ማርቆስ 12 - እንግደለውና ርስቱን እንውረስ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እግዚአብሔርንና ሰዎች መውደድ አለብን። የሐይማኖት መሪዎች ማስመሰልና ራሳቸውን ከፍ ማድረግ ይወዳሉ።
- ወንጌሎቹ ሁለት ትርጉም አላቸው
- መዳን ከአይሁዶች ተሻግሮ ወደ አሕዛብ አልፈ
- ብዙ የዳኑ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ
- የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን መተቸት ይፈልጋሉ
- ትዕዛዛቱ በፍቅር ላይ የተመሰረቱ ናቸው
- መለኮትን መረዳት አለብን
ወንጌሎቹ ሁለት ትርጉም አላቸው
ወንጌሎቹ ከኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት ጀምሮ የተከናወኑ ነገሮችን ይተርካሉ። ነገር ግን በመንፈስ ብናስብ ደግሞ እነዚህ ክስተቶች በሙሉ የዳግም ምጻቱ ጠቋሚዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ። ከዚያም እራሳችንን እና የቤተክርስቲያን መሪዎቻችንን በአይሁዶች እና በሐይማኖት መሪዎቻቸው ቦታ አስቀምጠን ማየት እንችላለን። እነርሱ ይሰሩ የነበሩትን ስሕተት እኛም አሁን እየሰራን ነን።
ታሪክ ራሱን የመድገም ባህርይ አለው።
በሰማይ ኢየሱስ በአራት እንስሳት ማለትም በክብር አጃቢዎች ታጅቧል።
ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤
ራዕይ 4፡6 … በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የስላሴ ትምሕርት በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን በመግባቱ የእውነት ፍቅር ከተገደለ በኋላ ጥጃው በ1,200 ዓመታት ውስጥ ጠንካራ በሬ እስኪሆን ድረስ አደገ። ከዚያ ወዲያ በ606 ዓ.ም ጀምሮ ፖፑ የዓለም ሁሉ ጳጳስ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እጅ ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ተገድለዋል። በሬ በሥራ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ የሚታረድ እንስሳ ነው።
አራቱ እንስሳት አራቱን ወንጌሎች የሚወክሉ ሲሆኑ በነዚህ ወንጌሎች ውስጥ የእግዚአብሔር እቅድ ማዕከል የክርስቶስ ሞት ነው።
ከልቡ መሃል ያለውን መስቀል ተመልከቱ።
ማቴዎስ ክርስቶስን እንደ አንበሳው ማለትም እንደ ንጉስ ይገልጠዋል።
ዮሐንስ ክርስቶስን እንደ ንስር ማለትም እንደ እግዚአብሔር ይገልጠዋል።
ማርቆስ ክርስቶስን የሚገልጠው ሸክም እንደሚሸከም አገልጋይ ነው። ስለዚህ ማርቆስ እግዚአብሔርን ከማገልገል ጋር የተያያዙ የተወሰኑ ጉዳዮችን ይገልጣል።
ማርቆስ 12፡1 በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፥ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
የወይን እርሻ የወይን ፍሬ የሚሰጥ የወይን ሐረግ የሚያድግበት ቦታ ነው።
ወይን መገለጥን በመቀበል የሚመጣ መነቃቃትን ይወክላል። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመረዳት የሚገኝ ደስታ ነው።
ይህ ምሳሌ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋረ ያደረገውን ቃልኪዳን በተመለከተ የሚናገር ነው፤ በዚህም ቃልኪዳን 12ቱ የእስራኤል ነገዶች እግዚአብሔርን እያገለገሉ እንዲኖሩበት የተስፋይቱ ምድር ተሰጠቻቸው።
ማርቆስ 12፡2 በጊዜውም ከወይን አትክልት ፍሬ ከገበሬዎቹ እንዲቀበል አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤
እግዚአብሔር አይሁዶች ምን ያህል ቃሉን ያምኑ እና እርሱንም እያገለገሉ እንደሆን ለማየት ነብይ ላከ።
ማርቆስ 12፡3 ይዘውም ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት።
ነብዩ ሲመጣ ስለደበደቡት ምንም ዓይነት የመንፈሳዊ እድገት ምልክት አላየባቸውም።
ማርቆስ 12፡4 ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት አዋርደውም ሰደዱት።
ቀጥሎ የተላከውን ነብይ በድንጋይ ወግረውት፤ አዋርደውት ሸኙት። የነብዩ ራስ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የነብዩን ራስ በድንጋይ መምታት እግዚአብሔርን በድፍረት መቃወም ነው።
ማርቆስ 12፡5 ሌላውንም ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፥ ከሌሎችም ከብዙዎች አንዳንዱን ደበደቡ አንዳንዱንም ገደሉ።
ግፍ እየበዛ ሄደ። አንዳንድ ነብያት ተገደሉ፤ አንዳንዶቹም ቆሰሉ። በእርግጥም የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን የማገልገል ፍላጎት አልነበራቸውም።
ማርቆስ 12፡6 የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ልጁን ላከ። ይህም የተወደደው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እግዚአብሔር በስጋ ተገለጠ። የእግዚአብሔር መንፈስ ፍጹም በሆነ ሰው ውስጥ ኖረ። እርሱም መሲሁ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ማርቆስ 12፡7 እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው፦ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለው፥ ርስቱም ለኛ ይሆናል ተባባሉ።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የመስዋእት እንስሳትን በመሸጥ ያከማቹትን ብዙ ገንዘብ ለመጠበቅ ሲሉ ትምሕርታቸውን የተቃወመውንና ከክፉ መንገዳቸው እንዲመለሱ ያስጠነቀቃቸውን መሲሁን ለመግደል ወሰኑ። በተለይ ደግሞ ቤተመቅደሱ ውስጥ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛ የገለበጠ ጊዜ ቁጣቸው ነደደበት። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብቡ ብዙ ሰዎች አያስተውሉም እንጂ ኢየሱስ ይህን ያደረገው ሶስት ጊዜ ነው።
ማርቆስ 12፡8 ይዘውም ገደሉት፥ ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ ጣሉት።
ለምንድው ልጁን የገደሉት? በሐሰተኛ ሐይማኖታቸው አማካኝነት የሰበሰቡትን ገንዘብ ላለማጣት ብለው ነው። ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ የሔሮድስ ወገኖች፣ እና ረቢዎች ናቸው የሐይማኖት መሪዎች፤ እነዚህ ሰዎች የሚጠሩባቸው ማዕረጎችም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሰው አያውቁም። ሁሉም ሰው ሰራሽ ማዕረጎች ስለሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው የአመራር ስልጣኖች ናቸው።
ታሪክ ራሱን ይደግማል። “ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሐዋርያት ፓስተርን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው አልሾሙም። ዛሬ ግን ብዙዎቹ ቤተክርስቲያኖች የሚተዳደሩት በፓስተር ነው። ስሙ ስምኦን ከሆነ ስምኦን ብላችሁ ልትጠሩት አትችሉም፤ ፓስተር ስምኦን እንድትሉት ይፈልጋል። ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ ምክንያቱም አዲስ ኪዳን ውስጥ አገልጋዮች በዚህ ዓይነት ማዕረግ አልተጠሩም። ፓስተር እረኛ ተብሎ አያውቅም።
ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ፓስተሮች ስድስት ጊዜ ተወግዘዋል። በብሉይ ኪዳን ሕግ ውስጥ ፓስተሮች ስላልነበሩ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ ፓስተሮች የተጻፈው ውግዘት ትንቢታዊ ነበረ።
ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የፋሲካ በዓልን ሊያከብር ወደ ቤተመቅደስ በሄደ ጊዜ ገንዘብ ለዋጮችን እየገረፈ ከቤተመቅደስ አባረራቸው።
ዮሐንስ 2፡15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን የሚገልጥልን የዮሐንስ ወንጌል ከመጀመሪያው ጀምሮ ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎች ትልቅ ስሕተት ገንዘብ መውደዳቸው መሆኑን ያሳየናል። ኢየሱስ በዚህ በጣም ተቆጥቷል ምክንያቱም ይህ የገንዘብ ፍቅር መንፈስ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ የቤተክርስቲያን መሪዎችን እንደሚያበላሻቸው አውቋል። በዘመን መጨረሻ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ባለ ብዙ ገንዘብ እና ባለጠጋ ትሆናለች ነገር ግን ዕውር መሆኗንና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አለመቻሏን አታውቅም። እግዚአብሔር ዛሬ ገንዘብ ሰብሳቢ ሰባኪዎችን ከቤተክርስቲያን እየገረፈ አያባርራቸውም። ለምን? የዛሬዋ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስሕተቶች እና በገንዘብ ፍቅር እጅግ በጣም ከመበላሸቷ የተነሳ ቤተክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ከአፉ ይተፋታል። ቃሉ በእግዚአብሔር አፍ ውስጥ ነው ያለው። የዛሬ ሰባኪዎች አስተምሕሮዋቸው እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ አያሳዩም። ከቃሉ ውስጥ ተተፍተዋል፤ ከዚህም የተነሳ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አይችሉም።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ እንደተጻፈው የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛ ገለበጠ።
ማቴዎስ ኢየሱስን በንጉስነቱ እየገለጠ ነው የጻፈው። የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ በአይሁድ ንጉስነት ክብር ኢየሩሳሌም ውስጥ አቀባበል የተደረገለት ቀን ነው።
ዘካርያስ 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
ስለዚህ ማቴዎስ በሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ያደረገውን እየገለጸ ነው የጻፈው።
ማቴዎስ 21፡7 አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም።
ማቴዎስ 21፡12 ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦
ማርቆስ ኢየሱስን ሸክም እንደሚሸከም አገልጋይ በሬ አድርጎ ነው የገለጸው።
ኢየሱስ በሆሳዕና ዕለት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።
ማርቆስ 11፡7 ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም።
ማርቆስ 11፡10 በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።
ማርቆስ 11፡11 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
ይህ የተጻፈው ስለ ሆሳዕና ዕለት ነው ነገር ግን ማርቆስ ኢየሱስ ቤተመቅደሱን ስለማጽዳቱ አልጻፈም።
የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ንጉስ ስለመሆኑ እውቅና ተሰጠው፤ ስለዚህ ንጉሱ ቤተመቅደሱ ውስጥ ምን እንዳደረገ ማርቆስ አልጻፈም፤ ማቴዎስ እንዲጽፍ ትቶለታል።
ከሆሳዕና በኋላ ሰኞ ዕለት ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደሱ ተመልሶ እውነትን ያስተምር ነበር። ይህ የትጉ አገልጋይ ባህርይ ነው።
ማርቆስ 11፡12 በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ።
በማግስቱም የተባለው ቀን ከሆሳዕና እሁድ ቀጥሎ የመጣው ቀን ነው።
ስለዚህ ቀኑ ሰኞ ነበር።
ስለዚህ እንደ ትጉህ አገልጋይ ኢየሱስ ቤተመቅደሱን በድጋሚ ለማጽዳት ወሰነ። ኢየሱም ምንም ዓይነት ስራ ደጋግሞ አያውቅም ነበር። አንድን ነገር በሁለት ተከታታይ ቀናት ደጋግሞ አያውቅም። እንደ አገልጋይ ሥራው ቤተመቅደሱን ከገንዘብ ጋር ከተያያዘ እድፍ ማጽዳት ነበር። ይህም አደገኛ ሥራ ነው። ኢየሱስ ትናንት አጽድቶት የነበረው ንግድ ወዲያው ሰኞ ዕለት ቤተመቅደሱ ውስጥ እንደገና ተደራጅቶ እየተሰራ ነበር።
ማርቆስ 11፡15 ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤
ቤተመቅደሱን በሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ አጸዳው። ይህም ለሐይማኖት መሪዎች ገቢ ታላቅ ስጋት ፈጠረባቸው፤ ስለዚህ ከሶስት ቀናት በኋላ ሐሙስ ዕለት ገደሉት። በዓሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሶስት ሌሊት እንዳደረው እንደ ዮናስ ኢየሱስም ሶስት ሌሊት መቃብር ውስጥ ቆየ። ሐሙስ ሌሊት፣ አርብ ሌሊት፣ እና ቅዳሜ ሌሊት። እሁድ ዕለት በጠዋት ከሞት ተነሳ።
አይሁዶች ዓላማቸው ተሳካ፤ መሲሁን ገደሉት። ስለዚህ ወደ ቤተመቅደሱ የሚገባውን ገንዘብ በሙሉ ለራሳቸው ማድረግ ይችላሉ ምክንያቱም ኢየሱስን ከገደሉ በኋላ ስለ ገንዘቡ የሚጠይቃቸው ማንም የለም።
የገቢ ምንጫው እስካልተቋረጠ ድረስ እውነትን መግደል (እውነት ኢየሱስ ነው) ለሐይማኖት መሪዎች ደስታቸው ነው። እስከ ዛሬም ድረስ የተለወጠ ነገር የለም።
ገንዘባቸውን ይዘው ለ37 ዓመታት ያህል ቆይተዋል፤ ከዚያ በኋላ ሮማውያን እነርሱን ገደሏቸውና ቤተመቅደሱን ደመሰሱት። ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ የቤተመቅደስ ካሕናት፣ እና የሔሮድስ ወገኖች የት እንደደረሱ ከዚያ ወዲያ ማንም አልሰማም።
ቤተመቅደሱ ከፈረሰ በኋላ በቤተመቅደሱ የሚገኘው ገቢ ተቋረጠ።
ለአጭር ጊዜ ገንዘባቸውን ያስጠበቁ መስሏቸው ነበር ግን ኋላ በአሰቃቂ ሞት ሁላቸውም አለቁ።
ዛሬም ቤተክርስቲያኖች ትኩረታቸው ገንዘብ ላይ ሆኗል። ነገር ግን የሚያከማቹትን ገንዘብ ፍለጋ የመጨረሻው ፖፕ ይመጣባቸዋል፤ እርሱም ሃብታቸውን ለመቀማት ብሎ ሁላቸውንም የሚገድል የአመጽ ሰው ነው።
ማርቆስ 12፡9 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል ገበሬዎቹንም ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።
አይሁዶች መሲሁን በመግደላቸው የተነሳ ከባድ ቅጣት ይመጣባቸዋል። በ70 ዓ.ም በሮማውያን እጅ የኢየሩሳሌም ከተማ እና ቤተመቅደሱ በተደመሰሱ ጊዜ 1,100,000 አይሁዶች ተገድለዋል።
በ132 – 135 በተደረገው የባርኮችባ አመጽ ወቅት 580,000 አይሁዶች በሮማውያን እጅ ተገድለዋል፤ ከዚያም በኋላ አይሁዶች ከገዛ ሃገራቸው ተባርረው በሮማ መንግስት ግዛቶች ውስጥ ተበታተኑ።
መዳን ከአይሁዶች ተሻግሮ ወደ አሕዛብ አልፈ
አይሁዶች ከመጣባቸው ቅጣት ሁሉ የባሰው ቅጣት ግን በ33 ዓ.ም በቀራንዮ እግዚአብሔር አይዶችን ትቷቸው ፊቱን ወደ አሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ማዞሩ ነው።
በቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት ውስጥ ናቡከደነጾር ባየው ሕልም ውስጥ በምስሉ እግር የተወከሉት አሕዛብ ናቸው መዳንን የተቀበሉት፤ አይሁዶችም ተቆረጡ።
በቀራንዮ መስቀል መዳን ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ተሻገረ።
የአሕዛብ ምስሉ እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
ነገር ግን የአሕዛብ ምስሉ እግሩ ላይ በድንጋይ ተመታ፤ ድንጋዩም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ የሚፈጸመውን የጌታን ምጻት ይወክላል።
ስለዚህ በስተመጨረሻ ቤተክርስቲያንም ተመሳሳይ ስሕተት ሰራች። አይሁዶች እንደ ሰው ተገልጦ የመጣውን ኢየሱስን አንቀበልም በማለታቸው በብዙ ሺ ተጨፈጨፉ። የዳኑ የቤተክርስቲያን አማኞች በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት የመጣውን የተገለተውን የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት አንቀበልም ብለዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መረዳት የማይችሉት የዳኑ የቤተክርስቲያን አማኞች በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።
ማርቆስ 12፡10 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው። የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?
አይሁዶች አንቀበልም ብለው የጣሉት መሲህ ታላቅ እና ራስ ሆነ። እርሱም ጌታ እና ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሆኗል።
ራዕይ 1፡8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
አይሁዶች ሰው የሆነውን ኢየሱስ አንቀበልም በማለታቸው ሁለት ጊዜ ነው የተጨፈጨፉት።
በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ስላሴ የተባለ ቃል ቤተክርስቲያን ላይ በግድ ተጫነባት። ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ የእውነትን ፍቅር ገደለ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት መንፈሳዊ እውነትን አይወክሉም። ብዙ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት ወደ ቤተክርስቲያን ገቡ። እግዚአብሔር ወልድ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ። አንድ አምላክ በሶስት አካላት። አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው። የመለኮት የመጀመሪያው አካል። የመለኮት ሶስተኛው አካል። ዘላለማዊ ልጅነት።
በዚህ መንገድ የእውነት ቃል የሆነው ኢየሱስ ተገደለ።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ አካባቢ ቤተክርስቲያኖች የተገለጡትን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት አንቀበልም ይላሉ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ስለሆነ ኢየሱስን እንደገና ይሰቅሉታል።
የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት ማለትም ንጹህ ሴቶች የዛሬዎቹ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ የዳኑ ሰዎች የሚያምኑትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶች ይወክላሉ፤ እነዚህም ወደ 45,000 ዓይነት ልዩ ልዩ ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች ተከፋፍለዋል። የሚያሳዝነው ነገር እነዚህ ሁሉ በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።
በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያኖች የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም በማለታቸው ኢየሱስን አንቀበልም ብለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ ቃሎች ሁሉ የሚያሳዝን ቃል ኢየሱስ ከበር ውጭ መቆሙን የሚናገረው ቃል ነው። በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ዛሬ ራሳቸውን የሚመዝኑት ለቤተክርስቲያናቸው ፓስተር ታማኝ በመሆናቸው እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን በመረዳታቸው አይደለም።
ልብ በሉ ቤተክርስቲያን “የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን” ሆናለች።
ሎዶቅያውያን የራሳቸውን ሐይማኖት እና የቤተክርስቲያን መመሪያዎች የሚያበጁ ሰዎች ናቸው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
ብዙ ቤተክርስቲያኖች ዛሬ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን አይቀበሉትም።
በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን አዘጋጅተዋል። ደግሞም 45,000 ዓይነት ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች ተፈልፍለዋል። በዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ ግርግር ውስጥ እውነትን ፈልጎ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል።
በዘመን መጨረሻ በተላከው ነብይ በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት ከኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው ኢየሱስ በዳግም ምጻት ተመልሶ ይመጣል። ከሙታን የተነሳችዋ ሙሽራ የፒራሚድ ጉልላት ድንጋይ ሙሽራይቱን በሰማይ ወደተዘጋጀው ሰርግ ወደ ላይ ነጥቆ ይወስዳታል። ነገር ግን የዚህ ጉልላት ድንጋይ መምጣት ናቡከደነጾር በሕልሙ ያየውን ምስል እግሩ ላይ ይመታዋል (እግሩ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል)፤ ከዚያም በ3½ ዓመታት ታላቅ መከራ ውስጥ የአሕዛብን ስልጣኔ በሙሉ ድምጥማጡን ያጠፋዋል፤ ይህም ጥፋት በአርማጌዶን ጦርነት ይጠናቀቃል።
እውነተኛዋ ሙሽራ የተጠላች ትሆናለች። ሙሽራዋ የምትነጠቅበት ትምሕርት የቤተክርስቲያንን እና የዓለምን ሥርዓት የሚያፈርስ ትምሕርት ነው። ሙሽራይቱ በአሕዛብ እና በቤተክርስቲያኖቻቸው ዘንድ ተረግጣ ትኖራለች።
ማርቆስ 12፡11 ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው። የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?
እየተሰደዱ ያሉትን ጥቂት እውነተኛ ሰዎች እግዚአብሔር ከምድር አንስቶ ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋል፤ ከዚያም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛ እና ስሕተት የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል አድርገው የማይቀበሉትን ሁሉ ያጠፋቸዋል።
እውነት በስተመጨረሻ እንደሚገለጥ ዳንኤል በትንቢቱ ተናግሯል።
ሙሽራይቱ በመገለጥ እንድትነቃቃ ብዙ መገለጦች ተሰጥተዋታል። ሙሽራይቱም የብሉይ ኪዳን ታላላቅ ነብያት ለመረዳት ይመኙ የነበሩትን ሚስጥራት በእግዚአብሔር ጸጋ መረዳት ትችላለች።
ዳንኤል 12፡9 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ እነርሱን እየነቀፈ መናገሩን አውቀዋል። በተመሳሳይ መንገድ የዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎችም የተገለጠው ቃል እንደሚነቅፋቸው ያውቃሉ። ለዚህ ነው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉት።
ማርቆስ 12፡12 ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፥ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ።
ብዙ የዳኑ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ ይሞታሉ
በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ አይሁዶች የእግዚአብሔር ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ቤተክርስቲያን በዞረ ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብነት ክብራቸውን አጥተዋል።
በጌታ ዳግም ምጻት ጊዜ ታሪክ ራሱን ይደግማል። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናት ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች በሚመለስበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብነቷ ያበቃል። የተገለጠውን መጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት የሚያበቃ ጥበብ ያላቸውና ለጌታ ዳግም ምጻት የሚዘጋጁ ክርስቲያኖች በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ ጥቂት ክርስቲያኖች ናቸው ልባሞቹ ቆነጃጅት የሚሆኑት።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ሰነፎቹ ቆነጃጅት በጣም ብዙ ሕዝብ ናቸው። ሰነፎቹ ቆነጃጅት የዳኑ ነገር ግን በዘመናዊ ፓስተሮች በመታለላቸው የተነሳ የተገለጠውን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የማይችሉ ክርስቲያኖች ናቸው።
እነዚህ ክርስቲያኖች በታላቁ መከራ ውስጥ ነው የሚስተካከሉት።
ራዕይ 7፡9 ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤
ራዕይ 7፡14 እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።
ከታላቁ መከራ በፊት ድነው ነበር ምክንያቱም ኢየሱስ ወደ ምድር ወርዶ ሙሽራይቱን ለመንጠቅ በሚመጣ ጊዜ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ይነሳል። ስለዚህ በ3.5 ዓመቱ የታላቁ መከራ ወቅት ለአሕዛብ መዳን የለም። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ስለ እምነታቸው ይገደላሉ።
አውሬው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያዋቀረችው ድርጅታዊ የቤተክርስቲያን ስርዓት ነው።
የአውሬው ምስል ደግሞ ካቶሊክ ያልሆኑ ነገር ግን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አወቃቀር እና ብዙዎቹን ትምሕርቶቿን ኮርጀው የተደራጁ የቤተክርስቲያኖች ጉባኤ ነው። እነዚህም ትምሕርቶች ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የስቅለት አርብ፣ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚሉ እና ቤተክርስቲያን ፖለቲካ ውስጥ መሳተፏ እንዲሁም ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን አለመቀበሏ፣ ወዘተ. ናቸው።
ራዕይ 13፡15 የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
የታላቁ መከራ አሰቃቂነት የሰነፎቹ ቆነጃጅት ዓይን እንዲበራ ያደርጋል፤ እነርሱም ዓይኖቻቸው ሲበሩ የዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ስሕተት ምን እንደሆነ ማየት ይጀምራሉ። ይህም ለእነርሱ የሞት ፍርድ ይሆንባቸዋል። ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ተቀብለው የነበረውን መዳናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ መሞት አለባቸው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን መተቸት ይፈልጋሉ
ማርቆስ 12፡13 በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ።
ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ ጊዜ ሰው ነበረ።
ኢየሱስ ከዳግም ምጻቱ በፊት የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል፣ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
“ፈሪሳዊ” የሚል ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ የለም፤ ስለዚህ ፈሪሳዊ የምኩራብ አለቃ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን አይደለም።
አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ እንኳ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን አልተሾመም። ስለዚህ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
የሔሮድስ ወገኖች ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ የሐይማኖት መሪዎች ነበሩ። ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች ተመሳሳይ ስሕተት እየሰሩ ናቸው።
እነዚህ የሔሮድስ ወገኖች እና ፈሪሳውያን ከኢየሱስ አንዳች ጠቃሚ እውነት ከመማር ይልቅ በነገር ሊያጠምዱት ፈለጉ።
ፈሪሳውያን እና የሔሮድስ ወገኖች ኢየሱስን እንደ ሰው ላለመቀበል የሚያመካኙነት ነገር ለማግኘት ብለው ሲተቹት ነበር።
የቤተክርስቲያን መሪዎችም ዛሬ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል ላለመቀበል ፈልገው ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተቸት ምክንያት ይፈልጋሉ።
ዛሬ ኢየሱስ በመካከላችን የሚገኘው እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ፓስተሮች ከኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውነትን መማር ትተው አቃቂር ሊያወጡሉት ይሞክራሉ።
ማርቆስ 12፡14 መጥተውም፦ መምህር ሆይ፥ የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ? አሉት።
እግዚአብሔር ለመንግስት ግብር እንድንከፍል ይፈልጋልን? ሮም እስራኤልን በግዛቷ ውስጥ በርቀት እንደምትገኝ አውራጃ ስታስተዳድራት ነበር።
ማርቆስ 12፡15 እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ፦ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ አላቸው።
እንዴት ነው ግብዝ የሆኑት?
አይሁዶች ለሮማውያን ምንም ዓይነት የተቀረጸ ምስልም ሆነ የወታደሮችን አርማ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስገቡ አይፈቅዱላቸውም። ይህ ቢደረግ አይሁዶች ከባድ የሆነ አመጽ ያስነሳሉ።
ማርቆስ 12፡16 እነርሱም አመጡለት። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው፤ እነርሱም፦ የቄሣር ናት አሉት።
ከአስርቱ ትዕዛዛት ሁለተኛው ትዕዛዝ የተቀረጹ ምስሎችን ሁሉ ይከለክላል። ነገር ግን ወደ ቤተመቅደሱ አምጥተው የሚከፍሉትን ሳንቲም ተመልከቱ። ሳንቲሙ የንጉሱ ምስል ተቀርጾበታል።
ስለዚህ ኢየሩሳሌም ውስጥ ወደ ቤተመቅደሱ ከሚመጣውና በሐይማኖት መሪዎች ከሚሰበሰበው ሳንቲም በቀር ማንኛውም ዓይነት የተቀረጸ ምስል እንዲገባ አይፈቀድም ነበር። ሳንቲሞቹ ሃብታም እስካደረጓቸው ድረስ ግን የሐይማኖት መሪዎች የተቀረጸ ምስል ያለባችውን ሳንቲሞች ያለ ምንም ሃሳብ ይቀበሏቸዋል። ይህም ግብዝነት ነው።
ማርቆስ 12፡17 ኢየሱስም መልሶ፦ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው። በእርሱም ተደነቁ።
ሕዝቡ ኢየሱስ በሰጠው ቀላል ነገር ግን በጣም አስደናቂ መልስ ተደነቁ። ግብር ለመንግስት ክፈሉ (ቄሳር ንጉስ እንደመሆኑ የሮማ መንግስት ራስ ነበረ)፤ እንዲሁም አስራታችሁን ለእግዚአብሔር ክፈሉ።
የኢየሱስ ንግግር ግን ትርጉሙ ከዚያም የጠለቀ ነው። የቄሳር ምስል የተቀረጸባቸውን ሳንቲሞች ለቤተመቅደሱ አምጥታችሁ አትክፈሉ። የቄሳር ገንዘብ የእግዚአብሔር አይደለም።
ሕዝቡ በዚህ ተደነቁ። ሕዝቡ የቄሳር ምስል የተቀረጸበትን የሮማ ሳንቲም ለቤተመቅደሱ መክፈል ቢያቆሙ የካሕናቱ እና የቤተመቅደሱ መሪዎች ሃብት በአንድ ጊዜ በብዙ ይቀንሳል። ይህም ቤተመቅደሱን የሚቆጣጠሩትን ሰዱቃውያንን በጣም ይጎዳቸዋል።
ስለዚህ ሰዱቃውያን የገቢ ምንጫቸው ላይ ለመጣባቸው ስጋት በፍጥነት ነው ምላሽ የሰጡት።
ኢየሱስ መመለስ የማይችለውን ጥያቄ ጠይቀው በሕዝብ ፊት ሊያሳጡት ፈለጉ። ኢየሱስ ጥያቄያቸውን መመለስ ካቃተው ያለ አግባብ የሚሰበስቡትን ገንዘብ በተመለከተ ለሚናገራቸው ቃል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት ይችላሉ።
ማርቆስ 12፡18 ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት፦
ሰዱቃውያን በትንሳኤ አያምኑም ነበር።
ማርቆስ 12፡19 መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።
ባሏ የሞተባት ሴት የባሏን ወንድም አግብታ ልጅ መውለድ ትችላለች።
ማርቆስ 12፡20 ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ዘር ሳያስቀር ሞተ፤
ማርቆስ 12፡21 ሁለተኛውም አገባት፥ ዘርም ሳይተው ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤
ማርቆስ 12፡22 ሰባቱም አገቡአት፥ ዘርም አላስቀሩም። ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች።
ሰዱቃውያን ይህንን ሃሳብ ተጠቅመው ትንሳኤ አለመኖሩን ሊያረጋግጡ ፈለጉ።
ሰባት ጊዜ ካገባች በመንግስተ ሰማይ ውስጥ ማነው ባሏ የሚሆነው? ትንሳኤ የሚባል ነገር ካለ የማን ሚስት ትሆናለች?
ማርቆስ 12፡23 ሰባቱ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀን ሲነሡ ከእነርሱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች?
ኢየሱስም በሰጣቸው መልስ እነርሱ ያለባቸው ችግር መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃቸው መሆኑን አስረዳቸው።
ማርቆስ 12፡24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?
በሰማይ ደም የለም። ደም በሌለበት የወንድ ብልት ሊቆም አይችልም ስለዚህ በሰማይ መጋባትም ሆነ ወሲባዊ ግንኙነት የለም።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
ማርቆስ 12፡25 ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፥ አይጋቡምም።
በሰማይ ጋብቻ የለም። በሰማይ አንድ ሰው እና ሚስቱ ወንድም እና እሕት ነው የሚሆኑት። ከሙታን የተነሱ ሰዎች የወሲብ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ሆርሞኖች አይኖሩዋቸውም፤ እንደ መላእክት ይሆናሉ።
ማርቆስ 12፡26 ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር፦ እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?
ሙታን በሰማይ ሙታን አይደሉም። እግዚአብሔር የሚኖረው በሰማይ ሲሆን እራሱን የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ እና የያዕቆብ አምላክ ብሎ ነው የሚጠራው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሕያዋን ናቸው ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘንድ ሞት የለም። እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወት ነው።
ማርቆስ 12፡27 የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። እንግዲህ እጅግ ትስታላችሁ።
ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎች ማለትም ሰዱቃውያን አስተምሕሮዋቸው በጣም የተሳሳተ ነበረ። ይህም ለዘመን መጨረሻ የቤተክርስቲያን መሪዎች ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ ነው ምክንያቱም እነርሱም በትምሕርታቸው በጣም ተሳስተዋል። የቤተክርስቲያን መሪዎች ከሚናገሯቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት መካከል እንደ ስላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ አንድ አምላክ በሶስት አካላት፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የስቅለት አርብ፣ ኩዳዴ፣ የሰባት ዓመት መከራ፣ እና ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው የሚሉ ይገኙባቸዋል።
ነገር ግን ሰዱቃውያን የሴቲቱ ባል ማን እንደሚሆን ማወቅ በፈለጉ ጊዜ ጥያቄያቸው እነርሱ ያላስተዋሉት ጠለቅ ያለ ትርጉም ነበረው።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ባል የሚስቱ ራስ ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሰዎችን እንደ ራስ ስትቀበል ቆይታለች። ይህ ቤተክርስቲያኖች የሰሩት ስሕተት ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ለተለያዩ የቤተክርስቲያን ዘመናት የላካቸው መልእክተኞች ቤተክርስቲያንን ወደ ኢየሱስ እንዲመልሷት ነበር የተላኩት። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ሁልጊዜ የቤተክርስቲያን ራስ መሆን የሚገባው እርሱ ነው እንጂ የሆነ ሌላ ሰው አይደለም።
ሁልጊዜ “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል” እያልን መጠየቅ አለብን።
ዮሐንስ 1፡37 ሁለቱም ደቀ መዛሙርት [መጥምቁ ዮሐንስ] ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር የሰሙ እንዲሁም ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር የተረዱ ደቀመዛሙርት እርሱን ከሰሙ በኋላ ኢየሱስን ተከትለዋል።
ወንድም ብራንሐም ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር ተረድተን ከሆነ እምነታችንን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት መርምረን እናጸናዋለን።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡21 የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
ምክር ፍለጋ ሰዎችን ልንሰማ እንችላለን ነገር ግን መከተል ያለብን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው።
ስለዚህ ሙታን አዲሱን አካላቸውን ለብሰው ሲነሱና የቤተክርስቲያን ዘመንም ሲጠናቀቅ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ ቅዱሳን ሁሉ አንድን ሰው ብቻ ነው መንፈሳዊ ባል እንዲሆናቸው ሊቀበሉ የሚነሱት፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ለዚያ ቀን ለመዘጋጀት እንድንችል ራስ ይሆነን ዘንድ መቀበል ያለብን በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጡትን ሚስጥራት ብቻ ነው። በነዚህም ሚስጥራት መገለጥ አማካኝነት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያት ወዳስተማሩት የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ አለብን።
ትዕዛዛቱ በፍቅር ላይ የተመሰረቱ ናቸው
ማርቆስ 12፡28 ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ፦ ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው።
ማርቆስ 12፡29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥
አንድ አምላክ ብቻ መኖሩን ማወቅ ከትዕዛዛት ሁሉ የሚበልጠው ትዕዛዝ ነው። ከዚያም ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሁሉ ሲፈጽም እና ታላላቅ ተዓምራትን ሲያደርግ ባያችሁ ጊዜ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ትረዳላችሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር አንድ ብቻ ነው።
ማርቆስ 12፡30 አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ ኢየሱስን መውደድ አለባችሁ። ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱን ሙሉ በሙሉ መውደድ አለባችሁ፤ ከውስጡም ምንም ነገር መለወጥ የለባችሁም።
ማርቆስ 12፡31 ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።
እግዚአብሔርን መውደድ ከተማራችሁ እና በምድር ላይ የምታገኙዋቸውን ሰዎች ሙሉ በሙሉ ከወደዳችሁ እግዚአብሔር ደግሞ ለመንግስቱ ሥራ ይጠቀምባችኋል። ስለዚህ እግዚአብሔርን እና ሰዎችን መውደድ አለብን።
እግዚአብሔር ቃሉ ነው። ስለዚህ የተጻፈውን ቃል መውደድና ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስን ሁልጊዜ ማጥናት አለባችሁ። የትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ቢሆን እንኳ የማይጠቅም ዝርዝር ነው አትበሉ። በጭራሽ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል አትበሉ። አንድም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አፈታሪክ ነው ብላችሁ አትለፉ። በጭራሽ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች አሉ አትበሉ።
ምሳሌ 30፡5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤
ስለዚህ ንጹህ የሆነውን የተፈተነው የእግዚአብሔር ቃል ለሰዎች ማስተማር አለብን። ስናስተምርም በፍጹም መጽሐፍ ቅዱስን መተቸት ወይም መጠራጠር የለብንም።
ማርቆስ 12፡32 ጻፊውም፦ መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤
ማርቆስ 12፡33 በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።
እግዚአብሔርን በማስተዋል ውደዱ።
የእግዚአብሔር ሃሳብ በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧል።
እግዚአብሔርን የእውነት የምንወደው ከሆነ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል የመረዳት ፍላጎት ይኖረናል።
ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ወደ ጻፉት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እስክንመለስ ድረስ ደስተኞች አንሆንም።
ስሕተቶችን ከማመንና ታላላቅ መስዋእቶችን ከማቅረብ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል ማመን ይበልጣል።
ማርቆስ 12፡34 ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ፦ አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።
ይህ ሰው እውነትን ከልቡ የሚፈልግ ይመስላል ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ቀረብ ማለት ችሏል።
ይህ ጸሐፊ የቤተክርስቲያን መሪ ነበር ነገር ግን ከኢየሱስ ማለትም ከቃሉ ጋር ለመከራከር አልሞከረም።
ኢየሱስን በነገር ለማጥመድ አልሞከረም። ከኢየሱስ ለመማር እውነተኛ ፍላጎት አሳየ። ልክ እንደዚሁ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ መማር የሚፈልጉ አንዳንድ የቤተክርስቲያን መሪዎች አሉ።
መልሱ ግን እግዚአብሔርን መውደድና ሰዎችን መውደድን የሚያጠቃልል ስለሆነ ሰዎች ጥያቄ መጠየቅ አቆሙ። ብዙ ሰዎች የሚፈልጉት ጠላቶቻቸውን መጥላትና ዕድሉን ካገኙ መበቀል ነው። ስለዚህ ጠላቶችችንን መውደድ እንዳለብን ሲነገርን መስማት አንፈልግም።
ማቴዎስ 5፡44 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ … ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤
ይህ ጥቅስ ጥሩ የክርስትና ሕይወት መኖርን ከባድ ያደርግብናል ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንገድ ከእኛ መንገድ በጣም ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሔር እኛ ስለ ሰዎች ያለንን አመለካከት የመስማት ፍላጎት የለውም። ሁሉንም ሰዎች መልካሞቹንም ሆነ ክፉዎችን መውደድ መልመድ አለብን።
መለኮትን መረዳት አለብን
ማርቆስ 12፡35 ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር መልሶ እንዲህ አለ፦ ጻፎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ?
የመለኮት ሚስጥር ሁልጊዜ እንቆቅልሽ ነበር። እግዚአብሔር አንድ አካል ነው ወይስ ሁለት ወይስ ሶስት አካል?
ማርቆስ 12፡36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ።
“ጌታዬ” የተባለው የዳዊት ጌታ ነው። ጌታ እንዴት ለዳዊት ጌታ ሊናገር ይችላል?
ጌታ ጌታዬን በቀኜ ተቀመጥ አለው፤ የሚለው ንግግር ሁለት ሰዎች ጎን ለጎን ተቀምጠው እንደሚነጋገሩ ይመስላል። አይሁዶች በአንድ እግዚአብሔር ብቻ ያምኑ ስለነበረ ለዚህ ማብራሪያ አልነበራቸውም።
የመለኮትን ሚስጥር አብራሩ።
ማርቆስ 12፡37 ዳዊትም ራሱ ጌታ አለው፤ እንዴትስ ልጁ ይሆናል? ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰሙት ነበር።
መሪዎቹ ከኢየሱስ ጋር ይጋጩ ነበር፤ ተራው ሕዝብ ግን ኢየሱስን ሲያዳምጡ ነበር።
ዛሬም ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በአክብሮት የሚቀበለው ተራው ሕዝብ ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች እና አላስፈላጊ የሆኑ ዝርዝሮች አሉ ብለው ለሕዝቡ ለመናገር ይቸኩላሉ። መሪዎች እንደዚህ የሚሉት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ማብራራት ሲያቅታቸው ነው።
ክርስቶስ የዳዊት ጌታ የዳዊት አምላክ ከሆነ ክርስቶስ እራሱ ደግሞ እንዴት የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል?
ሁልጊዜ እኛ ትክክል ነን የሚሉ የሐይማኖት መሪዎች ይህንን ጥያቄ መመለስ አቅቷቸው ዋጋቸውን ባገኙ ጊዜ ተራው ሕዝብ ደስ አላቸው።
እንደ ሰው ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው ምክንያቱም ወደፊት በሚመጣው የ1,000 መንግስት ውስጥ ንጉስ ሆኖ ይነግሳል።
ነገር ግን የመለኮት ሙላት በውስጡ ስለሚኖር ይህ እርሱን እግዚአብሔር ያደርገዋል።
እኛ ንቁ የሆነ አእምሮ አለን (ይህ ልጅ ነው) ደግሞም የተሰወረ አእምሮም አለን (ይህ አባት ነው)። ንቁ የሆነው አእምሮዋችሁ ከተሰወረው ሕሊናችሁ ጋር ሲከራከር በምታዩ ጊዜ እግዚአብሔር አብ (ማለትም ልዕለ ተፈጥሮአዊው መንፈስ) እና የእግዚአብሔረ ልጅ (ሰው የሆነው ኢየሱስ) ያላቸውን ዝምድና መረዳት ትችላላችኁ። ልብ በሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ወልድ ተብሎ የተጻፈ ቃል የለም።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
“ቀኝ” ኃይልን ወይም ስልጣንን የሚገልጽ ቃል ነው።
ኢየሱስ የተባለው ሰው ተዓምራትን ለማድረግ የእግዚአብሔርን ኃይል በሙሉ ተሞልቶ ነበር።
ዘጸአት 15፡6 አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤ አቤቱ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ፡፡
ማርቆስ 12፡38 ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤
በውድ ልብሶች እየዘነጡ በአደባባይ ሰላምታ የሚወዱና ሃብታም መሆናቸውን በንብረታቸው ብዛት በማሳየት ትኩረት ወደ ራሳቸው ከሚስቡ የሐይማኖት መሪዎች ተጠንቀቁ።
“ፓስተሮች” አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ተጠቅሰዋል። የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚሉ ሰዎች ግን እራሳቸውን “ፓስተር” ብለው ይጠራሉ ሰዎችም ፓስተር እከሌ እያሉ እንዲጠሩዋቸው ግድ ይላሉ። ለምሳሌ ፓስተሩ ስሙ ቶኒ ከሆነ “ቶኒ” ብቻ ተብሎ መጠራቱ አይበቃውም፤ ፓስተር ቶኒ ብላችሁ ጥሩኝ ይላል።
የሚገርመው ነገር ይህ ሰው ሰራሽ ሕግ ለሌሎች አገልግሎቶች አይሰራም። ለምሳሌ ቶኒ የተባለ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ከሆነ “ቶኒ” ብለው ይጠሩታል እንጂ “መምሕር ቶኒ” አይሉትም።
ማርቆስ 12፡39 በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤
የቤተክርስቲያን መሪዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፊተኛው ወንበር ላይ፤ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ከሁሉ የተሻለው ሥፍራ ላይ ተቀምጠው ከሰው ሁሉ እንደሚበልጡ ማሳየት ይወዳሉ። አንድ ቅዱስ ሰው ከምዕመናኑ ወየይም ከጉባኤው በላይ ከፍ ማለቱ የኒቆላውያን ትምሕርት ነው። እግዚአብሔርም ይጠላዋል።
ራዕይ 2፡15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
ማርቆስ 12፡40 የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።
ቤተክርስቲያኖች መበለቶች ገንዘባቸውን ለቤተክርስቲያን እንዲሰጡ ያበረታታሉ። ገንዘቡን የሚቆጣጠሩት የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው። በተቀበሉት ገንዘብ ፈንታ ለመበለቶቹ የሚያደርጉላቸው ነገር ቢኖር ረጅም ጸሎት መጸለይ ነው፤ ይህም ምንም ወጪ አያስወጣቸውም።
ማርቆስ 12፡41 ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤
ሰዎች ገንዘባቸውን ሲሰጡ የሚያስቀምጡበት ሳጥን ነበረ። ይህም ለሃብታሞች ይመቻቸው ነበር፤ ምክንያቱም ብዙ ገንዘብ ሲሰጡ ሰዎች አይተዋቸው ያደንቁዋቸዋል። ኢየሱስ ግን እንደዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች አላደነቀም።
ማርቆስ 12፡42 አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች።
አንዲት ድሃ መበለት ግን በጣም ትንሽ ገንዘብ በመስጠቷ ኢየሱስ አደነቃት።
ማርቆስ 12፡43 ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤
እግዚአብሔር የሰዎችን የስጦታ መጠን አይመዝንም። እግዚአብሔር ስጦታችሁን የሚመዝነው ከምታገኙት ገቢ ላይ በፐርሰንት ነው።
ማርቆስ 12፡44 ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው።
ብዙ ገንዘብ ካላችሁ ብዙ ብር ብትሰጡ ምንም አያስደንቅም፤ ምክንያቱም ከሰጣችሁም በኋላ ብዙ ብር ይተርፋችኋል። ስለዚህ ከሰጣችሁ በኋላ ምንም አይጎድልባችሁም። እግዚአብሔር በዚህ ዓይነቱ መስጠት አይገረምም።
ይህች ሴት ግን ለራሷ ለኑሮ የሚበቃ አልነበራትም፤ ሆንም ለመስጠት ዝግጁ ነበረች። ይህም በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ክብር አሰጥቷታል። እራሷን እስከሚጎዳት ድረስ ነው የሰጠችው። እግዚአብሔርም ተደነቀባት።
ይህ የእውነተኛ እምነት ምልክት ነው።