ዮሐንስ ምዕራፍ 09. ፍርድ - የማያዩ ያያሉ፤ የሚያዩ ይታወራሉ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 9፡1 ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ።
ዕውሩ ሰውዬ ኢየሱስን አላገኘውም። ኢየሱስ ነው እውሩን ያገኘው።
መዳናችን የሚከናወነው ኢየሱስ እኛን ሊያድነን በመምጣቱ ነው።
የዓለም ብርሐን የሆነው ኢየሱስ ብርሐን አይቶ ወደማያውቀው እውር መጣ።
የዚህን ሰው ፍጥረታዊ ዓይን በማብራት ኢየሱስ በመንፈስ የታወሩ ሰዎችን መንፈሳዊ ዓይን መክፈት እንደሚችል አሳየ፤ መንፈሳዊ ዓይኖቹ የበሩለትም ሰው አማኝ ይሆናል።
ዮሐንስ 9፡2 ደቀ መዛሙርቱም፦ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
የተለያዩ ችግሮች በሕይወታችን ውስጥ አይጠፉም።
ዮሐንስ 9፡3 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።
ችግሮችና በአካል ላይ የሚታዩ ጉድለቶች የግድ የሐጥያተኝነት ሕይወት አመላካች አይደሉም። በሕይወታችን ውስጥ የሚከሰቱ ከባባድ ችግሮች መንስኤያቸው ሐጥያት ብቻ አይደለም። በሕይወታችን ውስጥ ያሉ ከባድ ችግሮች እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጥባቸው መንገዶች ሊሆኑም ይችላሉ።
ዮሐንስ 9፡4 ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።
ለእግዚአብሔር ውጤታማ ሰራተኛ ለመሆን ሰራተኛው በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተላከ ሰው መሆን አለበት
ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ሊልካቸው የሚፈልጋቸው ሰዎች ቤተክርስቲያን ቀድማ ትልካቸዋለች። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሳይሆን ቤተክርስቲያን ትቆጣጠራቸዋለች። በዚያ ሰው እና በተገለጠው ቃል መካከል ከብዙሃኑ “የቡድን አስተሳሰብ” ይልቅ የጠነከረ የግል ሕብረት ያስፈልጋል።
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለዓላማ ነው፤ ይህም ዓላማ ተዓምራትን መስራትና መልካም ማድረግን ይጨምራል። የተሰጠውን ሥራ ለሚስራትና የመጽሐፍን ቃል ለመፈጸም ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ ነበረው። ኢየሱስ መጽሐፍ ስለሚናገረው ቃል እንጂ በዘመኑ ስለ ነበሩት በሰው ሰራሽ ልማዶች ስለተጠመዱ የሐይማኖት ድርጅቶች ግድ አልነበረውም።
ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጡ ሆኖ በቃልም በስራም ይመራው ነበር።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ኢየሱስ በቀጣዩ የፋሲካ በዓል ወቅት ከመሞቱ በፊት ምድራዊ አገልግሎቱን ማጠናቀቅ ላይ ነው ሙሉ ልቡ የነበረው።
ከፊታችን እየመጣ ካለው ከታላቁ መከራ የተነሳ ሕይወታችንን በስርዓት መምራት አለብን። ከታላቁ መከራ በፊት ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ወርዶ ሙሽራይቱን በአየር ላይ ልትቀበለው ስትመጣ በአየር ላይ ሊገናኛት ከምድር ይነጥቃታል።
ኢየሱስ ከምሕረት ዙፋኑ ላይ ከተነሳ በኋላ አሕዛብ በታላቁ መከራ ወቅት ሊድኑ አይችሉም።
መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው እውነትን ሊያስተምረን የሚችለው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
ነገር ግን የተገለጠውን ቃል መረዳት የሚፈልጉ በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ስለዚህ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የሙሽራይቱ አካል ሆነው ወደ ሰማይ የሚነጠቁት።
ሙሽራይቱ ጌታን በአየር ላይ ትቀበለው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ከምድር ላይ ከነጠቃት በኋላ ሕይወት በምድር ላይ አይገኝም።
ሮሜ 8፡10 መንፈሳችሁ ግን … ሕያው ነው።
ሕይወት ከምድር ከለቀቀ በኋላ በታላቁ መከራ ዘመን ሞት ወደ ዓለም ይገባል። መንፈስ ቅዱስ በሌለበት በምድር ላይ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በጨለማ ነው የሚመላለሱት።
አሁን የምንኖርበት ዘመን የወንጌሉ ሌሊት ነው። ከእኛ በኋላ የታላቁ መከራ ጨለማ ይመጣል። በዚያ ጊዜ ላልዳኑ አሕዛብ የሚቀርብ መዳን የለም። የትኛዋም ቤተክርስቲያን በዚያ ጊዜ ሕዝቧን ከታላቁ መከራ ሰቆቃ ማዳን አትችልም።
ዮሐንስ 9፡5 በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ።
ኢየሱስ በምድር ሲኖር ሳለ ልንከተል የሚገባንን አርአያ አሳይቶናል።
ዓለም ሁሉ ከኢየሱስ መማር እና እርሱን ለመምሰል መከተል ይችላል። እኛ ልንከተል መሞከር ያለብንን መንገድ የኢየሱስ አገልግሎት እንደ ብርሃን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ኢየሱስ ለፍጥረታዊ እውር ዓይን ብርሃን መስጠት መቻሉ የመንፈሳዊ ብርሃን ምንጭም እርሱ መሆኑን ያስረዳል። እርሱ ለእውር ሰው ፍጥረታዊ ብርሃን መስጠት ከቻለ መንፈሳዊ እውር ለሆንነው ለእኛም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማየት የምንችልበት መንፈሳዊ ዓይን ያበራልናል።
“ሔዋን የዛፍ ፍሬ በላች፤” “ኢየሱስ በዲሴምበር 25 ተወለደ፤” “ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፤” “ሰባተኛው መልአክ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው፤” “እግዚአብሔር ሥላሴ ነው፤” “የእግዚአብሔር ስም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ነው” … እነዚህ ሁሉ አባባሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆኑ ብርሃን የላቸውም። እነዚህን አስተሳሰቦች የምናምንባቸው ከሆነ ለተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እውር ነን ማለት ነው።
እነዚህን አባባሎች የምናምነው ለምንድነው? ምክንያቱም የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን ስላስተማሩን ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪ ማለትም ዘመናዊ ፈሪሳዊ ነው እውር አድርጎ የሚያስቀረን።
በዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ብዙውን ጊዜ እውነት መስለው የሚንቀሳቀሱ የሰው አመለካከቶች ናቸው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች የሕዝቡ አመለካከት እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ እስከሚቀረጽ ድረስ የተወሰኑ መረጃዎችን ብቻ መርጠው ይሰጡዋቸዋል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው ማረጋገጥ ያቆማሉ፤ ምክንያቱም መሪዎች ራሳቸው እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማሳየት አይችሉም። ከዚያ በኋላ ሕዝቡ የቤተክርስቲያን መሪዎች የነገሩዋቸውን ያለ ምንም ጥያቄ በመቀበል ቤተክርስቲያን ተመላላሽ ይሆናሉ -- እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ አማኝ አይሆኑም።
ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ከተሳሳተ እምነታቸው ጋር ታስረው ስለሚቀሩ እራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅሙም ሆነ ፈቃደኝነቱ አይኖራቸውም።
ዳንኤል 11፡26 መብሉንም የሚበሉ ሰዎች ይሰብሩታል፤
መብል የአስተምሕሮ ምሳሌ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ በማመን ፈንታ በከፊል የሚያምኑ ሰባኪዎችን መስማት የውድቀታችን መንስኤ ነው። አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አስፈላጊ አይደለም ወይም እንዲሁ አባባል ነው፤ ወይም በኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ አንድ ጥቅስ የትርጉም ስሕተት አለበት እያለ ቃሉን ከሚያጣጥል ሰባኪ ተጠንቀቁ። ሐሰተኛ ሰባኪ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተት አለ ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መረዳት የማያስፈልገን ክፍል አለ ይላል። እንደዚህ ዓይነት ሰባኪዎችን ከሰማናቸው እኛም እንስታለን።
ማቴዎስ 4፡4 እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
ትምሕርት ስልጣንን ይወክላል። ተግሳጽ ማለት ስሕተት ሰርተናል ማለት ነው። ልብን ማቅናት የሚያስፈልገው የተሳሳቱ እምነቶቻችንን ለማስተካከል ነው። ምክር ደግሞ እንዴት መልካም መሆን እንደምንችል ያሳየናል።
በመንፈሳዊ ዓይናችን በመታወራችን ማየት ባንችልም እንኳ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቃል እነዚህ ሁሉ በውጡ ይገኛሉ። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ጠለቅ ያሉ ሚስጥራት መረዳት እንድንችል ጥረት ማድረግ አለብን።
ሉቃስ 8፡18 እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፥ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።
የሰማኸውን የተገለጠ ቃል ካመንክ ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ ይሰጥሃል። የተገለጠ ቃል አልቀበልም ብለህ በካድክ ቁጥር ማየት የምትችለው ብርሃንም ይቀንሳል፤ ከዚያም በኋላ በፊት ታውቀው የነበረ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት እራሱ ይጠፋብሃል።
ዮሐንስ 9፡6 ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና።
የሐይማኖት መሪዎች ከፍ ያሉ ሰዎች ናቸው።
ነገር ግን ኢየሱስ ዕውሩን ሊፈውስ ሲፈልግ አፈርን ተጠቀመ። አፈር የምታገኙት ዝቅ በማለት ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ከሁሉ በታች ዝቅ የማለትን አስፈላጊነት እያስተማረን ነው። አዳም ሙሉ በሙሉ ከምድር አፈር ነው የተሰራው። እውር መሆን ማለት ከአካሉ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ክፍል ጎድሏል ማለት ነው። እነዚህ የጎደሉ ንጥረ ነገሮች ከአፈር ውስጥ ይገኛሉ።
ኢየሱስ ከአፉ እንትፍ ያለው ምራቅ ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን ቃል ይወክላል። ምራቁ ዝቅ ብሎ ከሚገኘው አፈር ጋር ተለውሶ ከሰውየው አካል ውስጥ የጎደለውን የአይን ክፍል ይሞላዋል።
ዮሐንስ 9፡7 ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።
ይህ ጠለቅ ያለ እውነት ነው። ዕውሩ ሰውዬ በነበረበት ቦታ ሆኖ ማየት አልቻለም ነበር። ከዚያ ቦታ ተነስቶ ሲሄድ ግን ማየት ይችላል።
የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን በሰው ሰራሽ አስተምሕሮዋቸውና አመለካከቶቻቸው አማካኝነት የእግዚአብሔርን ቃል ማየት እንዳንችል አሳውረውናል። ስለዚህ በመጨረሻው በሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሟል። ከቤተክርስቲያን ውጭ ስንሆን ብቻ ነው እርሱ የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማየት የምንችለው።
ቤተክርስቲያን ውስጥ ስንቀመጥ የፓስተሩን መንፈስ በመቀበል በፓስተሩ መልክ እና ምሳሌ ተሰርተን እንቀራለን።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
የሰሊሆም መጥመቂያ ውሃ ነበረ።
በቃሉ ውሃ መታጠብ መጽሐፍ ቅዱስን ማየትና መረዳት ያስችለናል።
በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ዓላማ መፈጸም የምንችለው እርሱ እንድንሰራለት ሲልከን ብቻ ነው። ሰው ሊልከን አይችልም። ቤተክርስቲያን ልትልከን አትችልም። የእግዚአብሔርን ፈቃን ማከናወን ከፈለግን እግዚአብሔር ሲልከን ብቻ ነው ማከናወን የምንችለው።
ኤፌሶን 5፡25 ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤
26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
እራሳችንን በመንፈስ አጥበን የምናነጻው የእግዚአብሔርን ቃል በማመን እና በቃሉ በመኖር ነው። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ስንናገር ነው ጌታ ኢየሱስ ልኮናል ማለት የምንችለው።
ዮሐንስ 9፡8 ጐረቤቶቹም ቀድሞም ሲለምን አይተውት የነበሩ፦ ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን? አሉ።
ሕዝቡ በሰውየው ላይ የሆነውን ለውጥ ማመን አልቻሉም። ዕውር የነበረ ሰው በድንገት ማየት ጀመረ። ይገርማል! እንዴት ያለ ለውጥ ነው።
የዚህ ሰው ዓይን መብራት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለማስተዋል የሚችል መንፈሳዊ እይታ ተቀብሎ ዳግመኛ መወለድን ያመለክታል። አንድ ሐጥያተኛ ተለውጦ ቅዱስ ሲሆን ሰዎች ለውጡን በግልጽ ማየት ይችላሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ሲቃወም የነበረው ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ ያለውን ብርሃን ማየት የሚችል አማኝ ይሆናል።
ዮሐንስ 9፡9 ሌሎች፦ እርሱ ነው አሉ፤ ሌሎች፦ አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ አሉ፤ እርሱ፦ እኔ ነኝ አለ።
ሰይጣን ሁል ጊዜ በተንኮሉ ሰዎች እውነቱን ፊት ለፊት ከማየት ዓይናቸውን እንዲመልሱ ያደርጋል። ይህ እርሱን የሚመስል ሰው ነው። ሰውየው ግን “ዕውር የነበረው ሰው እኔ ነኝ” ብሎ ተናገረ።
የተፈወሰው ሰውዬ ምንም የማያጠራጥር ምስክርነት ነበረው። መጠራጠር ለፈለጉት ሰዎች አመለካከት እጅ አልሰጠም።
የዛሬ ዘመን ትልቅ እርግማን በክርስትና ውስጥ እርስ በርስ ውድድር ማድረግ ነው።
ታላላቅ ተዓምራት እየተደረጉ ነው፤ ነገር ግን የሚደረጉት በእኔ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካልሆነ እኔን አይመለከተኝም፤ ደግሞም ቢጠፉ ደስ ይለኛል። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ሰው እርሱ የሚሄድባት ቤተክርስቲያን ብቻ ትክክለኛ እንደሆነች እርግጠኛ ነው። ሌሎቹ 45,000 ዲኖሚኔሽናል እና ዲኖሚኔሽናል ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ ስሕተት ውስጥ ናቸው። ለምን? ምክንያቱም የኔ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ትክክል። በዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እራሳችንን እናታልላለን።
ዮሐንስ 9፡10 ታድያ፦ ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ? አሉት።
አይሁዳዊ ጎረቤቶች ግራ ተጋቡ። እነርሱ ፈጽሞ ሊያደርጉ የማይችሉት አንድ ነገር ተደርጓል። ከአእምሮዋቸው በላይ ሆኖባቸዋል።
ስለዚህ አቃቂር ለማውጣት ፈልገው የተፈወሰውን ሰውዬ የፖሊስ ጥያቄ መጠየቅ ጀመሩ። የፈለጉት ነገር የተደረገውን ተዓምር ላለመቀበል ማመካኛ ለማግኘት ነው።
ዮሐንስ 9፡11 እርሱ መልሶ፦ ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና፦ ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ አለ።
ስለዚህ አሁን አይሁዳውያን ጎረቤቶች ኢየሱስ የት እንዳለ ማወቅ ፈለጉ።
ተዓምራቱ እውነተኛ መሆኑን መቀበል አልቻሉም። ተዓምራቱ ለነርሱ ትልቅ ራስ ምታት ሆነባቸው። በተዓምራት አያምኑም።
ብዙ ጥያቄ በማንጋጋታቸው ይች ችግር ዞር የሚልላቸው መስሏቸዋል።
ዮሐንስ 9፡12 ያ ሰው ወዴት ነው? አሉት። አላውቅም አለ።
ሰውየውም አላውቅም ብሎ መለሰ ምክንያቱም ኢየሱስ ወዲያው ከአካባቢው ፈቀቅ ብሎ ነበር።
በዚህ ጊዜ አለማመናቸው ጨመረ።
በኢየሱስ ማመን ስላልቻሉ የሐይማኖት መሪዎቻቸውን ጠሩ። የሐይማኖት መሪዎቻቸው ሲመጡ የልብ ልብ ተሰማቸው ምክንያቱም መሪዎቻቸውም በኢየሱስ አያምኑም።
ዮሐንስ 9፡13 በፊት ዕውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።
የሐይማኖት መሪዎቻቸውን የጠሩት ለአንድ ዓላማ ብቻ ብለው ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ያደረገውን ለመካድ ነው። ዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ቃል ይክዳሉ።
ሔዋን ስለ ማርገዟ እግዚአብሔር ለምን እንደቀጣት ቤተክርስቲያን የሚመላለስ ሰውን ጠይቁ። በጠየቃችሁት ጊዜ መልስ ፍለጋ ወደ ቤተክርስቲያን መሪዎች ይሮጣል። በዚህ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሽምጥጥ አድርገው ይክዳሉ።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
እግዚአብሔር እንደ ቅጣት የሔዋንን ጽንስ ለምን እንዳበዛው ጠይቋቸው፤ የዚያን ጊዜ የሚመልሱት ያጣሉ። እግዚአብሔር መጀመሪያ እንዲበዙ እንዲባዙና ምድርን እንዲሞሉዋት ብሏቸው ነበር።
አሁን ግን እግዚአብሔር የሔዋንን ጽንስ እጅግ ሊያበዛ ፈልጓል። መጀመሪያ ካሰበው የበለጠ ማለት ነው። ለምን?
ዘፍጥረት 1፡27 እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
የሔዋን ቅጣት ልጅ በምትወልድበት ሰዓት በጭንቅ ከመውለድ በተጨማሪ የጽንስ መብዛትንም ያካትታል። ነገር ግን ይህ ቅጣት በአዳም ላይ አልተጣለበትም።
እግዚአብሔር አዳም ሊካፈልበት የማይችለውን ቅጣት በሔዋን ላይ ያደረገባት ለምንድነው?
የቤተክርስቲያን መሪዎች ስለ መጀመሪያው ሐጥያት የሚመጡ ጥያቄዎችን መመለስ አቅቷቸው ቸል ሲሉ ሕዝቡ በመሪዎቻቸው አለማወቅ የተነሳ መሃይም ሆነው ይቀራሉ።
ስለዚህ የቤተክርስቲያን መሪዎች በሰባተኛው መልአክ ወይም መልእክተኛ የመጣውን የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ አንቀበልም ይላሉ። ትምሕርቱንም ለመቀበል እምቢ በማለታቸው የቤተክርስቲያን አባላት በጨለማ ውስጥ እንዲቀሩ ያደርጋሉ። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን የሚመላለሱ ሰዎች የመጀመሪያውን ሐጥያት በተመለከተ ዕውር ሆነው ይቀራሉ።
ራዕይ 10፡7 ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
ዛሬ ግን እውነት ተገልጧል። የቤተክርስቲያን መሪዎች ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መገለጦችን በመካድ ተጠምደዋል። የተገለጠውን ቃል ይክዳሉ።
እግዚአብሔር ለሐጥያት ለምን ስርየት የፈሰሰውን የእንስሳ ደም እንደተቀበለ ብትጠይቋቸው ግራ ከተጋባ ፊት በስተቀር ከእነርሱ መልስ አታገኙም።
ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎችን ሰው ሰራሽ ልማዶች ለወጠ።
ሐይማኖታዊ አገልግሎት ማከናወንና በቅዳሜ ሰንበት ቀን መስበክ ለሐይማኖት መሪዎች ከባድ ስራ ነበረ። የሙሴ ሕግ በሰንበት ሥራ አትስሩ ብሏል። ስለዚህ የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ሰንበትን መተላለፋቸውን እያዩ እንዳላዩ አስመሰሉ።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን መታዘዝ የአይሁድ ሕግ አካል ነው።
ኢሳይያስ 42፡18 እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።
የዕውሮችን ዓይን ማብራት ያስፈለገው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ፈሪሳውያን የዕውሮችን ዓይን ማብራት አይችሉም ምክንያቱም ይህ ከሰው አቅም በላይ የሆነ ሥራ ነው። ይህንን የትንቢት ቃል ሊፈጽመው የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 9፡14 ኢየሱስም ጭቃ አድርጎ ዓይኖቹን የከፈተበት ቀን ሰንበት ነበረ።
ኢየሱስ ምንም ሳይፈራ አንድ ዕውርን በሰንበት ቀን ፈወሰው - ይህ አስደንጋጭ ዜና ነው።
እግዚአብሔር ተዓምራት በማድረጉ በመደነቅ ፈንታ ተዓምራቱን ሥራ ነው አሉት። ሥራ ስለሆነም በሰንበት ቀን የሙሴን ሕግ ጥሷል። ይህ የግብዞች አስተሳሰብ ነው፤ ምክንያቱም ፈሪሳውያን በምኩራብ ውስጥ የሰንበት አገልግሎትን በሚያከናውኑ ጊዜ ብዙ ሥራ ነው የሚሰሩት።
ከዚያ ሌላ ደግሞ አደጋ ውስጥ ላሉ ሰዎች እርዳታ የመስጠት ጉዳይም አለ።
ሉቃስ 14፡5 ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው።
6 ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
አደጋ ውስጥ የወደቀ እንስሳን የምንደርስለት ከሆነ ዕውር የነበረ ሰውን ከችግሩ ነጻ ማውጣትስ ምንድነው ስሕተቱ?
ዮሐንስ 9፡15 ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት፦ እርሱም፦ ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም አላቸው።
ፈሪሳውያን ተበሳጭተዋል። ኢየሱስ ላይ ሞት ለመፍረድ የሚያመቻቸውን ምክንያት አግኝተዋል። ይህ “የቤተክርስቲያናዊነት” መንፈስ በሙላት በክፋቱ ሲገለጥ ነው። ተዓምሩ የተደረገው በእኔ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላልሆነ ትክክለኛ ተዓምር አይደለም የሚል አስተሳሰብ ነው።
ለፈሪሳውያን የማይገዛው ኢየሱስ ፈሪሳውያን ማድረግ የማይችሉትን ነገር አደረገ። እነርሱም እንደተበለጡ ተሰምቷቸው ተናደዱ። ስለዚህ እርሱ ላይ የሞት ፍርድ የሚፈርዱበት ምክንያት ይፈልጋሉ።
ዮሐንስ 9፡16 ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም አሉ። ሌሎች ግን፦ ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል? አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ።
ፈሪሳውያን ኢየሱስ እግዚአብሔር ሊሆን አይችልም አሉ ምክንያቱም በሰንበት መፈወስ አይፈቀድለትም። ሌሎች ግን ከፈሪሳውያን በተሻለ አስተዋይነት ሐጥያተኛ ሰው እንደዚህ ዓይነት ታላቅ ተዓምር ሊያደርግ አይችልም አሉ። ይህም ፈሪሳውያን እንኳ ሊያደርጉ ያልተቻላቸው ተዓምር ነው። የዕውሮችን ዓይን መክፈት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 9፡17 በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ደግሞ አሉት፦ እርሱም፦ ነቢይ ነው አለ።
ዕውሩ ሰውዬ አሁን ደግሞ ኢየሱስ ነብይ ነው አለ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የተናገረው እግዚአብሔር እራሱ የዕውሮችን ዓይን እንደሚከፍት ነው።
ኢሳይያስ 35፡4 ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው።
5 በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።
6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
ኢየሱስ እንደዚህ ያሉ ተዓምራትን አድርጓል። ደንቆሮዎች ጆሮዋቸው ተከፈተ፤ አንካሶች ዘለሉ፤ ዲዳዎች ተናገሩ።
የተፈወሰው ሰውዬ ከሁሉም የበለጠ ለኢየሱስ ታላቅ አክብሮት ነበረው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ማድረግ የሚችለውን ነገር ኢየሱስ አድርጎለታል።
አይሁድ ግን ተበሳጩ። የሆነ መንገድ ፈልገው ይህ ተዓምር ውሸት ነው ብለው ሰዎችን ማሳመን ፈልገዋል።
የተፈወሰው ሰውዬ ኢየሱስን ካገኘ በኋላ በኢየሱስ ይበልጥ እየተደነቀ ስለነበረ በፊት በምኩራብ ውስጥ መሪ የነበሩ ፈሪሳውያን አሁን ምንም አያስገርሙትም።
ዮሐንስ 9፡18 አይሁድ የዚያን ያየውን ወላጆች እስኪጠሩ ድረስ ዕውር እንደ ነበረ እንዳየም ስለ እርሱ አላመኑም፥
ፈሪሳውያን እና ጎረቤቶች ሰውዬው ዕውር ሆኖ አልተወለደም ለማለት የተቻላቸውን ያህል ይፍጨረጨራሉ። ዕውር አልነበረም ብለው ሰውን ካሳመኑ ምንም ተዓምር አልተደረገም ማለት ይችላሉ።
ጎረቤቶች ደግሞ ፈሪሳውያንን ስለሚፈሩ እነርሱ በሚሉት ሁሉ ይስማማሉ፤ አለበለዚያ ከምኩራብ ሊባረሩ ይችላሉ።
ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ዛሬ ተመሳሳይ ችግር አለባቸው። በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ተቀባይነትን ለማግኘት እና ተወዳጅ ለመሆን ብለው ፓሰተራቸው የተናገረውን ሁሉ ያምናሉ።
ነገር ግን ኢየሱስን እግዚአብሔር ነው ብሎ መቀበል ፈሪሳውያን ያልተዘጋጁበት ጉዳይ ነበር።
ስለዚህ የተፈወሰውን ሰውዬ ወላጆች አስጠርተው ጠየቋቸው፤ እነርሱም “እኛን ምን አስጠየቃችሁ? ልጃችንን ጠይቁት” አሏቸው።
ዮሐንስ 9፡19 እነርሱንም፦ እናንተ ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን? ታድያ አሁን እንዴት ያያል? ብለው ጠየቁአቸው።
ዮሐንስ 9፡20 ወላጆቹም መልሰው፦ ይህ ልጃችን እንደ ሆነ ዕውርም ሆኖ እንደ ተወለደ እናውቃለን፤
ዮሐንስ 9፡21 ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም፥ ወይም ዓይኖቹን ማን እንደ ከፈተ እኛ አናውቅም፤ ጠይቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ ራሱ ይናገራል አሉ።
ወላጆቹ ፈርተዋል። ልክ ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደሚመላለሱ ሰዎች ናቸው፤ የዛሬ ሰዎች ከቤተክርስቲያን እንዳይባረሩ ይፈራሉ።
ዮሐንስ 9፡22 ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፤ እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና።
ልክ ቤተክርስቲያን እንደሚመላለሱ ፈሪ ሰዎች የዚህ ሰውዬ ወላጆች ከሐይማኖት ተቋማቸው ውጭ ለተደረገውን ተዓምር እውቅና ለመስጠት ፈሩ። ስለ ኢየሱስ ለመጋፈጥ ፈርተው የተጠየቁትን ጥያቄ ወደ ልጃቸው አስተላለፉ።
ዮሐንስ 9፡23 ስለዚህ ወላጆቹ፦ ሙሉ ሰው ነው፥ ጠይቁት አሉ።
ዮሐንስ 9፡24 ስለዚህ ዕውር የነበረውን ሰው ሁለተኛ ጠርተው፦ እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን አሉት።
የፈሪሳውያንን ጥያቄ ተመልከቱ -- ኢየሱስ ሐጥያተኛ መሆኑን እናውቃለን። ስለዚህ ከእኛ ጋር መስማማት አለባችሁ።
የሐይማኖት መሪዎች ሁልጊዜ በዚህ መንገድ ነው ሰዎችን አስፈራርተው የሚገዙት። እኛ ብቻ ትክክለኞች ነን። ከእኛ ጋር ባትስማሙ ወዮላችሁ።
ጥያቄያቸውን የሚጠይቁት እውነቱን ለማጣራት አልነበረም። ኢየሱስን ላለመቀበል አስቀድመው ወስነዋል፤ አሁን ሙከራቸው ሰውየውን አስፈራርተውት ከእነርሱ ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ነው።
የቤተክርስቲያን መሪዎች አደራረጋቸው እንደዚሁ ነው። በሚያገለግሉት ሥርዓት ውስጥ አእምሮዋቸው የታሰረ ነው፤ ስለዚህ ሌሎች እነርሱ በሚሉት እንዲስማሙ ብቻ ነው የሚያስገድዱት።
ዮሐንስ 9፡25 እርሱም መልሶ፦ ኃጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዕውር እንደ ነበርሁ አሁንም እንዳይ ይህን አንድ ነገር አውቃለሁ አለ።
የተፈወሰው ሰውዬ ስለ ሐጥያት የተጠየቀውን ጥያቄ ሳይነካው አለፈ። ፈሪሳውያን የራሳቸው የሆነ የሐጥያት ትርጉም አላቸው። ሰውየው ውይይቱን በጥበብ ወደ ሚፈልገው ነጥብ አመጣው፤ ይህም ማንም ሊክደው የማይችለው ነጥብ ነው። ዕውር ነበረ፤ አሁን ግን ማየት ችሏል።
የሐይማኖት መሪዎች ሰውዬ ዕውር ሆኖ ቢቀር ደስ ይላቸው ነበር፤ ምክንያቱም ዕውር ከሆነ ምንም አያስቸግራቸውም። አሁን ግን ማየት በመቻሉ በራሱ አእምሮ ማሰብም ጀምሯል፤ ደግሞ ኢየሱስን ደግፎ መናገርም ጀምሯል።
ዮሐንስ 9፡26 ደግመውም፦ ምን አደረገልህ? እንዴትስ ዓይኖችህን ከፈተ? አሉት።
ፈሪሳውያንም ሰውየውን እንዴት እንደተፈወሰ በድጋሚ ጠየቁት። ይህን ያደረጉት ተዓምሩን የሚያወግዙበት አንዳች ነጥብ ለማግኘት ተስፋ አድርገው ነው።
ዮሐንስ 9፡27 እርሱም መልሶ፦ አስቀድሜ ነገርኋችሁ አልሰማችሁምም፤ ስለ ምን ዳግመኛ ልትሰሙ ትወዳላችሁ? እናንተ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትወዳላችሁን? አላቸው።
የተፈወሰውም ሰውዬ የሚሰጣቸው ከስብከት ያልተናነሰ መልስ ነው። የተፈወሰው ሰውዬ ነገርኳችሁ እኮ አላቸው። ምስክርነቴን በድጋሚ ለመስማት የምትጠይቁኝ እናንተም የኢየሱስ ደቀመዛሙርት መሆን ፈልጋችሁ ነው?
ሰውየው ከኢየሱስ ጋር ለጥቂት ደቂቃ ያሳለፈው ጊዜ እርሱን ለውጦታል፤ ስለዚህ የሐይማኖት መሪዎችን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ አልፈራም። ደግሞም ወዲያ የወንጌላዊ ዓይነት አመለካከትም አጎልብቷል፤ ማለትም የእርሱ ምስክርነት ሌሎች ሰዎችን ኢየሱስን ለመከተል ሊያነሳሳቸው ይችላል ብሎ አምኗል።
ዮሐንስ 9፡28 ተሳድበውም፦ አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፥ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን፤
ከዚያ በኋላ ፈሪሳውያን አፌዙበት። በሐይማኖት መሪነታቸው ያላቸው ዝና ሊጠፋ ነው። ስለዚህ ስልጣናቸውን ለማጽናት ብለው የሙሴን ሕግ ጠቀሱ።
“ነብዩ ሙሴ እንዲህ ብሏል…” ብሎ መጥቀስ ለእነርሱ ከኢየሱስ የበለጠ ስልጣን መስሏቸዋል። ፈሪሳውያን በተሳሳተ መንገድ የሚጠቅሱትን የሙሴን ሕግ በመከተል ፈንታ ኢየሱስን የተከተለውን ሰውዬ ገፉት።
ዛሬም ታሪክ እራሱን ይደግማል።
የሜሴጅ ሰባኪዎች ከዊልያም ብራንሐም ንግግር የወሰዱዋቸውን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ያከብሩዋቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን ከማመን ይልቅ እነርሱ “ነብዩ ዊልያም ብራንሐም እንዲህ ብሏል…” ማለት ይቀናቸዋል። ስለዚህ የእርሱን ንግግሮች ወስደው ሰነጣጥቀው እንዳሻቸው ተርጉመው ብዙ የተለያዩ የሜሴጅ ቤተክርስቲያኖች ከፈቱባቸው። ሁላቸውም የተለያዩ ናቸው ግን እያንዳንዱ እኔ ነኝ ትክክለኛ ይላሉ። በተመረጡ ጥቅሶች ላይ ትኩረት እንደማድረጋቸው መጠን እምነታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፈትሸው ስለማረጋገጥ ምንም ግድ የላቸውም።
ዮሐንስ 9፡29 እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፥ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም አሉት።
ሙሴ ብቻ ነው ስልጣን ያለው በማለት ኢየሱስን ወደ ጎን ጣል አደረጉት።
ግን ይህ ትልቅ ግብዝነት ነው። በሙሴ ሕግ ውስጥ አንድም ጊዜ ስለ ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን አልተጻፈም። ሰው ሰራሽ የሆነው የፈሪሳውያን አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው እንደመሆኑ ከንቱ አገልግሎት ነው።
ልክ እንደዚሁ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የትም ቦታ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ተብሎ የተጻፈ አናገኝም። ፓስተር የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። አንድ ጊዜ በተጠቀሰበትም የቤተክርስቲያን ራስ ተብሎ አይደለም የተጠቀሰው።
የሰዎች አሰራር ሁልጊዜም የመጽሐፍ ቅዱስን መርህ አይከተልም።
ፈሪሳውያን ሙሴን የእውነት ቢሰሙት ኖሮ ሙሴ እራሱ ሊመጣ ስላለው ታላቅ ነብይ ሙሴ መናገሩን ባወቁ ነበር። ሙሴ ደግሞ ይህንን ነብይ መስማት እንዳለባቸው ተናግሯቸዋል።
ዘዳግም 18፡15 አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።
ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን ባለመስማታቸው አላወቁም እንጂ ሙሴን አልታዘዝም እያሉ ነበር።
የአንድ ሰውን ፍጥረታዊ ዓይኖች በማብራት ኢየሱስ እውነተኛው አገልግሎቱ የሰዎችን መንፈሳዊ ዓይን ማብራት እንደሆነ መግለጡ ነበር።
ዮሐንስ 9፡30 ሰውዬው መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ከወዴት እንደ ሆነ እናንተ አለማወቃችሁ ይህ ድንቅ ነገር ነው፥ ዳሩ ግን ዓይኖቼን ከፈተ።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ክርስቶስን አላወቁትም። ኢየሱስ የሰዎችን ፍጥረታዊ ዓይን እና መንፈሳዊ ዓይን በመክፈት የእግዚአብሔርን ቃል ማስተዋል እንዲችሉ ይረዳቸዋል። የሐይማኖት መሪዎች ግን ስልጣናቸውንና ሰው ሰራሽ አመለካከቶቻቸውን በመጠቀም ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳያስተውሉ ዓይናቸውን ያሳውራሉ። ይህም ልክ የዘመን መጨረሻን የሚያመለክተው ምሳሌ አስሩም ቆነጃጅት (የዳኑ ክርስቲያኖችን የሚወክሉ ንጹህ ሴቶች) በሙሉ እንቅልፋቸውን መተኛታቸውን እንደሚናገረው ነው።
ማቴዎስ 25፡1 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
2 ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
5 ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
ራዕይ ምዕራፍ 3 የመጨረሻው ዘመን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ዕውር ናት ግን ዕውር መሆኗን አታውቀውም ይላል (ሎዶቅያ የሕዝቡ መብት ማለት ነው)።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
17 … ዕውርም … መሆንህን ስለማታውቅ፥
ይህም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ግራ መጋባት ውስጥ መሆኗን ነገር ግን ግራ መጋባቷ እንኳ እንዳልታወቃት ያመለክታል።
ክርስቲያኖች ሁሉ የየራሳቸውን ቤተክርስቲያን ያደንቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ቤተክርስቲያኖችን ይነቅፋቸዋል። ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ስለ እነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ እንቅልፍ ውስጥ መሆናቸውን እና ዕውር መሆናቸውን እንደሚናገር አያውቁም።
ቤተክርስቲያኖችን እንቅልፍ ውስጥ ያስቀራቸው ማነው? ሰባኪዎቻቸውና መሪዎቻቸው ናቸው።
ይህም በኢየሱስ ዘመን ከነበረው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነው። በዚያ ዘመን እርሱ ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ የሐይማኖት መሪዎችም አልቀበል አሉት።
ዛሬ ኢየሱስ በተገለጠው ቃል አማካኝነት ይገለጣል፤ የቤተክርስቲያን መሪዎች ግን አይቀበሉትም። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ያንኳኳል።
ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦
20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤
በዚህ ክፍል ኢየሱስ እያናገረ ያለው ሐጥያተኞችን ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ነው።
ዮሐንስ 9፡31 እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን።
የተፈወሰው ሰውዬ ለፈሪሳውያን እግዚአብሔር ሐጥያተኞችን እንደማይሰማ ያስታውሳቸዋል። እግዚአብሔር የሚሰማው እውነተኛ አማኞችን ነው።
ዮሐንስ 9፡32 ዕውር ሆኖ የተወለደውን ዓይኖች ማንም እንደ ከፈተ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አልተሰማም፤
የዕውር ዓይን መብራት ተሰምቶ የማያውቅ ተዓምር ነበር። ሙሴ እንኳ እንደዚህ ያለ ተዓምር ማድረግ አልቻለም።
ዮሐንስ 9፡33 ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ምንም ሊያደርግ ባልቻለም ነበር።
ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ባይመጣ ኖሮ እንዲህ ዓይነቱን ድንቅ ተዓምር ለማድረግ ባልቻለ ነበር።
ዮሐንስ 9፡34 መልሰው፦ አንተ ሁለንተናህ በኃጢአት ተወለድህ፥ አንተም እኛን ታስተምረናለህን? አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።
የሰዎቹን ትዕቢት ተመልከቱ። የሐይማኖት መሪዎች እንደመሆናቸው ምንም መማር አያስፈልገንም ብለው ያስባሉ። ሁሉንም ያወቁ መስሏቸዋል።
ልክ እንደ ዛሬዎቹ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖች “… ምንም አያስፈልገንም…” እንደሚሉት ይመስላሉ። ስለዚህ ማንም ምንም ሊያስተምራቸው አይችልም።
የሐይማኖት መሪዎች የተፈወሰውን ሰው አባረሩት። ዕውርና ምንም የማያውቅ ሰው በነበረ ጊዜ ይቀበሉት ነበር። አሁን ግን ማየትና ለራሱ ማሰብ ሲችል አንፈልግህም አሉት።
ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ነው እየሆነ ያለው። መጽሐፍ ቅዱስን በቅጡ የማያውቅ በመንፈስ ዕውር የሆነ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ አለው። ነገር ግን እግዚአብሔር የአንድ ሰውን መንፈሳዊ ዓይኖች ሲከፍትና ሰውየው የቤተክርስቲያን መሪዎች የማያውቋቸውን የእግዚአብሔርን ሚስጥሮች ማስተዋል ሲጀምር ቤተክርስቲያን ወዲያው ታባርረዋለች። የቤተክርስቲያን መሪዎች እነርሱ መመለስ የማይችሉትን ከባድ ጥያቄዎች የሚጠይቅ ሰው አይፈልጉም።
ፈሪሳውያን የተፈወሰው ሰውዬ በሐጥያት የተወለደ ሰው ነው ብለው ነው የሚያምኑት። ለዚህ ነው ዕውር ሆኖ የተወለደው።
ነገር ግን በሐጥያት ነው የተወለደው ብለው ማሰባቸው ከሚጠይቁት ጥያቄ ጋር ይጋጫል ምክንያቱም ጥያቄዎችን የሚጠይቁት ሲወለድ ዕውር አልነበረም ብለው ሰዎችን ለማሳመን ነው። ሲወለድ ዕውር አልነበረም ብለው ሰዎችን ካሳመኑ ተዓምርም አልተደረገም ብለው ማሳመን ይችላሉ። ነገር ግን ዕውር ሆኖ መወለድ የሐጥያተኝነት ማረጋገጫ ነውም ይላሉ። ስለዚህ ንግግራቸው እርስ በርሱ ይምታታል።
እውነተኛውን ቃል የሚቃወሙ የሐይማኖት መሪዎች መጨረሻቸው እራሳቸውን በራሳቸው መቃረን ነው።
ማቴዎስ 28፡19ን ጠቅሰው ሰዎች በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ አለባቸው የሚሉ ሰዎች የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ መጠመቅ የተጻፈውን ይክዳሉ። ደግሞም የእግዚአብሔርን ስም ማግኘትም አይችሉም ምክንያቱም የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን እንደሆነ አያውቁም። መጽሐፍ ቅዱስ ባይደግፋቸውም ሰዎች ሥላሴ የሚሉዋቸው ሶስቱ አካላት አንድ ስም ሊኖራቸው አይችልም። መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የለውም። አንዳንዶች ስሙ አጽናኝ ነው ይላሉ። ነገር ግን አጽናኝ የሚለው ቃል እርሱ የሚሰራውን ሥራ የሚገልጽ ቃል ነው። “አጽናኝ” ስም አይደለም። ስለዚህም ትምሕርታቸው ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ነው።
“እግዚአብሔር ወልድ” መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ መጠሪያ ነው። “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” የሚለውም ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። “እግዚአብሔር አብ” የሚለው መጠሪያ አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው ያለው እንጂ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የለም። ይህ ለምን እንደሆነ በሥላሴ የሚያምኑ ሰዎች ማብራራት አይችሉም።
ዮሐንስ 9፡35 ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ ሲያገኘውም፦ አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን? አለው።
አንድ ሰው የቤተክርስቲያን መሪዎችን ለመጋፈጥ እና ከቤተክርስቲያን ለመባረር ባይፈራ ይህንን ሰው ኢየሱስ ፈልጎ ያገኘዋል። ምክንያቱም ኢየሱስም እራሱ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው ያለው።
በዘመን መጨረሻ በሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሞ ያንኳኳል። ስለዚህ ኢየሱስን ከእንግዲህ ቤተክርስቲያን ውስጥ አታገኙትም። ቤተክርስቲያን የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል አልቀበልም ብላለች።
ከዚህ ቀጥሎ ያለው ሃሳብ ግራ ሊገባችሁ ይችላል። ከቤተክርስቲያን ስትባረሩ ብቻ ነው ኢየሱስን የምታገኙት፤ ምክንያቱም እርሱ ራሱ ከቤተክርስቲያን ውጭ ነው ያለው።
ዮሐንስ 9፡36 እርሱም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በእርሱ አምን ዘንድ ማን ነው? አለ።
ሰውየው ኢየሱስን ባገኘ ጊዜ ይበልጥ ለማወቅ ጓጓ። አንድ ሰው ኢየሱስን ስለ ማግኘቱ ትክክለኛ ማስረጃ ሰውየው ለእግዚአብሔር ቃል ያለው ረሃብና የመማር ፍላጎቱ ነው።
ዮሐንስ 9፡37 ኢየሱስም፦ አይተኸዋልም ከአንተ ጋርም የሚናገረው እርሱ ነው አለው።
የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አላወቁም። ነገር ግን ከቤተክርስቲያን ተባርሮ የወጣ ሰው በቀላሉ ኢየሱስን ሊያውቀው ችሏል።
ዮሐንስ 9፡38 እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አምናለሁ አለ፤ ሰገደለትም።
ሰውየውም ኢየሱስ አመለከ፤ ሰገደለት እንጂ ለሌላ ሰው አልሰገደም።
አንድ ሰው ከሐይማኖት ቤት ተባርሮ እስኪወጣ ድረስ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ቃል መረዳት አይችልም። ለምን? ምክንያቱም የሐይማኖት ቤቶች ስርዓት እና ቤተክርስቲያኖች ራሳቸው የተሳሳቱ ናቸው።
አዲስ ኪዳን ውስጥ ፓስተር ራስ የሆነባት አንድም ቤተክርስቲያን የለችም። ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ ማለት ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን መውጣት አለበት ማለት ነው። የትኛውም አካል ሁለት ራስ ሊኖረው አይችልም።
ዮሐንስ 9፡39 ኢየሱስም፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ።
ይህ እውነተኛ ፍርድ ነው። ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉት ሰዎች ማየት የማይችሉ የማያምኑ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔር የእነርሱን ዓይን ሊያበራ እና መጽሐፍ ቅዱስን እንዲታዘዙ ሊያደርግ ነው፤ እነዚህም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ ልማዶች እና አመለካከቶች የተሞሉ መሪዎች ስለሌሉዋቸው እውነቱን ለመቀበል አይቸገሩም።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ዓይን አለን እናያለን የሚሉ ሰዎች ግን ማየት የሚችሉት የቤተክርስቲያናቸውን ወግና ልማድ ብቻ እንዲሁም የቤተክርስቲያን መሪዎቻቸውን አመለካከት ብቻ ነው። የዓለም ሁኔታ እየተወሳሰበ ሲሄድ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በጣም እየራቁ ይሄዳሉ።
በጣም ትልቅ ምሳሌ የሚሆነን በ2016 ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፉ ነው። አብዛኞቹ ቤተክርስቲያኖች ትራምፕ ምርጫውን አያሸንፍም ብለው ነበር ምክንያቱም መጥፎ ሰው ነው። ነገር ግን አሸነፈ።
ለምን? ምክንያቱም ጥሩ ሰዎች የተባሉት ፕሬዚደንቶች እሥራኤል ምስራቃዊ ኢየሩሳሌምን የራሷ ማድረግ አትችልም ብለው የሚቃወሙትን ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች መጋፈጥ አልቻሉም። መጥፎ ሰውዬ ያሉት ትራምፕ ግን ሙስሊሞችን ተጋፍጦ ኢየሩሳሌም ሙሉ በሙሉ የእሥራኤል ዋና ከተማ መሆንዋን እውቅና ሰጠ። ይህም ድርጊቱ እሥራኤሎች ወደ ምድራቸው ስለ መመለሳቸው የተነገረው ትንቢት እውነት መሆኑን አረጋገጠ።
መጥፎ ሰውዬ የተባለው ትራምፕ ትንቢት እንዲፈጸም ምክንያት ሆነ። ዕውሩ ሰውዬ በድንገት መንፈሳዊ እውነትን ማየት ቻለ። በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ከ2,500 ዓመታት በፊት የተነገረ ትንቦት መፈጸሙ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ተገነዘበ።
ከትራምፕ ጋር ሲነጻጸሩ ከእርሱ የቀደሙት ፕሬዚዳንቶች መልካም ሰዎች ነበሩ፤ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈጸም አስፈላጊ መሆኑን ማየት እንዳይችሉ መንፈሳዊ ዓይናቸው ታውሮ ነበር። ሙስሊሞችንና አላህን ይፈሩ ነበር። ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ምንም አላደረጉም።
ስለዚህ አሁን እግዚአብሔር ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉትን ሰዎች መጠቀም ጀምሯል። ይህም በዘመን መጨረሻ የሚሆነውን አስደናቂ ለውጥ ያሳያል። ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መቆም ያቃታቸው መልካም ሰዎች የባሰ እየታወሩ ይሄዳሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ መጥፎ የተባሉ ሰዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ መልካም ሰዎች የተሻለ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተውላሉ።
ዮሐንስ 9፡40 ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሰምተው፦ እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን? አሉት።
የሐይማኖት መሪዎች በቁጣ አምባረቁ። የዛሬ የቤተክርስቲያን መሪዎችም ልክ እንደዚሁ ነው የሚቆጡት። ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዕውሮች መሆናቸውን መቀበል ያቅታቸዋል። ሐይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የገነቡት ሕዝቡን ጨቁነው ይገዙ ዘንድ መሪዎቻቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ እንዲመቻቸው ነው። በራሳቸው አመለካከት መሰረት እነርሱ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል የተለዩ ምርጦች ናቸው።
ዮሐንስ 9፡41 ኢየሱስም አላቸው፦ ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን፦ እናያለን ትላላችሁ፤ ኃጢአታችሁ ይኖራል።
ፍጥረታዊ ዕውርነት የሚመጣው ከሐጥያት የተነሳ አይደለም። ስለዚህ ፈሪሳውያን በስጋዊ ዓይናቸው ዕውራን ቢሆኑ ኖሮ ሐጥያት የለብንም ማለት በቻሉ ነበር። ዕውር የሆነ ሰው ማየት የማይችለው ሆን ብሎ ብርሃንን እንዳያይ ዓይኖቹን በመጨፈን አይደለም።
ነገር ግን ማየት እንችላለን የሚሉ ሰዎች ብርሃንን ላለማየታቸው ምንም ማመካኛ የላቸውም። ብርሃንን ለማየት እምቢ ማለት ሆን ብሎ ዓይኖችን እንደ መጨፈን ነው።
ፈሪሳውያን ኢየሱስን ከመውደድ ይልቅ ሐይማኖታዊ ቡድናቸውን ነው የሚወድዱት።
ከመረጡት ቡድናቸው ጋር ለመቆየት ብለው መጽሐፍ ቅዱስን ለመካድ ወሰኑ። (ይህም ቡድን ዛሬ ቤተክርስቲያን የምንለው ነው።)
ሐጥያት አለማመን ነው።
ዮሐንስ 8፡24 እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ ብርሃናችን ነው።
መዝሙር 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል አንቀበልም በማለት ብርሃናቸውን አጥፍተዋል፤ ስለዚህ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤ ያም ጨለማ መንፈሳዊ ዕውርነት ነው።
ያዕቆብ 3፡1 ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፥ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።
ሰዎች ራሳቸውን አስተማሪዎች አድርገው ሲሾሙ በጣም መጠንቀቅ አለባቸው (የትምሕርት ቤት አስተማሪ ሲሆኑም እንኳ)።
አስተማሪዎች በአስተምሕሮዋቸው ከሳቱ ለስሕተታቸው እራሳቸው ተጠያቂዎች ይሆናሉ - ከዚያም በላይ እነርሱን ተከትለው ስለሳቱ ሰዎችም ጭምር ተጠያቂዎች ይሆናሉ። አስተማሪዎች ተሳስተው ቢገኙ ቅጣታቸው በጣም ከባድ ነው የሚሆነው።
አስተማሪዎች አንድ ክፉ ባህርይ አላቸው። ሁል ጊዜ እነርሱ ትክክል እንደሆኑ ራሳቸውን ያሳምናሉ። ዛሬ ከ45,000 በላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ። እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ናቸው ግን ሁሉም እኔ ትክክል ነኝ ይላሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ብዙ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች እንደ መኖራቸው መጠን ያንኑ ያክል ብዙ ስሕተት በመካከላቸው መኖሩ አያጠራጥርም።
ምንድነው ይህን ሁሉ ስሕተት ያመጣው? የሰው አመራር ነው። እያንዳንዱ መሪ ወይም ፓስተር ቤተክርስቲያኑን በራሱ አምሳል ይሰራታል።
የቤተክርስቲያን መሪዎች እያንዳንዳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ በመውጣት ለሰሩት ስሕተት መልስ ይሰጡበታል። ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸውን መሪዎች አድርገው ሾመዋል ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብዛኛውን ክፍል ማብራራት እንኳን አይችሉም።
ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ዕውር ሆነው ይቀራሉ።
ሉቃስ 6፡39 ምሳሌም አላቸው፦ ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ በጕድጓድ አይወድቁምን?
ከፊታችን የተደቀነው ጉድጓድ ታላቁ መከራ ነው።
ራዕይ 18፡4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
ኢየሱስ ከሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ውጭ መቆሙን ልብ በሉ።
ኢሳይያስ 42፡16 ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።
በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር ቃሉን ከቤተክርስቲያኖች ውጭ ይገልጣል። እኛንም ከቤተክርስቲያኖቻችን ልማድ ውጭ በሆነ መንገድ ይመራናል።
እግዚአብሔር እራሱ ግለሰቦችን ይመራቸዋል።
ልክ ፈሪሳዊ የምኩራብ ራስ ወይም አለቃ ነኝ ማለቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳለመሆኑ መጠን ፓስተር የቤተክርስቲያን ራስ ነው ማለትም አዲስ ኪዳናዊ እውነት አይደለም ። ፈሪሳውያን በብሉይ ኪዳን ውስጥ አይታወቁም።
የቤተክርስቲያን ትልቁ ድክመቷ ሰውን ራስ አድርጋ መቀበሏ ነው። ሰዎች ግን ዋስትናቸው የሚጠበቀው የቤተክርስቲያን በመሆን ነው ብለው እስካመኑ ድረስ ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ ነው የሚለው ሃሳብ እውነት አለመሆኑን አይገነዘቡም።