ዮሐንስ ምዕራፍ 11. የአልዓዛር ትንሳኤ በአይሁድ መካከል መከፋፈልን አስከተለ



First published on the 21st of March 2021 — Last updated on the 21st of March 2021

ምዕራፍ 11 ኢየሱስ ወደ ሕይወቱ መጨረሻ ሲቃረብ አካባቢ የሆኑትን ክስተቶች ነው የሚተርከው። በቤተራባ ለአጭር ጊዜ ያደረገው ቆይታ አብቅቷል። ቤተራባ ትርጉሙ “መሻገር” ማለት ነው። በመስቀሉ አማካኝነት ወንጌሉ ከአይሁድ ወደ አሕዛብ ሊሻገር ነው።

 

 

ቤተራባ ኢያሱ የተስፋይቱን ምድር ለመውረስ በመጣ ጊዜ ኢያሪኮ አጠገብ የዮርዳኖስን ወንዝ “የተሻገረበት” “የመሻገሪያ ቦታ ነው”። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በዚህ ቦታ ሰዎችን ያጠመቀው መሲሁ በመጣ ጊዜ የብሉይ ኪዳን ሕግ ወደ አዲስ ኪዳን ጸጋ “እንደሚሸጋገር” ስለተረዳ ነው።

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከቤተራባ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመለስበት ጊዜ ደረሰ።

በኢየሩሳሌም ባለው ዋና ጽፈት ቤታቸው የተቀመጡ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን ጠልተውታል፤ ደግሞም ገፍተውታል። እርሱን በመግደል ያደረገውን ተጽእኖ ለማጥፋት አስበዋል። የሐይማኖት ተቋማት ጽፈት ቤቶች የራሳቸውን ሕግ ይደነግጉና የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን ይተዋሉ።

“ሄድኳርተርስ” ማለት ከጭንቅላታቸው አንድ አራተኛው ክፍል ብቻ ይሰራል ማለት ነው።

ነገር ግን በአላዛር ትንሳኤ ኢየሱስ ትልቅ ማስጠንቀቂያ እየሰጣቸው ነበር፤ ይህም ማስጠንቀቂያ “በሞትም ላይ ኃይል አለኝ” የሚል ነው።

የአይሁድ መሪዎች ግን ማስጠንቀቂያውን አላስተዋሉም።

በራሳቸው ሰው ሰራሽ ልማዶችና በራሳቸው ታላቅነት ተጠምደው ስለነበረ የአይሁድ መሪዎች እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ማለትም ኢየሱስ እነርሱ ከሚያምኑት እምነት የተለየ መሆኑን ማመን አልቻሉም። ስለ መሲሁ ለሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሰጡዋቸው ትርጓሜዎች በጣም የተሳሳቱ ነበሩ። ከዚህም የተነሳ በዘመናቸው እየተደረገ ስለነበረው ነገር አንዳችም አላወቁም። በዚህም ምክንያት በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ኢየሱስን በመከተልና በማመን ፈንታ እውነትን የሚቃወሙ ጠላቶች ሆኑ።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤

የሙት መንፈስ ሰው ከሞተ በኋላ የሚታይ የሰው መንፈስ ነው።

ኢየሱስን ገደሉት፤ ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ መንፈስ ወደ ሲኦል ወርዶ ዲያብሎን ድል አድርጎ መምጣት ቻለ። የኢየሱስ መሞት ሰይጣንን ያስፈራው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ከሞተ የኢየሱስ ቅዱስ መንፈስ የሙት ሰው መንፈስ ሆኖ ወደ ሲኦል የመግባት ፈቃድ ያገኛል። ሰይጣን የሞትና የሲኦልን ቁልፎች ከተቀማ በኋላ ሰይጣት ከደረሰበት ጉዳት እስከ ዛሬ ድረስ አላገገመም።

ኢየሱስ እንዲህ አለ።

ራዕይ 1፡18 ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

የአላዛር ትንሳኤ ዮሐንስ ከዘገባቸው ተዓምራት መካከል ሰባተኛው ተዓምር ነው።

ይህም የሚያመለክተው ሰባተኛው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን በሞቱ ቅዱሳን ትንሳኤ እንደሚጠናቀቅ ነው። የቅዱሳን ትንሳኤ ኢየሱስ በሞት፣ በሲኦል፣ በሰይጣን እና በመቃብር ላይ የተቀዳጀውን ታላቅ ድል የሚያሳይ ድርጊት ነው።

ዮሐንስ የጻፋቸው የኢየሱስ ተዓምራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡-

 

ውሃ ወደ ወይን ጠጅ (2:1-11)

የሹሙ ልጅ መፈወስ (4:46-54)

መጥመቂያው አጠገብ የነበረው በሽተኛው መፈወስ (5:1-15)

እንጀራዎቹንና ዓሳዎቹን ማብዛት (6:1-14)

በውሃ ላይ መራመድ (6:15-21)

ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ዓይን ማብራት (9:1-12)

 

አላዛር ከሞት ከተነሳ በኋላ አንዳችም ነገር አልተናገረም። አላዛር ከሞት በተነሳበት ሰዓት መደመጥ የሚገባው ሰው ኢየሱስ ብቻ ነበረ።

ይህም በመጨረሻው በቅዱሳን ከሙታን ትንሳኤ ሰዓትም ሊደመጥ የሚገባው ብቸኛው ሰው ሙታንን ለማስነሳት እንደ መላእክት አለቃ ሆኖ የሚመጣው ኢየሱስ ብቻ መሆንን ያሳያል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ የመላእክት አለቃ ብቻ ነው ያለው፤ እርሱም ሚካኤል ነው።

ይሁዳ 1፡9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።

የመላእክት አለቃ ሚካኤል የሙሴን ሥጋ ሰይጣን እንዳይወስደው ቀድሞ ወስዶታል፤ ስለዚህ ነው ሙሴ ከኤልያስ ጋር ኢየሱስ ክብሩን በገለጠበት ተራራ ላይ ተገኝቶ ሊታይ የቻለው።

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤

1964-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

ይህ የሆነው ከተፈጥሮ በላይ የሆነው ደመና ከፍላግስታፍ ከተማ በላይ ታይቶ ፎቶ ከተነሳ እና የመጀመሪያዎቹ ስድስት ማሕተሞች ከተፈቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ነበር። በዚያ ወቅት ወንድም ብራንሐም ያ ብርቱ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃው ወደ ምድር መጥቶ ሙታንን እንደሚያስነሳ ገና እየተጠባበቀ ነበር።

65-1127

ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየችህ

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አንድ ወር በፊት ድረስ መልአኩ ለትንሳኤ እንደሚመጣ ሲጠባበቅ ነበር።

 

ዮሐንስ 11፡1 ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢታንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር።

ማርያም ይበልጥ መንፈሳዊ ስለነበረች ትኩረቷ ኢየሱስ በሚናገረው ቃል ላይ ነበረ። ማርታ ይበልጥ ትኩረቷ ለመልካም ሥራ ባላት ቅናት ላይ ነበር።

ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት።

ሉቃስ 10፡38 ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።

39 ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።

ማርያም በኢየሱስ እና በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትኩረቷን ያደረገችውን ቤተክርስቲያን ትወክላለች።

ማርታ ግን ለሥራ የምትተጋዋን ሰዎችን የሚያስደንቁ ስራዎችን በመስራት ለመሯሯጥ ብላ የእግዚአብሔርን ቃል ቸል የምትለውን ቤተክርስቲያን ትወክላለች።

40 ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።

41 ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

42 የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።

መልካም ሥራዎችን መስራት ጥሩ ነው ግን በምናምነውና በምንሰራው ስራ ውስጥ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን ደግሞ ይበልጥ ያስፈልጋል።

ማርያም በሕይወቷ ውስጥ ኢየሱስን አንደኛ አድርጋለች። ኢየሱስ ሰው ነው ደግሞ የእግዚአብሔር ቃልም ነው።

ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለን አመለካከት ከኢየሱስ ጋር ያለንን ሕብረት ያሳያል።

ከኢየሱስ ጋር ጠለቅ ያለ ሕብረት ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሲፈጸም ለማየት ይጠባበቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስንም በሕይወታቸው ውስጥ ብቸኛ መሪ አድርገው ይከተላሉ።

ማርያም ለቃሉ ስለነበራት ፍቅር እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ሚስጥራት እንድታስተውል የጠለቀ መረዳትን በመስጠት ሸሟታል።

ዮሐንስ 11፡2 ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

የሰው እግሮች ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን መዳን ከአሕዛብ መንግሥታት ክልል ውጭ ነበረ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሥራውን ይሰራ የነበረው ከእሥራኤል ጋር ነበር።

 

 

የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነጾር በሕልሙ ያየውን በሕልሙ ያየውን የአሕዛብ ምስል እንመልከት።

በመስቀሉ አማካኝነት መዳን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ወደ አሕዛብ ይሻገራል። የብረቱ እግሮች አረማዊ የሆነውን የሮማውያንን መንግሥት ይወክላል። ከቁርጭምጭሚቱ በታች ያሉት እግሮቹ ግን የሸክላ እና የብረት ድብልቅ ናቸው። የሮማ መንግሥትን የሚወክለው ብረት በእግሩ ጣቶች ውስጥ የብረት ስብርባሪዎች ሆነ፤ ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ይወክላል፤ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም እውነተኞቹን አማኞች የክርስቶስን ሙሽራ ከሚወክለው ከሸክላው ጋር ይደባለቃሉ። የሕይወት ዘር ሊበቅል የሚችለው ሸክላ ወይም አፈር ውስጥ እንጂ ብረት ውስጥ ሊበቅል አይችልም።

 

ዮሐንስ 12፡3 ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።

የኢየሱስ እግሮች የቤተክርስቲያን ዘመናትን ይወክላሉ። በ2,000 ዓመታቱ የቤተክርስቲያን ውስጥ ሲከናወን የነበረው የቤተክርስቲያን መዋጀት በታላቅ ዋጋና በብዙ መከራ ነው የተከናወነው። ከሁሉም ታላቁ ዋጋ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ስለ ሐጥያታችን የከፈለው ዋጋ ነው።

ደስ የሚያሰኘው የሽቶ መዓዛ ቤቱን በሙሉ አወደው። ልክ እንደዚሁ የመዳን ወንጌል ለዓለም ስለ እግዚአብሔር ፍቅር የሚናገር ደስ የሚል መዓዛ ያለው ሽቶ ነው፤ የዚህም ሽቶ መዓዛ በምድር ላይ በንሰሃ የሚሆን የሐጥያት ይቅርታን የምሥራች ያሰራጫል። የቅድስናውን ውበትም ለዓለም ይገልጣል።

እግሮች ደስ የማይል ሽታ የሚያመነጭ እጢ አላቸው። ይህም እኛ አሕዛቦች ንሰሃ በገባን ጊዜ ጥሩ መዓዛ ያለውን የእግዚአብሔር ይቅርታ ከመቀበላችን በፊት የነበርንበትን አስቀያሚ የሐጥያት ሽታ ያመለክታል።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ማርያም ተንበርክካ እግሮቹን ያበሰችበት ረጅም ጸጉሯ የራሱ የሆነ ትርጉም አለው።

ኤፌሶን 5፡22 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፤ ቤተክርስቲያን የጌታ አካል ናት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ራስ ለሆናት ለጌታ ለኢየሱስ መገዛት አለባት።

የሴት ረጅም ያልተቆረጠ ጸጉር ለባሏ እና ለኢየሱስ የመገዛቷ ምልክት ነው።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡5 ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።

1ኛ ቆሮንቶስ 11፡15 ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።

ዮሐንስ 12፡7 ኢየሱስም፦ ለምቀበርበት ቀን እንድትጠብቀው ተውአት፤

ማርያም እምነቷን ለመግለጥ አልፈራችም። ሌሎቹ ተቃወሙዋት፤ ኢየሱስ ግን ተውአት አላቸው።

ማርያም የተባለችዋ ሴት ኢየሱስ በሕይወት ሳለ ሽቶ በነካው ረጅም ጸጉርዋ የኢየሱስን ሞት አከበረች (ረጅሙ ጸጉርዋ ለኢየሱስ ማለትም ለእግዚአብሔር ቃል የመገዛቷ ምልክት ነው)።

ይህም ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ መረዳትን ያመለክታል። የኢየሱስን ሞት እና ቀብር ውብ እንደሆነ እና መልካማ መዓዛ እንዳለው ነገር ነው የተመለከተችው። ሌሎች ስለ ኢየሱስ ሞት አልቅሰው ለቀብር ራሱን እና ሰውነቱን ዘይት ይቀቡታል፤ ይህም እነርሱ የኢየሱስ ሞት እንደ አሳዛኝ ፍጻሜ ማየታቸውን ያመለክታል።

ኤፌሶን 5፡2 ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።

“መዓዛ” ደስ የሚያሰኝ ሽታ ነው።

ማርያም የኢየሱስ ሞት ታላቅ ክብር ያለው እና ውድ በሆነ ደስ የሚል ሽታ ባለው ሽቶ ሊከበር የሚገባው እንደሆነ ገብቷታል። ጠለቅ ባለ እና ምስጢራዊ በሆነ መንገድ የኢየሱስ ሞት እና ቀብር ክብር የተሞላ እና መልካም መዓዛ ያለው ክስተት ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ኢየሱስ በትንሳኤ ከሙታን ከተነሳ ብቻ ነው። ማርያም የኢየሱስ ሞት እና ቀብር ለሰው መዳንን እና ደስታ የሚያመጣ ክስተት መሆኑ ተሰምቷታል።

ኤፌሶን 5፡2 ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።

ኋላ ቅዱስ ጳውሎስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቃላት የሚጽፈውን እውነት እርሷ አስቀድማ በተግባር ገለጠችው። የክርስቶስ ሞት ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው ሞት ነው። ይህም እኛ ሰዎች የኢየሱስን የመስቀል ሞት አሰቃቂ አሟሟት አድርገን ከምንቆጥርበት አመለካከት ፈጽሞ የተለየ ነው።

ስለዚህ በቀራንዮ የተደረገው የመጨረሻው ድርጊት ሰዎች ሊያስተውሉ በሰዓቱ በማይችሉት መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት የተፈጸመበት ትዕይንት ነው፤ ምክንያቱም በሰዓቱ የኢየሱስ ሞት ከሰዎች ሃሳብ የተለየ ነገር ነበረ። ኢየሱስ ሲሞት የተሸነፈ መስሏቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ መሞት የሰይጣን ሽንፈት መሆኑ አልገባቸውም ነበር። የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ከመነሳተቸው በፊት የተከናወኑት ክስተቶች በሙሉ ለሰው አእምሮ ግራ የሚያጋቡ ነበሩ።

እየተፈጸሙ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ካልተከታተላችሁ በስተቀር ትንሳኤ ለሰው ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው።

ኢየሱስ ሲሞት ወዲያው የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በሙሉ ከሙታን እንደሚነሱ ማንም አላወቀም ነበር።

ማቴዎስ 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

የኢዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን ወደሚነሱበት ጊዜ እየተቃረብን ስንሄድ ልክ እንደ በፊቱ አሁንም ብዙ ነገሮች ግራ የሚያጋቡ እየሆኑ እንደሚሄዱ መጠበቅ እንችላለን።

ስለዚህ እየተፈጸሙ ያሉ ትንቢቶችን ሲፈጸሙ ማስተዋል እንችል ዘንድ እንዲሁም እግዚአብሔር ሥራውን በሚሰራበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ የትጋ እንዳለን እናውቅ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ አለብን።

ዮሐንስ 11፡3 ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ።

ማርያም (ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ የምትሰጥ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት)፣ ማርታ ደግሞ (ለተግባር እና ለሥራ ቅድሚያ የምትሰጥ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት)፣ እነዚህ ሁለት ሴቶች ኢየሱስን ለመጥራት ወደ እርሱ ሰው ላኩ።

የቤተክርስቲያኖች ትልቅ ስሕተት ይህ ነው። ችግራቸውን ለመፍታት ኢየሱስ ምን ማድረግ እንዳለበት ይነግሩታል።

ትንሳኤ ሲቃረብ ትልቅ ችግራችን የሚሆነው ትዕግስት ማጣት ነው።

ለእግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለበት መንገር ሳይሆን እግዚአብሔርን መጠበቅ መልመድ አለብን።

ዮሐንስ 11፡4 ኢየሱስም ሰምቶ፦ ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ።

ኢየሱስ ጭንቀታቸውን አየና በዘመናቸው እየተከሰቱ የነበሩ ክስተቶችን በተሳሳተ አተረጓጎም እየተረጎሙ እንደነበረ አወቀ።

ኢየሱስ ሁልጊዜ አጠቃላዩን እውነታ ነው የሚያየው።

የኛ ችግሮች ትንንሽ ናቸው ግን አእምሮዋችንን በሙሉ ይቆጣጠሩብናል። እግዚአብሔር ሊፈጽም ያሰበውን ትልቅ እቅድ ማየት ያቅተናል።

ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

“ለሞት አይደለም” የሚለው ንግግር በትክክል ላይገባን ይችላል።

አላዛር ለጊዜው ይሞታል ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከሞት ይነሳና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚታወቁ ዝነኛ ሰዎች አንዱ ይሆናል።

ሞት መጥፎ የሚሆነው መጨረሻው ከእግዚአብሔር መለየት ሲሆን ብቻ ነው።

በሥጋ መሞት እና ኋላ ከሙታን መነሳት ሞት ሊባል አይችልም። ይህ ዓይነት ለጥቂት ጊዜ ምድር ላይ አለመኖር ብቻ ነው።

ልክ እንቅልፍ በወሰደን ጊዜ ለተወሰኑ ሰዓታት ከዚህ ዓለም ጋር ምንም ሕብረት እንደማናደግ ማለት ነው።

ክርስቲያኖችም ለአጭር ጊዜ ይሞታሉ። ከዚያ በኋላ ግን በዘላለም ሕይወት ለመኖር ከሙታን ይነሳሉ።

ማቆሚያ ከሌለው ዘላለማዊ ሕይወት አንጻር ሲታይ እኛ የምንሞተው ሞት የአጭር ሰዓት እንቅልፍ ነው የሚመስለው።

ልክ ልጅ ከወለደች በኋላ ሕጻን ልጇን ስታየው ካገኘችው ድል የተነሳ የተሰቃየችበትን የወሊድ ምጥ እንደምትረሳ እናት በአዲስ በከበረ አካል ለዘላለም ሕይወት ከሙታን ስንነሳ ትንሳኤያችን ሞትን ያስረሳናል።

ዮሐንስ 11፡5 ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር።

አላዛር እና ሁለቱ እሕቶቹ ከኢየሱስ ጋር የቀረበ ወዳጅነት ነበራቸው። ስለዚህ ኢየሱስ ለሁለት ቀን እነርሱጋ አለመምጣቱ አይወዳቸውም ማለት አይደለም።

እግዚአብሔር እኛን ከመርዳት ሲዘገይ ትቶናል ጥሎናል ማለት አይደለም።

ሲዘገይ ያሰበው ትልቅ ዓላማ አለው ማለት ነው።

ዮሐንስ 11፡6 እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤

አላዛርን መፈወስ በራሱ ተዓምር ይሆን ነበር።

የሞተውን አላዛርን ከሙታን ማስነሳት ግን ከመፈወስም የሚበልጥ ታላቅ ተዓምር ነው።

መበስበስ የጀመረ እሬሳን ማስነሳት ደግሞ የሞተውን ሰው ወዲያው ከማስነሳትም የሚበልጥ ተዓምር ነው።

የራሱ የትንሳኤ ጊዜ እየቀረበ ሲመጣ ኢየሱስ የአላዛርን ትንሳኤ ለአይሁድ እንደ ምሳሌ ሊያሳያቸው ፈለገ።

መልእክተኛው አላዛር ከሞተ አንድ ቀን አልፎ ደረሰ።

ስለዚህ መልእክተኛው ኢየሱስጋ ሲደርስ አላዛር ከሞተ አንድ ቀን አልፎታል።

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ወደ አይሁዳውያን ወዳጆቹ ከመሄድ ለሁለት ተጨማሪ ቀናት ዘገየ። ይህም ማለት ወደ አላዛር ከመሄዱ በፊት ሁለት ቀን ይፈጅና መሞቱን ከሰማ በሶስተኛው ቀን ይደርሳል። ስለዚህ አላዛር ከሙታን የሚነሳው ስለ እርሱ መሞት ኢየሱስ ወሬውን ከሰማ በኋላ በሶስተኛው ቀን ነው።

የቀኖቹ ቁጥር ሆሴዕ ከተናገረው ትንቢት ጋር አብሮ ይሄዳል።

ሆሴዕ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ780 አካባቢ ለአይሁድ ሕዝብ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

እርሱም አይሁዳውያን እንደሚመቱ (በሮማውያን) እና ከተስፋይቱ ምድር እንደሚፈናቀሉ ተናግሮ ነበር።

ከዚያም እግዚአብሔር ይመለስና አይሁዳውያንን ይፈውሳቸዋል።

ሆሴዕ 6፡1 ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።

2 ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፥ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን።

ሆሴዕ ነብይ እንደመሆኑ አይሁዳውያን ከእግዚአብሔር እየራቁ እንደነበረ አውቋል። ዳግመኛ የተወለዱ አይሁዶች ወደ መሲሃቸው ይመለሱ ዘንድ እግዚአብሔር በ1948 እግዚአብሔር የተስፋይቱን ምድር ለአይሁዳውያን መመለስ እንደሚጀምርም ተረድቷል።

ከሆሴዕ እይታ አንጻር በእግዚአብሔር የዘመን አቆጣጠር ይህ የሚሆነው ከሦስት ቀናት በኋላ ነው።

780 ዓ.ዓ + 1,000 = 220 ዓ.ም (1ኛ ቀን)

220 + 1,000 = 1220 ዓ.ም (2ኛ ቀን)

1220 + 1,000 = 2020 ዓ.ም (3ኛ ቀን)

ስለዚህ ሆሴዕ የተናገረው ሶስተኛ ቀን ዛሬ እኛ ዘመን ከምንቆጥርበት ካላንደር ጋር አብሮ ይሄዳል። እግዚአብሔር እንደተናገረው የተስፋ ቃል በዚህ በሶስተኛ ቀን አይሁዳውያንን እንደ ሕዝብ መልሶ ማስነሳት ጀምሯል።

በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት ነው።

2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

ሆሴዕ ዘመኑን መቁጠር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እግዚአብሔር ለሁለት ቀናት ያህል ማለትም ለሁለት ሺህ ዓመታት ጠብቋል። ከዚያም እግዚአብሔር አይሁዶችን ሕዝብ አድርጎ እንደገና ለማስነሳት አሁን ወደ እነርሱ ዞሯል።

ዮሐንስ 11፡7 ከዚህም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ፦ ወደ ይሁዳ ደግሞ እንሂድ አላቸው።

ኢየሱስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ይሁዳ ተመለሰ። ይሁዳ ማለት በኢየሩሳሌም ዙርያ ያለው ክልል ነው።

ዮሐንስ 11፡8 ደቀ መዛሙርቱ፦ መምህር ሆይ፥ አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፥ ደግሞም ወደዚያ ትሄዳለህን? አሉት።

አይሁዳውያን ኢየሱስን በጣም ከመጥላታቸው የተነሳ ሊገድሉት ፈለጉ።

ደቀመዛሙርቱ የእግዚአብሔር እቅድ አልገባቸውም። ኢየሱስ ከሞተ ጉዳቸው የሚፈላ መስሏቸዋል።

ዮሐንስ 11፡9 ኢየሱስም መልሶ፦ ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤

ኢየሱስ ይሞትና በሶስተኛው ቀን ይነሳል። ለሐጥያት መስዋእት ይሆን ዘንድ መሞት ነበረበት። መሞት እና ከዚያም ከመቃብር መውጣት መሰናከል አይደለም። ኢየሱስ ሞተና ከዚህ ምድር በመለየት ወደ ሲኦል ውስጥ ሰይጣንን ድል አድርጎ ተመለሰ። ከዚያም በኋላ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ ቅዱሳኑን ይዞ ከመቃብር ወጣ። ይህም ታላቅና ክብር የተሞላ ድል መጎናጸፍ እንጂ መሰናከልና መውደቅ አይደለም።

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው የተመላለሰው። ስለ እርሱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሙሉ ፈጽሟል። እርሱ እንዲሞት የእግዚአብሔር ፈቃድ በሆነበት ሰዓት መሞቱ ለዚህ ዓለም ታላቅ ብርሃን እንዲበራ አድርጓል። ከሁሉም ነገር በላይ አስፈላጊው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መፈጸም ነው።

ይህም ከሰዎች አስተሳሰብ ተቃራኒ ነው። በመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ዘመን በሮማውያን መንግስት ስር በተነሳው ስደት እንዲሁም በጨለማው ዘመን እና በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን በ18ኛው መቶ ዓመት ውስጥ እንደሆነው የእግዚአብሔርን ቃል መከተልና ሰማዕት ሆኖ መገደል መሰናከል አይባልም። እነዚህ በስደት ውስጥ የተገደሉ ሰማእታት ብርሃን ወደሞላው ክብር ውስጥ ገብተው ዘላለማዊ ሽልማታቸውን እየጠበቁ ነው።

ብዙውን ጊዜ ለእኛ ትርጉም ባይሰጠንም የእግዚአብሔር ፈቃድ “በአደገኛ” ሁኔታዎች ውስጥ ሲያሳልፈን ሁልጊዜም ወደ ፍጻሜው ሲደርስ ለመልካም ሆኖ ይጠናቀቃል።

ከአይሁዶች ከባድ ጥላቻ የተነሳ ደቀመዛሙርቱ ጊዜው በጣም አደገኛ መሆኑን ተረድተዋል። ሆኖም ግን የመጽሐፍ ቃል በሚፈጸምበት መንገድ ሲሄዱ ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው የሚሞቱት፤ እነርሱም ኢየሱስ እና የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው።

አንድ ሰው ሌሎችን ሰዎች ሁሉ ለማዳን መሞቱ ይህ እውነተኛው ብርሃን ነው።

በዚያ ሰዓት ምን እየተፈጸመ እንደነበረ የተረዳው ኢየሱስ ብቻ ነበር። እርሱ የዓለም ብርሃን ስለነበረ ምን ማለት እና ምን ማድረግ እንዳለበት በትክክል ያውቃል።

የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም የሚያደርገውን መንገድ ስለተከተለ የእግዚአብሔር ቃል መንገዱን አብርቶለታል፤ በሚናገረው ቃል እና በሚሰራውን ሥራ ውስጥ ሁሉ ይመራዋል።

ዛሬም እንኳን የሰው አእምሮ ስለ ፍጥረታዊው ዓለም ሁሉን አውቆ መጨረስ አልቻለም። የሰው አእምሮ የራሱ የሆኑ ውሱንነቶች አሉት። ትልቁ ችግራችን አለማወቃችንን አለማወቃችን ነው።

በኢየሱስ ዘመንም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች አእምሮ በዘመናቸው እየተከናወነ የነበረውን ነገር ሁሉ መረዳት አልቻለም። እነርሱም የራሳቸውን ሃሳብ በመከተል እራሳቸውን በስሕተት መንገድ መሩ። አካሄዳቸው በአእምሮአዊ ወይም በመንፈሳዊ ጭጋግ ውስጥ እየተደናበሩ እንደሚሄዱ ነበር የሚመስለው። የሚያደርጓቸው ውሳኔዎች ምን ያህል ለራሳቸው አደገኛ እንደነበሩ አልተረዱም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል እየተቃወሙ ነበረ።

ዮሐንስ 11፡10 በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው።

ከፊታችን የሚመጣው ሌሊት ታላቁ መከራ ነው።

ታላቁ መከራ በአርማጌዶን ጭፍጨፋ የሚጠናቀቅ የማያቋርት የሞት ዘመን ነው የሚሆነው።

ሁለቱ ነብያት ሙሴ እና ኤልያስ እንዲሁም 144,000ዎቹ አይሁዳውያንም ይገደላሉ።

እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት የሆኑ የዳኑ ክርስቲያኖች በሙሉ በታላቁ መከራ ውስጥ ይገደላሉ ምክንያቱም እግዚአብሔርን በመንፈስ ያመልኩ ነበር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያኖቻቸውን ትምሕርቶች እንደመከተላቸው መጠን እግዚአብሔርን በእውነት አላመለኩትም። የቤተክርስቲያን እምነቶች ምንም ኃይል አይኖራቸውም ስለዚህ ቤተክርስቲያን ተመላላሾችን በታላቁ መከራ ውስጥ ከመሞት ማዳን አይችሉም። ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች ሊያስደንቁ ይችላሉ ነገር ግን አንዳችም ብርሃን የሌለባቸው መንፈሳዊ ጨለማዎች ናቸው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች ያሉበት የዳኑ ሰዎች ቡድን ጌታ ሲመጣ አያዩም ምክንያቱም ከመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ የቤተክርስቲያን እምነቶችን ያስቀድማሉ፤ ስለዚህ በታላቁ መከራ ጨለማ ውስጥ ይወድቃሉ። በታላቁ መከራ ውስጥ ስለሚገደሉ በምድር ላይ የሚሆነው የ1,000 ዓመቱ የሰላም ዘመን ያመልጣቸዋል። ከዚያም በፍርድ ቀን በትንሳኤ ይነሳሉ። ታላቁ መከራ ከመምጣቱ በፊት ድነው ስለነበረ ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባሉ።

ዮሐንስ 11፡11 ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ፦ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው።

ኢየሱስ በሞት ላይ ያለውን ስልጣን ሊገልጥ ፈለገ፤ ይኸውም ሞትን እንቅልፍ እንደተኛ ሰው ከዚህ ዓለም ጉዳዮች ለጥቂት ሰዓት ብቻ ዘወር ብሎ እንደመመለስ አድርገን እንድናየው ነው።

ስለዚህ ክርስቲያኖች አይሞቱም፤ ለጥቂት ጊዜ ያንቀላፋሉ እንጂ።

ዮሐንስ 11፡12 እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ፦ ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል አሉት።

ደቀመዛሙርቱ አላዛር እንቅልፍ የተኛ መሰላቸው።

ኢየሱስ ግን ስለ ሞት ነበረ የተናገረው።

ዮሐንስ 11፡13 ኢየሱስስ ስለ ሞቱ ተናግሮ ነበር፤ እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ መተኛት እንደ ተናገረ መሰላቸው።

ዮሐንስ 11፡14 እንግዲህ ያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጥ፦ አልዓዛር ሞተ፤

ዮሐንስ 11፡15 እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ አላቸው።

ታላቅ ተዓምር ለማየት ከፈለግን ከባድ ችግር መፈጠር አለበት።

ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እምነት ለማጠንከር ብሎ አላዛርን ከሞት ያስነሳዋል። ከዚያ በኋላ ደቀመዛሙርቱ እምነታቸው ይጠነክርና ኢየሱስ ቢሞት እንኳ እራሱን ከሞት ማስነሳት እንደሚችል ማመን ይችላሉ።

ዮሐንስ 11፡16 ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት፦ ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ።

ቶማስ ምንም ፍርሃት አለነበረውም። በኢየሩሳሌም ኢየሱስ እንደ ፈላ ውሃ የሚንተከተከውን የሐይማኖት መሪዎች ቁጣ ለመጋፈጥ ሲሄድ አብሮት ሄዶ አብሮት ለመሞት ተዘጋጅቶ ነበር።

ዲዲሞስ ማለት መንታ ነው።

ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ መንታ ባህርይ አላቸው። ለኢየሱስ ለመሞት ድፍረት አላቸው፤ ኢየሱስ በዘመናቸው የሚያደርገውን ለማመን ግን ያመነታሉ። ቶማስ ከኢየሱስ ጋር ለመሞት ወኔ ቢኖረውም ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ግን ትንሳኤውን ለማመን በጣም ተቸግሮ ነበር፤ በእጆቹ ውስጥ የችንካሩን ምልክት ካላየሁ አላምንም ብሎ ነበር።

ዮሐንስ 11፡17 ኢየሱስም በመጣ ጊዜ በመቃብር እስከ አሁን አራት ቀን ሆኖት አገኘው።

በዚያ ሰዓት የአላዛር እሬሳ መበስበስ ጀምሮ ነበር።

እግዚአብሔር ቅዱስ የሆነው መሲህ በሦስት ቀን ውስጥ ከሞት እንደሚነሳ ቃል ገብቶ ነበር።

መዝሙር 16፡10 ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።

የሞተ ሰው ስጋው በሶስት ቀን ውስጥ ስጋ አይበሰብስም።

አላዛር ንጹህ የቅድስና ሕይወት ነው የኖረው። ኢየሱስ አላዛርን በሶስት ቀን ውስጥ ቢያስነሳው ሰዎች ትንቢቱ የተናገረው ስለ አላዛር ነው ይሉ ነበር። ለዚህ ነው ኢየሱስ እስከ አራተኛ ቀን የቆየው።

ስለዚህ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ፍንጭ እየሰጣቸው ነበር። የትኛውም ቅዱስ ሰው ከዚያ በፊት በሶስት ቀን ውስጥ ከሞት ተነስቶ አያውቅም። ስለዚህ ይህ ትንቢት የሚናገረው ስለ ኢየሱስ መሆኑን ማስተዋል ነበረባቸው።

የኢየሱስም ሞት ከሶሰት ቀን በኋላ በትንሳኤ ስለሚጠናቀቅ ሞቱ እንደ አደጋ መስሎ ሊታያቸው አይችልም።

ይህንን እውነት ለማጽናት የታላቁን መከራ መጨረሻ እንመልከት፤ በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ ሁለት ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ይገደላሉ። እሬሳቸው ለሦስት ቀን ተኩል በኢየሩሳሌም ጉዳናዎች ላይ ወድቆ ይቆያል። ከዚያ በኋላ ልክ መበስበስ ሲጀምሩ እግዚአብሔር ያስነሳቸውና ወደ ሰማይ ይወስዳቸዋል። እነርሱ ታላላቅ ቅዱሳን ይሆናሉ፤ ነገር ግን ማንም ሰው እነርሱ መበስበስን ያላየው ቅዱስ ከሁለቱ አንዱ ነው እንዳይል ከሶስት ቀን በላይ ሞተው መቆይት አለባቸው።

ራዕይ 11፡9 ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፥ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።

 

ኢየሱስ ከቢታንያ ከተማ የሚመለስበት ቦታ እንመለስ።

ዮሐንስ 11፡18 ቢታንያም አሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩሳሌም ቅርብ ነበረች።

በአንድ ማይል ውስጥ ስምንት ምዕራፎች አሉ። ስለዚህ ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ሁለት ማይል ወይም ሶስት ኪሎሜትር ተኩል ትርቃለች።

 

 

ዮሐንስ 11፡19 ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር።

አላዛር በጣም ታዋቂ ሰው ሳይሆን አይቀርም፤ ምክንያቱም በጣም ብዙ አይሁዶች ለቅሶውን ለመድረስ መጥተዋል።

ዮሐንስ 11፡20 ማርታም ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር።

ማርታ በሥራ የምትተጋ ሴት ነበረች። ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት። ጌዜው የኢየሱስ የመጀመሪያ ምጻት ወደሚጠናቀቅበት እየተቃረበ ነበር፤ ማርታ ደግሞ ልክ እንዘ ዛሬው ዘመን ቤተክርስቲያኖች ኢየሱስ ወደ እርሷ እስኪመጣ መጠበቅ አልቻለችም። የጌታን ምሪት መጠባበቅ አልለመደባትም። እርሷ በለመደባት ትጋት ስለምትንቀሳቀስ ሮጣ ወደ ኢየሱስ ሄደች። ማርያም ግን ከእሕቷ የተሻለች መንፈሳዊ ናት፤ ስለዚህ ጌታ እራሱ እስኪጠራት ድረስ ጠበቀች።

ዮሐንስ 11፡21 ማርታም ኢየሱስን፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤

ማርታ ኢየሱስ እስኪናገራት አልጠበቀችም። እርሷ ራሷ ቀድማ እርሱ ማድረግ የነበረበትን ነገረችው።

ዮሐንስ 11፡22 አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው።

ማርታ በኢየሱስ አምናለው ትላለች ግን እርሱ በሚሰራው ሥራ ላይ ጥያቄ ታነሳበታለች።

ዮሐንስ 11፡23 ኢየሱስም፦ ወንድምሽ ይነሣል አላት።

ዮሐንስ 11፡24 ማርታም፦ በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሣ አውቃለሁ አለችው።

ማርቷ ለዘመኗ የመጣውን ቃል አላወቀችውም። ስለ መጨረሻው ትንሳኤ ታውቃለች ግን በራሷ ዘመን ትንሳኤ ሊኖር እንደሚችል ማመን አልቻለችም።

ይህ የሰው አለማመን እንግዳ የሆነ ገጽታ ነው።

እግዚአብሔር ለብዙ ዘመናት ሞተው የቆዩትን ቅዱሳን ስጋቸው ሙሉ በሙሉ ቢበሰብስም እንኳ በመጨረሻው ቀን ከሙታን ሊያስነሳቸው እንደሚችል ታምናለች። ነገር ግን ኢየሱስ ወዲያ አላዛርን ሊያስነሳው እንደሚችል ማመን አልቻለችም ምክንያቱም አላዛር ከሞተ ብዙ ቆይቷል። ሰውን ከሙታን ማስነሳት የሚቻለው ስጋው ከመበስበሱ በፊት እንደሆነ መስሏታል። ይህ ግን ስለ መጨረሻው ቀን ትንሳኤ ከምታምነው ጋር ይቃረናል።

ስለዚህ አማኞች ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ በዘመናቸው የሚያደርገውን ነገር አያስተውሉም። አማኞች ደህንነት የሚሰማቸው ብዙ ሰው ያመነበትን ሲከተሉ ነው። ዛሬ አማኞች አባል የሆኑበትን ቤተክርስቲያን ለመቃረን በጣም ይፈራሉ። ክርስቲያኖች ሰላም የሚያገኙት ከብዙ ክርስቲያኖች መካከል ሲሆኑ ነው። ብቻቸውን ለመቆም እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ብቻ ለማመን በጣም ይፈራሉ።

ነገር ግን መንፈሳዊ ልምምዳችሁ የሚወሰነው እናንተ እና ኢየሱስ ብቻችሁን በምታደርጉት ሕብረት ነው እንጂ በቤተክርስቲያን አባልነታችሁ አይደለም።

ዮሐንስ 11፡25 ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤

ማርታ ኢየሱስ በሞት ላይ ያለውን ስልጣን ማስተዋል ትችል ዘንድ ኢየሱስ አሁን ማርታ ከእርሱ ጋር ጠለቅ ወዳለ ሕብረት እንድትገባ እየነገራት ነው። ይህንን በሞት ላይ ያለውን ስልጣኑን እውነት መሆኑን የሞተ ሰውን እርሷ እያየች በማስነሳት ያረጋግጥላታል።

ኢየሱስ ማርታ ስለ ትንሳኤው ከምታምነው የሩቅ ዘመን ተስፋ ሃሳቧን እንድትለውጥ ያደርጋታል፤ “በመጨረሻው ቀን” ሚሆነው ትንሳኤ ወደፊት ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው የሚሆነው። አይሁዶች ሁሉ በዚህ ያምናሉ ስለዚህ መንጋውን ተከትሎ መንጋጋት ሕዝቡ የሚያምንበትን አምኖ መመሳሰል ለማርታም ቀላል ነው። ነገር ግን እርሱ ብቻ ሙታንን ማስነሳት በሚችለውና ሰው ማድረግ የማይችለውን ማድረግ በሚችለው በኢየሱስ ላይ የግሏ የሆነ እምነት ያስፈልጋት ነበር። በኢየሱስ ለማመን በዙርያዋ ካሉ አይሁዶች ሁሉ የምትቃረንበት ድፍረት ያስፈልጋታል።

የዛሬ ዘመን ቤተክርስቲያን ተመላላሾችም ከቤተክርስቲያን አመለካከትና ልማዶች ጋር ለመቃረን ድፍረት የላቸውም። ስለዚህ መንጋውን ተከትለው ነው የሚሄዱት።

ዮሐንስ 11፡26 ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።

ፈተናው በድጋሚ መጣ። ሥጋዊ ሞት ለሰው መንፈስ ወደ መንግስተ ሰማይ የሚገባበትን በር እንደሚከፍትለት ማየት አንችልምን?

የዚያ የሞተው ሰው መንፈስ በሰማይ ውስጥ ሕያውና ደህና ከሆነ የሰማይ በር ለሆነው ለኢየሱስ በበሩ በኩል የሰውየው መንፈስ ተመልሶ እንዲመጣና ሕይወቱን በምድር ላይ መኖር እንዲቀጥል ማድረግ ቀላል ነው።

ዮሐንስ 11፡27 እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።

ማርታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንደምታምን አፏን ከፍታ መሰከረች።

ዮሐንስ 11፡28 ይህንም ብላ ሄደች እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ፦ መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል አለቻት።

ማርታ ኢየሱስ መምጣቱን ለማርያም በሚስጥር ነገረቻት፤ ምክንያቱም ኢየሱስ መምጣቱን ሰዎች ከሰሙ ፈሪሳውያን በጉልበት ይዘውት ይሄዳሉ ብላ ስለፈራች ነው። ለአላዛር ሊያለቅሱ የመጡት አይሁዶች ኢየሱስን ይጠሉት ነበር።

ዮሐንስ 11፡29 እርስዋም በሰማች ጊዜ ፈጥና ተነሣች ወደ እርሱም መጣች፤

ማርያም ኢየሱስ ሲናገር እስክትሰማ ድረስ ንቅንቅ አላለችም። ሲናገራት ከሰማች በኋላ ወዲያው ለቃሉ (ለኢየሱስ) ታዘዘች።

ዮሐንስ 11፡30 ኢየሱስም ማርታ በተቀበለችበት ስፍራ ነበረ እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር።

ዮሐንስ 11፡31 ሲያጽናኑአት ከእርስዋ ጋር በቤት የነበሩ አይሁድም ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ፥ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።

ማርያም ኢየሱስን ለማግኘት ቶሎ ብላ ከቤት ወጣች። አይሁዶች ግን አልገባቸውም። ወደ አላዛር መቃብር ሄዳ ልታለቅስ የወጣች መሰላቸው። ማርያም ግን ወደ መቃብር ሳይሆን ወደ ሕይወት ነበር የሄደችው። አይሁዶች ወደ ሙታን መንደር እየሄደች መሰላቸው።

ዮሐንስ 11፡32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር አለችው።

አሁን ደግሞ ማርያምም በኢየሱስ ላይ የነበራት እምነት ጠፋባት። በዙርያችሁ ያሉ ሰዎች ሁሉ እምነታቸውን ሲጥሉ እናንተም በቀላሉ እምነታችሁ ሊጠፋባችሁ ይችላል።

ይህ “መንጋውን የመከተል” ዝንባሌ በዚህም ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ችግር ነው። ሰዎች ብዙ ሕዝብ ያመነውን ያምናሉ እንጂ ቃሉ የተናገረውን አይደለም የሚያምኑት። ማርያም በዙርያዋ በነበሩት አይሁዶች ሐዘን ውስጥ ተውጣ ወደ ሐዘን መግባት ግዴታ መሰላት። በነዚያ ሰዎች ሁሉ ጥርጣሬ ፊት እርሷ ብቻ በኢየሱስ ማመንዋን ለማሳየት በጣም ፈራች።

ዮሐንስ 11፡33 ኢየሱስም እርስዋ ስታለቅስ ከእርስዋም ጋር የመጡት አይሁድ ሲያለቅሱ አይቶ በመንፈሱ አዘነ በራሱም ታወከ፤

ማርያም በዙርያዋ ለተሰበሰቡት ሰዎች ሐዘን እና ጥርጣሬ እጅ ሰጥታ ነበር። ስለዚህ ተስፋ እንደሌላቸው አረማውያን ሕዝቡ ሲያለቅሱ እርሷም አለቀሰች። ተስፋ መቁረጣቸውና ሐዘናቸው በትንሳኤ እንደማያምኑ የሚያሳይ ምልክት ነው። ሞት ጊዜያዊ ነገር ሳይሆን ማይለወጥ እውነታ መሰላቸው።

ኢየሱስ የታወከው ለምንድነው?

ሙታንን የማስነሳት ኃይል ያለው ብቸኛው ሰው እርሱ ነበረ።

ማርያም ደግሞ ኢየሱስን እንደማያምኑትና እንደሚቃወሙት አይሁዳውያን ማልቀስን መረጠች።

ሰዎች ኢየሱስን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ትተው ከቤተክርስቲያናቸው ቡድን ጋር ነው የሚቆሙት። ቤተክርስቲያን የምትላቸውን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን አያምኑም።

ለኢየሱስ በዋነኛነት ችግር የሆነበት ነገር ማርያም ከኢየሱስ ጋር በመቆም ፈንታ ከማያምኑ አይሁዳውያን ጋር አብራ ለመቆም መምረጧ ነው።

ዮሐንስ 11፡34 ወዴት አኖራችሁት? አለም። እነርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ መጥተህ እይ አሉት።

ጥያቄው ጠለቅ ያለ ጥያቄ ነው።

በዚህ ጥያቄው ማለት የፈለገው ይህ ነው፡-

“በሐዘናችሁ እና በተስፋ መቁረጣችሁ አላዛርን የት አኖራችሁት? መቸም መንግስተ ሰማያት ውስጥ አይደለም ያለው፤ ቢሆን ኖሮ ደስተኞች በሆናችሁ ነበር። የሐዘናችሁ ብዛት የሚያሳየው አላዛር ሲኦል ውስጥ ነው ያለው ብላችሁ እንደምታምኑ ነው።”

እነርሱ ግን በጥርጣሬያቸው እየባሱ ሄዱ።

“ጌታ” እያሉ ይጠሩታል ግን አያምኑበትም። ኢየሱስን ጌታ ብላችሁ መጥራታችሁ ብቻ አማኝ አያደርጋችሁም።

ማቴዎስ 7፡22 በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ካላመንን እና ካልታዘዝን መንፈሳዊ ስጦታዎች ከእግዚአብሔር ቁጣ ሊያድኑን አይችሉም።

ሰዎች ቃሉን ሰምተው የማያምኑና የማይታዘዙ ከሆነ ጌታ እያሉ ስለጠሩት ኢየሱስ አይደነቅባቸውም።

“መጥተህ እይ” - ይህ በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ከአራቱ ማሕተሞች የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉት አራት ሕያዋን ፍጥረታት የሚናገሩት ቃል ነው። አራቱም ሕያዋን ፍጥረታት ተራ በተራ ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እንዴት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እንደሚመላለስ ሚስጥር በገለጡ ጊዜ “መጥተህ እይ” ብለዋል።

በራዕይ ምዕራፍ 2 እና 3 ውስጥ በተገለጡት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ ዮሐንስ ወደ ሰማይ በተነጠቀ ጊዜ በዙፋን ላይ ተቀምጦ ያየው አንድ ብቻ ነው።

 

 

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

ዓይኖች የእውቀት ምልክት ናቸው። የወደፊቱን (አስቀድመው) ያውቃሉ፤ የበፊቱን (ያለፈውንም) ያውቃሉ። እነዚህ ዓይኖች በምድር ላይ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለውን እቅድ ይጠብቃሉ፤ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ተቃዋሚውን ተንኮለኛ መንፈስ እንድታሸንፈው ይረዱዋታል።

ራዕይ 4፡7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

ራዕይ 6፡1 በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

አንበሳው የይሁዳ አንበሳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስን ይወክላል፤ ይህም የተፈጸመው የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት እና ደቀመዛሙርት የእግዚአብሔርን ቃል ሲጽፉና ሲሰብኩ ነው።

“መጥተህ እይ” የሚለው ጥሪ ሐይማኖታዊ አታላይነትን የሚወክለውን ነጭ ፈረስ አጋለጠ። ይህም ፌዘኛ መንፈስ ደጋን ይዟል ቀስት ግን የለውም።

 

 

ራዕይ 6፡2 አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት [ደጋን] ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።

[በዚህ ቃል ውስጥ “ቀስት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ትክክለኛው ትርጉሙ ደጋን ማለት ቀስት ለመተኮስ የሚያገለግነው መሳሪያ ነው። በተጨማሪ በዘፍጥረት 9፡13-15 “ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ” የሚለው ቃል ውስጥ ቀስት ተብሎ የተተረጎመው ቃል ትክክል አይደለም። ቀስት ሳይሆን ደጋን ተብሎ ቢተረጎም ነው ትክክል የሚሆነው። ምክንያቱም የቀስተደመና ቅርጹ እንደ ደጋን እንጂ እንደ ቀስት አይደለም።]

 

 

 

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምሕርት በፖፑ ከምትገዛው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውጭ ሆኖ መዳን አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ አመነጨች። በ860 ዓ.ም አካባቢ ፖፕ ኒኮላስ ቀዳማዊ የተባለ ብርቱ ሰው የመጀመሪያው ዘውድ የጫነ ፖፕ ሆነ። ከ1300 ዓ.ም በኋላ ይህ ዘውድ ባለ ሶስር ድርብ ዘውድ ወደ መሆን ተለወጠ፤ ከዚያ በኋላ እስከዛሬ የካቶሊክ ፖፕ ይህንን ዘውድ ነው የሚጭነው።

ይህ የአንድ ቤተክርስቲያን አባል ከሆናችሁ እና ቤተክርስቲያኒቱን ለሚመራው ሰው ከተገዛችሁ ብቻ ነው መዳን የምትችሉት የሚለው የዲኖሚኔሽን መንፈስ ወደፊትም ብዙ ሰዎችን እየገዛ መሄዱን ይቀጥላል።

ይህ ሁሉ ውሸት ነው ምክንያቱም መዳን በካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ሆነ በየትኛውም ሰው ፈቃድ አይደለም። መዳን ንሰሃ በመግባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ሕብረት ውስጥ በመግባት ነው፤ ይህም የሚከናወነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመጠመቅ እና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ነው።

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

የሐዋርያት ሥራ 2፡39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ሐዋርያው ጴጥሮስ የተናገረው ቃል እውነተኛው የይሆዳ አንበሳ ድምጽ (እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል) ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስን የማያምኑ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ከሳቱበት ስሕተተት እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል አማኞችን ጠብቋቸዋል።

ራዕይ 6፡3 ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሁለተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፖለቲካ ውስጥ መግባት ጀመረች፤ ፖለቲካ ደግሞ እራስን የማሳት ጥበብ ነው። በመካከለኛው ዘመን ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አውሮፓ ውስጥ ታላቅ ፖለቲካዊ ኃይል ሆና ተነሳች፤ መካከለኛው ዘመን ሌላ መጠሪያው የጨለማው ዘመን ነው። በዚያ ዘመን ሰዎች ለቤተክርስቲያን እንዲገዙ ተብሎ በጦር መሳሪያ ኃይል ጭምር ተገድደዋል።

 

 

ራዕይ 6፡4 ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፥ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።

ቀጥሎ ሌላ ፈረስ ይመጣል፤ ግን ማንም አልተቀመጠበትም። የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በዚያ ጊዜ ሐይማኖት ወይም ቤተክርስቲያናዊነትን ከፖለቲካ ጋር አዳቀለና ነፍሰ ገዳይ እንስሳ ፈጠረ። ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር አንስማማም ያሉ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ስለ እምነታቸው ተገደሉ። በጥጃ የተወከለው ሕያው ፍጥረት ግን ለእነዚያ ሰማዕታት በሬ እርሻ ላይ ያለውን ዓይነት ብርታት ሰጣቸው፤ በሬ እርሻ በማረስ ካገለገለ በኋላ ይታረዳል ምክንያቱም ሥጋው በጣም ተፈላጊ ነው።

ራዕይ 6፡5 ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። አየሁም፥ እነሆም፥ ጕራቻ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።

 

 

የቤተክርስቲያንን ሐይማኖት መቆጣጠር እና ፖለቲካዊ ኃይል መያዝ ለክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ አላጠገበውም። ከዚያ በኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ሐይማኖትን ወደ ንግድ በመለወጥ በቁሳቁስ ሰብሳቢ የገንዘብ ወዳጅ መንፈስ ላይ እየጋለበ መሄድ ጀመረ። ቴትዜል የሚባል ቄስ ከሮም ወደ ጀርመኒ የስርየት ወረቀቶችን ለመሸጥ መጣ። ሰዎች የስርየት ወረቀቱን ከገዙ ሐጥያታቸው ይሰረይላቸዋል ብሎ ነበር ፖፑ። ገብስ እና ስንዴ ዳቦ ይጋገርባቸዋል፤ ይህም ዳቦ ወይም እንጀራ የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል። ስለዚህ ቤተክርስቲያን መዳንን ለሙታን በገንዘብ እየሸጠች ነበር። መዳን እና ሐይማኖት ያለምንም ማፈር በገንዘብ እና በመሬት እየተሸጡ ነበር። ቤተክርስቲያን ትልቅ የገንዘብ አፍቃሪ ነጋዴ ወደ መሆን እየተለወጠች ነበረ። ይህ በቤተመቅደሱ ውስጥ ኢየሱስን ያስቆጣው ስግብግቡ የገንዘብ ለዋጮች መንፈስ ነው።

ራዕይ 6፡6 በአራቱም እንስሶች መካከል ድምፅ፦ አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አትጕዳ ሲል ሰማሁ።

ሶስተኛው የሰው መልክ ያለው እንስሳ የሰው ጥበብ ነበረው። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሚስጥራት መፍታት አልቻሉም ነበር፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መሰረታዊ የሆኑ የወንጌል እውነቶችን ወደ ነበሩበት መመለስ ችለዋል። ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር ቴትዜልን እና ፖፑን ለመቃወም መዳን በእምነት ብቻ መሆኑን ሰበከ። ጆን ዌስሊ እንግሊዝ ውስጥ ቅድስና እና የወንጌል ስርጭትን ሰበከ። ይህንንም ተከትሎ በዓለም ዙርያ ታላቅ የወንጌል ስርጭት ዘመን ተጀመረ።

የሰው ጥበብ በእግዚአብሔር ተባረከና 47 ሰዎች በ1611 የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎም ቻሉ። ከዚያ በኋላ ሙሉ በሙሉ ተፈትሾ ቋንቋው ለ150 ዓመታት ተደጋግሞ ተከልሶ በስተመጨረሻ በ1969 አሁን ባለበት መልኩ ታተመ። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ እስከ አሁን ድረስ በዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ገበያዎች ላይ መሪነትን በመያዝ በ1790ዎቹ እንደ ዊልያም ኬሪ የመሳሰሉ ሰዎች ወደ ሕንድ በሄዱበት ጊዜ ለተጀመረው የታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን የጀርባ አጥንት ሆኗል።

እነዚህ ሰዎች የእብራይስጥ እና የግሪክ ቃላትን ወደ እንግሊዝኛ በትክክል እንዲተረጉሙ የእግዚአብሔር መንፈስ አግዟቸዋል። ሆኖም የሰው ጥበብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ብዙ ሚስጥራት መፍታት አልቻለም።

ዘይት መንፈስ ቅዱስን ይወክላል፤ ወይን ደግሞ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እየመራ ከጨለማው ዘመን ውስጥ ያወጣበትን መገለጥ የሚያመጣውን መነቃቃት ይወክላል።

ራዕይ 6፡7 አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ።

 

 

ሰባተኛው ወይም የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን የተከፈተው እንደ ንሥሩ እንስሳ ከፍ ብሎ በሚበርረው ከተፈጥሮ በላይ በሆነው ጴንጤ ቆስጤያዊ ኃይል ነው። ከዚያ በኋላ ለመጨረሻው ዘመን አሜሪካ ውስጥ የተላከው የአሕዛብ ነብይ ዊልያም ብራንሐም የፊተኛው ዝናቡን (ወይም የትምሕርት ዝናብ) የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት መገለጦቹን በድምጽ ቀድቶ አስቀመጠ። እነዚህ ሚስጥራት ሊገለጡ የሚችሉት ጠለቅ ብሎ ማየት በሚችለው በንሥሩ መንፈስ እይታ ብቻ ነው።

እነዚህን መገለጦች ይዞ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ በፊት ግልጽ ያልነበሩ ለመረዳት አስቸጋሪ የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ትረጉም ለራሳችን ማየት አለብን።

ሙሽራይቱ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት በተረዳች ጊዜ ሕይወት የሆነው መንፈስ ቅዱስ ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ትቀበለው ዘንድ ወደ ሰማይ ያነሳታል።

ሕይወት ከምድር ተሰናብቶ በሄደ ጊዜ ሞት ደግሞ ወደ ምድር ይገባል። ሞት ማለት የሕይወት አለመኖር ነው።

ታላቁ መከራም የሚጀምረው ሰነፎቹ ቆነጃጅት የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች በመሆን ፈንታ ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ሲሆኑና ሲገደሉ ነው። ሁለት ነብያት ማለትም ሙሴ እና ኤልያስ ወንጌልን ለ144,000 አይሁዳውያን ያደርሳሉ።

ራዕይ 6፡8 አየሁም፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

ሐመር ፈረስ ሦስት የተለያየ ቀለም ያለቸውን ፈረሶች ይወክላል፤ ምክንያቱም እነዚህ በአንድነት ተቀናጅተው ወደ ንግድ የተለወጠ ፖለቲካዊ ቤተክርስቲያን ይሆናሉ።

የቤተክርስቲያን ቡድኖች የተለያዩ እምነቶች አሉዋቸው ግን ሁላቸውም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው አቋም ተመሳሳይ ነው። አንዳንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ልክ በተጻፈው መሰረት ያምናሉ፤ ነገር ግን በዚያ ላይ ጨምረው ደግሞ አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፉ ነገር ግን መሪዎቻቸው የፈጠሩዋቸውን አስተምሕሮዎችም ያምናሉ። ስለዚህ ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን ሰው ይምራት በሚለው መርሃቸው ይስማማሉ። ይህ አቋማቸው በስተመጨረሻ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነው ፖፕ ሲነሳ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ በሁሉም ቤተክርስቲያኖች ላይ ራስ እንዲሆንና እርሱን የማይቀበሉትን ሁሉ እንዲያጠፋ መንገድ ይከፍትለታል።

“መጥተህ እይ” የሚለው ቃል የክርስቶስ ተቃዋሚ እንዴት ተነስቶ ዓለምን ሁሉ ወደሚቆጣጠርበት ስልጣን እንደሚወጣ እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ያቀረበልን ጥሪ ነው። በተጨማሪም እግዚአብሔር የክርስቶስ ተቃዋሚውን መንፈስ የተቃወመበትንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣብቀው የኖሩ አማኞችን ያዳነበትን አራት መንገዶች ያሳያል።

 

ወደ ኢየሱስ ሕይወት ተመልሰን እንሂድ።

አይሁዶች አሁን በስሕተታቸውና በአለማመናቸው አንድ ሆኑ። ኢየሱስ የትንሳኤ ኃይል መሆኑን ባለማመንና ባለማወቅ አይነሳም ብለው የሚያስቡትን እየበሰበሰ ያለ እሬሳ እንዲያይ ኢየሱስን “መጥተህ እይ” ይሉታል። ይህ ትልቁ የእምነት አልባነት መግለጫ ነው።

ዮሐንስ 11፡35 ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።

በዚህ አለማመንን በሚገልጥ አነጋገር ውስጥ ኢየሱስ የወደፊቷ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ እንደምትወድቅ አይቷል።

የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን የመጨረሻዋ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን በሚነሱበት ዘመን የምትኖረዋ ቤተክርስቲያን ናት።

በዚያ ጊዜ በማርታ እና በማርያም የተወከለችዋ ቤተክርስቲያን ለሕዝቧ በከፊል እውነት በከፊል ደግሞ የሞተ እና የበሰበሰ ትምሕርት ትሰብካለች። በዚህ ለብ ባለ የአለማመን መቃብር ውስጥ ተዘግታ ስትኖር የዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን በከፊል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በከፊል ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ናት።

ለዚህ ነው የአስሩ ቆነጃጅት (የዳኑ ቤተክርስቲያንን የሚወክሉ ንጹህ ሴቶች) ምሳሌ ሁላቸውም መንገስ ቅዱስ ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም እንቅልፍ ተኝተው ነበር የሚለው።

1963-0320 ሶስተኛው ማሕተም

ሙሽራዋ ገና መነቃቃት አላገኘችም። አያችሁ? መነቃቃት እስካሁን ድረስ አልሆነም፤ ሙሽራይቱን የሚያነቃቃ የእግዚአብሔር ኃይል መገለት አልመጣም። አያችሁ? እስካሁን እየተጠባበቅን ነን። ቤተክርስቲያንን ከእንቅልፏ ለማንቃት እነዚያ ሰባት የማይታወቁ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን እንደገና ማሰማት አለባቸው። እርሱም ይለከዋል። ቃል ገብቷል። አሁን፤ አሁን፣ ተመልከቱ።

ሰው የእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ በመቀመጥ በራሱ አመለካከት እየመራ የሚመራትን ቤተክርስቲያን ከትንሳኤውና ከመነጠቅ እንድትጎድል ያደርጋታል።

እግዚአብሔር የሚጠላው የኒቆላውያን ሥራ አንድ ሰውን ከጉባኤው በላይ ከፍ ማድረግ ነው። ቤተክርስቲያንን በዚህ ዘመን ወደ ሕይወት እና ወደ ትንሳኤ እንመራታለን የሚሉ ሰዎች መጨረሻቸው ቤተክርስቲያንን ይዘው ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባት ነው።

ኢየሱስ ያለ ምክንያት አይደለም እንባውን ያፈሰሰው።

እግዚአብሔር ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ከአፉ እንደተፋት ነግሯታል (አፉ ማለት ቃሉ ያለበት ነው)።

ስለዚህ አሁን ግለሰቦች መንቃት እና ቤተክርስቲያን አልቀበል ያለችውን እውነት መፈለግ አለባቸው።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡16 እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

 

ዮሐንስ 11፡36 ስለዚህ አይሁድ፦ እንዴት ይወደው እንደ ነበረ እዩ አሉ።

ይህ ንግግራቸው አይሁዳውያን ምን ያህል ማስተዋል እንደጎደላቸው ያሳያል፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ያለቀሰበትን ትክክለኛውን ምክንያት አላወቁም።

ኢየሱስ የበሰበሰ እሬሳን ማስነሳት አይችልም ብለው የሚያምኑ ብቻ ናቸው የሚያለቅሱት።

ኢየሱስ ግን የሞተው ሰው ሊነሳ መሆኑን አውቋል።

ዮሐንስ 11፡37 ከእነርሱ ግን አንዳንዶቹ፦ ይህ የዕውሩን ዓይኖች የከፈተ ይህን ደግሞ እንዳይሞት ያደርግ ዘንድ ባልቻለም ነበርን? አሉ።

ኢየሱስ ዕውሮችን እያበራ የታመመውን ሰውዬ ግን ለምን እንዳይሞት እንዳላደረገ አይሁዶች አላወቁም። እነዚህ እነዚህ አይሁዶች ከእግዚአብሔር ጋር አይተዋወቁም። ወደ ኋላ ፈቀቅ ብለው ቆመው ኢየሱስ የሚያደርገውን ለማየት በመጠባበቅ ፈንታ የራሳቸውን ሃሳብ መስጠት አበዙ።

ዛሬ ክርስቲያኖች የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ይተቻሉ፤ የተጻፈውን ቃል እንዲሁ ተቀብለው በማመን ፈንታ ያልተመቻቸውን ጥቅስ በራሳቸው አመለካከትና ወግ መተካት ይፈልጋሉ።

ዮሐንስ 11፡38 ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እርሱም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

ኢየሱስ የሰዎቹን ጥርጣሬ ለማስጣል ብዙ ታገለ። ሰዎቹ እምነታቸውን በእርሱ ላይ ማድረግ አቃታቸው።

በተመሳሳይ መንገድ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንም ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በቃል ማመን አልቻለችም። ዛሬ ክርስቲያኖች የተወሰነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያምናሉ፤ ሌላውን ክፍል ይቀይሩታል፣ ይቃረኑታል ወይ ደግሞ ቸል ብለው ያልፉታል።

ዮሐንስ 11፡39 ኢየሱስ፦ ድንጋዩን አንሡ አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል አለችው።

እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሳሳተ የአስተምሕሮ ድንጋይ አለ፤ ይህም ድንጋይ እውነተኛው ብርሃን እንዳይወጣ ይከድነዋል።

አንድ ሰው ሁሉም ቤተክርስቲያኖች ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ፈቀቅ ባሉበት ነገር ላይ ሁሉ ስሕተት ውስጥ መግባታቸውን ማየት መቻል አለበት።

ቤተክርስቲያን ያመነችውን ማመን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዳይከተሉ ያደርጋቸዋል።

“ቤተክርስቲያኔ ማስወገድ ያለባት ስሕተቶች አሉባት” የሚል ሰው በዚህ ዘመን ዓይኑ የበራለት ሰው ነው።

በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ስሕተቶች እጅግ ስር የሰደዱ ቢሆኑም አንድ ሰው ግን ከዚህ ሰው ሰራሽ የሙታን ትምሕርቶችና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የስሕተት ጥልቀት ውስጥ እራሱን ነጻ አውጥቶ በግሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ወደተመሰረተ እምነት መመለስ ይችላል፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱሰ ነው።

ዮሐንስ 11፡40 ኢየሱስ፦ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት።

እግዚአብሔር ዛሬ ምን እየሰራ እንደሆን ማየት ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስን ማመን አለብን እንጂ ቤተክርስቲያንን አይደለም ማመን ያለብን።

ለዚህ ነው በጣም ብዙ የሜሴጅ አማኞች በ2016ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ትራምፕ ይሸነፋል ያሉት። የሜሴጅ ፓስተሮች ያስተማሩዋቸውን የተመረጡ የሰው ንግግር ጥቅሶችን አመኑ፤ በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሩሳሌም ተመልሳ የእሥራኤል ዋና ከተማ እንደምትሆን የተናገረውን ትንቢት አንሰማም አሉ።

ዛሬ ግን ፓስተሮችን ትክክል አይደላችሁም ብሎ የሚጋፈጥ ሰው የለም። ስለዚህ ቤተክርስቲያኖች በስሕተቶቻቸው ታስረው ይቀራሉ። ስለዚህ በዓለም ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ በትክክል አያውቁም።

63-0320 ሶስተኛው ማሕተም

ዛሬ ለምናያቸው መነቃቃቶች ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው… አሁን ያሉን መነቃቃቶች በቤተክርስቲያን ዲኖሚኔሽን የተከፋፈሉ መነቃቃቶች ናቸው፤ እውነተኛ የሆነ መነቃቃት እስከ አሁን ድረስ አላየንም። በፍጹም፤ በጭራሽ። በፍጹም እውነተኛ መነቃቃት አላየንም። በእርግጥ ሚሊዮን፣ ሚሊዮን፣ ሚሊዮን የቤተክርስቲያን አባላት አሉዋቸው ግን የትም ቦታ መነቃቃት አላገኙም። በፍጹም የለም።

ሙሽራዋ ገና መነቃቃት አላገኘችም። አያችሁ? መነቃቃት እስካሁን ድረስ አልሆነም፤ ሙሽራይቱን የሚያነቃቃ የእግዚአብሔር ኃይል መገለት አልመጣም። አያችሁ? እስካሁን እየተጠባበቅን ነን። ቤተክርስቲያንን ከእንቅልፏ ለማንቃት እነዚያ ሰባት የማይታወቁ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን እንደገና ማሰማት አለባቸው። እርሱም ይለከዋል። ቃል ገብቷል። አሁን፤ አሁን፣ ተመልከቱ።

አሁን እርሷ ሞታ ነበርያ

 

ዮሐንስ 11፡41 ድንጋዩንም አነሡት፦ ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ፦ አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አወቅሁ።

ይህ ተዓምር የተደረገበት ዓላማ ኢየሱስ ሙታንን የማስነሳት ኃይል እንዳለው ገልጦ ለማሳየት ነው። ይህም ኃይል እርሱ መሲህ መሆኑን ያረጋግጣል።

አላዛርን ከሞት ማስነሳቱ የብሉይ ኪዳንን ቅዱሳን በሙሉ በራሱ ትንሳኤ ጊዜ አብሮ ከሞት እንደሚያስነሳቸው ቅድሚያ ማሳያ ነው።

በተጨማሪም ይህ የአላዛር ትንሳኤ ኢየሱስ በሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ በእርሱ አምነው የሞቱ ቅዱሳንን በመጨረሻው በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እንደሚያስነሳቸው ቅድሚያ ማሳያ ነው።

ዮሐንስ 11፡42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።

ኢየሱስ አላዛርን ከሞት አስነሳዋለው አለ። ኢየሱስ ሁልጊዜ አደርገዋለው ያለውን ያደርጋል። ይህ የስልጣኑ ማሕተም ነው።

ዛሬ በሚፈጽማቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች አማካኝነት የስልጣኑን ማሕተም እናያለን።

ዮሐንስ 11፡43 ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

አላዛርን በስም መጥራት አለስፈላጊ ነው። አለበለዚያ ኢየሱስ “ወደ ውጭ ና” ብሎ ብቻ ስም ሳይጠራ ቢጮህ ሙታን በሙሉ ይነሱ ነበር።

ኢየሱስ አላዛርን በግል ያውቀዋል።

የመጨረሻው ትንሳኤ ሁሉም ሰው በጂምላ የሚነሳበት ነው፤ ነገር ግን በዚህ ሁሉ ከሞት የሚነሳ የሕዝብ ብዛት ውስጥ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው በግል ያውቀዋል።

“በታላቅ ድምጽ ጮኸ።”

የራዕይ ምዕራፍ 10 ብርቱ መልአክም በምድርና በባሕር ላይ በቆመ ጊዜ ልክ እንደዚሁ በታላቅ ድምጽ ነው የሚጮኸው።

ራዕይ 10፡1 ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

2 የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥

3 እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ስለዚህ ይህ መልአክ የሚወርደው ሙታንን ለማስነሳት ነው።

ማሕተሞቹ ከተፈቱ እና ልዕለ ተፈጥሮአዊው ደመና ከተገለጠ ከአንድ ዓመት በኋላ እንኳ ወንድም ብራንሐም ስለ ትንሳኤ የሚናገረው ገና ወደ ፊት እንደሚሆን አድርጎ ነው።

1964-0119 ሻሎም

ነገር ግን አስታውሱ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብንገባ ኢየሱስ “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው” ብሎ ቃል ገብቶልናል። ታላቁ ንጉስ መሪ ሲመጣ በትሩንም ሲሰነዝር ከዚያ በኋላ “ጊዜ የሚባል ነገር አይኖርም።” ያ የራዕይ ምዕራፍ 10 መልአክ አንድ እግሩን በምድር አንድ እግሩን በባሕር ሲያደርገውና በራሱ ላይ ቀስተደመና ሲወጣ እንዲህ ብሎ ምሏል፡- “ወደፊት አይዘገይም”። ያ ጊዜ ሲደርስ ከሙታን መካከል ትነሳላችሁ። ሌሎቹ እዚያው ሲቀሩ እናንተ ግን ትገባላችሁ።

በ1965 እነዚህ ክስተቶች ገና ወደ ፊት እንደሚፈጸሙ አድርጎ ነበር የተናገረው።

1965 የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ ምዕራፍ 1

በዚህ ዘመን ውስጥ አንድ ቀን የእግዚአብሔር መለከት ሲነፋ ሁሉም ነገር ቀጥ ብሎ ይቆማል፤ በክርስቶስ ሆነው ያንቀላፉም ይነሳሉ

ሙታን ይነሳሉ፤ ይህ የሚሆነው ወደ ፊት ነው።

1965-12 04 መነጠቅ

በዚያ ቀን ከሰማይ ታላቅ ድምጽ ይመጣል፤ “በክርስቶስ ሆነው ያንቀላፉትም ቀድመው ይነሳሉ።”

ይህ እርሱ የሰበከው የመጨረሻ ስብከት ነው።

ወንድም ብራንሐም ከመሞቱ አንድ ወር በፊት የራዕይ ምዕራፍ 6፡1 ነጎድጓድ ድምጹን እንደሚያሰማ ሲጠባበቅ ነበር፤ እንዲሁም የመላእክት አለቃ ድምጽ ሲመጣ ለመስማት ሲጠባበቅ ነበር።

ከመሞቱ አንድ ወር በፊት

1965 – 1127 ሰምቼ ነበር አሁን ግን ዓይኔ አየችህ

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ወሳኝ ሰዓት ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዓት ይመጣል የነጎድጓድ ድምጽ የሚሰማበት ሰዓት፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ልጅ በታላቅ ድምጽ ከሰማያት ይወርዳል፤ በመላእክት አለቃ ድምጽ፣ በእግዚአብሔር መለከት ይመጣል፤ በክርስቶስም ሆነው የሞቱት ይነሳሉ።

ድምጹ መልእክቱ ነው። ነገር ግን ድምጹ እርሱ ከመሞቱ አንድ ወር በፊት እንደተናገረው ገና ወደ ፊት ነው የሚሰማው።

ስለዚህ ድምጹ የተሰማው እርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ገልጦ ያመጣውን መልእክት በተረዳውና በሰበከው ጊዜ አይደለም። ድምጹ የሚሰማው ሙሽራይቱ በስተመጨረሻ የወንድም ብራንሐም መልእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለራሷ ማረጋገጥ በቻለች ጊዜ ነው።

ከዚያም በኋላ አንድ ሚስጥራዊ ነጎድጓድ ድምጹን ያሰማል።

ከዚያ ቀጥሎ የመላእክት አለቃ ድምጽ የሞቱ ቅዱሳንን ያስነሳቸዋል።

63-0320 ሶስተኛው ማሕተም

ሙሽራዋ ገና መነቃቃት አላገኘችም። አያችሁ? መነቃቃት እስካሁን ድረስ አልሆነም፤ ሙሽራይቱን የሚያነቃቃ የእግዚአብሔር ኃይል መገለት አልመጣም። አያችሁ? እስካሁን እየተጠባበቅን ነን። ቤተክርስቲያንን ከእንቅልፏ ለማንቃት እነዚያ ሰባት የማይታወቁ ነጎድጓዶች ድምጻቸውን እንደገና ማሰማት አለባቸው። እርሱም ይለከዋል። ቃል ገብቷል። አሁን፤ አሁን፣ ተመልከቱ።

አሁን እርሷ ሞታ ነበር

የሞተችዋ ሙሽራም ከሙታን ተነስታ አዲሱን አካሏን የምትቀበልበት ጊዜ ነው፤ ከሰባቱ ነጎድጓዶች ድምጽ የተነሳ ብዙ ታላላቅ መነቃቃቶች ይመጣሉ።

ዮሐንስ 11፡44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም፦ ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነታችንን እየገደለ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ትምሕርቶች እና የሰዎች አመለካከቶች ናቸው፤ እነዚህ ትምሕርቶች የቤተክርስቲያን መሪዎች ሕዝባቸውን የሚጠቀልሉባቸው የእሬሳ መገነዣ ጨርቆች ናቸው። የሕዝቡ እጅና እግር በሙሉ በነዚህ አስተምሕሮዎች ተጠቅልሏል። በዚህ ምክንያት ከቤተክርስቲያናችሁ መውጣት አትችሉም፤ መስራት የምትችሉት ለቤተክርስቲያናችሁ ብቻ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ልማዶች ጋር የሚጋጭበት ክፍል ሲኖር ግለሰቦች መጽሐፍ ቅዱስን ለማመን ነጻ አይደሉም።

ስለዚህ ሕዝቡ የቤተክርስቲያን መሪዎች አንብበው መረዳት ያቃታቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ ቸል ብለው ማለፍ ግዴታ ይሆንባቸዋል። ማንም ሰው ፓሰተሩን ለመቃረን አይደፍርም

በዓለም ላይ 45,000 የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ ስለዚህ በቤተክርስቲያን መሪዎች መካከል እጅግ በጣም ብዙ የአመለካከት ልዩነቶች አሉ።

እያንዳንዱ ሰው አባል በሆነበት ቤተክርስቲያን ውስጥ እርሱ የሚከተላት ቤተክርስቲያን ብቻ በሁሉም ነገር ትክክል እንደሆነች አድርጎ እያሰበ ነው የሚኖረው።

“ፊቱም በጨርቅ እንደተጠመጠመ ነበር” የሚለው ቃል የግለሰብ ማንነት በቤተክርስቲያን ውስጥ ተጨፍልቆ እንደሚጠፋ ያመለክታል። ሁሉም መመሳል አለበት። እያንዳንዱ ሰው ቤተክርስቲያን ሁን እንዳለችው ነው የሚሆነው። ማንም ሰው የራሱን አመለካከት ወይም መረዳት መግለጥ አይችልም። እያንዳንዱ አባል ቤተክርስቲያኒቱ የተቀበለችውን አመለካከት እንደ ገደል ማሚቶ ሰምቶ መድገም አለበት።

ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እውነተኛ እምነት ያለው ሰው ከቤተክርስቲያን ልማዶችና የተሳሳቱ እምነቶች ነጻ ወጥቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስን መከተል ይችላል።

 

ነገር ግን የአላዛር ትንሳኤ ታላቅ መከፋፈልን አስከተለ።

አንዳንድ ሰዎች የአሕሁድ መሪዎቻቸው ቢቃወሙዋቸውም በኢየሱስ ማመን ችለዋል።

የቀሩት አይሁድ ግን ማመን ስላልቻሉ በፍጥነት ወደ ሐይማኖት መሪዎቻቸው ሮጠው ሄዱ፤ እነርሱም አለማመናቸውን አጸኑላቸው።

ዮሐንስ 11፡45 ስለዚህ ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤

ማርያም ከቃሉ ጋር በመቆየቷ ለስራ ከምትሯሯጠው ከእሕቷ ማርታ ይልቅ ጠንካራ መንፈሳዊ ሴት መሆን ችላለች።

ስለዚህ ከአይሁዶች መካከል ከማርያም ጋር የተወዳጁት ሰዎችን እንደ እርሷ መንፈሳዊ የመሆን አቅም ነበራቸው። እነዚህ አይሁዶች የትንሳኤው ኃይል ልባቸውን ሊለውጥላቸው የሚችል ሰዎች ናቸው።

የትንሳኤው ኃይል ብዙ አይሁዶች በኢየሱስ እንዲያምኑ አደረገ። የሐይማኖት መሪዎች የሆኑት ፈሪሳውያን በዚያ ስፍራ አልነበሩም። ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎቻቸው በሌሉበት አንዳንድ አይሁዶች ለማመን ነጻነት አግኝተዋል።

እውነትን ፈልገን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችን ማጥናት እና በራሳቸው አመለካከት አስረው ሊያስቀሩን ከሚፈልጉ እንዲሁም እነርሱ መረዳት ያልቻሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከመረዳት ሊከለክሉ ከሚፈልጉ የሐይማኖት መሪዎች መራቅ አለብን።

ዮሐንስ 11፡46 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው።

ትንሳኤው በሕዝቡ መካከል መከፋፈልን ፈጥሯል። በኢየሱስ በእውነተኛው ቃል ማመን ያልፈለጉ ሰዎች ተመልሰው እየሮጡ ወደ ሐይማኖት መሪዎቻቸው ወደ ፈሪሳውያን ሄዱ፤ ፈሪሳውያንም በኢየሱስ አላመኑም። ሕዝቡ መሪዎቻቸው የእግዚአብሔር ቃል የሚናረውን በሙሉ እንዳላመኑ ስላወቁ መሪዎቻቸው ኢየሱስ የተናገረውንና ያደረገውን አጥብቀው እንደሚቃወሙ አውቀዋል። ፈሪሳውያን ኢየሱስን በድንጋይ ወግረው መግደል ፈልገው አልሳካላቸውም።

አሁን ደግሞ ወደ ሰዱቃውያን ቀረብ ማለት ጀመሩ፤ ሰዱቃውያን ከሮማውያን ባለስልጣናት ጋር ፖለቲካዊ ቅርበት ነበራቸው። ሮማውያን የሞት ፍርድ መፍረድ ይችላሉ።

ይህም የአይሁድ መሪዎችን ውሸታምነት ያሳያል።

አስደናቂ በሆነው የትንሳኤ ታምራት የተነሳ ድምቀቱ የደበዘዘው የፈሪሳውያን ክብር ውርደቱ እንዳይበዛ ፈሪሳውያን በትንሳኤ ወደማያምኑት ወደ ሰዱቃውያን ዞር አሉ።

ግን ሕዝቡ ኢየሱስ በሰራው የትንሳኤ ተዓምር በጣም ተደንቀው ስለነበረ ሰዱቃውያን በሕዝቡ ላይ መንፈሳዊ ተጽእኖ የሌላቸው ቡድኖች እንደመሆናቸው መጠን ሕዝቡ እነርሱ ላይ እንዳይነሱባቸው ፈሩ። ስለዚህ ሰዱቃውያን በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ ለማስፈረድ ብለው አይሁድን በጽኑ ጥላቻ ከሚጠሉ ከሮማውያን ጋር ሕብረት ለመፍጠር ተዘጋጁ። ኢየሱስን ዝም ማሰኘት የሚችሉበትን አማራጭ እስካመጣላቸው ድረስ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም።

የቤተክርስቲያን መሪዎችም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በመነሳት የሚከራከራቸውን ወይም እነርሱ መረዳት ያቃታቸውን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳያቸውን ሰው ሁሉ በአስቸኳይ አፉን ማዘጋር ይፈልጋሉ። መሪዎች የተቻላቸውን ሁሉ አድርገው የእግዚአብሔርን ቃል ጸጥ ማሰኘት ይፈልጋሉ።

የዘመናቱ ታሪክ በአጭሩ - የቤተክርስቲያን ዘመን መጽሐፍ ምዕራፍ 10

ያ መንፈስ እና አስተምሕሮ እራሱ ፕሮቴስታንቶችን በሙሉ የሚቃወም ነው፤ እርሱም ዲኖሚኔሽን ይባላል። የኒቆላውያን ሥራ ድርጅታዊነት ነው፤ የቤተክርስቲያንን አመራር በሰው እጅ ማድረግ ነው እና በዚህም መንገድ መንፈስ ቅዱስን ከስልጣኑ ማውረድ ነው። የበለዓም መንገድ ዲኖሚኔሽን ነው፤ ይህም መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ፈንታ የቤተክርስቲያንን መተዳደሪያ ደንብ ይከተላል። እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ብዙዎቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በዲኖሚኔሽን ወጥመድ ተይዘዋል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ እያላቸው ነው፡- “ሕዝቤ ሆይ በሐጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሰፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ።” አያችሁ፣ እነርሱ አያውቁም። ነገር ግን አማኞች ከምድር ወደ ሰማይ ተነጥቀው የሚሄዱበት ሰዓት አሁን ቢሆን አለማወቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ማመካኛ ተደርጎ መቅረብ አይችልም።

የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ ምዕራፍ 9 የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን

ሁልጊዜም ካስተዋላችሁ ሐሰተኛ ነብይ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የቆመ ሰው ነው። ልክ “የክርስቶስ ተቃዋሚ” ማለት “የቃሉ ተቃዋሚ” ማለት እንደመሆኑ ሁሉ እነዚህ ሐሰተኛ ነብያትም ቃሉን እያጣመሙ የራሳቸውን ሰይጣናዊ ትርጉም እየሰጡት ነው የሚንቀሳቀሱት።

ሰዎችን በተሳሳተ መንገድ ይዘው የሚሄዱ ሰዎች ተከታዮቻቸውን በማስፈራራት ከራሳቸው ጋር እንዴት እንደሚያቆራኙዋቸው አስተውላችኋል? ሕዝቡ እነርሱ የሚሉትን የማያደርጉ ከሆነ ወይም ከእነርሱ ቡድን ለቅቀው ከሄዱ እንደሚጠፉ ይነግሩዋቸዋል። እንደዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ሐሰተኛ ነብያት ናቸው፤ ምክንያቱም እውነተኛ ነብይ ሰዎችን ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው የሚመራቸው፤ ሰዎችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው የሚያስተሳስራቸው፤ ደግሞም ሰዎች እርሱን እንዲፈሩትም አያደርግም፤ ከዚያ ይልቅ ቃሉ የሚናገረውን እንዲፈሩ ነው የሚያስተምራቸው። እነዚህ ሰዎች ልጅ እንደ ይሁዳ ዋናው ዓላማቸው ገንዘብ መሆኑን ልብ በሉ።

ዮሐንስ 11፡47 እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው፦ ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋልና።

 

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን በብዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አይስማሙም ነገር ግን ለኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው ጥላቻ ደግሞ አንድነት አላቸው።

የአላዛር ትንሳኤ ኢየሱስ ተዓምራት ማድረጉን መካድ እንዳይችሉ አደረጋቸው። እነርሱ እራሳቸው አንዳችም ኃይል ስለሌላቸው ኢየሱስ ለስልጣናቸው ስጋት እንደሚሆንባቸው ተገነዘቡ።

ኢየሱስ አንድም ትልቅ ሕንጻ ወይም ንብረቶች ሳይኖሩት እጅግ ብዙ ሕዝብ ማስከተል መቻሉ በጣም አስቀንቷቸዋል።

ኢየሱስ አንድም ጊዜ እንኳ ከሕዝብ ገንዘብ አለመሰብሰቡ በራሱ አስፈርቷቸዋል።

ያለማቋረጥ አስተማረ፤ ፈውስ እና ተዓምራትን አደረገ፤ ይህን ሁሉ በነጻ ነበር የሚያደርገው።

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ግን በደሞዝ የሚሰሩ ሰራተኞች ነበሩ፤ ዋናው ትኩረታቸው ለጥረታቸው ክፍያ የሚሆን ንብረት ማፍራት ነው።

ዮሐንስ 11፡48 እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ።

ኢየሱስ መሲሁ መሆኑን የሚያረጋግጡ ድንቅ ተዓምራቱን እያዩ ክደዋል። ሕዝቡም እነርሱን እንዲከተሉ ነው የሚፈልጉት እንጂ ኢየሱስን እንዲከተሉ አይደለም። ዛሬ ደግሞ ሕዝቡ የእነርሱን አመለካከት እንዲከተሉ ያደርጋሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲከተሉ አያደርጉም።

“አገራችን” ከ“ወገናችን” ቀድሞ ነው የተጠቀሰው።

የሐይማኖት መሪዎች ሃሳባቸው የተጠመደው በኃይላቸው፣ በተሰጣቸው ቦት እና በሕዝቡ ላይ ባላቸው ስልጣን ነው።

በዚያ ዘመን ሐይማኖት ወደ ንግድነት ከተለወጠ ቆይቷል።

የሐይማኖት መሪዎች የሕዝቡ ደህንነት የሚያሳስባቸው ይመስላሉ እንጂ ለአፋቸው ብቻ ነው፤ እውነተኛው ፍላጎታቸው የግል ክብር እና ጥቅማቸውን ማስጠበቅ ብቻ ነው። በአደባባይና በመድረኮች ላይ ከፍ ብለው መታየት እና አድናቆትን መቀበል ዋነኛ አንገብጋቢ ጉዳያቸው ነው።

ቀያፋ (በ18 ዓ.ም) ሊቀ ካሕናት ሆነ፤ ግን ካሕን አድርጎ የሾመው ሮማዊው ገዥ ቨለሪየስ ግራተስ ነው።

ቀያፋ በሊቀ ካሕናትነቱ የቆየው እስከ 36 ዓ.ም ነው፤ ከዚያ በኋላ እርሱን ጲላጦስንም ሮማውያን ከስልጣን አስወገዱዋቸው።

ሊቀካሕናቱ ሹመታቸው ሐይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ መሆኑን ልብ በሉ። የሾሙዋቸውም አይሁድን አምርረው የሚጠሉ ሮማውያን ናቸው።

ዮሐንስ 11፡49 በዚያችም ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ፦ እናንተ ምንም አታውቁም፤

50 ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው።

ቀያፋ ሳያውቅ ስለ ኢየሱስ ሞት ትንቢት ተናገረ። ሳያውቀው ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ የሚሞተው የመስዋእቱ በግ መሆኑን ትንቢት ተናገረ።

እግዚአብሔር በሊቀካሕናቱ በኩል ለሕዝቡ መናገር ይችላል። በዚህ ሰዓት ቀያፋ ኢየሱስ ሕዝቡን የሚያድን መስዋእት መሆኑን የእግዚአብሔር አፍ ሆኖ ተናገረ።

ዮሐንስ 11፡51 ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፥ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፤

ቀያፋ ሊቀካሕናት ስለሆነ እግዚአብሔር እንደ ነብይ ተጠቅሞበታል።

እግዚአብሔር ከፈለገ ክፉ ሰውን ተጠቅሞ መልካም ፈቃዱን መፈጸም ይችላል።

ዮሐንስ 11፡52 ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።

ይህ ትንቢት በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋእትነት የእግዚአብሔርን ልጆች በሙሉ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋል።

በዓለም ዙርያ የተበታተኑ ሕዝቦችን መሰብሰብ የሚለው ቃል ሐዋርያት በተሰጣቸው ተልእኮ በዓለም ዙርያ የተበታተኑትን አሕዛብ የሚያድኑበትን ተልእኮ ጭምር ያመለክታል፤ ከዚያ በተጨማሪ በዘመን መጨረሻ የተበታተኑ አይሁዳውያን ወደ እሥራኤል እንደሚሰበሰቡም ያመለክታል።

ቀያፋን እራሱን ጨምሮ ቀያፋ የተናገረውን ቃል ማናቸውም አልተረዱትም።

ዮሐንስ 11፡53 እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ።

ኢየሱስን ያለ ምክንያት ይቃወሙት ስለነበረ በእውነት ላይ ተመስርቶ መሲሃቸው መሆኑን ሲያሳያቸው መቀበል አለፈለጉም። በተወሰነ መንገድ ብቻ እንዲያስቡ ስላስተማሩዋቸው ባልለመዱት መንገድ ማሰብ አይችሉም።

ሁሌ ፖለቲካ ውስጥ የማይጠፋው ቅናትና ሃሜት በአይሁዶች ሐይማኖት ውስጥ ስር ሰዶ ነበር። የአይሁዶች ሐይማኖት ከሮማውያን ፖለቲካዊ ኃይል ጋር በፈጠረው አንድነት የሚያስከትለው ሞት ብቻ ነበረ።

ኢየሱስ ፍትሃዊ ፍርድ አልተፈረደለትም። እርሱን ይዘውት ለፍርድ ሳያቀርቡት በፊት ነው የሞት ፍርድ የፈረዱበት።

ስለዚህ አሁን የሚፈልጉት ቀድመው ያስተላለፉበትን የሞት ፍርድ የሚፈጽሙበት መንገድ ብቻ ነው።

ቀያፋ የክሕነት ልብሱን በመቅደድ የሙሴ ሕግ እንዲያበቃ አድርጓል።

እግዚአብሔርም ቀያፋ የሙሴ ሕግ እንዲያበቃ ማድረጉን መስክሯል። እግዚአብሔር የሙሴ ሕግ ማብቃቱን የመሰከረው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞት የቤተ መቅደሱን መጋረጃ ለሁለት በቀደደ ጊዜ ነው።

የመጀመሪያው ሊቀ ካሕናት አሮን ነበረ። አሮን ልዩ የሆነ የክሕነት ልብስ ተሰጥቶት ነበረ።

ከክሕነት ልብሱ ጋር አንድ የተሰጠ ትዕዛዝ ነበረ። የሊቀ ካሕናቱ ልብስ በፍጹም መቀደድ የለበትም።

ዘጸአት 28፡30 በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።

31 የኤፉዱንም ቀሚስ ሁሉ ሰማያዊ አድርገው።

32 ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።

ቀያፋ ኢየሱስን ጥያቄ በጠየቀ ጊዜ ሊቀ ካሕናቱ እራሱን መቆጣጠር ተስኖት የክሕነት ልብሱን ቀደደ።

ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።

ዮሐንስ 11፡54 ከዚያ ወዲያም ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ከዚያ በምድረ በዳ አጠገብ ወዳለች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።

ኢየሱስን ለመግደል የተነሳሱበት ፍላጎት በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ፈቀቅ አለ። ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ። ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ይህች ከተማ የጠፋች ትመስላለች።

 

 

ከተማይቷ ዝናዋን ብታጣም እንኳ ከስሟ ጋር የተያያዘ ልዩ ነገር አለ።

ዮሴፍ ሁለት ወንድ ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ምናሴ እና ኤፍሬም ነበሩ። የመጀመሪያው ልጅ ምናሴ የብኩርናውን በረከት ሊወርስ ነበረ። ነገር ግን የዮሴፍ አባት ያዕቆብ (ማለትም እሥራኤል) በረከቱን ሊያስተላልፍ በመጣ ጊዜ እጆቹን አጠላልፎ ቀኝ እጁን በምናሴ ላይ ሳይሆን በኤፍሬም ራስ ላይ ጫነ።

ዘፍጥረት 48፡1 ከዚህም ነገር በኋላ እንዲህ ሆነ፤ እነሆ አባትህ ታምሞአል ብለው ለዮሴፍ ነገሩት፤ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።

ዘፍጥረት 48፡13 ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፥ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አደረገው፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው።

14 እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፥ እርሱም ታናሽ ነበረ፥ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ በኵር ነበርና።

15 ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥

16 ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ።

17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው፤ የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።

18 ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው።

19 አባቱም እንቢ አለ እንዲህ ሲል፦ አወቅሁ ልጄ ሆይ፥ አወቅሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።

20 በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ በእናንተ እስራኤል እንዲህ ብሎ ይባርካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ። ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው።

የብኩርናው በረከት ከታላቅየው (አይሁዶችን ከሚወክለው) ወደ ታናሽየው (የአሕዛብ ቤተክርስቲያን) ተሻገረ።

እግዚአብሔር መጀመሪያ አይሁዶችን በመጥራት ታላቅ ወንድም አደረጋቸው። አይሁዶች አንቀበልም ያሉትን የቀራንዮ መድሐኒት ታናሽ ወንድም የነበሩት አሕዛብ ተቀበሉት።

ስለዚህ ኢየሱስ የሕይወቱ የመጨረሻ ክስተቶች ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢየሩሳሌም እስኪፈጸሙ ድረስ እየተጠባበቀ ለመቆየት ትክክለኛው ቦታ የኤፍሬም ከተማ ነበረ።

 

ዮሐንስ 11፡55 የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

ይህ የመጨረሻው የፋሲካ በዓል ብዙ ሕዝብ የተገኘበት በዓል ነበር። አይሁዳውያን ወደ በዓሉ እራሳቸውን ለማንጻት ይሄዱ ነበር፤ ነገር ግን የመጨረሻው ከሐጥያት መንጻት የሚፈጸመው በቀራንዮ ሊከናወን ጊዜው መቅረቡን አላወቁም።

እውነተኛው የፋሲካ በግ ሊሰዋ ቀርቧል፤ አይሁዶች ግን በዚህ በዓል ውስጥ የሚፈጸሙ ክስተቶች ትርጉም ሙሉ በሙሉ ጠፍቶባቸዋል።

ዮሐንስ 11፡56 ኢየሱስንም ይፈልጉት ነበር፤ በመቅደስም ቆመው እርስ በርሳቸው፦ ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣም ይሆንን? ተባባሉ።

ሁላቸውም ኢየሱስ ይመጣል ወይስ አይመጣም እያሉ ግምታቸውን እየሰጡ ነበር፤ ምክንያቱም ከመጣ የአይሁድ መሪዎች ሊይዙት ማሰባቸውን አውቀዋል። ለፋሲካ ሳይመጣ ቢቀር መቅረቱን ተጠቅመው ኢየሱስ በዓላቱን አያከብርም ይሉ ነበር። ነገር ግን ኢየሱሰ እራሱ የፋሲካው በግ መሆኑን አንዳችም አላወቁም።

ዮሐንስ 11፡57 የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቀው ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዘው ነበር።

ይህ ድርጊት በአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ውስጥ ስለነበረው እብደት በግልጥ የሚያሳይ ነበር።

ከተማይቱ በሙሉ በሰላዮች ተወርራ ነበር። የሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡ ኢየሱስን አሳልፈው እንዲሰጡዋቸው ለማስፈራራት ሞከሩ።

የአይሁዶች ሐይማኖት በጣም እየተበላሸ ሄዶ ንጹሕ ሰውን ለመግደል እስከመፈለግ ድረስ ዘቅጦ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችን በፊታቸው እየፈጸመ የነበረው ኢየሱስ በመካከላቸው መሆኑን መታገስ አልቻሉም።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23