ዮሐንስ ምዕራፍ 06. ኢየሱስ ብቸኛው የዘላለም ሕይወት ምንጭ ነው።
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዮሐንስ 6፡1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው።
ገሊላ ኢየሱስ ብዙውን ጊዜውን ያሳለፈባት አውራጃ ናት። ካርታው ላይ እንደምታዩት ከገሊላ ባሕር በስተ ግራ (ወይም በምዕራብ) በኩል የምትገኝ ሃገር ናት።
ኢየሱስ ከሰራቸው 33 ታላላቅ ተዓምራት ውስጥ 25ቱ የተደረጉት ገሊላ ውስጥ ነው፤ ደግሞም ከተናገራቸው 32 ምሳሌዎች መካከል 19ኙን ገሊላ ውስጥ ነው ያቀረባቸው። ገሊላ በገሊላ ባሕር በስተ ምዕራብ ዳርቻ በኩል የምትገኝ አውራጃ ናት።
በገሊላ ባሕር ምዕራባዊ ዳርቻ ግን ሌላ ደግሞ መጥፎ ስም ያላት ከተማ አለች። የጥብርያዶስ ከተማ ከባሕሩ አጠገብ ውብ በሆነ ቦታ ላይ ነው የተቆረቆችው ግን ደግሞ ቦታው ጥንታዊ መቃብሮች ያሉበት ስለሆነ በሰው ሁሉ አእምሮ ውስጥ ከተማይቱ ከሞት ጋር ተያይዛ ነው የምትታወሰው። ከተማይቱ የተቆረቆረችው መጥምቁ ዮሐንስን በገደለው ሔሮድስ ነው። መጥምቁ ዮሐንስን የገደለው ሔሮድስ ኢየሱስን ሊገድል የሞከረው የጨካኙ ሔሮድስ ልጅ ነው። ከተማይቱ የተሰየመቸው ኢየሱስ በተገደለበት ዘመን ይገዛ በነበረው በሁለተኛው ታላቅ የሮማ ገዥ በታይቢሪየስ ስም ነው። ታይቢሪየስ የነገሰው ከ14 ዓመተ ዓለም እስከ 37 ዓመተ ምሕረት ነበረ። እርሱም በግፍ፣ በነፍስ ግድያ፣ በንጥቂያና በቅሚያ ፈቃዱን የሚያስፈጽም ጨካኝ፣ ጠማማ፣ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ነበረ። ከሰዎች የቀማውን ንብረት በመሸጥ ገንዘብ ያከማች ነበር። ኢየሱስ የተሰቀለው ታይቢሪየስ በዙፋኑ ላይ በነበረበት ዘመን ነው። ለዚህ ነው ሮማዊው የይሁዳ አስተዳዳሪ ጲላጦስ አይሁዳውያን ለቄሳር እንናገርብሃለን ሲሉት ፈርቶ ኢየሱስን እንዲገድሉት አሳልፎ የሰጣቸው። ታይቢሪየስ ቄሳር ነበረ ማለትም የሁሉ ንጉስ። የስልጣኑ ብዛት ታይቢሪየስን ስላባለገው በየቀኑ ሁለት ወይም ሶስት የሞት ፍርድ ይፈርድ ነበረ። እርሱ ፈርዶባቸው የተገደሉ ሰዎች ወደ እሬሳቸው ተጎትቶ ታይበር ወንዝ ውስጥ ይጣላል። ጲላጦስ እንደ ታይቢሪየስ ግፈኛ ካልሆነ በቀር ጉዱ እንደሚፈላበት ገብቶታል። ሰዎች ሲሰቃዩ በማየት ይዝናና የነበረውና በውስጡ የርህራሄ ጠብታ ያልነበረው ታይቢሪየስ ጲላጦስ ኢየሱስን ባይገድለው እርሱ ጲላጦስን ይገድለው ነበር። ሔሮድስም ጲላጦስ ኢየሱስን ወደ እርሱ የላከው ጊዜ ኢየሱስን ይቅር ሊለው አልፈለገም፤ በዚያ ዓመት በ33 ዓ.ም ኢየሱስ ተከስሶ የቀረበ ጊዜ የተደረገበት የችሎት ሂደትም ቀልድ ነበረ። ሔሮድስም ልክ እንደ ጲላጦስ ለራሱ ነፍስ ፈርቶ ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። ሔሮድስ ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ መልሶ ሲልከው ልክ እንደ እርሱ በታይቢሪየስ ፍርሃት ተንቀጥቅጦ የነበረው ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ እንደሚፈርድበት እያወቀ ነው። እራሱ አለመፍረዱ ሔሮድስን ምንም አልጠቀመውም ምክንያቱ ሔሮድስ ያለ ዕድሜው በ39 ዓ.ም ነው የሞተው፤ ማለትም ታይቢሪየስ ታፍኖ ከሞተበት ዓመት ከ37 ዓ.ም ሁለት ዓመታት በኋላ። ጲላጦስ ደግሞ በ38 ዓ.ም በራሱ ፈቃድ ውሃ ውስጥ ሰጥሞ ሞተ። ስለዚህ እነዚህ ሶስት ክፉ ሰዎች በሞታቸው አልተነጣጠሉም።
ታይቢሪየስ “የታይበር” ማለት ሲሆን ታይበር በሮም ከተማ መሃል የሚወርደው ወንዝ ነው። የታይበር ወንዝ መከር በወንዙ ላይ ተጥለው እየተንሳፈፉ ወደ ባሕር የሚገቡ እሬሳዎእ ነበሩ። ስለዚህ ወንዙ የሞት ወንዝ በመሆን ነው የሚታወቀው። ባሕር እርፍት የሌላቸውንና በመሪዎቻቸው የግል አመለካከት ተጽእኖ የሚፍገመገሙና የሚናወጡ ሕዝቦችን ይወክላል። ያለማቋረጥ የሚፈጸመው የነፍስ ግድያ በፍርሃት የተያዙትን ሕዝቦች ያለ ዓመጽ ዝቅ ብለው እንዲገዙ አድርጓቸዋል።
በአንጻሩ ኢየሱስ ደግሞ መንፈሳዊ የሕይወት ወንዝ ነው። በኢየሱስ ዘላለማዊ መንግስት ውስጥ ባሕር አይኖርም።
ገሊላ “ኡደት” ወይም “በጀመረበት ቦታ ዞሮ የሚመጣ መንገድ” ማለት ነው።
ጊዜ ሲያልቅ፣ እያንዳንዱ አማኝ ዘመኑን ሲጨርስ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔር በመጀመሪያ ከ4,000 ዓመታት በፊት ለአብራሐም የተስፋ ቃሉን ወደ ሰጠበት ወደ እስራኤል ትመለሳለች።
ስለዚህ ኢየሱስም የሚሄድበት አቅጣጫ ኡደት አለው። በኡደት ውስጥ ስንሄድ ዞረን ወደ ተነሳንበት ቦታ እንመለሳለን።
ለእኛ ኡደት በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ወደ ተሰጠ እምነት ለመመለስ መታገል ማለት ነው።
ይሁዳ 1፡3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
በስተመጨረሻ በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ያሉ አማኞች የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የነበሩት አማኞች ያምኑ ወደ ነበረው እምነት ዞረው ሲመለሱ የሰባቱ ቤተክርስቲያን ዘመናት “ኡደት” ይጠናቀቃል። አንድ ተክል ያፈራው ዘር በመጀመሪያ የተዘራውን ዘር ሲመስል ነው ለመታጨድ የሚደርሰው።
ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ የሮማዊው መሪ እና የቅጥረኞቹ ተቃራኒ ነው። ኢየሱስ ሕይወት እና ቅድስናን ሲያቀርብልን ሮማዊው ንጉስ ግን ሞትን የሚያከፋፍል ጠማማ ሰው ነበረ። በግል ጥቅማቸው እየተነዱ የሚንቀሳቀሱት ቅጥረኞቹ የራሳቸውን ነፍስ ለማትረፍ ሲሉ ፈርተው ንጹህ ሰውን እንደ ሐጥያተኛ የሚኮንኑ እና የሚገድሉ ክፉዎች ናቸው።
ስለዚህ ኢየሱስ ከገሊላ ባሕር ምዕራባዊ ዳርቻ የታይቢሪየስ ከተማ ካለችበት በኩል ተነስቶ ወደ ማዶ ተሻገረ።
በዚህም ድርጊቱ እርሱ የሮማዊው ገዥ ተቃራኒ መሆኑን ገለጠ።
ዮሐንስ 6፡2 በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
ኢየሱስ የሚያደርጋቸው ተዓምራት ብዙ ሰዎችን ይስቡ ነበር። ጤና ትልቅ በረከት ነው። ስለዚህ ወንጌሉ በስጋ የሚገለጥ በረከት በሚሰጥ ጊዜ ሁሉ በጣም ብዙ ሰዎች በፍጥነት ይከተሉታል። የብልጽግና ወንጌል ሁልጊዜ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ነው። እግዚአብሔር ግን በዚህ አይደነቅም ምክንያቱም ሰዎች መለኮታዊ ተዓምር አይተው የተሳቡ ጊዜ ከልባቸው አይለወጡም። አይሁዳውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ብዙ ታላላቅ ተዓምራት አላዩምን? ሆኖም ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንደ እነርሱ እግዚአብሔርን ለመካድ የሚፈጥን አልነበረም።
የግል ጥቅም ማግኘት እግዚአብሔርን ለመከተል ጥሩ ምክንያት አይደለም።
ዮሐንስ 6፡3 ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጣና በዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።
ተራራ መውጣት አድካሚ ስራ ነው። ኢየሱስን መከተል በጣም ከባድ ነው። ኢየሱስ እርሱን ለመከተል ሁሉ ትተው ከመጡ ጥቂት ደቀመዛሙርት ጋር ጊዜ ማሳለፍ ይወድ ነበር። ተዓምራት ሲያዩ በጣም በሚደነቁ ብዙ ሕዝብ ብዙም አልተደነቀባቸውም። የሕዝቡ እምነት ላይ ላዩን ብቻ ነበረ። ችግር ሲገጥማቸው ወዲያው እግዚአብሔርን ጥለው ይሄዳሉ። የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት መለኮታዊ ተዓምራት ከማየትም በላይ በጣም አስፈላጊ ነው። ከነብያት ሁሉ ታላቅ የነበረው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ አንድም ተዓምር አላደረገም።
5,000 ሰዎች በጥቂት እንጀራ በልተው የጠገቡበት ተዓምር ነው ብቻ በአራቱም ወንጌሎች ውስጥ ተደጋግሞ የተጻፈው።
ሆኖም ግን ይህ ተዓምር የት አካባቢ እንደተደረገ በትክክል አናውቅም። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እስከ ዛሬ ስለ ቦታው ክርክር ውስጥ ናቸው።
ኢየሱስ ይህ ተዓምር እንዲወራለት ብሎ አይደለም የተናገረው። ከተዓምሩ ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ሚስጥር እንድንማር ብሎ ነው እንጂ።
ዮሐንስ 6፡4 የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።
በዓሉ ቀርቦ ነበረ። ይህም በዓል መቅረቡ ኢየሱስ ዓይኖቹን በወደፊቱ ጊዜ ላይ ማትኮሩን ያስረዳል።
የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስን እንደሚበር ንስር አድርጎ ነው የሚያቀርብልን። እርሱም የወደፊት ክስተቶችን አጥርቶ ማየት የሚችለው አስደናቂ ዓይኖች ያሉት የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
ጊዜው የሚያዝያ ወር ገብስ የሚታጨድበት ወቅት ነበረ። ገብስ ዳቦ ይጋገርበታል፤ እርሱም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮ ተምሳሌት ነው።
የፋሲካ በዓል የሚወክለው ኢየሱስ የፋሲካ በግ ሆኖ እንደሚሞት ነው። የእርሱም ሞት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት እንዲጀመሩ ያደርጋል ምክንያቱም አይሁድ ኢየሱስን አንቀበልህም በማለት እንዲገደልላቸው ጠየቁ።
ስለዚህ ኢየሱስ አሁን ወደ ማዶ በመሻገሩ ከታይቢሪየስ ከተማ ርቆ ባለበት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚወከሉበትን አንድ ክስተት ፈለገ፤ ደግሞም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ከሮም መንግስት ተጽእኖ ነጻ የምትሆንበትን እንዲሁም ወደ ፊት ከምትነሳዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተለይታ የምትቆምበትን አንድ ክስተት ፈለገ።
ዮሐንስ 6፡5 ኢየሱስም ዓይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን፦ እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን? አለው።
ዮሐንስ 6፡6 ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።
ፊሊጶስ ከዚህ ክስተት አንድ ትምሕርት ተምሯል። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የተናቁትንና በሰዎች የተጠሉትን እንዲሁም ብቁ ያልሆኑትንና ያልተጠበቁትን በመጠቀም ዓላማውን ይፈጽማል።
ዮሐንስ 6፡7 ፊልጶስ፦ እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም ብሎ መለሰለት።
ፊሊጶስ አስፍቶ እያሰበ ነበር። በወይኑ እርሻ ምሳሌ ውስጥ ኢየሱስ አንድ ዲናር የአንድ የቀን ሰራተኛ የአንድ ቀን ደሞዝ እንደሆነ ገልጧል። ስለዚህ 200 ዲናር ማለት ለአንድ ሰው የስድስት ወር ወይም ከዚያ በላይ ክፍያው ነው።
ስለዚህ ፊሊጶስ ይህ የማይቻል እንደሆነ አሰበ። ለእያንዳንዱ ሰው አንድ ጉርሻ ማብላት እንኳ እንደማይቻል ገብቶታል።
ሰዎቹ ፍጥረታዊ ሕይወታቸውን ለማቆየት የሚበሉት እንጀራ አስፈልጓቸዋል።
ስለዚህ ፊሊጶስ በመንፈስ ማሰብን መማር ነው ያለበት። ጊዜው የመከር ወቅት ስለነበረ የተሰበሰበው ብዙ ሕዝብ ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ የሚድኑ አማኞችን ነው የሚወክሉት።
ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚሰበሰቡ ቅዱሳን እግዚአብሔር ዓይኑን የጣለባቸው ዋኘኞቹ የነፍሳት አዝመራ ናቸው። እነዚህ ብዙ ሕዝብ የ2,000 ዓመታት የቤተክርስቲያን ታሪክን ይወክላሉ።
ስለዚህ ትልቁ ጥያቄ ይህ ነው፡- ቤተክርስቲያን በምድር ላይ በምትቆይበት የ2,000 ዓመታት ታሪኳ ውስጥ ምግቧን ከየት ታመጣለች? የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት እንጀራ ነው፤ ቃሉን ለሚያምኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛው የዘላለም ሕይወት ምንጭ ነው።
ዮሐንስ 6፡63 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
ደቀመዛሙርቱ በስጋ የሚያድጉዋቸው ጥረቶች ከንቱ ነበሩ። ለሕዝቡ የሚበቃ እንጀራ ማግኘት አልቻሉም።
ወንጌሉ ግን በጥቂት ነው የሚጀምረው።
ኢየሱስ አንድ ሰው ብቻ ሆኖ እውነተኛው ቃል ነው። እርሱ ጥቂት የሆኑትን ሐዋርያቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን እንዲጽፉ በመንፈስ ያነሳሳቸዋል። የአዲስ ኪዳን መጽሐፍም የሕይወት መጽሐፍ ነው። በየትኛውም ዘመን ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ የዘላለም ሕይወት የሚያገኙት የኢየሱስ ሐዋርያት የጻፉትን መጽሐፍ ቅዱስ በማመን ብቻ ነው።
የሕይወት እንጀራ ከኢየሱስ ይመጣና ወደ ደቀመዛሙርቱ ከዚያ ለሕዝቡ ይደርሳል።
ዘካርያስ 4፡10 የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው?
ጥቂት ነገር። አንድ ሰው፣ ያውም ምንም ያልጻፈ ሰው፣ አስራ ሁለት ደቀመዛሙርት ብቻ አሰልጥኖ (ከእነርሱ መካከልም አንዱ ሰይጣን ነበረ) ዓለምን ሊገለብጥን የዘመን አቆጣጠር ከእርሱ የልደት ቀን እንዲጀመር ማድረግ ይችላልን? የማይቻል ነገር ይመስላል።
እንድሪያስ ቢያንስ ለመሞከር ፈቃደኛ ነበረ። አንድ ምሳውን ከቤት ቋጥሮ ይዞ የመጣ ልጅ አገኘ። ትንሽም ቢሆን ምግብ ነው ግን እንድሪያስ ምግቡ ለማንም እንደማይበቃ ተረድቷል።
ሆኖም ግን ትንሽ ጥረት ወጤቱን በኢየሱስ እጅ ውስጥ ስንተወው ትልቅ ውጤት ማምጣት ይችላል።
ዮሐንስ 6፡8 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ፦
ዮሐንስ 6፡9 አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።
እንድሪየስ ያየው ምግብ በጣም ጥቂት ነበር።
ኢየሱስ ያየው ግን አምስት እንጀራ እና ሁለት ዓሳ በአንድ ላይ ሰባት ምግብ ሲሆን ይህም ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን አስተምሕሮ ይወክላል። አምስቱ የገብስ እንጀራዎች የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዘመናት እና የመጨረሻዎቹን ሶስት ዘመናት ይወክላሉ። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እውነትን ከሐዋርያት ተቀብሏ፤ ሁለተኛው ዘመንም እውነትን እንደያዘ ነበር ግን ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ በመሾም ቀስ በቀስ ከእውነት እየተንሸራተተ ነበር። ከዚያ ቀጥለው አንድ ጳጳስ በአንድ ከተማ ውስጥ ላሉ ቤተክርስቲያኖች በሙሉ ራስ እንዲሆን ሾሙ።
በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሮማዊው ንጉስ ኮንስታንቲን በ325 ዓ.ም በሮም ያለውን ጳጳስ በየከተሞች ውስጥ ላሉት ቤተክርስቲያኖች ለተሸሙት ጳጳሳት ሁሉ ሊቀ ጳጳሳት አድርጎ ሾመው። በ400 ዓ.ም የሮማው ጳጳስ ፖፕ ተብሎ ተሰየመ። በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ የሚነሳ ተቃውሞ ሁሉ በሮማ መንግስት ኃይል አማካኝነት ይጨፈለቅ ነበር፤ እውነተኛ ክርስቲያኖችም በሚስጥር ይገደሉ ነበር። ይህንንም የሚያመለክተው ውሃ ውስጥ ማንም ሳያየው የሚዋኝ ዓሳ ነው። በሶስተኛው ዘመን ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማሙ የሰዎችን አመለካከት እና ወጎች ለመጠበቅ ተብሎ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ተገፍቷል። ፖለቲካ እና የአሕዛብ ሐይማኖት ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው ገብተዋል። ይህንን ዘመን የገብስ እንጀራ ሊክለው አይችልም።
በአራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የሮማ መንግስት ሲፈርስ የሮማው ፖፕ ወደ ስልጣን ወጣ። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ሰዎችን ማሳደድ ጀመረች፤ በዚህም የጨለማ ዘመን ውስጥ ከአስር ሚሊዮን በላይ አማኞች ተገድለዋል። እውነተኛ አማኞችም በተራሮችና በሸለቆዎች ውስጥ ተደብቀው ነበር የሚኖሩት። አማኞች ማንም እንዳያያቸው በሚስጥር ይሰበሰቡ ነበር። ከውሃ በታች ተደብቆ የሚዋኝ ዓሳ ይህንንም ዘመን ይወክላል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይሰራጭ ለማገድ እና ሰዎችም በራሳቸው ቋንቋ እንዳያነቡት ለመከልከል የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች። ስለዚህ የገብስ እንጀራ ይህኛውን ዘመን ሊወክል አይችልም።
በአምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ማርቲን ሉተር ጻድቅ በስራ ሳይሆን በእምነት ነው የሚኖረው የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ። ሰዎችም በዚህ እውነት ዳኑ። በዚህ ዘመን ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ ተመጣው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በገብስ እንጀራ ነው የተመሰለው።
ስድስተኛው ዘመንም የገብስ እንጀራ ዘመን ነው፤ በዚህ ዘመን ውስጥ ጆን ዌስሊ ስለ ቅድስና እና የወንጌል ስብከት ሰብኮ ታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን እንዲጀመር አድርጓል።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን በ1906 ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በአዙዛ እስትሪት የተጀመረው ጴንጤ ቆስጤያዊ መነቃቃት የመለኮታዊ ኃይል መገለጥ ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ እንዲመጣ አድርጓል።
በ1963 ከሰባኪዎች ሁሉ በሚበልጥ መለኮታዊ ኃይልና በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መገለጥ የተነሳው ጴንጤ ቆስጤያዊ ሰባኪ ዊልያም ብራንሐም ራዕይ ምዕራፍ 6 ውስጥ ያሉትን ሰባቱን ማሕተሞች እንዲገልጥ በሰባት መላእክት አማካኝነት ትዕዛዝ ተቀበለ። የተቀበለው መገለጥ አዲስ ኪዳንን የጻፉ ሐዋርያዊ አባቶች ያስተማሩትን አስተምሕሮ ሙሉ በሙሉ መልሶ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲያመጣ አስችሎታል። ያም የመጨረሻው እንጀራ ነው።
ዮሐንስ 6፡10 ኢየሱስም፦ ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር።
ሰዎቹ መቀመጣቸው እግዚአብሔር የሰዎች ስጋዊ ጥረት እና ስራ እንዲሁም የሰዎችን ሃሳብ እንደማይፈልግ ያመለክታል። የሰዎች ጥረት ብዙውን ጊዜ ለእግዚአብሔር ስራ እንቅፋት ነው። እኛ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በጸጥታ ተቀምጠን እግዚአብሔር እስኪናገረን ድረስ አንጠብቅም። ቸኩለን መልካም የመሰለንን እናደርጋለን፤ ቸኩለን እውነት የመሰለንን እናምናለን።
ሳር። ሳር ምንም ጥረት አያደርግም፤ ዝም ብሎ ፀሃይ እስትወጣ ይጠብቃል እንጂ። ከዚያ ሳሩ እኛ የማናስተውለውን ተዓምር ይሰራል። ሳር የፀሃይ ብርሃንን ወደ ምግብ ይለውጣል፤ የትኛውም ሳይንቲስት ይህንን ኮርጆ ማድረግ አይችልም። ስለ ፎቶ ሲንተሲስ ጽንሰ ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ እናውቀዋለን ግን ሳሩ የሚያደርገውን መልሰን ልናደርገው አንችልም። ሳሩን ማንም የሚያስተውለው የሚያጨበጭብለት የለም፤ ግን ሳሩ ሰው ማድረግ የማችለውን ተዓምር ይሰራል። እግዚአብሔር በትህትናው የጻር ቡቃያ ውስጥ በሚሰራው ስራ ለእንስሳት ምግብን ያዘጋጃል። ሳይንቲስቶች መስራት ከማይችሏቸው ነገሮች ውስጥ ጥሩ ምግብ አንዱ ነው።
የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ለመቋቋም የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ምግብ የሰጠው፤ የሮማ መንግስት በፈራረሰ ጊዜ ሳትፈርስ ጸንታ የቆመችው ድርጅት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት።
ዮሐንስ 6፡11 ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፥ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።
እንጀራ እና ስጋ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮ ተምሳሌቶች ናቸው።
ኢየሱስ እንጀራዎቹን እና ዓሳዎቹን ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀመዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ።
ይህም ኢየሱስ እንጀራውን እንደሚቆርስ ማለትም በሌላ አነጋገር ለደቀመዛሙርቱ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች እንደሚገልጥላቸው ያሳያል። ደቀመዛሙርቱም አዲስ ኪዳንን ይጽፋሉ፤ አዲስ ኪዳንም እኛ ማመን ያለብን ብቸኛው አስተምሮ ተጽፎበታል፤ ደግሞም አዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ሙሉ ሃሳብ እና ፈቃድ እንዲገለጥልን ከብሉይ ኪዳን ጋር በትክክል ይገጥማል።
ከአዲስ ኪዳን ስንማር የሕይወትን እንጀራ መጀመሪያ ከተቀበሉት ደቀመዛሙርቶች በቀጥታ እየተማርን ነን፤ እነርሱ ደግሞ በመንፈስ ተመርተው የጻፉዋቸውን የአዲስ ኪዳን እውነቶች በቀጥታ ከኢየሱስ ነው የተቀበሉዋቸው።
ኢየሱስ ምስጋና ለማቅረብ ጸለየ። እግዚአብሔር ዓይናችንን በዓይን ኩል እንዲቀባን መጸለይ ያስፈልገናል፤ የዚያን ጊዜ እንጀራውን መቁረስ እንችላለን፤ ማለትም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት እንችላለን። ኢየሱስ ብቻ ነበር እንጀራውን የቆረሰው። እርሱ ብቻ ነው እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጥ ሊሰጣችሁ የሚችለው።
በፍጥረታዊ አእምሮዋችንና የመረዳት አቅማችን የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት መረዳት አንችልም።
ዮሐንስ 6፡12 ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው።
አይሁዶች በሉና ጠገቡ። ከዚያ በኋላ ግዴለሾች ሆኑ፤ ቁርስራሹ ሳሩ ላይ ሲወድቅ እያዩ ዝም ዘሉ፤ እንደውም እራሳቸውም ወደ ሳሩ ላይ እያራገፉት ነበር።
የሰው ነገር። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚስማማንን ጥቂት ቃል መርጠን እንበላለን ምክንያቱም እነዚያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይጠቅሙናል፤ ነገር ግን የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቸል እንለዋለን። ሰዎች አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አይጠቅሙም ወይም አያስፈልጉም ይላሉ። ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጥልቀት ማየት የሚያስችል የንስር ዓይን የላቸውም ማለት ነው።
“አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ” ማለት በመንፈሳዊ (በንስር) እይታ አንጻር አንድ ቡድን ቸል ብሎ የሚያልፋቸውን ጥቅሶች እግዚአብሔር ሰብስቦ ሌላ ቡድንን ይመግብበታል ማለት ነው።
እንጀራው እና ዓሳው የወንጌሉን አስተምሕሮ ይወክላል። እነዚህ ሆዳቸውን የሞሉ አይሁዶች በጲላጦስ የፍርድ ሸንጎ ውስጥ ኢየሱስ ይሰቀል ብለው በመጮህ ወንጌሉን መካዳቸው አይቀርም።
ሰዎች አልቀበልም ብለው ቸል የሚሉት የእግዚአብሔር ቃል ሕዝቡ ሳይበሉ በተዋቸው ቁርስራሾች ተመስለዋል።
አይሁድ ከ2,000 ዓመታት በፊት ወንጌልን አንቀበልም አሉ፤ ከዚያም ደቀመዛሙርቱ ያንኑ ወንጌል አዲስ ኪዳን አድርገው ጻፉ፤ በዚህም የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ለቀጣዮቹ 2,000 ዓመታት እየተመገበች መቆየት ችላለች።
ከዚያ ታሪክ እራሱን እንደሚደግም የአሕዛብ ቤተክርስቲያን ተመልሶ የተሰጣትን እውነት በዘመን መጨረሻ አካባቢ አልቀበልም በማለት ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ገፍታ በሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን ከቤተክርስቲያን ውስጥ ታስወጣዋለች።
አሁን እኛ ያለንበት ሁኔታ ይህንን ይመስላል።
እኛ አሕዛብ ሙሉውን የእግዚአብሔር ቃል ገፍተነዋል። ጠለቅ ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ ሲቀርብልን አንፈልግም ብለን ወርውረነዋል፤ በእርሱ ፈንታ ምንም ጥልቀት የሌለውን የሰው አመለካከት እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን አስተሳሰብ መርጠናል።
የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁልጊዜ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማወቅ እንዳለብን ገደብ ይጥሉብናል፤ ይህንንም የሚያደርጉት እራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን በደምብ አለማወቃቸውን ለመደበቅ ነው።
ዮሐንስ 6፡13 ስለዚህ አከማቹ፥ ከበሉትም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈውን ቍርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሞሉ።
በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ስለዚህ ተሟልቶ የመጣው ሙሉው የእግዚአብሔር ቃል በዘመናዊ ቤተክርስቲያኖቻችን ዘንድ እየተገፋ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የተጣለውን ቃሉን ሰብስቦ በታላቁ መከራ ዘመን 12ቱን የእሥራኤል ነገዶች ይመግብበታል።
ዮሐንስ 6፡14 ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
አይሁዳውያን ተፈጥሮአዊውን ተዓምር አይተዋል። ይህንን ተዓምር ለማድረግ ኢየሱስ የእነርሱን እርዳታ አልጠየቀም። ምግብ ከበሉ በኋላ እርሱ ለመንገስ የእነርሱን ድጋፍ የሚፈልግ መሰላቸው። የራሳቸውን ሰብዓዊ ሃሳብ በእርሱ ላይ ሊጭኑበት ፈለጉ።
ዮሐንስ 6፡15 በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።
የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስን እግዚአብሔር እንደሆነ፣ በሚበርረው ንስር የተመሰለው ታላቁ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አድርጎ ነው የሚያቀርብልን። ንስር አስደናዊ በሆነ የማየት ችሎታው ይታወቃል። ንስር ጥቃቅን ዝርዝሮችንና ሌሎች ማየት የማይችሉዋቸውን በሩቅ ያሉ ክስተቶችን ያያል።
ኢየሱስ አንዳችም ምድራዊ ስልጣን አልፈለገም። ሰው ሰራሽ መንግስት አልፈለገም። ሰዎች በራሳቸው ግላዊ ጥቅም የተጠመዱ እንደመሆናቸው መንግስታቸው እድሜ እንደማይኖረው አውቋል። ለመውጣት በጣም የሚያዳግት ተራራ ዘላቂ የሆነ ጽኑ መንግስት ተምሳሌት ነው። ይህም የወደፊት መኖሪያችንን በሚወክለው ስለ ጽዮን ተራራ በሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተገልጾአል።
የዳንኤል ራዕይ ውስጥ አንድ ድንጋይ የአሕዛብን ምስል እግሩ ላይ በመታው ጊዜ ያ ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሲሆን ነው ያየው። ያ ተራራ ከአርማጌዶን በኋላ የሚመጣውን የ1,000 ዓመት ሰላም ነው የሚወክለው። የዚያን ጊዜ ሰማይ በምድር ላይ የሚገለጥበት የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። ያ ነው የመጀመሪያው እውነተኛና መልካም የሆነ መንግስት። ስለዚህ ኢየሱስ እነዚህን ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች ትቶ ሄደ። የሆሳዕና እለት የዘመሩለት ሰዎች እራሳቸው ተመልሰው በቀጣዩ አርብ እለት ይሰቀል ብለው መጮሃቸው እንደማይቀር አውቋል። የሰው አድናቆትና ምስጋና ይህን ያህል ነው።
ኢየሱስ በውስጡ ከሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ሕብረት ማድረግ ሲፈልግ፣ ምሪትን መቀበል ሲፈልግ ከሰዎች እና ከሰዎች አመለካከት ተለይቶ ይሄድ ነበር። ኢየሱስ በሰዎች አድናቆት መደሰትና በሰዎች ፍላጎትና እቅድ መመራት ሞኝነት መሆኑን ያውቃል።
እውነተኛ ምሪት የምናገኘው በውስጣችን ከሚኖረው ከእግዚአብሔር እንጂ በዙርያችን ከሚኖሩ ሰዎች አይደለም።
ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
ብቻችንን ስንቀመጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እግዚአብሔር በውስጣችን ሲኖር ከእግዚአብሔር ምሪት ማግኘት እንችላለን። በግላችን ከእግዚአብሔር ምሪት ካላገኘን በሰዎች እና በቤተክርስቲያን ግፊት እየተገዛን እንኖራለን።
ዮሐንስ 6፡16 በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፥
የምሽት ሰዓት ቤተክርስቲያን በዘመን መጨረሻ የምትገኝበትን ሁኔታ ያመለክታል። በመጨረሻው በሎዶቅያውያን ዘመን ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ቆሞ ነው የሚገኘው። በዚህ ሰዓት ደቀመዛሙርቱም ከኢየሱስ ተለይተዋል።
በቡድን ተሰብስበው ውሳኔ አደረጉ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ከእነርሱ ጋር አለመሆኑን ልብ አላሉም።
ዮሐንስ 6፡17 በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። አሁንም ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤
ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ ፊታቸውን ወደ ቅፍርናሆም አደረጉ። ያም ከተማ ኢየሱስ ታላላቅ ተዓምራት ያደረገበት ቦታ ነበር።
ጨልሞ ነበር፤ እነርሱ ግን በጨለማው የዓለም ብርሃን የሆነው ኢየሱስ አብሯቸው ሳይኖር ተነስተው ሄዱ።
ይህም ድርጊታቸው የመጨረሻው ዘመን ውስጥ ያለችዋን የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን ውጭ ሳለ እነርሱ መሄድ ወደሌለባቸው አቅጣጫ ይሄዳሉ።
ደቀመዛሙርቱ በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ናቸው። ነፋስ ግጭት እና ጦርነትን ነው የሚወክለው። በዘመናችን ጦርነቶች፣ ስደተኛች፣ ሽብርተኝነት፣ እና በቦምብ የፈራረሱ ከተሞች እናያለን። ሌላ ደግሞ የንግድ ጦርነቶችም አሉ። እነዚህም ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋትን ያስከትላሉ።
የለውጥ ነፋስ በምድር ላይ ይነፍሳል። የማስጠንቀቂያው መለከት ድምጹ ይሰማል።
ዮሐንስ 6፡18 ብርቱ ነፋስም ስለ ነፈሰ ባሕሩ ተናወጠ።
ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስን የታላቁ እግዚአብሔርን ምልከታ ይሰጠናል። ነፋሱ ተቃወማቸው አይለንም። ለመቅዘፍ ይታገሉ ነበር አይለንም። እነዚህ ሁሉ ስጋዊ አካላዊ ነገሮች ናቸው።
መሄድ ወደሌለባቸው አቅጣጫ መንገድ ጀምረው ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከመንገዳቸው ሊመልሳቸውና ወደ ራሱ መንገድ ሊያመጣቸው ታላቅ ነፋስ ላከባቸው።
በሕይወታችን ውስጥ በልዩ ልዩ ችግሮች የምናልፍበት ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የእኛን ሃሳብ ከአእምሮዋችን እያስወጣ ወደ ራሱ አቅጣጫ ይመራናል።
በዚህ ዓለም ውስጥ የሚሆነውን ነውጥ ሁሉ በምናይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኛን ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን እምነት በመመለስ ላይ ትኩረት እንድናደርግ መፈለጉን መረዳት አለብን።
ተክሎች በጥራት የሚያድጉት ሲገረዙ ሲከረከሙ ነው።
ሁላችንም መከርከም ያስፈልገናል። ነገር ግን መከርከም ያሳምማል።
ዮሐንስ 6፡19 ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።
በአንድ ማይል ውስጥ ስምንት ምዕራሶች አሉ። ስለዚህ ከውሃው ዳር ሶስት ወይም አራት ማይል ርቀው ወደ ውስጥ ሄደዋል። ሶስት ከግማሽ ማይል ማለት እንችላለን። የገሊላ ባሕር ስፋቱ 7 ማይል ነው። ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ በባሕሩ መሃል ነበሩ ማለት ነው። በዚህ ሰዓት ከምድር እና ከሰው እርዳታ በጣም ርቀዋል። ቢቀዝፉ፤ ቢቀዝፉ መሄድ ወደፈለጉበት ወደ ቅፍርናሆም ሊደርሱ አልቻሉም፤ ምክንያቱም ነፋሱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እየገፋቸው ነበረ።
እንደ ሰው የሚያደርጉት ጥረት የትም እያደረሳቸው አልነበረም። ያሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮአቸው ነበር።
ነፋሱ ተስፋ እንዲቆርጡ ነበር የተላከባቸው። በራሳቸው ተስፋ የቆረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ እንዳለባቸው ያውቃሉ።
በራሳቸው ኑሮ የረኩ እና ግዴለሽ የሆኑ ሰዎች ግን እግዚአብሔርን እንደሚፈልጉ ያስመስላሉ።
የሎዶቅያውያን ቤተክርስቲያን ሃብታም ናት፤ ገንዘብ ሞልቷታል፤ ስለዚህ ምንም ነገር አያስፈልጋትም፤ እርማት እንኳ አያስፈልጋትም። የመጨረሻው ዘመን አማኞች ወደ ፍጻሜያቸው የደረሱ ይመስላቸዋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማናወጥ የነውጥ ነፋስ ይልክባቸዋል።
በችግሮቻቸው ሁሉ መካከል የሰው እርዳታ ማግኘት በማይችሉበት ርቀት ላይ ሳሉ ኢየሱስ ሊፈልጋቸው መጣ።
ዮሐንስ 6፡20 እርሱ ግን፦ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው።
ችግራቸውን የሚፈታላቸው የእርሱ መገኘት ነው።
መፍትሄ ከፈለጉ ማድረግ ያለባቸው እርሱን ወደ መርከባቸው ውስጥ ማስገባት ብቻ ነበር።
በሕይወታችን የሚገጥሙን ችግሮች የቃሉን ሙላት ወደ ልባችን ውስጥ እንድናስገባ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው።
ነገር ግን እርሱን ራሱን ፈልገነው በፈቃደኝነት መቀበል አለብን እንጂ ሌላ ጥቅም ፍለጋ መሆን የለበትም። የሆነ የግል ጥቅም እናተርፋለን በሚል ተስፋ አይደለም። እርሱን የምናገለግለው እንደ ፈቃዱ እንጂ እንደ ራሳችን ፈቃድ ወይም እንደ ቤተክርስቲያን ፈቃድ አይደለም።
ዮሐንስ 6፡21 ስለዚህ በታንኳይቱ ሊቀበሉት ወደዱ፤ ወዲያውም ታንኳይቱ ወደሚሄዱበት ምድር ደረሰች።
ይህ ቃል ዮሐንስ ኢየሱስን በዙፋኑ ዙርያ ካሉት ሕያዋን ፍጥረታት እንደ አራተኛው እንደሚበርረው ንስር አድርጎ ሊያሳየን የሞከረበት ቃል ነው። ይህም ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያሳየናል።
እንደ ንስር ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን በአየር ላይ ሊያገኛት ይመጣል።
በድንገት ሁሉም ነገር ያበቃል። የሆነ ነገር እንደጎደለ ይመስል ጭር የሚል ጊዜ ይመጣል። ሙሽራይቱ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ አታልፍም።
ሰባት ማይል ስፋት ያለው ባሕር መሃል ላይ ነበሩ። ስለዚህ ወደ ምድር ለመድረስ ሶስት ማይል ከግማሽ ርቀት ይቀራቸዋል። ሶስት ማይል ከግማሽ ግን የሌለ ይመስል ከዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል።
ይህ ምን ያሳየናል? ይህ የሚያሳየን በሰው ልጅ የምድር ኑሮ ውስጥ እጅግ ከባድ የሆነውን ወቅት የሶስት ዓመት ከግማሽ ጊዜ የሚፈጀውን የታላቁን መከራ ጊዜ ነው የሚያሳየን።
የጌታ ዳግም ምጻት ቤተክርስቲያንን ከዚህ ምድር ነጥቆ በሰማይ ወደተዘጋጀው የሰርግ ግብዣ ይወስዳታል።
ለአርማጌዶን እና በአዲሱ መንግስት ውስጥ ለሚሆነው የ1,000 ሰላም ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት የሶስት ዓመት ተኩል ክፍተት አለ።
ማርቆስ ወደ ጌንሰሬጥ ደረሱ ብሎ ይነግረናል።
ማርቆስ 6፡53 ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ።
“ተሻገሩ” ይላል። “መሻገር” ምን ማለት ነው?
ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን ከማብላቱ በፊት ጊዜው የፋሲካ በዓል እንደነበረ ዮሐንስ ጠቅሷል። ፋሲካ ማለት ተሻገረ አለፈ ማለት ስለሆነ “ተሻገሩ” የሚለው ቃል በጣም አስፈላጊ ነው።
ዮሐንስ 6፡4 የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።
ፋሲካ ላይ የተደረገው ትኩረት ድርብ ትርጉም አለው።
ኢየሱስ የፋሲካ በግ ሆኖ ስለተሰዋልን ለሐጥያታችን ስለሞተልን ሲኦል መሄድ ትተን “ተሻግረን ማለፍ” ችለናል። ይህም መዳን ይባላል። ይህ የተፈጸመው በቤተክርስቲያን ዘመናት መጀመሪያ ላይ ነው። ኢየሱስ በዘመናቱ መጀመሪያ ላይ ዋጋ ከፈለ፤ ስለዚህ ኢየሱስ አልፋ ተብሎ ይጠራል።
በቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ደግሞ ኢየሱስ ኦሜጋ ይሆንልናል፤ ምክንያቱም ታላቁ መከራ ውስጥ እንዳንገባ ወደ ሰርጉ ግብዣ “አሻግሮ” ያድነናል። ይህም ወደ ሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ተሃድሶ የሚያስገባን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
ጌንሰሬጥ ማለት የሃብት አትክልት ስፍራ ነው። ኢየሱስ መርከባቸው ውስጥ ስለገባ የሰማይን ሃብት በሙሉ ይወርሳሉ። በዘመን መጨረሻ የሚመጣው ኃይለኛ የግጭትና ጦርነት ነፋስ በሙላት የመጣልንን የእግዚአብሔር ቃል እንድናምን ሊያደርገን ነው የሚመጣው፤ ምክንያቱም ቃሉን ማመን ብቻ ነው ጌታ ሲመጣ እንድንቀበለው የሚያዘጋጀን። ሌት ተቀን ልንሮጥለት የሚገባን እውነተኛ ሃብት የእግዚአብሔር ቃል ሙላት ነው።
ዮሐንስ 6፡22 በነገው በባሕር ማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝቡ ከአንዲት ጀልባ በቀር በዚያ ሌላ ጀልባ እንዳልነበረች፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው እንደ ሄዱ እንጂ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ እንዳልገባ አዩ፤
እንጀራ በልተው የጠገቡት ሕዝብ አሁን ደግሞ እንደገና እንጀራ በነጻ ለመብላት ፈልገው ወደ ማዶ ተሸገሩ። እነርሱም ደቀመዛሙርቱ የተሻገሩበትን መርከብ ብቻ ነበር ያዩት። ደቀመዛሙርቱ መርከቡ ውስጥ ገብተው መሄድ ሲጀምሩ ኢየሱስ አብሯቸው እንዳልገባ ሕዝቡ አውቀዋል። ስለዚህ ኢየሱስ የት እንደነበረ አላወቁም።
የመለኮታዊ ተዓምራትን ጥቅም ሲያሳድዱ ኢየሱስ የት እነዳለ ጠፋባቸው።
ዮሐንስ 6፡23 ዳሩ ግን ሌሎች ጀልባዎች ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በሉበት ስፍራ አጠገብ ከጥብርያዶስ መጡ።
ምግብ በነጻ መብላት ጥሟቸው ስለነበረ በመርከብ ኢየሱስ ምግብ ባርኮ ካበዛበት ከጥብርያዶስ ተነስተው የገሊላ ባሕርን አቋረጡ። ኢየሱስ ግን በዚያ አልነበረም። ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ተዓምር በረከትን የተቀበሉ ሰዎች ለቃሉ ያላቸው ፍላጎት የአጭር ጊዜ ብቻ ነው። ፍላጎት የሚኖራቸው በረከትን እስከተቀበሉ ጊዜ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡24 ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ ራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ።
ቀጥለውም በቅፍርናሆም ውስጥ እየፈለጉት ነበር።
ዮሐንስ 6፡25 በባሕር ማዶም ሲያገኙት፦ መምህር ሆይ፥ ወደዚህ መቼ መጣህ? አሉት።
በጣም ተገርመዋል፤ ምክንያቱም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ መርከብ ውስጥ አልገባም ነበር፤ ነገር ግን ባሕሩን ተሻግሮ ቅፍርናሆም ውስጥ ሊገኝ ችሏል።
ዮሐንስ 6፡26 ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።
ኢየሱስን ይፈልጉ የነበረበት ምክንያት ጥሩ ምክንያት አልነበረም። እንደገና ምግብ በነጻ ለመብላት ብለው ነበር የሚፈልጉት። እኛ ሰዎች ሁልጊዜም ለትርፍ እንንገበገባለን።
ዮሐንስ 6፡27 ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።
ዓለማዊ ነገሮች ዘለቄታ ስለሌላቸው በእነርሱ ላይ መደገፍ የለብንም። ትኩረታችን መንፈሳዊ ነገሮች ላይ ነው መሆን ያለበት። የዘላለም ሕይወት በክርስቶስ ውስጥ ነው ያለው። መንፈስ ቅዱስ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው፤ እኛም ደግሞ ከእርሱ ለመቀበል መፈለግ ያለብን መንፈስ ቅዱስን ነው። ነፍሳችንን ወደ መንግስተ ሰማይ መውሰድ የሚችለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ይገለጡ ዘንድ በሰባት ማሕተም የታተመውን የቤዛነትን መጽሐፍ መፍታት የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡28 እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት።
አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ምን እንዲሰሩ እንደሚፈልግባቸው ለማወቅ ጓግተዋል። በራሳቸው ስራ መዳን ይችሉ ዘንድ ሐይማኖታዊ የስራ ዝርዝር እንዲሰጣቸው ነው የፈለጉት።
ዮሐንስ 6፡29 ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።
መዳን የሚገኘው ግን በስራ ሳይሆን በእምነት ነው። የሚያስፈልጋቸው በማን ማመን እንዳለባቸው ማወቅ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር የሚቀበለው አንድ ስራ ብቻ ነው፤ እርሱም በቃሉ በኢየሱስ ማመን ነው። ሳይንቲስቶች ቢግ ባንግ ቲዎሪ እና ኤቮልዩሽን ቲዎሪያቸውን ይዘው መምጣት ይችላሉ፤ የእግዚአብሔርን ስራ መስራት ከፈለጋችሁ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ማመን አለባችሁ፤ ደግሞም ለሳይንሳዊ ቲዎሪ ብላችሁ የመጽሐፍ ቅዱስን እምነት መጣል የለባችሁም።
ዓለማችን ስትፈጠር ከመጀመሪያው ያያት አንድም ሰው የለም። ስለዚህ ሳይንቲስቶች ስለ ዓለም አፈጣጠር እና ስለ ሕይወት አጀማመር የሚናገሩት በሙሉ ግምት ብቻ ነው። ግምት ብቻ ነው ያላቸው እንጂ አንዳችም የሚያሳዩት ማስረጃ የላቸውም። ያለ ማስረጃ በግምት ብቻ መናገር ደግሞ ጥሩ ሳይንስ አይደለም።
በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ እግዚአብሔር ጠፍተው የነበሩ እውነቶችን ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ የተለያዩ ሰዎችን ተጠቅሟል። እግዚአብሔር ቃሉን ለመፈጸም የተጠቀመውን ሰው እውቅና ስንሰጠው እግዚአብሔርን እናገለግላለን። እግዚአብሔር እኛ የማንወደውን ሰው ሊጠቀም ይችላል። እንደዚያ ከሆነ እግዚአብሔር ቃሉን ለመፈጸም የመረጠውን ሰው ስንቃወም እንዳንገኝ አሳባችንን መለወጥ አለብን።
የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል መፈጸም ትክክለኛው የእግዚአብሔር ስራ ነው።
ዮሐንስ 6፡30 እንግዲህ፦ እንኪያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?
ምልክት የመፈለግ ችግር ይህ ነው።
ይህ በምልክቶች ላይ የመደገፍ ድክመት ነው።
ልባችሁ ከመለወጡ በፊት ስንት ተዓምራት ማየት ያስፈልጋችኋል?
አንድ ትንሽ ልጅ ከያዘው ጥቂት እንጀራ 5,000 ሰዎች ጠግበው ሲበሉ አይተዋል። ኢየሱስ በሌሊት ያለ መርከብ ነፋስ የሚያናውጠውን ባሕር ተሻግሮ ሲመጣ አይተዋል።
ይህን ሁሉ አይተው ግን አሁንም ምልክት ይጠይቃሉ።
እየፈለጉ የነበረው ዓይናቸውን የሚያስደንቅ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ድንቅ እና ምልክት እነርሱ በጠየቁ ሰዓት እንዲደረግላቸውና አይተው ለመዝናናት ነው።
አሳየን ብለው ከመጠየቃቸው በፊት ቅፍርናሆም ውስጥ ያደረጋቸውን ታላላቅ ተዓምራት ረስተዋል።
ማቴዎስ 11፡23 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
ዮሐንስ 6፡31 ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ አሉት።
ከዚያ በኋላ ደግሞ እስራኤል ከግብጽ ያወጣና በምድረበዳ ከሰማይ መና ያበላቸውን ታላቁ ነብያቸውን ሙሴን ጠቀሱለት። ይህ ተዓምር ነው አሉ። በዚያ ዘመን ቢኖሩ ኖሮ ያለጥርጥር ሙሴን ይከተሉት ነበር።
ዮሐንስ 6፡32 ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤
ኢየሱስ ግን ሙሴ መናውን እንዳላዘጋጀ ነገራቸው። እግዚአብሔር ነው መናውን የሰጣቸው። ስለዚህ ኢየሱስ በፊቸው ያደረገው ተዓምር ሙሴ ከሰራው ስራ በጣም የሚበልጥ ነው። ምክንያቱም ሰዎቹ የበሉትን የተጋገረ እንጀራ እና የበሰለ ዓሳ ኢየሱስ ነው የፈጠረው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ልኮት የመጣው ኢየሱስ እውነተኛው እንጀራ አለው፤ እርሱም ነፍስን የሚያጠግብ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ዮሐንስ 6፡33 የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው።
አንድ እንጀራ ለጥቂት ሰዎች ብቻ ፍጥረታዊ ሕይወትን ያካፍላቸዋል። ፍጥረታዊ እንጀራ በራሳቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ያደርጋቸዋል። ጊዜያዊ በሆነው ምግብ ይደሰታሉ። ኢየሱስ ግን ለሁላቸው ዘላለማዊ ሕይወትን ያቀርባል። የዘላለም ሕይወት ለጥቂቶች ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ይዳረሳል። ስለዚህ ዘላለማዊ ሕይወት ትኩረታችንን በራሳችን ሳየሆን በሌሎች ላይ እንድናደርግ ይረዳናል።
ዮሐንስ 6፡34 ስለዚህ፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት።
ሕዝቡ ይህንን እንጀራ ፈለጉ። ልክ እንደ ፍጥረታዊ እንጀራ የሚጎርሱት ነገር መሰላቸው፤ ከጎረስነውም በኋላ ሁለተኛ አይርበንም ብለው አሰቡ።
ዮሐንስ 6፡35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።
የሕይወት እንጀራ ሆኖ የተወለደው ኢየሱስ ሲወለድ በግርግም ውስጥ ነው የተኛው፤ የተኛበትም ግርግም የዳቦ መጋገሪያ ቅርጽ ያለው ነበረ። ሔሮድስ ሊገድለው ፈለገ፤ ይህም የሕይወትን እንጀራ ለመጋገር የሚያስፈልገውን የእሳት ሙቀት ያመለክታል። በስተመጨረሻ ወታደሮች ምራቃቸውን ተፉበት ምክንያቱም እንጀራ አፋችን ውስጥ በምራቅ ሳይለሰልስና ሳይጠቀለል ሊዋጥ አይችልም።
እርሱ በእውነት የሕይወት እንጀራ ነው።
በሰማይ ረሃብም ሆነ ጥማት አይኖርም።
አንዴ መጽሐፍ ቅዱስን ካመናችሁ በኋላ ነፍሳችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እምነት አይናፍቃትም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የመጣ ሃሳብ ሁሉ ለናንተ ጣዕም አይኖረውም። ሁልጊዜ ነፍሳችሁን የሚያረካ ምግብ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
መጽሐፍ ቅዱስን የምትረዱበት የመገለጥ መነቃቃት ወደ ውስጣችሁ ሲመጣ ለአልኮል መጠጥ የነበራችሁ ፍላጎት ሳይቀር ይጠፋል።
ዮሐንስ 6፡36 ነገር ግን አይታችሁኝ እንዳላመናችሁ አልኋችሁ።
ለተጠራጣሪ ሰው ተዓምራት ማየትም እንኳ ምንም አይጠቅመውም። ኢየሱስን ቢያይ እንኳ ምንም አይጠቅመውም። አንድ ሰው ለማመን ካልፈለገ ምንም ቢደረግለት ሃሳቡን ወይም አቋሙን አይለውጥም። ለማያምን ሰው እግዚአብሔር ምንም ዓይነት ማስረጃ ቢያሳየው የሰውየው ነጻ ፈቃድ ማመን ያልፈለገውን የቀረበለትን ማስረጃ ሁሉ አሳማኝ እንዳልሆነ ቆጥሮ ትቶ ያልፈዋል።
ዮሐንስ 6፡37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤
እግዚአብሔር ሰዎች ከውስጣቸው ነው የሚስባቸው። እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ቃሉ ማለትም ወደ ኢየሱስ ይስባቸዋል። ወደ ኢየሱስ የሚመጣ ሰው ሁሉ መስቀሉ ላይ እየሞተ የነበረው ሰውም እንኳ ቢሆን ኢየሱስ ወደ ውጭ አይጥለውም።
ዮሐንስ 6፡38 ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።
የራሳችንን ፈቃድ በምንፈጽም ጊዜ እግዚአብሔርን ማገልገል አንችልም።
ኢሳይያስ 55፡8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔር መንገዶች እኛ ማሰብ ከምንችለው ነገር ሁሉ በላይ ናቸው። ስለዚህ በሰውኛ ብርታትና ጥበብ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜ ብክነት ብቻ ናቸው።
ዘካርያስ 4፡6 መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ለራሳችን እና ለፈቃዳችን መሞት አለብን - በዚህ መንገድ ብቻ ነው ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሕያው የምንሆነው።
ዮሐንስ 6፡39 ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው።
እግዚአብሔርን መታመን አለብን። እግዚአብሔር ከልጆቹ መካከል አንዳቸውንም እንኳ አያጣም። ከሞትን በኋላ እግዚአብሔር በትንሳኤ እንደገና ሕይወትን ሊሰጠን ከቻለ፤ ለራሳችን ፈቃድ ብንሞት ያለ ጥርጥር እርሱ የሚፈልግብንን ዓይነት ሕይወት የመኖር ፍላጎትን ይሰጠናል።
ዮሐንስ 6፡40 ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር በስጋ ነው። እግዚአብሔር በዓይን የሚታይ ሆኖ መምጣቱ ነው። ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን፤ እግዚአብሔር እንደ እኛው ሰው ሆኖ መመላለሱን ብናምን፤ እግዚአብሔር በውስጡ የተሰወረበትን የሰው ስጋ መጋረጃ አይተናል ማለት ነው።
በዓይን የሚታየው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን አብ ግን በውስጡ የሚኖረው የማይታየው መንፈስ ነው።
በአንድ እንጀራ ውስጥ የማይታይ ሕይወት እንዳለ ማለት ነው። ሕይወቱን የምንካፈለው ግን እንጀራው ወደ እኛ ውስጥ ሲገባ እና የእኛ አካል ሲሆን ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡41 እንግዲህ አይሁድ፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና፦
አይሁዳውያን ከፍጥረታዊው ባሻገር ማየት አልቻሉም። የሕይወት እንጀራ ሲባል ከግብጽ በወጡ ጊዜ ከሰማይ እንደወረደላቸው መና የሕይወት እንጀራም የሚታይ እንጀራ ሆኖ የሚወርድላቸው መስሏቸዋል። ምንም መንፈሳዊ እይታ አልበራቸውም። እንጀራ የእግዚአብሔር ቃል ተምሳሌት መሆኑን አላወቁም።
ሰዎች ዘፍጥረት ውስጥ አዳም እና ሔዋን የዛፍ ፍሬ በሉ የሚለውን ሲነብቡ እንደ ማንጎ ወይም ብርትኳን የመሰለ የፍጥረታዊ ዛፍ ፍሬ የበሉ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ሁለቱም ተመሳሳይ ሐጥያት ቢሰሩም እንኳ ለምንድነው የተለያየ ቅጣት የተቀጡት ተብለው ቢጠየቁ መመለስ አይችሉም። እግዚአብሔር ሔዋንን ጽንሷን በማብዛት ቀጣት። ጽንስ ካላት እርጉዝ ነበረች ማለት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ሐጥያት የዛፍ ፍሬ ከመብላትም ያለፈ ጠለቅ ያለ ጉዳይ ነው። አንድ የዛፍ ፍሬ ስለ በላች ልጅ በመውለድ ተቀጣች ሲባል እግዚአብሔርን የማያምኑ ሰዎች መጠራጠራቸው አያስደንቅም። ልጅ መውለድ አዳም ሊካፈልበት የማይችለው ሐጥያት ነው፤ ነገር ግን እርሱም ያንኑ ፍሬ በልቷል።
ስለዚህ ልክ ኢየሱስ በምድር በነበረበት ዘመን እንደሆነው ሁሉ ዛሬም ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራዊ አነጋገሮች መረዳት አይችሉም።
ዮሐንስ 6፡42 አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ፦ ከሰማይ ወርጃለሁ እንዴት ይላል? አሉ።
አሁን ደግሚ ኢየሱስን በፍጥረታዊ ዓይናቸው ተመለከቱት። ማርያምን እና ዮሴፍን ያውቋቸዋል፤ ስለዚህ እነርሱ የኢየሱስ ወላጆች እንደሆኑ አስበዋል። ነገር ግን ጠለቅ ብለው አልተመለከቱም፤ ከሃሳባቸው ጋር አብሮ የማይሄዱ ማስረጃዎችንም እንዳላዩ ሆነው አልፈዋል። ማርያም በጸነሰች ጊዜ ወደ ዘመዷ ወደ ኤልሳቤጥ ሄዳ ሶስት ወር ቆይታለች፤ ከዚያ በኋላ ነው ዮሴፍን ለማግባት የተመለሰችው። ይህም የዘመኑ ሞቅ ያለ ሐሜት ነበረ። ዮሴፍን ለማግባት ስትመለስ እርጉዝ ነበረችና ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑ ግልጽ ነበር፤ በተለይም ደግሞ ሰርጋቸው ከተደገሰ በስድስት ወር ውስጥ ኢየሱስ መወለዱ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አለመሆኑን ያሳብቃል።
በጥልቀት ለማሰብ ዝግጁ ካልሆናችሁ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ሁልጊዜ እውነቱን የሚቃረን ላይ ላዩን የሆነ መልስ ታገኛላችሁ።
ሳይንቲስቶስ አተሞች ሁሉ ጠጣር አካላት እንደሆኑ አድርገው ያስቡ እንደነበር ማለት ነው፤ እንደዚያ ያሰቡትም በዙርያችን ያሉ ጠጣር ነገሮች በሙሉ ከአተሞች ስተሰሩ ነበር። ነገር ግን ያ ሁሉ ስለ አተም የተሳሳተ አስተሳሰብ ነበረ።
ዮሐንስ 6፡43 ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ።
ሰዎች ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች በተፈጠሮዋቸው እግዚአብሔር መኖሩን አያምኑም። የእግዚአብሔር ቃል ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ትርጉም ሲኖረው ሰዎች በተፈጥሮዋቸው ሊከራከሩት የመነሳት ዝንባሌ አላቸው። ሰዎች ፍጥረታዊውን ዓለም ያዩና እግዚአብሔር የለም ይላሉ፤ ምክንያቱም ፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ እግዚአብሔርን ማየት አይችሉም።
አድማስ የፍጥረታዊ ዓይናች የማየት ችሎታ ወሰን መሆኑን ስናስብ ፍጥረታዊ አስተሳሰባችንም እንደዚሁ ውስን መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል። በየዕለቱ ጸሃይዋ ሰማዩ ላይ የምትሄድ ይመስለን ነበር፤ ቆይተን ግን ስናጣራ ምድር እራሷ ናት በዛቢያዋ ላይ የምትሽከረከረው። ግን ምድር ስትሽረከር እንቅስቃሴዋ አይሰማንም፤ ደግሞም አይታየንም። ከዚህም የተነሳ የምንማረው ነገር በዓይናችን የምናየውን ወይም በስሜታችን የሚሰማንን ማመን እንደማንችል ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁለት የስሜት ሕዋሳት ሁልጊዜ እውነትን አይነግሩንም። መሬት ላይ ስትቆሙ ምድር ምንም እንደማትንቀሳቀስ እርግጠኛ ናችሁ ምክንያቱም ምድር ስንትቀሳቀስ አይሰማችሁም።
ከቆማችሁበት ቦታ መኪና ተነስቶ ሲሄድ እናንተ ባላችሁበት መቆማችሁን እርግጠኛ ናችሁ። መኪና ውስጥ ስትቀመጡ እናንተ የትም ሳትንቀሳቀሱ ከመኪናው ውጭ ያለ ነገር ሁሉ በድንገት ወደ እናንተ ይሮጣል። ስለዚህ በፍጥረታዊ ዓይናችሁ አማካኝነት እውነቱን ማወቅ አትችሉም። ከዚህም ይልቅ ጠለቅ ያለ እውነታ ማየት ያስፈልጋችኋል።
እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች ከፍጥረታዊ እይታ ተነስተው ነው እግዚአብሔር የለም ብለው የሚከራከሩት። ሊያዩት አይችሉም። በዓይን የሚታዩ ቁሳቁስ ወይም ግኡዝ ነገሮች የአተሞችን ትክክለኛ ባህርይም ሆነ የእግዚአብሔርን እውነተኛ ባህርይ ሊገልጡልን አይችሉም። አተሞችን ወይም እግዚአብሔርን እንዲሁም ባሕር ላይ ያሉትን ማዕበሎች ማወቅ ከፈለግን ጠለቅ አድርገን ማሰብ አለብን።
ኃይለኛ ማዕበል ባለበት ሰዓት ውሃው ከባሕሩ ወደ የብስ እየፈሰሰ ይመስላል ግን አይደለም። የጨረቃ የስበት ኃይል ከባሕሩ ላይ ውሃውን ወደ ላይ እየተነሳ እነዲቆለል ያደርገዋል። ከዚያ ምድር ስትዞር የብሱ ወደዚህ የውሃ ክምር ውስጥ ይገባል። ስለዚህ ዓይናችሁ ከሚያየውና አእምሮዋችሁ ከሚያስበው ተቃራኒ ነው እውነታው። ከፍተኛ ማዕበል የሚፈጠረው መሬቱ ወደ ውሃው ክምር ውስጥ ሲገባ ነው።
በፍጥረታዊው ዓለም ውስጥ ሲሆን አየን በምንለው ነገር ሁሉ በቀላሉ እንታለላለን።
በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ በሚከናወነው ነገርማ ይበልጡን ነው የምንታለለው።
ዮሐንስ 6፡44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
የመሬት ስበት ሁላችንንም ወደ ምድር የሚስብ ኃይል ነው፤ ግን ምን እንደሆነ በትክክል የሚያውቅ ሰው የለም። መግፋት ቀላል ነው፤ መሳብ ግን ቀላል አይደለም። ጣቶቻችሁን ዘርግታሁ እጃችሁን በበር ላይ ብትጭኑ በቀላሉ ትገፉትና ትዘጉታላችሁ።
ነገር ግን ጣቶቻችሁን ዘርጉና በር ላይ ጭናችሁት ሳቡት ወይም ጎትቱት። በር ለመሳብ እጀታ መያዝ ያስፈልጋችኋል። እጃችሁ በእጀታ ላይ ሲሆን ጣቶቻችሁ ከእጀታ በስተኋላ ያልፉና እጀታውን ወደናንተ ይገፉታል።
ስለዚህ አንድን ነገር ለመጎተት በጣቶቻችሁ መያዝ ያስፈልጋችኋል፤ ከዚያም ነገሩን ወደ ራሳችሁ ስትጎትቱት ወደ እናንተ በኩል የሚታጠፍ ክንድ ያስፈልጋችኋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህንን ሁሉ ስራ የሚቆጣጠር አንጎል ያስፈልጋችኋል።
ምድር አንጎል የላትም፤ የሚታጠፍ ክንድ የላትም፤ ደግሞም አንድ ነገርንም እንኳ የምትይዝበት ጣቶች የሏትም። ታዲያ ምድር ወደ ራሷ የምትጎትተን እንዴት አድርጋ ነው? ምንም አናውቀም።
የመሬት ስበት ሚስጥራዊ ኃይል ነው። የምድር ስበት ወደ ምድር እንዲስበን የሚያደርገው ኃይል ምንድነው? ሳይንቲስቶች የስበት ኃይል እንዴት እንደሚሰራ አያውቁም።
በመንፈሳዊው ዓለምም እንደዚሁ ነው። እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ወደ ራሱ እንደሚስበን የምናውቀው ነገር የለም፤ ደግሞም እንዴት አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስን እንድናምን እንዳደረገን፤ ለመረዳት ከባድ የሆኑትን ክፍሎች ሁሉ ሳይቀር እንዴት እንድናምን እንዳደረገን አናውቅም።
ኢየሱስ ቃሉ ነው። ዳግመኛ የተወለደ ክርስቲያን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ይሳባል፤ ከዚያም በላይ መጽሐፍ ቅዱስን ያምነዋል፤ ለመረደት ቢከብድም እንኳ ይወደዋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ሳበን እና ዓይናችንን ስለከፈተልን ነው መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበውና የምናምነው።
እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ነው የሚስበን? ልክ እንደ መሬት ስበት እግዚአብሔርም እንዴት አድርጎ እንደሚስበን አናውቅም።
የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ አንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ሲገባ ያ ሰው ይለወጣል፤ ሐጥያተኛ የነበረው ሰው ቅዱስ ሰው ይሆናል። እግዚአብሔር የለም የሚለው ሰውዬ አማኝ ይሆናል።
ማድረግ ያለብን ነገር ንሰሃ መግባት እና ኢየሱስን ወደ ሕይወታችን ውስጥ መቀበል ነው። ካለንበት አለማመን እና መንፈሳዊ ሞት ሊያስነሳን የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። በስተመጨረሻም በትንሳኤው ከሞት ወደ ሕይወት ሊያስነሳን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።
ነብያት ቃሉን ጻፉልን። እኛ የምንማረው ከተጻፈው ቃል ነው። እግዚአብሔር የማይታየው ሚስጥራዊው ሳቢ ነው። እኛ መረዳትና ማስተዋል በማንችለው መንገድ ወደ ራሱ ይስበናል። ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ በተማርን ቁጥር ይበልጥ ወደ ኢየሱስ ስንጠጋ ራሳችንን እናገኛለን።
ኢየሱስን የምንወደው የእግዚአብሔርን ቃል የምንወድድ እና የምንታዘዝ ከሆነ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 14፡15 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።
ኢየሱስን መውደድ በውስጣችን እርሱን የመውደድ ስሜት አይደለም። እርሱን መውደድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በሙሉ የማመን ፍላጎት እና ችሎታ ነው። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን መታዘዝ አለብን።
ዮሐንስ 6፡46 አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።
ምድር ላይ አጣብቆ የያዘን የምድር ስበት ኃይል በዓይን አይታይም። እግዚአብሔርንም ማንም አላየውም። እግዚአብሔርን ያየው ብቸኛው ሰው ኢየሱስ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር በስጋ መገለጥ ነው።
ስለዚህ በኢየሱስ ውስጥ የሚኖረው እግዚአብሔር ሲስበን ወደ ቃሉ ወደ ኢየሱስ እንጠጋለን። ወደ ቃሉ ስንጠጋ መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ እንወደዋለን፤ በደምብ እንታዘዘዋለን። በምንወደው ሰው ውስጥ እንከን ማየት አይሆንልንም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚወድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሕተቶችና የሚጋጩ ሃሳቦች አሉ የሚለውን ሃሳብ አይቀበልም። ጠለቅ ያሉ መንፈሳዊ እውነቶችን ለማየት አብዝተን መትጋት አለብን።
ዮሐንስ 6፡47 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።
የዘላለም ሕይወትን የምናገኝበት ብቸኛው ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል በሙሉ ማመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ለማመን ሁልጊዜ መታገል አለብን፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ እውነት መሆኑን ማመን አለብን። በኢየሱስ እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልፎ አልፎ አንዳንድ ነጥቦችን የማትቀበሉ ከሆናችሁ ከኢየሱስም አንዳንድ ነገር አትቀበሉም። ይህ ጥበብ አይደለም።
ዮሐንስ 6፡48 የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።
ወዳጃችሁ የሆነ ሰው እንጀራ አብሯችሁ ይቆርሳል።
መጽሐፍ ቅዱስን የሚመክረን፤ የሚገስጸን፣ የሚመራን፤ የሚያበረታን የዘወትን ወዳጃችን ማድረግ አለብን።
በመንፈሳዊ ቋንቋ እንጀራ መቁረስ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቶ አንድን ሐሳብ ስናጠና መጽሐፍ ቅዱስ እራሱን በራሱ እንፈታልን እንዲተረጉምልን መፍቀድ ነው።
ዮሐንስ 6፡49 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤
እግዚአብሔር አይሁዳውያንን በሚታይ ነገር ባረካቸው፤ ከሰማይ ላይ እንጀራ አወረደላቸው። ይህ ድንቅ ተዓምር ነው። ግን ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ ሞቱ። እግዚአብሔር በፍጥረታዊ ነገር ሲባርከን ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም እየኖርን ነው ማለት ላይሆንም ይችላል።
ዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ ስናነብ አይሁዳውያን ታላላቅ ተዓምራት እንደተደረገላቸው እናያለን፤ ነገር ግን እምነት ሊሆናቸው አልቻለም። ያን ሁሉ ተዓምራት ካዩ በኋላ አናምንም አሉ። ተዓምራት ዋነኛው ነገር አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል ማመን ነው ዋነኛው ነገር።
ዮሐንስ 6፡50 ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው።
በእግዚአብሔር ዘንድ ጠለቅ ያለ ሕይወት አለ። ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር የሚታይ በረከትን ተቀብለው ይረካሉ። ከእግዚአብሔር በዋነኛነት የሚፈልጉት ያ ስለሆነ ነው የሚረኩት። እግዚአብሔር ፈቃዳቸውን እንዲያደርግላቸው ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ናቸው።
ደግሞ ልባሞቹ ቆነጃጅትም አሉ። እነዚህ የራሳቸው ፈቃድ የላቸውም። የሚያስፈልጋቸውን እንዲሰጣቸው በእግዚአብሔር ላይ ይደገፋሉ ነገር ግን ይህ በሕይወታቸው ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ነው የሚቀመጠው። ዋነኛው ፍላጎታቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ይችሉ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ እና መታዘዝ ነው። የዘላለም ሕይወት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያቀደው እቅድ አካል ያደርገናል።
ዮሐንስ 6፡51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።
ፕሮፓጋንዳ ማለት እራስህን መልካም አድርገህ በማቅረብ የሰዎችን አእምሮ መቆጣጠር ነው። የብልጽግና ወንጌል መሰረቱ ይህ ነው። መልእክቱ እግዚአብሔርን አገልግላችሁ ሃብታም ሁኑ የሚል ነው።
ኢየሱስ ያደረገው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። የወንጌልን እውነት ጠንከር አድርጎ ሲያቀርበው ማንንም ሳያባብል ነው። ይህ ዓይነቱ አቀራረብም ለሰው ስጋዊ አእምሮ የሚስብ አይደለም።
ኢየሱስ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ሊከተለው እንደማይችል ያውቃል። ስለዚህ ወንጌሉ ቀላል ወይም ሰዎችን የሚስብ መንገድ ነው ብሎ ማንንም አላባበለም።
ዮሐንስ 6፡52 እንግዲህ አይሁድ፦ ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል? ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ።
ኢየሱስ ተከታዮች እንዲበዙለት እየለመነ አይደለም። ሕዝብ ለመሳብ ብሎ የወንጌሉን መርህ ዝቅ አላደረገውም። ጠለቅ ያለ እውነት ሰበከ፤ ሰዎች ግን አእምሮዋቸው ፍጥረታዊ ነገር እንጂ መንፈሳዊ ነገር መረዳት አይችልም። ከዚህም የተነሳ የሰው ስጋ ብሉ የተባሉ መሰላቸው።
ዮሐንስ 6፡53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
ኢየሱስ ከፍጥረታዊው ዓለም አልፎ ስለ መንፈሳዊው ዓለም ነው የሚናገረው። የዘላለም ሕይወት ከፍጥረታዊው አካላችን ጋር የተያያዘ አይደለም፤ ፍጥረታዊው ስጋችን ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት ተፈርዶበታል።
ዮሐንስ 6፡54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
ኢየሱስ ምን ማለት እንደፈለገ በጭራሽ አልተረዱም። ፍጥረታዊ ሕይወትን ሳይሞት ለማቆየት ሰውነታችንን የሚመግቡ ምግቦች መብላት አለብን፤ ሰውነታችንን ለማጽዳት ደግሞ ውሃ መጠጣት አለብን። የውጭው ገላችን በውሃ መታጠብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የውስጡ የሰውነት ክፍላችንም በውሃ መታጠብና መጽዳት ያስፈልገዋል።
ይህ የመንፈሳዊ ሕይወት ነጸብራቅ ነው። የሕይወትን እንጀራ ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል መብላት አለብን። ፍጥረታዊ ሕይወት በዓይን አይታይም፤ እርሱም በስንዴ ወይም በገብስ ፍሬ ውስጥ ይኖራል።
በዓይን የሚታየውን የስንዴ ፍሬ እንበላለን፤ በዚህም መንገድ በስንዴው ፍሬ ውስጥ ያለውን የማይታይ ፍጥረታዊ ሕይወት እናገኛለን።
ለመንፈሳዊ ሕይወት ደግሞ የእግዚአብሔርን ሚስጥራዊ አሰራር ለማየትና ለመረዳት ማድረግ የምንችለው መጽሐፍ ቅዱስና ማንበብ ብቻ ነው። ቤተክርስቲያኖች ምንም የማይጠቅመውን የራሳቸውን ከንቱ ልማዶችና አመለካከቶች ያስተምራሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትና በራሳችን አእምሮ ማሰብ ስንጀምር የእግዚአብሔርን ምሪት ማግኘት እንችላለን፤ ይህም ከሰዎች ስሕተት ይጠብቀናል።
የመለኮት ሙላት በክርስቶስ ውስጥ ነው ያደረው። ስለዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን ማየት የቻሉት በኢየሱስ ስጋ በተገለጠው አካሉ አካሉ ብቻ ነው። ስለዚህ በዓይን የሚታይ ሆኖ የተገለጠ ስጋው በዓይን የሞታየውን መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።
የውስጥ ሃሳባችንና ስሜቶቻችን ከአለማመን ሐጥያትን አጥቦ ለማስወገድ ብቸኛው ኃይል ባለው በኢየሱስ ደም መንጻት ያስፈልጋቸዋል። አለማመን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ማመን ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ቃል አለማመን ነው። ደሙ ውስጣችን የሚያነጻ እና ግብዝ ከመሆን የሚያድነን መንፈሳዊ መጠጥ ነው፤ ምክንያቱም በውስጣችን በአለማመን ተሞልተን በውጪያችን ግን ሐይማኖተኛ መምሰል በጣም ቀላል ነው።
ዮሐንስ 6፡55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።
ለእግራችን ብርሃን ሆኖ ከሚመራን ከእግዚአብሔር ቃል እና ሐጥያታችንን አጥቦ ከሚያነጻው እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን የማያምነው ልባችንን እንዲያምን ከሚለውጠው ከኢየሱስ ደም የበለጠ ሕይወት ሰጭ ኃይል የለም።
ዮሐንስ 6፡56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስን እመኑና በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ትኖራላችሁ። ሕይወት ያለው በድሙ ውስጥ ነው። በጸሎት ደሙ እንዲያነጻን እንጠይቃለን፤ ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ማለትም በደሙ ውስጥ የነበረው ሕይወት ወደ እኛ ውስጥ ይገባና ይቆጣጠረናል፤ ወደ እውነትም ሁሉ ይመራናል።
ዮሐንስ 6፡57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።
የእግዚአብሔር መንፈስ በኢየሱስ ውስጥ ሆኖ ይቆጣጠረው ነበር። የእግዚአብሔር ውስጣዊው ሕይወት ማለት ኢየሱስ ሰው በሆነው አካሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም አይችልም ነበር ማለት ነው። ኢየሱስ የራሱ ሰብዓዊ ፈቃድ ወይም ፍላጎት ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ እንዲወጣ ፈቅዶ አያውቅም። ሁልጊዜ የራሱን ፈቃድ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እያስገዛ ነው የተመላለሰው።
እንጀራ እና ስጋ ብንበላ ሰውነታችን የበላነውን ይፈጨውና የአካላችን ክፍል ያደርገዋል።
ስለዚህ የበላነው ምግብ የምንኖርበት አካል ይሆንልናል።
ቃሉን በመብላት (ማለትም በማንበብና በማመን) እንፈጨውና ቃሉን ወደ ውስጣችን እናስገባዋለን (ማስተዋል እናገኛለን)፤ ወደ ውስጣችን ያስገባነው ቃልም የውስጠኛው ሰውነታችን አካል ይሆናል። ከዚያም በውስጣችን የሚኖረው የክርስቶስ ሕይወት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድንፈጽም ያስችለናል፤ ምክንያቱም ነገሮች በእግዚአብሔር መንገድ ማድረግ እንፈልጋለን እንጂ ከዚያ ወዲያ በራሳችን መንገድ የማድረግ ፍላጎት አይኖረንም።
ዮሐንስ 6፡58 ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል።
አይሁዶች በስጋ ብቻ ማሰባቸውን ቀጥለዋል። ከግብጽ በወጡ ጊዜ እንጀራ ከሰማይ ይወርድላቸው ነበር፤ እነርሱም መና ብለው ጠሩት። ነገር ግን መናውን የበሉት አይሁድ በስተመጨረሻ መሞታቸው አልቀረም።
ወንጌሉ ሁለት ገጽታዎች አሉት። አንደኛ ጊዜያዊ ለሆኑ ፍላጎቶቻችን እግዚአብሔር ጥያቄያችንን የሚመልስበት እና ጤናችንን የሚጠብቅበት ነው። ብዙ ሰዎች ከዚህ አልፈው አይሄዱም። ጤናማ እስከሆኑ ድረስ እና የሚበሉት ምግብ እንዲሁም ስራ፣ መኖሪያ ቤት እና ቁሳቁስ እስከተሟሉላቸው ድረስ እግዚአብሔርን በደስታ ያገለግሉታል። እግዚአብሔርን ለተደላደለ ኑሮ፣ ለብልጽግና፣ እና በጤና ለመኖር ብለው ነው የሚያገለግሉት።
ከግብጽ የወጡት አይሁዶች በመንገዳቸው በምድረበዳ ሳሉ ምግብ ከሰማይ፣ ውሃ ከዓለት ያገኙ ነበር፤ ልብሳቸውም አያልቅም ነበር። ከዚያም በላይ ደግሞ ከተስፋ ምድራቸው ላይ ተባረው የሚወጡት አሕዛብ የሰሩዋቸውን ቤቶች፣ የገነቡዋቸውን ከተሞች፣ ያረሱዋቸውን እርሻዎች ለመውረስ እየሄዱ ነበር። ከእነዚህ ሁሉ በረከቶች ጋር በፈለጉ ጊዜ ከሰማይ በነጻ ኬሚወርድላቸው መና እያለ እነዚያ አይሁዶች ሞቱ። ከመናው እና ከሌሎቹ በረከቶች ሁሉ የሚበልጥ አንድ ነገር ነበረ፤ እነርሱ ግን አላወቁትም።
እግዚአብሔር እንደ ራሱ ፈቃድ እንዲያገለግሉት ፈልጎ ነበር። እነርሱ የፈለጉት ግን የሚወርሱትን ሃብት ብቻ ነው።
ኢየሱስ ከፍጥረታዊ ቁሳቁሳዊ በረከት የሚበልጥ ነገር ነበረው። እርሱ የራሱን መንፈስ ቅዱስ ሊሰጣቸው አቅርቦላቸው ነበር። ቢቀበሉት ኖሮ መንፈስ ቅዱስ ወደ ውስጣቸው ገብቶ ጠለቅ ባለ መንፈሳዊ ደረጃ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያምኑ ያስችላቸው ነበር። የዘላለም ሕይወት ሚስጥር ይህ ነው። የዘላለም ሕይወት እንጀራችን የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ተከትሎ ነው የሚሰራው። የምንበላው ወይም የምናምነው የሕይወት እንጀራ የእኛ አካል በመሆን አስተሳሰባችንን እና አኗኗራችንን ቅርጽ ያስይዘዋል። በራሳችን መንገድ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንገድ በማሰብ ደስ ይለናል።
ዮሐንስ 6፡59 በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ።
ቅፍርናሆም ማለት የንሰሃ እርሻ ወይም የምቾት ከተማ ነው።
ይህች ከተማ በሁለት መንገዶች ልትሄድ ትችላለች። በከተማይቱ ከተደረጉት ታላላቅ ተዓምራት የተነሳ ሰዎች ንሰሃ ገብተው ጌታን የሚከተሉባት እርሻ መሆን ትችላለች። አለዚያ ደግሞ ሰዎች በሰው ሰራሽ ሐይማኖታዊ አስተምሕሮዋቸው ሰውን እንደ መሪ በመከተል ተመችቷቸው የሚኖሩባት ከተማ መሆን ትችላለች። ይህም የተደራጁ ዲኖሚኔሽናዊ እምነቶች ዘር ነው።
ቅፍርናሆም በውስጧ ወደ ፊት የምትነሳዋ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ዘር ይዛ ነበር። በምድር ላይ ታላቅ እና ኃይለኛ በሃብትም አንደኛ እንደሆነችዋ ቫቲካን ከፍ ብላ ነበር። ነገር ግን የመንፈሳዊ ስሕተት እና የአረማዊ እምነቶች ማዕከል እንደመሆኗ በታላቁ መከራ ውስጥ በአቶሚክ ቦምብ ተመትታ እየጋየች ወደ ሲኦል ትወርዳለች።
ማቴዎስ 11፡23 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
ድሆችን እና ችግርተኞችን ለመርዳት ብዙ ተዓምራትን ቢያደርግም እንኳ ገንዘብ ሰብሳቢዎች ግን ከኢየሱስ የፈለጉት የእርሱን ገንዘብ ነው። ይህም የፖፑን በቃኝ የማይል የገንዘብ ፍቅር ያሳያል፤ ልክ እንደ ይሁዳ።
ማቴዎስ 17፡24 ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፦ መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን? አሉት።
አንድ ቤተክርስቲያን በድርጅት መልክ ስትዋቀር በውጧ ብዙ የስራ ድርሻዎች ይፈጠራሉ። ወዲያው የስልጣን ተዋረድ ይከተላል፡ ጳጳሳት፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ካርዲናሎች፣ ፖፕ። እያንዳንዱ ከሌላው ለመብለጥ እና በስልጣን እያደገ ለመሄድ ይፈልጋል። ከሁላቸውም የሚበልጠው ሰው ከፍተኛውን የስልጣን ደረጃ ይይዛል።
ማርቆስ 9፡33 ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው።
34 እነርሱ ግን በመንገድ፦ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ።
ወደ ቅፍርናሆም ሲቀርቡ ሁሉም ደቀመዛሙርት ከሌሎች የመብለጥ ፍላጎት በውስጣቸው ተቀሰቀሰ።
ማቴዎስ 8፡5 ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ
ማቴዎስ 8፡14 ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤
የጴጥሮስ ቤት ቅፍርናሆም ውስጥ ነበር። ይህም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጴጥሮስን ከደቀመዛሙርት ሁሉ ይበልጣል ብላ እንደምትመርጥ የሚያሳይ ምልክት ነበረ። እርሱ ብቻ ነው የመንግስተ ሰማያት ቁልፎች ያሉት ብለው ይናገራሉ፤ ስለዚህ እርሱ ብቻ ነው የሰማይን ደጅ የሚከፍት ብለው ያስተምራሉ። ይህም እራሱን የጴጥሮስ ተተኪ ነኝ የሚለውን ፖፕ በጨለማው ዘመን ውስጥ በባርቤርያን ነገዶች መካከል ታላቅ ስልጣን ሰጠው። ሲሞቱ ወደ መንገስተ ሰማያት መግቢያውን በር ጴጥሮስ እንዲከፍትላቸው ከፈለጉ ለፖፑ መታዘዝ አለባቸው።
(ነገር ግን አንድ ስሕተት አለ፡- ጴጥሮስ አግብቷል፤ የካቶሊክ ፖፕ ደግሞ ማግባት አይችልም።)
ስለዚህ ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ መንገድ የተወሰኑ ቤተክርስቲያን የደነገገቻቸውን ስራዎች መስራት ሆኖ ቀረ። ፖፑን እስከታዘዙ ድረስ፣ መሬት እና ገንዘብ እስከሰጡት ድረስ፣ እስከተዋጉለትና የፖፑን ጠላቶች እስከገደሉለት ድረስ፣ እንዲሁም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች ላይ እስከተገኙ ድረስ መንግስተ ሰማያት መግባታቸው የተረጋገጠ ነው።
በዚህ መንገድ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የባርቤርያውያንን ሃብት በዘበዘች፤ በወደቀው በሮማ መንግስት ግዛት ላይ እያንሰራራች በምቾትና በድሎት ኖረች።
ስለዚህ ኢየሱስ ከግብጽ የወጡት አብዛኞቹ አይሁዶች የእግዚአብሔርን በዓይን የሚታይ በረከት ብቻ በመፈለጋቸው በምድረ በዳ ውስጥ የመሞታቸውን እውነት ገልጦ ሲናገር አብዛኞቹ አይሁዳውያን ተከታዮቹ ትተውት ወደ ኋላ ተመለሱ። እነርሱም ራሳቸው ልባቸውን የጣሉት በሃብት ሰብሳቢነት ወንጌል ነበር።
ዮሐንስ 6፡60 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።
በብዙሃኑ ዘንድ የተወዳጅነት ውስጥ ወድድር ብትገባ እውነት ሐሰትን ማሸነፍ አትችልም።
እውነት ከባድ ናት። እውነት ለብዙ ሰዎች ለመስማት እና ለመቀበል ከባድ ናት። የሐይማኖት መሪዎች ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተመሰረተ ለጆሮ የሚጥም አማራጭ ትምሕርት ያዘጋጃሉ። እነዚህ በውሃ የቀጠኑ ትምሕርቶችም ለብዙሃኑ ተስማሚና ምቹ ናቸው።
ዮሐንስ 6፡61 ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን?
ደቀመዛሙርቱ እንኳ ሳይቀሩ ጠንከር ባለው በእግዚአብሔር መርህ ተሰናከሉ። እነርሱም ጭምር ገንዘብ ማካበት እና ጤና ማግኘት ተመኙ። ሁላችንም ቀለል ያለ ወንጌል እንመርጣለን።
ዮሐንስ 6፡62 እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?
ኢየሱስ ግን ዓይኖቹን የጣለው በእግዚአብሔር ሰማያዊ ፈቃድ ላይ ነበር። ወደ ምድር የመጣው ለመበልጸግ እና ሃብታም ለመሆን አይደለም። እርሱ ከላይ ስለመጣ ሰዎች ያቀረቡለትን የመንገስ ግብዣ ንቆ ተወ፤ ምክንያቱም ከዚህ ምድር የሆነ ነገር ሁሉ እንደማያዛልቅ ገብቶታል። እርሱ የፈለገው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ብቻ ነው፤ ይህም ነፍሱን አሳልፎ መስጠት ሲሆን በዚህ መንገድ ወደ ሰማይ ተመልሶ በመሄድ እውነተኛውን መንግስት ማዘጋጀት ይችላል።
“ወደ ነበረበት ሲወጣ” ብሎ ሲናገር የምድር ነገሮች ሁሉ ዋጋቸው ምን ያህል ከቁም ነገር የማይቆጠር መሆኑን እያሳየ ነው። በዚህ በምድር ላይ ብቸኛው ትልቅ ቁምነገር የሰማይ ፈቃድ ነው።
ዮሐንስ 6፡63 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው የዘላለም ሕይወት ሊሰጠን የሚችለው። በስጋ የምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ጊዜ ማባከን ብቻ ናቸው። የሚያስገልገን የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማመን፤ መከተል እና መኖር አለብን። የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰራው በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ብቻ ነው እንጂ በሰዎች አመለካከትና ፍላጎት መሰረት አይደለም።
ዮሐንስ 6፡64 ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ። ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና።
በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ የማያምኑ ሰዎች ይኖሩበታል። ቢግ ባንግ እና ኤቮልዩሽን ቲዎሪ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረኑ ሳይንሳዊ ሃሳቦች ቢሆኑም እንኳ ብዙ ክርስቲያኖች ያምኑባቸዋል። በሳይንቲስቶች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ከመፈለጋቸው የተነሳ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር እስትንፋሰ የተጻፈ መሆኑን ይክዳሉ።
ፕሮፌሰሮች ልጆቻችንን ከእንስሳት ነው የመጣችሁት ብለው ካስተማሩ በኋላ ባህርያቸው እንደ እንስሳት ነው ብለው ቅሬታ ያቀርባሉ።
ዮሐንስ 6፡65 ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ።
በራሳችን ጥበብ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መምጣት አንችልም። ነገሮችን እግዚአብሔር በሚያይበት መንገድ ማየት እንድንችል ዳግመኛ መወለድ አለብን። ስለዚህ ንሰሃ መግባት እና አእምሮዋችንን እግዚአብሔር እንዲቆጣጠር መጋበዝ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንድንችል የሚያስፈልገንን ማስተዋል ሊሰጠን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
ይህ ስለ አውሬው ምልክት ስለ 666 የሚያሳየን መንፈሳዊ መገለጥ ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚ ማለት የቃሉ ተቃዋሚ ነው። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን መከተል አንፈልግም አሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ከማመን ስናፈገፍግ የዛኔ የአውሬውን ምልክት መቀበላችን ነው።
ምድራዊ ንጉሳቸው መሆንን እምቢ ሲል ከዚያ ወዲያ አልፈለጉትም፤ ስለዚህ ከዱት ምክንያቱም ከእርሱ ምንም ጊዜያዊ ጥቅም ማግኘት እንደማይችሉ ታያቸው። እርሱ ምድራዊ ንጉሳቸው ለመሆን እሺ ቢል ኖሮ ለእነርሱ ምድራዊ ብድራትና ሽልማት ይኖር ነበር።
ኢየሱስ ከገሊላ ባሕር ማዶ ሳለ ስ አውሬው ምልክት ጠቅሶ አልተናገረም ነበር። አሁን ግን ከታይቢርየስ (በሮማዊ መሪ ስም ነው ይህ አካባቢ የተጠራው) ጋር ከባሕሩ በአንድ ወገን በሆነ ሰዓት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አመራር ስርዓት የሚያመጣውን ውጤት ይገልጣል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካቶሊኮችን እና ፕሮቴስታንቶችን ከእግዚአብሔር ቃል ርቀው እንዲሄዱ ታደርጋለች።
ሥላሴ፣ ክሪስማስ፣ ዲኖሚኔሽኖች፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ የውሃ ጥምቀት በሶስት ማዕረጎች መፈጸም፣ ሰውን የቤተክርስቲያን ራስ ማድረግ። እነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካልሆኑት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነቶች በጥቂቱ ናቸው። ፕሮቴስታንቶችም ተቀብለዋቸዋል።
ልክ እንደዚሁ ሰይጣን በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካኝነት በሰው የምትመራ፣ ሃብታም የሆነች፣ ለሰዎችም ኩራት እና ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፍል ስራ መስጠት የምትችል፣ እና ማራኪ ስርዓቶች ያሏት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ለመመስረት ተነሳ።
ዮሐንስ 6፡67 ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ።
ኢየሱስ ግን በሕዝብ ብዛት አይገረምም። ምንም ያልተቀባባው እውነት ብዙ ሰዎችን እንዲሸሹ አድርጓቸዋል። እርሱ ግን አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ጭምር ሊከተሉት ዝግጁ ካልሆኑ እነርሱንም ለማጣት ተዘጋጅቶ ነበረ። ኢየሱስ የፈለገው የራሳቸውን አመለካከት የማይከተሉ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሙሉ በሙሉ የሚታዘዙ ደቀመዛሙርት ብቻ ነው።
ዮሐንስ 6፡68 ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
ጴጥሮስ ሊሄድ የጀመረው መንገድ ከባድ መሆኑን ተረድቷል። እውነት ለመረዳት ቀላል አይደለችም። እግዚአብሔር በሆነ መንገድ ለጴጥሮስ ጠለቅ ያለ መገለጥ ስለሰጠው ጴጥሮስ ኢየሱስ ዘንድ እውነት መኖሩን አውቋል፤ እውነት ለማስተዋል ከባድ ብትሆንም።
እውነት በባሕር ላይ እንደሚንሳፈፍ በረዶ ናት። ዘጠና በመቶው የሚሆነው አካሏ ለተመልካች አይታይም ምክንያቱም ከውሃው በታች ናት። የእውነትን ሚስጥራት እና ልዩ ልዩ ጥልቅ ተምሳሌቶች ለመረዳት ብዙ መቆፈርና አድካሚ ስራ መስራት ይጠይቃል። ወደ እውነት የሚያደርስ ቀላል መንገድ የለም። እውነት ብዙውን ጊዜ ብዙሃኑ ሕዝብ አይወዷትም። ስለዚህ ጴጥሮስ ትተው ወደ ኋላ ከተመለሱት ከብዙሃኑ ተነጥሎ ከእነርሱ ጋር አልስማማ ብሎ ጸንቶ ለመቅረት ወኔ ነበረው። ከኢየሱስ ጋር ጸንቶ የሚያቆይ እምነት ነበረው፤ ግን ይህ እምነት ደግሞ የብዙሃኑን ፈቃድ የመቃወም ድፍረት ይጠይቃል፤ ምክንያቱም የብዙሃኑ ፈቃድ ግለሰቦችን እስረኛ የሚያደርግ ኃይል ነው።
ነገር ግን መንጋውን የምትከተሉ ከሆነ ሳሩ ተግጦ አልቆ ነው የምትደርሱት።
ጴጥሮስ ኢየሱስን ለመከተል ዝግጁ ነበረ፤ በመከተሉ የትንሽዬ ቡድን አባል ሆኖ ቢቀርም እንኳ ወስኗል።
ዮሐንስ 6፡69 እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።
ጴጥሮስ የአስራ ሁለቱ ቃል አቀባይ ነበረ። በዙርያው ባለው ትንሽዬ “የቤተክርስቲያን” ቡድን የተነሳ ልበ ሙሉ ሆኗል። እነርሱም እውነቱን ያምኑ ነበረ።
ዮሐንስ 6፡70 ኢየሱስም፦ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።
ኢየሱስ አስራ ሁለቱን እንደመረጣቸው ተናገረ። እነርሱም የተመረጡት ለትልቅ ዓላማ ነው። የእግዚአብሔር እቅድ እንዲፈጸም በመካከላቸው አንድ ዲያብሎስ እንዲኖር ያስፈልጋል።
ስለዚህ የምንተማመነው በቤተክርስቲያን መሆን የለበትም፤ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ባለን ሕብረት ነው እንጂ።
ደቀመዛሙርቱ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ሕብረት ያላቸው መስሏቸው ነበር። ነገር ግን ይሁዳ በመካከላቸው ሳለ መልካም ሕብረት ውስጥ አልነበሩም።
በመካከላቸው ዲያብሎስ የሌላቸው የቤተክርስቲያን ሕብረቶች አሉ? እኛ ሰዎች አናውቅም።
የቤተክርስቲያን ዘመናት መጽሐፍ፤ የሰምርኔስ ቤተክርስቲያን ዘመን
ሞት የውሸተኛው ወይን ብቸኛው ዘር አልነበረም፤ ነገር ግን በእውነተኛው ወይን ውስጥ እንኳ ውስጥ ውስጡን ስር የሰደደ ድካምና ድንዛዜ ነበረ ምክንያቱም እነርሱ ከመጀመሪያዎቹ ጴንጤ ቆስጤያዊ ዓመታት ያልተቀላቀለው እውነት ወጥተው ሄደዋል፤ ደግሞም የትኛውም እውነተኛ አማኝ ቢሆን በብዙ የብሉይ ኪዳን ታሪክ ምሳሌዎች ውስጥ እንደምናየው በመንፈስ ሕያው እና ጤናማ የሚሆነው ንጹህ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ባመነበት እና በተደገፈበት መጠን ብቻ ነው። ድርጅታዊነት በፍጥነት እያደገ እና የአባልነትን ሞት እያሳየ ነበረ፤ ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ወደ ጎን ተትቶ የእግዚአብሔር ቃልም በሐይማኖታዊ መግለጫዎች፤ በዶግማዎች እና በሰው ሰራሽ ስርዓቶች ተተክቷል።
ዮሐንስ 6፡71 ስለ ስምዖንም ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ ተናገረ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነ እርሱ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አለውና።
ስምዖን የሚለው ስም ትርጉሙ “ስማ” ማለት ነው። ግን የሚያሳዝነው ነገር ይሁዳ ገንዘብን አብዝቶ ከመውደዱ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ከእርሱ ጋር ቃል የተገባቡትን የካሕናት አለቆች ሃሳብ ነው የሰማው።
ይሁዳ “ከብልጽግና እምነቱ” ተጠብቆ ቢኖር ኖሮ እና ኢየሱስን ማለትም ቃሉን ብቻ ቢያዳምጥ በሰላም መኖር ይችል ነበር። ነገር ግን ሐይማኖት ገንዘብ በማግኘት ፍላጎት እየተነዳ ሲሄድ ሐይማኖት እና ገንዘብ የሚፈጥሩት ውሕደት መርዛማ ነው የሚሆነው።
አንዳንድ ምሑራን “አስቆሮት” ማለት “የከተሞች ሰው” ማለት ነው ይላሉ። ከተሞች የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር መገለጹን ልብ በሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያዋ ከተማ የተሰራችው በቃየን ነበር (ዘፍጥረት 4፡17)፤ ቃየን በጉልበቱ የሚታመን ወንድሙን አቤልን የገደለ ሰው ነው። ገዢ የሆነ ሰው ወይም ሴት ተቀምጠው የሚገዙበት ከተማ ያስፈልጋቸዋል፤ ምክንያቱም በሕዝብ ላይ ስልጣን ለመለማመድ ከተፈለገ የሚቀለው እና የሚያመቸው ሰዎች በአንድ ቦታ ሰብሰብ ብለው ሲኖሩ ነው። ከመጀመሪያው ከናምሩድ መንግስት ጀምሮ ዓለምን መግዛት የፈለጉ ሰዎች ሁሉ ካሉበት ተነስተው ብዙ አካባቢዎችን በጦርነት እያንበረከኩ ብዙ ከተሞችን ይመሰርታሉ። ነገር ግን የመሰረቱዋቸው መንግስታት አልዘለቁም። በኃይል እና በጉልበት ሕዝብን አስጨንቆ የሚገዛ መንግስት ለረጅም ጊዜ ሰላም እና መረጋጋት የሚሆን የፍቅር መሰረት አይጥልም። የሮም ከተማ ጉልበተኛ መንግስት ግዛቱ ለረጅም ጊዜ የቆየለት ተቃዋሚዎችን በሙሉ በሰይፍ በመምታት በጭካኔ ያጠፋቸው ስለነበረ ነው። ገዢዎቹ ግን አንዴ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ከስግብግብነታቸው ብዛት የሚያስከፍሉትን ግብር መጠን በየጊዜው ይጨምሩ ነበር። በስተመጨረሻ ግዛቱ ሰፍቶ፤ ተለጥጦ ከአንድ ከተማ ሆኖ ለማስተዳደር አስቸጋሪ ሆነ። ወታደሮች ጡረታ ስንወጣ የምንኖርበት መሬት ይሰጠን ብለው ጥያቄ ማቅረብ አበዙ። ከዚህም የተነሳ ግዛቱ እየሰፋ መሄድ ግዴታ ሆነበት። ነገር ግን ለዚያ ሁሉ ግዛት ጥበቃ ማድረግ ብዙ ሰዎችን ወደ ውትድርና ማስገባትና በራሱ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ ስራ ሆነ። ከዚህም የተነሳ ግዛቱ በራሱ ክብደት ስር ወደቀ።
ስለዚህ ሰይጣን ዓለምን ለመግዛት ያለውን እቅድ እንደገና ማሰብ ግድ ሆነበት። ዓለምን ለመግዛት የቤተክርስቲያንን ኃይል ከተጠቀመ ይበልጥ ቀላል ይሆንለታል። ሰዎች ሰማይ ውስጥ ቦታ ለማግኘት ብለው ለቤተክርስቲያን ገንዘብ ይከፍላሉ፤ ቤተክርስቲያንም ለሰዎቹ በሰማይ ቦታ ለመስጠት ምንም ወጪ አያስወጣትም። በዚህ መንገድ ቤተክርስቲያን በቀላሉ ገንዘብ ታከማቻለች። አንድ ሰው ስልጣን በሚይዝበት ማዕከላዊ አገዛዝ ቤተክርስቲያን ራሷን የቻለች ትልቅ ንግድ ትሆናለች። የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ከዚያ በኋላ ወደ መንግስተ ሰማያት የሚኬድበትን ልዩ አስተምሕሮ ለሕዝቡ ያቀርብላቸዋል። ይህንን መሪ በመከተል ብቻ ነው ወደ መንግስተ ሰማያት መድረስ የሚቻለው። ከዚህ የተነሳ መሪው ሕዝቡ ላይ ሙሉ ስልጣን አለው። ሰዎች አንድ ጊዜ የቤተክርስቲያን አባል ከሆኑ በኋላ ቤተክርስቲያንን ትተው ለመውጣት በጣም ይፈራሉ፤ ምክንያቱም መሪያቸው የፈጠረው አስተምሕሮ ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ ብቸኛ መንገድ ነው። ደግሞም መሪው ብቻ ነው በመንፈሳዊ መረዳት እያደገ የሚሄደውና ተከታዮቹ የማያውቋቸውን ሌሎች ሚስጥራት ወደፊት እየገለጠላቸው የሚሄደው።
ስለዚህ ሰይጣን ሃሳቡን ለወጠ። እያደገ በሚሄድ ግዛት ውስጥ በጣም ብዙ “ከተሞች” በማስተዳደር ፈንታ በከተማው ውስጥ “የከተማ ቤተክርስቲያን” አስተዳደርን መረጠ።
በሮም ከተማ ዙርያ የባቲካንን ከተማ የሚያጠቃልል ግምብ አጥር ተሰራ።
ቫቲካን። በእንግሊዝኛ Vatican በውስጡ “ican” የሚለው ፊደል ብታው ሲለዋወጥ “Cain” ወይም ቃየን ይሆናል።
“I can” የሚለው ቃል በራስ አቅም የመተማመን የትእቢት መገለጫ እንዲሁም ከጥንት ጀምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ነው።
“ከተሞች” ማለት በከተማ ውስጥ ያለች ከተማ ሆነ። ቫቲካን በሰባቱ ተራሮች ላይ በተቆረቆረችው በሮም ከተማ ውስጥ ያለች ትንሽ ከተማ ናት (ደግሞም በምድር ላይ ካሉ መንግስታት ሁሉ ትንሽዋ የከተማ መንግስት ናት)።
ሆኖም ግን 1.2 ቢሊዮን ሮማን ካቶሊክ ተከታዮችን በማፍራት ታላቅ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ እና የገንዘብ አቅም ያላት ዓለም አቀፍ ኃይል ወደመሆን ልታድግ ችላለች። ከዓለም ሁሉ እጅግ ትልቋ ቤተክርስቲያነ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። ደግሞም ከመንግስታት ሁሉ የበለጠ ያልተቋረጠ የመሪዎች የመተካካት ሰንሰለት አስመስግባለች (በ400 ዓ.ም አካባቢ ጀምሮ ፖፕ የሆኑት የሮማ ጳጳሶች)፤ እነዚህም ከቤተክርስቲያን ጥንታዊ ዘመን ጀምሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን መርተዋል። ቫቲካን ትንሽና ኃይለኛ እንደመሆኗ የዳንኤል ትንቢት ውስጥ የተገለጠው “ታናሽ ቀንድ” ናት።
ቫቲካን የዘመናችን ይሁዳ ናት። ልክ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ እንደሰጠ ሁሉ ሰው ሰራሽ አስተምሕሮዎች የእግዚአብሔርን ቃል (ኢየሱስን) አሳልፈው ሰጥተዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መደገፍ የነበረበት እምነትም በዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች እና በወጎቻቸው ላይ ተደጓል።
የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያበጀችውን ዲኖሚኔሽናዊ ሰው ሰራጭ ማዕከላዊ ቁጥጥር ዘዴ ስለሚጠቀሙበት በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያኖች ሁሉ አንድነት በሚፈጠርበት ጊዜ ፖፑ የዚህ አንድነት መሪ ወይም ወደ አንድነት ለመጡት የቤተክርስቲያን ሕብረት ራስ መሆኑ የማይቀር ነው።
የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ቃል በሙሉ ልባቸው የማያምኑበት ሰዎች ሁሉ እጣ ፈንታቸው ይህ ነው። ኢየሱስ ማለትም ቃሉ ብቸኛው የቤተክርስቲያን ራስ ነው።