የእንስሳት ደም ለምን ሐጥያትን እንደሚያስተሰርይ ማብራሪያ



በሰማይ ደም የለም፤ ጾታም የለም። ስለዚህ የኤድን ገነት ውስጥ ጾታ እና ደም እንዴት እንደገቡ ማወቅ አለብን።

First published on the 6th of October 2022 — Last updated on the 6th of October 2022

ዘላለማዊ አካል ደም የለውም

 

 

ደም ሐጥያትን ያስተሰርያል ብሎ መረዳት ትክክል ነው ግን ማብራሪያ ያስፈልገዋል።

ይህ ብዙ ሰው የተታለለበት ጠለቅ ያለ ጥያቄ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጥቅሶችን በትክክል አገጣጥመን ሙሉ የሆነውን መገለጥ ማግኘት ያስፈልገናል።

ኢሳይያስ 28፡13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።

የእንቆቅልሹን ፍቺ የምናገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች ተበታትነው ከተጻፉ ጥቅሶች ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጥቅሶችን በሙሉ በትክክል መገጣጠም ከመቻላችሁ በፊት መጀመሪያ አጠቃላይ የሆነው ስዕል ወይም መረዳት ሊኖራችሁ ይገባል። ይህም አጠቃላይ የሆነ ስዕል ከመረዳታችሁ ጋር የማይጋጭ መሆን አለበት። ጥቅሶች ሁሉ ተገጣጥመው የአንድን እውነት የተለያዩ ገጽታዎች ማሳየት አለባቸው።

ትክክለኛው መረዳት ወይም መገለጥ ከሌላችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተበታትነው የሚገኙትን ጥቅሶች ሁሉ ልትገጣጥሙ አትችሉ። ካልቻላችሁ ደግሞ ትክክለኛውን እውነት በጭራሽ አታገኙትም።

ከዚህም የተነሳ ማቴዎስ ምዕራፍ 25 ውስጥ ከተጠቀሱት ሰነፍ ቆነጃጅት አንዳቸውን ትሆናላችሁ።

ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። ድንግል ሴት የዳኑ ነገር ግን ቤተክርስቲያን በምታስተምራቸው ትምሕርት የተነሳ የተታለሉ ክርስቲያኖችን ትወክላለች። በአሁኑ ሰዓት 45,000 ዓይነት የተለያ ቤተክርስቲያኖች ወይም ዲኖሚኔሽኖች ይገኛሉ። ሁሉም የተለያዩ ሆነው ግን ሁሉ ትክክል ነን ይላሉ። ስለዚህ በግልጽ እንደምናየው ዛሬ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እጅግ ብዙ ስሕተት አለ።

ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አግኝታችሁ ከሆነ ከእምነታችሁ ጋር የሚጋጩ ጥቅሶች ውስጡ አይገኙበትም። እምነታችሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት ጀምራችሁ እስከ ራዕይ ድረስ መፈተሽና ማረጋገጫዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

ሰማይ ውስጥ ምንም ደም አለመኖሩን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።

ሰማይ ውስጥ “ስጋና ደም” የሉም፤ ደግሞም ሰማይ ውስጥ “መበስበስም” የለም።

ስለዚህ “ስጋና ደም” ከመበስበስ ጋር የተያያዙ ናቸው።

በሌላ አነጋገር ከሐጥያት ጋር የተያያዘው መበስበስ ከደማችን ጋር የተቆራኘ ነው።

እግዚአብሔር ከአዳም የጎድን አጥንት ወስዶ ሴቲቱን በሰራት ጊዜ አዳም እንዲህ አለ፡-

ዘፍጥረት 2፡23 አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

በዚያ ጊዜ መበስበስ የሚባል ነገር አልነበረም። ሐጥያትም አልነበረም። ስለዚህ ደም አልተጠቀሰም።

“ስጋ እና አጥንት” በሰውየው እና በሴቲቱ መካከል በጣም የጠበቀ አንድነት መኖሩን ያሳያል። ቤተሰብ ነበሩ።

ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ ምን እንዳለ ስሙ።

ሉቃስ 24፡39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።

የኢየሱስ ደም በሙሉ በቀራንዮ መስቀል ላይ ፈስሶ አልቋል። ከሞት በተነሳ ጊዜ በለበሰው ስጋ ውስጥ ደም አልነበረም።

በኤድን ገነት በእግዚአብሔር የመጀመሪያ መንግስት ውስጥ አዳም እና ሚስቱ ስጋቸው ውስጥ ደም አልነበራቸውም።

ደም ቢኖራቸው ኖሮ ከመጀመሪያውም የሚሞቱ ሰዎች ነበሩ። ደም ውስጥ ዘላለማዊ ሕይወት የለም።

ሞት ወደ ሰው የመጣው ሐጥያት ወደ ዓለም ከገባ በኋላ ነው።

ሕዝቅኤል 18፡4 … ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።

ሐጥያት ባልነበረበት ጊዜ ሞትም አልነበረም። ስለዚህ የደም ስራቸው ውስጥ ደም አልነበራቸውም።

የዘላለም ሕይወት የሚገኘው በሰው የደም ስር ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ሲፈስስ ነው።

 

የአውሬው ምልክት በሰዎች አእምሮ ውስጥ የሚገኘው አለማመን ነው

 

 

አዳም እና ሚስቱ እምብርት አልበራቸውም። ከአፈር ስለተሰሩ እግዚአብሔር ሆዳቸው ላይ ጠባሳ ማድረግ አላስፈለገውም።

እባቡ ለሔዋን ስለ ወሲብ አስተማራት። የበኩር ልጇ ሆድ ላይ የነበረው የእምብርት ጠባሳ በስጋው ላይ የሚተይ የአውሬው ምልክት ነበረ። ስጋው በግፍ፣ በበሽታ፣ ወይም በእርጅና እንዲሞት ተፈርዶበታል። ከወሲባዊ ግንኙነት የተወለድን ሁሉ ሆዳችን ላይ የእምብርት ጠባሳ ያለን ሲሆን ይህም ምልክት እንደምንሞት ይመሰክራል።

በስተመጨረሻ የቤተክርስቲያን መሪዎች የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች እነዳናምን በማድረግ አእምሮዋችንን ያበላሹታል። የተደራጁ ቤተክርስቲያኖች ወይም ዲኖሚኔሽኖች የሚያስተምሩዋቸው አስተምሕሮዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆኑ የአውሬውን መንፈሳዊ ምልክት አእምሮዋችን ላይ ያስቀምጡብናል፤ አእምሮዋችንም የሚገኘው ጭንቅላታችን ውስጥ ከግምባራችን ኋላ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን እንዳንከተል የሚያደርገን አለማመን በግምባራችን በማሰቢያ አካልችን ላይ የሚገኝ የአውሬው ምልክት ነው። ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገሮችን እናምናለን።

ስላሴ። እግዚአብሔር ወልድ። ታህሳስ። የስቅለት አርብ። የፋሲካ ሰኞ። ኩዳዴ ጾም። ፖፕ። ካርዲናል። ሊቀ ጳጳስ። የሲኖዶስ አስተዳደር። ዲኖሚኔሽን። ካተኪዝም። የፋሲካ ጥንቸሎች። የፋሲካ እንቁላሎች። የፋሲካ ኮፍያዎች።

አለማመናችን ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነው አስተሳሰባችን ለአመጽ ሰው ለመጨረሻው ፖፕ ወይም ለአውሬው ተገዥ ያደርገናል።

ሰይጣን እግዚአብሔርን ይኮርጃል።

እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያትመው ግምባራቸው ላይ ማለትም በሚያምኑበትና በሚያስቡበት ቦታ ነው።

ራዕይ 9፡4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።

 

ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ

 

ማሕተማችን መንፈስ ቅዱስ ነው።

ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ

መንፈስ ቅዱስ አእምሮዋችንን የሚያትመው የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ለእኛ በመግለጥ ነው።

ከዚያ በኋላ እውነትን እናውቃለን፤ እናምናለን።

አእምሮዋችን ውስጥ የታተመው እውነት ማንኛውም ስሕተት ወደ አእምሮዋችን እንዳይገባ ይከላከላል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤

 

ራዕይ 14፡1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።

 

“እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ አይገኝም።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ አብን ለመገለጽ የተጻፉ ቃላት በሙሉ አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ አይገኙም።

ብሉይ ኪዳን ውስጥ በጣም ብዙ ጊዜ የሚገኘው የአብ ስም ያህዌ ነው፤ ነገር ግን ይህ ስም አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ አልተጠቀሰም።

እስካሁን 2,000 ዓመታት ሁሉ ሲያልፉ የአብ ስም አልተጠቀሰም።

144,000ዎቹ በግምባራቸው ውስጥ ባለው አእምሮዋቸው ላይ ስሙ ሲታተም የስሙን መገለጥ ያገኛሉ።

 

በሰው ነፍስ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ዘር ውሃ የሚያጠጣው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው

 

 

ሮሜ 8፡10 ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው

የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው ዘላለማዊ ሕይወት ያለው።

ከዚያ መንፈስ ላይ ተሰፍሮ አዳም ውስጥ እና ሔዋን ውስጥ እንዲኖር ተደርጓል፤ ይህም መንፈስ ዘላለማዊ ሕይወትን ሊሰጣቸው በስጋቸው ውስጥ ይንቀሳቀስ ነበር።

የኤድን ገነት ውስጥ እግዚአብሔር ለሰዎች ዘላለማዊ ሕይወትን እያሰበ ነበር። ሐጥያት አልነበረም፤ ሞትም አልነበረም።

በሰው እን በውስጡ በሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ መካከል ያለው አገናኝ እምነት ነው። እግዚአብሔር በውስጣችን መኖር የሚችለው ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ እምነት ሲኖረን ብቸ ነው።

እምነት መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

ኤፌሶን 3፡17 ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር … የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥

የእግዚአብሔርን ቃል መውደድና በቃሉ መመራት አለብን።

የእግዚብሔር እቅድ የእግዚአብሔር መንፈስ ቃሉን በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንዲኖረው ነበር።

ቃሉን መኖር ማለት እግዚአብሔር ሰዎችን እርሱ ራሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ደግሞም ከዘላለም ዘመናት በፊት ያበጀውን ዕቅድ እንዲከተሉ ያደርጋቸዋል ማለት ነው።

ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤

ከሰው ውስጥ ከእንስሳ የሚለይበት ክፍል ነፍስ ነው።

የምናምነው ከነፍሳችን ነው።

ነፍሳችን ታምናለች ወይም ትጠራጠራለች። ነገር ግን በአንድ ጊዜ ማመንም መጠራጠርም አትችልም። የሚወስነው ነጻ ፈቃዳችሁ ነው።

መንፈሳችሁ ሕይወታችሁ ሲሆን ከአንጎላችሁ ጋር በመሆን አእምሮ እንዲኖችሁ ያደርጋል።

1ኛ ሳሙኤል 25፡29 … የጌታዬ ነፍስ በሕያዋን ወገን … የታሰረች ትሆናለች፤

ነፍስ ሕይወት ከሆነው ከመንፈስ ጋር የተሳሰረች ናት።

እኛ የተሰራነው ከስጋ፣ ከነፍስ፣ እና ከመንፈስ ነው።

ኢዮብ 14፡22 ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥

ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።

“ለራሱም” የሚለው ቃል መንፈስን ያመለክታል።

ስለዚህ ነፍስ በመንፈስ ውስጥ ናት።

አካል ወይም ስጋ በግልጽ እንደምናውቀው ከውጭ ነው ያለው።

 

 

ወደ ነፍስ የሚያስገባ አንድ በር ብቻ ነው ያለው - ይህም ራስ ወዳድነት ነው።

የእግዚአብሔርን ቃል ማመን ትችላላችሁ (እምነት) ወይም የእግዚአብሔርን ቃል መጠራጠር ትችላላችሁ፤ ይህም አለማመን ወይም ሐጥያት ነው።

ዮሐንስ 16፡9 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤

ማንኛውም ዓይነት አለማመን ሐጥያት ነው።

1ኛ ተሰሎንቄ 5፡23 የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።

በዚህ ቅደም ተከተል አይደለም የሚገኘው።

በዚህ ቅደም ተከተል ነው የሚገኘው።

 

 

መንፈስ በእግዚአብሔር መንፈስ ይወቀሳል፤ የእግዚአብሔር መንፈስም የአትክልት ስፍራውን ማለትም ነፍስን ያጠጣል፤ ከዚያም ነፍስ የእግዚአብሔር ቃል እንድትቀበልና እንድትታዘዝ ያደርጋል። ቃሉ ውሃ በጠጣው አፈር ወይም ነፍስ ውስጥ የሚበቅለው ዘር ነው፤ ከዚያም በኋላ አካላችን ለቃሉ እንዲታዘዝ በማድረግ አካላችንን ይሰራዋል።

ኤርምያስ 31፡12 ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥

ዮሐንስ 7፡38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።

39 ይህን ግን … ስለ መንፈስ ተናገረ፤

ውሃ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው።

ሉቃስ 8፡11 ምሳሌው ይህ ነው፤ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

የእግዚአብሔር መንፈስ ተሰፍሮ በአዳም እና በሚስቱ ውስጥ በመግባት የዘላለም ሕይወት ሊሰጣቸው በደም ስራቸው ውስጥ ይንቀሳቀስ ነበር፤ ደግሞም አእምሮዋቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲስማማ በአንጎላቸውም ውስጥ ያልፍ ነበር።

እነርሱ ግን ይህን ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ሕብረት ጠብቀው ሊያቆዩ የሚችሉት በእምነት ብቻ ነው።

እምነት ሊገነባ የሚችለው ደግሞ በቃሉ ውስጥ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሙሉ በሙሉ በመገዛት ብቻ ነው።

ነፍሳችን ልትድን የምትችለው በማመን ብቻ ነው። በየትኛውም መልካም ስራ ልትድን አትችልም።

ዕብራውያን 10፡39 እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

 

ከደም ስለተወለድን 1,000 ዓመታት መኖር አንችልም

 

 

ስለዚህ ሴቲቱ ማመን ስታቆም በእግዚአብሔር ዘንድ የነበራትን ስፍራ አጣች።

ዘፍጥረት 3፡1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።

መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትጠራጠር አደረጋት። እግዚአብሔር አዟልን? እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልን?

ከዚያ በኋላ ሴቲቱ ከበድ ያለው ፈተና መጣባት። እባቡ “አትሞቱም” የሚለውን ቃል ከራሱ በመጨመር የእግዚአብሔርን ቃል ተቃረነ።

ዘፍጥረት 3፡4 እባብም ለሴቲቱ አላት፦ ሞትን አትሞቱም

ይህ ለሴቲቱ ወሳኝ ሰዓት ነበር።

የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሌለ ነገር ማመን ስትጀምር የእግዚአብሔር መንፈስ ከዚያ በኋላ በውስጧ መኖር አልቻለም።

ከዚህም የተነሳ የዚያኑ ዕለት ትሞት ነበር።

እግዚአብሔር ግን እንዲህ ብሎ ነበር።

ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።

የእግዚአብሔር ቀን 1,000 ዓመት ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

ስለዚህ ሴቲቱ እና ልጆቿ ይህንን ቃል ለመፈጸም 1,000 ዓመታት ያህል በሕይወት መቆየት አለባቸው።

እግዚአብሔርም ለሐጥያተኛ ሰዎች አዲስ የሕይወት ዓይነት ፈጠረላቸው፤ ይህም በደም ሴል ውስጥ የሚገኝ ሕይወት ነው።

ነገር ግን በሰውነቱ ውስጥ ደም ይዞ የተወለደ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ ሙሉ 1,000 ዓመታት አልኖረም።

ዘሌዋውያን 17፡11 የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤

መንፈስ ቅዱስ ከአዳም እና ከሔዋን ስጋ ውስጥ ከወጣ በኋላ በሕይወት እንዲቆዩ በደም ስራቸው ውስጥ ደም መሙላት ነበረበት። ነገር ግን ይህ የሞት ሕይወት ነው።

ስለዚህ ለአንድ ቀን እንኳ በሕይወት መቆየት አልቻሉም። በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን 1,000 ዓመት ነው።

ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤…

መልካም እና ክፉውን የምታሳውቀዋ ዛፍ ከሴቲቱ ማሕጸን ጋር የተያያዘች ናት፤ የሴቲቱ ማሕጸንም በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ሕይወት መፍጠር ይችላል (ይህም መልካም ይመስላል) ነገር ግን በዚህ መንገድ የተወለደ ሕጻን መሞቱ አይቀርም (ይህ ደግሞ ክፉ ነገር ነው)።

ከዚህም የተነሳ ሰው የሴትን ማሕጸን መንካት አልበረበትም።

ዘፍጥረት 2፡9 … በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

የሕይወት ዛፍም (የዘላለም ሕይወት ምንጭ) በገነት መካከል ከነበረ፣ የእውቀት ዛፍም (የሞት ሕይወት ምንጭ፤ የሚወለደው ሕጻን ኖሮ ኖሮ ሲያበቃ የሚሞትበት) በገነት መካከል ነው የነበረው።

የሴቲቱ ማሕጸን በድንግልና የሚወለደውን ልጅ (ሕይወትን) መውለድ ይችል ነበር፤ ወይም ደግሞ በወሲብ አማካኝት ልጆችን መውለድ ይችላል፤ የነዚህም ልጆች ሕይወት የመልካም እና የክፉ ድብልቅ ይሆናል።

መኃልየ መኃልይ 4፡12 እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።

ገነት የሚለው ቃል ከክፉ የተጠበቀች ሴትን ይወክላል። መጀመሪያ አባቷ ጥበቃ ያደርግላታል፤ ከዚያም ባሏ ጥበቃ ያደርግላታል። ማሕጸኗ በድንግልና ሕግ የታተመ የሕይወት ምንጭ ነው።

“በገነት መካከል የሕይወት ዛፍ” ማለት በሴቲቱ አካል መሃል የሚገኘው ማሕጸን ነው። የሴቲቱ ማሕጸን መንፈስ ቅዱስ ሲጋርደው ዘላለማዊ ሕይወትን መውለድ ይችላል፤ ወይም በወሲባዊ ግንኙነት ከጸነሰች ደግሞ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ የሚሞት ጊዜያዊ ሕይወት ልትወልድ ትችላለች።

በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት የተወለደው የሰው ሕይወት በስተመጨረሻ በአርማጌዶን ጦርነት በብዙ ደም መፋሰስ ይጠፋል። በዚያ ጦርነት የሚወድቁ እሬሳዎችና ደማቸው 200 ማይልስ የሚያህል ቦታ ይሸፍናሉ። አንድ ማይል 8 ምዕራፍ ነው።

የፈረስ ልጓም ከፍታው 1½ ሜትር ያህል ነው።

ራዕይ 14፡20 የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።

ሰውነታው በደም የተሞላ የሰው ልጆች በምድር ላይ ገዥነታቸውን የሚያጡት በዚህ ጊዜ ነው።

ያ ሁሉ ደም የተስፋይቱን ምድር ደረቅ አፈር ያረሰርሰውና በረሃው እንደ ጽገሬዳ አበባ እንዲፈካ የሚያደርግ ማዳበሪያ ሆኖ ያገለግላል።

ሕዝቅኤል 39፡17 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ኑ፥ ተከማቹ፥ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ መሥዋዕት፥ እርሱም ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየስፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ።

አውሬውን ማለትም የመጨረሻው ፖፕ ሆኖ የሚገለጠውን የአመጽ ሰው አመለኩ።

ስለዚህ በአውሬ ተበሉ።

አውሬዎች እና ጥምባንሳዎች እሬሳዎቹን ይበሉዋቸዋል።

በዚህም መንገድ በሰውነታቸው ውስጥ ደም ያላቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንደማይፈልግ ይገልጻል።

 

ስጋ እና ደም ንጹህ ምግብ እንኳ አይደለም

 

 

ዘፍጥረት 9፡4 ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፤

እግዚአብሔር ለአይሁዶች የእንስሳ ስጋ ከደሙ ጋር እንዳይበሉ ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል።

እግዚአብሔር የስጋን እና የደምን ቅልቅል ይህን ያህል ነው የሚቃወመው።

ዘዳግም 12፡23 ነገር ግን ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባህምና ደሙን እንዳትበላ ተጠንቀቅ።

ስጋ ከደም ተለይቶ መኖር አለበት።

ሐጥያት የገባው ሴቲቱ እግዚአብሔር ያልተናገረውን ነገር ስታምን የሕይወት መንፈስ ከውስጧ መውጣት ሲጀምር ነው። ከዚያ በኋላ ሴቲቱን በሕይወት ለማቆየጥ የሞት ሕይወት ወይም መንፈስ ወደ ውስጧ ገባ። ነገር ግን ይህ ሕይወት በስጋዋ ውስጥ እንዲሰራጭ የደም ስሮች እና ደም የሚያሰራጭ ልብ ያስፈልግ ነበር። ደሙን ከቆሻሻ ለማጣራት ኩላሊቶችና ጉበት ያስፈልጉ ነበር፤ ከዚያም ቆሻሻ ለማስወገድ ደግሞ ፊኛ ያስፈልግ ነበር። እነዚህ ሁሉ በስጋ ውስጥ የሚገኙ ብልቶች ያለ እረፍት ሲሰሩ ኖረው በመጨረሻ በእርጅና ደክመው ይሞታሉ።

በሰው አካል ውስጥ የሚገኘው ደም እግዚአብሔር በመጀመሪያ በክብር የፈጠረውን ሰው ከክብሩ ዝቅ አድርጎታል።

እግዚአብሔር ስጋ እና ደም እንዲነካኩ ወይም እንዲቀላቀሉ አልፈለገም።

በደም ውስጥ የሚገኘው ሕይወት በሐጥያት የተሞላ ነው፤ ስለዚህ የስጋ ምኞቶች ከዚህ ደም ነው የሚመነጩት።

ዘሌዋውያን 15፡19 ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።

ሴት ከሰውቷ ደም ከፈሰሳት እንደ ረከሰች ትቆጠራለች።

“ስጋና ደም” የሚለው ቃል ሰዎች የሚል ትርጉምም አለው። ስለዚህ ሃሳቦቻችንና አመለካከቶቻችን ለነፍሳችን ተስማሚ ምግብ አይሆኑም። በቀላሉ ተታልለን ወደ ስሕተት ውስጥ እንወድቃለን።

ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በእምነት ተጣብቀን መኖር ነው የሚያዋጣን።

 

ከተቀደደ መጋረጃ ጀርባ ዘላለማዊ ሕይወት አይገኝም

 

 

ዘሌዋውያን 17፡11 የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።

 

የሕይወት መንፈስ የሚገኘው ደም ውስጥ ነው።

ደም መፍሰስ ያለበት ለምንድነው?

ሴቲቱ ከእግዚአብሔር ቃል ፈቀቅ ብላ ሌላ ነገር ስታምን የእግዚአብሔር መንፈስ ከስጋዋ ውስጥ ወጣና ስጋዋ በደም የተሞላ አካል ሆነ።

እግዚአብሔር ሴቲቱ ወሲብ እንዳታደርግ ብሎ የድንግልና መጋረጃ ሰጥቷት ነበር።

ሰውነቷ በደም የተሞላ ጊዜ ያ የድንግልና መጋረጃም በደም ተሞላ።

የወንድ ብልት ለወሲብ ዝግጁ የሚሆነው ብልቱ በደም ሲሞላ ነው።

አዳም በሰውነቱ ውስጥ ደም ስላልነበረው ይህንን ማድረግ አይችልም ነበር፤ እስከዚያ ሰዓትም ድረስ እግዚብሔርን እየታዘዘ ነበር።

እባቡ ከምድር አውሬዎች ሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ ነበረ። በሌላ አነጋገር ከአጥቢ እንስሳት ሁሉ ታላቅ ነበረ። ደረጃው በሰው እና በዝንጀሮ መካከል ነበር።

ወሲባዊ ግንኙነት የእንስሳት መራቢያ መንገድ ነው ምክንያቱም የእንስቷ እንስሳ ወሲባዊ ፍላጎት በዓመት አንድ ጊዜ ግልገል ለመውለድ ካልሆነ በቀር ጠፍቶ ነው የሚቆየው። በቁጥር በቂ እንስሳት ከተወለዱ በኋላ እግዚአብሔር የእንስሳትን የወሲብ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል ምክንያቱም እንስሳት ነጻ ፈቃድ የላቸውም።

እባቡ ወሲባዊ ግንኙነት እንዴት እንደሚደረግ ለሴቲቱ ባሳያት ጊዜ የድንግልናዋን መጋረጃ ቀድዶ ነው ያሳያት።

የድንግልና መጋረጃዋ ሲቀደድ ደሟ ፈሰሰ፤ ደሟን ያፈሰሰውም እንስሳ ነው።

ይህ በጣም ተንኮለኛ እንስሳ ነው።

ከማሕጸኗ መጋረጃ በስተጀርባ የሐጥያተኛ ሕይወት ዘር ተጸነሰ።

የተቀደደው መጋረጃ ውጤታማ ሳይሆን የቀረ ስርዓት ምሳሌ ነው።

ከተቀደደ መጋረጃ በስተጀርባ ዘላለማዊ ሕይወት አይገኝም።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሐጥያትን ለማስተስረይ የንጹህ እንስሳ ደም ያስፈልጋል አለ።

የመገናኛው ድንኳን እና ቤተመቅደሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገባ ውስጠኛ መጋረጃ ነበራቸው።

ከዓመቱ በ7ኛው ወር ከወሩም በ10ኛው ቀን ሊቀካሕናቱ ብቻ ነበር ወደ ቅድስተ ቅድሳን መግባት የሚፈቀድለት።

ነገር ግን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት የመጋረጃውን ጫፍ ወደ ጎን መጎተት አለበት። ይህም ክፍተትን ስለሚፈጥር መጋረጃው ከዚያ ወዲያ የተዘጋ ተደርጎ አይቆጠርም። ስለዚህ ሕጉ በድንግልና መውለድን አይወክልም፤ በድንግልና መውለድ ከታተመው መጋረጃ ጀርባ ጽንስ ከተፈጠረ በኋላ ነው። ከዚህም የተነሳ ሕጉ የሚያበቃበት ቀን ተቆረጠለት። ሕጉ መልካም ነበረ ግን ፍጹም አልነበረም።

 

 

የድንግልና ጽንስና ልደት ብቻ ነው ከታተመ መጋረጃ በስተጀርባ ዘላለማዊ ሕይወትን ሊጸንስ የሚችለው። ሔዋን ይህን ነበር ማድረግ የነበረባት። ማርያም ይህንን ነው ያደረገችው።

ሰው ግን ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ስራ ይቃወማል።

ሊቀካሕናቱ ቀያፋ ኢየሱስን ፊት ለፊት ባገኘው ጊዜ ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን አውቋል፤ ነገር ግን እውቅና እንዳይሰጠው የራሱን ስልጣንና የገቢ ምንጭ አጣለሁ ብሎ ፈራ። የግል ጥቅሙን ለማስከበር ሲል በአጋንንታዊ ቁጣ ተሞልቶ ኢየሱስን መግደል መረጠና በሞኝነቱ ብዛት የክሕነት ልብሱን ቀደደ። (ንዴት ውስጥ ሆናችሁ ትልልቅ ውሳኔዎችን አታድርጉ። የራሳችሁን ጥቅም ዋነኛ ትኩረታችሁ አታድርጉ።)

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል … አለ።

ልብሱን በመቅደዱ ሕጉን አፈረሰ።

ከዚህም የተነሳ ሕጉ አበቃለት። እግዚአብሔርም የሕጉ ዘመን ማብቃቱን ለማመልከት የቤተመቅደሱን ውስጠኛ መጋረጃ ቀደደ።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ሰው ቢሆን ኖሮ መጋረጃውን የሚቀድደው ከታች ይጀምርና ወደ ላይ ይቀድ ነበረ። እግዚአብሔር ግን ከላይ ወደ ታች ቀደደው። ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ (ማለትም ዘላለማዊ ሕይወት) ከዚያ ወዲያ ከተቀደደው መጋረጃ ጀርባ አለመኖሩን ያመለክታል። እግዚአብሔር ከቅድስተ ቅዱሳን ወጥቶ ሄደ። ከዚያ ወዲያ ቤተመቅደሱ ባዶ ቀፎ ወይም ኦኖ ሆነ። ውብ የሐይማኖት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል ግን በተቀደደው መጋረጃ ምክንያት ውስጡ ሞት ብቻ ነው የነበረው።

ቤተመቅደሱ የነበረበት ሁኔታ ሔዋን የኤድን ገነት ውስጥ እንደነበረችው ነው። መጋረጃው በመቀደዱ ቤተመቅደሱ በእርግማን ውስጥ ነበረ፤ ከመጋረጃውም ጀርባ የዘላለም ሕይወት አልነበረም።

እግዚአብሔር ሊያድናት ጣልቃ ገባ።

ዘፍጥረት 3፡21 እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።

አዳም እና ሔዋን ከኤድን ገነት ተባረው ሲወጡ የለበሱት የእንስሳ ቆዳ ስር ያለው ደም ሰውነታቸውን እየነካነው ነው የወጡት።

አንድ ንጹህ እንስሳ ማለትም የበግ ጠቦት ሲታረድ የበጉ ንጽሕና ወዳረደው ሰው ይተላለፋል።

በዚያው ሰዓት ደግሞ በጉን ያረደው ሰው ሐጥያት ወደ በጉ ይተላለፋል፤ በጉ የሚሞተው የሰውየውን ሐጥያት ለማስተስረይ ነው።

ነገር ግን የበጉ ሕይወት ወደ ሐጥያተኛው መተላለፍና ሰውየውን የተሻለ ሰው ወይም ሐጥያት ማድረግ የማይፈልግ ሰው ማድረግ አይችልም

 

ቃየን እና አቤል ከተለያዩ አባቶች የተወለዱ መንታዎች ናቸው

 

 

እባቡ ተረግሞ በደረቱ የሚሳብ እና አፉ ውስጥ መርዝ ያለው እንስሳ ሆኖ ተለወጠ።

እባቡ ሴቲቱን ሐጥያት መስራት ያስተማራት ጊዜ ሴቲቱ ላይ በደረቱ ተኝቶ ነበር።

አፉ ውስጥ መርዝ የተፈጠረው የእግዚአብሔርን ቃል ባጣመመ ጊዜ ነው።

ሴቲቱ በድንግልና ስለመውለድ ምንም እውቀት አልነበራትም፤ ስለዚህ ብቸኛው የመዋለድ መንገድ ወሲባዊ ግንኙነት መስሏታል። ስለዚህ ምንም ሐጥያት እንደሰራች አላወቀችም። በእባቡ ተንኮል ተታለለች።

ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።

ቃየን በተወለደ ጊዜ ሔዋን ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር ዘንድ አገኘሁ አለች። ቃየን ከአዳም ተወለደ ለማለት ድፍረት አልነበራትም። ነገር ግን ሁሉም ሕይወት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሆነ ትክክል ተናግራለች።

ነገር ግን አልተታለልኩም ብላ ራሷን ለማሳመን ስለፈለገች የቃየን ትክክለኛ አባት ማን እንደሆነ አልተናገረችም። እስከ ዛሬ ድረስ ቤተክርስቲያኖችም ልክ እንደ ሔዋን ሰዎችን ለማሞኘት ብለው የቃየን ትክክለኛ አባት ማን እንደሆነ ሲክዱ ኖረዋል።

የወሲባዊ ግንኙነት ሕጋዊ ትርጓሜው ስጋዊ እውቀት ነው።

ከኤድን ገነት ከወጡ በኋላ

ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።

2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።

ከአንድ ወሲባዊ ግንኙነት መንታ ልጆች ተወለዱ።

ነገር ግን ሔዋን በኤድን ገነት ውስጥ ሳለች ጸንሳ ነበር።

ሔዋን የተቀጣችበት ሐጥያት የመጀመሪያው ጽንስ ነው፤ ይህም ጽንስ የተፈጠረው ሔዋን እና እባቡ ባደረጉት ወሲባዊ ግንኙነት ነው።

ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤

ሔዋን በመጀመሪያው እርግዝናዋ ምክንያት ነው የተቀጣችው። የኤድን ገነት ውስጥ አርግዛ ነበር።

ስለ እርግዝናዋ ተቀጣች ማለት የጽንሱ አባት አዳም አይደለም ማለት ነው።

ይህ የመጀመሪያ ጽንስ የተፈጠረው ከእባቡ ሲሆን ጽንሱ የተጸነሰው እባቡ ተረግሞ በደረቱ የሚሄድ እንስሳ ከመሆኑ በፊት ነው።

መጽሐፈ ዜና ቃየን ከአዳም ነው የተወለደው አይልም።

መንታዎቹ ልጆች ቃየን ከእባቡ የተጸነሰ ሲሆን አቤል ደግሞ ኋላ ከአዳም የተጸነሰ ልጅ ነው።

ከሁለት አባቶች ሁለት የተለያዩ ጽንሶች? እነዚህም እንደ መንታ ሊወለዱ ይችላሉ?

ከዚህ ቀጥሎ ከጋዜጣ የተወሰደውን ዘገባ ተመልከቱ።

አንዲት ሴት መንታ ልጆችን በሳምንት ልዩነት ወለደች

ማርሊ ሞክዌና እና ባሏ ቴቦጎ ለእርግዝና ክትትል በሄዱ በመጀመሪያ ጊዜያቸው ጽንሱ መንታ መሆኑ ሲነገራቸው ደንግጠዋል። የ31 ዓመቱ ቴቦጎ እንዲህ አለ፡- “ዶክተሩ አንዴ አልትራ ሳውንዱን አንዴ ደግሞ እኛን ሲያይ ከቆየ በኋላ ከሁለቱ ሕጻናት አንዱ የ14 ሳምንት ጽንስ ሁለተኛው ግን የ13 ሳምንት ጽንስ መሆኑን ነገረን”።

ይህ ዓይነቱ ያልተለመደ እርግዝና ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሁለቱ ሕጻናት ተጸንሰው ማሕጸን ውስጥ አንድ ላይ ሊያድጉ ይችላሉ።

MetroLifestyleTeam@Metro.co.uk

ሁለቱ እንደ መንታ የሚወለዱ ሕጻናት ከሁለት የተለያዩ አባቶች የተጸነሱ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቬሪዌልፋሚሊ

መንታዎች የተለያዩ አባቶች ሊኖሩዋቸው ይችላል?

በፓሜላ ፐሪነድል ፊየሮ፣ ጁን 27 ቀን 2020 በድጋሚ የታተመ

መረጃዎች በአዳ ቹንግ ተጣርተዋል

አንዲት ሴት ከሁለት የተለያዩ አባቶች በአንድ ጊዜ ልትጸንስ የምትችልበት መንገድ ሁለቱም የሴቷ እንቁላሎች በተዘጋጁበት ወቅት ውስጥ ከሁለት የተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ስትፈጽም ነው። ለምሳሌ ኒው ጀርሲ ውስጥ አንዲት የመንታ ልጆች እናት የመንግስትን ድጋፍ መጠየቅ በፈለገች ጊዜ የሕጻናቱ አባት ማን እንደሆነ ለማጣራት ምርመራ አድርጋ ነበር። የምርመራው ውጤት ባሏ ከመንታዎቹ ሕጻናት የአንዱ ብቻ አባት መሆኑን ሲያሳይ እናቲቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከባሏም ከሌላ ወንድ ጋርም መተኛቷን አምናለች።

በተመሳሳይ መንገድ ቴክሳስ ውስጥ አንዲት የመንታ ልጆች እናት መንታዎቹን በጸነሰችበት ሰሞን ከባሏ ውጭ ሌላ ውሽማ ይዛ እንደነበር ተናግራለች። የአባትነት ምርመራ ሲደረግም እጮኛዋ ከሁለቱ ልጆች የአንዱ ብቻ አባት መሆኑ እንዲሁም የሁለተኛው ሕጻን አባት ሌላኘው ሰውዬ መሆኑ ተረጋግጧል።

ቃየን ሐሰተኛ እና ነፍሰ ገዳይ ነበር። እባቡ ውስጥ የነበረው ሰይጣንም ባሕርዩ ይኸው ነው።

ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፤ በስተመጨረሻም የቤተክርስቲያን ሰዎች በማቴዎስ ምዕራፍ 25 የተጠቀሱት 10 ሰነፍ ቆነጃጅት እንቅልፍ እንደተኙት ሁሉም እንቅልፍ እስኪወስዳቸው ድረስ ይታለላሉ። ቆነጃጅት ወይም ድንግል ሴቶች የዳኑ ክርስቲያኖችን የሚወክሉ ንጹህ ሴቶች ናቸው፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ይታለላሉ።

እባቡ ወደ ሰው ቀረብ ያለ ትልቅ እንስሳ ነበረ። ይህም ኒፊሊሞች ወይም ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ለምን እንደነበሩ ያስረዳናል። የሰው ሴቶች ልጆች የተባሉት ትልልቅ የመሆን ዘር ያለባቸው የቃየን ዘሮች ናቸው።

የእግዚአብሔር ልጆች መላእክት አይደሉም። የሴት ልጆች ናቸው።

ቃየን የእባብ እና የሰው ዲቃላ ነው።

የቃየን ዘሮች ከሴት ዘሮች ጋር በጋብቻ ሲቀላቀሉ የሰው ዘር ተበላሸ። እግዚአብሔርም ይህን የተበላሸውን የሰው ዘር በኖህ የጥፋት ውሃ ከምድር ላይ አስወገደው።

ዕብራውያን 1፡5 ከመላእክትስ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ … ያለው ከቶ ለማን ነው?

ሰማይ ውስጥ ደም የለም። መላእክት ደም የላቸውም፤ ስለዚህ ወሲባዊ ግንኙነት ሊያደርጉ አይችሉም።

ማቴዎስ 22፡30 በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።

ጳውሎስ ሔዋን እባቢ እስኪያስታት ድረስ ድንግል ነበረች ይላል።

2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2 በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤

3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።

 

እግዚአብሔር የግል መገለጥ ሊሰጣችሁ ይገባል

 

 

ማቴዎስ 16፡17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

ስጋ እና ደም ሰዎችን የሚገልጽ ቃል ነው።

አንድ የተከበረ ወይም ታዋቂ ሰው ምንም ቢናገር የማድመጥ ዝንባሌ አለን። ይህ ግን አስተዋይነት አይደለም።

የቤተክርስቲያን መሪዎችን በመከተል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለትም ስለ እግዚአብሔር ቃል ትክክለኛውን ልንማር አንችልም።

መንጋውን ተከትላችሁ መሄድ አቁማችሁ በራሳችሁ አእምሮ የምታስቡበት ጊዜ ይመጣል።

የዚያን ጊዜ የቤተክርስቲያንን ልማድ ሳይሆን ትክክለኛውን እውነት መረዳት ትችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ዓይናችሁን እስከሚያበራ ድረስ መጸለይ አለባችሁ።

ምንም ነገር አንድ ታዋቂ ሰው ስለተናገረው ብቻ ማመን የለባችሁም።

የምታምኑት ሁሉ እውነት መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መርምራችሁ አረጋግጡ።

64-0823 ጥያቄዎችና መልሶች 1

ነገር ግን ቃሉን በሙላቱ ሊቀበሉት የሚችሉ እኔ ስለሰበክሁ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተናገረ ብለው የሚቀበሉ

ነጻ የሆነውን መቀበል የሚችሉ ምክንያቱም ቃሉ አስቀድሞ ተፈትኗል።

የ7ቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ ምዕራፍ 9 - የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን

… እውነተኛ ነብይ ሁልጊዜ ሰዎችን ወደ ቃሉ ይመራቸዋል፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያጣብቃቸዋል፤ ደግሞም ነብዩ ሰዎች እርሱን እንዲፈሩት ወይም የተናገረውን ቃል እንዲፈሩ አይነግራቸውም፤ ሁሌ ቃሉ የተናገረውን ብቻ እንዲፈሩ ነው የሚነግራቸው።

62-0318 የተነገረው ቃል የመጀመሪያው እውነተኛ ዘር ነው - 2

አሁን የተናገርኳቸው ነገሮች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማሙ ከሆነ ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማሙ ከሆነ ስሕተት ናቸው፤ ስሕተት ናቸው።

65-0801 የዚህ ክፉ ዘመን አምላክ

… ጌታ ኢየሱስ ለዚህ ሰዓት የሰጠኝን መልእክት ያመኑ ሰዎች በአሁን ሰዓት ምን እየተፈጸመ እንዳለ ያውቁ ዘንድ፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልገው ያገኙ ዘንድ

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23