ዮሐንስ 08፡21-29. ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 8፡20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።
ኢየሱስ አሁን በቤተመቅደሱ ግምጃ ቤት ውስጥ ነበረ። ከዚህ በፊት ገንዘብ ለዋጮችን አባርሮ ስለነበረ በግምጃ ቤቱ ውስጥ መሆን ለእርሱ ትልቅ አደጋ አለው። ግን ሁላቸውም ደግሞ ፈርተውታል። ስለ ገንዘብ ያላቸውን ስግብግብነት አይቶ ዓይኖቹ በቁጣ ተሞልተው ነበርና ሰዎች ከእርሱ ራቅ ብለው ቆሙ።
ኢየሱስ በገንዘብ ለዋጮች በጣም የተቆጣው ለምንድነው?
ምክንያቱም ወደፊት የቤተክርስቲያን ስሞች የንግድ ድርጅት ማስታወቂያ ሆነው እንደሚያገለግሉ ስላየ ነው።
ምክንያቱም በእነዚህ ስግብግብ ገንዘብ ለዋጮች ውስጥ ወደፊት በሉዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚነሳውን ትልቅ “የንግድ መንፈስ” አይቷል። የቤተክርስቲያን መሪዎች በጣም ሃብታም ይሆናሉ ነገር ግን ገንዘብ ሰብስበው ሰብስበው በቃን አይሉም። የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን ዓይነት ትሕትና ገንዘብ ወዳጆቹ ሎዶቅያውያን አልተጋባባቸውም፤ እነርሱም ገንዘብን በጣም ስለሚወዱ የነብዩን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርት አይቀበሉም።
ቤተክርስቲያን የተጀመረችው በአንድ ድሃ አናጺ ነው።
ዶ/ር ሪቻርድ ሃልቨርሰን የተባለ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር እንዲህ ብሏል፡- “ግሪኮች ወንጌልን ሲያገኙ ወደ ፍልስፍና ለወጡት፤ ሮማውያን ወንጌልን ሲያገኙ ወደ መንግስት ለወጡት፤ አውሮፓውያን ወንጌልን ሲቀበሉ ወደ ባሕል ለወጡት። አሜሪካውያን ወንጌልን ሲያገኙ ግን … ወደ ትልቅ ንግድ ለወጡት!”
የተደራጀ ሐይማኖት ትኩረቱ እግዚአብሔር አይደለም፤ ትኩረቱ በራሱ ላይ ነው። በጣም ብዙ ሕዝብ በረሃብ እየተሰቃየ የቤተክርስቲያን መሪዎች ግን ብዙ ሚሊዮን ብር ያከማቻሉ፤ በቅንጦትም ይኖራሉ።
የሳይንቶሎጂ ቤተክርስቲያን መስራች ሮን ኤል. ሃባርድ እንዲህ አለ፡- “በዛሬይቱ ዓለም ገንዘብ ማግኘት ከፈለጋችሁ ቤተክርስቲያን መክፈት አለባችሁ።”
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙርያ ብዙ መሬት አላት፤ በዓለም ዙርያ ካሉ ድርጅቶች ሁሉ በላይ የበለጠ ሰፊ መሬት ይዛለች። ቫቲካን በካዝናዎችዋ ውስጥ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ንጹህ ወርቅ አላት፤ ከዚህም ውስጥ አብዛኛው በአሜሪካ ፌደራል ሪዘርቭ ባንክ ውስጥ በጥፍጥፍ ወርቅ መልክ ነው የተቀመጠው፤ ከዚያ የተረፈው ደግሞ በእንግሊዝ እን በስዊትዘርላንድ ባንኮች ውስጥ ተቀምጧል። ቫቲካን አሜሪካ ውስጥ ያላት የሃብት መጠን አሜሪካ ውስጥ ያሉ አምስት ታላላቅ ኩባንያዎች ያለቸው ሃብት አንድ ላይ ቢደመር እንኳ እነዚህን ሁሉ የሚበልጥ ሲሆን ይህም ከሃብቷ በጣም ትንሹ ክፍል ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ተጨማሪ ሃብት በመሬት፣ በንብረት፣ በንግድ ሰነድ እና በአክሲዮን አማካኝነት ከማንኛውም ድርጅት፣ ኮርፖሬሽን፣ ባንክ እና መንግስት ሁሉ የበለጠ ያላት ሲሆን ይህም የዚህን ሁሉ ሃብት አስተዳዳሪ የሆነውን ፖፑን በምድር ታሪክ ውስጥ በሃብት አንደኛ አንደኛ አድርጎታል። በእርግጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሃብት እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ መጠኑን በትክክል ለማስላት እንኳ አስቸጋሪ ነው። ፖፑ ስንት ቢሊዮን ዶላር እንዳለው በትክክል መገመት የሚችል የለም። ቤተክርስቲያኒቱም ከተንኮሏ ብዛት አብዛኞቹን የኪነጥበብ ሥራዎችዋን ዋጋ በ1 ዩሮ ብቻ ግምት ታወጣላቸዋለች እንዳይሸጡ ብላ። ደግሞም ቤተክርስቲያኒቱ አንዳችም ግብር አትከፍልም።
የአይሁድ ሐይማኖት ማዕከል በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚደረገው አምልኮ ነው።
የሰዎች አመራር ውስጥ ስግብግብነት በግልጽ በታየበት በአይሁዳውያን መሪዎች ስር ግምጃ ቤቱ የአምልኮ ማዕከል ሆኗል። ሊቀ ካሕናቱ ለራሱ ቤተ መንግስት ሰርቷል። ሐይማኖት ትልቅ ንግድ ሆኗል።
ኢየሱስ በግምጃ ቤቱ ውስጥ ቆሞ የሐይማኖት መሪዎች ከተጠላለፉበት የንግድ መንፈስ የተነሳ እርሱ የቆመበትን የእውነት መንገድ ሊከተሉ ይቅርና ሊያገኙ እንኳ እንደማይችሉ ሊናገር ነው።
ከዚህ በፊት በተከበረው የፋሲካ በዓል ወቅት ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተ መቅደስ ውስጥ አባሮአቸዋል።
ዮሐንስ 2፡14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
ነገር ግን የሐይማኖት መሪዎች ለገንዘብ የነበራቸው ስግብግብነት የሚያመጣባቸውን አደጋ ሊያዩ አልቻሉም። በሐይማኖት ቤት ውስጥ ከገንዘብ ፍቅር ጋር ተያይዞ የመጣው ክፉ ዓመል ኋላ ሃብታም በሆነችው በሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን “ሃብታም ነኝና ባለ ጠጋ ሆኛለው” የሚለውን ኩራት ያስከትላል።
የዚያ ዘመን የገንዘብ ወዳጅነት መንፈስ በየዓመቱ “የክርስቶስን ልደት” በማክበር ሰበብ የመሸጥና የመግዛት ፍላጎትን የሚያጋግል መንፈስ ሆኖ ይገለጣል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የክርስቶስን ልደት አክብሩ ብሎ አልነገረንም። ከዚያ በኋላ ደግሞ በጥር ማለትም በፈረንጆቹ ጃንዋሪ ወር የሚፈጠረውን የገንዘብ እጥረት ጃኑ-ዎሪ ብለውት ቀልድ ቀለዱ።
አሕዛብ ስለ ክሪስማስ ምን ያስባሉ? ክሪስማስ ለአሕዛብ ምን ዓይነት አገልግሎት መስሎ ነው የሚታያቸው? ራሺያዊው ኮምዩኒስት መሪ ሌኒን እንዲህ ብሎ ነበር፡-
“ክሪስማስ ማለት ካፒታሊዝም በሐይማኖታዊ ዘዴ የሚቀጥልበት መንገድ ነው።”
ኢየሱስን ያስቆጣው የትልቅ ንግድ እና የሐይማኖት ጥምረት ነበር።
ስለዚህ ኢየሱስ በተገኘበት በመጨረሻው ፋሲካ ገንዘባቸውን ጥለው ኢየሱስን በመከተል ፈንታ ገንዘባቸውን ይዘው ኢየሱስን መግደል መረጡ። ይህም እርሱ ከተጠመቀ በኋላ አራተኛው ፋሲካ ነበር።
ልክ በራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ማሕተሞቹ ሲፈቱ እንደሆነው ዓይነት ነገር ሆነ፡- አራተኛው ማሕተም ሲፈታ ሞት ገባ።
የመጀመሪያው ማሕተም ሲፈታ የሐይማኖታዊ አታላይነት ነጭ ፈረስ ነበር የታየው። ከዚያ ቀጥሎ ነፍስ ግድያን የሚወክለው ቀይ ፈረስ። ቀጥሎ ደግሞ ገንዘብ የሚሰፈርበት የአጋንንታዊ አሰራርን የሚወክለው ጥቁር ፈረስ። ቀጥሎ ደግሞ በራተኛው ሐመር ፈረስ ላይ የተቀመጠው ሞት።
ስለዚህ ለሞት በሩን የከፈተለት ገንዘብ ነው።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችም ተመሳሳይ ድርጊት ነው የፈጸሙት።
ማቴዎስ 26፡3 በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥
4 ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤
ሊቀ ካሕናቱ ከእጁ እንዳይወጣ የሚፈልገው ቤተመንግስት አለው። ከቃ ለመማር ሳይሆን ቃሉን ለመግደል በአንድነት ተሰበሰቡ።
ዮሐንስ 8፡21 ኢየሱስም ደግሞ፦ እኔ እሄዳለሁ ትፈልጉኛላችሁም በኃጢአታችሁም ትሞታላችሁ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አላቸው።
ኢየሱስ ሐጥያት ስላልነበረበት የመለቀቅ እጣ እንደተጣለበቱ ፍየል ሐጥያታችንን ተሸክሞ ዲያብሎስ ላይ ለማራገፍ ወደ ሲኦል ጉድጓድ ውስጥ ገባ።
በኋላ ዮሐንስ በራዕይ ሲያየው እግሮቹ በእቶን እሳት ላይ ተራምደው የሄዱ ይመስላሉ።
ራዕይ 1፡15 እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥
ይህ የሚያመለክተው እርሱ በሐጥያት ላይ የፈረደውን ፍርድ ነው። የሲኦል እሳት ሐጥያተኞችን ማቃጠል ይችላል። እርሱ ግን ሐጥያት ስለሌለበት በዚያ እቶን ላይ ተራምዶ አንዳችም ሳይቃጠል ሐጥያታችንን በሰይጣን ላይ አራግፎ መመለስ ችሏል። የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ግን ሲሞቱና የራሳቸውን ሐጥያት ተሸክመው ከላያቸው ላይ ሊያራግፉት ወደ ሲኦል ሲወርዱ እዚያው ይቃጠላሉ። በዚህ መንገድ በሐጥያታቸው ይሞታሉ። የኢየሱስን ፈለግ መከተል አይችሉም። ኢየሱስ ያደረገውን ማንም ማድረግ አይችልም።
ሲሞቱ እና በኩነኔ ውስጥ መሆናቸውን ሲገነዘቡ የዚያን ጊዜ በታላቅ ፍርሃትና ጭንቀት ሆነው ከሲኦል ውስጥ የሚያድናቸውን ፍለጋ ይጮሃሉ። የዚያን ጊዜ ግን ኢየሱስን ሊያገኙት አይችሉም። አሁኑኑ በሕይወት እያለህ ኢየሱስን መቀበል እና መከተል አለብህ። ከሞትክ በኋላ የምትድንበት ጊዜ አምልጦሃል። የሞትክ ጊዜ መንፈስ ከስጋህ ወጥቶ ይሄዳል። መንፈስ ደም የለውም። ስለዚህ የኢየሱስ ደም የሞተ ሰውን መንፈስ ማዳን አይችልም።
ዮሐንስ 8፡22 አይሁድም፦ እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ አሉ።
የአይሁድ መሪዎች ጭራሽም አልገባቸውም። እርሱን ሊገድሉት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ያውቃሉ ግን ይህን እያወቁ እራሱን ሊገድል አስቧል ብለው ያስባሉ።
ዮሐንስ 8፡23 እናንተ ከታች ናችሁ፥ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፥ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም።
ዓለማዊ ጥቅማቸውን ማለትም በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ሐይማኖታዊ ስልጣን ለማስጠበቅ ብለው እርሱን ሊገድሉት መፈለጋቸው እና በቤተ መቅደሱ አማካኝነት ያከማቹት ገንዘብ ሰይጣን ከጥልቅ ሆኖ እየገፋፋቸው መሆኑን እንዲያውቁ አድርጓቸዋል።
ኢየሱስ አንዳችም ምድራዊ ስልጣን አልፈለገም። ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ንጉስ ሆኖ ሲገባ እንኳ በአህያ ተቀምጦ ነው የገባው። ከዚህ የበለጠ ትሕትና የለም።
ሰዎችን ገንዘብ ጠይቆ አያውቅም ግን 5,000 ሰዎችን ከዚያም በኋላ 4,000 ሰዎችን በነጻ አብልቷል።
ሕመሟን ላባባሱባት ሐኪሞች ገንዘቧን ሁሉ ከፍላ የጨረሰች ሴት እርሱጋ ስትመጣ ከደም መፍሰስ በሽታ በነጻ ተፈወሰች። ስለዚህ ኢየሱስ በተዓምራት የመፈወስ ችሎታውን ገቢ ማግኛ አድርጎ አልተጠቀመበትም።
ስለዚህ ዓላማው ምድራዊ አልነበረም። ስለዚህ ከምድር አንዳችም ዓለማዊ ትርፍ ወይም ጥቅም አለመፈለጉ የመጣው ከላይ መሆኑን ያረጋግጣል።
ዮሐንስ 8፡24 እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።
ሐጥያት በመሰረቱ አለማመን ነው።
ካላመንን ሐጥያት እንሰራለን። ክፉ ድርጊቶችን ስንፈጽም እነዚያ ድርጊቶች የአለማመን መገለጫዎች ናቸው። ሰውን የሚገድል ሰው የሚገድለው የማያምን ስለሆነ ነው። በልብ ውስጥ ያለ አለማመን እጆች ሐጥያትን እንዲፈጽሙ ያደርጋል።
ስለዚህ ለሐጥያት መድሐኒቱ በኢየሱስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን ነው። አንዴ በትክክል ካመንን በኋላ ሐጥያት ወይም አለማመን ከልባችን ውስጥ ይወገዳል፤ ከዚያ በኋላ ድርጊቶቻችን ሐጥያት መሆናቸው ይቀራል።
የአይሁድ ሐይማት መሪዎች በኢየሱስ ላለማመን ቆርጠው ነበር።
እግዚአብሔር እራሱን ለሙሴ “እኔ ነኝ” በማለት ነበር ያስተዋወቀው።
ዘጸአት 3፡14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።
ኢየሱስ እንዲህ አለ “እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በሐጥያታችሁ ትሞታላችሁና”።
“እኔ ነኝ” የሚለው ንግግር ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ይመሰክራል።
የአይሁድ መሪዎች ሁለት አማራጭ ብቻ ነበር ያላቸው። ወይ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን መቀበል አለዚያ ደግሞ ሳያምኑ በመቅረት ከነሐጥያታቸው መሞት። የእነርሱ ሐጥያት ኢየሱስን ለማመን እምቢ ማለታቸው ነው። ስለዚህ የዛኔውኑ ተፈርዶባቸዋል።
የተወሰኑ ወራት ካለፉ በኋላ መግደል የተባለውን የሐጥያት ድርጊት ይፈጽማሉ። ግን መግደላቸው ሐጥያት የሆነው የአለማመናቸው ውጤት ነው። ዋነኛው ሐጥያታቸው መሲሃቸውን በግፍ ሰቅለው እንዲገድሉ ያበቃቸው አለማመን ነው።
ዮሐንስ 8፡25 እንግዲህ፦ አንተ ማን ነህ? አሉት። ኢየሱስም፦ ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ።
“እኔ ነኝ” ብሎ በመናገሩ እግዚአብሔር ነኝ ማለቱ ገብቷቸዋል።
አሁን ጥያቄ ይጠይቁታል። እርሱም ሲመልስላቸው በግልጽ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ካለ ተሳደበ ብለው ይከስሱታል፤ በድንጋይ ወግረው ለመግደልም በቂ ምክንያት ያገኙበታል። እርሱ ግን በጥበብ እኔ የተናገርኳችሁ ነኝ ብሎ መለሰላቸው።
ኢየሱስ እኔ ማነኝ ብሎ ጴጥሮስን በጠየቀው ጊዜ የጴጥሮስ መልስ የሚከተለው ነው፡-
ማቴዎስ 16፡16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
ኢየሱስ ስለ ራሱ ማንነት ለጴጥሮስ አልነገረውም ነበር። ጴጥሮስ ስለተነገረው ሳይሆን በራሱ እንዲያምን ነው ኢየሱስ የፈለገው።
እውነትን ሰው ስለተናገረ ሰምቶ እንደ ገደል ማሚቶ በመድገም እና በግል ተረድቶ በማመን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።
ኢየሱስ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ስለ እርሱ በራሳቸው እንዲያውቁና እንዲገነዘቡ ፈለገ። እነርሱ ግን በራሳቸው የእርሱን ማንነት ለማወቅ ፈርተዋል። ካወቁትና ካመኑበት ስልጣናቸውን እና ገንዘባቸውን ማጣታቸው ነው።
ዮሐንስ 8፡26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።
ኢየሱስ አሁን በግልጽ ነገራቸው። መሲሁ ማለት አማኑኤል ነው - ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር።
ማቴዎስ 1፡23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
ሕጻኑ ኃያል አምላክ፤ የዘላለም አባት ነው።
ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ይህ እውን ሊሆን የሚችለው ኃያሉ የእግዚአብሔር መንፈስ በዚህ ሰው ውስጥ ከኖረ ብቻ ነው።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ሰው የሆነው ኢየሱስ በውስጡ ያለውን ከተፈጥሮ በላይ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዳምጣል።
ዮሐንስ 8፡27 ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።
ዮሐንስ 14፡10 ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
ዮሐንስ 8፡28 ስለዚህም ኢየሱስ፦ የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።
አይሁዳውያን ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ያኔ እርሱ ማን እንደሆነ ያውቃሉ።
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ። እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ለቆ ሄዷል። የኢየሱስ ሞት ተራ ሞት አይደለም። እርሱ ሲሞት ሶስት ሰዓት ሙሉ ምድር ጨለመች። ከዚያም የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ከሞት ሲነሳም በዘብ ከሚጠበቅና ከታሸገ መቃብር ውስጥ ወጣ። ከዚያም በተዓምራት የተሞላ አዲስ ሐይማኖት ተጀመረ።
በቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩ የሐይማኖት መሪዎች የሆነ ነገር እንደተሳሳቱ ገባቸው። ከዚያ በኋላ በ70 ዓ.ም በጀነራል ታይተስ መሪነት የመጡ የሮማውያን ጦር ሰራዊት ቤተ መቅደሱን አፍርሰው አይሁዳውያንን በተኑዋቸው።
ከዚያ በኋላም አይሁዳውያን ተበታትነው በቀሩ ጊዜ የፈሪሳውያን፣ የሰዱቃውያን እና የካሕናት ተፈላጊነትና ስልጣን ቀነሰ።
ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን እና ካሕናት ኢየሱስን የገደሉት ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ብለው ነበር። ነገር ግን ኢየሱስን በመግደላቸው የራሳቸውን ስልጣን ነው ያጠፉት፤ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ ሮማውያን መጥተው ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አይሁዶችን ጨፈጨፉ።
ዮሐንስ 8፡29 የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው።
የእግዚአብሔር አብ መንፈስ በኢየሱስ ውስጥ ይኖር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “እግዚአብሔር ወልድ” ተናግሮ አያውቅም ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ ሰው አይደለም። ስለዚህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ የኖረበት ፍጹም ሰው ነው። ኢየሱስ የተባለው ሰው እግዚአብሔር አልነበረም። ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ውስጥ ነው። ሁላችሁም በውስጣችሁ ያለውን ናችሁ።
የእግዚአብሔር ልጆች የምትሆኑት የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ ሲኖር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 8፡30 ይህን ሲናገር ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
ዮሐንስ 8፡31 ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ ዓይናቸውን ከሐይማኖታዊ ድርጅቶች አሻግረው እውነቱን በማየት በእግዚአብሔር ቃል የሚያምኑ ሰዎች ይኖራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስን በማመን እና የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል ብቻ ነው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት መሆን የምንችለው።
ዮሐንስ 8፡32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።
እውነት የሆነውን የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል ካመንን ለምንናገረው ነገር እግዚአብሔር ኃላፊነት ይወስዳል ምክንያቱም የምንናገረው የእርሱን ቃል ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ንግግራችን ከሚያስከትለው ውጤት ሁሉ ነጻ እንሆናለን ምክንያቱም ንግግራችን የእርሱ ቃል ነው።
ቃሉን ብቻ ተናገሩ ከዚያ በኋላ የሚሆነው ሁሉ መልካም ነው።
ዮሐንስ 8፡33 እነርሱም መልሰው፦ የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ፦ አርነት ትወጣላችሁ እንዴት ትላለህ? አሉት።
ይህ ንግግራቸው ልክ እንደ ሮማ ካቶሊኮች ይመስላል፤ እነርሱ እንደሚሉት ከጴጥሮስ ሲወርድ ሲዋረድ ስልጣን የተቀበሉ ጳጳሳት ስላሉዋቸው ብቻ እውነትን የያዙ ይመስላቸዋል። ጴጥሮስ ግን ሚስት ያለው ባለ ትዳር ሰው ነበረ፤ ፖፑ ደግሞ ማግባት አይፈቀድለትም። የመጀመሪያው ፖፕ ፖፕ ሊዮ ቀዳማዊ ሲሆን እርሱም በስልጣን የቆየው ከ440 እስከ 461 ዓ.ም ነበረ። ከእርሱ በፊት የነበሩ የሮም ጳጳሳት ፖፕ አልተባሉም ነበር። የቤተክርስቲያኖች ሁሉ ዋና ራስ ተብለውም አልተጠሩም።
የትኛውም የካቶሊክ ጳጳስ ጴጥሮስ ባጠመቀበት መንገድ አላጠመቀም።
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
ስለዚህ ለ1,600 ዓመታት እየተከታተሉ በስልጣን ላይ የተቀመጡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጴጥሮስ ካስተማረው የእውነት ምሳሌ እየራቀች እንድትሄድ አድርገዋታል።
አይሁዳውያንም እንደዚሁ የአብራሐም ልጆች ነን በማለት ከአብራሐም በስጋ የተወለዱ ዘሮች በመሆናቸው ብቻ በእግዚአብሔር የተመረጡ አድርገው ራሳቸውን ቆጥረው ነበር። ከዚህም የተነሳ የማንም ባርያ አይደለንም ብለዋል።
ሆኖም ግን ለቤተ መቅደሱ ሊቀ ካሕናት እና በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚደረገው ንግድ በመንፈስ ባሪያዎች ሆነው ነበር። ከዚያ በተጨማሪ ሕዝቡ የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች በሙሴ ሕግ ላይ ለጨመሩባቸው አላስፈላጊ ብዙ ትዕዛዞችም ባሪያ ሆነዋል። በጣም ግልጽ ሆኖ የሚታየው እነርሱ ግን እንዳላዩ የሚክዱት ባርነታቸው ደግሞ የሮማ መንግስት እነርሱን አሸንፎ መግዛቱ፤ መምራቱ፣ ግብር ማስገበሩ እና እንደፈለገ እነርሱን ማዘዝ መቻሉ ነው። ስለዚህ ውሸታቸውን ነው እንጂ እነርሱ ነጻ ሰዎች አልነበሩም።
ነገር ግን ትልቁ ባርነታቸው የአለማመን ባርነት ነበር።
ዮሐንስ 8፡34 ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።
ፈሪሳዊ እና ሰዱቃዊ ተብለው የተጠሩበት ማዕረግ እራሱ የእነርሱ ፈጠራ ነበር እንጂ በሙሴ ሕግ ውስጥ አልተጻፈም። እነርሱም የራሳቸውን ሐይማኖታዊ አስተምሕሮ እና እምነት አበጅተዋል፤ ይህም ሐጥያት ነው። እግዚአብሔርን ከተከተላችሁ የራሳችሁን ሃሳብ አትፈጥሩም።
ዮሐንስ 8፡35 ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል።
ሐጥያትና የሐጥያት ባርያቆች ጊዜያዊ ጉዳዮች ናቸው።
ቤተ መቅደሱ እና በውስጡ ያሉ የማያምኑ ሰዎች ሁሉ በ37 ዓመታት ውስጥ መጥፋታቸው አይቀርም። ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያንም በዚያ ጊዜ ይጠፋሉ፤ ሕዝቡ ከተበታተነ በኋላም ረቢዎች የእነርሱን ቦታ ይወስዳሉ።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የ2,000 ዓመታት ዕድሜ በሚኖራቸው በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በቤተክርስቲያኑ መካከል ይቆማል። የአይሁድ መሪዎች የእግዚአብሔርን ልጅ የገፉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው። ምርጫቸው የሰነፍ ምርጫ ነበረ።
ዮሐንስ 8፡36 እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ።
ከእግዚአብሔር መንፈስ ስንወለድ መጽሐፍ ቅዱስን ካለማመን ነጻ እንወጣለን። ክርስቶስ በእኛ ውስጥ መኖሩ ከዚህ ሕይወት ጭንቀቶች ሁሉ ነጻ ያደርገናል፤ ምክንያቱም ይህ የአሁኑ ሕይወታችን ወደ ፊት በሰማይ ቤታችን ለምንኖረው ኑሮ መለማመጃ ጊዜ ነው።
የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን በመኖሩ የቅድስና ሕይወት መኖር እንድንፈልግ ያደርገናል፤ ከሐጥያት ነጻ መውጣት የምንችለውም ክርስቶስ በውስጣችን ሲኖር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 8፡37 የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።
አይሁዶች በስጋ ከአብራሐም ዘር ነው የተወለዱት። ነገር ግን ተስፋ የተገባላቸውን መሲህ መግደል መፈለጋቸው የእግዚአብሔር ቃል በልባቸው ውስጥ ቦታ እንደሌለው ያሳያል። ትልቁ ቁምነገር የእግዚአብሔርን ቃል ማመን ነው።
ዮሐንስ 8፡38 እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።
ኢየሱስ የልቡ ፍላጎት በመጽሐፍ የተጻፈውን ቃል መፈጸም ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መፈጸም የእግዚአብሔር ወገን እንድትሆኑ ያደርጋችኋል።
አይሁዳውያን ስለ መሲሁ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን አላመኑም። መጽሐፍ ቅዱስን አለመስማት፤ ቃሉን መለወጥ፣ መቃረን በሰይጣን ድንኳን ውስጥ እንድታድሩ ያደርጋችኋል።
ዮሐንስ 8፡39 መልሰውም፦ አባታችንስ አብርሃም ነው አሉት። ኢየሱስም፦ የአብሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር።
የአይሁድ መሪዎች አጥብቀው የሚከራከሩለት አቋማቸው ከአብራሐም መወለዳቸው ነው። በስጋ ከአብራሐም በመወለዳቸው ብቻ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የተመላለሱ መስሏቸዋል። ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ትንቢቶችን ሲፈጽም እያዩ እርሱ መሲሁ መሆኑን አለማወቃቸው ወይም አለመቀበላቸው በራሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እየተመላለሱ አለመሆናቸውን ያሳያል። እነርሱ ግን ይህ እንኳ አልገባቸውም። ትንቢት በዓይናችን ፊት ሲፈጸም እያየን ካላስተዋልን የእግዚአብሔር ልጆች አይደለንም።
ዮሐንስ 8፡40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
ኢየሱስ ግን አብራሐም እውነት የሚናገር ሰውን መግደል እንደማይፈልግ ነገራቸው። ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሲፈጽም እያዩ መካዳቸው እንዲሁም በእርሱ በግልጽ የሚሰራውን መለኮታዊ ኃይል እያዩ እርሱን አለማመናቸው በእግዚአብሔር ሳይሆን በሰይጣን ማመናቸውን ይመሰክራል።
1ኛ ዮሐንስ 3፡12 ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤
ይህ ማለት “ከክፉው እንደተወለደው እንደ ቃየን አይደለም” ነው።
የእባቡ ዘር የሆነው ቃየን ወንድሙን መግደል ፈለገ። ይህም አይሁዳውያን ኢየሱስን መግደል ከመፈለጋቸው ጋር ይመሳሰላል።
በዘሪው ምሳሌ ውስጥ ዘሮች (የእግዚአብሔር ቃል) በመንገድ ዳር መሬት ላይ ይወድቃሉ (የመንገድ ዳር መሬት መንፈሳዊ መረዳት የሌለው ልብ ነው) ከዚያም ዘሮቹን ወፎች ይበሉዋቸዋል (ሰይጣን እና አጋንንቱ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይቀበሉ ያደርጓቸዋል)።
ማቴዎስ 13፡18 እንግዲህ እናንተ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
19 የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።
ክፉው ማለት በሰይጣን መንፈስ የሚመራ ሰው ነው።
ዮሐንስ 8፡41 እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃየን አባቱ ሰው አይደለም። ሔዋን ቃየን የተወለደው ከእግዚአብሔር ነው አለች፤ ይህም ትክክል ነው ምክንያቱም ሕይወት ሁሉ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው። ሔዋን ቃየን የተወለደው ከአዳም ነው አላለችም።
ሔዋን የሕያዋን ሁሉ እናት ተብላለች። አዳም ግን የሕያዋን ሁሉ አባት አልተባለም።
ሔዋን እግዚአብሔር የሚከተለውን ቃል በተናገራት ጊዜ ቃየንን አርግዛ ነበር፡-
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤
እግዚአብሔር ሔዋንን ከባሏ ስለ መጸነሷ አልቀጣትም። የቃየን መጸነስ ግን ከባሏ አልነበረም።
ሴቲቱ ማሕጸኗን ኢየሱሰ በድንግልና እንዲወለድበት ማዘጋጀት ነበረባት። እርሱም ከተወለደ በኋላ አድጎ ቅዱሳኑን ሁሉ ከምድር አፈር ይጠራቸው ነበር።
ሔዋን እባቡ እንዲያሳስታት ፈቀደች። ስለዚህ እንስሳ ድንግልና ወስዶ ደም አፈሰሰ። ሐጥያት የተጀመረው እንደዚህ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር የፈሰሰውን የእንስሳ ደም ለሐጥያት ማስተሰርያ እንዲሆን ተቀበለ።
ዘፍጥረት 4፡1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።
2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።
በአዳም እና በሔዋን መካከል አንድ ጽንስ ብቻ ነበር የተፈጠረው፤ ሆኖም ግን ሁለት ልጆች ተወለዱ። ምክንያቱም ሔዋን እግዚአብሔር ፊት በቀረበች ጊዜ አስቀድማ ከእባቡ አርግዛ ነበረ።
ምሳሌ 30፡20 እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ፦ አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት።
ሔዋን ዝሙት ፈጸመች፤ ግን ከዚያ በኋላ ምንም ክፉ አልሰራሁም ለማለት ብላ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች። ሕይወትን ሁሉ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን መጀመሪያ የወለደችው ልጅ ከአዳም ነው የተወለደው ለማለት ድፍረቱ አልበራትም።
ምግብ ስትበሉ ምግቡ ሆዳችሁ ውስጥ ይገባል። አንዲት ሴት ስታረግዝ ሆዷ ትልቅ ይሆናል። ስለዚህ መብላት የወሲባዊ ግንኙነት ተምሳሌት ነው።
ሰይጣን ከሰው በታች እና ከዝንጀሮዎች በላይ ሆኖ የተፈጠረውን ጥበበኛ ወይም ተንኮለኛ እንስሳ እባብን ሴቲቱ የእግዚአብሔርን ቃል እንድትተላለፍ ያስታት ዘንድ ላከው።
በድንግልና በመውለድ ፈንታ ሔዋን ሕይወት በግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲፈጠር አደረገች።
ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ትክክል ባልሆነ መንገድ ይወለዳሉ (በግብረ ስጋ ግንኙነት በኩል)፤ እግዚአብሔር ይህን መንገድ ቢፈቅድም እንኳ ፍጹም ፈቃዱ አይደለም፤ ፍጹም ፈቃዱ በድንግልና መውለድ ነው።
መዝሙር 51፡5 እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።
ከእናት ከአባቱ በንጹህ ጋብቻ ውስጥ ቢወለድም እንኳ ዳዊት የተጸነሰው በሐጥያት ነው።
ኢየሱስ በድንግልና የተወለደበት መወለድ ብቻ ነው የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ።
መጽሐፍ ቅዱስን መካድ፤ አለመስማት፤ መለወጥ እና መቃረን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሰይጣን ደቀመዛሙርት መለያ ምልክት ሆኗል።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑበትና የሚታዘዙት ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
የአይሁድ ሕዝብ መሪዎች ኢየሱስን በመካድና ሊገድሉት በመፈለግ ከአባታቸው ከዲያብሎስ መሆናቸውን አስመስክረዋል።
ከግብረ ስጋ ግንኙነት የተወለዱ ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውጭ ናቸው። ይህም የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎችን ያጠቃልላል። እነርሱም ከአብራሐም ዘር በመወለዳቸው ፍጹማን የሆኑ መስሏቸዋል። አሁን ግን ከግብረ ስጋ ግንኙነት መወለድ በዲያብሎስ መንፈስ ተሞልቶ ከነበረው እባብ የመጣ ሃሳብ መሆኑ ተገልጦላቸዋል።
ስለዚህ ተናደው ኢየሱስን ከዝሙት እንደተወለደ አድርገው መሳደብ ሞከሩ። ስለ ራሳቸው ደግሞ ልክ ሔዋን ስለ ቃየን እንደተናገረችው ከእግዚአብሔር እንደተወለዱ ተናገሩ።
ዮሐንስ 8፡41 እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት።
የኢየሱስ መወለድ በሰው ሐጥያት የተበላሸውን ማስተካከያ ነበር።
ኢየሱስ መሲህ እንደመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው የተጸነሰው።
ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያስቀምጥ ሰው ለሚለወደው ሕጻን አባት ነው።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አባት ነው።
መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው፤ ምክንያቱም አንድ ሕጻን ሁለት አባት ሊኖሩት አይችልም። ስለዚህ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ መጥራት የሚችለው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው።
የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች ግን መጽሐፍ ቅዱን ባለማመናቸው ጠንቅ የተነሳ በወላጆቻቸው ጋብቻ ውስጥ መወለዳቸውን በማየት እግዚአብሔር አባታችን ነው ይላሉ። እነርሱ ከዝሙት አልተወለድንም የሚሉት ኢየሱስ “ወላጆቹ” ሳይጋቡ በፊት መጸነሱን አስመልክተው እርሱን ሊከሱት ፈልገው ነው።
ማርያም እንግዳ ነገር አደረገች።
ኢየሱስ በማሕጸኗ ውስጥ በተጸነሰ ጊዜ ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ልትጎበኝ ሄደች፤ ኤልሳቤጥም በዚያ ጊዜ ዮሐንስን አርግዛ ስድስት ወር ሆኗታል። ማርያም ኤልሳቤጥጋ በሄደችበት ለሶስት ወራት እዚያው ቆየች። ከዚያ በኋላ ልክ ዮሐንስ ሊወለድ ሲል ማርያም ወደ ቤቷ ተመለሰች። በሰርጓ ጊዜ የሶስት ወር ነፍሰ ጡር ሆና በመገኘቷ ምክንያት ጽንሱ የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑን ሁሉም ሰው አውቋል። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሕዝቡ ማርያም በተዓምራት መጸነሷን እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።
ሉቃስ 1፡35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
38 ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
39 ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
40 ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
ኢየሱስ በድንግልና የተጸነሰበት ጽንስ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በኤደን ገነት ውስጥ የፈለገው ፍሬ ነው።
የአይሁድ መሪዎች ማርያም ከሰርጓ በፊት በመጸነሷ ከአንድ ከማይታወቅ ሰው ጋር ዝሙት ፈጽማለች ማለት ፈልገዋል። ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለነበረ ሕዝቡ ከጋብቻ በፊት በተፈጠረው ጽንስ ውስጥ እርሱ እንደሌለበት አውቀዋል።
ኢየሱስ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል በእናቱ በማርያም ማሕጸን ውስጥ ሆኖ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በማሕጸን ውስጥ ባለው ውሃ ውስጥ ነበረ (ይህ ውሃ አምኒዮቲክ ፍሉድ ይባላል)
ቃሉ በውሃ ውስጥ ወደ ነበረው ነብይ መጣ ማለት ነው።
ሉቃስ 1፡56 ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
57 የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች።
ልክ ዮሐንስ ከመወለዱ በፊት ማርያም ኤልሳቤጥን ትታ ሄደች። የማሕጸኗ ውሃ ሊፈስስ ነበረ፤ ከዚያም በኋላ ነብይ የሆነው ሕጻን በውሃ ውስጥ አይቆይም። ስለዚህ ቃሉ ትቶት ሄደ።
ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ነብዩ መጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ ውስጥ ቆሞ ነበር። ከዚያም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ እንደገና ወደ ነብዩ መጣ፤ ኢየሱስ ሊጠመቅ ሲመጣም ነብዩ እንደገና ውያ ውስጥ ነበረ።
ኤፌሶን 5፡26 በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት
በቃሉ ውሃ መታጠብ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ስንታዘዝ መንገዳችን ይነጻል ማለት ነው።
ይህ ጥምቀት የመስዋእቱ በግ ከሶስት ዓመት ተኩል በኋላ ከመታረዱ በፊት የታጠበበት ሰዓት ነው።
2ኛ ዜና 4፡6 ደግሞም አሥር የመታጠቢያ ሰኖች ሠራ፥ ለሚቃጠለውም መሥዋዕት የሚቀርበው ነገር ሁሉ ይታጠብባቸው ዘንድ አምስቱን በቀኝ፥ አምስቱንም በግራ አኖራቸው፤ ኵሬው ግን ካህናት ይታጠቡበት ነበር።
ከዚያም ሌላ ደግሞ የኢየሱስ ጥምቀት የሊቀ ካሕናቱ መታጠብ ነው ምክንያም ከተጠመቀ በኋላ ከውሃው ውስጥ ይወጣና በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር በቆመበት በእርሱ ላይ እንደ እርግብ ወርዶ ባረፈበት በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቷል።
ዘጸአት 29፡4 አሮንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ።
5 ልብሶችን ወስደህ ለአሮን ሸሚዝና የኤፉድ ቀሚስ ኤፉድም የደረት ኪስም ታለብሰዋለህ፥ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ ታስታጥቀዋለህ፤
7 የቅብዓትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባውማለህ።
መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሱስ ውስጥ አልገባም - ቢገባ ኖሮ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይሆን ነበር። መንፈስ ቅዱስ በርሱ ላይ ወርዶ አረፈበት፤ ይህም ቅባት ሆነ።
ዮሐንስ 1፡32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።
ማርቆስ 1፡11 የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
ይህ ንግግር የእግዚአብሔር አብ ድምጽ ነው።
ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያኖር ሰው የሕጻኑ አባት ነው።
ኢየሱስን በማርያም ማሕጸን ውስጥ የጸነሰው መንፈስ ቅዱስ ነው። አንድ ሕጻን ልጅ ሁለት አባቶች ሊኖሩት አይችልም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ነው እየወረደ ሳለ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ” ብሎ የተናገረው።
የእግዚአብሔር መንፈስ በአካል በክርስቶስ ውስጥ ነበረ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ መንፈስ በክርስቶስ አካል ውስጥ ሳለ ከአካሉ ውጭ የትኘውም ቦታም በማንኛውም ሰዓት ሊገኝም ይችላል።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
የሊቀ ካሕናቱ ልብስ በፍጹም መቀደድ የለበትም።
ዘጸአት 28፡30 በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
31 የኤፉዱንም ቀሚስ ሁሉ ሰማያዊ አድርገው።
32 ከላይም በመካከል አንገትጌ ይሁንበት እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ይሁንበት።
ጥሩር ከአንገት እስከ ወገብ ድረስ የሚሸፍን የብረት ልብስ ነው።
ቀያፋ የአይሁድ ሊቀ ካሕናት ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስን በከሰሰው ሰዓት ተናዶ ልብሱን ቀደደ። ይህም ድርጊቱ የሙሴ ሕግ ከዚያ በኋላ እንዳበቃለት አስታወቀ።
ማቴዎስ 26፡65 በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል? አለ።
ኢየሱስ ለብሶት የነበረውን ልብስ በመስቀሉ ዙርያ ቆመው የነበሩ አራት ወታደሮች አልቀደዱትም። ይህም እርሱ እውነተኛው ሊቀካሕናት መሆኑን ተረጋግጧል።
ዮሐንስ 19፡23 ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።
24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
ሊቀ ካሕናቱ የራሱን የክሕነት ልብስ ሲቀድ እግዚአብሔር ደግሞ የቤተ መቅደሱን መጋረጃ ከላይ ወደ ታች ለሁለት በመቅደድ ምላሽ ሰጠ፤ ይህም የሆነው ኢየሱስ በሞተበት ሰዓት የእግዚአብሔር መንፈስ ቤተ መቅደሱን ትቶ ሲወጣ ነው።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
ቅድስተ ቅዱሳኑ በአይሁድ ቤተ መቅደስ ውስጥ የምሕረት ዙፋን ነበረ። አዲሱ የምሕረት ዙፋን ደግሞ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ የነበረው ኢየሱስ ነው።
ሮማውያን ኢየሱስን በ33 ዓ.ም በመስቀል ሰቅለው ገደሉት። ኢየሱስ ሲሞት የእግዚአብሔር መንፈስ ከእርሱ ወጥቶ ሄደ። ነገር ግን ከሙታን ሲነሳ የእግዚአብሔር መንፈስ ተመልሶ ወደ አካሉ ውስጥ ገባ።
በ70 ዓ.ም በጀነራል ታይተስ የተመራው የሮማውያን ጦር ሰራዊት የኢየሩሳሌምን ከተማ እና የአይሁዳውያንን ቤተ መቅደስ ሙሉ በሙሉ አፈረሰ። በመቅደሱ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ መኖሩን ትቷል። ከዚህም የተነሳ መቅደሱ ከፈረሰ በኋላ ሁለተኛ ድጋሚ አልተሰራም።
ማቴዎስ 24፡15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
በ70 ዓ.ም ሮማውያን ወደ ኢየሩሳሌም ዘመቱ። አይሁዳውያን ማምለጥ ከፈለጉ ፈጥነው መውጣት ነበረባቸው። ሮማውያን በጥቂት ቀናት ውስጥ በኢየሩሳሌም ዙርያ አጥር ሰሩ። ከከተማይቱም ቀድመው ያልወጡ አይሁዳውያን ማምለጫ መንገድ አጡ። ከተማይቱ በጠፋች ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያን ሞቱ። ከተማይቱ ወደመች ኦና ሆና ቀረች በተለይም በተራራው ላይ ቤተ መቅደሱ የነበረበት ቦታ ጭር አለ።
ሮም የቤተክርስቲያን ጥንታዊ ጠላት ናት። በ705 ዓ.ም ሙስሊሞች ቤተ መቅደሱ በነበረበት ቦታ የኦማርን መስጊድ ሰሩ። ስለዚህ ሙስሊሞች ከሮማውያን ጋር በጥፋት እርኩሰት ውስጥ ተካትተዋል። በ2011 የተጀመረው የሶርያ ጦርነት የሶርያ ከተሞችን በሙሉ የድንጋይ ስብርባሪና የሕንጻ ፍርስራሽ ብቻ አድርጎ ለቀቃቸው። የየመን ጦርነትም ብዙ ሕዝብ ለችግር እንዲጋለጡ አደረጓል።
ዮሐንስ 8፡42 ኢየሱስም አላቸው፦ እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።
ኢየሱስ በሕይወቱ አንድ ዓላማ ብቻ ነበረው፤ እርሱም የራሱን ፈቃድ መፈጸም አልነበረም። እርሱ የመጣው ስለ እርሱ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለመፈጸም ነው። ስለዚህ በየትም በኩል ይምራው በየት እራሱን በውስጡ ሆኖ ለሚመራው ለእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ አሳልፎ ሰጠ።
ዮሐንስ 8፡43 ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው።
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ ምን እንደሚናገር መረዳት አልቻሉም ምክንያቱም ሕይወቱን እና ሥራዎቹን በመጽሐፍ ከተጻፈው ጋር አላመሳከሩም። እርሱ የሄደበት መንገድ ሁሉ የመጽሐፍን ቃል በመፈጸም ነበረ። እነርሱ ደግሞ ለመጽሐፍ ቅዱስ አንዳችም ትኩረት አልሰጡም።
ዮሐንስ 8፡44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።
ሰይጣን ከዝንጀሮ በላይ ሆኖ የተፈጠረውን እንስሳ እባብን መርጦ ሔዋን ቃየንን እንድትወልድ እንዲያደርጋት ላከው። ሐዋንም ቃየንን ስላረገዘች እግዚአብሔር እርሷን እና ሴቶችን ሁሉ ሲወልዱ በጭንቅ እንዲወልዱ ፈረደባቸው።
ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።
ሔዋን በእግዚአብሔር ፊት በቆመችበት ሰዓት እርጉዝ ነበረች። ያረገዘችውም ከእባቡ ነበር።
እግዚአብሔርም እባቡን ያደረገውን ሁለተኛ እንዳይደግመው ረገመውና በሆዱ የሚሳብ እንስሳ አደረገው
ዘፍጥረት 3፡14 እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
እባቡ የተቀጣው በሆዱ የሚሳብ እንዲሆን ነው፤ ስለዚህም እድሜውም በሙሉ በሆዱ እየተንፏቀቀ ያሳልፋል። ለምን? ምክንያቱም እባቡ ሐጥያት በሰራ ጊዜ በሔዋን ላይ በሆዱ ተኝቶባት ነበር።
ዘፍጥረት 3፡15 በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።
የእባቡ ዘር። የወንድ የዘር እስፐርም ሴል ቅርጹ እባብ ይመስላል፤ ጭንቅላትና ረጅም ጭራ አለው።
ከግብረ ስጋ ግንኙነት የተወለደው የመጀመሪያው ልጅ ቃየን ነው፤ እርሱም የሰው አባት አልነበረውም። ከግብረ ስጋ ግንኙነት የተወለዱ ሁሉ ይሞታሉ።
ዘፍጥረት 2፡17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።
በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ቀን አንድ ሺ ዓመት ነው። ከግብረ ስጋ ግንኙነት የተወለደ ሰው ለ1,000 ዓመታት መኖር አይችልም። ከሁሉም በላይ ረጅም ዕድሜ የኖረው ማቱሳላ 969 ዓመት ነበር የኖረው። ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች በሙሉ ከፍርድ በታች ነበሩ። ከግብረ ስጋ ግንኙነት ስለተወለዱ በስጋ ይሞታሉ።
ኢየሱስ በፈጸመው በእግዚአብሔር ቃል አለማመናቸው ደግሞ በመንፈስም እንዲሞቱ ያደርጋቸዋል።
የእባቡ የመጀመሪያ ዘር ቃየን የተባለው፣ ውሸታሙ፣ ነፍሰ ገዳዩ እና የሰው አባት የሌለው ሰው ከሆነ የሴቲቱ ዘርም የሰው አባት የሌለው ሰው ሆኖ ነው የመጣው፤ የተጸነሰውም በመንፈስ ቅዱስ ነው።
ኢሳይያስ 7፡14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ይህ መሲሁ ነው፤ እርሱም ለአይሁዳውያን ሐይማኖታዊ ተቋም ህልውና ትልቅ ስጋት ነበረ።
እግዚአብሔር ያንን ሕጻን በማርያም ማሕጸን ውስጥ ፈጠረው። ያ ጽንስ የሰው አባት የሌለው ሙሉ ሆኖ የተፈጠረ ዘር ነው። ስለዚህ ዘሩ የማርያም ዘር ሆነ። ስለዚህ ኢየሱስ የሴቲቱ ዘር ሆነ። (ዘሩ ግማሽ ከእግዚአብሔር ግማሽ ደግሞ ከማርያም አይደለም። ዘሩ ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ነው። ማርያም ማደሪያውን ማሕጸን ብቻ ነው ያዋጣችው።)
ኢሳይያስ 9፡6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ለሰው ልጆች ወንድ ልጅ በእግዚአብሔር የተሰጣቸው እግዚአብሔር ልጅን በማርያም ማሕጸን ውስጥ በፈጠረ ጊዜ ነው።
ነገር ግን ያ ልጅ በውስጡ የመለኮትን ሙላት በሰውነቱ ይዟል። በእርሱ ውስጥ የነበረው የእግዚአብሔር መንፈስ እግዚአብሔር አብ ነው።
ለዚህ ማረጋገጫ ትፈልጋላችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸማቸቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችና በአገልግሎቱ የገለጠው ከተፈጥሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ኃይል ማስረጃ ነው።
ከቃየን (ከመጀመሪያው የእባቡ ዘር) ጀምሮ ትምሕርታቸውን ከሰይጣን የተቀበሉ ሁሉ ሁልጊዜ ሲያስፈልጋቸው የእግዚአብሔርን ቃል ይክዳሉ፤ ይቃወማሉ። በዚህም መንገድ የሰው ልጆች ከእውነት ይልቅ ሐሰትን መረጡ።
ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት አክብሩ ባይለንም እንኳ ብዙ ክርስቲያኖች በክሪስማስ ያምናሉ። ኢየሱስ ተወለደ የተባለበት ቀን ከባድ ክረምትና ብርድ ስለሆነ በዚያ ሌሊት እረኞች በጎቻቸውን ይዘው ከቤት ውጭ ሊሆኑ አይችሉም። ኤርምያስ ምዕራፍ 10 አሕዛብን በመከተል ዛፍን በወርቅና በብር አታጋጊጡ ይለናል። እኛ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ከመታዘዝ ይልቅ የአሕዛብን ልማድ መከተል መርጠናል።
ለዚህ ነው በሥላሴ የምናምነው፤ ሥላሴ የሚል ቃል ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ የለም፤ ልክ “የመለኮት ሁለተኛው አካል” ወይም “አንድ አምላክ በሶስት አካላት” የሚሉ ቃላት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሌሉ ሁሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌለ እና እኛ ግን ካመንነው በጣም ሞኞች ሆነናል፤ በጣም ተሳስተናል። ፖፕ፣ ካርዲናል፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ኩዳዴ፣ ዲኖሚኔሽን፣ የኢስተር ጥንቸሎች፣ የኢስተር እንቁላሎች፣ ዩል ታይድ፣ የጸሎት መቁጠሪያ ጨሌዎች፣ መነኮሳት፣ ሴት መነኩሴዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት ቤቶች፣ ክሪስማስ፣ ዲሴምበር 25፣ የቤተክርስቲያን ሕንጻ፣ ጉልላት፤ እነዚህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም።
ዮሐንስ 8፡45 እኔ ግን እውነትን የምናገር ስለ ሆንሁ አታምኑኝም።
አንድ ሰው እውነትን ሲነግረን ግን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚናገረውን ማመን ያቅተናል። የሐይማኖት መሪዎችና የቤተክርስቲያን ልማዶች አእምሮዋችንን ስተቆጣጠሩት እድሜያችንን በሙሉ ከእነርሱ በሰማነው በማመን አሳልፈናል።
እኔ በግሌ መጀመሪያ ሰብዓ ሰገል ወደ ቤት ውስጥ መግባታቸውን ማመን አልቻልኩም ነበር። ምክንያቱም ወደ ቤት ገቡ ከተባለ ስንት ዓመት ሙሉ የክሪስማስ ድራማዎች ውስጥ ሰብዓ ሰገል ወደ በረት ውስጥ ሲገቡ ካየሁት ጋር ይጋጭብኛል። የክሪስማስ ፖስት ካርዶች ሁሉ ደግሞ ሰብዓ ሰገል ስጦታ ይዘው ወደ በረት ውስጥ ሲገቡ ያሳያሉ። ከጊዜ በኋላ ግን የክሪስማስ ፖስትካርዶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደማይስማሙ ተረዳሁ። ደግሞም ሰብዓ ሰገል በረት ውስጥ እንደ ገቡ የሚያሳዩ የክሪስማስ ድራማዎችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆኑ አስተዋልኩ። ቤተክርስቲያኖች መሳሳታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅሁት የዚያን ጊዜ ነው።
ከዚያ በኋላ ደግሞ ሐዋርያት የእውነት በኢየሱስ ስም ማጥመቃቸውን አላመንኩም ነበር። ሐዋርያት እንደ ተሳሳቱ የእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ደግሞ ትክክልና ከሐዋርያት የተሻለ የምታውቅ እንደሆነች ነበር የተነገረኝ፤ ስለዚህ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ አለብን አሉ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ እንደዚያ ብሎ ነው ያስተማረው። ከዚያ ብዙ ዓመታት አልፈው ነው ሰዎች ሁሉ የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን መሆኑን እንዳላወቁ የተረዳሁት። ለሥላሴያዊው አምላክ ስም አልነበረውም። ከዚያም በተጨማሪ ሥላሴያዊው እግዚአብሔር የትኛዋም ቤተክርስቲያን ወይም ሰባኪ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥር ነበረ።
ነገር ግን ራዕይ 10፡7 ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን የእግዚአብሔር ሚስጥር ይፈጸማል። ስለዚህ ስም የሌለው ሥላሴ ትክክለኛ የእግዚአብሔር መገለጥ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ሚስጥሩ ሁልጊዜ እንቆቅልሽ እንደሆነ ይቀራል።
ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር በሥጋ መገለጡ ከሆነ ሰብዓዊ ስም አለው፤ ስሙም - ኢየሱስ ነው።
ጥምቀት የኢየሱስ ሞት፣ ቀብር እና የትንሳኤ ምሳሌ ነው።
ሮሜ 6፡3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤
ከውሃ በታች ስንሰምጥ መተንፈስ አንችልም፤ ይህም መሞታችንን ያመለክታል።
አብ እና መንፈስ ቅዱስ አልሞቱም፤ ስለዚህ ሊቀበሩም አይችሉም። ስለዚህ እነርሱን እንደ ሌሎች አካላት አድርጎ ማሰብ ትርጉም የለውም፤ ምክንያቱም መንፈስ ሊጠመቅ አይችልም።
እግዚአብሔር አብ በአይሁዳውያን ላይ ጌታ እና አምላክ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ የተቀባው ነበር።
የሐዋርያት ሥራ 2፡36 እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።
ስለዚህ አብ፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ማለት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህ ስም እግዚአብሔር ሰው በመሆን በሰው አካል ውስጥ ሲኖር የተሰየመበት ስሙ ነው።
ዲያብሎስ በእባብ ውስጥ እና በአሳማዎች ውስጥ ኖሮ ያውቃል። እግዚአብሔር ግን በእንስሳት ውስጥ መኖር አይፈልግም - እርሱ የሚኖረው ንሰሃ በሚገቡ ሰዎች ውስጥ ብቻ ነው።
ስለዚህ በሰማይ ውስጥ ሶስት ሰዎች እንዳሉ እንድናስብ የሚያደርገን የሥላሴ ትምሕርት ትክክለኛ አይደለም። በሰማይ የሚኖሩ ሶስት ሰዎች በምድር ሁለት ያሉ ሁለት ሰዎች አዳም እና ሔዋን አምሳላቸው ሊሆኑላቸው አይችሉም። በተለይም ደግሞ ሔዋን ሴት በመሆኗ።
ስለዚህ “ከቤተክርስቲያናዊነትና” ከሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች ፈቀቅ እንበል።
ዮሐንስ 8፡46 ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነት የምናገር ከሆንሁ እናንተ ስለ ምን አታምኑኝም?
ኢየሱስን ማንም በሐጥያት ሊከስሰው አይችልም። ነገር ግን እውነትን ሲነገር የአይሁድ መሪዎች አናምን አሉት።
እኛ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎችን እንወዳለን። የቤተክርስቲያንን አመለካከቶች እንወዳለን። የቤተክርስቲያን ልማዶችን እንወዳለን።
በመጽሐፍ ቅዱስ ተገድበን መኖር አንፈልግም -- መጽሐፍ ቅዱስ ከተናገረው ውጭ መናገር እንፈልጋለን።
ዮሐንስ 8፡47 ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እናንተ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና ስለዚህ አትሰሙም።
የእግዚአብሔር መሆናችንን ማረጋገጥ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል ማመናችን ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የቤተክርስቲያን ወግና ልማድ የምንመርጥ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለንም።
ለሥላሴ አምላካችሁ ስም የሌለው ከሆነ ትምሕርታችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ስም አለው - ስሙም ኢየሱስ ነው።
ዮሐንስ 8፡48 አይሁድ መልሰው፦ ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን? አሉት።
ይህ ሙሉ በሙሉ የእውነት ተቃራኒ ነው።
አይሁዳውያን ለሚያገኙት ሐይማኖታዊ አገልግሎት ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ላሉት መሪዎቻቸው ገንዘብ ይከፍላሉ። ደጉ ሳምራዊ ግን በመንገድ የወደቀውን ሰው ሲረዳው አንዳችም ክፍያ አልጠየቀም። እንደውም እርሱ ራሱ ለቆሰለው ሰው መታከሚያ ገንዘብ አውጥቶ ከፈለ።
ኢየሱስ ለአገልግሎቱ ክፍያ ጠይቆ አያውቅም። ከዚያም በኋላ በራሱ ፈቃድ ለፈውሳችን እና ለመዳናችን የሚያስፈልገውን ዋጋ በመስቀል ላይ ከፈለ። ኢየሱስ በሥራው ሁሉ ዋነኛው ደጉ ሳምራዊ ሆኖ ተገልጧል፤ ነገር ግን በትውልዱ ሳምራዊ አልነበረም።
አሦራውያን ሰማሪያን ወረሩና አይሁዶችን ከሰማርያ አስወጡ። ከዚያ በኋላ ከሌላ ሃገር ያመጡዋቸውን አሕዛቦች ሰማሪያ ውስጥ እንዲኖሩ አሰፈሩዋቸው። ስለዚህ አይሁዶች እና እነዚህ አሕዛብ ተጋቡ፤ የወለዱዋቸውም ልጆች ሳምራውያን ተባሉ።
ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቃና መጣ። ሲካር የምትባል ቦታ ደርሶ እረፍት ለማድረግ ሲቆም የሰዎችን ሃሳብ የመመርመር ችሎታው አንዲትን ሳምራዊት ሴት እና በከተማይቱ የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ እርሱ መሲሁ መሆኑን እንዲያውቁ አደረጋቸው።
በኢየሩሳሌም የነበሩ የአይሁድ መሪዎች እርሱ መሲሁ መሆኑን እውቅና አንሰጥም አሉ።
ስለዚህ ሳምራውያን በመንፈሳዊነታቸው ከአይሁድ መሪዎች ይበልጡ ነበር ማለት ነው። ሆኖም ግን የአይሁድ መሪዎች ሳምራውያንን ከራሳቸው የሚያንሱ ሰዎች አድርገው ነው የሚቆጥሩዋቸው።
ስለዚህ የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች አሁን ደግሞ ኢየሱስን ሳምራዊ ነህ አሉት።
እናቱ ማርያም አይሁዳዊ ናት፤ እነርሱ ግን ማርያም በሰርጓ ቀን የሶስት ወር እርጉስ ስለነበረች አባቱ አንድ ያልታወቀ የአሕዛብ ሰው ሳይሆን አይቀርም ብለው አስበዋል።
ማርያም እንዲህ ያለ እንግዳ ነገር ያደረገችው ለምንድነው? የሶስት ወር እርጉዝ ከሆነች በኋላ ዮሴፍን ለማግባት ተመልሳ በመምጣቷ ማርያም ዮሴፍ የኢየሱስ አባት አለመሆኑን ለሁሉም ሰው ግልጽ አድርጋለች። ይህም ክስተት ኢየሱስ ከጋብቻ ውጭ የተወለደ ልጅ ተብሎ ስሙ እንዲጠፋ በር ከፍቷል።
ከዳዊት የመጡ ሁለት የዘር ሃረጎች ነበሩ።
ማቴዎስ በሰሎሞን በኩል የመጣውን ንጉሳዊ የዘር ሃረግ መዝግቦልናል። በዚህ የዘር ሃረግ ውስጥ የመጨረሻው ዘር ኢየሱስን እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ያሳደገው ዮሴፍ ነው። ሉቃስ ደግሞ ከሰሎሞን ታላቅ ወንድም ከናታን የመጣ ሌላ የዘር ሃረግ ነው የመዘገበው። ይህ ሁለተኛ የዘር ሃረግ የተጠቀሰው ለምንድነው? ምክንያቱም ይኸኛው ማርያም የተወለደችበት የዘር ሃረግ ስለሆነ ነው።
በሰሎሞን የዘር ሃረግ ውስጥ አንድ ትልቅ ችግር ነበረ። ኢኮንያን በጣም ክፉ ንጉስ ስለነበረ ከልጆቹ መካከል ማናቸውም ንጉስ አይሆኑም ብሎ እግዚአብሔር ተናገረ። ስለዚህ ዮሴፍ የአይሁዶች ንጉስ መሆን አልቻለም።
ኤርምያስ 22፡24 እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ እነቅልህ ነበር፥ ይላል እግዚአብሔር፤
ኤርምያስ 22፡28 በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?
ኤርምያስ 22፡30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።
ኢየሱስ የማርያም ልጅ እንደመሆኑ ከዚህ እርግማን ነጻ ነበር። ዮሴፍ ኢየሱስን እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ አሳደገው። በማደጎ የሚያድግ ልጅ እንደተወለደ ልጅ ሁሉም መብት አለው። ኢየሱስ የማርያም ልጅ በመሆኑ ከእርግማኑ ነጻ ሆኗል የዮሴፍ የማደጎ ልጅ እንደመሆኑ ደግሞ ንጉስ መሆን ይችላል።
ስለዚህ የዮሴፍ የኢየሱስ አባት አለመሆኑን ለማሳየት ማርያም ሰርጓን አዘግይታዋለች። የአይሁድ መሪዎች ግን ሙሉ በሙሉ በአተረጓጎማቸው ተሳስተዋል።
ዮሐንስ 8፡49 ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እኔስ ጋኔን የለብኝም ነገር ግን አባቴን አከብራለሁ እናንተም ታዋርዱኛላችሁ።
የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ጋኔን አለብህ ቢሉትም እንኳ እርሱ ግን አልነበረበትም። ከኢኮንያን ዘር የተወለደ ሰው የኢየሱስ አባት መሆን አይችልም። በድንግልና በመወለዱ አባቱ እግዚአብሔር ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈጸሙ እና እርሱ የሚሰራበት መለኮታዊ ኃይል እግዚአብሔር እርሱን እንዳከበረው ያሳያል፤ የአይሁድ መሪዎች ግን አላከበሩትም።
ዮሐንስ 8፡50 እኔ ግን የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የሚፈልግ የሚፈርድም አለ።
ኢየሱስ አገልግሎቱን ለማጠናቀቅና ለመሞት ተዘጋጅቶ ነበር። በሃሳቡ ውስጥ ትልቁን ስፍራ የያዘው የራሱ ክብር አልነበረም። በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈጸም በነገሮች ሁሉ ላይ ለመፍረድ ይፈልግ የነበረው በእርሱ ውስጥ ያደረው እግዚአብሔር አብ ነው።
ዮሐንስ 8፡51 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።
ትክክለኛው ሞት የእሳት ባሕር ነው። ከዚህ እሳት ውስጥ “የእሳት አደጋ ጊዜ መውጫ” የለም።
ራዕይ 20፡14 ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።
የመጀመሪያው ሞት የነፍስ ከስጋ መለየት ነው።
ያዕቆብ 2፡26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
ሁለተኛው ሞት ሰው በእሳት ባሕር ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ሲያበቃ የሰው ነፍስ ከመንፈስ የሚለይበት ጊዜ ነው። በዚያ ጊዜ ሰው ህልውናው ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ይጠፋል።
የሰው ነፍስ ሕይወቱ በሆነው በመንፈሱ ውስጥ ነው ያለችው።
1ኛ ሳሙኤል 25፡29 … የጌታዬ ነፍስ በሕያዋን ወገን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረች ትሆናለች፤
ሮሜ 8፡10 መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው
እኛ እንደ ሰው የምንሞተው ሞት ከእንቅልፍ ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው፤ ምክንያቱም በኢየሱስ ቃል ከማመናችን የተነሳ ስንሞት ወደተሻለ የእረፍት ስፍራ ነው የምንሄደው።
ዮሐንስ 8፡52 አይሁድ፦ ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም ስንኳ ሞተ ነቢያትም፤ አንተም፦ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።
የአይሁድ መሪዎች ትኩረታቸው በመጀመሪያው ሞት ላይ ነው፤ እርሱ የመጨረሻ ዋነኛ ሞት ይመስል። ነገር ግን ሁላቸውም ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ከሙታን እንዳስነሳ ያውቃሉ። ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳቱ የመጀመሪያው ሞት ለአማኝ የመጨረሻው እንዳልሆነ ያሳያል።
በተጨማሪም ደግሞ በትንሳኤ ቀን ኢየሱስ ሙታንን ማስነሳት እንደሚችል ያሳያል።
ዮሐንስ 8፡53 በእውኑ አንተ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞቱ፤ ራስህን ማንን ታደርጋለህ? አሉት።
ኢየሱስ ከአብራሐም እና ከነብያት እበልጣለሁ በማለቱ ተቆጡበት። ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ሁሉ ከብሉይ ኪዳን ገነት በማስወጣት ከራሱ ትንሳኤ በኋላ እንደሚያስነሳቸው አላወቁም።
ማቴዎስ 27፡50 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
51 እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ከሙታን መነሳታቸው ከብሉይ ኪዳን ተዓምራት ሁሉ ታላቁ ተዓምራት ነው።
ዮሐንስ 8፡54 ኢየሱስም መለሰ አለም፦ እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው፤
ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ ትንሳኤው ስለ አገልግሎቱ እውነተኛነት እንደሚመሰክርለት አውቋል።
እግዚአብሔር ቃሉ ስለሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መፈጸሙ ለእርሱ ትልቅ ክብር ነው የሚያመጣለት።
ዮሐንስ 8፡55 አላወቃችሁትምም፥ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
እግዚአብሔርን የማወቁ ማረጋገጫ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መታዘዝ መቻሉ ነው፤ ሕይወቱን ሁሉ ቢያስከፍለውም እንኳ መታዘዝ ችሏል።
ዮሐንስ 8፡56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።
አብራሐም ኢየሱስን አግኝቶታል፤ መቼ ብትሉ ኢየሱስ መልከጼዴቅ ሆኖ በተገለጠ ጊዜ።
ኢየሱስ የጎልማሳ ሰው አካል ለራሱ ፈጥሮ በመገለጥ አብራሐምን አናገረው፤ መጀመሪያ እንደ ሊቀ ካሕናት፣ ቀጥሎ የሰዶም እና የገሞራን ዕጣ ፈንታ ለመግለጥ እንዲሁም የተስፋ ቃል ልጅ ይስሐቅ እንደሚወለድ ለመናገር እንደ ነብይ ሆኖ አብራሐምን አናግሮታል።
ይህም ታላቁ የአብራሐም ልጅ - ኢየሱስ - እንደሚወለድ ምልክት ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው መልከጼዴቅ እናትም አባትም የሉትም። አልተወለደም፤ ደግሞም አይሞትም።
ዕብራውያን 7፡3 አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።
ዮሐንስ 8፡57 አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
ኢየሱስ ዕድሜው 33 እየሞላ ነበረ። ነገር ግን የ50 ዕድሜ ያለው ዓመት ሰው ይመስላል። ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብሎ ያለ እረፍት ደፋ ቀና ማለቱ በስጋ ሰውነቱን እየጎዳው ነበር።
ዮሐንስ 8፡58 ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።
የመጀመሪያው የእባቡ ዘር ቃየን “የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?” ብሎ ነበር።
ይህም እግዚአብሔር ለሙሴ ከተናገረው ግልባጭ ነው፤ እግዚአብሔር “እኔ ነኝ” ብሎ ነበርና።
ቃየን ወንድሙን መግደሉን ለመካድ ፈልጎ እግዚአብሔር ከተናገረው ተቃራኒ ግልባጭ ተናገረ።
ዘጸአት 3፡14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።
“እኔ ነኝ” እግዚአብሔር እራሱን ለሙሴ ያስተዋወቀው በጊዜ የማይገደብ አምላክ መሆኑን በመግለጽ ነው። “እኔ ነኝ” ኢየሱስ በዚህ አነጋገሩ እራሱን እግዚአብሔር ማለቱ ነው።
ቃየን በጻድቁ አቤል ፊት ነፍሰ ገዳይ ሆነ። የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች በእግዚአብሔር ፊት መቆማቸውን ሲሰሙ እነርሱም ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ። እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል መስማታቸው ኢየሱስን አጋንንታዊ በሆነ ጥላቻ እንዲጠሉ አደረጋቸው። እርሱን ጋኔን አለብህ ብለውት ነበር፤ ነገር ግን እንደዚያ ያሉት እራሳቸው አጋንንት ስለነበረባቸው ነው።
እነርሱ እራሳቸው የፈጠሩትና ያደራጁት ሐይማኖታዊ ተቋም አምላካቸው ሆኖባቸዋል። ከዚህ ሐይማኖት ነው ስልጣናቸውን፣ ኃይላቸውንና ገንዘባቸውን የሚያገኙት። የሚያገኙትን ጥቅማ ጥቅምና ክብር በጣም ነው የሚወዱት።
ስለዚህ ከእውነተኛው አምላካቸው ጋር ፊት ለፊት ሲጋፈጡ ልክ ቃየን በእውነት የተመላለሰውን ጻድቁን አቤልን ሲያገኘው ሊገድለው እንደተነሳ ተመሳሳይ ነበር መልሳቸው።
ድርጊታቸው እነርሱም ልክ እንደ ቃየን የእባቡ ዘሮች መሆናቸውን አጋልጧል፤ ምክንያቱም ድጊታቸውን የሚገፋፋው ኃይል በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አለማመናቸው ነበረ። የሚስማሙዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያምናሉ (መልካምን የምታሳውቀዋ ዛፍ) ነገር ግን እነርሱ የማያምኑዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያሳያቸውን ሊገድሉት ይፈልጋሉ (ክፉውን የምታሳውቀዋ ዛፍ)።
የእውነት እና የሐሰት ድብልቅ -- የእባቡ መንታ ምላስ፤ በአፉ ውስጥ ያለውን የሞት መርዝ ያሳያል።
ዮሐንስ 8፡59 ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።
ትክክለኛ ፍትሃዊ ፍርድ አልተፈረደም። ሆኖም ግን ኢየሱስን ሊገድሉት ተዘጋጅተዋል። በእርሱ ላይ የሞላባቸው ቁጣና የገዳይነት ስሜታቸው ይህን ያህል ነበር።
ኢየሱስ አሁንም በድጋሚ መለኮታዊ ኃይሉን ገለጠ። ነፍሱን ሊያጠፉ በሚፈልጉ ሰዎች መካከል በተዓምራት ተራምዶ አለፈ።
ይህም በሌላ ከፍ ባለ ዳይሜንሽን መንቀሳቀስ እንደሚችል ያሳያል።
የምንኖርበት ዓለም ባለ አንድ ዳይሜንሽን ጥቁር መስመር ብቻ እንደሆነ አስቡ። በዚህ መስመር ውስጥ ሰው አንድ አጭር መስመር ሆኖ ተወክሏል። በመጀመሪያው ምስል ውስጥ ቀዩ ሰውዬ በሁለት ሰማያዊ ሰዎች መካከል ስለቆመ ከሁለቱ አምልጦ መሄድ አይችልም።
ቀዩ ሰውዬ ከፍ ወዳለ ሁለተኛ ዳይሜንሽን መግባት ቢችል (ከመስመር አልፎ እንደ ወረቀት ጠፍጣፋ የሆነ ዓለም) ቀዩ ሰውዬ መስመሩ ውስጥ ካሉት ሁለት ሰዎች አልፎ መሄድ ይችላል።
ቀዩ ሰውዬ ይህንን ሃሳብ በሁለተኛው ምስል ውስጥ ያስባል።
በሶስተኛው ምስል ውስጥ ሰማያዊው ሰውዬ ቀዩ ሰውዬ ከእርሱ አልፎ እንዳመለጠው ያውቃል፤ ነገር ግን እንዴት አድርጎ እንዳመለጠው አንዳችም የሚያውቀው ነገር የለም።
ሰማያዊው ሰውዬ መስመሩ ውስጥ ካለው ነገር ውጭ ከመስመሩ ውጭ በቀጣዩ ዳይሜንሽን ውስጥ ካሉ ነገሮች ጋር አንዳችም ንክኪ የለውም።
በብዙ ሰዎች ተከቦ ሳለ ማምለጥ መቻሉ ያ ሰው ከሌላ ዳይሜንሽን መምጣቱን ማረጋገጫ ነው።
ኢየሱስ ከፍ ባለ መንፈሳዊ ዳይሜንሽን የአይሁድ መሪዎች መሄድ በማይችሉበት ዳይሜንሽን በመንቀሳቀስ እግዚአብሔር መሆኑን አሳይቷል። እንዴት አድርጎ እንደሆነ ባያውቁም ግን እንዳመለጣቸው አውቀዋል።
እግዚአብሔር የእርሱ አባት መሆኑን ክደዋል። ነገር ግን ከፍ ባለ ዳይሜንሽን ውስጥ በመግባት መሰወር እና ሲፈልግ ደግሞ መገለጥ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።