ማርቆስ 8 - አገልጋዮች ወንጌሉን ለአሕዛብ ያደርሳሉ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ አይሁዶች አላምን ብለው እምቢ ያሉትን ከሚያምኑ አሕዛብ መካከል የሆነችዋን ቤተክርስቲያን ለሰባት ዘመናት ትኩረት አድርጎባታል።
- ክርስቶስ በአሕዛብ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራውን ሥራ አስቀድሞ ገለጠ
- ልክ እንደ ቤተክርስቲያን አይሁዶችም በ7 ዘመናት ውስጥ አልፈዋል
- ኢየሱስ አሕዛብን ለማግኘት ገሊላ ውስጥ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ተመላልሷል
- የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሊያርሙ ይፈልጋሉ
- እንጀራ አስተምሕሮን ይወክላል
- ዓይነ ስውር ሰው የአሕዛብ ምሳሌ ነው
- ኢየሱስ የሚሰራው ከግለሰቦች ጋር ብቻ ነው
- የክርስቲያን አገልጋዮች መሰረታዊ መመሪያ
ክርስቶስ በአሕዛብ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራውን ሥራ አስቀድሞ ገለጠ
ማርቆስ ኢየሱስን እንደ ታላቁ አገልጋይ አድርጎ ነው የገለጠው። ስለዚህ እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል እንደሚገባን ማርቆስ ብዙ ያስተምረናል።
ይህ ምዕራፍ ኢየሱስ ወደፊት በአሕዛብ መካከል በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እንዴት እንደሚሰራ ይገልጻል።
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ኢየሱስ በአይሁዶች መካከል እየተመላለሰ ቢሆንም እንኳ የሚያደርጋቸው ድርጊቶች ግን ኋላ ሊመጡ ባሉት የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በአሕዛብ መካከል ሊሰራ ያሰበውን ሥራ የሚያሳዩ ናቸው።
ማርቆስ 8፡1 በዚያ ወራት ደግሞ ብዙ ሕዝብ ነበረ የሚበሉትም ስለሌላቸው ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፦
አሕዛብ አረማውያን ስለነበሩ ይድኑ ዘንድ ነፍሳቸውን የሚመግቡበት እውነተኛ አስተምሕሮ አልነበራቸውም።
ነገር ግን በዓለም ዙርያ ወንጌልን መስማት የሚያስፈልጋቸው እጅግ ብዙ አሕዛብ ያሉ ሲሆን እነርሱም በየሃገሩ እንዲሁም በ2,000 ዓመታት ውስጥ ተበታትነው ይገኛሉ።
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠራቸው። እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ በመምጣታቸው መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቆ መከተል አስፈላጊ መሆኑን እያሳዩ ናቸው፤ ምክንያቱም የወደፊቷን የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ መሰረት መጣል የእነርሱ ኃላፊነት ነበር። አስተምሕሮ በሙሉ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚያሳይ መሆን እና ወደ ኢየሱስ የሚጠቁም መሆን አለበት። ወደ ሌላ ሰው መጠቆም በጀመርን ጊዜ ነገሮች ይበላሻሉ። ትኩረት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው መሆን ያለበት።
እርሱን፣ ክርስቶስን ስሙት።
ማርቆስ 8፡2 ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤
ሶስት ቀን የሚለው ትልቅ ትርጉም አለው። ሶስት ዘመናት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበረ እውነት ሲጠፋ አይተዋል። ስለዚህ አራተኛው ዘመን አስጨናቂው የጨለማ ዘመን ነበረ።
ከዚያ በኋላ በሶስት የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እውነት ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያን መጣ።
በመጀመሪያ በሐዋርያት አገልግሎት ምክንያት የአሕዛብ ቤተክርስቲያን እውነቱን ይዛ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በቀጣዮቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቀስ በቀስ እውነት ጠፍቶ በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በጣም አሰቃቂ ወደ ሆነ ጨለማ ውስጥ ገባች።
ከዚያ በኋላ በመጨረሻዎቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋትን የአስተምሕሮ ምግብ በማቅረብ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወነደበረው እውነት እየመለሳት ነው።
በአምስተኛው ዘመን የተነሳው ማርቲን ሉተር በእምነት ብቻ መዳን የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ። ከዚያ ወዲያ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ተተርጉሞ እስከ 1769 ዓ.ም ድረስ ለ160 ዓመታት ተጣርቶ ታተመ።
በስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጆን ዌስሊ ቅድስና እና የወንጌል ስርጭትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። ይህም ለታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን መሰረት ጥሏል፤ በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ውስጥ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ዙርያ ሁሉ ተዳርሷል።
የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው እንዲመጡ ሲያደርግ ዊልያም ብራንሐም ደግሞ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት መገለጥ ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አምጥቷል፤ የነዚህም ሚስጥራት መገለጥ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት ይመልሰናል።
ስለዚህ ወሳኞቹ ዘመናት እውነት ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ የመጣባቸው ሶስቱ የመጨረሻ ዘመናት ናቸው። በተለይ ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉው እውነት ወደ ቤተክርስቲያን የተመለሰበት የመጨረሻው ዘመን እጅግ ወሳኝ ነው።
ማርቆስ 8፡3 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ አላቸው።
እነዚህ ፍጥረታዊ አይሁዳውያን ከቤታቸው ብዙ ርቀው መጥተዋል፤ ስለዚህ የሚበሉትን ምግብ ከቤታቸው እንደሚያገኙ ተስፋ ማድረግ የለባቸውም። መንፈሳዊያኑ አይሁዶች ማለትም ቤተክርስቲያን የአሕዛብ ባዕድ እምነት ውስጥ ገብተው ከእውነት ብዙ ርቀው ነበረ፤ ስለዚህ በራሳቸው ቤት (በቤተክርስቲያኖች) ውስጥ እውነትን እናገኛለን ብለው ተስፋ ማድረግ የለባቸውም፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል ርቀው ሄደዋል። በተለያ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ እራሱ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው የቆመው። ሰው ሰራሽ ስሕተቶች እና እንደ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ እና የስላሴ ትምሕርት የመሳሰሉ ባዕድ እምነቶች ቤተክርስቲያንን አጥለቅልቀዋታል።
ማርቆስ 8፡4 ደቀ መዛሙርቱም፦ በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።
ምድረ በዳ። ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች እንዲሁም ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሉ። በዚሁ ሁሉ ግርግር መሃል አንድ ሰው ዕድሜውን ሁሉ እውነትን ቢፈልግ ግራ ሲጋባ ይኖራል እንጂ አያገኝም። ይህ መንፈሳዊ ምድረ በዳ ነው።
“ሰው እነዚህን ሰዎች እንጀራ አግኝቶ ማጥገብ ይችላልን?” ማንም አይችልም።
ሉተር የተወሰኑ ስሕተቶችን አርሞ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ አደረገ።
ዌስሊ ስለ ቅድስና እና ስለ ወንጌል ስርጭት ተጨማሪ እውነቶችን ገለጠ።
የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን አመጣ ግን በ1917 በዲኖሚኖሽን ተከፋፍሎ ዓላማውን ሳተ።
ወንድም ብራንሐም እውነትን መልሶ አመጣ፤ ነገር ግን ተከታዮቹ የእርሱን ንግግር ከእግዚአብሔር ቃል በላይ አስበልጠው እርሱን የሰው ልጅ ነው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው አሉ። የእርሱን ንግግሮች አሳስተው በመተርጎም ያስተማረውን ትምሕርት ከ100 በላይ የተለያዩ ትምሕርቶች አድርገው አዘጋጅተዋል። ስለዚህ መንፈሳዊው ምድረ በዳ በሜሴጅ ተከታዮችና ራሳቸውን በሾሙ ፓስተሮቻቸው መካከል ተስፋፍቷል። አዲስ ኪዳን ፓስተርን የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንድናደርግ አላዘዘንም።
አመራር ሊሰጥ የሚችል አንድ ሰው ብቻ አለ፤ እርሱም ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ የወንድም ብራንሐምን ንግግሮች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መልሰን በመውሰድ እምነታችን ትክክል መሆኑን ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ብቻ በማመሳከር ማረጋገጥ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እንዴት እንደምንመለስ ስለሚያሳየን ቃሉን በመጥቀስ ብቻ ነው ትክክለኛ ምሪት የምናገኘው። ሐዋርያት የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት ጽፈዋል።
ማርቆስ 8፡5 እርሱም፦ ስንት እንጀራ አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም፦ ሰባት አሉት።
እንጀራ የአስተምሕሮ ምሳሌ ነው። ለአሕዛብ የተዘጋጁ ሰባት እንጀራዎች አሉ። እያንዳንዱ እንጀራ ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ተመድቧል።
እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ለዘመኑ ከተላከው መልእክተኛ ጋር የተመደበለት ትኩስ እንጀራ አለው። መልአክ ብለን የተረጎምነው “አንጌሎስ” የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉሙ መልእክተኛ ማለት ነው።
ማርቆስ 8፡6 ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘ። ሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፥ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ለሕዝቡም አቀረቡ።
ባላችሁበት ተቀመጡ። በተተከላችሁበት አብቡ። አሕዛብ በተተከሉበት ዘመን ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ ታዘዋል። በየትኛውም ሁኔታ፤ በመልካም ሁኔታም ይሁን በመከራ ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን ማገልገል አለባቸው። እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን እንዲሄድበት የተመደበለት አቅጣጫ አለው። አሁን የምንኖርበት የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንከን የሌለበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማመን አለበት እንዲሁም ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ አለብን።
ኢየሱስ ለሕዝቡ ምንም እንጀራ አልሰጣቸውም።
ኢየሱስ እንጀራውን ቆረሰው፤ ይህም ማለት ሰዎች መረዳት ማስተዋል እና ወደ ውስጣቸው ማስገባት እንዲችሉ የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት ገለጠ፤ አካፈለ ማለት ነው። እንጀራውን ቆርሶ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀመዛሙርቱም ለሕዝቡ አቀረቡላቸው። የእግዚአብሔር ቃል እውነት ከኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ፤ ከደቀመዛሙርቱ ደግሞ ወደ ሕዝቡ ደረሰ።
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን አስተማረ። ኋላም ጳውሎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ እና ይሁዳ ደቀመዛሙርት ሆኑ። እነዚህ ደቀመዛሙርት የአዲስ ኪዳንን አስተምሕሮ ለሕዝቡ አብራሩ፤ ሕዝቡም እነዚህን ደቀመዛሙርት አደመጧቸው። ቃሉ ብዙውን ጊዜ እንደ ምሳሌ በሚመስል አጻጻፍ ሲሆን የተጻፈው መረዳት የምትችሉት የምሳሌውን ትርጓሜውን ስታገኙ ነው። እነዚህን ጠለቅ ያሉ ሚስጥራት ለመረዳት ሕዝቡ ለየዘመናቸው የተመደበ መልእክተኛ ያስፈልጋቸው ነበር።
ደቀመዛሙርቱ አዲስ ኪዳንን ለሕዝቡ ያቀረቡት በተጻፈ ቃል መልክ ነበር።
ሕዝቡም ደቀመዛሙርቱ የጻፉትን ትምሕርት አንዳችም ስሕተት እንደሌለበት ፍጹም ቃል አድርገው መቀበል አለባቸው ምክንያቱም ደቀመዛሙርቱ ትምሕርታቸውን ያገኙት ከኢየሱስ ነው።
ኢየሱስ ደግሞ አንድም ስሕተት የለበትም። ስለዚህ ኢየሱስ ቃሉ ከሆነ ቃሉ ውስጥ አንዳችም ስሕተት የለም ማለት ነው።
ሕዝቡ አንድ ቁርጥ ውሳኔ ማድረግ ነበረባቸው። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል ነው ወይስ አይደለም?
በዚህ በመጨረሻ ዘመን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም መሆኑን ስለማይቀበሉ ደስ እንዳላቸው ቃላቱን ይቀያይራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን መለወጥ ክርስቶስን መስቀል ነው።
ማርቆስ 8፡7 ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸው፤ ባረከውም ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ።
ዓሣዎች ውሃ ውስጥ ጠልቀው ሰው የማያያቸው ቦታ ይዋኛሉ። ይህም በስደት ላይ የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው። በተለይም ደግሞ ከአስር ሚሊዮን በላይ አማኞች የተገደሉበትን የጨለማውን ዘመን ያመለክታል።
ትንንሽ ዓሣዎች። እውነተኛ አማኞች ሁልጊዜም ቢሆን በጥቂት ሰዎች ሕብረት ውስጥ ነው የሚገኙት። በሰዎች ዘንድ ተገፍተው፣ ማንም ሳያያቸው መመላለሳቸው ከትልልቆቹ ቤተክርስቲያን ዘንድ ከሚሰነዘርባቸው ስም የማጥፋት ዘመቻ ያተርፋቸዋል።
ማርቆስ 8፡8 በሉም ጠገቡም፥ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ።
እንጀራ የአስተምሕሮ ተምሳሌት ነው። በስፍራው ተሰብስበው የነበሩ የአይሁድ ሕዝብ አንበላም ብለው ያስተረፉት ቁርስራሽ ሲሰበሰብ ሰባት ቅርጫት ሞላ። ይህም አይሁዶች ደቀመዛሙርት ያቀረቡላቸውን የወንጌሉን መልእክት እምቢ አንቀበልም ማለታቸውን ያመለክታል።
አይሁዶቹ አንበላም ብለው የጣሏቸው የእንጀራ ቁርስራሾች በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት ተሰብስበው ሰባት ቅርጫቶችን ሞሉ። ይህም በአይሁድ ዘንድ ተቀባይነት ያጣውን የወንጌሉን መልእክት የሚወክል ሲሆን ደቀመዛሙቱ ግን ቁርስራሾቹን ሰብስበው አዲስ ኪዳንን በመጻፍ ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መልእክቱን አደርሰዋል። አይሁዶች አዲስ ኪዳንን አንቀበልም አሉ፤ ነገር ግን የአዲስ ኪዳን እውነት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያንን አዳነ።
ልክ እንደ ቤተክርስቲያን አይሁዶችም በ7 ዘመናት ውስጥ አልፈዋል
ማርቆስ 8፡9 የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ። አሰናበታቸውም።
አራት ሺህ የሚለው ምን ማለት ነው?
ሕጉ የጸጋ ጥላ ነው።
የ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጥላ በ7 ዋነኛ ዕብራውያን ሰዎች አማካኝነት ተገልጧል። ልክ እንደ 7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት 7ቱ የአይሁድ ዘመናትም የፈጁት ጊዜ 2,000 ዓመታት ነው።
የመጀመሪያው ዘመን አብራሐም ሚሰቱን ሣራን ትቶ ከአጋር እስማኤልን የወለደበት ነው። ከዚህም ስሕተት የተወለዱት አረቦች እና የእስልምና እምነት እስከ ዛሬ ድረስ ለአይሁድ ሕዝብ ጠላት ሆነዋል።
ራዕይ 2፡4 ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።
በሁለተኛው ዘመን ዮሴፍ ወደ እስር ቤት ተጣለ።
ራዕይ 2፡10 ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ።
በሶስተኛው ዘመን የተላከው መልእክተኛ ሙሴ ሲሆን እርሱን ለመቃወም የተነሳው ደግሞ በለዓም ነበር።
ራዕይ 2፡14 … የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
በአራተኛው ዘመን ኤልያስ መልእክተኛ ሆኖ መጥቶ ኤልዛቤል ከተባለችዋ ጨቋኝ ሴት ጋር ውግያ ገጠመ (ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ማለት ነው)።
ራዕይ 2፡20 ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤
በስተመጨረሻ እስራኤል በባቢሎን ተማርካ ሄደች።
የመጀመሪያው ቃል በመጀመሪያዎቹ አራት የአይሁድ ዘመናት ውስጥ ጠፋ።
በአምስተኛው ዘመን ዕዝራ የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ወደ ቤተመቅደሱ መለሳቸው።
ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት እና በጸጋ ነው የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ።
ስድስተኛ ዘመን። ነኅምያ ኢየሩሳሌምን እና ቤተመቅደሱን ከጠላት ለመጠበቅ ጠንካራ ቅጥር ሰራ።
ጆን ዌስሊ የቅድስና ትምሕርትንና የወንጌል ስርጭት አገልግሎትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ፤ ይህም ለዓለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት በር ከፈተ። የክርስትና ብርታት የወንጌል ስርጭት ነበር።
ሰባተኛ ዘመን። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን በሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ሰው አስተዋወቀ።
ዊልያም ብራንሐም ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መካከል እንደሚመላለሰው እንደተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል አስተዋወቀ።
የ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጥላ በብሉይ ኪዳን ዘመን ይኖሩ በነበሩ ዕብራውያን ሰዎች የሕይወት ታሪክ ሲገለጥ 2,000 ዓመታት ነበር የፈጀው።
ከዚያም በሙሽራይቱ ሕይወት ውስጥ የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ፍጻሜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በታየው ጥላ መሰረት ሲከናወን ተጨማሪ 2,000 ዓመታትን አስቆጥሯል።
ከዚያ በኋላ 7ቱ ነጎድጓዶች ለሙሽራይቱ አካላት አዲሱን አካላቸውን እንዴት እንደሚቀበሉ ያስተምሯቸዋል። የሙሽራይቱ አካላት አዲሱን የከበረውን አካላቸውን ከለበሱ በኋላ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ይጠናቀቃሉ።
2,000 + 2,000 = 4,000 ዓመታት
ኢየሱስ እንጀራውን በተዓምር ባበዛው ጊዜ የበሉት ሰዎች 4,000 መሆናቸው ሙሽራይቱ ማለትም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን እስክትገለጥ የፈጀውን 4,000 ዓመት ያመለክታል።
ሙሽራይቱ አይሁዶች አንበላም ብለው የጣሉትን የአዲስ ኪዳን እንጀራ ቁርስራሽ ጥርግ አድርጋ ትበላለች።
በስተመጨረሻም አብዛኞቹ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች እምነታቸውን በሰው ንግግር ትርጓሜ ላይ ከመመስረታቸው የተነሳ አንበላም ብለው የጣሉትን የተገለጠውን ቃል ሙሽራይቱ ተቀብላ ትበላለች። እነዚህ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ጥቅሶችን ተጠቅመው የመጽሐፍ ቅዱስን ጠለቅ ያሉ ሚስጥራት መረዳት ይችሉ ነበር፤ ነገር ግን ይህንን ዕድላቸውን አልተጠቀሙበትም።
ማርቆስ 8፡9 የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ። አሰናበታቸውም።
አይሁዶች እንጀራውን በሉ፤ በኋላ ግን ሰባት ቅርጫት ሙሉ ቁርስራሽ አንበላም አሉ፤ ጌታም አሰናበታቸው።
“አሰናበታቸው”። ይህ ቃል አይሁዶች ወንጌሉን አንቀበሉም ስላሉ እግዚአብሔር ከፊቱ እንዳባረራቸው ያመለክታል። አይሁዶች በቀራንዮ ሰው የሆነውን ኢየሱስን ገፉት።
“አሰናበታቸው” የሚለው ቃል በታላቁ መከራ ዘመን በመጨረሻ የተገለጡትን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት የማይቀበሉትን የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖችም ይመለከታል። ስለዚህ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ጨምሮ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማያውቁ እየሆኑ ይሄዳሉ፤ ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተጠቅመው እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ማሳየት የማይችሉ ይሆናሉ።
ኢየሱስ አሕዛብን ለማግኘት ገሊላ ውስጥ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ተመላልሷል
ኢየሱስ ሁሌም በሥራ ላይ ነበረ።
ጢሮስ እና ሲዶና የአሕዛብ ግዛቶች ናቸው፤ ኢየሱስ ወደነዚህ ከተሞች ሳይቀር ሄዷል። ይህም ድርጊቱ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንደሚል የሚያሳይ ትንቢታዊ ምልክት ነበረ።
ማርቆስ 7፡31 ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።
ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከገሊላ ባሕር በስተ ደቡብ በኩል ወደሚገኙት ወደ አስሩ ከተሞች መጣ፤ ይህም አካባቢ በብዛት አሕዛብ የሚኖሩበት ግዛት ነበረ። አስሩ ከተማ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተቀኝ (ማለትም በምሥራቅ በኩል) ነበር።
ኢየሱስ 4,000 ሰዎችን እንጀራ ያበላ ከገሊላ ባሕር በስተደቡብ የሚገኝ የሆነ ቦታ ነበር።
ከአሕዛብ ገሊላ ተነስቶ ወደ አሕዛብ አስሩ ከተማ በመሄድ ኢየሱስ በአሕዛብ ግዛት ውስጥ ሰነበተ። ይህም ይመጡ ዘንድ ላላቸው የቤተክርስቲያን ዘመናት ምልክት ነበር።
ማርቆስ 8፡10 ወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ።
“ወዲያውም”። ይህ ቃል ኢየሱስ ትጉህ አገልጋይ መሆኑን ያሳያል። በፍጹም ጊዜ አባክኖ አያውቅም። ሁልጊዜ በአገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ ነበር።
ዳልማኑታ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ቅርንጫፍ ማለት ነው።
ዳልማኑታ የሚባለው ሥፍራ የትጋ እንደሚገኝ በትክክል አይታወቅም። የምናውቀው ነገር ቢኖር መጌዶል ከሚባለው ከተማ አካባቢ የሚገኝ ሥፍራ መሆኑን ብቻ ነው።
ማቴዎስ አካባቢውን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል።
ማቴዎስ 15፡39 ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ።
ማርቆስ መጌዶል ማለትም ቅርንጫፍ የሚለውን ቃል በመጠቀም ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክለው ባለ ሰባት ቅርንጫፉ መቅረዝ ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
እያንዳንዱ የአሕዛብ የቤተክርስቲያን ዘመን በአንድ የመቅረዝ ቅርንጫፍ ተወክሏል።
ይህ ስዕል እውነት የነበረበትን የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዘመን ያሳያል።
ዳልማኑታ የሚባለው ሥፍራ የት እንደሆነ በውል የማይታወቅ እንደመሆኑ መጠን እውነተኛይቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያንም በዓለም ውስጥ የት እንዳለች ለማግኘት ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነበር። የዓለም ሕዝብ ቤተክርስቲያን ተብለው የተቋቋሙ ድርጅቶችንና ሕንጻዎችን ያያል። እነዚህ ሁሉ እውነተኞቹ አማኞች እንዳይታዩ የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው።
ይህንን አካባቢ ማቴዎስ የመጌዶል አገር ይለዋል። መግደላዊት ማርያም የመጣችው ከዚህ ሃገር ነው።
መግደላዊት ማርያም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የምትገኘዋን ሙሽራ የምትወክል ጠንካራ ተምሳሌት ናት።
ሴት እንደመሆኗ ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። መግደላዊት ማርያም 7 አጋንንት ወጥተውላታል። ይህም እግዚአብሔር የአረማውያን አጋንንትን ያባረረላቸውን 7ቱን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል።
መግደላዊት ማርያም። የስሟ ሁለት ቃለት በ“መ” ፊደል ነው የሚጀምሩት። ይህም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እንደሚመለስ ያሳያል። ስለዚህ ኢየሱስ 4,000ዎቹን ካበላ በኋላ ተመልሶ ትኩረቱን በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ላይ ያደርጋል። የመግደላዊት ማርያም ስም ሁለቱም ቃላት በመ ፊደል መጀመራቸው በተጨማሪ የመጨረሻው ዘመን ጠፍቶ የነበረውን የመጀመሪያውን ዘመን እውነት መልሶ እንደሚያገኝ ያመለክታል። የመጀመሪያውና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመናት እምነታቸው አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
የራዕይ ምዕራፍ 4 ንሥር ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል። ንሥሩ ወደመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አንበሳ ይመልሰናል።
ማቴዎስ 15፡39 ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ።
መጌዶል የመግደላዊት ማርያም መኖሪያ ነው። እርሷም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።
ብዙ ሕዝብን ማገልገል ከባድ ነው።
ኢየሱስ አሰናበታቸው። ኢየሱስ አሕዛብን በየግላቸው ማግኘት ነው የሚፈልገው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሊያርሙ ይፈልጋሉ
ማርቆስ 8፡11 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር።
በስተመጨረሻ ዋነኛው የእውነት ጠላት የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ የሚሉ ግለሰቦች ናቸው።
ፈሪሳውያን የዚያ ዘመን የቤተክርስቲያን ራሶች ነበሩ። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ፈሪሳውያን የሚናገር ጥቅስ አልነበረም። ካሕኑ፣ ቄሱ፣ ወይም ፓስተሩ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም።
ፈሪሳውያን በዘመን መጨረሻ ምግባረ ብልሹ የሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ይወክላሉ። የአሁኖቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን የራስነት ስልጣናቸውን ለመደገፍ ሲሉ እንደፈለጉ ቃሉን ይነቅፋሉ።
ከልባቸው ምልክት እየፈለጉ አልነበሩም። ሃሳባቸው ኢየሱስ አንድ ነገር እንዲያደርግና እነርሱም እርሱን የሚከስሱበትን ምክንያት ለማግኘት ነው። ስለዚህ ቅን አልነበሩም። ኢየሱስን ማስወገድ ፈልገዋል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆነው ስልጣናቸው ስጋት ሆኖባቸዋል። የዘመናችን ሰባኪዎች መጽሐፍ ቅዱስን አይከተሉም ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ከእነርሱ ድንቅ ሃሳብ ጋር አይሄላቸውም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ይላሉ ወይም እንደፈለጉ ይለውጡታል።
የነዚህ የሐይማኖት መሪዎች ዓላማ ኢየሱስን ከስሕተት ማረም ነው። የዘመናችን ሰባኪዎች ሁልጊዜ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ስሕተት ለማረም እንደተጉ ናቸው። በአእምሮዋቸው መሃይም ናቸው ግን ትዕቢታቸው በጣም ትልቅ ነው።
ማርቆስ 8፡12 በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም አለ።
እነዚህ መሪዎች የኢየሱስን ተዓምራት አይተዋል። ነገር ግን ልባቸው ደንድኖ ስለነበረ እርሱ መሲሁ ወይም ክርስቶስ መሆኑን ሊያምኑ አልቻሉም። የእነርሱ አለማመን ነው በውስጡ እንዲቃትት ያደረገው።
ለነዚህ ሰዎች የሚሰጣቸው ብቸኛው ምልክት ሞቱ እና ትንሳኤው ነው። ፈሪሳውያን ግን እርሱ እንዲሞት ይፈልጉ ስለነበረ በትንሳኤው ለማመን እሺ አይሉም። ደቀመዛሙርቱ አስከሬኑን ሰርቀው ወሰዱ ብለው ነው የሚያምኑት። ከዚህም የተነሳ የተሰጣቸውን ተዓምራዊ ምልክት ሊያዩ አልቻሉም። በዚህ ምክንያቱ የእነርሱ ዘመን ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም።
ማርቆስ 8፡13 ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ።
ኢየሱስ ከቤተሳይዳ ወጣና በመንገዱ መጀመሪያ 5,000 ሰዎችን እንጀራ አበላ። ወደ ቤተሳይዳ ለመሄድ ሲዘጋጅ ከመጌዶል እየወጣ ነበር። ስለዚህ ጉዞውን ከጀመረበት ቦታ አጠናቀቀ። ይህም ድርጊት የአሕዛብ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ይወክላል፤ ማለትም የመጨረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን ወደተጀመረችበት ወደ መጀመሪያው ወደ ኤፌሶን የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለበት።
እምነታቸውን በምልክት ላይ የመሰረቱ ሰዎች ትልቅ ስሕተት ውስጥ ይወድቃሉ።
ፈሪሳውያን ለዘመናቸው ትልቅ ምልክት ፈለጉ፤ ኢየሱስም ማለትም ቃሉ ትቷቸው ሄደ። አንድ አስተምሕሮ ለመመስረት ምልክት መፈለግ ትልቅ ስሕተት ነው።
ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች በ1963 ዓ.ም የታየው ልዕለ ተፈጥሯዊ ደመና የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአም መምጣት ነው ብለው ያምናሉ።
መልአኩ ሲመጣ ግን የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን የማስነሳት ተዓምር ሊሰራ ነው የሚመጣው።
የ1963ቱ ደመና ለ28 ደቂቃ ከምድር 26 ማይልስ ከፍታ ላይ ተንሳፍፎ መቆየቱንና ወደ ምድር አለመውረዱን እንዲሁም ከፀሃይ መጥለቅ በኋል መታየቱን ዘንግተዋል። ደመናው ወደ ምድር አልወረደም።
ስለዚህ ሰዎች ምልክት ሲፈልጉ ስሕተት ውስጥ ይገባሉ።
64-0119 ሻሎም
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
እንጀራ አስተምሕሮን ይወክላል
ማርቆስ 8፡14 እንጀራ መያዝም ረሱ፥ ለእነርሱም ከአንድ እንጀራ በቀር በታንኳይቱ አልነበራቸውም።
ደቀመዛሙርቱ ፍጥረታዊው እንጀራ ብቻ ነበር የሚታያቸው። የአስተምሕሮ ተምሳሌት መሆኑ አልገባቸውም።
ማርቆስ 8፡15 እርሱም፦ ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው።
እርሾ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስሕተትን የሚያሰራጩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች የሚያመጡትን ተጽእኖ ያመለክታል። ፈሪሳውያን መጽሐፍ ቅዱስ እውቅና ያልሰጣቸው የምኩራብ ራሶች ነበሩ (ምኩራቦች የአይሁድ ቤተክርስቲያኖች ናቸው)። ፈሪሳውያን ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልተጠቀሱም።
ማርቆስ 8፡16 እርስ በርሳቸውም፦ እንጀራ ስለሌለን ይሆናል ብለው ተነጋገሩ።
ደቀመዛሙርቱ ሃሳባቸው ፍጥረታዊ እንጀራ ላይ ነበረ።
የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ከፈለግን ጠለቅ ያሉትን መንፈሳዊ ሚስጥራት ለመረዳት ልባችንን መክፈት አለብን።
ማርቆስ 8፡17 ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ? ገና አልተመለከታችሁምን? አላስተዋላችሁምን?
ከእንጀራ ጋር በተያያዘ ሁለት ተዓምራት አይተዋል። የመጀመሪያው 5,000 ሰዎች ኋለኛው ደግሞ 4,000 ሰዎች እንጀራ የበሉበትን ተዓምር አይተዋል።
ማርቆስ 8፡18 ልባችሁስ ደንዝዞአልን? ዓይን ሳላችሁ አታዩምን? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን? ትዝስ አይላችሁምን?
አንድ ተዓምር ሲደረግ በፍጥረታዊ ዓይናችን ልናይ እንችላለን፤ ነገር ግን አብሮት የተገለጠውን መንፈሳዊ እውነት አናይም።
ማርቆስ 8፡19 አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ? እርሱም፦ አሥራ ሁለት አሉት።
ማርቆስ 8፡20 ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እነርሱም፦ ሰባት አሉት።
ማርቆስ 8፡21 ገና አላስተዋላችሁምን? አላቸው።
አይሁዶች የአዲስ ኪዳንን ወንጌል አንቀበልም አሉ ምክንያቱም ፈሪሳውያን ማለትም የሐይማኖት መሪዎቻቸው አይሁዶች ኢየሱስን እንዳይቀበሉ ነግረዋቸዋል።
አይሁዶች አንበላም ብለው የተዉት አስራ ሁለት ቅርጫት ሙሉ ቁርስራሽ እንጀራ አንቀበልም ብለው የጣሉት ወንጌል በታላቁ መከራ ዘመን ወደ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ተመልሶ እንደሚሄድ ያመለክታል።
አይሁዶች አንበላም ብለው የተዉት ሰባት ቅርጫት ቁርስራሽ እንጀራ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አሕዛብ አዲስ ኪዳንን እንደሚያምኑ ያመለክታል።
ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር እቅድ ነበረ። አይሁዶች ወንጌልን አንቀበልም ማለታቸው ወንጌል ወደ አሕዛብ እንዲሄድና ለኢየሱስ ሙሽራ የሚሆን ሕዝብ ለመቤዠት ምክንያት ሆነ። ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን ደግሞ የተገለጡትን ሚስጥራት አልቀበልም በምትልበት ጊዜ እነዚህ ሚስጥራት በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወደ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ይመለሳሉ።
144,000ዎቹ አይሁዶች የሙሽራይቱ ጠባቂዎች ይሆናሉ።
ዓይነ ስውር ሰው የአሕዛብ ምሳሌ ነው
ማርቆስ 8፡22 ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ። ዕውርም አመጡለት፥ እንዲዳስሰውም ለመኑት።
ቤተሳይዳ ጉዞው የተጀመረበት ቦታ ነው። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን እንጀራ አበላ። ከገሊላ ባሕር በደቡብ ጠረፍ በኩል እና ወደ ጢሮስ ሄዶ 4,000 ሰዎችን እንጀራ አበላ። ቀጥሎ ወደ መጌዶል ሄደና ከዚያም ወደ ቤተሳይዳ ተመለሰ።
ጉዞው በጀመረበት በቤተሳይዳ ተጠናቀቀ። መጀመሪያውና መጨረሻው አንድ ሆኑ። የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ይመለሳል።
በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዕውር ትሆናለነች ምክንያቱም ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ሆኖ በደጅ ቆሞ ያንኳኳል።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 … ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
ማርቆስ 8፡23 ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት፡- አንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው።
ከተማው ዕውሩ የሚኖርበትን ቡድን ወይም ቤተክርስቲያን ይወክላል።
ኢየሱስ ይህን ዕውር ሰው የግድ ከከተማ ውጭ ይዞ መሄድ ያስፈልገው ነበር። ቃሉን ማየት ከፈለግን ከቤተክርስቲያን መውጣት አለብን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሞ ነው ያለው።
ከእግዚአብሔር አፍ ምራቅ ወጣ። ይህም የእግዚአብሔርን አፍ ከሰው ዓይን ጋር ያገናኛል።
መንፈሳዊ ዓይኖቻችን እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ብቻ ማየት አለባቸው፤ እርሱም ቃሉ ማለትም ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ዛሬ እኛ አማኞች እምነታችንን ቤተክርስቲያን በተናገረችው ወይም ፓስተሩ በተናገረው ቃል ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ በተናገረው ቃል ላይ ማድረግን መልመድ አለብን። ከቤተክርስቲያን ተጽእኖ እና ከቤተሰብ ተጽእኖ ነጻ መውጣት አለብን። የመጽሐፍ ቅዱስን ተጽእኖ ብቻ ነው መቀበል ያለብን። ሁሉንም ነገር እራሳችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየት አለብን። እምነታችን ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸን ማረጋገጥ አለብን። የቤተክርስቲያንን እምነት እንከተል ብለን ማሰብ የለብን ምክንያቱም እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የተለያየ እምነት አለው። ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን የቷ ናት? ማንኛዋም? ኢየሱስ ለዚህ ነው ሰውየውን ከከተማ ውጭ ይዞት የሄደው።
ማርቆስ 8፡24 አሻቅቦም፦ ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ።
ዛፍ የሰውን መንፈስ ይወክላል።
መዝሙር 1፡1 ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
2 ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።
3 እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ዕውሩ ሰውዬ መንፈሳዊ ዓይኖቹ በርተውለታል። ከቃሉ ውሃ ወንዞች ጋር ያልተገናኘ ነገር ሁሉ እንደ ደረቅ ዛፍ ሆኖ ነው የሚታየው። ይህም ያልዳነ ሰው መንፈስ ምሳሌ ነው።
ዕውሩ ሰውዬ ታላቅ የመለየት ስጦታ ተሰጥቶታል። ልክ እንደ ደረቅ ዛፍ ያልዳነ ሰው መንፈስ ወደ እርሱ ይመለከታል።
ለሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የተላከው መልእክተኛ ዊልያም ብራንሐም ታላቅ የመለየት ስጦታ ተሰጥቶት ነበር። በመጨረሻው ዘመን ውስጥ የሰዎችን የልብ ሃሳብ መለየት ችሏል።
በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌ እና በቅኔ አማካኝነት የተሰወሩ መገለጦችን የማየት ጥበብም ተሰጥቶት ነበር። እነዚህ ጠለቅ ያሉ መገለጦች ሙሽራይቱን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሐዋርያት ዘመን እምነት ይመልሷታል።
ማርቆስ 8፡25 ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ።
ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ ነካውና ፍጥረታዊ ዓይኑ በራ።
ኢየሱስ ፍጥረታዊ ዓይንን እንዲሁም መንፈሳዊ ዓይንንም ማብራት ይችላል።
ማርቆስ 8፡26 ወደ ቤቱም ሰደደውና፦ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው።
ኢየሱስ ወደ እውነተኛ ቤቱ ሰደደው፤ ላከው (ይህም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እንደነበረችው በቤት የምትሰበሰብ ቤተክርስቲያን ማለት ነው) በከተማ የምትገኝ ቤተክርስቲያን አይደለችም (ይህ ትልቅ የቤተክርስቲያን ሰዎች ስብስብ ለመመስረት በከተማ ለብቻ ተነጥሎ የሚሰራ ትልቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ማለት ነው። የታሪክ ምሑራንን ብትጠይቋቸው ከ220 ዓ.ም በፊት የቤተክርስቲያን ሕንጻ የሚባል ነገር እንዳልነበረ ይነግሩዋችኋል።)
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ተብሎ ለብቻው የተሰራ ሕንጻ አልነበረም። ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ብቻ ነበሩ ቤተመቅደሱን ይጠቀሙ የነበሩት። ቤተመቅደሱም በ70 ዓ.ም ፈርሷል።
መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ለመረዳት እንድትችሉ ከቤተክርስቲያን መውጣት አለባችሁ። ከዚያ ወዲያ ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ የለባችሁም ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ያሉት እናንተ የምትናገሩትን መረዳት አይችሉም። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ሙሉውን እውነት የያዝኩት እኔ ነኝ ብላ ታምናለች። ከዚህም የተነሳ ከእነርሱ ጋር የማይስማማ ሰውን ሁሉ አይታገሱትም።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ስሕተቷን የሚያርማትን ሰው ሁሉ ትቃወመዋለች።
ኢየሱስ የሚሰራው ከግለሰቦች ጋር ብቻ ነው
ማርቆስ 8፡27 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድም፦ ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው።
ቄሳር ታላቁ የሮማ አምባገነን መሪ ነበር። ታላቁ የግሪኮች ንጉስ ፊሊጶስ የዓለም ሁሉ ገዥ የነበረው የታለቀቁ አሊግዛንደር አባት ነው።
ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ታሪክ ይገልጣል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአውሮፓ ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ ትገዛለች፤ ከዚያም የዓለም ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ ትገዛለች። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ላይ አንድ ካሕን አምባገነን መሪ አድርጋ ሾማለች። ይህ ዓይነቱ ድርጅታዊ መዋቅር ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ተሻግሯል፤ ስለዚህ ሪቨረንድ ወይም ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ሆኗል። ፖፑ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባገነን መሪ ሆነ። በስተመጨረሻ ፖፑ የዓመጽ ሰው ይሆንና የዓለም ቤተክርስቲያኖችን በሙሉ ይመራል።
ከዚያ በኋላ ከሲኦል የሚመጣው የጥፋት ልጅ በመሆን ዓለምን ሁሉ በፈላጭ ቆራጭነት ይገዛል።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።
ኢየሱስ በታላቁ ሮማዊ ንጉስ በዩልየስ ቄሳር ወደተሰየመችዋ ግዛት ሄደ፤ ዩልየስ ቄሳር ከክርስቶስ ልደት በፊት በ63 ዓመተ ዓለም የባቢሎናውያን ሚስጥራት ፖንቲፍ ሆኖ ተሹሟል። ዛሬ ሮም ውስጥ የሚገኘው ፖፕ ጭምር ፖንቲፍ ተብሎ ነው የሚጠራው።
ቀጥሎም በፊሊጶስ ቂሳሪያ ሳሉ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ጠየቃቸው።
ማርቆስ 8፡28 እነርሱም፦ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ ብለው ነገሩት።
ደቀመዛሙርቱ ወዲያ የተለያዩ መልሶችን ሰጡ። የሰዎች አመለካከት ሁልጊዜ የተለያየ ነው። አንዱ ሰው ይህን ይላል፤ ሌላውም ያን ይላል። በዚህ ዘመን 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚናሽዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ያሉት የቤተክርስቲያን መሪዎች አመለካከታቸው የተለያየ ስለሆነ ነው። እያንዳንዱ መሪ ደግሞ እርሱ ራሱ ትክክል እንደሆነ ሌሎቹ ሁሉ ግን ስሕተት እንደሆኑ ያምናል። በጣም ግራ ያጋባል። የሜሴጅ ፓስተሮችም ብዙ የተለያየ አመለካከት አላቸው፤ ከዚህም የተነሳ ከ100 በላይ የተለያዩ የሜሴጅ እምነቶችን ፈጥረዋል። እንዲህም ሆኖ እያንዳንዱ የሜሴጅ ፓስተር እኔ ነኝ ትክክለኛ፤ ሌሎቹ ሁሉ ግን ተሳስተዋል ይላል። ከዚህም የተነሳ መንፈሳዊ ውዝግቡ እየሰፋ ይሄዳል።
ደቀመዛሙርቱ የሌሎችን ሰዎች አመለካከት እያንጸባረቁ ነበር።
ኢየሱስ ግን እነርሱ በግላቸው ምን እንደሚያምኑ ማወቅ ነው የፈለገው።
ማርቆስ 8፡29 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት።
ከጴጥሮስ በቀር ደቀመዛሙርቱ ሁሉ ወደያው ጸጥ አሉ። ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ እውነቱ ተገልጦለታል፤ ክርስቶስ መሆኑን፣ መሲህ መሆኑን ተረድቷል።
ማርቆስ 8፡30 ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
የአይሁድ መሪዎች መሲሁ እርሱ መሆኑን ሲያውቁ በተቻላቸው መንገድ ሁሉ ሊገድሉት እንደሚሞክሩ ኢየሱስ አውቋል።
ኢየሱስ እውነተኛው ቃል እንደመሆኑ በአይሁድ መሪዎች ሊገፋ እና ሊገደል እንደሆነ አስቀድሞ ተረድቷል። ነገር ግን ከሶስተ ቀናት በኋላ ከሞት እንደሚነሳም አውቋል።
ሐሙስ ዕለት ይገደልና ይቀበራል። አርብ እና ቅዳሜ መቃብር ውስጥ ያሳልፋል። እነዚያ ሶስት ቀናት ከተፈጸሙ በኋላ እሁድ ዕለት ከሙታን ይነሳል።
ማርቆስ 8፡31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።
ይህ በኢየሱስ ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ እንደገና ተፈጽሞበታል። በ325 ዓ.ም በተደረገው በኒቅያ ጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፍቅር ተገደለ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት አፈር ውስጥ ተቀብሮ በጨለማው ዘመን አለማመን ነገሰ። በዚያ ጊዜ ስላሴ፣ የስቅለት አርብ፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ ኩዳዴ፣ አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው፣ እና ፍጹም ትክክል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የለም የሚሉ እምነቶች የሰዎችን አእምሮ ተቆጣጠሩ። ከዚያም ከ3 ቀናት በኋላ (ማለትም ከሉተር፣ ዌስሊ፣ እና ጴንጤ ቆስጤ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ) የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እውነት በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያን መጣ። ይህም በጨለማው ዘመን ውስጥ ከነበሩ አደገኛ ስሕተቶች ውስጥ ተቀብሮ የነበረው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ትንሳኤ ነው።
ኢየሱስ እንደሚሞት ሲናገር ግን ጴጥሮስ ገሰጸው።
ማርቆስ 8፡32 ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።
እኛ ሰዎች የምንሰራው ስሕተት የመጽሐፍ ቅዱስን አንዳንድ ክፍሎች መለወጥ እንደምንችል ማሰባችን ነው።
ጴጥሮስ ቃሉን (ኢየሱስን) ያዘ፤ ነገር ግን ቃሉ በተናገረው ላይ የራሱን ትርጓሜ ጫነበት። ስለዚህ ጴጥሮስ ቃሉን በመቃወሙ ኢየሱስን ተቃውሟል።
ኢየሱስ ጴጥሮስን እያየው ነበረ፤ ነገር ግን ጴጥሮስ ከእርሱ ጋር በተቃረነ ጊዜ ኢየሱስ ፊቱን ዘወር አደረገ።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ (የኢየሱስን ሃሳብ የሚገልጥልን መጽሐፍ) ውስጥ የተጻፈውን ቃል ብትቃረኑ ኢየሱስ ጀርባውን ያዞርባችኋል፤ ትቷችሁም ይሄዳል።
ማርቆስ 8፡33 እርሱ ግን ዘወር አለ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው።
ኢየሱስ ጴጥሮስን ሰይጣን አለው። ኢየሱስ ቃሉ ነው። ቃሉን የምትቃወሙ ከሆናችሁ ሰይጣን ሆናችኋል ማለት ነው።
ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ይቃረናሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ስትቃረኑ መጽሐፍ ቅዱስን በሚቃረኑ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ታገኛላችሁ።
ጴጥሮስ ኢየሱስ መሲሁ ወይም ክርስቶስ መሆኑን መስክሮ ነበረ። ነገር ግን ወዲያው ምስክርነቱን አበላሸ። አንድን ነገር በትክክል ስናውቅ ትዕቢተኛ ሊያደርገን ይችላል፤ የዚያን ጊዜ እንስታለን።
የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃረነው ወይም የሚለውጠው ሰይጣን ብቻ ነው።
ይህ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ ሊማሩት የሚገባ በጣም አስፈላጊ ትምሕርት ነው።
ሰዎች የራሳቸውን አመለካከት ለመደገፍ ብለው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ይለውጣሉ፤ እኛ ግን በፍጹም ቃሉን መለወጥ የለብንም።
የእግዚአብሔርን ነገር የምንወድ ከሆንን ከቃሉ ጋር ተጣብቀን እንኖራለን።
የክርስቲያን አገልጋዮች መሰረታዊ መመሪያ
ማርቆስ 8፡34 ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።
መስቀላችሁን ተሸከሙ። ሕይወት በችግር የተሞላች ናት። በነዚያ ችግር በሞላባቸው ሁኔታዎች ውስጥ መገኘታችሁ ምክንያት አለው። ድል ነሺ ሁኑ።
ራሳችሁን ካዱ። የግል አመለካከታችሁ ምንም አይጠቅማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስን ተከተሉ።
ክርስቶስን ተከተሉ። ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሁሉ ተከተሉ።
ማርቆስ 8፡35 ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።
ሥራ እንዳታጡ ወይም ጓደኛ ላለማጣት ብላችሁ እውነትን የምትክዱ ወይም የምታመቻምቹ ከሆናችሁ ከሙሽራይቱ አካል ውስጥ ትወገዳላችሁ።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የሚገልጥላችሁን እውነት ለመከተል ብላችሁ በሰው ዘንድ ያላችሁን ተወዳጅነትም ሆነ ሕይወታችሁን ጭምር ለማጣት ዝግጁ ከሆናችሁ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ከሞት በኋላ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣችኋል።
የመጨረሻው ግብ ላይ ማተኮር አለባችሁ፤ እርሱም መንግስተ ሰማያት ነው።
ጊዜያዊ በሆኑ ጥቅሞች አትዘናጉ።
ማርቆስ 8፡36 ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
የመጨረሻው ፖፕ ማለትም የአመጽ ሰው በመጨረሻ በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ዓለምን በሙሉ ይመራል። ከዚያ በኋላ ወደ ሲኦልና ወደ እሳት ባሕር ይወረወራል።
መጨረሻው ይህ ከሆነ ለጥቂት ጊዜ ዓለምን የመግዛት ዕድሉ የሚያዋጣ ነውን?
ማርቆስ 8፡37 ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
ነፍሳችሁ ትልቅ ሃብታችሁ ናት። በእናንተ ውስጥ እምነት የሚገኝባት ክፍላችሁ ነፍሳችሁ ናት። ነፍሳችሁ ናት በአፈጣጠራችሁ ከእንስሳት በላይ የምታደርጋችሁ።
የእግዚአብሔር ቃል በነፍስ የአትልክት ሥፍራ ውስጥ የሚያድግ ዘር ሲሆን የሚያድገውም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ውሃ ሲጠጣ ነው።
ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ኤርምያስ 31፡13 … ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ፥ አጽናናቸውማለሁ፥ ከኅዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።
ዮሐንስ 7፡38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።
39 ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤
የቃሉ ዘር የሚበቅለው እምነት ባለው ነፍስ ውስጥ ብቻ ነው።
አካላችን እግዚአብሔርን የሚያስደስተው በእግዚአብሐር ቃል ቁጥጥር ውስጥ ሲሆን ብቻ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡38 እግዚአብሔር ግን እንደ ወደደ አካልን ይሰጠዋል ከዘሮችም ለእያንዳንዱ የገዛ አካሉን ይሰጠዋል።
ቃሉ ሲቆጣጠረን አካላችን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ አካል ማለትም የክርስቶስ የአካሉ ብልት ይሆናል። የቤተክርስቲያን አካል ይሆናል
ዕብራውያን 10፡39 እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።
ማርቆስ 8፡38 በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈው ስለ እያንዳንዱ ቃል መቆም አለብን። አለዚያ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ብቁ አይደለንም።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ከተቃወሙ “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል” እያልን መከላከል አለብን።
በኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ሁሉ ማመንና መውደድ አለብን።
ግትር መሆን የለብንም፤ እውነት ሲገለጥልን ማመንና መከተል አለብን።
ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አይቋረጡም።
ማቴዎስ 7፡7 ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
ማንም መንፈሳዊ ስኬትን በባለቤትነት መያዝ አይችል፤ እንደ ኪራይ ነው የሚጠቀምበት እንጂ፤ ኪራዩንም በየቀኑ ይከፍለዋል።