ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይገልጣል፤ ክፍል 2
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
በኒቅያ ጉባኤ እና በጨለማው ዘመን ውስጥ እውነት ከስላሴ ጋር ሞተች። ከዚያ በኋላ ወደ መጀመሪያው ዘመን የመመለስ ትንሳኤ ሆነ።
First published on the 9th of March 2021 — Last updated on the 5th of November 2022ከሰባቱ “የመንግስተ ሰማያት” ምሳሌዎች ውስጥ ሁለተኛውን ምሳሌ እናያለን።
ማቴዎስ ኢየሱስን አንበሳው ወይም ንጉሱ አድርጎ ነው የሚገልጸው።
ንጉስ ግዛቱን ላይ ይገዛል።
ስለዚህ ኢየሱስ የሚገዛበት መንግስት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው። ባለፉት 2,000 ዓመታት ውስጥ የኢየሱስ ዋነኛ ትኩረቱ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።
ዘር ስለ መዝራት የተነገረው የመጀመሪያው ምሳሌ ቀርቦ በስፋት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። ይህም የጥንቷ ቤተክርስቲያን በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ብዙ እውነቶችን መቀበሏን ያመለክታል። የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ቃል ዘር በሐዋርያት መተከሉን የሚያሳየው ምሳሌ የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን የሚወክለው ሁለተኛው ምሳሌ ረዘም ይላል።
ይህ የሚያሳየው በስደታቸው ዘመን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈ አድርገው መቀበልና ማመን የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች እንደነበሩ ነው። ስለዚህ በዚያ ዘመን ውስጥ ሰዎች አብዛኛውን የመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያምኑ ነበር። ነገር ግን የምሳሌው ማብራሪያ አልተሰጠም። ከዚህም የተነሳ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የነበራው መረዳት በሁለተኛው ዘመን ውስጥ በቤተክርስቲያን ላይ ራሳቸውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ከተቀመጡ ሰዎች የተነሳ እየደበዘዘ መጥቷ። በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ የተገለጠው ክርስቶስ ከዚያ በኋላ የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑ ቀረ።
ሁለተኛውን ምሳሌ ባለማብራራቱ ኢየሱስ የሚያመለክተን ነገር በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ አማኞች ኤጲስ ቆጶሳትን የቤተክርስቲያን መሪዎች አድርገው በመቀበላቸው ምን ዓይነት ወጥመድ ውስጥ እየወደቁ እንደነበር አለማወቃቸውን ነው። የተከተሉት መንገድ ቤተክርስቲያንን ለመገንባት በጣም አዋጪ መንገድ ይመስል ነበር። ምንም ችግር የሌለበት መንገድ ይመስል ነበር። ለሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የተላከው ታላቁ መልእክተኛ አይሬንየስ እንኳ ሳይቀር ስለ ሮም ጳጳሳት መተካካት አድንቆ በመናገር ተጽእኖዋቸውን በዓለም ዙርያ እያስፋፋው ነበር። የሮማው ጳጳስ ጴጥሮስ የመጀመሪያው የሮም ፖፕ ነበር እያለ የውሸት ወሬ ያወራ ነበር። የሮማው ጳጳስ በችግር እና በገንዘብ እጦት ውስጥ ለወደቁ ቤተክርስቲያኖች እርዳታና ገንዘብ ይሰጥ ነበር በተለይም የሮማ መንግስት ባለስልጣናት ለሚያሳድዷቸው ቤተክርስቲያኖች። ይህም ድርጊቱ በቤተክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነቱን ከፍ አደረገለት። የዚያን ጊዜ ቤተክርስቲያኖች እያንዳንዷ ቤተክርስቲያን በሰው ቤት ውስጥ የምትሰበሰብ ትንሽዬ ብተክርስቲያን እና በሽማግሌዎች የምትተዳደር ትሁን ብለን ለምን ድርቅ እንላለን የሚል ጥያቄ ራሳቸውን መጠየቅ ጀመሩ።
ጳውሎስ ለፊሊሞን እንዲህ ብሎ ጻፈ፡-
ፊሊሞና 1፡2 ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤
1ኛ ጴጥሮስ 5፡1 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
ጴጥሮስ እራሱ ሽማግሌ ሆኖ ነው ለሽማግሌዎች የጻፈው።
ሐዋርያ ቢሆንም እንኳ እራሱን ከሌሎች በላይ ከፍ ባለማድረግ የወንድማማችን እኩልነት አጽንኦት ይሰጠዋል።
1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
ሽማግሌዎች የእግዚአብሔርን መንጋ መመገብ አለባቸው። ይህ ትዕዛዝ ለፓስተሮች አልተሰጠም።
መንጋውን መንከባከብ ገንዘብ ለማግኘት ከመፈለግ መሆን የለበትም።
ነገር ግን ጳጳሳቱ በቤተክርስቲያን ላይ ባለ ስልጣን ሆነው ተነሱ። እነርሱ ብቻ መጽሐፍ ቅዱስን መግለጥ እና መስበክ እንደሚችሉ ተናገሩ። ቤተክርስቲያን ላይ ለብቻው ሙሉ ስልጣንን የተቆናጠጠው ጳጳስ የሚሰበሰበውን የአስራት ገንዘብ በሙሉ ለራሱ ይወስዳል። በሚሰበሰበው አስራት ለራሱ እየተጠቀመ በመኖር የተረፈውን ገንዘብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ለሚስማሙ አገልጋዮች ደሞዝ ይከፍልበት ነበር። በዚህ መንገድ የጳጳሱ ወዳጆች ገንዘብ ያገኛሉ፤ የስልጣን እድገትም ያገኙ ነበር። የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ጳጳሱ ከእርሱ ጋር የማይስማሙ ሰዎች ገንዘብ እንዳያገኙ ያደርግ ነበር።
ቤተክርስቲያን የአምባገነን መሪዎች መንግስት ሆነች። በአንድ ሰው ብቻ ተመራች። እርሱ ብቻ ነው ለመስበቅ ፈቃድ የሚሰጥህ፤ ያውም ከእርሱ ጋር ከተስማማህ።
3ኛ ዮሐንስ 1፡9 ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10 ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
ጳጳሳት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሳዩ የነበረው ባህርይ ያሳዝናል። ዲዮጥራጢስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የጻፈውንና ይናገር የነበረውን ዮሐንስ በቤተክርስቲያን ውስጥ አይቀበለውም ነበር። በተጨማሪም ደግሞ ከእርሱ ጋር የማይስማማውን ማንኛውንም ሰው ከቤተክርስቲያን ያባርር ነበር። (ይህም ፓስተሮች ዛሬ ያላቸውን ባህርይ ያሳያል)።
ኒቆላውያን ቤተክርስቲያንን እየበሉዋት ነበር።
በዚህ መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ቃላት እና ሥርዓቶች ላይ የተመሰረተው የሰዎች ልማድ ሰዎች መሰረታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንዲረሱና እንዲጥሉ እያደረገ ነበር። መሃይምነት እና የተሳሳተ መረዳት የፈጠሩት ጉም ሰዎች እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማየት እንዳይችሉ እያደረገ ነበር። ቀስ በቀስ የሰው ጥበብ በተጻፈው ቃል በማመን ቦታ ሲተካ የጨለማ ኃይላት እውነትን እየሸረሸሩ አመነመኑት።
ቤተክርስቲያኖች እያደጉ ሲሄዱ የመጀመሪያ ቅንዓታቸው እየተዳከመ ሄደ፤ ክርስቲያኖችም ዓለምን እና በውስጧ ያሉትን በመከተል እየባሰባቸው ሄዱ።
(The Pilgrim Church by E H Broadbent page 11 )
በ200 ዓ.ም አካባቢ የተወለደው ሳይፕራያን “የካቶሊክ ቤተክርስቲያን” የሚለውን መጠሪያ በነጻነት መጠቀም ጀመረ፤ መዳንም ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ የለም ብሎ አመነ። ይህች ቤተክርስቲያን ያልተከተሉዋትን ሁሉ አውጥታ ትጥላለች።
በ1302 ዓ.ም Unam Sanctam የሮማ ካቶሊክ ይፋዊ አስተምሕሮዋ ሆኖ ጸደቀ፤ ማለትም ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ መዳን የለም። ለፖፑ በመገዛት ብቻ ነው መዳን የምትችሉት።
የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ አማኞች እነዚህ “ቀላል” ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን ሕጎች ምን ያህል ጎጂ እንደሚሆኑ አላወቁም።
በምዕመናን እና በካሕናት መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መጣ።
ኒቆላዊነት በሚል አሰራር አማካኝነት ካሕናቱ ምዕመናንን መጀመሪያ የበላይ ሆኑባቸው ከዚያም ገዥዎቻቸው ሆኑ። ሕዝቡ ተጨቁነው ነበር፤ ከዚያም ለቤተክርስቲያን መሪው አገዛዝ መታዘዝ ግዴታ ሆነባቸው።
ማቴዎስ 13፡24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።
25 ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።
26 ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።
27 የባለቤቱም ባሮች ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት።
28 እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም፦ እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።
29 እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።
30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።
እውነት እና ስሕተት አብረው ጎን ለጎን ያድጋሉ።
ይህ የእውነተኛ አማኞች ትልቅ ፈተና ነው።
በዙርያህ ያሉ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን እንድታምን በሚያስገድዱ መሪዎች እየተዳደሩ ትልልቅና ስኬታማ ቤተክርስቲያኖችን ሲከፍቱ እያየህ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ታማኝ ሆነህ መኖርህን ትቀጥላለህን?
ይሁዳ ከደቀመዛሙርት መካከል አንዱ ነበር። ስለዚህ የስሕተት ሰባኪዎችም በጉባኤው መካከል ትጉህ አገልጋዮች ሆነው ይኖራሉ።
ብልጥ የሆኑ ሰዎች በብልጠት ፍልስፍናቸው ብዙዎች እውነትን እንዳያውቁ ያሳውሩዋቸዋል።
በኦሪጌን ዘመን (184 – 253 ዓ.ም) አሌግዛንድሪያ ውስጥ የሥላሴን ጽንሰ ሃሳብ እንዲሁ ትክክል ነው ብሎ ተቀብሎ ክርስትናን ከአረማውያን ፍልስፍና ጋር ቀላቀለው።
ክርስትና (መጽሐፍ ቅዱን ማመን) እና ቤተክርስቲያናዊነት አብረው እያደጉ ነበር። ሰዎች ግን እውነት እየጠፋባቸው ነበር።
ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የተጠናቀቀው ኮንስታንቲን ተፎካካሪዎቹን እና ተከታዮቻቸውን ክርር ባለ ጦርነት ውስጥ ገድሎ የሮማ ገዥ በሆነ ጊዜ ነው። ክርስቲያን ሆኛለሁ አለና በ312 ዓ.ም ክርስቲያኖችን ማሳደድ አቆመ።
በ64 ዓ.ም ከንጉስ ኔሮ ጀምሮ የሮም ገዥዎች በክርስቲያኖች ላይ አስር ካባድ ስደቶችን አስነስተዋል፤ በእነዚያ ስደቶችም ውስጥ ከ3 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ከተገደሉ በኋላ ነው ኮንስታንቲን ግድያውን ያስቆመው።
ሁለተኛውን ምሳሌ ተናግሮ ሲያበቃ ኢየሱስ የምሳሌውን ፍቺ አልሰጠም፤ ይህም ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ርቃ በሰዎች መሪነት ስር በመሆን ወደ መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ መውደቋን የሚያመለክት ነው። ቤተክርስቲያናዊነት ክርስትናን እየተካው በር። የሰዎች ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ተክቷል።
ይህም ከፍ ከፍ ባሉ የሰው መሪዎች የተነሳ እውነት እየደበዘዘች በሄደች ጊዜ ቤተክርስቲያን ምን እንደምትመስል ያሳየናል።
ሶስተኛው ምሳሌ
ማቴዎስ 13፡31 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
32 እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
ይህንን ሶስተኛ ምሳሌ የሚያብራራ ብዙ የተጻፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም። ይህም ማለት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየጠፋ ነበር።
አንዲት ትንሽ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ላይ ጳጳስ መሾም ምንም ችግር የሌለው ይመስል ነበር።
ነገር ግን የሰው አመራር ቤተክርስቲያን ትልቅ ድርጅት ወደ መሆን እንድታድግ እና የአረማውያንን እምነት፣ ፖለቲካ፣ እና ሰው ሰራሽ ሕጎችን እንድትቀበል አደረጋት። ሙሉ የሆነ ሰው ሰራሽ ሥርዓት ተዘረጋ።
ካንሰር ማለት ለማደግ ብሎ ብቻ የሚያድግ እና ለእድገቱም ማቆሚያ የሌለው ነገር ነው።
በመጀመሪያው ምሳሌ ውስጥ ጠላቶች የነበሩት ወፎች አሁን የቤተክርስቲያን ተቆጣጣሪዎች ሆነዋል።
ትልቅ ዛፍ ወይም ድርጅት አድጓል፤ ይህም ትልቅነት እውነተኛው ሲጣመም ነው።
ሰናፍጭ ትንሽ ተክል ነው እንጂ እንደ ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናል፣ ፖፕ የመሳሰሉ የእውነት ጠላት የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ማዕረጎች የሞሉበት ትልቅ ዛፍ መሆን የለበትም። የጥንቷ ቤተክርስቲያን በየቤቱ የሚሰበሰቡ ትንንሽ ሕብረቶች ነበረች፤ በተለይም ብዙውን ጊዜ ይሰደዱና ይበታተኑ በነበረበት ጊዜ። ቀስ በቀስ ግን ይህ ሕብረት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ማዕረግን በተቀበሉ ሰዎች አማካኝነት ወደ ትልቅ ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ ድርጅትነት ተለወጠ።
ኮንስታንቲን የላተራን ቤተመንግስትን እና ከሮም መንግስት መዝገብ ውስጥ ብዙ ሃብት ለሮም ጳጳስ ሰጠ። የሮም ጳጳስም ኮንስታንቲን መናገሻውን በምስራቅ ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ ባደረገ ጊዜ በምዕራባዊው ዓለም ውስጥ የኮንስታንቲንን ፈቃድ አስፈጻሚ ሆነ። ስለዚህ የሮም ጳጳስም ፖለቲካዊ ኃይል አገኘ። ፖለቲካ እና ሐይማኖት በአንድ ላይ ሲጣመሩ እጅግ አደገኛ የክፋት ኃይል ይሆናሉ፤ ስለዚህ ሁሌ ተለያይተው መኖር አለባቸው።
የላተራን ቤተመንግስት በስተ ግራ ነው ያለው። የሮማ ጳጳስ ይህን ቤተመንግስት ከኮንስታንቲን በስጦ መልክ በተቀበለ ጊዜ የሚጨምርለትን ትልቅ ፖለቲካዊ ኃይል አስቡት።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ ከተማ ያለችው ቤተክርስቲያን በጳጳስ እንደምትተዳደር ሰው ሁሉ እንዲሁ ተቀበለ። ከሐዋርያት ጋር ታሪካዊ ትስስር የነበራቸው ከተሞች ተለቅ ያለ ክብር ተሰጣቸው፤ በነዚያ ከተሞች ውስጥ ያሉትም ጳጳሳት ከሌሎች በላይ ከፍ ተደረጉ። የሮም፣ የአንጾኪያ፣ የኢየሩሳሌም፣ እና የአሌግዛንድሪያ ጳጳሳት አንዱ ከሌላው በስልጣን ለመብለጥ ውድድር እያደረጉ በነበረ ሰዓት በዚያውም ሁሉም በያሉበት ተጽእኖዋቸው እየጨመረ ሄደ። ሁላቸውም ለስልጣን እና ለክብር ይሯሯጡ ስለነበረ በየከተማቸው ዋነኛ ሰዎች ሆኑ። ከዚያም ኮንስታንቲኖፕል የምስራቃዊው ግዛት ዋና ከተማ እንደመሆኗ የሮም ተቀናቃኝ ሆና ተነሳች። በክርስትና ውስጥ የተጀመረው ፉክክር ኒቆላውያን እንዲፈጠሩ አደረገ፤ እነዚህም እራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉ ስልጣን ፈላጊ ጳጳሳት ናቸው።
በሶስተኛው ዘመን ውስጥ እውነትን የገደለው ክስተት በ325 ዓ.ም የተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥላሴ የሚለውን ቃል ተጠቅማ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሄደችና ከዚያም በኋላ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን አከታተለች።
እግዚአብሔር ሶስት አካላት ያሉበት ሥላሴ ነው ብሎ ማመን ለእግዚአብሔር አንድ ስም ማግኘት አይቻለም ማለት ነው።
በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቃሉ፤ ግን ያ ስም ማን እንደሆነ መናገር አይችሉም።
ስሙን ካለማወቃቸው የተነሳ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለማጥመቅ እምቢ አሉ፤ ጴጥሮስ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው ያጠመቀው። ጴጥሮስ የመጀመሪያው ፖፕ ነው እያሉ እንኳ እርሱ እንዳጠመቀው አያጠምቁም።
በ378 ዓ.ም ቴዎዶሲየስ ንጉስ በሆነበት ዘመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖችን እንዲያሳድድ የቀረበችለትን ጥያቄ ተቀበለ።
ከዚያ ጊዜ 66 ዓመታት አስቀድሞ አረማዊ በሆነው የሮማ ንጉስ ነበር ቤተክርስቲያን ስደት የገጠማት። ከዚያ በኋላ ግን ቤተክርስቲያን እራሷ የአረማውያን አሳዳጅ ሆነች።
በ382 ዓ.ም ቴዎዶሲየስ ለሮም ጳጳስ ለዳማሰስ ፖንቲፍ ወይም ፖንቲፌክስ ማክሲመስ የሚል ማዕረግ ሰጠው፤ ማለትም የባቢሎናውያን ሚስጥራት ሊቀ ካሕናት።
በ450 ዓ.ም ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ አረማውያንን ማሳደዱን አጠናክሮ ቀጠለ፤ ከዚያም ጋር አያይዞ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር የማይስማሙ ክርስቲያኖችንም ጭምር አሳደደ።
ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ606 ዓ.ም አካባቢ ተጠናቀቀ፤ በዚያም ጊዜ የሮማው ጳጳስ እራሱን በክርስትና ሁሉ ላይ ስልጣን ያለው የዓለም ሁሉ ጳጳስ አድርጎ ቆጠረ።
ፖፑ እንደ “ወፍ” በዲኖሚኔሽናዊው የቤተክርስቲያን አወቃቀር አናት ላይ ተቀመጠ።
አራተኛው ምሳሌ
ማቴዎስ 13፡33 ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
ይህ ምሳሌ ሊያብራራው የሚችል ሌላ ጥቅስ የለም። አንድ ብቸኛ ጥቅስ ነው።
ይህ በቤተክርስቲያናት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ያልነበረበትን የጨለማውን ዘመን ይወክላል። የጨለማው ዘመን ከ606 እስከ 1520 ዓ.ም ነበር የቆየው። ራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ የተጠቀሰችዋ አራተኛዋ ቤተክርስቲያን ትያጥሮን የምትባል ቤተክርስቲያን ስትሆን ትያጥሮን ማለት ገዢ ወይም ጨቋኝ ሴት ነች። የሮማ ቤተክርስቲያን በዚያ ዘመን የአውሮፓ ሕዝብ ላይ ሙሉ በሙሉ ገዥ ሆና ነበር።
በ641 ዓ.ም ሙስሊሞች አንጾኪያ፣ ኢየሩሳሌም፣ እና አሌግዛንድሪያን በተቆጣጠሩ ጊዜ ሮም ብቻ ነበረች ከሐዋርያት ጋር የተያያዘች (እነርሱ እንደሚሉት) ምዕራባዊ ማዕከል ሆና የቀረችው። በፊት የነበሩ ተቀናቃኞቹ ሲወገዱለት የሮማ ጳጳስ በኃይሉ እና በተጽእኖ ፈጣሪነቱ እየጨመረ ሄደ።
የሮማ ቤተክርስቲያን ተቃውሞዎችን ሁሉ ለመደምሰስ በተነሳችበት ጊዜ ስደት እየተባባሰ ሄደ። ከሰላሳ ዓመታቱ ጦርነት በኋላ ተቃዋሚዎችን መግደል ባቆሙበት ዓመት በ1648 ከአስር ሚሊዮን በላይ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለዋል።
ዱቄት ዳቦ ለመጋገር ያገለግላል፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። ሴት ቤተክርስቲያንን ትወክላለች። እርሾ በውስጡ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ስለሚሰራ ይበሰብሳል፤ ከዚያ በኋላ በእንፋሎት መልክ ወደ ላይ ስለሚነሳ ሊጡን ኩፍ ያደርገዋል፤ ያቦካዋል። ስለዚህ አንዲት ሴት (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን) ዱቄት ወሰደች (ቃሉን ማለት ነው) እና በሶስት መስፈሪያ ከፋፈለችው (ሥላሴ እግዚአብሔርን በሶስት አካላት ይከፋፍለዋል) ይህም መበስበስ ወይም ብልሽት በቃ ውስጥ ሁሉ ተሰራጨ። በሥላሴ አስተምሕሮ ምክንያት ክርስቲያኖች አሁን የእግዚአብሔርን ስም (ኢየሱስ ክርስቶስ) እንዳያውቁ ተደርገዋል፤ በዚህም ምክንያት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ ትተው በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ይጠመቃሉ። ይህም ስሕተት እየተዛመተ በመሄዱ የተነሳ ሰዎች ያላቸው የእውነት እውቀት እየቀነሰ ነው። በስላሴ የሚያምኑ ሰዎች የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ አያውቁም።
ማቴዎስ 13፡34-35 ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
(መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውነት ከተለያዩ ምሳሌዎች እና ምልክቶች በስተጀርባ ተሰውራ ነው የተቀመጠችው።)
ኢየሱስ በምሳሌ የተናገረው ብዙሃኑ ሕዝብ እንዳያስተውሉ ነው።
ይህም ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ የነበረችበትን ሁኔታ ያሳያል። በዚያ ዘመን እውነትን መረዳት የሚችለው ሰው አልነበረም ማለት ይቻላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የተጻፉት ለማስተዋል ጥበብ በሚጠይቁ ምሳሌዎች እና ሚስጥራዊ አገላለጾች ነው። የሮማ ቤተክርስቲያን አውሮፓን በሙሉ ተቆጣጥራ ነበር ነገር ግን መንፈሳዊ መረዳት አልነበራትም። ስለዚህ አውሮፓ በሙሉ ከጥቂት ሃገሮች በቀር መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አለማወቅ ወድቀው ነበር፤ እርሱም ጨለማ ነው።
36 በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
ደቀመዛሙርቱ የሁለተኛውን ምሳሌ ትርጉም ማወቅ ፈልገዋል።
ያ ዘመን ሰዎች መሪ ሆነው ጳጳሳት ተብለው ተሹመው ቤተክርስቲያንን የተቆጣጠሩበት ዘመን ነበር።
የዚያ ዘመን ስሕተት ለመረዳት ከባድ አልነበረም።
ደቀመዛሙርቱ የሶስተኛውን እና የአራተኛውን ምሳሌ ሚስጥር አልጠየቁም።
አንድ ጊዜ ሥላሴ በሶስተኛው ዘመን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከገባ በኋላ ክርስቲያኖች ዓይናቸው ታውሯል፤ ስለዚህ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን እስኪደርስ ድረስ እውነትን የማየት ዕድል የላቸውም።
ማቴዎስ 13፡37 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
38 መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥
39 የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
40 እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
(ታላቁ መከራ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ ነው)
41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
(ስሕተት መሆኑን የሚያውቁትን ነገር እያወቁ ያደርጋሉ፤ ለምሳሌ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲያጠምቁ የሚያዝዛቸውን የሐዋርያት ሥራ 2፡38ን አልታዘዝም ይላሉ)
42 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን የተሰጠ የመጨረሻ ቃል እንዲህ የሚል ነው፡-
ራዕይ 3፡13 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።
የአራተኛው ቤተክርስቲያን ዘመን ጨለማ አብቅቷል፤ ስለዚህ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንደገና መስማት ይችላሉ።
በዚያን ጊዜ የሕትመት ማሽን ተፈጠረ። ስለዚህ በጨለማው ዘመን ውስጥ ታግዶ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ በቀላሉ ለሕዝብ ሁሉ መሰራጨት ቻለ።
አራተኛው ምሳሌ ሲጠናቀቅ ኢየሱስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ክርስትናን ወደ ስሕተት ውስጥ ጎትታ ባስገባችበት ጊዜ ምን እንደተፈጠረ ገለጠ። ስለዚህ በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ፣ መመካከለኛው ወይም በጨለማው ዘመን መጨረሻ ሃስ እና ዋይክሊፍ የተባሉ ሰዎች መጥተው ሕዝቡን ወደ መዳን የእውቀት ብርሃን መልሰዋቸዋል፤ ደግሞም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥንታዊቷ የእውነት ጠላት መሆኗን ሰዎች እንዲያውቁ አድርገዋል።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እራሷን እናት ቤተክርስቲያን ብላ ጠራች። ጨቋኟ ሴት፤ ትያጥሮን። የእግዚአብሔርን ቃል እንጀራ ሶስት ቦታ የከፋፈለችው፣ እግዚአብሔር ሥላሴ ያደረገው እርሷ ናት። ከዚህም የተነሳ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያዘጋጀችው እርሾ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገብቶ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን መለየት የፈለጉት ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም ውስጥ ሳይቀር ሊገባ ችሏል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል እንጀራ ሶስት ቦታ ከፋፍላዋለች፤ ነገር ግን ካቶሊኮች የፀሃይ አምላክ ምሳሌ አድርገው በክብ ቅርጽ የሚያዘጋጁትን እና በሰዎች አፍ ውስጥ የሚያስቀምጡትን ሕብስት አልከፋፈሉትም፤ እርሱንም ቅዱስ ቁርባን ይሉታል።
በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እውነተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ፈጽሞ ሊጠፋ ትንች ብቻ ነበር የቀረው።
አምስተኛው ምሳሌ
ኢየሱስ አምስተኛውን ምሳሌ ከመናገሩ በፊት ሁለተኛውን ምሳሌ ተረጎመላቸው።
ይህም አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲጠናቀቅ እና አምስተኛው ሲጀምር እውነት ወደ ቤተክርስቲያን እየተመለሰች ነበር ማለት ነው።
ዋይክሊፍ እና ሃስ ወደ አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማብቂያ አካባቢ ስለ መዳን ሰበኩ። ነገር ግን በአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ተሃድሶው የተስፋፋው የሕትመት ማሽን ከተፈጠረ እና ሉተር ያለ ምንም ፍርሃት የመዳንን እውነት ከሰበከ በኋላ ነው።
ማቴዎስ 13፡44 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
ይህንን ዘመን አንድ ጥቅስ ብቻ ነው የሚገልጸው። ስለዚህ በተሃድሶው ብዙም ተመልሶ የመጣ እውነት የለም።
ነገር ግን ከተሃድሶ መሪዎች ሁሉ ጀግና የሆነው ሉተር መዳን ከክርስቶስ ጋር በግል የምንለማመደው ልምምድ የመሆኑን እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አምጥቷል።
ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች መላቀቅ አልቻሉም ነበር፤ ሆኖም ግን ክርስቶስ የግል አዳኛቸው መሆኑን ተረድተው ተቀብለዋል። ስለዚህ ይህ ትልቅ እርምጃ ነበር።
በምሳሌው ውስጥ የተጠቀሰው ሰው ክርስቶስ ነው።
እርሱም በቀራንዮ ለዓለም ሁሉ ዋጋ ከፈለ። የዚያን ጊዜ ነው ዓለምን (እርሻውን) የገዛው።
በዚህም ምክንያት ማንኛውም ሐጥያተኛ ለመዳን ተፈቅዶለታል። ስለዚህ ለመዳን የሚያስፈልገው ኢየሱስ ስለ ሐጥያታችን በከፈለው መስዋእት ማመን እና ከሐጥያቱ ንሰሃ ለመግባት መፈለግ ብቻ ነው።
ኢየሱስ የነበረውን ሰማያዊ ክብር በሙሉ ሽጦ መከራን ለመቀበል አገልጋይ ሆኖ መጣ፤ ክብሩን ሁሉ ሽጦ የውርደት ሞት ሞተ። ስለዚህ እርሱ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ አሳልፎ መስጠት ለመዳናችን የሚያስፈልገውን ሙሉ ዋጋ ከፈለ።
ከዚያም መዝገቡን ማለትም መዳንን ሰወረው። መዳን በገንዘብ ሊገዛ አይችልም። ስለዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አንብበውም እንኳን ዋነኛውን ነጥብ ማለትም መዳን እንደሚያስፈልጋቸው ሳያስተውሉ ሊቀሩ ይችላሉ። የተሰወረው መዝገብ ከክርስቶስ ጋር በግል የሚሆን የመዳን ልምምድ ሲሆን እርሱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው ተሰውሮ የተቀመጠው። በገንዘብ ስለማይገዛ በነጻ ነው የሚገኘው። እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ስለወደደ ለዓለም ሁሉ (ለእርሻው) የሚያስፈልገውን ዋጋ ከፈለ። ስለዚህ ማንኛውም ሰው መዳን ይችላል።
“መዝገብ” የሚለው ቃል ሌላኛው ገጽታው መጽሐፍ ቅዱስ ለሮማ ካቶሊኮች በሚስማማቸው በላቲን ቋንቋ ብቻ መሆኑ ቀርቶ ተራው ሕዝብ ሊያነብብ በሚችለው ቋንቋ መተርጎሙ ነው። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በ1611 ዓ.ም ታተመ፤ ከዚያ በኋላ ለ150 ዓመታት በጥንቃቄ ሲፈተሽ ቆይቶ በስተመጨረሻ የተጣራው እትም በ1769 ተባዝቶ ተሰራጨ። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ዛሬ ድረስ የእንግሊዝኛ ሥነ ጽሑፍ እንቁ ተደርጎ ይቆጠራል። ከዚህም የተነሳ ከዚያ በኋላ በዓለም ዙርያ የተነሱ ታላላቅ የክርስትና እንቅስቃሴዎች በብዛት የተጀመሩት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሃገሮች ውስጥ ነው።
በ1750 እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና ስለ ወንጌል ስርጭት ሰበከ፤ ይህም በ1792 ለተጀመረው ለታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስብከት ዘመቻ መሰረት ጥሏል፤ በዚያም ዘመን ዊልያም ኬሪ ባፕቲስት ሚሽነሪ ሶሳይቲ አቋቋመና ወደ ሕንድ ሄደ።
በ1906 አሜሪካ ውስጥ የተቀጣጠለው የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት አማኞች በየግላቸው የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት እንዲቀበሉ አደረገ።
ከ1947 እስከ 1965 ዊልያም ብራንሐም አሜሪካ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት ገልጦ አስተማረ፤ ይህም ትምሕርት ሰፋ ያለ መረዳትን ስለሰጠን የሚጋጩ የሚመስሉ ጥቅሶችን አስታርቆ አሳይቶናል። ከቤተክርስቲያናቸው እና ከቤተክርስቲያን መሪዎች በተለየ መንገድ በራሳቸው አእምሮ ለማሰብ ለማይፈሩ ሰዎች ደግሞ ትክክለኛው እውነት ተመልሶላቸዋል።
በሉተር ታላቅ የተሃድሶ ዘመን ግን ከ1500 ዓ.ም እስከ 1750 ድረስ የወንጌል ስብከት ወደ ዓለም ሁሉ አልተዳረሰም ነበር። እንደ ሉተር፣ ካልቪን፣ ጆን ኖክስ የመሳሰሉ የተሃድሶ መሪዎች አውሮፓ ውስጥ አስደናቂ የወንጌል ስብከት ሥራ ሰርተዋል።
ነገር ግን ሁለት ዋና ዋና ችግሮች ነበሩ፡ የመጀመሪያው ችግር የቀረው ዓለምስ መች ነው ወንጌል የሚደርሰው? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማያውቁትን እውነትስ ምን ያደርጉታል?
ዓለም ከጨለማው ዘመን እየወጣች በነበረችበት ጊዜ ብዙ ሃገሮች ታላቁ የመዳን እውነት እና መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በራሳቸው ቋንቋ ያስፈልጋቸው ነበር።
ነገር ግን ሰዎች ከዚያ በተጨማሪ ቅድስናም ያስፈልጋቸው ነበር (ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና ሰብኳል)፤ ደግሞም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትም ያስፈልጋቸው ነበር (ይህ ደግሞ በጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት ጊዜ ሆኗል)።
ሕዝቡ ከዚህ ሌላ ደግሞ እውነትን ማወቅ ያስፈልጋቸዋል፤ ይህም የእውነት እውቀት እንደ ሥላሴ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን በመጠቀም እግዚአብሔርን በተሳሳተ መንገድ ከመግለጽ እና “አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ” ስሞች ናቸው ብለው ከማሰብ ያድናቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የመጀመሪያው ሐጥያት ምን እንደሆነ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልገናል። በዚህ ከባድ መንገድ ውስጥ እንዲመራን የተላከው ሰው ዊልያም ብራንሐም ነው።
የተሃድሶ መሪዎች ከሮም እና ከፖፑ ስልጣን አመለጡ፤ ተከታዮቻቸው ግን (ልክ ያዕቆብ የአማቱን ጣኦታት ሰርቆ እንደሄደው ሁሉ) በሰዎች መሪነት ስር ለመኖር መረጡ፤ ለምሳሌ አንግሊካን ቤተክርስቲያኖች አመንዝራ እና ነፍሰ ገዳይ የነበረው ንጉስ ሔንሪ ሳልሳዊ የቤተክርስቲያናቸው ራስ እንዲሆን ተቀብለዋል። አንግሊካኖች የራሳቸውን ካሕናት ሾሙ፤ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ኮርጀው የካሕና ቀሚስ አዘጋጁ። የተሃድሶ መሪዎች ከሮም አመለጡ (ሰርዴስ ማለት ያመለጡ ሰዎች ማለት ነው)፤ ነገር ግን የጀመሩት ተሃድሶ ከፍጻሜው ሳይደርስ ቀረ ምክንያቱም ተከታዮቻቸው እግዚአብሔርን በጥንቃቄ በመከተል አልጸኑም፤ ተከታዮች ቤተክርስቲያንን እንደ ካቶሊክ በማሰብ የካቶሊክን ስርዓቶች ተከትለው መሄድ ቀጠሉ፤ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ተቀበሉ፤ ከአንዳንድ ልዩነቶች በቀር ብዙ የካቶሊክ አስተሳሰቦችን ተቀበሉ፤ ለምሳሌ ሥላሴ፣ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማጥመቅ፣ ሰውን መሪ አድርጎ መቀበል (ቄስ ወይም ፓስተር)፣ ይህም መሪ የፈለገውን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀብሎ ያስገባል፤ ያልፈለገውን ሰው ደግሞ ወደ ውጭ አውጥቶ ይጥላል። እግዚአብሔር ተጨማሪ እውነቶችን እየገለጠ ባለበት ሰዓት እውነትን ለመቀበል እንቅፋት የሆነው ለቤተክርስቲያን መሪዎች የመገዛት አባዜ ነው።
ሆኖም ግን በጨለማው ዘመን የነበረው ወደ ጨለማ የመንሸራተት ዝንባሌ ተሰብሯል።
በመቅረዙ ላይ ያለው ብርሃን ወደ ሌላኛው ጎን ሄዶ ማብራት ጀምሯል፤ በዚያም መሰረት ጥሏል፤ መሰረቱ ጻድቅ በእምነት ይኖራል የሚል ነው፤ ከዚህም የተነሳ እውነት ቀስ በቀስ ወደ አማኞች ተመልሳ ትመጣለች።
ዕድሜ ለሉተር እና ለሌሎቹ የተሃድሶ መሪዎች፤ ሕዝቡ የመዳንን እውቀት አገኙ።
ስድስተኛው ምሳሌ
ፕሮቴስታንት በሆነችው አውሮፓ ውስጥ የነበሩት ሕዝብ እየዳኑ ነበር። ነገር ግን የመዳን እውነት ወደ ቀረው ዓለም ሁሉ መሰራጨት ነበረበት።
ማቴዎስ 13፡45 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤
46 ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።
ይህ ምሳሌ ሁለት ቁጥሮች ውስጥ የተጻፈ እንደመሆኑ ጥቂት ተጨማሪ እውነት ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ ነበር።
እርሻው ከዚህ በፊት በተነገረው ምሳሌ ውስጥ ተገዝቶ ስለነበረ እንደገና ሊገዛ አይችልም። ጆርጅ ዊትፊልድ እና ጆን ዌስሊ የወንጌል ስብከትን በር ከቤተክርስቲያን ሕንጻ ውጭ ከፈቱ፤ ይህም በስተመጨረሻ ወንጌል ወደ ዓለም ዙርያ ሁሉ እንዲሰራጭ ምክንያት ሆነ፤ ታላቁ ዓለም አቀፍ የወንጌል ስብከት ዘመቻም በ1782 ዊልያም ኬሪ የባፕቲስት ሚሽነሪ ሶሳይቲን አቋቁሞ ወደ ሕንድ በሄደ ጊዜ ተጀመረ።
ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና ሰበከ፤ ይህም የዳኑ ክርስቲያኖች ተመልሰው ወደ ሐጥያት ውስጥ እንዳይወድቁ እና ወደ ዓለማዊነት እንዳይገቡ ይረዳል።
የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ዕንቁ የሰማያዊቷ ከተማ ደጅ ነው።
ራዕይ 21፡21 አሥራ ሁለቱም ደጆች አሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እየአንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።
ራዕይ 3፡8 ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።
በስድስተኛው ማለትም በፊልደልፊያ (የወንድማማች መዋደድ) ቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን በቷ የተከፈተ በር ተሰጥቷታል።
የተከፈተ በር የወንጌል ሥርጭት አገልግሎት ምሳሌ ነው።
ስለዚህ ክርስቶስ ለወንጌል ስብከት ዘመን ዋጋ ለመክፈል በቀራንዮ ሞተ። እርሱም ክርስቲያኖች በሚያምኑት እምነት ውስጥ ብዙ ስሕተት ቢኖርም እንኳ በኢሱስ ክርስቶስ ስም የሚሆነውን የመዳን ወንጌልን ወደ ዓለም ሁሉ የሚያዳርሱ ሰባኪዎችን ያስነሳል።
የወንጌል ሰባኪዎቹ ዘመን ብዙ ፈተናዎች ቢበዙበትም በምድር ሁሉ ላይ የብርሃን ወገግታ አብርቷል። ይህ ዘመን ወርቃማው የወንድማማች መዋደድ (የፊልደልፊያ) ዘመን ነበረ፤ ምክንያቱም በዚህ ዘመን ውስጥ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና የሰበከው ስብከት የሰዎችን ስነ ምግባር ስላስተካከለው ወንጌል ወደ ብዙ ሃገሮች መሰራጨት ችሏል። ከዚህም የተነሳ ፕሮቴስታንት የነበረችው እንግሊዝ ካቶሊክ የነበረችውን ፈረንሳይ ብትንትኗን ካወጣው የፈረንሳይ አብዮት መዘዝ ልትተርፍ ችላለች። በቅድስና መኖር የሚፈልግ ሰው ጊሎቲን የተባለውን የሰዎችን አንገት መቀንጠሻ መሳሪያ መጠቀምም ሆነ በዚህ ዘግናኝ መሳሪያ የሰዎች አንገት ተቆርጦ ሲወድቅ ማየት አይፈልግም።
“ስሜንም አልካድክም።” ወንጌል ሰባኪ ሚስዮናውያን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። መዳን የሚያስችል ሌላ ምንም መንገድ የለም። ይህ ትኩረት በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ለመረዳት በር ከፈተ፤ ይህም መረዳት ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑ እና ሥላሴ አለመኖሩ ነው። ሰዎች በለመዱትና ተደላድለው በተኙበት ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ሳሉ ጠለቅ ያሉ እውነቶችን መረዳት ይከብዳቸዋል። ነገር ግን ጠለቅ ወዳለው መገለጥ የሚያስገባው በር እየተከፈተ ነበር፤ ደግሞም ኢየሱስ ሁሉን ቻይ ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን እየገለጠ ነበር። ሌላኛው ጠለቅ ያለ መገለጥ ደግሞ ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት የአውሬው ምልክት መሆኑ ነው። ይህም ደግሞ ሰዎች እውነትን እና ስሕተትን አደባልቀው የሚያስተምሩዋቸውን ሰዎች መሪ አድርገው መከተላቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ከስሕተታቸው ለመታረም ዝግጁ አይደሉም ምክንያቱም የራሳቸውን አመለካከት ብቻ እንጂ የሌላውን አመለካከት በጭራሽ አያዳምጡም።
ከሁሉ በላይ ለመቀበል ከበድ የሚለው መገለጥ የመጀመሪያው ሐጥያት ወሲባዊ ግንኙነት መሆኑ ነው። ሙስሊም ወንዶች በምድር ሲኖሩ በሰማይ 70 ድንግል ሴቶች እንደሚጠብቋቸው እያመኑ ነው የሚኖሩት። ይህም እምነት ብዙዎቹ አጥፍቶ የመጥፋት የሽብር ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ ያደፋፍራቸዋል፤ ምክንያቱም በሰማይ “ሽልማት” እናገኛለን ብለው ያምናሉ። ነገር ግን አንድ መሰረታዊ እውነት ዘንግተዋል። የማይለወጠው ወርቃማ ሕግ “አትግደል” የሚል ነው።
የሚሽነሪዎች ዘመን አስደናቂ ነበረ ነገር ግን ሁለት ነገሮች ጎድለውት ነበር፤ እነርሱም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እና በሩ ሲከፈት የመገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ እውነት ናቸው።
ብዙ ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የሚመስሉ ጥቅሶችን ሲያዩና ለማስታረቅ ሞክረው ሲያቅታቸው መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል እንደሚሉ ልብ በሉ።
በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት የለም። ሁልጊዜም ፍጹም ትክክል የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
ስሕተት ያለው ሁልጊዜ በእኛ መሃይምነት ውስጥ ነው፤ የእግዚአብሔርን ሙሉ ሃሳብ ባለማወቃችን ውስጥ ነው። ይህ ችግር የዘለቀው ዊልያም ብራንሐም መጥቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተቀበለውን አስደናቂ መረዳት እስኪገልጥ ድረስ ነበር። ንስር ድርብ ዓይን አለው። የዓይኑ የውጨኛው ክፍል በመሬት ላይ ሰፊ ቦታን በትኩረት ማየት ሲያስችለው የውስጠኛው ክፍል ደግሞ ወስን የሆነ ቦታን 10 ጊዜ ትልቅ አድርጎ በማሳየት ሌሎች ወፎች ማየት የማይችሉትን ብዙ ነገር አጥርቶ እንዲያይ ያስችለዋል።
በሰማይ የእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት አሉ።
ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
የአንበሳው ዘመን በቅዱስ ጳውሎስ እና በሐዋርያት አማካኝት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለቤተክርስቲያን አስተዋውቋል። የጥጃው ዘመን በጨለማው ዘመን ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ስለ እምነታቸው የሞቱበት ዘመን ነው። የሰው ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር የሰውን አእምሮ ስለባረከ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ወደ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መተርጎም ተችሏል። ይህ የሰው ዘመን የተሃድሶ መሪዎች መዳንን፣ ቅድስናን እና የወንጌል ስብከት አገልግሎትን ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው እንዲያመጡ አስችሏቸዋል።
የመጨረሻው ዘመን ማለትም የንስሩ ዘመን በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መልክ በጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት ቤተክርስቲያን ኃይልን ከላይ ልትለብስ ችላለች። ሰዎች ግን ያንን እንቅስቃሴ በፓስተሮች የሚተዳደር በዲኖሚኔሽኖች የተከፋፈለ እንቅስቃሴ አደረጉት። ከዚያ በኋላ ዊልያም ብራንሐም የተባለ ነብይ ባገኘው ድንቅ መረዳት አማካኝነት የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሐዋርያት ያስተማሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ገለጠ። ተከታዮቹ ግን ከእርሱ በኋላ ተከፋፈሉ፤ የተናገራቸውንም ቃላት ወስደው እየጠቀሱ በፓስተሮች የሚተዳደሩ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖችን ከፈቱ። ስለዚህ የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ማለት ሰባተኛው ምሳሌ ሊገለጥ ጊዜው ደርሷል። ከውጭ ሲመለከቱት በብልጽግና እና በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ይመስላል ነገር ግን የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በታላቅ ችግር ውስጥ ነው ያለው።
በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ኤጲስ ቆጶስ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ተሹሞ ከፍ ተደረገ፤ ከዚያ በኋላ ግን ቤተክርስቲያንን ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ይዟት ገባ።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ከፍ ይደረጋል፤ ከዚያም በኋላ ቤተክርስቲያንን ይዟት ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባል።
ሰባተኛው ምሳሌ
ማቴዎስ 13፡47 ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤
ባሕር ማለት እረፍት የሌለው የሕዝብ ብዛት ነው።
የወንጌል መረብ ሄዶ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ይሰበስባል።
“መረብ” የሚለው ቃል የመረጃ መረብ ወይም ኢንተርኔት የሚል ተጨማሪ ትርጉም አለው፤ ምክንያቱም ከዓለም ዙርያ ሁሉ ያሉ ሕዝብ መጥተው እውነትን ማግኘት የሚችሉበት መድረክ ነው።
እግዚአብሔር ሰዎች በኢንተርኔት መገናኘት እንዲችሉ አድርጓል።
ኮቪድ-19 በ2020 ዓ.ም ብዙ ድርጅቶት እንዲዘጉና ሰዎች በቤታቸው እንዲቀመጡ አድርጓል። የጥንቶቹ ቤተክርስቲያኖች በቤት ውስጥ ነበር የሚሰበሰቡት።
ትንንሽ ቡድኖች የዙም ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከየቤታቸው ሆነው መሰባሰብ ይችላሉ።
ሉቃስ 12፡32 አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።
በኢንተርኔት የሚገነኙ ታናናሽ ቡድኖች ከዚህ ቃል ጋር ይገጣጠማሉ።
ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
በጣም ጥቂቶች ናቸው ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንገድ የሚያገኙት።
ይህ የመለያ ጊዜ ነው። ትክክል የሆነው (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው) እና ስሕተት (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው) ተለይተው ስሕተት የሆነው ወደ ውጭ የሚጣልበት ዘመን ነው።
ማቴዎስ 13፡48 በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።
“በሞላችም ጊዜ” የሚለው ቃል የዘመንን ሙላት ያመለክታል።
“በሞላችም ጊዜ” የሚለው የሐጥያት እና የበደል ጽዋ መሙላቱን ያሳያል። ሰው ከዚያ የባሰ ሊበላሽ አይችልም።
ኢየሱስ በአገልግሎቱ መጀመሪያ እነዚህ ምሳሌዎች በመጠቀም ለመስበክ በባሕር ዳርቻ ተቀምጦ ነበር።
በመጨረሻው ምሳሌ ውስጥ የባሕሩን ዳርቻ ይጠቅሳል።
የባሕሩ ዳርቻ በመጀመሪያ እና በመጨረሻ ላይ ተጠቅሷል።
ይህም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የአማኞች እምነት ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር መመሳል እንዳለበት የሚያመለክት ተጨማሪ ፍንጭ ነው።
ልክ እንደ ዓሣ አጥማጆች አንዳንዶቹ ዓሣዎች መጥፎ አንዳነንዶቹ ደግሞ ጥሩ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ለእውነት ምላሽ ይሰጣሉ፤ ሌሎች ደግሞ ምላሽ አይሰጡም።
እውነትን አንቀበልም ብለው እምቢ ያሉ ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን በትክክል ቢያስተውሉት እውነት ናት እነርሱን አልቀበልም ያለቻቸው።
ሁለት ምርጫዎች ይጠብቁናል።
የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች ተጠቅመን እምነታችን ትክክል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸን እናረጋግጣለን።
የዚያን ጊዜ እንደ ልባሞቹ ቆነጃጅት መብራታችንን የምናበራበት ዘይት ይኖረናል፤ በዚህም መብራት መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን እንረዳለን። በዚህ መንገድ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት እንመለሳለን። ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት እንመለሳለን።
ሰባተኘው ዘመን እራሱን የቻለ ዘመን ይመስል በሰባተኛው ማቆም አንችልም።
ይህ ዘመናችን የመታደስ ዘመን ነው፤ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የምንመለስበት ዘመን ነው።
ሰባተኛው ዘመን የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ይቀበላል፤ ከዚያም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩት አማኞች እንዳመኑት ዓይነት እምነት ይኖረናል።
ምንም ነገር ብናምን “የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ይህን ያምኑ ነበር?” እያልን መጠየቅ አለብን።
የሚታጨደው ወይም በመከር የሚሰበሰበው ፍሬ መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
ከዚያ በኋላ ሰነፎቹ ቆነጃጅት የዳኑ ክርስቲያኖች ቢሆኑም እምነታቸውን የሚመሰርቱት ጥቅሶችን በተሳሳተ አተረጓጎም በመተርጎም ነው። በሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ እየተደገፉ ከእግዚአብሔር ቃል ርቀው ይሄዳሉ።
“ጥቅስ አለኝ” የሚለው አባባል “ተጽፏል” የሚለውን ይተካዋል።
መጽሐፍ ቅዱስን አለማወቅ እየጨመረ ሲሄድ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን እየደበዘዘ ይሄዳል።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቆመው ይቀሩና ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ ያቅታቸዋል። በሰው ፈቃድ ወደ ተጠመዘዙ እና ሰው እንደ ፍላጎቱ በተረጎማቸው የሰው ንግግር ጥቅሶች ውስጥ ተኝተው የሜሴጅ ተከታይ ሰነፍ ቆነጃጅት መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቃቸው ተዘፍቀው ይቀራሉ። በዚህ ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃናቸው እየደበዘዘ ይሄዳል። ጥቅሶቹን ተጠቅመው እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ መግለት አይችሉም። ከዚህ በታች ባለው ስዕል ውስጥ “ቀዩ ቀስት” እውነት አዲስ ኪዳንን ወደ ጻፉት ሐዋርያዊ አባቶች ተመልሳ እንደምትሄድ ያሳያል። ይህም ጥቅሶችን በመሰነጣጠቅና ያልተጻፉትን ሰባት ነጎድጓዶች፣ ሰባተኛ ማሕተም፣ እንዲሁም የኢየሱስ አዲስ ስም ለመተርጎም በመሞከር አይደረስበትም። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩ አማኞች እነዚህን ነገሮች አላመኑም። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፈ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀትህን ወዲያ ያቀጭጨዋል።
ማቴዎስ 13፡49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤
እውነተኛው ትግል ያለው እግዚአብሔር እና ሰይጣን በሚፋለሙበት በመንፈስ ዓለም ውስጥ ነው። ሥጋ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያለውን እውነተኛ ትግል ድብዝዝ አድርጎ የሚያሳይ ጥላ ነው። እኛ እግዚአብሔርን እያገለገልን ያለን ይመስለናል፤ ነገር ግን መላእክት እኛን ከክፉዎች በመለየትና በእውነተኛው መንገድ ላይ በመጠበቅ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። በዚህ አታላይ በበዛበትና ግራ አጋቢ ዘመን ውስጥ በእውነት ውስጥ ለመቆም ብዙ እርዳታ ያስፈልገናል።
ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተን ስለመመላለሳችን ብቸኛው ማረጋገጫ መጽሐፍ ቅዱስን መከተላችን እና በዘመናችን እየተገለጠ ያለውን እውነት እምቢ አለማለታችን ነው።
ማቴዎስ 13፡50 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
እውነትን አንቀበልም የሚሉ መጨረሻቸው ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው፤ እርሱም የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ነው።
የምታምነውን እምነት ትክክለኛነት መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም ማረጋገጥ ትችላለህን?
ካልቻልክ የተቀበልከው የስሕተት ብዛት በታላቁ መከራ እሳት ውስጥ ከአንተ ላይ ተራግፎ ይወድቃል።
ማቴዎስ 13፡51 ኢየሱስም፦ ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን? አላቸው አዎን አሉት።
የሰባተኛው ምሳሌ መጨረሻ የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ነው። ኢየሱስ እየተናገረ የነበረውን ነገር ደቀመዛሙርቱ በራሳቸው ያስተውላሉ ብሎ ጠብቋል። ዛሬም ኢየሱስ እኛ ቃሉን እንድናስተውል ይጠብቅብናል። የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ለራሳችን መረዳት ያስፈልገናል።
በሰባተኛው ዘመን ውስጥ በዊልያም ብራንሐም አማካኝነት በመጣው መገለጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ተመልሶ ይመጣል፤ ስለዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋር ተመሳሳይ እምነት ይኖራል።
ማቴዎስ 13፡52 እርሱም፦ ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል አላቸው።
የመጨረሻው ዘመን አማኞች የአይሁዶች ወደ እሥራኤል መመለስ እንዲሁም እኛ እንደ ጥንቶቹ አማኞች እግዚአብሔርን ማገልገል ወደምንችልበት እነርሱ በዚያን ጊዜ በጥንታዊው ዘመን ወደ ነበራቸው መረዳት ወደ ጥንቷ ወደ መጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን የሚመልሰን ኤልያስ እና የመሳሰሉ አዳዲስ ክስተቶችን መከታተል አለባቸው።
የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ ሚስጥራት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ሲገለጥ ማስተዋል መቻል አለበት።
ወንድም ብራንሐም ያስተማረው ሚስጥር ለምሳሌ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ትኩረት ሰጥቶ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያጠና ሰው ባልጠበቀ ቦታ ይታየዋል፤ ለምሳሌ ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ። የመለኮት ሚስጥር እና ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በአስርቱ ትዕዛዛትም ውስጥ ይገለጣሉ። አይሁዶችም ከአብራሐም ጀምሮ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ አልፈዋል።
ማቴዎስ 13፡53 ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።
ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚያበቃው ኢየሱስ ሙሽራይቱን ማለትም እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ለመውሰድ ሲመጣ ነው፤ ከዚያ በኋላ ሙሽራይቱን ይዞ በሰማያት ወደተዘጋጀው ሰርግ ይሄዳል።
የቀሩት ሕዝብ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ። እባካችሁ እነዚህ ሰዎች በቁጥራቸው ብዙ ቢሆኑም እንኳ ከእነርሱ እንደ አንዱ አትሁኑ። መጨረሻቸው ታላቁ መከራ ውስጥ ነው።