ማርቆስ 4 - እግዚአብሔር አሰራሩ ከሰዎች ይለያል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ትልልቅ ቤተክርስቲያኖች መሪዎች ጤናማ መንፈስ የላቸውም። ኢየሱስ አንድ አሕዛብ የሆነ እብድ ሰውን ለማዳን ማዕበል ያለበትን ባሕር አቋርጦ ሄዷል።
- በቃሉ ዘር ውስጥ ነፍስ የእምነት እርሻ ናት
- የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተመልሶ የሚመጣባቸው 3 ደረጃዎች
- መልካም አገልጋዮች ኢየሱስ በቅርበት እየተከተሉ እውነትን ይማራሉ
- ከእግዚአብሔር ተለይተን ልንቀር የምንችልባቸው 3 መንገዶች አሉ
- ቃሉ ቸል ከተባለ ወይም ከተለወጠ ብርሃን ይሰወራል
- ብታምኑ እግዚአብሔር ከዚህም የሚበልጥ ነገር ያሳያችኋል
- የመጨረሻው መከር የሚታጨደው በሞት ማጭድ ነው
- ትልቅ ከሆነ ነገር ተጠንቀቁ
- ጥበብ የሚጀምረው እግዚአብሔርን ከመፍራት ነው
በቃሉ ዘር ውስጥ ነፍስ የእምነት እርሻ ናት
ማርቆስ 4፡1 ደግሞም በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በታንኳ ገብቶ በባሕር ላይ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕር ዳር በምድር ላይ ነበሩ።
ማርቆስ ኢየሱስን እንደ ታላቅ አገልጋይ ነው የገለጠው፤ እርሱም ትልቅ በሬ ሆኖ ያደገው ጥጃ ሲሆን ሸክማችንንና ሐጥያታችንን ከእኛ ተቀብሎ በመሸከም አርቆ ጥሎልናል።
ስለዚህ ኢየሱስ በሐጥያት እና በጽድቅ መሃል ግልጽ መስመር ያሰመረ አገልጋይ ነው። በዚህም ምክንያት በምድር እና በባሕር መካከል የሚለይ ግልጽ መስመር ያለበትን ቦታ ማለትም የባሕሩን ዳርቻ መረጠ።
ባሕር እረፍት የሌለውን ብዙ ሕዝብ ይወክላል፤ ይህም ሕዝብ በሐይማኖታዊ ሽንገላ ሞገድ፣ በፖለቲካዊ ነውጥ እና በገንዘፍ ፍቅር ወዲያና ወዲህ እየተወሰደ ይንገላታል። ከዚህ ሁሉ እንግልትና ወከባ የተነሳ ሕዝቡ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ትኩረት ማድረግ ያቅተዋል።
ደረቀቁ ምድር ደግሞ ጻድቃንን ይወክላል።
ከዚህ መረዳት የምንችለው ነገር ቢኖር ሕዝቡን ጻድቅ ለማድረግ (ይህ እውነት ሕዝቡ በደረቁ ምድር ላይ በመቆማቸው ተመስሏል) ኢየሱስ ወደ ባሕር መሄድ አለበት። ኢየሱስ የእኛን ሐጥያት በራሱ ላይ ወስዶ በመሸከም ስለ እኛ ሐጥያት ሆነ፤ በዚህም መንገድ ሐጥያት የሚጠይቀውነ ዋጋ ማለትም መሞትና ወደ ሲኦል መግባትን ከፈለ። መርከብ ውስጥ ስለተቀመጠ ባሕሩ ሊጎዳው አልቻለም። እርሱ ፍጹም ስለነበረ ሲኦል ምንም ሊያደርገው አልቻለም። ስለዚህ በሲኦል እሳት ላይ እየተራመደ ሄዶ ሐጥያታችንን ሰይጣን ላይ አራግፎታል።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የመሰሉት በሲኦል እሳት ላይ እየተራመደ በመሄዱ ነው፤ ነገር ግን እሳቱ ፍጽምናውን አቃጥሎ ሊያጠፋ አልቻለም።
ማርቆስ 4፡2 በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበር፥ በትምህርቱም አላቸው፦ ስሙ፦
ኢየሱስ ምሳሌዎችን እየተጠቀመ ነው ያስተማረው፤ ምሳሌዎቹም ከገሃዱ ዓለም የተወሰዱ ሲሆኑ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ካልገለጠለት በቀር ኢየሱስ በተናገራቸው ምሳሌዎች ውስጥ የተሰወሩትን ጥልቅ መንፈሳዊ ሚስጥራት በራሱ ሊረዳቸው አይችልም። በማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ የተጠቀሱት ልባም ቆነጃጅት የያዙት መብራት ይህ ነው።
ኢየሱስ ታላቁ አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን ያደረገው ትልቅ አገልግሎት ቤተክርስቲያንን የ2,000 ዓመታት ባስቆጠሩት በሰባቱ የተለያዩ ደረጃዎች ወይም የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ተሸክሞ ማሳለፉ ነው።
ሁለቱ ታላላቅ ርዕሰ ጉዳዮች ኢየሱስ ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑና የእርሱ ሞትና ትንሳኤ የሐጥያታችንን ስርየት የምናገኝበት ብቸኛ መንገድ መሆኑ ነው።
ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ያመጣልን ድንቅ መረዳት ነው።
ማርቆስ 4፡3 እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።
ከሥራዎች ሁሉ የሚበልጠው ሥራ ግብርና ነው። ምክንያቱም ሁላችንም ምግብ ያስፈልገናል።
ፍጥረታዊው ሕይወታችን የሚኖረው እንደ ስንዴ በመሳሰሉ ሰብሎች ላይ ተደግፎ ነው። የመጀመሪያው ሥራ የስንዴውን ዘር መትከል ነው።
ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣ የእድገት ኡደት አለ። መጀመሪያ ቅጠል፣ ቀጥሎ አበባ እና ፖለን፣ ከዚያም ፍሬ ያፈራል።
መንፈሳዊ ሕይወታችን የተመሰረተው በነፍሳችን ውስጥ በምንተክለው መንፈሳዊ ዘር ነው ምክንያቱም ነፍሳችን ልክ እንደ እርሻ ነው። የመንፈሳዊ እድገት ኡደትም አለ፤ ይህም ኡደት መጽደቅ፣ መቀደስ፣ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ፣ እንዲሁም የተሰወሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መገለጥ መቀበልን ያካትታል።
ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው፤ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ኤርምያስ 31፡12 … ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥
ሰዎች ነፍስ አላቸው፤ ማመን የምንችለውም ለዚህ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ለማመን እምነት ሊኖረን ያስፈልጋል።
ዕብራውያን 10፡38 ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል
39 እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ
ማርቆስ 4፡4 ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።
ኢየሱስ ዘሪውን አልወቀሰም፤ ዘሪው የወንጌልን እውነት የሚሰብከውን ሰው ይወክላል። ኢየሱስ የወቀሰው መሬቱን ብቻ ነው፤ መሬቱም የአድማጩን ልብ ይወክላል።
ሰባኪው ጥሩ አድርጎ ሊሰብክም ላይሰብክም ይችላል። ሰባኪውን ልትወዱት ወይም ላትወዱት ትችላላችሁ።
ሆኖም ሰባኪው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተናግሮ እንደሆን ባትቀበሉት ችግር ውስጥ የምትገቡት እናንተው ናችሁ፤ ማመካኛም አይኖራችሁም።
ሰዎች መልእክቱን ላለመቀበላቸው ማመካኛ ፍለጋ መልእክተኛው ላይ አቃቂር ያወጡበታል። እግዚአብሔር ግን እንዲህ ዓይነቱን ማመካኛ አይቀበልም።
መንገድ ዳር የተባለው ቦታ እርሻው አጠገብ ያለው የሰዎች መመላለሻና ደረቅ የሆነ ቦታ ነው። እውነትን ላለመቀበል የደነደነ ልብ የአጋንንት ማደሪያ ይሆናል፤ በምሳሌው ውስጥ ወፎቹ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙ አጋንንትን ነው የሚወክሉት።
ብዙ የተማሪ ሳይንቲስቶች መጽሐፍ ቅዱስን አይቀበሉም። ሳይንስ ግን ዓለም ከየት እንደመጣች መናገር አይችልም ምክንያቱም በየትኛውም ሳይንሳዊ ቲዎሪ ኃይል ያለ ምንም ነገር ሊፈጠር አይችልም።
እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አይቀበሉም። ሰዎች ሲሞቱም ምንም ተስፋ የሚጡበት ነገር የላቸውም።
ሌሎች ሐይማኖቶች መጽሐፍ ቅዱስን አይቀበሉም። ለሰዎች የሚያቀርቡት ነገር በመልካም ሥራዎች ላይ የተመሰረተ ሰው ሰራሽ መዳን ነው። ነገር ግን ለሐጥያት ስርየት ተስማሚ የሆነ መስዋእት የላቸውም።
ማርቆስ 4፡5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤
እነዚህ በግማሽ ልባቸው ንሰሃ የገቡ ሰዎች ናቸው። ሐይማኖታቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን ከፍ ማድረግና የገንዘብ ጥቅም ማግኘት ይፈልጋሉ። ለራሳቸው አልሞቱም።
የሚያገለግሉት ለመስጠት ሳይሆን ለትርፍ ነው።
ማርቆስ 4፡6 ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።
የእውነተኛ አማኝ መፈተኛዎች መስዋእት፣ መከራ እና ችግር ናቸው።
ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ከልባቸው ያልቆረጡ ሰዎች ባሕሪያቸውን ለመቅረጽ መከራ እና ሽንፈት ሲገጥማቸው ወዲያው ተሰናክለው ይሄዳሉ።
ማርቆስ 4፡7 ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም።
ሌሎች ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ለመራመድ እውነተኛ ፍላጎት አላቸው ግን ለብቻቸው መቆም አይችሉም። በሌሎች ላይ ይደገፋሉ፤ ቤተክርስቲያንንም እንደ ምርኩዝ ይጠቀማሉ። አዘውትሬ ቤተክርስቲያን እስከ ሄደኩ ድረስ በሰላም እኖራለው ብለው ያስባሉ። ድጋፍ እና እርዳታ ሲያስፈልጋቸው ወደ እግዚአብሔር በማየት ፈንታ ወደ ሌሎች ሰዎች ያያሉ። አንዳንዶች ዓለማዊ ስኬትን ፍለጋ ወደ ብልጽግና ወንጌል ዘወር ይላሉ። ዓለም በሚያሳያቸውና በሚያቀርብላቸው ነገር ይዘናጋሉ። የግል ስኬት ጥማታቸው የእውነትን ፍቅር ከልባቸው ውስጥ ያስወጣዋል። የሃብት ወጥመድ መንፈሳዊነታቸውን ያንቀዋል። እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ ነገር ግን ዓለማዊ ስኬትና ታዋቂነትንም ይፈልጋሉ። ከዚይም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር እውነት ከሕይወታቸው በንኖ ይጠፋል።
እነዚህ ሰው አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ያምናሉ ግን ይህ በቂ አይደለም። አንድ እግዚአብሔር እንዳለ አጋንንትም ያምናሉ።
ያዕቆብ 2፡19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተመልሶ የሚመጣባቸው 3 ደረጃዎች
ነገር ግን ለዘመናቸው የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የሚያምኑ ሰዎች አሉ።
ማርቆስ 4፡8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።
እግዚአብሔር በየዘመኑ ለዚያ ዘመን የተገለጠውን እውነት በማመን እና በመታዘዝ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰዎች አሉት።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን በሐዋርያት በተመሰረተች ጊዜ ይህን ይመስል ነበር።
ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ ጳጳሳት ብቸኛ መሪ በመሆን ቤተክርስቲያንን መጨቆን ጀመሩ። በመጀመሪያ ግን የአመራር ኃላፊነት የተሰጠው በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያገለግሉ የሽማግሌዎች ሕብረት ነበር። በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ግለሰብ አለቃ ሆኖ ተሾመ።
በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሮማዊው ንጉስ ኮንስታንቲን በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ አማካኝነት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን ስላሴ የተባለ ቃል እንድትቀበል አስገደደ። ይህንንም ተከትሎ “አንድ አምላክ በሶስት አካላት፣” “እግዚአብሔር ወልድ፣” እና “አብ እና ወልድ አንድ ባህሪ ናቸው” የሚሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶች ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው “ስሉስ” አምላክ ስም አልባ ሆነ፤ ምክንያቱም ሶስት ሰዎች በአንድ ስም ሊጠሩ አይችሉም።
በአራተኛው ማለትም በትያጥሮን የቤተክርስቲያን ዘመን በጨለማው ዘመን ውስጥ የቤተክርስቲያንን ሐሰተኛ ትምሕርቶች የተቃወሙ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች በግፍ ተገደሉ፤ ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ማለት ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን ጨቁና ትገዛ ነበር።
እንደ ፖፕ እና ካርዲናል፣ ሊቃነ ጳጳሳት የተባሉ መጽሐፍ ቅዱስ እውቅና ያልሰጣቸው መሪዎች አጥቢያ ቤተክርስቲያኖችን ሊመሩ የሚገባቸውን የሽማግሌዎችን ቦታ ቀምተው ወሰዱ።
ቀስቱ እንደሚያመለክተው ነበልባሉ እያነሰ መሄዱ ቤተክርስቲያን ከአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ምሳሌ እየራቀች መሄዷን ያመለክታል።
እግዚአብሔር ግን በመጨረሻዎቹ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እውነተን ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ወሰነ።
በ1520 ዓ.ም ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን ትምሕርት በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልሶ ወደ ቤተክርስቲያን አመጣ (በእምነት መጽደቅ)። በዚያ ዘመን ሰዎች አብዛኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ገና አልተረዱትም ነበር፤ ነር ግን ቢያንስ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት 30% ያህሉ ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሷል።
ቤተክርስቲያን ቀስ በቀስ ወደ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እውነት መመለስ ጀመረች።
በ1750 ዓ.ም አካባቢ ጆን ዌስሊ የቅድስና (የመቀደስን) ትምሕርት እና የወንጌል ስርጭት አገልግሎትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። ይህም አገልግሎት ለታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን መጀመር ምክንያት ሆኗል።
አብዛኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገና አልታወቁም ነበር፤ ነገር ግን የሰው አእምሮ ንቃቱ ጨምሮ 60% ያህሉ እውነት ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ መጥቶ ነበር።
ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እስክትመለስ ድረስ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ማለትም 5ኛው፣ 6ኛው፣ እና 7ኛው ዘመን ፈጅቶባታል።
ጴንጤቆስጤያዊው እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው እንዲመጡ አደረገ፤ አሜሪካ ውስጥ ደግሞ በ1963 ዓ.ም ዊልያም ብራንሐም የሰባቱን ማሕተሞች ሚስጥራት ገለጠ። ይህም እውቀት ሙሽራይቱ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት እንድትረዳ አስችሏታል። ይህም የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን አካላት ሙሉ በሙሉ 100% ወደ መጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
ማቴዎስ 19፡30 ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።
ፊተኞች ኋለኞች እና ኋለኞችም ፊተኞች የሚሆኑ ከሆነ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እና በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን መካከል ልዩነት አይኖርም ማለት ነው። እነርሱ ያምኑ የነበሩትን ተመሳሳይ እምነት ነው እኛም ማመን ያለብን።
ማርቆስ 4፡9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ አለ።
ኢየሱስ ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክት ከተናገረ በኋላ ሲያጠቃልል ይህንን ቃል ነው የተናገረው።
ይህም ኢየሱስ ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ታሪክ እየተናገረ እንደነበረ ያሳያል።
እግዚአብሔርን በእውነት ያገለገሉት ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት የሞከሩት ብቻ ናቸው።
መልካም አገልጋዮች ኢየሱስ በቅርበት እየተከተሉ እውነትን ይማራሉ
ኢየሱስ ዛሬ የሚገለጠው እንደ ሰው ሳይሆን ሰዎች መረዳት እንደሚችሉት እንደ እግዚአብሔር ቃል ነው።
ስለዚህ የማርቆስ ወንጌል ለዘመናችን የተገለጡትን የእግዚአብሔር ሚስጥራት ካልተረዳን በቀር ጥሩ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ልንሆን እንደማንችል ያመለክታል።
የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ እንደተናገረው መልካሙ መሬት የሚወክለው መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት ጽንሰ ሃሳብን ነው ።
ማቴዎስ 13፡23 በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።
ማርቆስ 4፡10 ብቻውንም በሆነ ጊዜ፥ በዙሪያው የነበሩት ከአሥራ ሁለቱ ጋር ስለ ምሳሌው ጠየቁት።
ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት እውነተኛ ፍላጎት አልነበራቸውም። ኢየሱስ ስለ ምን እየነገራቸው እንደነበረ አላወቁም፤ ደግሞም የማወቅ ፍላጎት አልነበራቸውም። ስለዚህ ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ትተውት ሄዱ። ዛሬም ሰዎች እንዲህ ናቸው። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል ትተው ይሄዳሉ።
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ከ12 ደቀመዛሙርት ጋር አብረው በመቆየት የሚስጥሩ ፍቺ እንዲብራራላቸው ጠየቁ።
ከቃሉ ጋር የሚቆዩና ሚስጥሩን መረዳት የሚፈልጉ ሰዎች በጣም ጥቂት መሆናቸው ግን ያሳዝናል።
ማርቆስ 4፡11 እንዲህም አላቸው፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ … ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።
ኢየሱስ ሚስጥሩን የሚገልጠው የእውነት ማወቅ ለሚፈልጉ ነው። ከምሳሌዎች ጀርባ የተሰወረው ትርጉም ከልባቸው ፍላጎት ለሌላቸው ሰዎች ተሰውሮባቸው ይቀራል እንጂ አይገለጥላቸውም።
እውነትን መረዳት የሚቻለው በሰዎች ስርዓት የተደራጀች ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖ አይደለም። ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ ያላት “ትክክለኛ” ቤተክርስቲያን የለችም። እያንዳንዳችሁ በግል ተግታችሁ እውነትን ለማግኘት መፈለግ አለባችሁ።
ሉቃስ 17፡21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።
የእግዚአብሔር መንግስት ታላቅ ሚስጥር ናት። የእግዚአብሔር መንግስት ማለት በግለሰብ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
እግዚአብሔር አይሁዶችን እንደ ሕዝብ ነበር ያስተዳደራቸው፤ ቤተክርስቲያንን ግን በግለሰብ ደረጃ ነው የሚመራት።
በሰው ውስጥ የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ያ ሰው እውነትን ማወቅ እንዲችል እንዲሁም የሚያየውንና የሚሰማውን መረዳት እንዲችል የሚረዳው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቃችሁ ማስረጃው ለዘመናችን የተገለጠውን የእግዙአብሔር ቃል ሚስጥር መረዳት መቻላችሁ ነው።
ማርቆስ 4፡12 አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፥ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፥ እንዳይመለሱ ኃጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።
የቀሩት ከልባቸው እግዚአብሔርን ለመከተል ያልወሰኑ ሰዎች ያያሉ እንጂ የሚያዩትን አያስተውሉም። ምሳሌውን ይሰማሉ እንጂ በውስጡ የተሰወረውን መንፈሳዊ ሚስጥር መረዳት አይችሉም።
የሚያስፈራውም እውነት እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች አለመፈለጉ ነው።
በሕይወታቸው እግዚአብሔርን አላስቀደሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔርም በሕይወቱ ውስጥ አይፈልጋቸውም።
እግዚአብሔር በሕይወታችሁ ውስጥ የሁሉ ጌታ ካልሆነ በጭራሽም የናንተ ጌታ መሆን አይፈልግም።
በራሳችሁ መንገድ መሄድ የፈለጋችሁ ጊዜ እግዚአብሔር ስለናንተ ምንም ፍላጎት አይኖረውም።
እግዚአብሔር የናንተ ጌታ እንዲሆን ከፈለጋችሁ በሁሉ ነገር ትገዙለታላችሁ እንጂ ከዚያ ውጭ አይቀበላችሁም።
ማርቆስ 4፡13 አላቸውም፦ ይህን ምሳሌ አታውቁምን? እንዴትስ ምሳሌዎቹን ሁሉ ታውቃላችሁ?
ይህን ምሳሌ መረዳት እና ሌሎቹ ስድስት የቤተክርስቲያን ዘመናት የፈለቁበት የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መሆኑን ማየት ካቃተን የሌሎቹን ምሳሌዎች ትክክለኛ ትርጉም መረዳት አንችልም። ሁሉም ምሳሌዎች የሚገልጡት እግዚአብሔር ወይም ሰይጣን በተለያዩ ዘመናት ውስጥ ከቤተክርስቲያን ጋር ያደረጉትን ነገር ነው።
“ናዛራ” ማለት እውነት ማለት ነው።
ኔትዘርማለት ቅርንጫፍ ነው።
“ኔትዘሬት” ማለት የቅርንጫፍ ወይም ቅንጫፍ የሚወጣበት ቦታ ነው።
ናዛራ እና ኔትዘሬት አንድ ላይ ሲደረጉ ናዝሬት የሚለውን ቃል ይሰጡናል፤ ይህም የእውነት ቅርንጫፍ የሚያብብበት ቦታ ማለት ነው።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደ ቅርንጫፍ ሆነው የወጡት ከኢየሱስ ነው።
ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥
ይህ ምሳሌ ስለ መጀመሪያው እና ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ስለሆነው ስለ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚናገር መሆኑን ካልተረዳን ችግር ውስጥ ነን። የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሚስጥር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙና መረዳት ከሚያስፈልጉን ሚስጥራት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።
ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መካከል ቆሞ የመጀመሪያው ዘመን መልካም እንደነበረ ይነግረናል ምክንያቱም እርሱ በዚያ ቆሞ ነበር። ከዚያ በመቅረዙ ወደ ቀኝ ስንመለከት እውነት እየጠፋ መሄዱን እናያለን። ከዚያም ከግራ በኩል በመጨረሻዎቹ ሶስት ዘመናት ውስጥ እውነት ተመልሶ ሲመጣ እናያለን (እነርሱም 5ኛው፣ 6ኛው፣ 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው) ከዚህም የተነሳ 7ኛው ዘመን ወደ መጀመሪያው ዘመን መመለስ ይችላል።
በሰባተኛው ዘመን ውስጥ መሆን በራሱ በቂ አይደለም ምክንያቱም እግዚአብሔር በራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ ሰባተኛውን ዘመን አውግዞታል። ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለብን።
ቀጣዩ ስዕል በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሚገኙትን ሰነፎቹን ቆነጃጅት ያመለክታል፤ እነርሱም የዳኑ ነገር ግን የሚያምኑትን እምነት ትክክለኛነት የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም ማሳየት የማይችሉ ክርስቲያኖች ናቸው።
መብራታቸው ውስጥ ምንም ዘይት የላቸውም ስለዚህ ሊያበሩት አይችሉም።
የሚያሳዝነው ነገር ከያዙት የእውነት እና የስሕትት ቅልቅል ጋር ሆነው ወደ ታላቁ መከራ መግባታቸው ነው። በተለያዩ ፍልስፍናዎቻቸውና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ሃሳቦቻቸው የተነሳ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ሙሉ በሙሉ መመለስ አልቻሉም። የተወሰኑ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ተረድተዋል፤ ነገር ግን ጥልቅ የሆኑትን የመጽፍ ቅዱስ ሚስጥራት አልተረዱም።
ደግሞም ስለተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸውም እውቀታቸው በጣም ትንሽ ነው።
“ተብሎ ተጽፏል” በሚለው አባባል ቦታ “እከሌ እንዲህ ብሏል” የሚለው አባባል ተተክቷል።
ጳውሎስ በሚሰብክ ጊዜ የቤርያ ሰዎች ስብከቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይመዝኑ ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 17፡10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤
11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
ከእግዚአብሔር ተለይተን ልንቀር የምንችልባቸው 3 መንገዶች አሉ
የዘሪው ምሳሌ የጥንቷን ቤተክርስቲያን ነው የሚገልጠው።
ኢየሱስ የመጀመሪያውን ምሳሌ ማብራራት ጀመረ።
ይህ ማብራሪያ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የእግዚአብሔርን እውነት መረዳት ተሰጥቶት እንደነበረ የሚያሳይ ፍንጭ ይሰጠናል። ዘመናቸውን በደምብ ተረድተው ነበር።
ስለዚህ ለመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ምን ያህል እንደቀረብን በማየት ለእውነት ምን ያህል እንደቀረብን መለካት እንችላለን። ከመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ሰዎች ጋር የምንቃረን ከሆነ የተሳሳትነው እኛ ነን።
ትክክለኛው ዘር የሚታይበት ሁለት ጊዜ አለ።
ይህም ዘሩ በሚዘራበት እና በሚታጨድበት ጊዜ ነው። በመከር ጊዜ የሚታጨደው ዘር ሐዋርያት ከዘሩት ዘር ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው።
መከሩ የሚመጣው ሙሽራይቱ ከምድር ታጭዳ ወይም ተነጥቃ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ወደ ሰማይ በምትሄድበት ጊዜ ነው።
በመጀመሪያው ዘመን የነበሩ ቅዱሳን የማይሞተውን አካላቸውን ለብሰው ይነሳሉ፤ በምድር ላይ በሕይወት የሚገኙት ቅዱሳንም ወደ ማይሞት አካል ይለወጣሉ። እነዚህ ሁለት ወገኖች በመሰረታዊ እምነታቸው አንድ ዓይነት ይሆናሉ።
ማርቆስ 4፡14 ዘሪው ቃሉን ይዘራል።
ዋነኛው ትኩረት የሚደረገው ዘር በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ነው።
በመጀመሪያ የምናምነው ነገር ወሳኝ ነው።
ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እንደሆነና ሊለወጥ እንደማይችል ማመን አለባችሁ።
ማርቆስ 4፡15 ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል።
ሁልጊዜም ቢሆን የእግዚአብሔርን ቃል የማይቀበሉ ልበ ደንዳና ሰዎች ይኖራሉ።
ማርቆስ 4፡16 እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፥ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፥
ሌሎች ደግሞ ላይ ላዩን ብቻ የእግዚአብሔርን ቃል በደስታ የሚቀበሉ አሉ። ብዙ መከራ እስካላመጣባቸው ድረስ ይቀበሉታል። የመዳንን ነጻ ጥቅሞች ብቻ ነው የሚፈልጉት።
ማርቆስ 4፡17 ለጊዜውም ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፥ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ።
ቀላል በሆነ መንገድ በረከትን ማጨድ ፈለጉ። እግዚአብሔርን የሚያገለግሉት ለጥቅም ብለው ነው። በክርስትና ሕይወት መንገድ ላይ ያለውን ትግልና ፈተና አይፈልጉም።
ማርቆስ 4፡18 በእሾህም የተዘሩት ሌሎች ናቸው፥ ቃሉን የሰሙት እነዚህ ናቸው፥
እነዚህ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ከልባቸው ይከታተላሉ፤ ነገር ግን በተጨማሪ ደግሞ ልባቸው ወደ ገንዘብና ወደዚህ ዓለም ጥቅሞችም ያጋድላል።
ማርቆስ 4፡19 የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።
ድሎት መንፈሳዊ ቅናትን ይገድልና በቀብር ሰዓት እየሳቀ ይሄዳል።
ለዓለማዊ ሃብት ያለን ፍላጎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት ያቀጭጨዋል።
ዓለማዊ አድማሳችን እየሰፋ በሄደ ቁጥር መንፈሳዊ አድማሳችን እየጠበበ ይሄዳል። ለተገለጠው ቃል ያለን ፍላጎትም በየጊዜው ይቀንሳል።
ቃሉ ቸል ከተባለ ወይም ከተለወጠ ብርሃን ይሰወራል
ማርቆስ 4፡20 በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።
በስተመጨረሻም እንደ “መልካም መሬት” ዓይነት ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ቃሉን ተቀብለው ዘመናቸውን ተረድተው በየትኛው የመታደስ ደረጃ ላይ እንዳሉ ይገነዘባሉ። በሰባተኛው ዘመን ውስጥ አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት ይቀበላሉ፤ ከዚህም የተነሳ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ ይችላሉ። ዝም ብለው መፈላሰፍ ደስ ስለሚላቸው ብቻ አዳዲስ ሚስጥራትን መፍጠር እንደሌለባቸው ያውቃሉ።
የቃሉ ብርሃን ግን በቀላሉ ይሰወራል።
ማርቆስ 4፡21 እንዲህም አላቸው፦ መብራትን ከዕንቅብ ወይስ ከአልጋ በታች ሊያኖሩት ያመጡታልን? በመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት አይደለምን?
እንቅብ ማለት እሕል የሚሰፈርበት ትልቅ ቅርጫት ነው።
እንቅብ የመብራትን ብርሃን በቀላሉ ሊሸፍን ይችላል። ነገር ግን እንቅቡ በመብራቱ ላይ ከመከደኑ በፊት እንቅቡ ውስጥ ያሉት ዘሮች በሙሉ መደፋት አለባቸው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን ትክክለኛ እውነት አስወግደው የራሳቸውን ትክክለኛ ያልሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ያስተምራሉ።
ቤተክርስቲያን በሞኝነትና ባለማስተዋል ለጳጳሳት መገዛት ስትጀምር ጳጳሳቱ የእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ራስ ሆኑ። ይህ ዓይነቱ አምባገነናዊ አገዛዝ በመጀመሪያ ሐዋርያት ለሽማግሌዎች ሰጥተው የነበረውን የመሪነት በታ ነጥቆ ወሰደው።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ለአንድ ሰው መገዛት ስትጀምር ይህ አንድ ሰው ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዘወር እያደረጋት እንደ ስላሴ፣ የስቅለት አርብ፣ ክሪስማስ የመሳሰሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ሃሳቦችን እንድትከተል ከማድረግ በተጨማሪ ፖለቲካ ውስጥ እንድትገባ አደረጋት።
የመጽሐፍ ቅዱስ መብረት ሲጠፋ የጨለማው ዘመን መጣና በትያጥሮን ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን በሙሉ ጨቁና እንድትገዛ አደረገ፤ ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ማለት ሲሆን የአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጠሪያ ነው።
እግዚአብሔር ለትያጥሮን ምን እንደሚል ተመልከቱ።
ራዕይ 2፡22 እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤
60-1208 የትያጥሮን ዘመን
እነሆ በመኝታዋ ላይ እጥላታለሁ … (ምን ዓይነት መኝታ ነው? የዓለማዊነት መኝታ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው ውድቀቷ …) ከእርሷ ጋር አብረው የሚሴስኑትንም ሁሉ ንሰሃ ገብተው ካልተመለሱ በቀር ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ እጥላቸዋለሁ። (ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ።)
ልጆቿንም በሞት እገድላቸዋለሁ …
… ልጆቿን እገድላለሁ …
… ምን? የካቶሊክ ቤተክርስቲያን፤ ልጆቿ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ናቸው። አያችሁ፤ እነርሱ የሚያደርጉት ልክ እርሷ የምታደርገውን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነው ጥምቀታቸው ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አካል ውስጥ ተጠምቀዋል፤ “በኢየሱስ ስም” በመጠመቅ ፈንታ “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” እያሉ ይጠመቃሉ። ሁሉንም ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ነው የሚያደርጉት። እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን ያርጋሉ።
… “”ልጆቿን በሞት አልጋ ላይ ጥዬ እገድላቸዋለሁ። እስቲ በደምብ እንዲገባችሁ ላንብበው፤ ቁጥር 22 ላይ ነው መሰለኝ፡-
አልጋ ላይ እጥላታለሁ ፤ ከእርሷ ጋር የሚሴስኑትንም ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ እጥላቸዋለሁ (ታላቁ መከራ) …
[የሞት አልጋ ታላቁ መከራ ሲሆን በዚያ ይሞቱና ወደ ሲኦል ይገባሉ]
63-0321 አራተኛው ማሕተም
… በመኝታ ላይ እጥላታለሁ … (ይህ ሲኦል ነው።) …
የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ
በቁጥር 22 መሰረት መኝታው የመከራ መኝታ ማለትም ታላቁ መከራ ነው።
በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የዓለማዊነት አልጋ መጣና ፖፑ በስም ለመጥቀስ የሚያሳፍር የእርኩሰት ጉድጓድ ውስጥ ሲገባ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተሸፈነ። በጨለማው ዘመን አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተደበቀ።
ከጨለማው ዘመን እና ከኒቅያ ጉባኤ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የስሕተት አስተምሕሮ የሚያምኑ ቤተክርስቲያኖች ወደሚጠብቃቸው የ3½ ታላቅ መከራ ተንደርድረው እየሄዱ ናቸው።
ማርቆስ 4፡22 እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምና፤ ወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም።
በጨለማው ዘመን ውስጥ በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ብዙ ክፉ ነገሮች ተደብቀው ገብተዋል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመስቀል ዘመቻዎችን አዘጋጅታ ወታደሮች ብዙ ሕዝቦችን እንዲገድሉ፣ እንዲዘርፉና አስገድደው እንዲደፍሩ አደረች።
በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እውነት ጠፍታ የቆየችበት ጊዜ ወደ ማለቂያው ደረሰ።
ከ1520 በኋላ ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር እውነትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ማምጣት ጀመረ።
ማርቆስ 4፡23 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
ይህ እግዚአብሔር ለሁሉም የቤተክርስቲያን ዘመናት የሰጠው ማስጠንቀቂያ ነው። የምንሰማው ነገር ነው የወደፊታችንን እጣ ፈንታ የሚወስነው።
የጨለማው ዘመን ወይም መካከለኛው ዘመን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መካከል ነው የሚገኘው። ከዚያ በፊት የነበሩ ሶስት ዘመናት የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ እውነት ጥለዋል። ቀጣዮቹ ሶስት ዘመናት ደግመ ሐዋርያዊውን የአዲስ ኪዳን እውነት በመቀበል እየታደሱ ናቸው።
ብታምኑ እግዚአብሔር ከዚህም የሚበልጥ ነገር ያሳያችኋል
ማርቆስ 4፡24 አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም ይጨመርላችኋል።
ቤተክርስቲያን በጥንቃቄ ማዳመጥ አለባት። የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል የማይቀበሉ ሁሉ እግዚአብሔርም አይቀበላቸውም። የተገለጠውን ቃል የሚቀበሉ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርም ይቀበላቸዋል።
ለሚያዳምጡ ደግሞ እግዚአብሔር ብዙ ይጨምራላቸዋል።
በ1520 ዓ.ም አካባቢ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት ብቻ ነው የሚለውን እውነት መልሶ አመጣው።
ማርቆስ 4፡25 ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
በ1750 ዓ.ም አካባቢ ጆን ዌስሊ የቅድስና እና የወንጌል ስርጭት ትምሕርቶችን መልሶ አመጣ።
ዌልስ ውስጥ በ1904 ዓ.ም እና ሎስ አንጀለስ ውስጥ በ1906 ዓ.ም እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የጴንጤቆስጤ ስጠታዎችን ጨመረላት።
ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት መመለስ እንችል ዘንድ ከ1947 እስከ 1965 ዓ.ም ዊልያም ብራንሐም ተሰውረው የነበሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገለጦ አስተማረ።
ስለዚህ በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን እውነት እየጠነከረ ሄደ።
ግለሰብም እንደዚሁ ነው የሚሆነው። ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኝ አድርገህ ስትቀበለው እርሱ ደግሞ የቅድስና እና የወንጌል ስርጭትን መንገድ ያሳይሃል። ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራህ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ያሳይሃል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
እምነታችሁ ትክክለኛ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ወደ ማረጋገጥ ከተመለሳችሁ በኋላ ኢየሱስን በራዕይ ምዕራፍ 10 እንደተጠቀሰው ብርቱ መልአክ ከሰማይ የሚያወርደው ታላቅ ድምጽ ይህ ነው፤ በወረደም ጊዜ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንን ከሙታን ያስነሳቸዋል።
ወንድም ብራንሐም በሕይወቱ የመጨረሻ ወር ውስጥ እርሱ የሰበከውን መልእክት ታላቅ “ድምጽ” ሲጠባበቅ ነበር።
“ድምጹ” ማለት እርሱ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ የገለጠበት ጊዜ አይደለም።
“ድምጹ” የሚሰማው የሙሽራይቱ አካላት እውነትን ለራሳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ መግለጥ ሲችሉ ነው።
65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ማርቆስ 4፡26 እርሱም አለ፦ በምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ናት ሌሊትና ቀን ይተኛልም ይነሣልም፥
የእግዚአብሔር መንግስት በውስጣችሁ የሚገኘው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።
ነገር ግን መርሳት የሌለባችሁ ነገር እግዚአብሔር አስተሳሰቡ ከእናንተ ይለያል።
ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር የሚሰራው እኛ ከምንሰራበት በተለየ መንገድ ነው።
“ሰው።” ማን እንደሆነ እኛ አናውቅም። እግዚአብሔር እውነትን ለመስበክ ቢጠቀምብን ለራሳችን ምንም ክብር መውሰድ የለብንም። እግዚአብሔር ቃሉን ለማሰራጨት ሰባኪዎችን ይጠቀማል።
የቃሉ ዘር መጀመሪያ መሬት ውስጥ መቀበር አለበት። ወደ ላይ መውጫው መንገድ ወደ ታች ነው። ዘሩ ከመብቀሉና ወደ ላይ ከማደጉ በፊት መጀመሪያ መሞትና መቀበር አለበት። እንደ ግለሰብ እግዚአብሔር በእኛ ከመጠቀሙ በፊት መጀመሪያ ለራሳችን መሞት አለብን።
ማርቆስ 4፡27 እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድግማል።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ አማኞች አብዛኞቹ በዓለም ላይ ምን ዓይነት ታላቅ ኃይል እየለቀቁ እንደነበር አልተገነዘቡ ይሆናል። ይህም ኃይል ክርስትና በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ያመጣው አስደናቂ ለውጥ ነው።
“ይተኛል።” ስንተኛ በዙርያችን የሚደረገውን ነገር አናውቅም።
ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ምን እያደረገ እንዳለ አያውቁም። ቀን እና ሌሊት ሳንታክት ለእግዚአብሔር ደፋ ቀና እንላለን ነገር ግን እግዚአብሔርን የምናገለግለው ለራሳችን በሚመቸን መንገድ ነው። ሌላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች የሚያደርጉትን ኮርጀን ስናደርግ እግዚአብሔር የተደሰተብን ይመስለናል።
በየዓመቱ ዲሴምበር 25 ቀን ክሪስማስ እናከብራለን ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ቀኑን ታከብራለች። መጽሐፍ ቅዱስ የትም ቦታ የጌታን ልደት አክብሩ ብሎ አልተናገረንም። ስለዚህ የቤተክርስቲያንን ልማድ መከተል ከመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ እንድንወጣ ያደርገናል።
አንድ ዘር መሬት ውስጥ ከተቀበረ በኋላ እንዴት እንደሚበቅል ሰዎች ምንም አያውቁም። ይህንን ሂደት የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰዎች እግዚአብሔርን ለማገልገል ቀንና ሌሊት ሊነሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ካልሆንን ጥረቶቻችን በሙሉ ከንቱ ናቸው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ አይደለም።
አንድ ሰው እንዴት በጸጋ እንደሚያድግ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። በየትኛውም ዘመን ቤተክርስቲያን እንዴት እንደምታድግ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ቤተክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ያስደስተዋል ይጠቅመዋል ብለው የሚያስቡትን ብዙ ነገር ያደርጋሉ። እግዚአብሔር ግን የሚሰሩትን ሥራ በተለየ መንገድ ሊመለከት ይችላል።
ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
“ጌተ ሆይ፣ ጌታ ሆይ” ማለት ድግግሞሽ ነው። ድግግሞሽ አጽንኦት ነው። እነዚህ ክርስቲያኖ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን አጥብቀው ያምናሉ። ትንቢት ይናገራሉ አጋንንትንም ያስወጣሉ። ብዙ አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። በአስደናቂ ስጦታዎቻቸው እና በአገልግሎታቸው ሁላችንም እንገረማለን።
ማቴዎስ 7፡23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላቸዋል፡- “ከፊቴ ዞር በሉ። ላውቃችሁ እንኳ አልፈልግም።”
ማርቆስ የሚያስተምረን እንዴት አገልጋይ እንደምንሆን ነው። ወደ ስኬቶቻችሁ አትመልከቱ።
ሮሜ 11፡29 እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።
እግዚአብሔር ላልዳኑ ሰዎች እንኳ ስጦታ ሰጥቶ እና ተጠቅሞባቸው ያውቃል።
ማቴዎስ 5፡45 በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ … እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
የእግዚአብሔር ኃይል እና መልካምነት ለመልካሞችም ለክፉዎችም ሰዎች ሁሉ ይደርሳል።
ክፉ ሰው የነበረው በለዓም አስደናቂ ትንቢት ተናገሯል።
ጌዴዎን መወሰን ሲያቅተው እግዚአብሔር ለሁለት የጠላት ሰራዊት ወታደሮች አስደናቂ ሕልም ከነትርጓሜው ሰጣቸው፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያውቁ አልነበሩም።
ስለዚህ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታ ቢሰጣችሁ ታላቅ ሰዎች ሆናችሁ ማለት ነውን?
የመጨረሻው መከር የሚታጨደው በሞት ማጭድ ነው
ማርቆስ 4፡28 ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች።
ምድር ውስጥ ያለው አፈር ዘር እንዲበቅል ያደርጋል።
ቤተክርስቲያን ባለፉት ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ወደ እውነት ስትመለስ ያለፈችባቸው ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።
በ5ኛው ዘመን በሉተር የመጣው በእምነት የመዳን እውነት።
ዌስሊ በ6ኛው ዘመን ያስተማረው ቅድስና።
በ7ኛው ዘመን የመጡት ጴንጤቆስጤያዊ ስጦታዎችና በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት የተገለጡት ተሰውረው የነበሩ ሚስጥራት።
መጀመሪያ ቡቃያ ሲሆን ይህም በሰይፍ የተመሰለውን የእግዚአብሔርን ቃል ያስታውሰናል። የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ቃል እንደ ሰይፍ ይቆርጠናል፤ ነገር ግን እኛ መስማትና መታዘዝ አለብን።
ሁለተኛው እና ሶስተኛው ደረጃ ውስጥ ጆሮዋችን መስማት አለበት። ቃሉን መስማት አለብን፤ ለእኛ ባይመቸንም እንኳ ቃሉ የሚለውን ነው መስማት ያለብን።
የቃሉ ሚስጥራት ያለማቋረጥ እየተገለጡ ናቸው፤ እኛም ለዘመናችን የተሰጠን የእግዚአብሔር መገለጥ እንዳያልፈን መጠንቀቅ አለብን።
የእግዚአብሔርን ቃል ዘወትር ማዳመጥና ለዘመናችንም የተገለጠውን ፈቃዱንም ጠንቅቆ ማወቅ ለሁሉም ክርስቲያን የትክክለኛ ስኬት ምንጭ ነው።
በዘመናችን 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችና ዲኖሚኔሽኖች መኖራቸው ግራ ሊያጋባንና ሊያስተን ይችላል። በእውነተኛው መንገድ ሊመራን የሚችለው ብቸኛው አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ማዳመጥና መከተል እጅግ አስፈላጊ ነው።
ማርቆስ 4፡29 ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል።
መከሩ የሚመጣው ፍሬው ከተክሉ ላይ በሚታጨድበት ጊዜ ነው። መንፈሳዊው መከር የሚመጣው በሕይወት የሚኖሩት የሙሽራይቱ አካላት ስጋቸው ሲለወጥና ከምድር ተነጥቀው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ወደ ሰማይ ሲሄዱ ነው።
ከመጀመሪያው ዘመን ዘር ጋር የሚመሳሰለውና የመጨረሻውን ዘመን ሙሽራ የሚወክለው የስንዴው ዘር ከሞተው ተክል ላይ ታጭዶ ይሰበሰባል። የቀረው የቤተክርስቲያን ተክል ይሞታል ምክንያቱም ሰዎቹ በታለቁ መከራ ውስጥ ገብተው ሊሞቱ የተፈረደባቸው ሰነፍ ቆነጃጅት ናቸው።
ከዚያ በኋላ በቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች የተሞኙትን ክርስቲያኖች ማለትም ሰነፎቹን ቆነጃጅት (የዳኑ ክርስቲያኖችን የሚወክሉ ንጹሃን ሴቶች) የሞት ማጭድ ያጭዳቸዋል።
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት በተመለሰ ጊዜ ማጭዱ ስንዴውን እንዲያጭድ ይላካል። የስንዴው ዛላ ተቀጥቅጦ ነው ገለባው የሚራገፍለትና ከውስጡ የስንዴው ዘር የሚወጣው። ስለዚህ ከባድ ጊዜ እንደሚመጣ ይጠበቃል።
በ1917 የተጀመረው የሶቪየት ሕብረት ባንዲራው ላይ የማጭድ ምልክት ነበረው፤ ይህም የዘመን መጨረሻ መከር መድረሱን ያመለክታል።
ሩሲያ በ2022 ዩክሬይን ላይ ያደረገችው የግፍ ወረራ በታላቁ መከራ የ3½ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሚመጣው ሞት እና ጥፋት ማሳያ ወይም ቅምሻ ነው። ይህ ወረራ የተከሰተው ባልተጠበቀ ጊዜ ሲሆን ብዙ ጥፋትና ውድመትን እንዲሁም የንጹሃን ሕይወት መጥፋትን አስከትሏል። የታላቁ መከራ ዓመታትም ባልጠበቅነው ጊዜ በድንገት ይመጡብንና ከዚህ የባሰ ጥፋትን ያስከትሉብናል።
ትልቅ ከሆነ ነገር ተጠንቀቁ
ማርቆስ 4፡30 እርሱም አለ፦ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን?
ሰዎች እግዚአብሔር በአስደናቂ መንገድ ሲሰራ ያያሉ። በታላላቅ እንቅስቃሴዎች፣ ታላላቅ ቤተክርስቲያኖች እና አስደናቂ ፕሮግራሞች ላይ ዓይናቸውን ይጥላሉ። የእግዚአብሔር እውነተኛ መንግስት ግን ፈቃዱን በሚያገለግሉ ግለሰቦች ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ሉቃስ 17፡21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።
ሰዎች ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር መንግስት መገለጫ የሚመስላቸው የብዙ ሕዝብ መሰብሰብ፣ የአስደናቂ ነገሮች መታየትና አስገራሚ የሙዚቃ ዝግጅት ነው።
የእግዚአብሔር መንግስት ማለት የቃሉን ሚስጥር ሊያስተምራችሁ በእናንተ ውስጥ የሚያድረው እና በውስጣችሁ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ማርቆስ 4፡31 እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናት፥ እርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፥
ሁላችንም ትንንሽ ሆነን እንጀምራለን፤ ከዚያ ወዲያ ሰዎች የተጠሩት ታላቅ ለመሆን ይመስላቸዋል። ስለዚህ ሰዎች ስለ ቤተክርስቲያን እድገት ያስባሉ። ሰዎች መታየትና ዝና ማግኘት ይፈልጋሉ።
ከዚያም ቤተክርስቲያን ለማደግ ብላ ብቻ ታድጋለች።
እናት ቤተክርስቲያን የተዋጣለት ማዕከላዊ አስተዳደርና አመራር ለማበጀት ቅርንጫፎቿን በየሥፍራው ትዘረጋለች፤ በዚህም መንገድ በሩቅ ሁሉ ያሉ ሰዎችን ሃሳብ እየተቆጣጠረች የመሪውን ሃሳብ የሚቃወሙትን ሁሉ ትከላከላለች።
ይህም ራሺያ ውስጥ ፕሬዚዳንት ፑቲን እንዴት እንደሚሰራ ያሳየናል። የራሺያ ቲቪ ላይ የምትሰሙት የእርሱን አመለካከት ብቻ ነው። ከተቃወማችሁት ያስገድላችኋል።
ማርቆስ 4፡32 የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች።
አንዴ ተክሉ ቅርንጫፎች መያዝ እስኪችል ድረስ በደምብ ካደገ በኋላ የሰማይ ወፎች ከፍ ያሉ መሪዎች ይሆኑ ዘንድ በቅርንጫፎቹ ላይ ይሰፍራሉ።
ማርቆስ እንደ ጻፈው ቃሉን የማይቀበሉ ልበ ደንዳና ሰዎች በሰይጣን ሽንገላ ይታለላሉ።
ማርቆስ 4፡15 ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል።
ማቴዎስ እንደጻፈው ሰይጣን የሰማይ ወፎችን በመጠቀም ነው የሚሰራው፤ እነርሱም የቃሉን ዘር ከሕዝቡ ልብ ውስጥ አስወግደው በቦታው የቤተክርስቲያን ልማዶችንና ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎችን የሚያስቀምጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው።
ማቴዎስ 13፡4 እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።
ስለዚህ አገልጋይ ከትልልቅ ቤተክርስቲያኖች እና ከታላላቅ የቤተክርስቲያን መሪዎች እንዲጠነቀቅ ነው መመሪያ የሚያስፈልገው።
ማርቆስ ጽሑፉን በዚህ ሰዓት ቆም ያደርጋል። ከፍ ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ታላላቅ የቤተክርስቲያን ድርጅቶች በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንዳልሆኑ አሳይቷል።
ሰባኪዎች እግዚአብሔርን ሊያገለግሉ ሲነሱ የሚሰሩት አንዱ ትልቅ ስሕተት ይህ ነው። ትልቅ ቤተክርስቲያን መስራት ይፈልጋሉ፤ ከዚያም የዚያ ቤተክርስቲያን ራስ መሆን ይፈልጋሉ።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተክርስቲያን ተብሎ ለብቻ ሕንጻ መስራት የተጀመረው በ220 ዓ.ም ነው።
በጥንቷ ቤተክርስቲያን ሰዎች የሚሰበሰቡት በመኖሪያ ቤት ውስጥ ስለነበረ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ትልቅ ቤተክርስቲያን መሆን አይችሉም ነበር። እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን የምትመራው በአንድ ግለሰብ ሳይሆን በሽማግሌዎች ነበር። ከ170 ዓ.ም ጀምሮ ጳጳሳት ቤተክርስቲያንን እንዲመሩ የተደረገው በስሕተት ነው። በዚያ ጊዜ የሐዋርያት አስተምሕሮ እና እምነት እየተረሳ በእነርሱ ቦታ ስልጣን የሚወዱ ሰዎች እየተተኩ ነበር።
ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የጀመረው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሃሳቦች እየተጨመሩ ሲሄዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረኑ አዳዲስ ያለማቋረጥ ይጎርፉ ነበር።
ቀስ በቀስ ብዙ ስሕተቶች ወደ ቤተክርስቲያን ተጨመሩ።
ለሙታን መጸለይ።
የመስቀል ምልክት መጠቀም።
ቤተክርስቲያን ውስጥ ለተለያዩ ዓላማዎች የሚለኮሱ ጧፎችን መሸጥ።
ስላሴ እና የስቅለት አርብ። ከዚያም የፋሲካ ሰኞ እና የፋሲካ እንቁላሎች፣ እንዲሁም የፋሲካ ጥንቸሎች።
ሕጻናትን ውሃ እየረጩ ማጥመቅ።
የኢየሱስን ስም በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ መተካት።
መላእክትንና የሞቱ ቅዱሳንን ማምለክ።
ሃውልቶችንና ምስሎችን ማምለክ።
ማርያም የእግዚአብሔር እናት ነች ብሎ ማምለክ።
ዛሬ የሜሴጅ ተከታዮች ወንድም ብራንሐምን የሰባተኛው መልአክ ድምጽ ከመሆን በላይ ከፍ አድርገውት የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ብለውታል። አዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ድምጽ አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም።
ፀበል ወይም የተቀደሰ ውሃ።
ፍትሃት። ይህ ሰዎች ሊሞቱ ሲሉ የሚደረግላቸው ጸሎት ነው።
ፑርጋቶሪ።
ማርቆስ 4፡33 መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፥
ስለዚህ በዚህ ጊዜ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አድጋ ትልቅ ሆና ነበር ነገር ግን የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝቡን ከመጽሐፍ ቅዱስ መንገድ አስወጥተው አስተዋቸዋል። አረማዊ ትምሕርቶች በክርስቲያናዊ ቃል እየተዋቡ ወደ ቤተክርስቲያን ገቡ።
ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ የተወለደበት ቀን ነበረ፤ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጅ የተወለደበት ቀን ተባለ።
ኢየሱስ መናገሩን ቀጠለ ነገር ግን እነዚህን እውነቶች መስማት የሚፈልጉ ሰዎች ጥቂቶች ነበሩ። ብዙ ሰዎች በእንቅልፋም ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተመችቷቸው መኖር እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማግኘት አይፈልጉም።
ማንም ሰው ቢሆን የሚከተላት ቤተክርስቲያን የተወሰኑ እውነቶችን የተቀበለች ብትሆንም ብዙ ስሕተቶች ያሉባት እንደሆነች ማመን አይፈልግም።
የመልካም እና የክፉ እውቀት ዛፍ እውነት ያለበት መልካም አስተምሕሮ እንዲሁም ሰው ሰራሽ ስሕተቶች ያሉበት ክፉ አስተምሕሮ ይይዛል።
ማርቆስ 4፡34 ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።
ኢየሱስ በምሳሌዎች የተናገረው ጥልቁ ሚስጥር ከሕዝቡ እንዲሰወር ነው። እግዚአብሔር በብዙ ሕዝብ አይገረምም፤ ደግሞ አንዱ ሌላውን የሚከተልበትንና የሰዎችን ልማድ የሚያከብሩበትን የከብት መንጋ ዓይነት ባሕርይም አይወድም።
ነገር ግን ከደቀመዛሙርቱ ጋር ለብቻው በተቀመጠ ጊዜ የምሳሌዎቹን ትርጉም ገለጠላቸው።
እግዚአብሔር ጠለቅ ያሉ ሚስጥራትን የሚገልጠው ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለብቻቸው ጊዜ ለሚያሳልፉ ሰዎች ነው። እግዚአብሔር እንደ መንጋ ለሚያስቡ ብዙ ሕዝብ እውነትን ሊገልጥላቸው አይችልም።
ማርቆስ 4፡35 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፦ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው።
“በዚያም ቀን”። ይህ ቃል የኢየሱስ ሕይወት በስራ የተጠመደ እንደነበረ ያሳያል። አገልጋይ ተግቶ ይሰራል፤ ኢየሱስ ከማንም በላይ ተግቶ በመስራት ይህንን ጥሩ ምሳሌ አሳይቷል።
ኢየሱስ ቅፍርናሆም አካባቢ ነበረ። የገሊላ ባሕርን ተሻግሮ ጌንሰሬጥ ወይም ገደራ ወደተባለው አሕዛብ ወደሚኖሩበት ቦታ መሄድ ፈለገ።
ይህም በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ኢየሱስ ወደ አሕዛብ ተሻግሮ እንደሚመጣ ፍንጭ ይሰጠናል።
የምሽት ሰዓት ጌታ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ሊነጥቃት ሲመጣ ከሞት ባሻገር ወዳለው ከፍ ያለ ክልል የምንሻገርበትን የጌታን መምጫ ሰዓት ያስታውሰናል።
ማርቆስ 4፡36 ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ።
ብዙ ክርስቲያኖች ለጌታ ዳግም ምጻት ዝግጁ አይሆኑም ምክንያቱም የቤተክርስቲያኖቻቸውን ልማድ በመከተላቸው ሰው ሰራሽ ሃሳቦችን ስለመረጡ ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ (ከቃሉ) ርቀው ይሄዳሉ።
ደቀመዛሙርቱ “እንዲያው ወሰዱት”። ለሚሄዱበት መንገድ የሚያስፈልግ ተቀያሪ ልብስ ወይም ስንቅ ሳይይዙ እንዲያው ተነስተው ሄዱ። ከኢየሱስ ጋር ሲሄዱ ሸክም ሳያበዙ መጓዝን ለምደዋል። ስለ ምቾታቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡም። ለስራ የተዘጋጁ ብርቱ ሰዎች ነበሩ። ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ሥራ ነበረ፤ ማለትም አንድ አሕዛብ ሰው መዳን ያስፈልገው ነበር።
ኢየሱስ አንድን አሕዛብ ማዳኑ ስለ ወደፊቱ እቅዱ ፍንጭ የሚሰጥ ድርጊት ነበረ።
“እንዲያው ወሰዱት”። የእግዚአብሔርን “ቃል ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈ እንዲያው ልንወስደው” ይገባናል እንጂ ከውስጡ ምንም ነገር መቀየር የለብንም። ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር መርከብ ውስጥ ነበረ። የስኬታቸውም ሚስጥር እርሱ ከእነርሱ ጋር መገኘቱ ነው። ውጤታማ የሆኑት በራሳቸው ጥረት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው ስለተገኘ ነው።
በራሳቸው አቅም ሊከተሉ የሞከሩ ሌሎች ትንንሽ መርከቦች ነበሩ። ነገር ግን በጌታ ምጻት ወቅት ታላላቅ ፖለቲካዊ፣ መንፈሳዊ እና የገንዘብ ማዕበሎች ሊነሱ እና ምድርን በሙሉ ሊያትለቀልቁ እንደሚችሉ እናውቃለን። ሌሎቹ ትንንሽ መርከቦች ግን በመካከላቸው ኢየሱስ አልነበረም።
ታላቁ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ እነዚያ ትንንሽ መርከቦች ወዴት እንደሄዱ አልተጻፈም። ነፋስ የጦርነትና የግጭት ምሳሌ ነው። የሕይወታችን ማዕከል ኢየሱስ ካልሆነ ሊሳካልን አይችልም።
በመጨረሻው ሰዓት እንደ ተገለጠው ቃል ራሱን የሚገልጠው ኢየሱስ የሕይወታችን ማዕከል መሆን አለበት። አለበለዚያ በመጨረሻዎቹ ነውጠኛ ዘመናት ውስጥ የሚነሳው ማዕበል ጠራርጎ ይወስደንና የጌታን ምጻት ሳናይ ያመልጠናል።
ጥበብ የሚጀምረው እግዚአብሔርን ከመፍራት ነው
ማርቆስ 4፡37 ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር።
መርከቢቱ ውሃ ሞልቶባት ልትሰጥም ቀርባ ነበር። ኃይለኛ ነፋስ ስለተነሰ ከባድ የሆነ ማዕበል መርከቢቱ ያንገላታት ነበር። ሰይጣን በአየር ላይ የሚገዛው አለቃ ነው።
ኤፌሶን 2፡2 በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።
ሰይጣንና አጋንንት በስተመጨረሻ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማጥፋት ብዙ ግጭቶችን ይፈጥራሉ።
ማርቆስ 4፡38 እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ ሁሉ ረስተውት ስለነበረ ከመርከቧ ኋለኛ ክፍል ውስጥ ተኝቶ ነበር። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ እንደሚያደርጉት ነፋሱ አደገኛ ማዕበል ሲያስነሳ ሁላቸው ለነፍሳቸው ፈርተው ወዲያው ኢየሱስን ቀሰቀሱት። እኛም ልክ እንደነሱ ነን። ሕይወታችን ተደላድሎ ባለበት ሰዓት ዓይናችንን ስራችንና ስኬታችን ላይ በጣልን ጊዜ ኢየሱስን እንረሳለን። ነገር ግን ነገሮች ሲበላሹብን ወዲያው እርሱን እናስታውሰውና እንዲረዳን እንጮሃለን።
ማርቆስ 4፡39 ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።
ኢየሱስ ያደረገው ነገር ድንቅ ነው። ተፈጥሮን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይችላል።
ማርቆስ 4፡40 እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው።
ከኢየሱስ ጋር ስለነበሩ ምንም የሚፈሩበት ምክንያት አልነበራቸውም።
ማርቆስ 4፡41 እጅግም ፈሩና፦ እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ።
“ነፋስ” የጦርነት ምሳሌ ሲሆን “ባሕር” ደግሞ እረፍት የሌለውን ሕዝብ ያመለክታል። ሁለቱም በኢየሱስ ቁጥጥር ስር ናቸው። ስለዚህ ምንም ነገር ቢፈጠር ከኢየሱስ ቁጥጥር ውጭ አይደለም።
ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር ሆነውም እንኳ፤ ማዕበሉን ጸጥ ካደረገላቸውም በኋላ እንኳ እግዚአብሔርን በጣም ፈርተዋል። ኢየሱስ ሰው ብቻ አልነበረም፤ ከሰው በላይ ነበር። እርሱ በስጋ የተገለጠው እግዚአብሔር ነው።
በእግዚአብሔር ፊት መቆም በጣም አስፈሪ ነገር መሆኑን አገልጋዮች ማወቅ አለባቸው።
በእግዚአብሔር ፊት ስለመቆም ልንመካ እና በጉራ ልናወራ አንችልም።
ታላቁ ሐዋርያ ዮሐንስ ምን እንዳለ ተመልከቱ።
ራዕይ 1፡17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ።
ለተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ዓይነት ክብር ልንሰጥ ይገባናል።