የዳንኤል 70 ሱባኤ (ሳምንታት)



First published on the 26th of December 2018 — Last updated on the 27th of January 2019

መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜን የሚገልጽበት የተለያዩ መንገዶች አሉት።

በትንቢታዊ አገላለጽ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ሊወክል ይችላል። (መጽሃፍ ቅዱሳዊ የቀን አቆጣጠር በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ጥናት ተመልከቱ)
ላባ ያዕቆብን ሲናገረው የላባን ልጅ ራሔልን ማግባት ከፈለገ ተጨማሪ 7 ዓመታት በላባ ቤት ወስጥ መሥራት እንዳለበት ነግሮታል።

ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።

 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ወር ሠላሳ ቀን ነው

እስቲ አሁን ደግሞ አንድ ወር በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ውስጥ ሠላሳ ቀን መሆኑን እናረጋግጥ።

ራዕይ ምዕራፍ 11 በታላቁ መከራ ወቅት ሁለቱ ነብያት ወንጌልን ወደ አይሁድ ሕዝብ ይዘው በመሄድ 144,000 አይሁዳውያንን ወደ ኢየሱስ እንደሚመልሱ ይናገራል።

ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።

በዚህ ክፍል ውስጥ 1260 ቀን ተብሎ የተገለጸው ቁጥር 42 ወራት ተብሎም ተገልጧል። ስለዚህ በትንቢት ውስጥ እያንዳንዱ ወር ሰላሳ ቀናት አሉት።
ለዚህ ማረጋገጫ ዘፍጥረት ውስጥ የኖኅ መርከብ በጥፋት ውሃ ላይ ከተንሳፈፈችበት ቀን ጀምሮ መርከቢቱ በደረቅ ምድር ላይ እስካረፈችበት ቀን ድረስ የተቆጠሩት ቀናት ውስጥ ማግኘት እንችላለን። ቀኖቹ 150 ሲሆኑ እነርሱም 5 ወራት ተብለው ተገልጸዋል።

ዘፍጥረት 7፡24 ውኃውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።
ዘፍጥረት 8፡3 ውኃውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፥ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጎደለ።
ዘፍጥረት 7፡11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፥ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ፤
ዘፍጥረት 8፡4 መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።

ከሁለተኛው ወር 17ኛ ቀን ጀምሮ እስከ ሰባተኛው ወር 17ኛ ቀን ድረስ አምስት ወራት ተቆጥረዋል። ይህም ደግሞ 150 ቀናት ተብሎ ተገልጧል። ስለዚህ በትንቢት ውስጥ አንድ ወር 30 ቀን ነው።

 

ዳንኤል በተናገረው ትንቢት ውስጥ 70 ሱባኤ (ሳምንታት) መቁጠር የተጀመረው መች ነው?

መቁጠር የተጀመረው የፋርስ ንጉስ ትዕዛዝ ባወጣ ጊዜ ነው።

ሦስት ጊዜ ትዕዛዝ ወጥቷል።

 

1 - የመጀመሪያው ትዕዛዝ መቅደሱ እንዲሰራ።

2 - ሁለተኛው ዕዝራ የመቅደሱን የወርቅ እና የብር እቃዎች ወስዶ ወደ መቅደሱ እንዲመልስ።

3 - ሦስተኛው ደግሞ ነሕምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እና ወደ በሮቿ የሚያደርሱትን ጎዳናዎች እንዲያድስ የወጣው ትዕዛዝ።

እነዚህ ትዕዛዛት የወጡባቸው ቀናት የሚታወቁት ብዙዎቹ መደበኛ ኢንሳይክሎፔዲያዎች በሚስማሙበት መረጃ አማካኝነት ነው። የቤተክርስቲያናት የሥነጽሁፍ ሥራዎችን ያልተጠቀምነው ብዙዎቹ ቤተክርስቲያናት የራሳቸውን አመለካከት ለመደገፍ ብለው ቀኖቹን እንደሚመቻቸው ስለሚያሸጋሽጉ ነው።

 

የመጀመሪያው ትዕዛዝ የፈረሰው መቅደሱ እንዲሰራ ቂሮስ በ536 ዓመተ ዓለም ያስተላለፈው አዋጅ ነው።

ዕዝራ 1፡1 በኤርምያስም አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፥ ደግሞም በጽሕፈት አድርጎ እንዲህ አለ፡-

2 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤

3 ከሕዝቡ ሁሉ በእንናተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት ይሥራ፤

ታሪክ አዋቂዎች እንደሚሉት ይህ ትዕዛዝ የወጣው በ536 ዓመተ ዓለም ነው ሲሆን ሳይፈጸም ብዙ ጊዜ ከተስተጓጎለ በኋላ መቅደሱ በነብያቱ በሃጌ እና ዘካርያስ አበረታችነት በ515 ዓመተ ዓለም ተሰራ።

ዕዝራ 5፡1 ነቢያቱም ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው።
ዕዝራ 6፡15 ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ።
በዚህ ጊዜ መቅደሱ ተስርቶ ተጠናቀቀ።

 

ሁለተኛው ትዕዛዝ በኢየሩሳሌም ተሰርቶ ለተጠናቀቀው ቤተመቅደስ ማስጌጫ ይሆኑ ዘንድ የወርቅ እና የብር እቃዎችን ይዞ እንዲሄድ ለዕዝራ የተጻፈለት ደብዳቤ ነው።

ዕዝራ 7፡11 ንጉሡም አርጤክስስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቃልና ለእስራኤል የሆነውን ሥርዓት ይጽፍ ለነበረው ለጸሐፊው ለካህኑ ለዕዝራ የሰጠው የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው።
ዕዝራ 7፡12 ከንጉሠ ነገሥት ከአርጤክስስ ለሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ለዕዝራ፥ ሙሉ ሰላም ይሁን፤
15 ንጉሡንና አማካሪዎቹም መኖሪያው በኢየሩሳሌም ለሆነው ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ፥
16 በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ትወስድ ዘንድ በንጉሡና በሰባቱ አማካሪዎች ተልከሃልና
17 ስለዚህ በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችንና አውራ በጎችን ጠቦቶችንም የእህላቸውንና የመጠጣቸውን ቍርባን ተግተህ ግዛ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው
18 ከቀረውም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ ለማድረግ ደስ የሚያሰኛችሁን ነገር እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አድርጉ።
19 ስለ አምላክህም ቤት አገልግሎት የተሰጠህን ዕቃ በኢየሩሳሌም አምላክ ፊት አሳልፈህ ስጥ።
20 ከዚህም በላይ ለማውጣት የሚያስፈልግህን ለአምላክህ ቤት የሚያሻውን ነገር ከንጉሡ ቤተ መዛግብት አውጣ።
21 እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ላሉት በጅሮንዶች ሁሉ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ሁሉ አዘጋጁለት፤
22 እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን ስጡ።

ይህ ደብዳቤ የተሰጠው መች ነው?

ዕዝራ 7፡8 በንጉሡም በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።

አርጤክስስ ቀዳማዊ በ465 ዓመተ ዓለም ተገደለ፤ ከዚያም ልጁ አርጤክስስ በእርሱ ፈንታ ነገሰ።

የሞተበት ዓመት በጣም አጨቃጫቂ ነው። ኢንሳይክሎፔዲያዎች ዓመቱ 465 ዓመተ ዓለም ነው ይላሉ። ሁሉም ባይሆኑም አንዳንድ የክርስቲያን ማጣቀሻ መጻሕፍት ደግሞ 464 ዓመተ ዓለም ነው ይላሉ። ነገር ግን አንዳንድ ክርስቲያን ምሁራን ሰው ሁሉ እንዲቀበለው የሚፈልጉት የራሳቸው ጠንካራ አቋም አላቸው። ስለዚህ ዓመቱ እነርሱ ለትንቢቶች ከሚሰጡዋቸው አተረጓጎም ጋር እንዲገጣጠምላቸው ለማድረግ ይፈልጋሉ። በዚህም ምክንያት የኢንሳይክሎፔዲያዎቹን ቀን ለመከተል ወስነናል።

 

Year   BC  ዓመተ ዓለም 465 464 463 462 461 460 459
Year of rule የንግስና ዓመት 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ 5ኛ 6ኛ 7ኛ

 

ስለዚህ በ459 ዓመተ ዓለም ዕዝራ የመቅደሱን የወርቅና የብር እቃዎች ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ እንዲሄድ ትዕዛዝ ተቀበለ።

ንጉሱ ለቤተመቅደሱ ማስዋብያ እቃዎች ስለሰጠ ዕዝራ እግዚአብሔርን አመሰገነ።

ዕዝራ 7፡27 በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያሳምር ዘንድ እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ በንጉሡም በአማካሪዎቹም በንጉሡም ኃያላን አለቆች ሁሉ ፊት ምሕረቱን ወደ እኔ የላከ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

 

እዚህጋ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር ስለመገንባት የተጠቀሰ ነገር የለም። ደግሞም የከተማይቱን ቅጥሮች የሚያገናኙ ጎዳናዎችን ስለመስራትም አልተጠቀሰም።

የዳንኤል ትንቢት እንዲህ ይላል፡-

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

ስለዚህ የፋርስ ንጉስ ያወጣው ትዕዛዝ ብቻ ነው እነዚህን ሁኔታዎች ሁሉ የሚያሟላው።

ይህም የሆነው የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ይሰራ ዘንድ ንጉሱ ለነሕምያ ፈቃድ የሰጠው ጊዜ ነው።

ነህምያ 1፡2 እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ ከወንድሞቼ አንዱ አናኒ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን ከምርኮ የተረፉትን የአይሁድን ነገር የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው።
3 እርሱም፦ በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል አሉኝ።

በሮችዋ ከተዋይቱን በሚከብቧት ቅጥሮች ውስጥ ጎዳናዎች የሚያልፉባቸው መግቢያና መውጫ ናቸው።

ነህምያ 2፡1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር።
ነህምያ 2፡4 ንጉሡም፦ ምን ትለምነኛለህ? አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ።
5 ንጉሡንም፦ ንጉሡን ደስ ቢያሰኝህ፥ ባሪያህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ እሠራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባቶቼ መቃብር ከተማ ስደደኝ አልሁት።
ነህምያ የፈረሰውን ከተማ መልሶ መስራት ፈለገ።
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ነህምያ 2፡7 ንጉሡንም፦ ንጉሡ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ አገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤
8 በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማው ምቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ አልሁት። ንጉሡም በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነችው እንደ አምላኬ እጅ ሰጠኝ።
9 በወንዙም ማዶ ወዳሉት አለቆች መጥቼ የንጉሡን ደብዳቤ ሰጠኋቸው፤ ንጉሡም ከእኔ ጋር የሠራዊቱን አለቆችና ፈረሰኞች ሰደደ።

የንጉሱ ደብዳቤ ነህምያ ኢየሩሳሌምን መገንባት እንዲጀምር ይፈቅዱለት ዘንድ አለቆችን አዘዘ። የነህምያ ዋነኛ ሃሳቡ የከተማይቱ አትር ላይ ነው።

ነህምያ 2፡13 በሸለቆውም በር ወጣሁ፥ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ።

ነህምያ ዋና ሃሳቡ ለቅጥሩ ነው። ቅጥር (አጥር) የሌላት ከተማ ለጥቃት ትጋለጣለች።

ነህምያ 2፡17 እኔም፦ እኛ ያለንበትን ጕስቍልና ኢየሩሳሌም እንደፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደተቃጠሉ ታያላችሁ፤ አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ አልኋቸው።

ዳንኤል እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር።

ዳንኤል 9፡25 …እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

ቅጥሮች እና ጎዳናዎች በጭንቀት ዘመን ውስጥ ይሰራሉ።

ጭንቅ የሚፈጥሩ ሰዎች ስለመኖራቸው ምን ማስረጃ አለን? እነዚህ ሰዎች ቅጥሩን የሚሰሩትን የሚያውኩ ናቸው።

ነህምያ 4፡16 ከዚያም ቀን ጀምሮ እኵሌቶቹ ብላቴኖቼ ሥራ ይሠሩ ነበር፥ እኵሌቶቹም ጋሻና ጦር ቀስትና ጥሩርም ይዘው ነበር፤ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።
17 ቅጥሩንም የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፥ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር።
18 አናጢዎቹም ሁሉ እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለከትም የሚነፋ በአጠገቤ ነበረ።

በአንድ እጃቸው ጡብ በሌላኛው ጦር ይዘው ሰይፍ በወገባቸው እንደታጠቁ ይሰሩ ነበር። ሲተኙም እንኳ ልብሳቸውን ሳይቀይሩ ነበር የሚተኙት፤ ድንገት ሌሊት ጥቃት እንዳይሰነዘርባቸው። ጥቃት ቢሰነዘርባቸው ተነስተው ልብስ የሚቀይሩበት ጊዜ አያገኙም።

ነህምያ 4፡23 እኔና ወንድሞቼም ብላቴኖቼም በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር።

ነህምያ ይህንን ትዕዛዝ መቀበል የሚችለው የዳንኤል ትንቢት ውስጥ የተጠቀሱ ዝርዝር ሁኔታዎች ሁሉ ሲያሟላ ነው።

መች ነው ፈቃድ የተሰጠው? በአርጤክስስ ዘመነ መንግስት በሃየኛው ዓመት።

ነህምያ 2፡1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር።

 

Year   BC         ዓመተ ዓለም 465 464 463 462 461 460 459
Year of rule የንግሥና ዓመት 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ 5ኛ 6ኛ 7ኛ
Year   BC         ዓመተ ዓለም 458 457 456 455 454 453 452
Year of rule የንግሥና ዓመት 8ኛ 9ኛ 10ኛ 11ኛ 12ኛ 13ኛ 14ኛ
Year   BC         ዓመተ ዓለም 451 450 449 448 447 446
Year of rule የንግሥና ዓመት 15ኛ 16ኛ 17ኛ 18ኛ 19ኛ 20ኛ

 

ስለዚህ በ446 ዓመተ ዓለም ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትዕዛዝ ወጣ። ቆጠራ መጀመር ያለብን ከዚህ ዓመት ጀምሮ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ዓመት 360 ቀን ነው
በትንቢት ውስጥ አንድ ወር 30 ቀን ከሆነ እና በትንቢት ውስጥ አንድ ዓመት ማለት 12×30 = 360 ቀናት እንጂ እኛ እንደምንቆጥረው 365.24 ቀናት አይደለም።

የክርስቶስ ተቃዋሚን አሰራር በተመለከተ ዳንኤል እንዲህ አለ፡-

ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።

ምድር በዛቢያዋ ላይ ቀጥ ብላ ቆማ ትዞር ስለ ነበር እያንዳንዱ ዓመት 360 ቀናት ነበረ። በኖኅ ዘመን የጥፋት ውሃ በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር መሬትን ለጥቂት ጊዜ ከፀሃይ ራቅ ስላደረጋት የሕዋው ቅዝቃዜ እና ከሰማይ የወረደው ውሃ እንዲሁም ከምድር ውስጥ የፈለቀው ውሃ በአንድነት የፈጠሩት ቅዝቃዜ ምድር ላይ ተጽእኖ አምጥቷል። ይህም ያስከተለው የበረዶ ዘመን በዋልታዎች ላይ የበረዶ ግግር የፈጠረ ሲሆን እግዚአብሔር ምድርን አሁን ወዳለችበት ምሕዋሯ በመለሳት ጊዜ የበረዶ ግግሩ አልቀለጠም፤ ምሕዋሯም ከመጀመሪያው ምሕዋር በጥቂቱ ሰፋ ብሏል።

በደቡብ ዋልታ ያለው የበረዶ ግግር በሰሜን ዋልታ ካለው የበረዶ ግግር አሥር እጥፍ ይበልጣል ምክንያቱም የደቡቡ ዋልታ በረዶ ከሥሩ መሬት አለው፤ እርሱም ትልቁ የአንታርክቲካ አህጉር ነው። በሰሜን ዋልታ ካለው በረዶ ሥር ግን በመሬት ፈንታ ባሕር ነው ያለው።

የበረዶ ግግሩ ክብደት አለመመጣጠኑ ወይም መበላለጡ የመሬት ዛቢያ በ231/2ዲግሪ እንዲያጋድል አድርጎታል።

የመሬት ምሕዋር ተለቅ ማለቱ ከዚያ ወዲህ ዓመታቶችዋ ረዘም እንዲሉ ማለትም 365.24 ቀናት እንዲሆኑ አድርጓል።

ይህም ለጊዜው ነው እንጂ፤ በታላቁ መከራ ወቅት እግዚአብሔር መሬትን ወደ ፀሃይ ጠጋ ስለሚያደርጋት የፀሃይዋ ግለት በዋልታዎች ላይ ያለውን በረዶ ያቀልጠዋል። በረዶው ሲቀልጥ ክርስቶስ የ 1000 ዓመት መንግሥት በሚመሰርትበት ጊዜ መሬት ተመልሳ ቀጥ ባለ ዛቢያ ላይ ትሽከረከራለችር።

ራዕይ 16፡8 አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።
9 ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም።

ስለዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ሥርዓት 360 ቀናት የነበረውን ዓመት ወደ 365.24 ቀን እንዲለውጥ ፈቅዶ ነው። ይህም የተደረገው ሮም ውስጥ ነው። የሮማ አምባገነን ንጉስ ዩልየስ ቄሳር በ46 ዓመተ ዓለም በዓመቱ ላይ 67 ቀናት በመጨመር ዓመቱ 445 ቀናት እንዲሆን አደረገ። ከፌብርዋሪ ማለትም የካቲት በቀር እያንዳንዱ ወር 30 እና 31 ቀናት እንዲሆን ያደረጉት ሮማውያን ናቸው። ከዚያም በ1582 ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው 10 ቀናት በመቀነስ እና ዓመቱ ለ400 ሊካፈል (ለምሳሌ በ1600 ወይም በ2000 ግን በ1900 አይሆንም) በሚችልበት ጊዜ ብቻ ሊፕ ይር (ጳጉሜ) በመጨመር ካላንደሩን ለማስተካከል ሞከረ።
በዚህም የተነሳ ሌላ ከበድ ያለ ችግር ተፈጠረ። አይሁድ ብሉይ ኪዳንን ብቻ ይታዘዙ ነበር። ክርስቶስ ከመወለዱ ከ45 ዓመት በፊት የተለወጠውን ካላንደር ወይም የቀን አቆጣጠር፤ ያውም ጠላቶቻቸው ሮማውያን ያመጡላቸውን ካላንደር አንጠቀምም አሉ።ፖምፔይ የተባለ ሮማዊ ጀነራል በ65 ዓ.ም. በሰንበት ቀን አይሁድ አንዋጋም ብለው በተቀመጡበት ኢየሩሳሌምን ወግቶ ተሸንፏታል።

ስለዚህ አይሁድ ዘፍጥረት ውስጥ በኖኅ ዘመን እንዳየነው አንድ ወር 30 ቀን ነው ብለው ነው የሚቆጥሩት።

365.24 ቀን ብለን የምንቆጥረው ዓመት ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓመት በ5.24 ቀናት ያህል ይረዝማል፤ ትንቢታዊው ዓመት 360 ቀናት ነው።

ስለዚህ እኛ በምንቆጥረው ዓመት በ70 ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ 70×5.24 = 367 ቀናት ስለሚኖሩን አንድ ተጨማሪ ዓመት ይኖረናል። በዚህም ቀመር መሰረት የኛ 70 ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ 71 ዓመት ነው።

ሰባ ሱባኤ (ሳምንታት) ማለት 70 × 7 = 490 ቀናት ወይም 490 ትንቢታዊ ዓመታት ማለት ነው።

ነገር ግን በየ 70 ዓመታቱ እኛ አሕዛብ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ዓመት አንድ ዓመት ወደ ኋላ እንጎተታለን። ስለዚህ በ70 × 7 ዓመታት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱሱ ዓመታት ከእኛ 7 ዓመታት ይቀንሳል።በእኛ ካላንደር ሲቆጠር “ሰባው ሱባኤ” 490 – 7 = 483 ዓመታት ጋር እኩል ይሆናል።

የሰባው ሱባኤ የመጨረሻ ሱባኤ ወይም ሳምንት (የመጨረሻዎቹ ሰባት ዓመታት) የመሲሁ አገልግሎት ጊዜያት ናቸው።

ስለዚህ መሲሁ ከመምጣቱ በፊት ስንት ዓመታት ያልፋሉ? 483 – 7 = 476 ዓመታት።

 

መሲሁ የሚወለደው መች ነው?

ብዙዎቹ ኢንሳይክሎፔዲያዎች እንደሚያሳዩት መሲሁ ሊወለድ ዓመታቱ መቆጠር የተጀመሩት በ446 ዓመተ ዓለም ነው።

ስለዚህ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩት 446 ዓመታት ሲቀነሱ ምን ያህል ዓመታት ይቀራሉ?

476 – 446 = 30 ዓመታት። ይህም ኢየሱስ አገልግሎት የጀመረበት እድሜው ነው።

ሉቃስ 3፡1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥…
2 ሐናና ቀያፋም ሊቃነ ካህናት ሳሉ፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ።

ጢባርዮስ በሮማ ምክር ቤት አማካኝነት ንጉሠ ነገሥት ሆኖ የተሾመው በ14 ዓመተ ዓለም አውግስጦስ ሲሞት ነበር።

አውግስጦስ ጢባርዮስን እንደ ልጅ ወስዶ አሳደገው። በ12 ዓመተ ዓለም አውግስጦስ ከእርሱ ጋር አብሮ ገዢ አደረገው፤ ግን ይህም ኋላ ጢባርዮስ ለመንገሱ በቂ መተማመኛ አልነበረም። ምክንያቱም አውግስጦስ ንጉስ እንዳልሆነ አድርጎ ይቀልድ ነበር፤ በዚህም ምክንያት በማደጎ ያሳደገው ልጁ ጦባርዮስ አይነግስም። ከዚህም ሌላ አውግስጦስ አግሪጳ ፖስቱመስ የተባለ የተባለ የልጅ ልጅ ስለ ነበረው አውግስጦስ ቢሞት ሊነግስ የሚችለው አግሪጳ ነው። ስለዚህ በ14 ዓመተ ዓለም አውግስጦስ ሲሞት ወዲያ አግሪጳ ተገደለ። በዚህ ጊዜ ምክር ቤቱ ጢባርዮስ እንዲነግስ ጥያቄ አቀረቡለት። ጢባርዮስም በመጀመሪያ እምቢ አለ፤ ከጊዜ በኋላ ግን “እያቅማማ” ተስማማ።

ስለዚህ የጢባርዮስ አሥራ አምስተኛ ዓመት 14 + 15 = 29 ዓ.ም. ነው። ይህም መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን የጀመረበት ዓመት ነው።

ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር…

“30 ዓመት ያህል”። ድፍን ሠላሳ ዓመት አልሞላውም። ይህም የሆነው በ29 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ነበር።

ኢየሱስ በዮሐንስ በተጠመቀ እና መንፈስ ቅዱስ ወርዶበት በተቀባ ጊዜ እድሜው ይህን ያህል ነበረ።

መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጡ አልገባም፤ በእርሱ ላይ አረፈበት ወይም ወረደበት እና ኖረበት እንጂ።

ዮሐንስ 1፡32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።
33 እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።

እንዲህ በሕዝብ ፊት መቀባቱ እርሱ “የተቀባው” (በግሪክ) ክርስቶስ ወይም (በእብራይስጥ) መሲሁ መሆኑን አረጋገጠ።

ሉቃስ 3፡22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ማን ነው የተናገረው። እግዚአብሔር አብ ነው።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

የሕይወትን ዘር በአንዲት ሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያኖር ሁሉ የዚያ ሕጻን አባት ነው። የኢየሱስ ሥጋዊ አካል የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።

መንፈስ ቅዱስ አባቱ ስለሆነ እርሱ ራሱ ነው ኢየሱስን “የምወድህ ልጄ” ብሎ መጥራት የሚችለው።

ልጅ ተብሎ መጠራቱ ላይ ትኩረት መደረጉ አለቃው መሲሁ እርሱ መሆኑን ያረጋግጣል።

ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

አለቃው መሢሕ የሚለው መጠሪያ በ29 ዓ.ም. ማለቂያ አካባቢ አገልግሎቱን የሚጀምርበትን ጊዜ ያመለክታል።

በአገልግሎቱ መጨረሻ አካባቢ የሆሳእና ዕለት በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ እንደ ንጉሥ ተቀብለውታል። አለቃ ሆኖ አልቀረም።

ዘካርያስ 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

 

የኢየሱስ አገልግሎት ለምን ያህል ጊዜ ነበር?

የአይሁድ አንድ ዓመት እያንዳንዳቸው ስድስት ወራት በሚሆኑ ሁለት መንፈቆች ይከፈላል። ሁለቱም መንፈቆች በወር አጋማሽ አካባቢ ጀምረው በወር አጋማሽ አካባቢ ይጠናቀቃሉ።

 

Seed time የሚዘራበት ጊዜ Winter ክረምት Spring      ፀደይ Harvest    መከር Summer    በጋ Extreme heat ከባድ ሙቀት
Oct, Nov ጥቅምት፣ ሕዳር Dec, Jan ታሕሳስ፣ ጥር Feb, March የካቲት፣ መጋቢት April, May ሚያዚያ፣ ግንቦት June, July ሰኔ፣ ሐምሌ Aug, Sept ነሃሴ፣ መስከረም

 

በየዓመቱ የሚከበሩ ሰባት በዓላት ነበሩ።

የመጀመሪያው በዓል ፋሲካ እና ከዚያም ደግሞ የቂጣ በዓል ነበር፤ ይህም በመጋቢት አጋማሽ (በፀደይ ወቅት) ነበር የሚከበረው።

የበኩራት በዓል የሚከበረው ሚያዚያ ወር ውስጥ መከሩንመሰብሰብ በሚጀመርበት ወቅት ነው።

ግንቦት ውስጥ ደግሞ የጴንጤ ቆስጤ በዓል ይከበራል።

መስከረም ወይም ጥቅምት ውስጥ የሚከበሩ ሦስት በዓላት ደግሞ የማስተስረያ በዓል፣ የመለከት፣ እና የዳስ በዓል ናቸው፤ እነዚህም የዓመቱ መዝጊያ በዓላት ናቸው።

ዮሐንስ 2፡13 የአይሁድፋሲካምቀርቦነበር፥ኢየሱስምወደኢየሩሳሌምወጣ።

ይህም ኢየሱስ በውሃ ከተጠመቀ በኋላ ሁለተኛው ፋሲካ ነው።

ከላይ ባየነው ቃል ውስጥ የተጠቀሰው የ30 ዓ.ም. ፋሲካ ካለፈ በኋላ ኢየሱስ ሰማርያ ውስጥ በሲካር ከተማ መሃል አለፈ።

ሳምራውያኑን ካናገራቸው በኋላ የፍጥረታዊ እርሻቸው መከር ጊዜ ሊደርስ አራት ወር እንደቀረ ይነግራቸዋል።

ዮሐንስ 4፡5 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤
ዮሐንስ 4፡35 እናንተ፦ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ።

በሚያዚያ አጋማሽ ከመከር ወቅት አራት ወራት የሚቀድመው ጊዜ የታህሳስ አጋማሽ ነው። ማለትም ይህ ወቅት የ30 ዓ.ም. ማለቂያ ነበረ። የ30 ዓ.ም. በዓላት ሁሉ ተከብረው ተጠናቅቀዋል።

ዮሐንስ 5፡1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።

ይህ በቀጣዩ ዓመት በ31 ዓ.ም. ነበር፤ ምክንያቱም በታህሳስ እና በየካቲት መካከል አንዳችም በዓል የለም።

ዮሐንስ ምዕራፍ 5 ውስጥ ኢየሱስ በሲካር ከተማ ካለፈ በኋላ የተከበረው በዓል ፋሲካ ወይም ሌላ በዓል ነው። ሌላ በዓል ከሆነ ከዚህ በዓል በፊት ፋሲካ ተከብሮ ነበር ማለት ነው። ፋሲካ ሁልጊዜ መጀመሪያ ነው የሚከበረው። ስለዚህ በዚያ ዓመት ውስጥ ፋሲካ መከበሩን እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

ስለዚህ ከላይ የተጠቀሰው (ዮሐንስ 5፡1) የ31 ዓ.ም. ፋሲካ በዓል ነው አለዚያም በ31 ዓ.ም. ውስጥ ፋሲካን ተከትሎ የተከበረ ሌላ በዓል ነው። ያም ሆነ ይህ በ31 ዓ.ም. ውስጥ የፋሲካ በዓል ነበረ ማለት ነው።

አሁን ቀጣዩን የፋሲካ በዓል መከበር እናያለን፤ እርሱም በ32 ዓ.ም. ነበር። በአንድ ዓመት ውስት አንድ ፋሲካ ብቻ ነው የሚከበረው።

ዮሐንስ 6፡4 የአይሁድበዓልምፋሲካቀርቦነበር።

ከዚያ በኋላ በኢየሱስ አገልግሎት ውስት ከተከበሩት ፋሲካዎች የመጨረሻውን ፋሲካ በ33 ዓም. እናገኘዋለን።

ዮሐንስ 11፡55 የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

 

30 AD 31 AD 32 AD 33 AD
30 ዓ.ም. 31 ዓ.ም. 32 ዓ.ም. 33 ዓ.ም.

 

እያንዳንዱ ፋሲካ ከሌላው ፋሲካ በአንድ ዓመት ይራራቃል። ስለዚህ በአራቱ ፋሲካዎች መካከል የሦስት ዓመት ሦስት ክፍተቶች አሉ።
ስለዚህ ኢየሱስ ቢያንስ ለሦስት ዓመታት አገልግሏል።

ከዚያም ደግሞ ከተተመቀ በኋላ ለ40 ቀናት ተፈትኗል፤ ከትንሳኤው በኋላ ደግሞ ለተለያዩ ሰዎች ለ40 ቀናት ተገልጧል። እነዚህ 80 ቀናት ደግሞ ወደ ሦስት ወራት ይጠጋሉ።

ከ30 ዓ.ም. የመጀመሪያው ፋሲካ በፊት የሚመጡት ጥር፣ የካቲት እና የመጋቢት ግማሽ ተጨማሪ ሁለት ወር ከግማሽ ጊዜ ይሰጡታል። ይህንንም ስንደምረው 3 + 21/2 = 51/2 ወራት እናገኛለን።

የአገልግሎት ዘመኑ ሦስት ዓመት ተኩል እንዲሆን የሚያስፈልገው በ29 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የግማሽ ወር ጊዜ ብቻ ነው።
ስለዚህ የኢየሱስ የአገልግሎት ዘመን የመጨረሻው ሳምንት የመጀመሪያ አጋማሽ ነው።

 

የሳምንቱ የመጨረሻ ግማሽ

የመጨረሻዎቹ 7 ዓመታት ውስጥ ያሉት 31/2 ዓመታት፡- አይሁድ መሢሃቸውን አንቀበልም በማለታቸው በቀራንዮ መስቀል ላይ ተቆረጡ። ነገር ግን 31/2 ዓመታት ይቀራቸዋል።

 

የአይሁድ ሊቀ ካህን ሰማያዊ ቀለም ያለው የካህን ልብስ ይለብሳል፤ ቀሚሱም ካህኑ አንገቱን የሚያስገባበት ጠንከር ተደርጎ የተሰፋ የአንገትጌ አለው።
አሮን የመጀመሪያው ሊቀ ካህን ነበረ።

 

ዘጸአት 28፡30 በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁል ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።

31 የኤፉዱንም ቀሚስ ሁሉ ሰማያዊ አድርገው።
32 ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።

ጥሩር በአንገት እና በወገብ መካከል የሚለበስ የብረት ልብስ ነው።

ሊቀ ካህኑ ቀያፋ በኢየሱስ ላይ ሞት ፈረደበት እና የራሱን ልብስ ቀደደ።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦

ሊቀ ካህኑ ልብሱን በመቅደዱ ሕጉን ተላለፈ፤ እግዚአብሔርም የመቅደሱን መጋረጃ በመቅደድ ምላሽ ሰጠ።

ማቴዎስ 27፡51 እነሆም፥የቤተመቅደስመጋረጃከላይእስከታችከሁለትተቀደደ፥

በዚህ ጊዜ ከሳምንቱ ወይም ከሰባቱ ዓመታት አጋማሽ ላይ የአይሁድ ሕግ ተሻረ።

የእንስሳት መስዋእቶችም አስፈላጊነታቸውን አጡ። ከዚያ በኋላ ትርጉም የላቸውም። ማቅረባቸውን ቢቀጥሉም እንኳ ባዶ የማስመሰል ሥራ ብቻ ነው።

ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃልኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስመቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።

 

“በርኵሰትምጫፍላይአጥፊውይመጣል ፤ እስከተቈረጠውምፍጻሜድረስመቅሠፍትበአጥፊውላይይፈስሳል” ፤ መቅደሱ ከዚያ ወዲያ ትርጉሙን አጥቷል። ከዚያ ወዲያ መዳን በክርስቶስ መስቀል አማካኝነት ብቻ ሆኗል።

 

ስለዚህ ክርስቶስን የሰቀሉት ሮማውያን በ70 ዓ.ም. ደግሞ ኢየሩሳሌምን እና መቅደሱን አፈረሱ። በዚህ ጊዜ ደግሞ መስዋዕት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ማስመሰልም እንኳ ቀረ።መቅደሱ የነበረበት ቦታ ፈጽሞ ባድማ ሆነ።አንድም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አልቀረም።

 

በ135 ዓ.ም. ሮማዊው ንጉስ በባር ኮችባ ቀስቃሽነት የተነሳውን የአይሁድ ሕዝብ አመጽ በኃይል ጸጥ አሰኘ፤ የኢየሩሳሌምን ከተማ በድጋሚ አወደመ፤ አይሁድን በሙሉ ከኢየሩሳሌም አባረረ፤ ከዚያም በመቅደሱ ውስጥ ትራጃን የሚመለክበትን የአሕዛብ መቅደስ ለጁፒተር በማቆም እና ከመቅደሱ በር ፊት ለፊት በፈረስ ላይ የተቀመጠ የራሱን ሃውልት በማቆም የመጨረሻውን እርኩሰት ፈጸመ።

በ325 ዓ.ም. ሮማዊው ንጉስ ኮንስታንቲን ቤተክርስቲያንን በተቆጣጠረ ጊዜ የጁፒተርን መቅደስ አፍርሶ በመቅደሱ ተራራ ላይ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አቆመ። ይህም የእርኩሰት እና መጽሐፍ ቅዱስን የማታመም ሥራ እየተስፋፋ ሄዶ የመጽሐፍ ቅዱስን እምነት በየዘመናቱ ከንቱ ማድረጉን ቀጠለ። አሰራሩም መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ሳይሆን ቤተክርስቲያን የምትለውን እመኑ የሚል ነው።

በ700 ዓ.ም. ሙስሊሞች በመቅደሱ ተራራ ላይ ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለውን መስጊዳቸውን ሰሩ። መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃረን ብለው ቁርዓናቸውን ሲያስተምሩ በመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ላይ የሚደርሰው ጥፋት ይቀጥላል።

“በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።” ዶም ኦቭ ዘሮክ የተባለው መስጊድ እስከዛሬ ደረስ ለ1300 ዓመታት እዚያው ቆሟል። ይህም ጥፋት ዓለም ወደ ታላቁ መከራ ስትገባ እስከመጨረሻው ድረስ ይቆያል።

“እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል”። አይሁድ በጥፋት ውስጥ ቆይተዋል። በሃሪዳን አማካኝነት ከኢየሩሳሌም ተፈናቅለዋል። ለብዙ ዘመናት ያለማቋረጥ በብዙ ሃገሮች ውስጥ ተሰድደዋል፤ ከብዙ ሃገሮች ውስጥ ተባረዋል፤ ለጤና አስጊ በሆኑ የቆሻሻ መጣያ መንደሮች ውስጥ ኖረዋል፤ በብዙ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች ውስጥ በብዛት ተገድለዋል፤ “በክርስቲያን” የመስቀል ዘማቾች ተደፍረዋል ተዘርፈውማል። ሮማዊው ጀነራል ታይተስ በ76 ዓ.ም. ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ 1.1 ሚሊዮን አይሁድ ተገድለዋል። ሂትለር ባዘጋጀው ዘመናዊ የመግደያ ካምፖች ውስጥ 6 ሚሊዮን አይሁድ ተጨፍጭፈዋል።

እንደምንም ብለው በ1948 ዓ.ም. ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲመለሱ አራት ታላላቅ ጦርነቶችን ተዋግተዋል፤ እጅግ ብዙ ውስጣዊ እና ውጫዊ የሽብር ጥቃቶችን ተጋፍጠዋል። ሁል ጊዜ የአረብ እና የፍልስጥኤም የጥላቻ ኢላማ ናቸው።

ይህ ሁሉ ግፍ እንዲወርድባቸው እግዚአብሔር አስቀድሞ ወስኗል። ነገር ግን እግዚአብሔር የወሰነውን ያህል ብቻ ነው የሚደርስባቸው። ከዚያ በላይ በፍጹም አይደርስባቸውም። ስለዚህ የአይሁድ ዘር ከምድር አይጠፋም። በስተመጨረሻ ይህ ሁሉ መከራ እና ስደት እየገፋ ወደ መሢሃቸው ይመልሳቸዋል።

ታላቁ ሚስጥር መሢሁ ወደ አይሁድ በመጣበት በመጀመሪያው ምጻቱ መከራን መቀበሉ ነው። ከዚያም አይሁድ አንቀበልህም ይሉታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእሥራኤል ዘመን ይቆማል።

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በታላቁ መከራ ዘመን ወደ አይሁድ ይመለሳል።

ቆሞ የነበረውም ዘመን በመጨረሻዎቹ ሦስት ከግማሽ ዓመታት ይቀጥላል።

ራዕይ 11፡1 በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።
2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

42 ወራት ማለት 31/2 ዓመታት ነው።

ራዕይ 11፡3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።

1260 ቀናት ማለት እያንዳንዳቸው 360 ቀናት የሚረዝሙ 31/2 ዓመታት ነው።

 

ሁለት ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ወደ እሥራኤል ተመልሰው ይመጡና 144000 አይሁዳውያንን ወደ መሢሁ ወደ ክርስቶስ ይመልሱዋቸዋል።
ከዚያም 70ው ሱባኤ (ሳምንታት) ይጠናቀቃሉ።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23