ማርቆስ 15 - ሮም የእግዚአብሔርን ቃል ገደለችው



ከሰዎች ሁሉ በላይ ሐይማኖተኛ የሆኑ ሰዎች አንደኛ ቅድስት በሆነችው ከተማ ውስጥ በዘግናኘነቱ አንደኛ በሆነ ግፍ ከሰዎች ሁሉ ታላቅ የሆነውን ሰው ገደሉ።

First published on the 3rd of March 2023 — Last updated on the 3rd of March 2023

የሐይማኖት መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል አሰሩ

 

ኢየሱስ በመጀመሪያ ምጻቱ እንደ ሰው ሆኖ በመጣ ጊዜ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ያደረጉበትን ዛሬ ደግሞ በዳግም ምጻቱ የሚመጣበት ጊዜ ሲቀርብ የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሳሳይ ነገር እያደረጉበት ነው።

ማርቆስ 15፡1 ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

“ወዲያውም”። በፍጥነት።

የአይሁድ መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል (ኢየሱስን) ለማሰር ሲመጡ ምንም ጊዜ አልፈጁም።

ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት መሆኑን ይክዳሉ፤ የዚህንም መጽሐፍ ወዲያው ለማሰር ይፈጥናሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት ሰዎች ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይቀበሉና እንዲያጥላሉ ነው።

በሕገ ወጥ መንገድ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ለውጠው ከ100 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሶችን አዘጋጅተዋል።

ዮሐንስ በሰማይ ዙፋን ዙርያ አራት ሕያዋን ፍጥረታትን አየ፡-

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

 

ይህ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አራት ደረጃዎችን ይወክላል። የክርስቶስ መንፈስ የይሁዳ አንበሳ፣ የአራዊት ሁሉ ንጉስ ነው፤ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የእውነትን መሰረት የጣለ እርሱ ነው። ከዚያ በኋላ ተከትሎ በመጣው ረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ጥጃው አድጎ ብርቱ በሬ ሆነ፤ ይህም ለመታረድ የተዘጋጀ እንስሳ ነው፤ ስለዚህ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማኞች በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተገደሉ።

ከዚያ ወዲያ የክርስቶስ መንፈስ የሰዎችን አእምሮ ባረከ። ስለዚህ ማርቲን ሉተር መዳን በጸጋ አማካኝነት በእምነት ብቻ ነው የሚገኘው የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ። ጆን ዌስሊ ቅድስናን እና የወንጌል ስርጭትን ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ፤ ይህም ታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት እንዲጀመር ምክንያት ሆነ።

በ1604 እና 1769 ዓ.ም እግዚአብሔር ምሑራንን በማስተዋል ባረከና የግሪክ እንዲሁም የዕብራይስጥ ቋንቋ ቃላትን በትክክል መተርጎም እንዲችሉ አደረገ፤ በተጨማሪም ትክክለኞቹን የብራን ጽሑፎች መርጠው እንዲጠቀሙ መራቸው። እነርሱም ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ከመጀመሩ በፊት የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉመውና አርመው አጠናቀቁ። በዚህም ምክንያት በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ውስጥ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ዙርያ ሁሉ ሊዳረስ ቻለ።

ቀጥሎ የመጣው ደግሞ መንፈሳዊ መረዳት የተለቀቀበት የንስር ዘመን ነው፤ በዚህም ዘመን ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እንዴት መተርጎም እንዳለብን አስተማረን። ከዚህም የተነሳ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የነበሩ ጥንታዊ ሐዋርያት ወደነበሩበት እምነት መመለስ እንችላለን።

በቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ልክ ከዳግም ምጻት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ቃል (የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ) ሆኖ ስለሚገለጥ አይሁዶች ኢየሱስን እንደገፉት ሁሉ የአሁን ዘመን ሰዎችም መጽሐፍ ቅዱስን ይገፉታል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ወንድም ብራንሐም ያመጣውን የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ አንቀበልም ይላሉ፤ ነገር ግን የወንድም ብራንሐምን መልእክት ከ100 በላይ የተለያዩ ትርጓሜዎችን ሰጥተው ያቀርባሉ፤ እንዲሁም ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ይጠቀማሉ። በዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ ግርግር ውስጥ ሙሉውን እውነት ማግኘት በጣም ከባድ ነው።

የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን በማታ በጨለማ ይዘውት ሕገወጥ በሆነ ችሎት ፈረዱበት።

ሊገድሉት የፈለጉት እርሱ ራሱን ክርስቶስ፣ የሰው ልጅ ብሎ በመጥራት ተሳድቧል ብለው ነው ።

ሆኖም የአይሁድ መሪዎች ሮማውያን ይህንን እንደ በቂ ምክንያት ተቀብለው እንደማይገድሉት አውቀዋል። ስለዚህ ሮማውያን ኢየሱስን እንዲገድሉላቸው ሲጠይቁ ሌላ ምክንያት ፈጥረው በመናገር ነው። ሰውን የመግደል ስልጣን ያላቸው ሮማውያን ብቻ ነበሩ።

የሐይማኖት መሪዎች “ጉባኤ በሙሉ” የተሰበሰቡት ለአንድ ዓላማ ብቻ ነው።

ኢየሱስን “አሰሩት”።

ዛሬም ይኸው መንፈስ ነው በምድር ላይ የተለቀቀው። የቤተክርስቲያን መሪዎች ዛሬ ሲሰበሰቡ አንድ ዓላማ ብቻ ነው ያላቸው፤ ይህም ዓላማ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ላይ ያለውን ተጽእኖ አስሮ አፍኖ ማስቀረት ነው። ፍጹም የሆነ እና እንከን የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አይቀበሉም። ስለዚህ ሁልጊዜ ስሕተት አለበት፣ አፈታሪክ አለበት፣ እርስ በርሱ ይጋጫል፣ ምንም የማይጠቅሙ ዝርዝሮች አሉት ይላሉ።

ክርስቲያኖች ዛሬ እምነታቸውን ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ከእግዚአብሔር ቃል ብቻ በመጥቀስ ትክክለኛ መሆናቸውን ማሳየት አይችሉም።

ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ፖለቲካዊ መሪ ለሆነው ለጲላጦስ ተላልፎ ተሰጠ።

ቤተክርስቲያኖች ዛሬ ከፖለቲከኞች አመለካከት ጋር ላለመጋጨት ብለው ያመቻምቻሉ። ስለዚህ አሁን የቤተክርስቲያን መሪዎች የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መፍቀድ ጀምረዋል፤ ወንዶች ሴት ነኝ ብለው ሲያስቡ እና ሴቶችም ወንድ ነኝ ብለው ሲያስብ ዝም ብለው ይመለከቷቸዋል።

ቤተክርስቲያኖች የኤቮልዩሽን ቲዎሪ እና ቢግ ባንግ ቲዎሪን ይደግፋሉ፤ ደግሞም ሰዎች ስለ ዓለማዊ አለባበስ የሚያስቧቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተሳሰቦች በሙሉ ይቀበላሉ።

ማርቆስ 15፡2 ጲላጦስም፡- አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም፡- አንተ አልህ ብሎ መለሰለት።

ሮማዊው ገዥ ጲላጦስ ብዙውን ጊዜ በቂሳሪያ ነበር የሚኖረው።

 

 

ጲላጦስ በዚያ ሰዓት በኢየሩሳሌም የተገኘበት ምክንያት አይሁዶች በሆነ ሐይማኖታዊ ጉዳይ አመጽና ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ ብሎ ስለሰጋ ነው። የሕዝቡ ዓመጽ ከቁጥጥር ውጭ ከወጣ ሮማዊው ንጉስ ጢባርዮስ ጲላጦስን ከስልጣን ያባርረዋል።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ይህንን ስለሚያውቁ የሕዝቡን ስሜት አውከው አመጽ እንዲነሳ ማድረግ ቢችሉ ጲላጦስ ዓመጽ እንዳይነሳ ለማድረግ ብሎ ኢየሱስ እንዲገደል ያቀረቡትን ጥያቄ እንደሚቀበልላቸው አውቀዋል።

ጲላጦስ የገዥነት ሥራውን ለማትረፍ ብሎ ኢየሱስን ይገድላል።

ሰባኪዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ስልጣንና ደሞዝ ለማስጠበቅ ብለው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ይክዳሉ ይቃረናሉ።

የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን የአይሁድ ንጉስ ሊሆን ይፈልጋል ብለው ከሰሱት። ይህም የሁሉ ንጉስ ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሮማዊ ንጉስ በመቃወም እንደሆነ አድርገው ተረጎሙት።

ኢየሱስ የሆሳዕና ዕለት ንጉስ ነው ተብሎ ቢታወጅም እንኳ እኔ ንጉስ ነኝ ብሎ አያውቅም።

ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ናቸው እርሱን ንጉስ ያሉት።

ስለዚህ ለጲላጦስም የመለሰለት መልስ፡- “አንተ ንጉስ እንደሆንኩ ተናገርክ እንጂ እኔ አላልኩም” የሚል ነበር።

ማርቆስ 15፡3 የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም።

ከዚያም በኋላ የሐይማኖት መሪዎች በብዙ ነገሮች ከሰሱት፤ ኢየሱስ ግን ለነዚህ ክሶች ምንም ትኩረት አልሰጣቸውም።

ክርስቲያኖች ዛሬ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እምነታቸውን ለመደገፍ ብሎ ብዙ ነገሮችን ይጠመዝዛሉ፤ ውሸትም ይናገራሉ።

በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ውስጥ ፓስተር ቤተክርስቲያንን እንዲመራ ስልጣን አልተሰጠውም ብላችሁ ብትነግሯቸው እናንተ የፓስተሮች ተቃዋሚ ናችሁ ብለው ይመልሱላችኋል።

ይህ ግን እውነት አይደለም። እምነታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስ ማሳየት ስለማይችሉ ሐሰተኛ ክሶችን ይጠቀማሉ። ፓስተሮችን የሚቃወም አንድም ሰው የለም፤ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚለውን ሃሳብ ነው የምንቃወመው።

አንድን ሰው ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ ማድረግ የኒቆላውያን ሥራ ነው። ከሕዝቡ በላይ ራሱን ከፍ ያደረገ ሪቨረንድ፣ አገልጋይ፣ ቄስ፣ ጳጳስ፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ካርዲናል፣ ወይም ፖፕ፤ እነዚህ ሁሉ የኒቆላውያን ሥራ ናቸው።

እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በሽማግሌዎች ሕብረት ነው መመራት ያለባት። የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚል አንድ ግለሰብ ቤተክርስቲያንን መምራት የለበትም።

ኢየሱስ ለሰዎቹ ሐሰተኛ ክስ ምንም ትኩረት አልሰጠም።

ማርቆስ 15፡4 ጲላጦስም ደግሞ፦ አንዳች አትመልስምን? እነሆ፥ በስንት ነገር ያሳጡሃል ብሎ ጠየቀው።

ኢየሱስ ራሱን ለመከላከል ምንም ነገር ባለመናገሩ ጲላጦስ ተደንቋል።

ማርቆስ 15፡5 ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም።

 

በሕይወት ራስ ፈንታ ነፍሰ ገዳዩን ፈለጉ

 

በፋሲካ በዓል ወቅት ሞት የተፈረደበትን አንድ እስረኛ የመልቀቅ ልማድ ነበረ።

ማርቆስ 15፡6 በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር።

በርባን የሚለው ስም አመጣጡ ባር አባ ከሚለው ቃል ሲሆን ትርጓሜው “የአባቱ ልጅ” ማለት ነው።

በርባን ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ ስለዚህ የዲያብሎስ ልጅ ነው።

ማርቆስ 15፡7 በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።

የሰላም አለቃ የሆነው ኢየሱስን በመምረጥ ፈንታ የአይሁድ ሕዝብ በርባን ከዚያ በኋላ እየዘረፋቸውና እየገደላቸው ቢኖርም እንኳ በርባን ይፈታልን ብለው ጮሁ።

ማርቆስ 15፡8 ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር።

ማርቆስ 15፡9 ጲላጦስም፦ የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን? ብሎ መለሰላቸው፤

ጲላጦስ የአይሁድ ንጉስ የሆነውን ኢየሱስን ለመፍታት ነበር ሃሳቡ። ጲላጦስ ኢየሱስ አንዳችም ጥፋት አለመስራቱን አውቋል።

ማርቆስ 15፡10 የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይልና በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀቱ በጣም ይቀኑበት ነበር።

ማርቆስ 15፡11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።

ይህ በጣም የሚያሳዝን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው።

የአይሁድ ሕዝብ ማንም ተጽእኖ ያላደረገባቸው ጊዜ በሆሳዕና እሁድ ኢየሱስን በክብር ተቀብለውት ነበር።

የሐይማኖት መሪዎቻቸው ግን ሕዝቡ ኢየሱስን እንዲጠሉ አሳመኑዋቸው።

ዘካርያስ 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

ይህ ትንቢት የተፈጸመው በሆሳዕና እሁድ ዕለት ነው።

ኢየሱስ ሁለት ደቀመዛሙርትን አዘዛቸው፡-

ማቴዎስ 21፡2 እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

የዚያን ጊዜ ሕዝቡ ኢየሱስን የዳዊት ልጅ ብለው ተቀበሉት። ይህ የንግስና ማዕረጉ ነው።

ማቴዎስ 21፡9 የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።

ጲላጦስ ለሕዝቡ ምርጫ አቀረበላቸው ምክንያቱም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች አካሄዳቸው ትክክል እንዳልሆነ ገብቶታል።

ሐሙስ ጠዋት (ኢየሱስ ለፍርድ የቀረበበት ቀን) ጲላጦስ ለአይሁድ ሕዝብ ከሳምንት በፊት እሁድ በሆሳዕና ዕለት ንጉስ ነው ብለው ያከበሩትን ሰው እንዲሞት አቀረበላቸው።

እሑድ ዕለት ሲያወድሱት የነበሩት ሕዝብ እራሳቸው ሐሙስ ዕለት ይገደል ይገደል እያሉ ይጮሁ ነበር።

የሰው ተለዋዋጭነት ይህን ይመስላል።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችም በሕዝቡ ላይ የነበራቸው ኃይል እና ተጽእኖ ይህን የመሰለ ነበር።

ዛሬም ሰዎች የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ትተው ዘመናዊ የቤተክርስቲያን መሪዎችን አመለካከት ይከተላሉ። ነገር ግን ከቤተክርስቲያን መሪዎች አንዳቸውም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ ብቻ እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ማሳየት አይችሉም።

ክርስቲያኖች ዛሬ ቤተክርስቲያናቸውን እና የቤተክርስቲያን መሪያቸውን ለመተቸት ፈቃደኛ አይደሉም፤ ነገር ግን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት አለበት ብለው በማሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ይተቻሉ።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የሕዝቡን አእምሮ መርዘውት ሕዝቡ ኢየሱስ ይገደልልን ብለው እንዲጠይቁ አደረጉ።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ ስለሚሉ ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲነቅፉና እንዳይቀበሉ ያደርጋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ግን የኢየሱስን ሃሳብ ስለሚገልጥልን የእግዚአብሔር ቃል ነው።

መሪዎች ሕዝቡን ለማስደሰት ብለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎችን አይቀበሉም።

ማርቆስ 15፡12 ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶ፦ እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ? አላቸው።

ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ አንዳችም ጥፋት አላገኘበትም።

ነገር ግን ጲላጦስ ከባድ ስሕተት ሰራ። ሕዝቡን አረጋጋለሁ ብሎ በፊቱ ቆሞ የነበረውን ንጹህ ሰው ምን ላድርገው ብሎ ጠየቃቸው። ከሳምንት በፊት ኢየሱስ ንጉሥ ነው እያሉ ሲያውጁ እንደነበር አስታወሳቸው።

ማርቆስ 15፡13 እነርሱም ዳግመኛ፦ ስቀለው እያሉ ጮኹ።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ተጽእኖ ግን በጣም ኃይለኛ ስለነበረ ባለፈው እሑድ ኢየሱሰን ሲያወድሱ የነበሩ ሰዎችን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አእምሮዋቸውን ጠምዝዘው ካልተገደለልን ብለው እንዲጮሆ አደረጓቸው።

ይህም ዛሬ ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ስናስብ በጣም አስፈሪ ነገር ነው። አንዳቸው ከሌላው የሚለያዩ 45,000 ዓይነት ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ እነዚህ ሁሉ ግን ትክክል ነን ብለው ያስባሉ። አንድ ሰውን የቤተክርስቲያን መሪ አድርጎ የመሾም መጨረሻው ይህ ነው። አገልጋይም ይበሉት ወይም ፓስተር ወይም ቄስ፣ እርሱ አመለካከቱን በሕዝቡ ላይ ጭኖባቸው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ቃል ቸል እንዲሉ ያደርጋቸዋል። ከዚያ በኋላ እነዚሁ ሰዎች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እናምናለን የሚሉ ሰዎችን ይገፉዋቸዋል።

1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡12 ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።

ሴት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ እንድትሆንና ለወንድ ምን ማመን እንዳለበት እንድትነግረው አልተፈቀደላትም። ዛሬ ግን ሴቶች የቤተክርስቲያን መሪነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ፓስተር ነን እያሉ ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስን መቃረን ማለት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እያመጸች ናት ማለት ነው። ይህም ልክ የአይሁድ ሕዝብ በሐይማኖት መሪዎቻቸው አማካኝነት መሲሃቸውን እንዲገፉ እንደተደረጉት ነው።

ማርቆስ 15፡14 ጲላጦስም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱ ግን፦ ስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ።

ጲላጦስ ኢየሱስ የሰራው ጥፋት ምን እንደሆነ እንዲያብራሩለት ጠየቃቸው። ለዚህ ጥያቄ ምንም ምላሽ አልሰጡም። ጥያቄውን መመለስ ትተው ኢየሱስ እንዲገደልላቸው አጥብቀው መጠየቃቸውን ቀጠሉ።

ማርቆስ 15፡15 ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።

ጲላጦስ ሕዝቡን ላለማስቆጣት ብሎ ፈርቷል። ስራውንም ሊያጣ ይችላል። ስለዚህ የጠየቁትን ሁሉ ሊሰጣቸው ፈቃደኛ ነበር።

ዛሬ የቤተክርስቲያን ሰዎች የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መብት እንዲፈቀድላቸው ይጠይቃሉ፤ የሴት ሰባኪዎች መብት፣ እና እንደፈለግን የመልበስ መብት ብለው ይጠይቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ነገር ሁሉ ስለሚፈቀድ ሕዝቡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸው እምነት እየሞተ ይሄዳል። የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡ የወደዱትን ሁሉ ሊፈቅዱላቸው ዝግጁ ናቸው። በዚህም መንገድ የቤተክርስቲያን መሪዎች በስልጣናቸው ላይ መቆየት ይችላሉ ምክንያቱም ሕዝቡን የሚያስቆጣ ነገር አይናገሩም።

ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ 2፡38 እና የመሳሰሉ ጥቅሶችን ይቃወማሉ።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ቤተክርስቲያኖች ይህንን ጥቅስ አይቀበሉትም። ስሕተት ነው ይላሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ሲሉ እግዚአብሔር ይሳሳታል እያሉ ነው።

 

እሾኮች እርግማን ናቸው፤ የኢየሱስንም ደም ነኩ

 

ማርቆስ 15፡16 ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱት፥ ጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ።

ይህ በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው። ፍትህ በጥቂት ወታደሮች እጅ ተተወ። ብዙውን ጊዜ እስረኞችን በመስቀል ላይ የመቸንከር ሥራ የሚሰጠው ከሮማውያን ወታደሮች በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙት ወታደሮች ነው።

ፕራይቶሪዮን የተባለው ሥፍራ ሮማዊው ገዥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ የሚያርፍበት ቦታ ነው። ስለዚህ ገዥው ጲላጦስ የአይሁድ መሪዎች በኢየሱስ ላይ ያደረጉት ነገር ሕገ ወጥ መሆኑን በደምብ ያውቃል። እርሱ ራሱ ሲመረምረው ምንም ጥፋት አላገኘበትም። ሕዝቡ ግን ያለ አንዳች የወንጀል ማስረጃ በደፈናው እንዲገደልላቸው ብቻ ይጠይቁ ነበር። ወታደሮቹም በእጃቸው አልፎ ሲሰጣቸው ያሰቃዩትና ያዋርዱት ጀመሩ።

ማርቆስ 15፡17 ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤

ቀይ ልብስ የነገስታት ልብስ ነው። ስለዚህ ኢየሱስን ቀይ ልብስ ያለበሱት የአይሁድ ንጉስ ብለው በንጉስነቱ ላይ ለማላገጥ ነው።

ወይራ አረንጓዴ ነው፤ ሲበስል ቀይ ይሆንና ከዚያም ይጠቁራል።

አረንጓዴ ቀለም ሳር እና አትክልቶች ሁሉ ላይ የምናየው የሕይወት ምልክት ነው። አረንጓዴ ቅጠል የፀሃይ ብርሃንን ስቦ ይወስድና ተዓምራዊ በሆነ መንገድ ወደ ምግብነት ይለውጠዋል። ስለዚህ ኢየሱስ ሕዝቡን ስለ ዘላለም ሕይወት በሚያስተምርበት ጊዜ ትምሕርቱን የሚወክለው ቀለም አረንጓዴ ነበር። ነገር ግን ጌቴሴማኒ ውስጥ በነበረ ሰዓት የእኛን ሐጥያት ለመሸከም ፈቃደኛ ሆነ። ወይራ ሲበስል ቀይ ይሆናል። የወይራ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲሆን እርሱም ኢየሱስ በመከራው አማካኝነት በተጨመቀ ጊዜ ከኢየሱስ ውስጥ ተጨምቆ ወጥቶ ንሰሃ ስንገባ ወደ ልባችን ሊገባ ችሏል።

በዚህም ምክንያት ኢየሱስን ቀይ ልብስ ማልበስ አስፈላጊ ነበር። ምክንያቱም ሊሞትልን ሐጥያታችንን ተሸክሞ ነበር።

ሰዓቱ ገና ማለዳ ነበረ። ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ይሰቅሉትና እኩለ ቀን ላይ ፀሃይ ብርሃኗን አልሰጥም ስትል ዓለም በሙሉ ለሶስት ሰዓታት ያህል በጥቁር ጨለማ ተሸፈነች። ይህ ክስተት የፀሃይ ግርዶሽ አልነበረም፤ ምክንያቱም በጣም ረጅሙ የፀሃይ ግርዶች 7 ደቂቃ ብቻ ነው። ይህ ክስተት የክርስቶስ መንፈስ ከጨለማ ኃይላት ጋር ያደረገውን ትግል የሚያሳይ በሕይወት እና በሞት መካከል የተደረገውን ፍልሚያ የሚያሳይ ምልክት ነው።

ንጉስ ዘውድ ይጭናል። ስለዚህ ሶስት እሾኮች ልክ እንደ ዘውድ ተጎንጉነው በራሱ ላይ ተጫኑ፤ እሾኮቹም እስኪደማ ድረስ ግምባሩን ወጉት።

ምድር የተረገመችው እሾክ እንድታበቅል ነበር።

ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤

18 እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።

እሾኮቹ በኢየሱስ ደም ስለተነኩ በምድር ላይ የነበረው እርግማን ተወግዷል። ወደፊት በሚመጣው የሺህ ዓመት መንግስት ውስጥ ምድር ላይ ምንም እሾህ አይኖርም።

ስለዚህ በኢየሱስ ላይ እናፌዛለን ብለው እና በእሾክ ሊያሰቃዩት አስበው ሳያውቁት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያገለገሉ ነበር።

 

ስምኦን ያለ ፈቃዱ መስቀል እንዲሸከም ተገደደ

 

እያላገጡ ቢሆንም እንኳ ንጉስ ሆይ ብለው ሰላምታ ሲሰጡት ትክክለኛውን ነገር እያደረጉ ነበር።

ማርቆስ 15፡18 የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ዛሬ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ፤ ይህም መልካም ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው ያምናሉ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል ከሰዎች አመለካከት ያነሰ ነው ብሎ በቃሉ ላይ ማፌዝ ነው።

ማርቆስ 15፡19 ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።

የእሾክ አክሊል በጫኑበት ራሱ ላይ ሲመቱት ስቃዩን ሊያበዙበት ፈልገው ነው። እያላገጡበት ሰገዱለት። ፊቱ ላይ መትፋታቸው ትርጉም አለው። ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው። እንጀራን መጀመሪያ ሳታላምጡና በምራቅ ሳታለሰልሱት ልትውጡት አትችሉም። ፊቱ ላይ ምራቅ ሊተፋበት መቻሉ ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ መሆኑን እና እኛም የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ይህንን እንጀራ በመንፈስ ወደ ውስጣችን እንደምናስገባ ያመለክታል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብሎ መናገር ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ብሎ ከመናገር እኩል ነው። ስለዚህ እያፌዙ ይሰግዳሉ ምክንያቱም ስለ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩትን ነገር በሙሉ ስለ ኢየሱስ መናገራችሁ ነው። አንድን ሰው ከሃሳቡ ነጥላችሁ ልታዩት አትችሉም፤ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የኢየሱስን ሃሳብ ይነግረናል። በኢየሱስ ሃሳብ ውስጥ ስሕተት ከተገኘበት እርሱ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ስሕተት አይገኝበትም።

ማርቆስ 15፡20 ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

በኢየሱስ ላይ ማፌዝ አልበቃቸውም። ከዚያም በኋላ ገደሉት። ልክ እንደዚሁ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው የሚያምኑትን እምነት በተቻላቸው መጠን ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ይገድላሉ። ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ አመሳክረው ማሳየት ትተዋል።

መድረክ ላይ ቆሞ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን መንቀፍ ማለት በዘመናችን ኢየሱስን በመስቀል ላይ መቸንከር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ብለው የሚናገሩት ንግግር ክርስቶስ እንደገና የተሰቀለበት የዘመናችን ችንካር ነው። ሕዝቡ ስሕተት ነው ብለው የሚያስቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማመን ትተዋል። ይህም አለማመን ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች ወደ እውነት ሊመራቸው አይችልም ማለት ነው።

63-0707 ክሱ

እስቲ አብረን እንይ። አዎ። ይህ ለንሰሃ የተደረገ ጥሪ ነው፤ እኔም ያቀረብኩት ክስ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው። አዲሱ ቀራንዮ - ቤተክርስቲያን፤ ለስሙ ቅዱስ የሚባሉ ቦታዎች፣ የካቶሊክ መሰዊያ፣ የካቲሊሲዝም መሰዊያ እና መድረኮቻቸው ናቸው። ሜተዲስቶች፣ ባፕቲስቶች፣ ፕሬስቢተሪያኖች፣ ሉተራኖች፣ ፔንቲኮስታሎች እና ሌሎችም ቅዱስ ቦታዎች ጌታን የወጉት ሰዎች የሚገኙባቸው ናቸው። አዲስ ቀራንዮ! የት ነው አዲስ ቀራንዮ ያለው? በተቀደሱ ሥፍራዎች በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ነው።

ክርስቶስ የተሰቀለው የት ነው? ፓስተሮች ባሉበት ነው። እናንተ ግብዞች እንዴት ይህን ታደርጋላችሁ!

እኔ አልተናደድኩም ነገር ግን በውስጤ የሆነ ነገር ይንቀሳቀሳል። እግዚአብሔር በሙሉ ክብሩ በመካከላችሁ ይኖራል። ጎኑን የተወጋበት ጦር ከየት ነው የመጣው? እጆቹንና እግሮቹን የተወጋው የት ነው? ቀራንዮ። ዛሬስ እየተወጋ ያለው የት ነው? በቤተክርስቲያን መድረኮች ላይ ነው። ገዳዮቹ ከየት መጡ? ከኢየሩሳሌም። ከየት ይመጣሉ? ከዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች። እወድሃለው ብሎ የተናገረው እርሱ ነው የከዳው። ዛሬም የሚከዳው እርሱ ነው። ቃሉ የተወጋበት ሁለተኛ ቀራንዮ፤ የቃሉ መወጋት የእርሱ መወጋት ነው። እርሱ ማነው? እርሱ ቃ ነው። እርሱ ቃሉ ነው።

ከሁሉ የበለጠውን ውጋት የተወጋው የት ነው? ያኔ ድሮም እንደነበረው በተቀደሱ ሥፍራዎች በሚገኙ መድረኮች ላይ።

ማርቆስ 15፡21 አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።

ማርቆስ ሁለተኛው የወንጌል መጽሐፍ ነው። ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ከዙፋኑ ዙርያ ከሚገኙት ሕያዋን ፍጥረታት መካከል ሁለተኛ ሆኖ የተጠቀሰው ጥጃው ነው። ጥጃው አድጎ ሸክም የሚሸከም ብርቱ በሬ ይሆናል።

ይህ የሚያሳዝን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። ኢየሱስ እገዛ ባስፈለገው ጊዜ ስምኦን መጥቶ እርሱን በማገዙ ትክክለኛ ነገር አድርጓል። ነገር ግን ተገድዶ ነው ያገዘው። ይህም እኛ ሰዎች በተፈጥሮዋችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማድረግ ዝንባሌ እንደሌለን ያሳያል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከእኛ ፈቃድ ተቃራኒ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አስገድዶን ነው ፈቃዱን የምናደርገው።

በሌላ አነጋገር ለራሳችን ፈቃድ ካልሞትን በቀር እግዚአብሔርን ልናገለግለው አንችልም።

ማርቆስ 15፡22 ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።

የራስ ቅል የሞት ምልክት ነው።

 

ወይን የመገለጥ መነቃቃት ምሳሌ ነው

 

ማርቆስ 15፡23 ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም።

ይህ ብዙ ደም ከፈሰሰው በኋላ ከባድ የውሃ ጥም ለሚያሰቃየው ሰው ተጨማሪ ስቃይ ነው። ከርቤ ሽታው ደስ ይላል፤ ነገር ግን ወይን ውስጥ ሲቀላቀል ወይኑን በጣም መራራ ያደርገዋል፤ ስለዚህ ከርቤ የተቀላቀለበትን ወይን መጠጣት በጣም ይከብዳል።

ከርቤ የሞት ምሳሌ ነው ምክንያቱም በዚያ ዘመን አስከሬኖችን ለማድረቅ ይጠቀሙበት ነበር።

ወይም በመገለጥ የመነቃቃት ምሳሌ ነው።

ከርቤ ተቀላቅሎበት መራራ የሆነ ወይም የሮማ አረማውያን በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የሚገኘውን መነቃቃት ለማጥፋት ያደረጉትን ነገር ይገልጻል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን አመጣች፤ እነዚህም ሁሉ የአረማውያን ሃሳቦች ናቸው። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ የሚገኘውን መነቃቃት ይገድለዋል። ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን እንደ እውነት ለመቀበል እንጋለጣለን፤ ስለዚህ የሚያነቃቃን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሃሳብ ነው። ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳቦችን እንድንቃወምና ለመቀበል እምቢ እንድንል ያደርገናል።

ስላሴያዊው አምላክ ስም የለውም ምክንያቱም ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ልታገኙላቸው አትችሉም። ከዚያ ቀጥላችሁ ደግሞ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ስም ሳይሆኑ ሶስት ማዕረጎች መሆናቸውን ባለማወቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲደረግ የታዘዘውን የውሃ ጥምቀት ትክዳላችሁ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

 

ማቴዎስ 28፡19 በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንድንጠመቅ ያዝዘናል። ስለዚህ ለነዚህ ሶስት ማዕረጎች አንድ ስም ማገኘት አለባችሁ።

በስላሴ ማመን ግን እግዚአብሔር የሚጠራበትን አንዱን ስም ልታገኙ አትችሉም ማለት ነው።

አንዱ ምክንያት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ስም ያልተሰጠው መሆኑ ነው።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ አልተጻፈም። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ የአብ ስሞች በሙሉ አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጠቀሱም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር ወልድ” ተብሎ አልተጻፈም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” ተብሎ አልተጻፈም።

“እግዚአብሔር አብ” ተብሎ የተጻፈው አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው። የስላሴ ትምሕርት ለነዚህ እውነታዎች መልስ የለውም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የክርስቶስን ልደት አክብሩ ተብሎ አልተነገረንም።

ዲሴምበር 25 ቀን በ274 ዓ.ም ሮማዊው ንጉስ ኦሬልያን የፀሃይ አምላክ የተወለደበት ቀን ነው ብሎ እንዲከበር ያዘዘው ቀን ነው።

በ350 ዓ.ም አካባቢ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህንን ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ልደት ቀን ነው ብላ አወጀች።

የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች በተሃድሶው ዘመን ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስለወጡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እራሷን እንደ እናት ቤተክርስቲያን ትቆጥራለች።

የባቢሎንን ሚስጥራት ሰብስባ ከተቀበለች በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የባቢሎን ሚስጥር ተብላለች። ነገር ግን እንደ ስላሴ እና ክሪስማስ የመሳሰሉ አረማዊ ትምሕርቿን ካቶሊክ ላልሆኑ ልጆቿ ማለትም ለፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች አስተላልፋለች።

ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።

ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።

ይህ በዘመናችን ባሉ እምነታቸውን ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከር ባቆሙ ቤተክርስቲያኖች ላይ የተሰነዘረ አስደንጋጭ ወቀሳ ነው።

ማርቆስ 15፡24 ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።

በግፍ ግድያ ከፈጸሙ በኋላ በኋላ ቀጥለው ስግብግብነታቸውን አሳዩ።

ልብሱን አራት ቦታ ቆራረጡ ምክንያቱም መስቀሉ አጠገብ እንዲጠብቁ የተመደቡ ሮማውያን ወታደሮች አራት ነበሩ። የልብስ አንድ አራተኛ ቁራጭ ምን ይጠቅማል? ምንም።

በቁማር መንፈስ ተይዘው ልብሱ ላይ እጣ ተጣጣሉበት።

ዮሐንስ 19፡23 ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

ማርቆስ 15፡25 በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ።

ሁለት ዓይነት የሰዓት አቆጣጠር አለ።

በሮማውያን አቆጣጠር አዲስ ቀን የሚጀምረው እኩለ ሌሊት ላይ ነው።

የአይሁዶች ቀን ደግሞ የሚጀምረው ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ፀሃይ ስትወጣ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስን መስቀል ላይ የቸነከሩት በአይሁዳውያን የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ነው።

በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የተጻጠቀሰው ሰዓት ሮማዊው ገዥ ጲላጦስ ኢየሱሰን እንዲሰቅሉት ለአይሁዶች አሳልፎ የሰጠበትን ሰዓት በሮማውያን አቆጣጠር ያመለክታል።

ዮሐንስ 19፡14 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው።

ይህም ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ማለት ነው።

ስለዚህ ችሎት የተቀመጡት ከንጋት በፊት ነው፤ ስለዚህ ችሎቱ ሕገወጥ ነበር ምክንያቱም በጭለማ ችሎት መቀመጥ አይፈቀድም።

ማርቆስ 15፡26 የክሱ ጽሕፈትም፦ የአይሁድ ንጉሥ የሚል ተጽፎ ነበር።

መስቀሉ ላይ ከአናቱ በላይ “የአይሁድ ንጉስ” የሚል ጽሑፍ ነበረ።

ይህ በጣም ያሳዝናል። አይሁዶች የራሳቸውን ንጉስ ለሞት አሳልፈው ሰጡ።

ማርቆስ 15፡27 ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዶች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።

ዮሴፍ ግብጽ ውስጥ ከሁለት ወንጀለኞች ማለትም ከሞተው ዳቦ ጋጋሪ እና በሕይወት እንዲኖር ከተደረገው ጠጅ አሳላፊ ጋር በእስር ቤት እንደ ነበረ ሁሉ ኢየሱስን በመስቀል ላይ ከሁለት ወንጀለኞች መካከል ነበረ። አንደኛው ወንበዴ ኢየሱስን አልቀበልም ብሎ ሞተና ወደ ሲኦል ወረደ፤ የዚህም ምሳሌው የተቆረሰው የዳቦ ጋጋሪው ዳቦ ነው። አንዱ ወንበዴ ደግሞ ኢየሱስን ተቀበለና ወደ ገነት ገባ፤ የዚህም ምሳሌው ወይኑ ውስጥ ያለው መንፈስ ወይም ሕይወት ነው።

ማርቆስ 15፡28 መጽሐፍም፦ ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ያለው ተፈጸመ።

ኢሳይያስ 53፡12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

በኢየሱስ ላይ ሐሰተኛ ክስ ተሰነዘረበት

 

ማርቆስ 15፡29 የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና። ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥

ይህ የሐሰት ክስ ነው። ኢየሱስ ቤተመቅደሱን አፈርሰዋለው አላለም።

ኢየሱስ የተናገረው የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ቤተመቅደስ የሆነውን የእርሱን አካል ቢያፈርሱት በ3 ቀን መልሶ እንደሚያስነሳው ነው የተናገረው።

ዮሐንስ 2፡19 ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።

ዮሐንስ 2፡21 እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።

ማርቆስ 15፡30 ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ።

አይሁዶች ሙሉ በሙሉ ተሳስተዋል። ኢየሱስ ራሱን ለማዳን ከመስቀል ላይ መውረድ አልፈለገም። እርሱ የፈለገው በመስቀል ላይ በመቆየት እኛን ለማዳን ነው።

ማርቆስ 15፡31 እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱ፦ ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤

ዋነኞቹ የሐይማኖት መሪዎች ልክ እንደ ዛሬዎቹ የሐይማኖት መሪዎች ጭንቀታቸው ስልጣናቸውን እና የቢ ምንጫቸውን ማስከበር ብቻ ነው። (ሐሙስ ዕለት የገደሉት ሁለት ጊዜ የገንዘብ ለዋጮቻቸውን ጠረጴዛ ስለገለበጠባቸው ነው፤ መጀመሪያ የሆሳዕና እሁድ ዕለት ቀጥሎ ደግሞ በድጋሚ በማግስቱ ሰኞ ዕለት። )

የአይሁድ መሪዎች መዳን ማለት ኢየሱስ እራሱን ማዳኑ መስሏቸዋል።

ማርቆስ 15፡32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።

ራሱን ለማዳን ከመስቀሉ ቢወርድ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ይጨነግፋል። ስለዚህ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ይሰብኩ የነበሩት ሃሳብ ሰዎችን ወደ ኩነኔ የሚያስገባ ነበር። ሰዎች ሊድኑ የሚችሉት ኢየሱስ ከመስቀሉ ሳይወርድ በመቆየት እዛው ከሞተ ብቻ ነው።

ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል እምነት የሚገድሉ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ይሰብካሉ።

ለምሳሌ የሚከተሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ልማዶችና እምነቶች ተመልከቱ፡-

ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ አንድ አምላክ በሶስት አካላት። እግዚአብሔር ወልድ፣ የመለኮት ሁለተኛው አካል፣ ኢየሱስ የመለኮት አንዱ አካል ነው። የጌታን ልደት አክብሩ፣ የስቅለት አርብ፣ የፋሲካ ሰኞ፣ የፋሲካ እንቁላሎች፣ የፋሲካ ጥንቸሎች፣ የፋሲካ ዳቦ። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣ ጾታችሁን እራሳችሁ መምረጥ ትችላላችሁ፣ “የናንተ እውነት” የምትወሰነው በያንዳንዳችሁ የግል መረዳት ነው።

ቤተክርስቲያኖች በሕጋዊ ጋብቻ ተጋብታችሁ ከዚያ መፋታትና እንደገና ማግባት ትችላላችሁ ብለው ያምናሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተብራሩትን የ7ቱን ነጎድጓዶች ሚስጥር ማብራራት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆነ ስብከት ዓይነተኛ ማስረጃ ነው።

አዲሱ የኢየሱስ ስም እና የዳግም ምጻቱ ሚስጥርም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም። በነዚህ ርዕሶች ላይ የሚሰብኩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ትምሕርታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎች የዳኑ ክርስቲያኖችን ይሸነግላሉ፤ ከዚህም የተነሳ የዳኑ ክርስቲያኖች በመዳናቸው ምክንያት በፍርድ ቀን ወደ መንግስተ ሰማያት ቢገቡም እንኳ እዚህ በምድር ግን ታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው አሰቃቂ ሞት ይሞታሉ፤ መንግስተ ሰማያት ቢገቡም የሙሽራይቱ አካል አይሆኑም።

ማርቆስ 15፡33 ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ፥ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።

አዲስ ቀን የሚነጋው ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ፀሃይ ስትወጣ ነው።

ስድስት ሰዓት ሲሆን ማለት እኩለ ቀን ምሳ የሚበላበት ሰዓት አካባቢ ነው።

9 ሰዓት ደግሞ ከስድስት ሰዓት ሶስት ሰዓታት ካለፉ በኋላ ነው።

የጨለማ ኃይላት ኢየሱስን እየገደሉት ሳለ ፀሃይ ብርሃኗን ለመስጠት እምቢ አለች። ለሶስት ሰዓታት ያህል ምድር ላይ ድቅድቅ ጨለማ ነበር። ብርሃንን ብትገድሉ ጨለማ ውስጥ ትገባላችሁ፤ ጨለማ ማለት የብርሃን አለመኖር ነውና።

ይህ ጨለማ የፀሃይ ግርዶች አልነበረም። ረጅሙ የፀሃይ ግርዶሽ 7 ደቂቃ ብቻ ነው።

ሶስት ሰዓት ሙሉ ጨለማ መሆኑ እግዚአብሔር በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይሉ ፀሃይ እንዳትበራ አድርጓት ነው። ይህንን የፀሃይ መጨለም በተመለከተ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ማብራሪያ የለም።

የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች እና የሮማ ፖለቲከኞች የወደዱትን አድርገዋል። ፈቃዳቸውን የማድረጋቸው የመጨረሻው ውጤት የእግዚአብሔር ቃል መጥፋት (ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው) ዓና ዓለም በሙሉ ጨለማ ውስጥ መውደቁ ነው። የሰው አመራር ውጤቱ ይህ ነው።

 

እግዚአብሔር የሐጥያተኞች አምላክ አይደለም

 

ማርቆስ 15፡34 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።

ኢየሱስ የሐጥያትን ዋጋ ለመክፈል የእኛን ቆሻሻ ሐጥያት ተሸክሞ ነበር።

እግዚአብሔር አብ በእግዚአብሔር ልጅ ውስጥ ይኖር ነበር። (መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል የለም)።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ልዕለ ተፈጥሮአዊው የእግዚአብሔር መንፈስ ሰው በሆነው በኢየሱስ ውስጥ አደረ። ኢየሱስ ቆሻሻውን ሐጥያታችንን ስለተሸከመ ሰማያዊው አባቱ ፊቱን አዞረበት፤ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም እምቢ አለ። ስለዚህ ኢየሱስ እንደ ሰው፣ እንደተጣለ ሐጥያተኛ ሞተ።

ኢየሱስ በውስጡ በሚኖረው ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንፈስ ነው የተጣለውና የተተወው፤ መለኮታዊው መንፈስም ከእርሱ ጋር ለመነጋገር እምቢ አለ። እግዚአብሔር የሐጥያተኞች አምላክ አይደለም።

ሐጥያተኞች እግዚአብሔርን በምንም ነገር መጠየቅ አይችሉም፤ አድነኝ ብለው ከመጮህ በቀር።

እግዚአብሔር ከሐጥያተኞች መካከል የሚሰማው ንሰሐ የሚገባውን ሐጥያተኛ ብቻ ነው።

ኢየሱስ የተባለው ሰው ስለ እኛ ሐጥያት ሆኖ ሞተ፤ በዚያም ሰዓት በውስጡ ከሚኖረው ልዕለ ተፈጥሮአዊ አባቱ ጋር መነጋገር ፈለገ።

ይህ ለሐጥያተኞች ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው። ሐጥያተኞች ሲሞቱ ንሰሃ በገባሁ እና ከእግዚአብሔር ጋር በተነጋገርኩ ብለው ይመኛሉ።

አንድ ምሳሌ እንመልከት።

በውስጣችሁ ንቁ አእምሮ (ወልድ) እና ንኡስ አእምሮ (አብ) አለ፤ እነዚህም የአእምሮ ክፍሎች እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ። ንቁው አእምሮዋችሁ የሆነ ነገር ሲረሳ ንኡስ አእምሮዋችሁ ሃሳቡን ተቀብሎ ከአእምሮው መዝገብ ውስጥ ፈትሾ የረሳችሁት ነገር የሆነ ሰዓት ባልጠበቃችሁበት አእምሮዋችሁ ውስጥ ብልጭ እንዲል ያደርጋል።

ሕሊናችሁ የንኡስ አእምሮዋችሁ ክፍል ነው። ሁላችንም ንቁው አአምሮዋችን የሆነ ስሕተትን ትክክል ለማለት ሲከራከርና ሕሊናችን አልተዋጠልኝም ሲለን አይተን እናውቃለን።

ኢሳይያስ 59፡2 ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።

ማርቆስ 15፡35 በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ እነሆ፥ ኤልያስን ይጠራል አሉ።

አይሁዶች ኢየሱስ ምን እያለ እንደሆነ ፈጽሞ አልገባቸውም። እርሱ ያለው “አምላኬ” ነበረ፤ እነርሱ ግን ነብዩ ኤልያስን እየጠራ ነው አሉ።

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ አካባቢ የቤተክርስቲያን ሰዎች የተገለጡትን የእግዚአብሔር ቃል ሚጥራት ፈጽሞ በተሳሳተ መንገድ ይረዳሉ።

ማርቆስ 15፡36 አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎ። ተዉ፤ ኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ እያለ አጠጣው።

አንድ ወታደር ለኢየሱስ ሆምጣጤ በማቅረብ በትንሹም ቢሆን ምሕረትና ርህራሄ ለማሳየት ሞከረ።

ሌሎቹ “ተዉ” አሉ። ተዉት። እስቲ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆን እናያለን።

ማቴዎስ 27፡48 ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው።

49 ሌሎቹ ግን፦ ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ።

ሆምጣጤ በሰጡት ጊዜ እንዲህ የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፡-

መዝሙር 69፡21 ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።

 

በመጨረሻም ለ10 ቆነጃጅት እንደተደረገው ጩኸት የሆነ ታላቅ ድምጽ

 

ማርቆስ 15፡37 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።

በአገልግሎቱ መጨረሻ በታላቅ ድምጽ ጮኸ። ከዚያም ሞተ።

የሙሽራይቱም አገልግሎት መጨረሻ በታላቅ ጩኸት ነው የሚጠናቀቀው፤ ይህም ታላቅ ድምጽ የተኙትን ልባም ቆነጃጅት ከእንቅልፍ ይቀሰቅሳቸውና ካሉበት ቤተክርስቲያን እንዲወጡ ይነግራቸዋል።

ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

ማርቆስ 15፡38 የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ።

እግዚአብሔር መጋረጃውን በመቅደድ የብሉይ ኪዳን ሕግ ማብቃቱን አወጀ።

ኢየሱስ የመጨረሻው መስዋእት ሆኖ ስለቀረበ የእንስሳት መስዋእት በሙሉ አበቃ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን የአይሁድ ሐጥያት በመሰዊያው ላይ ወደሚቀርበው እንስሳ ይተላለፍ ነበር፤ የእንስሳው ንጽሕና ደግሞ ወደ አይሁድ ይተላለፋል። ነገር ግን የንጹሁ እንስሳ ሕይወት ወደ አይሁዳዊው መስዋእት አቅራቢ ሊተላለፍ አልቻለም፤ ከዚህም የተነሳ ሰውየው ውስጥ ያለውን ሐጥያት የመስራት ፍላጎት ሊያስወግድለት አልቻለም።

ኢየሱስ ሲሞት ሐጥያታችን ከእኛ ወደ እርሱ ተሸጋገረ፤ ስለዚህ በእርሱ ውስጥ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ሐጥያታችንን ወደ ሲኦል ይዞ በመውረድ ሰይጣን ላይ አራገፈው። ከዚያም የኢየሱስ ንጽሕና ወደ እኛ በመሻገር እኛን ጻድቅ አደረገን።

ኢየሱስ ሰው ስለነበረ መንፈሱ ወደ ልባችን መሻገርና በውስጣችን በመሆን ሐጥያት የመስራት ፍላጎታችንን ማስወገድ ይችላል። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እውነተኛው የሰንበት እረፍት ነው። ይህም እረፍት ከሐጥያተ እና ከአለማመን ማረፍ ነው።

የሕጉን ማብቃት መጀመሪያ ያወጀው ሊቀ ካሕናቱ ቀያፋ ነው፤ እርሱም ልብሱን ቀደደ። ልብሱን በመቅደዱ ሕጉን ተላለፈ።

ከዚያም እግዚአብሔር የሕጉ ዘመን ማብቃቱን ማረጋገጫ ለመስጠት የቤተመቅደሱን መጋረጃ ቀደደው።

ማርቆስ 14፡63 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፦ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል?

ዘሌዋውያን 10፡6 ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፦ እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤

ሊቀ ካሕናቱ ልብሱን መቅደድ አልተፈቀደለትም።

ማርቆስ 15፡39 በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ፦ ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ አለ።

ይህ ሮማዊ መቶ አለቃ ታላቅ ወታደር አልነበረም። ወንጀለኞችን የመግደል ሥራ ከሮማውያን ወታደሮች መካከል ተራ ኩታራ ለሆኑት ነበር የሚሰጠው። ሆኖም ግን ይህ ልቡ የደነደነ አረማዊ ወታደር እንኳ ኢየሱስ የተለየ ሰው መሆኑን መረዳት ችሏል። ስለዚህ እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች እና ተጠራጣሪዎች የኢየሱስ ሕይወት እና ሞት ልዩ መሆኑን እውቅና ላለመስጠታቸው ምንም ማመካኛ የላቸውም።

 

የታላላቅ ሰዎች ቤተሰቦች ታላላቅ አይደሉም

 

ማቴዎስ 27፡56 ከእነርሱም መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።

የዘብዴዎስ ልጆች ከዋናዎቹ ደቀመዛሙርት መካከል ሁለቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው።

ማቴዎስ 10፡2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥

ከመጀመሪያዎቹ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት መካከል የኢየሱስ ሐዋርያ ለመሆን የበቃው እንድርያስ ብቻ ነበር። ነገር ግን እንድርያስ ከሶስቱ ታላላቅ ሐዋርያት አንዱ ለመሆን አልበቃም።

ልክ እንደዚሁ የነብዩ ዊልያም ብራንሐም ተከታይ መሆንም የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ታላቅ ተከታይ አያደርጋችሁም። ኢየሱስ ዛሬ የሚገለጠው እንደ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ ነው። የእግዚአብሔር ሚስጥር የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ዘመንና እምነት መመለስ ነው። ይህም ደግሞ ዊልያም ብራንሐም ወደተባለው ሰው በመቅረባችን የሚወሰን አይደለም።

ማቴዎስ 27፡56 ውስጥ መጀመሪያ የተጠቀሰችው መግደላዊት ማርያም ስትሆን እርሷም ከሐዋርያት የአንዳቸውም ዘመድ አይደለችም። ከዚያም ደግሞ የተጠቀሰችው የያዕቆብ እናት ማርያም ናት፤ ያዕቆብም የእልፍዮስ ልጅ ነበር። ስለዚህ ሁለተኛይቱ ማርያም የእልፍዮስ ሚስት ናት።

የደቀመዛሙርቱ ስም ዝርዝር እንዲህ ይላል፡-

ማቴዎስ 10፡3 የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ

በስተመጨረሻ የተጠቀሰችው የያዕቆብ እና የዮሐንስ እናት ናት። ስሟ አልተጻፈም። ከሶሰቱ ታላላቅ ሐዋርያት የሁለቱ የቅርብ ዘመድ መሆኗ ምን ያስገኘላት ክብር የለም።

የሐዋርያቱ እናቶች የተጠቀሱበት ቅደም ተከተል ወደ ኋላ ነው። የሁለቱ ታላላቅ ሐዋርያት እናት ከሁሉ መጨረሻ ሲሆን የተጠቀሰችው ስሟ አልተጻፈም። ስሟ ያልተጻፈላት የሁለቱ ታላላቅ ሐዋርያት የያዕቆብ እና የዮሐንስ እናት ከመጠቀሷ በፊት ማቴዎስ የእልፍዮስ ሚስት የሆነችዋን ማርያም ይጠቅሳታል። እሷም ብዙ ጊዜ የማይጠቀሰው ሐዋርያ የያዕቆብ እና ሐዋርያ ያልሆነው የዮሳ እናት ናት። (ያዕቆብ ተብለው የሚጠሩ ሐዋርያት ሁለት ናቸው)። (ይሁዳ የሚባሉ ሐዋርያትም ሁለት ናቸው)።

ታላቅ ያልሆኑት ሰዎች እናት ስሟ ቀድሞ የተጻፈ ሲሆን ታላላቅ የሆኑት ሰዎች እናት ግን ስሟ አልተጻፈም፤ የተጠቀሰችውም ኋላ ነው።

ስለዚህ የአንድ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ዘመድ ብትሆኑ ታላቅ ሰው የምትሆኑ ይመስላችኋልን? አትሆኑም።

ከሁሉም በፊት የተጠቀሰችዋ እና ሙሉ ስሟ የተጻፈላት መግደላዊት ማርያም ደግሞ ከሐዋርያት መካከል የአንዳቸውም ዘመድ አይደለችም።

ማርቆስ 15፡40 ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፥

ማርቆስ የኢየሱስ አገልጋይነት ላይ ትኩረት በማድረግ ነው ወንጌሉን የጻፈው። አገልጋይ የተመሰለበት ጥጃ አድጎ ሐጥያታችንን የሚሸከም በሬ ይሆናል፤ እርሱም ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል በመውረድ ሰይጣን ላይ አራግፎታል። ስለዚህ ኢየሱስ በሕጉ ውስጥ የተጻፈው የመለቀቅ ፍየልም ነው።

ስለዚህ ማርቆስ ትኩረቱን ያደረገው አገልግሎት ላይ ነው።

ከሁሉ በፊት መጀመሪያ የተጠቀሰችዋ መግደላዊት ማርያም ከየትኛውም ሐዋርያ ጋር የስጋ ዝምድና የላትም። ቀጥሎ የተጠቀሰችዋ ደግሞ የሐዋርያው ያዕቆብ እናት ማርያም ስትሆን ልጇ ታዋቂ ከሆነው ሐዋርያ ያዕቆብ ያነሰ ጊዜ ነው የተጠቀው።

“የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት።” ማርቆስ ታናሽ የሆነውን ሐዋርያ እናት አጽንኦት ሰጥቶ ነው የጠቀሳት። እንደውም ሐዋርያ ያልሆነው የዮሳ እናት መሆኗን ሁሉ ጭምር ጠቅሷል። ታናሽ የሆነው ሐዋርያ እናት ታላቅ ከሆነው ሐዋርያ እናት ይልቅ ቦታ ተሰጥቷት ተጠቅሳለች ምክንያቱም ታላላቅ የሆኑት ሐዋርያት የዮሐንስ እና የያዕቆብ እናት የማርቆስ ወንጌል ውስጥ ጭራሽም አልተጠቀሰችም። ማርቆስ ታዋቂ ያልሆነችዋን ሰሎሜ የተባለች ሴት ሁለት ጊዜ ጠቅሷታል።

ስለዚህ እግዚአብሔር በመጽሐፉ ጽፎ መታሰቢያ የሚይዘው ለማይታወቁ እና ሰው ለማያስተውላቸው አማኞች ነው።

እነዚህ ሴቶች (ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች) ርቀው ነበር የቆሙት፤ ግን ቢያንስ በስፍራው ተገኝተዋል።

የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያኖች በሐዋርያት ሥራ 2፡38 መሰረት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመጠመቅ እምቢ እስኪሉ ድረስ ከቃሉ በጣም ርቀው ሄደዋል። ነገር ግን ብዙዎቹ ስለዳኑ ጥቂትም ቢሆን እውነትን ያውቃሉ።

የእግዚአብሔር ሥራ የሚሰራው እግዚአብሔር ለጠራቸው ሰዎች የቅርብ ዘመድ በሆኑ ሰዎች አይደለም።

ዝምድና በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተፈላጊዎች አያደርገንም።

ማርቆስ 15፡41 ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ።

ሌሎች ሴቶችም ኢየሱስ ይከተሉና ያገለግሉ ነበር። እነማን እንደሆኑ አናውቅም ግን ኢየሱስ ዝና የማይፈልጉ የሰው ዓይንና ትኩረት ሳይስቡ የተከተሉትና ያገለገሉት ሰዎች አሉ።

ማርቆስ በጠቀሳቸው ስሞች መካከል ራሳቸውን ከፍ ለሚያረጉ ሰዎች አንዳችም ቦታ አልተሰጣቸውም። የስኬታማ አገልግሎት አንዱ ሚስጥር ይህ ነው።

ማርቆስ 15፡42 አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፥

የፋሲካ በግ የሚመረጥበት 10ኛው ቀን የሆሳዕና እሁድ ነው። የፋሲካ በግ የሚታረደው ረቡዕ ዕለት ሲሆን ይህ 14ኛው ቀን ሐሙስ ነው። ያም ቀን በጉ የሚታረድበትና በጥድፊያ የሚጠበስበት የመዘጋጀት ቀን ነው።

ሐሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአይሁዶች አቆጣጠር ቀኑ አልቆ አርብ የሚጀምርበት ሰዓት ነው። አርብ የፋሲካ እና የቂጣ በዓል ነው፤ ይህም ቀን የቂጣ በዓል ለሚከበርባቸው ሰባት ቀናት የመጀመሪያው ቀን ነው።

እርሾ የሌለበት ቂጣ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የኢየሱስን ቅድስና ያመለክታል። በመጀመሪያው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ልዩ ትኩረት ተደርጓል፤ ምክንያቱም ሙሉውን እውነት ይዞ የነበረው ብቸኛው ዘመን ያ ዘመን ነበረ። ስለዚህ ሙሉውን እውነት መያዝ ከፈለግን ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ አለበት።

የአይሁድ አዲስ ቀን የሚጀምረው ሲመሽ ነው።

ዘፍጥረት 1፡5 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።

በመንፈሳዊ አነጋገር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ሚጥራት መገለጦች ሲታወቁ የሚመጣው የምሽት ብርሃን ሙሽራይቱን ወደ ዳግም ምጻት ያደርሳታል። ከዚያ ወዲያ ሙሽራይቱ ምድርን ትታ በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ እራት ግብዣ ትሄዳለች።

ስለዚህ ሙሽራይቱ የታላቁን መከራ የምሽት ጨለማ አታየውም።

ከዚያ በኋላ ሙሽራይቱ ለ1,000 ዓመታት ምድርን በሰላም የሚገዛውን መንግስት ልትመሰረት ወደ ምድር ትመለሳለች።

ማርቆስ 15፡43 እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

ከተበላሹት የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች መካከል እግዚአብሔር ጥሩ ምክር መስጠት የሚችል አንድ ሰው ነበረው። ዮሴፍ ኢየሱስ ተራ ሰው እንዳልነበረ አውቋል፤ ስለዚህ ኢየሱስን በክብር በመቅበር ማገልገል ፈለገ።

ማርቆስ 15፡44 ጲላጦስም አሁኑን እንዴት ሞተ ብሎ ተደነቀ፥ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ ከሞተ ቆይቶአልን? ብሎ ጠየቀው፤

ጲላጦስ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ቃል በፍጥነት ሊሞት መቻሉን ሊያምን አልቻለም። ሮማውያን ኢየሱስን ሊገድሉት ይዘውት መሄዳቸውን ያውቃል፤ ስለዚህ ኢየሱስ የእውነትም ሞቶ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሮማውያኑን ጠየቃቸው። ዛሬም ማዕከላዊ አሰራር ያላት በሰው ሰራሽ ሃሳቦች የተሞላችዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ልማዶች ናቸው ካቶሊክ ወዳልሆኑ ቤተክርስቲያኖች እየተሰራጩ የተገለጠውን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ተጽእኖ የሚገድሉት።

እንዴት ባለ ፍጥነት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጥሉ ማድረጋቸን ማመን ይከብዳል።

ማርቆስ 15፡45 ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው።

ሮማውያን ማስረከብ የሚችሉት አንድ ነገር በድን ነው። ትኩታቸው እውነትን መግደል ላይ ነው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23