የጉልላት ድንጋዩ ገና አልመጣም
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ብዙዎች ተሳስተው የ1963ቱ ደመና የራስ ድንጋዩ መምጣት ነው ይላሉ፤ ይህም የኢየሱስ ዳግም ምጻት ነው ይላሉ።
First published on the 17th of April 2022 — Last updated on the 17th of April 2022
የጉልላት ድንጋዩ ገና አልመጣም።
ከላይ ባለው ፎቶ ውስጥ የሚታየው ትልቁ የጊዛ ፒራሚድ በጥንታዊነቱ፣ በትልቅነቱ፣ እንዲሁም በአሰራሩ ረቂቅነት የተነሳ ሰዎች ለብዙ ሺ ዓመታት አስደንቋል። ከምድር በላይ እልፍኞች ያሉት ፒራሚድ እንደመሆኑ ከፒራሚዶች ሁሉ የተለየ ፒራሚድ ነው። ከነዚህ እልፍኞች መካከል የንጉስ እልፍኝ የተባለው እልፍኝ (ከዚህ በታች ያለው ምስል ውስጥ በቀይ ቀለም ምልክት የተደረገበት) ውስጡ ባዶ የእሬሳ ሳጥን አለው። ይህ ከሙታን የመነሳት ምልክት ነው። ይህ ግልጽ የሆነ የክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻት ተምሳሌት ነው።
ሌላው ነገር ደግሞ ይህ ታላቅ ፒራሚድ አናቱ ላይ የጉልላት ድንጋይ የለውም። አናቱ ሰፊ ጠፍጣፋ ወለል ነው። ስለዚህ ፒራሚዱ የጉልላት ድንጋዩ እስኪመጣለት ድረስ በትዕግስት እየተጠባበቀ ይመስላል። ጉልላት የሌለው ፒራሚድ ተሰርቶ ያላለቀ መሆኑ ያስታውቃል። ይህ ፒራሚድ ዋነኛ ተምሳሌትነቱ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ያለፉ ቅዱሳንን ታሪክ መወከሉ ነው። ከአናቱ ላይ የጎደለው ጉልላት የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱ በኋላ ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ዳግም ምጻት እንደምትጠባበቅ የሚያሳይ ምሳሌ ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች በሙሉ የኖሩት ወይም የሚኖሩት በክርስቶስ የመጀመሪያና እና በዳግም ምጻት መካከል እንደመሆኑ መጠን ፒዳሚዱ 2,000 ዓመታት የፈጀውን የሰባቱን የቤተክስቲያን ዘመናት ታሪክ ይወክላል።
ፒዳሚዱ በድንጋይ ላይ ተቀርጾ የተጻፈውን ወንጌል ይወክላል።
ወንድም ብራንሐም በሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ ከሰበካቸው ስብከቶች መካከል ኖቬምበር 1965 ካቀረበው መልእክት የተወሰደ ጥቅስ ተመልከቱ። ይህ መልእክት የቀረበው ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ነው።
1965-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛ ስፍራ
አንድ ቀን የጉልላቱ ድንጋይ ተመልሶ ይመጣል፤ እርሱም የሁሉ ራስ ሲሆን የሚመጣው ሙሽራይቱን ሊወስዳት ነው፤ እርሷም የእርሱ አካሉ ናት።
ስለዚህ እስከ ነቬምበር 1965 ድረስ ወንድም ብራንሐም የጉልላቱን ድንጋይ መምጣት ማለትም የጌታን ዳግም ምጻት ይጠባበቅ ነበር።
1965-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛ ስፍራ
ሉተራኖች በእምነት የመጽደቅን ትምሕርት ማለትም እግሮች፤ ዌስሊ ደግሞ የቅድስናን ትምሕርት ይዞ ተነሳ። ፔንቲኮስታሎች ከክንድ በታች ስራንና ትጋትን ይዘው ተነሱ ወዘተ፤ ሌሎችም ካልቪኒስቶች፣ ወይም አርሚኒያኖች ወይም ሕግን መጠበቅ አለብን የሚሉ ናቸው። አሁን ግን ራስ ወደ ሆነው ወደ ጉልላቱ ድንጋይ ደርሰናል። የጉልላቱ ድንጋይ ድምጹን ከፍ አድርጎ “ጸጋ! ጸጋ!” ይላል።
የሁሉ ራስ የሆነው ድንጋይ ምን ይላል? “ጸጋ! ጸጋ!” ከሞት እና ከሐይማኖት አቋም መግለጫ ወደ ሕያው ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቃል ተሸጋግረናል።
ወደፊት የሚፈጸመው ይህ የጉልላቱ ድንጋይ መምጣ በጸጋ የታጀበ ነው የሚሆነው። ታድያ ምሕረት እንዴት በ1963 ሊያበቃ ይችላል?
ዘካርያስ 4፡7 ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።
9 የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
መሰረቱንም መደምደሚያውንም የሚሰራው አንድ ሰው ነው።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናትም ውስጥም ጀማሪውና ደምዳሚው አንድ ነው።
የመጀመሪያው ዘመን ሐዋርያዊ መሰረትን ጥሏል፤ በዚህም ዘመን ውስጥ እውነተኛው የቃሉ ዘር ተዘርቷል። የመጨረሻው ዘመን እምነት ከመጀመሪያው ዘመን እምነት ጋር አንድ መሆን አለበት። ከአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ጋር ስንስማማ እነርሱ መደምደሚያውን ያደርጋሉ።
መከር የሚሰበሰበው ኋላ የሚታጨደው ዘር መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ሲሆን ነው።
በዘመን ፍጻሜ ብዙ አማኞች አይገኙም። የሚያምኑ ሰዎች በጣም ጥቂት ነው የሚሆኑት። እነዚህን ሰዎች ቤተክርስቲያን ትገፋቸዋለች።
ዘካርያስ 4፡10 የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፤ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
በዘመን ፍጻሜ ላይ የሚገኙ በቁጥር ጥቂት የሆኑ አማኞች ከመጀመሪያው ዘመን ክርስቲያኖች ጋር አንድ ዓይነት በመሆን ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መረዳት ይችላሉ። በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ምን እንደተከናወነ መረዳት የሚችሉበት መንፈሳዊ ዓይን አላቸው።
63-1229 መብራቱን ሊያበራልን የሚችል ሰው እዚህ አለ
ተመልከቱ፤ ወደ ፊት በተራመደ ቁጥር እየበረታ ሄደ። ልክ እንደዚሁ በቁጥር ታናሽ የነበረችዋ እውነተኛ ቤተክርስቲያን በጽድቅ ትምሕርት ጀምራ ወደ ቅድስና፣ ወደ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እያደገች ሄዳ አሁን ደግሞ ቅርጹን እየያዘ ወዳለው ወደ ጉልላቱ ድንጋይ ደርሳለች። ከዚህ በኋላ ድርጅቶች አይኖሩም። ከዚህ በኋላ ድርጅት አይኖርም። አያችሁ፤ ድርጅት ሊኖር አይችልም።
እስከ 1963 ሁሉ ወንድም ብራንሐም ሊመጣ ስላለው የጉልላት ድንጋይ ይናገር ነበር።
ነገር ግን ግራ መጋባት ሊፈጠር ይችላል ምክንያቱም ሁለት የጉልላት ድንጋዮች አሉ።
1. ክርስቶስ በዳግም ምጻቱ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ሊደመድም እንደ ታላቅ የጉልላት ድንጋይ ሆኖ ይመጣል።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት አንድነት እንደ ታላቅ ፒራሚድ ይሆናሉ፤ የፒራሚዱ ጉልላትም የክርስቶስ ዳግም ምጻት ነው።
2. ከዚያም መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ሰው ለእግዚአብሔር መንግስት ሊለየው በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት በላዩ ላይ ሲመጣበት እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ መደምደሚያ ጉልላት ይኖረዋል።
ራዕይ 1፡4 ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ራዕይ 1፡20 በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
ኤፌሶን 2፡6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
ጳውሎስ ወደፊት የሚመጡ ሌሎች ዘመናት መኖራቸውን ተናግሯል። ሰባቱ ቤተክርስቲያኖች በዚያ ዘመን የነበሩ ሰባት አጥቢያዎች ሲሆኑ እያንዳንዳቸው ወደፊት ቤተክርስቲያን የምታልፍባቸውን ዘመናት ባህርይ ያንጸባርቁ ነበር። ለምሳሌ ስድስተኛዋ የፊልደልፊያ (ማለትም የወንድማማች መዋደድ) ቤተክርስቲያን የተከፈተ በር ተሰጥቷታል፤ ይህም ዓለም አቀፉን የወንጌል ስርጭት ዘመን የሚወክል ተምሳሌት ነው። ያ ዘመን የጆን ዌስሊ ትምሕርቶችን ተከትሎ ነው የመጣው፤ ጆን ዌስሊ ቅድስና እና የወንጌል ስርጭት ላይ ትኩረት በማድረጉ የተነሳ በሩቅ ሃገር ለነበሩ አሕዛብ ሁሉ የመዳን በር ተከፈተ።
በየትኛውም ዘመን በየትኛውም ስፍራ እያንዳንዱ አማኝ በተገኘበት ሁሉ የእግዚአብሔር ታላቅ መንፈሳዊ ቤተክርስቲያን አካል ነው።
ዳግመኛ መወለድ አማኙን የአንድ ታላቅ “ፒራሚድ” አካል ያደርገዋል፤ ይህም ፒራሚድ ስፍራ እና ዘመን ሳይገድበው እግዚአብሔር በመሰረታት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕያው ድንጋይ ሆኖ እየተጨመረ ለ2,000 ዓመታት “መንፈሳዊ ቤት” ለመሆን እየተሰራ ይገኛል።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡4 በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥
5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
ቀጣዩ ጠቃሚ ማስታወሻ ከታሪክ የተወሰደ ነው፡- ዴቪድ ሊቪንግሰተን (ይህ ስም ሕያው ድንጋይ የሚል ትርጉም አለው) አፍሪካውያንን ለእግዚአብሔር መንግስት ወደ “ሕያው ድንጋይነት” ሊለውጥ ወንጌልን ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ያደረሰ ታላቅ ሰባኪ ነበር።
እያንዳንዱ ግለሰብ እንዴት ነው ሕያው ድንጋይ የሚሆነው?
የእምነት መሰረት ያስፈልገናል።
ማቴዎስ 17፡20 ኢየሱስም፦ ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፦ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።
ዕብራውያን 11፡6 ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ቀጥለንም በእምነት ላይ ሰባት አስፈላጊ ባህርያት መጨመር አለብን።
2ኛ ጴጥሮስ 1፡5 ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥
6 በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥
7 እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።
ለአንድ ፍጹም ሰው ሙሉ ቁመና የሚሰጡት እነዚህ ባህርያት በእያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መታተም አለባቸው።
2ኛ ቆሮንቶስ 1፡22 ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።
ኤፌሶን 1፡13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
65-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛ ስፍራ
ጸጋን ጨምሩ፣ ይህን ጨምሩ፣ ይህን ጨምሩ እያለ ሰባት ጊዜ ጨምሩ ይላል፤ መደምደሚያውም ክርስቶስ ነው።
በእምነታችን መሰረት ላይ ሰባት ነገሮች መጨመር አለብን።
1962 1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ዘመን ያበቃል። ዘመን እንደሚያበቃ አውጇል። ከዚያ ምን ይሆናል? ምን ይሆናል? ወንድሞች ሆይ፣ ይህ አሁን ይሆን? በቁም ነገር አስቡበት። ከሆነ እንግዲያውስ ፒራሚዱ በሰባቱ ነጎድጓዶች ነው የሚደመደመው።
(ለማለት የተፈለገው፡ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የተገነባው ፒራሚድ ጉልላቱ የሚደመደመው በዳግም ምጻት ነው። ምንነታቸው ሚስጥር የሆነው ሰባቱ ነጎድጓዶች ናቸው የጌታን ምጻት ሚስጥረ የያዙት)
የፒራሚዱን መልእክት ታስታውሱታላችሁ? እርሱ መደምደሚያው ጉልላት ነው። ምን አደረገ? መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ግለሰብ መደምደሚያ አድርጎለት በእምነታችን ላይ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰልን፣ የወንድማማች መዋደድና የመሳሰሉትን ስንጨምርበት ያትመዋል።
ሰባተኛው ላይ እስክንደርስ ድረስ መጨመራችንን ቀጥለናል፤ ሰባተኛውም ፍቅር ነው፤ ፍቅር ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
(ማለት የተፈለገው፡ በእምነት መሰረት ላይ የተጨመረው ሰባተኛው ባህርይ ፍቅር ነው)
አንድን ግለሰብ እንዲህ አድርጎ ነው የሚሰራው። ሙሉ ያደርገውና በመንፈስ ቅዱስ ያትመዋል።
(ማለትም፡ አንድን ግለሰብ በእግዚአብሔር ሕይወት አማካኝነት ሙሉ የሚያደርገው መደምደሚያ)
ይህም እውነት ከሆነ ሰባት ሚስጥራትን ገልጧል፤ እንዲሁም ሰባት የቤተከርስቲያን ዘመናትን አሳልፏል፤ እነርሱም ይህንን ሚስጥር መልሰው ለማምጣት ሕይወታቸውን ሳይቀር መስዋእት አድርገዋል፤ የጉልላቱ ድንጋይም ቤተክርስቲያንን ሙሉ ሊያደርጋት ይመጣል።
(ማለትም፡ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ቤተክርስቲያንን ፍጹም ሊያደርጋት የሚመጣው የጉልላት ድንጋይ የጌታ ምጻት ነው)
ወንድሞቼ ሆይ፤ የነጎድጓዶቹ ትርጉም ይህ ነውን? ወገኖች እየተነጋገርን ያለነው ይህ ነውን?
62-1104 ሹመት
ዛሬ ጠዋት የተማርነውን ታስታውሳላችሁ? የመደምደሚያው ጉልላት ከመምጣቱ በፊት እነዚህ መልካም ባህርያት ቦታ ቦታቸውን መያዝ አለባቸው። ልትጮሁ ትችላላችሁ፤ ልትዘምሩ ትችላላችሁ፤ በልሳን ልትናገሩ ትችላላችሁ፤ ልትደንሱም ትችላላችሁ -- እነዚህ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አስፈላጊ ተብለው የተጠቀሱ ባህርያት ተሟልተው በናንተ ውስጥ እስኪታተሙ ድረስ ምንም ለውጥ አታመጡም … መንፈስ ቅዱስ በየግላችሁ ያትማችኋል። የዚያን ጊዜ እያንዳንዳችሁ ለእግዚአብሔር ወንድ ልጅ እና ሴት ልጅ ትሆናላችሁ።
(ማለትም፡ የአንድን ግለሰብ ሕይወት ለይቶ ለእግዚአብሔር የሚያትመው የመደምደሚያው ጉልላት መንፈስ ቅዱስ ነው።)
መንፈስ ቅዱስ የሚያትማችሁ በግላችሁ ነው፤ እንጂ እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አባል አይደለም።
62-1104 የስድብ ስሞች
እንግዲህ ተመልከቱ፤ እምነት፤ እነዚህ አምስት የውሃ ምንጮች … አንድ ትንሽ ቾክ ይዤ ነበር ነገር ግን እርሱ ያወጣው አይመስለኝም። ወደዚህ ስትመጡ የምታዩዋቸው አምስቱ ምንጮች ግን ይህንን ሁሉ ግልጽ ያደርጉታል። የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን የመሰረታት መንፈስ ቅዱስ ነው። የሰምርኔስን ቤተክርስቲያን የወለዳት መንፈስ ቅዱስ ነው። በጨለማው ዘመን ውስጥ የጴርጋሞንን ቤተክርስቲያን እንደሂሁም የትያጥሮንን ቤተክርስቲያን የጠራቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። በቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ውስጥ ከድርጅቶች ውስጥ የተመረጡትን ሰዎች እያወጣ ቤተክርስቲያንን የመሰረታት መንፈስ ቅዱስ ነው። የተመረጠችና አስቀድማ የተወሰነች የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ አለች፤ መንፈስ ቅዱስም እነዚህን ሰዎች የተመረጡና ተጠርተው የወጡ ይላቸወል። በዚህም ዘመን በዚያም ዘመን፣ በዚያኛውም ዘመን፣ በዚያኛውም ዘመን፣ በዚያኛውም ዘመን፣ በዘመናት ሁሉ የነበረውና ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው።
(ማለትም፡ ፍጹም ሙሉ ለመሆን የመደምደሚያ ጉልላት የሚያስፈልገው የሰባቱ የቤተክስቲያን ዘመናት ፒራሚድ)
ስለዚህ አሁን በግለሰቦች ሕይወት ውስጥ እንደሚሆነው እነዚህ መልካም ባህርያት (እውቀትና ራስን መግዛት) -- በእምነታችን ላይ ይጨመራሉ፤ ከዚያም የመደምደሚያው ጉልላት ሲመጣ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ያጣብቀዋል፤ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት ይህ ነው፤ በዚህ ዘመን አጭር የሆነበት ምክንያትም ይህ ነው።
(ማለትም፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተዘጋጀለት የመደምደሚያ ጉልላት አለው፤ ይህም መንፈስ ቅዱስ በእመነት ላይ መጨመር ያለባቸውን ባህርያት በግለሰቡ ሕይወት ውስጥ ሲያትማቸው ነው የሚፈጸመው። እያንዳንዱ ሰው መጀመሪያ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካክላል። ከዚያም በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ እያንዳንዱ ግለሰብ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት መደምደሚያ ጉልላቱን ካገኘ በኋላ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዳግም ምጻጽ አማካኝነት የቤተክርስቲያንን ታሪክ በሙሉ በመደምደሚያ ጉልላት ያትመዋል)።
62-1104 የስድብ ስሞች
መጀመሪያ መሰረቱ እምነት ነው። ሁለተኛ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤ በበጎነት ላይ እውቀት፤ በእውቀት ላይ ራስን መግዛት፤ ራስን በመግዛት ትዕግስት፤ በትዕግስት ላይ ደግሞ እግዚአብሔርን መምሰል ጨምሩ፤ እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ደግሞ የወንድማማች መዋደድ፤ በወንድማማች መዋደድ ላይ ደግሞ ደግነትን ጨምሩ፤ ከዚያ በኋላ መደምደሚያው ፍቅር ነው፤ እነዚህ ሰባቱ ባህርያት ያስፈልጋሉ።
(ማለትም፡ እምነት መሰረት ነው። በእምነት ላይ ሰባት ባህርያት ይጨመራሉ፤ ሰባተኛውም ፍቅር ሲሆን በተጨመረ ጊዜ የአማኙ መደምደሚያ ጉልላት ይሆናል)
ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት (አያችሁ?)፤ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ዘመናትን የሚወክሉ ሰባት ከዋክብት፤ ይህ ሁሉ በአንድነት በመንፈስ ቅዱስ ተጠቅሏል።
እንግዲህ የክርስቶስ አገልጋይ ለመሆን የሚያስፈልገው ይህ ነው። ክርስቶስ ሙሽራይቱን በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ነው የሚያዘጋጃት፤ እርሷም በሴት የምትመሰለዋ እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ናት። ሙሽራይቱ የምትሰራው በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ነው። የሙሽራይቱ አካላት አንዳንዶቹ ከዚህኛው ዘመን፣ ሌሎቹ ከዚያኛው ዘመን፣ ሌሎቹም ከዚያኛው ዘመን ተውጣጥተው በአንድነት እንደ ፒራሚድ ያድጋሉ።
(ማለትም፡ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በአንድነት ታላቅ ፒራሚድ ይሆናሉ፤ ከዚያም መደምደሚያ ጉልላት ያስፈልጋቸዋል፤ እርሱም ዳግም ምጻት ነው)
65-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ ያዘጋጀው ብቸኛ ስፍራ
የፒራሚዱ መሰረት … እስከ ንጉሱ እልፍኝ ድረስ ይደርሳል። ልክ ሰባተኛውን ግድግዳ ከመንካታችሁ በፊት ቆም ብላችሁ የምትጠብቁበት የጣውላ ወለል አለ፤ እዚያም በቆማችሁበት መልእክተኛ ይመጣና ወደ ንጉሱ ፊት ያቀርባችኋል። (ይህም ከንጉሱ ጋር ያስተዋወቀን መልእክተኛ መጥምቁ ዮሐንስ ነው)፤ የማዕዘን ራስ የሆነውን ድንጋይ ግን ናቁት። ነገር ግን የማዕዘኑን ራስ አያውቁትም፤ ስለዚህ አሁን የት እንዳለም አያውቁም ምክንያቱም ንቀው የተዉት ድንጋይ ነው። ነገር ግን ይህ ድንጋይ እራሱ ነው ራስ በመሆን ሁሉን የሚገዛውና በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የተገነባውን ፒራሚድ ሙሉ የሚያደርገው።
(ማለትም፡ የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ታላቅ ፒራሚድ)
ጸጋን ጨምሩ፣ ይህን ጨምሩ፣ ይህን ጨምሩ፣ ሰባት ጊዜ ጨምሩ ይላል፤ የመጨረሻው ክርስቶስ ነው። በፍቅራችሁ ላይ ይህንን ጨምሩ፤ በጸጋችሁ ላይ ጸጋ ጨምሩ፤ ሌላም ነገር ጨምሩ፤ ሌላም ነገር ጨምሩ፤ የማዕዘን ራስ የሆነው ክርስቶስ ዘንድ እስኪደርስ ድረስ፤ እርሱም “በሩ እኔ ነኝ” ብሏል።
(ማለትም፡ ሰባት ጊዜ ጨምሩ ተብሏል … እምነት ላይ ሰባት ባህርያት ይጨመራሉ። የመጨረሻው ፍቅር ነው። ስለዚህ በአጠቃላይ ስምንት ባህርያት አሉ። እነዚህ ባህርያት ተደምረው ነው ሰውን ፍጹም ሙሉ ሰው የሚያደርጉት። ከዚያ በኋላ የአማኙ ሕይወት መደምደሚያ ጉልላት የሚሆነው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ክርስቶስ እራሱ ነው። የግል ፒራሚድህ ውስጥ ያሉ መልካም ባህርያት መደምደሚያ ሲያገኙ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲገነባ በቆየው ታላቅ ፒራሚድ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ሆነህ ትገባለህ)
62-1014 የፍጹም ሰው ቁመና
ይህን ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? እሺ እኔ ልንገራችሁ፤ በደምብ አድምጡኝ። አያችሁ? የሰንሰለት ጥንካሬ የሚለካው ደካማዋ ማያያዣ ባለችበት ቀለበት ቦታ ነው። እውነት አይደል? ከዚያች ደካማ ቀለበት በላይ ሊበረታ አይችልም። ሰንሰለቱ ምንም ያህል ጠንካራ ተደርጎ ቢሰራ በመሃሉ ደካማ ቀለበት ካለው እዚያ ቦታ ላይ ነው ሰንሰለቱ የሚበጠሰው። ስለዚህ ሰንሰለቱ ከደካማዋ ቀለበት በላይ ሊበረታ አይችልም።
አለኝ የምትሉት ነገር ካላችሁ … ይህ አለኝ፣ ይህ አለኝ፣ ይህ አለን ትላላችሁ፤ ነገር ግን ይህ ደግሞ የላችሁም፤ ይህም የላችሁም፤ ልባችሁም በዚህ ያዝናል። ይህ ቢኖራችሁና ያ ደግሞ ባይኖራችሁ ቅር ይላችኋል። ይህ አለኝ፤ ያ ግን የለኝም፤ ይህ አለኝ፤ ያ ግን የለኝም። በዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ስንኖር ነው ቅስማችን የሚሰበረው። አያችሁ? እናንተም ደግሞ ይህን አግኝታችሁ ያኛው ካልተሟላላችሁ ደስተኛ አትሆኑም። ስለዚህ ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ስትሰጡ መንፈስ ቅዱስ መልካሞቹን ባህርያት በሙሉ ይዞ መጥቶ በእናንተ ውስጥ ይሞላል። በዚያ ጊዜ ሕያው ድንኳን ትሆናላችሁ።
የዚያን ጊዜ ሰዎች ዓይናቸውን አንስተው ያዩና እንዲህ ይላሉ፡- “ይህ ሰው በበጎነት፣ በእውቀት የተሞላ፣ ቃሉን የሚያምን፣ ራሱን የሚገዛ፣ ትዕግዝትና መልካምነት፣ ደግነትና የወንድማማች መዋደድ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር ተሞልቶ የሚመላለስ ሰው ነው። እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? የማያምኑ ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ይህንን ዓይነት ሰው ተመልክተው፡- ይህስ ክርስቲያን ነው ይላሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች የሚናገሩትን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች ናቸው። ከነዚህ ዓይነት ሰዎች የበለጠ በጎ፣ ደግ፣ መልካም ሰው አይታችሁ አታውቁም።”
ታትማችኋል። ማሕተም በሁለቱም በኩል ይታያል። እየሄዳችሁም ይሁን እየተመለሳችሁ ብትሆኑ ማሕተሙን በግልጽ ያዩታል። ልትደበቁ አትችሉም። አያችሁ? አንድ ሰው ወይም አንዲት ሴት ይህን ሁሉ ስታሟላ የመደምደሚያው ጉልላት ድንጋይ ይመጣና ወደ እግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያትማታል፤ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው።
(ማለትም፡ ይህ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ አስገብቷችሁ የሚያትማችሁ የመደምደሚያ ጉልላት መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህም በእግዚአብሔር ታላቅ ፒራሚድ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ያደርጋችኋል፤ ታላቁ የእግዚአብሔር ፒራሚድ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ላለፉት 2,000 ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል)
ከዚያም ቃሉ ሲመጣ በነዚህ ሁሉ ራሱን በድምቀት ይገልጣል (አያችሁ?) ከዚያም ይህንን ሰው ሙሉ በሙሉ የሕያው እግዚአብሔር ማደርያ ድንኳን ያደርጋል፤ ይህም ሰው ፍጹም የሆነ በሰዎች ፊት የተገለጠ የክርስትና ምሳሌ ይሆናል።
61-0806 የዳንኤል ሰባተኛ ሱባኤ
አሁን ሁሉም መልክ ስለያዘ … ይህን በእጄ የያዝኩትን የፒራሚድ ቅርጽ ታያላችሁ? ቅዱሳን በተነሱ ጊዜ ወደ ክብር ይገባሉ። አሁን ገብቷችኋል? ክርስቶስ የማዕዘን ራስ፣ ግምበኞች የናቁት ድንጋይ፣ ሁሉን የሚያየው ዓይን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደተናገረው የሚመጣ … ዳንኤል ደግሞ ይህንን የአሕዛብ ዘመን እንደተመለከተ ይናገራል፤ ያውም የማንም እጅ ሳይነካው ከተራራ ላይ ተፈንቅሎ የመጣው ድንጋይ እስኪመጣ ድረስ። በዚያ ፒራሚድ ላይ የመደምደሚያ ጉልላት አላደረጉበትም። በሰው እጅ የተጠረበ አይደለም። ድንጋዩን የጠረበው የእግዚአብሔር እጅ ነው። አያችሁ? ድንጋዩ ምን አደረገ? ምስሉን እግሩ ላይ መታውና ሰባበረው፤ በምድር ላይ እንደ ዱቄት ፈጭቶ አደቀቀው። ሃሌሉያ። ያ ድንጋይ በሚመጣ ጊዜ ምን ይሆናል? ቤተክርስቲያን በክብር ተነጥቃ ወደ ሰማይ ትሄዳለች፤ ምክንያቱም የድንጋዩ መምጣት የአሕዛብን ዘመን ወደ ፍጻሜ ያደርሰዋል። እግዚአብሔር በድንጋዩ መምጣት የአሕዛብን ዘመን ያጠናቅቀዋል።
የጉልላቱ ድንጋይ ሲመጣ የአሕዛብ ዘመን ያበቃል። የክርስቶስ ተቃዋሚም ለአጭር ዘመን የሆነውንና ብዙ ሰዎችን የሚገድልበትን መንግስት ይጀምራል፤ መንግስቱም ለሶስት ዓመት ከግማሽ ነው የሚዘልቀው።
ሙሽራይቱን በአየር ላይ ሊነጥቃት የሚመጣው የጉልላቱ ድንጋይ በዚያው ዛሬ የምንኖርበትን የዓለም ስርዓት ያጠፋዋል።
የባቢሎናውያን ሚስጥራት ፋርስ፣ ግሪክ፣ እና ሮም ውስጥ በነበሩ በአረማውያን የአሕዛብ መናፍስት አማካኝነት አልፈው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገቡ። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም በአሁኑ የቤተክርስቲያን ዘመን የባቢሎን ሚስጥራት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችንም ጭምር ተቆጣጥረዋል።
ዳንኤል ያየው ድንጋይ የጌታ ዳግም ምጻት ነው። ድንጋዩ ሲመጣ በ64 ዓ.ም ኔሮ በክርስቲያኖች ላይ መራራ ስደት ካስነሳበት ጊዜ ጀምሮ የክርስቶስን ሙሽራ ሲረግጣት የነበረው የአሕዛብ ምስል ይፈጨዋል። ደግሞም ድንጋዩ የሚመጣው እግዚአብሔር ባለፉት 2,000 ዓመታት ውስጥ በአማኞች አማካኝነት ሲሰራ ለነበረው ታላቅ ፒራሚድ የመደምደሚያ ጉልላት ለመሆንም ጭምር ነው። የመደምደሚያው ጉልላት ከሙታን በተነሳችው ቤተክርስቲያን አናት ላይ ቦታውን ከያዘ በኋላ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ ይዟት ይሄዳል (ለዚህ ነው ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ ምድርን የማይረግጠውና ቤተክርስቲያንም ልትቀበለው በአየር ላይ የምትነጠቀው)።
ነገር ግን ይህ ከመፈጸሙ በፊት ሕያው የሆነችዋ ቤተክርስቲያን የማይሞተውን አካሏን መልበስ አለባት።
በ1963 ዓ.ም ሰኔ ወር ውስጥ ዊልያም ብራንሐም ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ፒራሚዱ ላይ የመደምደሚያው ጉልላት ወደፊት እንደሚመጣ ይናገር ነበር (ይህም የኢየሱስ ዳግም ምጻት ነው)። ይህን የተናገረው ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከሶስት ወራት በኋላ ነው።
1963-0608 ኮንፈረንስ
ይህ እሳት አንዴ ከመጣ በኋላ እንቅስቃሴውን ቀጥሏል እንጂ ማንም ሊያስቆመው አልቻለም፤ አሁንም ይቀጥላል። በሉተር በኩል ጀመረ፣ በዌስሊ ቀጠለ፣ እስከ ጴንጤቆስጤ ደረሰ። ታያላችሁ፤ ፒራሚዱ በቅርቡ አንድ ቀን መደምደሚያውን ያገኛል።
ከዶላር ጀርባ ላይ ያለውን የፒራሚድ ምስል አይታችኋል አይደል፤ ጉልላት የለውም። “ታላቁ ማሕተም” ይላል። እኛም አሜሪካ ውስጥ የምንኖር ሰዎች የአሜሪካ ማሕተም በዚህ በኩል መሆኑን አይተናል። ምን ይላል መሰላችሁ፤ “ታላቁ ማሕተም” ይላል፤ ሔኖክ ያደረገው ማሕተም ነውን? አሁን ስለ ፒራሚዶች አስተምሕሮ እየተናገርኩ አይደለሁም ምክንያቱም በእንደዚያ ዓይነት ነገር አላምንም። ለምን? የመደምደሚያውን ድንጋይ ሰዎች ንቀውታል። ነገር ግን አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!
ደግሞም ተመልከቱ፤ እዚያ ፒራሚድ ውስጥ ገብቼ አውቃለሁ። በጣም አስገራሚ በሆነ ጥንታዊ ጥበብ ነው የተሰራው። በድንጋዮቹ መካከል ምንም ዓይነት ሲሚንቶ የለም። ድንጋዮቹ በጥንቃቄ ተጣብቀው ከመሰራታቸው የተነሳ ፒራሚዱ በሙሉ ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተጠረበ ይመስላል።
ቤተክርስቲያንም ልክ እንደዚሁ በክርስቶስ መልክ ፍጹም ሆና የተገነባች ጊዜ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል፤ ሲመጣም የሞቱትን ቅዱሳን በሙሉ ከሙታን ያስነሳና ከራሱ ጋር ይዟቸው ይሄዳል። የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ትነጠቃለች።
የመደምደሚያው ጉልላት መምጣት ትንሳኤን ያስከትላል፤ ከዚያም ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ትነጠቃለች።
የመደምደሚያው ጉልላት መጥቷል የሚሉ ሁሉ፤ ታዲያ እስከ ዛሬ እዚህ ምን ይሰራሉ?
የጌታ ምጻት ሳያዩት አምልጧቸዋል ማለት ነው። ታድያ ለምንድነው ትንሳኤ እስከ ዛሬ ያልሆነው?
ትንሳኤው ተፈጽሟል የሚሉ ከሆኑ ንግግራቸው በሙሉ ጤናማ አይደለም፣ ካንሰር ሞልቶበታል።
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡16 ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ኃጢአተኝነታቸውን ከፊት ይልቅ ይጨምራሉና፥
17 ቃላቸውም እንደ ጭንቁር ይባላል፤ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤
18 እነዚህም፦ ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል እያሉ፥ ስለ እውነት ስተው፥ የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።
ካንሰር (በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ካንከር” ይባላል)፤ ካንሰር ያለ ገደብ የሚያድግ ሴል ሲሆን አድጎ አድጎ ሰውን ይገድላል። ጌታ መጥቷል ብሎ መናገር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ማመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ማመን መንፈሳዊ ካንሰር ነው።
ትንሳኤ ተፈጽሞ አልፏል ብሎ መናገርና ማመን አደገኛ ካንሰር ነው። በሃብት መመካትም ሌላ ካንሰር ነው። የአፕል ኮምፒዩተሮች መስራች እስቲቭ ጆብስ ካምፓኒውን በዓለም ካሉ ድርጅቶች ሁሉ ታላቅ የንግድ ድርጅት አድርጎ መሰረተው። ያን ሁሉ ገንዘብ ማግኘቱ ከእግዚአብሔር ጋር በመልካም ሕብረት ውስጥ ለመሆኑ ዋስትና አልነበረም። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በካንሰር ሞተ።
ያዕቆብ 5፡3 ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጎአል፥ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል። ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል።
ኢዮኤል 1፡4 ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፤ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፤ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።
እነዚህ ፍጥረት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ጠላቶች ይወክላሉ።
ደጎብያ ብዙም የሚታወቅ ፍጥረት አይደለም። ምን እንደሚመስል እንኳ በትክክል የሚያውቅ ሰው የለም። ይህም የእግዚአብሔርን ቃል መበረዝና መሸቃቀጥ ውስጥ ያለውን ሚስጥራዊ አደጋ ያመለክታል፤ ስለዚህ ሰዎች ሳያውቁት ይደርስባቸዋል። እግዚአብሔር እንደተናገረው በመጨረሻው የሎዶቅያውያን ዘመን የምንገኝ አማኞች እውር ነን። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣብቀን አንኖርም ስለዚህ እንደ ሔዋን በመጽሐፍ ቅዱስ ሊረጋገጡ በማይችሉ በሚያባብሉ የጥበብ ቃላት እንታለላለን። ሚስጥራዊቷ ባቢሎን ደጎብያዎቿን በመካከላችን ልካለች። ስለዚህ ማንም ሰው ትንሳኤ ተፈጽሞ አልፏል ቢላችሁ ጠንቀቅ ብላችሁ ስሙት። ከመጽሐፍ ቅዱስ ልታረጋግጡት የማትችሉት ማንኛውም ትምሕርት ሲመጣ ጠንቀቅ በሉ።
ኢዮኤል 2፡25 የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
እውነተኛዋ ሙሽራ ግን ትታደሳለች። ከደጎብያ ነጻ ትሆናለች። ከማንኛውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆነ እምነት ነጻ ትሆናለች። ትንሳኤው አልፏል ከሚሉ ፍልስፍናዎች ነጻ ትሆናለች።
ስለ ካንሰር ማወቅ የሚያስፈልገው ለምንድነው? (በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ካንከር ይባል ነበር።) ምክንያቱም ከዘመናችን ምልክቶች አንዱ ስለሆነ ነው።
60-0518 ልጅነት 2
እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ እየተሰራ ነው ያለው። በመደምደሚያው ላይ ያለው ድንጋይም ተገኝቶ አያውቅም። የፒራሚዱ አናት ላይ መደምደሚያውን ጉልላት አላደረጉም። ታውቁ ወይም አታውቁ እንደሆን አላውቅም። በግብጽ ከሚገኙ ፒራሚዶች ሁሉ ታላቁ ፒራሚድ አናቱ ላይ ጉልላት የለውም። ለምን? የጉልላቱ ድንጋይ (ክርስቶስ የማዕዘን ራስ ድንጋይ) ተንቋል።
ከሉተር ዘመን፣ ከባፕቲስቶች ዘመን፣ ከሜተዲስቶች ዘመን፣ ከፔንቲኮስታሎች ዘመን አልፈን አሁን የመደምደሚያው ጉልላት የሚመጣበት ዘመን ላይ ደርሰናል (አያችሁ?) ያ የመደምደሚያ ጉልላት ድንጋይ እስኪመጣና ቦታው ላይ እስኪያርፍ እየጠበቅን ነን፤ የዛኔ ሕንጻው ይጠናቀቃል። “ድንጋዩ ተንቋል” የሚለውን ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አላነበባችሁም? በእርግጥ ያ ቃል የሚናገረው ስለ ሰሎሞን ቤተመቅደስ መሆኑን እናውቃለን። “ነገር ግን ግምበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ።” ይህንን የምናገረው በአእምሮዋችሁ ውስጥ ምስል ሆኖ እንዲታያችሁ ብዬ ነው።
(ማለትም፡ የግብጽ ታላቅ ፒራሚድ እግዚአብሔር ባለፉት 2,000 ዓመታት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሲገነባ የቆየውን መንፈሳዊ ፒራሚድ የሚወክል ምልክት ነው።)
አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ እየኖርን ነን፤ ይህ ዘመን የፒራሚዱ ጉልላት ዘመን ነው፤ በዞድያክ ውስጥ የካንሰር ዘመን ነው፤ ሊዮ ወይም አንበሳው የሚሰለጥንበት ዘመን ነው፤ ይህ የመደምደሚያው ጉልላት የሚመጣበት ዘመን ነው፤ አሁን የምንኖረው የእግዘአብሔር ልጆች የሚገለጡበት ዘመን ነው። አያችሁ? የት እንዳለን አያችሁ? በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ነን።
ዞዲያክ፣ የካንሰር ዘመን፣ ዓሳ፣ እና ሊዮ ሲል ምን ማለቱ ነው?
ፀሃይ በሰማይ ላይ ስትሄድ እናያታለን። ማታ ደግሞ ፀሃይ ባለፈችበት መስመር ላይ ብዙ ከዋክብት እናያለን። ባቢሎናውያን እነዚህን ከዋክብት በ12 ቡድኖች ከፋፍለዋቸው ሕያዋን ፍጡራንን ይወክላሉ ብለው በምናባቸው ስዕል ፈጠሩባቸው። ዞዲያክ የሚለው ቃል ትርጉሙ “የሕያዋን ፍጥረታት ክበብ ማለት ነው”። ነገር ግን ምንም ያህል ቢራቀቁና ቢፈላሰፉ እንኳ በሚዛን የተወከለው ሊብራ የተባለው የኮከቦች ቡድን በዚህ ምድባቸው ውስጥ ሊገጥምላቸው አልቻለም።
በጣም የሚያሳዝነው ነገር እነዚህን የከዋክብት ቡድኖች የሰዎችን እጣ ፈንታ ለመተንበይ መጠቀማቸው ነው። ይህ ትልቅ ውሸት ነው። በፍጹም በኮከብ ትንበያ እንዳታምኑ። የኮከብ ትንበያ እና የመሳሰሉ ጥንቆላዎች ከእግዚአብሔር አይደሉም። ኤሪስ የተባለው በግ በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ የጸደይ ወቅት ምልክት ሲሆን በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ግን የመጸው ምልክት ነው። ስለዚህ ሁለቱም በአንድ ጊዜ ትክክል ሊሆኑ አይችሉም። ደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ወቅቶቹ ከሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በስድስት ወር ያክል ይለያያል። በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ የበጋ ምልክት የሆነው ሊዮ ለምሳሌ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ የክረምት ምልክት ነው።
በደቂቃዎች ልዩነት ብቻ የተወለዱ መንታ ልጆች ፍጹም የተለያየ ሕይወት ሊኖራቸው ይችላል።
ቻይናውያን የኮከብ ትንበያ ጠንቋዮች ከምዕራባዊ የኮከብ ትንበያ ጠንቋዮች ይለያሉ።
እጣ ፈንታችሁን ለማወቅ የተለያዩ ጠንቋዮችጋ ብትሄዱ ከሁሉም የተለያየ ትንበያ ትሰማላችሁ። መሬት በራሷ ዛቢያ ላይ ስትዞር እንቅስቃሴዋ (ማለትም የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት እኩል የሚሆንበት ወቅት) ትንሽ ስለሚዛነፍ በ2,000 ዓመታት አንድ ጊዜ ፀሃይ ወደ አዲስ የዞዲያክ ምልክት ታልፋለች። ባቢሎን ውስጥ የነበሩ ሰዎች የዛሬ 4,000 ዓመታት አካባቢ ሆሮስኮፕ የሚባል የትንበያ ወይም የጥንቆላ ጥበብ አመጡ፤ ይህም የዞዲያክ ከዋክብትን በመጠቀም የሰዎችን እጣ ፈንታ የሚጠነቁሉበት ነው። ኤሪስ የተባለው የበጉ ምልክት የጸደይ ወቅት ምልክታቸው ነበር። ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ ግን መሬት በዛቢያዋ ላይ አቀማመጧ ትንሽ ተዛንፎ ስለነበረ የጸደይ ምልክት ፓይሲስ የተባሉት ዓሳዎች ነበሩ። ከጥቂት ዓመታት በፊት በ2,000 ዓ.ም ደግሞ መሬት ወደ አኳሪየስ ማለትም ውሃ ተሸካሚዋ ምልክት ውስጥ ስላለፈች የጸደይ ምልክት ፓይሲስ ሆኗል። ስለዚህ አሁን የዞዲያክ ምልክቶች ሁሉ በሁለት ምልክቶች ከነበሩበት ቦታ ተዛንፈዋል። ስለዚህ አስተማማኝ መተንበያ ሊሆኑ አይችሉም።
ውሃ ተሸካሚዋ አኳሪየስ የተባለች ምልክት ውሃ ስታፈስስ ነው ምስሏ የሚያሳየው። ይህም ምክንያት ይኖረዋል።
የዞዲያክ ከዋክብት ዋነኛ ዓላማቸው የኢየሱስን ታሪክ መተረክ ነበር። ከድንግል (ቨርጎ የሚባለው ምልክት) በመወለድ ከመጣበት ከመጀመሪያው ምጻቱ ጀምሮ እንደ ሊዮ አንበሳ ወይም የይሁዳ አንበሳ ሆኖ ዳግም እስከ መምጣቱ ድረስ የዞዲያክ ምልክቶች የኢየሱስን ታሪክ ነው የሚተርኩት። ይህ ከታላቁ ፒራሚድ ጋር አንድ ዓይነት ነው ምክንያቱም ፒራሚዱም የመጀመሪያውነ እና ዳግም ምጻቱን ነው የሚገልጸው። ከፒራሚዱ አጠገብ ስፊንክስ የተባለ ትልቅ የሴተ አንበሳ ሃውልት አለ፤ ምስሉ ጺም ስለሌለው የሴት አንበሳ ምስል ነው። ይህም ዞዲያክ የት እንደሚጀምርና የት እንደሚያበቃ የሚጠቁም ምልክት ነው፤ ከሴቲቱ (ቨርጎ) ይጀምራል ከዚያም በሊዮ (በአንበሳው) ያበቃል።
መዝሙር 19፡1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
2 ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
3 ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
4 ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥
5 እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
6 አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም
ስለዚህ ፀሃይ ክርስቶስን ትወክላለች፤ እርሱ ነው ከእልፍኙ ወጥቶ በመምጣት ሙሽራይቱን የዋጃትና ቀጥሎም እንደ ንጉስ ሆኖ ከመመለሱ በፊት በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ይመራታል፤ ከዚያም የይሁዳ አንበሳ ሙሽራይቱን ለራሱ ይወስዳታል።
ከድንግል (ቨርጎ) ተወልዶ በፍርድ (ሊብራ ሚዛን) ከነፍሰ ገዳዩ ከበርባን ጋር በአይሁዶች ተመዘነ። በሞት እና የዘላለም ሕይወት በሚሰጥ ሰው መካከል አመዛዝነው እንዲፈርዱ እድል ተሰጣቸው። እነርሱም ሞትን መረጡ።
መስቀሉ ላይ በሞተ ጊዜ እስኮርፒዮ በተባለው ምልክት የተወከለው ተናዳፊ ጊንጥ እንደሚነድፈው የሚያሳየው እውነት ተፈጸመ።
ከዚያ በኋላ የጥንቷ ቤተክርስቲያን እንደተመሰረተች የቀስተኛው (ሳጂታሪየስ) ኢላማ ሆነች፤ እርሱም በመጀመሪያው ማሕተም ውስጥ የተገለጠው ነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠውና ሐይማኖታዊ ሽንገላን የሚወክለው ፈረሰኛ ነው። ፈረሰኛው ደጋን አለው ግን ቀስት የለውም። ይህ ሽንገላ ነው። ኤፌሶን ማለት “ላላ” ማለት እንደመሆኑ ክርስቲያኖች ቀስ በቀስ ከተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈቀቅ እያሉ ሄዱ። በዚህ ዓይነቱ ግዴለሽነታቸው መርሆቻቸውን ላላ አደረጉና ፍየሎቹ (ካፕሪኮርን) ገብተው በጎችን እንዲመሩ ፈቀዱ። በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በማይፈቅደው መንገድ አንድ ኢጲስ ቆጶስ በያንዳንዱ ከተማ ብቸኛ የቤተክርስቲያን መሪ እንዲሆን ተደረገ። የሰው ገዥነት ስፍራውን ያዘ፤ በስተመጨረሻም በሂፖ ባለስልጣን እንደሆነው እንደ ኦጋስተን ይህ ልማድ ተቀባይነትን አግኝቶ ቀረ።
ነገር ግን በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ዓይነት አመራር አልነበረም።
ፊልጵስዩስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
በመጀመሪያው የአንድ ከተማ ጳጳሳት ብዙ ነበሩ። ይህንን በፊልጵስዩስ ከተማ ማየት እንችላለን። አዲስ ኪዳን ውስጥ በጳጳስ እና በሽማግሌ መካከል ምንም ልዩነት አልነበረም።
ነገር ግን ፍየሎቹ (ካፕሪኮርን) ከነበራቸው የስልጣን ጥማት የተነሳ የአመራርን ስፍራ ነጥቀው ያዙ። ቤተክርስቲያንም እያደገች ስትሄድ የሚገራርሙ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ የማዕረግ መጠሪያዎች ተፈጠሩ፤ ለምሳሌ ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናል፣ ፖፕ።
እያንዳንዱ ጉባኤ የግድ አንድ ሰው መሪ ሆኖ ይሾምበት ተባለ። ይህም አሰራር በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥጥረ ማድረግን ቀላል አደረገው። መሪውን ብቻ ከተቆጣጠሩት በመሪው ስር ያለው ጉባኤ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር ይወድቃል።
ስለዚህ በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በሰምርኔስ (መራርነትና ሞት) የሮማ ገዥዎች ክርስቲያኖችን በጭካኔ አሳደዱ። ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖች ዓለማዊ ተስፋቸው በሙሉ ስለጠፋ ቤተክርስቲያን ሙሉ ትኩረቷን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማድረግ ችላ ነበር። አራጆች በጎችን ወደ ቄራ ለማስገባት የሚጠቀሙት ፍየሎችን ነው። በጎች እንዲታረዱ ወደ ቄራ እየመራ የሚያስገባቸው ፍየል ይሁዳ ፍየል ይባላል። ፍየሉ ወደ ቄራ መግቢያ በር አጠገብ ባለ ጠባብ ቀዳዳ ሾልኮ ያመልጣል፤ በጎቹ ግን እንደ እውር ሳያዩ ግር ብለው ይገቡና ይታረዳሉ። በ64 እና በ312 ዓ.ም መካከል በተደረጉ አሰቃቂ ስደቶች ውስጥ ሶስት ሚሊዮን ክርስቲያኖች ሞተዋል።
አንዱ እጅግ ክፉ የክርስቲያኖ ገዳይ ንጉስ ኦሬልያን ሲሆን እርሱም በ274 ዓ.ም ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን ነው ብሎ አወጀ። ክርስቲያኖች እስከ ዛሬ ድረስ የፀሃይን አምላክ ልደት በየዓመቱ ያከብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት አስቡ ብሎ አላዘዘንም።
ውሃ ተሸካሚዋ አኳርየስ በነበረችበት በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የቃሉን ውሃ ደፉ (የዚህ ምልክት ምስል አንድ ሰው ከጉድጓዳ የውሃ እቃ ውስጥ ውሃ ሲያፈስስ ያሳያል)፤ በኒቅያ ጉባኤ ቤተክርስቲያን እንደ ስላሴ እና የመሳሰሉ ሰው ሰራሽ የአሕዛብ ትምሕርቶችን ተቀበለች። በተጨማሪ ደግሞ በሮማዊው ገዥ ኮንስታንቲን ስር በመሆን ፖለቲካዊ ስልጣንን ለመጨበጥ ተመኙ። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከአሕዛብ ጋር ለማመቻመች ብለው መጽሐፍ ቅዱስን በመተው የቃሉን ውሃ አፈሰሱ። ሕዝቡ ላይ ለመንገስ እና የሕዝቡን ገንዘብ ለራሳቸው ለመሰብሰብ በነበራቸው ምኞት በፖለቲካ ጭቃ ላይ ተንሸራትተው ወደቁ።
በ350 ዓ.ም አካባቢ የሮማ ጳጳስ ዲሴምበር 25ን የእግዚአብሔር ልጅ የልደት ቀን ነው ብሎ ተቀበለ። ይህም ክራይስትስ ማስ ተባለ። ዛሬ ክሪስማስ ይሉታል። (ይህም በአረማዊነት የተበረዘ ክርስትና ነው።) ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጴርጋሞን ይባላል። ጴርጋሞን ማለት “ሙሉ በሙሉ መጋባት” ነው። በተጨማሪ ጴርጋሞን የዚያ አካባቢ ዋና ከተማ ናት። ክርስትና ከአረማዊነት ጋር ተጋባ (ይህም የነጩ ፈረስ ሽንገላ ነው) ደግሞም ከፖለቲካ ጋር (ይህ የቀዩ ፈረስ ደም አፍሳሽ ባህርይ ነው)። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ ስልጣን ስላገኘች የሚቃወሙዋትን ሁሉ ማሳደድና የሚያምጹባትን ሰዎች ማጥፋት ቻለች። ስለዚህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የሚቃወሙ ሰዎችን መግደል ተጀመረ። የተገደሉ ሰዎችም ቁጥር በቀጣዮቹ 1,200 ዓመታት ውስጥ ከአስር ሚሊዮን አለፈ። ከዚያ በኋላ በጅምላ መግደል ያቆመው።
ዓሳ (ፓይሲስ) ጥንታዊ የክርስትና መለያ ምልክት ነበረ፤ ይህን ምልክት ክርስቲያኖች ካታኮምብ በተባሉ ዋሻዎች ውስጥ እየተደበቁ እግዚአብሔርን በሚያገለግሉበት ጊዜ ይጠቀሙበት ነበረ፤ በዚያ ዘመን የሮማ ወታደሮችና ሰላዮች ክርስቲያኖችን እያደኑ በመያዝ ኮሎሲየም በተባለ የመዝናኛ ሜዳ ላይ ለአንበሶች ይጥሏቸው ነበር። በዚህ የዞዲያክ ምልክት ውስጥ ሁለት ዓሳዎች በተቃራኒ መንገዶች በመዋኘት መስቀል ይሰራሉ፤ ይህም የአራተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ጨለማ ይወክላል። በመጀመሪያ የሮማ ቤተክርስቲያን በፖፑ አመራር ስር ሆና ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ስትሄድ እውነት ሙሉ በሙሉ ልትጠፋ ደረሰች። ከዚያ ቀስ በቀስ ነገሮች እየተለወጡ ሄደው ሕዝቡ እንደ ጆን ሃስ የመሳሰሉ ሰዎች ከሚያስተምሩት ትምሕርት የተነሳ የቤተክርስቲያንን ልማዶች ከመከተል ይልቅ ክርስቶስን እንደ አዳኝ የማወቅ ፍላጎት አደረባቸው። ስለዚህ ከሬናሰንስ ዘመን ጀምሮ ለውጥ መጣ። ሰዎች በግላቸው ማሰብ ጀመሩ። ተጨቁና የነበረችዋ ቤተክርስቲያን በተቃራኒው አቅጣጫ መዋኘት ጀመረች። በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ የተነሳ ተቃውሞ እያደገ እየተስፋፋ ሄደ።
ይህ ዘመን የትያጥሮን ጨለማ ዘመን ነበረ (ትያጥሮን ጨቋኝ ሴት ማለት ነው)፤ በዚህም ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓን በሙሉ በጭቆና ገዛች። የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የሚቃወሙ ሰዎችን በጭካኔ መግደል ቀጠለ።
ከዚያ በኋላ የበጉ (ኤሪስ) ማለትም የሉተር ተሃድሶ ዘመን መጣ፤ እርሱም ልክ እንደ ተዋጊ በግ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ግምባር ለግምባር ተጋጠመ። ሉተር ወኔያምና ምንም የማይፈራ ብርቱ ሰው ነበር። አምስተኛው ዘመን ሰርዴስ ነው፤ ሰርዴስ “ያመለጡ ሰዎች” ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች ከሮማ ካቶሊክ እምነት አምልጠው መዳንን በክርስቶስ አገኙ። ከዚያም ከሰላሳ ዓመታቱ ጦርነት በኋላ በ1648 ዓ.ም ጀርመኒ በወደመችበት ጊዜ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጦር ሰራዊት በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጅምላ ግድያ አቆመ። አውሮፓ፣ ደቡብ አሜሪካ፣ እስፔይን ውስጥ የሚኖሩት ሙር የተባሉ ሰዎች እንዲሁም አይሁዶች ከዚህ በሐይማኖት ከተቀሰቀሰ የነፍስ ግድያ አመለጡ።
ይህንን ዘመን ተከትሎ የመጣው የወንድማማች መዋደድ () እና ቅድስና የተገለጠበት ወርቃማው ስድስተኛ የቤተከርስቲያን ዘመን ነው፤ ይህ የወንጌል ስበከት በር የተከፈተበት ዘመን የተወከለው በበሬ (ታውረስ) ነው። የወንድማማች መዋደድ እና ቅድስና የክርስትና ብርታት ነው።
ከዚያ በኋላ በ1906 ዓ.ም አካባቢ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መንትያዎቹ (ጀሚኒ) መጡ፡ ዘመኑ በጴንጤቆስጤ የጀመረ ሲሆን የዘመን መጨረሻው ነብይ ደግሞ በ1960ዎቹ ወደ አገልግሎቱ ከፍታ ደረሰ። እነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል መገለጥ አንጻር ተቀራራቢ ነበሩ ግን ልዕለ ተፈጥሮአዊውን ኃይል ከቃሉ ሚስጥሮች መገለጥ ጋር አጣምሮ ማቅረብ የቻለው ነብዩ ብቻ ነበር።
ስለዚህ አሁን በካንሰር ዘመን ውስጥ ነን። ካንሰር አሁን በዘመናችን ብዙዎችን እየገደለ የሚገኝ አስፈሪ በሽታ ነው። ካንሰር የተወከለው ክራብ በሚባል የባሕር ዳርቻ ፍጡር ነው። ክራብ በምድርም በባሕርም ይኖራል፤ ማለትም ልም በራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ የተጠቀሰው ብርቱ መልአክ በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱትን ለማስነሳትና ከዚያ በኋላ ዘመን እንደማይቀጥል ለማወጅ ሲወርድ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ላይ አድርጎ እንደሚቆመው ማለት ነው። ክራብ የሚራመደው ወደ ጎን ነው። ይህም በሩ እየተዘጋ ስለሆነ እና ለመግባት በጣም ጠባብ ቀዳዳ ስለቀረ ነው። ስለዚህ ወደ ጎን መራመድ አለብን (ዓለም ከምትራመድበት የተለየ አረማመድ ማለት ነው)። ነገር ግን ክራብ ሁለት ጠንካራ ጥርሶች አሉት፤ እነዚህም የሚያገለግሉት መንፈሱንም ቃሉንም አጥብቆ ለመያዝ ነው። በዚህ የሰው ንግግር ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በተኩበት ዘመን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን አጥብቃቹ መያዝ አለባችሁ፤ ደግሞም አትልቀቁት። ክራቦች በጥፍራቸው አጥብቀው የመያዝ ጉልበት አላቸው። ደግሞም ጠንካራ ቅርፊትም አላቸው። ስለዚህ የሚመጣባቸውን ስድብ፣ መገፋት፣ እና የማያቋርጥ ተቃውሞ ሁሉ ችለው ያሳልፋሉ።
ራዕይ 10። መልአኩ በምድር እና በባሕር ላይ ይቆማል። የባሕሩ ዳርቻ የውሃ ጥምቀት የሚደረግበት ቦታ ነው። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ በዘመን መጨረሻ አካባቢ ትልቅ አከራካሪ ጉዳይ ሆኗል።
ከዚያ የመጨረሻው ምልክት ሊዮ ነው፤ እርሱም ሙሽራይቱን ሊወስዳት የሚመጣው የይሁዳ አንበሳ ነው። እኛም የምንጠብቅ የመደምደሚያ ጉልላት ይህ ነው።
53-0729 ዘፍጥረትን በመተለከተ የቀረቡ ጥያቄና መልሶች
እንግዲህ ይህን ተመልከቱ። እጅግ ውብ ነው … ፀሃይን ፈጠራት። ከዚያ መጀመሪያ የሆነው ነገር ምን መሰላችሁ፤ ከፀሃይ ላይ ትልቅ ድንጋይ ወደቀ፤ ክብደቱም ይህችን ምድር የሚያህል ነበር። ከዚያም ቃሉ ማለትም የእግዚአብሔር ልጅ እየተመለከተው ነበር። ለአንድ መቶ ሚሊዮን ዓመታት ያህል ሲወድቅ ዝም ብሎ ተመለከተውና ከዚያ አስቆመው። ቀጥሎ ሌላ ደግሞ ወደቀ - እርሱም ዝም ብሎ ሲወድቅ ለሚሊዮኖች ዓመታት ተመለከተውና አቆመው። አሁን ደግሞ እኛ ሲመጣ እናየዋለን።
አንድ ነገር በልቡ አስቧል። ምን እያደረገ ይመስላችኋል? የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱስ እየጻፈ ነው። ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያዩትና ያነበቡት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ከዋክብት ላይ ነው፤ በዞዲያክ ነው። ደግሞም ፍጹም የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ነው … በቃ … እዚህ እጃችን ላይ ካለው መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ፍጹም ይስማማል። ሲጀምር የመጀመሪያው የዞዲያክ ምልክት ቨርጎ ነው። ልክ አይደል ወይ? የዞዲያክ የመጨረሻው ምልክት ምንድነው? ሊዮ አንበሳው ነው። ይህም የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ነው፤ ከድንግል በመወለድ መጣ። ለዳግም ምጻቱ ደግሞ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ሆኖ ይመጣል። አያችሁ? ይህን ሁሉ ከዋክብቱ ላይ ጽፏል፤ ከካንሰር ዘመን
(ማለትም፡- ካንሰር የተባለው ክራብ፤ ከሊዮ ቀድሞ የሚመጣው ዘመን። ይህ አሁን ያለንበት ዘመን ነው)
ጀምሮ እስከ መጨረሻው ያለውን ሁሉ። ይህን ሁሉ እውነት ሰማይ ላይ ጽፎ አስቀምጦታል፤ እነዚህ ሁሉ ከዋክብት እና ሜሪዎሮች፣ ምድር ወይም ፀሃይ ሁሉ ለምልክት ነው የተቀመጡት።
60-0522 ልጅነት 4
የፒራሚዶችን ታሪክ ያጠናችሁ ስንቶች ናችሁ? ከመካከላችሁ አንዲት ሴት ብቻ እጇን አንስታለች። እሺ።
እግዚአብሔር ሶስት መጽሐፍ ቅዱስ ጻፈ። ከነዚህ አንዱ ሰማይ ላይ የተጻፈው ዞዲያክ ነው። እግዚአብሔር ከላይ መሆኑን ይገነዘብ ዘንድ ሰው ወደ ላይ ወደ ሰማይ እንዲመለከት ተደረገ። ዞዲያክን ተከተሉ፤ አጥንታችሁት ታውቃላችሁ? ስለያንዳንዱ ዘመን ይናገራል፤ ስለ ካንሰር ዘመን ሳይቀር። የክርስቶስን ልደት መጀመሪያ ይገልጣል። ዞዲያክ ውስጥ የመጀመሪያው ምልክት ምንድነው? የድንግል ሴት ምልክት ነው። የመጨረሳ ምልክትስ ምንድነው? ሊዮ አንበሳው። የመጀመሪያው ምጻት እና ዳግም ምጻት በግልጽ ዞዲያክ ውስጥ ተጽፈዋል።
ከዚያ በመቀጠል የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ በድንጋይ ነው፤ እርሱም ፒራሚድ ይባላል። እግዚአብሔር በፒራሚዶች ላይ ጽፏል። ፒራሚዶችን ብታጠኑ፤ የጥንት ጦርነቶችን እና ታሪኮችን ብትመለከቱ፤ ከጥፋት ውሃ በፊት እንዴት እነደተመሰረቱ ትገነዘባላችሁ።
64-0112 ሻሎም
ዞዲያክ ውስጥ እንኳ ሳይቀር ይታያል። አሁን ተመልሼ ስለ ዞዲያክ አላስተምራችሁም፤ ነገር ግን ሰማያት የእውነትም ክብሩን እንደሚገልጡ ላሳያችሁ እፈልጋለሁ። ዞዲያክ ውስጥ በከዋክብቱ ስብስብ አማካኝነት እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ሚስጥር በሙሉ እንዳስቀመጠ እናያለን። ዞዲያክን ስንመለከት መልእክቱን የጀመረበት የመጀመሪያው ምልክት የድንግሊቱ ምስል መሆኑን እናያለን፤ የመጨረሻው ምልክት ደግሞ ሊዮ አንበሳው ነው። ይህም ኢየሱስ በመጀመሪያ ወደ ምድር በድንግል በኩል ተወልዶ እንደሚመጣ እና ዳግም ሲመለስ ደግሞ የይሁዳ ነገድ አንበሳ ሆኖ እንደሚመጣ ያሳያል። አያችሁ? ከዚያ በፊት ግን እንደ መስቀል እርስ በራሳቸውን የሚያቋርጡት ዓሳዎች ውስጥ ያልፋል። የካንሰር ዘመን አሁን የምንኖርበት ነው። “ሰማያት ሁሉ ክብሩን ይናገራሉ” ይላል መጽሐፍ ቅዱስ።
65-1128 እግዚአብሔር ለአምልኮ የመረጠው ብቸኛው ስፍራ
ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፋ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ሰማይ ላይ ነው … ይህን አስተውላችኋልን? ይህ ሰማይ ላይ የተጻፈ መጽሐፍ በድንግል ምልክት ይጀምራል፤ ይህም ዞዲያክ ውስጥ የመጀመሪያው ምልክት ነው። የመጨረሻው ምልክት ሊዮ የተባለው አንበሳው ነው። መጀመሪያ ከድንግል ሴት በመወለድ ይመጣል፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ አንበሳ ሆኖ ይመጣል። ከዚያ በፊት ግን የካንሰር ዘመን፤ እርስ በራሳቸውን እንደ መስቀል የሚያቋርጡ ዓሳዎች ዘመን ይመጣል፤ ሌሎች ዘመኖችም ይመጣሉ። ጊዜ ቢኖረን ሁሉ በዝርዝር እናይ ነበር።
ትንሳኤ እስካሁን ስላልተፈጸመ የመደምደሚያ ጉልላት የሆነው ክርስቶስ እስከ ዛሬ ተመልሶ አልመጣም።
63 04 21 የድል ቀን
ሁላችንም ባለ ድል ነን። በብዙ ጦርነቶች ውስጥ ተዋግተን ድል ነስተናል። ገና ሌላ ታላቅ ድል ይጠብቀናል፤ እርሱም በደጅ ነው። የድል ቀናችን በጣም ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ሰማያትን ቀዶ ሲወርድና በመላእክት አለቃ ድምጽ በኃይል ሲጮህ ዳግም ሲመጣ ያ ቀን የድል ቀን ነው ለእኛ። በዚያ ቀን መቃብሮች ይከፈታሉ፤ ሙታንም ከመቃብራቸው ይወጣሉ።
ደመናው ታይቶ ሁለት ወራት ካለፉና ከሰባተኛው ማሕተም በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም ሙታን ገና ወደፊት እንደሚነሱ ሲጠባበቅ ነበር። የመደምደሚያው ጉልላት ከትንሳኤ በፊት አይመጣም።
65-0410 የፋሲካ ማሕተም
እውነት እላችኋለው፤ ልቤ በሐሴት ተሞላ። እንደ … ወንድሜ እንደዚህ ዓይነት ነገር ባየህ ጊዜ ስራህና ልፋትህ በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃለህ። የቻልከውን ያህል ሞክረሃል። እግዚአብሔርም በድጋሚ እንደሚያደርገው ተስፋ አደርጋለሁ፤ እኛ ወደዚያ ስለምንወርድ ሳይሆን የጌታን ምጻት ስለምንጠባበቅ ነው።
በ1965 ወንድም ብራንሐም የጌታን ምጻት ሲጠባበቅ ነበር።
65-1125 የክርስቶስ ሙሽራ ስውር አንድነት
አሁን ይህንን ልክ እንደ ሰንበት ትምሕርት ቤት ልንጠቀምበት ነው። ደግሞ ለየትኛውም ሰው በግል የተላከ አይደለም። የተላከው ለቤተክርስቲያን ማለትም ለክርስቶስ አካል ነው፤ እኛም ጠለቅ ወዳለ ሃሳብ እና ጠለቅ ወዳለ መረዳት ለመድረስ እየሞከርን ነን ምክንያቱም የጌታ ምጻት በደጅ መሆኑን እናምናለን። ይህን ከልብ እናምናለን። ደግሞም የጌታ ምጻት እኔ መጀመሪያ ወደ ሽሬቭፖርት ከመጣሁበት ጊዜ ይህል በሃያ ዓመታት ቀረብ ብሏል። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ብዙ ነገር ሆኗል! አሁን በዚህ ትውልድ መካከል የጌታን መምጣት እየተጠባበቅን ነን። በዚህ ዘመን መነቃቃት እንዲመጣ እየተጠባበቅሁ አይደለሁኝም። በዚህ ትውልድ መካከል የምጠባበቀው የጌታን ምጻት ነው።
ኖቬምበር 1965 ውንድም ብራንሐም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻዎቹን ስብከቶቹን የሰበከበት ወር ነው፤ በዚያ ጊዜ እንኳ የመደምደሚያው ጉልላት ማለትም የኢየሱስ ዳግም ምጻት ገና ወደፊት እንደሚሆን እየተጠባበቀ ነበር።
1965-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
በነዚህ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ያሉ ሰዎች የፈለጉትን ያህል ቢያስመስሉ ምንም ግድ የለኝም፤ “ጌታን እየተጠባበቅን ነው” ይላሉ፤ ድርጊታቸው ግን እየተጠባበቁ አለመሆናቸውን ይናገራል። ይህ እውነት ነው። ድርጊታችሁ ከንግግራችሁ የበለጠ ጮክ ብሎ ይናገራል። በልባቸው ሁሌ የሚያስቡት የዲኖሚኔሽናቸውን አባላት ቁጥር ስለ ማብዛት ብቻ ነው። ነገር ግን በእውነት የጌታን ምጻት የሚጠባበቁ እዚህ አንድ እዚያም አንድ ጥቂት ሰዎች አሉ። እነርሱ እየጠበቁ ናቸው … ቢሆንም። እርሱም ለነዚህ ብቻ ነው ራሱን የሚገልጠው፤ መረዳትን የሚያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው።
ይህ በ1965 ከሰበካቸው የመጨረሻው ስብከቱ ነው። መረዳት የሚችሉት የጌታን ምጻት የሚጠባበቁ ሰዎች ብቻ ናቸው ብሎ ያስጠነቅቀናል።
62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን
ጊዜ ያበቃል። ዘመን እንደሚያበቃ ያውጃል። ከዚያ በኋላ ምን ይሆናል? ወንድሞች ሆይ ይህ አሁን ሊሆን ይችላልን? ከልባችሁ አስቡበት። ከሆነ እንግዲያውስ ፒራሚዱ በሰባቱ ነጎድጓዶች አማካኝነት መደምደሚያ ጉልላቱን ያገኛል።
የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ፒራሚድ የመደምደሚያ ጉልላቱን ባገኘ ጊዜ ከዚያ ወዲያ ዘመን አይኖርም። ሁላችንም በጊዜ ውስጥ እየኖርን ስለሆንን ጊዜ አለማብቃቱ ግልጽ ነው፤ ስለዚህ ፒራሚዱ ገና መደምደሚያውን አላገኘም።
የመደምደሚያው ጉልላት እስካሁን አልመጣም። ስለዚህ ሰባቱ ነጎድጓዶች ገና ቃላቸውን አልተናገሩም ማለት ነው።
ወንድም ብራንሐም አንድም ጊዜ “ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰምተዋል” ብሎ አያውቅም።
ብሎ ተናግሯል የምትሉ ከሆነ በራሳችሁ የፈጠራችሁት አስተምሕሮ ነው።
ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የተጻፈው መጽሐፍ “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” ነው የፊተኛው ሽፋኑ ላይ ያለው ርዕስ።
ማሕተሞቹ ከመፈታታቸው በፊት ስለ ማሕተሞቹ መገለጥ መምጣት አለበት። የሰባቱ ማሕተሞች መከፈት የተከናወነው ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ቤተክርስቲያን በራዕይ ምዕራፍ 4 እንደተጻፈው ወደ ሰማይ ከተነጠቀች በኋላ ነው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት አስቀድሞ ይገልጠዋል።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
63.03. 24 ሰባተኛው ማሕተም
አሁን እዚህ ላይ ማቆም አለብኝ። አያችሁ? በቃ ማቆም እና ከዚህ ወዲያ ምንም ማለት እንደሌለብኝ ተሰማኝ። አያችሁ? ስለዚህ ሰባተኛውን ማሕተም እንዲሁም ያልተፈታበትን ምክንያት አስታውሱ (አያችሁ?)፤ ያልተፈታበት ምክንያት ሚስጥሩን ማንም ማወቅ ስለሌለበት ነው …
ደግሞም ስድስቱንም ማሕተሞች ገልጧቸዋል፤ ነገር ግን ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አይናገርም። የመጨረሻው ዘመን ማሕተም መከፈት ሲጀምር መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው የሚሆነው። ያንን ከማወቃችን በፊት … ደግሞ አስታውሱ፤ ራዕይ 10፡1-7 በሰባተኛው መልአክ መልእክት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች በሙሉ ይታወቃሉ። እኛ አሁን የምንኖረው በመጨረሻው ዘመን ነው፤ እርሱም ሰባተኛው ማሕተም የሚከፈትበት ዘመን ነው።
63 11 10 አሁን በወኅኒ የሚኖሩ ነፍሳት
ሰባተኛው ማሕተም ወደ ምድር ይመልሰዋል።
ስለዚህ 7ኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።
64 07 19 የመለከቶች በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተከፈተም። ይህም የጌታ ምጻት ነው።
የሰባተኛውን ማሕተም ሚስጥር በጭራሽ አልገለጠውም።
ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተከፈተም። እስካሁን ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነው። ሰባቱ ነጎድጓዶች እስካሁን ድምጻቸውን አላሰሙም። ስለዚህ በግልጽ እንደምናውቀው ጌታ እስካሁን አልመጣም።
ታላቁ ደመና ፎቶግራፍ የተነሳው ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ነው። ወንድም ብራንሐም ማርች 24 ቀን 1963 ስለ ሰባተኛው ማሕተም ሰብኮ ነበር። እነዚህ ሁለቱም ቀኖች የጌታ ምጻት ናቸው ተብሎ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው የአንድ ወር ክፍተት አለ። በዚህ ዓይነት ትምሕርት ውስጥ አንድ ግልጽ ስሕተት አለ፤ ምክንያቱም በግልጽ እንደምናውቀው ኢየሱስ ለዳግም ምጻት ሁለት ጊዜ አይመጣም።
63-0116 የምሽቱ መልእክተኛ
በተመሳሳይ ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- “ሁሉም … ዴማስም ትቶኛል። ሰዎች ሁሉ ዓለምን ወደው ትተውኛል።” ዴማስ ወደ ጭፈራ ቤትና መጠጥ ቤት የሄደ አይመስለኝም። ዴማስ ጳውሎስን ትቶ መሄድ ፈለገ፤ ዴማስ ሃብታም ሰው ነበረ። ስለዚህ ሕዝብ ካደነቀው ቡድን ጋር አብሮ መሄድ ፈለገ፤ ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደሄዱበት እርሱም አብሯቸው ሄደ።
ከዚያም ጳውሎስ፡- “ሁሉም ትተውኛል” አለ። ለምን? የጳውሎስ አገልግሎት ወደ ፍጻሜው ወደ መደምደሚያው ጉልላት እየደረሰ ነበር።
ሃብታም ሰዎች ሕዝብ በመረጠው መንገድ መሄድ ይወዳሉ። ይህም በከፊል ወርቅ የሰዎችን ባህርይ እንዴት እንደሚለውጥ ያሳያል። ሃብት በዚህ ዓለም ጉዳዮች ላይ እንድናተኩር ያደርገናል ምክንያቱም ወርቅ የሚያገለግለው ይህች ዓለም ያዘጋጀችውን ነገር ለመግዛት ነው።
ሃብት በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ያስገኝልናል።
ሌላም መደምደሚያ ጉልላት መኖሩን ልብ በሉ - እርሱም የሰው አገልግሎት ማብቂያ ነው።
ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የግል ሕይወታችንን በጌታ ዘንድ የሚያትም መደምደሚያ ጉልላት አለ፤ ይህም የትንሳኤን ኃይል እንድናገኝ በር ይከፍትልናል።
62-1231 ክርክሩ
ጌታ ሆይ በዚህ ዓመት የተሰወረውን መና ስጠን፤ የእግዚአብሔርን ዓላማ መረዳት እንችል ዘንድ ከዓለቱ ስር የተሰወረውን ዓለት ግለጥልን። የሕይወታችን ፒራሚዶች ላይ መደምደሚያ አድርግልን ጌታ ሆይ፤ መደምደሚያ ጉልላት የሆነውን ክርስቶስን በእያንዳንዳችን ላይ አስቀምጥ። ታላቅና ድንቅ የሆነው በረከቱ በሁላችን ላይ ይምጣልን። የመንፈስ ቅዱስ እሳት በእኛ ላይ ይምጣ። የትንሳኤ ኃይል ይገለጥ። እግዚአብሔር ሆይ እጅግ አድርገን እናመሰግንሃለን። እኛ ያንተ ነን። ጌታ ሆይ ሁለንተናችንን ለአንተ እንሰጣለን።