ዘፍጥረት 1፡26 እና 3፡22 ውስጥ እግዚአብሔር የተጠቀሰው በብዙ ቁጥር ነው
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ለምን? ይህ የብዙ ቁጥር አገላለጽ ነገስታት ታላቅነታቸውነ ለመግል የሚጠቀሙት ነው። የእግዚአብሔርን ባሕርያት በሙሉ ሊገልጽ የሚችል አንድ ቃል የለም።
- ሰውን በመልካችን እንፍጠር። 3 ሰዎች አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ፈጠሩ ማለት ነው?
- “ኤሎሂም” የሚለው ሰም ብዙ ቁጥር ነው፤ ነገር ግን አብሮት የሚገኘው “ባራ” የሚለው ግስ ነጠላ ነው
- ቀላሉን መንገድ መምረጥ የለብንም
- እግዚአብሔር ከእኛ በላይ (አብ)፣ ከእኛ ጋር (ወልድ) ነበረ፤ እንዲሁም በእኛ ውስጥ (መንፈስ ቅዱስ) ነው
- ሰማይን መግለጽ የሚችሉ ቃላት የሉንም
- ነገር ግን እግዚአብሔርን ያየ አንድ ስንኳ የለም
- ዮሐንስ 5፡22 አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም
- የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ብቻ ናት አፏን ከፍታ የምትናገር፤ የመጀመሪያው ቃሏም “እኔ” የሚል ነው
- 7ኛው መልአክ የሰው ልጅ አይደለም
- ሁለት ሰዎች ሳይሆኑ ሰውኛ ዘይቤ
ሰውን በመልካችን እንፍጠር። 3 ሰዎች አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ፈጠሩ ማለት ነው?
ዘፍጥረት ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን “ኤሎሒም” ብሎ ነው የሚጠራው፤ ይህም ነጠላ ሆኖ ግን የብዙ ቁጥር ቅርጽ ያለው ቃል ነው። አንድን ወይም ከአንድ ግለሰብ በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ሊወክል ይችላል።
ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤
ዘፍጥረት 3፡22 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤
ሰውን በመልካችን እንፍጠር።
ይህ “እንፍጠር” የሚለው ቃል ነገስታት የሚጠቀሙት አነጋገር ነው።
ዕዝራ 4፡11 ለንጉሡ ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤ ግልባጭ ይህ ነው፦ በወንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪያዎችህ
ደብዳቤውን የላኩት “ለንጉሡ” ነው እንጂ ለንጉሡ እና ለአማካሪዎቹ አይደለም።
ንጉሡ የሰጠውን መልስ ተመልከቱ።
ዕዝራ 4፡18 ሰላም አሁንም ወደ እኛ የላካችሁት ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነበበ።
“እኛ” የሚለው ቃል ንጉሳዊ “እኛ” ነው።
በምድር ላይ አዳምና ሔዋንን የፈጠሩ በሰማይ የሚኖሩ ሶስት አካላት የሚታዩዋችሁ ከሆነ የሚገጥማችሁን ችግር ተመልከቱ።
አዳም እና ሔዋን ማለትም አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በሰማይ የሚኖሩ የሶስት ሰዎች አምሳል አይደሉም።
ከዚህ በታች የሚገኙ ቃላትና ሐረጎች በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።
- ስላሴ
- እግዚአብሔር ወልድ
- እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
- አንድ አምላክ በሶስት አካላት
- በመለኮት ውስጥ የሚገኙ ሶስት አካላት
- ኢየሱስ የመለኮት አካል ነው
- ከመለኮት የመጀመሪያው አካል
- ከመለኮት ሁለተኛው አካል
- ከመለኮት ሶስተኛው አካል
- አብ እና ወልድ እኩል ናቸው
- አብ እና ወልድ አንድ ባህርይ ናቸው።
- የወልድ ዘላለማዊ ልጅነት
ከነዚህ ቃላትም ደግሞ የባሰ አለ። ይኸውም፡- “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመገኘቱ ነው።
“እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ አይገኝም፤ አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው የተጠቀሰው። ለምን? የስላሴ አስተማሪዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ የላቸውም።
“እንፍጠር” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር መጠቀሱን በተመለከተ የስላሴ አስተማሪዎች ፈጥነው የሚሰጡት መልስ፡- “እግዚአብሔር አብ፣” “እግዚአብሔር ወልድ፣” እና “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” በአንድነት ተሰብስበው እየተነጋገሩ ነው የሚል ነው። ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከነዚህ ሶስት መጠሪያዎች አንዱም አይገኝም። ስለዚህ የስላሴ አስተማሪዎች የሚሰጡት መልስ ትክክል አይደለም።
በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” ተብሎ ለምን እንዳልተጻፈ ማብራራት አይችሉም።
ስለዚህ ስላሴ የተባለው መለኮት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ንግግሮች ላይ ነው።
ይህም ከግሪክ ፍልስፍና የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን የማጣመም ስራ ነው።
አንድነት በሶስትነት እና አንድ ባህርይ የሚሉት አገላለጾች ምንጫቸው የግሪክ ፍልስፍና እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም።
ቀጥሎ ደግሞ ትልቅ ችግር አለ፡
ይህም ስላሴ የሚሉት አምላክ ስም የሌለው መሆኑ ነው።
አብ JHWH ወይም JHVH ወይም YHWH ነው ይላሉ (የተለያዩ ሰዎች የተለያየ አጠራር ይጠቀማሉ)።
ነገር ግን ያ “ስም” አጠራሩ አይታወቅም። ስለዚህ ሁልጊዜ “እግዚአብሔር” ተብሎ ይተረጎማል። “እግዚአብሔር” ደግሞ ስም አይደለም።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ስም ሚስጥር ነበረ።
“እኔ ነኝ” ስም አይደለም። ያለ ማንም ድጋፍ በራስ መኖርን የሚገልጽ አነጋገር ነው።
የሶምሶን ወላጆች እግዚአብሔርን በመልአክ መልክ እንደተገለጠ አካል አዩት። እግዚአብሔር መልአካዊ አካል ነው።
መሳፍንት 13፡18 የእግዚአብሔርም መልአክ፦ ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ? አለው።
መሳፍንት 13፡22 ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት።
የእግዚአብሔር ስም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሶ አያውቅም።
እንደ ኤሎሒም እና አዶናይ የመሳሰሉ “ስሞች” እግዚአብሔር ወይም ጌታ ወይም በራሱ የሚኖር የሚል ትርጉም ያላቸው ማዕረጎች እንጂ ስሞች አይደሉም።
JHVH ለተባሉት ተነባቢ ፊደሎች አናባቢ ብንጨምርላቸው ለአብ “ያህዌ” የሚል ስም እናገኝለታለን።
ይህ ግን ለስላሴ ትምሕርት ምንም አይጠቅምም ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ስም አልተሰጠውም።
ከያህዌ እና ከኢየሱስ ለሶስት አካላት ሁለት ስም እናገኛለን፤ ይህም አሳማኝ አይደለም ምክንያቱም ስላሴ ሶስት አካላት ናቸው። ከሶስቱ አንዱ ለምንድነው ስም የማይኖረው?
ስለዚህ በመለኮት ውስጥ ለሚገኙ ሶስት አካላት ሶስት ስሞች አናገኝላቸውም።
ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” እንደመሆኑ የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ስሙ ነው።
ለእግዚአብሔር የምናገኝለት ብቸኛው ስም ይህ ነው።
ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ካላችሁ “እግዚአብሔር ወልድ” አትበሉ።
“እግዚአብሔር ወልድ” እና “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” የሚሉ አነጋገሮች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም።
ለስላሴ አንድ ስም ፈልጋችሁ አግኙ። አይገኝም።
ስለዚህ ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ልናገኝ አንችልም።
ቤተክርስቲያኖች ሁልጊዜ “በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ይላሉ፤ ነገር ግን ይህ ስም ማን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም።
ስለዚህ ቤተክርስቲያን በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ያፈለቀውን ሽንገላ ተቀብላ የእግዚአብሔር ስም ጠፍቶባታል።
ግብጻውያን ለሚያምኑበት ስላሴ አንድ ስም ሊሰጡት ሞክረው አያውቁም።
የጥንት ግብጻውያን ሶስት ሰዎች አንድ ስም ሊኖራቸው እንደማይችል ተረድተዋል።
የስላሴ ሃሳብ ከየት እንደመጣ ገብቷችኋል? ግብጽ ትልቅ ሚና ተጫውታለች።
የእግዚአብሔር ስም እንደጠፋባት በደምብ ለማሳየት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለኢየሱስ “ኢየሱስ የሰዎች አዳኝ” ወይም በላቲን ቋንቋ "Iesus Hominum Salvatore" ብላ በሰጠችው ስም የግብጽን ስላሴ ስም የመጀመሪያ ፊደሎች ማለትም IHS ኮርጃለች።
መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ የአረማውያንን አማልክት ስም ኮርጀን ክርስቲያናዊ ትርጉም እንድንሰጠው አላዘዘንም።
ይህም ቢሆን “ኤሎሒም” የሚለው ስም በሰዋሰው ለምን ብዙ ቁጥር እንደሆነ አያብራራም።
“ኤሎሂም” የሚለው ሰም ብዙ ቁጥር ነው፤ ነገር ግን አብሮት የሚገኘው “ባራ” የሚለው ግስ ነጠላ ነው
ዘፍጥረት 1፡1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
በዕብራይስጥ “ኤሎሒም ባራ” ይላል። “እግዚአብሔር ፈጠረ”።
“ኤሎሒም” ብዙ ሆኖ አንድነትን የሚገለጽ ስም ነው፤ ልክ “በግ” አንድነትን የሚገልጽ ሆኖ የብዙ ቁጥር ስም እንደሆነው።
ስለዚህ ኤሎሒም አንድ አካልን ወይም ከአንድ በላይ አካልን ሊገለጽ ይችላል።
አንድ በግ ወይም ብዙ በግ ሊኖራችሁ ይችላል።
ስለዚህ ግሱን ማያት አለባችሁ።
“ባራ” የሚለው ግስ ነጠላ ነው፤ ልክ “ሮጠ” እንደሚለው።
ስለዚህ በግ የሚለው ቃል ከአንድ በላይ የሆኑ በጎችን ሊወክል ቢችልም “በጉ ሮጠ” ማለት አንድ በግ ነው የሮጠው።
“ባራ” የሚለው ግስ ነጠላ እንደመሆኑ መጠን “ኤሎሒም” አንድ አካል ብቻ መሆኑን ያሳያል።
ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤
ሶስት አካላት ያሉት ስላሴ ለክርስቲያኖች አምላክ አንድ ስም አይሰጠንም።
ከዚህም የተነሳ የዛሬ ክርስቲያኖች ተሸንግለዋል (ሰነፍ ቆነጃጅት ሆነዋል። እነዚህ ንጹህ የዳኑ ሰዎች ናቸው ነገር ግን በግሪክ ፍልስፍና ተታለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርት ተቀብለው) ስም የሌለው አምላክ ያገለግላሉ።
አሞጽ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የምንከለከልበት ዘመን እንደሚመጣ ትንቢት ተናግሮ ነበር።
አሞጽ 6፡10 ያን ጊዜ፦ የእግዚአብሔርን ስም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል ይለዋል።
በእኛ ዘመን የሚገርመን ነገር የሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ስም ኢየሱስ ነው ብለን እንዳንጠራ የምትከለክለን ቤተክርስቲያን መሆኗ ነው።
ሙሽራ የምትጠራው በባሏ ስም ነው።
የኢየሱስን ስም ልንቀበል የምንችለው በውሃ ጥምቀት ብቻ ነው።
ለዚህ ነው ቤተክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅን የሚከለክሉት። ይህም ሰነፎቹ ቆነጃጅት የኢየሱስነ ስም እንዳይቀበሉ ይከለክላቸዋል። ስለዚህ ለሙሽራነት ብቁ ሳይሆኑ ይቀራሉ።
አይሁዶች በቀይ ባሕር ውሃ ውስጥ ሙሴን (ስም) ተከተሉ። ከባሕሩ ውስጥ ሕያው ሆነው ወጡ።
ግብጻውያን ፈርኦንን (ማዕረግ) ተከትለው ውሃ ውስጥ ገቡና ሞቱ።
ስም በሌለው “በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም” የተጠመቁ ሰዎች እነዚህን ማዕረጎች ተከትለው 3.5 ዓመት የሚፈጀው ታላቅ መከራ ውስጥ ይገቡና ይሞታሉ።
ሙስሊሞችም ተመሳሳይ ችግር አለባቸው። በአረብኛ “አላህ” ማለት አምላክ ማለት ነው። ነገር ግን የአምላክ ስም “አምላክ” ሊሆን አይችልም። ስለዚህ “አላህ” የአምላክ ስም አይደለም፤ አላህ የሚለው ቃል የሚወክለው አምላክን ብቻ ነው። ስለዚህ ሙስሊሞችም የአምላክን ስም አያውቁም።
“በመልካችን” በሚለው ቃል ውስጥ ያለው ብዙ ቁጥር ነገስታት የሚጠቀሙት ዓይነት አነጋገር እንደመሆኑ የፍጥረታት ሁሉ ንጉስም እንዲህ ዓይነቱን ብዙ ቁጥር የሚገልጽ ቃል ተጠቅሟል፤ ነገር ግን “ባራ” የሚለው ግስ ነጠላ በመሆኑ “ኤሎሒም” የሚለው ስም በነጠላ አጠቃቀሙ እንደገባ ያመለክታል።
አንድ ንጉስ “እኛ” እያለ ሲናገር ግርማዊ ብዙነት እንጂ ንጉሱ አንድ ነው። ንጉስ ብዙ ክብርና ስልጣን፣ ኃይል ያለው እንደመሆኑ አንድ ቃል ይህን ሁሉ ክብሩን ሊገልጽለት አይችልም።
ስለዚህ ንጉሱን የሚገልጽ እያንዳንዱ ቃል ትክክለኛ ነው ግን ሙሉ አይደለም።
ንጉሱ አንድ ቃል ሊገልጸው ከሚችል በላይ ታላቅና ክቡር ነው። በተለይ እግዚአብሔርን በተመለከተ ደግሞ ይህ እውነት ነው።
እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። እግዚአብሔር አዳኝ ነው። እግዚአብሔር ጠባቂ ነው። እግዚአብሔር መካሪ ነው። እግዚአብሔር ፈዋሻችን ነው። ወዘተ።
ከላይ ያለው እያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር እውነት ነው፤ ነገር ግን አንዱም እንኳ እግዚአብሔርን በሙላት አይገልጸውም። ስለዚህ ብዙ ዓረፍተ ነገሮች (ብዙ ዓረፍተ ነገሮች) ተሰባስበው ነው አንዱን እግዚአብሔርን ሊገልጹልን የሚሞክሩት።
ዕዝራ 4፡18 ሰላም አሁንም ወደ እኛ የላካችሁት ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነበበ።
ስለዚህ ልክ “እኔ” እያልን እንደምናወራው የፋርስ ንጉስ ስለ ራሱ ሲናገር “እኛ” እያለ ተናግሯል።
ይህ ንጉሳዊ ብዙነት ነው። የትኛውም አንድ ቃል የንጉስን ስልጣን እና ክብር በሙላት ሊገልጽ አይችልም።
ቀላሉን መንገድ መምረጥ የለብንም
ቀላል የሆኑ መልሶች በአእምሮ ሰነፍ ያደርጉናል። ትግል ባለበት ነው ጠንክረን ለመስራት የምንነሳሳው።
መፈለግ እንዳለብንና የሚያገኙም ጥቂቶች መሆናቸውን እግዚአብሔር ተናግሯል።
የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት እውነትን በትጋት የማንከታተል ከሆነ እውነትን አናገኝም። ለጥቂት ጊዜ በወረት መፈለግ በቂ አይደለም። ቀላሉን የሰነፍ መንገድ መምረጥ የለብንም።
ተግተን ለማሰብና አጥልቀን ለመቆፈር ተዘጋጅተናል?
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ጥበብ ሊያስተውለው በማይችለው መንገድ ነው የተጻፈው።
እግዚአብሔር ሁለጊዜ በግልጽ ቢናገር እውነትን ከብዙሃኑ መሰወር አይችልም።
ማርቆስ ምዕራፍ 4 ጥልቅ የሆነና የሚያስፈራ እውነትን ይገልጣል።
የዘሪውን ምሳሌ እውነት ለደቀመዛሙርቱ ይገልጥላቸዋል ምክንያቱም ደቀመዛሙርቱ በዚያው ምዕራፍ ቁጥር 10 እንዲገልጥላቸው ጠይቀውታል።
ቁጥር 11-12 እንዲህ ይላል፡-
ማርቆስ 4፡11-12 እንዲህም አላቸው፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፥ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፥ እንዳይመለሱ ኃጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።
ኢየሱስ በግልጽ የተናገረን የእግዚአብሔርን ቃል የማንወድ ከሆንን እና የዲኖሚኔሽኖችን ሰው ሰራሽ አመለካከቶች የምንመርጥ ከሆንን እንደማይፈልገን ነው።
ስላሴ የተመሰረተው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ አነጋገሮች ነው፤ ግልጽና ቀጥተኛ ቃል ከፈለጋችሁ ግን የሚከተለውን ተመልከቱ፡-
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ [በኢየሱስ] የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
የእግዚአብሔር መንፈስ በሙሉ ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ በአካል ይኖራል።
ይህም ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ ያደርገዋል እንጂ “እግዚአብሔር ወልድ” አያደርገውም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ ሰው አይደለም። እግዚአብሔር ስጋ ሊሆን አይችልም።
ኢሳይያስ 43፡11 እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
ስለዚህ ኢየሱስ በሰማይ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመቱን ወይም መቆሙን እንዴት ብላችሁ እንደምትተረጉሙ ተጠንቀቁ፤ ለብቻው ተነጥሎ የሚኖር አካል አድርጋችሁ አታስቡ።
ለብቻው የተነጠለ አድርጋችሁ ካሰባችሁት ከእግዚአብሔር አጠገብ የቆመ ሌላ አዳኝ የሚታያችሁ።
ኢሳይያስ ደግሞ ከእግዚአብሔር ሌላ አዳኝ እንደሌለ ተናግሯል። ከእግዚአብሔር አጠገብ የቆመ አዳኝ የለም።
(ከእግዚአብሔር “ሌላ” የሚያድን የለም፤ ከእግዚአብሔር “አጠገብ” የቆመ አዳኝ የለም)።
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ሁሉ በትክክል መጋጠም አለባቸው። ግን ለማገጣጠም ተግተን ማጥናት ያስፈልገናል።
ወደ እውነት የሚያደርስ ቀላል መንገድ የለም።
ፊልጵስዩስ 2፡12 በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤
ከሲኦል የምንድነው በስራችን አይደለም።
ጳውሎስ እየተናገረ ያለው 3.5 ዓመት ታላቅ መከራ ስለመዳን ነው፤ የዳኑት ሰነፍ ቆነጃጅት በዚህ ታላቅ መከራ ውስጥ ገብተው አሰቃቂ ሞት ይሞታሉ።
አለማመን እና መጽሐፍ ቅዱስን አሳስቶ መተርጎም በዚህ ዘመን እየበዛ ነው፤ ከዚህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ መከተል የሚፈልግ ሰው ላይኖርም ይችላል።
ማቴዎስ 24፡22 እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።
ስህተቶቹ በጣም እየተራቀቁ ከመሄዳቸው የተነሳ እግዚአብሔር ዘመኑን ካላሳጠረው በቀር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እኛንም ሊያስቱን ይችላሉ።
የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን
ከዚህ በፊት እንደተናገርኩት እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ልክ በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈችው ቤተክርስቲያን መሆን ነው የምትፈልገው። ይህ እውነት ነው። ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን ጌታ ሊመጣ ጥቂት ጊዜ ሲቀረው እውነት ሙሉ በሙሉ እስክትጠፋ ድረስ የሰሐት ወረራ እንደሚመጣ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተመልክተናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ሶስት ሰዎች እንደ አንድ ሰው ታይተው አያውቁም።
አልፎ አልፎ ሁለት አካላት አብ እና ወልድ የምናይ ይመስለናል።
ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃል የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ “እግዚአብሔር ወልድ” ተብሎ አልተጻፈም።
እግዚአብሔር ከእኛ በላይ (አብ)፣ ከእኛ ጋር (ወልድ) ነበረ፤ እንዲሁም በእኛ ውስጥ (መንፈስ ቅዱስ) ነው
እግዚአብሔር መጀመሪያ የተገለጠበት መገለጥ ከአይሁድ ሕዝብ በላይ መንፈስ ሆኖ የተገለጠበት ነው። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር እራሱን “አባት” ብሎ ገልጧል እንጂ “እግዚአብሔር አብ” አላለም።
አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው “እግዚአብሔር አብ” የተባለው። ይህ ለምን እንደሆነ የስላሴ አስተማሪዎች ማብራራት አይችሉም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
እግዚአብሔር የተገለጠበት ቀጣዩ መገለጥ ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ ራሱን በሰወረ ጊዜ ነው።
ይህም አማኑኤል ነው፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር።
እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ውስጥ ኖረ፤ ይህም ሰው እግዚአብሔር ባህርያቱን ሙሉ በሙሉ በእርሱ እንዲገልጥ በመፍቀድ ታዘዘ፤ ኢየሱስ በውስጡ ይኖር ለነበረው ለእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ታዘዘ።
ስለዚህ ኢየሱስ የተባለው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ተባለ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ ይኖር ነበረ።
(እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ የምትሆኑት የእግዚአብሔር መንፈስ በከፊል በውስጣችሁ እንዲኖር ስትፈቅዱ ነው)።
እግዚአብሔር በሙላት የሚኖርበትን፣ ሐጥያት የማይሰራና የነብያትን ትንቢት ሁሉ የፈጸመ ሰው አገኘ። እግዚአብሔርም ለመጀመሪያ ጊዜ እራሱን “እግዚአብሔር አብ” ብሎ መጥራት ቻለ።
የኢየሱስ ሰብዓዊ ባሕርያት በለበሰው የሰው አካል ውስጥ እየዳበሩ ሄዱ።
ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር መንፈስ የልዕለ ተፈጥሮአዊው መንፈስ እና የክርስቶስ ሰብዓዊ መንፈስ ውህድ ሆነ።
በአሁኑ ዘመን መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገለጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
ስለዚህ አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ማለት እግዚአብሔር ከሕዝቡ በላይ፣ ከሕዝቡ ጋር፣ እና በሕዝቡ ውስጥ መገለጡ ነው።
አንዱ እግዚአብሔር አንዱ መንፈስ በተለያዩ ሶስት ዘመናት ውስጥ እራሱን በሶስት የተለያዩ መነገዶች ገልጧል።
እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ሲገለጥ ብቻ ነው በሰው ስም የተጠራው፤ ይህም ስም ኢየሱስ ነው።
በሰማይ ምን እንዳለ ለማብራራት መሞከር የአንድን ትምሕርት ትክክለኛነት ማረጋገጫ አይሆንም ምክንያቱም ሰማይ ከእኛ መረዳት እጅግ በጣም የራቀ ነው።
ኤርምያስ 23፡24 ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡
እግዚአብሔር ውስን አይደለም። የእግዚአብሔር መንፈስ በምንም ሊገደብ አይችልም። ውስን ያልሆነውን እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ልናውቀው አንችልም።
ኢሳይያስ 66፡1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤
እግዚአብሔር በሰማይ ውስጥ በዙፋን ላይ እንደተቀመጠ አድርገን በምናባችን እናስባለን። ይህም እጅግ ውስን የሆነ እይታ። ሰማይ የእግዚአብሔር ዙፋን ነው። ምድር የእግሩ መረገጫ ናት።
ለእግዚአብሔር በዙፋን ላይ ተቀምጦ እግሮቹን ደግሞ በእግር መረገጫ ላይ ማድረግ ቀላል ነው እኛ ግን ይህን መረዳት ቀላል አይሆንልንም።
እግዚአብሔር መንፈስ ነው። መንፈሶችን መረዳት አንችልም ምክንያቱም መንፈስ እኛ ከምናውቀው ግዑዝ ዓለም በላይ ነው። መንፈስ በአራተኛው ቀጠና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምንኖርበትን የጊዜ ቀጠናም ይጨምራል። ስለዚህ መንፈሶች እኛ መረዳት ከምንችለው ዓለም ውጭ ናቸው፤ ምክንያቱም ጊዜ እራሱ ምን እንደሆነ በትክክል መረዳት አልቻልንም።
ጊዜን መለካት እንኳ አንችልም። ሰዓት ላይ ወደ ቁጥሮች የሚያመለክት መርፌ ሲንቀሳቀስ እናያለን እንጂ ጊዜን እራሱን አንለካውም።
ሰማይን መግለጽ የሚችሉ ቃላት የሉንም
ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር እኛ መረዳት ከምንችለው ውጭ ከፍ ባለ ቀጠና ውስጥ ነው የሚኖረው።
በሰማያት የሚኖረውን እግዚአብሔርን መረዳት እችላለሁ ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ራሳችሁን እየሸነገላችሁ ናችሁ። ምንም ዓይነት ምስል በምናባችሁ ውስጥ ብትስሉ ከእውነታው ጋር ሊወዳደር አይችልም።
1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9 ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
ሰማይ ምን እንደሚመስል እንኳ ልንገምት አንችልም።
ስለዚህ መንፈስ የሆነው ሰማያዊ ዓለም ምን ዓይነት እንደሆነ ለመረዳት በመሞከር አትድከሙ።
ሰማይ ከጊዜ እና መናፍስት ከሚኖሩበት አራተኛ ቀጠና በላይ የሆነ ልዩ ቀጠና ነው። ስለ ጊዜ ያለን እውቀት ውስን እንደመሆኑ ስለ ሰማይ ያለን እውቀት ደግሞ ከዚያም ያነሰ ነው። ደግሞም ጊዜ እራሱ ምን እንደሆነ ትንሽም እንኳ ፍንጭ የለንም።
ሰማይን የምንገልጽበት ቃላት እንኳ የለንም።
2ኛ ቆሮንቶስ 12፡2 ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ።
3 እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤
4 ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ።
የማይነገረው ቃል
ሰው ሊናገር የማይገባው። ሰማይን የምንገልጽበት ቋንቋ የለንም።
ሰማይ ከጊዜ ቀጠና ውጭ በዘላለም ውስጥ ነው የሚገኘው። ሰማይ ከእኛ በላይ በከፍታ በጣም ርቆ ስለሚገኝ ስለ ሰማይ የምንናገረው ነገር ሁሉ ውጤቱ እኛን ግራ ማጋባት ብቻ እንጂ አንዳችም መረዳትን አይጨምርልንም ምክንያቱም ከጊዜ ቀጠና ውጭ የሆነ ነገርን መረዳት አንችልም።
እግዚአብሔር ሰማይን ለመግለጽ እንድንሞክር እንኳ አይፈልግም። ሰማይን ለመግለጽ ብንሞክር ጥፋት እንጂ አንዳችም መልካም አንሰራም።
ስለዚህ ስለ ሰማይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ ተቀበሉ፤ በዚህ ስጋዊ አካል ውስጥ እየኖራችሁ ሰማይን መረዳት እንደምትችሉ አይምሰላችሁ። አትችሉም።
ዮሐንስ 3፡12 ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
አሁን ስለምንኖርበት ፍጥረታዊ ዓለም እንኳ የማናውቀው ብዙ ነገር አለ። የመሬት ስበት ኃይል እንዴት እንደሚሰራ ሳይንቲስቶች አያውቁም።
የዓለማችን 99 ፐርሰንቱ ዳርክ ኤነርጂ ወይም ዳርክ ማተር ይባላል።
“ዳርክ” የሚለው ቃል ሳይንቲስቶቹ ይህ ነገር ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚሰራ ሊያውቁ እንዳልቻሉ ያሳያል።
ስለዚህ የምንኖርባት ፍጥረታዊ ዓለም ምን እንደሆነች እንኳ ብዙ ሳናውቅ ነው የምንኖረው። ፍጥረታዊው ዓለም ማለት በዓይናችን ማየት የምነችለው ነው። ከፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ በዓይን የሚታየው 4 ፐርሰንቱ ብቻ ነው። ከዚህም ውስጥ አብዛኛው ማለትም 3.6 ፐርሰንቱ ባዶ ስፍራ ነው።
ስለዚህ እኛ ማየት የምነችለው 0.4 ፐርሰንት ብቻ ነው።
እኛ ከምናያቸው ከዋክብት መካከል ያለው የስበት ኃይል እንዴት በአንድነት ይዞ እንደሚያቆያቸው መረዳት አንችልም።
ስለዚህ በዓይን ስለማይታየው ስለ መንፈሳዊው የሰማይ ዓለም ያለን እውቀት ከ0.4 ፐርሰንትም በታች ነው ምክንያቱም በዓይናችን ልናየው አንችልም።
ዮሐንስ 3፡13 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
ኢየሱስ በምድር ላይ ቆሞ ከኒቆዲሞስ ጋር እየተነጋገረ ሳለ በሰማይ ነው ያለሁት ብሎ ነበር። ይህም ስለ መንፈስ አሰራር ያለን እውቀት ምን ያህል ትንሽ መሆኑን ያስረዳል።
የእግዚአብሔርን መንፈስ ልትገድቡት አትችሉም። የእግዚአብሔር መንፈስ ወሰን የለውም። ውስን የሆነው አእምሮዋችን ወሰን የሌለውን መንፈስ መረዳት አይችልም።
ነገር ግን እግዚአብሔርን ያየ አንድ ስንኳ የለም
በሰማይ ሁለት ሰዎች እንዳሉ የሚመስል አንድ ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት። (ሁለት ሰዎች ማግኘትም ቢሆን ስላሴ እውነት መሆኑን አያረጋግጥም። በዚህ ትዕይንት ውስጥ ሶስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ለምን እንዳልተገኘ የስላሴ አስተማሪዎች ማብራራት አይችሉም።)
ዳንኤል 7፡13 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
እስቲ ስለ ስላሴ አስተምሕሮ ጥቂት እንመልከት። ኢየሱስ “እግዚአብሔር ወልድ” ሆኖ ዳኛ ወደሆነው ወደ “እግዚአብሔር አብ” ይመጣል። ይህ የተወሰኑ ችግሮች ይፈጥራል።
ብሉይ ኪዳን ውስጥ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ስያሜ የለም። ስለዚህ በዘመናት የሸመገለው እግዚአብሔር አብ ሊሆን አይችልም።
“እግዚአብሔር አብ” እግዚአብሔር ነው።
ዮሐንስ 1፡18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
እንዴት ነው የእግዚአብሔር ልጅ (መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ወልድ” ብሎ አይናገርም) የማይታየውን እግዚአብሔርን ሊተርከው የሚችለው?
ዮሐንስ 14፡8 ፊልጶስ- ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።
9 ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?
ኢየሱስን ስናይ አብን የምናየው እንዴት ነው?
ዮሐንስ 14፡10 እኔ በአብ እንዳለሁ…
ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ነው የኖረው።
… አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
አብ ማለት ሰው በሆነው በኢየሱስ አካል ውስጥ የሚኖረው ቅዱስ መንፈስ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ነፋስ አይታይም። ስለዚህ ነፋስን እንዴት ነው ልናይ የምንችለው?
ነፋስን የምናየው በሚሰራው ስራ ነው፤ የማይታየው ነፋው የሚታዩ ዛፎችን ይወዘውዛል።
የእግዚአብሔር መንፈስ አይታይም። ስለዚህ ደቀመዛሙርት የማይታየውን “እግዚአብሔር አብ” እንዴት ሊያዩት ይችላሉ?
እግዚአብሔር አብን ማየት የሚችሉት በሚታየው በእግዚአብሔር ልጅ ንግግርና በሚሰራቸው ስራዎች ነው።
የአካላችሁ እንቅስቃሴ እና ንግግራችሁ በውስጣችሁ ሆኖ የማይታየውን የሕይወት መንፈስ ይገልጣል።
ሰው የሆነው በዓይን የሚታየው ኢየሱስ ልክ እንደዚህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ በሙላት በእርሱ ውስጥ ሲኖር በምድር ላይ በመመላለስ በቃል እና በስራ የገለጠው።
ለዚህ ነው ኢየሱስ ሁልጊዜ ስራውና ንግግሩ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሆነው። ብቻውን መቆም ቢያስፈልገው እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻውን ይቆማል። ስለዚህ ዳንኤል ምን ሊነግረን እየሞከረ ነው?
ሰውኛ ዘይቤ።
የሰው እያንዳንዱ ባህርይ ራሱን የቻለ ሰው እንደሆነ ተደርጎ ነው የቀረበው።
ሁለቱ የእግዚአብሔር ባህርያት እግዚአብሔር የሰው ፈጣሪም ቤዛም መሆኑ ነው።
ስለዚህ ዳንኤል ፈጣሪ እና ቤዛ የሆነውን እግዚብሔርን ሰውን ለማዳን ተባብረው የሚሰሩ ሁለት አካላት እንደሆኑ አድርጎ ይገልጻል።
ነገር ግን ይህ የሚያሳየን እግዚአብሔር ሁለት የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ ነው።
እግዚአብሔር ሕይወት በመስጠት ይፈጥራት፤ ደግሞም ለሐጥያታችን በመሞት ይቤዠናል። አንድ ሰው እንዴት ሁለቱንም ሊያደርግ ይችላል?
ማንም ሌላ ሰው እነዚህን ሁለት ስራዎች ልስራ ቢል አይችልም።
ስለዚህ ዳንኤል ሁለት የተለያዩ ሰዎች እንዳሉ አድርጎ ነው የገለጸው።
ሁለት የተለያዩ ሰዎች ተጋግዘው እንደሚሰሩ መግለጽ አንድ ሰው ሁለት ተቃራኒ ስራዎችን እንደሚሰራ አድርጎ ከመግለጽ በጣም ይቀላል።
ኢሳይያስ 43፡1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤
ኢሳይያስ እውነቱን በቀጥታ ነው የገለጸው። እግዚአብሔር እራሱ ይፈጥራል፤ እርሱ ራሱ ደግሞ ይቤዣል።
ሆኖም ግን አንድ እግዚአብሔር ነው።
ኢሳይያስ 44፡8 ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም።
ይህ ስላሴን ዜሮ ያደርገዋል። “እግዚአብሔር ወልድ” “ከእግዚአብሔር አብ” አጠገብ ቆሞ አናየውም።
ኢሳይያስ 43፡11 እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
ይህ ጥልቅ ሚስጥር ነው። አዳኙን ኢየሱስን ከእግዚአብሔር አጠገብ ወይም ጎን ቆሞ አታዩትም።
ዮሐንስ 5፡22 አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም
ይህ ራዕይ ከስላሴ አስተምሕሮ አንጻር ሲተረጎም ምን እንደሚመሰል እንይ።
በዘመናት የሸመገለው ዳኛው ነው እርሱም “እግዚአብሔር አብ” ነው ምክንያቱም በዕድሜ ይበልጣል። ይህ አተረጓጎም ግን ችግር አለበት።
ዮሐንስ 5፡22 … ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።
“እግዚአብሔር አብ” በማንም ላይ አይፈርድም። ልጁ ኢየሱስ ብቻ ነው መፍረድ የሚችለው።
ዳኞች እንዴት ነው የሚፈርዱት?
በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ይነግረናል። አንድን ሰው ከሃሳቡ ልትነጥሉት አትችሉም።
ሃሳባችሁ ምን ዓይነት ሰው እንደሆናችሁ ያሳየናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹት ሃሳቦች ኋላ በፍርድ ቀን በነዚሁ ሃሳቦች ነው የሚፈረድብን።
ስለዚህ የኢየሱስን አስተሳሰብ የሚገልጸው የእግዚአብሔር ቃል ነው የሚፈርድብን።
ይህ ደግሞ አዲስ ችግር ይፈጥርብናል። በዘመናት የሸመገለው ኢየሱስ መሆኑን እንዴት አድርገን እናስረዳለን?
ዳንኤል 7፡9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።
“ጠጉሩም እንደ ጥጥ”።
ይህ ጥጥ የሚለው ከጥጥ የተሰራ የዳኛ ዊግ ነው።
ረጅም ፀጉር የመገዛት ምልክት ነው።
ፀጉሯን ያልተቆረጠች ሚስት ለባሏ ትገዛለች ማለት ነው። ዳኛ ከጥጥ የተሰራ ዊግ በራሱ ላይ ሲያደርግ ዳኛው ለሃገሪቱ ሕግ መገዛቱን እየገለጠ ነው። ስለዚህ ማንም ሰው እንዲያነብበው በተጻፈው ሕግ መሰረት ብቻ ይፈርዳል።
በፍርዱ ውስጥ አንዳችም ስውር ዓላማ አይኖረውም።
ስለዚህ ዳኛው ሕጉን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት።
ራዕይ 1፡14 ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥
ነጭ ፀጉር ዕድሜን ያመለክታል። እግዚአብሔር ግን አያረጅም። እግዚአብሔር ከጊዜ ውጭ በዘላለም ውስጥ ነው የሚኖረው። ነጭ ፀጉር ለረጅም ዘመናት ከመኖር የተነሳ የሚመጣውን ጥበብ ያመለክታል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ከመጀመሪያው ጀምሮ ነበረ።
በሰማያት መላእክት እግዚአብሔርን ማየት ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር የኖረበት መንፈሳዊ አካል ኢየሱስ ነው።
ይህም መንፈሳዊ አካል ደመና ሊመስል ይችላል፣ ወይም የእሳት አምድ ወይም ደግሞ ሰው ሊመስል ይችላል። ነጭ ፀጉር ማርጀትን አያመለክትም። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ስለሆነ ሊያረጅ አይችልም።
ዮሐንስ 1፡1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥
የእግዚአብሔር ልጅ ማለት እግዚአብሔር ሊያድርበት የሚፈልገው ሰብዓዊ ሰው ነው።
በዘመናት የሸመገለው ኢየሱስ ነው ምክንያቱም እርሱ ከጥንት ከመጀመሪያው ጀምሮ ነበረ።
ኢዮብ 12፡12 በሽምግልና ጊዜ ጥበብ፥
በዘመንስ ርዝመት ማስተዋል ይገኛል።
ዳንኤል ኢየሱስን በዘመናት የሸመገለው ብሎ ሲገለጽ ኢየሱስ ፍጹም የሆነው ዳኛ መሆኑን ለማሳየት ነው።
እርሱ ለረጅም ዘመናት ስለኖር እጅግ ጠቢብ ነው። ዳኛ ውሳኔ በሚያደርግ ጊዜ ጥበብ ያስፈልገዋል።
ዘመናት እያለፉ ሲሄዱ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ እና ስለ ሕይወት ያለው መረዳት እየጨመረ ይሄዳል።
ኢየሱስ ከሁሉም በላይ ረጅም ዕድሜ ኖሯል። ስለዚህ ሰዎችን በተመለከተ ኢየሱስ ከማንም ይልቅ የበለጠ እውቀትና ማስተዋል አለው።
ኢየሱስ እያንዳንዱ ሰው የሚያልፍበትን ሁኔታ፣ ፈተና እና ችግር በሙሉ ያውቃል።
ደግሞም እያንዳንዱ ሰው የሚያስበውንና የሚመኘውንም ያውቃል።
ደግሞም ስለ ባህርያችንና ለምን እንዳመንን ሁሉ በጥልቀት ያውቃል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ከዚህም የተነሳ ለፍርድ ቀን የሚከፈተውን ቃል ከማንም በላይ ያውቀወል።
የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ የሚጠብቀውን ሁሉ በደምብ ያውቃል።
ዳኛ እንደመሆኑ መጠን የእግዚአብሔር ቃል ካስቀመጣቸው መርሆች ውጭ በፍጹም ፈቀቅ አይልም።
በዘመናት የሸመገለ እንደመሆኑ መጠን ኢየሱስ በምድር ላይ እግዚአብሔር ሊመሰርት ስለሚፈልገው መንግስት በሚገባ ያውቃል።
በሰማያት ያለው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነም ያውቃል።
ማቴዎስ 6፡10 መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
አሁን ደግሞ ጠበቃ ወይም የሰው ልጅ እንደመሆኑ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሁሉ በሰማያት ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲታዘዙ የማድረግ ከባድ ኃላፊነት ተሸክሟል።
1ኛ ዮሐንስ 2፡1 ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጠበቃ ያለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ደምበኛውን ነጻ ያወጣል።
ፍርድ ቤት ውስጥ ሁሉም ነገር በሃገሪቱ ሕግ መሰረት ነው የሚከናወነው።
ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዲሆኑ የተቻለውን ሁሉ ይጥራል። ምክንያቱም ኋላ የሚፈረድብን በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ነው።
የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ብቻ ናት አፏን ከፍታ የምትናገር፤ የመጀመሪያው ቃሏም “እኔ” የሚል ነው
ቤተክርስቲያኖች ግን በገንዘብ፣ በዝነኝነት እና በሕዝብ ተወዳጅነት የሚንቀሳቀሱ የራሳቸውን ምድራዊ መንግስት መመስረት ይመርጣሉ።
የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ከተጠቀሱት 7 ቤተክርስቲያኖች መካከል ብቸኛዋ አፏን ከፍታ የምትናገረው ቤተክርስቲያን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ናት።
ሎዶቅያውያን ስለ ራሳቸው ጉራ ከመንዛት በቀር ምንም አያውቁም። ራስ ወዳዶች እና በገንዘብ ፍቅር የተጠመዱ ናቸው።
ራዕይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥
ቤተክርስቲያኒቱ የምትናገረው “እኔ” እያለች ነው። ይህም ራስ ወዳድና ስግብግብ የራሷን ነገር የምትፈልግ መሆኗን ያሳያል።
“አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም”። ዛሬም ክርስቲያኖች ምንም እርማት እንደማያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል። በፍጹም ልብ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አያስፈልገንም ይላሉ። እንዴት እንደሚለብሱ ወይም ፍታቸውን ምን እንደሚቀቡ ምንም ግድ የላቸውም።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን እኔ ነኝ ትክክለኛ ብቻ ታምናለች።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ደስ እንዳላት በፈለገችው መንገድ ማምለክ የምትችል ይመስላታል።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን የራሷን አስተምሕሮ ስላበጀች ትክክል ነኝ ብላ በግትርነት ስለትምመላለስ ማንም ሰው ከውጭ መጥቶ ሊያስተምራት አትፈቅድም።
ጠበቃ የሆነው ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ተገፍቶ ወጥቷል፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኖች በታማኝነት መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል አይፈልጉም።
ኢየሱስ ለቤተክርስቲያን የሚያቀርበው የመጨረሻ ጥሪ ለቤተክርስቲያን እንደ ሕብረት ሳይሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉ ግለሰቦች በተናጠል ነው።
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ
3.5 ዓመታት የሚፈጅ ታላቅ መከራ እየመጣ እንደሆነ እና በዚህም መከራ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል የሚሉ ብዙ የዳኑ ክርስቲያኖች በእሳት ውስጥ አልፈው እንደሚሞቱ ኢየሱስ ያውቃል።
ኢየሱስ ስለ ሐጥያታችን በእሳት በመቃጠል ዋጋ ከፍሏል። የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ካለማወቃቸው የተነሳ የዳኑ ክርስቲያኖች በእሳት በመቃጠል ዋጋ ይከፍላሉ።
“ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ”።
እንደ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ የእቶን እሳት ውስጥ የነበረውን መከራ ከሶስቱ ዕብራውያን ጋር ተካፍሏል።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
ኢየሱስ የሐጥያታችንን ዋጋ ለመክፈል በሲኦል እሳት ውስጥ ያለውን ስቃይ ተቀብሏል፤ ልክ እንደሚለቀቅ ፍየል የሐጥያታችንን ሸክም ተሸክሞ በሲኦል እሳት ላይ በመራመድ ሄዶ ሐጥያታችንን ዲያብሎስ ላይ አራግፎታል።
የሰው ልጅ እንደመሆኑ እኛን ለመቤዠት የሐጥያታችንን ዋጋ ከፍሏል። እኛ ማስተዋል ከምንችለው በላይ የሆነ መከራ ተቀብሏል።
ሐጥያት የሚያስከትላቸውን ከባድ ውጤቶች እና ሐጥያትን ለማሸነፍ የታገላቸውን ከባድ ትግሎች ያውቃቸዋል። ኢየሱስ ከሐጥያት ጋር ለመደራደር እምቢ ብሏል ለእኛ ግን የራሳችንን ምርጫ እንድናደርግ ነጻ ፈቃድ ሰጥቶናል ምክንያቱም በደመነፍስ የምንንቀሳቀስ እንስሳት አይደለንም።
ስለዚህ እኛ መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ ልብ አንድንከተል ለማድረግ ከባድ ትግል ይታገላል።
አሕዛብ እንደመሆናችን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌያችን መጽሐፍ ቅዱስን ወደ መታዘዝ አይደለም። የተወለድነው ከአረማውያን ቅድመ አያቶች ነው።
ሎዶቅያውያን ማለት “የሕዝቡ መብት” ሲሆን በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የራሳቸውን እምነት እና አስተምሕሮ የማበጀት መብት ያላቸው ይመስላቸዋል።
እስካሁን 45,000 ዓይነት ቤተክርስቲያኖችንና ዲኖሚኔሽኖችን ፈጥረዋል፤ ከዚህም በተጨማሪ ከ100 በላይ የተለያዩ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን አዘጋጅተዋል። ይህም የፈጠረው ብዙ ነፍሳት የሚሰጥሙበት መንፈሳዊ አረንቋ ነው።
7ኛው መልአክ የሰው ልጅ አይደለም
ኢየሱስ በዘመናት የሸመገለ እንደመሆኑ መጠን በጥንታዊው የባቢሎን ንጉስ በናቡከደነጾር ዘመንም ነበረ፤ ንጉሱ ሶስት ዕብራውያን የነብዩን የዳንኤልን ምስል እንዲያመልኩ ሊያስገድዳቸው ሞክሮ ነበር። ዳንኤል በዚያ ስፍራ አልነበረም ምክንያቱም የራሱን ምስል እንዲያመልክ አይጠየቅም። የባቢሎን መንግስት የመጀመሪያው የአሕዛብ መንግስት ነበረ።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
ዳንኤል 3፡25 እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።
ዛሬ በመጨረሻው የአሕዛብ መንግስት ዘመን ውስጥ የሜሴጅ ሰባኪዎች ሕዝቡ የአሕዛብ ነብይ የሆነውን ዊልያም ብራንሐም የእግዚአብሔር ድምጽ ነው፣ የሰው ልጅ ነው በማለት እርሱን እንዲያመልኩ እያደረጓቸው ነው። የእርሱን ንግግሮች ፍጹም ናቸው፣ እርሱ አይሳሳትም በላመት ንግግሮቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ ያደርጋሉ።
65-0725 በዘመን መጨረሻ የተቀቡት
በዚያ ቦታ ወንዙ ላይ የተገለጥኩት እኔ አይደለሁም፤ እኔ እርሱ በተገለጠ ሰዓት በዚያ ስፍራ ነበርኩ። እነዚህን ነገሮች የማደርግና ፍጻሜያቸውንም በትክክል የምተነብይ እኔ አይደለሁም፤ እኔ እርሱ በሚሰራበት ሰዓት አብሬው የምቆም ሰው ብቻ ነኝ እኔ እርሱ ቃሉን ለመናገር የተጠቀመብኝ ድምጽ ብቻ ነኝ።
እርሱ በእኔ የተናገረው እኔ እውቀት ስላለኝ አይደለም፤ በትሕትና ራሴን ለእርሱ ስለሰጠሁ ብቻ ነው እንጂ።
እኔ አይደለሁም፤ ሰባተኛው መልአክም አይደለም፤ በፍጹም፤ ይህ የሰው ልጅ መገለጥ ነው እንጂ። መልአኩ ሳይሆን መልእክቱ ነው፤ እግዚአብሔር ሊገልጥ የወደደው ሚስጥር ነው። ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው።
መልአኩ የሰው ልጅ አይደለም፤ እርሱ የሰው ልጅ የላከው መልእክተኛ ነው።
62-1007 የበሩ መክፈቻ
ይህ ነው ብዙ ነገሮችን የሚያበላሸው፤ አያችሁ። በዚህ ያሉ ሰዎች አንዳንድ ወንድሞች እኔ እንደላኳቸው እያወሩ ሰዎች ሚስታቸውን ትተው ትክክለኛዋን አጥንታቸውን ፍለጋ መውጣት አለባቸው እያሉ ይሰብካሉ፤ በተጨማሪ ደግሞ እኔ ልሳሳት እንደማልችል አድርገው ያወራሉ። … ከዚህም የባሱ አንዳንድ አስደንጋጭ ነገሮችን ይናገራሉ።
ሁለት ሰዎች ሳይሆኑ ሰውኛ ዘይቤ
ዳንኤል ጠለቅ ያለ ሚስጥር ሊገልጥልን እየሞከረ ነው።
ሁለቱን የኢየሱስ አገልግሎቶች ሁለት የተለያዩ ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአል። ይህም ሰውኛ ዘይቤ ነው።
ኢየሱስ ዳኛ እንደመሆኑ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ሊፈርድብን ይገባዋል።
ነገር ግን እንደ ዳኛ ደግሞ ለዘመናችን በተገለጠው በእግዚአብሔር ቃል ካመንን ስለ ሐጥያታችን ዋጋ ስለከፈለልን ከሐጥያት እና ከአለማመን አደጋ ሊጠብቀን ይችላል።
ኢየሱስ ብቻ ነው ነጩን የዳኛ ዊግ መልበስ የሚችለው ምክንያቱም እርሱ ሙሉው እውነት ነው። እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነው።
የአለማመናችንን እና የሐጥያታችንን ዋጋ የከፈለው ኢየሱስ ብቻ ነው። በዘመናችን የተገለጠውን እውነት ወደማመን ሊመራን የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። በዚህም በዘመናችን ከመጡ አሳሳች የቤተክርስቲያን አሰራሮች ይታደገናል።
ኢየሱስ 7ቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ እንዴት ለይተን ልናውቃቸውና ልናስተውላቸው እንደምንችል ያሳየናል፤ ምክንያቱም የነጎድጓዶቹን ድምጽ ሰምተን የሞሞተው አካላችንን እንዴት ወደማይሞት አካል እንደምንለውጥ መማር አለብን።
የዚያን ጊዜ አካላችን ሲለወጥ ብቻ ነው ኢየሱስ ከታላቁ መከራ ሊያድነንና ወደ ሰማይ ነጥቆ ሊወስደን የሚችለው።
እኛ ግን በራሳችን ነጻ ፈቃድ የራሳችንን ፈቃድ ለቃሉ ማስገዛት አለብን። ብቸኛው ፍላጎታችን ለቃሉ መገዛት መሆን አለበት።