የዮሐንስ ወንጌል እጅግ ብዙ ተዓምራት መደረጋቸውን ይናገራል ግን ሰባቱን ብቻ ይዘግባል። ለምን? ክፍል 1
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 21፡25 ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።
ኢየሱስ ብዙ በጣም ብዙ ተዓምራት አድርጓል፤ በእነዚህ ተዓምራትም ብዙ ሰዎችን ረድቷል፤ ነገር ግን ውጤታቸው ጊዜያዊ ነበረ። ሕዝቡ ተፈውሰዋል እርዳታ አግኝተዋል፤ ይህም መልካም ነው ነገር ግን የተፈወሱት ሰዎች በስተመጨረሻ ሞተዋል። ለዚህ ነው እነዚያን ሁሉ ታላላቅ ተዓምራት በሙሉ መመዝገብ ያላስፈለገው። በዘላለማዊ እቅድ ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ጥልቅ አልነበረም። በዚያ ዘመን የነበሩ ሰዎችን ብቻ ለጊዜው ረድተዋል፤ ሰዎቹም ከዚህ የተነሳ ዕድለኞች ነበሩ።
የዮሐንስ ወንጌል ግን ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር እንደሚበረው እንደ ታላቁ ንስር ነው የሚያቀርብልን።
ስለዚህ ዮሐንስ መርጦ የጻፋቸው ተዓምራት እግዚአብሔር ለሰዎች ልጆች ያለውን ጥልቅ የሆነ እቅድ የሚያንጸባርቁትን ብቻ ነው።
የአይሁዶችን የቤተመቅደስ አምልኮ ሥርዓት ተመልከቱ።
በዚህ የአይሁድ አምልኮ ውስጥ እግዚአብሔር ሰባት ቅርንጫፎች ባሉት መቅረዝ አማካኝነት ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት አስቀድሞ እያየ ነበረ።
ከዚያ በስተመጨረሻ እግዚአብሔር በታላቁ መከራ ወቅት ወደ 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ይመለስና ከመካከላቸው 144,000 አይሁዶችን ይጠራል። ከእያንዳንዱ ነገድ 12,000 ሰዎች ይጠራሉ። ይህንንም የሚያሳዩን 12ቱ ሕብስቶች ናቸው።
7ቱ የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ዘመናት እና የኢየሱስ በታላቁ መከራ ወቅት ወደ 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች መመለስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእሥራኤል ተሰውረው የነበሩ ታላላቅ ሚስጥራት ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሁለት ሚስጥራት በቤተመቅደሱ ውስጠ የሚደረገው አምልኮ አካል ነበሩ።
ስለዚህ እነዚህ ሁለት ታላላቅ ሚስጥራ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በብዙ ክፍሎች ተደጋግመው እንደምናገኛቸው እያሰብን እንፈልጋቸዋለን።
እስቲ በጥቂቱ ሰማይን እንመልከት።
ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
ዓይኖት ስለ ማስተዋል ይገልጻሉ። “በፊት እና በኋላ” ማለት የወደፊቱንም የድሮውንም ያውቃሉ ማለት ነው።
እነዚህ ጠባቂዎች ሥራቸው በሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት የተከፋፈለው 2,000 ዓመታት ውስጥ ለየቤተክርስቲያን ጥበቃ ማድረግ ነው።
ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት ጠባቂዎች አሉ።
አራቱን ወንጌሎች እንመልከት። እነዚህ አራት ወንጌሎች የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ዋነኛ ማዕከሎች ናቸው።
እያንዳንዱ ወንጌል ከአንድ ጠባቂ ጋር ይገጣጠማል።
እያንዳንዱ ጠባቂ መሰረታዊ የሆነውን የኢየሱስን ባህሪ ይገልጻል። ኢየሱስ በምድር ላይ ቤተክርስቲያንን ለማዳን የሚዋጋበት አራት የተለያዩ መንገዶች አሉት።
ማቴዎስ ኢየሱስን እንደ አንበሳ የአራዊት ንጉስ አድርጎ ይገልጻል። ኢየሱስ ታላቁ ንጉስ ነው።
ማርቆስ ኢየሱስን እንደ ጥጃ አድርጎ ያሳያል፤ እርሱም እስከ ሞት ድረስ የሚታዘዘው ባሪያ ነው። ሐጥያታችንን ተሸክሞ ወደ ሲኦል ጥልቅ ለመውረድና በሰይጣን ላይ አራግፎ ለመምጣት የታዘዘው ባሪያ።
ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ፍጹም ሰው ያሳየናል። እርሱም በሚሸት በረት ውስጥ በድህነት ነው የተወለደው። ለሞት የሚያበቃ አንዳች በደል ሳይገኝበት በግፍ ተገደለ፤ ሆኖም ግን ሃሳቡን ከራሱ መከራ ላይ አንስቶ አጠገቡ በሌላ መስቀል ላይ የተሰቀለ ሐጥያተኛን ማዳን ችሏል። ድሃ ሆኖ ነገር ግን ለሐጥያተኞች የሚራራ መሆኑና የሰዎችን ሕመም መረዳት መቻሉ እርሱን ፍጹም ሰው ያደርገዋል።
ዮሐንስ ኢየሱስን እንደሚበር ንስር ያየዋል፤ እርሱም በሰው አካል ውስጥ እንደ ታላቁ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ የሚኖረው እግዚአብሔር እራሱ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ምሳሌ ማለት ለመረዳት ቀላል እንዲሆን ተብሎ በምድራዊ ታሪክ ተጠቅልሎ የሚቀርብ መንፈሳዊ እውነት ነው።
ዮሐንስ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር መንፈስ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ስለዚህ ምንም ምሳሌ አይጠቀምም። ዮሐንስ መንፈሳዊ እውነቶችን በቀጥታ ነው የሚነግረን።
የአውሬው ምልክት፣ 666 ምንድነው?
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ፊታችሁን በምትመልሱ ጊዜ የአውሬውን ምልክት ትቀበላላችሁ።
ምልክቱ በግምባራችሁ ላይ ነው። ያም አእምሮዋችሁ ያለበት ቦታ ነው።
ቃሉን አልሰማ ያላችሁ ጊዜ ቃሉን እንዳታምኑ አእምሮዋችሁ ከቃሉ ተቃራኒ በሆኑ ሃሳቦች ይሞላል።
የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በአንዳንድ ነጥቦች ላይ ስሕተት አለው ብለህ ታስባለህ።
ይህም ኢየሱስ አንዳንድ ስሕተቶች አሉበት ማለትህ ነው ምክንያቱም ቃሉ ማለት ኢየሱስ እራሱ ነው።
እነዚህ አራት እንስሳት በራዕይ ምዕራፍ 6 በመጀመሪያዎቹ ሰባት ቁጥሮች አማካኝነት ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር ተያይዘዋል።
እያንዳንዱ ቁጥር አንድ የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
ቁጥር 1 እና 2 በሐዋርያት የተሰበከው እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል በሆነው በአንበሳው መንፈስ የተመሩትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
የነጎድጓድ ድምጽ የወደፊት ሚስጥርን ይወክላል።
1965-1127
ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየች
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
ከመሞቱ አንድ ወር አስቀድሞ ወንድም ብራንሐም ነጎድጓዱን፣ ታላቁን ጩኸት፣ ድምጹን፣ እና መለከቱን ይጠባበቅ ነበር።
ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
“መጥተህ” የሚለው ቃል መንፈሳዊ እውነቶችን ማየት ከፈለግን ካለንበት ተደላድለን ከተኛንበት ወጥተን መሄድ እንደሚያስፈልገን ያመለክታል።
ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት። [በዚህ ጥቅስ ውስጥ ቀስት ተብሎ የተተረጎመው ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ ደጋን ነው። በዘፍጥረትም ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ቀስተ ደመና በተናገረበት ክፍል ቀስት ተብሎ የተተረጎመው ቃል ደጋን ነው።]
ነጭ ቀለም የሐይማኖተኛነት ተምሳሌት ነው። በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ደጋን አለው ቀስት ግን የለውም። ይህም ቀልደኝነት ነው። የሐይማኖት አታላይነት። በምዕራቡ ዓለም ራሳቸው ላይ ዘውድ በመጫን የሚታወቁት የሀይማኖት መሪዎች ከ860 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1963 ድረስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን የገዙ ፖፕ ናቸው።
በፈረሱ ላይ የተቀመጠው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፤ እርሱም ሐይማኖታዊ አታላይነቱን የጀመረው ሰዎች የቤተክርስቲያን መሪ የሚሆኑበትን ዲኖሚኔሽናዊ የሐይማኖት ሥርዓት በማበጀት ነው። ይህ መንፈስ በዓለም ዙርያ ተሰራጭቷል፤ ዓለምን በሙሉ ተቆጣጥሯል። ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ዲኖሚኔሽኖች እና ቤተክርስቲያኖች አሉ።
ቁጥር 3 እና 4 ከ312 ዓ.ም እስከ 1520 ድረስ የዘለቀውን የጨለማው ዘመን በመባል የሚታወቀው ጊዜ ውስጥ የነበሩትን ሶስተኛውን እና አራተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላሉ። ይህም ጊዜ 1,200 ዓመታት ፈጅቷል።
ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
1,200 ዓመታት ለጥጃው አድጎ ትልቅ በሬ እስኪሆን በቂ ጊዜ ነው፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ አድጎ ከባድ ሥራ ለመሸከም እንዲሁም ለመታረድ ይደርሳል። 1,200 ዓመታት የጨለማ ዘመን የቤተክርስቲያን ዘመንን ዕድሜ ከግማሽ በላይ ነው። በዚህ ዘመን ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፈጽሞ ሊጠፋ ትንሽ ብቻ ነበር የቀረው።
ራዕይ 6፡4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።
“ሌላም” ፈረስ ነበረ። እርሱም ቀይ ቀለም ያለው ፖለቲካዊ ሥልጣን ነው። ነገር ግን በእርሱ ላይ የተቀመጠ መኖሩ አልተጠቀሰም። ስለዚህ ያው አንዱ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው ከሐይማኖታዊ አታላይነት ወደ ፖለቲካዊ ሥልጣን የሚዛወረው።
ፖለቲካ ውስጥ መግባቷ ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በትምሕርቷ ያልተስማሙ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን የምትገድልበት ሥልጣን ጨመረላት።
መጽሐፍ ቅዱሶች ሕገወጥ ተደረጉ። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በቤታቸው ስለተገኘ ብቻ ይገደሉ ነበር።
ቁጥር 5 ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር ተሃድሶ ያመጣበትን ዘመን ይወክላል።
ቁጥር 6 እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ የጀመረውንና ለታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመቻ መንገድ የጠረገውን የቅድስና ተሃድሶ እና አገልግሎት ዘመን ይወክላል።
ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።
ከአራቱ እንስሳት መካከል የሰው መልክ ያለው እንስሳ መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ ክርስቲያኖች መዳን፣ ቅድስና፣ እና የወንጌል ስብከት አገልግሎት እንደሚጠበቅባቸው መረዳት ችሏል።
ያው አንዱ በሚስጥር የሚንቀሳቀሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በአዲስ ጥቁር ፈረስ ላይ ተቀምጦ ታላላቅ የንግድ ሥራዎችን ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይዞ ገባ። ስለዚህ አሁን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በሶስት ፈረሶች ላይ ተቀምጦ ይሄዳል።
ካፒታሊዝም ያደገው የቅኝ ግዛት ብዝበዛ በተገዙ ሃገሮች ውስጥ ያለውን ገንዘብ አሟጦ መጨረስ ሲጀምር ነው።
የኢንዱስትሪ እድገት በቂ የጽዳት አጠባበቅ በሌለበት ብዙ ሰዎች ወደ ከተማ ገብተው እንዲከማቹ ምክንያት ሆነ። ፖፑ የባሪያ ሥርዓት ሕጋዊ እንዲሆን አደረገ፤ ለሐጥያት ስርየትም ገንዘብ ማስከፈል ጀመረ። በንግድ በኩል የሚንቀሳቀሰው አጋንንታዊ አሰራር ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ ለመጨረሻዋ ባለጠጋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን መንገድ ጠረገ።
ራዕይ 6፡6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።
ገብስ እና ስንዴ ዳቦ መጋገሪያዎች ናቸው። የሮማ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል እየሸጠች ነበረ። ሻማ፣ የቅዱሳን ምስል፣ የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾች፣ እና የሐጥያት ይቅርታ ሁሉ የሚገኙት ገንዘብ በመክፈል ሆነ። ሕዝቡ የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እወነት ባለማግኘታቸው ተራቡ።
ዘይት መንፈስ ቅዱስን ይወክላል፤ ወይን ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ የሚመጣውን መነቃቃት።
በእነዚያ ሁለት ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መልሶ ወደ ቤተክርስቲያንማምጣት ጀመረ። ምሑራን በእግዚአብሔር መንፈስ እገዛ የግሪክ እና የእብራይስጥ ቋንቋዎችን አንብበው በመረዳት ተርጉመው በ1611 ዓ.ም የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን ማዘጋጀት ችለዋል፤ እርሱም ለ150 ዓመታት ሲፈተሽ ቆይቶ በስተመጨረሻ በ1769 ዓ.ም ታትሟል። እግዚአብሔር የሰዎችን አእምሮ ስለባረከ የሰሩት ሥራ ፍሬያማ ሆነ። ማይክልኤንጅሎ፣ ሼክስፒር፣ እና ቢቶቨን አስደናቂ ሥራዎቻቸውን ሰሩ።
ቀጥሎ ደግሞ ቁጥር 7ን እናገኛል፤ እርሱም የሚወክለው 7ኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።
ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።
7ኛው ቁጥር የሚወክለው 7ኛውን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ነው። የሚበርረው ንስር ድምጽ የሚወክለው ከ1947 እስከ 1965 ድረስ በቴፕ የተቀዱትን የዊልያም ብራንሐም ስብከቶች ነው።
ከ1966 ጀምሮ “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን እየኖርን ነን። ትምሕርቶቹንና ንግግሮቹን በተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት መከታተል ከቻልን የዊልያም ብራንሐም መገለጦች የእግዚአብሔር (የመለኮት እና የመጽሐፍ ቅዱስ) ሚስጥር መጠናቀቂያ ናቸው።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
አሁን ጠለቅ ያለ መገለጥ እናያለን። አራተኛው ፈረስ ሌላ ፈረስ አይደለም። ሐመር የእሬሳ ቀለም ሲሆን ይህ ቀለም የሚገኘው ነጭ፣ ቀይ እና ጥቁርን በመደባለቅ ነው። ስለዚህ 7ኛው ዘመን (በቁጥር 7 እንደተገለጸው) ሐይማኖታዊ አሳሳችነት፣ ፖለቲካዊ ሥልጣን፣ እና የትልልቅ ንግድ አጋንንታዊ አሰራር በአንድነት ሆነው የመጨረሻውን የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚወልዱበት ዘመን ነው። ይህ ሁሉ ማዘናጊያ ዓላማው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በማወቅ እንዳናድግ እና እንደ እግዚአብሔር ቃል ማሰብ እንዳንለምድ ነው።
ፈረሶቹ ላይ የሚቀመጠው ሁልጊዜም አንድ ሰው ነው። አሁን ደግሞ ሶስቱ ፈረሶች በአንድነው ሆነው አንድ ሐመር ፈረስ ሆነዋል።
7 መጠናቀቅን የሚያመለክት ቁጥር ነው። ስለዚህ በዚህ ቁጥር ውስጥ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ይጠናቀቃሉ። የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ለመግለጥ የተጠቀመችዋ ሙሽራ መንፈስ ቅዱስ ምድርን ትቶ በሚሄድበት ጊዜ ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ትነጠቃለች።
ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።
ቁጥር 8። ስምንት አዲስ ሥርዓትን የሚወክል ቁጥር ነው።
ሕይወት ወጥቶ ሲሄድ ሞት ይገባል። ታላቁ መከራ ይጀምራል።
ያው አንዱ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ቤተክርስቲያኖችን ለታላቁ መከራ ያዘጋጃቸው ዘንድ ወደ አንድነት አምጥቷቸዋል። አሁን ደግሞ የአስር ወታደራዊ ፈላጭ ቆራጮች ኃይል ስለተሰጠው ማንም አያስቆመውም።
ራዕይ 17፡12 ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።
አውሬው ማለት በአውሮፓ ውስጥ ብቸኛው ፈላጭ ቆራጭ በሆነው በፖፑ የምትገዛው በቫቲካን የምትመራው የሮማ ካሊክ ቤተክርስቲያን ናት።
10ሩ ቀንዶች እንደ ንጉስ ዓይነት ሥልጣን ያላቸው መሪዎች ናቸው። ገና ዘውድ አልጫኑም ግን ሙሉ ሥልጣን አላቸው። ስለዚህ ፈላጭ ቆራጮች ናቸው።
ራዕይ 17፡13 እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።
10ሩ ፈላጭ ቆራጮች ወታደራዊ ሥልጣናቸውንና ሙሉ ኃይላቸውን ለመጨረሻው ፖፕ ያስረክባሉ።
በዓለም ዙርያ 1.5 ቢሊዮን ካቶሊኮች እና 0.8 ቢሊዮን ፕሮቴስታንቶች አሉ። ሁለቱ ቤተክርስቲያኖች በአንድ ላይ 2.3 ቢሊዮን ተከታዮች አሉዋቸው።
በምድር ላይ ያሉ 7.7 ቢሊዮን ሕዝብ አንድ አራተኛ 1.9 ቢሊዮን ሕዝብ ናቸው።
የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ፖፕ የመጀሪያ ጥቃቱን የሚሰነዝረው በቤተክርስቲያን ላይ ነው። 1.9 ቢሊዮን የዳኑ እና ያልዳኑ ቤተክርስቲያን ተመላላሾችን ከገደለ ከምድር ሕዝብ አንድ አራተኛውን ገድሏል ማለት ነው። ደግሞም በቤተክርስቲያን ዓለም ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎቹን በሙሉ አጥፍቷል ማለት ነው። በቤተክርስቲያን ልማዶች የተታለሉት የዳኑ ሰነፍ ቆነጃጅት ልክ እንደ ውሻ እየታደኑ ይገደላሉ።
ራዕይ 13፡15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።
ቤተክርስቲያንን የተቃወሙ በሙሉ ይገደላሉ።
ራዕይ 6፡9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
ይህ ደግሞ የተለየ ቡድን ነው ምክንያቱም በሰማይ ያሉ እንስሳት አንዳቸውም አልተጠቀሱበትም። እነዚህ አይሁዶች ናቸው። እነርሱ ስለ ምስክርነታቸው ቃል ነው የሞቱት። በ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አይሁዶች አይሁድ ስለሆኑ ብቻ ይሰደዱና ይገደሉ ነበር።
ራዕይ 6፡10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።
አይሁዶች በቀል ይፈቀድላቸዋል።
ዘጸአት 21፡24 ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥
እግዚአብሔር አይሁዶች ኢየሱስን እንዳያውቁት ስላሳወራቸው እግዚአብሔር ስለ አይሁድነታቸው ብቻ ለተገደሉ ጥሩ አይሁዶች መዳንን ይሰጣቸዋል።
ራዕይ 6፡11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።
ሙሽራዋ ወደ ሰማይ ገብታለች። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ እምነታቸው የተገደሉ አይሁዳውያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በገደሉዋቸው የዓለም ሕዝብ ላይ በፍጥነት የበቀል ፍርድ እንዲፈረድላቸው ይጠይቃሉ። ለአጭር ጊዜ እንዲጠብቁ ይነገራቸዋል፤ የሚጠብቁትም የ3½ የታላቁ መከራ ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ ነው። ከእነርሱ ጋር አብረው ባሪያ የሆኑት 144,000ዎቹ አይሁዶች ከታላቁ መከራ ውስጥ መውጣትና ክርስቶስን መቀበል አለባቸው። ከዚያ በኋላ መገደል አለባቸው። አይሁዶች በሙሉ ስለ እምነታቸው መገደል አለባቸው።
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ለአርማጌዶን ጦርነት እና አውሬውን ከነሰራዊቱ ለማጥፋት ይወርዳል።
ራዕይ 6፡12 ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥
ይህም በምድር የሚመጣው ታላቅ መከራ ነው። ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ውስጥ ስለማትገኝ እነዚህ ሁሉ ምሳሌዎች ምን ማለት እንደሆኑ አናውቅም።
ነገር ግን ሊመጣ ያለቅ ጥፋት እና ውድመት በደጅ መሆኑን ለማመልከት ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ይመጣል።
በሳን አንድሬያስ የሚከሰተው የምድር መናወጥ የሚፈጥረው ታላቅ መንቀጥቀጥ የሎሳንጀለስ ከተማ ወደ ባሕር ውስጥ እንድትሰጥም ያደርጋል። ከዚያም የምናውቀው ዓለም በታላቁ መከራ ውስጥ ይጠፋል።
እስቲ ወደ ዮሐንስ ወንጌል እንመለስ።
ዮሐንስ ኢየሱስ ብዙ ተዓምራትን እንደሰራ ይናገረል ነገር ግን ከሰራቸው ውስጥ ሰባቱን ብቻ ነው የጻፈው።
ስለዚህ እነዚህ ሰባት ተዓምራት ለሰዎች ካመጡት ጤና እና በረከት የተነሳ በዚያ ዘመን አስደናቂ ብቻ ሳይሆኑ ወደፊት ሊመጡ ካሉት ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ጋር በመያያዝ ትንቢትን የሚናገሩ ተዓምራትም ነበሩ።
እነዚህ በተለይ ተርጠው የተጻፉ 7 ተዓምራት ሊኖራቸው የሚችለው ትርጉም ይህ ብቻ ነው።
የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ይገልጣል።
ዮሐንስ እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግ የሚችላቸውን ተዓምራት በሙሉ ጠቅሶ ይጽፋቸዋል ብለን እንጠብቃለን። ዮሐንስ ግን ሁሉንም አይጽፍም። በዚህም ዮሐንስ የእግዚአብሔር ተዓምራት አስደናቂዎች ቢሆኑም እንኳ የእግዚአብሔር ዋነኛ ትኩረቶች እንዳልሆኑ ያሳየናል።
እግዚአብሔር ይበልጥ ትኩረቱን ያደረገው ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በመምራት ላይ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ በሃሳቡ ውስጥ የያዘው ትልቁ እቅዱ ይህ ነውቨ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ይመለሳል።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በጣም ወሳኝ ነው ምክንያቱም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው መመለስ አለበት።
ውሃ ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠበት የመጀመሪያው ተዓምር የተደረገው በሰርግ ቤት ነው። ውሃ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ወይን ደግሞ መገለጥን በመቀበል የሚመጣ መነቃቃት ነው።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት በመግለጥ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተማሩ ሐዋርያት ነበሩ። የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የእግዚአብሔር ሚስጥራት መገለጥ መኖር አለበት።
ውሃው ማለትም ቃሉ የተጻፈውን መረዳት እንችል ዘንድ ወደ መገለጥ መለወጥ አለበት።
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የሚጠናቀቀው የሙሽራይቱ አካላት ክቡር ወደ ሆነው ዘላለማዊ አካል ሲለወጡ ነው፤ የዛኔ ነው ተነጥቀን በሰማያት ወደተዘጋጀው ወደ በጉ የሰርግ እራት ግብዣ መሄድ የምንችለው።
ስለዚህ የመጀመሪያው ተዓምር (ውሃ ወደ ወይን ጠጅ መለወጡ) ትኩረቱ ለውጥ ላይ ነው።
ይህ የመጀመሪያ ተዓምር የበዓለ ሃምሳ ቀንን እና ሙሽራይቱ ወይም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ጌታን በአይር ላይ ለመገናኘት የምትነጠቅበትን ቀን የሚያመለክት ትንቢት ነው።
ዮሐንስ 2፡1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
ናዝሬት ከቃና 4 ማይል (6 ኪሎ ሜትር) ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። ስለዚህ ለማርያም ሰርጉ ላይ ቀድማ መገኘት ቀላል ነበር።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። በዚህም መሰረት ማርያም የበዓለ ሃምሳ ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መልክ የመጣውን ኢየሱስን ሲጠባበቁ የነበሩትን የጥንቷን ቤተክርስቲያን ትወክላለች።
ሶስተኛው ቀን።
ኢየሱስ ሊነግረን የፈለገው ቁልፍ ነጥብ ሙሽራይቱ ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነት የምትመለስባቸው ሶስት የተሃድሶ ዘመናት እንደሚኖሩ ነው ማሳየት ነው። እነዚህ እምነቶች በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍተው የነበሩ ናቸው።
5ኛው የማርቲን ሉተር ዘመን ውስጥ መዳን በእምነት ብቻ የሚለው እውነት በተሃድሶ መጣ። ይህ የመጀመሪያው ቀን ወይም የመጀመሪያው የተሃድሶ ደረጃ ነው።
6ኛው የጆን ዌስሌ ዘመን ቅድስና እና የወንጌል ስብከትን በተሃድሶ ወደ ቤተክርስቲያን መለሰ፤ ይህንንም ተሃድሶ ተከትሎ ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን መጣ። ይህም ሁለተኛው ቀን ወይም ከጨለማው ዘመን በኋላ እውነት በተሃድሶ የተመለሰበት ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ዘመን ነው።
7ኛው ዘመን ውስጥ በሎሳንጀለስ ከተማ የአዙዛ እስትሪት ጴንጤቆስጤያዊ መነቃቃት መጣ። ከዚያ በኋላ ከ1947 እስከ 1965 ድረስ በአሜሪካዊው ዊልያም ብራንሐም አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ተገለጡ። ይህም ሶስተኛው ቀን ወይም ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ዘመን ነው። በዚህ ዘመን ውስጥ ነው እውነት ሙሉ በሙሉ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እንደነበረችው እንደ ሐዋርያቱ እምነት በተሃድሶ የምትመለሰው።
የወንድም ብራንሐም ጥቅሶችን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት በመፈተሽ እና መገለጡ ከእግዚአብሔር ቃል የተወሰደ መሆኑን በማረጋገጥ ሙሽራይቱ ለበጉ የሰርግ እራት ግብዣ መዘጋጀት አለባት።
እነዚህ ሶስት ሰዎች ወይም መልእክተኞች በራዕይ ምዕራፍ 14 ውስጥ ካሉት ሶስት መላእክት ጋር ይዛመዳሉ። መልአክ መልእክተኛ ነው።
ይህ ስዕል ቤተክርስቲያን ወደ መጀመሪያው ቤተክርስቲያን እምነቶች በተሃድሶ ሙሉ በሙሉ እንድትመለስ የሚያስፈልጓትን ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ያሳያል።
በራዕይ ምዕራፍ 14 ውስጥ ያሉትን ሶስት መላእክት አስቡ።
ራዕይ 14፡6 በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤
7 በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ።
የዘላለም ወንጌል ንሰሃ ነው። ይህም በማርቲን ሉተር ተሃድሶ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን መጥቷል። መዳን በእምነት።
ራዕይ 14፡8 ሌላም ሁለተኛ መልአክ፦ አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች እያለ ተከተለው።
ዝሙት እርኩሰት ነው። ይህ ወንጌል ደግሞ ጆን ዌስሊ የሰበከው የቅድስና ወንጌል ነው። በዓለም የምትታወቀዋ ቤተክርስቲያን ባቢሎን ወደቀች (በመንፈስ)፤ ወደቀች (በስጋ ደግሞ ሐጥያት ወደ ሞላበት የኑሮ ዘይቤ)።
ራዕይ 14፡9 ሦስተኛም መልአክ ተከተላቸው፥ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ፦ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥
አውሬው ዓለም አቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። የካቶሊክ ማለትም የአውሬው ምስል ደግሞ ወደ አንድነት የመጡት የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖች ናቸው። ግምባራችን ውስጥ የምናስብበት እና የምናምንበት አእምሮዋችን ነው ያለው። የቤተክርስቲያን ዓለም ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ትምሕርቶች አእምሮዋቸውን ማሳት እና መቆጣጠር ነው ዓላማዋ።
አእምሮ እጆችን ይቆጣጠራል፤ በእጆቻቸው ደግሞ ሰዎች ሥራ ይሰራሉ ወይም ቤተክርስቲያንን ያገለግላሉ።
ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ሊገልጥልንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶች፣ የዘመናዊ ቤተክርስቲያኖች ሐይማኖታዊ አቋሞች የሚያመጠትን አደጋዎች ሊገልጥልን ነው የመጣው።
ወንድም ብራንሐም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች ገልጦልናል፤ ስለዚህ ስሕተትን የምናምንበት ማመካኛ የለንም። በተለይም የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ብዙ ስሕተቶች የምናምንበት ማመካኛ የለንም።
ራዕይ 14፡10 እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፥ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሳቀያል።
“ሳይቀላቅል”። እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከፖለቲካ፣ ከገንዘብ ማትረፊያ ንግድ፣ እና ከዓለማዊነት ጋር እንዲቀላቀል አይፈልግም።
ታላቁ መከራ የሚመጣው አምነው የዳኑ ነገር ግን የዘመናዊቷን ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች የሚያምኑ ክርስቲያኖች ላይ ነው።
በፍርድ ቀን የማያምኑ ሰዎች ወደ አስፈሪው የእሳት ባሕር ውስጥ ይወድቃሉ።
ራዕይ 14፡11 የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፥ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
የአውሬው ምልክት ዲኖሚኔሽናዊ ሐይማኖት ነው። ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ተከተው የቆሙት የሰው ልማዶች እና ሃሳቦች ናቸው።
እግዚአብሔርን መጠበቅ እና ቤተክርስቲያንን ወደ መጀመሪያው ሐዋርያዊ እምነት እስኪመልሳት መጠባበቅ ብቻ ነው ማድረግ የምንችለው ነገር።
ራዕይ 14፡12 የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው።
ኢየሱስ ተይዞ ከመገደሉ በፊት ከሰራቸው ተዓምራት ውስጥ ዮሐንስ የመዘገባቸውን ሰባት ተዓምራት አንድ በአንድ እንመልከት።
የመጀመሪያው ተዓምር የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
(ከዚህም የተነሳ የመጨረሻውን የቤተክርስቲያን ዘመንም ይወክላል ምክንያቱም የመጨረሻው ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ አለበት)።
ኢየሱስ አልፋ እና ኦሜጋ ነው። የመጀመሪያ እና የመጨረሻ። መጀመሪያ ያደረገው ተዓምር ውሃ ወደ ወይን ጠጅ መለወጥ ሲሆን ይህም የተደረገው ሰርግ ቤት ውስጥ ነው። የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ (በሕይወት ሰጪ ውሃ የተመሰለው) የተጻፈውን መረዳት ወደሚችሉበት መገለጥ ተለወጠ።
ይህም በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የአእምሮ መታደስን አምጥቷል።
ለሐዋርያቱ ቁልፍ የሆነው ቀን የተጻፈው ቃል ውስጥ የነበራቸው እውቀት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አማካኝነት ወደ ሕይወት ሰጪ መገለጥ የተለወጠበት የጴንጤ ቆስጤ ቀን ነው። በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ በጣም ከመሞላታቸው የተነሳ እንደ ሰከረ ሰው ይንገዳገዱ ነበር።
የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ሲመለስ የዚያን ጊዜ ሰውነታችን ወደ ከበረ ሰውነት ይለወጣል። ስለዚህ የመጨረሻው ተዓምር የሚሆነው ሙሽራይቱ በሰማያት ወደ ተዘጋጀው የበጉ ሰርግ እራት ግባዣ ለመታደም ስትነጠቅ ነው።
ዮሐንስ 2፡2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
ማቴዎስ 20፡16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።
ስለዚህ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እና የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን በመካከላቸው ምንም ልዩነት ስለሌለ ተመሳሳይ እምነት ሊኖራቸው ይገባል፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው የመጨረሻው ነው የመጨረሻውም የመጀመሪያው ነው።
የተጠሩ ብዙዎች ናቸው የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው።
ብዙ ክርስቲያኖች በልባቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ጥሪ ሰምተው ይድናሉ። በዚህም ከሰነፎቹ ቆነጃጅት ውስጥ ይቆጠራሉ። ይድናሉ ነገር ግን በሰው ሰራሽ ልማዶች በቀላሉ ይታለላሉ።
ከዚያ በኋላ ከዳኑ አማኞች መካከል የተሰኑቱ የሚያምኑትን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት ይላሉ፤ እነርሱም እግዚአብሔር የሙሽራይቱ አካል እንዲሆኑ ይመርጣቸዋል። ሔዋን ከአዳም ጎን የተወሰደች አካሉ፣ አጥንቱ እና ስጋው ነበረች። ሙሽራይቱ የተፈጠረችው ከኢየሱስ ስጋ ከፈሰሰው ውሃ፣ ደም፣ እና መንፈስ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል አካል መሆን አለብን። የምናምነው እያንዳንዱ ነገር ከእግዚአብሔር ቃል መረጋገጥ አለበት።
መጠራት የመጀመሪያው ደረጃ ነው።
ኢሱስ 12 ደቀመዛሙርትን ጠርቶ ነበረ። በተጠሩ ጊዜ ሁላቸውም ወደ ሰርጉ ሄደዋል። 12ቱም ኢየሱስን ለማገልገል እና ለመከተል ነው የተጠሩት። ይሁዳ ግን ኋላ ከመካከላቸው ወደቀ። ስለዚህ መጠራት ብቻ በቂ አይደለም።
ራዕይ 17፡14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
መጠራት አለብን፤ ከዚያ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የማመን አቋም በመያዛችን መመረጥ አለብን፤ ከዚያም በኋላ ደግሞ ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ ሆነን መኖር አለብን።
ብዙ ሰዎች የዳኑ ጊዜ ኢየሱስን ይከተሉታል። ከዚያ በኋላ ግን ዓይናቸውን ከእርሱ ላይ ያነሱና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ልማዶችን እንዲሁም ዝነኛ የሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎችን አመለካከት ይከተላሉ።
ዮሐንስ 2፡2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
ዮሐንስ 2፡3 የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
ይህንን ስናነብ ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የወይን ጠጅ እንዲቀርብላቸው የጠየቁ ይመስላል። ማርያም ናዝሬት ውስጥ በቅርበት በመኖሯ ቀድማ መጥታ ሥራ ስታግዝ ነበር። ስለዚህ የወይጠጅ ማለቁን አውቃለች።
ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።
ወይን የሌላት ቤተክርስቲያን። መገለጥ የሚያመጣው መነቃቃት የሌላት ቤተክርስቲያን።
ማርያም ከጴንጤ ቆስጤ ዕለት በፊት ቤተክርስቲያን የነበረችበትን ሁኔታ ትወክላለች።
ተመልከቷቸው ደቀመዛሙርቱ በጴንጤ ቆስጤ ዕለት እንደ ሰከረ ሰው ሲንገዳገዱ።
ሲፈልጉ የነበሩት ወይን ነው፤ እርሱም የመገለጥን መነቃቃት ይወክላል።
የሐዋርያት ሥራ 2፡13 ሌሎች ግን እያፌዙባቸው፦ ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ።
የሐዋርያት ሥራ 2፡14 ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ።
የሐዋርያት ሥራ 2፡15 ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤
እንደ ሰከረ ሰው እስኪንገዳገዱ ድረስ ነው መንፈስ ቅዱስ በእውነት ያነቃቃቸው።
በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ወዳለው ሰርግ እንመለስ።
ዮሐንስ2፡4 ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
ኢየሱስ ትልቁን እቅድ እየተመለከተ ነው።
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን እውነተኛ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት ለማግኘት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ያስፈልጋታል። ይህ ከመገለጥ የምንቀበለው መነቃቃት ከመጽሐፍ ቅዱስ ተጨረማሩ እውነትን የማግኘት ፍላጎታችንን ይጨምረዋል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቋ ማስረጃ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተገለጠውን ሐዋርያዊ እውነት በሙሉ መቀበል መቻሏ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ግን ሊመጣ የሚችለው ኢየሱስ ለሐጥያታችን ከሞተ በኋላ ብቻ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ለምትወክለው ማሪያም እንዲህ ያላት ይመስላል፡- “እውነተኛው ወይን ወይም የመገለጥ መነቃቃት እስከ ጴንጤ ቆስጤ ዕለት ቆይቶ ይገለጥ”።
ኢየሱስ ሁልጊዜ በሃሳቡ ዋነኛውን ታላቁን የእግዚአብሔር እቅድ እያሰበ ነው የሚንቀሳቀሰው። እያንዳንዱ እርምጃ የሚወሰደው በተያዘለት ጊዜ ብቻ ነው።
ለነገሩ እርሱ ስለ ምን እየተናገረ እንደነበር ማንም አላወቀም።
በዚያን ጊዜ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ምሳሌ የሆነችዋ ማርያምም ቀጥሎ ኢየሱስ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ አላወቀችም፤ ነገር ግን በኢየሱስ ላይ ሙሉ እምነት ሊኖራት እንደሚገባት በደምብ አውቃለች።
ስለዚህ “እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” የሚለውን መልእክት አስተላለፈችላቸው።
ዮሐንስ 2፡5 እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
ይህ የመጀመሪያው ዘመን ቤተክርስቲያን ለኢየሱስ የሰጠችው ምላሽ ሲሆን የመጨረሻው ዘመን ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ዓይነት ምላሽ መስጠት አለባት።
“በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ እመኑ፤ አድርጉ”።
ዮሐንስ 2፡6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
አንድ እንስራ 41 ሊትር ወይም 9 ጋሎን ያህል ፈሳሽ ነው የሚይዘው።
ስለዚህ እነዚህ እንስራዎች ትልልቅ እቃዎች ናቸው። ውሃው ለማንጻት ሥርዓት ነበር የተቀመጠው፤ ስለዚህ ትኩረት የተደረገው በቅድስና ላይ ነው። መጀመሪያ መዳን፤ ከዚያም ቅድስና፤ ቀጥሎ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት።
ስድስት የሰው ቁጥር ነው፤ ሰው የተፈጠረው በስድስተኛው ቀን ነው።
እያንዳንዱ እንስራ አንድ ሰውን ይወክላል። ውሃ የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል። እንስራዎቹ ብዙ ውሃ መያዝ መቻላቸው ሰዎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የመያዝ ብቃት አላቸው ማለት ነው።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
እንስራዎቹ የሚይዙት የውሃ መጠን የተለያየ ነበር፤ ሰዎችም ማስታወስ በምንችለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብዛት እንለያያለን።
ዮሐንስ 2፡7 ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
በግማሽ ልብ መቅረብ ተቀባይነት የለውም። እያንዳንዱ እንስራ እስከ አፉ ተሞልቶ ነበረ። ኢየሱስ እያንዳንዱ ሰው የሚችለውን ያህል የእግዚአብሔርን ቃል እንዲማር ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ሁላችንም የምንችለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ አለብን።
ዮሐንስ 2፡8 አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦
በትልቅ የሥልጣን ሥፍራ ላይ የነበሩ ሰዎች ምን እንደተደረገ አላወቁም። ይህ ስለ ዘመናችን የቤተክርስቲያን መሪዎች ምን ይነግረናል?
ባሪያዎች የነበሩ ሰዎች ምን እንደተፈጠረ አውቀዋል።
ስለዚህ ለውጥ ሆኗል ማለት ነው።
በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር ሰዎች አእምሮዋቸውን በቃሉ እንዲሞሉ ይጠብቅ ነበር። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የወሰነው ጊዜ ሲደርስ አእምሮውን በእግዚአብሔር ቃል ለሞላው ሰው እግዚአብሔር የቃሉን መገለጥ ይሰጠዋል።
እነዚህ እንስራዎች የሚችሉትን ያህል የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ውስጣቸው ያስገቡትን የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አማኞችን ይወክላሉ። ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እና ለማጥናት እውነተኛ ጥማት እንደነበራቸው ያሳያል።
ሉቃስ 24፡32 እርስ በርሳቸውም፦ በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ ትልቅ ፍላጎት ነበራቸው።
ከዚያ የሰርጉ አሳዳሪ እንዲህ አለ፡-
ዮሐንስ 2፡10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
ከዚህ ንግግር ውስጥ ጥልቅ የሆነ ሃሳብ እናገኛለን።
ለጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን የቃሉ መገለጥ ተሰጥቷታል።
ከዚያ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት በጨለማው ዘመን ውስጥ እየደበዘዘ ሄደ።
ነገር ግን በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ ላይ በዊልያም ብራንሐም በቀረቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጥ ትምሕርቶች አማካኝነት በመጀመሪያ የነበረው ጥሩ የወይን ጠጅ ባልታሰበ ሰዓት በድንገት በመጨረሻውም ሰዓት ተገኝቷል። ይህም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ከመጽሐፍ ቅዱስ እምነት አንጻር ወደ መጀመሪያው ቤተክርስቲያን ዘመን መመለስ እንዳለበት የሚጠቁም ግልጽ ፍንጭ ነው።
ዮሐንስ 2፡11 ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
አንበሳው የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመናት ነው የሚያጠቃልለው።
ስለዚህ የመጀመሪያው ተዓምር በግልጽ ተጠቅሷል። በአንበሳው ዘመን ሁሉም ነገር በግልጽ እና በትክክል ነው የሚደረገው። አንበሳው የሚወክለው በሐዋርያቱ አማካኝነት የተጻፈውን የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ሙሉ እውነት ነው።
ሁለተኛው ተዓምር ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
ይህኛውም ተዓምር የሆነው ኢየሱስ ቃና ውስጥ እያለ ነው፤ ነገር ግን ተዓምሩ የተፈጸመው ቃሉ እርሱ ከቆመበት 27 ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ በሄደበት በቅፍርናሆም ነው።
ይህም የሚያሳየው በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የተሰጡ የሐዋርያት ትምሕርቶች በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ልክ እንደ መጀመሪያው በአንበሳው ምሪት ውስጥ ለነበሩ አማኞች ተሻግረው መድረስ እንዳለባቸው ነው።
ዮሐንስ 4፡46 ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ።
ስለ ቤርያ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-
የሐዋርያት ሥራ 17፡11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
ልበ ሰፊዎች ማለት እነርሱ ከሚሰሙት ስብከት ጋር በየዕለቱ መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ልብ ተቀበሉት ማለት ነው።
ይህ የሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን አመለካከት ነበረ። የተቻላቸውን ያህል ከእነርሱ የቀደሙት ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምሕርት ያጠኑ ነበር።
በዚያኑ ጊዜ ሰይጣን ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶችን በሰው ሰራሽ ሕጎች እና ልማዶች አማካኝነት ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ነበር።
ዮሐንስ 4፡47 እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።
ይህ ሹም ኢየሱስን ሲያፈላልግ ነበረ። ይህም የሁለተኛው ቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ይመረምሩ እንደነበረ ያመለክታል።
ይህ ሹም አባት ለልጁ ሕይወት ማግኘት ብቸኛ መንገድ ነበረ።
ሐዋርያት የቤተክርስቲያን አባቶች ነበሩ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈው የሐዋርያቱ ቃል ከእነርሱ በኋላ ለመጣው ትውልድ በመንፈስ ልጆቻቸው ለሆኑት (በቀጣዩ የቤተክርስቲያን ዘመን) የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ብቸኛ መንገድ ነበረ።
ገላትያ 4፡19 ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።
ከሐዋርያዊ አባቶች መካከል ከሁሉም ታላቅ ሆነው ጳውሎስ ወደ ክርስቶስ ያመጣቸውን ሰዎች እንደ ልጆቹ ነበር የሚያያቸው። ይህም ከዚያ ወዲያ በቀጣይ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ ይሆናል ምክንያቱም ለሁሉም የቤተክርስቲያን ዘመናት የእውነትን መሰረት የጣለው ጳውሎስ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3፡10 የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
የምንገነባው በሙሉ ጳውሎስ ባስተማረው ትምሕርት ላይ መመስረት አለበት።
ኢየሱስ ጠንካራ ጥያቄ ነው የጠየቀው። ተዓምራት ካላያችሁ በቀር አታምኑም?
ዮሐንስ 4፡48 ስለዚህም ኢየሱስ፦ ምልክትና ድንቅ ነገር ካላያችሁ ከቶ አታምኑም አለው።
ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከገቡ ድክመቶች መካከል አንዳንድ ሰዎች ተዓምር ካላዩ በቀር አናምንም ማለታቸው ነው።
ተዓምራት አስደናቂ ናቸው፤ ነገር ግን እምነታችንን በተዓምራት ላይ መመስረት የለብንም። እምነት መመስረት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ነው።
ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ኢየሱስ ሰውየው ማየት የማይችለውን ተዓምር ከርቀት አደረገ።
የመጀመሪያው ተዓምር የተደረገባት ቃና የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ትወክላለች።
ከቃና እስከ ቅፍርናሆም ኢየሱስ 27 ኪሎሜትሮችን አቋረጠ፤ ቅፍርናሆም ሁለተኛው ተዓምር የተደረገበት ከተማ የአንበሳውን ዘመን፤ ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
ዮሐንስ 4፡49 ሹሙም፦ ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ አለው።
ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከሮማውያን ገዥዎች ከባድ ስደት ደርሶበታል። ንጉስ ዲዮክሊቲያን ክርስቲያኖችን እና መጽሐፍ ቅዱሶችን ከምድር ላይ ለማጥፋት የ10 ዓመታት መራራ ስደት አስነስቶ ነበር።
ክርስትና ፈጽሞ ሊጠፋ ቀርቦ ነበር።
ዮሐንስ 4፡50 ኢየሱስም፦ ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ አለው። ሰውዬውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ።
አባትየው ተዓምሩ ሲደረግ አላየም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ስለተናገረ ብቻ አምኖ ሄደ።
ይህ የሐዋርያዊ አባቶች እውነተኛ እምነት ነው። ተዓምራት ቢደረግም ባይደረግም እነርሱ የእግዚአብሔርን ቃል ያምናሉ።
የአባትየው እምነት ልጅየውን አዳነው።
ሐዋርያት የቤተክርስቲያን አባቶች ናቸው። ከታላቁ መከራ መዳን ከፈለግን አዲስ ኪዳን ውስጥ የተመዘገበውን የሐዋርያት እምነት እኛ ልጆቻቸው ማመን አለብን።
ነገር ግን አረማውያኑ ሮማውያን በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በነበሩ ክርስቲያኖች ላይ ስደት ቢያበዙባቸውም ኢየሱስ የሁለተኛው ዘመን ቤተክርስቲያን እንዳትጠፋ ጠበቃት። ቤተክርስቲያንም መኖሯን ቀጠለች። በጣም የሚደንቀው ነገር በቀጣዩ ሶስተኛ የቤተክርስቲያን ባርቤሪያውያን ጥቃት የሰነዘሩ ጊዜ የወደመው የሮማ መንግስት ነው።
ዮሐንስ 4፡51 እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና፦ ብላቴናህ በሕይወት አለ ብለው ነገሩት።
ሰዎች በቤተክርስቲያን ላይ እራሳቸውን መሪ አድርገው ሲሾሙ የሁለተኛው ቤተክርስቲያን ዘመን ብርሃን እየደበዘዘና እየጠፋ ነበረ።
ነገር ግን ስደቱ ስሕተት እንዳይስፋፋ አደረገ። ቤተክርስቲያን በዚያን ጊዜ በሕይወት ነበረች ግን እንደ መጀመሪያው ዘመን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አልነበረችም።
በስደት ምክንያት በየቦታው መበታተናቸው አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ትንንሽ እንዲሆኑ አደረገ። ይመሩዋቸውም የነበሩት የሽማግሌዎች ሕብረት እንጂ አንድ ግለሰብ አልነበረም።
የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
በ312 ዓ.ም ኮንስታንቲን የሮማ ንጉስ በሆነ ጊዜ በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ንጉስ ኮንስታንቲን በመንግስት ገንዘብ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን መገንባት ጀመረ። ቤተክርስቲያኒቱ አድጋ ትልቅ ስትሆን የሥልጣን ጥማት ያላቸው ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የመሪነት ቦታ መያዝ ጀመሩ።
ይህ መቅረዝ ሁለተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል። ነበልባሉ ደማቅ ነበረ፤ ነገር ግን የሰው አመራር ቤተክርስቲያንን ከመጀመሪያዋ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ከተመራችበት የእውነት ቃል እያራቃት ነበረ።
ዮሐንስ 4፡52 እርሱም [ሹሙ] በጎ የሆነበትን ሰዓት ጠየቃቸው፤ እርሱም፦ ትናንት በሰባት ሰዓት ንዳዱ ለቀቀው አሉት።
የአይሁዶች አዲስ ቀን የሚጀምረው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ነው። ጠዋት ነግቶ ሰባት ሰዓታት ካለፉ በኋላ ከቀኑ 7 ሰዓት ይሆናል።
የመጀመሪያው ተዓምር የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል። ስለዚህ ኋለኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የመጀመሪያውን እንደ አርአያ መከተል አለበት።
ሰባተኛው ሰዓት ፍጻሜን የሚያመለክት ሰዓት ነው። በተጨማሪም ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናትን ያመለክታል።
ስለዚህ ይህ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ድርሻውን ጨርሷል፤ ድርሻውም በሰዎች አመራር ምክንያት ከእውነት ተንሸራትቶ መውደቅ ነው። ነገር ግን አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፉትን አብዛኞቹን ዋነኛ የሐዋርያት አስተምሕሮዎች አጥብቀው መያዝ ችለዋል።
ዮሐንስ 4፡53 አባቱም ኢየሱስ፦ ልጅህ በሕይወት አለ ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ።
ሩቅ በሆነው ቅፍርናሆም ውስጥ የተደረገው ነገር ኢየሱስ በተናገረው ቃል መሰረት በትክክል ነበር የተፈጸመው።
ይህ ስደት የበዛበት ዘመን ሳይጠፋ የቆየው በዋነኝነት ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ስለተስማሙ ነው።
በስደት ምክንያት መበታተን ለእነርሱ ከባድ ፈተና ነበር፤ ነገር ግን የሰውን አመራር ማስቀረት ተደላድሎ ከመመስረት መከላከል በመቻሉ ጥሩ ተጽእኖም ነበረው።
ዮሐንስ 4፡54 ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛ ምልክት ነው።
ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የአንበሳው ዘመን አካል ነበረ፤ በዚያም ዘመን ሁሉም ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ቃል መሰረት ይደረግ ስለነበረ ሁሉም ነገር ትክክል ነበር። ስለዚህ ይህ ገሊላ ውስጥ ኢየሱስ ባደገበት አውራጃ እንደ ሁለተኛ ተዓምር ተደርጎ ተመዝግቧል።
ቃሉ በልባችን ውስጥ ማደግ አለበት። ለኢየሱስ ያለን አመለካከት ለኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ባለን አመለካከት አማካኝነት ይንጸባረቃል።
ሶስተኛው ተዓምር ሶስተኛውን የቤተክርስቲያን ዘመን ይወክላል።
በ325 ዓ.ም በኒቂያ የተደረገው የቤተክርስቲያን ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ሥላሴ የተባለ ቃል እንዲቀበሉ በማስገደድ ፖለቲካዊ ሥልጣንን ከሐይማኖታዊ ሥልጣን ጋር አንድ አድርጎ አደባለቀ።
የእግዚአብሔርን ቃል በመለወጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባላቶቿን እውነትን እንዳያውቁ ማሳወር ተሳክቶላታል፤ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳትም አቅም እንዲያጡ አድርጋቸዋለች።
እንደ ሥላሴ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን በማመን መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ እርስ በርሳቸው በሚጋጩ ሃሳቦች እንዲሞላ አደረጉ።
ኢየሱስ መለኮት ውስጥ ነው ያለው ይላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን መለኮት ኢየሱስ ውስጥ ነው ይላል።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ውስጥ ወደምትገኛው የቤተሳይዳ መጥመቂያ መጣ።
አንዳንድ ሰዎች ቤተሳይዳ “የምሕረት ቤት” ማለት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ “የውርደት ቤት” ማለት ነው ይላሉ።
በዚህ ምክንያት ቤተሳይዳ የሚለው ቃል ትርጉሙ አከራካሪ ነው።
ይህ መጥመቂያ የነበረበት ትክክለኛ ቦታ የት እንደሆነም አጨቃጫቂ ነው።
ከዚህም የተነሳ ሶስተኛው የጴርጋሞን (“ሙሉ በሙሉ የተጋባች” ማለት ነው) ቤተክርስቲያን ዘመንም አጨቃጫቂ ነው፤ በዚህ ዘመን ውስጥ ነው የሥላሴ ጽንሰ ሃሳብ (በ325 ዓ.ም የተጀመረው)፣ እና የክሪስማስ ጽንሰ ሃሳብ (በዲሴምበር 25 የአረማውያን የፀሃይ አምላክ የልደት ቀንን ከሚያከብሩ አረማውያን የተኮረጀ) በፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ አማካኝነት በ350 ዓ.ም ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባው። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት እንድናከብር አላዘዘንም። ከዚያ በኋላ በ380 ዓ.ም የሮም ጳጳስ እራሱን ፖንቲፌክስ ማክሲመስ (የባቢሎናውያን ሚስጥራት ሊቀ ካሕናት) ብሎ ሰየመ፤ ደግሞም ፖፕ ወይም ፖንቲፍ ተብሎ ተጠራ። በ450 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ሊዮ ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች ከባድ ስደት ሊደረግባቸው ወይም ሊገደሉ እንደሚገባ ወሰነ።
የመለኮት ጉዳይ እንደ “እግዚአብሔር ወልድ” እና ኢየሱስን “የመለኮት ሁለተኛው አካል” በመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ቃላት ይብራራ ስለነበረ አጨቃጫቂ ሆነ።
ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ወይስ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ? የእግዚአብሔር ማንነት በሰዎች አእምሮ ውስጥ መደብዘዝ ጀመረ።
ስለ ፖፑ ሥልጣን እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላሉ የሥልጣን ተዋረዶች ክርክሮች እና ግጭቶች እየተባባሱ ሄዱ።
ካሕናት ጉባኤዎችን እንዲመሩ ሥልጣን ተሰጣቸው። ጳጳሶች ደግሞ በካሕናት ላይ ተሾሙ። ከዚያ በኋላ ካርዲናሎች በጳጳሳት ላይ ተቆጣጣሪ ተደረጉ። ሁላቸውም ደግሞ በፖፑ ፈላጭ ቆራጭነት ሥር እንዲገዙ ተደረገ።
በብዙ ቦታዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ተከለከለ። ሰዎች በቤታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ከተገኙ ይገደሉ ነበር።
ከዚህም የተነሳ የሮማ ካቶሊክ ሰዎች በግላቸው የኢየሱስን ማዳን ሳይለማመዱ ቀሩ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሰበሰባሉ፤ በራሳቸው አእምሮ ማሰብን አቆሙ፤ ለመዳን የነበራቸው አማራጭ ለፖፑ መገዛት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስን አለማንበባቸው አሳወራቸው። መጽሐፍ ቅዱስን መለወጥ እንዲጠወልቁ እና በመንፈስ እንዲቀጭጩ አደረጋቸው።
ዮሐንስ 5፡3 በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።
ዮሐንስ 5፡4 አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
የውሃው መናወጥ። የእግዚአብሔር ቃል በሰው ሰራሽ የእምነት መግለጫዎች እና ሕጎች ተተካ። በዚህም የዚያ ዘመን እውነተኛ አማኞች ይረበሹበት ነበር። በጣም ብዙ ክርክሮች ነበሩ፤ ካቶሊክን የተቃወሙ ሰዎች ደግሞ ስደት ይደርስባቸው ነበር።
ዮሐንስ 5፡5 በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
ይህ ሰውዬ ሊጠፋ የቀረበውን አንካሳ የነበረውን የአይሁድ እምነት ይወክላል። ኢየሱስ በ33 ዓ.ም ከሞተበት ዓመት ጀምሮ እስከ ቤተመቅደሱ መፍረስ ያለፉት ዓመታት 38 ያህል ነበሩ። የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የአይሁድ ሕዝብ በብዙ ቁጥር ወደሚሞቱበት ሞት ሲነዱዋቻ ነበር። በጀነራል ታይተስ እየተመሩ በመጡ የሮማ ሰራዊት እጅ በ70 ዓ.ም ከ1 ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያን ተገድለዋል።
ከ33 ዓ.ም እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ያሉት ዓመታት በጥቁር ቀለም ተጽፈዋል። 33 ዓ.ም (በቀይ የተጻፈው) የመጀመሪያው ዓመት ከሆነ፤ 70 ዓ.ም ደግሞ 38ኛው ዓመት ይሆናል።
አይሁዶች ኢየሱስን በሮማውያን እጅ ካስገደሉበት ዓመት አንስቶ አይሁዶች በሮማውያን እጅ እስከጠፉበት ዓመት ድረስ 38 ዓመታት ናቸው ያለፉት።
ንጉስ ኮንስታንቲን የሮማ ጳጳስ የምዕራቡ ዓለም ዋነኛ ጳጳስ እንዲሆን ግፊት ማድረግ ጀመረ። ከዚያም በኋላ የሮም ቤተክርስቲያን በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል በመለወጥ ክርስቶስን በድጋሚ ሰቀለችው። ሥላሴ የተባለውን የአረማውያን ሃሳብ ወደ ክርስትና አስገብተዋል፤ ደግሞም የፋሲካን ቀን ቀይረዋል። ስቅለት የተፈጸመው በአርብ ቀን ነው አሉ። ነገር ግን ኢየሱስ እሁድ ጠዋት ከሆነ ከሞት የተነሳው እና በምድር ልብ ውስጥ ለሶስት ሌሊት ቆይቶ ከሆነ ሊሞት የሚችለው ሐሙስ ነው።
ማቴዎስ 12፡40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።
ዳንኤል ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ሲናገር እንደ ትንሽዬ ቀንድ ነው የገለጸው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደር የነበረው ሮም ከተማ ውስጥ ካኤልያን ኮረብታ ላይ ቤተክርስቲያን እና ቤተመንግስትን በአንድ ላይ በያዘው የላተራን ሕንጻ ውስጥ ነበር። የካኤልያን ኮረብታ ከሰባቱ የመጀመሪያ የሮም ኮረብታዎች አንዱ ነበር። ከዚያ በኋላ የሮማ ቤተክርስቲያን አንድ ኪሎ ሜትር ካሬ ስፋት ያለውን የቫቲካን ከተማ ቆረቆረች፤ እርሷም በምድር ላይ በስፋቷ ከሁሉ የምታንስ ትንሽዬ መንግስት ናት። ይህች ትንሽ የቫቲካን ከተማ ናት በዓለም ዙርያ የተስፋፋችዋን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምታስተዳድራት።
ዳንኤል 7፡25 [ትንሹ ቀንድ] በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥
[ኢየሱስን ሁሉን ቻይ አምላክ እግዚአብሔር ከመሆን የመለኮት ሁለተኛው አካል ወደ መሆን መለወጥ]
የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥
[መጽሐፍ ቅዱሶች በታገዱበት ወይም ተራው ሕዝብ ማበብ በማይችለው በላቲን ቋንቋ ብቻ በሚገኙበት በአስጨናቂዎቹ የጨለማው ዘመን 1,200 ዓመታት ውስጥ። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ስለመቃወማቸው ከአስር ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በተገደሉበት ጊዜ። ሥላሴን የሚቃወሙ ሰዎችን ጨፍጭፈው ጨርሰው አምላክ ማለት ሥላሴ ነው ብለው ባስተማሩበት ጊዜ። የሰው አመራር ዲኖሚኔሽናዊ የእምነት መግለጫዎችንና ልማዶችን በመሰረተ ጊዜ። አረማውያን ልማዶች ቤተክርስቲያን ውስጥ ሾልከው በገቡ ጊዜ]፤
ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤
[የክሪስማስ በዓልን በዲሴምበር 25 ማክበር የተጀመረው በፖፕ ዩልየስ ቀዳማዊ በ350 ዓ.ም አካባቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት እንድናከብር አላዘዘንም። ይህ ፖፑ የፈጠረው አዲስ ሕግ ነው።]
ፖፑ የስቅለትን ቀን ከሐሙስ ወደ አርብ ቀየረው።
የኩዳዴ ጾም፣ የፋሲካ እንቁላሎች፣ የፋሲካ ጥንቸሎች የመሳሰሉት ልማዶች በፖፑ አማካኝነት ነው የተጀመሩት።
ጥንቸሎች በመራባት ፍጥነታቸው ከብዙ እንስሳት ይበልጣሉ። እነርሱም ኢሽታር ከምትባለዋ አምላክ ጋር በልቅነታቸው ይዛመዳሉ። ሂዩ ሄፍነር ፕሌይቦይ ለተባለው ትልቅ የብልግና ንግድ ይጠቀም የነበረው እንደ ጥንቸል የለበሱ ሴቶችን ነበረ።
… እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።
[የእኩሌታ ዘመን ማለት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲሆኑ የዳንኤል ትንቢት ውስጥ የተጠቀሰውን 7 ዓመት ለሁለት የ 3½ ዓመታት ጊዜ ይከፍሉታል። የመጀመሪያው ሶስት ዓመት ተኩል የኢየሱስ አገልግሎት፤ ሁለተኛው ደግሞ ከ2,000 በኋላ የሚመጣው ታላቁ መከራ።]
ስለዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚው የቤተክርስቲያን ድርጅት እስከ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ድረስ እውነተኛ አማኞችን ይጨቁናቸዋል።
ማቴዎስ 24፡13 እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
[ከታላቁ መከራ]።
የቤተሳይዳ መጥመቂያ በመንፈስ የጠወለገችዋን የሮም ቤተክርስቲያን ነው የሚወክለው።
ፖፑ ቤተክርስቲያንን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ታገደበት እና ወደተገፋበት ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ ይዟት እየሄደ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ ገዳም ብቻ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ይፈቀድ ነበረ፤ ያውም መጽሐፍ ቅዱሱ በቤተ መጻሕፍት ጠረጴዛ ላይ በሰንሰለት ታስሮ ነው የሚቀመጠው። ያም መጽሐፍ ቅዱስ በላቲን ቋንቋ የተጻፈ ነበረ። ይህንን ቋንቋ ደግሞ ተራው ሕዝብ አንብበው መረዳት አይችሉም ነበር።
ዮሐንስ 5፡6 ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው።
ይህ ሰው ከኢየሱስ ጋር አንዳችም ልምምድ አልበረውም። ከኢየሱስ ለቀረበለት ቀጥተኛ ጥያቄ “አዎ” ብሎ መመለስ አልቻለም።
ሲጠየቅ ምን እንደሚፈልግ አልተናገረም። ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ሕብረት አልነበረውም። ዝም ብሎ የቤተክርስቲያን አባል ብቻ ነበረ።
ዮሐንስ 5፡7 ድውዩም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።
ሊፈወስ የሚችለው ሰው በራሱ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ የሆነ እና ሌሎችን ለመከተል ቁጭ ብሎ የማይተባበቅ ሰው ብቻ ነው።
በቤተክርስቲያን ውስጥ መንጋውን መከተል አደጋ አለው። ብዙ ከብቶች በእግራቸው የረገጡት ሳር ለመብላት አይሆንም።
በሽተኛው ሰውዬ ለራሱ ምንም ማድረግ አልቻለም። የሚረዳው ሌላ ሰው ያስፈልገው ነበር። የሚሸከመው ሰው።
የሰውዬው ምርኩዝ ወይም ክራንች ቤተክርስቲያን ነበረች።
ይህ ሰው ከፈሪሳውያን ጋር እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ የለውም። የሐይማኖት መሪዎች በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ቦታ ይዘዋል። በተመሳሳይ መንገድ የሮማ ካቶሊክ አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር የግል ትውውቅ የላቸውም፤ ትውውቃቸው ከቤተክርስቲያናቸው ሥርዓት ጋር እና በሚደገፉዎቸው የሰው አመራሮች ጋር ብቻ ነው።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰዎች በራሳቸው አእምሮ እንዳያስቡ አድርጋለች። አንዳችም ማስተዋል የሌላቸው በቀቀን የሚባሉ ወፎች የሰውን ንግግር አስመስለው እንደሚደግሙ እነዚህ ሰዎችም ሰው ሰራሽ ትምሕርቶችንና ሕጎችን ያለማስተዋል ይደጋግማሉ።
ለምሳሌ “የእግዚአብሔር ስም ማነው” ዓይነት ቀላል የእምነት ጥያቄዎችን መመለስ አይችሉም።
በመለኮት ውስጥ በሚኖሩ ሶስት የተለያዩ አካላት ያምናሉ።
ማንም ሰው ለሶስት የተለያዩ አካላት አንድ ስም ሊያገኝላቸው አይችልም።
ስለዚህ እራሳቸውም ስላልገባቸው ሕዝቡ የመጣባቸውን ጥያቄ ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ። “ፓስተሬን ጠይቀው”። ነገር ግን ፓስተርም ይሁን ካሕን ወይም ፖፕም ቢሆን ለሥላሴያዊ አምላክ ስም ማግኘት አልቻለም።
ታማኝነታቸው ለቤተክርስቲያን ወይም ለቤተክርስቲያን መሪ እንጂ ለኢየሱስ ወይም ለመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም።
ሥርዓቶች እውነታን ተክተዋል።
ዮሐንስ 5፡8 ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
በሌሎች ሰዎች አስተሳሰብ ታዝሎ በመዞር ፈንታ ኢየሱስ ለሰውየው በራሱ ሁለት እግሮች ቆሞ የሚሄድበትንና በራሱ አእምሮ ማሰብ የሚችልበትን ሕይወት ሊሰጠው አቀረበለት።
ሰውየው ኢሱስን ካገኘ በኋላ ሁኔታው እንዴት እንሚለወጥ አስተውሉ።
አልጋው እንዲሸመው የአልጋ ቁራኛ ነበረ። አሁን ግን እርሱ አልጋውን ተሸከመው።
ቤተክርስቲያን እንድታስብለትና ወደ እግዚአብሔር ፊት ታቀርበው ዘንድ በቤተክርስቲያን ላይ ጥገኛ ነበረ። አሁን ግን በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የራሱን ሃሳብ ወደ እግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ቻለ።
በሌላ አነጋገር በራሱ አእምሮ ማሰብ ቻለ ማለት ነው። ከኢየሱስ ሕይወት እና መገለጥ መቀበል ቻለ።
ዮሐንስ 5፡9 ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ።
ስለዚህ ከኢየሱስ በግል የመዳን ልምምድን መቀበሉ ሰውየውን በቤተክርስቲያን ላይ በነበረው ጥገኝነት እና በሌሎች ላይ ከሚደገፍበት ባርነት ነጻ አወጣው።
አንድን ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመከታተል ኢየሱስ በራሳችሁ አእምሮ ማሰብ ሲያስችላችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካንነት በራሳችሁ አእምሮ እንድታስቡ ከማይፈልጉ የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ያጣላችኋል። እነርሱ ላዘጋጇቸው ሰው ሰራሽ ልማዶች እና ትዕዛዛት ተገዢዎች እንድትሆኑ ይፈልጋሉ። ታስተውሉ ዘንድ ኢየሱስ አእምሮዋችሁን ሲከፍትላችሁ የተረዳችሁትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ይቃወማሉ።
ዮሐንስ 5፡10 ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው፦ ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።
የሐይማኖት መሪዎች ከሰንበት ሥርዓታቸው ጋር ተጣብቀው ቀርተዋል።
ልማዳዊ የሐይማኖት ሥርዓቶች የቤተክርስቲያን አንቀሳቃሽ ኃይሎች ናቸው።
የተለመደው ነገር ልማድን በመጽሐፍ ቅዱስ ሳይመረምሩ እንዲሁ መከተል ነው።
የሐይማኖት መሪ “በእኔ መንገድ አድርጉ፤ አለበለዚያ” ይላል።
“የእኛ ቤተክርስቲያን እንደዚህ አይደለም የምታደርገው። እኛ የምናምነው እንዲህ አይደለም”።
ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሆን የቤተክርስቲያንን ልማድ ይታዘዛሉ።
ዮሐንስ 5፡11 እርሱ ግን፦ ያዳነኝ ያ ሰው፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
ሰውየው ኢየሱስን እየታዘዝኩ ነኝ የእግዚአብሔርን ቃል እየታዘዝኩ ነኝ ብሎ ተከራከረ።
ለምሳሌ የቤተክርስቲያን መሪዎች እግር የማጠብ ሥነ ሥርዓት አያከናውኑም። እግር የማጠብ ሥነ ሥርዓት የትሕትና ምሳሌ ብቻ ነው ወይም ወደ ቤት ስትገቡ ከእግራችሁ ላይ አቧራ ለማራገፍ ቆሻሻ ይዞ ወደ ቤት ላለማስገባት የሚደረግ ነገር ብቻ ነው ይላሉ። ነገር ግን ኢየሱስ እግር ያጠበው ከእራት በኋላ ስለሆነ ሳይታጠቡ ወደ ቤት ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው።
ደግሞም ኢየሱስ ምን እያደረገ እንደነበረ በሰዓቱ ጴጥሮስ ሊያስተውል እንደማይችልም ተናግሮ ነበረ።
ጴጥሮስ ግን ስለ ትሕትና እና የእግርን ቆሻሻ ስለማጠብ በደምብ ያውቅ ነበር።
ዮሐንስ 13፡6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
ዮሐንስ 13፡7 ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች እግር ማጠብ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አያውቁም፤ ስለዚህም አያደርጉትም።
ደግሞም እንጀራ የመቁረሱን ሥነ ሥርዓት (የሕብረት የአንድነት ገዜ የሚሉትን) ኢየሱስ ከመሸ በኋላ ስላደረገው የጌታ እራት እያሉ ቢጠሩትም እነርሱ ግን በጠዋት ይፈጽሙታል።
የቤተክርስቲያን መሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እንደፈለጉ ያፈነግጣሉ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በትክክል ማመን እና በፍጹም ልብ የኢየሱስን ምሳሌ መከተል የሚፈልግ ሰውን እንደ ጠላት ይቃወሙታል።
ዮሐንስ 5፡12 እነርሱም፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰው ማን ነው? ብለው ጠየቁት።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ማን እንደሆነ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ኢየሱስን የሚያዩት እንደ አንድ ሰው እና የመለኮት ሁለተኛ አካል እንደሆነ ነው።
ድንግዝግዝ በሆነው የሥላሴ ቲዎሪያቸው ኢየሱስን አንዳንድ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ያዩታል በተለይም በእርሱ ላይ ብቻ ያተኮሩ ጊዜ። ሌላ ጊዜ ደግሞ የመለኮት ሁለተኛ አካል አድርገው ያዩታል በተለይም በሥላሴ ውስጥ ባሉት በሶስቱም አካላት ላይ ያተኮሩ ጊዜ።
ዮሐንስ 5፡13 ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም።
ሥላሴ ሰዎች ኢየሱስን በትክክል እንዳያውቁ አደረጋቸው። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከእግዚአብሔር አብ የሚያንስ የሥላሴ ሁለተኛ አካል ነው።
ሆኖም ግን ኢየሱስ “ከእግዚአብሔር አብ” ጋር እኩል ተብሎ ነው የሚታሰበው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እርሱን “እግዚአብሔር ወልድ” ብሎት አያውቅም።
ብሉይ ኪዳን አንድም ጊዜ “እግዚአብሔር አብ” አይልም። በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ይህ ለምን እንደሆነ ማብራራት አይችሉም።
ዮሐንስ 14፡28 … ከእኔ አብ ይበልጣልና
የሥላሴ ትምሕርት ግን ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ነው ይላል።
ስለዚህ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ማንነት ግራ ቢጋቡ አየስደንቅም።
ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ወይስ የመለኮት ሁለተኛ አካል ነው?
ሶስተኛው የጴርጋሞን ቤተክርስቲያን ዘመን ስለ በለዓም ይናገራል፤ እርሱም አይሁዶች ከሞዓብ ሴቶች ጋር እንዲሴስኑ ያደረገ ሐሰተኛ ነብይ ነው። እነዚህ ሴቶች የአብራሐም የወንድም ልጅ የነበረው የሎጥ የልጅ ልጆች እንደመሆናቸው ለአይሁድ ሕዝብ የቅርብ ዘመዶች ነበሩ። ሞዓብ ግን የሎጥ ሕገወጥ ልጅ ነው።
ሮም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን ዲኖሚኔሽናል ሐይማኖት አስፋፋች፤ እርሱም ብዙ ሰዎች የተሳቡባቸውን የተሳሳቱ ቤተክርስቲያኖች ፈለፈለ። ዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያኖች ለእውነት ቅርብ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስንም ያነብባሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ሕገወጥ እምነቶች አሉዋቸው። ደግሞም የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይለውጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በራሱ እንደሚቃረንና የተሳሳቱ ትርጉሞች እንዳሉበት ያምናሉ። ዘፍጥረት በአፈ ታሪክ እንደሚጀምር እና በቢግ ባንግ ቲዎሪ እንዲሁም በኤቮልዩሽን ቲዎሪ ያምናሉ። የሳይንቲስቶችን ወሬ ሰምተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያላቸውን እምነት ይጥላሉ። እነዚህ ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች በኢየሱስ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ናቸው ምክንያቱም ኢየሱስ ቃሉ ነው። ቃሉን በመተቸታቸው እምነታቸው ሕገወጥ ይሆናል።
ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የኒቆላውያንን ትምሕርት ወለደ፤ ይህም ሕዝቡን ወይም ጉባኤውን መግዛት ነው።
የኒቆላውያን ትምሕርት አንድን ቅዱስ ሰው በቤተክርስቲያን ላይ ከፍ ማድረግ ነው። ይህን ዓይነቱን የሰው አመራር እግዚአብሔር ይጠላዋል። ኢየሱስ ካዳናችሁ በኋላ የአንድ ቤተክርስቲያን አባል ትሆኑና ለእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን ለሰው ተገዢ ትሆናላችሁ።
ብዙውን ጊዜ ፓስተር ወይም ካሕን የሆነው የቤተክርስቲያን መሪ እንዲህ ይላል፡- “ምን ማድረግ እና ማመን እንዳለባችሁ እነግራችኋለው፤ የናንተም ሥራ ለእኔ መታዘዝ ነው”።
የተፈወሰው ሰውዬ በፊት ከተማረው ትምሕርት የተነሳ ሮጦ ወደ ሐይማኖት መሪዎች መሄድ እንዳለበት ይሰማዋል፤ እነርሱ ግን ከመጀመሪያውም ምንም ሊያደርጉለት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው።
ዮሐንስ 5፡14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።
ሰውየው ለሐይማኖት መሪዎች ለመናገር ወደ ቤተመቅደሱ በሩጫ ተመልሶ ሄደ፤ ስለዚህ በግሉ መዳኑን አልተረዳም (ማርቲን ሉተር በኋላ በተሃድሶ ለቤተክርስቲያን የመለሰላ እውቀት ይህ ነው) ደግሞም የቄሶቹ እርዳታ የሚያስፈልገው መስሎታል። ለራሱ በራሱ አእምሮ ማሰብ አልቻለም። ካሕናቱ ግን ሰውን በሰንበት ለመፈወስ እሺ አይሉም ምክንያቱም በሌሎች ቀናትም ቢሆን መፈውስ አይችሉም። የተፈወሰውን ሰውዬ እንደ ጠላት አዩት ምክንያቱም የኢየሱስን ማዳን በግሉ ተለማምዷል።
የተፈወሰው ሰውዬ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ሕብረት ልምምድ የለውም፤ ስለዚህ የሚረዳው ሰው በጣም ይፈልጋል። ለዚህ ነው ወደ ካሕናቱ ተመልሶ የሄደው፤ እነርሱ ግን በድን በሆኑ ሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ ሥርዓታቸው አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖረው የሚችለውን ሕብረት ያጠፉበት ናቸው። ሆኖም ግን እርሱም ልክ እንደ ሌሎች የታለሉ ሰዎች ሁሉ በሰዎች ላይ ተደግፎ በመኖር ደስተኛ ነው። በራሱ አእምሮ ማሰብና በራሱ እግር መቆም ለእርሱ ከባድ ሃላፊነት ሆኖበታል። በራሱ መቆም ለእርሱ ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነገር ስለሆነ በቤተክርስቲያኖች ልማድ ውስጥ እንደተማረው ዝም ብሎ ሕዝብ እንደሆነው መሆንን ከለመደበት ስንፍና ይለያል።
ኢየሱስ ለሰውየው ተገለጠለትና ሁለተኛ ሐጥያት እንዳይሰራ ነገረው። ይህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከግሪኮች ፍልስፍና፣ ከሮማውያን ፖለቲካዊ ሥልጣን እንዲሁም ከአረማውያን ልማዶች እና እምነቶች ጋር እየሴሰነች ሕዝብን በማታለል የተጠመደችበት ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው።
አንድ አምላክ በሶስት አካላት የግሪክ ፍልስፍና ነው እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት አይደለም።
በጣም ብዙ ሐጥያት ወደ ቤተክርስቲያን እየገባ ነበር።
ባርቤርያውያን የሮማ መንግስትን ማፈራረስ ሲጀምሩ የካቶሊክ ፖፕ በምዕራባዊ ባርቤሪያውያን ላይ የፖለቲካ ሥልጣን መቆናጠጥ የሚችልበትን ዕድል ተመለከተ።
ዮሐንስ 5፡15 ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ በይፋ የቤተክርስቲያንን ፈቃድ ሳይጠይቅ ሕዝቡን ማዳን እና መፈወስ እንደሚችል አወቁ።
ዮሐንስ 5፡16 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ በቤታቸው የተገኘባቸውንና የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ያመኑ ሰዎችን እያሳደደች መግደል ጀመረች። የሮማ ካቶሊክ ቄሶች መጽሐፍ ቅዱስን ይቃወሙ ነበረ፤ ሊያጠፉትም ይፈልጉ ነበር። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነቡ ማድረጊያ ጥሩ ዘዴ የተገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ላቲን ቋንቋ የተተረጎመ ጊዜ ነው ምክንያቱም ሕዝቡ የላቲን ቋንቋ አያውቁም።
ቄሶቹ በላቲን ይሰብኩ ነበረ፤ ከዚህ የተነሳ ተራው ሕዝብ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ጋር ተራራቀ።
ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ በመንፈስ አንካሳ ሆኑ። እውነትን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ጥቅሶች አማካኝነት መከታተል አልቻሉም ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ አልበራቸውም።
ሕዝቡ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመለየት ፈንታ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተገዥዎች ሆነው ቀሩ።
ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታቸው ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ እነርሱም ወደ መንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ወረዱ።