የዳንኤል 70 ሱባኤዎችን ዘመን መረዳት
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
ዳንኤል 9፡24 ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
70 x 7 = 490 ቀናት
ነገር ግን በትንቢት ውስጥ አንድ ቀን አንድ ዓመት ማለትም ሊሆን ይችላል።
ላባ ለያዕቆብ እንዲህ አለ፡-
ዘፍጥረት 29፡27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።
አንድ ሳምንት 7 ቀናት ከሆነ አንድ ሳምነት 7 ዓመታትን ይወክላል ማለት ነው።
ስለዚህ አንድ ቀን አንድ ዓመትን ይወክላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓመት 360 ቀናት ነው።
ራዕይ 11፡2 በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
3 ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
ስለዚህ 1,260 ቀናት = 42 ወራት ከሆኑ
1,260/42 = 30
ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ 1 ወር = 30 ቀናት
ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ወይም የአይሁዶች አንድ ዓመት ማለት 12 x 30 = 360 ቀናት።
ስለዚህ ባለ 365.24 ቀናቱ የአሕዛብ 69 ዓመታት ውስጥ 5.24 x 69 = 361 ትርፍ ቀናት አሉ።
ይህ በአንድ የአይሁዶች ዓመት አንድ መቶኛ ዓመት ግማሽ ውስጥ ነው።
ስለዚህ 69 የአሕዛብ ዓመታት = 70 የአይሁድ ዓመታት።
ወይም በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ የአይሁድ 70 ዓመት ከአሕዛብ ዓመት በአንድ ዓመት ያንሳል፤ ወይም ከ69 የአሕዛብ ዓመታት ጋር እኩል ነው።
490 የአይሁድ ዓመታት = 490 / 70 = ከአሕዛብ ዓመታት በ7 ዓመት ያንሳል።
490 የአይሁድ ዓመታት = 490 – 7 = 483 የአሕዛብ ዓመታት።
ስለዚህ የዚህ ትንቢት የጊዜ ገደብ ከአሕዛብ የዘመን አቆጣጠር አንጻር 483 ዓመታት ነው።
ትንቢቱ መፈጸም የሚጀምረው መች ነው?
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ይህ ቤተመቅደሱን መልሶ ስለመገንባት አይደለም።
ቤተመቅደሱ መልሶ የተገነባው መጀመሪያ ዕዝራ የቤተመቅደሱን እቃዎች ይዞ ለመሄድ ፈቃድ ከመቀበሉ በፊት ነው።
ዕዝራ 6፡15 ይህም ቤት በንጉሡ በዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባል ወር በሦስተኛው ቀን ተፈጸመ።
ዳርዮስ የነገሰባቸው ዓመታት ከ521 – 486 ዓመተ ዓለም ናቸው።
521 520 519 518 157 516 ዓመተ ዓለም
1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ 5ኛ 6ኛ የዳርዮስ የንገስ ዓመታት።
ስለዚህ ቤተመቅደሱ በ516 ዓመተ ዓለም አካባቢ ተሰርቶ ተጠናቀቀ።
ቤተመቅደሱን ሰርቶ ለመጨረስ 4 ዓመታት ፈጅቷል፤ ጠላቶቻቸው ግን እየረበሹዋቸው 17 ዓመታት አዘገዩዋቸው።
ከዚያ በኋላ በ459 ዓመተ ዓለም ዕዝራ የቤተመቅደሱን እቃዎች ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም እስኪመጣ ድረስ የ56 ዓመታት ክፍተት ነበረ።
ዕዝራ 7፡15 ንጉሡንና አማካሪዎቹም መኖሪያው በኢየሩሳሌም ለሆነው ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ፥
16 በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ የምታገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝቡና ካህናቱም በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላካቸው ቤት በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ትወስድ ዘንድ በንጉሡና በሰባቱ አማካሪዎች ተልከሃልና
27 በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያሳምር ዘንድ እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ … የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።
ዕዝራ 7፡8 በንጉሡም በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።
አርጤክስስ በ465 ዓመተ ዓለም ንጉስ ሆነ።
465 464 463 462 461 460 459 ዓመተ ዓለም
1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ 5ኛ 6ኛ 7ኛ የአርጤክስስ የንግስና ዓመታት
ስለዚህ ንጉስ አርጤክስስ ለዕዝራ የቤተመቅደሱን እቃዎች ይዞ ሄዶ ቤተመቅደሱን እንዲያስውብ ትዕዛዝ የሰጠው በ459 ዓመተ ዓለም ነው።
ነገር ግን ይህ የኢየሩሳሌምን አጥር ከመስራት ጋር አይገናኝም፤ የከተማይቱን መግቢያ በሮች ከመስራትም ጋር አይገናኝም። የከተማይቱ አውራ ጎዳናዎች በሙሉ ከበሮቿ ጋር ነው የሚገናኙት።
አስራ ሶስት ዓመታት ካለፉ በኋላ በ446 ዓመተ ዓለም ነህምያ የከተማይቱን አጥሮች ለመስራት መጣ።
ነህምያ በመጣ ሰዓት የኢየሩሳሌም አጥር እንደፈረሰ ነበር። ነህምያን ያሳሰበውም ይህ ነው።
ነህምያ 1፡3 እርሱም፦ በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል አሉኝ።
ዳንኤል 9፡25 … እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
የጭንቅ ዘመን። ነህምያ በ52 ቀናት ውስጥ የኢየሩሳሌም አጥር በሰራ ጊዜ በሁሉም ቀናት አብረውት የሚሰሩ ሰራተኞች የጦር መሳሪያ ታጥቀው ነበር የግንባታ ሥራቸውን የሚሰሩት፤ ምክንያቱም ድንገት ጠላት ጥቃት ቢሰነዝርባቸው መከላከል ያስፈልግ ነበር።
ነህምያ 4፡8 መጥተውም ኢየሩሳሌምን ይወጉና ያሸብሩ ዘንድ ሁሉም በአንድነት ተማማሉ።
ነህምያ 4፡17 ቅጥሩንም የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፥ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር።
ነህምያ ትዕዛዝ የተቀበለው ነህምያ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ በአርጤክስስ ንግስና 20ኛ ዓመት ላይ ነው።
ነህምያ 2፡1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር
አርጤክስስ የነገሰው በ465 ዓመተ ዓለም ነው፤ ስለዚህ የንግስና 20ኛ ዓመቱ የሚሆነው በእኛ የዘመን አቆጣጠር በ446 ዓመተ ዓለም ነው፤ የዘመን አቆጣጠራችን ከወቅቶች ጋር እንዲገጣጠም ተፈልጎ በዩልየስ ቄሳር ለውጥ ተደርጎበታል።
ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ በጥቁር ቀለም የተጻፉት ቁጥሮች ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩትን ዓመታት ሲወክሉ ቀዮቹ ቁጥሮች ደግሞ ንጉሱ በዙፋን ላይ የተቀመጠባቸውን ዓመታት ይወክላሉ።
ትንቢቱ ሊፈጸም የጀመረው በ446 ዓመተ ዓለም ነው፤ ግን የሚያበቃው መች ነው?
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
መሲሁ ኢየሱስ ነው።
መሲህ ማለት የተቀባ ሰው ማለት ነው።
ኢየሱስ በተጠመቀ ሰዓት መንፈስ ቅዱስ ሲወርድበት እና እንደ እርግብ ሲያርፍበት ነው በይፋ በአደባባይ የተቀባው።
ሉቃስ 3፡22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።
የሐዋርያት ሥራ 10፡38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
ሉቃስ 3፡23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር
ስለ መሲሁ መምጣት የተነገረው ትንቢት የሚጠናቀቀው በ30 ዓ.ም አካባቢ ነው።
እስቲ ትክክል መሆናችንን እናረጋግጥ።
ቀኖች የሚቆጠሩት አንድ ሮማዊ ንጉስ መንገስ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ነበር።
ከሮማውያን ነገስታት ሁሉ በላይ ዝነኛው ንጉስ አውግስጦስ ሲሆን እርሱም የሞተው በ14 ዓ.ም ነው።
በዚያው ዓመት መጨረሻ አውግስጦስ በማደጎ ያሳደገውን ልጅ ጢባርዮስን የሮማ ምክር ቤት ንጉስ አድርጎ ሾመው።
[ጢባርዮስ ንጉስ ሆኖ ስለ መሾሙ ጥቂት አስተያየት እናካፍላችሁ።
አውግስጦስ የዩልየስ ቄሳር እሕት የልጅ ልጅ ነበር። አውግስጦስ የሮማ ምክር ቤት እንደ መረጠው በማስመሰል በግብዝነት ስልጣን ተቆናጠጠ። በጭካኔው እና በነፍሰ ገዳይነት ሮምን እያስጨነቀ ነበር ወደ ስልጣን የወጣው። ምክር ቤቱም ለእርሱ የንጉስነትን ሹመት ላለመስጠት በጣም ፈሩ። አስመሳይነቱን በደምብ ለማሳየት ምክር ቤቱ ሹመቱን ያላጸደቀለት ሰው ንጉስ መሆን እንደማይችል የሚደነግግ ሕግ አወጣ። ነገር ግን የምክር ቤቱ አበላት እርሱ ምን እንዲያጸድቁለት እንደሚፈልግ ከእርሱ ጠይቀው ነበር የተረዱት። ከዚያም እርሱ የሚፈልገውን አደረጉ። እርሱም በማደጎ ያሳደገውን ልጁን ጢባርዮስን ከእርሱ ጋር አብሮ እንዲገዛ በ12 ዓ.ም ሾመው። ይህ ሹመት ግን አውግስጦስ በ14 ዓ.ም ሲሞት ጢባርዮስን ወዲያ ንጉስ አላደረገውም።
በሮማ ሕግ ምክር ቤቱ አስቀድሞ ሊያጸድቀውና የንጉስነት ሹመት ሊያቀርብለት ይገባል።
ይህ ግን በሶስት ምክንያቶች አመቺ አልነበረም።
መጀመሪያ፡- አውግስጦስ የመጀመሪያው የሮም ንጉስ ነበረ፤ ከዚህም የተነሳ ተተኪ የመሾም ልማድ አልነበረም።
ሁለተኛ፡- አውግስጦስ እና ጢባርዮስ ንጉስ እንዳልሆኑ ያስመስሉ ነበር። ንጉስ ብቻ ነው ስልጣኑን ለልጁ ማስተላለፍ የሚችለው። ንጉሰ ነገስት ስልጣኑን ለልጁ ማውረስ አይችልም። ሮማውያን ንጉሶችን ይጠሉ ነበር። አውግስጦስን እንደ ልጁ ያሳደገው ዩልየስ ቄሳር በሰው ተገድሎ ነው የሞተው ምክንያቱም ሕዝቡ እርሱ ራሱን ንጉስ ሊያደርግ አስቧል ብለው ይፈሩ ነበር። እርሱ ግን ራሱን የዕድሜ ልጅ አምባ ገነን አድርጎ ነበር።
በሮም ሕግ ለጅ ከመንገሱ በፊት አስቀድሞ ምክር ቤቱ የአባቱን ሞት ተከትሎ ሹመቱን ሊያጸድቅለት ይገባል። በዚህም መንገድ እንደ ንጉስ የሚመራው ንጉሰ ነገስቱ ንጉስ እንዳልሆነ እያስመሰለ ይኖራል። ስለዚህ ጢባርዮስ ከአውግስጦስ ጋር አብሮ ቢመራም እንኳ ወዲያው ሊነግስ አልቻለም።
ሶስተኛ፡- አውግስጦስ አግሪጳ የተባለ የልጅ ልጅ ነበር፤ አግሪጳ አውግስጦስን ለመግደል አስቧል ተብሎ ኮርሲካ አጠገብ የምትገኝ ደሴት ላይ ታስሮ ነበር። በ13 ዓ.ም አውግስጦስ አግሪጳን ጎብኝቶ ከእርሱ ጋር እርቅ እንዳደረገ ሞቅ ያለ ሰላምታ በማቅብ አሳወቀ። አግሪጳ የአውግስጦስ ልጅ ስለሆነ እና እንደ ጢባሪዮስ የማደጎ ልጅ ስላልሆነ ብዙዎች ቀጣዩ ሹመት ለአግሪጳ እንደሚገባ ይስማሙ ነበር።
ስለዚህ አውግስጦስ በ14 ዓ.ም በሞተ ጊዜ ሹመትን ለመውሰድ ከጢባርዮስ ጋር የሚፎካከር እንዳይኖር ተብሎ አግሪጳ ወዲያው እንዲገደል ታሰበ። ጢባርዮስ ስለ ግድያው ማንም እንዳያውቅ ዝም ካለ በኋላ አውግስጦስ መሞቱን ለምክር ቤቱ አስታወቀ። ከዚያም በኋላ እነርሱም ጢባርዮስን የመሾም ድራማ እንደሚጠበቅባቸው አድርገው ተጫወቱ። እርሱ ግን ከአንድ ወር በላይ መቀበል እንዳልፈለገ እያስመሰለ ቆየ። በስተመጨረሻ የሹመት ጥጠቄውን እያንገራገረ እንደተቀበለ አስመሰለ። ስለዚህ ምክር ቤቱ ጢባርዮስን ንጉስ አድርጎ ሹመቱን ያጸደቀለት በ14 ዓ.ም ነው።]
ሉቃስ 3፡1 ጢባርዮስ ቄሣርም በነገሠ በአሥራ አምስተኛይቱ ዓመት፥
2 … የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ በምድረ በዳ መጣ።
ከ14 ዓ.ም ተነስተን 15 ዓመታት ስንቆጥር 29 ዓ.ም ላይ እንደርሳለን።
ዮሐንስ ኢየሱስን በማጥመቅ አገልግሎቱን ሲጨርስ ጊዜው ወደ 30 ዓ.ም እየተቃረበ ነበር።
የዮሐንስ አገልግሎት በ30 ዓ.ም ስለመጠናቀቁ ይህ በጣም አስተማማኝ ማረጋገጫ ነው።
ትንቢቱ ሊፈጸም የጀመረው በ446 ዓመተ ዓለም ነው፤ የተጠናቀቀው ደግሞ በ30 ዓ.ም ስለሆነ በአጠቃላይ የፈጀው 476 ዓመታት ነው።
ነገር ግን የ69 ሳምንታት ሙሉ ርዝመት (7 + 62 ሳምንታት = 69 ሳምንታት) 69 x 7 = 483 ቀናት ወይም ዓመታት።
ስለዚህ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ 483 – 476 = 7 ዓመታት ለአይሁዶች ቀርቶላቸው ነበር።
ዳንኤል 9፡25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ሁለት ክፍለ ጊዜዎች አሉ። አንዱ የ7 ሳምንታት = 7 x 7 ቀናት = 49 ቀናት (ወይም ዓመታት)።
ዶ/ር እስኮፊልድ የሚልክያስ አገልግሎት በ397 ዓመተ ዓለም እንደነበረ ይናገራል።
ስለዚህ የኢየሩሳሌም አጥር እንዲሰራ ትንቢት ከተነገረ በኋላ ሚልክያስ ዕድሜው 49 ዓመት ይሆናል።
በመጨረሻው ሳምንት ማለትም በሰባኛው ሳምንት አጋማሽ መሲሁ ይገደላል።
“ዘመን” ማለት 7 ሳምንታት = 7 x 7 = 49 ዓመታት (አንድን ቀን እንደ አንድ ሳምንት ስንቆጥር)
“ዘመናት” 62 ሳምንታት ናቸው = 62 x 7 = 434 ዓመታት
ስለዚህ ከ446 ዓመተ ዓለም በኋላ አይሁዶች እግዚአብሔር በነብይ በኩል ሊናገረን ይችላል ብለው የሚጠባበቁበት የ49 ዓመታት ያህል ጊዜ ነበራቸው።
ይህንን ጊዜ ተከትሎ 62 የጸጥታ ሳምንታት መጡ። 62 x 7 = 434 የአይሁድ ዓመታት።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ግሪኮች የፋርስን መንግስት ካፈራረሱ በኋላ ብዙ ሁከት ተፈጠረ።
አይሁዶች ለአጭር ጊዜ ማለትም ለ100 ዓመታት ያህል ነጻ ሕዝብ ሆኑ፤ ከዚያ በኋላ ግን በ63 ዓመተ ዓለም በሮማውያን ተገዙ። ለሮማውያን የነበራቸው ጥላቻ ሮማውያንን የሚያጠፋላቸው መሲህ ይመጣላቸው ዘንድ እንዲናፍቁ አደረጋቸው። ከዚህም የተነሳ የሰላም አለቃ በመጣ ጊዜ ሳያውቁት ቀሩ።
ፖለቲካዊ ተሳትፎ በመንፈስ የመረዳትና የመለየት ችሎታን ያዳክማል።
በ29 ዓ.ም መጥምቁ ዮሐንስ በ62 ሳምንታት ማብቂያ ላይ ብቅ ሲል ነብይ ሳይነሳ የቆየበት ዘመን አበቃ።
ከ62ቱ ሳምንታት በኋላ ኢየሱስ የ3½ ዓመታት አገልግሎቱን ጀመረ።
ከዚያም በቀራንዮ ተገደለ። የሞተውም ለራሱ ብሎ አይደለም፤ የሞተው እኛ እንድን ዘንድ ስለ እኛ ሐጥያት ነው።
ዳንኤል 9፡26 ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።
በጀነራል ታይተስ መሪነት በ70 ዓ.ም ሮማውያን በአይሁዶች ላይ መራራ ጦርነት አውጀው ቤተመቅደሱን እና የኢየሩሳሌምን ከተማ አፈራረሱ። 1,100,000 አይሁዳውያን የሞቱበት ይህ አሰቃቂ እልቂት በሮም እና በአይሁዶች መካከል የነበረውን የጥላቻ ጥልቀት ይገልጻል።
“የሚመጣው አለቃ ሕዝብ።”
ቤተመቅደሱን እና የኢየሩሳሌምን ከተማ ያፈረሱ ሮማውያን ናቸው።
ስለዚህ የመጨረሻው የክርስቶስ ተቃዋሚ አለቃም የሚመጣው ከሮም መሆን አለበት። እርሱም የመጨረሻው ፖፕ ነው።
“መጨረሻ” የሚለው ቃል ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል።
ዳንኤል ትንቢት የሚናገርበት ስልት ወደፊት የሚሆን አንድ ክስተትን በመውሰድ እርሱን ተጠቅሞ በዘመን መጨረሻ የሚነሳውን የአመጽ ሰው ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚውን ሐይማኖታዊ ፖለቲካዊና የገንዘብ ኃይሉን ማጋለጥ ነው።
ምዕራፍ 7 እና 8 ውስጥ ዳንኤል ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ሲናገር “ታናሽ ቀንድ” ብሎ ይጠራዋል። ቀንድ የኃይል ተምሳሌት ነው። የቫቲካን ከተማ በምድር ላይ ካሉ መንግስታት ሁሉ ታናሽ መንግስት ናት፤ ዜጎቿም ከ800 በታች ናቸው፤ ግዟቷም 1 ኪሎ ሜትር ካሬ ብቻ ነው። ሆኖም ግን ቫቲካን የዓለም አቀፍ ሐይማኖታዊ ስልጣን ማዕከል እና በምድር ላይ ካሉ ድርጅቶች ሁሉ አንደኛ ሃብራም ድርጅት ናት። ለዚህ ነው ሰይጣን በስተመጨረሻ ከሰማይ ሲባረር ቀጥታ ዓይኑን ቫቲካን ላይ የሚያሳርፈው። ከዚያ በኋላ የፖፕ ስልጣን ነጥቆ በሚይዘውና ራሱን ዳግማዊ ጴጥሮስ ብሎ በሚጠራው በአመጽ ሰው ውስጥ ሰይጣን ይገባበታል። ስለዚህ “ታናሹ ቀንድ” ማለት በታናሽዋ በቫቲካን ከተማ የምትመራው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ናት። በአሁኑ ዘመን ፖፑ አውሮፓ ውስጥ ብቸኛው አምባገንን ወይም ፈላጭ ቆራጭ ነው።
ዳንኤል 9፡26 … ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።
በስተመጨረሻ የክርስቶስ ተቃዋሚ የሁሉን ድጋፍ ያገኛል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን እውቅና በሰጠ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ምክር ቤት አባላት ድምጽ ሲሰጡ 128 ለ9 የትራምፕን ሃሳብ ተቃወሙ።
ስለዚህ ሃገሮች ሁሉ በእሥራኤል ላይ በጠላትነት እየተሰባሰቡ ነው።
ሕዝቅኤል 38፡16 ምድርንም ትሸፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። በኋለኛው ዘመን ይሆናል፥ ጎግ ሆይ፥ በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
በስተመጨረሻ እሥራኤልን ሊወጋ የሚነሳው የመጨረሻውን የሮማ ፖፕ ለመደገፍ የዓለም ሕዝቡ ሁሉ ተንጋግቶ ይሄዳል።
በዚሁ የታላቅ መከራ ዘመን ውስጥ ሙሴ እና ኤልያስ የተባሉ ሁለት ነብያት 144,000ዎቹን አይሁዶች ለመጠበቅ የተፈጥሮ ኃይላትን ያስቆማሉ።
ሕዝቅኤል 38፡22 በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።
ስለዚህ በአይሁዶች እና በመጨረሻው የሮማ ፖፕ መካከል የሚሆነው ጦርነት ብዙ ጥፋትና ውድመት የሚሆነበት ጦርነት ነው።
ዳንኤል 9፡27 እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።
“እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል።” እግዚአብሔር ለአይሁዶች ኢየሱስ ሰባት ዓመታት ያህል እንዲያገለግላቸው ቃል ገብቷል።
“በሱባዔውም እኩሌታ መስዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል። ”
የ7 እኩሌታ 3½ ነው።
በሰባቱ ዓመታት አጋማሽ ላይ ኢየሱስ ይገደላል። በሌላ አነጋገር ለ3½ ዓመታት በአገልግሎት ያሳልፋል ማለት ነው።
የቤተመቅደሱ መስዋእቶች እና አምልኮ ሁሉ ዋጋ ያጡት የዚያን ጊዜ ነው።
የቤተመቅደሱ መጋረጃ ተቀደደ።
በሕግ እና የሕግን ሥራ በመፈጸም ላይ ተመስርቶ የነበረው የብሉይ ኪዳን ዘመን ተዘግቶ በተጻፈው ቃል እንዲሁም በመጽፍ ቅዱስ ውስጥ በተመሰከረላቸው የክርስቶስ ሥራዎች ላይ የተመሰረተው በእምነት የሆነው የጸጋው ዘመን ተጀመረ።
ስለዚህ ኢየሱስ ያገለገለው ለ3½ ዓመታት ነው።
አይሁዶች ያልተጠቀሙበት 3½ እስከ አሁን ድረስ ቀርቶላቸዋል። ይህ ቀሪ ጊዜ የታላቁ መከራ ዘመን ይሆናል።
በእነዚህ በሰባቱ ዓመታት ውስጥ ባሉት ሁለት ክፍለ ጊዜዎች መካከል ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ገብተዋል።
የበዓለ ሃምሳ ዕለት መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ለማስጀመር ወረደ፤ ከዚያም መንፈስ ቤተክርስቲያንን ወደ ሰማይ በሚነጥቃት ጊዜ ተመልሶ ወደ ሰማይ ይሄዳል። የዚያን ጊዜ ታላቁ መከራ ይጀምራል።
የመጀመሪያው ዝናብ የትምሕርት ዝናብ ነው፤ በዚህም ወቅት ወንድም ብራንሐም የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት ሊገልጥ መጣ። ይህ ወቅት የጀመረው በ1947 እርሱ ስብከቶቹን በቴፕ ድምጽ ቀርጾ ሲያስቀምጥ ነው።
ከ1966 ጀምሮ እነዚህን ስብከቶች በቴፕ ስናዳምጥ ወይም በመጻፍት ወይም በኢንተርኔት እያነበብን ትምሕርቶቹን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ወስደን መረመርን ስንችል እርሱ በ1965 ከዚህ ዓለም በሞት ቢሰናበትም እንኳ ሰባተኛው መልአክ ድምጹ በሚሰማበት ዘመን ውስጥ ኖረናል ማለት ነው።
መከር ማለት ፍሬው ከተክሉ ላይ የሚታጨድበት ጊዜ ነው።
የመከሩ ዝናብ ወይም የኋለኛው ዝናብ በክርስቶስ ሆነው ያንቀላፉት ወይም የሞቱት በትንሳኤ ጊዜ ከመቃብራቸው በሚወጡ ጊዜ ነው የሚጀምረው፤ የሚያበቃው ደግሞ ከ40 ቀናት በኋላ ሙሽራየቱ ሙሉ በሙሉ ከምድር ተነጥቃ ወደ ሰማይ ስትገባ ነው።
በእነዚያ 40 ቀናት ውስጥ ሰባቱ ነጎድጓዶች በሕይወት ያለችውን ሙሽራ አባላት አካላቸውን ወደ ማይበሰብሰው አካል እንዴት እንደሚለውጡ ያስተምሯቸዋል። በማይሞተው አካል ውስጥ ሆናችሁ ብቻ ነው ለመነጠቅ የሚያስፈልጋችሁን እምነት የምትቀበሉት። አሁን የለበስነው ስጋ መነጠቅ አይችልም።
የመጀመሪያው ዝናብ እና የኋለኛው ዝናብ ለአንድ ወር ያህል ቀኖቻቸው ይደራረባሉ፤ ይህም ጊዜ በሕይወት ያሉት የሙሽራይቱ አካላት ለመነጠቅ የሚያበቃቸውን እምነት ይቀበሉ ዘንድ የሚማሩበት ወቅት ነው።
ኢዩኤል 2፡23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።
ፍጥረታዊው ኋለኛ ዝናብ እሥራኤል ውስጥ የሚዘንበው ከመከር ወቅት ቀደም ብሎ መጋቢት እና ሚያዚያ ውስጥ ነው።
የኢየሱስን የአገልግሎት ዘመን ርዝመት አስቡ።
ኢየሱስ ወደ 29 ዓ.ም ማለቂያ አካባቢ ተጠመቀ።
የሞተው ደግሞ በ33 ዓ.ም የፋሲካ ሰሞን ማለትም ሚያዚያ ውስጥ ነበር።
የ 3 ዓመታት አገልግሎት ለማገልገል በምድር ላይ ለአራት የፋሲካ በዓላት መቆየት ያስፈልገዋል።
ዮሐንስ ግን መጋቢት/ሚያዚያ ውስጥ የሚከበሩ ሶስት የፋሲካ በዓሎችን ብቻ ነው የዘገበው።
ዮሐንስ 2፡13 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
(የመጀመሪያው ፋሲካ ኢየሱስ እያገለገለ በነበረ ወቅት ነው)
ዮሐንስ 5፡1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
ዮሐንስ 6፡4 የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።
ዮሐንስ 13፡1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥
ዮሐንስ 2፡13 የመጀመሪያው ፋሲካ ሲሆን የተከበረውም መጋቢት አጋማሽ አካባቢ በ30 ዓ.ም ነው።
ከዚያ በኋላ በዚያው ዓመት ውስጥ ኢየሱስ ሰማሪያ ውስጥ በሲካር ከተማ አለፈ።
ከሳምራውያን ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ ፍጥረታዊው የመከር ወቅታቸው ሊደርስ አራት ወራት ብቻ እንደቀሩ ይነግራቸዋል።
ዮሐንስ 4፡5 … ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤
ዮሐንስ 4፡35 እናንተ፦ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን?
ስለዚህ ኢየሱስ ሲካር ውስጥ የነበረው መች ነው?
የአይሁዶች ዓመት ሁለት ሁለት ወር ጥንድ እየተደረገ በስድስት ክፍለ ጊዜዎች የተከፋፈለ ነበር። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው እና የሚያበቃው በወሩ አጋማሽ ነበር።
ክረምት | ጸደይ | መከር | በጋ | ከባድ ሙቀት | ዘር የመዝራት ወቅት |
ታህሳስ፣ ጥር | የካቲት፣ መጋቢት | ሚያዚያ፣ ግንቦት | ሰኔ፣ ሐምሌ | ነሐሴ፣ መስከረም | ጥቅምት፣ ሕዳር |
ፋሲካ | ጴንጤ ቆስጤ | የዳስ በዓል | |||
የቂጣ በዓል | የስርየት ቀን | ||||
በኩራት | መለከት | ||||
3 በዓላት | 1 በዓል | 3 በዓላት |
ሰንጠረዡ ውስጥ ማየት እንደምትችሉት አይሁዶች በዓመት ሶስት ጊዜ ነበር በዓላት የሚያከብሩት።
ዘጸአት 23፡17 በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።
ኢየሱስ ሲካር ውስጥ ሳምራውያንን ሲያናግራቸው የሚያዚያ አጋማሽ ላይ የሚጀምረው መከር ሊደርስ አራት ወራት ቀርተዋል አለ።
ከሚያዚያ አጋማሽ አራት ወራት ወደ ኋላ ቀደም ብለን ስንቆጥር የታህሳስ አጋማሽ ላይ እንደርሳለን።
ስለዚህ ዮሐንስ ምዕራፍ 4 ውስጥ ኢየሱስ በታህሳስ ክረምት ወቅት ነበር ወደ ሲካር የሄደው።
ከዚህም የተነሳ የቀጣዩ ዓመት በዓላት በሙሉ ገና ከፊቱ ነበሩ።
ፋሲካ የመጀመሪያው በዓል ነው።
ስለዚህ ዮሐንስ 5፡1 ላይ የተጠቀሰው በዓል ስለ ሌሎቹ በዓላት ከሆነ ያለ ጥርጥር ከፋሲካ በዓል በኋላ ካሉት በዓላት አንዱ ነው። ስለዚህ የዮሐንስ 5፡1 በዓል ከመከበሩ በፊት የፋሲካ በዓል ተከብሮ ነበር ማለት ነው።
ከዚህ ተነስተን የዮሐንስ ወንጌል በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አራት ፋሲካዎችን መዝግቧል ማለት እንችለለን።
ፋሲካ በመጋቢት አጋማሽ ወይም ሚያዚያ አጋማሽ ውስጥ ነው የሚከበረው፤ ማለትም አዲስ ዓመት ከገባ በ3ኛው ወይም በ4ኛው ወር።
ስለዚህ ኢየሱስ የተጠመቀው አሮጌው ዓመት ከማለቁ 2 ወይም 3 ወራት በፊት ማለትም ጥቅምት አጋማሽ አካባቢ ነው።
አገልግሎቱ የፈጀው ሙሉ ጊዜ ዳንኤል እንደተናገረው 3½ ዓመታት ነበር።
ቃልኪዳኑን ማጽናት ማለት ምን ማለት ነው?
ሮሜ 15፡8 ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ … ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ።
እግዚአብሔር ለአይሁዶች የተስፋ ቃሎች ሰጥቷቸው ነበር ነገር ግን እነዚህ የተስፋ ቃሎች ጽኑ ቃል አልተደረጉም።
ገላትያ 3፡17 … አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን
ቃልኪዳን “ከመጽናቱ” በፊት መጀመሪያ የቃልኪዳን ስምምነት “ይደረጋል”።
እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከፍጥረታዊ ዘሩ (ይስሐቅ እና አይሁዶች) ጋር ቃልኪዳን አደረገ
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔት በቀራንዮ ከአብራሐም መንፈሳዊ ዘር ማለትም ከክርስቶስ ጋር በቀራንዮ ቃልኪዳኑን አጸናው።
ሶስት እንስሳት ተሰንጥቀው የተሰነጠቁት የእንስሳቱ አካላት ፊት ለፊት ተደርገው ተቀመጡ።
ይህም ከዲ.ኤን.ኤ ወይም ከፍጥረታዊ ሕይወት ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት አለው፤ ዲ.ኤን.ኤ ውስጥ ሁለት ሰንሰለቶች እንደ እስፕሪንግ ተደርገው እርስ በራሳቸው ይጠመጠማሉ፤ ከተጠመጠሙ በኋላ በአራት ማያያዣዎች ይያያዛሉ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ጂ፣ ሲ፣ ኤ፣ እና ቲ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል (ጉዋኒን፣ ሲስቶሲን፣ አዲናይን፣ እና ታያሚን)።
ይህንን የዘላለም ሕይወት ቋንቋ ከሆነው ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ጋር አነጻጽሩ።
አረንጓዴው እና ሰማያዊው የዲኤንኤ ሰንሰለቶች በአንድ ላይ የጠመጠሙትን ወይም በጥብቅ የተሳሰሩትን አዲስ ኪዳንን እና ብሉይ ኪዳንን ይወክላሉ። አዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይገኛል። ብሉይ ኪዳን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ፍጻሜ አግኝቷል። ሁለቱ ኪዳኖች እርስ በራሳቸው የተሳሰሩ ናቸው።
ነገር ግን ሁለቱን ኪዳኖች ያስተሳሰራቸው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ነው። የክርስቶስ አገልግሎት የተገለጠው አዲስ ኪዳን ውስጥ ሲሆን በዚያን ጊዜ እየተፈጸመ የነበረውን ሚስጥር የሚያውቀው ኢየሱስ ብቻ ነበር። ላይ ላዩን ሲታይ ሰይጣን እያሸነፈ በሚመስልበት ሰዓት ኢየሱስ ሰይጣንን እንዴት አድርጎ አጃጅሎ እንደጣለው በሰዓቱ ማንም አልገባውም ነበር።
ስለዚህ አራቱ ወንጌሎች አራቱን የዲኤንኤ ማሰሪያዎች ይወክላሉ።
ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ አራት እንስሳት አሉ።
አንበሳው - ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ ኢየሱስን በ30 ብር ተላልፎ የተሰጠው ንጉስ አድርጎ አሳይቷል። መንግስታት የሚንቀሳቀሱት በቀረጥ ገቢ አማካኝነት ነው። ማቴዎስ ስለ ገንዘብ በደምብ ያውቃል። አስራታችሁን ባትከፍሉ ማቴዎስ አያሳልፋችሁም።
በሬው - ማርቆስ 6፡31 መከራ የሚቀበለው አገልጋይ ኢየሱስ ያለበትን ቦታ እና ከአገልግሎት ብዛት የተነሳሰ ምግብ የሚበላበት ሰዓት እንኳ እንዳጣ ያሳየናል፤ ምክንያቱም ጊዜውን ሁሉ ለአገልግሎቱ ሰጥቷል፤ በተለይም እኛን ለማዳንና ስለ ሐጥያታችን ለመሞት፤ ከዚያም ሐጥያቶቻችንን ይዟቸው ወደ ሲኦል ለመውረድና በዲያብሎስ ላይ ለማራገፍ።
ሰውየው - ሉቃስ ኢየሱስን እንደ ፍጹም ሰው አድርጎ ያቀርብልናል፤ ይህም ፍጹም ሰው እየሞተ የነበረውን ሌባ ያድነዋል፤ የራሱን ሕይወት በዓመጽ ያባከነውን ልጅ ይቅር ይለዋል። ሉቃስ 4፡25-27 ስለ ኤልያስ እና ስለ ኤልሳዕ አሕዛብን ሲያገለግሉ በማሳየት እግዚአብሔር አንድ ቀን ሰው ለሆነው ለኢየሱስ መንፈሳዊ አካሉ የሆነችውን ቤተክርስቲያንን ሊመሰርት ወደ አሕዛብ እንደሚዞር ፍንጭ ይሰጠናል።
ንስሩ - ዮሐንስ ኢየሱስን ከፍጥረታዊ ነገር ይልቅ ለመንፈሳዊ ነገር የበለጠ ትኩረት እንደሚሰጥ እንደ እግዚአብሔር አድርጎ ይገልጥልናል። በዮሐንስ 6፡66 ውስጥ የአውሬው ምልክት ፍጥረታዊ ምልክት አይደለም። ይህ ምልክት በሰዎች የተታለለ አእምሮ ውስጥ የሚደረግ ምልክት ነው፤ በዚያ ዘመን ሰዎች ሰው የሆነውን ኢየሱስን መከተል ሲያቆሙ በአእምሮዋቸው ውስጥ ነው ይህ ምልክት የሚደረገው። ወይም በዚህ ዘመን ደግሞ ሰዎች ኢየሱስን እንደ ተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል መከተል ሲያቆሙ የአውሬውን ምልክት በአእምሮዋቸው ውስጥ ይቀበላሉ።
ዮሐንስ 6፡66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።
ዮሐንስ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ አድርጎ የገለጠበት መንፈሳዊ ወንጌል ነው የጻፈው። በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ማስረጃው ግለሰቡ በተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አማካኝነት እየተመራ ወደ ሙሉ እውነት ሊደርስ መቻሉ ነው።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤
እነዚህ አራት ወንጌሎች በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ያለውን የማዳን እቅድ ይገልጣሉ።
አራቱ ወንጌሎች ለሐዋርያት ሥራ መሰረት ናቸው።
የሐዋርያት ሥራ መንፈስ ቅዱስ ዳግም በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ የሰራቸው ሥራዎች ታሪክ ነው።
አራቱ የልብ ክፍሎች አራቱን እንስሳት ይወክላሉ።
ስለዚህ ንሰሃ የገባ ልብ ኢየሱስ ዙፋን አድርጎ ሊቀመጥበት የሚፈልገው ልብ ነው።
ራዕይ ምዕራፍ 4 ውስጥ ከዙፋኑ ዙርያ በተጨማሪ 24 ሽማግሌዎች አሉ።
እነዚህ ሃያ አራት ሽማግሌዎች 12ቱ የእሥራኤል ነገዶች አባቶች እና 12 ደግሞ ሐዋርያት ናቸው፤ በይሁዳ ቦታ ጳውሎስ ተተክቷል።
እነዚህ 24 ሽማግሌዎች በ24ቱ የሰው የጎድን አጥንቶች ተወክለዋል።
ጌታ ያስተማረን ጸሎት ውስጥ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” የሚል ቃል አለ።
ስለዚህ በሰማይ ወዳለው ዙፋን ልንጠጋ የምንችለው ኢየሱስ በምድር በሰዎች ልብ ውስጥ በሚገዛበት መንግስት አማካኝነት ነው።
የኢየሱስ አገልግሎት በሁለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ግማሽ ክፍሎች ማለትም በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መካከል ነው ያለው።
ይስሐቅን አብራሐም ሊሰዋው በነበረ ጊዜ አንድ በግ ነው የይስሐቅን ሕይወት ያተረፈው።
በጉ እያን ከሁለተኛው ሞት ማለትም ከመንፈሳዊ ሞት ወይም ከእሳት ባሕር ሊያድነን የመጣውን ጌታ ኢየሱስን ይወክላል።
እግዚአብሔር ከአብራሐም እና ከዘሩ ጋር ቃል ኪዳን እያደረገ ነበር።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ … ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ዘፍጥረት 15፡9 እርሱም [እግዚአብሔርም]፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።
ሴት የቤተክርስቲያን ማለትም የአማኞች ስብስብ ተምሳሌት ናት። እውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ትባላለች። ሁለት እንስት እንስሳት ከኢየሱስ ክርስቶስ መስዋእትነት በኋላ ስለሚመጡ ሁለት ሐይማኖታዊ ቡድኖች የሚያመለክቱ ተምሳሌቶች ናቸው።
መጀመሪያ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በዋናነት አሕዛብ ያሉባት ቤተክርስቲያን ለሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ትቆያለች። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በታላቁ መከራ ዘመን ውስጥ ኢየሱስን የሚቀበሉ 144,000 አይሁዶች ናቸው።
ፍየል ክርስቶስን ይወክላል፤ ምክንያቱም ዘሌዋውያን ውስጥ እንደተጻፈው የሕዝቡን ሐጥያት ተሸክሞ ወደ በረሃ እንደሚለቀቀው ፍየል ኢየሱስ የቤተክርስቲያንን ሐጥያት ተሸክሞ ወደ ሲኦል ከወረደ በኋላ ሐጥያታችንን በዲያብሎስ ላይ አራግፎታል።
ዘኁልቁ 19 ውስጥ የተጠቀሰችዋ ጊደር በእሳት ተቃጥላ አመዷ ውሃ ውስጥ ተጨምሮ የሚያነጻ ውሃ ይሰራበታል። አመዱ በታላቁ መከራ ዘመን የሚነሳው እሳት ምሳሌ ነው፤ በዚህም እሳት ውስጥ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር ተለይተው የነበሩ 144,000 አይሁዶች ይገቡና በቃሉ ውሃ ይነጹበታል።
“ሶስት” ቁጥር ላይ ትኩረት የተደረገው ከጨለማው ዘመን ወዲህ እውነት ተመልሳ የምትመጣው በሶስት ደረጃ ስለሆነ ነው።
አምስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም ሰርዴስ በእምነት መጽደቅ የሚለው እውነት በሉተር አማካኝነት የተገለጠበት ዘመን ነው።
ስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም ፊልደልፊያ ታላቁ የወንጌል ስብከት ዘመን እና የቅድስና እንቅስቃሴ በጆን ዌስሊ የተጀመረበት ዘመን ነው።
ሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም ሎዶቅያ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተመልሶ የመጣበት ጴንጤ ቆስጤያዊ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን የተጀመረበት ዘመን ነው፤ ከዚያም የተጻፈው ቃል ውስጥ የተሰወሩ ሚስጥራት በዊልያም ብራንሐም ተገልጠዋል።
የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን (የኤፌሶን) ሙሉ እውነት በ2ኛው፣ በ3ኛው እና በአራተኘው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደሚክረው የጨለማ ዘመን ውስጥ እየጠለቁ በገቡ ቁጥር ደብዝዞ ጠፍቷል። እነዚህ አራት የቤተክርስቲያን ዘመናት ራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ ሐዋርያት ከመሰረቷት የመጀመሪያ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ትምሕርት እየራቁ እንደሚሄዱ ተገልጧል።
ከዚያም በ5ኛው፣ በ6ኛው፣ እና በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ወደ መጀመሪያው የአዲስ ኪዳን እውነቶች ይመልሳታል።
እነዚህ ሶስት የቤተክርስቲያን ተሃድሶ ዘመናት ራዕይ ምዕራፍ 3 ውስጥ ተገልጸዋል።
የ”3 ዓመት” መስዋእቶች ላይ ትኩረት የተደረገበት ምክንያት እግዚአብሔር ሁልጊዜም ቢሆን በጨለማው ዘመን ውስጥ ጠፍቶ የነበረውን የመጀመሪያውን የአዲስ ኪዳን እውነት በሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ መልሶ በተሃድሶ ለማምጣት እንዳሰበ ያመለክታል።
እነዚህ ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው፤ ለዚህ ነው በቃልኪዳኑ ውስጥ “ሶስት” ቁጥር ላይ ልዩ ትኩረት የተደረገው። ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ሚስጥራትን መገለጥ በሕይወታቸው ውስጥ ከሁሉ እንደሚበልጥ ነገር ሊመለከቱ ይገባቸዋል።
ዘፍጥረት 15፡10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልከፈለም።
የእንስሳቱ አካላት ለሁለት ከተሰነጠቁ በኋላ ጥቂት ስፋት ካለው ክፍተት ዳር እና ዳር ሆነው ትይዩ ነበር የተቀመጡት። ይህም በሁለቱ ኪዳኖች መካከል የነበረውን ክፍተት ያሳያል፤ በዚያም ክፍተት ውስጥ የነበሩ ክስተቶች በኢየሱስ ቁጥጥር ውስጥ ነበሩ ምክንያቱም በዚያ ጊዜ ውስጥ የተደረገውን ነገር እርሱ ብቻ ነበር የሚያውቀው።
ሁለቱ ወፎች መዳንን እና ፈውስን ይወክላሉ። እነዚህ ሁለት በረከቶች ክርስቶስ በቀራንዮ ከተሰዋበት መስዋእት ሊነጠሉ አይችሉም። ለዚህ ነው ወፎቹ ለሁለት ያልተሰነጠቁት። ክርስቶስ ሊያድነን ከቻለ ሊፈውሰንም ይችላል።
ዘፍጥረት 15፡11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።
የትኞቹም ዲኖሚኔሽናዊ አሞራዎች ክርስቶስ ከሙሽራይቱ ጋር የገባው ቃልኪዳን ውስጥ እድል ፈንታ የላቸውም። ኢየሱስ እንደ ስላሴ፣ ክሪስማስ፣ ያለ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን ራሱን የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ የሾመ ፓስተር ከመሳሰሉ የቤተክርስቲያን ልማዶች ጋር ምንም ሕብረት የለውም (ፓስተር የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን የተጠቀሰው ብሉይ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ስድስት ጊዜ ተወግዟል)።
ስጋው እንስሳቱ ከታረዱ በኋላ ቆዳቸው ተገፍፎ የተቆራረጠ አካላቸው ነው፤ ልክ በዚሁ መንገድ ቤተክርስቲያኖች የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥር ቆራርጠው በመጣል ለመቀበል እምቢ ይላሉ። የተጻፈውን ቃል የሚወዱ ንስሮች ብቻ ናቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ማስተዋል የሚያገኙት፤ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት ያስችላቸው ዘንድ የወንድም ብራንሐምን ጥቅሶች መጠቀም እንዲችሉ ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ የመጣው ሰዎች በእርሱ እና በንግግሮቹ አማካኝነት ሰዎች ኢየሱስን ማየትና ማግኘት እንዲችሉ ለመርዳት ነው።
ዮሐንስ 1፡6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
ዮሐንስ 1፡7 ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።
ወንድም ብራንሐም የተናገረው ንግግር መጽሐፍ ቅዱስ ውጥ የተጻፈውን ቃል መሆኑን ማየት እስከምንችል ድረስ ከእርሱ ንግግ የተወሰዱትን ጥቅሶች ልብ ብለን መመልከት አለብን። አንድ ትምሕርት እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉ አያይዘን ማየት አለብን።
ዮሐንስ 1፡8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።
የዊልያም ብራንሐም ንግግሮች የእግዚብሔር ቃል አይደሉም።
የዊልያም ብራንሐም ንግግሮችን በእግዚአብሔር ቦታ ተክተን መቀበል የለብንም።
የዊልያም ብራንሐም ንግግሮች ዓላማቸው የአንድን አስተምሕሮ መገለጥ ለማግኘት እንዲረዱን ነው፤ ከዚያ በኋላ ይህንን እውነት ከአንድ ጥቅስ ወደ ሌላ ጥቅስ እየተዘዋወርን በምናጠና ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልዩ ልዩ ስፍራዎች ላይ ልናየው እንችላለን። እያንዳንዱ አስተምሕሮ ዘፍጥረት ውስጥ ይጀምርና በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ውስጥ አልፎ ዮሐንስ ራዕይ ላይ መጠናቀቅ አለበት።
ኢሳይያስ 28፡10 ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።
ማቴዎስ 24፡28 በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።
ቤተክርስቲያኖች የተገለጡትን የእግዚአብሔር ቃል ሚስጥራት አንቀበልም ይላሉ፤ የዘመን መጨረሻ ንስሮችን የሚስቧቸው ግን እነዚህ ሚስጥራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን መከተል የማይፈልጉ አሞራዎች ይባረራሉ፤ ምክንያቱም ሃሳባቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አያይዘው ማሳየት አይችሉም።
ዘፍጥረት 15፡12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤
ፀሃይም በገባች ጊዜ። የሰባተኛው ቤተክርስቲያን ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው ዘመን ነው።
ከባድ እንቅልፍ የሞት ተምሳሌት ነው። በተጨማሪም አብራሐም ምንም አቅም እንዳልነበረው ያመለክታል። አብራሐም ቃልኪዳኑ እንዲፈጸም የማድረግ ምንም ኃይል የለውም። የሰው ሥራ እና ጥረት ጊዜ ማባከን ብቻ እንጂ ምንም አይፈይድም።
ኢየሱስን ስለ ዘመን ፍጻሜ ሲጠይቁት እንዲህ ብሎ መለሰ፡-
ማቴዎስ 24፡4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ሰዎች በጣም ራስ ወዳዶች ነን፤ አስተዋይ የሆንን ይመስለናል፤ ስለዚህ በቀላሉ እንታለላለን።
ሉቃስ 17፡10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።
“የማንጠቅም”።
እግዚአብሔርን ለማገልገል ባለን አቅም ሁሉ ጥረት ብናደርግም ከምናለማው ይልቅ የምናጠፋው ይበዛል።
ስለዚህ ለእግዚአብሔር ኪሳራ ነን። እርሱም ያበላሸናቸውን ነገሮች ሁሉ በማቅናት ብዙ ጊዜ ያሳልፋል። እኛ ግን ባለማወቅ እንዴት አስደናቂ ሰዎች እንደሆንን እያወራን እንኮራለን።
እግዚአብሔር ሎዶቅያውያንን እንዲህ ብሎ ተናገረ፡- ራዕይ 3፡17 “…ዕውርም… መሆንህን ስለማታውቅ”።
እግዚአብሔር አብራሐምን ከባድ እንቅልፍ ያስተኛው እንቅፋት እንዳይሆ ብሎ ነው። እግዚአብሔር ብቻ ነው ቃልኪዳኑን መፈጸም የሚችለው።
“ድንጋጤ እና ታላቅ ጨለማ” ይህ በሐጥያት እና በአለማመን ጨለማ ውስጥ የመሞት ድንጋጤ ነው።
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
እግዚአብሔር የምሽቱ ሰዓት ላይ ትኩረት ሰጥቶበታል፤ እርሱም የሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን መጨረሻ፤ ዛሬ የምንኖርበት የጨለማ እና አሳሳቾች የበዙበት ዘመን ነው።
ሰባተኛዋ ቤተክርስቲያን ከኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ እየራቀች ስትሄድ ፀሃይ ገባች፤ ምድርም በሙሉ በጨለማ ተዋጠች።
በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከሁሉም ከባዱ ዘመን አሁን ያለንበት ነው። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ሐዋርያት ስለነበሩ ጥሩ መሰረት ጣሉ።
ወንድም ብራንሐም ከሞተ ከሃምሳ ዓመታት በኋላ የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ስሕተቶቸ ሊያሳስቱን ተሰብስበው መጥተውብናል። አሁን የምንኖርበት ዘመን ኢየሱስ አጽንኦት ሰጥቶ የተናገረበት የመጨረሻው ዘመን ማለቂያ ነው።
ስለ ቤተክርስቲያን የተነገሩ ትንቢቶች እና ምሳሌዎች በሙሉ በዘመን መጨረሻ ይገስጹናል
ሉቃስ 18፡8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
እምነት የሚመጣው ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ዛሬ ግን ኪንግ ጄምስ ቨርዥን ፍጹሙ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚቀበሉ በጣም ጥቂት ናቸው።
ብዙ ሰዎች የተወሰነ ጥቅሶችን ይቀይራሉ ወይም ትክክል አይደሉም ብለው ይከራከራሉ።
በተፈጥሮ ይህ አይነቱ አካሄድ “ጄኔቲክ ሞዲፊኬሽን” ይባላል፤ እርሱ የብዙ ነገሮች ብልሽት መነሻ ነው።
ዘፍጥረት 15፡17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፤ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።
ከባድን እንቅልፍ በሞት እና በሐጥያት ጨለማ ውስጥ ያሉ አስፈሪ ነገሮችን ሁሉ ይወክላል። ይህ ጢስ ከሲኦል እቶን እሳት ውስጥ የሚወጣ ድቅድቅ ጭስ ነው። ሁላችንም ሞትን እንጠላለን ምክንያቱም ሞት የሐጥያታችንን ዋጋ መክፈል የምንጀምርበት ጊዜ ነው።
ነገር ግን ተስፋ አለ።
በተሰነጠቁት መስዋእቶች መካከል የሚያልፈው የነበልባል ብርሃን።
በመሃል ያለፈው ነበልባል ምንድነው?
የዓለም ብርሃን የሆነው ታላቁ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ከስጋው ውስጥ ወጣ፤ ኢየሱስም በአዲስ ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን መካከል ወደ ሲኦል ወርዶ ሰይጣንን፣ ሞትን፣ እና ሲኦልን አሸነፈ።
እዚያ ብቻውን ሆኖ በሚጨሰው የሲኦል እቶን እሳት ውስጥ እኛን የማዳን ሥራውን አጠናቆ በሶስተኛው ቀን እሑድ ዕለት ከሙታን ተነሳ። የወንጌል ብርሃን እሑድ ዕለት ምድር ላይ በራ። “ኢየሱስ ተነስቷል። ሞት ተሸንፏል”።
እሑድ እሑድ መድረክ ላይ ቆመን ኢየሱስ መነሳቱን በደስታ ስናውጅ የበኩራቱን ፍሬ እንወዘውዛለን፤ ምክንያቱም ከሙታን የመጀመሪያ ሆኖ የተነሳው እርሱ ነው። ከዚያም የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ከእርሱ ጋር አስነሳቸው።
ዘሌዋውያን 23፡10 የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
11 እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው።
ሰንበት ቅዳሜ ነው። በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ያለው ቀን እሑድ ነው።
እሑድ ዕለት በሕዝቡ ፊት ኢየሱስን መወዝወዝ አለብን። በሕይወታችን ውስጥ ሐጥያትን እና አለማመንን ሊያሸንፍ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። ስለ ሰዎች መመካት የለብንም። ስለ መሪያችን መመካት የለብንም። ስለ ቤተክርስቲያኖ መመካት የለብንም። ስለ ገንዘብም መመካት የለብንም።
መመካት ያለብን ኢየሱስ ስላደረገው ሥራ ብቻ ነው። ምክንያቱም ያኔ እርሱ የሰራውን ሥራ ዛሬም ከዚያ የበለጠ መስራት ይችላል።
ዘፍጥረት 15፡18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤
ቃልኪዳን የተደረገው ከአብራም ጋር አይደለም። ከአብራም እና ከዘሩ ጋር ነው።
ፍጥረታዊው ዘር ይስሐቅ እና አይሁዶች ናቸው፤ እነርሱም የተስፋይቱ ምድር የተባለች ግዛት ተሰጠቻቸው።
የአብራሐም መንፈሳዊ ዘር ክርስቶስ እና ከክርስቶስ መንፈስ ዳግመኛ የተወለዱ ማለትም እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ናቸው
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው።
የተስፋ ቃላችን መንፈስ ቅዱስን መቀበል ነው። ምድራችን የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ይህ ተስፋ ለልጆቻችን ጭምር ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የመጽሐፍ ቅዱስን ሚስጥራት ለመረዳት ያስችለናል።
እሥራኤል በግብጽ (በዓለም) እና በባቢሎን (የቤተክርስቲያኖች ዲኖሚኔሽናዊ ስርዓት) መካከል የምትገኝ ምድር ናት
መንፈሳዊ እሥራኤል ማለትም እውነተኞቹ አማኞች በባህርይ እና በአለባበስ ዓለማዊ እንዲሆኑ አይፈቀድም።
እውነተኛዋ ቤተክርስቲያንም ከፖለቲካ፣ ከአሕዛብ ልማዶች፣ እና ከሰው ሰራሽ እምነቶች እና ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያኖች ጋር ንክኪ ሊኖራት አይገባም።
ዛሬ ክርስቲያኖች በብልጽግና ወንጌል ትምሕርት ተጠምደዋል። እምነታቸውን በባንክ ሒሳባቸው ነው የሚመዝኑት።
ሉቃስ 6፡24 ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥
ማቴዎስ 19፡24 ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።
በእስያ ያሉት 7 ቤተክርስቲያኖች ለዘመናቸው በተገለጠላቸው የእግዚአብሔር ቃል የሚኖሩትን ሰባቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ።
ቃሉን ለሰዎች እንዲገልጥ እግዚአብሔር ስለ መንፈስ ቅዱስ ተስፋ ሲሰጥ እንዲህ ብሏል።
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤
በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ማረጋገጫ የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራት የመረዳት ችሎታ ነው እንጂ በራስ ወይም በመሪ መመካት አይደለም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከአብራሐም ጋር አድርጎ የነበረውን ኪዳን በክርስቶስ አጸናው።