ትራምፕ የ2016ን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፈው ለምንድነው?



እግዚአብሔር የአረቡን ዓለም ተጋፍጦ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እውቅና የሚሰጥ ፕሬዚዳንት ይፈልግ ነበረ።

First published on the 14th of October 2018 — Last updated on the 5th of November 2022

ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለምን አሸነፈ?

ይህንን ጉዳይ እንደማንኛውም ሰው በፍጥረታዊ አእምሮ ብቻ ከማሰብ ከበስተጀርባው ምን አይነት መንፈሳዊ ሚስጥር ይኖር እንደሆን እንመልከት፡፡

ታላላቅ ክስተቶች ሰዎች በሚያስቡት ወይም በሚፈልጉት ነገሮች ላይ የተመሰረቱ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ነገሮችን በራሱ መንገድ ነው የሚያደርገው፡፡

ሴፕቴምበር ኢለቭን መንትዮቹ ሕንጻዎች የፈርሱበት እለት ለአሜሪካ ነገሮች የተለዋወጡበት የአደጋ ቀን ነበር፡፡ አሜሪካ የወሰደችው የበቀል እርምጃም ብዙ ዋጋ እና ከፍተኛ ውድመት የሚያመጡ ጦርነቶች በአፍጋኒስታንና በኢራቅ እንዲደረጉ ምክንያት ሆኗል፡፡

11/9 በአሜሪካ የድምፅ አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ እጅግ ያልተጠበቀና አስደናቂ ለውጥ የታየበት እግዚአብሔር እኛ ከምናስበው እጅግ በተለየ መንገድ መስራት መጀመሩ የታየበት ቀን ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን በደጅ ነውን?

ከ27 ዓመት በፊት በዚሁ ቀን አንድ ዝቅተኛ የሥልጣን እርከን ላይ የሚገኝና የበርሊን ግምብ በር ቁልፎችን በኃላፊነት የያዘ ሰው በዚያን ምሽት አለቆቹ በቤታቸው ስላልነበሩ ወይም ስልኮቻቸውን ስለማያነሱ በሩን በመክፈት በሰራው ስህተት ምክንያት የበርሊን ግምብ ባልተጠበቀ መንገድ ሊወድቅ ችሏል፡፡

ስለዚህ ያልተጠበቀ ነገር ሊሆን እንደሚችል መጠበቅን መለማመድ አለብን፡፡

በሕይወት መቆየት ከፈለግን መማር፣ በፊት የተማርነውን ስሕተት ማስወገድ እና እንደገና መማር ያስፈልገናል፡፡

የኤክስፐርቶች አስተያየት የነገረን በሙሉ ረብ የለሽ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለሚያስበው ነገር ምንም ፍንጭ የላቸውም፡፡

ብዙ ክርስቲያኖችም በጣም ተሞኝተው ኤክፐርቶቹ የሚሉትን ሲያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖችም የእግዚአብሔር ሃሳብ ምን እንደሆነ አንዳች አያውቁም፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ብዙ እውነት ብለን የተቀበልነውን ስሕተት ከአእምሮዋችን ማስወገድ ያስፈልገናል፡፡

መሪዎቻችንን የነገሩንን የተሳሳተ አመለካከት ኮርጀን ከማውራት ይልቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነቱን እንደገና አጣርተን የመማር ወኔ አለን ?

እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ሁሉን የሚጠቀልል ፍጹም ፈቃድ አለው፡፡ በዘመን መጨረሻ ሊፈጽም ስለሰበው ሃሳቡ ሃገራትንና ሕዝቦችን በሚፈልገው አቅጣጫ እያሰለፋቸው ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ በሰዎች ታሪክ ውስጥ እንደ ወንዝ በመፍሰስ ዓለምን ወደ ዳግም ምፅአቱና ወደ ታላቁ የመከራ ይዞ ይሄዳል፡፡

እግዚአብሔር ይህንን ለንጉስ ናቡከደነፆር እጅግ በግልጽ ነግሮታል፡፡

 

ዳንኤል 4፡32 ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፤ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል አለው።

ሰዎች የራሳቸውን ሃሳብ በማራመድ ቢጠመዱም እንኳ እግዚአብሔር የራሱን ዕቅድ ለማስፈጸም የሚሆኑትን ትክክለኛዎቹን ሰዎች በሥልጣን ላይ ያስቀምጣል፡፡

አብርሃም (አስቀድሞ አብራም ተብሎ ይጠራ የነበረው) የወንድሙን ልጅ ለማስጣል ብሎ ነገስታትን ገድሏል፡፡ በጦርነቱ ያገኙትን ምርኮ በሚካፈሉበት ወቅት ኤስኮል ድርሻውን እንዲወስድ አብራሃም ጠይቋል፡፡

 

ዘፍጥረት 14፡22 ፤ አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፡- ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤
23፤24፤ አንተ፡- አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፤ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።

 

እግዚአብሔር የፍልስጤምን ምድር ለአብርሃም በተስፋ ቃል ሰጥቶታል። ሮማውያን የአይሁድን ቤተመቅደስ በ70 ዓ.ም ካወደሙ በኋላ በ135 ዓ.ም አይሁድን አባረሩ፡፡ በ1948 የተባበሩት መንግስታት እግዚአብሔር ለአብርሃም ከሰጠው ግዛት ውስጥ ሦስት አነስተኛ ክፍሎችን ብቻ መልሰው ለአይሁድ ሰጧቸው፡፡ እስራኤል ግብፅን፣ ሶሪያንና ዮርዳኖስን በ1967 የስድስቱ ቀን ጦርነት እስካሸነፈችበት ጊዜ ድረስ የግብጹ ፕሬዝዳንት ናስር እስራኤልን እንደሚያጠፋት ሲዝት ነበር፡፡ በጦርነቱ ድል አድራጊዎች በመሆናቸው ከጦርነቱ በኋላ አሁን እንደአዲስ የያዙትን ግዛት በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማዋል ይችሉ ነበር፡፡ አሸናፊ እንደመሆናቸው ይህንን ክፍል የመውሰድ መብት ነበራቸው፡፡ ፕሬዝዳንታቸውም ሊቫይ ኤስኮል ነበር፡፡

በአብርሃም ጥያቄ መሠረት የመጀመሪያው ኤስኮል ከ4000 ዓመታት በፊት ድርሻውን እንደወሰደ ሁሉ ታሪክ ራሱን ሲደግም የአብርሃም የልጅ ልጅ ፕሬዝዳንት ኤስኮል ድርሻውን በዚህ ዘመን ወሰደ፡፡ አይደሁድ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ አንድም እንኳ ሌላ ሃገር ይህን ያህል ጥንታዊ የሆነ ትስስር አለኝ ማለት አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠውን ግዛት እስከዛሬ ድረስ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ ስለዚህ ዛሬም እስራኤልን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፡፡

 

ዘኍልቍ 24፡5 ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ!
ዘኍልቍ 24፡9 የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተገመ ይሁን።

 

ሁላችንም ልብ ማለት አለብን፡፡ እግዚአብሔር ይህንን የተስፋ ቃል እስከ ዛሬ ድረስ አልረሳውም፤ እንደውም ይህ የተስፋ ቃል ትንቢት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የመን ምንም ጥቅም በሌለው የእርስ በእርስ ጦርነትና የአሸባሪዎች ጥቃት ራስዋን በማውደም ላይ ትገኛለች፡፡ የመን ከእሥራኤል በጣም ርቃ የምትገኝ ሃገር ብትሆንም በ1948 እስራኤል እንደ ሃገር በተመሰረተች ጊዜ እስራኤልን ለማጥቃት ወይም ለመውጋት፣ የአይሁድን ሕዝብ ለማጥፋትና ምርኮ ለመካፈል በአንድ ጐራ ከቆሙት ሰባት ሀገራት መካከል የመን አንዷ እንደነበረች ረስተዋል፡፡ የመን እስራኤልን ረገመች፤ ስለዚህ አሁን ከእርግማን በታች ትኖራለች፡፡

እያንዳንዳችን በጌታ ከዳንን በኋላ ለራሳችን በሚበጅ መንገድ ወዳመቸን የራስ ወዳድነት አቅጣጫ ለመዋኘት በምንችልበት ትንዬ የነጻ ምርጫ ወይም ነጻ ፈቃድ ኩሬ ውስጥ ተመችቶን እንቀራለን፡፡ ይህ ደግሞ በመሰረቱ ወደ ታላቁ መከራ በስተቀር ወዴትም የማይወስድ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማስደሰት ብንፈልግ የራሳችንን ትናንሽ የግል ምርጫዎች ወደ እግዚአብሔር ትልቅ ዕቅድ ውስጥ ማስገባት አለብን፡፡ ይህንን ደግሞ የምናገኘው በተጻፈልን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቃድ ከእኛ ሃሳብ ተቃራኒ እንደመሆኑ እየተነጫነጭንና እየተቃወምንም ቢሆን ባልጠበቅነውና ልንሄድበት በማንፈልገው አቅጣጫ ይዞን ይሄዳል፡፡ ግን ያን ጊዜ ብቻ ነው በእውነት የእግዚአብሔርን ሃሳብ አገለገልን የሚባለው።

ለዚህ ነው ለራሳችን መሞት ያለብን፡፡ ለውጥን በተመለከተ የምናጉረመርም ከሆነ እኔነታችን አልሞተም ማለት ነው፡፡ ለራሳችን ብንሞት እግዚአብሔር የሚፈልገውን በእኛ ለመስራት በቀላሉ በመንገዱ ሊመራን ይችላል፡፡

ለምሳሌ የቀሬናው ስምዖን የተፈረደበትን ሰው መስቀል እንዲሸከም በመገደዱ ተበሳጭቶ ነበር፡፡ በኢየሱስ ደም «በመበከሉ» ከዚያ ወዲያ በአይሁድ የፋሲካ በአል ላይ መካፈል አይችልም ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ሳያውቅ የፋሲካ በዓል በዚያው ሰዓት ውስጥ በሚሻል ኪዳን የሚተካበት ሒደት ውስጥ ነበር፡፡ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ከራሱ ፈቃድ ውጭ በሆነ መንገድ ለአጭር ጊዜ የማይፈልገውን በማድረግ እንዲሁም ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እንኳን ምንም ሳይረዳ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ አካል ሆኗል፡፡ እኛ ሰዎች ለራሳችን እንደሚመስለን ያህል ብልህ አይደለንም፡፡ ስምዖን ምን ውስጥ እየተሳተፈ እንደሆነ ባያውቀውም እንኳ የእውነተኛው ፋሲካ የመጀመሪያ ተካፋይ ለመሆን በቅቷል፡፡ ስለዚህ እኛ ምን እየተካሄደ እንኳን ሳናውቀው እግዚአብሔር ሊጠቀምብን ይችላል፡፡

ኢየሱስን የገደሉት አይሁድ ለሚንቋቸው አሕዛብ ሳያውቁት የመዳንን በር ከፈቱላቸው፡፡

በመሆኑም ከዚህ የምንማረው ትምህርት እግዚአብሔር ከሰው ጥበብ እና ወይም ከብዙሃን አመለካከትውጭ ባልተጠበቀ ሁኔታ ሲሰራ ልናገኘው እንደምንችል ነው፡፡ የዓለም መገናኛ ብዙሃንና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ለሕዝቡ የራሳቸውን ሃሳብ ማስደመጥ በሚፈልጉና ሕዝቡን በራሳቸው አስተሳሰብ መምራት በሚፈልጉ ሃያላን ቡድኖች ሙሉ ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡

በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ውርጫ ውስጥ የሕዝብ አስተያየት ተንታኝ ኤክስፐርቶች የተሳሳቱት ለዚህ ነው፡፡ እነርሱ ያተኮሩት በሕዝብ እና በሕዝብ አመለካከት ላይ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ይህንን ሁሉ ስህተት ማመናቸው ደግሞ የክርስቲያኖችም አመለካከት ምን ያሕል ዋጋ ቢስ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል፡፡ ለሂላሪ ድምጽ የሰጡ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር እና ከሐሳቡ ጋር በጣም ተራርቀዋል፡፡

አዎን፤ ሂላሪ ክሊንተን በጣም ጥሩ ሰው እና ወግ አጥባቂ እንዲሁም የተዋጣላት ፖለቲከኛ ሆና ቀርባለች፡፡ ብሩህ፣ ንቁ፣ ብቁ እና ልምድ ያካበተች ሴት ናት፡፡
አዎን፤ ትራንፕ በብዙ አጋጣሚዎች እራሱ ላይ ሽንፈት ሊያስከትሉበት የሚችሉ ድርጊቶችን ፈጽሟል፡፡ የገዛ ምላሱ ቀንደኛ ጠላቱ ነበረ፡፡ ተራምፕ ተሳዳቢና፣ የመጣለትን የሚናገር ከመሆኑ በላይ ከሂላሪ ጋር ለሚያደርገው ክርክር በአግባቡ እንኳ የተዘጋጀ አልነበረም፡፡

ይህ ሁሉ ግን በስተመጨረሻ ምንም ያመጣው ልዩነት አልነበረም፡፡

ለምን?

እግዚአብሔር በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ አሜሪካ ላይ አይደለም፡፡

አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ለጥፋት የተዘጋጀች ሃገር ነች፤ ከዚያ በፊት ግን ዓለምን ሁሉ ወደ አውሬው ምልክት ትመራለች እርሱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ትምሕርቶችና እምነቶች ስብስብ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስካልሆነ ድረስ ማንኛውም ዓይነት እምነት ሊኖርህ ይችላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በክርስትና ውስጥ ከ30 ሺህ በላይ የሆኑት ልዩ ልዩ ቤተ እምነቶች ሰዎችን በየግላቸው በያዙት እምነት አቅፈው ይመራሉ፡፡ በመካከላቸው ያሉት ልዩነቶች ሁሉ እንዳሉ ቢሆንም እያንዳንዱ ቡድን እኔ ትክክል ነኝ የሚል አቋም ይዟል፡፡ ይህ ክርስትና አይደለም፤ ዝም ብሎ «ቤተክርስቲያናዊነት» ነው እንጂ፡፡ እንዲህ አይነት ቤተክርስቲያኖች የተጻፈውን ቃል ሳይሆን የሰዎችን ወግ እና አመለካከቶች ያምናሉ፡፡ ክርስቲያን ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆኖ የሚኖር ሰው ነው፡፡

ሌላው ቀርቶ «የመልዕክት ሰባኪዎችም» ጭምር ለገንዘብ፣ ለዝናና ለታዋቂነት ካላቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ ስህተትን እያስፋፉ ናቸው፡፡ በ1963 ሰማይ ላይ የታየው ታላቁ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ደመና የጌታ ዳግም ምጻት ነው ይላሉ፤ የዚህም ደመና ምስል አሁን ደግሞ የጌታ መገለጥ እየተባለ በስዕል ይሳላል። ይህ ታላቅ ደመና ከመሬት በ42 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ በራዕይ ምዕራፍ 10 ላይ በባህርና በመሬት ላይ ይቆማል ተብሎ የተጻፈለት የታላቁ መልአክ መገለጥ ፍፃሜ ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ በ20 ማይሎች ያህል የተራራቁ ሁለት ደመናዎች እንደነበሩ አይነግሩንም፡፡ የአደን ወቅት በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት በመሆኑ ደመናው ፎቶግራፍ በሚነሳበት ወቅት ዊልያም ብራንሃም በቦታው ላይ አልነበረም፡፡ የመልዕክት ሰባኪ ቡድኖች ሌሎች ቤተእምነቶች እንደሆኑት ያህል እነርሱም በዚህ ጉዳይ ላይ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርት ርቀው ሄደዋል። የዊልያም ብራንሃምን አባባሎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በላይ ከፍ አድርገዋል፡፡

አብዛኛዎቹ “የመልእክት” ሰባኪዎች ወንድም ብራንሃም ራዕይ አይቶ ከተናገረው ንግግር ደጋግመው እየጠቀሱ እንዲህ ይላሉ፡-

«በአሜሪካ ውስጥ እጅግ ውብና ጨካኝ የሆነች ሴት ትነሳለች (ውብም ጨካኝም የሚሉት ቃላት ሂላሪን አይገልጹዋትም) ሕዝቡንም በሙሉ በሥልጣንዋ ስር ታንበረክካለት»
ይህ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማናሰራራት ሊሆን እንደሚችል አምናለው፤ ግን ደግሞም በሴቶች አብላጫ ምርጫ በአሜሪካ ውስጥ ወደ ታላቅ ሥልጣን የምትወጣ የአንድ ሴት ራዕይ ሊሆን እንደሚችልም አውቃለው።
ሰባቱ የክርስቲያን ዘመናት - ማብራሪያ

አብዛኛዎቹ የመልዕክት ሰባኪዎች አስተዋይ ተደርገው ለመቆጠር ሲጣደፉ ሂላሪ ምርጫውን ታሸንፋለች ብለው ትንቢት ተናገሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በዌብሳይታቸው እንኳ ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ እንደውም በፍጥነት ከዌብሳይታቸው ላይ የለጠፉትን ትንቢት ሰርዘው በቦታው በጭራሽ እንደዚያ አይነት ትንቢት አልተናገርንም ብለው ክደዋል።

«መልዕክት» ሰባኪዎች ስህተት አንሰራም ብለው ያስባሉ፡፡ እንደውም ምስጢራትን ሁሉ እናውቃለን ብለው ያስባሉ፡፡ ሚስጥራትን ሁሉ ሲያውቁ ግን ምርጫውን ማን እንደሚያሸንፍ ብቻ ነው ያለወቁት፡፡ ይህ ሁኔታ የአሁኑን ጊዜ ክስተቶች በተመለከተ ምን ያህል አይናቸው እንደታወረ አጋልጦ አሳይቶባቸዋል፡፡

ዊልያም ብራንሃም በመሠረቱ በራዕዩ ያያት ሴት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደሆነች ያምናል፡፡

ምን አልባትም ሴት ፖለቲከኛ ልትሆን ትችላለች ብሏል፡፡

ነገር ግን ከክስተቱ ቀድሞ ለመተንበይ ሲጣደፉ እና አስተዋይ ለመባል ፈልገው የመልዕክት ተከታዮች ሂላሪ ልትሆን ትችላለች የተባለውን በእርግጥ ድሉ የሂላሪ ነው ወደሚል ትንቢት ለወጡት (ሂላሪ ደግሞ ካቶሊክም አይደለችም)። ይህ የዘህ ዘመን የመልእክት ሰባኪዎች አሳስተው በተረጎሙዋቸውና እምነታቸውን በመሰረቱባቸው ጥቅሶች ላይ ለሚሰብኩት ስብከት አይነተኛ ምሳሌ ነው። በመሆኑም እነዚህ የመልዕክት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ የሳቱ ሲሆን (መሳሳታቸውም እንግዳ ነገር አይደለም) በተመሳሳይ ሁኔታ ሂላሪን በመደገፍ የእግዚአብሔር ሐሳብ ምን እንደሆነ ግንዛቤው እንደሌላቸው ካሳዩት ከቀሪዎቹ ቤተ እምነቶች የተሻሉ አይደሉም፡፡

አብዛኛዎቹ «የመልዕክት» ሰባኪዎች ንስር ነን ይላሉ ግን ብዥ ያለ ዕይታቸው ሙሉ በሙሉ ከተሳሳቱት ዓለማውያን ኤክስፐርት ተብዬዎች አይለያቸውም፡፡
ይህም የዛሬ ክርስቲያኖች ምን ያህል እርባና ቢስ እንደሆኑ ያሳያል፡፡ በራሳቸው አስተሳሰብ ተሞልተው እየታበዩ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ብዙ ርቀዋል፡፡

በመሠረቱ ምን እየተከናወነ እንዳለ ማየት እስከሚያቅታቸው ድረስ ታውረዋል፡፡ ይህ ሂላሪ በምርጫ ታሸንፋለች የሚለው ፍጥጥ ያለ የተሳሳተ ትንበያ እንደ ናይጄሪያዊው ቲቢ ጆሹዋ የመሳሰሉ መሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ ከግዚአብሔር ሐሳብ ቅኝት ውጭ መሆናቸውን ያስተውሉ ዘንድ ክርስቲያኖችን ሁሉ ሊያነቃቸው ይገባል፡፡ነገር ግን ክርስቲያኖች እነዚህን ግልጽ ስህተቶች ቸል በማለት ወደ ታላቁ መከራ የሚመሯቸው መሪዎቻቸው ላይ መጣበቃቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ይህ የቀን ዝርፊያ ነው፡- ማለትም የቤተክርስቲያን መሪዎች ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ብርሃን ለመቀበል ያላቸውን መብት ዘርፈዋቸዋል፡፡

በእግዚአብሔርን ፍጹም ፈቃድ ላይ የሰው አእምሮ በቀላሉ ይስታል፡፡ የዚህን ዘመን ክስተቶች በተመለከተ ቤተክርስቲያኖቻችን አንዳች የሚረባ አስተያየት የላቸውም፡፡ ሰዎች እንዲድኑ ማድረጋቸው መልካም ሆኖ ሳለ ሰዎችን እንዲከተሉ ስህተትን ማስተማራቸው ግን መጥፎ ነው፡፡ ጥሩ ማሕበረሰብን በማፍራት ትልቅውጤት እያስመዘግቡ ናቸው፤ ይህም ያስመሰግናቸዋል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ክርስቲያንን አትጠይቁ፡፡

እና ስለትራምፕ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ለምንድነው ትራምፕ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ የፈለገው?

በተደጋጋሚ እራሱን የሚጠልፉ ድርጊቶችን እየፈጸመ፣ ከሂላሪ የሰላ የሕግ እውቀት ጋር በማይመጣጠን ሁኔታ በክርክሮች ላይ ከመስመር እየወጣ፣ በሪፐብሊካን መሪዎችና ሁለቱን ቀደምት ጆርጅ ቡሾችን ጨምሮ በተለያዩ ቡድኖች ዘንድ ጠላትነትን እየጫረ፣ ማንኛውንም የተከበረ እጩ ሊያሰጥም የሚችል የግብረ ገብ ስህተት ውስጥ ገብቶ ስሙ እየጠፋና እነዚህ ሁሉ ስህተቶች እየሰራ ነገር ግን
አንድ ትክክለኛ ነገር ለማድረግ ችሏል፡- ይህም ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንደሆነች እውቅና እሰጣለሁ ብሎ መናገሩ ነው፡፡

ይህ አንድ ንግግር ብቻ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድጋፍ ለማግኘት በቂ ነው፡፡

ለሙሴ እንዳደረገው ሁሉ፤ እረፍት ላጣው የአሜሪካ ሕዝብ ሂላሪን መምረጥ እንዳለባቸው ሲወተውቱ በነበሩት በኤክስፐርቶች የትንታኔ ባሕር መካከል እግዚአብሔር መንገድ ከፈተለት። (ባሕር የታወከ ወይም እረፍት ያጣ ሕዝብን ይወክላል።)

እግዚአብሔር የሰዎችን ሃሳብ በመለወጥ ለማን ድምጽ መስጠት እንዳለባቸው ይነግራቸዋል፡፡ ሂላሪ ክሊንተን በጥንቃቄ አዘጋጅታ ያቀረበቻቸው ክርክሮችና የምርጫ ዘመቻ ላይ የወጡ ብዙ ሚሊየን ዶላሮች ሁሉ በአንድነት ገደል ገቡ፡፡ ከዓለም መገናኛ ብዙሀንና ከቴሌቭዥን ጣቢያዎች ያገኘችው ድጋፍ ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡

እግዚአብሔር ሲነሳ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች ተጠርገው ከመንገድ ይወገዳሉ፡፡

ሂላሪ ያተኮረችው በአሜሪካ ፖሊሲ እና በውጭ ፖሊሲ ላይ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ምንም አያስደንቀውም፡፡ ኦባማ ፕሬዝዳንት ሆኖ ሳለ ምንም እንኳን የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሐሳቡን ያጸደቀው ቢሆንም እርሱ ግን ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጐ እውቅና ለመስጠት እጅግ ፈርቶ ነበር፡፡ ኦባማ ኢራንን በኑክሊየር ሃይል ማመንጨት ጉዳይ ውስጥ ደግፏል፤ ይህም ድርጊቱ ለእስራኤል ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ሂላሪም ሃሳቧ ይህንኑ ፖሊሲ በመደገፍ ልትቀጥል ነበር፡፡

በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ትራምፕም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የሚያሳጡት ብዙ የአሜሪካ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር፡፡

የትኩረት ማእከል አሜሪካ መሆኗ ቀርቷል፡፡ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እስራኤል እያዞረ ነው፡፡

ነገር ግን ትራምፕ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጌ እውቅና እሰጣለሁ በማለት የእስራኤልን ስም ጠቀሰ፡፡

ይህ ትንሽ የብርሃን ፍንጣቂ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ሃይል በመሳብ የተቃዋሚዎችና ጩኸትና ትርጉም የለሽ ትንታኔዎች ሁሉ ከጥቅም ውጭ አደረገች፡፡በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ትንሽዬ ነገር ብታደርጉ ከአእምሮ በላይ የሆኑ አስደናቂ ውጤቶችን ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ የቀሬናው ስምኦን በአንድ ወቅት ለግማሽ ሰዓት ያህል መስቀል ተሸክሞ ነበር፡፡ በአሁኑ ዘመን የምንኖር ሰዎች በስም የምናውቀው ብቸኛው የቀሬና ሰው እርሱ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቀሬና ምትባለው ሃገር የት እንደሆነች እንኳ አናውቅም። ስለ ስምኦን ግን ሁላችንም እናውቃለን። በእግዚአብሔር ትልቅ ሐሳብ ውስጥ የምታበረክቷት ትንሽዬ አገልግሎት ትላልቅ ጥቅሞችን ታስከትላለች፡፡

ማንም ያልፈለገው ትራምፕ ፕሬዝዳንትነቱን፣ ምክር ቤቱንና የተወካዮች ምክር ቤትን እንዲሁም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ለመቆጣጠር ቻለ፡፡ የራሱ ፓርቲ መሪዎች የሰደቡትና ያወገዙት ሰውዬ አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ችሏል፡፡ በትራምፕ ላይ የበሰበሰ እንቁላል የወረወሩ፣ ስለ አብዛኛው አሜሪካዊ ስሜት የተሳሳተ ግምት የነበራቸው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪዎች በአሁኑ ወቅት እፍረታቸውን ተከናንበው ተቀምጠዋል፡፡

ይህ ምርጫ ለእኛ በግልጽ የተላለፈ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ነገሮች እየተለወጡ ነው፡፡ ይህንንም እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት ከመገንጠሏ (ብሬክሲት) መማር ነበረብን፡፡ ምርጫው በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ አስተሳሰባችንን ጭምር ውድቅ ያደረገ ነበር፡፡

በእግር ኳስ ሌስተር ሲቲ ባለፈው ዓመት እዚህ ግባ የማይባል ቡድን ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን የእንግሊዝን የእግር ኳስ ሻምፒዮንሺፕ የዋንጫ አሸነፈ፡፡ወደ ቤዝቦል ስንመጣ አሜሪካ ውስጥ ቺካጐ ካብስ የተባለው ክለብ ከ108 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ አሸነፈ፡፡ ደግሞም የተናቀው የአየርላንድ የራግቢ ቡድን 18 ግጥሚያዎች ላይ በተከታታይ ዋንጫ የበላውን ኦል ብላክስ ራግቢ ቡድንንን ድባቅ በመምታት ሊያሸንፍ ችሏል፡፡ በ111 ዓመታት ውስጥ አየርላንድ ኒውዝላንድን ስታሸንፍ ይህ የመጀመሪያዋ ነበር፡፡

እግዚአብሔር የሆነ ነገር እየነገረን ነው፡፡ ዝነኞቹና ሰው የወደዳቸው ሊሸነፉ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ታዋቂዎች ምንም ተስፋ የሌላቸው በሚመስሉት ተሸንፈዋል፡፡ በብዙ መንገድ እግዚአብሔር ላልተጠበቁ ለውጦች እያዘጋጀን ነው፡፡ የሚያሸንፉትም ታላላቆቹ መሪዎች፣ ብዙሃኑ የወደዱዋቸው ሰዎችና ትልቅ ስም ያላቸው አይደሉም፡፡ የሚያሸንፉት አያሸንፉም ብለው ሰዎች ያጣጣሉዋቸው ናቸው፡፡
እንቅልፋቸውን በተኙ ቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ተቀምጠን ከአአደጋ ልናመልጥ አንችልም፡፡

እግዚአብሔር ፊቱን ወደ እስራኤል እያዞረ ሲሆን፤ እኛም አቅጣጫችንን ካልቀየርን ኋላ መቅረታችን ነው፡፡

መዳን ብቻ በራሱ ከታላቁ መከራ ለማምለጥ በቂ አይደለም፡፡ ዘመኑን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን፡፡

በጁላይ 4/1976 ዓ.ም. አሜሪካ ሁለት መቶኛ ዓመቷን ለማክበር ዝግጅት ስታደርግ በዲሞክራሲ ስትተዳደር 200 ዓመታትን ያስቆጠረች የመጀመሪያዋ ሃገር ነበረች፡፡ በዓሉ በዓለም ደረጃ ታላቅ ትኩረት ይስባል ተብሎ ሲጠበቅ ድንገት የዓለምን ሁሉ ትኩረት የሚገዛ ሌላ ክስተት ተፈጠረ፡፡ የአሜሪካ በዓል የተጠበቀውን ያህል ሳይደምቅ ቀረ፡፡ ትንሽዋ ሃገር እስራኤል በኢንተቤ አየር ማረፊያ የታገቱባትን ዜጎችዋን በሚያስደንቅ ወታደራዊ ስልትና ብቃት ተዋግታ አስለቀቀቻቸው፡፡ ይህ ወታደራዊ ዘመቻ ረጅም ርቀት የሸፈነ ከመሆኑ አንፃር አሜሪካኖቹ ስለታላቅነታቸው በዓለም ሁሉ ሊለፍፉ በተዘጋጁበት እለት የዓለምን የዜና አውታሮች ተቆጣጠራቸው፡፡ ስለዚህ ስራኤል በሥራዋ አርዕስተ ዜናዎቹን ሁሉ ልትቆጣጠር ችላለች፡፡ የአሜሪካ ጉራ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ አለ፡፡

እግዚአብሔር ፊት ለፊት እየተናገረን ያለው ነገር ፊቱን ከአሜሪካ ወደ እስራኤል እያዞረ መሆኑን ነው፡፡

ነገር ግን ዓለምና ቤተክስቲያን እየሰሙ አልነበሩም፡፡

በዘመቻው ውስጥ የሞተው አንድ ወታደር ብቻ ሲሆን እርሱም እሥራኤላውያኑን ታጋቾቹ ነጻ ያወጧቸውን ወታደሮች ይመራ የነበረው ዮኒ ኔታንያሁ ነበር፡፡ ይህ ሰው የእሥራኤል ፕሬዝዳንት የቤንጃሚን ኔታንያሁ ወንድም ነበር፡፡ ስለዚህ ልክ ሌላኛው ኔታንያሁ ታጋቾችን ያዳኑት የወታደሮች ዘመቻ መሪ እንደነበር ሁሉ አሁንም እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ ለማዳን በፈለገበት ወቅት ኔታንያሁ የአይሁድ ፕሬዚደንት ሆኖ ተሹሟል፡፡

ጀግናው የዘመቻ መሪ አይሁድ ወገኖቹን በሥጋ ለማዳን ሲል ሞቷል፡፡ የአይሁዳውያን መሲህም አይሁድን በመንፈሳዊ ሕይወት ለማዳን ሲል ሞቷል፡፡

በወቅቱ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ኢዲ አሚን ነበር፡፡ አይሁዳውያኑን ወደ ሃገራቸው በአውሮፕላን ሲመለሱ የኢዲ አሚን ልጅ ከዚህ በኋላ አይሁዶችን ያሳድዳቸው እንደሆነ አባቱን ጠየቀው፡፡ ልጅየው ከግፈኛ አባቱ ያገኘው እጅግ የሚያስገርም መልስ ይህ ነበር፡- «ልጄ፤ እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ናቸው፡፡ ከነካሃቸው አይለቁህም፡፡ እነሱን መተው ይመረጣል»። (ለአረብ ሃገሮች ጥሩ ምክር ይሆናል)፡፡

ከዚህ የምንወስደው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አንድ፡- ከጥቂት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመረኮዙ ሰዎች በስተቀር ቤተክርስቲያን ከጨዋታ ውጭ ሆናለች፤ ተሰሚነቷን አጥታለች፡፡ አሁን በቅርቡ በተደረገው ምርጫም ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ስታለች፡፡ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር እንደሚያስበው ማሰብ አቁማለች፡፡ አሁን የእግዚአብሔር ዋነኛ ፍላጐት ፊቱን ወደ እስራኤል መመለስ ነው፡

እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ዓለም፣ አሜሪካንና ሌሎች ሃገራትን እየተወ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዋነኛ ትኩረቱ እስራኤል ነች፡፡ ለአይሁድ ያልተፈጸመላቸው የግማሽ ሳምንት ወይም የሦስት ቀን ተኩል ትንቢቶች ይቀራሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ በትንቢት አንድ ቀን አንድ ዓመትን ይወክላል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለአይሁድ ያስቀረው ሦስት ዓመት ተኩል ይቀሩታል፡፡ የእግዚአብሔር ትልቁ ዕቅድ አይሁድን ወደ ሃገራቸው መመለስና ዓለም ሁሉ በእነርሱ ላይ እንዲነሳ ማድረግ ነው፡፡

ራሳቸውን እንዲያድኑ ብቻቸውን ቢታገሉ መጥፋታቸው የማይቀር በመሆኑ በሁለት ነብያት ማለትም በሙሴና በኤልያስ ላይ ለመደገፍ ይገደዳሉ (ልብ በሉ፤ እንደ ቀሬናው ስምኦን በአግባቡ እግዚአብሔርን የምናገለግለው ግዴታ በሚሆንብን ጊዜ ብቻ ነው)፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ብቻ በልዕለ ተፈጥሮአዊ ኃይላቸው ሆ ብለው የሚመጡትን የእስራኤልን ጠላቶች ሰራዊት ያስቆሟቸዋል፡፡ ይህ ተአምራዊ ማዳን ብዙዎቹ አይሁዶች ሁለቱን ነብያት እንዲያምኗቸው የሚያደርግ ሲሆን እነርሱም አይሁድ ኢየሱስን እንደ መሲሀቸው እንዲቀበሉ ያደርጓቸዋል፡፡ ይህ ቀላል ሥራ አይሆንም፡፡ ከዚያም ኢየሱስ እነዚህን በርካታ ጸረ-አይሁድ ሰራዊት አርማጌዶን ላይ ለመደምሰስ ይመጣል፤ የሚፈሰው የአይሁድ ጠላቶች ደምም ለእስራኤል አሸዋማ አፈር እንደ ማዳበሪያ በማገልገል ሃገሪቱ በሺህ ዓመት መንግስት ውስጥ እንደ ጽገሬዳ እንድትፈካ ያደርጋታል፡፡

ባለፉት ጊዜያት የአሜሪካ ምርጫዎች መሳካት ከእስራኤል ደህንነት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ እስራኤል በ1948 እንደ ሀገር ስትመሰረት ጠንካራ ተቃውሞ ቢገጥመውም ፕሬዚደንት ትሩማን ለእስራኤል እውቅና ለመስጠት የመጀመሪያው ነበር፡፡ የአምስት የአረብ ሀገራት ሰራዊት በአንድ ጊዜ ጥቃት እየፈጸሙባት ስለነበር እስራኤል ይህ ድጋፍ በጣም ያስፈልጋት ነበር፡፡

በ1948 ምርጫ የትሩማን ዴሞክራት ፓርቲ በሦስት አንጃ በመከፋፈሉ ሪፐብሊካኑን ዲዊ የማሸነፍ ተስፋ አልነበረውም፡፡ በመሆኑም ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ገና ምርጫው ሳይደረግ በፊት በፊት ገጹ ላይ ዲዊ አሸንፏል ብሎ ጽፎ ነበር፡፡ ሪፐብሊካኖች በአብዛኛው ገበሬዎች ነበሩ፡፡ እግዚአብሔርም የሪፐብሊካኖች እርሻ በብዛት ባለበት የሚሲሲፒ ተፋሰስና በሰሜን ካሊፎርኒያ ከባድ ዝናብ እንዲጥል አደረገ፡፡ ከባድ ጭቃ በመፈጠሩ ምክንያት የሪፐብሊካን ገበሬዎች ወጥተው ድምጽ መስጠት ሳይችሉ ቀሩ፡፡ ትሩማን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን አሸነፈ፤ እንደ አዲስ የተወለደችውን ሃገር እስራኤልን መደገፉን ቀጠለበት፡፡

በ1972 ኒክሰን ዎተርጌት በተባለ ቦታ ምርጫ አጭበርብሮ አሸነፈ፡፡ ክፉ ሥራ ቢሰራም፣ ከሕዝቡም ዘንድ የተቃውሞ ማዕበል ቢነሳበትም ለሁለት ዓመት ሥልጣኑን የሙጥን ብሎ መቆየት ቻለ፡፡ ከዚያም በ1974 ከሥልጣን ወረደ፡፡ ይህ አጭበርባሪነት በዋይት ሃውስ ውስጥ ለሁለት ዓመታት እንዲቆይ የተፈቀደው ለምንድነው?

በ1973 የአረብ ሃገራት ሰራዊቶች ባልተዘጋጀችው እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር አይሁድ ለመጥፋት እስኪቃረቡ ድረስ ለአንድ ሳምንት ከፍተኛ ድብደባ አደረጉባቸው፡፡ የአይሁድ ፕሬዚደንት የነበረችው ጐልዳ ሜይር ለኒክሰን ስልክ በመደወል በአስቸኳይ ዘመናዊ መሣሪያዎች እንዲልኩላት ጥያቄ አቀረበች፡፡ ኒክሰን ልጅ እያለ እናቱ ትነግረው የነበረ አንድ ነገርን አስታወሰ። « ሪቻርድ፡ ለእስራኤል ማድረግ የምትችለው ነገር ካለ እባክህ አድርገው ፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ናቸው» ትለው ነበር፡፡ በመሆኑም ኒክሰን በአየር ተጓጉዞ የሚቀርብ መሣሪያ እንዲዘጋጅ አደረገ፡፡ እሥራኤልም እነዚህን የጦር መሣሪያዎች ተጠቅማ በመዋጋት ጦርነቱን ልታሸንፍ ችላለች፡፡

ስለዚህ በ1973 ኒክሰን ለእሥራኤል አስፈልጓት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔር እንዲያደርግ የሚፈልገውን በማድረግ እስራኤል እስክትድን ድረስ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ችሏል፡፡ ያገኘውስ ሽልማት ምን ነበር ? ለፈጸመው የአጭበርባሪነት ወንጀል ወኅኒ መውረድ ይገባው ነበር ግን ፕሬዝዳንታዊ ምህረት አገኘ፡፡
እስራኤል ሃገር ሆና የተመሰረተችው እንዴት ነው? በሂትለር ምክንያት ነበር፡፡ ሂትለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ስድስት ሚሊዮን አይሁድን ጨፈጨፈ፡፡ የዓለም ሕዘዝብ ሁሉ በዚህ በመደናገጥ ለአይሁድ ሕዝብ ለአጭር ጊዜ አዘነላቸው፡፡ የተባበሩት መንግስታትም በሁለት አብላጫ ድምፅ ለደህንነታቸው ሲባል ለአይሁድ ፓለስታይን ውስጥ ሃገር እንዲሰጣቸው ተስማማ፡፡

ሂትለርስ ወደ ሥልጣን የመጣው እንዴት ነበር ? አነስተኛና የማይታወቅ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ከገባ በኋላ ለምርጫ መወዳደር ጀመረ፡፡
በተወዳደረበት ምርጫ ሁሉ ተስፋ ቢስ ተደርጐ ይቆጠር ነበር፡፡

መገናኛ ብዙሀን ስለሱ አሉታዊ ነገሮችን ያስተጋቡ የነበረ ሲሆን ዋና ታላላቆቹ የጀመርመኒ መሪዎች ይሳለቁበት ነበር፡፡

በዚህ ሁሉ ውስጥ በ1933 ቻንስለር ሆነ በኋላ ደግሞ የጀርመኒ አምባገነን መሪ ለመሆን በቃ፡፡

አይሁዳውያንን ማሳደዱ የአይሁድ ሕዝብ የተስፋይቱ ምድራቸው እስራኤልን በድጋሚ እንዲወርሱ አስቻላቸው፡፡ በመሆኑም የሂትለር ወደ ሥልጣን መውጣትና የሰራቸው የግፍ ሥራዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታቀዱ ነበሩ፡፡

ስለዚህ እስራኤልን ተመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር ወደዚያ እየሄደ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለትንቢትን ፍጻሜ ትልቅ ቦታ ይሰጣል፡፡

ሳዳም ሁሴን የባቢሎንን ከተማ በድጋሚ መገንባት ጀምረ ኩዌትንም ወረረ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ባቢሎን በድጋሚ አትገነባም ብሏል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ጆርጅ ኤች. ደብልዩ ቡሽን በመጠቀም በባሕረ ሰላጤው ጦርነት ሳዳምን ድራሹን አጠፋው፡፡ ሳዳም 600 የኩዌት የነዳጅ ጉድጓዶችን አቃጥሏል፡፡ ይህ እንደሚቃጠለው ቁጥቋጦ አይነት ምልክት ነበር፡፡ ሙሴ ያየው የሚቃጠል ቁጥቋጦ የመጀመሪያው የእሥራኤል ጉዞ ከግብጽ ወደ ከነዓን ጅማሬ ነበር፡፡

በ1991 የተደረገው የመጀመሪያው የባሕረሰላጤው ጦርነት ሌላኛው «የሚቃጠል ቁጥቋጦ» ሲሆን ይህም እግዚአብሔር አይሁድንን ወደ እስራኤል እየመለሰ መሆኑን ያመለክተናል፡፡

ሰዎች ጦርነቱ ስለ ነዳጅ ብቻ መስሏቸዋል፤ በእርግጥም የአሜሪካ ዓላማ ነዳጅ ዘይት ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቡሽን ተጠቅሞ የራሱን ዓላማ ማለትም የባቢሎንን ግንባት ማስቆም አስቆመ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ይህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አይሁዶች እየመለሰ እንደሆነና በዚያም በታላቁ መከራ ወቅት ሙሴ (እና ኤልያስ) ተመልሰው በመምጣት እንደሚመሩዋቸው የሚያመለክት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሳዳም በድጋሚ ባቢሎንን መገንባት ጀመረ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽን በማስነሳት ሳዳምን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋው፡፡ እግዚአብሔር ባቢሎን በድጋሚ እንድትገነባ አይፈቅድም፡፡ የኢራቅ የነዳጅ ዘይት አሜሪካኖችን ኢራቅ ውስጥ ወደ ሁለተኛው የባሕረሰላጤ ጦርነት ጎትቶ ያስገባቸው መንጠቆ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ዋነኛ አጀንዳ ግን ባቢሎን በድጋሚ እንዳትገነባ ማድረግ ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ከከበቧት ጠላት ጐረቤቶቿ ማለትም ከሶሪያ፣ ከሂዝቦላ እና ከሃማስ ጥበቃ ያስፈልጋት ነበር፡፡

በ2006 እስራኤል ከሂዝቦላህ አሰቃቂ ጦርነት የተዋጋች ሲሆን ሂዝቦላህ ያሸነፈ መስሎ ነበር፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር እስራኤልን እንዴት ነው ከጥፋት የሚጠብቃት? ሶሪያ ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ ፕሬዚደንት አሳድም ሂዝቦላህ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ አቀረበ፡፡ በዚህም ምክንያት ሶሪያም ሂዝቦላም በዚህ ከባድ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በመጠመዳቸው ከእስራኤል ጋር ሌላ ጦርነት የሚጀምሩበት አቅም አጥተዋል፡፡ ስለዚህ ለጊዜው እስራኤል ምንም የሚያሰጋት ነገር የለም፡፡ ከዚያም አይሲስ በድንገት በመነሳት ኢራቅና ሶሪያ ላይ ስራ አበዛባቸው፡፡ ሶሪያና ኢራቅ ከአይሲስ ጋር ውጊያ ውስጥ ስለሆኑ በእስራኤልን ለመውጋት ጊዜ የላቸውም፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር ለአይሁድ እፎይ የሚሉበት ጊዜ ሰጣቸው፡፡ ከአይሲስ ጋር መዋጋት ከፍተኛ ወጭ ስለሚጠይቅ ኢራቅ ባቢሎንን በድጋሚ ለመገንባት የሚያስችል ገንዘብ የላትም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግድየለሽዋ ቤተክርስቲያንና የመልዕክት ቡድኖች መሪዎቻቸውን በጭፍን ተከትለው እንቅልፋቸውን ተኝተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሜተዲስት የሚባል ቤተክርስትያን እንዳልተጠቀሰ ሁሉ የመልዕክት ቤተክርስቲያን የሚባልም እንዳልተጻፈ አስተውሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የምትከተሉ ከሆነ ራሳችሁን ክርስትያን ብቻ ብላችሁ ጥሩ፡፡

ነገር ግን አሁን በዚህ ምርጫ ፍጹም ያልተጠበቀ ውጤት አማካኝነት እግዚአብሔር ታላቅ የማንቂያ መልእክት ልኮልናል፡፡

 

1ኛ ቆሮንቶስ 15፡46 ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም።

 

እግዚአብሔር በመጀመሪያ ፍጥረታዊ ማስጠንቀቂያ ይልካል፡፡ ይህም ኤክስፐርቶች እያንቀላፉ ሳለ በድንገት የተከሰተ ሙሉ በሙሉ ያልተጠበቀ ፖለቲካዊ ነውጥ ነው፡፡ አሜሪካኖች አሁን መንገዳቸውን መቀየር አለባቸው፡፡

“ዘ ትራምፕ” በአማርኛ “መለከቱ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ መሆኑን ልብ በሉ፡፡

መለከት የመጨረሻውን ዘመን ክስተቶች ከሚያመለክቱ ምልክቶች አንዱ ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ ያልተጠበቀና ፍጥረታዊ በሆነው ትራምፕ (መለከት) መመረጥ አማካኝነት እግዚአብሔር ተመጣጣኝ የሆነ ያልተጠበቀ ለውጥ በመንፈሳዊው ዓለም ሊከሰት መሆኑን እያስጠነቀቀን ነው፡፡ ሁላችንም በመንገዳችን ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ልናደርግ እና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ልንመለስ ይገባናል፤ አለዚያ ታላቁ መከራ ውስጥ መግባታችን አይቀርም፡፡

 

1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16 ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አይሁድ እየመለሰ ነው፡፡

 

ቤተክርስቲያን የምትጠብቀው ቀጣዩ ክስተት በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሞቱት ትንሳኤ ነው፡፡

በመቀጠልም ወደ ሰማይ የሚጠራንን የእግዚአብሔር «መለከት» እንሰማለን፡፡

ፍጥረታዊው ሊነግረን የሚችለው ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር መለከት በፍጹም ያልተጠበቀና በሁሉም ቦታ በቤተክርስቲያንና የመልዕክት ኤክስፐርቶች ሁሉ በአንድነት እንደሚቃወሙት ነው፡፡ አሁንም እያዩት እየሰሙት ስለማያስተውሉት ይስቱበታል፡፡ ልክ የሪፐብሊካን መሪዎች ትራምፕን አምርረው ሲቃወሙ እንደነበረ መጨረሻው ሲመጣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና የመልዕክት መሪዎች የእግዚአብሔርን መለከት በተመሳሳይ መንገድ አምርረው ይቃወማሉ፡፡

ለምን?

ያልጠበቁት አይነት ስለነበረ እርሱን መቀበል ይችሉ ዘንድ አስተሳሰባቸውን ለማስተካከል አልቻሉም፡፡ ምርጫ ለማሸነፍ የሚጠቅሙ አሁን ግን ጊዜ ያለፈባቸው የማይጠቅሙ ዘዴዎቻቸውን መጣል አልቻሉም፡፡ ሲበዛ ኩሮ በመሆናቸው አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር አልፈቀዱም፡፡ በመሆኑም የሪፐብሊካን መሪዎች በመጨረሻ ቂሎች መስለው ታዩ፡፡

በመጨረሻ የቤተከርስቲያን መሪዎችና የመልዕክት ትምህርት መሪዎችም እንደዚሁ አይነት እጣ ይደርስባቸዋል፡፡

የቤተክርስቲያንና የመልዕክት ቡድኖች ትልቁ ኪሳራቸው በሰው መመራታቸው ነው፡፡ የፖለቲካውን ዓለም ተመልከቱ፡፡ የሪፐብሊካን መሪዎች ሁሉ ትራምፕን ሲተቹ እና ሲያወግዙ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ እንዲያውም ድምጻቸውን ለእርሱ ተፎካካሪዎች ሰጥተዋል፡፡ አሁን የወረወሩት እንቁላል ተመልሶ በፊታቸው ላይ አርፏል ምክንያቱም እርሱ ሪፐብሊካኖችን ከጠበቁት በላይ ወደሆነ ስልጣን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡

ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ እንዲጠይቁ ለአይሁድ የነገሯቸው የሐይማኖት መሪዎቻቸው ነበሩ፡፡

በመጨረሻ ሁልጊዜ መሪዎች ናቸው ወደ ስህተት የሚመሩን፡፡

ሁልጊዜ ቤተክርስቲያናዊነትን አክርረው መከተልን እና የሳቱ መሪዎቻቸውን ተከትለው መሳሳትን ትተው ክርስቲያኖች መች ነው ነቅተው በራሳቸው ማሰብ የሚጀምሩት?

ሂላሪ አሸንፋ ቢሆን ኖሮ ይህ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አንድምታ አይኖረውም፤ ክርስቲያኖችና የመልእክት ቡድኖቻቸውም ወደ ጣፈጠ እንቅልፋቸው መመለስ ይችሉ ነበር፤ መሪዎቻቸውም እያባበሉዋቸው እሽሩሩ እያሉዋቸው መቀጠል ይችሉ ነበር፡፡

ትራምፕ ማሸነፉ ግን በእግሮቻችን ጣቶች ሊያስቆመን ይገባናል፡፡ መጨረሻው ቅርብ ሊሆን ይችላል፡፡

እግዚአብሔር ነቅንቆ የሚያነቃ መልእክት ልኮልናል፤ እኛ ግን ቸል እያልን ነን፤ ይህም በራሳችን ላይ ጥፋትን መጋበዝ ነው፡፡

ተደላድለው የተኙትና የገደል ማሚቶ ማስተጋቢያ የሆኑ ቤተክርስቲያኖቻችን ውስጥ ከእንግዲህ መጠለያ አይሆኑንም፡፡

ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግመን ስንሰማ በመቆየታችን እና ከሃሳባችን ጋር ከሚስማሙ ሰዎች ጋር ብቻ በመክረማችን የእኛ አመለካከት እውነት መስሎን ቀርተናል። ይህ ደስ የሚልና ከአደጋ የተጠበቀ ኑሮ ነው፡፡ እኛም ራሳችንን እያሞካሸን እንኖራለን፡፡ አእምሮአችን ቀድሞ የተሞላነውን መቀበል ስለለመደ አማራጭ አመለካከቶችን ለመቀበል ዝግጁ አይደለም፡፡ እኔ የምለው ብቻ ልክ ነው የሚል አቋም ስለተጠናወተን ሌላ አመለካከት ሲመጣ ሳንመረምረው መቃወም ለምዶብናል። የራሳችንን አመለካከት መመርመር ያስፈራናል፤ ምክንያቱም ብንመረምረውና መሳሳታችንን ለማመን ድፍረቱን ካገኘን ሃሳባችንን የሚያስቡልንን እና በጭፍን የምንከተላቸውን መሪዎቻችንን መከተል እናቆማለን። በራሳችን ማሰብ ይኖርብናል፤ ይህም የለመድነውን ምቾት ያሳጣናል፡፡

ከዚያ የማን ወገን እንደሆንን አናውቅም፡፡ ብሬክሲት (እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት መገንጠሏ) ሰዎች በሃሳብ ከማይስማሟቸው ሰዎች ማውራትና መወያየት እንደሚያስፈልጋቸው አስተምሯቸዋል፡፡ መንግስታት ይተቹዋቸውና ስሕተቶቻቸውን ያሳዩዋቸው ዘንድ ለተቃዋሚዎቻቸው ይከፍላሉ፡፡

ቤተክርስቲያኖች ግን ትችቶችን ስለሚጠሉ እንዲህ አይነቱ ጥበብ የላቸውም፡፡ የቤተክርስቲያን መሪዎች 30¸000 የገደል ማሚቶ ማስተጋቢያዎችን ሰርተዋል፤ እነርሱም መሪዎቻቸው ያተናገሩትን ሰምተው የሚደግሙ ጉባኤዎች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ቤተክርስቲያንእኔ ነን ትክክል ብሎ ይከራከራል፡፡

በመካከላቸው ሰፊ ልዩነቶች በመኖራቸው ከውጭ ላሉ ሰዎች ይህ ቀልድ ሆኖ ይታያቸዋል፡፡ ግለሰቦች ብቻ ናቸው ወደተጻፈው ቃል በመመለስ ከዚህ የአእምሮ ድንዛዜ መውጣት የሚችሉት፡፡

 

ራእይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ

 

ይህች ሰባተኛዋ ወይም የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ና። ሎዶቂያ ማለት “የሕዝብ መብቶች” ማለት ነው፡፡ ይህ አሁን ያለንበትን ዘመን በትክክል ይገልፃል፡፡

 

ራእይ 3፡17 ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥

 

ክርስቲያኖች ሐብት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የማግኘታችን ማረጋገጫ ነው ብለው አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ ሆኖም ይህ ቃልየዘመናችንን ቤተክርስቲያን የሚያወግዝ ቃል ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የወደቅን ቤተክርስቲያን መሆናችንን እንኳ አላወቅንም፡፡ “አንድም እንኳ አያስፈልገኝም” እንላለን፡፡ እያንዳንዱ ቤተእምነትና የመልዕክት ቡድን ምንም እርማት አይፈልግም፡፡ ከቡድኑ ውጭ የሆነ ሰው ማንም አያደምጠውም፤ ምክንያቱም ከውጭ የሆነ ሰው ቡድኑ ውስጥ ካሉት የተሻለ እውነት ይኖረዋል ተብሎ አይታመንም።

ነገር ግን ኢየሱስ ስለቤተክርስቲያኒቱ ሲናገር “ዕውር” ይላታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የትኛዋም ቤተክርስቲያን በታማኝነት መጽሐፍ ቅዱስን አትከተልም፡፡ የሰዎች እምነት የተመሰረተው በወጎች፣ በሰዎች አመለካከት፣ በሰዎች ቃል ሆኗል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ አይደለም፡፡

 

ራእይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

 

ይህ ለቤተክርስያኖቻችን ትልቅ ኩነኔ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከበር ውጭ ቆሟል፡፡ ቃሉ እርሱ ነው፡፡ የየትኛውም ቤተክርስቲያን ሰባኪ ግን በተጻፈው ቃል አይሰብክም፡፡ ከቃሉ ቢሰብኩ ኢየሱስ ቤተከርስቲያን ውስጥ ይሆን ነበር፡፡

ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማንም ሰው የቤተክርስቲያን ራስ ተብሎ አልተጠቀሰም፡፡ ነገር ግን ፓስተሮችና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች የቤተክርስቲያኝ ራስ ነን ይላሉ፡፡ ማንም ሰው ሁለት ራሶች ሊኖሩት አይችልም፡፡ ፓስተሩ የቤተክርስቲያኑ ራስ ነኝ ካለ እውነተኛው ራስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊገኝ አይችልም፡፡ የፓስተሩ ቤተክርስቲያን እንጂ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አይደለም፡፡

 

ሉቃስ 18፡8 ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ይህ ኢየሱስ የተነገረው ትንቢት እኛን ክርስቲያኖችን ይወቅሰናል፡፡ የሰዎችን ወግ ከፍ የሚያደርግ ቤተክርስቲያናዊነት አጐልብተናል፡፡ ኢየሱስ የሚፈልገው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚያምኑ ሰዎችን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎችንም አገኛለሁ ብሎ አይተማመንም፡፡ በኖህ ጊዜም የተረፉት ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡

በአሁኑ ወቅት ካሉት 2 ቢሊዮን ክርስቲያኖችስ ምን ያህሉ ይተርፋሉ?

 

ሮሜ 10፡17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።

 

ይህንን ምሳሌ ተመልከቱ፡፡ እራት ተዘጋጅቶ የተጠሩ ሰዎች ሁሉ እምቢ አሉ፡፡ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ የምታምነዋን ሙሽራ ወደ በጉ የሰርግ እራት ግብዣ ወደ ሰማይ ሊወስዳት ይፈልጋል፤ ክርስቲያኖች ግን በራሳቸው የግል ፍላጐትና በተለያዩ የቤተክርስቲያናዊነት አጀንዳዎቻቸው ተተብትበዋል፡፡ ስለዚህ የተጋበዙት እንግዶች ማለትም የዳኑት ክርስቲያኖች ወደ ግብዣው እንዳይገቡ ተከልክለው በቀጥታ ወደ ታላቁ መከራ ይገባሉ፡፡ እግዝአብሔር በዚያን ጊዜ ያልታወቁ እና ያለተፈለጉ እንዲሁም በጣም ቸል የተባሉ ቤተክርስቲያን ያገለለቻቸውን ሰዎች ጎትቶ ያስገባል፡፡ እነዚህ በጎዳና ስርና በየጥጋጥጉ ወድቀው የሚገኙና መጠለያ የሌላቸው፣ ቤት አልባ መጠጊያ የሞሆናቸው ቤተክርስቲያን የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ምቹ ማንቀላፊያ እና የሚኮሩበት ስኬት የላቸውም፡፡ ተበታትነው የሚኖሩ ሲሆኑ ያለ ፈቃዳቸው ከየቦታው ተጎትተው ይመጣሉ፡፡ በነርሱ ዘንድ እውቅናም ሆነ ገንዘብ ስለማይገኝ ሥጋ ለባሽ የሆነ መሪ የላቸውም፡፡ እነርሱ ድሆች ናቸው፡፡

 

ሉቃስ 14፡ 16 እርሱ ግን እንዲህ አለው፡- አንድ ሰው ታላቅ እራት አድርጎ ብዙዎችን ጠራ፤
17 በእራትም ሰዓት የታደሙትን፡- አሁን ተዘጋጅቶአልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ።
18 ሁላቸውም በአንድነት ያመካኙ ጀመር። የፊተኛው፡- መሬት ገዝቼአለሁ ወጥቼም ላየው በግድ ያስፈልገኛል፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው።
19 ሌላውም። አምስት ጥምድ በሬዎች ገዝቼአለሁ ልፈትናቸውም እሄዳለሁ፤ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው።
20 ሌላውም። ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው።
21 ባሪያውም ደርሶ ይህን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ ባሪያውን፡- ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች ፈጥነህ ውጣ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ አግባ አለው።
22 ባሪያውም፡- ጌታ ሆይ፥ እንዳዘዝኸኝ ተደርጎአል፥ ገናም ስፍራ አለ አለው።
23 ጌታውም ባሪያውን፦ ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤
24 እላችኋለሁና፥ ከታደሙት ከእነዚያ ሰዎች አንድ ስንኳ እራቴን አይቀምስም አለው።

 

የዳኑ ነገር ግን ኩሩ እና በራሳቸው ብቁ እንደሆኑ የሚሰማቸው የዛሬ ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ ሲመጣ ሽልማት የሚቀበሉ የሚመስላቸው ኋላ ያፍራሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የተጣሉትን እያነሳ ወደ አሸናፊነት ሊያመጣቸው ነው፡፡

ከብሬክሲት እና ከአሜሪካ የትራምር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የምንማረው ትምህርት ይህ ነው፡፡ ሰዎች ትራምፕ ምርጫውን አያሸንፍም ምክንያቱም ለፕሬዝዳንትነት ብቁ አይደለም ብለው ነበር፡፡ ስህተቶቹና ድክመቶቹ ያለ ምንም ርህራሄ አጋልጠውበት ነበር፡፡

ለበጉ ሰርግ እራት ግብዣ ኢየሱስ ባሪያውን እንዲህ አለ «ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ አግባ»። እነዚህ ሰዎች ለሰርግ ጥሪ ተገቢ አይመስሉም፡፡ ነገር ግን ተጠርተው የሚገቡት የሚያሸንፉት እነርሱ ናቸው፡፡

የትራምፕ ምርጫ ለሁላችንም ታላቅ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል፡፡ በቤተከርስቲያን ውስጥ ወይም በመልዕክት ትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚገኝ ደህንነት የለም፡፡ እምነታችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን አረጋግጡ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ተመስርተው የሚሰጡ ትችቶችን አታጣጥሉ፡፡ ከእናንተ ቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ሌሎች ሰዎችም ሊረዱህ ይችላሉ፡፡ መሪዎችህ ሰዎች እንደመሆናቸው ሁሉን የሚያውቁ አይደሉም፡፡

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23