አትብሉ የተባሉት ፍሬ - ምን ማለት ነው?



ለምንድነው ሁላችንም በሐጥያት የተወለድነው? ምድርን በዘላለማዊ ሕይወት መሙላት የሚቻልበት አማራጭ መንገድ ምን ነበር?

First published on the 19th of October 2022 — Last updated on the 19th of October 2022

ለኤድን ገነት የእግዚአብሔር እቅድ ምን ነበር?

 

 

እግዚአብሔር የኤድን ገነትን ለዘላለማዊነት እያዘጋጃት ነበር። ምንም ነገር የማይሞትበት ዓለም ነበር የተፈጠረው። ሰው ከዚህ ሁሉ ከፍታ ነው የወደቀው፤ ሞትን የምንጠላው ለዚህ ነው። በውስጣችን የተፈጠርነው ለማርጀትና ለመሞት እንዳልሆነ ይሰማናል። ከመጀመሪያው ስንፈጠር የጊዜ ባሪያ እንድንሆን አልነበረም የተፈጠርነው።

መጀመሪያ እግዚአብሔር ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ መንፈስ የሆነውን አዳም ያለ ምንም ነገር ፈጠረ።

አዳም በመንፈሱ ውስጥ የተወሰኑ የሴት ባህርያትም ነበሩት።

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ስለዚህ አዳም በእግዚአብሔር አምሳል እንዲሆን መንፈስ ሆኖ ነው የተፈጠረው።

ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤

በመጀመሪያ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ውስጥ ነበረ። ሁላችንም በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ነበርን።

መልካም የሆኑ ሰብዓዊ ባህሪዎቻችን የመጡት ከእግዚአብሔር ነው።

 

 

ራዕይ 13፡8 ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።

እግዚአብሔር በዋነኝነት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፤ ነገር ግን በውስጡ የሰው ባህርያትም አሉት።

ዘፍጥረት 1፡27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

አዳም በዋነኝነት ወንድ መንፈስ ነው፤ ነገር ግን በውስጡ የሴት ባህርያትም ነበሩት።

ዘፍጥረት 5፡2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው።

 

 

ልክ እግዚአብሔር ውስጥ የሰው ባህርያት እንደነበሩ ሁሉ እግዚአብሔርም አዳምን ወንድ መንፈስ አድርጎ ነገር ግን በውስጡ የሴት ባህርያት አኑሮ ነው የፈጠረው።

ተፈጠረ ማለት ያለ ምንም ነገር ተሰራ ማለት ነው። ስለዚህ አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ መንፈስ ነበሩ። መልካም የሆነው የሰው መንፈስ የመጣው ከእግዚአብሔር ነው። የሁለቱ ስም አንድ ላይ አዳም ነበር። አንድ መንፈስ ነበሩ።

የሰው ስጋ ያለ ምንም ነገር የተፈጠረ አይደለም ምክንያቱም ከአፈር ነው የተሰራው።

 

እግዚአብሔር ያዘዘው በመንፈሳዊ መንገድ መባዛትን ነው

 

 

ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤

ይህ ቃል በተናገራቸውም ጊዜ ሁሉ መንፈስ ነበሩ። የሰው መንፈስ ገና በስጋዊ አካል ውስጥ እንዲኖር አልተደረገም ነበር።

ተባዙ ተብሎ የተነገራቸው ስለ መንፈሳዊ መባዛት ነው።

ይህም ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም ነበር።

እግዚአብሔር እስኪፈጽመው ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው። ማለትም ልክ እኛ የጌታን ምጻት እንደምንጠብቀው እነርሱም መጠበቅ ነበረባቸው። የጌታ ምጻት እንዲፈጸም ማድረግ አንችልም። ዳንኤል የጌታ ምጻት እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ እንደሚመጣ ድንጋይ ሲመጣ አየ። የጌታ ምጻት አንዳችም የሰው ድጋፍ አያስፈልገውም።

ዳንኤል 2፡34 እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የሆነውን የምስሉን እግሮች ሲመታና ሲፈጭ አየህ።

 

 

“ተባዙ” የሚለው ቃል ውስጥ የመንፈሳዊ መባዛት ሚስጥር አለ።

ዘፍጥረት 1፡11 እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

“ተባዙ” የሚለው ቃል የመባዛት ዘር በፍሬ ውስጥ መኖሩን ያመለክታል።

እንዚህ ምሳሌዎች ምን ማለት ናቸው?

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ልክ የአፕል ዘር የአፕል ፍሬ ውስጥ እንደሚገኝ ሁሉ ኢየሱስ በማርያም ማሕጸን ውስጥ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘርም የሚገኘው በኢየሱስ አካል ውስጥ ነው።

 

 

በድንግልና የተወለደው ወንድ ልጅ የማርያም የማህጸን ፍሬ ነው።

እናትየው የፍራፍሬ ዛፍ ናት።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው፡- ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ፍሬያማ ለመሆን ማርያም ውስጡ ዘር ያለበት ፍሬ ሊኖራት ያስፈልጋል። በውስጡ ሙሉውን የእግዚአብሔር ቃል የያዘ ልጅ መውለድ አለባት። አማኑኤል፡- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር።

ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ለመንፈሳዊ መዋለድ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች እነዚህ ነበሩ።

እግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነው፤ ነገር ግን በሰው አካል ውስጥ ሊገልጽ የፈለጋቸው ሰብዓዊ ባህርያትም ነበሩት።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር የሴትን ባህርያት ወንድ በሆነው የአዳም መንፈስ ውስጥ አኖረ።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ የአዳምን መንፈስ በወንድ አካል ውስጥ አኖረ።

ኋላ የሴቷን መንፈስ ከአዳም ውስጥ አውጥቶ ለብቻ በሌላ አካል ውስጥ አስቀመጣት።

ዘፍጥረት 2፡7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

አዳም ለመጀመሪያ ጊዜ በስጋዊ አካል የተገለጠው ምዕራፍ 2 ውስጥ ነው።

ዘፍጥረት 2፡9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

አዳም ስጋዊ አካል ውስጥ ከገባ በኋላ ለፈተና የተጋለጠ ሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር በኤድን ገነት መካከል ስለሚገኙ ስለ ሁለት ዛፎች አስጠነቀቀው። ይህ ምንን ያመለክታል?

 

የዘላለም ሕይወት ሊሰጥ የሚችል ፍጥረታዊ ዛፍ የለም

 

 

ጠቢብ ሊያደርጋችሁ የሚችል ፍጥረታዊ ዛፍ የለም።

የትኛውም ፍጥረታዊ የዛፍ ፍሬ መልካም እና ክፉውን መለየት አያስችላችሁም።

“በገነትም” መካከል የሕይወት ዛፍ፤ ይህም ማለት በገነት መካከል ሌላም ነገር ነበረ ማለት ነው። እርሱም መልካም እና ክፉውን የሚያስታውቀው ዛፍ ነው።

ዘፍጥረት 3፡22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤

ብቸኛው የዘላለም ሕይወት ምንጭ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ የሕይወት ዛፍ እርሱ ነው።

አዳም ሐጥያት ሰራ። እግዚአብሔር ደግሞ ለዘላለም የሚኖር ሐጥያተኛ አልፈለገም።

ሰዎች መሞት የማይችሉ ከሆኑ እግዚአብሔር ስለ ሰዎች መሞትና የሐጥያታቸውን ዋጋ መክፈል አይችልም። መሞት ካልቻሉ ለዘላለም ተኮንነውና ተረግመው ይቀራሉ።

ኤርምያስ 17፡7 በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።

8 በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ … ዛፍ ይሆናል።

ዛፍ የጻድቅ ሰው መንፈስ ተምሳሌት ነው። ያ መንፈስም ከሕይወት ውሃ ወንዝ ርቆ አይሄድም፤ የሕይወት ውሃ ወንዝም መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ኢየሱስ የሕይወት ዛፍ ከሆነ ሰይጣን ደግሞ አሳሳቹ መልካምና ክፉ መንፈስ ነው።

ይሁዳ ሐዋርያ ነበረ (የቤተክርስቲያን መሪ፤ ስለዚህ መልካም ነበረ) ነገር ግን ገንዘብ የሚወድ ሰውም ነበር (ክፉ)። የመልካም እና ክፉ ድብልቅ ውጤቱ መርዛማ ነው።

ከዚያም እግዚአብሔረ ከአዳም መንፈስ ውስጥ የሴትነትን ባህርይ አውጥቶ ሴተቱን ለብቻዋ አካል አዘጋጀላት።

 

ስጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግስት ሊወርሱ አይችሉም

 

 

በሰውነቱ ውስጥ ደም ያለው ፍጡር ለዘላለም መኖር አይችልም።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥

ስለዚህ በመጀመሪያ በአዳም እና ሔዋን ደም ስር ውስጥ ደም አልነበረም።

በደም ስራቸው ውስጥ እየተዘዋወረ ሕያው ያደርጋቸው የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነበረ።

ዘፍጥረት 2፡23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

ደም በጭራጭም አልተጠቀሰም።

ደም ከሌለ ወሲብ አይኖም ምክንያቱም የወንድ ብልት ለወሲብ እንዲዘጋጅ ደም ያስፈልገዋል። ከዚህም የተነሳ ራቁታቸውን መሆናቸው ምንም አልታወቃቸውም።

ዘፍጥረት 2፡25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።

በመካከላቸው የወሲብ ፍላጎት አልነበረም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ አዳም እና ሚስቱ መንፈስ ነበሩ። መንፈስ ወሲብ ሊያደርግ አይችልም። ወሲብ ሊፈጸም የሚችለው በስጋዊ አካል ብቻ ነው።

ምዕራፍ 1 ውስጥ ወንድም ሴትም የነበረውን መንፈስ እግዚአብሔር እንዲበዛ እንዲባዛና ምድርን እንዲሞላ ነገረው። ይህም መንፈሳዊ የሆነ መባዛት ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ አልገባቸውም ነበር።

ስለዚህ ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር እግዚአብሔር እቅዱን እስኪፈጽም ድረስ መጠበቅ ነው። አንዳች ነገር ቢያደርጉ ስሕተት ይሰራሉ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሃሳብ ከእኛ ሃሳብ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሔርም ምን እያሰበ እንደሆነ ማወቅ አንችልም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚአብሔር በሁለት የተለያዩ ስጋዊ አካላት ውስጥ ሲያኖራቸው የእውቀት ዛፍን በተመለከተ ለአዳም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል።

የወሲብ ትርጉሙ “ስጋዊ እውቀት” ነው።

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች።

ስጋ ለለበሰችዋ ሴት እግዚአብሔር በተጨማሪ የድንግልና ሕግ ሰጣት፤ ይህም ወሲባዊ ግንኙነት የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ አለመሆኑን እንዲያውቁ በማድረግ ወሲባዊ ግንኙነት እንዳያደርጉ ምልክት ይሆናቸዋል። በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ወደሚወለዱ ልጆች ዘላለማዊ ሕይወት ሊተላለፍ አይችልም።

ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ውስጥ አዳም ስጋ ከለበሰ በኋላ ከእውቀት ዛፍ እንዳይበላ እግዚአብሔር አስጠነቀቀው። ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ አዳም መንፈስ በነበረ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት ሊፈጽም የሚችልበት አጋጣሚ አልነበረም፤ ስለዚህ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠውም። ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጻፈው ፍጥረታዊ ዛፎች ሁሉ መልካም ነበሩ። ከዛፉቹ መካከል ክፉ ወይም መብላት የተከለከለ ዛፍ አልነበረም።

ስለዚህ የእውቀት ዛፍ ፍጥረታዊ ዛፍ አልነበረም። የእውቀት ዛፍ የሰይጣን መንፈስ ነው። የሰይጣን እውቀት አደገኛና ለሞት የሚያበቃ ነው።

የወሲብ አካል ለምን ተሰጣቸው?

መልካም ሥነ ምግባር መኖር አለመኖሩ ፈተና በሌለበት ሊረጋገጥ አይችልም ምክንያቱም ጠላት በሌለበት ግጭት አይኖርም፤ ግጭትም በሌለበት ድል የለም።

መልካም ባህርይ ሊገለጥ የሚችለው ከብርቱ ጠላት ጋር ጦርነት ከተደረገ በኋላ ነው።

ትዕግስት የሚገለጠው ከቁጥጥራችን በላይ የሆነ ፈተና ውስጥ ካለፍን በኋላ ነው።

መልካም ባህርይ እንደ ስጦታ ለሰው ሊሰጥ አይችልም። መልካም ባህርይ በትግል እና በሽንፈት ውስጥ ተቀጥቅጦ ተቀርጾ ነው የሚወጣው።

ጦርነት ከሌለ ድል የለም።

እምነት ሊዳብር የሚችለው በራሳችን መፍትሄ መስጠት የማንችልበት ፈተና ውስጥ ስንገባ ነው።

 

ባህሪያችንን ለማጠንከር ጠላት ያስፈልገናል

 

 

በሰዎች አእምሮ ውስጥ ያለው የራስን ፈቃድ የማድረግ ፍላጎት የማወቅ ጉጉትን ይፈጥራል። ሁልጊዜ አዲስ ነገር ማወቅ እንፈልጋለን። ነገር ግን በተፈጥሮ አብሮን ካለው መሃይምነት የተነሳ ለእምነታችንና ለባህሪያችን መሪ ያስፈልገናል። መመሪያዎችን የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለሆነ ቃሉን መማርና ማመን ያስፈልገናል።

ቀላል ያልሆነውን መንገድ ለመምረጥ ራሳችንን ማስለመድ አለብን።

የራስን ፈቃድ የማድረግ ፍላጎት ከሰው አእምሮ ውስጥ ዋነኛው ክፍል ነው። ይህ ፍላጎት ከሌለን ሮቦት እንሆናለን።

እግዚአብሔር እኛን አስገድዶ አንድ ነገር ማስደረግ ይችላል። ነገር ግን በራሳችን ነጻ ፈቃድ የማድረግ ፍላጎት ኖሮን ስናደርገው የተሻለ ነው።

ሆኖም ከፈለግን ማድረግ የምንችለውን ሌላ ነገር የሚያስደርገን ፈተና በሌለበት አማራጭ በሌለበት ነጻ ፈቃድ ሊኖረን አይችልም።

በራሳችሁ ምርጫና ፍላጎት ታማኝ እንድትሆኑ ብፈልግ የተወሰነ ገንዘብ መስረቅ የምትችሉበት ቦታ አስቀምጬ ዞር ማለት አለብኝ። ምንም ነገር የመስረቅ ዕድል ከሌላችሁ ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን ወይም አለመሆናችሁን ላውቅ አልችልም።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ሒትለርና የቅርብ ረዳቶቹ ከምድር በታች ተቆፍሮ የተዘጋጀ መጠለያ ውስጥ ነበሩ። እርሱም ረዳቶቹ ሲጋራ እንዳያጨሱ ከለከላቸው። ስለዚህ ሲጋራ ቢኖራቸውም እንኳ አላጨሱም። ሒትለር ሁሉም ሲጋራ ማጨስ ያቆሙ መሰለውና ባወጣው ሕግ ተደሰተ። ሒትለር ሲሞት መጀመሪያ ያደረጉት ነገር ሲጋራቸውን አውጥተው ማጨስ ነው። ስለዚህ ማጨስ ያቆሙ ይመስሉ ነበር እንጂ አላቆሙም።

ሰዎች እግዚአብሔርን የእውነት ሳይታዘዙ የታዘዙ መስሏቸው እንዲታለሉ እግዚአብሔር አይፈልግም። እግዚአብሔር የሚፈልገው ከልባቸው ፈልገው ደስ ብሏቸው እንዲታዘዙ ነው።

የእውነት ምን ማድረግ እንደፈለጋችሁ ማወቅ የምትችሉት የተሻለና ይበልጥ ደስ የሚልና አጓጊ አማራጭ አግኝታችሁ እምቢ ማለት ስትችሉ ነው። እግዚአብሔር ለአዳምና ሔዋን የወሲብ አካል በመስጠት ከፈለጉ እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ የሚፈታተናቸውን አማራጭ ሰጥቷቸዋል።

 

በወሲባዊ ግንኙነት መዋለድ ብዙ ችግሮች ያስከትላል

 

 

በምድራችን ላይ ከሚፈጸሙ ሐጥያቶች ሁሉ በቁጥር አንደኛው ወሲባዊ ሐጥያት ሊሆን ይችላል።

ወሲባዊ ሐጥያት ብዙ ሰዎች ሊከተሉ የሚፈልጉት የተሳሳተ መንገድ ነው። በዚህም መንገድ ሰዎች ከልባቸው እግዚአብሔርን መከተል የማይፈልጉ ከሆኑ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር እቅድ ያርቃሉ።

እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት እንዲዋለዱ ፈለገ ብለን እናስብ።

በወሲብ የሚወለዱት ልጆች ዘላለማዊ ሕይወት አይኖራቸውም። ወላጆች ለልጆቻቸው ዘላለማዊ ሕይወት ማካፈል አይችሉም።

አዳም ከ900 ዓመታት በላይ ኖረና ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ስለዚህ ስንት ልጆች ይወለዳሉ? ብዙ። በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ልጆቹ አይሞቱም። ከዚያም ምድር በሕዝብ ብዛት እስክትጨናነቅ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? ብዙ ጊዜ አይፈጅም።

ይህም ዓይነቱ መንገድ ለዘላለም መቀጠል የሚችል አይደለም። ይህ ወደ ዘላለማዊነት የሚደረስበት መንገድ አይደለም።

እግዚአብሔር የቤተሰብን ቁጥር ቢገድብ ሰዎች እንደፈለጉ ብዙ ልጅ የመውለድ ነጻ ፈቃዳቸውን እየነጠቃቸው ነው። እግዚአብሔር ግን ሰዎች ነጻ ፈቃድ እንዲኖራቸው ፈልጓል።

የአባለ ዘር በሽታዎች በሰዎች መካከል ብዙ ቀውስ አስከትለዋል። ከነዚህ ውስጥ ለምሳሌ እንደ ኤድስ ያሉት በሽታዎች ሊድኑ የማይችሉ ናቸው።

አስገድዶ መድፈር፣ ዝሙት፣ መዳራት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ሴቶችን ማማገጥ፣ እርኩሰት፣ ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት መጋባት፣ ሕጻናትን ማማገጥ ከወሲባዊ ግንኙነትና ከነጻ ፈቃድ የተነሳ የመጡና ምድርን የወረሩ ሐጥያቶች ናቸው።

ስለዚህ በወሲባዊ ግንኙነት ጥሩ የመራቢያ ስርዓት አይደለም።

እግዚአብሔር ከመጀመሪያው የተሻለ መንገድ አዘጋጅቶ ነበር።

እግዚአብሔር አዳምንና ሔዋንን በስጋዊ አካል ውስጥ ሲያኖራቸው ልክ እንደ ዮሴፍና እንደ ማርያም እንዲሆኑ ነበር የፈለገው። ዮሴፍና ማርያም እግዚአብሔርን ከመጠበቅ በቀር ምንም ማድረግ የሚችሉት ነገር አልነበረም። መጀመሪያ መንቀሳቀስ ያለበት እግዚአብሔር ነው።

አዳምና ሚስቱ የኤድን ገነት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ሔዋንን ይጋርዳትና እርሷም በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልድ ነበር፤ በድንግልና የሚወለደውም ሕጻን ከሔዋን ስጋዊ አካል አንዳችም ነገር ሳይካፈል በማሕጸኗ ውስጥ ይፈጠር ነበር። እርሷም ለሚወለደው ሕጻን ማሕጸኗን እስኪወለድ ድረስ ማቆያ አድርጋ ታገለግል ነበር።

ዕብራውያን 10፡5 … ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

መኃልየ መኃልይ 4፡12 እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።

ገነት ወይም የአትክልት ስፍራ የሴቲቱ ተምሳሌት ነው። በአትክልት ስፍራ ዙርያ ለጥበቃ አጥር ይታጠራል። ሴቶች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። የዘላለማዊ ሕይወት ምንጭ ሊፈልቅ የሚችለው በድንግልናዋ ከተጠበቀ ማሕጸን ብቻ ነው።

ዘፍጥረት 2፡9 … በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

የኤድን ገነት የሴቲቱ ምሳሌ ነው። የገነት መካከለኛ ስፍራ የሴቲቱ አካል መካከለኛ ስፍራ ነው። እርሱም ማሕጸኗ ያለበት ቦታ ነው። በድንግልና በመውለድ ዘላለማዊ ሕይወትን ልትወልድ ትችላለች። ወይ ደግሞ መልካምም ክፉም ባህርይ ያለው ፍጥረታዊ ሕይወትን ልትወልድ ትችላለች፤ ይህም የሚሞት ሕይወት ነው።

መልካም እና ክፉ። ዛሬ መልካምም ክፉም ተብለው ሊጠሩ የሚችሉ ድርጊቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ወሲብ ግን ሁለቱንም ሊባል ይችላል። ወሲባዊ ግንኙነት የእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ቢሆንም በጋብቻ ውስጥ መልካም ነው፤ ከጋብቻ ውጭ ግን በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ክፉ ነው።

እግዚአብሔርና ሰይጣን የሴቲቱን ማሕጸን ለማግኘት ይፎካከሩ ነበር።

እግዚአብሔር እንደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ሆኖ በሰማይ ሉሲፈርን ተዋጋው፤ ከዚያ በኋላ ረገመውና ዲያብሎስ እንዲሆን አደረገው።

የኤድን ገነት ውስጥ እግዚአብሔር ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ ከፍተኛው እንስሳ የነበረውን ማሰብና መናገር ይችል የነበረውን እባቡን ረገመውና በደረቱ የሚሳብ ባለ መንታ ምላስ። ውሸታሞች እስከ ዛሬ ድረስ መንታ ምላስ ይባላሉ። እባብ እስከ ዛሬ ድረስ አፉ ውስጥ መርዝ አለው። ለሔዋን የነገራት ውሸት መርዛማ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ ሰይጣን እንስሳ እንዲናገር አላደረገም። እባቡ ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ ታላቅ ስለነበረ መናገር ይችል ነበር።

 

ሔዋን ኢየሱስን በድንግልና እንድትወልድ ነበር የታሰበላት

 

 

የእግዚአብሔርም ሙላት በእርሱ ውስጥ ይሆናል።

ኢሳይያስ 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

በዕድሜ አድጎ ትልቅ ሰው ይሆናል ነገር ግን ሐጥያት በምድር ላይ ስለማይኖር መሞት አያስፈልገውም ነበር።

ከዚያም ኢየሱስ ቅዱሳኑን በቃሉ ተናግሮ ከምድር አፈር ይፈጥራቸው ነበር። ወደፊት በትንሳኤ ጊዜ ሲመጣ እንደዚሁ ነው የሚያደርገው። ከምድር አፈር ቢፈጥራቸው ኖሮ ምድርን ለመሙላት የሚበቃ ሕዝብ ብቻ ይፈጠር ነበር። ሲኦል ገብተው የሚቃጠሉ ሰዎች አይኖሩም ነበር። የመጀመሪያው እቅድ ይህ ነበረ።

ነገር ግን ባህርይ፣ ስነ ምግባር፣ ትዕግስት አዲስ ሆነው ለተፈጠሩ ሰዎች ችግር ይሆንባቸዋል። በተጨማሪ በትዕቢት እና በራስ ወዳድነትም ይቸገራሉ።

ኋላ ስናስበው ግን ሐጥያተኛ ሆነን መወለዳችንና በሐጥያት ይቅርታ አማካኝነት የእግዚአብሔርን ፍቅርና ጸጋ ማየታችን ለበጎ ነው። በእጆቹ ላይ ያሉት ጠባሳዎች ስለ እኛ የከፈለውን ዋጋ ለዘላለም ያስታውሱናል። የሚያድነን መፈለጋችን ትዕቢተኞች እንዳንሆን ያደርገናል። ሐጥያተኞች እና ክፉዎች መሆናችንን ስናውቅ እንዲሁም ዕጣ ፈንታችን ሲኦል እንደነበረ ስናስብ ሐጥያት ለማድረግ ያለን ፍላጎት ሁሉ ይጠፋል። ሐጥያት የሌለበትን ዓለም እንድንመኝ የሐጥያትን አስከፊነትና በሐጥያት የተነሳ የሚመጡ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ማየት አስፈልጎናል። እኛ ራሳችን ሐጥያተኞች የነበርንና ይቅር የተባልን ሰዎች መሆናችንን ማወቅ ሌሎች ላይ እንዳንፈርድ ይረዳናል፤ ስለዚህ ለሌሎች ሰዎች እንድናዝንና እንድናስባቸው ይረዳናል።

ችግርና መከራ ተስፋችን በኢየሱስ ላይ ብቻ እስኪሆን ድረስ እምነታችንን ያጠነክሩታል፤ ከዚያ ወዲያ በራሳችንም ይሁን በሌላ ሰው አናምንም።

 

እባቡ የሔዋንን ድንግልና ሲወስድ ሔዋን ደም ፈሰሳት

 

 

የሔዋንን ቅጣት ተመልከቱ።

እግዚአብሔር ለሔዋን፡- “ይህን ስላደረግሽ …” አላላትም።

እግዚአብሔር ሔዋንን ለመቅጣት ምንም ምክንያት አላቀረበም። ሔዋን ስሕተት መስራቷን እስከማታውቅ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተታልላለች። (ዛሬም የቤተክርስቲያን ሰዎች ሔዋን የሰራችው ስሕተት ምን እንደሆነ አያውቁም። የዛፍ ፍሬ በላች ይላሉ። እግዚአብሔር ግን የቀጣት ስላረገዘች ነው። ስለዚህ ዛሬም ቤተክርስቲያን ልክ እንደ ሔዋን የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደሆነ አታውቅም።)

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤

ሔዋን የተቀጣችው ስለ ጸነሰች ነው።

ጽንሱም ደግሞ ከባሏ ሊሆን አይችልም።

እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሉዋት ብሎ ሲያዝዛቸው በወሲባዊ ግንኙነት መስሏታል። ይህ ትዕዛዝ ሊፈጸም የሚችልበት ሌላ መንገድ አልታያትም።

ሰይጣን ማለትም የእውቀት ዛፍ ወይም መንፈስ ማሕጸኗን ተጠቅሞ ሐጥያተኛ ሕይወት እንዲወለድ ሊያደርግ እንደሚችል አላወቀችም። ወይም ደግሞ ማሕጸኗን እግዚአብሔር ማለትም የሕይወት ዛፍ ተተቅሞበት በድንግልና ወንድ ልጅ እንድትወልድ ሊያደርጋት እንደሚችልም አላወቀችም።

ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።

እግዚአብሔር ለእባቡ የሰራው ሐጥያት ምን እንደሆነ ነገረው። እግዚአብሔር እባቡን ረገመውና ታላቅ የነበረውን እስሳ በደረቱ የሚሳብ እግር አልባ አደረገው። የተረገመው በደረቱ ተኝቶ እንዲሄድ ነው። ስለዚህ የሰራው ሐጥያት ሔዋን ላይ በደረቱ ተኝቶ ሔዋንን ወሲብ ማስተማር ነበረ።

ሔዋን እባቡን ማመን ስትጀምር የእግዚአብሔር መንፈስ ትቷት ሄደ።

የእግዚአብሔር መንፈስ ከሐጥያት እና ከአለማመን ጋር አብሮ አይኖርም።

የእግዚአብሔር መንፈስ ትቷት ሲሄድ እግዚአብሔር ደም ስሯ ውስጥ ደም ሞላላት።

እባቡ ተረግሞ በደረቱ የሚሳብ እንስሳ ወደመሆን ከመለወጡ በፊት ሔዋንን አስረገዛት።

ሰው በሐጥያት የወደቀው በዚህ መንገድ ነበር።

ከዚያ ወዲያ ሔዋን እግዚአብሔር ሊጠቀምበት የሚችለው ድንግል ማሕጸን አልነበራትም።

ስለዚህ የመጀመሪያው ሐጥያት እንስሳ የሰውን ደም ማፍሰሱ ነው።

ከዚህም የተነሳ ለሐጥያት ማስተሰርያ እንዲሆን እግዚአብሔር የእንስሳ ደም ተቀበለ።

ሔዋን እንድትሞት ተፈረደባት።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤

ሔዋን ጸነሰች። አረገዘች። አዳም ባሏ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከአዳም አረገዝሽ ብሎ ሊቀጣት አይችልም።

ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ብሎ ነበር። ይህም ማለት ኢየሱስ በድንግልና ተወልዶ ሲያድግ ምድርን ለመሙላት በቁጥር በቂ የሆኑ ቅዱሳንን ከምድር አፈር ላይ ጠርቶ እንዲፈጥራቸው ነበረ። የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ይህ ነበር።

እግዚአብሔርም ከዚያ ወዲያ “በወሲብ እጅግ እንዲባዙ” አለ። በጣም ብዙ እንዲወልዱ ተናገረ። ጻድቃንም ክፉዎችም በወሲብ እና በነጻ ፈቃድ አማካኝነት ይወለዳሉ። ነገር ግን ወሲብ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ሳይሆን የይሁንታ ፈቃድ መሆኑን ለማሳየት እረግዝና እና ወሊድ አስጨናቂ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ወሲብን የሚፈቅደው በአንድ ሰው እና ባገባት ሴት መካከል ብቻ ነው። ሰይጣን ግን ሰዎች ይህንን ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፉ ያደርጋል።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።

ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እንደ ንጽሕት ድንግል እንድትሆንለት ይፈልጋል። ሔዋን እባቡ ከእርሷ ጋር ወሲብ ከፈጸመ በኋላ ንጽሕት ድንግል አልነበረችም።

እባቡ ሔዋንን አሞኛት ወይም አታለላት። ይህም ውርደት በሴቶች ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ይታያል፤ ምክንያቱም ሴቶች ላም ሲባሉ ወይም በሆነ እንስሳ ስም ሲጠሩዋቸው ይናደዳሉ።

አዳም አልተታለለም። ስለዚህ ወንዶችን ኮርማ ብትሏቸው እንደ አድናቆት ይቀበሉታል። መርከበኞች ራሳቸውን የባህር ውሻ ብለው ይጠራሉ። ወንድ በእንስሳ አልተታለለም፤ ሰለዚህ በየትኛውም እንስሳ ስም ሲጠሩት አይናደድም።

1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤

አዳም ሚስቱ ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ከእባቡ በመማር ሐጥያት መስራቷን አውቋል። ነገር ግን በጣም ስለሚወዳት ከእርሷ ጋር እርሱም አብሮ ሐጥያት ሰራ፤ ይህን ያደረገው እግዚአብሔር የማዳን እቅድ ይኖረዋል ብሎ በማመን ነው።

አዳም ከሚስቱ ላለመለየት ብሎ እያወቀ ሐጥያት ሰራ። አዳም በሐጥያት የወደቀው ለሚስቱ ስላለው ፍቅር ብሎ ነው። እስካሁን ድረስ “በፍቅር ስለመውደቅ” እናወራለን።

በሐጥያታችን ሳለን ኢየሱስ አይቶን ሐጥያታችንን ወስዶ ስለ እኛ ሐጥያት ሆነ። ከሙሽራይቱ ጋር መሆን እና ሙሽራይቱን ከሐጥያት ማዳን የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነበር። ለእኛ ያለው ፍቅር ይህን ያህል ነው።

 

የእባቡ ዘር የወንድ የዘር ፍሬ ነው ወይም እስፐርም ነው

 

 

እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን በኤድን ገነት ውስጥ ንሰሃ እንዲገቡ አልጠየቃቸውም ምክንያቱም ሔዋን ሊሰተካከል የማይችል ስሕተት ወይም ሐጥያት ነው የሰራችው። እግዚአብሔር ልጁ የሚወለድበት ድንግል ማሕጸን ፈልጓል። ሔዋን ከዚያ ወዲያ ድንግል አልነበረችም ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ ድንግልና ሊመልሳት አልቻለም። ስለዚህ እግዚአብሔር በማርያም እምነት አማካኝነት ቃሉ እስኪፈጸም ድረስ 4,000 ዓመታት ጠበቀ።

ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።

የእባቡ ዘር የወንድ የዘር ፈሳሽ ወይም እስፐርም ነው። ልክ እባብ ይመስላል።

 

 

የሰው ልጆች በሙሉ በዚሁ መንገድ ይወለዳሉ። ስለዚህ በሐጥያት ነው የተወለድነው። ያለ ሐጥያት የተወለደ ብቸኛው ሰው በድንግልና የተወለደው ኢየሱስ ነው።

ፍልሚያው የተካሄደው ቀራንዮ ላይ ነው።

በድንግልና የተወለደው መሲህ እጅግ ብዙ በሆኑ በወሲብ በተወለዱ ሰዎች ውግያ ገጠመው።

57-0915 ዕብራውያን ምዕራፍ ሰባት - 1

እግዚአብሔር ከአዳም ጎን አጥንት ወስዶ ሴቲቱን ሰራት። አይደል? ከዚያም ሴቲቱ ደግሞ በወሲባዊ ግንኙነት ወንድን ወለደች።

62-0211 አንድነት

በፍጹም የዛፍ ፍሬ አልነበረም! ራቁቷን መሆኗን እንዴት ልታውቅ ቻለች? ይህን በደምብ አይተናል። ጉዳዩ ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነው።

63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ

ሕጉ እንዲቤዥ የሚፈቅደው ለስጋ ዘመድ ነው፤ በምድር ላይ ደግሞ ሁሉም ሰው ከወሲባዊ ግንኙነት ነው የተወለደው።

አሁን አልገባችሁም ወይ፤ ሐጥያት የተጀመረው በዚህ ነው። አሁን የት እንደደረሰ ይታያችኋል? የእባቡ ዘር የመጣው በዚህ መንገድ ነው። ገባችሁ?

ከወሲባዊ ግንኙነት ጋር ተያይዞ ከመጣ ሞት ለመዳን በወሲባዊ ግንኙነት ያልተወለደ የስጋ ዘመድ ያስፈልገናል።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤

“ጭንቅሽን አበዛለሁ?” እንዲበዙ እንዲዋለዱ ከተነገራቸው በኋላ ይህ እንግዳ ንግግር ይመስላል።

እርሷ ግን እግዚአብሔር ባለፈቀደው መንገድ ወለደች።

በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አንድ ጽንስ ብቻ መጸነስ ነበረባት። ከዚህም ጽንስ የሚወለደው ሕጻን አድጎ ሰዎችን ሁሉ በቃሉ ንግግር ከምድር አፈር ይፈጥራቸው ነበር።

እርሷ ግን ከእባቡ ጸንሳ በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። አረገዘች።

ስለዚህ እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነቱን ጽንስ እንደሚያበዛው ተናገረ። ሰዎችም የሚወለዱት በዚህ መንገድ ነው። ሔዋንም በወሲብ አማካኝነት መውለድ ስሕተት መሆኑን ታውቀው ዘንድ ስትወልድ ጭንቅ ይበዛባታል።

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።

ከአዳም አንድ ጊዜ ጸነሰች ግን ሁለት መንታ ልጆች በአንዴ ወለደች።

የኤድን ገነት ውስጥ የጸነሰችው ጽንስስ? ያ ጽንስ ከአዳም አልነበረም።

ቃይንን ከእግዚአብሔር አገኘሁ በማለት ከማን እንደተወለደ ሸፋፈነችለት። ሕይወት ሁሉ ምንጩ እግዚአብሔር በመሆኑ ከእግዚአብሔር ማለቷ እውነት ነው። ነገር ግን ቃየንን ከአዳም ወለድኩ ያላለችው ለምንድነው?

ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።

ምግብ ስለትበሉ ምግቡ ወደ ሆዳችሁ ነው የሚገባው። ወሲብ እርግዝናን ያስከትላል፤ እርግዝናም ሆድን ያሳብጣል። ስለዚህ መብላት የወሲብ ተምሳሌት ነው።

በእንግሊዝኛ ፈሊጥ አንዲት ሴት በእርግዝና “ወደቀች” ይላሉ። ለምን? ምክንያቱም ውድቀት የመጣው በመጀመሪያው እርግዝና ነው። ቃየን የሰውና የእባብ ዲቃላ ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ አልነበረም።

ቃየን መጽሐፈ ዜና ውስጥ የአዳም የበኩር ልጅ ተብሎ አልተመዘገበም።

የመጀመሪያው ውሸታምና ነፍሰ ገዳይ ቃየን ነው። እባቡ ከሰው በታች ከዝንጀሮ በላይ በነበረ ጊዜ በውስጡ ያደረው የሰይጣን ባህርይ ውሸታምነትና ነፍሰ ገዳይነት ነበረ።

ስለዚህ የእውቀት ዛፍ እስከ ዛሬ ድረስ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የተወለዱ ሰዎች መንፈስ ነው።

ከዚህም የተነሳ በአንድ ቀን ውስጥ የሞት ፍርድ ሊፈረድብን ይገባናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን አንድ ሺ ዓመት ነው። ማቱሳላ 969 ዓመታት ኖረ። ከሴት የተወለደ አንድም ሰው 1,000 ዓመታት ኖሮ አያውቀም።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

 

እምብርት በሰውነታችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው

 

 

የፈለገውን ያህል ጥበብ ቢኖረን በሰውነታቸን ላይ የሚገኘው እምብርት እንደምንሞት የሚያመለክተን ጠባሳ ነው።

ከዚያም መቃብር እንገባለን። አፈርን ስትቆፍሩት ላዩ ላይ ጠባሳ ይቀራል። አፈሩ ከቆፈራችሁት በኋላ ተመልሶ እንደነበረ አይሆንም።

ብቸኛው ተስፋችን በድንግልና የተወለደ አዳኝ ነው። እርሱ ብቻ ነው ከመጀመሪያው ሐጥያት ነጻ የሆነው። ከዚህም የተነሳ የሕይወት ዛፍ ኢየሱስ መሆኑን እናውቃለን። በእርሱ እኛ ከስጋ ሳይሆን ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም እንወለዳለን።

ከ4,000 ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር የማርያምን ማሕጸን ተጠቅሞ ወንድ ልጅ በድንግልና እንዲወለድ አደረገ።

ኤልሳቤጥ ማርያምን እንዲህ አለቻት፡-

ሉቃስ 1፡42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ የሕይወት ዛፍ ነው።

ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት እንዳለው ለማሳየት ስለ እኛ በፈቃዱ ሞተና በትንሳኤ ከሙታን ተነሳ።

ሌሎቻችን ከእውቀት ዛፍ ስለተወለድን እስከ ዛሬ ድረስ እንሞታለን። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛችን አድርገን ካልተቀበልን በቀር ከመቃብር መነሳት አንችልም።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23