የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ ወደ ምድር አልወረደም



የ1963ቱ ደመና ከሰባቱ ማሕተሞች የስድስቱን ሚስጥር ይገልጥ ዘንድ ሚስጥራቱ ወደ ወንድም ብራንሐም መምጣታቸው የሚያመለክት ነበረ።

First published on the 4th of December 2021 — Last updated on the 4th of December 2021

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ እስካሁን ወደ ምድር አልወረደም።

 

 

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

ይህ ትንቢት በ1963ቱ ደመና አማካኝነት የተፈጸመ አይደለም። ደመናው ውስጥ ምንም ፊት አልነበረም።

ደመናው ካላይ ያለውን መልአክ አይመስልም።

 

 

ደመናው በፀሃይ መጥለቂያ ሰዓት በ42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ለ28 ደቂቃ ከፍላግስታፍ አሪዞና ከተማ በስተሰሜን እየተንሳፈፈ ሄደ።

ደመናው ወደ ምድር አልወረደም፤ ወደ ላይም አልወጣም። በነበረበት ከፍታ ላይ ነው የቆየው።

ደመናው ከመጀመሪያው እስከ መጨረስ ከሳንሴት ፒክ በስተ ሰሜን 200 ማይልስ ርቀት ላይ ነው የቆየው።

 

 

ከደመናው ጋር አንዳችም ቀስተ ደመና አልነበረም። ደመናው ውስጥ ያለው ፊት ጨለም ያለ እና የታየውም ፎቶግራፉ እጅ ሥራ ከተሰራበት በኋላ ነው እንጂ የመጀመሪያው ፎቶግራፍ ውስጥ ምንም ፊት አልነበረም።

ከዚህ በታች ያለው ፎቶ እጅ ሥራ ተሰርቶበታል።

 

 

ደመናው እግሮችም አልነበሩትም። በፎቶግራፉ ውስጥ ሁለት የእሳት አምዶችም አልነበሩም።

ፎቶው የተሰራበት እጅ ሥራ ፊት ሊያሳይ ይችላል፤ ነገር ግን ከፊቱ በታች አካልም ሆነ እግሮች የሉም።

በተጨማሪም ከዊንስሎው በተነሳው ፎቶግራፍ መሰረት ሁለት ደመናዎች ነበሩ።

ትልቁ ደመና የተሰራው ከሰባት መላእክት ክንፍ ነው። ትንሹ ደመና ደግሞ ቀደም ብሎ ከፈነዳው ሮኬት ጭስ ነው። ሁለቱም ደመናዎች በ43 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ነበሩ። ይህም ከፍታ ተፈጥሮአዊ የዝናብ ደመናዎች ሊገኙ ከሚችሉበት ከፍታ እጅግ በጣም የራቀ ነበረ።

 

 

ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥

ደመናው ውስጥ ምንም የሚታይ መጽሐፍ አልነበረም፤ ደመናውም ካሊፎርኒያ ውስጥ በቫንደንበርግ አየር ኃይል ጣብያ አካባቢ ከነበረው ባሕር 510 ማይልስ ያህል እሩቅ ነበረ።

መልአኩ የሚወርደው መጽሐፉን ለመክፈት አይደለም፤ መልአኩ የሚወርደው መጽሐፉ ስለተከፈተ ነው።

62-1230 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን

ነገር ግን ይህኛው ከምድር የመጣ አይደለም። የመጣው ከሰማይ ነው፤ ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተጠናቅቀዋል።

በ1963 ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ከሰባቱ ማሕተሞች ስድስቱን ገልጧቸዋል። እነዚህ መገለጦች የመጡለት ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ደመናውን በሰሩት በሰባቱ መላእክት አማካኝነት ነው። ነገር ግን መላእክቱ ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡት 8 ቀናት ካለፉ በኋላ ማርች 8 ቀን 1963 ነው፤ የመጡበትም ቦታ ከፍላግስታፍ በስተ ደቡብ 200 ማይልስ ርቃ በምትገኘው ሳንሴት ፒክ በምትባለው ቦታ ነው። በመጡም ጊዜ ወደ ጄፈርሰንቪል እንዲመለስና ማሕተሞቹን ገልጦ እንዲያስተምር አዘዙት። ከማርች 17 ቀን እስከ 24 ድረስ መላእክቱ የስድስቱን ማሕተሞች ሚስጥር ለወንድም ብራንሐም ገለጡለት፤ የሰባተኛውን ማሕተም ሚስጥር ግን አልገለጡለትም። ይህም የዓለማችን ታላቅ ሚስጥር የሆነው የኢየሱስ ዳግም ምጻት ነው።

የስድስቱ ማሕተሞች ሚስጥር ሲገለጥለት ወንድም ብራንሐም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ሚስጥራትን ማስተዋል ቻለ፤ ስለዚህ አሁን እርሱ በገለጠልን ቃል የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ተረድተን ለንጥቀት መዘጋጀት እንችላለን።

እነዚህ ሚስጥራት የታላቁን መከራ ዘመን ክስተቶች ማካተት አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም እነዚያ ክስተቶች አይሁዶችን ብቻ የሚመለከቱ ናቸው።

ቁልፍ ሃሳብ።

ሙሽራይቱ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መረዳት አለባት። የምናምነውን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረን ማረጋገጥ አለብን። ይህም ትምሕርቱን በደምብ ለማብላላታችን ማስረጃ ነው።

ሙሽራይቱ መጽሐፉን መክፈት ከቻለችና የተጻፉትን ሚስጥራት የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በተረዳችበት ልክ መረዳት ስትችል መልአኩ መጥቶ በምድርና በባሕር ላይ ይቆማል። እግሩን አሳረፈ ማለት ባሕርን እና ምድርን ተቆጣጠረ ማለት ነው። ስለዚህ እንዲህ በቆመበት ሰዓት ገዥ ነው። በሞት፣ በሲኦል እና በመቃብር ላይ ስልጣኑን ያውጃል። ምድርን እና ባሕርን በሙሉ ይቆጣጠራል፤ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ባለፉት 2,000 ዓመታት ውስጥ ምድርና ባሕር ውስጥ ነው የተቀበሩት።

ከዚያም ሙታንን ያስነሳቸዋል፤ ስለዚህ ከሞት የተነሱት የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን በእምነታቸው እነርሱን የሚመስሉትን በሕይወት የሚኖሩ ቅዱሳን ይገናኛሉ።

64-0119 ሻሎም

ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

 

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ

የተጻፈው ቃል ውስጥ የሚገኙት ሚስጥራት ከተገለጡ በኋላ

ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ ኪዳን ትምሕርቶች ከተመለሰች በኋላ።

በፊተኛው ዝናብ ወይም በተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትምሕርት ዝናብ አማካኝነት በሕይወት ያለችው ሙሽራ ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ጋር ፊት ለፊት መተያየት ከቻለች በኋላ።

ከዚያም በኋላ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሆነው ሁሉን ቻዩ መልአክ ለኋለኛው ዝናብ ወይም ለመከሩ ዝናብ ይመጣል። መከሩ ፍሬው ከተክል ላይ ታጭዶ የሚወሰድበት ሰዓት ነው። የመላእክት አለቃው ድምጽ የንጉሱ የአንበሳው ግሳት ነው። ድምጹም የሞቱትን ቅዱሳን አስነስቶ ከመቃብር ውስጥ ያወጣቸዋል።

ከዚያ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን በማሰማት ቅዱሳን አካላቸውን እንዲለውጡ ያስችሏቸዋል፤ በዚህም ለንጥቀት ይዘጋጃሉ። በሕይወት የሚኖሩት ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱት ቅዱሳን ጋር በአንድነት ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ስለሚነጠቁ እነርሱም የመከሩ አካል ናቸው።

ራዕይ 10፡4 ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።

ሰባቱ ነጎድጓዶች ታላቅ ሚስጥራዊ መልእክት አላቸው። ይህም ሚስጥር የሚገለጠው ከትንሳኤ በኋላ ብቻ ነው። ስለዚህ ዮሐንስ ነጎድጓዶቹ የተናገሩትን ቃል እንዳይጽፍ ተነገረው።

ራዕይ 10፡5 በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥

6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ፡- ወደ ፊት አይዘገይም፥ አለ

ጊዜ ለውጥን እና መበስበስን ያስከትላል፤ የዚህም ውጤቱ እርጅና እና ሞት ነው።

የሙሽራይቱ አካላት ሁሉ አንዴ የማይሞተውን ስጋቸውን ከለበሱ በኋላ ከጊዜ ክልል ውጭ ይሆናሉ።

ከዚያ በኋላ በጭራሽ ሊያረጁ፣ ሊጎሳቆሉ ወይም ሊለወጡ አይችሉም። ሙሽራይቱ ከዚያ ወዲያ በጊዜ ክልል ውስጥ አትሆንም። ቀሪው ዓለም ግን በጊዜ ተጽእኖ ውስጥ ይቆያል። ይህም የመከሩ የመጨረሻ ክፍል ስለሚሆን ሙሽራይቱ ከጊዜ ክልል ወጥታ ከፍ ባለው በዘላለማዊው ዓለም ውስጥ ኑሮዋን ትቀጥላለች።

ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ወንድም ብራንሐም የወጣትነት ዕድሜው ለአገልግሎት የሚዘጋጅበት ጊዜ ነበረ።

65-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

የዝግጅት ዓመታት ሳይሆኑ፣ “እርሱ መልእክቱን በሚያሰማበት ጊዜ እነዚህ ሚስጥራት የዛኔ ይገለጣሉ።”

መንፈሳዊ አገልግሎት ብዙ ስልጠና ይጠይቃል።

ወንድም ብራንሐም አገልግሎቱን በ1933 በፈውስ ስጦታ እና መናፍስትን በመለየት ስጦታ ነው የጀመረው።

በ1947 አካባቢ መሰረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መማር ጀመረ።

የአገልግሎቱ የመጨረሻ ዓመታት ወደ መጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን እምነት እንድንመለስ የሚረዱንን ጠለቅ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት እየገለጠ በማስተማር መልእክቱን ያሰማባቸው ዓመታት ናቸው።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

… የእግዚአብሔርን ሚስጥራት መግለጥ የሰባተኛው መልአክ ዋነኛ አገልግሎት ነው።

ሰባተኛው መልአክ የተሰጠው ተልእኮ የተጻፉትን ሚስጥራት በመግለጥ ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው ዘመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሕሮ መመለስ ነው።

ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከእነርሱ የበለጠ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ልናውቅ እንችላለን፤ ነገር ግን እነርሱ ያመኑትን ያንኑ መሰረታዊ አስተምሕሮ ነው የምናምነው። ሙሽራይቱ እነዚህን መገለጦች ከተማረችና መጽሐፍ ቅዱስን እንደተከፈተ መጽሐፍ ማንበብ ከቻለች በኋላ የዛኔ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል።

መልአኩ ወደ ምድር እንዳይወርድ ያዘገየው መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቃችን ነው።

63-03-18 የመጀመሪያው ማሕተም

እንደገና ላንብበው። ሳነበው በጣም ደስ ይለኛል፤ ይህን ቃል ማንበብ እወዳለው።

… ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፣ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና… ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት አምዶች ነበሩ

ስለዚህ አሁን በቃሉ ያየነው ክርስቶስ እራሱ ነው። ክርስቶስ ደግሞ ሁሌም የቤተክርስቲያን መልእክተኛ መሆኑን እናውቃለን። ክርስቶስ የእሳት አምድ፣ የቃልኪዳኑ መልእክተኛ እና ሌሎች ስሞች አሉት።

የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ … (ይህ የሆነው ማሕተሞቹ በሚፈቱበት ጊዜ ነው። አሁን ማሕተሞቹን እየፈታናቸው ነን፤ ይህች ትንሽ መጽሐፍ ግን ተከፍታለች።)

 

ወንድም ብራንሐም ማሕተሞቹን እየገለጠ ነው። መልአኩ የተከፈተችውን ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ይዞ ሲወርድ ግን “ማሕተሞቹ ከተፈቱ በኋላ” ነው የሚወርደው። ወንድም ብራንሐም “አሁን እየፈታናቸው ነው” አለ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ግን “ይህ … ነገር ተከፍቷል” ነው የሚለው።

ስለዚህ ትንሽዋ መጽሐፍ የምትከፈተው መልአኩ ወደ ምድር ሲመጣ ነው።

ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ መልአኩ ወደ ምድር የሚመጣው መጽሐፉን ለመክፈት አይደለም።

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው መጽሐፉ ስለተከፈተ ነው።

62-12-3 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

ሌሎቹ መላእክት መልእከተኞች ናቸው፤ ማለትም የምድር ሰዎች ናቸው። ይህኛው መልአክ ግን … ይህኛው ከምድር አይደለም፤

ይህኛው መልአክ ከሰማይ ይወርዳል፤ ምክንያቱም ሚስጥራቱ ሁሉ ተጠናቅቀዋል።

ሚስጥራቱ ሲጠናቀቁ መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከዚህ በኋላ አይዘገይም፣” ከዚያም ሰባት ነጎጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ

 

መልአኩ መጽሐፉን ለመክፈት ብሎ አይደለም የሚወርደው። ነገር ግን መጽሐፉ አስቀድሞ ስለተከፈተ ነው የሚወርደው።

 

ወንድም ብራንሐም ሁልጊዜ በስብከቱ ውስጥ የሚያነሳው ጭብጥ ሚስጥራቱ መገለጥ እንዳለባቸውና መልአኩም የሚመጣው ከዚያ በኋላ መሆኑን ነው።

ነጎድጓዶቹም ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ድምጻቸውን ማሰማት የሚችሉት።

ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ጊዜም የሚያበቃው።

63-01-12 ተጽእኖ

በመጨረሻው ቀን መልእክተኛ እንደሚመጣ ራዕይ ምዕራፍ 10 ይነግረናል፤ እርሱም ያልተቋጩ ነገሮችን ሁሉ ሰብስቦ ይቋጫቸዋል። ከዚያ ወዲያ የምድር መልእክተኛ የሆነው መልአክ ድምጹን ባሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል። ከዚያ በኋላ ከሰማይ ወደ ምድር የሚወርድ አለ፤ እርሱም እጆቹን ወደ ላይ ያነሳል፤ በራሱ ዙርያ ቀስተ ደመና ያበራል፤ ከዚያም ወዲያ ጊዜ እንደማይኖርና እንደማይዘገይ ማለ። ይህም ነገር መፈጸሙን በምናይበት ጊዜ እጅግ በጣም ትሁት ልንሆን ይገባናል።

ስለዚህ መልአኩ ወደ ምድር ሊመጣ የሚችለው ወንድም ብራንሐም የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የመግለጥ አገልግሎቱን ሲያጠናቅቅ ብቻ ነው። ወንድም ብራንሐም ከሰማይ ወደ እርሱ የመጡትን ሚስጥራት ለመግለጥ በምድር መቆየት ነበረበት።

ከዚያም አገልግሎቱ ሲጠናቀቅ ታሕሳስ 1965 ዓ.ም ሞተ።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ መልአኩ ወደ ምድር መምጣት አልቻለም።

አስቀድሞ የእግዚአብሔር ሚስጥር መጠናቀቅ አለበት። ይህም የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ነው። ከዚያ በኋላ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል።

የወንድም ብራንሐም አገልግሎት የተጠናቀቀው ታሕሳስ 1965 ስለሆነ መልአኩ ወደ ምድር ሊመጣ የሚችለው ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ብቻ ነው።

ትንቢትን መተርጎም ሁሌም ቀላል አይደለም።

1964-07-10 የመለከት በዓል

ከምዕራፍ 4 እስከ 19 ድረስ እግዚአብሔር ጉዳዩን የሚፈጽመው ከእስራኤል ጋር ነው።

 

ስለዚህ ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ሙሽራይቱ ወደ ሰማይ ከተነጠቀች እና ምዕራፍ 19 ውስጥ ተመልሳ ከመጣች፤ ምዕራፍ 10ን አሁን ላለንበት ዘመን አድርገን ከመተርጎም መጠንቀቅ አለብን።

ቁጥር 7 ስለ ዘመናችን የሚናር ቢሆንም ውስጡ “ግን” የሚል ቃል አለው፤ ይህም የመልእክቱ ጭብጥ ሊለወጥ መሆኑን ያመለክታል።

ራዕይ 10፡7 ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ራዕይ 10፡1-6 የወደፊት ክስተትን የሚያመለክት ነው፤ እርሱም ብርቱው መልአክ ወደ ምድር ወርዶ ሙታንን የሚያስነሳበት ነው። ይህ የሚፈጸመው በምድር ላይ በሕይወት ያለችው ሙሽራ የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ካገኘች በኋላ ነው።

እነዚህ ጥልቅ ሚስጥራት ከ1956 – 1965 በሰባተኛው መልአክ ሙሉ በሙሉ ተገልጠዋል።

ነገር ግን ከዚያ ወዲህ እነዚህን እውነቶች ያልተማሩ አዳዲስ ትውልዶች ተነስተዋል።

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም ያስተማራቸውን ትምሕርቶች አማኞች ወስደው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያመሳከሩ ትምሕርቱ እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ መልመድ አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ለእነርሱ የተከደነ ሳይሆን የተከፈተ መጽሐፍ ሊሆንላቸው ይገባል።

ነገር ግን ይህን እያደረጉ ያሉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።

የተገለጠው ቃል የተመሰለው በ “ትንሽ” መጽሐፍ ነው፤ ይህም ትንሽ መጽሐፍ እንደ “ታናሽ” መንጋ ጥቂት የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ተረድተውት የሚያምኑት።

ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።

 

ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።

ስለዚህ መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው መች ነው?

ይህ የሚሆነው የእግዚአብሔር ሚስጥር ተገልጦ ሲያልቅ ብቻ ነው።

ወንድም ብራንሐም ስለ ማሕተሞቹ እየሰበከ በነበረ ሰዓት መልአኩ ገና ወደ ምድር አልወረደም ነበር። ወንድም ብራንሐም ስለ ደመናው የሰማው ስለ ማሕተሞቹ ገልጦ ካስተማረ ከሁለት ወራት በኋላ ነው።

63-03-17 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞቹ መካከል ያለው ቅርንጫፍ

አሁንም ወደ 10ኛው ምዕራፍ ተመልሶ ከሚመጣው ጊዜ በኋላ ሚስጥራቱ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይናገራል፤ ማሕተሞቹም ይፈታሉ ከዚያም በኋላ ዘመን እንደማይኖር ይታወጃል። እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ሁሉ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል። ይህ የሚሆንበትም ጊዜ ሩቅ አይደለም።

 

ይህ ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከ18 ቀናት በኋላ ነው። ይህን የተናገረበት ቀን ድረስ የመልአኩን ወደ ምድር መምጣት ሲጠባበቅ ነበር። ነገር አስቀድሞ ሚስጥራቱ መጠናቀቅ ነበረባቸው። ይህም ሥራ የሚጠናቀቀው ታሕሳስ 1965 ነበር።

ስለዚህ ማሕተሞቹን መግለጥ በጀመረ ጊዜ መልአኩ ገና አልመጣም።

 

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

የክርስቶስ ሙሽራ ከምድር የምትወሰድበት ሰዓት ሲደርስስ? ያ ሰዓት ቢደርስስ፤ ጊዜም ለዘላለም ቢያበቃስ?

በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ያለበት መልአክ አንድ እግሩን በምድር ላይ አንድ እግሩን በባሕር ላይ አድርጎ ቆሞ “ጊዜ አብቅቷል” ብሎ ሊያውጅ ተዘጋጅቷል

 

ወንድም ብራንሐም የመጀመሪያውን ማሕተም በገለጠ ጊዜ መልአኩ ገና አልመጣም ነበር።

63-03-24

ራዕይ ምዕራፍ 10 ቁጥር ከ1 እስከ 7። ጊዜ ያበቃል። መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ከአሁን በኋላ ጊዜ አይኖርም” ይህ የሚሆነው እነዚህ ትልልቅ ነገሮች በሚፈጸሙ ጊዜ ነው። በሰባተኛው ማሕተም መጨረሻ ላይ በዚህ ዘመን ውስጥ ያለ ሁሉም ነገር ያበቃል።

ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባተኛው ማሕተም በሰበከ ጊዜም መልአኩ ወደ ምድር አልመጣም።

የመልአኩ ወደ ምድር መምጣት ገና ወደ ፊት ሊሆን ያለ “ክስተት” ነበረ።

ሰባተኛው ማሕተም ሲገለጥ የታወቀው ነገር ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑ ነው።

ስለ ሰባተኛው ማሕተም ምንም አናውቅም ምክንያቱም ስለ ጌታ ምጻት የሚገልጥ ነው።

ስለዚህ መልአኩ ወደ ምድር ሳይመጣ በፊት ወንድም ብራንሐም ስለ ሰባቱ ማሕተሞች ሰብኳል።

የስድስቱ ማሕተሞች መገለጥ እና ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር የመሆኑ መገለጥ፣ እነዚህ ሁሉ መልአኩ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ተገልጠዋል።

ስድስት ማሕተሞች ብቻ ናቸው የተገለጡት።

63-0803 ተጽእኖ

ሰባት መላእክት ወረዱና እንዲህ አሉ፡- “የባለ ስድስት ማሕተሙ የእግዚአብሔር ሚስጥር አሁን ይገለጣል።”

ሰባት መላእክት ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይልስ ወደ ደቡብ ርቃ በምትኘው ሳንሴት ፒክ የተባለች ቦታ መጥተው ወንድም ብራንሐምን ከመጎብኘታቸው ስምንት ቀን በፊት ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ደመናውን ሰሩ።

እነዚህ በዓይን ሳይታዩ ወደ ወንድም ብራንሐም የመጡ ሰባት መላእክት የብርቱው መልአክ መምጣት አይደሉም።

64-0816 ቃሉን ማረጋገጥ

ሰባተኛው መልአክ የስድስቱን ማሕተም ሚስጥር ሊገልጥ ነው የተላከው።

ይህም ደግሞ ሰባተኛው ማሕተም አለመገለጡን ያመለክታል።

64-0719 የመለከት በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተገለጠም። ምክንያቱም ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

እስከ 1964 ድረስ እንኳ ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተገለጠም።

63-0324 ሰባተኛው ማሕተም

ቃሉ ውስጥ እንደምንየው በጉ ወይም ክርስቶስ መጽሐፉን በእጁ ወስዶ ሰባተኛውን ማሕተም ይፈታዋል። ነገር ግን እንደምታዩት የተሰወረ ሚስጥር ነው። ማንም አያውቀውም

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም የሰባተኛውን ማሕተም መገለጥ አላገኘም። ሰባተኛው ማሕተም ዝምታ ብቻ ነበረ።

ስለዚህ ብርቱው መልአክ የማሕተሞቹን መገለጥ ሊሰጠው አልወረደም።

ስለ ሰባቱ ማሕተሞች የሰበከው መልአኩ ከመውረዱ በፊት ነው።

በሰባቱ መላእክት አማካኝነት ለወንድም ብራንሐም ስድስት ማሕተሞች ተገልጠውለት ነበር። እነዚያም የስድስት ማሕተም መገለጦች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት ዓይኖቹን አብርተውለታል፤ ነገር ግን የታላቁ መከራ ዝርዝር ጉዳዮች አልተገለጡለትም ምክንያቱም እነዚህ ሙሽራይቱን አይመለከቷትም። ደግሞም የጌታን ዳግም ምጻት ሚስጥር አናውቅም።

1963-1110 አሁን በሲኦል ያሉ ነፍሳት

“እርሱም ይህ መልአክ ሲወርድ አየ …

“እጆቹን ወደ ሰማይ አንስቶ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው ማለ፣” ዘላለማዊው አባት እግዚአብሔር “ከእንግዲህ አይዘገይም” ብሎ ማለ ይህ በሚሆንበት ሰዓት። ጊዜው አልቋል። ተፈጽሟል። አልቋል

 

ይህን የተናገረው በ1963 ሲሆን በዚህም ጊዜ እንኳን ስለ መልአኩ ወደ ፊት እንደሚመጣ ነበር የሚናገረው።

1964-0112 ሻሎም

ነዚህ ሚስጥራት ሁሉ ይፈጸሙ ዘንድ በሰባተኛው ሰዓት ሰባተኛው መልእክተኛ ይነሳል። አያችሁ? ሰባተኛው ምድራዊ መልእክተኛ፤ አያችሁ ይህ ብዙ ጊዜ የተባለው መልአክ በዚያ ጊዜ በምድር ነበረ። መልአክ ማለት መልእክተኛ ነው

ከዚያም ቀጥሎ ሌላ መልአክ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፣ ይህም በዚህ ምድር ላይ መልእክት የተሰጠው ምድራዊው መልአክ አይደለም፤ ነገር ግን (ሌላ) ብርቱ መልአክ ከሰማይ መጣ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረው፤ እግሮቹንም በምድር እና በባሕር ላይ አድርጎ በመቆም እንዲህ ብሎ ለዘላለም በሚኖረው ማለ፡- “ከእንግዲህ አይዘገይም።” አያችሁ? ነገር ግን ሰባቱን ማሕተሞች ከመፍታቱ በፊት አስቀድሞ ተዓምራዊ ምልክቶችን መጀመሪያ በሰማይ ያሳያል።

ያን ዕለት በደቡባዊቷ ዩናይትድ እስቴትስ እና ሜክሲኮ ውስጥ ፎቶ ሲያነሱ ዋሉ። ፎቶውም እስከ ዛሬ ድረስ ላይፍ መጽሔት ውስጥ አለ፤ ግን ምን ማለት እንደሆነ አልተረዱም። እርሱ ግን በምድር ሳይፈጽመው በፊት አስቀድሞ በሰማይ ያውጀዋል። ሁሌ እንዲህ ነው አደራረጉ። መጀመሪያ በሰማይ ምልክቶችን ያሳያል

ደመናው ፎቶግራፍ ከተነሳ ከዓመት በኋላ እንኳ ስለ ደመናው ሲናገር ምልክት ነው ብሎ ነው የሚናገረው።

በምድር ላይ ያለው መልእክተኛ ሚስጥራቱን ሁሉ መግለጥ እንዳለበት እና መልአኩም ወደ ምድር የሚወርደው “ከዚያ በኋላ” ብቻ እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል።

 

ወንድም ብራንሐም የመጨረሻ ስብከቱን የሰበከው ታሕሳስ 1965 ነበር። ያም ሚስጥራቱን ገልጦ የጨረሰበት ጊዜ ነው። ስለዚህ መልአኩ ወደ ምድር መውረድ የሚችለው ከታሕሳስ 1965 በኋላ ብቻ ነው።

 

ሶስተኛው ማሕተም

... ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ባሰማ ጊዜ ድምጹን በማሰማቱ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ይጠናቀቃሉ። ከዚያም ከተገለጠ በኋላ ብርቱው መልአክ ከሰማይ ይወርዳል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው (ይህ መልአክ በምድር ላይ የሚኖር መልእክተኛ እንደሆነ አስተውሉ)።

 

… እነዚህ ሰባት ነጎጓዶች ድምጻቸውን ከማሰማታቸው በፊት ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ያልቃሉ

 

መጀመሪያ የተጻፈው ቃል ሚስጥራት በወንድም ብራንሐም መገለጥ አለባቸው። ከዚያም ሚስጥራቱ ከተገለጡ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ወደ ምድር የሚመጣው።

ስለዚህ መልአኩ ሚስጥራቱን ለመግለጥ አይመጣም።

 

መልአኩ የመውረዱ ዓላማ ምንድነው?

 

64-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

 

በ1964 እንኳ ስለ መልአኩ መምጣት ወንድም ብራንሐም ወደ ፊት የሚሆን ነገር አድርጎ ነበር የሚናገረው።

ከሁሉም በላይ ግን መልአኩ ወደ ምድር ሲወርድ ምን ለማድረግ እንደሚመጣ ገልጧል።

ብርቱው መልአክ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ሙታንን ያስነሳቸዋል።

ስለዚህ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ የመላእክት አለቃ ነው።

 

50-04-05 መጠባበቅ

ወደ ጨለማ ዋሻ ውስጥ እየገባን ነው፤ እርሱም የሞት ዋሻ ነው። ሁሉም ሰው ወደዚህ ዋሻ ውስጥ ይገባል። በያንዳንዱ የልብ ምታችን ወደዚህ ዋሻ አንድ እርምጃ ቀረብ እንላለን። እኔ ራሴ አንድ ቀን ወደዚህ ዋሻ እገባለው። የመጨረሻዋ የልብ ትርታዬጋ ስደርስ እንደ ፈሪ እየተንቀጠቀጥኩ መግባት አልፈልግም፤ ራሴን በጌታ ጽድቅ መሸፈን እፈልጋለው፤ ጽድቁን ለብሼ ነው ወደዚህ ዋሻ ውስጥ መግባት የምፈልገው፤ እርሱን በትንሳኤ ኃይሉ ላውቀው እፈልጋለው። እነርሱም … መልአኩ ታላቅ ድምጽ ያሰማል፤ መለከቱም ድምጹን ያሰማል፤ በዚያ ጊዜ ከሙታን መካከል ወጥቼ መነሳት እፈልጋለው

 

1955-01-09 የአሕዛብ ዘመን መጀመሪያ እና ማብቂያ

“በዚያን ጊዜ ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” ሚካኤል በእርግጥ በሰማያት ከሰይጣን ጋር የተደረገውን ጦርነት የተዋጋው ክርስቶስ ነው። ሚካኤል እና ሰይጣን ተዋጉ።

57-10-06 ጥያቄዎችና መልሶች 3፤ ባሕርይ፣ ሥርዓት፣ አስተምሕሮ

ሙሴ እንዲህ አልነበረም … በፍጹም፤ አካሉ እንዳይገኝ ተደርጓል። መላእክት ይዘውት ሄደዋል እንጂ አልሞተም፤ አልበሰበሰም። ሙሴ ፍጹም የሆነ የክርስቶስ ጥላ ነበረ። ሞተ፤ መላእክትም ይዘውት ሄዱ፤ ስለዚህ ሰይጣን እንኳ የሙሴ አካል የት እንደተቀበረ አያውቅም። ሰይጣን ከመላእክት አለቃ ከሚካኤል ጋር ስለ ሙሴ ስጋ ተከራከረ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ይህ ነው። እግዚአብሔርም በንጥቀት ወስዶታል።

 

1949-12-25 የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት

አሮጌውን ጥምጣም በራሳችሁ ላይ አትጠምጥሙ፤ የክርስቶስን መጎናጸፊያ ልበሱ እርሱም መንፈስ ቅዱስን መልበስ ነው፤ ጳውሎስም እንደተናገረው፡- “ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ?” ሙታን ወደሚኖሩበት ወደ ጨለማው የሞት ዋሻ ስትገቡ የመላእክት አለቃውን ድምጽ እየሰማችሁ ግቡ፤ እርሱም ከሙታን መካከል ለይቶ ይጠራናል፤ እኛም ወዳጆቻችንን በድጋሚ እናገኛቸዋለን።

የመላእክት አለቃው ድምጽ ከሞት ያስነሳናል።

ኢየሱስ የመላእክት አለቃ ሆኖ ሲገለጥ ስሙ ሚካኤል ይባላል።

1963-04-21 የድል ቀን

ሁላችንም ድል ነስተናል። በብዙ ጦርነቶች ውስጥ ድል አድራጊዎች ሆነናል። ደግሞም በጣም በቅርቡ ታላቅ ድል እየመጣልን ነው። የድል ቀናችን የእግዚአብሔር ልጅ ሰማያትን ቀዶ በመላእክት አለቃ ድምጽ ሲመጣ በቅርቡ ይገለጣል፤ ጌታም ዳግም ይመጣል። መቃብሮች ይከፈታሉ፤ ሙታንም ከመቃብሮቻቸው ወጥተው ይሄዳሉ።

 

አራተኛው ማሕተም

ከዚያም ሰባቱ ማሕተሞች ከተጠናቀቁ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች እናገኛለን፤ ዮሐንስ ያያቸውንና የሰማቸውን ነገሮች እንዲጽፍ ታዞ ነበር፤ ነገር ግን የነጎድጓዶቹን ቃል አትጻፍ ተባለ። ነጎዶጓዶቹም ድምጻቸውን በሚያሰሙበት ሰዓት ክርስቶስ ወይም ብርቱው መልአክ በራሱ ላይ ቀስተ ደመና አድርጎ ሲወርድ እናያለን፤ እግሮቹንም በምድር እና በባሕር ላይ አሳርፎ ከዚያ ወዲያ እንደማይዘገይ ይምላል።

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ሰባቱ ማሕተሞች ከተጠናቀቁ በኋላ ነው።

67-0719M የመለከቶች በዓል

እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም እስካሁን አልተፈታም። ሰባተኛው ማሕተም የጌታ ምጻት ነው።

ነገር ግን በ1964 ሰባታኛው ማሕተም አልተፈታም ነበር፤ ስለዚህ በዚያ ዓመት መልአኩ ወደ ምድር አልወረደም።

63-1110 አሁን በወኅኒ ያሉ ነፍሳት

በጉ ከስድስተኛው ማሕተም በኋላ ልክ ሰባተኛው ማሕተም ሊፈታ ጊዜው ሲደርስ መጽሐፉን ይወስደዋል። ሰባተኛውን ማሕተም ግን ከእኛ እንደሰወረው አትርሱ። ስለዚህ አልገለጠልንም።

ሰባተኛው ማሕተም ለማንም ተገልጦ አያውቅም።

ወንድም ብራንሐም በተቀበለው ትዕዛዝ መሰረት መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉትን ሚስጥራት ገለጠ።

ሰባተኛው ማሕተም ከተገለጠ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ሊወርድ የሚችለውና ሰባቱ ነጎድጓዶችም ድምጻቸውን ሊያሰሙ የሚችሉት።

 

1962 12 30 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

(ታላቅ ማሕተም) … ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው፤ አትጻፈውም።

ጀርባው አይደለም። መጽሐፍ ተጽፎ ሲጠናቀቅ … በፊለፊቱ በኩል አላለም፤ በጀርባው ነው ያለው። ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ማለት ነው፤ ከዚያም እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች የተናገሩት ነገር ብቻ ነው ከመጽሐፉ ውስጥ ሳይገለጥ የቀረው። መጽሐፉ ውስጥ እንኳ አልተጻፈም።

… እነዚህ ማሕተሞቹ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ነው ያሉት፤ ሰባተኛው መልአክም ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ መጽሐፉ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራት በሙሉ ይጠናቀቃሉ።

 

የመጽሐፉ ጀርባ ማለት የጀርባ ሽፋኑ ነው፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፈው የሚገኙ ሚስጥራት በሙሉ መገለጣቸውን ያሳያል።

ስለዚህ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ የተቀመጡት ሰባቱ ነጎድጓዶች መጽሐፉ ውስጥ ሊጻፉ አይችሉም። ሰባቱ ነጎድጓዶች ሊገለጡ የሚገባቸው የተጻፉት ሚስጥራት አካል አይደሉም።

1962 12 30 ይህ የመጨረሻው ምልክት ነውን?

“ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን መጽሐፉ ውስጥ የተጻፈው ሚስጥር በሙሉ ይጠናቀቃል።” በዚያ ቀን ሁሉም ነገር ያልቃል። ምን ማለቴ እንደሆነ ገብቷችኋል? እየተከታተላችሁኝ ናችሁ?

ከዚያ ቀጥሎ የራዕይ ምዕራፍ 10 ሰባት ድምጾች የሚገለጡበት ሰዓት ይመጣል።

መጽሐፉ ሲጠናቀቅ አንድ ነገር ብቻ ይቀራል፤ እርሱም የሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥራዊ ድምጽ ነው፤ ይህም ዮሐንስ እንዳይጽፍ የተከለከለው መጽሐፍ ጀርባ ላይ ይገኛል።

 

ሁለት የተለያዩ ምጻቶች አሉ።

ሚስጥራቱ እንደ እግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ምድር ይመጣሉ። (ፊተኛው ወይም የትምሕርት ዝናብ ይጀምራል)።

ከዚያ በኋላ ብርቱው መልአክ ሙታንን ለማስነሳት ወደ ምድር ይወርዳል። (ይህም ኋለኛው ወይም የመከሩ ዝናብ የሚጀምርበት ወቅት ነው)።

1963-03-17 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ

… ሰባተኛው መልአክ የተሰጠውን ሚስጥር መግለጥ ሲጀምር እነዚህ ሰዎች ነካክተው መርመረው የተዉአቸውን በሙሉ ይቋጫል፤ ሚጥራቱም በእግዚአብሔር ቃል መልክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ምድር ይወርዳሉ፤ ሲወርዱም የእግዚአብሔርን መገለጥ በሙሉ ይገልጣሉ። ከዚያ በኋላ የመለኮት ሚስጥር እንዲሁም ሌላውም የተሰወረ ነገር ሁሉ ግልጽ ይሆናል። ሚስጥራት ሁሉ፣ የእባቡ ዘር እና ሌሎችም ይገለጣሉ።

ሰባተኛው ማለትም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በዚህ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሰዎች ሲመረምሯቸው የነበሩ ሚስጥራት ሁሉ በአንድነት ይጠቃለላሉ።

ማሕተሞቹ ሲፈቱና ሚስጥሩ ሲገለጥ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል፤ መልእክተኛው ክርስቶስ ከራሱ በላይ ቀስተ ደመና አድርጎ እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ አድርጎ ይቆማል።

ይህንን አስታውሱ፤ በዚህ ምጻት ጊዜ ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ ይኖራል።

ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ የሚኖረው በየትኛው ምጻት ጊዜ ነው።

ምስጢራቱ ከሰማይ ሲወርዱ ነው ወይስ መልአኩ ወደ ምድር ሲወርድ?

ወንድም ብራንሐም በመቀጠል እንዲህ አለ፡-

1963-03-17 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ

አሁንም ወደ 10ኛው ምዕራፍ ተመልሶ ከሚመጣው ጊዜ በኋላ ሚስጥራቱ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይናገራል፤ ማሕተሞቹም ይፈታሉ ከዚያም በኋላ ዘመን እንደማይኖር ይታወጃል።

እርሱም እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ማሰማት ሲጀምር የዚያን ጊዜ ሚስጥራቱ ሁሉ ይፈጸማሉ፤ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል

በጣም ቀርበናል፤ ጊዜው ደርሷል። እውነት ነው።

መልአኩ የሚመጣው ሊገለጡና ሊጠናቀቁ የሚገባቸው ሚስጥራት ከመጡ በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

“ሚስጥራቱ ይፈጸማሉ መልአኩም የሚገለጥበት ጊዜ ይመጣል”።

ነገር ግን ሚስጥራቱ የተጠናቀቁት በ1965 ነው። ስለዚህ መልአኩ ከዚያ ዓመት በፊት ሊገለጥ አይችልም።

ቀጣዩን ዓረፍተ ነገር በጥንቃቄ አንብቡ፡

ማሕተሞቹ ሲፈቱ እና ሚስጥራቱ ሲገለጡ የዚያን ጊዜ መልአኩ ይወርዳል፤ መልእክተኛው ማለትም ክርስቶስ ይመጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ ያሳርፋርል፤ ከራሱም በላይ ቀስተደመና ይታያል።

እንግዲህ ልብ በሉ፤ ይህ ሰባተኛ መልአክ በዚህ ምጻት ጊዜ በምድር ላይ ነው።

 

መልአኩ ወደ ምድር የሚወርደው ማሕተሞቹ ከተፈቱና ሚስጥሩ በሙሉ ከተገለጠ በኋላ ነው።

ሚስጥሩ ሙሉ በሙሉ ተገልጦ የተጠናቀቀው የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ታሕሳስ 1965 ሲያበቃ ነው።

ሰባተኛው ማሕተም እስከ ዛሬ ድረስ አልተገለጠም።

ራዕይ 8፡1 ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።

ዝምታው ምን ማለት እንደሆነ እስከ ዛሬ ድረስ አናውቅም።

ስለዚህ መልአኩ እስከ ዛሬ ድረስ ወደ ምድር አልወረደም።

ነገር ግን የተጻፈው ቃል ውስጥ ያሉት ሚስጥራት ወደ ምድር በሚወርዱበት ጊዜ ሰባተኛው መልአክ በምድር ላይ መገኘት ነበረበት ምክንያቱም የእርሱ አገልግሎት ሚስጥራቱን መግለጥ ነበር።

ስለዚህ “የዚህ ምጻት” ጊዜ የሚለው “የሚስጥራቱን ወደ ምድር” መምጣት የሚያመለክት ነው።

 

ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ መልአኩ ወደ ምድር ወርዷል የምትሉ ከሆነ መልአኩ የወረደበት ቀን መች ነው?

በ1964 ወንድም ብራንሐም የመልአኩን መውረድ ሲጠባበቅ ነበር። ስለዚህ የ1963ቱ ደመና መልአኩ አልነበረም። ደመናው ወደ ምድር አልወረደም። ከፀሃይ መጥለቅ በኋላ በ42 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ለ28 ደቂቃ እየታየ ነው የቆየው።

በወንድም ብራንሐም አገልግሎት ውስጥ የትኛው ሌላ ክስተት ነው የመልአኩ መውረድ ተብሎ ሊቆጠር የሚችለው? የትኛውም አይደለም።

መልአኩ ከወረደ በኋላ ሙታንን ያስነሳቸዋል። ይህ ደግሞ እስካ አሁን ድረስ ያልተፈጸመ ነገር ነው።

 

ስለዚህ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ መልአኩ ወደ ምድር መጥቷል ማለት ከንቱ እና አሳሳች ንግግር ነው። ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የተተረጎመ የሰው ንግግርን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፈንታ የሰው ንግግር ጥቅሶችን የእምነታችሁ መሰረት ማድረግ መጨረሻችሁ ታላቁ መከራ ውስጥ እንዲሆን ያደርጋል።

 

63-0321 አራተኛው ማሕተም

ከዚያም ሰባቱ ማሕተሞች ከተጠናቀቁ በኋላ ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች እናገኛለን፤ ዮሐንስ ያያቸውንና የሰማቸውን ነገሮች እንዲጽፍ ታዞ ነበር፤ ነገር ግን የነጎድጓዶቹን ቃል አትጻፍ ተባለ።

ነጎዶጓዶቹም ድምጻቸውን በሚያሰሙበት ሰዓት ክርስቶስ ወይም ብርቱው መልአክ በራሱ ላይ ቀስተ ደመና አድርጎ ሲወርድ እናያለን፤ እግሮቹንም በምድር እና በባሕር ላይ አሳርፎ ከዚያ ወዲያ እንደማይዘገይ ይምላል።

ሰባቱ ማሕተሞች ካለቁ በኋላ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል። እስከ አሁን ግን ሰባተኛው ማሕተም አልተጠናቀቀም። ዝምታ እንደነበረ እናውቃለን፤ ነገር ግን ዝምታውን ልንተረጉመው አንችልም።

63-06-23 በክፍተቱ መካከል መቆም

የሰባተኛው መልአክ መልእክት በተሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ይገለጣሉ። ከዚያም ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ

መጀመሪያ ሙሽራይቱን ወደ ሰማይ ለመነጠቅ የሚያዘጋጁዋት ሚስጥራት በሙሉ መገለጥ አለባቸው። ከዚያ በኋላ ብርቱው መልአክ ወደ ምድር መውረድ ይችላል። ሰባቱ ነጎድጓዶችም ቃላቸውን ማሰማት የሚችሉት ከዚያ በኋላ ነው።

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

… ያልተቋጩትን ነገሮች ሰብሰብ አድርጎ ቤተክርስቲያን ለመነጠቅ ትዘጋጅ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሚስጥራት በሙሉ የሚገልጥልንን መልእክተኛ መቀበል አለብን። ቀጥሎ ደግሞ ሰባት ሚስጥራዊ ነጎድጓዶች ይመጣሉ፤ እነዚህም ነጎድጓዶች ምን ብለው እንደተናገሩ አልተጻፈም።

ሙሽራይቱ ለቤተክርስቲያን ንጥቀት መዘጋጀት እንድትችል የእግዚአብሔርን ሚስጥር መገለጥ ሙሉ በሙሉ ማግኘት አለባት። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው መልአኩ ሙታንን ለማስነሳት እና ለሙሽራይቱ ንጥቀት ወደ ምድር መምጣት የሚችለው። ያም ወቅት የመከሩ ዝናብ ወይም ኋለኛው ዝናብ ይባላል። የሚታጨዱት ብቻ ናቸው መከሩ ውስጥ የሚሆኑነት።

1963 03 20 ሶስተኛው ማሕተም

ሰባተኛው መልአክ ድምጹን ባሰማ ጊዜ ድምጹን በማሰማቱ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ይጠናቀቃሉ። ከዚያም ከተገለጠ በኋላ ብርቱው መልአክ ከሰማይ ይወርዳል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው (ይህ መልአክ በምድር ላይ የሚኖር መልእክተኛ እንደሆነ አስተውሉ)። ክርስቶስ ወደ ምድር ይወርዳል (ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ታዩታላችሁ)፤ ከዚያም አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን ደግሞ በባሕር ላይ ያኖራል፤ ከራሱ በላይ ቀስተደመና አለ፤ እግሮቹ -- እግሮቹ እንደ እሳት ወዘተ. ፤ እርሱም እጆቹን አንስቶ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖው ምሎ ከዚያ ወዲያ ጊዜ እንደማይኖር ይናገራል።

… ይህንንም መሃላ በማለ ጊዜ ሰባት ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰሙ

 

… እነዚህ ሰባት ነጎጓዶች ድምጻቸውን ከማሰማታቸው በፊት ሚስጥራት ሁሉ ተገልጠው ያልቃሉ

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የሚገለጡት ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ከማሰማታቸው በፊት ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ከተገለጡ በኋላ መልአኩ ወደ ምድር ይወርዳል።

 

63-0318 የመጀመሪያው ማሕተም

ከዘመናት በፊት ያለፉ ሚስጥራትን በሙሉ ይገልጣል፤ ሁሉንም ይገልጣል፤ ራዕይ 10፡1-7። ይህ ነው የሚሆነው። ይህም መፈጸም አለበት

ራዕይ 10፡1-7 የሚናገረው ስለ ወደፊቱ ነው።

ራዕይ 10፡7 … ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ …

ለዚህ ነው ቁጥር 7 ውስጥ “ግን” የሚል ቃል የምናገኘው፤ ምክንያቱም መልአኩ ወደ ምድር የሚመጣው ገና ወደ ፊት ሲሆን የእግዚአብሔር ሚስጥር (ቃሉ) ግን አስቀድሞ በሰባተኛው መልአክ ተገልጧል።

በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍተው የነበሩ ሚስጥራት በሙሉ መገለጥ አለባቸው። ይህም ሊሆን የሚችለው ወንድም ብራንሐም የስድስቱን ማሕተሞች መገለጥ ካገኘ በኋላ ብቻ ነው። ስድስቱ ማሕተሞች ከተገለጡ በኋላ የጥንቷ ቤተክርስቲያን የምታውቃቸው ሌሎቹ ሚስጥራትም እንዲገለጡ በር ተከፍቷል።

አሁን ቁልፍ ወደ ሆነው ሃሳብ ደርሰናል።

መልአኩ ወደ ምድር ከመውረዱ በፊት ሚስጥራቱ ለሙሽራይቱ መገለጥ አለባቸው

ወንድም ብራንሐም ሚስጥራቱን ማወቁ በቂ አይደለም። ሙሽራይቱም ጭምር ሚስጥራቱን ማወቅ አለባት።

አስደናቂው የወንድም ብራንሐም አገልግሎት ኋላ መጨረሻው ላይ ለመጣው ለአገልግሎቱ ማሳረጊያ ለሆነው ትምሕርት ትኩረት መሳቢያ ነበረ።

ስለዚህ በምድር ላይ ካደረገው አገልግሎቱ አንጻር ራዕይ 10፡7 ተፈጽሞ ያለፈ ነገር ነው።

ነገር ግን ገና ወደፊት ሊፈጸም ያለ ጭምር ነው፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ የሙሽራይቱ አካል ወንድም ብራንሐም ካዘጋጀም ትምሕርት ውስጥ እርሱ የተናገራቸውን ቃሎች ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስዶ በመመርመር ጠለቅ ያለ መረዳት ማግኘት አለበት፤ በዚህም መንገድ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት መጀመር እንችላለን

መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ የተከፈተ መጽሐፍ መሆን አለበት።

 

ወንድም ብራንሐም በ1965 ከምድር ተለይቶ ሄዷል፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ መልእክቱ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ውስጥ ይቀጥላል።

ከመሞቱ በፊት እና ከሞተበት ቀን በኋላ በነበሩት ቀናት ሁሉ በድምጽ ተቀርጸው የተቀመጡት እና በጽሑፍ የታተሙት መልእክቶቹ በሙሉ አሉ።

እርሱ ከሞተ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደፊት በሚመጡ ዓመታት ውስጥ የስብከቱን መልእክት መረዳት አለብን። ከዚያ በኋላ እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ መመሰረተ አለብን። ብርቱው መልአክ ሙታንን ለሚያስነሳበት ጊዜ መዘጋጀትና ወደ ጥንቶቹ ሐዋርያት እምነት መመለስ እንድንችል እነዚህን መረዳቶች እርሱ ካስተማራቸው ትምሕርቶች ውስጥ ማገኘት ይጠበቅብናል።

ቁም ነገሩ ዊልያም ብራንሐም የተባለው ግለሰብ አይደለም።

ቁም ነገሩ እርሱ የሰበከው መልእክት ነው።

 

ለዚህ ነው ሰባቱን ማሕተሞች ለወንድም ብራንሐም ሊገልጡለት የመጡት ሰባት መላእክት በልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና መልክ ታይተው ወንድም ብራንሐም በአካባቢው ባልነበረበት ሰዓት ፎቶግራፍ ሊነሱ የቻሉት። ስለ ማሕተሞቹ ሰብኮ ከጨረሰ በኋላ የተወሰኑ ወራት እስኪያልፉ ድረስ ስለ ደመናው ምንም አልሰማም ነበር።

 

ቁም ነገሩ የተገለጠው ቃል ነው እንጂ ቃሉን የገለጠው ግለሰብ አይደለም።

ዮሐንስ 3፡30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።

ይህ መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው አስደናቂ ቃል ነው። መጥምቁ ዮሐንስ የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት አስተዋውቆ የኢየሱስን ዳግም ምጻት በመልእክቱ ለሚያስተዋውቀው ነብይ ምሳሌ ትቶለት አለፈ።

ዮሐንስ ኢየሱስን በሰዎች መካከል እንደሚመላለስ ሰው ገለጠው።

ወንድም ብራንሐም ደግሞ ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች መካከል ሲመላለስ ገለጠው።

ነገር ግን ትልቅ ልዩነት አለ። ለዳግም ምጻት መንገድ ጠራጊው ዊልያም ብራንሐም አይደለም፤ ነገር ግን እርሱ ያስተላለፈው መልእክት ለዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።

61-0316 ቤተክርስቲያን በጸጋ ፈንታ ሕግን ስትመርጥ

ካጠመቅኳቸው ሰዎች መካከል አስራ ሰባተኛው ሰው በድንገት “ወደ ላይ ተመልከት” ሲል ሰማሁ። እየተመለከትኩም ሳለ የእሳት አምድ ከሰማይ እየተሽከረከረ ወረደ። ልክ እኔ የቆምኩበት ቦታ መጥቶ ቆመ፤ ከዚያም እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “መጥምቁ ዮሐንስ ለመጀመሪያው የክርስቶስ ምጻት መንገድ ጠራጊ ሆኖ እንደተላከ ሁሉ ያንተ መልእክት ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።”

 

“The Revelation of the Seven Seals” ወይም “የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ” በሚል ርዕስ በ1993 በታተመው መጽሐፍ ውስጥ አሳታሚዎች የሰሩትን ስሕተት ልብ በሉ።

ከወንድም ብራንሐም ራስ በላይ በፎቶግራፍ ውስጥ የሚታየው የእሳት አምድ መልአኩ እንደሚከተለው ብሎ እንደተናገረ ያሳያል፡-

“መጥምቁ ዮሐንስ ለመጀመሪያው የክርስቶስ ምጻት መንገድ እንደ ጠረገ ሁሉ አንተ ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ ትጠርጋለህ።”

ይህ ትክክል አይደለም። ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ የሚጠርገው እርሱ ሳይሆን መልእክቱ ነው።

በድምጽ የተቀዱት መልእክቶቹ ከ1947 እስከ 1965 ማለትም ለ18 ዓመታት ነው የተቀረጹት።

መጽሐፎቹ፣ በድምጽ የተቀዱ መልእክቶቹ፣ MP3ዎቹ፣ የኢንተርኔት ገጾቹ መልእክቱን በዓለም ዙርያ ከ1965 እስከ 2020 ድረስ አሰራጭተዋል። ይህም 55 እና ከዚያ በላይ ዓመታት ማለት ነው።

 

ስለዚህ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን መልእክቱ እርሱ ሲሰብክ ካሳለፋቸው ዓመታት በሶስት እጥፍ ለሚበልጡ ዓመታት ሲደመጥ ቆይቷል።

 

65-0218 ዘሩ ከገለባው ጋር አይደለም የሚወርሰው

ድምጽ መጣና እንዲህ አለ፡- “መጥምቁ ዮሐንስ ለመጀመሪያው የክርስቶስ ምጻት መንገድ ጠራጊ ሆኖ እንደተላከ ሁሉ ያንተ መልእክት ለክርስቶስ ዳግም ምጻት መንገድ ይጠርጋል።”

 

ወንድም ብራንሐም ከሞተ ወደ 60 ዓመታት ያህል አልፈዋል፤ ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን በቴፕ ተቀድተው የተቀመጡ ስብከቶቹን እያደመጥን እምነታችንን ማቃናት እንችላለን። ስለዚህ ዋናው ነገር ያስተላለፈው መልእክቱ ነው። ዋናው ነገር ሰውየው ራሱ አይደለም።

እንደ ሰው ሟች በመሆኑ በምድር ላይ የሚኖርበት ዘመን ውስን ነው፤ መልእክቶቹ ግን እርሱ ከሞተ በኋላም ወደፊት ለረጅም ዘመናት ይደመጣሉ።

የሚያሳዝነው ነገር የመልእክቶቹ አሳታሚ ሰውየው ላይ ትኩረት ማድረግ መፈለጉ ነው።

ይህም ጥሩ ሃሳብ አይደለም።

 

አሳታሚዎች የሰሩትን ሌላ ስሕተት እንመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ፡- “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” ይላል።

መጻሐፎቹ እንዲህ ነበር የሚታተሙት። ዛሬ ግን በድንገት መጽሐፎቹ እና በድምጽ የተቀዱት ስብከቶች “የእግዚአብሔር ድምጽ” ተብለዋል። ይህም ትክክል አይደለም።

“የእግዚአብሔር ድምጽ” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜም እንኳ አይገኝም።

 

ስለዚህ “የእግዚአብሔርን ድምጽ” እንደምንሰማ ተስፋ አልተሰጠንም።

አሁንም አሳታሚዎቹ የግል አመለካከታቸውን ተከትለው ዊልያም ብራንሐም የተባለውን ሰው ሊመዝኑ ሞክረዋል፤ አመለካከታቸውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።

ማጋነን እና የሕዝብ አድናቆት መፈለግ ስሕተት እና ጽንፈኝነትን ያስከትላል።

የተረጋጋ አእምሮ እና የጠንቃቆች ምክር ያስፈልገናል።

 

1955-0725 በዘመን መጨረሻ የተቀቡ ሰዎች

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ጥያቄው ይህ ነው። ራዕይ ምዕራፍ 10 ውስጥ ማንሳት የፈለግሁት ሃሳብ ይህ ነው። በጥቂት ደቂቃ ውስጥ እሱን እና ሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እናያለን።

እንዲህ አለ፡- “ሰባተኛው መልአክ መልእክቱ በሚሰማበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል።”

ጥያቄው ይህ ነው፡- ይህንን ቃል አሁን ብትሰሙት አሁን ይፈጸማልን?

“እምነት አገኝ ይሆን?”

ሚልክያስ ምዕራፍ 4 በዚህ ዘመን ይፈጸማልን?

“የልጆች እምነት ወደ አባቶች ወደ መጀመሪያው እምነት የሚመለሰው አሁን ነውን?” አያችሁ?

 

ወንድም ብራንሐም በሕይወቱ የመጨረሻ ወራት አካባቢ አማኞች ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እውነት አይመለሱ ይሆናል ብሎ ሲጨነቅ ነበር። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ላይመሉ ይችላሉ ብሎ ይጨነቅ ነበር።

እምነት የሚመጣው ከተጻፈው ቃል ነው።

የሜሴጅ አማኞች ግን የወንድም ብራንሐምን ንግግር ወስደው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ መመርመር አቁመዋል። ምክንያቱም ስለማይችሉ ብቻ ነው። ትርጓሜያቸውም የተሳሳተ ነው።

 

ጊዜ ያበቃል።

63-1110 በእናንተ ውስጥ ያለው

ልብ በሉ፤ እግዚአብሔር ተናግሮ ከሆነና እውነትን ከተናገረ ይህ ዘመን የታሪክ የመጨረሻ ዘመን ነው። ይህ የዓለም ታሪክ መጨረሻ ነው። የዓለም ታሪክ ሊዘጋ ነው። ከሆነ ጊዜ በኋላ ጊዜ የሚባል ነገር ፈጽሞ ይወገዳል

ደመናው ከታየ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ጊዜ ወደፊት አንድ ቀን እንደሚያበቃ ሲናገር ነበር።

64-0830 ጥያቄዎችና መልሶች - 3

ጥያቄ፡ ማሕተሞቹ ሲፈቱ ጊዜ ቢያበቃ የሺ ዓመት መንግስትም ይሰረዛል ማለት ነዋ፤ አይደለም?

መልስ፡ በፍጹም፤ በፍጹም። ማሕተሞቹ ሲፈቱ ጊዜ አላበቃም። በትክክል አልተረዳህም። የሆነው ነገር ምንድነው፤ ማሕተሞቹ ተገለጡ፤ ጊዜ ግን አላበቃም … ምክንያቱም፤ አያችሁ? ቤተክርስቲያን ተነጥቃ ወደ ሰማይ ከሄደችና ተመልሳ ከመጣች በኋላ የአንድ ሺ ዓመት ጊዜ አለን። ከዚያ በኋላ በአዲሱ ሰማይና በአዲሱ ምድር ውስጥ ነው ጊዜ የሚያበቃው

65-1127 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

… ከሰማይ መጣና እግሮቹን በምድር እና በባሕር ላይ አድርጎ ቆመ፤ ከዚያም ለዘላለም በሚኖረው ምሎ ከእንግዲህ አይዘገይም አለ።” ልክ አይደል? በራሱ ዙርያ ቀስተ ደመና አለ፤ እነዚህ ነገሮችም በሙሉ ይፈጸማሉ። ይህ መልአክ ክርስቶስ ነው! ያለ ምንም ጥርጥር እርሱ ነው! ምን ብሎ ተናገረ? “በሰባተኛው መልአክ ዘመን፣ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን።” ሁልጊዜ በቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ ነው ሰዎች ብዙ ነገር የሚያበላሹት ስለዚህ … አገልጋዮች ብዙ ነገር አበላሹ፤ እግዚአብሔር ግን መልእክተኛ ይልካል፤ በመልእክተኛውም የተላከው መልእክት ለዚያ የቤተክርስቲያን ዘመን የሚሆን መልእክት ነው። እነርሱም መልእክቱን ይወስዳሉ፤ ምክንያቱም መልእክተኛው የሚኖረው ለአጭር ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔርም … ከዚያም እነርሱ መልእክቱን ተቀብለው ሊኖሩበት ሲገባቸው የራሳቸውን ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ለመክፈት ይጠቀሙበታል። ከዚያም ቀጥለው ሌላ ዲኖሚኔሽን ይፈጥራሉ፤ ሌላ መልእክተኛ ከመካከላቸው ይነሳል፤ እርሱንም ይከተላሉ።

የሜሴጅ ፓስተሮች ራሳቸውን መልእክተኛ ለማድረግ እና ወንድም ብራንሐምን ተከትለው የእርሱን መልእክቶች ሊያሻሽሉ ራሳቸውን አዘጋጅተዋል። ስለዚህ እርሱ የተናገራቸውን ጥቅሶች እየወሰዱ ይተረጉሙዋቸዋል፤ በዚህም ድርጊታቸው ሌላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያን ከፍተው ሰውን ይሾሙበታል።

አሁን 45,000 ዓይነት የተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ከዚህ በላይ ሌላም ያስፈልገናል?

1965-12-04 ንጥቀት

ጩኸት፤ ከዚያም የንግግር ድምጽ፤ ከዚያም መለከት።

ጩኸት፡ መልእክተኛ ሕዝቡ እንዲዘጋጁ ያደርጋል።

ሁለተኛው የትንሳኤ ድምጽ ነው፡ ዮሐንስ 11፡38-44 ውስጥ የተሰማው አላዛርን ከሙት የቀሰቀሰው ያ ድምጽ እራሱ ነው።

ሙሽራይቱ እንድትዘጋጅ ማድረግ፤ ከዚያም የሙታን ትንሳኤ፤ አያችሁ፤ ከዚያ አብሮ በንጥቀት መሄድ። አሁን ሶስቱን የሚፈጸሙ ነገሮች ልብ በሉ። ቀጣዩ ምንድነው? መለከት። ድምጽ … ጩኸት፤ ድምጽ፤ መለከት።

ሶስተኛው ነገር መለከት ነው። ሁልጊዜ በመለከት በዓል መለከት ሲነፋ ሕዝቡ የዓል ድግስ ለመብላት ይሰበሰባሉ። ይህም በሰማይ የሚደገሰው የሙሽራይቱ እና የበጉ ሰርግ እራት ድግስ ነው። አያችሁ?

መጀመሪያ የሚመጣው መልእክቱ ነው። መልእክቱም ሙሽራይቱን ይሰበስባታል። ቀጣዩ ደግሞ ያንቀላፋችው ሙሽራ ከሙታን የምትነሳበት ነው፤ በሌሎች የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ የሙሽራይቱ አካላት በሕይወት ካሉት ጋር አብረው ይነጠቃሉ።

መለከቱም በሰማይ የሚደረገውን ድግስ የሚያውጅ ነው። ወገኖች የሚሆነው ነገር ይህ ነው።

የመጨረሻው መለከት ወደ ሰማይ ይጠራናል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዘመኑ ምልክት ነውን? ወደ መጨረሻው መቅረባችንን የሚያሳይ ምልክት አይደለምን? ስሙ ራሱ ትርጉም አለው።

ትራምፕ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ማድረግ ይፈልጋል።

እኛ መጽሐፍ ቅዱስን እንደገና ታላቅ ማድረግ አለብን።

“ድምጹ” ማለት ወንድም ብራንሐም መልእክቱን ሲሰብክ ማለት አይደለም።

ድምጹ የሚሆነው የሙሽራይቱ አካላት መልእክቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ በቻሉ ጊዜ ነው።

ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ ወንድም ብራንሐም ድምጹን እና የመልአኩን ወደ ምድር መውረድ ሲጠባበቅ ነበር።

65-1127

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

63-0317 በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በሰባቱ ማሕተሞች መካከል ያለው ቅርንጫፍ

ከዚያም በመጨረሻው ዘመን እነዚህ ሚስጥራት ሁሉ ይፈቱና ይገለጣሉ፤ ማሕተሞቹንም በጉ ይፈታቸዋል፤ ለቤተክርስቲያንም ይገልጣቸዋል፤ ከዚያ ወዲያ ጊዜ የሚባል ነገር ፈጽሞ አይኖርም …

ሰባተኛው ማሕተም በተፈታ ጊዜ በእነዚህ ሚስጥራዊ ማሕተሞች ውስጥ የታተመውና የተሰወረው የእግዚአብሔር ሚስጥር ይጠናቀቃል። ያ ማሕተም እስከሚፈታበት ቀን ድረስ በውስጡ ያለው ነው የሚገለጠው።

… የምልጃ አገልግሎቱ ያበቃል። ይህ መልአክ መጥቶ የሚቆመው በዚያ ጊዜ ነው (ስለ ማሕተሞቹ እስክንነጋገር ድረስ ጠብቁ።) ከዚያ በኋላ ጊዜ አይኖርም።

… ጊዜ እያለቀ ነው። ራዕይ 10፡6 ጊዜ ያበቃል ይላል

ወደፊት አንድ ቀን ጊዜ ፈጽሞ ያልቃል።

ማርጀት መጃጀት ስታቆሙ ከጊዜ ቀጠና ወጥታችኋል ማለት ነው።

ከጊዜ ቀጠና የምትወጡት አዲሱን ዘላለማዊውን አካላችሁን ስትለብሱ ብቻ ነው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23