የሥላሴ ትምሕርት በ325 ዓ.ም. በተደረገው የኒቂያ ጉባኤ አማካኝነት እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን እንደገባ
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የጌታ ኃዋርያት “ሥላሴ” የሚለውን ቃል ተጠቅመው አያውቁም። ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን ለመጠቀም የወሰነች ጊዜ ሥላሴ የሚለው ቃል ሰተት ብሎ ለመግባት በር አገኘ።
በ70 ዓ.ም. ሮማውያን ኢየሩሳሌምን አፈረሱ። ይህም የሆነው ኃዋርያው ጳውሎስ እና ብዙዎቹ ኃዋርያት ከሞቱ በኋላ ነው። በዚህም ምክንያት ክርስትናን አንድ የሚያደርገው ማእከል አልነበረም፤ ከዚያ ይልቅ የሃሳብ ወንድማማችነት ብቻ ነው የነበረው።
እጅግ የሚገርመው ነገር በቤተክርስቲያን ውስጥ በ70 እና በ120 ዓ.ም. መካከል በነበረው ጊዜ ውስጥ ምን እንደተፈጠረ የታሪክ ምሁራን አንዳች አለማወቃቸው ነው። በ120 ዓ.ም. በአዲስ ኪዳን ከምናውቃት የተለየች አዲስ አይነት ቤተክርስቲያን ተነሳች። በዚህች አዲስ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሪው ራሱን የአንድ ከተማ ጳጳስ ብሎ የሚሾም ሰው ሆነ። የኃዋርያት አስተምህሮ በሰው አመራር መተካት ጀመረ። ሽማግሌዎችም ጉባኤውን በራሳቸው ሃሳብ እንደፈቃዳቸው መግዛት በሚፈልጉ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገፉ።
ከዚያ በኋላ አፈታሪኮች ተፈጠሩ፤ ለምሳሌ ከእነዚህ አፈታሪኮች አንዱ ጴጥሮስ ሮም ሄዶ እንደነበረ ይናገራል ነገር ግን ይህን የሚያረጋግጥ አንድ ማስረጃ እንኳ የለም። ጳውሎስ ለሮማውያን በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ 27 ሰዎችን በስም እየጠቀሰ ሰላም ሲል ጴጥሮስን ግን በጭራሽም አልጠቀሰም። በዚህ መንገድ ውሸት ወደ ቤተክርስቲያን ገባ፤ ከዚያም ዘወትር ሲደጋገም ከጊዜ በኋላ ሰዎች እንደ እውነት ተቀበሉት።
ስልጣን ፈላጊ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሮም ዓለምን የምትገዛበትን ፖለቲካዊ ሥርዓት አይተው እነርሱ ደግሞ ቤተክርስቲያን የሮማ ግዛትን በሙሉ ልትገዛ እንደተጠራች አድርገው አሰቡ። ይህንን እቅዳቸውን ለማሳካት የሮማውያንን ፖለቲካዊ ሥርዓት የመሰለ ጠንከር ያለ ድርጅታዊ መዋቅር እና ቤተክርስቲያንን ከላይ ሆኖ በፈላጭ ቆራጭነት የሚገዛ እንዲሁም ሁሉ የሚታዘዙለት አንድ ግለሰብ መሪ ያለበት ሥርዓት እንደሚያስፈልጋቸው አመኑ።
በ170 ዓ.ም. ሹመት ያገኙ የቤተክርስቲያን መሪዎች በእያንዳንዱ ሕብረተሰብ ውስጥ ስልጣን ይዘው በአስተዳዳሪነት ተቀመጡ። የእነዚህ መሪዎች የበላይ ሃላፊ ጳጳስ የተደረገ ሲሆን ይህም ጳጳስ ለአካባቢው ሕብረተሰብ ተወካይ ሆነ። ጳጳሳቱ ወዲያው መንግስትን እንደሚቃወም ፓርቲ ወደ ትግል ውስጥ የሚገቡ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ሆኑ።
ቤተክርስቲያን ራሷን እንደ ዓለም አቀፍ ድርጅት ማየት ጀመረች፤ ማለትም ልክ እንደ ሮማ መንግስት።
ቤተክርስቲያን አስተዳደጓን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ቃል ትታ በአካባቢዋ ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታ መመሪያዋ አድርጋ ተቀበለች። ቤተክርስቲያን የሮማውያንን የፖለቲካ አገዛዝ በመኮረጅ እለታዊና ማሕበራዊ የኑሮ ችግሮችን በተመለከተ ድጋፍ የምትሰጥ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆነች። በዚህም ምክንያት በመንደሮች፣ ከተሞች እና አውራጃዎች በተለያየ የስልጣን ተዋረድ ተሸመው የሚያስተዳድሩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተሸመው መንቀሳቀስ ጀመሩ። ከዚያ ወዲያ ቤተክርስቲያን ሰዎችን የክልል ወይም የክፍለሃገር አስተዳዳሪ አድርጋ መሾም ጀመረች። መሪዎችም የዓለምን ሕዝብ በወንጌል የመድረስ ፍላጎታቸው እየቀዘቀዘ መጣ። ስለዚህም የመሪዎች ትኩረታቸው በዋነኝነት ፖለቲካዊ ንክኪ ያለው የበጎ አድራጎት ሥራ ወደመሆን አዘነበለ። በእምነታቸው እንኳ ሳይቀር ከመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ እየራቁ ሄዱ።
የተለያ ሕብረተቦች ሁሉ የአንዲት ዓለም አቀፋዊ (ማለትም፣ ኢግናሺየስ እንዳለው፡ የካቶሊክ) ቤተክርስቲያን አባላት እየሆኑ ሄዱ።
በብሉይ ኪዳን ዘመን የኖሩት አይሁድ ሁሉን ቻዩ አምላክ እግዚአብሔር ሰው መሆን ይችላል የሚል እምነት አልነበራቸውም። በዚህም ምክንያት አይሁድ እግዚአብሔር ወደ ምድር ወርዶ በሰው ውስጥ መኖሩን እና ኢየሱስ በተባለው ሰው ውስጥ መገለጡን ሊያምኑ አልቻሉም።
ጳውሎስ የእግዚአብሔር የመለኮት ሙላት በሰውነት በሥጋ ተገልጦ በኢየሱስ እንደኖረ በመልእክቶቹ ገልጧል።
ዮሐንስ 4: 24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው።
ዮሐንስ 1:18 መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤
ሰው መንፈስን ሊያይ አይችልም። እግዚዘብሔርን በአይኔ አይቼዋለው ማለት አትችልም። ማየት የምትችለው እግዚአብሔር የሚኖርበትን አካል ብቻ ነው። ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ የኖረበት ሰብዓዊ አካል ነው።
ቆላስይስ 2:9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3: 16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለጥርጥር ታላቅነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ ...
የማይታየው የእግዚአብሔር አብ መንፈስ ልጁ፣ ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰራቸው ሥራዎች ተገለጠ (ራሱን አሳየ)። ኢየሱስ ክርስቶስን ልብ ብለን ስናይ እግዚአብሔር የሚሰራውን ሥራ ማየት እንችላለን።
ስለዚህ ኢየሱስ ሰውም አምላክም ነው። ሥጋዊ አካሉ አምላክ አልነበረም። እግዚአብሔር ሥጋ እና ደም አይደለም።
እግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ሥጋዊ አካል ውስጥ የሚኖረው የማይታየው ሁሉን ቻይ መንፈስ ነው። ሥጋዊ አካሉ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ስያሜ አይጠቀምም። ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ሥጋ አይደለም።
ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ነኝ ቢል ትክክል ነው፤ ምክንያቱም እርሱ ማለትም ሰው የሆነው ኢየሱስ እና መለኮታዊው አባት አንድ ናቸው።
ፊልጵስዩስ 2: 6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
በእርሱ ውስጥ ያለው የማይታየው መንፈስ እርሱ ማድረግ የሚገባውን ይነግረው ነበር ስለዚህም ከሥጋዊ ሰውነቱ ይበልጣል።
የዮሐንስወንጌል 14: 28 ከእኔ አብ ይበልጣልነ።
መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ጊዜ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንደነበረ አይነግረንም።
ስለዚህ ኢየሱስ እግዚአብሔር መታየትን በፈለገ ጊዜ ሊኖርበት የመረጠው የሚታይ አካል ነበረ፤ በዚህም አካል ውስጥ ሥራውን በመስራት ተገለጠ።
ከዚህ በኋላ የመረዳት ችግሮች ተፈጠሩ። ኋዋርያት ከሞቱ ከአንድ ወይም ሁለት ትውልድ በኋላ ከአሕዛብ ወገን የመጡ አማኞች ሰው የሆነው ኢየሱስ ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ሊሆን ይችላል ብለው ለማመን መታገል ጀመሩ።
እርሱን “የእግዚአብሔር ልጅ” ብቻ አድርጎ መመልከት ለሰው አእምሮ በጣም ቀላል ነበር። ቀስ በቀስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ በሰማይ ደግሞ የእርሱ አባት የሆነ ሌላ ማለት “እግዚአብሔር አብ” የሚባል አለ ማለት ነው የሚለው ሃሳብ ሥር እየሰደደ መጣ።
በመጀመሪያ ይህ የሁለት አካላት ሃሳብ ጥርት ያለ አመለካከት አልነበረም ግን እየዋለ እያደረ ስለ እግዚአብሐየር ባህርይ ብዙ አይነት የሰው አስተሳሰቦች እንዲመሰረቱ በር ከፈተ። ቀስ በቀስ እነዚህ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው እውነት እየራቁ ሄዱ።
በመጀመሪያ ሥላሴ የሚለው ጽንሰ ሃሳብ አልነበረም ምክንያቱም በዙፋናት የተቀመጡ ሦስት አካላት በሰማይ ስለመኖራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት አልተጻፈም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሁለትነት ትምሕርት ማለትም አብ እና ወልድ በተናጠል ሥር መስደድ ጀመረ። ቆየት ብሎ ደግሞ ሦስተኛ አካል ተጨመረ። ከዚያ በኋላ ሁለት ወይም ሦስት አካላት መኖራቸውንና እነርሱም እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር ሆነው ነገር ግን አንድ አምላክ ብቻ ናቸው ብሎ የመገንዘብ እና የማመን ችግር ተፈጠረ። ይህ ውዝግብ ለዘመናት ቀጥሏል፤ እስከዛሬም ድረስ አልተፈታም።
ክርስቲያኖች ከግሪክ ፍልስፍና የወሰዱዋቸውን መከራከሪያ ሃሳቦች እንዲሁም ፕሌቶ የተባለ የግሪክ ፈላስፋ የፈጠረውን “ትራያድ” የሚል ቃል መጠቀም ጀመሩ። ፕሌቶ እንቁላል ትራያድ ነው ብሎ አስተማረ፤ ሲያብራራም አስኳል፣ ዞፍ፣ እና ቅርፊት አለው ነገር ግን ሦስት ባህርያት ያሉት አንድ እንቁላል ነው አለ። ግን ሦስቱ የእንቁላል አካላት አስኳል፣ ዞፍ እና ቅርፊት በምንም አይነት መንገድ አንዱ ከሌላው ጋር እኩል አይደሉም። አስኳልም ብቻውን እንቁላል አይሆንም። ደግሞም እግዚአብሔርን በእንቁላል መመሰልም ተገቢ አይደለም። ፕሌቶ እንዲህ አለ፡- ምድር የብስ፣ ባሕር፣ እና ሰማይን ታጠቃልላለች። ውሃ ደግሞ ጠጣር፣ ፈሳሽ፣ እና ጋዝ ወይም አየር ሆኖ ይገለጣል። (በዚያ ዘመን ስለ ፕላዝማዎች ገና አላወቁም ነበር።) ሦስትነት በአንድነት ወይም አንድነት በሦስትነት የግሪኮች የባእድ አምልኮ ፍልስፍና ነበር። ይህ አይነቱ ውስብስብ አስተሳሰብ ቀስ በቀስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለውን “ሥላሴ” የተባለ ቃል ወለደ።
የአሕዛብ ሃይማኖቶች ለብዙ ዘመናት የሥላሴን ጽንሰሃሳብ ለመግለጽ ሲሞክሩ ኖረዋል።
በግብጽ የሚገኝ አንድ የድንጋይ ቅርጽ ምስል በአንድ ዙፋን ላይ የተቀመጡ ሦስት ሰዎችን ያሳያል፤ ይህም የእነርሱስ ሥላሴያዊ መለኮት ያመለክታል።
“IHS” የሚል ምልክት በአንዳንድ ቤተክርስቲያናት የመድረክ ጨርቅ ላይ እስካሁንም ድረስ ይታያል። ይህ ምልክት በጥንታዊ ግብጽ ባእድ አምልኮ ውስጥ ከሚያገለግሉ ካህናት ልብስ ላይ የተኮረጀ ነው።
አንድ የቅርብ ዘመን ሰዓሊ የሳለው የሥላሴ ሥዕልም ተመሳሳይ አስተሳሰብን ይወክላል።
የሒንዱዊዝም ሃይማኖት ተከታዮች በአንድ ራስ ላይ ሦስት ፊቶች ያሉት ሃውልት ነበራቸው ።
ስለዚህ አሕዛብ በተለያዩ ባእድ እምነታቸው ውስጥ ስለ አምላካቸው የነበራቸው ግንዛቤ "አንድም ሦስትም" የሚል የሥላሴ ትምሕርት ነበረ። የድንጋይ ምስሎቻቸውን ተመልክተን ለመረዳት ብንሞክር የሚያስተላልፉልን መልእክት እጅግ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። ስለዚህ ለአሕዛብ በሦስት አማልክት ማመን ከባድ አልነበረም። ከዚያ በኋላ ከሶስት በላይ በሆኑ አማልክት ወደ ማመን ሁሉ ሄደዋል።
በሥላሴ ትምሕርት መሰረት ክርሰቲያኖች ሦስት አካላት ባሉት ነገር ግን አንድ በሆነ አምላክ ማመን ይፈለጋሉ ።
ከዚህ በታች ያለው ስዕል በመለኮት ውስጥ ያሉት ሦስት አካላት ምን እንደሚመስሉ ክርስቲያኖች የሚያስቡትን ያሳያል።
እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር የሆኑ ሦስት አካላት ነገር ግን አንድ አምላክ ብሎ ማመን ያኔ ትልቅ የአእምሮ ፈተና ነበር፤ አሁንም ትልቅ የአእምሮ ፈተና ነው። ክርስቲያኖቹ የግሪክ ባእድ እምነት ተከታዮች በአስተሳሰባቸው የረቀቁ መሆናቸውን ባዩ ጊዜ እነርሱም የግሪኮችን የባእድ እምነት አስተሳሰብ መከተል ጀመሩ። እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው። አንድ ምን? ሮማዊው ንጉስ ኮንስታንቲን በ325 ዓ.ም. በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡትን ጳጳሳት “ማንነት” (“essence”) የሚለውን ቃል እንዲቀበሉ አስገደዳቸው። እግዚአብሔር አንድ ኤሰንስ ነው። ይህ የግሪክ ፍልስፍና ነው። ግሪኮቹ ግልጽ ያልሆኑ ሃሳቦችን ቁርጥ ያለ ትርጉም በሌላቸው ቃላት በመግለጽ የተካኑ ሰዎች ነበሩ። ይህ ሥላሴ የሚለው ሃሳብ ምንም ትርጉም የሌለው መሆኑን ለመደበቅ ውዥንብር ለመፍጠር የሚደረግ የቃላት ጋጋታ ነው። ስለዚህ በ325 ዓ.ም. በተሰበሰበው የኒቂያ ጉባኤ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ኤሰንስ ያሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ቃላትን መጠቀም ተጀመረ። ይህ ድርጊት ከባድ ጭቅጭቅ አስከተለ፤ ነገር ግን ንጉስ ኮንስታንቲን ተቃዋሚ ሃሳብ ያላቸው ጳጳሳት ላይ ከባድ ቅጣት እንደሚጥልባቸው ዛተ። ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉትን እንደ “ኤሰንስ” እና “ሥላሴ” ያሉ ቃላትን ለሚቀበሉ ጳጳሳት ትልቅ የገንዘብ ሽልማት ሰጠ። አንዴ እንዚህ ቃላት ተቀባይነት እንዲያገኙ ከተደረገ በኋላ የሥላሴን ጽንሰ ሃሳብ ለመተንተን ሲባል ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ሌሎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ቃላት በብዛት ተጨመሩ።
“በመለኮት ውስጥ ሦስት ስብዕናዎች አሉ” -- ይህ ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም እንኳ እንደ ትክክለኛ እምነት ተደርጎ ተተከለ። ከዚያ ወዲያ እግዚአብሔር በአንድ ስም ሊገለጽ አልቻለም። ሦስት አካላት ወይም ስብዕናዎች በአንድ ስም ሊጠሩ አይችሉም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ስም ጥለው ሦስት የማዕረግ ስሞችን ተኩበት። ከጊዜ በኋላ ሰዎች የእግዚአብሔር ሦስት ማዕረጎች ስሞቹ እንደሆኑ ተቀበሉ። ስለዚህ ሁሉም ነገር በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም መደረግ ተጀመረ። የእግዚአብሔር ስም እየተረሳ መምጣቱን ብዙ ሰዎች አላስተዋሉም።
አሞጽ 6: 10፤ ያን ጊዜ፡-የእግዚአብሔርን ስም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል ይለዋል።
ስለዚህ ዛሬ ክርስቲያኖች የአምላካቸውን ስም አያውቁም።
እግዚአብሔርን እንደ አንድ አምላክ ነገር ግን እንደ ሦስት የተነጣጠሉ አካላት አድርጎ መግለጽ የሚያደነጋግር ሃሳብ ነው። በዚህም ምክንያት ሥላሴ የሚለው ትምሕርት ሁል ጊዜ “እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር የሆኑ ሦስት አካላት” እና ነገር ግን አንድ እግዚብሔር ብቻ በሚሉ ሃሳቦች መካከል የሚዋልል፣ ግራ የሚያጋባ እና የሚያከራክር ሃሳብ ሆኖ ቀርቷል። “ሦስትነት በአንድነት” እና “አንድነት በሦስትነት” ሰዎች ሊገነዘቡ ባልቻሉዋቸው ሃሳቦች ላይ ውዥንብር ለመፍጠር ከግሪክ ፍልስፍና በተውሶ የገቡ አገላለጾች ናቸው።
በሥላሴ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ አይደለም፤ ምክንያቱም ሁለቱ የተለያዩ አካላት ናቸው።ነገር ግን ማርያምን የጋረዳት እና በማሕፀንዋ ውስጥ ኢየሱስ የሚወለድበትን ዘር ያስቀመጠ መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የኢየሱስ አባት ያደርገዋል። የሰው ልጅ እንደመሆኑ ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ አባቶች ሊኖሩት አይችልም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ነው። የሥላሴ ትምሕርት ከመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስን በመቃረን ስለተጀመረ ሃሳቡን ለመግለጽ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የተወሰዱ ቃላትን መጠቀም ግዴታው ነው። ከዚህም የከፋው ነገር ደግሞ ክርስቲያኖች የሥላሴ ትምሕርት እውነት አለመሆኑን የሚያጋልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን መቃወም መጀመራቸው ነው።
ማቴዎስ 1: 20 ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና
የልጁ አባት ብቻ በእናቱ ማሕፀን ውስጥ ልጁ እንዲፀነስ ማድረግ የሚችለው።
በኒቂያ ጉባኤ ክርር ያለ ክርክር ተነሳ፤ ነገር ግን ንጉስ ኮንስታንቲን የተቃውሞ ሃሳብ የሚያነሱትን ሁሉ ለማሳደድ ዛተ፤ ደግሞም እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦችን እና ቃላትን ለሚቀበሉ ጳጳሳት ታላላቅ የቤተክርስቲያን ሕንጻዎችን ለመገንባት ቃል ገባላቸው።
እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላትን በተመለከተ እያደገ የመጣው ቸልተኝነት ኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉ ግልጽ ትምሕርቶችን መካድ አስከተለ።
“እግዚአብሔር አብ” መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስያሜ ሲሆን “እግዚአብሔር ወልድ” ግን አይደለም። እንዲሁም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ” የሚለው አጠራርም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈጽሞ አይገኝም።
“እግዚአብሔር ወልድ” የሚል መጠሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤ ነገር ግን “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ። በሥላሴ የሚያምኑ ይህንን ልዩነት ማስረዳት አይችሉም።
“በመለኮት ውስጥ ሦስት አካላት” መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቋንቋ አይደለም።
አብ እና ወልድ “አብረው እኩል” ናቸው። “አብረው እኩል” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።
ይህም መለኮትን በተመለከት መሰረታዊ ችግር ሆነ።
ኢየሱስ አባቴ ከእኔ ይበልጣል ብሎ ተናገረ።
ዮሐንስ 14: 28 ከእኔ አብ ይበልጣልና
ፊልጵስዩስ 2: 5 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።
6 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
ኢየሱስ ደግሞ ከአብ ጋር እኩል ነኝ ብሎ ያውቃል።
አብ ከእርሱ ከበለጠ እንዴት ከአብ ጋር እኩል ይሆናል?
ሁለቱ የተለያዩ ስብዕናዎች እስከሆኑ ድረስ የሥላሴ ውስብስብ ቋጠሮ መቸም አይፈታም። “አብረው እኩል” የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆነ ምንም አይገልጽም። ከዚያም የባሰ ደግሞ ኢየሱስ አባቴ ከእኔ ይበልጣል ብሎ የተናገረውን ቃል ይቃረናል።
“በሥላሴ ውስጥ የመጀመሪያው አካል”፣ “በሥላሴ ውስጥ ሁለተኛው አካል” እና “በሥላሴ ውስጥ ሦስተኛው አካል” እነዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት ናቸው።
እግዚአብሔርን ለመግለጽ እነዚህን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ቃላት በመጠቀም ቤተክርስቲያን መሰረታዊ ከሆነው ከኃዋርያት እምነት ርቃ መሄዷ ግልጽ ነው።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን ኃዋርያት የጻፉትን አመነች። የጥንቷ ቤተክርስቲያን ኃዋርያት የጻፉትን አልተቃረነችም ደግሞም አልተከራከረችም።
ዮሐንስ 17: 20 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤
ስለ ኢየሱስ የምናውቀው ከደቀ መዛሙርቱ በምንሰማው ብቻ ነው ወይም ደግሞ ከኃዋርያቱ።
የትጋ ነው ስሕተት የተጀመረው? አንድን ሃሳብ እጅግ ማግዘፍ እና ሌሎችን ደግሞ ፈጽሞ ማስወገድ ትልቅ አደጋ አለው።
ችግሮች የተጀመሩት ክርስቲያኖች ኢየሱስን ከእግዚአብሔር አብ የተለየ አካል አድርገው ማሰብ ሲጀምሩ ነው።
አብን እና ወልድን ሁለት የተለያዩ አካላት አድርገው መመልከት የጀመሩ ጊዜ ይህ አመለካከት ልክ አለመሆኑን የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለመቀበል እምቢ አሉ።
በኒቂያ ጉባኤ የተነሳው የመጀመሪያው አከራካሪ ሃሳብ ስለ አብ እና ስለ ወልድ ነበረ። መንፈስ ቅዱስ ከጊዜ በኋላ ነው የተጨመረው። “በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን”። ለ56 ዓመታት የቆየ የጦፈ ክርክር ከተደረገ በኋላ በ381 ዓ.ም. በኮንስታንቲኖፕል ከተማ በተደረገው ጉባኤ ላይ የሥላሴ ትምሕርት በይፋ ጸደቀ። ጅማሬው ግን በኒቂያ በ325 ዓ.ም. ነበረ።
ናምሩድ ዛሬ ባግዳድ ተብላ በምትታወቀው ከተማ አካባቢ የመጀመሪያይቱን ጥንታዊ ዓለም አቀፍ መንግስት ባቢሎንን የመሰረተ ሰው ነው። ታላላቅና ኃይለኛ ሥራዎችን ከመስራቱ የተነሳ “ኤል ባር” ወይም “እግዚአብሔር ወልድ” የሚል ስያሜ ሰጡት። ይህ በሥራዎቹ የተነሳ የአምላክነትን ማዕረግ ያገኘ ሰው ነው።
በአፈታሪክ የሚታወቀው ሔርኩሊስ አስደናቂ ሥራዎችን በመስራቱ ወደ አምላክነት ከፍ ተደርጓል። እርሱም እግዚአብሔር ወልድ በሚል ስያሜ ተጠራ ማለትም ሰው የነበረ ኋላ ግን አምላክ የሆነ።
ታላቁ እስክንድር ታላላቅ የጦር ጀብዱዎችን ከመፈጸሙ የተነሳ የምሥራቅ ሕዝቦች በደስታ እንደ አምላክ ተቀብለውታል። ግሪኮችም እንኳ ሳይቀሩ እያንገራገሩም ቢሆን አምላክነቱን ተቀብለውለታል።
እስክንድር በሕዝብ አእምሮ ውስጥ እግዚአብሔር ወልድ በመሆን ወደ አምላክነት ከፍታ የወጣ የመጀመሪያው በገሃዱ ዓለም የሚታወቅ ሰው ነበረ፤ ይህም የሆነ እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎችን በሚያስገርሙ ሥራዎቹ አማካኝነት ነው።
ስለዚህ ስለ ሥላሴ ዋነኛው አስተማሪ አትናቴዎስ ኢየሱስን እጅግ አስደናቂ በመሆኑ “እግዚአብሔር ወልድ” ሆኗል ብሎ ገለጸው።
ይህም አባባል ሁለት አማልክት እንዳሉ በማመልከቱ ትልቅ ውዝግብ አስከተለ።
እያንዳንዳቸው አምላክ የሆኑ ሁለት አካላት (እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር ወልድ) ነገር ግን በአንድነት አንድ አምላክ የሆኑ ብሎ ማሰብ ትልቅ የአእምሮ ፈተና አስከተለ። ምንም ያህል ጥረት ቢደረግ የዚህ ሃሳብ አደናጋሪነት ሊወገድ አልቻለም። እሚያሳዝነው ነገር አብዛኛው ማብራሪያ የተገኘው ከግሪክ ፍስፍና በተወሰዱ ቃላት ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት የሥላሴን ሃሳብ አይደግፉም።
ይህ ውዥንብር የተጀመረው ኮንስታንቲን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነውን ኤሰንስ የሚለውን ቃል እንዲቀበሉ ባስገደዳቸው ጊዜ ነው። አብ እና ወልድ አንድ ኤሰንስ ያላቸው ሁለት አካላት ናቸው ተባለ። ይህ አንድ ኤሰንስ አንድ አምላካ አደረጋቸው።
እግዚአብሔር ግን ዘላለማዊ መንፈስ ሲሆን ኢየሱስ ከሰው የተወለደ ሥጋዊ አካል ነበረው። መንፈስ እና ሥጋ አንድ ኤሰንስ አይደሉም፤ የተለያዩ ናቸው። ስለዚህ ኤሰንስ የሚለው ሃሳብም ጭምር አጨቃጫቂ ነበር።
የኢየሱስ አካል ጅማሬ ስለነበረው ዘላለማዊ አልነበረም። አትናቴዎስ እና ተከታዮቹ ኢየሱስ ዘላለማዊ ልጅነት እንዳለው ለማረጋገጥ ሞከሩ። ይህ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካለመሆኑ በተጨማሪ በሚታወቅ ቀን የተወለደ ሰውን ከመወለዱ በፊትም ነበረ ሲባል አሳማኝ አይደለም።
ከዚህ በኋላ አብ እና ወልድ “አብረው እኩል” ናቸው የሚለው ሃሳብ ተወለደ። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቃል ተጨማሪ ጭቅጭቅ ፈጠረ።
ዮሐንስ 5: 36 አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።
ዮሐንስ 5: 19 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።
በዚህ ንግግሩ ኢየሱስ አብ ከእርሱ እንደሚበልጥ ግልጽ አድርጓል።
ሌላው ጣጣ ደግሞ ኢየሱስን በመለኮት ውስጥ ሁለተኛው አካል አድርጎ ማስገባት ነው። ምክንያቱም ዘዴኛ ክርክራቸውን ገድል የሚያስገባ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አለ። ይህም ቃል ኢየሱስን መለኮት ውስጥ በማስገባት ፈንታ መለኮትን በሙሉ በኢየሱስ ውስጥ ያኖረዋል።
ቆላስይስ 2: 8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
ይህ እንደ ኤሰንስ እና ሦስት በ አንድ የሚሉ ቃላትን ካበረከተልን የግሪክ ፍልስፍና እንድንጠነቀቅ የሚነግረን ግልጽ ማስጠንቀቂያ ነው።
ከክርስትና አስቀድሞ በአሕዛብ ዘንድ ብዙ ሥላሴዎች ነበሩ።
ክርስቲያኖች ደግሞ ሦስቱ አካላት እንደ ግብጻውያኑ ሥላሴ በአንድ ዙፋን ተቀምጠው እንደሆን ወይም በሦስት የተለያዩ ዙፋናት ተቀምጠው እንደሆን እርግጠኛ መሆን አልቻሉም።
መንፈስ ቅዱስ በዙፋን ተቀምጦ እንደሆን የሚናገር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊገኝ አልቻለም።
በሥላሴ ውስጥ ለማካተት ለረጅም ጊዜ አስቸጋሪ ሆኖ የቆየው አካል መንፈስ ቅዱስ ነበረ። የሥላሴ ትምሕርት መንፈስ ቅዱስ በመለኮት ውስጥ ራሱን የቻለ አንድ አካል፣ ከአብ እና ከወልድም ጋር እኩል የሆነ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም የሌለው ነበር። ስም የሌለው አካል? እዚህጋ ችግር አለ።
ስለዚህ ብልጣብልጥ ሰዎች “በሦስት ስብዕናዎች ውስጥ አንድ አምላክ” ወይም “በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት ስብዕናዎች” የሚለውን ምልከታቸውን በምናባቸው ለመሳል በከንቱ ታገሉ። ዛሬም ድረስ ተመሳሳይ ችግር ነው የሚገጥመን። ሰዎች አንድን ሃሳብ በምናባቸው ማየት ከመቻላቸው በፊት ሊገነዘቡት አይችሉም። (ኢየሱስ ለዚህ ነው ትምሕርቶቹን በዓይነ ሕሊና ለማየት በሚያመቹ ምሳሌያዊ ታሪኮች አማካኝነት ያቀርብ የነበረው።) በኒቂያ ጉባኤ ላይ የተገኙ ጳጳሳት በሙሉ በአእምሮዋቸው ውስጥ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል የሚያስቡት ምናባዊ ምስል ነበራቸው። ነገር ግን ይህ ምናባዊ ምስል በአንድ እና በሁለት አካላት መካከል እየዋዠቀ፣ እየደበዘዘ መጣ። (ጳጳሳቱ በ325 ዓ. ም. አሳማኝ ባልሆነ መንገድ በኒቂያ ጉባኤ ላይ መንፈስ ቅዱስንም ሊጨምሩ ቢሞክሩም እንኳ መንፈስ ቅዱስ በሥላሴ መለኮት ውስጥ የተጨመረው በ381 ኮንስታንቲኖፕል ውስጥ በተሰበሰበው ጉባኤ ነበር።) በዚህ ምክንያት ስለ እግዚአብሔር ጥርት ያለ ግንዛቤ ሊጨብጡ አልቻሉም። አንዳንዶች ሁለተኛውን አካል ከመጀመሪያው እንደሚያንስ አድርገው አሰቡ። ሌሎች ደግሞ አብ እና ወልድን አብረው እኩል እንደሆኑ አድርገው ቆጠሩ። ክርክሩ ለክፍለ ዘመናት ሁሉ ሳይፈታ ዘለቀ፤ በአንዱም ወገን የተሰለፉ ሰዎች በሌላው ወገን ያሉትን አሳደዱ፤ እርስ በስርሳቸው ተገዳደሉ። ሆኖም ድብዝዝ ያለ እና በአንዳንድ ገጽታው አሳማኝ የሚመስል በሌላ በኩል ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጣላ ትምሕርት አመጡልን። የሚያሳዝነው ከክርክሩ በሁለቱም ወገን የቆሙት የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘው ነበር። የሥላሴ ትምሕርት ዛሬም ድረስ የግራ መጋባት ምንጭ ነው። ሰዎች ስለ መለኮት ብዙ ይናገራሉ ነገር ግን ሥላሴን የሚገልጡባቸው ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ውዥንብር መፍጠሪያ ባእድ ቃላት ከመሆናቸው የተነሳ እውነትን በሚገባ ገልጠው ማሳየት አይችሉም። ከሚናገሩዋቸው ዓረፍተ ነገሮች የአብዛኞቹ ምንጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ አይለም። ሲናገሩ መስማት ፖለቲከኛን እንደማዳመጥ ይመስላል።
የሥላሴ ትምሕርት ትልቁ ሰለባ የሆነው የእግዚአብሔር ስም ነው። እግዚአብሔር አብ ያሕዌ በመባል ይወቅ ነበር። የእግዚአብሔር ልጅ ስሙ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ችግር የሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ስም አለመገኘቱ ነበር። በዚህም ምክንያት ሦስቱን አካላት ለመግለጽ የተገኙት ስሞች ሁለት ብቻ ነበሩ፡ እነርሱም ያሕዌ እና ኢየሱስ ናቸው።
ኢየሱስ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም (ስም በነጠላ እንደተጻፈ ልብ በሉ) እንድናጠምቅ አዘዘ። ለሦስት አካላት አንድ ነጠላ ስም ብቻ። ይህ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው።
ማቴዎስ 28: 19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤
ለሦስት አካላት የሚሆን አንድ ስም የለም።
ስለዚህ ቀስ ተብሎ የእግዚአብሔር ስም ተጣለ እና በሦስት የማዕረግ መጠሪያዎች ተተካ፤ እነርሱም፡- አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ። ሦስት የተለያዩ አካላትን ወደ መለኮት ውስጥ በማስገባት የክርስቲያን ጳጳሳት የእግዚአብሔርን ስም ማስወገድ ተሳካላቸው።
ከዚያ ሌላ ችግር ገጠማቸው። ኃዋርያት በኢየሱስ ስም እንዳጠመቁ ባዩ ጊዜ ጳጳሳቱ በድፍረት ጴጥሮስ ተሳስቶ እደነበረ ተናገሩ።
የሐዋርያት ሥራ 2: 38 ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤
ቀጥሎ ደግሞ ክርስቲያኖች ይህንን ቃል እንዳላዩ እንዲያልፉ ወይም እንዳይቀበሉት ተነገራቸው። ይህም እውነት የሚቀብር የከፋ ስህተት ነበር።
ጥምቀት ቀብርን የሚያመለክት ሥርዓት ነው። ኃጥያተኛው ንሰሃ ይገባል ከዚያም ለአሮጌው ሕይወቱ ይሞታል። ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ከውሃ በታች ይቀበራል (ይህ መሞቱን ያመለክታል) ከዚያ ደግሞ ከውሃው ውስጥ በመውጣት ከሞት ተነስቶ በክርስቶስ አዲስ ሰው ሆኖ ይነሳል።
ኢየሱስ ብቻ ነው የሞተው፣ የተቀበረው፣ እንዲሁም ከሙታን የተነሳው። እግዚአብሔር አብ ሞቶ አያውቅም፣ አልተቀበረም፣ አልተነሳምም። መንፈስ ቅዱስ አልሞተም፣ አልተቀበረም፣ አልተነሳምም። ስለዚህ ጥምቀት ከእነዚህ ሁለት የሥላሴ አካላት ጋር ዝምድና የለውም።
ሮሜ 6: 3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤
ሙሽራ የባሏን ስም ተቀብላ ትጠራበታለች። ልክ እንደዚሁ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ሙሽራ እንደመሆናቸው የባቸውን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም መቀበል አለባቸው። የኢየሱስን ስም የምንቀበልበት ብቸኛው ሥርዓት የውሃ ጥምቀት ነው።
ነገር ግን ለሥላሴ ትምሕርት ምስጋና ይግባውና ክርስቲያኖች ከ325 ዓ.ም. ጀምሮ የኢየሱስን ስም መቀበል አቁመዋል። አሁን የእግዚአብሔር ስም አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ነው የሚል ድብዝዝ ያለ ግንዛቤ ይዘው ተቀምጠዋል። ክርስቲያኖች አሁን አምላካቸን የሚጠሩበት ስም የላቸውም። ለሦስት የተለያዩ አካላት አንድ ስም መስጠት እጅግ ከባድ ነው።
የጥንት ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ስም የነበራቸው እምነት ምን ይመስል ነበር?
እግዚአብሔር አይታይም። እርሱ ምስል እና ቅርጽ የሌለው መንፈስ ነው። እግዚአብሔር ለራሱ መንፈሳዊ አካል ማዘጋጀት ይችላል። እግዚአብሔር በውስጡ በሙላት የሚኖርበትን እና ራሱን በሥጋ የሚገልጥበት ወይም ራሱን በሥራው የሚያሳይበት ኢየሱስ የተባለ ሰው ፈጠረ። ይህም ሰው የራሱን ደም ይዞ ወደ ሰማይ ሄዶ በስርየት መክደኛው ላይ የራሱን ሥጋ የኃጥያት መስዋእት አድርጎ አቀረበ። ከዚያም መንፈሱን በቤተክርስቲያን በአማኞች ውስጥ እንዲኖር ወደ ምድር ላከ።
እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር አብ በተለያዩ መንፈሳዊ አካላት በመገለጥ ከአይሁድ ሕዝብ በላይ ሆኖ ታይቷል፤ ለምሳሌ በእሳት አምድ፣ በደመና አምድ፣ ውሃ በሚያፈልቅ ዓለት፣ እና እንደ እግዚአብሔር መልዓክ።
በዚህ አይነቱ መገለጥ እግዚአብሔር የመዳንን መስፈርቶች በማሳየት እነዚህን መስፈርቶች መጠበቅ ለሰዎች የማይቻል መሆኑን አሳይቷቸዋል።
እግዚአብሔር አብ በአይሁድ ዘንድ “ያሕዌ” በሚል ስሙ ይታወቃል፤ ይህም እኛ “እግዚአብሔር” ብለን የምንተረጉመው ስም ነው።
በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ውስጥ በመኖር እግዚአብሔር ራሱን በሰው ሥጋ ውስጥ ገልጦ ሕጎቹን ፈጽሞ በመጠበቅ የራሱን መዳን መፈጸም የቻለ ብቸኛው ሰው ሆኖ ተገኝቷል። ከዚያም እኛ ብቁ ያልሆንን ሰዎች እርሱ በገዛ ክንዱ ያመጣው መዳን ውስጥ ድርሻችንን ልንካፈል እንድንችል የራሱን ሕይወት መስዋእት አድርጎ ለማቅረብ ወሰነ። እንደ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ አማኑኤል ነው፤ ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ልክ እንደ እኛ ሰው ሆኖ በመገኘት፤ የሚቤዠን የሥጋ ዘመድ ሆነን።
ማቴዎስ 1: 23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
እግዚአብሔር አንድ ሰብዓዊ ስም ብቻ አለው እርሱም ኢየሱስ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመሆን የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በሰው ሥጋ በተገለጠ ጊዜ የተጠራበት ስም ኢየሱስ ነው።
ኢየሱስ ደሙን ይዞ ወደ ሰማይ ሄደ፤ በዚያም ኃይጥያታችንን ይቅር ይለን ዘንድ እንደ እግዚአብሔር በግ መስዋእት ሆኖልን በስርየት መክደኛው ላይ ተቀምጧል። ደግሞም ተዓምራዊ በሆነ መንገድ መንፈሱን በእኛ ልብ ውስጥ ይኖር ዘንድ ወደ ምድር ላከው። ስለዚህ እንደ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በአማኞቹ ውስጥ ሆኖ ይገለጣል።
ዮሐንስ 14: 17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
ቅባቱ መንፈስ ቅዱስ ነው። ኢየሱስ፣ የተቀባው በግሪክኛ ቋንቋ ክርስቶስ ይባላል። እኛም በቋንቋችን ክርስቶስ እንለዋለን።
1ኛ ጢሞቴዎስ 3: 16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
በታሪክ ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር በመንፈስም በሥጋ ውስጥም ተገልጧል።
እንደ እግዚአብሔር አብ ለአይሁዶች መንፈስ ሆኖ ተገልቶላቸዋል። ለአይሁድ በተገለጠላቸው ጊዜ መጠሪያው ያሕዌ የሚለው የእብራይስጥ ስም ሲሆን ትርጓሜው ጌታ ማለት ነው።
እንደ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ በተባለው ሰው ሥጋ ውስጥ በመገለጥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ኖረ። ስለዚህም ሰብዓዊ ስም ነበረው፤ ሰብዓዊ ስሙም ኢየሱስ ይባላል።
እንደ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዳግመኛ በተወለዱ ሰዎች ልብ ውስጥ በማደር በእኛ ሥጋ ውስጥ ይገለጣል። እርሱም ክርስቶስ በሚባለው የማእረግ ስሙ የሚጠራው የተቀባው ነው።
“አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ” ማለት እግዚአብሔር ከእኛ በላይ እንደ ጌታ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ እንደ ክርስቶስ ማለት ነው።
ጌታ እና ክርስቶስ ማእረጎች ናቸው፤ ነገር ግን ስለየትኛው ኢየሱስ እንደምንናገር ግልጽ ማድረግ ይጠቅመናል። ኢየሱስ ሰብዓዊ ስሙ ነው። ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም ሁለት ማእረጎችን የያዘ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ ስም ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ጌታ ወይም ክርስቶስ የሚሉትን ማእረጎች መጨመር ለምን አስፈለገ? ምክንያቱም ኢየሱስ በሚለው ስም የሚጠሩ ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው። ነገር ግን አንድም ሰው ጌታ ኢየሱስ አይደለም። አንድም ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም። ለዚህ ነው በእንግሊዝኛ ተናጋሪ ሃገሮች የማያምኑ ሰዎች እንኳ ሲናደዱ ጂሰስ ክራይስት! የሚሉት። ኃጥያተኞች በዚህ ስም ውስጥ ኃይል እንዳለ ያውቃሉ። ይህ እግዚኢዘብሔርን እንደሚያሳዝን ያውቃሉ ምክንያቱም ትዕዛዙ የእግዚኢዘብሔር የአምላክን ስም በከንቱ አትጥራ ይላል። ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ስለሆነ በጣም አስፈላጊ ነው።
ዘጸአት 20: 7፤ የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤
በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚሳደብ ኃጥያተኛ የለም። ኃጥያተኞች እነዚህ ማዕረጎች የእግዚአብሔር ስም እንዳልሆኑ ያውቃሉ። ቤተክርስቲያንም ወደፊት ቢያንስ ይህንን ያህል እንኳ እንድትነቃ ተስፋ እናደርጋለን።