ዮሐንስ ምዕራፍ 08፡1-20. የሕግ ከንቱነት የተገለጠበት ጥልቅ ትምሕርት



First published on the 20th of March 2021 — Last updated on the 20th of March 2021

ይህ ምዕራፍ 8 ነው።

ሰባት ሙላትን የሚወክል ቁጥር ነው። በአንድ ሙሉ ሳምንት ውስጥ 7 ቀናት አሉ።

ስለዚህ ስምንት የአዲስ ሥርዓት ጅማሬ መሆን አለበት።

ኢየሱስ ይህንን ምዕራፍ ተጠቅሞ ሕጉ አለመሳካቱን ለማሳየት ይፈልጋል። ስለዚህ እግዚአብሔር አዲስ ሥርዓት ማምጣት አለበት፤ ይህም ሰዎች ከሐጥያት የሚድኑበት አዲስ ቃል ኪዳን ነው።

ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመያዝ ሞክረው ሳይሆንላቸው ቀርተዋል። ኒቆዲሞስ ደግሞ ለኢየሱስ ግልጽና ትክክለኛ የፍርድ ሂደት እንዲደረግለት ፈለገ። ስለ ኢየሱስ ትክክለኞቹን ማስረጃዎች መርምሮ ማየት ፈሪሳውያን የጠነሰሱትን ስውር የግድያ ሴራ ብትንትኑን ያወጣዋል። ፈሪሳውያን ልክ እንደ በረሮዎች እየተሯሯጡ ወደ ቤታቸው ገቡ። ለጊዜው ተሸንፈዋል ግን ደጋግመው የመሞከር ሃሳብ አላቸው። ዋነኛው ዓላማቸው ኢየሱስን መግደል ነው።

ኢየሱስ ቃሉ ነው።

ዛሬም ጭምር የተጻፈውን ቃል በተመለከተ የቤተክርስቲያን መሪዎች አንዳንድ የማይዋጥላቸው ነገር አለ።

በጣም የሚያሳዝነው ነገር የቤተክርስቲያን መሪዎች የማይስማሙዋቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዳላዩ ሆነው ማለፍ፣ ወይ መቃረን ወይም ማሻሻል መምረጣቸው ነው። ሌሎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ግን በጣም ደስ ብሏቸው ያምናሉ። በዚህ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን እንደተጻፈ የሚያምነው ብዙ ሰው የለም።

የፈሪሳውያን ቀጣዩ እርምጃ በኢየሱስ ላይ የተወሰነ የሐሰት ክስ ማዘጋጀት ነው።

ሕጋዊ ጥያቄ ብለው የሚያቀርቡት ጥያቄ ውስጥ ያለውን ቧልት ተመልከቱ። በልባቸው ውስጥ አስቀድመው የሞት ፍርድ ፈርደውበታል።

ስለዚህ በጥበብ ባዘጋጁት ወጥመድ ውስጥ ሊያጠምዱት ተዘጋጅተው መጡ።

የአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች በዘመናቸው ተጽፎላቸው የነበረውን የእግዚአብሔር ቃል ከፊሉን አያምኑም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ ለሥርዓታቸው ለስልጣናቸው ስጋት ስለሆነባቸው እርሱን የግድ ማስወገድ እንደሚያስፈልጋቸው አምነዋል።

ከዚህ ሁሉ በፊት አስቀድመው ሊገድሉት አቅደዋል።

ዮሐንስ 5፡16 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ያደርጉ የነበረው ነገር ዛሬም ይደረጋል። የሐይማኖት መሪዎች የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ኢየሱስን አልወደዱትም።

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን የእግዚአብሔርን ቃል ከሚወድዱት የበለጠ የራሳቸውን ሐይማኖታዊ ስርዓት ነበር የሚወድዱት።

ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል። ዛሬ 45,000 የተለያዩ ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አሉ። የእነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያን መሪዎች የራሳቸውን የቤተክርስቲያን ትምሕርት ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ከፍ ያደርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንከተል የሚሉ ሰዎች ለቤተክርስቲያን እንደ ጠላት ይቆጠራሉ።

ዮሐንስ 8፡1 ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።

ፈሪሳውያን ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደዋል። ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ።

ይህም የሚያመለክተው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደመሆኑ የራሳቸውን ሐይማኖታዊ አጀንዳ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን ከማይፈልጉ የሐይማኖት መሪዎች ሆን ብሎ እራሱን እንደለየ ነው።

ደብረ ዘይት የወይራ ዘይት የሚገኝበት የወይራ ዛፍን ያመለክታል፤ ዘይቱም የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌት ነው።

ስለዚህ ደብረ ዘይት መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከሚያስተምሩዋቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል ካልሆኑ ትምሕርቶች እራሳችንን ስንለይ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራን ያመለክታል።

በደብረ ዘይት ተራራና በቤተ መቅደሱ መካከል የቄድሮን ሸለቆ ስላለ ተራራው ከቤተ መቅደሱ በሸለቆው ተለይቷል።

 

 

ቄድሮን ማለት በደመና የተሸፈነ ወይም የተጋረደ፤ ወይም በግልጽ ሊታይ የማይችል ነገር ነው።

ይህም የሰውን ጥበብ ይወክላል። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ባለው የወይራ ዘይት ወደ ተመሰለው ወደ መንፈስ ቅዱስ ከፍታ ካልወጣን በቀር እግዚአብሔር ምን እየሰራ እንዳለ በግልጽ ማየት አንችልም።

መንፈሳዊ እውነትን ለመረዳት ከፈለግን ከቤተክርስቲያን አመለካከቶች እና ከባህላዊ አስተሳሰቦች መለየት አለብን።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ማቴዎስ 21፡1 ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥

2 እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

ቤተ ፋጌ ማለት ያልበሰሉ በለሶች ቤት ማለት ነው።

የበለስ ዛፍ የእሥራኤል ምሳሌ ናት። ያልበሰለ ማለት መሲሁን ለመቀበል አልተዘጋጁም ነበር ማለት ነው። የአይሁድ ሐይማኖት መሪዎች የአይሁድ ሕዝብ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳያውቅ አይኖቹን አሳውረውታል።

የመጨረሻው የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ዘመንም እውር ተብሎ ነው የተገለጸው።

ሕዝቡን የሚያሳውር ማነው? ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች የሚያዳምጡዋቸው ሰባኪዎች ብቻ ናቸው ሕዝቡን የሚያሳውሩት።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡17 አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ … ዕውርም … መሆንህን ስለማታውቅ፥

ስለዚህ ታሪክ እራሱን እየደገመ ነው።

 

 

ደቀመዛሙርቱ ከደብረ ዘይት ተነስተው ሁለት አህዮችን ለመፍታት ሄዱ።

አህዮቹን አስሮአቸው ከነበረው ሰውዬ ሊለዩዋቸው ሄዱ።

ይህም በምሳሌነት የሚያሳየን ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በቤተክርስቲያን ወጎች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ እምነቶች መታሰራቸውን ነው። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ በእነርሱ መጠቀም እንዲችል ሰው ካደረገባቸው እስራት መለየትና መፈታት ያስፈልጋቸዋል። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው አህዮቹ ትንቢትን ለመፈጸም ቃሉን ተሸክመው ወደ ኢየሩሳሌም መግባት የሚችሉት።

ሁለቱ አህዮች ከመጀመሪያው ጌታቸው እጅ ተፈትተው በደቀመዛሙርቱ አማካኝነት ወደ ኢየሱስ ተወሰዱ።

አዲስ ኪዳን የተጻፈው ኋላ ሐዋርያት በሆኑት በኢየሱስ ደቀመዛሙርት ነው። በዚህ በአዲስ ኪዳን ለማመን ከዘመናዊው የቤተክርስቲያን አስተሳሰብ መለየት እና የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት በጻፉት መመራት አለብን።

ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ቃል በልባችን መሸከም የምንችለው።

እነዚህ ሁለት አህዮች ሴት አህያ እና ውርንጫዋ ናቸው።

ሴት የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችዋ የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን ወደ ሙሉ ሰውነት ያደገችበት ዘመን ነበረ።

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ልጆች ሙሉ ሰው ወደ ሆኑት ወደ ሐዋርያዊ አባቶች የሚመለሱበት ዘመን ነው።

ኢየሱስ በትክቋ አህያ ላይ ተቀምጦ ነው የሄደው፤ ነገር ግን ግልገሏ አህያ ሙሉ በሙሉ በመስማማት ከጎን አብራ ትሄድ ነበረ። እውነቱ የተሸከሙት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ሐዋርያት ብቻ ናቸው።

 

 

የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው የመጀመሪያው የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ዘመን ያመናቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች እና ተመሳሳይ እምነት የሚቀበሉ ክርስቲያኖችን የሚወልደው።

እስቲ አሁን ደግሞ ፈሪሳውያን ኢየሱስን ሊያጠምዱበት ያዘጋጁትን ወጥመድ እንመልከት።

ራዕይ 8፡2 ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።

3 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦

4 መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።

5 ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።

6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ።

የሕግ አዋቂዎች ሙያቸውን ንጹሑን ሰው ጥፋተኛ ለማድረግ ሲጠቀሙበት ሙያቸው አደገኛ ይሆናል። በሕግ የተቀበሉትን ስልጠና እና ክህሎት ተጠቅመው ኢየሱስን ጥፋተኛ ለማስባል የሚያመች ሁኔታ እየፈጠሩ ነበር። ዓላማቸው እውነትን ለመግለጥ አልነበረም።

ራዕይ 11፡52 እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ

ሕግን ተጠቅሞ የተሰወረ ክፉ ዓላማ ማስፈጸም የሕጉን ሥርዓት ከንቱ ማድረግ ነው።

ፈሪሳውያን የራሳቸው የተደበቀ ተንኮል ነበራቸው። ፍላጎታቸው ኢየሱስን ለመግደል ብቻ ነው።

በጣም ብልጦች ስለነበሩ በሸረቡት የተንኮል መረብ ውስጥ ኢየሱስ የገባላቸው መስሏቸዋል።

ሴትየዋ ጥፋተኛ ነበረች፤ የሙሴ ሕግ ደግሞ ትገደል ይላል።

ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ቢስማማ የሞት ፍርድ እንዲፈርድ ይጠበቅበታል። በሰው ላይ የሞት ፍርድ ከፈረደ በኋላ ደግሞ የሕይወት ራስ መሲህ ነኝ ማለት አይችልም።

ሴትየዋን ለመግደል ከተስማማ እና ሊያድናት ካልቻለ የሰዎችን ነፍስ ከሐጥያት ለማዳን የመጣበት ዓላማ ሳይሳካ ይቀራል።

መሲሁ ይመጣል የተባለውም አይሁዳውያንን ሊያድን እንጂ ሊገድላቸው አይደለም።

በሌላ በኩል ደግሞ አትግደሏት ቢል የሙሴን ትዕዛዝ መተላለፉ ሊሆን ነው። ይህም ደግሞ እንዲገደል ያስፈርድበታል ምክንያቱም የሙሴን ትዕዛዝ ተቃወመ ብለው ሊከስሱት ይችላሉ።

ይህን ካደረጉ ደግሞ እነዚህ የሐይማኖት መሪዎች ዓላማቸው ተሳካላቸው ማለት ነው። እርሱን ሊገድሉ የሚፈልጉትን በቂ ምክንያት ያገኛሉ።

ሁሉን ነገር አመቻችተዋል። ሴትየዋን ሊገድሏት እንደፈለጉ አስመስለው ኢየሱስ እርሷን ለማዳን እንደሚነሳ እና ለዚህም ብሎ ሕግን ሲተላለፍ ሊይዙት ነው የፈለጉት። ከዚያ በኋላ ሕግን ተላልፏል በማለት ሊገድሉት ይችላሉ።

ዮሐንስ 8፡6 የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤

 

 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ከሆኑ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ይህ ነው።

ኢየሱስ ለሰዎቹ ጥያቄ ትክክለኛው መልስ አለው፤ ግን በመናገር ፈንታ ምድር ላይ በጣቱ ይጽፋል።

ኢየሱስ የሚያስበው ከእናንት እና ከኔ እጅግ በሚበልጥና ጠለቅ ባለ ደረጃ መሆኑን መርሳት የለብንም።

ሙሴ ከኮሬብ (ወይም ሲና) ተራራ ሲወርድ ጽሕፈት የተጻፈባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ይዞ ነው የመጣው።

ኢየሱስ ደግሞ ከደብረ ዘይት ተራራ ወረደና ምድር ላይ ጻፈ።

በእነዚህ ሁለት ትዕይንቶች መካከላ የሚያገናኝ ነገር ምንድነው?

ኢሳያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።

ኢየሱስ እንዲህ ማለቱ ነበር፡- “የሙሴን ሕግ ተጠቅማችሁ ልትይዙኝ ትፈልጋላችሁ። ነገር ግን ሙሴ እራሱ ነፍሰ ገዳይ መሆኑን ረስታችኋል። በዚያ ጊዜ ሙሴ ሕጉን ለመቀበል ወደ ተራራው ሲወጣ አይሁዳውያን ቅድመ አያቶቻችሁ ራቁታቸውን ሆነው ሲጨፍሩ ነበረ።”

ዘጸአት 32፡25 ሙሴም በጠላቶቻቸው ፊት እንዲነወሩ አሮን ስድ ለቅቋቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ፥

ሙሴ በንዴትና በቁጣ ውስጥ ሆኖ ጽላቶቹን ወርውሮ በሰበረ ጊዜ አስሩንም ሕጎች ያፈረሰ የመጀመሪያው የሕግ ተላላፊ ሆኗል።

 

 

ዘጸአት 32፡19 እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ፤ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፥ ጽላቶቹንም ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው።

በዚያ ጊዜ ስንት ዲቃላ ልጆች እንደ ተጸነሱ ማን ያውቃል። ስለዚህ ይህችን ሴት እየከሰሱ ከቆሞቱ ሰዎች መካከል አንዳቸው ከእነዚያ ከዝሙት ከተወለዱ ልጆች የተወለዱ ሊሆኑ ይችላሉ።

አይሁዳዊ ቅድመ አየቶቻቸው ያለ ምንም ጥርጥር አመንዛሪዎች ነበሩ። አያቶቻቸውን ካሰቡ አንዳችም የሚኮሩበት ነገር የላቸውም።

እጅግ በጣም ሴሰኛ ከመሆናቸው የተነሳ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከኢያሱ ጋር በገቡ ጊዜ የመጀመሪያዋ የዳነችው ሴት ጋለሞታዋ ረሃብ ነበረች። እርሷም አይሁዳውያን ሙሴ ሕጉን ለመቀበል ኮሬብ (ሲና) ተራራው ላይ በወጣ ጊዜ የነበራቸውን የግልሙትና ባህርይ የምትወክል ሴት ናት።

ኢየሱስም ቀጥሎ በጸጥታ የሚያስተምራቸውን ትምሕር ጠለቅ ወዳለ ደረጃ ወሰደው።

ለምን ነበር በጣቱ ምድር ላይ የጻፈው?

ሙሴ የድንጋይ ጽላቶችን ሰበረ። የተሰበረ ድንጋይ በዝናብ እና በነፋስ አማካኝነት ተሰባብሮ ድቅቅ ይልና ምድር ይሆናል።

 

 

የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ ኢየሱስ በምድር ላይ በጣቱ ጻፈ።

ሊነግራቸው የፈለገው እንደ እግዚአብሔር በመጀመሪያ እርሱ ሕጉን በድንጋይ ላይ በጣቱ ጽፎ እንደነበረ ነው።

ዘጸአት 31፡18 እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።

 

 

ኢየሱስ በዚህ ድርጊቱ እያላቸው የነበረው ይህ ነው፡- “በሙሴ ሕግ ተጠቅማችሁ ልታጠምዱኝ የምትችሉ ይመስላችኋልን? ለሙሴ ሕጉን የሰጠሁት አምላክ እኮ እኔ ነኝ።”

ነገር ግን ፈሪሳውያን ይህን ያክል የተጨነቁለት ሕግ ማንንም አልረዳም።

ሕጉ በአይሁዳውያን መካከል ፍቅር እና ርህራሄ እንዲያድግ አላደረገም።

ሕጉ ከተሰጣቸውም በኋላ እርስ በራሳቸው መገዳደል ይፈልጋሉ። ሙሴ እራሱ ድንጋዮቹ በተሰባበሩ ጊዜ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ሕጉን በሙሉ አፍርሷል።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ 10ቱን ትዕዛዛት በምድር ላይ በጣቱ ይጽፋል።

ልክ እንደ ሙሴ ኢየሱስም ከደብረ ዘይት ተራራ ወርዶ አየሁዶችን ስለ ሕጉ እያስተማራቸው ነው። ኢየሱስ ግን ሕጉ ሐጥያት የመስራት ፍላጎትን ሊያስወግድ እንዳልቻለ ማሳየት ላይ ነበረ ትኩረቱ።

ስለዚህ ኢየሱስ ልክ ሙሴ ትምሕርቱን ካቆመበት ቦታ ቀጠለ።

ሙሴ ድንጋዮቹን ሰበራቸው፤ ድንጋዮቹም ወደ አፈርነት ተለወጡ። ስለዚህ ኢየሱስ በአፈሩ ላይ ጻፈ።

ነገር ግን ይህም ቢሆን የጊዜ ብክነት ነው። ጽሕፈቱን ነፋስ እና ዝናብ ያጠፉታል። በዚህ ምሳሌ ሕጉ ሙሉ በሙሉ ዋጋ የሌለው መሆኑን እያሳየ ነበር።

በድንጋይ ላይ የተጻፈው ሕግ አይሁዳውያንን የተሻሉ ሰዎች ማድረግ አልቻለም።

ሕጉ ለአይሁዳውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ የተሰጣቸው እነርሱን ከዓለም ሕዝብ ሁሉ የተለዩ ሕዝብ ለማድረግ ነበረ።

ዘጸአት 33፡16 በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው።

እግዚአብሔር በዓለማዊ መንገድ ወይም በተሻሻሉ የአሕዛብ በዓላት አማካኝነት መመለክ አይፈልግም።

አይሁዳውያን ግን የተለዩ ሕዝብ ሆነው መቀጠል አልቻሉም። ስለዚህ ሕጉ ዓላማው አልተሳካም።

የተሰባበሩት ድንጋዮች ከደቀቁ በኋላ በምድር ላይ የተጻፈውም ሕግ እንደዚሁ ምንም የሚያመጣ አልነበረም።

ሙሴ ሕጉን ከሰጠ ከ1,500 ዓመታት በኋላ ሕጉ ምን ውጤት አመጣ?

ሐጥያተኛ አይሁዶች ማድረግ የሚፈልጉት አንድ ብቸኛ ነገር አንዲት ሐጥያተኛ አይሁድ ሴትን መግደል ነው።

ፈሪሳውያንም የነበረባቸው ጠማማነት እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ ሴትየዋን ብቻ እንጂ አብሯት ሐጥያት የሰራውን ሰውዬ ለመቅጣት አላሰቡም።

ይህ ፍትህ አይደለም። ሴትየዋን የተጠቀሙዋት ኢየሱስን ለማጥመድ እንዲያመቻቸው ብለው ብቻ ነው።

ከዚህም ይልቅ የሚከፋው ደግሞ መሲሃቸውን ለመግደል በጣም መፈለጋቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ለተንኮላቸው ራሳቸውን ሰጥተዋል።

ዘዳግም 18፡15 አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።

ሙሴን ቢሰሙት ኖሮ ኢየሱስን በተከተሉት ነበር።

ነገር ግን የሙሴን ሕግ የተጠቀሙት ኢየሱስን ለመግፋት ነው።

አሁንም ታሪክ ራሱን ይደግማል።

በዊልያም ብራንሐም ንግግሮች ውስጥ የምናገኛቸውን መገለጦች መጠቀም ያለብን እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውጥ ተከታትለን ለማረጋገጥ ነው።

ነገር ግን ብዙ የሜሴጅ ተከታዮች የወንድም ብራንሐም ንግግሮችንና ጥቅሶችን በመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ ተክተው እየተጠቀሙባቸው ነው፤ በዚህም አደራረጋቸው መጽሐፍ ቅዱስን እየገፉ ነው። ምንም መሰረት የሌለው እምነታቸወን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተጻፉት በሰባቱ ነጎድጓዶች ንግግር ላይ መስርተዋል።

ሆኖም ግን ኢየሱስ ሰይጣንን ያሸነፈበት ብቸኛው መልስ “ተብሎ ተጽፏል…” የሚል ነበረ።

ፈሪሳውያን ኢየሱስ ሕጉ ምንም እንዳልጠቀማቸው ሊያስተምራቸው ብሎ ያደረገውን የሚያስተውሉበት ብሩህ ልቦና አልነበራቸውም። ሕጉ አይሁዳውያንን የተሻሉ ሕዝብ አላደረጋቸውም። ደግሞም አይሁዳውያን መሲሃቸውን እንዲያውቁ እንኳ አላደረጋቸውም።

ስለዚህ ሴትየዋን ለመግደል ከኢየሱስ ፈቃድ ፍለጋ አጥብቀው መጠየቃቸውን ቀጠሉ።

ዮሐንስ 8፡7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።

ኢየሱስ የሰጣቸውን መልስ እስከ ዛሬ ድረስ ማንም አይረሳውም። ከዚህ መልስ ጋር ማንም መከራከር አይችልም።

ዮሐንስ 8፡8 ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

ስለዚህ 10ቱን ትዕዛዛት በምድር ላይ ጻፋቸው። የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ 10ቱን ትዕዛዛት በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጻፋቸው። ለምን?

ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር 10ቱን ትዕዛዛት ለሙሴ ለመስጠት ሁለት ጊዜ መጻፍ ነበረበት።

ዘጸአት 34፡1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።

እያንዳንዱ ሰው በውስጡ እንደ ፖሊስ የሚከታተለው ሕሊና አለው።

ክፉ ነገር ስንሰራ ሕሊናችን ይነግረናል። ከተሰበሰቡት ሁሉ በእድሜ ታላቅ የሆነው ሰው ረጅም እድሜ ስለ ኖረ ከሁላቸውም የበለጠ ብዙ ሐጥያት ሰርቷል። እርሱ መጀመሪያ ከሄደ በኋላ ሌሎቹ ሐጥያተኛ ከሳሾች በሙሉ ተከትለውት ሄዱ።

ዮሐንስ 8፡9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

አሁን ደግሞ ትዕይንቱ ከቅድሙ የተለየ ነው። አንዲት ሐጥያተኛ ሴት እና ኢየሱስ ብቻ ቀሩ።

ነገር ግን ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት ምክንያቱም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ናት።

ስለዚህ ይህ ትዕይንት ኢየሱስ ሐጥያተኛዋን ቤተክርስቲያን ሲያድናት ያሳያል።

አይሁዳውያን እንዲድኑ የመጣላቸውን እድል አንቀበልም ብለዋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ አሕዛብ ዘወር ይልና ሐጥያተኛዋን የአሕዛብ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያድናታል።

ዮሐንስ 8፡10 ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።

ሰዎች ሌሎች ሰዎችን መክሰሳቸውና በሌሎች ላይ መፍረዳቸው ከንቱ ነገር ነው። ምክንያቱም ሁላችንም ሐጥያት ሰርተናል። ስለዚህ እኛ ሌሎች ላይ መፍረዳችን ከንቱ ነገር ነው ምክንያም ሁላችንም ነቀፋ ያብን እቃዎች ነን።

ሮሜ 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤

ሮሜ 2፡1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።

እኛ ሰዎች እራሳችን የምንሰራቸውን ሐጥያቶች በሌሎች ሰዎች ላይ ስናይ ለመፍረድ እንፈጥናለን።

ዮሐንስ 8፡11 እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።

ይህ ቃል ወንጌሉን ጠቅለል አድርጎ ያቀርባል። ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁሉ ይቅር ሊል እና ሊያድን ነው። እርሱ የመጣው ሐጥያተኞችን ቅዱሳን ሊያደርግና በንሰሃ አማካኝነት ከእርሱ ጋር የግል ሕብረት ማድረግ እንዲችሉ ለማድረግ ነው።

ኢየሱስ ሐጥያት ለመስራት ያለንን ፍላጎት የሚያጠፋልን እንዴት አድርጎ ነው?

የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።

ከዚያ በኋላ የክርስቶስ ቅዱስ መንፈስ በልባችን ውስጥ ገብቶ ይኖርና ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ይህ አሰራር ውጤታማ የሚሆነው ለምንድነው?

እግዚአብሔር አዳምን ከምድር አፈር አበጀው።

ዘፍጥረት 2፡7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።

 

 

እንደ እግዚአብሔርነቱ ኢየሱስ ሕጉን በድንጋይ ጽላቶች ላይ በጣቱ ጻፋቸው። ድንጋይ ሲሰባበር አፈር ይሆናል።

እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ ኢየሱስ ሕጉን በምድር ላይ በጣቶቹ ጻፋቸው። ነገር ግን ከምድር ላይ እግዚአብሔር የሰዎችን ልብ የሰራበትን አፈር እናገኛለን።

ከዚያም እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስነቱ ኢየሱስ በሰው ልብ ውስጥ ገብቶ ይኖርና በልባችን ውስጥ ትዕዛዛቱን ይጽፋቸዋል።

ሕጉ ግን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ነበር የተጻፈው። የሰው ልብ ደግሞ ከድንጋይም በላይ ጠንካራ ነው።

ስለዚህ ልባችን መጀመሪያ በንሰሃ መሰበር አለበት።

 

 

ከዚያ በኋላ የልባችን ውስጠኛው ለስላሳው ክፍል በልባችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ለሚኖረው ኢየሱስ ይከፈትለትና በጣቱ ይጽፍበታል።

መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕግ በልባችን ውስጥ ይጽፈዋል፤ ይህም የእግዚአብሔርን ቃል እንድናምን ያደርገናል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ መታዘዝ ስላለብን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ ስለምንፈልግ ነው።

ውስጣዊ ፍላጎታችንና ማድረግ የምንፈልገው ነገር ሁሉ ምንጩ ከልባችን ነው።

ነገር ግን ድርጊታችን እና እምነታችን መነሻው ቅጣትን ከመፍራትም ሆነ ሽልማትን ከመጠባበቅ አይደለም።

 

 

የእግዚአብሔር ጣት የሆነው ታላቁ መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ የሚጽፈው እግዚአብሔርን እና ሰውን እንድንወድድ ብቻ ነው። ሰውን ስነወድድ ቤተሰባችንን፣ ጓደኞቻችንን እንዲሁም ጠላቶቻችንን ጭምር ነው።

የእግዚአብሔር ጣት በተጨማሪ ከመቀበል ይልቅ መስጠት የሚበልጥ በረከት መሆኑንም በልባችን ይጽፍልናል።

የእግዚአብሔር ጣት በልባችን የሚጽፍልን የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እንከን የሌለው ፍጹም መመሪያችን እንደሆነ ነው።

ስለዚህ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጥልቅ የሆነ ፍቅር አለን።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ማወቅ እንፈልጋለን ምክንያቱም ኢየሱስ የሚያስብበትን አስደናቂ አስተሳሰብ ይገልጥልናል።

ይህ ሶስት ደረጃ በእኛ ውስጥ ሲከናወን ብቻ ነው የተሻልን ሰዎች የምንሆነውና የእግዚአብሔር ታላቅ ዓላማ በሕይወታችን ውስጥ የሚከናወነው።

ኤርምያስ 31፡31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤

32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።

33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።

ትዕዛዛቱ በልባችን ውስጥ በተጻፉ ጊዜ ምን ይመስላሉ?

ማቴዎስ 22፡36 መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው።

37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

38 ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

39 ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።

40 በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።

ኢየሱስ እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ንሰሃ በገባን ጊዜ በልባችን ውስጥ በጣቱ ሲጽፍ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርንና ሰዎችን (ጠላቶቻችንን ጨምሮ) የምንወድድ ሰዎች እንሆናለን።

እግዚአብሔር ቃሉ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ከወደዳችሁ የተጻፈውን ቃሉንም ትወድዳላችሁ።

የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ስትማሩ የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ መውደድ ትጀምራላችሁ።

ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ መልክ በሰው ልብ ውስጥ የሚኖርበት አዲስ የሕይወት ዘይቤ ነው።

 

 

በሰው ልብ ውስጥ ያሉት አራቱ ክፍሎች በሰማያት በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ ያሉትን አራት ሕያዋን ፍጥረታት ያስታውሱናል።

ራዕይ 4፡2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም፥ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

ራዕይ 4፡6 በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።

7 ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።

 

 

ማቴዎስ 6፡10 ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤

በምድር የሚደረገው ነገር ሁሉ በሰማያት የተከናወነውን የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት።

ስለዚህ ኢየሱስ በምድር ላይ ያለው ዙፋኑ ንሰሃ የገቡ ሰዎች ልብ ብቻ ነው።

ኢየሱስ አራት ክፍሎች ባሉት በሰው ልብ ውስጥ ሲኖር በሰማያት በአራት ሕያዋን ፍጥረታት ኃያላን ክቡር ዘበኞች የተከበበ ዙፋኑ ትዝ ይለዋል። እነዚህ ሕያዋን ፍጥረታት የክርስቶስን ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚመሩ እና የሚጠብቁ መናፍስት ነቸው።

ብዙ ነገር በሚለዋወጥበት በሰው ታሪክ ዘመናት ውስጥ እነዚህ መናፍስት ቤተክርስቲያንን ምን ማድረግ እንዳለባት እና ምን ማመን እንዳለባት ያሳዩዋታል።

ስለዚህ ኢየሱስ ሕጉን ለምንድነው ሁለት ጊዜ በድንጋይ ላይ ሁለት ጊዜ ደግሞ በምድር ላይ የጻፈው?

ምክንያቱም ሶስተኛው ደረጃ በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሁለት ጊዜ ስለሚደገም ነው።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በኃይል ይከናወን ነበረ፤ እነርሱም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን የሐዋርያትን ትምሕርት ያምኑ ነበረ።

ከሐዋርያቱ ትምሕርት የተነሳ የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን በሕዝቡ ልብ ውስጥ ኢየሱስን ነበር ያነገሱት።

ከዚህም የተነሳ መንፈስ ቅዱስ ወደ አዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ሁሉ መርቷቸዋል።

ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ከዚያ በኋላ ግን ሐዋርያቱ ሞቱና ቤተክርስቲያንን የሰው አመራር ተቆጣጠራት ይህም የሰው አመራር ቤተክርስቲያንን ከመጽሐፍ ቅዱስ አርቆ ወሰዳት። እንደ ክሪስማስ፣ ሥላሴ፣ እና ሔዋን የዛፍ ፍሬ በላች የሚሉ የሰው ወጎች ቤተክርስቲያንን ለዘመናት በስሕተት ውስጥ አስረው አስቀሩዋት።

እግዚአብሔርም በመጨረሻው በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ብቻ ነው ወደ መጀመሪያው በሐዋርያት የሚመራው ዘመን ውስጥ ወደ ነበረው እምነት እንድንመለስ የሚያስተምረንን መልእክተኛ የላከው።

ማቴዎስ 17፡11 ኢየሱስም መልሶ፦ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

ስለዚህ በመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ አዲስ ኪዳንን የጻፉትን የሐዋርያትን ትምሕርት አጥብቀው የሚከተሉ ሰዎች ይነሳሉ።

በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ልክ የመጀመሪያው ዘመን ውስጥ የነበሩ ሰዎችን የሚመስሉ ሰዎች ይፈጠራሉ።

እህል ደርሶ በሚታጨድበት ጊዜ የሚታጨደው ዘር መጀመሪያ የተዘራውን ዘር ነው የሚመስለው።

 

 

ኢየሱስ ቃሉ በትልቅ አህያ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። አህያዋም ኢየሱስን ተሸክማ ስትሄድ በውርንጫ “በአህያዋ ልጅ” ታጅባ ነበር የሄደችው፤ ውርንጫዋም እናትየውን አህያ በመታዘዝ ተከተለች።

ለራሳችን ለመሞት እየተለማመድን ሳለን የክርስቶስ መንፈስ የእኛን አሮጌ መንፈስ መተካት አለበት።

 

 

መለየት

ኢየሱስ የሐይማኖት መሪዎችን ከነ ስውር አጀንዳቸውና ዓላማቸው ጋር አባሯቸው ሴቲቱ ብቻዋን ቀረች። ስለዚህ ኢየሱስ በራሳቸው ተንኮል ስላሸነፋቸው እነዚህ የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን ጠሉት፤ ኢየሱስን ቃሉን ሊገድሉትም ፈለጉ። ምክንያቱም እርሱ በሕዝቡ ላይ ለነበራቸው ስልጣን ስጋት ሆነባቸው። የሐይማኖት መሪዎች ደግሞ በሕዝቡ ላይ የነበራቸውን ስልጣን ማጣት አይፈልጉም።

ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችንም ከቤተመቅደሱ ውስጥ አስወጥቷቸዋል።

የሐይማኖት መሪዎችን ከገንዘባቸው መለያየት ለእነርሱ የሚዋጥላቸው ነገር አይደለም።

ዮሐንስ 2፡13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።

14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤

15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

ለእድሜ ልክ የሚያሳድድህ ጠላት ከፈለግህ የሐይማኖት መሪ የገቢ ምንጭ ላይ ስጋት ፍጠርበት።

ፓስተሮች አሥራት የእኛ ነው ይላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እንደዚያ ተብሎ አልተጻፈም።

ፓስተሩን ከገቢ ምንጩ ማለያየት። ይህ ጦርነት እንዲጀመር ያደርጋል።

እስቲ ወደ ተከሰሰችዋ ሴት እንመለስ፤ አሁን ከሐይማኖት መሪዎች ተለይታለች፤ እነርሱም ከኢየሱስ አጠገብ ሄደዋል ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ተለይተው ሄደዋል።

አሁን ኢየሱስ ተለይቶ ስለቆመ ሰው ማብራራት ይችላል፤ ልክ ከጌታ ጋር ለብቻዋ ተለይታ እንደ ቆመችዋ ሐጥያተኛ ሴት። ይህም ጌታ ኢየሱስን በልባቸው ተቀብለው ከእርሱ ጋር በግል ሕብረት የሚያደርጉ ሰዎችን ያሳያል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እየተገለጡ ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ በሚሰጡን ጊዜ የክርስቶስ ቅዱስ ምፈስ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት የሚመራን ውስጣዊ ብርሃን ይሆንልናል።

 

 

ዮሐንስ 8፡12 ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።

ኢየሱስ በልባችሁ ውስጥ ሲኖር እርምጃችሁን እና ውሳኔዎቻችሁን የሚመራ ውስጣዊ ብርሃን ይሰጣችኋል።

ከሁሉ በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታምኑ እና እንድትከተሉ ያደርጋችኋል።

ዮሐንስ 8፡13 ፈሪሳውያንም፦ አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህ፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም አሉት።

የሐይማኖት መሪዎች ኢየሱስን ስለ ራስህ መናገር አትችልም አሉት።

ሰባኪዎች ሁሉ ለራሳቸው ተከታዮችን ለማፍራት ብለው ስለ ራሳቸው እያጋነኑ ይናገራሉ። ነገር ግን ሕዝቡን ወዴት እየመሩት ነው?

ዮሐንስ 8፡14 ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እኔ ስለ ራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደ መጣሁ ወዴትም እንድሄድ አታውቁም።

ፈሪሳውያን አሳማኝ ነጥብ የተናገሩ መስሏቸዋል። እርሱ ስለ ራሱ የተናገረውን እንዴት አድርገው ሊያምኑ ይችላሉ?

ነገር ግን ኢየሱስ የሰራቸውን ተዓምራት ደግሞ እንዳላዩ አልፈዋል። ቃና በተደረገው ሰርግ ላይ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ መለወጡ። ቃና ውስጥ ቆሞ ቅፍርናሆም ውስጥ ያለውን ሰው መፈወሱ። አንድ ልጅ በቋጠረው ምሳ 5,000 ሰዎችን አብልቶ 12 መሶብ ቁርስራሽ እንዲተርፍ ማድረጉ። ነፋስ በሚያናውጠው ባሕር ላይ መራመዱ። የሳምራዊቷን ሴት የቀድሞ ታሪክ መግለጡ።

ይህ ሁሉ ሥራው የቃላት ምስክርነት የማያስፈልገው እውነተኛ ምስክር ነው። እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሰው እያያቸው ነው የተደረጉት።

የትኛውም ፈሪሳዊ ሆነ የሐይማኖት መሪ ከኢየሱስ ተዓምራዊ ኃይል ጋር ሊወዳደር አይችልም።

ስለዚህ ኢየሱስ ባደረጋቸው ተዓምራት ሙሉ በሙሉ የተበለጡት ፈሪሳውያን ኢየሱስ ተዓምራት የሚሰራበት ኃይል ከየት እንደመጣ ምንም አላወቁም። የኢየሱሰ የወደፊት እቅዱ ምን እንደሆነም አንዳች አያውቁም።

ፈሪሳውያን በሐይማኖታዊ ወጎቻቸውና ልማዶቻቸው እየተመሩ ነበር የሚኖሩት። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሰው ሰራሽ ሕጎችን በመከተል ነው የሚያውቁት፤ በዚህም መመሪያቸው አማካኝነት የማያቋርጥ ገቢ ያገኙበታል። ፈሪሳውያን የአይሁድን እምነት ሰው ሰራሽ የድግግሞሽ ሥርዓት አድርገው አስቀርተውታል።

ከእነርሱ ሐይማኖታዊ ስርዓት ውጭ ያለ እና በማይታየው በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመራ ሰው ሲገጥማቸው ምን እንደሚያደርጉ ግራ ገብቷቸዋል።

ፈሪሳውያን የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተጻፈውን ትንቢት ስለሚፈጽም ሰው የሚያውቁት ነገር አልነበራቸውም።

ፈሪሳውያን በተጨማሪ ደግሞ ሊሳሳቱ እንደሚችሉም አላወቁም። ሙሉውን እውነት አግኝተናል ብለው ነበር የሚያስቡት። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ቤተክርስቲያን እውርና እንቅልፋም ሆናለች ቢልም እንኳ ቤተክርስቲያን እንቅልፏን መተኛቷንና እውር መሆኗን አጥብቀው እንደሚክዱ እንደ ዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው ፈሪሳውያንም።

ኢየሱስ በዘመን መጨረሻ ስለሚኖሩ የዳኑ ክርስቲያኖች ሲናገር በአስር ንጹህ ቆነጃጅት ምሳሌ ነው የገለጻቸው። ግማሾቹ ልባሞች ግማሾቹ ደግሞ ሰነፎች። ነገር ግን ሁሉም እንቅልፋቸውን ተኝተዋል።

የመጨረሻዋ የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን እውር ተብላለች።

ዮሐንስ 8፡15 እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም።

ፈሪሳውያን መንፈሳዊ መረዳት አልነበራቸውም። ኢየሱስን ሊገድሉት ፈልገዋል ምክንያቱም እነርሱ በሕዝቡ ላይ ለነበራቸው ስልጣን ስጋት ሆኖባቸዋል። ደግሞም የገንዘብ ምንጫቸው ላይ ስጋት አምጥቶባቸዋል። ለእነርሱ የታያቸው ነገር ኢየሱስ ለስልጣናቸው እና ለገንዘባቸው የሚያመጣባቸው አደጋ ብቻ ነው። የሕዝቡ መዳን በእነርሱ ሃሳብ ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ ብልጭ አላለም። ኢየሱስ ላይ በሸመቁበት ጊዜ እያሰቡ የነበረው ስለ ራሳቸው ጥቅም ብቻ ነበር።

ኢየሱስ በማንም ላይ አልፈረደም። ለዚህ ነው ሐጥያተኛዋን ሴት ያዳናት።

ዮሐንስ 8፡16 የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።

ነገር ግን በፍርድ ትክክለኛ ሆኖ ካለፈ ፍርዱ ቅን ፍርድ ነው ማለት ነው። ለምን? የእግዚአብሔር መንፈስ የእርሱ አባት ነው እግዚአብሔር ደግሞ ሁልጊዜ ትክክል ነው። እግዚአብሔር በፍጹም አይሳሳትም።

እርሱ የሚያደርጋቸው ተዓምራት ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ ካሌለ በስተቀር ሊደረጉ የማይችሉ ነበሩ።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ዮሐንስ 8፡17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል።

ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ አልነበረም ስለ ራሱ የሚናረው። ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔርም ከሰማያት ይህ እርሱ የመረጠው ልጁ መሆኑን በግልጥ እየመሰከረ ነበረ። ኢየሱስ የሰራቸውን ተዓምራት ማንም ሊክድ አይችልም።

ዮሐንስ 8፡18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።

እንደ ሰው ኢየሱስ በምድር ላይ የተሰጠውን ተልእኮ መናገር ይችላል። ነገር ግን በእጆቹ የሚደረጉት ከተፈጥሮ ኃይል በላይ የሆኑ ምልክቶችና ድንቆች ግን ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔርም በሥራው ስለ እርሱ እየመሰከረ እንደነበረ ያሳያሉ።

ዮሐንስ 8፡19 እንግዲህ፦ አባትህ ወዴት ነው? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ እኔንም ወይም አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር አላቸው።

የእግዚአብሔር መንፈስ የሆነው አብ ሰው በሆነው በኢየሱስ ውስጥ እየኖረ ተዓምራትን አደረገ። እነዚህን ተዓምራዊ ሥራዎች መስራት የሚችል ሰው ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር በውስጡ መሆን አለበት።

ማቴዎስ 1፡20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።

የሕይወትን ዘር በሴት ማሕጸን ውስጥ የሚያስቀምጥ ሰው ለሚለወደው ሕጻን አባት ነው።

መንፈስ ቅዱስ የዘላለምን ሕይወት በማርያም ማሕጸን ውስጥ ዘር አስቀመጠ።

አንድ ሕጻን አንድ አባት ብቻ ነው ሊኖረው የሚችለው።

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው።

ዮሐንስ 8፡20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።

ኢየሱሰ አሁን ግምጃ ቤት ውስጥ ነበረ። ገንዘብ ለዋጮችን አባሮ ያስወጣቸው ከዚህ ቦታ ነው። ስለዚህ ሁሉም እርሱን ፈርተውታል። ስለ ገንዘብ የነበራቸውን ስግብግብነት አይቶ የተቆጣበት ቁጣ ዓይኖቹ ውስጥ ይታይ ስለነበረ ሁላቸውም ከእርሱ ራቅ ብለው ቆሙ።

ኢየሱስ በገንዘብ ለዋጮቹ ይህን ያህል የተቆጣው ለምንድነው?

ምክንያቱም በእነዚህ ገንዘብ ለዋጮች ውስጥ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያንን የነጋዴነት መንፈስ ስላየ ነው። የቤተክርስቲያን መሪዎች ሃብታሞች ይሆናሉ ነገር ግን ገንዘብ ሰብስበው፤ ሰብስበው አይበቃቸውም። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ቅንነት በገንዘብ ወዳዶቹ የሎዶቅያ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አይቀጥልም፤ እነዚህም ቤተክርስቲያኖች የገንዘብ ትርፍን አብዝተው ስለሚወድዱ የነብዩን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርት አይቀበሉም።

ቤተክርስቲያን የተጀመረችው በአንድ ድሃ አናጺ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር የሆነው ዶ/ር ሪቻርድ ሃልቨርሰን እንዲህ አለ፡- “ግሪኮች ወንጌልን ሲያገኙ ወደ ፍልስፍና ለወጡት፤ ሮማውያን ወንጌልን ሲያገኙ ወደ መንግስት ለወጡት፤ አውሮፓውያን ወንጌልን ሲያገኙ ወደ ባህል ለወጡት።

“ነገር ግን አሜሪካውያን ወንጌልን ሲያገኙ… ወደ ትልቅ ንግድ ለወጡት!”

የተደራጀ ሐይማኖት ትኩረቱ እግዚአብሔር አይደለም፤ ትኩረቱ በድርጅቱ ላይ ነው እንጂ። ብዙ ሰዎች በረሃብ እያለቁ ሳለ የቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙ ሚሊዮን ብር ለራሳቸው ያከማቻሉ፤ በድሎት እና በቅብጠት ይኖራሉ።

ኤል. ሮን ሃባርድ የተባለ የሳይንቶሎጂ ቤተክርስቲያን መሪ እንዲህ ብሎ ነበር፡- “በዚህ ዘመን ሃብታም መሆን ከፈለጋችሁ ቤተክርስቲያን ክፈቱ።”

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙርያ ብዙ መሬት አላት፤ በዓለም ዙርያ ካሉ ድርጅቶች ሁሉ በላይ የበለጠ ሰፊ መሬት ይዛለች። ቫቲካን በካዝናዎችዋ ውስጥ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ንጹህ ወርቅ አላት፤ ከዚህም ውስጥ አብዛኛው በአሜሪካ ፌደራል ሪዘርቭ ባንክ ውስጥ በጥፍጥፍ ወርቅ መልክ ነው የተቀመጠው፤ ከዚያ የተረፈው ደግሞ በእንግሊዝ እን በስዊትዘርላንድ ባንኮች ውስጥ ተቀምጧል። ባቲካን አሜሪካ ውስጥ ያላት የሃብት መጠን አሜሪካ ውስጥ ያሉ አምስት ታላላቅ ኩባንያዎች ያለቸው ሃብት አንድ ላይ ቢደመር እንኳ እነዚህን ሁሉ የሚበልጥ ሲሆን ይህም ከሃብቷ በጣም ትንሹ ክፍል ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ተጨማሪ ሃብት በመሬት፣ በንብረት፣ በንግድ ሰነድ እና በአክሲዮን አማካኝነት ከማንኛውም ድርጅት፣ ኮርፖሬሽን፣ ባንክ እና መንግስት ሁሉ የበለጠ ያላት ሲሆን ይህም የዚህን ሁሉ ሃብት አስተዳዳሪ የሆነውን ፖፑን በምድር ታሪክ ውስጥ በሃብት አንደኛ አንደኛ አድርጎታል። በእርግጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሃብት እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ መጠኑን በትክክል ለማስላት እንኳ አስቸጋሪ ነው። ፖፑ ስንት ቢሊዮን ዶላር እንዳለው በትክክል መገመት የሚችል የለም። ቤተክርስቲያኒቱም ከተንኮሏ ብዛት አብዛኞቹን የኪነጥበብ ሥራዎችዋን ዋጋ በ1 ዩሮ ብቻ ግምት ታወጣላቸዋለች እንዳይሸጡ ብላ። ደግሞም ቤተክርስቲያኒቱ አንዳችም ግብር አትከፍልም።

ዮሐንስ 13፡29 ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥

ከመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት መካከል የገንዘብ ከረጢቱን የሚቆጣጠረው ወይም ገንዘብ ያዡ ይሁዳ ነበረ።

የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን የውድቀቷ መንስኤ የሃብት ክምችት ነው።

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23