ማርቆስ 13 ሮም ጥንታዊት የእውነት ጠላት ናት



ሮማውያን ክርስቶስን ሰቀሉ። ይህም የሮማውያን ክፉ መንፈስ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ወደ 7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ተሰራጨ።

First published on the 20th of November 2022 — Last updated on the 20th of November 2022

የአይሁዶች ቤተመቅደስ ይፈርሳል

 

አራቱ ወንጌሎች በዙፋኑ ዙርያ የሚገኙትን አራቱን ሕያዋን ፍጥረታት ይወክላሉ።

በሰማያት አንድ አካል ብቻ ስለተቀመጠበት ዙፋን ይነግሩናል።

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 … በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
ማርቆስ ሁለተኛው ወንጌል እንደመሆኑ ሁለተኛው ሕያው ፍጥረት ላይ ነው የሚያተኩሩት፤ እርሱም ጥጃው ወይም በሬው ሲሆን ማደግናን ሸክም እንደሚሸከም አገልጋይ እግዚአብሔርን ስለ ማገልገል መማርን ይወክላል።

 

 

አድጎ ትልቅ ጠንካራ በሬ እስከሚሆን ድረስ የሚታገስ ጥጃ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ማገልገል እስከምንችል ድረስ ምንያህል ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅብን ያስተምረናል። በሬ ሸክም የሚሸከም እና የሚታረድ እንስሳ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ማገልገል የምትፈልጉ ከሆነ ስደት እንደሚደርስባችሁ ጠብቁ።

መታገስ፣ መቻል፣ እና መታረድ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ ከዲያብሎስ ጋር በምታደርገው ትግል የሚገጥሟት ሶስት ተግዳሮቶች ናቸው።

ማርቆስ 13፡1 እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ መምህር ሆይ፥ እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው።

ደቀመዛሙርቱ ሰዎች በሰሯቸው ውብ ሕንጻዎች ተገርመው ነበር። ቤተመቅደሱን ለመስራት ገንዘብ የሰጣቸው ሰውዬ ሔሮድስ መሆኑን ረስተዋል (እርሱም ደግሞ አይሁዳዊ አልነበረም፤ ምክንያቱም የመጣው ከእስራኤል በስተ ደቡብ ከምትገኘዋ ከኤዶምያስ ነው)።

 

 

ሔሮድን ንጉስ አድርገው በዙፋን ላይ ያስቀመጡት ሮማውያን ናቸው። ሔሮድስም እራሱ በዙፋን የተቀመጠው ዙፋኑን ቀምቶ መሆኑን ያውቀዋል። ስለዚህ ለስልጣኑ ተቀናቃኝ ብሎ የጠረጠረውን ሰው ሁሉ ያለ ምንም ርህራሄ ይገድላል፤ ምክንያቱም ሔሮድስ የዳዊት ዘር ስላልሆነ ሕጋዊ ንጉስ አይደለም። ለዚህ ነው እውነተኛውን ንጉስ ኢየሱስን የሁለት ዓመት ሕጻን እያለ ሊገድለው የሞከረው። ስለዚህ ቃሉን የመግደል እና ገንዘብ የማከማቸት መንፈስ ወደ ቤተመቅደስ ሾልኮ ገባ። የቤተመቅደሱ መሪዎች ኢየሱስን ይጠሉት ነበረ ምክንያቱም ለገንዘብ ንግዳቸው ስጋት ሆኖባቸዋል። ቤተመቅደሱ እጅግ ብዙ ሃብት ተከማችቶበት ነበረ። ሰዱቃውያን፣ ፈሪሳውያን፣ እና ረቢዎች ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልተጠቀሱም። ኢየሱስም እነዚህን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ ስልጣናቸው በተቀመጡ ሰዓት ነጻነት እንዳይሰማቸው አደረገ፤ ስለዚህ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እርሱን ሊያጠፉት ይፈልጉ ነበር።

ፓስተሮችም አዲስ ኪዳን ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪ ተደርገው አልተሾሙም። ስለዚህ ፓስተሮችም ብቻቸውን የቤተክርስቲያን ራስ ብለው እራሳቸውን በሾሙበት ሹመት የሚኖሩት በስጋት ነው። ልክ እንደ ሔሮድስ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው በትንንሽ ቡድኖች ሆነው በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሲሰበሰቡና የሚያስተዳድሯቸውም ሽማግሌዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲከተሉ ሲያስተምሯቸው ፓስተሮች ይቆጣሉ። ዛሬ ግን ዕድሜ ኮምፒዩተሮችና ሞባይሎች ላይ ለሚሰራው ለዙም ቴክኖሎጂ የተለያዩ ግለሰቦችና ትንንሽ ቡድኖች እውነትን ለመማማርና ሕብረት ለማድረግ በኢንተርኔት መገናኘት ይችላሉ።

ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ ስለ መንግስተ ሰማያት የሚናገሩ 7 ምሳሌዎች አሉ፤ እነዚህም ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ። ሰባተኛው ምሳሌ ውስጥ መረብ ተጠቅሷል (የመረጃ መረብ ወይም ኢንተርኔት)፤ ይህም መረብ እረፍት በሌለው የሰዎችና የሕዝቦች ባሕር ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ስዚህ ተራርቀው የሚኖሩ ግለሰቦች እግዚአብሔርን ለማገልገልና እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመማር መሰባሰብ ይችላሉ።

በመጨረሻው ዘመን የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት እንችል ዘንድ እውነትን ማወቅ ያስፈልገናል። ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን የማናውቅ ሆነን ሳለን በቸልተኝነት መንፈስ ማንቀላፋት የለብንም። ለመረዳት የሚከብዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንም ምንም የማይጠቅሙ ዝርዝሮች አድርገን ቸል ማለት የለብንም። ከባዶቹን ጥቅሶች ትተን የምናልፍ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃችንን እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን የተሳሳተ መረዳት ሸፋፍነን ማለፍ የምንፈልግ ሰዎች ነን።

 

የአይሁድ መሪዎች እግዚአብሔርን እያገለገሉ አልነበሩም ምክንያቱም የኢየሱስን አገልግሎት አንቀበልም ብለዋል።

ቤተመቅደሱ ግን ብዙ ሃብት ተከማችቶበት ስለነበረና ለብዙዎቹም የአይሁድ መሪዎች ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ የሥራ ዕድል ሰጥቷቸው ነበር።

የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ኢየሱስ መቅደሱን ትቶ ወጣ። ይህ የሆነው በ33 ዓ.ም ነው። ትኩረታችን ቃሉ ቤተመቅደሱን ትቶ መውጣቱ ላይ ነው።

ደቀመዛሙርቱን እያናገረ በነበረበት ሰዓት ከቤተመቅደሱ ወጥቶ ውጭ ቆሞ ነበር። ቤተመቅደሱ ለእግዚአብሔር ምንም የማይጠቅም የሆነው በዚህ መንገድ ነው፤ ምክንየቱም ቤተመቅደሱ ውስጥ ለቃሉ ምንም ቦታ አልተሰጠውም።

ቤተመቅደሱ የእውነትና የደህንነት መገኛ መሆኑ ቀርቶ ከ37 ዓመታት በኋላ በ70 ዓ.ም ሮማዊው ጀነራል ታይተስ ከተማይቱንና ቤተመቅደሱን በደመሰሰ ጊዜ ብዙዎችን ወደ ሞትና ወደ መታረድ የሚነዳ የስሕተት ወጥመድ ሆነ።

ይህም የአሕዛብ ቤተክርስቲያን “በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን” መጨረሻዋ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ክስተት ነው (ሎዶቅያውያን የራሳቸውን እምነትና አስተምሕሮ የሚፈጥሩ ናቸው)። እነርሱም ኢየሱስ በተገለጠው ቃል መልክ በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ሲመጣ ከቤተክርስቲያን ገፍተው አስወጥተውታል። ክርስቲያኖች ግን እስካሁን ድረስ የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በተመለከተ ፍጹም መሃይም ቢሆኑም እንኳ በቤተክርስቲያን ግምባታ ፕሮግራማቸው ግን እየተደሰቱ ይኖራሉ። ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ ማመን እና ማስተማር እንዳለባቸው አይሰማቸውም። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ትክክል ነው ብለው አያምኑም። ዛሬ ኢየሱስን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደተገለጠው ቃል አይቀበሉትም። ስለዚህ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

ማርቆስ 13፡2 ኢየሱስም መልሶ፦ እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አለው።

ቤተመቅደሱ ኢየሱስን አልቀበልህም ብሏል። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል።

ቤተመቅደሱ በነበረበት ሥፍራ “የለቅሶ ግድግዳ” የተባለው ቦታ ኢየሩሳሌም ውስጥ ከሔሮድስ ዘመን ጀምሮ የነበረ ከመሬት ወደ ላይ የሰባት ድንጋዮች ድርብርብ ከፍታ ያለው ግድግዳ ነው። ከምድር በታች ደግሞ 17 የድንጋይ ድርብርብ አለ። ይህ ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም አይሁዶች በ70 ዓ.ም እና ከ132 – 135 ዓ.ም በሮማውያን ላይ ባደረጓቸው ሁለት ዓመጾች የተነሳ ድንጋዮቹ በሙሉ ይወድቁ ነበር።

ሮማዊው ንጉስ ሐድሪያን አይሁዳውያንን ይጠላ ስለነበረ በ135 ዓ.ም ቤተመቅደሳቸውን መታሰቢያ እስከማይገኝለት ድረስ ደምስሶ ሊያጠፋው ፈልጎ ነበረ።

አሁን የሚገኘው የቤተመቅደሱ ሥፍራ ጆሲፈስ በ70 ዓ.ም በጻፈው ዘገባ ከገለጸው በሁለት እጥፍ የሚበልጥ መሆኑም የለቅሶውን ግድግዳ የሰራው ሔሮድስ ሳይሆን ሐድሪያን ስለ መሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።

ሐድሪያን ኢየሩሳሌም ውስጥ የሮማውያንን ምሽግ ሰራ። የሮማውያን ምሽጎች ለ5,000 ሰዎች የሚበቁ እና 36 ኤከር ስፋት ያላቸው አራት ማዕዘኖች ነበሩ። ቤተመቅደሱ በነበረበት ሥፍራ የነበረው ግምብ አጥር ስፋቱ 37 ኤከር ነበረ።

ስለዚህ ብዙ ሰዎች ተራራው ላይ የሚገኘው የቤተመቅደስ አጥር ሐድሪያን የሰራው የአንቶኒያ ሮማዊ ምሽግ አጥር ይመስላቸዋል። (በቀጣዩ ምስል ውስጥ ትልቁን ቀይ አራት ማዕዘን መስመር ተመልከቱ)።

ጽዮን ወንዞች ነበሯት። የተራራው ቤተመቅደስ ውስጥ ምንም ወንዝ የለም።

መዝሙር 87፡5 ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥

መዝሙር 87፡7 በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።

ስለዚህ የለቅሶ ግድግዶ (ከቀዩ አራት ማዕዘን ውስጥ ትንሽዬ ሥፍራ) በተባለው ቦታ የሚያመልኩ አይሁዶች በዚያ ሥፍራ በማምለካቸው ተሳስተዋል። በተመሳሳይ መንገድ ቤተክርስቲያኖችም ስላሴን በማምለካቸው፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ የሚባሉ በዓላትን በማክበራቸው፣ የ7 ዓመቱ ታላቅ መከራ፣ ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው፣ ወዘተ እያሉ በማመናቸው በትምሕርት ተሳስተዋል። እውነትን እና ስሕተትን አንድ ላይ አቅፎ በያዘው ሰብዓዊ ጥረታችን እግዚአብሔር የሚገረም ይመስለናል። ነገር ግን እግዚአብሔር እየፈለገ ያለው በቤተክርስቲያን ልማዶችና አመለካከቶች ያልተበረዘ ንጹህ እውነት ብቻ ነው።

ከሁሉም ቅርብ የሆነው ውሃ የግዮን ወንዝ ነው።

ብዙ ሰዎች ቤተመቅደሱ ከግዮን ወንዝ አቅራቢያ ነው የተሰራው ብለው ያምናሉ (ይህ ቦታ ትንሹ ቀይ አራት ማዕዘን ነው)፤ ከዚያ ወዲያ ግን ሙሉ በሙሉ ስለፈራረሰ አንድም ግድግዳ ቆሞ አልተገኘም። ኋላም ሮማዊው ገዥ ሐድሪያን ቤተመቅደሱ የነበረበት ሥፍራ በጭራሽ እንዳይታወቅ በማሰብ ሙሉ በሙሉ ቦታውን በአፈር ሸፈነው። በዚህም ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት ተፈጸም።

የጥንታዊቷ ከተማ አጥሮች በጥቁር ቀለም የተሰመሩት መስመሮች ናቸው። ተራራው ላይ የተሰራው ቤተመቅደስ ትልቁ ቀይ አራት ማዕዘን ነው። እነዚህ ትልልቅ ድንጋዮች በሙሉ አልወደቁም።

 

 

ይህም ተደላድለው በተቀመጡባቸው ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሚወዷቸው ሰባኪዎች ያስተማሩዋቸውን ብዙ የተሳሳቱ ሃሳቦች የሚያምኑ እና ምንም “የማያውቁ” ሎዶቅያውያንን ይወክላል። ለዚህ ነው 10ሩም ቆነጃጅት እንቅልፍ ተኝተዋል የተባሉት (ቆነጃጅት ማለት ቤተክርስቲያን ውስጥ የዳኑ ሰዎችን የሚወክሉ ድንግል ሴቶች ናቸው)። ንቁ የሚለው ጥሪ የሚመጣላቸውም መብራታቸውን ከዓለማዊነት እና ከቤተክርስቲያን ስሕተቶች እንዲያጸዱ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ከየትኛዋም ቤተክርስቲያን “ተለይታችሁ ውጡ” ብሎ የሚናገረውን ቃል መረዳት ይችሉ ዘንድ አጥርቶ የሚያሳያቸውን ብርሃን እንዲያገኙ ነው።

ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።

ኢየሱስ እንደ ሰው ሆኖ ተገልጦ በመጣ ጊዜ አይሁዶች አንቀበልህም አሉት።

ቤተክርስቲያኖች ደግሞ ኢየሱስ እንደ ቃል ማለትም ኪንግ ጀምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ ሲመጣ አንቀበልህም እያሉት ናቸው።

ማርቆስ 13፡3 በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም፦

ኢየሱስ ቤተመቅደሱ እንደሚፈርስ በሕዝብ ፊት በይፋ ተናግሯል።

ነገር ግን ወደ ፊት ሊፈጸሙ ስላሉ ጉዳዮች በተመለከተ ከተናገረው ጋር በተያያዘ ይበልጥ ለመረዳት ፍላጎት ያሳዩ ደቀመዛሙርት ከ12ቱ መካከል 4ቱ ብቻ ነበሩ። እነዚህም በግል ወደ እርሱ መጥተው ጥያቄ ጠየቁ።

ይህም ከክርስቲያኖች መካከል ስለ ወደፊቱ ማወቅ የሚፈልጉ ጥቂቶች ብቻ እንደሆኑ ያመለክታል። የቀሩት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንኳ ሳያውቁ ምንም ግድ ሳይኖራቸው እንቅልፍ ይተኛሉ።

ስለ ዳኑ ብቻ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ሊወስዳት በአየር ላይ ሲነጥቃት እነርሱም እንዲሁ አብረው የሚነጠቁ ይመስላቸዋል።

ምንም ዓይነት ሥራ በመስራት ከሲኦል መዳን አትችሉም።

ኢየሱስ መስራት ያለብንን የተወሰኑ ሥራዎች ይነግረናል።

ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ከሲኦል የማያድኑን ሥራዎች የዳኑ ክርስቲያኖች ወደ ፊት በቅርቡ ከሚመጣው ከታላቁ መከራ ለመዳን መስራት ያለባቸው ሥራዎች ናቸው።

ማርቆስ 13፡4 ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት።

ማርቆስ ሁለት ጥያቄዎችን ብቻ ይጠይቃል። ቤተመቅደሱ መች ነው የሚፈርሰው እና በጌታ ዳግም ምጻት ምክንያት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚያበቃው መች ነው?

የማርቆስ ወንጌል ውስጥ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ መች እንደሚመለስ አልጠየቁም። የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጠናቀቁን የሚያሳየው ምልክት ምን እንደሆነ ብቻ ነው የጠየቁት።

ማቴዎስ ኢየሱስን የአሕዛብ እና የአይሁድ ንጉስ እንደሆነ አድርጎ ነው የገለጸው።

ማቴዎስ ሶስት ጥያቄዎችን ይጠይቃል።

ቤተመቅደሱ መች እንደሚፈርስም ይጠይቃሉ። ከዚያ በኋላ ንጉሱ በጌታ ዳግም ምጻት ጊዜ ከምታበቃዋ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ጋር ጉዳይ ይኖረዋል። ደግሞም መች እንደሚመጣ አልጠየቁትም፤ የጠየቁት የመምጣቱ ምልክት ምን እንደሆነ ነው።

ከዚያም ክርስቶስ እንደ ንጉስ ከአይሁዶች ጋር ያለውን ጉዳይ ይፈጽማል፤ ይህም የዓለም ፍጻሜ በሚሆነው በአርማጌዶን ጦርነት ይጠናቀቃል። በዓለም መጨረሻ አርማጌዶን ሊመጣ ስለመቅረቡ የሚያሳዩ ምልክቶች ምንድናቸው?

ማቴዎስ 24፡3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

በዚህ ክፍል ውስጥ ደቀመዛሙርቱ ሶስት ጥያቄዎችን ጠየቁ።

የመጀመሪያው ጥያቄ፡- “ይህ መች ይሆናል?” ይህ ጥያቄ የቤተመቅደሱን መፍረስ በተመለከተ ነው።

የቤተመቅደሱ መፍረስ በሁለት ዙር ነው የተፈጸመው። ሮማዊው ጀነራል ታይተስ በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሱን አፈረሰው። ከዚያ ወዲያ በ135 ዓ.ም አረማዊው ንጉስ ሐድሪያን ቤተመቅደሱ የነበረበት ቦታ ምልክት እስከማይገኝ ድረስ ደመሰሰው። መቅደሱ የነበረበት ቦታ አንድ ድንጋይ እንኳ አልተገኘም፤ ቦታውም ሙሉ በሙሉ በአፈር ተሸፈነ። ሐድሪያን ፎርት አንቶኒያ የተባለውን ምሽግ በትልልቅ ግድግዳዎች ሰራ (ይህ ከላይ በሚገኘው ምስል ውስጥ ቀዩ አራት ማዕዘን ነው) ይህን ምሽግ የሰራው ሮማውያን ከተማውን እንዲጠብቁበትና አይሁዶች እንዳይገቡ ለመከላከል ነው። ቤተመቅደሱ በነበረበት ቦታ ጁፒተር ለተባለ ጣኦት ቤተመቅደስ ተሰራለት (ትንሹ ቀይ አራት ማዕዘን)። ክርስቲያን ሆኛለሁ የሚለው ሮማዊ ንጉስ ኮንስታንቲን ኋላ የጁፒተርን ቤተመቅደስ ሙሉ በሙሉ አፈረሰው።

 

በቀላሉ ስለምንታለል ትልቁ ጠላታችን ሽንገላ ነው

 

ማርቆስ 13፡5 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።

ኢየሱስን በአየር ላይ የምንቀበልበት ንጥቀት በመጣ ጊዜ መነጠቅ እንድንችል መስራት ያለብን የተወሰኑ ሥራዎች አሉ። የመጀመሪያው ሥራ ማንኛውም ሰው የሚናገረውን ነገር በጥንቃቄ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት መመርመር ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ነገር ያመንን ጊዜ ጉዳችን ፈላ።

ሔዋን አንድ ስሕተት ብቻ ሰርታ ነው ከኤድን ገነት የተባረረችው።

ማርቆስ 13፡6 ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ።

የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ ወደ ሮማ ካቶሊክ የገባው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ተገለጠ፤ ይህም መንፈስ ከገባ በኋላ በ1314 ዓ.ም ለሞተው ለፖፕ ክሌመንት አምስተኛው ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ጫነለት።

 

 

ያ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ደጋን ይዟል ግን ቀስት የለውም፤ ስለዚህ ውሸታምና ፌዘኛ ነው። አታላይ ነው። ነጩ ፈረስ ከሐጥያታችን ያነጻናል ተብሎ የሚታመንበት የሐይማኖት ተምሳሌት ነው። ስለዚህ ይህ መንፈስ ሐይማኖታዊ አሳሳች ነው፤ እርሱም ፈረሱን እየጋለበ ይመጣና ዘውዱን ተቀብሎ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነው አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው በሚለው ትምሕርቱ ፕሮቴስታንቶችን ያንበረክካል።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።

በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተቀቡ ነገር ግን በትምሕርታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የቤተክርስቲያን ሰባኪዎች በቀላሉ እንታለላለን። እነዚህ ሰባኪዎች የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ተሞልተዋል ግን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች አልተረዱም።

ማቴዎስ 5፡45 … በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ … እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።

ዝናብ የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌት ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዎችን በኃይል ይቀባል፤ የክፉ ሰዎችንም የመልካም ሰዎችንም ጸሎት ይመልሳል። ስለዚህ አንድን ሰው ጸሎቱ ኃይለኛ በመሆኑ አትመዝኑት፤ ነገር ግን ሰውየው ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ መዝኑት። ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆናችሁ ነው በክርስቶስ አካል ውስጥ ያላችሁን ሥፍራ የሚወስነው።

ማቴዎስ 7፡21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

“የእግዚአብሔር መንግስት” ምንድናት?

“ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” የሚለው አጠራር ውስጥ ድግግሞሹ ትኩረትን ያመለክታል። እነዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ኢየሱስ ለእነርሱ ጌታ መሆኑን በአጽንኦት ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የሚሉት ስሜታዊ ሆነው ነው። ስሜታቸውን ሲያፈስሱ እና ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ሲጮሁ በጣም ደስ ይላቸዋል፤ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች መረዳት እንደሚያስፈልጋቸው አላወቁም።

በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጡ እውነቶችን ለመረዳት እንኳ ጥረት አድርገው አያውቁም። የራሳቸውን አመለካከቶችና የቤተክርስቲያናቸውን ልማዶች ብቻ ነው የሚሰብኩት፤ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያኖቻቸው ውስጥ ተወዳጅነትን አትርፈዋል።

ቁልፉ ግን የተገለጠውን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በመረዳት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት ማለት በውስጣችሁ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው።

ሉቃስ 17፡21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።

እግዚአብሔር የሚኖረው ሰማይ ውስጥ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንግስት (መንፈስ ቅዱስ) በውስጣችሁ ሲኖር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያሳያችሁ ዓይናችሁን ይገልጥላችኋል። ዓይናችሁም ሲገለጥ እግዚአብሔር ለሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ያሰበው ፈቃድ ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ ያሳውቃችኋል። ይህም ፈቃድ ለዛሬ የተገለጠው የእግዚአብሔር መንግስት ነው።

ለመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ ትችሉ ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ከቃሉ እንዲገለጡ ነው። የመካከለኛው መብራት ብቻ ነው ዋስትና ያለው ምክንያቱም ዮሐንስ ኢየሱስን ያየው መካከለኛው መብራት አጠገብ ነው።

 

 

ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥

በመጨረሻው ወይም በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደ መንግስተ ሰማያት መድረስ የምንችለው አዲስ ኪዳን ወደ ተጻፈበት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት ስንመለስ ነው።

በመጨረሻው ዘመን የመጣው የወንድም ብራንሐም የንስር እይታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአንበሳው ዘመን በነበሩ ሐዋርያት ወደተጻፈው ቃል ይመልሰናል። ስለዚህ ከሁሉም በላይ የሚያስፈልገን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማወቅና ማመን ነው።

 

 

ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

እነዚህ ሰዎች እጅግ አስደናቂ የሆነ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል በመግለጥ ብዙ ተዓምራትን አድርገዋል።

ማቴዎስ 7፡23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

ዓመጽ ማለት ሐጥያትን እያወቃችሁ ስታደርጉ ነው።

እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እያወቁ ይቃረናሉ ወይም እንዳላወቁ መስለው ያልፋሉ፤ ደግሞም መረዳት የማይችሏቸው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች እንዳሉም ያውቃሉ።

ትኩረታቸውን በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ የሚደረግ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይልን በመግለጥ ላይ ብቻ አድርገው በዊልያም ብራንሐም የተገለጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚጥራትን መረዳት አያስፈልገም ብለው ራሳቸውን አታለሉ። ስለዚህ በዘመን መጨረሻ ሁላችንን ሊረዳን እግዚአብሔር የላከውን ነብይ ቸል ብለው ራሳቸውን ዝነኛ ማድረግ የሚችሉበት ነገር ላይ ብቻ ትኩረት አደረጉ። በዚህ መንገድ ራስን ከፍ ማድረግ የኒቆላውያን ሥራ ስለሆነ ዓመጽ ነው። የኒቆላውያን ሥራ ማለት አንድን ቅዱስ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ከሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ማድረግ ነው።

እነዚህ ሰባኪዎች በአገልግሎታቸው ውስጥ በሚገለጠው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል አማካኝነት ሰዎችን ማስደነቅ ይፈልጋሉ። ከዚያ ይልቅ ዊልያም ብራንሐም ያስተማረንን የተገለጡትን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለሕዝቡ በማስተማር ማስደነቅ ነበር የሚጠበቅባቸው።

ማርቆስ 13፡7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

ይህ ትንቢት ከተነገረ በኋላ ያሉት ቀጣዮቹ ሁለት ሺ ዓመታት የማያቋርጥ ጦርነት ይካሄድባቸዋል። የሰው ባህርይ ይህ ነው።

ጦርነት ጨካኝ አስተማሪ ነው፤ እኛም ከዚህ አስተማሪ እግር ስር ተቀምጠን እንዳንማር መጸለይ አለብን።

በጦርነት እልቂት ውስጥ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ተፈተው ሊለቀቁ ይችላሉ።

በ70 ዓ.ም ሮማያን ቤተመቅደሱንና ኢየሩሳሌምን በደመሰሱ ጊዜ በ5 ወራት ውስጥ ብቻ 1,100,000 አይሁዶች ተገድለዋል። ከ132 – 135 ዓ.ም ደግሞ 580,000 አይሁዶች በሮማዊው ንጉስ በሐድሪያን እጅ ተገድለዋል። ከዚያ ወዲያ አይሁዶች በሮማ ግዛት ውስጥ ተበታተኑ።

እነዚህ ጨካኝ አረማዊ መናፍስት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገቡ፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም በጨለማው ዘመን ውስጥ ካቶሊክ ያልሆኑ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ገደለች።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሰራችው ትልቅ ስሕተት ፖለቲካ ውስጥ መግባቷ ነው።

እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእኔ ጋር የማይስማሙ ሰዎችን መግደል አለብኝ ብሎ ከሚያምን ሰው በላይ ጨካኝ መሆን አይቻልም። ምሕረትን የማያውቅ ሐይማኖት ከአእምሮ በላይ በሆነ ጭካኔ የተሞላ ሐይማኖት ነው።

ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።

 

 

“ሌላ ፈረስ” ነገር ግን ሌላ ፈረሰኛ አልመጣም። ሐይማኖታዊ ሽንገላን ሲያስፋፋ የነበረው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እራሱ አሁን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆነችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራስ ለሆነው ለፖፑ ፖለቲካዊ ኃይል በመስጠት መስራት ጀመረ።

ይህ በጭካኔ የተሞላ ሐይማኖታዊ ነፍስ ግድያ ኋላ ጀርመኒ ውስጥ በተደረገው የ30 ዓመት ጦርነት ነው የተጠናቀቀው፤ ይህ ጦርነት በ1618 እና 1648 ዓ.ም መካከል በተደረገ ጊዜ ታላቅ ጥፋትንና እልቂትን አስከትሏል። ማለቂያ በሌለው ደም መፋሰስ ካቶሊኮችም ፕሮቴስታንቶችም ተማርረውበታል።

ከዚያ በኋላ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና የወንድማማች መዋደድ ሰበከ፤ ዌስሊ የጀመረው የወንጌል ስብከትም አስደናቂውን የወንጌል ስርጭት ዘመን አስጀመረ። ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር እየገነነ ሲመጣ ጨካኞቹ አረማዊ ነፍሰ ገዳይ መናፍስት ስራቸው መስራት አልቻሉም፤ ስለዚህ በቤተክርስቲያን ስም ሰዎችን መግደል ቀነሰ።

የሰይጣን ዓላማ እነዚህን ነፍሰ ገዳይ መናፍስት መልሶ ማሰማራት ነበር። ቤተክርስቲያኖች ግን ከዚያ ወዲያ በእግዚአብሔር ስም ሰዎችን መግደልን እምቢ አሉ።

ቀጥሎ ሁለት የዓለም ጦርነቶች፣ የኮርያ ጦርነት፣ የቬትናም ጦርነት፣ ሁለት የኢራቅ ጦርነቶች፣ አና የአፍጋኒስታን ጦርነት ተከትለው መጡ።

“የጦር ወሬ” የሚለው ለ45 ዓመታት የዘለቀውን ቀዝቃዛውን ጦርነት በተመለከተ ነው። አሜሪካ እና ሶቪየት ሕብረት ትንንሽ ሃገሮችን በመርዳት እርስ በራሳቸው ይዋጉ ነበር፤ እነርሱ ትንንሾቹን ሃገሮች ሲረዱ ትንንሾቹ ሃገሮች ጦርነቱን ይዋጋሉ። በዚህ ምክንያት ሁለቱ ታላላቅ ሃገራት እራሳቸው ጦር እየተማዘዙ አልተዋጉም፤ ቢዋጉ ኖሮ ኑክሊየር ቦምብ እና ሚሳኤሎቻቸውን ተጠቅመው ሁለቱም እርስ በራሳቸውን ያጠፉ ነበር።

ቀዝቃዛው ጦርነት ያን ያህል የተራዘመው በሁለት ምክንያቶች ነው፤ ለጦርነቱ የተዘጋጁ የኑክሊየር ጦር መሳሪያዎች ነበሩ፤ ስለዚህ ሁለቱ ሃገሮች ቀጥታ ቢፋጠጡ ኑክሊየር ቦምብ ተጠቅመው ሁለቱም ሊጠፉ ስለሚችሉ ጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ ከመሳተፍ ተቆጥበዋል። አሜሪካ እና ራሺያ የተዋጉት ትንንሽ ሃገሮችን በመጠቀም በተዘዋዋሪ መንገድ ነበር።

ሌላው ምክንያት ሶቪየት ሕብረት በሙስናዋ እና በኪሳራዋ ብዛት መውደቋ ነው፤ ውድድር በሌለበት ኢኮኖሚ ውስጥ ለማደግ የሚያነሳሳ ነገር ስለሌለና ገንዘባቸውን ያለ ገደብ የጦር መሳሪያ ላይ በማባከናቸው ለውድቀት ተዳርገዋል። የሲቪየት ሕብረት ውድቀት እስኪገለጥ ድረስ ረጅመ ጊዜ ፈጅቷል፤ ለዚህ ነው ቀዝቃዛው ጦርነት ለ45 ዓመታት የተንዛዛው።

ማርቆስ 13፡8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

በ1900ዎቹ በሃገሮች መካከል ትልልቅ ጦርነቶች ተደርገዋል። ምዕራባውያን ሃገሮች በቅኝ ግዛቶቻቸው አማካኝነት ዓለምን ተቆጣጥረው ነበር፤ ነገር ግን ሁለት የዓለም ጦርነቶችን በመዋጋት ራሳቸውን ካሳራ ውስጥ አስገቡ። ቅኝ ግዛቶቻቸውን አጡ፤ ከዚያም በኋላ ቅኝ ገዝተዋቸው በነበሩ ሃገሮች ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች እያንዳንዱን ሃገር ለመቆጣጠር ባደረጉት ሽኩቻ ምክንያት ድህነትና የሃብት መበላለት ስለተፈጠረ ብዙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ተደረጉ።

ከዚያም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙዎቹ አዲስ ሃገሮች ጎረቤት ሃገሮችን ወጉ።

ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 16 ታላላቅ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል።

ዩክሬይን ውስጥ በ2022 ዓ.ም የራሺያ ኃይሎች ዓለምን በታላቅ ረሃብ ለማስፈራራት ሆን ብለው የእረሻ ቦታዎችና የምግብ ማከማቻዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ዓለም አቀፍ የምግብ እጥረት ረሃብ እንዲመስልና የምግብ ቀውስ እንዲፈጠር ማድረግ ይፈልጋሉ። በዚህም መንገድ ችግርና ጫና በመፍጠር ምዕራባዊው ዓለም ከእነርሱ ጋር ድርድር እንዲያደርግ ማስገደድ ይፈልጋሉ።

የራሺያ እና የዩክሬይን ጦርነት ረሃብ፣ ጦርነት፣ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በመፍጠር የኑሮ ውድነት እየተባባሰ እንዲሄድ ያደርጋል። ስለዚህ ይህ የመጨረሻው ዘመን እየተቃረበ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው።

ሽብርና ረሃብ ወይም ታላቁ ረሃብ ተብሎ የሚታወቀው ሆሎዶሞር ከ1932 እስከ 1933 በሶቪየት ሕብረት ስር በነበረችዋ ዩክሬይን ውስጥ የተፈጠረ ሰው ሰራሽ ረሃብ ነበረ፤ ይህም በሊቀመንበር ጆሴፍ እስታሊን ትዕዛዝ የተፈጠረው ሰው ሰራሽ ረሃብ 4 ሚሊዮን ያህል ሰዎችን ፈጅቷል።

ከ1958 እስከ 1962 ድረስ ቻይና ውስጥ ኮምዩኒዝምን ለመመስረት በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ረሃብ ምክንያት 55 ሚሊዮን ቻይናውያን ሞተዋል።

ነገር ግን ከዚህም የበለጡ ትልልቅ ሃዘኖች ገና ወደ ፊት ይመጣሉ። ከዚህ በፊት ሆነው ያለፉት ታላላቅ ጥፋቶች ወደ ፊት ለሚመጣው ታለቅ ጥፋት ለታላቁ መከራ መንገድ ጠራጊዎች ናቸው።

ራሺያ በጦር ኃይሏ እና በግፈኝነቷ እንዲሁም ቻይና በንግድ ጥበቧ ለብዙ ሃገሮች አበድራ ብዙዎችን ባለ ዕዳ በማድረግ እንዲሁም ወደ ደቡባዊ የቻይና ባሕር በመስፋፋት አጀንዳቸውን ለማራመድ ሰው ሰራሽ ረሃብን ተጠቅመውበታል። እነዚህ ሁለት ሃገሮች በዓለም ወቅታዊ ጉዳዮች ሁሉ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ያደርጋሉ።

በዓለም ገበያ ላይ ከሚሸጠው የሱፍ ዘይት እና ስንዴ አብዛኛውን የምታቀርበው ዩክሬይን ናት።

በዓለም ገበያ ላይ ይቀርቡ የነበሩ እነዚህ ሁለት ምርቶች ራሺያ በ2022 ዓ.ም ዩክሬይንን ከወረረች ወዲህ ተቋርጠዋል።

ይህ የዘመኑ ምልክት ነው።

ሶስተኛው ማሕተም ሲፈታ ምግብ በአንድ ዲናር ሲሸጥ ይታያል፤ ይህም አንድ ዲናር በአስራ አንደኛው ሰዓት ስለተጠሩት ሰራተኞች በተነገረው ምሳሌ ውስጥ የአንድ ቀን የሰራተኛ ክፍያ ነው።

ማቴዎስ 20፡2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።

ይህ ሰዎች ምግብ ለመግዛት ምን ያህል ትግል እንደሚሆንባቸው የሚያሳይ አስፈሪ ትንቢት ነው።

ጌታ ባስተማረን ጸለት ውስጥ “የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ” የሚለው ጸሎት እጅግ ወሳኝ ጸሎት ነው።

ቤተክርስቲያኖች በጥቁሩ ፈረስ የተመሰለው ከትልልቅ ንግዶች ጋር የተያያዘው አጋንንታዊ አሰራር ውስጥ ገብተውበታል። ቫቲካን በምድር ላይ ከሚገኙ ድርጅቶች ሁሉ በሃብት አንደኛ ናት፤ ያላት ገንበዝ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያህል ይሆናል፤ ደግሞ ግብር አትከፍልም።

ታላላቅ ቤተክርስቲያኖች በሃብት ያደጉት የገበያ ቦታ የሽያጭ ቴክኒኮችን ተጠቅመው ነው።

ትልልቅ ቤተክርስቲያኖች ከሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የተሳሳተ የአመራር ስልት የሚከተሉ ፓስተሮች ስልጣናቸውን አላግባብ ሊጠቀሙ መቻላቸው ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ራስ ወዳዶች፣ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጽሙና ሰዎችን የሚያስፈራሩ መሆናቸው የታወቀባቸው የትልልቅ ቤተክርስቲያኖች ፓስተሮች ብዛት ብዙ ክርስቲያኖችንና ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችንም አስደንግጧል። የቤተክርስቲያን መሪዎች ገንዘባችሁን ለመንጠቅ ኃይል ካላቸው ጥሩ ሰዎች አይደሉም ማለት ነው።

በሶስተኛው ማሕተም ውስጥ ከተጠቀሱት አራት ነገሮች መካከል ሁለቱ ስንዴ እና የምግብ ዘይት ናቸው።

ዘይት የሚለው የዘመናችንን ነዳጅም ይጨምራል ምክንያቱም ነዳጅ የሚገኘው ከዘይት ነው።

ይህ ትንቢት ምግብ እና ነዳጅ ዋጋቸው እያሻቀበ እንደሚሄድ ይናገራል። ስለዚህ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ አሁን የምንገኝበት ቦታ ይህ ነው። ረሃብ በምድር ላይ እውነተኛ ስጋት እየሆነ መጥቷል። የነዳጅ ዋጋ እጅግ እያሻቀበ መጥቷል፤ ይህም የሁሉንም ነገር ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል ምክንያቱም እቃዎች ከቦታ ቦታ መጓጓዝ አለባቸው።

በ2022 ዓ.ም ገንዘብ ለሰዎች በጣም አስጨናቂ ነገር ሆነ። የራሺያ እና የዩክሬይን ጦርነት በዓለም ላይ የኢኮኖሚ ውድቀትና የዋጋ ንረትን እያመጣ ነው፤ በብዙ ሃገሮች የብድር ወለድ እየጨመረ ነው። ታላላቅ የዓለም ገበያዎች እየተንገዳገዱና የኑሮ ውድነትም እየጨመረ ነው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አሜሪካ 5 ትሪሊዮን ዶላር ተበድራ ለብዙ ቤተሰዎች አከፋፈለች፤ ይህን ያደረገችው ወረርሽኙ ሕዝቡ ላይ ያመጣባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጫና መቋቋም እንዲችሉ ለማገዝ ነው። ይህ ወቅት በወረርሽኙ ምክንያት በተፈጠረው የተለያዩ ቁሳቁሶች ፍላጎት የተነሳ የአቅርቦት ሥርዓቱ ላይ ትልቅ ጫና ፈጠረ። ኢንዱስትሪውም ለመጣው ብዙ የሸቀጥ ፍላጎት በቂ ምላሽ መስጠት አልቻለም። ገበያዎች የሸቀጥ ፍላጎት ሲጨምርና የሸቀጥ እጥረት ሲፈጠር ምላሽ የሚሰጡት የሸቀጥ ዋጋ ከፍ በማድረግ ነው። ማርች 2022 ዓ.ም የአሜሪካ የዋጋ ንረት በ8.6% ጨመረ። ይህም የንግድ እንቅስቃሴ ሕግ ነው እንጂ ታስቦበት የተደረገ አይደለም።

 

 

ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።

“ረሃብና መከራዎች”። በ2019 ዓ.ም የጀመረው የኮቪድ-19 ብዙ ድርጅቶች ተዘግተው ሥራ እንዲያቆሙ ስላደረገ ታላቅ ኢኮኖሚያዊ መከራ አስከትሏል፤ ከባድ የጤና ችግሮችንም አስከትሏል። የአሜሪካ ዕዳ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

ከዚህ በኋላ የዓለምን ኢኮኖሚ ሊያናጉ የሚችሉ የምድር መንቀጥቀጦች ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

ሳይንቲስቶች ለረጅም ዘመን ሲተነብዩ የቆዩት አንድ ከባድ የምድር መንቀጥቀጥ በተከሰተ ጊዜ የሎሳንጀለስ ከተማ በሙሉ ወደ ባሕር ውስጥ ይሰጥማል። ሎሳንጀል በሳን አንድሪያ የምድር መንቀጥቀጥ ክልል ውስጥ ነው የሚገኘው። ይህም የምድር መንቀጥቀጥ በአሜሪካ አንደኛ ሃብታም የሆነችዋን ካሊፎርኒያ ድምጥማጧን ያጠፋዋል። ይህም ጥፋት በዕዳ የተጨናነቀችዋን አሜሪካ ሽባ ያደርጋታል።

ይህም የኢኮኖሚ ውድቀት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አሜሪካን እንድትቆጣጠር በር ሊከፍት ይችላል። ከዚያም ሮም አሜሪካን ወደ ጥፋት ይዛት ትሄዳለች። ይህ ትንቢት በዘመን መጨረሻ በተነሳው ነብይ ዊልያም ብራንሐም በ1933 ዓ.ም ተነግሮ ነበር።

 

 

ቀጣዩ አስፈሪ ነገር የአራተኛው ማሕተም መፈታት ነው፤ ይህ ማሕተም ሲፈታ ሞት ለመጨረሻ ጊዜ ይመጣል።

ሞት መግባት የሚችለው ሕይወት ለቆ በሄደበት ቦታ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛዋን ሙሽራ ከምድር ነጥቆ ከጌታ ጋር በአየር ላይ እንድትገናኝ እና በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ እራግ ግብዣ ይወስዳታል።

ሞት የሚሰለጥነው ሕይወት በሌለበት ቦታ ነው። ከዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛው ማለትም 2 ቢሊዮን ያህል ሰዎች ይገደላሉ።

በዚህ ግድያ ውስጥ ዋነኛዋ ኢላማ የምትሆነው ቤተክርስቲያን ናት ምክንያቱም 2 ቢሊዮን ማለት የክርስቲያኖች ቁጥር ነው። እነዚህ ሰዎች ከንጥቀት በኋላ ምድር ላይ የቀሩ ክርስቲያኖች ናቸው። እነርሱም ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ያመኑ ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ሰነፎቹ ቆነጃጅት ናቸው። በጉ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ተነስቶ ሙሽራይቱን ለመቀበል ከመምጣቱ በፊት ማለትም ከታላቁ መከራ በፊት ድነው ነበር። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ በቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ምክንያት ተታልለዋል። ወደ ታላቁ መከራ እንዲገቡ የተደረጉት በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ላይ የነበራቸውን እምነት እንዲጥሉ ነው። ላልዳኑ አሕዛብ ግን በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ምንም ምሕረት ወይም መዳን የለም።

ዘመኑ ሲደርስ ታላቁ መከራ ይጀመራል። ታላቁ መከራ የዳኑ የቤተክርስቲያን አባላት መታለላቸውን የሚያውቁበት የታላቅ ፍርሃት እና የድንጋጤ ዘመን ነው።

ራዕይ 7፡9 ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤

ራዕይ 7፡13 ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ፦ እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ።

14 እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።

ታላቁ መከራ ከመድረሱ በፊት፣ በጉ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ሳይነሳ በፊት በበጉ ደም መታጠብ ነበረባቸው። በጉ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ተነስቶ በዳግም ምጻቱ ሙሽራይቱን ለመቀበል ወደ ምድር ወረደ። ስለዚህ ሰነፎቹ ቆነጃጅት በየቤተክርስቲያኖቻቸው ሳሉ ከሲኦል ድነዋል፤ ነገር ግን ከቤተክርስቲያን የተቀበሉዋቸውን የተሳሳቱ ትምሕርቶች ከእነርሱ ውስጥ አውጥቶ ለማራገፍ በታላቁ መከራ ውስጥ የግድ ያልፋሉ። ፓስተራቸው ሳይሆን ኢየሱስ (ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው) የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑን መማር አለባቸው።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ማሕተሞቹ ያሉባቸውን … መጻሕፍት ወስዶ ይፈታቸውና ሰባተኛውን መልአክ ያሳያል፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሚስጥራት የሰባተኛው መልአክ ሚስጥራት ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራትና ምሳሌዎች መረዳት እንድችል ዘንድ የንስር ዓይን እይታና መገለጥ ያስፈልገናል።

ከታላቁ መከራ ልናመልጥ የምንችለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆንና ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት በመመለስ ብቻ ነው።

 

 

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

ኢየሱስ ስለ ቤተክርስቲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከተናገረ በኋላ ሐዋርያት የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ሲመሰርቱ ስለሚገጥሟቸው ችግሮችና ፈተናዎች ይነግራቸዋል።

ማርቆስ 13፡9 እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።

ደቀመዛሙርት ከአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች እና ከሮማ መንግስት መሪዎች ዘንድ የማያቋርጥ መከራ ይደርስባቸዋል።

ሐዋርያትን መክሰስና ማሳደድ እጅግ በጣም ከባድ ሐጥያት ነበር። ሐዋርያት የቤተክርስቲያንን መሰረት መሰረቱ፤ ቤተክርስቲያንም እስከ ሰባተኛው ማለትም እስከ መጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰባተኛው ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እስኪመለስ ድረስ ለ2,000 ዓመታት በምድር ላይ ትዘልቃለች። ስለዚህ ለደቀመዛሙርቱ እጅግ ታላቅ ኃላፊነት ነበር የተሰጣቸው። ከተሰጣቸው ኃላፊነት መካከል የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትነ መጻፍ እና የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን መመስረት ይገኙበታል።

ቤተክርስቲያን በብዙ መከራ እና ስደት ውስጥ ነው የተመሰረተችው። በ64 ዓ.ም የሮማ ንጉስ ኔሮ በሮም ከተማ ላይ እራሱ ባስነሳው የእሳት ቃጠሎ ክርስቲያኖችን ተጠያቂ በማድረግ ክርስቲያኖችን በይፋ ማሳደድ ጀመረ። ሐዋርያው ዮሐንስን ፍጥሞ በተባለች ደሴት ላይ በግዞት ወስዶ ጣለው፤ በዚያም ዮሐንስ የራዕይ መጽሐፍን ጻፈ። ዮሐንስ በ68 ዓ.ም ኔሮ ሲሞት ከእስር ተፈታ።

በ81 ዓ.ም ዶሚሺያን የሮማ ንጉስ ሆነ። እርሱም ክርስቲያኖችን እንደ ገና ማሳደድ በመጀመር ዮሐንስን በዘይት ቀቅሎ ለመግደል ሙከራ ካደረገ በኋላ በፍጥሞ ደሴት ላይ እንደገና አሰረው። ዮሐንስም የራዕይ መጽሐፍን ጽፎ ጨረሰና ዶሚሺያን በ96 ዓ.ም ሲሞት ከእስር ተፈታ።

ደቀመዛሙርት የነበሩት ሐዋርያት እየሞቱ በብዛት በሰማእትነት እየተገደሉ ከምድር ሲለዩ የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ የስልጣን ጥማት የነበራቸው ሰዎች ቤተክርስያንን በመቆጣጠራቸው እውነት እየጠፋች ሄደች። ከዚያም ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ ካለፈች በኋላ እውነት ቀስ በቀስ ወደ ቤተክርስቲያን ተመለሰች። ይህ የእውነት መመለስ ሂደት የጀመረው በጀግናው ጀርመናዊ መነኩሴ በማርቲን ሉተር ነው። እርሱም የምንድነው በእምነት እንጂ በሥራ አይደለም የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ።

በ1604 ዓ.ም 47 ምሑራን ተሰብስበው ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ተረጎሙ። ይህም ትርጉም ብዙ ጊዜ ተመርምሮ በስተመጨረሻ በ1769 ሲታተም የታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት የጀርባ አጥንት ሊሆን ችሏል።

 

የዘመን መጨረሻ ሁኔታዎች ከባድ ናቸው

 

ማርቆስ 13፡10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።

ወንጌሉ ከሐዋርያው ጳውሎስ ጉዞዎች ጀምሮ ሲሰራጭ ኖሯል።

ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን የተጀመረው ዊልያም ኬሪ በ1793 ወደ ሕንድ ከሄደ በኋላ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወንጌል ሰባኪዎች ከእንግሊዝ ተነስተው ወደ ዓለም ዙርያ ሁሉ ሄደዋል። የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በዓለም ሁሉ ተሰራጨ።

ዛሬ ዕድሜ ለኢንተርኔት ይሁንና እውነት በኮምፒዩተሮችና እን በሞባይል ስልኮች አማካኝነት በዓለም ሁሉ ትሰራጫለች።

ማርቆስ 13፡11 ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።

ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ጀምሮ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እውነት በዓለም ዙርያ የሚያሰራጩ ሰዎችን ሁሉ ሰይጣን ሲቃወማቸውና ሲያሳድዳቸው ኖሯል።

ዛሬ ሰይጣን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እንዲቃወሙ እያደረገ ነው። ከዚያም ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን የገለጠውን የዊልያም ብራንሐም አገልግሎት ይቃወማሉ። ዛሬም ወንድም ብራንሐም ያስተማራቸውን ትምሕርቶች አጣምመው በመተርጎም አገልግሎቱን ያሰናክላሉ። እርሱ የተናገራቸውን ቃላት ወስደው ሲተረጉሙም አስተምሕሮዋቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ በማይችሉበት መንገድ ነው የሚተረጉሙት።

ማርቆስ 13፡12 ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መጥላት በጣም የተቀራረቡ የቤተሰብ አባላትን እንኳ ሳይቀር ይለያያል። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ከእነርሱ ጋር የማይስማሙ ሰዎችን ይጠላሉ፤ ስማቸውንም ያጠፋሉ።

በ325 ዓ.ም የስላሴ ትምሕርት በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ተፈጠረ፤ ከዚያ ወዲህ በዚህ ትምሕርት የተነሳ ብዙ እልቂትና ደም መፋሰስ ሆኗል። በጨለማው ዘመን ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮዋቸው ልዩነት የተነሳ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። ጥላቻ እና ግፍ በቤተክርስቲያን ውስጥ እየበዛ ሄደ።

 

ሰዎች በውሃ ጥምቀት ውስጥ የኢየሱስን ስም መጠቀም ይጠላሉ

 

ማርቆስ 13፡13 በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

በዘመን መጨረሻ ትልቁ ጉዳይ የሚሆነው የኢየሱስ ስም ነው። የስላሴ እምነት ሰነፎቹን ቆነጃጅት (የተሳሳቱ ትምሕርቶችን የተከተሉ ነገር ግን የዳኑ ክርስቲያኖችን) እጅግ በጣም ከማሞኘቱ የተነሳ “በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ሲሉ የእግዚአብሔርን ስም የጠሩ ይመስላቸዋል። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም የእግዚአብሔር ስም መሆኑን ይክዳሉ፤ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎችንም ያወግዛሉ። ከዚህም የተነሳ በሐዋርያት ሥራ 2፡38 በተጻፈው መሰረት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመጠመቅ ፈቃደኛ አይደሉም። ስለዚህ የዛሬ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች በመጀመሪያው ዘመን ወደነበሩ ሐዋርያት እምነት ሊመለሱ አይችሉም።

የዘመናችን ቤተክርስቲያኖችና የቤተክርስቲያን ሕብረቶች የሚፈቅዷቸው ብዙ ዓይነት የጥምቀት ሥርዓቶች አሉ። ነገር ግን ትልልቅ ሰዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቅን አይፈቅዱም። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚያጠምቁ ሰዎችን ሁሉ ይነቅፏቸዋል፤ ስማቸውንም ያጠፋሉ።

እስከ መጨረሻው በመጽናት ከሲኦል ልትድኑ አትችሉም።

እስከ መጨረሻው በመጽናት ከሲኦል ከዳናችሁ ይህ በሥራ መዳን ይሆናል፤ በሥራ መዳን ደግሞ አይቻልም።

ከሲኦል የዳናችሁት በክርስትና ሕይወታችሁ መጀመሪያ ላይ ንሰሃ ገብታችሁ ኢየሱስን የግል አዳኛችሁ አድርጋችሁ በተቀበላችሁት ጊዜ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ነው ብሎ መቀበልና መጽሐፍ ቅዱስን ማመን በስላሴ አማኞች ዘንድ የተጠላችሁ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል። የስላሴ አማኞች ለስላሴያዊ አምላካቸው አንድ ስም የላቸውም፤ ስለዚህ ኢየሱስ “እግዚአብሔር ወልድ” ነው ብለው ያምናሉ (እግዚአብሔር ወልድ የሚል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም)። ስለዚህ ኢየሱስ ስም ከሌለው ከሁሉን ቻዩ ከእግዚአብሔር አብ ያንሳል ብለው ያስባሉ። እግዚአብሔር አብ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይጠራባቸው ከነበሩ ስሞች መካከል አንዱ እንኳ አዲስ ኪዳን ውስጥ አልተጠቀሰም። ለስላሴ አማኞች ከባድ ችግር የሚፈጥረው ሌላው እውነታ ደግሞ “እግዚአብሔር አብ” የሚል አጠራር ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አለመገኘቱ ነው።

“እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” የሚል ደግሞ ብሉይ ኪዳንም ይሁን አዲስ ኪዳን ውስጥ የለም።

መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም አልተሰጠውም።

ስላሴ ነው ብለው ለሚያምኑት አምላክ ስም ማግኘት ቢያቅታቸውም እንኳ በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሔር ስም ኢየሱስ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ይተቻሉ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ስም ኢየሱስ ነው ምክንያቱም የመለኮት ሙላት ሁሉ በኢየሱስ ውስጥ በአካል ተገልጦ ነው የሚኖረው (ቆላስይስ 2፡9)።

የስላሴ አስተምሕሮ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ስም እንዲጠፋባት አድርጓል።

ኢሳይያስ 26፡13 አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ ከአንተ በቀር ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን በአንተ ብቻ ስምህን እናስባለን።

“ሌሎች ጌቶች”። እነዚህ በስላሴያዊው አምላክ ውስጥ የሚገኙ ሶስቱ ሰዎች ናቸው።

አዲስ ኪዳን ውስጥ ግን ስም ያለው አንድ አካል ብቻ ነው። እርሱም ኢየሱስ ነው።

“እግዚአብሔር አብ” አዲስ ኪዳን ውስጥ ስም የለውም። “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” ስም የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” ብሎ አያውቅም።

ኤርምያስ 23፡26 ትንቢትን በሐሰት በሚናገሩ፥ የልባቸውንም ሽንገላ በሚናገሩ በነቢያት ልብ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?

27 አባቶቻቸው ስለ በኣል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤ ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ

 

የስላሴ አስተምሕሮ የተመሰረተው በብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ውሸቶች ላይ ሲሆን መጨረሻውም ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም እንዳያውቁ ማድረግ ነው። ሶስት ሰዎች በአንድ ስም ሊጠሩ አይችሉም።

አሞጽ 6፡11 እነሆም፥ እግዚአብሔር ያዝዛል፤ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።

ዛሬም ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ለስላሴያዊ አምላካቸው መጠሪያ የሚሆን አንድ ስም መጥቀስ አይችሉም። ደግሞም “ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” መጠሪያ የሚሆን ስም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት አይችሉም።

እንዲሁም “ለእግዚአብሔር አብ” አዲስ ኪዳን ውስጥ ስም ማግኘት አይችሉም።

“በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ማለት ስም አይደለም።

ስለዚህ በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዳይባረሩ ከፈለጉ ያላቸው አማራጭ የስላሴያዊው አምላክ ስም ማነው ብለው ጥያቄ አለማንሳት ነው።

ቤተክርስቲያን ውስጥ የገቡ የአሕዛብ እርኩሰቶች የእግዚአብሔርን ስም አጥፍተውታል። ስላሴ የሚለውን ሃሳብ መጀመሪያ ያመነጩት አህዛብ ናቸው።

ይህን የአሕዛብ ሃሳብ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቀብላ አንድ አምላክ የሆኑ ሶስት አካላት ብላ ለራሷ እንዲመቻት አድርጋ ቀየረችው።

ይህን ማንም ሊያብራራ አይችልም።

ከዚያም ይህንን አንድ አምላክ በሶስት አካላት የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርት ፕሮቴስታንቶች ከካቶሊክ ኮረጁ።

 

ፖፑ ፑርጋቶሪ ውስጥ ላሉ አጋንንት ንጉስ ሆነ

 

ማርቆስ 13፡14 ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥

ይህ ለመረዳት ከባድ የሆነ ጥቅስ ነው።

በ70 ዓ.ም የአይሁድ ቤተመቅደስ ውስጥ የቆሙት ሮማውያን ናቸው፤ ሮማውያን ቤተመቅደስ ውስጥ የመግባት መብት የላቸውም።

ከዚያም ቤተመቅደሱንና ኢየሩሳሌምን ደመሰሱና ስፍራውን ባድማ አደረጉት።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በባርቤሪያውያን እጅ ጠፍቶ የነበረው የአረማዊው የሮማ መንግስት መንፈስ ትንሳኤ ናት። የአረማዊቷ የሮማ መንግስት መንፈስ በፈራረሰው የሮማ መንግስት ፍርስራሽ ላይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሆኖ መልኩን ቀይሮ ተነሳ።

እንደ ስላሴ የመሳሰሉ ብልጥ የአሕዛብ ፍልስፍናዎችን እና ከመጽሐፍ ቅዱስን የተወሰዱ ቃላትን መቀላቀል እርኩሰት ነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስም እንዲጠፋ አድርጓል። በስላሴ አምላክ ውስጥ ያሉ ሶስት አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ (ስላሴ የሚባል) ቃል መጠቀም ቤተክርስቲያን በውስጧ እውነት የሌላት ኦና ባዶ ቤት ሆና እንድትቀር አድርጓታል።

ዛሬ “ስላሴ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይኖርም እንኳ ክርስቲያኖች የስላሴ ትምሕርት እውነት መሆኑን ማመን እንችላለን ይላሉ። ከዚህም የተነሳ ሌሎችንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያሆኑ ትምሕርቶችና ልማዶች ለምሳሌ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የስቅለት አርብ፣ ኩዳዴ፣ አርብ ዕለት ዓሳ መብላት፣ ማርያምን ማምለክ፣ እና ወንድም ዊልያም ብራንሐም የማይሳሳተው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው የመሳሰሉትን ሁሉ ማመን ይችላሉ። አዲስ ኪዳን ውስጥ ግን የእግዚአብሔርን ድምጽ የመስማት ተስፋ አልተሰጠንም።

ዳንኤል 12፡11 የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

ሮማውያን የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን ሰቀሉት።

ይህም የአረማዊቷ የሮማ መንግስት መንፈስ ለእግዚአብሔር ቃል ያለውን ጥላቻ ይገልጻል።

በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ አረማዊው የሮማ መንፈስ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የእግዚአብሔርን ቃል እንድትለውጥ በማድረግ በክሏታል፤ የእግዚአብሔረን ቃል መለወጥ ክርስቶስን እንደገና መስቀል ነው።

1,290 ቀናት።

ኢየሱስ በቀራንዮ ሲሞት ዕለታዊው መስዋእት ተቋረጠ። ዋጋና ተቀባይነት ያለው መስዋእት የኢየሱስ ሞት ብቻ ነው። ሌሎቹ መስዋእቶች በሙሉ ዋጋቸውን አጥተዋል።

ትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ሊወክል ይችላል።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

የመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓመት 360 ቀናት ነው።

ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።

42 ወራት 1,260 ቀናት ነው። ስለዚህ 1,260/42 = 30 ቀናት ወይም 1 ወር።

የመጽሐፍቀ ቅዱስ አንድ ዓመት እያንዳንዳቸው 30 ቀናት ያሏቸው 12 ወራት ናቸው።

አሁን የምንጠቀምበት (በሮማዊው ዩልየስ ቄሳር ተጀምሮ በሮማ ካቶሊክ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው የተስተካከለው) የሮማውያን አቆጣጠር አንድ ዓመት 365.24 ቀናት ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ 70 ዓመት በሮማውያን አቆጣጠር 69 ዓመት ነው።

1,290 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት = 1,290/70 በእኛ አቆጣጠር የዓመታቱ ብዛት በ18 ይቀንሳል።

በእኛ ካላንደር መሰረት 18 ዓመታት ቀንሰን ነው የምንቆጥረው።

1,290 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት = 1,290 – 18 = 1,272 ዓመታት በእኛ አቆጣጠር።

ኢየሱስ የተሰቀለው በ33 ዓ.ም ነው።

33 + 1,272 = 1,305

በ1305 ዓ.ም ክሌመንት 5ኛው የተባለ አዲስ ፖፕ ተመረጠ። ይህም ፖፕ በ1314 ዓ.ም ሞተ፤ ነገር ግን ለሁለት ዓመታት ሌላ ፖፕ አልተመረጠም ነበር፤ ከዚያ በ1316 ዓ.ም ጆን 22ኛው ተመረጠ።

በ1315 ምንም ፖፕ በስልጣን ላይ ባልነበረ ሰዓት የፖፑ ንብረቶች ዝርዝር ተዘጋጅቶ ነበር፤ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ፖፑ በራሱ ላይ የሚጭነው ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ይገኝበታል።

ስለዚህ ክሌመንት 5ኛው ባለ ሶስት ድርቡን ዘውድ ለመጫን የመጀመሪያው ፖፕ ነበር። ይህም ክሌመንትን የሰማይ፣ የምድር፣ እና የፑርጋቶሪ ገዥ አደረገው።

የባቢሎን አጋንንታዊ ሥርዓትና የሮማ መንግስት አጋንንታዊ ሥርዓት በአጋንንታዊ አሰራር የሚመራ ንጉስ አገኙ፤ እርሱም ፖፑ ነው።

ክርስትናን እና የአሕዛብ እርኩሰትን በመደባለቅ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በውስጧ እውነት የሌላት ምድረበዳ ሆነች። ከዚያም ሐሰተኛ ትምሕርቶቿን ለፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች አስተላለፈች።

ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥

አረማውያኑ ሮማውያን በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሱ ውስጥ ገቡ፤ ከዚያ በኋላ በእሳት አቃጥለውት አፈራረሱት።

በ135 ዓ.ም ከቤተመቅደሱ ፍርስራሽ ቀርቶ የነበረ ድንጋይን ሁሉ ንደው ቦታው ላይ ቤተመቅደሱ እንደነበረ እስከማይታወቅ ድረስ ሥፍራውን በአፈር ሸፈኑት። አረማዊው የሮማ ገዥ ሐድሪያን ይህን ያህል ነበር አይሁዶችን የጠላቸው።

ክፉ እና ጨካኝ የሆነው የሮማ መንፈስ ግዛቱን በ476 ዓ.ም በተቆጣጠሩ በባርቤሪያውያን ተሸንፎ ነበር። ይህ ጨካኝ አረመኔ የሮማ መንፈስ በፈራረሰው የሮማ መንግስት ፍርስራሽ ላይ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መልክ ተመልሶ ተነሳ። ከዚያ በኋላ የሮማ ቤተክርስቲያን ከእርሷ በፊት የሮማ መንግስት ይገዛበት የነበረውን አጋንንታዊ አሰራር በሙሉ የራሷ አድርጋ ነገሰች።

እነዚህ የአሕዛብ እርኩሰቶች ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው የእግዚአብሔርን የማዳን ዕቅድ ከንቱ አደረጉ።

 

የመጨረሻው የአመጽ ሰው ሥራ ያሉት ሕዝቦች ሮማውያን ናቸው

 

ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።

 

ሮማውያን ቤተመቅደሱንና ከተማይቱን ደመሰሱ። ጀነራል ታይተስ እራሱ አለቃ ሊባል ይችላል ምክንያቱም አባቱ ቬስፓሲያን የዛኑ ሰሞን በጦር ሰራዊቱ አማካኝነት ንጉስ ሆኖ ተሹሞ ነበር። ስለዚህ ታይተስ ወደ ፊት የአመጽ ሰው እና የጥፋት ልጅ ሆኖ ለሚመጣው የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ጥላ ነው። ይህም ከሲኦል የሚመጣው የጥፋት ልጅ ነው።

አረማዊቷ ሮም ትንሽዋን እስራኤል ለማንበርከክ 80 ሺ ወታደሮችን ላከች። ሰዎች በዚህ ሳቁ። ታላቁ አሊግዛንደር የመጀመሪያዋን ዓለም አቀፋዊት መንግስት ፋርስን ለማንበርከክ 50,000 ወታደሮች ብቻ ነበር የላከው።

አረማዊቷ ሮም ተለውጣ በጣም ክፉ የሮማ ካቶሊክ ቫይረስ ሆነች።

ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።

ኢየሱስ አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ ለአይሁዳውያን የ7 ዓመታት ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበረ። በነዚህ ዓመታት አጋማሽ ማለትም 3.5 ዓመታት ካለፉ በኋላ ኢየሱስ ተገደለ፤ ይህም የቤተመቅደሱ መስዋእቶች ሁሉ እንዲያቆሙ ምክንያት ሆነ። ከዚያ በኋላ በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሱ በመፍረሱ ምክንያት ምንም ዓይነት መስዋእት ማቅረብ አልተቻለም።

ከዚያ በኋላ በ382 ዓ.ም ፖፕ ዳማሰስ ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ ተቀብሎ የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀ ካሕን በሆነ ጊዜ የአረማዊ ሮማውያን እርኩሰት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገባ። እርሱም በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ታላላቅ የስልጣን ቦታዎችን ለባቢሎን ካሕናት ሰጠ።

ከአረማዊያን ጋር የመጣው አለማመን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከቤተክርስቲያን እንዲጠፋ አደረገ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ ቤተክርስቲያን ዘመናት ፍጻሜ ድረስ ስሕተቶቿን እንደ ያዘች ቀጥላለች።

በሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ሳትጠፋ የዘለቀችዋ ብቸኛ ድርጅት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። በእያንዳንዱ ዘመናት የነበሩ እምነቶች ሁሉ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዘንድ ተግዳሮት ገጥሟቸው በሮማ ካቲሊክ የተሳሳቱ ትምሕርቶች አማካኝነት ጠፍተዋል።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ ያልሁኑትን ሁሉ እየሸነገለች ወደ ጉያዋ አስገብታቸዋለች። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቅ ምክንያት የተፈጠረው ጥፋት በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውስጥ ተሰራጭቶ የዳኑትን ሰነፍ ቆነጃጅትም ሁሉ እየሸነገላቸው ነው።

ለ3.5 ዓመታት የሚቆየው ታላቁ መከራ ሲጀምር ግን እግዚአብሔር በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑትን የቤተክርስቲያንን የተሳሳቱ ትምሕርቶች በተከተሉ ግን በዳኑ ሰነፍ ቆነጃጅት ላይ የሚያፈስሰው ቁጣ ምን ያህል እንደሚሆን አስቀድሞ ወስኗል።

 

ሮም ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ስትሰነዝር በፍጥነት ውጡ አለ ኢየሱስ

 

ስለ ቤተመቅደሱ መፍረስ የተጠየቀውን ጥያቄ ለመመለስ ኢየሱስ በ70 ዓ.ም ስለሚፈጸሙ ነገሮች ይናገራል።

ሁለት አሳዛኝ ክስተቶች ይከሰታሉ። አይዳዊ ወንበዴዎች፣ ሌቦች፣ እና ቀናተኞች ቤተመቅደሱን ይቆጣጠሩና ሊቀ ካሕናቱን ይገድላሉ። ከቤተመቅደሱም ወጥተው የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ለመግደልና ለመዝረፍ ይዘምታሉ።

የአዲሱ የሮም ንጉስ የቬስፓሲያን ልጅ ጀነራል ታይተስ ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ሰነዘረና በጥቂት ቀናት ውስጥ በዙርያዋ የጭቃ አጥር ሰራ። በጭቃ የተሰራው አጥር ሲጠናቀቅ አንድም አይሁዳዊ ከኢየሩሳሌም ማምለጥ አይችልም።

የአረማዊቷ ሮም መንፈስ ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለመግባት እየተዘጋጀ ነበር። አረማዊ ሐይማኖቶች በስላሴዎች ያምናሉ፤ እንዲሁም የእያንዳንዱ አረማዊ ቤተመቅደስ ራስ አንድ ግለሰብ እንደሆነ ያምናሉ። ሮማዊው አምባገነን መሪ ዩለየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ ነው ፖንቲፍ ወይም የባቢሎን ሚስጥራት ሊቀካሕን ሆኖ የተመረጠው። እስከ 382 ዓ.ም ድረስ እያንዳንዱ የሮማ ንጉስ ፖንቲፍ ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ከዚያ ወዲያ ግን የሮማ ንጉስ ቴዎዶሲየስ ይህንን ማዕረግ ዳማሰስ ለተባለው ለሮማ ጳጳስ አስተላለፈው። በ400 ዓ.ም የሮማ ጳጳስ መጠሪያው ፖፕ እና ፖንቲፍ ሆነ። ስለዚህ የባቢሎን ሐይማኖታዊ ሚስጥራት የጥንቷን ቤተክርስቲያን የመሰረቱትን የሐዋርያትን ተጽእኖ ለማጥፋት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገቡ።

የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ለማስተማሪያነት በመጠቀም ፈንታ ቤተክርስቲያን ከ606 ዓ.ም ጀምሮ ፖፑን ዓለም አቀፋዊ ጳጳስ አድርጋ ተቀበለች። ከዚያ ወዲያ ሁሉም ለፖፑ ይገዛ ተባለ።

ማርቆስ 13፡15 በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

አይሁዳዊ ወንበዴዎች በዝርፊያና በነፍስ ግድያ ተሰማርተው ከቁጥጥር ውጭ ነበሩ። ሕዝቡ ከኢየሩሳሌም በፍጥነት መውጣት ነበረባቸው። በጀነራል ታይተስ እየተመራ የመጣው የሮም ሰራዊት ከተማይቱን ከበበ። ሰዎች ከከተማይቱ በፍጥነት ካልወጡ በጥቂት ቀናት ውስጥ እዚያው ተጠምደው ይቀራሉ።

ሰዎች ከኢየሩሳሌም በወጡ ጊዜ ወንበዴዎች ተከትለዋቸው እየገደሉዋቸው ይዘርፏቸዋል። ስለዚህ ሰዎች በፍጥነት ወጥተው ማምለጥ አለባቸው። የቤት ዕቃ ይዙ ለመሄድ መሞከር ከንቱ ነው፤ ምክንያቱም አንደኛ ሸክሙ ፍጥነተን ይቀንሳል፤ ሁለተኛ ደግሞ ወንበዴዎች ሰዎች የተሸከሙትን ዕቃ ፍለጋ ተከትለው ይመጣሉ። በየመንገዱ ዳር እሬሳዎች ተዘርረው ነበር።

ማርቆስ 13፡16 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

አይሁዶች ወይም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ሮማውያን ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ያዩ ጊዜ ወዲያው ከኢየሩሳሌም እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። ምንም ነገር መሸከም የለባቸውም ምክንያቱም ሸክም ፈጥነው መውጣት እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል። ካልፈጠኑ ደግሞ መቅደሱ ውስጥ ገብተው የነበሩ ዘራፊዎች ተከትለዋቸው በመንገድ ላይ ይገድሏቸዋል። ቶሎ መውጣታቸውና አገር አቋራጭ መንገዶችን ትተው በተራሮች ላይ መሸሻቸው አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በተራሮች ላይ ሲሄዱ ከኋላ እየተከተሉ ከሚያሳድዷቸው ጠላቶች መደበቅ ይችላሉ።

ማርቆስ 13፡17 በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።

ነፍሰጡር ሴቶችና ሕጻናትን አዝለው የሚሄዱ እናቶች በተራሮች ላይ ለመሸሽ በጣም ይቸገራሉ።

ማርቆስ 13፡18 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤

በክረምት ወቅት እስራኤል በጣም ትቀዘቅዛለች፤ ደግሞም ከባድ ዝናብ ይዘንብባታል። በክረምት ብርድ እየተንቀጠቀጡና በዝናብ እየበሰበሱ በተራሮች ላይ አቋርጠው ወደ አስሩ ከተማ መድረስ በጣም አስቸጋሪ ነው።

 

 

ይህ ቃል ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው በ70 ዓ.ም በአይሁዶች ላይ ስለሚመጣው መከራ እየተናገረ መሆኑን ያረጋግጣል። አይሁዶችን ይጠሉ የነበሩ ሮማውያን በዚያ ጊዜ የኢየሩሳሌምን ከተማ በተለይም ቤተመቅደሱን ደመሰሱ።

 

አይሁዳውያን ወጡና በከባድ ስደት ተመለሱ

 

የኢየሩሳሌም መፍረስ ከሮማ መንግስት የጭካኔ ድርጊቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው። ይህ ድርጊት ሮማውያን አይሁዶችን ምን ያህል እንደሚጠሉና ማጥፋት እንደሚፈልጉ የሚያሳይ ነው። በ5 ወራት ብቻ 1,100,000 አይሁዶችን ገድለዋል። እንዲህ ዓይነቱን እልቁት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሌኒንግራድ ለ2½ በተከበበች ጊዜ ብቻ ነው ያየነው።

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት ዴሞክራሲያዊ የነበሩ መንግስታት ጦርነት ለማሸነፍ ሲሉ አምባገነን ሆነው በመለወጣቸው የአምባገነንነት መንፈስ በምድር ላይ ተለቀቀ።

ሙሶሊኒ የኢጣልያ አምባገነን መሪ ሆነ፤ በ1929 ዓ.ም ቫቲካን ራሷን የቻለች መንግስት ናት ብሎ አወጀ። በምድር ላይ ከሁሉም ታናሽ ሃገር እንደመሆኗ ቫቲካን ዳንኤል በትንቢ የተናገረላት ታናሽ ቀንድ ልትሆን በቅታለች። ፍጥረታዊ የፖለቲካ አምባገነን መሪዎች የሆኑትን ሒትለር እና ሙሶሊኒ ሁለቱንም ወደ ስልጣን እንዲመጡ ፖፑ ረድቷቸዋል።

ፖፑ ደግሞ እንደ መንፈሳዊ አምባገነን ሆኑ ቤተክርስቲያንን ይመራታል።

ዳንኤል 8፡8 አውራውም ፍየል ራሱን እጅግ ታላቅ አደረገ፤ በበረታም ጊዜ ታላቁ ቀንዱ ተሰበረ፥ ወደ አራቱም የሰማይ ነፋሳት የሚመለከቱ አራት ቀንዶች ከበታቹ ወጡ።

ከ20 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ አራት ጀነራሎች የአሊግዛንድን መንግስት ተከፋፈሉ።

ዳንኤል 8፡9 ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ፥

ይህ የሚናገረው ከአራቱ የግሪክ ጀነራሎች መካከል የላይሲማከስን ግዛት በተመለከተ ሲሆን ቦታው በጥቁር ምልክት የተደረገበት ነው። ይህም ግዛት የባቢሎን ፖነቲፍ ከባቢሎን ካሕናት ጋር ጴርጋሞን ውስጥ የሚኖርበትን ቦታ ያጠቃልላል።

ጀነራል ሴሉከስ ኤዥያን ሲወስድ ቶለሜ ደግሞ ግብጽን ወሰደ። ካሳንደር የግሪስ መሪ ሆነ።

 

 

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ133 ዓመተ ዓለም የጴርጋሞን ግዛት ለሮም ተሰጥቶ ነበር።

በ63 ዓመተ ዓለም ዩልየስ ቄሳር ጉቦ ከፍሎ ፖንቲፍ የተባለውን ማዕረግ ተቀበለ። ይህ ፖንቲፍ የተባለ የማዕረግ ስም ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የገባው በ382 ዓ.ም ዳማሰስ ለተባለው ለሮማ ጳጳስ በተሰጠው ጊዜ ነው። የሮማ ጳጳስ እስከ ዛሬ ድረስ ፖንቲፍ ተብሎ ይጠራል። የባቢሎን ሚስጥራት ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገቡ፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ታላቂቱ ባቢሎን ሆነች። ቫቲካን በምድር ካሉ ሃገሮች ሁሉ ታናሽ ሃገር ናት ነገር ግን በዓለም ዙርያ 1.4 ቢሊዮን ካቶሊኮችን ትመራለች። በምድር ካሉ ድርጅቶች ሁሉ በሃብት አንደኛ ድርጅት ቫቲካን ናት።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እንደ ሒትለር እና እስታሊን የመሳሰሉ ፍጥረታዊ አምባ ገነኖች ፍጥረታዊቷ እስራኤል ማለትም አይደሁዶች ላይ ነፍሰ ገዳይ መናፍስትን ለቀቁባት።

ይህም በሆነ ጊዜ እስታን ራሺያ ውስጥ ሒትለር ደግሞ ጀርመኒ ውስጥ ሆነው የጥንቷዊቷን አረማዊ ሮም ነፍሰ ገዳይ መንፈስ እንደገና በአይሁዶች ላይ ፈትተው የለቀቁባቸው ይመስላል።

በ70 ዓ.ም አይሁዶች ከሕዝባቸው መካከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተገደሉባቸው ነው ከተስፋይቱ ምድር ወጥተው የተሰደዱት። በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከጥንቱም የባሰ እልቂት ነበር የሆነው፤ ሒትለር ባስነሳው ሆሎኮስት ወይም እልቂት 6 ሚሊዮን አይሁዶች ተገድለዋል። ይህ አሰቃቂ መከራ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አይሁዶች የመለሰበት ጊዜ ነው።

በዚያ ጊዜ የዓለም ሁሉ ሃገሮች በጥቂቱም ቢሆን ለአይሁዶች አዝነውላቸው ፓለስታይን ውስጥ በ1947 ትንሽዬ መሬት እንዲሰጣቸው በድምጽ ብልጫ ወሰኑላቸው። አረቦች አራት ጊዜ ሊወጉዋቸው ተነሱ ግን አይሁዶች አሸነፉዋቸው።

ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከሄደች በኋላ እግዚአብሔር በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ፊቱን ወደ አይሁዶች ይመልሳል።

ዳንኤል 8፡9 ከእነርሱም ከአንደኛው አንድ ታናሽ ቀንድ ወጣ (ቫቲካን ሆኖ የተገለጠው መንፈስ)፥ ወደ ደቡብም (የደቡቧ ንግስት የተገኘችበት የቤተክርስቲያን ዓለም) ወደ ምሥራቅም (አጋንንታዊ አሰራር) ወደ መልካሚቱም ምድር (እስራኤል) እጅግ ከፍ አለ።

የደቡቧ ንግስት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች፤ ይህች ንግስት ሰሎሞንን ማለትም የዳዊትን ልጅ ለማመን ፈልጋ መጥታለች፤ የዳዊት ልጅ የሚለው መጠሪያ የኢየሱስ ማዕረግ ሲሆን በምድር ላይ ለ1,000 ዓመታት በሚነግስ ጊዜ በዚህ ማዕረግ ነው የሚጠራው።

ማቴዎስ 12፡42 ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

ቃየን ሐሰተኞቹንና ነፍሰ ገዳዮቹን መናፍስት ይዞ ወደ ምስራቅ ሄደ።

ዘፍጥረት 4፡16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፤ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ።

ዳንኤል 8፡10 እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ (ቫቲካን ውስጥ ያለው ፖፕ)፤ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም።

የሞቱ ጻድቃንን ፖፑ አማላጆች ናቸው ይላል። ስለዚህ ወደ ጴጥሮስና ወደ ማርያም መጸለይን ያስተምራል። ሙታንን ለመገናኘት መሞከር የጨለማው የመንፈስ አሰራር ስለሆነ አደገኛ ልምምድ ነው። ይህ ዓይነቱ ልምምድ ቅዱሳንን ከሰማይ ወደ ምድር ያወርዳቸውና በጥልቁ ዓለም አጋንንታዊ አሰራር ውስጥ የሚሳተፉ ይመስል ያዋርዳቸዋል።

ዳንኤል 8፡11 እስከ ሠራዊትም አለቃ ድረስ ራሱን ታላቅ አደረገ፤ ከእርሱም የተነሣ የዘወትሩ መሥዋዕት ተሻረ፥ የመቅደሱም ስፍራ ፈረሰ።

የሮማ ፖፕ የማዕረግ መጠሪያ ቪካሪየስ ክሪስቲ ይባላል። በክርስቶስ ቦታ ማለት ነው። ራሱን ምን ያህል ከፍ እንዳደረገ ተመልከቱ።

የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ያለው በጴጥሮስ እጅ ነው ስለዚህ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት አለመግባታችሁን የሚወስነው ጴጥሮስ ነው ይላሉ። በሩ ኢየሱስ ነው። ነገር ግን ፖፑ እንደሚለው በሩን ሊከፍትላችሁ የሚችለው ጴጥሮስ ብቻ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ትምሕርት ጴጥሮስን ከኢየሱስ በላይ ከፍ ያደርጋል።

ኢየሱስ ለጴጥሮስ እንዲህ አለ፡

ማቴዎስ 16፡19 የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ኢየሱስ በር ስለ መክፈትና ስለ መዝጋት ለሌለችም ደቀመዛሙርት ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።

ማቴዎስ 18፡18 እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።

ስለዚህ የመንግስተ ሰማያትን በር የሚከፍተው ምንድነው?

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

 

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ንሰሃ የመንግስተ ሰማያትን በር ይከፍትላችኋል ምክንያቱም ከሲኦል የሚያድናችሁ ንሰሃ ነው።

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ በሩን ይከፍትላችኋል ምክንያቱም በስላሴ ትምሕርት ከመታለል ስለሚያድናችሁ ለጌታ ዳግም ምጻት ያዘጋጃችኋል። በዚህም መንገድ ከሰነፎቹ ቆነጃጅት አንዳቸውን በመሆን ወደ ታላቁ መከራ ከመግባት የማምለጥ ዕድላችሁን ያሰፋዋል።

የሮማ ካቶሊክ መንፈስ በ70 ዓ.ም ሲሰራ ከነበረው የአረማዊው የሮማ መንግስት መንፈስ የመጣ ነው። ሮማውያን በ33 ዓ.ም ክርስቶስን ሰቀሉት፤ ኢየሱስም ሲሰቀል በየዕለቱ በቤተመቅደስ የሚቀርበው መስዋእት ተቋረጠ፤ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ የእንስሳት መስዋእት ዋጋ አልነበረውም። ከዚያም በ70 ዓ.ም ቤተመቅደሱን አፈረሱት፤ ስለዚህ ማንም ከዚያ ወዲያ እንስሳትን መስዋእት እያደረገ ማቅረብ አልቻለም።

ይህ ጥቅስ የዛሬዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መነሻዋ ከጥንቱ ጨካኝና ነፍሰ ገዳይ ከሆነው የሮማ መንግስት መሆኑን ያሳያል። ታላቁ መከራ ሲጀምር ይህንን ጭካኔና ነፍሰ ገዳይነት ሰዎች እንደገና ያዩታል።

ማርቆስ 13፡19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።

አይሁዶች ሁለት መከራዎችን ያያሉ። እነዚህም ሁለት መከራዎች የተስፋይቱ ምድራቸውን እንደገና እንዲቆጣጠሩ ምክንያት የሆናቸው ሆሎኮስት ወይ ጀርመኒ ውስጥ የተፈጸመባቸው እልቂት እና እምቢ ብለውት የነበረውን መሲሃቸውን የሚቀበሉበት ታላቁ መከራ ናቸው።

ኢየሱስ በሕይወት ያለችዋን ሙሽራ ወደ ሰማይ ሊወስዳት ሲመጣ በ3½ ዓመቱ ታላቅ መከራ ውስጥ ወንጌሉ ወደ አይሁደች ይመለሳል። ያም ጊዜ በምድር ላይ ከታዩ የጭፍጨፋ እና የመከራ ዘመኖች ሁሉ እጅግ የከፋ ዘመን ይሆናል። አይሁዶችም እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ዘመን ነው የሚጋፈጡት።

ክርስቶስን ባለመቀበላቸው ምክንያት በ70 ዓ.ም በሮማውያን እጅ ተጨፍጭፈው ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው ከመመለሳቸው በፊት ከሕዝባቸው ውስጥ 6 ሚሊዮን ያህል የሚሆኑት በሒትለር የመርዝ ጋዝ ቤት ውስጥ አልቀዋል። ፍጥረታዊው አምባገነን መሪ ሒትለር ጨካኙን ነፍሰ ገዳዩን የሮማ መንግስት መንፈስ በፍጥረታዊ እስራኤል ላይ ለቀቀው።

በስተመጨረሻ በታላቁ መከራ ውስጥ ሆነው ከአርማጌዶን ጦርነት በፊት መሲሃቸውን መቀበላቸው እጅግ በጣም አሰቃቂ ስደት እንዲነሳባቸው ሲያደርግ ከእነርሱ መካከል በዚህ መከራ ውስጥ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ይገደላሉ።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

 

ቤተክርስቲያን ውስጥ አጋንንት መንፈሳዊ ሞትን ያመጣሉ

 

ሒትለር የለቀቃቸው ነፍሰ ገዳይ የሮማ መንግስት መናፍስት ምን ሆኑ? አረማዊቷ ሮም ጣኦታትን እና አጋንንትን በማምለክ በጣም ሐይማኖተኛ ነበረች።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ ጀርመኖች አይሁዶችን መግደል አቆሙ። በዚህ ምክንያት ተለቀው የነበሩት ነፍሰ ገዳይ መናፍስት መንፈሳዊ እስራኤልን ማለትም ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ወደ መንፈሳዊው ዓለም ገቡ። ይህን ዓላማቸውን ለማሳካት በ1948 ዓ.ም የዓለም ቤተክርስቲያናት ምክር ቤት ሲመሰረት ወደ ምክር ቤቱ ገቡ።

የዳኑ ክርስቲያኖች የተገለጠውን የኪንግ ጅምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንዳያነብቡ በማድረግ እነዚህ አጋንንታዊ መናፍስት ሰነፎቹን ቆነጃጅት ይዘው ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይከቷቸዋል። ሰነፎቹም ቆነጃጅት በዚያ ታላቅ ደም መፋሰስ ውስጥ ይገደላሉ። እነዚህ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ሰነፎቹን ቆነጃጅት አሁን መግደል አይችሉም፤ ነገር ግን በነጻነት መግደል የሚችሉበት ጊዜ ይመጣል። አይሁዶችን ይጠላ የነበረ ክፉና ጨካኙ የሮማ መንፈስ ወደፊት ከአይሁዶች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑትን ይገለድላል።

ኢየሱስ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወይም ሙሽራይቱን ሊነጥቃት ከመምጣቱ በፊት እውነተኞቹ ቅዱሳን የሚገጥማቸው ተግዳሮት ይህ ነው፡- እንዴት ነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆንና ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያት እምነት መመለስ የምንችለው። ከዚያ ቀጥሎ እጅግ ዘግናኝ ግፎች የሚፈጸሙበት የ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ይጀምራል።

እውነተኛዋ ሙሽራ ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆንና ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም እንከን የሌለበት ፍጹም እውነት መሆኑን ማመን አለባት። ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ አለባት።

ነገር ግን በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሚሰራው ሐይማኖታዊ የአጋንንት መንፈስ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን በ45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች ከፋፍሏቸዋል።

እነዚህ ሐይማኖታዊ አጋንንት ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ሊያጠፉ ሲሞክሩ ቆይተዋል። ዛሬ ከ100 በላይ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። የፈለጋችሁትን መርጣችሁ አንብቡ። ይህ ቀልድ ነው።

ቅን የሆኑ ክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ስሐተት አለበት፣ እርስ በርሱ ይጋጫል፣ አፈታሪክ እና ሳይንሳዊ ስሕተቶች አሉበት ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ለእምነታቸው ንጹህ የሆነ መሰረት የላቸውም። ከዚህም የተነሳ እምነታቸው ንጹህ ሊሆን አይችልም።

በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ መረዳት እና ወደ ጥንታዊው የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል።

ማርቆስ 13፡20 ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።

ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማጠር አለበት።

ይህ ጥቅስ የሚናገረው ከሲኦል ስለመዳን አይደለም። ከሲኦል መዳን የሚቻለው ከልብ ንሰሃ በመግባት ነው።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚፈልግ ሰው ስለሌለ በአየር ላይ ወደ ጌታ የሚነቅና ከታላቁ መከራ የሚያመልጥ ስጋ ለባሽ አይኖርም።

በየዓመቱ ብዙ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ሽንገላ ይታለላሉ፤ ደግሞም ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት አለበት ብለው ያምናሉ።

ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስሕተት በጣም በዝቶ ከመሰራጨቱ የተነሳ ሙሉውን እውነት ፈልጎ ማግኘት ከባድ ሆኗል።

ቤተክርስቲያኖች እውነትና ስሕተትን ቀላቅለው እየሰበኩ ናቸው።

የዲኖሚኔሽን ሰባኪዎች እና የዊልያም ብራንሐም ተከታዮች ነን የሚሉ የሜሴጅ ሰባኪዎች የሚመሩዋቸው የቤተክርስቲያን አባላት መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ እየሆኑ ነው። ቅን የሆኑ ክርስቲያኖች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተቶች አሉበት እያሉ ናቸው። እራሳቸውን አስተዋይ ሰዎች እንደሆኑ በማሰብ ክርስቲያኖች በኤቮልዩሽን ቲዎሪ እና በቢግ ባንግ ቲዎሪ ያምናሉ። ሮማውያን የሚያመልኩት የፀሃይ አምላክ ልደት ዲሴምበር 25 ነው ተብሎ የታወጀው በ274 ዓ.ም በንጉስ ኦሬልያን ነበር፤ ይህም አዋጅ የታወጀው ኦሬልያን የሮም ጳጳስን አንገት ካስቆረጠ ከሶስት ቀናት በኋላ ነበር። በ350 ዓ.ም አካባቢ ፖፑ ዩልየስ ቀዳማዊ ዲሴምበር 25 የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ልደት ነው ብሎ አወጀ። ይህ በዓል ክራይስትስ ማስ ተብሎ ተጠራ ምክንያቱም የካቶሊኮች የአምልኮ ስርዓት ማስ ተብሎ ነው የሚጠራው።

መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት አክብሮ ብሎ አላዘዘንም።

ሆኖም ፕሮቴስታንቶች ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ማስ እንደ ክሪስማስ ተቀብለው ያከብሩታል።

ከዚህም የተነሳ ከሮማ ባዕድ እምነት ብዙ ትምሕርቶች ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊክ ወዳልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ሾልከው በገቡ ቁጥር የክርስትና ሐይማኖት ጥፋት እየተባባሰ ይሄዳል። ስላሴ። ኩዳዴ። ማስ። የስቅለት አርብ። ዓርብ ዕለት ዓሳ መብላት። ዲኖሚኔሽን። አንድ ሰው ካሕንም ይባል አገልጋይ ወይም ሬቨረንድ ወይም ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ መሆን ይችላል። የሰው ንግግር ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መተካት ይችላሉ። ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ስለሆነ አይሳሳትም ብሎ ማመን ልክ ፖፑ አይሳሳትም ተብሎ እንደሚታመነው።

ማርቆስ 13፡21 በዚያን ጊዜም ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም፦ እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

ኢየሱስ በዳግም ምጻት እስኪመለስ ድረስ በምድር ላይ ሁለተኛ አታዩትም። ሲመለስም እግሩ ምድርን አይረግጥም ምክንያቱም ከምድር በላይ አየር ላይ ሆኖ ነው እኛን ወደ አየሩ ላይ የሚነጥቀን።

ኢየሱስ እኛን ወደ ሰማይ ነጥቆ ሊወስደን ተመልሶ በስጋ ከመገለጡ በፊት ልታዩት የምትችሉበት ብቸኛ ሥፍራ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት በሚያስችሏችሁ በተገለጡት የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት ውስጥ ነው። በተገለጠው ቃል አማካኝነት ብቻ ነው ልታዩት የምትችሉት።

አሁን ያለንበት ሁኔታ የሚለወጠው የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ሲፈጸም ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ 7ቱ ነጎድጓዶች አካላችንን ወደ ማይሞት አካል መለወጥ ያስችሉናል።

ኢየሱስን በማይሞተው አካሉ ማየት የምትችሉት የዚያን ጊዜ ብቻ ነው።

1ኛ ዮሐንስ 3፡2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።

ማርቆስ 13፡22 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።

“ክርስቶስ” ማለት እውነተኛ ቅባት ነው። ሰባኪዎች አስደናቂ ተዓምር ሊያሳዩ ይችላሉ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አይችሉም፤ ደግሞም ሐሰተኛ ትምሕርቶችን ይሰብካሉ። የተገለጡትን ሚስጥራት እውነት ይክዳሉ።

የሰባኪዎቹ አገልግሎት እውነተኛ ቅባት ከሐሰተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ጋር ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አጥብቃችሁ የማትከተሉ ከሆናችሁ በነዚህ ሰዎች ሽንገላ አካማኝነት ትስታላችሁ።

እውነቱን እንሰብካለን የሚሉ ሐሰተኛ ክርስቶሶች ቤተክርስቲያንን በ45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች ከፋፍለዋታል። ደግሞም ማማረጥ የምትችሉበት ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። ስለዚህ አሁን ባለንበት መንፈሳዊ ግርግር ውስጥ እውነትን ፈልጎ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው።

ማርቆስ 13፡23 እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።

አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል።

 

ያን ጊዜ በአይሁዳውያን ላይ የተለቀቁ አጋንንት ኋላ ወደ ቤተክርስቲያኖች ገቡ

 

ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከመነጠቃችን በፊት የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ ሐዋርያት አስተምሕሮ መመለስ አለበት።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡17 ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

ከዚያ ወዲያ ወንጌሉ ወደ አይሁዶች ይሄዳል።

ሁለት ታላላቅ መከራዎች አሉ።

እግዚአብሔር አንድ የታወቀ መከራ (“ያ መከራ” የተባለው) በአይሁዶች ላይ እንዲመጣ በማድረግ ጀመረ፤ በዚያም መከራ ውስጥ ሒትለር ባስነሳው የሆሎኮውስት እልቂት በ1945 በተጠናቀቀው በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት 6 ሚሊዮን አይሁዶች አለቁ። የዓለም ሕዝብና ሃገሮች ሁሉ በዚህ በጣም ከመደንገጣቸው የተነሳ ለአይሁዶች የነበራቸውን ጥላቻ ለጥቂት ጊዜ ረስተው እስራኤል ውስጥ መኖሪያ ምድር እንዲሰጣቸው በድምጽ ብልጫ ወሰኑላቸው። ይህም እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር የመመለሷ መጀመሪያ ነበረ።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ተሰውረው የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ከ1947 እስከ 1965 በዊልያም ብራንሐም አገልግሎት አማካኝነት ሲገልጥ ቤተክርስቲያን ላይ ትኩረት ማድረግ ጀመረ።

ማርቆስ 13፡24 በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥

“ከዚያ መከራ” የሚለው 6 ሚሊዮን አይሁዶች የተገደሉበትን የሒትለር ሆሎኮስት ማለት ነው።

ሆሎኮስቱ በ1945 ዓ.ም ጦርነቱ ሲያበቃ አቆመ።

ፀሃያችን ወይም የብርሃናችን ምንጭ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ከ1945 በኋላ በጦርነቱ ወቅት ተለቀው የነበሩና አይሁዶችን ሲገድሉ የነበሩ አጋንንት መግደል አቆሙ። ቤተክርስቲያኖች የሕዝብ ጭፍጨፋዎችን አንቀበልም አሉ። እነዚህ አጋንንት ዘዴያቸውን ለውጠው ሰዎች በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የነበራቸውን እምነት መግደል ጀመሩ። ዊልያም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መረዳት እንደምንችል እያሳየን በነበረ ሰዓት ስለ ዘመን ፍጻሜ አስደናቂ መገለጦችን ቢያመጣም እንኳ እነዚህ አጋንንት ሰዎች መገለጦቹን ለማወቅ ፍላጎት እንዳይኖራቸው አደረጉ።

እነዚህ መናፍስት ወደ ቤተክርስቲያኖች ገብተው ለረጅም ጊዜ በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልቋረጠ ጥቃት ሰነዘሩ። ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አገኘንበት ብለው መጽሐፍ ቅዱስን ማመን ሲያቆሙ የእውነት ፀሃይ ጨለመች። አንዳችም ስሕተት የሌለበት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ችግር አለበት ተብሎ ተጣለ። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ይሰጥ የነበረው ድንቅ ብርሃን ወደ ጎን ተተወ። ስለዚህ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም ሲሉ መጽሐፉ የነበረውም ተጽእኖ ቀነሰ።

ጨረቃ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፤ ስለዚህ በጨለማው ዓለም ውስጥ ቤተክርስቲያን የፀሃይን ብርሃን (ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን) ታንጸባርቃለች። ጨረቃ የራሷ ብርሃን የላትም። ስለዚህ ቤተክርስቲያንም የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ብርሃን ማንጸባረቅ ብቻ ነው ያለባት።

ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላትን በመለወጥና ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን በመተቸት ቤተክርስቲያን የፀሃይን ብርሃን ማንጸባረቅ ትታ የራሷን ብዙ አመለካከቶች ብቻ እያንጸባረቀች ናት። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያኖች በጣም ጥቂት ብርሃን ብቻ ነው የሚያንጸባርቁት። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ማመንም ሆነ መጥቀስ ስላቆሙ ጨረቃ ብርሃኗን እየሰጠች አይደለችም።

ጀርመኒ ውስጥ ከተፈጸመው የአይሁዶች ጭፍጨፋ መከራ በኋላ ሒትለርና እስታሊን የለቀቋቸው ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ መናፍስት ሁሉ 2ኛው የዓለም ጦርነት ሲያበቃ አይሁዶችን መግደል አቆሙ። ይህ ደም መፋሰስ እንዲቀጥል የዓለም ሃገሮች አልፈቀዱም። ስለዚህ በ1948 እነዚያ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ አጋንንት ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱሱን በመጣል የእውነትን ፍቅር ለመግደል ወደ ዓለም የቤተክርስቲያኖች ምክር ቤት ሰተት ብለው ገቡ። ደግሞም ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖችም የዊልያም ብራንሐምን አገልግሎት እንዳይቀበሉ አደረጓቸው፤ ይህን ያደረጉበት ምክንያት በዘመን መጨረሻ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ልጆች ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት እንዳይመለሱ እና በመንፈሳዊ ድንቁርናቸው ውስጥ ሆነው እንዲሞቱ ነው። ከዚያ በኋላ እነዚህ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ ገብተው ይገደላሉ።

በመጀመሪያው ፍልሰት አይሁዶች ከግብጽ ወጡ፤ በዚያ ጊዜ ፈርኦን ሕጻናትን ገድሎ ነበር። በሁለተኛው ፍልሰት ቤተክርስቲያን ከአይሁድ ሕዝብ መካከል ወጣች፤ በዚያም ጊዜ ሄሮድስ ሕጻናትን ገደለ። በሶስተኛው ፍልሰት ደግሞ ሙሽራይቱ ከቤተክርስቲያኖች ውስጥ ትወጣለች፤ በዚህም ጊዜ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶቻቸው የዛሬዎቹን ልጆች ይገድላሉ። እነዚህም ትምሕርቶች ስላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ አብ እና ወልድ እኩል ናቸው፣ አብ እና ወልድ አንድ ባህርይ ናቸው የሚሉ ናቸው። በተጨማሪ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የስቅለት አርብ፣ የ7 ዓመቱ መከራ፣ ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔረ ድምጽ ነው፣ ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም የሚሉ ይገኙበታል።

ማርቆስ 13፡25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።

ከዋክብት ለጉዞ እና አቅጣጫ ለመለየት ይጠቅሙናል። በመንፈሳዊ ሕይወታችን የሚመሩን ከዋክብት የቤተክርስቲያን መሪዎችና ሰባኪዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ኃላፊነታቸው እኛን በመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ማሳደግ ነው። የዘመናችን ሰባኪዎች ግን ከሰማይ የተሰጣቸውን ጥሪ ትተዋል። ገንዘብ በማሳደድና ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ በመናገር ተጠምደዋል። ትምሕርታቸው እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማሳየት ስለማይችሉ ከቤተክርስቲያን ልማዶችና ከሰው ሰራሽ አመለካከቶች ተነስተው ነው የሚሰብኩት። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጠው ባለማስተማራቸው ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ምሪት እየሰጡ አይደሉም፤ ስለዚህ በጨለማ ውስጥ ናቸው። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይምነታቸው እየተባባሰባቸው ነው።

ከዚያም በ1963 እግዚአብሔር ሰባቱን ማሕተሞች ገለጣቸው፤ የነዚህ ማሕተሞች መገለጥ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ሁሉ እንዲገለጡ መንገድ ይከፍታል።

ሰባቱ ማሕተሞች መገለጣቸው ታላቅ የሆነ ክስተት ስለሆነ የሰዎችን ትኩረት ወደዚህ ክስተት ለመሳብ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም ሰባት መላእክት ከፍላግስታፍ ከተማ 42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ሰሩ። በዚህ ከፍታ ላይ አየሩ በጣም ስስ ከመሆኑ የተነሳ ደመና ሊፈጠር አይችልም። በዚህ ከፍታ ላይ የውሃ ትነት አይገኝም።

በዚያ ከፍታ ላይ ተንሳፍፎ የታየው ይህ ደመና የፊዚክስ ሕጎችን ሁሉ አናወጣቸው። ከምድር ከፍ ብሎ የሚገኘውን ሥፍራ “ሰማይ” እንለዋለን። በፊዚክስ ሕግ መሰረት በዚያ ከፍታ ላይ ምንም ዓይነት የዝናብ ደመና ሊፈጠር አይችልም። ደመናው ግን ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ እንኳ ደምቆ ይታይ ነበረ። ይህም ደመናው በዚያ ከፍታ ላይ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ማለትም በመላእክት ክንፍ የተሰራ መሆኑን ያመለክታል።

 

 

ከስምንት ቀናት በኋላ እነዚያው ደመናውን የሰሩ መላእክት ሳንሴት ፒክ ወደተባለ ከተማ ወርደው የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥር እንዲገልጥ ለወንድም ብራንሐም ትዕዛዝ ሰጡት። የነዚህ ማሕተሞች መገለጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት እንዲገለጡ በር ከፈተ።

ወንድም ብራንሐም እምነቱ ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማሳየት ይችላል። ስለዚህ አሁን የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ግለሰቦችም እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማሳየት ወደሚችሉበት ብቃት መድረስ አለባቸው።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ የመላእክት አለቃ ድምጽ እንደሚመጣ ሲጠባበቅ ነበር።

65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

“ድምጹ” ወንድም ብራንሐም እምነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ገልጦ ማሳየት መቻሉ አይደለም።

“ድምጹ” ማለት የሙሽራይቱ አካላት የሆኑ ግለሰቦች የወንድም ብራንሐም ትምሕርት ትክክል መሆኑን በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ማረጋገጥ ወደ መቻል መድረሳቸው ነው።

62-111 የተደራጁ ሐይማኖቶችን የማልቀበልበት ምክንያት

ልብ በሉ ቀጣዩ ምዕራፍ 19ኛው ምዕራፍ ነው፡- “ከነዚህ ነገሮች በኋላ” ይላል። በዚህ በ19ኛው ምዕራፍ ውስጥ “ከነዚህም ነገሮች በኋላ” የሚለውን አስተውላችኋል? ከነዚህ ነገሮች በኋላ ምን?

ከምን በኋላ? “ከእርሷ ውጡ!” ከሚለው መልእክት በኋላ።

“ከነዚህ ነገሮች በኋላ” የሚለው “የሙሽራይቱ አካላት የሆኑት ቅዱሳን እና የሙሽራው ድምጽ ነው፤ ድምጻቸውም ወደ በጉ ሰርግ ሲታደሙ የሚሰማው ድምጽ ነው”። ምን ያህል ጊዜ ነው የሚቀረው? የመጨረሻው ጥሪ ምንድነው? ከባቢሎን ውጡ!

 

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ እኔ የምቃወምበት ምክንያት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። እውነትና ትክክለኛ አይደለም። ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። እግዚአብሔር በዚህ ውስጥ የለበትም፤ አልነበረበትም፤ ወደፊትም አይገኝበትም። እንግዲህ በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ እውነተኛ ሰዎች የሉም ማለቴ አይደለም፤ ከነዚህ ዓይነት ሰዎች ነው ቤተክርስቲያን የተሰራችው።

ነገር ግን በዚያ ዓይነት ድርጅት ውስጥ በቆያችሁ መጠን የድርጅቱ አካል ትሆናላችሁ።

የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 9

ይህን በጥንቃቄ እንመለከተዋለን። ይህ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ቡድን ለብ ያለ ነው ይላል። እንዲህ ዓይነቱ ለብታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣት ያመጣል።

ቅጣቱም ከእግዚአብሔር አፍ ውስጥ መተፋት ነው።

ስለዚህ ብዙ ሰዎች እንደሚስቱት እኛ በዚህ መሳት አንፈልግም። ባለማወቃቸው የተነሳ እግዚአብሔር ከአፉ አውጥቶ ሊተፋችሁ ይችላል ስለሚል የቅዱሳን ጽናት የሚባል ትምሕርት እንደሌለ በዚህ ማረጋገጥ ይቻላል ይላሉ። ይህን አስተሳሰባችሁን አሁኑኑ ማረም እፈልጋለሁ።

ይህ ጥቅስ የተሰጠው ለግለሰብ አይደለም። የተሰጠው ለቤተክርስቲያን ነው።

እየተናገረ ያለው ለቤተክርስቲያን ነው።

የቤተክርስቲያን አባል መሆናችን ከአደጋ የመትረፍ ዋስትና አይደለም። የወንድም ብራንሐም መልእክት በ100 ዓይነት የተለያዩ አተረጓጎሞች መኖሩ በራሱ የዚህ ማስረጃ ነው። ከነዚህ መካከል አንዱንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማረጋገጥ አይቻልም።

እያንዳንዱ ግለሰብ ጥቅሶችን በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እንዴት መተርጎም እንደሚገባው መማር አለበት። ጥቅሶችን በመተርጎም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ መረዳት ላይ መድረስ የለባቸውም።

ከዚያ ወዲያ የመላእክት አለቃ “ድምጽ” ሙታንን ያስነሳቸዋል።

ከዚያ ቀጥሎ ክርስቶስ ሲመጣ ሲያዩት የእግዚአብሔር መለከት ሙሽራይቱ በአየር ላይ ተነጥቃ ክርስቶስን እንድትቀበለው ይጠራታል።

ማርቆስ 13፡26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።

 

ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ስትሄድ እግዚአብሔር ወደ አይሁዳውያን ይመለሳል

 

ጌታ ከአሕዛብ የሆነችዋን ሙሽራ ሊወስዳት ከመጣ በኋላ እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ይመለሳል።

ማርቆስ 13፡27 በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።

በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር መላእክትን (ብዙ ቁጥር) ሁለት መላእክትን ይልካል። እነርሱም ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው። የእነርሱም ሥራ 144,000ዎቹን የተመረጡ አይሁዶች መሰብሰብ ነው። መሰብሰብ አለባቸው ምክንያቱም እነዚህ የተመረጡ ሰዎች በምድር ዙርያ ልዩ ልዩ ቦታ ተበታትነዋል። ከኢየሩሳሌም በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምዕራብ፣ እና በምስራቅ ሁሉ ተበታትነዋል። እነዚህ ሰዎች ከሰማይ ዳግም ይወለዱ ዘንድ በእግዚአብሔር ተመርጠዋል። ስለዚህ የታላቁ ንጉስ ሰማያዊ ባሮች ናቸው። እነዚህ 144,000 ምርጦች ለበጉ ሙሽራ ጥበቃ ያደርጉላታል።

በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ውስጥ ለነዚህ ሁለት አይሁዳዊ ነብያት መንገድ ለመጥረግ እግዚአብሔር መጀመሪያ አይሁዶችን ወደ ተስፋይቱ ምድር ይሰበስባቸዋል።

ማርቆስ 13፡28 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

የበለስ ዛፍ የእስራኤል ምሳሌ ናት። በሕይወቱ የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ዕለት ኢየሱስ የበለሷን ዛፍ ፍሬ ባለማፍራቷ ረገማት፤ ይህም ቀን ከሆሳዕና ዕለት ቀጥሎ ነበር። በነጋታው ማክሰኞ ዕለት ዛፊቱ ደረቀች። ይህም የእስራኤል ሕዝብ በዚያው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ኢየሱስን ሲሰቅሉ መንፈሳዊ ድርቀት ውስጥ እንደሚገቡ እና ከእግዚአብሔር የማዳን እቅድ እንደሚሰረዙ እና የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ወደ አሕዛብ እንደሚተላለፍ የሚያመለክት ነበር።

ስለዚህ በ1947 ዓ.ም ከተስፋይቱ ምድር ትንሽ ቁራሽ ለማግኘት እንዲዋጉ ለአይሁዶች ከተባበሩት መንግስታት ፈቃድ ተሰጣቸው። በ1948 የአምስት አረብ ሃገራት ጦር ሰራዊቶች አይሁዶች ላይ ጦርነት አወጁባቸው፤ አይሁዶችም ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠላቶቻቸውን በሙሉ ድባቅ መቱ።

የአይሁዶች ባንዲራ የዳዊት ኮከብ ነው። ዳዊት ከ3,000 ዓመታት በፊት ነው የኖረው። የትኛዋም ሃገር በታሪክ የዚህን ያህል ወደ ኋላ የሚሄድ ባንዲራ የላትም። የዳዊት ኮከብ ባንዲራ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1948 ዓ.ም የተውለበለበው ዴቪድ ቤን ጉሪየን በተባለው አይሁዳዊ ፕሬዚዳንት ነው። ከ3,000 ዓመታት በኋላ እንኳ የስሙ በትክክል መገጣጠም አስገራሚ ነው።

በ1967 ዓ.ም አረቦች አይሁዶችን ሊያጠፉ ዛቱ ነገር ግን በ6 ቀን ጦርነት ተሸነፉ።

ሙሴ አይሁዶችን ስድስት ቀን እየሰሩ በሰባተኛው ቀን እንዲያርፉ ነግሯቸው ነበር። አይሁዳዊው የመከላከያ ሚኒስትር ሙሴ (ሞሼ) ዳያን ለስድስት ቀናት በመዋጋት ግብጽን፣ ዮርዳኖስን፣ እና ሶሪያን አሸነፋቸው። ከዚያም በሰባተኛው ቀን አረቦች እጅ ሲሰጡ እረፍ አደረገ። ከ3,500 ዓመታት በኋላ የመጣው መሪ እንኳ ስሙ በትክክል ተገጣጥሟል። ሶስት ሃገሮችን በስድስት ቀናት ውስጥ በጦር ሜዳ ማሸነፍ ተሰምቶ የማይታወቅ ታሪክ ነበር፤ ነገር ግን ይህ ሊሆን የቻለው እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ስለተመለሰ ነው።

አብራሐም (አብራም ይባል የነበረው) ለእግዚአብሔር አስራት ሰጠና ለኤስኮል ድርሻው እንዲሰጠው ጠየቀ። አስራት የሚሰበስበው የሙሴ ልጅ ልጅ ልጅ ሊዊ ነበረ።

አይሁዶች ከተስፋይቱ ምድር ዋነኛውን ክፍል በጦርነት አሸንፈው በወሰዱ ጊዜ የእስራኤል ፕሬዚዳንት የነበረው ሰው ስሙ ሌዊ ኤስኮል ነበረ። ይህም ከ4,000 ዓመታት በላይ ስሙ ተገጣጠመ። ስለዚህ አስራት መክፈል ዋጋ አለው።

ዘፍጥረት 14፡20 ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።

ዘፍጥረት 14፡23-24 አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።

ሌዊ ኤስኮል ድርሻውን ተቀበለ።

ማርቆስ 13፡28 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው ሲመለሱ ስናይ ይህ የመጨረሻው ዘመን ቅርብ መሆኑን የሚያመለክት ነገር ነው።

1948 ታላቅ ትርጉም ያለው ዓመት ነው ግን በዚያ ዓመት ከተስፋይቱ ምድር በጣም ትንሽ ብቻ ነበር የተቆጣጠሩት።

በታሪክ በጣም የተሻለ ምልክት ጥሎ ያለፈው ዓመት 1967 ነው። በዚያ ዓመት አይሁዶች ከተስፋይቱ ምድራቸው ብዙውን ክፍል ሊቆጣጠሩ ችለዋል። ነገር ግን አንድ ችግር ነበረ። የሲና የባሕር ወሽመጥንም ከግብጾች ላይ ነጥቀው ተቆጣጠሩ፤ እግዚአብሔር ግን ይህንን ምድር ለአብራሐም አልሰጠም ነበር። ስለዚህ በ1973 አረቦ ጥቃት ሰንዝረውባቸው ብዙ ጥፋት አደረሱባቸው። በስተመጨረሻም አይሁዶች ሊያሸንፉ ችለዋል ግን ሊሸነፉ ጥቂት ሲቀራቸው ነው። ስለዚህ ስፍራውን ለቀቁና የሰላም ስምምነት አደረጉ።

በ1982 ሲናን መልሰው ለግብጽ አስረከቡና የሰላም ስምምት ፈረሙ።

ከዚያ ቀን ጀምሮ በትክክለኛዋ የተስፋይቱ ምድራቸው መኖር ጀመሩ።

ይህም ክርስቲያኖች ዓለማዊ አለባበስና ፋሽን መከተል እንደሌለብን ያስተምረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ካበጀልን ገደብ ሳንወጣ መኖር አለብን እንጂ ወደ ሰይጣን ግዛት ውስጥ ሰተት እያልን መግባትና ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ አደንዛዥ እጽ መጠቀም፣ እና ቁማር መጫወት የለብንም። እንደነዚህ ዓይነት ልማዶች ሰይጣን ጥቃት እንዲሰነዝርብንና ጉዳት እንዲያደርስብን በር ይከፍታሉ።

ማርቆስ 13፡29 እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ።

እስራኤሎች ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው ገቡ፤ ወደ ግብጽ ግዛት ውስጥ ዘው እያሉ መግባትንም አቆሙ። መጨረሻው ቅርብ ነው።

ማርቆስ 13፡30 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።

በፈረንጆች 1982 ዓ.ም አካባቢ የተወለዱ ሰዎች በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ አማካኝነት የሚጠናቀቁት የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች ሲፈጸሙ በሕይወት ኖረው የማየት ዕድል አላቸው፤ እነዚህም ክስተቶች በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት ይዘጋሉ።

በ2018 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማንንም ሳይፈራ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ብሎ እውቅና ሰጠ። በ1000 ዓመተ ዓለም አካባቢ ንጉስ ዳዊት ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና አድርጓት ነበር።

የዛሬዋ እስራኤል ወደ ጥንቱ አጀማመሯ እየተመለሰች ናት።

ሙሽራይቱም ሐዋርያቱ ወደነበሩበት የጥንቱ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ አለባት።

ማርቆስ 13፡31 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።

ከኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቃል ሊለወጥ አይችልም። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን እንከን እንደሌለበት ፍጹም እውነት መቀበል አለብን። ከኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም ዓይነት መንገድ ፈቀቅ ማለት ሐጥያት ነው።

በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገር በሙሉ ይፈጸማል።

 

በመጨረሻው ሰዓት ንቁ መሆን አለብን እንጂ ማንቀላፋት የለብንም

 

ማርቆስ 13፡32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።

የጌታ ዳግም ምጻት መች እንደሚሆን ማንም አያውቅም። እግዚአብሔርም እንድናውቅ አይፈልግም። ነገር ግን ሁልጊዜ ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ይፈልጋል።

ማርቆስ 13፡33 ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።

መጽሐፍ ቅዱስን አንብቡ፤ የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ በውስጡ የተጻፉ ምሳሌዎችም ሆኑ ትንቢቶች ሁሉ ያለ ዓላማ እንዳልተጻፉ እወቁ።

ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ትተው ወዴት እየሄዱ እንደሆኑ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ ደግሞም የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ማብራራት አቅቷቸዋል።

ቤተክርስቲያኖች ምን ያህል በፖለቲካ ልባቸው እንደጠፋ ተመልከቱ።

ቤተክርስቲያኖች ምን ያህል ገንዘብ በማከማቸት ልባቸው እንደጠፋ ተመልከቱ።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ከተሰራጩ ስሕተቶች ማምለጥ እንችል ዘንድ የተገለጠው የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ በደምብ እንዲገባችሁ ጸልዩ።

ማርቆስ 13፡34 በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።

ቤተክርስቲያንን ለመመስረት ሶስት አገልግሎቶች ተሰጥተዋል።

የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት፣ የብሉይ ኪዳን ነብያት እና በዘመን መጨረሻ ለአሕዛብ የተላከው የመጨረሻዋን ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት የሚመልሰው ነብይ።

ከዚያም የዊልያም ብራንሐምን ንግግር ጥቅሶች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እየወሰዱ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያረጋግጡ አስተማሪዎች ተሰጥተዋል።

ፓስተሮች ግን አልተጠቀሱም። ስለዚህ ማንን እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል

1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።

ማርቆስ 13፡35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና

ኢየሱስ መች እንደሚመጣ አናውቀም፤ ነገር ግን ባልጠበቅንበት ሰዓት ይመጣል።

ስለዚህ የማይጠበቀውን መጠባበቅ መልመድ አለብን።

ይህን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተምረናል። የኮቪድ ምርመራ ተመርምሮ በሽተኛ ሆኖ መገኘት ከባድ ነገር ነበር።

ማርቆስ 13፡36 ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ።

እርሱ ሲመጣ እንቅልፍ ተኝተን ብንገኝ ጉዳችን ፈላ።

ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ቆነጃጅት ወይም ድንግል ሴቶች ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ የዳኑ ሰዎችን ይወክላሉ።

ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ የተጻፈ ምሳሌ የዳኑ ሰዎችን ሁሉ በ10 ቆነጃጅት ይመስላቸዋል፤ ከነዚህም ግማሹ ልባሞች፣ ግማሹ ግን ሰነፎች ናቸው። ነገር ግን ሁላቸውም አንቀላፍተዋል፤ በዙርያቸው እየሆነ ያለውን ነገር አያውቁም፤ ግድም የላቸውም።

ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

ይህ ማቴዎስ ውስጥ የተጻፈ ምሳሌ የዳኑ ክርስቲያኖች ሁሉ በየቤተክርስቲያናቸው ውስጥ እንቅልፍ ተኝተዋል ይላል።

ማርቆስ ውስጥ የተጻፈ ሌላ ምሳሌ ደግሞ እንቅልፋችንን ከተኛን ሁላችንም ችግር ውስጥ እንደምንገባ ይነግረናል።

ስለዚህ በከባድ ፈተና ውስጥ ነው ያለነው።

እግዚአብሔር እንደ ቤተክርስቲያን ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ነው ሊያናግረን የሚፈልገው።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

ኢየሱስ የቤተክርስቲያንን በር ያንኳኳል። የቤተክርስቲያን በር ግን አይከፈትም።

ኢየሱስም ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል የሆነ ግለሰብ ሰምቶ ይከፍትልኛል ብሎ ተስፋ ያደርጋል።

ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

እግዚአብሔር ግለሰቦችን ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ነው ከአፉ አውጥቶ የሚተፋት።

ማቴዎስ 25፡6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።

ውካታው ጭንቀትን ያመለክታል።

በሌሊት ተነሱ ውጡ የሚል ጥሪ። ይህ እንደ ምድር መንቀጥቀጥ የመሰለ ታላቅ አደጋ ይሆን?

ተነሱ የሚለው ጥሪ ከየትኛውም ቤተክርስቲያን እንድንወጣ የሚነግረን ጥሪ ነው። “ውጡ”።

የመጨረሻዎቹ የሙሽራይቱ አካላት አማኞች ከቤተክርስቲያን የሚወጡበት ይህ የሶስተኛው ፍልሰት መጨረሻ ነው።

ማቴዎስ 25፡7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።

የማንቂያ ጥሪው ሰነፎቹን ቆነጃጅት ጨምሮ ሁላችንንም እራሳችንን እንድንመረምርና እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሰረት እንድናስተካክል ያደርገናል።

ማርቆስ 13፡37 ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።

ቁልፉ ቃል “ትጉ” የሚለው ነው። ሁልጊዜ ንቁ መሆን አለብን። ሁልጊዜ ለመማርና ራሳችንን ለማሻሻል ዝግጁ መሆን አለብን። ሙሉ በሙሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንመለስ ዘንድ እርማት ለመቀበል ፈቃደኞች መሆን አለነብን።

ዘመናት ውስጥ ተሰራጨ።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23