ማርቆስ 5 - መጀመሪያ የተላከልን ወንጌላዊ አንድ እብድ አሕዛብ ነው
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ኢየሱስ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ሰውን ካዳነ በኋላ አንዲት አይሁዳዊ ልጅን ከሞት አስነሳት። የአሕዛብ ቤተክርስቲያንን ካዳነ በኋላ ኢየሱስ ወደ 144,000ዎቹ አይሁዳውያን ይመለሳል።
- ኢየሱስ ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ተሻገረ
- ኢየሱስን ማምለክ ጤናማ መንፈስ እንዳላችሁ አያረጋግጥም
- አጋንንት ከአንድ የሚበልጥ አንድ መንፈስ አላቸው
- አሕዛብ ገንዘብ የሚያስወጣቸው ከሆነ ኢየሱስን አይፈልጉትም
- አስር መጨረሻን የሚያመላክት ቁጥር ነው
- ኢየሱስ ወደ አይሁዶች ለመመለስ አሕዛብን ትቶ ይሄዳል
- የ12 ዓመታት ደም መፍሰስ በሽታ አንዴ በመንካት ብቻ ተፈወሰ
- አይሁዶች ለ2,000 ዓመታት መንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ ቆይተዋል
ኢየሱስ ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ተሻገረ
እግዚአብሔር አይሁዶችን እንደ አንድ ሕዝብ ነው የሚመራቸው። እኛን አሕዛብን ግን እንደ ግለሰብ በየግላችን ነው የሚመራን።
ኢየሱስን እንደ ታላቅ አገልጋይ አድርጎ በሚገልጸው በማርቆስ ወንጌል ውስጥ በዚህ ምዕራፍ እንደምናየው ኢየሱስ ከገሊላ ባሕር በላይ ቅፍርናሆም ውስጥ የሚኖሩትን አይሁዶች ትቶ ከገሊላ ባሕር በታች የሚኖር አንድ እብድ አሕዛብን ለማዳን ይሄዳል።
ኢየሱስ የገሊላ ባሕርን ተሻግሮ መሄዱ ምሕረት ለማይገባቸው አሕዛብ ጸጋን ሊያሳይ የአይሁዶችን ሕግ ትቶ መሄዱን ያመለክታል።
ኢየሱስ በቅፍርናሆም ዙርሪያ አይሁዶችን እያገለገለ ነበር።
ከዚያ በኋላ የገሊላ ባሕርን ተሻግሮ ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጣ።
ማርቆስ 5፡1 ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ።
“ማዶ” የሚለው ቃል በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያለውን ቅዱስ ሥፍራ እንድናስብ ያደርገናል።
የመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁስ አቀማመጣቸው በመስቀል ቅርጽ ነበረ።
በአንዱ በኩል 12ቱ የገጹ ሕብስት የሚገኙ ሲሆን እነዚህም አስራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች ይወክላሉ። በ3½ ዓመታት የታላቁ መከራ ወቅት 144,000 አይሁዶች ኢየሱስን ይቀበላሉ።
“ማዶ” ከሕብስቱ ባሻገር ባለ 7 ቅርንጫፉ መቅረዝ ይገኛል፤ እሱም በ2,000 ዓመታት ዘመን ውስጥ የሚበራውን የወንጌሉን ብርሃን ይወክላል፤ እነዚህም ዓመታት 7ቱ አሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።
እግዚአብሔር ከመጀመሪያውም ጀምሮ ሁለቱን ወገኖች ማለትም አይሁድን እና አሕዛብን አንድ ላይ ባይጠራቸውም ሁለቱንም አስቧቸዋል።
ማርቆስ 5፡2 ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤
ኢየሱስ እንደ አገልጋይነቱ የሥራ ሰው ነበረ። የእረፍት ጊዜ አልነበረውም። በአጋንንት ተይዞ የነበረው አሕዛብ ሰውዬ ወደ ኢየሱስ መጣ። በኢየሱስ ውስጥ ያለው የሆነ ነገር ይህንን በአጋንንት የተያዘ አሕዛብ ስቦታል። ስለዚህ በአሁኑ ዘመን የሚኖሩ በአእምሮዋቸው ጤናማ የሆኑ አሕዛብ ወደ ኢየሱስ ላለመምጣታቸው ምንም ማመካኛ የላቸውም።
ማርቆስ 5፡3 እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፥ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፤
በዛሬው ጊዜ ይህ ሰው በመነፈስ ሙት የሆኑ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚከተሉ ሰው ሰራሽ ቤተክርስቲያኖች መካከል የሚኖርና ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ዓይነት ሰው ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች አመራራቸው አምባ ገነን ቢሆንም እንኳ የዚህን ሰው ሃሳብ ሊያስሩና በራሱ እንደፈለገ ከማሰብ ሊያስቆሙት አልቻሉም። በቤተክርስቲያን ልማዶች የተፈጠረ ሰንሰለት አስሮ ሊይዘው አልቻለም።
ይሰው ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ፈለገ።
የትኛውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሰው ሰራሽ ቃል፣ ለምሳሌ ስላሴ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ አንድ አምላክ በሶስት አካላት፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ ኩዳዴ፣ ፖፕ፣ ዲኖሚኔሽን፣ አብ እና ወልድ በመለኮት አንድ ናቸው፣ ወዘተ. የመሳሰሉ ቃላት አስረው ሊይዙት አልቻሉም።
ማርቆስ 5፡4 ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበርና ዳሩ ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፥ ሊያሸንፈውም የሚችል አልነበረም፤
ዛሬም ሰው ሰራሽ በሆኑ የቤተክርስቲያን ስርዓቶች እና በራስ ወዳድነት በተቀረጹ የቤተክርስቲያን ሕጎች የማይደነቁ ግለሰች አሉ። እነዚህ ግለሰቦቸ የቤተክርስቲያን ሃሳቦችንና ስርዓቶችን የሚደግፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች አለመኖራቸውን መርምረው በማጣራት የቤተክርስቲያን ስርዓቶችን ጥሰው ያልፋሉ።
እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው እውነትን ፈልገው አላገኙም፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያኖች በሐሰተኛ ትምሕርቶች የተሞሉ መሆናቸውን ደርሰውበታል።
አንድ ግለሰብ ቤተክርስቲያንን ደፍሮ ቢቃወም ከቤተክርስቲያን ይባረራል።
ስለዚህ ብቻውን ጸንቶ መቆም አለበት።
ማርቆስ 5፡5 ሁልጊዜም ሌሊትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮኽ ነበር ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር።
ይህ ሰው በክፉ መንፈስ ታስሮ ስለነበረ ለኑሮ ምቹ ባለሆኑ ቦታዎች እየተቀመጠ በብዙ ራሱን ጎድቷል።
ክፉ መናፍስት በሚጎዱ ነገሮች ሱስ እንድንጠመድ ያደርጉናል።
ሰዎች ሲያጨሱ ሳምባቸውን ይጎዳሉ፤ አልኮል ሲጠጡ ጉበታቸውን እና ኩላሊታቸውን ይጎዳሉ ምክንያቱም ጉበታቸውና ኩላሊታቸው አልኮል ውስጥ ያለውን መርዝ የማጣራት ሥራ ይበዛባቸዋል። ሰዎቹም ሱሰኞች ስለሚሆኑ በየዕለቱ ያጨሳሉ ይጠጣሉ።
አንዳንዶች ደግሞ ፖርኖግራፊ የማየት ሱስ አለባቸው፤ ይህም አእምሮዋቸውን ይመርዘዋል።
ሌሎች ደግሞ አደንዛዥ ዕጾችን ይጠቀማሉ፤ ዕጾቹም አእምሮዋቸውን ያበላሻሉ።
በቁማር ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ደግሞ በገንዘብ ፍቅር ሰክረው ይኖራሉ።
ኢየሱስን ማምለክ ጤናማ መንፈስ እንዳላችሁ አያረጋግጥም
ማርቆስ 5፡6 ኢየሱስንም ከሩቅ ባየ ጊዜ ሮጦ ሰገደለት፥
ይህ ሰው መጥፎ ሕይወት እየኖረ ቢሆንም እንኳ ለኢየሱስ ሊሰግድ ከሩቅ እየሮጠ መጣ።
ስለዚህ ክፉ መናፍስት እንኳ ለኢየሱስ ይሰግዳሉ።
ለኢየሱስ መስገዳችሁ በመልካም መንፈስ መሞላታችሁን አያሳይም።
ሰዎች “ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ” ሲሉ ስሙን ደጋግመው መጥራታቸው ከልባቸው መሆኑን ያሳያል። የእውነታቸውን ኢየሱስ ጌታ ነው ማለታቸው ነው። ነገር ግን ይህን በማለታቸው ብቻ ወደ መንገስተ ሰማያት አይገቡም።
ማቴዎስ 7፡21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
ዛሬ የሚያስፈልገን የሚያመልኩ ሰዎች ለመምሰል የምናደርገው ነገር አይደለም። ማስመሰል ውሸታምነት ነው። ዛሬ የሚያስፈልገን ነገር እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ምን እያደረገ እንዳለ መረዳት እንችል ዘንድ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ነው።
እግዚአብሔር ሊመጣ ካለው ከታላቁ መከራ ማምለጥ እንድንችል እያዘጋጀን ነው።
ደግሞም ታላላቅ ተዓምራዊ ምልክቶችን ያደረጉ ሰዎች አሉ።
ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
የነዚህ ሰዎች ሥራ እኛን በጣም ሊያስደንቀን ይችላል፤ ኢየሱሰን ግን ምንም አያስደንቀውም።
ማቴዎስ 7፡23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
ኢየሱስ እንደውም እነዚህን ተዓምራት ከመቀበል ይልቅ እንደ ዓመጽ ሥራ ይቆጥራቸዋል። እነዚህ ሰዎች ስሕተት እየሰሩ እንደነበረ አውቀዋል። የተዓምራቱ ክብር ላይ አተኮሩ እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል እውነት መረዳትን በፍጹም አልፈለጉም።
ዛሬ የተጠራንበት ታላቅ ጥሪ የተለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደሚነግረን በመንፈስ ቅዱስ ስለ መጠመቃችን ማስረጃው የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳታችን ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን እውነት ሳይረዱ የእግዚአብሔርን ኃይል መለማድ አመጻ ነው።
ማርቆስ 5፡7 በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ፤
አጋንንቱ ኢየሱስ ማን እንደሆነ አውቀዋል። ከሰውየው አስወጥቶ ቢያባርራቸው መሄጃ ስለሌላቸው ምሕረት ለመኑ።
ይህም አጋንንት በሰው ስጋ ውስጥ መኖር በጣም እንደሚፈልጉ ያስረዳናል።
ይህ የአጋንንት እስራት ነው። አጋንንት ሁልጊዜ ሃሳባቸውን በሰው አእምሮ ውስጥ ማስቀመጥ ይፈልጋሉ።
የአጋንንት እስራት ማለት አጋንንት የሰውን አእምሮ ተቆጣጥረው ሰውየው በሚጎዳ ነገር ሱስ እንዲጠመድ ሲያደርጉት ነው።
አጋንንት ሰውን ሲቀጣጠሩ ሰው በመጥፎ ልማዶች ይጠመዳል ወይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችን ይቀበላል።
አጋንንት ከአንድ የሚበልጥ አንድ መንፈስ አላቸው
ማርቆስ 5፡8 አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና።
ኢየሱስ እርኩሱ መንፈስ ከሰውየው አንዲወጣ አዘዘው።
ማርቆስ 5፡9 ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፥
ሰውየው ውስጥ በአንድ ስም የሚጠራ አንድ እርኩስ መንፈስ ነበረ። ሆኖም ብዙ መናፍስትም ነበሩ። ይህ የአጋንንት ሚስጥር ነው። ብዙ መናፍስት የሆነ አንድ መንፈስ።
የአሕዛብ ስላሴ ትምሕርት መሰረቱ ይህ ነው።
ሶስት አካላት የሆነ አንድ አምላክ ይላሉ። ነገር ግን እያንዳንዱ አካል አምላክ ነው።
ማርቆስ 5፡10 ከአገርም ውጭ እንዳይሰዳቸው አጥብቆ ለመነው።
እርኩሱ መንፈስ በአስሩ ከተማ አካባቢ ካለው የአሕዛብ ክልል መውጣት አልፈለገም።
እነዚህ ብዙ ሆነው አንድ ወይም ሶስት ሆነው አንድ የሆኑ መናፍስት በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አሕዛብን ሲያሰቃዩ ይኖራሉ።
ማርቆስ 5፡11 በዚያም በተራራ ጥግ ብዙ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበርና።
በዚያም አካባቢ 2,000 የሚያህሉ አሳማዎች ተሰማርተው ነበር። አሳማዎች ለአይሁድ እርኩስ እንስሳት ናቸው።
ማርቆስ 5፡12 ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን ብለው ለመኑት።
እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ብቻ ነው መኖር የሚፈልገው። ሰይጣን በእንስሳት ውስጥም ገብቶ እንደ እንስሳ መሆን ደስ ይለዋል።
ማርቆስ 5፡13 ኢየሱስም ፈቀደላቸው። ርኵሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፥ ሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና በባሕር ሰጠሙ።
አሳማዎቹም አጋንንት ከገቡባቸው በኋላ ራሳቸውን ወደ ባሕር ከተቱ።
ባሕር እረፍት ያጣ ተንከራታች ሕዝብን ይወክላል።
አሳማዎቹ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ፤ አጋንንቱ ግን አልሰጠሙም። አጋንንቱ ሰላምና እረፍት የሌላቸው ሕዝብ (መንፈሳዊ ባሕር) ማለትም የሮማ መንግስት ውስጥ ገቡና አንድ አምላክ በሶስት አካላት የሚባለውን የስላሴ ቲዎሪያቸውን አዘጋጁ።
እነዚህም መናፍስት በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት የሰዎችን አእምሮ እየተቆጣጠሩ ሲሄዱ ይህ የስላሴ እምነት በአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ በፍጥነት ተዛመተ።
ማርቆስ 5፡14 እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ።
አሳማዎቹን ያሰማሩ የነበሩ ሰዎች ከኢየሱስ ሸሹ። ስላሴ እውነት መሆኑን ከቃሉ ማሳየት አትችሉም። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከቃሉ ማለትም ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ይሸሻሉ። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ከመቶ በላይ በሆኑ ልዩ ልዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሶች ለውጠውታል። ከዚህም የተነሳ ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ፍጹም ስሕተት የሌለበት መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት አይቻልም ብለው ያምናሉ።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩትን በሙሉ ስለ ኢየሱስ እየተናገራችሁ ነው ምክንያቱም ኢየሱስ ቃሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ይነግረናል። ስለዚህ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ የምትሉ ከሆነ በኢየሱስ አስተሳሰብ ውስጥ ስሕተት አለ እያላችሁ ነው። አንዲህ ዓይነቱ አነጋገር ሐጥያት ነው።
አሕዛብ ገንዘብ የሚያስወጣቸው ከሆነ ኢየሱስን አይፈልጉትም
ማርቆስ 5፡15 ወደ ኢየሱስም መጡ፥ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ።
በብዙ አጋንንት ተይዞ የነበረው ሌጌዎን ራቁቱን ነበር። ከአጋንንቱ ነጻ ከወጣ በኋላ ግን ማንም ሳይነግረው ልብስ ለበሰ፤ ምክንያቱም አእምሮው ጤናማ የሆነ ሰው ሁሉ ልብስ መልበስ ይፈልጋል።
ሰዎች ኢየሱስ ነጻ ካወጣቸው በኋላ በአለባበሳቸው ስርዓት ያላቸው ይሆናሉ።
ኢየሱስ ያዳናቸው ሁሉ ገላቸውን መሸፈን ይፈልጋሉ።
በአጋንንት የተያዙ ሰዎች እርቃናቸውን ማሳየት ይፈልጋሉ።
ማርቆስ 5፡16 ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እሪያዎቹ ተረኩላቸው።
ሰውየው ነጻ ወጣ፤ አሳማዎቹ ግን ጠፉ። ባለ አሳማዎቹም ከዚህ የተነሳ ብዙ ገንዘብ ከሰሩ። ልክ እንደ ይሁዳ ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ገንዘብን መረጡ።
ማርቆስ 5፡17 ከአገራቸውም እንዲሄድላቸው ይለምኑት ጀመር።
ኢየሱስን መከተል ዋጋ ስለሚያስከፍላቸው እርሱን መከተል አልፈለጉም።
የእግዚአብሔር ቃል እንድንተው የሚጠይቀን ነገር በሚኖርበት ጊዜ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን በመተው ለራሳቸው የሚመች ትምሕርት ይፈጥራሉ።
ለአሕዛብ ሰፈር ኢየሱስ ይዞላቸው የመጣው ተልዕኮ አሕዛብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ገንዘብን በመምረጣቸው ተቋረጠ።
ኢየሱስ ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ይዞላቸው የመጣው አገልግሎት የሚያበቃው ቤተክርስቲያን ውስጥ ገንዘብ ሲበዛና ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ተገፍቶ ከቤተክርስቲያን ውጭ ሲቆም ነው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ … ስለማታውቅ፥
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
ማርቆስ 5፡18 ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው።
ይህ ነጻ የወጣ አሕዛብ ከኢየሱስ ጋር አብሮ መሄድ ፈለገ።
ኢየሱስ ግን አልፈቀደም። ምክንያቱም በዚህ ትዕይነት ኢየሱስ እየገለጠ የነበረው ሚስጥር በዳግም ምጻቱ የአሕዛብን ቤተክርስቲያን ወደ መንግስተ ሰማይ ካሻገረ በኋላ በዚያ ትቶ አይሁዶችን ፍለጋ ወደ ምድር እንደሚመለስ ነበር።
ስለዚህ ኢየሱስ አሕዛቡን ሰውዬ ትቶ አይሁዶቹን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም ተመለሰ።
ማርቆስ 5፡19 ኢየሱስም አልፈቀደለትም፥ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው አለው።
ሂድና እግዚአብሔር ያደረገልህን ለሰዎች ንገራቸው።
ማርቆስ 5፡20 ሄዶም ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት አሥር ከተማ በሚባል አገር ይሰብክ ጀመር፥ ሁሉም ተደነቁ።
ሰውየው ያዳነው ጌታ ኢየሱስ መሆኑን በግልጥ ተናገረ።
በሰውየው ስብከት ውስጥ ስላሴ የሚባል ነገር የለም።
አሕዛብ በሚኖሩበት በአስሩ ከተማ ውስጥ በአጋንንት ተይዞ እብድ የነበረው ኋላም ነጻ የወጣው ሰውዬ የመጀመሪያው አሕዛብ ወንጌላዊ ሆነ። በዚህ ቃል ውስጥ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነጻ የወጣ አሕዛብ የወንጌል አገልጋይ እንደሚሆን ነው።
አሕዛብ ወንጌልን እስከ ምድር ዳርቻ የማዳረስ ኃላፊነት አለባቸው።
ማቴዎስ 24፡14 ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
የዳኑ አሕዛብ ሁሉ እውነትን በዓለም ዙርያ ሁሉ የማሰራጨት ኃላፊነት አለባቸው።
አስር መጨረሻን የሚያመላክት ቁጥር ነው
አስሩ ከተማ።
ሙሴ 12 ሰላዮችን ወደ ተስፋይቱ ምድር ላከ፤ ነገር ግን ከመካከላቸው አስሩ ምድሪቱን ልንወርስ አንችልም የሚል መጥፎ ወሬ ይዘው ተመለሱ። ስለዚህ አስር በመጀመሪያው ፍልሰታቸው የገጠማቸውን ውድቀት የሚያመለክት ቁጥር ነው።
በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሚሽነሪዎች ዘመን ወርቃማው ዘመን ነበረ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሚሽነሪዎች ከእንግሊዝና ከእስኮትላንድ በመውጣት የመዳን ወንጌልን እና ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ይዘው ወደ ብዙ የዓለማችን ሃገራት ሄዱ። ግን ብዙ ሃገሮች ወንጌል ሳይደርሳቸው ቀሩ።
ነገር ግን ዕድሜ በ2,000 ዓ.ም አካባቢ አሜሪካኖች ለፈጠሩት ኢንተርኔት ይሁንና ወንጌሉ በዓለም ዙርያ ሊሰራጭ ችሏል።
አስሩ ከተማ የሚባለው ካርታው ላይ በብጫ ቀለም የተመለከተው ቦታ ነው።
አስሩ ከተማ የሚባለው አስር ከተሞች ተጠጋግተው የሚገኙበት ክልል ነው (እነርሱም ካናታ፣ ሂፐስ፣ ዲዮን፣ ግራሳ፣ ገደራ፣ ፕላ፣ ፊልደልፊያ፣ ራፋና፣ እስካይቶፖሊስ ሊሆኑ ይችላሉ)፤ እነዚህ ከተሞች ከዮርዳኖስ በስተ ምስራቅ ከገሊላ ባሕር በስተ ደቡብ የሚገኙ የግሪክና የሮማ ኮንፌደሬሽኖች ናቸው። ይህ አካባቢ ምስራቃዊው የምናሴ ግዛት ነበረ።
ዛሬ ፊልደልፊያ አማን ተብሎ የሚጠራው የዮርዳኖስ ዋና ከተማ ነው።
ይህ ፊልደልፊያ እስያ ውስጥ ከሚገኙት ሰባት ቤተክርስቲያናት አንዱ አይደለም።
ፔላ ደግሞ ኢየሱስ በማቴዎስ ምዕራፍ 24 በተናገረው ትንቢት መሰረት በ70 ዓ.ም ሮማውያን ኢየሩሳሌምን ከማፍረሳቸው በፊት በከበቡዋት ጊዜ ክርስቲያኖች ሸሽተው የሄዱበት ከተማ ነው።
10ሩ የአሕዛብ ከተሞች 10 ቁጥር ላይ ትኩረት እንድናደርግ ያሳስቡናል።
10 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ የሚፈጸሙ ክስተቶችን የሚወክል ቁጥር ነው።
በዘመን መጨረሻ ላይ የምትገኘዋን ቤተክርስቲያን ለመግለጽ ኢየሱስ የ10ሩን ቆነጃጅት ምሳሌ ተጠቅሟል።
ማቴዎስ 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
ይህ የቤተክርስቲያንን የመጨረሻ ሁኔታ ይወክላል። ሁሉም አንቀላፍተው ነበር። ሁላቸውን ከተኙበት ነቅተው ከየቤተክርስቲያኖቻቸው እንዲወጡ የሚቀሰቅስ ጥሪ ያስፈልጋቸው ነበር። ይህም ጥሪ እየመጣ ነው፤ አመጣጡም በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ መናወጥን በሚያስከትል ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ አማካኝነት ሊሆን ይችላል። ሎስ አንጀለስ ከባሕር በታች በምትሰጥም ጊዜ ምን እንደሚፈጠር አስቡ።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
ጌታ ሙሽራይቱን ከምድር ነጥቆ ወደ ሰማይ ይወስዳታል፤ በዚያም ጊዜ ዓለም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ትገባለች።
ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ የተጠቀሰው ስድስተኛው ማሕተም ከታላቁ መከራ ጋር የተያያዙ ክስተቶችን በተመለከተ ነው የሚናገረው።
ራዕይ 6፡12 ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥
ታላቁ መከራ ሲጀምር በሚመጣው ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ አማካኝነት 7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ያበቃሉ።
ዳንኤል በራዕይ ያየው የአሕዛብ ምስል እግሮቹ ሸክላ እና ብረት ሲሆኑ እነዚህም ሙሽራይቱንና ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖችን ይወክላሉ። እግሮቹ 10 ጣቶች አሉዋቸው። የቤተክርስቲያን አስር አምባ ገነን መሪዎች ስልጣናቸውን ለመጨረሻው ፖፕ ሲያስረክቡ ነው።
61-0806
የዳንኤል ሰባኛው ሳምንት
በዚህ በዘመን መጨረሻ አስተውሉ … ዳንኤል በ2ኛው ምዕራፍ እና በ34ኛው እንዲሁም በ35ኛው ቁጥር ይህን ታላቅ ምስል ልብ ብሎ ተመለከተ። እየተመለከተም ሳለ እጅ ሳይነካው አንድ ድንጋይ ከተራራ ተፈንቅሎ ወጣ፤ እየተንከባለለ መጣና ምስሉን እግሩ ላይ መታው፤ ሰባበረው … ልብ በሉ … ጭንቅላቱን አይደለም የመታው እግሮቹን ነው።
እነዚህ አስር የእግር ጣቶች የሚያመለክቱት የመጨረሻውን ዘመን ነው።
62-0909 ጊዜው እያለቀ ነው
ነገር ግን ይህ ላብራራላችሁ እሞክራለሁ፤ አስር ቁጥር “ዓለማዊነትን” የሚያመለክት ቁጥር ነው።
አስር ዓለማዊነትን የሚወክል ቁጥር ነው።
ስለዚህ በመጨረሻ ዘመን ትኩረት የሚደረገው በዓለማዊነት ላይ ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ ዮሐንስ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉት አውሬ ላይ የተቀመጠች አንዲት ሴት አየ፤ እርሷም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት።
ራዕይ 17፡3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
“እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።” እነዚህ ነገሥታት ዘውድ አልጫኑ ግን የንጉሥ ዓይነት ስልጣን አላቸው። እነዚህ አምባገነን መሪዎች ናቸው። እነዚህ 10 ፈላጭ ቆራጮች በአውሬው ማለትም በመጨረሻው ፖፕ ስር ሆነው ነው ስልጣናቸውን የሚቀበሉት።
እግዚአብሔር የተስፋው ልጅ ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት ሰዶም ውስጥ 10 ጻድቅ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን አንደማያጠፋት ለአብርሐም ቃል ገባለት። አብርሐም ግን 10 ጻድቅ ሰዎችን ሊያገኝ አልቻለም።
ይመጣል ተብሎ የተስፋ ቃል የተነገረለት ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በሚመጣበት ጊዜ አካባቢ 10 አመጸኛ አምባ ገነን መሪዎች በዛሬው እንደ ሰዶም በሚመስለው ግብረ ሰዶማውያን በበዙበት ዓለማችን ውስጥ ይነሳሉ። ስለዚህ በሰዶም እንደሆነው በምድራችን ላይ ሚሳኤሎችና ኑክሊየር ቦምብ ከሰማይ እሳት የሚያዘንቡበት ጊዜ ተቃርቧል።
ኑክሊየር ቦምብ ያላቸው ሃገሮች እነዚህ ናቸው።
1. ራሺያ - 6,257 (1,458 ሊተኮሱ የተዘጋጁ፤ 3,039 ያላቸው ኑክሊየር ቦምብ ብዛት፤ 1,760 ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ)
2. አሜሪካ - 5,550 (1,389 ሊተኮሱ የተዘጋጁ፤ 2,361 ያላቸው ኑክሊየር ቦምብ ብዛት፤ 1,800 ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ)
3. ቻይና - 350 (የኑክሊየር ቦምብ ክምችቷን በትጋት እያሳደገች ናት)
4. ፈረንሳይ - 290 አላት
5. እንግሊዝ - 225 አላት
6. ፓኪስታን - 165 አላት
7. ሕንድ - 156 አላት
8. እስራኤል - 90 አላት
9. ሰሜን ኮሪያ - 40 – 50 አላት (በግምት)
መጨሻው ሲቀርብ ኮምፒዩተር አሁን በሚጠቀምበት ባይናሪ ዲጂት ዓለምን እየተቆጣጠረ ነው፤ ቁጥሮቹም 1 እና 0 ናቸው።
እነዚህ ሁለት ቁጥሮች በአንድነት ሲሆኑ 10 ቁጥርን ይሰጡናል። ይህም በኮምፒዩተር ቁጥጥር ሥር እየወደቀ ያለውን ዓለማችንን ያመለክታል።
ዓለማዊ ጌሞችና ሞባይል ስልኮች የሚሩት በኮምፒዩተር ቺፕ አማካኝነት ነው። እነዚህ ሁሉ የሰዎችን አእምሮ እና ትኩረት ይቆጣጠራሉ።
ኢየሱስ ወደ አይሁዶች ለመመለስ አሕዛብን ትቶ ይሄዳል
ማርቆስ 5፡21 ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ በባሕርም አጠገብ ነበረ።
ኢየሱስ አሕዛብ ከሚኖሩበት ከአስሩ ከተማ ወጥቶ ሄደ። ከዚያ ተመልሶ አይሁዶች መካከል ገባ።
ይህም ኢየሱስ ከሰባቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያኖች ጋር ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ወደ አይሁዶች እንደሚመለስ ያመለክታል።
“በባሕርም አጠገብ ነበረ።”
ራዕይ 17፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
ባሕር በታላቁ መከራ ዘመን የሚኖረውን እረፍት የሌለውን የሰው ዘር በሙሉ ይወክላል።
ታላቁ መከራ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ጊዜ የሚሞቱበት ዘመን ነው።
በዚያ ነውጥ በሚነግስበት የ3½ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ኢየሱስ 144,000ዎቹን አይሁዶች ለመጥራት ወደ አይሁድ ሕዝብ ይመለሳል።
ዛሬ በሕይወት ከሚኖሩ 18 ሚሊዮን አይሁዶች ውስጥ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ይገደላሉ።
ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።
በእንደዚህ ዓይነት ዘመን ውስጥ ከአሕዛብ ወገን የሆነችዋ የክርስቶስ ሙሽራ ተነጥቃ ወደ ሰማይ ስትሄድ ወንጌል ተመልሶ ወደ አይሁዶች ይሄዳል።
ማርቆስ 5፡22 ኢያኢሮስ የተባለ ከምኵራብ አለቆች አንዱ መጣ፤ ባየውም ጊዜ በእግሩ ላይ ወደቀና፦
ይህም አይሁዶች ወደ ኢየሱስ እንደሚመለሱ ያመለክታል።
ማርቆስ 5፡23 ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው።
ልጅቱ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የክፉዎች ሰራዊት ተሰብስበው እስራኤል ሊያጠፉት የተነሱበትን ጊዜ ትወክላለች።
ማርቆስ 5፡24 ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።
ሰዎች ኢየሱስን ከበውት የሚያዋክቡበት ሰዓት ነበረ።
የ12 ዓመታት ደም መፍሰስ በሽታ አንዴ በመንካት ብቻ ተፈወሰ
ማርቆስ 5፡25 ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥
ደም የሚፈሳት ሴት መጣች። 12ቱ ዓመታት 12ቱን የእስራኤል ነገዶች ያስታውሱናል።
ማርቆስ 5፡26 ከብዙ ባለ መድኃኒቶችም ብዙ ተሠቃየች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ከስራ ባሰባት እንጂ ምንም አልተጠቀመችም፤
ማርቆስ ኢየሱስን እንደ አገልጋይ አድርጎ ነው የገለጸው። ማርቆስ የሰራተኛን ወይም በቀን ሥራ የተቀጠረ የቀን ሰራተኛን ድካምና ንዴት ያሳየናል። ሴቲቱ ገንዘቧን ሁሉ በውድ የሕክምና ወጪዎች አውጥታ ከጨረሰች በኋላ ስታይ ተሽሏት ሳይሆን ሕመሟ ብሶባት ታገኘዋለች።
በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ የሚኖሩ አይሁዶች የሚገጥማቸው ፈተና ከባድ ነው። የመጨረሻው ፖፕ ወይም የአመጽ ሰው በሚነሳበትና በነሱ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ማንም ሊረዳቸው አይችልም። የመጨረሻው ዘመን ፖፕ የአይሁዶችን እስቶክ ኤክስቼንጅ ገንዘብ ፍለጋ ከእነርሱ ጋር ውል ይፈራረማል፤ ከዚያ በኋላ የአይሁዶችን ገንዘብ የሚያወድምበት ሰይጣናዊ መንገድ በመፍጠር ከእነርሱ ጋር የነበረውን ውል ያፈርሳል። ልክ እንደዚህች ሴት አይሁዶችም ምንም ገንዘብ አይኖራቸውም።
ማርቆስ 5፡27 የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች።
ትሕትና። የልብሱን ጫፍ እንደምንም ብላ ለመንካት ከኋላው መጣች።
ማርቆስ 5፡28 ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ ብላለችና።
ሐሰተኛውና ለራሱ ስልጣን እንጂ ለአይሁድ ሕዝብ ምንም የማይገደው ካሕን ቀያፋ ልብሱን ቀደደ፤ በዚህም ምክንያት የሕጉ ዘመን አበቃ፤ ስለዚህ ሮማውያን የኢየሩሳሌምን ከተማ እን ቤተመቅደሱን በ70 ዓ.ም ባፈረሱ ጊዜ ከ1 ሚሊዮን በላይ አይሁዶች ሊሞቱ ችለዋል።
እውነተኛው ሊቀ ካሕናት ኢየሱስ መጣ።
ሮማውያኑ ወታደሮች በቀራንዮ መሰቀል አጠገብ የኢየሱስን ልብስ አልቀደዱም።
በዚህ ክፍል እንደምናነበው ልብሱ ደም ይፈሳት የነበረችዋን ሴት ፈውሷታል። ይህም በታላቁ መከራ ውስጥ የሚቀሩትን አንድ ሶስተኛ አይሁዶች ሊፈውሳቸው የሚችለው ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ያመለክታል። እንዲሁም 144,000 አይሁዶችን በመንፈስ ቅዱስ የሚሞላቸው ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 19፡23 ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።
24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
ሴቲቱ የኢየሱስን ልብስ በመንካት ብቻ ተፈወሰች።
ማርቆስ 5፡29 ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።
በጌታ ኃይል እና በእምነቷ ተፈወሰች።
ማርቆስ 5፡30 ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ፦ ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው? አለ።
የሴቲቱ እምነት ከኢየሱስ ውስጥ ኃይል ስቦ በመወሰድ ኢየሱስን አደከመው።
ማርቆስ 5፡31 ደቀ መዛሙርቱም፦ ሕዝቡ ሲያጋፉህ እያየህ፦ ማን ዳሰሰኝ ትላለህን? አሉት።
ደቀመዛሙርቱ ግራ ተጋቡ። ብዙ ሰዎች እያጋፉት ነበር። ነገር ግን ከኢየሱስ ውስጥ ኃይል ስቦ ሊወስድ የሚችለው እምነት ብቻ መሆኑን አልተረዱም። ለምሳሌ ወንድም ብራንሐም ለብዙ ሰዎች ከጸለየ በኋላ ይደክመዋል። የሚጸልይላቸው ሰዎች እምነት ከእርሱ ውስጥ ኃይል እየሳበ ስለሚወስድ ያደክመዋል።
ዳንኤል 8፡27 እኔም ዳንኤል ተኛሁ፥ አያሌም ቀን ታመምሁ፤
ዳንኤል ታላላቅ ራዕዮችን ከማየቱ የተነሳ ደክሞት ታመመ።
ማርቆስ 5፡32 ይህንም ያደረገችውን ለማየት ዘወር ብሎ ይመለከት ነበር።
ኢየሱስ በእምነቷ ከእርሱ ኃይል የወሰደችዋን ሴት ማየት ፈለገ።
ማርቆስ 5፡33 ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀች፥ እየፈራች እየተንቀጠቀጠችም፥ መጥታ በፊቱ ተደፋች እውነቱንም ሁሉ ነገረችው።
ይህ በመጨረሻ በታላቁ መከራ ዘመን መሲሁን የሚያገኙትን 144,000 አይሁዶች ያመለክታል። እነዚህ ሰዎች መሲሁ አይሁዶች አንቀበልም ብለው የገደሉት ኢየሱስ መሆኑን ሲያዩ በታላቅ ፍርሃት ይፈራሉ።
ማርቆስ 5፡34 እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት።
ኢየሱስ 144,000ዎቹን በመንፈስ ቅዱስ ይሞላቸውና የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል።
አይሁዶች ለ2,000 ዓመታት መንፈሳዊ እንቅልፍ ውስጥ ቆይተዋል
ማርቆስ 5፡35 እርሱም ገና ሲናገር ከምኵራብ አለቃው ቤት ዘንድ የመጡት፦ ልጅህ ሞታለች፤ ስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ? አሉት።
ልጅቱ ሞታለች። ታላቁ መከራ ብዙዎች የሚሞቱበትና ብዙዎች በፍርሃት የሚኖሩበት ዘመን ነው።
እንቅልፍ ማለት ሰው በዙርያው የሚሆነውን ነገር የማያውቅበተ ሰዓት ነው።
አይሁዶች ለ2,000 ዓመታት ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ቆይተዋል።
ኢየሱስ ከአሕዛብ ወገን የሆነችዋን ሙሽራውን ወደ ሰማይ ከወሰዳት በኋላ 144,000ዎቹን አይሁድ ከእንቅልፍ ሊቀሰቅሳቸው ወደ ምድር ይመለሳል።
ከሞቱበት መንፈሳዊ ሞት ያስነሳቸዋል።
ማርቆስ 5፡36 ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው።
በእምነት ከኖርን ሁኔታዎቻችን ሊያስፈሩን አይችሉም።
ማርቆስ 5፡37 ከጴጥሮስም ከያዕቆብም ከያዕቆብም ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም።
ከኢየሱስ ጋር ተከትለው እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ደቀመዛሙርት ሶስት ብቻ ነበሩ።
ጴጥሮስ የተጻፈውን ቃል ማመንን ይወክላል፤ የተጻፈው ቃል ማለት ኢየሱስ ነው። ያዕቆብ በትንሳኤው ላይ ያለንን ተስፋ ይወክላል። ከሁሉ በፊት መጀመሪያ የተገደለው ደቀመዝሙር እርሱ ነው። ዮሐንስ ደግሞ ለሰዎች ሁሉ ሊኖረን የሚገባንን ፍቅር ይወክላል።
እምነት፣ ተስፋ፣ እና ፍቅር ከሌለን ኢየሱስን እየተከተልን አይደለንም።
ኢየሱስ ስለጠራን ከሌሎች የተሻልን ነን ማለት አይደለም። ከጸጋው የተነሳ የማይገባንን ቸርነት ስላደረገልን ሕይወታችን በፊት ከነበረው የተሻለ ይሆናል።
ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሐንስን ይዞ መግባት ማለት ኢየሱስ የሐዋርያቱን አስተምሕሮ ይዞ ወደ 144,000ዎቹ አይሁዶች ይሄዳል ማለት ነው። 144,000ዎቹ አይሁዶች የአዲስ ኪዳን እውነቶችን ተቀብለው ያምናሉ።
ማርቆስ 5፡38 ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ፤
ለቅሶ እና ዋይታው የታላቁን መከራ ዘመን ያመለክታሉ።
ማርቆስ 5፡39 ገብቶም፦ ስለ ምን ትንጫጫላችሁ ታለቅሳላችሁም? ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም አላቸው።
ትንሳኤው ከሞትንበት እንድንነቃ ይረዳናል። ስለዚህ በትንሳኤው ካመንን ሞት ረጅም እንቅልፍ ብቻ ነው።
ማርቆስ 5፡40 በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናትም ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ።
“በጣምም ሳቁበት።” ሐዘናቸው የውሸት የማስመሰል ነበር። ከልባቸው አልነበረም። የእውነታቸውን አዝነው ቢሆን ኖሮ ወዲያው ኢየሱስ ላይ በማፌዝ ሊስቁ አይችሉም ነበር።
ይህ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ የሚገቡ ሰዎችን ነው የሚገልጸው፤ እነርሱም ሰነፎቹ ቆነጃጅት ናቸው። ሰነፎቹ ቆነጃጅት ለመጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው ፍቅር ጥልቀት የለውም። ለዚህ ነው በሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች የተታለሉት፤ ምክንያቱም እምነታቸው ትክክል መሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይረጋገጥል ብለው አልጠየቁም።
ነገር ግን ኢየሱስ ከሕዝብ ራቅ ብሎ 144,000ዎቹን ለብቻቸው ያገኛቸዋል።
ማርቆስ 5፡41 የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ፦ ጣሊታ ቁሚ አላት፤ ፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው።
አይሁዶች እንደ ሕዝብ ለለ2,000 ዓመታት ያህል ሞተዋል። እብራይስጥ ቋንቋ ሞቶ ነበር። አይሁዶች በ1948 ዓ.ም ወደ ተስፋይቱ ምድር መመለሳቸው ከሙታን በትንሳኤ እንደመነሳት ነው። በተለይ ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በተደረገባቸው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ውስጥ 6 ሚሊዮን አይሁዶች ከተገደሉ በኋላ ተመልሰው ወደ ሃገራቸው መግባታቸው ከሙታን እንደመነሳት ነው።
ማርቆስ 5፡42 ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።
12 ዓመት። ልክ ለ12 ዓመት ደም እንደፈሰሳት ሴት። ይህ ቁጥር 12 በተጠቀሰበት ሁሉ 12ቱን የእስራኤል ነገዶች ያስታውሰናል። መንፈስ ቅዱስን የሚቀበሉት 144,000 አይሁዳውያን የሚወለዱት ከነዚህ አስራ ሁለት ነገዶች ነው። ይህም ታላቅ መደነቅን ይፈጥራል ምክንያቱም በዚያ ጊዜ የአመጽ ሰው እና ሰራዊቱ አይሁዶችን በሙሉ ጨፍጭፈው አጥፍተዋል ተብሎ ይታሰባል። የአመጽ ሰው በዚያ ጊዜ 12 ሚሊዮን አይሁዳውያንን ይገድላል፤ እነዚህም በአሁኑ ዘመን ካሉት 18 ሚሊዮን አይሁዳውያን ውስጥ ሁለት ሶስተኛዎቹ ናቸው።
144,000ዎቹን እና ቀሪዎቹን ወደ 1,000 ዓመት መንግስት የሚገቡትን 6 ሚሊዮን አይሁዳውያን ከሞት የሚያድናቸው የኢየሱስ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ብቻ ነው።
በሕይወት የሚተርፉ አይሁዶች ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ጋር አብረው ለ1,000 ዓመታት በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ይኖራሉ። በዚህም እግዚአብሔር ለአብራሐም ሰጥቶት የነበረው የተስፋ ቃል ይፈጸማል።
በአምስተኛው ማሕተም መሰረት የተገደሉት አይሁዶች የሰማዕት መጎናጸፊያ ይሰጣቸውና ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ። ታላቁ መከራ በብዙ ሰቆቃ ቢጠናቀቅም እንኳ ለአይሁዶች ግን ድል ይሆንላቸዋል። የእግዚአብሔር ጸጋ ይህን ሁሉ ያደርጋል።
ራዕይ 6፡9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
ብሉይ ኪዳንን አምነዋል። አይሁዶች የራሳቸው ምስክርነት አላቸው። ክርስቲያኖች የሚመሰክሩት ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳዳናቸው ነው።
ራዕይ 6፡10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።
እነዚህ በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የተሰዉ አይሁዶች ናቸው፤ አብዛኞቹ በቤተክርስቲያን ሰዎች እጅ ነው የተገደሉት። እነርሱም በሰማይ ይኖራሉ። ስለዚህ ሙሽራይቱ ተነጥቃ ወደ ሰማይ በምትሄድበት ጊዜ አይሁዶቹ ወደ ምድር ወርደው በዲኖሚኔናዊ ቤተክርስቲያኖች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ ይፈልጋሉ።
አይሁዶች በቀል ይፈልጋሉ። ሕጉ ዓይን ለዓይን በማለት በቀል ይፈቅድላቸዋል።
ክርስቲያኖች ግን ልክ እንደ ኢየሱስ እና እንደ እስጢፋኖስ ለገደሏቸው ሰዎች ምሕረትን ይለምናሉ።
ራዕይ 6፡11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።
አሕዛብ የእግዚአብሔር ሙሽራ ናቸው።
አይሁዶች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። ሌሎቹ አገልጋዮች ደግሞ በ3½ ዓመታት ታላቅ መከራ ውስጥ የሚሞቱት 144,000 አይሁዶች ናቸው፤ በተጨማሪ ደግሞ በመጨረሻው ፖፕ እና በሰራዊቱ እጅ ከሚሞቱት አይሁዶች መካከል ሁለት ሶስተኛዎቹም አገልጋዮች ናቸው።
ማርቆስ 5፡43 ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸው፦ የምትበላውን ስጡአት አላቸው።
ኢየሱስ 144,000ዎቹን አይሁዶች በሚስጥር ያገኛቸዋል። ይህን ማድረጉን ማንም አያውቅም።
እነዚህም አይሁዶች መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው አዲስ ኪዳንን እንደ ምግብ እየበሉ ሙሽራይቱ የተረዳቻቸውን አስተምሕሮዎች እነርሱም ወደ መረዳት ይደርሳሉ።