ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነውን?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
እያንዳንዱ ሰው እንከን ያለበትና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የማያውቃቸውና የሚስትባቸው ነገሮች አሉት። ኢየሱስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ መሆን የሚችለው።
- አረማውያን እያንዳንዱን የሐይማኖት ቡድን የሚመራ ካሕን ነበራቸው
- ሐዋርያት እያንዳንዷን አጥቢያ ቤተክርስቲያን እንዲመሩ ሃላፊነት የሰጡት ለሽማግሌዎች ነው
- የቤተክርስቲያን መሪ ግን ሰዎች እርሱን እንዲከተሉት ይፈልጋል
- መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፓስተሮች የሚናገረው
- ስለ ፓስተሮች ከተጻፉ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ 6ቱ ፓስተሮችን የሚያወግዙ ናቸው
- እግዚአብሔር ፓስተሮችን አይቀበልም፤ ቃሉን እንዲመግቡን ያስቀመጠው እረኞችን ነው
- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መረዳት የምንችለው በትምሕርት ነው
- ፓስተሮች የ1963ቱን ደመና አስተምሕሮ እንዴት እንዳመሰቃቀሉት
አረማውያን እያንዳንዱን የሐይማኖት ቡድን የሚመራ ካሕን ነበራቸው
ማንኛውም የሰዎች ቡድን ፖሊሲውንና ገንዘቡን የሚቆጣጠር አንድ መሪ ሲኖረው ውጤታማነቱ ይጨምራል። ሃገሮች የሚተዳደሩት በዚህ መንገድ ነው። የሐይማኖት ቡድኖች ይህንን እንደ ምሳሌ ወስደው ከፖለቲካ ይኮርጃሉ።
ሰዎች ይሰባሰቡና ቤተክርስቲያን ይመሰርታሉ፤ ከዚያም ቤተክርስቲያናቸው ውጤታማ የምትሆነው በንግድ ስራ መርሆች ከተጠቀሙ መሆኑን ያስተውላሉ። ከዚህም የተነሳ ሐይማኖት እና ገንዘብ ሁልጊዜ ተቆራኝተው ኖረዋል። አንድ ብቁ የሆነ አስተዳዳሪ በስልጣን ላይ ካስቀመጡ ነገር ሁሉ ይሳካላቸዋል።
አረማውያን አንድ ካሕን በአካባቢው ላለው ቤተመቅደስ አለቃ እንዲሆን ይሾሙ ነበር፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህንን አሰራር ኮርጃለች።
ካሕኑ ለጉባኤው ምን ማመን እንዳለባቸውና እንዴት መኖር እንዳለባቸው ይነግራቸዋል። ማን መስበክ እንደሚችልና ማን መስበክ እንደማይችል የሚወስነው ካሕኑ ነው። የአስራት ገንዘብ ምን ላይ እንደሚውል የሚወስነው ካሕኑ ነው። ስለዚህ ጉባኤው በሙሉ በዚህ አንድ ሰው አመራር ስር ይወድቃል።
ሕዝቡ የካሕኑን ጥበብ ተመልካች ብቻ ሆነው ይቀራሉ።
ግን በተጨማሪ ደግሞ ከካሕኑ አለማወቅና ውስንነት የተነሳ ጉዳትም ይደርስባቸዋል።
ከዚያ ሌላ ደግሞ ሕዝቡ በራሳቸው አእምሮ ማሰብ ያቆማሉ። በሐይማኖት ውስጥ ያሉ ስሕተቶችን መለየት ያቅታቸዋል።
ከተለያየ ቤተክርስቲያን የመጡ ካሕናት ደግሞ በአንድ ጳጳስ ማዕከላዊ ቁጥጥር ስር ይሆናሉ።
ካሕኑ ለሕዝቡ የበላይ ነው፤ ጳጳሱ ደግሞ ለካሕናቱ የበላይ ነው። ይህም አንድን ቅዱስ ሰው በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል ከፍ ማድረግ ነው። ከጉባኤው በላይ ከፍ ያሉ ካሕናት ድክመታቸው ይህ ነው። እነዚህን ካሕናት መጽሐፍ ቅዱስ ኒቆላውያን ይላቸዋል። ትርጉሙ ምዕመናንን ወይም ጉባኤውን የሚያንበረክኩ የሚጨቁኑ ማለት ነው።
በዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል የሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ በካሕናቱ ይደገፋሉ።
በስተመጨረሻም ሕዝቡ ካሕኑ ወይም ጳጳሱ የተናገረውን ቃል ከሁሉ አስበልጠው ይቀበላሉ። ከጳጳሱ ንግግር የተወሰደውን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስበልጠው ያያሉ፤ መሪያቸው የተናገረውን የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ከተናገረው በላይ አክብረው ይቀበላሉ።
“ቃሉ እንዲህ ይላል” ከማለት ይልቅ “ጳጳሱ እንዲህ ብሏል” ይላሉ።
ሕዝቡ በቁጥራቸው ብዛት ይመካሉ። መሪያቸው እርሱ ብቻ እውነትን ማግኘት እንደሚችለው አድርገው ይቆጥሩታል። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳቸው እየመረመሩ ከማጥናት ይልቅ መሪያቸውን በጭፍን ያምኑታል። መጽሐፍ ቅዱን በራሳቸው ማጥናት እንደ ከባድ ስራ ይሆንባቸዋል።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች በየግላቸው መጽሐፍ ቅዱስን እያጠኑ እግዚአብሔርን በማወቅ ከማደግ ይልቅ በቡድን መሆናቸውና አንድ ሃሳብ በመያዛቸው ይመካሉ።
አንድ መሪ ቡድኑን በራሱ ሃሳብ ሲቆጣጠር ለቤተክርስቲያን እድገት የሚያዋጣ ሞዴል ነው።
ለዚህ ነው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከክርስቲያናዊ ድርጅቶች ሁሉ ትልቅ የሆነችውና 1.4 ቢሊዮን ተከታዮችን ያፈራችው።
ይህ ዓይነቱ ዘዴ የሚያዋጣ መሆኑ ተረጋግጧል ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምትከተለው አንድ ካሕን አንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያንን የሚቆጣጠርበት ዘዴ ለ2,000 ዓመታት ጸንቶ ኖሯል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከሁሉም ትልቅ እና ከሁሉም በሃብት አንደኛ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ወደ መሆን አድጋለች፤ ይህችን ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ አውሬው በማለት ይገልጻታል።
ፕሮቴስታንቶችም አንድ ሰው የአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ የሚመራበትን ዲኖሚኔሽናዊ አሰራር መገንባት ከፈለጉ የሚያገኙት ትልቅ ስኬት ለካቶሊካዊው አውሬ ፕሮቴስታንታዊ ምስል ማበጀት ብቻ ነው።
ልዩ ልዩ የሆኑት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ተሰብስበው የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ካደራጁ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነው የአውሬው ምስል ሙሉ ሆኖ ይገለጣል።
ስለ ቤተክርስቲያን ግንባታ የሮማ ካቶሊኮች የፈጠሩዋቸውንና ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች የኮረጁዋቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች ለይተን ማወቅ አለብን፤ የዚያን ጊዜ በሐይማኖታዊ ሽንገላ አማካኝነት የሚንቀሳቀሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንዴት እንደሚሰራ መረዳት እንችላለን።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።
ደጋን ሳይኖረው ቀስት ብቻ ይዞ ወጣ። ይህ ሽንገላ ነው። ነጭ ቀለም ሐይማኖተኝነትን ይወክላል፤ ሐይማኖተኝነት የሚሰራው አንድን መሪ ከሕዝቡ በላይ ከፍ አድርጎ በመሾም ነው። በ960 ዓ.ም ፖፕ ኒኮላስ ዘውድ ጭኖ ነበር፤ ይህንም ያደረገው ከቤተክርስቲያን መሪዎች በላይ እና ከነገስታት እኩል ለመሆን ነው። በ1316 ዓ.ም ፖፑ ባለ ሶስት ድርብ ዘውድ ጫነ፤ ይህን ያደረገው ከነገስታትም በላይ ለመሆን ነው። ስለዚህ አንድን ሰባኪ ከፍ ማድረግ ከተጀመረ ሰባኪው “ቪካሪየስ ክሪስቲ” እስኪባል ማለትም “በክርስቶስ ቦታ” እስኪቆም ድረስ ከፍ ማድረጉ አይቋረጥም።
አረማዊ አደረጃጀት ስርዓት በመጠቀም በዚህ መንገድ መሪዎችን ከፍ እያደረጉ ቤተክርስቲያኖችን መቆጣጠር የአርማጌዶን ጦርነት እስኪጀምር ድረስ አይቋረጥም።
ኤርምያስ 9፡8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ፤
የቤተክርስቲያን መሪዎች የሚናገሯቸው ውሸቶች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች በቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ሞትን የሚያመጡ መርዛማ ቀስቶች ናቸው።
ፕሮቴስታንት ወይም ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን የምታምነዋን በመጽሐፍ ቅዱስ ለሚያምኑ እውነተኛ አማኞች እናት የሆችዋን የመጀመሪያ ዘመን ቤተክርስቲያን ይከተላሉ፤ አለዚያ ደግሞ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አርአያነት ይከተላሉ። የሮማ ካቶሊኮች በ325 ዓ.ም ከተደረገው የኒቅያ ጉባኤ የመጣውን የስላሴ ትምሕርት እና ከተማን የሚያስተዳድር ጳጳስ በመጠቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነችዋን እናት ቤተክርስቲያን መሰረቱ፤ ሮማ ካቶሊክም ሴቶች ሎጆቿን ፕሮቴስታንቶችን ወለደች።
ራዕይ 17፡5 በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።
ሕዝቅኤል 16፡44 እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ እንደ እናቲቱ እንዲሁ ሴት ልጂቱ ናት እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።
አንድ የፕሮቴስታንት ቡድን ማደግ ከፈለገ ውጤታማነቱን በዘመናት ያስመሰከረውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እድገት ሞዴል ይከተላል። ይህም ሞዴል አንድን ሰው የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ መሾም ነው።
በተጨማሪ ፕሮቴስታንቶች ብዙ የካቶሊክ እምነቶችን ይቀበላሉ፤ ለምሳሌ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ የስቅለት አርብ፣ ስሙ ማን እንደሆነ ሳይጠቅሱ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማጥመቅ። ስላሴ ነው ብለው የሚያምኑትን አምላካቸውን የሚጠሩበት ስም የላቸውም።
ካቶሊክ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖችም የተወሰኑ ከካቶሊኮች (እና ከፕሮቴስታንት ቡድኖች) የተለዩ የሚያደርጓቸው እምነቶች አሏቸው፤ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ስልጣንን በአንድ ሰው እጅ በማድረግ ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር በሚቻልበት የካቶሊክ ዘዴ ያምናሉ።
ይህንን አንድ ባለ ስልጣን ሰው ቄስ ይሉታል፣ ሪቨረንድ፣ ጳጳስ፣ ዶሚኒ፣ በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ደግሞ ፓስተር ይሉታል፤ ፓስተር ማለት ለፕሮቴስታንቶች ካሕን ወይም ቄስ እንደማለት ነው። ይህ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ነው ይላሉ፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያንን የሚገዛት እርሱ ነው። ይህም አሰራር ውጤታማ ነው፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
ሐዋርያት እያንዳንዷን አጥቢያ ቤተክርስቲያን እንዲመሩ ሃላፊነት የሰጡት ለሽማግሌዎች ነው
ኢየሱስ የጥንቷትን ቤተክርስቲያን ይመሰርቱ ዘንድ ሐዋርያትን ትቶ ሄደ። ሐዋርያትስ ማንን ነው ትተው የሄዱት?
ሽማግሌዎችን እንጂ አንድ ግለሰብን አይደለም።
ሐዋርያው ጳውሎስ የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ለመሰረቱት ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች መልእክት ላከ፤ የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበረችዋ ቤተክርስቲያን ለመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን ሞዴል ናት። ይህች ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳን ሲጀመር የነበረች ናት።
የሐዋርያስ ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
መንጋውን መንከባከብ የእረኛ ስራ ነው።
ሽማግሌዎች ኃላፊነታቸው መንጋውን ምግብ ማብላት ነው። ይህ የአንድ ግለሰብ ብቻ አገልግሎት አይደለም።
በኃላፊነታቸው እኩል የሆኑ ሽማግሌዎች በሕብረት ለመንጋው እንደ እረኛ ሆነው ያገለግላሉ።
ጳውሎስ አንድ ሰው ፓስተር ሆኖ ቤተክርስቲያንን እንዲገዛ አልሾመም። አንድ ሰው ሪቨረንድ እንዲሆንም አልሾመም። አንድ ቄስ ቤተክርስቲያን ላይ አለቃ እንዲሆንም አላስቀመጠም።
በየትኛውም ስፍራ በእግዚብሔር አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ አስተዳዳሪዎች የአጥቢያ ሽማግሌዎች ናቸው።
ስለዚህ እረኛ ማለት ብዙ ሽማግሌዎች በአንድነት ሲያገለግሉ ነው። አንድ ግለሰብ ብቻውን ሆኖ ለእረኝነት የሚበቃ እውቀትም ሆነ ክሕሎት ሊኖረው አይችልም።
በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ መጨረሻ አካባቢ ጴጥሮስም ተመሳሳይ ሃሳበ ተናግሯል።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
4 የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
ጴጥሮስ ሽማግሌዎችን ሰላም ሲል እራሱም ሽማግሌ መሆኑን በመግለጽ ነው እንጂ ሐዋርያ ነኝ እያለ አይደለም።
57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1
መጽሐፍ ቅዱስን አሳዩኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ከአጥቢያዋ ሽማግሌ የሚበልጥ ስልጣን ያለው ማነው?
ትክክል ነው፤ አጥቢያ ቤተክረስቲያን ራሷን በራሷ ለማስተዳደር በቂ ናት፤ እያንዳንዷ ለራሷ።
12ቱ ሐዋርያት ጊዜያቸውን ጠብቀው ሲሞቱ ቤተክርስቲያንን በኃላፊነት የተረከቡዋት ሽማግሌዎች ናቸው።
ሽማግሌዎች የሚያገለግሉት ቤተክርስቲያንን ሊመግቧት ነው … እንጂ ለገንዘብ ብለው አይደለም።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ጴጥሮስ እንደ ጻፈው በቤተክርስቲያን አመራር ውስጥ ትልቅ ችግር ፈጣሪው ገንዘብ ነው። ገንዘብ የስልጣን ጥማት እና ስግብግብነትን ያስከትላል።
ለስግብግብ ሰው ገንዘብ መስጠት እሳት ውስጥ ደረቅ እንጨቶች እንደመጨመር ነው፤ ስግብግብነቱ እየባሰበት ይሄዳል።
ቁጥር 2ን ስናየው አንድ ሰው ብቻውን የቤተክርስቲያን መሪ በመሆን አስራት መሰብሰብ ይችላል የሚል ሃሳብ አይሰጠንም። ሽማግሌዎች ናቸው ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሯትና ገንዘብን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ሁሉ የሚቆጣጠሩት።
አንድ ግለሰብ ሁሉን መቆጣጠር የለበትም።
ዛሬ ሁሉ ነገር በገንዘብና በቁሳቁስ በሚለካበት ዘመን አንድ ሰው ከቤተክርስቲያን ገንዘብ ላይ መጠቀም ከጀመረ የቤተክርስቲያን ገንዘብ ምን ላይ መዋል እንዳለበት የመወሰን መብት ሊኖረው አይገባም። ለቤተሰብ በማድላት የሚደረግ የወጪ ምደባ ሌብነት ነው።
ዛሬ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ገንዘብ “በፓስተሩና በሚስቱ” ወይም “በፓስተሩና በልጁ” እጅ ነው የሚደረገው፤ ይህም ገንዘቡ ከቤተሰብ እጅ እንዳይወጣ ይረዳል።
ቁጥር 3 የሚናገረው አንድ ግለሰብ ጉባኤው ላይ ገዥ እንዳይሆን ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡3 ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
ማንም ሰው በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ጌታ መሆን የለበትም። አንድም ሰው የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አይችልም።
ቁጥር 4 ስለ እረኞች አለቃ ስለ ኢየሱስ ይናገራል፤ ቤተክርስቲያንን መምራት ያለበት እርሱ ነው። ስለዚህ ሽማግሌዎች ለሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው መንገር ያለባቸው፤ ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ ነው ሕዝቡን ወደ እረኞች አለቃ የሚመራቸው።
ቁጥር 5 – “ሁላችሁም እርስ በርስ እየተዋረዳችሁ”። ለጥንቷ ቤተክርስቲያን ስኬት ሚስጥሩ ይህ ነበር። ሽማግሌዎች ሁሉ እኩል ነበሩ። ከመካከላቸው ማንም አለቃ ወይም የበላይ አልነበረም። ማንም ለብቻው ኃላፊ አልነበረም።
በእኩልነት እየተያዩ ቤተክርስቲያንን በሕብረት ይመሩ ነበር።
የቤተክርስቲያን መሪ ግን ሰዎች እርሱን እንዲከተሉት ይፈልጋል
ተኩላዎች ሰብሰብ ብለው በሕብረት ሲንቀሳቀሱ ከመካከላቸው አንድ ኃይለኛ ወንድ ተኩላ እንደ “ፊታውራሪ” ሲመራቸው ነው ውጤታማ የሚሆኑት።
የተኩላዎች ቡድን መሪ በጣም ጨካኝ ነው።
የተኩላዎቹ አካሄድ ለቤተክርስቲያናዊነት እድገትና ዘላቂነት ጥሩ ሞዴል ነው።
ጳውሎስ እንዲህ ብሎ አስጠንቅቋል፡-
የሐዋርያት ሥራ 20፡29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
ይህንን ዘዴያቸውን ልብ በሉ፡- “ደቀመዛሙርትነን ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ”፤ ይህ አንድን ሰው ከፍ አድርጎ ቤተክርስቲያን በሙሉ እንድትከተለው ማድረጊያ ዘዴ ነው።
ስለዚህ ሁሉን ነገር አንድ ሰው ይቆጣጠርና ሕዝቡ ለእርሱ አመለካከት ተገዢ ይሆናሉ።
ይህ ዓይነቱ የአመራር ዘዴ የቤተክርስቲያን ቡድኖችን ለመገንባት አዋጪ መንገድ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከተኩላዎች ጋር ያመሳስለዋል።
ሮሙለስ እና ሬሙስ ከአንዴት ሴት ተኩላ ጡት ጠብተው ያደጉ መንታዎች ናቸው ተብሎ ይወራል፤ ከዚያም ከሁለቱ መንታዎች አንዱ ሮሙለስ ከእርሱ ጋር እኩል የነበረውን ብቸኛው ሰው ማለትም መንታ ወንድሙን ሬሙስን ገደለው። ልክ ቃየን አቤልን እንደገደለው ሮሙለስ ሬሙስን ገደለው።
ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች ስም በማጥፋት መጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎችን “ይገድላሉ”።
ይህንን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ሮሙለስ ተቀናቃኝ የሌለው መሪ ሆነ፤ ወዲያውም ሮምን መገንባት ቻለ። ከዚህ ዓይነቱ መንፈስ ራቅ በሉ። አንድን ሰው አትከተሉ። እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ አይታችሁ ያላረጋገጣችሁትን ነገር አትመኑ።
ቤተክርስቲያን እንዴት መተዳደር እንዳለባት ጳውሎስ ጽፏል።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፡28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
ቤተክርስቲያንን በስርዓት ለማደራጀት ሶስት ቁልፍ የሆኑ አገልግሎቶች ተመድበዋል፤ እነርሱ ሐዋርያት፣ ነብያት፣ እና አስተማሪዎች ናቸው።
ፓስተሮች ጭራሽ አለመጠቀሳቸውን ልብ በሉ። ቄሶች ወይም ካሕናትም አልተጠቀሱም። ሪቨረንዶች አልተጠቀሱም።
“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል።
“አስተማሪዎች” አዲስ ኪዳን ውስጥ 11 ጊዜ ተጠቅሰዋል።
አዲስ ኪዳን ውስጥ “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ስድስት ጊዜ እንዲሁም “ሽማግሌዎች” የሚለው ቃል ደግሞ ሃያ አራት ጊዜ ተጠቅሷል። ይህም ሲደመር ሰላሳ ጊዜ ማለት ነው።
የሽማግሌዎች ሕብረት ቄስ ነኝ ወይም ሪቨረንድ ወይም ፓስተር ነኝ ከሚል አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ ከሚመራበት አመራር የተሻለ አመራር ነው።
አዲስ ኪዳን ውስጥ አስተማሪዎች እንኳ በቁጥር ከፓስተሮች አስር እጥፍ ጊዜ ተጠቅሰዋል።
ኤፌሶን 2፡20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ሐዋርያት አዲስ ኪዳንን መሰረቱ፤ አዲስ ኪዳንም ነብያት በመሰረቱት ብሉይ ኪዳን ላይ ነው የተመሰረተው።
ነገር ግን የብሉይ ኪዳን ነብያት የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ከጻፉት ጋር መስማማት አለባቸው ምክንያቱም ሐዋርያት በተሰጣቸው ስልጣን ይበልጣሉ።
ብሉይ ኪዳንን ስትተረጉሙ አዲስ ኪዳንን በሚቃረን መንገድ መተርጎም አትችሉም።
ኤለን ጂ. ዋይት ቅዳሜ የአዲስ ኪዳን ሰንበት ነው ብላ ባስተማረች ጊዜ ሐዋርያትን ተቃርናለች። እውነተኛው የአዲስ ኪዳን ሰንበት ከሐጥያታችን ሸክም የሚያሳርፈን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
ዕብራውያን 4፡10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
እግዚአብሔር ፍጥረትን ከመፍጠር ስራው ካረፈ በኋላ እንደገና ወደ መፍጠር አልተመለሰም።
ቅዳሜ እረፍት አድርጋችሁ ከዚያ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ስራ የምትመለሱ ከሆነ እግዚአብሔር ያደረገውን እረፍት እያደረጋችሁ አይደላችሁም።
ነገር ግን ሐጥያት ስትሰሩ ከኖራችሁ በኋላ ንሰሃ ገብታቸሁ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ስትቀበሉ ወደ ሐጥያት ስራችሁ እና ወደ አለማመናችሁ ተመልሳችሁ አትሄዱም። ስለዚህ ከሐጥያት እና ከአለማመን የሚያሳርፍ እውነተኛው ሰንበት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
መጀመሪያ የመጡት ሐዋርያት ናቸው። ኢየሱስ እራሱ ካሰለጠናቸው በኋላ እንከተላቸው ዘንድ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያንን ስርዓት እና ደንቦች አበጅተዋል። የመጀመሪያዎቹ 12 ሐዋርያት ከሁሉ የበለጠ ስልጣን ነበራቸው። ሌሎች ሐዋርያት ወይም ወንጌል ሰባኪ ሚሽነሪዎች ለመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት መገዛት አለባቸው።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች ሾልከው በመግባታቸው ምክንያት እነዚህ እውነቶች እና ስርዓቶች በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ተረስተው ጠፍተዋል።
ራዕይ 2፡2 ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
ማንኛውም በዚህ ዘመን የሚነሳ ሐዋርያ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካስቀመጡት እውነት የተለየ ነገር መናገር አልተፈቀደለትም።
በሁለተኛ ደረጃ የተጠሩት ነብያት ናቸው። እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ሕዝቡን ለመምራት የነብያትን ድምጽ ተጠቅሟል፤ ነገር ግን ዋነኞቹ የነብያት አገልግሎቶች የጳውሎስ፣ የጴጥሮስ፣ እና የዮሐንስ አገልግሎቶች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች የአዲስ ኪዳንን ትንቢቶች ጽፈዋል።
“የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ዘመን” የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 7
ስለዚህ ሉተር ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሙሉው እውነት መልሶ ሊወስዳት አልቻለም፤ ጳውሎስ ሐዋርያም ነብይም ነበረ።
ሌላ ደግሞ በልዩ የነብይ አገልግሎት የተጠራ ነብይ አለ፤ እርሱም ልጆችን (እኛን) ወደ አባቶች (ወደ መጀመሪያዎቹ ሐዋርያት) የሚመልሰው የዘመን መጨረሻ ኤልያስ ነው።
ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
ይህ ነብይ የተሰጠው አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት መግለጥ ብቻ ነው፤ ዓላማውም እኛ መጽሐፍ ቅዱስን ተረድተን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ ነው።
ከሐዋርያት ዘንድ የተጻፈውን ቃል አግኝተናል። ከዘመን መጨረሻው ነብይ ደግሞ በድምጽ የተነገረውን ቃል አግኝተናል።
መረዳታችንን ወይም መገለጥ የምናገኘው በድምጽ ከተነገረው ቃል ነው።
ከዚያ በኋላ የሰማነውን ሃሳብ ትክክል ወይም እውነት መሆኑን ከተጻፈው ቃል አስተያይተን ማረጋገጥ አለብን፤ የተጻፈው ቃል ምንጊዜም የበላይ ነው።
ቤተክርስቲያን ግን የወደቀችበት ፈተና ይህ ነው። ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎች በድምጽ ተቀርጾ ከሰሙት መልእክት ውስጥ መገለጥ ካገኙ በኋላ እውነት መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው አያረጋግጡም።
ማስተማር ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ለዚህ ነው።
የማስተማር አገልግሎት ትኩረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።
ሰው ሲያስተምር የተናገረውን ቃል ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ወስዶ እውነት መሆኑን ፈትሾ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።
“በእናንተ ውስጥ ያለው” ኖቬምበር 10 ቀን 1963
መልዕክቱን በሙሉ እመኑ። የእውነት እመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌለ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካልተጻፈ ግን አትመኑ።
የማስተማር አገልግሎት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሰዎች ያመኑትን እውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ ያስገድዳቸዋል።
የዚያን ጊዜ ብቻ ነው ስለምታወሩት ነገር እንኳ እርግጠኛ የምትሆኑት።
“ሶስተኛው ማሕተም” ማርች 20 ቀን 1963
ያ የጌታ መልአክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ አንዳች ነገር ቢነግረኝ በጭራሽ አላምነውም ነበር።
ነብያት ደስ ያላቸውን ሁሉ መናገር አይችሉም። ነብያት ሲናገሩ ትንቢታቸው እውነተኛ መሆኑ ሁልጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አማካኝነት ይፈተሽ ነበረ።
“ዕብራውያን ምዕራፍ ሁለት” ክፍል 1 ኦገስት 25 ቀን 1957
ብሉይ ኪዳን ውስጥ የነብይ ቃል ተፈጽሞ ከመታየቱ በፊት እውነተኛነቱ ይመረመርና ይፈተን ነበር።
እኛ ዛሬ ቸልተኛ እንደሆነው እነርሱ ስለ ነብይ ቃል ግዴለሾች አልነበሩም።
ዝም ብላቹ አስደናቂ ነገር የምትከታተሉ ብቻ ከሆናችሁ “ሃሌሉያ! አሜን” የሚያሰኝ ነገር ብቻ የምትፈልጉ ከሆናችሁ ተሳስታችኋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አያበረታታም፤ “በመጨረሻው ዘመን ሰይጣን ክርስትናን ጥሩ አድርጎ ስለሚኮርጅ ቢቻለው የተመረጡትን እንኳ ሳይቀር ያስታል።” ይህ እውነት ነው።
ስለዚህ ሁሉንም ነገር ማጣራት አለብን።
የብሉይ ኪን ሰዎች በዘመናቸው ትንቢትን እንዴት ነበር የሚፈትኑት? በኡሪም እና ቱሚም ነው። የአሮን ልብስ የኤፉዱ የደረት ኪስ ላይ ኡሪም እና ቱሚም የተባሉ ድንጋዮች አሉ፤ እነርሱም፡- የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፣ አልማዝ፣ ሰንፔር፣ ኢያስጲድ ናቸው። የአስራ ሁለቱን አባቶች መወለድ የሚወክሉ የከበሩ ድንጋዮች በሙሉ የአሮን ልብስ የደረት ኪስ ላይ አሉ። ስለዚህ አንድ ነብይ ትንቢት ሲናገር የደረት ኪሱ ላይ ያለው የከበረ ድንጋይ ብርሃን ካበራበት ትንቢቱ ትክክለኛ ነው፤ ስለዚህ ድንጋዩ ሲያበራበት እግዚአብሔር “ይህ እውነት ነው” ብሎ እየመሰረ ነው። ነገር ግን ምንም ያህል እውነት ቢመስል ብርሃን ካላበራበት እውነት አይደለም። ስለዚህ መለያው በካሕኑ ልብስ ላይ ያለው የከበረ ድንጋይ ነው።
ዛሬ ግን የእግዚአብሔር ኡሪም እና ቱሚም ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለዚህ ዛሬ ነብይ ትንቢት ሲናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ካላበራበት እውነት አይደለም።
ሁሉን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ መፈተሸ የሚወድ ብዙ ሰው የለም፤ ለአስተማሪ ግን ሁሌም ኃላፊነቱ ነው።
ምክንያቱም ይህ ኃላፊነት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ማወቅ ይጠይቃል፤ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ ደግሞ ጊዜ እና ትጋት የሚጠይቅ ከባድ ስራ ነው።
ነብይ የተናገረውን ቃል መፈተሽ እና ንግግሩ በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ መሆኑን ማረጋገጥ ቀላል አይደለም።
ቄሶች፣ ሪቨረንዶች፣ እና ፓስተሮች እንዲህ ዓይነት በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ አገልግሎት የላቸውም፤ ስለዚህ እንዲሁ ሰው የተናገረውን ቃል በማገጣጠም ደስ ብሏቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን ይሰብካሉ።
ከዚህም የተነሳ በአንድ ሰው የሚመሩ ቤተክርስቲያኖች ስብከታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ መሆኑን እያሳየ የሚያርማቸው አስተማሪ አይወዱም።
በቤተክርስቲያን ላይ አንድን ሰው ባለ ስልጣን አድርጋችሁ ብትሾሙ ውጤቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይምነት እያደገ መሄድ ነው።
ወንጌላውያን እና ጴንጤቆስጤያውያን ቤተክርስቲያኖች የሚተዳደሩት በፓስተሮች ነው፤ ደግሞም አብዛኞቻቸው በስላሴ፣ በክሪስማስ፣ በስቅለት አርብ፣ በሰባት ዓመት መከራ ያምናሉ፤ በተጨማሪ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከአውሮፓ የሚነሳ ፖለቲካዊ መሪ ነው ወዘተ. ብለው ያምናሉ፤ ግን እንደዚህ የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
ብዙ ወንጌላውያን እና ጴንጤቆስጤያውያን ቤተክርስቲያኖች በ2021 ዓ.ም የተዘጋጀው የቫይረስ መከላከያ ክትባት የአውሬው ምልክት ነው ብለው ሲያስተምሩ ነበር። ስለዚህ ትከሻችሁ ላይ በወሰዳችሁት ክትባት ግምባራችሁ ላይ ምልክት ይደረጋል የተባለው ይፈጸማል አሉ። የምራቸውን ነው?
እነዚህ ሁሉ የተሳሳቱ ሃሳቦች ምንጫቸው ቤተክርስቲያንን ለብቻቸው የሚመሩ ግለሰቦች ጠለቅ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በትክክል መረዳት አለመቻላቸው ነው። ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥር መግለጥ ለእነርሱ የተሰጠ አገልግሎት አይደለም።
ራሳቸውን በራሳቸው የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ስለሾሙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ትክክል አለመሆናቸውን የሚያሳዩዋቸውን አስተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ያባርራሉ፤ ቀጥለውም የማስተማሩን ኃላፊነት ነጥቀው ለራሳቸው በመውሰድ ጥልቅ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገልጠው ሊያስተምሩ ይሞክራሉ።
ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በአንድ ካሪዝማዊ መሪ ስር እየተገዙ መማር ሲፈልጉ እያየ እግዚአብሔር ምን ያስባል። በዚህ ዓይነት ምልልሳቸው የሚያምኑትን እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው ማረጋገጥ አይጠበቅባቸውም፤ ምክንያቱም እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ፈትሸው እንዳያረጋግጡ ለዚህ የሚበቃ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት የላቸውም። ስለዚህ እምነታቸው የተመሰረተው ለመሪያቸው ታማኝ በመሆንና አዘውትረው ቤተክርስቲያን በመሄድ ነው።
ኢየሱስ ቃሉ ነው።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የምትናገሩት ማንኛውም ንግግር ስለ ኢየሱስ ያላችሁን አቋም ይገልጣል።
ዛሬ በዚህ ዘመን ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለበት እውነተኛው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው የሚል ክርስቲያን በፍለጋ እንኳ አይገኝም።
የዛሬ ክርስቲያኖች ደስ እያላቸው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አቃቂር ያወጣሉ (ይህን በማድረጋቸው ኢየሱስ እየተቹ ናቸው) ነገር ግን ፓስተሩን ወይም ቤተክርስቲያናቸውን በጭራሽ አይተቹም።
ይህን ሁሉ ስታዩ ታድያ እግዚአብሔር በመጨረሻ ዘመን ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን እንትፍ ብሎ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ሊተፋት መሆኑ ያስደንቃችኋል?
63-0630 ሶስተኛው ፍልሰት
የእግዚአብሔር ድምጽ በቃሉ በኩል ሲጠራቸው በግልጽ መስማት ይችላሉ
… መጽሐፍ ቅዱስን አድምጡ፤ በዚህ ዘመን የሚጠራችሁ የእግዚአብሔር ድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፓስተሮች የሚናገረው
አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙም አልተጻፈም። “ፓስተር” የሚለው ቃል አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚገኘው።
ኤፌሶን 4፡11 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
12 … ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
አማኞችን በትክክለኛው መንገድ ለመምራት የአስምቱ ቢሮዎች አገልግሎት አስፈላጊ ነው፤ በነዚህ መካከል ፓስተሮች በአራተኛ ደረጃ ነው የተጠቀሱት።
አራተኛ ማለት ትልቅ ደረጃ አይደለም። በአራተኛ ደረጃ ላይ መጠራት ፓስተሩ ቤተክርስቲያን ላይ እንዲሰለጥን ያበቃዋልን? በፍጹም።
የአምስቱ ቢሮዎች አገልግሎት ዛሬ የት ነው ያለው?
ምክንያቱም ዛሬ ከአንዱ የቤተክርስቲያን መሪ ግለሰብ ጋር ያልተስማማ ማንኛውም ሰው መስበክ አይፈቀድለትም።
አንድ አገልጋይ እንኳ ፓስተሩን ቢቃረነው ፓስተሩ ከአገልግሎት መደቡ ላይ ያግደዋል። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪ ልክ እንደ ካቶሊክ ጳጳስ ነው አካሄዱ፤ ማለትም ሌሎቹን አራት አገልግሎቶች ይቆጣጠራቸዋል። ቤተክርስቲያንን በብቸኝነት የሚያስተዳድር በተጨማሪ የሚሰበሰበውን አስራት ይቆጣጠረዋል። ይህንንም የሚያደርገው ሌሎቹ አራት የአገልግለት ዘርፎች ውስጥ የሚፈጠር ሃሳብ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሳይፈጸም እንዲቀር ነው።
ልክ ካቶሊካዊው ንጉስ ቤተክርስቲያኖች እንዲታዘዙለት እና እርሱም እንደ ፍላጎቱ ሊያሽከረክራቸው እንዲችል ብሎ የገንዘብ ድጎማ እንዳደረገላቸው ሁሉ የቤተክርስቲያን መሪ የሆነ ሰውም ከእርሱ ጋር ለሚስማሙ አገልጋዮች ብቻ ነው የገንዘብ ድጎማ የሚያደርገው። ጉባኤው የሚያገኘው አገልግሎት መሪው የፈቀደውን ዓይነት አገልግሎት ብቻ ነው። ሁልጊዜ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሪው የሚከራከረውን ክርክርና የመሪውን አመለካከት ብቻ እንጂ የነገሩን ሌላ ተቃራኒ ገጽታ ለመስማት ዕድል የላቸውም። ይህም ሚዛናዊነት የጎደለው አመለካከት እንዲፈጠር ያደርጋል።
ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ብቻቸውን የሚተውኑ ሁሉን አዋቂ መሪዎች ይሆናሉ። ሁሉን ማድረግ የሚችል አንድ ሰው ሆነው ይነሳሉ፡- ይሰብካሉ፣ ያስተምራሉ፣ ወንጌል ያሰራጫሉ፣ ቤተክርስቲያንን ያስተዳድራሉ፣ ቤተክርስቲያንን ለቀረጹት የእምነት መግለጫ ያስገዛሉ፣ ወዘተ። ሕዝቡ ከዚህ መሪ ጥንካሬ ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን በድካሙ፣ በስሕተቶቹ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቁ ደግሞ ይጎዳሉ።
3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ራሱን አለቃ ያደረገና ከሚገባው በላይ በስልጣን ጥም የጠሞላው ይህ ነው መንጋውን እየመራ በእነርሱ ላይ ለብቻው አምባ ገነን ሆኖ ነገሰባቸው።
ዛሬ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን እና ከመድረክ የሚያባርር ማነው? ራሱን በራሱ የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ የሾመ ሰው ነዋ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ማነው ዛሬ ከሁሉ የበለጠ ስልጣን የያዘው? ፓስተር ነው።
ፓስተር ተብሎ ሲጠራ ሁልጊዜ እንሰማለን።
ማቴዎስ 23፡2 ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።
ጻፎች እና ፈሪሳውያን ከነብዩ ሙሴ እየጠቀሱ ነው የሚናገሩት። ሲጠቅሱም ለሃሳባቸው እንዲመች እየመረጡ ነው የሚጠቅሱት። ከሙሴ የሰሙት ቃል ከኢየሱስ ሙሉውን ቃል ሲሰሙ ከመቃወም አላገዳቸውም።
ዛሬም የቤተክርስቲያን መሪዎች በጥንቃቄ በመረጡዋቸው ጥቅሶች ላይ ነው ስብከት የሚያዘጋጁት።
“ነብዩ እንዲህ ብሏል …”፤ “ነብዩ እንዲያ ብሏል …”
የቤተክርስቲያን መሪዎች ባላቸው መረዳት ላይ ተመስርተው ጥቅሶችን በጥንቃቄ መርጠው ነው የሚሰብኩት። ከዚህም የተነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጥቅሶችን ለመቀበል እምቢ ይላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ በመመርመር ትምሕርታቸው ትክክል መሆኑን ፈትሸው አያረጋግጡም። መረዳታቸው በተወሰኑ በተመረጡ ጥቅሶች ስብስብ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ስለዚህ ሃሳባቸውን የሚቃረኑ ሌሎች ጥቅሶችን እንዳላዩ አድርገው ያልፋሉ። ልክ የባሕር ላይ ዘራፊ እንዳለ ሁሉ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነት መሪዎችን የኩሬ ላይ ዘራፊ ይሏለቸዋል። እነዚህ ዘራፊዎች ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በጥልቀት እንዳይረዱ መረዳትን ይዘርፉዋቸዋል።
እስቲ፡- “ፓስተሩ ለምንድነው የጉባኤው መሪ የሆነው” የሚል ጥያቄ ጠይቁ፤ የዛኔ የጥቅስ ጋጋታ ይቀርብላችኋል፤ የሚቀርብላችሁ ግን የሰው ንግግር ጥቅስ ጋጋታ ነው እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋጋታ አይደለም፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ነው ብሎ ነው የሚናገረው።
ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ …
ኢየሱስ የአይሁዶች የሐይማኖት መሪ ስለሆኑት ስለ ፈሪሳውያን ሲናገር እንዲህ አለ፡-
ማቴዎስ 23፡6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥
የሐይማኖት መሪዎች ራሳቸውን ታላቅ ማድረግ ይወዳሉ። ይህም የሰው ተፈጥሮአዊ ድክመት ነው።
“የከበሬታ ወንበር”።
ዛሬ ዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ከፊት ለፊት ለታላላቅ ሰዎች ተብለው የተዘጋጁ ወንበሮች እንዳሉዋቸው አላያችሁምን? ቦታው የተዘጋጀው ከቤተክርስቲያን መሪው ጋር ለሚስማሙ ሰባኪዎች ነው። ማንኛውም አገልጋይ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያኒቱ ቄስ፣ ሪቨረንድ ወይም ፓስተር ጋር የሚቃረን ከሆነ በዚያ ቦታ መቀመጥ አይችልም።
ግለሰቦች ብቸኛ የቤተክርስቲያን መሪ ሲሆኑ ተቃዋሚዎችን አያስጠጉም፤ ፖፕ ሊዮ አስረኛውም ማርቲን ሉተርን ለማስገደል የተቻለውን ሁሉ አድርጓል፤ ማርቲን ሉተር ግን በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከነበሩ መነኮሳት ሁሉ የተሻለ መነኩሴ ነበረ።
አንድ ሰው ብቻውን የቤተክርስቲያን መሪ በሚሆንበት ጊዜ የሚታይበት ትልቅ ድክመት ይህ ነው። ሌላው ሰው ለጌታ እየሰራ ያለውን መልካም ስራ ማየት አይችልም። ለእርሱ የሚታየው ሌላኛው ሰውዬ የእርሱን ምኞትና ሃሳብ እያደናቀፈበት እንደሆነ ብቻ ነው።
ራሱን የቤተክርስቲያን መሪ አድርጎ የሾመ አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን ራስ አይደለም ማለት የሚሰበሰበውም አስራት ራሱን የቤተክርስቲያን ራስ ብሎ ለሚጠራው አንድ ግለሰብ አይደለም ማለት ነው። ይህንን እውነት ገልጣችሁ ስትናገሩ የቤተክርስቲያን መሪ ገቢው አደጋ ላይ ይወድቃል። ይህም ለእርሱ ጦርነት እንደከፈታችሁበት ይቆጠራል።
ሉተር የስርየት ወረቀት በመሸጥ ፖፑ የሚያገኘው ገቢ በሐሰት የሚገኝ ገቢ እንደሆነ በ1517 ዓ.ም ሲያጋልጥ በ1520 ዓ.ም ፖፑ ሉተርን አወገዘው፤ ፖፑ ሉተርን ሊያገኘው ቢችል ውግዘት ማለት የሞት ፍርድ ማለት ነው።
በሆሳዕና ዕለት ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ ውስጥ አባሮ አስወጣቸው፤ እንደገና ደግሞ በቀጣዩ ቀን ሰኞ ዕለትም አስወጣቸው። የሐይማኖት መሪዎችም አሁንስ አበዛው አሉ። ስለዚህ ሐሙስ ዕለት ይገደልልን አሉ።
ኢየሱስ በሐይማኖት መሪዎች የገቢ ምንጭ ውስጥ ጣልቃ ገባ። ይህም ሕይወቱን አሳጣው። የአንድ የቤተክርስቲያን መሪን የገቢ ምንጭ ንኩበትና ጉዳችሁ ይፈላል። በተኩላዎች መንጋ ላይ መሪ የሆነውን ጨካኝ ተኩላ አስቡ። ብቻቸውን ቤተክርስቲያንን እንመራለን የሚሉ ግለሰቦችን ጳውሎስ “ተኩላዎች” ብሎ የጠራቸው ያለ ምክንያት አይደለም።
ኢየሱስ አርብ ዕለት ነው የሞተው ብለው ቤተክርስቲያኖች ቢያስተምሩም እንኳ የሞተው አርብ አይደለም፤ ምክንያቱም እሑድ ጠዋት ከሞት ከመነሳቱ በፊት 3 ሌሊት በመቃብር ውስጥ አሳልፏል።
“የስቅለት አርብ” እና “የፋሲካ ሰኞ” የሚባሉት አነጋገሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ አይደሉም። እነዚህ ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማር ችሎታ ከሌላቸው ብቃት ከጎደላቸው አስተማሪዎች የፈለቁ ሃሳቦች ናቸው፤ ምክንያቱም እነዚህ አስተማሪዎች እንደ ገደል ማሚቶ የቤተክርስቲያንን ልማድ ይደግማሉ እንጂ ቃሉን አያጠኑም።
ልክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደማይታወቀው ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ እና የገና ዛፍ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በቀቀኖችን አይጠቅስም፤ ምክንያቱም በቀቀኖች መናገር ቢችሉም እንኳ ምን እንደተናገሩ መረዳት አይችሉም። ስለ ክሪስማስ፣ ስለ ስቅለት አርብ፣ እና ስለ ፋሲካ ሰኞ የሚሰብኩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ስለ ምን እያወሩ እንደሆን አያውቁም። እነዚህ ሁሉ ከባዕድ እምነቶች የመጡ ሃሳቦች እና በዓላት ናቸው።
በዛሬዎቹ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በኃላፊነት ላይ የተቀመጡው ሰው ሁልጊዜ ትክክል እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል፤ እርሱን የተቃረነ ሁሉ ደግሞ እንደተሳሳተ ይቆጠራል። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ቤተክርስቲያናዊነት ይባላል፤ እርሱም በስውር የሚንቀሳቀስ የክርስቲያናዊነት ጠላት ነው።
ማቴዎስ 23፡7 በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።
“ፓስተር” የሚለውን ማዕረግ ስንት ጊዜ ነው የምንሰማው? ብዙ ጊዜ።
አንድ “አበበ” የተባለ ሰው ፓስተር እንደሆነ አስቡ
ፓስተሩ በጭራ “አበበ” ተብሎ አይጠራም። ሁልጊዜ “ፓስተር አበበ” ተብሎ ነው የሚጠራው።
ብዙ ፓስተሮች “ወንድም አበበ” ተብለው ሲጠሩ ይቆጣሉ ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ አጠራር ታላቅነታቸውን ይቀንስባቸዋል። “ፓስተር” የሚለው ማዕረግ ስማቸው ላይ እንዲለጠፍላቸው ይፈልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከማንም ስም ጋር “ፓስተር” የሚባል ማዕረግ ተልጥፎ አያውቅም።
ከፓስተሩ ሌላ በሌላ አገልግሎት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ግን እንደዚህ ሁልጊዜ በማዕረግ አይደለም የሚጠሩት።
አንድ ሰው የቤተክርስቲያን ራስ የሆነበትን አሰራር በተመለከተ የቀረቡ እነዚህ ትችቶች ግለሰቡ ላይ ያነጣጠሩ ትችቶች አይደሉም። የቤተክርስቲያን መሪዎች መልካም ሰዎች ናቸው። ማንም ቢሆን መጥፎ ሰው ለመሆን ብሎ እግዚአብሔርን ወደ ማገልገል አይገባም።
ትችቱ ያነጣጠረው በቤተክርስቲያኖች ውስጥ የተፈጠረው አንድ ሰው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ራስ ተደርጎ የሚቀመጥበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አሰራር ላይ ነው።
ስለዚህ አንድ መልካም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ባልሰጠው ስፍራ ላይ ይቀመጣል፤ ይህም ስሕተት ነው።
ፖፕ ፍራንሲስ መልካምና ደስ የሚል ባህርይ ያለው ሰው ነው። እንደ ግለሰብ በእርሱ ላይ አንዳችም የተሰነዘረ ቅሬታ የለም። ነገር ግን ፖፕ የተባለው ስልጣን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ማንም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ባልሰጠው የአገልግሎት ወይም የስልጣን ስፍራ ተቀምጦ እግዚአብሔርን ማገልገል አይችልም።
ትችቶች ሁሉ የሚያነጣጥሩት እነዚህን ትክክል ያልሆኑ የስልጣን ስፍራዎች በፈጠሩ የቤተክርስቲያን አሰራሮች ላይ ነው፤ እንጂ ባለማወቅ ወይም በስሕተት በነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስፍራዎች ላይ በተቀመጡ መልካም ሰዎች ላይ አይደለም።
የፓስተር አገልግሎት እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ሊደግፍ የሚችልበት መልካም የሆነ የአገልግሎት ዘርፍ ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከተናገረው ውጭ ፓስተሩ ከፍ ተደርጎ የቤተክርስቲያን ራስ ሲሆን እግዚአብሔር ያሰበለትን መልካም አገልግሎት እየፈጸመ አይደለም።
በተመሳሳይ መንገድ እንደ ፍራንሲስ ያለ መልካም ሰው “የሮም ጳጳስ” ወይም “ፖፕ” ወይም “ፖንቲፍ” የተባለ ማዕረግ ይዞ መቀመቱ ስሕተት ነው፤ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት ስልጣን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
አበበ አስተማሪ ከሆነ በቃ “አበበ” ተብሎ ይጠራል፤ ወይም “ወንድም አበበ” ይባላል እንጂ በጭራሽ “መምሕር አበበ” ተብሎ መጠራት የለበትም።
“ፓስተራችሁ ማነው?”
የሜሴጅ ተከታዮች ሰዎችን የሚጠይቁት የመጀመሪያ ጥያቄ ይህ ነው፤ ጥያቄውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን እንዲህ ዓይነቱን አነጋገር አታውቅም።
ማቴዎስ 23፡8 እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
“ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ”።
ሁላችንም እኩል መሆን አለብን። አስተማሪ መምሕር አበበ ተብሎ መጠራት የለበትም፤ ወንድም አበበ ተብሎ ከተጠራ ይበቃዋል። ፓስተሮች ግን ፓስተር አበበ ብላችሁ ካልጠራችሁኝ ይላሉ። (ስማቸው አበበ ከሆነ)
ዊልያም ብራንሐም ነብይ ብራንሐም ብላችሁ ጥሩኝ አላለም። ወንድም ብራንሐም ተብሎ በመጠራቱ ደስተኛ ሆኖ ይኖር ነበር። ወንዶችን በሙሉ ወንድም ብለን መጥራት አለብን እንጂ ከእኛ በላይ መሆናቸውን የሚያሳይ ማዕረግ ስማቸው ላይ መለጠፍ የለብንም።
ኮንስታንቲን በ312 ዓ.ም ክርስቲያኖችን ማሳደድ እንዲቆም ከማድረጉ በፊት ክርስቲያኖች በየሰው ቤት ውስጥ ነበር የሚሰባሰቡት።
ደግሞም በየጊዜው ከሚነሱባቸው ታላላቅ ስደቶች የተነሳ ከቤት ውጭ ሜዳ ላይ ወይም በሚስጥር በተዘጋጁ ቦታዎች ይሰባሰቡ ነበር። ከተማ መሃል በሚገኙ ሕንጻዎች ውስጥ ቢሰባሰቡ እነዚህ ሕንጻዎች ሊወረሱባቸው ይችላሉ። ተርቱሊያን (160 – 228 ዓ.ም) እንዲህ ብሎ ጻፈ፡- “ከበባ ይደረግብናል፤ እንደ ዱር እንስሳ አደን ይፈጸምብናል፤ በሚስጥር በተሰበሰብንበት በድንገት መጥተው ይይዙናል”።
የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚናገሩት ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕንጻ ውስጥ መሰብሰብ የጀመረችው በ220 ዓ.ም ነው። በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ለቤተክርስቲያን ተብሎ ተለይቶ የተዘጋጀ ሕንጻ አልነበራቸውም። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በ170 ዓ.ም ነው የተጠናቀቀው። እኛ ደግሞ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ምሳሌ መመለስ አለብን።
ይደርስባቸው የነበረው ከባድ ስደት ከመስመር እንዳይወጡ አድርጓቸዋል። ከ312 ዓ.ም በኋላ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ የነበረው ስደት ሲቆም የቤተክርስቲያን ሕንጻዎች በየቦታው እንደ ዛፍ በቀሉ፤ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ አስተዳዳሪ ቄስ ተመደበ።
አንዳንድ አካባቢዎችን ከሌሎች ለማስበለጥ ተብሎ ባሲልካዎች (ትልልቅና ውብ የሆኑ ሕንጻዎች) ይገነቡ ነበር፤ በውስጣቸውም የሚደረገው የአምልኮ ስርዓት በንጉሱ ቤተመንግስት ለንጉሱ የሚ የሚደረገውን አምልኮ ስርዓት የሚመስል ነበር።
ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን አምልኮ ለንጉስ በሚቀርበው አምልኮ መሰረት አደረጉት። ቤተክርስቲያናዊነት የክርስቲያናዊነትን ቦታ ወሰደ።
መንግስት በሰው ማለትም በንጉሱ ነው የሚመራው። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖችም መሪያቸው ሰው እንዲሆን አደረጉ።
ቤተክርስቲያን ፖለቲከኞችን መኮረጅ ጀመረች።
የቤተክርስቲያን መሪዎች ከቤተክርስቲያን አባላት በላይ ከፍ ተደረጉ፤ በሕዝቡም ላይ ልክ እንደ ፖለቲካ መሪዎች ገዥና ጌታ ሆኑባቸው።
ስለ ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡-
ራዕይ 2፡12 በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
13 የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ …
15 እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።
የቤተክርስቲያን ሕንጻዎች ብዙ ሕዝብ እንዲሰበሰብ እና ይህ ሁሉ ሕዝብ በአንድ ሰው ስልጣን ስር ተደራጅቶ እየተገዛ እንዲኖር ምቹ ሁኔታ ፈጠሩ።
“ኒቆ” ማለት ገዥ ነው። “ላውያን” ማለት ጉባኤ ውስጥ የተሰበሰበ ሕዝብ ማለት ነው።
እግዚአብሔር በአሮን ክሕነት የተሾሙ አምስት አገልጋዮችን ከቀረው ሕዝብ በላይ ከፍ ከፍ አላደረገም።
ከዚያም ብሶ ደግሞ አንድ ሰው ብቻውን ከሁሉ በላይ ከፍ እንዲል፤ ሕዝቡን እንዲገዛ፤ እንዲቆጣጠር፤ በሕዝቡ ላይ ጌታ እንዲሆንና እንዲሰለጥን አልፈቀደም። ሕዝቡን ሁሉ ለራሱ ፈቃድ እንዲያንበረክክ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም።
“የሰይጣን ዙፋን”። ይህ ከበድ ያለ ኩነኔ ነው።
ሰዎች ከልባቸው በቅንነት እግዚአብሔርን እያገለገሉ እንዳሉ ቢሰማቸውም እንኳ ይህ ሰይጣን ቤተክርስቲያንን በስውር የሚቆጣጠርበት ዋነኛ ዘዴው ነው።
ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ፓስተሮች የሚናገረው ኤርምያስ ብቻ ነው፤ እርሱም ስለ ፓስተሮች ብዙ መልካም ነገር አልተናገረም።
ኤርምያስ 3፡15 እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።
ይህ መልካም ነው። ፓስተሮች በትክክለኛው ቦታቸው ቢገኙ መልካምና ጠቃሚ አገልግሎት ሊሰጡ ይችላሉ።
የፓስተር አገልግሎት ሰዎችን በግል ሕይወታቸው፣ በቤተሰብ፣ እና በስራ የሚገጥማቸውን ችግር መፍታት ነው።
ፓስተሮች ሰዎች ከሰዎች ጋር እና ከኢየሱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ በሚገጥማቸው ችግር መርዳት ነው።
63-0724 እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቅ ወደ ፍርድ አያመጣውም
ነገር ግን እንደምታዩት ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተሩ አለ፤ ፓስተሩም ልዩ ሰው ተደርጎ ይቆጠራል። ስለዚህ ሰዎች በእርሱ ላይ የሚያነሱበትን ጥያቄ ሁሉ ንቆ ማለፍ እስኪችል ድረስ ከፍ ተደርጓል።
እርሱ በቡድኑ መካከል እንደ በሬ ሸክም ተሸካሚ ነው።
አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ተጣልቶ በከሰሰ ጊዜ በመካከላቸው መቀመጥና መዳኘት ማስታረቅ የሚችል ሰው ነው፤ በሁለት ቤተሰቦች መካከል ተቀምጦ (ለሁለታቸውም ሳይወግን ሳያዳላ) ሁለቱንም አዳምጦ በምክንያታዊነት በመፍረድ ሁለቱንም ወደ ወዳጅነት ሊመልሳቸው የሚችለው ሰው ነው ፓስተሩ። አያችሁ? እርሱ ፓስተር ስለሆነ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል።
ፓስተሮች አጥቢያ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች ሕብረት አካል ናቸው።
ፓስተሮች ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን እንዲፈቱና እንዲገልጡ አልተቀቡም። ሚስጥራትን መግለጥ የአስተማሪ አገልግሎት ነው።
ኤርምያስ 17፡16 እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልቸኰልሁም፥ የመከራንም ቀን አልወደድሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣው በፊትህ ነበረ።
ይህ ምንም ቁጣ የሌለበት ንግግር ነው። ከኤርምያስ አፍ የወጣው ቃል እውነት ነበር። ይህም መልካም ነው።
ነገር ግን ፓስተር መሆን እግዚአብሔርን እንዲከተል አላደረገውም። እግዚአብሔርን ይከተል ዘንድ ከፓስተርነት ፈቀቅ ለማለት አልፈጠነም። ይህም መልካም አይደለም።
እንደ ፓስተር በቤተክርስቲያን ላይ እና ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ ስልጣን ያለው መሰለው፤ ይህም በሕዝቡ ላይ የነበረው ስልጣን እግዚአብሔርን ለመከተል እንዲያመነታ አድርጎታል።
ስልጣን ያባልጋል።
ሰዎች አንዴ ስልጣን ከያዙ በኋላ ስልጣናቸውን መልቀቅ አይፈልጉም።
ስለ ፓስተሮች ከተጻፉ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ 6ቱ ፓስተሮችን የሚያወግዙ ናቸው
“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ተጽፏል፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ በትንቢት ስምንት ጊዜ ተጽፏል።
ፓስተሮች ብሉይ ኪዳን ውስጥ አገልጋይ አልነበሩም።
ከ8ቱ ትንቢቶች መካከል 6ቱ ፓስተሮችን የሚያወግዙ ስለሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ባልፈቀደው መንገድ ፓስተሮችን የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆኑ ከፍ ከፍ ማድረግ ብዙ ጥፋት እንዳስከተለ እንገነዘባለን።
ፓስተሮች ሰዎችን በመርዳትና በማማከር ብዙ መልካም ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያንን እንዲያስተዳድሩ ከፍ ከተደረጉ ብዙ ጉዳት ያደርሳሉ።
ቀጣዮቹ ጥቅሶች የተጠቀሱት የፓስተሮችን አገልግሎት ለመንቀፍ አይደለም። የፓስተሮች አገልግሎት ትኩረቱን ሕዝቡን በግል ችግራቸው መርዳት ላይ እስካደረገ ድረስ በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ አገልግሎት ነው።
ፓስተሮች የተነቀፉት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከሰጣቸው ስፍራ ወጥተው የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ከሕዝቡ በላይ ከፍ ከፍ ሲደረጉ ነው።
ቀጥለው ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት እንገልጣለን ብለው የግል አመለካከታቸውን ያስተምራሉ።
ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እየገለጠ እንዲያስተምር የተቀባው አስተማሪ ነው።
ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ባልሰጣቸው ስፍራ የቤተክርስቲያን ራስ ነኝ ብለው ከተቀመጡ በኋላ ማን መስበክ እንዳለበትና በቤተክርስቲያን ገንዘብ ምን መደረግ እንዳለበት የመወሰን ስልጣን አለኝ ይላሉ። ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ከቤተክርስቲያን አባላት መካከል ከሁሉም የተሻለ ቤት ያለው ሰው ብዙውን ጊዜ ፓስተሩ ነው። ከዚያም በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ለእርሱ ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ የመኪና ማቆሚያ አለው።
ስልጣን ያባልጋል፤ በሕዝቡ ላይ እና በቤተክርስቲያን ገንዘብ ላይ ሙሉ ስልጣን ሲኖራቸው ፓስተሮች በጣም ይባልጋሉ፤ ለዚህ ነው ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ ፓስተሮች ከተጻፉት ጥቅሶች መካከል 6ቱ የሚያወግዙዋቸው።
ፓስተሮች እና ጉባኤዎቻቸው እንደሚያስቡት ፓስተሮች የቤተክርስቲያን ብቸኛ ከዋክብት አይደሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አይልም።
ኤርምያስ 2፡8 ካህናቱም፡- እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።
“ገዢዎችም አመጹብኝ”። አመጽ ማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ያፈነገጠ እምነት ነው።
ፓስተርን የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማፈንገጥ ስለሆነ ትልቅ አመጽ ነው።
ኤርምያስ 10፡21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ፓስተሮች ሰነፎች ሆነዋል፤ እግዚአብሔርንም አይፈልጉም።
አጀንዳቸው ሁልጊዜ የራሳቸው ትርፍ እና የራሳቸው ታላቅነት ነው።
በሰዎች ላይ መሰልጠን ሰዎች ላይ ጌታ መሆን ይወዳሉ። እነርሱን የተቃወመ ሁሉ ይባረራል። መጽሐፍ ቅዱስን የሚወዱ አማኞች ይባረራሉ። ከዚያ በኋላ ጉባኤው ሊታረም አይችልም።
ጉባኤው ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ ለተባለው ስሕተት እጅ ስለሰጡ ወደ ታላቁ መከራ እየተነዱ ይሄዳሉ።
ተኩላዎች ጨካኞች ናቸው። ማንኛውም ተኩላ መሪውን ከተቃወመ፤ የተኩላዎች መሪ ተቃዋሚውን ተኩላ ይገድለዋል።
ኤርምያስ 12፡10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
እምነታችን ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ አለብን። እውነተኛው የወይን እርሻችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥረት ትርጉም ስናገኝ ትክክለኛ መገለጥና መነቃቃት የሚመጣልን ከቃሉ ነው።
ፓስተሮች ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ሚስጥራትን ሊገልጡ ወስነዋል፤ ለምሳሌ ሰባቱ ነጎድጓዶች እና የኢየሱስ አዲስ ስም፣ ወዘተ።
ፓስተሮች ሰዎች እምነታቸውን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሳይሆን በተመረጡ የሰዎች ጥቅሶች ላይ እንዲመሰርቱ አድርገዋል። ሰዎች ደግሞ ጥቅሶችን እንደ ገደል ማሚቶ ይደጋግማሉ። ትምሕርቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ትተዋል። የሜሴጅ ተከታዮችና ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እምነታቸው ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አይችሉም።
ኤርምያስ 22፡22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትጐሳቈይማለሽ።
ነፋስ የሚያመለክተው መንፈሳዊ ውጊያን ነው። ክርክራቸው ሁሉ መነሻው የተመረጡ ጥቅሶች እና መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃቸው ነው።
“ነፋስ …” ፓስተሮች የተመረጡ ጥቅሶችን ወንድም ብራንሐም ሊያስተላልፍ ከፈለገው ሃሳብ ውጭ በመተርጎም እራሳቸው እንደ ነፋስ ባዶ ሆነው ይቀራሉ።
ወንድም ብራንሐም፡- “ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን አሰምተዋል” ብሎ አልተናገረም፤ ፓስተሮች ግን ይህንን ንግግር የእምነታቸው መሰረት ያደርጉታል።
ፓስተሩን ከተቃወማችሁ ከቤተክርስቲያን ትባረራላችሁ።
ኤርምያስ 23፡1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።
2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ፓስተሮች የሰውን ንግግር ወስደው እንደየፍላጎታቸው በመተርጎም በእነርሱ ስር ያሉ ሰዎች እምነታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ እንዳይመሰረትና የፓስተሮቹን አመለካከት ብቻ እንዲከተሉ ያደርጓቸዋል። በነዚህ በተመረጡ ጥቅሶች ላይ ፓስቱ የሚሰጠው ትርጓሜና የፓስተሩ አመለካከት እውነት ተደርገው ይወሰዳሉ።
ከፓስተሩ ጋር አንስማማም ያሉ ሰዎች በሙሉ ይባረራሉ፤ ይበተናሉ።
“ፓስተራችሁ እስከ መጨረሻው አብሯችሁ ይሆናል”። (ይህ አባባል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም)። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በብዙ ቡድኖች ስለተከፋፈሉ አንድ ፓስተር ከሌላ ፓስተር በጣም ይለያል።
ስለዚህ የትኛው ፓስተር እና የትኛው የሜሴጅ የትምሕርት ዓይነት ነው ትክክለኛው? የትኛውም ቤተክርስቲያን ቢሆን ትክክል ይሆናልን?
ለነገሩ ሕዝቡ የራሳቸውን እምነት በራሳቸው አስተሳሰብ በሚመሩበት በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ኢየሱስ ከሁሉም ቤተክርስቲያኖች በር ውጭ ነው የቆመው።
የቤተክርስቲያን አባላት ቁጥር መብዛት እና የቤተክርስቲያን ሃብት መጠን ማደግ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ መስፈርት ከሄድን ካቶሊኮች በሕዝብ ብዛትም ይሁን በገንዘብ ክምችት አንደኛ ስለሆኑ ከሁሉም በላይ ትክክለኛ እነርሱ ናቸው።
ነገር ግን ማንኛውም ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እርስ በርሳቸው እያገናኘ እውነትን መማር ከፈለገ ከቤተክርስቲያን ይባረራል።
እነዚህን ዓይነት ሰዎች ፓስተሮች አይጎበኙዋቸውም። በጉባኤያቸውም ውስጥ እንዲገኙ አይፈልጉም።
ስለዚህ አማራጩ ምንድነው?
እግዚአብሔር ፓስተሮችን አይቀበልም፤ ቃሉን እንዲመግቡን ያስቀመጠው እረኞችን ነው
ሰዎች ፓስተሩ እረኛ ነው ይላሉ፤ ነገር ግን ይህን የሚመሰክር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም።
ኤርምያስ 23፡2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸውማል አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ የሥራችሁን ክፋት እጐበኝባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
3 የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል።
4 የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነሱም አንድ አይጐድልም፥ ይላል እግዚአብሔር
ሕዝቡን የተሳሳት ትምሕርት ያስተማሩ ፓስተሮችን እግዚአብሔር ያወግዛቸዋል። ማንም ሰው ቢሆን የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አይችልም፤ ኢየሱስ ብቻ ነው የቤተክርስቲያን ራስ። ሰዎች ካለባቸው ድክመት፣ ውስንነት እና መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ የተነሳ የቤተክርስቲያን ራስ መሆን አይችሉም።
ሕይወት እጅግ ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሰው ብቻውን ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ ሊሰጥ አይችልም።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ትክክለኛውን ምግብ የሚያበሉ እረኞችን እሰጣለሁ ብሏል። አንድ ሰው ብቻውን የቤተክርስቲያን ራስ በመሆን ቤተክርስቲያንን ሊመግብ ከሚችለው በላይ የሽማግሌዎች ሕብረት ልምዳቸውን ጥበባቸውን ወደ አንድ በማምጣት አጥቢያ ቤተክርስቲያንን በደምብ መመገብ ይችላሉ።
ሕዝቡ “ዳግመኛ አይፈሩም”። ከፓስተሩ ጋር አልስማማም ቢሉም እንኳ በፓስተሩ ማስፈራሪያ እየተጨነቁ አይኖሩም። የፓስተሩን ስሕተት የተቃወሙ ሰዎች ከዚህ በኋላ ሊባረሩ አይችሉም። ለመቃረን ድፍረት ስላላቸው ብቻ ከሕዝቡ መካከል እንደማይፈለግ እቃ አይገለሉም።
እግዚአብሔር ፓስተሮችን ትቶ እረኞችን ያስነሳል። እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?
እነዚህ ጥቂት ሰዎች ናቸው።
ሉቃስ 18፡7 እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
እረኞች ሁልጊዜ ወደ ቃሉ ነው የሚሄዱት።
ልክ እረኞች በመልአኩ ተልከው ወደ ሕጻኑ ኢየሱስ እንደሄዱት ማለት ነው።
መዝሙር 23፡1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
ብቸኛው እውነተኛ እረኛ ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 10፡11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
ዮሐንስ 10፡2 በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
ወደ ሰማይ መግቢያው በር ኢየሱስ ነው እርሱም ቃሉ ነው። ቃሉን ብቻ ነው መስበክ ያለባችሁ። እውትን በእግዚአብሔር ቃል መርምራችሁ ካረጋገጣችሁ ሕዝቡን ወደ ቃሉ ትመልሱታላችሁ፤ ቃሉም ወደ መንግስተ ሰማይ መግቢያ ብቸኛ በር ነው። የመጽሐፍ ቅዱስም ትኩረቱ በኢየሱስ ላይ እንድትደገፉ ማድረግ ነው።
ዮሐንስ 10፡5 ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
የሰዎች አተረጓጎም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማገናኘት አይችልም። አንድ ሰው ሃሳቡን ከሰው ንግግር ጥቅስ ውስጥ ሊወስድ ይችላል። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ገኘውን ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመርመር አለበት። ሃሳባችሁ ትክክል መሆኑን ወደ ሰው ንግግር ጥቅስ ሳትሄዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መርምራችሁ ካላረጋገጣችሁ ስለ ምን እንደምታወሩ እንኳ አታውቁም ማለት ነው። የዛኔ እምነቱን በተጻፈው ቃል ላይ ሊገነባ የሚፈልግ እውነተኛ አማኝ የሆነ ሰው የናንተን አመለካከት አይከተልም።
አምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ማለት ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም። ሰዎች ቤተክርስቲያንን የሚመራ አዲስ የአሮን ክሕነት የተባለ አገልግሎት መጥቷል ይላሉ። ነገር ግን የአሮን ክሕነት ሊቀካሕናቱ ቀያፋ ልብሱን ከቀደደ በኋላ በቀራንዮ መስቀል አብቅቷል።
እውነተኛው የመልከጼዴቅ ክሕነት እያንዳንዱን አማኝ የሚያካትት ሲሆን ይህም ክሕነት ሁሉን እኩል የሚያደርግ ነው።
እያንዳንዳችሁ ከማንም ባልተናነሰ መልኩ የዚህ ክሕነት አካል ናችሁ።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ … ናችሁ፤
በእናንተ እና በኢየሱስ መካከል ማንም የለም። ሽማግሌዎች ወደ ኢየሱስ የሚመሩዋችሁ አቅጣጫ ጠቋሚዎች ወይም ታፔላዎች ብቻ ናቸው። ታፔላን የሚያመልክ የለም። ስለ ታፔላ እግዚአብሔርን ልታመሰግኑ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ከታፔላው አልፋችሁ ታፔላው ወደሚጠቁመው ወደ ኢየሱስ መሄድ አለባችሁ፤ ምክንያቱም ታፔላው የሚጠቁመው መንገድ እርሱ ነው።
አምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች ማለት ቃሉን የሚሰብኩ ሽማግሌዎች ናቸው። ቤተክርስቲያንን በማስተዳደር ስራ ውስጥ የተጠመዱ ሌሎች ሽማግሌዎችም አሉ፤ እነዚህ ስብከት ውስጥ ላይሳተፉ ይችላሉ። ነገር ግን ሁሉም ሽማግሌዎች ናቸው።
እያንዳንዱ ሽማግሌ የራሱ የሆነ የስራ ድርሻ አለው፤ ነገር ግን የስራ ድርሻ ማንንም ከቦታው ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርገው አይችልም።
“መመለሻው መንገድ” ኖቬምበር 23 ቀን 1962
አሁን ልጸልይላችሁ ነው። አሁን እጄን ልጭንባችሁ ነው። አጋልጋይ ወንድሞች አብረውኝ እንዲያገለግሉ እጠይቃለሁ ምክንያቱም ሁሉን እኔ ብቻዬን እንደማላደርገው እንድታዩ እፈልጋለሁ። አገልጋይ እኔ ብቻ አይደለሁም። ማንኛውም አገልጋይ ለበሽተኞች የመጸለይ መብት አለው። እግዚአብሔር በመምሰል የሚኖርና እግዚአብሔር የላከው ማንኛውም አገልጋይ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ካለው እግዚአብሔር ይሰማዋል፤ የማንንም ጸሎት እንደሚሰማ ሁሉ የእርሱንም ጸሎት እግዚብሔር ይሰማዋል።
ላይገለጥላቸው ይችላል እንጂ መጸለይ ግን ማንም አይከለክላቸውም።
ሲገለጥም ደግሞ ሁልጊዜ አይደለም። ይህን ታውቃላችሁ።
ነገር ግን የሚገለጥለትም ሰው ቢሆን ስለተገለጠለት ከሌሎች አይበልጥም።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
ሁላችንም አንዳችን ለሌላችን መገዛት አለብን። ሁላችንም ለእግዚአብሔር ቃል መገዛት አለብን። ማንም ሰው አንድን እውነት የሚገልጥ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አግኝቶ ቢያሳየን ሁላችንም ለዚያ እውነት እንገዛለን። በዚህ መንገድ ነው ሁላችንም እርስ በራሳችንን ማረም የምንችለው።
በአጥቢያ ጉባኤ ውስጥ ማንም ሰው አለቃ አይደለም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፡17 በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።
አንዳንድ ሽማግሌዎች በቃሉ እና በአስተምሕሮ ይተጋሉ። እነዚህ ናቸው በአምስቱ አገልግሎቶች ውስጥ የሚሳተፉት። ሰባኪ ያልሆኑ ሌሎች ሽማግሌዎችም አሉ፤ እነርሱ ደግሞ ቤተክርስቲያንን የማስተዳደር ሚና ይጫወታሉ።
ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩዋት የሚያስተምሩ፣ የሚሰብኩ፣ እና የማይሰብኩ ሽማግሌዎች በአንድነት በመስራት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መረዳት የምንችለው በትምሕርት ነው
“እግዚአብሔር ሰውን አስቀድሞ ሳያስጠነቅቀው ወደ ፍርድ አያመጣውም”
አስተማሪ ልዩ ሰው ነው። ቁጭ ብሎ የመንፈስ ቅዱስን ቅባት እየተቀበለ ቃሉን ይወስድና በመንፈስ ቅዱስ እያገናኘ ስለሚያስተምር ወንጌላዊም ይሁን ፓስተሩ ከአስተማሪ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም።
አስተማሪው መገለጡን ወይም መረዳቱን ከጥቅሶች ውስጥ ያገኛል።
ከዚያም እነዚህን ሃሳቦች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አግኝቶ ሃሳቦቹ እውነት መሆናቸውን ለማረጋገጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር ያገናኛል።
አንድን እውነት ለማረጋገጥ የሰው ንግግር ጥቅስ አስፈላጊ አይደለም። ለማረጋገጥ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻውን በቂ ነው።
በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ ያሉ አገልጋዮች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር በማገናኘት ከአስተማሪው እኩል ሊሆኑ አይችሉም፤ በዚህ የተቀባው አስተማሪው ነው።
ከሰው ንግግር የተወሰዱት ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስ ሊረጋገጡ ከቻሉ እነዚህ መገለጦች እውነተኞች ናቸው ማለት ይቻላል። ፓስተሮች፣ ወንጌላውያን፣ እና ሌሎች ሰባኪዎች ትሑት ሆነው ከአስተማሪው ለመማር ፈቃደኛ ቢሆኑ የአስተማሪነት አስፈላጊነት ለዚህ ነው።
“እርዳታ”። ቤተክርስቲያን በአንድ ሰው አትተዳደርም። ሁሉም ሰው መሳተፍ አለበት። ማንኛውም ሰው መርዳት እና አንድ የስራ ድርሻ ማከናወን ይችላል። ይህ ሰዎች ሁሉ በአገልግሎት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የቀረበ ግብዣ ነው።
“አገዛዝ” የሚለው ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎችን ነው የሚመለከተው (የሚሰብኩም የማይሰብኩም ሽማግሌዎችን ያጠቃልላል)።
“ያህዌ ይርኤ” ጁላይ 7 ቀን 1962
የምንሄድበትን መንገድ አሳየን ጌታ ሆይ። አስተምረን አባት ሆይ። እኛም እንሰማሃለን። የሚያስተምረን ሰው ከቃልህ ጋር የማይስማማ ነገር ቢነግረን ስሕተት መሆኑን አውቀን ፈቀቅ እንላለን።
መንፈስ ቅዱስ አስተማሪያችን ነው። ቃሉን የጻፈው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ከቃሉ ውጭ የሆነ ነገር አያስተምረንም።
ደግሞም በዚህ ምሽት መንፈስ ቅዱስ ለልባችን ቃሉን እንዲገልጥልን እንጸልያለን። ጌታ ሆይ ግለጥልን።
“ጥያቄዎችና መልሶች” ሜይ 15 ቀን 1954
እናንተስ እንዲህ ትላላችሁ፡- “ክብር ለጌታ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሏል፤ መንፈስ ቅዱስ ሰመጣ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ መንፈስ ቅዱስ እራሱ አስተማሪያችሁ ነው።” ኦ ወንድሞች ሆይ። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንዴት እንዲህ ታጣጥላላችሁ …
እንዲህ ከሆነ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ ለምንድነው በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪዎችን ያስቀመጠው?
“ማንም ሰው ሊያስተምረኝ አያስፈልገኝም፤ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረኛል” ልትሉ ትችላላችሁ።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምራችሁ በአስተማሪ በኩል ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪዎችን አስቀምጧል።
እንዲህ ብሏል፡- “ሁሉ አስተማሪዎች ናቸውን፤ ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን፤ ሁሉስ የፈውስ ስጦታ አላቸውን?” መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ሁሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀምጧል። መንፈስ ቅዱስ በነዚህ ሁሉ ይሰራል፤ እነዚህ ሁሉ አገልጋዮች በስነ ስርዓት ያገለግላሉ።
“አንድነት” ፌብሩዋሪ 11 ቀን 1962
ይህ ምንድነው?
እግዚአብሔር የላከው አስተማሪ በትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁልጊዜ ከቃሉ ፈቀቅ ሳይል ያስተምራል፤ ድርጅቶች የፈለጉትን ቢሉ እንኳ ከቃሉ ውጭ አይወጣም፤ እነርሱ ግን ከቃሉ ጋር ሕብረት የላቸውም።
ነብያት፣ እንደ ነብይ የሚያስመስሉ ሳይሆኑ እውነተኛዎቹ ነብያት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለው ይናገራሉ፤ ደግሞም ሁልጊዜ እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራሉ። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ ያስቀመጠው አሰራር ይህ ነው። ይህንኑ እንደሚያደርግ ነው የተናገረው። እውነተኛ ነብይ ቃሉን ነው የሚያምነው እንጂ የሐያማኖት መግለጫ ወይም ዶግማ አይደለም፤ ቃሉን ነው የሚያምነው … በዚህም መንገድ እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል ቃሉን በመፈጸም ራሱን ይገልጣል። ቃሉን በምድር ላይ በመፈጸም እርሱ በፊት ኖሮት የነረውን ሕይወት በአማኞች ሕይወት ውስጥ በድጋሚ ይኖረዋል። ይህ በጣም አስገራሚ ነው።
“ነብይ እንደሆንክ አያለሁ” ጁን 14 ቀን 1953
በዚህ ዘመን የአዲስ ኪዳን ነብይ ማለት ሰባኪ ነው። “መተንበይ” ማለት “ወደፊት የሚሆነውን መናገር ወይም ለአንድ ሰው ስለ ግል ጉዳዩ ገልጦ መናገር” ነው።
በሌላ አነጋገር አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ቢያነብና መናገር ቢጀምር …. ይህ ሰው አስተማሪ ነው።
አያችሁ? “መተንበይ” ግን “መመስከር ወይም ስለወደፊቱ አስቀድሞ መናገር” ነው። አሁን ደግሞ … የክርስቶስ መንፈስ ትንቢት ነው።
“ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት” ሜይ 12 ቀን 1954
እዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኜ የራዕይን መጽፍ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር ማጥናቴን አስታውሳለሁ። ማስተማር ውስጥ ደስ የሚለኝ ነገር ይህ ነው።
በቃ ማስተማር በጣም ወዳለሁ። በጣም አስደናቂ አገልግሎት ነው። መሰረት ያስይዛል፤ ቤተክርስቲያንንም ያረጋጋታል።
ወደ ስብከት ስንመጣ ደግሞ ሰባኪዎች ሆነው የተቀቡ አንዳንድ ሰዎች አሉ። በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ተቀብተው አንድ ቃል ይወስዱና የሰዎችን ነፍስ ማረስረስ ይችሉበታል።
ይህም አገልግሎታቸው አስተማሪው የዘራቸውን ዘሮች ውሃ ማጠጣት ነው።
አያችሁ?
መጀመሪያ ዘር መዝራት ያስፈልጋል፤ ከዚያ በኋላ ዘሩን ውሃ ማጠጣት ያስፈልጋል። በትምሕርት የተዘራው ዘር ውሃ የሚጠጣው ቃሉ ሲሰበክ ነው።
በአስተማሪ እና በሰባኪ መካከል ትልቅና ሰፊ ልዩነት አለ።
አያችሁ? አስተማሪነትና ሰባኪነት ሁለት የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ናቸው። እኔ ግን በትሕትና ልንገራችሁ የሁለቱም ስጦታ የለኝም።
“የእግዚአብሔር ማሕተም” ሜይ 14 1954
በአሁኑ ሰዓት ኡሪም እና ቱሚም አንጠቀምም፤ እነርሱ ቀርተዋል፤ ነገር ግን አሁን የእግዚአብሔር ኡሪም እና ቱሚም መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ነብይ ወይም ሕልመኛ ወይም ማንኛውም ዓይነት አገልጋይ ወይም አስተማሪ የሚናገረው ነገር እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ በተናገረው ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ አላምነውም። አያችሁ? ይኸው መጽሐፉ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በእጃችን አለ። ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአንድ ጥቅስ ብቻ አይደለም፤ በመጽሐፉ በሙሉ ተምርምሮ ትክክል መሆን አለበት። እያንዳንዱ ትምሕርት ወይም ትንቢት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ከሚናገረው ጋር መስማማት አለበት። እንደዚያ ካልሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጥቅስ በመምዘዝ ይህ ፑርጋቶሪ ነው ብላችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ የካቶሊክ አስተምሕሮ ልታስተምሩ ትችላላችሁ።
ሁሉም ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ካለው ሃሳብ ሁሉ ጋር መጋጠምና ግልጽ ምስል መፍጠር አለበት።
አዎን።
ይህንን የመረዳት ምስል በልባችሁ ውስጥ የሚስለው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው። ከፈቀዳችሁለት ያደርገዋል። ወደ ብርሃን ይመራችኋል። ይህን እንደሚያደርግ መጽሐፍ ቅዱስ ተናግሯል። ይህን እንደሚያደርግ ኢየሱስም ተናግሯል።
“እርሱን ስሙ” ሜይ 19 ቀን 1957
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከቃሉ ጋር ነው። መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ሕጻን ሊያስተምርበት የተቀበለው መመሪያ ይህ ነው። ለምንም ብሎ ይህንን አቋሙን አይጥለውም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቃል አውጥቶ አይጥልም፤ አንድም ቃል ደግሞ አይጨምርበትም። ሁሌ ከቃሉ ጋር ነው።
ጌታ በፍጹም ከቃሉ ውጭ አንዳች ነገር አያደርግም።
መጽሐፍ ቅዱስ “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፣ ዛሬ፣ እስከ ለዘላለምም ያው ነው” ብሎ ከተናገረ መንፈስ ቅዱስም ይህንኑ ነው የሚናገረው።
ሰዎች “ይህንማ ማስተማር አትችልም። ይህ ትክክል ሊሆን አይችልም” ይላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “ደዌህን ሁሉ የምፈውስ ፈዋሽህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።”
ሰው እንዲህ ይላል፡- “ይህን እንኳ ማመን አንችልም።”
መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “አሜን። እውነት ነው።”
አያችሁ? ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው። “እኛ ፕሬስቢተሪያን ነን፤ እኛ ፔንቲኮስታል ነን፣ እኛ አሴምብሊ ነን፣ እኛ እንዲህ ነን፣ እኛ እንዲያ ነን፤ ስለዚህ ይህን አናምንም።”
ለምንድነው ቃሉን የማታምኑት? ምክንያቱም እግዚአብሔር የላከውን አስተማሪ መንፈስ ቅዱስን መስማት ትታችሁ ሰዎችን እየሰማችሁ ነው። ምክንያቱ ይህ ነው። ከቃሉ ጋር ተጣበቁ። መንፈስ ቅዱስ ሲያስተምራችሁ ከቃሉ ምንም አያጎድልም፤ በቃሉም ላይ ምንም አይጨምርበትም። ሁሌ ከቃሉ ፈቀቅ አይልም፤ እርሱ እግዚአብሔር የላከልን አስተማሪያችን ነው።
“በክርስቶስ ውስጥ የተሰወረ ሕይወት” ኖቬምበር 10 ቀን 1955
እኛ ግን ብዙ ጊዜ በቃሉ ቦታ ብዙ ነገር እንተካለን በተለይ ደግሞ በዚህ ዘመን። ብዙ ነገሮችን በቃሉ ቦታ ተክተን እየተጠቀምን ነን፤ ግን እንደዚህ ማድረግ የለብንም።
ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት ዓላማ ቃሉን ለመስበክ ነው። ምስክርነቶች ጥሩ ናቸው፤ ሌሎችም የምናደርጋቸው ልዩ ልዩ ነገሮች መልካም ናቸው። ነገር ግን ቅድሚያ መስጠት ያለብን ለቃሉ ነው፤ ምክንያቱም ቃሉ ለሐጥያተኛውም ይናገራል፤ በመንፈስ ቅዱስ ለተሞሉ ሰዎችም ይናገራል።
ሰይጣን በፈተነው ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል።” አያችሁ?
መንፈስ ቅዱስ የሚመግበን የእግዚአብሔርን ቃል ነው።
መንፈስ ቅዱስ … ቃሉን ይወስደውና ልባችሁ ውስጥ ያስቀምጠዋል፤ ቃሉም ልባችሁ ውስጥ ሲሆን እንድታድጉ እንድትበረቱ ያደርጋችኋል፤ ቃሉ ይገለጥላችኋል። ይህ በጣም ደስ ይለኛል።
ቃሉን አንብቦ በመገለጥ አብራርቶ የሚያስተምር አስተማሪ እግር ስር ተቀምጬ መማር ያስደስተኛል።
ክትምሕርቱ ጋር የደግነትና የየዋሕነት መንፈስ አብሮ ሲኖር ቃሉ በለሰለሰ መሬት ውስጥ ስር ሰድዶ ያድጋል።
“ሙሉ በሙሉ ነጻ መውጣት” ጁላይ 12 ቀን 1959
እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ ሙሴ ብቁ ነብይ ነበረ። እግዚአብሔር አንድን ሰው ለስራ ሲልከው ለስራው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አዘጋጅቶ አስታጥቆ ነው የሚልከው። እግዚአብሔር አንድን ሰው ስበክ ብሎ ሲልከው በውስጡ የሚሰብከውን ቃል ሰጥቶ ነው የሚልከው። አስተማሪ እንዲሆን ሲልከው የሚያስተምረውን ነገር በውስጡ አስቀምጦ ነው የሚልከው።
እግዚአብሔር አንድን ሰው ነብይ እንዲሆን ሲልከው በውስጡ ራዕይ እንዲያይና ትንቢት እንዲናገር የሚያስችለውን ጸጋ አስቀምጦ ነው የሚልከው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ የጠራውን ሰው ያስታጥቀዋል።
“እርሱን ስሙ” ጁላይ 12 ቀን 1960
ትክክለኛ አስተማሪ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ በግልጽ ይነግራችኋል ምክንያቱም እርሱ ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ነው የተቀባው። ደግሞ ልብ ብላችሁ ተመልከቱት፤ አንድ እርምጃ እንኳ ከቃሉ ፈቀቅ አይልም። ቃሉ የሚለውን ብቻ ይናገራል፤ ሁሌ ከቃሉ ጋር ተጣብቆ ይኖራል። እግዚአብሔርም ቃሉን ይባርከዋል። በማንኛውም ጊዜ እግዚአብሔር እንደሰጠው ተስፋ ቃሉን ይባርከዋል።
“ጥያቄዎችና መልሶች” ጃንዋሪ 12 ቀን 1961
“እግዚአብሔር ቃሉን እንዳስተምር ጠርቶኛል።” ደግሞም ቃሉን እንዴት እንደሚተረጉም ተመልከቱ።
አያችሁ? ሁሉን ነገር ያደበላልቀዋል፤ የዛኔ በግልጽ ታያላችሁ። አያችሁ?
ነገር ግን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ግልጽ ይሆንላችኋል፤ ማድረግ ትችሉ ወይ አትችሉ እንደሆን ታውቃላችሁ።
“አጽናኙ” ኦክቶበር 1 ቀን 1961
በቅርቡ ከአንድ ቄስ ጋር ሳወራ ነበርና እንዲህ አልኩት፡- “አንተም እኮ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ነህ።” እንዲህ አልኩት፡- “ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈቀቅ አትበል።”
“ሶስተኛው ማሕተም” ማርች 20 ቀን 1963
የመጀመሪያው ደረጃ ነጭ ፈረስ ነው (አያችሁ?) እርሱም አስተማሪ ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነ አስተማሪ፤ ይህ አስተማሪ ቃሉን የሚቃወም ሰው ነው።
እንዴት ነው የክርስቶስ ተቃዋሚ ልትሆኑ የምትችሉት?
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሙሉ በሙሉ እውነት መሆኑን የሚክድ ሁሉ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው፤ ምክንያቱም ቃሉን ክዷል፤ ክርስቶስ ማለት ቃሉ ስለሆነ ቃሉን የሚክድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 3
“እንዲሁም ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ።”
ይህ ጠንከር ያለ ንግግር ነው። “እንዲሁም ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ።” ይህ ድፍረት አይደለምን? ራሳቸውን ሐዋርያ ብለው የሚጠሩ ሰዎችን ሕዝቡ ሊመረምራቸው ምን መብት አለው? የሚመረምሩዋቸውስ እንዴት ነው? ኦ እኔስ ይህ ደስ ይለኛል።
መመርመሪያው ይኸው ገላትያ 1፡8፡-
“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።”
… የእግዚአብሔር ቃል ግን ሊለወጥ አይችልም። ዘሩ የመጣው ልክ እንደተገለጠ ነው። ሃሌሉያ። እነዚያ ሐሰተኛ ሐዋርያት ያደረጉትንም ተመልከቱ። እነርሱም የራሳቸውን ዘር ይዘው መጡ። የኤፌሶን ሰዎች ጳውሎስ ሲያስተምራቸው የሰሙት ቃል እውነት መሆኑን ያውቃሉ። ጳውሎስ እጁን ከጫነባቸው በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር። ሐሰተኞቹን ሐዋርያት ዓይን ዓይናቸውን እያዩ እንዲህ አሉዋቸው፡- “እናንተ የምታስተምሩን ጳውሎስ ካስተማረን ጋር አንድ አይደለም። ስለዚህ ሐሰተኞች ናችሁ።” ይህንን ስናገር ልቤ እንደ እሳት ይቃጠልብኛል። ወደ ቃሉ እንመለስ!
ሐዋርያውን፣ ነብዩን፣ አስተማሪውን የምትመረምሩ እናንተ አይደላችሁም፤ የሚመረምራቸው ቃሉ ነው።
ብዙ ሳይቆይ በቅርቡ ለዚህ ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዘመን የተላከ ነብይ ይመጣል፤ እርሱም ከእግዚአብሔር የተላከ እውነተኛ ነብይ ይሁን አይሁን ታውቃላችሁ። እውነት ነው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ከሆነ ታውቃላችሁ፤ እውነተኛ ከሆነ እግዚአብሔር ለጳውሎስ የሰጠውን ቃል በትክክል ይናገራል። ለጥቂት ደቂቃ እንኳ ከቃሉ ፈቀቅ አይልም። በዚያ በመጨረሻ ዘመን ውስጥ ብዙ ሐሰተኛ ነብያት በሚነሱ ጊዜ እነርሱ የሚናገሩትን ባታምኑ እንደምትጠፉ ደጋግመው ሲነግሩዋችሁ በጥንቃቄ ስሟቸው፤ የመጨረሻው ዘመን ነብይ ሲገለጥ ግን የእውነት ትክክለኛው ነብይ ከሆነ እንዲህ ብሎ ይጮሃል፡- “ወደ ቃሉ ተመለሱ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ።”
የራሱን መገለጥ ይዞ አይደለም የሚመጣው፤ የራሱን ትርጓሜ ይዞ አይመጣም፤ ቃሉን ብቻ ይዞ ይመጣል እንጂ። አሜን፤ አሜን!
ፓስተሮች የ1963ቱን ደመና አስተምሕሮ እንዴት እንዳመሰቃቀሉት
ወንድም ብራንሐም የ1963ቱ ደመና የጌታ ምጻት ነው ብሎ ተናግሮ አያውቅም። ደመናው ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ ሰማይ ላይ ለ28 ደቂቃ እየተንሳፈፈ በቆየበት የቱክሰን ጠፈር ምርምር ማዕከል ፎቶግራፍ አንስቶታል። ደመናው ወደ ምድር አልወረደም፤ ወደ ላይም አልወጣም።
ከደመናው ስር ምንም ተራራ አልነበረም። ደመናው ሳንሴት ማውንቴን የተባለው ተራራም አካባቢ አልነበረም።
ወንድም ብራንሐም ደመናው በነበረ ሰዓት ከደመናው ስር ቆሞ እንደነበረ በማሰቡ እጅግ ተሳስቷል።
ደመናው በታየ ጊዜ እርሱ ስለ ደመናው ምንም አልሰማም ነበር። ከዚያ በኋላ ደመናው ስለ ታየበት ጊዜ እና ቦታ ሲናገር በጣም ተሳስቷል።
የሜሴጅ ፓስተሮች እርሱ ሲናገር የሰራውን ስሕተት በመጠቀም የተለያዩ የፈጠራ አስተምሕሮዎችን አስተምረዋል፤ ለምሳሌ፡- “ጌታ ተመልሶ መጥቷል፤ በመካከላችን በሚስጥር እየተመላለሰ ነው”፤ “ምሕረት አብቅቷል”፤ “ወንድም ብራንሐም ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ መጥቷል”፤ “ታላቁ ድምጽ ተሰምቷል”።
ደመናው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነው ፎቶግራፍ የተነሳው። ወንድም ብራንሐም ጌታን ወደ ምድር መልሶ የሚያመጣው ሰባተኛው ማሕተም ነው ብሎ ከተናገረ እንዴት ደመናው እንዴት የጌታ ምጻት ሊሆን ይችላል? ስለ ሰባተኛው ማሕተም የተሰበከው ማርች 24 ቀን 1963 ነው። ከዚያ በተጨማሪ ስለ ሰባተኛው ማሕተም ማርች 25 ቀን 1963 ጥቂት ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል። እና የጌታ ምጻት የተፈጸመው በየትኛው ቀን ነው?
“አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት” ኖቬምበር 10 ቀን 1963
ሰባተኛው ማሕተም ወደ ምድር መልሶ ያመጣዋል።
“የመለከቶች በዓል” ጁላይ 19 ቀን 1964
በዚያም ስፍራ ሲናገር ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም ብሏል።
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።
ሰባተኛው ማሕተም ካልተፈታ ኢየሱስ በዚያ ዕለት ወደ ምድር አልመጣም ማለት ነው።
“የእግዚአብሔር ልዩ የእጅ ስራ” ዲሴምበር 5 ቀን 1964
እንግዲህ አሁን በዚህ ከተማ ዩማ አሪዞና ውስጥ እገኛለሁ። ሃሌሉያ! ዛሬ በዚህ ስታርደስት ሆቴል ውስጥ አንድ እምነት ካላቸው ሰዎች ጋር አንድ ተደርጌ ተቆጥሬያለሁ። “በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ አብረን ተቀምጠናል።” ሃሌሉያ!
በቅርቡ ጌታ በክብሩ ተመልሶ እንደሚመጣ እየተበቅሁ ነኝ።
ከእርሱ ጋር አንድ ነን!
ደመናው ፎቶግራፍ ተነስቶ ሁለት ዓመታት ካለፉ በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም የጌታን መምጣት እየተጠባበቀ ነበር።
የሜሴጅ ተከታዮች ከዊንስሎው ከተማ ፎቶግራፍ የተነሱት ደመናዎች ሁለት መሆናቸውን በጭራሽም አይጠቅሱም።
ትልቁ ደመና የተፈጠረው በ7 መላእክት ክንፍ ነው። ከትልቁ ደመና ኋላ በ20 ማይልስ ርቀት ላይ የታየው ትንሹ የጭስ ደመና የተፈጠረው ከቫንደንበርግ አየር ኃይል ተወንጭፎ በፈነዳ ሮኬት ነው።
ደመናው ፎቶግራፍ የተነሳው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተ ሰሜን ነው፤ ይህም ቦታ ከሳንሴት ፒክ 200 ማይልስ ወደ ሰሜን ራቅ ብሎ ነው የሚገኘው። ትልቁን ደመና የሰሩት 7 መላእክት ከስምነት ቀናት በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ወደ ሳንሴት ፒክ መጥተው ወንድም ብራንሐምን ጎብኝተውት ስለ 7ቱ ማሕተሞች ገልጦ እንዲያስተምር ትዕዛዝ ሰጡትና ሄዱ። ማርች 8 ቀን ሲመጡም ሆነ ሲመለሱ የማይይታዩ ሆነው ነበር የመጡትና የተመለሱት፤ ስለዚህ ምንም ደመና አልሰሩም።
ደመናው ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ፎቶግራፍ በተነሳ ጊዜ ወንድም ብራንሐም ቱክሰን ከተማ ውስጥ ነበረ። የተወሰኑ ወራት እስኪያልፉ ድረስ ስለ ደመናው ምንም አላወቀም ነበር። ደግሞ ስለ ሁለተኛው የጭስ ደመናም ምንም አልሰማም ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤
አንድ ተራ የዝናብ ደመና የሚፈጠረው በውሃ ትነት አማካኝነት ነው። ወደ ሰማይ በጣም ከፍ ባለ ከፍታ ላይ “የጢስ ጭጋግ” የሚፈጥረው የጭስ ደመና ነው።
ጴጥሮስ በከፍታ ላይ የጢስ ጭጋግ እንደሚታይ ትንቢት ተናግሮ ነበር።
ይህ ትንቢት እንዲፈጸም በታላቅ ከፍታ ላይ የጭስ ደመና መታየት አለበት።
ይህንን ያላየውን ደመና በተመለከተ ብዙ አስተያየቶችን ከሰጠ በኋላ ወንድም ብራንሐም በስተመጨረሻ ከመሞቱ 5 ወራት በፊት ይህ ደመና በሰማያት ላይ የሚታይ የሰው ልጅ ምልክት ነው ብሎ ተናገረ።
የሜሴጅ ሰባኪዎች በጣም ከባድ ስሕተት ሰርተዋል።
ምልክቱን ዋናው ክስተት ነው ብለው ተቀብለዋል።
65-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር
በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!
“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል ከዚያ በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል።”
ደመናው የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አልነበረም።
64-0119 ሻሎም
ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
ደመናው ታይቶ አንድ ዓመት ካለፈ በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም መልአኩ ወደ ምድር መጥቶ ሙታንን እንዲያስነሳ ሲጠባበቅ ነበረ።
ይህ ብርቱ መልአክ ድምጹ ሙታንን የማስነሳት ኃይል አለው።
65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ከመሞቱ አንድ ወር በፊት እንኳ ወንድም ብራንሐም ሙታንን የሚያስነሳውን የመልአኩን ድምጽ ሲጠባበቅ ነበረ። በተጨማሪም የመልእክቱ “ታላቅ ድምጽ” እስኪመጣም እየተጠባበቀ ነበረ። ታላቁ ድምጽ ማለት ወንድም ብራንሐም ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ገልጦ ሲያስተምር ማለት አይደለም። ድምጹ ማለት በሙሽራይቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መገለጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች ብቻ በመጠቀም ለየግላቸው መረዳት ሲችሉ ነው።
“እግዚአብሔር በቃሉ የገለጠውን ሃሳብ ይለውጣልን?” አፕሪል 18 ቀን 1965
ምን ሆነ መሰላችሁ? በለዓም እስራኤልን አዳከመ። ምን አደረገ? ሰራዊታቸውን ሁሉ አዳከመ። ሄዶ እንዲያዳክማቸው እግዚአብሔር ፈቀደለት፤ እርሱም ሄዶ ጉባኤውን ሁሉ አረከሰ። የመጽሐፍ ቅዱስ እውመት ያልሆነ አንድ አስተምሕሮ ሲመጣ ጉባኤን በሙሉ ያረክሳል። አንድ ሰው ልክ እንደ ቆሬ የተለየ ሃሳብ ይዞ ይነሳና እንዲህ ይላል፡- “እኔ እንዲህ እና እንደዚያ የመሰለ ልዩ ሃሳብ አለኝ” ብሎ በመናገር ጉባኤውን በሙሉ ያረክሳል። ዛሬ በቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውስጥ እየተደረገ ያለው ይህ ነው።
ወደ ቃዴስ ባርኔ ከመድረሳቸው በፊት ጉባኤውን ሁሉ እንግዳ በሆነ ትምሕርቱ አዳከመ። ወደ ቃዴስ ባርኔ ሲደርሱ ጉባኤው በሙሉ ተዳክሞ ነበረ። ተመልሰው መጡ። መንገዳቸውን አልፈው በመሄድ ….
ልብ በሉ፤ እነዚህ ሰዎች የመላእክትን ምግብ በልተው የሚያውቁ ናቸው። በየዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል ይገለጥላቸው ነበር። ምግብም ይበሉ ነበር። ውሃ ከዓለት እየፈለቀላቸው ይጠጡ ነበር። ብዙ ተዓምራት አይተዋል። ሙሴ ሲናገር፤ የተናገራቸውም ትንቢቶች ሲፈጸሙ ሁሉንም ነገር አይተዋል።
ከዚያ በኋላ ግን ወደ መካከላቸው ገብቶ ሐሰተኛ ትምሕርት ያስተማራቸውን ይህን ሐሰተኛ አስተማሪ ሲያዳምጡ ጉባኤያቸው በሙሉ በሰሙት ሐሰተኛ ትምሕርት ምክንያት ተዳከመ።
አንድ ሰው ባለ ሚሊዮን ዶላር ሕንጻ ሊሰራ ይችላል። ትልቅ ቤቴክርስቲያን ሊመሰርት ይችላል።
እጅግ በጣም ብዙ አስደናቂና ታላላቅ ስራዎችን ሊሰራም ይችላል፤ ታላላቅ ድንቅ ስረዎችን የሰራ ታላቅ ነብይ ሊሆንም ይችላል። ይህ ሁሉ ምንም ችግር የለውም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ካልሆነ ትታችሁት ብትሄዱ ይሻላችኋል።
እግዚአብሔር ሃሳቡን አይለውጥም።
ሁልጊዜ በቃሉ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ምክንያቱም እስከ መጨረሻው የሚያዛልቃችሁ ቃሉ እና ቃሉ ብቻ ነው።
“ከቃሉ አንዳች የሚያጎድል ወይም ቃሉ ላይ አንዳች የሚጨምርበት” የሚል ማስጠንቀቂያ አለ። ስለዚህ በቃሉ መኖር ያስፈልጋል።
ከዚህ በታች ያለው ፖስተር ምስል የሜሴጅ ፓስተሮች በተመረጡ ጥቅሶች ላይ አስተምሕሮ ሲመሰርቱ ምን ያህል ሊሳሳቱ እንደሚችሉ ለማረጋገጥ በዓለም ዙርያ ተሰራጭቶ ነበረ።
ደመናው ማለት ጌታ በሳንሴት ተራራ ላይ መውረዱ ነው ብለው እያያስተማሩ ነበሩ።
ደመናው ከሳንሴት ፒክ በስተሰሜን በ200 ማይልስ ርቀት ላይ ከፍላግስታፍ ከተማ አጠገብ ነበር የታየው። እነዚህ ሰዎች ግን ይህን እንኳ በትክክል አላጣሩም።
ሳንሴት ፒክ የሚገኘው በታላቁ ሶኖራን በረሃ ውስጥ ነው።
ኢየሱስ ደግሞ በረሃ ውስጥ እንደማይመጣ ተናግሯል።
ማቴዎስ 24፡26 እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
ፓስተሮች አስገራሚ የሆነ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ትምሕርት ፈጥረው ያስተምራሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ማሰብ ያቆሙትን ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ለማስገረም ነው።
ፓስተሮች የተሰጣቸው ስራ አማኞችን መጎብኘትና መንከባከብ፤ እንዲሁም የግል ችግር ያለባቸውን ሰዎች ማማከር ነው።
ጥልቅ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥረት መረዳት የፓስተሮች ጥሪ አይደለም።
በለዓ በሐሰተኛ ትምሕርቶ እስራኤልን እንዴት እንዳዳከመ አስታውሱ፤ እርሱ ራሱ ግን በገንዘብ በለጸገበት። ዛሬም ያለብን ችግር ይኸው ነው።