ማርቆስ 14 ክፍል 1 - ለጌታ ሞት መታሰቢያ አደረገች
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የአይሁድ መሪዎች ሊገድሉት አሴሩ። ደቀመዛሙርቱ ሸሹ። አንዲት ስሟ ያልተጠቀሰ ሴት ብቻ (ቤተክርስቲያን) የጌታን ሞት ለማክበር ገንዘብ አወጣች
- የአይሁድ መሪዎች እውነትን ለማጥፋት ሲነሱ ምንም አላመነቱም
- አንዲት ያልታወቀች ሴት ያመጣችው ታላቅ መገለጥ ብዙ ወጪ አስከተለባት
- ይሁዳ በገንገዘብ ፍቅር የተጠለፈ የቤተክርስቲያን መሪ ነው
- የፋሲካ እራት መብላት የተለመደ የምግብ ፕሮግራም ነበር
- የቤተክርስቲያን መሪ ኢየሱስን ካደ
- እንጀራ እና ወይን የስጋው እና የደሙ ምሳሌ ናቸው
- ደቀመዛሙርቱ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ሸሹ
- ከሶስት ክሕደቶች ጋር የተያያዙ ሁለት ግንዛቤዎች
- እውነት ተመልሳ ስትመጣ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ዘንድ ተቃውሞ ይገጥማታል
- ዶሮው የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማወጅ ይጮሃል
- ትክክል እንደሆንን ይመስለናል፤ ነገር ግን ተሳስተናል
የአይሁድ መሪዎች እውነትን ለማጥፋት ሲነሱ ምንም አላመነቱም
ማርቆስ 14፡1 ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።
ፋሲካ ቀኑ ሐሙስ ዕለት ነበረ። ስለዚህ ሊገለድሉት የተማከሩት ሰኞ ዕለት ነበር።
የቤተመቅደሱ ካሕናት ኢየሱስን ለመግደል ቸኩለዋል። ኢየሱስ በሆሳዕና እሁድ ዕለት ወደ ቤተመቅደስ ገብቶ ገንዘብ ለዋጮቹን ወንበዴዎች አባሯቸዋል። የገቢ ምንጫቸውን ስለነካባቸው ሊታገሱት አልቻሉም። የሆሳዕና እሁድ ኢየሱስ በሕዝብ ፊት እውቅና ያገኘበትና ለንጉስነት የታጨበት ቀን ነው።
ዘጸአት 12፡3 ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።
ዘጸአት 12፡6 በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።
ኢየሱስ ፋሲካችን ሆኖ ሐሙስ ዕለት በመስቀል ላይ ሞተልን።
እግዚአብሔር ለዚያ ጠማማ ትውልድ የሰጠው ብቸኛ ምልክት የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ ብቻ ነው።
ማቴዎስ 12፡39 እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።
ማቴዎስ 12፡40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
ሶስት ሌሊት። ሐሙስ ሌሊት። አርብ ሌሊት። ቅዳሜ ሌሊት። ከዚያ እሁድ በሌሊት ከሞት ተነሳ። በመጀመሪያው ምጻቱ ሰው ሆኖ ከሙታን ነተሳ።
ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ተደግሟል። በጨለማው ዘመን ውስጥ እውነት ከሞተ በኋላ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት እንዳለፉ እውነት ተመልሶ ከሞተበት ተነስቷል፤ ስለዚህ አማኞች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደነበሩ ወደ ሐዋርያት እምነት ይመለሳሉ።
መጽደቅ የሚቻለው በእምነት ብቻ ነው የሚለው እውነት በአምስተኛው የቤተክርስቲያን በሉተር አማካኝነት ተመልሶ መጥቷል። በስድስተኛው ዘመን ዌስሊ ቅድስና እና የወንጌል ስብከትን መልሶ አምጥቷል። የመንፈስ ቅዱስ ኃይለ በጴንጤቀስጤያዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ሙሉው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ደግሞ በዊልያም ብራንሐም በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ተመልሶ መጥቷል። በዚህም ምክንያት ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ ትችላለች።
ኢየሱስ በዳግም ምጻቱ እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ ነው ከሙታን የሚነሳው።
የፋሲካ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው ታላቁ ነብይ ሙሴ አይሁደችን ከግብጽ ባርነት ነጻ ሲያወጣቸው ነው፤ እነርሱም በነጋታው ከግብጽ ወጡ። ከዚያ ወዲያ በግብጽ አልተቀመጡም።
ፋሲካ የዓመቱ የመጀመሪያ በዓል ነው። ኢየሩሳሌም ውስጥ ወደ በዓሉ የታደሙ እጅግ ብዙ ሕዝብ ታላቁ መሲህ ከአስጨናቂው የሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ እንደሚያወጣቸው ተስፋ አድርገው ሲጠባበቁ ነበር። ጸረ ሮማዊ በሆነው ፖለቲካቸው አእምሮዋቸው ተይዞ ለነበሩት የአይሁድ ሕዝብ ያልገባቸው ነገር መሲሁ ነጻ ሊያወጣቸው የፈለገው ከሐጥያታቸው መሆኑ ነው።
ሁለቱ የሐይማኖት መሪዎች ሰዎችን መፈወስ እና በተዓምር ብዙ ሕዝብ ማብላት የሚችለውን የእግዚአብሔርን ልጅ ለመግደል ምንም አልፈሩም። ያስጨነቃቸው ነገር በኢየሱስ የፈውስ ኃይል የተደነቁት ሕዝብ ሃሳባቸውን እንዳይቃወሙ ብቻ ነው። ስለዚህ በፖለቲካ ውስጥ ተቀባይነት ባለው መንገድ በሮማውያን እጅ ሊያስገድሉት ሴራቸውን ጠነሰሱ። የሆሳዕና ዕለት ሕዝቡ ኢየሱስን በደስታ ተቀብለውት ነበር። የአይሁድ መሪዎች ሕዝቡ ከሁለት ቀን በኋላ ሕዝቡን በኢየሱስ ላይ ሊያስነሱበትና ይገደል ብለው እንዲጮሁ ሊያደርጉዋቸው ተዘጋጅተዋል።
ማርቆስ 14፡2 የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን ይሉ ነበርና።
የሆሳዕና ዕለት ሕዝቡ ኢየሱስን እንዴት ባለ ታላቅ አቀባበል እንደተቀበሉት ባዩ ጊዜ በበዓሉ ቀን ኢየሱስን መያዝና ለመግደል መሞክር አደገኛ እንደሚሆንባቸው ተገነዘቡ፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሊከላከሉ ይችላሉ።
የፋሲካ በዓል ሐሙስ ዕለት ማታ ጀመረ።
በአይሁድ ዘንድ ቀን የሚጀምረው ፀሃይ ስጥጠልቅ ነው።
ስለዚህ ሮማውያን ረቡዕ ማታ ብለው የሚቆጥሩት ሰዓት ለአይሁዶች ሐሙስ ማታ ነው፤ ቀጥሎም ሐሙስ ጠዋት እና ሐሙስ ከሰዓት በኋላ።
ሐሙስ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት የአይሁድ አርብ ይጀምራል።
አንዲት ያልታወቀች ሴት ያመጣችው ታላቅ መገለጥ ብዙ ወጪ አስከተለባት
እነዚህ ሁለት ጥቅሶች የዘመናዊቷ ቤተክርስቲያንመሪዎች ምሳሌ ናቸው፤ የዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች በጥንቃቄ አቅደው ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቀው ከመከተል እንዲመለሱ ለማድረግ ይዘጋጃሉ። የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ይቃወማሉ፤ አይቀበሉምም።
ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ የሰውን ቃል ከፍ ያደርጋሉ።
የሐይማኖት መሪዎች እግዚአብሔርን ያገለገሉ መስሏቸው የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደገፉ ካሳየን በኋላ ማርቆስ አንዲት ኢየሱስን እንደሚገባው ያገለገለች ሴትን ያሳየናል (ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት)።
ማርቆስ 14፡3 እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
ለምጻም ሰው ከተማ ውስጥና ቤት ውስጥ ሳይሆን ከሰው ርቆ ከከተማ ውጭ ነው የሚኖረው። ብቻውን ይኖራል እንግዳ መቀበልም አይችልም።
ዘሌዋውያን 13፡45 የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል።
ዘሌዋውያን 13፡46 ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻውን ይቀመጣል፤ መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።
ለምጽ በጣም ከባድ በሽታ ነው፤ ነገር ግን ጥቂት ሰዎች ከለምጽ እንደተፈወሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል።
ስምኦን ለምጽ ቢኖርበትና ኢየሱስ ቢፈውሰው ኖሮ ይህ ያልተለመደና እጅግ አስደናቂ ፈውስ ከስሙ ጋር ተያይዞ ይቀር ነበር።
የመጀመሪያው ትምሕርት ይህ ነው። ይህ ለምጻም ሰው ከማሕበረሰቡ የተገለለ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ፈወሰውና በቤቱና በእቅዱ ውስጥ ቦታ ሰጠው። ስለዚህ በሰው ዘንድ የተገፉ ሰዎችን እግዚአብሔር ይጠቀምባቸዋል። እነዚህ ሰዎች በብዙ ችግርና ሐጥያት ውስጥ ያለፉ ሰዎች እግዚአብሔር እስኪደርስላቸውና እስኪያነሳቸው ድረስ ለራሳቸው ምንም ማድረግ አይችሉም ነበር። ስምኦን በራሱ የሚመካበት ምንም ነገር አድርጎ አያውቅም።
ከዚህ የምንማረው እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው ሰዎች ታላላቅ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሳይሆኑ ማንም ያልጠበቃቸው ሰዎች ናቸው።
ይህች ሴት ታዋቂ አልነበረችም። ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።
ቤተክርስቲያን ወደ ራሷ ትኩረት መሳብ የለባትም። ለራሷ ስም አልሰጠችም።
እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ማንም ያልጠበቀውን ተራ ሰው ይጠቀማል፤ ደግሞም እግዚአብሔር ዓላማውን ሊፈጽም በፈለገ ጊዜ ብቁ ሰዎችን ትቶ አልፏል።
ኢየሱስ ራስ መሆኑን በማወቅ በራሱ ላይ ዘይት ወይም ሽቱ አፈሰሰችበት።
በእርሷ እና በኢየሱስ መካከል አንድም የሐይማኖት መሪ አልነበረም። ከደቀመዛሙርት መካከል አንዳንዶች ቢቃወሟትም እንኳ ይህ የእርሷ እና የኢየሱስ የግል ሕብረት ነበር።
ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ማስቀደም መልመድ አለብን ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ነው የእግዚአብሔርን ሃሳብ የሚገልጥልን። ሰው የሚያስበው ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ከሆነ ስሕተት ነው።
በዘመን መጨረሻ የቤተክርስቲያን መሪዎች ዋነኛ ተልእኮዋቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እውነት መቃወም ነው።
ሽቶው በጣም ውድ ነበር። ሴቲቱ ለእግዚአብሔር ያቀረበችው አገልግሎት ትልቅ ዋጋ አስከፍሏታል።
ብልቃጡን ሰበረችው። ለራሷ ብላ ያስቀረችው ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔርን ለማገልገል ብላ ሙሉውን ዋጋ ከፍላለች።
ሌሎቹ ሴቶች ከሰንበት በኋላ አስከሬኑን ሽቶ ሊቀቡ ሄዱ ምክንያቱም ከሞት ይነሳል ብለው አላመኑም።
ይህች ሴት ግን ሕያው የነበረው ስጋውን ነው ሽቶ የቀባችው፤ ይህም ከሞተ በኋላ ተመልሶ ሕያው እንደሚሆን ያመለክታል።
ይህች ሴት (ወይም ቤተክርስቲያን) ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሳ በአስደናቂ መገለጥ ተረድታ ነበር።
የገዛችው ሽቶ ዋጋው በጣም ውድ መሆኑ በራሱ ኢየሱስ ስለ ሐጥያታችን ሲሞትልን የሚከፍለው ዋጋ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
ሴቲቱ ብልቃጡን የሰበረችው ኢየሱስ የታላቁ ጠላታችንን የሞትን ቀንበር እንደሚሰብረው ለማመልከት ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡26 የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤
የከበረው ሽቶ እኛ ምንም ክብር የማይገባን ሐጥያተኞች ሳለን ኢየሱስ ግን ሊሞትልን የሚገባን አድርጎ እስኪያስብ ድረስ እንዳከበረን የሚገልጽ ምሳሌ ነው።
ማርቆስ 14፡4 አንዳንዶችም፦ ይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው? … ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤ እርስዋንም ነቀፉአት።
ለእግዚአብሔር አንድ መልካም ነገር ማድረግ ምንጊዜም ከሰዎች ዘንድ ተቃውሞ ያስነሳል።
ሽቶ በጥቂቱ ነው የሚቀባው፤ ይህች ሴት ግን ለምንድነው በኢየሱስ ራስ ላይ ሽቶዋን በሙሉ ያፈሰሰችው? ደቀመዛሙርቱ ገንዘብ እያባከነች ነው ብለው አሰቡ።
ሰዎች ሁልጊዜም ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት ስለሚፈልጉ ልባቸው ገንዘብ ላይ ነው።
ሴቲቱ አንድ ልዩ የሆነ ነገር እንዳገኘች እያመለከተች ነበር። ይህች ሴት መንፈሳዊ ልቦናዋ በርቶላታል።
ማርቆስ 14፡5 ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤
ሶስት መቶ ዲናር የአንድ ዓመት ደሞዝ ያህል ነው። እርሷ ግን መስዋእቷ ታላቅ ቢሆንም ኢየሱስ ከእርሷ መስዋእት እጅግ የሚበልጥ ታላቅ መስዋእት ሆኖ ሊሰዋ መሆኑ ገብቷታል። እርሱ ስለ ሐጥያታችን ሊሞት ተዘጋጅቶ ነበር።
ማርቆስ 14፡6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።
ኢየሱስ የሴቲቱን ድርጊት ሙሉ በሙሉ ደግፏል።
እግዚአብሔርን ስታገለግሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተከተሉ እንጂ ለሰዎች ትችት ምንም ቦታ አትስጡ።
ይህች ሴት ኢየሱስን (ቃሉን) ስላስቀደመች የሐይማኖት መሪዎች የሚሏትን በፍጹም አልሰማችም።
ማርቆስ 14፡7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።
ድሆች ሁልጊዜም ስለሚኖሩ ለእነርሱ እርዳታ የማድረግ እድል ሁሌም አለ። ኢየሱስ ግን ከእነርሱ ጋር ለብዙ ጊዜ አይቆይም።
በኢየሱስ ማለትም በእግዚአብሔር ቃል ላይ ትኩረት ማድረግ ምንጊዜም መልካም ነገር ነው።
ማርቆስ 14፡8 የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።
ያሏት አማራጮች በጣም ጥቂት ቢሆኑም እንኳ እርሷ ግን የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች። ኢየሱስ ሊሞት መሆኑን አውቃለች፤ ስለዚህ ቤቱን በሽቶው መልካም መዓዛ በማወድ የኢየሱስ ሞት ክብር ያለው ሞት መሆኑን እየገለጠች ነበር።
ማርቆስ 14፡9 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል።
በኢየሱስ ሞት ስለሚመጣው ተስፋ ደስ ተሰኝታ ነበር።
ስለዚህ የኢየሱስ ሞት ታላቅ ድል ስለመሆኑ ለመታሰቢያ ታላቅ ዋጋ ከፍላ ሽቶ ገዝታ አፈሰሰችለት እንጂ ድርጊቷ የሃዘን መግለጫ አልነበረም።
ክርስቶስ ስለ ሐጥያታችን የሞተልን ሞት የክርስትና ዋነኛ መሰረት ነው። የእርሱ ሞት ከሐጥያታችን ስለሚያጥበን በልባችን ልዩ ስፍራ እንሰጠዋለን።
ይሁዳ በገንገዘብ ፍቅር የተጠለፈ የቤተክርስቲያን መሪ ነው
ማርቆስ 14፡10 ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።
ኢየሱስን የሚደግፈው ሕዝብ ብዙ ነበር ምክንያቱም በሽተኞችን ሲፈውስና ብዙ ሕዝብ እንጀራ ሲያበላ ነበረ። ኢየሱስ የአይሁድ መሪዎች ክርክር ስንፍና እንዲመስል አደረገ። ከዚያ ቀጥሎ ማቴዎስ እንደጻፈው ኢየሱስ የሆሳዕና ዕለት ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አስወጣ። ማርቆስ እንደጻደው ደግሞ በቀጣዩ ቀን ማለትም ሰኞ ዕለት በድጋሚ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አስወጣ። ቤተመቅደሱ ትልቅ የገቢ ምንጭ ነበረ ስለዚህ የቤተመቅደሱ አስተዳዳሪዎች በገቢ ምንጫቸው ላይ የተሰነዘረባቸውን ትልቅ ጥቃት ሊታገሱ አልቻሉም።
ማርቆስ 14፡11 ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር።
ኢየሱስን በግልጽ ሊይዙት ያልደፈሩት ሕዝቡ ሊቃወሙን ይችላሉ ብለው ስለፈሩ ነው። ስለዚህ ከደቀመዛሙርቱ መካከል በጨለማ አሳልፎ የሚሰጣቸው ሰው ይፈልጉ ነበር።
ይሁዳ ኢየሱስን “ጌታ” ብሎ ጠርቶት እንደሆነ አንድም ጊዜ አልተጻፈም።
ሴት ማሳደድ፣ ገንዘብ መውደድ እና ዝና መፈለግ ብዙ ሰባኪዎች እግዚአብሔር ከሰጣቸው አገልግሎት የሚወድቁባቸው መንገዶች ናቸው።
ይሁዳ የወደቀው በገንዘብ ፍቅር ነው።
ብዙ ሰባኪዎች የሚሰብኩት ስብከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ጥሩ ክፍያ እስካገኙበት ድረስ ምንም አይመስላቸውም። ሃብት ማከማቸት የእግዚአብሔር በረከት ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል።
የፋሲካ እራት መብላት የተለመደ የምግብ ፕሮግራም ነበር
“የፋሲካ እራት” የበሉት “በፋሲካ በዓል ዋዜማ” ነው።
የፋሲካ በዓል የበግ ጠቦት ስጋ ተጠብሶ የሚበሉበት የበዓል ቀን ነው።
የፋሲካ ዋዜማ በሮማውያን አቆጣጠር ረቡዕ ምሽት ነው። በዚህ ምሽት የሚበሉት እራት ስጋ እና መረቅ ያለው ወጥ ነው።
የፋሲካ በዓል በሮማውያን አቆጣጠር ሐሙስ ምሽት ሲሆን በዚህ በዓል ቀን የተጠበሰውን የበግ ጠቦት ስጋ እየበሉ በዓሉን ያከብራሉ።
ረቡዕ ምሽት ለአይሁዳውያን ሐሙስ ነው። የአይሁድ አዲስ ቀን የሚጀምረው ፀሃይ ስትጠልቅ ነው።
ማርቆስ 14፡12 ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ፦ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት።
“ፋሲካ” በተጨማሪ የቂጣ በዓል ቀንም ነው። ይህም የፋሲካ በግ የሚታረድበት ቀን ነው።
ቀጣዩ ቀን “የፋሲካ በዓል” ሲሆን በዚያ ዕለት የተጠበሰው የበግ ጠቦት ስጋ ይበላል፤ ከዚያም ለ7 ቀናት ቂጣ ይበላል።
ስለዚህ የቂጣ በዓል ቀናት በድምሩ 8 ቀናት ናቸው።
ቂጣ የክርስቶስን ቅድስና ይወክላል። ኢየሱስ በፋሲካ ቀን ሲሞት ቅዱስ ነበረ። እርሱ የሞተበት ቀን የቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን ነው።
ከዚያ ቀጥለው የሚመጡት ሰባት ቀናት ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅድስና እና በእግዚአብሔር ቃል እየታገዘች እንደምታሳልፍ የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው።
ኢየሱስ የሆሳዕና እሁድ ዕለት በሕዝብ ፊት ተመርጧል፤ ያም ከወሩ 10ኛ ቀን ነው። ከዚያ በኋላ አራት ቀናት ስንቆጥር ሐሙስ ላይ እንደርሳለን። የአይሁድ ሐሙስ የሚጀምረው በሮማውያን ረቡዕ ምሽት ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ረቡዕ ምሽት (በሳምንቱ እኩሌታ) ነው የተያዘው፤ ከዚያም በቀጣዩ ቀን ማለትም ሐሙስ እለት ተሰቀለ።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤
ኢየሱስን ሕገወጥ በሆነ መንገድ በሮማውያን ረቡዕ ዕለት መያዛቸውና ሐሙስ ዕለት መሲሁ እንዲገደል ማድረጋቸው ሕግን የመተላለፍ ድርጊት በመሆኑ ከዚያ ወዲያ የቤተመቅደሱ መስዋእቶች ተቋረጡ፤ ምክንያቱም ሕጉ ከተጣሰ በኋላ ምንም ዋጋ የላቸውም።
ማርቆስ 14፡13 ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ከተማ ሂዱ፥ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤
ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ የፋሲካ እራት የበሉት በሮማውያን ረቡዕ ምሽት ነው፤ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ሐሙስ ዕለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ቀናት የሚጀምሩት ፀሃይ ስትጠልቅ ነው። የሮማውያን ቀናት የሚጀምሩት እኩለ ሌሊት ላይ ነው።
ብዙውን ጊዜ ውሃ የሚቀዱት ሴቶች ነበሩ። ወንድ ውሃ መቅዳቱ ያልተለመደ ነገር ነው። ይህም የሚነግረን እግዚአብሔርን መከተል ከፈለግን እርሱ ከተለመደው መንገድ ውጭ የሚሰራበትን አሰራር መልመድ እንዳለብን ነው። የእርሱ መንገድ ከእኛ መንገድ ይለያል።
ማርቆስ 14፡14 ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ፦ መምህሩ፦ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል በሉት።
ኢየሱስ እርሱን በማያውቁ ሰዎች ላይ እንኳ ሳይቀር እንዲህ ዓይነት ስልጣን ነበረው።
ማርቆስ 14፡15 እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም አሰናዱልን።
ማርቆስ 14፡16 ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ።
እንደ ሮማውያን አቆጣጠር የፋሲካ እራት የበሉት ረቡዕ ምሽት ነው። ይህ በተጨማሪ የቂጣ በዓል ቀን ነው። የፋሲካውን በግ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ አረዱና ጠበሱት። ሐሙስ ምሽት የፋሲካ በዓል እና የቂጣ በዓል ነበረ፤ የቂጣ በዓልም የሚያበቃው ከ7 ቀናት በኋላ ነው።
ሐሙስ ምሽት ለአይሁዶች አርብ ነው። ከዚያም አርብ ማታ የፋሲካ በዓል እና የቂጣ በዓልን ድግስ በሉ።
ያ አርብ ልዩ የበዓል ቀን ስለነበረ ትልቅ ሰንበት እና የማዘጋጀት ቀን ነበረ።
ዮሐንስ 19፡31 አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።
ቀጣዩ ቀን ደግሞ ቅዳሜ ማለትም የተለመደው ሳምንታዊ ሰነበት ነበረ።
የቤተክርስቲያን መሪ ኢየሱስን ካደ
ማርቆስ 14፡17 በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።
ይህ ቀን በእኛ አቆጣጠር ረቡዕ ምሽት ሲሆን ለአይሁዶች ግን ሐሙስ ምሽት ነው።
አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ለመጨረሻ ጊዜ መጡ። የመጨረሻው ዕራት የተለያዩበት ሰዓት ነበረ። ይሁዳ አጭበርባሪ ነበረ፤ ነገር ግን እስከዚህ ሰዓት ድረስ ማንነቱን ደብቆ ቢቆይም በመጨረሻው እራት ላይ የጥፋት ልጅ መሆኑ ተጋልጧል። የሲኦል ልጅ።
የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን አሳልፎ ሰጠ። ስለዚህ ቃሉን መካድ እጅግ ክፉ ድርጊት ነው። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል መቃረን ወይም መቃወም የለባችሁም። አንዳች አትጨምሩበት፤ ከተጻፈውም አንዳች አትቀንሱበት።
ማርቆስ 14፡18 ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ።
ሰይጣን በደቀመዛሙርት መካከል ሲሰራ ነበር። ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጠ። ጴጥሮስ ደግሞ ኢየሱስን ካደ።
ሰይጣን እውነትን ለማጥፋት የኮምዩኒስቶችን ወይም የሙስሊሞችን ድጋፍ አይጠቀምም። ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱስን የማይከተሉ እና ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን የሚተቹ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ይጠቀማል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን የሚሰብኩ ሰባኪዎች የተከፈተ አፍ የገሃነም ደጅ ነው።
ኢየሱስ እርሱን አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ከደቀመዛሙርት መካከል እንደሆነ ገልጦ በመናገር አስደነገጣቸው።
ዛሬም እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፈው ማሳየት የማይችሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች የፈጸሙት ክሕደት ብዛቱን ብናይ በጣም እንደነግጣለን።
ይሁዳ የመጨረሻውን እራት በመብላቱ በጣም ትልቅ ስሕተት ሰርቷል ምክንያቱም የተጋለጠው በዚያ ነው።
ይህ ስነስርዓት በብዙዎች ዘንድ ሕብረት ተብሎ ይጠራል። የተደረገውም በማታ ነው።
ዛሬ ቤተክርስቲያኖች የጌታ እራት የሚያደርጉት በጠዋቱ የአምልኮ ፕሮግራማቸው ሲሆን እግር ማጠብን ፈጽመው ትተውታል።
በዚህም ድርጊታቸው ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን አለመቻላቸውን እያጋለጡ ናቸው።
ማርቆስ 14፡19 እነርሱም ያዝኑ፥ እያንዳንዳቸውም፦ እኔ እሆንን? ይሉት ጀመር።
እውነተኛ የነበሩት ደቀመዛሙርት በሙሉ ኢየሱስን አሳልፈው የሚሰጡት እነርሱ ይሆኑ እንደሆን በፍርሃት ይጠይቁ ነበር።
ማርቆስ 14፡20 እርሱም መልሶ፦ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው።
ፋሲካውን በልተው ከጨረሱ በኋላ ስጋ እና መረቅ ያለው ምግብ ቀርቶ ነበር። እጁን የሚያጠልቀው ሲል ቂጣ ወስዶ መረቁ ውስጥ የሚያጠቅሰው ማለቱ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እንዳለው አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ቂጣ ይወስድና መረቁ ውስጥ ያጠቅሳል። ነገር ግን ሰዎች ስሕተትን ለማስተዋል የታወርን ስለሆንን ኢየሱስ ለይሁዳ እንጀራ አጥቅሶ በሰጠው ጊዜ ምን ማለት እንደሆነ ከደቀመዛሙርት መካከል አንዳቸውም እንኳ አልገባቸውም።
ማርቆስ 14፡21 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው።
ኢየሱስ አልፎ በተሰጠ ጊዜ ይሞታል፤ አሳልፎ ሰጭው ግን በሲኦል ይሰቃያል። ይህ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።
ዛሬም ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን እና ለመጠቀም እምቢ ስንል ኢየሱስን አሳልፈን እየሰጠነው ነን።
ከ100 በላይ ሌሎች የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ያሉ ሲሆን ሁሉም የተለያዩ ናቸው። 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እና ዲኖሚኔሽኖች አሉ። እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ናቸው። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች ልዩ ልዩ አመለካከቶች የሚገኙባቸው መንፈሳዊ አረንቋ ሆነዋል። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቀይሩ እና የሚተቹ ሁሉ እውነትን አሳልፈው ሰጥተዋል።
እንጀራ እና ወይን የስጋው እና የደሙ ምሳሌ ናቸው
ማርቆስ 14፡22 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና፦ እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ።
የጌታ እራት የነፍስ ምግብ ነው። ስለዚህ ለምልክት እንዲሆን ትንሽ ቂጣ እና ትንሽ ወይን ብቻ ይበቃል።
ቂጣው ይቆረሳል። አፋችን ውስጥ ስናላምጠው ለመዋጥ እና በሆዳችንም ለመፍጨትና ከውስጡ ንጥረ ነገሩን ለማግኘት እንዲቀለን በምራቅ ይሸፈናል።
ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው። የሮማ ወታደሮች ኢየሱስ ላይ ተፉበት፤ ሲተፉበት በምራቅ ተሸፈነ። ምራቅ ከተተፋበት በኋላ ብቻ ነው ቃሉን ማላመጥና ከሰውነታችን ጋር ማዋሃድ የምንችለው።
ዮሐንስ 6፡35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤
ማቴዎስ 27፡30 ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።
ማርቆስ 14፡23 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።
ጽዋው አስተምሕሮን ይወክላል።
ወይኑ ደግሞ በአስተምሕሮው አማካኝነት በሚገኘው መገለጥ የምንቀበለውን መነቃቃት ይወክላል።
ወይን በውስጡ አልኮል የተባለ መንፈስ አለው። ደም ደግሞ በውስጡ የሕይወት መንፈስ አለው።
ማርቆስ 14፡24 እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።
ደሙ የፈሰሰው ለብዙዎች ከሆነ እኔስ ለምን ለእኔ ነው ብዬ አልቀበለውም?
ስለዚህ ልባችን ለንሰሃ ዝግጁ ከሆነ ሁላችንም የኢየሱስን ማዳን ለራሳችን መቀበል እንችላለን።
መዳን በመስቀሉ ላይ ተጠናቋል።
ንሰሃ ስንገባ ሐጥያታችን ከእኛ ላይ ተነስቶ ወደ ኢየሱስ ይተላለፋል። የእርሱ ንጽሕና ደግሞ ወደ እኛ ስለሚተላለፍ በመካከላችን ሽግግር ይደረጋል።
የኢየሱስ ደም ውስጥ የኢየሱስ ሕይወት ወይም ቅዱስ መንፈሱ አለበት። ደሙ ከሐጥያታችን ያጥበናል፤ ከዚያም ቅዱስ መንፈሱ ወደ ልባችን ውስጥ ገብቶ በመኖር ለሐጥያት ያለን ፍላጎት እንዲለቀን ያደርጋል።
ቅዱስ መንፈሱ መጽሐፍ ቅዱስን እንድንታዘዝ ያነሳሳናል፤ የምንታዘዘውም ተገደን ሳይሆን ከልባችን ፈልገን ነው።
ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል።
ማርቆስ 14፡25 እውነት እላችኋለሁ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ደግሞ አልጠጣውም አላቸው።
ወይን መገለጥን ከመቀበል የሚመጣውን መነቃቃት ይወክላል። ሰማይ ቤት ውስጥ እጅግ ብዙ መገለጥ ስለሚኖር ሁሌ ተነቃቅተን እንኖራለን። ያለማቋረጥ ለዘላለም አዲስ ነገር እንማራለን።
የእግዚአብሔር ዙፋን በቃላት ሊገለጥ የማይችል የእግዚአብሔር ጥልቀት ሃሳብ ተደርጎ ሊታሰብ ይችላል። ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ሲቀመጥ የእግዚአብሔርን ሃሳብ እኛ በጥቂቱ መረዳት በምንችልበት ደረጃ ያወርድልናል። የእግዚአብሔር ሃሳብ ግን በጣም ጥልቅ እና ማለቂያ የሌለው ስለሆነ ይህ ሂደት ለዘላለም አይቋረጥም። ጠለቅ ያሉ እና በክብር የላቁ መገለጦችን በተቀበልን ቁጥር መረዳታችን እየጨመረ ይሄዳል።
ማርቆስ 14፡26 መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።
የመጨረሻው እራት ያበቃው በመዝሙር ነው።
ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ጉባኤ በመዝሙር ሲዘጋ በጣም ደስ ይላል። ደቀመዛሙርቱም ከእራት ፕሮግራሙ በኋላ በደስታ ተሞልተው እየዘመሩ ሲወጡ ኢየሱስ ሁላቸውም እንደሚሰናከሉና እንደሚወድቁ ነገራቸው።
ማርቆስ እግዚአብሔርን ስለማገልገል ሲነግረን በፍጹም በስሜታችን ላይ እንዳንደገፍ ነው የሚመክረን።
ደቀመዛሙርቱ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ሸሹ
ማርቆስ 14፡27 ኢየሱስም፦ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛዉን እመታለሁ በጎችም ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና።
ኢየሱስ ይህንን ቃል ጠቀሰላቸው።
ዘካርያስ 13፡7 … እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፤
ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ ደቀመዛሙቱ ፈርተው ነፍሳቸውን ለማዳን ይሸሻሉ።
የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደመሆናቸው መጠን መሸሻቸው ትልቅ ስሕተት ነው። ፈተና ሲገጥማቸው ቃሉን ትተው ሮጡ። ሃሳባቸው ነፍሳቸውን ለማዳን ብቻ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ አገልግሎት እራስን ማዕከል ያደረገ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም።
በዚህ ሁሉ ግን አንድ ቁልፍ ትምሕርት ያገኛሉ።
ቃሉን ብቻ ተከተሉ። ለራሳቹ የሚመቻችሁን ፍለጋ አታስቡ።
ፈሪነታቸው ኋላ እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ ያደርጋቸዋል። ያለ ኢየሱስ የሚሄዱበት አቅጣጫ አይኖራቸውም፤ እግዚአብሔርን ሊያገለግሉም አይችሉም።
ስለዚህ በመጨረሻ ኢየሱስ በደቀመዛሙርቱ እንደማይተማመን ግልጽ አደረገ። እነርሱም ስለ ራሳቸው እንደሚያስቡት አልነበሩም።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ የእግዚአብሔር ቃል በቤተክርስቲያን እንደማይተማመንባት ግልጽ ያደርጋል። እኛ ራሳችን ስለ ራሳችን እንደምናስበው አይደለንም።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያ የተናገረው ቃል ትችትና ወቀሳ ብቻ ነው።
ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን እግዚብሔር እንዲህ አለ፡- “የማታውቅ ስለሆንክ”።
በሌላ አነጋገር ራሳቸውን የሚያሞግሱ የዘመናችን ቤተክርስቲያኖች ስላሉበት ሁኔታ አንዳችም የሚያውቁት ነገር የለም።
ለመዳን የሚበቃ እውቀት አግኝተዋል፤ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አይችሉም።
ማርቆስ 14፡28 ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው።
ትልቅ ትምሕርት ይጠብቃቸዋል። ወንጌሉ የተመሰረተው በትንሳኤ ሃይል ነው እንጂ በሰው ጥረት አይደለም።
ከሁሉ በላይ ደግሞ ኢየሱስን መከተል አለባቸው እንጂ ከእርሱ ጋር መከራከር ወይም ከእርሱ መቅደም የለባቸውም።
ለዓለም የተሰጠ ብቸኛው ምልክት የኢየሱስ ትንሳኤ ነው። የትኛውም የሐይማኖት መሪ በጠላቶቹ እጅ ተገድሎ ከዚያም ከሶስት ቀናት በኋላ ከሞት ተነስቶ አያውቅም። ይህ ነው ኢየሱስን ከሁሉም ልዩ ያደረገው።
ማቴዎስ 12፡39 እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።
40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
ማርቆስ 14፡29 ጴጥሮስም፦ ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው።
ታላቁ እረኛ በመከራ ውስጥ አንድም ስሕተት ሳይሰራ ቢያልፍም እንኳ ተከታዮቹ ግን በታዘዘላቸው ትንንሽ ፈተና ውስጥ ተበታትነዋል። ሰዎች በተፈጥሮችን ስለ ራሳችን ትልቅ ነገር ነው የምናስበው ነገር ግን ሞኝነታችን የሚገለጠው በተፈተንን ጊዜ እንደምናስበው ሆነን ባለመገኘታችን ነው። ጴጥሮስ ስለ ራሱ ብርታትና ታማኝነት ለጌታ በልበ ሙሉነት መናገሩ ልክ አይደለም። ጴጥሮስም ሆነ ሌሎቻችንም በፍርሃት፡- “ጌታ ሆይ አንተን እንዳልክድ የሚያስችለኝን ጸጋ ስጠኝ” ብለን ብንመልስ ይሻለናል።
ክርስቲያኖች ገጽታቸውን ወልውለው በማሳመር የተዋጣላቸው ናቸው። ስለራሳችን ስናስብ ራሳችንን ብርቱና ታማኝ የቃሉ ተከታዮች አድርገን ነው የምንቆጥረው። እያንዳንዱ ክርስቲያን የሚያስበው ሌሎች ሰዎች ቢወድቁ እንኳ እኔ ግን አልወድቅም ብሎ ነው።
ጴጥሮስ ሰነፎቹን ቆነጃጅት ይወክላል፤ እነዚህ ቆነጃጅት የዳኑ ነገር ግን በሰዎች እና በቤተክርስቲያን አመለካከት የተታለሉ ክርስቲያኖች ናቸው። ድነዋል፤ ደግሞም እግዚአብሔርን ከልባቸው የማገልገል ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን በቤተክርስቲያን አስተምሕሮ ስለተታለሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራ መረዳት አይችሉም።
ከሶስት ክሕደቶች ጋር የተያያዙ ሁለት ግንዛቤዎች
ማርቆስ 14፡30 ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው።
ይህ ቃል ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት በአጭሩ ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ ሲሆን በዚህ ውስጥ ጴጥሮስ ሰነፎቹን ቆነጃጅት ይወክላል።
አውራ ዶሮ ሲጮህ ጥርት ያለ ድምጽ ያወጣል።
ቤተክርስቲያን የሰማችው የመጀመሪያው ጥርት ያለ ድምጽ ሐዋርያት የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ሲመሰርቱ በመሰረቷት ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። በተለይም ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ጠለቅ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ሲያብራራ ነው። የዶሮው መጮህ ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምሕርት ያመኑትን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰዎችን ይወክላል።
የመጀመሪያው ዘመን ስኬት የተመሰረተው ሐዋርያት እውነቱን በማስተማራቸው ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ እውነትን ለራሳቸው ተቀብለው እንዲያምኑ ማድረግ በመቻላቸው ጭምር ነው። ከዚህም የተነሳ ሐዋርያቱ ሰማዕት እየሆኑ በሞት ከተለዩ በኋላም እንኳ እውነት እየተስፋፋ ሄዷል።
ባለ ራዕዩ ዮሐንስ ኢየሱስን በመብራቶች መቅረዝ መካከል ቆሞ አየው።
ስለዚህ ይህ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነበር ዋስትና ያለው ምክንያቱም የመሰረቱት በቀጥታ ከኢየሱስ እግር ስር ተቀምጠው የተማሩ ሐዋርያት ነበሩ።
ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥
ራዕይ 1፡17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን አንድ ዓይነት ነው የሚሆኑት።
እነዚህ እውነቶች በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፉ፤ የጨለማው ዘመንም እስከ አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ድረስ ነው የዘለቀው።
ይህም ሂደት ምን እንደሚመስል ራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ ተገልጾአል።
እውነት ተመልሳ ስትመጣ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ዘንድ ተቃውሞ ይገጥማታል
እግዚአብሔር ጠፍቶ የነበረውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን የመለሰው በሶስት ተከታታይ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ነው። ማርቲን ሉተር ስለ መጽደቅ የተቀበለው መገለጥ የምንድነው በሥራ ሳይሆን በእምነት ብቻ መሆኑን አሳይቶናል። ጆን ዌስሊ ስለ መቀደስ አስተማረ። በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ደግሞ በጴንጤቆስጤ አማካኝነት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ተከትሎ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት ተገልጠዋል።
ነገር ግን ተሃድሶ በተደረገባቸው በሶስቱ ዘመናት ሁሉ ሰነፎቹ ቆነጃጅት በተሃድሶ ተመልሶ ከመጣው እውነት ይተዋሉ፤ የተቀበሉትንም እውነት ይክዳሉ። ከዚያም በኋላ ለዚያ ዘመን የመጣው ተሃድሶ የተሃድሶ መሪው ሲሞት ያበቃል። በተሃድሶ ዘመን ውስጥ የመጀመሪያው ክህደት የመጣው ከሉተራኖች መካከል አንዳንዶች ሜተዲስቱ አገልጋይ ጆን ዌስሊ ያመጣውን የቅድስና መልእክት ካዱ። በሜተዲስቶች መካከል የነበሩ ሰነፍ ቆነጃጅት ደግሞ በጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ የመጣውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ባለመቀበል እና በወንድም ብራንሐም አማካኝነት የመጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ባለመቀበል ሁለተኛውን ክሕደት ፈጸሙ። በዚህ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ይህ ዓይነቱ አሳዛኝ ክሕደት ከተፈጸመ በኋላ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ተቀብለው የነበሩ የጴንጤቆስጤያዊ እንቅስቃሴ መሪዎች በወንድም ብራንሐም የመጣውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ተቃወሙ።
የመጨረሻዎቹ ሶሰት የቤተክርስቲያን ዘመናት የተተናቀቁት በክህደት ነው። ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የዳኑ ሰነፍ ቆነጃጅት ሶስተኛውን ክሕደት ይፈጽማሉ፤ ለዚህ ነው ዊልያም ብራንሐም ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በተሃድሶ እንድንመለስ የሚያደርገን።
ትክክለኛውን ጴንጤቆስጤያዊ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተቀበሉ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ከዊልያም ብራንሐም ንግግሮች ውስጥ ጥቅስ እየወሰዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትርጉም እየሰጡ ናቸው። በዚህም መንገድ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ እንዳለብን ባለመቀበል የእውነትን ትምሕርት የሚያደናቅፍ ሌላ የቤተክርስቲያን ቅርንጫፍ ከፍተዋል።
ስለዚህ ተሃድሶ በሶስት ደረጃዎች እንደመጣ ሁሉ ተሃድሶውን ተከተለው ሶስት ክሕደቶች መጥተዋል።
ዶሮው የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማወጅ ይጮሃል
ከሶስት ክሕደቶች በኋላ ዶሮው እንደገና የሚጮህበት ሰዓት ይመጣል።
ዶሮው የሚጮኸው ሙሽራይቱ ውስጥ ያሉት አካላት እውነትን ለራሳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲያረጋግጡ ነው።
64-0823 ጥያቄዎችና መልሶች 1
ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ግን እኔ ስለሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ይቀበላሉ። የሚቀበሉ ሁሉ ለመቀበል ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃሉ እውነት መሆኑ ተረጋግጧል።
የ7ቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ - ምዕራፍ 9 - የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን
… እውነተኛው ነብይ ሰዎችን ሁልጊዜ ወደ ቃሉ በመምራት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስተሳስራቸዋል እንጂ እኔን ፍሩኝ እኔ የምናገረውን ንግግር ፍሩ አይልም፤ ቃሉ ፍሩ ነው የሚለው።
62-0318 የተነገረው ቃል እውነተኛው ዘር ነው - 2
አሁን እነዚህ የተናገርኳቸው ነገሮች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማሙ ከሆኑ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይገጥሙ ከሆኑ በሙሉ ስሕተት ናቸው።
65-0801 የዚህ ክፉ ዘመን አምላክ
… ጌታ ኢየሱስ ለዚህ ሰዓት የሰጠኝን ይህንን መልእክት ያመኑ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ምን እየተደረገ እንዳለ ያውቁ እና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ምን ተብሎ እንደተጻፈ ይገነዘቡ ዘንድ
1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ እንደተጻፈው የመላእክት አለቃው ድምጽ የሞቱትን የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ያስነሳቸዋል።
ስለዚህ “ድምጹ” ምንድነው?
ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ “ድምጹ” ገና ወደፊት ይመጣል ብሎ ይጠባበቅ ነበረ።
65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
“ድምጹ” ማለት ወንድም ብራንሐም ያስተምራቸው የነበሩ ትምሕርቶችን ትክክል መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ባረጋገጠ ጊዜ አይደለም። “ድምጹ” ማለት የሙሽራይቱ አካላት የወንድም ብራንሐምን ትምሕርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው ማረጋገጥ ሲችሉ ነው።
ከዚያ በኋላ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት እንመለሳለን፤ ከዚህም የተነሳ ለአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ዝግጁ ሆነን እንገኛለን።
ራዕይ 18፡1 ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።
2 በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
ይህ ቃል ወንድም ብራንሐም ራሳቸውን ከሕዝቡ በላይ ከፍ ያደረጉትን ኒቆላውያን የቤተክርስቲያን መሪዎችን ያወገዘበትን ኃይለኛ አገልግሎት በአጭሩ ይገልጻል። አዲስ ኪዳን ውስጥ ቤተክርስቲያንን የማስተዳደር ሃላፊነት ለፓስተሩ አልተሰጠውም።
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ … ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
ሌላ ድምጽ ማለት የወንድም ብራንሐም ድምጽ አይደለም ማለት ነው።
ሌላ ድምጽ የተባለው በውስጣችን የሚናገረን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ነው፤ ይህም ድምጽ ለእያንዳንዱ ሰው በግል በመናገር መጽሐፍ ቅዱስን ከማይከተሉ ቤተክርስቲያኖች እንዲወጡ ያሳስባቸዋል።
ራዕይ 19፡1 ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።
62-1111
ልብ በሉ ቀጣዩ ምዕራፍ 19ኛው ምዕራፍ ነው፡- “ከነዚህ ነገሮች በኋላ” ይላል። በዚህ በ19ኛው ምዕራፍ ውስጥ “ከነዚህም ነገሮች በኋላ” የሚለውን አስተውላችኋል? ከነዚህ ነገሮች በኋላ ምን?
ከምን በኋላ? “ከእርሷ ውጡ!” ከሚለው መልእክት በኋላ።
“ከነዚህ ነገሮች በኋላ” የሚለው “የሙሽራይቱ አካላት የሆኑት ቅዱሳን እና የሙሽራው ድምጽ ነው፤ ድምጻቸውም ወደ በጉ ሰርግ ሲታደሙ የሚሰማው ድምጽ ነው”። ምን ያህል ጊዜ ነው የሚቀረው? የመጨረሻው ጥሪ ምንድነው? ከባቢሎን ውጡ!
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ እኔ የምቃወምበት ምክንያት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። እውነትና ትክክለኛ አይደለም። ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። እግዚአብሔር በዚህ ውስጥ የለበትም፤ አልነበረበትም፤ ወደፊትም አይገኝበትም። እንግዲህ በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ እውነተኛ ሰዎች የሉም ማለቴ አይደለም፤ ከነዚህ ዓይነት ሰዎች ነው ቤተክርስቲያን የተሰራችው።
ነገር ግን በዚያ ዓይነት ድርጅት ውስጥ በቆያችሁ መጠን የድርጅቱ አካል ትሆናላችሁ።
“ድምጹ” እውን የሚሆነው የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ክርስቲያኖች በሙሉ ከቤተክርስቲያኖች ሲወጡ እና እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ በማመሳከር ሲያረጋግጡ ነው።
ይህም የዶሮው ሁለተኛ ጩኸት ነው።
62-0627 ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን
… የምናገረውን ሁሉ በጥንቃቄ መርምሩ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ከሆነ በፍጹም አትቀበሉ።
ትክክል እንደሆንን ይመስለናል፤ ነገር ግን ተሳስተናል
ማርቆስ 14፡31 እርሱም ቃሉን አበርትቶ፦ ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።
ኢየሱስ ትክደኛለህ ብሎ በድጋሚ ሲነግረው ጴጥሮስ ይበልጥ ግትር ብሎ አልክድህም አለ።
መጽሐፍ ቅዱስ የዛሬዎቹን ቤተክርስቲያኖች ደጋግሞ ጠንከር አድርጎ ሲነቅፋቸው የቤተክርስቲያን አባላት ቤተክርስቲያናቸውን በመደገፍ ይበልጥ ግትር ብለው ይናገራሉ። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ይነቅፋሉ፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያናቸውን ወይም ፓስተራቸውን አይነቅፉም።
ክርስቲያኖች እራሳቸውን ጥሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አድርገው ይቆጥራሉ። በአፋችን የምንናገረው ትልልቅ ነገር ነው።
ኢየሱስ ግን ቃሉ እንደመሆኑ ስለ ራሳችን የምንናገረውን ትልልቅ ነገር አልተቀበለም።
መጽሐፍ ቅዱስን ገልጠን ስናነብብ ስለ መጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን አንዳችም እንኳ መልካም ነገር የሚናገር አንድ ትንቢት ወይም አንድ ምሳሌ እንኳ ልናገኝ አልቻልንም።
ቤተክርስቲያን እራሷን ስኬታማ አስመስላ ሰዎችን እያታለለች ናት።
ይህም ራሺያ በ2022 ዓ.ም ዩክሬይንን መውረር ስትጀምር ብቁ ወታደራዊ ዝግጅት እንዳላት አድርጋ ስለ ራሷ ከማሰቧ ጋር ይመሳሰላል።