የዮሐንስ ወንጌል እጅግ ብዙ ተዓምራት መደረጋቸውን ይናገራል ግን ሰባቱን ብቻ ይዘግባል። ለምን? ክፍል 2



First published on the 19th of March 2021 — Last updated on the 19th of March 2021

አራተኛው ተዓምር አራተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል

በዚህ 5,000 ሰዎችን በተዓምር ያበላበት ተዓምር ውስጥ ኢየሱስ ትኩረቱ ብዙ ሕዝብ ምግብ መብላቱ ላይ አይደለም። ይህ ትልቅ ተዓምር ቢሆንም የኢየሱስ ትኩረቱ ብዙ ሕዝብ መብላቱ ላይ አይደለም።

የአንድ ትንሽ ልጅ ምሳ ወስዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ስላበላበት ተዓምር ሲናገር ኢየሱስ ትኩረቱን ያደረገው ሰዎች አንበላም ያሉትን ቁርስራሽ ደቀመዛሙርቱ በስንት መሶብ እንደሰበሰቡ ነው።

ሰዎች ለዘመናቸው የተሰጣቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አንቀበልም ይላሉ። ኢየሱስን በጣም የሚያሳስበው ይህ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎችን ቤተክርስቲያን አትቀበላቸውም።

ስለዚህ ቁልፉ ነጥብ አለመቀበል ነው።

ማርቆስ 8፡19 አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ? እርሱም፦ አሥራ ሁለት አሉት።

20 ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እነርሱም፦ ሰባት አሉት።

21 ገና አላስተዋላችሁምን? አላቸው።

ይህ ተዓምር የተደረገው ጠለቅ ያለ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።

7 ቁጥር እና 12 ቁጥር ሚስጥራዊ ትርጉም አላቸው፤ ትርጉማቸውንም ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ እና እኛ እንድናስተውል ይፈልጋል።

እንጀራ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው፤ ስለዚህ መልካም ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ነው።

ዮሐንስ 6፡35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤

እርሾ የመበስበስ ምሳሌ ነው፤ ይህም መበስበስ መንስኤው እንደ ፈሪሳውያን የመሳሰሉ የሐይማኖት መሪዎች የሚያስተምሩት ሰው ሰራሽ አስተምሕሮ ነው።

ማቴዎስ 16፡12 እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ።

ለፋሲካ በዓል እግዚአብሔር ያዘዘው እርሾ የሌለው ቂጣ እንዲበሉ ነው።

ከተጻፈው ቃል ውስጥ የተወሰዱ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ብቻ ነው መታዘዝ ያለብን፤ ያውም አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎችን አመለካከት ሳንቀላቅል። የሐይማኖት መሪዎች የራሳቸውን ሃሳብ ለማራመድ ሲሉ የእግዚአብሔርን ቃል ያጣምማሉ።

ኢየሱስ በሆሳዕና እለት በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲገባ ተራው ሕዝብ በደስታና በምስጋና ተቀበሉት። ከዚያ በኋላ ግን የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የሕዝቡን አእምሮ መረዙ፤ ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ በደስታ ተቀብለውት ሳምንት ሳይሞላቸው ኢየሱስ እንዲገደል መጠየቅ ጀመሩ።

በኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ጊዜ ዋነኞቹ ጠላቶች የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ነበሩ።

ኢየሱስ ለአይሁዳውያን 3 ዓመት ከ6 ወር ሰብኳል ግን በስተመጨረሻ እንደሚገፉት ያውቅ ነበር።

ስለዚህ አይሁዶች አንቀበልም ብለው የገፉት ወንጌል በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት ተሰብስቦ በአዲስ ኪዳን መጻሐፍት ወደ አሕዛብ ይወሰዳል።

አዲስ ኪዳን 2,000 ዓመታት በሚፈጁት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ይመራታል።

በዚህ ዘመን ውስጥ አዲስ መንገድ የሚጀመረው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጨለማው ዘመን ውስጥ አዲስ ኪዳንን በገፋች ጊዜ ነው።

 

 

አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የመበስበስ ጥግ የተደረሰበት ዘመን ነው፤ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን አረማዊነትን እና ፖለቲካዊ ተሳትፎን በእምነት ውስጥ ቀላቅላ ታራምድ ነበረ።

ከፍ ያሉት መሪዎች፣ ፖፕ፣ ካርዲናሎች እና ጳጳሳት ተንደላቀው ሲኖሩ የቀረው ሕዝብ ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባለማወቁ በድሕነት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ብዙ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ውስጥ ታስሮ ይኖር ነበር።

ይህንን ተከትሎ ቤተክርስቲያን በዘመን መጨረሻ በተላከው ነብይ አማካኝነት የተሰጣትን የእውነት መገለጥ በድጋሚ ገፍታ ከማስወጣቷ በፊት ሶስት የተሃድሶ ዘመናት መጥተዋል።

እርሱም እኛን ልጆችን ወደ ሐዋርያዊ አባቶች እምነት ሊመልሰን የቃሉን ሚስጥሮች ገለጸልን።

 

 

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ሁሉንም ነገር ያቃናል። ይህም በማርቲን ሉተር የተጀመረውን የእውነት ተሃድሶ ወደ ፍጻሜ ያመጣዋል።

ተበላሽቶ የነበረ ነገር ብቻ ነው ሊታደስ የሚችለው።

መጥምቁ ዮሐንስ ተሃድሶ አላመጣም።

እርሱ አይሁዳውያን ከዚያ በፊት አይተው የማያውቁትን የውሃ ጥምቀት አስተዋወቀ። ከዚያ በኋላ ደግሞ መሲሁን አስተዋወቀ፤ ያም አዲስ ነገር ነበር።

በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት የሚለውን የእውነት ተሃድሶ አመጣ።

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ዘመን ነበር የተዘጋጀው። መጀመሪያ የታተመው በ1611 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ በኋላ እስከ 1769 ድረስ ለ150 ዓመታት በጥንቃቁ ተፈትሾ ተስተካክሎ ተጠናቋል።

እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ የቅድስና እና የወንጌል ስብከት ተሃድሶ አመጣ፤ ይህም ሕዝቡ በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ለተደረገው ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመቻ እንዲዘጋጁ አድርጓል። ሚሽነሪዎች ወይም የወንጌል ሰባኪዎች እምነታቸውን የመሰረቱት በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

አሜሪካ ውስጥ በጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት አማካኝነት በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በ1906 ዓ.ም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ተሃድሶ መጥቷል።

ያን ተከትሎ አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም የተሰወሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ገልጧል። ይህም ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የሐዋርያት እምነት ትመለስ ዘንድ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ላይ ትኩረት እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል።

ከዚያ ቀጥሎ ኢየሱስ እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ከእርሱ ጋር ትሆን ዘንድ በአየር ላይ ከነጠቃት በኋላ ወንጌሉ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወደ 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ተመልሶ ይሄዳል።

እስቲ ኢየሱስ ሕዝቡን እንጀራ ወዳበላበት ተዓምር እንመለስ።

ሉቃስ 9፡10 ሐዋርያትም ተመልሰው ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። ከእርሱ ጋርም ወስዶአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ ምድረ በዳ ለብቻው ፈቀቅ አለ።

“ወደ ምድረ በዳ ለብቻው”።

እግዚአብሔር ሰውን ሲያስተምር በብቸኝነት ውስጥ ነው የሚያስተምረው። እግዚአብሔርን ሕዝብ በበዛበት ቦታ ውስጥ አናገኘውም። ከኢየሱስ ጋር የግል ሕብረት ለማድረግ ተግተን መፈለግ አለብን።

በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ መሆን የዚህ ልምምድ አካል አይደለም።

ቤተሳይዳ “የአደን ቤት” ወይም “ዓሳ የማጥመድ ቤት” ናት።

ከገሊላ ባሕር በላይ ያለች ከተማ ናት።

ቤተሳይዳ ከኢየሩሳሌም እና በውስጧ ራሳቸው ከፍ ካደረጉ የሐይማኖት መሪዎች ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። በቤተመቅደሱ ውስጥ ካሉ ገንዘብ ለዋጮች ርቃ ነው የምትገኘው።

 

 

በዚህ በጨለማ ዘመን ውስጥ ሰይጣን በአምባ ገነኑ የሮማ ፖፕ ሥልጣን ስር ያሉትን ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ተጠቅሞ ነፍሳትን ለዲኖሚኔሽናዊ የቤተክርስቲያኖች ሥርዓት ባሪያ ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነበር።

ሕዝቡም የቤተክርስቲያን መሪ የመንግስተ ሰማያት በር መሰላቸው።

ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ ከቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ለመከራከር ድፍረት አልነበራቸውም።

ለቤተክርስቲያናቸው ሥርዓት ታማኝ በመሆን ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የሚችሉ መስሏቸዋል። ስለዚህ እነርሱ እንደመሰላቸው አዘውትሮ ቤተክርስቲያን መሄድ የመዳን ቁልፍ ነው።

ዘፍጥረት 10፡9 … ስለዚህም፦ በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ።

እግዚአብሔር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጸው ናምሩድ ነው።

በፍጥረታዊው ዓለም አሰራር የዱር እንስሳትን ያድን ነበር፤ ነገር በሐይማኖታዊ አስተምሕሮው አማካኝነት ደግሞ ነፍሳትን እያደነ ከራሱ ጋር ወደ ሲኦል ይጎትታቸው ነበር።

“በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ”።

ሕዝቡ የናምሩድን ቃል ከእግዚአብሔር ቃል በላይ ይቀበሉ ነበር።

ናምሩድ የተናገረውን ያምናሉ፤ እግዚአብሔር የተናገረውን ግን አያምኑም።

ናምሩድ አብዛኛው ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲክዱ አድርጎ እራሱን እንዲከተሉ አደረገ። ከዚያ በኋላ የተቀሩት ሰዎች አብዛኛው ሕዝብ በሄደበት አብረው በጭፍን ተከትለው ሄዱ።

ኢሳይያስ 17፡12 እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚተምሙ ለወገኖች ብዛት፥ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ ወዮላቸው!

ባሕር የአብላጫውን ሕዝብ አመለካከት ይወክላል፤ ይህም አንድ ግለሰብ በራሱ አስቦ መምረጥ እንዳይችል ከባድ ጫና የሚያደርግ ሞገድ ነው።

የቤተክርስቲያን መሪዎችን መፍራት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ነበር።

በተለይም የቤተክርስቲያን መሪዎች ፖለቲካዊ ሥልጣን ተቀብለው እርሱን የሚቃወሙ ሰዎችን ማሳደድ በቻሉበት ዘመን እነርሱን ሕዝቡ በጣም ይፈሩዋቸው ነበር። ይህም ፍርሃት ሰዎች ወደ ሩቅ ቦታዎች እንዲሸሹ አስገደዳቸው።

 

 

እግዚአብሔር ግን እውነተኛይቱን ቤተክርስቲያን፣ ማለትም ጥቂቶቹን አማኞች ተጠቅሞ ከዚህ የሰው ሰራሽ እምነቶች ሞገደኛ ባሕር ውስጥ ነፍሳትን እያጠመደ ያወጣ ነበር። እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን እንደ ዋልደንሳውያኖች ፈረንሳይ ውስጥ ከሊዮንስ ከተማ ተባራ ድንጋያማና አደገኛ በሆኑት የአልፕስ ተራሮች ውስጥ ለመኖር ተገዳ ነበር። በዚያ ተሸሽገው ብቻ ነው በሙሉ ሊገድሉዋቸው ከሚፈልጉ የሮማ ካቶሊክ ሰራዊቶች ማምለጥ የቻሉት።

የዋልደንሳውያን ወላጆች ለልጆቻቸው የልደት ስጦታ ሰጥተው አያውቁም። የሮማ ካቶሊኮች ቢያገኙዋቸው ያለ ጥርጥር እንደሚሞቱ ለልጆቻቸው በግልጽ ይነግሩዋቸው ነበር። ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን በአስቸጋሪ ሕይወት ውስጥ መኖርን በማለማመድ ወደፊት ስለ ወንጌሉ የሚጠብቃቸውን ሞት ለመቀበል ያዘጋጁዋቸው ነበር። በዚያ ዘመን በእጃችሁ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ቢገኝ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ስታነቡ ብትገኙ ትገደላላችሁ።

በደቡባዊ ፈረንሳይ ውስጥ የነበሩ አልቢጀንሶች እንደ ዋልደንሶች የሚሸሸጉበት ቦታ አላገኙም ነበር። ስለዚህ በ20 ዓመታት ስደት ውስጥ ተገድለው አለቁ።

 

 

ጨለማ በነገሰበት በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰይጣን ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ አርቆ በመውሰድ ተሳክቶለት ነበር። ሕዝቡም በመንፈሳዊ ጠኔ ውስጥ ነበሩ።

ደግሞም ሕዝቡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን አንቀበልም እንዲሉና እንዲጥሉ ነበር የተማሩት፤ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን ትተው የቤተክርስቲያን ልማዶችን መከተል ይመርጡ ነበር።

እንጀራ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። ሕዝቡ ከዚህ እንጀራ ውስጥ የማይፈልጉትን ክፍል አንበላም ብለው ይጥሉ ነበር። ዛሬም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የማይስማሟቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ቸል ብለው ያልፋሉ ወይም ይጥላሉ።

ይህንንም የሚያደርጉት ጠማማዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው የሚያስተምሩዋቸውን ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች ስለተቀበሉ ነው።

ማቴዎስ 16፡9 ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

11 ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉምን?

12 እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ።

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች የእውነት ጠላቶች ናቸው። ሰይጣንም ወደ ቤተመቅደስ አምልኮ ውስጥ ሾልኮ ገብቶ ነበር።

በጨለማው ዘመን ውስጥ ሰይጣን የቤተክርስቲያንን አመራር ተቆጣጥሮ ነበር።

5,000ው ሕዝብ በቤተሳይዳ ከተማ አካባቢ በነበረው አረንጓዴ ለምለም ሃገር ውስጥ ነበሩ። በዚያም ሆነው ራባቸው።

 

 

ሰባት የሚበሉ ነገሮች ነበሩ። እነርሱም ሁለት ዓሳዎች እና አምስት እንጀራዎች ናቸው።

እንጀራው የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። አምስት እንጀራዎች ማለት የእግዚአብሔርን ቃል የተመገቡ አምስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።

እነርሱም 1ኛ፣ 2ኛ፣ 5ኛ፣ 6ኛ፣ 7ኛ የቤተክርስቲያን ዘመናት ናቸው።

ዓሳ በስደት ምክንያት ከውሃ በታች ተደብቃ ከእይታ የተሰወረች ቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን በድብቅ በምትንቀሳቀስበት ጊዜ የምትጠቀመው ሚስጥራዊ ምልክት ዓሳ ነበረ።

በሶስተኛው እና በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የጨለማ ወቅት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በተጠና ዘዴ ከሕዝቡ ይደበቅ ነበረ።

ዮሐንስ 6፡9 አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።

አምስት ጸጋን የሚወክል ቁጥር ነው። እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ በአምስት መንፈሳዊ እንስሳት ተከብቦ ነው የሚቀመጠው። ይህም እግዚአብሔር በ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ለሕዝቡ ጥበቃ የሚያደርግበት የምሪት ዘዴ ነው።

 

 

ሰባቱ የሚበሉ ነገሮች በተጨማሪ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናትም ይወክላሉ።

ዮሐንስ 6፡10 ኢየሱስም፦ ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር።

ሕዝቡ እንዲቀመጡ ታዘው ነበር። ኢየሱስ ሕዝቡ ለራሳቸው ምግብ ያዘጋጃሉ ብሎ አላመነባቸውም። አዘጋጁ ቢባሉ ዲኖሚኔሽናዊ ልማዶችን ነው ለራሳቸው የሚያዘጋጁት።

እንጀራ እና ስጋ አስተምሕሮን ይወክላሉ።

ዮሐንስ 6፡11 ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፥ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።

እውነተኛ አስተምሕሮ የሚጀምረው ኢየሱስ ከተናገረው ቃል ነው። ኢየሱስ እውነተኛው አስተምሕሮውን ለደቀመዛሙርቱ አስተላለፈ፤ እነርሱም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጽፈው አስቀመጡት። እኛም እምነታችንን በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት በመፈተሽ እውነትን ከደቀመዛሙርቱ እናገኛለን።

በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በተለያዩ ጊዜዎች ውስጥ የተለያዩ የቤተክርስቲያን ቡድኖች በዓለም ዙርያ በተለያዩ ሥፍራዎች መንፈሳዊ ምግባቸውን ማግኘት የሚችሉት ሐዋርያቱ ከጻፉዋቸው የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች ውስጥ ነው።

ዮሐንስ 6፡12 ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው።

“አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ”።

እግዚአብሔር የገጠመው ችግር ይህ ነው፡- ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልጣማቸውን ቃል በቀላሉ አውጥተው ይጥላሉ። እግዚአብሔር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቃል እንኳ እንዳይጠፋ ይፈልጋል።

እግዚአብሔር ሁሉንም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ተረድተን እናምን ዘንድ የቃሉ እውነት ተሃድሶ እንዲመጣ ይፈልጋል።

አይሁዶች ግዴለሾች ነበሩ። ብዙ ቁርስራሾችን አንበላም ብለው ጥለዋል።

አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ቤተክርስቲያን ግዴለሽ ነበረች። ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን አንቀበልም አሉ ወይም በሚገባ አላወቁትም። ደግሞም ያልጣማቸውን እንዲሁም ያልገባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ አንፈልግም ብለው አውጥተው ጣሉ።

ዮሐንስ 6፡13 ስለዚህ አከማቹ፥ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ።

5ቱ እንጀራዎች እና ሁለቱ ዓሳዎች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲጠናቀቁ አሕዛብ ለመጨረሻው ዘመን የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አንቀበልም ብለው ይገፉታል።

ለዚህ ነው ኢየሱስ በሰባተኛው በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ከቤተክርስቲያን በር ውጭ የቆመው።

ሎዶቅያውያን የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ልማዶችና እምነቶች አበጅተዋል።

ከዚያም እግዚአብሔር እነዚያን የተጣሉ ቁርስራሾች በሙሉ ሰብስቦ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ወደ 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ይመለሳል።

ራስ ከአካል ጋር የተጋጠመው በጀርባ አጥንት አማካኝነት ነው።

 

 

ኢየሱስ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን እና የአይሁድ ነገዶች ራስ ነው።

ራስ የሆነው ኢየሱስ ከምድራዊ አካሉ ጋር የተጋጠመው በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት እና በታላቁ መከራ ዘመን ወደ 144,000ው ሲመለስ በ12 የእሥራሴል ነገዶች አማካኝነት ነው የተጋጠመው።

ኤፌሶን 3፡4 ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤

ክርስቶስ ውስጥ ታላቅ ሚስጥር አለ።

ኤፌሶን 3፡5 ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።

አይሁዳውያን መጥምቁ ዮሐንስ መጥቶ ሰባተኛውን እና የአይሁዳውያንን የመጨረሻ ዘመን እስኪያውጅ ድረስ በስድስት የብሉይ ኪዳን ዘመናት ውስጥ ሲያልፉ ይህ ሚስጥር አልተገለጠላቸውም ነበር።

አይሁዳውያን ግን ሰባተኛውን የመሲሁን ዘመን አንቀበልም አሉ።

ኤፌሶን 3፡6 ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥

ከዚያ በኋላ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔር አሕዛብንም አካሉ ለማድረግ ወደ አሕዛብ ዞረ።

በመስቀል ቅርጽ ከተሰራው ከአይሁዳውያን የቤተመቅደስ ድንኳንም ተመሳሳይ እውነት እንማራለን።

ይህም ኢየሱስ ለሁለት ዓይነት ሕዝቦች እንደሞተ ያስረዳል።

ሰባት ቅርንጫፎች ያሉት መቅረዝ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላል፤ በጠረጴዛው ላይ ያሉት 12ቱ ሕብስቶችን ደግሞ በቅድስት ሥፍራ ነው የሚበሉት። ይህም 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች መሲሁን ለመቀበል ወደ ተስፋይቱ ምድር መመለስ እንዳለባቸው ያመለክታል።

 

 

ሰባቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት እና 144,000ው አይሁዶች በመዳን እቅድ ውስጥ የራሳቸው ሚና አላቸው።

አምስተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን የሚወክለው አምስተኛው ተዓምር።

አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማርቲን ሉተር በ1520 ዓ.ም ጀርመኒ ውስጥ ታላቁን ተሃድሶ የጀመረበት ዘመን ነው።

ይህም በታሪክ ውስጥ ከተመዘገቡ አብዮቶች ትልቁ ነው። ከዚያ ወዲያ ሰዎች በራሳቸው አእምሮ ማሰብ እና ከእግዚአብሔር ጋር መዳንን በግል መለማመድ ጀመሩ። ከዚያ በኋላ ለመዳን ቤተክርስቲያን የግድ ታስፈልጋለች ከሚለው ሃሳብ ነጻ ወጡ።

ፖፑ በሕዝቡ ላይ የሞት እና የሕይወት ኃይል ነበረው።

ነገሥታት እና ገዢዎችም በቤተክርስቲያን ላይ ሥልጣን ነበራቸው።

በታሪክ ውስጥ ከሚታወቁ ጀግኖች አንዱ የሆነው ሉተር የፖፑን፣ የነገስታትን እና የገዢዎችን ሥልጣን ማፍረስ ጀመረ። በበኩላቸው እነርሱም ደግሞ ቢቻላቸው ሉተርን ቢገድሉ ደስ ይላቸው ነበር።

ዮሐንስ 6፡16 በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፥

ባሕር እረፍት የሌላቸውን ሕዝቦች ይወክላል። ባሕር በጨለማው ዘመን ሲታወኩ የኖሩትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአውሮፓ ሕዝብ በትክክል ይገልጻል።

ዮሐንስ 6፡17 በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤

ቅፍርናሆም ማለት ሁከት ወይም በሐዘን ውስጥ ተጠብቆ መኖር ማለት ሊሆን ይችላል።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሁከት ውስጥ ነበረች። ፖፑ የስርየት ወረቀቶችን እየሸጠ ነበር። ይህም የሐጥያት ይቅርታ በገንዘብ መግዛት ትችላላችሁ ማለት ነው። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ስም ጠፍቶባት ነበር። ስለ አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ስም ያወራሉ ግን ያ ስም ማን እንደሆነ አያውቁም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት አክብሩ አላለንም። ዲሴምበር 25ን የኢየሱስ ልደት ብሎ ያወጀው ፖፑ ነው። ይህ ቀን የተኮረጀው ከአረማውያን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀን ነው።

ቤተክርስቲያን የአቅጣጫ ለውጥ ያስፈልጋት ነበር።

 

 

ጨለማ ነበረ። በፖፑ ጭቆና ስር ታላቅ የዓለማመን ጨለማ ዓለምን ውጦ ነበር።

ኢየሱስ ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር። ያን ጊዜ ከኢየሱስ ጋር በግል ሕብረት በማድረግ የዳነ ብዙም ሰው አልነበረም። በዚያ ጊዜ ሕዝቡ የሚያውቁት ለቤተክርስቲያን ልማዶች ባሪያ መሆንን ብቻ ነበር።

ቤተሳይዳ አጠገብ በመርከብ ተሳፈሩና ወደ ቅፍርናሆም አቅጣጫ ሄዱ። እዚያም ሲደርሱ በቀጣዩ ቀን ወደ ጌንሰሬጥ ከመሄዳቸው በፊት ሌሊቱን እረፍት አድርገው ሊያድሩ አሰቡ።

ነገር ግን ወዲያው ከመንገዳቸው የሚያስወጣቸው ነፋስ ተነሳ።

በብዙ ጭቅጭቅና ሁከት መካከል ማርቲን ሉተር ቤተክርስቲያንን ለፖፑ እየተገዛች ከምትሄድበት መንገድ ሊያስወጣት ነበረ።

ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት የሚለውን እውነት በተሃድሶ መልሶ አመጣው። ይህም ትምሕርት ከልብ ንሰሃ መግባት እና ከሐጥያት መመለስ ነው።

የእውነት በሐጥያታችን ከተጸጸትን እግዚአብሔር ይቅር ይለንና ከሰይጣን ክፉ ሃሳብ ይጠብቀናል።

ዮሐንስ 6፡18 ብርቱ ነፋስም ስለ ነፈሰ ባሕሩ ተናወጠ።

ዮሐንስ የእግዚአብሔርን እይታ ያሳየናል።

ባሕር እረፍት የሌለውን ብዙ ሕዝብ ይወክላል። ነፋስ ግጭትን እና ጦርነትን ይወክላል። ታላቅ መንፈሳዊ ጦርነት ነበረ፤ ይህም መንፈሳዊ ጦርነት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሉተርን ለመቃወም ውጊያ ስትጀምር ስጋዊ ጦርነት ወደ መሆን ተለወጠ።

ፖፑ ቫቲካን ውስጥ የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተክርስቲያን ለመገንባት ባሰበ ጊዜ በውስጡ ከነበረው የገንዘብ ምኞትና ስግብግብነት የተነሳ ትልቅ ሁከት ተፈጠረ። ፖፑ ከሞታችሁ በኋላ የምትቀጡበት ፑርጋቶሪ የሚባል ሥፍራ አለ ብሎ የራሱን ትምሕርት ፈጠረ። ከዚያ በኋላ ገንዘብ ከፍላችሁ ከፑርጋቶሪ ታመልጡ ዘንድ የስርየት ወረቀት መሸጥ ጀመረ። ሉተር ይህንን ሐሰት ፊት ለፊት ተጋፈጠ። ፖፑ ሰዎችንም ገንዘብን በማጣቱ የተነሳ ተሃድሶውን ለመቃወም ጭካኔ እና ብዙ ግፍ እንዲሁም ደም መፋሰስ የሞላበት ከባድ ስደት አስነሳ።

በዚህ በመጨረሻው ጥቅስ ውስጥ ደቀመዛሙርቱ ወደ ውሃው ዳር ለመድረስ ሲታገሉ የሚገልጽ ቃል የለም። ንፋሱም እንደተቃወማቸው የሚናገር ቃል የለም።

ከእግዚአብሔር እይታ አንጻር ለዚያ ዘመን የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እነዚያ ናቸው። ስለዚህ ሁሉ መልካም ነበረ።

ደቀመዛሙርቱ ለመቅዘፍ እየታገሉ ነበረ። ከባድ ነፋስ እየተቃወማቸው ነበረ። ማዕበሉና ሞገዶቹ እጅግ ታላቅ ስለነበሩ ማንኛውንም ሰው የሚያስፈሩ ነበሩ። ወደ ቅፍርናሆም ለመድረስ እና አንድ ሌሊት ለማረፍ አስበው ነበር፤ ግን ነፋሱ ደግሞ ከመንገዳቸው ገፍቶ እያስወጣቸው ነበረ። ዮሐንስ ግን እነዚህን በዝርዝር አይጠቅስም። ከመንፈሳዊ እይታ አንጻር ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ባቀደው መሰረት ወደ ግቡ እየሄደ ነበር።

እግዚአብሔር ማዕበሉን እና ነፋሱን ለማስወገድ ቃል አልገባም። ቃል የገባልን ማዕበሉን እና ነፋሱን የምናሸንፍበትና ድል የምንጎናጸፍነትን ብርታት እንደሚሰጠን ነው።

ማርቆስ በወንጌሉ ውስጥ ኢየሱስ መከራን የሚቀበል አገልጋይ ከመሆኑ አንጻር ነው የሚያቀርብልን እይታ።

ማርቆስ 6፡48 ነፋስ ወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር።

ማርቆስ ከሰው በኩል ያለውን እይታ ያቀርብልናል። ከሰው አንጻር ሲታይ አድካሚ ነው። ደቀመዛሙርቱ ለመቅዘፍ እየታገሉ ነበረ። ነፋሱ ከእነርሱ በተቃራኒ አቅጣጫ ነበረ የሚነፍሰው። እያንዳንዱ ትጋት የሶስት ሰዓት ርዝመት ነበረው፤ የሚጀምረውም ፀሃይ ስትጠልቅ በ12 ሰዓት ነው። ሁለተኛው ትጋት ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት ይጀምርና ከሌሊቱ 06፡00 ሰዓት ያበቃል። ሶስተኛው ትጋት ከሌሊቱ 09፡00 ሰዓት ላይ ያልቃል። የመጨረሻው ወይም አራተኛው ትጋት ከሁሉም በላይ አድካሚ ነው ምክንያቱም ሌሊቱን ሙሉ ሲቀዝፉ ነበር። እርሱም ከ09፡00 ሰዓት ጀምሮ ፀሃይ እስከምትወጣበት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ ነው።

በሉተር ዘመን ብዙ ብጥብጥ ነበረ። ሉተር የጀመረው ሥራ በሕዝቡ ላይ ተጭኖ የነበረውን የፖፑን ቀንበር መስበር ነበር። ፖፑ በአጸፋው በጭካኔ ተዋጋ። የዚያን ጊዜ ተሃድሶውን በመቃወም በተጀመረው ዘመቻ ካቶሊኮች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል።

ካቶሊኮች በሙስሊሞች የመስቀል ጦርነቶችን አውጀዋል፤ እንዲሁም በደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ ካቶሊክ ባልሆኑ በአልቢጀንሶች ላይ ባደረጉት ዘመቻ ሙሉ በሙሉ አጥፍተዋቸዋል። ነፍሰ ገዳዮቹ ካቶሊኮች የአልቢጀንሶችን ንብረቶች በሙሉ ወረሱ። የመስቀል ዘመቻ ጎረቤቶቻችሁን በመግደል እና በመዝረፍ በግፍ ሃብታም የምትሆኑበት መንገድ ነው።

ማርቲን ሉተር የወንጌልን ተሃድሶ በ1520 ዓ.ም መልሶ እስካመጣበት ቀን ድረስ ዘመኑ ለክርስትና የድቅድቅ ጨለማ ሌሊት ነበረ።

ዊልያም ቲንዴል መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝና ስለተረጎመ በአደባባይ በእሳት አቃጥለውታል። እየተረጎመ ሳለ በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ከሚኖሩ ጨካኝ አጋንንታዊ ኃይላት ጋር የማይቋረጥ ተጋድሎ ውስጥ ነበረ።

ተሃድሶው አውሮፓን ለውጧት በአዲስ ጎዳና ላይ መንገድ አስጀመራት።

ፀሃይዋ እስክትወጣ ድረስ ደቀመዛሙርቱ ረጅሙን ሌሊት ሲደክሙ አድረዋል፤ በስተመጨረሻም የእግዚአብሔር ልጅ በማዕበሉ ላይ እየተራመደ ሲመጣ አዩት። ይህም እኛን በሚያስጨንቁን ክስተቶች ሁሉ ላይ ኢየሱስ ሥልጣን እንዳለው ያሳያል።

ስለዚህ የገጠሙንን ተግዳሮቶች የምንቋቋምበትን የምናሸንፍበት እምነትና ብርታት ይሰጠናል።

ዮሐንስ 6፡19 ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።

የፖፑ ጭካኔ ብዛት እንዲሁም ተሃድሶውን ለማጥፋት የተጀመረው ዘመቻ ማንኛውንም ሰው ለማስፈራራት በቂ ነበረ።

በአንድ ማይል ውስጥ ስምንት ምዕራፎች አሉ። ስለዚህ ሶስት ወይም አራት ማይል ወደ ባሕሩ ውስጥ ገብተው ነበር።

የገሊላ ባሕር 7 ማይል ያህል ሰፊ ነው።

ስለዚህ ከባሕሩ ስፋት ግማሹ ላይ ደርሰው ነበር።

የጨለማው ዘመን ውስጥ የነበረው ጨለማ በተሃድሶ ለመጣው እውነት ቦታውን ለቆ መሄድ ጀመረ። ይህም ብርሃን ጨለማን ተክቶ የሚበራበት የለውጥ ሰዓት ነው።

ማርቆስ 6፡47 በመሸም ጊዜ ታንኳይቱ በባሕር መካከል ሳለች እርሱ ብቻውን በምድር ላይ ነበረ።

በመሸም ጊዜ። ጨልሟል። በትግል እየቀዘፉ ሰዓት በጣም ሳይረፍድባቸው ወደ ቅፍርናሆም ሊደርሱ ይችሉ ነበር። ሰው እንደመሆናቸው በሰው አቅም ያቀዱት እቅድ ይህ ነበር። ሌሊቱን በቅፍርናሆም አርፈው በቀጣዩ ቀን ወደ ጌንሰሬጥ ለመሄድ ነበረ ዓላማቸው።

ነገር ግን አንድ ነገር ረስተዋል። ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዳንዶቹ ልምድ ያላቸው ዓሳ አጥማጆች ስለሆኑ ባሕሩን በማወቃቸው በመተማመን ቤተሳይዳ አጠገብ ኢየሱስን በምድር ላይ ትተውት ነበር የሄዱት።

ስለዚህ ነፋሱ ከመንገዳቸው አስወጣቸው። የእግዚአብሔር መንገዶች ሁልጊዜ ከእኛ ዓላማዎች ይለያሉ።

ከዚያም ጊዜ ሳይፈጅባቸው ወደ ባሕሩ መሃል ሲደርሱ ነፋሱ እየተቃወማቸው ነፈሰ፤ እነርሱም ለመቅዘፍ ብዙ ቢታገሉ እንኳ ካሉበት መንቀሳቀስ አልቻሉም።

ሌሊቱን ሙሉ ቢታገሉ ቢታገሉ የትም ሊደርሱ አልቻሉም።

ስለዚህ በራሳችን ብርታት እና በራሳችን ችሎታ እግዚአብሔርን ለማገልገል ስንሞክር ከባድ ኪሳራ እንከስራለን።

በተወሰነ ደረጃ የተሳካልን ሊመስለን ይችላል። በራሳችን ብርታት ስንንቀሳቀስ የምናደርገው ነገር ቢኖር ከእግዚአብሔር ፈቃድ መውጣት ብቻ ነው።

እነርሱ እየታገሉ መቅዘፋቸውን ቀጠሉ፤ ነፋሱም ትግላቸውን ከንቱ ለማድረግ ከእነርሱ በተቃራኒ ነፈሰ።

ይህም ትግል ሌሊቱን ሙሉ ቀጠለ።

ነገሮች የተለወጡት ልክ ከንጋት በፊት ኢየሱስ ሲመጣ ብቻ ነው።

ከታች ካርታው ላይ በአረንጓዴ ሶስት ማዕዘን የተመለከተው 5,000 ሰዎች በተዓምር እንጀራ ከበሉበት ቦታ ነበር ጉዞ የጀመሩት። ወደ ቅፍርናሆም እየሄዱ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን የሄዱት ገሊላ ባሕር ውስጥ ጥቁር መስቀል ወደ ተሳለበት ቦታ ነበር።

 

 

ዮሐንስ 6፡20 እርሱ ግን፦ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው።

ሉተር ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለመለየት መፍራት የለበትም። አዲስ ኪዳንን ወደ ጀርመንኛ ለመተርጎም በዋርትበርግ ግምብ ውስጥ ከሰዎች ተነጥሎ ለብቻው መቀመጥን መፍራት የለበትም። መዳንን በጸጋ የተቀበሉ ክርስቲያኖች የፖፑን ጭካኔ እና ግፍ የሞላበት እርምጃ መፍራት የለባቸውም።

ሁላችንም ቤተክርስቲያኖቻችን የግል አጀንዳ ባላቸው ሰዎች እንደሚመሩ ስናውቅ ተመሳሳይ ፍርሃት ይወድቅብናል። መሪዎቻችን የተወሰኑ ትክክለኛ አስተምሕሮዎች አሉዋቸው ግን ስሕተቶች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችም አሉዋቸው።

ቤተክርስቲያንን ለቆ መሄድ ያስፈራናል ምክንያቱም ዕድሜያችንን ሙሉ በሰው ስንመራ ቆይተናል፤ ሰውንም በእግዚአብሔር እና በራሳችን መካከል ማስገባት ለምደናል።

አሁን ግን ኢየሱስን ወደ ልቤ ውስጥ ማስገባት እና መቀበል አለብኝ። ይህም ሰውን ጣልቃ የማያስገባ በኢየሱስ እና በእኔ መካከል ብቻ የሚሆን የግል ሕብረት ነው። ይህ ሕብረት እርሱን የእኔ ራስ ያደርገዋል። ይህ ሕብረት የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ብቸኛው እውነተኛ መመሪያዬ ያደርገዋል። የትኛውም ሰው ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስን ከተቃረነ አላምነውም።

ዮሐንስ 6፡21 ስለዚህ በታንኳይቱ ሊቀበሉት ወደዱ፤ ወዲያውም ታንኳይቱ ወደሚሄዱበት ምድር ደረሰች።

እንደ ሰው ጥረት ሲያደርጉ ቢያድሩም የትም አልደረሱም። ይህ ሁሉ ድካም እና ተስፋ መቁረት ኢየሱስን ሲያዩ ሁሉን በደስታ ለእርሱ እንዲያስረክቡ አደረጋቸው።

ውድቀት ወይም አለመሳካት ከኢየሱስ ጋር የሚያጣብቀን ፍቱን ማጣበቂያ ነው።

መከራ እና ሽንፈት ባህርያችንን በመቅረጽ የተሻልን ሰዎች እንድንሆን ይረዱናል።

ብዙ ለፍተን በሕይወት ውስጥ የትም ሳንደርስ መቅረት ኢየሱስን ለመቀበል እንድንወስን ይረዱናል።

ዮሐንስ ባሕሩ ላይ የገጠማቸውን ችግር አልጠቀሰም፤ ምክንያቱም የነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ በፈቃደኝነት ኢየሱስን ወደ መርከቡ ውስጥ እንዲቀበሉ አድርጓቸዋል።

ኢየሱስን ወደ ልባችሁ ውስጥ እንድትቀበሉ የሚያደርጋችሁ ማንኛውም ነገር መልካም ነው እንጂ ክፉ አይደለም።

 

አሁን ደግሞ በጣም እንቆቅልሽ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እናገኛለን።

ለምንድነው መርከባቸው ወዲያው ወደሚሄዱበት ቦታ የደረሰችው?

ይህ ከእኛ የሰዎች አመለካከት ጋር አይሄድም። በዚያ ሰዓት ከባሕሩ መሃል ላይ ነበሩ።

ዮሐንስ ግን የእግዚአብሔርን እይታ ያቀርብልናል።

አንድ ጊዜ ንሰሃ ገብታችሁ ኢየሱስን የግል አዳኛችሁ አድርጋችሁ ከተቀበላችሁ በኋላ ሐጥያታችሁ ይቅር ተብሎላችኋል፤ እናንተም ወዲያው የሰማይ ልጅ ወይም የሰማይ ዜጋ ሆናችኋል። ከዚያ በኋላ የቀረው ምድራዊ የሕይወት ጉዞዋችሁ ከሲኦል መዳናችሁ ላይ አንዳችም ተጽእኖ ሊያደርግ አይችልም ምክንያቱም የዳንነው በሥራ አይደለም።

ንሰሃ ከገባህበት ሰዓት ጀምሮ በመንፈስ መንግስተ ሰማይ ደርሰሃል።

የሕይወት ጉዞ ዋና ዓላማው ለመንግስተ ሰማይ እንድንዘጋጅ ነው።

አንዴ ከዳንክ በኋላ አካልህ በምድር ላይ ቢሆንም እንኳ ነፍስህ በሰማይ ውስጥ ናት።

ኢየሱስን የግል አዳኝህ አድርገህ መቀበል ውስጥ የሁለትዮሽ ልውውጥ አለበት።

ሐጥያትህ ወደ እርሱ ተላልፏል፤ ስለዚህ እርሱ ወደ ሲኦል መውረድ ግድ ሆኖበታል (ይህንን በ33 ዓ.ም ፈጽሞታል)፤ ይህንንም ያደረገው ሐጥያትህን በዲያብሎስ ላይ ለማራገፍ ነው። የእርሱ ንጹህነት ወደ ልብህ ውስጥ ይተላለፋል፤ አንተም ወዲያው ከሐጥያት ነጽተህ በዚያው ሰዓት ብትሞት ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት ትችላለህ። ወደ መንግስተ ሰማያት መግባትህን እርግጠኛ ለመሆን እስክትሞት ድረስ መጠበቅ አያስፈልግህም። ንሰሃ ከገባህበት ሰዓት ጀምሮ መዳንህን በእርግጥ ታውቃለህ። ነፍስህን ፍለጋ ሲደረግ የነበረው መንፈሳዊ ጦርነት አብቅቷል፤ ኢየሱስም ድል አድርጓል።

ሉተር የተቀበለው ታላቅ መገለጥ ይህ ነው። የምንድነው በጸጋው አማካኝነት በእምነት ብቻ ነው። ይህም እምነት የሚመጣው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማመን ነው። ከሰው መሪ ጋር የተያያዘ ነገር የለበትም። አንዳችም ከሰው መሪ ጋር ወይም ከቤተክርስቲያን ጋር የተነካካ ነገር የለበትም። መዳንህ የሚወሰነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለህ የግል ሕብርት ብቻ ነው።

ጴጥሮስ ዓይኖቹን ከኢየሱስ ላይ እስካነሳበት ሰዓት ድረስ በውሃ ላይ መራመዱን ማቴዎስ ጽፏል። ከዚያ በኋላ መስመጥ ጀመረ።

በተሃድሶው ውስጥ የሰሩት ስሕተት ዓይናቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ላይ አንስተው ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተቀበሉትን እንደ ሥላሴ የመሳሰሉ አስተምሕሮዎች፣ በፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ መግባት፣ እንዲሁም የሉተራን ቤተክርስቲያንን መንግሥት እንዲረዳት መፍቀዳቸው ነው። ደግሞም እንደ ክሪስማስ እና ኩዳዴ ጾም የመሳሰሉ የአሕዛብ ልማዶችን ተቀብለው ቀጠሉ። ልክ ጴጥሮስ በውሃ ላይ መራመድ ከጀመረ በኋላ እንደሰመጠው እነዚህ የካቶሊክ ልማዶችና ስሕተቶች ተሃድሶው በጥሩ ሁኔታ ከተጀመረ በኋላ እንዲሰጥም ምክንያት ሆነዋል።

ማርቆስ የአገልጋይን አገልግሎት ይገልጻል። መዳናችን እውን መሆኑ ወዲያው በእምነት ይረጋገጣል።

በስጋችን ግን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የእግዚአብሔርን አገልግሎት ፈጽመን ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል። በስተመጨረሻም ስንሞት ወደ ሰማይ ደጅ እንሄዳለን።

ማርቆስ 6፡53 ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ።

ጌንሰሬጥ የሚለው ስም ትርጉሙ የአለቃው የአትክልት ቦታ ነው።

መንግስተ ሰማያችን የኤደን ገነት ታድሳልን ስናገኛት ማለት ነው።

ኢየሱስ እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ስትቀበል መጨረሻ የምትገባበት ቦታ ወዲያውኑ ይረጋገጥልሃል።

አዲሱ ቤተህ መንግስተ ሰማይ ነው።

ዮሐንስ በዚህ ምድር ላይ ያሉትን ትግሎች አያይም። ዮሐንስ የሚያየው ዘላለማዊውን ዓለም ነው። በምድር ላይ የምናሳልፋቸው ዓመታት ከዘላለማዊው ዓለም ጋር ሲወዳደሩ ኢምንት ከመሆናቸው የተነሳ ልንጨነቅላቸውም አያስፈልግም።

ስለዚህ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ በኋላ ዘላለማዊ ሕይወትህ እውን መሆኑ ተረጋግጧል።

የዘላለም ሕይወት፣ ታላቁ መንፈስ ቅዱስ ወዲያው ወደ ሰማያዊ ሥፍራ ይወስድሃል። በመንፈስ ወደ ፍጻሜህ ደርሰሃል።

ኤፌሶን 2፡5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

6 ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

 

 

ስድስተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን የሚወክለው ስድስተኛው ምሳሌ።

ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰውን ዓይኖች መክፈት። ይህ የተፈጸመው ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው።

ይህ ተዓምር ጆን ዌስሊ በእንግሊዝ ውስጥ ያደረገውን የቅድስና ዘመቻ እና ታላቁን የወንጌል ስርጭት ዘመን የሚገልጽ ውብ ምሳሌ ነው።

ዮሐንስ 9፡1 ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ።

ፍጥረታዊ ዕውርነት ከመንፈሳዊ ዕውርነት ጋር በጣም ይመሳሰላል።

መንፈሳዊ ዕውርነት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ምሳሌዎች እና ሚስጥሮች ትርጉም መረዳት አቅቶሃል ማለት ነው። መንፈሳዊ ዕውርነት ሰዎች በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች እና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ ብለው እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል። መንፈሳዊ ዕውርነት ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር መሆኑን እንዳያዩ ያደርጋቸዋል።

ዮሐንስ 9፡5 በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ።

ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው።

ዮሐንስ 1፡14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥

መዝሙር 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ብርሃናችን ከሆነ የወንጌል ስብከት ዘመን ዓላማው የቃሉን ብርሃን ማሰራጨት ነው።

ዮሐንስ 9፡6 ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና፤

ሰው የተሰራው ከአፈር ነው።

ኢየሱስ የዕውሩን ዓይኖች በእርጥብ አፈር ቀባው። የሰውየው ዓይኖች የጎደለባቸው ነገር ቢኖር የተሰራው ከአፈር ነው። ስለዚህ ጉድለቱን ለመሙላት የሚያስፈልገው ከኢየሱስ አፍ የሚወጣ ነገር (ቃሉ ከአፉ ነው የሚወጣው) ዝቅ ወዳለው አፈር ወርዶ ከዚያ ወደ ሰውየው ዓይን ነው የሚመጣው።

አፈር እግራችን የሚራመድበት ቦታ ነው። ትኩረቱ እግር ላይ ነው። ለዚህ ነው የሸክላ አፈር የተጠቀሰው።

የብረት እና የሸክላ እግሮች በናቡከደነጾር የአሕዛብ ምስል ሕልም ውስጥ።

 

 

እግሮቹ እጅ የማይሰጠውን አረማዊ የሮማ መንግስት ይወክላሉ፤ ይህም መንግስት ቅርጹን ለውጦ አረማዊው የሮማ መንግስት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሚሆንበት ጊዜ በእግሮቹ ውስጥ የብረት ስብርባሪ ይሆናል። አንድ የታሪክ ምሑር የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ሲገልጽ ክርስትና የተነሳ ወይም የተጠመቀ አረማዊነት ብሏል።

እግሮቹ ከብረት እና ከሸክላ የተሰሩ ነበሩ።

ዳንኤል 2፡43 ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥

“ሸክላ” ነው፤ በእግሩ ውስጥ ያለው እርጥብ ሸክላ ነው። ለምን እርጥብ ሸክላ ሆነ? ይህ ምንድነው የሚነግረን?

ዕውሩ ሰው ወዳየበት ተዓምር እንደመለስ።

ከዚያ ቀጥሎ ጌታ ስለ መታጠብ ይናገራል።

ዮሐንስ 9፡7 ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።

ታጠበ። አየ። ተላከ። እነዚህ ቁልፍ ቃላት ጥልቅ ትርጉም አላቸው።

መታጠብ ቅድስናን ያመለክታል።

ዕብራውያን 12፡14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።

ሰላም እና ቅድስና እግዚአብሔርን ማየት ያስችሉናል።

ሰሊሆም የተላከ ማለት ነው። ይህም የሚገልጸው በዓለም ዙርያ በቅድስና የቃሉን ብርሃን ሊያበሩ ወደ ዓለም ዙርያ ተልከው የሚሄዱ ወንጌል ሰባኪዎችን ነው።

በዚህ መንገድ ያልዳኑ አረማውያን የእውነትን ብርሃን ማየት ይችላሉ።

በናቡከደነጾር የአሕዛብ ምስል ውስጥ መዳን ከአይሁድ ሆኖ ከአሕዛብ ምስሉ ውጭ ነበረ። ከዚያ በኋላ በመስቀሉ መዳን ወደ አሕዛብ ተሻግሮ ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይጀምር ዘንድ በምስሉ ውስጥ ወዳለው እግር ውስጥ ገባ።

ሸክላው እውነተኞቹን አማኞች ማለትም ሙሽራይቱን ይወክላል። ከብረቱ እግሮች ውስጥ የሕይወትን ዘር ማብቀል የሚችለው ክፍል ሸክላው ብቻ ነው።

ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜ ለጴጥሮስ ታላቅ ሚስጥር ያለበትን ቃል ነገረው።

ዮሐንስ 13፡6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።

7 ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።

ዓመታት ካለፉ በኋላ ጴጥሮስ ምንድነው የተረዳው?

የተረዳው ወንጌል ለአሕዛብ መድረስ እንዳለበት ነው።

እግዚአብሔር ሶስት ጊዜ “እርኩስ” እንስሳት ያሉበትን ሸማ አሳየውና አርደህ ብላ አለው።

ጴጥሮስ በቆርኔሌዎስ ቤት ውስጥ ሲሰብክ መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ ወደቀባቸው።

ጴጥሮስ እንዲህ አለ፡-

የሐዋርያት ሥራ 11፡15 ለመናገርም በጀመርሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ደግሞ በመጀመሪያ እንደ ወረደ ለእነርሱ ወረደላቸው።

16 ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ ያለውም የጌታ ቃል ትዝ አለኝ።

17 እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?

ስለዚህ ጴጥሮስ እግዚአብሔር አሕዛብንም ለማጥመድ እርሱን እንደ ዓሳ አጥማጅ እንደተጠቀመው ተረዳ። ጴጥሮስ በጴንጤ ቆስጤ ዕለት አይሁዶችን አጥምዶ ወደ እግዚአብሔር እንዳመጣው ሁሉ አሕዛብንም አጠመደ።

እንግዲያውስ እግር በማጠብ ሥነስርዓቱ አማካኝነት ኢየሱስ ምን እያለ ነው። ?

ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት

ይህም በድጋሚ ስለ መታጠብ፤ ስለ ቅድስና ይናገራል።

በፍጥረታዊ ውሃ አይደለም፤ በቃሉ ውሃ ነው እንጂ።

በምስሉ እግሮች ውስጥ ያለው እርጥብ እግር ከአሕዛብ የሆነችዋን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በቃሉ ውሃ ታጥባ የምትነጻዋን ሙሽራይቱን ይወክላል።

ሐዋርያቱ የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትን የመጻፍ ሃላፊነት ይቀበላሉ፤ በዚህም በአዲስ ኪዳን የቃል ውሃ የአሕዛብን ቤተክርስቲያን አጥበው ያነጻሉ። እግር የማጠብ ሥነስርዓቱ የሚወክለው ይህንን ሚስጥር ነው። ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወክለው የአሕዛብ ምስሉ እግር ብቻ ነው ለወንጌሉ ምላሽ የሚሰጠው።

ጥንታውያኑ የአሕዛብ መንግስታት በታሪክ ውስጥ ጠፍተው ተረስተዋል።

ጴጥሮስ እንዲህ አለ፡-

ዮሐንስ 13፡9 ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።

የአሕዛብ ምስሉ ውስጥ ያሉት እጆች የሜዶን እና የፋርስ መንግስታት ናቸው፤ እነርሱም ከረጅም ጊዜ በፊት በታሪክ ውስጥ ጠፍተዋል። ታላቁ አሌግዛንደር በጦርነት አሸንፏቸው ደመሰሳቸው።

ራሱ ባቢሎን ነው፤ እርሱም ቀደም ብሎ በሜዶናውያን እና በፋርሶች አማካኝነት ተገልብጧል።

ዮሐንስ 13፡10 ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።

የአረማዊው የሮማ መንግስት የብረት እግሮች በክርስቲያን ቤተክርስቲያን ላይ የመጨረሻዎቹን 10 ስደቶች ያስነሳባታል። አረማዊው የሮማ መንግስት የመጀመሪያው ጨካኝ የቤተክርስቲያን ጠላት ነበረ፤ ከዚያ ወዲያ ግን እነዚያ አጋንንት ስልታቸውን በመቀየር በንጉስ ኮንስታንቲን ዘመን ወደ ሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልከው ገቡ። ይህም የሆነው በ325 ዓ.ም በተደረገው የኒቅያ ጉባኤ ነው።

 

 

የወደፊቷ ቤተክርስቲያን ብቻ ነበረች በወንጌሉ ውስት እግሯን መታጠብ የቀራት።

ይሁዳ ግን ኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥ ሐጥያተኛ ነበረ። ስለዚህ እግሩን በውሃ ቢታጠብም እንኳ አልነጻም ነበረ። ስለዚህ በውሃ መታጠቡ ምሳሌያዊ ድርጊት ነበረ።

እውነተኛው መታጠብ የሰዎች ልብ ከአለማመን ቆሻሻ በእግዚአብሔር ታጥቦ በእምነት ሲነጻ ነው።

ኢየሱስ በተገኘበት በመጨረሻው እራት ላይ ለእኛ ሲሞትልን የሚቆረሰውን ስጋውን በምሳሌ ለማሳየት የተቆረሰ እንጀራ ተጠቀመ። አጥንቶቹ ግን አንዳችም አልተሰበሩም። ስጋው በ39 የጂራፍ ግርፋቶች በመገረፍ ተቆረሰ።

ወይኑ በኢየሱስ ደም ውስጥ ያለውን ሕይወት የሚወክል ነው። እርሱም በመገለጥ መነቃቃት ለእኛ የማይገባንን መዳን ይሰጠን ዘንድ ወደ ልባችን የሚገባው ታላቁ መንፈስ ቅዱስ ነው።

የእግር መታጠብ ሥነስርዓት የተደረገበት ውሃ ስለ ቅድስና እና በአሕዛብ መካከል ስለሚሰረጨው የዘላለም ሕይወት ዘር የሚያመለክት ነው። አሕዛብም በሙሉ በሸክላ ሰሪው እጅ ትክክለኛ ቅርጽ የሚያገኙ የሸክላ እቃዎች ናቸው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

በጥምቀት ውስጥ አሕዛብ የኢየሱስን ስም ሲቀበሉ በውሃ ይረሰርሳሉ።

ሙሽራይቱ የባሏን የኢየሱስን ስም የምትቀበልበት መንገድ ይህ ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመን ሲጠናቀቅ ይህ የውሃ ጥምቀት “የሸክላውን አፈር” እስከ አስሩ የእግር ጣቶች ድረስ ያረሰርሰዋል።

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በጥምቀት ውሃ የረሰረሱትም ከተጠመቁ በኋላ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ይቀበላሉ።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በሚነግረን እውነት ሁሉ መመራት ከአለማመን እና ከስሕተት እድፈት በቃሉ ውሃ አማካኝነት የምንታጠብበት መንገድ ነው።

 

 

ሰባተኛው ምሳሌ ሰባተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።

የአላዛር ትንሳኤ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ እና የእኛ ራስ ወዳድ ፈቃድ።

ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚጠናቀቀው ከሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን ሲነሱ ነው።

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ኢየሱስን ይጠሉት ነበረ። የሐይማት መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል አይቀበሉትም ምክምያቱም ከእምነታቸው ጋር ይቃረናል።

በጣም ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ሲተቹ፣ ሲነቅፉ እና ሲያጣጥሉ መስማት በጣም አስደንጋጭ ነገር ነው። ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ ሊያስወግዱት ይፈልጋሉ። ነገር ግን በዓለም ሁሉ እስከ ዛሬ በሽያጭ አንደኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ዮሐንስ 10፡39 እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ [ኢየሱስ] ከእጃቸውም ወጣ።

40 ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ።

ዮሐንስ ማጥመቅ የጀመረው ከቤተራባ ከተማ አጠገብ ነው።

ማቴዎስ 3፡1 በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ … በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

ዮሐንስ 1፡28 ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ።

ቤተራባ ማለት የመሻገሪያ ቦታ ማለት ነው።

 

 

ይህ ቦታ ኢያሱ እና አይሁዶች ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲገቡ ዮርዳኖስን የተሻገሩበት ቦታ ነው።

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ውስጥ ከሚጠሉት እና ሊገድሉት ከሚፈልጉ አይሁዶች ራቅ ማለት በፈለገ ጊዜ እዚህ ቦታ ነው ዮርዳኖስን የተሻገረው።

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ አላዛር ወደ ሞተበት ቦታ ወደ ቢታኒያ ለመሄድ በድጋሚ ዮርዳኖስን መሻገር ነበረበት።

የአላዛር ትንሳኤ ኢየሱስ ሞታንን በማስነሳት ኃይሉ ላይ እንዲያተኩር አደረገው።

ወደ አላዛር እየሄዱ ሳለ ሙታንን ማስነሳት እንደሚችል ደቀመዛሙርቱን ሊያሳምናቸው ሞከረ። እነርሱ ግን አልገባቸውም።

ደቀመዛሙርቱ የሚያስቡት ከሞተ በኋላ ምንም ማድረግ እንደማይቻል ነው።

ልክ እንደዚሁ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ የሞቱ ቅዱሳን የትንሳኤያቸው ጊዜ ሲደርስ እኛም ሁሉ ነገር ከቁጥጥር ውጭ የሆነ መስሎ ይሰማናል። እግዚአብሔር የሚሰራበትን መንገድ ለማወቅ የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ ማየት ያስፈልገናል።

ለምሳሌ ሰዎች ሁሉ ዶናልድ ትራምፕ መጥፎ ሰው እንደሆነ እና የ2016ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የማያሸንፍ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን እርሱ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እውቅና እሰጣለው ብሎ ቃል በመግባቱ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት ፈጽሟል። ስለዚህ ዋነኛው ጉዳይ ይህ ነው። የመጀመሪያውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ፍልሰት የመራው ሙሴ ነፍሰ ገዳይ ነበረ።

እግዚአብሔር በማን በኩል ነው የሚሰራው ብለን ከመጨነቅ ይልቅ እግዚአብሔር ምን እየሰራ እንዳለ ለማቅ ነው መፈለግ ያለብን።

ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

ነገር ግን ኢየሱስ ከሙታን ሲነሳ ደቀመዛሙርቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያንም የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ መቀበል እንደምትችል ተረዱ። ይህም እውነተኛው መኖሪያ ምድር የትኛው እንደሆነ እንዲያውቁ ረድቷቸዋል፤ እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው።

ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ድል ለእኛ ለመስጠት የሞትን ወንዝ መሻገር ግድ ሆኖበታል። ከዚያም የሞትን ወንዝ ድል መንሳቱን ለማሳየት ከሙታን ተነሳ፤ ደግሞም ድሉ የእርሱ መሆኑን ሊነግረን ያንኑ ወንዝ በድጋሚ ተሻግሮ መጣ።

የእኛ ተስፋ መንፈስ ቅዱስ ነው። የእኛ የተስፋ ምድር መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

የኢየሱስ ትንሳኤ ድል የእኛ መሆኑን የሚያሳይ በክብር የደመቀ ምልክት ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ከመሞቱ እና ከሙታን ከመነሳቱ በፊት በአላዛር ትንሳኤ ላይ ትኩረት አድርጓል።

ዮሐንስ 11፡1 ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር።

ቢታንያ ማለት የመከራ ቤት ነው።

አላዛር ደግሞ “እግዚአብሔር የሚረዳው ሰው” ማለት ነው።

ከዚህ ውስጥ የምናገኘው ትምሕርት በመከራ ውስጥ ስንሆን እግዚአብሔር እንደሚረዳን ነው፤ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ቸል ያለን ቢመስልም ይረዳናል።

ዮሐንስ 11፡2 ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

ማርታ ተግታ ትሰራለች፤ ተስፋዋ እና ትምክህቷም በመልካም ሥራዋ ላይ ነው፤ መልካም ሥራዋም ለእርሷ ጥሩ ስም አስገኝቶላታል።

ማርያም ግን የኢየሱስን ቃል ለመስማት ነው ትኩረት የሰጠችው። እርሷ ከእሕቷ ይልቅ መንፈሳዊ ነበረች። ማርያም ስለ ኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ ባታውቅም፤ ናቡከደነጾር በሕልሙ ያየው የአሕዛብ ምስል እግሮች 7ቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት እንደሚወክሉ ባይገለጥላትም እግሮቹ ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው አውቃለች።

ስለዚህ ኢየሱስ በሕይወት ሳለ እግሮቹን በሽቶ አበሰቻቸው፤ ይህም እርሱ በሞት ላይ ድል ተጎናጽፎ እንደሚነሳ የሚያመለክት ምሳሌያዊ ድርጊት ነው። ሌሎቹ ሴቶች ኋላ በኢየሱስ አስከሬን ላይ ሽቶ ሊቀቡ ሄዱ፤ ይህም እነርሱ እርሱን ሞት ያሸነፈው እንደመሰላቸው ያመለክታል።

ማርያም በረጅም ጸጉሯ የኢየሱስን እግር አበሰች። ረጅም ጸጉር የሴት ክብር ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡15 ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።

ረጅም ጸጉር ሴት ራስ ለሆናት ለባሏ መገዛቷን ያመለክታል።

ማርያም ሴት እንደመሆኗ እንዲሁም ከኢየሱስ እግር ስር በመቀመጧ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለቃሉ የምትገዛ ቤተክርስቲያንን ትወክላለች።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡15 ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።

 

 

ለኢየሱስ የድረስልን ጥሪ ተላከ። ኢየሱስ ግን ጥሪው ከደረሰው በኋላ ተጨማሪ ሁለት ቀን በቤተራባ ምድረበዳ ውስጥ ቆየ።

ዮሐንስ 11፡6 እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤

ይህን ያህል መዘግየቱ አላዛር በእርግጥ እንደሚሞት ያሳያል። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ትዕግስታችንን ይፈትናል። ደግሞም ጸሎታችንን እኛ ልክ አይደለም ብለን በምናስበው መንገድ ይመልስልናል። እኛም ጠንቃቃ መሆንና ይበልጡን ጊዜ የራሳችንን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈለግ ማሳለፍ አለብን። የራሳችን ፈቃድ ብዙውን ጊዜ የራሳችንን ጥቅም በማሳደድ ላይ የተመሰረተ ነው።

ማርያም እና ማርታ አላዛር እንዲሞት አልፈለጉም። ይህ የራስ ፈቃድ ነው።

ኢየሱስ ሙታንን የማስነሳት ኃይል እንዳለው ለዓለም ማሳየት ፈለገ። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

ዮሐንስ 11፡7 ከዚህም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ፦ ወደ ይሁዳ ደግሞ እንሂድ አላቸው።

8 ደቀ መዛሙርቱ፦ መምህር ሆይ፥ አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፥ ደግሞም ወደዚያ ትሄዳለህን? አሉት።

ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ ይበልጥ የከፋ አደጋ አለ፤ እርሱም ኢየሩሳሌም ውስጥ ያሉ አይሁዶች ሊገድሉት መፈለጋቸው ነው።

ይህም በመጨረሻው የሙታን ትንሳኤ ጊዜ እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ አደጋ እንዳለው የሚናገር ትንቢት ነው።

ዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያኖች እና የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ እውነተኛዋን ሙሽራ ይቃወሙዋታል፤ ሊያፍኗትም ይፈልጋሉ።

ዮሐንስ 11፡9 ኢየሱስም መልሶ፦ ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤

“ቀን” ማለት ልንመላለስበት የሚገባን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ስንሆን በመጨረሻው በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያሉ አደጋዎችን ልናልፋቸው እንችላለን።

ይህ ክስተት የሚያመለክተው ወደ ሙታን ትንሳኤ ጊዜ እየቀረብን ስንሄድ ይህ ዓለም ለእውነተኛ አማኞች ይበልጥ አደገኛ እየሆነ እንደሚሄድ ነው።

ዮሐንስ 11፡10 በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው።

የተጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የተገለጡበትን የዊልያም ብራንሐም መገለጦች ቸል ብለን በመተው ያለ ምንም ችግር መኖር የምንችል ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን ወዲያ በሌሊቱ ጨለማ የተመሰለው ታላቁ መከራ ይመጣል። ከዚያ በኋላ በሥፍራ ሁሉ ሞት ይሆናል።

ዮሐንስ 11፡11 ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ፦ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው።

የአስሩ ቆነጃጅት ምሳሌ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ የኖሩትን የዳኑ ሰዎችና ቤተክርስቲያኖች ይወክላል። ነገር ግን ሁላቸውም እንቅልፍ ተኝተው ነበር፤ በዘይት ወይም በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉትም እንኳ ሳይቀሩ እንቅልፍ ስለተኙ የሚቀሰቅሳቸው ያስፈልጋቸው ነበር።

የኢየሱስ ኃይል እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ሙታንን ማስነሳት ለእርሱ እንቅልፍ የተኛ ሰውን ከመቀስቀስ ብዙም ልዩነት የለውም።

ዮሐንስ 11፡14 እንግዲህ ያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጥ፦ አልዓዛር ሞተ፤

ዮሐንስ 11፡15 እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ አላቸው።

ኢየሱስ አላዛርን በመጠቀም በሞት ላይ ሥልጣን እንዳለው ሊያሳይ አስቧል።

ዮሐንስ 11፡16 ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት፦ ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ።

የኢየሱስን ትንሳኤ ስለመጠራጠሩ የምንነቅፈው ቶማስ በዚህ ጊዜ ግን ከደቀመዛሙርት መካከል ደፋር ጀግና መሆኑን አሳይቷል። በፍጹም ፈሪ አልነበረም።

በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ትልቅ ተቃውሞ ስለሚበዛ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ሳይፈሩ ስለ እውነት የሚቆሙትና ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ተቃውሞ ጸንተው የሚጋፈጡት።

በሰው ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ወይም መወደድ የሚፈልጉ ሰዎች ይሰናከላሉ።

ዮሐንስ 11፡17 ኢየሱስም በመጣ ጊዜ በመቃብር እስከ አሁን አራት ቀን ሆኖት አገኘው።

አላዛር ሞቶ አራት ቀን እስኪሞላው ድረስ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ የሚመለስበትን ቀን አዘገየ።

ሶስት ቀን ካለፈ በኋላ አስከሬን መበስበስ ይጀምራል።

መዝሙር 16፡10 ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።

አላዛር በቅድስና ነበር የኖረው። ኢየሱስ አላዛርን በሶስት ቀን ውስጥ ቢያስነሳው ኖሮ ሕዝቡ አላዛር የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት ፈጸመ ይሉ ነበር። ነገር ግን አላዛር የአይሁድን ሕግ ስለጠበቀ በሞተ ጊዜ ወደ ሲኦል አይወርድም።

አራተኛው ቀን እምነት የሚታደስበትን አራት ደረጃዎች ያመለክታል።

ማርቲን ሉተር በ5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ጀርመኒ ውስጥ መዳን በእምነት እንጂ በሥራ አይደለም የሚለውን ተሃድሶ ይዞ መጣ።

ጆን ዌስሊ በ6ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እንግሊዝ ውስጥ ቅድስናን እና የወንጌል ስብከት ተሃድሶ ይዞ መጣ። ይህም ተሃድሶ ለወንጌል ስርጭት ዘመን መሰረት ነበረ።

በ1904 የተነሳው የዌልሽ መነቃቃት እና በ1906 አዙዛ እስትሪት በሚባል አካባቢ ሎሳንጀለስ ውስጥ የተጀመረው የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይል ተሃድሶ በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጀመሪያ ላይ እንዲመጣ አድርገዋል።

በ1947 እና በ1965 መካከል አሜሪካ ውስጥ ዊልያም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥሮች በመግለጥና መልእክቶቹን በድምጽ በመቅረጽ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያመነችባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ተሃድሶ እንዲመጣ አድርጓል። ስዚህ የ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መንፈሳዊ ልጆች ወደ 1ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች እምነት ይመለሳሉ።

 

 

እኛ አሁን በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መልእክተኛ ድምጹ በቴፕ በተቀረጸበት ዘመን ውስጥ ነን፤ እርሱ ያስተማረውን ትምሕርት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት እየፈተሽን ስናጠና የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት እንችላለን።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ይህም የመጀመሪያዋ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ወዳመነችበት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተሃድሶ የመመለስ መጨረሻ ነው።

 

 

ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ቀጥሎ የምታልፍበት ክስተት ከሰባቱም ቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው የነበሩ ቅዱሳን ትንሳኤ ነው።

ከዚያ አንጻር ከአላዛር ትንሳኤ በፊት (የሞቱ ጻድቃን) ቤተክርስቲያን እንደ ሁለቱ ሴቶች ናት፤ ማርያም (ቃሉ ላይ ትኩረት ያደረገች መንፈሳዊ ቤተክርስቲያን) እና ማርታ (ሥራ ላይ ያተኮረች ስጋዊ ቤተክርስቲያን)።

ዮሐንስ 11፡18 ቢታንያም አሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩሳሌም ቅርብ ነበረች።

ስምንት ምዕራፍ አንድ ማይል ነው። ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ሁለት ማይል ነው ርቀቷ።

ዮሐንስ 11፡19 ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር።

ይህም ከትንሳኤ በፊት ሕዝብ ሁሉ መጽናናትን የሚመኙበት የነውጥ ጊዜ እንደሚሆነው ነው የሚያመለክተው።

ዮሐንስ 11፡20 ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር።

ሁልጊዜ በሥራ ለመትጋት የምቀናው ማርታ ኢየሱስን ለማግኘት እየሮጠች ወጣች።

ይህ ለእኛ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። ጌታን ለማግኘት ያሳየችው ቅናት ታላቅ ነው፤ ነገር ግን እውቀት የጎደላት መሆንዋ ለእርሷ ሐዘን ነው የሚያመጣባት።

ደግሞም ትዕግስት አላሳየችም። በኢየሱስ ጥሪ ሳይሆን በራሷ ፈቃድ ነበረ የምንትንቀሳቀሰው።

ሁሉጊዜ መንፈሳዊ የሆነችዋ ማርያም ኢየሱስን በራሷ ልታገኝ አልሮጠችም።

ይህንን ምን ያህል ቅናት እንዳላቸው ለማሳየት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በራሳቸው ችሎታ የሚፈቱ ሰዎች ጋር ማነጻጸር እንችላለን።

ማርያም ግን በጸጥታ ተቀምጣ ጌታ የሚናገራትን ለመስማት ስትጠባበቅ ነበረ።

ዮሐንስ 11፡21 ማርታም ኢየሱስን፡- ጌታ ሆይ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር አለችው።

ኢየሱስን ለማግኘት ቅናት ቢኖራትም እንኳ ሳታውቀው ግን ባለማስተዋል ኢየሱስን ትነቅፈዋለች። (ሰነፎቹ ቆነጃጅት እንቅልፋቸውን በመተኛታቸው ምን እየተደረገ እንዳለ እንኳ አያውቁም)

ኢየሱስ ቃሉ ነው። ስለመጽሐፍ ቅዱስ የምንናገረው ሁሉ ስለ ኢየሱስ የምንናገረው ነው።

ዛሬ ክርስቲያኖች ጌታ ኢየሱስን እንወደዋለን ይላሉ፤ እርሱን ለማገልገልም ቅናት እንዳላቸው ይናገራሉ። ነገር ግን ስለ እርሱ ያላቸው ትክክለኛው አመለካከታቸው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ባላቸው አመለካከት ውስጥ ነው የሚንጸባረቀው። የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ስሕተቶች አሉበት፤ እርስ በርሱ ይጋጫል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን በመንቀፋቸው ኢየሱስን እየነቀፉ ነው።

ዮሐንስ 11፡22 አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው።

ልክ እንደ ዛሬዋ ቤተክርስቲያን ማርታ ኢየሱስን ትነቅፈዋለች ደግሞም ታምንበታለች።

የዛሬዋ ቤተክርስቲያን በኢየሱስ ታምናለች ግን የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ትነቅፋለች። ኢየሱስ ግን ቃሉ ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን በአንካሳ እግር እየተመላለሰች ናት። ኢየሱስ ፍጹም ነው ብለው ያምኑበታል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን እናምናለን እያሉ ነገር ግን በትክክል አልተተረጎመም ይላሉ። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንከኖችና ስሕተቶች አሉበት ይላሉ።

ዮሐንስ 11፡23 ኢየሱስም፦ ወንድምሽ ይነሣል አላት።

24 ማርታም፦ በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ አለችው።

ማርታ ግራ የምታጋባ ሴት ናት። በመጨረሻው ቀን አላዛር ሰውነቱ አልቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ አፈር ከተለወጠ በኋላ እግዚአብሔር ከሙታን ሊያስነሳው ይችላል ብላ ታምናለች። ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ሰውነቱ መበስበስ በጀመረበት ከሞት ሊነሳይችላል ብላ ማመን ያቅታታል።

ዮሐንስ 11፡25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤

26 ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።

ኢየሱስ በእርሱ ማመን ሙታንን እንደሚያስነሳ በግልጽ ተናግሯል፤ ምክንያቱም ትንሳኤ ኢየሱስ እራሱ ነው።

27 እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።

ማርታ በትንሳኤ አምናለው ብላ አትናገርም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ብቻ ነው የምትመሰክረው።

ዛሬም ሰነፎቹ ቆነጃጅት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሥላሴ ሁለተኛው አካል ነው ይላሉ።

ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ያላቸው እውቀት የተሳሳተ ነው። ደግሞ ስለ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምንም አያውቁም። ስለ ትንቢት ያላቸው እውቀት ስሕተት የሞላበት ስለሆነ የሙታን ትንሳኤ ጊዜ ሲደርስ እንኳ አያውቁም።

የትንሳኤው ጊዜ እውነተኛ የእምነት ፈተና ነው የሚሆነው።

ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከዚህ ዘመን ክስተት ጋር ማገጣጠም ይችሉ እንደሆን ይታያል።

ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ብለው ተንብየው የነበሩ የሜሴጅ ሰባኪዎች ምን ያህል ከእግዚአብሔር ሃሳብ ወጥተው ርቀው እንደሄዱ አሳይተዋል።

ማርታ በኢየሱስ ታምናለች ግን መበስበስ የጀመረ አስከሬን ከሞት መነሳት ይችል እንደሆን ለማመን የሚበቃ እርግጠኝነት የላትም።

ስለዚህ ልክ ከትንሳኤ በፊት ነገሮች ሁሉ ከምንጠብቃቸው በጣም የተለዩ ይሆናሉ፤ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ምን እየሰራ እንደሆነ መከታተል ያቅተናል። ስለዚህ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሆነው እየተበላሹ ያሉ ይመስለናል።

ከዚያም በጣም ጠንቃቃ ካልሆንን የተሳሳተ ነገር አምነን እንቀመጣለን።

ልክ ሒላሪ የ2016ቱን ምርጫ ታሸንፋለች ብለው እንዳሉት።

ዮሐንስ 11፡28 ይህንም ብላ ሄደች እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ፦ መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል አለቻት።

አሁን እውነቱን ተናገረች።

በትንሳኤ ዘመን እውነት እጅግ በጣም ስለምትሰደብና ስሟ ስለሚጠፋ እውነተኛ አማኞች እርስ በራሳቸው መነጋገር የሚችሉት በሚስጥር ብቻ ይሆናል።

በ2016 ትራምፕን የሚሰድቡና የሚያወግዙ ሰዎች እጅግ ከመብዛታቸው የተነሳ ትራምፕ በምርጫው ያሸንፋል ለማለት ሰዎች በጣም ይፈሩ ነበር።

በትምሕርት ቤቶች ውስጥ ጸሎት እና መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ሲከለከል እውነትን በግልጥ መናገር የማይቻልበት ጊዜ እንዳለ አይተናል።

በተጨማሪ ደግሞ ክርስቲያኖችን በሚያሳድዱና በሚገድሉ በሙስሊም ሃገሮች ውስጥ ክርስቲያኖች እንደሚታፈኑም እናውቃለን።

አንድ አውስትራሊያዊ ራግቢ ተጫዋች በአደባባይ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሶ ስለተናገረ ሃገሩን ወክሎ መጫወት ተከልክሏል።

ዮሐንስ 11፡29 እርስዋም በሰማች ጊዜ ፈጥና ተነሣች ወደ እርሱም መጣች፤

ዮሐንስ 11፡32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር አለችው።

መንፈሳዊ የሆኑት አማኞች ምሳሌ የሆነችው መንፈሳዊ ሴት ማርያም እርሷም ጭምር ኢየሱስን ነቅፋዋለች።

ዛሬ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን የማይነቅፍ ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት እና ችግር አለበት ብለው ለማሳመን ብዙ ምክንያቶች ያቀርባሉ። ከፍተኛ ትምሕርት መማራቸው አለማመናቸውን ብቻ ነው ያጠናከረው።

የሜሴጅ ሰባኪዎች በሰው ንግግር ጥቅሶች ትርጓሜ ላይ የተመሰረቱ አስተምሕሮዎችን ያዘጋጃሉ፤ ትምሕርቶቻቸው ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫሉ። እነርሱ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ትተው የሰው ንግግር ጥቅስ ትርጓሜዎችን ያምናሉ።

በዚህ መንገድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ አስተምሕሮዎችን ይፈጥራሉ። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶቻቸውን “ትክክለኛ” ለማለት ብለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃልት ይጠቀማሉ።

መንፈሳዊ የሆኑት ልባሞቹ ቆነጃጅት እንኳ (ማርያም የእነርሱ ምሳሌ ናት) በሌሎች ሰዎች አለማመን እና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አለመከተል በጣም ስለተከበቡ እነርሱም ጭምር ቃሉን ኢየሱስን ይጠራጠሩታል።

መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ መከተል ለብዙዎች አስቸጋሪ ነው።

ዮሐንስ 11፡33 ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤

ሰዎች ስሜታቸው ተቆጣጥሮአቸዋል። ሐዘናቸው ጎልቷል። ሞት ለመሸከም በጣም ከባድ ሆኗል።

የተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ በሐዘን ተውጧል። ስለዚህ ማርያምም በሐዘን ተቀላቀለቻቸው።

ኢየሱስ የሞተውን ሰው ሊያስነሳው እየመጣ ነበር፤ እነርሱ ግን ከእግዚአብሔር ሃሳብ በመራቃቸው የተነሳ ከሐዘናቸው በቀር ሌላ ምንም ማሰብ አይችሉም።

በትንንሽ ዓለማቸው በራሳቸው ፈቃድ ውስጥ ተውጠው ታላቁን የእግዚአብሔርን እቅድ ማለትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማየት ተስኗቸዋል።

ልክ እንደዚሁ ሙሽራይቱ በመጨረሻው ዘመን በራሷ ሐዘን ተውጣ ለራሷ ማልቀስ ከማብዛቷ የተነሳ በጣም ካልተጠነቀቅን በቀር እግዚአብሔር ምን እያደረገ እንዳለ እንኳ ላናውቅ እንችላለን።

ለዚህ ነው ሙሽራዋ የማንቂያ ጥሪ የሚያስፈልጋት። ማንኛውም በራሳችን ፈቃድ የተዋጥንበትን ባሉን የሚያስተነፍስ ነገር ሁሉ ይጠቅመናል።

ዮሐንስ 11፡34 ወዴት አኖራችሁት? አለም። እነርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ መጥተህ እይ አሉት።

“መጥተህ እይ” የሚለው አነጋገር ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እየመሩ ሳለ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉት አራቱ እንስሳት እያንዳንዳቸው የተናገሩት ቃል ነው።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

የአራተኛው እንስሳ “ድምጽ” ከወንድም ብራንሐም በድምጽ የተቀረጹ መልእክቶች ውስጥ ነው የሚወጣው።

እነዚህ መገለጦች እያንዳንዳቸው ቤተክርስቲያን እንዴት በክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንደተታለለች የሚገልጡ አስደንጋጭ መልእክቶች ናቸው። ሆኖም ግን በእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር እነዚህ በዙፋኑ ዙርያ ያሉ እንስሳት በሚገልጡት የእውነት መገለጥ የሚመሩ አማኞች ነበሩት።

“መጥተህ እይ” ማለት እግዚአብሔር እና ሰይጣን በ2,000 ዓመቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንዴት ይዋጉ እንደነበረ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ይገለጥልናል ማለት ነው።

ነገር ግን መንፈሳዊ የሆነችዋ ማርያምም ሆነች የአይሁድ ሕዝብ መጥተህ እይ የሚለውን አነጋገር የሚጠቀሙት አስደናቂ መገለጥ ማግኘታቸውን ለማሳየት ሳይሆን በስብሶ ወደሚሸት እሬሳ ለመጠቆም ነው።

ዮሐንስ 11፡35 ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።

ኢየሱስም መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቃቸው በጣም አዘነ። እምነታቸውን እርሱ በተናገረው ቃል ላይ ከማድረግ ይልቅ በሁኔታዎች ስለመጨነቃቸው በጣም አዘነ። ዛሬ የኢየሱስ ቃል በእጃችን የያዝነው መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

ዮሐንስ 11፡36 ስለዚህ አይሁድ፦ እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ አሉ።

እነዚህ አይሁዶች ምንም ነገር አልገባቸውም። አይሁዶች መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ካለማወቃቸው የተነሳ ኢየሱስ ለምን እንዳለቀሰ ለማስረዳት ሲሞክሩ ትልቅ ሳይኮሎጂካዊ ስሕተት ሰርተዋል። በእርሱ የተገለጠውን ስሜት ሊተነትኑ ባረደጉት ሙከራ እጅግ ተሳስተዋል።

ዮሐንስ 11፡37 ከእነርሱ ግን አንዳንዶቹ፦ ይህ የዕውሩን ዓይኖች የከፈተ ይህን ደግሞ እንዳይሞት ያደርግ ዘንድ ባልቻለም ነበርን? አሉ።

አሁንም ኢየሱስን ሲተቹ እናገኛቸዋለን።

የእግዚአብሔር እቅድ ከሰዎች ሃሳብ ጋር አይገጣጠምም።

ስለዚህ እኛ እግዚአብሔር የተሳሳተ ይመስለናል።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ክርስቲያኖች ዛሬ በጣም ከማወቃቸው የተነሳ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶች እና እንከኖችን ማግኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል።

ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነ ያምናሉ።

እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ከሆነ በዘመናችን ፍጹም የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማዘጋጀት እንዴት ይሳነዋል ብለው በልባቸው ይጠይቃሉ። እነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አገኘን የሚሉዋቸውን ስሕተቶች እግዚአብሔር አላወቃቸውምን?

ዮሐንስ 11፡38 ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እርሱም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

ኢየሱስን የሚቃወመው ዋነኛው ጠላጥ የእኛ አለማመን ነው።

ለኢየሱስ ትልቁ የሐዘን ምክንያት የሰዎች አለማመን ነው።

 

ማቴዎስ 13፡58 በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።

“መጥተህ እይ” የሚለው ቃል ዓይናቸውን አላበራውም። ወደ መቃብር መራቸው እንጂ።

የሞተ ዲኖሚኔሽናዊ የቤተክርስቲያን ሥርዓት። መሪዎቻቸው ኮሌጆች ውስጥ ሰልጥነው ይመጣሉ፤ ግን የሚሰለጥኑባቸው ኮሌጆች መንፈሳዊ መቃብሮች ናቸው።

ሰው ሰራሽ የሆነ ትልቅ ድንጋይ ሰዎች በመንፈሳዊ መቃብር ውስጥ ተዘግቶባቸው እንዲቀሩ ያደርጋል።

የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ለምሳ የሚከተሉትን ዓይነት ስሕተቶች ማመን አለባችሁ፡-

ሥላሴ፣

የሰባቱ ዓመታ መከራ፣ እና

ፓሰተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው።

የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በተጨማሪ ሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን አሰምተዋል እንዲሁም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክም ወደ ምድር ከወረደ ቆይቷል ይላሉ።

በጣም የሚገርመው ነገር ከዚህ በፊት ጌታ በ1977 ተመልሶ ይመጣል ብለው በማመን መናገራቸውን መርሳታቸው ነው።

ብዙዎች ጌታ በ1970 ይመለሳል ብለው ነበር።

ሌሎች ደግሞ መልአኩ ወይም ጌታ በ1963 መጥቷል ብለው ነበር።

በጣም የሚያሳዝነው ሌላው ነገር ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በስተሰሜን ሰማዩ ላይ ታይቶ ፎቶግራፍ የተነሳው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የተፈጠረው ማርች 8 ቀን 1963 ሰባቱ መላእከት ከወንድም ብራንሐም ጋር ተነጋግረው ወደ ሰማይ ሲመለሱ ነው ይላሉ፤ ብራንሐም ግን ከፍላግስታፍ ከተማ 200 ማይል ርቃ በምትገኘው ሳንሴት ፒክ ከተማ ውስጥ ነበረ። በሁለቱ ክስተቶች መካከል የ8 ቀናት እና የ200 ማይል ርቀት ነበረ። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ግን ለራሳቸው የሚጥማቸውን ታሪክ እውነት እንዲያፈርስባቸው አይፈልጉም።

ዮሐንስ 11፡39 ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው።

አንድ ተስፋ ብቻ ነው ያለው። ይህም ራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ፓስተሮች የሰሩትን የአለማመን ድንጋይ ማስወገድ ነው። እነዚህ የተሳሳቱ እምነቶች በሰዎች አእምሮ ላይ እንደ ድንጋይ ተጭነው ከቆዩ ሰዎች በመንፈሳዊ መቃብሮቻቸው ውስጥ ተዘግቶባቸው ይቀራሉ ማለት ነው። ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ይል ቅ ቤተክርስቲያናቸውን ይመርጣሉ። ፓስተሩን ከኢየሱስ በላይ ያከብሩታል።

ማርታ ዛሬ ብትኖር “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶቻቸው ይሸታሉ” ትል ነበር።

ይህ የሰዎች ስሕተት መጥፎ ሽታ ሙታን ሲነሱ እና ቤተክርስቲያን ተመላላሾችም ይህ ትንሳኤ ሲያመልጣቸው ጎልቶ በመውጣት ይሸታል። ከሙታን የተነሱ ሰዎች የሚፈልጉት በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን እውነቶች ብቻ ነው።

የሰዎችን አመለካከት እና አተረጓጎም ፈጽመው አይፈልጉም።

ኢየሱስ ስለ ትንሳኤው ጊዜ የሚያስፈራ ምሳሌ ተናገረ።

ሉቃስ 16፡31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ማመን ካልቻልን ከሙታን የተነሱ ሰዎች እንኳ የሚነግሩንን ማመን አንችልም።

ይህም የሚያሳየው የቤተክርስቲያን መሪዎች ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን አእምሮ ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ስሕተቶች እንደሚሞሉት ነው።

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ የሚወርደው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሞተው በባሕር ወይም በምድር ውስጥ የተቀበሩ ቅዱሳንን ከሙታን ለማስነሳት ነው።

ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሰባቱ ነጎድጓዶች ሚስጥር ሆኖ የቆየውን ቃላቸውን የሚያሰሙት።

በደመናው ትምሕርትና በነጎድጓዶች ትምሕርት የሳቱ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች የዚያን ጊዜ እውነትን ይቃወማሉ። ከዚያ በኋላ ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይገባሉ።

አዲስ ኪዳን ውስጥ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚል አንድም ቃል የለም። አንድም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፓስተሩ እረኛ ነው አይልም፤ ፓስተሩን ከበጎች በላይ ከፍ አያደርግም።

በገሃዱ ዓለም ውስጥ ግን እንደ ይሁዳ የመሰለ ፍየል በጎችን ወደ እርድ መርቶ ይወስዳቸዋል።

ዮሐንስ 11፡40 ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት።

“ብታምኚስ” የቤተክርስቲያን መሪ የተናገረውን እንደ ገደል ማሚቶ ከምትደጋግሚ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ቃል ብታምኚ።

ጥቅሶቹ ምንም ማለት እንደሆኑ ሳይገባቸው እነዚህን የሰው ንግግር ጥቅሶች እንደ ገደል ማሚቶ መድገም ቤተክርስቲያን ተመላላሾች እና የሜሴጅ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እንደማይችሉ ያሳያል።

ዮሐንስ 11፡41 ድንጋዩንም አነሡት፦ ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ፦ አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ።

ዮሐንስ 11፡42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።

ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

“በታላቅ ድምጽ ጮኸ”።

ይህም የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ያደረገው ነገር ነው።

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥

3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ባሕር እና ምድር ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የነበሩ ቅዱሳን ሞተው የተቀበሩባቸው ቦታዎች ናቸው።

ስለዚህ ይህ ብርቱ መልአክ “በታላቅ ድምጽ ሲጮህ” የኢየሱስ ሙሽራ አካል የሆኑት የቤተክርስቲያን ዘመን ቅዱሳን ከሙታን የሚነሱበት ጊዜ ይመጣል።

ይህ የአንበሳው የድል ጩኸት ነው፤ እርሱም የይሁዳ ነገድ አንበሳ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆኖ በመገለጥ በሰይጣን ላይ ኃይሉን በግልጽ ለማሳየት ሙታንን ያስነሳቸዋል።

እንደ መላእከት አለቃ ኢየሱስ ወደ ምድር መውረድ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ የጌታ ምጻት አይደለም።

ነገር ግን ሙታንን ማስነሳት ለጌታ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ዝግጅት ነው።

ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

በታላቅ ድምጽ ከጮኸ በኋላ፣ የሞቱ ቅዱሳን ከሙታን ከተነሱ በኋላ ከዚያ ቀጥሎ ሰባቱ ነጎድጓዶች የሚገለጡበት ሰዓት ነው የሚሆነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተጻፉም፤ ነገር ግን በሚፈጸሙበት ጊዜ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን ሊያገኙዋቸው በሚችሉበት መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰውረው ተቀምጠዋል።

እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ሰውነታችንን እንዴት ወደ ከበረ ሰውነት እነደምንለውጠው ያሳዩናል።

በአዲሱ አካላችን ውስጥ ከገባን በኋላ ወደ ሰማይ የምንነጠቅበት እምነት መቀበል እንችላለን። አሁን በለበስነው ስጋ ውስጥ ሳለን ጌታን ለመገናኘት በአየር ላይ መነጠቅ አንችልም።

ዮሐንስ 11፡44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም፦ ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

አላዛር በመቃብር ውስጥ ከተገነዘበት ጨርቅ ሙሉ በሙሉ መፈታት ነበረበት።

እኛም ከሰው ሰራሹ የቤተክርስቲያኖች ስሕተት እና በጭንቅላትችን ላይ ከጠመጠሙብን ከጠቀለሉብን ቁጥር ስፍር ከሌለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምሕርታቸው መላቀቅ አለብን።

ዮሐንስ 11፡45 ስለዚህ ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤

በኢየሱስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ።

ዮሐንስ 11፡46 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው።

ነገር ግን ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን መሪዎቻቸው ሮጠው ይመለሳሉ። ከፍ ላሉት መሪዎቻቸው ባሪያ ሆነዋል።

“አይዞህ ፓስተርሩ አለልህ”። እንደዚህ የሚል ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

ደግሞ በጣም ብዙ የሜሴጅ ትርጉሞች አሉ። እና ሙሉውን እውነት የያዘው ፓስተር የትኛው ነው?

ሙሉውን እውነት የያዘ ፓስተር አለ?

“ፓስተር” የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተጠቀሰው፤ ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስድስት ጊዜ ተወግዟል።

ዮሐንስ 11፡47 እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው፦ ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋልና።

የቤተክርስቲያን መሪዎች በአንድነት ይማከራሉ።

ዮሐንስ 11፡48 እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ።

ሰዎች በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ቢያምኑ የቤተክርስቲያን ራስ ወይም መሪ የመሆን ሥልጣናችንን እናጣለን። ምክንያቱም አዲስ ኪዳን ፓስተሩን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ አልሾመውም።

የምንወዳቸው “የሜሴጅ አስተምሕሮዎች” ውድቅ ይሆኑብናል ምክንያቱም እውነት መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አንችልም።

“ነገር ግን በሥልጣን መቆየታችን አስፈላጊ ነው” ይላሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች።

ሥልጣናቸውን እና ገንዘባቸውን ለማስጠበቅ እስከመጨረሻው መራራ የሆነ ውጊያ ይዋጋሉ።

የቤተክርስቲያን ገቢ እንዳይቋረጥባቸው ብለው አስራት ሁሉ የፓስቱ ድርሻ ነው በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ያስተምራሉ።

ፓስተሮች በሥልጣን ላይ ካልቆዩ የገንዘብ ምንጫቸው ይቋረጣል። ይህም ሃሳብ ያስፈራቸዋል። አስቀድመው ብዙ ሚሊዮን ብር ካጠራቀሙ ፓስተሮች በስተቀር አብዛኞቻቸውም ደግሞ ሌላ የገቢ ምንጭ የላቸውም።

“ፓስተር እና ልጆቹ” ንግዱን በቤተሰብ ውስጥ ማቆያ ጥሩ ዘዴ ነው።

ይህም አፍሪካ ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ሥልጣን ለማስረከብ እምቢ ከማለታቸው ጋር በጣም ይመሳሰላል። አፍሪካ ደግሞ ከአሕጉሮች ሁሉ ድሃ አሕጉር ናት። መሪዎቿ ግን ድሃ አይደሉም።

ዮሐንስ 11፡49 በዚያችም ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ፦ እናንተ ምንም አታውቁም፤

50 ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው።

51 ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፥ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፤

ዮሐንስ 11፡52 ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።

ዛሬ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ መርምረው ያገኙትን ብቻ ካመኑ ብዙዎች ያወግዟቸዋል።

ጥቅሶችን ወስደን ወንድም ብራንሐም ያስተማረው እውነት መሆኑን እስክናረጋግጥ ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መመርመርና መፈተሸ አለብን።

ዮሐንስ 11፡53 እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ።

ሰዎች እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንዳይመሰርቱ ከተፈለገ ቃሉ መጥፋት አለበት።

ነገር ግን የቤተክርስቲያን ፓስተሮች አብዛኛውን እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከር አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስን ቢቀበሉ ኖሮ የቤተክርስቲያናቸው ራስ ለመሆን ባልፈለጉ ነበር።

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማመን የሚፈልጉ ሰዎችን ማውገዝ እየጨመረ ይሄዳል።

ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች እና የሜሴጅ አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማያያዝ እምነታቸው ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ትተዋል።

ዮሐንስ 11፡54 ከዚያ ወዲያም ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ በምድረ በዳ አጠገብ ወዳለች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።

 

 

መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አምናለው የምትሉ ከሆኑ ብዙ ተቃውሞ ይነሳባችኋል። ሰዎች ከእናንተ ጋር መሆን አይፈልጉም።

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚል ሰው ከማሕበረሰቡ ይገለላል፤ ሁሉም ይገፋዋል።

ኤፍሬም ማለት ግን “ፍሬያማ” ማለት ነው።

ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማመን እውነተኛ በረከቱ ይህ ነው።

ማቴዎስ 13፡12 ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አምናለው ብላችሁ ጽኑ አቋም ብትይዙ እግዚአብሔር ሰባቱ ነጎድጓዶች ከትንሳኤው በኋላ ድምጻቸውን በሚያሰሙ ጊዜ ማስተዋል ትችሉ ዘንድ ብዙ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን እየገለጠላችሁ ዓይናችሁን ያበራዋል።

እምነታችሁን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገሮችን በማመን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት ማረጋገጥ የማትፈልጉ ከሆነ ግን እግዚአብሔር ዓይናችሁን ወይም እይታችሁን ብዥ ስለሚያደርገው መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት አቅማችሁ ይቀንሳል።

የዚያን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ የማትችሉትን በማመን ትደሰታላችሁ።

መለያየቱም የሚመጣው ወደፊት የሰባቱን ነጎድጓዶች ሚስጥር ማስተዋልም ሆነ መከተል ባቃታችሁ ጊዜ ነው። የዚያን ጊዜ ወደ ኋላ ትቀራላችሁ።

ማቴዎስ 24፡12 ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።

ዓመፃ ማለት እውነት መሆናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ አመሳክረን ማረጋገጥ የማንችላቸውን ነገሮች እያወቅን ግን ዚህ ዘመን ፈሪሳውያን ከሆኑት ከቤተክርስቲያን መሪዎች በኩል ጫና ስለበዛብን ብቻ ፈርተን ማመን ማለት ነው።

“ተመልከቱ ይህንን በሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ የተመሰረተ አስደናቂ አመለካከት” ይላሉ።

ሰዎች ሁሉ እነርሱ ምን ያህል አስተዋይ መሆናቸውን እንዲያውቁላቸው ይፈልጋሉ።

ነገር ግን እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አመሳክረው የያዙት አቋም ትክክለኛ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማስረጃነት ማሳየት አይችሉም።

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ከልባቸው ይጠፋል።

ማቴዎስ 24፡13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

እስከ መጨረሻ መጽናት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መቆም አለባችሁ።

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ስትጸኑ ብቻ ነው ከታላቁ መከራ ልትድኑ የምትችሉት።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23