ማርቆስ 11 የቤተመቅደሱ ካሕናት እውነትን ሳይሆን ገንዘብን ይወዳሉ



የቤተክርስቲያን መሪዎች የአጭር ጊዜ የስልጣን ዘመናቸውንና ገንዘባቸውን ይወዳሉ። ስልጣናቸው ገንዘባችሁን ለመውሰድ ነው። እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል አይቀበሉም።

First published on the 13th of January 2024 — Last updated on the 13th of January 2024

ውርንጫይቱ የእግዚብሔርን ቃል ተሸከመች

 

ማርቆስ 11፡1 ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉቱ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ፦

በዚህ ቃል ውስጥ እንደምናየው ቢታንያ ወደተባለው መንደር በደረሱ ጊዜ ሁለት ደቀመዛሙርት ቀደም ብለው በደብረ ዘይት ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ቤተፋጌ መንደር እንዲሄዱ ተላኩ። ቢታንያ የምትገኘው ከኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ በ2 ማይልስ ርቀት ላይ ነው። ከቢታንያ እስከ ቤተመቅደሱ በእግር ሲኬድ 40 ደቂቃ ያህል ይፈጃል።

ቤተፋጌ ከቤተመቅደሱ ¾ ማይል ያህል ነው፤ ማለትም በእግር ሲኬድ 20 ደቂቃ ይወስዳል።

 

 

ቤተፋጌ ማለት ያልበሰሉ በለሶች ቤት ማለት ነው። በዘመን መጨረሻ ላይ የሚገኙ ልጆች መብሰል አይችሉም ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ልማዶችና አስተምሕሮዎች እስረኛ ሆነዋል።

ልንበስል የምንችለው የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያት ወዳስተማሩት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ስንመለስ ብቻ ነው።

ቢታንያ ማለት የበለሶች ቤት ማለት ነው። አላዛር ከሞት የተነሳው ቢታንያ ውስጥ ነው።

ስለዚህ የአህያ ውርንጫ ከቤተፋጌ ተነስታ የቤተክርስቲያንን ልማዶች ሳይሆን ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ተሸክማ ወደ ቤተመቅደሱ እንድትሄድ መጀመሪያ በደቀመዛሙርቱ መፈታት አለባት። በዘመን መጨረሻ የሚገኙ ልጆችም በዚሁ መንገድ ነው ለትንሳኤ የሚዘጋጁት።

ማርቆስ 11፡2 በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

ውርንጫ የአህያ ግልገል ናት። ይህም በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ከሚገኙና ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች መመለስ የሚፈልጉ ልጆችን ይወክላል።

ይህች ውርንጫ ከቤተክርስቲያን ጋር ታስራለች ምክንያቱም የዳኑ ሰዎች ሁሉ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው አባል መሆን ግዴታ ይመስላቸዋል። ነገር ግን 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች መኖራቸውን አያስተውሉም። ሁሉም የተለያዩ ናቸው ግን እያንዳንዱ እውነት ያለው እኔጋ ነው ይላሉ። ስለዚህ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን የመምረጥ ዕድላችን ከ45,000 አንድ ነው። ይህም የትኛውም ቤተክርስቲያን ዘንድ ትክክለኛ መልስ የለም ማለት ነው።

“ወዲያውም ወደ እርሷ ገብታችሁ” ማለት ውርንጫይቱ ከመንደሩ ዳር አካባቢ ነበረች ማለት ነው (መንደሩ ቤተክርስቲያንን ይወክላል)። ውርንጫይቱ ዳር ላይ ነበረች፤ በቤተክርስቲያን ልማዶች ብዙም አልተሳበችም፤ ነገር ግን እውነቱንም ደግሞ አላወቀችም።

“ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ።” ይህ ውርንጫ በሰው ወይም በቤተክርስቲያን መሪ ጫና ያልተደረገበት ውርንጫ ነው።

ይህም በራሱ ለማሰብ ብቁ የሆነ ሰውን ይወክላል። እንዲህ ዓይነቱ ሰው የቤተክርስቲያን አባላት ያሉትን ሰምቶ አንደ ገደል ማሚቱ አይደግምም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለመስማት ልቡ ክፍት ነው።

የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የጻፉ ደቀመዛሙርት ውርንጫውን ፈተውት ከቤተክርስቲያን አመለካከትና ልማድ ነጻ በማውጠት ወደ ኢየሱስ፣ ወደ ቃሉ ወሰዱት።

ማርቆስ 11፡3 ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው።

ኢየሱስ የአህያውን ባለቤት ሳያስፈቅድ ውርንጫውን በቀጥታ ተቀበለ። ከቤተክርስቲያን ልማዶች ለመላቀቅ ከምታደርጉት ጥረት ማንም እንዲያስቆማችሁ አትፍቀዱ፤ ከዚያ በኋላ ቃሉን እንድትሸከሙ እግዚአብሔር ይጠቀምባኋል።

ማርቆስ 11፡4 ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፥ ፈቱትም።

የእግዚአብሔር መንገድና የእናንተ መንገድ አንድ ሲሆኑ ሁለት መንገዶች ይገናኛሉ።

“በደጅ ውጭ ታስሮ።” ክርስቶስ እውነተኛው በር ነው። ውርንጫው ከቤተክርስቲያን በር ተነስቶ እውነተኛው በር ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ በደስታ ሄደ። ከዚህም የምንረዳው በሎዶቅያውያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ መሆኑን ነው። ቃሉን መሸከም የምትፈልጉ ከሆነ ከቤተክርስቲያናችሁ ተፈታችሁ መውጣት ያስፈልጋችኋል።

ማርቆስ 11፡5 በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ፦ ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው።

ውርንጫው ከቤተክርስቲያን ልማዶች ሲፈታ ሰዎች ይቃወማሉ።

ማርቆስ 11፡6 እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም።

ደቀመዛሙርቱ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ኢየሱስ የተናገራቸውን ማለትም ቃሉን ሰጡ። ሲቃወሙ የነበሩ ሰዎች እውነቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲጠቀስላቸው ምንም መናገር አልቻሉም።

ለምሳሌ፡-

ክሪስማስን ማክበር ለምን ተውክ? ቤተክርስቲያናችን ለዘመናት ስታከብር ኖራለች።

መልስ፡ መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ልደት እንድናከብር አላዘዘንም። ዲሴምበር 25 ቀን የጌታ ልደት የተባለው 274 ዓ.ም በሮማዊው ንጉስ ኦሬልያን አማካኝነት ከተሰየመው “ሶል ኢንቪክተስ” (ድል ነሺው ፀሃይ) ከተባለው ከሮማውያን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን የተወሰደ ነው። ኦሬልያን ይህን ያደረገው የሮማ ጳጳስን አንገት ቆርጦ ከገደለ ከሶስት ቀን በኋላ ነው።

ዩልየስ ቀዳማዊ የተባለ የሮማ ጳጳስ በ350 ዓ.ም ይህን የአሕዛብ በዓል ቀን ተቀበለ። ካቶሊኮች “ማስ” ያከብራሉ፤ ፕሮቴስታንቶች አያከብሩም። ይህም በዓል ክራይስትስ ማስ ተባለ፤ ኋላ ክሪስማስ ሆነ። ስለዚህ የአሕዛብ በዓል እና የካቶሊክ ማስ ነው፤ ሁለቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም። “ሜሪ ክሪስማስ” የሚለው አባባልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

ስለዚህ የሰዎች አመለካከትና አስተሳሰብ ለማይከተልና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል ለሚፈልግ ውርንጫ የቤተክርስቲንን ልማድ ትቶ መሄድ ቀላል ነው።

አህዮች ለሥራ ፈረሶች ደግሞ ለጦርነት ነበር አገልግሎታቸው። የማርቆስ ወንጌል ኢየሱስን እንደ በሬ፣ ነው የሚገልጠው፤ ማለትም አገልጋይ፣ ሸክም ተሸካሚ፤ ሰራተኛ ማለት ነው።

ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ ባመጡት ጊዜ ሃሳባቸው ሥራ እንዲሰራ ነበር። እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ የሚገኙ ልጆች የተገለጠውን ቃል እውነት እንዲያገኙ እና ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት እንዲመለሱ ይጠብቃል። ከዚያም እግዚአብሔር ኢንተርኔትን እየተጠቀሙ እውነትን በዓለም ዙርያ እንዲያሰራጩ ይጠብቃል። ስለዚህ እነርሱም እውነትን ከኢንተርኔት መማር ይችላሉ።

ማቴዎስ 13 ውስጥ ስለ መንግስተ ሰማያት የሚናገሩ 7 ምሳሌዎች አሉ፤ እነዚህም 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

የመጨረሻው ምሳሌ ከባሕር ውስጥ ሁሉን ዓይነት ስለሰበሰበች መረብ ይናገራል።

ማቴዎስ 13፡47 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤

ባሕር እረፍት የሌለውን ሕዝብ ይወክላል። መረቡ ደግሞ የዓለም ሕዝብን ሁሉ የሚደርሰውን የመረጃ መረብ ወይም ኢንተርኔት ይወክላል።

ማቴዎስ 13፡48 በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።

አንዳንድ ዌብሳይቶች ሰዎች እውነትን እንዲማሩ፣ እውነትን እንዲጽፉ እና እውነትን ወደ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዲተረጉሙ ዕድል ይሰጣሉ።

ማቴዎስ 13፡49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥

50 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ወንድም ብራንሐም የገለጣቸውን ሚስጥራት የማይቀበሉ ሰዎች ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ።

እነዚህ ሰዎች በማቴዎስ 25 የተጠቀሱት ሰነፍ ቆነጃጅት ናቸው።

ቆነጃጅት ማለትም ድንግል ሴቶች የዳኑ የቤተክርስቲያን አባላትን ይወክላሉ።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ከሲኦል ድነዋል ግን በቤተክርስቲያን መሪዎች አማካኝነት ተታለው ወደ 3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ በመግባት ይሞታሉ።

ማርቆስ 11፡7 ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም።

እነዚህ ዮሐንስ በራዕይ ምዕራፍ 7 ያያቸው ከታላቁ መከራ የመጡ ብዙ ሕዝብ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ነው የዳኑት ምክንያቱም ታላቁ መከራ ከጀመረ በኋላ ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ተነስቶ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ሊነጥቃት ስለሚወርድ በዚያ ዘመን የማዳን ሥራውን አይሰራም፤ (ሲመጣ ወደ ሰማይ የሚነጥቃቸው በቤተክርስቲያኖች ያልተታለሉትን ልባም ቆነጃጅት ነው)።

ውርንጫው ልብሶችን ብቻ ተቀበለ (እነዚህም ሐይማኖታዊ አስተሳሰቦችን ይወክላሉ) ነገር ግን ሐይማኖታዊ አስተሳሰቦች ከኢየሱስ ማለትም ከእግዚአብሔር ቃል በታች ናቸው። ልብሶች በሙሉ ከኢየሱስ በታች ነበሩ፤ ማለትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደመሆናቸው ወደ እርሱ ወደ ተገለጠው ቃል ይመራሉ። ቃሉን በልባችን መሸከም ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርቶችን ብቻ መቀበል አለብን። ኢየሱስ ብቻ ነው ሊከብር የሚገባው።

ማርቆስ 11፡8 ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር።

ቃሉ (ኢየሱስ) ወደ ቤተመቅደስ (ወደ ክርስቶስ አካል) የሚመለስበት ብቸኛው መንገድ ሰዎች የራሳቸውን ልብስ (የራሳቸውን ጽድቅ) ወስደው ቃሉን የተሸከመው ውርንጫ እንዲራመድበት ሲያነጥፉ ነው። የትኛውም የሰው ጽድቅ በኢየሱስ ፊት ሊቆም አይችልም። የዘንባባ ዝንጣፊ የመቁረጥ መልካም ሥራቸውም ቢሆን በውርንጫው ሊረገጥ መሬት ላይ ተነጥፏል። ከቃሉ መመለስ አንጻር ሲታይ መልካም ሥራችን ምንም ዋጋ የለውም። ከዘላለም አንጻር ሲታይ ሃሳባችን እና ጥረታችን ምንም ዋጋ የለውም። ማድረግ የምንችለው ነገር ቢኖር ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን እየጠቀስን፣ እምነታችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን እያሳየን ቃሉን መሸከም ነው።

64-0823M ጥያቄዎችና መልሶች 1

ቃሉን በሙላት መቀበል የሚችሉ ግን እኔ ስለሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ይቀበላሉ። የሚቀበሉ ሁሉ ለመቀበል ነጻ ናቸው ምክንያቱም ቃሉ እውነት መሆኑ ተረጋግጧል።

የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መገለጥ ምዕራፍ 9 - የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን

… እውነተኛ ነብይ ምንጊዜም ሰዎችን ወደ ቃሉ ይመራል፤ ሕዝቡንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስተሳስራል፤ እውነተኛ ነብይ ለሕዝቡ እኔን ወይም ንግግሬን ፍሩ አይልም፤ ቃሉ የሚለውን እንዲፈሩ ነው የሚነግራቸው።

ደቀመዛሙርቱ ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ ይዘውት ሄዱ፤ ውርንጫውም ኢየሱስን ተሸከመ።

ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስን ሊገልጥልን መጣ፤ እኛም የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል እንሸከማለን።

ማርቆስ 11፡9 የሚቀድሙትም የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤

ይህም በዘመን መጨረሻ ከሙታን የተነሳችዋን ሙሽራ ይወክላል። ባለፉት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔርን ያገለገሉ ሰዎች እንዲሁም ከእኛ በኋላ የሚመጡት እውነተኞቹ የሙሽራይቱ አካላት ሁሉ በአንድ ነገር ይስማማሉ። ክብርና ምስጋና ሁሉ ለኢየሱስ ነው። ክብር የሚገባው ለእርሱ ብቻ ነው። ኢየሱስን ሊተካው የሚችል አንድም ሰው የለም።

እነዚህ ሰዎች በሶስት አካላት የሚያምኑ እና ለአምላካቸው አንድ ስም የሌላቸው የስላሴ አማኞች አይደሉም። ሶስት ሰዎች አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም።

የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ስም አውቀዋል። እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው፤ ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል።

“ሆሳዕና” የሚለው ጩኸት እግዚአብሔር መዳናችንን እንዲገልጠው የሚቀርብ ጥያቄ ነው። በውርንጫው ዙርያ የተሰበሰቡት ሕዝብ ትልቅ ደስታ ውስጥ ነበሩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል ተረድተዋል። እራሳቸውን ማዳን አይችሉም።

ማርቆስ 11፡10 በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።

ዳዊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ነበረ። አሁን ደግሞ ከዳዊት የሚበልጥ ንጉሥ መጥቷል።

“ሆሳዕና በአርያም።” ሰዎች በደስታ ይጠባበቁት የነበረው መዳን የሚመጣው ከላይ ከአርያም ብቻ ነው። ሕዝቡ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ መሆኑን ተቀብለዋል። እርሱ ሁሉን የሚችል አምላክ ነው። ከእርሱ በላይ ማንም የለም። ስለዚህ ስላሴ የለም።

በዘመን መጨረሻ ላይ የሚገኙ ልጆችን የሚወክለው ውርንጫ የስላሴ አማኞች ቤተክርስቲያን አይደለም።

 

የፋሲካ በግ የሚመረጠው የሆሳዕና ዕለት ነው

 

ማርቆስ 11፡11 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።

ኢየሱስ በድል እና በታላቅ ትሕትና ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ይህም ቀን እርሱ ንጉሥ መሆኑ የታወጀበት የሆሳዕና ዕለት ነው።

ዘካርያስ 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

ነገር ግን ማርቆስ በወንጌሉ ውስጥ ኢየሱስ ንጉሥ ስለመሆኑ አንድም ጊዜ አልጠቀሰም ምክንያቱም ማርቆስ ስለ ኢየሱስ የገለጸው አገልጋይ መሆኑን ነው።

በተጨማሪ ማርቆስ ስለ ውርንጫው እናት ምንም አልጠቀሰም። የአህያው እናት የምትወክለው እናት ቤተክርስቲያንን ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ እውነትን የተሸከመችው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የነበረችዋ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ናት።

ማርቆስ እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል እንዳለብን እየነገረን ነው። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የተሸከመችውን ቃል ነው መሸከም ያለብን።

ዘጸአት 12፡3 ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።

ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት መርጦ ይውሰድ።

የእግዚአብሔር ሙላት እንደ እግዚአብሔር አብ ተገልቶ በክርስቶስ ውስጥ አደረ። እግዚአብሔር ያደረበት ኢየሱስ የተባለው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ወልድ” ብሎ አይናገርም ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ እግዚአብሔር ስጋ እና አጥንት ያለው ሰው አይደለም።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ቤተመቅደሱ የእግዚአብሔር አብ ቤት ነበር።

 

ኢየሱስ ሐይማኖተኞቹን ገንዘብ ለዋጮች ሶስት ጊዜ ነው ከቤተመቅደስ ያስወጣቸው

 

ኢየሱስ በመጀመሪያው ምጻቱ በስግብግብነታቸው እና በንግዳቸው የአይሁድን ቤተመቅደስ ሲያረክሱ የነበሩ ገንዘብ ለዋጮች አባረራቸው። የገንዘብ ፍቅር አይሁዶችን እና በዚህ ዘመን የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች አበላሽቷቸዋል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ … ስለማታውቅ፥

የዘመናችን ቤተክርስቲያኖች በንግድ ሥራ ተጠምደዋል።

ነገር ግን የማያውቁት ብዙ ነገር እንዳለ አያውቁም።

ዮሐንስ 2፡16 ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።

በአገልግሎቱ መጀመሪያ፣ በመጀመሪያው ፋሲካ ኢየሱስ ሐይማኖተኞቹን ገንዘብ ለዋጮች ከቤተመቅደሱ አስወጥቷቸው ነበር።

የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ንጉሥ ነው ተብሎ ስሙ ታወጀ፤ ከዚያም የፋሲካ በግ ሆኖ ወደ አባቱ ቤት ወደ ቤተመቅደሱ ገባ።

ማርቆስ ስለ ኢየሱስ የጻፈው አገልጋይነቱ ላይ ትኩረት በማድረግ ነው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮቹን ከቤተመቅደሱ ስለ ማባረሩ አልጠቀሰም።

ማቴዎስ ኢየሱስ ንጉሥ ስለመሆኑ ነው አጉልቶ የጻፈው፤ ስለዚህ ማቴዎስ የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደሱ ስለ ማባረሩ ጽፏል። የሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ ሲያባርር ሁለተኛው ነው።

ማቴዎስ 21፡7 አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም።

ማቴዎስ 21፡11 ሕዝቡም፦ ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ለሕዝቡ አስተዋውቆ ስለነበረ ሕዝቡ ኢየሱስን ሲያዩት ታላቅ ነብይ መሆኑን ወዲያው መረዳት ችለዋል።

በተለይም ደግሞ ግልጽ የሆነላቸው ዮሐንስ ኢየሱስ ከመጥምቁ ዮሐንስ እንደሚበልጥ ሲነግራቸው ነው።

ማቴዎስ 21፡12 ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦

ማርቆስ ኢየሱስ ንጉስ ተብሎ ታውጆ ወደ ኢየሩሳሌም ከገባ በኋላ የሆሳዕና ዕለት በገንዘብ ለዋጮች ላይ የገለጠውን ቁጣ አልጻፈም፤ ለማቴዎስ ትቶለታል።

ማርቆስ በቀጣዩ ቀን ማለትም ሰኞ ዕለት ኢየሱስ አገልጋይ መሆኑን የሚገልጡ ድርጊቶችን በማመልከት ጽሑፉን ይቀጥላል።

ማርቆስ 11፡12 በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ።

“በማግሥቱም” የሚለው ከሆሳዕና ቀጥሎ የነበረው ቀን ስለሆነ ሰኞ ነው።

ኢየሱስ ራበው። ያለ እረፍት በትጋት የሚሰሩ ሰዎች ሁሉ ይርባቸዋል። ሰውነታቸው እንዳይዝል ምግብ መብላት ያስፈልጋቸዋል።

ማርቆስ 11፡13 ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።

ቢታንያ ማለትም የበለስ ቤት አላዛር ከሞት የተነሳበት መንደር ነው።

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት መጨረሻ ላይ እርሱ እራሱ እንዲሁም የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት ይነሳሉ።

በዳግም ምጻቱ ጊዜ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሞት ይነሳሉ።

ኢየሱስ በለስ ሲያይ ትንሳኤን ያስባል።

አይሁድ ግን ኢየሱስን ላለመቀበል ወስነዋል። አይሁድ ለብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ አልተዘጋጁም ነበር። የአይሁድ ዛፍ አንዳችም የበለስ ፍሬ አልተገኘባትም።

በዳግም ምጻቱ ጊዜ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ለአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ዝግጁ አትሆንም። በዘመን መጨረሻ ላይ ስለምትገኘው ቤተክርስቲያን በተመለከተ መልካም ነገር የሚናገር አንድም ትንቢት ወይም አንድም ምሳሌ የለም።

ማርቆስ 11፡14 መልሶም፦ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።

አይሁዶች እንደ ሕዝብ ተፈርዶባቸዋል። በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት የመጣላቸውን ጉብኝት አልተቀበሉም። ኢየሱስ ይህን ቃል የተናገረው በ33 ዓ.መ ነበር፤ በ70 ዓ.ም ሮማውያን ቤተመቅደሱን እንዲሁም ኢየሩሳሌምን አፈረሱ። አይዶች ከሃገራቸው ተሰደው በዓለም ዙርያ ተበተኑ፤ ለጸጋው ወንጌልም ባዕድ ሆኑ።

ስለዚህ በመጨረሻ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከሙታን በሚነሱ ጊዜ አይሁዶች ምንም አይጠቀሙም። ከዚያ ይልቅ ከአይሁድ ሕዝብ መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት በ3½ ዓመቱ ታላቅ መከራ ውስጥ ይገደላሉ።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

ሰነፎቹ ቆነጃጅት የዳኑ ነገር ግን እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የስቅለት አርብ፣ እና ሰባት የመከራ ዓመታት በመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶች የታለሉ ክርስቲያኖች ናቸው። እነዚህ ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ትንሳኤ ያመልጣቸዋል። የእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም በር የሆነው ኢየሱስ ይዘጋባቸዋል ምክንያቱም ብዙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ክፍል መረዳት አይችሉም። ስለዚህ ወደ ታላቁ መከራ ሰቆቃ ውስጥ ገብተው ሁላቸውም ይሞታሉ።

ማርቆስ 11፡15 ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤

የቤተክርስቲያን መሪዎች ቄሶች፣ ሪቨረንዶች፣ ጳጳሳት እና ፓስተሮች ናቸው። እነዚህ መሪዎች ቤተክርስቲያንን በመቆጣጠር ክርስትናን ንግድ አድርገውታል። ብዙ ክርስቲያኖች ለጌታ ዳግም ምጻት ዝግጁ ያልሆኑበት ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው። መሪዎች ትልቁ ትኩረታቸው አስራት መሰብሰብ ሆኗል።

ኢየሱስ ይህንን የገንዘብ ፍቅር ቤተመቅደሱ ውስጥ ባየ ጊዜ በጣም ከመቆጣቱ የተነሳ በቀጣዩ ቀን ማለትም ሰኞ ዕለት ገንዘብ ለዋጮችን በጂራፍ ገርፎ ከቤተመቅደስ አባረራቸው። ከዚያ በፊት የሆሳዕና ዕለትም እንዲሁ አድርጎ ነበር።

ወንጌል የሚሰራጨው በእምነት እንጂ በዘመናዊ የንግድ ስልቶች አማካኝነት አይደለም።

ስለዚህ ኢየሱስ በተከታታይ ለሁለት ቀናት ገንዘብ ለዋጮችን እየገረፈ አስወጣ።

ገንዘብ በማሳደድ ለተጠመዱ የቤተክርስቲያን መሪዎች ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያቸው ነው።

 

አሜሪካ ክርስትናን ወደ ትልቅ ንግድ አደረገችው

 

በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ከአፉ አውጥቶ ይተፋታል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

በዚህ ዘመን ቲቪ ላይ የሚቀርቡ ወንጌላውያን ሁልጊዜ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚሸጡት ነገር አላቸው።

ቤተክርስቲያን ትልቅ የንግድ መናኸሪያ ሆናለች። ገንዘብ ያላቸውም እውነትን መግዛት ይችላሉ።

ለድሆች ግን ወዮላቸው። እውነተን የሚገዙበት በቂ ገንዘብ የላቸውም። እና ምን ሊሆኑ ነው?

ማርቆስ 11፡16 ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም።

ቤተመቅደሱ ውስጥ አንዳችም ንግድ አልተፈቀደም ነበር።

ዛሬ ግን ሰባኪዎች መድረክ ላይ ቆመው አስራት የመክፈልን አስፈላጊነት በአጽንኦት ይናገራሉ።

ተጋብዞ የመጣ ሰባኪ ወይም ወንጌላዊ በቂ ገንዘብ ካላገኘ ሌላ ጊዜ አይጋበዝም። ገንዘብ መሰብሰቢያ ኮሮጆዎች አዲስ ኪዳን ውስጥ አልተጠቀሱም፤ አሁን ግን በየቤተክርስቲያን ውስጥ የግድ አስፈላጊ ሆነዋል። አንዳንዶች እንደውም ቅርጫት ይጠቀማሉ። ጌባኤው የተሳካ መሆን አለመሆኑ የሚመዘነው በተሰበሰበው ገንዘብ ብዛት ነው። በቲቪ የሚቀርቡ ወንጌላውያን ያላቸው ጊዜ ሰላሳ ደቂቃ ሲሆን በዚያ ሰዓት ውስጥ ገንዘብ የሚሰሩበት ዘዴ አላቸው። ሁሌም የሚሸጡ መጻሕፍትና ዲቪዲዎችን ያቀርባሉ። ገንዘብ ከከፈላችኋቸው ወደ መንግስተ ሰማያት የምትገቡበትን መንገድ ያሳዩዋችኋል።

ማርቆስ 11፡17 አስተማራቸውም፦ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።

በዚህ ዘመን ለመንፈሳዊ ነገር ቦታ የሚሰጥ ሰው ጠፍቷል። የሙዚቃ ጩኸት እና በንግድ ቤቶች እንዲሁም በመዝናኛ ቦታዎች ውስጥ ያለው ዓይነት ቦግ ብልጭ የሚል መብራት፣ የመድረክ ማስዋብያዎች ብቻ ናቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሞሉት።

ማርቆስ 11፡18 የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።

የኢየሱስ አስትሕሮዎች ከተለመዱ የቤተክርስቲያን ትውፊቶች የተለዩ ነበሩ። ስብከቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ነገር ግን ስለ ገንዘብ ትኩረት ሰጥቶ አያውቅም። ከዚህም የተነሳ የሐይማኖት መሪዎች ሊገድሉት ፈለጉ። ቤተክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል ማለትም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ሊያጠፉ ይፈልጋሉ።

ማርቆስ 11፡19 ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።

ማታ ማታ። በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያኖችን ትቶ ይወጣል። በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ነው የሚቆመው (ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ቃሉን ሳይሆን የፈለጉትን ነው የሚያምኑት)።

ማርቆስ 11፡20 ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።

ማክሰኞ ዕለት ጠዋት በለሷ ደረቀች። የአይሁድ ሕዝብ ልክ እንደ በለሷ ዓይነት ፍርድ ይጠብቃቸዋል። በለሷ እስራኤልን ትወክላለች።

ማርቆስ 11፡21 ጴጥሮስም ትዝ ብሎት፦ መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው።

ጴጥሮስ የተናገረው ነገር ለማንም ሰው በግልጽ የሚታይ ነው። የእግዚአብሔር ቃል (ማለትም ኢየሱስ) የፈረደበት ነገር ሁሉ ይደርቃል።

ማርቆስ 11፡22 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ።

የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረውን ሰምተን ማመን አለብን። በዘመናችን ያለችዋን ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ከፈረደባት ከቤተክርስቲያናችን ጋር ተጣብቀን መቅረታችን ምንም አይጠቅመንም።

 

አንድ ቀን እምነት ተራራን ነቅሎ ባሕር ውስጥ ይጥለዋል

 

ማርቆስ 11፡23 እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።

ይህ እስከዛሬ ሆኖ አያውቅም።

ነገር ግን ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ በ3½ ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ሲገለጡ በተፈጥሮ ላይ ታላቅ ስልጣን ይኖራቸዋል። እነሱ ሲመጡ ይህ ቃል ይፈጸም ይሆናል።

የዓመጽ ሰው ማለትም የመጨረሻው ፖፕ በሜዲተራንያን ባሕር ላይ ብዙ የጦር መርከቦች በመላክ አስራኤል ላይ ጥቃት ይሰነዝራል፤ በዚያ ጊዜ ሙሴ እና ኤልያስ ተራራ ነቅለው ወደ ባሕር ይወረውራሉ። ይህም ድርጊት የሚፈጥረው ታላቅ ሞገድ የጦር መርከቦችን ሁሉ ያሰጥማቸዋል። ይህ ዓይነቱ ታላቅ ኃይል በተፈጥሮ ላይ ሲገለጥ 144,000ዎቹ አይሁድ ኢየሱስን እንደ አዳኝ እስኪቀበሉና በመንፈስ ቅዱስ እስኪሞሉ ድረስ ከሞት ይጠብቃቸዋል።

ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ በተነሳ ጊዜ ሎሳንጀለስ ከባሕር በታች እንደምትሰጥም ወንድም ብራንሐም ትንቢት ተናግሯል። በሎሳንጀለስ አካባቢ ካሉ ተራሮች አንዱ ወደ ባሕር ሊሰጥም ይችላል።

ማርቆስ 11፡24 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።

በጸሎት የጠየቅነውን ልናገኝ እንችላለን፤ ነገር ግን ጸሎታችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር መስማማት አለበት። ስለዚህ በዘመን መጨረሻ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው። እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ ምድር ላይ በሕይወት የምትኖረዋ ሙሽራ ወንድም ብራንሐም ገልጦ በኢንተርኔት ላይ ያስቀመጠውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እንድታሰራጭ ይፈልጋል፤ በዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት አማካኝነት የዘመን መጨረሻ ልጆች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ ነበረው ወደ ሐርያዊ አባቶች እምነት ይመለሳሉ።

 

ይቅር የማለት አቅም ያስፈልጋል

 

ማርቆስ 11፡25 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።

በዚህ ስሕተት በነገሰበት ዘመን ይቅርታ በጣም አስፈላጊ ነው። ሰዎች ብዙ ሊበድሉንና እምነታችንንም ሊያጣጥሉ ይችላሉ ምክንያቱም የሚያደርጉትን አያውቁም። ነገር ግን ይህ ዓይነቱ ከሰዎች የሚመጣብን ተቃውሞ ስለሚያጠነክረንና የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለማወቅ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንመረምር ስለሚያነሳሳን ይጠቅመናል። ተቃውሞ በሌለበት እምነታችን ስር ሊሰድድ አይችልም። ስለዚህ ተቃዋሚዎቻችን እኛን በማጠንከርና እምነታችንን በማጽናት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

በእምነታችን እናድግ ዘንድ የተቃዋሚዎቻችን አስተዋጽኦ ያስፈልገናል።

ማርቆስ 11፡26 እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።

ጠላቶቻችንን ይቅር ማለት አለብን። ከሚቃወማችሁ ኃይል ጋር ስትታገሉ ብቻ ነው ሥራ መስራት የምትችሉት። ስለዚህ እውነትን የሚቃወሙ ሰዎች ለእድገታችሁ ይተቅሙዋችኋል። ትግል የእድገት ሕግ ነው። ተቃዋሚዎቻችሁ ይህ የተሰጣቸው ሥራ ስለሆነ አትፍረዱባቸው። ይቅር በሏቸው።

ጠላቶቻችሁ ለእናንተ እድገት አስተዋጽኦ ማድረጋቸው የሚገለጥላችሁ መጨረሻ ላይ ነው።

 

መጥምቁ ዮሐንስ እና ዳንኤል ኢየሱስ የሚገለጥበትን ትክክለኛ ዘመን አሳዩ

 

ማርቆስ 11፡27 ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው።

ይህ የሆነው ማክሰኞ ዕለት ነው፤ ኢየሱስ የሞተው ደግሞ ሐሙስ ነው።

የዚያ ዘመን የቤተክርስቲያን መሪዎች አጥብቀው ይቃወሙ የነበሩት ምንድነው? የሰበከው ስብከት አይደለም። ትምሕርቶቹ ላይ አንድም ነቀፋ አላገኙባቸውም።

የተቆቱት ባደረገው ነገር ነው። ለሁለት ቀናት በተከታታይ የገቢ ምንጫቸው ላይ ጥቃት ሰነዘረባቸው። የሐይማኖት መሪዎች ትልቅ ውድቀት ገንዘብን መውደዳቸው ነው።

ገንዘባቸውን የሚያስጠብቅላቸውና የስልጣን ዘመናቸውን የሚያራዝምላቸው ሐይማኖታዊ ሥርዓት አበጅተዋል። ሃብትና ስልጣንን በጣም ይወዳሉ። የቤተክርስቲያን ፓስተሮች ገንዘባችሁን ሃብታችሁን የመውሰድ ስልጣን አላቸው። ኢየሱስ በዚህ ስልጣናቸው ላይ ነው ስጋት የጣለባቸው፤ ስለዚህ ሊገድሉት ፈለጉ።

ማርቆስ 11፡28 እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።

የወጣላቸው ግብዞች። ግፍ ሊፈጽሙ እየተዘጋጁ ጻድቅ ሆነው ሊታዩ ይፈልጋሉ። የሚያስተምረውን ትምሕርት አልነቀፉም ምክንያቱም ትምሕርቶቹን በመጽሐፍ ቅዱሰ ሲመዝኑ እንከን ሊያገኙ አልቻሉም።

በመጀመሪያው ፋሲካ ወቅትም ቤተመቅደሱን ባጸዳ ጊዜ ይህንኑ ጥያቄ ጠይቀውታል።

ዮሐንስ 2፡15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

16 ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።

ዮሐንስ 2፡18 ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት።

በምን ስልጣን ነው እነዚህን ነገሮች ያደረገው?

ኢየሱስ ንግዳቸውን የገቢ ምንጫቸውን ስላቃወሰባቸው ሊገድሉት እንደፈሉ አውቋል።

ስለዚህ አስጠነቀቃቸው። ቢገድሉት በሶስት ቀን ተመልሶ ከሞት እንደሚነሳ ነገራቸው። ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ። ከዚያ እሑድ ሌሊት ፀሃይ ሳትወጣ በፊት ከሞት ይነሳል።

ኢየሱስ የሚያሳያቸው ይህ ምልክት የትንሳኤው ምልክት ነው። የትኛውም የሐይማኖት መሪ ተመልሶ በማይሞት በከበረ አካል ከሞት ተነስቶ አያውቅም።

ኢየሱስ መሲሁ ለመሆኑ ማረጋገጫ ይህ ነው።

ዮሐንስ 2፡19 ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።

ስለዚህ ቤተመቅደሱን ሲያጸዳው የንግድ ሥራቸውን የገቢ ምንጫቸውን ስላቋረጠባቸው ጠሉት። ነገር ግን የሕዝቡን ገንዘብ እየወሰዱ በቤተመቅደሱ ገንዘብ በመለወጥ ሕዝቡን እያጭበረበሩ እንደነበር ሁላቸውም ያውቃሉ። የቤተመቅደሱን እንስሳት ለመስዋእት እንዲገዙ ሕዝቡን እያስገደዱዋቸው ነበር። ሕዝቡ ለመስዋእት ይዘው የሚያመጡዋቸውን እንስሳት ለመስዋእት ብቁ አይደሉም ብለው እየፈረዱባቸው ሕዝቡ ከእነርሱ እንዲገዙ ያስገድዷቸዋል። የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ሌቦችና ስግብግቦች ነበሩ።

ማርቆስ 11፡29 ኢየሱስም፦ እኔም አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፥ እናንተም መልሱልኝ፥ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ።

የኢየሱስ ስልጣን መሲህ መሆኑ ነው።

ዳንኤል ነሕምያ በኢየሩሳሌም ዙርያ ቅጥሩን ከሰራበት ጊዜ አንስቶ እስከ መሲሁ መገለጥ ድረስ ለአይሁዶች 70 ሱባኤዎችን ወይም 70 x 7 = 490 ቀናት (490 ዓመታት) ቀጥሮላቸዋል።

ዳንኤል 9፡24 … በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።

በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ይወክላል።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመት 360 ቀናት ስለሆነ እያንዳንዱ 70 ዓመት በአሕዛብ አቆጣጠር 69 ዓመት ነው ምክንያቱም በእኛ አቆጣጠር አንድ ዓመት 365.24 ቀን ነው።

ስለዚህ 490 /70 = 7 በአሕዛብ አቆጣጥር መሰረት 7 ዓመታት እንቀንሳለን።

በ490 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ውስጥ 490 – 7 = 483 የአሕዛብ ዓመታት አሉ።

መሲሁ ግን በ69 ሱባኤ ውስጥ ነው የሚመጣው፤ ማለትም ከሰባ ሱባኤዎች ላይ 7 ዓመታት እንቀንሳለን።

483 – 7 = 476ዓመታት

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

7 ሱባኤ + 62 ሱባኤዎች እስከ መሲሁ ድረስ።

ነሕምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር የሰራው በ446 ዓመተ ዓለም ነበር። ኢየሱስ መሲህ ሆኖ የተጠመቀው በ30 ዓ.ም ነው።

በዚህ መሃል ያለፉ ዓመታት 446 + 30 = 476 እስከ ኢየሱስ ጥምቀት ድረስ።

ስለዚህ ኢየሱስ 30 ዓመት ሞልቶት የተጠመቀው ልክ ዳንኤል በትንቢት የተናገረው ዓመት ሲፈጸም ነው።

ዳንኤል የተነበየው ዓመት ሲፈጸም መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ የዓለምን ሐጥያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው ብሎ አስተዋወቀ። በዚህም ኢየሱስ መሲህ መሆኑ ተገለጠ።

የሐይማኖት መሪዎች ከኢየሱስ ጋር የሚከራከሩት ይህ ሁሉ ከሆነ 3½ ዓመታት በኋላ ነው።

ሕዝቡ ዮሐንስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነብይ መሆኑን አምነው ተቀብለዋል። ዮሐንስን ከልብ ቢያደምጡት ዮሐንስ ማጥመቅ ሲጀምር መሲሁ ሊገለት ጊዜው መቅረቡን መረዳት ይችሉ ነበር።

ማርቆስ 11፡30 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ አላቸው።

ኢየሱስ የጠየቃቸው ጥያቄ ትርጉሙ እንዲህ ማለት ነበር፡- ዮሐንስ እውነተኛ ነብይ ነውን?

ማርቆስ 11፡31 እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ነው ብንል፦ እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤

የሐይማኖት መሪዎች “አዎ” ዮሐንስ እውነተኛ ነብይ ነው ብለው ቢመልሱ ዘመኑም እንደሚመሰክረው ዮሐንስ መሲሁን ገልጦታል ማለት ይሆናል።

ማርቆስ 11፡32 ነገር ግን፦ ከሰው ነው እንበልን? አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።

የሐይማኖት መሪዎቹ ዮሐንስ ተራ ሰው ነበረ እንዳይሉ ሕዝቡ ይቃወሙዋቸዋል ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስ ነብይ ነው ብለው አምነዋል።

ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎች እውነቱን ለመቀበል ፈርተው አናውቅም አሉ።

ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለዘመን መጨረሻ በተላከው ነብይ በዊልያም ብራንሐም መገለጣቸውን ለቀመበል ይፈራሉ። ስለዚህ ከመቀበል ይልቅ ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ምን ማለት እንደሆኑ አናውቅም ብለው ለጉባኤዎቻቸው መናገርን ይመርጣሉ። ወይም ደግሞ ሲያሰኛቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በብዙ በተለያዩ የተሳሳቱ መንገዶች ይተረጉሙዋቸዋል። በዚህም ሆነ በዚያ ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን ሳያውቁ እንዲኖሩ ያደርጋሉ።

ማርቆስ 11፡33 ለኢየሱስም መልሰው፦ አናውቅም አሉት ኢየሱስም፦ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።

በመጀመሪያው ምጻቱ መጨረሻ ላይ የሐይማኖት መሪዎች ለእርሱ መንገድ ሊጠርግለት የመጣው የነብዩ የዮሐንስ አገልግሎት ዓላማው ምን እንደነበር እንዳልገባቸው ገለጹ።

ከዚያ ቀጥለው ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን ገደሉ።

ዛሬም ዳግም ምጻቱ ሲቃረብ የቤተክርስቲያን መሪዎች ብቸኛው እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም እያሉ ናቸው። ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እና 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች በሞሉበት በአሁኑ ዘመን ፓስተሮችም “እውነት” ምን እንደሆነ ማወቅ ተስኗቸዋል።

ስለዚህ ኢየሱስ ምንም ሳይገልጥላቸው ሄደ። እነርሱም የተገለጡትን ሚስጥራት ሳያውቁ ቀሩ።

ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ እነርሱ እና እነርሱን የተከተሏቸው ሰነፍ ቆነጃጅት ወደ ታላቁ መከራ ጨለማ ውስጥ ይገባሉ። ይህም አስፈሪ ጊዜ የእግዚአብሔር ቀን ተብሎ ይጠራል።

አሞጽ 5፡20 እግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23