ማርቆስ 16 - እምነት ሲያብብ ጥርጣሬ ይወገዳል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ትንሳኤው መጀመሪያ ለአንዳንድ ግለሰቦች ተገለጠ። ከዚያም ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ተናገራቸው፤ እነርሱም በታላቅ ኃይል ቤተክርስቲያንን መሰረቱ።
- እግዚአብሔርን ልናገለግል የምንችለው ራሳችንን ዝቅ ስናደርግ ነው
- አንድ መልአክ የሚወክለው በዘመን መጨረሻ የሚገለጠውን የአሕዛብ ነብይ ነው
- ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ ከሁሉ ሊቀድም ይገባዋል
- ሰው ምንም ቦታ የማይሰጣቸው ሰዎች ናቸው ስለ ትንሳኤው ቀድመው ያወቁት
- ኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ገሰጻቸው
- ወንጌሉ አሁን ለሰዎች ሁሉ እና ለሁሉም ሕዝብ ሆኗል
- ንሰሃ ግቡ፤ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ
እግዚአብሔርን ልናገለግል የምንችለው ራሳችንን ዝቅ ስናደርግ ነው
ማርቆስ 16፡1 ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ።
የቅዳሜ ሰንበት እንደተጠናቀቀ ሶስት ሴቶች የኢየሱስን አስከሬን ሽቱ ሊቀቡ መጡ።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተወከሉት በባለ ሰባት ቅርንጫፍ መቅረዝ ነው።
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሐዋርያት እውነት ነበረ።
ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ቃል በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መካከል ቆሟል። ይህንንም እውነት ከላይ ባለው ምስል ውስጥ የሚወክለው በመካከለኛው መቅረዝ ላይ ያለው እሳት ነው።
ከዚያ በኋላ በቀጣዮቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እስከ ጨለማው ዘመን ማብቂያ ድረስ እውነት ጠፍታ ነበር።
በነዚህ ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን ከአዲስ ኪዳን እውነት ርቃ ሄደች።
ርቃ ከሄደችበት ስትመለስ ነው እንደገና እውነትንና ሕይወትን የተቀበለችው።
ስለዚህ የጨለማው ዘመን ሲያበቃ ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው እውነት ተመለሰች።
ለእግዚአብሔር ትልቅ ተግዳሮት የሆነበት እውነትን መልሶ ከሞት ማስነሳት ነበር፤ ምክንያቱም ሰዎች አንዴ ስሕተትን አምነው ለብዙ ዘመናት ከኖሩ በኋላ አስተሳሰባቸውን መቀየር በጣም ከባድ ነው።
ከዚያ ተከትለው ሶስቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጡ ሲሆን እነርሱም 5ኛው፣ 6ኛው፣ እና 7ኛው ዘመናት ናቸው፤ እነዚህ ዘመናት ትልቅ ስፍራ አላቸው ምክንያቱም እውነት ተመልሳ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የምትመለሰው በነዚህ የመጨረሻ ዘመናት ውስጥ ነው።
እነዚህ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ትንሳኤን ይወክላሉ ምክንያቱም በነዚህ ዘመናት ነው እውነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ተቀብራ ከነበረበት አፈር ውስጥ ተመልሳ የምትወጣው። ይህም ትንሳኤ ቀላል አይሆንም ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ አእምሮዋቸው በቤተክርስቲያን ልማዶች ተሞልቷል። ሰዎች ለደህንነታቸው የሚታመኑት በቤተክርስቲያናቸው ሲሆን ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ስሕተት መኖሩን ማመን ያቅታቸዋል። የቤተክርስቲያናቸው መሪ ሊሳሳት የሚችል አይመስላቸውም።
እነዚህ ቤተክርስቲያኖች ግድ የለሾች ከመሆናቸው የተነሳ ምንም እንደማያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እርማት ያስፈልጋችኋል ሲባሉ አይቀበሉም። ቤተክርስቲያንን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ ነበረው ሐዋርያዊ እውነት መመለስ ከተፈጥሮአዊ ዝንባሌያችን ተቃራኒ ነው። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ የሆነ ፍቅር ካለን እግዚአብሔር ብቻ ነው እውነተን ማየት እንችል ዘንድ ጸጋ ሊሰጠን የሚችለው።
ማርቆስ የጠቀሳቸው ሶስት ሴቶቸ በመጨረሻዎቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ማለትም በተሃድሶ ውስጥ የምትገኘዋን ቤተክርስቲያን ይወክላሉ።
ሶስተኛይቱ ሴት ስሟ ሰሎሜ መሆኑ በራሱ ልዩ ትርጉም አለው። ስሟን የጠቀሰው ማርቆስ ብቻ ነው።
ይህች ማርቆስ ሶስተኛውን የእውነት ተሃድሶ ዘመን እንድትወክል የመረጣት ሴት በሰዎች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያላት ሴት አይደለችም። ስለዚህ ማርቆስ የሚነግረን በመጨሻው ዘመን እውነት የምትገኘው እዚህ ግቡ በማይባሉ ሰዎች ዘንድ መሆኑን ነው።
ሐዋርያው ዮሐንስ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ኢየሱስን በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ በአራት ሕያዋን ፍጥረታት ተከብቦ አየው፤ እነዚህም አራት ሕያዋን ፍጥረታት ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲጠብቁ የነበሩ አራቱ የመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ናቸው።
ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
ሁለተኛው ወንጌል የማርቆስ ወንጌል ነው፤ ማርቆስ ትኩረቱ በሁለተኛው ሕያው ፍጡር ማለትም በጥጃው ላይ ነው። ጥጃው አድጎ በሬ ወይም አገልጋይ ይሆናል፤ ማለትም እግዚአብሔርን ስለማገልገል ይማራል።
ማርቆስ አጽንኦት ሰጥቶ የሚነግረን እግዚአብሔርን ለማገልገል ምን መማር እንዳለብን ነው።
ስለዚህ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም የአዲስ ኪዳን ትንሳኤ ወቅት ግራ የሚያጋባ ጊዜ ነው።
እግዚአብሔርን ከልብ የሚያገለግሉት በሰው ዘንድ ቦታ ያልተሰጣቸው ሰዎች ናቸው
ማርቆስ 16፡2 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።
ፀሃይዋ ስትወጣ በጠዋቱ አስከሬኑን ሊቀቡ ተዘጋጅተው መጡ።
ነገር ግን የፀሃይዋ መውጣት የጌታን ትንሳኤ የሚያበስር ምልክት ነበር።
ማርቆስ 16፡3 እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤
እግዚአብሔርን ማገልገል አስቸጋሪ የሚሆንበት ምክንያት ስናገለግል የሚገጥሙን ችግሮች በራሳችን አቅም ልናሸንፍ ከምንችለው በላይ መሆናቸው ነው።
ከዚህም የተነሳ በራሳችን ብርታት ልንመካ አንችልም። ድጋፍ ያስፈልገናል።
ማርቆስ 16፡4 ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።
ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ሲደርሱ አስገራሚ ነገር ገጠማቸው፤ ድናጋዩ ተንከባልሎ አገኙት።
እግዚአብሔርን ሊያገለግሉ ማልደው ተነሱ። ነገር ግን እግዚአብሔር ደግሞ ከእነርሱ ቀድሞ በመገኘትና ከአቅማቸው በላይ የነበረውን ትልቅ ችግር በመፍታት አስገረማቸው።
ለዚህ ነው ታላላቅ ሰዎች የማያስፈልጉት። እግዚአብሔር እርሱን ለሚያገለግሉ ደካሞች ችግራቸውን ይፈታላቸዋል።
አንድ መልአክ የሚወክለው በዘመን መጨረሻ የሚገለጠውን የአሕዛብ ነብይ ነው
በትንሳኤው ሰዓት ሌላ አስደንጋጭ ነገር ገጠማቸው። አስከሬኑን ፍለጋ ሲመጡ መቃብሩ ባዶ ሆኖ አገኙት። ሰማይ ምድሩ ተገለባበጠባቸው። ምንም ነገር እነርሱ እንደጠበቁት ሆኖ አልተገኘም።
የቤተክርስቲያናችንን ልማድ በመከተል እግዚአብሔርን ልናገለግል አንችልም።
ከሚለዋወጡ ሁኔታዎች ጋር አብረን መሄድ አለብን። እግዚአብሔር ስናገለግለው ማድረግ ያለብንን ነገር እየለወጠ ነው።
ፍንጭ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር አለብን።
ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡
ያልተጠበቀ ነገር ሊመጣ እንደሚችል መጠበቅ አለብን። የእግዚአብሔር መንገድ ከእኛ መንገድ ይለያል።
ማርቆስ 16፡5 ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።
መቃብሩ ግራ እና ቀኝ ጎን አለው።
ወንድም ብራንሐምን የሚወክለው ይህ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ነበር የተቀመጠው፤ ማለትም ስለ መጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥር በትክክል ተረድቷል።
ማርቆስ በዋነኝነት ትኩረት ሰጥቶ የጻፈው ስለ አሕዛብ ቤተክርስቲያን ስለሆነ በታላቁ መከራ ዘመን ስለሚኖሩት 144,000 አይሁዶች ዝርዝር መረጃ አልሰጠንም። ለዚህ ነው ማርቆስ ሁለተኛውን መልአክ ያልጠቀሰው።
በመጨረሻው ዘመን ሁለት መላእክት ወደ አይሁዶች ይመጣሉ፤ ወደ አሕዛብ የሚላከው የመጨረሻው ዘመን መልአክ ወይም መልእክተኛ-ነብይ አንድ ብቻ ነው።
ሌላኛው ጎን ክፍት የተተወው ወንጌልን ከ2,000 ዓመታት በፊት ትተው ለሄዱ ለአይሁዶች ለሚላከው መልእክተኛ ነው።
ማቴዎስ እና ማርቆስ መቃብሩጋ ያዩት አንድ መልአክ ነው፤ ይህም አንድ መልእክተኛ-ነብይ የሚላክላትን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን የሚያመለክት ሲሆን ይህም መልእክተኛ ለአሕዛብ የእግዚአብሔርን ቃል ሚስጥር የሚገልጠው ነብይ ዊልያም ብራንሐም ነው።
(ሉቃስ እና ዮሐንስ ብዙ ትኩረት ያደረጉት አይሁዶች ላይ ስለሆነ ነው ስለ ሁለት መላእክት የሚናገሩት)።
“አንድ ጎልማሳ።” ወደ መጨረሻው ዘመን አካባቢ የሚኖሩ መንፈሳዊ ልጆች ለአሕዛብ በተላከው ነብይ ዊልያም ብራንሐም አማካኝነት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ አለባቸው።
(ሉቃስ እና ዮሐንስ ሁለት መላእክትን አዩ፤ ይህም የሚያመለክተው በታላቁ መከራ ዘመን አይሁዶችን እየመሩ ወደ መሲሁ የሚመልሷቸውን ሁለት ነብያት ሙሴ እና ኤልያስን ነው።)
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
የእግዚአብሔር ቀን ማለት የ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ነው።
ሚልክያስ 4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
እርግማኑ በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ወቅት ከሚፈነዳው አቶሚክ እና ኑክሊየር ቦምብ ፍንዳታ በኋላ ለብዙ ጊዜ በምድር ላይ የሚቆየው ሬድዮ አክቲቭ ጨረር ነው።
ኤልያስ ሁለት ነገሮችን ማድረግ አለበት።
በኤልያስ መንፈስ የመጣው አይሁዳዊ ሰው መጥምቁ ዮሐንስ ነበር። ዮሐንስ የማያምኑትን አይሁዳውያን አባቶች ወደ ልጆቻቸው ማለትም ወደ ኢየሱስ እና ወደ ሐዋርያት እምነት እንዲመለሱ አደረገ። እነርሱም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የአሕዛብን ቤተክርስቲያን መሰረት ጥለዋል።
ከዚያ በኋላ በመጀመሪያ ልጆች የነበሩት ሐዋርያት አድገው የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች ሆኑ፤ ይህችም ቤተክርስቲያን በዋነኝነት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ናት። እነርሱ ያስተማሩት ሐዋርያዊ እውነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፋ።
በመጨረሻው ዘመን ከ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ በፊት በኤልያስ መንፈስ የሚነሳ የአሕዛብ ነብይ ከአሕዛብ የሆኑ መንፈሳዊ ልጆችን ወደ ሐዋርያዊ አባቶቻቸው እምነት ይመልሳቸዋል።
መጥምቁ ዮሐንስ ሁለቱንም ሥራዎች ሊሰራ አልቻለም።
ዮሐንስ በዘመኑ በሚልክያስ 4፡6 ከተጠቀሱት ሥራዎች ውስጥ አንዱን ብቻ ነው መስራት የቻለው። ይህም ሥራ አመጸኞቹን አባቶች ወደ ታዛዥ ልጆቻቸው መመለስ ነው።
ሉቃስ 1፡17 እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ዮሐንስ ሁሉን አላቀናም። ዮሐንስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የማይታወቅ አዲስ የውሃ ጥምቀት ይዞ መጣ። መሲሁን ለሕዝብ አስተዋወቀ። ይህ ሁሉ ለአይሁዶች አዲስ ልምምድ ነው። ቤተመቅደሱ ለአይሁዶች የአምልኮ ማዕከላቸው ቢሆንም እንኳ ዮሐንስ ወደ ቤተመቅደስ አልመጣም።
ዮሐንስ ኤልያስ ነህ ወይ ተብሎ ሲጠየቅ አይደለሁም አለ ምክንያቱም የሚልክያስ ትንቢት እርሱን ብቻ ሳይሆን ሁለት ሰዎችን በተመለከተ መሆኑን ስላወቀ ነው።
ዮሐንስ 1፡21 እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።
ዮሐንስ በምድር ላይ ከሚመጣው የኑክሊየር ሬድዮ አክቲቭ ጨረር እርግማን 2,000 ዓመታት ቀድሞ ነው የመጣው።
ስለዚህ ልክ ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ለአሕዛብ ተልኮ የሚመጣ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ሌላ ነብይ አለ ማት ነው።
“አትደንግጡ።” ሰዎች ቤተክርስቲያን የምታስተምራቸውን ስሕተት አንቀበልም በማለት እና የቤተክርስቲያኖችን ስሕተት ለይተው በማወቅ ሂደት ውስጥ የሚከፍሉት ዋጋ ያስፈራቸዋል።
ማርቆስ 16፡6 እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።
ዲያብሎስ እውነተኛ አማኞችን የሚያጠቃበት ዋነኛ መሳሪያው መገፋት እና ውግዘት ነው። ነገር ግን ከቃሉ መገለጥ የምናገኘው ኃይል ልባችንን ስለሚሞላውና ስለሚያነቃቃን ምንም ነገር መፍራት አያስፈልገንም። ለብዙ ዘመናት ከሰዎች ተሰውረው የቆዩትን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት የመረዳት ዕድል ተሰጥቶናል።
ናዝሬት የሚለው ስም የተገኘው ሁለት የዕብራይስጥ ቃላት ወደ ግሪክ ሲተረጎሙ ነው።
“ናዛራ” ማለት እውነት ማለት ነው።
“ኔትዘሬት” ደግሞ ቅርንጫፉ የሚወጣበት ቦታ ማለት ነው።
እነዚህ ሁለት ዕብራይስጥ ቃላት ሲጣመሩ የሚሰጡን ትርጉም “እውነት እንደ ቅርንጫፍ የሚወጣበት ቦታ” የሚል ነው።
ይህ ሃሳብ ወደ ግሪክ ቋንቋ ሲተረጎም “ናዝሬት” የሚለውን ስም ይሰጠናል።
ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥
የመቅረዙ መካከለኛ መብራት ሐዋርያዊ እውነት ተገልጦ የነበረበትን የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
ወንጌሉ ከዚህ ነው እንደ ቅርንጫፍ የወጣው እና የጠፋው፤ ከዚያም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ተመልሶ በተሃድሶ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቷል።
እግዚአብሔርን በአግባቡ የምናገለግለው ከሆነ የመጨረሻው ማለትም ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ አለበት። አዲስ ኪዳን ውስጥ ከተጻፈው ቃል ውጭ አንዳች የምናደርግ ከሆነ በትክክለኛው መንገድ ላይ አይደለንም ማለት ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ ከሁሉ ሊቀድም ይገባዋል
ጴጥሮስ ኢየሱስን ሶስት ጊዜ በመካዱ ትልቅ ስሕተት ሰርቷል።
ነገር ግን መልአኩ የጴጥሮስን ስም በመጥቀሱ ጴጥሮስ ይቅር እንደተባለ መረዳት እንችላለን።
ከአገልግሎት የምንማረው ይህን ነው። ስናገለግል እየወደቅን እየተነሳን ነው የምናገለግለው፤ ይህም እኛ ሰዎች ሁልጊዜ የኢየሱስ እርዳታ እንደሚያስፈልገን ያስታውሰናል። ብቻችንን ተነስተን እናገልግል ካልን እንሳሳታለን።
ማርቆስ 16፡7 ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።
ኢየሱስ ቀድሟቸው ስለሄዴ መልአኩ ኢየሱስን ኢንዲከተሉ ነገራቸው።
በሌላ አነጋገር የምናምነው ነገር በሙሉ የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል መሆን አለበት።
ወንድም ብራንሐም ሲያስተምር የተናገራቸውን ቃሎች በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረን በማየት እርሱ የተናገረው እንደ ቃሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።
ማርቆስ 16፡8 መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩም።
ኢየሱስ ከሙታን በተነሳበት ጊዜ ታላቅ ፍርሃት ነበረ።
ይህ የአዲስ ኪዳን አማኞች ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማውራት በሚፈሩበት ነውጠኛ በሆነ ሰዓት ከሙታን እንደሚነሱ የሚያመለክትና ለእኛ ማስጠንቀቂያ ነው
አሞጽ 6፡10 ያን ጊዜ፦ የእግዚአብሔርን ስም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል ይለዋል።
የስላሴ ትምሕርት ቤተክርስቲያንን ከመቆጣጠሩ የተነሳ ሰዎች ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ስለመሆኑ ለማሰብ እንኳ ይፈራሉ። ስለዚህ ሶስት አካላት አንድ እግዚአብሔር ናቸው ብለው ያምናሉ። ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ስም አልባ ሆኗል ምክንያቱም ለሶስት የተለያዩ አካላት አንድ ስም ማውጣት አይቻልም።
ሰው ምንም ቦታ የማይሰጣቸው ሰዎች ናቸው ስለ ትንሳኤው ቀድመው ያወቁት
ማርቆስ 16፡9 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።
መግደላዊት ማርያም ሴት እንደመሆኗ በ2,000 ዓመታት ዘመን ውስጥ የነበረችዋን ቤተክርስቲያን ትወክላለች። ቤተክርስቲያን በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ታልፋለች። በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ዓለምን ከሚገዙ እና ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልከው በመግባት ቤተክርስቲያንን ማሰናከል ከሚፈልጉ አጋንንታዊ ኃይላት የተነሳ ቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ይገጥሙዋታል። በእያንዳንዱ ዘመን እግዚአብሔር እነዚህን ክፉ መናፍስት ከቤተክርስቲያን ማስወጣት አለበት። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ዋነኛው ጠላታችን አታላይ መንፈስ ይህ መንፈስ ይዞ የሚያመጣቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች ናቸው።
ማርቆስ 16፡10 እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤
ይህ በጣም ይገርማል። አንዲት ሴት ኢየሱስን ከሙታን ተነስቶ አየችው፤ ደቀመዛሙርት ግን አናምንሽም አሏት። ማመን ትተው በሃዘን ቆዝመው መቀመጥን መረጡ። በሃዘን መቀመጣቸው ለሚያያቸው ሰው ሊያስገርም ይችላል ግን ጊዜ ከማባከን ውጭ ምንም ጥቅም አልነበረውም።
ማርቆስ 16፡11 እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።
በጣም የከፋው ችግር አላስፈላጊ በሆነው ሃዘናቸው ተቆራምደው መቀመጣቸው ሲሆን ይህም እውነትን እንዳያምኑ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
ይህ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ነው። የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ በሚፈጸምበት ጊዜ ብዙ ሰዎች ትንሳኤ መፈጸሙን አያምኑም።
ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ እራሱ ተገልጦ ካናገራቸው ብቻ ነው የሚያምኑት። ኢየሱስ ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ የቀረቡትን ደቀመዛሙርትን ዝም ብሎዋቸው አስቀድሞ ለአንዲት ሴት ሊገለጥ ይችላል ብለው አልጠበቁም።
የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተሰጠን ማስጠንቀቂያ እንደሚነግረን የአዲስ ኪዳን አማኞች ትንሳኤ በሚፈጸምበት ጊዜ ቤተክርስቲያኖች ሳይሆኑ ግለሰቦች ናቸው የሚያዩት።
በስተመጨረሻ የእግዚአብሔር ትኩረት በቤተክርስቲያን ቡድኖች ላይ ሳይሆን በግለሰቦች ላይ ነው የሚያርፈው።
ማርቆስ 16፡12 ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤
ከዚህ በፊት ትኩረት የሚደረገው ኢየሩሳሌም ላይ ነበር። የቀሬናው ስምኦን ከገጠር ወጥቶ ወደ ከተማ ሲመጣ ኢየሱስ መስቀል ተሸክሞ እየሄደ ሳለ መስቀሉን በመሸከም አገዘው።
በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት ሰዎች አሉ፤ ማርቆስ ግን ሰዎች በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆንን ለማሳየት ብሎ ስማቸውን አልጠቀሰም። እነዚህ ሰዎች ታላቂቱን ከተማ ትተው ወደ ታናሽ ገጠር እየሄዱ ነበሩ። ከሙታን የተነሳውም ኢየሱስ በመንገድ ላይ ከእነርሱ ጋር አብሮ በመሄድ ከብሉይ ኪዳን ነብያት ሕይወት እየጠቀሰ ስለራሱ ሚስጥርን ገለጠላቸው። ለነዚህ ሰዎች ተሰውሮ የነበረውን የብሉይ ኪዳን ሚስጥር መረዳት በጣም አስፈላጊ ነበር።
ይህም በአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ጊዜ እዚህ ግቡ የማይባሉና በሰው ዘንድ ቦታ የሌላቸው ሰዎች የተገለጡትን የቃሉን ሚስጥራት ይረዳሉ ማለት ነው።
በትንሳኤው ጊዜ ኢየሱስ ገጠር ውስጥ ገብቶ በስም ላልተጠቀሱ ሰዎች ተገልጦ እውነትን አስተማራቸው። ይህን ማድረጉ እነዚህን ሰዎች ከሌላው ሰው ልዩ ወይም ታላቅ አያደርጋቸውም።
ኢየሱስ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደማያውቁት አንድ እንግዳ ሰው መስሎ ነው የቀረባቸው።
የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን በሚነሱበት ጊዜ እዚህ ግቡ ለማይባሉ ሰዎች እንደ እንግዶች ሆነው ይገለጡላቸዋል። ከሙታን የተነሱትን የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ልናውቃቸው የምንችለው እነዚህ ሰዎች ስለ ምን እንደሚያወሩ መረዳት እንችል ዘንድ ሙሉ በሙሉ ወደ አዲስ ኪዳናዊው የሐዋርያት እምነት ከተመለስን ብቻ ነው።
ማርቆስ 16፡13 እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም።
እነዚህ ሰው ቦታ የማይሰጣቸው ግለሰቦች በቡድን ተሰብስበው ወደ ተቀመጡት ደቀመዛሙርት (ማለትም ወደ ቤተክርስቲያን) ሄደው ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ነገሯቸው፤ ነገር ግን በቡድን የጠቀመጡት ደቀመዛሙርት ኢየሱስ አስቀድሞ ወደ እነርሱ አለመምጣቱን ሊያምኑ አልቻሉም። ስለዚህ የነበሩበት የቡድን መንፈስ ለሁለቱ ግለሰቦች የተገለጠላቸውን እውነት መቀበል እንዳይችሉ አደረጋቸው።
ኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ገሰጻቸው
ማርቆስ 16፡14 ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።
ኢየሱስ በመጀመሪያ ምጻቱ ወቅት ከሞት በተነሳ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ከሞት መነሳቱን ያዩ ሰዎች ሲነግሯቸው አላመኑም።
ይህም ዳግም ምጻቱ ሲቀርብ ተመሳሳይ ነገር በድጋሚ እንደሚሆን ያመለክታል።
ኢየሱስ ራሳቸውን ከሌላው የሚበልጡ አድርገው በማየታቸው የተነሳ ስለተፈጠረባቸው የልብ ድንዳኔ ገሰጻቸው። ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ መጀመሪያ ወደነሱ ቡድን የሚመጣ መስሏቸው ነበር። ኢየሱስ መጀመሪያ ለግለሰቦች ሲገለጥ በቡድን ይንቀሳቀሱ የነበሩ ደቀመዛሙርት ግለሰቦችን ለማመን እምቢ አሉ።
በትንሳኤ ጊዜ ቡድኖች (ቤተክርስቲያኖች) እውነትን ከማወቃቸው ቀድመው የሚያውቁት ግለሰቦች ናቸው፤ ምክንያቱም በመጨረሻው ጊዜ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ነው የሚቆመው።
ወንጌሉ አሁን ለሰዎች ሁሉ እና ለሁሉም ሕዝብ ሆኗል
ማርቆስ 16፡15 እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
“ለፍጥረት ሁሉ።” ወንጌሉ ውስጥ ዘረኝነትና ብሔርተኝነት የለም።
ወንጌሉ ውስጥ በጎሳና በነገድ ክፍፍል የለም። ሁሉም እውነትን የመስማት እኩል መብት አላቸው።
እውነቱ እስከ ምድር ዳርቻ መድረስ አለበት። ዛሬ እውነት እስከ ምድር ዳርቻ የሚደርሰው በኢንተርኔት ነው። ዌብሳይት ላይ የተጫነ እውነት በዓለም ዙርያ ሁሉም ቦታ ሊገኝ ይችላል።
ኢንተርኔት ከሁሉም የተሻለና ውጤታማ የሆነ እውነትን ማሰራጫ መንገድ ነው።
በራሺያ እና በዩክሬይን መካከል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ ኢሎን ማስክ እሩቅ ቦታዎች ሁሉ የኢንተርኔት መስመር እንዲዘረጋ አድርጓል። ስለዚህ እሩቅ ቦታ የሚገኙ አማኞች የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች የሚያብራሩ የኢንተርኔት ገጾችን ማግኘት ይችላሉ።
ስለዚህ አሁን ዓላማችን በምድር ላይ የትም ቦታ ያሉ ሰዎች መማር ይችሉ ዘንድ የተገለጡትን ሚስጥራት በኢንተርኔት ማሰራጨት ነው።
ንሰሃ ግቡ፤ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ
ወደ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን ወደነበሩ ሐዋርያት እምነት ለመመለስ ልክ እነርሱ እንዳጠመቁ ማጥመቅ አለብን።
ማርቆስ 16፡16 ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
የመጀመሪያው እርምጃ ንሰሃ መግባት ሲሆን ይህም አማኙን ከሲኦል ያድነዋል።
ስናጠምቅ ሐዋርያት አዲስ ኪዳን ውስጥ ባጠመቁበት መንገድ ነው ማጥመቅ ያለብን።
ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ ጥምቀት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም በኢየሱስ ስም ነው የተጠመቁት። ይህም ኢየሱስ ከአይሁድ ሕዝብ በላይ የነበረው አብ፣ በመካከላቸው እንደ አማኑኤል (እግዚአብሔር ከእኛ ጋር) ተገልጦ ከአይሁዶች ጋር የነበረው ወልድ፣ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን የሚገልጥ እውነት ነው።
ጴጥሮስ ታላቁ ዓሣ አጥማጅ ነበር። የበዓለ ሃምሳ ዕለት ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት አይሁዶችን አጠመደ። በኢየሱስ ስም በውሃ ማጥመቃቸው ስለ መለኮት የነበራቸው መረዳት ትክክለኛ መሆኑን ያሳያል። የሁሉን ቻዩ አምላክ ስም ማን እንደሆነ አውቀዋል።
(ጌታ እና ክርስቶስ ልዩ ማዕረጎች ናቸው። ስሙ ግን ኢየሱስ ነው። ነገር ግን ስለ የትኛው ኢየሱስ እያወራን መሆናችን ግልጽ እንዲሆን ከማዕረጎቹ አንዱን መጠቀም አለብን ምክንያቱም ኢየሱስ የተባሉ ሌሎችም ሰዎች አሉ።)
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
ፊሊጶስ ወደ ሰማርያ ሄደ።
የሐዋርያት ሥራ 8፡12 ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።
በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ብለው አጠመቁ የሚል አንድ ጊዜ እንኳ አልተጠቀሰም።
የሐዋርያት ሥራ 8፡14 በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው።
የሐዋርያት ሥራ 8፡15 እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፤
16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
ጴጥሮስ ሲመጣ ለሳምራውያን ጸለየላቸው ምክንቱም እነርሱ አስቀድመው በትክክለኛው የውሃ ጥምቀት ተጠምቀው ነበር።
ጳውሎስ በኤፌሶን የነበሩ አሕዛብን በተመሳሳይ መንገድ ነው ያጠመቃቸው።
የሐዋርያት ሥራ 19፡1 አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፥ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ፦
የሐዋርያት ሥራ 19፡5 ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤
ይህ የመለኮት እውቀት ማለትም ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር መሆኑን ማወቅ በ325 ዓ.ም ከተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲያስት ከቆየው ከስላሴ የስተት ትምሕርት ቤተክርስቲያንን ያድናታል። ልባሞቹን ቆነጃጅት ከሰነፎቹ የቤተክርስቲያን ቆነጃጅት የሚለያቸው መለኮትን በትክክል ማወቅ ነው። በስተመጨረሻም ይህ እውቀት ሙሽራይቱን ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ተከትሎ ከሚመጣው ከታላቁ መከራ ያድናታል። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ሶስት ማዕረጎች አንድ ስም ናቸው በሚል ትምሕርት በመታለላቸው ምክንያት በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያሉ ያጠምቃሉ።
ኢየሱስ ስለ ውሃ ጥምቀት ምን ብሎ እንደተናገረ ተመልከቱ።
ማቴዎስ 28፡19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
ኢየሱስ ሁለት ጊዜ ስለ ትምሕርት ተናግሯል። ለምን ሁለቴ ተናገረ? ትምሕርት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ነው ኢየሱስ አጽንኦት የሰጠው።
አብም፣ ወልድም፣ መንፈስ ቅዱስም የሆነውን የአንዱን አምላክ ስም ማወቅ አለብን።
በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ አብ ያህዌ ወይም አሁን ምን ተብሎ እንደሚነበብ በማይታወቀው JHVH ወይም YHWH በሚባለው ስም ይጠራ ነበር። እግዚአብሔር ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር አብ ተብሎ ተጠርቶ አይታወቅም።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጡት ስሞች አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አልተደገሙም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ከአይሁድ ሕዝብ በላይ በእሳት ወይም በደመና አምድ ተገልጦ ነበር።
ወንጌሎቹ ውስጥ እግዚአብሔር ኢየሱስ በተባለው ሰው አማካኝነት ከአይሁዶች ጋር በመኖር ተገለጠ።
መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር ወልድ” አይልም።
ልዕለ ተፈጥሮአዊው መንፈስ ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ አደረ፤ በዚህም እግዚአብሔር ኢየሱስ የተባለውን የሰው ስም ወሰደ።
እግዚአብሔር “እግዚአብሔር አብ” የሆነው ሰው በሆነው “በእግዚአብሔር ልጅ” ውስጥ ያደረ ጊዜ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 14፡16 እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
ስለዚህ አጽናኙ የእውነት መንፈስ ኢየሱስ ነው።
ከወንጌሎቹ በኋላ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር የተገለጠው በቤተክርስቲያን በኩል ነው።
አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ማለት እግዚአብሔር ከአይሁድ ሕዝብ በላይ፣ ከአይሁድ ሕዝብ ጋር፣ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ማለት ነው።
ኢየሱስ በአማኞቹ ልብ ውስጥ ይገለጣል።
ኢየሱስ የግል አዳኛችን መሆኑን ካላመንን ግን ጠፍተናል። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተትና እንከን የሌለበት ፍጹሙ እውነት መሆኑን የማያምኑ ሰዎችም ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይጠፋሉ።
ማርቆስ 16፡17 ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤
አማኞች ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ኃይል ማግኘት ይችላሉ።
ጴንጤቆስጤያዊ ኃይል የተገለጠው በልሳን በመናገር እና አጋንንትን በማስወጣት ነው።
ማርቆስ 16፡18 የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
እግዚአብሔር በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ታላቅ ኃይልን ገለጠ። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ አማኞች ሰዎች መርዝ ቢያበሉዋቸው መርዙ በእነርሱ ላይ ኃይል አይኖረውም። በሽታ ሁሉ በጸሎት ይፈወስ ነበር። ሐዋርያት ያገለግሉ በነበረበት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ታላላቅ ምስክርነቶች ተሰምተዋል።
ታላቁ የጴንጤቆስጤ ኃይል ለሚያምኑ ሰዎች ዛሬም አለ።
ማርቆስ 16፡19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።
ኢየሱስ ለሐዋርያት የመጨሻውን መመሪያ ሰጥቷቸው ወደ ሰማይ አረገ።
የእግዚአብሔር ቀኝ ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው።
ማቴዎስ 26፡64 ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።
ዘጸአት 15፡6 አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤ አቤቱ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ፡፡
ወንጌሉ የሚሰራጨው ሐዋርያት ለመስበክ በወጡ ቁጥር የእግዚአብሔር ኃይል በሚያደርግላቸው ድጋፍ ነው።
ማርቆስ 16፡20 እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።
ሐዋርያት የትኛውም ሰው ሰራሽ ገደብ አላስቆማቸውም። በየስፍራው ሁሉ እየሄዱ ሰበኩ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በተሰበከበት ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል እየተገለጠ ስለ እውነት ይመሰክር ነበር።
ሁለቱ ወሳኝ የወንጌል ገጽታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እና አስደናቂው የእግዚአብሔር ኃይል ናቸው።
ስለዚህ ትኩረት ይደረግ የነበረው የሆነ ሰው ላይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ማለትም ኢየሱስ ላይ ነበር። የዚያ ዘመን ታላላቅ ሰዎች ሕዝቡን ወደ ራሳቸው ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ኃይል እና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ያመለክቱ ነበር።
የቤተክርስቲያን ድካም ሰዎች ወደ ራሳቸው ትኩረት መሳብ መፈለጋቸው ነው።