የቤተክርስቲያን ዘመናት - ራዕይ ምዕራፍ 1 - ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አልፋለችን?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ራዕይ ምዕራፍ 1
ቤተክርስቲያን በሁለቱ የሰው ታሪክ ዋነኛ ክስተቶች ማለትም ክርስቶስ ስለ ኃጢያታችን ሊሞት በመጣበት የመጀመሪያው ምጽአቱ እና ሙሽራውን ከምድር ላይ ሊነጥቅ፤ ወደ ሰመይ ሊወስዳትና በሰማይም ሰርግ ሊያደርግላት በሚመለስበት በዳግም ምጽአቱ መካከል ለረጅም ጊዜ ሰንብታለች።
በእነዚህ ሁለት ታላላቅ ክስተቶች መካከል ያለፉት 2000 ዓመታት የቤተክርስቲያንን ታሪክ አስተናግደዋል።
ቤተክርስቲያን መሬት ውስጥ በሚተከል ዘር ትመሰላለች። ሰሩ በአፈር ውስጥ ይሞታል፤ ይበሰብሳል፤ ከዚያም ሳይንስ ሊኮርጀው በማይችለው ተዓምራዊ መንገድ ቅጠሎች አፈሩን እየቀደዱ ወደ ላይ ብቅ ይላሉ። ይህንንም ተከትሎ ተክሉ ያድግ እና አበባ ያብባል፤ ከዚያም በአበባ ውስጥ በንፋስ እየበነነ የሚሄድ ዱቄት ይፈጠር። ቀጥሎ ደግሞ እያደገ ያለውን ዘር የሚሸፍን ቅርፊት ይፈጠራል። ዘሩ ሲያድግ ተክሉ ሙሉ በሙሉ መድረቅ ይጀምራል።
ከዚያም መጀመሪያ የተዘራውን ዘር የሚመስሉ ዘሮች ብቅ ይላሉ። መከር ሲደርስ ዘሮቹ ከሰብሉ ላይ ይለቀማሉ። ከዚያም በእርሻው ላይ የሚኖሩ እንስሳት በሬዎች እና ላሞች ከመከሩ ጋር ወደ ጎተራ ያልገቡትን ደርቀው የቀሩትን ሰብሎች ይበሉዋቸዋል።
በ2000 ዓመታት ውስጥ ሰባት የተለያዩ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲፈራረቁ ቤተክርስቲያን ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር በተጋፈጠች ጊዜ በዓራት መሰረታዊ ደረጃዎች ውስጥ አልፋለች፤ ክርስቲያኖችም ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር እየተጋፈጡ ተዋግተዋል።
ደረጃ 1
ይህ የመጀመሪያው እግዚአብሔር የተከለው ዘር ነው።
የቤተክርስቲያን ዘመን 1። የመጨረሻው ሐዋርያ ዮሐንስ ከመሞቱ በፊት ሐዋርያት በ33 እና በ100 ዓ.ም. መካከል እውነትን መሥርተው አጠናቅቀዋል። በዚያ ጊዜ አዲስ ኪዳን ተጽፎ አልቆ የጥንቷ ቤተክርስቲያን መሠረት ሆኗል።
የቤተክርስቲያን ዘመን 2። 200 ዓ.ም. እንዳለፈ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ቤተክርስቲያኖች ስሕተትን ለመከላከል ሰነፉ። ስሕተት እንደ ሜዳ አረም ነው፤ ሁሌም አለ። ከቅን ልቦናቸው ተነስተው በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው መሪ እንዲሆን ሾሙ። ይህም አሰራርን የሚያቀላጥፍ ይመስል ነበር ግን ሌላ ስሕተት ይዞ መጣ። ይህም ስሕተት ሰው የቤተክርስቲያን መሪ መሆኑ ነው። እነዚህን የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉ በአንድ ሃሳብ ለማስኬድ እያንዳንዱ ከተማ በአንድ ከተማ ውስጥ ያሉ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ የሚያስተዳድር አንድ ጳጳስ ሾሙ። ይህም ጳጳስ እንደ አይሬኒየስ አይነት እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ሲሆን ጳጳስ መሾሙ ስሕተት አይመስልም ነበር። ግን ብዙ ሰዎች እንደ አይሬኒየስ አልነበሩም። እነዚህ ሰዎች ወይም ጳጳሳት ቤተክርስቲያኖችን የራሳቸው አመለካከት እሥረኛ አደረጓቸው። እግዚአብሔር በሮማ መንግስት አማካኝነት በተከታታይ ከባድ ስደቶችን እያስነሳ ክርስቲያኖችን በመበታተን ሰው በሆኑ መሪዎች አማካኝነት ሊደርስ የሚችለው ጥፋት እንዳይበዛ አድርጓል።
ደረጃ 2
በዚህም የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን የእውነት ዘር በጨለማው ዘመን ሥር እንዲቀበር አደረገ።
የቤተክርስቲያን ዘመን 3። ኮንስታንቲን በ312 ዓ.ም. የሮማ ንጉስ በሆነ ጊዜ ፖለቲካ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገባ። እርሱም በ325 ዓ.ም. የተደረገውን የኒቂያ ጉባኤ በመጠቀም የቤተክርስቲያንን ይፋዊ አስተምህሮ ደነገገ፤ ማእከላዊና ድርጅታዊ የሆነች የቤተክርስቲያንን በሮም ከተማ መሰረተ፤ ይህንንም ያደረገው ኮንስታንቲን ወደ ምስራቅ ወደ ኮንስታንቲኖፕል በሚሄድበት ጊዜ በምዕራባዊው የሮማ ግዛት ውስጥ ለእርሱ ጠንካራ ደጋፊ የሚሆን ጳጳስ ለመሾም ፈልጎ ነው። ከኮንስታንቲን የተቀበለውን እጅግ ብዙ ገንዘብ በመጠቀም የሮማው ጳጳስ ለሌሎች ቤተክርስቲያኖች በተቸገሩ ጊዜ ሁሉ ገንዘብ በመስጠት በቀላሉ በእነርሱ ላይ ስልጣንን መግዛት ችሏል።
አረማዊነት (ፓጋኒዝም) ወደ ቤተክርስቲያን ገባ። በ400 ዓ.ም. አካባቢ የሮማው ጳጳስ ማዕረጉን ወደ ሊቀጳጳስ (ፖፕ) ከፍ አደረገ፤ ይህም በእርሱ ስልጣን ስር ለሚሆኑት ጳጳሳት ሁሉ አለቃ አደረገው። በ450 ዓ.ም. የሮማ ጳጳስ ራሱን ፖንቲፍ ብሎ ጠራ -- ይህም የባቢሎናውያን ምስጢሮች ሊቀካህናት ማለት ነው። እውነት ከብዙ የአረማውያን ልማዶች ስር ተቀበረች (ለምሳሌ ዲሴምበር 25ን አስቡ፤ ይህ ቀን የፀሃይ አምላክ ልደት የነበረ ሲሆን ያጌጠው የአረማውያን ዛፍ የቤተክርስቲያን የገና ዛፍ ሆነ)። የቤተክርስቲያን ሰዎችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወዳልሆኑ አጉል እምነቶች ውስጥ ገቡ። ለምሳሌ በመስቀል ምልክት ማማተብ፤ ረድኤት ፍለጋ ወደ ማርያም እና ወደ ሞቱ ቅዱሳን መጸለይ።
የቤተክርስቲያን ዘመን 4። በ606 ዓ.ም. ሊቀጳጳሱ ወይም የሮማው ጳጳስ እራሱን የዓለም ሁሉ ጳጳስ ብሎ ሰየመ። በዓለም ዙሪያ ላሉት ጳጳሳት ሁሉ የበላይ የሁሉ ታላቅ ጳጳስ ነኝ ብሎ አወጀ።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተገገደሉ፤ ቤተክርስቲያኒቱም ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ የተቻላትን ሁሉ አደረገች። አውሮፓ መንፈሳዊ ጨለማ፣ ብርድ እና እድፈት ውስጥ ወደቀች። በሮማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባው እርኩሰት እና ክፋት እጅግ አስከፊ ሆነ። በዚህ አይነት የጨለማ ዘመን ቆሻሻ ውስጥ ነው የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን የእውነት ዘር የተቀበረውና ከሰው ዓይን የተሰወረው። ነገር ግን በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩ ሰማእታት የፈሰሰው ደም ለበሰበሰው አፈር ማዳበሪያ ሆነው።
ደረጃ 3
እግዚአብሔር የሕይወት መታደስን ወደ ቤተክርስቲያን አመጣ።
የቤተክርስቲያን ዘመን 5። ከ1500 ዓ.ም. በኋላ በጀግናው ማርቲን ሉተር መሪነት ጀርመኒ ውስጥ የተጀመረውን ተሃድሶ ተከትሎ በኢየሱስ መስዋእትነት በማመን የመዳን እውነት ለቤተክርስቲያን ሲመለስላት በደም የተነከረው አፈር ላይ አዳዲስ ቅጠሎች በተሃድሶ መሪዎች መልክ ማቆጥቆጥ ጀመሩ።
ኖክስ፣ ካልቪን፣ ዝዊንሊ፣ ሜላንክተን እና ሌሎችም የተሃድሶ መሪዎች እንደ አረንጓዴ ቅጠሎች አቆጠቆጡ፤ ነገር ግን በኋላ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴው ተጠሪነታቸውን ሰው ለሆኑ መሪዎች አሳልፈው በሰጡ የቤተክርስቲያን ጎራዎች በመከፋፈል ፍጥነቱ ተገታ። አሁንም የሰው መሪነት ሾልኮ ገባ፤ ከዚያም የክርስትና እምነት አንድ ቤተክርስቲያን ከሌላ ጋር የምታደርገው ሽኩቻ እና ፉክክር ሆነ። “የኔ ቤተክርስቲያን ካንተ ቤተክርስቲያን ትበልጣለች”።
እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን ራሷን ከሌሎች የምትከላከልበት የአስተምህሮ አጥር በዙሪያዋ ገነባች።
የቤተክርስቲያን ዘመን 6። በ1750 ዓ.ም. እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ በቅድስና እና ከቤተክርስቲያን ውጭ ላሉ ኃጢያተኞች የመስበክ እንቅስቃሴ ጀመረ። ይህም እንቅስቃሴ ዊሊያም ኬሪ በ1793 ወደ ሕንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሄደበት ታላቅ የወንጌል ስብከት ሚሽን መሰረት ጣለ። የእርሱ አርአያነት በአስር ሺ የሚቆጠሩ ሰባኪዎች ሕይወት ሰጪውን የወንጌል ቃል በዓለም ዙሪያ ሁሉ እንዲዘሩ አነሳሳቸው። ይህ የወንጌል ስብከት ወርቃማ ዘመን ክርስቲያኖች ከአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ግድግዳ አልፎ የሚሄድ ራዕይ እንዲኖራቸው አደረገ። ለወንጌል ስብከት የሚኬድባቸው ሃገሮች የማይመቹ እና ለሕይወት የሚያሰጉ ነበሩ። ነገር ግን እግዚአብሔር ለምንም የማይበገሩ ጀግና የእምነት ሰራዊት አስነሳ፤ ታሪካቸውም እስከዛሬ ብዙዎችን ያበረታታል።
እነዚህ ሚሽነሪዎች እጅግ አስደናቂ ሰዎች ናቸው። በዚያ ዘመን ሰዎች ለወንጌል አገልግሎት ራሳቸውን አሳልፈው በሰጡበትና ነፍሳቸውን በሰዉበት ጊዜ ዲያብሎስ ዋጋውን አግኝቷል። ነገር ግን የቆሰለ ሰይጣን አደገኛ ነው። ቁስሎቹን ልሶ ሲነሳ የሰዎችን አእምሮ ለመቆጣጠር የመጨረሻውን ዙር ታላቅ ጦርነት በእግዚአብሔር ላይ ለማስነሳት ተዘጋጀ።
ደረጃ 4
ሙሽራይቱ ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያት የእውነት ትምሕርትና ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ መመለስ አለባት። ይህም የሚከናወነው የእግዚአብሔር ስጦታ በፈሰሰበት ነገር ግን ጨለማ በሆነ ዘመን ውስጥ ነው።
የቤተክርስቲያን ዘመን 7። ከ1906 ዓ.ም. ጀምሮ ሎሳንጀለስ ውስጥ በተነሳው የጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እና መለኮታዊ ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው መጡ። ነጻ እንቅስቃሴ ነበረ፤ ግን በ1917 ዓ.ም. ጴንጤቆስጤያዊነት በድርጅት ውስጥ ሲታቀፍ እሳቱ ወዲያው በረደ። በ1940ዎቹ መጨረሻ ዊልያም ብራንሃም እና ኦራል ሮበርትስ የጴንጤቆስጤን እሳት እንደገና አቀጣጠሉት፤ መነቃቃትም ተጀመረ። ነገር ግን ይህ ዘመን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፈጣን እድገት ምክንያት ከበፊት ይልቅ ሃብት የተትረፈረፈበት ዘመን ሆነ። የሚያሳዝነውም ነገር መንፈሳዊው ተሃድሶ በሃብት እና በሥጋዊ ቁሳቁስ ፍቅር ተውጦ መቅረቱ ነው። የብልጽግና አስተምሕሮ የሰዎችን ስግብግብነት ፈቶ ለቀቀው። ስግብግብነት አንዳችም መልካም ነገር የለውም፤ የሚረባ ነገርም አይሰራም።
ምቾት እና ተድላ ተወዳጅነትን ባገኘበት በዚህ ዘመናዊ ጊዜ ነገር ግን አለመረጋጋት በነገሰበትና እርግጠኝነት በጠፋበት፤ ወከባ፣ ጭንቀት፣ አውሬነት እና ጭካኔ በበዙበት በዚህ ዘመን ሰዎች በራሳቸው ጉዳይ በመጠመዳቸውና የራሳቸውን ተድላ ፈላጊ ብቻ በመሆናቸው የተነሳ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ደጅ ውጭ ቆሞ ሲጠራቸው መስማት አልቻሉም። የዚህ አመን አሳዛኝ ውድቀት ይህ ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስን ከሰዎች ልብ ውስጥ ፈጽመው አስወግደውታል። ኢየሱስ መጀመሪያ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችም ይህንኑ ነው ያደረጉት።
ስለዚህ እውነትን የሚፈልጉ የሙሽራይቱ አካል የሆኑ ግለሰቦች ወደ አዲስ ኪዳን የሐዋርያት ትምሕርት መመለስ አለባቸው። እውነትን ሕብረት ከሚያደርጉበት ቤተክርስቲያን ውጭ ማግኘት አለባቸው። እውነትን ማግኘት ከፈለጉ እንደ ሚሽነሪዎቹ ቆራጥ እና ደፋር መሆን ያስፈልጋቸዋል። አንዳንዶች ግን ከሚመጣውና በታላቁ መከራ ውስጥ ዓለምን ሁሉ ጠራርጎ በሚወስደው ፍርድ ውስጥ በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ የራሳቸውን መዳን ነጥቀው ያወጣሉ።
ልክ ይህ ከመሆኑ በፊት የከመጀሪያይቱን ቤተክርስቲያን ትመስል ዘንድ የተመለሰችው ሙሽራ - የመጀመሪያው ዘር እና የኋለኛው ዘር በተመሳሰሉ ጊዜ - በኋለኛው ዝናብ መከር ወቅት ከደረቀችው የቤተክርስቲያን ሰብል ውስጥ ተለይታ ትወሰዳለች፤ እግዚአብሔርም በሰማይ ወደተዘጋጀው የበጉ እራት ይወስዳታል። የቀረው ዓለም ወደ አውሬው ይሄዳል። ሙሽራዋ እራት ትበላለች፤ የቀሩት አውሬው ይበላቸዋል።
የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 1 እነዚህን ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት በአጭሩ የሚያስተዋውቅ ክፍል ነው።
ማቴዎስ 13 ስለ እግዚአብሔር መንግስት የሚገልጡ ሰባት ምሳሌዎችን ያቀርብልናል። እነዚህ ምሳሌዎች ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር ይዛመዳሉ።
ማርቆስ 4፡11-12 እንዲህም አላቸው፦ ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፥ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፥ እንዳይመለሱ ኃጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።
ኢየሱስ ለሐዋርያት ከእነርሱ በኋላ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ስለሚከሰቱ ክስተቶች መረዳትን ሰጥቷቸዋል። አይሁድ መሲሃቸውን ሲሰቅሉ ከእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ተጥለው እንደሚወጡ ነግሮአቸዋል። ከዚያም እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ይዞራል። ይህ በሰዓቱ አይሁድ ያልተረዱት ሚስጥር ነበር።
ነገር ግን ከዚያም በኋላ የሰዎች አመራር እና የሰዎች ወግ የአሕዛብን ቤተክርስቲያን እየወረሰ ሲመጣ ደግሞ ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን የመሰረቱበት እውነት እየጠፋ ይሄዳል። በስተመጨረሻም የቤተክርስቲያን ዘመናት ታሪክ ሚስጥር በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ይገለጣል። ይህም በዘመን መጨረሻ የሚኖሩትን አማኞች (ልጆች) ሐዋርያት (አባቶች) በመጀመሪያ ወደነበራቸው መረዳት እንዲመለሱ ያስችላቸዋል።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ሮሜ 11፡25 ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤
ነገር ግን ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ ወደ ሐዋርያቱ እምነት የመመለሱን ሃሳብ እምቢ ትላለች። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ተዘግቶበት ይቆማል። ከዚያም እግዚአብሔር እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ ይነጥቃትና ትኩረቱን ወደ አይሁድ ይመልሳል።
ሮሜ 16፡25-26 እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥
ጳውሎስ የወንጌሉን ምስጢር መሰረተ። የክርስትና መሰረታዊ እውነት የተሰጠው በጳውሎስ ነው። ጳውሎስ ወዳስተማረው እውነትና እምነት መመለስ አለብን።
ኤፌሶን 2፡6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።
ጳውሎስ ዘመናት እንደሚመጡ ተናግሯል። ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እውቀት ነበረው። ነገር ግን እያንዳንዱ ዘመን የራሱ የሆነ ባህርይ ይኖረዋል።
1ኛ ጴጥሮስ 2፡5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
እያንዳንዱ ክርስቲያን ለ2000 ዓመታት ሲገነባ በቆየው ታላቁ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መቅደስ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን የክሕነት አካል ነው። አምስቱ ስጦታዎች ያሉበት አገልግሎት በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል የሚቆም የአሮን ክሕነት አይደለም። አማኞች ሁሉ የክሕነቱ አካል ናቸው። ስለዚህ አማኞች ሁሉ እኩል ናቸው። አንድም ሰው ከሌሎቹ በላይ ከፍ አይልም።
ገላቲያ 1፡8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።
9 አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
ጳውሎስ ለምንድነው ይህን ሁለቴ የሚናገረው?
በመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን የነበሩ ክርስቲያኖች ጳውሎስ የአዲስ ኪዳንን ሃምሳ በመቶ የሚሆኑ መጻሕፍት ሲጽፍ ያደምጡት ነበር። የትኛውም ሐዋርያ ጳውሎስን ጨምሮ የተጻፈውን መለወጥ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉ የበላይ ነው። ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን መስበክ ብቻ ነው የሚችለው።
2ኛ ተሰሎንቄ 2፡3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።
ከዚያም እውነቱ ይጠፋና በጨለማ ዘመን ውስጥ ይቀበራልና በመጨረሻው ዘመን ብቻ ነው ክርስቲያኖች ወደ ጳውሎስ ትምሕርቶች የሚመለሱት።
ስለዚህ ሲደግመው በዚህ በመጨረሻው ዘመን ውስጥ የምንኖረውን እያስጠነቀቀን ነው። ጳውሎስ የተናገረውን ብናምን ይሻለናል፤ አለዚያ እንረገማለን።
ጳውሎስን ብንቃወም ትልቅ አደጋ ውስጥ ነን። ታላቁ መከራ እንደ ደራሽ ውሃ እየመጣብን ነው፤ ብቸኛው ማምለጫችንም ጳውሎስ ወዳስተማረው ትምሕርት በመመለስ ነው። ዊልያም ብራንሃምም እራሱ ከጳውሎስ ትምሕርቶች ጋር መስማማት አለበት።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9 የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።
10 የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እያንዳንዱ አማኝ በ2000 ዓመታት ውስጥ የሚገነባው የእግዚአብሔር ታላቅ ቤተመቅደስ ውስጥ ሕያው ድንጋይ ነው። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምንም ብትገነቡ የምትገነቡት ጳውሎስ በመሰረተው መሰረት ላይ መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ።
ከጳውሎስ ጋር “አብረን” እንሰራለን። የራሳችሁን አስደናቂ ሃሳብ አታፍልቁ። ጳውሎስ ወደተናገረው ቃል ተመለሱ።
ሮሜ 16፡25 እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥
የጳውሎስ ወንጌል ከዚያ በኋላ ተከትለው ለመጡት የቤተክርስቲያን ዘመናት መሰረት ነበረ። ይህም ከአይሁድ ተሰውሮ የነበረ ታላቅ ምስጢር ነው። ከዚያ ቤተክርስቲያንም የሰው መሪዎችን ስትከተል ይህ እውቀት ጠፋባት። ከዚህም የተነሳ ስለ ቤተክርስቲያን ዘመናት የተሰጠው ትምሕርት በመጨረሻው ወይም በሰባተኛው ቤተክርስቲያን ዘመን እስኪመለስ ድረስ ከአሕዛብ መካከል ጠፋ።
ኤፌሶን 1፡9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን ታሪክ ለሰዎች ሚስጥር በሆነ መንገድ እንዲገለጥ አድርጓል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከእኛ ፈቃድ በጣም ይለያል።
ኤፌሶን 3፡3 አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍሁ፥ ይህን ምሥጢር በመግለጥ አስታወቀኝ፤
4 ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤
5 ይህም… ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።
አይሁድም ራሳቸው ሳራ ሚስቱ ሳትሆን እሕቱ እንደሆነች በመናገር የመጀመሪያ ፍቅሩን ከተወው ከአብራሃም ጀምሮ በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አልፈዋል። ከዚያም መጥምቁ ዮሐንስ በአይሁድ የመጨረሻ ወይም ሰባተኛ ዘመን በመምጣት ለኢየሱስ መንገድ ጠረገ፤ ኢየሱስም አይሁድ እምቢ አንቀበልም ያሉት ንጉስ ሆኖ ከአይሁድ የተደራጀ የሃይማኖት ሰፈር ውጭ ሞተ። የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ጻፎች እና ፈሪሳውያን መሲሃቸውን እንዳያውቁ የሕዝቡን ዓይን አሳወሩ።
ነገር ግን በአይሁድ ታሪክ ውስጥ ሁሉ ለ2000 ዓመታት የሚዘልቅ የቤተክርስቲያን ታሪክ የሚለው ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ሚስጥር ነበረ።
ኤፌሶን 5፡32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
ቆላስይስ 2፡2 ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ፤
የእግዚአብሔር አምላክነት ታላቅ ሚስጥር ነው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥
ከሰዎች አእምሮ በላይ በሆነ መንገድ ኢየሱስ ሰውም አምላክም ነው። ይህ ለማስተዋል ቀላል አይደል። ኢየሱስ ኃያል አምላክ መሆኑን ቤተክርስቲያንም ከጊዜ በኋላ ጠፋባት።
የሚገርመው ነገር አይሁድ ኃያሉ አምላክ ሰው ኢየሱስ መሆን እንደሚችል ማመን አቃታቸው። ቤተክርስቲያን ደግሞ ዛሬ ሰው የሆነው ኢየሱስ ሁሉን የሚችል አምላክ መሆኑን ማመነ አቅቷታል። የእግዚአብሔር ልጅ አድርገው ብቻ ያዩታል።
ግን የተፈጥሮ ብርሃንም ሚስጥር ነው። ብርሃን ልክ እንደ ጥይት በአንድ አቅጣጫ ብቻ እንደሚጓዝ ይመስላል ግን ደግሞ በአንድ ጊዜ ወደ ሁሉም አቅጣጫ እንደሚንቀሳቀስ ሞገድም ያረገዋል (ለምሳሌ አንድ ኩሬ ውስጥ ድንጋይ ብትጥሉ ሞገዶች በሁሉም አቅጣጫ እየሰፉ ይሄዳሉ)። ለመረዳት ቢከብድም እያየነው ይከሰታል።
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡7 የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።
የሃይማኖት አሳሳችነት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጀመረው ገና ከጥንቱ ዘመን ነው። ይህም የማሳሳት ሥራ እጅግ ስውር ከመሆኑ የተነሳ ቤተክርስቲያን ከሚሄዱ ሰዎች ብዙዎች ተታልለውበታል። የቤተክርስቲያንን ስሕተቶች በሚገባ የሚያጋልጡ በጣም ጥቂቶች ናቸው። እግዚአብሔር በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ምድርን ትቶ እስከሚሄድ ድረስ ይህንን ክፋት ያለማቋረጥ ይዋጋዋል። ከዚያ በኋላ ሰዎች ትልቅ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ። ዲያብሎስ በስተመጨረሻ የጥፋት ተልእኮውን እንደልቡ ይፈጽም ዘንድ ተፈትቶ ይለቀቃል።
ኤፌሶን 1፡10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
እግዚአብሔር የመጨረሻውን ዘመን እና የመጀመሪያውን ዘመን ወደ አንድ አይነት እምነት ይጠቀልላቸዋል።
ገላቲያ 1፡11 ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤
12 ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።
ማንም ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳች መጨመር አይችልም። ማንም መጽሐፍ ቅዱስን መለወጥ አይችልም። የዮሐንስ ራዕይ ወንጌል በየዘመናቱ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያልፍበትን ታሪክ በግልጽ ያሳያል። ሰይጣን ያለማቋረጥ የተለያዩ መሰናክሎችን አመጣ፤ እግዚአብሔር ግን እንዴት አድርጎ አንደሆን አማኞችን በተለያ ጊዜ በገጠማቸው ልዩ ልዩ ፈተናዎች ውስጥ ሁሉ በድል እንዲሻገሩ አደረገ።
1ኛ ጴጥሮስ 1፡13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
1ኛ ጴጥሮስ 1፡17 ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ብናስተውል በዚህ ዘመን መታለል አደጋው ምን ያህል ታላቅ መሆኑን እንገነዘባለን፤ በእግዚአብሔርም ፀጋ ላይ ያለን እምነት እርሱን እንድንፈራው ያደርገናል። በራስ ወዳድነት የግል ፍላጎታችንን እና ምኞታችንን ለመሙላት አንሯሯጥም።
የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ አጽንኦት የሚሰጠው ለኢየሱስ ነው፤ እንጂ ለአንድ ታላቅ ሰው አይደለም።
ራዕይ 1፡1 ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥
ምዕራፉ የሚጀምረው ኢየሱስ ላይ ትኩረት በማድረግ ነው። ኢየሱስ ማን ስለመሆኑ መገለጥ ካልተቀበልን ዓይናችንን ከእርሱ ላይ አንስተን አንድ ሰው ላይ እናሳርፋለን።
“ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር” -- ማለትም ኋላ የቤተክርስቲያን ታሪክ ሆኖ የሚታወቀውን። ልዩ ልዩ ፈተናዎች ሳይታሰቡ ክርስቲያኖች ፊት ይደቀናሉ። ጠላትን በምትጋፈጡ ጊዜ ከእግዘአብሔር ቃል ጋር ቁሙ እንጂ በራሳችሁ ሃሳብ አትራመዱ። ስሕተትን ስለመዋጋት ያላችሁ የራሳችሁ ሃሳብ ወደ ቤተክርስቲያን እየገቡ ካሉት የተሳሳቱ የሰው አመለካከቶች ላይ ተጨማሪ ስሕተት ብቻ ነው የሚሆነው።
ራዕይ 1፡2 እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ቁሙ። የኢየሱስ ምስክር ማለት ነገሮችን በእርሱ መንገድ ታደርጋላችሁ እንጂ በራሳችሁ መንገድ አታደርጉም ማለት ነው። የኢየሱስ መንገድ ሁልጊዜም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ይገኛል።
ራዕይ 1፡3 ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስን ነው የምናነበው እንጂ የአንድን ግለሰብ አመለካከት አይደለም። አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ሲነብብ ስትሰሙ ብቻ ነው የምትባረኩት፤ ነገር ግን በተጻፈው ቃል መጽናት አለባችሁ። የእግዚአብሔርን ቃል ጠብቁ እንጂ ለራሳችሁ እንዲስማማችሁ አትለውጡት። እውነት ሁልጊዜ ለእኛ ሰውኛ ምቾትና ድሎት ላይስማማ ይችላል። ደግሞም እውነት ከሰዎች አመለካከትም ጋር አይገጥምም።
ራዕይ 1፡4 ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ … ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን…
ይህ የዮሐንስ ራዕይ በዋነኛነት የተጻፈው ለሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እውነትን ከሐዋርያት ተቀብለዋል። የእነርሱ ፈተና አዲስ ኪዳንን ማመን እና ላመኑበት ለመሞት ዝግጁ መሆን ነበር። በ64 ዓ.ም. ሮማዊው ንጉስ ኔሮ ክርስቲያኖች ላይ ከባድ መከራ አስነሳ። በቤተክርስቲያን ታሪክ በመጀመሪያዎቹ 250 ዓመታት ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ክርስቲያኖች በሮማውያን ነገሥታት ተገድለዋል። ሞትን እንደ ዋነኛ ጠላታቸው ነበር የተጋፈጡት።
ከዚያም እውነት ጠፋች። ስለዚህም በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ የተሰጡ ምልክቶች ትርጉማቸው ምን እንደሆን ሰዎች አንዳችም እውቀት አልነበራቸውም። በመጨረሻው ዘመን ምልክቶቹ በሙሉ ምን ማለት እንደሆኑ እንደገና ይገለጣል። ስለዚህ ዮሐንስ መልዕክቱን የጻፈው በቀጥታ ለመጨረሻው ዘመን ክርስቲያኖች ነው። እነርሱ ብቻ ናቸው እርሱ ምን ማለቱ እንደሆነ የሚረዱት።
የእግዚአብሔር ጸጋ ምትክ የለውም። እግዚአብሔር ብቻ ነው ክርስቲያኖችን ሊረዳ የሚችለው። በክፉና አታላይ ዓለም ውስጥ ስንኖር ከእግዚአብሔር የሆነ ውስጣዊ ሰላም ያስፈልገናል። ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው። እኛ ለፈቃዱ መገዛትን መልመድ አለብን።
ሰባት የሙላት ምልክት ነው። ሰባት ቀናት የአንድ ሳምንት ሙላት ናቸው። በቀስተ ደመና ውስጥ ጎልተው የሚታዩ ቀለማት ናቸው። ሙዚቃ ውስጥ ዋነኞቹ ድምጾችም ሰባት ናቸው፤ እነርሱም “ዶ፣ ሬይ፣ ሚ፣ ፋ፣ሶ፣ ላ፣ቲ”። እግዚአብሔርም የቤተክርስቲያንን ታሪክ ሙሉ እቅድ ለመግለጥ የሚያስፈልጉት ሰባት ቤተክርስቲያኖች ብቻ ናቸው።
እግዚአብሔርም እስያን መረጠ። እስያ በእንግሊዝኛ ፊደሎች Asia ተብሎ ሲጻፍ የመጀመሪያም የመጨረሻም ፊደሉ A ነው። ስለዚህ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር አንድ አይነት መሆን አለበት። እስያ የአሕዛብ ግዛት ነው። ይህም የሚያመለክተው (የዮሐንስ ራዕይ እየተጻፈ በነበረበት ሰዓት ለነበሩ ሰዎች) የወደፊቷ ቤተክርስቲያን በዋነኝነት አሕዛብ እንደሚኖሩባት ነው።
“ካለው” (አሁን እኛ ያለንበት ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን) “ከነበረው” (የበፊቱ፤የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ለሁሉም ዘመናት የሃላፊ ወይም ያለፈ ጊዜ ነው። እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን እግዚአብሔርን ያገለገሉት ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በተመለሱበት መጠን ነበር) “ከሚመጣውም” (የወደፊቱ ዘመን። ኢየሱስ “የሚመጣው” የመጨረሻው ዘመን ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ ወደ መጀመሪያው ዘመን ክርስቲያኖች ሲመለሱ ነው። ከታላቁ መከራ ነጻ የሚሆነውና ታላቅ ተሥፋ ያለው ይህ ማሕበር ብቻ ነው።)
ሰባቱ መናፍስት። እግዚአብሔር አማኞች በየዘመናቱ የሚነሱ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶችን ማሸነፍ ይችሉ ዘንድ የመንፈሱን የተለያዩ ባሕርያት ያካፍላል። በእያንዳንዱ ዘመን የተለየ የእግዚአብሔር ባሕርይ እንደሚገለጥ ሁሉ አንዱ ዘመን ከሌላው የተለየ ነው። እኛ የምንኖርበት ሰባተኛው ዘመን በሃብት ብዛት ውስጥ እየዋኘ ነው፤ ነገር ግን የስሕተት አስተምሕሮ ሲስፋፋ በስውር እንደመሆኑ መጠን ስሕተትን ለመቋቋም እንድንችል ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ያስፈልገናል። በአራተኛው ዘመን በተነሳው የጨለማ ዘመን የነበራቸው እውነት ትንሽ ብቻ ነበር ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይነበብ ታግዶ ነበር፤ ከዚህም የተነሳ የያዟትን ጥቂት እውነት ላለመካድ እና ስለ እውነት ብሎ ተሰቅሎ በእሳት ለመቃጠል ትልቅ ወኔ ይጠይቅ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር የእያንዳንዱ ዘመን ቤተክርስቲያን በሚገጥማት ልዩ ፈተና ውስጥ ተቋቁማ የምታልፍበትን አቅም ታገኝ ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን በሰባት የተለያዩ መንገዶች ገልጧል።
ለምሳሌ አንዲት ሴት የአንድ ወንድ ሚስት፣ ለእናቷ ሴት ልጅ፣ ለልጆቿ እናት፣ ለጎረቤቶቿ ባልንጀራ፣ በሥራ ቦታ ላሉት ባልደረባ፣ በእርዳታ ሥራ ውስጥ አጋዥ ልትሆን ትችላለች። በእያንዳንዱ ወቅት አብረዋት ካሉት ሰዎች አንጻር እንደያስፈላጊነቱ በተለየ ባሕርይ ትገለጣለች። ሁሌም ያው የማትለወጥ አንዲት ሴት ነች፤ ግን በውስጧ ያለውን መንፈስ በሰባት የተለያዩ መልኮች ትገልጣለች። እንደ ሚስት “ባሌ ያዘዘኝን አደርጋለው” ስትል እንደ እናት ደግሞ “ልጄ እኔ ያዘዝኳትን ታደርጋለች”። ሴትየዋ ግን አንድ ነች።
ራዕይ 1፡5 … ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
በሚለዋወጠው የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንድ ብቸኛ ታማኝ ምስክር አለ፤ እርሱም ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ የማይሞት አካል የተነሳው እርሱ ነው። የመጨረሳ የቤተክርስቲያን ዘመን የሚዘጋው በሙታን ትንሳኤ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ለትንሳኤው ዝግጁ እንሆን ዘንድ የሚያስፈልገንን ፍንጭ ሁሉ ይሰጠናል።
ልዑሉ ከንጉሱ ስልጣን ይረከባል። ኢየሱስ የምድር ነገስታት ሁሉ አለቃ (ልዑል) ነው። ተመልሶ ሲመጣ ከምድር ላይ ከሚጠፉ ነገስታት ሁሉ ስልጣናቸውን ይወስድና መንግስቱን በምድር ላይ ይመሰርታል።
ኢየሱስ ይወደናል፤ ስለዚህ ከታላቁ መከራ ያድነን ዘንድ እውነትን እንድናምን ጥረት እያደረገ ነው።
ከሲኦል ለመዳን መንገዱ አንድ ብቻ ነው። እርሱም ሐጢያታችንን መናዘዝ እና በኢየሱስ ደም መታጠብ ነው። በዚህ መንገድ ከሲኦል እንድናለን። ይህ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ጸንቶ የቆየ ወሳኝ አስተምሕሮ ነው።
የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ግን ተጨማሪ ችግር ያጋጥማታል ምክንያቱም ዘመኗ የሚጠናቀቀው በታላቁ መከራ ነው፤ እኛ ደግሞ ከሲኦል ብንድንም እንኳ ከታላቁ መከራም መዳን ያስፈልገናል። የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን መመለስ ማለት ይህ ነው። የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን የነበራት አይነት እምነት ብቻ ነው ከታላቁ መከራ የሚያድነን።
ራዕይ 1፡6 መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።
በሺ ዓመት መንግስት ውስጥ ከክርስቶስ ጋር ነገስታት ሆነን በምድር ላይ እንገዛለን። የሙሽራይቱ አካል ሁሉ የክሕነቱ አካል ነው። በአምስቱ ስጦታዎች አማካኝነት በመስራት በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል የሚቆም የአሮን ክሕነት አይኖርም። ነገስታት እና ካሕናት እንደመሆናችን ከበላያችን ከፍ የሚልብን ሰው አይኖርም። ልክ በዚህ መንገድ ቤተክርስቲያን በእኩልነት ላይ የተመሰረተች የወንድማማች ሕብረት ሆና መንቀሳቀስ ያስፈልጋታል፤ እንጂ ሕዝቡ ዝቅ ብለው የሚገዙለት ከፍ ያለ ቄስ ወይም ፓስተር አያስፈልግም።
ካሕናት እና ፓስተሮች የሕዝቡን አክብሮት እና ለራሳቸው ከፍ ያለ ስልጣን ይወዳሉ። በሰዎች ላይ ገዥ መሆንን ይወዳሉ። ይህም ለራሳቸው ያላቸውን ከፍ ያለ ግምት ይጨምርላቸዋል። በሰዎች ላይ ክብር እና ስልጣን ሁሉ የኢየሱስ ብቻ ነው። ሰውን ማሞገስ የውድቀት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። በሰው ላይ መደገፍ ወደ ተሳሳተ መንገድ ይመራናል።
ራዕይ 1፡7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።
የሚመጣው ከደመናት ጋር ነው፤ በእንግሊዝኛው ደመናዎች ብሎ በብዙ ቁጥር ነው የተጻፈው። የክብር ደመናዎች አካሉን ከብበውት ይታያሉ። ከደመናዎች ጋር ይመጣል እንጂ እንደ ደመና አይመጣም።
ዓይን ሁሉ ሲያየው የሚመጣበት ጊዜ በታላቁ መከራ ማብቂያ ላይ ለአርማጌዶን ጦርነት የሚመጣበት ሦስተኛ ምጻቱ ነው። እንቅልፋሞቹ ቆነጃጅት በሙሉ በታላቁ መከራ ውስጥ ተገድለዋል። 144000ዎቹም ተገድለዋል። አውሬውና እርሱን የሚያገለግሉት ብቻ ሌሎችን ሁሉ አጥፍተው እነርሱ ቀርተዋል። ለዚህ ነው ሁሉም ዋይ ዋይ የሚሉት። ለሰሩት ጥፋት ሁሉ እና ንጹሆችን ስለመግደላቸው እንደሚጠየቁበት ያውቃሉ።
“አዎን።” እንዲህ ነው መሆን ያለበት። የመጽሐፍ ቅዱስዋ ሙሽራ መከራውን ታመልጣለች። የቀሩት ክርስቲያኖች በመከራው ውስጥ ይገደላሉ።
የሐዋርያት ሥራ 1፡9 ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።
ከደመና ጋር ሄደ እንጂ እንደ ደመና አልሄደም።
11 ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።
በደመና ይመጣል እንጂ እንደ ደመና አይመጣም።
ራዕይ 1፡8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
የመጀመሪያ እና የመጨረሻ መሆኑን ሁለት ጊዜ በመናገር አጽንኦት ይሰጠዋል። ለምን? የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያን እንደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እንድታምን ስለሚፈልግ ነው። ጅማሬው ላይ የተዘራው ዘር ፍጻሜው ላይ ከሚታጨደው ጋር አንድ አይነት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ የሚሰጠን ማስጠንቀቂያ -- ልክ የጥንቷን ቤተክርስቲያን የምንመስል ካለሆንን ሙሽራይቱን ከምድር ላይ በሚወስድበት ጊዜ ከመኸሩ ውስጥ አንገኝም።
“ያለው” ማለትም አሁን። “የነበረው” ድሮ ወይም በፊት። ሌላ ማስጠንቀቂያ -- አሁን በምንኖርበት ዘመን የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ወደነበረችበት መመለስ አለብን። ከመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ስንሆን ብቻ ነው እቅዱን መፈጸም የሚችለው፤ ማለትም ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ለመውሰድ “የሚመጣው”። ይህ የወደፊት ጊዜን አመልካች ነው። ስለዚህ ወደ ቀድሞ ቦታዋ የተመለሰችዋ ሙሽራ ታላቅ ተስፋ አላት።
ግን ደግሞ እየተከታተሉ የሚመጡትን ሊቀ ጳጳሶች ተመልከቱ።
ራዕይ 17፡8 …አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ…
አንድ ሊቀ ጳጳስ እየመራ ነበረ። ሲሞት የለም። አዲስ ሊቀ ጳጳስ ሲመርጡ ደግሞ እንደገና አለ። የጳጳሶች መተካካት በምዕራቡ ዓለም ከተመዘገቡ ስርወ መንግስታት ሁሉ ረጅሙ ነው። ነገር ግን ልብ በሉ፤ “ነበረ” ማለት ያለፈ ጊዜን ያመለክታል። “እንደሌለ” ደግሞ የአሁን ጊዜን ያመለክታል። “ነገር ግን እንዳለ” የሚለውም የአሁንን ጊዜ ነው የሚያመለክተው። ስለዚህ የሊቀ ጳጳሶች መተካካት የአሁን ጊዜን እና ያለፈ ጊዜ በሚያመለክቱ ቃላት ነው የተገለጸው። ይህም የወደፊት ጊዜ እንደሌለ ነው የሚነግረን። ማለትም በሌላ አነጋገር ለሊቀ ጳጳሶቹ መኖሪያ ለሆነችው ከተማ ለቫቲካን ወይም የባቢሎን ሚስጥር የወደፊት ተስፋ የላትም። እነርሱም በኑክሊየር ቦምብ ይጠፋሉ።
ራዕይ 18፡9 ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤
10 ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው፦ አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
ለምንድነው በርቀት ቆመው የሚጮሁት? ለምን ወደ ውስጥ ገብተው እሳቱን አያጠፉትም? ምክንያቱም ማንም ሊያጠፋው የማይችል የኑክሊየር ቦምብ ፍንዳታ በመሆኑ ከውስጡ የሚወጡ አደገኛ ጨረሮች ቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለሚገድሉ ነው። የኑክሊየር ቦምብ በፈነዳበት ማንም ጠጋ ብሎ ማየት አይፈልግም።
“ሁሉን የሚገዛ ጌታ”። ኢየሱስ ነው ሁሉን የሚገዛ ጌታ። እርሱን የሚተካከል ማንም የለም። ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ለማድረግ ከፍ አታድርጉት። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንደሆነ ካሰባችሁ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ምንም አላወቃችሁም። እግዚአብሔር እንደ ፀሃይ ቢሆን ሰው እንደ ኮከብ ነው። ፀሃይ በወጣችበት ሰዓት ከከዋክብት ሁሉ ደማቁ ኮከብ ሊያበራ አይችልም።
ራዕይ 1፡9 እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
“ሰው የቤተክርስቲያን መሪነትን ሲመኝ እንዲህ ይላል፡- ፓስተር በሉኝ። እኔ ከእናንት በላይ ነኝና ተገዙልኝ”። ዮሐንስ ግን ምን እንደሚል ስሙ “እኔ ወንድማችሁ”። ይህ ታላቅ ሐዋርያ በታላቅነቱ እና በማዕረጉ ሊያሸማቅቀን አይሞክርም። እርሱ ከተመረጡት ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር። የሐዋርያነት ማዕረግ እንዳለው በየጊዜው ሁሉ ማወጅ ይችል ነበር። ግን አያረገውም። በዘመናት ውስጥ በቤተክርስቲያን ላይ ትልክ ጥፋት ያደረሱት የመሪነት ማዕረግ እና መጠሪያቸውን አብዝተው የሚወዱ ሰዎች ናቸው። ሰው የቤተክርስቲያን መሪ መሆኑ ሁሌም ትልቅ ጥፋት ነው። ስለዚህ ይህ ትልቅ ሐዋርያ “እኔ ወንድማችሁ” በማለት ድንቅ ምሳሌ ሆኖልናል። እናንተ ከእኔ ጋር እኩል ናችሁ ማለቱ ነው። ከሕዝቡ በላይ ከፍ የሚል የአሮን ክሕነት አገልግሎት የለም።
ሰውን ከፍ ማድረግ የኒቆላውያን ትምሕርት ነው። እርሱም ክፉ ትምህርት ነው።
“ከናንተም ጋር አብሬ መከራውን … የምካፈል”። ቤተክርስቲያን ብዙ የምትቀበለው መከራ አለባት። በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ አማኞች ለእምነታቸው ሕይወታቸውነ በመሰዋት ዋጋ ይከፍላሉ። ክርስትና ለቦቅቧቆች አይደለም። ዮሕንስ የጽገሬዳ አልጋ አላነጠፈላችሁም። ያቀረበላችሁ መከራ ነው። ሊሰብኩ ወደ ሩቅ ሃገሮች የሄዱ በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጌል መልእክተኞች ሚሽነሪዎችን እንዴት እንደታገሉ እና ሊሰብኩ በሄዱበት ሃገር እንዴት እንደሞቱ ጠይቁዋቸው። የቴሌቪዥን ወንጌላውያንን እና በሞልቃቃ ቤታቸው የሚኖሩትን የትልልቅ ቤተክርስቲያን ሕንጻ ባለቤቶችን አትጠይቁዋቸው። እነርሱ የሳቱት ነገር አለ።
በጣም ቀላል የሆነ የበለጸገ የክርስትና ሕይወት እየኖርክ ከሆነ ተጠንቀቅ። ምናልባት ለሰይጣን ምንም ስጋት እየፈጠርክበት አይደለህም፤ ለዚህም ይሆናል በሰላም ትቶህ ዞር ያለው።
ፍጥሞ ደሴት በሮማ ግዛት ውስጥ እጅግ ቆሻሻ ለተባሉ ወንጀለኞች መጣያ እስር ቤት እንድትሆን የተለየች ደሴት ናት። ዮሐንስ በኔሮ ትዕዛዝ በግፍ ነው ወደ ፍጥሞ ደሴት ግዞት ቤት የተጣለው። ኔሮ ከ54 እስከ 68 ዓ.ም. በስልጣን የተቀመጠ ሲሆን ከሮማውያን ነገስታት ሁሉ በክፋቱ አንደኛ ነበረ። ኔሮ በ68 ዓ.ም. ሲሞት በእርሱ ዘመን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እርሱ ሲሞት ተፈትተው ተለቀቁ። ከዚያም ዶሚቲያን ከ81 እስከ 96 ዓ.ም. ሲነግስ ዮሐንስን መልሶ የፍጥሞ ደሴት እስር ቤት ውስጥ ጣለው። ዮሐንስ በስተመጨረሻ የተፈታው ዶሚቲያን ሲሞት ነው። የታሪክ ምሁራን እንደሚሉት ዮሐንስ ከእስር ቤት ሲወጣ ለፍጥሞ ቅርብ ወደሆነችው ወደ ኤፌሶን ሄዶ ለመጨረሻ ጊዜ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን አሰባስቦ ጠረዘ፤ በሕይወት የተረፈ ሐዋርያ እርሱ ብቻ እንደመሆኑ ይህን ለማድረግ የሚበቃ ምሪት ከእግዚአብሔር ሊቀበል የሚችለው እርሱ ነው። ዮሐንስ እግዚአብሔርን በምድር ላይ በሰው መልክ ኢየሱስ ተብሎ ሲኖር ያውቀው ነበር።
ዮሐንስ የታሰረው ለመጽሐፍ ቅዱስ በመቆሙ ነው።
እኛም በስተመጨረሻ የምንፈተንበት ፈተና ይኸው ነው። በዙርያህ ያሉ ሕዝብ ሁሉ የሆነ ሰው በተናገረው ቃል ላይ ሲቆሙ ለመጽሐፍ ቅዱስ መቆም ትችላለህ?
ራዕይ 1፡10 በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥
የጌታ ቀን ከሳምንቱ ቀናት አንድ ሳይሆን የመከራ ቀን ነው።
ኢሳያስ 13፡6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
9 እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
አሞጽ 5፡20 የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?
ኤርምያስ 46፡10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።
የራሺያ ሰራዊት። ራሺያ ከእስራኤል በስተ ሰሜን ትገኛለች። የሰሜኑ ንጉስ በስተመጨረሻ በታላቁ መከራ ውስጥ ይደመሰሳል።
ራዕይ 1፡11 እንዲሁም፦ የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ።
ኢየሱስ በድጋሚ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው የሚለውን ቃል በአጽንኦት ይናገራል። የመጨረሻው ዘመን ወደ መጀመሪያው ዘመን መመለስ አለበት።
እስያ “ASIA ” የሚለው ቃል እራሱ በእንግሊዝኛ ፊደሎች ሲጻፍ የመጨረሻ ፊደሉ “ASIA” በመሆኑ ከመጀመሪያው ፊደል “ASIA” ጋር አንድ ነው።
ሰባቱ ቀያይ ነጠብጣቦች በእስያ ያሉትን ሰባቱን ቤተክርስቲያኖች ይወክላሉ። አረንጓዴ ነጥብ ያለበት ቦታ ሮም ነች።
እነዚህ ሰባት ከተሞች በመልእክት ማመላለሻ መንገድ ላይ ይገኛሉ። እግዚአብሔር ባሕርያቸውን ከገለጸ በኋላ በመልእክት ማመላለሻ መንገዱ ላይ ብቻ አይደለም መልእክት የላከው፤ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚከሰቱ ታሪኮችንም በመግለጥ “በዘመናት የመልእክት ማመላለሻ መንገድም” ላይ ጭምር ነው መልእክቱን የላከው። ሰይጣን የወደፊቱን ማየት ስለማይችል ሁልጊዜ በጊዜ እንደተሸነፈ ነው። እግዚአብሔር በጊዜ ላይ ስልጣን እንዳለው ለማሳየት ስለወደፊቱ ትንቢት ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስን ልዩ የሚያደርገው ትንቢት ነው። ትንቢት የእግዚአብሔር ማሕተም ነው።
ሰባቱ ቤተክርስቲያኖች
ከላይ የቀረበው ካርታ ከኤፌሶን (1) እስከ ሎዶቂያ (7) የተዘረጋውን የመልእክት ማመላለሻ መንገድ በአካባቢው ያሉትን ሁለት ወንዞች ያሳያል።
አሁን የመልእክቱን ሃይለኛነት እናያለን። እግዚአብሔር የእያንዳንዱ ከተማ ባሕርይ ወደፊት ከሚመጡት የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር እንዲመሳሰል አድርጓል። እነዚያም ወደፊት የሚመጡ ዘመናት የሚገለጡበት ቅደም ተከተል ከተሞቹ በመልእክት ማመላለሻ መንገዱ ላይ በተሰለፉበት ቅደም ተከተል መሰረት ይሆናል። ይህም በሰው ታሪክ ውስጥ የሚፈጠሩ ክስተቶች ሁሉ ምን ያህል በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ እንደሆኑ ያመለክታል።
ቅደም ተከተሉ አንድ በአንድ ይገለጣል።
መንገዱ ከኤፌሶን ተነስቶ የፖለቲካ ከተማ ወደሆነችው ጴርጋሞን (3) እስኪደርስ ወደ ላይ ይሄድና ይታጠፋል። ይህም ንጉስ ኮንስታንቲን ፖለቲካ እና ፓጋዝምን (አረማዊነትን) ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በግድ ያስገባበት ጊዜ ነው። ኮንስታንቲን ለሮማው ጳጳስ በሰጠው ሃብት እና ትልቅ የላተራን ቤተመንግስት የሮማው ጳጳስ በማዕከላዊነት ለተደራጀችው ቤተክርስቲያን ራስ ሆነ፤ እርሷም የሮማ መንግስት በባርቤሪያን ወረራ አማካኝነት ከፈራረሰ በኋላ እንኳ ብቸኛዋ ሳትወድቅ የቀረችው ሮማዊ ድርጅት ናት። ከዚያ ረሃብ፣ ወረርሽኝ፣ ሁከት እና በጨለማው ዘመን በሃይማኖት ምክንያት ግድያ ተጀመረ። ሊቀ ጳጳሶቹም የመስቀል ጦርነት ብለው ወደ ፓለስታይን ዘመቻ በመላክ በሙስሊሞች ላይ የተደረገውን ግድያ አበረታቱ። በዚያው ዘመን ውስጥ ትንንሽ የመነቃቃት ብርሃን ፍንጣቂዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነበር፤ ለምሳሌ በደቡባዊ ፈረንሳይ ውስጥ የአልቢጀንሶች መነቃቃት፤ በአልፕስ ተራሮች ውስጥ ዋልደንሶች፤ እና የቦኸሚያው ጃን ሁስ፤ ነገር ግን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁሉንም አዳፈነቻቸው። ከዚያም ቤተክርስቲያን በማርቲን ሉተር (5) ተሃድሶ አማካኝነት እና በጆን ዌስሊ (6) የሚሽነሪ ወይም የወንጌል ስብከት ዘመን እንዲሁም ሎሳንጀለስ ውስጥ በ1906 የሎዶቂያ ቤተክርስቲያንን ዘመን ባስጀመረው በጴንጤ ቆስጤ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት አማካኝነት ኤፌሶን ወደ ነበረችበት ደረጃ መመለስ ጀመረች (7)።
በስተመጨረሻም ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት መነቃቃት አስፈለጋት። ሁሉ ወደተጀመረበት ወደ ሐዋርያዊ አባቶች ትምህርት የሚመልሰን እንደ ኤልያስ ያለ ነብይ አስፈለገን።
ነገር ግን ቤተክርስቲያን የጀመረችው አንድን ሰው ፓስተር አድርጎ ሹሞ ሰውን መሪ የማድረግ ልማድ የመነቃቃት እና ወደ ሐዋርያዊ እውነት የመመለሱን እንቅስቃሴ አሰናከለው። ከዚያም ደግሞ እነዚህን ከፍ ያሉ ፓስተሮችን የሰዎችን ጥቅሶች ተርጓሚ አድርጎ የመከተል አባዜ ተጀመረ፤ ትርጓሜያቸውም ወደፊት የሚከሰቱ ነገሮችን ያለፉ አድርጎ መተርጎም ነበር። የ1963 ታላቁ ደመና የጌታ ምጽአት እና የራዕይ 10 ታላቅ መልአክ መውረድ ተባለ። በሜሴጅ አማኞች ዐይን የወንድም ብራንሃም ምስል ከነብይነት “የሰባተኛው መልአክ ድምጽ” ወደመሆን ተለወጠ። ብራንሃም የማይሳሳት ተደርጎ ተቆጠረ፤ ከእርሱ ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች እንደ አምላክ ቃል እንደ “የእግዚአብሔር ድምጽ” ከፍ ተደርገው ባስፈለገ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን መተካት ይችላሉ ተባለ። እርሱም “የሰው ልጅ መገለጥ” ነው ተብሎ ከሰው ደረጃ ከፍ አለ። በአሕዛብ የመጀመሪያ ዘመን ላይ ባቢሎን ውስጥ የነብዩ ዳንኤልን ምስል በግዴታ “ማምለክ” ተጀምሮ ነበር። በመጨረሻው የሎዶቂያ የአሕዛብ ዘመን ባቢሎናዊ ምስጢሮችን ወደተገለጡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ውስጥ እያሾለኩ መቀላቀል የሜሴጅ አማኞችን ወደ ስሕተት ጥልቀት ይዟቸው ገብቶ ነብያቸውን ፍጹም የማይሳሳት፤ ከንግግሩ የተወሰዱ ጥቅሶችን በእግዚአብሔር ቃል ፈንታ መቆም የሚችሉ ቃሎች አድርጎ የመውሰድ ቅዠት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር። (Vicarius Filii Dei “በእግዚአብሔር ልጅ ፈንታ” ማለት ነው። ይህ 666 ነው፤ የአውሬው ምልክት ቁጥር። እነዚህ የሜሴጅ አማኞች በአደጋ ውስጥ ናቸው)።
ማንም ኢየሱስን ሊተካ ወይም በእርሱ ቦታ ሊቆም አይችልም።
ስለዚህ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የመጨረሻ ምስጢር አላቸው።
ግለሰቦች ከተመረጡ ጥቅሶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትርጓሜዎችን ካባጁ ከሜሴጅ ቡድኖች ውስጥ መውጣት ያስፈልጋቸዋል።
አንድ ፓስተር ለብቻው የያዘው ስልጣን በሽማግሌዎች ጉባኤ መተካት አለበት፤ እነርሱም መንጋውን መመገብ አለባቸው።
አስራት ለፓስተሩ ነው የሚል አንድም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
የቤተክርስቲያን ሕንጻ ውስጥ ወይም ድንኳን ውስጥ መሰብሰብ አለብን የሚል አንድም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
የጥንት አማኞች በቤቶች ውስጥ ነበር የሚሰበሰቡት። ስለዚህ ብንከተለው ለስሕተት የማያጋልጠው ምሳሌ ይህ ነው፤ ወደዚህ መመለስ አለብን።
ሮሜ 16፡3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
5 በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ…።
1ኛ ቆሮንቶስ 16፡19 የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
የሐዋርያት ሥራ 8፡3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።
ቆላስያስ 4፡15 በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልን።
የመጨረሻው እንቅስቃሴ ከሎዶቂያ (7) ቤተክርስቲያን አምልጠው ወደ ኤፌሶን (1) መመለስ ለሚችሉ ግለሰቦች ነው፤ ይህም የሚሆነው ሙሉ በሙሉ ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን መመለስ እንድንችልና ተቆራርጠው የቀረቡ ጥቅሶችን በመገጣጠም ከሚፈጠሩ ስሕተቶች ነጻ እንድንወጣ ነው።
በአንድ ሰው አገዛዝ ከሚመራ የሰው ቤተክርስቲያን ነጻ እንድንወጣ ነው።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
ኢየሱስ ከሎዶቂያ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ውጭ በደጅ ቆሟል። ይህ መልእክት የማይመለከተው የለም። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን ሁሉ በየአይነታቸው ይመለከታቸዋል። ኢየሱስ ጥሪውን የሚያቀርበው ለግለሰቦች ነው።
ዛሬ ሊኖረን የሚችለው ግብ አንድ ብቻ ነው፡- የቤተክርስቲያን ዘመን ወደተጀመረችበት ወደ ኤፌሶን መመለስ አለብን። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው ማድረግና መመን ያለብን።
የከተሞቹ ስሞች ራሳቸው ሲተረጎሙ በታሪካቸው ውስጥ የተገለጡትን ክስተቶች ነው የሚመሰክሩት።
“ወደ ኤፌሶን (የተዘናጋች፣ ኢላማ ያለመች) ወደ ሰምርኔስ (መራራነት፣ ሞት) ወደ ጴርጋሞንም (ሙሉ በሙሉ የተዳረች) ወደ ትያጥሮንም (አምባገነን ሴት) ወደ ሰርዴስም (ያመለጡ ሰዎች) ወደ ፊልድልፍያም (የወንድማማች መዋደድ) ወደ ሎዶቅያም (የሕዝብ መብቶች)”።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በጳውሎስ እና በሐዋርያት ምክንያት እውነትን ይዛ ነበር ግን ሐዋርያቱ ሲሞቱ አማኞች ተዘናጉ። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለመሆን አለሙ ነገር ግን ነቅተው መጠበቅን ትተው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እንግዳ የሰው ሃሳቦች ሲገቡ ቸል በቸልታ ተመለከቱ። የሰው አመራር በቤተክርስቲያን ላይ ገዥ እየሆነ ሲመጣ እግዚአብሔር ስደትን በማስነሳት በቤተክርስቲያን ላይ የሰው ገዥነት ይቀንስ ዘንድ ተበታትነው በትናንሽ ቡድኖች እንዲሰበሰቡ አደረጋቸው። በዚህ የሮማ መንግስት ውስጥ በተነሳው መራራና ከባድ ስደት ሶስት ሚሊዮን ክርስቲያኖች ሞቱ። የሮማ መንግስት ከምድር ገጽ ሊያጠፋቸው በተነሳ ጊዜ መራራነት እና ሞት የክርስቲያኖች የዘወትር ባልንጀራቸው ነበሩ። በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የሮማው ንጉስ ኮንስታንቲን አስቆመ ነገር ግን ይህ ያስከተለው ክፍያ ቤተክርስቲያንን ወደራሱ ፖለቲካዊ ቁጥጥር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተድራ እንድትገባ በማድረግ ነው። በተጨማሪም ኮንስታንቲን ቤተክርስቲያን ከፓጋን አረማዊ ባሕሎች ጋር ሙሉ በሙሉ እንድትጋባ አስገደዳት ይህንንም ያደረገው አረማውያን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደራሳቸው ቤት ምቾት እንዲሰማቸው በማሰብ ነው። ለምሳሌ ዲሴምበር 25 የፀሃይ አምላክ ልደት ቀን የኢየሱስ ልደት ነው በማለት። ከዚያም በባርቤሪያን ወረራ የሮማ መንግስት ፈራረሰ፤ ባርቤሪያኖችም ንጉሶቻቸው እንዳይገደሉባቸው ብለው እንዲቀቡላቸው ስለሚፈልጉ በዚህ አጋጣሚ የሮማ ሊቀ ጳጳስ ወደ ስልጣን ወጣ። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተቀባ ሰው ብቻ ነበር ሕጋዊ ንጉስ መሆን የሚችለው። ስለዚህ የባርቤሪያውያን ነገስታት ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥበቃ አደረጉላት፤ ቤተክርስቲያኒቱም በታላቅ ኃይል በመሰልጠን አውሮፓ በሙሉ ተቆጣጠረች።
ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ትባላለች።
በዚህ መንገድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጨለማው ዘመን አምባገነን ሴት ሆነች።
ከዚያም ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር የካቶሊክን ትምሕርት እምቢ ብለው ከፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ጋር የተቀላቀሉትን ከእጇ ያመለጡትን ሰዎች የመራበት ተሃድሶ መጣ። ቀጥሎም ጆን ዌስሊ ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉትን ለማዳን የስብከት አገልግሎት ጀመረ። ከዚያም ሚሽነሪዎች ለአሕዛብ ወንድሞቻቸው ባላቸው ፍቅር የተነሳ ባሕር አቋርጠው ለስብከት የሄዱበትና አሕዛብን ለማዳን የደከሙበት እንዲሁም በባእድ ሃገር ሕይወታቸውን የሰዉበት የወንድማማች ፍቅር የተገለጠበት የወንጌል ስርጭት ዘመን ተከትሎ መጣ።
ከዚያምደ ደግሞ ወከባ እና ውዥንብር የበዛበት የኛ ዘመናዊ ጊዜ ሁለት አስከፊ የዓለም ጦርነቶችን፣ አስደናቂ የቴክኖሎጂ እድገቶችን፣ እጅግ አስገራሚ የእቃ ምርትና እና የሃብት መብዛትን እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ እምነትን የሚያጠፉ ኤቮሉሽን ወይም አዝጋሚ ለውጥ እና ቢግ ባንግን የመሳሰሉ ነጻ አስተሳሰቦችነ አስከትሎ መጣ። ሰዎች ዓይናቸውን ከእግዚአብሔር ላይ ዞር አድርገው ስግብግብነትና ራስወዳድነትን ለመከተል መብታቸውን እና በሐጢያት የመኖር ነጻነታቸውን የማስከበር አባዜ ተጠናወታቸው። የሕዝቡ መብቶች ሰዎች የሕይወት ዘይቤያቸውን እና ካሉት 30000 አይነት ቤተክርስቲያነች ውስጥ የፈለጉት ቤተክርስቲያን በመሄድ እምነታቸውን የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠይቁ አደረገ። ክርስቲያኖች የመረጡትን ፓስተር ከፍ የማድረግ እና የመከተል መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ይፈልጋሉ። ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶችን በራሳቸው ፈቃድ የተርጎም እና እነዚህን ጥቅሶች የማይሻሩ እውነቶች አድርገው የመቀበል መብት እንድከበርላቸው ይሻሉ። እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ወደተጻፈው ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት ትምሕርት ከልብ መመለስ የሚፈልጉ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። የሚያሳዝነው ይህ ብዙ ጥበብ የተለቀቀበት ዘመን በሃብት እና በሰው ብልሃት መታወሩ መጨለሙ እውነተኛ ራስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከቤት ውጭ አስወጥቶ በር መቆለፉ አሳዛኝ ነው።
ከውስጥ ሌላ ራስ አለ፤ እርሱም ፓስተሩ ነው። ነገር ግን እውስጥ ጨለማ ነው ያለው ምክንያቱም ብርሃኑ ከውጭ ቆሟል።
ዮሐንስ 3፡19 ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
በእንደዚህ አይነቱ ዓለም ላይ ታላቁ መከራ እንደ ደራሽ ውሃ እና እንደ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በድንገት ይመጣል።
ራዕይ 1፡12 የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፥
ራዕይ 1፡20 …ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
እግዚአብሔር በሚፈልገን ሥፍራ አይደለንም። እግዚአብሔር እንድናይ በሚፈልገው አቅጣጫ እያየን አይደለንም። የሚናገረውን ድምጽ ለማየት ዮሐንስ ዘወር ማለት አስፈልጎታል። ዘወር ማለት እና በሌላ መንገድ መሄድ ንሰሃ የመግባት ምሳሌ ነው። ለመንፈሳዊ ስኬት ቁልፉ ያለመቋረጥ ንሰሃ መግባት ነው። ከምናስበው እጅግ የበዛ ስሕተቶች አሉብን። ዘመናችንም እውር ነው እኛ ግን ይህን አናውቅም። አስተዋይ የሆንን መስሎናል።
ኢሳይያስ 55፡9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ነገር በገለጠ ጊዜ እኛ ከምናስበው የተለየ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ሁልጊዜ ንሰሃ መግባት ማለትም በአስተሳሰባችን መለወጥ ያስፈልገናል ምክንያቱም የእኛ አስተሳሰብ የእግዚአብሔር አስተሳሰብ ላይ መድረስ አይችልም።
ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
የማያዋጣ ንግድ ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው ይበዛል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ስለሚል ምንም ያህል ጥረት ብናደርግ ከመልካም ሥራ ይልቅ ብዙ የማይጠቅም ሥራ እንሰራለን ማለት ነው። ከመጻሕፍት፣ ከቄሶች፣ ከፓስተሮች እና ከሌሎችም ሰዎች እንዲሁም ከራሳችንም አስደናቂ መገለጦች የሰበሰብናቸው ብዙ ልክ ያልሆኑ እምነቶች አሉን። ስለዚህ በጣም ብልሆች ነን ብለን ስናስብ በእርግጥ ለእግዚአብሔር የዘወትር ኪሳራዎች እየሆንን ነው። ሥራዎቻችን ወይም ብልህ ሃሳቦቻችን ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው ያኖረን።
ራዕይ 1፡13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።
ሰባቱ መቅረዞች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ። በመቅረዞቹ መሃል አንድ ሰው ብቻ ይታያል። ከእርሱ ጋር አብሮ ማንም አይታይም። አንድም ሰው ከእርሱ ጋር በምንም አይነት መወዳደር አይችልም። ዮሐንስ ማንንም አላየም፤ ጳውሎስን አላየም፤ ዊሊያም ብራንሃምንም አላየም። እኛ ክርስቲያኖች ኢየሱስን ከሰዎች ሁሉ በላይ ከፍ ማድረግን መማር አለብን። በእነዚህ ሰባት ዘመናት ውስጥ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል ነው። ክርስቲያኖች በምንም ውስጥ ቢያልፉ ኢየሱስ በመከራቸው ሊረዳቸው አብሮአቸው ነው ያለው። በሰባቱ ዘመናት ውስጥ ሁሉ ያለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው ምንም ያህል አስተዋይ ቢሆን ለአንድ ዘመን ክፍል ብቻ ነው መኖር የሚችለው። ስለዚህ ከኢየሱስ ጋር ሊወዳደር የሚችል ሰው የለም።
ራዕይ 1፡14 ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤
እንደ ነጭ የበግ ጸጉር፤ የዳኛ ጸጉር። ሽበት የእድሜ አመልካች ነው፤ ነጭ ጸጉር ግን የጥበብ አመልካች ነው። እርስ በራሳችን ላይ መፍረድ የለብንም፤ ኢየሱስ ብቻ ነው የመፍረድ ጥበብ ያለው።
ዮሐንስ 5፡22 … ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።
ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ሳይሆን እንደ ሰው ይዳኘናል። እንደ እኛ ሰው በመሆን እኛን መረዳት ይችላል።
ዮሐንስ 12፡48 የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
የሚፈረድብን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ነው።
ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ። ፍርዱ ከባድ ነው የሚሆነው። የሰዎችን ሃሳብ ይመረምሩ ዘንድ ዓይኖቹ ወደ ሰው ልብ ውስጥ ዘልቀው ይገባሉ። አጥብቀን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ካልተከተልን ከባድ ችግር ውስጥ እንወደቃለን።
በፍርድ ወንበር ፊት የሚያልፈው አንድ ዓረፍተ ነገር ብቻ ነው፤ እርሱም፡- “እንዲህ ተብሎ ተጽፏል…” የሚለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካልተጻፈ ተወው።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።
እግሮቹ ናስ ይመስሉ ነበር።
ዘዳግም 28፡15 ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል።
23 በራስህም ላይ ሰማይ ናስ ይሆንብሃል፥ ከእግርህም በታች ምድሪቱ ብረት ትሆንብሃለች።
ናስ ጠንካ ነው ስለዚህ የፍርድ ምሳሌ ነው። እርሱ እራሱ እውነትን መስርቶ ለማቆም አስፈሪ የሞት ጣር ውስጥ ተሰቃይቶ አልፏል። እምነቱ የተፈተነበት የእሳት ፈተና መከራን እየተቀበለ ሐጢያታችንን ተሸክሞ ስለ እኛ በሲዖል እሳት ውስጥ ተራምዶ ሄዶ ሐጢያታችንን በዲያብሎስ ላይ ባራገፈ ጊዜ በባዶ እግር በእሳት ላይ የመሄድ ያህል ነበር። ድምጹ ግን በቃሉ ለሚያምኑት ነፍስን እንደሚያሳርፍ የሕይወት ድምጽ እንደ ብዙ ውሆች ድምጽ ነው።
ለማይምኑት ግን ድምጹ ለፍርድ እንደሚመጣ አስፈሪ የነጎድጓድ ድምጽ ነው።
ራዕይ 1፡16 በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።
ኤፌሶን 6፡17 …የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ቃል የውጊያ ሰይፋችን ነው፤ ግን በስጋ ሰዎችን የምንገድልበት መሳሪያ አይደለም፤ ይልቁንም ሰይጣን በአእምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጣቸውን ሃሳቦች የምንገድልበት እንጂ። የቃላት ጦርነት ነው፤ በእውነት እና በስሕተት መካከል የሚደረግ ፍልሚያ።
የእግዚአብሔር ቃል በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ነው፤ የራሳችንንም የሌሎችንም ሐጢያት ቆርጦ ይጥላል። እውነት የብሉይ ኪዳንን ስለታም ጠርዝ እና የአዲስ ኪዳንን ስለታም ጠርዝ በአንድ ላይ ይዛለች። እውነትን ይዘናል የምንል ከሆነ ሁለቱም ኪዳኖች በአንድነት ያስፈልጉናል።
ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሃይ ነበረ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ ከእርሱ ጋር ልንከራከር አንችልም። የእርሱ ብርሃን፣ ጥበቡ፣ ምሳሌነቱም በድምቀቱ የሰዎችን ሥራ ሁሉ ያደበዝዛል። የእኛ ሰው ሰራሽ መብራቶች ትንሽ ቦታ ብቻ ነው የሚያበሩት። ምድር በዛቢያዋ ስትሽከረከር ፀሃይ በምድር ሁሉ ላይ ታበራለች። የፀሃይ ብርሃንም የምናገኘው በነጻ ነው። የእንግሊዝኛው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ከኮፒ ራይት ወይም ከቅጂ መብት ነጻ ነው። ማንም ሰው ቅጂ ማዘጋጀት ይችላል። በእግዚአብሔር ቃል ላይ ማንም የቅጂ መብት ባለቤት መሆን አይችልም። ሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራዎች የቅጂ መብት አላቸው ምክንያቱም የሰዎችን አስተሳሰብ ነው የሚያንጸባርቁት። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ልክ እንደ ፀሃይ ለሰዎች ሁሉ በነጻ ያበራል። የሰው ደማቅ መብራቶች ልክ እንደ ደማቅ ሃይማኖታዊ ሃሳቦቹ ናቸው -- ፀሃይ እስክትጠፋ ድረስ ብቻ የሚበሩ ውስን ብርሃናት ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው። የጥቅሶችን ኩሬ በመተርጎም እውነት ብላችሁ አትጥሩ።
ራዕይ 1፡17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
በኢየሱስ ፊት ዮሐንስ ታላቁ ነብይ ራሱን ከመጤፍ አልቆጠረም። የእውነት ወደ ኢየሱስ ፊት ቀርበን ብናይ ለራሳችን እና ለአመለካከቶቻችን ሁሉ እንሞታለን። ቀኝ እጁ የኃይል እና የስልጣን ምልክት ነው።
ማቴዎስ 26፡64 ኢየሱስም፦ አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው።
ለራሳችን አብዝተን ስንሞት ነው የእግዚአብሔር ኃይል በእኛ ውስጥ ይበልጥ እየተገለጠ የሚመጣው። በራሳችን ሃሳብ እና ልማዶች እጅግ ከመጠመዳችን የተነሳ እግዚአብሔርን ለማገልገል የምናደርጋቸው ጥረቶች ለእርሱ ምንም አይጠቅሙትም። ለራሳችን ብንሞት እግዚአብሔር ፈቃዱን በእኛ መፈጸም ይችላል፤ ምክንያቱም በራሳችን ጥበብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልናስተውል አንችልም። እግዚአብሔርን ለማገልገል እግዚአብሔር እኛ በማንፈልገው አቅጣጫ ሊመራን መቻል ይገባዋል። ለዚህ የምንወደውን ቤተክርስቲያን ስንመርጥ ፍሬያማ የማንሆነው። ያም የእኛ ፈቃድ እንጂ የእርሱ ፈቃድ አይደለም።
“ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ” -- አሁንም በድጋሚ ይህንን ይናገራል። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጠ የነበሩት እውነትን ይዘው ነበር።
ከዚያ ወዲያ እውነት ጠፋች። በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው ሙሽራይቱ ወደ ቀድሞዋ ቤተክርስቲያን ትምሕርቶች የምትመለሰው።
አንዳችም የራሳችን ብልህ አስተሳሰቦች አያስፈልጉንም። ለጥቅሶች በሚሰጡ አሳማኝ አተረጓጎሞች እና የመጀመረያዋ ቤተክርስቲያን ያላመነችባቸው ሃሳቦች ላይ መደገፍ የለብንም። የሆነ ሰውን መከተለም የለብንም። እግዚአብሔርን ልናስደስት የምንፈልግ ከሆነ የአዲስ ኪዳን ምሳሌነት እና ትምሕርቶችን ብቻ መከተል እና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ባመኑት ላይ አንዳችም ጌጣ ጌጥ ወይም ብልህ ሃሳቦች መጨመር የለብንም። አስተዋዮች የሆንን ይመስለናል። ለጥቀሶች የምንሰጠው ትርጉም ጥበብ የሞላበት ይመስለናል። ነገር ግን ሞኞች ሆነናል። ጥበባችን ሊጠፋ እንደቀረበ ሻማ ነው። ሻማን ከፀሃይ ጋር ማወዳደር አትችሉም። ኢየሱስ ብቻ ነው እንደ ፀሃይ የሚያበራው። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ብርሃናችን ሊሆን የሚገባው።
ራዕይ 1፡18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
ኢየሱስ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሕያው መሆኑን በድጋሚ በአጽንኦት ተናግሮ ሞቱን እና የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ያስጀመረበትን ትንሳኤውን እንደገና ይጠቅሳል። ስለዚህ የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን እንደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን እንድትሆን ይፈልጋል ምክንያቱም በመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን የተመሰረተው እውነት ለዘላለም አይለወጥም፤ ለዘላለም ጳውሎስ እና ሌሎቹ ሐዋርያት በትንሳኤው ኃይል እንደ ሰበኩት ሆኖ ይቀጥላል። ወደ ምሳሌነታቸው እና ወደ አስተምሕሮዋቸው መመለስ አለብን። ዘመናዊው አተረጓጎማችን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ያላስተማረችው ትምሕርት ከሆነ ያለጥርጥር ስሕተት ነው።
ኢየሱስ ወደ ጠፉት ሄደ ዲያብሎስን አሸንፎ በሞት እና በሲዖል ላይ የነበረውን ስልጣን ገፎታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ፈቃድ ካልሰጠ በቀር አንድም ክርስቲያን መሞት አይችልም። ክርስቲያኖች ሞትን መፍራት የለባቸውም ምክንያቱም እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር ለሊሞቱ አይችሉም፤ ቢሞቱም እንኳ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነው የሚሞቱት።
በሶስተኛው እና በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን ወደ ሃይማኖታዊ ስሕተት ጥልቀት ውስጥ እና ወደ አሕዛብ ልማዶች ውሰጥ ወደ ፖለቲካ ውስጥ ወድቃለች፤ እነዚህ ሁሉ ቀጥታ መንፈሳዊ ሞትን የሚያመጡ ናቸው። ኢየሱስ ግን የሞት እና የሲዖል ቁልፍ በእጁ ይዟል። ስለዚህ በጨለማው ዘመን ውስጥ ሁሉ የጠፋ በመሰለ ጊዜ የሰዎችን የእውቀት በር ከፍቶ የሬናይሰንስ እውቀት ዘመንን በማምጣት የሕትመት ጥበብን ለሰዎች በመስጠት በተሃድሶ ዘመን በእምነት መዳን ወደሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሰዎች መመለስ እንዲችሉ ብርታትን በመስጠት የጨለማው ዘመን እንዲያበቃ አደረገ። በእምነት መጽደቅ የሚለው እውነት ሲገለጥ አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ተጀመረ። ይህም ቤተክርስቲያንን ወደ መጀመሪያዋ የሐዋርያት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የመመለስ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። የክርስትና ብርታት የሚለካው ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በተመለሰበት መጠን ነው።
ራዕይ 1፡19 እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።
ዮሐንስ በዚህ ራዕይ ውስጥ ያየውን መጻፍ አለበት፤ ይኸውም “አሁንም ያለውን” ሰባቱ ቤተክርስቲያኖች በዚያው ሰዓት ያሉበትን ሁኔታ እና ሰባቱ ቤተክርስቲያኖች የመጪዎቹን የሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ታሪክ የሚገልጡበትን አስደናቂ ባሕሪዮቻቸውን “ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን” በ2000 ዓመታት ውስጥ በቤተክርስቲያን ታሪክ ሊገለጥ ያለውን። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ምን አይነት እንደሚሆን ከኤፌሶን ቤተክርስቲያን ባሕርይ አንጻር የዛኔውኑ ማየት ችሏል። የሰው መሪነት ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት ሾልኮ እንደገባ እና እንዴት ሰዎች ከሐዋርያት አስተምሕሮ እያራቀ እንደነበረ አይቷል።
3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ (በሐዋርያት) ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
ይህ የጥንተዋ ቤተክርስቲያን መሪ ልክ እንደዛሬዎቹ ፓስተሮች ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠረ፤ በሐዋርያት የተጻፉትን የእግዚአብሔር ቃሎች አልቀበልም አለ፤ ከእርሱ ጋር አልስማማ ያሉ ሰዎችን ደግሞ ከቤተክርስቲያን አባረረ። ዮሐንስ የሰው አመራር ቤተክርስቲያንን እንዴት እንደሚገዛ እያሳየን ነው። የሰው አገዛዝ ደስ አይልም።
ሆኖም ዮሐንስ እውነትን ለሚፈልጉ ሁሉ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እውነት እንዳላት አውቋል።
ዮሐንስ በመልእክቱ ራሱን እንደ ሽማግሌ ነው የሚያስተዋውቀው። ቤተክርስቲያንን መምራት ያለባቸው ሽማግሌዎች እንጂ አንድ አምባገነን ፓስተር አይደለም። ዮሐንስ ጠንከር አድርጎ የሚናገረው የወንድማማች እኩልነትን ነው። ኒቆላዊነትን ወይም አንድ ሰው ፓስተር ስለተባ ከጉባኤው በላይ ከፍ መደረጉን አይደግፍም። “ፓስተር” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ሰባት ጊዜ ተወግዟል።
3ኛ ዮሐንስ 1፡1 ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።
4 ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።
“ልጆቼ”። እነዚህ የሐዋርያትን ትምሕርት የሚከተሉ ሰዎች ናቸው፤ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ብቻ ናቸው የእግዚአብሔርን ቃል የመጻፍ ስልጣን የነበራቸው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚካተቱትን መጻሕፍት ለመጨረሻ ጊዜ የመረጠው ዮሐንስ ነው። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች እና ሌሎቹ ሐዋርያት በሙሉ ከሞቱ በኋላ በምድር ላይ በሕይወት የቆየው ሐዋርያ ዮሐንስ ብቻ ነበር፤ እርሱም በምድራዊው የፍጥረት ዓለም እና ከዓይናችን በተሰወረው ከፍ ባለው ሰማያዊው መንፈሳዊ ዓለም መካከል በስልጣን መመላስ የቻለ ታላቅ መንፈሳዊ ሰው ነው። ከኢየሱስ ጋር ከነበረው ከሌሎች ሰዎች የበለጥ ቅርበት እና ከኢየሱስ እግር ስር ከመማሩ አንጻር የትኞቹ መጻሕፍት በአዲስ ኪዳን ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ይህንን ትልቅ ውሳኔ ለማድረግ በቂ መረዳት እና መገለጥ የነበረው እርሱ ነው። ስምንቱን የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ለመምረጥ በቂ የሆነ የማስተዋል እና የመለየት ስጦታ ነበረው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ማንም ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳች መጨመር አይችልም።
ነፍሳችን እጣ ፈንታዋ ዮሐንስ በመረጣቸው የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ነው የሚወሰነው።
ሚክያስ 5፡5 ይህም ለሰላም ይሆናል፤ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።
ክፉውና ደም አፍሳሹ የአሦር መንግስት ዲያብሎስን ይወክላል። ቤተክርስቲያን ሰውን መሪ አድርጋ ከተቀበለች በኋላ መሪ ሊሆኑ የማይገባቸው ሰዎች ወደ ስልጣን እስኪመጡ እና ጥሩ ሰዎች በስልጣን እና በሃብት ፍቅር እስኪበከሉ ድረስ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠብቁት። ሰይጣን በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ እየበዛ በመጣው ሃብት እና ቤተመንግስት በመሰሉ ሕንጻዎች ውስጥ ከፍ እያለ መጣ። በ312 ዓ.ም. ንጉስ ኮንስታንቲን በካየሊያን ኮረብታ ላይ ያለውን ውብ የላተራን ቤተመንግስት ለሮም ጳጳስ ስጦታ ካበረከተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሮማ ሊቀ ጳጳስ መኖሪያ ሆኗል። ከዚያም በ1500 አካባቢ ቫቲካን ከሰፋፊ እና ውብ ሕንጻዎቿ ጋር ሮም ውስጥ ተመሰረተች። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለመሪዎችዋ ቤተመንግስት በመስራት ከሷ ኋላ ለሚመጡ ምሳሌ ተወች። ፕሮቴስታንቶችም ለመሪዎቻቸው እንዲህ አይነት የተንደላቀቀ መኖሪያ ቤት መስራትን ለመከተል አልዘገዩም። ነገር ግን ሰይጣን ወዲያ በእነዚህ ሕንጻዎች ውስጥ ለመመላለስ እና መኖሪያው ሊያደርጋቸው ተመቸው። ሰይጣን ትልልቅ ያማሩ ያጌጡ ሕንጻዎችን ይወዳል።
እግዚአብሔር ግን ስለ እውነት የሚቆሙ ስምንት ታላላቅ ሰዎችን አስነሳ። እነዚህም አዲስ ኪዳንን የጻፉ ስምንት ሰዎች ናቸው። ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ እና ዮሐንስ ወንጌሎቹን ጻፉ። ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን ጻፈ። ጳውሎስ ከሮሜ እስከ ዕብራውያን ጻፈ። ያዕቆብ፣ ጴጥሮስ እና ይሁዳ መልእክቶቻቸውን ጻፉ። ከዚያም ዮሐንስ እራሱ ሦስቱን የመጨረሻ መልእክቶቹን እና የኢየሱስ ክርስቶስን ራዕይ ጻፈ።
ከዚያም እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሰባት መላእክት ወርደው የሰባት ሰዎችን ሃሳብ እንዲመሩ በማድረግ እያንዳንዳቸው በራሳቸው ዘመን ላለችው ቤተክርስቲያን መሪ ወይም መልእክተኛ እንዲሆኑ አደረገ። ጳውሎስ የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት እንዲጽፍ መለኮታዊ እርዳታ አግኝቷል። ሌሎቹ ስድስቱም ለዘመናቸው በተመደበው መልአክ አማካኝነት ቤተክርስቲያንን ወደ አዲስ ኪዳን እምነት ሊመልሱ ጥረት ሲያደርጉ እያወቁም ይሁን ሳያውቁ እርዳታ ተቀብለዋል። መልአክ የሰማይ መልእክተኛ ነው። እነዚህ ሰዎች ይህንን የመልአክ ምሪት እና እገዛ እየተቀበሉ ስለነበሩ እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር የተላኩ መልእክተኞች ወይም መልአክ ብሎ ጠራቸው፤ ምክንያቱም ለዘመናቸው የቤተክርስቲያን ሕዝብ የእግዚአብሔርን የፈቃዱን መልእክት አምጥተዋል።
ስለዚህ ታላቅ መሆንን በሚፈልጉ የራሳቸውን እምነት ትምሕርት እንዲሁም ልማድ በፈጠሩ የሰው መሪዎች እና ለራሳቸው በሞቱ፣ በዚህ ዓለም ታዋቂ መሆን ባልፈለጉ፣ በሐዋርያት የተጻፈውን እውነት መከተል ብቻ በፈለጉ እውነተኛ አማኞች መሃል የማያቋርጥ ጠርነት አለ።
ራዕይ 1፡20 በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
ለመጀመሪያው ዘመን የተላከው መልአክተኛ ጳውሎስ ነበር፤ እርሱም አንዳንድ የሥጋ ድካሞች ቢኖሩበትም ሕዝቡ እንደ መልአክ ተቀብለውታል። ምናልባት በደማስቆ መንገድ ላይ የበራበትን የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ድምቀት ሲመለከት ዓይኖቹ ሳይጎዱ አይቀሩም።
ገላቲያ 4፡13 በመጀመሪያ ወንጌልን በሰበክሁላችሁ ጊዜ ከሥጋ ድካም የተነሣ እንደ ነበረ ታውቃላችሁ፥
14 በሥጋዬም ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትምና አልተጸየፋችሁትም ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ዘመን ያስነሳውን ታላቅ ሰው መልአክ ብሎ ጠርቷል - መልእክተኛ፣ ኮከብ ለዘመኑ የሚያስፈልገውን ብርሃን የያዘ የሚነድ ብርሃን።
ሰባቱ መቅረዞች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ፤ እያንዳንዱ መቅረዝ አንድ የቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል።
ሰባት ቅርንጫፎች ያሉትን የአይሁድ መቅረዝ በመጠቀም የቤተክርስቲያንን ታሪክ እንከተል፡-
በጴንጤ ቆስጤ እለት መለኮታዊ የእሳት ልሳኖች የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን አበሩ።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንደተገለጸው የእግዚአብሔር ምርጥ ቤተክርስቲያን ነበረች። ብቸኛዋ ፍጹም ትክክለኛ ቤተክርስቲያን ናት።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ከመጀመሪያው በሚፈልገው መንገድ ነው የመሰረታት።
አሁን ደግሞ ቤተክርስቲያንን መጀመሪያ እንደመሰረታት እንድትሆንለት ይፈልጋል።
ከዚያም በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሰው አመራር ቦታ ሲይዝ የቤተክርስቲያን አቋም ከመስፈርቱ እየወረደ መጣ። የሰዎች አመለካከትና ልማድ ወግ ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ የመጀመሪያው የወንጌሉ መንፈሳዊ ብርሃን ደበዘዘ።
የሮማ ንጉስ ኮንስታንቲን የአሕዛብ ሃሳቦችን እና ፖለቲካን ወደ ቤተክርስቲያን አስገባ። ስለዚህ በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ብርሃኑ ይበልጥ ደበዘዘ። በጳጳሱ ስር የሚመራ ማእከላዊ ድርጅት ተፈጠረ።
ከዚያም አውሮፓ በባርቤሪያኖች ወረራ ከፈራረሰች በኋላ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተፍጨርጭራ በአውሮፓ ሁሉ ላይ ስልጣን በተቆናጠጠችበት በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጭካኔ የተሞላ ክፉ ፖለቲካ እና የብዙ ሕዝብ ግድያ ብተክርስቲያንን ደግፎ አቆያት።
መጽሐፍ ቅዱስ በመታገዱ እውነት ደብዛዋ ጠፋ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ የተሰራው ክፋት መንስኤው ከመጀመሪያዋ ዘመን ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን እምነት ርቀው በመሄዳቸው ነው።
ክፋት
ነገር ግን ከዚያ ወዲያ እግዚአብሔር ወደ አዲስ ኪዳን የሚመልስ ተሃድሶ ጀመረ።
ኢዮኤል 2፡25 የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
ጠላት ያወደመውን ሁሉ መልሶ ለማደስ አራት የተሃድሶ ደረጃዎች አሉ።
ሕዝቅኤልም እንደዚሁ ነው ያለው።
ውሃ በሕይወት ሰጭ ባሕሪው የተነሳ የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል።
እያንዳንዱ የተሃድሶ ደረጃ ጠለቅ ያለ እውነትን መልሶ አመጣ።
ሉተር በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በእምነት የመዳንን እውነት መልሶ አመጣ።
ሕይወት ክፋት
ዌስሊ በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ቅድስናን እና የወንጌል ስብከትን መልሶ አመጣ።
ሕይወት ክፋት
የተሃድሶ ዋነኛ ዓላማ ወደ ቀደመው የሐዋርያት እምነት የመመለስ ፍላጎት ነው።
በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ።
ሕይወት
ያም ቢሆን በቂ አልነበረም። ኢየሱስ መንፈስ እና እውነት እንደሚያስፈልጉን ተናግሯል።
ዮሐንስ 4፡24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው በአዲስ ኪዳን ወደተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት መመለስም ያስፈልገናል። ሰባተኛው ዘመን ከአንደኛው ዘመን ጋር አንድ መሆን አለበት።
የሚታጨደው መኸር መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር ሁልጊዜ አንድ አይነት መሆን አለበት።
ሕይወት
እነዚህ ቃሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ በጥልቀት ይገኛሉ።
ሕዝቅኤል 47፡3 ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።
4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።
5 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።
በእያንዳንዱ የተሃድሶ ደረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ጥልቀት እየጨመረ መጥቷል። የመጨረሻው ደረጃ ከሁሉም የበለጠ ጥልቀት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ነው። 1. መጽደቅ 2. መቀደስ 3. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት 4. የእውነት መታደስ።
ሕዝቅኤል በተጨማሪ የደረቁ አጥንቶች የሞሉበትን ሸለቆ አይቷል።
እነዚያ አጥንቶች በሕይወት እንዲኖሩ ለማድረግ አራት ደረጃዎችን ማለፍ ያስፈልጋቸዋል። ጅማት። ሥጋ። ቁርበት። እስትንፋስ።
ሕዝቅኤል 37፡3 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ።
6 ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ከዚያ በኋላ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ወደ ሙላት ተመልሶ የሚመጣው።
ሕይወት ክፋት
እንግዲህ ባለ ሰባት ቅርንጫፉ መቅረዝ በመካከል ካለው የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ከሚወክለው መቅረዝ ጋር ቤተክርስቲያን እንዴት በመንፈስ ቅዱስ እሳት እንደተለኮሰች እና እንዴት ከእውነት እንደራቀች፤ ከዚያም እግዚአብሔር እንዴት በሉተር ተሃድሶ ሊመልሳት እንደጀመረ እና በስተመጨረሻ ሙሽራዋ እንዴት ወደ ቀድሞው የአዲስ ኪዳን እውነት በሙላት እንደምትመለስ ይነግረናል።