ፓስተሮች የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው አያውቁም
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በስደት ምክንያት ስለተበታተነች አማኞች በትንንሽ ቡድን ነበር ለአምልኮ የሚሰባሰቡት። እያንዳንዱ ሕብረት የሚመራው በሽማግሌዎች ነበር።
First published on the 26th of May 2022 — Last updated on the 26th of May 20221ኛ ጢሞቴዎስ 1፡2 በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤
ይህ ጳውሎስን የጢሞቴዎስ መንፈሳዊ አባት አያደርገውም። ትርጉሙ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ወደ ጌታ አምጥቶታል፤ ጢሞቴዎስ ደግሞ ገና ወጣት ነበረ ማለት ነው።
ነገር ግን ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ሃሳብ ነው። ማንንም ሰው መንፈሳዊ አባታችን ብለን እንድንጠራ አይፈቀድልንም።
ማቴዎስ 23፡9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።
ስጋዊ አባት አላችሁ ግን መንፈሳዊ አባት የላችሁም።
ይህም ማለት የትኛውም ሰው በመንፈስ ከእናንተ በላይ አይደለም።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰራ ትልቅ ሐጥያት አንድ ቅዱስ ሰውን ከምዕመናን ወይም ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ ነው። እነዚህ ከፍ ከፍ የተደረጉ የቤተክርስቲያን መሪዎች ኒቆላውያን ይባላሉ (ኒቆ ማለት ገዥ ነው። ማለትም በምዕመናን ላይ የሚሰለጥን ሰው)።
ራዕይ 2፡6 ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።
በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪዎች ሕዝቡን መጨቆን ጀመሩ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ታላቅ ሆነው መታየት ይፈልጉ ነበር።
ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
ይህ ደግሞ በ312 ዓ.ም እና በ606 ዓ.ም መካከል የነበረው ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። የሰዎቹ ልምምዶች ወደ አስተምሕሮ አደጉ። ስለዚህ ሰዎች ከፍ ያደረጉት አንድ ቄስ ወይም ፓስተር የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነ። ከዚያ ወዲያ አንድ ጳጳስ ደግሞ በብዙ ቄሶች ወይም ፓስተሮች ላይ አለቃ ሆነ።
አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ጳጳሳት እና ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ ሆነው የተሾሙ ካርዲናሎች ነበሩ።
እግዚአብሔር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰው ከጉባኤው በላይ ከፍ ተደርጎ ሲሾም ይጠላል።
ይህንን መሰረታዊ መርህ መርሳት የለብንም።
ራዕይ 5፡10 … ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥
“አደረግሃቸው” የሚለው በብዙ ቁጥር ስለሆነ ሁሉንም ማለት ነው። እያንዳንዱ የዳነ ክርስቲየን ንጉስ እና ካሕን ነው። ካሕን ስራው በአይሁድ እና በእግዚአብሔር መካከል መቆም ነው። እያንዳንዱ የዳነ ክርስቲያን ላልዳነ ሰው ካሕን ነው፤ ምክንያቱን ያልዳነውን ሰው ወደ ጌታ ሊያመጣው ይችላል። ያ ሐጥያተኛ ክርስቶስን ከተቀበለ በኋላ ግን እርሱም ራሱ ካሕን ይሆናል።
ከካሕን በላይ ስልጣን ያለው ሊቀ ካሕን ነው። እርሱም ኢየሱስ ነው።
የዳኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ካሕናት ስለሆኑ አንድም ሰው ከእነርሱ በላይ በእነርሱ ላይ ስልጣን የለውም። ኢየሱስ ብቻ ነው ከካሕናት በላይ ስልጣን ያለው። ካህናት በሙሉ እርስ በርሳቸው እኩል ናቸው። በእግዚአብሔር መንግስት ሕግ መሰረት ካሕነት የበላይነታቸው ለሐጥያተኞች ብቻ ነው።
ዕብራውያን 3፡1 ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤
ነገስታት ሁሉ እኩል ናቸው። ከንጉስ በላይ አንድ ብቻ አለ፤ እርሱም የነገስታት ንጉስ ነው። የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ነው።
ራዕይ 19፡16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።
ስለዚህ የትኛውም ክርስቲያን ከሌላ ክርስቲያን በላይ አይደለም። አንዱ ከሌላው በላይ ሲሆን ኒቆላዊነት ይባላል።
ክርስቲያን ለመሆን መዳን አለባችሁ። የዳኑ አማኞች በሙሉ ወንድማማች ናቸው፤ ስለዚህ እኩል ናቸው።
ወንድማማች ቤተሰብ ውስጥ ወንድማማች አንዳቸው ከሌላው ባይ አይደሉም። ሁሉም እኩል ናቸው።
ኤፌሶን 3፡14-15 ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤
ቤተክርስቲያን በሙሉ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ናት። እንደ እግዚአብሔር ልጆች ሁላችን እኩል ነን።
ማቴዎስ 12፡48 እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።
49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፦ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤
50 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
ወንድማማችነት የሚመሰረተው በአንድ ነገር ብቻ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል መሆንና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ነው። በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚኖራችሁ ስፍራ የሚወሰነው ፈቃዱን በማድረጋችሁ ነው። የትኛውም የአካል ብልት ከየትኛውም አያንስም። በአካል ውስጥ ከፍ ያለው ስፍራ የራስ ብቻ ነው ምክንያቱም አካል በሙሉ በራስ ቁጥጥር ስር ስለሆነ ነው።
ራስ ብቻ ነው ከሰውነት ክፍሎች ወይም ከብልቶች ሁሉ በላይ የሆነው እና የሚቆጣጠራቸው። ይህም የራስ ስፍራ የኢየሱስ ብቻ ነው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ
ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የለም።
ማንኛውም የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚል ፓስተር ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተሰጠውን ስልጣን በራሱ ሰርቆ ወስዷል።
ማቴዎስ 23፡8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
ረቢ ማለት ሰው ሰራሽ የሆነ የምኩራብ መሪ ነው። ኢየሱስ ይህንን ስፍራ መያዝ እንደሌለብን ተናግሯል።
ብዙ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ፓስተሩ ሰው ሰራሽ በሆነ ስልጣን የቤተክርስቲያን ራስ ሆኗል። በፍጹም ይህንን ስፍራ መያዝ የለብንም።
ማንም ሰው (ለምሳሌ አበበ) መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ፓስተር አበበ” ተብሎ አያውቅም።
የፓስተርነት ስፍራ ብዙም ታላቅ ስፍራ ስላልነበረ አዲስ ኪዳን ውስጥ “ፓስተር” የሚለው ቃል አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጻፈው። የፓስተሮች ስራ ለሰዎች ድጋፍ ማድረግ ነው። ሰዎች በቤተሰብ እና በልዩ ልዩ ችግሮቻቸው ውስጥ ያላቸውን ጥያቄ አድሞጦ የማማከር አገልግሎት መስጠት ነው። ሌላው አገልግሎታቸው ደግሞ አዳዲስ ክርስቲያኖችን በእምነታቸው መገንባት፤ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ማስተማር፤ እና በእግዚአብሔር እንዲታመኑ ማበረታታት ናቸው።
ፓስተሮች ግን በጭራሽ የቤተክርስቲያን ራስ ተብለው አያውቁም። ፓስተሮች የጥቅሶች ትርጓሜ ላይ አብዝተው በመመሰጥ ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ እንዲያስወጡ ያዘዛቸው የለም።
ስለዚህ ፓስተሮች አገልግሎታቸው ምን ሊያስከትል እንደሚችልና በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊፈጽሙ የሚችሉት ክፉ ስራ በትንቢት መንፈስ አስቀድሞ ታይቶ በብሉይ ኪዳን የኤርምያስ መጽሐፍ ውስጥ ስድስት ጊዜ ተወግዘዋል።
ኤርምያስ 2፡8 ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥
ፓስተሮች ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ ሆነው አይጸኑም።
ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
በቤተክርስቲያን ላይ በአለቅነት ተቀምጠዋል፤ ይህም እግዚአብሔር ያልሰጣቸው ስፍራ ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ስፍራ እግዚአብሐየርን ሊጠይቁና ሊፈልጉ አይችሉም። ሔዋንን ከእግዚአብሔር ቃል ያሳታት የመጀመሪያው አውሬ እባቡ ነው።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገጣጠም የእግዚአብሔርን ቃል ሚስጥራት መግለጥ የእግዚአብሔር ደስታውና ዕድል ፈንታው ነው። የሰው ጥቅሶችን ማሰደድና እነርሱን አገጣጥሞ የራስን አመለካከት የሚደግፍ መላ ምት ማምጣት የጥፋት መነሻ ነው። ጥፋትን ስለሚያመጣው እርኩሰት ኢየሱስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶናል። ይህ በጣም አደገኛ ነገር ነው።
ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥
ነፋስ ጥል እና ጦርነትን ነው የሚወክለው። እያንዳንዱ ፓስተር የራሱን አተረጓጎም በትጋት ይሰብካል፤ ከእርሱ ሀሳብ ጋር የማይስማሙትን ሁሉ ያሳድዳቸዋል።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፡፡
የሰው ንግግር ጥቅስ እየገጣጠሙ መስበክ እጅግ ብዙ የተለያዩ ዓይነት አስተምሕሮዎች እንዲፈለፈሉ ምክንያት ሆኗል፤ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የሚቆዩ ሰዎች እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማረጋገጥ አልቻሉም፤ ፓስተሩን የሚቃወሙ ሰዎች ደግሞ ከቤተክርስቲያን ይባረራሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ካለማወቃቸው የተነሳ የሜሴጅ ተከታዮች ወደ ጥፋት እየሄዱ ናቸው።
የሜሴጅ ተከታዮች የሆነ ጊዜ ዲኖሚኔሽኖችን መጽሐፍ ቅዱስ በደምብ አያውቁም ብለው ይነቅፉዋቸው ነበር። አሁን ግን እነርሱ እራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁም።
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ፓስተሮች የማስተማሩን አገልግሎት በሙሉ የራሳቸው አድርገውታል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ብቻ በመጠቀም እምነታቸው ትክክል መሆኑን የማረጋገጥ ብቃት የላቸውም። ስለዚህ ለአመለካከታቸው የሚመቻቸውን ጥቅስ ብቻ እየመረጡ ይጠቀማሉ፤ የማይመቻቸውን ደግሞ ትተው ያልፋሉ። እርስ በርሳቸው በሚጋጩ ልዩ ልዩ አመለካከቶች ብዛት ሰዎች ግራ ተጋብተው በራሳቸው ጭንቅላት ማሰብ አቁመዋል፤ ስለዚህ እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ሳያረጋግጡ የሰዎችን ጥቅስ እንደ ገደል ማሚቶ ይደግማሉ።
ፓስተሮች ላይ የተነገረው ይህ አስፈሪ ውግዘት የሚያመለክተን ክርስቲያኖች ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን በላያቸው ላይ ከፍ ማድረጋቸው ጥበብም መጽሐፍ ቅዱሳዊነትም አለመሆኑን ነው። ደግሞም ፓስተሩ ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ የሚነግራቸው አዛዥ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ይህ ሁሉ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተወረሰ ዲኖሚኔሽናዊ ልማድ ነው።
እኛም ለምዶብን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ የሰዎችን ዲኖሚኔሽናዊ ልማድ እንከተላለን።
ማርቆስ 7፡6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች፦ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
9 እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።
ኢየሱስ አንድም ደቀመዝሙር ከሌላ ደቀመዝሙር እንዲበልጥ አልፈለገም። ለስኬት ቁልፉ ወንድማማችነት ነው። ስለዚህ ማንም አይታበይም።
በአንድ ክርስቲያን እና በእግዚአብሔር መካከል ቅዱሳን ካሕናት የሚባሉ የሉም። ኢየሱስ በሞተ ጊዜ እግዚአብሔር የመቅደሱን መጋረጃ ከቀደደው በኋላ የአሮን ክሕነት ተሽሯል። የወንጌሉ ቁልፍ እኩልነት ነው እንጂ የሰው የበላይነት አይደለም።
ሰዎች የተለያዩ ችሎታዎችና ተሰጥኦዎች ሊኖሩዋቸው ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም እኩል ናቸው።
አንድ ሰውን ስታናግሩ በስሙ ላይ ረቢ ወይም ፓስተር የሚል ማዕረግ አትለጥፉበት። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች እንደዚያ አላደረጉም።
ማቴዎስ 25፡39 ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
40 ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።
ከክርስቲያኖች ሁሉ ታናሽ የሆነውን ክርስቲያን ኢየሱስ ወንድም ብሎ ነው የሚጠራው። በቤተሰብ ውስጥ ወንድሞች ሁሉ እኩል ናቸው።
ብሉይ ኪዳንን የጻፉ ነብያት የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል እየጻፉ ስለነበሩ ልዩ ስፍራ ነበራቸው።
ማንም ሰው ዳንኤልን ሲያናግር “ነብይ ዳንኤል” ብሎት አያውቅም። ነገር ግን አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ስለ ዳንኤል ሲያወራ ነብዩ ዳንኤል ቢል ችግር የለውም።
ጳውሎስ ስለ ራሱ ሲጽፍ “ሐዋርያ ጳውሎስ” ብሎ አያውቅም፤ “ሐዋርያየሆነ ጳውሎስ” ብለው ነው የጻፈው።
ጳውሎስ በራሱ ስም ላይ ማዕረግ የመቀጠል ፍላጎት አልነበረውም።
2ኛ ቆሮንቶስ 1፡1 ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ
ማንም ሰው ጳውሎስን “ሐዋርያ ጳውሎስ” ብሎ አልጠራውም። ሲጠሩት “ወንድም ጳውሎስ” ነው የሚሉት።
አንድን ሰው ስታናግሩ በስሙ ላይ መለጠፍ የምትችሉት ብቸኛው ማዕረግ “ወንድም” ነው።
የሐዋርያት ሥራ 22፡13 እርሱም ወደ እኔ መጥቶ በአጠገቤም ቆሞ፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ እይ አለኝ። እኔም ያን ጊዜውን ወደ እርሱ አየሁ።
አንድን ፓስተር ከሌላ ክርስቲያን አብልጦ ማክበር ትልቅ ስሕተት ነው።
ያዕቆብ 2፡1 ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ።
ለሰው ፊት ማድላት ማለትም አንድን ሰው ከሌላ ሰው ማስበለጥ ስሕተት ነው። ክርስቲያኖች ወንድማማች ናቸው እንጂ በስልጣን ተዋረድ የሚበላለጡ ሰዎች አይደሉም። ክርስቲያኖችን ስታናግሯቸው በስማቸው ላይ ማዕረግ አትለጥፉ፤ ማዕረግ እየቀጠሉ መጥራት እንዲታበዩ ብቻ ነው የሚያደርጋቸው።
አዲስ ኪዳንን የጻፉ ሐዋርያት ልዩ ክብር ነበራቸው ምክንያቱም የእግዚአብሐየርን ቃል እንዲጽፉ እና የጥንቷን ቤተክስቲያን እንዲያስጀምሩ ኃላፊነት የተሰጠው ለእነርሱ ነው። እነዚህ ሰዎች ልዩ ሰዎች ናቸው። ከመካከላቸው አምስቱ አዲስ ኪዳንን እንዲጽፉ ተመርጠዋል።
ሌሎች ሁሉ ግን ሽማግሌ ወይም ወንድም ነበሩ።
ሽማግሌዎች ማለት በእምነታቸው የቆዩ እና የበሰሉ ወንድሞች ናቸው። እያንዳንዱ ወንድም በእምነቱ ወደ መብሰል ሲደርስና የእግዚአብሔርን ቃል በደምብ ሲያውቅ ሽማግሌ ይሆናል።
የሐዋርያት ሥራ 15፡23 እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
በ100 ዓ.ም አካባቢ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት በሙሉ ሞተው አልቀዋል።
እነርሱም 12 ብቻ ነበሩ። ቤተክርስቲያንን እየተከሉ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሱ ነበር። ቤተክርስቲያንን የሚተክሉባቸው ስፍራዎች ከመብዛታቸው የተነሳ አንድ ስፍራ ብዙ መቀመጥ አይችሉም ነበር። ስለዚህ የተከሉዋቸውን አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች እንዲያስተዳድሩ በየስፍራው ሽማግሌዎችን ይሾሙ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 20፡31 ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
ጳውሎስ ኤፌሶን ውስጥ ሶስት ዓመታት አሳልፏል። ጳውሎስ በአንድ ቦታ ካሳለፈው ጊዜ ሁሉ ይህኛው በጣም ረጅም ጊዜ ነው።
በመጀመሪያ ኢየሩሳሌም በቤተክርስቲያናት መካከል ከፍ ያለ ክብር ነበራት።
የሐዋርያት ሥራ 16፡4 በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው።
እነዚህ አዋጆች በቁጥር አራት ብቻ ነበሩ። ለጣኦት ከተሰዋ ምግብ፣ (ከደም እና ታንቀው ከሞቱ እንስሳት) እና ከዝሙት እንድትርቁ የሚሉ ናቸው።
የሐዋርያት ሥራ 15፡28-29 ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።
ከበዓለ ሃምሳ ቀን ጀምሮ የነበረችው የመጀመሪያዋ እናት ቤተክርስቲያን ኢየሩሳሌም ጥቂት መመሪያዎችን ብቻ ነው ያስተላለፈችልን።
ከዚያ ወዲያ በ70 ዓ.ም እንደገና ደግሞ በ135 ዓ.ም ኢየሩሳሌም በሮማውያን እጅ ፈራረሰች። ስለዚህ ከዚያ በኋላ በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ላይ ስልጣን አለኝ የምትል ቤተክርስቲያን አልነበረችም።
እግዚአብሔር በአንድ ስፍራ የሚገኙ ሰዎች በሌላ ስፍራ የሚገኙ ሰዎችን እንዲገዙ አይፈልግም።
በእያንዳንዱ ቦታ የሚገኙ የአጥቢያ ሽማግሌዎች የአጥቢያው አስተዳዳሪ ናቸው። ሌላ ቦታ የሚኖር ሰው በእነርሱ ላይ አንዳችም ስልጣን የለውም።
ከውጤታማነት አንጻር ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሶስት አገልግሎቶች ብቻ ነው የተናገረው።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
መጀመሪያ የመጡት ሐዋርያት ናቸው ምክንያቱም አዲስ ኪዳንን የጻፉት እነርሱ ናቸው፤ አዲስ ኪዳንም ፍጹም እውነት ነው። ቤተክርስቲያን ውጤታማ መሆን ከፈለገች አዲስ ኪዳንን ማመን አለባት። የተጻፈው ቃል ማለት እግዚአብሔር በሐዋርያት በኩል ሲናገረን ነው።
ቀጥለው የመጡት ቤተክርስቲያንን በውሳኔዋ ለመምራት ያግዙ ዘንድ ወደፊት የሚከሰቱ ነገሮችን አስቀድመው መግለጥ የሚችሉ ነብያት ናቸው። ለአካባቢ የሚሆን ትንቢት እግዚአብሔር በነብይ በኩል ሲናገረን ነው። ነብይ ነኝ የሚል ነገር ግን ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን መግለጥ የማይችል ሰው ብቁ ነብይ አይደለም።
ከዚህ በተጨማሪ ግን አንድ ሌላ ዓይነት አስፈላጊ የነብይነት አገልግሎት አለ፤ እርሱም በጨለማው ዘመን ጠፍተው የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን የመግለጥ እንዶሁም በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ወደ ነበረው ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ትምሕርት የሚመልሰን የነብይ አገልግሎት ነው።
ይህ አገልግሎት ሐዋርያት ለጻፉት ቃል ተገዥ ስለሆነ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍተው የነበሩ እውነቶችን መገለጥ የሚቀበለው ይህ ኤልያስ ብቻ ነው። እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚጨምረው አዲስ አስተምሕሮ የለውም። የእርሱ አገልግሎት እኛን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ታስተምር ወደነበረው ትምሕርት መመለስ ብቻ ነው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ነገር ግን የዘመን መጨረሻ ላይ የሚመጣው ኤልያስ ለመጀመሪያዎቹ አዲስ ኪዳንን ለጻፉት ሐዋርያት ተገዥ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም መጀመሪያ የመጡት ሐዋርያት ናቸው። ኤልያስ ሊነግረን የሚችለው ጳውሎስ የሰበከውን ብቻ ነው። ስለዚህ አገልግሎቱ ወደ መጀመሪያው እውነት እንድንመለስ መርዳት ነው።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ሶስተኛው አገልግሎት ማስተማር ነው።
አስተማሪ በመጨረሻው ዘመን ነብይ የተገለጡ መገለጦችን ተቀብሎ እነዚያን መገለጦች በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መርምሮ እውነተኛ መሆናቸውን ያረጋግጥና ያጸናቸዋል። የነብዩን ንግግር ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመውሰድና ወንድም ብራንሐም ያስተማረው ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን በማረጋገጥ አስተማሪው ለወንጌላዊውና ለፓስተሩ መንገድ ያመቻችላቸዋል (ጳውሎስ ስለ አገልግሎት አደረጃጀት በጻፈው መልእክት ውስጥ ወንጌላዊውና ፓስተሩ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም)።
ወንጌላውያንና ፓስተሮች የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምሕሮ ከአስተማሪው መማር አለባቸው። ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ የሆኑትን አስተማሪዎች አንሰማቸውም የሚሉ ከሆኑ የሰውን ንግግር ጥቅስ ወስደው መገጣጠምና እንደየፍላጎታቸው መተርጎም እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ መላ ምቶችን ወደ ማስተማር ፈቀቅ ይላሉ። ዲኖሚኔሽኖች በሙሉ እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው።
የሰውን ንግግር ጥቅሶች በመተርጎም ሒላሪ የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው የተነበዩ የሜሴጅ ፓስተሮች በዚህ ዘመን ለምናየው መጽሐፍ ቅዱስን ያለማወቅ ችግር ዓይነተኛ ምሳሌ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ ሆነውም ግን መሪዎቹ እነርሱ ናቸው! በዚህ ምክንያት ነገሮች ምን ያህል እንደተበላሹ ማሰብ እራሱ አስፈሪ ነው። ለማያስተውሉ ተከታዮቻቸው ሲያቀርቡ የቆዩት ሐሰተኛ ዜና ብቻ ነው። ስለ ታላቁ መከራም እንዲሁ የተሳሳት ትምሕርት ነው የሚያስተምሩዋቸው።
2ኛ ቆሮንቶስ 11፡5 ከእነዚህ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በአንድ ነገር እንኳ እንደ ጎደልሁ ራሴን አልቆጥርም።
ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ በሕዝቡ ዘንድ ታላላቅና ቀደምት ሐዋርያት ተደርገው ቢቆጠሩም እንኳ በአገልግሎታቸው ግን ከእነርሱ ኋላ ዘግይቶ ከመጣውና የቤተክርስቲያን አሳዳጅ ከነበረው ከጳውሎስ ሊበልጡ አልቻሉም።
በቤተክርስቲያን ጅማሬ ላይ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስ ዋነኞቹ ሐዋርያት ነበሩ። ኢየሱስ እራሱ ነበረ በቀጥታ ያሰለጠናቸው። ከዚያ በኋላ ጳውሎስ መጣ ግን ከሐዋርያት አልተማረም። ከእነርሱ ኋላ ተነስቶ ግን በለጣቸው። ያዕቆብ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በሔሮድስ እጅ ተገደለ። ጴጥሮስን ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 12 በኋላ አናገኘውም። ጴጥሮስ አንጾኪያ ውስጥ በነበረ ጊዜ ዘግይቶ የመጣው ጳውሎስ የበዓለ ሃምሳ የመጀመሪያ ሐዋርያ የነበረውን ጴጥሮስን ከስሕተቱ አረመው።
ኬፋ የጴጥሮስ ሌላኛው ስሙ ነው።
ገላትያ 2፡2 እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆን በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው፤ ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
ገላትያ 2፡9 ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
ገላትያ 2፡11 ነገር ግን ኬፋ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና።
ጳውሎስ አገልግሎት በጀመረ ጊዜ ጴጥሮስ ዝነኛ ሐዋርያ ነበረ፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከአእማድ አንዱ ነበረ። ቢሆንም ግን ሰው ስለሆነ ሲሳሳት የሚያርመው ያስፈልገው ነበር።
ሐዋርያው ዮሐንስ አገልግሎቱ መጻሕፍትን በመጻፍ ላይ ያተኮረ ነበረ፤ እርሱም አምስት መጻሕፍትን ጽፏል፤ በተለይ ደግሞ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይ በእስር ቤት በቆየበት ወቅት የዮሐንስ ራዕይ የተባለውን ታላቅ መጽሐፍ ጽፏል።
ጳውሎስ ደግሞ ኔሮ በ68 ዓ.ም ከመሞቱ በፊት በኔሮ እጅ ተገድሏል።
በዚያ ጊዜ ሐዋርያቱ የመጀመሪያዎቹን ቤተክርስቲያኖች ተክለዋል፤ ቤተክርስቲያኖቹም ራሳቸውን መምራትና ወንጌልን ማሰራጨት ጀምረዋል።
የሐዋርያት ሥራ ውስጥ አንድም ጊዜ ፓስተር አልተጠቀሰም።
አንዳንድ ጉዳዮች ሲነሱ ሽማግሌዎች ይወያዩባቸዋል፤ ከሐዋርያትም ምክር ይቀበላሉ።
የሐዋርያት ሥራ 15፡6 ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።
ዛሬም የአጥቢያ ሽማግሌዎች አዲስ ኪዳንን ሲወያዩ ልክ የጥንቷ ቤተክርስቲያን እንዳደረገችው ሐዋርያትን እያማከሩ ናቸው ማለት ነው።
የሐዋርያት ሥራ 15፡7 ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ።
የሐዋርያት ሥራ 15፡12 ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፥ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር።
13 እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ።
ከዚያ በኋላ ሐዋርያው ያዕቆብ የውይይታቸውን ማጠቃለያ አቀረበ። ማጠቃለያውም አሕዛብ ከጣኦት አምልኮ እና ከዝሙት መራቅ አለባቸው የሚለው ነው።
የሐዋርያት ሥራ 15፡19 ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥
20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
የሐዋርያት ሥራ 15፡22 ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።
አንዳንድ ሰዎች በእውቀትና በክሕሎታቸው ላቅ ያሉ ስለነበሩ ጎልተው ይታዩ ነበር። ነገር ግን ከወንድሞች መካከል ተመላለሱ እንጂ ራሳቸውን ከፍ አላደረጉም። በስማቸውም ላይ ምንም የተለየ ማዕረግ አልለጠፉም።
23 እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳን ውስጥ በተጻፈው በሐዋርያት አስተምሕሮ ነበር የተመሰረተችው። ከዚያም እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎችና በወንድሞች ነበር የምትተዳደረው።
የሐዋርያት ሥራ 15፡32 ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።
ነብይ ስለ ወደፊቱ መናገር ይችላል። የነብይ አገልግሎት ስለ ወደፊቱ ከመናገር ስጦታው አንጻር በጣም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ማንም ነብያቱን ሲያናግራቸው “ነብይ አጋቦስ” ወይም “ነብይ ሲላስ” እያለ አልጠራቸውም። ዋነኞቹ ሰዎች አስራ ሁለቱ ሐዋርያት ነበሩ። እነዚህ የተመረጡ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ሰዎች ነበሩ ምክንያቱም የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት እንዲጽፉ ኃላፊነት የተሰጠው ለእነርሱ ነው። እነርሱ ሲሞቱ አዲስ ኪዳንን የመጻፍ ሥራ ተጠናቀቀ።
ከዚያ ወዲያ እጅግ አስፈላጊ የሆነው አገልግሎት የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ነበረ፤ እርሱም የተሰጠው ኃላፊነት በጨለማው ዘመን ጠፍተው የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መግለጥ ነው። እርሱ አንዳችም አዲስ አስተምሕሮ አልፈጠረም። እርሱ ያደረገው አገልግሎት ዓላመው እኛ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እንድንመለስ መርዳት ነው። የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ቤተክርስቲያን ነበረች። የተቻለንን ያህል የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን መከተል አለብን።
የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ብቻ ነበሩ ልዩ ክብር ያላቸው ሰዎች፤ ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስን መጻሕፍት የመጻፍ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
ወንድም ብራንሐም የመጣው እነርሱ የጻፉትን ለመግለጥ ነው። ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳችም አልጨመረበትም፤ ከመጽሐፍ ቅዱስም አንዳች አላጎደለም።
ሌሎቻችን ተራ ሰዎች እንደመሆናችን ሁላችንም እኩል ነን።
እኛ ዋጋ ያለን ክርስቶስ ስለ እኛ ዋጋ ስለከፈለ ነው። ነገር ግን ከአመለካከታችን አንጻር ምንም ዋጋ የለንም፤ ምክንያቱም አመለካከታችን ምንም ትርጉም የለውም፤ ደግሞም ስንሞት አብሮን ይሞታል።
አሁን ያለንባትን የመጨረሻዋን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚያወግዛት ተመልከቱ። ስለዚህች ቤተክርስቲያን የተነገረን ቃል ለብ ያልን እንደሆንን እና ጌታም ተጸይፎ ሊተፋን እንተዘጋጀ ነው። ከዚህ ሁኔ ውጭ የሆነች ቤተክርስቲያን አሁን የለችም። እና ፓስተሮች ከሌላው ክርስቲያን የተለዩ ይመስሉዋችኋል?
ብቸኛው እውነተኛ አገልግሎት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት አስትምሕሮዎች ትክክለኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። አንዳችን ሌላችንን ልናስተምር የምነችለው ሐዋርያት ከጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻ ነው። ወንድም ብራንሐም የተናገራቸውን ንግግሮች በትክክል ከተረዳናቸው መጽሐፍ ቅዱስን ይገልጡልናል።
ወንድም ብራንሐም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንድንመለስ ሊያደርገን ይገባል። የራሱን አመለካከቶች ሊያስተምር አይችልም። የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን እምነቷ ከመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ዓይነት እንዲሆን ማድረግ አለበት።
ማቴዎስ 23፡10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።
ኢየሱስ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት አለቆች ወይም ጌቶች እንዲሆኑ አልፈለገም። “ጌታ” የሚለው ቃል በዚህ ዘመን አነጋገር “አለቃ” ማለት ነው። አዲስ ኪዳን አንዴ በሐዋርያት ከተጻፈ በኋላ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ አንድም ሰው አለቃ እንዲሆን አልፈለገም። የሐዋርያቱ ስራ የእግዚአብሔርን ቃል ለእኛ መንገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ስንታዘዝ እግዚአብሔርን እየታዘዝን ነው እንጂ የጻፉትን ሐዋርያትን እየታዘዝን አይደለንም።
ማቴዎስ 23፡11 ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።
ፓስተሮች ራሳቸውን ከሌሎች አገልጋዮችና ከጉባኤው በላይ ከፍ ያደርጋሉ። ይህ ስሕተት ነው። አገልጋይ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ባሪያ ነው። አገልጋይ ራሱን ታላቅ አያደርግም። ራስን ከፍ ማድረግ እርግማን ነው።
ማቴዎስ 23፡12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
ሰባኪዎች በሰው ዓይን ውስጥ ለመግባትና የተቻላቸውን ያህል ብዙ ገንዘብ ለመሰብሰው ብለው ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
ሰባኪዎች ታላቅ ሰዎች ናቸው ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ግን እንደዚያ አያስብም።
ማቴዎስ 18፡1 በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት።
በቁጥር ጥቂት የነበሩት ሐዋርያት ገና ከመጀመሪያቸው አንስተው አንዳቸው ከሌላቸው እንደሚበልጡ በማሰብ ተጠምደው ነበረ። ኢየሱስ በዚህ ሃሳባቸው አልተሳበም። በመካከላቸው የነበረው ሽኩቻ ግን በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ያለውን መሰረታዊ ችግር ይገልጣል። ሰዎች በተፈጥሮዋችን ራሳችንን እንወዳለን፤ ታላቅ መሆንን እንፈልጋለን። ለዚህ ነው ሰዎች “ሰልፊ” የሚነሱት፤ ራሳቸውን በሞባይል ፎቶ የሚያነሱት። እዩኝ! ማለታቸው ነው። የሌሎችን ትኩረት ወደ ራሳቸው ለመሳብ መፈለጋቸው አሳዛኝ ነገር ነው።
ከሁሉ በላይ የሚያስቀው ራሱን ሰልፊ ፎቶ ያነሳው ዝንጀሮ ጉዳይ ነው። ይህ የዝንጀሮ ፎቶ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” ተብሎ ተመረጧል። የአንድ ዝንጀሮ ፎቶ የብዙ ራስ ወዳድ ሰዎችን ሰልፊ ሁሉ አሸንፎ አንደኛ ወጣ። በዚህ ውስጥ እንኳ እግዚአብሔር የሆነ ነገር ሊነግረን እየሞከረ ነው።
ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ውስጥ እኔነትን ነቅሎ ለማውጣት ፈልጓል፤ ምክንያቱም ኋላ ከጲላጦስ ፍርድ ወንበር ፊት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ጥላቻ በእርሱ ላይ እንደ ጎርፍ ሲወርድበት ደቀመዛሙቱ እግሬ አውጭኝ ብለው እንደሚሸሹ ቀድሞ ተረድቷል። ይህም በትዕቢት ተወጥሮ የነበረውን ልባቸውን አስተነፈሰው። መከራ ፍጥጥ ብሎ በመጣባቸው ጊዜ በፍጥነት እየፈረጠጡ ጠፉ። ከዚያ በፊት ግን እራሳቸውን እንደ ታላላቅ ሰዎች አድርገው ቆጥረው ነበር።
አንድ ቀን ወደ ቅፍርናሆም ከተማ እየሄዱ ሳሉ በመንገዳቸው ሁሉ ከእነርሱ መካከል ማን ታላቅ እንደሆነ ነበር የሚከራከሩት። ይህ በጣም የሚያሳፍር ነገር ነበር። ስለ ምን እየተከራከሩ እንደበር ኢየሱስ ሲጠይቃቸው በጣም አፍረው ጸጥ አሉ። አንድን ፓስተር ከኢየሱስ ጎን አቁማችሁ አስቡትና የዛኔ ከኢየሱስ ጋር ሲወዳደር ፓስተሩ ምን ያህል የማይረባ ተራ ሰው መሆኑን ትገነዘባላችሁ።
ሰዎች ዋጋ ሊኖረን የቻለው ክርስቶስ ስለ እኛ ታላቅ ዋጋ ስለከፈለ ነው። በራሳችን ግን ዋጋ ቢስ ነን፤ ምክንያቱም አመለካከቶቻችን ምንም ዋጋ የላቸውም።
ማርቆስ 9፡33 ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው።
34 እነርሱ ግን በመንገድ፦ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ።
እነርሱ ግን ቶሎ አይገባቸውም ነበር።
ታላቅነትን መፈለጋችን ሰዎች ሁሉ በተፈጥሮአችን ያለብን ችግር ነው።
የያዕቆብና የዮሐንስ እናት ሁለቱ ልጆቿ ከሌሎች ሁሉ ከፍ እንዲደረጉላት ጠየቀች።
ማቴዎስ 20፡21 እርሱም፦ ምን ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም፦ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ አለችው።
እርሷ አላወቀችም እንጂ ከሁሉ በፊት መጀመሪያ የሚገደለው ሐዋርያ ልጇ ያዕቆብ ነበር። ስለዚህ አገልግሎቱ ከእርሱ ይልቅ እጅግ አስደናቂ በሆነው በጳውሎስ አገልግሎት የተነሳ ይደበዝዛል። የሐዋርያት ሥራን አንብባችሁ ስትጨርሱ ከሁሉ ደምቆ የወጣው ሐዋርያ ጳውሎስ እንጂ ያዕቆብ እንዳልሆነ በግልጽ ማየት ትችላላችሁ። እራሷንና ቤተሰቧን ከሁሉ አስበልጣ የምታየዋ እናት መጨረሻዋ ይህ ሆነ።
ታላቅነት ከቤተሰባዊ ትስስር ጋር እንዴት እንደሚያያዝ አስተውሉ። ቤተሰቤ ታለቅና ታዋቂ እንዲሆን እፈልጋለሁ። የኔ ቤተሰብ ከናንተ ቤተሰብ ይበልጣል። ለራስ ወገን ማድላት በሰው ታሪክ ውስጥ አሳዛኝ ጠባሳዎችን አሳርፏል። ለዘመድ ማድላት የሙስና ስርና መሰረት ነው። አባት እና ልጅ ሁለቱም ፓስተር የሚሆኑበት አሰራር የዘመድ ቤት አሰራር ነው። ይህም ገንዘቡ ከቤተሰቡ እጅ እንዳይወጣ ማድረጊያ ዘዴ ነው። ቤተክርስቲያን ምን ያህል ነው ከእውነት ርቃ የወደቀችው?
ኢየሱስ ሴትየዋንም ሆነ ልጆቿን አላደነቀም።
ኋላ የሐዋርያት ሥራ ውስጥ ይህን ታያላችሁ፡-
የሐዋርያት ሥራ 15፡36 ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ አለው።
አንድም ከተማ ውስጥ ፓስተሮችን በኃላፊነት አስቀምጠው አልሄዱም።
የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥
በኃላፊነት ቦታ ተቀምጦ ትዕዛዝ የሚሰጥ ፓስተር የለም።
ወንድሞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወስኑ በሕብረት እየተጋገዙ ነበር የሚሰሩት።
የሐዋርያት ሥራ 17፡14 በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ።
ምን መደረግ እንዳለበት በወንድማማች መካከል ውይይት ተደረገ። አጥቢያ ቤተክርስቲያን የራሷን ውሳኔ አደረገች። አንድም እንደ አለቃ ተቀምጦ ትዕዛዝ የሚሰጥ ፓስተር አልነበረም። የትኛውም ታላቅ አገልጋይ ሌላ ከተማ ውስጥ ተቀምጦ ትዕዛዝ አላስተላለፈላቸውም።
ሲላስ እና ጢሞቴዎስ በራሳቸው አመራር ለመንቀሳቀስ ነጻ ነበሩ።
እግዚአብሔር ነበር ቤተክርስቲያንን የመራት እንጂ የሆነ ሰው አልነበረም።
የሐዋርያት ሥራ 18፡27 እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አጸናኑት፥ ይቀበሉትም ዘንድ ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤
ወንድሞች ውሳኔ ለማድረግ የነበራቸውን ነጻነት ተመልከቱ። አንድም ሰው በመካከላቸው አለቃ አልነበረም።
ውሳኔ ማድረግ ሲያስፈልጋቸው ፓስተሩን ወይም ዋናውን እንጠይቅ ብለው እንደማያውቁ ልብ በሉ። ለዚህ ነው የጥንቷ ቤተክርስቲያን በአገልግሎቷ ውጤታማ የነበረችው።
የሐዋርያት ሥራ 21፡17 ወደ ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።
18 በነገውም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ዘንድ ገባ ሽማግሌዎችም ሁሉ መጡ።
ያዕቆብ ሐዋርያ ነበረ። የቀሩት ሽማግሌዎችና ወንድሞች ነበሩ። እንደ ዛሬዎቹ አገልጋዮች በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ የተሾሙ ፓስተሮችና ዋናው ፓስተር ካሳለፈው ውሳኔ ጋር ካልተስማሙ በቀር ማገልገል የማይፈቀድላቸው ሰዎች አልነበሩም።
ዛሬ ቤተክርስቲያኖች በአሮን ሹመት የተሾሙ ካሕናትንና አምስት አገልግሎቶችን ከጉባኤው በላይ ከፍ ያደርጋሉ። ፓስተሩ ደግሞ ከአምስቱ አገልግሎቶችም በላይ ከፍ ይደረጋል።
ያለ ጥርጥር የቤተክርስቲያንን አወቃቀር አበላሽተናል።
የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያኖች ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው በመሾም የሮማ ካቶሊክን ዲኖሚኔሽናዊ አሰራር ይከተላሉ። የጋለሞታዎች እናት ጋለሞታ የሆኑትን ልጆቿን ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች የሰው ልማዶችን እና ስርዓቶች መከተል አስተምራቸዋለች።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
መጽሐፍ ቅዱስ ዳግመኛ ስለተወለድን የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንደተጠራንና ስለዚህም ወንድማማቾች እንደሆነን ይናገራል። ወንድማማችነት እኩልነት ነው።
ሮሜ 8፡29 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
አስቀድሞ መወሰን ማለት ከመካከላቸን ታላቅ ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ከወንድሞች ሁሉ የበኩር እርሱ ነው። ከዚህ ውጭ በወንድሞች መካከል መበላለጥ ወይም የስልጣን ተዋረድ የለም፤ ፓስተሩ ከሁሉ በላይ የተቀመጠበት እርከንም የለም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በትንንሽ ሕብረቶች በየቤቱ ነበር የምትሰበሰበው።
1ኛ ቆሮንቶስ 16፡19 የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
ሮማውያን ክርስቲያኖችን እስከ 312 ዓ.ም ድረስ አሳደዱዋቸው። ስለዚህ ክርስቲያኖች በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ አይሰበሰቡም ነበር፤ ምክንያቱም በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ መሰብሰብ በቀላሉ ያስይዛል። በየቤቱ በመሰብሰብ አማኞች የአሳዳጆቻቸው ዓይን ውስጥ ቶሎ ከመግባት ይተርፋሉ።
ከዚያ በኋላ በክርስትና ውስጥ ፉክክር ተጀመረ። ይህም ቤተክርስቲያናዊነት ይባላል። የኛ ቤተክርስቲያን ከናንተ ቤተክርስቲያን ትሻላለች። የኛ ፓስተር ከናንተ ፓስተር ይሻላል። የቀሎዔ ቤት ውስጥ ይሰበሰቡ የነበሩ አማኞች (ቤተክርስቲያን) ሌሎች ሕብረቶች አብሮዋቸው ከሚገኝ ስመ ጥር ሰው የተነሳ ከእነርሱ እንበልጣለን እንደሚሉ ለጳውሎስ ነግረውታል።
1ኛ ቆሮንቶስ 1፡11 ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና።
12 ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ።
አንድ ቤተክርስቲያን ከሌላ ቤተክርስቲያን እበልጣለሁ ብላ መፎካከሩዋን ጳውሎስ ምንም አልወደደውም። አንድ መሪ ከሌላ መሪ እበልጣለሁ ማለቱ በእውነተኛ አማኞች መካከል ተቀባይነት የለውም።
1ኛ ቆሮንቶስ 4፡6 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ፦ ከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።
የትኛውም ክርስቲያን ወይም የትኛውም ፓስተር ታላቅ ነኝ ብሎ በትዕቢት መነፋት የለበትም። ፓስተር የሚለው ቃል እራሱ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ብሉይ ኪዳን ውስጥ በኤርምያስ ብቻ ስድስት ጊዜ ተወግዟል። ስለዚህ ቤተክርስቲያንን መግዛት ያለበት እንዲህ ብዙ የተወገዘ የአገልግሎት ዘርፍ አይደለም።
1ኛ ቆሮንቶስ 14፡26 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን።
ጳውሎስ ወንድሞች ሁሉ በአገልግሎት ውስጥ እንዲሳተፉ ይፈልጋል። ፓስተሩ የበላይ ሆኖ ስብከቶችን ሁሉ እርሱ ብቻ ያቅርብ፤ ሕዝቡ ደግሞ ተቀምጠው እንደ እስፖንጅ ፓስተሩ የሰበከውን ሁሉ ይጠጡ አላለም ጳውሎስ።
ገላትያ 4፡28 እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
ክርስቲያኖች ሁሉ እኩል ነን፤ ምክንያቱም ሁላችንም እግዚአብሔር ለየዘመናቱ ሊሰጥ ቃል የገባውን አብረን የምንቀበል ልጆች ነን።
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አንድ ልጅ ከሌሎች ልጆች የበለጠ አስፈላጊ አይደለም።
ቆላስይስ 1፡1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ጢሞቴዎስም ወንድሙ፥
2 በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤
ጳውሎስ እራሱን ሐዋርያ ይላል። እርሱ ሐዋርያ ነው። ጢሞቴዎች ታላቅ ሰው ቢሆንም እንኳ ወንድም ነው የተባለው። የቆላስይስ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ክርስቲያኖ በሙሉ ቅዱሳን እና ወንድሞች ተብለው ነው የተጠሩት።
አንድም ከሌሎች በላይ ከፍ ያለ ፓስተር አልተጠቀሰም። ትሑት ፓስተር እንኳ አልተጠቀሰም።
ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
ሎዶቅያ ከተማ ውስት ፓስተር አንዴም አልተጠቀሰም። ይህ አሁን ለምንኖርበት የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ነው። ክርስቲያኖች ወንድሞች ብቻ ተብለው ነው የሚጠሩት። በንምፉ ቤት እንደ ቤተክርስቲያን የሚሰበሰቡ የአማኞች ሕብረት ነበሩ።
ትንንሽ ሕብረቶች በየሰዉ ቤት መሰብሰባቸው ለሎዶቅያ የቤተክርስቲያን ዘመን ትልቅ ሞዴል ነው። በመካከላቸው እንደ አለቃ የሚገዙ ፓስተሮች አልነበሩም። በዚህኛው ሕብረት ውስጥ የሚሳተፍ የትኛውም ታላቅ ነኝ የሚል ሰው በዚያኛው ትንሽ ሕብረት ውስጥ በሚሰበሰቡ ሰዎች ላይ አለቃችሁ ነኝ ሊል አይችልም። እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በራሷ ሽማግሌዎች ነበር የምትመራው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡1 ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥
ሽማግሌዎች ታላላቅ ወንድሞች ናቸው። በእምነታቸው የበሰሉና ልምድ ያላቸው ሰዎች ናቸው።
1ኛ ተሰሎንቄ 5፡12 ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም ታውቁ ዘንድ፥ ስለ ሥራቸውም በፍቅር ከመጠን ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን።
በተሰሎንቄ ከተማ ውስጥ ቤተክርስቲያንን ይመሩ የነበሩ በቁጥር ብዙ ሰዎች ነበሩ እንጂ አንድ ሰው አይደለም።
“በጌታ”። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን እየጠቀሱ ብቻ ነበር መግዛት የሚችሉት።
እነርሱ ማን ነበሩ?
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
ቤተክርስቲያንን ይመሩዋት የነበሩት ሽማግሌዎች ናቸው።
ከነዚህ ሽማግሌዎች አንዳንዶቹ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች ናቸው። ነገር ግን ሁሉም ሰባኪዎችና አስተማሪዎች አልነበሩም። ሁሉም ሽማግሌዎች ክብር የሚገባቸው ሰዎች ናቸው፤ በተለይ ግን የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩ ሽማግሌዎች የሚበልጥ ክብር ይገባቸዋል።
የማይሰብኩትም ሽማግሌዎች ቢሆኑ ቤተክርስቲያንን በመምራት ውስጥ የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ።
ብዙ ሽማግሌዎች በሕብረት ቤተክርስቲያንን ይመራሉ፤ ነገር ግን በዚህ ውስጥ ቤተክርስቲያንን የሚቆጣጠር ፓስተር አልተጠቀሰም።
ያዕቆብ 3፡1 ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፥ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።
የትምሕርት ቤት አስተማሪዎች ያስተምራሉ። አስተማሪዎች እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራሉ። ነገር ግን ማናችሁም ብትሆኑ ወደ ማስተማረ አገልግሎት ፈጥናችሁ አትግቡ። ትምሕርትን አሳስተው የሚያስተምሩ ሰዎች ከበድ ያለ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ማስተማር ማለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማገናኘትና መግለጥ ነው እንጂ የሰው ንግግር ጥቅሶችን እየወሰዱ ማገጣጠም አይደለም።
የሐዋርያት ሥራ 16፡5 አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።
ጳውሎስ ኤፌሶን ውስጥ ቤተክርስቲያንን ለመመስረት የተከተለው ዘዴ ምንድነው?
ይህች ቤተክርስቲያን ለኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን እና ከዚያ ወዲያ ተከትለዋት ለመጡት የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ሞዴል ናት።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
መንጋውን ማለትም ኤፌሶን ውስጥ ያለችዋን የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መጠበቅ የእረኛ ኃላፊነት ነው፤ ነገር ግን ይህ ኃላፊነት ለአንድ ግለሰብ አልተሰጠም። ይህ በኤፌሶን ላሉ የሽማግሌዎች ሕብረት የተሰጠ ስራ ነው። ሽማግሌዎች ኃላፊዎች ወይም ኤጲስ ቆጶሳት ናቸው።
የሐዋርያት ሥራ 20፡29 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ … እኔ አውቃለሁ።
የክርስቲያኖች መንጋ ለተኩላ ቀላል ኢላማ ነው። የተኩላ መንጋ በአንድ ብርቱና ጨካኝ ተኩላ ነው የሚመራው። ስለዚህ ተኩላ የሆነ ፓስተር ከመንጋው ውስጥ የሚቃወመውን ያጠፋል፤ ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ያልሰጠውን ስልጣን ወስዶ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ይላል። በጣም አደገኛ በሆነ ዘመን እየኖርን ነን።
የአዲስ ኪዳን ጅማሬ አካባቢ ጳውሎስ ያስተማረው ይህንን ነው።
በአዲስ ኪዳን መጨረሻ አካባቢ ጴጥሮስ ምን እንዳለ እንመልከት።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
4 የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
ጴጥሮስ ሽማግሌዎችን የራሱ አቻ አድርጎ ነው የሚያያቸው። ምንም ዓይነት የማዕረግ ልዩነት አላደረገም። እራሱን እንደ ሐዋርያ ከፍ አላደረገም።
“በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ።” ይህ የእረኛ ስራ ነው። ይህ የአንድ ግለሰብ ብቻ ስራ አይደለም። ሽማግሌዎች በሕብረት ተጋግዘው የሚሰሩት ስራ ነው። እዚህ አገልግሎት ውስጥ ፓስተር አልተጠቀሰም። ጴጥሮስ ማንም በሕዝቡ ላይ አለቃ መሆን እንደሌለበት በጥብቅ ያስጠነቅቃል። የትኛዋም ቤተክርስቲያን አንድ አለቃ አያስፈልጋትም።
ቤተክርስቲያን ውስጥ ምንም የስልጣን ተዋረድ የለም። የተለያዩ ሽማግሌዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ያከናውናሉ። ሌሎች ሽማግሌዎች የተለየ የስብከት አገልግሎት የላቸውም። ልዩ ልዩ አገልግሎቶችና ኃላፊነቶች አሉ፤ ነገር ግን ሁላቸውም አንድ ሹመት ነው ያላቸው፤ ማለትም ሽማግሌ ናቸው።
ነገር ግን ሽማግሌዎች በሙሉ ከጉባኤው መካከል ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ቃል ስሕተታቸውን ቢያርማቸው መቀበል ግዴታቸው ነው።
ማንኛውም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል መጥቀስ ለሚችል ለማንኛውም ሰው መገዛት አለበት። አለቃ የለም። ዋና የተባለ የለም። ፈላጭ ቆራጭ የለም።
አፍሪካ ውስጥ ሙጋቤ የተባለው ፈላጭ ቆራጭ መሪ መውደቁ ለቤተክርስቲያናት ጊዜውን የሚያሳይ ምልክት ነው። ፈላጭ ቆራጮች ተፈላጊ አይደሉም።
ከዚያ ጴጥሮስ እውነተኛውን እረኛ ይጠቅሳል፤ እርሱም ኢየሱስ ነው። “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው”።
ኤጲስ ቆጶስ ሽማግሌ ነው፤ ምክንያቱም ወደ አገልግሎት የሚገባበት መስፈር ከዲያቆን ጋር አንድ ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡2 እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
3 የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥
4 ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡8 እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥
11 እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
12 ዲያቆናት ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤቶች በመልካም እየገዙ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።
1957-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1
የአጥቢያ ጉባኤ ሙሉ ስልጣን አለው ብዬ አምናለሁ። አዎ። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ነጻ ሆና ራሷን ታስተዳድር፤ የራሷ ፓስተሮች፣ የራሷን ዲያቆናት፣ የራሷን አገልጋዮች እየመረጠች ትሹም። በዚህ መንገድ ከተንቀሳቀሰች በውስጧ ያሉ ሰዎች በላያቸው ጳጳስ አይነግስባቸውም። ለዚያች ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ እራሱ ሲፈልግ ይናገራታል እንጂ ይህን ወይም ያን ማድረግ ይችሉ እንደሆን ማንንም መጠየቅ አያስፈልጋቸውም። እያንዳንዱ ሰው በግሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ይገናኛል። በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአጥቢያዋ ሽማግሌ የሚበልጥ ማን እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ። እውነቴን ነው ወገኖች፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነጻ መሆን አለባት፤ እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራሷን ታስተዳድር። ወንድማማችነት መልካም ነው። ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በወንድማማችነት መንፈስ መተያየትና መደጋገፍ አለባቸው። ሆኖም ግን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ራሷን በራሷ ማስተዳደር አለባት።
የኒቆላውያን አስተምሕሮ አንድን ሰው ከፍ ያደርግና የቤተክርስቲያን አለቃ ያደርገዋል።
1965 የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 5
ይህ አስተምሕሮ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በወጣ ደምብ ነው የተጀመረው። ችግሩ ያለው በሁለት ቃላት ውስጥ ነው፡- እነርሱም “ሽማግሌዎች” (ፕሬስቢተርስ) እና “ጠባቂዎች” (ቢሾፕስ) ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሽማግሌዎች እንዳሉ ቢያሳይም አንዳንዶች (ከእነርሱም መካከል ኢግናሺየስ አንዱ ነው) ቢሾፕ ወይም ጳጳስ ከፍ ያለ ከሽማግሌዎችም በላይ የሆነ ሥልጣን ያለው አገልጋይ ነው ብለው ማስተማር ጀመሩ።
እውነታው ግን ምን መሰላችሁ፤ “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ሰውየውን የሚያመለክት ሲሆን ቢሾፕ ወይም ጳጳስ የሚለው ቃል ግን የዚህኑ ሽማግሌ የአገልግሎት ክፍል ወይም ዘርፍ የሚያመለክት ቃል ነው። ሽማግሌው ሰውየው ነው። ቢሾፕ የሰውየው የአገልግሎት ዘርፍ ነው። “ሽማግሌ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰውየው በጌታ ሆኖ ያሳለፋቸውን ዓመታት ብዛት ነው። የዚህ ቃል ትርጉሙ በፊትም ሁልጊዜም እንደዚሁ ነው። ሰውየው ሽማግሌ የሆነው ስለተመረጠ ወይም ስለተቀባ አይደለም፤ ነገር ግን በጌታ ሆኖ ከሌሎች በላይ እድሜ የገፋ ስለሆነ ነው። ይህ ሰው ከሌሎች ይልቅ የበሰለ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በደምብ የተማረ፣ ሊታመን የሚችል፣ ጀማሪ ወይም አዲስ ክርስቲያን ያልሆነ ነው፤ ልምድ ያለው እና በረጅም ዓመታት የክርስትና ሕይወቱ የተመሰከረለት ሰው ነው።
ነገር ግን ጳጳሳቱ የጳውሎስን መልእክቶች መከተል አቁመዋል፤ መልእክቱን ትተው ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20 ውስጥ ሽማግሌዎችን ከኤፌሶን ወደ ሚሊጢን ያስጠራበት ታሪክ ላይ ብቻ አተኮሩበት። ቁጥር 17 “ሽማግሌዎች” መጠራታቸውን ይናገርና እነዚሁ ሽማግሌዎች ደግሞ በቁጥር 28 ጠባቂዎች (ጳጳሳት) ተብለው መጠራታቸውን ያሳያል። እነዚህ ጳጳሳት (ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የተሞሉ እና የሥልጣን ጥማት እንደነበራቸው አያጠራጥርም) ጳውሎስ “ጠባቂዎች” ወይም ጳጳሳት ለሚለው ቃል የአንድ ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ብቻ ከሚለው ትርጉም የበለጠ ትርጉም ሰጥቷል ብለው በመከራከር የጳጳሳት ሥልጣን ከአንድ ቤተክርስቲያን የሚያልፍ ነው አሉ። ስለዚህ በእነርሱ አስተሳሰብ ጳጳስ ማለት ከአንድ ቤተክርስቲያን አልፎ በብዙ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ላይ ስልጣን ያለው ሰው ነው። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በታሪክ አይታወቅም፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም፤ ነገር ግን ፖሊካርፕ እንኳ ሳይቀር በዚህ የተሳሳተ አቋም ተስቧል።
ጳውሎስ ከኤፌሶን ከተማ የጠራቸው ብዙ ሽማግሌዎች ነበሩ። የቤተክርስቲያን አገልግሎት የአንድ ግለሰብ ትወና አይደለም።
ቤተክርስቲያንን በሙሉ የአንድ ቄስ ወይም ፓስተር የተባለ ሰው ባሪያ የማድረግ አሰራር እንደዚህ ነው የተጀመረው። ቀጥሎ ደግሞ ቄሶችን ወይም ፓስተሮችን የሚቆጣጠር ጳጳስ ተነሳ። (አልፎ አልፎ ይህ ሰው በጳጳስ ፈንታ ሐዋርያ እየተባለ ይጠራል)። ከዚያ በኋላ ደግሞ በጳጳሳት ላይ አለቃ ነኝ የሚል ሊቀ ጳጳስ ተነሳ። በ700 ዓ.ም አካባቢ ደግሞ ሊቀ ጳጳሳትን የሚቆጣጠር ካርዲናል ተሾመ። ከሁሉ በላይ ደግሞ ፖፑ በካርዲናሎች ላይ አለቃ ሆነ።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን በአንድ ከተማ ውስጥ ያሉ ቤተክርስቲያኖች በአንድ ጳጳስ ስር ሆነው አያውቁም።
ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
ይህ ጥቅስ በፊልጵስዩስ ከተማ ብዙ ኤጲስ ቆጶሳት እንደነበሩ ያሳያል። እነዚህ ኤጲስ ቆጶሳት ማለት ሽማግሌዎች ናቸው።
እና ዲያቆናት እነማን ናቸው?
ዲያቆናት በየቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የቁሳቁስ እና የገንዘብ ችግር እንዲፈቱ የተመረጡ ሽማግሌዎች ናቸው። በአማኞች መካከል የተለያዩ ነገሮችን ለምሳሌ ምግብ ማከፋፈል የዲያቆናት ኃላፊነት ነው።
የሐዋርያት ሥራ 6፡1 በዚህም ወራት ደቀ መዛሙርት እየበዙ ሲሄዱ ከግሪክ አገር መጥተው የነበሩት አይሁድ በይሁዳ ኖረው በነበሩት አይሁድ አንጐራጐሩባቸው፥ በየቀኑ በተሠራው አገልግሎት መበለቶቻቸውን ችላ ይሉባቸው ነበርና።
አስተውሉ፤ ትንንሽ የነበሩ ቡድኖች በቁጥር እያደጉ ሲመጡ በመካከላቸው ችግር እየሰፋ ሄ።
2 አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።
3 ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤
ቤተክርስቲያኖች ጉባኤያቸው ጥቂት ሰው በሆነ ጊዜ ሁሉ ዲያቆናትን መሾም አላስፈለጋቸውም።
በኢየሩሳሌም የነበረችዋ ቤተክርስቲያን በሰዎች ቁጥር አደገችና እናት ቤተክርስቲያን ነኝ ማለት ቻለች፤ በዚህም ክብርን አገኘች። ስለዚህ በ70 ዓ.ም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን አፈራረሳት፤ እዚያ ተከማችተው የነበሩ ክርስቲያኖችን በፍጥነት ተበታትነው በየስፍራው ሁሉ ሄዱ።
1962 06 01 ከኢየሱስ ጋር መወገን
እነዚያ የጥንት ሰዎች ሲወጡ አንዳንዴ ስድስት አንዳንዴ ደግሞ ስምነት ብቻ ሆነው ይወጡ እንደ ነበር ታውቃላችሁ? ጥቂት ሆነው ግን ሃገሩን በሙሉ አንቀጠቀጡ። እንደምታውቁት በአቂላ እና ጵርስቅላ ዘንድ አጵሎስ የጀመረው ታላቅ መነቃቃት ውስጥ በዚያች ቤተክርስቲያን የነበረው የሕዝብ ብዛት ስድስት ወይም ስምንት ወንዶችና ሴቶች ብቻ ነበሩ። አንድ ቤተክርስቲያን ሙሉ ማለት ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ። አሁን እዚህ ጉባኤ ውስጥ የተሰበሰብን ሰዎች በዚያች ቤተክርስቲያን ከነበሩ ሰዎች በቁጥር ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ እንበልጣለን።
እንደምታውቁት የኢየሱስ ደቀመዛሙርት አስራ ሁለት ብቻ ነበሩ። እኛ ሁልጊዜ ትልቅ ነገር ብቻ ነው የምናስበው። እግዚአብሔር ግን ሲሰራ በሕዝብ ብዛት አይደገፍም። እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራው በጥቂት ሰዎች አማካኝነት ነው። አያችሁ? በየዘመናቱ ሰዎችን ያናገረበትን ጊዜ ተመልከቱ። ሁልጊዜ ጌታ ይሰራ የነበረው ከጥቂት ሰዎች ጋር ነው፤ እነርሱን ይጠራል፤ ያናግራል፤ ለአገልግሎት ይልካል። በዚህ መንገድ መስራት የእግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ነው። እንዲህ መስራት ነው እርሱ የሚወደው። እኛ ደግሞ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን እንዲሆንና ለስራ እንዲልከን እንፈልጋለን።
እግዚአብሔር በትንንሽ ቡድኖች መካከል ውጤታማ ስራ ይሰራል። ትልልቅ ቤተክርስቲያኖች ግን በውስጣቸው የማመቻመች መንፈስ አለባቸው።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
ዘካርያስ 4፡10 የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፤ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
ኢሳይያስ 1፡9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።
ስለዚህ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች እግዚአብሔርን በማገልገል ውጤታማ መሆን ይችላሉ።
ማቴዎስ 23፡2 ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።
ወንበር ስልጣንን ይወክላል።
ፈሪሳውያን በአይሁድ ምኩራቦች ውስጥ እራሳቸውን አንድ መሪ አድርገው አስቀመጡ። ስልጣናቸውን ያገኙት ነብዩን ሙሴን በመጥቀስ ነው። “ነብዩ እንዲህ ብሏል …”። “ነብዩ እንዳለው …”። በዚህ መሃል የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን ሳይቀበሉት ቀሩ።
ልክ እንደዚሁ ዛሬም ፓስተሮች በወንድም ብራንሐም የስልጣን ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።
ስልጣናቸውን ያገኙት ነብዩ ዊልያም ብራንሐም የተናገረውን በመጥቀስ ነው። “ነብዩ እንዲህ ብሏል …”። “ነብዩ እንደተናገረው …”።
በዚህ መሃል የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ሳይቀበሉ ይቀራሉ።
ማቴዎስ 23፡6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥
ማቴዎስ 23፡7 በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
የቤተክርስቲያን መሪዎች የሁሉ ታላቅ መሀን ይፈልጋሉ። መድረክ ላይ ወንበር እንዲዘጋጅላቸው ይፈልጋሉ። ፊትለፊት ጉባኤውን እያዩ መቀመጥ ይወዳሉ። ከፍ ብለው ወይም ከጉባኤው ተለይተው መቀመጥ ይወዳሉ። ስታናግሩዋቸው ወይም ስለ እነርሱ ስታወሩ ከስማቸው ላይ “ፓስተር” የሚለውን ማዕረግ እንድትለጥፉላቸው ይፈልጋሉ። ፓስተር እከሌ፤ ፓስተር እንዲህና እንዲያ ብሎ እየተባለ ፓስተር የሚለው ማዕረግ ብዙ ጊዜ ይደጋገማል።
ሌሎች አገልጋዮች ይህን አያደርጉም።
ማቴዎስ 23፡8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
በአይሁዶች መካከል ኢየሱስን እንዲክዱ ያደረጉዋቸው ረቢዎቹ ናቸው። ስለዚህ ረቢ ከተባለው ማዕረግ ራቅ በሉ።
በአሕዛብ መካከል ደግሞ ከተጻፈው ቃል እንድትርቁ እና በሰው ንግግር ጥቅስ እንድትተኩት የሚያስቷችሁ ፓስተሮች ናቸው። ስለዚህ ፓስተሩ ስክ እንደ ረቢው አሳሳች ሰው ነው።
የሐዋርያት ሥራ 8፡1 በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።
ወንጌልን ለመስበክ ምንም ፈቃድ አያስፈልግም።
ዝም ብለው እየሄዱ ይሰብኩ ነበር።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲሰደዱና ለነፍሳቸው ብለው ሮጠው እንዲበታተኑ አደረገ። በየደረሱበትም ወንጌልን ሰበኩ። ታላቅ እንቅስቃሴ ጀመሩ። ወዴት እንደሚሄዱ ማንም ሊቆጣጠር አልቻለም።
በ64 ዓ.ም ከኔሮ ጀምሮ የሮማ ነገስታት ሶስት ሚሊዮን ክርስቲያኖችን ገድለዋል። ይህን ጭፍጨፋ በስተመጨረሻ ንጉስ ኮንስታንቲን ነው በ312 ዓ.ም ያስቆመው። ስለዚህ በዚያ ዘመን ክርስቲያን መሆን ብቻ አደጋ አለው። ስደት በማንኛውም ጊዜ በድንገት ሊነሳ ይችላል። ብዙ ክርስቲያኖች በትልቅ “የቤተክርስቲያን” ሕንጻ ውስጥ ቢሰበሰቡ ሮማውያን ለመያዝና ለማሰር ሲፈልጉ በቀላሉ ያገኙዋቸዋል። ክርስቲያኖች በአካባቢያቸው ስደት በሚነሳ ጊዜ ወዲያው ሸሽተው ማምለጥ አለባቸው። ነውጥ እና ስደት ብዙ ጊዜ ስለሚነሳ በአንድ ቡድን ለአምልኮ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሁልጊዜ ጥቂት ነበሩ። ወዲያውም ደግሞ ይበተኑ ነበር። ከዚህም የተነሳ መሪዎች ተነስተው በቀላሉ በቤተክርስቲያኖች ላይ አለቃ የመሆን ዕድል አልነበራቸውም።
ሁለተኛው ማለትም በ312 ዓ.ም በተጠናቀቀው የሰምርኔስ የቤተክርስቲያን ዘመን (ሰምርኔስ ምሬትና ሞት ማለት ነው) እግዚአብሔር ካልነቀፋቸው ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት አንዱ ነው። ለነፍሳቸው ብለው ከስደት ለማምለጥ መሮጣቸው የሰዎችን ወይም የመሪዎችን ስም የሚያስጠራ ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ለመስራት ጊዜ አልሰጣቸውም።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
ይህ አምስት አገልግሎት የሚከናወነው እንዴት ነው?
የመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ የተነሱ ሌሎች ሐዋርያት ሚሽነሪዎች ወይም ወንጌል ሰባኪዎች ነው የሚባሉት። እነዚህ የሆነ ሃገር ሄደው በመቆየት ወንጌልን እየሰበኩ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።
ነብያት። ይህ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል የሚከናወን አገልግሎት ሲሆን ጥቅሙ ወደፊት ሊሆኑ ያላቸውን ነገሮች አስቀድሞ በመግለጥ ቤተክርስቲያን እንድትዘጋጅ መርዳት ነው። ይህ አገልግሎት እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ በነቢያት በኩል ለግለሰቦች የሚልክላቸውን የግል መልእክት ያካትታል።
ወንጌላውያን ሐጥያተኞችን ወደ ክርስቶስ እያመለከቱ እንዲድኑ እያደረጉዋቸው ወደ ጌታ ቤት ያስገቡዋቸዋል።
የፓስተሮች አገልግሎት አማኞች በግል እና በቤተሰብ ዙርያ የሚገጥሟቸውን ችግሮች አድምጦ ማማከርና መፍትሄ ማሳየት ነው። እምነታቸው ይጠነክር ዘንድ በክርስቶስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስተምሯቸዋል።
እምነት የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ብቻ ነው የሚመጣው እንጂ የሰዎችን አመለካከት እና ልማድ በመስማት አይደለም።
የተወሰኑ መሰረታዊ የሆኑ አስተምሕሮዎች አሉ። እነርሱም ንሰሃ፣ እምነት፣ ጥምቀቶች፣ እጆችን መጫን፣ ትንሳኤ፣ እና ፍርድ ናቸው።
የፓስተርነትን አገልግሎት በትክክል እየፈጸመ የሚያገለግል ፓስተር ለአዲስ አማኞች በነዚህ ርዕሶች ላይ መሰረት የሚያስይዝ እውቀት ይሰጣቸዋል፤ ይህም አዳዲሶቹ አማኞች ከእግዚአብሔር እና ከሰዎች ጋር መልካም ሕብረት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።
መጀመሪያ ፓስተሩ ወተት ሊሰጣቸው ያስፈልጋል። አዳዲሶቹን አማኞች ማሰልጠን አለበት።
ከዚያ በኋላ ነው ጽኑ መብል የሚመጣው። ጽኑ መብል ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የሚገኝ ጠለቅ ያለ አስተምሕሮ ነው።
ጠለቅ ያሉ እውነቶችን ሲማሩ ቀስ በቀስ ወደ ፍጹምነት እያደጉ ይሄዳሉ።
የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ከየትኛውም ወንጌላዊ ወይም ፓስተር በተሻለ ብቃት የመጽፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማገናኘት ይችላሉ። ስለዚህ ወንጌላዊው ወይም ፓስተሩ መሰረታዊ ትምሕርቶችን ካስተማሩዋቸው በኋላ አማኞችን በክርስቶስ አካል ውስጥ በትክክለኛ ስፍራቸው ለማስቀመጥ የአስተማሪዎች አገልግሎት በጣም ወሳኝ ነው።
ዕብራውያን 6፡1 ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥
ዕብራውያን 6፡2 ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።
አማኞች መሰረታዊ የሆኑትን አስተምሕሮዎች ከተማሩና ከተረዱ በኋላ ቀጥለው ጠለቅ ያሉ አስተምሕሮዎችን መማር አለባቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በትክክል እያገናኙ ሲያስተምሩ አማኞች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እና ሚስጥራት ላቅ ያለ መረዳት እያገኙ ያድጋሉ።
ኤፌሶን 4፡12-13 ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
በእምነት ለሚሆን አንድነት እኛም የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችውን ማመን አለብን።
14 እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
ተንኮለኞች እንደ ፍላጎታቸው ባገጣጠሙዋቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ በመመስረት ብዙ ልዩ ልዩ አስተምሕሮዎች ይመሰረታሉ።
የሰው ንግግር ጥቅሶች ከተተረጎሙበት አተረጓጎም በመነሳት የሜሴጅ አማኞች ሒላሪ የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው ሲያስቡ ነበር። የሰሩት ይህ ትልቅ ስሕተት የሰው ንግግር ጥቅሶች ትርጓሜ እየተከተሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ለሚያምኑ ሁሉ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው።
አማኞች የተለያዩ መሪዎችን ለመከተል በመወሰናቸው የጥንቷ ቤተክርስቲያን ተከፋፍላ ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ገና ሕጻናት ናችሁ አላቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
2 ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤
ወተት መሰረታዊ አስምሕሮዎችን ይወክላል፤ እነዚህም በፓስተሩ አማካኝነት ለአዲስ አማኝ የሚቀርቡ ናቸው። ጽኑ መብል ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ብቻ በትክክል እየተነተነ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እያረጋገጠ ሊያስተምር የሚችለውን ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ይወክላል። ፓስተሮች ጠለቅ ያሉ ሚስጥራትን እናስተምራለን ብለው ሲሞክሩ ግራ ይገባቸውና መጽሐፍ ቅዱስን ትተው የሰው ንግግር ጥቅሶችን እየገጣጠሙ ማቅረብ ላይ ያተኩራሉ። ለሰው ንግግር የሚሰጡት ትርጓሜ ከአንድ ፓስተር ወደ ሌላ ፓስተር የተለያየ ስለሆነ ሕዝቡ ወዲያ እና ወዲህ እየተጎተቱ እየተፍገመገሙ ይኖራሉ።
በሰው ንግግር ጥቅሶች እና በመላ ምቶች ላይ የተመሰረቱ የሜሴጅ አስተምሕሮዎች አማኞችን በብዙ ቡድን ይከፋፍሏቸዋል።
ከዚያ እያንዳንዱ ቡድን የእኛ መሪ ከሁሉ የተሻለ ነው እያሉ መሪያቸውም ከሌሎች በላይ ከፍ ማድረግ ይፈልጋሉ።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡3 ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?
4 አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?
እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ስለ ፓስተሩ ይታበያል፤ የእነርሱ ፓስተር ብቻ እውነትን ያገኘ ይመስላቸዋል። ሁላቸውም እርስ በርሳቸው በአስተምሕሮዋቸው የሚቃረኑ እጅግ ብዙ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በትምርታቸው የማይስማሙ 45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖም አሉ።
ፓስተሮች የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆኑ መፍቀድ አማኞች ወደተለያዩ ቡድኖች እንዲከፋፈሉ ያደርጋል፤ ምክንያቱም አማኞች እርስ በራሳቸው የማይስማሙ መሪዎቻቸውን ተከትለው ወደተለያየ አቅጣጫ ይበታተናሉ።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።
ፓስተሮች ለሕዝቡ እምነታቸውን እንዴት በመሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ላይ እንደሚመሰርቱ ማሳየት አለባቸው። ነገር ግን ፓስተሮች ይህን አገልግሎታቸውን ትተው የተወሰኑ የሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ በማተኮር እነዚህኑ “ጥልቅ” መገለጥ በማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊረጋገጥ የማይችል ነገር ያስተምራሉ።
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ፓስተሮች እነርሱን የተቃወመ ሰውን ሁሉ በማባረር ወይም በማውገዝ የተካኑ ሰዎች ናቸው፤ በተለይም ደግሞ የተቃወማቸው ሰው ፓስተሩ መሳሳቱን የሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ከጠቀሱለት በጣም ይጠምዱታል።
እነዚህ ሁሉ ክፍፍሎች የሚፈጠሩት ስር በሰደደ ጥላቻ ነው፤ ይህም ጥላቻ በቀላሉ ወደ መሪር ሊገነፍል ይችላል።
ዮሐንስ ከራዕይ መጽሐፍ በፊት የጻፈው የመጨረሻው መልእክት አምባገነናዊ ዓይነት የስልጣን አጠቃቀምን የሚያጋልጥ አስደንጋጭ መልእክት ነው።
ዲዮጥራጢስ የተባለ ሰው አንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠረና ሐዋርያው ዮሐንስን አልቀበልህም አለው፤ ከእርሱ ጋር ያልተስማሙ ሰዎችንም ከቤተክርስቲያን አስወጥቶ አበረራቸው።
በዘመናችን ፓስተሮችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነው።
ከፓስተሩ ጋር ከተስማማችሁ የእምነት አምድ እንደሆናችሁ ይቆጥራችኋል። ፓስተሩን ብትቃወሙ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ትባረራላችሁ። ደግሞ የፓስተሩ እምነትና አስተሳሰብ ስሕተት መሆኑን የሚያጋልጡ በሐዋርያት የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ብታሳዩት ወዮላችሁ። ፓስተሩ የሚመራው ለራሱ በሰበሰባቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች ነው። ስለዚህ ብትቃወሙት መዘዙ በናንተው ላይ ነው።
3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት አይታችሁ ወይም ሰምታችሁ አታውቁም?
ይህ አንድ ፓስተር ሰዎች ስሕተቱን ሲያሳዩት የሚወስድባቸውን እርምጃ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የራሳቸውን ክብር ማስጠበቅ ይፈልጋሉ። ፓስተሮች ሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጻፉትን እውነት ይቃወማሉ። የፓስተሮች ታላቅነት እና የገቢ ምንጭ የተመሰረተው የሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ላይ አይደለም።
3ኛ ዮሐንስ 1፡11 ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።
ዲዮጥራጢስ ያደረገው ነገር ክፉ ነው ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔርን አላወቀም። የዚህ ዘመን ፓስተሮች ልብ አድርጉ።
የሐዋርያት ሥራ 11፡28 ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።
29 ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤
30 እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጉዳዮቿን የምታከናውንበት ልዩ መንገድ ነበራት። በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰባኪ ነብይ ለሚለው ቃል የሆነ ረቀቅ ያለ ትርጉም በመፈለግ እራሱን “ነብይ” ብሎ አይጠራም። ነብይ ስለ ወደፊቱ ገልጦ ይናገራል፤ ልክ እርሱ እንደተናገረውም ይፈጸማል። ይህ የነብይ አገልግሎት የወደፊቱን አስቀድሞ የሚገልጥ ስለነበረ አማኞች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማድረግ እንዳይጠፉ ጥበቃ ያደርግላቸው ነበር።
የገንዘብ አሰጣጥም ተተምኖ አንድ አስረኛ ወይም አስራት ተብሎ አልነበረም የሚሰጠው። ሰዎች እንደ አቅማቸው ይሰጡ ነበር። ዳዊት መስዋዕት እንዲያቀርብ የእህል አውድማው በነጻ ሲቀርብለት ገንዘብ ከፍሎ ገዛው። ወጪ በማያስወጣኝ ነገር እግዚአብሔርን አላገለግልም አለ። ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጉድለት ባለበት ሁሉ ትሰጥ ነበር።
ድርቅ ወይም ረሃብ በተነሳበት ቦታ ገንዘብ ለሽማግሌዎች ይላክ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለፓስተራችሁ አስራት ስለ መክፈል አንድም ጊዜ አልተጻፈም። ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ውጭ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እረኛ ማለት ፓስተር የሚጠራበት ሌላ ስም ነው የሚል ቃል የለም።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል ቃል የለም።
በዚህ ዘመን ያለው የቤተክርስቲያኖቻችን አወቃቀር ዲኖሚኔሽናዊ ሃሳብ ነው እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ የመጣ አሰራር አይደለም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ክርስቲያኖች በሕብረት እንደ አንድ ቤተሰብ ይኖሩ ነበር። ራሳቸውን ለመርዳት ሥራ ይሰራሉ፤ ደግሞም ያገኙትን በመካከላቸው በነጻ ይካፈሉ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡44 ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤
45 ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።
2ኛ ቆሮንቶስ 12፡11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና።
ከሐዋርያት ሁሉ ታላቅ የነበረው ሐዋርያ ጳውሎስ እራሱን ከምንም አልቆጠረም።
ፓስተሮች ራሳቸውን ከሁሉ ይልቅ ታላቅ አድርገው መቁጠራቸውና መታበያቸው በጣም አስጸያፊ ነገር ነው። ስለዚህ የመጨረሻውን የቤተክርስቲያን ዘመን እግዚአብሔር ከአፉ መትፋት መፈለጉ አያስደንቅም።
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።