ዘፍጥረት 46 - ጥቂት በተጻፈበት ብዙ ማየት



ወደ ግብጽ የሄዱ አይሁዶች 66 ነበሩ ወይስ 70 ወይስ 75? ሳይቆጠሩ ከቀሩት በጣም ጠቃሚ ትምሕርት መማር እንችላለን። ለምንድነው ያልተቆጠሩት?

First published on the 5th of October 2022 — Last updated on the 5th of October 2022

 

መጽሐፍ ቅዱስ ተደጋጋሚ የሚመስሉ ታሪኮች አሉት

 

አባቶች ለብሉይ ኪዳን አይሁዶች ጠንካራ መሰረት ናቸው፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ አባቶች የመንፈሳዊ ሚስጥር ምሳሌዎች ናቸው፡- አብርሃም (እምነት)፣ ይስሐቅ (ፍቅር)፣ ያዕቆብ (ጸጋ፤ ምክንያቱም ጠማማ የነበረው ሰው ተለውጦ የእግዚአብሔር ጀግና ሆነ)፣ ዮሴፍ (ፍጹምነት ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ውስጥ ዮሴፍ የኢየሱስ ሕይወት ነጸብራቅ ነው)። እግዚአብሔር በነብያት አመራር አማካኝነት የአይሁድን ሕዝብ በዚህ መሰረት ላይ መሰረተ፤ ነብያትም እንደ ሃውልት ሲሆኑ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ እንደ አንገታቸው ነበር። እነዚህ ሁሉ ራስ የሚሆናቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይጠባበቁ ነበር። ዮሐንስ አንገቱ በተቆረጠ ጊዜ እሬሳው ከአንገቱ በላይ ራስ ስላልነበረው የአይሁድ ሕዝብ በዚያ ሰዓት ራስ እንዳልነበረው ያሳያል። በዚያ ሰዓት የሚያስፈልጋቸው ራስ ነበረ፤ እርሱም ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ለ7 ዓመታት አገልግሎ የ1,000 ዓመት የሰላም መንግስት ሊመሰርትና በዚህም መንግስት ውስጥ አይሁዶች ዓለምን እንዲገዙ ለማድረግ ነበር የመጣው።

ነገር ግን የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን እንቀበልም በማለታቸው ታሪካቸው ለጊዜው ተቋረጠ።

ነኅምያ በ446 ዓመተ ዓለም የፈረሰውን የኢየሩሳሌም ቅጥር በ52 ቀናት እንዲያድስ ትዕዛዝ በተሰጠው ጊዜ እግዚአብሔር ዘመኑን መቁጠር ጀመረ። ኢየሱስ የ7 ዓመት አገልግሎቱን ለመጀመር በ29 ዓ.ም ማለቂያ አካባቢ ነበር የተጠመቀው፤ ይህም ሰባት ዓመት በ37 ዓ.ም ይጠናቀቅ ነበር።

 

 

ስለዚህ በአገልግሎት ዘመኑ አጋማሽ ላይ ኢየሱስን ገደሉት። ከዚያም እግዚአብሔር ለ2,000 ዓመታት ወደ አሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘወር አለ፤ ነገር ግን ለአይሁዶች ይቀራቸው የነበረውን 3½ ዓመታት አልተወውም፤ እነዚህም ቀሪ ዓመታት በ3½ ታላቅ መከራ ይጠናቀቃሉ።

እግዚአብሔር ለአይሁዶች እያንዳንዳቸው 360 ቀናት ያሏቸው 490 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ሊሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል (አሁን እኛ በምንቆጥረው ባለ 365.24 ቀናት ዓመት መሰረት 483 ዓመታት ማለት ነው)። የ1,000 ዓመቱ የሰላም መንግስትም በ37 ዓ.ም ይጀምር ነበር ማለት ነው።

2,000 ዓመታት ባስቆጠረው በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ዘኖች ነበሩ። ዲኖሚኔሽናዊው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያን ድርጅት እያደገ ሲሄድ አንድን ሰው የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ በመሾም ይተዳደር ነበር። ይህም ሐሰተኛ ዘር ነው። አንድን ቄስ አንድ አጥቢያ እንዲያስተዳድር እየሾሙ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን አደረጉ። ከዚያ ጳጳስ ደግሞ አንድ ከተማ እንዲያስተዳድር አደረጉ። ከጳጳሱ በላይ ሊቀ ጳጳስ፣ ካርዲናል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁሉንም ብቻውን የሚመራ ፖፕ።

እውነተኛው ዘር በየሰው ቤት ውስጥ የሚሰበሰቡት ትንንሽ የቤተክርስቲያን ሕብረቶች ነበሩ፤ እነዚህም የሚተዳደሩት በሽግሌዎች ሕብረት እንጂ በአንድ ግለሰብ አልነበረም። ብዙውን ጊዜ ታዋቂ አልነበሩም። የሚያምኑትም ሐዋርያት በጻፉት የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ብቻ ነው።

ዋነኛው ትኩረታቸው የነበረው ከበዓለ ሃምሳ ቀን ጀምሮ ሐዋርያት ወደ መሰረቷት ቤተክርስያን የመጀመሪያ እምነት መመለስ ነው።

እግዚአብሔር ለሰርጉ የእራት ግብዣ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ሲነጥቃት የዚያን ጊዜ ወንጌል ወደ አይሁዶች ይመለሳል፤ ከዚያም የተነሳ 144,000ዎቹ አይሁዶች በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ ዳግመኛ ይወለዱና በመንፈስ ቅዱስ ይሞላሉ።

ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆችና 51 የልጅ ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዘፍጥረት ምዕራፍ 46 ውስጥ ተጠቅሰዋል። አንድ ሴት ልጅ (ዲና) እና አነድ ሴት የልጅ ልጅ (ሤራሕ) ብቻ በስም ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ያዕቆብ በስም ያልተጠቀሱ ብዙ ሴቶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 37፡35 ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፤ መጽናናትን እንቢ አለ፥

አንዲት ሴት ልጅ በልጆች ዝርዝር ውስጥ ተጽፋለች ግን ስሟ አልተጠቀሰም።

አራት የልጅ ልጆች በዝርዝር ውስጥ በተጨማሪ ተጠቅሰዋል። ከዲና፣ ከሤራሕ፣ እና በስም ካልተጠቀሰችዋ ሴት ልጅ በቀር ሌሎቹ በልጆች ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ስለዚህ በነዚህ ተጨማሪ ልጆች እና በልጆች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ በቀሩት ልጆች አማካኝነት እግዚአብሔር ምን እየነገረን ነው።

 

እግዚአብሔር ሳይናገር በተወው ነገር አማካኝነት ጥልቅ የሆኑ ሃሳቦችን መግለጽ ይችላል

 

 

ከዚህ በታች የሌሊቱ ሰዓት ያልተጠቀሰበትን ቃል ተመልከቱ።

ዘፍጥረት 1፡5 … ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።

የማታው ብርሃን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት የሚገልጠው የዘመን መጨረሻ መልእክት ነው። ጠዋቱ ደግሞ ክርስቶስ መንግስቱን የሚመሰርትበት የ1,000 ዓመቱ መጀመሪያ ነው። ሌሊቱ ሳይጠቀስ የቀረው ለምንድነው? ምክንያቱም በዘመን መጨረሻ የምትገኘው ሙሽራ ለሰርጉ የእራት ግብዣ ወደ ሰማይ ትሄዳለች። ሙሽራይቱ ወደ 3.5 ዓመቱ የታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ አትገባም፤ ይህ የመከራ ዘመን የተመሰለው በሌሊቱ ጨለማ (ብርሃን አልባነት) ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ሌሊቱን አለመጥቀሱ ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ እንደማታልፍ መናገሩ ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይናገር ካለፈው ነገር ውስጥ ትልቅ ትምሕርት መማር እንችላለን።

ኢሳይያስ 45፡4 ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።

ያዕቆብ (በቁልምጫ ስሙ እስራኤል ተብሎ የተጠራው) ወደ ግብጽ መውረዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ እንደ ሕዝብ የእስራኤልን ጅማሬ ያሳየናል፤ እንዲሁም ወደፊት ስለምትመጣዋ ቤተክርስቲያንም ፍንጭ ይሰጠናል። ከእስራኤል በፊት እግዚአብሔር የሚሰራው ከግለሰቦች ጋር ነበረ፤ እነዚህም አዳም፣ ሴት፣ ሄኖክ፣ ኖኅ፣ አብርሐም፣ ይስሐቅ፣ እና ያዕቆብ ናቸው። ያዕቆብ ግን ልዩ ጥሪ ነበረው። የአይሁድ ሕዝብ የተጀመረው በእርሱ ነው። ኋላ ከአይሁዶች ደግሞ ቤተክርስቲያን ትወጣለች። ስለዚህ ወደፊት ሊሆን ያለው ነገር ሁሉ ፍንጩ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል።

ዘፍጥረት 46፡1 እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ መጣ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።

ቤርሳቤህ ማለት “የመሃላ ጉድጓድ” ወይም “የሰባት ጉድጓድ” ማለት ነው።

መሃላ ማለት በቃል የተነገረው ነገር ይፈጸማል ማለት ነው።

እግዚአብሔር ያዘጋጀው እቅድ አለ፤ ይህም እቅድ ይፈጸማል። ቤርሳቤህ በሚለው ስም ውስጥ 7 ቁጥር አለበት፤ ይህም ወደፊት የሚመጡትን 7 የቤተክርስቲያን ዘመናት ያመለክታል። ይስሐቅ ከርብቃ ጋር በነበር ውብ የፍቅር ታሪክ የተነሳ ታዋቂ ነው፤ ይህም ወደፊት በኢየሱስ እና ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በምትወጣው በሙሽራይቱ መካከል የሚኖረውን ፍቅር ያመለክታል።

 

ዘፍጥረት 46፡2 እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ።

“እነሆኝ” ማለት እግዚአብሔር ነው። ያዕቆብ በጣም ተጠንቅቆ ነው “እነሆኝ” የሚለው።

በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔርን ስፍራ ማንም አይወስደውም ማለቱ ነው።

“ያዕቆብ ያዕቆብ” ማለት ድግግሞሽ ነው። ወደ ግብጽ የተደረገው ጉዞ አይሁዶች በብሉይ ኪዳን ዘመን የኖሩትን ኑሮ ይገልጻል። በተጨማሪ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ስለምትኖረዋ የእግዚአብሔር ሙሽራ ይገልጽልናል።

ዘፍጥረት 46፡3 አለውም፦ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።

አባቱ ይስሐቅ ነበር፤ ይስሐቅም በመልእክተኛ-አገልጋይ አማካኝነት ተፈልጋ ወደ ማታ አካባቢ ከተገኘችዋ ርብቃ ጋር ከነበረው የፍቅር ታሪክ የተነሳ ታዋቂ ነው።

ርብቃ መልእክተኛውን-አገልጋይ አዳመጠች፤ ግን ፍቅር የያዛት ከይስሐቅ ጋር እንጂ ከአገልጋዩ ጋር አይደለም።

ይህም ተምሳሌት ክርስቶስ ዊልያም ብራንሐምን ወደ ማታ አካባቢ እንደተላከ አገልጋይ ተጠቅሞ የተሰወሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በመግለጥ ሙሽራይቱን እንደሚያወጣት ያሳያል። የእውነተኛይቱ ሙሽራ አካላት መጽሐፍ ቅዱስን ከመውደዳቸው የተነሳ በመጨረሻው ዘመን የተገለጠውን እውነት ከልብ ይቀበሉታል።

የሚቀርቡት ወደ ክርስቶስ ማለትም ወደተገለጠው ቃል እንጂ ወደ ሰው አይደለም።

65-0429 ሙሽራ መምረጥ

እውነተኛዋ ሙሽራ ቃሉን በመጠበቅ ነው የእግዚአብሔርን ትኩረት የምትስበው።

ያዕቆብ ቁልፍ ቦታ ነው ያለው። ማሕበራዊ ሁኔታዎች እየተለወጡ ነበር። እግዚአብሔር የመረጠውን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ማስነሳት የጀመረበት ጊዜ ነበር። ይህም ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም አለው። ይህ ሕዝብ በብሉይ ኪዳን ዘመን ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ስርዓቶች እና በትንቢት ላይ የተመሰረተ ሕዝብ ነው። እግዚአብሔርም ስራውን ከግለሰቦች ጋር ከመስራት አልፎ ከሕዝብ ጋር መስራት ጀመረ።

ዘፍጥረት 46፡4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።

ግብጽ የዓለማዊነት ተምሳሌት እንደመሆኗ ወደ ግብጽ መውረድ ወደ ኋላ መሄድ ይመስል ነበር። እግዚአብሔር ግን መልሶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊያመጣቸው አቅዷል።

ቤተክርስቲያንም በዚሁ ዓይነት መንገድ ነው የምትሄደው። በኒቅያ ጉባኤ አማካኘነት ስላሴ የሚባል ትምሕርት በመጣ ጊዜ ቤተክርስቲያን እውነት ጠፋባት፤ ከዚያ በኋላ በጨለማው ዘመን ውስጥ ወደ ዓለማዊነት ገባች። እግዚአብሔር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን እስኪገለጥ ድረስ ቤተክርስቲያንን በተሃድሶ መሪዎች አማካኝነት ወደ መንፈሳዊነት ይመልሳታል።

የኢየሱስ ተምሳሌት የሆነው ዮሴፍ ያዕቆብ ሲሞት ተገኝቶ የያዕቆብን “ዓይኖች ይከድናቸዋል”።

ይህም ኢየሱስ እንዴት የሞትን መውጊያ ማለትም ሐጥያትን በቀራንዮ እንደሚያስወግድና የሞትን ኃይል እንደሚሰብር ያሳያል። ስለዚህ ንሰሃ የገቡ ክርስቲያኖች በሙሉ ሲሞቱ በሰላም ዓይናቸውን መክደን ይችላሉ ምክንያቱም የመዳናቸውን ዋጋ ኢየሱስ ከፍሎላቸዋል።

 

ዘር የእግዚአብሔር ቃል ተምሳሌት ነው

 

 

ዘፍጥረት 46፡5 ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውን ሴቶቻቸውንም ወሰዱ።

ስለዚህ ቤተሰቡ በሙሉ በግብጻውያን ሰረገሎች ወደ ግብጽ ወረዱ።

ዘፍጥረት 46፡6 እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

አዲስ ኪዳን ውስጥ የሕይወት ዘር ቤተክርስቲያን ዳግመኛ እንድትወለድ የሚያደርጋት የእግዚአብር ቃል ነው። የእግዚአብሔር ቃል ዘር በክርስቶስ ውስጥ ነው። ከክርስቶስም ቤተክርስቲያን ዳግመኛ ትወለዳለች።

የብሉይ ኪዳን የአይሁድ ሕዝብ ከያዕቆብ ዘር ነው የተወለዱት።

ዘር የሚለው ቃል ወንዶች ልጆችንና የልጅ ልጆችን ይወክላል (እንዲሁም 4 ተጨማሪ የልጅ ልጆች)።

አራት ትውልዶች በአንድ ሰው ወገብ ውስጥ ናቸው።

ዕብራውያን 7፡9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤

10 መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና።

ሌዊ የልጅ ልጅ ልጅ ነበር ግን አብርሐም አባቱ ተብሏል

ይህ የወንድ ዘር ውስጥ ያለው ሚስጥራዊ ኃይል ነው። አራት ትውልድ ሁሉ በአንድ ሰው ውስጥ ነው ያለው፤ ስለዚህ አራቱም ትውልድ ያንን ሰው “አባት” ብለው መጥራት ይችላሉ ምክንያቱም የሆነ ጊዜ ሁላቸውም እርሱ ውስጥ ነበሩ።

ይህም እግዚአብሔር አያቶች እንደማይፈልግ ያሳየናል። እያንዳንዳችሁ ልጆቹ እንድትሆኑ ነው የሚፈልገው እንጂ አያቶች እንድትሆኑ አይደለም። እያንዳንዳችን እግዚአብሔርን “አባት” ብለን እንጠራው ዘንድ ከክርስቶስ መንፈስ መወለድ አለብን። ኢየሱስ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች በሆነች ቤተክርስቲያን ወይም በሆነ ፓስተር በኩል ወደ እርሱ እንዲቀርቡ አይፈልግም። ከኢየሱስ ጋር የግል ሕብረት ያስፈልጋችኋል፤ ስለዚህ በማንም ሰው ላይ ጥገኛ መሆን አያስፈልጋችሁም።

ዘፍጥረት 46፡7 ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው።

ያዕቆብ ውስጥ የነበረው ዘር እንደ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ሆኖ ይገለጣል። ነገር ግን ቀጣዩን ትውልድ ለመውለድ ዘር ያላቸው ወንዶች ልጆቹ ብቻ ናቸው። የልጆቹ ሚስቶች እንደ ዘር አይቆጠሩም።

የክርስቶስ ዘር ልንሆን የምንችለው ከመጀመሪያው በእርሱ ውስጥ በሃሳቡ ውስጥ ከነበርን ነው።

ኢዮብ በደረሰበት መከራ ምክንያት እያማረረ ነበር። እግዚአብሔርም ምድርን መፍጠር በጀመረ ጊዜ በእግዚአብሔር ውስጥ የነበሩ የእግዚአብሔር ልጆች እየተሰራላቸው የነበረውን መኖሪያ አይተው በደስታ እንደዘመሩ ለኢዮብ አስታወሰው። ቀጥለውም ወደፊት አንድ ቀን በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ሃሳብ ከመሆን አልፈው በስጋዊ አካል ውስጥ እግዚአብሔር ወደ መገለጥ እንደሚያመጣቸው አወቁ።

ሚስጥሩ ምንጩ ውስጥ ነው የነበረው። ከመጀመሪያው በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ሃሳብ ወይም ዘር ሆነው ከጀመሩ ወደ ምድር ሲመጡም ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ። በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ስለነበሩ ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ሃሳብ በልባቸው ተጽፎ ስለሚቀመጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምላሽ ይሰጣሉ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ነው የሚገልጠው።

ኢዮብ 38፡4 ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ?

ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።

ኢዮብ 38፡7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥

የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥

መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር?

ከመጀመሪያው በእግዚአብሔር ልብ ወይም መንፈስ ውስጥ ስለነበርን ልባችን ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ሃሳብ ይደነቃል። ስለዚህ በሰው ሃሳብ አንደነቅም። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ስሕተት የሌለበት ፍጹሙ መመሪያችን ነው፤ ስለዚህ እያነበብነው አንድ ጥቅስ ምን ማለት እንደሆነ እንዲሁም አንድን ጥቅስ ከሌላ ጥቅስ የምናገናኝበትን ጥበብ በውስጡ እንፈልጋለን። ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከገለጠው ሃሳብ ጋር መከራከር አንችልም። ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ስሕተት አለ ማለት አንችልም።

መዝሙር 42፡7 በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፤

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት የሚከብደን ክፍል ስናገኝ አለማወቃችንን ለመሻር ጠለቅ ያለ መገለጥ ይሰጠን ዘንድ እንጸልያለን። የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት ቸል አንልም፤ ደግሞም አንለውጥም።

ዘፍጥረት 46፡8 ወደ ግብጽም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ ልጆቹ፣ የያዕቆብ በኩር ሮቤል።

ቀጥሎ የተጻፈው የያዕቆብ ወንዶች ልጆችና ወንዶች አያቶች ስም ዝርዝር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን አያቶች ብሎ አይናገረም፤ ልጆቹ እና የልጆቹ ልጆች ነው የሚለው።

እዚህ ውስጥ የተገለጠው ሃሳብ እግዚአብሔር በልጆቹ ማትም ከመንፈሱ ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ይሰራል ማለት ነው። እግዚአብሔር በእርሱ እና በእናንተ መካከል ማንም ሰው እንዲገባ አይፈልግም። ካሕናት ሁሉ እኩል ነበሩ። ሊቀካሕኑ (ኢየሱስ) ብቻ ነው ከካሕን የሚበልጠው። ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሉ ካሕናት ናቸው፤ ስለዚህ ሁሉም እኩል ናቸው። ከጉባኤው ወይም ከምዕመናን በላይ ከፍ ያሉ ኒቆላውያን መኖር የለባቸውም። ምዕመናን ወይም ጉባኤው የቤተክርስቲያን ራስ ለሆነ አንድ ሰው እንዲገዙ ማድረግ እግዚአብሔር የሚጠላው ነገር ነው።

1ኛ ጴጥሮስ 2፡9 እናንተ ግን … የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ … ናችሁ፤

 

የያዕቆብ የመጀመሪያ ሚስት የሆነችዋን የሊያን 6 ልጆች አስቡ

 

 

ዘፍጥረት 46፡9 የሮቤልም ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ።

1. ሮቤል 4 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡10 የስሞዖን ልጆች፤ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል።

2. ስምዖን 6 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡11 የሌዊም ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።

3. ሌዊ 3 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡12 የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፤ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።

4. ይሁዳ 3 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ተጨማሪ 2 የይሁዳ የልጅ ልጆችም ተጠቅሰዋል። ኤስሮም እና ሐሙል የይሁዳ ልጅ የፋሬስ ልጆች ናቸው።

ዘፍጥረት 46፡13 የይሳኮርም ልጆች፤ ቶላ፥ ፉዋ፥ ዮብ፥ ሺምሮን።

5. ይሳኮር 4 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡14 የዛብሎንም ልጆች፤ ሴሬድ፥ ኤሎን፥ ያሕልኤል።

6. ዛብሎን 3 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

እስካሁን የቆጠርናቸው የልጅ ልጆች ድምር፡ 4 + 6 + 3 (+ 2) + 3 + 4 + 3 = 25 እና 6ቱ የያዕቆብ ልጆች = 31

ዘፍጥረት 46፡15 ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው።

እግዚአብሔር የልጅ ልጆች የሉትም። ስለዚህ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ የልጅ ልጆቹም ቢሆኑ ልጆች ነው የሚባሉት ምክንያቱም ልጆቹ በወገቡ ውስጥ ሳሉ የልጆቹ ልጆች ደግሞ በልጆቹ ወገብ ውስጥ ነበሩ። ስለዚህ የልጅ ልጆቹም በእርሱ ወገብ ውስጥ ነበሩ፤ ከዚህም የተነሳ ልጆቹ ተብለው ይጠራሉ።

 

ዲና እና ስሟ ያልተጠቀሰች ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናቸው

 

 

ዲና የተባለች አንዲት ሴት ልጅ በስም ተጠቅሳለች። 31 + 1 = 32

ስለዚህ ቁጥራቸው 33 እንዲሞላ ቢያንስ በስም ያልተጠቀሰች አንዲት ሴት ልጅ አለች ማለት ነው።

ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት። እግዚአብሔር እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን በሰው ስም እንድትጠራ አይፈልግም። ይህች ሴት ልጅ ስሟ አልተጠቀሰም። እርሷም በውስጧ የነበሩ ሰዎች ክርስቲያን ብቻ ተብለው የሚጠሩባትን የጥንቷን ቤተክርስቲያን ትወክላለች። ቤተክርስቲያን በየሰው ቤቱ ውስጥ በጥቂት ሰዎች ሕብረት ነበር የምትሰበሰበው፤ እነርሱም የሚተዳደሩት በሽማግሌዎች ነበር። በእነርሱም ላይ ጳጳስ ወይም ፓስተር የተባለ እንደ ራስ ሆኖ የተሾመ ሰው አልነበረም።

ክርስቲያን ብቻ መሆን አለብን። ባፕቲስት፣ ሜተዲስት፣ ፔንቲኮስታል ወይም ሜሴጅ ውስጥ መሆን የለብንም (ሜሴጅ ውስጥ መሆን ምን ማለት እንደሆን እንጃ)።

ዲና ተደፈረች፤ ይህም የቤተክርስቲያንን መሰደድ ያመለክታል። በተጨማሪ ቤተክርስቲያን እጅግ ትልቅ በመሆንና የስልጣን ጥማት ባለው አንድ ግለሰብ ወይም ጳጳስ በመተዳደርም ተደፍራለች። አንዲት ሴትን (ወይም ቤተክርስቲያንን) ለወንድ ፈቃድ እንድትገዛ ማስገደድ መንፈሳዊ አስገድዶ መድፈር ነው።

በስተመጨረሻ ፖፑ በቤተክርስቲያኖች ሁሉ ላይ በመንገስ ወደ ጨለማው ዘመን ይዟቸው ገባ፤ በጨለማውም ዘመን ቤተክርስቲያን የሰው ሰራሽ ሃሳቦችና አስተምሕሮዎች መከማቻ ሆነች።

ክርስትናም በባዕድ አምልኮ እና በባቢሎን ሚስጥራት መበረዙ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የባቢሎን ሚስጥር አደረጋት። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በቂ የሆኑ የአረማውያን ልማዶችን ስለተቀበለች ባርቤሪያውያንን መሳብ ችላለች፤ ከዚህም የተነሳ ምዕራባዊው የሮማ መንግስት ከወደቀ በኋላ ጸንታ እስከ ዛሬ የቆየችዋ ብቸኛዋ ተቋም ልትሆን ችላለች።

የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን

ንሰሐ ለመግባት ቅና።” ይህች ሐሰተኛ ቤተክርስቲያን ቅናት አላት፤ ምንም ጥርጥር የለውም። ቅናቷ የአይሁዶች ዓይነት ቅናት ነው፤ ዮሐንስ 2፡17፡- “የቤትህ ቅናት ይበላኛል።”

ነገር ግን ትክክለኛ ቅናት አይደለም። ቅናታቸው እራሳቸው ለሰሩት ቤት ነው። ለራሳቸው የሐይማኖት መግለጫ፣ ዶግማ፣ ድርጅቶች፣ እና ለራሳቸው ጽድቅ ነው የሚቀኑት።

የራሳቸውን ሃሳብ ለማራመድ ብለው ቃሉን ከቤተክርስቲያን አስወጥተውታል።

መንፈስ ቅዱስን ከስልጣን አውርደው በቦታው ሰዎችን ሾመዋል።

የዘላለም ሕይወት የሆነውን ኢየሱስን ወደ ጎን ትተው መልካም ስራዎችን ወይም ከመልካም ሥራዎች ይልቅ ከቤተክርስቲያን ጋር መስማማትን የዘላለም ሕይወት ማግኛ መንገድ አድርገዋል።”

 

መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ኢየሱስ በተጻፈ ቃል መልክ ነው ምክንያቱም የሚገልጠው የእርሱን ሃሳብ ነው።

አሁን ግን ቤተክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያዘናጉን እና የሚያስቱን ሆነዋል።

በሩ ላይ ያለው ማስታወቂያ “ክርስቲያን” ይላል፤ ውስጥ ያለው ስራ ግን “ማሳሳት” ነው።

57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት

በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአጥቢያዋ ሽማግሌ የሚበልጥ ማን እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ። እውነቴን ነው ወገኖች፤ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነጻ መሆን አለባት፤ እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራሷን ታስተዳድር።

65-0220 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ሥፍራ

ወደዚያ እነርሱ ወደሚሉት ቤተክርስቲያን ካልሄዳችሁ መንግስተ ሰማያት የማትገቡ ይመስላቸዋል። ይህ ስሕተት ነው። እንደዚህ ብሎ ማመን የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆን ነው። እኔም እንዲህ እላለው፡- እንዲህ ዓይነቱን መንፈስ ካመናችሁ ጠፍታችኋል።

 

በስም ያልተጠቀሰችዋ የያዕቆብ ልጅ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ትሁት እና የማትታወቅ እንደምትሆን፤ በውስጧ ያሉትም ሕዝብ ዝግ ብለው እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉና ቃሉን እንደሚታዘዙ ታመለክታለች።

እነርሱም ትንንሽ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ሲሆኑ የሚሰበሰቡት በሰው ቤት ውስጥ ነበር።

የሎዶቅያ ቤተክርስቲያንም በሰው ቤት ውስጥ ነበር የምትሰበሰበው።

ቆላስይስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።

እነዚህ ቤተክርስቲያኖች እያንዳንዳቸው የሚተዳደሩት በሽማግሌዎች ሕብረት ነው፤ እነዚህም ሽማግሌዎች ተባብረው የስብከትን እና ውሳኔ የማድረግን ስራ ይሰራሉ። የቤተክርስቲያን ራስ ለመሆን ብሎ ፓስተር ነኝ የሚል ግለሰብም አልነበረም።

የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

እነዚህ ቤተክርስቲያኖች በሰው ስም ተጠርተው አያውቁም።

እራሳቸውን ካቶሊክ፣ ሉተራን፣ ብራሕማይትስ፣ ሜሴጅ፣ ወዘተ. ብለው አልጠሩም።

62-0601 ከኢየሱስ ጋር መወገን

እነዚያ ጥንታዊ ሰዎች ሲወጡ አንዳንዴ ለስድስት ወይም ለስምንት ብቻ ሆነው ይወጡ እንደ ነበር ታውቃላችሁ? ጥቂት ሆነው ግን ሃገሪቱን አንቀጠቀጡ። እንደምታውቁት አቂላ እና ጵርስቅላ እንዲሁም በዚያ ስፍራ አጵሎስ የጀመረው ታላቅ መነቃቃት ውስጥ ስድስት ወይም ስምንት ሰዎች ብቻ ናቸው የነበሩት። አንድ ቤተክርስቲያን ሙሉ ምዕመናኑ ስድስት ወይም ስምንት ብቻ። ዛሬ እዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰበሰባችሁ ሰዎች ከእነርሱ አምስት፣ ስድስት ወይም ሰባት እጥፍ ትበልጣላችሁ።

እንደምታውቁት የኢየሱስ ደቀመዛሙርት አስራ ሁለት ብቻ ነበሩ። እኛ ሁልጊዜ ትልቅ ነገር መጀመር ነው የምናስበው። እግዚአብሔር ግን ከብዙ ሕዝብ ጋር አይደለም የሚሰራው። እግዚአብሔር የሚሰራው ከታናናሽ ሕብረቶች ጋር ነው። አያችሁ? በዘመናት ውስጥ ሁሉ ሰዎችን ለአገልግሎት ሲጠራ እንዴት እንደነበር ተመልከቱ። ታናናሽ ሕብረቶችን ነበር የሚጠራው፤ እነርሱንም ይናገራቸውና ለአገልግሎት ይሾማቸው ነበር። እግዚአብሔር መስራት የሚወደው እንዲህ ነው። እኛም እግዚአብሔር በመካከላችን ሁሌ እንዲገኝና ያዘዘንን ነገሮች ማድረግ እንፈልጋለን።

ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን የተጀመረችው በተበታተኑ ትንንሽ ሕብረቶች አማካኝነት ነው፤ ይህም ከአረማዊው የሮማ መንግስት የሚደርስባቸውን ከባድ ስደት ለመቋቋም ያመቻቸው ነበር። ባለስልጣናቱ እንዳያውቋቸው ይጠነቀቁ ነበር።

እነዚህ የጥንት ክርስቲያኖች የኢየሱስን ስም በዓለም ዙርያ ሁሉ ሰብከዋል፤ ነገር ግን የራሳቸውን ስም ዝነኛ የማድረግ ፍላጎት አልነበራቸውም። ከዚህም የተነሳ የታሪክ ምሑራን አላወቋቸውም። ወንጌሉ ውስጥ የሰዎች ስም ትልቅ ቦታ የለውም።

ከ222 -235 ዓ.ም በፊት የቤተክርስቲያን ሕንጻ ተሰርቶ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ የለም።

 

እግዚአብሔር የያዕቆብን ዘር በ3 የተለያዩ መንገዶች ያበዛቸዋል

 

 

እግዚአብሔር የያዕቆብን ዘር ሲቆጥር በ3 የተለያዩ መንገዶች ነው የሚደምራቸው፤ ይህም 3 የተለያዩ ትልልቅ ነጥቦችን እንድናስተውል ነው።

ግብጽ ውስጥ የኖሩ የዮሴፍ ዘሮች 70 ናቸው ግን 66 ወይም 75 እንደሆኑ ተደርጎ ነው የተጻፈው። ስለዚህ ማብራሪያ ያስፈልገናል።

ልጆችን ሁሉ እና የልጅ ልጆችን እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ ስንደምር 70 ነፍሶች እናገኛለን።

የዚህ ቁጥር ትርጉሙ ምንድነው?

ቀጣዩ ቁጥር ደግሞ ከያዕቆብ ጋር የመጡት 66 ናቸው ይላል።

ዮሴፍ እና ሁለቱ ልጆቹ ግብጽ ውስጥ ስለነበሩ ከያዕቆብ ጋር 67 ሰዎች እንደመጡ ይመስላል።

እነዚህ ልዩነቶች ምንድነው የሚያሳዩን? የተጠቀሱት 66 ከሆኑ አንድ ሰው ሳይጠቀስ ቀርቷል። ለምን?

የሐዋርያት ሥራ 7፡14 ውስጥ የሚገኘው ቁጥር 75 ነው። ለምን ይህ ቁጥር ተጻፈ? ተጨማሪዎቹ ሰዎች ማናቸው?

እግዚአብሔር ከእነዚህ ከያዕቆብ ትውልዶች እንድንማር የሚፈልገው ሶስት የተለያዩ ትምሕርቶች አሉት።

ዘፍጥረት 46፡26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት፥ ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ፥ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው።

የያዕቆብ ዘር ማለትም ያዕቆብ ወጣት በነበረ ጊዜ በወገቡ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ልጆቹና የልጅ ልጆቹ 66 መጻሕፍት ያሉትን የእግዚአብሔር ቃል ይወክላሉ።

ይህን ቁጥር ለመሙላት 4 የልጅ ልጅ ልጆች ያስፈልጋሉ (እነዚህም ከልጆችና ከልጅ ልጆች መካከል የማይቆጠሩ ናቸው)።

(2 የልጅ ልጅ ልጆች ከይሁዳ እና ከአሴር)

መጽሐፍ ቅዱስ በ4 ወንጌሎች የሚያያዙ የብሉይ ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አሉት። የኢየሱስ በድንግልና መወለድ። ከሙታን መነሳት። እግዚአብሔር በአንድ ሰው አካል ውስጥ በሙላት መኖሩ። ስለረከሱ ሐጥያተኞች ፍጹም መስዋእት ሆኖ መሞት።

እነዚህ ሁሉ አነጋገሮች የተለመዱ አልነበሩም። በዘመኑ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እንግዳ ናቸው። ምንጫቸው ከተለመደው ምድራዊ ሕይወት አይደለም፤ ነገር ግን እነዚህ አነጋገሮች ብሉይ ኪዳን ከአይሁዶች እና በቤተመቅደስ ከሚያደርጉት የመስዋእት ስርዓት እየራቀ የሄደበትን የሽግግር ዘመን ይወክላሉ። አይሁዶች ዘመናቸው እየተሻረ እንደነበረ አላወቁም።

ሆኖም ኢየሱስ ጊዜውን ሁሉ ከአይሁዶች ጋር ያሳለፈው ይቀበሉት ዘንድ ዕድል ሊሰጣቸው አስቦ ነው።

ማቴዎስ 10፡5 እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ

ወንጌሎቹ የመስዋእቶች ሁሉ የመጨረሻ መስዋእት የሆነውን የኢየሱስን ሞት ያብራራሉ፤ በዚህም መስዋእት ሕጉ ይናገር የነበረው ሁሉ ስለተፈጸመ ከዚያ ወዲያ የእንስሳት መስዋእት አብቅቷል።

ኢየሱስ በአይሁዶች መካከል የተመላለሰው እነርሱ አንቀበልህም ሲሉት የሐዋርያት ሥራ ውስጥ ወደ አሕዛብ ዘወር ማለት ይችል ዘንድ ነው። ስለዚህ አራቱ ወንጌሎች በአይድና በአሕዛብ መካከል በሁለቱም ዘመን የሚገኙ የመሸጋገሪያ መጽሐፎች ናቸው።

አይሁዶች እና አሕዛብ የተለያዩ ወገኖች ናቸው ግን በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ ወደ አንድነት መጥተዋል።

አራቱ ወንጌሎች ልዩ መጻሕፍት ናቸው። እነዚህ መጻሕፍት እግዚአብሔር በሰው መልክ ተገልጦ በምድር ላይ የኖረበትን ብቸኛውን ዘመን ይተርካሉ።

ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው፤ እንደገና የአዲስ ኪዳን ጀማሪም ነው።

ማቴዎስ እና ማርቆስ ልትመጣ ስላለችዋ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ብዙ ይናገራሉ። የአዲስ ኪዳን ቅዱሳንንም ትንሳኤ አስቀድሞ በትንቢት መልክ በሚያሳየው በትንሳኤ ሰዓት ወደ አሕዛብ ስለተላከ አንድ መልአክ ወይም ትንቢታዊ መልእክተኛ ይናገራሉ። እርሱም አሜሪካዊው ወንድም ብራንሐም ነው።

ማቴዎስ እና ማርቆስ የክርስቶስን ሕይወት ከአሕዛብ አንጻር ነው የሚመለከቱት።

ሉቃስ እና ዮሐንስ አይሁዶች ወደፊት ምን እንደሚሆኑ ብዙ ይናገራሉ፤ በተለይም በታላቁ መከራ ዘመን ስለሚኖሩት ስለ 144,000ዎቹ። በትንሳኤ ሰዓት 144,000ዎቹን አይሁዶች ወደ ክርስቶስ ስለሚያመጡዋቸው ሁለት መላእክት ወይም ትንቢታዊ መልእክተኞች ይናገራሉ። እነዚህም መልእክተኞች ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው።

ሉቃስ እና ዮሐንስ የክርስቶስን ሕይወት ይበልጥ ከአይሁዶች አንጻር ነው የሚመለከቱት።

አዲስ ኪዳን የሐዋርያት ሥራ ውስጥ በበዓለ ሃምሳ ቀን ተመስርታ ስለተጀመረችዋ ቤተክርስቲያን ይነግረናል።

ደቀመዛሙርቱም ሆኑ አሕዛብም ምን እየተደረገ እንደነበር ምንም ባያውቁም እንኳ 4ቱ ወንጌሎች ቤተክርስቲያንን መሰረት እያዘጋጁ ነበረ።

ኋላ አሕዛብ የመዳናቸውን እቅድ መቁጠር የሚችሉበት ዘመን ከወንጌሎቹ መጀመሪያ አንስቶ እንደሆነ ይገነዘባሉ። ወንጌሎቹ ባይኖሩ ኖሮ አሕዛብ መነሻ ቦታ አይኖራቸውም ነበር።

በአራቱ ወንጌሎች ዘመን ምን እየተፈጸመ እንደነበር ያወቀው ኢየሱስ ብቻ ነበር

ለደቀመዛሙርቱ የወንጌሎቹ አጨራረስ ግራ የሚያጋባ ወቅት ነበረ፤ ምክንያቱም ወንጌሎቹ የሚጠናቀቁት በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ ነው። ይህም ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ምን እንደሚመስል ያሳያል፤ ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚጠናቀቀው የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ትንሳኤ ሲፈጸም ነው።

ኢየሱስ የጴጥሮስን እግር ሊያጥብለት ዝቅ ብሎ ሲቀርብ ጴጥሮስ ተቃወመ። አስቡት እስቲ ከኢየሱስ ጋር መከራከር።

ዮሐንስ 13፡6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።

7 ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።

ኢየሱስም በዚያ ሰዓት ጴጥሮስ የወንጌሉን ዓላማ መረዳት እንደማይችል አስታወሰው። ነገር ግን አሕዛብም ከአይሁድ ጋር አብረው ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደሚገቡ ይህም ከሮማዊው መቶ አለቃ ከቆርኔሌዎስ ቤት እንደሚጀምር ጴጥሮስ ኋላ በሐዋርያት መጽሐፍ ውስጥ ነው የሚያስተውለው።

4ቱ የልጅ ልጅ ልጆች የሚወክሏቸው 4ቱ ወንጌሎች ራሳቸውን ችለው ለብቻቸው ተነጥለው የቆሙ መጻሕፍት ይመስላሉ።

4ቱ ወንጌሎች የሽግግር ወቅት ናቸው። ብሉይ ኪዳን ፍጻሜውን የሚያገኘው አዲስ ኪዳን ውስጥ ነው።

አዲስ ኪዳን መነሻው፣ ምንጩ ወይም ጥላው የሚገኘው ብሉይ ኪዳን ውስጥ ነው።

4ቱ ወንጌሎች ልዩ መሆናቸው ዘፍጥረት ምዕራፍ 15 ውስጥ እግዚአብሔር ከአብርሐም ጋር ባደረገው ቃልኪዳን ታይቷል።

አብርሐም ሶስት እንስሳትን ለሁለት ሰንጥቆ ወዲያ እና ወዲህ ከመካከላቸው ክፍተት አድርጎ ፊት ለፊት አስቀመጣቸው። ይህም ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪንን ይወክላል፤ በእንስሳቱ መካከል ያለው ክፍተትም በሁለቱ ኪዳኖች መካከል የሚገኙት አራቱ ወንጌሎች ናቸው።

ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤

አብርሐም እንቅልፍ ተኛ (ይህም የሞት ምሳሌ ነው) ታላቅ ጨለማ እና ፍርሃትም ወደቀበት (የሰው ሐጥያት) ጢስ እና የእሳት ነበልባል (የሲኦል እሳት) በተከፈሉት እንስሳት መካከል አለፈ።

ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ

በተሰነጠቁት እንስሳት መካከል ያለፈው የእሳት ነበልባል ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን ከአካሉ ሲለቀው (በሞተ ጊዜ መንፈሱ ከእርሱ ሲወጣ) ሐጥያታችንን ተሸክሞ በሰይጣን ላይ ሊያራግፋቸው ወደ ሲኦል መውረዱን የሚያመለክት ነው። ይህ ታላቅ ክስተት የተፈጸመው በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መካከል በሚገኙት በ4ቱ ወንጌሎች ውስጥ ነው።

 

ልጆች፣ የልጅ ልጆች፣ እና የልጅ ልጅ ልጆች ሁሉ በአንድ ወጣት ወንድ ወገብ ውስጥ ነው የሚገኙት። ስለዚህ የአንድ ሰው ተጽእኖ በሶስት ትውልዶች ሁሉ ይደርሳል።

ዕብራውያን 7፡9 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤

ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈላቸው ሰዎች ሁሉ ከዓለም መፈጠር በፊት በክርስቶስ ልብ ውስጥ ሃሳብ ወይም ዘር ሆነው የተቀመጡ ነበሩ። ቤተክርስቲያን የክርስቶስ መንፈሳዊ ዘር ናት፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

የአይሁድ ሕዝብ ጅማሬ የያዕቆብ ፍጥረታዊ ዘር ነው።

ስለዚህ የአይሁድ ሕዝብን ያስጀመረው የያዕቆብ ፍጥረታዊ ዘር ወደፊት ልትመጣ ስላለችው ቤተክርስቲያንም አስቀድሞ ፍንጭ ሰጥቷል።

 

ሊያ 33 ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯት፤ ኢየሱስ የሞተው በ33 ዓ.ም ነው

 

 

ከሊያ ልጆች የተወለዱት 33ቱ ነፍሶች ኢየሱስ በምድር ያሳለፋቸውን 33 ዓመታት ይወክላሉ።

ዘፍጥረት 46፡15 ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው።

አዲስ የተወለደ ሕጻን በጀርባው አጥንት ውስጥ 33 ተንቀሳቃሽ አጥንቶች አሉት። ቀጥ ብለን ቆመን እንድንራመድ የሚያደርገን የጀርባ አጥንታችን ነው።

በመጀመሪያ ሚስቱ በሊያ በኩል የተወለዱት 33ቱ የያዕቆብ ልጆች የአይሁድ ሕዝብን መወለድና መሰረት ናቸው።

ትልቅ ሰው ስንሆን 9 አጥንቶች ተዋህደው አንድ ስለሚሆኑ ተንቀሳቃሽ አጥንቶቻችን 24 ይሆናሉ። ይህም በዙፋኑ ዙርያ የሚገኙትን 24 ሽማግሌዎች ይወክላል።

ራዕይ 4፡4 በዙፋኑ ዙሪያም ሀያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፥ በዙፋኖቹም ላይ … ሀያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።

 

 

ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 33ኛው መጽሐፍ ሚክያስ ነው። ይህም መጽሐፍ ሁለት ቁልፍ ትንቢቶችን ይዟል። አንዱ ትንቢት ስለ ክርስቶስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለ ቤተክርስቲያን ነው።

ስለዚህ ብሉይ ኪዳን መድረኩን ለቤተክርስቲያን ሲያዘጋጅ ነበር።

ሚክያስ 5፡2 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።

ይመጣል የተባለው ገዥ ኢየሱስ ነው።

እርሱም ቤተክርስቲያንን ሊወስዳት ይመጣል፤ ቤተክርስቲያን አዲስ ኪዳንን በጻፉ በ8 ዋና ዋና ሰዎች ነው የተመሰረተችው። አዲስ ኪዳን ፍጹም እውነት ነው። ቀጥሎም 7 እረኞች አሉ፤ እነርሱም ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተላኩ ሰባት መልእክተኞች ናቸው፤ እነዚህ መልእክተኞች ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን እንድትከተል ለማድረግ የተቻላቸውን ያህል ጥረዋል።

አሶራዊው የቤተክርስቲያን ጠላት የሆነውን ሰይጣንን ይወክላል። በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የተቃወመችዋ ብቸኛ ድርጅት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት።

ሚክያስ 5፡5 ይህም ለሰላም ይሆናል፤ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።

 

ያዕቆብ የሊያ ደንገጡር ከነበረችው ከዘለፋ 16 ልጆች ወልዷል

 

 

ዘፍጥረት 46፡18 ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች።

ጋድ እና አሴር የዚልፓ ልጆች ናቸው።

ዘፍጥረት 46፡16 የጋድም ልጆች፤ ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤስቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥ አርኤሊ።

7. ጋድ 7 ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡17 የአሴርም ልጆች፤ ዪምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሪዓ፥ እኅታቸው ሤራሕ፤ የበሪዓ ልጆችም፤ ሔቤር፥ መልኪኤል።

8. አሴር 4 ልጆች ነበሩት።

አሴር ሁለት የልጅ ልጆች እንዳሉት ተጠቅሷል (ሔበር እና መልኪኤል)፤ ልክ እንደ ይሁዳ የልጅ ልጆች (ኤስሮም እና ሐሙል)።

እነዚህ የያዕቆብ የልጅ ልጅ ልጆች ስለሆኑ ከያዕቆብ የልጅ ልጆች ውስጥ አይቆጠሩም። እነዚህ 4 ልጆች የኢየሱስን ሕይወት የሚተርጉትን ልዩ መጻሕፍት ማለትም 4ቱን ወንጌሎች ይወክላሉ።

አሴር ሴት ልጅም አለችው (እርሷም የያዕቆብ የልጅ ልጅ ነች) ግን ሌላ ቦታ አልተጠቀሰችም።

ስሟ ሤራህ ሲሆን ከአብርሐም ሚስት ከሣራ ጋር ይመሳሰላል። እርሷ የምትወክለው ምንድነው? እርሷ የምትወክለው በመጨረሻ የምትገኘዋን የመጀመሪያዋን ዕብራዊት ሴት ወይም ቤተክርስቲያንን ነው።

ያዕቆብ ዲና የምትባል ሴት ልጅ፣ ሌላ ደግሞ ስሟ ያልተጻፈ ሴት ልጅ፣ እና ሤራህ የምትባል የልጅ ልጅ ነበረችው፤ ሤራህ ስሟ የተስፋ ቃል ልጅ የሆነውን ይስሐቅን የወለደችውን የሣራን ስም ይመስላል።

ሣራ የመጀመሪያዋ ዕብራዊት ሴት እንደመሆኗ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ትወክላለች።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኙት ሴቶች በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩትን ቤተክርስቲያኖች ይወክላሉ።

በስም ያልተጠቀሰችዋ ሴት ልጅ እና የልጅ ልጅ የሆነችዋ ሤራህ ሁለት ትውልድ ናቸው። ይህም በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚገኙ ልጆች በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ለነበረው ጥንታዊ ትውልድ ጀርባቸውን እንደሚሰጡ ያሳያል።

የሆሳዕና ዕለት አህያ እና ውርጫዋ ቃሉን ተሸክመው ገቡ። እነዚህም ሁለት ትውልድ ናቸው። እነዚህ ሁለት ትውልዶች የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበሩትን ሐዋርያዊ አባቶች እና በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚገኙ ልጆችን ይወክላሉ፤ እነዚህ ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመማርና ይዘው ለመቀጠል ወደ አባቶች መመለስ አለባቸው።

ሣራ የመጀመሪያዋ ዕብራዊት ሚስት ናት። ስለዚህ ሤራህ ለመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ጀርባቸውን የሚሰጡ ልጆችን ትወክላለች።

2 የያዕቆብ ልጆች ጋድ እና አሴር ናቸው።

7 + 4 = 11 የልጅ ልጆች። 2 የልጅ ልጅ ልጆች። 1 ሴት የልጅ ልጅ። በዚህ ስብስብ ውስጥ የሚገኙት 16 ነፍሶች ናቸው።

ሚክያስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 33ኛ መጽሐፍ ነው። ሚክያስ ገዥ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ እና አዲስ ኪዳንን ስለጻፉ ስለ 8ቱ ዋነኛ ሰዎች ይናገራል። ቀጥሎ 7ቱ መልእክተኞች ቤተክርስቲያንን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠጋት ጥረዋል።

ሚክያስ ላይ 16 መጽሐፎች ስንደምር የኤፌሶን መልእክት ላይ እንደርሳል፤ የኤፌሶን መልእክት የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ተምሳሌት ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ዓላማ በኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን እምነት ላይ የተመሰረተ ነው።

 

ዮሴፍ እና ብንያም የኢየሱስ እና የ144,000ዎቹ አይሁዶች ተምሳሌት ናቸው

 

 

ዘፍጥረት 46፡19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው።

ዮሴፍ አሕዛብ ሚስት በማግባቱ የክርስቶስ ተምሳሌት ነው፤ የክርስቶስም ሙሽራ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ናት።

ብንያም 144,000ዎቹን አይሁዶች ይወክላል። ገና ሲወለድ እናቱ ሞተች። 144,000ዎቹ ክርስቶስን በሚቀበሉበት በ3.5 የታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ ከአይሁዶች መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ይሞታሉ።

ዘካርያስ 13፡8 በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።

ዘፍጥረት 46፡20 ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምናሴና ኤፍሬም ተወለዱለት፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው።

9. ዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ዘፍጥረት 46፡21 የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ናዕማን፥ አኪ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም፤ ጌራም አርድን ወለደ።

10. ብንያም 10 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

ድምር፤ 2 ወንዶች ልጆች + 12 የልጅ ልጆች = 14

ዘፍጥረት 46፡22 ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሁሉም አሥራ አራት ነፍስ ናቸው።

ያዕቆብ ለልያ (አይሁዶች) እና ለራሔል (ቤተክርስቲያን) ሲል አስራ አራት ዓመታት አገለገለ።

ያዕቆብ ስለ እያንዳንዷ ሚስት 7 ዓመት ሰራ።

ይህም ኢየሱስ ስለ ሙሽራይቱ ብሎ ለ7 የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደሚሰራ ያመለክታል።

አይሁዶችም በ7 ዘመናት ውስጥ አልፈዋል።

የአይሁድን ታሪክ ራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ ከተጻፉት 7ቱ ቤተክርስቲያኖች ጋር አነጻጽር።

(1) አብርሐም የመጀመሪያ ፍቅሩን ሣራን ትቶ ወደ አጋር ገባ። (2) ዮሴፍ እስር ቤት ገባ። (3) ሙሴ በለዓምን ተጋፈጠ። (4) ኤልያስ ኤልዛቤልን ተጋፈጠ። (5) ዕዝራ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ወደ ቤተመቅደስ አስገባ። ይህም ሉተር በእምነት ብቻ መዳን የሚለውን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ እንደሚያመጣ የሚያሳይ ነው። (6) ነሕምያ የኢየሩሳሌምን ጠንካራ ቅጥር ሰራ፤ ይህም ቅድስና እና የወንጌል ስርጭት የክርስትና ጥንካሬ መሆናቸውን ያሳያል፤ ይህም ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲጀመር አደረገ። (7) ከዚያም መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን አስተዋወቀ። ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት እንዴት መረዳት እንደምንችል አስተማረን፤ ይህንም ያደረገው ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ማየት እንድንችል ነው።

ዘፍጥረት 46፡23 የዳንም ልጆች፤ ሑሺም።

11. ዳን 1 ወንድ ልጅ ነበረው።

ዘፍጥረት 46፡24 የንፍታሌምም ልጆች፤ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም።

 

12. ንፍታሌም 4 ወንዶች ልጆች ነበሩት።

2 ወንዶች ልጆች + 5 የልጅ ልጆች = 7 ነፍሶች።

ዘፍጥረት 46፡25 ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው።

አሁንም አጽንኦት የተደረገው 7 ቁጥር ላይ ነው።

7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚያበቃው 7ቱ ማሕተሞች በ7ኛው መልአክ ሲገለጡ ነው።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ከዚያም ሰባቱ ማሕተሞች አካላችን እንዲለወጥ ያደርጋሉ፤ የምንነጠቅበት እምነት የሚመጣው በተለወጠው አካል ውስጥ ስንሆን ነው ምክንያቱም በዚህ አሮጌ አካል ውስጥ ሆነን መነጠቅ አንችልም።

ከዚያ በኋላ ሰባቱ የመቅሰፍት ጽዋዎች በዓለም ላይ እየፈሰሱ ሳለ ሰባቱ መለከቶች አይሁዶችን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ይጠሩዋቸዋል።

 

የያዕቆብ ቤተሰብ ብዛት 33 + 16 + 14 + 7 = 70 ነው

 

 

ዮሴፍ እና 2 ወንድ ልጆቹ ግብጽ ውስጥ ነበሩ።

ወደ ግብጽ የመጡ ሰዎች ቁጥር 70 – 3 = 67 ነው

ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የመጡት 66 ብቻ ናቸው።

ዘፍጥረት 46፡26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት፥ ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ፥ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው።

እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ቃሉ ውስጥ ያሉትን መጻሕፍት የሚወክል ቁጥር ለማምጣት እንደሚመቸው አድርጎ ደምሯል።

በሌላ አነጋገር ሁሉም ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተሰመረለት መስመር ነው የሚሄደው። እርሱ ከእቅዱ ውስጥ የተወሰኑ ነገሮችን ለመግለጥ እንደሚመቸው መደመር ወይም የፈለገውን ከቁጥር ማስወጣት ይችላል።

 

ታድያ እግዚአብሔር ሳይቆጥር የተወው ማንን ነው? ደግሞስ ለምን?

 

 

ከያዕቆብ የተወለዱ በሙሉ 70 ነበሩ።

66 + ዮሴፍ + 2 የዮሴፍ ወንዶች ልጆች = 69

ዘፍጥረት 46፡27 በግብፅ ምድር የተወለዱለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።

ወደ ግብጽ ከወረዱት ሰዎች መካከል የልያ ልጅ እንደሆነች የተመዘገበችዋን በስም ያልተጠቀሰችዋን ሴት ልጅ እግዚአብሔር አልቆጠራትም።

ለምን? ምክንያቱም ግብጽ የዓለም ተምሳሌት ናት። ወደ ግብጽ መሄድ ወደ ዓለም የመመለስ ተምሳሌት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በስም ያልተጠቀሰችዋን የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን የምትወክለዋን ሴት አልቆጠራትም። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖች ሐዋርያት በሕይወት ሳሉ ሙሉው እውነት ነበራቸው፤ ደግሞም ወደ ዓለም አልተመለሱም። ግለሰቦች ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ በአጠቃላይ በሐዋርያት አስተምሕሮ ጸንታ ቆመች።

ዮሴፍ ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን በወገቡ ይዞ ነው ወደ ግብጽ የወረደው።

ዮሴፍ ወደ ግብጽ የሄደው በፍላጎቱ አይደለም። ባርያ ሆኖ ተሽጦ ነው የሄደው። ያለ ፈቃዱ በግድ ነው የሄደው።

ኢየሱስ ያለ ፍላጎቱ ሐጥያታችንን ተሸከመ።

ማርቆስ 14፡36 አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 70 ቁልፍ ቁጥር ነው።

አይሁዶች ባለመታዘዛቸው የተነሳ ባቢሎን ውስጥ ለ70 ዓመታት በግዞት አሳለፉ።

ስለዚህ 70 ነፍሶች ወደ ግብጽ መግባታቸው ኋላ ወደ ባቢሎን ባሪያ ሆነው እንደሚሄዱ የሚያመለክት ነው።

በተመሳሳይ መንገድ ቤተክርስቲያንም መጽሐፍ ቅዱስን መከተል በተወች ጊዜ ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ገብታለች።

ዳንኤል እንደተናገረው ለአይሁዶች 70 ሱባኤዎች ተቆርጠውላቸዋል። ይህም 490 ዓመታት ማለት ነው።

አንድ ቀን አንድን ዓመትን ይወክላል።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

ኢየሩሳሌምን መልሶ ለመገንባት ለነሕምያ በ446 ዓመተ ዓለም ከተሰጠው ትዕዛዝ ጀምሮ አይሁዶች የነበራቸው ጊዜ ባለ 360 ቀን 490 የመጽሐፍ ቅዱስ ዓመታት ነበር። ይህም አንድ ዓመት 365.24 ቀን ነው ብለን ለምንቆጥር ለአሕዛብ 483 ዓመታት ማለት ነው።

ይህ በ37 ዓ.ም መጠናቀቅ ነበረበት። እነሱ ግን በ33 ዓ.ም ኢየሱስን ገደሉት።

ስለዚህ አይሁዶች እስካሁን 3.5 ዓመት ይቀራቸዋል፤ ይህም በታላቁ መከራ ውስጥ ይጠናቀቃል።

 

 

ግብጽን በረሃብ ከመጥፋት የታደጋት ዮሴፍ እኛን ለማዳን የሞተውን ክርስቶስን ይወክላል።

ብንያም በ3.5 ዓመቱ ታላቅ መከራ ውስጥ የሚድኑትን 144,000 አይሁዶች ይወክላል። ከቀራንዮ መስቀል ጀምሮ እግዚአብሔር የአይሁዶችን ዘመን መቁጠር አቁሟል። ቤተክርስቲያን ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከተነጠቀች በኋላ እግዚአብሔር የአይሁዶችን ዘመን እንደገና መቁጠር ይጀምራል። ታላቁ መከራ የሚጀምረው የዛኔ ነው።

ዘፍጥረት 46፡28 ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከ፤ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ።

ጌሴም ከናይል ወንዝ በምስራቅ በኩል ነበር።

 

 

ይህ ቦታ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በኤድን ምስራቅ ገነትን የተከለበትን ቦታ ይመስላል።

ዘፍጥረት 2፡8 እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ

የይሁዳ ነገድ አንበሳ ኢየሱስ መንገዱን ሊያሳየን በመንገድ ይመራናል።

ዘፍጥረት 46፡29 ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ፤ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ።

ዘፍጥረት 46፡30 እስራኤልም ዮሴፍን፦ አንተ ገና በሕይወት ሳለህ ፊትህን አይቼአለሁና አሁን ልሙት አለው።

ዘፍጥረት 46፡31 ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤

ዘፍጥረት 46፡32 እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና፤ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ።

ዘፍጥረት 46፡33 ፈርዖንም ቢጠራችሁ፦ ተግባራችሁስ ምንድር ነው? ቢላችሁ፥

ዮሴፍ እንዲዋሹ ፈለገ ምክንያቱም ግብጻውያን እረኞችን ይጠሉ ነበር። ይህም ትልቅ ስሕተት ነው።

ሰዎች እንዲቀበሉን ብለን ማመቻመች የለብንም።

ዘፍጥረት 46፡34 በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኵስ ነውና፤ በጌሤም እንድትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን።

ግብጻውያን በግ ይጠላሉ። እግዚአብሔር ደግሞ ለፋሲካ መስዋእት የመረጠው በግ ነው። ግብጻውያን በዚህ አይስማሙም።

ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ከተከተሉ በሰዎች ዘንድ የተጠሉ ይሆናሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎች ስላሴን፣ ክሪስማስን፣ የስቅለት አርብን፣ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚለውን ትምሕርት፣ ወንድም ብራንሐም አይሳሳትም የሚባለውን ወሬ አይቀበሉም።

እነዚህን ሁሉ ሃሳቦች አስወግዱዋቸውና በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰው ሁሉ ሲጠላችሁ ታያላችሁ።

የሐዋርያት ሥራ 7፡14 ዮሴፍም አባቱን ያዕቆብንና ሰባ አምስት ነፍስ የነበረውን ቤተ ዘመድ ሁሉ ልኮ አስጠራ።

ቤተዘመዱ ሁሉ ሲመጡ ቁጥራቸው ከ66 ወደ 75 ደረሰ። 9 ተጨማሪ ሰዎች ነበሩ። እነዚህም ያልተጠቀሱ የያዕቆብ ሴት ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ።

ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ከአውሬው ምልክት ማለትም ከ666 ጋር እንድትቆጠር አይፈልግም።

እግዚአብሔርም ይህን ያሳየው ሴቶቹን ባለመቁጠር ነው።

ዘፍጥረት 37፡34 ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።

35 ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፤

ያዕቆብ ብዙ ሴቶች ልጆች ነበሩት። እነዚህ ሴቶች ልጆች ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልተጠቀሱም ምክንያቱም ሴቶች እንደመሆናቸው ቤተክርስቲያንን ነው የሚወክሉት። ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የብሉይ ኪዳን ትልቅ ሚስጥር ነበሩ፤ አይሁዶችም ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምንም አላወቁም። ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ሴቶች ብዙ አልተናገረም።

ሮሜ 16፡25 እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23