መልከጼዴቅ እና አስራት እና ትንሳኤ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ከማጨድ በፊት መዝራት ያስፈልጋል። በመከር ወቅት ፍሬው ከተክሉ ላይ ይለቀማል። ዋነኛው መከር ቅዱሳን ከምድር ሲወሰዱ ነው።
- እውነተኛው ንጉስና ካሕን እግዚአብሔር ብቻ ነው
- እግዚአብሔር ቅዱሳኑን ማመን አይችልም
- እንጀራ እና ወይን የሚያመለክቱት የመጨረሻውን እራት ነው
- ብርሃናችሁ እንዲበራ ያላችሁን ነገር ማጣት አለባችሁ
- የእግዚአብሔር በረከት ከሐጥያት ማረፍ ነው
- እግዚአብሔር ስለ እኛ ጦርነቱን ያሸንፋል
- በእግዚአብሔር ፊት መቆየቱ መስጠት እንዲፈልግ አደረገው
- ጌታ ያስተማረን ጸሎት ውስጥ የአብ ስም መጠራት አለበት
- በሕይወታችን ውስጥ መጀመሪያ የእግዚአብሔር ፈቃድ መፈጸም አለበት
እውነተኛው ንጉስና ካሕን እግዚአብሔር ብቻ ነው
ይህ ሰው ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ በድንገት ብቅ ይላል ነገር ግን ታላቅ ሰው ነው።
ነገስታት ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሱት ዘፍጥረት ምዕራፍ 14 ውስጥ ነው።
ነገስታት ራሳቸውን ከፍ አድርገው ሌሎችን የሚገዙ እና የሚጨቁኑ ብርቱ ሰዎች ናቸው። ነገስታት ጭንቅላታቸው ላይ ዘውድ የሚጭኑ አምባ ገነኖች ናቸው፤ ንጉስ ያደረጋቸውም የስልጣን ጥማትና የገንዘብ ፍቅር ነው። ስልጣን የሚፈልጉት ገንዘባችሁን ለመውሰድ ነው። የሰዎች ኑሮ ወይም “ገቢ መበላለጥ” የጀመረው በዚህ ነው፤ ይህም የሃብት ልዩነት እስከ ዛሬ ድረስ በምድር ላይ እንደ ዋነኛ እርግማን ቀጥሏል። ስግብግብነት ብዙ ሰዎች በችግር እየኖሩ ሳለ ጥቂቶች በራስ ወዳድነት ብዙ ሃብት አከማችተው እንዲኖሩ ያደርጋል። ለስግብግብ ሰው ገንዘብ መስጠት እሳት ውስጥ እንጨት እንደመጨመር ነው። ነበልባሉ በደምብ እንዲነድድ ያደርጋል። ስግብስግነትና የሰው ደደብነት አንድ ናቸው ምክንያቱም ሁለቱም ገደብ የላቸውም።
ነገስታት የጦር ሰራዊት ያደራጁና ፖለቲካዊ ኃይላቸውን በደካማ ሕዝቦች ላይ ያሳያሉ። የንጉሱ ፖለቲካ የሚራመደው “ኃይል ያለው ትክክል ነው” በሚል ፍልስፍና ነው። ይህንን በ2022 ፑቲን በዩክሬን ላይ ከሰነዘረው የጭካኔ ጥቃት ማየት እንችላለን፤ ፑቲን ዩክሬን ላይ ጥቃት የሰነዘረው (አውሮፓ ውስጥ ከሁሉም ትልቅ የሆነችዋን አገር) ዩክሬንን ለመግዛት ስለፈለገ ነው። ፑቲን መጀመሪያም በምድር ላይ ትልቅ የሆነችዋን ራሺያ የተባለች ሃገር እየገዛ ነበር። ነገር ግን ለእርሱ ራሺያ አልበቃችውም።
እግዚአብሔር ሰዎችን ማስተዳደር የፈለገው በነገስታት እና በጨቋኝ አገዛዛቸው አማካኝነት አይደለም።
ነገስታት የጦር ሰራዊት ስላላቸው ጦርነት ማወጅና ሌሎች ሃገሮችን መግዛት መብታቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል።
2ኛ ሳሙኤል 11፡1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ …
ነገስታት ሌሎች ነገስታት ላይ ጦርነት እንዲያውጁ የሚያነሳሳቸው በሌሎች ላይ የመሰልጠንና ግዛታቸውን የማስፋት ፍላጎት ነው። የጦርነት መሰረቱ ይህ ነው።
ጦርነት ማን ትክክል እንደሆነ አያሳይም። ጦርነት የሚያሳየው ማን (በሕይወት) እንደ ቀረ ብቻ ነው።
ኮሎዶጎምር ከሁሉም በላይ ብርቱ ንጉስ ነበረ። ወዳጆቹ ከሆኑ ጥቂት ነገስታት ጋር በመተባበር ሌሎች ነገስታትን ደመሰሳቸው።
ከዚያም አብራም ኋላም አብራሐም ጨካኝና ስልጣን የማይጠግበውን ፖለቲከኛ ኮሎዶጎምርን ገደለው። ከሰው እይታ አንጻር ይህ አብራሐምን ዋነኛው ንጉስ እንዲሆን ያደርገዋል።
አዲሱ የሰዶም ንጉስ ከኃይለኛው አብራሐም ጋር ወዳጅነት መፍጠር ፈለገ። የአዲሱ የሰዶም ንጉስ አባት የነበረው የቀድሞው የሰዶም ንጉስ በጦር ሜዳ ሲሸሽ በኮሎዶጎምር እጅ ተገድሎ ወደቀ።
ዘፍጥረት 14፡10 በሲዲም ሸለቆ ግን የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥ የገሞራ ንጉሥም ሸሹና ወደዚያ ወደቁ፤
የንግስና እርግማን የንጉስ ልጅ በአባቱ ቦታ ተተክቶ መንገሱ ነው።
ንጉስ ወደ ዙፋን የሚወጣው በብቃቱ ሳይሆን ከንጉስ ቤተሰብ በመወለዱ ነው።
የንጉስ ልጅ ለንግስና ሃገርን ለመምራት ብቃት ባይኖረውም እንኳ አባቱ ሲሞት መንገስ ያለብኝ እኔ ነኝ ይላል። ይህም የእግዚአብሔር ሃሳብ አልነበረም።
እግዚአብሔር ሕዝቡን መምራት የፈለገው በነብይ ነበር። አይሁዶች ሕዝብ ሲሆኑ በሙሴ ቦታ ኢያሱ ተተክቶ ነበር። ከኤልያስ በኋላ ደግሞ ኤልሳዕ ተተክቶ ነበር።
ዛሬ ብዙዎቹ ፓስተሮች እንደሚያደርጉት ገንዘብን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ለማቆየት አባት ፓስተር ከሆነ ልጅየው በእርሱ ቦታ እንዲተካ የእግዚአብሔር ቃል አላለም።
እግዚአብሔር ቅዱሳኑን ማመን አይችልም
ዘፍጥረት 14፡17 ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰ በኋላም የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነ በሴዊ ሸለቆ [አብራሐምን]ሊቀበለው ወጣ።
አብራም የተባለውን ጻድቅ ሰው በዘመኑ ታላቅ ንጉስ አድርገው እውቅና ሊሰጡት ሲዘጋጁ እግዚአብሔር ጣልቃ ገባ።
እግዚአብሔር አንድ ጻድቅ ሰው የምድር ፖለቲካዊ መሪ እንዲሆን አልፈለገም። እግዚአብሔር ሰው ገዥ እንዲሆን አልፈለገም።
ሰው በስልጣን ስፍራ በተቀመጠ ጊዜ ስሕተቶችን ይሰራል።
ኢዮብ 15፡15 እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤
ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ከታዘዛችሁ በኋላ እንኳ ትክክል ካደረጋችሁት ነገር ይልቅ የሰራችሁት ስሕተት ይበልጣል።
ስለዚህ ጥቂት መልካም ነገር ብናደርግም እንኳ ብዙ ነገር እናበላሻለን።
ከትርፍ ይልቅ ኪሳራ በለጠ ማለት እግዚአብሔር ከሰዎች ጥረት ምንም አይጠቀምም ማለት ነው። ለዚህ ነው ሰዎች ገዥ እንዲሆኑ የማይፈልገው። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በአንድ ግለሰብ እንድትተዳደር የማይፈልገው።
ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
(በዚያ ዘመን የእግዚአብሔር ታላቅ ሰው አብራሐም ነበረ። ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሐም ልጅ ለመስጠት የነበረውን ፈቃድ አብርሐም ሲተረጉመው አጋር ከተባለች ከግብጻዊት ሴት ጋር አመነዘረና እስማኤልን ወለደ። ከእስማኤልም የተወለዱ አረቦች የእስራኤል ቀንደኛ ጠላት ሆኑ።
እንግዲህ ታላላቅ ሰዎች እንደመረዳታቸው እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ እንዲህ ዓይነት ስሕተት ውስጥ ነው የሚወድቁት። ከሚሰሩት መልካም ነገር የሚያመጡት ጉዳት ይበልጣል። እግዚአብሔርን መጠበቅ መልመድ አለብን።)
ሰለዚህ አብራሐም ታላቁን ንጉስ ኮሎዶጎምርን ደምስሶ ታላቅ ድል ውስጥ በነበረ ሰዓት መልከጼዴቅ መጣና ጦርነቱን እንዲያሸንፍ የረዳው እግዚአብሔር መሆኑን ነገረው፤ ከድሉም በኋላ የማረፍን በረከት ሊሰጠው የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን አስታወሰው።
ይህ የሆነበት ጊዜ ትልቅ ትርጉም አለው። የእረፍት በረከት የመጣው ድል ከተገኘ በኋላ ብቻ ነው።
አብራሐም በጦር ሜዳ ታላቅ ድል ተጎናጽፏል። እራሱን ታላቅ ንጉስ ብሎ መሾም ይችል ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም።
በዚያ ፈንታ እግዚአብሔር ትቂት የምድር አፈር ወስዶ ለራሱ ስጋ አዘጋጀ። እግዚአብሔር በዚህ አዲስ ሰው አካል ውስጥ አደረና ራሱን መልከጼዴቅ ብሎ ጠራ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንደ መልከጼዴቅ ሆኖ ነገስታትን በደመሰሰው በአብራሐም ፊት ቆመ። እግዚአብሔር ግን እንደ መልከጼዴቅ ማትም የሰላም (ሳሌም) ንጉስ ሆኖ ነው የተገለጠው።
ሰላም ከጦርነት ይበልጣል።
በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔር መንገዶች ከእኛ መንገዶች ተቃራኒ ናቸው። “ትክክለኛው ንጉስ እኔ ብቻ ነኝ። ሰላምን ማምጣት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ”።
እንጀራ እና ወይን የሚያመለክቱት የመጨረሻውን እራት ነው
ዘፍጥረት 14፡18 የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።
መልከጼዴቅ ንጉስም ካህንም ነበረ።
እግዚአብሔር ብቻ ነው ንጉስም (ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማዘዝ) ካሕንም (ምን ማመን እንዳለባችሁ መንገር) የመሆንን ስልጣን በአንድ ጊዜ መሸከም የሚችለው። ሌላ ማንም ሰው በምታደርጉት እና በምታምኑት ላይ እንዲህ ዓይነት ስልጣን ሊኖረው አይገባም።
ነገስታት በሕዝብ ላይ ግብር ይጭናሉ። ገንዘባችሁን የመውሰድ ኃይል አላቸው።
መልከጼዴቅ ግን ይህን አላደረገም። ገንዘብ እንዲሰጡት አልጠየቀም። ከአብራሐም አንዳች በመውሰድ ፈንታ እግዚአብሔር ለአብራሐም ከጠላቶቹ እረፍት መስጠትን መረጠ፤ ይህንም ያደረገው አብራሐም በሰላም መኖር ይችል ዘንድ ነው።
መልከጼዴቅ ዘመድ አልነበረውም ምክንያቱም ከሴት አልተወለደም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ቀን አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ነው የሚጀምረው።
ዘፍጥረት 1፡5 … ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።
ለንጉስ የሚገባ ግብር ገንዘብ በመጠየቅ ፈንታ መልከጼዴቅ እንጀራ እና የወይጠጅ ሰጠ፤ ይህም ወደፊት ለሚደረገው ከሁሉ የሚበልጥ ታላቅ እራት ትንቢታዊ ተምሳሌት ነበረ። ይህም ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የበሉት የመጨረሻ እራት ነው። ይህ እራት የተበላው በወሩ በ14ኛው ዕለት ምሽት ነው፤ ከዚያም ዕለት በቀጣዩ ቀን ከሰዓት በኋላ የፋሲካ በግ ይታረዳል።
እንጀራው የተቆረሰው ክርስቶስ የሐጥያትን ኃይል ሲደመስስ የሚሞተውን ሞት በምሳሌ ለማመልከት ነው።
አብራሐም ሰዎችን አሸነፈ። ነገር ግን የሰው እውነተኛ ጠላቶች ሐጥያት እና ሞት ናቸው። በሐጥያት እና በሞት ላይ ድልን መጎናጸፍ የሚችለው ክርስቶስ ብቻ ነው። የክርስቶስ ሞት የሐጥያትን ዋጋ ከፈለ። ወይን ቀይ ነው፤ በውስጡም የሕይወት መንፈስ ይኖራዋል። ይህም ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ደሙን ሲያፈስስ በደሙ ውስጥ የነበረውን ሕይወት ይወክላል። ሕይወት ከስጋው ውስጥ ወጥቶ በትንሳኤ በከበረ አካል ውስጥ ተነሳ።
በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ሞቶ የተነሳ ብቸኛ የሐይማኖት መሪ ሆነ።
ኢየሱስ ከሞት እና ከሐጥያት ጋር ያደረገው ትግል የክርስትና ዋነኛ መሰረተ ነው።
ብርሃናችሁ እንዲበራ ያላችሁን ነገር ማጣት አለባችሁ
ክርስቶስ የሚያሸንፈው አብራሐም እንዳደረገው ሌሎችን በመግደል አይደለም፤ ነገር ግን በመሞት እና ሌሎችን ለመቤዠት ደሙን በማፍሰስ ነው።
ከሐጥያት ጋር በምናደርገው ተጋድሎ ውስጥ ለራስ ሌሎችን ከመግደል ይልቅ ለእኔነት መሞት ነው ውጤታማ የሚያደርገን።
አይንሽታይን እንደሚለው አንድ ነገር የብርሐን ኃይል ሲያመነጭ ክብደቱን ያጣል።
ብርሐናችንን ማብራት እንድንችል የሆነ ነገር ማጣት አለብን።
ክርስቶስ ክብሩን አውልቆ የእኛን ሐጥያት ለብሶ የሐጥያተኛ ሞት ሞተ፤ ይህን ያደረገው የሐጥያታችንን ዋጋ ለመክፈልና እኛ ይቅር እንድንባል ነው። ክብሩን እና ሕይወቱን በማጣት ክርስቶስ የዓለም ብርሐን መሆኑን አስመሰከረ።
ስለዚህ ንጉስ ነኝ በማለትና ግብር ይከፈለኝ በማለት ፈንታ መልከጼዴቅ በዓይን የሚታዩ የንጉስነት ባህርያትን ትቶ መንፈሳዊ የሆኑ የክህነት ስራዎች ላይ አተኮረ። እንጀራው እና የወይን ጠጁ ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የበሉትን የመጨረሻ እራት የሚያመለክቱ ግልጽ የሆኑ ትንቢታዊ ምልክቶች ናቸው።
እነዚህ ትንቢታዊ ምልክቶች የሆኑ እንጀራ እና ወይን ወደ ክርስቶስ ሞት ነው የሚያመለክቱት። ክርስቶስ በመልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካሕን ሆኖ ይመጣል ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያንን ሊመራት የሚችለው። ከአብራሐም ዘመን አልፈው ወደፊት ሊሆኑ ያላቸው ዋነኛ ነገሮች እነዚህ ናቸው።
ከዚህ ክፍል የምንማረው ትምሕርት ግልጽ ነው። በክሕነት በተመሰለው መንፈሳዊው ገጽታ ላይ ትኩረት ብናደርግ ትኩረታችን በክርስቶስ እና እርሱ በሰራው ስራ ላይ ይሆናል። ከዚያ ውጭ በራሳችን ታላላቅ ድሎች ላይ ትኩረታችንን አናደርግም።
ክሕነቱ ሰላም እና የእግዚአብሔርን በረከት እንዲሰጠን ነው ምክንያቱም ክርስቶስ ሸክማችንን ተሸክሞልናል። ክርስቶስም እኛ በደረስንበት በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ባሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ይመራናል።
የእግዚአብሔር በረከት ከሐጥያት ማረፍ ነው
ዘፍጥረት 2፡3 እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።
እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን የባረከው ቀኑ ሰባተኛ ቀን ስለሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን የባረከው በዚያ ቀን ስላረፈ ነው።
ስለዚህ እረፍታችን የሚገኘው የእግዚአብሔር በረከት ውስጥ ነው።
በብሉይ ኪዳን ዘመን እረፍት የሚየደርጉት ከአካላዊ ስራዎቻቸው ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር እረፍት የሰጠን ከሐጥያት ሥራችን ነው።
እግዚአብሔር ይህን የሚያድርገው እኛን በመንፈስ ቅዱስ በመሙላት እና ሕይወታችንን በመቆጣጠር እንዲሁም የቃሉን ሚስጥራት ለእኛ በመግለጥ ነው። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳታችን እያደገ ሲሄድ እግዚአብሔረ አለማመናችንን እና ስጋዊ ሐጥያታችንን ከእኛ ያስወግዳል።
ኢሳይያስ 11፡10 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
እሰይ የዳዊት አባት ነው። ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው።
ሰንደቅ ዓላማ ተሰቅሎ የሚውለበለብ ባንዲራ እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም በመስቀል ላይ ተሰቀለ።
እረፍታችንን ያገኘነው እርሱ ስለ ሐጥያታችን ዋጋ በመክፈሉ ነው።
የበዓለ ሃምሳ ዕለት መንፈስ ቅዱስ 120 አማኞች ውስጥ ሞላ፤ እነርሱም እራሳቸው በማያውቁዋቸው በሌሎች ሃገሮች ቋንቋዎች ተናገሩ፤ ነገር ግን አጠገባቸው ቆመው የነበሩ የሌላ ሃገር ታዛቢዎች የንግግራቸውን ቋንቋ ማዳመጥ ችለው ነበር።
ኢሳይያስ 28፡11 በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ እርሱም፦ ዕረፍት ይህች ናት፥
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እግዚአብሔር ከሐጥያት እና ከአለማመን ሊያሳርፈን የሰጠን ተስፋ ነው።
ኢሳይያስ 28፡12 የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ።
ኢየሱስ እረፍታችንን ማግኘት የምንችለው በእርሱ ውስጥ ብቻ መሆኑን ተናግሯል ምክንያቱም የሐጥያትን ዋጋ የከፈለ እርሱ ብቻ ነው፤ ሐጥያትን ይቅር ማለት የሚችለውም እርሱ ብቻ ነው።
ማቴዎስ 11፡28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
የሐጥያት ውጤት በጣም የሚያስጨንቅ ከባድ ሸክም ነው።
በደለኝነት፣ ፍርሃት፣ እና ቁዘማ ከባድ ሸክሞች ናቸው። ይቅርታንና ውስጣዊ ብርታትን ማግኘት የምንችለው በክርስቶስ ብቻ ነው።
የክርስቶስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሕይወታችንን ልንኖር የምንችልበትን የተሻለ መንገድ ያሳየናል።
ወደ መልከጼዴቅ እንመለስ።
ዘፍጥረት 14፡19 ባረከውም፦ አብራም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔር የተባረከ ነው፤
ከአብራሐም አንዳች ለመቀበል በመጠየቅ ፈንታ (አብራሐም ከጦርነት በሰበሰበው ምርኮ የተነሳ ባለጠጋ ነበረ) እግዚአብሔር አብራሐምን ባረከው።
አብራሐም ግን የቁሳቁስ ሃብት አልፈለገም። ከዚያ በፊት እንኳ ከሚበቃው በላይ ንብረት ነበረው።
ነገር ግን ከጠላቶቹ ማረፍ ፈልጓል። ከጦርነት እና ከግጭት ማረፍ ፈልጓል።
መልከጼዴቅ እንደ እግዚአብሔር ሲገለጥ ከአብራሐም ምንም ቁሳቁስ አልጠየቀም። ለምንድነው ያልጠየቀው?
ምክንያቱም እግዚአብሔር “ሰማይና ምድር የሚገዛ” አምላክ ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ነገር ስላለው ከእኛ ምንም አይፈልግም።
አብራሐም በእግዚአብሔር ተባርኳል። የእግዚአብሔር በረከት ለአብራሐም በረከት ሰጥቶታል፤ ስለዚህ ሁለተኛ ለላ ጦርነት መዋጋት አላስፈለገውም።
የእረፍት በረከት ከማንኛውም የቁሳቁስ ወይም የሃብት በረከት አብዝቶ ይበልጣል።
እኛንም በዚህ ዓይነት በረከት ነው እግዚአብሔር ሊባርከን የፈለገው።
እግዚአብሔር ስለ እኛ ጦርነቱን ያሸንፋል
ዘፍጥረት 14፡20 ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።
ይህ በጣም አስፈላጊ ትምሕርት ነው።
ለሰው ሁሉ ጦርነቱን አብራሐም እንዳሸነፈ ቢመስልም አብራሐም ጦርነቱን አላሸነፈም።
እግዚአብሔር ነው ጦርነቱን ያሸነፈው።
እውነተኛው ጦርነት በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ሲሆን ይህም ጦርነት በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ነው የተደረገው። በምድር ላይ የሚታየው ነገር በመንፈሳዊ ዓለም ለሚከናወነው ጥላ ነው።
በዚያ መንፈሳዊ ጦርነት ውስጥ ልናደርግ የምንችለው አስተዋጽኦ በእግዚአብሔር ቃል ማለትም በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ማመን እና መጸለይ የመሳሰሉ መንፈሳዊ ግብአቶችን ብቻ ነው። ሁለቱ ታላላቅ የጦር እቃዎቻችን ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ናቸው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነታችንን ይገነባሉ።
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቅ በሰይጣን ከመታለል ያድነናል፤ ከዚህም የተነሳ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት መካከል ከመሆን እናመልጣለን። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ማለት የዳኑ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ያልተረዱ ክርስቲያኖች ናቸው። ኢየሱስን አዳኝ ነው ብለው በማመን ድነዋል ነገር ግን ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችን በመቀበል ተታለዋል። የቤተክርስቲያን አመለካከቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ ማድረግ የዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን አደገኛ በሽታ ነው።
እምነትና ጸሎት ትኩረታችንን ከስጋዊ ፍላጎታችን ላይ አንስተው በእግዚአብሔር መንግስት ላይ እንድናደርግ ይረዱናል።
በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር ትልቅ ፍላጎቱ ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እንድትመለስ ነው። ወንድም ብራንሐም የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበረውን እምነት ማወቅ እንችል ዘንድ የዘመን መጨረሻ ሚስጥራትን ሊገልጥልን ነው የተላከው።
በእግዚአብሔር ፊት መቆየቱ መስጠት እንዲፈልግ አደረገው
ዘፍጥረት 14፡20 አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።
አብራሐም አስራት እንዲሰጥ አልተጠየቀም።
አብራሐም በጦር ሜዳ ድል በሰጠው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙን ሲያውቅ ከሃብቱ ሁሉ አንድ አስረኛውን ለእግዚአብሔር ሰጠ።
አስራት የማይሰጡ ሰዎች በእግዚአብሔረ ፊት ቆመው አያውቁም።
አብራሐም ሁሉን ያደረገለት እግዚአብሔር መሆኑ ሲገባው በምስጋና ተሞልቶ ምስጋናውን ለመግለጥ ለእግዚአብሔር የሆነ ነገር መልሶ መስጠት እንዳለበት ተሰማው።
አንድ ሰው የሆነ ነገር ቢሰጣችሁ በተፈጥሮዋችሁ ለዚያ ሰው የሆነ ነገር መልሳችሁ መስጠት መፈለጋችሁ አይቀርም።
አብራሐም ከአፈር የተሰራ ሰው ነው። ከምድር አፈር ጋር የሚሰሩ ገበሬዎች የተፈጥሮን ሕግ ተረድተዋል። ምድር ጥሩ ምርት እንድትሰጥህ ከፈለግህ መጀመሪያ ለምድር ማዳበሪያ መስጠት አለብህ። አለበለዚያ ዝም ብለህ ከምድር ላይ የመከሩን ፍሬ እያጨድክ መውሰድ አትችልም።
አብራሐምም የትንሳኤ መከር አካል መሆን ስለፈለገ ከእግዚአብሔር መቀበል ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔርም መልሶ መስጠት እንዳለበት ተረድቷል።
ኢየሱስ በትንሳኤ መከር ወቅት ቅዱሳንን ከምድር አፈር እንዲሁ አፍሶ መውሰድ እንደማይችል ገብቶታል።
መጀመሪያ ኢየሱስ በምድር ውስጥ ለሶስት ቀን እና ለሶስት ሌሊት ተቀብሮ ማደር ነበረበት።
ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሊነሳ እና ከትንሳኤው በኋላ አብራሐምንና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን ሊያስነሳ የሚችለው።
በትንሳኤው ውስጥ ለመገኘት ስለፈለገ አብራሐም በደስታ ለእግዚአብሔር አስራት ከፈለ።
መጀመሪያ ስጡ፤ ከዚያ ትቀበላላችሁ።
ነገር ግን የአብራሐም አስራት ጠለቅ ያለ ትርጉም ነበረው።
የሰዶም ንጉስ የምርኮውን ሃብት በሙሉ ለአብራሐም አቀረበለት። አብራሐም አልቀበልም አለ። አብራሐም ለራሱ ምንም አልፈለገም፤ አብረውት ለነበሩ ሶስት ሰዎች ብቻ የተወሰነ እንዲሰጣቸው ጠየቀ።
ዘፍጥረት 14፡24 ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።
አብራሐም በራሱ ነጻ ፈቃድ አስራት ከፈለ፤ እግዚአብሔርም ለአብራሐም ዘር (የአይሁድ ሕዝብን) እና የተስፋይቱን ምድር እስራኤልን ሰጠው።
የሌዊ ነገዶች ካሕናት ሆኑ፤ ስለዚህ አስራት የሚሰበስቡ እነርሱ ናቸው።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ቃልኪዳኑ የተደረገው ከአብራሐም ዘር ጋር መሆኑን ልብ በሉ።
የአብራሐም ፍጥረታዊ ዘሮች አይሁዶች ናቸው።
መንፈሳዊ ዘሩ ክርስቶስ ነው።
መመሪያ፡ ምድር ላይ ዘር ከመዝራታችሁ በፊት የመከር ፍሬ ልታጭዱ አትችሉም።
የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር (ኢየሱስ) መጀመሪያ በምድር ውስጥ ሳይቀበር በፊት ፍጥረታዊው ዘር (የብሉይ ኪዳን አይሁዶች) በመጀመሪያው ትንሳኤ መከር ሊታጨዱ አይችሉም።
ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
አይሁዶች ኋላ ሐጥያት ሰሩና በ70 ዓ.ም እና በ135 ዓ.ም ከተስፋይቱ ምድር በሮማውያን አማካኝነት ተባረሩ።
ከ1,800 ዓመታት በኋላ አይሁዶች በ1967 ዓ.ም የስድስቱ ቀን ጦርነት በተባለ አስደናቂ ውግያ አሸንፈው የተስፋይቱ ምድራቸውን መልሰው ተቆጣጠሩ። በስተመጨረሻ አይሁዶች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ምድር መልሰው በእጃቸው አስገቡ። በዚያ ጊዜ የእስራኤል ፕሬዚዳንት የሆነውና በጦርነት አሸንፈው የተቆጣጠሩትን ምድር የተቀበለው ሰው ስሙ ሊዊ ኤስኮል ነው።
አብራሐም አስራት ከፈለ፤ እግዚአብሔርም ለአሁኑ ዘመን ኤስኮል ድርሻውን ሰጠው። አራት ሺ ዓመት ሁሉ ካለፈ በኋላ እንኳ የሰውየው ስም ትክክል ሆኖ መጣ። እግዚአብሔር ተጣድፎ አያውቅም።
አስራት መክፈል የእውነትም ያዋጣል።
የአብራሐም የተቀበለው ትልቁ በረከት ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ አካል ሲሆን ነው።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ያረገ ዕለት አብራሐም ከብሉይ ኪዳን መከር ውስጥ ሆኖ እርሱም ከምድር ተወስዶ ወደ ሰማይ ሄዷል።
መከር ማለት ፍሬው ከሰብሉ ላይ ታጭዶ ሲወሰድ ነው።
ጌታ ያስተማረን ጸሎት ውስጥ የአብ ስም መጠራት አለበት
የጌታን ጸሎት ተመልከቱ።
ከሰዎች ፍላጎትና ምኞቶች ጋር የተያያዘ ብዙም ነገር የለውም።
ማቴዎስ 6፡9 እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤
የጸሎቱ ማዕከል እግዚአብሔር አብ ነው። እግዚአብሔር አብ የሚኖረው በሰማይ ስለሆነ ይህ ጸሎት ትኩረታችንን ከምድራዊ ፍላጎታችን ላይ አንስቶ ወደ እግዚአብሔር ሰማያዊ እቅድ ይወስደዋል።
በዙርያችን ያለው ነገር ሲከፋ ዓይናችንን ወደላይ ማድረግ አለብን።
እግዚአብሔር አብ የተቀደሰ ስም አለው። ይህም ስም ከጸሎት ተገቢውን ዋጋ ለማግኘት ይረዳል።
ቤተክርስቲያኖች ግን የእግዚአብሔር አብን ስም አያውቁም።
የስላሴ ትምሕርት እግዚአብሔርን ሶስት ሰዎች አድርጎ ይከፋፍለዋል። እግዚአብሔር አብ። እግዚአብሔር ወልድ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ።
ይህ ግን የግሪክ ፍልስፍና ነው። “አንድ አምላክ በ3 አካላት” የሚለው ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
ይህ ምን ዓይነት ችግር እንደሚፈጥር ተመልከቱ።
“እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” የሚልም የለም። የስላሴ አስተማሪዎች ለዚህ መልስ የላቸውም።
“እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አለ ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ የለም። አሁንም የስላሴ አስተማሪዎች ለዚህ ማብራሪያ የላቸውም።
የእግዚአብሔር አብ ስም ማነው?
የስላሴ አስተማሪዎች በግምት ሲመልሱ፡- ኤል፣ ኤሎሄ፣ ኤሎሂም ይላሉ። እነዚህ ቃላት ሁሉ ትርጉማቸው “አምላክ” ማለት ነው።
ነገር ግን የአምላክ ስም አምላክ አይደለም።
ከዚያ በኋላ “እኔ እኔ ነኝ” ነው ይላሉ። ይህ ግን ስም አይደለም፤ ለዘላለም በራሱ እንደሚኖር የሚገልጥ ቃል ነው እንጂ።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሁሉም ስሞች በላይ ዝነኛ የሆነው ስም ያህዌ ነው። ያህዌ ማለት ጌታ ማለት ነው። ጌታ ደግሞ ስም አይደለም።
ስለዚህ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ስም ሚስጥር ነበረ።
ማኖሄ የሶምሶን አባት ነበረ፤ እርሱም የእግዚአብሔርን መልአክ አየ። ነገር ግን እግዚአብሔርን አየሁ አለ።
እግዚአብሔርን ስምህ ማነው ብሎ ጠየቀው ግን መልስ አላገኘም።
መሳፍንት 13፡18 የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው።
መሳፍንት 13፡22 ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት።
የአብ ስም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሚስጥር ነበረ።
የአብ ስም ነው ብላችሁ የትኛውንም ስም ብትመርጡ ያ የመረጣችሁት የአብ ስም አዲስ ኪዳን ውስጥ ለምን እንደማይገኝ ማብራራት ይጠበቅባችኋል።
ስለዚህ የስላሴ አስተማሪዎች የጌታን ጸሎት የመጀመሪያውን ስንኝ መጸለይ አይችሉም።
ምክንያቱም አዲስ ኪዳን ውስጥ የአብን ስም ማግኘት አይችሉም።
ስላሴ ለሆነው አምላካቸው ስም ማግኘት አይችሉም ምክንያቱም ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ማግኘት አይቻልም።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ከአይሁዶች በላይ ያለ መንፈስ ነበረ። እርሱን የሚያውቁት እንደ አብ ነበረ።
አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።
ኢየሱስ በምድር ላይ የሚኖር ሰው እንደመሆኑ እግዚአብሔር አልነበረም። እግዚአብሔር ስጋ እና ደም አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ነው።
ነገር ግን የመለኮት ሙላት በእረሱ ውስት በአካል ተገልጦ ይኖር ነበር።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
እናንተ በውስጣችሁ ያለውን ነገር ሁሉ ናችሁ።
ኢየሱስን እግዚአብሔር ያደረገው በውስጡ የኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
የቤዛነት የመጀመሪያው ደረጃ እግዚአብሔር ኢየሱስ በተባለ በአንድ ሰው ውስጥ መኖሩ ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ ሰብዓዊ ባህርይ “በእግዚአብሔር ልጅ” ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊዳብር ችሏል።
ኢየሱስ ከሞተ እና በውስጡ ደም የሌለው (ምክንያቱም ደሙ በቀራንዮ ፈስሷል) የከበረ አካል ይዞ በትንሳኤ ከተነሳ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ወደ ሰማይ አረገ። በውስጡም የእግዚአብሔር መንፈስ አደረ።
ወልድ ወይም ልጁ ሰው ነው፤ አብ ደግሞ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው። ሰውም ልዕለ ተፈጥሮአዊም መሆን የመንፈስ ቅዱስ ባህርይ መገለጫ ነው።
ዮሐንስ 14፡16 ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
ሌላ አጽናኝ ማለት መንፈስ ቅዱስ በሌላ መልክ መምጣቱ ነው።
መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ውስጥ ነበረ፤ ስለዚህ መጀመሪያም ከደቀመዛሙርት ጋር ኖሯል።
ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ተመልሶ ይመጣና ተከፋፍሎ በእያንዳንዱ ደቀመዝሙር ውስጥ ያድራል።
ዮሐንስ 14፡17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
ልብ በሉ መንፈስ ቅዱስ የሰውንም ልዕለ ተፈጥሮአዊ የሆነውን የእግዚአብሔርንም ባህርይ በአንድነት አዋህዶ ይዟል።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጣችሁ ሲገባ እግዚአብሔር የሚፈልጋችሁ ዓይነት ሰው ነው የሚያደርጋችሁ።
ከዚህም የተነሳ አሮጌው የሰውነት ባህርያችሁ መሞት አለበት።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ በተገለጠ ጊዜ ከአይሁዶች በላይ ነበረ።
መንፈስ ቅዱስ እንደ ልጅ ከአይሁዶች ጋር ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሙላት በኢየሱስ ውስጥ በአካል ነበረ።
ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በምሕረት ዙፋን ላይ በክርስቶስ ውስጥ እንደሆነ ቆየ ነገር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥም ለመኖር ወደ ምድር መምጣት ችሏል።
ክርስቶስ በምሕረት ዙፋን ላይ ተቀምጦ ባለበት ሰዓት ጳውሎስ የክርስቶስን መንፈስ በደማስቆ መንገድ ላይ አየው።
ይህም ቴሌቪዥን እንደማየት ነው።
እስቱድዮ ውስጥ ቆሞ የሚናገረው ሰው አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን የሰውየው ምስል ቴሌቪዥን በተከፈተበት ሁሉ በየቲቪው ውስጥ ይታያል።
ቴሌቪዥን ሲከፈት እስቱድዮ ውስጥ የሚናገረው ሰው ምስል ቲቪ ውስጥ ይታያል፤ የሰውየው ምስል ቴሌቪዥን ባለበት ሁሉ ይሰራጫል።
ይህም የክርስቶስ ተምሳሌት ነው።
ኢየሱስ በሰማያት በምሕረት ዙፋን ላይ ተቀምጧል፤ ነገር ግን መንፈሱን እያካፈለ ንሰሐ በገቡ ሐጥያተኞች ሁሉ ልብ ውስጥ መላክ ይችላል።
1ኛ ዮሐንስ 5፡7 መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። በሰማይ የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም አብ፣ ቃሉ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱም አንድ ናቸው። (ኪንግ ጄምስ ቨርዥን KJV)
ቃሉ ሰው የሆነው ኢየሱስ ነው፤ እርሱም የሰው ባህርይ አለው። አብ ደግሞ ስጋ በለበሰው በኢየሱስ ውስጥ የሚኖረው ልዕለ ተፈጥሮአዊው መንፈስ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ የሚወጣው መለኮታዊ እና ሰብዓዊ ባሕርይ ውህደት ሲሆን ይህም ከኢየሱስ እየወጣ ይከፋፈልና በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ አካል ብልት ያሉትን ሰዎች እያንዳንዳቸውን ይሞላቸዋል።
አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ማለት እግዚአብሔረ ከአይሁዶች በላይ፣ እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር፣ እና እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ማለት ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
“ተገለጠ” ማለት “ራሱን አሳየ ማለት ነው”።
እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ልጅ እራሱን በኢየሱስ አሳየ።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ራሱን ያሳየው በቤተክርስቲያን በኩል በመንፈስ ቅዱስ ነው።
አንድ አምላክ። አንድ ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንፈስ ለእኛ ምሳሌ ሆኖ ራሱን በአንድ ሰው (በኢየሱስ) ገለጠ፤ ከዚያ (እኛን የቤተክርስቲያን አካላት አድርጎ) በእኛ ውስጥ ተገለጠ።
አዲስ ኪዳን ውስጥ አብ ስም የለውም ምክንያቱም የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ሆኗል።
አንዲት ሴት ባል አግብታ በባሏ ስም ከተጠራች በኋላ ተመልሳ ከማግባቷ በፊት በነበራት ስም አትጠራም።
እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ለመኖር ወደ ምድር ሲወርድ ኢየሱስ በተባለ በሰው ስም ተጠራ። ለእግዚአብሔር ይህ አዲስ ስም ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእርሱ ስም አድርገው በሚያስቡዋቸው ስሞች ተመልሶ አልተጠራም።
አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አንድ አካል ነው። እነዚህ ሶስቱ አንድ ናቸው።
ስለዚህ የአብ ስም ኢየሱስ ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ስም ኢየሱስ ነው።
መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔረ አብ ነው።
የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያደርግ ሰው የሕጻኑ አባት ነው።
መንፈስ ቅዱስ ማርያምን ጋረዳት፤ ስለዚህ በድንግልና ለወለደችው ልጅ ለኢየሱስ አባት ነው።
ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
የጸሎቱ የመጀመሪያ ስንኝ በጣም አስፈላጊ ነው። የአብን ስም ጠርታችሁ መጸለይ አትርሱ።
የአብ ስም ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 14፡14 ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
ቆላስይስ 3፡17 እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
አብ ማለት በኢየሱስ ስጋ ውስጥ ያደረው ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንፈስ ነው (ቆላስይስ 2፡9)።
ወልድ ሰው የሆነው ኢየሱስ በምድር ላይ በሕይወት ሲኖር በውስጡ የነበረው የሰው መንፈስ እንዲሁም ስጋዊ አካሉ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ እንደ ሰው እግዚአብሔር አይደለም። ለዚህ ነው “እግዚአብሔር ወልድ” ተብሎ ያልተጻፈው።
በኢየሱስ ውስጥ የሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ኢየሱስን እግዚአብሔር ያደረገው።
ዘኁልቁ 23፡19 እግዚአብሔር ሰው አይደለም
መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ሰውነት እና በውስጡ የሚኖረው የእግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሮአዊ ባህርይ ውህደት ነው።
መንፈስ ቅዱስ በከፊል ሰው ስለሆነ ነው በእኛ ውስጥ ማደርና እኛን የእግዚአብሔር መልክ ማድረግ የቻለው። የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ነው።
ቆላስይስ 1፡27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።
መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ሰውነት እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው የእግዚአብሔር ባህርይ ውህደት ነው።
ስለዚህ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” አንልም ምክንያቱም እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ይኖራል ግን ልዕለ ተፈጥሮአዊው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ሰብዓዊ ባህርይ አይደለም።
በሕይወታችን ውስጥ መጀመሪያ የእግዚአብሔር ፈቃድ መፈጸም አለበት
ማቴዎስ 6፡10 መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
ትኩረታችን መሆን ያለበት እዚህ ላይ ነው።
ትኩረታችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ላይ መሆን አለበት።
አሁን የምንኖርበትን ዘመን መረዳት እና ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ እንደሚያስፈልገን ማወቅ አለብን።
አለበለዚያ ከዳኑት ነገር ግን ወደ ታላቁ መከራ እየተነዱ ካሉት ሰነፍ ቆነጃጅት እንደ አንዷ እንሆናለን።
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ምሪት የመጣው ከሰማይ ነው። የእግዚአብሔር ሰማያዊ ፈቃድ በምድር ላይ የሚፈጸመው የጥንቷ ቤተክርስቲያን ከምታምነው ውጭ ምንም እንዳናምን መሆኑን መገንዘብ አለብን።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰምተዋል ብላ አላመነችም። እናንተም ነጎድጓዶቹ ድምጻቸውን አሰምተዋል ብላችሁ ማመን የለባችሁም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ሰዎች የኢየሱስን አዲስ ስም እናውቃለን አላሉም። በሐጥያተኛው አካላችሁ ውስጥ እየኖራችሁ ሳለ የኢየሱስን አዲስ ስም እናውቃለን ለማለት መድፈር የለባችሁም።
በምድር ላይ ስንኖር ብቸኛው ፍላጎታችን በሰማይ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም እንችል ዘንድ ሕይወታችንን እና እምነታችንን መለወጥ መሆን አለብን።
በራሳችን ፍላጎቶችን እቅዶች ተጠምደን መቅረት የለብንም።
ማቴዎስ 6፡11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
በዚህ ዝነኛ ጸሎት ውስጥ የግል ፍላጎታችንን የምንጠይቅበት “የዕለት እንጀራችንን” በሚለው ስንኝ ውስጥ ብቻ ነው።
በሌላ አነጋገር ይህ ጸሎት ስለምንበላው ምግብ ከፍላጎታችን ሁሉ ቀላሉን በተመለከተ ነው።
ነገር ግን እንጀራ ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው፤ ምናልባትም በዚህ ጸሎት ውስጥ ሊገለጥ የተፈለገው ዋነኛው ሃሳብ መንፈሳዊ ትርጉሙ ነው።
እንጀራ የሚወክለው አስተምሕሮን ነው። ለዛሬ የሚያስፈልገንን አስተምሕሮ መጠየቅ አለብን። እግዚአብሔር ለዛሬ የሚገልጥልን ምንድነው? ለዛሬ የሚገልጥልን እውነት ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እንድንመለስ ይረዳናል።
ለራሳችን ጥቅም ብለን ጥያቄ የምንቀርብበት ብቸኛው ስንኝ ይህ ነው። ይህም በቀላሉ ቁሳቁስ አሳዳጅ ያደርገናል።
ስለዚህ የጸሎቱ ቀጣይ ስንኝ ያለንን ለማጉደል ዝግጁ መሆን እንዳለብን ይነግረናል። ያለንን ማጉደል ከገንዘብ ወዳጅነት የሚፈውስ ፍቱን መድሐኒት ነው።
ማቴዎስ 6፡12 እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
ማንም ሰው ከእናነተ የተበደረው ነገር ቢኖር እንዲመልስላችሁ አትጠይቁት።
ስጡ እንጂ አታበድሩ።
ብትሰጡ የሰጣችሁት ሰው ወዳጃችሁ ሆኖ ይቀራል።
ብታበድሩ ያበደራችኋቸው ሰዎች አይመልሱላችሁም። ከዚህም የተነሳ ትጠሉዋቸዋላችሁ። በዚህም መንገድ ገንዘባችሁንም ወዳጃችሁንም ታጣላችሁ።
ይቅር መባል እንፈልጋለን፤ ስለዚህ እኛም ይቅርታን ለሌሎች መስጠት አለብን። ሌሎች ሰዎችም ልክ እንደ እኛ ይቅር መባል ይፈልጋሉ።
ይቅር መባል እና ሌሎችን ይቅር ማለት ሊነጣጠሉ የማይችሉ ነገሮች ናቸው።
እግዚአብሔር ፍቅሩን ለመግለጥ ሐጥያቴን ይቅር ይለኛል። የበደለኝን ሰው ይቅር ማለት አለመቻሌ ፍቅር እንደሌለኝ የሚያሳይ ምልክት ነው።
ያለኝን ለማጣት ዝግጁ መሆን አለብኝ።
የብረሃን ኃይል የሚሰጡ ነገሮች የብርሃን ኃይልን ለመፍጠር ክብደታቸውን ያጣሉ።
ስለዚህ የሆነ ነገር ከራሳችን ስናጎድል ብቻ ነው ብርሃናችን የሚበራው።
ሰዎችም ይህን ያስተውላሉ። ራስወዳድ እና ስግብግብ በሆነ ዓለም ውስጥ ከራሱ ሊያጎድልና ለሌሎች ሊሰጥ የተነሳ ሰው በቀላሉ ደምቆ ይታያል።
ማቴዎስ 6፡13 ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
እኛ ሰዎች በቀላሉ ፈተና ውስጥ ልንገባ እና ልንሸነፍ እንችላለን። እግዚአብሔር ወደ ፈተና የሚያስገቡ በሮችን እንዲዘጋልን መጸለይ አለብን። እግዚአብሔር በሩን ክፍት ቢተወው እኛ በሞኝነት እንገባበታለን። የራሳችንን ሕይወት በብቃት ልንመራ እንደምንችል እግዚአብሔር አያምንብንም። ፍላጎታችንና ራስ ወዳድነታችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር አብሮ አይሄድም።
ከምኞታችንና ከራስ ወዳድነታች እግዚአብሔር ሊጠብቀን ያስፈልገናል።
1ኛ ቆሮንቶስ 10፡13 ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
ዋነኛው ግባችን የእግዚአብሔር መንግስት መሆን አለበት።
ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
የእግዚአብሔር መንግስት ወደ መጀመሪያው ሐዋርያዊ የቤተክርስቲያን ዘመን ሊመልሰን ይፈልጋል።
የራሳችንን ፍላጎት ትተን የእግዚአብሔርን መንግስት ብናስቀድም እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ሁሉ ይሞላብናል። በራሱ መንገድ።
እግዚአብሔር አብርሐምን ባልጠበቀው ሰዓት ባረከው። አብርሐም መልከጼዴቅ በመንገድ እንደሚገናኘውና እንደሚባርከው አስቀድሞ አላወቀም ነበር።
አብርሐም ሎጥን ለማስጣል በመሄድ እግዚአብሔርን አገለገለ። አብርሐም የእግዚአብሔርን ፈቃድ አስቀደመ።
ማቴዎስ 6፡13 መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
መንግስት የእግዚአብሔር ናት እንጂ የእኛ አይደለችም። በራሳችን መንገድ ሳይሆን እርሱ በወደደው መንገድ እናገለግለዋለን።
ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን የምንመለስበት ኃይል የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ክብሩን ሁሉ መቀበል ይፈልጋል። የጸሎታችንም ትኩረት መሆን ያለበት የእግዚአብሔር ክብር ነው። እግዚአብሔር ከሁሉ መቅደም አለበት።