅት ናት። እግዚአብሔር ግን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በወርቅ ዋንጫዋ የምታቀርብለትን መስዋእት አይወደውም። ከውጭዋ ሲያየዋት ውብ ትመስላለች። በውስጧ ግን ክፋት ሞልቶባታል።
የካርዲናሎች ልብስ ቀለሙ ሐምራዊ እና ሰማያዊ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምትተዳደርበት ከፍተኛው ምክር ቤት ካርዲናሎች ናቸው።
“ወርቅ”። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ አንደኛ ሃብታም ድርጅት ናት።
ይህ ሳንቲም የአረማዊውን የሮማ ገዥ የጢባርዮስን ምስል ያሳያል፤ እርሱም ማክሲም ፖንቲፍ በሚባል ማዕረግ ከ14-37 ዓ.ም ነገሰ። ማክሲም ፖንቲፍ ማለት የባቢሎን ሚስጥራት ከፍተኛ ሊቀካሕናት ነው። ኢየሱስ በተሰቀለበት ዘመን የሮማ መንግስት ገዥ ጢባርዮስ ነበረ።
ፖፕ ሊዮ 12 በ1825 የሴት ምስል ያለበት ሜዳልያ አስቀረጸ፤ ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ መቀመጧን የሚያሳይ ምስል ነው።
ሜዳልያው ላይ የተጻፉት ቃላት እንዲህ ይላሉ፡- “ከምድር ሁሉ በላይ ተቀምጣለች” ወይም “ምድር ሁሉ የእርሷ መቀመጫ ናት”።
ሁሉም ፖፕ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓለምን መግዛት እንዳለባት ያምናሉ። የፖፑ ዓላማ እስከዛሬም ድረስ ዓለምን መግዛት ነው።
በእጇ የእምነቷን እና የአስተምሕሮዋን ጽዋ መያዟን አስተውሉ። ፖፑ መዳን ከፈለጋችሁ ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መታዘዝ አለባችሁ ይላሉ። ይህንን ሃሳብ ፖፕ ቦኒፌስ 8ኛው ነው በ1302 ዓ.ም ያወጀው።
ከላይ የምታዩት ምስል የፖፕ ፖል 6ኛው- ፖንቲ(ፌክስ) ማክሲ(መስ) 100 ሊሬ ሳንቲም ነው (የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት) - ቫቲካን ከተማ 1963።
ስለዚህ ፖፑ ከአረማውያኑ የሮማ መንግስት ገዥዎች ፖንቲፍ ወይም የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕናት የሚለውን ማዕረግ ተቀብሏል።
ሳንቲሙ ላይ Fides የሚለው እምነት ማለት ነው። የሴቲቱ ምስል የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ይወክላል፤ እርሷም ለፖፑ እና ፖፑ ለሚያምንበት ነገር ሁሉ ታማኝ ናት። በእጇ ጽዋ ይዛለች፤ ይህም ዓለምን ለማዳን ለዓለም ያቀረበችውን እምነቷን ወይም አስተምሕሮዋን ይወክላል።
ፖፑ ስለ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚያስበው ዓለምን ለማዳን የሚያስፈልገውን አስተምሕሮ በእጆቿ የያዘች ቤተክርስቲያን እንደሆነች ነው።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ሮም ውስጥ ካኤልያን ኮረብታ (ከሰባቱ የመጀመሪያ ኮረብታዎች አንዱ) ላይ ያለችዋ ላተራን ቤተክርስቲያን በምዕራቡ ዓለም ውስጥ በዕድሜዋ ከሁሉም ይልቅ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ናት። ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች በጣም ዘግይተው ነው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተገነጠሉት፤ ስለዚህ እናት ለሆነችው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሴት ልጆቿ ተብለው ይጠራሉ። ሉተር ፖፑ በ1520 ዓ.ም ካወገዘው በኋላ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተለይቶ ከመውጣቱ በፊት የካቶሊክ መነኩሴ ነበረ።
ከዚህ በታች ያለው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ የላተራን ቤተክርስቲያን (ወይም ባሲልካ) ላይ የተቀረጸ ነው።
በቀጥታ ሲተረጎም እንዲህ ይላል፡- “ቅድስቲቷ የከተማይቱ እና የመላው ዓለም ላተራን ቤተክርስቲያን፤ የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ራስ እና እናት”።
ስለዚህ የላተራን ቤተክርስቲያን ራሷን እናት ቤተክርስቲያን ብላ አውጃለች። እኛ ፕሮቴስታንቶች ከካቶሊክ በኋላ ቆይተን ነው የመጣነው። ፕሮቴስታንቶች ከመጀመሪያዎቹ የተሃድሶ መሪዎች ስር ንጹሕ ድንግል ሴቶች ሆነን ቢንለድም እንኳ ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ በንጽሕናችን አልቆየንም። ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያናችንን ለመገንባት ብለን (ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል ነው) የካቶሊክን ምሳሌነት ተከተልንና የሰውን አመራር ብቃት ተቀበልን። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ የእኛ ራስ መሆኑ ቀረ። አሁን እንዲሁ መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን በመጥቀስ ፈንታ የተለያዩ ሰዎችን ንግግር እና አመለካከት እናምናለን። ስለዚህ የእኛ ባል ለሆነው ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ አይደለንም። እግዚአብሔር በእኛም ይሁን በካቶሊኮች አይገረምም፤ ምክንያቱን ሁላችንንም፣ ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ ጠንከር ባለ ቃል ነቅፎናል።
ጥንታዊት ባቢሎን የሐይማኖታዊ ስሕተቶች ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ እነዚህ ሚስጥራት ካርዲናሎች በተባሉ ሰዎች ለሕዝብ ተገልጠዋል። “ካርዶ” ማለት የበር ማጠፊያ ነው። እዚህ ካርዲናሎች ወደ ሚስጥራቱ የሚያስገባውን በር የሚቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው። በቂ ገንዘብ ከከፈላችሁ፤ ሐጥያታችሁንም ለእነርሱ ከተናዘዛችሁ (የተናዘዛችሁትን ሐጥያት ኋላ ከቤተክርስቲያናቸው እንለቃለን ብትሉ እናጋልጣለን ብለው ለማስፈራራት ይጠቀሙበታል)፤ ደግሞም በእነርሱ እስካመናችሁ ድረስ በማጠፊያው ላይ በሩን በጥቂቱ ከፈት አድርገው ከበሩ በስተጀርባ ያለውን ሚስጥር ጥቂት በጥቂት እየገለጡ ያሳዩዋችኋል።
ለብዙ ዘመናት ካቶሊኮች የመንግስተ ሰማያት በር ቁልፉ በጴጥሮስ እጅ ነው ያለው፤ እርሱም ለፖፑ ለሚታዘዙ ሰዎች ብቻ የመንግስተ ሰማያትን በር ይከፍትላቸዋል እያሉ አስተምረዋል። “Unam Sanctam” የሚባለው አስተምሕሮ በ1302 ዓ.ም ታወጀ፤ ትርጉሙም ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን አይቻልም ማለት ነው። ልብ በሉ እንግዲህ፤ መዳን በኢየሱስ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ በጴጥሮስ እጅ ውስጥ ነው ያለው፤ ጴጥሮስ በሩን ካልከፈተላችሁም መዳን አትችሉም። እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነቱን ሃሳብ የሚቀበል ይመስላችኋል?
ራዕይ 17፡6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።
የሮማ መንግስት ገዥዎች በ64 ዓ.ም ክርስቲያኖችን መግደል ከጀመረው ከኔሮ ጀምሮ በ312 ዓ.ም ወደ ስልጣን እስከ መጣውና ክርስቲያኖችን መግደል እስካስቆመው እስከ ኮንስታንቲን ድረስ 3 ሚሊዮን ያህል ክርስቲያኖችን አስገድለዋል።
በ400 ዓ.ም አካባቢ ኦጋስተን የተባለ ኃይለኛ የሮማ ካቶሊክ ሰባኪ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር የማይስማሙ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ይቻላል ብሎ አስተማረ። አንዳንድ የታሪክ ምሑራን ኦጋስተንን የአሳዳጆች ንጉስ ብለውታል። በ450 ዓ.ም አካባቢ ሊዮ ቀዳማዊ የተባለ በሮም ከተማ የተቀመጠ የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ የኦጋስተንን ትምሕርት ካቶሊኮች የሚቃወሙ ክርስቲያኖችን መግደል ይችላሉ ማለት ነው ብሎ ተረጎመ። እስፔይን ውስጥ ፕሪሲሊያኒስትስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ሲጨፈጨፉ ተደሰተ። ሊዮ ቀዳማዊ የሮማ ጳጳስ የክርስቲያኖች ሁሉ አለቃ ነው የሚለው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙከራ አደረገ። ስለዚህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ጨለማው ዘመን እና እስከ ጸረ ተሃድሶ ዘመን ድረስ ካቶሊኮች ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎችን የገደሉበት የግድያ ዘመቻ ተጀመረ። በደም መፋሰስ የተሞላው የጸረ ተሃድሶ ዘመቻም በብዙ ሃገሮች ውስጥ ተሃድሶው እንዳይሰራጭ አድርጓል። በሐይማኖት ስም ይደረግ የነበረው ግድያ የቆመው በ1648 ዓ.ም ሲሆን ያበቃውም ጀርመኒ ውስጥ የተደረገው የ30 ዓመታት ጦርነት ሲያበቃ ነው። ይህ ጦርነት ጀርመኒ ላይ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት የከፋ ውድመት አድርሶባታል።
ከዚህም ሌላ የካቶሊኩ ፖፕ አርባን ዳግማዊ በቀሰቀሰው የመስቀል ዘመቻ ጦርነት ውስጥ ብዙ ሙስሊሞች እና አይሁዶች ተገድለዋል። ፖፕ አርባን ያስተማረው ነገር ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችን የገደለ ሰው በመንግስተ ሰማያት ውስጥ ቦታ ያገኛል የሚል ነው። ይህ ከስሕተቶች ሁሉ የከፋ ስሕተት ነው፡- “አንተን ገድዬ መንግስተ ሰማያት እገባለው”። ሰው ከዚህ የባሰ ዝቅጠት ውስጥ ሊገባ አይችልም። የታሪክ ምሑራን እንደሚናገሩት እስፔይኖች ደቡብ አሜሪካን ሊገዙ የቻሉት 15 ሚሊዮን የሚሆኑ የአህጉሪቱን ቀደምት ነዋሪዎች በመግደል ነው።
የሰው ደም ጠጥቶ መስከር። የሟቾች ቁጥር ከአእምሮ በላይ ነው። ለዚህ ሁሉ ደም መፋሰስ በቂ ምክንያት አልነበረም።
ከካቶሊክ የወጡ ፕሮቴስታንት ልጆችም በዚህ ደም መፋሰስ ተለክፈው ነበር። ፕሮቴስታንቶችም ካቶሊኮችን እና አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ ከእነርሱ ጋር አልስማማ ያሉ ፕሮቴስታንቶችን ገድለዋል። ውሃ ውስጥ በማጥለቅ የሚያጠምቁ አናባፕቲስቶች በሌሎች ፕሮቴስታንቶች እጅ ውሃ ውስጥ እንዲሰጥሙ በመደረግ ተገድለዋል። ስለዚህ በሐይማኖት ውስጥ ያለው ጭካኔ እና ነፍሰ ገዳይነት ከካቶሊኮች ወደ ፕሮቴስታንቶች ተጋብቷል። የሞርሞኖች መሪ ጆሴፍ እስሚዝ አሜሪካ ውስጥ በሜተዲስቶች እጅ በጥይት ተመቶ ሞቷል። ፕሮቴስታንቶች የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር በፖፑ እና በቫቲካን ከተገደሉ ሰዎች በጣም ያንሳል፤ ሆኖም ፕሮቴስታንቶች የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር ከካቶሊክ በጣም የሚያንስ ቢሆንም እያንዳንዱ የፈጸሙት ግድያ የግፍ ግድያ ነበር። ፕሮቴስታንት የነበረችዋ ንግስት ኤልሳቤጥ ቀዳማዊ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ የሚያህሉ አየርላንዳውያን ካቶሊኮች እንዲገደሉ አድርጋለች።
ታላቁ የተሃድሶ መሪ ጆን ካልቪን እግዚአብሔር አንድ ነው እንጂ ስላሴ አይደለም ብሎ የሚያምነውን ሰርቬተስ በእሳት በማቃጠሉ የተነሳ የራሱን ምስክርነት አበላሸ። ሰው በሰው ላይ የሚጨክንበት ጭካኔ ዘግናኝ ነው።
ስለዚህ እኛ ፕሮቴስታንቶችም ብንሆን ንጹህ ታሪክ የለንም።
“ታላቅ አድናቆት”።
ዮሐንስ በታላቅ ድንቅ ተደነቀ። የቫቲካን ሕንጻዎች እንዴት ውብ ናቸው? የሲስቲን ቻፕል ኮርኒስ ላይ ያሉ ስዕሎች በሙሉ የዓለም አንደኛ ታላቅ ሰዓሊ በነበረው በማይክል ኤንጅሎ ነው የተሳሉት። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአምልኮ ስርዓቷ እንዴት የደመቀና በቀለማት ያሸበረቀ ነው። ተጽእኖዋ በዓለም ዙርያ ሁሉ ባሉ ሕዝቦች እና የሃገራት መሪዎች ዘንድ የተስፋፋ ነው። እማሆይ ቴሬዛ የተባለችው ያች አስገራሚ የካቶሊክ መነኩሲት ዓለም ሁሉ እስኪደነቅባት ድረስ በሚገድል በሽታ የተያዙ በሽተኞችን ተንከባክባለች፤ ብዙ ድሆችን ረድታለች። በኖቤል ሽልማት ያገኘችውን ብዙ ሚሊዮን ዶላር በሙሉ ለድሆች ሰጥታለች። እንደዚህ ዓይነት መስዋእትነት የሚጠይቅ አስደናቂ ምሳሌ ትተው ያለፉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሚገርም ውበት አላት። ለዚህ ነው እንዴት እንዲህ ሁሉ ነፍስ አጥፊ ገዳይ ልትሆን ቻለች ብሎ ዮሐንስ የተደነቀባት። የመጀመሪያው የካቶሊክ ፖፕ ጴጥሮስ ነበረ ይላሉ። ነገር ግን ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ እንደሰጠ ባየ ጊዜ ጴጥሮስ ተነስቶ ከሊቀ ካሕናቱ አገልጋዮች የአንዱን ጆሮ በሰይፍ ቆረጠው። ኢየሱስም ሰይፉን ወደ ሰገባው እንዲመልስ ነገረው። እና ጴጥሮስን እከተላለው የምትል ቤተክርስቲያን በአስተምሕሮ ከእኔ ጋር አልተስማሙም በሚል ሰበብ አንዴት በሰይፍ ብዙ ሚሊዮን ክርስቲያኖችን ትገድላለች?
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እስከ ዛሬ ሚስጥር እና እንቆቅልሽ ናት። በብዙ መንገድ አስደናቂ ናት፤ ድሆችን ለመደገፍ ብዙ ሰብዓዊ እርዳታ አድርጋለች። ካቶሊኮች ለብዙ ሰዎች መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት እና እርዳታ ይሰጣሉ። ከዚያ በኋላ በዓለማዊ ፖለቲካ ውስጥ በግባት የእረኝነት አገልግሎታቸውን ያበላሻሉ። ደግሞም ከልክ በላይ የሆነ የግድያ እና የማንገላታት ታሪክም አላቸው።
ራዕይ 17፡7 መልአኩም አለኝ፦ የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።
ዮሐንስ የእነዚህን ተምሳሌቶች ፍቺ ተቀብሏል።
መልአኩ መጥቶ ለዮሐንስ ይህች የወደቀች ሴት ወይም ይህች የወደቀች ቤተክርስቲያን ማን እንደሆነች ለዮሐንስ አብራርቶለታል።
ከምንድነው የወደቀችው? መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈ በትክክል ከመከተል ነው የወደቀችው።
ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ አስፈሪ ጭራቅ ነው። ቤተክርስቲያን የምትጋልበው አስፈሪ የሆነ ኃይለኛ መንፈስ ላይ ተቀምጣ ነው። ይህ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ የሆነ የሮማ ካቶሊክ ድርጅት ዓለምን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ፍርድ እየነዳ ነው፤ በዚህ ድርጅት ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን እግዚአብሔርን እያገለገሉ መስሏቸው ተታለዋል። ለዚህ ነው ዮሐንስ የተደነቀው።
እንዴት ይህን ያህል ብዙ ቅን ሰዎች ይታለላሉ? እነዚህ ቅን ሰዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ፕሮቴስታንት ልጆቿ በሙሉ ናቸው።
ራዕይ 17፡8 ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።
ጥልቁ ጉድጓድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለውም። ስለዚህ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ሰባኪዎች በሰዎች አመለካከት እና ልማዶች ላይ የተመሰረቱ ብዙ ሃሳቦችን እየመዘሙ ያመጣሉ። ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አስፈላጊ መሆኑን አያምኑም።
እኛም አሕዛብ የሆንን አማኞች በፊት በብሉይ ኪዳን ዘመን በአረማዊነት ጉድጓድ ውስጥ ወድቀን ነበር። ኢየሱስ ከዚህ መንፈሳዊ እስር ቤት ሊያወጣን ነው የመጣው። አሁን “የቤተክርስቲያናዊነት” ዲኖሚኔሽናዊ አሰራር ወደነዚያ አረማዊ ሚስጥራት ገትቶ ሊመልሰን እየሞከረ ነው። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይታወቁ ስሜትን የሚያባብሉ ግን ባዶ የሆኑ የአምልኮ ስርዓቶች ላይ በመገኘት ይደሰታሉ፤ ለምሳሌ ትልልቅ ካቴድራሎች፣ ሐይማኖታዊ የክሕነት ልብሶች፣ የመስቀል ምልክት፣ የጸሎት መቁጠሪያዎች፣ የገና ዛፎች፣ የፋሲካ እንቁላሎች፣ ዲስኮ ሙዚቃ፣ እና ግብረ ሰዶማዊነት።
ክርስቲያኖች ትክክለኛው ቦታ እንዳልሆኑ የሚያሳውቃቸውን የሚነዘንዝ ስሜት ጸጥ ለማሰኘት ዘመናዊ የሆኑ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ መንፈሳዊ ማደንዘዣዎችን ይቀበላሉ። በእምነታችን ተሳስተን እንደሆን ማንም እንዲነግረን አንፈልግም። ቁሳቁስ በማከማቸት ላይ የተመሰረተ ስጋዊነት የሞላበትን ሕይወታችንን የሚያናውጥብን የአስተምሕሮ ጉዳይ መስማትም አንፈልግም።
ዛሬ ብዙዎቻችን እምነታችን በመጽሐፍ ቅዱስ መመስረት አያስፈልገውም ብለን እናምናለን። ፖፕ፣ ካርዲናል፣ እና ሊቀ ጳጳሳት የሚሉ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልጋችሁ አምጡ። አረማዊ እምነቶች ከጥልቁ ጉድጓድ ተጎትተው ይወጡና ክርስቲያናዊ ካባ ለብሰው ወደ ቤተክርስቲያን ይገባሉ። ኢሽታር የተባለችዋ አምላክ እንቁላል ውስጥ ሆና ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ መጣችና በዚያ ተፈለፈለች። የፋሲካ (ኢስተር) እንቁላል ማለትም የኢሽታር እንቁላል አመጣጡ ከዚህ ነው።
“እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፣ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ”።
ይህ የሚያሳየው አንድ ፖፕ በሌላ ፖፕ እየተተካካ ለብዙ ዘመናት እንደሚቀጥል ነው። የቤተክርስቲያን ድርጅት እነዚህን ኃይለኛ ነገር ግን ክፉ የሆኑ መናፍስት ይጠቀምባለቸዋል። ፖፑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አለቃ እና ራስ ነው። ዘመን ሲያልፍ አዲስ ፖፕ ይመርጣሉ፤ የተመረጠውም ፖፕ መሪያቸው ነበረ፤ ከዚያም ሞተ። ሰውየው ይሞታል የፖፕነት ስለጣን ግን አይሞትም ምክንያቱም በካርዲናሎች ምክር ቤት አማካኝነት አዲስ ፖፕ ተመርጦ ይተካል። የአሁኑ ፖፕ ቢሞትም፤ የእርሱን ቦታ የሚተካ ሌላ ፖፕ አለ።
ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነው በማለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከጥንትም ከመጀመሪያውም ጀምሮ ሁልጊዜ ፖፕ ነበረ ትላለች።
ስለዚህ የካርዲናሎች ምክር ቤት አዲስ ፖፕ እንዲሾም በማድረግ የፖፑ ስልጣን በነበረበት ይቀጥላል። ይህ ዘዴ በዓለም ላይ ለረጅም ዘመናት ያልተቋረጠ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር አድርጓል።
ፖፑ የሐይማኖታዊ ድርጅት ራስ ነው። “አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ” (ይህ ማለት በካርዲናሎች ከተመረጠ በኋላ ፖፑ ይገዛ በነበረበት ዘመን ነው) “አሁንም እንደሌለ” (ፖፑ ሲሞት) “ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ” (በቦታው እንዲቀመጥ አዲስ ፖፕ ይመረጣል ማለት ነው)።
የፖፑ መተካካት የተቀበልነው ስልጣን ከጴጥሮስ የመጣነው በማለታቸው እና ከጥንቶቹ ጳጳሳት የተቀበልነው ነው በማለታቸው ላይ የተመሰረተ ነው። ይህም አስገራሚ ስርወ መንግስት ነው። የትኛውም ሌላ መንግስት ለዚህን ያህል ዘመን ሳይቋረጥ መቀጠል አልቻለም። በሚለዋወጥ ዓለም ውስጥ ሳይጠፉ ለረጅም ዘመናት መቀጠል በመቻላቸው ሰዎች በጣም ይገረሙባቸዋል።
ጴጥሮስ ግን ወደ ሮም ሄዶ አያውቅም። ጴጥሮስ ሮሜ ሄዶ እንደነበረ የሚመሰክር አንድም የታሪክ ማስረጃ የለም። ጴጥሮስ የአይሁዶች ሐዋርያ ነበረ። ቂሮስ አይሁዶችን በባቢሎን ከነበሩበት ግዞት ነጻ በለቀቃቸው ጊዜ ወደ እስራኤል ያልተመለሱትን አይሁዶች ለመጎብኘት ወደ ባቢሎን ሄዶ ነበር። ካቶሊኮች ጴጥሮስ ወደ ሮም መጥቶ ነበር ለማለት በግድ ሮማ ባቢሎን ናት ይላሉ። ይህ ግን እውነት አይደለም። ሮም ባቢሎን አይደለችም። ሴቲቱ ማለትም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በግምባሯ ላይ ሚስጥር ባቢሎን ተብሎ ተጽፎባታል። ግምባር የሚያመለክተው ከግምባር በስተኋላ ያለውን አእምሮ ነው። ስለዚህ የሮማ ቤተክርስቲያን በአእምሮዋ የባቢሎን ሚስጥራትን ታምናለች። ለዚህ ነው እግዚአብሔር የሚያወግዛት። ባቢሎን ግን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳር ያለች ከተማ ናት። ጴጥሮስም የሄደው ወደዚያ ነው።
በ399 ዓ.ም የሞተው ሲሪሲየስ የተባለው ጳጳስ እራሱን ፖፕ ብሎ በመጥራት የመጀመሪያው የሮም ጳጳስ ነበር። ስለዚህ ፖፕ የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ እስኪዳብር ድረስ 400 ዓመታት ያህል ጊዜ ወስዷል። ይህ ሃሳብ ግን የመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። አንድ ጳጳስ አንድ ከተማን ያስተዳድር የሚለው ሃሳብ ዮሐንስ እስከሞተበት እስከ 100 ዓ.ም ድረስ አልተፈጠረም። አብዛኞቹ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ከ60 እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ተገድለዋል፤ አንዳንዶቹ ከኢየሩሳሌም በጣም ርቀው ሄደዋል፤ ለምሳሌ ቶማስ ወደ ሕንድ ሄዷል። ከሐዋርያት ሁሉ መጨረሻ የሞተው ዮሐንስ በ81 ዓ.ም አካባቢ ዶሚቲያን ገዥ ከሆነ በኋላ በፍጥሞ ደሴት ላይ ታስሮ ነበር። ዶሚቲያን በ96 ዓ.ም ሲሞት ዮሐንስ ከእስር ተፈታ።
አውሬው ማለት ሰዎች አንድን ሰው ከፍ እንዲያደርጉ እንዲከተሉና እንዲያመልኩ የሚያደርግ መንፈስ ነው። ከዚያም ከፍ የተደረገው ሰው ሰዎች ሁሉ የእርሱን ሃሳብ እና አመለካከት እንዲቀበሉ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ እንዲታዘዙለት ይፈልጋል። የዚህ ዓይነቱ መሪ መፈክር፡- “ሁሉም ሰው የእኔን ሃሳብ የመቀበል መብት አለው” የሚል ነው።
በሐይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ውስጥ ያሉ መሪዎች በቀላሉ የስልጣን ሱስ ይይዛቸዋል። ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ትልቅ የንግድ ስራ ሆናለች።
የዚህ ኃይለኛ መንፈስ ራስ ፖፑ ነው፤ ይህም መንፈስ ታላቅ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ወይም ዲኖሚኔሽን መስርቷል (ዲኖሚኔሽን የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም)።
ራዕይ 17፡9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
የመንፈስ ቅዱስ ታላቅ ስጦታ ልሳን ሳይሆን ትበብ ነው። ይህም ጥበብ ጥቅሶችን ከጥቅሶች ጋር እንዲሁም ከቤተክርስቲያን ታሪካዊ መረጃዎች ጋር በትክክል እየገጣጠምን በአሁኑ ሰዓት ምን እየሆነ እንዳለ እና በፊት ደግሞ በታሪክ ውስጥ ምን ተደርጎ እንዳለፈ የምናውቅበት ጥበብ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እርስ በራሳቸው አይጋጩም። የተጋጩ በሚመስሉን ጊዜ እኛ በርዕሱ ላይ ያለን እውቀት እና መረዳት ገና ያላደገ መሆኑን ያመለክታል።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥
10 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡31 ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።
በመጀመሪያ የተጠቀሰው ስጦታ የጥበብ ቃል ነው። ያለ ጥበብ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን መረዳት አንችልም።
ማርከስ ቴሬንቲየስ ቫሮ (116 ዓመተ ዓለም - 27 ዓመተ ዓለም) በላቲን ቋንቋ ቁ. 4 እንደ ጻፈው፡-
“አሁን ሮም ያለችበት ቦታ ሴፕቲሞንቲየም ይባል ነበር፤ ይህም ስም የተራሮችዋን ብዛት ያመለክታል፤ ከጊዜ በኋላ በከተማይቱ አጥር ተከበቡ።”
ሴፕቲሞንቲየም “ሰባት ተራሮች” ማለት ነው።
ከላይ ያለው ምስል በንጉስ ቬስፓሲያን (69-79) ዘመን የተቀረጸ ሳንቲም ነው፤ በሳንቲሙ ላይ ያለው ምስል የሮም ከተማ በ7ቱ ተራሮች ላይ የተቀመጠች አምላክ መሆኗን ያሳያል። ገዝዎቿ ቄሳር ይባላሉ።
ሳንቲሙ ላይ PM የሚለው ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ወይም ፖንቲፍ ማለት ነው።
በዚያ ዘመን የነበሩ አረማዊ ሮማውያን ሮማ የተባለችዋን አምላክ ያመልኩ ነበር። ዛሬ ብዙ ካቶሊኮች ማርያምን ያመልካሉ። ከሁሉም ፖፕ ታላቅ የሆነው ፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ ማርያም አምላክ እንደሆነች ተቀብሏል። የባቢሎናውያን አረማዊ ሚስጥር እና አያቶችን የማምለክ ልማድ ወደ ሮም የገባው ዝነኛው ሮማዊ ዩልየስ ቄሳር በ63 ዓመተ ዓለም ጉቦ ከፍሎ የፖንቲፍነትን (ወይም ፖንቲፌክ ማክሲመስ) ሹመት የተቀበለ ጊዜ ነው። ከዚያ በኋላ ተከማቸበትን ብዙ እዳ ለመክፈል የሚሆን ሃብት ለመዝረፍ ለጦርነት ወደ ጋውል (ዛሬ ፈረንሳይ ወደምትባለው) ሄደ። አንዳንድ የታሪክ ምሑራን 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ጋውሎችን ገድሏል ይላሉ። ሐይማኖት እና ነፍሰ ገዳይነት ለገንዘብ ተባብረው ይሰራሉ። ይህ የሐይማኖት እና የገንዘብ መርዘኛ ድብልቅ መጠጥ እስከ ዛሬም ድረስ በብዛት አለ።
ስለዚህ የአረማዊቷን ሮም አርአያነት እየተከተልን ነን። ከላይ በሳንቲሙ ላይ ያየነው ሴትን የማምለክ የሮማውያን ልማድ የባቢሎናውያን ሚስጥራት እስከ ዛሬ ድረስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ ያሳያል። አምልኮው ሮማ ከምትባለዋ አምላክ ማርያምን ወደ ማምለክ ተለውጧል። የክርስትና ካባ ለበሰ እንጂ አሁንም የአረማውያን ጣኦት አምልኮ ነው። የባቢሎን ካሕናት እስከ ዛሬ እየተገረምን እንድንከተላቸው ሊያደርጉ የቻሉት በእርግጥ የረቀቀ አስገራሚ ሃሳብ ቢኖራቸው ነው።
ከላይ ባለው የሳንቲም ምስል ውስጥ PM የሚለው ፖንቲፌክስ ማክሲመስ ማለት ነው፤ እርሱም የባቢሎናውያን ሚስጥር ሊቀካሕናት ማለት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በ63 ዓ.ም ይህንን ማዕረግ ለራሱ የወሰደው ዩልየስ ቄሳር የተባለው የሮማ ገዥ ነው። እስከ 379 ዓ.ም ድረሰ የሮማ ገዥዎች ይህንን ማዕረግ ተጠቅመውበታል፤ ከዚያም በኋላ ቴዎዶሲየስ ክርስቲያን ከሆንኩ በዚህ አረማዊ ማዕረግ መጠቀም የለብኝም ብሎ ማዕረጉን መጠቀም አቆመ። በ450 ዓ.ም የሮም ጳጳስ በ450 የሮም ጳጳስ ሊዮ ቀዳማዊ እራሱን ፖፕ እና ፖንቲፌክስ ማክሲመስ (ፖንቲፍ) ብሎ መጥራት ጀመረ።
ሮም በመጀመሪያ ራሳቸውን ከጠላት ለመከላከለ እንዲያመቻቸው ብለው የንግድ መስመር የታይበር ወንዝን የሚያቋርጥበት ቦታ በሰባት ኮረብታዎች ላይ የተሰሩ መንደሮች ነበረች። ሮሙለስ በመሻገሪያው ቦታ የክፍያ ጣቢያ ከፈተ፤ ይህም ሕጋዊ መልክ ያለው ዝርፊያ ነበር። የሮሙለስ ሽፍታዎች ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ ሕዝቡ በሰባቱ ኮረብታዎች መካከል ባሉ ሜዳማ ቦታዎች ላይ ቤቶችን መገንባት ጀመሩ።
ለእነዚህ ሕዝቦች ጥበቃ ለማድረግ በሰባቱ ኮረብታዎች ዙርያ ግምብ አጥር መስራት አስፈላጊ ነበር።
በአንድ መንደር ወይም በቤቶች ዙርያ ግምብ አጥር ከተሰራ በውስጡ የሚኖሩ ሰዎች ያን ቦታ ከተማ ይሉታል። ስለዚህ ይህች ከተማ የሰባቱ ኮረብታዎች ከተማ ተባለች። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሰባቱ ተራሮች ይላቸዋል። ለምን? ይህን ጥያቄ ኋላ እንመለስበታለን።
ለአሁን ከሮማውያን ሁሉ ታዋቂ ሮማዊ ወደ ነበረው ዩልየስ ቄሳር እንመለስ። ቄሳር የምክር ቤቱን ስልጣን በመሻር የሮማ ሪፓብሊክን አፈረሰ፤ ይህን ያደረገው ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ለመሆን ፈልጎ ነው። ይህን በማድረጉ ቄሳሩ ለሮማ ቤተክርስቲያን አስቀድሞ መንገድ ቀይሶላታል። ፖፑ ቤተክርስቲያንን እንደ ፈላጭ ቆራጭ ነው የሚመራት ምክንያቱም በስልጣን ከካርዲናሎቹ በታች መሆን አልፈለገም። ከሞተ በኋላ አምላክ ነው ተብሎ የተመለከ የመጀመሪያው ሮማዊ ቄሳር ነው። ሕዝቡ ቄሳር በእግዚአብሔር ቦታ የቆመ መሰላቸው። ስለዚህ ፖፑም በክረስቶስ ምትክ ነኝ በማለት ነው ወደ ስልጣን የወጣው።
ሐይማኖታዊ ግፍ በመፈጸም ቄሳር በአንደኛ ደረጃ ታዋቂ ነው። ኃይል ያለው ሰው ሁሌ ትክክል ተደርጎ ይቆጠራል። በጨለማው ዘመን እና 100 ዓመታት ያህል በፈጀው የጸረ ተሃድሶ ዘመቻ ዘመን ውስጥ የካቶሊክ ፖፕ የሚቃወሙዋቸውን ከአስር ሚሊዮን ሰዎች በላይ ገድለዋል። ስለዚህ ያለ ምንም ጥርጥር የቄሳርን አርአያነት ተከትለዋል ማለት ነው።
በቄሳር ዕድሜ ውስጥ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ዓመታት ከኢየሱስ ዕድሜ የመጨረሻዎቹ ዓመታት ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ዩልየስ ቄሳር ስሙ በእንግሊዝኛ ሲጻፍ የመጀመሪያዎቹ ፊደሎች JC ነው፤ ቢዘህም የተነሳ የኢየሱስ ክርስቶስ ተቀናቃኝ ነው ምክንያቱም የኢየሱስም ስም በእንግሊዝኛ ሲጻፍ የመጀመሪያዎቹ ፊደሎች JC ናቸው። ቄሳር ከአራት ዓመት ያነሰ ጊዜ ከገዛ በኋላ ብሩተስ በተባለው ጓደኛው ተገደለ። ኢየሱስ ለሶስት ዓመት ከግማሽ ካገለገለ በኋላ በጓደኛው በይሁዳ ተላልፎ ተሰጠ።
ዩልየስ ቄሳር - ሮም ውስጥ የመጀመሪያውን የገዥዎች “ንጉሳዊ ቤተሰብ” የመሰረተ ሰው።
ስልጣን ከአንድ ንጉስ ወደ ቀጣዩ ንጉስ በሰላም ማሸጋገር ሁልጊዙ አስቸጋሪ ነበር። የሮማ ገዥዎች ሁሉ በስልጣን ነጣቂዎች ተገድለው ነው ያለፉት።
የሮማ ቤተክርስቲያን የጴጥሮስ ተወካይ ነኝ በማለት ይህንን ችግር አስወገደች። ጴጥሮስ ሮም ውስጥ ነው የተገደለው በማለት ብቻ ታሪክን ለወጡ። ጴጥሮስ ሮም ውስጥ መገደሉን የሚያመለክት አንዳችም ታሪካዊ ማስረጃ የለም። ጴጥሮስ ሮም ሄዶ አያውቅም።
ጴጥሮስ ግን የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ነበረው፤ ስለዚህ ፖፑ የጴጥሮስ ምትክ ነኝ አለ፤ ስለዚህ ፖፑ ብቻ ነው ሰዎች ወደ መንግስተ ሰማያት እንዲገቡ መፍቀድ የሚችለው። ይህም ሃሳብ የሮማ መንግስትን የወረሩ እና ያፈራረሱ ባርቤሪያውያንን ሁሉ አስገርሟቸዋል። የሮማ መንግስትን ያፈረሱ ብዙ ባርቤሪያውያን ከዚያ በኋላ ወደ ካቶሊክ ተለውጠዋል።
በመጨረሻም በ1059 ዓ.ም ፖፕ ኒኮላስ ዳግማዊ አዲስ ፖፕ መመረጥ የሚችለው በካርዲናሎች ብቻ ነው የሚል ሕግ አወጣ። ስለዚህ በዚህ ስልጣን መተካካቱ በካቶሊኮች እጅ ቆየ። ከካርዲናሎቹ ምርጫ ውጭ የሆነ አዲስ ፖፕ በጭራሽ የጴጥሮስ ምትክ ነው የሚለውን እውቅና ማግኘት አይችልም።
ነገር ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ጠለቅ ያለ እውነት አለ። መጽሐፍ ቅዱስ ሰበት ኮረብታዎች ሳይሆን ሰባት ተራሮች ይላል።
ዳንኤል ባየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ አንድ ድንጋይ የምስሉን እግሮች መታ እና ድንጋዩ ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ይህም ተራራ ኢየሱስ በምድር ላይ ለ1,000 ዓመታት የሚገዛበትን የእግዚአብሔርን መንግስት ይወክላል።
ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ መንግስተ ሰማያትን በተመለከተ የተነገሩ ሰባት ምሳሌዎች አሉ። (ይህን በተመለከተ በስፋት ለማወቅ “ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይገልጻል” የሚለውን ጥናት ማንበብ ትችላላችሁ)። እያንዳንዱ ምሳሌ አንድ የቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል። ስለዚህ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን መንግስት ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሳቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ወይም መንግስታት ወይም ተራሮች ውስጥ የእግዚአብሔር ጠላት ናት። ለ2,000 ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ ለእውነት ጠላት ሆኖ የዘለቀ ሌላ አካል የለም።
ራዕይ 17፡10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።
54-0513 የአውሬው ምልክት
ሰባት ነገስታት ናቸው፤ አምስቱ ደግሞ ወድቀዋል…
ታሪክን ብንመረምርና ነገስታት ሮም ውስጥ የወደቁበትን፣ ከባቢሎን መንግስት ጀምሮ ያለፉትን መንግስታት ወደ ኋላ ተመልሰን ብናይ፤ … አንድ ሰው … (ኔሮ) እናገኛለን… አንዱ ደግሞ ገና ሊመጣ ነው፤…
እርሱም ለጥቂት ጊዜ ይኖራል … (ሲመጣ ለስድስት ወራት ይቆያል)።
ኔሮ (54-68 ዓመተ ዓለም) ዮሐንስ ፍጥሞ ደሴት ላይ በታሰረበት ጊዜ ሲገዛ ነበር። ኔሮ በ68 ዓ.ም ሲሞት ዮሐንስ ከእስር ቤት ተለቀቀ። ከዚያ በኋላ ዶሚቲያን የተባለ ሌላ ንጉስ (81-96 ዓ.ም) ዮሐንስን እንደ ገና እስር ቤት ጣለው፤ ዶሚቲያን በ96 ዓ.ም ሲሞት ዮሐንስ ከእስር ተፈታ። የፖለቲካ እስረኞች ሁልጊዜ እስር ቤት የጣላቸው ንጉስ ሲሞት ነበር ከእስር የሚፈቱት። ዮሐንስ ራዕዩን የተቀበለው በሁለት ደረጃ ነው። መጨረሻ ከእስር ቤት ሲለቀቅ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ መጠናቀቁን አወቀ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ምንም የሚጨመርበት ነገር አልነበረም (ራዕይ 22፡18)። ወደ ኤፌሶንም በተመለሰ ጊዜ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በዘመኑ ከነበሩ ብዙ ጽሑፎች እና መልእክቶች መካከል መርጦ በአንድ ጥራዝ ለመጠረዝ መንፈሳዊ ብቃት የነበረው እርሱ ብቻ ነበር።
እስፔይን ውስጥ የነበረ ሮማዊ ጀነራል ጋልባ የገዥነትን ስልጣን ቀምቶ ከያዘ በኋላ ለ7 ወራት ብቻ በዙፋን ላይ ቆየ፤ ይህም በጣም “አጭር ዘመን” ነው። ከእርሱ በኋላ የዩልየስ ቄሳር ስርወ መንግስት አበቃ። አረማዊቷ ሮም ሁልጊዜም የስልጣን ሽግግር ችግር ነበረባት።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህንን ችግር የፈታችው ካርዲናሎች ሚስት እንዳያገቡ በመከልከል ነው። ስለዚህ በሞተ ፖፕ ቦታ ሌላ ፖፕ ለመተካት የፖፑ ልጅ አያስፈልግም። ካርዲናሎቹ ለፖፕ ስልጣን ብቁ ነው ብለው ያሰቡትን ሰው ከራሳቸው መካከል መምረጥ ይቻላሉ። ስለዚህ በቅርቡ ጆን ፖል ዳግማዊ እና ፍራንሲስ የተባሉ ሰዎችን ፖፕ አድርገው መርጠው መሾም ችለዋል፤ እነዚህም ሰዎችም ምንም የስጋ ዝምድና የላቸውም።
በምስራቁ ዓለም ሕዝቡ መሪያቸውን እንደ አምላክ መምለካቸው የተለመደ ነበረ። ነገር ግን በምዕራቡ ዓለም የተለመደ አልነበረም። ታላቁ አሌግዛንደር ከግሪክ ወደ ፋርስ ሄደ፤ ከተቀዳጀውም ታላቅ ስኬት የተነሳ መሪ እንደ አምላክ በሚመለክበት በምስራቁ ዓለም ውስጥ እንደ አምላክ የተመለከ የመጀመሪያ ምዕራባዊ ንጉስ ሆነ። አሌግዛንደር በትዕቢት እና በኩራት ተሞልቶ አንዳንዶች መቄዶናውያን እና ግሪኮችም እንደ አምላክ እንዲያመልኩት አስገደደ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ወዲያው ሞተ። ሰውን አምላክ አድርጎ የማምለክ ሃሳብ ግን ተተክሎ ቀረ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምዕራባዊ ሰውም አምላክ ሊባል ቻለ። ምዕራባውያን መሪዎች የአሌግዛንደር አድናቂዎች ስለነበሩ ከዚያ በኋላ ቄሳርን የማምለክ ልማድ የሮማ መንግስት ውስጥ ተጀመረ።
ዩልየስ ቄሳር በንግስና ዘመኑ እጅግ ዝነኛ ከመሆኑ የተነሳ በ44 ዓመተ ዓለም ከሞተ በኋላ እንደ አምላክ የተመለከ የመጀመሪያው ሮማዊ መሆን ችሏል፤ ጴርጋሞን ውስጥ በ29 ዓ.ም በስሙ ቤተመቅደስ ተሰርቶለታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሮማ መንግስት ውስጥ ገዚዎቻቸውን እንደ አምላክ ማምለክ ተጀመረ። ቄሳር በሕይወት ሳለ የባቢሎናውያን ሚስጥራት ፖንቲፍ ነበረ፤ ይህንንም ማዕረግ የሮማ ገዥዎች መጠሪያ አደረገው። ፖፑ እራሱን ፖንቲፍ ወይም የእነርሱ ሊቀ ካሕናት ብሎ በመጥራት የሮማ መንግስትን በደመሰሱ በአረማውያኑ ባርቤሪያኖች ላይ ገዥ ሆኖ ተነሳ። ፖፕ ሁሉ ብዙዎቹን የባቢሎናውያን ሚስጥራት አምነው ተቀብለው አሰራጭተዋል፤ ምክንያቱም ይህ በባርቤሪያውያን ነገዶች ዘንድ ተሰሚነትና ስልጣን አጎናጽፏቸዋል። ከዘመናት በኋላ የካቶሊክ ልጆች የሆኑት ፕሮቴስታንቶች የእናታቸውን የካቶሊክን ምሳሌ በመከተል ከባቢሎናውያን ሚስጥራት መካከል የተወሰኑትን ተቀብለው አምነዋል።
ሕዝቅኤል ኢየሩሳሌም በዙርያዋ በነበሩ አሕዛብ ሃገራት ተጽእኖ የተነሳ ስለመበላሸቷ እየነቀፈ ተናግሯል።
ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
በተፈጥሮ ሴት ልጅ እናቷን ትከተላለች። እናትየውን በደምብ ማየት ልጅየዋ ወደፊት ስታድግ ምን ዓይነት ሴት እንደምትሆና ለማወቅ ያስችላል።
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ እኛ ፕሮቴስታንት ልጆች የእናታችን የካቶሊክን አረማዊነት ኮርጀን ተከትለናል።
አውግስጦስ
ቄሳርን ተክቶ ገዥ የሆነው የእሕቱ የልጅ ልጅ አውግስጦስ ነው። እርሱም ምክር ቤቱን የሚያከብር እና ምክራቸውን የሚያዳምጥ ቢመስልም ስልጣናቸውን ሙሉ በሙሉ ሻረና የራሱ አደረገ። የሚሰማቸው እያስመሰለ ነበር እንጂ በጭራሽ አይሰማቸውም ነበር። ከዚያ በኋላ ለእነርሱ ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ብቻውን እንደ ፈላጭ ቆራጭ በመምራት እራሱን ገዥ ብሎ ጠራ። መፈክሩም “አንድ ሰው ብቻ አለቃ ነው” የሚል ነበር። የካቶሊክ ቄሶችም ቤተክርስቲያናቸውን በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚመሩት። የአረማዊቷ ሮም መንፈስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቷል። አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ፓስተሮችም ቤተክርስቲያናቸውን በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚመሩት። ልጅየዋ ቤተክርስቲያን ልክ እንደ እናትየው ቤተክርስቲያን እየሆነች ናት።
መንፈሱ ከአረማውያኑ ሮማኖች ዘሎ ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገባ፤ ከዚያ በኋላ ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ገባ። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ፍላጎቷ የራሷን ስልጣንና ኃይል ማጠናከር እና የሕዝቡን ገንዘብ መዝረፍ ሆኖ ሳለ መጽሐፍ ቅዱስን እንደምትከተል ታስመስላለች።
ቀሪዎቹ የዩልየስ ቄሳር ቤተሰብ አባላት ወደፊት ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ፖፕ የሚከተሉትን ምግባረ ብልሹ አሰራር አበጅተዋል።
ጢባርዮስ
ጢባርዮስ የአውግስጦስ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ በማደጉ አደገ። ከአውግስጦስ በኋላ ነገሰና እጅግ ክፉ ጨካኝ ሰው ሆነ። እርሱም የስልጣን እና የኃይል ብዛት ሰዎችን እንሴት እንደሚያባልግ ጥሩ ማሳያ ሆነ። በየቀኑ ቢያንስ አንድ ሰው ይገድል ነበር። ሕጻናትን ያማግጥ ነበር። በምክር ቤቱ ውስጥ ከነበሩ አማካሪዎች መካከል 300 ሰዎችን ከመግደሉ የተነሳ አማካሪዎቹ እርሱን መከራከር ይፈሩ ነበር። በጨለማው ዘመን የካቶሊክ ጳጳሳት ይህንኑ አሰራር ተከትለዋል። እነርሱም አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ገድለዋል።
ካሊጉላ
ጢባርዮስ በማደጎ ያሳደገው የልጅ ልጅ ካሊጉላ ቀጣዩ የሮማ ንጉስ ሆነ። እርሱም አምላክ ነኝ ብሎ አሰበ። ስለዚህ ማንንም አይሰማም ነበር። ሰው ሁሉ እርሱን እንዲታዘዝ ፈለገ። እጅግ ጨካኝ እና ክፉ ሰው ሆነ።
በ1302 ዓ.ም ፖፑ ሰዎች ለእርሱ ካልተገዙ በቀር መዳን እንደማይችሉ አወጀ። ፖፑ የሰዎችን ሐጥያት ይቅር ማለት እችላለው አለ፤ ነገር ግን ሐጥያትን ይቅር ማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ፖፑ “ቪካሪየስ ክሪስቲ” የሚባል ማዕረግ ለራሱ ተጠቀመ፤ ትርጉሙ የክርስቶስ ምትክ ማለት ነው። እርሱም በምድር ላይ እራሱን እግዚአብሔር ማድረጉ ነው።
እስከዚያ ጊዜ ድረስ የሮማ ምክር ቤት ብቻ ነበር አንድን ሰው ገዥ አድርጎ የሚሾመው።
ክሎዲየስ
የካሊጉላ ደካማ አጎት ክሎዲየስ በፕሬቶሪያን ጋርድ አማካኝነት ነበር ገዥ ሆኖ የተሾመው፤ ፕሬቶሪያን ጋርድ ኢጣሊያ ውስጥ እንዲቀመጥ የተፈቀደለት ብቸኛ ጦር ሰራዊት ነው። ክሎዲየስ ለፕሬቶሪያን ጋርድ ልዩ ጉርሻ ሰጣቸው፤ ስለዚህ ጦር ሰራዊቱ ስለተቀበሉት ክፍያ ክሎዲያስን ገዥ አደረጉት። ጋውል (ፈረንሳይ) ውስጥ የተወለደው ክሎዲየስ የመጀመሪያው ከኢጣልያ ውጭ የተወለደ ገዥ ነበር። ምክር ቤቱ ውሳኔ ሳያደርግ ገዥ ተብሎ የተሾመ የመጀመሪያው ሰው እርሱ ነበር።
ክሎዲየስ ደካማ ግን ጨካኝ ነበር። አንዳንድ ፖፕ ነበሩ ልክ እንደ ክሎዲየስ ደካማ የሆኑ ነገር ግን በጣም ክፉ ነገር የሰሩ። እንደዚያም ሆኖ ፖፕ ሆና በስልጣናቸው እስከ ዕድሜያቸው መጨረሻ ተቀምጠዋል። በጨለማው ዘመን ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምግባረ ብልሹ እና ጨካኝ ግፈኛ ፖፕ በመሩዋት ጊዜ ብዙ የሚያስነቅፋትን ነገር አድርጋለች።
ክሎዲየስ የኔሮን እናት አገባ እና ኔሮን የራሱ ልጅ አድርጎ አሳደገ። የኔሮ እናት ክሎዲየስን መርዝ አብልታው ኔሮ በእርሱ ቦታ እንዲነግስ አደረገች።
ኔሮ
ኔሮ ንጉስ ሆነና በ64 ዓ.ም የሮም ከተማ ስትቃጠል ያቃጠሏት ክርስቲያኖች ናቸው በማለት የመጀመሪያውን መራራ ስደት በክርስቲያኖች ላይ አስነሳ። እጅግ በጣም ክፉ ሰው ከመሆኑ የተነሳ ሃብታሞች ንብረታቸውን በሙሉ ለእርሱ እንዲናዘዙ ያስገድዳቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ራሳችሁን ግደሉ ብሎ ያዛቸውና ሃብታቸውን ይወርሳል። እርሱ ራሱ በ68 ዓ.ም ራሱን ገደለ።
በ450 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር አልስማማም የሚሉ ክርስቲያኖችን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መግደል ትችላለች ብሎ አወጀ። ይህም የግድያ ፈቃድ ብዙ ሕዝብ የተጨፈጨፈበትን የመስቀል ዘመቻ እንዲሁም ብዙ የጭካኔ ተግባር የተፈጸመበትን እስፓኒሽ ኢንክዊዚሽንን አስከተለ።
ጋልባ
አስፔይን ውስጥ የተመደበውን የሮማ ሰራዊት የሚመራው ጀነራል ጋልባ እስፔይን ውስጥ የነበረው ጦር ሰራዊት ገዥ አድርጎ ሲመርጠው ሄዶ በሮም የገዥነትን ስልጣነ ቀምቶ ያዘ። የዛኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የሮማ ገዥ ከኢጣልያ ውጭ ተመረጠ። ደግሞም ለመጀመሪያ ጊዜ የንጉሳውያን ቤተሰብ አባል ያልሆነ ሰው ገዥ ሆኖ ተመረጠ። የቄሳርም የቤተሰብ ስርወ መንግስት ተቆረጠ።
ወደ ፊት በዓለም መጨረሻ የክርስቶስ ተቃወሚ መንፈስ አንድ ሰው ውስጥ ይገባና ዓለምን ሁሉ ለመምራት የፖፑን ስልጣን ቀምቶ ይወስዳል። ይህም ታላቅ ሐይማኖታዊ ስልጣን፣ ብዙ ሃብት፣ እና ብዙ ፖለቲካዊ ኃይል ያጎናጽፈዋል። የሚጎድለው ወታደራዊ ኃይል ብቻ ይሆናል፤ እርሱንም ቢሆን ከ10ሩ ፈላጭ ቆራጭ ወታደራዊ መሪዎች ተቀብሎ ያሟላል።
ዳንኤል 11፡21 በእርሱም ስፍራ የተጠቃ ሰው ይነሣል የመንግሥቱንም ክብር አይሰጡትም፤ በቀስታ መጥቶ መንግሥቱን በማታለል ይገዛል።
አውሬው ማለት የፖፕ መተካካት ነው። ስምንት ቁጥር የአዲስ ስርዓት አመልካች ነው። ጨካኝ የቤተክርስቲያን ድርጅት የመጀመሪያውን ጨካኝ አረማዊ የሮማ ገዥ ቤተሰቦችን ተካች። ከዚያ በካርዲናሎች ምክር ቤት ሳይመረጥ የፖፑን ስልጣን የሚቀማ የመጨረሻ ፖፕ ይነሳል።
ራዕይ 17፡11 የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
የመጀመሪያዎቹ ሳት ሮማውያን ፈላጭ ቆራጮች የሮማ መንግስትን መሰረቱ። ከዚያ በኋላ ሲተካኩ የቆዩ ፖፕ እንደ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መሩ። የቄሳር ቤተሰብ ፍጥረታዊውን የሮማ መንግስት መራ፤ ይህንን ፍጥረታዊ መንግስት ባርቤሪያውያን ደመሰሱት። ነገር ግን ኋላ ደግሞ የካቶሊክ ጳጳሳት እያንዳንዱ ፖፕ ሙሉ ስልጣን የሚጎናጸፍበትን መንፈሳዊ መንግስት ወይም ቤተክርስቲያን መሰረቱ። ይህች መንፈሳዊ መንግስት፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ባርቤሪያውያን በሮማ መንግስት ላይ ወረራ ሲያደርጉ ሳትጠፋ ቆየች፤ ደግሞም ባርቤሪያውያን ነገዶችን ወደ ካቶሊክ ሐይማኖት ለወጠቻቸው።
ባርቤሪያውያን የሮማ መንግስትን ግዛት ሁሉ ተቆጣጠሩ ነገር ግን የሮማ ቤተክርስቲያን የባርቤሪያውያንን አእምሮ ተቆጣጠረች።
በዚህ መንገድ ፖፑ በባርቤሪያውያን መካከል ከፍ ብሎ ወደ ስልጣን ወጣ።
ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ የቄሳር ቤተሰብ አባላት እና ስልጣን ቀምቶ የያዘው ጋልባ አስቀድመው የቀየሱትን የአሰራር መንገድ ነው የካቶሊክ ፖፕ የሆኑት ጳጳሳት ሆሉ የተከተሉት።
“ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው፤ ከሰባቱም አንዱ ነው።”
“ራሱ” የተባለው ይህ ፖፑን ይወክላል፤ ምክንያቱም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋናው ራስ ፖፑ ነው። የካቶሊክ ፖፕ ስልጣን በምዕራቡ ዓለም መንግስታት የስልጣን ሽግግር ውስጥ ሳይቋረጥ በመቆየት ከሁሉም አንደኛ ረጅም ሽግግር ነው። ፖፑ እስካሁንም ድረስ የሮማ መንግስት በሚመራበት ዓይነት የአንድ ሰው አምባ ገነን አገዛዛ መሰረት ይገዛል። ፕሮቴስታንት ፓስተሮችም ይህንኑ አምባ ገነናዊ አሰራር ኮርጀው ተጠቅመውበታል፤ ስለዚህ በእነርሱም ዘንድ አንድ ፓስተር እንደ ቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ይገዛል።
የቄሳሮቹ አረማዊ የሮማ መንግስት ሲፈራርስ ከዚያ ቀጥሎ ቄሳሮቹ ሲጠቀሙበት የነረውም የጭካኔ ኃይል ይዞ የተነሳው የካቶሊክ ፖፕ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰባት የሙላት ወይም የፍጻሜ ቁጥር ነው። አንድ ሳምንት በሰባት ቀናት ይጠናቀቃል። እግዚአብሔር ምድርን በውሃ ካጠፋ በኋላ ከምድር ጋር ቃል ኪዳን ያደረገበት ምልክት ቀስተ ደመና በሰባት ደማቅ ቀለሞች ይገለጣል። ስለዚህ 8 የአዲስ ስርዓት ጅማሬ ነው። አረማውያኑ የሮማ መንግስት ገዥዎች ወይም ቄሳሮች መንፈሳዊ በሆኑን በሮማ ፖፕ ተተክተዋል። ዳንኤል በራዕይ ያየው የአሕዛብ ምስል ውስጥ ያሉት የሮማ መንግስትን የሚወክሉት የብረት እግሮች በእግሮቹ ጣቶች አካባቢ የሮማ ካቶሊክን ወደሚወክሉት የብረት ስብርባሪዎች ተለወጡ። ሰዎችን በጭካኔ እና በጉልበት ይገዛ የነበረው አረማዊው የሮማ መንግስት ተንኮታኩቶ ወደቀ፤ ነገር ግን ወዲያው የሰዎችን አእምሮ በተቆጣጠረችው መንፈሳዊ በሆነችው በሮማ ቤተክርስቲያን እና በቤተክርስቲያኒቷ ፖፕ ተተካ።
የአሕዛብ ምስሉ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
በብሉይ ኪዳን ዘመን መዳን ለአይሁዶች ነበር። አሕዛብ መዳን ከፈለጉ ወደ ይሁዲነት መለወጥ ነበረባቸው። በቀራንዮ መስቀል መዳን 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ወደሚወክሉት እግሮች ለመግባተ ወደ አሕዛብ “ተሻገረ”።
የመጀመሪያዎቹ ሰባቱ የሮማ መንግስት መሪዎች ከአንድ ቤተሰብ የመጡ ሰዎች ነበሩ። ዩልየስ ቄሳር እራሱን ገዥ ብሎ አያውቅም ነበር፤ የእርሱ ተተኪ አውግስጦስ ግን ራሱን ገዥ አለ። ፖፑ መነሻው “ከሰባቱ” አረማውያን መሪዎች ነው። ፖፑ ባህርዩ ከሰባቱ የሮማ መንግስት መሪዎች ጋር አንድ ዓይነት ነው።
ልክ እንደ ቄሳሮች ፖፑ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስልጣንን ሙሉ በሙሉ በራሱ እጅ አድርጓል። የመጀመሪያዎቹ ጳጳሶች ራሳቸውን ፖፕ ብለው አልጠሩም። ፖፕ የሚለውን ማዕረግ መጠቀም የጀመሩት በ400 ዓ.ም አካባቢ ነው። ቤተክርስቲያን በሰው አገዛዝ ስር ወደቀች። ልክ እንደ ቄሳሮቹ ጳጳሶቹም ፖንቲፍ ወይም የባቢሎናውያን ሚስጥር ሊቀካሕነት ተብለው መጠራት ጀመሩ። የባቢሎን ሚስጥራት ፖንቲፍ እንደመሆናቸውም የተወሰኑ አረማዊ አስተምሕሮዎችን እና ስርዓቶችን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ አስገብተዋል፤ እነዚህኑ አረማዊ አስተምሕሮዎችና ስርዓቶች የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ከካቶሊክ ተቀብለው ቀጠሉ። ከመጀመሪያዎቹ ሰባት የሮማ መንግስት መሪዎች ብቃት የነበራቸው ቄሳር እና አውግስጦስ ብቻ ነበሩ። ልክ እንደዚሁ እስከ አሁን ከኖሩት 260 ፖፕ መካከል እንደ ግሪጎሪ ቀዳማዊ የመሳሰሉ ብቃት ያላቸው ፖፕ ይኖራሉ፤ ነገር ግን በየመሃሉ ልክ እንደ ጢባርዮስ፣ ካሊጉላ፣ እና ኔሮ ብቃትም ስነ ምግባርም የሌላቸው ሰዎችም የፖፕ ስልጣን ይዘው ነበር።
ከቄሳር ቤተሰቦች አምስት አባላት በምድር ላይ ከነበሩ ዓለም አቀፍ መንግስታት ሁሉ ሕዝቦችን በመጨቆንና ባሪያ በማድረግ ትልቁን ግዛት ይዞ በነበረው የሮማ መንግስት ውስጥ ከነገሱ በኋላ ሞተው ነበር (“አምስቱ ወድቀዋል”)።
ዮሐንስ ይህንን ራዕይ ባየበት ወቅት የሮማ መንግስት ግዛት ላይ ነግሶ የነበረው ሰው ኔሮ ነበር (“አንዱም አለ”)። ኔሮ ከሮማ ነገስታት ሁሉ በጭካኔው እና በምግባረ ብልሹነቱ አንደኛ ነበር። እራሱን መለኮት እንደሆነ አድርጎ ይቆጥር ስለነበረ “አምላክ” ብለው እንዲተሩት ያስገድድ ነበር። የሮም ከተማን በእሳት አቃጠለና ክርስቲያኖች ናቸው ያቃጠሉት አለ። ክርስቲያኖችን መግደል ጀመረ፤ የካቶሊክ ፖፕም ይህንኑ የነፍሰ ገዳይነት መንፈስ ተከተሉ። በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ተገድለዋል።
እነዚህ የመጀመሪያዎቹ የቄሳር ቤተሰብ ስድስት አባላት ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መነሳት መሰረት የሆነውን መመሪያ አበጁ። ከሁሉ በላይ የሆነው ሰው ማለትም የሮም ጳጳስ እንደ ፍጹም አምባ ገነን መሪ መምራት አለበት። እርሱ ስለማይሳሳት ሁሉም ሊታዘዙት ይገባል ተባለ። ስለዚህ እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በቄስ መመራት አለባት፤ ቄሱ ደግሞ ለፖፑ ታዛዥ መሆን አለበት።
ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ለመገንባት መሰረቱ የሰው አመራር ነው።
ፖፑ ያለ ልክ ከፍ ከፍ ከማለቱ የተነሳ አስተምሕሮ ላይ ንግግር ካደረገ የእርሱ ድምጽ የእግዚአብሔር ድምጽ ተደርጎ ይቆጠራል። በ1870 ዓ.ም ፖፑ ፍጹም የማይሳሳት ሰው ነው ተብሎ ታወጀ። ፖፑ በምድር ላይ በእግዚአብሔር ምትክ ነው። ቪካር ኦቭ ክራይስት (“በክርስቶስ ምትክ”) ብለው ይጠሩታል። ልክ ባሮች ጌቶቻቸውን እንደሚታዘዙ ሕዝቡ ፖፑን መታዘዝ አለባቸው።
በጣም የሚያሳዝነው ነገር የሜሴጅ ቡድኖችም ይህንኑ ዓይነት መንፈስ እየተከተሉ ናቸው። የሜሴጅ ቡድኖች ዊልያም ብራንሐም አይሳሳትም፣ እርሱ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ይላሉ። ይህም የካቶሊክን መንፈስ መከተል ነው እንጂ አዲስ ነገር አይደለም።
በነጭ ፈረስ ላይ የሚጋልበው ሐይማኖተኛ አሳች ሲያሸንፍና ድል ሲነሳ ይታያል። እርሱም በሜሴጅ ቡድኖች መካከል ይህንን ትንቢት በማስፈጸም ላይ ነው። ድል መንሳቱን እንዲያቆም አልተነገረውም። ስለዚህ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችንም አሞኝቷቸዋል፤ ደግሞም እያሞኛቸው ይቀጥላል።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
ከዚያ በኋላ ኔሮ ክርስቲያኖችን የመግደል የጭካኔ መንፈስን ለቀቀ። ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ተቃዋሚዎችን እየለቀሙ በግፍ መግደል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ለብዙ ዘመናት በልዩ ልዩ ስፍራ ተቃዋሚዎቿን በማጥፋት ስልጣኗን እንድታጠናክር ረድቷታል።
ጋልባ ከንጉሳዊ ቤተሰብ ውጭ የሆነ ስልጣን ተናጣቂ ነበር። ስለዚህ የመጨረሻው ፖፕ ከካርዲናሎች ምክር ቤት አይደለም የሚመጣው። እርሱ የሚመጣው የአስር ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጮችን ድጋፍ በመጠቀም እና የፖፑን ቦታ በኃይል በመቀማት ነው። በዚያ ጊዜ የታላቁ መከራ ጅማሬ ይሆናል።
ስለዚህ ይህ ጥቅስ አዲስ የሮማ ቤተክርስቲያን ስርዓት ከፈራረሰው የሮማ መንግስት ውስጥ ስትበቅል ያሳያል። አረማዊው የሮማ መንግስት ግፍ እና ጭካኔ የክርስቲያን ካባ ለብሶ ስራውን ቀጠለ።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
እነዚህ ዘውድ የጫኑ ነገስታት አይደሉም ምክንያቱም እንደ ነገስታት ኃይል ይቀበላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ በዚህ ዘመን ፈላጭ ቆራጭ ይባላሉ።
ፈላጭ ቆራጭ ማለት እንደ ንጉስ ዓይነት ስልጣን ያለው ነገር ግን ዘውድ ያልጫነ ሰው ነው።
የራሺያ ፕሬዚዳንት ፑቲን ልክ እንዲህ ዓይነት ሰው ነው። መጀመሪያ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ነበር የተመረጠው፤ ነገር ግን በጣም ጠንካራ ሰው ከመሆኑ የተነሳ እርሱን ከስልጣን የሚያስወግደው ብቁ ተፎካካሪ አልተገኘም። ስለዚህ ፑቲን ራሺያ ውስጥ ልክ እንደ ፈለጭ ቆራጭ ሙሉ ስልጣን ያለው ሰው ነው። በ2015 ለፕሬዚዳንትነት ታጭቶ የነበረው ቦሪስ ኔምስቶቭ ከክሬምሊን በጥቂት ሜትር ርቀት ላይ በጥይት ተመቶ ተገደለ። ሒትለር እና እስታሊን ተቃዋሚዎቻቸውን በመግደል የተካኑ ናቸው። በፈላጭ ቆራጭነታቸው የቆዩትም በዚሁ ዘዴ ነው።
ፑቲን በ2000 ዓ.ም ወደ ስልጣን የመጣው NTV የተባለ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ በመጠቀም ተፎካካሪዎቹን ደህና አድርጎ ስማቸውን በማጥፋት አፍረው ከፕሬዚዳንታዊ ውድድር አቋርጠው እንዲወጡ በማድረግ ነው። ወደ ስልጣን ከወጣ በኋላ NTV የተባለውን ተሌቪዥን ጣቢያ ተቆጣጠረውና ስልጣኑን ለማራዘም የእርሱን ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ እና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጭ የመንግስት ተሌቪዥን አደረገው። ራሺያ ዴሞክራሲያዊ ሃገር ነኝ ትላለች፤ እውነታው ግን ብዙዎቹ ፓርቲዎች በክሬምሊን ቁጥጥር ውስጥ መሆናቸው ነው። ምርጫዎችም የሚደረጉት ገዢውን የመንግስት ፓርቲ በስልጣን ለማቆየት ተብለው ነው። ፕሬዚዳንት ፑቲን ለስምንት ዓመት በስልጣን ከቆየ በኋላ ሲወርድ እራሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አደረገና የርሱ ታማኝ ረዳት የነበረውን ሜድቬዴቭን ፕሬዚዳንት አደረገው፤ ከዚያ በኋላ ሜድቬዴቭ ለአራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ቆይቶ ሲወርድ ፕሬዚዳንትነቱን መልሶ ለፑቲን አስረከበው። ይህ በዴሞክራሲያዊነት ውስጥ የተደበቀ ፈላጭ ቆራጭነት ነው። የነፑቲን ግብዝነትና አጭበርባሪነት አውግስጦስ የሮማ መንግስትን ሲመሰርት ያደርግ ከነበረው አጭበርባሪነትና ተንኮል ጋር ተመሳሳይ ነው።
ቻይና ዛሬ ኢኮኖሚያዊ ስርዓቷ ካፒታሊስት ነው፤ የመሪዎቿ አገዛዝ ግን ሰው ሰራሽ በሆነ ረሃብ 77 ሚሊዮን ቻይናውያንን ከገደለው ከማኦ ሴቱንግ ጀምሮ የኮምዩኒስት ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት ነው። የራሺያ ኮምዩኒስት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ሌኒን እና እስታሊን ከራሳቸው ሕዝብ መካከል 35 ሚሊዮን “ብቻ” ገድለዋል።
ኮምዩኒስት ፈላጭ ቆራጮች በመግደል የሚወዳደራቸው የለም።
ወደፊት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ እንደነዚህ ዓይነት አስር ፈላጭ ቆራጮች ይነሳሉ።
ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት። ይህ ከታላቁ መከራ በፊት የተወሰነ አጭር ጊዜ ነው።
የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ የካቶሊክ ካርዲናል አይሆንም። ልክ እንደ ጀነራል ጋልባ ከውጭ ከሌላ ቦታ ይመጣና በታላቁ መከራ ዘመን ከአስር ኃይለኛ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ጋር ስምምነት ይፈራረማል። ታላቁ መከራ ለሶስት ዓመት ከግማሽ ይቆያል።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
እነዚህ አስር ፈላጭ ቆራጮች በአንድነት በመጨረሻ በሚመጣው ታላቅ ፖፕ ስር ይሆኑና ለፖፑ እጅግ ታላቅ የሆነ ወታደራዊ ኃይል ይሰጡታል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖፕ እንደመሆኑ መጠን እርሱም እጅግ ታላቅ ሐይማኖታዊ ስልጣን እና ታላቅ የገንዘብ ኃይል ባለቤት ይሆናል።
በዚህ ላይ ተጨምሮ ደግሞ የተባበሩት የአስሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች የተጣመረ ወታደራዊ ኀይል በእጁ ይሆናል።
ይህ ሁሉ ኃይል ማንም የማያስቆመው መሪ እንዲሆን ያደርገዋል። እንደ ብረት የጠነከረው የሮም ኃይል በዓለም ዙርያ ሁሉ ይለቀቃል።
ራዕይ 17፡14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
የታላቁ መከራ ዘመን ጥፋትና ያልተገደበ ውድመት መጨረሻው የሚሆነው የክርስቶስ ተቃዋሚ የጦር ሰራዊቱን ይዞ ወደ አርማጌዶን ሲሄድ ነው።
እዚያ በደረሰም ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር መሞከሩ ይገባዋል።
ስለ ኃይል ብትጠይቁ ኢየሱስን የሚተካከለው የለም።
በአርማጌዶን ጦርነት ኢየሱስ የክፉዎችን ጉልበት በመደምሰስ ኃይሉን ይገልጣል። ይህ ጦርነት ታላቅ የደም መፋሰስ የሚደረግበት ጦርነት ነው።
የክርስቶስ ሙሽራ ግን በዚያ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር ትሆናለች። እነርሱ በክርስቶስ የተጠሩ እና የተመረጡ ናቸው። ብዙ ክርስቲያኖች የተጠሩ እና የተመረጡ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ነገር ግን ሶስተኛው መስፈርት ከበድ ያለ ነው፤ እርሱም ታማኝነት ነው።
ከክርስቲያኖች መካከል ለእግዚአብሔር ቃል ብቻ ታማኝ የሆነ ማነው? ይህ ታማኝነት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለሚቃረኑ ቤተክርስቲያኖች ታማኝ መሆን አይደለም። ይህ ታማኝነት ኒቆላዊነት ወይም አንድን ሰው፣ አንድን የቤተክርስቲያን መሪን ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ ከሚያደርጉ ጋር መተባበር አይደለም። ሶስት በአንድ ወይም አንድ በሶስት የሚሉ ከግሪክ የመጡ የአረማውያን ፍልስፍና መከተል አይደለም። አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሶስት ማዕረጎች የኢየሱስ ክርስተስን ስም መተካትም አይደለም። ሁሉን ቻይ አምላክ የሆነውን ኢየሱስን በስላሴ መተካትም አይደለም።
እነዚህን ሁሉ መስፈርቶች ብንመለከታቸው ጌታን ለመከተል ታማኝ የሆኑ ክርስቲያኖች ብዙ እንዳልሆኑ እናያለን።
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
እረፍት የሌላቸው፣ ሁሉም የራሳቸውን መብት ማስከበር የሚፈልጉ፣ የአለባበስ እና የስነ ምግባር መርሆችን የሚቃወሙ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የማይቀበሉ ብዙ ሕዝቦች የተመሰሉት ያለማቋረጥ በሚንገላታው የባሕር ሞገድ ነው።
ራዕይ 17፡16 ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።
የክርስቶስ ተቃዋሚው ፖፕ ዙፋኑን በእግዚአብሔር ከተማ በኢየሩሳሌም በማድረግ እግዚአብሔርን ለመኮረጅ ይሞክራል። ስለዚህ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባትና ከተማይቱን ለመያዝ የሚበቃ ኃይል ለማግኘት የሮማ ቤተክርስቲያንን ኃይል ይጠቀማል። ይህንን ዓላማውን ለማስፈጸም የቫቲካንን ኃይል ከተጠቀመ በኋላ ረዳቶቹ የሆኑት ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት ቫቲካን ላይ አቶሚክ ቦምብ እንዲጥሉ ይልካቸዋል። ሰይጣን አሰራሩ እንዲህ ነው። ብታገለግሉት በደስታ ይጠቀምባችኋል። አገልግላችሁት ስትጨርሱ እንደ ቆሻሻ ይጥላችኋል። በአብዮቱ የረዱትን ምዕራባውያን ሰዎች ሌኒን ጠቃሚ ደደቦች ይላቸዋል።
ጨካኙ የራሺያ ፈላጭ ቆራጭ መሪ እስታሊን ሁልጊዜ ተቃዋሚዎቹን የሚገድሉለት ፈቃደኛ ነፍሰ ገዳዮች ነበሩት። ከዚያ በኋላ የገደሉለት ሰዎች ኋላ እንዳያጋልጡት እነርሱኑ ይገድላቸዋል። እነዚህ ፈቃደኛ ገዳዮች ምንም አልገባቸውም። ሲልካቸው ሄደው ይገድላሉ፤ ቀጥሎ ራሳቸው ይገደላሉ። ሰይጣን መልካምነት የለውም። የተቻላችሁን ያህል ከሰይጣን ራቁ።
ራዕይ 17፡17 እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አግብቶአልና።
እግዚአብሔር ጠላቶቹን እንኳ ሳይቀር ይቆጣጠራል። እነዚህ ክፉ አምባገነን መሪዎች ማድረግ ያለባቸውን ግፍ እና ውድመት እስከሚያደርጉ ድረስ አንድነታቸውን ጠብቀው ይቆያሉ። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በየቦታቸው ያስቀምጣቸዋል። የእግዚአብሔር ጠላቶች እንኳ በስተመጨረሻ ፍጹም ግራ ይጋቡ ዘንድ ሲያደርጉት የነበረው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የፈለገውን እንደሆነ በስተመጨረሻ ያውቃሉ።
ሒትለር አውሮፓ ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ 9 ሚሊዮን አይሁዶች መካከል 6 ሚሊዮኑን በጅምላ ጭፍጨፋ ካምፖቹ ውስጥ ጨፍጭፎ ጨረሰ። ሒትለር አይሁዶችን ፈጽሞ ለማጥፋት ሙከራ አደረገ። ነገር ግን የዓለም ሃገራት ሁሉ በዚህ ጭፍጨፋ እጅግ ከመደናገጣቸው የተነሳ ለጥቂት ጊዜ ለአይሁዶች አዝነው በተባበሩት መንግስታት አማካኝነት አይሁዶች ፓለስታይን ውስጥ ለራሳቸው ሃገር የሚሆን ሶስት ትንንሽ መሬት እንዲሰጣቸው ውሳኔ አስተላለፉ። የቀረውን የፓለስታይን ምድር አረቦች እንዲይዙ ተደረገ። ለዚህ ውሳኔ ድምጽ በተሰጠ ጊዜ የሚቃወሙ ድምጾች ቁጥር ከደጋፊዎች ቁጥር ሊበልጥ ጥቂት ብቻ ነበር የቀረው። ውሳኔው በሁለት ድምጾች ልዩነት ለአይሁዶች አመዘነ። ስለዚህ የሒትለር ግፍ አይሁዶች የራሳቸው ሃገር እንዲያገኙ አደረገ።
ከዚያ በኋላ አረቦች በስግብግብነታቸውና ለአይሁዶች ባላቸው ጥላቻ ለአይሁዶች መሬት ተካፍሎ እንዲሰጣቸው የተደረገውን ውሳኔ ተቃወሙ። አረቦቹ አይሁዶች ፓለስታይን ውስጥ አንዳችም መሬት እንዲኖራቸው አልፈለጉም። አረቦች አምስት የጦር ሰራዊቶችን ሰብስበው አይሁዶችን የተባበሩት መንግስታት ከሰጡዋቸው ሶስት ትንንሽ ግዛቶች ላይ ሊያጠፉዋቸው ተነሱ። በዚህም መንገድ አረቦች አይሁዶችን በሙሉ በመግደል ፓለስታይንን በሙሉ ለራሳቸው ሊይዙ አሰቡ። የአረብ ጎልያዶች ከብዙ ሰራዊቶቻቸው ጋር ተሰልፈው ጥቃት ሰነዘሩ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ተዓምር የአይሁዶቹ ታናሽ ልጅ ዳዊት አሸነፋቸው፤ አይሁዶች በዚህ ጦርነት ማሸነፉቸውን ተከትለው የተባበሩት መንግስታት ከሰጡዋቸው በጣም የሚበልጥ ግዛት መያዝ ቻሉ። በ1967 አረቦች እንደገና ጦርነት ሊከፍቱ ዛቱ። እስራኤል አስቀድማ ጥቃት ሰነዘረችና በ6 ቀናት ውስጥ አረቦችን ጠራርጋ አስወጣች። በዚህም ድል አማካኝነት አይሁዶች ኢየሩሳሌምን ሊቆጣጠሩ ችለዋል። ስለዚህ የአረቦች ጥላቻ እና እብሪት ለእስራኤል ተጨማሪ ግዛት እያሰፋላት ነበረ። አረቦቹ ቁጣቸው እነርሱ ያላሰቡትን ውጤት አመጣባቸው።
እስራኤል ግን ስሕተት ሰራች። በ1967 እስራኤሎች የሲና በረሃን ይዘው አንለቅም አሉ፤ የሲና በረሃ በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ከተሰጣቸው ግዛት ውስጥ አልነበረም። በጦርነት ሲያሸንፉ ቸልተኞች ሆኑ። ስለዚህ በ1973 አረቦች ትልቅ ጥቃት አደረሱባቸው። በዚህ ጦርነትም እስራኤል አሸንፋለች ግን ከባድ ጉዳት ደርሶባታል። ከዚያ በኋላ ከግብጽ ጋር ሰላም ለማስፈን የሲና በረሃን ለግብጽ መልሰው አስረከቡ።
ከዚህ ምን እንማራለን? የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተሰጣቸው ገደብ ብቻ መንቀሳቀስ አለባቸው። ከዚህ ገደብ ብትወጡ እግዚአብሔር መልሶ ያስገባችኋል። ማንኛውም መልካም አባት ይህንኑ ማድረጉ አይቀርም። ሲጀመርም እግዚአብሔር ገደቦችን ያስቀመጠበት የራሱ ምክንያት አለው። ገደቦች እና መመሪያዎች የተሰጡን ለእኛ ጥቅም ተብለው ነው።
በ2018 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና ሰጠ። ይህም የትንቢት ፍጻሜ ነው፤ ከዚህ ፍጻሜ የተነሳ አይሁዶች በተስፋይቱ ምድራቸው ውስጥ ሆነው መሲሃቸው ሲመጣ መጠባበቅ ይችላሉ።
በ2020 ከባይደን፣ ሃሪስ እና ፔሎሲ ጋር በመሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አሜሪካን ተቆጣጠረች።
ጆን ኬኔዲ የሚባል ካቶሊካዊ ሰው በ1960 ፕሬዚዳንት ነበረ፤ እርሱም ለቬትናም ጦርነት መቀስቀስ ምክንያት ሆነ። በቬትናም ጦርነት አሜሪካ ያልተጠበቀ ሽንፈትና ውርደት ገጥሟታል፤ ሃገሪቱ ራሷን የገደለችበት ጦርነት ነው። ፍልሚያዎች ላይ ቢያሸንፉም የአሜሪካ ፖለቲከኞች በጦርነቱ ተሸንፈዋል።
አዲሱ ካቶሊካዊ ፕሬዚዳንት የገንዘብ ቀውስ በተፈጠረ ሰዓት ሃገሪቱን ያስተዳድራታልን? አንድ ነገር መደረግ አለበት ምክንያቱም አንድ ቀን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አሜሪካን ትገዛለች፤ ከዚያም አመሪካን ባርነት ውስጥ ታስገባታለች።
ራዕይ 17፡18 ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።
ይህ እንቆቅልሽ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴት ቤተክርስቲያንን ነው የምትወክለው። በዚህ ክፍል ውስጥ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሴቲቱ ከተማ ናት ይላል። እነዚህን ሁለት ሃሳቦች እንዴት ነው የምናስታርቃቸው? ሙሉ በሙሉ በቤተክርስቲያን ከመገዛቷ የተነሳ ስሟ በቤተክርስቲያኒቱ ስም የምትጠራ ከተማ አለች ወይ?
ይህች ከተማ ቫቲካን ናት። ሮም ውስጥ የምትገኘው ቫቲካን ከተማ።ቫቲካን ከተማ ዋና ጽሕፈት ቤቷ ላተራን ቤተመንግስት ውስጥ እና በካኤልያን ኮረብታ ላይ የሚገኘው ባሲልካ (ትልቅ ቤተክርስቲያን) ነው፤ ይህም ከሰባቱ የመጀመሪያ የሮም ኮረብታዎች አንዱ ነው።
ቫቲካን ከተማ በምድር ላይ ካሉ መንግስታት ወይም ሃገሮች ሁሉ ትንሽዋ ናት። ይህች ከተማ ዳንኤል በራዕይ ያያት “ታናሽ ቀንድ” ናት።
ቫቲካን ከተማ ወይም ቤተክርስቲያን መቀመጫዋ በ7ቱ ኮረብታዎች ላይ ነው።
ኮንስታንቲኖፕል እና ኢየሩሳሌም በ7 ተራሮች ላይ የተመሰረቱ ከተሞች ቢሆኑም እንኳ ኮንስታንቲኖፕልም ሊሆን አይችልም ኢየሩሳሌምም ሊሆን አይችልም። የትኛዋ ቤተክርስቲያን ናት ኮንስታንቲኖፕልን የተቆጣጠረችው? “የኮንስታንቲኖፕል” ቤተክርስቲያን የምትባል የለችም። ፖለቲካን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቆጣጠረች ቤተክርስቲያን ኮንስታንቲኖፕል ውስጠ የለችም። የዓለም መንግስታት መሪዎች የቤተክርስቲያን መሪ ለማማከር ወደ ኮንስታንቲኖፕል ወይም ወደ ኢየሩሳሌም አይሄዱም። የትኛዋ ቤተክርስቲያን ናት ኢየሩሳሌምን የተቆጣጠረች? የለችም። ኢየሩሳሌም ውስጥ ብዙ ቤተክርስቲያኖች አሉ። አንዳቸውም ግን ገዥ አይደሉም።
በ2005 ዓ.ም ፖፕ ጆን ፖል ዳግማዊ ሲሞት በቀብሩ ላይ የተሰበሰቡ የዓለም መንግስታት መሪዎች ብዛት የሚያህሉ የመሪዎች ብዛት በየትኛውም ሌላ ዝግጅት ላይ ተገኝተው አያውቁም።
ሮም ይህን ያህል ትልቅ ፖለቲካዊ ተጽእኖ አላት፤ ይህም ዓለም ሁሉ ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካላት አድናቆት የተነሳ ነው።
የሮማ ቤተክርስቲያን ለ2,000 ያህል ሳትጠፋ የቆየችበት ታሪክ አላት፤ የሚገርመው ነገር የሮማ መንግስት እንኳ ፈራርሶ በባርቤሪያውያን ነገዶች መካከል ተከፋፍሎ በጨለማው ዘመን ውስጥ ሲጠፋ የሮማ ቤተክርስቲያን ግን አልጠፋችም። ከዚያ የአውሮፓ ሃገሮች ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ነው ራሳቸውን የቻሉ መንግስታት የሆኑት። ዛሬ ብዙዎቹ የሶስተኛ ዓለም ሃገሮች አውሮፓ እና አሜሪካ የደረሱበት ለመድረስ ይፍጨረጨራሉ። ባለፈው ክፍለ ዘመን ውስጥ ሁለት የዓለም ጦርነቶች እና ቀጥሎ ኮምዩኒስቶች ከምዕራባውያን ጋር ያደረጉት ቀዝቃዛ ጦርነት አልፈዋል። እነዚህ ጦርነቶች ሁሉ ከመነሳታቸው በፊት ማንም ቀድሞ ያወቀ አልነበረም፤ ነገር ግን በነዚህ ጦርነቶች ሁሉ ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሳትጠፋ አልፋለች ተስፋፍታለች። የሮማ ቤተክርስቲያን በጥፋት መካከል ሳትጠፋ በማለፍ ትታወቃለች።
ሳትጠፋ እንድትቆይ ያስቻላት ምንድነው?
ለረጅም ዘመን የሚቆይ መንግስት ለመመስረት የተወሰኑ እንደ አምድ የሚያገለግሉ ቁልፍ ሃሳቦች ያስፈልጋሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተራራ መንግስትን ይወክላል።
ዳንኤል 2፡34 እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ።
35 የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፥ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፥ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ፈጽሞ ሞላ።
44 በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።
ራዕይ 17፡9 ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥
የሰባቱን ተራሮች ትርጉም በጥልቀት ለመረዳት መንፈሳዊ ጥበብ ያስፈልገናል።
ሮም የተገነባችው በሰባት ኮረብታዎች ላይ ነው። ኮረብታዎች ከሆኑ ለምን ተራሮች ይባላሉ?
ይህ ቃል የሚናገረው ከኖህ የጥፋት ውሃ ዘመን ጀምሮ ሰይጣን ሲገነባው የቆየ መንግስትን በተመለከተ ነው። የሰይጣን መንግስት ወደ ሙላቱ የሚደርሰው በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ነው።
ሰይጣን የፖፑን ስልጣን ቀምቶ ለራሱ ይወስደዋል ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፍ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል አንዳንድ መሰረታዊ የሆኑ ባህርያት አሉዋት።
በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ በቤተክርስቲያን የሚተዳደር አንድ ዓለም አቀፍ መንግስት ይመሰረታል።
ይህም መንግስት የሚመሰረተው በሰባት መርሆች ላይ ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚ ከቤተክርስቲያኖች ስድስት አስፈላጊ ነገሮችን ያገኛል፤ ሰባተኛውም ነገር ከአስር አምባ ገነን መሪዎች የሚቀበለው ወታደራዊ ኃይል ነው።
ይህን እቅድ ለማሳካት የክርስቶስ ተቃዋሚ ሰዎች በሐይማኖት በማሳሳት፣ በፖለቲካዊ ተንኮል፣ እና ሰዎችን ስግብግብ በማድረግ በገንዘብ ኃይል ይጠቀማል።
ሐይማኖት የሚከተሉትን ይይዛል-
1 ኒቆላዊነት - እያንዳንዱን ጉባኤ ለመቆጣጠር አንድ ቅዱስ ሰውን ከምዕመናን ወይም ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ። ይህም በስተመጨረሻ የሚያስከትለው ነገር አንድ ቅዱስ ሰውን ልክ እንደ ታላቁ እስክንድር ኃያል ገዥ ይመስል የምድር ሁሉ ፈላጭ ቆራጭ መሪ አድርጎ መቀበል። በፍጹም የማይሳሳት ፖፕ ብቻውን አምባ ገነን ሆኖ በመቀመጥ በቫቲካን አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ማዕከላዊ የሆነ ቁጥጥር ያደርጋል።
2 መዳን በአንድ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ብቻ ነው ብሎ ማስተማር፤ ይህም ትምሕርት ፖፑ የቅዱስ ጴጥሮስ ምትክ ወይም ተተኪ ነው ይላል ምክንያቱም ለአማኝ የመንግስተ ሰማያት በር የሚከፈትበት ቁልፍ በጴጥሮስ እጅ ብቻ ነው ብለው ያምናሉ።
3 ድንግዝግዝ የሞላበት የስላሴያዊ አምላክ ትምሕርት፤ ይህ ትምሕርት በበቂ ሁኔታ ድብዝዝ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ አይነት ትምሕርቶችን ለማስተናገድ ይመቻል ምክንያቱም በእርግጥ እንዲህ ነው ተብሎ ሊነገር የማይችል ስለሆነ። ደግሞም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን እንዲቀበሉ በቂ ምክንያት ይሰጣቸዋል። ስላሴ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ ካልተገኘ ነገር ግን እውነት ነው ብዬ ካመንኩት እንኪያስ ማንኛውንም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ሌላ ትምሕርት የማመን መብት አለኝ። ይህም በቀላሉ ከተጻፈው ቃል ርቄ እንድሄድ ያደርገኛል።
4 ፖለቲካ ዋነኛውን ሚና ይጫወታል። ፖለቲካዊ ተጽእኖ ከብዙ የዓለም መንግስታት መሪዎች ጋር እንደ መረብ ያገናኛል፤ መንግስታትም ሐይማኖትን ይወዳሉ ምክንያቱም ብዙ የገንዘብ ጥቅም እንደሚያገኙበት ያውቃሉ። የእያንዳንዱን መንግስት ፖለቲካዊ ኃይል እና ፖሊሶችን፣ ፍርድ ቤቶችን፣ እስር ቤቶችን እና የጦር ሰራዊቱን በመጠቀም ተቃዋሚዎችን በጭቆና ማፈን እና በግፍ መግደል የፖለቲካ ሚና ነው።
5 ብዙ ገንዘብ። ከዓለም ሁሉ አንደኛ ሃብታም ድርጅት ቫቲካን ናት። ይሁዳን አስታውሱት፤ ይሁዳ ከደቀመዛሙርት መካከል ገንዘብ ያዥ ነበረ።
6 የሮማ ቤተክርስቲያን ገዥዎቿን ትገዛለች። የሮማ መንግስትን ያፈራረሱትን ባርቤሪያውያንን ፖፑ ገዛቸው። ካቶሊኮች ከእነርሱ ተገንጥለው የወጡ ፕሮቴስታንቶችን በስላሴ እንዲያምኑ አደረጓቸው፤ ደግሞም የውሃ ጥምቀትን በሶስት ማዕረጎች እንዲፈጽሙ አሳመኑዋቸው። ኮምዩኒዝም ፖላንድን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ተቆጣጠራት፤ ነገር ግን ፖላንዳዊው ፖፕ ጆን ዳግማዊ ፖላንዶች ከራሺያ መገንጠል እንዲችሉ ረዳቸው።
7 በቀላሉ ሊቃወሙት የማይቻል ሙሉ ወታደራዊ ኃይል እና ገዥነት። ይህ ዓይነቱ ስልጣን የሚገኘው በአስር ጨካኝ አምባ ገነን መሪዎች ድጋፍ ነው።
እነዚህ ሰባት አምዶች ከተደላደሉ በኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚውን መንግስት በዓለም ዙርያ ሁሉ ለማስፋፋት የሚያገለግሉ መሰረቶች ይሆናሉ፤ ከዚያ በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ብዙ ሰዎችን ለመግደል የሚያበቃው የአጭር ጊዜ መንግስት መመስረት ይችላል።