ራዕይ 10 - ለመረዳት ከባድ ምዕራፍ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ከትንሳኤ ቀን እስከ መነጠቅ ድረስ የሚያልፉ 40 ቀኖች አሉ፤ እነዚህም ቀኖች 7 ነጎድጓዶች አካላችንን እንዴት እንደምንለውጥ ለእኛ የሚያሳዩበት ጊዜ ነው።
First published on the 6th of July 2021 — Last updated on the 31st of July 2021ራዕይ ምዕራፍ 10 ለመረዳት በጣም ከባድ የሆነ ምዕራፍ ነው፤ ምክንያቱም ጌታ ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ የሆነችዋን ሙሽራ በአየር ላይ ትቀበለው ዘንድ ሊነጥቃት ከመምጣቱ በፊት ስለሚፈጸሙ ክስተቶች ነው የሚናገረው። ይህም ክስተት ብዙውን ጊዜ መነጠቅ ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ለሰርጉ ግብዣ ወደ ሰማይ ይወሰዳሉ። ከእነርሱ ውጭ ያሉት ቤተክርስቲያን ተመላላሽ ሰዎች ሁሉ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ፤ ይህም መከራ በ200 ማይልስ የደም ወንዝ እና አይሁዶችን የሚጠሉ ሰዎችን እሬሳ በአርማጌዶን ጦርነት መጨረሻ ላይ አሞራዎች እና በዱር አራዊት ሲበሉ ነው የሚጠናቀቀው።
በስተመጨረሻ ምርጫ አለን። ለመብላት ወይም ለመበላት።
የአውሬው ድግስ። (የፖፑን ቦታ ቀምቶ የሚቀመጥበት የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ የአይሁዶችን እስቶክ ገበያ ገንዘብ በእጁ ለማስገባት ብሎ ከእርነሱ ጋር ቃልኪዳን ያደርጋል። እርሱም የ10ሩን ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ኃይል ይጠቀማል።)
በአይሁዶች እና በአሕዛብ መካከል የሚደረገውን የቦታ መለዋወጥ ልብ ባለችሁ ተመልከቱ።
እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር ቃልኪዳኑ እስከ ቀራንዮ ድረስ ነበር። በዚያ ዘመን መዳን ከአረማውያን አሕዛብ መንግስታት ውጭ ነበረ። አሕዛብ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት ከፈለጉ ወደ አይሁዶች እምነት መለወጥ ነበረባቸው። ይህም እውነት በተምሳሌት የተገለጠው ናቡከደነጾር በሕልም ባየው ምስል አማካኝነት ነው።
ከዚያ በመስቀሉ አማካኝነት መዳን ናቡከደነጾር ወዳየው ምስል እግር ውስጥ ተላለፈ። እግዚአብሔርም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አይሁዶችን ተዋቸው።
እግሮቹ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ፤ እነዚህ ዘመናትም የሚጠናቀቁት በእግሮቹ ጣቶች የተወከሉት 10ሩ ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጮች የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ ፖፕ አንዲት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ሊመሰርት ሲነሳ ድጋፍ በሚሰጡበት ጊዜ ነው።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የራሳቸው የሆነ አካሄድ አላቸው። የአዲስ ኪዳን እውነት ዘር በሐዋርያት አማካኝነት ተተክሎ ነበር፤ ነገር ግን እውነቱ ሰዎች ራሳቸውን የቤተክርስቲያን መሪ ባደረጉ ጊዜ ሞተ፤ ከዚያ በጨለማው ዘመን አፈር ውስት ተቀበረ። ከዚያ በኋላ ጀርመኒ ውስጥ በተሃድሶ ዘመን ማርቲን ሉተር ዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው ብሎ ባስተማረ ጊዜ እውነት በቀለና አዲስ ቅጠል አቆጠቆጠ። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ድጋፍ የተተረጎመ መጽሐፍ ቅዱስ ነበረ፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ እንግሊዝ ውስጥ ለጆን ዌስሊ የቅድስና እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንት ከመሆኑ ባሻገር በወንጌል ስርጭት ዘመን በዓለም ዙርያ ሁሉ አገልግሏል። ከዚያ በኋላ በ1906 ዓ.ም አሜሪካ ውስጥ በአዙዛ እስትሪት ሎሳንጀለስ ውስጥ የተጀመረው የጴንጤቆስጤ መነቃቃት ተመልሶ ለሚመጣው ዘር እንደ መከለያ ቅርፊት ሆኖ አገልግሏል።
ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ተነስቶ በመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት አማካኝነት የወንጌሉ ብርሃን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ይሄዳል። ከጨለማው ዘመን በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተሃድሶ ከጀርመኒ ወደ እንግሊዝ ወደ አሜሪካ ተሰራጨ።
ማቴዎስ 24፡27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤
የሰው ልጅ መምጣት። ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ እያየነው ሲገለጥልን። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ወይም ሙሽራይቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት እያገኘች ትሄዳለች። የተሃድሶ መሪዎች ግን ያልተረዷቸው ብዙ ጥልቅ ሚስጥራት ነበሩ። ዛሬም ቢሆን ብዙዎች ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ለመረዳት ከባድ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ምንም ጥቅም የሌላቸው ዝርዝሮች ናቸው፤ በስሕተት የገቡ ናቸው፣ ወይም የአተረጓጎም ስሕተቶች ናቸው ይላሉ፤ እንዲህ የሚሉት መሃይምነታቸውን ለማስተባበል ነው።
ስለዚህ ከአሜሪካ ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መገለጥ መቀበል አለብን፤ በዚህም መገለጥ አማካኝነት ወደ አዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ሐዋርያት እምነት መመለስ እንችላለን።
መከር የሚሆነው ዘር ከተክል ላይ ተቀጥፎ በሚወሰድበት ጊዜ ነው፤ ይህም ሙሽራይቱ በንትቀት ሰዓት ከምድር ወደ ሰማይ የመወሰዷ ምሳሌ ነው። ይህ የሚሆነው በስተመጨረሻ የሚታጨደው ዘር በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በሐዋርያት ከተዘራው ዘር ጋር በሚመሳሰልበት ጊዜ ነው።
የመጀመሪያው እና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን አንድ ዓይነት መሆን አለባቸው። ለዚህ ነው ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል የመጀመሪያ እና የመጨረሻ የሆነው። የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያኖች ብቻ ናቸው በጣም ጥልቅ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት የሚያገኙት።
ራዕይ 1፡8 አልፋ እና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ይህንን ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የምናገኛው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን ሚስጥራትን ሲገልጥ ብቻ ነው መረዳት የምንችለው።
ዳንኤል 12፡8 ሰማሁም ነገር ግን አላስተዋልሁም፤ የዚያን ጊዜም፦ ጌታዬ ሆይ፥ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድር ነው? አልሁ።
9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤
ስለዚህ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ይገልጥልን ዘንድ እግዚአብሔር መልአክ ወይም መልእክተኛ ሊልክልን ይገባል።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ሰባተኛው መልአክ ወይም መልእክተኛው የሚመጣው በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው።
የዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል ነገር ግን የሚፈጸመው ሙሽራይቱ የሰባተኛውን መልአክ መገለጦች ሰምታ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መሰረት እየመረመረች ከተቀበለች ብቻ ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
በዚህ በዘመን መጨረሻ በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችሁ ማረጋገጫ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መረዳት መቻላችሁ ነው።
አይሁድ እና አሕዛብ ታሪኮቻቸው ከ7 እና ከ12 ቁጥር ጋር የተሳሰሩ ናቸው።
ማቴዎስ ምዕራፍ 14 ውስጥ ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ ቋጥሮ በያዘው እንጀራ እና ዓሳ 5,000 አይሁዶችን አበላ። ኢየሱስ ከመስቀሉ በፊት ካደረጋቸው ተዓምራት መካከል በአራቱም ወንጌሎች ውስጥ የተጻፈው ተዓምር ይህ ብቻ ነው።
ስለዚህ ለየት ያለ ዓላማ ይኖረዋል። ኢየሱስ እራሱ ሕዝቡ አንበላም ብለው ከጣሉት ቁርስራሾች የተሰበሰቡ መሶቦች ቁጥር ላይ ትኩረት አድርጓል። እንጀራው ውስጥ ያለው እርሾ የሰዱቃውያንን እና የፈሪሳውያንን የተሳሳተ ትምሕርት ይወክላል።
ማቴዎስ 16፡9 ገና አታስተውሉምን? ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
ቁርስራሽ 12 መሶብ ተሰበሰበ። 12 ሁለት ቁጥር ትርጉሙ ምንድነው?
አይሁዶች በሉና ከዚያ በኋላ አያስፈልገንም ብለው ያሰቡትን እንጀራ ጣሉት።
ይህም በቀራንዮ መስቀል አንቀበልም ብለው የገፉትን ወንጌል ይወክላል፤ ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ከሚባሉ ሐሰተኛ መምሕሮቻቸው የተነሳ ወንጌሉን አንቀበልም አሉ።
ሕዝቡ አንቀበልም ያሉትን ወንጌል በሙሉ ደቀመዛሙርት ሰብስበው ለሰባቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ጻፏቸው። በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር እንደሆነ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አልቀበልም ብላ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመጠመቅ እምቢ ትላለች። ስም የሌለውን ስላሴያዊ አምላክ ያመልካሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር ባይጠይቀንም እንኳ አሕዛብ ያመልኩት የነበረ የፀሃይ አምላክ በተወለደበት ቀን ክሪስማስን ያከብራሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጡትን ሚስጥራት አልቀበልም በማለት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልማዳቸውን እያደረጉ በመቀጠል የቤተክርስቲያን ሰዎች ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ አላውቃችሁም እንዲላቸው ያደርጋሉ። ከዚያም ታላቁ መከራ ሲጀምር ቤተክርስቲያን አልቀበልም ያለችው ወንጌል በሙሴ እና በኤልያስ ማለትም በአይሁድ ነብያት አማካኝነት ወደ አይሁድ ይሄዳል።
ኢየሱስ ይህንን ተዓምር ማቴዎስ ምዕራፍ 15 ውስጥ በድጋሚ አድርጎታል። በዚህ ጊዜ 4,000 ሰዎችን ካበላ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ሰዎች አንበላም ብለው የተዉትን ቁርስራሽ 7 መሶብ ሰበሰቡ።
ማቴዎስ 16፡9 ገና አታስተውሉምን? ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?
ኢየሱስ 7 እንጀራዎችን ተጠቅሞ 4,000 ሰዎችን አበላ። ደቀመዛሙርቱም ሰዎቹ አንበላም ብለው የተዉትን ቁርስራሽ እንጀራ 7 መሶብ ሰበሰቡ።
ይህም በኢየሱስ አገልግሎት ወቅት አይሁዳውያን አንቀበልም ብለው የተዉአቸው አስተምሕሮዎች በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት ተሰብስበው በአዲስ ኪዳን እንደተጻፉ ያመለክታል፤ ከዚያም ለአሕዛብ ምግብ ሆነው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቀርበዋል።
ይህም አካሄድ ግልጽ ነው። በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ወንጌሉ ወደ አሕዛብ ይሄዳል። በ7ኛው ዘመን መጨረሻ ላይ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ተነጥቃ ስትሄድ ወንጌሉ እንደገና በታላቁ መከራ ዘመን 144,000ውን አይሁዶች ለመጥራት ተመልሶ ወደ እስራኤል ይሄዳል።
ይህ ሚስጥር በቤተመቅደሱ የአምልኮ ስርዓት ውስጥ ተሰውሮ ተቀምጧል።
ቅድስት ቦታ ውስጥ ባለ 7 መብራት መቅረዝ ነበረ (የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ብርሃን) እና ድንኳኑ ውስጥ የሚበላው 12 እንጀራዎች ያሉት የገጹ ሕብስት። ለዚህ ነው አይሁዶች፣ 12 የእስራኤል ነገዶች ወደ እስራኤል እየተመለሱ ያሉት፤ በዚያም መሲሁ ወደ እነርሱ ይመለሳል።
ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሷም አካሉ ናት። እርሱ ብቻ ነው አካሉን ሊያድን የሚችለው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።
የሰው ራስ ከአካሉ ጋር በጀርባ አጥንት አማካኝነት ይጋጠማል።
ክርስቲያኖች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መቆም እንዲችሉ የጀርባ አጥንት ያስፈልጋቸዋል።
የመጀመሪያዎቹ 7 አጥንቶች አንገትን ይደግፋሉ። ቀጣዮቹ 12 አጥንቶች ደግሞ ጎድኖችን ይደግፋሉ።
7 እና 12 ቁጥሮች በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ልዩ ስፍራ አላቸው።
ኢየሱስ በ29 ዓ.ም አካባቢ የ30 ዓመት ሰው ከነበረበት ጊዜ አንስቶ የ7 ዓመታት አገልግሎት ሊያገለግል ነበር የመጣው። ከዚያም በኋላ በምድር ላይ አይሁዶች ዓለምን ሁሉ የሚመሩበትን የ1,000 ዓመታት የሰላም መንግስት ሊመሰርት ነበር ሃሳቡ።
ነገር ግን አይሁዶች በሮማውያን ላይ በነበረባቸው ፖለቲካዊ ጥላቻ ታውረው፤ እንዲሁም በሕዝቡ ላይ የነበራቸውን ስልጣን ላለማጣት እና የገቢ ምንጭ የሆናቸውን ስራ ላለመልቀቅ ብለው መሲሁን ከመጥላታቸው የተነሳ የ3½ ዓመት አገልግሎት ካገለገለ በኋላ በ33 ዓ.ም ኢየሱስን ገደሉት። ከዚያ በኋላ 7 የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት ጣልቃ ገቡ፤ እግዚአብሔር ግን ከንጥቀት በኋላ ወደ አይሁዶች ይመለሳል።
መሲሁ የተገደለው በ33 ዓ.ም ነው። ከዚያም ሃምሳ ቀናት እንዳለፉ በጴንጤ ቆስጤ ዕለት የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ለማስጀመር መንፈስ ቅዱስ መጣ።
ሰባተኛውና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚጠናቀቀው መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ትቀበለው ዘንድ ሲነጥቃት ነው።
ከዚያም ቀጥሎ ታላቁ መከራ ይጀምራል።
በታላቁ መከራ ውስጥ በሚያልፈው የሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ 144,000ዎቹን አይሁድ ወደ መሲሁ ይመልሱዋቸዋል።
ስለዚህ ከባድ የሚሆነው ጊዜ የሚመጣው ልክ ከመነጠቅ በፊት ባለው ጊዜ ነው።
ሙሽራይቱ ወይም የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን አካላት የሚሞት ስጋቸውን ወደ ማይሞተው አካል ለመለወጥ በጣም ብዙ መለኮታዊ ኃይል ያስፈልጋቸዋል። ይህም ኃይል ከጊዜ እና ከምናውቀው ባለ ሶስት ዳይሜንሽን ዓለም ወጥተው ወደ ዘላለማዊነት በመግባት መነጠቅ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ጊዜ እርጅና፣ መበስበስ፣ እና ሞትን ያስከትላል። ከወሲባዊ ግንኙነት ስለተወለድን ሁላችንም እምብርት አለን፤ ይህም ለሞት የሚዳርገን በሰውነታችን ላይ ያለ የአውሬው ምልክት ነው። አዲሱ የማይሞተው አካላችን ላይ እምብርት አይኖርም ደምም አይኖረንም ምክንያቱም ደም እና ስጋ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም። በሰዎች የደም ስር ውስጥ የሚዘዋወረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።
ከሟችነት ወደ አለመሞት ለመለወጥ ሶስት መሳሪያዎች ያስፈልጋሉ፤ እነዚህም “ጩኸት፣ ድምጽ፣ እና መለከት” ናቸው።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
“ድምጹ” የሚመጣው የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ሙሽራ አካላት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ሲያውቁ እና ለየግላቸው እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ እውነተኛ መሆኑን ማሳየት ሲችሉ ነው። የመጀመሪያው ዝናብ ወይም የትምሕርት ዝናብ እስካሁንም እየዘነበ ነው፤ ምክንያቱም እውነተኞቹ አማኞች እምነታቸውን በበቂ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፤ ከዚህም የተነሳ እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የማሳየት ብቃት ያገኛሉ። እያንዳንዱ አማኝ እምነቱን በራሱ በየግሉ መርምሮ ማረጋገጥ መቻል አለበት።
የመላእክት አለቃ ድምጽ የሚመጣው ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ የሞቱትን ቅዱሳን ከሙታን ለማስነሳት። ይህም ሞተው የነበሩ ቅዱሳን ይዟቸው ከቆየው መቃብር ውስጥ ተጎትተው የሚወጡበት የትንሳኤው መጀመሪያ ነው። መከር ፍሬውን ከተክል ላይ ጎትተን የምንቀጥፍበት ጊዜ ነው።
የእግዚአብሔር መለከት ድምጹ የሚሰማው በሕይወት ያሉትን ቅዱሳን ሁሉ ከሙታን ከተነሱት ቅዱሳን ጋር በአንድነት ጌታን በአየር ላይ እንዲቀበሉ ለመሰብሰብ ነው። ይህም የመከሩ ማብቂያ ይሆናል። ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ በታላቁ መከራ ውስጥ ወደ አይሁዶች ዘወር ይላል።
“በክርስቶስ ሆነው ያንቀላፉት መጀመሪያ ይነሳሉ።”
ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን መነሳት ለመነጠቅ የቀሩትን የመጨረሻ ጊዜያት መቁጠር የሚጀመርበት ወሳኝ ክስተት ነው።
ይህ ትንሳኤ አስቀድሞ የሚሆን ወሳኝ ክስተት ነው።
በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተገለጸው ወሳኝ ክስተት ይህ ትንሳኤ ነው።
ከዚህ ምዕራፍ በትንሳኤው ጊዜ ምን እንደሚከሰት ጥቂት ፍንጮች እናገኛለን።
ከአእምሮ በላይ የሆነ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ይገለጣል።
ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተውጣጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ከሙታን ይነሳሉ።
ይህም ትንሳኤ ልክ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ከተከሰተው የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ጋር ተመሳሳይ ነው የሚሆነው።
ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ማለት ከሙታን በሚነሱበት ሰዓት በምድር ላይ በሕይወት ለሚኖሩ ሰዎች ተገልጠው ይታያሉ ማለት ነው። እንዴት ልናውቃቸው እንችላለን?
ዮሐንስ 20፡19 ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።
አደጋ ተፈርቶ በር በተዘጋበት ክፍል ውስጥ በር ሳይከፈት ገብተው ውስጥ መገኘት ይችላሉ።
ይህም ከዚህ ምድራዊ ዳይሜንሽን ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላሉ ማለት ነው። በዚያ የትንሳኤ አካል ሆነው በሰማይ ውስጥም መኖር ይችላሉ ምክንያቱም ሰማይ ከፍ ያለ ዓለም ነው።
ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ መንቀሳቀሱ ኢየሱስ በግድግዳ ውስጥ አልፎ ወደ ክፍል ውስጥ የገባ እንዲመስል አድርጎታል።
በተመሳሳይ መንገድ መልአኩ ገብርኤልም ማርያም በምትኖርበት ቤት ግድግዳ ወይም በጣራው ውስጥ አልፎ የሄደ ይመስላል፤ ልክ ግድግዳው ወይም ጣራው በቦታቸው የሌሉ ይመስል። ስለዚህ ገብርኤል ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ በክፍል ውስጥ ተገኝቶ ስለ ኢየሱስ መወለድ ለማርያም ነገራት።
ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ መንቀሳቀስ ልክ በሃሳብ ከመሄድ ጋር ይመሳሰላል። አሁን እዚህ ሆናችሁ ከመቅስፈት ደግሞ ሌላ ቦታ ናችሁ።
በሚሌኒየሙ ወይም በ1,000 ዓመቱ የሰላም መንግስት ውስጥ ሙሽራይቱ ሊኖራት የሚገባ አካል ይህ ዓይነት አካል ነው። አንድ ቦታ ሄዳችሁ አንድ ሰው እየጎበኛችሁ ሳለ ደስ ሲላችሁ ከዚያ ቦታ ትሰወሩና በዓይን ጥቅሻ ጊዜ ውስጥ በምድር ላይ ሌላ ቦታ ትገለጣላችሁ።
ኢየሱስ ያለ ምንም ትግል በቀላሉ ከምድር ተነስቶ ወደ ሰማይ በሄደ ጊዜ እኛ “የመሬት ስበት” ከምንለውና ሁሉን ነገር ወደ ታች ይስባል ከምንለው ኃይል በላይ መሆኑን እና አስደናቂ ኃይል እንዳለው አሳይቶናል።
ኢየሱስ በውሃ ላይ የተራመደው በተጨማሪ ከስፍራ ጽንሰ ሃሳብም ውጭ መሆኑን ለማሳየት ነው።
በዚህች ዓለም ውስጥ ሆኖ ነገር ግን ከዚህች ዓለም ያለመሆን ሁለተኛው ምሳሌ ኃይለኛ ማዕበል በነበረበት የገሊላ ባሕር ላይ በእግር መራመድ ነው (ኢየሱስ ይህንን ያደረገው ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ ሆኖ ነው)። የመሬት ስበት የምንለው ኃይል በመኖሩ የተነሳ እና ወደ ውሃው ውስጥ ስቦን ስለሚያሰምጠን ሰው ውሃ ላይ መራመድ አይችልም።
ለዚህ ነው ሉቃስ ኢየሱስን በሰው መልክ እየገለጠ በጻፈበት ወንጌል ውስጥ ውሃ ላይ መራመዱን ያልጠቀሰው። ውሃ ላይ ከተራመደ እንዴት ሰው መሆን ይችላል? ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ ከተመላለሰ እንዴት ሰው ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ እንዴት አድርጎ በውሃው ላይ እንደተራመደ ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማብራራት አይቻልም፤ ሉቃስም ሳይዘግበው የተወው ለዚህ ነው።
እኛ ከምንኖርባቸው የተፈጥሮ ሕጎች በላይ በመንቀሳቀስ ኢየሱስ እርሱ የሚመላለስበት ዳይሜንሽን የተለየ መሆኑን አሳይቶናል፤ ምክንያቱም እኛ ሁላችን ለመሬት ስበት ተገዥዎች ነን። ያለ አውሮፕላን፣ ያለ ሮኬት ወይም ያለ ትልቅ ባሉን የመሬት ስበትን ኃይል ማምለት አንችልም።
ከዚህም ሌላ ደግሞ ውስብስብ ነገር አለ። ጠቢቡ ሳይንቲስታችን አልበር አይንሽታይን ጊዜ እና ስፍራ ተቀላቅለው የጊዜ እና የስፍራ ውሁድ እንደሚፈጥሩ አስተምሮናል። (የጊዜና የስፍራ ውህደት ምን እንደሚመስል ማሰብም አንችልም፤ ምክንያቱም የሚታይ ነገር አይደለም)። ብቻ መሰረታዊ ትርጉሙን ስናየው ስፍራ ከጠፋ ጊዜም ይጠፋል። በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ስፍራ እና ጊዜ ያስፈልገናል። አንዱን ያለ ሌላው መጠቀም አንችልም።
ፍጥረታዊ ልደት ማለት እያንዳንዱ ሰው በስፍራ ውስጥ የሚመላለስበት አካል ይቀበላል ማለት ነው፤ ከዚህም የተነሳ ጊዜ ለሚያመጣበት ለውጥ ሁሉ ተገዥ ይሆናል። በአካል ታድጋላችሁ፤ ለጥቂት ጊዜ ብርቱዎች ትሆናላችሁ፤ ከዚያም አርጅታችሁ ትሞታላችሁ።
የእምብርት ጠባሳ ከእናታችሁ ጋር የተገናኛችሁበት ገመድ ነው፤ እናታችሁ ደግሞ ከእናትዋ ጋር የተገናኘችበት እምብርት አላት፤ ይህም ወደ ኋላ የሕያዋን ሁሉ እናት እስከሆነችው እስከ ሔዋን ይደርሳል። ይህም እግዚአብሔር እንዲሁ ይሁን ብሎ የፈቀደው ነገር ነው።
የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ሔዋን በድንግልና ወንድ ልጅ እንድትወልድ፤ እርሱም ሲያድግ የሚሞትለት ሐጥያት ስለማይኖር ቅዱሳኑን ከምድር አፈር ጠርቶ እንዲያመጣቸው ነበር።
በስተመጨረሻ በትንሳኤ ቀን ኢየሱስ ቅዱሳኑን ከምድር አፈር ውስቶ ጠርቶ ያስወጣቸዋል።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
ሔዋን በሰው እና በጦጣ መካከል ከፍተኛ አጥቢ እንስሳ ከሆነው ከእባቡ በማርገዟ ተቀጣች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እባቡ ተረገመና እግር እንዳይኖረው በደረቱ እንዲሳብ ተደረገ።
ስላረገዘች ከዚያ ወዲያ ማሕጸኗ ድንግል አልነበረም።
እግዚአብሔር ሔዋንን ከባሏ ከአዳም ስለ ጸነሰች ብሎ አይቀጣትም።
ዘፍጥረት 3፡20 አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።
ይህ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃዱ ሳይሆን የይሁንታ ፈቃዱ ነው፤ ሰዎችም በዚህ መንገድ በግብረ ስጋ ግንኙነት አማካኝነት ይወለዳሉ።
አዳም የሕያዋን ሁሉ አባት ተብሎ አያውቅም።
የእባቡ ዘር የወንድ የዘር ፈሳሽ ወይም እስፐርም ነው። የእስፐርም ሴል እባብ ይመስላል።
ደግሞም ከአይንሽታይን የስፍራ እና ጊዜ ጽንሰ ሃሳብ ጋር ሙሉ በሙሉ ይገጥም ዘንድ ኢየሱስ ከስፍራ ጽንሰ ሃሳብ ውጭ መንቀሳቀሱን ሊያሳየን ከፈለገ ከጊዜ ጽንሰ ሃሳብም ውጭ ነበር ማለት ነው።
በጊዜ ላይ ስልጣን ካላችሁ ከመቅስፈት የምትፈልጉበት ቦታ መድረስ ትችላላችሁ። ካልፈለጋችሁ ረጅም መንገድ በመሄድ ጊዜ አለመፍጀት ትችላላችሁ። ከጊዜ ክልል ውጭ ከተንቀሳቀሳችሁ ጊዜ የሚባል ነገር በእናንተ ላይ አይሰራም።
ውሃ ላይ መራመዱ የእኛ የስፍራ ጽንሰ ሃሳብ በእርሱ ላይ አልሰራበትም ማለት ነው። በራሱ ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስት እየተንቀሳቀሰ ነበር፤ ከዚያም በገሊላ ባሕር ከባሕሩ ዳርቻ በ3½ ማይልስ ርቀት ውሃው መሃል ወደነበረችው መርከብ ውስጥ ገባ። ከዚያ በኋላ እኛ ከምናውቀው የጊዜ ጽንሰ ሃሳብም ውጭ መንቀሳቀስ መቻሉ እናይ ዘንድ በርቀት ከነበረው የባሕር ዳርቻ ዘንድ መርከቢቱ ወዲያው እንድትደርስ አደረገ። ጊዜ የሚባል ነገር ጠፋ።
ዮሐንስ 6፡21 ስለዚህ በታንኳይቱ ሊቀበሉት ወደዱ፤ ወዲያውም ታንኳይቱ ወደሚሄዱበት ምድር ደረሰች።
ኢየሱስ በምድር እና በባሕር ላይ ሙሉ ስልጣን እንዳለው አሳየ።
በምድር እና በባሕር ላይ እንዲህ ዓይነት ስልጣን እንዳለው ማሳየት የፈለገው ለምንድነው? ምክንያቱም ይህ ስልጣን በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ከተጠቀሰው ትንሳኤ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው።
የባሕሩ ዳርቻ ለኢየሱስ ወሳኝ ቦታ ነው ምክንያቱም ምድር እና ባሕር የሚጋጠሙበት ቦታ ነው።
በዚህ “ወዲያው” በሚለው ቃል መረዳት ውስጥ ኢየሱስ ጊዜን ወደ ዘላለማዊነት በመለወጥ የጊዜ መጨረሻ እንዲመጣ ማድረግ እንደሚችል ያሳየናል።
ነገሮችን ከዘላለማዊነት አንጻር ስናያቸው ኢየሱስ ከመጀመሪያው ላይ ሆኖ መጨረሻውን ማየት እንደሚችን እንገነዘባለን።
ራዕይ ምዕራፍ 10 “ጊዜ ስለሚያበቃበት” ዘመን ይናገራል።
ራዕይ 10፡6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ ወደ ፊት አይዘገይም፥ አለ
ሰማይ፣ ምድር፣ እና ባሕር በዘላለማዊነት ይገናኛሉ። ለምን?
ምክንያቱም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ የሞቱ ቅዱሳን ምድር ውስጥ ወይ ደግሞ ባሕር ውስጥ ተቀብረዋል።
ይህ ብርቱ መልአክ በምድር ወይም ባሕር ውስጥ ካሉ መቃብሮች ሲያስነሳቸው የማይሞት አካል ለብሰው ይነሱና ጌታን በአየር ላይ ከተቀበሉት በኋላ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ።
እስካሁን የማናውቀው የሆነ የእምነት ሚስጥር ወደፊት ሊገለጥልን ተዘጋጅቶልናል።
በዚህም መንገድ የሙሽራይቱ አካላት በማይሞት አካላቸው ሆነው ከስፍራ ጽንሰ ሃሳብ ውጭ (ወደ ሰማይ ሲነጠቁ) እና ከጊዜ ጽንሰ ሃሳብ ውጭ ወጥተው ወደ ዘላለማዊነት ይገባሉ።
ለሙሽራይቱ አካላት ሊገለጥላቸው የሚያስፈልግ አንድ ጥልቅ ሚስጥር አለ፤ ይህም ሚስጥር ሲገለጥ ለዚህ አስደናቂ ለውጥ የሚያስፈልገውን እምነት ይሰጣቸዋል።
ሰብዓዊ አካላችንን ለተፈጥሮ ሕጎች እስረኛ አድርጎ ከያዘን ከጊዜ እና ከስፍራ ክልል እንዴት አድርገን ነው የምንወጣው?
አሁን በለበስነው ለሐጥያት እና ለምድር ስበት ተገዥ በሆነው በሚሞት እና በሚበሰብስ አካል ውስጥ ሆነን መነጠቅ እና ኢየሱስን በአየር ላይ መቀበል አንችልም።
ወደፊት የምንነጠቅበት ጊዜ ሲደርስ በአየር ላይ ተነስተን መሄድ የሚያስችለንን እምነት የሚሰጠን ነገር ሊኖር ይገባል። በአሁኑ ሰዓት ውሃ ላይ መራመድ እንኳ አንችልም።
ይህም ታላቅ ሚስጥር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውሮ ተቀምጧል ግን በግልጽ አልተጻፈም።
በግልጽ ያልተጻፉ ሆነው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወሩ ሚስጥራትን መረዳት ከመቻላችን በፊት መጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስን የተጻፉ ሚስጥራት መረዳት ያስፈልገናል።
ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ አልፈን ወደ ሰማይ ለመሄድ እስካሁን ከምናውቀው ከባለ ሶስት ዳይሜንሽኑ (3-D) ውስን ዓለም መውጣት ያስፈልገናል። እንደ መልአክ የመሰለ የከፍተኛው ዳይሜንሽን ፍጡር እኛ በምንኖርበት 3-D ዓለም ውስጥ ብቅ ብለው መታየት ወይም ሲያስፈልግ በግድግዳዎች ውስጥ የሚያልፉ መምሰል ይችላሉ። እነርሱ ግን ሁልጊዜ ለእኛ በዓይን የማይታይ ከፍ ያለ ዳይሜንሽን ውስጥ ሆነው እየተንቀሳቀሱ ናቸው።
ኢየሱስ በአንድ ወቅት ሊገድሉት በተዘጋጁ አይሁዶች ተከብቦ ነበር። ግፈኛ ወይም ተደባዳቢ ሰው ስላልነበረ ገፍትሯቸው አላለፈም። ስለዚህ ምን አደረገ?
እራሱን እነርሱ ሊያዩ በማይችሉት ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ ሰወረ። እነርሱም ሊያዩት ይቅርና እንዲህ ዓየነቱ ዳይሜንሽን መኖሩንም አያውቁም።
ዮሐንስ 8፡59 ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።
ከዚያም እነርሱ ሊያዩም ሆነ ሊያውቁ በማይችሉት ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ ሆኖ በመካከላቸው አለፈ።
ዮሐንስ 3፡13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
በዚህ ቃል ውስጥ ኢየሱስ እኛ ባለንበት ባለ ሶስት ዳይሜንሽን ዓለም ውስጥ እየተመላለሰ እንኳ ያለማቋረጥ ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ ይኖር እንደነበረ ተገልጧል።
በአንድ ጊዜ በምድርም በሰማይም ውስጥ መኖር እንድንችል የማይሞተውን አካላችንን መልበስ ያስፈልገናል።
ማን ወደ ሰማይ እንደሚሄድ እና ማን ደግሞ ወደ ታላቁ መከራ እንደሚገባ የሚወስነው የአካል መለወጥ ነው።
ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ የዳኑ ክርስቲያኖች በሙሉ ልባሞች እና ሰነፎች ቆነጃጅት ተብለው ተገልጸዋል፤ እነዚህም ንጹህ ሴቶች ናቸው። ልባሞቹ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት አንብበው ለመረዳት የሚበቃ ብርሃን የሚያበሩበት ዘይት አላቸው። ሰነፎቹ ወይም ማስተዋል የጎደላቸው ቤተክርስቲያን ተመላላሾች መጽሐፍ ቅዱስን በከፊል እውነት እንደሆነ በከፊል ደግሞ አፈታሪክ እንዳለበትና እርስ በርሱ የሚጋጭ ሃሳብ፣ የአተረጓጎም ስሕተት እና የማይጠቅሙ ዝርዝሮች እንዳሉበት እስኪያስቡ ድረስ ማስተዋል አጥተዋል።
ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ያለባቸው ችግር ሁላቸውም ማንቀላፋታቸው ነው። በአሜሪካ ውስጥ የተከሰተው የ9/11 ጥፋት የመጣው ጠላፊዎች አውሮፕላኑን ከተቆጣጠሩ በኋላ ሕዝቡን ሰላም ነው ወንበራችሁ ላይ ዘና ብላችሁ ተቀመጡ ምንም አታስቡ በማለታቸው ነው። ሕዝቡም እውነት መስሏቸው ራሳቸውን ለመከላከል ባይነሱ ሁሉ ሰላም የሚሆን መስሏቸው ዝም ብለው ሄዱ ግን አደጋ ውስጥ ወደቁ
ልክ እንደ አውሮፕላን ጠላፊዎቹ የቤተክርስቲያን ፓስተሮች ቤተክርስቲያኖችን ጠልፈው ሕዝቡን የቸልተኛነት እንቅልፍ አስተኝተዋቸዋል። መጨረሻቸውም የታላቁ መከራ እሳት ውስጥ መውደቅ ነው።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። ቤተክርስቲያኖች ሁሉ እንቅልፋቸውን ተኝተዋል። ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ። እንዲሁም ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች እና ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችም።
ሕዝቡን ወደ ጌታ ምጻት መምራት የምትችል አንድም ቤተክርስቲያን የለችም።
ማቴዎስ 25፡6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
ወደፊት በቅርቡ ሕዝብን ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ ታላቅ የጥሪ ድምጽ ይመጣል።
አስደንጋጭ የሆነ ታላቅ ሞገድ ቤተክርስቲያኖችን ይመታቸዋል። ሞገዱ እጅግ ታላቅና አስደንጋጭ ከመሆኑ የተነሳ ብዙዎች የተማመኑባት ቤተክርስቲያን የማታዋጣቸው መሆኑን ያያሉ።
እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የሚመላለስ የዳነ ሰው፡- “ውጡ” የሚል ታላቅ ድምጽ ይሰማል። ኢየሱስን መገናኘት ከፈለጋችሁ ከቤተክርስቲያናችሁ ውጡ።
ማቴዎስ 25፡7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
የዳኑ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች በስተመጨረሻ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ቤተክርስቲያኖቻቸው በሙሉ ብቁ እንዳልነበሩ ያስተውላሉ፤ የዚያን ጊዜም መብራታቸውን ያጨለመውን ጥቀርሻ (ሰው ሰራሽ ስሕተቶችን የሚወክለውን ጥቀርሻ) ጠርገው ወልውለው ለማጽዳትና መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት በቂ ብርሃን ለማግኘት ይጣደፋሉ። የቤተክርስቲያን አባላት ፓስተሮቻቸውን በጭፍን በመከተል ስሕተትን ተምረው ሳያውቁት እውነትን ሲቃወሙና ሲገፉ ኖረዋል።
ለምንድነው ከቤተክርስቲያን መውጣት የሚያስፈልጋቸው?
ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ለሎዶቅያውያን (የሕዝቡ መብት ማለት ነው፤ የራሳቸውን የእምነት አቋም ለመያዝ መብት አላቸው) ኢየሱስ ሲናገራቸው ከቤተክርስቲያን ደጅ ውጭ መቆሙንና ግለሰቦች ወደ እርሱ ይወጡ ዘንድ ጥሪ እያቀረበ መሆኑን ይናገራቸዋል፤ እንጂ ቤተክርስቲያንን በሙሉ አይደለም የሚጠራት።
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ
ይህ ቃል ለሁሉም ቤተክርስቲያኖች ነው፤ የማይመለከታት ቤተክርስቲያን የለችም።
ስለዚህ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያኖች በር ውጭ ቆሞ ከሆነ ወደ ኢየሱስ መቅረብ የምትችሉበት ብቸኛው መንገድ ከቤተክርስቲያን መውጣት ነው።
በ2020 ዓ.ም የመጣው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ እንዲዘጉ እና ሰዎች በየቤታቸው እንዲቀመጡ አስገደዳቸው። እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊነግረን እየሞከረ ነበር እኛ ግን ጆሮ አልሰጠነውም።
የምንናገረው ነገር ማንነታችንን ይገልጣል።
ማቴዎስ 26፡73 ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፦ አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት።
“አነጋገርህ ይገልጥሃል”። ይገልጥሃል ማለት ያጋልጥሃል ያሳብቅብሃል ማለት ነው።
ከቀራንዮ መስቀል በፊት የነበረው ሌሊት የፍርሃት መንፈስ የነገሰበት ሰዓት ነበረ። በጣም የሚያስፈራ ጊዜ ነበረ። ችኩልና ደፋር የነበረው ጴጥሮስ እንኳ ፈርቶ ከኢየሱስ ጋር እንደነበረ ሲጠየቅ ካደ። ግን አነጋገሩ ውስጥ የሆነ ነገር ክሕደቱን አጋልጦበታል።
በተመሳሳይ መንገድ ወደ ፊት የትንሳኤ ጊዜ ሲቀርብ ሰይጣን በሰዎች ላይ ፍርሃት እና ግራ መጋባትን ያሰራጫል። ነገር ግን በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት መጽሐፍ ቅዱስን በመከተልና ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት በመመለስ በአሳሳችነት የተሞላው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን አካል አለመሆናቸውን ይገልጣሉ።
ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብቻ መሆን እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳታችን ከሙታን የተነሱ ቅዱሳን በሚያናግሩን ጊዜ ማን መሆናችንን ለእነርሱ የሚገልጠን ንግግራችን ነው። እነርሱ ስለ ስላሴ አይናገሩም፤ ስለ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ አይናገሩም፤ ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያኖች አይቀበሉዋቸውም፤ ከሙታን የተነሱ ቅዱሳን መሆናቸውንም አያውቁም።
ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን ሁሉ አንድ ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት ይኖራቸዋል፤ እኛም እነርሱን የምናውቃቸው በዚህ ነው።
ከነበሩበት የቤተክርስቲያን ዘመን የተቀበሉትን ብዙ ዝርዝር መገለጥ ይገልጣሉ፤ ይህም መገለጣቸው ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ የቤተከርስቲያን ዘመናት ካስተማረን ትምሕርት ጋር በትክክል ይገጥማል።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
ከሙታን የተነሱት ቅዱሳን ደም ስራቸው ውስጥ ደም አይኖራቸውም። በደም ስራቸው ውስጥ የሚዘዋወረው የዘላለም ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ መልክ ነው። የጣታቸውን ጫፍ ጭምቅ ብታደርጉ የጣታቸው ጫፍ እንደማይቀላ ታያላችሁ።
የሞቱ ቅዱሳን ሁሉ በአስደናቂ ሁኔታ ከሙታን ከተነሱ በኋላ በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት የሚሞት አካላቸው ወደማይሞት አካል ይለወጣል።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤
አካላችን የሚለወጥበትን እምነት እንቀበል ዘንድ የሆነ እስከዛሬ ያልተለመደ እንግዳ ነገር ይከሰታል።
አሁን ያለን እምነት አካላችንን ሊለውጥና ወደ ሰማይ ሊነጥቀን በቂ አይደለም።
የሆነ ነገር አስተሳሰባችንን መለወጥ አለበት።
እስካሁን ድረስ የምናምነውን እያመንን እና እስካሁን የለመድነውን በማድረግ እየቀጠልን ወደፊት ልንለወጥ እንችላለን ብለን ተስፋ ማድረግ አንችልም።
የአካላችን መለወጥ እስከ ዛሬ የማናውቀው ዓይነት ታላቅ ክስተት ነው የሚሆነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡53 ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
54 ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።
በሞት ላይ የመጨረሻው ድል የሚሆነው የሙሽራይቱ አካላት የማይሞተውን አካላቸውን በለበሱ ጊዜ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡55 ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?
አዲሱ አካላችሁን ስትለብሱ ሞት የማይነካችሁ ሰዎች ትሆናላችሁ። ትንሳኤው ከሆነ በኋላ መቃብር ይሸነፋል።
መሞት አለመቻል ማለት ከጊዜ ዳይሜንሽን ውጭ ትሆናላችሁ ማለት ነው።
ዲያብሎስ ግን በአራተኛው የጊዜ ዳይሜንሽን ውስጥ ታስሮ ይቀራል፤ ምክንያቱም በስተመጨረሻ ተፈርዶበት ቅጣቱን በእሳት ባሕር ውስጥ ይቀበላል።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡56 የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤
ሰይጣን በ4ኛው የጊዜ ዳይሜንሽን ውስጥ እስረኛ ሆኖ በሚኖርበት ጊዜ ከጊዜ ዳይሜንሽን ውጭ በሆኑት ላይ ተጽእኖ ሊያደርግባቸው አይችልም። ከዚህም የተነሳ ሐጥያት የማይነካን ሰዎች እንሆናለን ምክንያቱም ከጊዜ ዳይሜንሽን ውጭ ስንሆን ሐጥያት የመስራት ፍላጎት አይኖረንም።
የሐጥያት ደሞዝ ሞት ነው። በስተመጨረሻ ከሞት እጅ ካመለጥን በኋላ አንዳችም ሐጥያት የመስራት ፍላጎት አይኖረንም።
ሮሜ 6፡23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡57 ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
በሞት ላይ ይህንን ድል ሊሰጠን የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ነው።
በአቅም ከእኛ እጅግ ብዙ የሚበልጠንን ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ ልክ ዳዊት ጎልያድን እንደገደለ ሞትን መግደል የሚችል ጀግና ኢየሱስ ብቻ ነው።
እስቲ እስካሁን በተመለከትናቸው ሃሳቦች መሰረት ራዕይ ምዕራፍ 10ን አብረን እንይ።
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
ብርቱ መልአክ የሚለው ቃል ስለ ታላቅ ኃይል ነው የሚገልጸው። በጣም ልዩ ነገር ሊሆን ነው።
ቀስተ ደመናው ከጥፋት ውሃ በኋላ በእግዚአብሔር እና በምድር መካከል ሁለተኛ ሕያው ፍጥረታትን እንዳይጠፉ እግዚአብሔር ያደረገው ቃልኪዳን ነው።
ዘፍጥረት 9፡13 ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
ስለዚህ ከቀስተደመና ጋር የሚገለጠው ብርቱ መልአክ የቃልኪዳኑ መልእክተኛ ነው።
እግዚአብሔር ከአብርሃም እና ከዘሩ ጋር ቃልኪዳን አደረገ። በፍጥረታዊ ትርጉሙ ይህ የሚናገረው ስለ አይሁዶች ነው። በመንፈሳዊ ትርጉሙ ግን እውነተኛው የአብርሃም ዘር ክርስቶስ ነው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ቃልኪዳኑ የተደረገው 3 እንስሳትን ማለትም ጊደር፣ እንስት ፍየል፣ እና አውራ በግ በማረድ እና እያንዳንዳቸውን ለሁለት ሰንጥቆ ስጋቸውን ወዲያ እና ወዲህ ትይዩ አድርጎ በመሃል ክፍተት ትቶ በማስቀመጥ ነው።
ዘፍጥረት 15፡10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልከፈለም።
ከዚያም አብርሃም ላይ ከባድ እንቅልፍ መጣበት (ይህም ሞትን የሚያመለክትና በቃልኪዳኑ ውስጥ አብርሃም ምንም ሚና እንደማይጫወት የሚያሳይ ነው። ሁሉን የሚያደርገው እግዚአብሔር ብቻ ነው) ከእንቅልፉ ጋር ደንጋጤ እና ጨለማ ሆነበት (ይህም መሞትን እና የሐጥያትን ዋጋ መክፈልን ያመለክታል)።
ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
የምድጃ ጢስ (የሐጥያት ዋጋ የሚከፈልበት ቦታ ውስጥ ያለው የሲኦል እሳት) እና የእሳት ብርሃን በተከፈሉት እንስሳት መካከል አለፉ።
ይህም በቃልኪዳኑ ውስጥ ብቸኛው ብርሃን ብቸኛው ተስፋ ነው። መብራት ወይም ብርሃኑ መንፈስ ቅዱስን ይወክላል እርሱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ወይም አማኑኤል የተባለው ኢየሱስ ነው።
ለሁለት የተከፈሉት የእንስሳቱ ስጋዎች ብሉን ኪዳን እና አዲስ ኪዳንን ይወክላሉ። በእኛ በሰዎች አስተያየት አንጻር አዲስ ኪዳን የሚጀምረው ከሐዋርያት ሥራ ነው ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ብቻ ነው ሰዎች የኢየሱስ አገልግሎት ዓላማው ምን እንደሆነ መረዳት የጀመሩት። በአራቱ ወንጌሎች ውስት ኢየሱስ ብቻ ነበር አገልግሎቱ ምን እንደሆነ ያውቅ የነበረው። መጥምቁ ዮሐንስ እንኳ የኢየሱስ አገልግሎት ምን እንደሆነ አላውቀም ነበር፤ ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን መጠራጠር ጀምሮ ነበር።
በሁለቱ ኪዳኖች መካከል ባሉት በአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ኢየሱስ የሐጥያታችንን ዋጋ ለመክፈል ሞተ። አገልግሎቱም ለግማሽ ሳምንት ነበረ፤ ማለትም ለ3½ ዓመታት። (ስለዚህ ለአይሁዶች የሚቀሩ 3½ ዓመታት አሉ፤ እነዚህ ቀሪ ዓመታት የሚፈጸሙት በታላቁ መከራ ውስጥ ሲሆን የሚጀምሩትም ልክ ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው፤ በእነዚህም ዓመታት ከዳንኤል 70ኛ ሱባኤ ላይ የቀረው ጊዜ ይጠናቀቃል)።
ወደ ምድረበዳ እንደሚሰደደው ፍየል የኢየሱስ ቅዱስ መንፈስ (ለዘላለም የሚበራው የእውነት ብርሃን) ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል በመውረድ ዲያብሎስ ላይ አራገፈው፤ ስለዚህ ንሰሃ ብንገባ ከሐጥያታችን ያነጻናል። ከዚያም የሞትን እና የሲኦል ቁልፍ ይዞ ከሙታን ተነሳ። የኢየሱስ ትንሳኤ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋረ ያደረገውን ቃልኪዳን አጽንቷል።
ገላትያ 3፡16 ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።
ገላትያ 3፡17 ይህንም እላለሁ፤ ... አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም።
ኢየሱስ በቀራንዮ እራሱን መስዋእት አድርጎ ያቀረበው መስዋእት በኢሩሳሌም ባለው ቤተመቅደስ ውስጥ የሚቀርቡ መስዋእቶችን ሁሉ አስቀርቷቸዋል።
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
ስለዚህ የባለ ሰባት ቀለማቱ ቀስተደመና፣ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክሉ ሰባት ቀለማት፣ የቃልኪዳን መልእክተኛ የሆነው ብርቱ መልአክ ኢየሱስ እራሱ ነው እንደ መልአክ ሆኖ ወደ ምድር የሚመጣው።
በዚህም መንገድ በምድር ላይ በለበሰው የሰው አካል ሆኖ ዳግም ምጻት ሳይመጣ በፊት መስራት የሚፈልገውን ስራ ይሰራል።
በሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ የኖረው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ን፤ እርሱም በሰባቱ መቅረዞች ተወክሏል።
ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
“ፊቱም እንደ ፀሃይ ነበረ”። ኢየሱስ ከት በተነሳ ጊዜ የእርሱ ቅዱስ መንፈስ ሞትን፣ ሲኦልን እና መቃብርን ከ2,000 ዓመታት በፊት ድል የነሳ ብርሃን ነው። አሁን ደግሞ ኢየሱስ እንደ መልአክ ሆኖ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳንን ሁሉ ሊያስነሳ ይመጣል።
እንደ ፀሃይ ከሚያበራው ፊቱ የተነሳ የሞት እና የሐጥያት ጨለማ ተገፍገው ይወገዳሉ።
“እግሮቹ እንደ እሳት አምዶች”። አምዶች። ብዙ ቁጥር። ሁለት የእሳት አምዶች እንደ እግሮች።
የእሳት አምድ አይሁዶችን በምድረበዳ ውስጥ መርቷቸዋል። በዕድሜያቸው እና በኖሩበት የቤተክርስቲያን ዘመን የሚመራቸውን የመንፈስ ቅዱስን ብርሃን በታማኝነት የተከተሉ ሁለት ቦድኖች አሉ። እነዚህ ሁሉ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ሞተው ባሕር ውስጥ ወይም ምድር ውስጥ ተቀብረዋል። እነዚህ ታማኝ ቅዱሳንም ከሙታን ሊነሱ ጊዜው ቀርቧል።
ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
“ትንሽ መጽሐፍ”። በትንሳኤው ጊዜ በሕይወት የሚኖሩ የሙሽራይቱ አካላት በጣም ጥቂት ነው የሚሆኑት።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
መጽሐፉ ተከፍቷል። አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ከባድ ጥቅሶችን ልክ እንደተከፈተ መጽሐፍ በቀላሉ አንብበን እንድንረዳ ኢየሱስ ይጠብቅብናል።
ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤
10 ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ።
ሙሽራይቱ በስተመጨረሻ ብቻ ነው የዳንኤልን ራዕዮች መረዳት የምትችለው። እውነተኛውን መልስ የሚያገኞች ጥቂቶች ብቻ ናቸው። እነዚያ ጥቂቶችም ልባሞቹ ቆነጃጅት ናቸው።
ዮሐንስ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ መጽሐፍ ይዞ ተቀምጦ ያየው ዘንድ ወደ ሰማይ ተነጠቀ።
ራዕይ 5፡1 በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።
መጽሐፉ በውስጡ በኩል የተጻፈበት ሲሆን በሰባት ማሕተሞች ታሽጓል፤ እነዚህም ማሕተሞች በተጻፉት ሚስጥራት ላይ ታትመዋል።
ሰባቱ የተጻፉት ማሕተሞች ራዕይ ምዕራፍ 6 እና ራዕይ 8፡1 ላይ ይገኛሉ።
ግን ደግሞ በውስጥ ብቻ ሳይሆን በኋላም በኩል ጽሕፈት አለ። ይህ ጽሑፍ የተጻፈው በመጽሐፉ ከውስጥ በኩል አይደለም። መጽሐፉ ውስጥ ሆኖ ግን ባልተጻፈ መልኩ ተሰውሮ ነው ያለው። ይህም የተሰወረ ጽሑፍ በሰባት የታተሙ ወይም የተሰወሩ ማሕተሞች አማካኝነት ተሰውሯል፤ እነዚህም ሰባቱ ነጎድጓዶች ይባላሉ።
የተከፈተው መጽሐፍ የሚያመለክተው ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ለመነጠቅ የሚያስፈልጓት ሚስጥራት ሁሉ መገለጣቸውን ነው። አንዳንድ ሚስጥራት ለምሳሌ እንደ 7ቱ መለከቶች እና 7ቱ ጽዋዎች የመሳሰሉት በታላቁ መከራ ውስጥ የሚሆኑትን አይሁዶች ብቻ የሚመለከቱ ናቸው። ሙሽራይቱ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ስለማትገባ እነዚያ ሚስጥራት አያስፈልጓትም።
የተጻፉት ሚስጥራት አንድ ጊዜ ብቻ ተገልጠዋል፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስን እንደተከፈተ መጽሐፍ እናነበው ዘንድ ነው፤ ከዚያ ወዲያ ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥራቸውን የሚገልጡበት ጊዜ ይመጣል፤ እነዚህም ያልተጻፉ ሚስጥራት ናቸው።
የመጽሐፉ ኋላው የሚያመለክተው በመጀመሪያ በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት ማወቅ እንደሚያስፈልገን ነው። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ያልተጻፉትን የሰባቱን ነጎድጓዶች ሚስጥራት ማግኘት የምንችለው።
“ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ”
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የኖሩ ቅዱሳን ሞተው በምድር ወይም በባሕር ውስጥ ነው የተቀበሩት።
የኢያሱ እግር ያረፈበትን ቦታ ሁሉ እግዚአብሔር የተስፋይቱ ምድር ርስት አድርጎ ይሰጠዋል።
ኢያሱ 1፡3 ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።
ይህ ብርቱ መልአክ እግሩ የረገጠበት ቦታ ሁሉ የእርሱ ግዛት ይሆናል።
እርሱም የሞቱትን ቅዱሳን ከባሕር እና ከምድር ውስጥ ጠርቶ ያስወጣቸዋል።
ቀጣዩ ጥቅስ ቁልፍ ጥቅስ ነው።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
“ጮኸ” የሚለው ቃል ሁለት ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ሁለቱንም ጊዜ የሚናገረው ከትንሳኤ ጋር በተያያዘ ነው።
(በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፍ እንዲነቁ የመጣው ጥሪ በጩኸት መሆኑን ልብ በሉ። ስለዚህ ያ ጩኸት ምናልባት የትንሳኤ ጊዜ ሲቀርብ ይሆናል የሚመጣው።)
“በታላቅ ድምጽ ጮኸ” እና “በጮኸ ጊዜ” የሚሉት ሁለቱም ቃላት ከትንሳኤ ጋር የተያያዙ ናቸው።
“በታላቅ ድምጽ ጮኸ” የሚለው ኢየሱስ አላዓዛርን ባስነሳ ጊዜ ያደረገውን ይገልጻል።
ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።
“በጮኸ ጊዜ” የሚለው ቃል ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነ
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ አስቀድሞ ከኢየሱስ መቀበር በፊት ተነግሯል።
ይህም ለብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ “ጮሆ ድምጹን ያሰማው መች” እንደሆነ አያይዘን እንድናስብ ያደርገናል።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
“ጮኸ” ተብሎ ሁለት ጊዜ በተጻፈው ቃል መካከል የይሁዳ ነገድ አንበሳ ሲያገሳ ይሰማል።
ይህም የአንበሳ ድምጽ የሚያገሳው በሞት፣ በሲኦል፣ እና በመቃብር ላይ የተቀዳጀውን የመጨረሻ ድል ለማወጅ ነው፤ በዚያም ጊዜ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን በሙሉ ከሙታን ይነሱና መቃብሮች ባዶዋቸውን ይቀራሉ።
ከዚያም ከጮኸ በኋላ፣ ማለትም ከትንሳኤው በኋላ ብቻ ነው ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን የሚያሰሙት።
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ በትንሳኤው እና ወደ ሰማይ በመሄዱ መካከል 40 ቀናት አልፈው ነበር።
የብሉይ ኪዳን ነብያት ከእርሱ በኋላ ከሙታን ተነስተው አብረውት እንደ ደመና ያሉ ምስክሮች ሆነው ወደ ሰማይ ሄዱ።
የሐዋርያት ሥራ 1፡3 ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።
በመጀመሪያው ምጻቱ እና በዳግም ምጻቱ መካከል የተወሰኑ ነገሮች ይመሳሰላሉ ብለን መጠበቅ እንችላለን።
የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ እና ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ወደ ሰማይ መሄዳቸውም ምናልባት በ40 ቀናት ያህል ሊራራቅ ይችላል።
ሰለዚህ በነዚያ 40 ቀናት ውስጥ ታላላቅ ነገሮች ይከሰቱ ይሆናል።
ልባሞቹ ቆነጃጅት መብራታቸውን ደመቅ አድርገው ማብራት ይኖርባቸዋል፤ በዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወረውን ፊት ለፊት በግልጽ ያልተጻፈውን መረዳት ይችላሉ።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52 ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
ነገሮች የሚሆኑበት ቅደም ተከተል ግልጽ ነው። ሙታን ይነሳሉ፤ በሕይወት ያሉ የሙሽራይቱ አካላት ደግሞ አካላቸው ይለወጣል።
ማወቅ ያለብን አንድ ታላቅ ሚስጥር አለ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተብራርተው ያልተጻፉትም ሰባቱ ነጎድጓዶች እነዚህን ሚስጥራት በሕይወት ላለችው ሙሽራ ይገልጡላታል። አካላችንን ወደማይሞተው አካል እንዴት እንድንለውጠው እናውቅ ዘንድ እነዚያን ሚስጥራት ማወቅ ያስፈልገናል።
ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።
ዮሐንስ እንዲጽፋቸው አልተፈቀደለትም፤ ስለዚህ ታላቅ ሚስጥር ሆነው ቆይተዋል።
ማንም እንዳያውም ያልተፈቀደው ይህ ታላቅ ሚስጥር ምንድነው?
የጌታ ምጻት ነው።
በዓለማችን ውስጥ ካሉ ሚስጥራት ሁሉ ታላቁ ሚስጥር ይህ ነው።
መች ነው ጌታ የሚመጣው? ለምጻቱ እንዴት ነው የምንዘጋቸው? ለማን ብሎ ነው የሚመጣው?
እነዚህ ሚስጥራት ሲገለጡ ያንገዳግዱናል። የነዚህ ሚስጥራት መገለጥ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ከሚሰበከው ስብከት በጣም የተለየ ይሆናል። ለዚህ ነው በዚያ ጊዜ ከቤተክርስቲያኖች ውጭ መሆን የሚያስፈልገን።
ጳውሎስ አንድ ጊዜ ከአካል ውጭ ሆኖ መንፈሱ ወደ ሶስተኛ ሰማይ በተነጠቀ ጊዜ የነበረውን ልምምድ ተርኳል።
2ኛ ቆሮንቶስ 12፡4 ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።
በሰማይ የምንሰማው እውነት እኛ የምድር ሰዎች ለመስማት ከምንጠብቀው ፍጹም የተለየ እውነት ነው።
ሁላችንም የምናስበው ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ በእኛ ደስ እንደሚለው ነው። እውነታው ግን ከምናስበው ግልባጭ ሊሆን ይችላልና ሁላችንም አስተሳሰባችንን መለወጥ ይኖርብናል።
እነዚህን የመጨረሻ እወነቶች እግዚአብሔር ሚስጥር አድርጎ አቆይቷቸዋል፤ ምክንያቱም በአሁኑ ሰዓት ቢገለጡልን ልንሸከማቸውም አንችል ይሆናል። ነገር ግን ብዙ አስፈሪ አደጋዎች በቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ እንዲሁም በራሳችን አመለካከት ላይ የጣልነውን እምነት ካጠፉብን በኋላ ለአጭር ጊዜ ተስፋ መቁረጣችን እነዚያ ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች የሚናገሩትን እንድናምን ያደርገናል። ነጎድጓዶቹም የሚናገሩት ነገር እኛ በተለምዶ ከምናስበው የተለየ ነው የሚሆነው።
ስንሰማቸው እንንገዳገዳለን።
ራዕይ 10፡5 በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥
ይህ ብርቱ መልአክ ምድርን እና ባሕርን ከሰማይ ጋር ያገናኛቸዋል። ይህም ማለት ከ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ሁሉ ከሙታን ሲነሱ በምድር እና በባሕር ውስጥ ነገሮች ይለወጣሉ ማለት ነው።
ራዕይ 10፡6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ ወደ ፊት አይዘገይም፥ አለ።
እግዚአብሔር ምድርን እና ባሕርን ፈጥሯቸዋል፤ ስለዚህ ለምድር እና ለባሕር የሞቱትን ሰዎች አምጡ ይላቸዋል። ከዚያ በኋላ በሕይወት ላለችው ሙሽራ ጊዜ ያበቃል። ማለትም የሙሽራይቱ አካላት አሁን የለበሱትን ስጋ አውልቀው የማይሞተውን ስጋ ይለብሳሉ። ከጊዜ የምትላቀቁበት ብቸኛው መንገድ ወደ ዘላለማዊነት በመግባት ነው።
ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
የተጻፉትን ሚስጥራት ለሙሽራይቱ የሚገልጠው ታላቅ ድምጽ ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ከተላኩ መላእክት መካከል የ7ኛው ወይም የመጨረሻው መልአክ አገልግሎት ነው። የሙሽራይቱ አካላት የሰባተኛውን መልእክተኛ መገለጦች ተቀብለው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ መልአኩ የተናገረው እውነት መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት ብቻ ማረጋገጥ አለባቸው። የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። እያንዳንዱ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ብቻ እውነትን መናገር ሲችል ያ ትንሳኤን የሚያመጣው የእግዚአብሔር ታላቅ ድምጽ ይሆናል።
ያ የመላእክት አለቃ ድምጽ ነው።
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
የሙሴን አካል አንስቶ ወደ ሰማይ የወሰደው የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው፤ ስለዚህም ሙሴ ኢየሱስ በተራራ ላይ መልኩ ባንጸባረቀበት ሰዓት አብሮ መገለጥ ችሏል።
ይሁዳ 1፡9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመላእክት አለቃ ተብሎ የተጠቀሰው ሚካኤል ብቻ ነው።
ዳንኤል 10፡21 ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
ሚካኤል የአይሁዶች አለቃ ነው።
የአይሁዶችም አለቃ መሲሁ ነው።
ዳንኤል 9፡25 … እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ …
ስለዚህ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ማለት የቃልኪዳኑ መልእክተኛ ኢሱስ ነው።
እግዚአብሔር ሰው የሆነው የኢየሱስ መምጣት ሳይፈጸም በምድር ላይ እራሱን እንደ መላእክት አለቃ አድርጎ በመገለጥ ፈቃዱን ይፈጽማል።