ሰንበት ቅዳሜ ነው ወይስ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት?
We update studies as the Lord Jesus leads us. You can find the latest update of this study at ChurchAges.net
የሰንበት እረፍት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተምሳሌት ነው፤ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከሐጥያት ሥራችን ያሳርፈናል።
First published on the 10th of October 2018 — Last updated on the 5th of November 2022ማቴዎስ 15፡9 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
የሰንበት አስተምህሯችን ትክክል መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡
የመጀመሪያው ጉዳይ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች እሁድን ሰንበት ወይም የእረፍት ቀን ብለው መጥራታቸው ነው፡፡
ይህ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡
የሰንበት ቀን እሁድ አይደለም፡፡ እሁድ ለክርስቲያኖች የአምልኮ ቀን ሊሆን የቻለው የኢየሱስን (ሞትን ድል የነሳና የዘላለም ሕይወትን ሊሰጠን ከሞት የተነሳ ብቸኛው የሃይማኖት መሪ) ትንሳኤ ለማክበር እና መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን የጴንጤ ቆስጤ ቀን ለማክበር ነው (መንፈስ ቅዱስ ደቀመዛሙርትን ከአለማመን ነጻ ስላወጣቸው ከኃጢአት እረፍት አግኝተው ወደ ቀደመው የኃጥያት ሥራ አልተመለሱም)፡፡ ከጊዜ በኃላ ግን ብዙ ክርስቲያኖች ዳግመኛ እንዲወለዱ የሚያደርጋቸውንና ከአለማመን ነጻ አድርጎ ውስጣዊ እረፍት የሚሰጣቸውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ቸል እያሉ ሄዱ፡፡ ከዚያም በየሳምነቱ እሁድ ማምለክ ላይ ትኩረታቸውን አደረጉ፤ እሁድ ከሥራ እረፍት የሚደረግበት ቀን በመሆኑ በዚያውም የአምልኮ ቀን ሆነ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከድሮ ጀምሮ ይህንን ሰው ሰራሽ አስተምህሮ ካስተዋወቀች በኋላ የተወሰኑ መቶ ዓመታት ሲያልፉ ይህ እምነት ተቀባይነት ያለው ልማድ ሆኖ ቀረ፡፡ ልማዶችን ደግሞ ከመቃወም ይልቅመቀበል ይቀላል፡፡
እሁድን የአምልኮ ቀን ማድረጉ ምንም አይነት ስህተት የለበትም፡፡ ስህተቱ እሁድን የሰንበት ቀን ብሎ መጥራቱ ነው፡፡ ከሳምቱ ቀናት መካከል ሰንበት ብለህ የምትቆጥረው ቀን ከፈለክ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚለው ሰባተኛው ቀን ቅዳሜ ነው፡፡ ሰንበት ከኃጢአት ስራዎችህ የምታርፍበትና የምትገላገልበት ውስጣዊ ልምምድ እንዲሆንልህ ከፈለክ የሰንበት ቀን ላንተ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የምትቀበልበት ቀን ነው፡፡
እሁድን ሰንበት አድርጎ መውሰድ በሰዎች የተፈጠረና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተመሰረተ የቤተክርስቲያን ልማድ ነው፡፡
የአምልኮ ቀን በመሆኑ ሰዎች ለእሁድ ተጨማ አጽንኦት በመስጠት እሁድን የጌታ ቀን ብለው ጠሩት፡፡
የጌታን ቀን ማለት ሰው በምድር ላይ ያመጣውን የኃጥያት እና የቴክኖሎጂ ትርምስ የሚያጠራበት የታላቅ መከራ ጊዜ ነው፡፡ አሁን ሰው የፈለገውን የሚፈጽበት “የሰው ቀን” ነው። በቅርብ ግን እግዚአብሔር የፈለገውን የሚያደርግበት “የጌታ ቀን’’ ይመጣል፤ ይህም ኃጥያትን ጠራርጎ የሚያስወግድበት ቀን ነው፡፡
ኢሳይያስ 13፡6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
ኢሳይያስ 13፡9 እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
ኢዮኤል 3፡14 የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፡፡
ውሳኔ። ሁላችንም ውሳኔ መወሰን አለብን፡፡ ዝም ብለን ብዙዎች በፈሰሱበትና ተቀባይነት ባለው መንገድ እንሄዳለን ወይስ ብቻችንን ብንቀርም እንኳ በቃሉ ጸንተን እነቆማለን?
አሞጽ 5፡18 የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
ሚልክያስ 4፡5 እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመልሰን፤ ወደ ጥንቷ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እምነቶች የሚመልሰን ነቢይ ያስፈልገናል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ፤ምንም ያህል ቅን ብንሆን እንኳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እምነቶቻችን ወደ ታላቁ መከራ ውስጥ ይዘውን ይወርዳሉ፡፡
1ኛ ተሰሎንቄ 5፡2 የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡10 የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
እሁድ የጌታ አለመሆኑ እጅግ በጣም ግልጽ ና፡፡
እስቲ የሰንበት ቀን ቅዳሜ ሊሆን የመቻሉን ሁኔታ እንመልከት፡-
የሰንበት ቀን በሳምቱ የሥራ ቀኖች መጨረሻ እና ቀጣዩ ሳምንት ከመጀመሩ በፊት ከሳምንቱ ስራዎች የምናርፍበት ቅዳሜ ነውን?
ወይም ሌላ አማራጭ እንመልከት፡
የሰንበት ቀን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነውን? የሰንበት ቀን መንፈስ ቅዱስ አለማመንህን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቃሉ ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ እምነት እንዲተካልህ መፍቀድ ነውን?
ክርስቶስ አስተሳሰብህንና ድርጊትህን ሲቆጣጠርና እንዲሁም ካለማመንን ትተህ ከኃጢአት ስራዎችህ እረፍት ስታገኝ የዚያን ጊዜ ክርስቶስየሕይወትህ ጌታ ይሆናል፡፡
በድጋሚ ወደ ኃጢአት ሥራዎችህ እና ወደ አለማመንህ ተመልሰህ አትሄድም፡፡
እግዚአብሔር ከአይሁድ በላይ (ከውጭ) በነበረበት ጊዜ ሰንበት የእረፍት ቀን ነበር፡፡
ከአለም ውጫዊ ቁሳዊ ነገሮች ፍላጎት እረፍት የሚደረግበት ቀን ነበር።
እግዚአብሔር ከአይሁድ ውጭ ስለነበረ ለስጋዊ ቁሳዊ ጥቅማቸው ከማሰብ ተላቅቀው እርሱ ላይ የሚያተኩሩበ አንድ ነጻ ቀን እንዲኖራቸው ይፈልግ ነበር፡፡
እግዚአብሔር በአንተ ውስጥ ሲያድር ሰንበት አንተ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖርህ አዲስ ሕብረት ነው የሚሆነው፡፡ እውነተኛ እረፍት ማለት በውስጥህ ለሚኖረው እግዚአብሔር ያለህ ውስጣዊ መሻት ነው፡፡
አዲሰ ኪዳን በዚህ ቁሳዊ ዓለም የምናገኘውን ግላዊ ጥቅም ተስፋ በማድረግ ከመሯሯጥ አቅጣጫችንን ለውጠን ፍላጎታችንን ከክርስቶስ ጋር ወዳለ ጥልቅ መንፈሳዊ ሕብረት ዘወር ማድረግ ነው፡፡
ኤርምያስ 31፡31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤
32 ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ካላንደርን/የቀን መቁጠሪያን ተመልከት፡፡ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እሁድ ነው፡፡ የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ደግሞ ቅዳሜ ነው፡፡ እሁድን የአሮጌው ሳምንት ስምንተኛ ቀን አድርገንም መውሰድ እንችላለን፡፡
እሁድ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሐሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ
1 2 3 4 5 6 7 8
እሁድ በእርግጠኝነት ሰባተኛው ቀን አይደለም፤ ስለዚህ እሁድ የሰንበት ቀን ሊሆን አይችልም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የሰንበትን ቀን የሚያስተዋውቀው እንደሚከተለው ነው፡፡
ዘፍጥረት 2፡3 እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።
ይህ ቀን ሰባተኛው ቀን በመሆኑ ቅዳሜ ነበር።
ነገር ግን የዚህ ቃል ትኩረቱ በእግዚአብሔር በረከት ላይ ነበር፡፡ ቀኑን የባረከው ሰባተኛ ቀን (ቅዳሜ) በመሆኑ ሳይሆን እግዚአብሔር ያረፈበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡
በመሆኑም በረከቱ ያለው በሰባት ውስጥ ሳይሆን በእረፍት ውስጥ ነው፡፡
ስለዚህ ሰንበት የእግዚአብሔር እረፍት ነው፡፡
በመሰረቱ “ሰንበት” ማለት “እረፍት” ማለት ነው፡፡
የሰንበትን ጉዳይ በትክክል የምንረዳው ለእኛ የተዘጋጀልንን የእግዚአብሔርን እረፍት ስናገኝ ብቻ ነው፡፡
ዕብራውያን 4፡9 እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
ዕብራውያን 4፡10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
የእግዚአብሔርን እረፍት የምናገኘው እግዚአብሔር ባረፈበት መንገድ ከሥራዎቻችን ስናርፍ ብቻ ነው፡፡
ለሳምንት ያህል ሰርተህ ቅዳሜ እረፍት ብታደርግ ከዚያም ወደ ሥራ ብትመለስ፤ እግዚአብሔር እንዲህ አይደለም ያረፈው። ፡፡
እግዚአብሔር የፍጥረት ሥራውን ካከናወነ በኋላ መፍጠርን አቆመ፡፡ ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ፍጥረታትን ወደ መፍጠር አልተመለሰም ምክንያቱም ፍጥረት ተሰርቶ ተጠናቅቋል፡፡
እግዚአብሔር ሊያርፍ የቻለው ኃጢአት ባለመኖሩና የሰው ልጅም የሚያፋ ሥራ ስላልነበረው ነው፡፡
ኃጢአት ከገባ በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ስለረገማት ሰው በሕይወት ለመኖር ጥሮ ግሮ ለመብላት ተገደደ፡፡
ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፡- የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ዘፍጥረት 3፡18 እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።
ዘፍጥረት 3፡19 ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።
በኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር ሰው በልፋት እንዲኖር ፈረደበት፡፡
እና ኑሮን ለማሸነፍ የራሳችንን ሥራ ከመስራት አርፈን ወደ ልፋት ተመልሰን ላለመሄድ እንዴት እንችላለን?
በጉልበታችን እየሰራን ስለመኖር የምናስብ ከሆነ ወደ እረፍት መግባት የሚቻል አይደለም። ሁላችንም ያለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ሁላችንም በሳምንት አንድ ቀን እረፍት ያስፈልገናል፤ ከዚያም ተመልሰን ወደ ሥራ መግባት ይጠበቅብናል፡፡
ስለዚህ አይሁድ ሲያደርጉ የነበረው የእውነተኛው እረፍት ጥላ ነበር፡፡ይሰራሉ፣ ያርፋሉ፣ ተመልሰው ወደ ሥራ ይገባሉ ይህም ማቆሚያ የሌለው ኡደት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ያረፈው እንደዚህ አይደለም፡፡
በመሆኑም “ሥራ” የሚለው ቃል እዚህ ላይ እኛ ለኑሮአችን የምንሰራቸውን ሥራዎች የሚመለከት አይደለም፡፡ ከዚህ ይበልጥ ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው፡፡ “ሥራዎቻችን” ማለት ማቆም ያለብን የኃጢያት ሥራ ማለት ነው። በኃጢአት ተወለድን፤ የራሳችንን ስራ እንሰራለን፡፡ “የራሳችን ሥራ” የሚለው ቃል በተጨማሪ ፍላጐታችንን፣ መሻቶቻችንና አጀንዳዎቻችንን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር የራሳችን ዕቅድ አካል ሳይሆን የእርሱ ዕቅድ አካል እንድንሆን ይፈልጋል፡፡
ሮሜ 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
ከዚያም ክርስቶስን እንደ አዳኛችን አድርገን በመቀበል ከኃጢአት ስራዎቻችን ተመልሰን ንስሀ እንገባለን፡፡ ይህ ግን ጅማሬ ብቻ ነው፡፡
ማጨስን፣ መጠጣትን፣ መቆመርን ወዘተ ወደ መሳሰሉት የኃጢአት ስራዎቻችን ተመልሰን ከመሄድ እንዲጠብቀን እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ ሊኖር ያስፈልገናል፡፡ ከገዛ ራስህ ሥራ ሊያሳርፍህ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው በልብህ ውስጥ እንዲኖር ከፈቀድክለት ነው፡፡
በእውነት የኃጢአት ሥራዎቻችንን ከመስራት ማቆም የምንችለው እግዚአብሔር ወደ ልብችን ገብቶ ሕይወታችንን ሲቆጣጠር እንዲሁም አዳዲስ የተቀደሱ መሻቶችን ሲሰጠን ብቻ ነው፡፡ ከቀደሙ የኃጢአት ስራዎቻችን ስናርፍና ወደነዚህ የኃጢአት ስራዎች ተመልሰን የማንሄድ ጊዜ እውነተኛውን ሰንበት አግኝተነዋል፡፡
ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተብሎ ይጠራል፡፡
ከመጀመሪያውም ጀምሮ የእግዚአብሔር ዓላማ በሕንፃዎች ውስጥ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ለመኖር ነበር፡፡ እግዚአብሔር በልብህ ውስጥ መኖሩ የተባረክህ ሰው ያደርግሃል፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህንን የእግዚአብሔር ሚስጥር በመሳት ቀኑን በየሳምነቱ ማክበር ላይ ብቻ ያተኩራሉ፡፡
ሰውነታችን ልክ እንደ ታክሲ ነው፡፡ እጅግ በርካታ ክፉ መናፍስትን እንጭናለን፡፡ መዳን ማለት ቆም ብለን ክርስቶስን ወደ ታክሲያችን እንዲገባ መጋበዝ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ክፉዎቹ መናፍስት ታክሲውን ለቀው ይወጣሉ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማለት ደግሞ የመኪናውን መሪ ለኢየሱስ ስናስረክበውና ሕይወታችንን እርሱ በፈቀደው መንገድ እንዲመራ ስንተውለት ማለት ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስን የምንቀበለው እንዴት ነው?
መንገዱ በግልጽ በሐዋርያት ሥራ 2፡38 ላይ ተቀምጧል፡፡
የሐዋርያት ሥራ 2፡38 ጴጥሮስም፡- ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።
በመሆኑም የቅዳሜ ሰንበት ቀን የእግዚአብሔርን እረፍት በድንግዝግዝ የሚያሳይ ምሳሌ ነበር፡፡
ኃጢአተኛ ሰውን ለማስተካከል ሁሉንም ጉዳዮች አንድ በአንድ ሊሸፍን የሚችል ሕግ ሊቀረፅ አይችልም፡፡
ሌላው ቀርቶ ሰንበት እንኳን ፍጹም የሆነ ሕግ አልነበረም፡፡
በሕጉ ውስጥ መተላለፍ የሚፈቀዱባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።
መተላለፍ የሚፈቀድበት ሁኔታ 1
ማቴዎስ 12፡5 ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?
ካህናቱ ሐይማኖታዊ ተግባራቸውን ማከናወን አለባቸው፡፡ ይህ ማለት የሐይማኖት መሪዎች በሰንበት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ብለው ሥራ ይሰሩ ስለነበር በዚህ ሰንበትን እያፈረሱ ነበር፡፡ ምንም ማድረግ ስለማይቻል ተፈቅዷል፡፡
ይሁን እንጂ የሰንበትን ሕግ እየሻሩ ነበር፡፡
በቅዳሜ ቀን ማረፍ የሚለውን ሕግ መጠበቅ የሰንበት ፍጻሜ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር አይሁድ በእረፍት ቀናቸው (ቅዳሜ) እንዲያመልኩት ይፈልግ የነበረ ሲሆን ይህም ደግሞ የሐይማኖት መሪዎቻቸው በቅዳሜ ቀን ተግተው እንዲሰሩ የሚጠይቅ ሁነታ ነበር፡፡
መተላለፍ የሚፈቀድበት ሁኔታ 2
ማቴዎስ 12፡11 እርሱ ግን፡- ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?
ያልተጠበቁ ክስተቶች ለሰንበት አይገዙም፡፡ ድንገተኛ ሁኔታዎችን ምንም ማድረግ ስለማይቻል እግዚአብሔር ይታገሳቸው ነበር፡፡ የሚታገሳቸውም ስቃይንና ለመቀነስ እና ሞትን ለመከላከል ነው፡፡ ዓላማቸው መልካም ቢሆንም ሰንበትን በመጣስ ነበር እነዚህ መልካም ዓላማዎች የሚፈጸሙት፡፡
መተላለፍ የሚፈቀድበት ሁኔታ 3
ሉቃስ 13፡15 ጌታም መልሶ፡- እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን?
እንስሳት በሰንበት ቀን እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለእንስሳት እንክብካቤ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በድጋሚ በዚህም ምክንያት ቅዳሜ ቀን ያለመስራት የሚለው ሕግ ይሻራል፡፡
የሰንበት ቀን ለግርዛትም ቦታ ለመልቀቅ ይገደዳል፤ ግርዛት ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ነው የሚፈጸመው።
ስለዚህ የግርዛት ሥርዓት ሰንበትን ይጋፋ ነበር። ፡፡
የቅዳሜ ሰንበት ከግርዛት ጋር አብሮ ሊሄድ አልቻለም፡፡ ወንድ ልጅ ከተወለደ ስምንተኛ ቀኑ ቅዳሜ ከዋለ ቅዳሜ መገረዙ ግድ ነበር፡፡
በመሆኑም የግርዛትን ሕግ ለማክበር ተብሎ የሰንበት ሕግ ይጣስ ነበር፡፡
ለኃጢአተኛ ሰው የሚሰጠው ሕግ ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን ሁሉ ሊሸፍን አይችልም፡፡
ዘፍጥረት 17፡9 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
10 በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ቃል ኪዳን ያተኮረው አብርሃም የመንፈስን ምሪት መከተል ይችል ዘንድ የሥጋን ሸለፈት በመቁረጥ ነበር፡፡
በሥጋ የሆነው መገረዝ የኃጥያት ፍላጎት ከውስጣችን ይወጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሥጋዊ ፍላጎቶቻችንን ከልባችን ላይ ቆርጦ የሚያስወግድበትን ጠለቅ ያለ መንፈሳዊ ልምምድ የሚያሳይ ጥላ ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰንበት ታላቁ ቃልኪዳናቸው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ሰንበት ለሕጻን ልጅ ስምንተኛ ቀኑ ቅዳሜ በሚውልበት ጊዜ በሚፈጸም ግርዛት ይጣስ ነበር፡፡
ዘፍጥረት 17፡12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤
ዮሐንስ 7፡22 ስለዚህ ሙሴ መገረዝን ሰጣችሁ፤ ከአባቶችም ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም፤ በሰንበትም ሰውን ትገርዛላችሁ።
ለሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ ከረጅም ጊዜ አስቀድሞ ለአብርሐም ግርዛት ተሰጥቶት ነበር፡፡
ዮሐንስ 7፡23 የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሰው በሰንበት መገረዝን የሚቀበል ከሆነስ ሰውን ሁለንተናውን በሰንበት ጤናማ ስላደረግሁ ትቈጡኛላችሁን?
ስጋን እጅግ የሚያሳምም መቆረጥ ማለትም ግርዛት በሰንበት መፈጸም ተፈቅዷል፡፡ ነገር ግን አይሁድ በሰንበት ፈውስ በመደረጉ ተበሳጩ፡፡
ከሁሉ የሚበልጠው ፈውስ ከኃጢአት ፍላጐት መፈወስ ነው፡፡ ይህንን በልባችን ውስጥ ማከናወን የሚቻለው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡
የሕጻን ልጅ ስምንተኛ ቀን ከሳምነቱ ሰባተኛ ቀን የበለጠ ተመራጭነት አገኘ፡፡ በስምንተኛው ቀን መገረዝ በሰባተኛው ቀን ከማረፍ የበለጠ አስፈላጊ ነበር፡፡
አሁንም የቅዳሜ እረፍት ገደቦች እንዳሉበት በዚህ ማየት እንችላለን፡፡
የሸለፈት መቆረጥ ወይም መገረዝ በቅዳሜ ቀን ከሥራ ከማረፍ ይበልጥ አስፈላጊ ነው፡፡
ለምን?
ሮሜ 2፡29 ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም፤ የእርሱ ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ከልባችን ላይ የስጋን የኃጥያት ፍላጐት ቆርጦ ማስወጣት የሚቻለው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡
በመሆኑም መገረዝ እግዚአብሔር የልባችንን መሻት ወይም ፍላጐር የሚቆጣጠርበት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ የልባችን ፍላጎት ከሥጋ ክፉ መሻቶች ሲለይ ብቻ ነው ከኃጢአት ሥራዎቻችን ማረፍ የምንችለው፡፡
ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው ከመንፈስ ዳግመኛ ስንወለድ ብቻ ነው፡፡
ልባችን ከሥጋ ፍላጐቶች ተለይቶ ካልተቆረጠ (ካልተገረዘ) በስተቀር መንፈሳዊ እረፍት (ሰንበት) ማግኘት አንችልም፡፡
የሥጋ መገረዝ የስጋ ፍላጐቶችን በመቁረጥ ዓለማዊ አኗኗርና አለባበስ እንዳንከተል ማድረግ የሚቻለው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጥላ ነበር፡፡
በሥጋ ስንመላለስ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ይልቅ የዚህ ዓለም ፋሽንና አኗኗር ይስበናል፡፡
ልባችን በውስጣችን በሚኖረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መንፈስ በማመን ከስጋ ፍላጐት ተለይቶ ነጻ ሲወጣ ብቻ ነው ለዓለምና ለጊዜያዊ ደስታዎችዋ ፍላጎታችን እየጠፋ ከኃጢአት ማረፍ የምንችለው፡፡
ዘሌዋውያን 23፡39 ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የምድሩን ፍሬ ካከማቻችሁ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን በዓል ሰባት ቀን ጠብቁ፤ በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት ይሁን፥ በስምንተኛውም ቀን ዕረፍት ይሁን።
የወሩ 15ኛ ቀን ማንኛውም የሳምንቱ ቀን ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ቀኑ ሰንበት ነበር፡፡
ከስምንት ቀናት በኋላ ደግሞ ሌላ ሰንበት አለ፡፡
ይህ 15ኛ ቀን ቅዳሜ ላይ የሚውለው በሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን በዚያ ዓመትም እንኳ ከስምንት ቀናት በኋላ ቅዳሜ አይውልም፡፡
በዚህ ጊዜ ሰንበት ሰባተኛ ቀንነቱን መሆኑ ይቀራል፡፡
በዚህ ጊዜ ሰንበት ማለት የሰባተኛው ወር 15ኛ ቀን የሚውልበት ማንኛውም የሳምንቱ ቀን ነው፡፡
ስለዚህ በዚህ ጊዜ ሰንበት ማለት ሰባተኛውን ቀን ሳይሆን እረፍት ነው፡፡
ዘሌዋውያን 16፡29-30 29፤30፤ ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ።
31 ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፤ የዘላለም ሥርዓት ነው።
የሰባተኛው ወር አስረኛው ቀንም ደግሞ ሌላ ሰንበት ነበር፡፡ እርሱም የማስተስረያ ቀን ይባላል፡፡
ቀኑ ቅዳሜ ባይሆንም እንኳ በዚያ ቀን ማረፍ አስፈላጊ ነበር፡፡
ስለዚህ ቅዳሜ ሁልጊዜ ሰንበት አይደለም ወይም ሁልጊዜ የተለየ የአምልኮ ቀን አልነበረም፡፡
ዘሌዋውያን 23፡27 በዚህ በሰባተኛው ወር አሥረኛው ቀን የማስተስረያ ቀን ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት ቍርባንን አቅርቡ።
ዘሌዋውያን 23፡32 የዕረፍት ሰንበት ይሁንላችሁ፥ ሰውነታችሁንም አዋርዱ፤
በወሩ በዘጠነኛው ቀን በማታ ጊዜ፣ ከማታ ጀምራችሁ እስከ ማታ ድረስ፣ ሰንበታችሁን አድርጉ፡፡
ስለዚህ ይህኛው ሰንበት የግድ ቅዳሜ መሆን አላስፈለገውም፤ የ አስረኛው ወር ሰባተኛ ቀን ነበር እንጂ፡፡
ዘሌዋውያን 23፡24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡- በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።
አሥረኛው ወር በመጀመሪያውም ቀን እንዲሁም በአሥረኛውም ቀን ሰንበት ነበረው።
ስለዚህ ሰንበት በቅዳሜ ተገድቦ አልቀረም፤ ነገር ግን በቅዳሜም ይሁን በሌላ ቀን ሰንበት ሁሌም እረፍት ነበር፡፡
አንዳንድ ሰዎች የሰንበት ቀን (በነጠላ ቁጥር) የሚለው ቅዳሜን የሚያመለክት ሲሆን የሰንበት ቀናት (ብዙ ቁጥር) የሚለው ደግሞ የሰንበት ቀን እንዲሆኑ የታወጁትን ሌሎች የሳምንት ቀናት የሚያመለክት ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡
ነገር ግን ከዚህ በታች የተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቅዳሜን የሚያመለክት ሆኖ ሰንበትን በብዙ ቁጥር ይጠቅሰዋል ደግሞም በነጠላ ቁጥር ይጠቅሰዋል፡፡
ማቴዎስ 12፡10 እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ፡- በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት።
ማቴዎስ 12፡11 እርሱ ግን፡- ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?
ማቴዎስ 12፡12 እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው።
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሕጉ የሚወክለውን ጥልቅ ሚስጥር ማግኘት አለብን፡፡
ውሃ እና ሥጋ የአስተምህሮ ለነፍስ የሚሆነው ምግብ ምሳሌ ናቸው።
ሰንበት ማለት ከሥራ ማረፍ ሳይሆን ከኃጢአት ማረፍ ነው፡፡ ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው፡፡
ቆላስይስ 2፡16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።
17 እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
ይህ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ ሰንበት የተጠቀሰበት ቦታ ነው፡፡
በእርግጠኝነት ይህ ቃል ትኩረቱ የሰባተኛው ቀን የቅዳሜ ሰንበት ላይ አይደለም፤ ነገር ግን ሰንበትን አንድ ቀን እንዳናስበው ያስጠነቅቀናል፡፡
እንደውም ቀንን የሰንበት ቀን ወይም የበዓል ቀን ብለን እያልን ልዩ ትኩረት ከመስጠት አይናችንን ዘወር እንድናደርግ ይመክረናል፡፡
የቅዳሜው ሰንበት ሊመጣ ላለው ጠለቅ ያለ እውነታ ጥላ ብቻ ነበር፡፡
እውነታውን ከጨበጥክ በኋላ ስለ ምን ወደ ጥላው ትመለሳለህ?
ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
እንደ ቅዳሜ ባሉ ቀናት ወይም ደግሞ በዓመቱ ውስጥ እንደ ገና በመሳሰሉ የበዓል ቀናት ላይ መደገፍ የሚናቅ ነገር ነው፡፡ በ274 ዓ.ም. የፀሐይ አምልኮን ለማበረታታት የሮማው ንጉሰ ነገስት ኦሬልያን ዲሴምበር 25ን የፀሐይ አምላክ የልደት ቀን አድርጐ አወጀ፡፡ ይህ በዓል በመጀመሪያዋ የቤተክርስቲያን ዘመን አልነበረም፡፡ የክርስቶስ የልደት ቀን ነው ብለን ብናምን እንኳ እምነታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር አብሮ አይሄድም ወይም ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ጋርም አይጣጣምም፤ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት እምነት አልነበራቸውም፡፡
እውነተኛ እረፍት የሚገኘው በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ በመሆን ነው፡፡
ዘጸአት 33፡14 እግዚአብሔርም፡- እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው።
በብሉ ኪዳን ውስጥ እንኳ ሳይቀር የቅዳሜ እረፍት በራሱ የተሟላ እረፍት አልነበረም፡፡
ዘዳግም 12፡9 አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና።
በየሳምንቱ ቅዳሜ እረፍት ያደርጉ ነበር። ነገር ግን ገና ሌላ እረፍት በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ይጠብቃቸው ነበር፡፡
ዘዳግም 12፡10 ዮርዳኖስን ግን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ፥
በየሳምንቱ ቅዳሜ እረፍት ቢያደርጉም እንኳ ከጠላቶቻቸውም ጭምር ማረፍ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡
ስለዚህም የቅዳሜው እረፍት ከስራ በማረፍ ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው እረፍት አይሰጣቸውም ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ማረፍ እንዲችሉ ሃገራቸው ፓለስታይን (ከነዓን ተብላ የምትጠራው) ጠንካራ መሆን ያስፈልጋታል ፡፡
ኢሳይያስ 14፡3 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።
ከመከራና ከፍርሃት እንዲሁም ከባርነትም ማረፍ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡
ይህ ደግሞ እውን ሊሆን ይሚችለው በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ጠንካራ ሕዝብ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡
በቅዳሜ ቀን ሥራ አለመስራት ሰዎችን ከሐዘን፣ ከፍርሐትና ከባርነት ሊያሳርፋቸው አይችልም፡፡
በተጨማሪም ቅዳሜ እንደ አምልኮ ቀን የነበረውን ቦታም አጥቷል፡፡
ለአይሁድ ልዩ በዓል ተሰጥቷቸዋል፡፡
የመከር ነዶዋቸውን የመወዝወዝ በዓል የተሰጣቸው ሲሆን ይህንንም የሚያደርጉት እሁድ እለት ነው፡፡
በዚህ ቃል ውስጥ እሁድ በግልጽ እንደ አምልኮ ቀን ተጠቅሶአል ፡፡
ዘሌዋውያን 23፡10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡- ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
በኩራት ማለት ቀድሞ ለመታጨድ የደረሰው ነዶ ነው፡፡
እያንዳንዱ ዘር ሲዘራ ይሞትና ከዚያም በኋላ አዲስ ተክል ሆኖ ነፍስ ዘርቶ ያድጋል፡፡
ይህ የትንሳኤ አመላካች ነው፡፡ ሰው ይሞታል፤ ይቀበራል ወይም አፈር ውስጥ ይተከላል፤ ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስነሳዋል፡፡
ኢየሱስ ሞቶ ተቀብሮ ከዚያም ሁለተኛ ሞትን በማይቀምስ አዲስ አካል የተነሳ የመጀመሪያው ሰው ነው።
በመሆኑም ኢየሱስ የትንሳኤ በኩራት ነው፡፡
1ኛ ቆሮንቶስ 15፡20 አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።
1ኛ ቆሮንቶስ 15:23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
መከር መሰብሰብ ሰዎች ምግባቸውን እንዲያገኙ ቢጠቅምም የበኩራትን በዓል ስናከብር ግን ምድራዊ ለሆነ የሰብሎች መከር ብለን አይደለም።
የምናከብረው የሞተውና ተመልሶ ሞትን በማያይ አካል በመነሳት የመጀመሪያው የሐይማኖት መሪ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ ነው፡፡
ተቀብሮበት የነበረበት መቃብር ባዶ ሆኖ መገኘቱ የክርስትና የድል ምልክት ነው፡፡
በመሆኑም ሰባኪዎች ክርስቶስን በሰዎች ፊት ማውለብለብ አለባቸው፡፡
ማወዛወዝ እንቅስቃሴ እንጂ ቆሞ የቀረ ወግ አይደለም። ኢየሱስ ሞትን ድል የነሳ ብቸኛ ሰው ነው፡፡
ዘሌዋውያን 23፡11 እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው፤ በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው።
ሰባኪዎች ከሞት የተነሳውን አዳኝ በሰዎች ፊት ማውለብለብ ያለባቸው መቼ ነው?
በነጋታው፤ ከሰንበት ማግስት ነው።
ሰንበት ቅዳሜ ነው፤ ስለዚህ ከሰንበት ማግስት ያለው ቀን ደግሞ እሁድ ነው፡፡
ለምንድነው በድንገት ይህን ያህል ትኩረት ለእሁድ የተሰጠው?
ምክንያቱም ኢየሱስ ከሞት የተነሳው እሁድ ስለሆነ ነው፡፡
የእሁድ አምልኮ ይህኛውን የሕግ ክፍል ያሟላል፡፡
ዘሌዋውያን 23፡15 የወዘወዛችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቍጠሩ፤
ዘሌዋውያን 23፡16 እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ፤ አዲሱንም የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ።
የኢየሱስ የዕሁድ ትንሳዔ ጥላ የሆነው የበኩራት በዓል ከተከበረ በኋላ አይሁድ ሰባት ሰንበቶችን ማለትም ሰባት ሳምንታትን (7X7=49 ቀናት) ይጠብቁ ነበር፡፡ ከዚያም ከሰባተኛው ሰንበት ወይም ቅዳሜ በኋላ ማትም እሁድ ዕለት የጴንጤቆስጤ በዓል ያከብሩ ነበር(ጵንጤቆስጤ ሃምሳኛው ቀን ነው)።
ይህ በዓል የሚወክለው ምንድ ነው?
የሚወክለው በጴንጤቆስጤዕለተ በእሁድ ቀን የተፈጸመውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው።
የሐዋርያት ሥራ 2፡1 በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
እሁድ በድንገት ገነነ።
ኢየሱስ በእሁድ ቀን ከሞት ተነሳ፡፡ በመሆኑም “እነሆ ተነስቷል” የሚለው የወንጌሉ ብርሃን በእለተ እሁድ ምድርን አጥለቀለቃት፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የጀመረውም በእለተ እሁድ ነው፡፡
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ፍጥረታዊውን ብርሃን ሲፈጥር ይህ ብርሃን ምድር ላይ በመጀመሪያው ቀን አበራ፤ ይህም ቀን እሁድ ነበር፡፡ በመሆኑም እሁድ ብርሃንን የሚወክል ቀን ነው፡፡
የጴንጤቆስጤ ቀንም እሁድ ነበር፡፡ ይህ ቀን ደቀመዛሙርቱ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የተቀበሉበትና ቤተክርስቲያንም ተልዕኮዋን የጀመረችበት ቀን ነበር፡፡
እሁድ ሁልጊዜ የአይሁድ አምልኮ አካል ነበር፡፡ ነገር ግን አይሁድ የእሁድ በዓላትን ጥልቅ ሚስጥር መረዳት አልቻሉም ነበር፡፡
የቀን ፅንሰ ሐሳብ የሚጀምረው ዘፍጥረት ውስጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር አንድ ቀን አንድ ሺህ ዓመት ነው፡፡
ዘፍጥረት 1፡3 እግዚአብሔርም፡- ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።
ተፈጥሯዊው ብርሃን ለመጀመሪያ ጊዜ ምድር ላይ ያበራበት ቀን እግዚአብሔር ፍጥረትን የጀመረበት የሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር እሁድ ነው፡፡
በእግዚአብሔር ፊት አንድ ቀን አንድ ሺህ ዓመት ነው፡፡
የሰው ቀን 24 ሰዓት ነው፡፡
በመጀመሪያ ሰው አልነበረም፤ ስለዚህ ለፍጥረት የእግዚአብሔርን ጊዜ ነው የምንቆጥረው፡፡
መዝሙር 90፡4 ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና።
2ኛ ጴጥሮስ 3፡8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
የሰው ሳምንት የመጀመሪያው ቀን እሁድ ነው፡፡ ያም ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሳቱ የትንሳኤ መንፈሳዊ ብርሃን ምድርን ያጥለቀለቀበት የትንሳኤ ቀን ነው፡፡
በተጨማሪም በጴንጤቆስጤ ቀን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ወደ ሥራ እንድትገባ ያስቻላት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን እሁድ ነበር (የሐዋርያት ሥራ)፡፡ ይህ ለመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርስቲያን ምሳሌ ወይም ሞዴል ነው፡፡
ዘፍጥረት 1፡5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።
ቀኑ ከምሽት ይጀምርና በቀጣዩ ንጋት ይቀጥላል፡፡ ለምን?
ብርሃን የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
መዝሙር 119፡105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪይቷ ቤተክርስቲያን ይታመን ነበረ፤ በጨለማው ዘመን ግን ጠፋ፡፡ ከዚያም በኋላ ሉተር ሰዎች መዳን አለባቸው ብሎ መስበክ በጀመረበት ዓመታት የእግዚአብሔር ቃል በከፊል ተመልሶ የነበረ ሲሆን በመቀጠልም ዌስሊ ስለ ቅድስናና ወንጌልን ስለመስበክ በሚያስተምርባቸው ዓመታት የሚሽነሪ/ሚሲዮን ዘመን ተጀምረ፤ ከዚያም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመልሶ የመጣበት የጴንጤቆስጤያዊ መነቃቃት መጣ፡፡ ነገር ግን ከነዚህ ታላላቅ ንቅናቄዎች ውስጥ የትኛውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩትን የእግዚአብሔር ምስጢራት ጥልቅ ግንዛቤ መልሶ ለማምጣት አልቻለም፡፡
የመጀመሪያው ሐጢአት ምንድን ነበር? የእባቡ ዘር ምንድነው? አውሬው ማን ነው? የአውሬው ምስል ምንድነው? የግዚአብሔር ስም ማን ነው? (አብ፤ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ስም አይደለም) እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጉዳዮች…
ዘካርያስ 14፡7 አንድ ቀንም ይሆናል፥ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።
ነገር ግን እውነት በወንድም ብራንሐም አገልግሎት አማካኝነት ልክ ጌታ ከመምጣቱ በፊት በምሽት ትመለሳለች፡፡
ባለለፉት 2000 የቤተክርስቲያን ዘመን ዓመታት ውስጥ በክርስቶስ የሞቱ ይነሳሉ፤ በሕይወት ያለችው ቤተክርስቲያንም ትለወጣለች፡፡ ስለዚህ ሁሉም እውነተኛ አማኞች ልክ ጌታ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ለአጭር ጊዜ በምድር ላይ ይሆናሉ፡፡
ነጭ ብርሃን ከሰባት ዓይነት ቀለማት የተሰራ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰባቱ ቤተክርስቲያናት ዘመናት የሆነችው ሙሽራ በምድር ላይ እውነተኛውን ብርሃን ትወክላለች፡፡
ነገር ግን ብርሃን ከጨለማ ጋር መቀላቀል አይችልም፡፡ ታላቁ መከራ የጨለማ ምሳሌ ነው፡፡
ከዚያም ወደ ሰማይ ስትወሰድ ሙሽራዋ የምታመልጠው የመከራ ምሽት ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው የዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 5 ምሽቱን የማይጠቅሰው፡፡
ከዚያም በኋላም ክርስቶስና ሙሽራው ተመልሰው የሚመጡበት የሺህ ዓመቱ ማለዳ ወይም ንጋት የሚመጣ ሲሆን ምድርም እውነተኛ ብርሃን በሆነው በክርስቶስ ለ1000 ዓመት ትገዛለች፡፡
ራእይ 20፡6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
እግዚአብሔር በምድር ላይ በስድስቱ የእግዚአብሔር ቀናት (6000 ዓመታት) ውስጥሕይወትን ፈጠረ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ (አዳም) እና ሙሽራው በሰባተኛ ቀን ለ1000 ዓመት ምድርን እንዲገዙ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ዕቅድ ግን በኃጢአት ምክንያት ተሰናከለ፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ እና ሙሽራው (እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን) በምድር ላይ ለ1000 ዓመት ሲነግሱ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ሃሳቡ ይፈጸማል፡፡ ይህ ሺህ ዓመት እውነተኛው የእግዚአብሔር ሰባተኛ ቀን ነው፡፡
እግዚአብሔር ሕጉን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘርዝሯል፤ ነገር ግን ይህ ሕግ ጠለቅ ላለው ሃሳብ ወይም ለአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ፀጋ መገለጥ ምልክት ወይም ጥላ ብቻ ነበር፡፡
አሮጌው ሕግ ከባድ ነው፤ ምክንያቱም ሕግ በባህሪው ከባድ ወይም ጥብቅ ነው፡፡
ሕግ ማለት ሰው በራሱ ስራዎችና ጥረቶች የእግዚአብሔርን መስፈርቶች ጠብቆ ለመኖር ያደርገው የነበረ ሙከራ ነው፡፡
የእንስሳ ደም የኃጢአትን ስርየት ቢያስገኝም የኃጢአትን ፍላጐት ማስወገድ አልቻለም፡፡ በእንስሳ ደም ውስጥ የሚኖረው የእንስሳ ሕይወት ወይም መንፈስ በሰው ልብ ውስጥ ማደር አይችልም፤ ስለዚህ የኃጢአት ፍላጐቶችን ማስወገድ አይችልም፡፡
ፀጋ ኃጢአታችንን ለማንፃት የኢየሱስን ደም ወደ እኛ አመጣ፤ ደግሞም የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ይዞልን መጣ እርሱም በክርስቶስ ደም ውስጥ የሚኖረው ሕይወት ነው፡፡
ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ወደልባችን በመግባት የሐጢት ፍላጐቶቻችንን አስወግዶ የተሻለ ሕይወት ለመኖር እንድንፈልግ ያደርገናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ከባህሪችን ጋር የሚቃረኑ ሕጐች ዝርዝር አድርጎ መመልከት ሳይሆን፤ ፍላጎታችንን የሚለውጥ በውስጣችን የሚኖር መንፈስ ነው በእግዚአብሔር ፊት በቅድስና ለመኖር እንድንፈልግ የሚያደርገን፡፡
ለእርሱ ፍላጐቶች መገዛት አለብን፡፡ ነገር ግን ከሁሉ በላይ እርሱን መውደድና እርሱን ለመታዘዝና ለመከተል መፈለግ አለብን፡፡ በግድ ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡ ግድ ሆኖብን ሳይሆን ስለምንፈልግ ነው፡፡
ዕብራውያን 8፡10 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።
“ሕግ” እራስን ስለመግዛት ሲያመለክት “ልብ” ደግሞ ግላዊ ፍላጐቶችን ያመለክታል፡፡
የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችን ውስጥ እንዲኖር፣ ከኃጢያት እንዲያነጻንና ቃሉን መታዘዝ የሚፈልግ አዲስ ባሕርይ እንዲሰጠን ስንፈቅድለት ግላዊ ፍላጐቶቻችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ተስማምተው መሄድ ይጀምራሉ።
ሰንበት የእግዚአብሔር ሕግ ክፍል ነው፡፡
ሕጉ በራሱ ፍጹም ነው፡፡
መዝሙር 19፡7 የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
በሕጉ ላይ ምንም ዓይነት ችግር የለበትም፤ ሕጉ ፍጹም ነው፡፡
ችግሩ ሕግን ሙሉ በሙሉ ብንጠብቀውም እንኳ ፍጹም ሊያደርገን አለመቻሉ ነው፡፡
ሕጉ ሰዎች በተግባር ሊለማመዱ የማይችሉት ጥሩ መርሕ ነው፡፡
ዕብራውያን 7፡18-19 ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።
ሕጉ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ሊፈጽም የሚችለውን ብዙ መስፈርቶች ይዟል፡፡
ሕጉ የሆነ አንድ ጥልቅ ነገርን የሚያሳይ ተምሳሌት ወይም ጥላ ነበር፡፡
እያንዳንዱ በመሰዊያ ላይ የሚቀርብ የመስዋዕት በግ እውነተኛውን በግ ክርስቶስን የሚያመለክት ነበር፡፡
የበግ ደም ኃጢአትን ይሸፍናል፤ ነገር ግን የሐጢአተኛውን ባህሪ መቀየር አይችልም፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ኃጥያትን አጥቦ ያነጻል፤ ይህም ከመሸፈን እጅግ በጣም የተሻለ ነው። ከዚያም በደሙ ውስጥ ያለው ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ወደ ልባችን ውስጥ በመግባት የኃጢአት ፍላጐታችንን ያስወግድልናል፡፡
ዕብራውያን 10፡1 ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።
ሕጉ ጥላ ነበር፡፡ ጥላ የአንድን ነገር ቅርጽ ያሳያል እንጂ ራሱ እውነተኛው ነገር አይደለም፡፡
ሕጉ ያለማቋረጥ መደጋገም አለበት፡፡ መድሐኒት እየደጋገምክ መውሰድ ካለብህ ይህ መድሐኒቱ ፈጽሞ እንዳልፈወሰህ የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡
የቀራንዮ መስቀል ላይ መሞቱ ኃጢአታችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶታል፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ በተደጋጋሚ ከሥራ የሚደረግ እረፍት በእግዚአብሔር መንፈስ ስንሞላ ከኃጥያት የምንገላገልበትን ዘላቂ እረፍት የሚያሳይ ጥላ ነበር፡፡
ኢሳይያስ 42፡21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።
ሕጉ ላይ ምንም ችግር የለበትም ነበር፤ ነገር ግን ጥላ ወይም ምሳሌ ብቻ የነበረ በመሆኑ ውስን ነበረ፡፡ ሕጉ ትክክለኛ ትርጉሙን ያገኘው በክርስቶስ ከብሮ ተፈጻሚነትን ያገኘ ጊዜ ነው፡፡ ክርስቶስ ሕጉን ልፈጽም እና ጠለቅ ያለ ትርጉም ሊሰጠው መጥቷል፡፡ እርሱ እውነተኛው የመስዋዕት በግ ነው፡፡ እርሱ እውነተኛው ሊቀ ካህን ነው፡፡
በተመሳሳይ መንገድ ክርስቶስ ከልባችን ውስጥ እንዲያድር ስንፈቅድለት ለሕይወታችን ጥልቅ ትርጉምና ዓላማ ይሰጠዋል፡፡
ማቴዎስ 5፡17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
ሕጉ የሰውን ልጅ ለማዳን አቅም አልነበረውም፡፡ ሕጉ የሚጠቁመው ወደ ክርስቶስ ነበር፡፡
በመሆኑም አዳኝ ለመሆን የሚችለው ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ እውነተኛው የሕግ ፍፃሜ ነው፡፡
ፀጋ ይህ ታላቅ አዳኝ በእኛ ውስጥ እንዲያድርና የታላቁ የቤዛነት ሥራው አካል እንድንሆን ፈቀደ፡፡
ገላትያ 3፡10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።
በራሳችን መልካም ሥራ ልንድን አንችልም፤ ምክንያቱም እኛ ሰዎች ሕግን ሁሉ መፈጸም አንችልም፡፡
ለምሳሌ በቅዳሜ ቀን ማንም ሰው አንዳች ሥራ ሳይፈጽም ማደር እንደማይችል ክርስቶስ በቀላሉ አሳይቷል፡፡ ሰባኪዎች መስበክ አለባቸው፡፡ ለእንስሳት እንክብካቤ መደረግ አለበት፡፡ ድንገተኛ ክስተቶች በአግባቡ መስተናገድ አለባቸው፡፡ ከዚያም ሌሎች የወሩ ቀናት እንደሰንበት ቀናት ሆነው ይመጣሉ፤ ከዚያም በላይ እሁድም እንኳ ሁለት ጊዜ ልዩ የአምልኮ ቀን ሆኖ ይመጣል፡፡
ገላትያ 3፡13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤
ክርቶስ የተቤዠን ወይም ያዳነን ከሕግ አይደለም፡፡ የተቤዠን ከሕግ እርግማን ነው፡፡ የሕግ እርግማን ማለት ኃጢአት ምን እንደሆነ ቢነግረንም ኃጢአት ለማድረግ ከመፈለግ እንድንቆጠብ ሊያደርገን አለመቻሉ ነው፡፡
በመሠረቱ ሕጉ ውስን ነው፡፡ ትክክለኛው ነገር ገልጦ ሲያሳይን እንኳ ራሳችንን በመግዛት መፈጸም የሚጠበቅብንን ውጫዊ የሥርዓቶች ስብስብ ነው፡፡ ሕግን ማድረግ ማለት እኛ ሰዎች እግዚአብሔርን ለማስደሰት በራሳችን አቅም የምናደርገው ከፍተኛ ጥረት ነው፡፡ የእርሱን አዎንታ ለማግኘት ልንታዘዘው ይገባል፡፡ ይህ አይነቱ ግዴታ አንድ ሰው ፍላጎቱ ሌላ ቢሆንም እንኳ ሳይወድ ታዛዥ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህም የሕጉ አስከፊ ውስንነት ነው፡፡
በእግዚአብሔር ቃል የመኖር ፍላጐት ላይ እስኪያድርብን ድረስ ውስጣዊ ባህሪያችንን ሊለወጥ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር እንደ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ በውስጣችን በማደር ለቃሉ መታዘዝን እንድንፈልግ ያደርገናል፡፡ የምንታዘዘው ሽልማት (መንግስተ ሰማይ) እናገኛለን ብለን ወይም ቅጣትን (ሲኦልን) በመፍራት አይደለም፡፡
ኤርምያስ 31፡33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ዳግመኛ መወለድ ማለት እግዚአብሔር በውስጣችን ስለሚኖር አዳዲስ ፍላጐቶችን ይሰጠናል ማለት ነው፡፡
ከዚያም የእርሱን ሥራዎች እንሰራለን፤ ምክንያቱም የሚመራንና ፈቃዱን ለማድረግ እንድንፈልግ የሚያደርገን እርሱ ነው፡፡
ከዚያ ወዲያ የራሳችንን ሃሳብ ወይም ፍላጎት አንከተልም፤ የራሳችንን ሥራዎችም አንሰራም፡፡
መልካም ሥራዎች በራሳቸው በቂ አይደሉም፤ ከእግዚአብሔር ሰፊ ዕቅድ ጋር ካልተጣጣሙ በቀር፡፡
ሮሜ 7፡6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።
ሮሜ 8፡2 በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።
የክርስቶስ መንፈስ እኛን በመለወጥ ለእግዚአብሔር መታዘዝን እንድንፈልግ ያደርገናል፡፡
ሕጉ እግዚአብሔርን እንድንታዘዝ ያስገድደናል፤ ነገር ግን በፈቃደኝነት እንድንታዘዝ ሊያደርገን አይችልም፡፡
ዘዳግም 6፡4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
5 አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።
እኛ አህዛብ አመጣጣችን እግዚአብሔርን ከማያውቁ ብዙ አማልክትን ከሚያመልኩ ወገኖች ነው። ስለዚህ በመለኮት ውስጥ ከአንድ በላይ አካል አለ ብለን በቀላሉ ልናምን እንችላለን፡፡
እግዚአብሔርን ብንወድም እንኳ ከራስ ወዳድነት ጋር፣ ከፋሽን እና ከቁሳቁስ እንዲሁም ከገንዘብ እና ከትርፍና ከዝና ወዘተ. ፍቅር ጋር እንታገላለን፡፡
እርሱ ብቻውን አምላክ እንደሆነ እንድንረዳ ኢየሱስ ወደ ልባችን ሊገባ ያስፈልገናል፡፡ እርሱ ብቻውን ልንወድደው በሚገባን መጠን በሙሉ ልባችን እድንወድደው ማድረግ ይችላል፡፡
ነህምያ። 13፡9 ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ።
በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።
ሸክም የሰንበት እረፍት አካል አይደለም፡፡
ማቴዎስ 11፡28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ኢየሱስ ሸክም ለከበዳቸው ሰዎች የቅዳሜ እረፍት አይደለም ያቀረበላቸው። የቅዳሜ እረፍትማ ቀድሞውንም ተሰጥቶአቸዋል፡፡
እውነተኛው ሸክማችን ኃጢያት ነው፡፡አለማመናችንን እና ኃጢያታች ን ያጥብልን ዘንድ ኢየሱስ ያስፈልገናል፡፡ ከዚያም በእርሱ ማረፍ እንችላለን፡፡
ማቴዎስ 11፡29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ኢየሱስ ከኃጢአት የምናርፍበትን እረፍት አቅርቦልናል፡፡ነፍሳችን አይደክማትም። ሥጋችን ነው የሚደክመው፡፡
ነገር ግን ነፍሳችን በኃጢአት በተሞላ ሕይወት ውስጥ እረፍት ማግኘት አትችልም፡፡
ኢሳይያስ 58፡13 ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
እኔነት የሰንበት አካል አይደለም፡፡ የራሳችንን ፈቃድ እየፈጸምን እውነተኛ መንፈሳዊ እረፍት ማግኘት አንችልም፡፡
ኢሳይያስ 66፡1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?
እግዚአብሔር በሰዎች ልብ ውስጥ ማደር ይፈልጋል፡፡
የራሳችንን ሃሳብ እየተከተልን ስንሯሯጥ እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ ማረፍ አይችልም፡፡
ኢሳይያስ 11፡2 የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ያረፈበትና በውስጡ በሙላት የኖረበት የመጀመሪያው ሰው ነበር ምክንየቱም እንደ ሰው ሁል ጊዜ በውስጡ ለሚኖረው ለእግዚአብሔር መንፈስ በፍጹም ታዟል።
መኪና ሁል ጊዜ አሽከርካሪውን መታዘዝ አለበት፡፡ እኛ እግዚአብሔር ሊያሽከረክር የሚፈልገው መኪና ነን፡፡ ፈቃዳችንን ሰውተን ያለምንም ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ፍቃድ ብቻ ካልታዘዝን ሊታመንብን ወይም በእኛ ውስጥ ሊያርፍ አይችልም፡፡
ማቴዎስ 26፡39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፡- አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።
ኢሳይያስ 63፡14 ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፤ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።
እረፍት የሚያያዘው ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ነው፡፡
እረፍት ማግኘታችን የሚወሰነው የራሳችንን ነጻ ፈቃድ ሰውተን በዚያ ፋንታ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስንቀበል ነው፡፡
ኢሳይያስ 28፡11 በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ እርሱም፡- ዕረፍት ይህች ናት፥
12 የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ።
ይህ የሚናገረው በልዩ ልዩ ልሳኖች የተናገሩበትን የጴንጤቆስጤ ቀን ነው፡፡
በዚያ ቀን መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰዎች ልብ ውስጥ ገባ፡፡ ደቀመዛሙርትን እውነተኛ ቤተክርስቲያን ያደረጋቸውም ይኸው ነው፡፡
የሐዋርያት ሥራ 2፡1 በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
2 ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
4 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።
መዝሙር 95፡11 ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።
አይሁድ ቅዳሜ ቅዳሜ ከሥራ እረፍት ማድረግ ላይ አክራሪዎች ነበሩ። ይህ ግን እውነተኛው እረፍት አልነበረም፡፡
ከኃጢያት እውነተኛ እረፍት የሚሰጣቸው ክርስቶስ ነበር ምክንያቱም የኃጢአታቸውን ዋጋ መክፈል የሚችለው እርሱ ብቻ ነው።
ነገር ግን አዳኛቸውን በመቀበል ፋንታ በመስቀል ላይ መቸንከርን ስለመረጡ ይህንን እረፍት አላገኙም፡፡
ዮሐንስ 12፡32 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከፍ ብሏል፤ የእርሱ ሞት ከምድር ወደ ሰማይ የሚያስገባ በር መሆኑን ሰው ሁሉ ያይ ዘንድ ከምድር እና ከሰማይ መሃል እንደ ባንድራ ተውለብልቧል።
ኢሳይያስ 11፡10 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን (ከፍ ብሎ የተሰቀለ ባንድራ…ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከፍ ብሏል) የእሴይን ሥር (ኢየሱስ የዳዊት ልጅ፤ ዳዊት የእሰይ ልጅ) አሕዛብ ይፈልጉታል፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል። (ደሙ ኃጥያታችንን አጥቧል፤ ቅዱስ መንፈሱም ማለትም በደሙ ውስጥ ያለው ሕይወት ልባችን ውስጥ ለመኖርና የኃጥያትን ፍላጎት ሊያስወግድልን መጥቷል። የዚያኔ ብቻ ነው ከኃጥያት እረፍት የምናገኘው።)
በመስቀል የተሰቀለው፤ አይሁድ ያልተቀበሉት አዳኝ አሕዛብ ይቀበሉታል፡፡
ሰዎች ንስሀ ይገባሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጠመቃሉ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ይሞላሉ፡፡ ይህ እውነተኛው ከኃጢአት ማረፍ ነው፡፡
ኢሳያስ 42፡21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።
ገላትያ 3፡2 ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን?
ሕጉ (ብሉ ኪዳን) የሚለውን ካወቅንና ካመንበት በአዲስ ኪዳን መፈጸሙን ተገንዝበን ወደ ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጓሜውና ፍጻሜው እንገባለን፡፡
ገላትያ 3፡5 እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው?
ተአምራት የሚደረገው በመልካም ሥራዎቻችን ሳይሆን በውስጣችን በሚያድረው መንፈስ ቅዱስ፣ እምነትና ፀጋ ነው፡፡
ሮሜ 6፡15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም።
ልክ ሕጉ የሚጠይቀውን ያህል ፀጋም መልካም ሥራዎችን ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው በሚል ሰበብ ኃጢአትን የማድረግ መብት አለኝ ብሎ ማመን ልክ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ አያድርም ብሎ እንደማመን ይቆጠራል፡፡ እግዚአብሔር ፈጽሞ ኃጢአትን መስራት አይፈልግም፡፡
ነገር ግን እውነተኛው ኃጢአት አለማመን ነው፡፡
የኃጢያት ሥራዎች ሁሉ (ማጨስ፣ መጠጣት፣ መዋሸት፣ ስርቆት ወዘተ) የአለማመን መገለጫዎች ናቸው፡፡
ዮሐንስ 16፡8 እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤
9 ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤
እግዚአብሔርን በእውነት ብናምነው እነዚያን ነገሮች አናደርጋቸውም ነበር፡፡
በውስጣችን የሚያድረው መንፈስ ቅዱስ ብቻ አለማመንን ሙሉ በሙሉ ከእኛ በማስወገድ ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን ይችላል፡፡
ዮሐንስ 16፡13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
በራሳችን መንገድ እውነትን ሁሉ ለማግኘት መሞከር አያዋጣንም፡፡ በአለማወቃችን፣ በልማዶቻችን እና በራስ ወዳድነታችን ወዘተ. ምክንያት እጅግ ውስን ነን፡፡
ሕጉ የሚያስለምደን ራስን የመግዛት ባሕርይ ኃጢአት ማድረጋችንን እንድናቆም ሊረዳን ይችላል፤ ነገር ግን ኃጢአት የመሥራት ፍላጐታችንን ሊያስወግድልን አይችልም፡፡
ሕግን በመታዘዝ የሚመጣው ራስን የመግዛት ባሕርይ ሕግ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያገኘውን ጥልቅ ተፈጻሚነት እንድናይ ዓይናችንን ሊከፍትልን አይችልም፡፡
መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ኃጢአትን የመውደድ ዝንባሌያችንን ሊያስወግድልን የሚችለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ዓይኖቻችንን ከፍቶ የሕጉን እውነተኛና መንፈሳዊ ትርጉምና ምንን እንሚወክል ሊያሳየን የሚችለው፡፡
ዮሐንስ 16፡21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።
ሕፃን ልጅ ለመወለድ የሚደርገው ምንም ዓይነት ጥረት የለም፡፡ ስለዚህ ጥረታችን ወይም ሥራዎቻችን እረፍትን ወይም ዳግመኛ መወለድን ሊያስገኙልን አይችሉም፡፡
አይሁድ የቅዳሜን ሰንበት ጠብቀዋል ግን ወደ እውነተኛው እረፍት አልገቡም፡፡
ባአለማመን ምክንያት ሳይገቡ ቀሩ፡፡
አለማመን ዋነኛው ኃጢአት ነው፡፡ አለማመን ዋነኛው የኃጢአት ምንጭ ነው፡፡
አለማመን በነፍሳችን ውስጥ መጥፎ ሃሳብ ሆኖ ይጀምራል፤ ከዚያም ሃሳቦቻችን በስጋችን ክፉ እንድንሰራ ይገፋፉናል። የተገለጡ ኃጢያቶች በሙሉ (ማጨስ፣ መጠጣት ወዘተ.) የአለማመን መገለጫዎች ናቸው፡፡ በእውነት ብናምን ክፉ ነገሮችን አናደርግም ነበር፡፡
ዮሐንስ 8፡24 …እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።
የማናምን ከሆነ እንግዲያውስ ኃጢአተኞች ነን፡፡
እግዚአብሔር ኃጢአትን አይሰራም፡፡
ኃጢአት መስራታችንን እስካላቆምን ድረስ እውነተኛ እረፍት አናገኝም ምክንያቱም ኃጥያቶቻችን ከእግዚአብሔር ይለዩናል፡፡
ኢሳይያስ 59፡2 ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
ከአካላዊ ስራ ማረፍ እንችላለን፤ ነገር ግን ኃጢአትን ስንሰራ ህሊናችን እረፍት አያገኝም፡፡
መዝሙር 38፡3 ከቍጣህ የተነሣ ለሥጋዬ ጤና የለውም፤ ከኃጢአቴም የተነሣ ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።
ስለዚህ እውነተኛው ሰንበት ከኃጢአት ማረፍ ነው፡፡
ይህንን እንዴት ልናገኝ እንችላለን?
ዕብራውያን 4፡5 በዚህ ስፍራም ደግሞ፣ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።
6 እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ
እግዚአብሔር ለእኛ የእረፍት ቦታን አዘጋጅቶልናል፤ የምንቀበለው ግን ስናምን ብቻ ነው፡፡
መንፈሱ ወደ ልባችን ሲገባ በእምነት ወደ እረፍቱ እንገባለን፡፡
ያለማመን ግን ወደ እረፍቱ ከመግባት ያስቀረናል፡፡
ዕብራውያን 4፡11 እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
አለማመን ወደ እውነተኛው እረፍት ከመግባት ያስቀረናል ምክንያቱም የማያምኑ ሰዎች ዳግመኛ እንዲወለዱ የሚያበቃቸውን መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችሉም።
ከላይ የተጠቀሰው ጥቅስ እርስ በራሱ የሚጋጭ ይመስላል፡- “ያለትጋት እረፍት የለም” ይላል።
ነገር ግን “ትጋት” የሚለው ቃል ልጅ የመወለድን ምጥ ያስታውሰናል፡፡
ይህ ደግሞ ዳግመኛ መወለድን ይመስላል፡፡
ዮሐንስ 16፡21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።
እናት ልጅዋ እስኪወለድ ድረስ ታምጣለች፡፡ ከዚያም በኋላ ከምጧ ታርፋለች፡፡ ምጧ ተጠናቋልና፡፡
መንፈስ ቅዱስ ፍላጎታችን እስኪለውጥልን ድረስ እንታገላለን፤ ከዚያም ኃጥያትን አንፈልገውም፡፡
ዘጸአት 20፡8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
ስድስት የሰው ቁጥር ነው፡፡
ሰው የተፈጠረው በስድስተኛው ቀን ነው፡፡ ምሉዕ ከሆነው ሰባት ጥቂት ጎድለናል፡፡
ለምን? በሕይወታችን ውሰጥ ኃጢአት ስላለ፡፡
“ስድስት” የሚያሳየው በኃጢአት እና በወደቀው የሰው ተፈጥሮ ምክንያት የሰው ሥራዎች ዋጋቸውን እንዳጡ ነው፡፡
ሰው እንደመሆናችን አጠቃላዩን እውነታ ማየት አንችልም፡፡ በጣም ራስ ወዳድና ስለ ራሳችን በማሰብ ብቻ የተጠመድን ነን፡፡
ስድስቱ ቀናትም ሰው በምድር ላይ ያሳለፋቸውን የስድስት ሺህ ዓመታት ስራዎች ይወክላል፡፡
እግዚአብሔር ገነትን ፈጠረ ሰው ደግሞ ኃጢያትንና የራሱን ፈቃድ በመምረጥ የእግዚአብሔርን ገነት አበላሸ። የሰው ታሪክ ሰው የራሱን ችግሮች መፍታት እንደማይችልና ሰው በምድር ላይ ገነትን መፍጠር እንደማይችል አሳይቶናል፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር ከኃጢአት ነጻ ሊያወጣን ይፈልጋል።
ነፃ የሚያወጣንም በመንፈሱ እና በደሙ እንጂ በራሳችን ሥራ አይደለም፡፡
ለስድስት ቀናት ሥራን መስራት የሰውን ጥረት የሚወክል ምሳሌ ነው፡፡ የሰው ጥረቶች በሙሉ አይሳኩም፡፡
ስለዚህ መዳን፣ በቅድስና መኖር እና በእግዚአብሔር መንፈስ መሞላት ያስፈልገናል፡፡
በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥረ ስር ስንሆን ዳግመኛ መወለድ ማለት ይህ ነው፡፡
ከዚያ የራሳችንን ሕይወት መኖር አቁመን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እየኖረ አረማመዳችንን እንዲመራ እንፈቅዳለን፡፡
ቆላስይስ 1፡27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።
ክርስቶስ ብቻ ነው ኃጢያትን ይቅር ማለት የሚችለው፡፡
ራእይ 1፡ 5 ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ኢሳይያስ 64፡6 ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
መልካም ሥራዎቻችን ከኃጢአት ሊያነጹን አይችሉም፡፡
ዘሌዋውያን 23፡3 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።
መዳንን ማግኘት የሚያስችሉ መልካም ሥራዎችን ልንሰራ አንችልም፡፡
ኤፌሶን 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ሮሜ 7፡18 በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፥ መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም።
የእግዚአብሔር ፈቃድ እና የእግዚአብሔር ቃል ሕይወታችንን እንዲቆጣጠር የራሳችንን ፈቃድ መተው አለብን፡፡
ፊልጵስዩስ 2፡13 ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።
እረፍት ማግኘት የምንችለው ድርጊታችንና አነሳሽ ከምክንያታችን (ከሞቲቫችን) ጋር ብቻ ነው፡፡
በራሳችን ሥራ መዳን አንችልም፡፡ በራሳችን ሥራ ብንድን ትምክህተኞች እንሆናለን፤ ራሳችንን ከፍ እናደርጋለን፡፡
ይህ ግን መልካም ሥራዎች አያስፈልጉም ማለት አይደለም፡፡ ሆኖምየምንሰራቸው መልካም ሥራዎች በራሳችን የምናደርጋቸው መሆን የለባቸውም፡፡ እነዚህ መልካም ስራዎች በውስጣችን በሚኖረውና እኛን በሚቆጣጠረን በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የተሰሩ መሆን አለባቸው፡፡
ያዕቆብ 2፡18 ነገር ግን አንድ ሰው፡- አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
ያዕቆብ 2፡22 እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?
ያዕቆብ 2፡24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።
ያለ መልካም ሥራዎች እምነታችን መሆን ያለበትን አይሆንም፡፡
እምነታችን መልካም ሥራዎችን እንድንሰራ ሊያስችለን ይገባል፡፡
የሚታዩት ሥራዎቻችን ለማይታየው እምነታችን ማሳያ ወይም ነፀብራቅ ናቸው፡፡
እምነት ሕይወትን ይሰጠናል፤ መልካም ሥራዎች ግን በእምነት ያገኘውን ይህንን ሕይወት ይጠብቃሉ፡፡
እምነት በዕፅዋት/በዛፍ ውስጥ እንዳለ የሕይወት ንጥረ ነገር ነው፡፡ ከዛፍ ላይ ቅርፊቱን ወይም ቆዳውን ብትገሸልጡ ሕይወት ሰጭው ፈሳሽ ይደርቃል።
ኢየሱስ ብቻ ነው ወደ ፍጹም ፈቃዱ ሊመራህና እንድትፈጽመው ሊያነሳሳህ የሚችለው።
እግዚአብሔር ብቻ ነው ምን እንድትሰራለት እንደሚፈልግ የሚያውቀው።
ዕብራውያን 10፡7 በዚያን ጊዜ፡- እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ
ማድረግ ያለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን ብቻ ነው፡፡ ማድረግ ያለብን ለቤተክርስቲያን ዘመን የተጻፈውን ነው፡፡
ዕብራውያን 10፡8 በዚህ ላይ፡- መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥
9 ቀጥሎ፡- እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።
በምድር ላይ የተፈጠርንበት ብቸኛ ዓላማ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሳችንን ፈቃድ አይደለም፡፡
እግዚአብሐየርን ደስ ሊያሰኘው የሚችለው ብቸኛው መስዋእት ፈቃድህን በፍላጎትህ ለእግዚአብሔር ስትሰዋለት እና በቦታው ለሕይወትህና ለዚህች ምድር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስትቀበል ነው፡፡
ከኃጢአትና ካለማመን በሚያሳርፈን በመንፈስ ቅዱስን በመሞላት ፋንታ ሰንበትን ለማክበር ብለን በቅዳሜ ቀን ከሥራ ብናርፍ፤ የእግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን ያለውን ዕቅድ አልተረዳነውም ማለት ነው፡፡
ይህ ማለት እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረን አይደለም፤ ስለዚህም ወደ እውነቱ ሙላት እና ወደ ፍጹም ፈቃዱ በአግባቡ ሊመራን አይችልም ማለት ነው፡፡
የቅዳሜ ሰንበትን የሚያካትተው ሕግ ከጊዜ ጋር የተያያዙ ሌሎች ገደቦችም ነበሩት፡፡
ዘሌዋውያን 25፡4 በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር ሰንበት፥ ትሁን፤ እርሻህን አትዝራ፥ ወይንህንም አትቍረጥ።
ሰንበት የሚያመለክተው ቀንን ብቻ አይደለም፤ ዓመትንም ጭምር ነው፡፡
በዚህ ቃል ውስጥ ሰንበት ምድርርን ያመለክታል ነው፡፡ ይህ ዓመት ሙሉ የሚደረግ እረፍ ከቅዳሜ ጋር በምንም አይገናኝም፡፡ በኃጢያት የተነሳ እግዚአብሔር ምድርን ረገማት። ስለዚህ ምድርም ሳትቀር እህል ከማፍራት ማረፍ ያስፈልጋታል፡፡
ዘፍጥረት 3፡17 አዳምንም አለው፡- የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
18 እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።
19 ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና።
በመጀመሪያው ኃጢአት የተነሳ ምድር ተረግማ ነበር፡፡ ምድር አሁን መልካም ምግብን፣ እሾክ እና አሚኬላ አረም ወዘተ ታበቅላለች፡፡
የግብርና ሥራ በዚህ ዘመን ከአረምና ከተባዮች ጋር በመታገል ነው የሚሰራው፡፡
ምግብር ለማምረት ሰውም ምድርም መልፋት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰው በየሰባት ቀኑ መሬት ደግሞ በየሰባት ዓመቱ እንዲያርፉ ተፈቀደላቸው።
ነገር ግን በስተመጨረሻ ኃጢያት ሲሻር ይህ እርግማን ይነሳል፡፡
ከዚያ በኋላ ልፋትና ድካም ስለሚቀር የቀን እረፍትም ሆነ የዓመት እረፍት አያስፈልጉም፡፡ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ግን ከልፋት ልናመልጥ ስለማንችል እረፍት ያስፈልገናል፤ ክርስቶስ በውስጣችን ሲኖር ደግሞ ከኃጢአት ፍላጐቶች እረፍት እናገኛለን፡፡
ኃጢአትን ለማስተስረይ ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ቦታ የደም ላብ አልቦታል፡፡ላብ የእግዚአብሔር እርግማን አንዱ አካል ሲሆን፤ ይህ ላብ የኢየሱስ ደምን ነክቷል፡፡
ሉቃስ 22፡44 በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ።
በራሱ ላይ የሾህ አክሊል ደፍተውበታል፡፡
እሾህ የእግዚአብሔር እርግማን አካል የነበረ ሲሆን እሾህም የኢየሱስን ደም ነክቷል፡፡
ማቴዎስ 27፡29 ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥… አኖሩ፥
አይሁድ እጅግ ይጠሉት ስለነበር በኮረብታ ላይ በመስቀል ላይ ሊቸነክሩት ከከተማዋ ውጭ ወሰዱት፡፡ ይዘውት ሲሄዱ ደሙ በከተማይቱ የድንጋይ ንጣፎች ላይ ሳይሆን ቀጥታ በምድር ላይ ተንጠባጠበ፡፡
እግዚአብሔር ምድርን ረግሟታል፡፡ የኢየሱስም ደም በምድር ላይ ተንጠባጠበ፡፡
በመሆኑም በኤደን ገነት የታወጀው እርግማን ይሻር ዘንድ ላብ፣ እሾህ እና ምድር በኢየሱስ ደም ጋር ተነክተዋል፡፡
ስለዚህ ወደፊት እርግማን አይኖርም፡፡ እሾህ፣ አሜከላ፣ አረም እና ተባዮች ስለማይኖሩ ምድር በቀላሉና አትረፍርፋ እህል ትሰጣለች፡፡
ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ አሁን ልባችን በኢየሱስ ደም ከተነካ እኛም ይቅርታ ተቀብለን ከኃጢአታችን ማረፍ እንችላለን፡፡
ለጊዜው ምድር መልካም አይደለችም፡፡
እናንተጋ ፀሐይ ስትጠልቅ በተቃራኒው የምድር ጎን ፀሐይ ትወጣለች፡፡
ጊዜ ራሱ ጊዜያዊ ነገር ነው፡፡
በስተመጨረሻ ወደ ዘላለማዊነት ስንገባ ጊዜ ይሻራል፡፡
ሰንበትን ጨምሮ በሕጉ ላይ ሌላ የጊዜ ገደብ አለበት፡፡ ሕግ ተፈፃሚ የሚሆነው በዚህ ዓለም ሕይወት ብቻ እንጂ ከሞት በኋላ አይቀጥልም፡፡
ሮሜ 7፡1 ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?
ከሞት በኋላ በሚመጣው ሕይወት ሕጉ ምንም ስልጣን የለውም፡፡ ጊዜ እግዚአብሔር በምድር ላይ የፈጠረው ነገር በመሆኑ ሞታችሁ ወደ ሰማይ ስትሄዱ ቅዳሜ የሚባል ነገር በዚያ የለም፡፡ ሰማይ በጊዜ ቀመር አይገደብም፡፡
በሰማይ ምሽት ወይም ሌሊት የለም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ ውስጥ እንቅልፍ ስለመተኛት አንዴም አይናገርም፡፡
በራእይ ምዕራፍ 10 ላይ የክርስቶስ ሙሽራ ለሰርጉ ድግስ ወደ ሰማይ ትወሰድ ዘንድ ሙታንን ለማስነሳት እና ሕያዋንን ወደ ማይሞት ሰውነት ለመቀየር ታላቁ መልአክ በሚወርድበት ጊዜ ከሞት ለሚነሱ ቅዱሳን ጊዜ የሚባል ነገር መኖሩን ያቆማል (የማትሞቱ ስትሆኑ ጊዜ በናንተ ላይ ምንም ተፅዕኖ አይኖረውም)፡፡
ጊዜ ልክ ሕግ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የራሱን ሚና ተጫውቶ የሚያልፍ ነገር ነው፡፡
ዘላለማዊነት ሲመጣ ጊዜ ይጠፋል፡፡
ራእይ 10፡5 በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥
6 ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ።
ስለዚህ ጊዜ የዘላለማዊነት አካል ባለመሆኑ በስተመጨረሻ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡
እኛ በጊዜ ውስጥ ተወልደን በጊዜ ውስጥ ስለምንኖር እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እንዴት እንደነበረ መረዳት አንችልም፡፡
በዘላለማዊነት ውስጥ ለመኖር በአዲስ አካል እንደገና መፈጠር አለብን፡፡ በዚህም ጊዜ ለእኛ ትርጉም አይኖረውም፡፡
ጊዜ የሚባል ነገር በሌለበት ወቅት የቅዳሜ ጽንሰ ሐሳብም አብሮ ይጠፋል፡፡
በመጨረሻ በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ውስጥ የፀሐይ ብርሃን እንኳ አይታወቅም፡፡ ቁሳዊ ነገሮች ሁሉ በፍጥረታዊ ዓይኖቻችን ልናይ የማንችለውን ጥልቅ መንፈሳዊ እውነታ የሚወክሉ ጥላዎች ናቸው፡፡
ራእይ 21፡9 ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፡- ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።
10-11 በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤
ከተማይቷ የራስዋ ብርሃን ነበራት፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡
በመጨረሻም ቅድስቲቷ ከተማ (የፒራሚድ ዓይነት ቅርጽ ያላት) ወደ ምድር ስትወርድ እግዚአብሔር የከተማይቱ ጉልላት ይሆናል፡፡
ከተማይቱ በማያቋርጥ ብርሃን ትሞላለች፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብርሃን ነው፡፡
በፒራሚድ አናት ላይ ያለ መብራት በፒራሚዱ ጐኖችና በዙሪያው ላይ ምንም ዓይነት ጥላ አይጥልም፡፡
1ኛ ዮሐንስ 1፡5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፡- እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
ራእይ 21፡23 ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።
ስለዚህ በስተበመጨረሻ በዚያች ከተማ ውስጥ ቀንም የለም ሌሊትም የለም፡፡
ስለዚህ በየሰባተኛው ቀን የሚመጣ የሰንበት ቀን ፅንሰ ሐሳብ የማያቋርጥ ብርሃን ባለበት ቦታ ትርጉም አይኖረውም፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ በሁሉ ላይ ስለሚነግስ በዚያም ኃጢያት ስለማይኖር ከኃጢያት እና ከመዘዞቹ፣ ከጸጸቶቹሁሉ ለዘላለም እረፍት ይሆናል፡፡
ራእይ 21፡22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።
የክርስቶስ ሙሽራ በመጨረሻ የምትኖርበት ከተማ በማያቋርጥ ዘላለማዊ ብርሃን ትጥለቀለቃለችች፡፡ የፀሃይ ብርሃን አስፈላጊነቱ ይቀራል ምክንያቱም ምሽት ቀንን ተከትሎ በተደጋጋሚ ኡደት ስለሚመጣ የፀሃይ ብርሃን እየተቆራረጠ ነው የሚበራው፡፡
ክርስቶስ ግን ለከተማይቱ ዘላለማዊ እና የማይቋረጥ ብርሃን ነው፡፡በእርሱ ዘንድ ጨለማ የለም። ካልመሸ ቀንን መቁጠር አይቻልም፤ ምክንያቱም የቀንን መጠናቀቅ የሚያመለክተው ጨለማ ነው፡፡ ስለዚህ የቅዳሜ ጽንሰ ሃሳብ ራሱ ይጠፋል፡፡
ራእይ 21፡24 አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤
25 በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥
ጨለማ (የኃጢአት ምሳሌ) በስተመጨረሻ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፡፡
በዚያች ታላቅ ከተማ ሌሊት የሚባል ነገር አይኖርም፡፡
የቀኑን መጠናቀቅ የሚያመለክት ምሽት በሌለበት ቅዳሜ ሊኖር አይችልም፡፡ የሚኖረው ማቆሚያ የሌለው አንድ ዘላለማዊ ቀን ብቻ ነው፡፡
በመጨረሻም ቅዳሜ የሚባሉ ቀናት አይኖሩም፡፡ ነገር ግን በዚያች ታላቅ ከተማ የሚኖር ሁሉ ለዘላለም ከኃጢአት ያርፍ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡
አሁን በዚህች ምድር ላይ በጊዜ ተገድበን ስለምንኖር ቅዳሜ ብለን የምንጠራውን ቀን መኖሩን መገንዘብ እንችላለን፡፡
የሚቀጥለው ምዕራፍ ክርስቶስና እውነተኛዋ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን (ሙሽራዋ) ምድርን ለሺህ ዓመት የሚገዙበት ወቅት ነው፡፡ ከታላቁ መከራ የሚተርፉት አሕዛብ ተገዢዎቹ ሕዝብ ይሆናሉ፡፡
ኃጢአት በሺህ ዓመት መንግስት ውስጥም በምድር ላይ ይኖራል ግን በብረት በትር ስለሚገዛ ሰዎች በዚያን ጊዜ ሥርዓት ይዘው ይኖራሉ፡፡
ራእይ 21፡26-27 ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤
ኢየሱስ በዚያን ጊዜ በምህረቱ ዙፋን ላይ ስለማይቀመጥ በዚያ የሺህ ዓመት ሰላም ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ከኃጢአታቸው ለመንጻት በብሉይ ኪዳን ጊዜ በነበረው ዓይነት መንገድ የመቅደስ የአምልኮ ሥርዓትን ይፈጽማሉ፡፡ ይህም ከመከራ ለተረፉት ሰዎች ኃጢአታቸውን ለመሸፈን የቅዳሜ አምልኮ እና ሰንበትን በድጋሚ ይዞላቸው ይመጣል፡፡
ኢሳይያስ 66፡22 እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
23 እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።
በሺህ ዓመቱ ውስጥ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በጊዜ ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ኃጢአት ግን ይገደባል፡፡ ስለዚህ እንደ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” ይሆናል፡፡ ዓለም በሙሉ በኢየሱስ ይገዛል ልክ ኃጢአት በማይኖርባት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ውስጥ እንደሚሆነው። ሆኖም በሺህ ዓመቱ ውስጥ ኃጢያት ይኖራል፡፡ ስለዚህ ኃጢአትን ለማስተስረይ የመቅደስ ሥርዓትና አምልኮ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ኢየሱስ በምድር ላይ ለሺህ ዓመታት የሚገዛበት ጊዜ የመጀመሪያው ሰማይ ወይም የአዲሱ ሰማይ እና ምድር ቅምሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሕዝቡ መካከል ኃጢአት ይኖራል፡፡
ሺህ ዓመታቱ ሲፈፀሙ ሰዎች ያምጹና ከሰማይ በሚወርድ እሳት ይጠፋሉ፡፡ ባሕር ይፈነዳና ይጠፋል፡፡ ይህም አጠቃላይ የምድርን ገፅ ጠራርጐ በሽታ አምጭ ሕዋሳትንና በሽታዎችን እንዲሁም የሰው ልጅ ስልጣኔ ምልክቶችን ሁሉ ጠራርጐ ያጠፋል፡፡
ራእይ 21፡1 አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።
ከዚያም በኋላ ስፋቷ 1500 ማይል በ1500 ማይል የሆነች አራት ማዕዘን ቅርፅ ያላት ግዙፍ ከተማ ከሰማይ ትወርዳለች፡፡ ከተማይቱ የፒራሚድ ቅርፅ ያላትና ከዙሪያዋ ወደ መሃል ያጋደለ የ1500 ማይል ከፍታ ይኖራታል፡፡
ራእይ 21፡16 ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፥ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት አሥራ ሁለትም ሺህ ምዕራፍ ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።
እግዚአብሔር በከተማይቱ ጉልላት ላይ ስለሚቀመጥ የከተማዋ መራብት ይሆናል፡፡ ከላይ መብራት ሲደረግበት በዙሪያው ጥላ የማይፈጥር ቅርጽ ፒራሚድ ብቻ ነው።
ራእይ 21፡23 ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።
በዚህ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ውስጥ ባህር የለም፣ ጊዜ የለም፣ ኃጢአትም አይኖርም፡፡ በመሆኑም የቅዳሜ ፅንሰ ሐሳብ ራሱ ምንም ትርጉም አይኖረውም፡፡
በመጀመሪያው ኃጢያት የተነሳ ከመጣብን ድካም የምናርፈውን እረፍት ይወክል የነበረው ቅዳሜ ከዚያ ወዲያ ይቀራል፡፡
እያንዳንዱ ሰነድ የገዥው ምልክት ወይም ማህተም አለበት።
ለምሳሌ፡- የእንግሊዟ ንግስት የኤልሳቤጥ ማሕተም።
ማሕተሟ ስሟን፣ ማዕረጓንና የግዛቷን ክልል ያሳያል፡፡
እግዚአብሔር እራሱ የጻፈው ብቸኛ ሰነድ አስርቱ ትዕዛዛት የያዘው ሰነድ ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ ሰነድ የእግዚአብሔር ማሕተም ያስፈልገው ነበር፡፡
ዘጸአት 20፡8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
11 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
ቁጥር 11 የእግዚአብሔር ማሕተም ነው።
እግዚአብሔር (ስሙ ያህዌ ይባላል) ሰማይን፣ ምድርንና ባህርን (ግዛቱ) ፈጠረ (ፈጣሪ ማዕረጉ ነው፡፡ እኛን ስለፈጠረን ምን ማድረግ እንዳለብን ሊነግረን መብት አለው፡፡)
በእግዚአብሔር ግዛት ውስጥ መኖር ካልፈለክ ያለህ ብቸኛ አማራጭ ሲኦል ነው፡፡
ስለዚህ አራተኛው ትዕዛዝ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የአስርቱ ትዕዛዛት ማሕተም ነው፡፡
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ግን የእግዚአብሔር ማሕተም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
ኤፌሶን 4፡30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ አራተኛው ትዕዛዝ የሆነው ሰንበት በአዲስ ኪዳን ለሚመጣው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጥላ ነበር፡፡
ደሙ ያጥበናል፤ መንፈስ ቅዱስም በመንግስቱ ውስጥ እንድንኖር ያትመናል፡፡
ከዚያ በኋላ ነው በክርስቶስ አርፈን ከኃጢያት ፍላጎቶችና ሥራዎች የምናርፈው፡፡
ዘጸአት 20፡8 የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
9 ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
እኛ ራስ ወዳዶችና ኃጢአተኞች በመሆናችን እግዚአብሔር ስራችንን አይፈልገውም፡፡
እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ መኖርና የራሱን ስራዎች ለመሥራት ሊጠቀምብን ይፈልጋል፡፡
የመርከባችን ካፒቴን መሆን ይፈልጋል፡፡
ሕይወታችንን ራሳችን የምንመራ ከሆነ እግዚአብሔርን ልናስደስት አንችልም፡፡
እግዚአብሔር ንጹህ እና የተቀደሰ ሕይወት እንድንኖር ፈቃዱም በሕይወታችን እንዲከናወን ይፈልጋል፡፡
እግራችንን መምራት ይፈልጋል፡፡
በውስጣችን ሲኖርና ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረን ብቻ ነው እውነተኛ እረፍት የምናርፈው፡፡