ራዕይ ምዕራፍ 1 – 3



እውነት በጨለማው ዘመን ውስጥ ተቀብራ ነበር። ተሃድሶ የተጀመረው የለውጥ መሪዎች ከተነሱበት ጊዜ ጀምሮ ዊልያም ብራንሐም የመጨረሻዎቹን ሚስጥራት እስከገለጠበት ጊዜ ድረስ ነው።

First published on the 4th of December 2021 — Last updated on the 16th of January 2022

የዮሐንስ ራዕይ የ2,000 ዓመታት ውስጥ ያለፉ የቤተክርስቲያን ዘመናትን ታሪክ የሚገልጹ ተምሳሌቶች የሞሉበት መጽፍ ነው።

የራዕይ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ምዕራፎች ሰባት መቅረዞችን የሚመለከቱ ናቸው።

ይህ ምንድነው የሚያስተምረን?

የሚነግረን ነገር ቢኖር የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የተከሉት “መልካም ዘር” የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንደሆነ ነው። ከዚያ በኋላ ክርስቲያኖች በመንፈስ ግድ የለሾችና እንቅልፋሞች ሆኑ፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ለመከተል ስላልቆረጡ ስሕተት ወደ መካከላቸው ሾልኮ ገባ።

የእውነት ዘር በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ በነበረው በጨለማው ዘመን ውስጥ ተቀበሮ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ማርቲን ሉተር ባመጣው ተሃድሶ አማካኝነት የእውነት ዘር ተመልሶ በቀለ። የተሃድሶ መሪዎቹ የመጀመሪያዎቹ ቀንበጥና ቡቃያ ናቸው። ቤተክርስቲያንም ቀስ በቀስ እየታገለች ሐዋርያቱ በአዲስ ኪዳን ዘመን ያምኑ ወደነበረው እምነት ለመጠጋት ሞከረች።

በስተመጨረሻው የበቀለው ተክል መጀመሪያ የተዘራውን ዘር የሚመስል ፍሬ ያፈራል።

ወደ መጀመሪያው ትምሕርት የመመለሱ እንቅስቃሴ ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁልጊዜ በአመራር፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆኑ አስተምሕሮዎች፣ በፖለቲካዊ ሽኩቻ፣ በገንዘብ ፍቅር፣ እና በባዕድ አምልኮ ልማዶች ላይ ትኩረት ባደረጉ መናፍስት ተቃውሞ ሲገጥመው ኖሯል።

ይህ የመናፍስት ግጭት በቤተክረስቲያን ውስጥ የተፈጠረ ሲሆን እስከ መጨረሻው ድረስ ይቀጥላል።

ማቴዎስ 13፡24 ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።

25 ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።

26 ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።

27 የባለቤቱም ባሮች ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት።

28 እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም፦ እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።

29 እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።

30 ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን፦ እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።

በመጀመሪያ እይታ ሲታይ ቤተክርስቲያን በሰባቱም የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ብርሃኗ እኩል ደምቆ የበራ ይመስላል።

ነገር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ስንዴዎችም እንክርዳዶችም ነበሩ።

 

 

ስለዚህ የቤተክርስቲያን ብርሃን የእውነት እና የስሕተት ድብልቅ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት የወይን ተክሎች ነበሩ።

በቤተክርስቲያን ውስጥ በእያንዳንዱ ዘመን የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንደነበረ በጥንቃቄ ብንመለከት፤ ይህንንም ከሰዎች ልማድ እና ሽንገላ ለይተን ብናየው በየዘመኑ የነበረው እውነተኛው ብርሃን ይህንን ይመስላል፡-

 

 

በራዕይ የመጀመሪያ ሶስት ምዕራፎች ውስጥ የተጠቀሰውን ባለ ሰባት ቅርንጫፉን መቅረዝ እንመልከተው። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን መሃከል ላይ ያለው ከሁሉም የሚበልጥ ነበልባል ያለው መቅረዝ ነው።

የጳውሎስንና የሐዋርያትን ትምሕርት ልናሻሽለው አንችልም። አዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ምን ዓይነት እንድትሆን እንደፈለገ የገለጠበት መጽሐፍ ነው።

ከመሃከለኛው መቅረዝ እየራቅን ስንሄድ ከሐዋርያዊ እውነት እየራቅን ወደ ጨለማው ዘመን ውስጥ እንገባለን።

ከመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን እምነቶች እየራቅን መሄድ ወደ ክፋት ውስጥ መግባት ነው።

ይህም ራዕይ ምዕራፍ 2 ውስጥ በአራቱ ቤተክርስቲያኖች ተገልጧል።

 

 

 

አቅጣጫ ቀይረን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ብንመለስ ከክፋት እየራቅን ስንመጣ ወደ ሕይወት እንገባለን።

ራዕይ ምዕራፍ 3 በተሃድሶ እውነት ከጨለማው ዘመን ውስጥ ወጥታ እንደምትመለስ ይነግራናል።

ጀርመኒ ውስጥ ማርቲን ሉተር መዳን በእምነት የሚለውን እምነት በተሃድሶ መልሶ አመጣ። እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ቅድስና እና የወንጌል ስብከትን ወደ ቤተክርስቲያን በተሃድሶ በማምጣቱ የወንጌል ስርጭት ዘመን ተጀመረ። የጴንጤ ቆስጤ መነቃቃት የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ አመጣ፤ አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ዊልያም ብራንሐም የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አማኞች ያምኑት ወደነበረው እምነት መመለስ እንችል ዘንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሚስጥራትን ገለጠ። የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ሙሽራዋ በዘይት መብራቷ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን አንብባ መረዳት የሚያስችላት በቂ ብርሃን ሲኖራት ነው።

 

 

 

ራዕይ ውስጥ ያሉት ሰባቱ መቅረዞች በአይሁድ ቤተመቅደስ ውስጥ በቅድስት ስፍራ የነበረው ባለ ሰባት ቅርንጫፍ መቅረዝ ነጸብራቅ ናቸው። ይህ መቅረዝ ቤተመቅደሱ ውስጥ ከ12ቱ ሕብስት ጋር ነበረ።

ቤተመቅደሱ ውስጥ የነበሩት እቃዎች አቀማመጣቸው በመስቀል ቅርጽ ነው።

በዚህ መልኩ የመቅደሱ እቃዎች በአዲስ ኪዳን ዘመን ውስጥ 2,000 ያህል የሚፈጁት ሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ሲገለጡ ሊሆኑ ያላቸውን ነገሮች የሚያንጸባርቁ ነበሩ።

 

 

 

ሁለቱን ቁልፍ የሆኑ ቁጥሮች፡ 7 እና 12 ልብ በሉ።

ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው፤ የዳኑ ሰዎች ደግሞ አካሉ ናቸው።

ኤፌሶን 5፡23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

ራስ ከአካል ጋር የሚጋጠመው በጀርባ አጥንት አማካኝነት ነው።

 

 

 

የመጀመሪያዎቹ 7 አጥንቶች አንገት ውስጥ ናቸው።

ቀጣዮቹ 12 አጥንቶች ጎድኖችን ይሸከማሉ።

ኢየሱስ እነዚህን ሁለት ቁጥርሮች ከሰራቸው ከሁለት ታላላቅ ተዓምራት ውስጥ ይጠቅሳቸዋል።

እነዚህም ተዓምራት አንድ ትንሽ ልጅ በያዘው ጥቂት እንጀራ እና ዓሣ በሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዶችን ማብላቱ ነው።

ማቴዎስ 16፡9 ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

ኢየሱስ የሆነ ነገር እንድናስተውል ፈልጓል። ትልቁ ቁም ነገር ምግብ የበሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አይደሉም፤ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ ደቀመዛሙርቱ ስንት መሶብ ቁርስራሽ መሰብሰባቸው ነው።

ማቴዎስ 16፡10 ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

ሰዎቹ ጠግበው አንበላም ብለው የተዉት የእንጀራ እና የዓሣ ቁርስራሽ መጠኑ 12 መሶብ እና 7 መሶብ ነበር።

ሰዎች እምቢ አንበላም ብለው ከዚያ ስለተሰበሰቡት ቁርስራሾች ምን መረዳት እንችላለን?

እንጀራና ስጋ የሚወክሉት አስተምሕሮን ነው።

አይሁዶች መሲሁንና ያስተማረውን አስተምሕሮ እንደማይፈለግ የምግብ ቁርስራሽ አንቀበልም ይላሉ። ደቀመዛሙርቱ ይህን አይሁዶች የጣሉትን ወንጌል አንስተው ወደ አሕዛብ ይወስዱታል፤ አሕዛብም በቀጣዮቹ ሰባት የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ወደ ክርስቶስ ይመጣሉ። ወደፊት የሚወለዱ ክርስቲያኖችን ለማሳደግ ተቀባይነት ያለው ምግብ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያት የጻፉት አስተምሕሮ ብቻ ነው።

አዲስ ኪዳን በባለ ሰባት ቅርንጫፉ መቅረዝ የተመሰለ የዓለም ብርሃን ነው። በብሉይ ኪዳን ላይ የተመሰረተው አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች መካከል ስታልፍ የሚመራት ብርሃን ነው። ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት በኋላ ቤተክርስቲያን ከሙታን ተነስታ ከዚህ ዓለም ተለይታ ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከተነጠቀች በኋላ ወንጌል በታላቁ መከራ ዘመን ወደ አይሁዶች፣ ወደ 12 የእስራኤል ነገዶች ይሄዳል። በስተመጨረሻም አይሁዶች የጥንት አያቶቻቸው ከ2,000 ዓመታት በፊት አንበላም ብለው የጣሉትን የአዲስ ኪዳን አስተምሕሮ ቁርስራሽ ከሁለቱ ነብያቶችቸው ይቀበላሉ።

 

 

 

ኢየሱስ አይሁዶችን ለሶስት ዓመት ከግማሽ አገልግሏል። ከዚያ በኋላ አይሁዶች አንቀበልህም አሉት። እግዚአብሔርም በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ከአይሁዶች ወደ አሕዛብ ዘወር አለ። መንፈስ ቅዱስም ቤተክርስቲያንን በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ሊመራ ወደ ምድር ወረደ፤ ቤተክርስቲያን ወደ ሰማይ በምትነጠቅበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ምድርን ትቶ ይሄዳል። ከዚያ በኋላ በመጨረሻዎቹ ሶስት ከግማሽ ዓመታት ውስጥ በታላቁ መከራ ዘመን እግዚአብሔር ወደ አይሁዶች ይመለሳል።

12ቱ የእስራኤል ነገዶች የተወከሉት ቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት 12 ሕብስቶች ነው።

1ኛ ዜና 9፡32 በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።

ሕብስቶቹ ቤተመቅደሱ ውስጥ ለሰባት ቀናት ይቆያሉ፤ ከዚያም ሌሎች አዲስ 12 ሕብስቶች ተጋግረው በቀጣዩ ሰንበት የመጀመሪያዎቹን ሕብስቶች ይተካሉ።

የመጀመሪያዎቹን ሕብስቶች ካሕናቱ በቅድስት ሥፍራ ይበሏቸዋል። ሕብስቱ በቅድስት ሥፍራ ነው የሚቆየው።

 

 

 

12ቱ ሕብስቶች በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ (ከባለ 7 ቀኑ ሳምንት መጨረሻ) ከ12ቱ እስራኤል ነገዶች የሚመጡትን 144,000 ሰዎች ይወክላሉ፤ እነዚህም ሰዎች መሲሁን ለመገናኘት ወደ ተስፋይቱ ምድራቸው ይመለሳሉ (ይህንን የሚወክለው የቤተመቅዱስ ቅድስት ሥፍራ ነው)።

ላለፉት መቶ ዓመታት ያህል አይሁዶች ወደ እስራኤል ሲመለሱ አይተናል። መሲሁ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለስ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ናቸው። በ7ቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት መጨረሻ ላይ 12 የእስራኤል ነገዶች ወደ ተስፋይቱ ምድር እየተመለሱ ናቸው።

ስለዚህ 12 እና 7 በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ጠለቅ ያለ ትርጉም አላቸው።

 

ዮሐንስ ራዕዩን ጽፎ ከዚያም በ100 ዓ.ም አካባቢ በሞተበት ሰዓት አንዳንድ የታሪክ ምሑራን እንደሚሉት ትያጥሮን ከተማ ውስጥ ቤተክርስቲያን አልነበረም። ትያጥሮን ውስጥ ቤተክርስቲያን የሆነው ከዮሐንስ ሞት በኋላ ነው። ስለዚህ የዮሐንስ መልእክቶች በእነዚያ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ የነበሩ ክስተቶችን ብቻ አልነበረም የሚገልጡት። ከዚያ በተጨማሪ ወደፊት ሊሆኑ ያላቸውን ክስተቶችም ጭምር ነበር የሚገልጡት። በነዚያ ጥንታዊ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ “በለዓም” ወይም “ኤልዛቤል” የተባሉ ሰዎች አልነበሩም።

እነዚህ ስሞች በእስራኤል ታሪክ ውስጥ በጥንት ዘመን የእግዚአብሔርን ሰዎች ሊቃወሙ የተነሱ ሐሰተኛ መሪዎችን የሚወክሉ ናቸው፤ በጊዜው የነበሩ የእግዚአብሔር ሰዎችም ሙሴ እና ኤልያስ ነበሩ። ሙሴ እና ኤልያስ ደግሞ በታላቁ መከራ ዘመን (ራዕይ ምዕራፍ 11) 144,000ዎቹን አይሁዶች ወደ መሲሁ ሊመልሷቸው ወደ እስራኤል የሚመጡ የሁለቱ ምስክሮች ስሞች ናቸው።

የትያጥሮን ቤተክርስቲያን በሐዋርያቱ ዘመን ውስጥ አልተመሰረተችም ነበር፤ ነገር ግን ከሐዋርያቱ በኋላ ወዲያው ተመስርታለች። ይህም የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን ማለትም የጨለማው ዘመን ቤተክርስቲያን ከመቸውም ጊዜ በላይ ከሐዋርያት ተጽእኖ እና ትክክለኛ አስተምሕሮ ርቃ የነበረበት ዘመን እንደነበረ ያመለክታል።

ራዕይ 1፡19 እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።

ዮሐንስ በዘመኑ ስለኖረበት ስለ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን አንዳንድ ነገሮችን ይነግረናል። ቀጥሎም ወደፊት በቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ስለሚሆኑ ነገሮች፤ ከዚያም በስተመጨረሻ በታላቁ መከራ ዘመን ውስት አይሁድ እንደሚመለሱ ይነግረናል።

ስለዚህ “የሰባቱ ቤተክርስቲያኖች ሚስጥር ማለት” በዚያ ጊዜ የነበሩት ስድስቱ ቤተክርስቲያኖች እንዲሆም ከዚያ ወዲያ ቶሎ የተመሰረተችዋ የትያጥሮን ቤተክርስቲያን በውስጣቸው ወደፊት በሚመጡ የቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ቤተክርስቲያን የምታልፍባቸውን ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይዘዋል ማለት ነው።

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በሰባት የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሊያሳልፋት ፈለገ።

በስተመጨረሻም ምንም ዓይነት ተግዳሮቶች ቢመጡ እንኳ፤ ሰይጣንም ቤተክርስቲያንን በብዙ ዓይነት አጋንንታዊ አሰራሮች ቢያጠቃትም እንኳ እግዘአብሔር ድል የሚነሱ ሰዎች ይኖሩታል። የነዚህ ድል ነሺዎች ምስክርነት በክርስትና ጸንቶ ለመኖር ፈተናው ከአቅማችን በላይ ስለሆነብን ነው እምነታችንን የካድነው የሚሉ ሰዎችን አፍ ያዘጋል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ላልሆነ ነገር እና ውሸት ለሆነ ነገር እጅ አንሰጥም ብለው ከጸኑ በሚያልፉበት በማናቸውም የፈተና እሳት ውስጥ ኢየሱስ ሊረዳቸው ይችላል። በጥንቷ ባቢሎን ውስጥ እንደነበረው የእግዚአብሔር መርህ ግልጽ ነው፡- አንሰግድም ብትሉ እግዚአብሔር ደግሞ ስለ እናንተ አይቃጠሉም ብሎ ይነሳላችኋል።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 1 የተጀመረው በ33 ዓ.ም የበዓለ ሃምሳ ዕለት ነው።

በ100 ዓ.ም አካባቢ ሐዋርያው ዮሐንስ ሲሞት የስልጣን ጥም ያለባቸው ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ መነሳት ጀመሩ።

ኤፌሶን ማለት ኢላማ ያለትና የተረጋጋች ማለት ነው።

ትንንሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ስሕተቶች ወደ ሾልከው መግባት ጀመሩ። አንድ ሰው የቤተክርስቲያን መሪ ይሁን የሚለውም ሃሳብ ሾልኮ መግባ ጀመረ።

ሰዎችም ግድየለሽ በመሆን ስለ ጥቃቅን ስሕተቶች ብዙም መጨነቅ እንደማያስፈልግ አሰቡ፤ ነገር ግን ጠብታ የነበሩት ስሕተቶች ኋላ በቀጣይ ዘመናት ውስጥ የስሕተት ጎርፍ ሆኑ።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ያበቃው በሮማዊው ገዥ በማርከስ ኦሬልየስ (161-180 ዓ.ም) ሲሆን በዚያም ዘመን ክርስቲያኖች ይሰደዱ ነበር። በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የክርስቲያኖች ስደት ተባባሰ።

ኔሮ በ64 ዓ.ም ባስነሳውና በንጉስ ዳዮክሊቲያን ዘመን እስከ 312 ዓ.ም ድረስ በዘለቀው ስደት 3 ሚሊዮን ያህል ክርስቲያኖች በሮማ መንግስት ውስጥ ተገድለዋል። ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ የተገደሉት በሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ከ170 – 312 ዓ.ም ነው።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የተመሰረተው በአዲስ ኪዳን እና በሐዋርያት አስተምሕሮ ነው። ፍጹም የሆነው መሪያቸው የእግዚአብሔር ቃል ነበር። እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የምትተዳደረው በሽማግሌዎች ሕብረት ነበር። አማኞች የሚጠሩበትም ብቸኛ ስም “ክርስቲያን” ነበረ። ሐዋርያት በሕይወት በነበሩበት ዘመን ዲኖሚኔሽኖች ወይም በተለያዩ ስሞች የሚጠሩ ቤተክርስቲያኖች አልነበሩም።

የሐዋርያት ሥራ 20፡17 ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤

የሐዋርያት ሥራ 20፡28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

ጳውሎስ በኤፌሶን በነበረችው ቤተክርስቲያን ላይ ፓስተር አልሾመም።

የሐዋርያት ሥራ 20፡29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

የስልጣን ጥም የነበረባቸው ሰዎች ኋላ ለስልጣንና ለገንዘብ ተስገብግበው ራሳቸውን በቤተክርስቲያን ላይ ገዥ አድርገው ሰየሙ።

የሐዋርያት ሥራ 20፡29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

የአዲስ ኪዳን ክርስትና ሰዎች ሁሉ እኔ ያልኩትን ካልተከተሉ በሚል በአንድ ሰው አምባገነናዊ መሪነት ወይም አለቅነት ምክንያት ወደ ዲኖሚኔሽናዊ ቤተክርስቲያናዊነት እያሽቆለቆለ ወረደ። ከዚያ ወዲያ የቤተክርስቲያን ትልቁ ውድቀቷ የሆነውም ይህ ነው።

የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን በቀጣይ ዘመናት ቤተክርስቲያን ምን መምሰል እንዳለባት አርአያ ነበር።

ሐዋርያት ፖለቲካ ውስጥ ገብተው አያውቁም። ነፍሰ ገዳዩ ኔሮ በጳውሎስ ዘመን ነው ገዥ የነበረው። ጳውሎስ የኔሮን ጥፈቶች እየዘረዘረ መጻፍ ይችል ነበር፤ ነገር ግን የጻፈው ለመሪዎች መጸለይ አለብን ብሎ ነው።

ጳውሎስ ሁልጊዜ ክርስቶስን እያከበረ የእግዚአብሔር ሙላት ክርስቶስ መሆኑን እያወጀ ነው የኖረው።

ቆላስይስ 2፡9 በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

ኔሮ መሞቱ አይቀርም ነበር፤ ስለዚህ ጳውሎስ ምንም ትኩረት አልሰጠውም። ኢየሱስ ግን ሁሌም ሕያው ነው፤ ስለዚህ ጳውሎስ እርሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ነበር።

 

 

ይህ መቅረዝ የመጀመሪያውን የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ዘመንን ይወክላል። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን የክርስቲያን ቤተክርስቲያን ምን መምሰል እንዳለባት ጥሩ ምሳሌ ነው።

የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እንደ ሞዴል አይተን ልንከተላት የሚገባት ቤተክርስቲያን ናት፤ የምንመለሰውም ወደ መጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ነው።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 2

ዘመን እያለፈ ሲሄድ የሰው አመራር ስሕተቶችን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት ከመጽሐፍ ቅዱስ ርቀን እንድንሄድ አድርጓል። ሰዎች እንግዳ በሆኑና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማይታወቁ ስሞች ራሳቸውን መጥራት ጀመሩ፤ ለምሳሌ፡- “የአንጾኪያ ጳጳስ”።

ፊልጵስ 1፡1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤

በፊልጵስዩስ ከተማ ውስጥ ብዙ ጳጳሶች ነበሩ።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የከተማ ጳጳስ አልነበራትም።

ጳጳስ የሽማግሌ ሌላ መጠሪያው ነው።

57-0908 ዕብራውያን ምዕራፍ አምስት እና ስድስት - 1

ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ከአጥቢያ ሽማግሌ የሚበልጥ ስልጣን ያለው ሰው ካለ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ።

እውነት ነው ወገኖች፤ እያንዳንዷ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በራሷ ነጻ ናት።

የአጥቢያ ሽማግሌዎች ናቸው አጥቢያ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሯት።

የሰባቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት ማብራሪያ፡ ጴርጋሞን፡ ኒቆላውያን

ይህ አስተምሕሮ በመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ በወጣ ደምብ ነው የተጀመረው። ችግሩ ያለው በሁለት ቃላት ውስጥ ነው፡- እነርሱም “ሽማግሌዎች” (ፕሬስቢተርስ) እና “ጠባቂዎች” (ቢሾፕስ) ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሽማግሌዎች እንዳሉ ቢያሳይም አንዳንዶች (ከእነርሱም መካከል ኢግናሺየስ አንዱ ነው) ቢሾፕ ወይም ጳጳስ ከፍ ያለ ከሽማግሌዎችም በላይ የሆነ ሥልጣን ያለው አገልጋይ ነው ብለው ማስተማር ጀመሩ።

እውነታው ግን ምን መሰላችሁ፤ “ሽማግሌ” የሚለው ቃል ሰውየውን የሚያመለክት ሲሆን ቢሾፕ ወይም ጳጳስ የሚለው ቃል ግን የዚህኑ ሽማግሌ የአገልግሎት ክፍል ወይም ዘርፍ የሚያመለክት ቃል ነው። ሽማግሌው ሰውየው ነው። ቢሾፕ የሰውየው የአገልግሎት ዘርፍ ነው። “ሽማግሌ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰውየው በጌታ ሆኖ ያሳለፋቸውን ዓመታት ብዛት ነው። የዚህ ቃል ትርጉሙ በፊትም ሁልጊዜም እንደዚሁ ነው። ሰውየው ሽማግሌ የሆነው ስለተመረጠ ወይም ስለተቀባ አይደለም፤ ነገር ግን በጌታ ሆኖ ከሌሎች በላይ እድሜ የገፋ ስለሆነ ነው። ይህ ሰው ከሌሎች ይልቅ የበሰለ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በደምብ የተማረ፣ ሊታመን የሚችል፣ ጀማሪ ወይም አዲስ ክርስቲያን ያልሆነ ነው፤ ልምድ ያለው እና በረጅም ዓመታት የክርስትና ሕይወቱ የተመሰከረለት ሰው ነው።

ነገር ግን ጳጳሳቱ የጳውሎስን መልእክቶች መከተል አቁመዋል፤ መልእክቱን ትተው ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 20 ውስጥ ሽማግሌዎችን ከኤፌሶን ወደ ሚሊጢን ያስጠራበት ታሪክ ላይ ብቻ አተኮሩበት። ቁጥር 17 “ሽማግሌዎች” መጠራታቸውን ይናገርና እነዚሁ ሽማግሌዎች ደግሞ በቁጥር 28 ጠባቂዎች (ጳጳሳት) ተብለው መጠራታቸውን ያሳያል። እነዚህ ጳጳሳት (ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የተሞሉ እና የሥልጣን ጥማት እንደነበራቸው አያጠራጥርም) ጳውሎስ “ጠባቂዎች” ወይም ጳጳሳት ለሚለው ቃል የአንድ ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ብቻ ከሚለው ትርጉም የበለጠ ትርጉም ሰጥቷል ብለው በመከራከር የጳጳሳት ሥልጣን ከአንድ ቤተክርስቲያን የሚያልፍ ነው አሉ። ስለዚህ በእነርሱ አስተሳሰብ ጳጳስ ማለት ከአንድ ቤተክርስቲያን አልፎ በብዙ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ላይ ስልጣን ያለው ሰው ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በመጽሐፍ ቅዱስም በታሪክም የለም፤ ሆኖም ግን ፖሊካርፕን የሚያህል ሰው እንኳ ሳይቀር ወደዚህ ሃሳብ አዘነበለ።

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የጥቂት ሰዎች ሕብረት ስብስብ የነበረች ሲሆን አስተዳዳሪዎቿም ሽማግሌዎች ነበሩ።

“ፓስተር የሚለው ቃል” አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ኤርምያስ ውስጥ በትንቢት ስድስት ጊዜ ተወግዟል። ፓስተሩ የቤተክርስቲያን ራስ እንዲሆን ስልጣን የሰጠው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ የለም። (ዛሬ 45,000 ዓይነት የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች አሉ፤ እነዚህን የሚመሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፓስተሮች አሉ። እነዚህ ሁሉ ፓስተሮች የተለያየ እምነት አላቸው። ይህ ከባድ መንፈሳዊ አረንቋ ነው።)

ዘመን ሲያልፍ ቤተክርስቲያን ከአዲስ ኪዳን መርሆች እየራቀች ሄደች። ሐይማኖታዊ ሽንገላ ሾልኮ መግባት ጀመረ። ኢየሱስ በማቴዎስ 24፡4 እንዲህ ብሎ አስጠንቅቆ ነበረ፡- “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤” ሰዎች ግን ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የሰውን ጥበብ መረጡ።

ሰምርኔስ ማለት ምሬትና ሞት ማለት ነው። ስደትና ድህነት ቤተክስቲያን ከእውነት ብዙ ርቃ እንዳትሄድ አድርጓት ነበር። እግዚአብሔር የሰምርኔስን የቤተክርስቲያን ዘመን አድንቋል።

ድህነት እና ስደት ለቤተክርስቲያን ጥሩ መሆኑ ዛሬ ለብዙዎች የማይዋጥላቸው እውነት ነው።

 

 

በሁለተኛውም ዘመን ቤተክርስቲያን ደምቃ እያበራች ትመስላለች ነገር ግን ከብርሃኗ የተወሰነው ክፍል የራሳቸውን ሃሳብ በሚያፈልቁ በሰዎች ጥበብ የመጣ ነው። የአይሁድ ሕዝብ የሐይማኖት መሪዎች ሕዝቡን እያሳቱ ስለነበረ ኢየሱስ እና መጥምቁ ዮሐንስ የሐይማኖት መሪዎች በትሕትና አልነበረም የሚያናግሯቸው። በሁለተኛው የቤተክርስቲያና ዘመን ሰዎች መሪ ሆነው ቤተክርስቲያንን በተሳሳተ መንገድ እየመሯት ነበር፤ እውነትም በአሳዛኝ ሁኔታ እየደበዘዘች ነበር።

ስለዚህ ሁለተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ይህን የሚመስል ነበር፤ እውነትን የሚወክለው የመቅረዙ ነበልባል እየደበዘዘ ነበር።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 3

በ325 ዓ.ም የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤ በመንግስት እውቅና የተሰጣትን ቤተክርስቲያን በአንድ ጨካኝ ፖለቲካዊ መሪ ስር እንድትተዳደር አደረጋት፤ እርሱም ንጉስ ኮንስታንቲን ነው።

ንጉስ ኮንስታንቲን በ312 ዓ.ም ክርስቲያኖችን ማሳደድ አቆመ፤ ስለዚህም በዚህ ደስ የተሰኙ ክርስቲያኖች ይህንን ጨካኝ አረመኔ ፖለቲከኛ የቤተክርስቲያን ራስ አድርገው ተቀበሉት። ይህም ትልቅ ስሕተት ነበር።

የሮም ጳጳስ ለንጉሱ እንዲታዘዝ ለማድረግ ሮም ውስጥ ውብ የሆነው የላተራን ቤተመንግስት ተሰጠው። የሮማ ጳጳስ የሮማ ንጉስ የኮንስታንቲንን ድጋፍ ስላገኘ የስልጣን ጥማቱ ጨመረና በሌሎች ከተሞችም ላይ ተቆጣጣሪ መሆን ፈለገ። ሮም የሮማ ግዛት ዋና ከተማ ነበረች፤ ስለዚህ የሮማ ጳጳስ ከሌሎች ከተሞች ጳጳሳት እበልጣለሁ ብሎ አሰበ።

እንደ ክሪስማስ፣ ስላሴ፣ እና ፖፕ የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌሉ ቃላት የቤተክርስቲያን ትኩረት ሆነው ቀሩ። ፖለቲካ ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲገባ አረማውያን ስደተኞች ሆኑ። በስተመጨረሻም ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር የማይስማሙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ።

አረማዊ ልማዶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞችን ተከናንበው ገቡ።

የሮማውያንን የፀሃይ አምላክ በመኮረጅ ዲሴምበር 25 የክሪስማስ ቀን ነው ተብሎ የቤተክርስቲያን በዓል እንዲሆን የተደረገው የሮም ጳጳስ በነበረው ዩልየስ 350 ዓ.ም አካባቢ ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን ልደት እንድናስብ አልነገረንም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እውቅና የሌለውን ክሪስማስ በዓለም ዙርያ ዋነኛው የክርስትና በዓል አድርገው መሰየማቸው የሮምን ስልጣን በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ላይ ለማጽናት አስተዋጽኦ አድርጓል።

የሮማ ጳጳስ ክሪስማስን ፈጠረ። ስለዚህ ክሪስማስን የተቀበሉ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ በሮም ተጽእኖ ስር ወደቁ። ሮም የክሪስማስ ሕግ አወጣች።

ሮም እንዳለችው ክሪስማስ በክረምት አጋማሽ ላይ አረማውያን በዓላቸውን በሚያከብሩበት ቀን የሚከበር ታላቅ በዓል መሆን አለበት። በክረምት ከቤት ውጭ በጣም ቀዝቃዛ በመሆኑ እረኞች ሜዳ ላይ ሊገኙ አይችሉም። ይህም በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱን መቃረን ነው። ሰብአ ሰገል ወደ በረት ሄዱ ይላሉ፤ ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ፊት ለፊት መካድ ነው። በዚህ ሰበብ ተጠቅመው ኮከብ እና ስጦታ ለማዘጋጀት ምክንያት አገኙ። ኮከብ አየር ላይ ከፍ ብሎ ነው መቀመጥ ያለበት፤ ስለዚህ ያጌጠው የአሕዛብ “የገና ዛፍ” ወደ ቤተክርስቲያን ገባ።

ሰብዓ ሰገል ግን ወደ በረት ውስጥ ሳይሆን ወደ ቤት ነው የገቡት።

ማቴዎስ 2፡11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥

አይሁዶች ኮከብን ማምለክ የጀመሩ ጊዜ ከእውነት ስተው ወደቁ።

አሞጽ 5፡26 ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ የሞሎክን ድንኳንና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ።

አሕዛብ አምላክ ብለው ኮከብን ያመልኩ ነበር። ከማታዋ እና ከጠዋቷ ኮከብ ከቪነስ በቀር ቀጣይዋ የምትመለከው ደማቅ ኮከብ ሳተርን ነበረች። በዚያ ዘመን ፕላኔት መሆኗን አያውቁም ነበር።

ለዚህ ነው ሰብዓ ሰገል ኮከብ ተከትለው ወደ በረት መጡ የሚሉት። ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ ኮከቡ ምንም ከበረት ጋር የተያያዘ ነገር አልነበረውም። ሰብዓ ሰገል ወደዚያ የደረሱት ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ነው። ነገር ግን የአረማውያን የሚያመልኩት ኮከብ ዲሴምበር ውስጥ በክረምት አጋማሽ የሚያከብሯቸው በዓለት አካል ነበረ።

ኤርምያስ 10፡2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም [የዞዲያክ ምልክቶች] አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና።

3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።

4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።

ተቆርጦ ጌጣጌጥ እና ጫፉ ላይ ኮከብ የተደረገበት ዛፍ የተለመዱ የአሕዛብ የክረምት አጋማሽ በዓል ምልክቶች ነበሩ። ዩል የሚባለው ቃል በከለዳውያን (በባቢሎናውያን ቋንቋ) ልጅ ማለት ነው። ከእነርሱ ዩልታይድ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል መጣ። ስለዚህ አሕዛብን ለማስደሰት የክረምቱ አጋማሽ የኢየሱስ ልደት በዓል እንዲሆን ተደረገ።

በአዲሱ በ45 ዓመተ ዓለም በሮማዊው ገዥ በዩልየስ ቄሳር አማካኝነት በተቀየረው የሮማውያን ካላንደር መሰረት የተመረጠው ዲሴምበር 25 ቀን ይህ የሮማውያን ካላንደር በሌሎች ሃገሮች ሁሉ ላይ ስልጣን እንዲኖረው አስቻለው። በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተፈጠውን የክሪስማስ ሕግ ለማክበር ሕዝቡ አዲሱን የሮማ ካላንደር መቀበል ግድ ሆነባቸው። ይህም ሮም በሕዝቦች ላይ የነበራት ስልጣን እንዲጨምር አደረገ።

ዳንኤል 7፡25 በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።

ኋላ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው በካላንደሩ ላይ የመጨረሻዎቹን ለውጦች አደረገበት። ይህም ለውጥ የሮማ ካላንደር በዓመቱ ውስጥ ካሉት ክረምት እና በጋ እንዲሁም ሌሎች ወቅቶች ጋር በትክክል እንዲገጥም አድርጓል፤ ዓለምም በሙሉ ይህንን የሮማውያን ካላንደር ነው የሚጠቀምበት። አረማዊው የሮማ ቄሳር እና የሮማው ጳጳስ ፖፕ ግሪጎሪ 13ኛው ለሁለት ተባብረው የዓለማችንን አንደኛ ምርጥ ካላንደር አዘጋጅተዋል። ይህም የፖፑን ስልጣን በቤተክርስቲያን በዓላት ሁሉ ላይ አስፋፍቷል።

ገላትያ 4፡9 አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?

10 ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።

11 ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።

ዓመታዊ የቤተክርስቲያን በዓላትን ማክበር የለብንም። ለዓመታዊ በዓላት የሚሆኑ ልዩ ቀናት የሉም።

ጳውሎስ የገላትያ ክርስቲያኖችን እንዴት ቀንን (25) ወር (ዲሴምበር) ዘመን (የክሪስማስ ወቅት) ዓመትንም (ዓመታዊ በዓል) በመጠበቅ ባሪያ ትሆናላችሁ ብሎ ወቅሷቸዋል።

በነዚህ ከአሕዛብ ሐይማኖቶች በመጡ በዓላት አማካኝነት አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ትተው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያወጣቻቸውን ሕጎች መከተል ጀመሩ። ይህም ትልቅ ስሕተት ነው።

ዘመንን የምንቆጥርበትን ካላንደር ሮም ቀየረችው።

የክሪስማስ በዓልን ሕግ እና የኢሽታር እንቁላል እንዲሁም የኢሽታት ጥንቸሎችን ማለትም በጸደይ ወቅት መጋቢት እና ሚያዚያ ውስጥ የሚከበረውን የልቅ ወሲብ በዓል ሕግ ያስተዋወቀች ሮም ናት። ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ሕጻናት በታህሳስ አጋማሽ አካባቢ ይወለዳሉ፤ ይህም ዩል ወይም የልጅ ወቅት ይባላል።

ናምሩድ በተገደለ ጊዜ ሚስቱ ሰሚራሚስ የሰማይ ንግስት ኢሽታር ነኝ በማለት በሚያዚያ አጋማሽ በሚከበረው የጸደይ በዓል ውስጥ በሚደረገው ልቅ ወሲብ ተሳተፈችና ልጄ ታሙዝ የተወለደው በዲሴምበር አጋማሽ ነው አለች። ይህም ልጅ የሞተው የባሏ የናምሩድ ትንሳኤ ነው አለች። ዛፍ ከተቆረጠ በኋላ ብዙውን ጊዜ ተመልሶ ያድጋል። ስለዚህ የሚቆረጠው የክሪስማስ ዛፍ የተገደለውን ናምሩድን ይወክላል፤ ዛፉ ላይ የሚደረገው ጌጣጌጥ ደግሞ የናምሩድ “ትንሳኤ” ሆኖ የተወለደውን ታሙዝን ይወክላል።

በክብ ቅርጽ የሚጋገር ዳቦ ሰሚራሚስ ወይም ራሷን የሰማይ ንግስት ጨረቃ ብላ የሰየመችውን ኢሽታርን ይወክላል። ዳቦው ላይ ያለው “†” ደግሞ ከ9 ወራት በኋላ የሚወለደው የልጇ የታሙዝ ስም የመጀመሪያ ፊደል ነው። ፈረንጆች ሆት ክሮስ በንስ የሚሉት ዳቦ መነሻው ይህ ነው።

በሶስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን የአሕዛብ ባዕድ አምልኮ መንፈስ የአሕዛብ ልማዶችን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞች እየጠራ ወደ ቤተክርስቲያን ሰተት ብሎ ገባ። ኢሽታር ኢስተር ወይም ፋሲካ ሆነ።

ሂዩ ሄፍነር በፕሌይቦይ መጽሔቱ እና በኒ ገርልስ በሚላቸው ሴቶች ብዙ ሚሊዮን አሜሪካኖችን አበላሸ። ሴቶቹን ለምንድነው የጥንቸል ቅርጽ ያላቸው ልብሶች የሚያለብሳቸው? ይህስ ስለ ኤስተር በኒስ ወይም ስለ ፋሲካ ጥንቸሎች አመጣጥ ምን ይነግረናል? ጥንቸሎች ከእንስሳት ሁሉ በመዋለድ ፈጣኖች ናቸው።

አሁንም ሮም ከባዕድ አምልኮ ባመጣቻቸው የበዓላት ቀኖቿ አጠላልፋናለች።

ኢየሱስ የሞተው አርብ ከሰዓት ነው ብሎ ፖፑ አወጀ። ሰው ሁሉ ምንም ነገር ሳያመዛዝን ለፖፑ ይታዘዛል።

ማቴዎስ 12፡40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

ሶስት ሌሊት በመቃብር ውስጥ መቆየት ማለት ኢየሱስ የሞተው ሐሙስ ከሰዓት በኋላ መሆኑን ያመለክታል። ሐሙስ ሌሊት፣ አርብ ሌሊት፣ እና ቅዳሜ ሌሊት መቃብር ውስጥ ነበረ። ከዚያም እሑድ ጠዋት ከሞት ተነሳ።

የፋሲካ በግ በ10ኛው ቀን በሕዝብ ፊት በይፋ ይመረጥና በ14ኛው ቀን ወደ ሰውየው ቤት ተወስዶ ይታረዳል።

ዘጸአት 12፡3 ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።

 

ዘጸአት 12፡6 በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።

ኢየሱስ የሆሳዕና ዕለት በሕዝብ ፊት የአይሁድ ንጉስ ተብሎ ተመረጠ፤ ይህም የወሩ 10ኛ ቀን ነበር።

ስለዚህ 14ኛው ቀን እርሱ የተገደለበት ቀን ሐሙስ ነው የሚሆነው።

“የስቅለት አርብ” የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ፈጠራ ነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም።

15ኛው ቀን የቂጣ በዓል የሚከበርበት የመጀመሪያው ቀን ነው። ይህም ታላቅ ሰንበት ወይም የማዘጋጀት ቀን ነው።

ስለዚህ የ15ኛው ቀን አርብ የማዘጋጀት ቀን የሰንበት ቀን ነበረ።

ዲኖሚኔሽንም ቤተክርስቲያን ላይ የተጫነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቃል ነው።

ኮንስታንቲን ቤተክርስቲያንን በፖለቲካዊ ስልጣን፣ በገንዘብ፣ እና በሕንጻዎች አምበሸበሻት።

ስለዚህ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መስማት ትታ ኮንስታንቲንን መስማት ጀመረች።

ጴርጋሞን ማለት ሙሉ በሙሉ የተጋባች ማለት ነው። ቤተክርስቲያን ከአረማዊነት፣ ከዓለማዊነት፣ ከሃብት፣ እና ከፖለቲካ ጋር ተጋባች።

 

 

ቤተክርስቲያን እንደ ስላሴ በመሳሰሉ የሰው ጥበቦች ደምቃ አበራች፤ ስለ ስላሴም በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሲከራከሩ ቆይተው ብዙዎችን አሳመኑ። የእግዚአብሔርም ስም ተረስቶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰዎችን በስም ፈንታ በሶስት ማዕረጎች ማጥመቅ ጀመሩ። በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው የምናጠምቀው ብለው ያወራሉ ግን ያ ስም ማን እንደሆነ መናገር አይችሉም። ለሶስት ሰዎች አንድ ስም ማውጣት አይቻልም።

ስላሴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል ነው።

ስለዚህ እውነትን ከማጸባረቅ አንጻር ሶስተኛው የቤተክርስቲያን ከላይ ያለውን መቅረዝ ይመስላል።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የቤተክርስቲያን አስተምሕሮ የሆነው ስላሴ በሚለው ቃል ነው። ዛሬ ይህንን እንደ ሰበብ ተጠቅመው የፈለጉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ቃል አስተምሕሮዋቸው ውስጥ ያስገባሉ። ክርክራቸውም የሚከተለውን ይመስላል፡-

“ስላሴ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ሆኖም እውነት ከሆነ ሌላም ቃል (ለምሳሌ) ክሪስማስም እውነት መሆን አለበት”።

በዚህ መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ሃሳቦች እንደ ቫይረስ ተዛመቱ።

ራዕይ 13፡2 … ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።

የሮማ ገዥ የነበረው ኮንስታንቲን የላተራን ቤተመንግስትን ለሮማ ጳጳስ ሰጠው፤ እስከ ዛሬም ድረስ ይህ ቤተመንግስት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት ሆኖ ቀጥሏል፤ ፖፑም ይህ ቤተመንግስት የቅዱስ ጴጥሮስ መናገሻ ነበረ ይላል።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 4

የንጉሱን ድጋፍ በመጠቀም የሮማ ጳጳስ ወዲያ በሌሎች ቤተክርስቲያኖች ላይ ስልጣን አለኝ ማለት ጀመረ። ከዚያም በኋላ ፖንቲፌክስ ማክሲመስ (ፖንቲፍ) የሚለውን ማዕረግ ከተቀበለ ጊዜ ጀምሮ ፖፕ ሆነ፤ ፖንቲፌክስ ማክሲመስ የሚለው ማዕረግ የባቢሎናውያን ሚስጥር ሊቀካሕናት እንደመሆኑ የሮማ ግዛትን በወረሩትና ባፈራረሱት ባርቤሪያውያን ነገዶች ላይ ትልቅ ስልጣን አጎናጸፈው።

ቀጥሎም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማይታወቁ የማዕረግ ስሞች የሚጠሩ ብዙ የቤተክርስቲያን የስልጣን ተዋረዶች ተፈጠሩ፤ በጨለማውም ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በላቲን ቋንቋ ብቻ ስለነበረ የሚገኘው ብዙው ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አልቻለም።

ሰዎች ብዙውን ጊዜ በእጃችሁ ወይም በቤታችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ተገኘ ወይም የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ለምን ተቃወማችሁ ተብለው ይገደሉ ነበር።

ከፖፑ ጋር የማይስማሙ መናፍቃንን መግደል እንደ ሐጥያትም አይቆጠርም ነበር።

ይህ የትያጥሮን ቤተክርስቲያን ዘመን ነበር፤ ትያጥሮን ማለት ጨቋኝ ሴት ማለት ነው። ሴት የቤተክርስቲያን ተምሳሌት ናት።

የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክ ራዕይ ምዕራፍ 17 ውስጥ ተጽፏል።

ክፉዎቹ የቦርጂያ ፖፕስ የክፋት የርኩሰት ሁሉ ጥግ ሲሆን በዘመናቸው እውነት ተቀብራ እንድትጠፋ አድርገዋል።

ፖለቲካዊ ስልጣን፣ የቤተክርስቲያን ሕጎች፣ እና የሰዎች ስግብግብነት ቤተክርስቲያንን ጨቆኗት።

በመንግስት እውቅና ያገኘችዋ የሮማ ቤተክርስቲያን አውሮፓን ተቆጣጠረች፤ ከዚህም የተነሳ መጽፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የቤተክርስቲያን ልማዶችና አስተምሕሮዎች ካመጡት ተጽእኖ የተነሳ እውነት ተቀበረች። እውነተኛ አማኞች ወደ ምድረበዳ ሸሹ። ዋልደንሶች ልዮንስ ከተማ ውስጥ ነበር የጀመሩት፤ ነገር ግን ከነፍሰ ገዳዮቹ የሮማ ካቶሊክ ወታደሮች ለማምለጥ ወደ አልፕስ ተራሮች ውስጥ ሄደው ተሸሸጉ። በቀጣዩ ካርታ ውስጥ ራይን እና ሮን የተባሉትን ወንዞች ማየት ይቻላል።

 

 

ፖፕ፣ ካርዲናል፣ ሜትሮፖሊታን፣ ሊቀ ጳጳሳት፣ ሊቀ ዲያቆናት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ማዕረጎች ናቸው፤ ቤተክርስቲያን ግን ስትመራ የቆየችው በነዚህ ነው።

ቤተክርስቲያን ተንኮለኛ በሆኑ የሰው አስተምሕሮዎች፣ ፍልስፍናዎችና በገንዘብ ማግኛ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ደምቃ አበራች።

አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ይህንን ስዕል ነበር የሚመስለው።

 

 

ራዕይ ምዕራፍ 2 አራት ቤተክርስቲያኖችን ይጠቅሳል።

አራቱ ቤተክርስቲያኖች አራቱን የቤተክርስቲያን ዘመናት ይወክላሉ። አራት የሰባት መካከለኛ ቁጥር ነው። ስለዚህ አራተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ቤተክርስቲያን አውሮፓን የመራችበት ዘመን መካከለኛው ዘመን ወይም የጨለማው ዘመን ተብሎ ይታወቃል።

እውነት ቀስ በቀስ ከሐዋርያት ጀምሮ እየወደቀች ወደ ክፉውና ጭካኔ ወደ ሞላበት የቤተክርስቲያናዊነት ዘመን ገብታ እስከ መጥፋት ደርሳለች። የሰው ልማዶች እና የቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከተጻፉት የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ርቀው ሄደዋል

አራተኛው መቅረዝ ከአንደኛው መቅረዝ ጋር ሲወዳደር በጣም ትንሽ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነበር የያዘው።

 

 

የመጀመሪያዎቹ አራቱ የቤተክርስቲያን ዘመናት የሚያመሳስላቸው ነገር አላቸው፤ ይህም ከአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን እየራቁ መሄዳቸው ነው።

 

ሶስት የቤተክርስቲያን ዘመናት የተጠቀሱበት ራዕይ ምዕራፍ 3 የሚናገረው ደግሞ ከቀደሙት ተቃራኒ ነው።

የተሃድሶ መሪዎች ቤተክርስቲያንን ወደ መጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመንና ወደ ሐዋርያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ሊመልሷት እየሞከሩ ነበር።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 5

 

 

ተሃድሶው ከመቅረዙ ሌላኛ ጎን ተነስቶ አዲስ ጅማሬ ጀመረ።

ቤተክርስቲያን ውስጥ ያኔም ብዙ ያልተረዱት ነገር ቢኖርም የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት ወደሚያምኑት እምነት እና አስተምሕሮ ለመመለስ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት እና መነቃቃት ነበረ።

ከዚያም ጀግናው ማርቲን ሉተር ጀርመኒ ውስጥ ነፍሰ ገዳይ የሆነውን የቤተክርስቲያን ስርዓት ሳይፈራ ተነሳ፤ ከእርሱ ጀምሮ የነበሩት የተሃድሶ መሪዎች የእግዚአብሔር ቃል ዘር ሲበቅል ማቆጥቆጥ የጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ቅጠሎች ሆነው ተነሱ። የተሃድሶ መሪዎች መዳን በሥራ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን ነው የሚለውን ትምሕርት ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው አመጡ። ከዚያም በአጸፋው ሰይጣን መዋጋት ሲጀምረ ፖለቲካና ግፍ ተመልሰው ወደ ቤተክርስቲያን ገቡ። ነገር ግን ሐዋርያት ወዳስተማሩት እውነት ለመመለስ መንገድ ተጀምሯል። ይህም የሰርዴስ ወይም ያመለጡ ሰዎች የቤተክርስቲያን ዘመን ይባላል።

ተሃድሶው ሲጀምር ሉተር በጨለማ ውስጥ እንደ ብቸኛ ብርሃን ሆኖ ቆመ። መዳን በእምነት ብቻ ነው ብሎ ሰበከ። ወዲያው እርሱን ተከትለው ሌሎች የተሃድሶ መሪዎች ተነሱ።

5ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከላይ ያየነውን መቅረዝ ይመስላል፤ በዚያ ዘመን ውስጥ ሉተር እና ሌሎች የተሃድሶ መሪዎች ወደ ሌላኛው የመቅረዙ ጎን በመሄድ አዲስ እንቅስቃሴ ጀመሩ። ሉተር መዳን በክርስቶስ ብቻ የሚለውን የሐዋርያትን ትምሕርት ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ለማምጣት ፈለገ። በመልካም ሥራዎች አማካኝነት መዳን እንችላለን በማለት ከአዲስ ኪዳን መጽሐፍ እየራቀ መሄድ አልፈለገም።

ኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ በ1611 ዓ.ም ተዘጋጅቶ መጽሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝኛ እንዲነበብ አደረገ፤ ከዚያም በተደጋጋሚ ተፈትሾና ተጣርቶ በ1769 ተጠናቀቀ። ከዚያ በኋላ በዓለም ዙርያ ለተደረገው ወርቃማ የወንጌል ሥርጭት አገልግሎት የጀርባ አጥንት ሆኖ አገልግሏል።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 6

ከዚያም እንግሊዝ ውስጥ ጆን ዌስሊ ፖለቲካን ከመስበክ በመቆጠብና ግፍን በመቃወም ቅድስና እና የወንጌል አገልግሎት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ አደረገ። ይህም በታላቁ የወንጌል ስርጭት ዘመን ለወንጌል ስብከት ለተከፈተው በር መሰረት ሆነ፤ በዚህም ዘመን ሕይወት ሰጭው የእግዚአብሔር ቃል ዘር በዓለም ዙርያ ሁሉ ተበተነ። ይህም ወርቃማው የፊልድልፍያ የቤተክርስቲያን ዘመን ወይም የወንድማማች መዋደድ ዘመን ይባላል።

 

 

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እየበረታ ሄደ፤ ስለዚህ ስድስተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ከላይ የምናየውን ስዕል ይመስል ነበር።

 

የቤተክርስቲያን ዘመን 7

አሁን ያለንበት የሎዶቅያውያን የቤተክርስቲያን ዘመን የመጨረሻው የቤተክርስቲያን ዘመን ነው (በዚህ ዘመን ሰዎች የራሳቸውን ቤተክርስቲያን እንደመሰረቱ ልብ በሉ)።

እንደ ጥነቷ የሐዋርያት የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ነው መሆን ያለብን።

 

 

በ1904 ዌልስ ውስጥ የሆነው የጴንጤቆስጤ መነቃቃት እና በ1906 ሎሳንጀለስ ውስጥ ብዙም በማይታወቀው አዙዛ እስትሪት የመጣው የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ልዕለ ተፈጥሮአዊ የሆነው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለስ አድርጓል። ቤተክርስቲያንም ወደ አዲስ ኪዳን ሐዋርያዊ እምነቶች ልትመለስ መንገድ ጀመረች። ይህም ዘሩ እንዳይጠፋ የሚጠብቅ ቅርፊት ነው። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በ1917 ልክ ሌሎቹ ቤተክርስቲያኖች እንዳደረጉት ሁሉ የጴንጤ ቆስጤ እንቅስቃሴም በሰዎች መካከል በተለያዩ ቡድኖች መከፋፈል ጀመረ።

እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመልሶ መምጣቱን ብቻ አይደለም የፈለገው፤ ሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትም ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመለስ ፈልጓል።

ዮሐንስ 16፡13 ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤

ዛሬ ዘሩ ማለትም የእግዚአብሔር ቃል በተገለጠው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ውስጥ መብሰል አለበት።

 

 

አንድ ተክል መጨረሻ ላይ የሚያፈራው ፍሬ መጀመሪያ ከተዘራው ዘር ጋር አንድ ዓይነት ነው። በሁለቱ መካከል ምንም ልዩነት የለም።

7ኛው ዘመን ከመጀመሪያው ዘመን የተለየ ዘር ቢያፈራ 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ሰው ሰራሽ ድብልቅ ዘር ነው ማለት ነው።

እግዚአብሔር እያንዳንዱ ዘር እራሱን የመሰለ ፍሬ እንዲያፈራ ነው የሚፈልገው። እግዚአብሔር ቅልቅል ዘር እንዲኖር አላደረገም።

 

ቤተክርስቲያን ተመላላሾች ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ይልቅ ለቤተክርስቲያን ታማኝነትን ይመርጣሉ። እያንዳንዱ ሰው ቤተክርስቲያኑ ያስተማረችውን ብቻ ያምናል። የሚሄዱባት ቤተክርስቲያን ካስተማረቻቸው ትምሕርት የተለየ ነገር ግን የተገለጠ እውነት ሲሰሙ አልቀበልም ይላሉ።

ሰባተኛዋ ቤተክርስቲያን በሰው ሰራሽ ትዕዛዛትና በሰው አስተምሕሮ ተተብትባ የመጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ እውነት ማግኘት ባልቻለችበት ሁኔታ ውስጥ ይህን ትመስላለች።

ቤተክርስቲያን ከጨለማው ዘመን ብዙ ርቃ መጥታለች፤ ነገር ግን እስካሁን ወደ መጀመሪያዎቹ ሐዋርያት እምነት አልተመለሰችም።

የቤተክርስቲያን መሪዎችን ብታደምጧቸው በኪንግ ጄምስ ቨርዥን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ውስጥ ያሉትን ስሕተቶች፣ እርስ በርስ የሚጋጩ ሃሳቦች፣ የትርጉም ስሕተቶች ያወሩላችኋል። ስለዚህ ሙሉ ትኩረታቸውን የሚያደርጉበት ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ቃል የላቸውም።

ስለዚህ በመጨረሻው የሎዶቅያ (የሕዝቡ መብት) ቤተክርስቲያን ውስጥ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ ጠፍቶባታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እያደጉ ከመሄድ ይልቅ በገንዘብና በቁሳቁስ ክምችት እያደጉ ሄደዋል።

በመጨረሻ 7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ክርስቲያኖች ወደ አዲስ ኪዳን እምነት አልመለስም ካሉ በአሁኑ ሰዓት ባሉት ልዩ ልዩ የመለካከት ብዛት ውስጥ ጠፍተው ይቀራሉ፤ የተገለጠውንም የዘመን መጨረሻ እውነት አንቀበልም ብለው ይገፋሉ። ከዚህም የተነሳ ብዙዎቹን እምነቶቻቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ ያቅታቸዋል። በ7ኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ወደ ጥንቷ ቤተክርስቲያን እምነት መመለስ አለብን ለሚሉ ሰዎች ከተዘጋጀላቸው የዘመን መጨረሻ የእውነት እውቀት መጠን አንጻር በሰባተኛው የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ የሚገኘው የእውነት መጠን እየቀጨጨ እያነሰ ይሄዳል።

ሰባተኛዋ ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን መንፈስ እና እውነት መመለስ ብትፈልግ ይህንን መቅረዝ ነበረ መምሰል ያለባት።

 

 

ዛሬ 45,000 ዓይነት ዲኖሚኔሽናዊ እና ዲኖሚኔሽናዊ ያልሆኑ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ይህም ብዙ ዓይነት ልዩ ልዩ እምነቶች እንዳሉ ያመለክታል።

ዛሬ በቤተክርስቲን ውስጥ ሰዎች ይድናሉ (ይህም መልካም ነገር ነው) ደግሞም ስለ መንፈስ ቅዱስ እና መልካም ሕይወት ስለ መኖር ብዙ ጥሩ ትምሕርቶችን ያስተምሩዋቸዋል። ከዚያ በኋላ ግን ቤተክርስቲያን በገንዘብ ኃይል በሚነዳ፤ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ አስተምሕሮዎች በሞሉበት የፉክክር ዓለም ውስጥ ከውሃ ጥምቀት ጀምሮ አቅጣጫዋ ይጠፋባታል (ይህም ክፉ ነገር ነው)። ይህም የመልካም እና የክፉ ድብልቅ ቤተክርስቲያንን ለብ ያለች እንድትሆን ያደርጋታል። ከዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያኖች የዘመን መጨረሻ የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጦችን ለመቀበል እምቢ ይላሉ።

የሰባት ዓመታት መከራ አለ ብለው በማመን ቤተክርስቲያኖች ለራዕይ መጽሐፍ የተሳሳተ ትርጓሜ ይሰጡታል። በቤተክርስቲያን ዘመናት ውስጥ ስለሚሰሩ የክርስቶስ ተቃዋሚ መናፍስት የሚናገሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች የታላቁ መከራ ዘመን አድርገው ይተረጉሟቸዋል።

ከዚህ የተነሳ ኢየሱስ ከቤተክርስቲያን በር ውጭ ቆሟል።

ራዕይ 3፡14 በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦

ራዕይ 3፡20 እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤

የዘመን መጨረሻ ላይ ያለችዋ ቤተክርስቲያን ኢየሱሰን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ገፍታ አስወጥታዋለች። የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲሰራ ይፈልጋሉ ነገር ግን የተገለጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይፈልጉም።

 

ስለዚህ ወደ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ምሳሌነት የምንመለስበት የመንፈስ እና የእውነት ተሃድሶ በ1520 ከጀመረው ተሃድሶ ጀምሮ ይህንን ስዕል ይመስላል፡-

 

 

ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የእውነት ብርሃን አንጻር ሙሉውን መቅረዝ መመልከት ሁለት አካሄዶችን ይገልጣል።

መካከለኛው መቅረዝ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ዘመን ነበረ።

የቤተክርስቲያን ዘመናት 1 እስከ 4 ከመጽሐፍ ቅዱስ እየራቁ ወደ ቀኝ እንደሄዱ ያሳያል።

የቤተክርስቲያን ዘመናት 5 እስከ 7 ደግሞ ከግራ በኩል ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ለመመለስ የሚደረግን እንቅስቃሴ ያሳያል፤ ይህም መጨረሻው የሚሆነው የመጨረሻዋ ቤተክርስቲያን ልክ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ስትመስል ነው።

 

 

አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው መስማማት አለባቸው።

የዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ያሉ ተምሳሌቶች ጥልቅ ትርጉም እንዳላቸው ልብ በሉ።

የራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ብዙ ተምሳሌቶች የቤተክርስቲያንን ታሪክ እና ወደ ጌታ ምጻት የሚያደርሱ ክስቶችን ሁሉ የሚወክሉ ናቸው፣ እንዲሁም ወንጌል ወደ አይሁዶች በሚሄድበት ጊዜ የሚጀምረውን ታላቁን መከራም ያካትታሉ። ከዚያ በኋላ አዲሲቷ ምድርና አዲስ ሰማይ ከመገለጣቸው በፊት ታላቁ የአርማጌዶን ጦርነት እና የ1,000 ዓመቱ የሰላም መንግስት ይመጣሉ።

ከዚያ ወዲያ ባሕር አይኖርም።

ራዕይ 21፡1 አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም

ባሕር እንደ ቦምብ ይፈነዳና የምድርን ገጽ ሙሉ በሙሉ ያጠፋታል፤ በዙርያዋ የሚንሳፈፉ ሳተላይቶችን ሁሉ ያቃጥላቸዋል። ከሳይንሳዊና ከቴክኖሎጂ “ድንቃድንቆቻችን” መካከል አንድም የሚተርፍ ነገር አይኖርም፤ ሳይንሳዊ ፈጠራዎቻችን ብዙ መልካም ነገሮችን ቢያመጡም እንኳ ብዙ ጥፋት እና የተፈጥሮ ሚዛን መዛባትም አስከትለዋል። ይህም የመልካም እና ክፉ እውቀት የምትሰጠዋ ዛፍ ፍሬ ክፉ ውጤት ነው።

ዘላለማዊው ዓለም እጅግ በተሻለ መሰረት ላይ ነው የሚመሰረተው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ ከመንፈስ እና ከእውነት ለተወለዱ ሰዎች ሁሉ በረከት እና ጥቅም ይሆን ዘንድ ሰማይንና ምድርን ወደ አንድነት ያመጣቸዋል።

 

 

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።” — 1 ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16:23