ዘፍጥረት 3 - ሐጥያት በጾታዊ ግንኙነትና በነጻ ፈቃድ በኩል ወደ ዓለም ገባ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
በዚህ ክፍል ሁሉ ነገር እንዴት እንደተበላሸ እንማራለን። ኢየሱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈውን እየሰማን መታለል እንደሌለብን ተናግሮናል።
- የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ነበረ
- የተቀደደ መጋረጃ የሞት ሕይወትን ያመጣል
- ትዕቢትና እኔነት ሐጥያትን ወለዱ
- ሔዋን በመሃይምነት ባሕር ላይ መንሳፈፍ የምትችል መሰላት
- ሰዎች የፈለጉትን ያህል ቢጥሩ እንኳ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም
- ክርስቲያኖች ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ይደበቃሉ
- አዳም ማመካኛዎችን በማቅረብ ጥፋቱን በሚስቱና በእግዚአብሔር ያላክካል
- በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል በምድር ላይ ታላቅ ጦርነት ተጀመረ
- በጭንቅ መውለድ የመጀመሪያው ሐጥያት ዋጋ ነው
- ሴት ለባሏ መታዘዝ አለባት
- አዳምና ሔዋን የደም ነጠብጣብ በነካው ቆዳ ተሸፍነው ከኤደን ወጡ
- የሕይወት ዛፍ መንገድ መስቀሉ ነው
የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ነበረ
ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
እባቡ ከእንስሳት ሁሉ ይልቅ ተንኮለኛና ብልህ ነበረ። በዚህም ምክንያት እባቡ ዛሬ ከእንስሳት መካከል አንደኛ ብልጥ ከሆኑት ከዝንጀሮና ከጦጣ በላይ ነበረ። እባቡ የመናገር፣ የመከራከር፣ እና የማሳመን ችሎታ ነበረው። ስለዚህ በሰው እና በእንስሳት መካከል “የጠፋው አገናኝ” የሚባለው እባቡ ነበር። ከዚያ ግን እግዚአብሔር እባቡን ረገመውና በደረቱ የሚሳብ እንስሳ አደረገው። ከዚህም የተነሳ ሳይንቲስቶች ለምርምር የመጀመሪያውን እባብ አጥንቶች ማግኘት አይችሉም። ዳርዊን በ1859 ዓ.ም “On the Origin of the Species” ወይም “የእንስሳት ዘር አመጣጥ” የሚለውን መጽሐፍ (ለነገሩ መጽሐፉ ስለ እንስሳት ዘር አመጣጥ ምንም አይነግረንም) ካሳተመ ወዲህ ሳይንቲስቶች “ስለጠፋው አገናኝ” ማስረጃ ለማግኘት ብዙ ሲደክሙ ቆይተዋል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወጪ የሚጠይቅ ጉዞ እና አሰሳ ካደረጉ በኋላ ሳይንቲስቶች ስለ ጠፋው አገናኝ ያገኙት ማረጋገጫ ቢኖር መጥፋቱን ብቻ ነው።
እባቡ በልቡ “አይ” እያለ በአፉ ግን “አዎ” ብሎ ነው ንግግሩን የጀመረው። ይህ ሽንገላ ነው።
ውሸትን ለማጋለጥ በፈለጋችሁ ጊዜ “አዎ” አትበሉ።
ያዕቆብ 5፡12 ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።
“እግዚአብሔር ብሏልን” በማለት እባቡ ሔዋን በእግዚአብሔር ቃል እንድትጠራጠር አደረገ። ስሕተት ሁሉ ዋነኛ ምንጩ አንድ ነው፡- እርሱም መጽሐፍ ቅዱስን መቃረን ነው።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት እና እርስ በራሱ የሚጋጭ ሃሳብ አለ ይላሉ። ከዚያም የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በራሳቸው ፍላጎት ይለውጣሉ።
ለብዙ ሰዎች የሚያስቸግራቸው አንድ ነገር መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈው ማመን ነው።
ዘፍጥረት 3፡2 ሴቲቱም ለእባቡ አለችው፦ በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤
ሴቲቱ በገነት ውስጥ ከበቀሉት ፍጥረታዊ ዛፎች ፍሬ ሁሉ መብላት እንችላለን ብላ መለሰች።
የአንድ ፍጥረታዊ ዛፍ ፍሬ መብላት ዓለም ሁሉ የሞትና የመከራ ፍርድ እንዲፈረድበት አያደርግም።
ደግሞም ለሐጥያት ስርየት የእንስሳ ደም እንዲፈስስ የሚደረገው ለምን እንደሆነም አያስረዳም።
እግዚአብሔር ሰውየውና ሴቲቱን ለምን ንሰሃ ግቡ ብሎ እንዳላዘዛቸውም አያስረዳም። ይህ መረሳቱ በጣም አስደናቂ ነገር ነው።
ምክንያቱም በቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ሐጥያተኞችን ንሰሃ ግቡ ብሎ ይናገራቸዋል። የኤድን ገነት ውስጥ ለምንድነው ንሰሃ ግቡ ያላላቸው?
ይህ የሚያሳየን ሴቲቱ ይቅር የማይባል ሐጥያት መስራቷን ነው።
ዘፍጥረት 3፡3 ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ፦ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።
ሴቲቱ፡- “በገነት መካከል ግን መንካት የሌለብን አንድ ዛፍ አለ” አለች።
ዲያብሎስ የሴቲቱን አለማወቅ ተረዳ።
በገነት መካከል ያለው ዛፍ አንድ ብቻ መስሏታል።
የነዚህን ተምሳሌቶች መንፈሳዊ ትርጓሜ እንመልከት።
ዘፍጥረት 3፡22 … አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤
የሕይወት ዛፍ አዳምን ለዘላለም ሊያኖረው ይችላል።
የዘላለም ሕይወት ሊሰጥ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ስለዚህ የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ነው።
1ኛ ዮሐንስ 5፡11 እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
ዘፍጥረት 2፡9 … በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
የሕይወት ዛፍም በገነት መካከል የሚገኝ ከሆነ በገነት መካከል ሁለተኛ ዛፍም ነበረ ማለት ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ሁለቱ ዛፎች ሙሉ በሙሉ ተጠላልፈው ከሆነና አንድ ዛፍ ከመሰሉ ነው።
ሌላኛው ዛፍ መልካምና ክፉውን የሚያሳውቅ ዛፍ ነው፤ ማለትም የሰይጣን መንፈስ ነው።
“ስጋዊ እውቀት” ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ነው።
ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።
ይህ እንግዳ ነገር ነው፤ ሔዋን ቃየንን ስትወልድ ልጅ ከአዳም አገኘሁ አላለችም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ስለዚህ ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እያንዳንዱ ሕጻን ልጅ የሚመጣው ከእግዚአብሔር በመሆኑ ሔዋን ትክክል ናት። የትኛዋም ሴት በማሕጸኗ ውስጥ ልጅ ልትጸንስ አትችልም። እግዚአብሔር ብቻ ነው ይህን ተዓምር ሊያደርግላት የሚችለው።
ወሲብ መልካምም ክፉም ነው። ወሲብ በጋብቻ ውስጥ መልካም ነው፤ ከጋብቻ ውጭ ግን ክፉ ነው።
እጮኛሞች ከሰርጋቸው ቀን በፊት ግንኙነት ቢያደርጉ ክፉ ነው። ከተጋቡበት ቀን ጀምሮ ቢያደርጉ ግን መልካም ነው።
የተቀደደ መጋረጃ የሞት ሕይወትን ያመጣል
ገነት ማለት ምን ማለት ነው?
መኃልየ መኃይል 4፡12 እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።
ሴት የተመሰለችው በዙርያዋ አጥር እንዳላት ገነት ነው። ማሕንዋ እንደ ሕይወት ምንጭ ነው ምክንያቱም ከማሕጸንዋ ውስጥ በሕጻን ልጅ መልክ ሕይወት ይመነጫል።
ነገር ግን ይህ ምንጭ በድንግልና መጋረጃ ተዘግቷል። የሴት ልጅ ማሕጸን በድንግልና ሕግ ታትሟል።
እግዚአብሔር የሴቲቱን ድንግል ማሕጸን የእግዚአብሔር ልጅ ሕጻኑ ኢየሱስ እንዲወለድበት ፈልጎ ነበር። በዚያ መንገድ በድንግልና በታተመ ማሕጸን ውስጥ የዘላለም ሕይወት በሕጻን ልጅ መልክ ሊጸነስ ይችል ነበር። ከዚያም የሴቲቱ ማሕጸን የሕይወት ዛፍ ይሆን ነበር። ኢየሱስም ከተወለደ በኋላ አድጎ ቅዱሳንን ሁሉ ከምድር አፈር ይጠራቸው ነበር።
በዚህ መንገድ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ዘር ይሆን ነበር። ማለትም ለሰዎች ሁሉ የዘላለም ሕይወትን መስጠት የሚችል አንድ ልጅ ይሆን ነበር።
ሰይጣን የሴቲቱን የድንግልና ማሕተም መቅደድና ከተቀደደው ድንቅልናዋ ጀርባ ማሕጸንዋ ውስጥ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ልጅ እንዲጸነስ ማድረግ ፈለገ። በዚያም መንገድ የተወለደው ልጅ ጊዜያዊ ሕይወት ነው የሚኖረው፤ ማለትም እስከሚሞት ድረስ ብቻ ይኖራል። ከዚህም የተነሳ የሔዋን ማሕጸን መልካምና ክፉውን የሚያሳውቅ ዛፍ ይሆናል ምክንያቱም በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ከተወለዱ ሰዎች መካከል አንዳንዶች ኢየሱስ ክርስቶስን ይቀበሉታል፤ ይህም መልካም ሲሆን አንዳንዶች ግን ኢየሱስ ክርስቶስን አንቀበልም ይላሉ፤ ይህም ክፉ ነው።
የሴቲቱን ማሕጸን ለመጠቀም በሔዋን አእምሮ ውስጥ ሁለት መናፍስት ማለትም ክርስቶስ እና ሰይጣን እየተፎካከሩ ነበር።
እነዚህ በገነት መካከል የሚገኙ የሕይወት ዛፍ እና የእውቀት ዛፍ ናቸው። ገነት የሚወክለው ሴቲቱን ነው። “የገነት መካከል” ደግሞ የሚወክለው የአካሏን መካከለኛ ቦታ ነው። ይህም ማሕጸንዋ የሚገኝበት ቦታ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለሔዋን ወሲባዊ ግንኙነት የምታደርግበት ብልት ሰጥቷት እንዴት እንደምትጠቀምበት ግን ምርጫውን ለእርሷ ተወላት። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ነጻነትን ሰጥቷል።
እግዚአብሔር ለአዳምም ወሲባዊ ግንኙነት ማድረጊያ ብልት ሰጠው። አለዚያ ሲቲቱ እና አዳም የተሳሳተ ምርጫ ሊያደርጉ አይችሉም ነበር። ነጻ ፈቃድ ማለት የሚፈልጉ ከሆነ የተሳሳተ ምርጫ የማድረግ መብት አላቸው ማለት ነው።
ዘፍጥረት 3፡4 እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም፤
ይህ ማለት እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሙሉ በሙሉ መካድ ነው።
እያንዳንዱ ስሕተት ራሱን እውነት ለማስመሰል ጥቂት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቀስ ያደርጋል፤ ነገር ግን ሁልጊዜ የሆነ ቦታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ነገር በማዳመጧ ሴቲቱ እጣ ፈንታዋ ክፉ ሆነባት።
የማንነታችን መፈተሻ ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን እያንዳንዱን ቃል ማመን አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት ያገኘን የመሰለን ጊዜ ወዲያው ልባችን ከእምነት ፈቀቅ እያለ መሆኑን መረዳት አለብን። ነፍሳችን ያላት ቦታ እምነትን ማስተናገድ የሚችል ብቻ ነው። ጥርጣሬ ወደ ልባችን እንዲገባ በፈቀድን ጊዜ እምነት ከልባችን ወጥቶ ይሄዳል፤ አለማመን ደግሞ በቦታው ተተክቶ ይቀመጣል። በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሴቲቱ ውስጥ መቆየት አልቻለም። መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው ከእምነት ጋር ብቻ ነው።
ከወሲባዊ ግንኙነት መወለድ ማለት የድንግልና መጋረጃ በተቀደደበት ማሕጸን መወለድ ነው፤ ይህም እንደምንሞት ያመለክታል።
እግዚአብሔር ትሞታላችሁ ብሎ ነገራቸው። እባቡ ደግሞ አትሞቱም አላቸው።
የእባቡ መልስ የሚከተሉትን ይመስላል። ወሲባዊ ግንኙነት ካደረጋችሁ እንዴት ትሞታላችሁ? መዋለድና ምድርን መሙላት አለባችሁ። እግዚአብሔር ትሞታላችሁ ሲል ለአለማወቅ ትሞታላችሁ ማለቱ ነው። ወሲባዊ ግንኙነት ብታደርጉና በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ብትሞቱ ምድር እንዴት ነው ልትሞላ የምትችለው?
ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።
መብላት ወሲባዊ ግንኙነትን የሚገልጽ ተምሳሌት ነው። መብላት ምግብ ወደ ሴት ሆድ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል፤ ሆድዋም ክብደቷ ሲጨምር ያብጣል። ወሲባዊ ግንኙነት ሕጻን ልጅ እንዲጸነስ ያደርጋል፤ ይህም ጽንስ የሴት ሆድ እንዲያብጥ ያደርጋል።
ይህ ከላይ ያየነው ቃል ከማመንዘር ጋር የተያያዘ መሆኑ በራሱ ያለ ምክንያት አይደለም፤ ማመንዘር ሕገወጥ ድርጊት ነው።
ሴቲቱ ወሲባዊ ግንኙነት አድርጋ ቃየንን ከወለደች በኋላ ቃየንን ያገኘችው ከእግዚአብሔር ነው በማለት ስሕተት መስራቷን ካደች። ሕይወት ሁሉ የሚገኘው ከእግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን ከእግዚአብሔር አገኘሁ ማለቷ እውነት ነው።
ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።
ነገር ግን ቃየን ከአዳም ነው የመጣው አለማለቷ እንግዳ ነገር ነው።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
ከወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ ሕይወት በሙሉ በ1,000 ዓመት እንደሚሞት፤ ማለትም በእግዚአብሔር አቆጣጠር በአንድ ቀን እንደሚሞት አላወቀችም።
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የሚቃወም ሰው ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ሕብረት እያቋረጠ ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች የተቃወሙትን ቃል መንፈስ ቅዱስ አይገልጥላቸውም። ያ ትምሕርት በተቃወመው ሰው አእምሮ ውስጥ ሁሌ ስሕተት ሆኖ ይቀራል ምክንያቱም እውነት ከመጽፍ ቅዱስ ቃል ልትለይ አትችልም። ሔዋን የሰራችው ስሐተት በጣም ከባድ ስሕተት ከመሆኑ የተነሳ የሰውን ዘር በሙሉ ይዞ ገደል ከተተው።
ይህ በጣም ከባድ ጉዳይ ነበረ። የሰው ዘር ውስን ዕድሜ እና ሞት በሚያስከትለው ወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ነው የሚባዛው ወይስ የሴቲቱ ማሕጸን በድንግልና ለሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ማደሪያ ሆኖ እርሱም ሲወለድ ቅዱሳንን ሁሉ በቃሉ ከአፈር ውስጥ ጠርቷቸው በውስጣቸው የዘላለምን ሕይወት ያኖራል?
ከወሲባዊ ግንኙነት በመወለዳችን ምክንያት አካላችን አስቀያሚ ጠባሳ ይዞ ይመጣል፤ እርሱም ሆዳችን ላይ የምናየው እምብርት ነው።
ይህ በአካላችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው። ትርጉሙም እኛ ያለ ዘላለም ሕወት ነው የተወለድነው ማለት ነው።
ከዚህ በታች በፎቶ እንደምታዩት ባለ እምብርት ብርትኳን ነን፤ ብርትኳኑ ትልቅ እምብርት አለው፤ ይህም በውስጡ የሕይወት ዘር እንደሌለ ያመለከታል።
ከወሲባዊ ግንኙነት ስለተወለድን ከ1,000 ዓመት በማይበልጥ ዕድሜ ውስጥ እንሞታለን።
ረጅሙ የእትብት ገመድ እግዚአብሔር የሰጠንን ነጻ ፈቃድ ያመለክታል። እግዚአብሔር በዚህ መንገድ እንድንወለድ አላሰበም። እትብት ከእናታችን ጋር ያገናኘናል፤ እናታችንንም ከእናቷ ጋር እያለ እስከ የሕያዋን ሁሉ እናት እስከሆነችው ሔዋን ድረስ ያገናኘናል። ሴቲቱ ውሳኔዋን ካደረገች በኋላ እግዚአብሔር ወሲባዊ ግንኙነትን ፈቀደ፤ ነገር ግን የፈቀደው በጋብቻ ውስጥ በወንድ እና በሴት መካከል ብቻ ነው። ስለዚህ (በጋብቻ ውስጥ) የመልካም ነገር ተምሳሌት ሲሆን (ከጋብቻ ውጭ ደግሞ) የክፉ ተምሳሌት ነው። ነገር ግን ሔዋን ያደረገችው ምርጫ ውጤቱ ጸንቷል፤ በጋብቻ ውስጥ የተወለደም ከጋብቻ ውጭ የተወለደም ይሞታል። እስከ ዛሬ ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው ሞትን ያመለጡ፤ እነርሱም ሔኖክ እና ኤልያስ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ ዳግም በሚመጣበት ጊዜ የምትነጠቀዋ ሙሽራ ተምሳሌት ናቸው።
ሔዋን ሞትን በመረጠች ጊዜ ሕይወት የሆነው መንፈስ ቅዱስ በእርሷ ውስጥ ሊቆይ አልቻለም። ሔዋን የእግዚአብሔርን ቃል መጠራጠር መረጠች (ይህም ሞት ነው)፤ ቀጥሎ ደግሞ በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ሕይወትን ማስቀጠል ፈለገች (ይህም ስጋዊ ሞትን ያስከትላል)።
በውስጧ ይኖር የነበረው መንፈስ ቅዱስ ከነዚህ ሁለት ድርጊቶች ማናቸውንም ሊደግፍ አልቻለም።
ስለዚህ በሔዋን የደም ስሮች ውስጥ ሞልቶ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ለቆ ወጣ፤ እግዚአብሔርም የደም ስሮቿ በደም እንዲሞሉ አደረገ፤ ይህም ደም ሰዎችን ለጊዜው ለውስን አመታት በሕይወት ማቆየት የሚችል ነው። ከዚያ በኋላ ሔዋን በላይዋ ላይ የሞት ፍርድ የተሸከመች ሴት ሆነች ምክንያቱም ሕይወቷ ከ1,000 ዓመታት ዕድሜ በላይ መቆየት አይችልም። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ሰው ሊሞት የሚችልበት ብዙ ዓይነት መንገድ መኖሩን አለማወቋ ነው።
ትዕቢትና እኔነት ሐጥያትን ወለዱ
ዘፍጥረት 3፡5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።
ሰይጣን በተንኮሉ እንዴት እንዳታለላት ተመልከቱ። ከሁሉ በፊት አነጣጥሮ የመታው ድክመቷን ነው፤ ማለትም ኩራቷን። ሰዎች በራሳቸው መኩራታቸው በተፈጥሮ ያለባቸው ትልቅ ድክመት ነው። ሰይጣን ይናገራት የነበረው ነገር ሁሉ ወደ ራሷ እንድትመለከት የሚያደርግ ነበረ።
ዓይኖችሽ ይከፈታሉ። ዓይን የማስተዋል ወይም የጥበብ ተምሳሌት ነው። በሌላ አነጋገር ሰይጣን እያላት የነበረው በጣም አስተዋይ እንደምትሆንና ሁሉንም ነገር የመረዳት ብቃት እንደሚኖራት ነው።
አሁን የሁሉ መቋጫ መጣ።
እንደ እግዚአብሔር ትሆኛለሽ፤ ፈጣሪና የምትመለኪ አምላክ ትሆኛለሽ።
አምላክ ከሆነች በማሕጸኗ ውስጥ ሕይወት መፍጠርና ልጅ መውለድ ትችላለች። የሕያዋን ሁሉ እናት ትሆናለች። ሰው ሁሉ ወደ እርሷ ይመለከታል። ሰው ሁሉ እንደ ታላቅ ሴት እንደ ጀግና ያመልካታል። ያላንቺ ልንፈጠር አንችልም ነበር ይሏታል።
የሴት ማሕጸን ብቻ ነው ሕይወትን ወደ ምድር ሊያመጣ የሚችለው። አማልክት ብቻ ናቸው መፍጠር የሚችሉት። ስለዚህ ሔዋን አምላክ ትሆናለች። የሰው ትዕቢት ከዚህ አልፎ ሊሄድ አይችልም።
ልክ እንደ እግዚአብሔረ መልካም እና ክፉውን ታውቃለች። እግዚአብሔር እስከዚያ ቀን ድረስ መልካም እና ክፉውን ስለምታሳውቀዋ ዛፍ እንዳታውቅ ሰውሮባት ነበር። አሁን ግን ለራሷ ለማወቅ ዕድል አገኘች። ስለዚህ የዚህችን ዛፍ ፍሬ በልታ ከእግዚአብሔ ጋር እኩል ልትሆን ነው።
እስከዚያ ቀን ድረስ አዳም ነበረ የሚያስተምራት። አዳም አስተማሪዋ ነበረ። ሔዋን ከአዳም በተወሰደ አጥንት ተሰርታ ከመፈጠሯ በፊት እግዚአብሔር አዳምን አስተምሮት ነበር። ስለዚህ በእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ሰውየው የሴቲቱ አስተማሪ ነበረ። አዳም ለሔዋን የእውቀትን ዛፍ አትንኪ ብሎ ነግሯት ነበር። አሁን ግን ስለዚህ የእውቀት ዛፍ ያላት እውቀት የሚያድግበትና እስከ ሰማይ የሚመጥቅበት እርሷም እስከ እግዚአብሔር እውቀት ደርሳ አዳምን የምታስተምርበት ዕድል አገኘች። ይህ እጅግ በጣም የሚያጓጓ ክብር ነው። እርሷም ይህን በማሰብ በትዕቢት ተሞላች።
ሴቲቱ ሰውየውን ልታስተምር አሰበች።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ሰውየው የቤተክርስቲያን ባል የሆነውን ክርስቶስን ማለትም ቃሉን ይወክላል።
ቤተክርስቲያንን በቃሉ በኩል ማስተማር ያለበት ኢየሱስ ነው። ዛሬ ግን ቤተክርስቲያን አስተዋይ ነኝ ብላ በማሰብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ብላ ይምታስበውን ስሕተት ሁሉ ልታርም ትፈልጋለች። ስለዚህ ቃሉ ማለትም ኢየሱስ ከሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን በራሷ መንገድ እየተመራች ወደፈለገችበት አቅጣጫ ስንትቀሳቀስ ዕጣ ፈንታዋ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው የሚሆነው።
ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ተናገረ፤ በዚህም ምሳሌ ውስጥ አንድ ንጉስ ለልጁ ሰርግ ደግሶ አዘጋጅቶ መልካም የሆኑ እንግዶቹን (የዳኑ ክርስቲያኖችን) ሁሉ ጋበዘ፤ ተጋባዦቹ እንግዶች ሁሉ ግን በየራሳቸው የግል ጉዳይ ተጠምደው ነበር። ስለዚህ ንጉሱ አልፈልጋችሁም አትምጡ አላቸው። ይህንን ማስጠንቀቂያ ልብ ማለት አለብን።
ሔዋን በመሃይምነት ባሕር ላይ መንሳፈፍ የምትችል መሰላት
ታላቅ የመሆን ቅዠትና እራሷን አዋቂ አድርጓ መቁጠሯ ሔዋን የራሷን ዕጣ ፈንታ ልትወስን የምትችልበትን መንገድ የጀመረች እንዲመስላት አደረጋት። ልታደርግ ያሰበችው ምን ያህል የጅል ድርጊት መሆኑን አለማወቋ በምኞቷ ታላቅነት ተሸፋፍኖ የሚቀር መስሏታል።
ሒትለር ጭካኔውና የፈጸመው ግፍ ለአይሁዶች ካለው ጥላቻ ጋር ሆኖ መንግስቱን ለ1,000 ዓመታት የሚያቆይለት መስሎት ተታለለ። እርሱም በስልጣኑ ከ12 ዓመታት በላይ አልዘለቀም፤ ብዙ ግፍ የፈጸመባቸው የሞት ካምፖቹም የዓለም ሕዝብ ሁሉ ለእስራኤል እንዲያዝኑና በ1947 የተባበሩት መንግስታት ለእስራኤል የራሳቸው የሆነ ሃገር እንዲሰጧቸው ምክንያት ሆኑ። ስለዚህ ሒትለር 6 ሚሊዮን አይሁዶችን መጨፍጨፉ አይሁዶች ማንም ሊያሸንፈው የማይችል ጠንካራ የአየር ኃይል እና የራሳቸው ሃገር እንዲኖቸው ምክንያት ሆነ። ይህ ሁሉ ሰዎች ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ማወቅ እንደማይችሉ ያሳያል። ፍጻሜያችን ወይም ዕጣ ፈንታችን በእኛ እጅ አይደለም።
ዘፍጥረት 3፡6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ዛፉ ለመብላት መልካም ነበረ። ነገር ግን ፍጥረታዊ ምግብ አይደለም። በኤድን ገነት ውስጥ መብላት የሚገልጉት የዛፍ ፍሬ ሁሉ አስቀድሞ ተሰጥቷቸዋል።
የእውቀት ዛፍ የሰጣት ምግብ ለሃሳብ ወይም ለአእምሮ የሚሆን ምግብ ነው።
“ይኸውልሽ” አላት እባቡ፡- “እግዚአብሔር ተባዙ ብሏችኋል። ለእንስሳት ሁሉ የተናገራቸው ይህንኑ እንዲያደርጉ ነው። እንስሳት ሁሉ ደግሞ የሚባዙት በወሲባዊ ግንኙነት ነው። እግዚአብሔር እናንተንም በስጋዊ የሰው አካል ውስጥ ነው የፈጠራችሁ። ስጋ የለበሱ ፍጡራን ደግሞ ሊዋለዱ የሚችሉበት ብቸኛ መንገድ ወሲባዊ ግንኙነት ነው። ስለዚህ ቶሎ ብላችሁ ብትጀምሩ ቶሎ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መፈጸምና መባዛት ትችላላችሁ።”
ይህ ማብራሪያ ሴቲቱ በጣም ሐይማኖተኝነት እንዲሰማት አደረገ። ይህንን ድርጊት ብትፈጽም ሴቲቱ የእግዚአብሔርን ቃል የምትታዘዝ መሰላት።
ሐይማኖት ያመጣብን ትልቁ እርግማን ይህ ነው። አንድ ሰው በሚከተለው ጠባብ አመለካከት መሰረት መጽሐፍ ቅዱስን ሲተረጉም ብዙ ነገሮችን ያበላሻል። በድንግልና የመውለድ አማራጭ ስለመኖሩ አንዳችም የምታውቀው ነገር አልነበረም።
ደግሞም የእግዚአብሔርን ቃል ፊት ለፊት የሚቃረን መልእክት ለመቀበል ዝግጁ ሆነች፡- በእርግጥ አትሞቱም።
“ይኸውልሽ” አላት እባቡ፡- “ወሲባዊ ግንኙነት ብታደርጉና እግዚአብሔር ወዲያ ቢገድላችሁ የሰው ዘር እንዴት ሊባዛ ነው? በወሲባዊ ግንኙነት ለመባዛት ብዙ ወንዶች ልጆችና ብዙ ሴቶች ልጆች ያስፈልጓችኋል። ይህም ረጅም ጊዜ ይወስዳል። ከዚያ በኋላ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችሽ እርስ በርሳቸው ተጋብተው ብዙ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን መውለድ አለባቸው።”
“በቂ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ሳትወልጂ ልትሞቺ አትችይም። ስለዚህ እግዚአብሔር በስጋ ትሞታላችሁ ማለቱ አይደለም። እግዚአብሔር ሊነግራችሁ የፈለገው ስለ እውቀት ዛፍ ላለማወቃችሁ ትሞታላችሁ ነው። ከዚያ በኋላ ስለ እውቀት ዛፍ ሁሉን ታውቃላችሁ። የዛኔ መልካሙንም ክፉውንም ስለምታውቁ ክፉውን ወደ ጎን እየተዋችሁ መልካሙ ላይ ማተኮር ትችላላችሁ። በተጨማሪ ልጆቻችሁንም እንዴት ከክፉ መራቅ እንደሚችሉ ታስተምራላችሁ። ስለዚህ ለሰው ዘር በሙሉ ምን ያህል ጠቃሚ እንደምትሆኚ አስቢ።”
ሴቲቱ እንዲህ ዓይነቱ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃረን አስተሳሰብ ለመከተል በአእምሮዋ ውስጥ ስትወስን መንፈስ ቅዱስ ትቷት ሄደ። ከዚያ በኋላ ሕይወቷን ለተወሰኑ ዓመታት ለማቆየት እግዚአብሔር የደም ስሮቿን በደም እና የወሲባዊ ፍላጎት እንዲኖራት በሚያደርጉ ሆርሞኖች ሞላ።
ከዚያ በኋላ ዕርቃን የነበረውን ገላዋን አየችና እጅግ ውብ መሆኗን እንዲሁም ለወሲባዊ ግንኙነት ማራኪ መሆኗን ተረዳች።
ጥበብ ሲኖራችሁ አንድን ሌላ ሰው በራሳችሁ ተጽእኖ ስር እንዲወድቅ ማድረግ ትችላላችሁ። በሴትነቷ ገላዋን ለወንድ በማቅረብ ወንድን በተጽእኖዋ ስር ማድረግ እንደምትችል አወቀች። በዚያን ጊዜ የዓለም እጅግ ጥንታዊ ሙያ የተባለው የግልሙትና ጽንሰ ሃሳብ ተፈጠረ።
“ፍሬውን ወሰደች።” ይህ ሐጥያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተለማመደችበት ነው። እባቡ ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ ከፍተኛው ፍጡር እንደመሆኑ እንደ ሰው ይመስል ነበር። ስለዚህ በቀላሉ አሽኮረመማትና ድንግልናዋን ወሰደ።
ከዚህ አንድ የምናስተውለው እውነት አለ። እባቡ ሴቲቱን እስኪየስታት ድረስ ስድስት ቁጥሮች ብቻ ነው የፈጀበት። አዳም ግን ወደ ሐጥያት የወደቀው በፍጥነት ነው። ሴቲቱ ከአዳም ጋር አልተከራከረችም ወይም ልታሳምነው ምንም አልተናገረችም። ይህ ለምን ሆነ?
አዳም እግዚአብሔር ስላስተማረው እጅግ ጠቢብ ነበረ።
ሴቲቱ ወደ አዳም ተመልሳ ስትመጣ ከእባቡ ጋር ከዋለች በኋላ መለወጧን አይቷል። የጣቶቿን ጫፍ ቀስ ብሎ ቢጨምቃቸው ቀይ ሲሆኑ ማየት ይችል ነበር። ገላዋ አሁን በውስጡ ደም አለው። ይህም በኤድን ገነት ለመኖር ብቁ እንዳትሆን አድርጓታል።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 … ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
ሴቲቱ እንዴት ሐጥያት እንደምትሰራ ተምራለች። በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ሕይወትን ስለመፍጠር ተምራለች። ከዚህም የተነሳ ወደ ሞት መሄድ ጀምራለች።
ሐጥያት ሞትን ያስከትላል።
ሮሜ 6፡23 የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤
ስለዚህ ሴቲቱ ራሷን ለአዳም ባቀረበች ጊዜ እጅግ በጣም እርሷን ከመውደዱ የተነሳ ከእርሷ ጋር ለመኖር ብሎ ሐጥያት መስራትን መረጠ።
እርሷ ግን አስቀድማ ከእባቡ አርግዛ ነበር። ይህም ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሐየር ፈቃድ ውጭ ነው። ሔዋን ከዚያ ወዲያ በድንግልና ለሚወለደው ሕጻን የሚሆን ድንግል ማሕጸን አልነበራትም።
አዳም ስለፈጸችው ዝሙት በድንጋይ ሊወግራት ይገባ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር ሕጻን ልጅን በድንግልና የምትወልድ አዲስ ሚስት ይፈጥርለት ነበር።
ስለዚህ አዳም ከሚስቱ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት በፈጸመ ጊዜ ከሐጥያቷ ጋር ተባበረ ምክንያቱም ይህ ድርጊቱ በሔዋን ማሕጸን ውስጥ ለነበረው የሰውና የእባብ ክልስ ዘር ጥበቃ አደረገለት፤ ይህም ክልስ ዘር ቃየን ነው። በዚህ መንገድ የአውሬው ባህርይ ወደ ሰው ዘር ውስጥ በመግባቱ ስድስት ሺ ዓመታት ሙሉ ጦርነትና ደም መፋሰስን አስከተለ።
አዳም ሚስቱን ሊያዳምጥ በወሰነበት ሰዓት የሰው ዘር በወሲባዊ ግንኙነት እንዲዋለድ በማድረጉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላለፈ። ስለዚህ በደም ስሮቹ ውስጥ የነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ አዳምን ለቆ ወጣ፤ እግዚአብሔርም አዳም ለተወሰነ ጊዜ በሕይወት እንዲቆይ የአዳምን ደም ስሮች በደም ሞላለት። ከዚይም የተነሳ አዳምም ሞት የተፈረደበት አካል ውስጥ ኖረ። የእግዚአብሔርም የመጀመሪያ እቅድ ተበላሸ። የሰው ዘር ብዙ ሐዘን እና መከራ በሚያመጣ አንሸራታች ቁልቁለት ላይ መራመድ ጀመረ።
ሮሜ 5፡12 ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤
ሰዎች የፈለጉትን ያህል ቢጥሩ እንኳ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም
ዘፍጥረት 3፡7 የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።
እኛ ሰዎች ሐጥያት ስንሰራ ያረደግነውን የመሸፋፈን ዝንባሌ አለን። ለዚህ ነው የሐጥያተ መድሐኒቱ ሐጥያታችንን ለእግዚአብሔር በመናዘዝ ንሰሃ መግባት የሆነው።
የአዳም እና የሔዋን የመጀመሪያ ሐጥያት ራቁታቸውን መሆናቸውን እንዲያዩ አደረጋቸው። እነርሱም ብልቶቻቸውን ለመሸፈን ሞከሩ። ስለዚህ የመጀመሪያው ሐጥያት በወሲባዊ ግንኙነት ልጆችን መውለድ ነው። የዘላለም ሕይወት በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ሊመጣ አይችልም። ስለዚህ ልጆች የሚወለዱት ከዓመታት በኋላ በሚሞት ስጋ ውስጥ ነው። እግዚአብሔርም የሰውን ዕድሜ እስከ 1,000 ዓመት አድርጎ ገደበው።
የእባቡ ወሲባዊ ድርጊት የሴቲቱን የድንግልና ማሕተም ቀደደው፤ ከዚህም የተነሳ ሴቲቱ ደም ፈሰሳት።
ይህም የአውሬውን ባህርይ ይወክላል፤ አውሬው ዝንባሌው ግፍ መፈጸምና ደም ማፍሰስ ነው።
የሰው ባሕርይ ግን ከጥፋት ውሃ በፊት እጅብ በመበላሸቱ ምክንያት ሁለት ቀን ወይም 2,000 ዓመታት ሳይሞላቸው እግዚአብሔር በሙሉ አጠፋቸው።
ክፋት፣ ወሲብ፣ እና ነጻ ፈቃድ በአንድ ላይ ሲሆኑ ውጤታቸው እጅግ በጣም መጥፎ ሆነ።
ከዚያ እግዚአብሔር በኖኅ ቤተሰብ ውስጥ በነበሩ ስምንት ሰዎች ሥራውን እንደገና ጀመረ።
ደግሞም የሰውን ዕድሜ ወደ ሰባ ዓመታት አሳጠረው። ይህ የዕድሜ ገደብ በመደረጉ እግዚአብሔር ይመስገን ለአራት ቀናት (ማለትም 4,000 ዓመታት) የሰው ዘር በምድር ላይ መቆየት ችሏል። አሁን ደግሞ የሕዝብ አለልክ መብዛትና የክፋት መጨመር እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጠው እግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎች መብዛታቸው እንደ ደራሽ ውሃ ወደ አርማጌዶን ጠራርጎ ይዞን እየሄደ ነው።
አሁንማ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ የሚቃወሙ ሕጎች ሁሉ እየጸደቁ ነው። ነፍስ መግደል የሆነው ጽንስን ማቋረጥ በነጻ ምርጫ እና በሐይማኖታዊ ነጻነት ሰበብ እንዲፈቀድ እየተደረገ ነው። ጋዜጦች በዓለም ዙርያ እንደ ወረርሽኝ የተስፋፋውን ወሲባዊ ሐጥያት እና ግፍ በየቀኑ ይተርኩልናል። ኢየሱስ ስለ ዘመናችን የገለጸው ከሰዶም እና ከገሞራ ዘመን ጋር በማስተያየት ነው።
አዳም እና ሴቲቱ ዓለምን በሰው ዘር ለመሙላት የሚሆን ጊዜያዊ መፍትሄ ማየት ይችሉ ዘንድ ዓይናቸው በራ፤ ነገር ግን ይህ መፍትሄ ለብዙ ሞትና መከራ መንስኤ የሆነ መፍትሄ ነው። ወሲብ ከሕመምና ከስቃይ ነጻ የሆነ ዘላለማዊ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም።
አዳም እና ሴቲቱ ራቁትነታቸውን ለመሸፈን የበለስ ዛፍ ቅጠል ሰፉ። ይህም የሰው ሰራሽ ሐይማኖት ተምሳሌት ነው።
ሐይማኖት ማለት ሰዎች መልካም መስለው እንዲታዩ የሚያደርግ መልካም ስራ ነው። ነገር ግን የመጀመሪያውን ሐጥያት ፈጽሞ ቸል ይለዋል።
አንድ እንስሳ ሰዎች ሐጥያት እንዲሰሩ አደረገ፤ ሐጥያትንም ተከትሎ ደም ፈሰሰ። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ልጅ የሚወለድበት ድንግል ማሕጸን አልተገኘም።
ስለዚህ በምድር ላይ ልዩ ልዩ መልካም ስራዎችን (መልካም ስራ ጥሩ ነው) የሚሰሩ ሐይማኖቶች በሙሉ በመልካም እና በክፉ በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ውጊያ በሚደረግበት በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ምንም ዋጋ የላቸውም።
ሐይማኖት ማለት ለሰዎች የሚስማማ ስርዓት መፈጸም እና ይህንንም ስርዓት የሰው ቅንነት ተቀባይነት ያስገኝለታል ብሎ በማሰብ ለእግዚአብሔር የማቅረብ ልማድ ነው።
ለሰዎች ሐይማኖታዊ እንቅስቃሴ እግዚአብሔር ምላሽ የሰጠው ሰዎችን ከኤድን ገነት በማስወጣት ነው።
በመልካም ስራዎችም ይሁን በብልህ ሃሳቦቻችን ራሳችንን ማዳን አንችልም።
መዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሰው የሚመጣ ዕቅድ ነው፤ ይህም እቅድ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው።
ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን የእግዚአብሔርን እቅድ በጥንቃቄ መከተል አለበት ምክንያቱም እግዚአብሔር በሰዎች አመለካከትና በሰዎች ጥረት ምንም አይመሰጥም።
ሰው የእግዚአብሔርን ሃሳብና የእግዚአብሔርን ሥራ መውደድ አለበት።
አዳም እና ሴቲቱ ከእግዚአብሔር ፊት ተደበቁ።
እግዚአብሔር እነርሱን ፍለጋ ወጣ።
ዛሬም እንደዚሁ ነው። አሁን በምንኖርበት በመጨረሻው ዘመን ኢየሱስ ከሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል። ቤተክርስቲያን በሙሉ በመካከሏ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ አልሰጥም ባለችበት በአሁኑ ዘመን ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ድምጽ ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑ ግለሰቦችን እየፈለገ ነው።
ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ የሚገኘው የአስሩ ቆነጃጅት (ቤተክርስቲያን ውስጥ የዳኑ ሰዎችን የሚወክሉ መልካምና ንጹህ ሴቶች) ምሳሌ ውስጥ ሙሽራው ከመምጣቱ በፊት ቆነጃጅቱ በሙሉ እንቅልፋቸውን ተኝተዋል። ከእንቅልፋቸው የሚያነቃቸው የጩኸት ድምጽ ያስፈልግ ነበር።
ያ ጩኸት ምን ነበር? ያ ጩኸት ሰነፎቹን ቆነጃጅት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰ እና ከልባሞቹ ቆነጃጅት እርዳታ እንዲለምኑ የደረገ ድምጽ ነበረ።
ይህ እስካሁን ገና አልተፈጸመም።
ማቴዎስ 25፡5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
6 እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
7 በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
8 ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።
ይህ ማለት ሁላችንም እስከ ዛሬ እንቅልፍ ውስጥ ነን ስለዚህ በምትናወጠው ዓለማችን ውስጥ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አናውቅም ማለት ነው።
ሔዋንም ስለ ገሃዱ ዓለም ምንም አታውቅም ነበር፤ እኛም እንደ እርሷ ነው የሆንነው።
ሉቃስ 18፡8 ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ይህ ጥቅስ እስካሁን ከእግዚአብሔር ቃል እየተደበቅን እንደሆነ ያሳያል ምክንያቱም እምነት የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት ብቻ ነው።
“ቤተክርስቲያናዊነት” - የቤተክርስቲያን አባል መሆን፣ ሁልጊዜ በቤተክርስቲያን ፕሮግራም ላይ መገኘት ቤተክርስቲያናችን በምትጠራበት ስም ራሳችንን መጥራት (ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ፔንቲኮስታል፣ ኒው ኤጅ፣ ሜሴጅ፣ ወዘተ.) አና ራሱን ከፍ ያደረገውን የቤተክርስቲያን ፓስተር መከተል ማለት ነው።
አዲስ ኪዳን የትም ቦታ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ብሎ አይናገርም። ይህ አምነን ከዳንን በኋላ ተደላድለን ለመኖር የምንፈጥረው ቅዠት ነው።
ነገር ግን በተዘናጋንበት ታላቁ መከራ ሊያጠምደን እየመጣብን ነው።
የቤተክርስቲያን አባል መሆናችን የሚያድነን ከበለስ ቅጠል የሰፉት ልብስ ያዳናቸውን ያህል ነው። የዳኑ ክርስቲያኖች ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ብዥታ መሆኑን ቆይተው ያስተውላሉ ምክንያቱም ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን ማየት እንዳይችሉ ይጋርድባቸዋል።
ክርስቲያኖች ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ይደበቃሉ
ዘፍጥረት 3፡8 እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
ሐጥያት ሰዎች ከእግዚአብሔር እንዲደበቁ ያደርጋል።
ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስን ብዙ የማናነበው።
ምክንያቱም ሃሳባችንን እና እምነታችንን የሚቃረኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንደሚያጋጥሙን እናውቃለን።
ስለዚህ በስራ ተጠምደን በመኖር ከእግዚአብሔር ቃል እንደበቃለን፤ ትርፍ ጊዜያችንን ደግሞ ምንም በማይጠቅሙና ጊዜ በሚያባክኑ ጉዳዮች እናሳልፋለን።
ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ቸል ስለማለታችን ማመካኛ እናቀርባለን፤ ምክንያታችንም በቂ ጊዜ አላገኘንም የሚል ነው።
እውነተኛ ማንነታችንን ደብቀን ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ስንኮርጅና ሌሎች ያደረጉትን ስናደርግ እኛም እንደ ሌሎች ትክክል ነን ብለን ስናስብ ደህንነት ይሰማናል። ምን ማመን እና ምን ማድረግ እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲነግረንና እንዲያስታውሰን አንፈልግም።
መሳሳታችንን አምነን መቀበል አንፈልግም፤ በዚህም ምክንያት ንሰሃ የመግባት አቅማችን እየጠፋ ነው።
ዋነኛው ሃሳባችንን በምክንያቶችና ራሳችንን በማጽደቅ መሸፋፈን እንመርጣለን።
መጽሐፍ ቅዱስ መሳሳታችንን ሲያሳየን ንሰሃ ለመግባት ፈቃደኛ አይደለንም። ንሰሃ ለመግባት ካለብን ሃላፊነት ተሹለክልከን ለመውጣት ቃሉ የሚናገረውን እንለውጠዋለን ወይም ደግሞ እኛ እንደምንፈልገው የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ፈልገን እናገኛለን።
መሹለክለክ የእባቦች አካሄድ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ እስካሁንም ለሕሊናችን መናገር ይችላል፤ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስን የማናነበው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረንን የማንወድ ከሆነ አሁንም ሕሊናችን ሊወቀስ ይችላል።
ልማዶቻችንና ቤተክርስቲያኖቻችን ደጋግመው ያስተማሩን ትምሕርቶች የሕሊናችንን ለስላሳ ድምጽ ሊያዳፍኑ ይችላሉ። ስለዚህ በብዙ ሰዎች መካከል ተደብቀን በሰላም መኖርን እንመርጣለን።
ብዙ ሰው ይህን ስላመነ ወይም ብዙ ሰው ይህን ስላደረገ ይህ ስሕተት ሊሆን አይችልም ብለን ራሳችንን እናሞኛለን።
ከዚያ ጠንከር ያለ ጥያቄ የሚያነሳብንን ሰው ሁሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት እንችላለን።
በጣም ብዙ ጊዜያችንን ምንም በማይጠቅሙና በሚያዘናጉ ነገሮች ላይ እናጠፋለን።
ዘፍጥረት 3፡9 እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው።
እግዚአብሔር አዳም በስጋ የትጋ እንደነበረ አውቋል።
እየጠየቀው የነበረው በመንፈሳዊ አቋሙ የት እንደነበረ ነው።
አዳም መጀመሪያ መንፈስ ሆኖ ተፈጠረና እግዚአብሔር ብዙ አስተማረው። ከዚያም እግዚአብሔር አዳምን በሰው አካል ውስጥ አኖረው፤ ይህም አካል በውስጡ ሆኖ ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ስለሚኖርበት የማይሞት አካል ነበረ። ለአዳምም ውብ በሆነችው የኤድን ገነት ውስጥ መኖሪያ ተሰጠው።
ነገር ግን ያ ሁሉ ለአዳም አልበቃውም።
እኛ ሰዎች እግዚአብሔር በሰጠን ረክተን መኖርን አናውቅበትም። ሁሌ ሌላ ነገር እንፈልጋለን፤ ይህም ለሰይጣን በር ይከፍትለታል። አዳም በሐጥያት መውደቅን መረጠ።
አዳም በስጋው ከፍ ባለ ዓለም ውስጥ ይኖር ነበር ምክንያቱም ከጊዜ ክልል ውጭ ስለነበረ በጊዜ ውስጥ ላሉ ውሱንነቶች እስረኛ አልነበረም። በመንፈስ ግን ሰማይ ብለን ከምንጠራው ከፍ ካለው መንፈሳዊ ክልል ጋር ሕብረት ያደርግ ነበር።
(አራተኛው ቀጠና እግዚአብሔር ለወደቁ መላእክት ኋላም አጋንንት ለሆኑት መኖሪያ የፈጠረው መንፈሳዊ ክልል ነው። ኢየሱስን የግል አዳኛችን አድርገን ካልተቀበልን ወደፊት እጣ ፈንታችን ወደዚህ ስፍራ መሄድ ነው። ጊዜ የአራተኛው ቀጠና አካል ነው። ለዚህ ነው ክፉ መናፍስት በአራተኛው ቀጠና ውስጥ የሚኖሩት ምክንያቱም ጊዜ ተቃጥሎ ወደሚጠፋበት የእሳት ባሕር ውስጥ እነርሱም ገብተው እንዲጠፉ ተፈርዶባቸዋል።)
አዳም ሐጥያት ለመስራት ሲወስን መንፈስ ቅዱስ ትቶት ሄደ።
ከዚያም አዳም ከእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ወጥቶ ለራሱ ፈቃድ ተላልፎ ተሰጠ።
በሕይወት እንዲቆይ ለማድረግ እግዚአብሔር የአዳምን ደም ስሮች በደም ሞላቸው። የሰው ሕይወት መንፈስ በደሙ ውስጥ ነው ያለው፤ ነገር ግን ከ969 ዓመታት በላይ በሕይወት ሊያቆየን አይችልም፤ ይህም ማቱሳላ የኖረበት ከሁሉ ረጅሙ ዕድሜ ነው።
ስለዚህ አዳም ከሰማይ ጋር የነበረውን ሕብረት ባቋረጠ ጊዜ በከፍታ ካለው ከመንፈሳዊው ክልል ወደቀ። ከጊዜ ነጻ ከሆነው ቀጠና በመውደቁ የጊዜ እስረኛ እና ጊዜ ለሚያስከትለው እርጅና ባሪያ ሆነ።
ጊዜ ማርጀትንና መበስበስን እንዲሁም ሞትን ለሚያስከትሉ ለውጦት ባሪያ ያደርገናል።
ሰው በጊዜ ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ አይችልም። በጊዜ ቱቦ ውስጥ ታፍነን በመኖራችን ከትናንት ወደ ነገ ብቻ ነው መንቀሳቀስ የምንችለው።
እግዚአብሔር አዳምን የት ነህ ብሎ በጠየቀው ጊዜ የት እንደነበረ እንዲያስታውስና በስጋም ይሁን በመንፈስ ምን ያህል ርቆ እንደወደቀ እንዲያስተውል አድርጎታል።
አዳም በደም ስሮቹ ውስጥ ደም እስካለው ድረስ በሰማይ ካለው መንፈሳዊ ክልል ጋር የነበረውን የጠለቀ ሕብረት እንደበፊቱ ሊቀጥል አይችልም።
ዘፍጥረት 3፡10 እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።
ይህ የሐጥያተኞች ሁሉ ባህርይ ነው። የእግዚአብሔርን ድምጽ ላለመስማት እንደበቃለን።
እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ የሚናገረንን መስማት አንፈልግም።
መጽሐፍ ቅዱስ ራሳችንን የምናጸድቅበትን ሰው ሰራሽ ሐይማኖት ያለበሰንን ብትቶ ጨርቅ በመግፈፍ ያለንበትን አሳዛኝ ሁኔት በትክክል እንድናይ ያጋልጠናል።
መጽሐፍ ቅዱስን ከልባችን ብንቀበለው በሕሊናችን ብርሃን ፊት እርቃናችንን ያሳየናል።
ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት መዋሸት፣ መካድ ወይም በሌሎች ሰዎች ማሳበብ አንችልም። የምንችለው መሸሽ ብቻ ነው። እግዚአብሔረ እኛን ፍለጋ ከመጣ ግን ሸሽተንም ቢሆን መደበቅ አንችልም።
ዘፍጥረት 3፡11 እግዚአብሔርም አለው፦ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?
ሰውየው ደም ስሮቹ ውስጥ ደም ያልነበረው ጊዜ ራቁቱን መሆኑን አያውቅም ነበር። የወሲብ አካላት መስራት የሚችሉት በደም እና በሆርሞን አማካኝነት ነው። ትንንሽ ሕጻናት ሆሮሞናቸው ብዙም የዳበረ ስላልሆነ ራቁትነታቸው አይታወቃቸውም።
አዳም ራቁቱን መሆኑን እንዴት እንዳወቀ እግዚአብሔረ ማወቅ ፈለገ። አዳም ራቁቱን መሆኑን ሊያውቅ የሚችለው ሰውነቱ ከተለወጠና በደም ከተሞላ ብቻ ነው።
ይህ የሚሆነው ደግሞ አዳም በፊት በውስጡ የነረውን መንፈስ ቅዱስ ከሰውነቱ ውስጥ ካስወጣና ሰውነቱ በደም ከተሞላ ነው። የነጻ ፈቃድ ኃይል ይህን ሁሉ ማድረግ ይችላል። ሰው እግዚአብሔርን እምቢ ማለት ይችላል።
ሰው ሲፈልግ ራሱን ማጥፋት ካልቻለ ነጻ ፈቃድ የለውም።
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን የጠየቀው ለምን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት እንደጣለ ነው።
እግዚአብሔር ለአዳም ሁሉን ሰጥቶት ነበር፤ አዳም ግን ምንም ለማይጠቅም ነገር ብሎ እግዚአብሔር የሰጠውን ሁሉ ጣለ።
እግዚአብሔር አዳም ለምን እንዲህ እንዳደረገ ማወቅ ይፈልጋል።
አዳም ማመካኛዎችን በማቅረብ ጥፋቱን በሚስቱና በእግዚአብሔር ያላክካል
አዳምም ሐጥያቱን በመናዘዝ ፈንታ ሰዎች ሁሉ የሚሰጡትን መስልስ ይመልሳል፡-
መልሱም ማመካኛ እና በእግዚአብሔር እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ማመካኘት ነው።
ዛሬም ሰዎች ሐጥያታቸውንና ስሕተታቸውን ለመሸፋፈን ብዙ ማመካኛ ያቀርባሉ። ሰዎች በራሳቸው ላለባቸው ጉድለት ወይም ድክመት ሌሎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ። በምድር ላይ ለሚሆኑ ክፉ ነገሮች በየዕለቱ ሰዎች እግዚአብሔረን ተጠያቂ ሲያደርጉ ትሰማላችሁ።
የሰው ባህርይ በ6,000 ዓመታት ውስጥ አልተለወጠም።
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከኤድን ገነት አባረረው፤ እኛም ደግሞ የማንጠነቀቅ ከሆንን ከእንቅልፋችን ዘግይተንም ቢሆን እንድንነቃ ለ3.5 ዓመታት ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ያባርረናል።
ዘፍጥረት 3፡12 አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።
ይህ የሐጥያተኛ ሰዎች ዓይነተኛ ባህርይ ነው። ለሰራነው ስሕተት በሌሎች ሰዎች እናሳብባለን።
አዳም መጀመሪያ በሴቲቱ አሳበበ፤ ጥፋቱ የእርሷ ነው አለ።
ለሰራው ስሕተት በራሱ ሃላፊነትን አልተቀበለም። ስለፈጸመው ድርጊት ተጠያቂነት እንዳለበት አላሰበም።
ከዚያ ቀጠሎ ደግሚ በእግዚአብሔር አሳበበ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ነው ሴቲቱን የሰጠው። በአዳም አስተሳሰብ እግዚአብሔር አጥፍቷል። እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎች ለክፉ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን ጥፋተኛ ያደርጋሉ።
የአዳም ትልቅ ስሕተት ሐጥያት መስራቱን አለማመኑ ነው። ልክ ዛሬም ሰዎች እራሳቸውን ለማጽደቅ ማመካኛዎችን እንደሚፈጥሩት አዳምም እያመካኘ ነበር።
ማመካኛዎችና ሌሎች ሰዎች ጥፋተኛ ማድረግ የትም አያደርሱንም።
ሐጥያተኞች ራሳቸውን ቅዱስ አድርገው ያስባሉ፤ ቅዱሳን ግን ሐጥያተኛ መሆናቸውን ስለ ራሳቸው ያውቃሉ።
ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅ የሆነ ሰው አንድ ጊዜ ሲናገር፡- “ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም” አለ።
ዘፍጥረት 3፡13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ።
ሴቲቱ ሳየችው ባህርይ ዛሬም የምናየው የሰው ባህርይ ነው።
እኔ አይደለሁም ተጠያቂ፤ እባቡ ነው። እባቡ አሳስቶኝ ነው።
ነገር ግን ይህ ድርጊት በሴቶች አእምሮ ውስጥ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አንድን ሰው ኮርማ ቢሉት ደስ ብሎት ፈገግ ይላል። ኮርማ መባሉን እንደ አድናቆት አድርጎ ይቀበለዋል። የሚሰጠው ትርጉም ጠንካራ ሰው ማለት ነው።
አንዲትን ሴት ግን ላም ወይም ሴት ውሻ ቢሏት እንደ ሰደቧት ትቆጥራለች። በጥንት ጊዜ አንድ እንስሳ ሴቲቱን አታሏታል፤ ሴቶችም ከዚያ አሳዛኝ አጋጣሚ እስካሁን አላገገሙም።
ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
እግዚአብሔር ለእባቡ ስላደረገው ድርጊት አብራራለት። እባቡ በዚያ ጊዜ ከዝንጀሮዎች በላይ ልባም የሆነ እንስሳ ነበረ።
ከዚያም እግዚአብሔር እባቡን ረገመውና በደረቱ የሚሳብ እንስሳ አደረገው።
እባቡ ለሴቲቱ፡- “ዓይኖችን ይከፈታሉ” አላት። ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር የእባቡን የዓይን ቆብ ስለወሰደበት እባብ መጨፈን አይችልም። የእባብ ዓይኖች ዓይኑን ከቆሻሻ እና ከጎጂ ነገሮች በሚከላከል ስስ ቆዳ የተሸፈነ ነው። ነገር ግን በጭራሽ ዓይኖቹን መክደን ወይም መጨፈን አይችልም። እባብ ዓይኖቹን መጨፈን ስለማይችል መተኛትና ማንቀላፋትም አይመቸውም።
እባቡ “በውኑ” ብሎ መናገር በመጀመሩ እውነት እየተናገረ ይመስል ነበር፤ ነገር ግን “እግዚአብሔር ብሏልን?” ብሎ ሲጠይቅ እየዋሸ ነበር።
አሜሪካኖች ከሃገራቸው መጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ጋር ያደረጉትን ስምምነት ባፈረሱ ጊዜ የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች እንዲህ አሉ፡- “ነጮች በመንታ ምላስ ይናገራሉ”።
ስለዚህ እባቡ እውነትን ከሐሰት ጋር በመቀላቀሉ እግዚአብሔር ለእባቡ መንታ ምላስ ሰጠው።
ከእባቡ አፍ የወጣው ንግግር የሰውን ዘር ሁሉ ወደ ሞት ነዳ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከእባቡ ምላስ ስር መርዝ አስቀመጠ።
እንስሳት ከመጀመሪያውም በወሲባዊ ግንኙነት መራባትን ያውቃሉ። ከዚህም የተነሳ እባቡ ለሴቲቱ ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ሊነግራት ችሏል፤ ወሲባዊ ግንኙነትም ወንዱ በሴቷ ላይ በሆዱ እንዲተኛ ያደርገዋል።
በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር እባቡን ሁልጊዜ በሆዱ ተኝቶ እንዲሳብ አደረገው። አፉም በቀላሉ አፈር ይገባበታል።
“አፈር ትበላለህ”።
ይህ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ትርጉም አለው። እባቦች ፍጥረታዊ አፈር አይበሉም። ወደ አፋቸው የሚገባውን አፈር ይውጡታል፤ ነገር ግን የሚበሉት እንደ እንቁራሪትና አይጥ የመሳሰሉ ትንንሽ እንስሳትን ነው። የእባብ ረጅም አካል የሲኦል ጉድጓድ ተምሳሌት ነው።
ሰው የተሰራው ከአፈር ነው። ሳንድን ብንሞት የሲኦል እባብ ይውጠናል። የሲኦል እባብ የስጋ መጨረሻው እና በስጋ ለሚኖሩ ሁሉ መጨረሻቸው ነው።
ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ብንወለድ የሲኦል እባብ ሊውጠን አይችልም፤ ምክንያቱም የሲኦል እባብ ምግቡ አፈር ብቻ ነው ማለትም ስጋ።
በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል በምድር ላይ ታላቅ ጦርነት ተጀመረ
ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።
ይህ ትንቢት ነው።
ሰይጣን እባቡ ውስጥ ነበረ፤ እባቡ ውስጥ የገባውም የእግዚአብሔርን እቅድ ለማበላሸት ነው። ልክ ገደራ በሚባል ቦታ አጋንንቱ ወደ አሳማዎች ውስጥ እንደገቡት ሁሉ ሰይጣን እንስሳት ውስጥ መኖር ይወዳል።
እግዚአብሔር ግን መኖር የሚፈልገው በሰዎች ውስጥ ብቻ ነው።
የሴቲቱ ዘር ኢየሱስ ነው፤ እርሱም ያለ ወንድ ዘር ከማርያም የድንግልና መጋረጃ ጀርባ ነው ተጸንሶ የተወለደው።
ሴት ዘር የላትም። ሴት ዘር የሚቀበል ማሕጸን ነው ያላት። እግዚአብሔር ለሴቲቱ በማሕጸንዋ ውስጥ ዘር በመፍጠር ዘር ሰጣት። ይህ ዘር የሰው አባት ስለሌለው የሴቲቱ ዘር ሊባል ይችላል ምክንያቱም ከወንድ የተገኘ አይደለም።
የእባቡ ዘር የወንድ እስፐርም ወይም መራቢያ ሕዋስ ነው። ወሲብን የሚፈጥረው ዘር ይህ ነው።
የወንድ ዘር ጭንቅላቱና ረጅም አካሉ ሲታይ እባብ ይመስላል። ከተቀደደ የድንግልና ማሕተም ጀርባ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ስለተጸነስን ስንወለድ ሁላችንም “የእባቡ ዘር” ነን።
እምብርታችን ላይ ያለው ጠባሳ በሰውነታችን ላይ የቀረ የአውሬው ምልክት ነው።
እምብርት የሚፈጠረው በማሕጸን ውስጥ የሚያድገውን ጽንስ ከእናትየው ጋር በሚያገናኝ የእትብት ገመድ ነው።
በዚሁ እትብት እናት ከእናቷ ጋር እየተገናኘች እስከ ሔዋን ድረስ እትብት ሁሉን ያገናኛል።
ይህ የእትብት ገመድ እግዚአብሔር ሰዎችን ለራሳቸው ፈቃድ አሳልፎ የሰጠበትን ፈቃድ ያመለክታል፤ በዚህም ፈቃድ ሰዎች በጋብቻ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ልጆችን ይወልዳሉ። በዚህ መንገድ ተወልደን የምንኖረው ሕይወት ግን በጊዜ የተገደበ ስለሆነ ተወልደን እንኖርና እንሞታለን። ይህ የዘላለም ሕይወት መንገድ አይደለም።
ይህ የጊዜ ቱቦ እና የእትብታችን ገመድም ከእባብ ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ።
ኮብራ የተባለው እባብ በከፊል ወደ ላይ ቀና ሲል በጣም አደገኛ ይሆናል። በዚህ ስጋዊ አካል ውስጥ ስንኖር ጥቂት መልካም ነገር እናደርጋለን፤ ይህም ጥያተኞች እራሳቸውን እንደ ጻድቅ እንዲቆጥሩ ያደርጋቸዋል።
ነገር ግን ክፉ ነገርም እናደርጋለን፤ የሰራነውን ክፉ ነገር ፍቀን የምናጠፋበት መንገድ ደግሞ የለንም። ስለዚህ እባቡ አፈር እንዲበላ ተነገረው። ይህም ከሴት የተወለዱ የመልካም እና የክፉ እውቀትን የተካፈሉ ሰዎችን ዕጣ ፈንታ ያሳያል። ሰዎች በስጋ ይኖሩና ሲሞቱ ሲሞቱ እባቡ ይውጣቸዋል፤ የእባቡም አካል የሲኦል ጉድጓድ ተምሳሌት ነው።
እምብርታችን በስጋችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው፤ ይህም አካላችንን ወደ መቃብር ይወስደዋል ምክንያቱም አካላችን የወሲባዊ ግንኙነት ውጤት ነው። ይህም የመጀመሪያው ሞት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን ካላመንን በግምባራችን የአውሬውን ምልክት እንቀበላለን፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተሳሰቦችንና እምነቶችን ወደ አእምሮዋችን እናስገባለን።
አእምሮዋችን ውስጥ የገባው ሃሳብ ድርጊታችንን ስለሚወስነው ድርጊታችን በእጃችን ላይ የአውሬውን ምልክት መቀበላችንን ያሳያል። ከዚያም ወደ ሁለተኛው ሞት ማለትም ወደ እሳት ባህር እንሄዳለን።
ከእባቡ ልናመልጥ የምንችለው ዳግመኛ ከተወለድን ብቻ ነው። ቅዱሳን ሐጥያተኛ መሆናቸውን ስለሚያውቁ ንሰሃ ይገባሉ።
ሐጥያተኞች ግን ጥቂት መልካም ስራዎችን ይሰራሉ፤ ያም ቅዱስ እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል። መልካም ስራ ክፉ ስራን የሚያካክስና የሚያስተሰርይ ይመስላቸዋል።
ፍጹም የሆነው የኢየሱስ ደም ስናምንበት ከሐጥያታችን በሙሉ ያጥበናል። ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም መወለድ አዲስ መንፈሳዊ አካል ይሰጠናል፤ ከዚያም ስንሞት ወደ ሰማይ ይወስደናል ምክንያቱም እባቡ መንፈስን የመብላት ፈቃድ አልተሰጠውም።
በቀራንዮ መስቀል ኢየሱስ የሰይጣንን ራስ ረግጦታል። ጭንቅላት ሲረገጥ ከውስጥ የደም ስር ሊተረተር ይችላል። ጭንቅላት ውስጥ የፈሰሰ ደም ብዙ ሲፈስ አንጎልን ሲነካ የተረገጠው ሰው ይሞታል።
የኢየሱስ ደም በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አየበዛ ሄዶ አንጎል ማለትም የዘመናችንን ሳይንሳዊ ብልጠት ይነካል፤ የዚያን ጊዜ የምንኖርበት የሎዶቅያውያን ዘመን ታላቁ መከራ ውስጥ ገብቶ በአርማጌዶን ጦርነት ይጠፋል።
መስቀሉ ላይ በተደረገው ታላቅ ተጋድሎ ኢየሱስ እግሩን ተጎድቷል። በዚህም ምክንያት መራመድ ስላልቻለ ለተወሰነ ጊዜ አልታየም። ነገር ግን እግሩ ተሻለውና ሞትን አሸንፎ በድል ተነሳ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሺ ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ተራምዷል።
በጭንቅ መውለድ የመጀመሪያው ሐጥያት ዋጋ ነው
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
እግዚአብሔር ሴቲቱን ሲናገራት “ምክንያቱም” አላለም። ለምንድነው ያላለው? ሴቲቱ ሙሉ በሙሉ ስለተሞኘች እግዚአብሔር አስረድቶ ሊያሳምናት አይችልም።
በወሲባዊ ግንኙነት በቀር ልጅ የሚወለድበት ሌላ መንገድ መኖሩን በጭራሽ አላወቀችም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ብሎ የሰጠውን ትዕዛዝ የፈጸመች መስሏታል።
ደግሞም ሚስት ከባሏ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረጓ በሕግ የተፈቀደ ስለሆነ ከአዳም ጋር ባደረገችው ወሲባዊ ግንኙነት ስሕተት አልሰራችም። ከአጠቃላዩ የእግዚአብሔር እቅድ አንጻር ግን በድንግልና ስለ መውለድ ምንም አላወቀችም። ከእባቡ ጋር የፈጸመችውን ዝሙት እንደ መለማመጃ አድርጋ ልትቆጥረው ትችላለች። በመባዛት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም መለማመዷ ነው።
ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።
ነገር ግን አንዴ ማሕጸኗ በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ከጸነሰ በኋላ እግዚአብሔር ለእቅዱ ሊጠቀምባት እንደማይችል አልገባትም። እግዚአብሔር ትዕዛዙን የምትጠብቀዋ ማርያም እስትወለድ ድረስ 4,000 ዓመታት ጠበቀ።
ከሁሉም የባሰው ነገር ደግሞ ሔዋን ከእንስሳ ምክር መቀበሏ ነው። እንስሳት መካከል አንድ ወንድ እንስሳ ብዙ እንስት እንስሳትን አግብቶ መኖሩ የተለመደ ነው። ስለዚህ ሴቲቱ እንስሳት በሚራቡበት መንገድ መራባትን ከመረጠች ልክ እንደ እንስሳት አንድን ወንድ ለብዙ ማግባት እንድትችል እግዚአብሔር ወሰነ። ስለዚህ እያንዳንዷ ሴት ለአንድ ሰው ከብዙ ሚስቶች አንዷ ትሆንለታለች። ይህም ለሴቶች ውርደትና ከወንድ የበታች የሚያደርጋቸው ነገር ነው።
ቀጥሎ እንግዳ የሆነ የፍርድ ቃል ተነገረ። “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ”። ይህ ሁለት ትርጉሞች አሉት።
እግዚአብሔር ለሴቲቱ ስለ ሐጥያቷ እየነገራት ነው፤ ሲናገራትም ስለ እርግዝና እንጂ የዛፍ ፍሬ ስለመብላቷ አልተናገራትም።
ስለዚህ የመጀመሪያው ሐጥያት ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነው።
“በፀነስሽ ጊዜ”። ሴቲቱ በዚያ ሰዓት ፀንሳ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በዚህ ፅንስ ደስተኛ አልነበረም። በሐዘን ልጆችን ትወልዳለች።
እስከ ዛሬ ድረስ ልጅ መውለድ ጭንቅ እና ሕመም ያለበት ከባድ ነገር ነው። ባለፉት የ6,000 ዓመታት የሰው ታሪክ ውስጥ ስንት ሴቶች ልጅ በመውለድ እንደሞቱ ማንም አያውቅም። የእርግዝና ጊዜ በጣም ከባድ ጊዜ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ይህንን መፍቀዱን ግልጽ አድርጓል፤ ይህ ግን ፍጹም ፈቃዱ አይደለም።
ወሲብ ሰዎች እንዲዋለዱ እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ያሰበበት መንገድ ቢሆን ኖሮ ሴቲቱን ስል እርግዝናዋ አይቀጣትም ነበር።
እግዚአብሔር ወሲብ ማድረግን ፈቅዶላት ቢሆን ኖሮ ወሲብ ማድረጓ እንዴት ስለ ራቁትነቷ እንድታፍርና ለራሷ የበለስ ቅጠል ሰፍታ እንድትለብስ ሊያደርጋት ቻለ? እንስሳት በወሲባዊ ግንኙነት ይዋለዳሉ፤ ስለ ራቁትነታቸውም አያፍሩም።
አንድ አስደንጋጭ ቃል እንመልከት። “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ”።
እግዚአብሔር ያሰበላት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አንድ ጊዜ እንድትጸንስና ኢየሱስን እንድትወልድ ነው። ከዚያ ኢየሱስ ደግሞ ጻድቃንን በሙሉ ይፈጥራቸዋል። ስለዚህ የሚያስፈልገው በመለኮት ኃይል የሆነው አንድ ጽንስ ብቻ ነበረ።
ነገር ግን ሴቲቱ ከእባቡ የፀነሰችው ፅንስ ቃየን ሆኖ ተወለደ። ይህም ፅንስ እጅግ እንዲበዛ ተደረገ። ከዚያ ሴቶች ሁሉንም ሰው ይፀንሳሉ፤ ወደፊት የሚወለዱትን ጻድቃንን እንዲሁም በቁጥር ከእነርሱ የሚበልጡትን ያልዳኑ ሰዎችንም ፀንሰው ይወልዳሉ።
ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ እግዚአብሔር ተባዙ ብሎ ነበር። ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ አንድ ፅንስ ኢየሱስ ተፀንሶ ከዚያም ሲወለድ ያድግና ቅዱሳንን በሙሉ በቃሉ ከምድር አፈር እንዲወጡ ያደርግ ነበር።
ምዕራፍ ሶስት ውስጥ ደግሞ እጅግ አበዛለሁ አለ።
ስለዚህ ሴቶች ጻድቃንን ሁሉ ይፀንሳሉ፤ ደግሞም በቁጥር ከጻድቃን እጅግ የሚዙትን ወንጌልን እምቢ ብለው ወደ ሲኦል የሚወርዱትንም ሰዎች ይፀንሳሉ።
እግዚአብሐየር የተናገራት ብዙ ፅንስ መፀነስን እንደሚፈቅድላት ነው። ለመባዛትም ብዙ ወንዶች ልጆች እና ሴቶች ልጆችን መውለድ አለባት፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው መጋባት ያስፈልጋቸዋል። አንድ ፅንስ ብቻ ፀንሳ ካቆመች የሰው ዘር መባዛቱን ያቆማል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ብዙ እርግዝና እና ብዙ ወሊድ በመስጠት ቀጣት። ይህ ቅጣት ከሆነ ለሰው ልጆች የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ሃሳብ ይህ አይደለም ማለት ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ምን ማለቱ ነው?
ሴቲቱ አንድ ፅንስ ብቻ ነበር እንድትፀንስ እግዚአብሔር ያሰበላት፤ እርሱም በድንግልና የሚወለደውን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ነው። እርሱም ሲወለድ አድጎ ትልቅ ሰው ይሆንና ቅዱሳንን በሙሉ በቃሉ ከምድር አፈር ይፈጥራቸው ነበር። እነርሱም ምድርን ለመሙላት በሚበቃ ቁጥር ይፈጠሩ ነበር እንጂ ሲኦል ውስጥ የሚቃጠሉ ትርፍ ሰዎች አይፈጠሩም ነበር።
ሔዋን ግን ድንግልናዋን ስላልጠበቀች ያ እቅድ ተበላሸ። ከዚህም የተነሳ ሰዎች ሁሉ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት እንዲወለዱ ተወሰነ።
ሴት ለባሏ መታዘዝ አለባት
“ባልሽ ገዥሽ ይሆናል”።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሴቲቱ ባሏ የቤቱ ራስ እንደሆነ እንድትቀበል ተገደደች።
ሰይጣን ሴቶች በባሎቻቸው ላይ ገዥ እንዲሆኑ በማበረታታት ይህንን ስርዓት ይቃወማል።
ዘመናዊ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ባሎቻቸውን አያከብሩም።
ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል።
ይህ እንግዳ የሆነ ቅጣት ነው። ባሏን የምትወድ ሴት በተፈጥሮዋ ፈቃድዋ ወደ ባሏ ነው የሚሆነው። ነገር ግን ወሲባዊ ፍላጎት ወደ ብዙ ሌሎች ወንዶች እንድትሳብ ያደርጋታል፤ ሆኖም ወደተሳበችባቸው ወንዶች ሁሉ መሄድ አትችልም። ባሏን ብቻ ልትወድ ትችላለች። ነገር ግን እንስሳት መካከል አንድ ወንድ እንስሳ ብዙ እንስት እንስሳትን ስለሚያገባ እና እርሷም የእንስሳ ቃል ስላዳመጠች ለአንድ ወድን ከብዙ ሚስቶች መካከል አንድ ሚስት ሆና እንደ እንስሳ ልትኖርም ትችላለች። ስለዚህ ባሏ ብዙ ሴቶችን ማግባት ይችላል፤ እርሷ ግን ለእርሱ ብቻ ታማኝ ሆና መኖር ግዴታዋ ነው። ይህም ለሴቲቱ ደስ የሚያሰኝ ነገር አይደለም። ደግነቱ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ማግባቱ የተፈቀደው ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብቻ መሆኑ ነው።
ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚአብሔር ለአዳም ስለ መልካምና ክፉ የምታሳውቀዋ ዛፍ በነገረው ጊዜ አዳም መንፈስ ነበረ።
የሴቲቱ ባህርያት በሙሉ በሰውየው ውስጥ ነበሩ ነገር ግን ሴቲቱ የተደረገውን ነገር አታውቅም ነበር። ስለዚህ ሴቲቱ እግዚአብሔር ለአዳም ስላስተማረው ነገር ከአዳም በመስማት ነበር የምታውቀው።
ሁለቱ የተሰጣቸውን ሚና ሲለዋወጡነሰ ሴቲቱ ለሰውየም ምን ማመን እንዳለበት ስትነግረው ሐጥያት ወደ ዓለም ገባ።
የመጀመሪያዋ ሴት ሰባኪ ሔዋን ነበረች፤ የሴት ሰባኪነትም ያመጣው ውጤት ሞት ነው። አዳም የሰራው ትልቅ ስሕተት ሚስቱን ማዳመጡ ነው። እርሱ ከመጀመሪያው እውነትን ያውቅ ነበር፤ እርሷ ደግሞ አታውቅም ነበር። ቤተሰባችንን ለማስደሰት ብለው በእውነት ላይ መደራደር የለብንም።
ደግነቱ እግዚአብሔር አዳምን አልረገመውም። እግዚአብሔር የረገመው አዳም የተፈጠረባትን ምድር ብቻ ነው።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በቀላሉ ብዙ እሕል ትሰጥ የነበረችዋ ምድር ኃይሏን መቆጠብና በብዙ ልፋት በብዙ ድካም ጥቂት እህል መስጠት ጀመረች። ለብዙ ሰዎችም ከምድር ላይ ምግባቸውን ማግኘት ጀርባቸውን በሚሰብር ከባድ ሥራና ልፋት ሆነ። ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ከባድ ዝናብ፣ አነበጣ፣ ተምች፣ ከባድ ሙቀት፣ እና ብዙ ተባዮች ገበሬዎች ላይ ብዙ ኪሳራ እና ብዙ ሐዘን ያደርሳሉ። ከመከር በኋላ በጎተራ የተከማቸውን እህል ደግሞ አይጦችና ብል ያበላሹታል። ከዓለም ሕዝብ የተወሰነ ክፍሉ ሁልጊዜ በረሃብ ይሰቃያል፤ ይህም በሰዎች ላይ ብዙ ሐዘን ያመጣል። ስግብግብ ነጋዴዎች የእህል ዋጋ እንዲወደድ ብለው ብዙ እህል ወደ ባሕር ውስጥ ይጥላሉ። የእርሻ መሬቶችን ምግብ ለማምረት መጠቀም ትተው ባዮፊዩል ለማምረት ይጠቀሙባቸዋል ምክንያቱም ባዮፊዩል ከእህል የበለጠ ትርፍ ያስገኛል። ምግብ የሚያስፈልጋቸው ድሆች፤ ሁልጊዜ በረሃብ የሚቃጠሉ ስደተኞች የሚያስብላቸው የለም። በድርቅ እና በረሃብ ምክንያት ራሺያ እና ቻይና ውስጥ ኮምዩኒስት መንግስታት ወደ ስልጣን ይመጣሉ።
ዘፍጥረት 3፡18 እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።
እግዚአብሔረ ኑሮን ለሰው ከባድ አደረገው። እግዚብሔር ሰውን ከምድር አፈር ካበጀው በኋላ በስጋ ውስጥ ቀላል ኑሮ እንዲኖር ፈቅዶ ነበር። ነገር ግን እኛ ሰዎች የተሰጠንን በረከት በደስታ ተቀብለን ማመስገን አናውቅበትም፤ ስኬታማ እና ሃብታም የሆኑ ሰዎች ሕይታቸውን ሙሉ ለማድረግ እስካሁንም ልክ እንደ አዳም አትብሉ የተባለውን ፍሬ መብላት ይፈልጋሉ።
ምግባችንን የምናገኘው ከምድር አፈር ነው። ነገር ግን እህል ማብቀልና ማሳደግ ከባድ ስራ ነው። ከእህል ውጭ ምድር በተጨማሪ እሾክና አረም ታበቅልብናለች። እነዚህን ደግሞ መብላት አንችልም ግን ስራና ድካም ያበዙብናል።
መዳንና ጠለቅ ያለ እውነትን ለመማር የምንሄድባቸው ቤተክርስቲያኖች ውሸት፣ ፖለቲካ፣ የሰዎች ልማድ፣ ፍልስፍና፣ እና ስሕተትም ያበሉናል። ስለዚህ እውነትና ስሕተት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመደባለቃቸው የተነሳ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው እውነትን የሚያገኙዋት። እግዚአብሔርም ስሕተት እውነትን በመውረር ሙሉ በሙሉ ከማጥፋቱ በፊት ጊዜን አሳጥሮ ይቆርጠዋል።
እግዚአብሔር ለሐጥያተኛ ሰው ኑሮን ማቅለልና ማመቻቸት እንደማያስፈልግ ተረድቷል ምክንያቱም ሐጥያተኛ መንገዱ ቢመቻችለት የባሰ እየተበላሸ ይሄዳል። ለእኛ ለሰዎች ከባድ ስራ እና ብዙ መሰናክል የተሸለ መኖሪያችን ነው።
ዘፍጥረት 3፡19 ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።
የሰው ፊት ግምባሩን የሚያጠቃልል ሲሆን ግምባሩም የእውቀቱና የማስተዋሉ የአእምሮው ኃይል ተምሳሌት ነው። የምድር ገጽም የምድር ፊት ይባላል። እግዚአብሔር አዳምን የሰራው ከምድር አፈር ነው። ሰው በአእምሮው ምንም ያህል ቢጠበብና ቢራቀቅ እንኳ ዕድሜውን ሲጨርስ ከመሞትና ሁሉን ትቶ ወደ ምድር አፈር ውስጥ ገብቶ ከመቀበር ሊያመልጥ አልቻለም። እያንዳንዱ መቃብር በምድር ፊት ላይ ጠባሳ ሲሆን ይህም የእግዚአብሔር የመጀመሪያ እቅድ አካል አልነበረም።
የሰው እምብርት በሰውነቱ ላይ የሚገኝ ጠባሳ ነው፤ ይህም በስጋችን ላይ የቀረ የቀደመው እባብ ወይም የአውሬው ምልክት ነው። ስንወለድ ጀምሮ እምብርት አለ፤ ስለዚህ እንደ ባለ እምብርቱ ብርቱካን ነን፤ ይህም ብርቱካን በፍሬው (በልጁ) ውስጥ ምንም ዘር (የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት) የለውም። በዚህ ጠባሳ ባለው አካል ውስጥ ሆነን ከወሲባዊ ግንኙነት ስለተወለድን በስጋችን የሞት ፍርድ ተሸክመን እንኖራለን፤ በምድር ፊት ላይ በፊታችን ላብ የምንሰራውም ሆነ የምናከማቸውን ነገር ሁሉ ትተን መቃብር ወደሚባል የምድር ጠባሳ እንመለሳለን። ስጋችን በምድር ውስጥ አንድ ሜትር ተኩል ብቻ ጠልቆ ይቀበራል፤ ነፍሳችን ግን ጥልቅ ወደሆነው ወደ ሲኦል ጉድጓድ ትገባለች። ስለዚህ አዳኝ ያስፈልገናል። እርሱም መከራ የተቀበለልንና ሐጥያታችንን ለማስተስረይ ስለ መቁሰሉ ማስረጃ የሚሆን ጠባሳ ሊያሳየን የሚችል አዳኝ ያስፈልገናል።
አዳምና ሔዋን የደም ነጠብጣብ በነካው ቆዳ ተሸፍነው ከኤደን ወጡ
የሐጥያተኞች ብቸኛ ተስፋ ከደሙ ስር መሆን ነው።
ዘፍጥረት 3፡20 አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።
ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ሙራ ተብላ ተጠርታለች። ሴቲቱ በራሷ ስም የተጠራችው በሐጥያት ከወደቀች በኋላ ብቻ ነው። ቤተክርስቲያኖችም ወደ ሐጥያትና አለማመን ከወደቁ በኋላ ብቻ ነው እንደ ሜተዲስት፣ ባፕቲስት፣ ፔንቲኮስታል፣ ሜሴጅ የተባሉ ስሞችን የሚጠቀሙት።
ልጆች በሙሉ የተወለዱት ከሔዋን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ለምንድነው አዳምን የሕያዋን ሁሉ አባት ያላለው? ሳይል መቅረቱ በጣም ያስገርማል።
መጽሐፈ ዜና ውስጥ ለምድነው ቃየን የአዳም የበኩር ልጅ ተብሎ ያልተጠቀሰው?
ያላስተዋልነው ነገር ይኖር ይሆን? ከዚህ ጋር የተያያዘ ጠለቅ ያለ ሚስጥር ይኖር ይሆን?
ስለ አንድ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ካልተጻፈ ያ ጉዳይ ጠለቅ ያለ ሚስጥር አለው ማለት ነው።
ዘፍጥረት 3፡21 እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።
አዳም እና ሔዋን ሰውነታቸው ውስጥ ደም ከኖራቸው ጊዜ ጀምሮ በቅድስና መጎናጸፊያ አልተሸፈኑም ነበር። በሰው ሕይወት ውስጥ ነጻ ፈቃድ እና ወሲባዊ ፍላጎት ሲጣመሩ በጣም አደገኛ ናቸው።
ስለዚህ ሰዎች በራሳቸው ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመገደብ እግዚአብሔር ሁለት መመሪያዎችን አዘጋጀ። እግዚአብሔር ሰዎች ራቁታቸውን እንዳይሆኑ አደረገ። ራቁትነት የእንስሳት ባህርይ ሲሆን ሔዋንን ያሳታትም እንስሳ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰውን ራቁትነት በመሸፈን ሰውን ከእንስሳት ለየው።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በአንድ ሰው እና በአንዲት ሴት መካከል ወሲባዊ ግንኑነት የሚፈቀደው ከጋብቻ ጥምረት በኋላ ብቻ እንዲሆን አደረገ።
ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ማርያም ድንግል ነበረች። እግዚአብሔር ከጋብቻ ውጭ ወሲባዊ ግንኙነት አይፈቅድም።
ሐጥያት ወደ ሰው እንዲገባ ያደረገው እንስሳ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር እንስሳ በመግደል የእንስሳውን ቆዳ በደም የተሞላውና በሐጥያት የረከሰውን የሰው ገላ ለመሸፈን ተጠቀመበት።
እግዚአብሔር እባቡን መግደል አልቻለም ምክንያቱም ረግሞት በደረቱ ወደሚሳብ እንስሳ ለውጦታል። አፉ ውስጥ መርዝ ያለው እባብ የሰይጣን ተምሳሌት ሆነ። እግዚአብሔረ ወደ ሐጥያት እንዲገቡ ያደረጋቸውን እባብ ቆዳ ተጠቅሞ ሊያለብሳቸው አልፈለገም፤ እባቡም ከተረገመ በኋላ በደረቱ የሚሳብ እንስሳ ሆኖ ተለውጧል።
እግዚአብሔር ልጆቹን በንጹህ እንስሳ ቆዳ መሸፈን ፈለገ። እግዚአብሔር ከእንስሳት ሁሉ ተንኮለኛ የሆነውን እንስሳ ሐጥያት ለመሸፈን በምድር ላይ ካሉት እንስሳት ሁሉ ንጹህና የዋህ የሆነውን እንስሳ መረጠ። ስለዚህ እግዚአብሔር በግን መረጠ።
ሐይማኖት ሐጥያታችንን ይሸፍናል ግን ሐጥያታችንን አያስወግድም።
እግዚአብሔር የበጉን ጸጉር ብቻ ተጠቅሞ የአዳምና የሔዋንን ራቁትነት መሸፈን ይችል ነበር። ይህም ተስማሚ ሐይማኖት ወይም ሽፋን መሆን ይችል ነበር ነገር ግን የመጀመሪያውን ሐጥያት ሊሸፍን አይችልም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር በጉን ገደለው። ሐጥያትን የሚሸፍነው የገቡ ጸጉር አይደለም፤ ሐጥያትን የሚሸፍነው የፈሰሰው የበጉ ደም ነው።
አዳም እና ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት ልጅ ሲወልዱ እግዚአብሔር በድንግልና የሚወለደው ልጁ ኢየሱስ የሚወለድበት ድንግል ማሕፀን እንዳይገኝ አደረጉ። የሔዋን የድንግልና ማሕተም በስጋዊ እውቀት ወይም በወሲባዊ ግንኙነት ጊዜ ተቀደደ፤ በዚህም ምክንያት ደም ፈሰሳት። ስለዚህ የሐጥያት መነሻው የደም መፍሰስ ከሆነ ሐጥያትን የሚያስተሰርየውም የደም መፍሰስ ነው።
ቃየን ያልተገለጠለት ሚስጥር ይህ ነው። ቃየን ፍራፍሬ እና አበባ ይዞ በመምጣት ውብ መሰዊያ ሊያዘጋጅ ሞከረ፤ ይህም የራሱ መልካም ስራ ሲሆን በመልካም ስራው እግዚአብሔርን ሊያስደስት የሚችል መሰለው። እግዚአብሔር የሰው እጅ ስራ የሆነውን መሰዊያ አልተቀበለም። ይህ ከመጀመሪያው ሐጥያት ጋር ምን ያያይዘዋል?
አቤል በበግ ደም የተጨማለቀ የማያምር መሰዊያ ሰራ። አቤል የእግዚአብሔር ሃሳብ ተገልጦለታል። እግዚአብሔርም በአቤል ደስ ተሰኘ።
ነገር ግን ከተቀደደ ድንግልና በስተጀርባ የዘላለም ሕይወት ሊገኝ አይችልም። ለዚህ ነው በማሕፀን ውስጥ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኘነት ተፀንሰው የተወለዱ ሁሉ የሚሞቱት።
መሲሁ ሲሞት እግዚአብሔር የቤተመቅደሱን መጋረጃ ቀደደው፤ ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ከቤተመቅደሱ ውስጥ ወጥቶ መሄዱን እና ከተቀደደው የቤተመቅደስ መጋረጃ በስተጀርባ የዘላለም ሕይወት እንደማይገኝ ለማሳየት ነው።
አንዲት ድንግል ማሕፀን ብቻ ናት አማኑኤልን የማሕፀን ፍሬ፣ የአብርሃም ዘር፣ በስጋ ሙላት የተገለጠውን ቃል ወይም በሰው አካል የተገለጠውን ልትወልድ የቻለችው። ይህም የሆነው ያለ ወሲባዊ ግንኙነት - የድንግልና መጋረጃ ሳይቀደድ ነው። ሐጥያት በዚህ ሒደት ውስጥ አልገባም።
ይህም ኢየሱስ ሐጥያት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ ሆኖ አደገ፤ ንጹህ የሆነው ደሙ በቀራንዮ የመጨረሻ የሐጥያት ማስተሰርያ ሆኖ ፈሰሰ።
ይህ መስዋእት ብቻ ነው ሐጥያትን ሙሉ በሙሉ አጥቦ ሊያስወግድ የሚችለው። ከዚያም በደሙ ውስጥ ያለው ሕይወት ማለትም መንፈስ ቅዱስ ንሰሃ ወደሚገባው ሐጥያተኛ ልብ ውስጥ ይመጣና ያ ሰው ሐጥያትን አሸንፎ እንዲኖር ያስችለዋል።
በቀራንዮ መስቀል ላይ ሽግግር ተደርጓል።
ንሰሃ ስንገባ ሐጥያታችን ወደ ኢየሱስ ይተላለፋል፤ የእርሱ ንጽሕና ደግሞ ወደ እኛ ልብ ይተላለፋል።
ዘፍጥረት 3፡22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤
መልካምን እና ክፉውን ማወቅ ለሰው ከአቅሙ በላይ የሆነ ኃላፊነት ነው። መልካምና ክፉውን ከማወቅ የሚፈጠሩ ችግሮችን ሁሉ ለመቋቋም የሚበቃ የአእምሮ ኃይል የለንም። ይህ እውቀት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ያጋፍጠናል፤ ሞትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ደግሞ ለእኛ ከአእምሮዋችን በላይ የሆነ ጉዳይ ነው። ፈንጂዎች መንገድ ለመስራት፣ በተራራዎች ውስጥ ማለፊያ ዋሻ ለመክፈት፣ ወደቦችን ለማበጀት ይጠቅሙናል፤ ነገር ግን እነዚሁ ፈንጂዎች በጦር ሜዳ ብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላሉ።
ሰው የክፉውን በር ስለከፈተ አሁን ሊፈታ የማይችላቸውን ችግሮች እየተጋፈጠ ነው።
ክፉ ባለበት ዓለም ውስጥ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ማመን ያቆማሉ፤ በተለይ ደግሞ መልካም ሰዎች ክፉ ነገር ሲደርስባቸው ሲያዩ።
በዓለም ውስጥ ክፉ መኖሩ ለሰው ሁሉ እንቆቅልሽ የሆነበት ችግር ነው። ምናልባትም በሰዎች አእምሮ ውስጥ እግዚአብሔር አለ ብሎ ለማመን የሚያችቸግራቸው ትልቅ መሰናክል ክፉ መኖሩ ነው። ስለዚህ ከክፉ ጋር መጋፈጥ ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ማመን እንዲያቅታቸው አድርጓል።
“ክፉ” እኛ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ልናስተውለው የማንችለው ውስብስብ ጽንሰ ሃሳብ ነው።
ክፉው የሐጥያት አገልጋይ ነው። ሐጥያት እኛ ማሰብ ወይም ማስተዋል ከምንችለው በላይ ክፉና ጠማማ ነገር ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከሐጥያት ጋር ምንም ዓይነት ድርደር አይፈልግም። ነገር ግን አዳም ሐጥያት ከሰራ በኋላ የሕይወት ዛፍን ፍሬ ቢበላ “ለዘላለም የሚኖር ሐጥያተኛ” ይሆን ነበር።
ሐጥያት ለዘላለም መኖሩ በጣም ዘግናኝ ሃሳብ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ዓለምን ሊያጸዳ ፈለገ። በመጀመሪያ አዳምን ከኤድን ገነት አባረረ። ይህም ውሳኔ የኤድን ገነት እንዳትበላሽ ያደርጋል፤ ሐጥያትን ግን አያስወግድም።
የዘላለም ሕይወት ምንጭ አንድ ብቻ ነው - እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ። ስለዚህ ይህ የሕይወት መንፈስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ዛፍ ነው።
ዘፍጥረት 3፡23 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።
እግዚአብሔር በፊቱ ሐጥያተኛ ሰዎችን ማየት አይፈልግም። ሰው ኃይሏን ለመስጠት እምቢ ከምትል ምድር ጋር እየታገለ እንዲኖር ተፈረደበት። በምድር ላየ ካሉ ኢንዱስትሪዎች ሁሉ እጅግ አስፈላጊው ግብርና ነው፤ ምክንያቱም ለመኖር የሚያስፈልገንን ምግብ የምናገኘው ከእርሻ ነው። የግብርና ስራ ማለት ከአረሞች፣ ከተባዮች እና ከድርቅ ጋር የማያቋርጥ ትግል ማድረግ ነው። ግብርና ከባድ ስራ ነው በተለይ ደግሞ ንጥረ ነገር በጎደለው አፈር ውስጥ ዘር በተዘራ ጊዜ።
ስለዚህ ለሐጥያተኛ የሰው ዘር ተስማሚው ኑሮ በከባድ ስራ እና በልፋት መኖር ነው። የሚያለፋ ስራ ስንሰራ በሐጥያት የምናሳልፈው ጊዜ ያጥራል። ጠንክሮ መስራት ጠቃሚ ነገሮችን እንድናመርት ያደርገናል። ጠንክሮ መስራት በምድር ላይ ለምናሳልፈው ጊዜ መልካም የሆነ መታሰቢያ ሰርተን እንድናልፍ ይረዳናል። ሰይጣን ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ በተለይም በወጣቶች መካከል ስንፍናን በማበረታታት ነው።
የሕይወት ዛፍ መንገድ መስቀሉ ነው
ዘፍጥረት 3፡24 አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።
መዞር የሚቻለው ወደ አራት አቅጣጫዎች ነው። ሰሜን። ደቡብ። ምዕራብ። ምስራቅ። ስለዚህ አራት ኪሩቤሎች ያስፈልጋሉ።
ሰው ሐጥያተኛ ከሆነ በኋላ በገነት እንዲቆይ አልተፈቀደለትም። አዳም ወደ ምስራቅ ሲሄድ እግዚአብሔረ በኤድን ገነት ምስራቅ በኩል ጠባቂ በማቆም አዳም ተመልሶ ወደ ኤድን ገነት እንዳይገባ እና በሐጥያቱ ኤድን ገነትን እንዳያረክስ ከለከለው።
የአጋንንት አሰራር መፈልፈያው በምስራቅ ነው፤ በተለይም ባቢሎን በተመሰረተችበት በኤፍራጥስ ወንዝ ዳር ዳር።
ራዕይ 9፡14 መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ፦ በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።
ራዕይ 9፡15 የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።
ራዕይ 9፡16 የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፥ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። ይህ ማለት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነው።
ራዕይ 9፡17 ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፥ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።
እነዚህ ፍጥረታዊ ፈረሰኞች አይደሉም። ዮሐንስ በጽሑፉ እየገለጠ ያለው መንፈሳዊ ፈረሰኞችን ነው።
የሕይወትን ዛፍ “መንገድ” ለመጠበቅ።
ፍጥረታዊ ዛፍ ወደ ሌላ ቦታ ሊንቀሳቀስ አይችልም። ኢየሱስ መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወትም ነው።
ታሪኩ ወደ ኤድን ገነት ምስራቅ በኩል ተንቀሳቀሰ። ፍጥረታዊ ዛፎች ከቦታ ቦታ አይንቀሳቀሱም። የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ነው፤ እርሱም በኤድን ገነት ውስት የእግዚአብሔር እቅድ ማዕከል ነው፤ ስለዚህ ለአዳም እና ለሔዋን ወደ ኤድን ገነት ተመልሶ መግቢያ መንገድ ይሆን ዘንድ ወደ ምስራቃዊው ድንበር ተንቀሳቀሰ።
ሰው በእግዚአብሔር መንገድ ከሄደ ብቻ ነው ከእግዚአብሔር ጋር ወደነበረው ሕብረት መመለስ የሚችለው።
ስለዚህ አራት ኪሩቤሎች በሕይወት ዛፍ ዙርያ ቆሙ፤ ይህም የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ነው።
መዝሙር 99፡1 እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።
እግዚአብሔር የሚኖረው በኪሩቤሎች መካከል ነው። በራዕይ ምዕራፍ 4 አራት እንስሳት (ወይም ኃይላት) በሰማይ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ እንዳሉ ተጽፏል። የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ፣ እና የዮሐንስ ወንጌሎች በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በነበረ ጊዜ የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ስራ ከተገለጠበት ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ዙርያ ይገኛሉ።
ማንኛውንም ሰው ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቢቀርብ የነበልባል ሰይፍ ይገድለዋል።
እግዚአብሔር ያሰበው የነበልባሉ ሰይፍ ክርስቶስን እንዲገድለው ነው።
ወታደር ሲሞት የሚተው ወታደር ሰይፍ ወታደሩ የሞተበትን ቦታ ለማመልከት መሬት ላይ ይተከላል። ይህም ሰይፍ እንደ መስቀል ሆኖ ይቆማል።
ስለዚህ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት የነበልባሉ ሰይፍ ጉዳት የማያደርስ ሰይፍ እንዲሆን አደረገው፤ ምክንያቱም የሰይፉ ስለታም ጫፍ ምድር ውስጥ ተተሏል።
በመስቀሉ ዙርያ አራት ሮማዊ ወታደሮች መቆማቸው እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ያሳያል።
ዮሐንስ 19፡23 ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤
ስለዚህ ብቸኛው ከወሲባዊ ግንኙነት ውጭ የተወለደው ሰው ለሐጥያታችን ዋጋ ለመክፈል ደሙን አፈሰሰና በውስጡ ደም የሌለበትን አካል ይዞ ከሞት ተነሳ፤ ይህን ያደረገው በኤድን ገነት ውስጥ ወደነበርንበት ወደ መጀመሪያው ሁኔታችን ሊመልሰን ነው።
ሉቃስ 24፡39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።
ከትንሳኤው በኋል ደም እንዳለው አልተጻፈም።
አዳም ከሐጥያት በፊት ስለ ሚስቱ ሲናገርም ደም የሚባል ነገር ጠቅሶ አያውቅም።
ዘፍጥረት 2፡22 እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።
23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።
ስለዚህ ብሉይ ኪዳን ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበትን ጥብቅ የሆነ ሕግ አስቀመጠልን። ሰዎችም በራሳቸው መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቢቀርቡ ይሞታሉ። ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ጨዋታ አይደለም፤ ከባድ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፉት መመሪያዎች መሰረት ብቻ መደረግ አለበት። ከዚያ ውጭ ምንም ነገር ተቀባይነት የለውም።
ንሰሃ የሚገባ ሐጥያተኛ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችልበት ብቸኛ መንገድ ቀራንዮ ነው።