ዮሐንስ ምዕራፍ 15. ቤተክርስቲያንን የሚሸከማት ኢየሱስ ነው



First published on the 22nd of March 2021 — Last updated on the 22nd of March 2021

ዮሐንስ 15፡1 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።

ፍጹም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቲያኖችን የሚሸከመው እውነተኛ የወይን ግንድ እርሱ ነው።

በሚነድደው ቁጥቋጦ እግዚአብሔር ለሙሴ ሲገለጥ “እኔ ነኝ” በማለት ነበር ራሱን ያስተዋወቀው።

ዘጸአት 3፡14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው፤

ኢየሱስ ሰው ቢሆንም እንኳ ሁሉን ቻይ አምላክ መሆኑንም በአጽንኦት ይናገራል።

ሰው እንደመሆኑ ለእኛ ፍጹም የሆነ ምሳሌ ትቶልናል፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ተናግሮናል። እግዚአብሔር እንደመሆኑ ደግሞ ቃሉን እየገለጠልን ለእርሱ ታዛዦች እንድንሆን መንፈሳችንን ያቀናዋል።

ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን የሚሸከም የሚታይ የወይን ግንድ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚመራት የእግዚአብሔር ቃል ነው።

አብ በኢየሱስ ውስጥ የሚኖረው የማይታይ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ከዚህ መንፈስ ነው በቃሉ ውስጥ የተገለጹት ጠለቅ ያሉ ሃሳቦች የሚፈልቁት።

መዝሙር 42፡7 በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።

የእግዚአብሔር ጥልቅ ሃሳብ የእግዚአብሔርን ቃል በሚወዱ ሰዎች ውስጥ ጥልቅ የሆነ ምላሽን ያስገኛል። በተለይም በፈተና ጊዜ።

ጥልቅ እና ሚስጥራዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለእኛ ለሰዎች የሚገልጥልን ሰው የሆነው ኢየሱስ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር እና በእኛ መሃል መካከለኛ ነው።

በምድር ላይ ጥልቅ ከሆኑ ተፈጥሮአዊ ነገሮች ሁሉ በጣም ጥልቅ የሆነው ባሕር ነው። ቻሌንጀር ዲፕ የተባለው ቦታ 11 ኪሎሜትር ያህል ጥልቅ ነው። ስሙ እራሱ ጥልቅነቱን ይገልጣል። ጥልቅ ነገሮች በጣም ፈታኝ ናቸው፤ ደግሞም በቀላሉ አይደረስባቸውም። አንድ የጥልቅ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ በ1960 እስከ ባሕር ወለል ድረስ ወረደ፤ ከዚያ በኋላ ሁለተኛ ሌላ በአንድ መርከበኛ ብቻ የሄደ ሰርጓጅ መርከብ የተመለሰው በ2012 ነው። ጥልቅ ነገሮች ን ማሰስ የተለመደ ሥራ አይደለም፤ ደግሞም በጣም ከባድ ሥራ ነው።

ወንድም ብራንሐም በ1960 ዓ.ም በራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ የተጻፉትን የሰባቱን ቤተክርስቲያን ዘመናት እንዲሁም በምዕራፍ 4 እና 5 የተገጸውን ከመነጠቅ በኋላ በሰማይ ውስጥ ስላለው ትዕይንት ማጥናት ጀመረ። ይህ እርሱ ያዘጋጀው ተከታታይ ትምሕርት የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ተብሎ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ከራዕይ ምዕራፍ 6 በ1963 ዓ.ም ከሰባቱ ማሕተሞች አስደናቂው የስድስቱ ማሕተሞች መገለጥ መጣ። ማሕተሞቹ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በስውር የሚሰሩትን መናፈስት አጋለጡ።

አሁን ግለሰቦች የጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነቷ ምን ዓይነት እንደነበረ ለማወቅ ወደነዚህ ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መመለስ አለባቸው። ለዘመናችን የእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ ምን እንደሆነ መርምረን ማግነት አለብን።

 

 

ፌብሩዋሪ 28 ቀን 1963 ዓ.ም በሰሜን አሪዞና ውስጥ ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ አንድ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና ለ28 ደቂቃ ያህል ታይቶ ነበር። አሪዞና አሜሪካ ውስጥ በምዕራብ በኩል የሚገኝ ግዛት ነው።

ደመናው ውስጥ የሚታይ ፊት አልነበረም።

ደመናው ታክሶን ውስጥ ካለው የጠፈር ምርምር ማዕከል ፎቶ ተነስቷል።

 

 

ከስምነት ቀን በኋላ ደመናውን የሰሩት ሰባት መላእክት ከዚያ ቦታ 200 ማይል ይህል ርቆ በሚገኘው ሳንሴት ፒክ በሚባለው ቦታ ወንድም ብራንሐምን ጎበኙ። ሰባቱን ማሕተሞች እንዲገልጥ ተልዕኮ ሰጡት። ከዚያ በኋላ ደመና ሳይሰሩ ሄዱ።

ወንድም ብራንሐም አንድ ሳምንት በፈጀ ተከታታይ ስብከት ስለ ማሕተሞቹ ገልጦ አስተማረ፤ ሰባተኛው ማሕተም ግን ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆኑን ተናገረ። በዚህ የሰባቱ ማሕተሞች ትምሕርት ውስጥ ሰባቱ ነጎድጓዶችም ሙሉ በሙሉ ሚስጥር መሆናቸው ተገልጧል። ይህም የሆነበት ምክንያት ሰባቱ ነጎድጓዶች እና ሰባተኛው ማሕተም ታላቅ ሚስጥር ከሆነው ከጌታ ምጻት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ ነው። ያም አንድ ሰው እንኳ የማያውቀው ሚስጥር ነው። እናውቃለን የሚሉ የተሞኙ እና ራሳቸውን በማታለል የሚኖሩ ሰዎች ብቻ ናቸው። ይህም የሚኖሩበት የሞኝነት ድንኳን በታላቁ መከራ ውስጥ በቀላሉ ይፈርሳል።

ነገር ግን የማሕተሞቹ መፈታት ለአማኞች ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት አምጥቶላቸዋል።

ይህ የተገለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያበራው ብርሃን እጅግ ደማቅ ከመሆኑ የተነሳ በ1963 የሮማ ካቶሊክ ፖፕ ሞተ እንዲሁም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው ካቶሊክ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ በጥይት ተመቶ ሞተ። የጨለማ ኃይላት የተገለጠው ቃል ያመጣውን እውነተኛ ብርሃን ሊቋቋሙት አልቻሉም።

በምዕራብ የተገለጠውንና ፎቶግራፍ የተነሳውን ደመና ተከትሎ የመጀመሪያ ዝናብ ወይም የታላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ትምሕርት ዝናብ መጣ።

ይህም የሆነው ሙሽራዋን ለኋለኛው ዝናብ ማለትም ለመከር ጊዜ የሚሆነው ዝናብ ሲመጣ እንድትዘጋጅ ለማድረግ ነው፤ በዚያ ጊዜ ዘሩ ከተክሉ ላይ ይታጨዳል። በትንሳኤው ጊዜ በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በክርስቶስ ሆነው የሞቱ ሁሉ ከመቃብራቸው ውስጥ ተጎትተው ይወጣሉ። ከዚያ በኋላ በሕይወት ያለችዋ ሙሽራ በሰባቱ ነጎድጓዶች ወቅት ጌታን ለመቀበል ከምድር ላይ ለመቀበል ከመነሳቷ በፊት ሰባቱ ነጎድጓዶች ቃላቸውን ያሰማሉ።

ሉቃስ 12፡54 ደግሞም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ ደመና ከምዕራብ ሲወጣ ባያችሁ ጊዜ፥ ወዲያው፦ ዝናብ ይመጣል ትላላችሁ፥ እንዲሁም ይሆናል፤

65-0718 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል መሞከር

በዚያ የጠፈር ጣቢያ ውስጥ ሆነው የቀረው ዓለም ደግሞ ከውጭ ሆኖ ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት እያሰቡ ነበር። ታክሰን ውስጥ እነዚያ ትልልቅ የጠፈር መመራመሪያ መሳሪያዎች ደመናውን ፎቶ አነሱት፤ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ምንድነው? እስካሁን ድረስ ጋዜጣ ላይ “ይህ ምን እንደሆነ የሚያውቅ፤ እንዴትስ ሊፈጠር እንደቻለ የሚያውቅ ሰው አለ?” እያሉ ይጠይቃሉ። በዚያ ቦታ ምንም ጉም የለም፤ አየር የለም፤ እርጥበት የለም፤ ከምድር አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምንም የለም። ይገርማል!

“በላይ በሰማይ ምልክቶች ይሆናሉ። እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበትም ጊዜ የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ይሆናል ከዚያ በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል።”

ገበሬው የወይን እርሻውን ይንከባከባል።

እግዚአብሔር ለዘመን መጨረሻ የተላከውን የአሕዛብ ነብይ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንዲያስችለን ተጠቅሞበታል። ነብዩም በ1965 ከምድር ተሰናብቷል።

ነብዩ የተሰጠው ዋነኛ ተልእኮ መጽሐፍ ቅዱስን መግለጥ ነበር፤ ይህንኑ ሥራውን በ1965 አጠናቅቆታል። እኛም ተቀድተው ከተቀመጡ ስብከቶቹ ውስጥ ድምጹን ከ50 ዓመታት በላይ ማዳመጥ ችለናል።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

ስለዚህ “ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን” የሚለው ከ1965 ወዲህ ያሉትን ዓመታት ነው የሚያመለክተው፤ ይህም ነብዩ በምድር ላይ የሌለበት ዘመን ነው። ይህ ዘመን ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ለራሳችን እየመረመርን እንድናገኝ እግዚአብሔር የሰጠን ጊዜ ነው።

የወንድም ብራንሐም መልእክት ዓላማው እምነታችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባሉት ጥቅሶች አማካኝነት እየፈተሽን ትክክለኛነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንድናረጋገጥ ማስቻል ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎችና ፈሊጦች በቃላት ውስጥ የተቆለፉ መገለጦች ናቸው።

አብዛኞቹ የሜሴጅ ተከታዮች ከሰው ንግግር የተወሰዱ ጥቅሶች ላይ በመፈላሰፍና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እርስ በራሳቸው ሳያገናኙ በግምት የሆነ የራሳቸውን ትርጉም በመስጠት አቅጣጫ ጠፍቶባቸዋል። ያለፉትን ብዙ ዓመታት አባክነዋል። አሁን ቅናታቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም ብቻ ነው። ስለዚህ በሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ መሃይምነት እና መጽሐፍ ቅዱስን አሳስቶ መተርጎም እንደ አሸን ፈልቷል።

በመጽሐፍ ቅዱስ እየፈተሽን ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን የሚሉ ጥንቁቆች ቀስ በቀስ እንዲተኙ ተደርገዋል።

እውነትን ከፈለግን እግዚአብሔር ሕይወታችንን ይገርዘዋል፤ ይህም የራሳችንን ክብር ይቀንሰዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ተፈትሸው ያልተረጋገጡ የቤተክርስቲያናችን አመለካከቶች ተቆርተው መውደቅ አለባቸው። አሁን እንኳ በሜሴጅ ቤተክርስቲያን ብቻ ብዙ ዓይነት ሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ተከፍተዋል።

በዚህም መሰረት ሰዎች የራሳቸው አእምሮ በሰራው እስር ቤት ውስጥ እራሳቸውን እስረኛ አድርገው ይዘው በራሳቸው ላይ ዘግተዋል።

የሰው ንግግርን የተመረኮዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አተረጓጎሞችን ሁሉ እግዚአብሔር ቆርጦ ያስወግዳቸዋል።

በስተመጨረሻ አስተሳሰባችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ከእግዚአብሔር አስተሳሰብ ጋር አንድ መሆን አለበት።

ይህ ሰባኪዎችንም ሕዝቡንም ይመለከታል።

ዮሐንስ 15፡2 ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።

ብዙውን ጊዜ ከቅርንጫፎች አብዛኞቹ ይቆረጣሉ።

የሰው ፈቃድ የእግዚአብሔርን እቅድ ለመፈጸም አይጠቅምም።

ማድረግ የምንችለው ነገር ቢኖር ለራሳችን ፈቃድ መሞት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡31 ዕለት ዕለት እሞታለሁ።

ሰዎች ራስ ወዳድነት፣ የሥልጣን ጥማት፣ ግብዝነት፣ ትዕቢት፣ ሥራ ፈትነት፣ ስግብግብነት፣ ጥላቻ እና በቀል ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ ሲፈቅዱ እነዚያ ሰዎች ከእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ተቆርጠው ይወጣሉ ወይም ይወገዳሉ።

ለግል ጥቅም ወይም ለዝና መስገብገብ ውድቀትን ያመጣል።

ሰዎች የአንድ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ከሌሎች ክርስቲያኖች የተሻሉ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ይመስላቸዋል።

የሞቱ ዓሳዎች ብቻ ናቸው የውሃውን አወራረድ ተከትለው የሚሄዱት።

የጥሩ ስብከት ዓላማው ተደላድሎ የተቀመጠው ሰው መቀመጫው እንዳይመቸው ማድረግ ነው።

ማርቆስ 8፡36 ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?

ገንዘብ፣ ግብዝነት፣ ራስ ወዳድነት - ያልተቀደሱ ሥላሴዎች።

የራሳችንን ፍላጎትና ምኞት መከተል እግዚአብሔርን ለማገልገል ትክክለኛው መንገድ አይደለም።

ነገር ግን የእውነት ከልባቸው እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚጥሩ ሰዎች መከራን ይቀበላሉ።

ሕይወት የሚጀምረው ድሎታችሁ ሲያበቃ ነው።

ሕመም የእድገት አመላካች እና በትክክለኛው መንገድ ላይ የመሆናችሁ ምልክት ነው።

ራዕይ 3፡19 እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።

እንግዲህ ቅና፤ ንሰሃም ግባ።

ብዙ ንሰሃ የምንገባበት ነገር አለ። አብዛኛው የምናምነው እና የምናደርገው ነገር ስሕተት ነው። ነገር ግን ቤተክርስቲያኖቻችን እኛ የምናደርገው ነገር ሁሉ ምንም ችግር የለውም ብለን እንድናምን አታልለውናል።

ከልክ ያለፈ ኩራት ወይም በራስ መተማመን እራሳችንን በትክክለኛው ማንነታችን እንዳናይ ያደርገናል።

ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን በማጥራት ሂደት ውስጥ ከእኛ ላይ ብዙ ቆርጦ የሚጥለው ነገር አለው።

የሰው ንግግር ጥቅሶች “የመጽሐፍ ቅዱስ ያልሆኑ” ሃሳቦች ስለሆኑ በቀላሉ እንደ መጋረጃ ዓይናችንን ይጋርዳሉ።

እግዚአብሔርን እያስደሰትነው ከመሰለን ያለንበትን ሁኔታ በትክክል አልተረዳነውም ማለት ነው።

የወይን ግንድ ላይ በትክክል ያላደገ ፍሬ ተቆርጦ ይጣላል። በዚህ መንገድ በጣም ብዙ ፍሬ ይጠፋል፤ ነገር ግን የቀረው ያልተቆረጠው ፍሬ እጅግ በጣም ጥሩ ይሆናል፤ የተሻለ ዋጋም ይኖረዋል።

በራሳቸው መንገድ ከሚያድጉ ዝቅተኛ ጥራት ካላቸው ብዙ ፍሬዎች ይልቅ (ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማሙ ዘንድ) ከተገረዙ ቅርንጫፎች ከፍተኛ ጥራት ካላቸው ጥቂት ፍሬዎች ብዙ ትርፍ ይገኛል።

ነብዩ የመጣው የአዲስ ኪዳንን የመጀመሪያ እውነት ተረድተው ወደ መጀመሪያው እውነት ለመመለስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ለመምራት ነው።

ማቴዎስ 7፡14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።

ዛሬ እውነትን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን የሚመረምሩ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው።

እግዚአብሔር የሚፈልገው መልካም ፍሬ የሚመጣው በውስጣችን ካለው ከእግዚአብሔር መንፈስ ነው።

ገላቲያ 5፡22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።

23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።

እግዚአብሔር የሚገርዘን ወይም የሚከረክመን ለምንድነው? እግዚአብሔር የሚከረክመን ቃሉን ለመታዘዝ ይበልጥ እንድንጠነቀቅ ነው።

ዮሐንስ 14፡23 ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤

እግዚአብሔርን የምንወደው ስለ እርሱን ስለ መውደዳችን ስሜታችንን የሚገልጹ ቃላት በመናገር አይደለም።

እግዚአብሔርን የምንወደው መጽሐፍ ቅዱስን ለመታዘዝ ራሳችንን የምንገዛ ከሆነ ብቻ ነው።

3ኛ ዮሐንስ 1፡4 ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡14 ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥

ውስጣዊ ሰላም የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል እውነት መመላለሳችንን ስናውቅ እና ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን በትጋር መከተላችን እርግጠኛ ስንሆን ነው።

ከዚያም በመንፈስ ፍሬ ውስጥ ትዕግስት ይኖረናል፤ እርሱም በመከራ ውስጥ ተረጋግቶ ደስ በሚል መንገድ ማለፍ ነው ምክንያቱም የምናልፍበት መከራ እምነታችንን ያሳድገዋል። እምነት ልክ በተንቀሳቀሱ ቁጥር እየበረቱ እንደሚሄዱ ጡንቻዎች ነው። መከራ እና ስቃይ በመንፈስ ጠንካራ ያደርጉናል። በመከራ ውስጥ በትዕግስት እና ያለ መነጫነጭ ብናልፍ እግዚአብሔር እንደረዳን እናውቃለን። ይህም ትሁት እንድንሆን ያደርገናል ምክንያቱም ያሳለፈን የራሳችን ጥረት ሳይሆን ከላይ የተቀበልነው እርዳታ ነው። ከዚህም የተነሳ በራሳችን መመካት አንችልም።

ትሑት ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት ያለ ጭንቀት እና ያለ ጥርጣሬ ይቀበላሉ። ልክ በረከትን በምንቀበልበት ዓይነት ልብ መከራንም መቀበል እንለምዳለን ምክንያቱም ሁለቱም የሚመጡት ከእግዚአብሔር እጅ ነው። ሁለቱም ለጥቅማችን ነው የሚመጡት።

ሮሜ 8፡28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።

እግዚአብሔር ሲገርዘን ወይም ሲያጠራን እየባረከን ላይመስል ይችላል፤ ይህም የሚሆነው የሚያሰናክለንን ስሕተት ቆርጦ እየጣለልን ስለሆነ ነው።

የሐዘን ቢላዋ ደስታችንን የያዘውን ጽዋ ቀርጾ ይሰራልናል።

በዚህ ክፍል ትኩረት የተደረገው እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ መጠራት ላይ ነው እንጂ የራሳችንን ፍላጎት ለማሳካት እርዳታ ማግኘት ላይ አይደለም። እግዚአብሔር ለዘመናችን ያለውን ታላቅ እቅድ ፈልገን ማግኘት አለብን፤ እርሱም ወደ መጀመሪያው የሐዋርያት እምነት መመለስ እንችል ዘንድ የእግዚአብሔርን ሚስጥራት በበቂ መጠን መረዳትና ማወቅ ነው።

እግዚአብሔር በጸጥታ ውስጥ ሆነነ አርፈን እንድንረጋጋ ይፈልጋል፤ ይህም ዓላማው በጭንቅ ጊዜም በስኬት ጊዜም ራሳችንን መቆጣጠር እንድንችል ነው። አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር የባረከው ጊዜ ያ ክርስቲያን በቀላሉ በራሱ መመካት ሊጀምር ይችላል። ይህም አደጋ ነው። በምድር ላይ በሃብት አንድኛ የሆኑ ሰዎች ክርስቲያኖች አይደሉም። በባንክ ያስቀመጥከው የገንዘብ ብዛት ወደ እግዚአብሔር መቅረብህን አያመለክትም።

ሰዎች አደጋ ሲደርስባቸው መከራ ውስጥ ሲገቡ በቀላሉ እግዚአብሔርን ይክዳሉ። ሁኔታዎች ስሜታችንን እንዲገዙ መፍቀድ የለብንም። አለበለዚያ ሕይወታችን በሙሉ ምላሽ ለምንሰጣቸው ሁኔታዎች ባሪያ ይሆናል።

መንፈስ ቅዱስ መከራንም ድልንም በቀላሉ እኛን ሊያሰናክሉ የሚችሉ “አስመሳዮች” እንደሆኑ አድርጎ ነው የሚያያቸው። ለጌታ ዳግም ምጻት እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን ማወቅ እንችል ዘንድ ትኩረታችን ማረፍ ያለበት የእግዚአብሔርን ቃል መከተል ላይ ነው።

ገንዘብ እያተረፍን ይሁን ወይ ደግሞ እያጣን ይሁን ትኩረታችን ገንዘብ ላይ መሆን የለበትም።

ማቴዎስ 6፡33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

ያለንበት ሁኔታ መልካምም ይሁን ክፉ ዓይኖቻችንን ከሁኔታ ላይ አንስተን የራሳችንን ፈቃድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም እንችል ዘንድ ቃሉን ለመረዳት እና ለመከተል መፈለግ አለብን።

እግዚአብሔር የሚፈልገውን ብንፈልግ እግዚአብሔር ደግሞ የሚያስፈልገንን ስለሚያውቅ የሚያስፈልገንን በመስጠት ችግሮቻችንን ይፈታቸዋል። ይህም ዕድሜያችንን ሁሉ የምንፈልገውን እያሳደድን ከመባከን ይሻላል፤ የምንፈልገውን ማሳደድ ሰይጣን እኛን ከእውነተኛው መንገድ አስቶ የሚያስወጣበት ዘዴ ነው።

ዛፍ ከላዩ አንድ ቅርንጫፍ ሲቆረጥበት ወይም ሲከረከምበት እንደገና ለማቆጥቆጥና ለማደግ ተጨማሪ ኃይል እንዲያመነጭ ያበረታታዋል። ደግሞም ሲከረከም ቅርንጫፉ ሊይዘው ከጀመረው ከበሽታ ነጻ ይሆናል። አዲስ ሆኖ ያቆጠቆጠውም ቅርንጫፍ ይበልጥ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

ችግርን ማሸነፍ እምነታችንን ያነቃቃዋል።

ችግር እና ሽንፈት የሰው ባህሪ ተቀርጾ የሚወጣበት ቦታ ነው።

ያለ ልክ ተንዠርግገው ያደጉ ቅርንጫፎች ሲከረከሙ ከስር የወጡ አዳዲስ ቅጠሎች የፀሃይ ብርሃን ያገኛሉ። ጊዜ ሲያልፍ ለኢየሱስ የነበረንን የቀደመ ፍቅራችንን በቀላሉ እንረሳለን። ቤተክርስቲያን መሄድ የመጽሐፍ ቅዱስን ቦታ ይይዝብናል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሳይሆን ከሰዎች ጋር መስማማት እንጀምራለን።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው “ክሪስማስ” የተባለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነው ዲሴምበር 25 ቀን ባጌጠ ከአሕዛብ ልማድ በተኮረጀ “የክሪስማስ” ዛፍ መከበሩ ኤርምያስ ምዕራፍ 10 የአሕዛብን ልማድ አትከተሉ ብሎ ከሰጠን ማስጠንቀቂያ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ መንገድ ምን ያህል አፈንግጠን እንደወጣን ያሳየናል።

በቀላሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ረግረግ መንገዶች ውስጥ እንገባለን ወይ ደግሞ በራሳችን ችሎታ እንደገፋለን። እንደ ቅርንጫፍ ስንከረከም ይበልጥ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን እንለምዳለን።

ዮሐንስ 15፡3 እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤

ኢየሱስ ደጋግሞ የሚናገረው እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መመስረት እንዳለብን ነው። በጸጋው አማካኝነት በእምነት ከዳንን በኋላ ወደ ሰው ሰራሽ እና ወደ አሕዛብ ልማዶች እየተፍገመገምን መሄድ የለብም ወይም እንደ ቢግ ባንግ እና ኤቮልዩሽን የመሳሰሉ ሳይንሳዊ ስሕተቶችን መከተል የለብንም።

እግዚአብሔርን ማስደሰት የምንችለው በምናምነው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆን ነው።

ዮሐንስ 15፡4 በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መጽናት አለብን። በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ሥራውን መስራት የሚችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምልክቶችና በዘይቤዎች የተሰወረውን እውነት ወደ ማወቅ እንዲመራን ስንፈቅድለት ብቻ ነው።

ቅርንጫፍ ከግንዱ ጋር ካልተጣበቀ በቀር ማደግ አይችልም። የወይኑ ግንድ ለቅርንጫፉ የሚያስፈልገውን ውሃ እና ንጥረ ነገሮች ከአፈር ውስጥ እየሳበ ያመጣለታል። ቅርንጫፉ ከአፈር ውስጥ ውሃ እና ንጥረ ነገሮችን በራሱ የሚያመጣበት መንገድ የለውም። የዛፉ ስሮች ብቻ ናቸው ውሃ እና ንጥረ ነገሮችን ስበው ማምጣት የሞችሉት። ስለዚህ እውነትን ለማወቅ እና ስሕተትን ለማስወገድ የሚያስፈገልገንን መረጃ ለማግኘት ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጥገኞች ነን። በውስጣችን ያለው መንፈስ ቅዱስ እርሱ ብቻ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት የተለያዩ ጥቅሶች አማካኝነት የእውነትን መገለጥ እንድናገኝ የሚመራን።

ዮሐንስ 15፡5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

የሚያስፈራ ንግግር ነው። እንደ ሰው ያለን ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች ምንም አይጠቅሙንም። አብዛኞቹ ማራኪ የንግግር ችሎታ ያላቸው ሰዎች የሚያማልል የንግግር ችሎታቸውን ተጠቅመው ሕዝብን ያታልላሉ። ሲሰብኩም እነርሱን ተወዳጅ የሚያደርጉዋቸውን እና ሕዝቡን ደግሞ የሚያዝናኑዋቸውን ትምሕርቶች መርጠው ነው የሚሰብኩት። ከቁም ነገር እና ከእውነት ይልቅ ትኩረታቸው ለአቀራረብ ውበት ነው። እውነት ቁንጥጥ ስለሚያደርግ ሰዎች ሊሰሙት አይፈልጉም። ስለዚህ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ ሰባኪዎች ብዙ እውነት አይሰብኩም።

በግል ሕይወታችን ውስጥ የመንፈስ ፍሬ ማፍራት አለብን። እነዚህ ፍሬዎች ግን ሌሎች ሰዎች ላይ ጌታ እንድንሆን የሚያደርጉ አይደሉም።

ደግሞም ኢየሱስ እየመራን ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን ይመልሰን ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን መገለጠም ማግኘት አለብን።

ይህንን ለማሳካት አንድን ሃሳብ ወይም እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እየተከታተለን ስናጠና ጥቅስን ከጥቅ ጋር ማያያዝ ያስፈልገናል። ስለ አንድ ትምሕርት የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ እንደ ወይን ዘለላ በአንድነት ይሰበሰባሉ።

ትምሕርታችሁ በጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ የተመሰረተ ከሆነ ዘለላ ውስጥ እንዳሉ ጥቂት ፍሬዎች ነው ማለት ነው። ይህም ምንም ዋጋ ስለሌለው ገበሬው ቆርጦ ይጥለዋል።

ዋጋ የሚኖረን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተነስተን ስንናገር ብቻ ነው። የትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምን ማለት እንደሆነ ከሌላ ቃል ጋር በማስተያየት ነው ማብራራት ያለብን። እውነቱን የምናምነው ከሆነ ኢየሱስ ትምሕርታችን በጥልቀት ይመሰረት ዘንድ የሚያጠናክሩትን ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሶችን ያሳየናል።

ስሕተትን የምንቀበል ከሆነ ሃሳባችንን ለማስረዳት ብለን መጽሐፍ ቅዱስን ትተን እንሄዳለን። ከዚያም በኋላ እምነታችንን የሚቃረኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እናገኛለን። ይህም ኢየሱስ መሳሳታችንን እየነገረን ነው ማለት ነው። የዚያን ጊዜ እርሱ ከሙሽራይቱ አካል ውስጥ ቆርጦ ሳይጥለን በፊት ያንን የተሳሳተውን እምነታችንን ከሃሳባችን ውስጥ ቆርጠን መጣል አለብን።

ልብ በሉ፤ ለኢየሱስ ጥራት ያለው ጥቂት የወይን ዘለላ ይበቃዋል።

ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

እግዚአብሔር ዛሬ በምድር ላይ የእውነት እና የሐሰት ድብልቃቸውን በሚያሰራጩ በ45,000ው የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ይመጣል።

ነገር ግን በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ጸንተው የቆሙት። እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው እንጂ ከስሜታችን አይደለም። አዘውትሮ ቤተክርስቲያን ከመሄድም አይመጣም።

ዮሐንስ 15፡6 በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።

የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የሚቀርቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች እና አብረዋቸው የተደባለቁ የሰው አመለካከቶች በሙሉ ኢየሱስ የሚፈልጋቸው ቅርንጫፎች አይደሉም። እንደ ኤቮሉሽን እና ቢግ ባንግ የመሳሰሉ የሳይንስ ንድፈ ሃሳቦች እና እንደ ሥላሴ የመሳሰሉ የአረማውያን እምነቶች የጠወለጉ ቅርንጫፎች ናቸው፤ እነዚህም ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎችን ወደ ታላቁ መከራ እሳት ውስጥ ያስገቡዋቸዋል። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው በመቀበል ከሲኦል ሊድኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማይከተሉ ከሆነ ወደ ታላቁ መከራ ለመግባት በመንገድ ላይ ናቸው።

ሉቃስ 8፡18 እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፥ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣብቀው የሚቆዩ ሰዎች እምነታቸውን የሚያጸናላቸው ተጨማሪ ጥቅስ ማግኘት ይችሉ ዘንድ አጥርቶ የሚያየው የንስር ዓይን ይሰጣቸዋል። የተገለጠውን እውነት የሚክዱ ግን በፊት ያወቁት ትንሽ እውነት እስኪጠፋባቸው ድረስ የሰዎችን ስሕተት እየተከተሉ ይሄዳሉ።

“ከሲኦል የምትድኑት በሜሴጅ ቡድን ውስጥ ከሆናችሁ ብቻ ነው ወይም የዚህ ቤተክርስቲያን አባላ ከሆናችሁ ብቻ ነው” የሚለው አነጋገር የዳንነው የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል በማመን እና በጸጋው ብቻ መሆኑን የጠፋበት ሰው የሚናገረው አነጋገር ነው።

ዮሐንስ 15፡7 በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።

ኢየሱስ በድጋሚ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣበቅ እንዳለብን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፤ ምክንያቱም የዛኔ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የምንሆነው።

የተገለጠ ትንቢት እና መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንኖርበት ዘንድ ለጊዜው የተሰጠን ወርቃማ ዕድል ነው፤ ያውም ይህን የተሰጠንን ውብ ዕድል ከያዝነው እና ከተጠቀምንበት።

የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መተርጎም የምንችለው በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ብቻ ነው።

ዮሐንስ 15፡8 ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ስናምን የማይታየው የእግዚአብሔር መንፈስ ይከብራል።

ይህ በሕይወት የምንፈተንበት መድረክ ነው።

45,000 የተለያዩ የቤተክርስቲያን እምነቶች በፊታችን ቀርበውልናል።

እያንዳንዳቸው በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው፤ በከፊል ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ናቸው፤ ልክ መልካም እና ክፉውን እንደምታሳውቀዋ ዛፍ። ለእኛ የቀረበልን ፈተና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማገናኘት ማረጋገጥ የማይቻሉ እምነቶችን ሁሉ እምቢ ማለት ነው። እውነቱን ለማረጋገጥ በርከት ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማገናኘት በቻልን ቁጥር በርከት ያለ ፍሬ እናፈራለን።

የፈለግነውን የመምረጥ መብት አለን፤ ነገር ግን የምርጫችንን ውጤት የመወሰን ነጻነት የለንም።

ሚክያስ 7፡13 ምድሪቱ ግን በሚኖሩባት በሥራቸው ፍሬ ምክንያት ባድማ ትሆናለች።

ሆሴዕ 10፡13 ክፋትን አርሳችኋል፥ ኃጢአትንም አጭዳችኋል፥ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በኃያላንህ ብዛት፥ በመንገድህም ላይ ታምነሃልና።

በታላላቅ ሰባኪዎች በሚታመኑ ትልልቅ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አባል መሆን ሰባኪዎቹ እንደማይዋሹን ዋስትና አይሰጠንም።

ሆሴዕ 10፡1 እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያውን አብዝቶአል፤

ለራስ በሚሆን ትርፍ ላይ ትኩረት ማድረግ የመንፈሳዊ ባዶነት ምልክት ነው።

ኤርምያስ 12፡2 … በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።

ልጓም ፈረስን ይመራዋል። ይህ ምሳሌ ሃሳብ የሰውን ንግግር እና ድርጊት እንደሚመራ ያመለክታል።

ሰዎች እግዚአብሔርን ስለመውደድ ደስ የሚሉ ቃላትን በቀላሉ በአፋቸው ይላሉ። ነገር ግን ሃሳባቸው ወይም ልባቸው ከእግዚአብሔር ቃል እሩቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለመከተል እውነተኛ ፍላጎት የላቸውም።

ኤርምያስ 6፡19 ምድር ሆይ፥ ስሚ፤ እነሆ፥ ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።

መጽሐፍ ቅዱስን የማንታዘዝ ከሆነ ሃሳባችን የሚያፈራው ፍሬ ክፉ ነው።

ኢሳይያስ 37፡31 ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፥ ወደ ላይም ያፈራል።

ወደ ላይ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት ወደ ታች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጠለቅ ያለ ሥር መስደድ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን የማታምኑ እና የማትታዘዙ ከሆነ እግዚአብሔርን በመንፈስ ማስደሰት አትችሉም።

ምሳሌ 18፡21 ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል የማመን እና የመናገር ፍሬ ወይም ውጤቱ የዘላለም ሕይወት ነው።

የቤተክርስቲያን ልማዶችን እና አመለካከቶችን የማመን ፍሬ ወይም ውጤቱ በታላቁ መከራ ውስጥ መሞት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ነው የምንወደው ወይስ ቤተክርስቲያንን?

ምሳሌ 8፡12 እኔ ጥበብ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥

19 ፍሬዬም ከምዝምዝ ወርቅ ይሻላል፥

የጥበብ ፍሬ ሰዎችን አርቀው ማየት የሚችሉ አስተዋዮች እና ጠቢባን ያደርጋቸዋል።

ጥበብ ትኩረቷ በእግዚአብሔር ትልቅ እቅድ ላይ ነው።

ሰው ሰራሽ ጥረቶች ዘላለማዊነትን ማፍራት አይችሉም።

ዮሐንስ 15፡9 አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።

የማይታየው እግዚአብሔር ሃሳቡን በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ገልጧል።

የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ፍቅር ጥልቅ ሃሳቦች ይገልጥልናል።

ነገር ግን ቃላት የእግዚአብሔር አስተሳሰብ ጥልቀት በሙላት መግለጥ አይችሉም።

ቃላት የእግዚአብሔርን ሙሉ የሆነውንና ጥልቀቱ የማይደረስበትን ፍቅር መግለጥ አይችሉም።

የኢየሱስ መስዋእትነትና የተቀበለው መከራ እና ስቃይ በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ የነበረውን የስሜት ጥልቀት በጥቂቱ ያሳየናል።

ኢየሱስ ለእኛ ከሞተልን እኛ ደግሞ ከራሳችን ሕይወት አብልጠን እርሱን ልንወደው ይገባናል።

ለእርሱ ያለንን ይህን ፍቅር የምንገልጠው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ነው።

በኢየሱስ ውስጥ ይኖር የነበረው የማይታየው የእግዚአብሔር መንፈስ ኢየሱስ ያቀረበውን መስዋእት ወደደው። ኢየሱስ እራሱን ሊሰዋ የቻለው የእውነት ስለወደደን ነው። ከእርሱ ሌላ ማንም ሊያድነን አይችልም።

ስለዚህ ገብቶን ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን ትዕዛዛ የምንታዘዘው ለእግዚአብሔር ቃል ካለን ጽኑ ፍቅር በመነሳት ነው።

ዮሐንስ 15፡10 እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።

ፍቅር በልባችን ውስጥ መኖሩን ማረጋገጫ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ የሰጠንን ትዕዛዛት መታዘዝ ብቻ ነው።

ኢየሱስ በውስጡ ይኖር ለነበረው ለእግዚአብሔር መንፈስ አልታዘዝም ብሎ አያውቅም።

1ኛ ሳሙኤል 15፡22 መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ … ይበልጣል።

ዮሐንስ 15፡11 ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ።

ደስታችን ፍጹም ሙሉ የሚሆነው የእውነትን መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አማካኝነት መከተላችንን ስናውቅ ነው።

ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃሉን ሙሉ በሙሉ መከተላችንን ሲያይ በታላቅ ደስታ ይደሰታል።

ዮሐንስ 15፡12 እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።

ክርስቲያኖች ለመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ታዛዥ በመሆን እግዚአብሔርን መውደዳቸው በጣም አስፈላጊ ነው። ቃሉ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ወደ ኢየሱስ በመቅረብ ወደ እርስ በራሳችን እንቀርባለን።

እግዚአብሔርን መውደዳችን ማረጋገጫው መጽሐፍ ቅዱስን ስንታዘዝ ነው። ሌላው ማስረጃችን ደግሞ እርስ በራሳችን መዋደዳችን ነው ምክንያቱም ለእርስ በራሳችን ቅርብ ነን።

ዮሐንስ 15፡13 ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

የፍቅር ትልቁ መገለጫው አንድ ሰው ስለ ወዳጆቹ ለመሞት ፈቃደኛ ሲሆን ነው።

ኢየሱስ ይህንን የተናገረው ልክ በቀራንዮ ከመሞቱ በፊት ነው።

ስለዚህ በቀራንዮ ስለ እኛ መሞቱ ኢየሱስ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚገልጥበት ትልቅ የፍቅር መግለጫው ነው።

ዮሐንስ 15፡14 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እርሱን የእኛ ራስ አድርገን በመቀለብ ትዕዛዛቱን የምንጠብቅበት ልብ ቢኖረን እርሱ ደግሞ ከሁሉ የሚበልጠውን ክብር ይሰጠናል። ማለትም ወዳጆቼ ብሎ ይጠራናል።

ይህ የሚያንገዳግድ እውነት ነው። የእግዚአብሔር ወዳጅ ተብሎ መጠራት።

ዮሐንስ 15፡15 ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።

የእግዚአብሔርን እቅድ ብዙም የማያውቁ ነገር ግን እግዚአብሔርን ማገልገል የሚፈልጉ ሰዎች ባሪያ ተብለው ይጠራሉ።

እነዚህም ሰዎች ብዙ ነገር ያበላሻሉ ምክንያቱም እግዚአብሔር እቅዱ ምን እንደሆነ አያውቁም። ነገር ግን የተወሰኑ ነገሮችን ደግሞ አስተካክለው ይሰራሉ። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ሕይወታቸው ይህንን ነው የሚመስለው፤ እነርሱ ቤተክርስቲያን አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንደምትቃወም፣ እንደምትቃረን ወይም ቸል ብላ እንደምታልፍ እያዩ ቤተክርስቲያናቸው የምነትግራቸውን ብቻ ነው የሚያምኑት።

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው የሚያምኑ አማኞች እግዚአብሔር የቃሉን ሚስጥር እንዲያበራላቸው ይፈቅዱለታል።

እነርሱም ለዘመናቸው የሚሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ያገኛሉ። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች መረዳት የማይችሉትን ትምሕርት በማመን እግዚአብሔርን በተሻለ መንገድ ያገለግላሉ።

ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።

እኛ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እመነት መመለስ እንችል ዘንድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሚስጥር እንዲፈጸም ይፈልጋል።

የጥንቷን ቤተክርስቲያን እምነት በመከተል ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትኩረት ይኖረናል። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ከሙታን ስትነሳ በጥቷ ቤተክርስቲያን የነበሩ አማኞች የእኛ እምነት ከእነርሱ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ እንዲሆን ይጠብቃሉ።

የሚታጨረው ዘር ከተዘራው ዘር ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው።

ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ዲኖሚኔሽናዊ በሆነ መንገዳቸው በከፊል እውነት በከፊል ደግሞ ሐሰት በከፊል መጽሐፍ ቅዱስን ባለማወቅ በሆነ መንገዳቸው እንዲቀጥሉ አይፈልግም። ይህ ዓይነቱ አካሄድ 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፤ ይህም ማለት ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በዚህ ሁሉ የተለያየ መንገድ ውስጥ ገብተው አቅጣጫ ጠፍቶባቸዋል ማለት ነው።

ዮሐንስ 15፡16 እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።

እውነተኞቹ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን አይመርጡትም። ኢየሱስ ነው እነርሱን የሚመርጣቸው።

የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት አዲስ ኪዳንን እንዲጽፉ ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የእግዚአብሔር ቃል የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል።

አዲስ ኪዳን እስከ መጨረሻው ጸንቶ ይኖራል።

ይህ የእያንዳንዱ ሰው የእምነት መሰረት ነው። ከአዲስ ኪዳን ፈቀቅ ብትሉ ቤታችሁን በአሸዋ ላይ ነው የምትሰሩት፤ ቤታችሁም በታላቁ መከራ ውስጥ ይወድቃል።

ደቀመዛሙርቱ አዲስ ኪዳንን የሚጽፉበት ጥበብ እና የመንፈስ ምሪት ለማግኘት እግዚአብሔርን ጠይቀውታል፤ በተለይም ከትንቢት ጋር የተያያዙትን ክፍሎች ሲጽፉ። ምክንያቱም የወደፊቱን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

እኛም ደግሞ በተራችን የጥንቶቹ ደቀመዛሙርት የጻፉትን መረዳት የምንችልበትን ጥበብ እና የመንፈስ ምሪት ለማግኘት እግዚአብሔርን መጠየቅ አለብን። እነርሱ እውነቱን አግኝተዋል እኛ ግን አላገኘንም። ስለዚህ ከእነርሱ መማር አለብን።

እነርሱ መንፈሳዊ አባቶቻችን ናቸው። እነርሱ ወደሚያምኑት እምነት ስንመለስ የእነርሱ መንፈሳዊ ልጆች እንሆናለን።

ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።

የእግዚአብሔር ቀን ታላቁ መከራ ነው።

ዊልያም ብራንሐም የመጣው ከታላቁ መከራ ማምለጥ የሚያስችሉንን ሚስጥሮች ለመግለጥ ነው። ታላቁ መከራ የሚመጣው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከተነጠቅን በኋላ ነው።

ኢሳይያስ 57፡1 ጻድቅ ይሞታል፥ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፥ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።

ሚልክያስ 4፡6 መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

እርግማን ይቆያል። የኑክሊየር ቦምብ ከፈነዳ በኋላ በምድር ላይ ቶሎ ሳይጠፋ የሚቆየውን ሬድዮ አክቲቭ ጨረር አስቡ።

ዮሐንስ 15፡17 በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።

ኢየሱስ ክርስቲያኖች እርስ በእርስ መዋደድ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል። ከአስር ሚሊዮን የሚበልጡ ክርስቲያኖች በጨለማው ዘመን ውስጥ ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር ስላልተስማሙ ተገድለዋል። በሕዝቡ መካከል ልዩነት ቢኖርም እንኳ ፖፑ እና ካርዲናሎቹ ይህንን እርስ በርስ ተዋደዱ ደሚለውን ትዕዛዝ ቢታዘዙ ኖሮ ያ ሁሉ ብዙ ሰው ባልተገደለ ነበር።

ነገር ግን ጳጳሶቹ እና ፖፑ ዓለምን ሁሉ የምትገዛ ቤተክርስቲያንን መገንባት ላይ ትኩረት ሲያደርጉ የተቃወማቸውን ሁሉ ማስወገድ እንደሚያስፈልጋቸው አመኑ። ትልቁ ስሕተታቸው ትኩረታቸውን በኢየሱስ ላይ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ላይ ማድረጋቸው ነው።

ፕሮቴስታንቶችም ካቶሊኮችን ተከትለው መጽሐፍ ቅዱስን በማመን ፈንታ ቤተክርስቲያናቸውን የማመን ተመሳሳይ ስሕተት ሰርተዋል።

ቤተክርስቲያን በምትለው ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ላይ ትኩረት ስናደርግ የሕዝብ መብዛት ወይም አለመብዛት ከምንም አይቆጠርም።

ማቴዎስ 18፡20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።

ከመጀመሪያው ጥቂት ሰዎች በቤት ውስጥ ነበር የሚሰበሰቡት። በቤተክርስቲያን ላይ ፖፕ ገዢ መሆኑ የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ሃሳብ አይደለም።

1ኛ ቆሮንቶስ 16፡19 የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

ዮሐንስ 15፡18 ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።

እውነት ሁልጊዜ ሰዎች ይጠሉዋታል። ሰዎች ስሕተታቸው ሲነገራቸው ደስ አይላቸውም፤ ድክመታቸውን ሲያሳዩዋቸውም ይበሳጫሉ።

ዮሐንስ 15፡19 ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።

ይህች ዓለም ስሕተትን ትወዳለች፤ መጽሐፍ ቅዱስን የሚነቅፉ ሰዎችንም ታበረታታለች። ለጥንታዊ የስነምግባር መርሆች የሚቆሙ ሰዎችን የመገናኛ ብዙሃን ያፌዙባቸዋል።

ዘፍጥረትን የአፈታሪክ ስብስብ ነው ይሉታል። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ ብለው በሚያምኑ ሰዎች ሳይንቲስቶች ይቀልዱባቸዋል። እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች በሕዝባዊ ሕንጻዎችና ትምሕርት ቤቶች ውስጥ ጸሎት እንዳይደረግ እና መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይነበብ ይከለክላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስን እና መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ ሰዎችን የሚነቅፍ ከባድ የጥላቻ ሞገድ አለ። ሌሎች ሐይማኖቶች ግን በመገናኛ ብዙሐን በተመሳሳይ መጠን ሲነቀፉና ሲሰደቡ አናይም።

ዮሐንስ 15፡20 ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።

ኢየሱስ ሕዝቡ እንደሚያሳድዱት ተናግሮ ነበር፤ እነርሱም አሳደዱት።

ስለዚህ ደቀመዛሙርቱንም እንደሚያሳድዱዋቸው ሲናገር ሕዝቡ ይህንን ትንቢት በመጪዎቹ ዓመታት ውስጥ መፈጸም ይቀጥላሉ።

ስለዚህ ሕዝቡ ደቀመዛሙርቱን አሳደዱዋቸው። ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ዮሐንስ ብቻ ነው ሸምግሎ የሞተው። ነገር ግን እርሱም በፍጥሞ ደሴት ላይ ሁለት ጊዜ ታስሮ ነበር። ሁለቱንም ጊዜ እንዲታሰር የተፈረደበት ፍርድ ላልተወሰነ ጊዜ የነበረ ሲሆን የእስሩ ዘመን የሚያበቃው እንዲታሰር የፈረደበት ሮማዊ ንጉስ ሲሞት ብቻ ነው።

ንጉስ ኔሮ ክርስቲያኖችን ማሳደድ የጀመረው በ64 ዓ.ም ነው። ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት በእስር ቤት ውስጥ ኔሮ በ68 ዓ.ም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ቆይቷል።

ዶሚቲያን በ81 ዓ.ም የሮም ንጉስ ሆነ፤ እርሱም ክርስቲያኖችን አሳደደ። የሆነ ዓመት ላይ ይህ ንጉስ ዮሐንስን ይዞ በዘይት እንዲቀቀል አደረገ፤ ዮሐንስ ግን አልሞተም። ከዚያም ዶሚቲያን ዮሐንስን እንደገና በፍጥሞ ደሴት ላይ አሰረው። ዮሐንስም ዶሚቲያን በ96 ዓ.ም እስከ ሞተበት ዓመት ድረስ በፍጥሞ ደሴት እስር ቤት ውስጥ ቆየ።

ኢየሱስ እና የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ተሰድደዋል። ልክ እንደዚሁ ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ተሰድዳለች። ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ቢያምኑ እና ጸንተው ቢኖሩ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተፈላጊ አይሆኑም። ይህም የዚህ ዘመን መንፈሳዊ ስደት ነው። ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጸንተው ቢቆሙ ቤተክርስቲያን በሚሄዱ ሰዎች ዘንድ የተጠሉና የተናቁ ይሆናሉ።

ዮሐንስ 15፡21 ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ስለ ስሜ ያደርጉባችኋል።

የሥላሴ አስተምሕሮ በመለኮት ውስጥ ሶስት እኩል የሆኑ አካላት አሉ ይላል። ነገር ግን ለሶስቱ አካላት አንድ ስም ማግኘት አይችሉም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ለክርስቲያኖች አምላክ ስም የላቸውም።

ከማቴዎስ 28፡19 በመነሳት በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቃሉ፤ ምክንያቱም የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም የሆነውን አንድ ስም አያውቁም። ሶስት የማዕረግ መጠሪያዎችን እየተጠቀሙ ይህ የእግዚአብሔር ስም ነው በማለት ራሳቸውን ያታልላሉ።

ስሕተታቸውም የተገለጠ ነው ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናጠምቅ የሚነግረንን የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ቸል ይላሉ።

ስሙ ኢየሱስ ነው።

ሁለቱን ጥቅሶች ማስታረቅ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ የአብ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ሰብዓዊ ስም ኢየሱስ መሆኑን መረዳት ነው።

እግዚአብሔር የማይታየው የአብ መንፈስ ሆኖ ከአይሁዶች በላይ ነበረ። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር እንደ ልጅ ሆኖ በመካከላችን ሊኖር ወረደ። ቀጥሎ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመኖር ተመልሶ መጣ።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ አብ የተለያዩ ባህርያቱን የሚገልጹ ብዙ ስሞች ነበሩት።

መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት ስም የለውም።

እግዚአብሔር የተጠራበት ብቸኛው ሰብዓዊ ስም ኢየሱስ ነው።

ነገር ግን ሌሎች ሰዎችም ራሳቸውን ኢየሱስ ብለው ስለሚጠሩ ስንናገር የትኛውን ኢየሱስ ማለታችን እንደሆነ በስሙ ላይ ቢያንስ አንድ ማዕረግ በመጨመር ለይተን ማሳወቅ አለብን።

ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት አለብን።

በእነዚህ አጠራሮች ሁሉ ውስጥ ሰብዓዊው ስም ኢየሱስ ነው። ጌታ እና ክርስቶስ የሚሉት ማዕረጎች የትኛውን ኢየሱስ ማለታችንን ለመለየት ያስችሉናል።

ዛሬ ግን በጣም ብዙ ቤተክርስቲያኖች በኢየሱስ ሰብዓዊ ስም ለማጥመቅ እምቢ ይላሉ።

እንደውም ሰዎች ይህንን ጉዳይ ካነሱባቸው ይጠሉዋቸዋል፤ ይገፉዋቸዋል።

ስም የሌለው የሥላሴ አምላክ ቤተክርስቲያኖን ተቆጣጥሯል፤ እነርሱም በማዕረጎቹ ካልተጠመቅን ይላሉ።

1ኛ ቆሮንቶስ 10፡1 ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤

2 ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤

የአይሁዶች ጥምቀት የተፈጸመው እግዚአብሔር ባሕሩን ከከፈለላቸው በኋላ በውስጡ ባለፉ ጊዜ ነው። ሙሴን ተከትለው በመሄድ በሕይወት ሆነው ከባሕሩ ወጡ። ሙሴ ስም ነው።

ግብጻውያን ፈርኦንን ተከትለው ወደ ኤርትራ ባሕር ውስጥ ገቡ። ከዚያ ሁላቸውም ሰጠሙ። ፈርኦን የማዕረግ መጠሪያ ነው።

ስለዚህ በጥምቀት ውስጥ የሙሴ ስም ወደ ሕይወት መራቸው። ፈርኦን የሚባለው ማዕረግ በጥምቀት ውስጥ ወደ ሞት ወሰዳቸው።

የጌታ ኢየሱስን ስም ልንቀበል የምንችልበት ብቸኛው መንገድ በጥምቀት ነው።

ልብ በሉ፤ ሙሽራዋ የባሏን ስም መቀበል አለባት፤ እርሱም ኢየሱስ ነው።

አቶ ኢየሱስ ክርስቶስ የተጋባው ከወይዘሪት አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ጋር አይደለም።

ጥምቀት የኢየሱስን ሞት፣ ቀብር፣ እና ትንሳኤ ይወክላል።

አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሁለት የተለያዩ አካላት ከሆኑ እነርሱ አልሞቱም፤ ደግሞም አልተቀበሩም። ስለዚህ በውሃ ጥምቀት ውስጥ ምንም ሚና የላቸውም፤ መጠቀስም የለባቸውም።

ዮሐንስ 15፡22 እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።

ኢየሱስ መጣና እውነት ምን እንደሆነ እንዲሁም ስሕተትም ምን እንደሆነ ገለጠ። እርሱ የተናገረው በአራቱ ወንጌሎች ውስጥ ተጽፏል። በዚህም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ልትመሰረት እና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሊጻፍ ችሏል። ቀሪው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን እምነት እና ለቤተክርስቲያን የተሰጡዋትን ትንቢቶች ያብራራል።

ኢየሱስ ለአይሁዶች ተናግሯል፤ ስለዚህ አይሁዶች እውነትን አናውቅም ብለው ማመካኘት አይችሉም። ነገር ግን አይሁዶች አልተቀበሉትም።

በተመሳሳይ መንገድ ኢየሱስ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ ለመጨረሻው ዘመን ለሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሙሉውን እውነት ገልጦላታል። ስለዚህ ዛሬ የትኛዋም ቤተክርስቲያን እውነትን ላለማወቋ ማመካኛ የላትም።

ዮሐንስ 15፡23 እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዱንም ቃል ቸል የሚሉ፤ የሚለውጡ፤ ወይም የሙቃወሙ ሰዎች በእርግጥ ቸል ያሉት፤ የለወጡት፤ ወይም የተቃወሙት ኢየሱስን ነው። ቃሉ ላይ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት የእግዚአብሔርን ቃል ያመጣውን የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ ስለሚጠሉ ነው።

አስተሳሰባቸው ከእግዚአብሔር አስተሳሰብ እንዲስማማ የራሳቸውን ሃሳብ በመለወጥ ፈንታ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ቆራርጠው ከራሳቸው አስተሳሰብ ጋር እንዲስማማ ያደርጉታል። አንድ ነገርን ካልጠላችሁት በቀር ልትቆራርጡት አትችሉም።

ዮሐንስ 15፡24 ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።

ኢየሱስ ማንም ሰው ያላደረጋቸውን ተዓምራት በተከታታይ አድርጓል። ለየትኛውም አይሁዳዊ ኢየሱስ ያደረጋቸውን ተዓምራት አይቶ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን አላምንም ማለት የማይታሰብ ነገር ነው። ስለዚህ ኢየሱስን የተቃወሙት አይሁዶች ግልጽ የሆነውን እውነት በመካድ እራሳቸውን እያሳወሩ ነበር። ይህም ከባድ ሐጥያት ነው። አንድ ሰው የራሱን ዓይኖች ጎልጉሎ በማውጣት እራሱን ካሳወረ የአእምሮ በሽተኛ ወይም እብድ ነው እንለዋለን። ስለዚህ ኢየሱስ የሰራቸውን ተዓምራት እያየ በመካድ የራሱን መንፈሳዊ ዓይኖች ያሳወረ ሰውም ለእብደት መንፈስ ተገዢ ሆኗል ማለት ነው። አይሁዶች ለመሪዎቻቸው ታማኝ ሆነው ለመኖር ሲሉ የከፈሉት ዋጋ ይህ ነው። እነርሱ ከኢየሱስ ይልቅ የሐይማኖት መሪዎቻቸውን መረጡ።

ከዚያ አልፈው በስተመጨረሻ እብደታቸው ሲብስባቸው በኢየሱስ ፈንታ ነፍሰ ገዳዩን በርባንን መረጡ።

በዚያ ሰዓት አላበድንም ብለው ራሳቸውን ማሞኘት እንኳ አልቻሉም። ነገር ግን ለእግዚአብሔር አስተሳሰብ የነበራቸው ጥላቻ ይህን ያህል ከመብዛቱ የተነሳ እግዚአብሔር በውስጡ የሚኖርበትን ኢየሱስን እንዲሞት ሲፈርዱበት በጩኸት ነበር የፈረዱት።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ (በኢየሱስ) የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ኢየሱስ በጠጣመም ብዙ መልካም አደድርገጓል። እርሱን አለመቀበል ሞኝነት ነው።

ዮሐንስ 15፡25 ነገር ግን በሕጋቸው፡- በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

ኢየሱስ ያደረገው ነገር ሁሉ ሰዎችን ለመርዳት ነው። ሲሰብክ፤ ሲፈውስ፤ ብዙ ሰዎችን ሲመግብ፤ ሙታንን ሲያስነሳ ሰዎችን ለመርዳት ነው ይህን ሁሉ ያደረገው።

ኢየሱስ የሰራቸው ተዓምራትም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ከሰሩዋቸው ሥራዎች ሁሉ በለጡ።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ በመጠየቅ ሊያጠምዱት ሲሞክሩ የሚመልስላቸው የጥበብ መልስ በራሳቸው መኩራራት እንዳይችሉ ስላደረጋቸው እርሱን ጠሉት። ነገር ግን ይህ ሁሉ እርሱን ለመጥላት በቂ ምክንያት አይደለም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ አንዳችም ክፉ ነገር አልተናገረም አንድም ክፉ ነገር አላደረገም።

ዮሐንስ 15፡26 ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤

ኢየሱስ እነርሱን ለማጽናናት ተመልሶ እንደሚመጣ ተናግሯል።

ዮሐንስ 14፡18 ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

አብ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከአይሁዶች በላይ ይኖር የነበረው ልዕለ ተፈጥሮአዊው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ውስጥ በኖረበት ሰዓት በሰው አካል ውስጥ መኖሩ ለእግዚአብሔር ሰብዓዊ ባሕርያትን ለመውረስ አስችሎታል።

ስለዚህ ተመልሶ መጥቶ ወደ አማኞች ልብ ውስጥ የገባው መንፈስ ቅዱስ ልዕለ መለኮታዊም ነው ሰብዓዊም ነው።

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሚፈልገንን ዓይነት ሰዎች አድርጎ እኛን መስራት ይችላል፤ ደግሞ ለእኛ መንፈሳዊ ስጦታዎችን መስጠትም ይችላል።

መንፈስ ቅዱስ የሚመነጨው ከእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ነው።

የመንፈስ ቅዱስ ሥራው የእግዚአብሔርን ጥልቅ አስተሳሰብ መግለጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ እውነትን የሚነግረን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወደተጻፈው ጥልቅ እውነት እየመራን ነው።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማስረጃው ይህ ነው።

መንፈስ ቅዱስ ለመለኮታዊ ኃይሉ ብቻ አይደለም ትኩረት የሚሰጠው፤ የቃሉን እውነት መግለጥ ላይ ትልቅ ትኩረት ያደርጋል።

መንፈስ ቅዱስ ታላቅ መለኮታዊ ኃይል አለው፤ ነገር ግን ዋነኛው ሥራዬ ብሎ የሚቆጥረው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መግለጥ ነው።

መንፈስ ቅዱስ ስለ ራሱ አይናገርም። እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሰው ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ወደ ተገለጠው ቃል ነው የሚመራቸው።

ሁልጊዜ ትኩረት መደረግ ያለበት ኢየሱስ ክርስቶስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል ላይ ነው እንጂ የተቀባው ሰባኪ ላይ አይደለም።

ዮሐንስ 15፡27 እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ።

ደቀመዛሙርቱ ታላቅ እና የማይፈሩ ሰዎች ናቸው።

ነገር ግን ሰይጣን በሕዝቡ ላይ የፍርሃት መንፈስ በለቀቀባቸው ሰዓት እነርሱም ጌታን ትተው ሄዱ። ሁላቸውም ለኢየሱስ ለመቆም ፈሩ፤ የሐይማኖት መሪዎችን ለመቃወምም ድፍረት አልነበራቸውም።

ደቀመዛሙርቱ በሸሹ ጊዜ የተዋረዱበት ውርደት ሰዎች ያውም ከሰዎች መካከል ታላላቅ መሪዎችም እንኳ ምን ያህል ደካማ እና የማይረቡ መሆናቸውን ያስታውሳቸዋል።

በውርደት ከሸሹ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ማድረግ የሚችሉት ሰዎችን ሁሉ ወደ ኢየሱስ መጠቆም ነው፤ ምክንያቱም እርሱ ብቻ ነው ያልተሰናከለውና ያልወደቀው።

አንድ ሰውን አንድ መሪን ከጉባኤው በላይ ከፍ ከፍ ማድረግ ከባድ ስሕተት ነው፤ ቤተክርስቲያንን ወደ ውድቀት ውስጥ የከተታት ይህ ነው።

ሰባኪዎች ሕዝቡን ወደ ኢየሱስ ብቻ ነው መጠቆም ያለባቸው፤ ኢየሱስም በአንድ ርዕስ ላይ እውነትን የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ነው የሚገለጠው። ሰባኪዎች ወደ ራሳቸው ወይም ወደ ሌሎች ሰባኪዎች ማመልከት የለባቸውም።

አንድ ትምሕትር ዝነኛ የሆነ ሰው እውነት ነው ስላለው እውነተኛ አይሆንም። አንድ ትምሕርት እውነተኛ የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው ብሎ ሲመሰክርለት ብቻ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ኢየሱስ በጽሑፍ መልክ ነው።

ኢየሱስ ዛሬ በምድር ላይ ቢገለጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው የተለየ ነገር አይናገርም።

ጉባኤው ሰውን መከተል ከጀመረ በኋላ ሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያኖች ነው የሚሆኑት።

ደቀመዛሙርት ኢየሱስን ከመጀመሪያው አውቀውታል፤ በተጨማሪ የራሳቸውንም ድክመት አውቀዋል። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገችውን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መሰረቱ።

እግዚአብሔር ደቀመዛሙርቱ ታላላቅ ነገሮችን እንዲሰሩ ተጠቀመባቸው። የተሸከማቸው፤ ደግሞም የቃሉን እውቀት እና ኃይል የሰጣቸው የወይን ግንድ ኢየሱስ ነው።

ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት መሰረት ክርስቲያኖች ለኢየሱስ ኃይል እና ክብር በራሳቸው ሕይወት የመሰከሩበት ነው።

የዛሬ ሰባኪዎች የኢየሱስን ኃይል ተጠቅመው ለራሳቸው ታላቅነት ምስክርነት ማድረግ የለባቸውም። እንደዚያ ማድረግ አጭበርባሪነት ነው።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23