ዮሐንስ ምዕራፍ 16. ወደ እውነት ሁሉ መመራት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማስረጃ ነው።
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 16፡1 እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።
ኢየሱስ ሐይማኖተኛ ሰዎች ለእውነት ያላቸውን ከባድ ጥላቻ በተመለከተ ለደቀመዛሙርቱ ማስጠንቀቂያ እየሰጣቸው ነው።
በዚያ ሰዓት ስለ አይሁድ ሲነግራቸው በምኩራብ ውስጥ ካሉት ሰዎች አንጻር ነው። ምክንያቱም እነርሱ በዚያ ሰዓት ሊገባቸው የሚችለው በዚያ መንገድ ሲነግራቸው ነው።
ከዚያ በኋላ ስለምትመጣው የአሕዛብ ቤተክርስቲያን አንዳችም አያውቁም ነበር።
ነገር ግን ታሪክ እራሱን ይደግማል።
አይሁዶች ደቀመዛሙርቱን በጣም የሚቃወሙዋቸው ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ስላመኑ ነው።
ከዚያ በኋላ በሚመጡ ዘመናት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በሚያምኑ ክርስቲያኖች ላይ ቤተክርስቲያን ከሚመላለሱ የቤተክርስቲያናዊነት አባላት ዘንድ ከባድ ጥላቻ ይሰነዘራል።
ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን እንደ ሰው ያውቁታል። እኛ ደግሞ ኢየሱስን የምናውቀው እንደ ተገለጠው ቃል ነው። ኢየሱስ በሰው መልክም በቃሉም ሲገለጥ እኩል ተጠልቷል።
ፌዝ፣ ጥላቻ፣ እና ከቤተክርስቲያን መባረር መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ማመን አለብን በሚሉ ሰዎች ላይ ሲሰነዘር የቆየ ጥቃት ነው። ኢየሱስንም እንደዚሁ ነው ያደረጉበት።
ኢየሱስ አስቀድሞ ያስጠነቀቃቸው ስደት በመጣባቸው ጊዜ እንዳይደናገጡ ነው።
ዮሐንስ 16፡2 ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
ደቀመዛሙርቱን ምኩራብ ውስጥ ያሉት አይሁዶች አሳደዋቸዋል።
ከሐዋርያው ዮሐንስ በቀር ሁሉም ሐዋርያት ገድለዋል። ሐዋርያው ቶማስ የተገደለው ሕንድ ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ብራሕሚኖች ነው። ሐዋርያው ማቴዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የተገደለው ተብሎ ይታመናል።
በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ እነርሱም በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተገድለዋል። ሐይማኖታዊ ጦርነቶች ተደርገዋል። በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተገዛችው አውሮፓ ውስጥ ካቶሊክ ያልሆኑ ሰዎችን በእግዚአብሔር ስም መግደል እንደ ጽድቅ ተደርጎ ይቆጠር ነበር።
ይህ አስተሳሰብ ፓለስታይን ውስጥ አውሮፓውያን ሙስሊሞችን የገደሉበትን የመስቀል ዘመቻ አስከተለ። ሙስሊሞችን መግደል የዘላለም ሕይወት የሚገኝበት መንገድ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ዛሬ የሙስሊም ጂሃዲስት ተዋጊዎች ክርስቲያኖችን መግደል ገነት በግቢያ መንገድ ነው ብለው ያምናሉ። አላህ ታላቅ ነው ብለው እየጮሁ ይገድላሉ። ስለዚህ አሸባሪነት እንደ ቫይረስ መልኩን እየለወጠ ይመጣል።
ዮሐንስ 16፡3 ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።
የእግዚአብሔር ጥልቅ ሃሳቦች አባት ይባላሉ። እነዚህ ሃሳቦች እንደ ቃሉ ሆነው ሲገለጡ ወልድ ወይም ልጁ ይባላሉ።
ሐዋርያትን መግደል ትክክል እደለም ምክንያቱም ሐዋርያትን የገደሉ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንፈስ ሃሳብ አላወቁም። ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስንም አላወቁትም።
እግዚአብሔር ጥልቅ ሃሳቦቹን የገለጠው በቃሉ ውስጥ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ እግዚአብሔር ምን እያሰበ እንደነበረ ካልገለጠልን በቀር በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በሚስጥር የተቆለፉት ቃሎች ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት አንችልም።
ዛሬ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ጥቅሶችን አንቀበልም ሲሉ ሐዋርያቱ በሕዝቡ ላይ ሊኖራቸው የሚችሉትን ተጽኖ እየተከላከሉ ነው። ሐዋርያት አዲስ ኪዳንን ጽፈዋል።
ዛሬ የሕዝቡ ትኩረት ሰዎችን ለማስደነቅ ትልቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችን መስራት ላይ ነው። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች የተመሰረቱት በከፊል በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ሲሆን በከፊል ደግሞ በሰዎች አመለካከት ላይ ነው። ቤተክርስቲያኖች በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ስለሚናፍቁ መዝናኛ ያዘጋጃሉ፤ በተለይም ዲስኮ ሙዚቃ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንድንመራ እንደሚፈልግ አላወቁም። ድራም የሚባለው የሙዚቃ መሳሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዴም አልተጠቀሰም።
ትኩረታችን መሆን ያለበት የተገለጠውን ቃል መገለጥ ማግኘት ላይ ነው። በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲገለጥልን ይፈልጋል።
ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የእግዚአብሔርን (የአብን) ሃሳብ አያውቁም፤ ለዛሬ ያለውን እቅዱንም አያውቁም። ይህም የእግዚአብሔር ሃሳብ ሰዎች ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት እንዲመለሱ ነው። ደግሞ ቃሉ (ልጁ) የመጨረሻዋ ዘመን የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን በክህደት ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቅ ውስጥ መሆኗንም አያውቁም። እያንዳንዷ የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ምንም ችግር እንደሌለባት አድርጋ ነው የምታስበው።
ዮሐንስ 16፡4 ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።
ኢየሱስ እነርሱንም እኛንም አስቀድሞ እያስጠነቀቀ ነበር።
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሊሆን ያለውን ከመሆኑ በፊት ነው የሚገልጠው።
ወደ ስቅለት ያመራው አጋንንታዊ ጥቃት የጀመረ ጊዜ ሰይጣን ከደቀመዛሙርቱ ጋር የነበረው ኢየሱስ ላይ ጥቃት ሰነዘረበት። ሰይጣን ሃሳቡ በሙሉ ኢየሱስን ማጥፋት ላይ ስለነበረ በፍርሃት ሲርበደበዱ የነበሩት ደቀመዛሙርት ኋላ ምንም የማያመጡ መስሎት ቸል አላቸው። ከዚህም የተነሳ ተንጋግተው የመጡት ሕዝብ ሐዋርያቱን ምንም አላደረጉዋቸውም። ነገር ግን በቀላሉ ሊገድሉዋቸው ይችሉ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ከሰይጣን የተሰነዘረውን ጥቃት ሙሉ በሙሉ በራሱ ላይ በመቀበሉ ሐዋርያቱን አድኗቸዋል።
ከጴንጤ ቆስጤ ቀን በኋላ ግን እነዚህ ከጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ሸሽተው የጠፉ ፈሪ ሐዋርያት በፍጹም የማይሸነፉ አደገኛ መንፈሳዊ ወታደሮች ሆነው መለወጣቸውን ሲያይ እነርሱን ቀድሞ አለማጥፋቱ ቆጨው።
ከዚያ በኋላ ሰይጣን የአይሁዶችን እና የሮማውያንን ጥላቻ በደቀመዛሙርቱ ላይ እንዲሆን አደረገ። ደቀመዛሙርቱ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ሐዋርያት ተብለው ነበር የሚታወቁት። ወንጌሉ እየተሰራጨ ሲሄድ ሰይጣን የአሕዛብ ሕዝቦችን በሐዋርያት ላይ አስነሳባቸው። ዓመታት ሲያልፉ ቀስ በቀስ ሐዋርያት በሙሉ ተገድለው አለቁ። ነገር ግን የእነዚህ ሰማዕታት ደም ቤተክርስቲያን የምታድግበት ማዳበሪያ ሆነ።
በሮማውያን ነገሥታት ብቻ ሶስት ሚሊዮን ክርስቲያኖች ተገድለዋል።
ከዚያ በኋላ በጨለማው ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ተገድለዋል።
ኢየሱስ አስቀድሞ እንዳስጠነቀቃቸው ክርስትና እና የግፍ ሞት የማይነጣጠሉ ናቸው። ነገር ግን የሚሞቱት ክርስቲያኖች ኢየሱስ አስቀድሞ በሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ውስጥ የሚያጽናና መልእክትም ተሰጥቷቸዋል። አካላቸው ሊሞት ይችላል፤ ነፍሳቸው ግን ምንም አይሆንም።
ዮሐንስ 16፡5 አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
ኢየሱስ ወደ ሞት እየሄደ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ ፈቃድ ነው። ኢየሱስ ባይሞት ክርስትና የሚባል ነገር አይኖርም ነበር። ሞት ማለት መንፈስ ከሥጋ ተለይቶ ሲሄድ ነው። ይህም የሰው መንፈስ ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ ነጻ ያደርገዋል።
እራት አብቅቷል። ሰዓቱም በጣም እየመሸ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ከመሸ በኋላ ወዲያ ወዲህ ሲሄድ አይተው ባያውቁም እንኳ ከደቀመዛሙርቱ አንዳቸውም ወዴት እንደሚሄድ አልጠየቁትም።
ዮሐንስ 16፡6 ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።
ኢየሱስ ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮች ደቀመዛሙርቱን አስጠንቅቋቸዋል። ተመችቶን የምንኖርበትን ቦታ የሚረብሽ ነገር ሲመጣ እኛ ሰዎች እንጨነቃለን፤ እንፈራለን፤ እናዝናለን። የለመድነው ቦታ ውስጥ ተቀምጠን መቅረት እንወዳለን።
ሐዋርያቱ ጥቁር ደመና እየመጣ መሆኑን እና ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እየወጡ መሆናቸውን አውቀዋል። ስለዚህ እያዘኑ ነበር።
ዮሐንስ 16፡7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
ኢየሱስ መሄድ ነበረበት። የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ውስጥ ሆኖ ለሠላሳ ሶስት ዓመታት በምድር ላይ በመኖር ሰብዓዊ ባሕርያትን አዳብሯል። ስለዚህ አሁን ሰዎችን ከሐጥያት ለማዳን እንደ ሰው ሆኖ መሞት አለበት።
ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በከፊል ተመልሶ በመምጣት የሰውንም የመለኮትንም ባህርያት በአንድነት ይዞ በግለሰቦች ልብ ውስጥ በመግባት መኖር ይችላል።
መለኮታዊ የሆነው ባህርይ ከእግዚአብሔር ቃል በስተጀርባ ያለውን የእግዚአብሔር አስተሳሰብ እንድናስተውል አእምሮዋችንን ይከፍተዋል።
ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው የመንፈስ ቅዱስ መጠን እና በውስጡ የያዘው ሰብዓዊ ባሕርይ እንድን ሰው እግዚአብሔር የሚፈልገው ዓይነት ሰው እንዲሆን ይለውጠዋል።
ለእኛ መጽናኛ የሚሆነን ነገር እግዚአብሔርን በራሳችን አቅም እንድናገለግለው አለመጠየቃችንን ማወቅ ነው፤ ምክንያቱም ብንሞክረውም አይሳካልንም። ደግሞም ሰብዓዊ መሃይምነታችንም የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ ማወቅ አይችልም።
እግዚአብሔር በመለኮታዊ ኃይሉ አእምሮዋችንን ያበራዋል፤ ደግሞም የእግዚአብሔር ሰብዓዊ ባሕርዩ ሐጥያተኛው ባሕሪያችንን ይተካዋል።
የእርሱ ሰብዓዊነት እኛን ሆኖ ስለሚኖር ይህ እርሱን የምናገለግልበት ብርታት ይሰጠናል።
ኢየሱስ የሰይጣንን ቁጣ በሙሉ በራሱ ላይ በመቀበል ደቀመዛሙርቱን እንዳዳናቸው ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ ሕይወታችንን በመቀበልና በእኛ ውስጥ በመኖር እኛን ያድነናል።
ሰይጣን እኛን ለማጥቃት ይመጣል ግን ሲመጣ በውስጣችን ከሚኖረው ኢየሱስ ጋር ነው የሚጣላው። ይህ ለእኛ ትልቅ መጽናናት ነው። ምንም ይምጣ ምን ኢየሱስ ሁሌ ያሸንፋል።
ቆላስይስ 1፡27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።
ክርስቲያኖች ማሸነፍ የሚችሉት ክርስቶስ በልባቸው እንዲኖርና እንዲቆጣጠራቸው፤ እንዲመራቸው እንዲሁም የሰይጣንን ጥቃቶች እንዲያሸንፍ ሲፈቅዱለት ብቻ ነው።
ዮሐንስ 16፡8 እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤
ዮሐንስ 16፡9 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤
አያምኑም። የእነርሱ ሐጥያት አለማመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ነገርን አለማመን የሐጥያት መሰረት ነው።
በልባችን ውስጥ አለማመን ካለ ሐጥያትን እንድንፈጽም ያደርገናል።
ለምሳሌ እንሰርቃለን (ይህ የሐጥያት ድርጊት ነው) የምንሰርቀውም ስለማናምን ነው (እርሱም የሐጥያት መንስኤ ነው)።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ መጽሐፍ ቅዱስን እንድናምን ያስተምረናል።
ዮሐንስ 16፡10 ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤
ዘፍጥረት 15፡6 አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።
አብራሐም በእግዚአብሔር ቃል አመነ። የአብራሐም ጽድቅ ይህ ነው።
ዘዳግም 33፡19 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤
በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ።
በቀራንዮ ተራራ ላይ ኢየሱስ የጽድቅን መስዋእት አቀረበ። ሰው ከሐጥያቱ ይቅር የሚባለውና ጽድቅን የሚያገኘው በመስቀሉ ስር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 16፡11 ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።
ቀራንዮ የመጨረሻው የሐጥያት ፍርድ ነው። ኢየሱስ ለእያንዳንዳችን ሙሉውን ዋጋ ከፍሏል። ከዚህ በኋላ የሚከፈል ሌላ ክፍያ የለም።
እኛ ማድረግ የምንችለው ነገር ንሰሃ መግባት እና እርሱ የከፈለልንን ይቅርታ መቀበል ብቻ ነው።
የራሳችን ሥራ በምንም መንገድ የሐጥያት ይቅርታን ሊገዛልን አይችልም።
ኤፌሶን 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
በእግዚአብሔር ለማመን የሚያስፈልገን እምነት ከእግዚአብሔር ነው የሚሰጠን።
ኤፌሶን 2፡9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ስለዚህ ከሐጥያት መዳን በእኛ ጥረት የሚመጣ ነገር አይደለም።
ኢየሱስ ሙሉውን ዋጋ በመስቀል ላይ ከፍሎታል። ይህንን በማድረግ ሙሉ በሙሉ ከፈሰሰው የሰይጣን ጥቃት እኛን ታድጎናል፤ አለዚያ እንጠፋ ነበር።
ኢየሱስ የእኛ ዳዊት ነው፤ ስለዚህ የሞትን፣ የሲኦልን፣ እና የመቃብርን ጎልያድ ተጋፍጦልናል። ከዚያ በተጨማሪ የሲኦልን አጋንንታዊ ሰራዊት ሁሉ ተጋፍጦልናል።
በጎልያድ ግንባር ላይ አንድ ጠጠር በመወርወር የአለማመንን ጦርነት አሸንፎታል። በሥላሴ ለሚያምኑ ሰዎች አእምሮ አንድ ጥያቄ እናቅርብ።
“የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማነው?”
በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች መልስ የላቸውም። ለሶስት አካላት የሚሆን አንድ ስም ማምጣት አይችሉም።
ሥላሴያዊው አምላክ ስም የለውም።
ስለዚህ እውነተኛ አምላክ ሊሆን አይችልም።
ዮሐንስ 16፡12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።
የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ ሙሉ በሙሉ መፈጸም ነበረበት።
አይሁውያንም ወንጌሉ ለአሕዛብ መድረስ እንዳለበት መማር አለባቸው።
ደቀመዛሙርቱ ከዓመታት በኋላ የሚማሩት ብዙ ነገር ነበረ።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማስረጃው ይህ ነው።
መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ይገልጥልናል።
“ከራሱ አይናገረም።” ልክ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስ ትኩረት የሚሰጠው ሰዎችን ሁሉ ወደ ኢየሱስ ለመጠቆም ነው።
ሰባኪዎች ከዚህ መማር ይችላሉ። የራሳቸውን ታላቅነት ለማስተዋወቅ መሯሯጥ የለባቸውም። ወደ ኢየሱስ ብቻ ነው መጠቆም ያለባቸው።
“የሚመጣውንም ይነግራችኋል”። መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል መተርጎም ከለመድን አንዳንድ ክስተቶች እየተፈጸሙ ሳለ ምን ማለት እንደሆኑ ማወቅ እንችላለን።
ሒላሪ ክሊንተን የ2016ቱን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታሸንፋለች ሲሉ የነበሩ ሰባኪዎች በእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልተመሩ በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን።
እነዚህ ክስተቶች እግዚአብሔር ከማን ጋር እየሰራ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ የማስጠንቀቂያ ደወሎች ናቸው።
ዮሐንስ 16፡14 እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።
መንፈስ ቅዱስ ትኩረት የሚያደርገው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ነው እንጂ በሌላ ሰው ላይ አይደለም።
ክርስቶስ ብቻ ነው መክበር የሚገባው። የትኛውም ነብይ የእርሱን ክብር መካፈል አይችልም።
ኢሳይያስ 42፡8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ … አልሰጥም።
ነብይ መገለጥን መቀበል የሚችለው ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ይህንን መገለጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አማካኝነት እንዴት ልንከታተለው እንደምንችል ሊያሳየን ይገባል። እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከሌሎች ጥቅሶች አንጻር መብራራት አለበት።
ዮሐንስ 16፡15 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።
በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ያሉት መገለጦች በሙሉ በቃሉ ውስጥ አሉ፤ እርሱም ኢየሱስ ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የሆነው አብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ይወስዳቸውና የተሰወረውን ትርጉማቸውን ይገልጣል።
ማቴዎስ 1፡20 … ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና…
በእናት ማሕጸን ውስጥ ዘር ያስቀመጠ ማንኛውም ሰው የሕጻኑ አባት ነው። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አባት ነው።
ኢየሱስ እንደ ሰው ሕጻን ሆኖ ሁለት አባቶች ሊኖሩት አይችልም።
ዮሐንስ 16፡16 ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
ይህ አስደንጋጭ አነጋገር ነው። አታዩኝም። ከዚያ ታዩኛላችሁ።
ይህ የሆነው ሁለት ጊዜ ነው።
ሲሞት ከአጠገባቸው ዞር አለ። ከዚያ በኋላ ከሙታን ተነስቶ ሕያው ሆነ።
ቀጥሎ ደግሞ እንደ ሰው ወደ ሰማይ አረገ እና ከዚያ በኋላ እንደገና አላዩትም። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መጻሐፍትን ሲጽፉ በእግዚአብሔር ቃል መልክ አይተውታል።
ስለዚህ እንደ ሰው በአካል ያዩት ሐዋርያት ከዚያ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ ነው የሚያዩት። ስለ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የጻፉት በሙሉ ሌሎች ሰዎችም ኢየሱስን በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ ሲመላለስ እንዲያዩት ረድቷቸዋል።
የአዲስ ኪዳንም የብሉይ ኪዳንም ትኩረት ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 16፡17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው፦ ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፤ ደግሞ፦ ወደ አብ እሄዳለሁና የሚለን ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ።
በዚያ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ አልገባቸውም ነበር።
ኢየሱስ እንደ ሰው ከእነርሱ ተለይቶ ሄደ፤ ይህንንም ያደረገው መንፈሱ (ማለትም አብ) ተመልሶ መጥቶ በእነርሱ ውስጥ መኖር ይችል ዘንድ ነው።
ዮሐንስ 14፡18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
አጽናኙ ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 16፡18 እንግዲህ፦ ጥቂት የሚለው ይህ ምንድር ነው? የሚናገረውን አናውቅም አሉ።
ደቀመዛሙርቱ በጣም ግራ ተጋብተዋል። ሰዎች የእግዚአብሔርን እቅድ መርምረው ሊደርሱበት አይችሉም።
ዮሐንስ 16፡19 ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ ስላልሁ፥ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?
ዮሐንስ 16፡20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
ኢየሱስ ሊሞት ነው። ደቀመዛሙርቱ በሐዘን ያለቅሳሉ። አይሁዶች ግን ኢየሱስን ገደልነው ብለው ይደሰታሉ።
ከዚያ በኋላ ግን ትንሳኤው እና የጴንጤ ቆስጤ ቀን ይመጣል። የዚያን ጊዜ ደግሞ ሐዋርያቱ ይደሰታሉ።
ዮሐንስ 16፡21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።
ሕጻን ልጅ ከተወለደ በኋላ ሴት ምጧን ትረሳለች።
በበዓለመ ሃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወደ እነርሱ ውስጥ ሲገባ ደቀመዛሙርቱ ዳግመኛ ተወለዱ፤ ከዚያም በኋላ በፊት የነበረባቸውን ውድቀት እና ፍርሃት በሙሉ ረሱ።
ዮሐንስ 16፡22 እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።
ኢየሱስ በመሰቀሉ ምክንያት የመጣው ሐዘን ጊዜያዊ ነበረ። ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኋላ እንደገና ያገኛቸዋል፤ እንደዚያም ሆኖ ግን ከእነርሱ ውጭ የሆነ የተለየ ሰው ነው የሚሆነው።
ስለዚህ ሐዋርያቱ ኢየሱስን የእውነት የሚያገኙት በጴንጤ ቆስጤ ቀን እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ በመምጣት ወደ ውስጣቸው በገባ ጊዜ ነው።
ከዚያ በኋላ ክርስቶስ ሊመራቸው እና ቃሉን ሊገልጥላቸው በውስጣቸው ይኖራል።
ዮሐንስ 16፡23 በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
ከዚያ ወዲያ ከእነርሱ ውጭ እንደሚኖር እንደ ሌላ ሰው አያናግሩትም። በውስጣቸው የሚኖረውን መንፈስ ቅዱስ (አብን) የጠየቁት ነገር ሁሉ ይሰጣቸዋል። ምክንያቱም ምን መጠየቅ እንዳለባቸው እንኳ የሚመራቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር እና ሰው ተዋሕደው አንድ ይሆናሉ።
ዮሐንስ 16፡24 እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።
እስከ አሁን ድረስ እንደ ደቀመዛሙርት ስትማሩ ቆይታችኋል። ነገር ግን እኔ ከሞትኩ እና ወደ ሰማይ ከሄድኩ በኋላ እናንተ ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን መመስረት ትጀምራላችሁ። ኢየሱስ ለዚያ ትልቅ ሥራ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ያቀርብላቸዋል።
ዮሐንስ 16፡25 ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል።
በዚህ ሰዓት ደቀመዛሙርቱ እግዚአብሔር ምን ሊያደርግ እንዳቀደ የማያውቁበት ጊዜ ነበር።
መንፈስ ቅዱስ ወደ እነርሱ ውስጥ ከገባ በኋላ የዛኔ መረዳት ይጀምራሉ።
ይህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የእግዚአብሔርን ቃል እንድናስተውል ነው የሚያደርገን።
ዮሐንስ 16፡26 በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤
መንፈስ ቅዱስ ውስጣቸው ከገባ በኋላ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ሕብረት ይኖራቸዋል ምክንያቱም እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
ዮሐንስ 16፡27 እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና።
የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ ሃሳብ የተመረጠ ቃል መሆኑን ማመን አለብን። ቃሉን (ኢየሱስን) መውደድ አለብን፤ ደግሞም የተጻፈው በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ሃሳብ መሪነት የተጻፈ መሆኑን ማመን አለብን።
አንዳችም ስሕተት የለም፤ እርስ በርሱ የሚጋጭ ሃሳብ የለም፤ የተሳሳተ ትርጓሜም የለም፤ ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይጠቅም ዝርዝር ሃሳብ የለም።
ዮሐንስ 16፡28 ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።
29 ደቀ መዛሙርቱ፦ እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ በምሳሌም ምንም አትነግርም።
አሁን ደቀመዛሙርቱ የገባቸው መሰላቸው።
ዮሐንስ 16፡30 ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት።
አሁን ደግሞ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ነው የመጣው አሉ። ስለዚህ ከእርሱ ጎን ይቆማሉ።
ዮሐንስ 16፡31 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ አሁን ታምናላችሁን?
ኢየሱስ ማለት የፈለገው “በውኑ የቆማችሁለት እምነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?” ነው።
ዮሐንስ 16፡32 እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
“የአይሁድ መሪዎች ለተጻፈው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ እን በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ስለ መፈጸሙ ያላቸው ጥላቻ ገንፍሎ እስከሚፈስስ ብቻ ጠብቁ።
የዚያን ጊዜ ኢየሱስን ለማመን የሚበቃ ወኔ እንደሌላችሁ ታውቃላችሁ”።
በዘመን መጨረሻ ልክ እንደዚሁ ዓይነት ፈተና ይመጣል።
በጥንቃቄ የመረጡዋቸውን የሰው ንግግር ጥቅሶች እንደ ፍላጎታቸው ከሚተረጉሙ ከሜሴጅ አማኞች ዘንድ እምነታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሚገነቡ ሰዎች ላይ ብዙ ጥላቻ ይመጣል። ከዚህም የተነሳ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለመቆም ድፍረት ስለማይኖራቸው የተጻፈውን ቃል ትተው ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ ማመን አለብን ብለህ በአቋምህ ከጸናህ በሰዎች ዘንድ ትናቃለህ፤ ከሜሴጅ እና ከዲኖሚኔሽናል ቤተክርስቲያኖች ትባረራለህ።
እግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ውስጥ ይኖር የነበረው መንፈስ ነው። ይህም መንፈስ በእርሱ ውስጥ ጸንቶ ይኖራል።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን በሙሉ እየፈጸመ ነበር። የሐይማኖት መሪዎችም ከዚህ የተነሳ ጠሉት።
ዛሬም እኛ ተመሳሳይ ችግር አለብን።
በ1963 ዓ.ም ስድስቱ ማሕተሞች በዊልያም ብራንሐም ከተፈቱ ወዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ተገልጠዋል። ቤተክርስቲያኖች የተገለጡትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ይቃወማሉ። የእነርሱ ቤተክርስቲያን አባል ያልሆነ የዘመን መጨረሻ ነብይ እንዲያስተምራቸው አይፈልጉም። የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች የማሕተሞቹ መከፈት መገለጥ የማሕተሞቹ መፈታት መስሏቸው ተሳስተዋል።
ሰባተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የጌታ ምጻትን የሚመለከት ሚስጥር መሆኑ ተገልጧል፤ ስለዚህ ማሕተሙ አልተፈታም። ስለ ጌታ ምጻት ምንም አናውቅም።
1964-0719 የመለከት በዓል
እንደምታውቁት ሰባተኛው ማሕተም ገና አልተፈታም። እርሱም የጌታ ምጻት ነው።
ሰባተኛው ማሕተም ለወንድም ብራንሐም አልተፈታለትም።
የስድስተኛውን ማሕተም መገለጥ አግኝተናል፤ እርሱም በታላቁ መከራ ውስጥ የተፈጥሮ ኡደቶች መቋረጥ ነው።
ነገር ግን ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት ወደ እሥራኤል የሚላኩት ሁለቱ ነብያት ብቻ ናቸው።
ወንድም ብራንሐም ስድስተኛውን ማሕተም ፈትቻለሁ ብሎ አያውቅም።
ታላቁ መከራ በብዛት ለእርሱ ሚስጥር ሆኖበት ቀርቷል ምክንያቱም ስለ 144,000 አይሁዶች ነው የሚናገረው እንጂ ስለ አሕዛብ አይደለም።
ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ስለ መለከቶች በዓል እንዲሰብክ አልፈቀደለትም።
ደግሞም ስለ ሰባቱ ጽዋዎችም አልሰበከም።
መለከቶቹ እና ጽዋዎቹ በታላቁ መከራ ዘመን ነው የሚፈጸሙት እንጂ በቤተክርስቲያን ውስጥ አይደለም።
63-0323 ስድስተኛው ማሕተም
ምንድነው? እነዚህ ነገሮች እንዲፈጸሙ የሚያደርገው ቃሉ አይደለምን? በተፈጥሮ ላይ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ተመልከቱ። ስድስተኛው ማሕተም እንዲፈጸም የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው። ይገልጡትና ይፈቱታል። ተፈጥሮን ማስቆም የእግዚአብሔር ኃይል ነው። ተመልከቱ ስድስተኛው ማሕተም ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ መቋረጥ ነው።
አሁንስ ገብቷችኋል? ያውላችሁ ማሕተሙ። ማነው እንዲፈጸም የሚያደርገው? ከመነጠቅ በኋላ የሚመጡት ነብያት ናቸው። በእግዚአብሔር ኃይል፣ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ላይ ይፈርዳሉ። የምድር መንቀጥቀጥ እንዲመጣ ማድረግ ይችላሉ፤ ጨረቃ ወደ ደም እንድትለወጥ ማድረግ ይችላሉ፤ ፀሃይዋ የእነርሱን ትዕዛዝ ተከትላ ልትጠልቅ ወይም ያዘዙዋትን ሁሉ ልትሆን ትችላለች። አሜን።
1963-0323 ስድስተኛው ማሕተም
አሁን ተመልከቱ እነዚህን ሁለት ነብያት፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሆነው በመቆም በፍጥረት ላይ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ፤ ምድርንም ያናውጣሉ። እነዚህንም ነገሮች የሚያደርጋቸው ማን እንደሆነ ያስታውቃል። ሙሴ እና ኤልያስ ናቸው፤ ምክንያቱም የእነርሱ አገልግሎት ነው በድጋሚ በምድር ላይ የሚገለጠው፤ የሁለቱም። ገባችሁ አሁን? ስድስተኛው ማሕተም ምን እንደሆነ ገባችሁ? እነዚያ ነብያት ናቸው። አሁንም ልብ በሉ፤ አትጨነቁ፤ በዚያ ማሕተም ምን እንደመጣ ተመልከቱ፡ ነብያት። አያችሁ? አሜን። ይኸው ነው። ኦ ወንድሞቼ በንስሩ ዘመን ነው የምንኖረው፤ ራሳችንን በደመናት ውስጥ አድርገናል። ያንን ስድስተኛ ማሕተም ይፈቱታል። ይህን የማድረግ ኃይል አላቸው። አሜን። ይኸው፤ ስድስተኛው ማሕተማችሁ ሲገለጥ ተመልከቱ።
ሙሴ እና ኤልያስ ብቻ ናቸው እሥራኤልን ለመጠበቅ አውሬውን በተቃወሙ ጊዜ ተፈጥሮን በማቋረጥ ስድስተኛውን ማሕተም መፍታት የሚችሉት።
አራተኛው ማሕተም ሲፈታ ሞት በሐመር ፈረስ ላይ እየጋለበ ይወጣል። ይህ የሚፈጸመው በታላቁ መከራ ውስጥ ብቻ ነው። ስለዚህ ዓለምን የሚመራው የመጨረሻው ፖፕ ማን እንደሆነ አናውቅም። ለመጨረሻው ፖፕ ወታደራዊ ኃይላቸውን የሚያስረክቡ አስሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች እነማን እንደሆኑ አናውቅም።
ስለዚህ ከአራተኛው ማሕተም ውስጥ ይህኛው ክፍል አልተከፈተም። የሚናገረውም በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚፈጸሙ ክስተቶች ነው፤ እግዚአብሔርም እነዚህን ክስተቶች ለወንድም ብራንሐም በዝርዝር አልገለጠለትም።
ነገር ግን ቤተክርስቲያኖች ሁሉ የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ እንዲሰጠን የተላከው ወንድም ብራንሐም መሆኑን በጣም ይጠላሉ። ሰይጣንም ደግሞ የማሕተሞቹን መገለጥ የእውነትም የማሕተሞቹ መፈታት እንዲመስላቸው የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖችን አታሏቸዋል።
ከሰባቱ ማሕተሞች ስብከት ሰይጣን ሃሳቦችን ወስዶ በማጣመም ብዙ የተሳሳቱ ሃሳቦች እንዲሰራጩ አድርጓል።
ከስብከቶቹ ተወስዶ የተጻፈውን መጽሐፍ ርዕስ ልብ በሉ።
ርዕሱ የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት አይልም።
ርዕሱ የሚለው የሰባቱ ማሕተሞች መገለጥ ነው።
የሜሴጅ ቡድኖች ግን የሰባቱ ማሕተሞች መፈታት ነው በማለት በጣም ተሳስተዋል።
የማሕተሞቹን መገለጥ የማሕተሞቹ መፈታት አድርገው ወስደዋል።
የክስተቱ መገለጥ እራሱ ክስተቱ መፈጸሙ ነው ይላሉ። ይህ ሙሉ ለሙሉ ስሕተት ነው።
አሞጽ 3፡7 በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
ልክ አይሁዶች ኢየሱስን እንደተቃወሙት የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች በጽኑ የሚቃወሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይህ ነው።
ሰባቱ ማሕተሞች በሰማይ ውስጥ ከመፈታታቸው በፊት የሰባቱን ማሕተሞች መገለጥ ለመስጠት ሰባት መላእክት ወደ ምድር ወርደው ወንድም ብራንሐምን ከዘመናት መጋረጃ በስተጀርባ ወስደውት ወደፊት ስለሚፈጸሙ ነገሮች በራዕይ አሳይተውታል።
ከዚያም ወደፊት ማሕተሞቹ ሲፈቱ በራዕይ ካየ በኋላ ወደ እኛ ዘመን ተመልሶ በመምጣት እንደተፈጸሙ አድርጎ መናገር ይችላል።
ማሕተሞቹ ተፈተዋል ግን በተከታታይ ራዕዮች እና ከሰባቱ መላእክት ጋር በተደረጉ ውይይቶች ብቻ ነው። በእውነታው ወይም በገሃዱ ዓለም ግን አልተፈቱም። ያ ሁሉ የሚፈጸመው ከመነጠቅ በኋላ ነው።
ነገር ግን እርሱ የተቀበለው የማሕተሞቹ መፈታት መገለጥ ውስን ነው።
እርሱ የተቀበለው መገለጥ ወደፊት የሚከሰቱ ነገሮችን በአጠቃላይ ብቻ ነው የሚያሳየን። ሙሉ ዝርዝሮቹን አልሰጠንም። ለምሳሌ አራተኛው ማሕተም ሲፈታ እንደ ሞት በፈረስ ላይ እየጋለበ የሚመጣው የመጨረሻው ፖፕ ማን እንደሆነ አላየም። የተፈትሮ ኡደት መቋረት እሥራኤልን ከጥፋት ለመጠበቅ የሚጠቅም ኃይል መሆኑን በተግባር ሊያስረዳ አልቻለም፤ ምክንያቱም ያንን ሊያደርጉ የሚችሉት ሁለቱ አይሁዳዊ ነብያት ብቻ ናቸው።
የጌታን ምጻት አላየም። ይህም የሰባተኛው ማሕተም ሚስጥር ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ እርሱ ባየው ራዕይ ውስጥ ሙሽራይቱ በሰማይ ከዙፋኑ አጠገብ አልነበረችም፤ ነገር ግን ማሕተሞቹ ጊዜያቸው ደርሶ ሲፈቱ ሙሽራይቱ በዚያ ነው የምትገኘው።
ቁልፉ ነጥብ ሰባቱ ማሕተሞች የእውነት የሚፈቱት (በራዕይ ሳይሆን በገሃዱ ዓለም) ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከተነጠቀች በኋላ ምዕራፍ 6 ውስጥ ነው፤ ይህም በዮሐንስ ወደ ሰማይ መነጠቅ ተምሳሌትነት ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ተገልጧል።
እግዚአብሔር በ1963 የሰባቱን ማሕተሞች መፈታት ገልጧል።
ነገር ግን ማሕተሞቹ የሚፈቱት በሰማይ ሙሽራዋ ከተነጠቀች እና በራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ እንደተገለጸው በዙፋኑ አጠገብ ከሆነች በኋላ ነው።
63-0324 ስለ ማሕተሞቹ ጥያቄዎች እና መልሶች
በራዕይ ምእራፍ 5 ቁጥር 9 በጉ መጽሐፉን ሲወስድ የሚዘምሩት እነማን ናቸው? የተነጠቁት ቅዱሳን ናቸውን?
… “ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከሕዝብ ዋጅተኸናል ብለው የሚዘምሩት መዝሙር።”
ያለ ጥርጥር እነርሱ ናቸው።
ራዕይ ምዕራፍ 5 ውስጥ ያለው ክስተት ከራዕይ ምዕራፍ 4 በኋላ ነው የሚፈጸመው።
ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ምዕራፍ 1
ዮሐንስም ሲመለከት ዙፋኑ ላይ “አንድ” ብቻ ነው ያየው። በራዕይ 4፡2-3 እና 9-10 እንደምናየው በጉ መጽሐፉን በዙፋን ላይ “ከተቀመጠው” እጅ ሲወስድ የምናየው ከራዕይ 5፡6-8 በፊት አይደለም (እርሱም በጊዜ ቅደም ተከተል ራዕይ 4፡2-3ን ተከትሎ ነው የሚሆነው)።
ዮሐንስ 16፡33 በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።
ስለ እግዚአብሔር አንድ ትልቅ ሚስጥር እነሆ። እግዚአብሔር አንድ ነገር ሳይፈጸም በፊት ቀድሞ ይነግረናል። አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት ስለ ክስተቱ በቅድሚያ መገለጥ እናገኛለን።
ኢሳያስ የኢየሱስን በድንግልና መወለድ ኢየሱስ ከመወለዱ 700 ዓመታት ቀድሞ ነው ያየው።
ኢሳይያስ 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ውስጣዊ ሰላም የሚኖረን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ጸንተን ከቆምን ብቻ ነው።
ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ታላላቅ መሪዎች አሉዋቸው፤ የመሪዎቻቸውንም ጥቅሶች እንደ ባሪያ ይከተላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ካልጠቀሰልን የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞችን ይጠሉዋቸዋል።
በአሁኑ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ስም በማጥፋት ዘመቻ ላይ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም እምነቱ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት የሚሞክር ሰውን ሁሉ የሚያመጣውን ተጽእኖ ለማጥፋት ይሞክራሉ።
ነገር ግን የፈለጉትን ያህል ቢታገሉ የሜሴጅ ሰባኪዎች በ1963 የታየውን ደመና ከራዕይ ምዕራፍ 10 ጋር ሊያገጣጥሙት አይችሉም።
በዚህ ሙከራቸው የሚያገኙት ቲፎዞ ለብዙ ጊዜ አይቆይም ምክንያቱም በቲዎሪያቸው ውስጥ የሆነ ስሕተት መኖሩን ያውቃሉ። እነርሱ የሰሩት ስሕተት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አለመገንባታቸው ነው።
በጥንቃቁ በተመረጡ የሰው ንግግር ጥቅሶች ላይ በመገንባታቸው የሚገጥማቸው ትልቅ ችግር ሌሎች ጥቅሶች የእነርሱን ሃሳብ የሚያፈርሱ ሆነው መገኘታቸው ነው። ይህም ሃሳባቸው እንዲንገዳገድ ያደርገዋል። ይህም የአእምሮ ሰላም አይሰጣቸውም።
ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ ሳለ የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክ ወርዶ ነበር ብለው ያምናሉ።
ነገር ግን መልአኩ እስኪወርድ የሚጠባበቁ ሁሉ ብጹአን ናቸው። የእግዚአብሔር ቃል ጊዜውን ጠብቆ ይፈጸማል።
ሳያስተውሉ ያለፉት ነገር ደግሞ መልአኩ የሚወርደው የሙታንን ትንሳኤውን ለመፈጸም መሆኑን ነው።
በምድር እና በባሕር ላይ በመቆም በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሁሉ ውስጥ የሞቱ ቅዱሳን የተቀበሩባቸውን ቦታዎች ሁሉ ይቆጣጠራል።
ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
ራዕይ 10፡2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
ራዕይ 10፡3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
“በታላቅ ድምጽ ጮኸ”። ይህ በአላዛር ትንሳኤ ጊዜም ሆኗል።
ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።
“በጮኸም ጊዜ”።
ይህ ጩኸት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን እንዲነሱ አድርጓል።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
የ1963 ደመና ከታየ ከአንድ ዓመት በኋላ ወንድም ብራንሐም የመልአኩን መውረድ እየተጠባበቀ ነበር።
ስለዚህ ደመናው መልአኩ አልነበረም።
1964-0119 ሻሎም
ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲ+
መጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።
በመንፈሱ ውስጥ ቆዩ። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ቆዩ። ምንም ያህል ከባድ ቢሆን እንኳ ከቃሉ ጋር ጸንታችሁ ቆዩ፤ እግዚአብሔር በሚመራችሁ መንገድ ቆዩ።
65-1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን አያለው
እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።
በሕይወቱ የመጨረሻ ወር ላይ ወንድም ብራንሐም መልአኩ ወርዶ ሙታንን እንደሚያስነሳ ሲጠባበቅ ነበር።
ስለዚህ ወንድም ብራንሐም በምድር ላይ በሕይወት ሳለ መልአኩ አልወረደም።
ሙታን እስከ ዛሬ ድረስ አልተነሱም፤ ስለዚህ ይህ መልአክ አልወረደም ማለት ነው።