ዘፍጥረት 2 - አዳም በስጋዊ አካል ውስጥ ሲኖር ሊወድቅ ይችላል
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
አዳም እና ሚስቱ በስጋዊ አካል ውስጥ እንዲኖሩ ተደረጉ። እግዚአብሔርም ስለ እውቀት መስጠንቀቂያ ሰጣቸው። ስጋዊ እውቀት ማለት ወሲብ ነው።
- ውሃ የመጀመሪያዋን ምድር በሸፈናት ጊዜ ምንም ቅርጽ አልነበረውም
- እግዚአብሔር ምድርን የሰራት የሰውን ሕይወት ጠብቆ ለማቆየት ነው
- ለሰው ትልቁ ፈተና እግዚአብሔር እስኪንቀሳቀስ መጠበቅ ነው
- እግዚአብሔር ለታላቁ እቅዱ ያዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ነበረው
- የሰው ጥበብ ከእግዚአብሔር ቃል እምነት ጋር ሲነጻጸር
- ከኤድን የሚወጡ 4 ወንዞች ነበሩ ነገር ግን አንዱ ብቻ ነው መልካም ወደ ሆነ ምድር የሚፈስሰው
- ስጋዊ እውቀት ማለት ወሲብ ነው
- መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ቃየን የተወለደው ከክፉው ነው ይላል
- ኤድን ውስጥ ሴቲቱ የታተመች የሕይወት ምንጭ ነበረች
- በመጀመሪያ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ደም አልነበረም
ውሃ የመጀመሪያዋን ምድር በሸፈናት ጊዜ ምንም ቅርጽ አልነበረውም
ዘፍጥረት 1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
እግዚአብሔር ሰማይን (ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ እና ሕዋ) እና ምድርን ያለ ምንም ነገር ፈጠረ፤ ምክንያቱም መጀመሪያ ምንም ነገር አልበረም።
እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ምን ያህል ጊዜ እንደፈጀበት አናውቅም ምክንያቱም ፀሃይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን፣ እና ምድርን ሲፈጥር ምን ያህል ጊዜ እንደወሰደበት አልነገረንም። ነገር ግን በምድር ላይ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ከመፍጠሩ በፊት ውሃ ፈጥሯል። ይህም ውሃ በሕዋ ቅዝቃዜ ምክንያት የበረዶ ግግር ሆነ። ምድርም በበረዶ ስትሸፈን የበረዶ ኳስ ትመስል ነበር።
ምድር መጀመሪያ እግዚአብሔር ወደ ፀሃይ ሳያስጠጋት በፊት በበረዶ ተሸፍና ነበር። በረዶው ሲቀልጥ ትልልቅ የበረዶ ግግር እየተላቀቀ ውሃው ላይ መንሳፈፍ ጀመረ። እግዚአብሔር እነዚህን ትልልቅ የበረዶ ግግሮች ወዲያና ወዲህ ሲያንቀሳቅሳቸው የበረዶ ግግሮቹ ምድርን እየጠረቡ ቅርጽ ሰጧት። በረዶው በሙሉ ቀልጦ ሲያልቅ ምድር በውሃ ተሸፈነች፤ ከዚህም ውሃ የተወሰነው ሲተንን ከውሃው ላይ የተነሳው እንፋሎት የፈጠረው ወፍራም ደመና የፀሃይን ብርሃን ጋረደ።
ዘፍጥረት 1፡2 ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤
(የምድር ፊት በሙሉ በውሃ ተሸፍኖ ነበር፤ የውሃውም ገጽ ጠፍጣፋና ቅርጽ አልባ ነበረ)
ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ
(ወፍራም ደመና የፀሃይን ብርሃን ስለጋረደ የፀሃይ ብርሃን ወደ ውሃው ገጽ መድረስ አልቻለም)።
ከዚያም እግዚአብሔር፡- “ብርሃን ይሁን” አለ፤ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ሄዶ ወፍራሙን ደመና መታውና በታተነው። ስለዚህ የፀሃይ ብርሃን ወደ ምድር መድረስ ቻለ።
ሙሴ ይህን ሁሉ በራዕይ እያየ ነበር። በራዕይ ሲመለከት በምድር ላይ ከአንድ የሰማይ ጥግ እስከ ሌላ ሰማይ ጥግ ውሃ ብቻ ነበር የሚታየው። የውሃውም ገጽ ጠፍጣፋና ቅርጽ አልባ ነበረ። ውሃው ባዶ ነበር፤ ምንም ቅርጽ አልነበረውም ምክንያቱም ውሃ ተራራ እና ሸለቆ የለውም።
እግዚአብሔር ምድርን የሰራት የሰውን ሕይወት ጠብቆ ለማቆየት ነው
ከዚያም እግዚአብሔር ጣልቃ ሊገባና ምድርን ሕይወት ላላቸው ፍጡራን ምቹ ለማድረግ ሥራውን ጀመረ።
ይህን ለማድረግ እግዚአብሔር “ስድስት” ቀናትን መደበና በነዚህ ቀናት በምድር ላይ ሕይወት ያላቸውን ፍጡራን ፈጠረ።
በመጀመሪያ ሰዎች አልነበሩም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሰዎች የሚቆጥሩትን ባለ 24 ሰዓት ቀኖች መጠቀም አላስፈለገውም።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ … እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
ሰዎች ስላልነበሩ እግዚአብሔር ጊዜን የቆጠረው በራሱ ቀኖች ነው። አንዱ የእግዚአብሔር ቀን በሰው አቆጣጠር 1,000 ዓመታት ነው።
ምድር ላይ የነበረው ከባድ ድቅድቅ ጨለማ ከመሆኑ የተነሳ ፀሃይዋን እንኳ ማየት አይቻልም ነበር። በዚያ ጊዜ ቀን እና ሌሊት ተብሎም አይታወቅም፤ ስለዚህ የሰው ቀን አልነበረም።
በአራተኛው ቀን እግዚአብሔር ምንም ነገር አልፈጠረም።
ፀሃይ እና ጨረቃ አስቀድመው ተፈጥረው ነበር። እግዚብሔርም በአራተኛው ቀን የተፈጠሩበትን ሥራ እንዲሰሩ አደረጋቸው፤ የፀሃይና የጨረቃ ሥራ በቀን እና በሌሊት ላይ መሰልጠን ነበር።
እግዚአብሔር ምድርን ከፀሃይ እና ከጨረቃ ትክክለኛው ርቀት ላይ በማስቀመጥ ፀሃይ በቀን እንድትሰለጥን ጨረቃ ደግሞ በሌሊት እንድትሰለጥን አደረገ።
ምድር በራሷ ዛቢያ ላይ በትክክለኛው ፍጥነት ስትዞር ቀኑ ትክክለኛ ርዝመቱን ያገኛል። ምድር ፍጥነቷን ብትቀንስ የቀኑ ሙቀት ከልክ በላይ ያልፋል። እግዚአብሔር ምድር በፀሃይ ዙርያ በምሕዋርዋ የምትዞርበትን ፍጥነት ስላስተካከለ እያንዳንዱ ዓመት ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቆ ያልፋል።
ዘፍጥረት 1፡16 እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በትክክለኛ ቦታው በጥንቃቄ በትክክለኛ ርቀቱ ነው ያስቀመጠው።
ከዋክብት በየስፍራው ሰብሰብ ብለው ስለተቀመጡ ከምድር ሲታዩ የተለያዩ ምስሎችን የሚፈጥሩ ኮንስተሌሽንስ ወይም ስብስቦች ሆነዋል።
በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ የከዋክብት ስብስቦች ይታያሉ። ስለዚህ የመጀመሪያው ካላንደር ሰማዩ ነበር።
ዘፍጥረት 1፡17 እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ [ከዋክብቱን] በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤
ሳዘርን ክሮስ ወይም ደቡባዊው መስቀል የተባለው የከዋክብት ስብስብ ሰዎች በጉዞ ላይ አቅጣጫ እንዳይስቱ ይረዳቸዋል። ይህም ወደ ሰማይ የምንሄድበትን አቅጣጫ የምናገኘው በቀራንዮ መስቀል በኩል ከሄድን ብቻ መሆኑን ያመለክታል።
ዘፍጥረት 2፡2 እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።
እግዚአብሔር በዘፍጥረት 1፡1 እንደተጻፈው በመጀመሪያ ምድርን ፈጠራት ግን በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደፈጠራት አልገለጠልንም።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና (ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ሕዋ) ምድርን ያለ ምንም ነገር ፈጠረ።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የራሱን ስድስት ቀናት ማለትም የእኛን 6,000 ዓመታት ተጠቅሞ ምድርን ለሕያዋን ፍጥረታት ምቹ መኖሪያ አድርጎ አበጃት። የእግዚአብሔር ልጅ አዳም እና ሚስቱ በሰባተኛው ቀን ምድርን እንዲገዙ ተሰጣቸው፤ ይህም ሰባተኛ ቀን በሰዎች አቆጣጠር የ1,000 ዓመታት ዘመን ነበር። እግዚአብሔርም አረፈ ምክንያቱም ሁሉን ሰርቶ ስለጨረሰ ምን የቀረ ሥራ አልነበረውም።
ዘፍጥረት 2፡1 ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።
ለሰው ትልቁ ፈተና እግዚአብሔር እስኪንቀሳቀስ መጠበቅ ነው
ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ተጣብቀው ይቆያሉ ወይም እውነት የሚመስል ሌላ ሃሳብ ፈጥረው ያምናሉ?
እግዚአብሔር ፍሬያማ በመሆን እንዲበዙና እንዲባዙ (የማሕጸን ፍሬ የሚሆን) ልጅ እንዲወልዱ፤ ይህም ልጅ የቃሉ ሙላት ያለው (የዘላለም ሕይወትን ዘር በውስጡ የያዘ) እንዲሆን ነግሯቸው ነበር።
ከአዳም የሚጠበቀው እግዚአብሔር ያሰበውን እስኪፈጽም ድረስ መጠበቅ ብቻ ነበር።
የፍራፍሬ ዛፎች በውስጡ ዘር የያዘ ፍሬ ያፈራሉ።
ዘፍጥረት 1፡11 … ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን
ዘፍጥረት 1፡27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ስለዚህ አዳምን ሲፈጥረው በእግዚብሔር አምሳል የሆነ መንፈስ የሆነ ነው የፈጠረው። የሰው መንፈሱ ብቻ ነው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው እንጂ አካሉ አይደለም። አዳም በመንፈሱ ውስጥ የሴት ባህርያትም ነበሩት።
ዘፍጥረት 5፡2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው።
እግዚአብሔር መንፈስ የሆነ ሰውን ፈጠረና በውስጡ ወደፊት ሚስቱ ሆና የምትገለጠውን ሴት ባህርያትም አኖረ። በዚያ ሰዓት እርሷ ራሷን አታውቅም። ኋላ እግዚአብሔር የሴቲቱን ባህርያት ለይቶ አወጣና ለብቻዋ በአንድ አካል ውስጥ አኖራት። እርሷም ለብቻዋ ራሷን የምታውቅ ሰው ሆነች።
ዘፍጥረት 1፡28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
አዳም መንፈስ በነበረ ጊዜ ስጋ ሳይለብስ በፊት እንዲበዛ እንዲባዛ ተነግሮታል። ይህም ከወሲብ ጋር የተያያዘ ነገር አይደለም። እንስሳት በደመነፍስ ነው የሚንቀሳቀሱት፤ ስለዚህ እንስቲቱ እንስሳ መውለድ የፈለገች ጊዜ የወሲብ ፍላጎቷ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ ይህ ፍላጎት ይጠፋል። ስለዚህ እግዚአብሔር በምድር ላይ እንስሳት በበቂ ቁጥር ከተባዙ በኋላ የሁሉንም እንስሳት የወሲብ ፍላጎት ያጠፋና ከልክ በላይ እንዳይበዙ ያደርጋቸዋል።
ለሰዎች ግን እግዚአብሔር አሰራሩ የተለየ ነበር። ሰዎች ነጻ ፈቃድ አላቸው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሰዎች ወሲባዊ ግንኙነት እንዲያደርጉ ቢፈቅድላቸው ማድረግ እንዲያቆሙ ሊከለክላቸው አይችልም (ቢከለክላቸው ነጻ ፈቃዳቸውን ጣሰ ማለት ነው) ሰዎችም በምድር ላይ ያለ ልክ ይበዛሉ። ባለፉት 40 ዓመታት ብቻ የምድር ሕዝብ በእጥፍ ጨምሯል። ይህ የሕዝብ ቁጥር እንዲሁ እየጨመረ ከቀጠለ ብዙ ነገር ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ይበላሻል። ጦርነት፣ በሽታዎች እና ሞት በየጊዜው የሰውን ቁጥር ቢቀንሱም እንኳ ቁጥራችን ግን መጨመሩን አላቆመም። ማንም ባይሞትና ሁሉም ሰው ወጣት ሆኖ ቢኖር እንዲሁም ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ የፈለገውን ያህል ልጆች ቢወልድ ምን ዓይነት ዓለም ውስጥ እንደምንኖር አስቡ። ሕዝብ እንዴት እንደሚበዛ ገምቱ።
በወሲባዊ ግንኙነት መባዛት ከነጻ ፈቃድ ጋር ሲደመር ለኤድን ገነት ዘላቂነት የሚስማማ ሃሳብ አልነበረም።
እንስሳት ሐጥያት አይሰሩም ምክንያቱም በመልካም እና በክፉ መካከል ያለውን ልዩነት አያውቁም። ስለዚህ ከመጀመሪያው እንስሳት እንዲሞቱ አልነበረም የተፈጠሩት። ለዘላለም መኖር ይችሉ ነበር።
ነገር ግን ችግር የተፈጠረው እዚህጋ ነው።
ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ለሰው ነጻ ፈቃድ ሰጠው።
ነጻ ፈቃድ ደግሞ በተለያዩ አማራጮች መካከል የመምረጥን ኃላፊነት ያስከትላል። ስለዚህ ትክክል እና ስሕተት የሆኑ አማራጮች መኖር አለባቸው።
ሰው ስሕተት የሆነውን አማራጭ ቢመርጥ ይህ ሐጥያት ይባላል፤ ውጤቱም ሞትን ያስከትላል።
ስለዚህ እግዚአብሔር በመልካም እና በክፉ መካከል ያለውን ልዩነት ለአዳም አስረዳው። ከዚያ በኋላ አዳም ነጻ ፈቃዱን ይጠቀምበት ዘንድ በኤድን ገነት ውስጥ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለአዳም ተወለት።
ነገር ግን ሰዎች ሁለት ድክመት አለባቸው፡- አንደኛው ትዕግስት ማጣት ሲሆን ሁለተኛው እግዚአብሔርን እርሱ በፈለገው መንገድ ሳይሆን በራሳቸው መንገድ የማገልገል ፍላጎት ነው።
እኛ ሰዎች ራስ ወዳዶች ነን፤ እግዚአብሔርን ስናገለግልም ፈቃዱን ሳንረዳ ማገልገል እንፈልጋለን። የሐይማኖት መሰረቱ ይህ ነው። በሐይማኖት ውስጥ ደግሞ መዳን የለም።
እውነተኛው ዓለም ውስብስብ ስለሆነና እኛም የየራሳችን ምርጫ ስላለን ማየት የምንፈልገውን ብቻ ወደ ማየት እናዘነብላለን፤ የምንመርጠውም ለራሳችን የሚመቸንን ብቻ ነው። ራሳችንን እንደ ጻድቅ በመቁጠር ያገኘነውን መረጃ ሁሉ ለራሳችን ወደሚስማማ እውነት እንለውጠዋለን።
አዳም እና ሔዋን የሰባተኛውን ቀን አንድ ሺ ዓመታት በትዕግስት አሳልፈው ሴቲቱ መንፈስ ቅዱስ ጋርዷት በድንግልና የሚወለደውን የእግዚአብሔር ልጅ - ኢየሱስ ክርስቶስን እስክትወልድ ይጠብቁ ይሆን? ኢየሱስ የዛኔ ቢወለድ ኖሮ ያድጋል፤ ነገር ግን የሚሞትለት ሐጥያት አይኖርም። ከዚያም ቅዱሳኑን በሙሉ ቃል ተናግሮ ከምድር አፈር ውስጥ ይራቸው ነበር፤ በትንሳኤ ቀን ይህንኑ ነው የሚያደርገው። ከዚያ በኋላ ምድር በቂ በሆነ የሰዎች ቁጥር ትሞላለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ ደስ የሚለው ነገር ሲኦል ውስጥ መቃጠል የሚገባቸው ክፉ ሰዎችም አይገኙም።
እግዚአብሔር ምን አቅዶ እንደነበር ለአዳም አልነገረውም። አዳምም እግዚአብሔር ምን እንዳሰበ ገምቶ ሊደርስበት አይችልም። አዳም በእውቀቱ ውስን ስለነበረ ምን ምን እንደሚቻል አያውቅም።
አዳም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ሊፈጽመው አይችልም ስለዚህ አዳምና ሴቲቱ የሚጠበቅባቸው እግዚአብሔረን መጠበቅ ብቻ ነበር። እግዚአብሔርም በስተመጨረሻ ቃሉን ይፈጽመው ነበር።
ሰዎች ግን እግዚአብሔር እስኪንቀሳቀስ ድረስ ለመጠበቅ በቂ ትዕግስት አላቸውን?
ዘፍጥረት 2፡3 እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።
ይህ ጥቅስ በመፍጠርና በመስራት መካከል ያለውን ልዩነት ያሳያል።
“መፍጠር” ማለት ዓለምን እና ምድርን ያለ ምንም ነገር ወደ መኖር ማምጣት ነው።
እግዚአብሔር ያለ ምንም ነገር የሕይወትን መንፈስ ፈጠረ። ከዚያም የፈጠረውን አፈር ወሰደና ለእጽዋት እና ለእንስሳት ሁሉ አካል ሰራላቸው። ሳይሰራ ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ሁሉም ነገር ተሰርቶ ተጠናቀቀ። ስለዚህ እግዚአብሔር አረፈ።
እግዚአብሔርም የእግዚአብሔር ልጅ አዳም ከሚስቱ ጋር ምድርን ለ1,000 ዓመታት እንዲገዛ ወሰነ (በዚያ ጊዜ ሚስቱ ስም አልነበራትም)። ሴት ማለት ከወንድ ባህርይ የተወሰደች ማለት ነው።
ሰይጣን ይህንን እቅድ አበላሸ። ስለዚህ እግዚአብሔር ይህ እቅዱ ወደፊት እንዲፈጸም ወሰነ። ለዚህ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም ከቤተክርስቲያን የሆነችዋ ሙሽራው ከአርማጌዶን ጦርነት በኋላ በምድር ላይ ለ1,000 ዓመታት የሚነግሱት። ሙሽራይቱ (ካቶሊክ፣ አንግሊካን፣ ሜተዲስት፣ ሜሴጅ አማኝ የመሳሰሉ) የራሷ ስም ሊኖራት አይችልም።
“ክርስቲያን” ማለት የክርስቶስ ባህርይ አላት ማለት ነው።
እግዚአብሔር ለታላቁ እቅዱ ያዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ነበረው
ዘፍጥረት 2፡4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።
እግዚአብሔር ሰማይን (ሕዋ) እና ምድርን ያለ ምንም ነገር ፈጠረ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም ሥራቸውን እንዲሰሩ አደረገ። እግዚአብሔር ሐጥያተኞችን ይቤዥና በውስጣቸው አዲስን መንፈስ ይፈጥራል። ከዚያ በኋላ እነዚህ የዳኑ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን በማገልገል ፍጹም ፈቃዱን መፈጸም እንዲችሉ ይደረጋሉ።
“እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥” ይህ አንድ ቀን ምን ዓይነት ቀን ነው?
ይህ ቀን እግዚአብሔር ለሰው የነበረውን እቅድ ሁሉ ያሰበበት ቀን ነው።
እግዚአብሔር በልቡ ውስጥ እቅዱን በአጠቃላይ እና እያንዳንዱን ዝርዝር ሁሉ አስቦ አጠናቀቀ። ከዚያም እግዚአብሔር እቅዱ ሁሉ እርሱ በፈለገበት መንገድ በትክክል ተፈጽሞ ይጠናቀቅ እንደሆን ልጅ እንደ ቪዲዮ በምናቡ ተመለከተ። እግዚአብሔር ምንም ነገር ላይ ቸልተኛ አይደለም።
እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ በጥንቃቄ አቅዶና አስቦ በመስራት ነው የሚታወቀው።
ነገሮች ዝም ብለው በዘፈቀደ እየሄዱ አይደሉም። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያ አስቦበት አቅዶታል።
ዘፍጥረት 2፡5 የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤
እያንዳንዱ ተክል ከመጀመሪያው በእግዚአብሔር አእምሮ ውስጥ ተመዝግቦ ነበር። ከዚያ የእግዚአብሔር ሃሳብ በንግግር ቃል ተገለጠ። የእግዚአብሔርም ንግግር ኃይሉ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ የተናገራቸው ቃላት በዓይን የሚታዩ ተክሎችና እጽዋት ሆነው ተገለጡ። ነገር ግን የሚታዩ እጽዋት ሆነው ከመገለጣቸው በፊት በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ሃሳብ ሆነው ሥፍራ ይዘው ነበር።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሥራ የሰጠው ትኩረት ይህን ያህል ታላቅ ስለሆነ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠሩት ተክሎች ሁሉ እያንዳንዳቸው የት እንደሚበቅሉ አውቋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶናል ማለት አንችልም።
የእግዚአብሔር እቅድ በዝርዝር የተጠና ስለሆነ ምንም ነገር ቢሆን ወይም ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ትኩረት ሊያመልጥ አይችልም።
ዝናብ አልዘነበም ነበር። ዝናብ የሚመጣው ቀዝቃዛ አየር ከሙቅ አየር ጋር ሲገናኝ ነው። በክረምት ከአፋችሁ የሚወጣው ሞቅ ትንፋሽ የመኪናውን ቀዝቃዛ መስታወት ሲነካው ጉምና የውሃ ጠብታ ይፈጥራል።
ከመጀመሪያው ምድር ሞቃት አካባቢ እና ቀዝቃዛ አካባቢ አልነበራትም። ምድር በዛቢያዋ ላይ ቀጥ ብላ ነበር የቆመችው፤ እግዚአብሔርም ከከባቢ አየር (ከጠፈር) በላይ ውሃ አድርጎ ነበር።
ዘፍጥረት 1፡7 እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ።
ከዚያ በኋላ ከጠፈር በላይ ያለውን ውሃ እግዚአብሔር ወደ ሐይድሮጅን እና ኦክስጅን አተሞች በታተነውና በምድር ዙርያ ለምድር ጥበቃ የሚያደርግ የማይታይ መጋረጃ አደረገው። የፀሃይ ከባድ ሙቀት ወደ ምድር ሲመጣ መጀመሪያ የነዚህ ጋዞች መጋረጃ ይውጠውና የቀረው ሙቀት ሲያልፍ ምድር ሁሉ ላይ እኩል ሆኖ ይሰራጫል። ይህም ሙቀት ወደ ምድር ሲመጣ በምድር ሁሉ ላይ እኩል ሙቀት ይደርስ ነበር። ቀዝቃዛ እና ሞቃት የሆኑ አካባቢዎች ስላልነበሩና ሁሉም ቦታ ሙቀቱ እኩል ስለነበረ ሞቃት እና ቀዝቃዛ አየሮች አይጋጩም ነበር፤ ስለዚህ ዝናብ አልነበረም።
ዘፍጥረት 2፡6 ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር።
ለስለስ ያለ ጉም ተክሎችን ውሃ ያጠጣ ነበር። ስለዚህ ምንም የአፈር መሸርሸር አልነበረም። ምድር ሁሉ እንደ ግሪን ሃውስ ነበረች። ሁሉም ስፍራ በአረንጓዴ እጽዋት ተሸፍኖ ነበር።
ዘፍጥረት 2፡7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
እስከዚህ ጊዜ ድረስ በዓይን የማይታይ መንፈስ ሰው ነበረ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አዳምን በስጋ አካል ውስጥ ሊያኖረው ወሰነ። የአዳም መንፈስ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ውስጥ ያለ ምንም ነገር ነበር የተፈጠረው።
ስጋውን ግን ያለ ምንም ነገር አይደለም የፈጠረው፤ መጀመሪያ በተፈጠረው አፈር ተጠቅሞ አበጀው እንጂ። አዳምም ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይን የሚታይ አካል ያለው ሰው ሆኖ ተገለጠ።
ዘፍጥረት 2፡8 እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።
እግዚአብሔር ለልጁ ለአዳም ውብ የሆነ የአትክልት ቦታ መኖሪያ አድርጎ አዘጋጀለት። ይህም ስፍራ ምድራዊ ገነት ነበረ።
የሰው ጥበብ ከእግዚአብሔር ቃል እምነት ጋር ሲነጻጸር
ዘፍጥረት 2፡9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
ሁሉም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ በገነት ውስጥ ነበረ። አዳምም ለስጋዊ አካሉ የሚያስፈልገውን ፍሬ ከዛፎቹ እየቀጠፈ መብላት ይችላል።
አዳም ስጋዊ አካል ከለበሰ በኋላ መንፈስ ሰው መሆኑ ቀረ።
ስጋ ከለበሰ በኋላ አማራጮች ተሰጡት።
ነጻ ፈቃድ ይዞ ለመንቀሳቀስ የግል ምርጫዎች ማድረግ መቻል አለበት።
ማቴዎስ 26፡41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።
የድክመታችን ምንጩ ስጋ ነው።
አዳም መንፈስ በነበረ ጊዜ ከብዙ አደጋዎች መጠበቅ ይችል ነበር ምክንያቱም ሌሎችን መናፍስት ማየት ይችላል። ስጋ ከለበሰ በኋላ ግን ስጋው መንፈሱን ስለጋረደው በፍጥረታዊ ዓይኖሩ መናፍስትን ማየት አይችልም። ስለዚህ ተንኮለኛ መንፈስ መጥተ ሊያሳስተው ይችላል ምክንያቱም መንፈሱ ለአዳም አይታየውም።
አንዳንዶቹ ብሪስልኮን የተባሉ የአሜሪካ ዛፎች ከአራት ሺ አምስት መቶ እስከ አምስት ሺ ዓመታት ያህል ዕድሜ አላቸው። ስለዚህ በምድር ላይ ሕይወት ካላቸው ፍጡራን ሁሉ ረጅሙን ዕድሜ የኖሩት ዛፎች ናቸው። ስለዚህ በምድር ላይ ለረጅም ዘመናት የኖሩ ዛፎች ለዘላለም ሕይወት ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው። የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መንፈስ ምሳሌ ነው። በኤድን ገነት ውስጥ ለአዳም ዋነኛ መስህብ የክርስቶስ መንፈስ ነው። ከክፉው እጅ እንዲያመልጥ የሚመራውና የሚያስተምረው የክርስቶስ መንፈስ ነው።
የገነት መካከል የሚባለው ቦታ አንድ ቦታ ብቻ ነው።
“… በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ …”
ይህም የሕይወት ዛፍ በገነት መካከል ብቻውን አልነበረም ማለት ነው። መልካም እና ክፉውን የምታሳውቀውም ዛፍ በገነት መካከል ነበረች። ሁለቱም እንዴት ከገነት መካከል ሊሆኑ ይችላሉ? ሁለቱ ዛፎች ሙሉ በሙሉ እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ነበሩ። ሁለቱ አንድ ላይ አንድ ዛፍ ይመስሉ ነበር። አዳም የትኛው የሕይወት ዛፍ የትኛው ደግሞ መልካም እና ክፉውን የሚያሳውቀው ዛፍ መሆኑን መለየት ይችል ዘንድ እግዚአብሔር ለአዳም የመለየት ችሎታ ሊሰጠው ያስፈልጋል። አዳም የትኛው መንፈስ ሕይወት እንደሚሰጥ የትኛው ደግሞ ማወቅ ያስፈልገዋል። አዳም መልካም እና ክፉውን በሚያሳውቀው ዛፍ ማለትም በሰይጣን እውቀት ዛፍ እንዳይታለል የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ መከተል አለበት።
ለይቶ ማወቁን ከባድ የሚያደርገው ነገር የእውቀት ዛፍ (ወይም መንፈስ) መልካምም ክፉም እውቀት የያዘ መሆኑ ነው። መልካም የሆነውን ገጽታውን ብቻ አይታችሁ ክፉውን ገጽታ ሳታዩ ብትቀሩ ትታለላላችሁ። ከሰው እውቀት የመነጩ መኪኖች በፍጥነት ለመጓጓዝ ይጠቅሙናል፤ ነገር ግን እነዚሁ መኪኖች በአደጋ ብዙ ሰው ይገድላሉ። ማዳበሪያ ተክሎች እንዲያድጉ ይረዳል ነገር ግን ውሃ አጥቦት ወደ ወንዞችና ምንጮች ውስጥ ሲገባ ደግሞ ውሃን ይበክላል። የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ይሰጡናል፤ ነገር ግን አየሩን በመበከል የአየር ንብረት ለውጥ ያስከትላሉ። የወሊድ መከላከያ “ክኒን” የሕዝብ ቁጥርን ለመቆጣጠር ይረዳል ነገር ግን ልቅ ዝሙትን ያበረታታል። ኢንተርኔት ጠቃሚ መረጃ ያቀርብልናል፤ ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ የሐሰት ዜና እና ፖርኖግራፊ ያመጣብናል።
ስለዚህ እውቀት መልካምም ክፉም ነገር ያለበት የተቀላቀለ በረከት ነው።
በሐይማኖቱ ዓለም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እማሆይ ተሬዛ የተባለች ደግ መነኩሲትን ሰጥታናለች፤ ይህች ሴትዮ ኮልካታ ሕንድ ውስጥ የሚኖሩ ድሆችን በመርዳት ወደር አልተገኘላትም። ከዚህችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተነገኙ ካሕናት ሕጻናትን በወሲብ አስነውረዋል።
ሰው የማይታየውን የክርስቶስን መንፈስ እና የማይታየውን የሰይጣንን መንፈስ በሚወክሉ ሁለት ዛፎች መካከል እንዴት አድርጎ ሊለይ ይችላል? እነዚህ ሁለት መናፍስት የሰውን አእምሮ ለማግኘት ሲወዳደሩ ነበር።
የሰው አእምሮ ሰይጣን እግዚአብሔርን ማሸነፍ የሚችልበት ብቸኛው የጦር ሜዳ እንደሆነ ያምናል።
እግዚአብሔር ሰው ቃሉን እንዲያምን ይፈልጋል (ይህም እምነት ነው)፤ ሰይጣን ደግሞ ሰው ማንኛንም በሰው እውቀት እና ጥበብ አማካኝነት የመጣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሃሳብ እንዲያምን ይፈልጋል።
ስለዚህ በሰው አእምሮ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በጥበብ እና በእምነት መካከል ነው። ይህ ከጦርነቶች ሁሉ ታላቁ ጦርነት ነው።
በሰው አእምሮ ውስጥ ባለው ውስብስብና የተጠላለፈ ሃሳብ ውስጥ የነዚህ ሁለት ተቃራኒ መናፍስት ተጽእኖዎች ተቀላቅለው ነው የተቀመጡት። መልካም እና ክፉ ሃሳቦች አእምሮዋችን ውስጥ ያለማቋረጥ ይመላለሳሉ። ስለዚህ ምን እንደምናምን እና ለማን እንደምንገዛ ሁልጊዜ መምረጥ ይጠበቅብናል።
ሰው እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ የነገረውን አጥብቆ መከተል አለበት፤ ምክንያቱም ከሰይጣን እጅ ሊያድነን የሚችለው ብቸኛው መመሪያ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ሰይጣን አንድን ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ አጥብቆ ከመከተል ፈቀቅ ሊያደርገው ከቻለ ሰይጣን እውነት የሚመስሉ ሌሎች አማራጮችን ለሰዎች ያቀርብላቸዋል። ይህም እውነት መሳይ አማራጭ ሐይማኖት ሆኖ ይመጣል፤ ሐይማኖት ማለት ሰው እግዚአብሔርን በራሱ መንገድ የሚያገለግልበት ስርዓት ነው፤ መጨረሻውም ሞት ነው።
ከኤድን የሚወጡ 4 ወንዞች ነበሩ ነገር ግን አንዱ ብቻ ነው መልካም ወደ ሆነ ምድር የሚፈስሰው
ዘፍጥረት 2፡10 ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።
ውሃ የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌት ነው።
ዮሐንስ 7፡38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።
39 ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤
አንዱ ወንዝ ወደ አራት ወንዞች ተከፍሎ ይሄዳል።
ከነዚህ ወንዞች አንዱ መልካም ወደ ሆነው ወደ ኤውላጥ ምድር ይፈስሳል። ሌሎችም ሶስት ወንዞች ነበሩ።
ይህ ስለ እግዚአብሔር አንድነት የሚደረገውን ክርክር ይመስላል።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን የሚችል አምላክ ነው የሚለው እምነት እና አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ 3 የተለያዩ የስላሴ አካላት ናቸው የሚለው ትምሕርት።
ዘፍጥረት 2፡11 የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል
ዘፍጥረት 2፡12 የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤ ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል።
የመጀመሪያው ወንዝ መልካም በሆነው ምድር ውስጥ ያልፋል። ከሰማይ የሚወርደው መና መልኩ ሉል ይመስላል። የአይሁዶች ሊቀ ካሕናት በልብሱ ላይ ሁለት የከበሩ ድንጋዮች አሉት።
ዘኁልቁ 11፡7 መናውም እንደ ድንብላል ዘር ነበረ፥ መልኩም ሙጫ ይመስል ነበር።
ዘጸአት 28፡9 ሁለትም የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ስማቸውን ቅረጽባቸው፤
ሌሎቹ ሶስት ወንዞች ኋላ የእስራኤል ጠላት በሆኑ ሃገሮች ምድር ውስጥ ያልፋሉ። ይህም ከመጀመሪያው እግዚአብሔርን በመከተል የሚጀምር ነገር ግን ኋላ ወደ ስሕተትና እግዚአብሔርን ወደ መቃወም የገባ ሰውን ያመለክታል።
ዘፍጥረት 2፡13 የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።
2ኛ ዜና 14፡9 ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው [በእስራኤልና በይሁዳ ላይ]፤ ወደ መሪሳም መጣ።
ዘፍጥረት 2፡14 የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።
አሦር የእስራኤልን ሰሜናዊ ግዛት ባሪያ አደረገ።
ኤፍራጥስ በባቢሎን በኩል ያልፋል፤ ባቢሎንም ደቡባዊውን የእስራኤል መንግስት ባሪያ አደረገ።
የአንድ ወንዝ ውሃ ብቻ ወደ መልካም ምድር ፈሰሰ፤ ሶስት ወንዞች ግን ኋላ ጠላት ወደ ሆኖ ሃገሮች ግዛት ውስጥ ፈሰሱ። ይህም አይሁዶች በአንድ አምላክ እንደሚያምኑ ባቢሎናውያን ግን በስላሴ እንደሚያምኑ ያመለክታል።
የስላሴ ሃሳብ ኋላ ወደ ሕንድ እና ግብጽ እንዲሁም ወደ ጴርጋሞን እና ወደ ሮም ተዛመተና የአረማውያን አምልኮ ውስጥ ዋነኛ ትምሕርት ሆነ። ይህም ትምሕርት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከገባ በኋላ ካቶሊክ ወዳልሆኑ እና ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ሾልኮ ገባ። የስላሴ ትምሕርት ከግሪክ ፍልስፍና በመጡ ሃሳቦች ላይ የተመሰረተ ትምሕርት ነው።
“አንድ አምላክ በሶስት አካላት”።
“አብ እና ወልድ አንድ ባህርይ ናቸው”።
“ዘላለማዊ ልጅነት”።
“የመለኮት ሁለተኛው አካል”።
“ኢየሱስ በመለኮት ውስጥ ነው”።
ከላይ ከተዘረዘሩት አነጋገሮች መካከል አንዱም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም፤ ስላሴ የሚለውም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው የስላሴ ትምሕርት እየተስፋፋ ሄዶ የነካውን ነገር ሁሉ አረከሰው።
እግዚአብሔርም ስሙ ጠፋ ምክንየቱም ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ማግኘት አይቻልም።
ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያኖች ጴጥሮስ የተናገረው ስሕተት ነው በማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማጥመቅ አቆሙ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38) ።
አሁን ቤተክርስቲያኖች በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቃሉ፤ ነገር ግን ይህ ስም ማን እንደሆነ የሚያውቁት ነገር የለም። ከዚያም እነዚህ ሶስት ማዕረጎች አንድ ስም ናቸው ይላሉ። ይህም አማርኛን የሚያጣምም አነጋገር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈ አንዳችም ነገር በውስጡ ሳንለውጥ ጠብቀን ማቆየት አለብን ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ ቃል እውነት ነው።
ዘፍጥረት 2፡15 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።
እውነቱን ወደ መረዳት ስንመጣ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ስም ነው (እግዚአብሔር ከአይሁዶች በላይ) የወልድ ስም ነው (እግዚአብሔር ከአይሁዶች ጋር) እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው (እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ)።
ወሳኝ ትምሕርት፡ እግዚአብሔር ሰውየውን የኤድን ገነት ውስጥ አኖረው። አዳም በፈቃደኝነትና በሙሉ ፍላጎት በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ ነበረ።
እግዚአብሔር ለአዳም ሥራው የኤድን ገነትን መንከባከብና እግዚአብሔር ሲፈጥራት እንደነበረች አድርጎ መጠበቅ መሆኑን ነገረው።
እግዚአብሔር የ1769 ዓመተ ምሕረቱን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው እውነት አድርጎ ሰጥቶናል፤ እኛም እያንዳንዱን ጥቅስ እንደተጻፈ ማንበብና ማመን አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን መጠበቅና ልክ እንደተጻፈ ማብራራት አለብን።
ስጋዊ እውቀት ማለት ወሲብ ነው
ዘፍጥረት 2፡16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ መልካም እንደሆኑ ተናግሯል።
ዘፍጥረት 1፡12 ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ፍጥረታዊ የሆነ የዛፍ ፍሬ ምንም ችግር ሊፈጥር አይችልም። እስከ ዛሬ ድረስ ፍራፍሬ መብላት ጤናማ ሆኖ ለመኖር ይመከራል።
ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
ለአዳም የተሰጠው ማስጠንቀቂያ የእውቀት ዛፍን በተመለከተ ነው።
ዛፎች ሁሉ መልካም ነበሩ ስለተባለ ይህ ዛፍ ፍጥረታዊ ዛፍ አይደለም።
ይህ አዳም ሊጠነቀቅበት የሚገባው ሌላ ነገር ነበረ። አዳም ስሕተትን ለይቶ እንዲያውቅና ከመታለል ይተርፍ ዘንድ እግዚአብሔር ስለዚህ የእውቀት ዛፍ በተመለከተ ለአዳም አስተምሮታል።
የሴቲቱ ሕልውና እና ባሕርያት በሰውየው ውስጥ ነበሩ ስለዚህ ሴቲቱ ምን እየተደረገ እንደነበረ አንዳችም የምታውቀው ነገር የለም።
እግዚአብሔር ለአዳም ሚስት አዘጋጀለት፤ የእርሷም ኃላፊነት በድንግልና የሚወለደውን ልጅ ኢየሱስን ጸንሳ መውለድ ነበር።
ኢየሱስም አድጎ ቅዱሳኑን ሁሉ ከምድር አፈር በቃሉ ጠርቶ ይፈጥራቸው ነበር።
ሰይጣን አዳም እና ሚስቱ ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ልጅ እንዲወልዱ አሳመናቸው። አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ቢፈጽም ሐጥያት አይደል። ታድያ አዳምና ሔዋን ወሲብ መፈጸማቸው እንዴት ነው ስሕተት የሚሆነው? ችግሩ የሚወለደው ሕጻን የዘላለም ሕይወት የሌለው መሆኑና አንድ ቀን የሚሞት መሆኑ ነው።
እግዚአብሔር በወሲባዊ ግንኙነት መባዛት ላይ የጊዜ ገደብ አደረገ። ይህም አንድ ቀን ነው የሚሆነው።
የእግዚአብሔር አንድ ቀን የእኛ 1,000 ዓመት ነው።
በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የተወለደ ሰው ለ1,000 ዓመታት ሊኖር አይችልም። እስካሁን ከሁሉም የበለጠ ረጅም ዘመን የኖረው ማቱሳላ ዕድሜው 969 ዓመት ነው።
ዘፍጥረት 5፡27 ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
እውቀት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ሊሆንም ይችላል ምክንያቱም ወሲብ በሕጉ ውስጥ “ስጋዊ እውቀት ተብሏል”።
ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።
አዳም ሚስቱን አወቀ ማለት ከእርሷ ጋር “በስጋ ተዋወቀ” ማለት ነው። አዳም መልካም እና ክፉውን የምታሳውቀውን ዛፍ ፍሬ በልቷል። በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የተወለዱ ሰዎች ወይ መልካም ወይ ደግሞ ክፉ ሰዎች ይሆናሉ። በወሲብ የመባዛት ችግሩ እንደ ሒትለር ዓይነቶቹ ክፉ ሰዎች ወደ ሲኦል ገብተው መቃጠላቸው ነው።
በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የተወለደው የመጀመሪያው ሰው ቃየን ሲሆን እርሱም ወንድሙን ከገደለው በኋላ እግዚአብሔር ስለ ወንድሙ ስለ አቤል ሲጠይቀው ለእግዚአብሔር ዋሽቶ መለሰ። ስለዚህ በወሲባዊ ግንኙነት የተወለደው የመጀመሪያው ሰው ውሸታምና ነፍሰ ገዳይ ሆነ።
መጽፍ ቅዱስ ክፉውን ሲገልጽ እንዲህ ይላል።
ዮሐንስ 8፡44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።
ስለዚህ ቃየን የአዳም ልጅ ሳይሆን የሰይጣን ልጅ ነበረ።
በወሲባዊ ግንኙነት አማካኘነት መወለድ ከመጀመሪያውም ጀምሮ መጥፎ ነገር ነበረ።
የሚገርመው ነገር ቃየን የበኩር ልጅ ቢሆንም እንኳ መጽሐፈ ዜና ውስጥ አልተጠቀሰም። በኩሮች ክብር ያላቸው ከመሆናቸውና ርስት ሲቀበሉም እጥፍ ድርብ የሚሰጣቸው ሆነው ሳለ ቃየን በበኩርነቱ አለመጠቀሱ እንግዳ ነገር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ቃየን የተወለደው ከክፉው ነው ይላል
1ኛ ዮሐንስ 3፡12 ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል
ማቴዎስ 13፡19 የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።
ክፉው የተባለው ሰይጣን ሲሆን ዋነኛ ስራው ሰዎች እንዳያምኑ ማድረግ ነው።
ሰይጣን በሰዎች በኩል ነው የሚሰራው፤ ሰይጣን የሚሰራባቸውም ሰዎች ሄደው ሌሎች ሰዎችን በማናገር የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይቀበሉ ያደርጓቸዋል።
“ክፉው” የሚለው ሁለት ትርጉም አለው።
ይህ ቃል በሰው ውስጥ የሚሰራውን ሰይጣን እንዲሁም አእምሮውን ለሰይጣን መጠቀሚያ እንዲሆን አሳልፎ የሰጠውን ሰውም ያመለክታል።
“ክፉው” የሚለው አዳምን ሊወክል አይችልም ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል።
ሉቃስ 3፡38 … የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ።
ሔዋን የተቀጣችው ስረገዘች ነው ምክንያቱም በማሕጸኗ ውስጥ ጽንስ ተሸክማ ነበር።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤
አዳም አባት አልነበረም።
የትኛውም ባል ሚስቱን ስላስረገዘ ተብሎ ሊቀጣ አይችልም።
ኤድን ውስጥ ሴቲቱ የታተመች የሕይወት ምንጭ ነበረች
ዘፍጥረት 2፡18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።
ኤድን ገነት ውስጥ ለታላቅ ፍጥጫ መድረክ እየተዘጋጀ ነው። አዳም መንፈስ በነበረ ጊዜ ሌሎች መናፍስትን ማየት ይችል ነበር፤ ከዚህም የተነሳ ሰይጣንን በቀላሉ ስለሚለየው አይታለልም ነበር። ደግሞም በመንፈሱ ውስጥ ወደፊት ሚስቱ የምትሆነዋን ሴት ባህርይም መያዙ ለእርሱ መልካም ነበር። በዚያ ጊዜ ይሆኑ የነበሩ ነገሮችን እርሷ ምንም አታውቅም ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ እናንተም አባታችሁ ወጣት በነበረ ጊዜ የዘር ሕዋስ ሆናችሁ በአባታችሁ ውስጥ ነበራችሁ፤ ግን አባታችሁ ውስጥ መሆናችሁን አታውቁም ነበር። ከእናታችሁ ስጋዊ አካል ለብሳችሁ ስትወለዱ ብቻ ነው በዙርያችሁ ስላሉ ነገሮች ማወቅ የጀመራችሁት።
አሁን ግን አዳም ስጋ ስለለበሰ እንደበፊቱ መናፍስትን ማየት አልቻለም፤ ከዚህም የተነሳ በማይታዩ መናፍስት የሚታለል ሰው ሆነ። ስጋ ከለበሰ በኋላ የሴቲቱን ባህርያት በውስጡ ይዞ መኖሩ ለእርሱ ምንም ጥቅም አልነበረውም። ወንድ እና ሴት ራሳቸውን በየግላቸው የሚገልጡበት የተለያዩ አካላት ያስፈልጓቸዋል።
ስጋ የለበረው ሰው በድንግልና የሚወለደውን ወንድ ልጅ ለመውለድ ሚስት እንደምታስፈልገው እግዚአብሔር ወሰነ። የዘላለም ሕይወት ወደ ምድር የሚመጣበትና በምድር ላይ የሚኖርበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነበር።
አዳም እና ሔዋን በወሲባዊ ግንኙነት በኩል ልጅ ከወለዱ የወለዱት ልጅ የሰው ሕይወት ብቻ ነው የሚኖረው ስለዚህ ለ1,000 ዓመታት መኖር አይችልም።
የአዳም ሚስት ሕይወት ያለው ልጅ በወሲባዊ ግንኙነትም ይሁን በድንግልና ለመውለድ የመራቢያ አካላት ያስፈልጓታል። ከሁለቱ መንገዶች በአንዱ መውለድ የእርሷ ምርጫ ነው።
አዳምም የመራቢያ አካላት ሊኖሩት ያስፈልገዋል፤ አለበለዚያ በድንግልና ከመውለድ ውጭ አማራጭ አይኖረውም። ነገር ግን የአዳም መራቢያ አካላት በምድር ላይ ዘላለማዊ ሕይወትን ማምጣት አይችሉም።
በተመሳሳይ መንገድ ሰዎች ሐይማኖታዊ ስርዓቶችን ሊያበጁ ይችላሉ ነገር ግን እነዚህ ስርዓቶች ምንም አየጠቅሙም ምክንያቱም ዘላለማዊ ሕይወትን ሊያመጡ አይችሉም።
ስለዚህ የሕይወት ዛፍ ወይም መንፈስ (በድንግልና የተወለደ ልጅ) እና የእውቀት መንፈስ (በወሲባዊ ግንኙነት የተወለደ ልጅ) የሴቲቱን ማሕጸን ለማግኘት ይሽቀዳደማሉ።
ማሕጸኗ በአካሏ መካከል ነው የሚገኘው።
ሁለቱም ዛፎች በገነት መካከል ነበሩ።
መኃልየ መኃልይ 4፡12 እሕቴ ሙሽራ የተቆለፈ ገነት፣ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።
ገነት የሴት ምሳሌ ናት። የተቆለፈ ገነት በዙርያው አጥር አለው። ሴቶች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል።
የተዘጋ የሕይወት ምንጭ፡- የሴት ትልቁ ሃብቷ ክብረ ንጽሕናዋ ነው። እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወት ምንጭ ማለትም የክርስቶስ መንፈስ በተዘጋ ማሕጸን ውስጥ ተሰውሮ በነበረ ሕጻን በኩል እንዲገለጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ የክርስቶስ መንፈስ አዳም እና ሚስቱ ለ1,000 ዓመታት እንዲጠብቁ ይፈልጋል፤ ከዚያም በኋላ መንፈስ ቅዱስ ሴቲቱን ይጋርዳትና ወንድ ልጅ - ሕጻኑን ኢየሱስን በድንግልና ጸንሳ እንድትወልድ ያደርጋታል።
በፍሬ (በሕጻኑ) ውስጥ የሚገኘው ዘሩ (ቃሉ) ነው። በዚህ ዓይነቱ ጽንስ የተገኘው ፍሬ ማለትም ኢየሱስ በውስጡ ዘር ስለሚኖረው ኋላ ኢየሱስ አድጎ ከምድር አፈር ጠርቶ ለሚያመጣቸው ቅዱሳን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ያድላል።
የሰይጣን የመልካም እና ክፉ እውቀት ዛፍ የድንግልናን መጋረጃ መቅደድ እና ከመጋረጃው ኋላ በማሕጸን ውስጥ መጸነስን ያስከትላል። ይህም ለ1,000 ዓመታት እንኳ መቆየት የማይችል ተራ የሰው ሕይወት እንዲወለድ ያደርጋል።
ሁለቱ ዛፎች ተጠላልፈው እንደ አንድ ዛፍ ነው የቆሙት። ሁለቱም መናፍስት በሴቲቱ ማሕጸን ውስጥ ዘር ለማስቀመጥ የሴቲቱ አእምሮ ውስጥ ሃሳብ ያስቀምጣሉ፤ የሚያስቀምጡዋቸው ሃሳቦች ሁለት የተለያዩ አወላለዶችን የሚመለከቱ ናቸው።
አዳም እና ሚስቱ በኤድን ገነት ውስጥ 24 ርዝመት ላለው አንድ ቀን ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ነው የቆዩት።
ዘፍጥረት 2፡19 እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።
አዳም ከፊቱ የሚጠብቅ ብዙ ሥራ ነበረው። አዳም በቁጥር ብዙ ዓይነት ለሆኑት እንስሳትና ወፎች ሁሉ ስም የማውጣት ሥራ ይጠብቀዋል። ዛሬ በምድር ላይ 9,000 ዓይነት የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች አሉ። 9,000 ዓይነት ሁሉ የተለያዩ ስሞችን አስቦ ማምጣት ጊዜ ይፈልጋል። በአንድ ደቂቃ ለአንድ ወፍ ስም ቢያወጣ የምሳ እረፍት ሳይወስድ በየቀኑ ለ12 ሰዓታት ቢሰራ 13 ቀናት ይፈጅበታል።
አዳም ግን ለእያንዳንዱ እንስሳ እና ወፍ ተስማሚ ስም ከማውጣቱ በፊት እያንዳንዱን እንስሳ እና ወፍ ለተወሰነ ጊዜ በትኩረት ማጥናት አለበት። ስለዚህ ለእያንዳንዱ ወፍ እና ለእያንዳንዱ እንስሳ ስም የማውጣቱ ስራ የተወሰነ ጊዜ ይፈጃል።
ደግሞም በኤድን ገነት ውስጥ የነበሩትን አትክልት እግዚአብሔር ሲፈጥራቸው እንደነበሩ አድርጎ ለመጠበቅ ስለ አትክልት እንክብካቤ ማወቅም ያስፈልገዋል።
ስለዚህ ስድስተኛው እና ሰባተኛው ቀን ባለ 24 ሰዓት ቀኖች ብቻ ሊሆኑ አይችሉም።
ዘፍጥረት 2፡20 አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።
በምድር ላይ ዛሬ 5,500 ያህል የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች አሉ። አዳም በነበረበት ዘመን ምናልባት ዛሬ ካሉት የበለጠ ብዙ ዓይነት እንስሳት ይኖሩ ይሆናል። ስለዚህ ለነዚህ ሁሉ ዓይነት እንስሳት ስም ማውጣት ጊዜ መፍጀቱ አይቀርም።
አንድ ቀን በእኛ አቆጣጠር 1,000 ዓመታት ከሆነ ስራ ለማጠናቀቅ ጥድፊያ አይኖርም ማለት ነው።
በመጀመሪያ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ደም አልነበረም
ዘፍጥረት 2፡21 እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው።
እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና ሲሰራ ማደንዘዣ ተጠቅሞ ነው የሰራው። እግዚአብሔር ከአዳም አካል ውስጥ አንድ የጎድን አጥንት አውጥቶ ስጋውን የቀደደበትን ቦታ ዘጋው። እግዚአብሔር የቀዶ ጥገና ስራው ፍጹም ስለሆነ የአዳም አካል በተቀደደበት ቦታ ጠባሳ አይገኝም። ከአካሉ የተጣውን አጥንት ተጠቅሞ እግዚአብሔር ድንቅ ተዓምር ሰራበት። አንዲት አዲስ ሴትን አበጀ። ይህም ስራ ክሎኒንግ አይደለም ምክንያቱም ሴቲቱ ከሰውየው በጣም የተለየች ናት። የአዳም አጥንት ከልቡ አጠገብ ነው የተወሰደው ይህም አዳም ለሚስቱ የሚኖረውን ጥልቅ ፍቅር ያመለክታል።
ዘፍጥረት 2፡22 እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።
እግዚአብሔር በመጀመሪያ አዳምን በኤድን ገነት አኖራው። ከዚያም እግዚአብሔር ለአዳም ሚስት አመጣለት። ሁላችንም የራሳችንን ፍላጎትና ምኞት ለማሟላት ከመሯሯት ይልቅ እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ነገር ተደስተን መኖር ይገባናል።
ዘፍጥረት 2፡23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።
ደም በጭራሽ አልተጠቀሰም። ይህ ትልቅ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። አዳም ስለ ስጋ እና ስለ አጥንት ብቻ ነው የተናገረው። ደም ከሌላቸው ደም ስራቸው ውስጥ የሚመላለሰው መንፈስ ቅዱስ ነበረ ማለት ነው።
ደም ከሌለ ወሲባዊ ግንኙነት ሊኖር አይችልም ምክንያቱም ወሲባዊ ግንኙነት ለማድረግ የወንድ ብልት ውስጥ ደም መሰራጨትና ብልቱን ዝግጁ ማድረግ አለበት።
ስለዚህ አዳምም ሚስቱም እግዚአብሔር ባዘጋጀላቸው በመጀመሪያው አካል ውስጥ ሳሉ ወሲብ መፈጸም አይችሉም ነበር።
ሴቲቱ ድንግልናዋን የሚያመለክት ሕግ ነበራት፤ ይህም እርሷ ወሲብ እንድትፈጽም እግዚአብሔር አለመፈለጉን ያመለክታል።
አዳም እና ሚስቱ ሁለቱም የዘላለም ሕይወት ነበራቸው፤ ይህም የዘላለም ሕይወት በደም ስራቸው ውስጥ ይመላለስ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥
የዘላለም ሕይወት የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ነው። ደም የዘላለም ሕይወት አካል አይደለም። ደም ያለበት ሕይወት ጊዜያዊ የሆነውን የእግዚአብሔር የይሁንታ ፈቃድ ይወክላል።
ኢየሱስ ሐጥያታችንን ለማስተስረይ በሰውነቱ ውስጥ የነበረውን ደም በሙሉ በቀራንዮ መስቀል ላይ አፈሰሰው።
ከዚያ በኋላ በትንሳኤ የተገለጠበት አካል ስጋ እና አጥንት አለው ግን ደም እንዳለው ምንም አልተጠቀሰም።
ሉቃስ 24፡39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።
ደም የእግዚአብሔር መንግስት አካል አይደለም።
ደም የዘላለማዊነት አካል አይደለም።
የሐጥያት ሚስጥር ሐጥያት ሲገባ ደም የሰው አካል ውስጥ መግባቱ ነው።
ስለዚህ ደም ሁልጊዜ የሐጥያት ተምሳሌት ነው። ሐጥያትን ለማስተስረይ የእንስሳ ደም ለምን እንዳስፈለገ ማወቅ አለብን።
በዝንጀሮ እና በሰዎች መካከል የሚገኘው እባብ የተባለው እንስሳ የሔዋንን ድንግልና በወሰደ ጊዜ ደሟን አፈሰሰ። የመጀመሪያው ሐጥያት እንስሳ ደም ማፍሰሱ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ሐጥያትን ለማስተስረይ የእንስሳ ደም መፍሰስ አለበት አለ።
ደግሞም አዳም እና ሔዋን ሐጥያት ከሰሩ በኋላ እግዚአብሔር ለምን ንሰሃ ግብ እንዳላላቸው ማወቅ አለብን።
ሔዋን ድንግልናዋ ተወስዷል። ስለዚህ በድንግልና ለሚወለደው ሕጻን እግዚአብሔር የእርሷን ማሕጸን መጠቀም አይችልም። ሊሻር የማይችል ሐጥያት ሰርታለች።
እግዚአብሔር ንሰሃ ግቡ ያላላቸው ረስቶ ይመስላል። እግዚአብሔር ለቀረነው ሰዎች ሁሉ ንሰሃ የመግባት እድል ሲሰጠን ለአዳም እና ለሔዋን ለምንድነው ንሰሃ እንዲገቡ እድል ያልሰጣቸው?
ዘፍጥረት 2፡24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
ይህ ስለ ወደፊቱ የሚናገር ትንቢት ነው።
እግዚአብሔር ሐጥያት እንደሚመጣና የሰዎችን ኑሮ እንደሚበጠብጥ ቀድሞ አውቋል።
ስለዚህ በዚህ ነውጥ በሞላበት ዓለም ውስጥ እግዚአብሔር ጋብቻን ለሰዎች የተረጋጋ ኑሮ መፍጠሪያ አድርጎ አዘጋጀ።
እግዚአብሔር በባል እና በሚስት መካከል ያለው አንድነት በወላጆች እና በልጆች መካከል ካለው አንድነት በላይ የጠነከረ እንደሆነ ከመጀመሪያው አወጀ። ይህም ከፍቅሮች ሁሉ ታላቅ የሆነውን በኢየሱስ እና በሙሽራይቱ ማለትም በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ፍቅር የሚያሳይ ነው። ብዙ ጋብቻዎች የሚፈርሱት በተጋቡት ልጆች መካከል ወላጆች ጣልቃ ስለሚገቡ ነው። በሚስት እና በአማቷ መካከል ግጭት በቀላሉ ይፈጠራል።
ልጆቹን ከልክ በላይ የሚቆጣጠር አባት ከተጋቡ በኋላ እንኳ መቆጣጠር ሊፈልግ ይችላል።
ስለዚህ አዲስ የተጋቡ ወንድ እና ሴት ከወላጆቻቸው ተነጥለው ኑሮ በራሳቸው ቢጀምሩና ኃይለኛ ወላጆች ጣልቃ ከሚገቡባቸው እግዚአብሔር ብቻ ቢመራቸው ይሻላቸዋል።
ዘፍጥረት 2፡25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።
የለበሱት ስጋ ደም አልነበረውም። ሰውነታቸው ውስጥ ደም ከሌለ ወሲብ አይፈጽሙም። ወሲብ ስለማይፈጽሙ ሐፍረተ ስጋቸውን ከምንም አይቆጥሩትም ነበር ምክንያቱም አይጠቀሙበትም። ልክ ሕጻናት ራቁታቸውን ሲሆኑ ምንም የማያሳፍራቸውን ያህል በሃሳባቸው ንጹህ ነበሩ።
ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር በሰጣቸው መመሪያ ቢኖሩ ምንም ችግር ባልገጠማቸው ነበር።
እግዚአብሔር ከተናገራቸው ቃል የተለየ ብልጣ ብልጥ ትርጓሜ ካዳመጡ በሽንገላ ይወድቃሉ።
ነጻ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል። ምርጫም ስለቀረበላቸው መምረጥ የእነርሱ ፈንታ ነው።